am_ulb/24-JER.usfm

2616 lines
331 KiB
Plaintext

\id JER
\ide UTF-8
\h ኤርሚያስ
\toc1 ኤርሚያስ
\toc2 ኤርሚያስ
\toc3 jer
\mt ኤርሚያስ
\s5
\c 1
\p
\v 1 ይህ የኬልቅያስ ልጅ የሆነው የኤርምያስ ቃል ነው፤ እርሱ በብንያም ምድር ከነበሩት ካህናት አንደኛው ነበር።
\v 2 የአሞጽ ልጅ በሆነው በይሁዳ ንጉሥ ዐሥራ ሦስተኛ ዓመት አገዛዝ ዘመን ላይ የእግዚአብሔር ቃል ወደ እርሱ መጣ።
\v 3 ቃሉ የመጣው በይሁዳ ንጉሥ የኢዮስያስ ልጅ በሆነው ኢዮአቄም ዘመን፣ የኢዮስያስ ልጅ በሆነው የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ የዐሥራ አንደኛው አመት አገዛዝ አምስተኛ ወር ድረስ፣ የኢየሩሳሌም ሕዝቦች ምርኮኛ ሆነው ሲወሰዱ ነበር።
\s5
\v 4 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፣
\v 5 "በማኅፀን ሳልሠራህ አውቄሃለሁ፥ ከማኅፀንም ሳትወጣ ቀድሼሃለሁ፥ ለአሕዛብ ነቢይ አድርጌሃለሁ።"
\v 6 እኔም፣ "ወዮ ጌታ እግዚአብሔር፥ ገና ብላቴና በመሆኔ እንዴት እንደምናገር አላውቅም" አልሁ።
\s5
\v 7 ነገር ግን እግዚአብሔር "'ገና ብላቴና ነኝ' አትበል። ወደምልክህ ሁሉ ልትሄድ ይገባል፣ የማዝዝህንም ሁሉ ልትናገር ይገባል!
\v 8 ላድንህ ከአንተ ጋር ስለሆንኩ አትፍራ - ይህ የእግዚአብሔር ንግግር ነው።" አለኝ።
\s5
\v 9 እግዚአብሔርም እጁን ዘርግቶ አፌን ዳሰሰ፣ እንዲህም አለኝ "ቃሌን በአፍህ ውስጥ አኑሬአለሁ፤
\v 10 ትነቅልና ታፈርስ ዘንድ፥ ታጠፋና ትገለብጥ ዘንድ፥ ትሠራና ትተክል ዘንድ በአሕዛብና በመንግሥታት ላይ ዛሬ ሾሜሃለሁ" አለኝ።
\s5
\v 11 የእግዚአብሔር ቃል "ኤርምያስ ሆይ፥ ምን ታያለህ?" እያለ ወደ እኔ መጣ። እኔም "የለውዝ በትር አያለሁ" አልሁት።
\v 12 እግዚአብሔርም "መልካም አይተሃል፣ እፈጽመው ዘንድ በቃሌ እተጋለሁና" አለኝ።
\s5
\v 13 የእግዚአብሔር ቃል ለሁለተኛ ጊዜ "ምን ታያለህ?" እያለ ወደ እኔ መጣ። እኔም "ፊቱ ከሰሜን አቅጣጫ የሆነ የሚፈላ ማሰሮ አያለሁ" አልሁ።
\v 14 እግዚአብሔርም "በዚህች ምድር በሚኖሩት ሁሉ ላይ ከሰሜን አቅጣጫ ክፉ ነገር ይገለጣል" አለኝ።
\s5
\v 15 በሰሜን ያሉትን የመንግሥታትን ወገኖች ሁሉ እጠራለሁና ይላል እግዚአብሔር። እነርሱም ይመጣሉ፣ እያንዳንዳቸውም በኢየሩሳሌም መግቢያ በራፍ ላይ፣ በዙሪያዋ ባሉት በአጥሮቿ ሁሉ ላይ፣ በይሁዳም ከተሞች ሁሉ ላይ ዙፋናቸውን ያኖራሉ።
\v 16 እኔን ስለተዉበት ክፋታቸው ሁሉ፣ ለሌሎችም አማልክት ስላጠኑ፣ በገዛ እጃቸው ለሠሯቸውም ስለሰገዱላቸው፣ ፍርዴን በእነርሱ ላይ እናገራለሁ።
\s5
\v 17 አንተ ራስህን አዘጋጅ! ተነሥና ያዘዝሁህን ሁሉ ንገራቸው። በእነርሱ ፊት አትፍራ፣ አሊያ እኔ በእነርሱ ፊት አስፈራሃለሁ!
\v 18 ተመልከት! ዛሬ በምድሪቱ ሁሉ ላይ በይሁዳም ነገሥታት -በአለቆችዋና በካህናትዋ ላይ በምድሪቱም ሕዝብ ላይ እንደ ተመሸገ ከተማ እንደ ብረትም ዓምድ እንደ ናስም ቅጥር አድርጌሃለሁ።
\v 19 ይዋጉሃል፣ ነገር ግን አድንህ ዘንድ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አያሸንፉህም" ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\c 2
\p
\v 1 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ መጣ፣ እንዲህም አለኝ፣
\v 2 "ሂድና በኢየሩሳሌም ጆሮ ጩኽ። እንዲህም በል 'እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በወጣትነትሽ የነበረሽን የኪዳን ታማኝነት፣ በታጨሽበት ጊዜ የነበረሽን ፍቅር፣ ዘር ባልተዘራበት ምድረ በዳ እንደ ተከተልሽኝ ስለአንቺ አስታውሳለሁ።
\v 3 እስራኤል ለእግዚአብሔር ቅዱስ ነበረ፣ የእርሻው መከር በኩራትም ነበረ! ከበኩራቱ የበሉት ሁሉ ኃጢአት አድርገዋል! ክፉም ነገር ይመጣባቸዋል ይላል እግዚአብሔር።'"
\s5
\v 4 የያዕቆብ ቤትና የእስራኤልም ቤት ቤተሰቦች ሁሉ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።
\v 5 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "አባቶቻችሁ ምን ክፋት አግኝተውብኝ ነው እኔን ከመከተል የራቁት፣ ከንቱ ጣዖታትንም የተከተሉት፣ እና ራሳቸውም ከንቱ የሆኑት?
\v 6 እነርሱም 'ከግብጽ ምድር ያወጣን እግዚአብሔር፣ በምድረ በዳ ጉድጓድ ወዳለበት የአረባህ ምድር፣ በውኃ ጥምና በሞት ጥላ ምድር፥ ማንም በማያልፍበትና ማንም በማይቀመጥበት ምድር የመራን እግዚአብሔር ወዴት አለ?' አላሉም።
\s5
\v 7 ነገር ግን ፍሬዋንና ሌሎች መልካም ነገሮቿን እንድትበሉ ወደ ቀርሜሎስ ምድር አገባኋችሁ! ይሁን እንጂ በመጣችሁ ጊዜ፣ ምድሬን አረከሳችሁ፣ ርስቴንም አጐሳቈላችሁ!
\v 8 ካህናቱም 'እግዚአብሔር ወዴት አለ? አላሉም፥ ባለ የኦሪቶች ሊቅ የሆኑትም ስለ እኔ ግድ አላላቸውም! እረኞችም በደሉኝ፥ ነቢያትም ለበኣል ትንቢት ተናገሩ፣ ትርፍ የሌለውንም ነገር ተከተሉ።
\s5
\v 9 ስለዚህ እከስሳችኋለሁ - የልጆቻችሁንም ልጆች እከስሳለሁ።
\v 10 ወደ ኪቲም ደሴቶች እለፉና ተመልከቱ። ወደ ቄዳርም መልእክተኞችን ላኩና እንደዚህ ያለ ነገር ህኖ እንደ ሆነ መርምራችሁ እዩ።
\v 11 አማልክት ባይሆኑ እንኳን አማልክት ያልሆኑትን አማልክቱን የለወጣቸው አንድ ሕዝብ አለን? ነገር ግን ሕዝቤ ሊረዳቸው ለማይችለው ነገር ክብሩን ለወጠ።
\s5
\v 12 ሰማያት ከዚህ የተነሣ ተደነቁ! ተንቀጥቀጡ እና ደንግጡ ይላል እግዚአብሔር።
\v 13 ሕዝቤ ሁለቱን ክፉ ነገሮች በእኔ ላይ አድርገዋልና፦ ውሃ ለመያዝ የማይችሉትን የተቀደዱ ጉድጓዶች ለራሳቸው በመቆፈር እኔን የሕያውን ውኃ ምንጭ ትተውኛል!
\s5
\v 14 እስራኤል ባርያ ነውን? ወይስ በቤት የተወለደ አይደለምን? እናስ ብዝበዛ የሆነው ለምንድነው?
\v 15 የአንበሳ ደቦሎች በእርሱ ላይ አገሡ። ብዙ ድምጽ በማሰማት ምድሩን አስፈሪ አደረጉት! ከተሞቹም የሚኖርባቸው እንዳይኖር ሆኖ ተደመሰሰ።
\v 16 የሜምፎስና የጣፍናስ ልጆች የራስ ቅልሽን ላጭተው ባርያዎችን ከአንቺ ወሰዱ!
\v 17 ይህን ሁሉ በራስሽ ላይ ያደረግሽው በመንገድ ላይ ሲመራሽ አምላክሽን እግዚአብሔርን ስለተውሽ አይደለምን? ይላል እግዚአብሔር አምላክሽ።
\s5
\v 18 አሁንስ በግብጽ መንገድ ሄደሽ የሺሖርን ውኃ የምትጠጪው ለምንድነው? በአሦርስ መንገድ ሄደሽ የኤፍራጥስንም ውኃ የምትጠጪው ለምንድነው?
\v 19 ክፋትሽ ይገሥጽሻል፣ ክዳትሽም ይቀጣሻል፤ አምላክሽንም እግዚአብሔርን መተውሽ እኔንም መፍራት ማቆምሽ ክፉና መራራ ነገር እንደ ሆነ እወቂ፥ ተመልከቺ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
\s5
\v 20 ከጥንት ጀምሮ የነበረብሽን ቀንበር ሰብሬአለሁና፣ እስራትሽንም ቈርጫለሁ። እንዲህም ሆኖ አንቺ 'አላገለግልም!' አልሽ፥ ነገር ግን ከፍ ባለው ኮረብታ ሁሉ ላይ ከለምለምም ዛፍ ሁሉ በታች ተጋደምሽ፣ አንቺ አመንዝራ።
\v 21 እኔ ራሴ ግን የተመረጠች ወይን፣ ፈጽሞ እውነተኛ የሆነ ዘር አድርጌ ተክዬሽ ነበር። አንቺ ግን ክፉ የእንግዳ ወይን ግንድ ሆነሽ እንዴት ተለወጥሽብኝ?
\v 22 በወንዝ ብትታጠቢ ወይም በብርቱ ሳሙና ብትታጠቢ፣ በእኔ ፊት በኃጢአትሽ ረክሰሻል ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
\s5
\v 23 'አልረከስሁም! በአሊምንም አልተከተልሁም' እንዴት ትያለሽ? በሸለቆዎች ያለውን ባህርይሽን ተመልከቺ! ያደረግሽውንም ተገንዘቢ፣ በመንገዷ ላይ እንደ ተለቀቀች ፈጣን ግመል ሆነሻል፤
\v 24 በምኞትዋ ከንቱ ነፋስን እንደምታሸትት፣ ምድረ በዳ እንደ ለመደች እንደ ሜዳ አህያ ነሽ! ከምኞትዋ የሚመልሳት ማን ነው? የሚፈልጋት ሁሉ ራሱን አያደክምም። ወደ እርሷ ሄደው በትኩሳቷ ወራት ያገኟታል።
\v 25 እግርሽን ባዶ ከመሆን፣ ጉሮሮሽንም ከውኃ ጥም ከልክዪ! አንቺ ግን 'ተስፋ-ቢስ ነው! አይሆንም፣ እንግዶችን ወድጄአለሁና እከተላቸዋለሁ!' አልሽ።
\s5
\v 26 ሌባ ሲያዝ እንደሚያፍረው ሁሉ፣ እንዲሁ የእስራኤል ቤት፣ እነርሱ፣ ንጉሦቻቸው፣ አለቆቻቸው፣ ካህናቶቻቸውና ነብያቶቻቸውም ያፍራሉ።
\v 27 ለዛፉ፣ 'አንተ አባቴ ነህ፣' ድንጋዮንም 'አንተ ወለድከኝ' ይላሉ። ፊታቸውንም ሳይሆን ጀርባቸውን ሰጡኝ። በመከራቸው ጊዜ ግን 'ተነሥና አድነን!' ይላሉ።
\v 28 ለአንተ የሠራሃቸው አማልክትህ ወዴት ናቸው? ይሁዳ ሆይ፥ አማልክትህ እንደ ከተሞችህ ቊጥር እንዲሁ ናቸውና ይነሡ በመከራህም ጊዜ ያድኑህ!
\s5
\v 29 ስለዚህ እኔ እንዳጠፋሁ አድርጋችሁ የምትከስሱኝ ለምንድር ነው? ሁላችሁ በእኔ ላይ ኃጢአት ሠርታችሁብኛል ይላል እግዚአብሔር።
\v 30 ሕዝባችሁን በከንቱ ቀጥቼአቸዋለሁ፤ ተግሣጽን አልተቀበሉም፤ እንደሚሰብር አንበሳ ሰይፋችሁ ነቢያቶቻችሁን በልቶአል!
\v 31 ከዚህ ትውልድ የሆናችሁ እናንተ! የእግዚአብሔር ቃል ለሆነው ለቃሌ ትኩረት ስጡ! በውኑ ለእስራኤል ምድረ በዳ፣ ወይስ የጥልቅ ጨለማ ምድር ሆንሁባትን? ሕዝቤስ ስለ ምን 'እኛ እንቅበዝበዝ፣ ከእንግዲህ ወዲህ ወደ አንተ አንመለስም' ይላል?
\s5
\v 32 ደናግሏ ጌጥዋን፣ ወይስ ሙሽራ ዝርግፍ ጌጥዋን ትረሳለችን? ሕዝቤ ግን ለማይቈጠሩ ቀናት ረስቶኛል።
\v 33 ፍቅርን ለመሻት መንገድሽን እንዴት በደህና ታቀኛለሽ። እንደውም መንገድሽን ለክፉዎች ሴቶች እንኳ አስተምረሻል።
\v 34 የንፁሐን ሕይወት የሆነው ደም፣ የድሆችም ደም በልብሶችሽ ላይ ተገኝቷል። እነዚህ ሰዎች በስርቆሽ ተግባር የተያዙ አልነበሩም።
\s5
\v 35 ይልቊን፣ ይህ ሁሉ ሆኖ ሳለ፣ 'ወቀሳ የለብኝም፤ በእውነት የእግዚአብሔር ቊጣ ከእኔ ተመልሶአል' አልሽ። ነገር ግን ተመልከቺ! 'ኃጢአት አልሠራሁም' ብለሻልና ይፈረድብሻል።
\v 36 መንገድሽን ትለዋውጪ ዘንድ ነገሩን ለምን ታቀልያለሽ? አሦር እንዳሳፈረሽ ግብጽ ያሳፍርሻል።
\v 37 እግዚአብሔር የታመንሽባቸውን ጥሎአልና፥ በእነርሱም አይከናወንልሽምና እጅሽን በራስሽ ላይ አድርገሽ ከዚያ ደግሞ ትወጫለሽ።
\s5
\c 3
\p
\v 1 በሰው ዘንድ፣ 'ሰው ሚስቱን በፍቺ ቢያባርራት፣ ከእርሱም ሄዳ የሌላ ሰው ሚስት ትሆናለች። በድጋሚ ወደ እርሷ ሊመለስ ይገባዋልን? እርሷ ፈጽሞ የረከሰች አይደለችምን?' ይባላል። ያቺ ሴት ማለት ይህች ምድር ናት! አንቺ እንደ ሴተኛ አዳሪ ከብዙ ውሽሞች ጋር አመንዝረሻል፣ ወደ እኔም ትመለሻለሽን? ይላል እግዚአብሔር።
\v 2 ዓይንሽን ወደ ተራቆቱት ኮረብቶች አንሺና ተመልከቺ! ያልተነወርሽበት ስፍራ ወዴት አለ? ዘላን በምድረ በዳ እንደሚቀመጠው፣ አንቺ በመንገድ ላይ ተቀምጠሽ አፍቃሪዎችሽን ትጠብቂያቸው ነበር። በዘማዊነትሽና በኃጢአትሽ ምድሪቱን አረከስሽ።
\s5
\v 3 ስለዚህ የጸደይ ዝናብ ተከለከለ፣ የኋለኛውም ዝናብ አልመጣም። ነገር ግን እንደ ዘማዊት ሴት ፊት፣ ፊትሽ የእብሪተኛ ነበር። ልታፍሪም እንቢ ብለሻል።
\v 4 ከእንግዲህ ወዲህ 'አባቴ! የወጣትነቴ የቅርብ ወዳጅ ነህ።' ብለሽ ወደ እኔ አልጮኽሽልኝምን?
\v 5 እስከ ለዘላለም ትቆጣለህን? ቊጣህንስ እስከ ፍጻሜ ድረስ ትጠብቀዋለህን?' ብለሽ ተናገርሽ። ተመልከቺ! ክፋትን እንደምትፈጽሚ ተናገርሽ፣ አደረግሸውም። ስለዚህ ማድረግሽን ቀጥይ!"
\s5
\v 6 እግዚአብሔርም በንጉሡ በኢዮስያስ ዘመን እንዲህ አለኝ "እስራኤል እኔን መክዳቷን ታያለህ? ከፍ ወዳለው ተራራ ሁሉ፣ ወደለመለመ ዛፍም ሁሉ በታች ሄደች፣ በዚያም እንደ ዘማዊት ሴት ሆነች።
\v 7 'ይህንም ሁሉ ካደረገች በኋላ፣ ወደ እኔ ትመለሳለች' ብዬ ነበር፤ ነገር ግን አልተመለሰችም። ከዚያም እምነት የለሿ እኅቷ ይሁዳ እርሷ ያደረገችውን አየች።
\s5
\v 8 ስለዚህ፣ ለእነዚህ ምክንያቶች ሁሉ ማመንዘሯን አየሁ። ከዳተኛይቱ እስራኤል! ፈትቼያት አባርሬያታለሁ፣ ደግሞም የፍችዋንም ወረቀት ሰጥቻታለሁ። አታላይ እኅትዋ ይሁዳ ግን አልፈራችም፣ እርስዋም ደግሞ ሄዳ ዝሙትን ፈጸመች።
\v 9 በዝሙትዋ ምድሪቱ መርከሷ ምንም አልመሰላትም፣ ስለዚህ ከድንጋይና ከግንድ ጣዖታትን አደረጉ።
\v 10 ከዚያም ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ፣ እምነት-የለሿ ይሁዳ በውሸት እንጂ በፍጹም ልብዋ ወደ እኔ አልተመለሰችም!"-ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 11 ከዚያም እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፣ "ከእምነት-የለሿ ይሁዳ ይልቅ እምነት-የለሿ እስራኤል ጸደቀች!
\v 12 ሂድና ይህን ቃል ለሰሜን ተናገር። 'እምነት የለሿ እስራኤል ሆይ፥ ተመለሽ! ይላል እግዚአብሔር፤ ለሁልጊዜ አልቈጣብሽምና። እኔ ታማኝ ስለሆንኩ - ለዘላለም እንደተቆጣሁ አልቆይም ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 13 በአምላክሽ በእግዚአብሔር ላይ እንዳመፅሽ፥ መንገድሽንም ከለመለመ ዛፍ ሁሉ በታች ለእንግዶች እንደ ዘረጋሽ፥ ቃሌንም እንዳልሰማሽ ኃጢአትሽን ዕወቂ ይላል እግዚአብሔር።
\v 14 አግብቻችኋለሁና እምነት-የለሽ የሆናችሁት ሕዝቦች፣ ተመለሱ! ይላል እግዚአብሔር፤ አንዱንም ከአንዲት ከተማ ሁለቱንም ከአንድ ወገን እወስዳችኋለሁ! ወደ ጽዮንም አመጣችኋለሁ!
\v 15 እንደ ልቤም የሆኑ እረኞችን እሰጣችኋለሁ፣ እነርሱም በዕውቀትና በማስተዋልም ይጠብቁአችኋል።
\s5
\v 16 በእነዚያ ቀናት ትበዛላችሁ፣ በምድሪቱም ላይ ታፈራላችሁ ይላል እግዚአብሔር። "የእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑ ታቦት!" ብለው ከእንግዲህ ወዲህ አይናገሩም። ከእንግዲህ አያስቡትምና፣ ወይም አያስተውሉትምና ይህ ጉዳይ ከእንግዲህ በልባቸው አይመጣም። ከእንግዲህ ወዲህም ይህ ንግግር አይኖርም።'
\s5
\v 17 በዚያም ዘመን ስለ ኢየሩሳሌም 'ይህች የእግዚአብሔር ዙፋን ናት' ብለው ይናገራሉ፣ ደግሞም ሌሎች አሕዛብ ሁሉ በእግዚአብሔር ስም ኢየሩሳሌም ላይ ይሰበሰባሉ። ከእንግዲህም ወዲህ በእልከኛ ልባቸው አይሄዱም።
\v 18 በእነዚያም ቀናት፣ የይሁዳ ቤት ከእስራኤል ቤት ጋር ይሄዳል። በአንድም ሆነው ከሰሜን ምድር ርስት አድርጌ ለአባቶቻቸው ወደ ሰጠኋት ምድር ይመጣሉ።
\s5
\v 19 እኔ ግን 'እንደ ወንድ ልጄ ላከብርሽና በሌሎች አሕዛብ ካለው ይልቅ የበለጠ ውብ የሆነውን አስደሳቹን ምድር ልሰጥሽ እንዴት ፈለግሁ!' ብዬ ነበር። "አባቴ" ብለሽ ትጠሪኛለሽ። እኔንም ከመከተል አትመለሽም' ብዬ ነበር።
\v 20 ነገር ግን ለባሏ ታማኝ እንዳልሆነች ሴት፣ እንዲሁ የእስራኤል ቤት የሆናችሁት ከዳችሁኝ ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 21 "የእስራኤል ልጆች መንገዳቸውን ቀይረዋልና፣ አምላካቸውንም እግዚአብሔርን ረስተውኛልና በወና ኮረብቶች ላይ የልመናቸውና ልቅሶአቸው ድምፅ ተሰማ።
\v 22 ከዳተኞች ሕዝቦች ሆይ ተመለሱ! ከዳተኛነታችሁንም እፈውሳለሁ!" እነሆ! አንተ አምላካችን እግዚአብሔር ነህና ወደ አንተ እንመጣለን።
\s5
\v 23 የኮረብቶችና የብዙ ተራሮች ሐሰት ብቻ መጥቷል። በእርግጥም የእስራኤል መዳን በአምላካችን በእግዚአብሔር ነው።
\v 24 ይሁን እንጂ አሳፋሪ ጣዖታት ለበጎቻቸውና ላሞቻቸው፣ ለወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸው አባቶቻችን የሠሩትን በልተውባቸዋል።
\v 25 በእፍረት እንጋደም። በአምላካችን እግዚአብሔር ላይ ኃጢአት ሠርተናልና እፍረታችን ይሸፍነን። ከትንሽነታችን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኛና አባቶቻችን በአምላካችን በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት ሠርተናልና፣ የአምላካችንንም የእግዚአብሔርን ቃል አልሰማንምና!"
\s5
\c 4
\p
\v 1 እስራኤል ሆይ፣ ብትመለሺ፣ የምትመለሺው ወደ እኔ ይሁን፣ ይላል እግዚአብሔር፤ ከፊቴ ርኩሰትሽን ብታስወግጂ፣ በድጋሚም ከእኔ ባትርቂ
\v 2 'ሕያው እግዚአብሔርን!' ብለሽ በእውነትና በፍትሕ፣ በጽድቅም ብትምይ፥ አሕዛብ በረከቴን ይጠይቃሉ፣ እኔንም ያመሰግኑኛል።
\v 3 ለይሁዳና ለኢየሩሳሌም ሰዎች እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ 'ጥጋቱን እርሻ እረሱ፣ በእሾህም ላይ አትዝሩ።
\s5
\v 4 እናንተም የይሁዳ ሰዎች፣ የኢየሩሳሌምም ነዋሪዎች፣ ስለ ሥራችሁ ክፋት ቊጣዬ እንደ እሳት እንዳይወጣ የሚያጠፋውም ሳይኖር እንዳያቃጥል፥ ለእግዚአብሔር ተገረዙ፥ የልባችሁንም ሸለፈት አስወግዱ።
\v 5 ይሁዳ ውስጥ ተናገሩ፣ በኢየሩሳሌምም ላይ አውሩ። "በአገሪቱ ላይ መለከት ንፉ" በሉ፤ ጮኻችሁም "ሁላችሁ ተሰብሰቡ። ወደ ተመሸጉትም ከተሞች እንግባ" በሉ።
\v 6 ከሰሜን ክፉ ነገርንና ጽኑ ጥፋትን አመጣለሁና ወደ ጽዮን ሰንደቅ ዓላማን አንሡ፤ ሽሹ፥ አትዘግዩ።
\s5
\v 7 አንበሳ ከጥቅጥቅ ዱር እየወጣ ነው፣ አሕዛብንም የሚያጠፋ እየወጣ ነው። ምድርሽን ለማሸበር፣ ከተሞችሽም ሰው የሌለባቸው ፍርስራሾች ለማድረግ ከስፍራው ወጥቶአል።
\v 8 ከዚህ የተነሣ፣ ራስሽን በማቅ ልብስ ሸፍኚ፣ ሙሾ አውጪ፣ አልቅሺም። የእግዚአብሔር ጽኑ ቊጣ ከእኛ ዘንድ አልተመለሰምና።
\s5
\v 9 በዚያም ቀን፥ ይላል እግዚአብሔር፥ የንጉሡና የመኳንንቱ ልብ ይሞታል። ካህናቱም ይደነቃሉ ነቢያቱም ይደነግጣሉ።
\v 10 እኔም "ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! ወዮ፥ 'ሰላም ይሆንላችኋል' በማለት ይህን ሕዝብና ኢየሩሳሌምን በእርግጥም ፈጽመህ አታልለሃል። ሆኖም 'ሰይፉ እስከ ነፍስ ድረስ ያጠቃል።"
\s5
\v 11 በዚያ ጊዜ ለዚህ ሕዝብና ለኢየሩሳሌም፣"የሚያቃጥል ነፈሳስ በምድረበዳ ካሉት ወና ኮረብቶች ወደ ሕዝቤ ሴት ልጅ ይመጣል። እነርሱን አያበጥርም ወይም አያጠራም።
\v 12 ከዚያም ይልቅ እጅግ ብርቱ የሆነ ነፋስ በትእዛዜ ይመጣል፣ ደግሞም እኔ ፍርዴን በእነርሱ ላይ እናገራለሁ።
\s5
\v 13 ተመልከቱ እንደ ደመና ያጠቃል፣ ሠረገሎቹም እንደ ዐውሎ ነፋስ ናቸው። ፈረሶቹም ከንስር ይልቅ ፈጣኖች ናቸው። ጠፍተናልና ወዮልን!
\v 14 ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ትድኚ ዘንድ ልብሽን ከክፉ ነገር እጠቢ። እንዴት ኃጢአት እንደምትሠሪ ክፉ አሳብ የሚኖርብሽ እስከ መቼ ድረስ ነው?
\v 15 የተናጋሪ ድምፅ ከዳን ይናገራል። የሚመጣውም ጥፋት ከኤፍሬምም ተራሮች ይሰማል።
\s5
\v 16 አሕዛብ ይህንን እንዲያስቡ አድርጉ፦ ተመልከቱ፣ ወራሪዎች በይሁዳ ከተሞች ላይ የጦርነት ጩኸት ለመጮኽ ከሩቅ ምድር እየመጡ ነው ብላችሁ አውሩ።
\v 17 በእኔ ላይ ዓመፀኛ ሆናለችና የለማ እርሻን ከብበው እንደሚጠብቊ ይሆናሉ ይላል እግዚአብሔር።
\v 18 ባሕርይሽና ሥራሽ ይህን አድርጎብሻል። ይህ ቅጣትሽ ይሆናል። እንዴት አስጨናቂ ይሆናል! የገዛ ልብሽም ይመታል።
\s5
\v 19 ልቤ! ልቤ! በልቤ ተጨንቄያለሁ። ልቤ በውስጤ ታውኮብኛል። የመለከትን ድምፅና የጦርነት ማንቂያን ሰምቻለሁና ዝም ልል አልችልም።
\v 20 በጥፋት ላይ ጥፋት ተጠርቶአል፣ መላዋ ምድርም ተበዝብዛለች። በድንገትም ድንኳኔንና መጋረጃዬን አጠፉ።
\s5
\v 21 መስፈርቱን የምመለከተው እስከመቼ ነው? የመለከቱንስ ድምፅ እሰማ ይሆን?
\v 22 ሕዝቤ ተሞኝተዋልና አላወቁኝም። ሰነፍ ሕዝብ ናቸው፣ ማስተዋልም የላቸውም። ክፉ ነገርን ለማድረግ ብልሃተኞች ናቸው፣ በጎ ነገርን ማድረግ ግን አያውቁም።
\s5
\v 23 ምድሪቱን አየሁ፣ እነሆም፥ ባዶ ነበረች አንዳችም አልነበረባትም፤ ለሰማያትም ብርሃንም አልነበረባቸውም።
\v 24 ተራሮችን አየሁ። እነሆም፣ ይንቀጠቀጡ ነበር፣ ኮረብቶችም ሁሉ ተናወጡ።
\v 25 አየሁ። እነሆ፣ ሰው አልነበረም፣ የሰማይም ወፎች ሁሉ ሸሽተው ነበር።
\v 26 ተመለከትሁ። እነሆ፣ ፍሬያማ እርሻ ምድረ በዳ ሆነች፣ ከተሞችም ሁሉ ከእግዚአብሔር ፊት ከጽኑ ቊጣው የተነሣ ፈርሰው ነበር።
\s5
\v 27 እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል "ምድር ሁሉ ትጠፋለች፣ ነገር ግን ፈጽሜ አላጠፋቸውም።
\v 28 ስለዚህ ምድር ታለቅሳለች፣ ከላይ ያለው ሰማይ ይጠጨልማል። ተናግሬአለሁና፥ አስቤአለሁም፤ አልጸጸትም ከመፈጸምም አልመለስም።
\v 29 ከፈረሰኞችና ከቀስተኞች ጫጫታ የተነሣ እያንዳንዱ ከተማ ሁሉ ይሸሻሉ፤ ወደ ጫካም ይገባሉ። እያንዳንዱ ከተማ በቋጥኝ ላይም ይወጣሉ። ከተሞቹ ይተዋሉ፣ የሚኖርባቸው ሰው አይኖርምና።
\s5
\v 30 አንቺም ባድማ ሆንሽ፥ ምን ታደርጊአለሽ? ቀይ በለበስሽ ጊዜ፥ በወርቅ አንባርም አጌጥሽ፣ ዓይንሽንም ተኳልሽ፣ የሚመኙሽ ወንዶች ገፉሽ። ይልቊን፣ ነፍስሽን ይሹአታል።
\v 31 ስለዚህ የምጥ፣ የበኩር ልጅ እንደሚወለድበት ያለ የጭንቅ ድምጽ፣ የጽዮን ሴት ልጅን ድምጽ ሰምቻለሁ። ለመተንፈስ ትታገላለች። እጆቿንም ትዘረጋለች፣ ከገዳዮቹ የተነሣ ነፍሴ ዝላለችና 'ወዮልኝ!' አለች።
\s5
\c 5
\p
\v 1 በኢየሩሳሌም መንገድ እየተመላለሳችሁ ሩጡ፤ በአደባባዮችዋም ፈልጉ። ከዚያም ተመልከቱ፣ ስለዚህም አስቡ፦ ፍትሕን የሚያደርገውን በታማኝነትም ለማድረግ የሚሞክረውንም ሰው ታገኙ እንደሆነ፣ ይቅር እላታለሁ።
\v 2 እነርሱም 'ሕያው እግዚአብሔርን!' ቢሉ የሚምሉት በሐሰት ነው።
\v 3 እግዚአብሔር ሆይ፣ ዓይንህ ታማኝነትን የምትመለከት አይደለችምን? አንተ ቀሥፈሃቸዋል፣ ነገር ግን አላመማቸውም። ሙሉ ለሙሉ አሸንፈሃቸዋል፣ ነገር ግን ተግሣጽን እንቢ አሉ። ፊታቸውን ከድንጋይ ይልቅ አጠንክረዋል፤ ይመለሱ ዘንድ እንቢ አሉ።
\s5
\v 4 ስለዚህ እኔም "እነዚህ ድሆች ብቻ የሆኑ ሕዝቦች ናቸው። የእግዚአብሔርን መንገድና የአምላካቸውን ሕግ አላወቁምና እነዚህ ሰነፎች ናቸው፤
\v 5 ወደ ጠቃሚዎቹ ሕዝቦች እሄዳለሁ የእግዚአብሔርን መልእክት እናገራቸዋለሁ፤ የእግዚአብሔርን መንገንድና የአምላካቸውን ሕግ ያውቃሉና። ነገር ግን እነርሱ በሙሉ ቀንበሩን በአንድነት ሰብረዋል፣ ለእግዚአብሔር ያሰራቸውንም ሰንሰለቶች ቈርጠዋል።
\v 6 ስለዚህ ኃጢአታቸው በዝቶአልና፣ የክዳታቸውም ብዛት አይቆጠርምና አንበሳ ከዱር ወጥቶ ይሰብራቸዋል፣ የበረሀም ተኵላ ያጠፋቸዋል፣ ነብርም በከተሞቻቸው ላይ ይተጋል፣ ከዚያም የሚወጣ ሁሉ ይነጠቃል።
\s5
\v 7 እነዚህን ሰዎች ይቅር የምላቸው ለምንድነው? ልጆችሽ ትተውኛል አማልክትም ባልሆኑትም ምለዋል። ሞልቼ መገብኳቸው፣ እነርሱ ግን አመነዘሩ የምንዝርና ቤትን ምልክቶችንም ወሰዱ።
\v 8 በትኩሳት እንዳሉ ፈረሶች ሆኑ፤ ወዳጅነት ፈልገው ተንከላወሱ። እያንዳንዱ ሰው ወደባልንጀሮቻቸው ሚስቶች አሽካኩ።
\v 9 ስለዚህ ልቀጣ አይገባኝምን? ይላል እግዚአብሔር፤ ነፍሴስ እንደዚህ ባለ ሕዝብ ላይ አትበቀልምን?
\s5
\v 10 ወደ ወይን ከፍታዋ ወጥታችሁ አፍርሱ። ነገር ግን ፈጽማችሁ አታጥፏቸው። ወይኖቻቸውን ቊረጡ፣ እነዚህ ወይኖች ከእግዚአብሔር አልመጡምና።
\v 11 የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት በእኔ ላይ ፈጽሞ ከድተውኛልና ይላል እግዚአብሔር።
\v 12 እነርሱም ከድተውኛል። 'እርሱ እውነተኛ አይደለም። ክፉ ነገርም አይመጣብንም፣ ሰይፍንና ራብንም አናይም' አሉ።
\v 13 ነብያትም የነፋስን ያህል ጥቅም የለሽ ሆነዋል የእግዚአብሔርንም ቃል ለእኛ የሚነግረን የለም። ዛቻቸው በራሳቸው ላይ ይምጣባቸው።
\s5
\v 14 ስለዚህም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል "በዚህ ቃል ተናግራችኋልና ተመልከት፣ በአፍህ ውስጥ ቃሌን አኖራለሁ። እንደ እሳት ይሆናል፣ ይህም ሕዝብ እንደ እንጨት ይሆናል! እሳቱም ይበላቸዋል።
\v 15 ተመልከቱ! የእስራኤል ቤት ሆይ፣ ሕዝብን ከሩቅ አመጣባችኋለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ ኃያል ጥንታዊ ሕዝብ ነው! ቋንቋቸውንም የማታውቋቸው፣ የሚናገሩትንም የማታስተውሉት ሕዝብ ነው።
\s5
\v 16 የፍላጻቸውም ሰገባ እንደ ተከፈተ መቃብር ነው። ሁሉም ኃያላን ናቸው።
\v 17 መከሮቻችሁንና እንጀራችሁን ይበላሉ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁንም ይበሏቸዋል፤ በጎችንና ላሞቻችሁንም ይበላሉ፤ ወይናችሁንና በለሶቻችሁንም ይበላሉ። የምትታመኗቸውን የተመሸጉ ከተሞችን በሰይፍ ይደበድባሉ።
\s5
\v 18 ነገር ግን በዚያ ዘመን እንኳን ይላል እግዚአብሔር፣ ፈጽሜ ላጠፋችሁ አላስብም።
\v 19 እንዲህም ይሆናል፤ እናንተ እስራኤል እና ይሁዳ፣ 'አምላካችን እግዚአብሔር ይህን ነገር ሁሉ ስለምን አደረገብን?' ስትሉ፣ አንተ ኤርምያስ ያን ጊዜ፣ 'እግዚአብሔርን እንደተዋችሁ እና በምድራችሁም ሌሎችን አማልክት እንዳመለካችሁ፣ እንዲሁ ለእናንተ ባልሆነ አገር ለሌሎች ሰዎች በባርነት ትገዛላችሁ' ትላቸዋለህ።
\s5
\v 20 ይህን ለያዕቆብ ቤት አውሩ፣ በይሁዳም ይሰማ።
\v 21 ይህን ስሙ፣ እናንተ ሰነፎች! ጣዖታት ፈቃድ የላቸውምና፤ ዐይን አለባቸው፣ ነገር ግን ሊያዩ አይችሉም። ጆሮዎችም አሉባቸው፣ ነገር ግን አይሰሙም።
\v 22 እኔን አትፈሩኝምን? በፊቴስ አትደነግጡምን? ይላል እግዚአብሔር፤ የአሸዋን ድንበር እንዳይተላለፈው በማይቋረጥ ትእዛዝ በባሕሩ ላይ አድርጌአለሁ። የባህሩ ነውጥ ቢጮኽም አያቋርጠውም።
\s5
\v 23 ነገር ግን ይህ ሕዝብ ግን ዐመፀኛ ልብ አለው። በዐመፅ ሸፍቶ ሄዷል።
\v 24 በልባቸውም፣ 'የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ በትክክለኛው ጊዜ የሚሰጠውን፣ ለመከርም የተመደቡትን ወራት የሚጠብቅልንን አምላካችንን እግዚአብሔርን እንፍራ አላሉም።
\v 25 በደላችሁ እነዚህ እንዳይሆኑ አስቀርታለች። ኃጢአታችሁም መልካምን ነገር ወደ እናንተ እንዳይመጣ አስቆመ።
\s5
\v 26 በሕዝቤ መካከል ክፉዎች ሰዎች ተገኝተዋል። አንድ ሰው ወፎችን ለመያዝ ሲያደባ እንደሚመለከቱ፣ ወጥመድን ይዘረጋሉ ሰዎችንም ያጠምዳሉ።
\v 27 ዋሻ ወፎችን እንደሚሞላ፣ እንዲሁ ቤታቸው ሽንገላን ሞልታለች። እንዲሁም ተልቀዋል፣ ባለ ጠጎችም ሆነዋል።
\v 28 ወፍረዋል፣ በደህንነታቸውም ያብረቀርቃሉ። ክፋታቸውንም ያለ ልክ አብዝተዋል። ለሰዎች፣ ወይም ለወላጅ አልባዎች ነገር አልተምዋገቱላቸውም። ለችግረኞች ፍትሕን ባያደርጉም እንኳን በልጽገዋል።
\v 29 ስለእነዚህ ነገሮች አልቀጣምን? ይላል እግዚአብሔር፤ እንደዚህ ባለ ሕዝብ ላይ ለራሴ አልበቀልምን?
\s5
\v 30 በምድር ላይ የምታስደንቅና የምታስደነግጥ ነገር ሆናለች፤
\v 31 ነቢያት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፣ ካህናትም በገዛ ኃይላቸው ይገዛሉ። ሕዝቤም እንዲህ ያለውን ነገር ይወድዳሉ፣ ነገር ግን በፍጻሜው ምን ይፈጠራል?
\s5
\c 6
\p
\v 1 እናንተ የብንያም ሕዝቦች፣ ከኢየሩሳሌም በመሸሽ ደህንነትን አግኙ። በቴቁሔ መለከትን ንፉ። ታላቅ ጥፋት የሆነ ክፉ ነገር ከሰሜን እየመጣ ነውና በቤትሐካሬም ላይ ምልክትን አንሡ።
\v 2 የተዋበችውና ሰልካካዋን የጽዮንን ልጅ እደመስሳለሁ።
\v 3 እረኞችና መንጐቻቸው ወደ እርስዋ ይሄዳሉ፣ በዙሪያዋም ድንኳኖቻቸውን ይተክሉባታል፣ እያንዳንዱም እረኛ በገዛ እጁ መንጋውን ይጠብቃል።
\s5
\v 4 ነገሥታት "ለአማልክቶቻችሁ እንድትዋጉ ራሳችሁን አስገዙ። ተነሡ፣ በቀጥርም እናጥቃ። ቀኑ እየመሸ መሆኑ፣ የማታውም ጥላ እየረዘመ መሆኑ እጅግ መጥፎ ነው።
\v 5 ነገር ግን በሌሊትም እናጥቃ፣ አምባዎችዋንም እናፍርስ።
\s5
\v 6 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ዛፎችዋን ቍረጡ፥ በኢየሩሳሌምም ላይ የከበባ አፈርን ደልድሉ፤ ይህች በግፍ የተሞላች ከተማ በመሆኗ ለማጥቃት ትክክለኛዋ ከተማ ነች።
\v 7 ጕድጓድ ውኃ ማፍለቊን እንደሚቀጥል፣ እንዲሁ ይህች ከተማ ክፋትን ማፍለቋን ትቀጥላለች። ዐመጽና ሥርዓተቢስነት በእርስዋ ዘንድ ይሰማል። መከራና መቅሠፍትም ሳይቋረጥ በፊቴ አለ።
\v 8 ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ከአንቺ እንዳልለይ፣ አንቺንም ባድማና ወና እንዳላደርግሽ፣ ተግሣጽን ተቀበዪ።"
\s5
\v 9 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ሰው ወይኑን እንደሚለቅም፣ እንዲሁ ከእስራኤል የቀሩትን በእርግጥ ይቃርሟቸዋል፤ በድጋሚ እጅህን ዘርግተህ ወይንን ከግንዱ እንደሚለቅም አድርግ።
\v 10 ይሰሙኝስ ዘንድ ለማን እናገራለሁ፣ ለማንስ አስጠነቅቃለሁ? ተመልከቱ! ጆሮአቸው ያልተገረዘ ነው፤ በትኩረት ለመስማት አይችሉም! ተመልከቱ! የእግዚአብሔር ቃል ሊያቀናቸው መጥቶባቸዋል፣ ነገር ግን አይፈልጉትም።"
\s5
\v 11 ነገር ግን በእግዚአብሔር ቍጣ ተሞልቻለሁ። በውስጤ ይዤ ልታገሠው ደክሜአለሁ። እንዲህ አለኝ፣ "በጎዳና ሕፃናት ላይ፣ እንዲሁም በወጣቶችም ስብስብ ላይ አፍስሰው። እያንዳንዱ ባል ከሚስቱ ጋር እድሜ ጠገቡ ሽማግሌም ከጎበዙ ጋር ይወሰዳልና።
\v 12 ቤቶቻቸው እርሻዎቻቸውም ሚስቶቻቸውም በአንድነት ለሌሎች ይሆናሉ። በምድር የሚገኙ ነዋሪዎችን አጠቃለሁና ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 13 ከታናሻቸው ጀምሮ እስከ ታላቃቸው ድረስ እያንዳንዳቸው በኃቅ ላልሆነ ትርፍ ስስታሞች ናቸው። ከነቢዩም ጀምሮ እስከ ካህኑ ድረስ እያንዳንዳቸው በተንኰል ይመላለሳሉ።
\v 14 የሕዝቤንም ስብራት የሚፈውሱት ግን በጥቂቱ ነው፣ ሰላም ሳይኖር 'ሰላም ሰላም!' ይላሉ።
\v 15 ርኩስን ነገር ስለሠሩ አፍረዋልን? በጭራሽ አልፈሩም፣ ማንኛውንም እፍረት አላወቁም። ስለዚህ በምቀጣቸው ጊዜ ከሚወድቁ ጋር ይወድቃሉ። ይገለበጣሉ፣" ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 16 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "በመንገድ ማቋረጫ ላይ ቁሙና ተመልከቱ፣ የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ። 'መልካሚቱ መንገድ ወዴት ናት?' በሉና በእርስዋ ላይ ሄዳችሁ ለነፍሳችሁ ዕረፍትን አግኙ። ሕዝቡ ግን፣ 'አንሄድባትም' አሉ።
\v 17 እኔም የመለከቱን ድምፅ እንዲያደምጡ ጠባቂ ጉበኞችን ሾምሁላችሁ። እነርሱ ግን፣ 'አናደምጥም' አሉ።
\v 18 አሕዛብ ሆይ፥ አድምጡ! ተመልከቱ፣ በእነርሱ ላይ የሚደርስባቸውን ትመሰክራላችሁ።
\v 19 ምድር ሆይ፣ ስሚ! ተመልከቺ፣ የአሳባቸው ፍሬ የሆነ ጥፋትን በዚህ ህዝብ ላይ ላመጣ ነው። ለቃሌ ወይም ለህጌ ምንም ትኩረት አልሰጡም፣ ነገር ግን ከዚያ ይልቅ አጣጣሉት።"
\s5
\v 20 ከሳባ የሚቀርበው ዕጣን ለእኔ ምን ማለት ነው? ወይስ ከሩቅም አገር የሆነው ጣፋጭ ሽታ ምንድነው? የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን፣ እንዲሁም መስዋዕቶቻችሁን አልቀበለውም።
\v 21 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል 'ተመልከቱ፣ በዚህ ሕዝብ ፊት ዕንቅፋቶችን አደርጋለሁ። አባቶችና ልጆች በአንድነት ይሰናከሉባቸዋል። ነዋሪዎችና ጎረቤቶቻቸው ይጠፋሉ።
\v 22 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል 'ተመልከቱ፣ ሕዝብ ከሰሜን ምድር ይመጣል። ታላቅ ሕዝብም ከምድር ዳርቻ ይነሣል።
\s5
\v 23 ቀስትንና ጦርን ያነሣሉ። ጨካኞች ናቸው፣ ምሕረትንም የላቸውም። ድምፃቸው እንደ ባሕር ጩኸት ነው፣ በጽዮን ሴት ልጅ ላይ እንደሚዋጉ በፈረሶችም ላይ ይጋልባሉ።"
\v 24 ስለ እነርሱ ወሬውን ሰምተናል። እጃችን በጭንቀት ዝላለች። ምጥ ወላድን ሴት እንደሚይዛት ጭንቀት ይዞናል።
\s5
\v 25 የጠላት ሰይፍና ሽብር ስለከበባችሁ ወደ ሜዳ አትውጡ፣ በመንገድም ላይ አትሂዱ።
\v 26 የሕዝቤ ሴት ልጅ ሆይ፣ ማቅ ልበሺና ለብቸኛ ልጅ መቀበሪያ አፈር ውስጥ ተንከባለዪ። አጥፊው በድንገት ይመጣብናልና ለራስሽ መራራ የሆነ የቀብር ለቅሶን አድርጊ።
\s5
\v 27 "ኤርምያስ፣ መንገዳቸውን እንድትመረምርና እንድትፈትን በሕዝቤ መካከል ብረትን እንደሚፈትን አድርጌሃለሁ።
\v 28 እነርሱ ሁሉ ሌሎችን የሚወነጅሉ እጅግ ዐመፀኞች ናቸው። በብልሹነት የሚመላለሱ ናስና ብረት ናቸው።
\v 29 ወናፍ በሚያቃጥላቸው እሳት አናፋ፣ እርሳሱም በእሳቱ ቀለጠ። ክፋት ስላልተወገደ፣ የማጥራቱ ሥራ በመካከላቸው ይቀጥላል።
\v 30 እግዚአብሔር ጥሎአቸዋልና የተጣለ ብር ብለው ይጠሯቸዋል።"
\s5
\c 7
\p
\v 1 ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል ይህ ነው፣
\v 2 በእግዚአብሔር ቤት በራፍ ላይ ቁም! እንዲህ በል፣ 'ይሁዳ ሁሉ ሆይ፣ እግዚአብሔርን ልታመልኩ በእነዚህ በራፎች የምትገቡ ሆይ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።
\s5
\v 3 የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ መንገዳችሁንና ሥራችሁን መልካም አድርጉ፣በዚህም ስፍራ መኖር እንድትቀጥሉ አደርጋችኋለሁ።
\v 4 ራሳችሁን አታላይ በሆኑ ቃሎች ላይ ታምናችሁ፣ "የእግዚአብሔር መቅደስ! የእግዚአብሔር መቅደስ! የእግዚአብሔር መቅደስ!" አትበሉ።
\s5
\v 5 መንገዳችሁንና ሥራችሁን ፈጽማችሁ መልካም ብታደርጉ፤ በሰውና በጎረቤቱ መካከል ቅን ፍርድ ብትፈርዱ፤
\v 6 በምድሪቱ የሚቆየውን እንግዳ፣ ወላጅ አልባውን፣ ወይም መበለቲቱንም ባትበዘብዙ፣ በዚህም ስፍራ ንጹሕ ደምን ባታፈስሱ፣ ለገዛ ጉዳታችሁ እንዲሆንባችሁ ሌሎች አማልክትን ባትከተሉ፤
\v 7 ያን ጊዜ ከጥንቱ ጊዜ ጀምሮ እስከ ለዘላለም ለአባቶቻችሁ በሰጠኋቸው ምድር በዚህ ስፍራ አሳድራችኋለሁ።
\s5
\v 8 እነሆ! በማይረዳችሁ የሐሰት ቃል እየታመናችሁ ናችሁ።
\v 9 ትሰርቃላችሁ፣ ትገድላላችሁ፣ ታመነዝራላችሁ? ደግሞም በሐሰትም ትምላላችሁ፣ ለበኣልም ታጥናላችሁ፣ የማታውቋቸውንም ሌሎች አማልክት ትከተላላችሁ?
\v 10 ከዚያም መጥታችሁ ስሜም በተጠራበት በዚህ ቤት በፊቴ ቆማችሁ፣ እነዚህን ሁሉ ጥፋቶች ማድረግ እንድትችሉ "ድነናል፣" አላችሁ።
\v 11 ይህስ ስሜ የተጠራበት ቤት በዓይናችሁ ፊት የሌቦች ዋሻ ሆኖአልን? ነገር ግን፣ እነሆ፣ እኔ አይቻለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 12 'ስለዚህ በቀድሞ ዘመን ስሜን ከመጀመሪያ ወዳሳደርሁበት በሴሎ ወደ ነበረው ስፍራዬ ሂዱ፣ ከሕዝቤም ከእስራኤል ክፋት የተነሣ ያደረግሁበትን እዩ።
\v 13 ስለዚህ አሁንም፣ ይህን ሥራችሁን ሁሉ ስላደረጋችሁ፣ በተደጋጋሚ ጊዜ ተናገርኳችሁ፣ እናንተ ግን አልሰማችሁም። በጠራኋችሁም ጊዜ፣ አልመለሳችሁም።
\v 14 ስለዚህ፣ በሴሎ እንዳደረግሁ፣ እንዲሁ ስሜ በተጠራበት በምትታመኑበት ቤት፣ ለእናንተና ለአባቶቻችሁም በሰጠኋችሁ ስፍራ ላይ እንዲሁ አደርጋለሁ።
\v 15 የኤፍሬምንም ዘር የሆኑትን ወንድሞቻችሁን ሁሉ እንደ ጣልሁ፣ እንዲሁ ከፊቴ እጥላችኋለሁ።
\s5
\v 16 ደግሞም አንተ፣ ኤርምያስ አልሰማህምና ለዚህ ሕዝብ አትጸልይ፣ ስለ እነርሱም ልመናና ጸሎት አታድርግ፣ አትማልድላቸው።
\v 17 እነርሱ በይሁዳ ከተሞች ውስጥና በኢየሩሳሌም ጎዳናዎች ላይ የሚያደርጉትን አታይምን?
\v 18 ያስቈጡኝ ዘንድ፣ ለሰማይ ንግሥት እንጐቻ እንዲያደርጉ ለሌሎችም አማልክት የመጠጥ ቍርባን እንዲያፈስሱ፣ ልጆች እንጨት ይሰበስባሉ፣ አባቶችም እሳት ያነድዳሉ፣ ሴቶችም ዱቄት ያቦካሉ።
\s5
\v 19 በእውነት እኔን ያስቈጣሉን? ይላል እግዚአብሔር፤ ለእነርሱስ እፍረት እንዲሆንባቸው የሚያስቆጡት ራሳቸውን አይደለምን?
\v 20 እንግዲያው ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ተመልከቱ፣ ቍጣዬና መዓቴ በዚህ ስፍራ ላይ ይፈስሳል፣ በሰውና በአውሬው ላይ፣ በዱር ዛፎችና በምድር ፍሬ ላይ ይፈስሳል። ይነድዳል፣ መቼም አይጠፋም።'
\s5
\v 21 የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ለመሥዋዕታችሁ የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን ጨምሩ፣ ከዚያም ላይ ሥጋውን ጨምሩ።
\v 22 አባቶቻችሁን ከግብጽ ምድር ባወጣኋቸው ቀን፣ የትኛውንም ነገር ከእነርሱ አልጠየቅሁም። ስለሚቃጠል መሥዋዕትና ስለ ሌላ መሥዋዕት አላዘዝኋቸውምም።
\v 23 ይህንን ትእዛዝ ብቻ ሰጠኋቸው፣ "ቃሌን ስሙ፣ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ እናንተም ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ። መልካምም ይሆንላችሁ ዘንድ ባዘዝኋችሁ መንገድ ሁሉ ሂዱ።"
\s5
\v 24 ነገር ግን በክፉ ልባቸው አሳብና እልከኝነት ሄዱ ወደ ፊትም ሳይሆን ወደ ፊታቸው ሳይሆን ወደ ኋላቸው ሄዱ እንጂ አልሰሙም ጆሮአቸውንም አላዘነበሉም።
\v 25 አባቶቻችሁ ከግብጽ ምድር ከወጡበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ፣ አገልጋዮቼን፣ ነቢያትን ሁሉ ልኬባችሁ ነበር። እነርሱን ተግቼ ላክሁባችሁ።
\v 26 ነገር ግን አልሰሙኝም። ምንም ትኩረት አልሰጡም። ይልቊን፣ አባቶቻቸውም ካደረጉት ይልቅ የባሰ አደረጉ።
\s5
\v 27 እነዚህን ቃሎች ሁሉ ንገራቸው፣ ነገር ግን አይሰሙህም። እነዚህን ነገሮች አውጅላቸው፣ ነገር ግን አይመልሱልህም።
\v 28 የአምላኩን የእግዚአብሔርን ቃል ያልሰማ፣ ተግሣጽንም ያልተቀበለ ሕዝብ ይህ ነው። እውነት ጠፍቶአል ከአፋቸውም ተቈርጦአል በላቸው።
\s5
\v 29 ፀጕርሽን ቍረጪ፣ ተላጪው፣ ጣዪውም። በወናዎች ኮረብቶችም ላይ ሙሾን አውጪ። እግዚአብሔር በቍጣው ይህንን ትውልድ ጥሎአልና፣ ትቶታልምና ።
\v 30 የይሁዳ ልጆች በፊቴ ክፉን ነገር ሠርተዋል፣ ይላል እግዚአብሔር፤ ያረክሱትም ዘንድ ስሜ በተጠራበት ቤት ርኵሰታቸውን አኑረዋል።
\s5
\v 31 ከዚያም ቶፌት ውስጥ በቤን ሄኖም ሸለቆ መስገጃዎችን ገነቡ። እኔም ያላዘዝሁትንና ፈጽሞ በልቤ ያላሰብሁትን ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በእሳት ያቃጥሉ ዘንድ ይህንን አድርገዋል።
\v 32 ስለዚህ፣ ተመልከቱ፣ ቶፌት ወይም የቤን ሄኖም ሸለቆ ተብሎ ዳግመኛ አይጠራም። የእርድ ሸለቆ ይባላል፤ የሚተርፍ ስፍራ እስኪታጣ ድረስ በቶፌት በድኖችን ይቀብራሉ ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 33 የዚህም ሕዝብ ሬሳ ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል ይሆናል፣ የሚያስፈራራቸውም አይኖርም።
\v 34 ምድሪቱም ወና ትሆናለችና ከይሁዳ ከተሞችና ከኢየሩሳሌም ጎዳናዎች ላይ የእልልታን ድምፅና የደስታን ድምፅ፣ የወንድ ሙሽራን ድምፅና የሴት ሙሽራን ድምፅ አጠፋለሁ።
\s5
\c 8
\p
\v 1 በዚያን ዘመን፥ የይሁዳን ነገሥታት አጥንትና የመኳንንቶቹን አጥንት፥ የካህናቱን አጥንትና የነቢያቱን አጥንት፥ የኢየሩሳሌምንም ሰዎች አጥንት ከመቃብራቸው ያወጣሉ ይላል እግዚአብሔር።
\v 2 በተከተሉአቸው፣ ባገለገሏቸውና በፈለጉአቸው፣ ባመለኳቸውም በፀሐይና በጨረቃ በሰማይም ሠራዊት ሁሉ ፊት ይዘረጉአቸዋል። አጥንቶቻቸው አይሰባሰቡም ወይም በድጋሚ አይቀበሩም። በምድር ፊት ላይ እንደ ጕድፍ ይሆናሉ።
\v 3 እኔም ባሳደድኋቸው ስፍራ ሁሉ የቀሩት፣ ከዚህ ክፉ ሕዝብ የተረፉት ቅሬታዎች ሁሉ፣ ከሕይወት ይልቅ ሞትን ይመርጣሉ ይላል የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር።
\s5
\v 4 እንዲህም ትላቸዋለህ፣ 'እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የትኛውም የወደቀ ሰው አይነሣምን? የጠፋስ ለመመለስ አይሞክርምን?
\v 5 ይህ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ዘላቂ በሆነ አለመታመን ስለ ምን ወደ ኋላው ይመለሳል? ተንኰልን ይዞአል ንስሃ ለመግባትም እንቢ ብሎአል።
\s5
\v 6 አደመጥሁ ሰማሁም፣ ትክክለኛ ነገር አልተናገሩም፤ ማንም ስለ ክፋቱ ንስሃ አልገባም፣ ማንም "ምን አድርጌአለሁ?" አላለም። ወደ ጦርነት እንደሚሮጥ ፈረስ ሁላቸውም በየመንገዳቸው ሄዱ።
\v 7 ሽመላ በሰማይ ትክክለኛ ጊዜዋን አውቃለች፤ ዋኖስና ጨረባ ዋልያም ያውቃሉ። እነርሱ ወደ ሚሰደዱበት የሚሄዱት በትክክለኛ ጊዜ ነው፣ ሕዝቤ ግን የእግዚአብሔርን ፍርድ አላወቁም።
\s5
\v 8 እናንተስ፣ "ጥበበኞች ነን! የእግዚአብሔርም ሕግ ከእኛ ጋር ነው" እንዴት ትላላችሁ? በእርግጥ ተመልከቱ! የአታላይ ጸሐፊ ብዕር ማታለልን አድርጎአል።
\v 9 ጥበበኞች ያፍራሉ። ደንግጠውማል ተጠምደዋል። ተመልከቱ! የእግዚአብሔርን ቃል ጥለዋል፣ ስለዚህ ጥበባቸው ምን ጥቅም አለው?
\v 10 ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ስስታሞች ናቸውና፣ ከነቢዩም ጀምሮ እስከ ካህኑ ድረስ ሁሉ ያታልላሉና፣ ስለዚህ ሚስቶቻቸውን ለሌሎች፥ እርሻቸውንም ለሚወርሱባቸው እሰጣለሁ።
\s5
\v 11 ቀላል ነገር እንደሆነ በማድረግ የሕዝቤን ሴት ልጅ ስብራት በጥቂቱ ይፈውሳሉ። ሰላም ሳይሆን፣ "ሰላም፣ ሰላም" ይላሉ።
\v 12 አስጸያፊ ነገርን ስለ ሠሩ አፍረዋልን? ምንም አላፈሩም። ትሕትናም አልነበራቸውም። ስለዚህ በሚቀጡ ጊዜ ቀድሞውኑ ከወደቊት ጋር ይወድቃሉ ይላል እግዚአብሔር።
\v 13 ፈጽሜ አጠፋችኋለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ በወይን ላይ ፍሬ፣ በበለስ ዛፍ ላይ በለስ አይሆንም። ቅጠልም ይረግፋልና የሰጠኋቸውም ያልፋልና።
\s5
\v 14 ለምን ዝም ብለን እንቀመጣለን? በአንድነት ኑ፤ ወደ ተመሸጉ ከተሞች እንሂድ፣ በዚያም በሞት ዝምተኞች እንሆናለን። እግዚአብሔር ዝም ያሰኘናልና። ስለ በደልነው መርዝ አጠጥቶናል።
\v 15 ሰላምን በተስፋ ተጠባበቅን፣ ነገር ግን መልካም ነገር አልተገኘም። የፈውስ ጊዜን በተስፋ ተጠባበቅን፣ ነገር ግን ሽብር እንደሆነ ተመልከቱ።
\s5
\v 16 የፈረሰኞች ድምጽ ከዳን ተሰማ። ከአርበኞች ፈረሶች ማሽካካት የተነሣ ምድር ሁሉ ተንቀጠቀጠች። ምድሪቱንና በእርስዋም ያለውን ሁሉ፥ ከተማይቱንና የሚኖሩባትንም ሊበሉ ይመጣሉና።
\v 17 ተመልከቱ፣ አስማት የማይከለክላቸውን እባቦችንና እፉኝቶችን እሰድድባችኋለሁ። እነርሱም ይነድፉአችኋል" ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 18 ኅዘኔ ፍጻሜ የለውም፣ ልቤም ታምሞአል።
\v 19 ተመልከቱ! እግዚአብሔር በጽዮን የለምን? ወይስ ንጉሥዋ በእርስዋ ዘንድ የለምን? የሚል የሕዝቤ ሴት ልጅ ጩኸት ድምፅ ከሩቅ ምድር ተሰማ። በተቀረጹ ምስሎቻቸውና በባዕድ ከንቱ ጣዖታት ያስቈጡኝ ስለ ምንድር ነው?
\s5
\v 20 መከሩ አልፎአል፣ በጋው አብቅቷል። እኛ ግን አልዳንነም።
\v 21 በሕዝቤ ሴት ልጅ ስብራት እኔ ተሰብሬአለሁ። በደረሰባት ነገር በጭንቀት አለቅሳለሁ፤ ጠቁሬማለሁ።
\v 22 በገለዓድ መድኃኒት የለምን? ወይስ በዚያ ፈዋሽ የለምን? የሕዝቤ ሴት ልጅ ፈውስ ስለ ምን አልሆነም?
\s5
\c 9
\p
\v 1 ተወግተው ስለ ሞቱ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ሰዎች ሌሊትና ቀን አለቅስ ዘንድ ራሴ ውኃ፣ ዓይኔም የእንባ ምንጭ በሆነልኝ!
\v 2 ሁሉም አመንዝሮች፣ የከዳተኞች ጉባኤ በመሆናቸው ሕዝቤን እተዋቸው ዘንድ ከእነርሱም እለይ ዘንድ በምድረ በዳ የመንገደኞች ማደሪያን ማን በሰጠኝ!
\v 3 "አታላይ ቀስታቸው በሆነው በምላሳቸው ሐሰት ተናገሩ፣ ነገር ግን በምድር ላይ በታማኝነት ግሩም አይደሉም። ከክፋት ወደ ክፋት ይሄዳሉ። እኔንም አላወቁምና፣" ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 4 እያንዳንዱ ወንድም ሁሉ ያታልላልና፣ እያንዳንዱ ጎረቤትም ሁሉ ሐሜተኛ ስለሆነ እናንተ ሁሉ ከጎረቤቶቻችሁ ተጠንቀቁ፣ በወንድሞቻችሁም አትታመኑ።
\v 5 እያንዳንዱ ሰውም ሁሉ ጎረቤቱን ያታልላል በእውነትም አይናገርም። ምላሶቻቸው የማታለል ነገሮችን ያስተምራል። በደልንም በማድረግ ይደክማሉ።
\v 6 በማታለል መካከል ትኖራላችሁ፣ ከሽንገላም የተነሣ እኔን ያውቁኝ ዘንድ እንቢ ብለዋል፣ ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 7 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ተመልከቱ፣ እፈትናቸዋለሁ። እመረምራቸዋለሁ። ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ክፋት ከዚህ ሌላ የማደርገው ምንድር ነው?
\v 8 ምላሳቸው የተሳለ ፍላጻ ነው፤ ያልታመኑ ነገሮችን ይናገራሉ። ከጎረቤቶቻቸው ጋር በአንደበታቸው በሰላም ይናገራሉ፣ በልባቸው ግን ያደቡበታል።
\v 9 በውኑ ስለዚህ ነገር አልቀጣቸውምን? ይላል እግዚአብሔር፤ እንደዚህስ ባለ ሕዝብ ላይ አልበቀልምን?
\s5
\v 10 ለተራሮች የልቅሶና የዋይታን ዝማሬ እዘምራለሁ፣ ለምድረ በዳ ማሰማርያዎችም የቀብር ዋይታን እዘምራለሁ። ማንም ሰው እንዳያልፍባቸው በእሳት ተቃጥለዋልና። ሰዎችም የየትኛውንም ከብት ድምፅ አይሰሙም። የሰማይ ወፎች ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ ሁሉ ሸሽተው ሄደዋል።
\v 11 ኢየሩሳሌምን የፍርስራሽ ክምር፣ የቀበሮም ማደሪያ አደርጋታለሁ። የይሁዳንም ከተሞች ሰው የማይኖርባት ወና አደርጋቸዋለሁ።
\v 12 ይህን የሚያስተውል ጠቢብ ሰው ማን ነው? ለሌሎች እንዲነግር የእግዚአብሔር አፍ ምን ተናገረው? ምድሪቱስ ስለምን ጠፋች? ማንም እንደማያልፍባት እንደ ምድረ በዳስ ስለ ምን ተደመሰሰች?
\s5
\v 13 እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፣ "በፊታቸው የሰጠኋቸውን ሕጌን ስለተዉ፣ ድምጼንም አልሰሙምና ወይም አልተጓዙበትምና።
\v 14 አባቶቻቸው እንዳስተማሯቸው በልባቸውን ምኞት ተመላልሰዋልና፣ በኣሊምን ተከትለዋልና።
\s5
\v 15 ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል 'ተመልከቱ፣ ይህን ሕዝብ እሬትን አበላዋለሁ የተመረዘንም ውኃ አጠጣዋለሁ።
\v 16 እነርሱና አባቶቻቸውም ባላወቁአቸው አሕዛብ መካከል እበትናቸዋለሁ፣ እስካጠፋቸውም ድረስ በበስተኋላቸው ሰይፍን እሰድድባቸዋለሁ።"
\s5
\v 17 የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ይህንን አስቡ፦ የቀብር አስለቃሾችን ጥሩ፤ ይምጡ። ወደ ብልሃተኛ አልቃሾች ላኩ።
\v 18 ይፍጠኑና ዓይኖቻችንም እንባ እንዲያፈስሱ የዓይናችንም ሽፋሽፍቶች ውኃን እንዲያፈልቁ የለቅሶ ዝማሬን ይዘምሩልን።
\s5
\v 19 'እንዴት ተበዘበዝን። ቤቶቻችን ስለፈረሱ ምድሪቱንም ትተናልና እንዴት አፈርን!' የሚል የልቅሶ ድምፅ በጽዮን ተሰምቶአል።
\v 20 ስለዚህ እናንተ ሴቶች ሆይ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፣ ከአፉ ለሚወጣው ቃል ትኩረት ስጡ። ከዚያም ለሴቶች ልጆቻችሁም የልቅሶውን ዝማሬ አስተምሩ፣ ለእያንዳንዷም የጎረቤታችሁ ሴት የቀብሩን ሙሾ አስተምሩ።
\s5
\v 21 ሞት ወደ መስኮታችን መጥቷልና፤ ወደ ቤተ መንግሥቶቻችን ሄዷል። ሕፃናቱን ከውጪ፣ ወጣቶቹንም ከከተማይቱ አደባባይ ያጠፋል።
\v 22 'የሰውም ሬሳ በሜዳ ላይ እንደ ጕድፍ፣ ከአጫጆች በኋላ እንደሚቀር ቃርሚያ ይወድቃል፣ ማንምም አይሰበስበውም።
\s5
\v 23 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ጠቢብ በጥበቡ እንዲመካ አትፍቀዱ፣ ወይም ጦረኛ በኃይሉ አይመካ። ባለ ጠጋም በብልጥግናው እንዲመካ አትፍቀዱ።
\v 24 ሰው በየትኛውም ነገር የሚመካ ከሆነ፣ በዚህ ይሁን፣ ማስተዋል ያለውና የሚያውቀኝ በመሆኑ። የኪዳን ታማኝነት፣ ፍትሕንና ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር ነኝና። ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸውና፣ ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 25 ተመልከቱ፣ በሰውነታቸው ብቻ የተገረዙትን እቀጣለሁ።
\v 26 ግብጽንና ይሁዳን፣ የአሞን ሕዝቦች የሆኑትን ኤዶምያስና ሞዓብንም፣ እንዲሁም በምድረ በዳም የተቀመጡትን ፀጉራቸውን የተላጩትን ሁሉ፣ ባለመገረዛቸው ምክንያት የምቀጣበት ዘመን እነሆ ይመጣል። እነዚህ ሁሉ ሕዝቦች ያልተገረዙ ናቸውና፣ ደግሞም የእስራኤል ልብ አልተገረዘምና" ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\c 10
\p
\v 1 እናንተ የእስራኤል ቤት ሆይ፣ እግዚአብሔር ለእናንተ የተናገረውን ቃል ስሙ።
\v 2 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'የአሕዛብን መንገድ አትማሩ፣ ከሰማይ በሚሆኑት ምልክቶችም አትፍሩ፣ አሕዛብ እነዚህን ይፈራሉና።
\s5
\v 3 የአሕዛብ ልማድ ከንቱ ነውና። አንድ ሰው ዛፍን ከጫካ ይቈርጣል፤ የሠራተኛም እጅ በመጥረቢያ ይህንን ይሠራል።
\v 4 ከዚያም በብርና በወርቅ ያስጌጡታል። እንዳይወድቅም በመዶሻና በሚስማር ይቸነክሩታል።
\v 5 እነዚህ ጣዖታት ምንም ማለት ስለማይችሉ፣ በዱባ ማሳ ላይ እንደ ተቀረጸ ዓምድ ናቸው። ጨርሶ መራመድ ስለማይችሉ ሊይሸከሟቸው ይገባል። ክፉ መሥራት አይቻላቸውምና፣ ደግምም የትኛውንም መልካም ነገር ይሠሩ ዘንድ አይችሉምና አትፍሩአቸው።
\s5
\v 6 እግዚአብሔር ሆይ እንደ አንተ ያለ የለም። አንተ ታላቅ ነህ፣ ስምህም በኃይል ታላቅ ነው።
\v 7 የአሕዛብ ንጉሥ ሆይ፣ የማይፈራህ ማነው? በአሕዛብ ጥበበኞች ሁሉ መካከል ወይም በታማኝ መንግሥታቸውም ሁሉ መካከል እንደ አንተ ያለ ስለሌለ፣ አንተ ይህ ይገባሃል።
\s5
\v 8 እነርሱ ሁሉም ተመሳሳይ ናቸው፣ ደንዝዘዋል፣ ደንቍረውማል፤ እንጨት ብቻ እንጂ ምንም ላልሆኑ ጣዖቶቻቸው ደቀመዛሙርት ናቸው።
\v 9 ከጠርሴስ አንጥረኛ የቀጠቀጠውን ብር፣ ከአፌዝም ወርቅ ያመጣሉ። ልብሳቸውም ሰማያዊና ቀይ ግምጃ ነው። ብልሃተኞች ሰዎቻቸው እነዚህን ሁሉ ነገሮች ይሠራሉ።
\v 10 እግዚአብሔር ግን እውነተኛ አምላክ ነው። እርሱም ሕያው አምላክና የዘላለም ንጉሥ ነው። ከቍጣው የተነሣ ምድር ትንቀጠቀጣለች፣ አሕዛብም ቊጣውን መቋቋም አይችሉም።
\s5
\v 11 እናንተም "ሰማይንና ምድርን ያልፈጠሩ አማልክት ከምድር ላይ ከሰማይም በታች ይጠፋሉ" ትሏቸዋላችሁ።
\v 12 ምድርን በኃይሉ የፈጠረው፣ ደረቊን ምድር በጥበቡ የመሠረተው ሰማያትንም በማስተዋሉ የዘረጋ እርሱ ነው።
\v 13 ድምፁ በሰማይ የውኾችን ድምፅ ይፈጥራል፣ ከምድርም ጠርዝ ደመናትን ከፍ ያደርጋል። ለዝናቡም መብረቅን ያደርጋል፣ ነፋስንም ከግምጃ ቤቱ ያወጣል።
\s5
\v 14 እያንዳንዱ ሰው እውቀት አጥቶ አላዋቂ ሆኗል። እያንዳንዱ አንጥረኛ ቀልጦ የተሠራ ምስሉ ውሸት ነውና፣ ሕይወትም የለባቸውምና በቀረጸው ጣዖት አፍሮአል።
\v 15 እነርሱ ጥቅም የለሽ፣ የቀልደኞች ሥራ ናቸው፤ በሚቀጡበት ጊዜ ይጠፋሉ።
\v 16 የያዕቆብ እድል ፈንታ እንደ እነዚህ አይደለም፣ እርሱ የሁሉ ፈጣሪ ነውና። እስራኤልም የርስቱ ነገድ ነውና፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ስሙ ነው።
\s5
\v 17 በከበባ ውስጥ የምትኖሩ እናንተ ሕዝቦች፣ ዕቃችሁን ሰብስቡና ምድሪቱን ትታችሁ ውጡ።
\v 18 እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፣ "ተመልከቱ፣ በዚህ ጊዜ በምድሪቱ የሚኖሩትን ልወረውራቸው ነው። አስጨንቃቸዋለሁ፣ እንደዚያም ሆኖ ያገኙታል።
\s5
\v 19 ስለ ተሰበረው አጥንቴ ወዮልኝ! ቍስሌም መርቅዟል። ስለዚህ እኔ፣ "በእውነት ይህ የመከራ ጩኸቴ ነው ልሸከመውም ይገባኛል" አልሁ።
\v 20 ድንኳኔ ተበዘበዘ፣ አውታሬም ሁሉ ለሁለት ተቈረጠ። ልጆቼም ከእኔ ወሰዷቸው፣ ስለዚህ ከእንግዲህ የሉም። ድንኳኔንም ከእንግዲህ ወዲህ የሚዘረጋ መጋረጃዎችንም የሚያነሣ የለም።
\s5
\v 21 እረኞች ደንቆሮዎች ሆነዋል። እግዚአብሔርን አልፈለጉትምና። ስኬት አልሆነላቸውም፤ መንጎቻቸውም ሁሉ ተበትነዋል።
\v 22 የወሬን ድምፅ ስሙ፣ "ተመልከቱ! እየመጣ ነው! የይሁዳን ከተሞች ባድማና የቀበሮ ማደሪያ ያደርጋቸው ዘንድ ከሰሜን ጽኑ የምድር ነውጥ መጥቶአል።"
\s5
\v 23 እግዚአብሔር ሆይ፣ የሰው መንገድ ከራሱ እንዳይመጣ አውቃለሁ። የሚራመድ የትኛውም ሰው የገዛ አካሄዱን አያቀናም።
\v 24 እግዚአብሔር ሆይ እንዳታጠፋኝ በቊጣህ ሳይሆን በፍትህ ቅጣኝ።
\v 25 በማያውቁህ አሕዛብ፣ ስምህንም በማይጠሩ ወገኖች ላይ መዓትህን አፍስስ። ያዕቆብን በልተውታልና፣ ፈጽመው ሊያጠፉት ውጠውታልና ማደሪያውንም አፍርሰዋልና።
\s5
\c 11
\p
\v 1 ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው፣ እንዲህም አለ።
\v 2 የዚህን ቃል ኪዳን ቃል ስማ፣ ለእያንዳንዳቸው የይሁዳ ሰዎች፣ በኢየሩሳሌምም ለሚኖሩትም ተናገር፥
\s5
\v 3 እንደዚህም በላቸው 'የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የዚህን ቃል ኪዳን ቃል የማይሰማ ሰው ርጉም ይሁን።
\v 4 ከግብጽ አገር ከሚቀልጠው የብረት ምድጃ ባወጣኋቸው ቀን ለአባቶቻችሁ ያዘዝሁበት ኪዳን ይህ ነው። "ድምፄን ስሙ፣ ያዘዝኋችሁንም ነገሮች ሁሉ አድርጉ፣ እናንተ ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ፣ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁና።"
\v 5 ይህም ዛሬ የምትኖሩባትን ወተትና ማር የምታፈስሰውን ምድር እሰጣቸው ዘንድ ለአባቶቻችሁ የማልሁትን መሐላ አጸና ዘንድ ነው።" ከዚያ እኔ ኤርምያስ "አዎን፣ እግዚአብሔር ሆይ!' ብዬ መለስሁለት።
\s5
\v 6 እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፣ "ይህችን ቃል ሁሉ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም ጎዳናዎች ተናገር። እንዲህ በል፣ 'የዚህን ቃል ኪዳን ቃል ስሙ ፈጽሙትም።
\v 7 አባቶቻችሁን ከግብጽ ምድር ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ፥ "ቃሌን ስሙ" በማለት በጽናት አስጠንቅቄአቸው ነበር።
\v 8 እነርሱ ግን አልሰሙም ወይም ትኩረት አልሰጡም። እያንዳንዱ ሰው በክፉ ልባቸው እልከኝነት ሄዱ። ስለዚህ እንዲመጡባቸው ያዘዝኋቸውን እርግማን ሁሉ አመጣሁ። ሕዝበ ግን እንደዚያም ሆኖ አልታዘዙም።"
\s5
\v 9 ቀጥሎ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፣ "በይሁዳ ሰዎችና በኢየሩሳሌም በሚኖሩ ዘንድ አድማ ተገኝቶአል።
\v 10 ቃሌንም ይሰሙ ዘንድ እንቢ ወዳሉ፣ ይልቊንም ያመልኩአቸው ዘንድ እንግዶችን አማልክት ወደተከተሉ ወደ አባቶቻቸው ኃጢአት ተመለሱ። የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት ከአባቶቻቸው ጋር ያደረግሁትን ቃል ኪዳን አፈረሱ።
\s5
\v 11 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ተመልከቱ፣ ሊያመልጡት የማይችሉትን ጥፋት አመጣባቸዋለሁ። ከዚያም ወደ እኔ ይጮኻሉ፣ እኔ ግን አልሰማቸውም።
\v 12 የይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም የሚኖሩት ሄደው ወደሚሰዉላቸው አማልክት ይጮኻሉ፤ ነገር ግን በጥፋታቸው ጊዜ ከቶ አያድኑአቸውም።
\v 13 ይሁዳ፣ አማልክትህ እንደ ከተሞችህ ቍጥር እንዲሁ ጨምረዋል። በኢየሩሳሌምም መንገዶች ቍጥር ልክ አሳፋሪ መሠዊያ፣ ለበዓለም የማጠኛ መሠዊያ አድርጋችኋል።
\s5
\v 14 ስለዚህ አንተ ራስህ፣ ኤርምያስ፣ ለዚህ ሕዝብ ልትጸልይ አይገባም። ስለእነርሱ አታልቅስ ወይም አትጸልይ። በጥፋታቸው ጊዜ ወደ እኔ ሲጮኹ አልሰማቸውምና።
\v 15 እጅግ ብዙ ክፉ ፍላጎት የነበረው ተወዳጁ ሕዝቤ በቤቴ ውስጥ ያለው ለምንድነው? ለመስዋዕታችሁ የተጠበቀው ሥጋ ክፋትን አድርጋችኋልና ሊረዳችሁ አይችልም፣ ከዚያም በዚያ ደስተኛ አትሆኑም።
\v 16 በጥንቱ ጊዜ እግዚአብሔር በተወዳጅ ፍሬ የተዋበች የለመለመች የወይራ ዛፍ ብሎ ጠራሽ። ሆኖም ግን እንደ ዐውሎ ነፋስ ጩኸት እሳትን አነደደባት፣ ቅርንጫፎችዋም ተሰብረዋል።
\s5
\v 17 ለበኣልም በማጠናቸው ያስቈጡኝ ዘንድ ለራሳቸው ስለ ሠሩአት ስለ እስራኤልና ስለ ይሁዳ ቤት ክፋት የተከለሽ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ክፉን ነገር ተናግሮብሻል።
\s5
\v 18 እግዚአብሔርም እነዚህን ነገሮች አውቃቸው ዘንድ አስታወቀኝ፤ አንተ እግዚአብሔር ሥራቸውን እንዳይ አደረግኸኝ።
\v 19 እኔም ለመታረድ እንደሚነዳ እንደ የዋህ የበግ ጠቦት ሆንሁ። እነርሱም፣ "ዛፉን ከፍሬው ጋር እንቍረጥ! ስሙም ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይታሰብ ከሕያዋን ምድር እናጥፋው" ብለው ምክርን እንዳሰቡብኝ አላወቅሁም ነበር።
\v 20 ይሁን እንጂ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር አእምሮንና ልብን ይመረምራል፣ በቅንም ይፈርዳል። ጉዳዬን አቅርቤልሃለሁና በእነርሱ ላይ በቀልህን እመሰክራለሁ።
\s5
\v 21 ስለዚህም 'በእጃችን እንዳትሞት በእግዚአብሔር ስም ትንቢት አትናገር' ብለው ነፍስህን ስለሚሹ ስለ ዓናቶት ሰዎች እግዚአብሔር እንዲህ ይላል።
\v 22 ስለዚህ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ይህንን ይላል፣ 'ተመልከት፣ እቀጣቸዋለሁ። ኃያላን ወጣቶቻቸው በሰይፍ ይሞታሉ። ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውም በረሃብ ይሞታሉ።
\v 23 በምቀጣቸውም ዓመት በዓናቶት ሰዎች ላይ ክፉ ነገር አመጣባቸዋለሁና ማንም ከእነርሱ የሚቀር የለም።
\s5
\c 12
\p
\v 1 እግዚአብሔር ሆይ፣ ከአንተ ጋር በተሟገትሁ ጊዜ አንተ ጻድቅ ነህ። የማጉረመርምበትን ምክንያት በእርግጥ ልነግርህ ይገባኛል። የኃጢአተኞች መንገድ ስለምን ይሳካል? እምነት-የለሽ የሆኑት ሁሉ ተሳክቶላቸዋል።
\v 2 አንተ ተክለሃቸዋል፣ እነርሱም ሥር ሰድደዋል። ፍሬ ማፍራታቸውን ቀጥለዋል። በአፋቸው አንተ ቅርብ ነህ፣ ከልባቸው ግን ሩቅ ነህ።
\s5
\v 3 ይሁን እንጂ አንተ እግዚአብሔር ታውቀኛለህ። አይተኸኛል፣ ልቤንም ፈትነሃል። እንደ ሚታረዱ በጎች ለያቸው። ለመታረድም ቀን ነጥላቸው።
\v 4 ምድሪቱ የምታለቅሰው፣ የአገሩ ሣርስ ሁሉ ከነዋሪዎቹ ክፋት የተነሣ የሚደርቀው እስከ መቼ ነው? አራዊት እና ወፎች ተወስደዋል። በእርግጥም ሕዝቡ "በእኛ ላይ የሚሆነውን እግዚአብሔር አያውቅም፤" ብለዋል።
\s5
\v 5 "አንተ ኤርምያስ ከእግረኛ ወታደሮች ጋር በሮጥህ ጊዜ እነርሱ ቢያደክሙህ፣ ከፈረሶች ጋር መወዳደር እንዴት ትችላለህ? በአስተማማኝ የገጠር ምድር ውስጥ ብትሰናከል፣ በዮርዳኖስ ጥሻዎች ውስጥ እንዴት ትሆናለህ?
\v 6 ወንድሞችህና የአባትህ ቤት እነርሱ ጭምር አሳልፈው ሰጥተውሃልና፣ ጮኸው ክደውሃልና። መልካም ነገሮችንም ቢናገሩህ አትታመናቸው።
\s5
\v 7 ቤቴን ትቼአለሁ፣ ርስቴንም ጥያለሁ። ተወዳጁን የገዛ ሕዝቤን በጠላቶቹ እጅ አሳልፌ ሰጥቻለሁ።
\v 8 ርስቴ በጥሻ እንዳለ አንበሳ ሆናብኛለች፤ ድምፅዋን አንሥታብኛለችና ስለዚህ ጠልቻታለሁ።
\v 9 ርስቴ እንደ ጅብ ሆነችብኝ፣ ዝንጕርጕር አሞሮችም ለማጥመድ በላይዋ ይዞራሉ። ሂዱ፣ የምድር አራዊትን ሁሉ ከሜዳ ሰብስቡና ይበሉም ዘንድ አምጡአቸው።
\s5
\v 10 ብዙ እረኞች የወይኑን ቦታዬን ደምስሰዋል። እድል ፈንታዬ የሆነውን ምድር ሁሉ ረግጠዋል፤ የምደሰትበትን እድል ፈንታ ወና ምድረ በዳ አድርገውታል።
\v 11 ባድማ አድርገውታል። ፈርሳለችና አለቅስላታለሁ። ምድር ሁሉ ባድማ ሆናለች በልቡም የሚያስባት የለም።
\s5
\v 12 በወና ኮረብቶች ሁሉ ላይ አጥፊዎች መጥተዋል፣ የእግዚአብሔር ሰይፍ ከአንደኛው የምድር ዳር ጀምሮ እስከ ሌላኛው የምድር ዳር ድረስ ይበላልና። በሕይወት ላለ ሥጋ ለባሽ ሁሉ ደህንነት የለም።
\v 13 ስንዴን የዘሩ ቢሆንም እሾህን አጨዱ። በሥራቸው ደከሙ፣ ምንም አላገኙም። ስለዚህ ከእግዚአብሔር ቍጣ የተነሣ ባገኛችሁት ፍሬ ታፍራላችሁ።
\s5
\v 14 ሕዝቤ እስራኤል እንዲወርስ ያደረግሁትን ርስት ለሚነኩት ክፉዎች ጐረቤቶች ሁሉ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ተመልከቱ፣ ከገዛ ምድራቸው የምነቅላቸው እኔ ነኝ፣ የይሁዳንም ቤት ከመካከላቸው እነቅለዋለሁ።
\v 15 ከነቀልኋቸውም በኋላ መልሼ እራራላቸዋለሁ፣ እያንዳንዱንም ወደ ርስቱ እያንዳንዱንም ወደ ምድሩ እመልሳለሁ።
\s5
\v 16 በበኣል ይምሉ ዘንድ ሕዝቤን እንዳስተማሩት ሁሉ እነዚያው ሕዝቦች 'ሕያው እግዚአብሔርን!' ብለው ይምሉ ዘንድ የሕዝቤን መንገድ በጥንቃቄ ቢማሩ፣ በዚያን ጊዜ በሕዝቤ መካከል ይመሠረታሉ።
\v 17 ነገር ግን ማናቸውም ባይሰሙኝ ያንን ሕዝብ ፈጽሜ እነቅለዋለሁ። በእርግጥም ይነቀላል፣ ይጠፋማል" ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\c 13
\p
\v 1 እግዚአብሔር እንዲህ ይለኛል፣ "ሂድ፣ ከተልባ እግር የተሠራ የውስጥ ሱሪ ግዛና ወገብህን ታጠቅ፤ ነገር ግን አስቀድመህ በውኃ ውስጥ አትንከረው።
\v 2 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዳለው የውስጥ ሱሪን ገዛሁና ወገቤን ታጠቅሁበት።
\v 3 ከዚያም የእግዚአብሔር ቃል ለሁለተኛ ጊዜ ወደ እኔ መጣና እንዲህ አለኝ፣
\v 4 በወገብህ ያለውን የገዛሃውን መታጠቂያ ወስደህ ተነሥና ወደ ኤፍራጥስ ሂድ። በዚያም በተሰነጠቀ ዓለት ውስጥ ሸሽገው" አለኝ።
\s5
\v 5 እግዚአብሔርም እንዳዘዘኝ ሄድሁና በኤፍራጥስ ሸሸግሁት።
\v 6 ከብዙ ቀንም በኋላ፣ እግዚአብሔር፣ "ተነሥተህ ወደ ኤፍራጥስ ሂድ። በዚያም እንድትሸሽገው ያዘዝሁህን የውስጥ ሱሪ ከዚያ ውሰድ" አለኝ።
\v 7 እኔም ወደ ኤፍራጥስ ሄድሁ ቆፈርሁም፣ ከሸሸግሁበትም ስፍራ የውስጥ ሱሪውን ወሰድሁ። ነገር ግን እነሆ! የውስጥ ሱሪው ተበላሽቶ ነበር፣ ለምንም የማይጠቅም ሆኖ ነበር።
\s5
\v 8 ከዚያም የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ በድጋሚ መጣና እንዲህ አለኝ፣
\v 9 "እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እንዲሁ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ታላቅ እብሪት አጠፋለሁ።
\v 10 ቃሌን ይሰሙ ዘንድ እንቢ የሚሉ፣ በልባቸውም እልከኝነት የሚሄዱ፣ ያመልኩአቸውና ይሰግዱላቸው ዘንድ ሌሎችን አማልክት የሚከተሉ እነዚህ ክፉ ሕዝብ አንዳች እንዳማይረባ እንደሆነው እንደዚ የውስጥ ሱሪ ይሆናሉ።
\v 11 የውስጥ ሱሪው በሰው ወገብ ላይ እንደሚጣበቅ፣ እንዲሁ ሕዝብና ስም ምስጋናና ክብር ይሆኑልኝ ዘንድ የእስራኤልን ቤት ሁሉ የይሁዳንም ቤት ሁሉ ከእኔ ጋር አጣብቄአለሁ ይላል እግዚአብሔር። ነገር ግን አልሰሙኝም።
\s5
\v 12 ስለዚህ ይህንን ቃል ለእነርሱ ልትናገር ይገባል፣ 'የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ማድጋ ሁሉ የወይን ጠጅ ይሞላል።' እነርሱም 'ማድጋ ሁሉ የወይን ጠጅ እንዲሞላ በውኑ እኛ አናውቅምን?' ይሉሃል።
\v 13 ስለዚህ እንዲህ በላቸው፣ 'እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተመልከቱ፣ በዚህች ምድር የሚኖሩትን ሁሉ፣ በዳዊት ዙፋን የሚቀመጡትን ነገሥታት፣ ካህናቱን፣ ነቢያቱንና በኢየሩሳሌምም የተቀመጡትን ሁሉ በስካር እሞላቸዋለሁ።'
\v 14 ሰውንም በሰው ላይ፣ አባቶችንና ልጆችን በአንድ ላይ፣ እቀጠቅጣለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ አጠፋቸዋለሁ እንጂ አልራራም፣ አላዝንላቸውም፣ አልምርም።"
\s5
\v 15 ስሙ፣ አድምጡም። እግዚአብሔር ተናግሮአልና እብሪተኞች አትሁኑ።
\v 16 ሳትጨልም እግራችሁም በጨለመችው ተራራ ላይ ሳትሰናከል፥ በተስፋ የምትጠባበቁትን ብርሃን ለሞት ጥላና ለድቅድቅ ጨለማ ሳይለውጠው ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ክብርን ስጡ።
\v 17 ይህን ባትሰሙ፣ ስለ ትዕቢታችሁ ብቻዬን አለቅሳለሁ። የእግዚአብሔርም መንጋ ተማርኮአልና ዓይኔ ታነባለች፣ እንባንም ታፈስሳለች።
\s5
\v 18 ለንጉሡና ንግሥቲት ለሆነችው እናት፣ 'የክብራችሁ አክሊል ከራሳችሁ ወርዶአልና ራሳችሁን አዋርዳችሁ ተቀመጡ' በል።
\v 19 የደቡብ ከተሞች ተዘግተዋል፣ የሚከፍታቸውም የለም። ይሁዳ ሁሉ ተማርኮአል፣ ፈጽሞ ተማርኮአል።
\s5
\v 20 ዓይናችሁን አንሥታችሁ እነዚህን ከሰሜን የሚመጡትን ተመልከቱ፤ ለአንቺ የሰጠው መንጋ፣ ለአንቺ የተዋበው መንጋሽ ወዴት አለ?
\v 21 ወዳጆችሽ እንዲሆኑ ያስተማርሻቸውን እግዚአብሔር በራስሽ ላይ አለቆች ባደረጋቸው ጊዜ ምን ትያለሽ? እንደ ወላድ ሴት ምጥ አንቺንም የሚይዝሽ የምጥ ስቃይ ጅማሬ አይደለምን?
\s5
\v 22 በልብሽም፣ 'እንዲህ ያለ ነገር ስለ ምን ደረሰብኝ?' ብትዪ፣ የቀሚስሽ ዘርፍ ተገልጦ የተገፈፍሽው ከብዙ ኃጢአትሽ የተነሣ ነው።
\v 23 የኩሽ ሕዝቦች የቆዳ ቀለማቸውን፣ ወይስ ነብር ዝንጕርጕርነቱን ይለውጥ ዘንድ ይችላልን? ከሆነ፣ በዚያን ጊዜ ክፋትን የለመዳችሁ እናንተ ደግሞ መልካምን ማድረግ ትችላላችሁ።
\v 24 ስለዚህ እንደሚያልፍ እብቅ በምድረ በዳ ነፋስ እበትናቸዋለሁ።
\s5
\v 25 ረስተሽኛልና፣ በሐሰትም ታምነሻልና የሰጠኹሽ፣ የደነገግሁልሽም እድል ፈንታ ይህ ነው፣ ይላል እግዚአብሔር።
\v 26 ስለዚህም የቀሚስሽን ዘርፍ እኔ ራሴ በፊትሽ እገልጣለሁ፣ የእፍረት አካልሽም ይታያል።
\v 27 አስጸያፊ ሥራሽን፣ ምንዝርናሽን፣ ማሽካካትሽን፣ የግልሙትናሽንም መዳራት በኮረብቶች ላይ በሜዳም የሆኑትን እነዚህን አስፀያፊ ነገሮች እንዲታዩብሽ አደርጋለሁ! ወዮልሽ፣ ኢየሩሳሌም! አልነፃሽም። ይህስ እስከ መቼ ይቀጥላል?"
\s5
\c 14
\p
\v 1 ስለ ድርቅ ወደ ኤርምያስ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፣
\v 2 "ይሁዳ ታልቅስ፣ ደጆችዋም ይውደቊ። ስለ ምድራቸው እያለቀሱ ናቸው፤ ለኢየሩሳሌም የሚያለቅሱት ከፍ ብሎአል።
\v 3 ኃያላኖቻቸውም አገልጋዮቻቸውን ለውኃ ሰደዱ። ወደ ጕድጓድ ሲመጡ ውኃ ሊያገኙ አልቻሉም። ሁሉም ሳይሳካላቸው ተመለሱ፤ አፍረውና ተዋርደው ራሳቸውን ተከናነቡ።
\s5
\v 4 ከዚህ የተነሣ በምድሪቱ ላይ አልዘነበምና መሬቱ ስንጥቅጥቅ ሆነ። አራሾች አፈሩ ራሳቸውንም ተከናነቡ።
\v 5 ዋላ በምድረ በዳ ወልዳ ሣር ባለመኖሩ ግልገልዋን ተወች።
\v 6 የሜዳ አህዮችም በወና ኮረብታ ላይ ቆመው እንደ ቀበሮ ወደ ነፋስ አለከለኩ። ልምላሜ የለምና ዓይኖቻቸው ፈዘዙ።
\s5
\v 7 ኃጢአታችን ቢመሰክርብንም፣ እግዚአብሔር ስለ ስምህ ሥራ። ያልታመንንባቸው ተግባራቶቻችን ጨምረዋልና፣ በአንተ ላይ ኃጢአት ሠርተናል።
\v 8 የእስራኤል ተስፋ ሆይ፣ በጭንቀት ጊዜ የምታድነው አምላክ ወደ ማደሪያ ዘወር እንደሚል መንገደኛ በምድሪቱ ላይ ለምን እንደ እንግዳ ትሆናለህ?
\v 9 ግራ እንደተጋባ ሰው፣ ያድንም ዘንድ እንደማይችል ኃያል ለምን ትሆናለህ? አንተ ግን፣ በመካከላችን ነህ፣ እግዚአብሔር ሆይ እኛም በስምህ ተጠርተናል። አትተወን።
\s5
\v 10 እግዚአብሔር ለዚህ ሕዝብ እንዲህ ይላል፣ "መቅበዝበዝን ወድደዋልና፣ እግራቸውንም እንዲህ ከማድረግ አልከለከሉም፤" ስለዚህ እግዚአብሔር በእነርሱ ደስ አላለውም። አሁን በደላቸውን ያስባል ኃጢአታቸውንም ይቀጣል።
\v 11 እግዚአብሔርም፣ "ለዚህ ሕዝብ መልካም እንዲሆንላቸው አትጸልይላቸው።
\v 12 ቢጾሙ ጸሎታቸውን አልሰማም፣ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን ባቀረቡ ጊዜ አልቀበላቸውም። በሰይፍና በራብ በቸነፈርም አጠፋቸዋለሁ አለኝ።
\s5
\v 13 ከዚያም፣ "ኦ፣ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፣ ወዮ! እነሆ! ነቢያት ለሕዝቡ፣ 'በዚህ ስፍራ በእውነት ሰላምን እሰጣችኋለሁ እንጂ ሰይፍን አታዩም፣ ራብም አያገኛችሁም ይሉአቸዋል" እያሉ ናቸው።
\v 14 እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፣ "ነቢያቱ በስሜ የውሸት ትንቢት ይናገራሉ። አልላክኋቸውም፣ አላዘዝኋቸውም፣ አልተናገርኳቸውምም። ነገር ግን፣ የውሸት ራእይና ጥቅም የለሽ የሆነ ከንቱ ምዋርትን፣ የልባቸውንም ሽንገላ ይተነብዩላችኋል።"
\s5
\v 15 ስለዚህ እግዚአብሔር፣ "በዚህች አገር ሰይፍና ራብ አይሆንም ስለሚሉ፣ ነገር ግን በስሜ ትንቢት ስለሚናገሩ ስላልላክኋቸው ነቢያት እንዲህ ይላል፦ እነዚህ ነብያት በሰይፍና በራብ ይጠፋሉ።
\v 16 ትንቢት የሚናገሩላቸውም ሰዎች ከራብና ከሰይፍ የተነሣ በኢየሩሳሌም አደባባይ ይበተናሉ፤ ክፋታቸውንም አፈስስባቸዋለሁ እነርሱንና ሚስቶቻቸውን፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውንም የሚቀብራቸው አይገኝም።
\s5
\v 17 ይህንን ቃል ንገራቸው፦ 'ዐይኖቼ ሌሊትና ቀን ሳያቋርጡ እንባ ያፍስሱ። ድንግሊቱ የሕዝቤ ልጅ በታላቅ ስብራትና እጅግ ክፉ በሆነ ቍስል ተሰብራለችና ።
\v 18 ወደ ሜዳ ብወጣና ባይ! በሰይፍ የሞቱ አሉ። ወደ ከተማም ብገባ፣ ያኔም በራብ የታመሙ አሉ። ነቢዩና ካህኑም ወደማያውቋት አገር ሄደዋል።"
\s5
\v 19 በውኑ ይሁዳን ፈጽመህ ጥለኸዋልን? ጽዮንንስ ጠልተሃታልን? ፈውስ በማይኖረን ጊዜ ስለ ምን መታኸን? ሰላምን በተስፋ ተጠባበቅን፣ መልካምም አልተገኘም፤ ፈውስን በተስፋ ተጠባበቅን፣ ተመልከቱ፣ ያለው ግን ድንጋጤ ብቻ ነው።
\v 20 እግዚአብሔር ሆይ፣ በአንተ ላይ ኃጢአትን ሠርተናልና ክፋታችንንና የአባቶቻችንን በደል እናውቃለን።
\s5
\v 21 አትጣለን! ስለ ስምህ፣ የክብርህንም ዙፋን አታስነውር። ከእኛ ጋር ያደረግኸውን ቃል ኪዳንህን አስብ እንጂ አታፍርስ።
\v 22 በውኑ በአሕዛብ ጣዖታት መካከል የጸደይን ዝናብ ከሰማይ ያዘንብ ዘንድ የሚችል ይገኛልን? ይህንን የምታደርግ አምላካችን እግዚአብሔር አንተ አይደለህምን? እነዚህን ሁሉ አድርገሃልና ስለዚህ አንተን ተስፋ እናደርጋለን።
\s5
\c 15
\p
\v 1 እግዚአብሔርም እንደዚህ አለኝ፣ "ሙሴና ሳሙኤል በፊቴ ቢቆሙም እንኳን፣ ለዚህ ሕዝብ አላደላም። እንዲወጡ ከፊቴ አባርራቸው።
\v 2 እነርሱም፣ 'ወዴት እንሂድ?' ቢሉህ፣ ያኔ አንተ 'እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ለሞት የተወሰኑት ወደ ሞት፣ ለሰይፍም የተወሰኑት ወደ ሰይፍ፣ ለራብም የተወሰኑት ወደ ራብ፣ ለምርኮም የተወሰኑት ወደ ምርኮ' ትላቸዋለህ።
\s5
\v 3 አራቱን ዓይነት ጥፋት አዝዝባቸዋለሁ፣ እነርሱም አንዳንዶችን የሚገድል ሰይፍ፣ አንዳንዶችን የሚጎትቱ ውሾችን፣ አንዳንዶችን የሚበሉ የሰማያትን ወፎች፣ የምድርንም አራዊት ናቸው ይላል እግዚአብሔር።
\v 4 የይሁዳም ንጉሥ የሕዝቅያስ ልጅ ምናሴ በኢየሩሳሌም ስላደረገው ሁሉ ለምድር መንግሥታት ሁሉ መጨነቂያ አደርጋቸዋለሁ።
\s5
\v 5 ኢየሩሳሌም ሆይ የሚራራልሽ ማን ነው? የሚያዝንልሽስ ማን ነው? ወይስ ስለ ደኅንነትሽ ይጠይቅ ዘንድ ዘወር የሚል ማነ ነው?
\v 6 አንቺ እኔን ጥለሻል፣ ይላል እግዚአብሔር፣ ወደ ኋላሽም ተመልሰሻል። ስለዚህ እጄን በአንቺ ላይ ዘርግቼ እመታሽና አጠፋሻለሁ። ለአንቺ ምሕረት ማድረግ አድክሞኛል።
\v 7 በአገርም ደጆች ውስጥ በመንሽ አበጥራቸዋለሁ። ልጆቻቸውንም እነጥቃለሁ። ከመንገዳቸውም አልተመለሱምና ሕዝቤን አጠፋለሁ።
\s5
\v 8 መበለቶቻቸውን ከባሕር አሸዋ ይልቅ አበዛለሁ። በቀትር ጊዜ ላይ በብላቴኖች እናት ላይ አጥፊውን እልካለሁ። ድንጋጤና ሽብር በድንገት እንዲወድቅባቸው አደርጋለሁ።
\v 9 ሰባት የወለደች ትደክማለች። ታለከልካለች። ገና ቀን ሳለ ፀሐይዋ ትገባባታለች። የተረፉትንም በጠላቶቻቸው ፊት ለሰይፍ አሳልፌ እሰጣለሁና ታፍራለች፣ ትዋረድማለች።
\s5
\v 10 እናቴ ሆይ፣ ወዮልኝ! በምድሪቱ ሁሉ የክርክርና የጥል ሰው የሆንሁትን እኔን ወልደሽኛልና። አላበደርሁም፣ ከማንም አልተበደርኩም፣ ነገር ግን ሁሉ ይረግመኛል።
\v 11 እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ "በእውነት ለደኅንነትህ አልታደግህምን? በእርግጥ በመከራና በጭንቅ ጊዜ ጠላቶችህ እንዲለምኑህ አደርጋለሁ።
\v 12 ሰው ብረትን ይሰብራልን? በተለይ ከሰሜን የሆነውን ከናስ ጋር የተቀየጠውን ብረት የሚሰብር አለን?
\s5
\v 13 ባለጠግነትህንና መዝገብህን ለመበዝበዝ በነፃ እሰጣለሁ። ይህንንም የማደርገው በድንበሮችህ ሁሉ ስለፈጸምከው ኃጢአትህ ሁሉ ነው።
\v 14 ከዚያም፣ ጠላቶችህ ወደማታውቀው ምድር እንዲወስዱህ አደርጋለሁ፣ የምታቃጥላችሁ እሳት ከቍጣዬ ትነድዳለችና።
\s5
\v 15 አንተ ራስህ ታውቃለህ፣ እግዚአብሔር ሆይ! አስበኝ እርዳኝም። የሚያሳድዱኝንም ተበቀላቸው። በትእግሥትህ አታርቀኝ። ስለ አንተ ነቀፌታን እንደ ጠገብሁ እወቅ።
\v 16 ቃሎችህ ተገኝተዋል እኔም በልቼያቸዋለሁ። የሠራዊት አምላክ ሆይ፣ በስምህ ተጠርቻለሁና ቃሎችህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆኑልኝ።
\s5
\v 17 በሚፈነድቁትና በደስተኞች ዙሪያ አልተቀመጥሁም። በቍጣህ ሞልተኸኛልና በኃይለኛው እጅህ ፊት ለብቻዬ ተቀመጥሁ።
\v 18 ስለ ምን ሕመሜ አዘወተረኝ፣ ቍስሌስ ስለ ምን ፈውስን የማይቀበልና የማይሽር ሆነ? በውኑ እንደ አታላይ ምንጭ፣ እንደደረቅ ውኃ ትሆናለህን?
\s5
\v 19 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ኤርምያስ ሆይ፣ ንስሃ ብትገባ፣ እንደ ቀድሞው እመልስሃለሁ፣ በፊቴም ቆመህ ታገለግለኛለህ። የተዋረደውንም ከከበረው ብትለይ፣ እንደ አፌ ትሆናለህ። ሕዝቡ ወደ አንተ ይመለሳሉ፣ አንተ ራስህ ግን ወደ እነርሱ አትመለስም።
\v 20 ለዚህም ሕዝብ የማይጣስ የናስ ቅጥር አደርግሃለሁ፣ ይዋጉሃል። ነገር ግን እኔ ላድንህ ከአንተ ጋር ነኝና አያሸንፉህም ይላል እግዚአብሔር።
\v 21 ከክፉ ሰዎችም እጅ እታደግሃለሁ፣ ከጨካኞችም ቡጢ እቤዥሃለሁ።
\s5
\c 16
\p
\v 1 ከዚያም የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፣
\v 2 "በዚህ ስፍራ ሚስት አታግባ፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆችም አይኑርህ።
\v 3 እግዚአብሔር በዚህ ስፍራ ስለ ተወለዱ ወንዶችና ሴቶች ልጆች፣ ስለወለዱአቸውም ስለ እናቶቻቸው፣ በዚህችም ምድር እንዲወለዱ ስላደረጉ አባቶቻቸው እንዲህ ይላል፣
\v 4 በበሽታ ሞት ይሞታሉ። አይለቀስላቸውም ወይም አይቀበሩም። በመሬትም ላይ እንደ ጕድፍ ይሆናሉ። በሰይፍና በራብ ይጠፋሉ፣ ሬሳቸውም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል ይሆናሉ።'
\s5
\v 5 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ልቅሶ ወዳለበት የትኛውም ቤት አትግባ። ታለቅስም፣ ታዝንም ዘንድ አትሂድ። ሰላሜን፣ ቸርነትና ምሕረትን፣ ከዚህ ሕዝብ አስወግጄአለሁና!
\v 6 ታላላቆችና ታናናሾች በዚህች ምድር ይሞታሉ። አይቀበሩም፣ ሰዎችም አያለቅሱላቸውም። ስለ እነርሱም ገላን አይነጩላቸውም ራስንም አይላጩላቸውም።
\s5
\v 7 ሰዎችም ስለ ሞቱት ለማጽናናት የእዝን እንጀራን ሊካፈሉ አይገባም፣ ለአባታቸውና ለእናታቸውም ማንም የመጽናናት ጽዋ ሊሰጧቸው አይገባም።
\v 8 ትበላና ትጠጣ ዘንድ ከእነርሱ ጋር ለመቀመጥ ወደ ግብዣ ቤት አትግባ።'
\v 9 የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፣ 'ተመልከት፣ በዐይናችሁ ፊት በዘመናችሁም የእልልታን ድምፅና የደስታን ድምፅ፣ የወንድ ሙሽራን ድምፅና የሴት ሙሽራን ድምፅ ከዚህ ስፍራ አስቆማለሁ።'
\s5
\v 10 ከዚያም ለዚህ ሕዝብ ይህን ቃል ሁሉ በተናገርህ ጊዜ፣ 'እግዚአብሔር ይህን ሁሉ ታላቅ የሆነ ክፉ ነገር ለምን ተናገረብን? በደላችንስ ምንድር ነው? በአምላካችንስ በእግዚአብሔር ላይ የሠራነው ኃጢአታችን ምንድር ነው? ሲሉህ፣
\v 11 እንዲህ በላቸው፣ 'አባቶቻችሁ እኔን ስለ ተው ነው፣ ይላል እግዚአብሔር፤ እነርሱም ሌሎችን አማልክት ተከተሉ አመለኩአቸውም ሰገዱላቸውም። እነርሱም ትተውኛል፣ ሕጌንም አልጠበቁም።
\s5
\v 12 ነገር ግን፣ እናንተ ራሳችሁ ከአባቶቻችሁ ይልቅ ክፉ አድርጋችኋል፤ ተመልከቱ፣ እያንዳንዱ ሰው በክፉ ልብ እልከኝነት ሄዷል፣ እኔንም የሚሰማ የለም።
\v 13 ስለዚህ ከዚህች ምድር እናንተና አባቶቻችሁ ወዳላወቃችኋት ምድር እጥላችኋለሁ፣ ሞገስን አላደርግላችሁምና በዚያ ሌሎችን አማልክት ቀንና ሌሊት ታመልካላችሁ።
\s5
\v 14 ስለዚህ ተመልከቱ! ከእንግዲህ 'የእስራኤልን ልጆች ከግብጽ ምድር ያወጣ ሕያው እግዚአብሔርን!' የማይባልበት ዘመን ይመጣል፣ ይላል እግዚአብሔር።
\v 15 ነገር ግን፣ የእስራኤልን ልጆች ከሰሜን ምድር፣ ካሳደዳቸውም ምድር ሁሉ ያወጣ ሕያው እግዚአብሔርን ይባላል፤ እኔም ለአባቶቻቸው ወደ ሰጠኋት ወደ ምድራቸው እመልሳቸዋለሁ።
\s5
\v 16 ተመልከቱ! ብዙ ዓሣ አጥማጆችን እሰድዳለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ እነርሱም ሕዝቡን ሊያወጡ ያጠምዱአቸዋል። ከዚህም በኋላ ብዙ አጥማጆችን እሰድዳለሁ፣ እነርሱም ከየተራራውና ከየኮረብታው ሁሉ ከየድንጋዩም ስንጣቂ ውስጥ ያጠምዷቸዋል።
\v 17 ዓይኔ በመንገዳቸው ሁሉ ላይ ነውና፤ ከፊቴም ሊሰወሩ አይችሉም። በደላቸውም ከዓይኔ ሊሰወር አይችልም።
\v 18 በተጠሉ ጣዖቶቻቸው ሬሳዎች ምድሬን አርክሰዋልና፣ ርስቴንም አስጸያፊ በሆኑ ነገሮች ሞልተዋልና፣ አስቀድሜ የበደላቸውንና የኃጢአታቸውን ዕዳ ሁለት እጥፍ እከፍላቸዋለሁ።"
\s5
\v 19 እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ ምሽጌ፣ አምባዬ፣ በመከራም ቀን መጠጊያዬ ነህ። አሕዛብ ከምድር ዳርቻ ወደ አንተ ሄደው፣ "በእርግጥ አባቶቻችን ውሸትን ወርሰዋል። ባዶ ናቸው፤ በእነርሱ ዘንድ ትርፍ የለም ይላሉ።
\v 20 በውኑ ሕዝቦች አማልክት ያልሆኑትን ለራሳቸው አማልክትን አድርገው ይሠራሉን?
\v 21 ስለዚህ ተመልከቱ! በዚህ ጊዜ አስታውቃቸዋለሁ፣ እጄንና ኃይሌን አስታውቃቸዋለሁ፤ ከዚህም የተነሣ ስሜ እግዚአብሔር እንደ ሆነ ያውቃሉ።"
\s5
\c 17
\p
\v 1 "የይሁዳ ኃጢአት የሾለ አልማዝ ባለው የብረት ብዕር ተጽፎአል። በልባቸው ጽላትና በመሠዊያቸው ቀንዶች ላይ ተቀርጾአል።
\v 2 ልጆቻቸውም ከለመለሙ ዛፎች በታችና በከፍተኞቹ ኮረብቶች ላይ ያሉትን መሠዊያቸውንና አሼራ የምትባለውን ጣዖታቸውን ያስባሉ።
\s5
\v 3 በገጠር ባሉት ተራሮች ላይ ያሉትን መሠዊያዎቻቸውን ያስታውሳሉ። ባለጠግነታችሁንና መዝገባችሁን ሁሉ፣ የኮረብታውን መስገጃዎቻችሁንም በኃጢአታችሁ ምክንያት እንዲበዘበዙ አደርጋለሁ።
\v 4 አናንተም የሰጠኋችሁን ርስት ትለቅቃላችሁ። በማታውቋትም ምድር ለጠላቶቻችሁ ባሪያ አደርጋችኋለሁ፤ ለዘላለም የሚነድደውን እሳት በቍጣዬ አንድዳችኋልና።
\s5
\v 5 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "በሰው የሚታመን፣ ሥጋ ለባሹንም ብርታቱ የሚያደርግ፣ ልቡን ግን ከእግዚአብሔር የሚመልስ ሰው ርጉም ነው።
\v 6 በአረብ ምድር እንዳለ ትንሽ ቍጥቋጦ ይሆናል፣ የሚመጣውንም መልካም ነገር አያይም። ሰውም በሌለበት ዐለታማ ምድር ውስጥ ደረቅ በሆነ ምድረ በዳ ይቀመጣል።
\s5
\v 7 ነገር ግን በእግዚአብሔር የታመነ፣ የልበ-ሙሉነቱ ምክንያት እግዚአብሔር ነውና ቡሩክ ነው።
\v 8 በውኃ አጠገብ እንደ ተተከለ፣ በወንዝም ዳር ሥሩን እንደሚዘረጋ ተክል ይሆናልና። ሙቀት ሲመጣ አያይም፣ ቅጠሉ ይለመልማልና። ከዚያም፣ በድርቅ ዓመት ላይ አይሠጋም፣ ማፍራቱንም አያቋርጥም።
\s5
\v 9 ልብ ከየትኛውም ነገር ይልቅ ተንኰለኛ ነው። በሽተኛ ነው፤ ማንስ ያስተውለዋል?
\v 10 ለሰው ሁሉ እንደ መንገዱ፣ እንደ ሥራው ፍሬ ልሰጥ ልብን የምመረምር፣ ኵላሊትንም የምፈትን እግዚአብሔር እኔ ነኝ።
\v 11 ያልጣለችውን እንቁላል እንደምታቅፍ ቆቅ፣ እንዲሁ አንድ ሰው ያለፍትህ ባለጠጋ ይሆን ይሆናል። ነገር ግን በእኩሌታ ዘመኑ ላይ ብልጥግናው ይተወዋል፣ በፍጻሜውም ሰነፍ ይሆናል።
\s5
\v 12 የመቅደሳችን ስፍራ ከመጀመሪያም ጀምሮ ክፍ ያለ የክብር ዙፋን ነው።
\v 13 እግዚአብሔር የእስራኤል ተስፋ ነው። አንተን የሚተዉህ ሁሉ ያፍራሉ። ከአንተም የሚለዩ የሕይወትን ውኃ ምንጭ እግዚአብሔርን ትተዋልና በምድር ላይ ይቆረጣሉ።
\v 14 እግዚአብሔር ሆይ፣ ፈውሰኝ እኔም እፈወሳለሁ! አድነኝ እኔም እድናለሁ። አንተ የምስጋናዬ ዝማሬ ነህና።
\s5
\v 15 ተመልከቱ፣ 'የእግዚአብሔር ቃል ወዴት ነው? ይምጣ!' ይሉኛል።
\v 16 እኔም አንተን ተከትዬ እረኛ ከመሆን አልሮጥሁም። የመከራንም ቀን አልታገሥሁም። ከከንፈሬ የመጣውን አንተ ታውቃለህ። በህልውናህ ፊት ተነግረዋል።
\s5
\v 17 መሸበሪያ አትሁንብኝ። በመከራ ቀን አንተ መጠጊያዬ ነህ።
\v 18 አሳዳጆቼ ይፈሩ፣ እኔ ግን አልፈር። እነርሱ ይደንግጡ፣ እኔ ግን አልደንግጥ። የጥፋትን ቀን አምጣባቸው፣ በሁለት እጥፍ ጥፋት አጥፋቸው።
\s5
\v 19 እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ "ሂድና የይሁዳም ነገሥታት በሚገቡበትና በሚወጡበት የሕዝቡ በር፣ ከዚያም በኢየሩሳሌምም በሮች ሁሉ ቁም።
\v 20 እንዲህም በላቸው፣ 'በእነዚህ በሮች የምትገቡ እናንተ የይሁዳ ነገሥታት፣ የይሁዳም ሕዝብ ሁሉ፣ የኢየሩሳሌምም ነዋሪዎች ሁሉ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።
\s5
\v 21 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ለራሳችሁ ሕይወት ተጠንቀቁ፥ በኢየሩሳሌምም በሮች እንድታገቡ በሰንበት ቀን ሸክምን አትሸከሙ።
\v 22 በሰንበት ቀን ከቤቶቻችሁ ሸክምን አታውጡ። የትኛውንም ሥራ ሁሉ አትሥሩበት፣ ነገር ግን አባቶቻችሁንም እንዳዘዝሁት የሰንበትን ቀን ቀድሱ።"
\v 23 እነርሱ ግን ትኩረት ሰጥተው አልሰሙም፣ እንዳይሰሙና ተግሣጽን እንዳይቀበሉ አንገታቸውን አደነደኑ።
\s5
\v 24 እኔን ፈጽሞ ብትሰሙ ይሆናል፤ ይላል እግዚአብሔር፤ ደግሞም በሰንበት ቀን በዚህች ከተማ በሮች ሸክም አታምጡ፣ ይልቊንም የሰንበትን ቀን ለእግዚአብሔር ቀድሱ የትኛውንም ሥራ አትሠሩበት፤
\v 25 በዳዊት ዙፋን ላይ የሚቀመጡ ነገሥታትና መሳፍንት በሰረገሎችና በፈረሶች ላይ እየተቀመጡ በዚህች ከተማ በሮች ይገባሉ፣ እነርሱና መሳፍንቶቻቸው የይሁዳም ነዋሪዎች በኢየሩሳሌምም የሚቀመጡ ይመጣሉ። ይህችም ከተማ ለዘላለም የሰው መኖሪያ ሆና ትቀራለች።
\s5
\v 26 የሚቃጠለው መሥዋዕትና ሌላ መሥዋዕትን የእህሉንም ቍርባን ዕጣኑንም የምስጋናውንም መሥዋዕት ይዘው ከይሁዳ ከተሞች ከኢየሩሳሌምም ዙሪያ ከብንያምም አገር ከቈላውም ከደጋውም ከኔጌቭም ወደ እግዚአብሔር ቤት ይመጣሉ።
\v 27 ነገር ግን የሰንበትን ቀን ልትቀድሱ፣ በሰንበትም ቀን ሸክምን ተሸክማችሁ በኢየሩሳሌም በሮች ልትገቡ የነገርኋችሁን ባትሰሙኝ፣ እሳትን በበሮችዋ ላይ እለኩሳለሁ፣ የኢየሩሳሌምንም ምሽጎች ትበላለች፣ እሳቱም አይጠፋም።
\s5
\c 18
\p
\v 1 ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል እንዲህ አለው፣
\v 2 "ተነሥተህ ወደ ሸክላ ሠሪው ቤት ውረድ፣ በዚያም ቃሌን አሰማሃለሁና።
\v 3 ስለዚህም ወደ ሸክላ ሠሪው ቤት ወረድሁ፣ ሸክላ ሠሪውም ሥራውን በመንኵራኩር ላይ ይሠራ ነበር።
\v 4 ከጭቃም ይሠራው የነበረ ዕቃ በሸክላ ሠሪው እጅ ተበላሸ፣ ሸክላ ሠሪውም እንደ ወደደ መልሶ ሌላ ዕቃ አድርጎ ሠራው።
\s5
\v 5 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፣
\v 6 "የእስራኤል ቤት ሆይ፣ ይህ ሸክላ ሠሪ እንደሚሠራ በውኑ እኔ በእናንተ ዘንድ መሥራት አይቻለኝምን? ይላል እግዚአብሔር። ተመልከቱ! ጭቃው በሸክላ ሠሪ እጅ እንዳለ፣ እንዲሁ እናንተ በእኔ እጅ ውስጥ አላችሁ።
\v 7 በአንድ ወቅት፣ አባርር፣ አፈርስ፣ ወይም አጠፋ ዘንድ ስለ ሕዝብ ወይም ስለ መንግሥት አንዳች ነገር እናገር ይሆናል።
\v 8 ነገር ግን ያንን የተናገርኩበት ሕዝብ ከክፋቱ ቢመለስ፣ ያኔ እኔ ላደርግበት ያሰብሁትን ክፉ ነገር እተወዋለሁ።
\s5
\v 9 በሌላ ጊዜ፣ ስለ ሕዝብ ወይም ስለ መንግሥት እንደምሠራው ወይም እንደምተክለው እናገራለሁ።
\v 10 ነገር ግን ድምፄን ባለመስማት በፊቴ ክፉን ነገር ቢያደርግ፣ ያኔ እኔ ላደርግለት የተናገርሁትን መልካም ነገር አቆማለሁ።
\s5
\v 11 አሁን እንግዲህ፣ ለይሁዳ ሰዎችና በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ ተናገርና እንዲህ በላቸው፣ 'እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተመልከቱ፣ ክፉ ነገር ልፈጥርባችሁ ነው። እቅድንም ላወጣባችሁ ነው። መንገዶቻችሁ እና ልምምዶቻችሁ መልካምን እንዲያመጡላችሁ፣ እያንዳንዱ ሰው ከክፉ መንገዱ ንስሃ ይግባ'
\v 12 እነርሱ ግን፣ 'ይህ ጥቅም የለውም። እንደ እቅዶቻችን እናደርጋለን። እያንዳንዳችን ክፉ የሆነው ልባችን እንደተመኘው እልከኝነትን እናደርጋለን' አሉ።
\s5
\v 13 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'እንዲህ ያለውን ነገር ማን ሰምቷል ብላችሁ አሕዛብን ጠይቊ። የእስራኤል ድንግል አስደንጋጭ ነገርን አድርጋለች።
\v 14 በውኑ የሊባኖስ በረዶ በሜዳ ያሉትን ድንጋያማ ኮረብቶች ይተዋልን? ወይስ ከሩቅ የምትመጣው ቀዝቃዛይቱ ፈሳሽ ውኃ ትደርቃለችን?
\s5
\v 15 ሕዝቤ ግን ረስተውኛል። ጥቅም ለሌላቸው ጣዖታት ሠውተዋል፤ ከመንገዳቸውም ተሰናክለዋል፤ በአነስተኞቹ መንገዶች ለመሄድ ሲሉ የቀደሙትን መንገዶች ትተዋል።
\v 16 ምድራቸው ለመደንገጪያና ለዘላለም ማፍዋጫ ይሆናል። የሚያልፍባት ሁሉ ይደነቃል፣ ራሱንም ይነቀንቃል።
\v 17 እንደ ምሥራቅ ነፋስ በጠላቶቻቸው ፊት እበትናቸዋለሁ። በጥፋታቸውም ቀን ፊቴን ሳይሆን ጀርባዬን አሳያቸዋለሁ።"
\s5
\v 18 እነርሱም፣ "ሕግ ከካህናት፣ ወይም ምክር ከጠቢባን፣ ወይም ቃልም ከነቢያት አይጠፋምና ኑ፣ በኤርምያስ ላይ እናሲር። ኑ፣ በቃላችን እናጥቃው፣ የሚናገረውንም ሁሉ ትኩረት አንስጠው" አሉ።
\v 19 እግዚአብሔር ሆይ፣ አድምጠኝ! የጠላቴንም ድንፋታ ስማ።
\v 20 ጕድጓድ ቈፍረውልኛልና መልካም ስለሆንኩላቸው ከእነርሱ የሚሆን ጥፋት ክፍያዬ ይሆናልን? ለደህንነታቸው ለመናገር፣ ከእነርሱ ቊጣህን ለመመለስ በፊት እንደቆምኩ አስታውስ።
\s5
\v 21 ስለዚህ ልጆቻቸውን ለራብ ስጥ፣ ለሰይፍም ኃይል አሳልፈህ ስጣቸው። ሚስቶቻቸውም የወላድ መካንና መበለቶች ይሁኑ፣ ወንዶቻቸውም ይገደሉ፣ ወጣቶቻቸውም በጦርነት ጊዜ በሰይፍ ይመቱ።
\v 22 ሊይዙኝ ጕድጓድ ቆፍረዋልና፣ ለእግሮቼም ድብቅ ወጥመድ አኑረዋልና በላያቸው ጭፍራን በድንገት ባመጣህ ጊዜ፣ ከቤታቸው ጩኸት ይሰማ።
\v 23 አንተ ግን፣ እግዚአብሔር ሆይ፣ ይገድሉኝ ዘንድ በላዬ ያቀዱትን ዕቅድ ሁሉ ታውቃለህ። በደላቸውንና ኃጢአታቸውን ይቅር አትበል። ኃጢአታቸውንም ከአንተ ዘንድ አትደምስስ። ይልቅ፣ በፊትህ ይውደቁ። በቍጣህ ጊዜ እንዲሁ አድርግባቸው።
\s5
\c 19
\p
\v 1 እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፣ "ሂድና ከሸክላ ሠሪ ገምቦ ግዛ፤ ከሕዝቡም ሽማግሌዎችና ከካህናት ሽማግሌዎች ከአንተ ጋር ውሰድ።
\v 2 የገል በር በሚከፈትበት ወዳለው ወደ ሄኖም ልጅ ሸለቆ ሂድ፣ በዚያም የምነግርህን ቃል ተናገር።
\v 3 እንዲህም በል፣ 'ይሁዳ ነገሥታትና በኢየሩሳሌም የምትኖሩ ሆይ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ! የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ተመልከቱ! የሰማውን ሰው ጆሮ የሚያስጨንቅ ክፉ ነገር በዚህ ስፍራ አመጣለሁ።
\s5
\v 4 ይህንን የማደርገው ስለተዉኝና ይህንን ስፍራ የባዕድ አማልክት አድርገውታልና ነው። እነርሱና አባቶቻቸው ለማያውቋቸው ለሌሎች አማልክት አጥነዋል፣ የይሁዳም ነገሥታት ይህንን ስፍራ በንጹህ ደም ሞልተዋል።
\v 5 እኔም ያላዘዝሁትን የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገው ወንዶች ልጆቻቸውን ለበኣል በእሳት ያቃጥሉ ዘንድ የበኣልን የኮረብታውን መስገጃዎች ሠርተዋል። ይህንን እንዲያደርጉ አልተናገርኳቸውም፣ በልቤም አላሰብሁትም።
\s5
\v 6 ስለዚህም፣ ተመልከቱ፣ ይህ ስፍራ የእርድ ሸለቆ ይባላል እንጂ ከእንግዲህ ቶፌት ወይም የሄኖም ልጅ ሸለቆ የማይባልበት ዘመን ይመጣል ይላል እግዚአብሔር።
\v 7 በዚህ ስፍራ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን እቅድ ከንቱ አደርጋለሁ። በጠላቶቻቸው ፊት በሰይፍና ነፍሳቸውን ደግሞ በሚሹት እጅ እጥላቸዋለሁ። ከዚያም ሬሳቸውንም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል አድርጌ እሰጣለሁ።
\v 8 ከዚያም ይህችን ከተማ አጠፋና መደነቂያ አደርጋታለሁ፣ ስለ ተደረገባት መቅሠፍት ሁሉ የሚያልፍባት ሁሉ ይደነቃል፣ ከንፈሩንም ይመጥጣል።
\v 9 የወንዶችና የሴቶች ልጆቻቸውንም ሥጋ አበላቸዋለሁ፣ ሁሉም ጠላቶቻቸውንና ነፍሳቸውን የሚሹት በሚያስጨንቋቸው ጭንቀትና መከበብ የጎረቤቶቻቸውን ሥጋ ይበላሉ።
\s5
\v 10 ከዚያም ገምቦውን ከአንተ ጋር በሚሄዱ ሰዎች ፊት ትሰብራለህ።
\v 11 እንዲህም ትላቸዋለህ፣ 'የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የሸክላ ሠሪውን ዕቃ ኤርምያስ እንደሰባበረው፣ ደግሞም በድጋሚ ይጠገን ዘንድ እንደማይቻል፣ እንዲሁ ይህን ሕዝብና ይህችን ከተማ እሰብራለሁ፤ የሚቀብሩበትም ስፍራ እስከማይኖር ድረስ በቶፌት ይቀበራሉ።
\s5
\v 12 ይህችንም ከተማ እንደ ቶፌት ሳደርግ ለዚህ ስፍራና በሚኖሩበት ላይ የማደርገው ይህንኑ ነው ይላል እግዚአብሔር።
\v 13 የረከሱትም የኢየሩሳሌም ቤቶችና የይሁዳ ነገሥታት ቤቶች፣ እነዚያ በሰገነታቸው ላይ ለሰማይ ከዋክብት ሁሉ ያጠኑባቸው ለሌሎችም አማልክት የመጠጥን ቍርባን ያፈሰሱባቸው ቤቶች ሁሉ፣ እንደ ቶፌት ስፍራ ይሆናሉ።"
\s5
\v 14 ከዚያም ትንቢት እንዲናገር እግዚአብሔር ልኮት ከበረው ስፍራ፣ ከቶፌት ኤርምያስ መጣ። በእግዚአብሔርም ቤት አደባባይ ቆሞ ለሕዝብ ሁሉ እንዲህ አለ፣
\v 15 "የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ቃሌን እንዳይሰሙ አንገታቸውን አደንድነዋልና፣ በዚህች ከተማና በመንደሮችዋ ሁሉ ላይ የተናገርሁባትን ክፉ ነገር ሁሉ አመጣለሁ።"
\s5
\c 20
\p
\v 1 በእግዚአብሔርም ቤት የተሾመው አለቃ የካህኑ የኢሜር ልጅ ጳስኮር ኤርምያስ በዚህ ነገር ትንቢት ሲናገር ሰማ።
\v 2 ስለዚህ ጳስኮር ነቢዩን ኤርምያስን መታው፣ በእግዚአብሔርም ቤት ውስጥ ባለው በላይኛው የብንያም በር በእግር ግንድ አሰረው።
\s5
\v 3 በቀጣዩ ቀን ጳስኮር ኤርምያስን ከግንድ እስር አወጣው። ከዚያም ኤርምያስ እንዲህ አለው፣ "እግዚአብሔር ስምህን፣ ማጎርሚሳቢብ እንጂ ጳስኮር ብሎ አይጠራህም።
\v 4 እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፣ 'ተመልከት፣ ለራስህና ለወዳጆችህ ሁሉ ፍርሃት አደርግሃለሁ፤ እነርሱም በጠላቶቻቸው ሰይፍ ይወድቃሉና ዓይኖችህም ያንን ያያሉ። ይሁዳንም ሁሉ በባቢሎን ንጉሥ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ። እርሱም በባቢሎን ምርኮኛ ያደርጋቸዋል ወይም በሰይፍ ይገድላቸዋል።
\s5
\v 5 የዚህችንም ከተማ ባለጠግነት ሁሉ ጥሪትዋንም ሁሉ ክብርዋንም ሁሉ የይሁዳንም ነገሥታት መዝገብ ሁሉ በጠላቶቻቸው እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ። እነዚህን ነገሮች በጠላቶቻችሁ እጅ አኖራለሁ፣ እነርሱም ይይዟቸዋል። እነርሱም ይወስዷቸዋል ደግሞም ወደ ባቢሎን ያመጧቸዋል።
\v 6 አንተ ግን፣ ጳስኮር ሆይ፣ በቤትህም የሚኖሩት ሁሉ ተማርካችሁ ትሄዳላችሁ። ወደ ባቢሎን ትሄዳለህ ደግሞም በዚያ ትሞታለህ። አንተና የሚያታልሉ ነገሮችን የተነበይክላቸው ወዳጆችህ ሁሉ በዚያ ትቀበራላችሁ።"
\s5
\v 7 እግዚአብሔር ሆይ፣ አሳመንኸኝ፣ እኔም አምኛለሁ። ያዝኸኝ ደግሞም አሸነፍኸኝ። መላገጫ ሆኛለሁ። ሕዝቡ በየቀኑ፣ ቀኑን ሁሉ ይሳለቊብኛል።
\v 8 በተናገርሁ ቍጥር፣ 'ግፍና ጥፋት' ብዬ እጮኻለሁ። የእግዚአብሔርም ቃል ቀኑን ሁሉ ነቀፌታና ዋዛ ሆኖብኛልና።
\v 9 እኔም፣ 'ከእንግዲህ ወዲህ የእግዚአብሔርን ስም አላስብም። ከእንግዲህ ወዲህም ስሙን አላውጅም' ብል፣ ያን ጊዜ በአጥንቶቼ ውስጥ እንደሚነድድ፣ በልቤ ውስጥ እንዳለ እሳት ሆነብኝ። ስለዚህ ልሸከመው ታገልሁ፣ ነገር ግን አልቻልሁም።
\s5
\v 10 በዙሪያዬ ካሉ ብዙ ሰዎች የሚያሽብር አሉባልታን ሰምቻለሁ። የቅርቤ ሰዎች የሆኑት ውድቀቴን ለማየት ጠበቊ፣ 'ምናልባት እንበረታበት እንደ ሆነ፣ ከዚያም እንበቀለው እንደ ሆነ 'ክሰሱት፣ እኛም እንከስሰዋለን' ይላሉ።
\v 11 እግዚአብሔር ግን እንደ ኃያል ጦረኛ ከእኔ ጋር ነው፤ ስለዚህ አሳዳጆቼ ይሰናከላሉ። አያሸንፉኝም። አይከናወንላቸውምና፣ በእጅጉ ያፍራሉ። መቼም የማይረሳ በሚሆን እፍረት የማያበቃ እፍረት ያፍራሉ።
\s5
\v 12 ጻድቅን የምትመረምር፣ አእምሮንና ልብን የምትመለከት የሠራዊት ጌታ ሆይ፣ ክርክሬን አሳይቼሃለሁና በላያቸው በቀልህን ልይ።
\v 13 ለእግዚአብሔር ዘምሩ! እግዚአብሔርን አመስግኑ! የተጨቆኑትን ሰዎች ሕይወት ከክፉ አድራጊዎች እጅ አድኖአልና።
\s5
\v 14 የተወለድሁባት ቀን የተረገመች ትሁን። እናቴ እኔን የወለደችባት ቀን የተባረከች አትሁን።
\v 15 'ወንድ ልጅ ተወልዶልሃል' ብሎ ለአባቴ የነገረው ሰው የተረገመ ይሁን።
\s5
\v 16 ያም ሰው እግዚአብሔር ያለምሕረት እንደ ገለበጣቸው ከተሞች ይሁን። በማለዳም እርዳታ የሚለምን ጩኸትን በቀትርም የጦርነት እሪታን ይስማ።
\v 17 እግዚአብሔር በማኅፀን ውስጥ አልገደለኝምና ወይም እናቴን መቃብሬ አላደረገኝምና፣ ይህ ይከሰት።
\v 18 ችግርንና ጣርን አይ ዘንድ፣ ዘመኔም በእፍረት ይሞላ ዘንድ ለምን ከማኅፀን ወጣሁ?
\s5
\c 21
\p
\v 1 ንጉሥ ሴዴቅያስ የመልክያን ልጅ ጳስኮርንና ካህኑን የመዕሤያን ልጅ ሶፎንያስ ወደ ኤርምያስ በላከ ጊዜ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው።
\v 2 "የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ይወጋናልና ስለ እኛ፣ እባክህ፣ እግዚአብሔርን ጠይቅ። ምናልባት ከእኛ ይመለስ ዘንድ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር እንደ ተአምራቱ ሁሉ ያደርግ ይሆናል።"
\s5
\v 3 ስለዚህ ኤርምያስ እንዲህ አላቸው፣ "ለሴዴቅያስ እንዲህ በሉት፣
\v 4 'የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተመልከት፣ የባቢሎንን ንጉሥ ከቅጥርም ውጭ የከበቡአችሁን ከለዳውያንን የምትወጉበትን በእጃችሁ ያለውን ዕቃ ጦራችሁን እመልሰዋለሁ! እነዚያንም ወደዚህች ከተማ አማከይ እሰበስባቸዋለሁ።
\v 5 ያን ጊዜ እኔ ራሴ በተዘረጋች እጅና በብርቱ ክንድ፣ በቍጣና በመዓት በታላቅም መቅሠፍት እወጋችኋለሁ።
\s5
\v 6 በዚህችም ከተማ የሚኖሩትን፣ ሰዎችንና እንስሶችን እመታለሁ፣ በጽኑም መቅሰፍት ይሞታሉ።
\v 7 ከዚህ በኋላ፣ ይላል እግዚአብሔር፣ የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስን፣ ከቸነፈርና ከሰይፍ ከራብም በዚህች ከተማ የቀሩትንም ባሪዎቹንና ሕዝቡን፣ በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ በጠላቶቻቸውና ነፍሳቸውንም በሚሹት እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ። ከዚያም እርሱ በሰይፍ ስለት ይመታቸዋል። አያዝንላቸውም፣ አይራራላቸውም፣ ወይም አያዝንላቸውም።'
\s5
\v 8 ከዚያም ለዚህ ሕዝብ እንዲህ ልትል ይገባል፣ 'እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተመልከቱ፣ የሕይወትን መንገድና የሞትን መንገድ በፊታችሁ አደርጋለሁ።
\v 9 በዚህች ከተማ ውስጥ የሚቆይ የትኛውም ሰው በሰይፍ፣ በራብ፣ በመቅሠፍትም ይሞታል፤ ነገር ግን ወጥቶ ወደ ከበቡአችሁ ወደ ከለዳውያን የሚገባ ግን በሕይወት ይኖራል። በሕይወትም ያመልጣል።
\v 10 መልካምን ሳይሆን ጥፋትን ለማምጣት ፊቴን በዚህች ከተማ ላይ አድርጌአለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር። ለባቢሎን ንጉሥ እጅ ተሰጥታለች፣ እርሱም በእሳት ያቃጥላታል።'
\s5
\v 11 የይሁዳ ንጉሥ ቤትን በተመለከተ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።
\v 12 የዳዊት ቤት ሆይ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'በማለዳ ፍርድን አድርጉ። የተዘረፈውንም ከአጨቋኙ እጅ አድኑ፣ አሊያ ቍጣዬ እንደ እሳት ይወጣና ያቃጥላል። ከሥራችሁ ክፋት የተነሣ ሊያጠፋው የሚችል ማንም አይኖርም።
\s5
\v 13 ተመልከቱ፣ የሸለቆው ነዋሪዎች! በሜዳው ላይ ያለው ዓለት ሆይ በእናንተ ላይ ነኝ ይላል እግዚአብሔር። "ሊያጠቃን በእኛ ላይ የሚወርድ ማነው?" ወይም "ወደ ቤታችን የሚገባ ማን ነው?" ለምትሉት፣ እኔ በእናንተ ላይ ነኝ።
\v 14 የሥራችሁ ፍሬ በእናንተ ላይ እንዲመጣባችሁ መድቤያለሁ ይላል እግዚአብሔር፤ በዱርዋም ውስጥ እሳትን አነድዳለሁ፣ በዙሪያዋም ያለውን ሁሉ ይበላል።
\s5
\c 22
\p
\v 1 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ወደ ይሁዳ ንጉሥ ቤት ውረድና በዚያም ይህን ቃል ተናገር።
\v 2 እንዲህም በል፣ 'በዳዊት ዙፋን የምትቀመጥ የይሁዳ ንጉሥ ሆይ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስማ። አንተና የእርሱ ባርያዎች የሆናችሁ፣ በእነዚህም በሮች የመትገቡት ሕዝቦቹ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።
\v 3 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ፍርድንና ጽድቅን አድርጉ፣ የተዘረፈውንም ከጨቋኙ እጅ አድኑ። በምድራችሁ ያለውን እንግዳ፣ ወይም የትኛውንም ወላጅ አልባ ወይም መበለቲቱን አትበድሉ። አታምፁባቸው፣ ወይም በዚህ ስፍራ ንጹሕ ደምን አታፍስሱ።
\s5
\v 4 እነዚህንም ነገሮች ብታደርጉ፣ ያን ጊዜ በዳዊት ዙፋን የሚቀመጡ ነገሥታት በሰረገሎችና በፈረሶች ላይ ተቀምጠው በዚህ ቤት በሮች ይገባሉ። እርሱም፣ ባርያዎቹም፣ ሕዝቡም እንዲሁ ይገባሉ!
\v 5 ነገር ግን ከእኔ የተነገሩትን እነዚህን ቃሎች ባትሰሙ፣ ይህ ንጉሣዊ ቤተመንግሥት እንደሚጠፋ በራሴ ምያለሁ" ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 6 እግዚአብሔር ስለ ይሁዳ ንጉሥ ቤት እንዲህ ይላልና፣ 'አንተ በእኔ ዘንድ እንደ ገለዓድ፣ ወይም እንደ ሊባኖስ ራስ ነህ። ነገር ግን፣ በእርግጥ ምድረ በዳ፣ ማንም እንደማይቀመጥባቸው ከተሞች አደርግሃለሁ።
\v 7 እንዲመጡባችሁ አጥፊዎችን በእናንተ ላይ አዘጋጅቻለሁ! የተመረጡትንም የዝግባ ዛፎቻችሁን ይቈርጣሉ፣ በእሳትም ውስጥ ይጥሉአቸዋል።
\s5
\v 8 ከዚያም ብዙ አሕዛብ በዚህች ከተማ አጠገብ ያልፋሉ። ሁሉም ባልንጀሮቻቸውን፣ "እግዚአብሔር በዚህች ታላቅ ከተማ ለምን እንዲህ አደረገ?" ይላሉ።
\v 9 ሌላኛውም፣ "የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ትተው ለሌሎች አማልክት ስለ ሰገዱ ስላመለኩአቸውም ነው" ብለው ይመልሳሉ።
\s5
\v 10 ለሞተው አታንቡ። አታልቅሱለትም። ነገር ግን ከእንግዲህ ወዲህ አይመለስምና፣ የተወለደባትንም አገር አያይምና ወደምርኮ ለሚሄደው በእርግጥ አልቅሱ።
\s5
\v 11 በአባቱ በኢዮአስ ፋንታ ስለ ነገሠው ከዚህም ስፍራ ስለ ወጣው ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮስያስ ልጅ ስለ ሰሎ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል።
\v 12 'በተማረከባት አገር ይሞታል እንጂ ወደዚህ አይመለስም፣ ይህችንም አገር ከእንግዲህ ወዲህ አያይም።'
\s5
\v 13 ቤቱን ያለ ጽድቅ ሰገነቱንም በግፍ ለሚሠራ፣ ሌሎችንም አሠርቶ፣ ክፍያ ለማይሰጣቸው።
\v 14 'ለራሴ ሰፊ የላይኛ ቤት፣ ትልቅም ሰገነት እሠራለሁ ለሚል፣ መስኮትንም ለሚያወጣ፣ በዝግባም ሥራ ለሚያስጌጥ፣ በቀይ ቀለምም ለሚቀባው ወዮለት።'
\s5
\v 15 የዝግባ እንጨት እንዲኖርህ ስለፈለግህ መልካም ንጉሥ የሚያደርግህ ይህ ነውን? በውኑ አባትህ አይበላምና አይጠጣም ነበርን፣ ፍርድንና ጽድቅንስ አያደርግም ነበርን? በዚያም ጊዜ ነገሮች መልካም ሆነውለት አልነበረምን።
\v 16 ለድሀውና ችግረኛው ፍርድን ይፈርድ ነበር። በዚያም ጊዜ መልካም ሆኖለት ነበር። እኔን ማወቅ ማለት ይህ አይደለምን? ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 17 ዓይንህና ልብህ ግን ለስስት፣ ንጹሕ ደምንም ለማፍሰስ፣ ዓመፅንና ግፍንም ለመሥራት ብቻ ካልሆነ በቀር ሌላ ነገር የለውም።
\v 18 ስለዚህ እግዚአብሔር ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮስያስ ልጅ ስለ ኢዮአቄም እንዲህ ይላል፦ "ወዮ፣ ወንድሜ ሆይ!" ወይም፣ "ወዮ፣ እኅቴ ሆይ!' እያሉ አያለቅሱለትም፣ ወይም 'ወዮ፣ ጌታዬ!' አሊያም 'ወዮ፣ ግርማዊነትዎ!' እያሉ አያለቅሱለትም።
\v 19 በአህያ ቀብር ይቀበራል፣ ከኢየሩሳሌምም በር ወደ ውጭ ተጐትቶ ይጣላል።
\s5
\v 20 ወደ ሊባኖስ ወጥተሽ ጩኺ። በባሳን ድምፅሽን አንሺ። ውሽሞችሽ ሁሉ ይጠፋሉና ከበዓባሪም ተራሮች ሆነሽ ጩኺ።
\v 21 በደኅንነትሽ ጊዜ ተናገርሁሽ፣ አንቺ ግን 'አልሰማም' አልሽ። ከወጣትነትሽ ጀምሮ ቃሌን አለመስማትሽ ልማድሽ ነው።
\s5
\v 22 በግ ጠባቂዎችሽን ሁሉ ነፋስ ይጠብቃቸዋል፣ ውሽሞችሽም ተማርከው ይሄዳሉ። በዚያን ጊዜም ስለ ክፋትሽ ሁሉ ታፍሪያለሽ ትዋረጂማለሽ።
\v 23 አንቺ በሊባኖስ የምትቀመጪ፣ በዝግባ ዛፍም ውስጥ ጎጆሽን የምትሠሪ ሆይ፣ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ሕማም በያዘሽ ጊዜ እንዴት ታጓሪያለሽ።"
\s5
\v 24 "እኔ ሕያው ነኝና የይሁዳ ንጉሥ የኢዮአቄም ልጅ ኢኮንያን የቀኝ እጄ ማኅተም ቢሆን ኖሮ እንኳ፣ ከዚያ እነቅልህ ነበር፤ ይላል እግዚአብሔር።
\v 25 ነፍስህንም ለሚሹት ለምትፈራቸውም እጅ፣ ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር ለከለዳውያንም እጅ እሰጥሃለሁ።
\v 26 አንተንም የወለደችህንም እናትህን ወዳልተወለዳችሁባት ወደ ሌላ አገር እጥላችኋለሁ፣ በዚያም ትሞታላችሁ።
\s5
\v 27 ይመለሱባትም ዘንድ ወደሚመኟት ወደዚያች ምድር ተመልሰው አይመጡም።
\v 28 በውኑ ይህ ሰው ኢዮአቄም የተናቀና የተሰበረ የሸክላ ዕቃ ነውን? ወይስ እርሱ ለአንዳች የማይረባ የሸክላ ዕቃ ነውን? እርሱና ዘሩስ በማያውቋት ምድር ስለ ምን ተጥለው ወደቁ?
\s5
\v 29 ምድር ሆይ፣ ምድር ሆይ፣ ምድር ሆይ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሚ!
\v 30 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ከዚህ ሰው ዘር የሚከናወን በዳዊትም ዙፋን ላይ የሚቀመጥ በይሁዳም የሚነግሥ እንግዲህ አይገኝምና። መካን በዘመኑም የማይከናወንለት ሰው ብላችሁ ጻፉ።"
\s5
\c 23
\p
\v 1 "የማሰማርያዬን በጎች ለሚያጠፉና ለሚበትኑ እረኞች ወዮላቸው! ይላል እግዚአብሔር።"
\v 2 ስለዚህ፣ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሕዝቡን ለሚጠብቁ እረኞች እንዲህ ይላል፣ "በጎቼን በትናችኋል ደግሞም አባርራችኋቸዋል። በጭራሽ አልተንከባከባችኋቸውም። ይህንን እወቊ! ለሥራችሁ ክፋት መልሼ እከፍላችኋለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር
\s5
\v 3 እኔ ራሴ የመንጋዬን ቅሬታ ካባረርኋቸው ምድር ሁሉ እሰበስባለሁ፣ ፍሬያማ ወደሚሆኑበትና ወደሚበዙበት ወደ መሠማሪያቸው እመልሳቸዋለሁ።
\v 4 ከዚያም ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይፈሩና እንዳይደነግጡ የሚጠብቋቸውን እረኞች አስነሣላቸዋለሁ። ከእነርሱ አንዳቸውም አይጐድሉም፣ ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 5 ተመልከቱ፣ ለዳዊት ጻድቅ ቅርንጫፍን የማስነሣበት ዘመን ይመጣል፣ ይላል እግዚአብሔር። እርሱም እንደ ንጉሥ ይገዛል፤ ብልፅግናን ያመጣል፣ በምድሪቱም ላይ ፍትህንና ጽድቅን ይፈጽማል።
\v 6 በዘመኑም ይሁዳ ይድናል፣ እስራኤልም በአስተማማኝ ደህንነት ይቀመጣል። የሚጠራበትም ስም፦ እግዚአብሔር ጽድቃችን ነው ተብሎ ነው።
\s5
\v 7 ስለዚህ፣ ተመልከቱ፣ ከእንግዲህ 'የእስራኤልን ልጆች ከግብጽ ምድር ያወጣ ሕያው እግዚአብሔርን!' የማይባልበት ዘመን ይመጣል፣ ይላል እግዚአብሔር።
\v 8 ይልቊን፣ 'የእስራኤልን ቤት የዘር-ሐረግ ከሰሜን ምድርና ከተሰደዱባቸው ምድሮች ሁሉ ያወጣና የመራ ሕያው እግዚአብሔርን!' ይባላል፤ እነርሱም በገዛ ራሳቸው ምድር ይቀመጣሉ።"
\s5
\v 9 ስለ ነቢያት፣ ልቤ በውስጤ ተሰብሮአል፣ አጥንቶቼም ሁሉ ታውከዋል። ከእግዚአብሔር እና ከቅዱስ ቃሉም የተነሣ እንደ ሰካራም ሰው፣ የወይን ጠጅ እንዳሸነፈውም ሆኛለሁ።
\v 10 ምድር በአመንዝሮች ተሞልታለችና። ከዚህ መርገም የተነሣ ምድር አለቀሰች። የምድረ በዳ ማሰማርያዎች ደርቀዋል። የእነዚህ ነብያት አካሄድ ክፉ ነው፤ ኃይላቸውም በትክክለኛው መንገድ ጥቅም ላይ አልዋለም።
\s5
\v 11 "ነብያትና ካህናትም ረክሰዋል። እንደውም፣ በቤቴ ውስጥ ክፋታቸውን አግኝቻለሁ! ይላል እግዚአብሔር።
\v 12 ስለዚህ መንገዳቸው በጨለማ እንዳለች ድጥ ስፍራ ትሆንባቸዋለች። እነርሱም ይገፈተሩበታል። በውስጧም ይወድቁባታል። እኔም በምቀጣቸው ዓመት ክፉ ነገርን እልክባቸዋለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 13 በሰማርያ ነቢያት ላይ የሚያስቀይም ነገርን አይቻለሁ። በበኣል ትንቢት ይናገራሉ፣ ደግሞም ሕዝቤንም እስራኤልን ያስታሉ።
\v 14 በኢየሩሳሌምም ነቢያት ላይ የሚያስደነግጥ ነገሮችን አይቻለሁ፦ ያመነዝራሉ ደግሞም በሐሰት ይመላለሳሉ። የክፉ አድራጊዎችን እጅ ያበረታሉ፤ ማንም ከክፋቱ አልተመለሰም። ሁሉም እንደ ሰዶም ነዋሪዎቿም እንደ ገሞራ ሆኑብኝ!"
\v 15 ስለዚህ ነብያትን በተመለከተ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ተመልከቱ፣ ከኢየሩሳሌም ነቢያት ዘንድ ርኵሰት በምድር ሁሉ ላይ ወጥቶአልና እሬትን አበላቸዋለሁ የተመረዘንም ውኃ አጠጣቸዋለሁ።"
\s5
\v 16 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ትንቢት የሚናገሩላችሁን የነቢያትን ቃል አትሰሙ። ሐሰተኝነትን ያስተምሩአችኋል! ከእግዚአብሔር አፍ ሳይሆን ከገዛ አሳባቸው የወጣውን ራእይ ይናገራሉ።
\v 17 ያለማቋረጥ ለሚንቁኝ እንዲህ ይላሉ፣ 'እግዚአብሔር ሰላም ይሆንላችኋል ብሎአል።' በገዛ ራሱ የልብ እልከኝነት ለሚሄድ ሁሉ፣ 'ክፉ ነገር አያገኛችሁም።' ይላሉ።
\v 18 ይሁን እንጂ ቃሉን ያይና ይሰማ ዘንድ በእግዚአብሔር ምክር የቆመ ማን ነው? ለቃሉ አትኩሮት ሰጥቶ የሰማ ያደመጠስ ማን ነው?
\s5
\v 19 ተመልከቱ፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ እየመጣ ያለ ዐውሎ ነፋስ አለ! የእርሱም ቍጣና የሚገለባብጥ ዐውሎ ነፍስ ወጥቶአል። በዓመፀኞች ራስ ላይ ይገለባበጣል።
\v 20 የእግዚአብሔር ቍጣ የልቡን አሳብ ሠርቶ እስኪፈጽም ድረስ አይመለስም። በመጨረሻው ዘመን፣ ትገነዘቡታላችሁ።
\s5
\v 21 እነዚህን ነብያት እኔ አልላክኋቸውም። በድንገት ተገኙ። ምንም አልነገርኳቸውም፣ ነገር ግን እንደዚያም ሆኖ ትንቢትን ተናገሩ።
\v 22 በምክሬ ግን ቆመው ቢሆን ኖሮ፣ ለሕዝቤ ቃሌን ባሰሙ ነበር፤ ከክፉም ቃሎቻቸው እንዲሁም ከብልሹ ሥራቸው በመለሱአቸው ነበር።
\s5
\v 23 እኔ የቅርብ አምላክ ብቻ ነኝ ደግሞም የራቀ አምላክ አይደለሁም? ይላል እግዚአብሔር።
\v 24 ሰው ላየው እንዳልችል በስውር ሊሸሸግ ይችላልን? ሰማይንና ምድርንስ አልሞላምን? ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 25 በስሜ ሐሰትን የሚናገሩት የነብያት ያሉትን ነገር ሰምቻለሁ። እነርሱም 'ህልም አልሜ ነበር! ህልም አልሜ ነበር!' ብለዋል።
\v 26 ሐሰትን ከአሳባቸው በሚተነብዩ፣ የልባቸውንም ማታለል በሚተነብዩ ነቢያት ይህ የሚቀጥለው እስከ መቼ ነው?
\v 27 በሚናገሯቸው ሕልሞች ሕዝቤ ስሜን እንዲረሳ ለማድረግ ያቅዳሉ፣ እያንዳንዱ ለጎረቤቱ ልክ አባቶቻቸው ለበኣል ሲሉ ስሜን እንደ ረሱ ያደርጋሉ።
\s5
\v 28 የሚያልም ነቢይ ሕልሙን ይናገር። ነገር ግን ቃሌን የነገርኩት፣ ቃሌን በእውነተኝነት ይናገር። ገለባ ከስንዴ ጋር ምን አለው? ይላል እግዚአብሔር።
\v 29 ቃሌ እንደ እሳት፣ ድንጋዩም እንደሚያደቅቅ መዶሻ አይደለችምን? ይላል እግዚአብሔር።
\v 30 ስለዚህ፣ ተመልከቱ፣ እኔ ቃልን ከሌላኛው ሰው ሰርቆ ቃሉ ከእኔ ዘንድ መጥቷል በሚሉት ነብያት ላይ ነኝ፣ ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 31 ተመልከቱ፣ ትንቢትን ለማወጅ ምላሳቸውን በሚጠቀሙት ነብያት ላይ ነኝ፣ ይላል እግዚአብሔር።
\v 32 ተመልከቱ፣ በሐሰት በሚያልሙ፣ ከዚያም በሚናገሩትና በዚህም መልኩ በሐሰታቸውና በትምክህታቸውም ሕዝቤን በሚያስቱ በነቢያት ላይ ነኝ፣ ይላል እግዚአብሔር። እኔም አልላክኋቸውምና ትእዛዛትንም አልሰጠኋቸውምና በእነርሱ ላይ ነኝ። ስለዚህም ለዚህ ሕዝብ በእርግጥም አይጠቅሟቸውም ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 33 ይህ ሕዝብ ወይም ነቢይ ወይም ካህን፣ 'የእግዚአብሔር ዐዋጅ ምንድር ነው?' ብለው ቢጠይቊህ፣ 'እናንተን ትቻችኋለሁና የምን ዐዋጅ ነው?' ይላል እግዚአብሔር ልትላቸው ይገባል።
\v 34 'የእግዚአብሔር ዐዋጅ ይህ ነው፣' የሚሉትን ነብያትን፣ ካህናትን እና ሕዝቡን በተመለከተ፣ ያን ሰውና ቤቱን እቀጣለሁ።
\s5
\v 35 እያንዳንዱ ሰው ለጎረቤቱ፣ እንዲሁም እያንዳንዱ ሰው ለወንድሙ፣ 'እግዚአብሔር የመለሰው ምንድር ነው?' ደግሞስ 'እግዚአብሔር ምን ዐወጀ?' ማለትህን ቀጥል።
\v 36 ከእያንዳንዱ ሰው የሆነው እያንዳንዱ ዐዋጅ የገዛ ራሱ መልእክት ይሆንበታልና፣ እንዲሁም የሕያው እግዚአብሔርን ቃል ለውጣችኋልና፣ ስለ እግዚአብሔር ዐዋጅ ከእንግዲህ ልትናገሩ አይገባችሁም።
\s5
\v 37 ለነቢዩ የምትጠይቀው ይህንን ነው፣ 'እግዚአብሔር ምን መለሰልህ? እግዚአብሔር ምን ዐወጀ?'
\v 38 ከዚያም፣ ከእግዚአብሔር የሆነውን ዐዋጅ ትናገራለህ፣ ነገር ግን እግዚአብሔር ይህንን ይላል፣ "ይህ የእግዚአብሔር ዐዋጅ ነው አትበሉ።" ብዬ ትእዛዝን የላክሁባችሁ ቢሆንም፣ እናንተ ግን "የእግዚአብሔር ዐዋጅ ይኸውላችሁ፣" አላችሁ።
\v 39 ስለዚህም፣ ተመልከቱ፣ አንሥቻችሁ ለእናንተና ለአባቶቻችሁ ከሰጠሁት ከተማ ጋር ከእኔ ዘንድ ልወረውራችሁ ነው።
\v 40 ከዚያም የማይረሳ ዘላለማዊ እፍረትን እና ስድብን አኖርባችኋለሁ።"
\s5
\c 24
\p
\v 1 እግዚአብሔር አንድ ነገር አሳየኝ። እነሆ፣ በእግዚአብሔር መቅደስ ፊት ሁለት ቅርጫት በለስ ተቀምጠው ነበር። (ይህ ራእይ የታየው የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር የይሁዳን ንጉሥ የኢዮአቄምን ልጅ ኢኮንያንን፣ የይሁዳንም አለቆች፣ ጠራቢዎችንና ብረት ሠራተኞችን ከኢየሩሳሌም ማርኮ ወደ ባቢሎን ካፈለሳቸው በኋላ ነበር።)
\v 2 በአንደኛው ቅርጫት አስቀድሞ እንደበሰለ በለስ የሚመስል እጅግ መልካም በለስ ነበረበት፤ ነገር ግን በሁለተኛው ቅርጫት ውስጥ ከክፋቱ የተነሣ ይበላ ዘንድ የማይቻል እጅግ ክፉ በለስ ነበረበት።
\v 3 እግዚአብሔርም፣ "ኤርምያስ ሆይ፣ ምንታያለህ?" አለኝ። እኔም፣ "በለስን። እጅግ መልካም የሆነ በለስ፣ ከክፋቱም የተነሣ ይበላ ዘንድ የማይቻል እጅግ ክፉ የሆነ በለስ አያለሁ።" አልሁ።
\s5
\v 4 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፣
\v 5 "የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እንደዚህ እንደ መልካሙ በለስ፣ እንዲሁ ከዚህ ስፍራ ወደ ከለዳውያን ምድር የሰደድሁትን የይሁዳን ምርኮ ለጥቅማቸው እመለከተዋለሁ።
\v 6 ዓይኔንም ለመልካም በእነርሱ ላይ አደርጋለሁ፣ ወደዚህችም ምድር እመልሳቸዋለሁ። እገነባቸዋለሁ እንጂ አላፈርሳቸውም። እተክላቸዋለሁ፣ እንጂ አልነቅላቸውም።
\v 7 ከዚያም፣ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ የሚያውቅ ልብ እሰጣቸዋለሁ፣ እኔ እግዚአብሔር ነኝና። በፍጹምም ልባቸው ወደ እኔ እንዲመለሱ፣ ሕዝብ ይሆኑኛል፣ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ።
\s5
\v 8 ነገር ግን ከክፋቱ የተነሣ ይበላ ዘንድ እንደማይቻል እንደ ክፉው በለስ፣ እንዲሁ የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን አለቆቹንም በዚህችም አገር የሚቀሩትን የኢየሩሳሌም ቅሬታ በግብጽም አገር የሚቀመጡትን እጥላቸዋለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር።
\v 9 በማሳድዳቸውም ስፍራ ሁሉ ለስድብና ለምሳሌ፣ ለማላገጫና ለእርግማን ይሆኑ ዘንድ በምድር መንግሥታት ሁሉ ለመበተን አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ።
\v 10 ለእነርሱና ለአባቶቻቸውም ከሰጠኋቸው ምድር እስኪጠፉ ድረስ በመካከላቸው ሰይፍንና ራብን፣ ቸነፈርንም እሰድዳለሁ።"
\s5
\c 25
\p
\v 1 በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም በአራተኛው ዓመት፣ በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር በመጀመሪያው ዓመት፣ ስለ ይሁዳ ሕዝብ ሁሉ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው።
\v 2 ይህንም ቃል ነቢዩ ኤርምያስ ለይሁዳ ሕዝብ ሁሉና በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ ሁሉ እንዲህ ሲል ተናገረ።
\s5
\v 3 "ከይሁዳ ንጉሥ ከአሞጽ ልጅ ከኢዮስያስ አሥራ ሦስተኛው ዓመት ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ባሉት በእነዚህ በሀያ ሦስቱ ዓመታት፣ የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ ሲመጣ ነበር። እነግራችሁም ነበር። እነግራችሁ ነበር፣ ነገር ግን አልሰማችሁም።
\v 4 እግዚአብሔርም ባርያዎቹን ነቢያትን ሁሉ ወደ እናንተ ላከ። እነርሱም ለመውጣት ጉጉዎች ነበሩ፣ ነገር ግን እናንተ አላደመጣችሁም ትኩረትም አልሰጣችሁትም።
\s5
\v 5 እነዚህ ነብያት፣ 'እያንዳንዱ ሰው ከክፉ መንገዱና ከሥራችሁ ብልሹነት ተመለሱና እግዚአብሔር ከጥንት ጊዜያት ጀምሮ ቋሚ ስጦታ አድርጎ ለእናንተና ለአባቶቻችሁ በሰጣችሁ ምድር ተቀመጡ።
\v 6 ታመልኩአቸው፣ ትሰግዱላቸውም ዘንድ ሌሎችን አማልክት አትከተሉ፣ ክፉም እንዳያደርግባችሁ በእጃችሁ ሥራ አታስቈጡኝ አለ።
\s5
\v 7 ለእናንተ ጕዳት እንዲሆን በእጃችሁ ሥራ ታስቈጡኝ ዘንድ አልሰማችሁኝም፣ ይላል እግዚአብሔር።
\v 8 ስለዚህ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ቃሌን አልሰማችሁምና፣
\v 9 ተመልከቱ፣ የሰሜንን ወገኖች ሁሉ ባርያዬ ከሆነው ከባቢሎን ንጉሥ ናብከደነዖር ጋር ለመሰብሰብ ትእዛዝን እልካለሁ፤ በዚህችም ምድር በሚቀመጡባትም ሰዎች፣ በዙሪያዋም ባሉ በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ ላይ አመጣቸዋለሁ። ለማጥፋትም እለያቸዋለሁ። ለመጨነቂያና ለማፍዋጫም ለዘላለምም ባድማ አደርጋቸዋለሁ።
\s5
\v 10 ከእነርሱም የእልልታን ድምፅና የደስታን ድምፅ፣ የወንድ ሙሽራን ድምፅና የሴት ሙሽራን ድምፅ፣ የወፍጮንም ድምፅ የመብራትንም ብርሃን አጠፋለሁ።
\v 11 ከዚያም ይህች ምድር ሁሉ ባድማና መደነቂያ ትሆናለች፣ ከዚያም እነዚህ አሕዛብ ለባቢሎን ንጉሥ ሰባ ዓመት ይገዛሉ።
\s5
\v 12 ሰባው ዓመትም የሚፈጸምበት ጊዜ ይመጣል፣ የባቢሎንን ንጉሥና ያንን ሕዝብ፣ የከለዳውያንን ምድር ስለ ኃጢአታቸው እቀጣለሁ፣ የማያበቃ ባድማ አደርጋታለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር።
\v 13 በዚያችም ምድር ላይ የተናገርሁትን ቃሌን ሁሉ፣ እንዲሁም፣ ኤርምያስ በአሕዛብ ሁሉ ላይ የተነበየውን በዚህች መጽሐፍ የተጻፈውን ሁሉ በዚያች ምድር አመጣለሁ።
\v 14 ብዙ ሌሎች አሕዛብና ታላላቆች ነገሥታት ከእነዚህ ሕዝቦች ውስጥ ባርያዎችን ያደርጋሉ። እኔም ስለ አደራረጋቸውና ስለ እጃቸው ሥራ እከፍላቸዋለሁ።"
\s5
\v 15 የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይለኛል፣ "የዚህን ቍጣ የወይን ጠጅ ጽዋ ከእጄ ውሰድ፣ አንተን ለምሰድድባቸው አሕዛብ ሁሉ አጠጣቸው።
\v 16 ከምሰድድባቸውም ሰይፍ የተነሣ ይጠጣሉ፣ ይሰናከላሉ፣ በእብደት ይለፈልፋሉ።
\s5
\v 17 ስለዚህ ጸዋውን ከእግዚአብሔር እጅ ወሰድሁ፣ ከዚያም እግዚአብሔርም እኔን ለላከባቸው አሕዛብ ሁሉ አጠጣኋቸው።
\v 18 በዚህ ዛሬ እንደሆኑት ሁሉ ባድማና መደነቂያ፣ ማፍዋጫም፣ እርግማንም አደርጋቸው ዘንድ ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች፣ ነገሥታትዋንም፣ አለቆችዋንም አጠጣኋቸው።
\s5
\v 19 ሌሎች ሕዝቦችም እንዲሁ ሊጠጡት ይገባል፦ የግብጽ ንጉሥ ፈርዖንና ባርያዎቹ፤ አለቆቹና ሕዝቦቹ ሁሉ፤
\v 20 የተደባለቀ ቅርስ ሕዝቦች ሁሉ፣ የዖፅ ምድር ነገሥታት ሁሉ፣ የፍልስጥኤም ምድር ነገሥታትንም ሁሉ፣ አስቀሎና፣ ጋዛ፣ አቃሮን የአዞጦን ቅሬታ ሁሉ፤
\v 21 ኤዶምያስ፣ ሞዓብ፣ እና የአሞንም ሕዝቦች፤
\s5
\v 22 የጢሮስና ሲዶና ነገሥታ፣ በባህሩ ማዶ ያለች የደሴት ነገሥታትም፣
\v 23 ድዳን፣ ቴማን፣ ቡዝን፣ በራሳቸው ጎንና ጎን ጠጕራቸውን የሚቈርጡትን ሁሉ።
\s5
\v 24 እነዚህም ሕዝቦች እንዲሁ ሊጠጡት ይገባል፦ የዓረብ ነገሥታት ሁሉ፣ በምድረ በዳ የሚኖሩት የድብልቅ ቅርስ ሕዝብ ነገሥታት ሁሉ፣
\v 25 የዘምሪ ነገሥታት ሁሉ፣ የኤላም ነገሥታት ሁሉ፣ የሜዶን ነገሥታት ሁሉ፤
\v 26 የቀረቡና የራቁ፣ አንዱ ከሌላው ጋር ያሉ የሰሜን ነገሥታትንም ሁሉ፣ በምድር ገጽ ላይ ያሉ የዓለም መንግሥታት ሁሉ አጠጣኋቸው። በመጨረሻም፣ የባቢሎን ንጉሥ ከእነርሱ በኋላ ይጠጣል።
\s5
\v 27 "'የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመካከላችሁ ከምሰድደው ሰይፍ የተነሣ ጠጡ፣ ስከሩ፣ አስታውኩ፣ ውደቁ፣ ከእንግዲህም ወዲህ አትነሡ' በላቸው፤ አለኝ።
\v 28 እንዲጠጡ ጽዋውን ከእጅህ ለመቀበል እንቢ ቢሉ፣ 'የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በእርግጥ ትጠጡታላችሁ፤ በላቸው።
\v 29 ተመልከቱ፣ ስሜ በተጠራባት ከተማ ላይ ጥፋትን አመጣለሁ፣ እናንተ ራሳችሁ ያልተቀጣችሁ ትሆናላችሁን? በምድር በሚኖሩ ሁሉ ላይ ሰይፍን እጠራለሁና ከቅጣት ነፃ አትሆኑም፣ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።'
\s5
\v 30 ስለዚህ፣ አንተ ራስህ፣ ኤርምያስ እነዚህን ቃሎች ሁሉ ትተነብይባቸዋለህ፣ እንዲህም ትላቸዋለህ፦ 'እግዚአብሔር ከበላይ ሆኖ ይጮኻል፣ ከቅዱስ ማደሪያውም ሆኖ ድምፁን ያሰማል። በማደሪያው ላይ እጅግ ይጮኻል፣ ወይንን ሲሚጠምቁ እንደሚዘምሩት በምድር በሚኖሩ ሁሉ ላይ ይጮኻል።
\v 31 እግዚአብሔር ከአሕዛብ ጋር ክርክር አለውና ድምፅ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ይደርሳል። ከሥጋ ለባሽ ሁሉ ጋር በፍትህ ይፋረዳል። ኃጢአተኞችንም ለሰይፍ አሳልፎ ይሰጣል፣ ይላል እግዚአብሔር።'
\s5
\v 32 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ተመልከቱ፣ ጥፋት ከሕዝብ ወደ ሕዝብ ይወጣል፣ ደግሞም ጽኑም ዐውሎ ነፍስ ከሩቅ የምድር ዳርቻ ይነሣል።
\v 33 ያን ጊዜ የእግዚአብሔር ግዳዩች ከምድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ይበዛሉ፤ አይለቀስላቸውም፤ አይሰበሰቡም፣ ወይም አይቀበሩም። በምድር ላይ እንደ ጉድፍ ይሆናሉ።
\s5
\v 34 እረኞች አልቅሱ፣ ለእርዳታም ጩኹ! በመንጋው ውስጥ አውራ የሆናችሁት ሕዝቦች በመሬት ላይ ተንከባለሉ። ትታረዱና ትበተኑ ዘንድ ቀናችሁ መጥቷልና። እንደ ተመረጡ በጎች ትወድቃላችሁ።
\v 35 ወደእረኞች ለመሸሸግ ማምለጥ ይቀራል።
\v 36 እግዚአብሔር ማሰማርያቸውን አጥፍቶአልና የእረኞች ጩኸት ድምፅ፣ የመንጋ አውራዎችም ልቅሶ ሆኖአል።
\s5
\v 37 ከእግዚአብሔር ጽኑ ቊጣ የተነሣ የሰላም ማሰማሪያ ይፈርሳል።
\v 38 እንደ ታዳጊ አንበሳ መደቡን ለቅቆአል፣ ከአስጨናቂውም ሰይፍና ከጽኑ ቍጣው የተነሣ ምድራቸው አስፈሪ ሆናለችና።"
\s5
\c 26
\p
\v 1 በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም መንግሥት መጀመሪያ ይህ ቃል ከእግዚአብሔር ዘንድ መጣና እንዲህ አለ፣
\v 2 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በቤቴ አደባባይ ቁም፣ በእግዚአብሔርም ቤት ውስጥ ይሰግዱ ዘንድ ለሚመጡት ለይሁዳ ከተሞች ሁሉ ንገራቸው። እንድትነግራቸው ያዘዝሁህን ቃል ሁሉ ንገራቸው። አንዲትም ቃል አትጉደል!
\v 3 ምናልባት ይሰሙ፣ ከክፉ መንገዳቸውም ይመለሱ ይሆናል፤ እኔም ስለ ሥራቸው ክፋት ያሰብሁባቸውን ክፉ ነገር እተዋለሁ።
\s5
\v 4 ስለዚህ እንዲህ በላቸው፣ 'እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በፊታችሁ በሰጠኋት ሕጌ ትሄዱ ዘንድ ባትሰሙኝ፣
\v 5 በጽናት ወደ እናንተ የላክኋቸውን የባሪያዎቼን የነቢያትን ቃል ባትሰሙ፣ ነገር ግን አላደመጣችኋቸውም!
\v 6 ያኔ ይህንን ቤት እንደ ሴሎ አደርገዋለሁ፤ ይህችንም ከተማ ለምድር አሕዛብ ሁሉ እርግማን አደርጋታለሁ።"
\s5
\v 7 ኤርምያስ በእግዚአብሔር ቤት ይህንን ቃል ሲናገር ካህናቱ፣ ነቢያቱ፣ ሕዝቡም ሁሉ ሰሙ።
\v 8 ኤርምያስም ለሕዝቡ ሁሉ ይናገር ዘንድ እግዚአብሔር ያዘዘውን ነገር ሁሉ በፈጸመ ጊዜ፣ ካህናት፣ ነቢያትና ሕዝቡም ሁሉ፣ ያዙትና "በእርግጥ ትሞታለህ!
\v 9 በእግዚአብሔር ስም ተንብየህ ይህ ቤት እንደ ሴሎ ይሆናል፣ ይህችም ከተማ ነዋሪ የማይገኝባት ወና ትሆናለች ብለህ ለምን ትንቢት ተናገርህ?" አሉት። ሕዝቡም ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ በኤርምያስ ላይ በዐመጽ ተሰብስበው ነበር።
\s5
\v 10 ከዚያም የይሁዳ አለቆች ይህን ሰሙና ከንጉሥ ቤት ወደ እግዚአብሔር ቤት ሄዱ። በአዲሱም በእግዚአብሔር ቤት ደጅ መግቢያ ተቀመጡ።
\v 11 ካህናቱና ነብያቱም ለአለቆቹና ለሕዝቡ ሁሉ ተናገሩ። እንዲህም አሉ፣ "በጆሮአችሁ እንደ ሰማችሁ በዚህች ከተማ ላይ ትንቢት ተናግአልና ይህ ሰው ሞት የሚገባው ነው!" አሉ።
\v 12 ስለዚህ ኤርምያስ ለአለቆችና ለሕዝቡ ሁሉ እንዲህ ብሎ ተናገረ፣ "በሰማችሁት ቃል ሁሉ፣ በዚህች ቤትና በዚህች ከተማ ላይ ትንቢት እናገር ዘንድ እግዚአብሔር ልኮኛል።
\s5
\v 13 አሁንም መንገዳችሁንና ሥራችሁን አሳምሩ፣ እግዚአብሔርም የተናገረባችሁን ጥፋት እንዲተው፣ የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ድምፅ ስሙ።
\v 14 ተመልከቱኝ! እኔ ራሴ በእጃችሁ ነኝ። በዐይናችሁ ፊት መልካምና ቅን የመሰላችሁን አድርጉብኝ።
\v 15 ነገር ግን ይህን ቃል ሁሉ በጆሮአችሁ እናገር ዘንድ በእውነት እግዚአብሔር ወደ እናንተ ልኮኛልና ብትገድሉኝ ንጹሕ ደምን በራሳችሁና በዚህች ከተማ በሚኖሩባትም ላይ እንድታመጡ በእርግጥ እወቁ።"
\s5
\v 16 አለቆቹና ሕዝቡም ሁሉ ለካህናትና ለነቢያት፣ "ይህ ሰው በአምላካችን በእግዚአብሔር ስም ተናግሮናልና ሊሞት አይገባውም" አሉ።
\v 17 ከዚያም ከምድሪቱ ሽማግሌዎች ሰዎች ተነሥተው ለመላው የሕዝቡ ጉባኤ ሁሉ እንዲህ ብለው ተናገሩ።
\s5
\v 18 እነርሱም፣ "ሞሬታዊው ሚክያስ በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ዘመን ይተነብይ ነበረ። ለይሁዳም ሕዝብ ሁሉ ተንብዮ 'የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጽዮን እንደ እርሻ ትታረሳለች፣ ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፣ የቤተመቅደሱም ተራራ እንደ ዱር ከፍታ ይሆናል' ብሎ ተናገረ።
\v 19 በውኑ የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስና ሕዝቡ ሁሉ ገደሉትን? በውኑ እግዚአብሔርን አልፈራምን? ወደ እግዚአብሔርስ አልተማለሉምን? እግዚአብሔርስ የተናገረባቸውን ክፉ ነገር አይተውምን? እኛም በገዛ ሕይወታችን ላይ ታላቅ ክፋት እናደርጋለንን?"
\s5
\v 20 ደግሞም በእግዚአብሔር ስም ትንቢት የተናገረ አንድ ሰው ነበረ፣ እርሱም የቂርያትይዓሪም ሰው የሸማያ ልጅ ኦርዮ ይባል ነበር፤ በዚህችም ከተማ በዚህችም ምድር ላይ ከኤርምያስ ቃል ጋር የተስማማ ትንቢት ተናገረ።
\v 21 ነገር ግን ንጉሡ ኢዮአቄም እና ወታደሮቹ ሁሉ እንዲሁም አለቆቹም ሁሉ ቃሉን በሰሙ ጊዜ ንጉሡ ሊገድለው ሞከረ፤ ነገር ግን ኦርዮም ይህን ሲሰማ ፈርቶ ሸሸ ወደ ግብጽም ገባ።
\s5
\v 22 ንጉሡም ኢዮአቄም የዓክቦርን ልጅ ኤልናታንን ከእርሱም ጋር ሌሎችን ሰዎች ወደ ግብጽ ላካቸው፤
\v 23 ኦርዮንን ከግብጽ አውጥተው ወደ ንጉሡ ኢዮአቄም ይዘውት መጡ። ከዚያም ኢዮአቄም በሰይፍ ገደለውና ሬሳውን ተራ በሆኑ ሰዎች መቃብር ውስጥ ጣለው።
\v 24 ነገር ግን በሕዝቡ እጅ እንዳይሰጥና እንዳይገድሉት የሳፋን ልጅ የአኪቃም እጅ ከኤርምያስ ጋር ነበረች።
\s5
\c 27
\p
\v 1 በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም መንግሥት መጀመሪያ ይህ ቃል ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ መጣ።
\v 2 እግዚአብሔር እንዲህ ይለኛል፣ "እስራትና ቀንበር ለራስህ ሥራ። በአንገትህም ላይ አድርግ።
\v 3 ከዚያም ወደ ይሁዳ ንጉሥም ወደ ሴዴቅያስ፣ ወደ ኢየሩሳሌም በመጡት መልእክተኞች እጅ ወደ ኤዶምያስ ንጉሥ፣ ወደ ሞዓብም ንጉሥ፣ ወደ አሞንም ልጆች ንጉሥ፣ ወደ ጢሮስም ንጉሥ፣ ወደ ሲዶናም ንጉሥ ላካቸው።
\v 4 ለጌቶቻቸውም እንዲነግሩ እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፣ 'የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ለጌቶቻችሁ ልትነግሯቸው የሚገባው ይህንን ነው፣
\s5
\v 5 እኔ ራሴ ምድሪቱን በታላቅ ኃይሌና በተዘረጋችው ክንዴ ፈጥሬአለሁ። በምድርም ፊት ላይ ያሉትን ሰዎችንና እንስሶችን ጭምር ፈጥሬያለሁ። በዐይኔም ዘንድ ትክክል ለሆነው ለማንኛውም ሰው እሰጣታለሁ።
\v 6 አሁንም፣ እነዚህን ምድሮች ሁሉ ለባርያዬ ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር እጅ አሳልፌ እሰጣታለሁ። እንዲሁም ያገለግሉት ዘንድ በሜዳዎች ያሉትን ሕያዋን ነገሮችን ደግሞ ሰጥቼዋለሁ።
\v 7 የገዛ ራሱም ምድር ፍጻሜ እስኪመጣ ድረስ አሕዛብ ሁሉ ለእርሱና ለልጅ ልጅ ልጁም ይገዛሉ። ከዚያም ብዙ አሕዛብና ታላላቆች ነገሥታት እርሱን ያስገዙታል።
\s5
\v 8 ለባቢሎን ንጉሥም ለናቡከደነፆር የማያገለግለውን፣ ከባቢሎንም ንጉሥ ቀንበር በታች አንገቱን ዝቅ የማያደርገውን ሕዝብና መንግሥት፣ ያን ሕዝብ በእጁ እስካጠፋው ድረስ በሰይፍና በራብ፣ በመቅሰፍትም እቀጣለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 9 እናንተ ደግሞ! 'ለባቢሎን ንጉሥ አታገልግሉ' የሚሉአችሁን ነቢያቶቻችሁን፣ ሟርተኞቻችሁን፣ ሕልም አላሚዎቻችሁንና ቃላተኞቻችሁን፣ መተተኞቻችሁንም መስማት አቊሙ።
\v 10 ከምድራቸሁ አርቀው ሊልኳችሁ፣ እኔም እንዳሳድዳችሁ፣ እናንተም እንድትሞቱ ሐሰተኛ ትንቢትን ይናገሩላችኋልና።
\v 11 ነገር ግን ከባቢሎን ንጉሥ ቀንበር በታች አንገቱን ዝቅ የሚያደርገውንና የሚያገለግለውን ሕዝብ በአገሩ ላይ እተዋቸዋለሁ፤ እነርሱም ያርሱአታል ቤቶችንም ይሠሩባታል።"
\s5
\v 12 ለይሁዳ ንጉሥ ለሴዴቅያስም በዚህ ቃል ተናገርሁ ይህንንም መልእክት ሰጠሁት፣ "ከባቢሎን ንጉሥ ቀንበር በታች አንገታችሁን ዝቅ አድርጉና ለእርሱና ለሕዝቡ አገልግሉ፣ በሕይወትም ትኖራላችሁ።
\v 13 ለባቢሎን ንጉሥ ይገዛ ዘንድ እንቢ ስላለ ሕዝብ እግዚአብሔር እንደ ተናገረ፣ አንተና ሕዝብህ በሰይፍና በራብ በመቅሰፍትም ለምን ትሞታላችሁ?
\s5
\v 14 ሐሰተኛን ትንቢት ይናገሩላችኋልና፣ 'ለባቢሎን ንጉሥ አታገልግሉ' የሚሉአችሁን የነቢያትን ቃል አትስሙ።
\v 15 'እኔ አልላክኋቸውምና፤ ነገር ግን እኔ እንዳሳድዳችሁ፣ እናንተና ትንቢት የሚናገሩላችሁ ነቢያትም እንድትጠፉ በስሜ ሐሰተኛ ትንቢትን ይናገራሉ፣' ይላል እግዚአብሔር።"
\s5
\v 16 ይህንን ለካህናትና ለዚህ ሕዝብ ሁሉ እንዲህ ብዬ ተናገርሁ፣ "እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተንብየውላችሁ 'ተመልከቱ! የእግዚአብሔር ቤት ዕቃ አሁን ከባቢሎን ይመለሳል!' የሚሉአችሁን የነቢያቶቻችሁን ቃል አትስሙ። እነርሱ ውሸትን ይተነብዩላችኋል።
\v 17 እነርሱንም አትስሟቸው። የባቢሎንን ንጉሥ ልታገለግሉና በሕይወት ልትኖሩ ይገባችኋል። ይህችስ ከተማ ስለ ምን ባድማ ትሆናለች?
\v 18 እነርሱ ግን ነቢያት ከሆኑ፣ የእግዚአብሔርም ቃል በእውነት ወደእነርሱ ቢመጣ፣ በእግዚአብሔር ቤትና በይሁዳ ንጉሥ ቤት በኢየሩሳሌምም የቀረችው ዕቃ ወደ ባቢሎን እንዳትሄድ ወደ ሠራዊት ጌታ ወደ እግዚአብሔር ይለምኑ።
\s5
\v 19 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር የይሁዳን ንጉሥ የኢዮአቄምን ልጅ ኢኮንያንንና የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ከበርቴዎች ሁሉ ማርኮ
\v 20 ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን ባፈለሳቸው ጊዜ ስላልወሰዳቸው ዓምዶች ስለ ኵሬውም፣ ስለ መቀመጫዎቹም በዚህችም ከተማ ስለ ቀረች ዕቃ ሁሉ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል።
\s5
\v 21 በእግዚአብሔር ቤትና በይሁዳ ንጉሥ ቤት በኢየሩሳሌምም ስለ ቀረችው ዕቃ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣
\v 22 'እነርሱ ወደ ባቢሎን ትወሰዳለች እስከምጐበኛትም ቀን ድረስ በዚያ ትኖራለች፣ ይላል እግዚአብሔር፤ ከዚያም አወጣታለሁ ወደዚህም ስፍራ እመልሳታለሁ።"
\s5
\c 28
\p
\v 1 በዚያም ዓመት በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ መንግሥት መጀመሪያ በአራተኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ነቢዩ የገባዖን ሰው የዓዙር ልጅ ሐናንያ በእግዚአብሔር ቤት በካህናትና በሕዝብ ሁሉ ፊት እንዲህ ብሎ ተናገረኝ።
\v 2 "የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ይናገራል፣ የባቢሎን ንጉሥ ያኖረውን ቀንበር ሰብሬአለሁ።
\s5
\v 3 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ከዚህች ስፍራ ወደ ባቢሎን ያጋዛትን የእግዚአብሔርን ቤት የሆኑትን ዕቃዎች ሁሉ በሁለት ዓመት ውስጥ ወደዚህች ስፍራ እመልሳታለሁ።
\v 4 ከዚያም ወደ ባቢሎንም የሄዱትን የይሁዳን ንጉሥ የኢዮአቄምን ልጅ ኢኮንያንንና የይሁዳን ምርኮ ሁሉ ወደዚህች ስፍራ እመልሳቸዋለሁ፤ የባቢሎንን ንጉሥ ቀንበር እሰብራለሁና።"
\s5
\v 5 ነቢዩ ኤርምያስም በካህናቱና በእግዚአብሔር ቤት በቆሙት ሕዝብ ሁሉ ፊት ለነቢዩ ሐናንያ ተናገረ።
\v 6 ነብዩም ኤርምያስ እንዲህ አለ፣ "እግዚአብሔር እንዲህ ያድርግ! የእግዚአብሔርን ቤት ዕቃ ምርኮውንም ሁሉ ከባቢሎን ወደዚህ ስፍራ በመመለስ እግዚአብሔር የተናገረውን ትንቢት ይፈጽም።
\v 7 ይሁን እንጂ፣ በጆሮህና በሕዝብህ ጆሮ ሁሉ የምናገረውን ይህን ቃል ስማ።
\s5
\v 8 ከጥንት ከእኔና ከአንተ በፊት የነበሩ ነብያት በብዙ አገርና በታላላቅ መንግሥታት ላይ ስለ ሰልፍና ስለ ክፉ ነገር፣ ስለ መቅሰፍትም ትንቢት ተናገሩ።
\v 9 ስለዚህም ሰላም እንደሚኖር የተናገረ ነቢይ፣ የነቢዩ ቃል በተፈጸመ ጊዜ፣ ያኔ እግዚአብሔር በእውነት የሰደደው ነቢይ እንደ ሆነ ይታወቃል።"
\s5
\v 10 ነቢዩም ሐናንያ ቀንበሩን ከነቢዩ ከኤርምያስ አንገት ወስዶ ሰበረው።
\v 11 ከዚያም ሐናንያ በሕዝብ ሁሉ ፊት፣ "እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ልክ እንደዚሁ፣ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ የባቢሎንን ንጉሥ የናቡከደነፆርን ቀንበር ከአሕዛብ ሁሉ አንገት እሰብራለሁ" አለ። ከዚያም ነብዩ ኤርምያስ መንገዱን ሄደ።
\s5
\v 12 ነቢዩም ሐናንያ ቀንበሩን ከነቢዩ ከኤርምያስ አንገት ከሰበረ በኋላ፣ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፣
\v 13 "ሂድና ለሐናንያ እንዲህ ብለህ ንገረው፣ 'እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ አንተ የእንጨት ቀንበርን ሰብረሃል፣ እኔ ግን በእርሱ ፋንታ የብረትን ቀንበር እሠራለሁ።'
\v 14 የእስራኤልም አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር እንዲያገለግሉ የብረትን ቀንበር በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ አንገት ላይ አድርጌአለሁ። እነርሱም ያገለግሉታል። እንዲገዛቸውም የምድረ በዳ አራዊትን ደግሞ ሰጥቼዋለሁ።"
\s5
\v 15 ቀጥሎ፣ ነብዩ ኤርምያስ ነብዩን ሐናንያን፣ "ሐናንያ ሆይ፣ አድምጥ! ይህ ሕዝብ በሐሰት እንዲታመን አድርገሃል እንጂ እግዚአብሔር አልላከህም።
\v 16 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተመልከት ከምድር ላይ እሰድድሃለሁ። በእግዚአብሔር ላይ ዐመፅን ተናግረሃልና በዚህ ዓመት ትሞታለህ።" አለው።
\v 17 ነብዩም ሐናንያ በዚያው ዓመት በሰባተኛው ወር ሞተ።
\s5
\c 29
\p
\v 1 ነቢዩ ኤርምያስ ከምርኮ ሽማግሌዎች መካከል ወደ ተረፉት፣ ወደ ካህናቱም፣ ወደ ነቢያቱም፣ ናቡከደነፆር ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን ማርኮ ወዳፈለሰውም ሕዝብ ሁሉ ከኢየሩሳሌም የላከው የደብዳቤው ቃል ይህ ነው።
\v 2 ይህም የሆነው ንጉሡ ኢኮንያን፣ እቴጌይቱ እናቱ፣ ከፍተኛ መኮንኖቹ፣ የይሁዳና የኢየሩሳሌም አለቆች፣ ጠራቢዎችና ብረት ሠራተኞችም ከኢየሩሳሌም ከወጡ በኋላ ነው።
\v 3 ኤርምያስ የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ ወደ ባቢሎን ንጉሥ ወደ ናቡከደነፆር በላካቸው በሳፋን ልጅ በኤልዓሣና በኬልቅያስ ልጅ በገማርያ እጅ ደብዳቤውን እንዲህ ሲል ላከው።
\s5
\v 4 ጥቅሉ እንዲህ ይላል፣ "የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን ላስማረክኋቸው ምርኮኞች ሁሉ እንዲህ ይላል፣
\v 5 'ቤት ሠርታችሁ ኑሩባቸው፣ አታክልትም ተክላችሁ ፍሬዋን ብሉ፤
\s5
\v 6 ሚስቶችን ውሰዱ፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ውለዱ፤ ከዚያም ለወንዶች ልጆቻችሁ ሚስቶችን ውሰዱ፣ ሴቶች ልጆቻችሁንም ለባሎቻቸው ስጡ። እነርሱም ወንዶችንና ሴቶችን ልጆች ይውለዱ፤ ከዚያም ተባዙ ጥቂቶችም አትሁኑ።
\v 7 በእርስዋም ሰላም ይሆንላችኋልና ወደ እርስዋ ላስማርክኋችሁ ከተማ ሰላምን ፈልጉ፣ ከእኔ ዘንድ ማልዱ።'
\s5
\v 8 የእስራኤልም አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፣ 'በመካከላችሁ ያሉት ነቢያቶቻችሁና ምዋርተኞቻችሁ አያታልሉአችሁ፣ እናንተም ራሳችሁ የምታልሙትን ሕልም አትስሙ።
\v 9 በስሜ ሐሰተኛ ትንቢትን ይናገሩላችኋልና። እኔም አልላክኋቸውም። ይላል እግዚአብሔር።'
\s5
\v 10 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ባቢሎን ለሰባ ዓመታት በገዛቻችሁ ጊዜ፣ ወደዚህም ስፍራ እመልሳችሁ ዘንድ እረዳችኋለሁ፣ ደግሞም መልካሚቱን ቃሌን እፈጽምላችኋለሁ።
\v 11 ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ ራሴ አውቃለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የጥፋት አይደለም።
\s5
\v 12 እናንተም ወደ እኔ ትጠራላችሁ፣ ሄዳችሁም ወደ እኔ ትጸልያላችሁ፣ እኔም እሰማችኋለሁ።
\v 13 እናንተ ትሹኛላችሁ፣ በፍጹም ልባችሁም ከሻችሁኝ ታገኙኛላችሁ።
\v 14 ከእናንተም ዘንድ እገኛለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ ምርኮአችሁንም እመልሳለሁ፤ ከአሕዛብም ሁሉ ዘንድ እናንተንም ከበተንሁበት ስፍራ ሁሉ እሰበስባችኋለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ እናንተንም ለምርኮ ወዳፈለስሁበት ስፍራ እመልሳችኋለሁ።'
\s5
\v 15 እናንተም፣ እግዚአብሔር በባቢሎን ነቢያትን አስነሥቶልናል ብላችኋልና፣
\v 16 እግዚአብሔር በዳዊት ዙፋን ስለ ተቀመጠ ንጉሥ፣ በዚያች ከተማ ለቆዩት ሕዝቦች ሁሉ፣ ከእናንተም ጋር ስላልተማረኩት ወንድሞቻችሁ፣ እንዲህ ይላል።
\v 17 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ተመልከቱ፣ ሰይፍንና ራብን፣ በሽታንም እሰድድባቸዋለሁ። ከክፋቱም የተነሣ ይበላ ዘንድ እንደማይቻል እንደ ክፉ በለስ አደርጋቸዋለሁ።
\s5
\v 18 በሰይፍም፣ በራብም፣ በመቅሠፍትም አሳዳድዳቸዋለሁ፣ ባሳደድሁባቸውም አሕዛብ ሁሉ ዘንድ ለመጠላት፣ ለመደነቂያ፣ ለማፍዋጫም፣ ለመሰደቢያም እንዲሆኑ በምድር መንግሥታት ሁሉ ዘንድ ለመበተን አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ።
\v 19 ይህም የሆነው ቃሌን ስላልሰሙ ነው፣ ይላል እግዚአብሔር፤ በማለዳ ተነሥቼ ባሪያዎቼን ነቢያትን ወደ እነርሱ ሰድጃለሁና፤ በተደጋጋሚ ላክኋቸው፣ እናንተ ግን አልሰማችሁም፣ ይላል እግዚአብሔር።'
\s5
\v 20 ስለዚህ ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን የሰደድኋችሁ ምርኮኞች ሁሉ ሆይ፣ እናንተ ራሳችሁ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፣
\v 21 'የእስራኤል አምላክ፣ እኔ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በስሜ ሐሰተኛ ትንቢትን ስለሚናገሩላችሁ ስለ ቆላያ ልጅ ስለ አክዓብና ስለ መዕሤያ ልጅ ስለ ሴዴቅያስ እንዲህ እላለሁ፦ ተመልከቱ፣ በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ። በዓይኖቻችሁም ፊት ይገድላቸዋል።
\s5
\v 22 ከዚያም በባቢሎን ያሉ የይሁዳ ምርኮኞች ሁሉ ስለ እነዚህ ሰዎች እርግማንን ይናገራሉ። እርግማኑም፦ እግዚአብሔር የባቢሎን ንጉሥ በእሳት እንደ ጠበሳቸው እንደ ሴዴቅያስና እንደ አክዓብ ያድርግህ የሚል ነው።
\v 23 በእስራኤል ዘንድ ስንፍና አድርገዋልና፣ ከጎረቤቶቻቸውም ሚስቶች ጋር አመንዝረዋልና፣ ያላዘዝኋቸውንም ቃል በስሜ በሐሰት ተናግረዋልና ይህ ይሆናል። እኔም አውቃለሁ ምስክርም ነኝ፣ ይላል እግዚአብሔር።"
\s5
\v 24 "ለኔሔላማዊው ለሸማያ እንዲህ በል፦
\v 25 'የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በኢየሩሳሌም ወዳለው ሕዝብ ሁሉ፣ ወደ ካህኑም ወደ መዕሤያ ልጅ ወደ ሶፎንያስ፣ ወደ ካህናቱም ሁሉ ደብዳቤዎችን በገዛ ስምህ እንዲህ ስትል ልከሃል፣
\v 26 "እያበደ ትንቢት የሚናገርን ሰው ሁሉ በእግር ግንድና በሠንሰለት ታኖረው ዘንድ በእግዚአብሔር ቤት አለቃ እንድትሆን እግዚአብሔር በካህኑ በዮዳሄ ፋንታ ካህን አድርጎሃል።
\s5
\v 27 አሁንስ፣ ትንቢት ተናጋሪውን የዓናቶቱን ሰው ኤርምያስን ስለ ምን አትገሥጸውም?
\v 28 እርሱ፣ 'ጊዜው የረዘመ ነው። ቤት ገንቡና በውስጡ ኑሩበት፣ አትክልትንም ተክላችሁ ፍሬዋን ብሉ' ብሎ ወደ እኛ ወደ ባቢሎን ልኮአል።"
\v 29 ካህኑም ሶፎንያስ ይህን ደብዳቤ ነብዩ ኤርምያስ እየሰማ አነበበው።
\s5
\v 30 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፣
\v 31 "'እግዚአብሔር ስለ ኔሔላማዊው ስለ ሸማያ እንዲህ ይላል፣ ብለህ ወደ ምርኮኞች ሁሉ ላክ፦ 'እኔ ሳልልከው ሸማያ ትንቢት ተናግሮላችኋልና፣ በሐሰትም እንድትታመኑ አድርጎአችኋልና፤
\v 32 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተመልከቱ፣ ኔሔላማዊውን ሸማያንና ዘሩን እቀጣለሁ። እኔም የማደርግላችሁን መልካሙን ነገር የሚያይ አንድም የእርሱ ሰው በመካከላችሁ አይኖርም። ለሕዝቤ የማደርገውን አንዱንም መልካም ነገር አያይም ይላል እግዚአብሔር። እርሱ በእኔ፣ በእግዚአብሔር ላይ በእምነት ያልሆነ ነገርን ተናግሯልና።"
\s5
\c 30
\p
\v 1 ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው፣ እንዲህም አለ፣
\v 2 "የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'የነገርኩህን ቃል ሁሉ በጥቅልል ላይ ጻፈው።
\v 3 ተመልከት፣ የሕዝቤን የእስራኤልንና የይሁዳን ምርኮ የምመልስባት ዘመን ይመጣልና፣ ይላል እግዚአብሔር። ለአባቶቻቸውም ወደ ሰጠኋት ምድር እመልሳቸዋለሁ፣ እነርሱም ይገዙአታል።
\s5
\v 4 እግዚአብሔር ስለ እስራኤልና ስለ ይሁዳ የተናገረው ቃል ይህ ነው፣
\v 5 "እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'የሚያስፈራ ድምፅ ሰምተናል፤ የፍርሃት ነው እንጂ የሰላም አይደለም።
\s5
\v 6 ጠይቁ፣ ወንድ ይወልድ እንደ ሆነ ተመልከቱ። እያንዳንዱ ወጣት ሰው እጁን በወገቡ ላይ ያደረገው ለምንድነው? እንደ ወላድ ሴት፣ ፊታቸው ሁሉ ወደ ጥቁረት የተለወጠው ለምንድነው?
\v 7 ወዮ! ያ ቀን ታላቅ ይሆናልና፣ እርሱንም የሚመስል የለምና። ያ የያዕቆብ የመከራ ዘመን ነው፣ ነገር ግን ከእርሱ ይድናል።
\s5
\v 8 በዚያ ቀን እንዲህ ይሆናል፣ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ቀንበርን ከአንገትህ እሰብራለሁ፣ እስራትህንም እበጥሳለሁ፣ ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ ለሌላ አትገዛም።
\v 9 ነገር ግን ለአምላካቸው ለእግዚአብሔር፣ በእነርሱ ላይ ንጉሥ ለማደርግላቸው ለንጉሣቸው ለዳዊትም ያገለግላሉ።
\s5
\v 10 ስለዚህ፣ ባሪያዬ ያዕቆብ ሆይ፣ አትፍራ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ አንተም እስራኤል ሆይ፣ አትደንግጥ። ተመልከቱ፣ አንተን ከሩቅ፣ ዘርህንም ከምርኮ አገር አድናለሁና። ያዕቆብም ይመለሳል ሰላምም ይሆናል፤ ደህንነቱም ይጠበቃል፣ ከዚያም በኋላ ማንም አያስፈራውም።
\v 11 አድንህ ዘንድ ከአንተ ጋር ነኝና፣ ይላል እግዚአብሔር። አንተንም የበተንሁባቸውን አሕዛብ ፍጹም ማብቂያቸው እንዲመጣ አደርጋለሁ። አንተን ግን ፈጽሜ አላጠፋህም፣ በፍትህ እቀጣሃለሁ፣ ያለ ቅጣትም ከቶ አልተውህም።'
\s5
\v 12 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ስብራትህ የማይፈወስ፣ ቍስልህም ያመረቀዘ ነው።
\v 13 ጉዳይህን የሚሟገትልህ የለም፣ ቍስልህንም የሚፈውስ መድኃኒት የለህም።
\s5
\v 14 አፍቃሪዎችሽ ሁሉ ረስተውሻል። አይፈልጉሽምም፣ በደልሽ ታላቅ ስለሆነ ኃጢአትሽም ስለ በዛ፣ በጠላት ማቍሰልና በጨካኝ አሠሪ ቅጣት አቍስዬሻለሁና።
\v 15 ሕመምሽ የማይፈወስ ሆኖአልና ስለ ስብራትሽ ለምን ትጮያለሽ? በደልሽ ታላቅ ስለሆነ ኃጢአትሽም ስለ በዛ፣ ይህን አድርጌብሻለሁ።
\s5
\v 16 ስለዚህ የሚበሉሽ ሁሉ ይበላሉ፣ ጠላቶችሽም ሁሉ ወደ ምርኮ ይወሰዳሉ። የዘረፉሽም ይዘረፋሉ፣ የበዘበዙሽንም ሁሉ ለመበዝበዝ አሳልፌ እሰጣለሁ።
\v 17 እኔ ጤናሽን እመልስልሻለሁ ቍስልሽንም እፈውሳለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ ይህንንም የማደርገው፦ ማንም የማይሻት፤ የተጣለች ጽዮን" ብለው ጠርተውሻልና።
\s5
\v 18 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ተመልከቺ፣ የያዕቆብን ድንኳን ምርኮ እመልሳለሁ፣ ለቤቱም እራራለሁ። ከተማይቱም በፍርስራሽ ጉብታዋ ላይ ትሠራለች፣ ምሽጉም እንደ ዱሮው ይሆናል።
\v 19 ከዚያም ከእርሱ ዘንድ የምስጋናና የዘፋኞች ድምፅ ይወጣል፣ እኔም አበዛቸዋለሁ አላሳንሳቸውም፤ እንዳይዋረዱ እኔ አከብራቸዋለሁ።
\s5
\v 20 ከዚያም ሕዝቦቻቸው እንደ ቀድሞ ይሆናሉ፣ ማኅበራቸውም በፊቴ ጸንቶ ይኖራል፤ የሚያስጨንቋቸውንም ሁሉ እቀጣለሁ።
\v 21 መሪያቸው ከእነርሱ ውስጥ ይወጣል። እኔ ሳቀርበውና እርሱም ሲቀርበኝ ከመካከላቸው ይወጣል። ይህንን ባላደርግ፣ ወደ እኔ ለመቅረብ የሚደፍር ማን ነው? ይላል እግዚአብሔር።
\v 22 እናንተም ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ፣ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ።
\s5
\v 23 ተመልከቱ፣ የእግዚአብሔር ዐውሎ ነፋስ፣ ቍጣው ወጥቷል። ሳይቋረጥ የሚያገለባብጥ ዐውሎ ነፋስ ወጥቶአል። የክፉዎችንም ራስ ይገለባብጣል።
\v 24 የእግዚአብሔር ጽኑ ቍጣ የልቡን አሳብ ሠርቶ እስኪፈጽም ድረስ አይመለስም። በመጨረሻው ዘመን ታስተውሉታላችሁ።"
\s5
\c 31
\p
\v 1 "በዚያን ዘመን፣ ይላል እግዚአብሔር፣ ለእስራኤል ወገኖች ሁሉ አምላክ እሆናቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል።"
\v 2 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "እስራኤልን ለማረድ ከመጣው ሰይፍ የተረፈው ሕዝብ በምድረ በዳ ሞገስ አገኘ።"
\v 3 እግዚአብሔር በኃላፊው ጊዜ ተገለጠልኝና እንዲህ አለኝ፣ "እስራኤል ሆይ፣ በዘላለም ፍቅር ወድጄሻለሁ። ስለዚህ በኪዳን ታማኝነት ወደራሴ ሳብሁሽ።
\s5
\v 4 የእስራኤል ድንግል ሆይ፣ እንደ ገና እገነባሻለሁ አንቺም ትገነቢያለሽ። እንደ ገናም ከበሮሽን አንሥተሽ ከዘፋኞች ጋር ወደ ደስታ ጭፈራሽ ትወጫለሽ።
\v 5 እንደ ገናም በሰማርያ ተራሮች ላይ የወይን ቦታዎችን ትተክያለሽ፤ ገበሬዎች ይተክላሉ፣ ፍሬውንም በመልካም ይጠቀሙበታል።
\v 6 በኤፍሬምም ተራሮች ላይ ያሉ ተመልካቾች፣ 'ተነሡ፣ ወደ ጽዮን ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር እንውጣ.' ብለው የሚጮኹበት ቀን ይመጣልና።"
\s5
\v 7 እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፣ "ስለ ያዕቆብ በደስታ ጩኹ! ስለ አሕዛብም አለቆች በደስታ ጩኹ! ምስጋና ይሰማ። 'እግዚአብሔር ሕዝቡን፣ የእስራኤልን ቅሬታ አድኖአል' በሉ።
\s5
\v 8 ተመልከቱ፣ ከሰሜን ምድር አመጣቸዋለሁ። ከምድርም ዳርቻ እሰበስባቸዋለሁ። በመካከላቸውም ዕውሩና አንካሳው፣ ያረገዙ ሴቶችና ሊወልዱ ያሉ ሴቶች በአንድነት ይሆናሉ። ታላቅ ጉባኤ ሆነው ወደዚህ ይመለሳሉ።
\v 9 በልቅሶ መጡ፤ ልመናቸውን ሲያደርጉ እመራቸዋልሁ። በወንዝ ዳር በቀጥተኛ መንገድ አስኬዳቸዋለሁ። በእርሱም አይሰናከሉም፣ እኔ ለእስራኤል አባት እሆናለሁና፣ ኤፍሬምም በኵሬ ነውና።"
\s5
\v 10 "አሕዛብ ሆይ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፣ በሩቅም ላሉ ደሴቶች አውሩ። እናንተ አህዛብ፣ "እስራኤልን የበተነ እርሱ ይሰበስባታል፣ እረኛም መንጋውን እንደሚጠብቅ ይጠብቃታል" በሉ።
\v 11 እግዚአብሔር ያዕቆብን ተቤዥቶታል፣ ከበረታበትም እጅ አድኖታል።
\s5
\v 12 ከዚያም ይመጡና በጽዮን ተራራ ይፈነድቃሉ። ወደ እግዚአብሔርም መልካምነት፣ ወደ እህልና ወደ ወይን ጠጅ፣ ወደ ዘይትም፣ ወደ በጎችና ወደ ላሞች ይሰበሰባሉ። ነፍሳቸውም እንደ ረካች ገነት ትሆናለች፣ ከእንግዲህም ወዲህ ኃዘን አይሰማቸውም።
\s5
\v 13 በዚያን ጊዜ ደናግሉ በዘፈን ደስ ይላቸዋል፣ ወጣቶቹና ሽማግሌዎቹም በአንድ ላይ ይሆናሉ። ለቅሷቸውን ወደ ክብረ-በዓል እለውጣለሁና። እራራላቸዋለሁ፣ ከኅዘናቸውም ይልቅ እንዲፈነድቁ አደርጋቸዋለሁ።
\v 14 ከዚያም የካህናቱን ነፍስ በብዛት አረካታለሁ። ሕዝቤም መልካምነቴን ይጠግባል ይላል እግዚአብሔር።"
\s5
\v 15 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "የዋይታና የመራራ ለቅሶ ድምፅ በራማ ተሰማ። ስለ ልጆችዋ የምታለቅሰው ራሔል ናት። ከእንግዲህ አይኖሩምና ስለ ልጆችዋ መጽናናትን እንቢ አለች።"
\s5
\v 16 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ድምፅሽን ከለቅሶ፣ ዐይንሽንም ከእንባ ከልክዪ፤ ምክንያቱም ለመከራሽ ካሳ አለ፤ ልጆችሽ ከጠላት ምድር ይመለሳሉ።
\v 17 ለፍጻሜሽ ተስፋ አለ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ ልጆችሽም ወደ ዳርቻቸው ይመለሳሉ።"
\s5
\v 18 "ኤፍሬም፣ 'ቀጣኸኝ፣ እኔም ተቀጣሁ። እንዳልተገራ ወይፈን መልሰህ አምጣኝ፣ አንተ እግዚአብሔር አምላኬ ነህና እኔም እመለሳለሁ።
\v 19 ወደ አንተ ከተመለስሁ በኋላ፣ ተጸጸትሁ፤ ከሠለጠንሁም በኋላ፣ በኃዘን ጭኔን መታሁ፤ በወጣትነቴ በደልን ተሸክሜአለሁና አፈርሁ፣ ተዋረድሁ።'
\v 20 ኤፍሬም ለእኔ የከበረ ልጅ አይደለምን? ወይስ የምደሰትበት ሕጻን ነውን? በእርሱ ላይ በተናገርሁ ቍጥር፣ እንደዚያም ሆኖ በፍቅር አስበዋለሁ። በዚህ መልኩ ልቤ ትናፍቀዋለች። በእርግጥም እራራለታለሁ ይላል እግዚአብሔር።"
\s5
\v 21 ለራስሽ የመንገድ ምልክት አድርጊ። ለራስሽም መንገድን የሚመሩ ዓምዶችን ትከዪ። አሳብሽንም ልትሄጂበት ወደሚገባው ትክክለኛ መንገድ አድርጊ። የእስራኤል ድንግል ሆይ፣ ተመለሺ! ወደ እነዚህም ወደ ከተሞችሽ ተመለሺ።
\v 22 አንቺ እምነት የለሽ ልጅ ሆይ፣ እስከ መቼ ትቅበዘበዣለሽ? እግዚአብሔር በምድር ላይ አዲስ ነገር ፈጥሮአልና፤ ብርቱ ወንዶችን ለመጠበቅ ሴቶች ይከብባሉ።
\s5
\v 23 የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ሕዝቡን ወደ ምድራቸው ባመጣኋቸው ጊዜ፣ በይሁዳ ምድርና በከተሞችዋ እንዲህ ይላሉ፣ 'እርሱ የሚኖርብሽ የጽድቅ ማደሪያ፣ የቅድስና ተራራ ሆይ፣ እግዚአብሔር ይባርክሽ።'
\v 24 ይሁዳና ከተሞቹ ሁሉ በአንድነት በእርስዋ ይኖራሉ። ገበሬዎችና እረኞች ከመንጎቻቸው ጋር በዚያ ይገኛሉ።
\v 25 ለደከሙት የሚጠጡትን ውሃ እሰጣለሁና፣ በጥማት የሚሰቃዩትን ሁሉ በእርካታ እሞላለሁ።
\v 26 ከዚህም በኋላ ነቃሁ፣ እንቅልፌ የሚያነቃ እንደሆነ አስተዋልኩኝ።
\s5
\v 27 "ተመልከቱ፣ የእስራኤልን ቤትና የይሁዳን ቤት በሰውና በእንስሳ ዘር የምዘራበት ዘመን፣ እንደሚመጣ ተመልከቱ ይላል እግዚአብሔር።
\v 28 እንዲህም ይሆናል፣ አፈርሳቸውና፣ ክፉ አድርግባቸው ዘንድ እንደ ተጋሁባቸው፣ ነገር ግን በሚመጡት ዘመናት፣ እንዲሁ እሠራቸውና፣ እተክላቸው ዘንድ እተጋለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 29 በዚያ ዘመን ሰው ዳግመኛ እንዲህ አይልም፣ 'አባቶች መራራ የወይን ፍሬ በሉ፣ ነገር ግን የልጆች ጥርሶች ጠረሱ።'
\v 30 ነገር ግን ሰው ሁሉ በገዛ በደሉ ይሞታል፤ መራራውን የወይን ፍሬ የሚበላ ሁሉ ጥርሶቹ ይጠርሳሉ።
\s5
\v 31 ተመልከቱ፣ ከእስራኤል ቤትና ከይሁዳ ቤት ጋር አዲስ ቃል ኪዳን የምገባበት ወራት ይመጣል፣ ይላል እግዚአብሔር።
\v 32 ከግብጽ ምድር አወጣቸው ዘንድ እጃቸውን በያዝሁበት ቀን ከአባቶቻቸው ጋር እንደ ገባሁት ያለ ቃል ኪዳን አይደለም። ምንም እንኳን እኔ ባላቸው ብሆንም፣ እነርሱ ኪዳኔ ላይ ዐምጸዋልና፣ ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 33 ከእነዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ግን ይህ ነውና፣ ይላል እግዚአብሔር፦ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ፣ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ፣ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል።
\v 34 ከዚያም እያንዳንዱ ሰው ባልንጀራውን፣ ወይም እያንዳንዱ ሰው ወንድሙን፣ 'እግዚአብሔርን እወቅ ብሎ አያስተምርም፤ ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ያውቁኛልና፣ ይላል እግዚአብሔር። በደላቸውን እምራቸዋለሁና፣ ኃጢአታቸውንም ከእንግዲህ ወዲህ አላስብምና።"
\s5
\v 35 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ ፀሐይን በቀን የጨረቃንና የከዋክብትን ሥርዓት በሌሊት ብርሃን አድርጎ የሚሰጥ እግዚአብሔር ነው። እንዲተምሙም የባሕርን ሞገዶች የሚያናውጥ እርሱ ነው። ስሙ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው። እርሱ እንዲህ ይላል፣
\v 36 "እነዚህ ቋሚ ነገሮች ከእይታዬ ቢወገዱ፣ ይላል እግዚአብሔር፣ በዚያን ጊዜ ደግሞ የእስራኤል ዘር በፊቴ ሕዝብ እንዳይሆን ለዘላለም ይቀራል።"
\s5
\v 37 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ከፍ ያሉት ሰማያት ሊለኩ ቢችሉ፣ የምድርም መሠረት ከታች ቢመረመር፣ በዚያን ጊዜ ስላደረጉት ነገር ሁሉ የእስራኤልን ዘር ሁሉ እጥላለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር።"
\s5
\v 38 "ተመልከቱ፣ ከሐናንኤል ግንብ ጀምሮ እስከ ማዕዘኑ በር ድረስ ከተማ ለእግዚአብሔር የሚሠራበት ዘመን ይመጣል፣ ይላል እግዚአብሔር።
\v 39 የተለካበትም ገመድ ወደ ጋሬብ ኮረብታ በቀጥታ ወደ ፊት ይሄዳል፣ ወደ ጎዓም ይዞራል።
\v 40 የሬሳም ሸለቆ ሁሉ የአመድም እርሻ ሁሉ እስከ ቄድሮን ወንዝ ድረስ በምሥራቅ በኩል እስካለው እስከ ፈረሰ በር ማዕዘን ድረስ ለእኔ፣ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ይሆናል። ከእንግዲህም ወዲህ ለዘላለም አይነቀልም አይፈርስምም።"
\s5
\c 32
\p
\v 1 በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ በዐሥረኛው ዓመት፣ በናቡክደነፆር በዐሥራ ስምንተኛው ዓመት፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው።
\v 2 በዚያን ጊዜ፣ የባቢሎን ንጉሥ ሠራዊት ኢየሩሳሌምን ከብቦ ነበር፤ ነቢዩም ኤርምያስ በይሁዳ ንጉሥ ቤት በነበረው በግዞት ቤት አደባባይ ታስሮ ነበር።
\s5
\v 3 የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ በእስር አቆይቶት እንዲህ አለው፣ "ለምን እንዲህ ብለህ ትንቢት ትናገራለህ፣ 'እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተመልከት፣ ይህችን ከተማ ለባቢሎን ንጉሥ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፣ እርሱም ይይዛታል።
\v 4 የይሁዳም ንጉሥ ሴዴቅያስ ከከለዳውያን እጅ አያመልጥም፣ በእውነት በባቢሎን ንጉሥ እጅ አልፎ ይሰጣል፣ አፉ ለአፉ ይናገረዋል፣ ዐይኑም የንጉሡን ዐይን ያያል።
\v 5 ሴዴቅያስ ወደ ባቢሎን ይሄዳል፣ እኔም እስክጐበኘው ድረስ በዚያ ይሆናል፤ ይላል እግዚአብሔር፤ ከከለዳውያን ጋር ብትዋጉ አይሳካላችሁም።"
\s5
\v 6 ኤርምያስም እንዲህ አለ፣ "የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፣
\v 7 'ተመልከቱ፣ የአጐትህ የሰሎም ልጅ አናምኤል ወደ አንተ መጥቶ፣ "ትገዛው ዘንድ መቤዠቱ የአንተ ነውና በዓናቶት ያለውን እርሻዬን ግዛ ይልሃል።"
\s5
\v 8 ከዚያም፣ እግዚአብሔር እንደተናገረው ቃል፣ የአጐቴ ልጅ አናምኤል እኔ ወዳለሁበት ወደ ግዞቱ ቤት አደባባይ መጥቶ እንዲህ አለኝ፣ 'በብንያም አገር በዓናቶት ያለውን እርሻዬን፣ እባክህ ግዛ፤ የርስት መብቱ የአንተ ነውና፣ የመቤዠቱ መብትም የአንተ ነውና ለአንተ ግዛው።' ያን ጊዜ ይህ የእግዚአብሔር ቃል እንደ ሆነ አወቅሁ።
\v 9 ስለዚህ፣ በዓናቶት ያለውን እርሻ ከአጐቴ ልጅ ከአናምኤል ገዛሁ፣ ዐሥራ ሰባት ሰቅል ብርም መዘንሁለት።
\s5
\v 10 በውሉም ወረቀት ላይ ፈረምሁ አተምሁትም፣ ምስክሮችም እንዲመሰክሩ አስደረግሁ። ከዚያም ብሩን በሚዛን መዘንሁለት።
\v 11 ቀጥሎ፣ የታተመውንና የተከፈተውን የግዢ ውል ወረቀት ወሰድሁ፤
\v 12 የአጐቴም ልጅ አናምኤል፣ የውሉንም ወረቀት የፈረሙ ምስክሮች፣ በግዞትም ቤት አደባባይ የተቀመጡ አይሁድ ሁሉ እያዩ የውሉን ወረቀት ለመሕሤያ ልጅ ለኔርያ ልጅ ለባሮክ ሰጠሁት።
\s5
\v 13 በፊታቸውም እንዲህ ብዬ ባሮክን አዘዝሁት።
\v 14 'የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ እንዲህ ይላል፡- የታተመውንና የተከፈተውን ይህን የውል ወረቀት ውሰድ። ብዙ ቀን እንደተጠበቊ እንዲቆዩ በሸክላ ዕቃ ውስጥ አኑራቸው።
\v 15 የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ሰዎች በዚህች ምድር ቤትን፣ እርሻን፣ የወይን ቦታንም እንደ ገና ይገዛሉ።'
\s5
\v 16 ለኔርያ ልጅ ለባሮክም የውሉን ወረቀት ከሰጠሁት በኋላ፣ እንዲህ ብዬ ወደ እግዚአብሔር ጸለይሁ፣
\v 17 'ወዮ፣ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! ተመልከቱ! አንተ ብቻህን ሰማይንና ምድርን በታላቅ ኃይልህና በተዘረጋች ክንድህ ፈጥረሃል። ለአንተም እንደሚያቅትህ የተናገርከው ነገር የለም።
\v 18 ለብዙ ሺህ ምሕረት ታደርጋለህ፣ የአባቶችንም በደል ከእነርሱ በኋላ በልጆቻቸው ጭን ላይ ትመልሳለህ። ስምህ ታላቅና ኃያል አምላክ፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው።
\s5
\v 19 በጥበብ ታላቅ በአደራረግም ብርቱ ነህ፣ ለሁሉም እንደ መንገዱና እንደ ሥራው ፍሬ ትሰጥ ዘንድ ዐይኖችህ በሰዎች መንገድ ሁሉ ላይ ተገልጠዋል።
\v 20 እስከ ዛሬም ድረስ ምልክትንና ድንቅን ነገር በግብጽ ምድር አድርገሃል። እስከዛሬ ድረስ፣ በዚህ በእስራኤልና በሌሎች ሰዎች ሁሉ መካከል ስምህን አግንነሃል።
\v 21 በምልክትና በድንቅ ነገር፣ በብርቱ እጅና በተዘረጋች ክንድ በታላቅም ግርማ ሕዝብህን እስራኤልን ከግብጽ ምድር አውጥተሃልና።
\s5
\v 22 ከዚያም ትሰጣቸውም ዘንድ ለአባቶቻቸው የማልህላቸውን፣ ወተትና ማርን የምታፈስሰውን ምድር፣ ሰጠሃቸው።
\v 23 እነርሱም ገብተው ወረሱአት። ነገር ግን ቃልህን አልሰሙም ለሕግህም በመታዘዝ አልሄዱም። ይደረግ ዘንድ ካዘዝሃቸው ሁሉ ምንም አላደረጉም፣ ስለዚህ ይህን ጥፋት ሁሉ አመጣህባቸው።
\s5
\v 24 ተመልከቱ! የአፈር ድልድል ሊይዙአት እስከ ከተማይቱ ድረስ ቀርበዋል። ከሰይፍ፣ ከራብና፣ ከመቅሠፍት የተነሣ፣ ከተማይቱ ለሚዋጓት ለከለዳውያን እጅ ተሰጥታለች። እንደሚሆን የተናገርኸው ሆኖአልና፣ ደግሞም ተመልከቱ፣ አንተ ታየዋለህ።
\v 25 ከዚያም አንተ ራስህ፣ "ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፣ ምንም እንኳን ይህች ከተማ ለከለዳውያን እጅ ተላልፋ የምትሰጥ ቢሆንም፣ እርሻውን በብር ግዛ ምስክሮችንም ጥራ" አልኸኝ።
\s5
\v 26 ወደ ኤርምያስ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፣ እንዲህም አለ፣
\v 27 "ተመልከቱ! የሰው ዘር ሁሉ አምላክ እግዚአብሔር እኔ ነኝ። እፈጽመው ዘንድ የሚያቅተኝ ነገር አለን?
\v 28 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ተመልከቱ፣ ይህችን ከተማ ለከለዳውያን እጅና ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ። እርሱም ይይዛታል።
\s5
\v 29 ይህችን ከተማ የሚወጉ ከለዳውያን መጥተው በእሳት ያነድዱአታል፣ ያስቈጡኝም ዘንድ በሰገነታቸው ላይ ለበኣል ካጠኑባቸው፣ ለሌሎችም አማልክት የመጠጥን ቊርባን ካፈሰሱባቸው ቤቶች ጋር ያቃጥሉአታል።
\v 30 የእስራኤል ልጆችና የይሁዳ ልጆች ከወጣትነታቸው ጀምሮ በዐይኔ ፊት ክፉ ነገርን ብቻ አድርገዋል። የእስራኤልም ልጆች እኔን በእጃቸው ሥራ ከማስቈጣት በቀር ሌላ ሥራ አላደረጉምና፣ ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 31 ከፊቴ አስወግዳት ዘንድ ይህች ከተማ ከገነቧት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ቍጣዬንና መዓቴን ለማነሣሣት ሆናለችና። ስለዚህም ከፊቴ አስወግዳታለሁ።
\v 32 ምክንያቱም እኔን ያስቈጡኝ ዘንድ፣ እነርሱና ነገሥታቶቻቸው፣ አለቆቻቸውም፣ ካህናቶቻቸውም፣ ነቢያቶቻቸውም፣ የይሁዳም ሰዎች፣ በኢየሩሳሌምም የሚኖሩ፣ ስላደረጉት ስለ እስራኤል ልጆችና ስለ ይሁዳ ልጆች ክፋት ሁሉ ነው።
\s5
\v 33 ምንም እንኳን በጉጉት ያስተማርኳቸው ቢሆንም፣ ፊታቸውን ሳይሆን ጀርባቸውን ወደ እኔ መለሱ። ላስተምራቸው ሞከርኩ፣ ነገር ግን ተግሣጽን ይቀበሉ ዘንድ አንዳቸውም እንኳን አልሰሙም።
\v 34 ከዚያም፣ ያረክሱት ዘንድ፣ ስሜ በተጠራበት ቤት ውስጥ ርኩሰታቸውን አኖሩ።
\v 35 ቀጥሎም ይሁዳን ኃጢአት እንዲሠራ ለማድረግ፣ ይህንን ርኩሰት ያደርጉ ዘንድ፣ እኔ ያላዘዝሁትንና በልቤ ያላሰብሁትን ነገር፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ለሞሎክ በእሳት ያሳልፉ ዘንድ፣ በሄኖም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ያሉትን የበኣልን የኮረብታውን መስገጃዎች ሠሩ።
\s5
\v 36 አሁን እንግዲህ፣ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር፣ አንተ ስለ እርስዋ፣ 'በሰይፍና በራብ በመቅሰፍትም ለባቢሎን ንጉሥ እጅ ተሰጥታለች' ስለምትላት ከተማ እንዲህ ይላል።
\v 37 ተመልከቱ፣ በቍጣዬ፣ በመዓቴና በታላቅም መቅሠፍቴ እነርሱን ካሳደድሁባት አገር ሁሉ እሰበስባቸዋለሁ። ወደዚህም ስፍራ እመልሳቸዋለሁ፣ ተዘልለውም እንዲኖሩ አደርጋለሁ።
\s5
\v 38 ከዚያም እነርሱ ሕዝብ ይሆኑኛል፣ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ።
\v 39 ለእነርሱም፣ ከእነርሱም በኋላ ለልጆቻቸው መልካም ይሆንላቸው ዘንድ ለዘላለም እንዲፈሩኝ አንድ ልብና አንድ መንገድ እሰጣቸዋለሁ።
\v 40 ለእነርሱም ከማደርገው በጎነት አልመለስም ስል፣ ከእነርሱ ጋር የዘላለምን ቃል ኪዳን እገባለሁ። መፈራቴን በልባቸው ውስጥ አኖራለሁ። ከዚህ የተነሣ እኔን ከመከተል አይመለሱም።
\s5
\v 41 ከዚያም ለእነርሱ መልካምን በማድረግ ደስ ይለኛል። በታማኝነት በፍጹም ልቤና በፍጹም ነፍሴ በዚህች ምድር እተክላቸዋለሁ።
\v 42 እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፣ 'ይህን እጅግ ክፉ ነገር ሁሉ በዚህ ሕዝብ ላይ እንዳመጣሁ፣ እንዲሁ እንደማደርግላቸው የተናገርሁላቸውን በጎነት ሁሉ አመጣላቸዋለሁ።
\s5
\v 43 ከዚያም፣ እናንተ፣ "ይህች ያለ ሰውና ያለ እንሰሳ ያለች ባድማ ምድር ናት። ለከለዳውያንም እጅ ተሰጥታለች።" በምትሉአት ምድር እርሻን ይገዛሉ።
\v 44 ምርኮኞቻቸውንም እመልሳለሁና፣ በብንያም አገር በኢየሩሳሌምም ዙሪያ ባሉ ስፍራዎች፣ በይሁዳም ከተሞች በደጋውም ባሉ ከተሞች በቈላውም ባሉ ከተሞች፣ በደቡብም ባሉ ከተሞች፣ ሰዎች እርሻውን በብር ይገዛሉ በውሉም ወረቀት ፈርመው ያትማሉ ምስክሮችንም ይጠራሉ።"
\s5
\c 33
\p
\v 1 ኤርምያስ ገና በግዞት ቤት አደባባይ ታስሮ ሳለ የእግዚአብሔር ቃል ሁለተኛ ጊዜ መጣለትና እንዲህ አለው፣
\v 2 "ስሙ እግዚአብሔር የሆነ፣ ያደረገው እግዚአብሔር፣ ያጸናውም ዘንድ የሠራው እግዚአብሔር እንዲህ ይላል።
\v 3 'ወደ እኔ ጩኽ፣ እኔም እመልስልሃለሁ። አንተም የማታስተውለውን ታላቅና ኃይለኛ ነገርን አሳይሃለሁ።'
\s5
\v 4 የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር፣ ለአፈር ድልድልና ለምሽግ ስለ ፈረሱ ስለዚህች ከተማ ቤቶች፣ ስለ ይሁዳም ነገሥታት ቤቶች እንዲህ ይላልና።
\v 5 'ስለ ክፋታቸው ሁሉ ፊቴን ከዚህች ከተማ ስሰውር፣ ከለዳውያን ለመዋጋትና በቊጣዬ፣ እንዲሁም በመዓቴ በምገድላቸው ሰዎች ሬሳዎች ሊሞሏቸው እየመጡ ናቸው።
\s5
\v 6 ነገር ግን ተመልከቱ፣ ፈውስንና መድኃኒትን አመጣላታለሁ፣ እፈውሳቸውማለሁ፤ መትረፍረፍንም አመጣላቸዋለሁ፣ ሰላምንና የታማኝነትን ብዛት አመጣላቸዋለሁ።
\v 7 የይሁዳን ምርኮና የእስራኤልን ምርኮ መልሼ አመጣለሁ፣ ቀድሞም እንደ ነበሩ አድርጌ እሠራቸዋለሁ።
\v 8 እኔንም ከበደሉበት ኃጢአት ሁሉ አነጻቸዋለሁ። እኔንም የበደሉበትን ያመፀብኝንም ኃጢአታቸውን ሁሉ ይቅር እላለሁ።
\v 9 ይህችም ከተማ እኔ የምሠራላቸውን በጎነት ሁሉ በሚሰሙ እኔም ስላመጣሁላቸው መልካምነትና ሰላም ሁሉ በሚፈሩና በሚደነግጡ አሕዛብ ሁሉ ፊት ለደስታ ስም ለምስጋናም ለክብርም ትሆናለች።
\s5
\v 10 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ እናንተ፣ "ያለ ሰውና ያለ እንስሳ ያለች ባድማ ናት በምትሉአት በዚህች ስፍራ፣ የሚቀመጥባቸው በሌላ፣ ያለ ሰውና ያለ እንስሳ ባድማ በሆኑ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም ጎዳናዎች ጥፋት ሆኗል።"
\v 11 የሐሤት ድምፅና የደስታ ድምፅ፣ የወንድ ሙሽራ ድምፅና የሴት ሙሽራ ድምፅ፣ "እግዚአብሔር ቸር ነውና፣ ምሕረቱም ለዘላለም ነውና የሠራዊትን ጌታ እግዚአብሔርን አመስግኑ" የሚሉ ድምፅ በድጋሚ ይሰማል። ወደ እግዚአብሔርም ቤት የምስጋናን መሥዋዕት አምጡ፣ የምድርን ምርኮ ቀድሞ እንደ ነበረ አድርጌ እመልሳለሁና፣' ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 12 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ 'ባድማ ሆኖ፣ ያለ ሰውና ያለ እንስሳ ባለው በዚህ ስፍራ፣ በከተሞችም ሁሉ መንጎቻቸውን የሚያሳርፉት የእረኞች መኖሪያ ይሆናል።
\v 13 በደጋው ላይ ባሉ ከተሞች፣ በቈላውም ባሉ ከተሞች፣ በደቡብም ባሉ ከተሞች፣ እንዲሁም በብንያምም ምድር በኢየሩሳሌምም ዙሪያ ባሉ ስፍራዎች፣ በይሁዳም ከተሞች መንጎቹ በተቈጣጣሪው እጅ እንደ ገና ያልፋሉ፣' ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 14 'ተመልከቱ! ስለ እስራኤል ቤትና ስለ ይሁዳ ቤት የተናገርሁትን መልካም ቃል የምፈጽምበት ዘመን ይመጣል፤ ይላል እግዚአብሔር።
\v 15 በዚያም ዘመን በዚያም ጊዜ ለዳዊት የጽድቅን ቍጥቋጥ አበቅልለታለሁ፣ እርሱም ፍትህንና ጽድቅን በምድር ላይ ያደርጋል።
\v 16 በዚያም ዘመን ይሁዳ ይድናል ኢየሩሳሌምም በአስተማማኝ ሁኔታ ትቀመጣለች፤ የምትጠራበትም ስም፣ "እግዚአብሔር ጽድቃችን" ተብሎ ነው።
\s5
\v 17 እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ 'በእስራኤል ቤት ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ሰው ከዳዊት ዘንድ አይታጣም፤
\v 18 የሚቃጠለውንም መሥዋዕት የሚያቀርብ፣ የእህሉንም ቍርባን የሚያቃጥል፣ ሁልጊዜም የሚሠዋ ሰው ከሌዋውያን ካህናት ዘንድ በእኔ ፊት አይታጣም።"
\s5
\v 19 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፣
\v 20 "እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ 'ቀንና ሌሊት በወራቱ እንዳይሆን የቀን ቃል ኪዳኔንና የሌሊት ቃል ኪዳኔን ማፍረስ ብትችሉ፣
\v 21 ያኔ በዙፋኑ ላይ የሚነግሥ ልጅ ከእንግዲህ እንዳይሆንለት ከባሪዬ ከዳዊት ጋር፣ ከአገልጋዮቼም ከሌዋውያን ካህናት ጋር ያለው ቃል ኪዳኔ ደግሞ ይፈርሳል።
\v 22 የሰማይ ሠራዊት መቍጠር፣ የባሕርንም አሸዋ መስፈር እንደማይቻል፣ እንዲሁ የባሪያዬን የዳዊትን ዘርና የሚያገለግሉኝን ሌዋውያንን አበዛለሁ።"
\s5
\v 23 የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፣
\v 24 "ይህ ሕዝብ፣ 'እግዚአብሔር መርጧቸው የነበሩትን ሁለቱን ወገን ጥሎአቸዋል፤' ያለውን ነገር አትመለከትምን? በዚህ መልኩ በፊታቸው ከእንግዲህ ወዲህ ሕዝብ እንዳይሆን ሕዝቤን አቃልለዋል።
\s5
\v 25 እኔ፣ እግዚአብሔር እንዲህ እላለሁ፣ 'የቀንና የሌሊት ቃል ኪዳኔ የማይኖሩ ከሆነ፣ ወይም የሰማይንና የምድርንም ሥርዓት ያልጠበቅሁ እንደሆነ፣
\v 26 ያን ጊዜ በአብርሃም፣ በይስሐቅና፣ በያዕቆብም ዘር ላይ ገዦች ይሆኑ ዘንድ ከዘሩ እንዳልወስድ፣ የያዕቆብንና የባሪያዬን የዳዊትን ዘር እጥላለሁ። ምርኮአቸውን እመልሳለሁና፣ እምራቸውማለሁና።"
\s5
\c 34
\p
\v 1 ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል ይህ ነው። ይህ ቃል የመጣው የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆርና ሠራዊቱ ሁሉ፣ ከእጁም ግዛት በታች ያሉ የምድር መንግሥታት ሁሉ አሕዛብም ሁሉ ኢየሩሳሌምንና ከተሞችዋን ሁሉ ይወጉ በነበረ ጊዜ ነበር።
\v 2 'የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሂድ ለይሁዳም ንጉሥ ለሴዴቅያስ ተናገር እንዲህም በለው፣ "እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተመልከት፣ ይህችን ከተማ በባቢሎን ንጉሥ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ። በእሳትም ያቃጥላታል።
\v 3 አንተም በእርግጥ ትያዛለህ፣ በእጁም ተላልፈህ ትሰጣለህ እንጂ ከእጁ አታመልጥም። ዐይንህም የባቢሎንን ንጉሥ ዐይን ታያለች፤ ወደ ባቢሎን ስትሄድ፣ እርሱ ከአንተ ጋር አፍ ለአፍ ይነጋገራል።'
\s5
\v 4 የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ ሆይ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስማ! ስለ አንተ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'በሰይፍ አትሞትም።
\v 5 በሰላም ትሞታለህ። እንደ አባቶችህ የቀብር መቃጠል፣ ከአንተ በፊት እንደነበሩት ነገሥታት፣ እንዲሁ አካልህን ያቃጥላሉና። "ወየው፣ ጌታ ሆይ!" እያሉ ያለቅሱልሃል። አሁን እኔ ቃልን ተናግሬአለሁና፣ ይላል እግዚአብሔር።"
\s5
\v 6 ነቢዩ ኤርምያስ እነዚህን ቃሎች ሁሉ ለይሁዳ ንጉሥ ለሴዴቅያስ በኢየሩሳሌም ነገረው።
\v 7 የባቢሎንም ንጉሥ ሠራዊት ኢየሩሳሌምንና የቀሩትን የይሁዳን ከተሞች ሁሉ፦ ለኪሶንና ዓዜቃን ወጋ። እነዚህ የይሁዳ ከተሞች የተመሸጉ ከተሞች ሆነው ቀሩ።
\s5
\v 8 ንጉሡ ሴዴቅያስ በኢየሩሳሌም ከነበሩ ሕዝብ ሁሉ ጋር ነፃነትን ለማወጅ ስምምነት ካደረገ በኋላ፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው።
\v 9 እያንዳንዱ ሰው እስራኤላዊ የሆነውን ወንድ ባርያውንና ሴት ባርያውን ነፃነት ሊለቅ ይገባል። ማንም ሰው ከእንግዲህ ወዲህ በይሁዳ ውስጥ መሰል እስራኤላዊን ባርያ ሊያደርግ አይገባም።
\s5
\v 10 ስለዚህም ስምምነቱን የተቀላቀሉት መሪዎች ሁሉ እና ሕዝቡ ታዘዙ። እያንዳንዱ ሰው ወንድ እና ሴት ባርያዎቻቸውን ከእንግዲህ ወዲህ ባርያ ላያደርጓቸው ነፃ አደረጓቸው። እነርሱም ሰሙ፣ ሰደዷቸውም።
\v 11 ነገር ግን ከዚህ በኋላ አሳባቸውን ቀየሩ። ነፃነት የለቀቋቸውን ባርያዎቻቸውን መልሰው አመጡ። በድጋሚ ባርያዎች እንዲሆኑ አስገደዷቸው።
\s5
\v 12 ስለዚህ የእግዚአብሔር ቃል ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፣
\v 13 "የእስራኤል አምላክ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'አባቶቻችሁን ከባርነት ቤት ከግብጽ አገር ባወጣኋቸው ቀን ከእነርሱ ጋር እንዲህ ብዬ ቃል ኪዳን አደረግሁ።
\v 14 "ሰባት ዓመት በተፈጸመ ጊዜ፣ ራሱን የሸጠላችሁን፣ ስድስትም ዓመት የተገዛላችሁን ዕብራዊ ወንድማችሁን እያንዳንዳችሁ ነፃነት ልታወጡት ይገባል። ነፃ አድርጋችሁ ስደዱት።" ነገር ግን አባቶቻችሁ አልሰሙኝም ጆሮአቸውንም አላዘነበሉም።
\s5
\v 15 እናንተም ዛሬ ተመልሳችሁ ሰው ሁሉ ባልንጀራውን አርነት ለማውጣት ዐዋጅ በመንገር ለዐይኔ ትክክል የሆነውን ነገር አድርጋችሁ ነበር። በስሜም በሚጠራበት ቤት ውስጥ በፊቴ ቃል ኪዳን አድርጋችሁ ነበር።
\v 16 ነገር ግን ያን ጊዜ ተመልሳችሁ ስሜን አስነቀፋችሁ፤ እያንዳንዳችሁም በፈቃዳቸው እንዲሄዱ ነፃነት ያወጣችኋቸውን ወንድና ሴት ባርያዎቻችሁን አስመለሳችሁ። በድጋሚ ወንዶችና ሴቶች ባርያዎች እንዲሆኑላችሁ አስገደዳችኋቸው።'
\s5
\v 17 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'እናንተ ራሳችሁ አልሰማችሁኝም። እያንዳንዳችሁ፣ ለወንድሞቻችሁና ለመሰል እስራኤላውያን ነፃነትን ልታውጁ በተገባ ነበር። ስለዚህ ተመልከቱ! እኔ ለሰይፍ፣ ለመቅሰፍት፣ ለራብም የነፃነት ዐዋጅ እናገርባችኋለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ በምድርም መንግሥታት ሁሉ መካከል አስደንጋጭ ነገር አደርጋችኋለሁ።
\v 18 ከዚያም ቃል ኪዳኔን የተላለፉትን ሰዎች፣ እንቦሳውንም ቈርጠው በቍራጩ መካከል ባለፉ ጊዜ በፊቴ ያደረጉትን የቃል ኪዳንን ቃል ያልፈጸሙትን እቀጣለሁ፤
\v 19 ከዚያም የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን አለቆች ጃንደረቦችን ካህናትንም፣ በእንቦሳም ቍራጭ መካከል ያለፉትን የአገሩን ሕዝብ ሁሉ።
\s5
\v 20 ለጠላቶቻቸው እጅ፣ ሕይወታቸውንም ለሚሹአት ሰዎች እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ። ሬሳቸውም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል ይሆናል።
\v 21 የይሁዳንም ንጉሥ ሴዴቅያስንና አለቆቹን ለጠላቶቻቸው እጅ፣ ሕይወታቸውንም ለሚሹአት እጅ፣ ከእናንተም ለተመለሱት ለባቢሎን ንጉሥ ሠራዊት እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ።
\v 22 ተመልከቱ፣ ትእዛዝ እሰጣለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ ጦርነትን እንዲከፍቱባትና እንዲወስዷት፣ እንዲያቃጥሏትም ወደዚህች ከተማ እመልሳቸዋለሁ። የይሁዳንም ከተሞች ሰው የሌለበት ባድማ አደርጋቸዋለሁ።"
\s5
\c 35
\p
\v 1 በይሁዳ ንጉስ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም ዘመን ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል ይህ ነው፣ እንዲህም አለ፣
\v 2 "ወደ ሬካባውያን ወገን ሄደህ አነጋግራቸው። ወደ ቤቴ፣ ከክፍሎቹ ወደ አንዲቱ፣ አግባቸው የወይን ጠጅም አጠጣቸው።"
\s5
\v 3 የከባስንን ልጅ የኤርምያስን ልጅ ያእዛንያን፣ እንዲሁም ወንድሞቹን፣ ልጆቹንም ሁሉ፣ ብሎም የሬካባውያንን ወገን ሁሉ ወሰድኋቸው።
\v 4 ወደ እግዚአብሔር ሰው ወደ ጌዴልያ ልጅ ወደ ሐናን ልጆች ጓዳ ወሰድኳቸው። እነዚህ ክፍሎች የእግዚአብሔር ቤት በበረኛው በሰሎም ልጅ በመዕሤያ ጓዳ በላይ ባለው የአለቆች ክፍል አጠገብ ነበሩ።
\s5
\v 5 በሬካባውያንም ልጆች ፊት የወይን ጠጅ የሞላባቸውን ማድጋዎችንና ጽዋዎችን አኑሬ፣ "ጥቂት የወይን ጠጅ ጠጡ፤" አልኳቸው።
\v 6 እነርሱ ግን እንዲህ አሉ፣ "የትኛውንም የወይን ጠጅ አንጠጣም፣ አባታችን የሬካብ ልጅ ኢዮናዳብ 'እናንተና ልጆቻችሁ ለዘላለም የወይን ጠጅ አትጠጡ' ብሎ አዝዞናልና።
\v 7 እንደ እንግዶች በምትኖሩባት ምድር ላይ ብዙ ዘመን እንድትኖሩ፣ በዕድሜአችሁ ሙሉ በድንኳን ውስጥ ተቀመጡ እንጂ ቤትን አትሥሩ፣ የትኛውንም ዘር አትዝሩ፣ የትኛውንም ወይን አትትከሉ፣ ይህ ለእናንተ አይደለም።'
\s5
\v 8 እኛም የአባታችንን የሬካብ ልጅ የኢዮናዳብን ቃል ባዘዘን ነገር ሁሉ ታዝዘናል፤ እኛም፣ ሚስቶቻችንም፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችንም፣ ዕድሜአችንን ሙሉ የወይን ጠጅ አልጠጣንም።
\v 9 የምንቀመጥበትንም ቤት አልሠራንም፣ የወይን ቦታና እርሻ ዘርም የለንም።
\v 10 በድንኳንም ውስጥ ኖረናል፣ አድምጠናል፣ አባታችንም ኢዮናዳብ ያዘዘንን ሁሉ አድርገናል።
\v 11 ነገር ግን የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ምድሪቱን ባጠቃ ጊዜ፣ 'ኑ ከከለዳውያን ሠራዊትና ከሦርያ ሠራዊት ፊት የተነሣ ወደ ኢየሩሳሌም እንሂድ' አልን። ስለዚህ በኢየሩሳሌም እየኖርን ነን።"
\s5
\v 12 ከዚያም የእግዚአብሔርም ቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፣
\v 13 "የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ እንዲህ ይላል፣ 'ሂድና ለይሁዳ ሰዎችና በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ ተናገር እንዲህም በላቸው፣ "ቃሌን ትሰሙ ዘንድ ተግሣጽን አትቀበሉምን? ይላል እግዚአብሔር።
\v 14 ልጆቹ የወይን ጠጅ እንዳይጠጡ የሬካብ ልጅ ኢዮናዳብ ያዘዛቸው ቃል እስከ ዛሬ ድረስ ተፈጸመ። ለአባታቸውም ትእዛዝ ታዝዘዋል። እኔ ግን በተደጋጋሚ ተናግሬአችኋለሁ፣ ሆኖም አልሰማችሁኝም።
\s5
\v 15 'እያንዳንዳችሁ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፣ ሥራችሁንም አሳምሩ፤ ታመልኩአቸውም ዘንድ ሌሎችን አማልክት አትከተሉ፣ ለእናንተና ለአባቶቻችሁም በሰጠሁት ምድር ትቀመጣላችሁ እያልሁ በተደጋጋሚ ባርያዎቼን፣ ነቢያትን ሁሉ ልኬባችሁ ነበር። እናንተ ግን ጆሯችሁን አላዘነበላችሁም፣ ወይም እኔንም አልሰማችሁኝም።
\v 16 የሬካብ ልጅ የኢዮናዳብ ልጆች አባታቸው ያዘዛቸውን ትእዛዝ ፈጽመዋልና፣ ይህ ሕዝብ ግን ሊሰማኝ አልፈለገም።"
\s5
\v 17 ስለዚህ፣ የእስራኤል አምላክና የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ተመልከቱ፣ በተናገርኋቸው ጊዜ አልሰሙምና፣ በጠራኋቸውም ጊዜ አልመለሱልኝምና የተናገርሁባቸውን ክፉ ነገር ሁሉ በይሁዳ ላይ፣ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ሁሉ ላይ አመጣባቸዋለሁ።"
\s5
\v 18 ኤርምያስም ለሬካባውያን ቤተሰብ እንዲህ አላቸው፣ "የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ለአባታችሁ ለኢዮናዳብ ትእዛዝ ታዝዛችኋልና፣ ትእዛዙንም ሁሉ ጠብቃችኋልና፣ ያዘዛችሁንም ፈጽማችኋልና፤
\v 19 ስለዚህ፣ 'በፊቴ የሚቆም ሰው፣ ከሬካብ ልጅ ከኢዮናዳብ ወገን ለዘላለም አይታጣም።" ይላል የሠራዊት አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
\s5
\c 36
\p
\v 1 እንዲህም ሆነ፣ በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም በአራተኛው ዓመት ይህ ቃል ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ መጣ፣ እንዲህም አለው፣
\v 2 "ለራስህ አንድ የመጽሐፍ ጥቅልል ውሰድና በእስራኤልና በይሁዳ ላይ፣ በአሕዛብም ሁሉ ላይ የተናገርሁህን ቃል ሁሉ ጻፍበት። ከኢዮስያስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ለአንተ የተናገርሁትን ጻፍበት።
\v 3 ምናልባት የይሁዳ ሕዝብ እኔ አደርግባቸዋለሁ ያልሁትንና ያሰብሁትን ክፉ ነገር ሁሉ ይሰሙ ይሆናል። ከክፋ መንገዳቸው ይመለሱ፣ እኔም በደላቸውንና ኃጢአታቸውን ይቅር እል ዘንድ።
\s5
\v 4 ኤርምያስም የኔርያን ልጅ ባሮክን ጠራ፣ ባሮክም ከኤርምያስ አፍ እግዚአብሔር ለእርሱ የተናገረውን ቃል ሁሉ በመጽሐፉ ጥቅልል ላይ ጻፈ።
\v 5 ቀጥሎም ኤርምያስ ለባሮክ እንዲህ ሲል አዘዘው። "እኔ በእስር ላይ ስለሆንኩ ወደ እግዚአብሔር ቤት መሄድ አልችልም።
\v 6 ስለዚህ አንተ መሄድና ከአፌም የጻፍኸውን የእግዚአብሔርን ቃል ልታነብብ ይገባል። በጾም ቀን፣ በእግዚአብሔር ቤት ሕዝቡ እየሰሙ አንብብ፣ ደግሞም ከከተሞቻቸው የሚወጡ የይሁዳ ሰዎች ሁሉ እየሰሙ አንብበው። እነዚህን ቃሎች አውጅላቸው።
\s5
\v 7 ምናልባት የምሕረት ልመናቸው በእግዚአብሔር ፊት ትመጣ ይሆናል። እግዚአብሔር በዚህ ሕዝብ ላይ የተናገረው ቍጣውና መዓቱ ታላቅ ነውና፣ ሁሉም ከክፉ መንገዱ ይመለስ ይሆናል።"
\v 8 ስለዚህ የኔርያም ልጅ ባሮክ ነቢዩ ኤርምያስ ያዘዘውን ሁሉ አደረገ። በእግዚአብሔርም ቤት የእግዚአብሔርን ቃል በመጽሐፉ አነበበ።
\s5
\v 9 በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም በአምስተኛው ዓመት በዘጠነኛው ወር በኢየሩሳሌም የተቀመጡ ሕዝብ ሁሉ ከይሁዳም ከተሞች ወደ ኢየሩሳሌም የመጡ ሕዝብ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ለመጾም አዋጅ ነገሩ።
\v 10 ባሮክም የኤርምያስን ቃል በእግዚአብሔር ቤት በላይኛው አደባባይ በእግዚአብሔር ቤት በአዲሱ በር መግቢያ ባለው በጸሐፊው በሳፋን ልጅ በገማርያ ጓዳ ሕዝቡ ሁሉ እየሰሙ መጽሐፉን አነበበ።
\s5
\v 11 የሳፋንም ልጅ የገማርያ ልጅ ሚክያስ የእግዚአብሔርን ቃል ሁሉ ከመጽሐፉ ጥቅልል ሰማ።
\v 12 ወደ ንጉሡ ቤት ወደ ጸሐፊው ክፍል ወረደ። በዚያም፣ አለቆች ሁሉ፦ ጸሐፊው ኤሊሳማ፣ የሸማያ ልጅ ድላያ፣ የዓክቦር ልጅ ኤልናታን፣ የሳፋን ልጅ ገማርያ፣ የሐናንያ ልጅ ሴዴቅያስ፣ እንዲሁም አለቆቹ ሁሉ በዚያ ተቀምጠው ነበር።
\s5
\v 13 ሚክያስም ሕዝቡ እየሰሙ ባሮክ ከመጽሐፉ ባነበበ ጊዜ የሰማውን ቃል ሁሉ ነገራቸው።
\v 14 አለቆቹም ሁሉ፣ "በሕዝቡ ጆሮ ያነበብኸውን ጥቅልል በእጅህ ይዘህ ና" የሚል መልእክት በኵሲ ልጅ፣ በሰሌምያ ልጅ፣ በናታንያ ልጅ፣ በይሁዲ እጅ፣ ወደ ባሮክ ላኩ። ስለዚህ የኔርያ ልጅ ባሮክ ጥቅልሉን በእጁ ይዞ ወደ እነርሱ ሄደ።
\v 15 ከዚያም፣ "ተቀመጥና እየሰማንህም ይህንን አንብብልን፤" አሉት። ባሮክም በጆሮአቸው አነበበው።
\s5
\v 16 እነዚህን ቃሎች ሁሉ በሰሙ ጊዜ ፈሩና እርስ በእርሳቸው ተመካከሩ፣ ባሮክንም፣ "ይህን ቃል ሁሉ በእርግጥ ለንጉሡ ልንናገር ይገባል" አሉት።
\v 17 ከዚያም ባሮክን፣ "ይህን ሁሉ ቃላት ከኤርምያስ አፍ እንዴት እንደ ጻፍኸው ንገረን" ብለው ጠየቁት።
\v 18 ባሮክም፣ "ይህን ቃል ከአፉ ይነግረኝ ነበር፣ እኔም በመጽሐፍ ጥቅልል ላይ በቀለም እጽፍ ነበር" ብሎ መለሰላቸው።
\v 19 አለቆቹም ለባሮክ፣ "አንተና ኤርምያስ ሄዳችሁ ተሸሸጉ። የት እንደሆናችሁ ማንም አይወቅ" አሉት።
\s5
\v 20 ወደ ንጉሡም ሸንጎ ገቡና ቃሉን ሁሉ ንጉሡ እየሰማ ተናገሩ። ነገር ግን አስቀድመው ጥቅልሉን በጸሐፊው በኤሊሳማ ክፍል አኑረውት ነበር።
\v 21 ከዚያም ንጉሡ ጥቅልሉን ያመጣ ዘንድ ይሁዲን ላከ። እርሱም ከጸሐፊው ከኤሊሳማ ክፍል ወሰደው። ከዚያም ይሁዲ ንጉሡና በንጉሡ አጠገብ የቆሙት አለቆች ሁሉ እየሰሙ አነበበው።
\v 22 ያኔ፣ ንጉሡ በዘጠነኛው ወር በክረምት ቤት ተቀምጦ ነበር፣ በፊቱም በምድጃ ውስጥ እሳት ይነድድ ነበር።
\s5
\v 23 ይሁዲ ሦስት ወይም አራት ዓምድ ያህል ባነበበ ቍጥር፣ ንጉሡ በካራ እየቀደደ ጥቅልሉ በምድጃ ውስጥ ባለው እሳት ፈጽሞ እስኪቃጠል ድረስ በምድጃ ውስጥ ወዳለው እሳት ጣለው።
\v 24 ነገር ግን ንጉሡ ወይም ይህንን ቃል ሁሉ የሰሙ ባሪያዎቹ ሁሉ አልፈሩም፣ ልብሳቸውንም አልቀደዱም።
\s5
\v 25 ነገር ግን ኤልናታን፣ ድላያና፣ ገማርያ ጥቅልሉን እንዳያቃጥል ንጉሡን ለመኑት፣ እርሱ ግን አልሰማቸውም።
\v 26 ንጉሡም ጸሐፊውን ባሮክንና ነብዩን ኤርምያስን ይይዙ ዘንድ የንጉሡን ልጅ ይረሕምኤልን፣ የዓዝርኤልን ልጅ ሠራያን፣ የዓብድኤልንም ልጅ ሰሌምያን አዘዘ፣ እግዚአብሔር ግን ሰውሯቸው ነበር።
\s5
\v 27 ከዚያም ንጉሡ ጥቅልሉንና ባሮክ ከኤርምያስ አፍ እየቀዳ የጻፈውን ቃል ካቃጠለ በኋላ፣ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ።
\v 28 "ዳግመኛ ሌላ ጥቅልል ውሰድ፣ የይሁዳም ንጉሥ ኢዮአቄም ባቃጠለው ጥቅልል ላይ የነበረውን የቀድሞውን ቃል ሁሉ ጻፍበት።
\v 29 ከዚያም፣ የይሁዳን ንጉሥ ኢዮአቄምን እንዲህ በለው፦ 'እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ አንተ፣ "የባቢሎን ንጉሥ በእርግጥ ይመጣል ይህችንም አገር ያፈርሳታል ከሰውና ከእንስሳም ባዶ ያደርጋታል" ብለህ ለምን ጻፍህበት? ብለህ ይህን ጥቅልል አቃጥለሃል።"
\s5
\v 30 ስለዚህ፣ ስለ አንተ፣ የይሁዳ ንጉሥ፣ ስለ ኢዮአቄም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ "በዳዊት ዙፋን ላይ ተቀማጭ አይኖርለትም። ሬሳውም በቀን ለትኩሳት፣ በሌሊትም ለውርጭ ይጣላል።
\v 31 ስለ ኃጢአታቸውም እርሱንና ዘሩን፣ ባሪያዎቹንም እቀጣለሁ። እነርሱም አልሰሙምና የተናገርሁባቸውን ክፉ ነገር ሁሉ በእነርሱ ላይና፣ በኢየሩሳሌም በሚቀመጡ፣ በይሁዳም ሰዎች ላይ አመጣለሁ።
\s5
\v 32 ሰለዚህ ኤርምያስ ሌላ ጥቅልል ወሰደ ለኔርያም ልጅ ለጸሐፊው ለባሮክ ሰጠው። እርሱም የይሁዳ ንጉሥ ኢዮአቄም በእሳት ያቃጠለውን የመጽሐፉን ቃል ሁሉ ከኤርምያስ አፍ እየቀዳ ጻፈበት። በተጨማሪም፣ ከቀድሞው ቃል ጋር የሚመሳሰል ብዙ ቃል ተጨመረበት።
\s5
\c 37
\p
\v 1 የባቢሎንም ንጉሥ ናቡከደነፆር በይሁዳ ያነገሠው የኢዮስያስ ልጅ ሴዴቅያስ በኢዮአቄም ልጅ በኢኮንያን ፋንታ ነገሠ።
\v 2 ነገር ግን ሴዴቅያስም ሆነ ባርያዎቹ፣ የአገሩም ሕዝብ በነቢዩ በኤርምያስ እጅ የተናገረውን የእግዚአብሔርን ቃል አልሰሙም።
\s5
\v 3 ስለዚህ፣ ንጉሡ ሴዴቅያስ፣ የሰሌምያን ልጅ ዮካልንና ካህኑን የመዕሤያን ልጅ ሶፎንያስን ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ ላከ። እነርሱም "ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ስለ እኛ ጸልይ" አሉት።
\v 4 በግዞት ቤት ገና አላገቡትም ነበርና ኤርምያስ በሕዝቡ መካከል ይወጣና ይገባ ነበር።
\v 5 የፈርዖንም ሠራዊት ከግብጽ ወጣ፣ ኢየሩሳሌምንም ከብበዋት የነበሩ ከለዳውያን ይህን ወሬ በሰሙ ጊዜ ከኢየሩሳሌም ተመለሱ።
\s5
\v 6 ከዚያም፣ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፣
\v 7 "የእስራኤል አምላክ፣ እግዚአብሔር፣ እንዲህ ይላል፦ ከእኔ ትጠይቁ ዘንድ የላካችሁን የይሁዳን ንጉሥ እንዲህ በሉት፦ 'ተመልከቱ፣ ሊረዳችሁ የወጣው የፈርዖን ሠራዊት ወደገዛ ምድሩ ወደ ግብጽ ይመለሳል።
\v 8 ከለዳውያንም ይመለሳሉ። ይህችን ከተማ ይዋጉአታል፣ ይይዟትማል፣ በእሳትም ያቃጥሉአታል።'
\s5
\v 9 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ስለማይሄዱ 'ከለዳውያን በእርግጥ ከእኛ ዘንድ ይሄዳሉ' ብላችሁ ራሳችሁን አታታልሉ።
\v 10 እናንተም የሚዋጉትን የከለዳውያንን ሠራዊት ሁሉ አሸንፋችሁ ቢሆን እንኳን፣ ከእነርሱም የቆሰሉት ብቻ በድንኳኖቻቸው ቀርተው ቢሆን ኖሮ፣ይህችን ከተማ በእሳት ባቃጠሉአት ነበር።
\s5
\v 11 ስለዚህ የከለዳውያን ሠራዊት ከፈርዖን ሠራዊት ፊት የተነሣ ከኢየሩሳሌም በተመለሰ ጊዜ፣
\v 12 ያኔ ኤርምያስ ወደ ብንያም አገር ሊሄድ ከኢየሩሳሌም ወጣ። እርሱ የርስቱን እድል ፈንታ በዚያ ከሕዝቡ መካከል ይቀበል ዘንድ ፈለገ።
\v 13 በብንያምም በር በነበረ ጊዜ፣ የዘበኞች አለቃ በዚያ ነበር። ስሙም የሐናንያ ልጅ የሰሌምያ ልጅ የሪያ ነበረ። እርሱም "ወደ ከለዳውያን መኰብለልህ ነው" ብሎ ነቢዩን ኤርምያስን ያዘው።
\s5
\v 14 ኤርምያስ ግን፣ "ይህ እውነት አይደለም። ወደ ከለዳውያን መኰብለሌ አይደለም" አለ። ነገር ግን የሪያ አልሰማውም። ኤርምያስንም ይዞ ወደ አለቆች አመጣው።
\v 15 አለቆችም በኤርምያስ ላይ ተቈጡ። መቱትና የጸሐፊውንም የዮናታንን ቤት እስር ቤት አድርገውት ነበርና በዚያ አኖሩት።
\s5
\v 16 ስለዚህ ኤርምያስ ብዙ ቀናት በተቀመጠበት ከምድር በታች ባለ ክፍል ተጣለ፤
\v 17 ከዚያም ንጉሡ ሴዴቅያስ አንድ ሰው ልኮ ወደ ቤተመንግሥት አስመጣው። ንጉሡም በቤቱ፣ "በውኑ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሆነ ቃል አለን?" ብሎ በድብቅ ጠየቀው። ኤርምያስም፣ "አዎን አለ፦ ለባቢሎን ንጉሥ እጅ አልፈህ ትሰጣለህ" አለ።
\s5
\v 18 ከዚያም ኤርምያስ ንጉሡን ሴዴቅያስን፣"በእስር ቤት የጣላችሁኝ አንተን፣ ወይስ ባርያዎችህን፣ ወይስ ሕዝብህን ምን በድያችሁ ነው?
\v 19 የባቢሎን ንጉሥ በእናንተና በዚህች ምድር አይመጣባችሁም ብለው ትንቢት ይናገሩላችሁ የነበሩ ነቢያቶቻችሁ ወዴት አሉ?
\v 20 ንጉሡ ጌታዬ ሆይ፣ እንድትሰማኝ እለምንሃለሁ! ልመናዬ ወደ አንተ ይድረስ። በዚያ እንዳልሞት ወደ ጸሐፊው ወደ ዮናታን ቤት አትመልሰኝ።"
\s5
\v 21 ስለዚህ ንጉሡ ሴዴቅያስ አዘዘ። አገልጋዮቹም ኤርምያስን በግዞት ቤት አደባባይ አኖሩት። እንጀራም ሁሉ ከከተማ እስኪጠፋ ድረስ ዕለት ዕለት አንድ አንድ እንጀራ ከጋጋሪዎች መንገድ ይሰጡት ነበር። ስለዚህ ኤርምያስ በእስር ቤት አደባባይ ተቀምጦ ነበር።
\s5
\c 38
\p
\v 1 ኤርምያስም ለሕዝቡ ሁሉ የተናገረውን ቃል የማታን ልጅ ስፋጥያስ፣ የጳስኮርም ልጅ ጎዶልያስ፣ የሰሌምያም ልጅ ዮካል፣ የመልክያም ልጅ ጳስኮር ሰሙ። ኤርምያስ እንዲህ ሲል ነበር፣
\v 2 "እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዚህች ከተማ የሚቀመጥ ማንኛውም ሰው በሰይፍ፣ በራብ፣ በመቅሠፍትም ይሞታል። ወደ ከለዳውያን የሚወጣ ግን በሕይወት ይኖራል። ሕይወቱንም ያስመልጣል፣ በሕይወትም ይኖራል።
\v 3 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ይህች ከተማ በባቢሎን ንጉሥ ሠራዊት እጅ በእርግጥ ትሰጣለች፣ እርሱም ይይዛታል።"
\s5
\v 4 ስለዚህ አለቆቹ ለንጉሡ እንዲህ አሉት፣ "ይህን የመሰለውን ቃል ሲነግራቸው በዚህች ከተማ የቀሩትን የሰልፈኞቹን እጅ የሕዝቡንም ሁሉ እጅ ያደክማልና ይህ ሰው ይገደል። ይህ ሰው ጥፋትን እንጂ ለዚህ ሕዝብ ሰላምን አያበጅለትምና እነዚህን ቃሎች እየተናገረ ነው።
\v 5 ስለዚህ ንጉሡ ሴዴቅያስ፣ "ተመልከቱ፣ እናንተን የሚቋቋም ንጉሥ የለምና፣ በእጃችሁ ነው" አለ።
\s5
\v 6 ከዚያም ኤርምያስን ወሰዱትና ወደ ንጉሡ ልጅ ወደ መልክያ ጕድጓድ ጣሉት። ጉድጓዱ በእስር ቤቱ አደባባይ ነበረ። ኤርምያስንም በገመድ አወረዱት። በጕድጓድም ውስጥ ውኃ አልነበረበትም፣ ነገር ግን ጭቃማ ነበርና ኤርምያስ ጭቃው ውስጥ ገባ።
\s5
\v 7 ኩሻዊ የሆነው አቤሜሌክ በንጉሡም ቤት ከነበሩት ጃንደረቦች አንዱ ነበር። ኤርምያስን በጕድጓዱ ውስጥ እንዳኖሩት ሰማ። ንጉሡም በብንያም በር ተቀምጦ ነበር።
\v 8 ስለዚህ አቤሜሌክ ከንጉሡ ቤት ወጥቶ ከንጉሡ ጋር ተነጋገረ።
\v 9 "ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፣ እነዚህ ሰዎች ነቢዮን ኤርምያስን በጕድጓድ ውስጥ በመጣላቸው ክፉ አድርገዋል። በከተማይቱም ውስጥ እንጀራ ስለሌለ በዚያ በራብ እንዲሞት ወደ ጉድጓድ ጥለውታል።"
\s5
\v 10 ከዚያም ንጉሡ ለኩሻዊው አቤሜሌክ ትእዛዝ ሰጠ። "ከአንተ ጋር ሠላሳ ሰዎች ከዚህ ውሰድ፣ ነብዩ ኤርምያስ ሳይሞት በፊት ከጕድጓድ አውጣው" ብሎ አዘዘው።
\v 11 ስለዚህ አቤሜሌክ ከእርሱ ጋር ሰዎችን ይዞ ሄደና ከቤተ መዛግብቱም በታች ወደ ነበረው ወደ ንጉሥ ቤት ገባ። ከዚያም አሮጌ ጨርቅና እላቂ ልብስ ወሰደና ወደ ኤርምያስ ወደ ጉድጓድ ውስጥ በገመድ አወረደው።
\s5
\v 12 ኩሻዊው አቤሜሌክ ኤርምያስን፣ "ይህን አሮጌ ጨርቅና እላቂውን ልብስ በብብትህ እና ከገመዱ በታች አድርግ" አለው። ስለዚህ ኤርምያስ እንዲሁ አደረገ።
\v 13 ከዚያም ኤርምያስን በገመዱ ጐተቱት። በዚህ መልኩ ከጕድጓድ አወጡት። ስለዚህ ኤርምያስ በግዞት ቤት አደባባይ ተቀመጠ።
\s5
\v 14 ከዚያም ንጉሡ ሴዴቅያስ ልኮ በእግዚአብሔር ቤት ወደ ነበረው፣ ወደ ሦስተኛው መግቢያ፣ ወደ እርሱ ነቢዩን ኤርምያስን አስመጣው። ንጉሡም ኤርምያስን፣ "አንዲት ነገር ልጠይቅህ እፈልጋለሁ። መልሱን አትደብቅብኝ" አለው።
\v 15 ኤርምያስም ሴዴቅያስን፣ "ብመልስልህ፣ በእርግጥ አትገድለኝምን? ምክር ብሰጥህም፣ አትሰማኝም" አለው።
\v 16 ንጉሡ ሴዴቅያስ ግን "እኛን የፈጠረንን ሕያው እግዚአብሔርን፣ አልገድልህም፣ ወይም ነፍስህን ለሚሹ ለእነዚህ ሰዎች እጅ አሳልፌ አልሰጥህም" ብሎ በድብቅ ለኤርምያስ ማለ።
\s5
\v 17 ስለዚህ ኤርምያስ ሴዴቅያስን፣ የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት አምላክ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወደ ባቢሎን ንጉሥ አለቆች ብትወጣ፣ በሕይወት ትኖራለህ፣ ይህችም ከተማ አትቃጠልም። አንተና ቤተሰብህ በሕይወት ትኖራላችሁ።
\v 18 ነገር ግን ወደ ባቢሎን ንጉሥ አለቆች ባትወጣ ግን፣ ይህች ከተማ በከለዳውያን እጅ ትሰጣለች። በእሳትም ያቃጥሉአታል፣ አንተም ከእጃቸው አታመልጥም" አለው።
\s5
\v 19 ንጉሡ ሴዴቅያስም ኤርምያስን፣ "ነገር ግን ወደ ከለዳውያን ክፉኛ እንዲያፌዙብኝ፣ በኰበለሉት በአይሁድ እጅ አሳልፈው ይሰጡኛል ብዬ እፈራለሁ" አለው።
\s5
\v 20 ኤርምያስም እንዲህ አለው፣ "ለእነርሱ አሳልፈው አይሰጡህም። እኔ እየነገርኩህ ያለሁትን የእግዚአብሔርን መልእክት ታዘዝ፤ ነገሮችም መልካም ይሆኑልሃል፣ በሕይወትም ትኖራለህ።
\v 21 ነገር ግን ትወጣ ዘንድ እንቢ ብትል፣ እግዚአብሔር ያሳየኝ ይህንን ነው፦
\s5
\v 22 ተመልከት! በይሁዳ ንጉሥ ቤት የቀሩትን ሴቶች ሁሉ ወደ ባቢሎን ንጉሥ አለቆች ያወጣሉ። እነዚያም ሴቶች ለአንተ፣ "ወዳጆችህ አታልለውሃል፤ አበላሽተውህማል። እግሮችህ ግን አሁን በጭቃ ውስጥ ሰጥመዋል፣ ወዳጆችህም ይሸሻሉ።'
\v 23 ሚስቶችህንና ልጆችህንም ሁሉ ወደ ከለዳውያን ያወጣሉ፣ አንተም ራስህ አታመልጥም። በባቢሎን ንጉሥ እጅ ትያዛለህ ይህችም ከተማ በእሳት ትቃጠላለች።"
\s5
\v 24 ከዚያም ሴዴቅያስ ኤርምያስን እንዲህ አለው፣ "እንዳትሞት ስለእነዚህ ቃሎች ለማንም አትናገር።
\v 25 አለቆቹ ግን እኔ ከአንተ ጋር እንደ ተነጋገርሁ ከሰሙ፣ ወደ አንተ መጥተው፣ 'ለንጉሡ የነገርከውን ንገረን። ከእኛም አትሸሽገን፣ አሊያ እንገድልሃለን። ንጉሡ ደግሞ ያለህን ንገረን' ቢሉህ፣
\v 26 ያን ጊዜ 'በዚያ እሞት ዘንድ ወደ ዮናታን ቤት አትመልሰኝ' ብዬ በንጉሡ ፊት ለመንሁ" በላቸው።
\s5
\v 27 ከዚያም አለቆቹ ሁሉ ወደ ኤርምያስ መጥተው ጠየቁት፣ ንጉሡም እንዳዘዘው እንደዚህ ቃል ሁሉ ነገራቸው። በኤርምያስና በንጉሡ መካከል የነበረው ውይይት አልተሰማምና ከእርሱ ጋር መነጋገርን ተዉ።
\v 28 ስለዚህ፣ ኢየሩሳሌም እስከ ተያዘችበት ቀን ድረስ ኤርምያስ በእስር ቤት አደባባይ ተቀመጠ።
\s5
\c 39
\p
\v 1 ኢየሩሳሌምም በተያዘች ጊዜ፣ በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ በዘጠነኛው ዓመት በዐሥረኛው ወር የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ከሠራዊቱ ሁሉ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም መጥተው ከበቡአት።
\v 2 በሴዴቅያስም በዐሥራ አንደኛው ዓመትና በአራተኛው ወር ከወሩም በዘጠነኛው ቀን ከተማይቱ ተሰበረች።
\v 3 ከዚያም የባቢሎን ንጉሥ አለቆች ሁሉ፣ ኤርጌል ሳራስር፣ ሳምጋርናቦና፣ ዋና አለቃው ሠርሰኪም፤ ኤርጌል ሳራስር በከፍተኛ ደረጃ ያለ አለቃ ነበርና ከቀሩት የባቢሎን ንጉሥ አለቆች ሁሉ ጋር ገብተው በመካከለኛው በር ውስጥ ተቀመጡ።
\s5
\v 4 የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ፣ ሰልፈኞቹም ሁሉ፣ ባዩአቸው ጊዜ ሸሹ። በሌሊትም በንጉሡ አትክልት መንገድ በሁለቱ ቅጥር መካከል ከነበረው ደጅ ከከተማይቱ ወጡ። ንጉሡ በዓረባ መንገድ ወጣ።
\v 5 ነገር ግን የከለዳውያን ሠራዊት ተከታተላቸውና ሴዴቅያስን በኢያሪኮ ሜዳ አቅራቢያ ባሉት የዮርዳኖስ ሸለቆ ሜዳዎች ላይ አገኙት። ከዚያም ይዘውት በሐማት ምድር ወዳለችው ወደ ሪብላ ወደ ባቢሎን ንጉሥ ወደ ናቡከደነፆር አመጡት፣ እርሱም ፍርድን በእርሱ ላይ ተናገረ።
\s5
\v 6 የባቢሎንም ንጉሥ የሴዴቅያስን ልጆች በገዛ ዐይኑ ፊት በሪብላ አረዳቸው። እርሱም የይሁዳን ከበርቴዎች ሁሉ ገደለ።
\v 7 ከዚያም የሴዴቅያስን ዐይን አወጣና ወደ ባቢሎን ሊወስደው በመዳብ ሰንሰለት አሰረው።
\s5
\v 8 ከዚያም ከለዳውያን የንጉሡንና የሕዝቡን ቤቶች በእሳት አቃጠሉ። የኢየሩሳሌምንም ቅጥር አፈረሱ።
\v 9 የዘበኞቹም አለቃ ናቡዘረዳን በከተማይቱ የቀሩትን ሕዝብ፣ ወደ እርሱም የኰበለሉትን ሰዎች፣ የቀረውንም የሕዝቡን ቅሬታ ወደ ባቢሎን ማረካቸው።
\v 10 አንዳች የሌላቸውን የሕዝቡን ድሆች ግን የዘበኞቹ አለቃ ናቡዘረዳን በይሁዳ አገር ተዋቸው። የወይኑን ቦታና እርሻውን በዚያው ቀን ሰጣቸው።
\s5
\v 11 የባቢሎንም ንጉሥ ናቡከደነፆር ስለ ኤርምያስ፣
\v 12 "ውሰደውና በመልካም ተንከባከበው። አትጉዳው። የሚነግርህንም የትኛውንም ነገር አድርግለት።" ብሎ የዘበኞቹን አለቃ ናቡዘረዳንን አዘዘ።
\v 13 ስለዚህ የዘበኞቹ አለቃ ናቡዘረዳን ላከ፣ የጃንደረቦች አለቃ ናቡሽዝባን፣ ዋናው አለቃ ራፋስቂስም ኤርጌል ሳራስርም፣ ራብማግም የባቢሎንም ንጉሥ ዋና ዋና አለቆች ሁሉ ሰዎችን ላኩ።
\v 14 ሰዎቻቸውም ኤርምያስን ከግዞት ቤት አደባባይ አወጡት፣ ወደ ቤቱም ይወስደው ዘንድ ለሳፋን ልጅ ለአኪቃም ልጅ ለጎዶልያስ ሰጡት፤ ስለዚህ ኤርምያስ በሕዝብ መካከል ተቀመጠ።
\s5
\v 15 በግዞትም ቤት አደባባይ ታስሮ ሳለ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ ኤርምያስ መጣ፣
\v 16 "ለኩሻዊው ለአቤሜሌክ እንዲህ በለው፣ 'የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ እንዲህ ይላል፦ ተመልከት፣ ለበጎነት ሳይሆን ለጥፋት ቃሌን በዚህች ከተማ ላይ አመጣለሁ። በዚያም ቀን በፊትህ እውነት ሆኖ ይፈጸማል።
\s5
\v 17 ነገር ግን በዚያ ቀን እታደግሃለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ በምትፈራቸው ሰዎች እጅ አልሰጥህም።
\v 18 በእርግ አድንሃለሁ ነፍስህም እንደ ምርኮ ትሆንልሃለች እንጂ በሰይፍ አትወድቅም። በእኔ ታምነሃልና፣ ይላል እግዚአብሔር።"
\s5
\c 40
\p
\v 1 ወደ ባቢሎን በተማረኩት በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ምርኮኞች መካከል የዘበኞቹ አለቃ ናቡዘረዳን፣ከራማ ከለቀቀው በኋላ፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ መጥቶ የነበረው ቃል ይህ ነው። ኤርምያስ ተወስዶ የነበረው ወደዚህ ቦታ የነበረ ሲሆን፣ እርሱም በሠንሰለት ታስሮ ነበር። እርሱ በምርኮ ከተወሰዱት የኢየሩሳሌም እና ይሁዳ ምርኮኞች ሁሉ መካከል አንዱ ነበር።
\v 2 የዘበኞቹም አለቃ ኤርምያስን ወሰደውና እንዲህ አለው፣ "አምላክህ እግዚአብሔር ይህን ክፉ ነገር በዚህ ስፍራ ላይ ተናገረ።
\s5
\v 3 ስለዚህ እግዚአብሔር ነገሩን አመጣው። እናንተ ሕዝቦች በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት ሠርታችኋልና፣ እንደ ተናገረው አደረገ። ይህ ነገር እየሆነባችሁ ያለው፣ ቃሉን አልሰማችሁምና ነው።
\v 4 አሁን ግን ተመልከት! እጅህ የታሰረችበትን ሰንሰለት ዛሬ ፈታሁልህ። ከእኔ ጋር ወደ ባቢሎን መምጣት በዐይኖችህ ዘንድ መልካም መስሎ ቢታይህ፣ ና፣ እኔም እንከባከብሃለሁ። ነገር ግን ከእኔ ጋር ወደ ባቢሎን መምጣቱ በዐይኖችህ ዘንድ መልካም መስሎ ባይታይህ ግን፣ አትምጣ። በፊትህ ያለችውን ምድር ሁሉ ተመልከት። በዐይኖችህ ዘንድ ልትሄድበት መልካም መስሎ ወደሚታይህና ትክክል ወደሚመስልህ ስፍራ ሂድ።"
\s5
\v 5 እርሱም ገና መልስ ሳይሰጥ፣ ናቡከደነፆር "የባቢሎን ንጉሥ በይሁዳ ከተሞች ላይ ወደ ሾመው ወደ ሳፋን ልጅ ወደ አኪቃም ልጅ ወደ ጎዶልያስ ተመለስ። ከእርሱም ጋር በሕዝቡ መካከል ተቀመጥ ወይም ልትሄድበት ደስ ወደሚያሰኝህ ስፍራ ሁሉ ሂድ" አለው። የዘበኞቹም አለቃ የምግብ ስንቅና ስጦታ ሰጥቶ አሰናበተው።
\v 6 ስለዚህ ኤርምያስ የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ወዳለበት ወደ ምጽጳ ሄደ። ከእርሱም ጋር በአገሩ ውስጥ በቀሩት ሕዝብ መካከል ተቀመጠ።
\s5
\v 7 በየገጠሩ የነበሩት የጭፍራ አለቆችና ሰዎቻቸው ሁሉ የባቢሎን ንጉሥ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በምድር ላይ እንደ ሾመ ሰሙ። እንዲሁም ወደ ባቢሎን ያልተማረኩ የምድሪቱ ድሆች የሆኑት ወንዶች፣ ሴቶችና ልጆች ላይ እንደሾመው ሰሙ።
\v 8 ስለዚህ ወደ ጎዶልያስ ወደ ምጽጳ መጡ። እነዚህም ሰዎች የናታንያ ልጅ እስማኤል፣ የቃሬያም ልጅ ዮሐናንና ዮናታን፣ የተንሑሜትም ልጅ ሠራያ፣ የነጦፋዊውም የዮፌ ልጆች፣ የማዕካታዊውም ልጅ ያእዛንያ፣ እነርሱና ሰዎቻቸው ነበሩ።
\s5
\v 9 የሳፋንም ልጅ የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ለእነርሱና ለሰዎቻቸው ማለ፣ እንዲህም አላቸው፣ "ለከለዳውያን አለቆች ለማገልገል አትፍሩ። በምድሪቱ ላይ ተቀመጡ ለባቢሎንም ንጉሥ አገልግሉ፣ መልካምም ይሆንላችኋል።
\v 10 ተመልከቱ፣ ወደ እኛ ከሚመጡት ከለዳውያን ጋር ለመገናኘት ምጽጳ ውስጥ እኖራለሁ፤ እናንተ ግን ወይንን፣ የበጋ ፍሬንና፣ ዘይትን በየዕቃዎቻችሁ አከማቹ። በያዛችኋቸውም ከተሞቻችሁ ውስጥ ኑሩ።"
\s5
\v 11 በሞዓብ፣ በአሞንም ልጆች መካከል፣ እንዲሁም በኤዶምያስና በእያንዳንዱ ምድር ሁሉ ላይ የነበሩ አይሁድ ሁሉ የባቢሎን ንጉሥ የይሁዳን ቅሬታ እንዳስቀረ፣ የሳፋንንም ልጅ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በላያቸው እንደ ሾመው ሰሙ።
\v 12 ስለዚህ አይሁድ ሁሉ ከተበተኑበት ስፍራ ሁሉ ተመለሱ። ጎዶልያስ ወዳለበት፣ ወደ ይሁዳ ምድር፣ ወደ ምጽጳ መጡ። ወይንና የበጋንም ፍሬ በመሰብሰብ እጅግ ብዙ አከማቹ።
\s5
\v 13 የቃሬያም ልጅ ዮሐናን፣ በየገጠሩም የነበሩ የጭፍራ አለቆች ሁሉ ወደ ጎዶልያስ ወደ ምጽጳ መጡ።
\v 14 "የአሞን ልጆች ንጉሥ በኣሊስ ይገድልህ ዘንድ የናታንያን ልጅ እስማኤልን እንደ ሰደደ ታውቃለህን?" አሉት። የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ግን አላመናቸውም።
\s5
\v 15 ስለዚህ፣ የቃሬያም ልጅ ዮሐናን ምጽጳ ላይ ጎዶሊያስን እንዲህ በማለት በሚስጢር አነጋገረው፣"ሄጄ ማንም ሳያውቅ የናታንያን ልጅ እስማኤልን እንድገድለው ፍቀድልኝ። ማንም አይጠረጥረኝም። ሊገድልህ የሚገባው ለምንድነው? ወደ አንተ የተሰበሰቡ አይሁድ ሁሉ እንዲበተኑ፣ የይሁዳም ቅሬታ እንዲጠፋ ለምን ትፈቅዳለህ?"
\v 16 ነገር ግን የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ግን የቃሬያን ልጅ ዮሐናንን፣ "በእስማኤል ላይ ሐሰት ተናግረሃልና ይህን ነገር አታድርግ" አለው።
\s5
\c 41
\p
\v 1 በሰባተኛውም ወር ከመንግሥት ወገንና፣ ከንጉሡ ዋና ዋና አለቆች አንዱ የኤሊሳማ ልጅ የናታንያ ልጅ እስማኤል ከዐሥር ሰዎች ጋር ወደ ምጽጳ ወደ አኪቃም ልጅ ወደ ጎዶልያስ መጣ። በዚያም በምጽጳ በአንድ ላይ እንጀራ በሉ።
\v 2 የናታንያም ልጅ እስማኤል፣ ከእርሱም ጋር የነበሩት ዐሥሩ ሰዎች ተነሥተው የሳፋንን ልጅ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በሰይፍ መቱ። የባቢሎን ንጉሥ በአገሩ ላይ የሾመውን እስማኤል ገደለው።
\v 3 ከዚያም እስማኤል ከጎዶልያስ ጋር በምጽጳ የነበሩትን አይሁድ ሁሉ፣ በዚያም የተገኙትን የከለዳውያንን ሰልፈኞች ሁሉ ገደላቸው።
\s5
\v 4 ጎዶልያስን ከገደለ በኋላ ሁለት ቀን ሆነ፣ ነገር ግን ማንም አላወቀም ነበር።
\v 5 ጢማቸውን ላጭተው፣ ልብሳቸውንም ቀድደው፣ ገላቸውንም ነጭተው፣ ወደ እግዚአብሔር ቤት ያቀርቡ ዘንድ የእህል ቍርባንና ዕጣን በእጃቸው እየያዙ፣ ሰማንያ ሰዎች ከሴኬም፣ ከሴሎና፣ ከሰማርያ መጡ።
\s5
\v 6 የናታንያም ልጅ እስማኤል ከምጽጳ ወጥቶ እያለቀሰ ሊገናኛቸው ሄደ። ባገኛቸውም ጊዜ፣ "ወደ አኪቃም ልጅ ወደ ጎዶልያስ ኑ!" አላቸው።
\v 7 ወደ ከተማም መካከል በመጡ ጊዜ፣ የናታንያ ልጅ እስማኤል ከእርሱም ጋር የነበሩ ሰዎች አረዷቸውና በጉድጓድ ውስጥ ጣሉአቸው።
\s5
\v 8 ነገር ግን በመካከላቸው እስማኤልን፣ "የምንሰጥህ በሜዳ የተሸሸገ ስንዴ፣ ገብስ፣ ዘይትና፣ ማር ስላለን አትግደለን" የሚሉት ዐሥር ሰዎች ነበሩ። እርሱም ከሌሎች ወዳጆቻቸው ጋር አልገደላቸውም።
\v 9 ጉድጓዱ እስማኤል ከጎዶልያስ ጋር የገደላቸውን የሰዎች ሬሳ ሁሉ የጣለበት ጕድጓድ ነበር። ይህ ጥልቅ ጉድጓድ ንጉሡ አሳ የእስራኤልን ንጉሥ ባኦስን ስለ ፈራ የሠራው ጉድጓድ ነበረ። የናታንያም ልጅ እስማኤል የገደላቸውን ሞላበት።
\s5
\v 10 ቀጥሎ እስማኤል በምጽጳ የነበረውን የሕዝቡን ቅሬታ ሁሉ፣ የንጉሡን ሴቶች ልጆች፣ የዘበኞቹም አለቃ ናቡዘረዳን ለአኪቃም ልጅ ለጎዶልያስ የሰጠውን በምጽጳ የቀሩትን ሕዝብ ሁሉ ማረካቸው። ስለዚህ የናታንያም ልጅ እስማኤል ማርኮ ወደ አሞን ልጆች ይሄድ ዘንድ ተነሣ።
\s5
\v 11 የቃሬያም ልጅ ዮሐናን፣ ከእርሱም ጋር የነበሩት የጭፍራ አለቆች ሁሉ የናታንያ ልጅ እስማኤል ያደረገውን ክፋት ሁሉ ሰሙ።
\v 12 ስለዚህ ሰዎቻቸውን ሁሉ ይዘው ከናታንያ ልጅ ከእስማኤል ጋር ሊዋጉ ሄዱ። በገባዖንም ባለው በታላቁ የውኃ ጉድጓድ አጠገብ አገኙት።
\s5
\v 13 ከዚያም ከእስማኤል ጋር የነበሩት ሕዝብ ሁሉ የቃሬያን ልጅ ዮሐናንን፣ ከእርሱም ጋር የነበሩትን የጭፍራ አለቆችን ሁሉ ሲያዩ እጅግ ደስ አላቸው።
\v 14 ስለዚህ እስማኤል ከምጽጳ የማረካቸው ሕዝብ ሁሉ ዞረው ወደ ቃሬያም ልጅ ወደ ዮሐናን ሄዱ።
\s5
\v 15 ነገር ግን የናታንያ ልጅ እስማኤል ከስምንት ሰዎች ጋር ከዮሐናን አመለጠ። ወደ አሞንም ሕዝቦች ሄደ።
\v 16 የቃሬያም ልጅ ዮሐናን፣ ከእርሱም ጋር የነበሩት የጭፍራ አለቆች ሁሉ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በምጽጳ ከገደለው በኋላ ከናታንያ ልጅ ከእስማኤል ያስመለሱአቸውን የሕዝቡን ቅሬታ ሁሉ፣ ከገባዖን ያስመለሱአቸውን ሰልፈኞች፣ ሴቶችንም፣ ልጆችንም፣ ጃንደረቦችንም፣ ወሰዱ።
\s5
\v 17 ከዚያም ሄደው ለተወሰነ ጊዜ በቤተልሔም አቅራቢያ ባለው በጌሮት ከመዓም ተቀመጡ። ሊሄዱ የነበረው ወደ ግብጽ ነበር።
\v 18 ይህም ከከለዳውያን ፍርሃት የተነሣ ነበር። የባቢሎን ንጉሥ በአገሩ ላይ የሾመውን የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን እስማኤል ስለ ገደለው ፈሯቸው።
\s5
\c 42
\p
\v 1 ከዚያም የጭፍራ አለቆች ሁሉ፣ የቃሬያም ልጅ ዮሐናን፣ የሆሻያም ልጅ ያእዛንያ፣ ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ያሉት ሕዝብ ወደ ነብዩ ኤርምያስ ቀረቡ።
\v 2 እንዲህም አሉት፣ "ልመናችን በፊትህ ይድረስ። እንዳየኸው ከብዙዎቹ መካከል የቀረነው ጥቂቶች ነንና፣
\v 3 የምንሄድበትን መንገድና፣ የምናደርገውን ነገር እንዲያሳየን ስለ እኛና ስለዚህ ቅሬታ ሕዝብ ወደ አምላክህ እግዚአብሔር ጸልይ" አሉት።
\s5
\v 4 ስለዚህ ነቢዩ ኤርምያስ፣ "ሰምቻችኋለሁ። ተመልከቱ፣እንደጠየቃችሁት ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ። እግዚአብሔርም የሚመልስላችሁን ሁሉ እነግራችኋለሁ። ከእናንተ ምንም አልሸሽግም፤" አላቸው።
\v 5 እነርሱም ለኤርምያስ፣ "አምላክህ እግዚአብሔር ወደ እኛ የላከውን ነገር ሁሉ ባናደርግ፣ እግዚአብሔር በመካከላችን እውነተኛና ታማኝ ምስክር ይሁን።
\v 6 የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ቃል በመስማታችን መልካም እንዲሆንልን፣ መልካም ወይም ክፉ ቢሆን፣ አንተን ወደ እርሱ የምንልክህ የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ድምፅ እንሰማለን አሉት።"
\s5
\v 7 ከዚያም ከዐሥር ቀን በኋላ፣ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤርምያስ መጣ።
\v 8 ስለዚህ ኤርምያስ የቃሬያንም ልጅ ዮሐናንን ከእርሱም ጋር የነበሩትን የሠራዊቱን አለቆች ሁሉ ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሕዝቡንም ሁሉ ጠራ።
\v 9 እንዲህ አላቸው፣ "ጸሎታችሁን በፊቱ አቀርብ ዘንድ ወደ እርሱ የላካችሁኝ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣
\v 10 'በእናንተ ላይ ያመጣሁባችሁን ጥፋት እመልሳለሁና ተመልሳችሁ በዚህች ምድር ብትኖሩ፣እሠራችኋለሁ እንጂ አላፈርሳችሁም፣ እተክላችኋለሁ እንጂ አልነቅላችሁም።
\s5
\v 11 የምትፈሩትን የባቢሎን ንጉሥ አትፍሩ። አድናችሁ ዘንድ፣ ከእጁም አስጥላችሁ ዘንድ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝና አትፍሩ፣ ይላል እግዚአብሔር።
\v 12 ምሕረትን እሰጣችኋለሁና። እርሱ እንዲምራችሁ ወደ ምድራችሁም እንዲመልሳችሁ እኔ እራራላችኋለሁ።
\s5
\v 13 እናንተ ግን፣"በዚህች ምድር አንቀመጥም" ብትሉ፣ የእኔን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል ባትሰሙ፣
\v 14 እናንተም፣ "አይሆንም! የትኛውንም ጦርነት ወደማናይባት፣ የመለከትም ድምፅ ወደማንሰማባት፣ ወደማንራብባት ወደ ግብጽ ምድር እንሄዳለን። በዚያ እንኖራለን" ብትሉ፣
\s5
\v 15 አሁን የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፣ እናንተ የይሁዳ ቅሬታ የሆናችሁ። የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ወደ ግብጽ እንድትገቡ፣ በዚያም እንድትኖሩ በእርግጥ ፊታችሁን ብታቀኑ፣
\v 16 ያኔ የምትፈሩት ሰይፍ በዚያ በግብጽ ምድር ያገኛችኋል። የምትደነግጡበት ረሃብ በዚያ በግብጽ ይደርስባቸኋል። በዚያም ትሞታላችሁ።
\v 17 ስለዚህ ወደ ግብጽ እንዲገቡ፣ በዚያም እንዲኖሩ ፊታቸውን የሚያቀኑ ሰዎች ሁሉ በሰይፍ፣ በረሃብ፣ ወይም በመቅሠፍት፣ ይሞታሉ። እኔም ከማመጣባቸው ክፉ ነገር ማንም አይተርፍም፣ ማንም አያመልጥም።
\s5
\v 18 የእስራኤል አምላክ፣የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ እንዲህ ይላልና፦ ቊጣዬና መዓቴ በኢየሩሳሌም በሚኖሩ ላይ እንደ ፈሰሰ፣ እንዲሁ ወደ ግብጽ የምትገቡ ከሆነ መዓቴ ይፈስስባችኋል። እናንተም ለእርግማንና ለመደንገገጪያ፣ ለመረገሚያና ለመዋረጂያ ትሆናላችሁ። ደግሞም ይህንን ስፍራ ከእንግዲህ ወዲህ አታዩትም።"
\v 19 ከዚያም ኤርምያስ እንዲህ አለ፣ "እናንተ የይሁዳ ቅሬታዎች፣ እግዚአብሔር፣ ወደ ግብጽ አትሂዱ ብሎ ተናግሯችኋልና ዛሬ ምስክር እንደሆንኩባችሁ በእርግጥ እወቁ።
\s5
\v 20 'ስለ እኛ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ጸልይ። አምላካችንም እግዚአብሔር የሚናገርህን ሁሉ ንገረን፣ እኛም እንፈጽመዋለን' ብላችሁ ወደ እግዚአብሔር ወደ አምላካችሁ ስትልኩኝ የሕይወት ዋጋ የሚያስከፍላችሁን ነገር አድርጋችኋልና።
\v 21 እኔም ዛሬ ነግሬአችኋለሁ፣ ወደ እናንተም በላከኝ ነገር ሁሉ የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል አልሰማችሁም።
\v 22 ስለዚህ፣ አሁንም ሄዳችሁ እንድትኖሩበት በወደዳችሁበት ስፍራ በሰይፍ፣ በራብ፣ በቸነፈር እንድትሞቱ በእርግጥ እወቁ።"
\s5
\c 43
\p
\v 1 ኤርምያስ አምላካቸው እግዚአብሔር ለእነርሱ የላከውን ይህንን የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን ቃል ሁሉ፣ለሕዝቡ ሁሉ ተናግሮ ጨረሰ።
\v 2 የሆሻያ ልጅ ዓዛርያስ፣ የቃሬያም ልጅ ዮሐናን፣ ትዕቢተኞችም ሰዎች ሁሉ ኤርምያስን፣ "ሐሰትን እየተናገርክ ነህ። አምላካችን እግዚአብሔር፣ 'በዚያ ትቀመጡ ዘንድ ወደ ግብጽ አትግቡ ብሎ አልላከህም፤'
\v 3 ነገር ግን ከለዳውያን እንዲገድሉን ወደ ባቢሎንም እንዲማርኩን በእጃቸው አሳልፈህ ትሰጠን ዘንድ የኔርያ ልጅ ባሮክ በላያችን ላይ አነሣሥቶሃል" አሉት።
\s5
\v 4 ስለዚህ የቃሬያ ልጅ ዮሐናን፣ የጦር ሠራዊቱ አለቆች ሁሉ፣ ሕዝቡም ሁሉ በይሁዳ ምድር ይኖሩ ዘንድ የእግዚአብሔርን ቃል አልሰሙም።
\v 5 የቃሬያም ልጅ ዮሐናን የጭፍራ አለቆችም ሁሉ በይሁዳ ምድር ለመኖር ከተሰደዱባቸው ከአሕዛብ ሁሉ የተመለሱትን የይሁዳን ቅሬታ ሁሉ ወሰዱ።
\v 6 እነርሱም ወንዶችንና ሴቶችን ልጆችን፣ የንጉሡንም ሴቶች ልጆች፣ የዘበኞቹንም አለቃ ናቡዘረዳን፣ ከሳፋን ልጅ፣ ከአኪቃም ልጅ ከጎዶልያስ ጋር የተዋቸውን ሰዎች ሁሉ፣ ነቢዩንም ኤርምያስን የኔርያንም ልጅ ባሮክን ወሰዱ።
\v 7 የእግዚአብሔርንም ቃል ስላልሰሙ ወደ ግብጽ ምድር ሄዱ፣ እስከ ጣፍናስ ድረስ መጡ።
\s5
\v 8 ስለዚህ የእግዚአብሔር ቃል በጣፍናስ ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፣
\v 9 "ታላላቆችን ድንጋዮች በእጅህ ውሰድ፣ የይሁዳም ሰዎች እያዩ በጣፍናስ ባለው በፈርዖን የጡብ ቤት ደጅ መግቢያ ሸሽጋቸው።"
\v 10 ከዚያም እንዲህ በላቸው፣ "የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ተመልከቱ፣ የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን አገልጋዬ ለማድረግ መልእክተኛ እልክበታለሁ። ዙፋኑንም አንተ፣ ኤርምያስ በሸሸግሃቸው በእነዚህ ድንጋዮች ላይ አኖራለሁ። ናቡከደነፆር ማለፊያ ድንኳኑን በላያቸው ይዘረጋል።
\s5
\v 11 መጥቶም የግብጽን ምድር ያጠቃል። ለሞት የተመደበውን ለሞት ይሰጣል። ለምርኮም የተመደበው ለምርኮ ይወሰዳል። ለሰይፍ የተመደበው ለሰይፍ ይሰጣል።
\v 12 ከዚያም፣ በግብጽ አማልክት ቤቶች ላይ እሳትን አነድዳለሁ። ናቡከደነፆር ያቃጥላቸዋል ወይም ይማርካቸዋል። እረኞች ከደበሏቸው ተባይን እንደሚያራግፉ፣ እንዲሁ የግብጽን አገር ያጸዳል። ከዚያም ስፍራ በድል ይወጣል።
\v 13 በግብጽም ምድር ያለውን የሄልዮቱን ከተማ ሐውልቶች ይሰብራል። የግብጽንም አማልክት ቤቶች በእሳት ያቃጥላል።"
\s5
\c 44
\p
\v 1 በግብጽ ምድር በሚግዶልና በጣፍናስ በሜምፎስም በጳትሮስም አገር ስለ ተቀመጡ አይሁድ ሁሉ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው።
\v 2 "የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ያመጣሁትን ክፉ ነገር ሁሉ እናንተ ራሳችሁ አይታችኋል። ተመልከቱ፣ ዛሬ ጠፍተዋል። የሚኖርባቸው የለም።
\v 3 ይህም የሆነው ለሌሎች አማልክት በማጠንና በማምለክ ያስቀይሙኝ ዘንድ ስላደረጉት ክፋት ነው። እነዚህም አማልክት እነርሱ ራሳቸው፣ አንተም ራስህ፣ እንዲሁም አባቶቻቸው የማያውቋቸው ናቸው።
\s5
\v 4 ስለዚህ በተደጋጋሚ ባርያዎቼን ነብያትን ሁሉ ሰደድሁባችሁ። 'እንደነዚህ ያሉ የጠላኋቸውን ርኩስ ነገሮች ማድረጋችሁን አቊሙ' ልላቸው ላክኋቸው።
\v 5 ነገር ግን አልሰሙም። ከክፋታቸው ተመልሰው ለሌሎች አማልክት እንዳያጥኑ አትኩሮታቸውን ለመስጠት አልፈለጉም።
\v 6 ስለዚህ መዓቴና ቍጣዬ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም ጎዳናዎች ላይ ፈሰሱ፣ ደግሞም እንደ እሳት ተቀጣጠሉ። ዛሬም እንደ ሆነው ፈረሱ፣ ባድማም ሆኑ።"
\s5
\v 7 አሁንም ቢሆን፣ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ወንድንና ሴትን፣ ብላቴናንና ሕፃንን ከይሁዳ እንድታጠፉ ይህን ታላቅ ክፋት በራሳችሁ ላይ ለምን ታደርጋላችሁ? ከመካከላችሁ የአንዳችሁም ቅሬታ አይተርፍም።
\v 8 ሰውነታችሁንም ታጠፉ ዘንድ፣ በምድርም አሕዛብ ሁሉ መካከል መረገሚያና መሰደቢያ ትሆኑ ዘንድ፣ ለመቀመጥ በገባችሁባት በግብጽ ምድር ለሌሎች አማልክት በማጠናችሁ በእጃችሁ ሥራ ለምን ታስቈጡኛላችሁ?
\s5
\v 9 በይሁዳ ምድርና በኢየሩሳሌም አደባባይ ያደረጉትን የአባቶቻችሁን ክፋት፣ የይሁዳንም ነገሥታት ክፋት፣ የሚስቶቻቸውንም ክፋት፣ የእናንተንም ክፋት፣ የሚስቶቻችሁንም ክፋት ረስታችሁታልን?
\v 10 እስከ ዛሬ ድረስ ትሑታን አልሆኑም። በእነርሱና በአባቶቻቸውም ፊት ያኖርሁትን ሕጌን ወይም ሥርዓቴን አላከበሩም፣ አልሄዱበትም።"
\s5
\v 11 ስለዚህም የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ እንዲህ ይላል፦ "ተመልከቱ፣ በእናንተ ላይ ጥፋትን ለማድረግ እና ይሁዳን ሁሉ ላጠፋ ፊቴን በላያችሁ ላይ አደርጋለሁ።
\v 12 ወደ ግብጽ ሄደው በዚያ እንዲኖሩ ፊታቸውን ያቀኑትን የይሁዳን ቅሬታ እወስዳለሁና። ይህን የማደርገው ሁሉም በግብጽ ምድር እንዲጠፉ ነው። እነርሱ በሰይፍና በራብ ይጠፋሉ። ከታናሹም ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ በሰይፍና በራብ ይሞታሉ፤ ለጥላቻና ለመደነቂያ፣ ለመረገሚያና ለመሰደቢያ ይሆናሉ።
\s5
\v 13 ኢየሩሳሌምን በሰይፍ፣ በረሃብ እና በመቅሠፍት እንደ ቀጣሁ፣ እንዲሁ በግብጽ ምድር የሚኖሩትን እቀጣለሁ።
\v 14 በዚያ ለመኖር ወደ ግብጽ ምድር ከሄዱ እንኳን ወደ ይሁዳ አገር ተመልሰው በዚያ ይኖሩ ዘንድ ከሚወድዱ ከይሁዳ ቅሬታ ወገን የሚያመልጥና የሚቀር፣ ወደዚያም የሚመለስ የለም። ከዚህ ከሚያመልጥ በቀር ማንም አይመለስም።"
\s5
\v 15 ከዚያም ሚስቶቻቸው ለሌሎች አማልክት ማጠናቸውን ያወቁ ሰዎች ሁሉ፣ በዚያም የቆሙ ሴቶች ሁሉ፣ በግብጽ ምድር በጳጥሮስ የተቀመጡ ሕዝብ ሁሉ፣ ታላቅ ጉባኤ ሆነው እንዲህ ሲሉ ለኤርምያስ መለሱለት።
\v 16 እነርሱም እንዲህ አሉ፣ "በእግዚአብሔር ስም የነገርኸንን ቃል አንሰማህም።
\v 17 እኛና አባቶቻችን፣ ነገሥታቶቻችን፣ አለቆቻችንም በይሁዳ ከተሞች በኢየሩሳሌም አደባባይ እናደርገው እንደ ነበረ፣ ለሰማይ ንግሥት እናጥን ዘንድ የመጠጥንም ቊርባን እንድናፈስስላት ከአፋችን የወጣውን ቃል ሁሉ በእርግጥ እናደርጋለን። ያን ጊዜ እንጀራ እንጠግባለን፣ ደግሞም የትኛውም ጥፋት ሳይደርስብን እንበለጽጋለን።
\s5
\v 18 ለሰማይ ንግሥት ማጠንን ለእርስዋም የመጠጥን ቍርባን ማፍሰስን ከተውን ወዲህ ግን፣በድህነት ተሰቃይተናል፣ ደግሞም በሰይፍና በረሃብ አልቀናል።"
\v 19 ሴቶቹም እንዲህ አሉ፣ "እኛስ ለሰማይ ንግሥት ባጠንንላት፣ የመጠጥንም ቍርባን ባፈሰስንላት ጊዜ፣ ባሎቻችን ሳያውቊ ምስልዋን ለማበጀት እንጐቻ አድርገንላት ኖሮአልን? የመጠጥንም ቍርባን አፍስሰንላት ኖሮአልን?"
\s5
\v 20 ኤርምያስም ይህን ቃል ለመለሱለት ሕዝብ ሁሉ፣ ለወንዶቹና ለሴቶቹ፣ ለሕዝቡም ሁሉ፣ መለሰላቸው እንዲህም አለ፣
\v 21 "እናንተና አባቶቻችሁ፣ ነገሥታቶቻችሁና አለቆቻችሁም፣ የምድርም ሕዝብ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም አደባባይ ያጠናችሁትን ዕጣን እግዚአብሔር ያሰበው በልቡም ያኖረው አይደለምን?
\s5
\v 22 ከክፉ ልምምዳችሁ የተነሣ፣ ከእንግዲህ ወዲህ የሥራችሁን ክፋትና ያደረጋችሁትን ርኵሰት እግዚአብሔር ይታገሥ ዘንድ አልቻለም። ስለዚህ ምድራችሁ ባድማ፣ መደነቂያ፣ መረገሚያም ሆናለች ዛሬም እንደሆነው የሚኖርባት የለም።
\v 23 እጣን ስላጠናችሁና በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት ስለሠራችሁ፣ ድምፁንም ስላልሰማችሁ፣ በሕጉ፣ በሥርዓቱና በምስክሩም ስላልሄዳችሁ፣ ዛሬ እንደሆነው ይህች ክፉ ነገር አግኝታችኋለች።"
\s5
\v 24 ከዚያም ኤርምያስ ለሕዝቡ ሁሉ፣ ለሴቶቹም ሁሉ እንዲህ አለ፣ "በግብጽ ምድር የምትኖሩ ይሁዳ ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።
\v 25 የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'እናንተና ሚስቶቻችሁ በአፋችሁ፣ "ለሰማይ ንግሥት እንድናጥን፣ የመጠጥንም ቍርባን እንድናፈስስላት የተሳልነውን ስእለታችንን በእርግጥ እንፈጽማለን።" ብላችሁ በእጃችሁ አደረጋችሁት፤ እንግዲህ ስእለታችሁን አጽኑ፣ ፈጽሙትም።'
\s5
\v 26 ስለዚህ፣ እናንተ በግብጽ ምድር የምትኖሩ ይሁዳ ሁሉ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፣ 'ተመልከቱ፣ በግብጽ ምድር ሁሉ በሚኖር በይሁዳ ሰው ሁሉ አፍ ስሜ ከእንግዲህ ወዲህ፣ "ሕያው እግዚአብሔርን!" ተብሎ እንዳይጠራ በታላቅ ስሜ ምያለሁ፤" ይላል እግዚአብሔር።
\v 27 ተመልከቱ፣ ለመልካም ሳይሆን ለጥፋት እተጋባቸዋለሁ። በግብጽ ምድር ያሉት የይሁዳ ሰዎች ሁሉ እስኪጠፉ ድረስ በሰይፍና በራብ ያልቃሉ።
\v 28 ከዚያም ከሰይፍ የሚያመልጡ ጥቂት ሰዎች ብቻ ሆነው ከግብጽ ምድር ወደ ይሁዳ ምድር ይመለሳሉ። ሊቀመጡም ወደ ግብጽ ምድር የገቡት የይሁዳ ቅሬታ ሁሉ ከእኔ ወይም ከእነርሱ የማናችን ቃል እንዲጸና ያውቃሉ።
\s5
\v 29 ቃሌም በላያችሁ ለክፋት እንዲጸና ታውቁ ዘንድ በዚህች ስፍራ እንድቀጣችሁ ምልክታችሁ ይህ ነው፣' ይላል እግዚአብሔር።
\v 30 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ተመልከቱ፣ የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን ጠላቱ ለሆነው፣ ነፍሱንም ለሚፈልገው ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ። ሁኔታው የግብጹን ንጉሥ ፈርዖን ሖፍራንን ለጠላቶቹ ነፍሱንም ለሚፈልጉ እጅ አሳልፌ እንደሰጠሁት ይሆናል።"
\s5
\c 45
\p
\v 1 ኤርምያስ ለኔርያ ልጅ ለባሮክ የነገረው ቃል ይህ ነበር። ይህም የሆነው በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም በአራተኛው ዓመት ኤርምያስ እየነገረው በመጽሐፍ በጻፋቸው ጊዜ ነበር፤ እርሱም እንዲህ አለ፣
\v 2 "ባሮክ፣ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይልሃል፦
\v 3 አንተ፣ 'እግዚአብሔር በሕመሜ ላይ ኀዘንን ጨምሮብኛልና ወዮልኝ። በልቅሶዬ ጩኸት ደክሜአለሁ፤ ዕረፍትንም አላገኘሁም' ብለሃል።
\s5
\v 4 ልትለው የሚገባህ ይህንን ነው፦ 'እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተመልከት፣ የሠራሁትን፣ አሁን እያፈረስኩ ነው። የተከልሁትንም፣ እየነቀልሁ ነው። ይኽም በምድር ሁሉ ላይ እውነት ነው።
\v 5 ነገር ግን ለራስህ ታላቅ ነገር ተስፋ ታደርጋለህን? ያንን ተስፋ አታድርግ። በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ ክፉ ነገርን እንደማመጣ ትመለከታለህና አትፈልገው፣ ይላል እግዚአብሔር። ነገር ግን በሄድህበት ስፍራ ሁሉ ነፍስህን እንደ ምርኮ አድርጌ እሰጥሃለሁ።"
\s5
\c 46
\p
\v 1 ስለ አሕዛብ ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው።
\v 2 ስለ ግብጽ፦ "ይህ በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ በከርከሚሽ ስለ ነበረው ሠራዊት ነው። በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም በአራተኛው ዓመት የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ስለ መታው ስለ ግብጽ ንጉሥ ስለ ፈርዖን ኒካዑ ሠራዊት፦
\v 3 ትንንሾቹን እና ትልልቆቹን ጋሻዎች አዘጋጁና ወደ ውጊያ ሂዱ።
\v 4 ፈረሰኞች ሆይ፣ ፈረሶችን ለጉሙና ውጡ፣ ራስ ቍርንም ደፍታችሁ ቁሙ። ጦርንም ሰንግሉ፣ የጦር ዕቃንም ልበሱ።
\s5
\v 5 በዚህ የማየው ምንድነው? ወታደሮቻቸው ተሸንፈዋልና፣ በፍርሃት ተሞልተው ወደ ኋላ ተመለሱ። ወደ ኋላቸውም ሳይመለከቱ ፈጥነው ሸሹ። ድንጋጤ በሁሉ ቦታ አለ፣ ይላል እግዚአብሔር።
\v 6 ፈጣኑ ሊሸሽ አይችልም፣ ወታደሮችም ሊያመልጡ አይችሉም። በሰሜን ተሰናከሉ፣ በኤፍራጥስ ወንዝ በኩል ደግሞ ወደቁ።
\s5
\v 7 ይህ እንደ አባይ ወንዝ የሚነሣ፣ ውኃውም እንደ ወንዝ የሚናወጥለት ማን ነው?
\v 8 ግብጽ እንደ አባይ ወንዝ ይነሣል፣ ውኃውም እንደ ወንዙ ይናወጣል። እርሱም፣' እነሣለሁ ምድርንም ሁሉ እከድናለሁ። ከተሞችንና የሚኖሩባቸውን አጠፋለሁ ብሎአል።
\v 9 ፈረሶች ሆይ፣ ውጡ። ሠረገሎችም ሆይ፣ ንጐዱ፤ ጋሻም የሚያነግቡ የኢትዮጵያና የፋጥ ኃያላን፣ ቀስትንም ይዘው የሚስቡ የሉድ ኃያላን ይውጡ።'
\s5
\v 10 ያ ቀን የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር የበቀል ቀን ነው፣ ደግሞም ጠላቶቹን እርሱ ራሱ ይበቀላቸዋል። ሰይፍ በልቶ ይጠግባል። ደማቸውንም ተሞልቶ ይጠጣል። ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር በሰሜን ምድር በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ መሥዋዕት አለውና።
\s5
\v 11 ድንግሊቱ የግብጽ ሴት ልጅ ሆይ፣ ወደ ገለዓድ ውጪና መድኃኒት ውሰጂ። መድኃኒትን በራስሽ ላይ ማብዛትሽ ጥቅም የለሽ ነገር ነው። ለአንቺ የሚሆን ፈውስ የለም።
\v 12 ወታደሩ በወታደሩ ላይ ተሰናክሎ፣ ሁለቱ በአንድነት ወድቀዋልና አሕዛብ እፍረትሽን ሰምተዋል። ምድር በለቅሶሽ ተሞልታለች።"
\s5
\v 13 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር መጥቶ የግብጽን ምድር ሲያጠቃ እግዚአብሔር ለነብዩ ኤርምያስ የተናገረው ቃል ይህ ነው።
\v 14 "ለግብጽ ተናገሩ፣ በሚግዶልና በሜምፎስ ይሰማ። በጣፍናስ 'ሰይፍ በዙሪያህ ያለውን በልቶአልና፣ ተነሥተህ ተዘጋጅ' ብለዋል።
\s5
\v 15 የከፍታ አምላክሽ ለምን ሸሸ? በበሬ የተመሰለው ጣዖትሽስ ለምን አይቆምም? እግዚአብሔር ገፍትሮ ጥሎታል።
\v 16 እርሱ የሚሰናከሉትን ቊጥር ያበዛል። እያንዳንዳቸው ወታደሮች አንዱ በሌላው ላይ ይወድቃል። እነርሱም፣ "ተነሡ። ወደቤት እንጂድ። ወደገዛ ሕዝባችን፣ ወደ ተወለድንባት ምድር እንሂድ። ይህንን እየቀጠቀጠን ያለውን ሰይፍ ትተን እንሂድ።" ይላሉ።
\v 17 በዚያም፣ 'የግብጽ ንጉሥ ፈርዖን ያገኘውን ዕድል የሚያሳልፍ ኁከተኛ ብቻ ነው" ብለው ይናገራሉ።
\s5
\v 18 "እኔ ሕያው ነኝና በተራሮች መካከል እንዳለ እንደ ታቦር፣ በባሕርም አጠገብ እንዳለ እንደ ቀርሜሎስ፣ እንዲሁ በእውነት ይመጣል፣ ይላል ስሙ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የተባለው ንጉሥ።
\v 19 አንቺ በግብጽ የምትቀመጪ ልጅ ሆይ፣ ለምርኮ የምትሄጂበትን ዕቃ አዘጋጂ። ሜምፎስ የምትሸበር ትሆናለችና፣ ማንም በዚያ የማይኖርባት እንድትሆን ትፈራርሳለችና።
\s5
\v 20 ግብጽ እጅግ የተዋበች ጊደር ናት፣ ነገር ግን ከሰሜን በኩል የሚያሰቃይ መዥገር ይመጣባታል።
\v 21 በመካከሏም ያሉ ቅጥረኛ ወታደሮች እንደ ሰቡ ወይፈኖች ናቸው፣ ነገር ግን እነርሱም እንዲሁ ይመለሱና ይሸሻሉ። የጥፋታቸው ቀን እየመጣባቸው ነውና፣ የቅጣታቸው ጊዜ መጥቶባቸዋልና በአንድነት አይቆሙም።
\v 22 ጠላቶቿ በእርሷ ላይ ይሰለፉባታልና ግብጽ እንደ እባብ ድምፅ ትጮኻለች፣ በደረቷም ተስባ ትሸሻለች። በመጥረቢያ እንደሚቆርጡ እንደ እንጨት ቈራጮች ሆነው ይመጡባታል።
\s5
\v 23 በጣም ጥቅጥቅ ያሉ ቢሆኑም እንኳን ጫካዎቿን ይቈርጣሉ፣ ይላል እግዚአብሔር። ጠላቶቿ ሊቆጠሩ እስከማይችሉ ድረስ ከአንበጣ ይልቅ ብዙ ይሆናሉና።
\v 24 የግብጽ ሴት ልጅ እንድታፍር ትደረጋለች። ከሰሜን ለሚሆኑ ሕዝቦች እጅ ተላልፋ ትሰጣለች።"
\s5
\v 25 የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ እንዲህ ይላል፣ 'ተመልከቱ፣ የኖእ አሞንን፣ ፈርዖንንም፣ ግብጽንና አማልክቶችዋን፣ ፈርዖን ነገሥታቶችዋንና በእነርሱም የሚታመኑትን እቀጣለሁ።
\v 26 ነፍሳቸውንም በሚፈልጉ ሰዎች እጅ፣ በባቢሎን ንጉሥ በናቡክደነፆር እንዲሁም በባርያዎቹም እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ። ከዚያም በኋላ አንደ ቀድሞው ዘመን የሰው መኖሪያ ትሆናለች፣" ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 27 "ነገር ግን፣ አንተ ባርያዬ ያዕቆብ ሆይ፣ አትፍራ። አንተም እስራኤል ሆይ፣ አትደንግጥ። እነሆ፥ አንተን ከሩቅ ዘርህንም ከተማረከባት ምድር አድናለሁ። ከዚያም፣ ያዕቆብ ይመለሳል፣ ሰላም ያገኛል፣ በዋስትናም ይቀመጣል፣ የሚያስፈራራው ማንም አይገኝም።
\v 28 አንተ፣ ባርያዬ ያዕቆብ፣ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ አንተን ያሰደድሁባቸውን አሕዛብን ሁሉ ፈጽሜ አጠፋለሁና አትፍራ ይላል እግዚአብሔር። ነገር ግን አንተን ፈጽሜ አላጠፋህም። በመጠን እቀጣሃለሁ፥ ያለ ቅጣትም አልተውህም።"
\s5
\c 47
\p
\v 1 ስለ ፍልስጥኤማውያን ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው። ይህ ቃል ወደ እርሱ የመጣው ፈርዖን ጋዛን ሳይመታ በፊት ነው።
\v 2 "እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተመልከት፣ ውኃ ከሰሜን ይነሣል። እነርሱም እንደሚያጥለቀልቅ ፈሳሽ ይሆናሉ! ከዚያም በምድሪቱና በመላዋ ሁሉ፣ በከተማይቱና በሚኖሩባት ላይ ይጐርፋሉ! ስለዚህ እያንዳንዱ ሰው ለእርዳታ ይጮኻል፣ በምድሪቱም የሚኖሩ ሁሉ ያለቅሳሉ።
\s5
\v 3 ከኃይለኞች ፈረሶች ከኮቴያቸው መጠብጠብ ድምፅ፣ ከሰረገሎቹና ከጎማዎቻቸውም መሸከርከር ሁከት የተነሣ፣ አባቶች በገዛ ራሳቸው ድካም ምክንያት ልጆቻቸውን አይረዱም።
\v 4 ይህም የሚሆነው ፍልስጥኤማውያንን ሁሉ ያጠፋ ዘንድ የቀሩትንም ረዳቶች ሁሉ ከጢሮስና ከሲዶና የሚቆርጥ ቀን ስለሚመጣ ነው። እግዚአብሔር ፍልስጥኤማውያንና የከፍቶርን ደሴት ቅሬታ ያጠፋልና።
\s5
\v 5 ራሰ ቡሀነት በጋዛ ላይ መጥቶአል። አስቀሎናን በተመለከተ፣ በሸለቋቸው የተተዉት ሕዝብ ዝም እንዲሉ ይደረጋሉ። እስከ መቼ ድረስ በለቅሶ ራሳችሁን ትነጫላችሁ?
\v 6 ወዮ፣ የእግዚአብሔር ሰይፍ! ዝም እስከምትል ምን ያክል ትቆያለህ? ወደ ሰገባህ ተመለስ! ቊም ደግሞም ጸጥ በል።
\v 7 እግዚአብሔር አዝዞሃልና እንዴት ዝም ልትል ትችላለህ። በአስቀሎናና በባሕር ዳር ላይ ጥቃት እንድትፈጽም አዘጋጅቶሃልና።"
\s5
\c 48
\p
\v 1 ስለ ሞዓብ፣ የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ናባው ጠፍታለችና ወዮላት። ቂርያታይም ተይዛለች አፍራለችም። ምሽጓ ተደምስሷል፣ ተዋርዷልም።
\v 2 ከእንግዲህ ወዲህ ሞዓብ ትምክሕት የላትም። በሐሴቦን ያሉ ጠላቶቿ በእርሷ ላይ ጥፋትን አሲረዋል። 'ኑ ሕዝብ እንዳትሆን እናጥፋት። ማድሜንም እንዲሁ ትጠፋለች፣ ሰይፍም ይከታተልሻል።' ብለዋል።
\s5
\v 3 አድምጡ! መፍረስና ታላቅ ጥፋት ያለበት የጩኸት ቃል ከሖሮናይም ተሰማ።
\v 4 ሞዓብ ጠፍታለች። ልጆችዋም ጩኸታቸውን አሰምተዋል።
\v 5 በሉሒት ኮረብታ ለቅሶ እያለቀሱ ይወጣሉ፣ ከጥፋቱም የተነሣ፣ በሖሮናይምም ቍልቍለት ጩኸትን ሰምተዋል።
\s5
\v 6 ሸሹ! ሕይወታችሁን አድኑና በምድረ በዳ እንዳለ ቊጥቋጦ ሁኑ።
\v 7 በሥራሽና በኃብትሽ ታምነሻልና፣ አንቺ ደግሞ ትያዢያለሽ። ከዚያም፣ ካሞሽ ከካህናቱና ከመሪዎቹ ጋር በአንድነት ወደ ምርኮ ይሄዳል።
\s5
\v 8 አጥፊው ወደየከተማው ሁሉ ይመጣል፣ አንዲትም ከተማ አታመልጥም። ስለዚህ እግዚአብሔርም እንደ ተናገረው ሸለቆው ይጠፋል፣ ሜዳውም ይበላሻል።
\v 9 በእርግጥም በርራ እንድትጠፋ ለሞዓብ ክንፍ ስጡአት። ከተሞችዋ በውስጣቸው አንድም የማይኖርባቸው ወና ይሆናሉ።
\v 10 የእግዚአብሔርን ሥራ በስንፍና የሚሠራ ርጉም ይሁን! ሰይፉን ደም ከማፍሰስ የሚከለክል ርጉም ይሁን!
\s5
\v 11 ሞዓብ ከወጣትነቱ ጀምሮ ደህንነት ይሰማው ነበር። እርሱ ከዕቃ ወደ ዕቃ ተገላብጦ እንደማያውቀው ወይኑ ነው። ወደ ምርኮም ሄዶ አያውቅም። ስለዚህ ጣዕሙ ከመቼውም ጊዜ በላይ መልካም ነው፣ መዓዛውም አልተለወጠም።
\v 12 ስለዚህ ተመልከቱ፣ የሚያገላብጡትን ሰዎች የምልክበት ዘመን ይመጣል፣ ይላል እግዚአብሔር፤ እነርሱም እያፈሰሱ ጋኖቹን ባዶ ያደርጋሉ፣ መስቴዎቹንም ይሰብራሉ።
\s5
\v 13 የእስራኤል ቤት ከታመነበት ቤተል እንዳፈረ ሁሉ፣ እንዲሁ ሞዓብ ከታመነበት ካሞሽ ያፍራል።
\v 14 እናንተ፣ 'እኛ ወታደሮች ነን፣ ጽኑዓን ተዋጊዎች ነን' እንዴት ትላላችሁ?
\s5
\v 15 ሞዓብ ይፈርሳል፣ ከተሞቹም ጥቃት ይፈጸምባቸዋል። የተመረጡትም ጕልማሶች ወደ መታረድ ወርደዋል። ይህ የንጉሡ አዋጅ ነው! ስሙም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው።
\v 16 የሞዓብ ጥፋት ሊመጣ ቀርቦአል፤ መከራውም እጅግ ይፈጥናል።
\v 17 በሞዓብ ዙሪያ ያላችሁ ሁሉ፣ አልቅሱ። ዝናውንም የምታውቁ ሁሉ፣ 'ብርቱው በትር፣ የከበረው ሽመል ተሰብሯልና ወዮለት' ብላችሁ አልቅሱለት።
\s5
\v 18 በዲቦን የምትኖሪ ሴት ልጅ ከክብር ስፍራሽ ውረጂና በደረቅ መሬት ላይ ተቀመጪ። ሞዓብን የሚያጠፋው፣ ምሽግሽንም የሚሰብረው ወጥቶብሻልና።
\v 19 በአሮዔር የምትኖሩ ሕዝቦች በመንገድ አጠገብ ቆማችሁ ተመልከቱ። እየሸሹ ያሉትንና የሚያመልጡትን ጠይቊ። 'ምን ተፈጠረ?' በሉ።
\v 20 ሞዓብም ፈራርሷልና አፈረ። አልቅሱ፣ ጩኹ፣ ለእርዳታም ተጣሩ። ሞዓብ እንደ ተዘረፈ በአርኖን አጠገብ ለሰዎች አውሩ።
\s5
\v 21 አሁን በኮረብታማው ገጠር ላይ ባሉት በሖሎን፣ በያሳ፣ በሜፍዓት ላይ፣
\v 22 በዲቦን፣ በናባው፣ በቤት ዲብላታይም ላይ፣
\v 23 በቂርያታይም፣ በቤትጋሙል፣
\v 24 በቤትምዖን ላይ፣ በቂርዮት፣ በባሶራ፣ እና በሞዓብ ምድር ባሉ የቅርብና ሩቅ ከተሞች ሁሉ ላይ ቅጣት መጥቶአል።
\v 25 የሞዓብ ቀንድ ተቈረጠ፤ ክንዱም ተሰበረ፣ ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 26 በእኔ በእግዚአብሔር ላይ ኰርቷልና አስክሩት። እንግዲህ ሞዓብ በገዛ ራሱ ትውከቱ ላይ በጥላቻ እጆቹን ያጨበጭባል፣ ደግሞም መሳለቂያ ይሆናል።
\v 27 እስራኤል ለአንተ መሳለቂያህ አልሆነምን? ወይስ ስለ እርሱ በተናገርህ ጊዜ ሁሉ ራስህን እንድትነቀንቅ በሌቦች መካከል ተገኝቶአልን?
\s5
\v 28 እናንተ በሞዓብ የምትኖሩ ሆይ፣ ከተሞችን ትታችሁ በቋጥኝ ውስጥ ተቀመጡ። በዐለታማ ገደል አፋፍ ቤትዋን እንደምትሠራ ርግብ ሁኑ።
\v 29 እጅግ እንደ ታበየ ስለ ሞዓብ ትዕቢት፣ ስለ ትምክህቱም፣ ስለ ኩራቱም፣ ራሱን ስለማክበሩም፣ ስለ ልቡም ትዕቢት ሰምተናል።
\s5
\v 30 ምንም ሆኖ የማይቆጠረውን የድንፋታ ንግግሩን እኔ ራሴ አውቃለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ ፉከራው ምንም አልሠራም።
\v 31 ስለዚህ ለሞዓብ አለቅሳለሁ፣ በኃዘኔታ ለመላዋ ሞዓብ እጮኻለሁ። ለቂርሔሬስ ሰዎች አለቅሳለሁ።
\v 32 አንቺ የሴባማ ወይን ሆይ፣ ከኢያዜር ልቅሶ ይልቅ ለአንቺ አለቅሳለሁ! ቅርንጫፎችሽ የጨው ባሕርን ተሻግረው ወደ ኢያዜር ባሕር ደርሰዋል። አጥፊዎች በሰብልሽና በወይንሽ ላይ ጥቃት ፈጽመዋል።
\s5
\v 33 ክብረ-በዓላዊ ሐሤትና ፍንደቃ ከፍሬያማው እርሻና ከሞዓብ ምድር ጠፍተዋል። የወይን ጠጁን ከመጥመቂያው አጥፍቻለሁ። ጠማቂውም በደስታ እልልታ አይጠምቅም። እልልታቸውም የደስታ እልልታ አይሆንም።
\s5
\v 34 ከሐሴቦን ጩኸት እስከ ኤልያሊና፣ እስከ ያሀጽ ድረስ ድምፃቸውን ሰጥተዋል፤ ከዞዓር እስከ ሖሮናይምና እስከ ዔግላት ሺሊሺያ ድረስ ይደርሳል፤ የኔምሬም ውኃዎች ደርቀዋልና።
\v 35 በኮረብታው መስገጃ ላይ የሚሠዋውን ለአማልክቱም የሚያጥነውን ከሞዓብ ፍጻሜያቸውን አደርጋለሁ ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 36 ልቤ ለሞዓብ እንደ እንቢልታ ይጮኻል። ልቤም ለቂርሔሬስ ሰዎች እንደ እንቢልታ ይጮኻል። ያገኙት ትርፋቸው ጠፍቶባቸዋልና።
\v 37 ራስ ሁሉ መላጣ፣ ጢምም ሁሉ የተላጨ ነውና። በእጅም ሁሉ ላይ ክትፋት በወገብም ላይ ማቅ አለና።
\s5
\v 38 በሞዓብ ሰገነት ሁሉ ላይ፣ በእያንዳንዱም የተደላደለ ጣራ እና በሁሉም የሞዓብ አደባባዮች ላይ ለቅሶ አለ። ሞዓብን ማንም እንደማይፈልጋቸው የሸክላ ዕቃዎች ሰብሬአለሁና፣ ይላል እግዚአብሔር።
\v 39 እንዴት ተገለበጠ! ከለቅሶም የተነሣ ሞዓብ እያፈረ ጀርባውን እንዴት መለሰ! ብላችሁ አልቅሱ። ስለዚህ ሞዓብ በዙሪያው ላሉት ሁሉ መሳቂያና ድንጋጤ ይሆናል።"
\s5
\v 40 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ተመልከቱ፣ ጠላት እንደ ንስር እየበረረ፣ ክንፉንም በሞዓብ ላይ እየዘረጋ ይመጣል።
\v 41 ከተሞቹ ተይዘዋል፣ ምሽጎቹም ተይዘዋል። በዚያም ቀን የሞዓብ ወታደሮች ልብ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ልብ ይሆናል።
\s5
\v 42 ስለዚህ ሞዓብ በእኔ በእግዚአብሔር ላይ እብሪተኛ ሆኗልና ሕዝብ ከመሆን ይጠፋል።
\v 43 በሞዓብ የምትኖሩ ሆይ፣ ፍርሃትና ጉድጓድ፣ ወጥመድም በእናንተ ላይ አለ፣ ይላል እግዚአብሔር።
\v 44 በፍርሃት የሸሸ በጕድጓድ ውስጥ ይወድቃል፥ ከጉድጓድም የወጣ በወጥመድ ይያዛል፤ በሞዓብ ላይ የምበቀልበትን ዓመት አመጣበታለሁና፣ ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 45 የሸሹ ያለ ምንም ብርታት ከሐሴቦን ጥላ በታች ቆመዋል፤ እሳት ከሐሴቦን፣ ነበልባልም ከሴዎን ወጥቶአልና፣ የሞዓብንም ማዕዘን የሤትንም ልጆች አናት በልቶአልና።
\s5
\v 46 ሞዓብ ሆይ፣ ወዮልህ! የካሞሽ ሕዝብ ተደምስሰዋል፣ ወንዶች ልጆችህ ተማርከዋልና፣ ሴቶች ልጆችህም ወደ ምርኮ ሄደዋልና።
\v 47 ነገር ግን በኋለኛው ዘመን የሞዓብን ምርኮ እመልሳለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር።" የሞዓብ ፍርድ እዚህ ላይ ያበቃል።
\s5
\c 49
\p
\v 1 ስለ አሞን ልጆች፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "እስራኤል ልጆች የሏትምን? ወይስ የትኛውንም ነገር ከእስራኤል የሚወርስ የላትምን? ሚልኮም ጋድን ለምን ወረሰ? ሕዝቡስ በከተሞቿ ላይ ስለ ምን ተቀመጠ?
\v 2 ስለዚህ ተመልከቱ፣ በአሞን ልጆች ከተማ በረባት ላይ የጦርነት ውካታን የማሰማበት ዘመን ይመጣል፣ ይላል እግዚአብሔር፤ የፍርስራሽ ክምርም ትሆናለች፣ ሴቶች ልጆችዋም በእሳት ይቃጠላሉ። እስራኤልም የወረሷትን ትወርሳለች፣" ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 3 "ሐሴቦን ሆይ፣ ጋይ ፈርሳለችና አልቅሺላት! እናንተም የረባት ሴቶች ልጆች ጩኹ! ማቅ ልበሱ። ሚልኮም ካህናቱና አለቆቹም በአንድነት ይማረካሉና ጩኹ፣ ማቅም ታጠቁ፣ አልቅሱም፣ በቅጥሮችም መካከል ተሯሯጡ።
\v 4 ማን ይመጣብኛል ብለሽ በብርታትሽ የታመንሽ አንቺ ከዳተኛ ልጅ ሆይ፣ በሸለቆችሽ፣ ውኃ በሚያረካቸው ሸለቆችሽ፣ ስለ ምን በብርታትሽ ትመኪያለሽ?
\s5
\v 5 ተመልከቺ፣ ሽብርን አመጣብሻለሁ፣ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ይህ ሽብር በዙሪያሽ ከከበቡሽ ሁሉ ዘንድ ይሆናል። እያንዳንዳችሁም በፊታችሁ ወዳለው ስፍራ ትበተናላችሁ። የሚሸሹትንም የሚሰበስብ አይኖርም።
\v 6 ነገር ግን ከዚያ በኋላ የአሞንን ልጆችን ምርኮ እመልሳለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር።"
\s5
\v 7 ስለ ኤዶምያስ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "በውኑ በቴማን ከእንግዲህ ጥበብ አይገኝምን? ማስተዋል ካላቸውስ መልካም ምክር ጠፍቶአልን? ጥበባቸው ተበላሽቷልን?
\v 8 ሽሹ! ተመለሹ! እናንተ በድዳን የምትኖሩ ሆይ፣ በጥልቅ ውስጥ ተቀመጡ። የዔሳውን ጥፋት እርሱን በምቀጣበት ጊዜ አመጣበታለሁና
\s5
\v 9 የወይን አዝመራ ለቃሚዎች ወደ አንተ ቢመጡ፣ቃርሚያውን አይተውልህምን? ሌቦችስ በሌሊት ቢመጡ፣ የሚሠርቁት እስኪበቃቸው ድረስ አይደለምን?
\v 10 እኔ ግን ዔሳውን ዐራቈትሁት። የተሸሸገበትንም ስፍራዎች ገለጥሁ። ስለዚህ ይሸሸግ ዘንድ አይችልም። ልጆቹ፣ ወንድሞቹ፣ እንዲሁም ጎረቤቶቹ ጠፍተዋል፤ እርሱም የለም።
\v 11 ድሀ አደጎችህን ተዋቸው። እኔም ለሕይወታቸው እንክብካቤ አደርጋለሁ፤ መበለቶችህም በእኔ ሊታመኑ ይችላሉ።"
\s5
\v 12 እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፣ "ተመልከቱ ያልተገባቸው ሰዎች ጽዋውን በእርግጥም ሊጠጡት ይገባቸዋል። አንተም ሳትቀጣ የምትቀር ይመስልሃልን? በእርግጥ ትጠጣለህ እንጂ ያለ ቅጣት አትቀርም።
\v 13 ባሶራ መደነቂያና መሰደቢያ፣ መረገሚያም እንድትሆን በራሴ ምያለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር። ከተሞችዋም ሁሉ ለዘላለም ባድማ ይሆናሉ።
\s5
\v 14 ከእግዚአብሔር ዘንድ ወሬ ሰምቻለሁ፣ መልእክተኛም በአሕዛብም መካከል ተልኳል፣ 'ተሰብሰቡ፣ እርስዋንም አጥቊ። ለጦርነትም ተነሡ' ይላል።
\v 15 "ተመልከቱ፣ በንጽጽር ስትታይ በአሕዛብ ዘንድ የተጠቃህ፣ በሰዎችም ዘንድ የተናቅህ አድርጌሃለሁ።
\s5
\v 16 በዓለት ንቃቃት ውስጥ የምትኖር፣ የተራራውን ከፍታ የምትይዝ ሆይ፣ ድፍረትህና የልብህ ኵራት አታልለውሃል። ቤትህን ምንም እንደ ንስር ከፍ ብታደርግ፣ ከዚያ አወርድሃለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 17 ኤዶምያስም የሚያልፉባት ሁሉ እስኪደነቁ ድረስ መሸበሪያ ትሆናለች። ስለ መጣባትም መቅሠፍት ሁሉ እንዲህ ያሉ ሰዎች ሁሉ ተደናግጠው ያፍዋጩባታል።
\v 18 "ሰዶምና ገሞራ፣ በእነርሱም አጠገብ የነበሩት ከተሞች እንደ ተገለበጡ፣" ይላል እግዚአብሔር፣ "እንዲሁ በዚያ ሰው አይቀመጥም የሰው ልጅም አይኖርባትም።
\s5
\v 19 ተመልከቱ፣ ከእርስዋ ዘንድ በቶሎ አባርራቸዋለሁና በጠነከረው አምባ ላይ ከዮርዳኖስ ትዕቢት እንደ አንበሳ ይወጣል፤ የተመረጠውንም በእርስዋ ላይ እሾመዋለሁ፤ እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ወይስ ለእኔ ጊዜ የሚወስን ማን ነው? ወይስ ፊቴን የሚቃወም እረኛ ማን ነው?
\s5
\v 20 "ስለዚህ እግዚአብሔር በኤዶምያስ ላይ የመከረባትን ምክር፣ በቴማንም በሚኖሩ ሰዎች ላይ ያሰባትን አሳብ አድም። በእውነት ትንንሽ መንጎች ሳይቀሩ ይጐተታሉ። በእውነት ማደሪያቸውን ባድማ ያደርግባቸዋል።
\s5
\v 21 ከመውደቃቸው ድምፅ የተነሣ ምድር ተናወጠች። የጩኸታቸውም ድምፅ በቀይ ባሕር ተሰማ።
\v 22 ተመልከቱ፣ አንዱ መጥቶ እንደ ንስር ወጥቶ ያጠቃል፣ እያንዣበበ ክንፉን በባሶራ ላይ ይዘረጋል። ያን ጊዜ በዚያ ቀን፣ የኤዶምያስ ወታደሮች ልብ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ልብ ይሆናል።"
\s5
\v 23 ስለ ደማስቆ፣ "ክፉ ወሬ ሰምተዋልና ሐማትና አርፋድ አፈሩ። ቀለጡ! ሊረጋጋ በማይችል ባሕር ላይ ኅዘን አለ።
\v 24 ደማስቆ እጅግ ደከመች። ትሸሽም ዘንድ ዘወር አለች፤ ሽብር ያዛት፣ እንደ ወላድም ሴት ጣርና ምጥ ያዛት።
\v 25 ሕዝቦቿም፣ 'የተመሰገነችው ከተማ፣ የደስታዬ ከተማ፣ ስፍራውን ሳትለቅቅ እንዴት ቀረች?' ይላሉ።
\s5
\v 26 ስለዚህ ጐበዛዝትዋ በአደባባይዋ ላይ ይወድቃሉ፣ በዚያም ቀን ተዋጊዎቿ ሁሉ ይጠፋሉ፣ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።"
\v 27 "በደማስቆም ቅጥር ላይ እሳት አነድዳለሁ፣ የወልደ አዴርንም አዳራሾች ትበላለች።"
\s5
\v 28 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ስለ መታ ስለ ቄዳርና ስለ አሶር መንግሥታት፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ "ተነሡ ወደ ቄዳርም ውጡ፣ የምሥራቅንም ልጆች አጥፉ።
\v 29 ጦር ሠራዊቱ ድንኳናቸውንና መንጋቸውን ይወስዳል፤ መጋረጆቻቸውንና ዕቃቸውን ሁሉ ግመሎቻቸውንም ለራሳቸው ይወስዳሉ። በዙሪያቸውም ሁሉ ጥፋትን ጥሩባቸው፣ 'ሽብር በዙሪያቸው ሁሉ አለ!"
\s5
\v 30 ሽሹ! በሩቅ ቦታም ተቅበዝበዙ! እናንተ በአሶር የምትኖሩ ሆይ፣ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ተማክሮባችኋልና፣ አሳብም አስቦባችኋልና በጥልቅ ውስጥ ተቀመጡ፣ ይላል እግዚአብሔር። ሽሹ! ዙሩና ተመለሱ!
\v 31 ዕርፊት ወዳለበት በዋስትናም ወደ ተቀመጠው፣ ደጅና መወርወሪያ ወደሌለው ብቻውንም ወደ ተቀመጠው ሕዝብ ውጡ፣ ተነሡ! አጥቊ!።
\s5
\v 32 ግመሎቻቸው ይበዘበዛሉ፣ የእንስሶቻቸውም ብዛት በጦርነት ይማረካል። ጠጉራቸውንም በዙሪያ የሚላጩትን ሰዎች ወደ ነፋሳት ሁሉ እበትናቸዋለሁ፤ ከየዳርቻቸውም ሁሉ ጥፋት አመጣባቸዋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።
\v 33 አሶርም የቀበሮ መኖሪያና የዘላለም ባድማ ትሆናለች። በዚያም ሰው አይኖርም፣ የሰው ልጅም አይቀመጥባትም።"
\s5
\v 34 ስለ ኤላም ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው። ይህ የሆነው በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ መንግሥት መጀመሪያ ነው። እንዲህም አለ፣
\v 35 "የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ዋና የኃይላቸው መሣሪያ የሆነውን የኤላምን ቀስት እሰብራለሁ።
\v 36 ከአራቱም ከሰማይ ማዕዘናት አራቱን ነፋሳት በኤላም ላይ አመጣለሁ፣ የኤላምን ሕዝብ ወደ እነዚያ ነፋሳት ሁሉ እበትናቸዋለሁ። ከኤላም የተሰደዱ ሰዎች የማይበተኑበት ሕዝብ አይገኝም።
\s5
\v 37 ስለዚህ በጠላቶቻቸውና ነፍሳቸውን በሚሹአት ፊት ኤላምን አስደነግጣለሁ። ክፉ ነገርን እርሱም ጽኑ ቍጣዬን አመጣባቸዋለሁና፣ ይላል እግዚአብሔር። እስካጠፋቸውም ድረስ በኋላቸው ሰይፍ እሰድድባቸዋለሁ።
\v 38 ከዚያም፣ ዙፋኔንም በኤላም አኖርና ንጉሡን ከእነአለቆቹ አጠፋለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር።
\v 39 ነገር ግን በኋለኛው ዘመን የኤላምን ምርኮ እመልሳለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር።"
\s5
\c 50
\p
\v 1 እግዚአብሔር ስለ ከለዳውያን ምድር ስለ ባቢሎን በነቢዩ በኤርምያስ የተናገረው ቃል ይህ ነው፣
\v 2 "በአሕዛብ መካከል ተናገሩና እንዲሰሙ አድርጉ። ዓላማውን አንሡና እንዲሰሙ አውሩ። አትደብቁት። 'ባቢሎን ተወሰደች። ቤል አፈረ። ሜሮዳክ ደነገጠ። ጣዖቶችዋ አፈሩ። ምስሎችዋ ደነገጡ' በሉ።
\s5
\v 3 ሕዝብ ከሰሜን ወጥቶባታል ምድርዋንም ባድማ ያደርጋል፣ የሚቀመጥባት እንዳይገኝባት። ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ በውስጥዋ አይኖሩም። ሸሽተው ሄደዋል።
\v 4 በእነዚያም ወራት፣ በዚያም ጊዜ፣ ይላል እግዚአብሔር፣ የእስራኤል ልጆችና የይሁዳ ልጆች በአንድነት ሆነው እያለቀሱና አምላካቸውን እግዚአብሔርን እየፈለጉ ይመጣሉ።
\v 5 ፊታቸውንም ወደጽዮን አቅንተው ይሄዳሉ። ከቶ በማይረሳ በዘላለም ቃል ኪዳን ወደ እግዚአብሔር ሄደው ራሳቸውን ከእግዚአብሔር ጋር ያገኛኛሉ።
\s5
\v 6 ሕዝቤ የጠፉ በጎች ሆነዋል። እረኞቻቸው በተራሮች ላይ አስተው አቅበዘበዟቸው፤ ከኮረብታ ወደ ኮረብታ አለፉ። ሄዱ፣ የኖሩበትንም በረታቸውን ረሱ።
\v 7 ሲሄዱባቸው ያገኙአቸው ሁሉ በሉአቸው። ጠላቶቻቸውም፣ 'በጽድቅ ማደሪያ በእግዚአብሔር ላይ፣ በአባቶቻቸው ተስፋ በእግዚአብሔር ላይ፣ ኃጢአት ስለ ሠሩ እኛ አልበደልንም' አሉ።
\s5
\v 8 ከባቢሎን መካከል ሽሹ፤ ወደ ከከለዳውያን ድር ውጡ፤ በመንጎችም ፊት እንደ አውራ ፍየሎች ሁኑ።
\v 9 ተመልከቱ፣ ከሰሜን ምድር የታላላቅ አሕዛብን ጉባኤ አስነሣለሁ በባቢሎንም ላይ አመጣቸዋለሁ። በእርስዋም ላይ ይሰለፋሉ። ባቢሎን ከዚያ ስፍራ ትወሰዳለች። ፍላጾቻቸውም ባዶውን እንደማይመለስ እንደ ተካነ ተዋጊ ፍላጻ ናቸው።
\v 10 የከላውዴዎንም ምድር ትበዘበዛለች። የሚበዘብዙአትም ሁሉ ይጠግባሉ፣ ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 11 ርስቴን የምትበዘብዙ እናንተ፣ ደስ ይበላችሁ፤ በመስክ ላይም እንዳለች ጊደር ሆናችሁ ሐሤት እያደረጋችሁ ዝለሉ፤ እንደ ብርቱ ፈረሶች አሽካኩ።
\v 12 እንዲሁ እናታችሁ በእጅጉ ታፍራለች፤ የወለደቻችሁም ትጐሰቍላለች። ተመልከቱ፣ በአሕዛብ መካከል አነስተኛይቱ ትሆናለችና፣ ምድረ በዳና ደረቅ ምድር፣ በረሀም ትሆናለች።
\v 13 ከእግዚአብሔር ቍጣ የተነሣ ባድማ ትሆናለች እንጂ ሰው አይኖርባትም። በባቢሎንም በኩል የሚያልፍ ሁሉ ይደነቃል፣ በመጣባትም መቅሠፍት ሁሉ ያፍዋጫል።
\s5
\v 14 በባቢሎን ላይ በዙሪያዋ ተሰለፉ። እናንተ ቀስትን የምትገትሩ ሰዎች ሁሉ። በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት ሠርታለችና ወርውሩባት ፍላጾችንም አትመልሱ።
\v 15 የእግዚአብሔር በቀል ነውና ድል እያደረጋችሁ በዙሪያዋ ጩኹባት። እጅዋን ሰጠች፤ ግንቦችዋ ወደቁ፣ ቅጥሮችዋም ፈረሱ ይህ የእግዚአብሔር በቀል ነውና። እርስዋን ተበቀሉ! እንደ ሠራችውም ሥሩባት።
\s5
\v 16 ዘሪውንና በመከር ጊዜ ማጭድ የሚይዘውን ከባቢሎን አጥፉ። ከሚያስጨንቅ ሰይፍ ፊት እያንዳንዱ ወደ ወገኑ ይመለሳል እያንዳንዱም ወደ አገሩ ይሸሻል።
\s5
\v 17 እስራኤል ባዝኖ የተበተነ በግ እና አንበሶች ያሳደዱት ነው። መጀመሪያ የአሦር ንጉሥ በላው፤ በመጨረሻም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር አጥንቱን ቈረጠመው።
\v 18 ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተመልከቱ፣ የአሦርን ንጉሥ እንደ ቀጣሁ፣ እንዲሁ የባቢሎንን ንጉሥና ምድሩን እቀጣለሁ።
\s5
\v 19 እስራኤልንም ወደ ማሰማርያ ምድሩ እመልሳለሁ፤ በቀርሜሎስና በባሳንም ላይ ይሰማራል። በኤፍሬም ተራራና በገለዓድ ላይ ይጠግባል።
\v 20 በእነዚያም ቀኖች፣ በዚያ ጊዜ፣ እነዚህን ያስቀረኋቸውን ይቅር እላቸዋለሁና፣ ይላል እግዚአብሔር፣ የእስራኤል በደል የይሁዳም ኃጢአት ይፈለጋል ምንም አይገኝም።"
\s5
\v 21 "በምራታይም ምድር ላይ፣ በፋቁድም በሚኖሩት ላይ ተነሥና ውጣ፤ ግደላቸው ፈጽመህም አጥፋቸው፤ ይላል እግዚአብሔር፣ እንዳዘዝሁህም ሁሉ አድርግ።
\v 22 የሰልፍና የታላቅ ጥፋት ውካታ በምድሪቱ ላይ አለ።
\s5
\v 23 የምድር ሁሉ መዶሻ እንዴት ደቀቀ እንዴትስ ተደመሰሰ። ባቢሎንስ በአሕዛብ መካከል እንዴት መሸበሪያ ሆነች።
\v 24 ባቢሎን ሆይ፣ አጥምጄብሻለሁ። አንቺም ሳታውቂ ተይዘሻል፤ ከእኔ ከእግዚአብሔር ጋር ስለ ተዋጋሽ ተገኝተሻል ተይዘሽማል።
\s5
\v 25 እግዚአብሔር ዕቃ ቤቱን ከፍቶ የቍጣውን ዕቃ ጦር አውጥቶአል። የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በከለዳውያን ምድር ይሠራ ዘንድ ሥራ አለውና።
\v 26 ከየበኩሉ በእርስዋ ላይ ጥቃትን ፈጽሙ። ጎተራዎችዋንም ክፈቱ። እንደ ክምርም አድርጓት፣ ፈጽማችሁም አጥፉአት። አንዳችም አታስቀሩላት።
\s5
\v 27 ወይፈኖችዋን ሁሉ እረዱ። ወደ መታረድም ስፍራ ላኳቸው። ቀናቸው፣ የመቀጣታቸው ጊዜ፣ ደርሶአልና ወዮላቸው!
\v 28 የአምላካችንን የእግዚአብሔርን በቀል፣ የመቅደሱንም በቀል በጽዮን ይነግሩ ዘንድ ሸሽተው ከባቢሎን አገር ያመለጡት ሰዎች ድምፅ ተሰምቶአል።"
\s5
\v 29 ቀስትን የሚገትሩትን ቀስተኞችን ሁሉ በባቢሎን ላይ ጥሩአቸው። በዙሪያዋ ስፈሩባት፣ አንድም አያምልጥ። በእስራኤል ቅዱስ ላይ በእግዚአብሔር ላይ ኰርታለችና እንደ ሥራዋ መጠን መልሱላት። እንዳደረገችም ሁሉ አድርጉባት።
\v 30 ስለዚህ ጐበዛዝትዋ በአደባባይዋ ላይ ይወድቃሉ፣ በዚያም ቀን ሰልፈኞችዋ ሁሉ ይጠፋሉ፣ ይላል እግዚአብሔር።"
\s5
\v 31 ትዕቢተኛው ሆይ፣ አንተን የምቀጣበት ጊዜ፣ ቀንህ ደርሶአልና በአንተ ላይ ነኝ፣ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
\v 32 ስለዚህ ትዕቢተኞቹ ተሰናክለው ይወድቃሉ። የሚያነሣቸው ማንም አይኖርም። በከተሞቻቸውም ውስጥ እሳት አነድዳለሁ፤ በዙሪያቸው ያለውን ሁሉ ትበላለች።
\s5
\v 33 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የእስራኤል ልጆችና የይሁዳ ልጆች በአንድነት ተጨቊነዋል። የማረኳቸውም ሁሉ አሁን ድረስ በኃይል ይዘዋቸዋል፤ ይለቅቁአቸውም ዘንድ እንቢ ብለዋል።
\v 34 የሚቤዣቸው ብርቱ ነው። ስሙም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው። ምድርንም ያሳርፍ ዘንድ፣ በባቢሎንም የሚኖሩትን ያውክ ዘንድ ሙግታቸውን ፈጽሞ ይሟገታል።
\s5
\v 35 ሰይፍ በከለዳውያንና በባቢሎን በሚኖሩ ላይ፣ በአለቆችዋና በጥበበኞችዋ ላይ አለ፣ ይላል እግዚአብሔር።
\v 36 ጥንቆላን በሚናገሩት ላይ ሰይፍ አለ፣ ራሳቸውን ሰነፎች አድርገው ይገልጣሉ። ሰይፍም በጦረኞችዋ ላይ አለ፣ እነርሱም በሽብር ይሞላሉ።
\v 37 ሰይፍ በፈረሶቻቸውና በሰረገሎቻቸው ላይ በመካከልዋም ባሉት በልዩ በልዩ ሕዝብ ሁሉ ላይ አለ፣ እነርሱም እንደ ሴቶች ይሆናሉ። ሰይፍ በቤተ መዛግብቷ ላይ አለ፣ ለብዝበዛም ይሆናል።
\s5
\v 38 እርስዋ የተቀረጹ ምስሎች ምድር ናት፣ እነርሱም በጣዖታት ይመካሉና ድርቅ በውኆችዋ ላይ ይሆናል እነርሱም ይደርቃሉ።
\v 39 ስለዚህ የምድረ በዳ አራዊት ከተኵላዎች ጋር ይኖሩባታል፣ ሰጐኖችም ይኖሩባታል፤ ሰውም ከዚያ ወዲያ ለዘላለም አይኖርባትም፣ እስከ ልጅ ልጅም ድረስ የሚኖርባት የለም።
\v 40 ሰዶምንና ገሞራን በአጠገባቸውም የነበሩትን ከተምች እግዚአብሔር እንደ ገለበጣቸው፣ ይላል እግዚአብሔር፣ እንዲሁ ሰው በዚያ አይኖርም የሰውም ልጅ አይኖርባትም።"
\s5
\v 41 "ተመልከቱ፣ ሕዝብ ከሰሜን ይመጣል፣ ታላቅ ሕዝብና ብዙ ነገሥታትም ከምድር ሩቅ ዳርቻዎች ይነሣሉ።
\v 42 ቀስትንና ጦርን ይይዛሉ። ጨካኞች ናቸው ምሕረትም አያደርጉም። ድምፃቸው እንደ ባሕር ይተምማል፣ በፈረሶችም ላይ ይቀመጣሉ፤ የባቢሎን ሴት ልጅ ሆይ፣ ለሰልፍ እንደ ተዘጋጀ ሰው እያንዳንዳቸው በአንቺ ላይ ተሰለፉ።
\v 43 የባቢሎን ንጉሥ ወሬአቸውን ሰምቶአል፣ እጁም ዝላ ደክማለች። ጭንቀትም ይዞታል፣ ምጥ ወላድ ሴትን እንደሚይዛት ጭንቀት ይዞታል።
\s5
\v 44 ተመልከቱ! ከእርስዋ ዘንድ በቶሎ አባርራቸዋለሁና በጠነከረው አምባ ላይ ከዮርዳኖስ ትዕቢት ውስጥ እንደ አንበሳ ይወጣል። የተመረጠውንም በእርስዋ ላይ እሾመዋለሁ። እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ወይስ ለእኔ ጊዜ የሚወስን ማን ነው? ወይስ ፊቴን የሚቃወም እረኛ ማን ነው?
\s5
\v 45 ስለዚህ እግዚአብሔር በባቢሎን ላይ የመከረባትን ምክር፣ በከለዳውያንም ምድር ላይ ያሰባትን አሳብ ስሙ። በእውነት የመንጋ ትናንሾች ሳይቀሩ ይጎተታሉ። በእውነት ማደሪያቸውን ባድማ ያደርግባቸዋል።
\v 46 ከባቢሎን መያዝ ድምፅ የተነሣ ምድር ተናወጠች፤ ጩኸትም በአሕዛብ መካከል ዘንድ ተሰማ።"
\s5
\c 51
\p
\v 1 "እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ ተመልከቱ፣ በባቢሎን ላይና በከለዳውያን ምድር በሚኖሩት ላይ አጥፊውን ነፋስ አስነሣለሁ።
\v 2 በባቢሎንም ላይ የውጪ ሰዎች እልካለሁ። እነርሱም ይበትኗታል፣ ምድርዋንም ባዶ ያደርጋሉ፤ በመከራም ቀን በዙሪያዋ ይከብቡአታል።
\s5
\v 3 በወርዋሪው ላይ በጥሩርም በሚነሣው ላይ ቀስተኛው ቀስቱን ይገትር፤ ለጐበዛዝትዋ አትዘኑ፣ መላውን ሠራዊትዋንም አጥፉ።
\v 4 የቆሰሉት ሰዎች በከለዳውያንም ምድር ተገድለው፣ በሜዳዋም ላይ ተወግተው ይወድቃሉና።
\s5
\v 5 ምድራቸው በእስራኤል ቅዱስ ላይ በተሠራው በደል ምንም እንኳ የተሞላች ብትሆን፣ እስራኤልም ሆነ ይሁዳ በአምላኩ በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ዘንድ አልተጣለም።
\v 6 ከባቢሎን ውስጥ ሽሹ፤ እያንዳንዳችሁም ራሳችሁን አድኑ። በበደልዋ አትጥፉ። የእግዚአብሔር የበቀል ጊዜ ነውና። እርሱም ብድራትዋን ይከፍላታል።
\s5
\v 7 ባቢሎን በእግዚአብሔር እጅ ውስጥ ምድርን ሁሉ ያሰከረች የወርቅ ጽዋ ነበረች፣ አሕዛብም ከጠጅዋ ጠጥተዋል፤ ስለዚህ አሕዛብ እብድ ሆነዋል።
\v 8 ባቢሎን በድንገት ወድቃ ጠፍታለች። ለእርሷ አልቅሱላት! ትፈወስም እንደ ሆነ ለቊስልዋ መድኃኒት ውሰዱላት።
\s5
\v 9 'ባቢሎንን ለመፈወስ ተመኘን፣ እርስዋ ግን አልተፈወሰችም። ፍርድዋ እስከ ሰማይ ደርሶአልና፣ እስከ ደመናም ድረስ ከፍ ከፍ ብሎአልና ትታችኋት እያንዳንዳችን ወደ ምድራችን እንሂድ።'
\v 10 እግዚአብሔር ጽድቃችንን አውጥቶአል። ኑ፣ በጽዮን የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ሥራ እንናገር።'
\s5
\v 11 ፍላጾችን ሳሉ ጋሻዎችንም አዘጋጁ። እግዚአብሔር ያጠፋት ዘንድ አሳቡ በባቢሎን ላይ ነውና የሜዶንን ነገሥታት መንፈስ አስነሥቶአል፤ የእግዚብሔር በቀል፣ የመቅደሱ መጥፊያ በቀል ነውና።
\v 12 በባቢሎን ቅጥር ዓላማውን አንሡበት፣ ጥበቃን አጽኑ። ተመልካቾችን አቁሙ፣ ከከተማዋ የሚወጡትን ለመያዝ ድብቅ ጦር አዘጋጁ። እግዚአብሔር በባቢሎን በሚኖሩት ላይ የተናገረውን አስቦአልና፣ አድርጎአልምና።
\s5
\v 13 አንቺ በብዙ ውኃ አጠገብ የተቀመጥሽ፣ በመዝገብም የበለጠግሽ፣ እንደ ስስትሽ መጠን ፍጻሜሽ ደርሶአል።
\v 14 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል በራሱ ምሏል፣ 'በእውነት ሰዎችን እንደ አንበጣ እሞላብሻለሁ፣ እነርሱም የጦርነት ጩኸት ያነሡብሻል።'
\s5
\v 15 ምድርን በኃይሉ ፈጠረ፤ ዓለሙን በጥበቡ መሠረተ። ሰማያትንም በማስተዋሉ ዘረጋ።
\v 16 ድምጹን ባሰማ ጊዜ ውኆች በሰማይ ይታወካሉ፣ ከምድርም ዳር ደመናትን ከፍ ያደርጋል። ለዝናብም መብረቅን ያደርጋል፣ ነፍስንም ከቤተ መዛግብቱ ያወጣል።
\s5
\v 17 ሰው ሁሉ እውቀት አጥቶ እንደ እንስሳ ሆኗል፤ እያንዳንዱ አንጥረኛ ሁሉ ከቀረጸው ምስል የተነሣ አፍሮአል። ቀልጦ የተሠራ ምስሉ ውሸት ነውና፤ እስትንፋስም የላቸውምና።
\v 18 እነርሱም ምናምንቴና፣ የቀልድ ሥራ ናቸው፤ በሚቀጡበት ጊዜ ይጠፋሉ።
\v 19 የያዕቆብ እድል ፈንታ እንደ እነዚህ አይደለም፣ እርሱ የሁሉ ፈጣሪ ነውና። እስራኤልም የርስቱ ነገድ ነው፤ ስሙም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው።
\s5
\v 20 አንቺ መዶሻዬና የጦር መሣሪያዬ ነሽ። በአንቺ አሕዛብን እሰባብራለሁ፤ በአንቺም መንግሥታትን አጠፋለሁ።
\v 21 በአንቺ ፈረሱንና ሠረገላውን እሰባብራለሁ፤
\s5
\v 22 በአንቺም በላዩ የሚቀመጡትን ወንድ እና ሴት እሰባብራለሁ፤ በአንቺም ሽማግሌውንና ብላቴናውን እሰባብራለሁ። በአንቺም ጐልማሳውንና ልጃገረዲቱን እሰባብራለሁ።
\v 23 በአንቺም እረኛውንና መንጋውን እሰባብራለሁ፤ በአንቺም አራሹንና ጥማጁን እሰባብራለሁ፤ በአንቺም አለቆችንና ሹማምቶችን አሰባብራለሁ።
\s5
\v 24 በጽዮን በዓይናችሁ ፊት ስለሠሩት ክፋታቸው ሁሉ በባቢሎንና በከለዳውያን ምድር በሚኖሩ ሁሉ ላይ ፍዳቸውን እከፍላለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 25 "ተመልከት፣ አንተ ምድርን ሁሉ የምታጠፋ አጥፊ ተራራ ሆይ፣ እኔ በአንተ ላይ ነኝ፣ ይላል እግዚአብሔር። እጄንም እዘረጋብሃለሁ፣ ከድንጋዮችም ላይ አንከባልልሃለሁ። የተቃጠለም ተራራ አደርግሃለሁ።
\v 26 ከአንተም ለማዕዘንና ለመሠረት የሚሆን ድንጋይ አይወስዱም፣ ለዘላለምም ባድማ ትሆናለህ፣ ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 27 "በምድር ላይ ዓላማን አንሡ። በአሕዛብም መካከል መለከት ንፉ። እንዲያጠቋት አሕዛብን አዘጋጁባት፤ የአራራትንና የሚኒን የአስከናዝንም መንግሥታት ሰብስቡባት፣ አለቃንም በላይዋ አቁሙ። እንደ ጠጉራም አንበጣ ኩብኩባ ፈረሶችን በላይዋ አውጡ።
\v 28 አሕዛብን የሚዶንንም ነገሥታት አለቆችንም ሹማምቶችንም ሁሉ የግዛታቸውንም ምድር ሁሉ አዘጋጁባት።
\s5
\v 29 ማንም እንዳይቀመጥባት የባቢሎንን ምድር ባድማ ያደርጋት ዘንድ የእግዚአብሔር አሳብ በባቢሎን ላይ ጸንቶአልና ምድር ተናወጣለች ታመመችም።
\s5
\v 30 የባቢሎን ወታደሮች መዋጋትን ትተዋል፤ በምሽጎቻቸውም ውስጥ ተቀምጠዋል። ኃይላቸውም ጠፍቶአል እንደ ሴቶችም ሆነዋል። ማደሪያዎችዋም ነድደዋል፣ መወርወሪያዎችዋም ተሰብረዋል።
\v 31 ከዳር እስከ ዳር ድረስ ከተማው እንደ ተያዘች መልካምዎችዋም እንደ ተያዙ፣ ቅጥርዋም በእሳት እንደ ተቃጠለ፣ ሰልፈኞችም እንደ ደነገጡ
\v 32 ለባቢሎን ንጉሥ ይነግር ዘንድ ወሬኛው ወሬኛውን፣ መልእክተኛውም መልእክተኛውን ሊገናኝ ይሮጣል።"
\s5
\v 33 የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፣ አውድማ እንደ ተረገጠ ጊዜ፣ እንዲሁ የባቢሎን ልጅ ናት። ጥቂት ቈይታ የመከር ጊዜ ይደርስላታል።
\s5
\v 34 ኢየሩሳሌም፣ 'የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በላኝ። አድርቆ አሟጠጠኝ፣ እንደ ባዶ የሸክላ ዕቃም አደረገኝ። እንደ ዘንዶም ዋጠኝ። ከሚጣፍጠውም ምግቤ ሆዱን ሞላ። እኔንም ወደ ውጪ ጣለኝ።' አለች።
\v 35 የጽዮን ነዋሪዎች እንዲህ ይላሉ፣ 'በእኔና በሥጋዬ የተደረገ ግፍ በባቢሎን ላይ ይሁን።' ኢየሩሳሌምም፣ 'የሚፈስሰው ደሜ ጥፋት በከለዳውያን ምድር በሚኖሩት ላይ ይሁን" ትላለች።
\s5
\v 36 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተመልከቺ፣ እምዋገትልሻለሁ በቀልሽንም እበቀልልሻለሁ። ባሕርዋንም ድርቅ አደርገዋለሁ፣ ምንጭዋንም አደርቀዋለሁ።
\v 37 ባቢሎንም የድንጋይ ቊልልና የቀበሮ ማደሪያ፣ መደነቂያም ማፍዋጫም ትሆናለች፤ የሚቀመጥባትም ሰው አይገኝም።
\s5
\v 38 በአንድነትም እንደ አንበሶች ያገሣሉ። እንደ አንበሳም ደቦሎች ያጕረመርማሉ።
\v 39 በስስት በሞቃቸው ጊዜ ደስ እንዲላቸው፣ ለዘላለምም አንቀላፍተው እንዳይነቁ፣ የመጠጥ ግብዣ አደርግላቸዋለሁ፣ አሰክራቸውማለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር።
\v 40 እንደ ጠቦቶችና እንደ አውራ በጎች እንደ አውራ ፍየሎችም ወደ መታረድ አወርዳቸዋለሁ።"
\s5
\v 41 "ባቢሎን እንዴት ተያዘች! የምድርም ሁሉ ምስጋና እንዴት ተወሰደች። ባቢሎንም በአሕዛብ መካከል መደነቂያ እንዴት ሆነች።
\v 42 ባሕር በባቢሎን ላይ ወጣ! በሞገዱም ብዛት ተከደነች።
\s5
\v 43 ከተሞችዋ ባድማና ደረቅ ምድር ምድረ በዳም፣ ሰውም የማይኖርበት፣ የሰውም ልጅ የማያልፍበት ምድር ሆኑ።
\v 44 በባቢሎንም ውስጥ ቤልን እቀጣለሁ፤ የዋጠውንም ከአፉ አስተፋዋለሁ፣ አሕዛብም ከዚያ ወዲያ ወደ እርሱ አይሰበሰቡም። የባቢሎንም ቅጥር ይወድቃል።"
\s5
\v 45 "ሕዝቤ ሆይ፣ ከመካከልዋ ውጡ። እያንዳንዳችሁም ከእግዚአብሔር ጽኑ ቍጣ ራሳችሁን አድኑ።
\v 46 በምድርም ከሚሰማ ወሬ የተነሣ አትፍሩ፣ ልባችሁም የዛለ አይሁን፤ በአንድ ዓመት ወሬ ይመጣል፣ ከዚያም በኋላ በሌላው ዓመት ወሬ፣ በምድርም ላይ ግፍ ይመጣል፣ አለቃም በአለቃ ላይ ይነሣል።
\s5
\v 47 ስለዚህ፣ ተመልከቱ፣ የተቀረጹትን የባቢሎን ምስሎች የምቀጣበት ዘመን ይመጣል። ምድርዋም ሁሉ ታፍራለች፣ ተወግተውም የሞቱት ሁሉ በመካከልዋ ይወድቃሉ።
\v 48 አጥፊዎች ከሰሜን ይመጡባታልና ሰማይና ምድር በእነርሱም ያለው ሁሉ ስለ ባቢሎን እልል ይላሉ፣ ይላል እግዚአብሔር።
\v 49 ባቢሎንም ከእስራኤል ተወግተው የሞቱት እንዲወድቁ እንዳደረገች፣ እንዲሁ በባቢሎን ከምድሩ ሁሉ ተወግተው የሞቱት ይወድቃሉ።"
\s5
\v 50 "ከሰይፍ ያመለጣችሁ፣ ሂዱ! ተረጋግታችሁ አትቁሙ። እግዚአብሔርን ከሩቅ ጥሩት፤ ኢየሩሳሌምንም በልባችሁ አስቡ።
\v 51 ስድብን ስለ ሰማን አፍረናል፤ ባዕዳን ሰዎችም ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ገብተዋልና ነውር ፊታችንን ከድኖታል።"
\s5
\v 52 "ስለዚህ፣ ተመልከቱ፣ የተቀረጹትን ምስሎችዋ የምቀጣበት ዘመን ይመጣል፣ ይላል እግዚአብሔር፤ በምድርዋም ላይ ሁሉ የተወጉት ያንቋርራሉ።
\v 53 ባቢሎን ምንም ወደ ሰማይ ብትወጣ፣ የኃይልዋንም ምሽጎች ብታጸና፣ ከእኔ ዘንድ አጥፊዎች ይመጡባታል፣ ይላል እግዚአብሔር።"
\s5
\v 54 ከባቢሎን ጩኸት፣ ከከለዳውያንም ምድር የታላቅ ጥፋት ድምፅ ተሰምቶአል።
\v 55 እግዚአብሔር ባቢሎንን አጥፍቶአታልና፣ ከእርስዋም ታላቁን ድምፅ ዝም አሰኝቶአልና፤ ሞገዳቸውም እንደ ብዙ ውኆች ይተምማል፣ የድምፃቸውም ጩኸት በብርቱ ተሰምቶአል።
\v 56 አጥፊው በባቢሎን ላይ መጥቶባታልና፣ ኃያላኖችዋ ተያዙ፣ ቀስታቸውም ተሰባበረ፤ እግዚአብሔር ፍዳን የሚከፍል አምላክ ነውና፣ ፍዳንም በእርግጥ ይከፍላል።
\s5
\v 57 "መሳፍንቶችዋንና ጥበበኞችዋን፣ አለቆችዋንና ሹማምቶችዋን፣ ወታደሮችዋንም አሰክራለሁ፥ ለዘላለምም አንቀላፍተው አይነቁም፣ ይላል ስሙ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የተባለው ንጉሥ።"
\v 58 "የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሰፊው የባቢሎን ቅጥር ፈጽሞ ይፈርሳል፤ ረጃጅሞችም በሮችዋም በእሳት ይቃጠላሉ፤ የወገኖችም ድካም ከንቱ ትሆናለች፣ የአሕዛብም ሥራ ሁሉ ለእሳት ትሆናለች፤ እነርሱም ይደክማሉ።"
\s5
\v 59 የመሕሤያ ልጅ የኔርያ ልጅ ሠራያ የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ በነገሠ በአራተኛው ዓመት ከእርሱ ጋር ወደ ባቢሎን በሄደ ጊዜ ነቢዩ ኤርምያስ ያዘዘው ቃል ይህ ነው፣ ያን ጊዜ ሠራያ የቤት አዛዥ ነበረ።
\v 60 በባቢሎንም ላይ የሚመጣውን ክፉ ነገር ሁሉ፣ ስለ ባቢሎን የተጻፈውን ይህን ቃል ሁሉ፣ ኤርምያስ በመጽሐፍ ላይ ጻፈው።
\s5
\v 61 ኤርምያስም ሠራያን እንዲህ አለው፣ "ወደ ባቢሎን በገባህ ጊዜ ይህ ቃል ሁሉ መነበቡን እርግጠኛ ሁን።
\v 62 አንተም ደግሞ፣ 'ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ ማንም እንዳይቀመጥባት፣ ለዘላለምም ባድማ እንድትሆን ታጠፋት ዘንድ በዚህች ስፍራ ላይ ተናግረሃል' በል።
\s5
\v 63 ከዚያም ይህንን ጥቅልል መጽሐፍ ማንበብ ከፈጸምህ በኋላ፣ ድንጋይን እሰርበትና በኤፍራጥስ ወንዝ መሃከል ጣለው።
\v 64 አንተ፣ 'እኔ ከማመጣባት ክፉ ነገር የተነሣ እንዲሁ ባቢሎን ትሰጥማለች፣ አትነሣምም" በል። የኤርምያስ ቃል እዚህ ላይ ያበቃል።
\s5
\c 52
\p
\v 1 ሴዴቅያስ መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሀያ አንድ ዓመት ጕልማሳ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም አሥራ አንድ ዓመት ነገሠ። እናቱም አሚጣል የምትባል ነበረች፤ እርሷ የሊብና ሰው የኤርምያስ ልጅ ነበረች።
\v 2 ኢዮአቄምም እንዳደረገ ሁሉ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገርን አደረገ።
\v 3 ከፊቱም አውጥቶ እስኪጥላቸው ድረስ ይህ በእግዚአብሔር ቍጣ፣ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ላይ ሆኖአልና። ከዚያም ሴዴቅያስ በባቢሎን ንጉሥ ላይ ዐመፀ።
\s5
\v 4 ሴዴቅያስም በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት በዐሥረኛው ወር፣ ከወሩም በዐሥረኛው ቀን፣ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆርና ሠራዊቱ ሁሉ በኢየሩሳሌም ላይ መጥተው ከበቡአት፤ በዙሪያዋም ቅጥር የሚሆን ግድግዳ ገነቡ።
\v 5 ስለዚህ ከተማይቱ እስከ ንጉሡ እስከ ሴዴቅያስ እስከ ዐሥራ አንደኛው ዓመት ድረስ ተከብባ ነበር።
\s5
\v 6 በአራተኛውም ወር፣ በዐመቱ ዘጠነኛ ቀን፣ በከተማይቱ ራብ ጸንቶ ነበር። ለምድሪቱም ሰዎች እንጀራ ታጣ።
\v 7 ከተማይቱም ተሰበረች፣ ተዋጊዎች ሁሉ ሸሹ፣ በሁለቱም ቅጥር መካከል ባለው በር ወደ ንጉሡ አትክልት በሚወስደው መንገድ በሌሊት ከከተማይቱ ወጡ። ከለዳውያንም በከተማይቱ ዙሪያ ነበሩ። ስለዚህ በዓረባ መንገድ ሄዱ።
\v 8 ነገር ግን የከለዳውያን ሠራዊት ንጉሡን ተከታተሉት፣ በኢያሪኮም ሜዳ ሴዴቅያስን ያዙ። ሠራዊቱም ሁሉ ከእርሱ ዘንድ ተበትነው ነበር።
\s5
\v 9 ንጉሡንም ይዘው የባቢሎን ንጉሥ ወዳለባት በሐማት ምድር ወዳለችው ወደ ሪብላ አመጡት፤ እርሱም ፍርድን በእርሱ ላይ ተናገረ።
\v 10 የባቢሎንም ንጉሥ የሴዴቅያስን ልጆች በዐይኖቹ ፊት ገደላቸው፣ የይሁዳንም አለቆች ሁሉ ደግሞ በሪብላ ዐረዳቸው።
\v 11 ከዚያም የሴዴቅያስን ዐይኖች አወጣ፣ የባቢሎንም ንጉሥ በሰንሰለት አሰረው። ወደ ባቢሎንም ወሰደው፣ እስኪሞትም ድረስ በግዞት ቤት አኖረው።
\s5
\v 12 በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር በዐሥራ ዘጠነኛው ዓመት በአምስተኛው ወር፣ ከወሩም በዐሥረኛው ቀን፣ በባቢሎን ንጉሥ ፊት የቆመው የዘበኞቹ አለቃ ናቡዘረዳን ወደ ኢየሩሳሌም መጣ።
\v 13 የእግዚአብሔርን ቤትና የንጉሡን ቤት አቃጠለ፤ የኢየሩሳሌምንም ቤቶች ሁሉ፣ ታላላቆችን ቤቶች ሁሉ፣ በእሳት አቃጠለ።
\v 14 ከዘበኞቹም አለቃ ጋር የነበረው የከለዳውያን ሠራዊት ሁሉ የኢየሩሳሌምን ቅጥር ሁሉ ዙሪያዋን አፈረሱ።
\s5
\v 15 የዘበኞቹም አለቃ ናቡዘረዳን የሕዝቡን ድኆች፣ በከተማም ውስጥ የቀረውን ሕዝብ፣ ሸሽተውም ወደ ባቢሎን ንጉሥ የተጠጉትን፣ የሕዝቡንም ቅሬታ አፈለሰ።
\v 16 ነገር ግን የዘበኞቹ አለቃ ናቡዘረዳን ከአገሩ ድኆች ወይን ተካዮችና አራሾች እንዲሆኑ አስቀረ።
\s5
\v 17 ከለዳውያንም በእግዚአብሔር ቤት የነበሩትን የናስ ዓምዶች፣ በእግዚአብሔርም ቤት የነበሩትን መቀመጫዎችና የናሱን ኵሬ ሰባበሩ፣ ናሱንም ወደ ባቢሎን ወሰዱ።
\v 18 ምንቸቶቹንና መጫሪያዎችንም፣ መኰስተሪያዎችንና ድስቶችን፣ ጭልፋዎችንም የሚያገለግሉበትንም የናስ ዕቃ ሁሉ ወሰዱ።
\v 19 የዘበኞቹም አለቃ ጽዋዎቹንና ማንደጃዎቹን፣ ድስቶቹንና ምንቸቶችን፣ መቅረዞችንና ጭልፋዎቹን፣ መንቀሎችንም፣ የወርቁን ዕቃ በወርቅ፣ የብሩንም ዕቃ በብር፣ አድርጎ ወሰደ።
\s5
\v 20 ንጉሡ ሰሎሞንም ለእግዚአብሔር ቤት ያሠራቸውን ሁለቱን ዓምዶች፣ አንዱንም ኵሬ፣ ከመቀመጫዎቹም በታች የነበሩትን ዐሥራ ሁለቱን የናስ በሬዎች ወሰደ፤ ለእነዚህ ዕቃዎች ሁሉ ናስ ሚዛን አልነበረም።
\v 21 ዓምዶቹም የአንዱ ዓምድ ቁመት ዐሥራ ስምንት ክንድ ነበረ። የዙሪያውም መጠን ዐሥራ ሁለት ክንድ ነበረ። ውፍረቱም አራት ጣት ያህል ነበረ፣ ባዶም ነበረ።
\s5
\v 22 የናሱም ጕልላት በላዩ ነበረ። የአንዱም ጉልላት ቁመት አምስት ክንድ ነበረ፣ በጕልላቱም ላይ በዙሪያው ሁሉ ከናስ የተሠሩ መረበብና ሮማኖች ነበሩበት። በሁለተኛውም ዓምድ ደግሞ እንደዚህ ያለ ነገርና ሮማኖች ነበሩበት።
\v 23 በስተውጭም ዘጠና ስድስት ሮማኖች ነበሩ። በመረበቡም ዙሪያ የነበሩ ሮማኖች ሁሉ አንድ መቶ ነበሩ።
\s5
\v 24 የዘበኞቹም አለቃ ታላቁን ካህን ሠራያን ሁለተኛውንም ካህን ሶፎንያስን ሦስቱንም በረኞች ወሰደ።
\v 25 ከከተማይቱም በሰልፈኞች ላይ ተሹመው ከነበሩት አንዱን ጀንደረባ፣ በከተማይቱም ከሚገኙት በንጉሡ ፊት ከሚቆሙት ሰባቱን ሰዎች፣ የአገሩንም ሕዝብ የሚያሰልፈውን የሠራዊቱን አለቃ ጸሐፊ፣ በከተማይቱም ከተገኙት ከአገሩ ሕዝብ ስድሳ ሰዎች ወሰደ።
\s5
\v 26 የዘበኞቹም አለቃ ናቡዘረዳን ወስዶ የባቢሎን ንጉሥ ወዳለበት ወደ ሪብላ አመጣቸው።
\v 27 የባቢሎንም ንጉሥ ገደላቸው፣ በሐማትም ምድር ባለችው በሪብላ ገደላቸው። እንዲሁ ይሁዳ ከአገሩ ተማረከ።
\s5
\v 28 ናቡከደነፆር የማረከው ሕዝብ ይህ ነው፤ በሰባተኛው ዓመት፣ 3, 023 አይሁድ፤
\v 29 ናቡከደነፆርም በአሥራ ስምንተኛው ዓመት 832 ሰዎችን ከኢየሩሳሌም ማርኮአል፤
\v 30 በናቡከደነፆር በሀያ ሦስተኛው ዓመት የዘበኞቹ አለቃ ናቡዘረዳን ከአይሁድ 745 የይሁዳ ሰዎችን ማርኳል። የተማረኩት ሰዎች ሁሉ 4, 600 ነበሩ።
\s5
\v 31 እንዲህም ሆነ፤ የይሁዳ ንጉሥ ዮአኪን በተማረከ በሠላሳ ሰባተኛው ዓመት፣ በአሥራ ሁለተኛው ወር ከወሩም በሀያ አምስተኛው ቀን፣ የባቢሎን ንጉሥ ዮርማሮዴክ በነገሠ በአንደኛው ዓመት የይሁዳን ንጉሥ የዮአኪንን ራስ ከፍ ከፍ አደረገ ከወህኒም አወጣው።
\s5
\v 32 በመልካምም ተናገረውና ዙፋኑን ከእርሱ ጋር በባቢሎን ከነበሩት ነገሥታት ዙፋን በላይ አደረገለት።
\v 33 ክፉው ዮርማሮዴክ በወህኒ ውስጥ ዮአኪን ለብሶት የነበረውን ልብስ ለወጠለት፣ ዮአኪንም በሕይወቱ ዘመን ሁሉ በፊቴ ሁልጊዜ እንጀራ ይበላ ነበር።
\v 34 የባቢሎንም ንጉሥ በሕይወቱ ዘመን ሁሉ እስኪሞት ድረስ የዘወትር ቀለብ ዕለት ዕለት ይሰጠው ነበር።