am_ulb/25-LAM.usfm

306 lines
27 KiB
Plaintext

\id LAM
\ide UTF-8
\h ሰቆቃው ኤርሚያስ
\toc1 ሰቆቃው ኤርሚያስ
\toc2 ሰቆቃው ኤርሚያስ
\toc3 lam
\mt ሰቆቃው ኤርሚያስ
\s5
\c 1
\p
\v 1 በሰዎች ተሞልታ የነበረችው ከተማ አሁን ፈጽማ ብቻዋን ተቀምጣለች! ኃያል የነበረችው አገር እንደ መበለት ሆናለች! በሕዝቦች መካከል እንደ ልዕልት ነበረች፥ አሁን ግን በባርነት ውስጥ ወድቃለች!
\v 2 በሌሊት ታለቅሳለች፥ታነባለችም፤እንባዎቿም ጉንጮቿን ከድነዋል። ከፍቅረኞቿ መካከል የሚያጽናናት የለም። ጓድኞቿ ሁሉ አሳልፈው ሰጧት። ጠላቶቿም ሆነዋል።
\s5
\v 3 ከድህነቱና ከመከራዉ የተነሳ ይሁዳ ወደ ምርኮ ሄደች። በሕዝቦች መካከል ኖረች፥ ዕረፍትንም አላገኘችም። በጭንቀቷ ጊዜ አሳዳጆቿ ሁሉ በረቱባት።
\s5
\v 4 ወደ ተቀጠሩት በዓላት የሚመጣ የለምና የጽዮን መንገዶች ያለቅሳሉ። ደጆቿ ሁሉ ባዶ ናችው። ካህናቶቿ ይቃትታሉ። ደናግሎቿ ሐዘንተኞች ናቸዉ፥እራስዋም በፍጹም ጭንቀት ውስጥ አለች።
\v 5 ባላንጣዎቿ ጌቶቿ ሆኑ፥ጠላቶቿ በለጸጉ። ስለ ብዙ ኃጢአቷ እግዚአብሔር መከራን አመጣባት። ልጆቿ ለጠላቷ ተማርከው ወደ ግዞት ሄዱ።
\s5
\v 6 የጽዮን ሴት ልጅ ውበቷ ተለያት። ልዑላኖቿ መሰማሪያ እንዳላገኙ አጋዘኖች ሆኑ፥ በአሳዳጆቻቸው ፊት በድካም ሄዱ።
\s5
\v 7 በመከራዋና ቤት አልባ በሆነችባቸው ቀናት፥ ኢየሩሳሌም በቀደሙት ቀናት የነበሯትን የከበሩ ነገሮች ታስባለች፤ሕዝቦቿ በጠላት እጅ በወደቁ ጊዜ ማንም የረዳት አልነበረም። ጠላቶቿ ተመለከቷት፥ በጥፋቷም ሳቁ።
\s5
\v 8 ኢየሩሳሌም ታላቅ ኃጢአት ሠርታለች፥ ስለዚህ እንደ አደፈ ነገር ተንቃለች። ዕርቃናዋን ከተመለከቱበት ጊዜ አንስቶ ያከበሯት ሁሉ ናቋት። ታጉተመትማለች፥ ዘወር ለማለትም ትሞክራላች።
\v 9 ከቀሚሷ በታች አድፋለች። የወደፊቷን አላሰበችም። አወዳደቋ አስፈሪ ነበር። የሚያጽናት ማንም አልነበረም። «እግዚአብሔር ሆይ፥ መከራዬን ተመልከት፥ ጠላት እጅግ ታላቅ ሆኖአልና» እያለች ትጮኻለች!።
\s5
\v 10 ጠላት በከበረ ነገሯ ሁሉ ላይ እጁን አደረገ። ወደ ጉባዔህ እንዳይገቡ አዝዘህ የነበረ ቢሆንም እንኳን፥ ሕዝቦች ወደ መቅደሷ ሲገቡ አየች።
\s5
\v 11 ሕዝቦቿ ሁሉ ምግብ እየፈለጉ ይጮኻሉ። ሕይወታቸውን ለማቆየት የከበረ ኃብታቸውን ስለ ምግብ ይሰጣሉ። የማልጠቀም ሆኟለሁና፥ እግዚአብሔር ሆይ ተመልከት አስበኝም።
\v 12 እናንተ መንገደኞች ሁሉ ይህ ለእናንተ ምንም አይደለምን? እግዚአብሔር እኔን መቅጣት ከጀመረበት ከጽኑ ቁጣው ቀን አንስቶ፥ የደረሰብኝን ሐዘን የሚመስል የማንም የሌላ ሰው ሐዘን ካለ ተመልከቱ፥ እዩም።
\s5
\v 13 ወደ ዉስጥ ወደ አጥንቶቼ ከላይ እሳት ላከ፥ አሸነፋቸዉም። ለእግሮቼ መረብን ዘረጋ ወደ ኋላም መለሰኝ። ያለማቋረጥ ባዶና ደካማ አደረገኝ።
\v 14 የመተላለፌ ቀንበር በእጆቹ በአንድ ላይ ታስረዋል። በአንድ ላይ ተገምደዋል፥በአንገቴም ላይ ተደርገዋል። ብርታቴን ከንቱ አደረገው። ጌታ በእጃቸው አሳልፎ ሰጠኝ፥ መቆምም አልችልም።
\s5
\v 15 ጌታ፥የሚመክቱልኝን ኃያላን ወንዶች ሁሉ ወዲያ ጣላቸው። ጽኑዓን ወንዶቼን ለማድቀቅ ጉባዔን በላዬ ጠራብኝ። ጌታ ድንግሊቱን የይሁዳ ልጅ በወይን መጥመቂያ እንዳለ ወይን ረገጣት።
\s5
\v 16 ስለ እነዚህ ነገሮች አለቅሳልሁ። ሕይወቴን የሚያድሳት አጽናኙ ከእኔ ርቋልና ከዓይኖቼ ውኃ ይፈሳል፥ ከዓይኖቼ።
\v 17 ጽዮን እጆቿን እጅግ ዘረጋች፥ የሚያጽናናት ማንም የለም። እግዚአብሔር በያዕቆብ ዙሪያ ያሉ ጠላቶቹ እንዲሆኑ አዘዘ። ኢየሩሳሌም በእነርሱ ዘንድ እንደ ርኩስ ነገር ተቆጠረች።
\s5
\v 18 በትዕዛዙ ላይ ዐመጽ አድርጌእለሁና እግዚአብሔር ጻድቅ ነው። እናንተ ሕዝቦች ሁሉ ስሙ፥ ሐዘኔንም ተመልከቱ። ደናግሎቼና ኃያላን ወንዶቼ ተማርከዉ ሄደዋል።
\v 19 ፍቅረኞቼን ጠራኋቸው፥ ነገር ግን ከዳተኞች ሆኑብኝ። ካህናቶቼና ሽማግሌዎቼ ሕይወታችውን ለማኖር ምግብ እየፈለጉ በከተማ ውስጥ ሞቱ።
\s5
\v 20 እግዚአብሔር ሆይ ተጨንቄአለሁና ውስጤም ተንጦአልና ተመልከት። እጅግ ዓመጽ አድርጌአለሁና ልቤ በውስጤ ታውኮአል። በመንገዶች ላይ ሰይፍ ልጆቻችንን ይነጥቃል፥በቤትም እንደ ሙታን መንደር ነው።
\s5
\v 21 ሲቃዬን ስማ። የሚያጽናናኝ ማንም የለም። ጠላቶቼ ሁሉ ስለ መከራዬ ሰምተዋል። አንተ ስለ አደረግከው ደስ አላቸው። እነርሱም እንደ እኔ ይሆኑ ዘንድ ያወጅክባቸውን ቀን አምጣ።
\v 22 ክፋታቸው ሁሉ በፊትህ ይታይ። መቃተቴ ብዙ ነውና፥ ልቤም ደክሞአልና፤ስለ መተላለፌ ሁሉ እንዳሰቃየኽኝ አሰቃያቸው።
\s5
\c 2
\p
\v 1 ጌታ በቁጣው ጥቁር ደመና የጽዮንን ሴት ልጅ ፈጽሞ ከደናት! የእስራኤልን ውበት ከሰማይ ወደ ምድር ጣለ፥ በቁጣው ቀን የእግሩን መር ግጫ ችላ አለ።
\v 2 ጌታ የያዕቆብን ከተማዎች ሁሉ ዋጠ፥ ርኅራኄም አልነበረውም። በቁጣው የጽዮንን ሴት ልጅ የተመሸጉ ከተማዎች ጣለ፤ መንግሥቱ ንና ልዑላኗን አቃለለ፥አዋርዶ ወደ ምድር መትቶ ጣላችው።
\s5
\v 3 በብርቱ ቁጣው የእስራኤልን ብርታት ሁሉ ቆረጠ፥ ከጠላት ፊት ቀኝ እጁን ወደ ኋላ መለሰ፥ በዙሪያው ያለውን ሁሉ እንደሚበላ የሚንቦገቦግ እሳት ያዕቆብን አቃጠለ።
\v 4 እንደ ጠላት ቀስቱን በእኛ ላይ ገተረ፥ እንደ ባላጋራ ወርውሮ ሊገድል እጆቹ ተዘጋጅተው በተጠንቀቅ ቆመ። ለዓይን እጅግ የከበሩትን ሰዎች ሁሉ አረደ፥ በጽዮን ሴት ልጅ ድንኳን ውስጥ ቁጣውን እንደ እሳት አፈሰሰ።
\s5
\v 5 ጌታ እንደ ጠላት ሆነ። እስራኤልን ዋጠ። ቤተ መንግሥቶቿን ሁሉ ዋጠ፤ምሽጎቿን አጠፋ። በይሁዳ ሴት ልጅ ውስጥ ለቅሶንና ሰቆቃን አበዛ።
\v 6 ድንኳኑን እንደ አትክልት ቦታ አጠፋ። የታላቁን ጉባዔ ስፍራ አፈረሰ። በቁጣው ትኩሳት ንጉሡንና ካህኑን ንቋልና እግዚአብሔር በጽዮን ታላቁን ጉባዔና ሰንበትን እንዲረሱ አደረገ።
\s5
\v 7 ጌታ መሠዊያውን ጣለ፥ መቅደሱን አልተቀበለም። የቤተ መንግሥቶቿን ግንቦች በጠላት እጅ አሳልፎ ሰጠ። በታላቅ ጉባዔ ቀን እንደሚሆን በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ የድል ድምጽ አሰሙ።
\s5
\v 8 እግዚአብሔር የጽዮንን ሴት ልጅ የከተማ ቅጥር ለማፍረስ ወሰነ። የመለኪያውን ገመድ ዘረጋ፥ቅጥሩን ከማፍረስ እጁን አልመለሰም። ምሽጎቿ እንዲያለቅሱ፥ቅጥሮቿ አቅመ አልባ እንዲሆኑ አደረገ።
\v 9 በሮቿ ወደ መሬት ሰመጡ፥ የበሮቿን መቀርቀሪያዎች አጠፋ፥ ሰበረም።ንጉሧና ልዑላኖቿ የሙሴ ሕግ በሌለበት በአሕዛብ መካከል ናቸው። ነቢያቶቿም እንኳን ሳይቀሩ ከእግዚአብሔር ዘንድ ራዕይ አላገኙም።
\s5
\v 10 የጽዮን ሴት ልጅ ሽማግሌዎች መሬት ላይ ተቀምጥዋል፥ በዝምታም ይቆዝማሉ። በራሳቸው ላይ አቧራ ነሰነሱ፥ የሐዘንም ልብስ ለበሱ። የኢየሩሳሌም ደናግል ራሳቸውን ወደ መሬት ዝቅ አደረጉ።
\s5
\v 11 እንባዬ ደረቀ፥ዓይኖቼ ቀሉ፥ የውስጥ ሰዉነቴ ታወከ። ልጆችና የሚያጠቡ ሕጻናት በመንደሮች መንገዶች ላይ ያለ ምንም ተስፋ ደክመዋልና፥ የሕዝቤም ሴት ልጆች ደቅቀዋልና ጉበቴ በመሬት ላይ ተዘረገፈ።
\v 12 በከተማይቱ መንገዶች ላይ እንደ ቆሰለ ሰው ዝለው ሳሉ፥ በእናቶቻቸው እቅፍ ነፍሳቸው እየፈሰሰች ሳሉ፥ እናቶቻቸውን፦ «እሕሉና ወይኑ የት አለ?» ይላሉ።
\s5
\v 13 የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ሆይ፥ ስለ አንቺ ምን ማለት እችላለሁ? የጽዮን ድንግል ሆይ አጽናናሽ ዘንድ ከምን ጋር አመሳስልሻለሁ? ውድቀትሽ እንደ ባሕር ታላቅ ነው። ሊፈውስሽ የሚችል ማነው?
\v 14 ነቢያቶችሽ የሚያስትና ከንቱ ራዕይ አይተውልሻል። በረከትሽን ይመልሱ ዘንድ በደልሽን አለገለጡም፤ ነገር ግን የሚያስት ትንቢትና የሚያጠምድ ራዕይ ተቀበሉ።
\s5
\v 15 በመንገድ የሚያልፉ ሁሉ እጃቸውን በአንቺ ላይ ያጨበጭባሉ። በኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ይዝታሉ፥ራሳቸውንም ይነቀንቃሉ፥ ደግሞም «'የውበት ሁሉ መጨረሻ'፥ 'የምድር ሁሉ ደስታ' ብለው የሚጠሯት ከተማ ይህቺ ናትን?» ይላሉ።
\v 16 ጠላቶችሽ ሁሉ አፋቸውን እጅግ ይከፍታሉ፥ ያላግጡብሻልም። እያፏጩና ጥርሳቸውን እያፋጩ፦ «ዋጥናት! በእርግጥም የተጠባበቅናት ቀን ይህቺ ናት! አገኘናት! አየናትም!» ይላሉ።
\s5
\v 17 እግዚአብሔር የወሰነውን አደረገ። ከረዥም ጊዜ በፊት ያወጀውን ቃሉን ፈጸመ። አፈረሰ፥ርኅራኄም አልነበረውም፤ ጠላትሽ በአንቺ ላይ እንዲደሰት ፈቀደ፥ የጠላቶሽን ብርታት ከፍ ከፍ አደረገ።
\s5
\v 18 ልባቸው ወደ ጌታ ጮኽ፤የጽዮን ሴት ልጅ ቅጥር ሆይ እንባሽ እንደ ወንዝ ቀንና ሌሊት ይፍሰስ። ለራስሽ የእፎይታ ጊዜ አትስጪ። የአይኖችሽን ማፍሰስ አታስቁሚ።
\v 19 በሌሊት ተነሺና ጩኺ፥ ከሌሊቱ መጀመሪያ አንስቶ በጌታ ፊት ልብሽን እንደ ውኃ አፍስሺ። በየመንገዱ ራስ ላይ በረሀብ ደክመው ስለወደቁት ልጆችሽ ሕይወት እጆችሽን ወደ እርሱ አንሺ።
\s5
\v 20 እግዚአብሔር ሆይ ተመልከት፥ ጽኑ መከራን ስላመጣህባቸው ስለ እነዚያ ሰዎች ግድ ይበልህ። ሴቶች የራሳቸውን ፍሬ፥ የሚሳሱላቸውን ልጆቻቸውን ይብሉን? ካህኑና ነቢዩ በጌታ መቅደስ ውስጥ ይታረዱን?
\s5
\v 21 ወጣቱና ሽማግሌው በአንድነት በየመንገዶቹ በመሬት ላይ ወደቁ። ደናግሎቼና ኃያላን ወንዶቼ በሰይፍ ወደቁ። በቁጣህ ቀን አረድሃቸው፥በጭካኔ ገደልካቸው፥ ርኅራኄም አልነበረህም።
\v 22 በከበረው ጉባዔ ቀን እንደሚሆን ከዙሪያው ሁሉ ሽብርን ጥራህብኝ፤ ማንም አላመለጠም፥ በእግዚአብሔር ቁጣ ቀን የተረፈ ማንምአልነበረም። የተንከባከብኳቸውንና ያሳደግኋቸውን ጠላቴ አጠፋቸው።
\s5
\c 3
\p
\v 1 በእግዚአብሔር የቁጣ በትር መከራ ያየ ሰው እኔ ነኝ።
\v 2 አባረረኝ፥ በብርሃን ሳይሆን በጨለማ እንድሄድ አደረገኝ።
\v 3 በእርግጥ ሊቃወመኝ ወደ እኔ ዘወር አለ፥ ቀኑን ሙሉ እጁን በላዬ መለሰ።
\v 4 ሥጋዬንና ቆዳዬን ቀደደ፥ አጥንቶቼን ሰበረ።
\s5
\v 5 ቅጥር በዙሪያዬ ገነባብኝ፥ በምሬትና በመከራም ከበበኝ።
\v 6 ከሞቱ ረዥም ጊዜ እንደሆናቸው በጨለማ ስፍራ እንድኖር አደረገኝ።
\v 7 በዙሪያዬ ቅጥርን ገነባ፥ ማምለጥም አልችልም። የእግሬን ሰንሰለት አከበደ።
\v 8 ለርዳታ ብጮኽና ብጣራም ጸሎቴን ዘጋ።
\s5
\v 9 ከጥርብ ድንጋይ በተሰራ ቅጥር መንገዴን ዘጋ፤የምሄድብት የትኛውም መንገድ ጠማማ ሆን።
\v 10 መንገዴን ቀየረው።
\v 11 ገነጣጠለኝ፥ብቸኛም አደረገኝ።
\s5
\v 12 ቀስቱን ለጠጠ፥ ለፍላጻውም የዒላማ ምልክት አደረገኝ።
\v 13 ቀስቱን ለጠጠ፥ ለፍላጻውም የዒላማ ምልክት አደረገኝ። ለሰዎች ሁሉ መሳለቂያ፥ ዘወትርም ለሽሙጥጯ ዝማሬያቸው ምክንያት ሆንኩ። ምሬት ሞላብኝ፥ እሬት እንድጠጣ አስገደደኝ።
\v 14 ለሰዎች ሁሉ መሳለቂያ፥ ዘወትርም ለሽሙጥጯ ዝማሬያቸው ምክንያት ሆንኩ።
\v 15 ምሬት ሞላብኝ፥ እሬት እንድጠጣ አስገደደኝ።
\s5
\v 16 ጥርሴን በድንጋይ ሰበረ፥ ወደ መሬት ውስጥ ረገጠኝ።
\v 17 ሰላምን ከሕይወቴ አስወገድክ፤ ከእንግዲህ መቼም የትኛዉንም ደስታ አላስብም።
\v 18 ስለዚህም«ጽናቴ ጠፍቷል፥ በእግዚአብሔር ላይ ያለ ተስፋዬም ሄዷል» አልሁ።
\s5
\v 19 መከራዬንና እሬትና ምሬት ወደ አለበት መጥፋቴን አስባለሁ።
\v 20 በእርግጥ አስበዋለሁ፥ተስፋ በመቁረጥ በውስጤ አቀረቀርኩ ።
\v 21 ነገር ግን ይህን አስባልሁ፥ ተስፋ ሊኖረኝ የቻለውም ከዚህ የተነሳ ነው።
\s5
\v 22 ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር የኪዳኑ ታማኝነት የተነሳ ነው፥ የምሕረቱ ሥራዎች አያልቁምና።
\v 23 የምሕረቱ ሥራዎች ማለዳ ማለዳ አዲስ ናችው፤ ታማኝነትህ ምንኛ ታላቅ ነው!
\v 24 ለራሴ እንዲህ አልኩ «እግዚአብሔር ዕጣ ክፍሌ ነው» ስለዚህ ተስፋ አደርገዋለሁ።
\s5
\v 25 ለምጠብቀው፥ ለምትፈልገውም ሕይወት እግዚአብሔር መልካም ነው።
\v 26 የእግዚአብሔርን ማዳን በዝምታ መጠበቅ መልካም ነው።
\v 27 በወጣትነቱ ቀንበርን ቢሸከም ለሰው መልካም ነው።
\v 28 እግዚአብሔር አሸክሞታልና ለብቻው ይቀመጥ ዝምም ይበል።
\v 29 ምናልባት ተስፋ ሊኖር ይችላልና አፉን በአፈር ዉስጥ ያኑር።
\s5
\v 30 ለሚመታው ጉንጩን ይስጥ። ዉርደትንም ይጥገብ፤
\v 31 እግዚአብሔር ለዘላለም አይጥለውምና!
\v 32 ሐዘንን ቢያመጣም እንኳን ከታላቁ የኪዳኑ ታማኝነት በሚሆን ርኅራኄ ይራራል።
\v 33 ምክንያቱም ከልቡ አይጨቁንም፥ወይንም የሰዎችን ልጆች አያሰቃይም።
\s5
\v 34 በምድር ያሉ ምርኮኞችን ሁሉ ከእግሩ በታች ሲያደቅቅ፥
\v 35 በልዑል ፊት የሰውን ፍርድ ሲያጣምም፥
\v 36 ፍትህ ፈላጊውን ሲያፍን- ጌታ አያይምን?
\s5
\v 37 ጌታ ካላዘዘው በቀር የሚናገርና የሚፈጽመው ማን ነው?
\v 38 ጥፋትና ስኬት ከልዑል አፍ የሚወጡ አይደሉምን?
\v 39 ታዲያ ማንም ሕያው የሆነ ሰው እንዴት ሊያጉረመርም ይችላል? ማንም ሰው ስለ ኃጢአቱ ቅጣት እንዴት ሊያጉረመርም ይችላል?
\s5
\v 40 መንገዳችንን እንፈትን እንመርምርም፥ ወደ እግዚአብሔርም እንመለስ።
\v 41 ልባችንንና እጃችንን በሰማይ ወደ አለው ወደ እግዚአብሔር እናንሣና እንዲህ ብለን
\v 42 እንጽልይ፦ተላልፈናል በአንተም ላይ ዐምፀናል፥ስለዚህ ይቅር አላልከንም።
\v 43 ራስህን በቁጣ ሸፈንክ አሳደድከንም። አረድከን፥ አራራህልንምም።
\s5
\v 44 ራስህን በደመና ሸፈንክ፥ስለዚህም ማለፍ የሚችል ጸሎት የለም።
\v 45 በአሕዛብም መካከል ቆሻሻና ውዳቂ አደረግኽን ።
\v 46 ጠላቶቻችን በእኛ ላይ በማላገጥ አፋቸውን ከፈቱ።
\v 47 የአሳር ጉድጓድ ፥የባዶነትና የጥፋት ፍርሃት መጣብን።
\s5
\v 48 ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ጥፋት ዓይኔ ያለማቋርጥ ውኃ አፈሰሰች።
\v 49 ዓይኖቼ ያፈሳሉ አያቆሙምም፥ለለቅሷቸውም ፍጻሜ የለውም፥
\v 50 እግዚአብሔር ውደ ታች እስኪመለከት ከሰማይም እስኪያይ ድረስ።
\s5
\v 51 ከከተማዬ ሴቶች ልጆች የተነሳ ዓይኔ ጽኑ ስቃይ በሕይወቴ ላይ አመጣች።
\v 52 ጠላቶቼ ያለ ምንም ምክንያት፥ያለመታከት እንደ ወፍ አደኑኝ።
\v 53 ሕይወቴን በጉድጓድ ዉስጥ አጠፉ፥ ድንጋይንም በላዬ ከመሩ።
\v 54 ውኆች በራሴ ላይ አለፉ፤እኔም፦ «ተቆርጬአለሁ!» አልኩ።
\s5
\v 55 እግዚአብሔር ሆይ፥ ከጥልቅ ጉድጓድ ስምህን ጠራሁ።
\v 56 «እርዳታ ፈልጌ ስጮህ፥እረፍት ፈልጌ ስጣራ ጆሮህን አትሰውር» ባልኩኝ ጊዜ ድምጼን ሰማህ።
\v 57 በጠራሁህ ቀን ወደ እኔ ቀርበህ «አትፍራ» አልከኝ።
\s5
\v 58 ጌታ ሆይ በተከሰስሁ ጊዜ ስለ ነፍሴ ተሟገትህ፤ ሕይወቴንም አዳንክ።
\v 59 እግዚአብሔር ሆይ እንዴት እንደ ጨቆኑኝ አይተሃል፥ ክርክሬን በጽድቅ ፍረድልኝ።
\v 60 በእኔ ላይ የዶለቱትን ሁሉ፥የበቀላቸውን ሥራ ሁሉ አይተሃል።
\v 61 እግዚአብሔር ሆይ በእኔ ላይ የዶለቱትን ሁሉና እሽሙጥጫቸውን ሰምተሃል።
\s5
\v 62 በእኔ ላይ የተነሱብኝን ከንፈሮች ሰምተሃል፤ቀኑን ሁሉ እኔን በመቃወም የሚያስቡትን ጥልቅ አሳቦች ሰምተሃል።
\v 63 እግአብሔር ሆይ! ተመልከት፥ በመቀመጣቸውም ሆነ በመነሳታችው የስላቅ ዘፈናቸው ምክንያት ነኝ።
\s5
\v 64 እግዚአብሔር ሆይ እጆቻቸው እንዳደረጉት ክፉ ነገር እንደዚያው መልሰህ ክፈላቸው።
\v 65 ፍርሃትን በልባቸው አድርግ፥ ርግማንህንም በላይቸው አድርግ።
\v 66 እግዚአብሔር ሆይ! በቁጣህ አሳድዳችው፥ከሰማይት በታች በየስፍራው አጥፋቸው።
\s5
\c 4
\p
\v 1 ወርቁ ፈጽሞ ደበዘዘ፤ ንጹሁ ወርቅ ተለወጠ! የተቀደሱት ድንጋዮች በየመንገዱ ዳር ተበተኑ።
\v 2 የጽዮን ልጆች የከበሩ፥ከንጹህ ወርቅ በላይ የሚቆጠሩ ነበሩ። አሁን ግን በሸክላ ሠሪ እጅ እንደተሠሩ የሸክላ ዕቃዎች እንጂ ከምንም አልተቆጠሩም።
\s5
\v 3 ቀበሮዎች እንኳን ግልገሎቻቸውን ለማጥባት ጡቶቻቸውን ይገልጣሉ፥የሕዝቤ ሴት ልጅ ግን እንደ ምድረ በዳ ሰጎን ጨካኝ ሆነች።
\s5
\v 4 ከጥም የተነሳ የሚጠባው ሕጻን ምላስ ከላንቃው ጋር ተጣበቀ፤ሕጻናት እንጀራ ለመኑ፥ ነገር ግን የሚሰጣችው የለም።
\v 5 በውድ ዋጋ የሚገዛ ምግብ ይመገቡ የነበሩ ተጥለዋል፥ በየመንገዱ ተርበዋል፤ቀይ ግምጃ ይለብሱ የነበሩ አሁን በቆሻሻ ክምር መካከል ናቸው።
\s5
\v 6 ምንም እጅ ሳይወድቅባት በድንገት ከተገለበጠች ከሰዶም ኃጢአት ይልቅ የሕዝቤ ሴት ልጅ ኃጢአት ታላቅ ነው።
\s5
\v 7 መሪዎቿ እንደ በረዶ የሚያንጸባርቁ ነበሩ፥እንደ ወተትም ነጭ ነበሩ። ሰውነታቸው ከቀይ ዕንቁ ይልቅ ቀይ ነበረ፥ መልካቸውም እንደ ሰንፔር ነበረ።
\v 8 አሁን ጨለማው ገጽታቸውን አጥቁሮታል፥ ቆዳቸው ከመነመኑ አጥንቶቻቸው ጋር ስለተጣበቀም በመንገዶች ላይ ማንነታቸው አልታወቀም።
\s5
\v 9 በሰይፍ የተገደሉት በረሃብ ከሞቱት ይሻላሉ፥አንዳችም ሰብል ከእርሻ በመጥፋቱ በረሃብ ተወግተው ከተወገዱት ይሻላሉ።
\v 10 የርኁሩኆቹ ሴቶች እጆች የገዛ ልጆቻቸውን ቀቀሉ፤ በሕዝቤ ሴት ልጅ የጥፋት ቀን እነዚህ ልጆች መብል ሆኑአቸው።
\s5
\v 11 እግዚአብሔር ቁጣውን አረካ። ጽኑ ቁጣውን አፈሰሰ፤ በጽዮን እሳትን አያያዘ፥ መሠረትዋንም በላ።
\s5
\v 12 የምድር ነገሥታት ወይም በዓለም ከሚኖሩ ማናቸውም፥ ባላጋራ ወይም ጠላት በኢየሩሳሌም በሮች ይገባል ብለው አላመኑም።
\v 13 ነገር ግን የጻድቅን ደም በመካከልዋ ካፈሰሱ ከነቢያቶቿ ኃጢአትና ከካህናቷ በደል የተነሳ ይህን አደረጉ።
\s5
\v 14 አሁን እነዚያ ነቢያትና ካህናት እንደ ዓይነ ስውራን ሰዎች በየጎዳናዎቹ ይቅበዘበዛሉ። ማንም ልብሶቻቸውን መንካት እስከማይችል ድረስ በደም ረክሰዋል።
\v 15 «እናንተ ርኩሳን ለቃችሁ ሂዱ!» እያሉ በነቢያቱና ካህናቱ ላይ ይጮሁባቸዋል።«ለቃችሁ ሂዱ፥ለቃችሁ ሂዱ! አትንኩን!» ይሏቸዋል። ስለዚህ ወደ ሌላ ምድር ይቅበዘበዛሉ፥ ነገር ግን አሕዛብ እንኳን፥«ከእንግዲህ ወድያ በዚህ እንደ እንግዳ መኖር አይችሉም» ይላሉ።
\s5
\v 16 እግዚአብሔር ከማደሪያው በትኖአቸዋል፥ ከእንግዲህ ወድያ ወደ እነርሱ በርኅራኄ አይመለከትም። ማንም ከእንግዲህ ወድያ ካህናቱን በምንም መልኩ አክብሮ አይቀበላቸውም፥ ለሽማግሌዎቹም ግድ አልተሰኙም።
\s5
\v 17 የማይጠቅሙ ረዳቶችን እንኳ ለማግኘት ዓይኖቻችን ድከሙ፤ሊያድነን ወደማይችል ሕዝብ በጉጉት ተመለከቱ።
\v 18 በመንገዶቻችን ሁሉ እርምጃዎቻችንን ተከታተሉ። ፍፃሜያችን መጥቶአልና መጨረሻችን ቀርቦአል፥ ቀኖቻችንም አልቀዋል።
\s5
\v 19 አሳዳጆቻችን ከሰማይ ንስሮች ይልቅ ፈጣኖች ናቸው። በተራሮች ላይ አሳደዱን በምድረ በዳም ሸመቁብን።
\v 20 በእግዚአብሔር የተቀባው ንጉሣችን፥ የአፍንጫችን እስትንፋስ፥ በጉድጓቸው ተያዘ፤«በአሕዛብ መካከል በጥበቃው ሥር እንኖራልን» ብለን የተናገርንለት ንጉሣችን ነበር።
\s5
\v 21 በዖፅ ምድር የምትኖሪ የኤዶም ሴት ልጅ ሆይ፥ጽዋው ወደ አንቺም ያልፋልና ደስ ይበልሽ ሐሴትም አድርጊ። ትሰክሪያልሽ፥ እርቃንሽንም ትቀሪያልሽ።
\v 22 የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ በደልሽ ተፈጸመ። ከእንግዲህ ወዲያ በምርኮ አያኖርሽም። ነገር ግን የኤዶም ሴትልጅ ሆይ በደልሽን ይቀጣል። ኃጢአትሽንም ይገልጣል።
\s5
\c 5
\p
\v 1 እግዚአብሔር ሆይ የሆነብንን አስብ። እፍረታችንን እይ፥ተመልከትም።
\v 2 ርስታችን ለእንግዶች፥ ቤቶቻችን ለባዕዳን ታልፈው ተሰጡ።
\v 3 አባቶች ስለሌሉ፥ እናቶቻችንም መበለቶች ስለሆኑ ወላጅ አልባ ሆን።
\v 4 ለመጠጣት ውኃችን የብር ዋጋ ጠየቀ፥ የገዛ እንጨታችንም ተሸጠል ን።
\s5
\v 5 ጠላቶቻችን ያሳድዱናል፥ አንገታችንም ላይ ደርሰዋል። እኛ ደክመናል፥ ዕረፍትም የለንም።
\v 6 ምግብ ለመጥገብ ለግብፃውያንና ለአሦራውያን እጃችንን ሰጠን።
\v 7 አባቶቻችን ኃጢአት ሠሩ፤ እነርሱ የሉም፥እኛ ግን ኃጢአታቸውን ተሸከምን።
\s5
\v 8 ባሮች ይገዙናል፥ ከእጃቸውም የሚያድነን የለም።
\v 9 ከምድረ በዳው ሰይፍ የተነሳ እንጀራ ለማግኘት በሕይወታችን ፈረድን።
\v 10 ቆዳችን እንደ ምድጃ ሆኖአል፥ ከረሃቡ ትኩሳት የተነሳ ተቃጥሎአል።
\s5
\v 11 በጽዮን ሴቶችን፥ በይሁዳ ከተሞች ደናግላንን ደፈሩ።
\v 12 በገዛ እጆቻቸው ልዑላኑን ሰቀሉ፥ሽማግሌዎችንም አላከበሩም።
\s5
\v 13 ኃያላን ወንዶችን ወደ ወፍጮ ቤት አመጡአቸው፥ ወጣት ወንዶችም ከእንጨት በታች ተንገዳግዱ።
\v 14 ሽማግሌዎችን ከከተማይቱ ደጅ፥ ኃያላን ወንዶችንም ከዘፈናቸው አስወገዷቸው።
\s5
\v 15 የልባችን ደስታ ተወግዶአል፥ ጭፈራችንም ወደ ለቅሶ ተለውጦአል።
\v 16 አክሊል ከራሳችን ወድቋል! ወዮልን! ኃጢአት ሠርተናልና!
\s5
\v 17 ልባችን ታምሞአል፥ዓይኖቻችንም ፈዝዘዋል፤
\v 18 ምክንያቱም ባድማ በሆነችው በጽዮን ተራራ ላይ ቀበሮዎች ፈንጭተውበታልና።
\s5
\v 19 ነገር ግን አንተ እግዚአብሔር ነህ፤ ለዘላለም ትገዛለህ፥ ዙፋንህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ነው።
\v 20 ስለ ምን ለዘላለም ትረሳናለህ? ለረዥም ዘመናትስ ትተወናለህን?
\v 21 እግዚአብሔር ሆይ፥ወደ አንተ መልሰን፥እኛም ንስሐ እንገባልን። ቀኖቻችንን እንደ ጥንቱ ዘመን አድስ፥
\v 22 ፈጽመህ ካልጣልከንና እጅግም ካልተቆጣኽን።