am_ulb/23-ISA.usfm

2812 lines
276 KiB
Plaintext

\id ISA
\ide UTF-8
\h ኢሳይያስ
\toc1 ኢሳይያስ
\toc2 ኢሳይያስ
\toc3 isa
\mt ኢሳይያስ
\s5
\c 1
\p
\v 1 የይሁዳ ነገሥታት በሆኑት በዖዝያንና በኢዮአታም በአካዝና በሕዝቅያስ ዘመን ስለ ይሁዳና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው የአሞጽ ልጅ የኢሳይያስ ራእይ።
\s5
\v 2 ስሙ፣ ምድርም አድምጪ፤ "ልጆችን ወለድሁ አሳደግሁም፣ እነርሱም አመጹብኝ።" ሲል እግዚአብሔር ተናግሮአልና።
\v 3 በሬ የገዢውን፣ አህያም የጌታውን ጋጣ አወቀ፤ እስራኤል ግን አላወቀም፥ እስራኤል አልተገነዘበም"
\s5
\v 4 ወዮላችሁ! ኃጢአተኛ ወገንና በደል የተሞላበት ሕዝብ፣ የክፉ አድራጊዎች ልጆች፣ ርኵሰትን የምታደርጉ ልጆች ሆይ! እግዚአብሔርን ትተዋል፣ የእስራኤልንም ቅዱስ አቃልለዋል ወደ ኋላቸውም እየሄዱ ተለይተዋል።
\s5
\v 5 አሁን ድረስ ለምን ትቀሰፋላችሁ? አሁንም አሁንም ዓመፃ ለምን ትጨምራላችሁ? ራስ ሁሉ ለሕመም፣ ልብም ሁሉ ለድካም ሆኗል።
\v 6 ከእግር መርገጫ አንስቶ እስከ ራስ ድረስ ያልታመመ የለውም፤ ቍስልና እበጥ፣ የሚደማ ቊስል ነው፤ አልፈረጠም፣ አልተጠገነም፣ በዘይትም አልለዘበም።
\s5
\v 7 ምድራችሁ ባድማ ናት፤ ከተሞቻችሁ በእሳት ተቃጠሉ፤ እርሻችሁንም በፊታችሁ እንግዶች ይበሉታል፤ ባዕድ እንዳፈረሳት ምድር ባድማ ሆነች።
\v 8 የጽዮንም ሴት ልጅ በወይን ቦታ እንዳለ ዳስ፣ በዱባ አትክልትም እንዳለ ጎጆ፣ እንደተከበበችም ከተማ ሆና ቀረች።
\s5
\v 9 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ጥቂት ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ፣ እንደ ሰዶም በሆንን፣ እንደ ገሞራም በመሰልን ነበር።
\s5
\v 10 የሰዶም አለቆች ሆይ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ እናንተ የገሞራ ሕዝብ ሆይ፣ የአምላካችንን ሕግ አድምጡ።
\v 11 "የመሥዋዕታችሁ ብዙ ጋጋታ ለእኔ ምን ይጠቅመኛል?" ይላል እግዚአብሔር። "የሚቃጠለውን የአውራ በግ መሥዋዕትንና የፍሪዳን ስብ ጠግቤያለሁ፤ የበሬና የበግ ጠቦት የአውራ ፍየልም ደም ደስ አያሰኘኝም።
\s5
\v 12 በእኔ ፊት ልትታዩ ብትመጡ፣ ይህን የመቅደሴን አደባባይ መርገጣችሁን ከእጃችሁ የሚሻ ማን ነው?
\v 13 ምናምንቴውን ቍርባን ጨምራችሁ አታምጡ፤ ዕጣን በእኔ ዘንድ አጸያፊ ነው፤ መባቻችሁንና ሰንበታችሁን በጉባኤ መሰብሰባችሁን አልወድድም - እነዚህን የረከሱ ጉባዔዎች አልታገሥም።
\s5
\v 14 መባቻችሁንና በዓላቶቻችሁን ነፍሴ ጠልታለች፤ ሸክም ሆነውብኛል፥ ልታገሣቸውም ደክሜያለሁ።
\v 15 ስለዚህም እጃችሁን በጸሎት ወደ እኔ ብትዘረጉ ዓይኔን ከእናንተ እሰውራለሁ፣ ልመናንም ብታበዙ አልሰማችሁም፤ እጆቻችሁ ደም ተሞልተዋል።
\s5
\v 16 ታጠቡ፣ ሰውነታችሁንም አንጹ፤ የሥራችሁን ክፋት ከዓይኔ ፊት አስወግዱ፤ ክፉ መሆንን ተዉ፤
\v 17 መልካም ማድረግን ተማሩ፣ ፍርድን ፈልጉ፣ የተጨቆነውን እርዱ፣ አባት ለሌለው ፍረዱለት፣ ስለ መበለቲቱም ተምዋገቱ።"
\s5
\v 18 "አሁን ኑና በአንድ ላይ እንዋቀስ" ይላል እግዚአብሔር፤ "ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን፣ እንደ በረዶ ትነጻለች፤ እንደ ደምም ብትቀላ፣ እንደ ባዘቶ ትጠራለች።
\s5
\v 19 እሺ ብትሉ ብትታዘዙ፣ የምድርን በረከት ትበላላችሁ።
\v 20 ነገር ግን እምቢ ብትሉ፣ ብታምፁም፣ ሰይፍ ይበላችኋል፣" የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሮአልና።
\s5
\v 21 ፍርድ ሞልቶባት የነበረችው የታመነችይቱ ከተማ እንዴት ጋለሞታ ሆነች! ጽድቅ ሞልቶባት ነበር፣ አሁን ግን ገዳዮች ሞልተውባታል።
\v 22 ብርሽ ወደ ዝገት ተለወጠ፣ የወይን ጠጅሽ ከውሃ ጋር ተደባለቀ።
\s5
\v 23 አለቆችሽ አመጸኞችና የሌቦች ባልንጀሮች ሆኑ፤ ሁሉ ጉቦ ይወድዳሉ፣ ዋጋም ለማግኘትም ይሮጣሉ። ለድሀ አደጉ አይፈርዱም፣ የመበለቲቱም ሙግት ወደ እነርሱ አይደርስም።
\s5
\v 24 ስለዚህ የእስራኤል ኃያል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ወዮላቸው! የሚቋቋሙኝ ላይ ቍጣዬን እፈጽማለሁ፣ በጠላቶቼ ላይ እበቀላለሁ።
\v 25 እጄንም በአንቺ ላይ አመጣለሁ፣ ዝገትሽንም በጣም አነጻለሁ፣ አለመንጻትሽንም ሁሉ አወጣለሁ፤
\s5
\v 26 ፈራጆችሽንም እንደ ቀድሞ፣ አማካሪዎችሽንም እንደ መጀመሪያው ጊዜ መልሼ አስነሣለሁ፤ ከዚያም በኋላ የጽድቅ ከተማ፣ የታመነችም ከተማ ተብለሽ ትጠሪያለሽ።"
\s5
\v 27 ጽዮን በፍርድ፣ ከእርሷም በንስሃ የሚመለሱ በጽድቅ ይድናሉ።
\v 28 በደለኞችና ኃጢአተኞች ግን በአንድነት ይሰበራሉ፣ እግዚአብሔርንም የሚተዉ ይጠፋሉ።
\s5
\v 29 "በተመኛችኋት የተቀደሰች የአድባር ዛፍ ታፍራላችሁና፣ በመረጣችኋትም አትክልት ስፍራ ላይ እፍረት ይይዛችኋልና፤
\v 30 ቅጠልዋ እንደ ረገፈ ዛፍ፣ ውሃም እንደሌለባት አትክልት ትሆናላችሁና።
\s5
\v 31 ኃይለኛውም እንደ ተልባ ጭረት፣ ሥራውም እንደ ጠለሸት ይሆናል፤ አብረውም ይቃጠላሉ፣ እነርሱንም የሚያጠፋ የለም።"
\s5
\c 2
\p
\v 1 የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ስለ ይሁዳና ስለ ኢየሩሳሌም በራእይ ያያቸው ነገሮች።
\v 2 በኋለኞቹ የፍጻሜ ቀናት፣ የእግዚአብሔር ቤት ተራራ በተራሮች ከፍታ ላይ ጸንቶ ይቆማል፣ ከኮረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፤ አሕዛብም ሁሉ ወደ እርሱ ይጎርፋሉ።
\s5
\v 3 ሕግ ከጽዮን የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና ብዙዎች አሕዛብ መጥተው፣ "ኑ፣ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፣ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ እርሱም መንገዱን ያስተምረናል፥ በጎዳናውም እንሄዳለን ይላሉ።"
\s5
\v 4 በአሕዛብም መካከል ይፈርዳል፣ በብዙ አሕዛብም ላይ ይበይናል፤ ሰይፋቸውንም ማረሻ ጦራቸውንም ማጭድ ለማድረግ ይቀጠቅጣሉ፤ ሕዝብም በሕዝብ ላይ ሰይፍ አያነሣም፣ ጦርነትንም ከእንግዲህ ወዲህ አይማሩም።
\s5
\v 5 እናንተ የያዕቆብ ቤት ሆይ፣ ኑ፣ በእግዚአብሔር ብርሃን እንሂድ።
\v 6 የምሥራቅን ሰዎች አመል ስለ ተሞሉ፣ እንደ ፍልስጥኤማውያንም ምዋርተኞች ስለ ሆኑ፣ ከባዕድ ልጆችም ጋር ስለ ተባበሩ፣ የሕዝብህን የያዕቆብን ቤት ትተሃል።
\s5
\v 7 ምድራቸው በብርና በወርቅ ተሞልታለች፣ ለመዛግብቶቻቸውም ፍጻሜ የለውም፤ ምድራቸውም ደግሞ በፈረሶች ተሞልታለች፣ ለሠረገሎቻቸውም ፍጻሜ የለውም።
\v 8 ምድራቸው ደግሞ በጣዖታት ተሞልታለች፤ ጣቶቻቸውም ላደረጉት ለእጃቸው ሥራ ይሰግዳሉ።
\s5
\v 9 ታናሹም ሰው ዝቅ ብሎአል፣ ግለሰቦችም ይዋረዳሉ፤ ስለዚህ አትቀበላቸው።
\v 10 ከእግዚአብሔር ማሸበርና ከግርማው ክብር የተነሣ ወደ ድንጋይ ዋሻ ግቡ፣ በመሬትም ውስጥ ተሸሸጉ።
\v 11 ከፍ ያለችውም የሰው ዓይን ትዋረዳለች፣ የሰዎችም ኵራት ተጎትታ ትወድቃለች፣ በዚያም ቀን እግዚአብሔር ብቻውን ከፍ ይላል።
\s5
\v 12 የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቀን በትዕቢተኛውና በኵራተኛው ሁሉ ላይ፣ ከፍ ባለውም ላይ ይሆናል፣ እርሱም ይዋረዳል፤
\v 13 ደግሞም በረጅሙ ከፍ ባለው በሊባኖስ ዝግባ ሁሉ ላይ፣ በባሳንም ዛፍ ሁሉ ላይ ይሆናል፣
\s5
\v 14 በረጅሞቹም ተራራዎች ሁሉ ላይ፣ ከፍ ባለውም ኮረብቶች ሁሉ ላይ፣
\v 15 በረጅሙም ግንብ ሁሉ ላይ፣ በተመሸገውም ቅጥር ሁሉ ላይ፣
\v 16 በተርሴስም መርከቦች ሁሉ ላይ፣ በሚያማምሩ ጣዖታትም ሁሉ ላይ ይሆናል።
\s5
\v 17 የሰው ሁሉ ክብር ይዋረዳል፣ የሰውም ኵራት ይወድቃል፤ በዚያም ቀን እግዚአብሔር ብቻ ከፍ ከፍ ይላል።
\v 18 ጣዖቶቻቸውም ሁሉ ፈጽመው ይጠፋሉ።
\v 19 እግዚአብሔርም ምድርን ያናውጥ ዘንድ በተነሣ ጊዜ፣ ሰዎችን ከማስደንገጡና ከግርማው ክብሩ የተነሣ፣ ወደ ድንጋይ ዋሻና ወደ ምድር ንቃቃት ውስጥ ይገባሉ።
\s5
\v 20 በዚያን ቀን ሰው ይሰግድላቸው ዘንድ ያበጁአቸውን የብሩንና የወርቁን ጣዖቶቻቸውን ለፍልፈልና ለሌሊት ወፍ ይጥላሉ።
\v 21 እግዚአብሔርም ምድርን ያናውጥ ዘንድ በተነሣ ጊዜ ከማስደንገጡና ከግርማው ክብር የተነሣ ወደ ድንጋይ ዋሻና ወደ ተሰነጠቁ ዓለቶች ውስጥ ይገባሉ።
\v 22 እስትንፋሱ በአፍንጫው ውስጥ ያለበትን ሰው ተዉት፣ እርሱ ስለ ምን ይቈጠራል?
\s5
\c 3
\p
\v 1 ተመልከቱ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከኢየሩሳሌምና ከይሁዳ ድጋፍንና ብርታትን፡ የእንጀራን ድጋፍ ሁሉ የውኃውንም ድጋፍ ሁሉ ይወስዳል፤
\v 2 ኃያሉንም፣ ተዋጊውንም፣ ፈራጁንም፣ ነቢዩንም፣ ምዋርተኛውንም፣ ሽማግሌውንም፤
\v 3 የአምሳ አለቃውንም፣ ከበርቴ የሆነውን ዜጋ፣ አማካሪውንም፣ የብልኃት ሠራተኛውንም፣ አስማት አዋቂውንም ይነቅላል።
\s5
\v 4 "አለቆቻቸው እንዲሆኑ ተራ ወጣቶችን አስነሣባቸዋለሁ፣ ብላቴናውም ይገዛቸዋል።
\v 5 ሕዝቡም ይጨቆናሉ፣ ሰው በሰው ላይ፣ ሰውም በባልንጀራው ላይ ይገፋፋል፤ ብላቴናውም በሽማግሌው ላይ የተጠቃውም በከበርቴው ላይ ይኰራል።
\s5
\v 6 ሰውም በአባቱ ቤት ውስጥ ወንድሙን ይዞ፣ 'አንተ ልብስ አለህ፤ አለቃም ሁንልን፣ ይህችም ባድማ ከኃላፊነትህ በታች ትሁን' ይለዋል።
\v 7 በዚያ ቀን ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ ይላል፣ 'እኔ በቤቴ ውስጥ እንጀራ ወይም ልብስ የለኝምና ባለ መድኃኒት አልሆንም። በሕዝቡም ላይ አለቃ አታደርጉኝም" ይላል።
\s5
\v 8 ንጉሣዊ ሥልጣኑን ያረክሱ ዘንድ ንግግራቸውና ሥራቸው በእግዚአብሔር ላይ ነውና ኢየሩሳሌም ተፈታች ይሁዳም ወደቀ።
\v 9 የፊታቸውም እፍረት ይመሰክርባቸዋል፤ እንደ ሰዶምም ኃጢአታቸውን ያወራሉ፤ አይሠውሩአትም። በራሳቸው ላይ ጥፋትን ሠርተዋልና ለነፍሳቸው ወዮ!
\s5
\v 10 የሥራውን ፍሬ ይበላልና፣ ጻድቁን መልካም ይሆንልሃል በሉት።
\v 11 እንደ እጁ ሥራ ፍዳው ይደረግበታልና ለበደለኛ ወዮ! ክፉም ደርሶበታል።
\v 12 ሕዝቤን አስገባሪዎቻቸው ይገፉአቸዋል፣ ሴቶችም ይሠለጥኑባቸዋል። ሕዝቤ ሆይ፣ መሪዎቻችሁ ያስቱአችኋል የምትሄዱበትንም መንገድ አቅጣጫ ያጠፋሉ።
\s5
\v 13 እግዚአብሔር በፍርድ ቤት ሊፈርድ ተነሥቶአል፣ በሕዝቡም ላይ ሊፈርድ ቆሞአል።
\v 14 እግዚአብሔር ከሕዝቡ ሽማግሌዎችና ከአለቆቻቸው ጋር ይፋረዳል፡ "የወይኑን ቦታ የበላችሁ እናንተ ናችሁ፤ ከድሆች የበዘበዛችሁት በቤታችሁ አለ፤
\v 15 ሕዝቤንስ ለምን ታደቅቁአቸዋላችሁ? የድሆችንስ ፊት ለምን ትፈጫላችሁ?" ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
\s5
\v 16 ደግሞም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፣ የጽዮን ቈነጃጅት ኰርተዋልና፣ አንገታቸውንም እያሰገጉ በዓይናቸውም እያጣቀሱ፣ ፈንጠርም እያሉ፣ በእግራቸውም እያቃጨሉ ይሄዳሉ።
\v 17 ስለዚህ ጌታ የጽዮንን ቈነጃጅት አናት በበሽታ ቡሀነት ይመታል፣ እግዚአብሔርም መላጣ ያደርጋቸዋል።
\s5
\v 18 በዚያም ቀን ጌታ የእግር አልቦውን ክብር፣ መርበብንም፣ ጨረቃ የሚመስለውንም ጌጥ፣
\v 19 የጆሮ እንጥልጥሉንም፣ አንባሩንም፣ መሸፈኛውንም፣
\v 20 ቀጸላውንም፣ የቁርጭምጭሚት ሰንሰለቱንም፣ መቀነቱንም፣ የሽቱውንም ዕቃ።
\s5
\v 21 አሸንክታቡንም፣ የእጅና የአፍንጫ ቀለበቱንም ያስወግዳል፤
\v 22 የዓመት በዓል ልብሶችን፣ መጐናጸፊያውንም፣ መሸፈኛውንም፣ ከረጢቱንም፤
\v 23 የእጅ መስተዋቱንም፣ ከጥሩ በፍታ የተሰራውንም ልብስ፣ ራስ ማሰሪያውንም፣ ዓይነ ርግቡንም ያስወግዳል።
\s5
\v 24 በሽቱ ፋንታ ግማት፣ በመታጠቂያውም ፋንታ ገመድ፣ ጠጕርንም በመንቀስ ፋንታ ቡሀነት፣ በመጐናጸፊያ ፋንታ ማቅ፣ በውበትም ፋንታ ጠባሳ ይሆናል።
\v 25 ጕልማሶችሽ በሰይፍ፣ ኃያላንሽም በውጊያ ይወድቃሉ።
\v 26 በሮችዋ ያዝናሉ ያለቅሱማል፤ እርስዋም ብቻዋን በምድር ላይ ትቀመጣለች።
\s5
\c 4
\p
\v 1 በዚያም ቀን ሰባት ሴቶች "የገዛ እንጀራችንን እንበላለን የገዛ ልብሳችንንም እንለብሳለን፤ ስምህ ብቻ በእኛ ላይ ይጠራ፥ ውርደታችንንም አርቅ" ብለው አንዱን ወንድ ይይዙታል።
\v 2 በዚያም ቀን የእግዚአብሔር ቍጥቋጥ ውብና የከበረ ይሆናል፣ ከእስራኤልም ወገን ላመለጡ ሰዎች የምድሪቱን ፍሬ ለትምክሕትና ለውበት ይሆናል።
\s5
\v 3 ከዚያም፣ ጌታ የጽዮንን ቈነጃጅት እድፍ ባጠበ ጊዜ፣ የኢየሩሳሌምንም ደም በፍርድ መንፈስና በሚያቃጥል መንፈስ ከመካከልዋ ባነጻ ጊዜ፣
\v 4 በጽዮን የቀረ በኢየሩሳሌምም የተረፈ፣ በኢየሩሳሌም ለሕይወት የተጻፈ ሁሉ፣ ቅዱስ ይባላል።
\s5
\v 5 እግዚአብሔርም በጽዮን ተራራ ላይ ባለ ማደሪያ ሁሉ በጉባኤያቸውም ላይ፣ በቀን ዳመናንና ጢስን፣ በሌሊትም የሚቃጠለውን የእሳት ብርሃን ይፈጥራል፤ በክብርም ሁሉ ላይ መጋረጃ ይሆናል።
\v 6 በቀን ከሙቀት ለጥላ፣ ከዐውሎ ነፋስና ከዝናብም ለመጠጊያና ለመሸሸጊያ ጎጆ ይሆናል።
\s5
\c 5
\p
\v 1 አሁን ስለ ወዳጄና ስለ ወይን ቦታው ለወዳጄ ቅኔ እቀኛለሁ። ለወዳጄ በለመለመው ኮረብታ ላይ የወይን ቦታ ነበረው።
\v 2 በዙሪያው ቈፈረ፣ ድንጋዮችንም ለቅሞ አወጣ፣ ምርጥ የሆነውንም ወይን ተከለበት። በመካከሉም ግንብ ሠራ፣ ደግሞም የመጥመቂያ ጕድጓድ ማሰበት። ወይንንም ያፈራ ዘንድ ጠበቀ፣ ዳሩ ግን ሆምጣጣ ፍሬ አፈራ።
\s5
\v 3 ስለዚህ አሁን፣ እናንተ በኢየሩሳሌም የምትኖሩ የይሁዳ ሰዎች ሆይ፤ በእኔና በወይኑ ቦታዬ መካከል ፍረዱ።
\v 4 ለወይኔ ያላደረግሁለት፥ ከዚህ በተጨማሪ አደርግለት ዘንድ የሚገባኝ ምንድር ነው? መልካም ወይንን ያፈራል ብዬ ስትማመን፣ ስለ ምን ሆምጣጣ ፍሬ አፈራ?
\s5
\v 5 አሁንም በወይኔ ላይ የማደርገውን አስታውቃችኋለሁ፤ አጥሩን እነቅላለሁ፤ ለማሰማርያም ይሆናል፤ ቅጥሩንም አፈርሳለሁ፣ ለመራገጫም ይሆናል።
\v 6 ባድማ አደርገዋለሁ፤ አይቈረጥም፣ አይኰተኰትም፤ ኵርንችትና እሾህ ይበቅልበታል፤ ዝናብንም እንዳያዘንቡበት ዳመናዎችን አዝዛለሁ።
\s5
\v 7 የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ወይን ቦታ እርሱ የእስራኤል ቤት ነው፣ የደስታውም አትክልት የይሁዳ ሰዎች ናቸው፤ ፍርድን ይጠብቅ ነበር፣ እነሆም ግድያ ሆነ፤ ጽድቅንም ይተማመን ነበር፣ ይልቅ እርዳታ የሚለምን ጩኸት ሆነ።
\s5
\v 8 ስፍራ እስከማይቀር ድረስ እናንተም በምድር ላይ ብቻችሁን እስክትቀመጡ ድረስ፣ ቤትን ከቤት ጋር ለሚያያይዙ እርሻንም ከእርሻ ጋር ለሚያቀራርቡ ወዮላቸው!
\v 9 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፣ ታላላቆቹና መልካም የሆኑት ቤቶች ሳይቀሩ ባድማ ይሆናሉ፣ የሚኖርባቸውም አይገኝም።
\v 10 ከወይኑ ቦታ ዐሥር ጥማድ በሬ ካረሰው አንድ የባዶስ መስፈሪያ ብቻ ይወጣል፤ አንድ የቆሮስ መስፈሪያ ዘር አንድ የኢፍ መስፈሪያ ብቻ ይሰጣል።
\s5
\v 11 ጠንካራ መጠጥን ለማፈላለግ በጠዋት ለሚነቊ፣ የወይን ጠጅም እስኪያቃጥላቸው እስከ ሌሊት ድረስ ለሚዘገዩ ወዮላቸው!
\v 12 መሰንቆና በገና፣ ከበሮና እምቢልታም፣ የወይን ጠጅም በግብዣቸው አለ፤ የእግዚአብሔርን ሥራ ግን አልተመለከቱም፣ እንዲሁም እጁ ያደረገችውን አላስተዋሉም።
\s5
\v 13 ስለዚህ ሕዝቤ ባለማወቃቸው ወደ ምርኮ ሄዱ፣ መሪዎቻቸውም ተራቡ፣ ሕዝባቸውም የሚጠጡት የላቸውም።
\v 14 ስለዚህም ሲኦል የመዋጥ ፍላጎትዋን አስፍታለች፣ አፍዋንም ያለ ልክ ከፍታለች፤ ከበርቴዎቻቸውና አዛውንቶቻቸው፣ ባለጠጎቻቸውም ደስተኞቻቸውም ወደ ሲዖል ይወርዳሉ።
\s5
\v 15 ሰውም ይጐሰቍላል፣ ሰውም ይዋረዳል፣ የትዕቢተኞችም ዓይን ትዋረዳለች።
\v 16 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ግን በፍርድ ከፍ ከፍ ብሎአል፣ ቅዱሱም አምላክ በጽድቅ ተቀድሶአል።
\v 17 የበግ ጠቦቶች በገዛ መሰማርያቸው ውስጥ፣ እንዲሁም በባለጠጋ ሰዎች ጥፋት ውስጥ ይሰማራሉ፣ ጠቦቶችም ይግጣሉ።
\s5
\v 18 በደልን በምናምንቴ ገመድ፣ ኃጢአትንም በሰረገላ ማሰሪያ ወደ ራሳቸው ለሚስቡ፣ እናይ ዘንድ ይቸኵል፣
\v 19 "ሥራውንም ያፋጥን፤ እናውቃትም ዘንድ የእስራኤል ቅዱስ ምክር ትቅረብ፣ ትምጣ ለሚሉ ወዮላቸው!"
\s5
\v 20 ክፉውን መልካም፣ መልካሙን ክፉ ለሚሉ፤ ጨለማውን ብርሃን፣ ብርሃኑንም ጨለማ ለሚያደርጉ፤ ጣፋጩን መራራ፣ መራራውንም ጣፋጭ ለሚያደርጉ ወዮላቸው!
\v 21 በገዛ ዓይናቸው ዘንድ ጥበበኞች፣ በነፍሳቸውም አስተዋዮች ለሆኑ ወዮላቸው!
\s5
\v 22 የወይን ጠጅ ለመጠጣት ኃያላን፣ የሚያሰክረውንም ብርቱ መጠጥ ለማደባለቅ ጨካኞች ለሆኑ፤
\v 23 በደለኛውን ስለ ጉቦ ጻድቅ ለሚያደርጉ፣ የጻድቁንም ጽድቅ ለሚያስወግዱበት ወዮላቸው!
\s5
\v 24 ስለዚህ የእሳት ወላፈን ቃርሚያን እንደሚበላ፣ እብቅም በነበልባል ውስጥ እንደሚጠፋ፣ እንዲሁ የእነርሱ ሥር የበሰበሰ ይሆናል፣ ቡቃያቸውም እንደ ትቢያ ይበንናል፣ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔርን ሕግ ገፍተዋልና፣ የእስራኤልም ቅዱስ የተናገረውን ቃል አቃልለዋልና።
\s5
\v 25 ስለዚህ የእግዚአብሔር ቍጣ በሕዝቡ ላይ ነድዶአል፣ እጁንም በላያቸው ዘርግቶ ቀጥቷቸዋል፤ ተራሮችም ተንቀጠቀጡ፣ ሬሳቸውም በአደባባይ ላይ እንደ ጕድፍ ሆኖአል። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አልተመለሰችም፣ ነገር ግን እጁ በድጋሚ ለመምታት ገና ተዘርግታለች።
\s5
\v 26 ለአሕዛብም በሩቅ ምልክትን ያቆማል፣ ከምድርም ዳርቻ በፉጨት ይጠራቸዋል። ተመልከቱ፣ እየተጣደፉ ፈጥነው ይመጣሉ።
\s5
\v 27 በመካከላቸው ደካማና ስንኵል የለባቸውም፣ የሚያንቀላፋና የሚተኛም የለም፤ የወገባቸውም መቀነት አይፈታም፣ የጫማቸውም ማሰሪያ አይበጠስም፤
\v 28 ፍላጾቻቸው ተስለዋል፣ ቀስቶቻቸውም ሁሉ ተለጥጠዋል፤ የፈረሶቻቸውም ኮቴ እንደ ቡላድ፣ የሰረገሎቻቸውም መንኰራኵር እንደ ዐውሎ ነፋስ ነው።
\s5
\v 29 ጩኸታቸው እንደ አንበሳ ነው፣ እንደ አንበሳ ደቦሎችም ያገሣሉ። ንጥቂያንም ይዘው ያገሣሉ፣ ይወስዱትማል፣ የሚታደግም የለም።
\v 30 በዚያም ቀን እንደ ባሕር መትመም ይተምሙባቸዋል፤ ወደ ምድርም ቢመለከቱ፣ ጨለማና መከራ ይመለከታል፤ ብርሃንም በደመናዎችዋ ውስጥ ጨልሞአል።
\s5
\c 6
\p
\v 1 ንጉሡ ዖዝያን በሞተበት ዓመት፣ እግዚአብሔርን በረጅምና ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ተቀምጦ አየሁት፣ የልብሱም ዘርፍ መቅደሱን ሞልቶት ነበር።
\v 2 ሱራፌልም ከእርሱ በላይ ቆመው ነበር፤ ለእያንዳንዱም ስድስት ክንፍ ነበረው፤ በሁለት ክንፍ ፊቱን ይሸፍን ነበር፣ በሁለቱም ክንፍ እግሮቹን ይሸፍን ነበር፣ በሁለቱም ክንፍ ይበር ነበር።
\s5
\v 3 አንዱም አንደኛውን በመጥራት፣ "ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር! ምድር ሁሉ በክብሩ ተሞልታለች" እያለ ይጮኽ ነበር።
\s5
\v 4 የመድረኩም መሠረት ከሚጮኹት ድምፅ የተነሣ ተናወጠ፣ ቤቱም ጢስ ሞላበት።
\v 5 ከዚያ እኔ፣ "ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው በመሆኔ፣ ከንፈሮቻቸውም በረከሱባቸው ሕዝብ መካከል በመቀመጤ ዓይኖቼ የሠራዊትን ጌታ ንጉሡን እግዚአብሔርን ስለ አዩ፣ ጠፍቻለሁና ወዮልኝ!" አልሁ።
\s5
\v 6 ከዚያም ከሱራፌል አንዱ እየበረረ ወደ እኔ መጣ፤ በእጁም ከመሠዊያው በጕጠት የወሰደው ፍም ነበረ።
\v 7 በዚያም አፌን ዳሰሰበትና። "ተመልከት፣ ይህ ከንፈሮችህን ነክቶአል፤ በደልህም ከአንተ ተወገደ፣ ኃጢአትህም ተሰረየልህ።" አለኝ።
\s5
\v 8 የጌታንም ድምፅ፣ "ማንን እልካለሁ? ማንስ ይሄድልናል?" ሲል ሰማሁ። እኔም፣ "እኔ አለሁ፤ እኔን ላከኝ።" አልሁ።
\v 9 እርሱም፣ "ሂድና ይህን ሕዝብ፣ ትሰማላችሁ፣ አታስተውሉምም፤ ታያላችሁ፣ አትመለከቱምም" በላቸው።
\s5
\v 10 በዓይናቸው እንዳያዩ፣ በጆሮአቸውም እንዳይሰሙ፣ በልባቸውም እንዳያስተውሉ፣ ተመልሰውም እንዳይፈወሱ፣ የዚህን ሕዝብ ልብ አደንድን፣ ጆሮአቸውንም አደንቍር፣ ዓይናቸውንም አሳውር" አለኝ።
\s5
\v 11 ከዚያም እኔ፣ "ጌታ ሆይ፣ እስከ መቼ ድረስ ነው?" አልሁ። እርሱም ሲመልስ፣ "ከተሞች የሚኖርባቸውን አጥተው እስኪፈርሱ ድረስ፣ ቤቶችም ሰው የሌለባቸው እስኪሆኑ፣ ምድርም ፈጽሞ ባድማ ሆና እስክትቀር ድረስ፣
\v 12 እግዚአብሔርም ሰዎችን እስኪያርቅ፣ በምድርም መካከል ውድማው መሬት እስኪበዛ ድረስ ነው።" አለ።
\s5
\v 13 በእርስዋም ዘንድ አንድ ዐሥረኛ ሰው ቀርቶ እንደ ሆነ እነርሱ ደግሞ በድጋሚ ይቃጠላሉ፤ በተቈረጡ ጊዜ ጉቶቻቸው እንደ ቀሩ እንደ ግራርና እንደ ኮምበል ዛፍ ሆኖ፣ ጉቶው የተቀደሰ ዘር ይሆናል።"
\s5
\c 7
\p
\v 1 በይሁዳ ንጉሥ በዖዝያን ልጅ በኢዮአታም ልጅ በአካዝ ዘመን የሶርያ ንጉሥ ረአሶን፣ የእስራኤልም ንጉሥ የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ፣ ኢየሩሳሌምን ሊወጉ ወጡ፣ ሊያሸንፉአትም አልቻሉም።
\v 2 ለዳዊትም ቤት፣ ሶርያ ከኤፍሬም ጋር እንደተባበሩ ወሬ ተነገረ። የእርሱም ልብ፣ እንዲሁም የሕዝቡም ልብ፣ የዱር ዛፍ በነፋስ እንድትናወጥ ተናወጠ።
\s5
\v 3 ከዚያም እግዚአብሔር ኢሳይያስን፣ "አንተና ልጅህ ያሱብ አካዝን ትገናኙት ዘንድ በልብስ አጣቢው እርሻ መንገድ ወዳለው ወደ ላይኛው የኵሬ መስኖ ጫፍ ውጡ።
\v 4 እንዲህም በለው፣ 'ተጠንቀቅ፣ ዝምም በል፣ ስለ እነዚህ ስለሚጤሱ ስለ ሁለት የእንጨት ጠለሸቶች፣ ስለ ሶርያና ስለ ረአሶን፣ ስለ ሮሜልዩም ልጅ ቍጣ አትፍራ፣ ልብህም አይድከም።
\s5
\v 5 ሶርያና ኤፍሬም የሮሜልዩም ልጅ፣
\v 6 "ወደ ይሁዳ እንውጣ እናስጨንቃትም፣ እንስበራትም፣ የጣብኤልንም ልጅ እናንግሥባት" ብለው ክፋት ስለ መከሩብህ፤
\s5
\v 7 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ይህ ምክር አይጸናምና አይሆንም፣
\v 8 የሶርያ ራስ ደማስቆ ስለሆነ፣ የደማስቆም ራስ ረአሶን ስለሆነ አይከናወንም። በስድሳ አምስት ዓመት ውስጥ ኤፍሬም ይሰባበራልና ከእንግዲህ ወዲህ ሕዝብ አይሆንም፤
\v 9 የኤፍሬምም ራስ ሰማርያ ነው፣ የሰማርያም ራስ የሮሜልዩ ልጅ ነው። በእምነት ባትጸኑ፣ በእርግጥም በዋስትና አትጸኑም።"
\s5
\v 10 እግዚአብሔርም ደግሞ አካዝን እንዲህ ብሎ ተናገረው፣
\v 11 "ከጥልቁ ወይም ከከፍታው ቢሆን ከአምላክህ ከእግዚአብሔር ምልክትን ለምን።"
\v 12 አካዝ ግን፣ "አልለምንም፣ እግዚአብሔርንም አልፈታተንም" አለ።
\s5
\v 13 ስለዚህ ኢሳይያስ ሲመልስ፣ "እናንተ የዳዊት ቤት ሆይ፣ ስሙ። በውኑ የሰውን ትእግሥት መፈታተናችሁ ቀላል ነውን? ዩአምላኬን ትእግሥት ደግሞ ልትፈታተኑ ይገባችኋልን?
\v 14 ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ ተመልከቱ፣ ድንግል ትፀንሳለች፣ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፣ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።
\v 15 ክፉን ለመጥላት መልካሙንም ለመምረጥ ሲያውቅ ቅቤና ማር ይበላል።
\s5
\v 16 ሕፃኑ ክፉን ለመጥላት መልካሙን ለመምረጥ ከማወቊ በፊት፣ የፈራሃቸው የሁለቱ ነገሥታት አገር ባድማ ትሆናለች።
\v 17 እግዚአብሔርም ኤፍሬም ከይሁዳ ከተለየበት ቀን ጀምሮ ያልመጣውን ዘመን በአንተና በሕዝብህ በአባትህም ቤት ላይ ያመጣል፤ እርሱም የአሦር ንጉሥ መምጣት ነው።"
\s5
\v 18 በዚያም ጊዜ እግዚአብሔር በግብጽ ወንዝ ርቀት ያለውን ዝምብ፣ በአሦርም አገር ያለውን ንብ በፉጨት ይጠራል።
\v 19 ሁሉም ይመጡና በበረሃ ሸለቆ፣ በድንጋይም ዋሻ ውስጥ በእሾህ ቍጥቋጦ ሁሉ ላይ፣ በማሰማርያውም ሁሉ ላይ ይሰፍራሉ።
\s5
\v 20 በዚያም ቀን እግዚአብሔር ከወንዙ ማዶ በተከራየው ምላጭ በአሦር ንጉሥ የራሱንና የእግሩን ጠጕር ይላጨዋል፤ ምላጩም ጢሙን ደግሞ ይላጫል።
\v 21 በዚያም ቀን፣ ሰው አንዲት ጊደርንና ሁለት በጎችንም በሕይወት ያቆያል፣
\v 22 ደግሞም ከሚሰጡት ወተት ብዛት የተነሣ ቅቤ ይበላል፤ በአገሪቱም መካከል የቀረ ሁሉ ቅቤና ማር ይበላል።
\s5
\v 23 በዚያም ቀን፣ ሺህ ብር የተገመተ ሺህ የወይን ግንድ በነበረበት ስፍራ ሁሉ ለኵርንችትና ለእሾህ ብቻ ይሆናል።
\v 24 ኵርንችትና እሾህ በምድር ሁሉ ላይ ነውና በፍላጻና በቀስት ወደዚያ ይገባሉ።
\v 25 በመቈፈርያም ወደ ተቈፈሩ ኮረብቶች ሁሉ ከኵርንችትና እሾህ ፍርሃት የተነሣ ወደዚያ አትሄድም፤ ነገር ግን የበሬ ማሰማርያና የበግ መራገጫ ይሆናል።
\s5
\c 8
\p
\v 1 እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፣ "ታላቅ ሰሌዳ ወስደህ፣ 'ምርኮ ፈጠነ፣ ብዝበዛ ቸኰለ' ብለህ ጻፍበት።
\v 2 የታመኑትን ሰዎች፣ ካህኑን ኦርዮንና የበራክዩን ልጅ ዘካርያስን ምስክሮች አድርግልኝ" አለኝ።
\s5
\v 3 ወደ ነቢይቱም ቀረብሁ፣ እርስዋም ፀነሰች ወንድ ልጅንም ወለደች።
\v 4 ከዚያም እግዚአብሔር፣ "ሕፃኑ 'አባባ' እና 'እማማ' በማለት መጣራት ከማወቊ በፊት የደማስቆን ሀብትና የሰማርያን ምርኮ በአሦር ንጉሥ ፊት ይወስዳልና ስሙን ምርኮ ፈጠነ፣ ብዝበዛ ቸኰለ ብለህ ጥራው፤" አለኝ።
\s5
\v 5 እግዚአብሔር በድጋሚ ተናገረኝ፣ እንዲህም አለኝ፣
\v 6 "ይህ ሕዝብ በቀስታ የሚሄደውን የሰሊሆምን ውኃ ጠልቶአልና፣ ረአሶንንና የሮሜልዩንም ልጅ ወዶአልና፣
\v 7 ስለዚህ እግዚአብሔር ብርቱና ብዙ የሆነውን የወንዝ ውኃ፣ የአሦርን ንጉሥና ክብሩን ሁሉ፣ ያመጣባቸዋል። መስኖውንም ሁሉ ሞልቶ ይወጣል፣ በዳሩም ሁሉ ላይ ይፈስሳል፤
\s5
\v 8 እስከ አንገት እስኪደርስ ድረስ እየጐረፈ ወደ ይሁዳ ይገባል፣ እያጥለቀለቀም ያልፋል። አማኑኤል ሆይ፣ የክንፉ መዘርጋት የአገርህን ስፋት ትሞላለች።"
\s5
\v 9 አሕዛብ ሆ፣ እወቁና ደንግጡ፣ እናንተም አገራችሁ የራቀ ሁሉ፣ አድምጡ፤ ታጠቁም፣ ደንግጡ፤ ታጠቁ፤ ደንግጡ።
\v 10 ዕቅድን አብጁ፣ ነገር ግን አይከናወንም፤ ትእዛዙን ተናገሩ፣ ነገር ግን አይከናወንም፣ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነውና።
\s5
\v 11 እግዚአብሔር በጽኑ እጁ ጭምር እንዲህ ተናገረኝ፣ በዚህም ሕዝብ መንገድ አንዳልሄድ አስጠነቀቀኝ፣ እንዲህም አለኝ።
\v 12 ይህ ሕዝብ፣ አድማ ነው የሚሉትን ሁሉ፣ አድማ ነው አትበሉ፤ ማስፈራታቸውንም አትፍሩ፣ አትደንግጡ።
\v 13 ነገር ግን የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን ቀድሱት፤ የሚያስፈራችሁና የሚያስደነግጣችሁም እርሱ ይሁን።
\s5
\v 14 እርሱም ለመቅደስ ይሆናል፤ ነገር ግን ለሁለቱ ለእስራኤል ቤቶች ለዕንቅፋት ድንጋይና ለማሰናከያ ዓለት ይሆናል። በኢየሩሳሌምም ለሚኖሩ ለወጥመድና ለአሽክላ ይሆናል።
\v 15 ብዙዎችም በእርሱ ይሰናከላሉ፣ ይወድቁማል፣ ይሰበሩማል፣ ይጠመዱማል፣ ይያዙማል።
\s5
\v 16 ምስክሬን እሰር፣ በደቀ መዛሙርቶቼም መካከል ሕጉን አትም።
\v 17 ከያዕቆብም ቤት ፊቱን የሰወረውን እግዚአብሔርን እጠብቃለሁ፣ እጠብቀዋለሁም።
\v 18 ተመልከቱ፣ እኔና እግዚአብሔር የሰጠኝ ልጆች ለእስራኤል በጽዮን ተራራ ከሚኖረው ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ ምልክትና ተአምራት ነን።
\s5
\v 19 እነርሱ፣ "የሚጮኹትንና ድምፃቸውን ዝቅ አድርገው የሚናገሩትን መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን ጠይቁ" ባሉአችሁ ጊዜ፣ ሕዝቡ ከአምላኩ መጠየቅ አይገባውምን? ወይስ ለሕያዋን ሲሉ ሙታንን ይጠይቃሉን?
\v 20 ስለዚህ ለሕግና ለምስክር ትኩረት ልትሰጡ ይገባል! እንዲህም ያለውን ቃል ባይናገሩ፣ የንጋት ብርሃን ስለሌላቸው ነው።
\s5
\v 21 እነርሱም ተጨንቀውና ተርበው ያልፋሉ። በተራቡም ጊዜ፣ ተቈጥተው ንጉሣቸውንና አምላካቸውን ይረግማሉ፣ ፊታቸውን ወደ ላይያቀናሉ።
\v 22 ወደ ምድርም ይመለከታሉ፣ ተመልከቱ፣ መከራና ጨለማ፣ የሚያስጨንቅም ጭጋግ አለ። ወደ ድቅድቅም ጨለማ ይሰደዳሉ።
\s5
\c 9
\p
\v 1 ነገር ግን ተጨንቃ ለነበረች ጨለማ አይሆንም። በመጀመሪያው ዘመን የዛብሎንንና የንፍታሌምን ምድር አቃለለ፣ በኋለኛው ዘመን ግን በዮርዳኖስ ማዶ በባሕር መንገድ ያለውን የአሕዛብን ገሊላ ያከብራል።
\v 2 በጨለማ የሄደ ሕዝብ ታላቅ ብርሃን አየ፤ በሞት ጥላ አገርም ለኖሩ ብርሃን በራላቸው።
\s5
\v 3 ሕዝቡን አብዝተሃል፣ ደስታንም ጨምረህላቸዋል፤ በመከር ደስ እንደሚላቸው፣ ሰዎችም ምርኮን ሲካፈሉ ደስ እንደሚላቸው በፊትህ ደስ ይላቸዋል።
\s5
\v 4 በምድያም ጊዜ እንደ ሆነ የሸክሙን ቀንበር የጫንቃውንም በትር የአስጨናቂውንም ዘንግ ሰብረሃል።
\v 5 የሚረግጡ የሰልፈኞች ጫማ ሁሉ፣ በደምም የተለወሰ ልብስ ለቃጠሎ ይሆናል፣ እንደ እሳት ማቃጠያም ሆኖ ይቃጠላል።
\s5
\v 6 ሕፃን ተወልዶልናልና፣ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፣ ኃያል አምላክ፣ የዘላለም አባት፣ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።
\v 7 ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም ድረስ በፍርድና በጽድቅ ያጸናውና ይደግፈው ዘንድ በዳዊት ዙፋንና በመንግሥቱ ላይ አለቅነቱ ይበዛል፣ ለሰላሙም ፍፃሜ የለውም። የእግዚአብሔር ቅንዓት ይህን ያደርጋል።
\s5
\v 8 ጌታ በያዕቆብ ላይ ቃልን ሰደደ፣ በእስራኤልም ላይ ወደቀ።
\v 9 በትዕቢትና በልብ ኵራት የሚናገሩ በኤፍሬምና በሳርያ የሚኖሩ ሕዝብ ሁሉ።
\v 10 "ጡቡ ወድቆአል፣ ነገር ግን በተወቀረ ድንጋይ እንሠራለን፤ የሾላ ዛፎች ተቈርጠዋል፣ ነገር ግን ዝግባን እንተካባቸዋለን" የሚሉት ሁሉ ያውቃሉ።
\s5
\v 11 ስለዚህ እግዚአብሔር በረአሶን ላይ በጽዮን ተራራ ተቋቋሚ ያስነሣበታል፣
\v 12 ጠላቶቹን ሶርያውያንንም ከምሥራቅ፣ ፍልስጥኤማውያንንም ከምዕራብ ያንቀሳቅስበታል፤ እስራኤልንም በተከፈተ አፍ ይበሉታል። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አልተመለሰችም፣ ነገር ግን እጁ ገና ተዘርግታ ትኖራለች።
\s5
\v 13 ሕዝቡ ግን ወደ ቀሠፋቸው አልተመለሱም፣ የሠራዊትንም ጌታ እግዚአብሔርን አልፈለጉም።
\v 14 ስለዚህ እግዚአብሔር ራስና ጅራትን፣ የሰሌኑን ቅርንጫፍና እንግጫውን በአንድ ቀን ከእስራኤል ይቆርጣል።
\v 15 ሽማግሌውና ከበርቴው እርሱ ራስ ነው፤ በሐሰትም የሚያስተምር ነቢይ እርሱ ጅራት ነው።
\s5
\v 16 ይህን ሕዝብ የሚመሩ ያስቱአቸዋል፤ በእነርሱ የሚመሩትም ይዋጣሉ።
\v 17 ስለዚህም ሰው ሁሉ ዝንጉና ክፉ ሠሪ ነውና፣ አፍም ሁሉ ስንፍናን ይናገራልና ስለዚህ ጌታ በጕልማሶቻቸው ደስ አይለውም፥ ለድሀ አደጎቻቸውና ለመበለቶቻቸውም አይራራም። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አልተመለሰችም፣ ነገር ግን እጁ ገና ተዘርግታ ትኖራለች።
\s5
\v 18 ክፋት እንደ እሳት ይቃጠላል፤ ኵርንችቱንና እሾሁን ይበላል፤ ጭፍቅ የሆነውንም ዱር ያቃጥላል፥ ጢሱም ተትጐልጕሎ እንደ ዓምድ ይወጣል።
\v 19 በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ቍጣ ምድር ተቃጥላለች፤ ሕዝቡም እሳት እንደሚበላው እንጨት ሆኖአል፤ ሰውም ለወንድሙ ራርቶ አያድንም።
\s5
\v 20 ሰው ከቀኙ በኩል ሥጋ ቆርጦም ይራባል፤ ሥጋውን በግራ በኩል ይበላል አይጠግብምም። እያንዳንዱም የገዛ ራሱን ክንድ ሥጋ ይበላል፤
\v 21 ምናሴ ኤፍሬምን፣ ኤፍሬምም ምናሴን ይበላል፤ እነርሱም በአንድነት የይሁዳ ጠላቶች ይሆናሉ። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አልተመለሰችም፣ ነገር ግን እጁ ገና ልትመታ ትዘረጋለች።
\s5
\c 10
\p
\v 1 መበለቶችም ቅሚያቸው እንዲሆኑ፣ ድሀ አደጎችንም ብዝበዛቸው እንዲያደርጉ፣ የድሀውን ፍርድ ያጣምሙ ዘንድ፣
\v 2 የችግረኛውንም ሕዝቤን ፍርድ ያጐድሉ ዘንድ የግፍን ትእዛዛት ለሚያዝዙ፣ ክፉንም ጽሕፈት ለሚጽፉ ወዮላቸው!
\s5
\v 3 በፍርድ ቀን፣ መከራም ከሩቅ በሚመጣበት ዘመን ምን ታደርጉ ይሆን? ለእርዳታስ ወደ ማን ትሸሻላችሁ? ብልጥግናችሁንስ ወዴት ትተዉታላችሁ?
\v 4 ከእስረኞች በታች ይጐነበሳሉ፣ ከተገደሉትም በታች ይወድቃሉ። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አልተመለሰችም፣ ነገር ግን እጁ ገና ልትመታ ተዘርግታለች።
\s5
\v 5 ለቍጣዬ በትር ለሆነ፣ የመዓቴም ጨንገር በእጁ ላለ ለአሦር ወዮለት!
\v 6 እርሱንም በዝንጉ ሕዝብ ላይ እልካለሁ፣ ምርኮውንና ብዝበዛውንም ይወስድ ዘንድ እንደ አደባባይም ጭቃ የተረገጡ ያደርጋቸው ዘንድ በምቈጣቸው ሰዎች ላይ አዝዘዋለሁ።
\s5
\v 7 እርሱ እንዲሁ አያስብም፣ በዚህ ሁኔታ አይወጥንም። ነገር ግን በልቡ በርካታ አሕዛብን ለማጥፋትና ለመቍረጥ በልቡ አለ።
\v 8 እንዲህ ብላልና፣ "መሳፍንቴ ሁሉ ነገሥታት አይደሉምን?
\v 9 ካልኖ እንደ ከርከሚሽ አይደለችምን? ሐማትስ እንደ አርፋድ አይደለችምን? ሰማርያስ እንደ ደማስቆ አይደለችምን?
\s5
\v 10 የተቀረጹ ምስሎቻቸው ከኢየሩሳሌምና ከሰማርያ ምስሎች የበለጡትን የጣዖቶችን መንግሥታት እጄ እንደረታች፣
\v 11 በሰማርያና በጣዖቶችዋም እንዳደረግሁ፣ እንዲሁስ በኢየሩሳሌምና በጣዖቶችዋ አላደርግምን?"
\s5
\v 12 ስለዚህ እንዲህ ይሆናል፤ ጌታ ሥራውን ሁሉ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም ላይ በፈጸመ ጊዜ፣ "የአሦርን ንጉሥ የኩሩ ልብ ፍሬን የዓይኑንም ከፍታ ትምክሕት እቀጣለሁ።"
\v 13 እርሱ እንዲህ ብሎአልና፣ "አስተዋይ ነኝና በእጄ ኃይልና በጥበቤ አደረግሁት፤ የአሕዛብን ድንበሮች አራቅሁ፣ ሀብታቸውንም ዘረፍሁ፣ እንደ ጀግናም ሆኜ በምድር የተቀመጡትን አዋረድሁ፤
\s5
\v 14 እጄም የአሕዛብን ባለጠግነት እንደ ወፍ ቤት አገኘች፤ የተተወም እንቍላል እንደሚሰበሰብ፣ እንዲሁ እኔ ምድርን ሁሉ ሰበሰብሁ። ክንፉን የሚያራግብ አፉንም የሚከፍት የሚጮኽም የለም።"
\s5
\v 15 በውኑ መጥረቢያ በሚቈርጥበት ሰው ላይ ስለ ራሱ ይመካልን? ወይስ መጋዝ በሚስበው ላይ ራሱን ይክባልን? ይህስ፣ በትር የሚያነሣውን እንደ መነቅነቅ ዘንግም እንጨት ያይደለውን እንደ ማንሣት ያህል ነው።
\v 16 ስለዚህም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በወፍራሞች ጦረኞቹ ላይ ክሳትን ይልካል፤ ከክብሩም በታች ቃጠሎው እንደ እሳት መቃጠል ይነድዳል።
\s5
\v 17 የእስራኤልም ብርሃን እንደ እሳት፣ ቅዱሷም እንደ ነበልባል ይሆናል፤ እሾሁንና ኵርንችቱን በአንድ ቀን ያቃጥላል ይበላውማል።
\v 18 ከነፍስም እስከ ሥጋ ድረስ የዱሩንና የሚያፈራውን እርሻ ክብር ይበላል፣ ይህም የታመመ ሰው እንደሚሰለስል ይሆናል።
\v 19 ታናሽ ብላቴናም ይጽፋቸው ዘንድ እስኪችል ድረስ የቀሩት የዱር ዛፎች በቍጥር ጥቂት ይሆናሉ።
\s5
\v 20 በዚያም ቀን፣ የእስራኤል ቅሬታ ከያዕቆብም ቤት ያመለጡት ከእንግዲህ ወዲህ በመቱአቸው ላይ አይደገፉም፣ ነገር ግን በእስራኤል ቅዱስ በእግዚአብሔር ላይ በእውነት ይደገፋሉ።
\v 21 የያዕቆብም ቅሬታ ወደ ኃያል አምላክ ይመለሳሉ።
\s5
\v 22 እስራኤል ሆይ፣ የሕዝብህ ቍጥር እንደ ባሕር አሸዋ ቢሆን ቅሬታው ይመለሳል። ጽድቅ የተትረፈረፈበትም ጥፋት ተወስኖአል።
\v 23 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም ያለቀ የተቈረጠ ጥፋትን በምድር ሁሉ መካከል ይፈጽማል።
\s5
\v 24 ስለዚህ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "በጽዮን የምትኖር ሕዝቤ ሆይ አሦርን አትፍራ። አሦር በበትር ይመታሃል፣ ግብጽም እንዳደረገ ዘንጉን ያነሣብሃል።
\v 25 ቍጣዬ እስኪፈጸም መዓቴም እስኪያጠፋቸው ድረስ በጣም ጥቂት ጊዜ ቀርቶአልና አትፍራው።"
\s5
\v 26 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም ምድያምን በሔሬብ ዓለት በኩል እንደ መታው ጅራፍ ያነሣበታል፤ በትሩንም በባሕር ላይ ያነሣል፣ በግብጽም እንዳደረገ ያነሣዋል።
\v 27 በዚያም ቀን፣ ሸክሙ ከጫንቃህ ቀንበሩም ከአንገትህ ላይ ይወርዳል፤ ቀንበሩም ከአንገትህ ከፍተኛ ውፍረት የተነሣ ይሰበራል።
\s5
\v 28 ጠላት ወደ አንጋይ መጥቶአል፤ በመጌዶን በኩል አልፎአል፤ በማክማስ ውስጥ ዕቃውን አኑሮአል፤
\v 29 በመተላለፊያ አልፎአል፤ በጌባ ማደሪያው ነው፤ ራማ ደንግጣለች፤ የሳኦል ጊብዓ ኰብልላለች።
\s5
\v 30 አንቺ የጋሊም ልጅ ሆይ፥ በታላቅ ድምፅሽ ጩኺ፤ ላይሳ ሆይ፥ አድምጪ! አንቺ ምስኪን ዓናቶት ሆይ፣ መልሽላት!
\v 31 መደቤና እየሸሸች ናት፣ በግቤርም የሚኖሩ ቤተሰቦቻቸውን አሽሽተዋል።
\v 32 ዛሬ በኖብ ይቆማል፤ በጽዮን ሴት ልጅ ተራራ በኢየሩሳሌም ኮረብታ ላይ ቡጢውን ይንጣል።
\s5
\v 33 ተመልከቱ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ቅርንጫፎቹን በሚያስፈራ ኃይል ይቈርጣል፤ በቁመት የረዘሙትም ይቈረጣሉ፣ ከፍ ያሉትም ይዋረዳሉ።
\v 34 ጭፍቅ የሆነውንም ዱር በመጥረቢያ ይቈርጣል፣ ሊባኖስም በኃያሉ እጅ ይወድቃል።
\s5
\c 11
\p
\v 1 ከእሴይ ግንድ በትር ይወጣል፣ የሥሩም ቍጥቋጥ ፍሬን ያፈራል።
\v 2 የእግዚአብሔር መንፈስ፣ የጥበብና የማስተዋል መንፈስ፣ የምክርና የኃይል መንፈስ፣ የእውቀትና እግዚአብሔርን የመፍራት መንፈስ ያርፍበታል።
\s5
\v 3 እግዚአብሔርን በመፍራት ደስታውን ያያል፤ ዐይኑም እንደምታይ አይፈርድም፣ ጆሮውም እንደምትሰማ አይበይንም፤
\v 4 ነገር ግን ለድሆች በጽድቅ ይፈርዳል፣ ለምድርም የዋሆች በቅንነት ይበይናል። በአፉም በትር ምድርን ይመታል፣ በከንፈሩም እስትንፋስ ክፉዎችን ይገድላል።
\v 5 የወገቡ መታጠቂያ ጽድቅ፣ የጎኑም መቀነት ታማኝነት ይሆናል።
\s5
\v 6 ተኵላ ከበግ ጠቦት ጋር ይኖራል፣ ነብርም ከፍየል ጠቦት ጋር ይተኛል፤ ጥጃና የአንበሳ ደቦል፣ ፍሪዳም በአንድነት ያርፋሉ፤ ትንሽም ልጅ ይመራቸዋል።
\v 7 ላምና ድብ አብረው ግጦሽ ይውላሉ፣ ግልገሎቻቸውም በአንድነት ያርፋሉ። አንበሳም እንደ በሬ ገለባ ይበላል።
\s5
\v 8 ሕፃን በእባብ ጕድጓድ ላይ ይጫወታል፣ ጡት የጣለውም ሕፃን በእፉኝት ቤት ላይ እጁን ይጭናል።
\v 9 በተቀደሰው ተራራዬ ሁሉ ላይ አይጐዱም አያጠፉምም፤ ውኃ ባሕርን እንደሚከድን ምድር እግዚአብሔርን በማወቅ ትሞላለችና።
\s5
\v 10 በዚያም ቀን፣ ለአሕዛብ ምልክት ሆኖ ይቆማል። የእሴይን ሥር አሕዛብ ይፈልጉታል፣ ማረፊያውም የተከበረ ይሆናል።
\v 11 በዚያም ቀን፣ የቀረውን የሕዝቡን ቅሬታ ከአሦርና ከግብጽ፣ ከጳትሮስና ከኢትዮጵያ፣ ከኤላምና ከሰናዖር ከሐማትም፣ ከባሕርም ደሴቶች ይመልስ ዘንድ ጌታ እንደ ገና እጁን ይገልጣል።
\s5
\v 12 ለአሕዛብም ምልክትን ያቆማል፣ ከእስራኤልም የተጣሉትን ይሰበስባል፣ ከይሁዳም የተበተኑትን ከአራቱ የምድር ማዕዘኖች ያከማቻል።
\v 13 የኤፍሬምንም ምቀኝነት ያቆማል፣ ይሁዳንም የሚጠሉ ይቆረጣሉ። ኤፍሬምም በይሁዳ አይቀናም፣ ይሁዳም ኤፍሬምን አይጠላም።
\s5
\v 14 በምዕራብም በኩል በፍልስጥኤማውያን ጫንቃ ላይ እየበረሩ ይወርዳሉ፣ የምሥራቅንም ልጆች በአንድነት ይበዘብዛሉ። በኤዶምያስና በሞዓብም ላይ እጃቸውን ይዘረጋሉ፣ የአሞንም ልጆች ለእነርሱ ይታዘዛሉ።
\v 15 እግዚአብሔርም የግብጽን ባሕር ያጠፋል፤ በትኩሱም ነፋስ እጁን በኤፍራጥስ ወንዝ ላይ ያነሣል፣ ሰባት ፈሳሾች አድርጎም ይከፋፍለዋል፣ ስለዚህም በጫማ ሊሻገሩት የሚችሉት ይሆናል።
\s5
\v 16 ከግብጽም በወጣ ጊዜ ለእስራኤል እንደ ነበረው ሁሉ ለቀረውም ሕዝብ ቅሬታ ከአሦር የሚወጣበት ጐዳና እንዲሁ ይሆናል።
\s5
\c 12
\p
\v 1 በዚያም ቀን፣ "እግዚአብሔር ሆይ፣ አመሰግንሃለሁ። ተቈጥተኸኛልና፣ ቍጣህንም ከእኔ መልሰሃልና፣ አጽናንተኸኛልምና።
\v 2 ተመልከቱ፣ እግዚአብሔር መድኃኒቴ ነው፤ ጌታ እግዚአብሔር ኃይሌና ዝማሬዬ ነውና፣ አዎን፣ በእርሱ ታምኜ አልፈራም። መድኃኒቴም ሆኖአልና" ትላለህ።
\s5
\v 3 ውኃውንም ከመድኃኒት ምንጮች በደስታ ትቀዳላችሁ።
\v 4 በዚያም ቀን እንዲህ ትላላችሁ፣ "እግዚአብሔርን አመስግኑ፣ ስሙንም ጥሩ፤ በአሕዛብ መካከል ሥራውን አስታውቁ፤ ስሙ ከፍ ያለ እንደ ሆነ ተናገሩ።
\s5
\v 5 ታላቅ ሥራ ሠርቶአልና ለእግዚአብሔር ተቀኙ፤ ይህንም በምድር ሁሉ ላይ የታወቀ እንዲሆን አድርጉ።
\v 6 አንቺ በጽዮን የምትኖሪ ሆይ፣ የእስራኤል ቅዱስ በመካከልሽ ከፍ ከፍ ብሎአልና ደስ ይበልሽ እልልም በዪ።"
\s5
\c 13
\p
\v 1 የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ያየው ስለ ባቢሎን የተነገረ ሸክም።
\v 2 ምድረ በዳ በሆነ ተራራ ላይ ምልክትን አቁሙ፣ ድምፅንም ከፍ አድርጉባቸው፤ በአለቆችም ደጆች እንዲገቡ እጃችሁን አንስታችሁ አሳዩ።
\v 3 ቍጣዬን ይፈጽሙ ዘንድ ቅዱሳኔን አዝዣለሁ፣ እኔ ኃያላኔንና በታላቅነቴ ደስ የሚላቸውን ጠርቻለሁ።
\s5
\v 4 በተራሮች ላይ እንደ ታላቅ ሕዝብ ድምፅ የሆነ የብዙ ሰው ድምፅ አለ! የተከተማቹት የአህዛብ መንግሥታት የውካታ ጫጫታ አለ! የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሠራዊትን ለሰልፍ አሰልፎአል።
\v 5 እግዚአብሔርና የቍጣው የጦር ዕቃ ምድርን ሁሉ ያጠፉአት ዘንድ ከሩቅ አገር፣ ከሰማይ ዳርቻ ይመጣሉ።
\s5
\v 6 የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአልና፣ አልቅሱ፤ ሁሉን ከሚችል አምላክ ዘንድ እንደሚመጣ ጥፋት ይመጣል።
\v 7 ስለዚህ፣ እጅ ሁሉ ትዝላለች፣ የሰውም ሁሉ ልብ ይቀልጣል፤
\v 8 ይደነግጣሉ፤ ምጥና ሕማም ይይዛቸዋል፣ እንደምትወልድ ሴትም ያምጣሉ። አንዱም በሌላው ይደነቃል፣ ፊታቸውም የነበልባል ፊት ነው።
\s5
\v 9 ተመልከቱ፣ ምድሪቱን ባድማ ሊያደርግ፣ ኃጢአተኞችዋንም ከእርስዋ ዘንድ ሊያጠፋ ጨካኝ ሆኖ በመዓትና በጽኑ ቍጣ ተሞልቶ የእግዚአብሔር ቀን ይመጣል።
\v 10 የሰማይም ከዋክብትና ሠራዊቱ ብርሃናቸውን አይሰጡም፣ ፀሐይም በወጣች ጊዜ ትጨልማለች፣ ጨረቃም በብርሃኑ አያበራም።
\s5
\v 11 ዓለሙን ስለ ክፋታቸው ክፉዎቹንም ስለ በደላቸው እቀጣለሁ። የእብሪተኞችንም ኵራት፣ የጨካኞቹንም ትዕቢት አዋርዳለሁ።
\v 12 የቀሩትም ከጥሩ ወርቅ ይልቅ የከበሩ ይሆናሉ፣ ሰውም ከኦፊር ወርቅ ይልቅ የከበረ ይሆናል።
\s5
\v 13 ስለዚህ በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር መዓት፣ በጽኑ ቍጣ ቀንም ሰማያትን አነቃንቃለሁ፣ ምድርም ከስፍራዋ ትናወጣለች።
\v 14 እንደ ተባረረም ሚዳቋ፣ ማንም እንደማይሰበስበው እንደ በግ መንጋ፣ ሰው ሁሉ ወደ ወገኑ ይመለሳል፣ ሁሉም ወደ አገሩ ይሸሻል።
\s5
\v 15 የተገኘ ሁሉ ይገደላል፣ የተያዘም ሁሉ በሰይፍ ይሞታል።
\v 16 ሕፃናቶቻቸውም በዐይናቸው ፊት እስኪቆራረጡ ድረስ ይጨፈጨፋሉ። ቤቶቻቸውም ይበዘበዛሉ፣ ሚስቶቻቸውም ተይዘው ይነወራሉ።
\s5
\v 17 ተመልከቱ፣ ብር የማይሹትን፣ ወርቅም የማያምራቸውን ሜዶናውያንን በላያቸው አናውጣለሁ።
\v 18 ፍላጾቻቸውም ጎበዞችን ይወጋሉ። ጨቅላዎችን አይምሩም፣ ዓይኖቻቸውም ለሕፃናት አይራሩም።
\s5
\v 19 እግዚአብሔርም ሰዶምንና ገሞራን ባፈረሰ ጊዜ እንደ ነበረው፣ የመንግሥታት ክብር፣ የከለዳውያንም ትዕቢት ጌጥ ባቢሎን እንዲሁ ትሆናለች።
\v 20 ከትውልድ እስከ ትውልድ ድረስ ማንም ሰው አይኖርባትም፤ ዓረቦቹ ድንኳንን በዚያ አይተክሉም፣ እረኞችም መንጎቻቸውን በዚያ አያሳርፉም።
\s5
\v 21 በዚያም የምድረ በዳ አራዊት ያርፋሉ። ጕጕቶችም በቤቶቻቸው ይሞላሉ፤ ሰጎኖችና የበረሃ ፍየሎች በዚያ ይኖራሉ።
\v 22 ጅቦችም በግንቦቻቸው፣ ቀበሮችም በሚያማምሩ አዳራሾቻቸው ይጮኻሉ። ጊዜዋም ለመምጣት ቀርቦአል ቀንዋም አይዘገይም።
\s5
\c 14
\p
\v 1 እግዚአብሔርም ያዕቆብን ይምረዋል፣ እስራኤልንም ደግሞ ይመርጠዋል፣ በገዛ አገራቸውም ያኖራቸዋል። መጻተኛም ከእርሱ ጋር ይተባበራል፣ ከያዕቆብም ቤት ጋር ይጣበቃል።
\v 2 አሕዛብም ይዘው ወደ ስፍራቸው ያመጡአቸዋል። የእስራኤልም ቤት በእግዚአብሔር ምድር እንደ ወንዶችና ሴቶች ባሪያዎች አድርገው ይገዙአቸዋል። የማረኩአቸውን ይማርካሉ፣ አስጨናቂዎችንም ይገዛሉ።
\s5
\v 3 በዚያም ቀን፣ እግዚአብሔር ከኀዘንህና ከመከራህ ከተገዛህለትም ከጽኑ ባርነት ያሳርፍሃል።
\v 4 ይህንም ምሳሌ በባቢሎን ንጉሥ ላይ ታነሣለህ፣ "አስጨናቂ እንዴት በፍጻሜው ዐረፈ፣ ኩሩውስ እንዴት ጸጥ አለ!" ይላሉ።
\s5
\v 5 እግዚአብሔር የአሕዛብ ገዢዎችን በትር በመዓትና በማያቋርጥ መምታት መታ፣
\v 6 አሕዛብንም ባልተከለከለ መከራ፣ በቍጣው የገዛውን የኀጥኣንን በትር የአለቆችንም ዘንግ እግዚአብሔር ሰብሮአል።
\s5
\v 7 ምድርም ሁሉ ዐርፋ በጸጥታ ተቀምጣለች፤ በዝማሬ ክብረ-በዓላቸውን ማድረግ ጀምረዋል።
\v 8 ጥድና የሊባኖስ ዝግባ፣ 'አንተ ከተዋረድህ ጀምሮ ማንም ይቈርጠን ዘንድ አልወጣብንም' ብለው በአንተ ደስ አላቸው።
\v 9 ሲኦል በመምጣትህ ልትገናኝህ በታች ታወከች፤ የሞቱትንም፣ የምድርን ታላላቆች ሁሉ፣ ለአንተ አንቀሳቀሰች፣ የአሕዛብንም ነገሥታት ሁሉ ከዙፋኖቻቸው አስነሣች።
\s5
\v 10 እነዚህ ሁሉ ተናግረው፣ 'አንተ ደግሞ እንደ እኛ ደክመሃል። እኛን መስለሃል። ጌጥህና የበገናህ ድምፅ ወደ ሲኦል ወረደ፤
\v 11 በበታችህም ብል ተነጥፎአል። ትልም ይሸፍንሃል' ብለው ይመልሱልሃል።
\s5
\v 12 አንተ የንጋት ልጅ አጥቢያ ኮከብ ሆይ፣ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ! አሕዛብንም ያዋረድህ አንተ ሆይ፣ እንዴት እስከ ምድር ድረስ ተቈረጥህ!
\v 13 አንተ በልብህ፣ 'ወደ ሰማይ ዐርጋለሁ፣ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አደርጋለሁ፣ በሰሜንም ዳርቻ በመሰብሰቢያ ተራራ ላይ እቀመጣለሁ፤
\v 14 ከዳመናዎች ከፍታ በላይ ዐርጋለሁ፣ በልዑልም እመሰላለሁ' አልህ።
\s5
\v 15 ነገር ግን ወደ ሲኦል፣ ወደ ጕድጓዱም ጥልቅ ትወርዳለህ።
\v 16 የሚያዩህ አፍጥጠው ይመለከቱሃልና። በውኑ ምድርን ያንቀጠቀጠ፣ መንግሥታትንም ያናወጠ፥
\v 17 ዓለሙን ሁሉ ባድማ ያደረገ፣ ከተሞችንም ያፈረሰ ምርከኞቹንም ወደ ቤታቸው ያልሰደደ ሰው ይህ ነውን? ብለው ያስተውሉሃል።
\s5
\v 18 የአሕዛብ ነገሥታት ሁሉ፣ በየመቃብራቸው በክብር አንቀላፍተዋል።
\v 19 አንተ ግን እንደ ተጠላ ቅርንጫፍ ከመቃብርህ ተጥለሃል፤ በሰይፍም የተወጉት፣ ተገድለውም ወደ ጕድጓዱ ድንጋዮች የወረዱት ከድነውሃል፤ እንደ ተረገጠም ሬሳ ሆነሃል።
\v 20 ምድርህን አጥፍተሃልና፣ ሕዝብህንም ገድለሃልና ከእነርሱ ጋር በመቃብር በአንድነት አትሆንም፤ የክፉዎች ዘር ለዘላለም የተጠራ አይሆንም።"
\s5
\v 21 እንዳይነሡም፣ ምድርንም እንዳይወርሱ፣ የዓለሙንም ፊት በከተሞች እንዳይሞሉ ስለ አባቶቻቸው በደል ለልጆቹ ሞትን አዘጋጁላቸው።
\v 22 "በእነርሱ ላይ እነሣለሁ" ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ከባቢሎን ስምንና ቅሬታን፣ ዘርንና ትውልድንም እቈርጣለሁ ይላል እግዚአብሔር።
\v 23 "የጃርት መኖርያ የውኃም መቋሚያ አደርጋታለሁ፤ በጥፋትም መጥረጊያ እጠርጋታለሁ" ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
\s5
\v 24 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ምሎአል፣ "እንደ ተናገርሁ በእርግጥ ይሆናል፣ እንደ አሰብሁም እንዲሁ ይቆማል።
\v 25 አሦርን በምድሬ ላይ እሰብረዋለሁ፣ በተራራዬም ላይ እረግጠዋለሁ። ከዚያም ቀንበሩ ከእነርሱ ላይ ይነሣል፣ ሸክሙም ከጫንቃቸው ላይ ይወገዳል።"
\s5
\v 26 በምድር ሁሉ ላይ እግዚአብሔር ያሰበው አሳብ ይህ ነው፣ በአሕዛብም ሁሉ ላይ የተዘረጋች እጅ ይህች ናት።
\v 27 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ይህን አስቦአል፤ የሚያስጥለውስ ማን ነው? እጁም ተዘርግታለች፤ የሚመልሳትስ ማን ነው?
\s5
\v 28 ንጉሡ አካዝ በሞተበት ዓመት ይህ ዐዋጅ ወጣ።
\v 29 ፍልስጥኤም ሆይ፣ ከእባቡ ሥር እፉኝት ይወጣልና፣ ፍሬውም የሚበርርና እሳት የሚመስል እባብ ይሆናልና የመታሽ በትር ስለ ተሰበረ ሁላችሁም ደስ አይበላችሁ።
\v 30 የድሆችም የበኵር ልጆች ይሰማራሉ፣ ችግረኞችም ተዘልለው ይተኛሉ፤ ሥርህንም በራብ እገድላለሁ፣ ቅሬታህም ይገደላል።
\s5
\v 31 አንተ በር ሆይ፣ ወዮ በል አንቺም ከተማ ሆይ፣ ጩኺ፤ ፍልስጥኤም ሆይ፣ ሁላችሁም ቀልጣችኋል፤ ጢስ ከሰሜን ይመጣል ከጭፍራውም ተለይቶ የሚቀር የለም።
\v 32 ለሕዝቡም መልእክተኞች ምን ብሎ መመለስ ይገባል? እግዚአብሔር ጽዮንን እንደ መሠረተ፣ የሕዝቡም ችግረኞች በእርስዋ ውስጥ እንደሚጠጉ ነው።
\s5
\c 15
\p
\v 1 ስለ ሞዓብ የተነገረ ሸክም፣ በእርግጥ፣ የሞዓብ ዔር በሌሊት ፈርሶ ጠፋ፤ ቂር የሚባልም የሞዓብ ምሽግ በሌሊት ፈርሶ ጠፋ።
\v 2 ወደ ባይት ወደ ዲቦንም ወደ ኮረብታ መስገጃዎችም ለልቅሶ ወጥተዋል፤ ሞዓብ በናባው በሜድባ ላይ ታለቅሳለች፤ ራሳቸው ሁሉ ተነጭቶአል፥ ጢማቸውም ሁሉ ተላጭቶአል።
\s5
\v 3 በየመንገዳቸውም በማቅ ታጥቀዋል፤ በየሰገነቶቻቸውና በየአደባባዮቻቸው እንባ እጅግ እያፈሰሱ ሁሉም አልቅሰዋል።
\v 4 ሐሴቦንና ኤልያሊ ለእርዳታ ጮኹ፤ ድምፃቸው እስከ ያሀጽ ድረስ ይሰማል። ስለዚህ የሞዓብ ሰልፈኞች ጮኹ፤ ነፍስዋ በውስጥዋ ተንቀጠቀጠች።
\s5
\v 5 ልቤ ስለ ሞዓብ ጮኸ፤ ከእርስዋም የሚሸሹ ወደ ዞዓር ወደ ዔግላት ሺሊሺያ ኰበለሉ፤ በሉሒት ዓቀበት ላይ እያለቀሱ ይወጣሉ፣ በሖሮናይምም መንገድ የዋይታ ጩኸት ያነሣሉ።
\v 6 የኔምሬም ውኆች ይደርቃሉ፤ ሣሩም ደርቋል፣ ለጋውም ጠውልጓል፥ ልምላሜውም ሁሉ የለም።
\v 7 ስለዚህ የሰበሰቡትን ሀብትና መዝገባቸውን ወደ አኻያ ዛፍ ወንዝ ማዶ ይወስዱታል።
\s5
\v 8 ጩኸት የሞዓብን ዳርቻ ሁሉ ዞረ፤ ልቅሶዋም ወደ ኤግላይምና ወደ ብኤርኢሊም ደረሰ።
\v 9 የዲሞንም ውኃ ደም ተሞልታለች፤ በዲሞንም ላይ ሥቃይን እጨምራለሁ፣ ከሞዓባውያንም በሚያመልጡ፣ ከምድርም በሚቀሩ ላይ አንበሳን አመጣለሁ።
\s5
\c 16
\p
\v 1 በምድርም ላይ ለሠለጠነው አለቃ የበግ ጠቦቶችን በምድረ በዳ ካለችው ከሴላ ወደ ጽዮን ሴት ልጅ ተራራ ስደዱ።
\v 2 እንደሚበርር ወፍ፣ እንደ ተበተኑም ጫጩቶች፣ እንዲሁ የሞዓብ ሴቶች ልጆች በአርኖን መሻገሪያዎች ይሆናሉ።
\s5
\v 3 "መመሪያን ስጪ፣ ፍርድን አድርጊ፣ በቀትር ጊዜ ጥላሽን እንደ ሌሊት አድርጊ፤ የተሰደዱትን ሸሽጊ፣ የሸሹትን አትግለጪ።
\v 4 ከሞዓብ የተሰደዱት ከአንቺ ጋር ይኑሩ፤ ከሚያጠፋቸው ፊት መጋረጃ ሁኛቸው።" ጭቆናው ይቆማልና፣ ጥፋትም ይቆማልና፣ ይጨቍኑ የነበሩ ከምድር ይጠፋሉና።
\s5
\v 5 ዙፋንም በኪዳን ታማኝነት ይመሠረታል፤ ከዳዊት ድንኳን የሆነው በታማኝነት በዚያ ይቀመጣል። ፍርድን የሚሻ ጽድቅንም የሚያደርግ እንደመሆኑ ይፈርዳል።
\s5
\v 6 ስለ ሞዓብ ትዕቢት፣ ስለ እብሪተኝነቱ፣ ስለ ኵራቱና፣ ስለ ቁጣው ሰምተናል። ትምሕክቱ ባዶ ቃላት ናቸው።
\v 7 ስለዚህ ሞዓብ ስለ ሞዓብ ያለቅሳል፤ ሁሉም ያለቅሳል። ፈጽሞ ስለሚጠፋው ስለ ቂርሐራሴት የዘቢብ ጥፍጥፍ ታለቅሳላችሁ።
\s5
\v 8 የሐሴቦን እርሻዎችና የሴባማ ወይን ግንዶች ደርቀዋል። የአሕዛብ አለቆች የሰባበሩአቸው ቅርንጫፎች እስከ ኢያዜር ደርሰው ወደ ምድረ በዳ ተበትነዋል። ቍጥቋጦቹም ተንሰራፍተው ወደ ባሕር ሄደው ነበር።
\s5
\v 9 በእርግጥ በኢያዜር ልቅሶ ስለ ሴባማ ወይን ግንድ አለቅሳለሁ። ሐሴቦንና ኤልያሊ ሆይ፣ በእምባዬ አረሰርሳችኋለሁ። በበጋሽ ፍሬና በመከር ላይ የደስታን ጩኸት ትቻለሁና።
\v 10 ደስታና ሐሤትም ከፍሬያማው የእርሻ ደን ተወስዶአል፤ በወይኑም ቦታዎች ዝማሬና የደስታ እልልታ የለም። በመጥመቂያም ወይን የሚረግጥ የለም፤ የረጋጮቹን እልልታ አጥፍቻለሁ።
\s5
\v 11 ስለዚህ ልቤ ስለ ሞዓብ አንጀቴም ስለ ቂርሔሬስ እንደ መሰንቆ ትጮኻለች።
\v 12 ሞዓብም መጥቶ በኮረብታ መስገጃ ላይ ራሱን በደከመና ለጸሎት ወደ መቅደሱ በገባ ጊዜ፣ ጸሎቱ ምንም ነገር አያሳካም።
\s5
\v 13 እግዚአብሔር በሞዓብ ላይ አስቀድሞ የተናገረው ነገር ይህ ነው።
\v 14 አሁን ግን እግዚአብሔር፣ "በሦስት ዓመት ውስጥ እንደ ምንደኛ ዓመት የሞዓብ ክብርና የሕዝቡ ሁሉ ብዛት ይዋረዳል፣ ቅሬታውም እጅግ ያነሰና የተጠቃ ይሆናል" ይላል።
\s5
\c 17
\p
\v 1 ስለ ደማስቆ የተነገረ ሸክም። እነሆ፣ ደማስቆ ከእንግዲህ ከተማ አትሆንም፤ የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች።
\v 2 የአሮኤር ከተሞች ይጣላሉ። ለመንጋ ማሰማሪያ ሆናሉ፣ የሚያስፈራቸውም የለም።
\v 3 የተመሸጉ ከተሞች ከኤፍሬም ይጠፋሉ፣ መንግሥትም ከደማስቆ፤ የሶርያም ቅሬታ እንደ እስራኤል ልጆች ክብር ይሆናል ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
\s5
\v 4 በዚያም ቀን የያዕቆብ ክብር ይከሳል፣ የሥጋውም ውፍረት ይሸበሸባል።
\v 5 አጫጅ የቆመውን እህል በእጁ ሰብስቦ ዛላውን እንደሚያጭድ ይሆናል። በራፋይም ሸለቆ ቃርሚያ እንደሚለቅም እንዲሁ ይሆናል።
\s5
\v 6 ወይራ በተመታ ጊዜ ሁለት ወይም ሦስት ፍሬ በራሱ ላይ እንደሚቀር፥ አራት ወይም አምስት በዛፊቱ ጫፍ እንደሚገኝ፣ በእርሱ ዘንድ ቃርሚያ ይቀራል ይላል የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር።
\v 7 በዚያ ቀን ሰው ወደ ፈጣሪው ይመለከታል፣ ዐይኖቹም ወደ እስራኤል ቅዱስ ያያሉ።
\s5
\v 8 እጁም የሠራችውን መሠዊያ አይመለከትም፣ ጣቶቹም ወደ አበጁአቸው፣ ወደ አሼራ ዐምዶች ወይም ወደ ፀሐይ ምስሎች አያይም።
\v 9 በዚያም ቀን በእስራኤል ልጆች ፊት የአሞራውያንና የኤውያውያን ከተሞች እንደ ተፈቱ እንዲሁ ከተሞችህ ይፈታሉ ባድማም ይሆናሉ።
\s5
\v 10 የደኅንነትህን አምላክ ረስተሃልና፣ የብርቱነትህንም ዐለት አላሰብክምና። ስለዚህ ያማረውን ተክል ተክለሃል፣ እንግዳንም ዘር ዘርተሃል
\v 11 በዚያ ቀን ተክለህ ታጥርለትና ታበቅለዋለህ። ብዙም ሳይቆይ ዘርህ ያብባል፣ ነገር ግን መከሩ የሚሆነው በኀዘንና በጥልቅ ኃዘን ነው።
\s5
\v 12 ወዮላችሁ! እንደ ባሕር ሞገድ ድምፅ ለሚጮኹ፣ እንደ ኃይለኛም ውኃ ጩኸት ለሚጮኹ አሕዛብ!
\v 13 አሕዛብ እንደ ብዙ ውኃ ጩኸት ይጮኻሉ፣ እግዚአብሔር ግን ይገሥጻቸዋል። እነርሱም ወደ ሩቅ ይሸሻሉ፣ በተራራም ላይ እንዳለ እብቅ፣ በነፋስ ፊት ዐውሎ ነፋስ እንደሚያዞረው ትቢያ ይበተናሉ።
\v 14 በመሸ ጊዜ፣ ተመልከቱ፣ ድንጋጤ አለ፤ ከማለዳም በፊት አይገኙም። የዘረፉን ሰዎች እድል ፈንታ፣ የበዘበዙን ዕጣ ይህ ነው።
\s5
\c 18
\p
\v 1 ከኢትዮጵያ ወንዞች ማዶ የክንፎች ድምፅ ለሚሰማባት አገር ወዮላት፤
\v 2 መልእክተኞችን ከደንገል በተሠራ ጀልባ በአባይ ወንዝ ላይ ለምትልከው አገር፤ ሕዝብዋ ረጃጅሞችና ቆዳቸው ለስላሳ፣ አገራቸው በወንዞች የተከፋፈለች፣ ጠንካሮችና ኃያላን በመሆናቸው በዓለም ሁሉ ወደሚፈሩት ሕዝቦች እናንት ፈጣን መልእክተኞች ሂዱ!
\s5
\v 3 በዓለም የምትኖሩ ሁሉ እና በምድር የምትኖሩ፣ በተራሮች ጫፍ ላይ የተተከለ የሰንደቅ ዓላማ ምልክት ሲውለበለብ አስተውሉ፤ መለከት ሲነፋ ስሙ።
\s5
\v 4 እግዚአብሔር ያለኝ ነገር እንዲህ ነው፣ "በቀትር ጊዜ በጸጥታ እንደምታበራ ፀሐይ፣ በመከርም ወራት በሞቃት ሌሊት እንደሚታይ ጤዛ ከሰማያዊ መኖሪያዬ ጸጥ ባለ መንፈስ ቊልቊል እመለከታለሁ።"
\v 5 የወይን መከር ከመሰብሰቡ በፊት አበቦች ረግፈው የወይን ፍሬ በሚበስልበት ጊዜ የወይን ሐረግ ቅርንጫፎች በስለት ተቈርጠው እንደሚጣሉ እርሱ የዚያችን አገር ሕዝብ ያጠፋል።
\s5
\v 6 በአንድነት ለተራራ ወፎችና ለምድረ በዳ አራዊት ይተዋሉ። በበጋ ወፎች፣ በክረምትም አራዊት ይቀራመቷቸዋል።
\v 7 የሠራዊት አምላክ በዓለም ሁሉ የመፈራት ግርማ ካላቸው፣ ቆዳቸው ለስላሳ፣ ቁመታቸው ረጅም ኀያላንና ብርቱዎች ከሆኑት፣ በወንዞች የተከፋፈለች ምድር ካላቸው ከእነዚያ ሕዝብ መባ የሚቀበልበት ጊዜ ይመጣል፤ እነርሱም የሠራዊት አምላክ ወደሚመለክባት ወደ ጽዮን ኰረብታ ይመጣሉ።
\s5
\c 19
\p
\v 1 ስለ ግብጽ የተነገረ የእግዚአብሔር ቃል የሚከተለው ነው። ተመልከቱ፣ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና ሆኖ ወደ ግብጽ ይመጣል፤ የግብጻውያን ጣዖቶች በእርሱ ፊት ይናወጣሉ፤ የግብጽ ሕዝብም በፍርሃት ይቀልጣሉ።
\v 2 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ "ግብጻዊያንን በግብጻዊያን ላይ አስነሣለሁ፤ ወንድም በወንድሙ ላይ፣ ጐረቤትም በጐረቤቱ ላይ በጠላትነት እንዲነሣ አደርጋለሁ፤ ከተሞች በከተሞች ላይ፣ ነገሥታት በነገሥታት ላይ በጠላትነት ተነሥተው ይዋጋሉ።
\s5
\v 3 የግብጻውያን መንፈስ በውስጡ ይዳከማል። የጣዖቶቻቸውን የጠንቋዮቻቸውን የሙታን መናፍስት ጠሪዎችን ምክር ቢፈልጉም ምክሩን እደመስሳለሁ።
\v 4 እነርሱን በጭካኔ ለሚገዛቸው ጌታ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ እኔ ጌታ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።"
\s5
\v 5 በዓባይ ውስጥ ያለው ውሃ ይደርቃል፣ ወንዙም እየደረቀ ሄዶ ባዶ ይሆናል
\v 6 ወንዞቹ ይገማሉ፤ የግብጽ ምንጭ እየጐደለ ይደርቃል፤ ደንገሎቹና ቄጤማዎቹ ይጠወልጋሉ።
\s5
\v 7 በዓባይ ወንዝ ዳርቻ ያለው ቄጤማ ሁሉ ይደርቃል፤ በወንዙ አጠገብ የተዘራውም ሰብል ሁሉ ደርቆ ወደ አፈርነት በመለወጥ ነፋስ ይወስደዋል።
\v 8 ዓሣ አጥማጆችና መንጠቆአቸውን ወደ አባይ ወንዝ የሚጥሉ ሁሉ ያዝናሉ፤ ያለቅሳሉም፤ መረቦቻቸውንም በውሃ ላይ የሚዘረጉ ተስፋ ይቈርጣሉ፤
\s5
\v 9 የተበጠረውን የተልባ እግር የሚሠሩ እና ቀጭን ሐር የሚሠሩ ያፍራሉ።
\v 10 የግብጽ ሸማኔዎች ግራ ይጋባሉ፤ ደመወዝተኞችም በውስጣቸው ያዝናሉ።
\s5
\v 11 በጾዓን ያሉ ልዑላን ፍጹም ሞኞች ናቸው። ጠቢባን የሆኑት የፈርዖን አማካሪዎች ምክር ትርጉም የለሽ ይሆናል። ለፈርዖን "እኔ የብልኅ ሰው ልጅ ነኝ የጥንት ነገሥታት ልጅ ነኝ እንዴት ይላሉ?"
\v 12 እንግዲያው እነዚያ ጠቢባን ወዴት ናቸው? የሠራዊት አምላክ በግብጽ ላይ ያቀደውን ይንገሩህ፣ ደግሞም ያሳውቁህ።
\s5
\v 13 የጾዓን ልዑላን ሞኞች ሆኑ፤ የሜምፊስ ልዑሎችም ተታለሉ፤ የነገዶችዋ ማእዘናት የሆኑት ግብጽን አሳትዋት።
\v 14 የተቀያየጠ ምክር እንዲሰጡ ያደረጋቸውም እግዚአብሔር ነው፤ በመጨረሻም ግብጽ በሁሉ ነገር በመሳሳት የገዛ ትውከቱ አዳልጦት እንደሚጥለው ሰካራም ትንገዳገዳለች።
\v 15 በግብጽ ራስም ሆነ ጭራ፣ የዘንባባ ዝንጣፊ ቢሆን ወይም ቄጤማ የሆነ ምንም ነገር ማድረግ አይችልም።
\s5
\v 16 በዚያ ቀን፣ ግብጻዊያን እንደ ሴቶች ይሆናሉ። በእነርሱ ላይ ከሚነሣው የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር የቅጣት እጅ አንጻር ይሸበራሉ፣ ደግሞም ይፈራሉ።
\v 17 ይሁዳ ለግብጽ ሕዝብ የምታንገዳግድ ትሆናለች። ማንኛውም ሰው ስለ እርሷ ሲያስታውሳቸው፣ ከእግዚአብሔር የመቅጣት እቅድ የተነሣ ይሸበራሉ።
\s5
\v 18 በዚያን ቀን በግብጽ ምድር ውስጥ የሚገኙ አምስት የዕብራውያን ቋንቋ የሚናገሩ ከተሞች ይኖራሉ፤ በዚያም የሚኖሩ ሕዝቦች በሠራዊት አምላክ ስም ይምላሉ፤ ከእነዚህ ከተሞች አንዲቱ የፀሐይ ከተማ ተብላ ትጠራለች።
\s5
\v 19 በዚያን ቀን በግብጽ ምድር መካከል ላይ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ይሠራል፤ እንዲሁም በግብጽ ጠረፍ ላይ ለእግዚአብሔር የተለየ የድንጋይ ዐምድ ይተከላል።
\v 20 እነርሱም የሠራዊት አምላክ በግብጽ ምድር ለመኖሩ ምልክትና ምስክር ይሆናሉ። ከጭቆና የተነሣ እግዚአብሔር እንዲረዳቸው በሚጠይቁበት ጊዜ፣ የሚታደጋቸውን አዳኝ ይልክላቸዋል፣ እርሱም ከጠላቶቻቸው ያድናቸዋል።
\s5
\v 21 እግዚአብሔር ለግብጽ ሕዝብ የታወቀ ይሆናል፤ ደግሞም በዚያን ጊዜ እነርሱ ያውቁታል። መሥዋዕትና መባም ያቀርቡለታል፣ ለእግዚአብሔርም ስእለት ይሳላሉ፤ ስእለታቸውንም ሁሉ ይፈጽማሉ።
\v 22 እግዚአብሔር ግብጻውያንን ይቀጣል፤ ነገር ግን መልሶ ይፈውሳቸዋል፤ ወደ እርሱ ይመለሳሉ፤ እርሱም ጸሎታቸውን ሰምቶ ይፈውሳቸዋል።
\s5
\v 23 በዚያን ጊዜ በግብጽና በአሦር መካከል አውራ ጎዳና ይከፈታል፤ አሦራዊያን ወደ ግብጽ፣ ግብጻዊያንም ወደ አሦር ይመጣሉ፤ ደግሞም ግብጻዊያን ከአሦራዊያን ጋር ያመልካሉ።
\s5
\v 24 በዚያን ቀን፣ እስራኤል ከግብጽና ከአሦር ጋር ሦስተኛ አገር ትሆናለች፤ እነዚህም ሕዝቦች በዓለም መካከል በረከት ይሆናሉ።
\v 25 የሠራዊት አምላክም፣ "እናንተ በግብጽ የምትኖሩ ሕዝቤ፣ የፈጠርኳችሁ አሦራውያንና የመረጥኳችሁ የእስራኤል ሕዝብ የተባረካችሁ ሁኑ" ይላቸዋል።
\s5
\c 20
\p
\v 1 የአሦር ንጉሥ ሳርጎን ተርታንን በሰደደ ጊዜና ወደ አዛጦን በመጣ ጊዜ አዛጦንም ወግቶ በያዛት ጊዜ፥
\v 2 በዚያ ጊዜ እግዚአብሔር የአሞጽን ልጅ ኢሳይያስን፣ "ሂድና ማቅህን ከወገብህ አውጣ፣ ጫማህንም ከእግርህ አውልቅ" ብሎ ተናገረው። እንዲህም አደረገ፣ ራቁቱንም ባዶ እግሩንም ሄደ።
\s5
\v 3 እግዚአብሔርም አለ፣ "ባሪያዬ ኢሳይያስ በግብጽና በኢትዮጵያ ላይ ሦስት ዓመት ለምልክትና ለተአምራት ሊሆን ራቁቱንና ባዶ እግሩን እንደ ሄደ፣
\v 4 በዚህ መንገድ የአሦር ንጉሥ የግብጽንና የኢትዮጵያን ምርኮ፣ ጐበዛዝቱንና ሽማግሌዎቹን፣ ራቁታቸውንና ባዶ እግራቸውን አድርጎ ገላቸውንም ገልጦ፣ ለግብጽ ጕስቍልና ይነዳቸዋል።
\s5
\v 5 እነርሱም ከተስፋቸው ከኢትዮጵያ ከትምክሕታቸውም ከግብጽ የተነሣ ይፈራሉ ያፍሩማል፤
\v 6 በዚያም ቀን በዚች ባሕር ዳርቻ የሚኖሩ፣ "በእርግጥ፣ ከአሦር ንጉሥ እንድን ዘንድ ለእርዳታ ወደ እነርሱ የሸሸንበት ተስፋችን ይህ ነበረ፤ እኛስ እንዴት እናመልጣለን?" ይላሉ።
\s5
\c 21
\p
\v 1 በባሕር አጠገብ ስላለው ስለ ምድረ በዳ የተነገረ ዐዋጅ። ዐውሎ ነፋስ ከኔጌቭ እንደሚወጣ፣ እንዲሁ ከሚያስፈራ አገር በምድረ በዳ አልፎ ይወጣል።
\v 2 የሚረብሽ ራእይ ተነገረኝ፤ ወንጀለኛው በወንጀል ይሠራል፣ አጥፊውም ያጠፋል። ኤላም ሆይ፣ ወደ ላይ ውጪ፣ ሜዶን ሆይ ክበቢ፤ ትካዜውን ሁሉ አስቀርቻለሁ።
\s5
\v 3 ስለዚህ ወገቤ በሕመም ተሞላ፤ እንደምትወልድ ሴት ምጥ ያዘኝ፤ ከሰማሁት የተነሣ ጎበጥኩ፤ ካየሁት ነገር የተነሣ ተረበሽኩ።
\v 4 ልቤ ተርበደበደ፣ መንቀጥቀጥ አስፈራኝ፤ የተመኘሁት ሌሊት የሚያንቀጠቅጠኝ ሆነብኝ።
\s5
\v 5 ማዕዱን ያዘጋጃሉ፣ ምንጣፉንም ይዘረጋሉ፣ ይበሉማል፣ ይጠጡማል፤ እናንተ ልዑላን ሆይ፣ ተነሡ፣ ጋሻውን በዘይት ቀቡ።
\s5
\v 6 ጌታ ያለኝ እንዲህ ነው፣ "ሂድ፣ ጉበኛም አቁም፣ የሚያየውንም ይናገር።
\v 7 በከብት የሚቀመጡትን፣ ሁለት ሁለት እየሆኑ የሚሄዱት ሠረገሎች፥ በአህዮች የሚጋልቡትንና በግመሎች የሚጋልቡትን ባየ ጊዜ፣ በጽኑ ትጋት አስተውሎ ተግቶም ያድምጥ።"
\s5
\v 8 ያየውም። ጌታ ሆይ፥ ቀኑን ሁሉ ዘወትር በማማ ላይ ቆሜአለሁ፥ ሌሊቱንም ሁሉ በመጠበቂያዬ ላይ ተተክያለሁ፣"
\v 9 እነሆም፣ በፈረሶች የሚቀመጡ፣ ሁለት ሁለት ሆነው የሚሄዱ ፈረሰኞች ይመጣሉ ብሎ ጮኸ፤ እርሱም መልሶ፣ "ባቢሎን ወደቀች፣ ወደቀች፣ የተቀረጹም የአማልክቶችዋ ምስሎች ሁሉ በምድር ላይ ተጥለው ደቀቁ" አለ።
\s5
\v 10 እናንተ በአውድማዬ ላይ የተወቃችሁ የአውድማዬ ልጆች ሆይ! ከእስራኤል አምላክ፣ ከሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሰማሁትን ነገርኋችሁ።
\s5
\v 11 ስለ ኤዶምያስ የተነገረ ዐዋጅ። አንዱ ከሴይር ይጣራል፣ "ጕበኛ ሆይ፣ ከሌሊቱ ምን ያክል ሰዓት ቀረ? ጕበኛ ሆይ፣ ከሌሊቱ ምን ያክል ሰዓት ቀረ?" ብሎ ጠራኝ።
\v 12 ጕበኛውም እንዲህ አለ፣ "ማለዳው ይመጣል፣ ድግሞም ምሽቱ፤ ብትጠይቁ፣ ጠይቁ፤ ተመልሳችሁም ኑ" አለ።
\s5
\v 13 ስለ ዓረብ የተነገረ ዐዋጅ። የዴዳናውያን ነጋዴዎች ሆይ፣ በዓረብ ዱር ውስጥ ታድራላችሁ።
\v 14 በቴማን የምትኖሩ ሆይ፣ ወደ ተጠሙት ሰዎች ውኃ አምጡ፣ እንጀራ ይዛችሁ የሸሹትን ሰዎች ተቀበሉአቸው።
\v 15 ከሰይፍ፣ ከተመዘዘው ሰይፍ፣ ከተለጠጠውም ቀስት ከጽኑም ሰልፍ ሸሽተዋልና።
\s5
\v 16 ጌታ ያለኝ እንዲህ ነውና፣ "ምንደኛ ለአንድ ዓመት እንደሚቀጠር፣ በአንድ ዓመት ውስጥ የቄዳር ክብር ሁሉ ይጠፋል፤
\v 17 ከቀስተኞች ቍጥር ጥቂቶቹ ብቻ፣ የቄዳር ልጆች ኃያላን፣ ያንሳሉ፤" የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ተናግሮአልና።
\s5
\c 22
\p
\v 1 ስለ ራእይ ሸለቆ የተነገረ ዐዋጅ፤ እናንተ ሁላችሁ ወደ ቤት ሰገነት መውጣታቸሁ ምን ሆናችኋል?
\v 2 ጩኸትና ፍጅት የተሞላብሽ ከተማ፣ ደስታ ያለሽ ከተማ ሆይ፣ በአንቺ ውስጥ የተገደሉት በሰይፍ የተገደሉ አይደሉም፣ በሰልፍም የሞቱ አይደሉም።
\s5
\v 3 ገዚዎችሽ ሁሉ በአንድነት ሸሹ፣ ያለ ቀስትም ተማረኩ፤ ከሩቅ ሸሽተው ከአንቺ ዘንድ የተገኙት ሁሉ በአንድነት ታሰሩ።
\v 4 ስለዚህም፣ "ወደ እኔ አትመልከቱ፣ መራራ ልቅሶ አለቅሳለሁ፤ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ጥፋት ታጽናኑኝ ዘንድ አትድከሙ" አልሁ።
\s5
\v 5 ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ የድንጋጤና የመረገጥ የድብልቅልቅም ቀን፣ የቅጥርም መፍረስ ወደ ተራራም መጮኽ በራእይ ሸለቆ ውስጥ ሆኖአል።
\v 6 ኤላምም ከሰዎች ሠረገለኞችና ከፈረሰኞች ጋር ሆኖ አፎቱን ተሸከመ፣ ቂርም ጋሻውን ገለጠ።
\v 7 መልካሞቹንም ሸለቆችሽን ሠረገሎች ሞሉባቸው፣ ፈረሰኞችም መቆሚያቸውን በበር ላይ አደረጉ።
\s5
\v 8 የይሁዳንም መጋረጃ ገለጠ፤ በዚያም ቀን በዱር ቤት የነበረውን የጦር ዕቃ ተመለከትህ።
\v 9 የዳዊትም ከተማ ፍራሾች እንደ በዙ አይታችኋል፣ የታችኛውንም ኵሬ ውኃ አከማችታችኋል።
\s5
\v 10 የኢየሩሳሌምን ቤቶች ቈጥራችሁ ቅጥሩንም ለማጥናት ቤቶችን አፈረሳችሁ።
\v 11 በአሮጌው ኵሬ ላለው ውኃ በሁለቱ ቅጥር መካከል መጠባበቂያ ማከማቻ ሠራችሁ፤ ይህን ያደረገውን ግን አልተመለከታችሁም፣ ቀድሞ የሠራውንም አላሰባችሁም።
\s5
\v 12 በዚያም ቀን የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ወደ ልቅሶና ወደ ዋይታ ራስን ወደ መንጨትና ማቅንም ወደ መልበስ ጠራ።
\v 13 ነገር ግን ተመልከቱ፣ ሐሜትና ደስታ በሬውንና በጉንም ማረድ፣ ሥጋንም መብላት፣ የወይን ጠጅንም መጠጣት ሆነዋል። እናንተ፣ ነገ እንሞታለንና እንብላ እንጠጣ ብላችኋል።
\v 14 ይህም ነገር በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ጆሮ ተገለጠ፡- "እስክትሞቱ ድረስ ይህ በደል በእውነት አይሰረይላችሁም" ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
\s5
\v 15 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "በቤቱ ውስጥ ወደ ተሾመው ወደዚህ አዛዥ ወደ ሳምናስ ሂድ እንዲህም በለው፣
\v 16 "መቃብር በዚህ ያስወቀርህ ከፍ ባለው ስፍራ መቃብር ያሠራህ በድንጋይም ውስጥ ለራስህ መኖርያ ያሳነጽህ በዚህ ምን አለህ? በዚህስ በአንተ ዘንድ ማን አለ?"
\s5
\v 17 እነሆ፣ እግዚአብሔር ወርውሮ ይጥልሃል፣ ኃያል ሰውም አጠንክሮ ይወረውርሃል፤ በኃይል ይጎትትሃል።
\v 18 ጠቅልሎም ያንከባልልሃል ወደ ሰፊይቱም ምድር እንደ ኳስ ይጥልሃል። በዚያ ትሞታለህ በዚያም የክብርህ ሰረገላዎች ይሆናሉ። አንተ የጌታህ ቤት እፍረት ትሆናለህ!
\v 19 ከአዛዥነትህና ከጣቢያ ሥራህ አሳድድሃለሁ። ከሹመትህም ትወርዳለህ።
\s5
\v 20 በዚያም ቀን ባሪያዬን የኬልቅያስን ልጅ ኤልያቄምን እጠራለሁ፥
\v 21 መጐናጸፊያህንም አለብሰዋለሁ፣ በመታጠቂያህም አስታጥቀዋለሁ፣ ሹመትህንም በእጁ አሳልፌ እሰጠዋለሁ። በኢየሩሳሌምም ለሚኖሩ ለይሁዳም ቤት አባት ይሆናል።
\v 22 የዳዊትንም ቤት መክፈቻ በጫንቃው ላይ አኖራለሁ፤ እርሱም ይከፍታል የሚዘጋም የለም እርሱም ይዘጋል የሚከፍትም የለም።
\s5
\v 23 በአስተማማኝ ስፍራ እንደ ችንካር እተክለዋለሁ፣ ለአባቱም ቤት የክብር ዙፋን ይሆናል።
\v 24 የአባቱንም ቤት ክብር ሁሉ ልጆቹንም የልጅ ልጆቹንም፣ ከጽዋ ዕቃ ጀምሮ እስከ ማድጋ ዕቃ ድረስ፣ ታናናሹን ዕቃ ሁሉ ይሰቅሉበታል።
\s5
\v 25 በዚያ ቀን፣ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ በታመነው ስፍራ የተከለው ችንካር ይወልቃል፤ ተሰብሮም ይወድቃል፣ በእርሱም ላይ የተሰቀለው ሸክም ይጠፋል እግዚአብሔር ተናግሮአልና።
\s5
\c 23
\p
\v 1 ስለ ጢሮስ የተነገረ ሸክም። የተርሴስ መርከቦች ሆይ፣ አልቅሱ፤ ፈርሶአልና ቤት የለም፣ መግቢያም የለም፤ ከኪቲም አገር ጀምሮ ተገልጦላቸዋል።
\v 2 እናንተ በደሴት የምትኖሩ፣ በባሕርም የምትሻገሩ የሲዶና ነጋዴዎች፣ ወኪሎቻችሁ የሚያቀርቡላችሁ፣ ጸጥ በሉ።
\v 3 የሺሖር ዘርና የዓባይ ወንዝ መከር በብዙ ውኆች ላይ ገቢዋ ነበረ፤ እርስዋም የአሕዛብ መናገጃ ነበረች።
\s5
\v 4 እፈሪ፣ ሲዶና ሆይ፣ ባሕር ተናግሯልና፣ የባሕሩ ኃያል ተናግሯል። እንዲህ አለ፣ "አላማጥሁም፣ አልወለድሁምም፤ ጐበዛዝትንም አላሳደግሁም፤ ወጣት ሴቶችንም አላሳደግሁም" ብሎ ተናግሮአልና እፈሪ።
\v 5 ወሬዋ ወደ ግብጽ በደረሰ ጊዜ፣ በጢሮስ ወሬ ስለ እርሷ ምጥ ይይዛቸዋል።
\s5
\v 6 ወደ ተርሴስ ተሻገሩ፤ እናንተ በደሴት የምትኖሩ አልቅሱ።
\v 7 ደስተኛዋ ከተማ፣ ከቀድሞ ዘመን ጀምሮ የነበርሽ፣ ይህ ደርሶብሻልን፣ እንግዳ በሆነ ስፍራዎች ለመኖር እግሮችዋ ወደ ሩቅ ያፈለሱአት የደስታችሁ ከተማ ይህች ናትን?
\s5
\v 8 አክሊል ባስጫነች ከተማ ነጋዴዎችዋ ልዑላን በሆኑ፣ በእርስዋም የሚሸጡና የሚለውጡ የምድር ክቡራን የሆኑባት ጢሮስ ላይ ይህን የወጠነ ማን ነው?
\v 9 የክብርን ሁሉ ትዕቢት ይሽር ዘንድ የምድርንም ክቡራን ሁሉ ያስንቅ ዘንድ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ወስኖታል።
\s5
\v 10 የተርሴስ ልጅ ሆይ፣ የሚከለክልሽ የለምና እንደ ዓባይ ወንዝ በአገርሽ ላይ እረሺ።
\v 11 እግዚአብሔር በባሕር ላይ እጁን ዘረጋ፣ መንግሥታትንም አናወጠ፤ ምሽጎችዋንም ያጠፉ ዘንድ እግዚአብሔር ስለ ከነዓን አገር አዘዘ።
\v 12 እርሱም፣ "አንቺ የተበደልሽ የሲዶና ድንግል ልጅ ሆይ፣ ተነሺ፣ ከእንግዲህ ወዲህ በድጋሚ ደስ አይልሽም፤ ወደ ኪቲም ተሻገሪ፣ በዚያም ደግሞ አታርፊም አለ።
\s5
\v 13 ተመልከቱ የከለዳውያን ሰዎች። ይህ ሕዝብ መኖሩ ይቆማል፤ አሦራውያን ለምድረ በዳ አራዊት ሰጥተውታል። የወረራ ግንቦቻቸውን ሠሩ፥ አዳራሾችዋንም አፈረሱ፣ የጥፋት ባድማም አደረጓት።
\v 14 እናንተ የተርሴስ መርከቦች ሆይ፣ ምሽጋችሁ ፈርሶአልና ዋይ በሉ።
\s5
\v 15 በዚያም ቀን፣ ጢሮስ እንደ ንጉሥ ቀናት ሁሉ ሰባ ዓመት ያህል የተረሳች ትሆናለች። ከሰባ ዓመት በኋላ ግን ለጢሮስ በጋለሞታ ዘፈን እንደሚሆን እንዲሁ ይሆናል።
\v 16 አንቺ የተረሳሽ ጋለሞታ ሆይ፣ መሰንቆ ያዢ፣ በከተማ ላይም ዙሪ፤ መታሰቢያም ይሆንልሽ ዘንድ ዜማን አሳምሪ ዘፈንሽንም አብዢ።
\s5
\v 17 ከሰባ ዓመትም በኋላ እግዚአብሔር ጢሮስን ይረዳታል፣ ወደ ተቀጠረችበት ትመለሳለች። ደግሞም በምድር ፊት ላይ ከሆኑ ከዓለም መንግሥታት ሁሉ ጋር ትገለሙታለች።
\v 18 ንግድዋና ዋጋዋ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ይሆናል። ንግድዋም በልተው ይጠግቡ ዘንድ ማለፊያም ልብስ ይለብሱ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት ለሚኖሩ ይሆናል እንጂ በዕቃ ቤትና በግምጃ ቤት ውስጥ አይከተትም።
\s5
\c 24
\p
\v 1 ተመልከቱ፣ እግዚአብሔር ምድርን ባዶ ያደርጋታል፣ ባድማም ያደርጋታል፣ ይገለብጣትማል፣ በእርስዋም የሚኖሩትን ይበትናል።
\v 2 እንደ ሕዝቡም እንዲሁ ካህኑ፣ እንደ ባሪያውም እንዲሁ ጌታው፣ እንደ ባሪያይቱም እንዲሁ እመቤትዋ፣ እንደሚገዛም እንዲሁ የሚሸጠው፣ እንደ አበዳሪውም እንዲሁ ተበዳሪው፣ እንደ ዕዳ አስከፋዩም እንዲሁ ዕዳ ከፋዩ ይሆናል።
\s5
\v 3 ምድር ፈጽሞ ትጠፋለች፣ ፈጽማም ትበላሻላች፤ እግዚአብሔር ይህን ቃል ተናግሮአልና።
\v 4 ምድር ደረቀች ረገፈችም፤ ዓለም ተናወጠች ረገፈችም፤ የምድርም ስመ-ጥር ሕዝብ ደከሙ።
\v 5 ሕጉን ተላልፈዋልና፣ ሥርዓቱንም ለውጠዋልና፣ የዘላለሙንም ቃል ኪዳን አፍርሰዋልና፣ ምድርም ከሚቀመጡባት በታች ረክሳለች።
\s5
\v 6 ስለዚህ መርገም ምድርን ትበላለች፣ የሚኖሩባትም ጥፋተኞች ይሆናሉ። ስለዚህ የምድር ነዋሪዎች ይቃጠላሉ፣ ጥቂት ሰዎችም ይቀራሉ።
\v 7 አዲስ የወይን ጠጅ ይደርቃል፣ የወይን ንግድ ደከመች፣ ልባቸው ደስ ያለው ሁሉ ተከዙ።
\s5
\v 8 የከበሮው ደስታ ቆሟል፣ የደስተኞች ድምፅ ዝም ብሎአል፣ የመሰንቆ ደስታ ቀርቶአል።
\v 9 እየዘፈኑም የወይን ጠጅን አይጠጡትም፣ የሚያሰክርም መጠጥ ለሚጠጡት መራራ ይሆናል።
\s5
\v 10 የተቃወሰችው ከተማ ፈረሰች፤ ቤት ሁሉ ተዘግቶ ባዶ ሆነ።
\v 11 ስለ ወይኑም ጠጅ በአደባባይ ለቅሶ ይሆናል፤ ደስታ ሁሉ ጨልሞአል፥ የምድርም ደስታ ጠፍቷል።
\s5
\v 12 ከተማይቱም ባድማ ሆናለች፣ በርዋም በጥፋት ተመትቶአል።
\v 13 የወይራን ዛፍ እንደ መምታት፣ ከወይንም መከር በኋላ ቃርሚያውን እንደ መልቀም፣ እንዲሁ በምድር መካከል በአሕዛብም መካከል ይሆናል።
\s5
\v 14 እነዚህ ድምፃቸውን አሰምተው እልል ይላሉ፣ ስለ እግዚአብሔር ክብርም ከባሕር በደስታ ይጮኻሉ።
\v 15 ስለዚህ እግዚአብሔርን በምሥራቅ፣ የእስራኤልንም አምላክ የእግዚአብሔርንም ስም በባሕር ደሴቶች አክብሩ።
\s5
\v 16 "ለጻድቁ ክብር ይሁን!" የሚለውን ዝማሬ ከምድር ዳርቻ ሰምተናል። እኔ ግን፣ "ባከንሁ፣ ባከንሁ፣ ወዮልኝ! ወንጀለኞች ወንጅለዋል፤ አዎን፣ ወንጀለኞች እጅግ ወንጅለዋል" አልሁ።
\s5
\v 17 በምድር ላይ የምትኖር ሆይ፣ ፍርሃትና ገደል ወጥመድም በአንተ ላይ አሉ።
\v 18 ከፍርሃት ድምፅ የሸሸ፣ በገደል ይወድቃል፤ ከገደልም የወጣ በወጥመድ ይያዛል። የሰማይ መስኮቶች ተከፍተዋል፣ የምድርም መሠረት ተናውጣለች።
\s5
\v 19 ምድር ፈጽሞ ትሰባበራለች፣ ምድር ፈጽማ ደቀቀች፤ ምድር በኃይል ትነዋወጣለች።
\v 20 ምድር እንደ ሰካራም ሰው ትንገዳገዳለች፣ እንደ ዳስም ትወዛወዛለች። መተላለፍዋ ይከብድባታል፣ ትወድቃለች ደግማም አትነሣም።
\s5
\v 21 በዚያም ቀን እንደዚህ ይሆናል፤ እግዚአብሔር በከፍታ ያለውን ሠራዊት በከፍታ ላይ፣ በምድርም ያሉትን ነገሥታት በምድር ላይ ይቀጣቸዋል።
\v 22 ግዞተኞች በጕድጓድ እንደሚከማቹ በአንድነት ይከማቻሉ፣ በግዞት ቤትም ውስጥ ተዘግተው ይኖራሉ፣ ከብዙ ቀንም በኋላ ይፈረድባቸዋል።
\v 23 ከዚያም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም ላይ ይነግሣልና፣ በሽማግሌዎቹም ፊት ክብር ይሆናልና ጨረቃ ያፍራል፣ ፀሐይም ይዋረዳል።
\s5
\c 25
\p
\v 1 እግዚአብሔር፣ አንተ አምላኬ ነህ፤ ድንቅን ነገር፣ ከጥንት የታቀዱትን በፍጹም ታማኝነት አድርገሃልና ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፤ ስምህንም አመሰግናለሁ።
\v 2 ከተማይቱን የድንጋይ ክምር፣ የተመሸገችውን ከተማ ውድማ እንድትሆን፣ የኀጥአንንም አዳራሽ ከተማ እንዳትሆን አድርገሃል፤ ከቶ አትሠራም።
\v 3 ስለዚህ ኃያላኑ ወገኖች ያከብሩሃል፤ የጨካኞች አሕዛብ ከተማም ትፈራሃለች።
\s5
\v 4 የጨካኞችም ቍጣ እስትንፋስ ቅጥርን እንደሚመታ ዐውሎ ነፋስ በሆነ ጊዜ፣ ለድሀው መጠጊያ፣ ለችግረኛው በጭንቁ ጊዜ መጠጊያ፣ ከውሽንፍር መሸሸጊያ ከሙቀትም ጥላ ሆነሃል።
\v 5 እንደ በረሃ ሙቀት፣ የኀጥአንን ጩኸት ዝም ታሰኛለህ፤ ሙቀትም በደመና ጥላ እንዲበርድ እንዲሁ የጨካኞች ዝማሬ ይዋረዳል።
\s5
\v 6 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ለሕዝብ ሁሉ በዚህ ተራራ ላይ ታላቅ የሰባ ግብዣ፣ የተመረጠ የወይን ጠጅ፣ ቅልጥም የሞላባቸው የሰቡ ነገሮች፣ የጥሩና ያረጀ የወይን ጠጅ ግብዣ ያደርጋል።
\v 7 በዚህም ተራራ ላይ በወገኖች ሁሉ ላይ የተጣለውን መጋረጃ፣ በአሕዛብም ሁሉ ላይ የተዘረጋውን መሸፈኛ ያጠፋል።
\v 8 ሞትን ለዘላለም ይውጣል፣ ጌታ እግዚአብሔርም ከፊት ሁሉ እንባን ያብሳል፣ የሕዝቡን ስድብ ከምድር ሁሉ ላይ ያስወግዳል፤ እግዚአብሔር ተናግሮአልና።
\s5
\v 9 በዚያም ቀን፣ "ተመልከቱ፣ አምላካችን ይህ ነው፤ ጠብቀነዋል፣ ያድነንማል። እግዚአብሔር ይህ ነው፤ ጠብቀነዋል፤ በማዳኑ ደስ ይለናል ሐሤትም እናደርጋለን" ይባላል።
\v 10 የእግዚአብሔርም እጅ በዚህ ተራራ ላይ ታርፋለች፣ ጭድም በጭቃ ውስጥ እንደሚረገጥ እንዲሁ ሞዓብ በስፍራው ይረገጣል።
\s5
\v 11 ዋናተኛ ለመዋኘት እጁን እንደሚዘረጋ፣ እንዲሁ በመካከሉ እጁን ይዘረጋል፤ ነገር ግን ምንም ያክል እጆቹ ቢወራጭም እግዚአብሔር ትዕቢቱን ያዋርዳል።
\v 12 ከፍ ያሉት የተመሸገው ቅጥርህን እስከ ትቢያ ድረስ ዝቅ ያደርገዋል።
\s5
\c 26
\p
\v 1 በዚያም ቀን ይህ ቅኔ በይሁዳ ምድር ላይ ይዘመራል። የጸናች ከተማ አለችን፤ ለቅጥርና ለምሽግ መድኃኒትን አድርጎባታል።
\v 2 እውነትን የሚጠብቅ ጻድቅ ሕዝብ ይገባ ዘንድ በሮችን ክፈቱ።
\s5
\v 3 በአንተ ታምናለችና በአንተ ለምትጸና አእምሮ ፈጽመህ በሰላም ትጠብቃታለህ።
\v 4 ጌታ እግዚአብሔር የዘላለም ዐለት ነውና ለዘላለም በእግዚአብሔር ታመኑ።
\s5
\v 5 በኩራት የሚኖሩትን ሰዎች ዝቅ ያደርጋል፤ የተመሸገችውን ከተማ ወደ ምድር ያዋርዳል፤ እስከ መሬት ድረስ ያወርዳታል፤ እስከ አፈርም ድረስ ያርዳታል።
\v 6 በድሆች እንዲሁም በችግረኞች ረገጣ የምትረገጥ ትሆናለች።
\s5
\v 7 የጻድቃን መንገድ ደልዳላ ናት፣ አንተ ጻድቅ የሆንህ የጻድቃንን መንገድ ታቃናለህ።
\v 8 አዎን፣ በፍርድህ መንገድ ጠብቀንሃል፤ ስምህም መታሰቢያህም ምኞታችን ነው።
\v 9 ነፍሴ በሌሊት ትናፍቅሃለች፥ መንፈሴም በውስጤ ወደ አንተ ትገሠግሣለች። ፍርድህ ወደምድር በመጣ ጊዜ በዓለም የሚኖሩት ጽድቅን ይማራሉና።
\s5
\v 10 ለኃጢአተኛ ሞገስ ይደረግለት፣ ነገር ግን ጽድቅን አይማርም። በቅኖች ምድር ክፉን ነገር ያደርጋል፤ የእግዚአብሔርንም ግርማ አያይም።
\s5
\v 11 እግዚአብሔር ሆይ፣ እጅህ ከፍ ብላ ተነሣች፣ ነገር ግን አላስተዋሉም። ነገር ግን በሕዝብህ ላይ ያለህን ቅንዓት አይተው ያፍራሉ፤ ምክንያቱም እሳትም ጠላቶችህን ትበላቸዋለች።
\v 12 እግዚአብሔር ሆይ፣ ሥራችንን ሁሉ ሠርተህልናልና ሰላምን ትሰጠናለህ።
\s5
\v 13 አቤቱ አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ፣ ከአንተ በተጨማሪ ሌሎች ጌቶች ገዝተውናል፤ ነገር ግን የአንተን ስም ብቻ እናስባለን።
\v 14 እነርሱ ሞተዋል፣ በሕይወት አይኖሩም፤ ሞተዋል፣ አይነሡም፤ በእርግጥ፣ አንተ በፍርድ መጥተህ አጥፍተሃቸዋል፣ መታሰቢያቸውን ሁሉ እንዲጠፋ አድርገሃል።
\s5
\v 15 እግዚአብሔር ሆይ፣ ሕዝብን አበዛህ፣ ሕዝብን አበዛህ፤ አንተም ተከበርህ፣ የአገሪቱን ዳርቻ ሁሉ አሰፋህ።
\s5
\v 16 እግዚአብሔር ሆይ፣ በመከራ ጊዜ ተመለከቱህ፤ ቅጣትህ በእነርሱ ላይ በሆነ ጊዜ ድግምታቸውን ሳይቀር በክፉው ላይ ተናገሩ።
\v 17 የፀነሰች ሴት ለመውለድ ስትቀርብ እንደምትታመምና በምጥ እንደምትጮኽ፣ አቤቱ፣ እንዲሁ በፊትህ ሆነናል።
\s5
\v 18 እኛ ፀንሰናል፣ ምጥም ይዞናል፣ ነገር ግን ነፋስን እንደምንወልድ ሆነናል፤ ድነትን ወደምድር አላመጣንም፣ በዓለምም የሚኖሩ አልወደቊም።
\s5
\v 19 ሙታንህ ሕያዋን ይሆናሉ፤ ሬሳዎችም ይነሣሉ። በምድር የምትኖሩ ሆይ፣ ጠልህ የመድሃኒት ጠል ነውና፣ ምድርም ሙታንን ታወጣለችና ንቁ ዘምሩም።
\s5
\v 20 ሂድ ሕዝቤ ሆይ፣ ወደ ክፍሎችህ ግባና ደጅህን በኋላህ ዝጋ፤ ቍጣ እስኪያልፍ ድረስ ጥቂት ጊዜ ተሸሸግ።
\v 21 ተመልከት፣ በምድር በሚኖሩት ላይ በበደላቸው ምክንያት ቍጣውን ያመጣባቸው ዘንድ፣ እነሆ፣ እግዚአብሔር ከስፍራው ይወጣል፤ ምድርም ደምዋን ትገልጣለች፣ ሙታኖችዋንም ከእንግዲህ ወዲህ አትከድንም።
\s5
\c 27
\p
\v 1 በዚያም ቀን እግዚአብሔር ፈጣኑን እባብ ሌዋታንን ጠማማውንም እባብ ሌዋታንን በጠንካራ፣ በታላቅ፣ በብርቱም ሰይፍ ይቀጣል፥ በባሕርም ውስጥ ያለውን አውሬ ይገድላል።
\v 2 በዚያም ቀን፣ ለተወደደው የወይን ቦታ ተቀኙለት።
\v 3 "እኔ፣ እግዚአብሔር ጠባቂው ነኝ፤ ሁልጊዜ አጠጣዋለሁ፤ ማንም እንዳይጐዳው በሌሊትና በቀን እጠብቀዋለሁ።
\s5
\v 4 እሾህና ኵርንችት ለሰልፍ በመኖራቸው አልተቈጣሁም! በውጊያ በእነርሱ ላይ ተራምጄ፣ በአንድነት ባቃጠልኋቸው ነበር።
\v 5 ከለላነቴን ካልያዙና ከእኔ ጋር ሰላም ካላደረጉ፣ ከእኔ ጋር ሰላም ያድርጉ።
\s5
\v 6 በሚመጣው ዘመን ያዕቆብ ሥር ይሰድዳል፣ እስራኤልም ያብባል ይጨበጭብማል፤ በፍሬያቸውም የዓለሙን ፊት ይሞላሉ።"
\s5
\v 7 በውኑ የመቱትን እንደ መታ እንዲሁ እርሱን መታውን? ወይስ እነርሱ እንደ ተገደሉበት መገደል ያዕቆብና እስራኤል ተገድሎአልን?
\v 8 ያዕቆብና እስራኤልን ለማባረር በታገልክበት መጠን፣ እርሱ ነዳቸው ሰደዳቸው ቀሠፋቸው፤ የምሥራቅ ነፋስ በሚነፍስበት ቀን በጠንካራ ዐውሎ ነፋስ አስወገዳቸው።
\s5
\v 9 ስለዚህም በዚህ መንገድ፣ የማምለኪያ ዐፀዶችና የፀሐይ ምስሎች ዳግመኛ እንዳይነሡ የመሠዊያውን ድንጋይ ሁሉ እንደ ደቀቀ እንደ ኖራ ድንጋይ ባደረገ ጊዜ፣ እንዲሁ የያዕቆብ በደል ይሰረያል፣ ይህም ከኀጢአት የመመለስ ፍሬ ሁሉ ነው።
\s5
\v 10 የተመሸገችው ከተማ ጠፋች፣ እንደ ምድረ በዳ የተፈታችና የተተወች መኖሪያ ናት። በዚያም ጥጃ ይሰማራል፣ በዚያም ይተኛል ቅርንጫፍዋንም ይበላል።
\v 11 ጫፎችዋ በደረቁ ጊዜ ይሰበራሉ። ሴቶችም መጥተው ያቃጥሉአቸዋል፤ የማያስተውል ሕዝብ ነውና ስለዚህ ፈጣሪው አይራራለትም ሠሪውም ምሕረት አያደርግለትም።
\s5
\v 12 በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ እግዚአብሔር ከኤፍራጥስ ወንዝ ምንጭ ጀምሮ እስከ ግብጽ ወንዝ ድረስ እህሉን ይወቃል፥ እናንተም የእስራኤል ሕዝቦች ሆይ፣ አንድ በአንድ ትሰበሰባላችሁ።
\v 13 በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ታላቅ መለከት ይነፋል፣ በአሦርም የጠፉ፣ በግብጽ ምድርም የተሰደዱ ይመጣሉ፣ በተቀደሰውም ተራራ በኢየሩሳሌም ለእግዚአብሔር ይሰግዳሉ።
\s5
\c 28
\p
\v 1 ለኤፍሬም ሰካሮች ትዕቢት አክሊል፣ በወይን ጠጅ ለተሸነፉ በወፍራም ሸለቆአቸው ራስ ላይ ላለችም ለረገፈች ለክብሩ ጌጥ አበባ ወዮ!
\v 2 እነሆ፣ በጌታ ዘንድ ኃያል ብርቱ የሆነ አለ። እንደ በረዶ ወጨፎ፣ እንደሚያጠፋም ወጀብ፣ እንደሚያጥለቀልቅም እንደ ታላቅ ውኃ ፈሳሽ በጠነከረ እጅ ምድርን ያጠቃል።
\s5
\v 3 የኤፍሬም ሰካሮች ትዕቢት አክሊል በእግር ይረገጣል፤
\v 4 በወፍራሙ ሸለቆ ራስ ላይ ያለች የረገፈች የክብሩ ጌጥ አበባ፣ ከመከር በፊት አስቀድማ እንደምትበስል በለስ ትሆናለች፤ ሰው ባያት ጊዜ በእጁ እንዳለች ይበላታል።
\s5
\v 5 በዚያ ቀን የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ለቀሩት ሕዝቡ የክብር ዘውድና የጌጥ አክሊል ይሆናል፤
\v 6 በፍርድ ወንበር ላይ ለሚቀመጥም የፍርድ መንፈስ፣ ሰልፉን ወደ በር ለሚመልሱም ኃይል ይሆናል።
\s5
\v 7 እነዚህም ደግሞ ከወይን ጠጅ የተነሣ ይስታሉ፤ ከሚያሰክርም መጠጥ የተነሣ ይፋንናሉ። ካህኑና ነቢዩ ከሚያሰክር መጠጥ የተነሣ ይስታሉ፣ በወይን ጠጅም ይዋጣሉ። ከሚያሰክርም መጠጥ የተነሣ ይፋንናሉ፤ በራእይ ይስታሉ፣ በፍርድም ይሰናከላሉ።
\v 8 በእውነት፣ ገበታው ሁሉ ትውከትን ተሞልቷል፤ ንጹሕ ስፍራ እንኳ የለም።
\s5
\v 9 እውቀትን ለማን ያስተምረዋል፣ ወይስ መልእክቱን ለማን ያስረዳል? ወተትን ለተዉ ወይስ ጡትን ለጣሉ ነውን?
\v 10 ትእዛዝ በትእዛዝ ላይ፣ ትእዛዝ በትእዛዝ ላይ፣ ሥርዓት በሥርዓት ላይ፣ ደንብ በደንብ ላይ፣ እዚህ ጥቂት፣ ጥቂት በዚያ ነው።
\s5
\v 11 በእርግጥ፣ በፌዘኛ አፍ በሌሎችም ልሳን ለዚህ ሕዝብ ይናገራል፤
\v 12 "ይህች እረፍት ናት፣ የደከመውን አሳርፉ፤ ይህችም የምታድስ ማረፊያ ናት" አላቸው፤ እነርሱ ግን አልሰሙም።
\s5
\v 13 ስለዚህ ሄደው ወደ ኋላ እንዲወድቁ እንዲሰበሩም ተጠምደውም እንዲያዙ የእግዚአብሔር ቃል ትእዛዝ በትእዛዝ ላይ፣ ትእዛዝ በትእዛዝ ላይ፣ ሥርዓት በሥርዓት ላይ፣ ሥርዓት በሥርዓት ላይ፣ ጥቂት በዚህ ጥቂት በዚያ ይሆንላቸዋል።
\s5
\v 14 ስለዚህ በኢየሩሳሌም ያለውን ይህንን ሕዝብ የምትገዙ ፌዘኞች ሆይ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።
\v 15 እናንተም፣ "ከሞት ጋር ቃል ኪዳን አድርገናል፣ ከሲኦልም ጋር ተማምለናል፤ ስለዚህ ሐሰትን መሸሸጊያችን አድርገናልና፣ በሐሰትም ተሰውረናልና የሚትረፈረፍ መቅሠፍት ባለፈ ጊዜ አይደርስብንም" አላችሁ።
\s5
\v 16 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። "ተመልከቱ፡ በጽዮን የመሠረት ድንጋይን አስቀምጣለሁ፤ የተፈተነውን ድንጋይ፣ የከበረውን፣ መሠረቱ የጸናውን የማዕዘን ድንጋይ። የሚያምን እርሱ አያፍርም።
\s5
\v 17 ለገመድ ፍርድን፣ ለቱንቢም ጽድቅን አደርጋለሁ። በረዶውም የሐሰትን መሸሸጊያ ይጠርጋል፣ ውኆችም መሰወሪያውን ያሰጥማሉ።
\s5
\v 18 ከሞትም ጋር ያደረጋችሁት ቃል ኪዳን ይፈርሳል፣ ከሲኦልም ጋር የተማማላችሁት መሐላ አይጸናም። የሚትረፈረፍ መቅሠፍት ባለፈ ጊዜ ትረገጡበታላችሁ።
\v 19 ባለፈም ጊዜ ይወስዳችኋል፤ ማለዳ ማለዳ ቀንና ሌሊት ያልፋል፤ መልእክቱ በገባቸው ጊዜ ድንጋጤ ይሆናል።
\s5
\v 20 ሰው በእርሱ ላይ ተዘርግቶ ቢተኛ አልጋው አጭር ነው፤ ሰውም ሰውነቱን መሸፈን ቢወድድ ብርድልብሱ እጅግ ጠባብ ነው።"
\v 21 እግዚአብሔርም ሥራውን፣ ማለትም እንግዳ የሆነ ሥራውን ይሠራ ዘንድ፣ አድራጎቱንም ማለት ያልታወቀውን አድራጎቱን ያደርግ ዘንድ በፐራሲም ተራራ እንደ ነበረ ይነሣል፣ በገባዖንም ሸለቆ እንደ ነበረ ይቈጣል።
\s5
\v 22 አሁንም እስራት እንዳይጸንባችሁ አታፊዙ። በምድር ሁሉ ላይ የሚጸናውን የጥፋት ትእዛዝ ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ ሰምቻለሁና።
\s5
\v 23 በትኩረት አድምጡና ድምፄን ስሙ፤ ልብ አድርጉ ንግግሬንም ስሙ።
\v 24 በውኑ ገበሬ ሊዘራ ሁልጊዜ ያርሳልን? ወይስ ሁልጊዜ እርሻውን ይጎለጉላልን?
\s5
\v 25 እርሻውን ባስተካከለ ጊዜ ጥቁሩን አዝሙድ፣ ከሙኑንም፣ ስንዴውንም፣ በተርታ፣ ገብሱንም በስፍራው፣ አጃንም በደረጃው የሚዘራ አይደለምን?
\v 26 አምላኩ ያስታውቀዋል፣ በብልሃት ያስተምረውማል።
\s5
\v 27 በተጨማሪም፣ ጥቁሩ አዝሙድ በተሳለች መሄጃ አያስኬድም፣ የሰረገላም መንኰራኵር በከሙን ላይ አይዞርም፤ ነገር ግን ጥቁሩ አዝሙድ በሽመል ከሙኑም በበትር ይወቃል።
\v 28 የእንጀራ እህል ይደቅቃል፣ ነገር ግን ለዘላለም አያኬደውም፤ የሰረገላውን መንኰራኵርና ፈረሶቹን ምንም ቢያስኬድበት አያደቅቀውም።
\s5
\v 29 ይህም ደግሞ ድንቅ ምክር ከሚመክር በግብሩም ማለፊያ ከሆነው ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ወጥቶአል።
\s5
\c 29
\p
\v 1 ዳዊት ሰፍሮባት ለነበረችው ከተማ ለአርኤል፣ ወዮላት! ዓመት በዓመት ላይ ጨምሩ፣ በዓላትም ተመልሰው ይምጡ።
\v 2 ነገር ግን አርኤልንም እከብባለሁ፣ ለቅሶና ዋይታም ይሆንባታል፤ ለእኔም እንደ አርኤልም ትሆንልኛለች።
\s5
\v 3 በዙሪያሽም እሰፍራለሁ፣ በቅጥርም ከብቤ አስጨንቅሻለሁ፣ አምባም በላይሽ አቆማለሁ።
\v 4 ትዋረጂማለሽ፣ በመሬትም ላይ ሆነሽ ትናገሪያለሽ፣ ቃልሽም ዝቅ ብሎ ከአፈር ይወጣል፤ ድምፅሽም ከመሬት እንደሚወጣ እንደ መናፍስት ጠሪ ድምፅ ይሆናል፣ ቃልሽም ከአፈር ወጥቶ በደካማነት ይጮኻል።
\s5
\v 5 ነገር ግን የጠላቶችሽ ብዛት እንደ ደቀቀ ትቢያ፣ የጨካኞችም ብዛት እንደሚያልፍ ገለባ ይሆናል። በድንገት፣ በፍጥነትም ይሆናል።
\v 6 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በነጐድጓድ፣ በምድርም መናወጥ፣ በታላቅም ድምፅ፣ በዐውሎ ነፋስም፣ በወጨፎም፣ በምትባላም በእሳት ነበልባል ይጐበኛታል።
\s5
\v 7 በአርኤልም ላይ የሚዋጉ፣ እርስዋንና ምሽግዋንም የሚወጉ የሚያስጨንቋትም፣ የአሕዛብ ሁሉ ብዛት እንደ ሕልምና እንደ ሌሊት ራእይ ይሆናል። ሊያስጨንቋት እርሷንና ምሽጎቿን ያጠቃሉ።
\v 8 የተራበ ሰው በሕልሙ ሲበላ እንደሚያይ፣ ነገር ግን ሲነቃ ሆዱ ባዶ እንደሆነው ያክል ነው። የተጠማም ሰው በሕልሙ እየጠጣ እንደሚያይ፣ ነገር ግን ሲነቃ ጥሙ ሳይቆርጥለት ይዝላል። እንዲሁ የጽዮንን ተራራ የሚወጉ የአሕዛብ ሁሉ ብዛት ይሆናል።
\s5
\v 9 ለራሳችሁ ተደነቁ፣ ተገረሙም፤ ራሳችሁን አሳውሩ፣ የታወራችሁ ሁኑ! በወይን ጠጅ አይሁን እንጂ ሰከሩ፤ በሚያሰክር መጠጥ አይሁን እንጂ ተንገደገዱ።
\v 10 እግዚአብሔር የጥልቅ እንቅልፍ መንፈስ አፍስሶባችኋል። ዐይኖቻችሁን አጨፍኗል፣ ራሶቻችሁን ደግሞ ነቢያት አጨፍነውባችኋል።
\s5
\v 11 ራእይ ሁሉ እንደ ታተመ መጽሐፍ ቃል ሆኖባችኋል፤ ማንበብንም ለሚያውቅ። ይህን አንብብ ብለው በሰጡት ጊዜ እርሱ። ታትሞአልና አልችልም ይላቸዋል፤
\v 12 ደግሞም መጽሐፉን ማንበብን ለማያውቅ "ይህን አንብብ" ብለው በሰጡት ጊዜ እርሱ፣ "ማንበብ አልችልም" ይላቸዋል።
\s5
\v 13 ጌታም አለ፣ "ይህ ሕዝብ በአፉ ወደ እኔ ይቀርባልና፣ በከንፈሮቹም ያከብረኛልና፣ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው። የሚያከብሩኝ ሰዎች ባስተማሩት ትእዛዝ ነው።
\v 14 ስለዚህ፣ ተመልከቱ፣ ድንቅ ነገርን በዚህ ሕዝብ መካከል ለማድረግ እቀጥላለሁ፤ ድንቅ ነገርን በድንቅ ነገር ላይ አደርጋለሁ። የጥበበኞቻቸውም ጥበብ ትጠፋለች፣ የአስተዋዮችም ማስተዋል ትሰወራለች።"
\s5
\v 15 ምክራቸውን ጥልቅ አድርገው ከእግዚአብሔር ለሚሰውሩ፣ ሥራቸውንም በጨለማ ውስጥ አድርገው፣ "ማን ያየናል፣ ወይስ ማን ያውቀናል?" ለሚሉ ወዮላቸው!
\s5
\v 16 ነገሮችን ገለባብጣችኋል! የተሠራው ነገር የሠራውን "አልሠራኝም፣" ይለው ዘንድ ሸክላ ሠሪው እንደ ጭቃው ሊቆጠር ይገባልን? ወይስ የተበጀው ነገር ያበጀውን "አታስተውልም" ይለዋልን?
\s5
\v 17 ሊባኖስ እንደ ፍሬያማ እርሻ ሊለወጥ ፍሬያማውም እርሻ እንደ ዱር ሊቈጠር ጥቂት የቀረው አይደለምን?
\v 18 በዚያም ቀን ደንቆሮች የመጽሐፍን ቃል ይሰማሉ፣ የዕውሮችም ዓይኖች ከጭጋግና ከጨለማ ተለይተው ያያሉ።
\v 19 የተጨቆኑ ደስታቸውን በእግዚአብሔር ያበዛሉ፣ በሰዎች መካከል ያሉ ድሆችም ሐሤትን በእስራኤል ቅዱስ ያደርጋሉ።
\s5
\v 20 ጨካኙ ይቋረጣልና፣ ፌዘኛውም ይጠፋልና። ክፋትን ማድረግ የሚወድዱ ይወገዳሉ።
\v 21 እነዚህም ሰውን በነገር በደለኛ የሚያደርጉ። በበርም ለሚገሥጸው ወጥመድ የሚያኖሩ፣ ጻድቁንም በከንቱ ውሸት የሚያስቱ ናቸው።
\s5
\v 22 ስለዚህ አብርሃምን የተቤዠ እግዚአብሔር ስለ ያዕቆብ ቤት እንዲህ ይላል፣ "ያዕቆብ ከእንግዲህ አያፍርም፣ ፊቱም አይገረጣም።
\v 23 ነገር ግን የእጄ ሥራ የሆኑትን ልጆቹን ባያቸው ጊዜ ስሜን ይቀድሳሉ። የያዕቆብንም ቅዱስ ይቀድሳሉ፣ የእስራኤልንም አምላክ ይፈራሉ።
\v 24 በመንፈስም የሳቱ ማስተዋልን ያገኛሉ፣ የሚያጕረመርሙም ትምህርትን ይቀበላሉ።"
\s5
\c 30
\p
\v 1 "ለዓመፀኞች ልጆች ወዮላቸው፣" ይላል እግዚአብሔር። "ከእኔ ዘንድ ያልሆነን ዕቅድ ይመክራሉ፣ ኃጢአትንም በኃጢአት ላይ ይጨምሩ ዘንድ በመንፈሴ ያልተመራውን የትብብር ኪዳን ያደርጋሉ።
\v 2 ከእኔም ምሪትን ሳይጠይቁ ወደ ግብጽ ይሄዱ ዘንድ ይወጣሉ። በፈርዖን ኃይል ይጸኑ ዘንድ በግብጽም ጥላ ይታመኑ ዘንድ ይፈልጋሉ።
\s5
\v 3 ስለዚህ የፈርዖን ከለላ እፍረት፣ በግብጽም ጥላ መታመን ውርደት ይሆንባችኋል።
\v 4 አለቆቻቸው በጣኔዎስ ቢሆኑ እንኳን፣ መልክተኞቻቸውም ወደ ሓኔስ ቢደርሱ እንኳን።
\v 5 ሁላቸው ይጠቅሙአቸው ዘንድ ስለማይችሉ፣ እፍረትና ስድብ እንጂ ረድኤትና ረብ ስለማይሆኑ ሕዝብ ያፍራሉ።
\s5
\v 6 በኔጌቭ ስላሉ አውሬዎች የተነገረ ሸክም፦ ተባትና እንስት አንበሳ እፉኝትም ነዘር እባብም በሚወጡባት በመከራና በጭንቀት ምድር በኩል ብልጥግናቸውን በአህዮች ጫንቃ ላይ መዛግብቶቻቸውንም በግመሎች ሻኛ ላይ እየጫኑ ወደማይጠቅሙአቸው ሕዝብ ይሄዳሉ።
\v 7 የግብጽ እርዳታ ከንቱና ምናምን ነው፤ ስለዚህ ስሙን፣ ተረጋግጦ የሚቀመጥ ረዓብ ብዬ ጠርቼዋለሁ።
\s5
\v 8 አሁንም ሂድ፣ ለሚመጣውም ዘመን ለምስክርነት እንዲሆን በሰሌዳ ላይ በመጽሐፍም ውስጥ ጻፍላቸው።
\v 9 እነዚህ ዓመፀኛ ሕዝብ ናቸውና፣ የእግዚአብሔርን ሕግ ለመስማት የማይወድዱ የሐሰት ልጆች ናቸውና።
\s5
\v 10 ለባለ ራእዮች፣ "አትመልከቱ፤" ይላሉ፣ ለነቢያትም፣ "የለዘበውን ነገር፣ አታላዩን ነገር እንጂ፣ ቀጥተኛውን እውነት አትንገሩን፤
\v 11 ከመንገድ ፈቀቅ በሉ፤ ከጐዳናውም ዘወር በሉ፤ የእስራኤልንም ቅዱስ ከእኛ ዘንድ አስወግዱ" ይሉአቸዋል።
\s5
\v 12 ስለዚህ የእስራኤል ቅዱስ እንዲህ ይላል፣ "ይህችን ቃል አቃልላችሁ፣ በግፍና በጠማምነት ታምናችኋልና፣ በእርሱም ተደግፋችኋልና፣
\v 13 ስለዚህ ይህ በደል አዘብዝቦ ለመፍረስ እንደ ቀረበ፣ አፈራረሱም ፈጥኖ ድንገት እንደሚመጣ እንደ ረጅም ቅጥር ይሆንባችኋል።"
\s5
\v 14 የሸክላ ሠሪ ማድጋ እንደሚሰበር ይሰብረዋል፤ ሳይራራም ያደቅቀዋል፤ ከስባሪውም እሳት ከማንደጃ የሚወስዱበት ወይም ውኃ ከጕድጓድ የሚቀዱበት ገል አይገኝም።
\s5
\v 15 የእስራኤል ቅዱስ፣ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፣ "በመመለስና በማረፍ ትድናላችሁ፤ በጸጥታና በመታመን ኃይል ይሆንላችኋል። እናንተም እንቢ አላችሁ።
\v 16 ነገር ግን፣ 'አይሆንም፣ በፈረስ ላይ ተቀምጠን እንሸሻለን እንጂ እንዲህ አይሆንም' አላችሁ፣ ስለዚህም ትሸሻላችሁ፤ ደግሞም፣ 'በፈጣን ፈረስ ላይ እንቀመጣለን' አላችሁ፣ ስለዚህም የሚያሳድዱአችሁ ፈጣኖች ይሆናሉ።
\s5
\v 17 ከአንድ ሰው ዛቻ የተነሣ ሺህ ሰዎች ይሸሻሉ፤ እናንተም በተራራ ራስ ላይ እንዳለ ምሰሶ፣ በኮረብታም ላይ እንዳለ ምልክት ሆናችሁ እስክትቀሩ ድረስ፣ ከአምስት ሰዎች ዛቻ የተነሣ ትሸሻላችሁ።"
\s5
\v 18 ይሁን እንጂ እግዚአብሔርም የፍርድ አምላክ ነውና ስለዚህ እግዚአብሔር ይራራላችሁ ዘንድ ይታገሣል፣ ይምራችሁም ዘንድ ከፍ ከፍ ይላል፤ እርሱን በመተማመን የሚጠባበቁ ሁሉ ብሩካን ናቸው።
\v 19 በኢየሩሳሌም ውስጥ በጽዮን የምትኖሩ ሕዝብ ሆይ፣ ከእንግዲህ ወዲህ አታለቅሱም፤ በጩኸትም ድምፅ ይራራላችኋል፣ በሰማችሁም ጊዜ ይመልስላችኋል።
\s5
\v 20 ጌታም የጭንቀትን እንጀራና የመከራን ውኃ ቢሰጥህም፣ አስተማሪህ ከእንግዲህ ከአንተ አይሰወርም፣ ነገር ግን አስተማሪህን በገዛ ራስህ ዐይኖች ታያለህ።
\v 21 ወደ ቀኝም ወደ ግራም ብትዞር ከበስተኋላህ ጆሮችህ "መንገዱ ይህች ናት፣ በእርስዋም ሂድ" የሚለውን ቃል ይሰማሉ።
\s5
\v 22 በብርም የተለበጡትን የተቀረጹትን ምስሎችህን በወርቅም የተለበጡትን ቀልጠው የተሠሩትን ምስሎችህን ታረክሳለህ፤ እንደ ርኩስ ጨርቅ ትጥላቸዋለህ። "ከዚህ ውጡ" ትላቸውማለህ።
\s5
\v 23 በምድርም ለተዘራው ዘርህ ዝናብ ይሰጣል፣ ከምድርም ፍሬ የሚወጣ እንጀራ ወፍራምና ብዙ ይሆናል። እህሉም ብዙ ይሆናል። በዚያም ቀን ከብቶችህ በሰፊ መስክ ይግጣሉ።
\v 24 መሬትንም የሚያርሱ በሬዎችና አህዮች በመንሽና በወንፊት የነጻውን ጨው ጨው የሚለውን ገፈራ ይበላሉ።
\s5
\v 25 በታላቅም እልቂት ቀን ግንቦች በወደቁ ጊዜ በረጅሙ ተራራ ሁሉ ከፍ ባለውም ኮረብታ ሁሉ ላይ ወንዞችና የውኃ ፈሳሾች ይሆናሉ።
\v 26 እግዚአብሔርም የሕዝቡን ስብራት በጠገነ ዕለት፣ መቅሰፍቱ ያቈሰለውንም በፈወሰ ዕለት፣ የጨረቃ ብርሃን እንደ ፀሐይ ብርሃን፣ የፀሐይም ብርሃን እንደ ሰባት ቀን ብርሃን ሰባት እጥፍ ይሆናል።
\s5
\v 27 ተመልከቱ፣ የእግዚአብሔር ስም ከሚነድድ ቍጣ ከሚትጐለጐልም ጢስ ጋር ከሩቅ ይመጣል፤ ከንፈሮቹም ቍጣን የተሞሉ ናቸው፣ ምላሱም እንደምትበላ እሳት ናት።
\v 28 እስትንፋሱም አሕዛብን በአጥፊ ወንፊት ሊነፋቸው እንደሚያጥለቀልቅ እስከ አንገትም እንደሚደርስ ወንዝ ነው፣ በሕዝብም መንጋጋ የሚያስት ልጓም ይሆናል።
\s5
\v 29 ዝማሬ በተቀደሰች የዐውደ ዓመት ሌሊት እንደሚሆን ዝማሬ ይሆንላችኋል፤ ወደ እግዚአብሔርም ተራራ ወደ እስራኤል አምባ ይመጣ ዘንድ እንቢልታ ይዞ እንደሚሄድ ሰው የልብ ደስታ ይሆንላችኋል።
\s5
\v 30 እግዚአብሔርም ክቡር ድምፁን ያሰማል፣ የክንዱንም መውረድ በሚነድድ ቍጣውና በምትባላ እሳት ነበልባል፣ በዐውሎ ነፋስም በወጨፎም፣ በበረዶ ጠጠርም ይገልጣል።
\s5
\v 31 አሦርም በበትር ከመታው ከእግዚአብሔር ድምፅ የተነሣ ይደነግጣል።
\v 32 እግዚአብሔር በላዩ በሚያወርድበት የታዘዘበቱ የበትር ድብደባ ሁሉ በከበሮና በመሰንቆ ይሆናል፤ በጦርነትም ክንዱን አንሥቶ ይዋጋቸዋል።
\s5
\v 33 ከጥንት ጀምሮ የማቃጠያ ስፍራ ተዘጋጅታለች። በእርግጥ፣ ለንጉሥም ተበጅታለች፣ እግዚአብሔርም ጥልቅና ሰፊ አድርጎአታል። እሳትና ብዙ ማገዶ ተከምሮአል፤ የእግዚአብሔርም እስትንፋስ እንደ ዲን ፈሳሽ ያቃጥለዋል።
\s5
\c 31
\p
\v 1 ስለ እርዳታ ወደ ግብጽ ለሚወርዱ በፈረሶችም ለሚደገፉ፣ ስለ ብዛታቸውም በሰረገሎች፣ (እጅግ ብርቱዎችም) ስለ ሆኑ፣ በፈረሰኞች ለሚታመኑ (የማይቆጠሩ ስለሆኑ) ፣ ወደ እስራኤልም ቅዱስ ለማይመለከቱ፣ እግዚአብሔርንም ለማይፈልጉ ወዮላቸው!
\v 2 እርሱ ደግሞ ጠቢብ ነው፣ ክፉንም ነገር ያመጣል፣ ቃሉንም አይመልስም። በክፉም አድራጊዎች ቤት ላይ በደልንም በሚሠሩ ረዳት ላይ ይነሣል።
\s5
\v 3 ግብጻውያን ሰዎች እንጂ አምላክ አይደሉም፣ ፈረሶቻቸውም ሥጋ እንጂ መንፈስ አይደሉም። እግዚአብሔርም እጁን በዘረጋ ጊዜ፣ ረጂው ይሰናከላል ተረጂውም ይወድቃል፣ ሁለቱም በአንድ ላይ ይጠፋሉ።
\s5
\v 4 እግዚአብሔር የሚለኝ እንዲህ ነውና፣ "አንበሳ ወይም የአንበሳ ደቦል በንጥቂያው ላይ ሲያገሳ፣ ብዙ እረኞች ቢከማቹበት ከቃላቸው እንደማይፈራ፣ ከድምፃቸውም እንደማይዋረድ፣ እንዲሁ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በጽዮን ተራራና በኮረብታዋ ላይ ይዋጋ ዘንድ ይወርዳል።
\s5
\v 5 እንደሚበርር ወፍ፣ እንዲሁ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን ይጋርዳታል፤ ይከልላታል፥ በላይዋ ሲያልፍ ይታደጋታል ያድናታልም።
\v 6 እናንተ የእስራኤል ልጆች ሆይ፣ አጥብቃችሁ ወደ ዐመፃችሁበት ተመለሱ።
\v 7 በዚያም ቀን እያንዳንዳቸው እጆቻቸው ለኃጢአት የሠሩላቸውን የብሩንና የወርቁን ጣዖቶቻቸውን ይጥላሉና።
\v 8 አሦርም በሰይፍ፣ የሰው ባልሆነ ሰይፍ ይወድቃል፣ የሰውም ያልሆነ ሰይፍ ይበላዋል፤ ከሰይፍም ይሸሻሉ ጐበዛዝቱም ገባሮች ይሆናሉ።
\v 9 አምባው ከፍርሃት የተነሣ ያልፋል፣ መሳፍንቱም ከዓላማው የተነሣ ይደነግጣሉ፤" ይላል እሳቱ በጽዮን፣ እቶኑም በኢየሩሳሌም የሆነ እግዚአብሔር።
\s5
\c 32
\p
\v 1 ተመልከቱ፣ ንጉሥ በጽድቅ ይነግሣል፣ መሳፍንትም በፍርድ ይገዛሉ።
\v 2 ሰውም ከነፋስ እንደ መሸሸጊያ፣ ከዐውሎ ነፋስም እንደ መጠጊያ፣ በጥም ቦታም እንደ ወንዝ ፈሳሽ፣ በበረሃም አገር እንደ ትልቅ ድንጋይ ጥላ ይሆናል።
\v 3 ከዚያም፣ የሚያዩትም ሰዎች ዓይኖች አይደበዝዙም፣ የሚሰሙትም ጆሮች በትኩረት ያደምጣሉ።
\s5
\v 4 ጥንቃቄ የሌላቸው ሰዎች ልብ እውቀትን ታስተውላለች፣ የተብታቦችም ምላስ በቀላሉ አድርጋ ትናገራለች።
\v 5 ከእንግዲህ ወዲህ ሰነፍ ከበርቴ ተብሎ አይጠራም፣ አታላዩም የተገራ አይባልም።
\v 6 ሰነፍ ግን ስንፍናን ይናገራል፣ ልቡም ዝንጉነትን ይፈጽም ዘንድ በእግዚአብሔርም ላይ ስሕተትን ይናገር ዘንድ፣ የተራበችውንም ሰውነት ባዶ ያደርግ ዘንድ፣ ከተጠማም ሰው መጠጥን ይቈርጥ ዘንድ በደልን ይሠራል።
\s5
\v 7 የንፉግም ዕቃ ክፉ ናት። ችግረኛ ትክክል ነገርን በተናገረ ጊዜ እንኳ እርሱ በሐሰት ቃል ድሀውን ያጠፋ ዘንድ ክፉን አሳብ ያስባል።
\v 8 ነገር ግን፣ ከበርቴው ሰው ለመከበር ያስባል፤ በመከበርም ጸንቶ ይኖራል።
\s5
\v 9 እናንተ ዓለመኞች ሴቶች ሆይ፣ ተነሡ፣ ድምፄንም ስሙ፤ እናንተ ተማምናችሁ የምትቀመጡ ሴቶች ልጆች ሆይ፣ ንግግሬን አድምጡ።
\v 10 እናንተ ተማምናችሁ የምትቀመጡ ሴቶች ሆይ፣ ወይንን መሰብሰብ ይቀራልና፣ ፍሬም ማከማቸት አይመጣምና ከዓመትና ከጥቂት ቀን በኋላ ትንቀጠቀጣላችሁ።
\s5
\v 11 እናንተ ዓለመኞች ሴቶች ሆይ፣ ተጠንቀቁ፤ ተማምናችሁም የምትቀመጡ ሆይ፣ ተንቀጥቀጡ፤ የቅምጥል ልብሳችሁን አውልቁ፣ ዕራቁታችሁን ሁኑ፣ ወገባችሁንም በማቅ ታጠቁ።
\v 12 ስለ ተወደደችውም እርሻ፣ ስለሚያፈራውም ወይን ደረታችሁን ድቁ።
\v 13 በሕዝቤ ምድር ላይ፣ በደስታ ከተማ ባሉት በደስታ ቤቶች ሁሉ ላይ እሾህና ኵርንችት ይወጣባቸዋል፤
\s5
\v 14 አዳራሹ ወና ትሆናለችና፣ የብዙ ሰውም ከተማ ትለቅቃለችና፣ አምባውና ግንቡም ለዘላለም ዋሻ፣ የምድረ በዳም አህያ ደስታ፣ የመንጎችም ማሰማርያ ይሆናልና፤
\v 15 ይህም፣ መንፈስ ከላይ እስኪፈስስልን፣ ምድረ በዳውም ፍሬያማ እርሻ እስኪሆን፣ ፍሬያማውም እርሻ ጫካ ተብሎ እስኪቈጠር ድረስ ይሆናል።
\s5
\v 16 ከዚያ በኋላ ፍርድ በምድረ በዳ ይኖራል፤ ጽድቅም በፍሬያማው እርሻ ያድራል።
\v 17 የጽድቅም ሥራ ሰላም፣ የጽድቅም ፍሬ ለዘላለም ጸጥታና መታመን ይሆናል።
\v 18 ሕዝቤም በሰላም ማደሪያ፣ በታመነም ቤት በጸጥተኛ ማረፊያ ይቀመጣል።
\s5
\v 19 በረዶ ግን በዱር ላይ ይወርዳል፣ ከተማም ፈጽማ ትዋረዳለች፣
\v 20 እናንተ የበሬና የአህያ እግር እየነዳችሁ በውኃ ሁሉ አጠገብ የምትዘሩ ትባረካላችሁ።
\s5
\c 33
\p
\v 1 አንተ ሳትጠፋ የምታጠፋ፣ በአንተም ላይ ወንጀል ሳይደረግ ወንጀል የምታደርግ ወዮልህ! ማጥፋትን በተውህ ጊዜ ትጠፋለህ፣ አሳልፎ መስጠትንም በተውህ ጊዜ አሳልፈው ይሰጡሃል።
\s5
\v 2 እግዚአብሔር፣ ማረን፤ አንተን ተማምነናል፤ በየጠዋቱ ክንድ፣ በመከራም ጊዜ ማዳን ሁነን።
\s5
\v 3 ከታላቅ ጫጫታ ወገኖች ሸሹ፣ ስትነሣም አሕዛብ ተበትነዋል።
\v 4 አንበጣ እንደሚሰበስብ፣ ምርኮአችሁ ትሰበሰባለች፣ ኩብኩባም እንደሚዘልል፣ ሰዎች ይዘልሉበታል።
\s5
\v 5 እግዚአብሔር ገነነ። እርሱ በአርያም ይኖራል። ጽዮንን በፍትህና በጽድቅ ሞላት።
\v 6 የዘመንህም ጸጥታ፣ የመድኃኒት ብዛት፣ ጥበብና እውቀት ይሆናል፤ እግዚአብሔርን መፍራት መዝገቡ ነው።
\s5
\v 7 ተመልከቱ፣ ባለሥልጣናቶቻቸው በጎዳና ይጮኻሉ፤ የሰላም መልእክተኞች መራራ ለቅሶ ያለቅሳሉ።
\v 8 መንገዶች ተራቆቱ፣ ተላላፊም ቀረ፤ እርሱም ቃል ኪዳንን አፈረሰ፣ ከተሞችንም ናቀ ሰውንም አልተመለከተም።
\s5
\v 9 ምድሪቱ አለቀሰች ከሳችም፤ ሊባኖስ አፈረ ጠወለገም፤ ሳሮን እንደ ምድረ በዳ ሆነ፤ ባሳንና ቀርሜሎስ ቅጠላቸውን አረገፉ።
\s5
\v 10 "አሁን እነሣለሁ" ይላል እግዚአብሔር፤ "አሁን እከበራለሁ፤ አሁን ከፍ ከፍ እላለሁ።"
\v 11 ገለባን ትፀንሳላችሁ፣ እብቅንም ትወልዳላችሁ፤ እስትንፋሳችሁ የምትበላችሁ እሳት ናት።
\v 12 አሕዛብም እንደ ተቃጠለ ኖራ፣ ተቈርጦም በእሳት እንደ ተቃጠለ እሾህ ይሆናሉ።
\s5
\v 13 እናንተ በሩቅ ያላችሁ፣ የሠራሁትን ስሙ፣ እናንተም በቅርብ ያላችሁ ኃይሌን እወቁ።"
\v 14 በጽዮን ያሉ ኃጢአተኞች ፈሩ፣ መንቀጥቀጥ ዝንጉዎቹን ያዘ፤ ከምትበላ እሳት ጋር መኖርን የሚችል ከእኛ ማን አለ? ለዘላለምም ከምትነድድ እሳት ጋር መኖርን የሚችል ከእኛ ማን አለ?
\s5
\v 15 በጽድቅ የሚሄድ ቅን ነገርንም የሚናገር፤ በሽንገላ የሚገኝ ትርፍን የሚንቅ፥ መማለጃ ጉቦን ከመጨበጥ እጁን የሚያርቅ፣ ደም የማፍሰስ ወንጀልን ከመስማት ጆሮቹን የሚያደነቍር፣ ክፋትንም ከማየት ዓይኖቹን የሚጨፍን ነው።
\v 16 እርሱ ከፍ ባለ ስፍራ ይቀመጣል፣ ጠንካራ አምባ መጠጊያው ይሆናል፣ እንጀራም ይሰጠዋል፣ ውኃውም የታመነች ትሆናለች።
\s5
\v 17 ዓይኖችህ ንጉሥን በውበቱ ያዩታል፤ እነርሱም በሩቅ ያለች ሰፊ ምድርን ያዩአታል።
\v 18 ልብህም፣ ጸሐፊ ወዴት አለ? ገንዘቡንስ መዛኝ ወዴት አለ? ግንቦቹንስ የቈጠረ ወዴት አለ? ብሎ የሚያስፈራ ነገር ያስባል።
\v 19 ጨካኝን ሕዝብ፣ ቋንቋው ለማስተዋል ጥልቅ የሆነውንና አንደበቱ ለማስተዋል ጸያፍ የሆነውን ሕዝብ፣ አታይም።
\s5
\v 20 የበዓላችንን ከተማ ጽዮንን ተመልከት፣ ዓይኖችህ የሰላም ማደሪያ፣ ካስማውም ለዘላለም የማይነቀል፣ አውታሩም ሁሉ የማይበጠስ፣ የማይወገድ ድንኳን የሆነውን ኢየሩሳሌምን ያያሉ።
\v 21 ይልቅ፣ እግዚአብሔር በዚያ የሰፉ ወንዞችና የመስኖች ስፍራ ሆኖ ከእኛ ጋር በግርማ ይሆናል። የሚቀዘፉ መርከቦች አይጓዙባትም፣ ታላላቆችም መርከቦች አያልፉባትም።
\s5
\v 22 እግዚአብሔር ፈራጃችን ነውና፣ እግዚአብሔር ሕግን የሰጠን ነውና፣ እግዚአብሔር ንጉሣችን ነው፤ እርሱ ያድነናል።
\s5
\v 23 ገመዶችህ ላልተዋል፣ ደቀላቸውንም አላጸኑም፣ ሸራውንም መዘርጋት አልቻሉም፤ በዚያም ጊዜ የብዙ ምርኮ ብዝበዛ ተከፈለ፤ አንካሶች እንኳ ብዝበዛውን በዘበዙ።
\v 24 በዚያም የሚኖር፣ "ታምሜአለሁ፣" አይልም፤ በእርስዋም ለሚቀመጡ ሰዎች በደላቸው ይቅር ይባልላቸዋል።
\s5
\c 34
\p
\v 1 እናንተ አሕዛብ ሆይ፣ ቅረቡ፣ ስሙ፤ እናንተ ሕዝቦች ሆይ፣ አድምጡ! ምድርና ሞላዋ፣ ዓለምና ከእርስዋ የሚወጣ ሁሉ ይስሙ።
\v 2 የእግዚአብሔር ቍጣ በአሕዛብ ሁሉ ላይ፣ መዓቱም በሠራዊታቸው ሁሉ ላይ ነው፤ ፈጽሞ አጠፋቸው፣ ለመታረድም አሳልፎ ሰጣቸው።
\s5
\v 3 ከእነርሱም የተገደሉት ይጣላሉ፣ የሬሳቸውም ግማት በሁሉ ቦታ ይሸታል፣ ተራሮችም በደማቸው ይርሳሉ።
\v 4 የሰማይም ሠራዊት ሁሉ ይበሰብሳሉ፣ ሰማያትም እንደ መጽሐፍ ጥቅልል ይጠቀለላሉ፣ ከወይንና ከበለስም ቅጠል እንደሚረግፍ፣ ሠራዊታቸው ሁሉ ይረግፋል።
\s5
\v 5 ሰይፌ በሰማይ ሆና እስክትረካ ድረስ ጠጥታለች፤ ተመልከቱ፣ በኤዶምያስና በረገምሁት ሕዝብ ላይ አሁን ለፍርድ ትወርዳለች።
\v 6 የእግዚአብሔር ሰይፍ በደም ተሞልታለች፣ በስብም፣ በበግ ጠቦትና በፍየል ደምም፣ በአውራም በግ ኵላሊት ስብ ወፍራለች። እግዚአብሔር መሥዋዕት በባሶራ፣ ታላቅም እርድ በኤዶምያስ ምድር አለውና።
\s5
\v 7 ጎሽ ከእነርሱ ጋር፣ ወይፈኖችም ከኮርማዎች ጋር ይወድቃሉ፤ ምድራቸውም በደም ትረካለች፣ አፈራቸውም በስብ ትወፍራለች።
\s5
\v 8 የእግዚአብሔር የበቀሉ ቀን፣ ስለ ጽዮንም ክርክር የብድራት ዓመት ነው።
\v 9 የኤዶምያስም ምንጮች ዝፍት ሆነው ይለወጣሉ፣ አፈርዋም ዲን ይሆናል፣ መሬትዋም የሚቀጠል ዝፍት ትሆናለች።
\v 10 በሌሊትና በቀንም ይቃጠላል፣ ጢስዋም ለዘላለም ይወጣል፤ ከትውልድ እስከ ትውልድም ድረስ ባድማ ሆና ትኖራለች፤ ለዘላለም ዓለም ማንም አያልፍባትም።
\s5
\v 11 ነገር ግን፣ ጭልፊትና ጃርት ግን ይኖሩባታል፤ ጕጕትና ቍራም መረባቸውን ይሠሩባታል። በላይዋም የመፍረስ ገመድና የባዶነት ቱንቢ ይዘረጋባታል።
\v 12 መሳፍንቶችዋን ወደ መንግሥት ይጠራሉ፣ ነገር ግን ማንም አይገኝባትም፤ አለቆችዋም ሁሉ ምናምኖች ይሆናሉ።
\s5
\v 13 በቤተ መንግሥቶቿ እሾህ፣ በቅጥሮችዋም ሳማን፣ አሜከላ ይበቅሉባታል፤ የቀበሮም ማደሪያና የሰጐን ስፍራ ትሆናለች።
\v 14 የምድረ በዳም አራዊት ከተኵሎች ጋር ይገናኛሉ፣ አጋንንትም እርስ በርሳቸው በጩኸት ይጠራራሉ፤ ጅንም በዚያ ትኖራለች ለእርስዋም ማረፊያ ታገኛለች።
\v 15 በዚያም ዋሊያ ቤትዋን ትሠራለች፣ እንቍላልም ትጥላለች ትቀፈቅፈውማለች ልጆችዋንም በጥላዋ ትሰበስባለች፤ በዚያም ደግሞ አሞራዎች እያንዳንዳቸው ከባልንጀሮቻቸው ጋር ይሰበሰባሉ።
\s5
\v 16 በእግዚአብሔር የመጽሐፍ ጥቅልል ውስጥ ፈልጉ፣ አንዳቸውም አይጠፉም። አፌ አዝዞአልና፣ መንፈሱም ሰብስቦአቸዋልና ከእነዚህ አንዲት አትጠፋም፣ ባልንጀራውንም የሚያጣ የለም።
\v 17 እርሱም ዕጣ ጣለባቸው፣ እጁም በገመድ ከፈለችላቸው፤ ለዘላለም ይገዙአታል፣ ከትውልድም እስከ ትውልድ ድረስ ይቀመጡባታል።
\s5
\c 35
\p
\v 1 ምድረ በዳውና ደረቁ ምድር ደስ ይላቸዋል፣ በረሀውም ሐሤት ያደርጋል እንደ ጽጌ ረዳም ያብባል።
\v 2 እጅግ ተትረፍርፎ ያብባል፣ በደስታና በዝማሬ ሐሤትን ያደርጋል፤ የሊባኖስ ክብር፥ የቀርሜሎስና የሳሮን ግርማ ይሰጠዋል፤ የእግዚአብሔርንም ክብር የአምላካችንንም ግርማ ያያሉ።
\s5
\v 3 የደከሙትን እጆች አበርቱ፣ የላሉትንም ጕልበቶች አጽኑ።
\v 4 ፈሪ ልብ ላላቸው፣ "ተመልከቱ፣ አምላካችሁ በበቀል በእግዚአብሔርም ብድራት ይመጣልና፣ መጥቶም ያድናችኋልና በርቱ፣ አትፍሩ" በሉአቸው።
\s5
\v 5 በዚያን ጊዜም የዕውሮች ዓይን ያያል፣ የደንቆሮችም ጆሮ ይሰማል።
\v 6 በዚያን ጊዜ አንካሳ እንደ ሚዳቋ ይዘልላል፣ የድዳም ምላስ ይዘምራል፤ በምድረ በዳ ውኃ፣ በበረሀም ፈሳሽ ይፈልቃልና።
\v 7 ደረቂቱ ምድር ኵሬ፣ የጥማት መሬት የውኃ ምንጭ ትሆናለች፤ ቀበሮ የተኛበት መኖሪያ ልምላሜና ሸምበቆ ደንገልም ይሆንበታል።
\s5
\v 8 በዚያም ጐዳናና መንገድ ይሆናል እርሱም የተቀደሰ መንገድ ይባላል። ንጹሐንም ያልሆኑ አይጓዙበትም። ነገር ግን ለሚጓዙበት ይሆናል፤ ተላላፊዎችና ሰነፎች አይጓዙበትም።
\v 9 አንበሳም አይኖርበትም፣ ነጣቂ አውሬም አይወጣበትም፣ ከዚያም አይገኙም፤ የዳኑት ግን በዚያ ይሄዳሉ፤
\s5
\v 10 እግዚአብሔርም የተቤዣቸው ይመለሳሉ እየዘመሩም ወደ ጽዮን ይመጣሉ፤ የዘላለም ደስታ በራሳቸው ላይ ይሆናል፤ ሐሤትንና ደስታን ያገኛሉ፣ ኀዘንና ትካዜም ይሸሻሉ።
\s5
\c 36
\p
\v 1 እንዲህም ሆነ፣ በንጉሡ ሕዝቅያስ በዐሥራ አራተኛው ዓመት፣ የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም ወደ ይሁዳ ወደ ተመሸጉት ከተሞች ሁሉ ወጥቶ ያዛቸው።
\v 2 ከዚያም፣ የአሦርም ንጉሥ ራፋስቂስን ከብዙ ሠራዊት ጋር ከለኪሶ ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝቅያስ ወደ ኢየሩሳሌም ላከ፣ እርሱም በአጣቢው እርሻ መንገድ ባለችው በላይኛይቱ ኵሬ መስኖ አጠገብ ቆመ።
\v 3 የቤቱም አዛዥ የኬልቅያስ ልጅ ኤልያቄም ጸሐፊውም ሳምናስ ታሪክ ጸሐፊም የአሳፍ ልጅ ዮአስ ወደ እርሱ ወጡ።
\s5
\v 4 ራፋስቂስም እንዲህ አላቸው፣ "ለሕዝቅያስ እንዲህ ብላችሁ ንገሩት፣ ታላቁ የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፣ "ይህ የምትታመንበት መተማመኛ ምንድር ነው?
\v 5 እኔ፣ ለሰልፍ የሆነው ምክርህና ኃያልህ ከንቱ ነገር ነው አልሁ፤ አሁንም በእኔ ላይ ያመፅኸው በማን ተማምነህ ነው?
\s5
\v 6 ተመልከት፣ እየታመንክ ያለኸው በዚህ በተቀጠቀጠ በሸምበቆ በትር በግብጽ ነው። ሰው ቢመረኰዘው ተሰብሮ በእጁ ይገባል ያቈስለውማል። የግብጽ ንጉሥ ፈርዖን ለሚታመኑበት ሁሉ አንዲሁ ነው።
\v 7 አንተም፣ "በአምላካችን በእግዚአብሔር እንታመናለን ብትለኝ፣ ሕዝቅያስ ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን፣ "በዚህ መሠዊያ ፊት ስገዱ" ብሎ የኮረብታ መስገጃዎቹንና መሠዊያዎቹን ይስፈረሰ ይህ አይደለምን?
\s5
\v 8 አሁን እንግዲህ፣ ከጌታዬ ከአሦር ንጉሥ ጋር በመልካም ተደራደር። የሚጋልቡባቸውንም ሰዎች ማግኘት ቢቻልህ እኔ ሁለት ሺህ ፈረሶች እሰጥሃለሁ።
\s5
\v 9 ስለ ሰረገሎችና ስለ ፈረሶኞች በግብጽ ስትታመን፣ ከጌታዬ ባሪያዎች የሚያንሰውን የአንዱን አለቃ ፊት ትቃወም ዘንድ እንዴት ይቻልሃል?
\v 10 አሁንም በውኑ ያለ እግዚአብሔር ትእዛዝ ይህን አገር አጠፋ ዘንድ ወጥቻለሁን? እግዚአብሔር፣ "ወደዚህ አገር ወጥተህ አጥፋው" አለኝ።
\s5
\v 11 ከዚያም ኤልያቄምና ሳምናስ፣ ዮአስም ራፋስቂስን፣ "እኛ እንሰማለንና እባክህ፣ በሶርያ ቋንቋ ለባሪያዎችህ ተናገር፤ በቅጥርም ላይ ባለው ሕዝብ ጆሮ በአይሁድ ቋንቋ አትናገረን" አሉት።
\v 12 ራፋስቂስ ግን፣ "ጌታዬ ይህን ቃል እናገር ዘንድ ወደ አንተና ወደ ጌታህ ልኮኛልን? ከእናንተ ጋር ዐይነምድራቸውን ይበሉ ዘንድ ሽንታቸውንም ይጠጡ ዘንድ በቅጥር ላይ ወደ ተቀመጡት ሰዎች አይደለምን?" አላቸው።
\s5
\v 13 ራፋስቂስም ቆሞ በታላቅ ድምፅ በአይሁድ ቋንቋ እንዲህ ብሎ ጮኸ፣ "የታላቁን የአሦርን ንጉሥ ቃል ስሙ፤
\v 14 ንጉሡ እንዲህ ይላል፣ 'ያድናችሁ ዘንድ አይችልምና ሕዝቅያስ አያታልላችሁ።
\v 15 ሕዝቅያስም፣ "እግዚአብሔር በእርግጥ ያድነናል ይህችም ከተማ በአሦር ንጉሥ እጅ አትሰጥም" ብሎ በእግዚአብሔር እንድትታመኑ አያድርጋችሁ።
\s5
\v 16 ሕዝቅያስንም አትስሙ፣ የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላልና፦ 'ከእኔ ጋር ታረቁ ወደ እኔም ውጡ። እያንዳንዳችሁም ከወይናችሁና ከበለሳችሁ ብሉ፣ ከጕድጓዳችሁም ውኃ ጠጡ።
\v 17 ይህም መጥቼ ምድራችሁን ወደምትመስለው ምድር፣ እህልና የወይን ጠጅ፣ እንጀራና ወይን ወዳለበት ምድር እስካፈልሳችሁ ድረስ ነው።'
\s5
\v 18 ሕዝቅያስም፣ 'እግዚአብሔር ያድነናል' ብሎ እንዳያታልላችሁ ተጠንቀቁ። በውኑ የአሕዛብ አማልክት አገሮቻቸውን ከአሦር ንጉሥ እጅ አድነዋቸዋልን?
\v 19 የሐማትና የአርፋድ አማልክት ወዴት አሉ? የሴፈርዋይም አማልክት ወዴት አሉ? ሰማርያን ከእጄ አድነዋታልን?
\v 20 እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን ከእጄ ያድን ዘንድ ከእነዚህ አገሮች አማልክት ሁሉ አገሩን ከእጄ ያዳነ ማን ነው?"
\s5
\v 21 ነገር ግን ንጉሡ አንዳይመልሱለት አዝዞ ነበርና ሕዝቡ ዝም አሉ፣ አንዳችም አልመለሱለትም።
\v 22 ከዚያም የቤቱ አዛዥ የኬልቅያስ ልጅ ኤልያቄም ጸሐፊውም ሳምናስ ታሪክ ጸሐፊም የአሳፍ ልጅ ዮአስ ልብሳቸውን ቀድደው ወደ ሕዝቅያስ መጡ፣ የራፋስቂስንም ቃል ነገሩት።
\s5
\c 37
\p
\v 1 እንዲህም ሆነ፣ ንጉሡ ሕዝቅያስ ይህን በሰማ ጊዜ ልብሱን ቀደደ፣ ማቅም ለበሰ፣ ወደ እግዚአብሔርም ቤት ገባ።
\v 2 የቤቱንም አዛዥ ኤልያቄምን፣ ጸሐፊውንም ሳምናስን የካህናቱንም ሽማግሌዎች ማቅ ለብሰው ወደ ነቢዩ ወደ አሞጽ ልጅ ወደ ኢሳይያስ ይሄዱ ዘንድ ላካቸው።
\s5
\v 3 እነርሱም፣ "ሕዝቅያስ እንዲህ ይላል፣ 'ይህ ቀን የመከራና የተግሣጽ የዘለፋም ቀን ነው፤ ልጆች የሚወለዱበት ጊዜ ደርሶአል፣ እናታቸው ግን ለመውለድ ኃይል የላትም።
\v 4 ምናልባት በሕያው አምላክ ላይ ይገዳደር ዘንድ ጌታው የአሦር ንጉሥ የላከውን የራፋስቂስን ቃል አምላክህ እግዚአብሔር ይሰማ እንደ ሆነ፣ አምላክህ እግዚአብሔር ስለ ሰማው ቃል ይገሥጸው እንደ ሆነ፣ ስለዚህ አሁን ድረስ እዚህ ላለው ቅሬታ ጸልይ" አሉት።
\s5
\v 5 ስለዚህ የንጉሡ የሕዝቅያስ ባሪያዎች ወደ ኢሳይያስ መጡ፣
\v 6 ኢሳይያስም እንዲህ አላቸው፣ ለጌታችሁ እንዲህ በሉት፦ 'እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ የአሦር ንጉሥ ባሪያዎች ስለ ሰደቡኝ፣ ስለ ሰማኸው ቃል አትፍራ።
\v 7 ተመልከት፣ በላዩ መንፈስን እሰድዳለሁ፣ ወሬንም ይሰማል፣ ወደ ምድሩም ይመለሳል። በምድሩም በሰይፍ እንዲወድቅ አደርጋለሁ" በሉት" አላቸው።
\s5
\v 8 ከዚያም የአሦርም ንጉሥ ከለኪሶ እንደ ራቀ ሰምቶ ነበርና ራፋስቂስ ተመልሶ በልብና ሲዋጋ አገኘው።
\v 9 እርሱም፣ የኢትዮጵያ ንጉሥ ቲርሐቅ እና ግብጽ ሊወጉህ መጥቶአል የሚል ወሬ ሰማ። በሰማም ጊዜ ወደ ሕዝቅያስ መልእክተኞችን ላከ፦
\v 10 እንዲህ ሲል፣ "ለይሁዳ ንጉሠ ለሕዝቅያስ እንዲህ ብላችሁ ንገሩት፣ 'ኢየሩሳሌም በአሦር ንጉሥ እጅ አትሰጥም ብሎ የምትታመንበት አምላክህ አያታልልህ።'
\s5
\v 11 ተመልከት፣ የአሦር ነገሥታት በምድር ሁሉ ላይ ያደረጉትን፣ እንዴትስ ፈጽመው እንዳጠፉአቸው ሰምተሃል። አንተስ ትድናለህን?
\v 12 አባቶቼ ያጠፉአቸውን ጎዛንን፣ ካራንን፣ ራፊስን፣ በተላሳር የነበሩትንም የዔድንን ልጆች የአሕዛብ አማልክት አዳኑአቸውን?
\v 13 የሐማት ንጉሥ፣ የአርፋድ ንጉሥ፣ የሴፈርዋይም ከተማ ንጉሥ፣ የሄናና የዒዋ ንጉሥ ወዴት አሉ?"
\s5
\v 14 ሕዝቅያስም ደብዳቤውን ከመልእክተኞች እጅ ተቀብሎ አነበበው። ሕዝቅያስም ወደ እግዚአብሔር ቤት ወጥቶ በእግዚአብሔር ፊት ዘረጋው።
\v 15 ሕዝቅያስም ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ጸለየ፣
\v 16 "አቤቱ፣ በኪሩቤል ላይ የምትቀመጥ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ ሆይ፣ አንተ ብቻህን የምድር መንግሥታት ሁሉ አምላክ ነህ፤ ሰማይንና ምድርን ፈጥረሃል።
\s5
\v 17 አቤቱ፣ ጆሮህን አዘንብልና ስማ። አቤቱ፣ ዐይኖችህን ክፈትና እይ፤ በሕያው አምላክ ላይ ይገዳደር ዘንድ የላከውን የሰናክሬም ቃል ስማ።
\v 18 አቤቱ፣ በእውነት የአሦር ነገሥታት ዓለሙን ሁሉ አገሮቻቸውንም አፍርሰዋል፣
\s5
\v 19 አማልክቶቻቸውንም በእሳት ላይ ጥለዋል፣ የእንጨትና የድንጋይ የሰው እጅ ሥራ ነበሩ እንጂ አማልክት አልነበሩምና ስለዚህ አጥፍተዋቸዋል።
\v 20 እንግዲህም አምላካችን አቤቱ፣ የምድር መንግሥታት ሁሉ አንተ ብቻ እግዚአብሔር እንደ ሆንህ ያውቁ ዘንድ ከእጁ አድነን።"
\s5
\v 21 ከዚያም የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ እንዲህ ብሎ ወደ ሕዝቅያስ መልእክት ላከ፣ "የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ስለ አሦር ንጉሥ ስለ ሰናክሬም ወደ እኔ ለምነሃልና
\v 22 እግዚአብሔር ስለ እርሱ የተናገረው ቃል ይህ ነው፣ ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ ቀላል ንቃሃለች፣ በንቀትም ስቃብሃለች፤ የኢየሩሳሌም ልጅ ራስዋን ነቅንቃብሃለች።
\v 23 የተገዳደርኸው የሰደብኸውስ ማን ነው? ቃልህንስ ከፍ ከፍ ያደረግህበት ዓይንህንስ ወደ ላይ ያነሣህበት ማን ነው? በእስራኤል ቅዱስ ላይ ነው።
\s5
\v 24 አንተም፣ በሰረገላዬ ብዛት ወደ ተራሮች ከፍታ፣ ወደ ሊባኖስ ጥግ ላይ ወጥቻለሁ፤ ረጃጅሞቹንም ዝግባዎች የተመረጡትንም ጥዶች እቈርጣለሁ፣ ወደ ከፍታውም ዳርቻ ወደ ቀርሜሎስ ዱር እገባለሁ።
\v 25 ቈፈርሁም ውኃም ጠጣሁ የግብጽንም ወንዞች ሁሉ በእግሬ ጫማ አደርቃለሁ ብለህ በባሪያዎችህ እጅ በጌታ ላይ ተገዳደርህ።'
\s5
\v 26 እኔ ጥንቱን እንደ ሠራሁት፣ ቀድሞውንም እንዳደረግሁት አልሰማህምን? አሁንም የተመሸጉትን ከተሞች የፍርስራሽ ክምር እስኪሆኑ ድረስ እንድታፈርስ አደረግሁህ።
\v 27 ስለዚህ የሚኖሩባቸው ሰዎች እጃቸው ዝሎአል፣ ደንግጠውም ታውከዋል። እንደ ምድረ በዳ ሣር፣ እንደ ለመለመም ቡቃያ፣ በሰገነትም ላይ እንዳለ ሣር፣ ሳይሸት ዋግ እንደ መታው እህል ሆነዋል።
\s5
\v 28 ነገር ግን እኔ መቀመጫህንና መውጫህን፣ መግቢያህንም በእኔም ላይ የተቈጣኸውን ቍጣ አውቄአለሁ።
\v 29 ቍጣህና ትዕቢትህ ወደጆሮዬ ደርሶአልና ስለዚህ ስናጋዬን በአፍንጫህ ልጓሜንም በከንፈርህ አደርጋለሁ፣ በመጣህበትም መንገድ እመልስሃለሁ።"
\s5
\v 30 ይህም ምልክት ይሆንሃል፦ በዚህ ዓመት የገቦውን፣ በሁለተኛውም ዓመት ከገቦው የበቀለውን ትበላላችሁ። በሦስተኛውም ዓመት ትዘራላችሁ ታጭዱማላችሁ፣ ወይንም ትተክላላችሁ ፍሬውንም ትበላላችሁ።
\s5
\v 31 ያመለጠው የይሁዳ ቤት ቅሬታ ሥሩን ወደ ታች ይሰድዳል፣ ወደ ላይም ያፈራል።
\v 32 ከኢየሩሳሌም ቅሬታ፣ ከጽዮንም ተራራ ያመለጡት ይወጣሉና።' የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቅንዓት ይህን ያደርጋል።"
\s5
\v 33 ስለዚህም እግዚአብሔር ስለ አሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፣ "ወደዚህች ከተማ አይመጣም፣ ፍላጻንም አይወረውርባትም። በጋሻም አይመጣባትም፣ የአፈርንም ምሽግ አይደለድልባትም።
\v 34 በመጣበት መንገድ በዚያው ይመለሳል፤ ወደዚችም ከተማ አይመጣም፤ ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 35 ስለ እኔም፣ ስለ ባሪያዬም ስለ ዳዊት፣ ይህችን ከተማ አድናት ዘንድ እጋርዳታለሁ።"
\s5
\v 36 የእግዚአብሔርም መልአክ ወጣ፣ ከአሦራውያንም ሰፈር መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ገደለ። ማለዳም በተነሡ ጊዜ፣ እነሆ፣ ሁሉ በየሥፍራው በድኖች ተረፍርፈው ነበሩ።
\v 37 የአሦርም ንጉሥ ሰናክሬም ተነሥቶ ሄደ፣ ተመልሶም በነነዌ ተቀመጠ።
\s5
\v 38 ኋላ ላይ፣ በአምላኩም በናሳራክ ቤት ሲሰግድ፣ ልጆቹ አድራሜሌክና ሳራሳር በሰይፍ ገደሉት። ወደ አራራትም አገር አመለጡ። ልጁም አስራዶን በእርሱ ፋንታ ነገሠ።
\s5
\c 38
\p
\v 1 በዚያም ወራት ሕዝቅያስ ለሞት እስኪደርስ ድረስ ታመመ። ስለዚህ፣ ነቢዩ የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ወደ እርሱ መጥቶ፣ "እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ትሞታለህ እንጂ በሕይወት አትኖርምና ቤትህን አስተካክል' አለው።
\v 2 ከዚያም፣ ሕዝቅያስም ፊቱን ወደ ግድግዳው መልሶ እንዲህ ሲል ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፣
\v 3 "አቤቱ፣ በፊትህ በእውነትና በፍጹም ልብ እንደ ሄድሁ ደስ የሚያሰኝህንም እንዳደረግሁ ታስብ ዘንድ እለምንሃለሁ።" ሕዝቅያስም እየጮኸ አለቀሰ።
\s5
\v 4 ከዚያም የእግዚአብሔርም ቃል ወደ ኢሳይያስ እንዲህ ሲል መጣ፣
\v 5 "ሂድ፣ ሕዝቅያስን እንዲህ በለው፣ 'የአባትህ የዳዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጸሎትህን ሰምቻለሁ፣ እንባህንም አይቻለሁ። ተመልከት፣ በዕድሜህ ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት አጨምራለሁ።
\v 6 አንተንና ይህችንም ከተማ ከአሦር ንጉሥ እጅ እታደጋለሁ፣ ይህችንም ከተማ እጋርዳታለሁ።
\s5
\v 7 እግዚአብሔርም የተገረውን ነገር እንዲፈጽመው ከእግዚአብሔር ዘንድ ምልክቱ ይህ ይሆንልሃል፦
\v 8 ተመልከት፣ በአካዝ የጥላ ስፍረ-ሰዓት ላይ ከፀሐይ ጋር የወረደውን በደረጃዎች ያለውን ጥላ ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ እንዲመለስ አደርጋለሁ።" ስለዚህ ፀሐይም በጥላ ስፍረ-ሰዓት ላይ የወረደበት ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ ተመለሰ።
\s5
\v 9 የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስ ታምሞ ከደዌው በተፈወሰ ጊዜ የጻፈው ጽሕፈት ይህ ነው፦
\v 10 "እኔ፣ በሕይወት ዘመኔ መካከል ወደ ሲኦል በሮች እገባለሁ፤ የቀረው ዘመኔ ጐደለብኝ አልሁ።
\v 11 ደግሞም፣ በሕያዋን ምድር እግዚአብሔርን አላይም፤ በዓለምም ከሚኖሩ ጋር ሰውን እንግዲህ አልመለከትም አልሁ።
\s5
\v 12 ማደሪያዬ ተነቀለች፣ እንደ እረኛ ድንኳንም ከእኔ ዘንድ ተወገደች፤ ሕይወቴንም እንደ ሸማኔ ጠቀለልሁ፤ እርሱም ከመጠቅለያው ይቈርጠኛል፤ ከማለዳም ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ታጠፋኛለህ።
\v 13 እስኪነጋ ድረስ ቈይቼ ነበር፤ እርሱ እንደ አንበሳ አጥንቴን ሁሉ ሰበረ፤ ከማለዳ ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ታጠፋኛለህ።
\s5
\v 14 እንደ ጨረባና እንደ ሽመላ ተንጫጫሁ፣ እንደ ርግብም አጕረመረምሁ፤ ዓይኖቼ ወደ ላይ ከማየት ደከሙ። ጌታ ሆይ፣ ተጨንቄአለሁና መከታ ሁነኝ።
\v 15 ምን እላለሁ? እርሱ ተናግሮኛል፣ እርሱ ራሱም ይህን አድርጎአል፤ በዘመኔ ሁሉ ስለ ነፍሴ ምሬት ቀስ ብዬ እሄዳለሁ።
\s5
\v 16 ጌታ ሆይ፣ የላክኸው መከራ ለእኔ መልካም ነው፤ ሕይወቴ ተመልሶ ይሰጠኝ፤ አንተም ፈወስኸኝ ወደ ሕይወትም መለስኸኝ።
\v 17 ታላቅ ምሬት ለጥቅሜ ሆነ። አንተም ነፍሴን ከጥፋት ጕድጓድ አዳንሃት፤ ኃጢአቴንም ሁሉ ወደ ኋላህ ጥለሃልና።
\s5
\v 18 ሲኦል አያመሰግንህምና፤ ሞትም አያከብርህምና፤ ወደ ጕድጓዱ የሚወርዱ እውነትህን ተስፋ አያደርጉም።
\v 19 እኔ ዛሬ አንደማደርግ ሕያዋን እነርሱ ያመሰግኑሃል፤ አባት ለልጆች እውነትህን ያስታውቃል።
\s5
\v 20 እግዚአብሔር ያድነኛል፣ ስለዚህ በዕድሜያችን ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት ቅኔዎችን አውታር ባለው ዕቃ እንዘምራለን።"
\s5
\v 21 አሁን ኢሳይያስም፣ "የበለስ ጥፍጥፍ አምጥተው በእባጩ ላይ ይለብጡት፣ እርሱም ይፈወሳል" ብሎ ነበር።
\v 22 ሕዝቅያስም፣ "ወደ እግዚአብሔር ቤት እወጣ ዘንድ ምልክቱ ምንድር ነው?" ብሎ ነበር።
\s5
\c 39
\p
\v 1 በዚያ ጊዜ የባቢሎን ንጉሥ የባልዳን ልጅ መሮዳክ ባልዳን፣ ሕዝቅያስ ታምሞ እንደ ተፈወሰ ሰምቶ ነበርና ደብዳቤና እጅ መንሻ ላከለት።
\v 2 ሕዝቅያስም በእነዚህ ነገሮች ደስ አለው፣ ግምጃ ቤቱንም፣ ብሩንና ወርቁንም፣ ቅመሙንና የከበረውንም ዘይት፣ መሣርያም ያለበትን ቤት ሁሉ፣ በቤተ መዛግብቱም የተገኘውን ሁሉ አሳያቸው፤ በቤቱና በግዛቱ ሁሉ ካለው ሕዝቅያስ ያላሳያቸው የለም።
\s5
\v 3 ከዚያም ነቢዩ ኢሳይያስ ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝቅያስ መጥቶ፣ "እነዚህ ሰዎች ምን አሉህ? ከወዴትስ መጡ?" አለው። ሕዝቅያስም፣ "ከሩቅ አገር ከባቢሎን መጡልኝ" አለው።
\v 4 እርሱም፣ "በቤትህ ያዩት ምንድር ነው?" አለው። ሕዝቅያስም፣ "በቤቴ ያለውን ሁሉ አይተዋል፤ በቤተ መዛግብቴ ካለው ያላሳየኋቸው የለም" አለው።
\s5
\v 5 ኢሳይያስም ሕዝቅያስን፣ "የሠራዊትን ጌታ የእግዚአብሔርን ቃል ስማ።
\v 6 'ተመልከት፣ በቤትህ ያለው ሁሉ፣ አባቶችህም እስከ ዛሬ ድረስ ያከማቹት ሁሉ፣ ወደ ባቢሎን የሚፈልስበት ወራት ይመጣል። ምንም አይቀርም፥ ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 7 ከአንተም ከሚወለዱት ልጆችህ ማርከው ይወስዳሉ፤ በባቢሎንም ንጉሥ ቤት ውስጥ ጃንደረቦች ይሆናሉ" አለው።
\v 8 ሕዝቅያስም ኢሳይያስን፣ "የተናገርኸው የእግዚአብሔር ቃል መልካም ነው" አለው። ደግሞም፣ "በዘመኔ ሰላምና እውነት ይሁን" አለ።
\s5
\c 40
\p
\v 1 "አጽናኑ፣ ሕዝቤን አጽናኑ" ይላል አምላካችሁ።
\v 2 ለኢየሩሳሌም ልብ ተናገሩ የተቀጠረችበት ወራት እንደ ተፈጸመ፣ ኃጢአትዋም እንደ ተሰረየ፣ ከእግዚአብሔርም እጅ ስለ ኃጢአትዋ ሁሉ ሁለት እጥፍ እንደ ተቀበለች ወደ እርስዋ ጩኹ።
\s5
\v 3 የሚጮኽ የአዋጅ ነጋሪ ቃል፣ "የእግዚአብሔርን መንገድ በምድረ በዳ አዘጋጁ፤ ለአምላካችንም ጐዳና በበረሀ አስተካክሉ።"
\v 4 ሸለቆው ሁሉ ከፍ ይላል፣ ተራራውና ኮረብታውም ሁሉ ዝቅ ይላል፤ ጠማማውም ይቃናል፣ ስርጓጕጡም ሜዳ ይሆናል፤
\v 5 የእግዚአብሔርም ክብር ይገለጣል፣ ሥጋ ለባሹም ሁሉ በአንድነት ያየዋል፣ የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሮአልና።
\s5
\v 6 አንድ ድምጽ፣ "ጩኽ" ይላል፣ "ምን ብዬ ልጩኽ?" አልሁ። "ሥጋ ለባሽ ሁሉ ሣር ነው፣ ክብሩም ሁሉ እንደ ምድረ በዳ አበባ ነው።
\v 7 የእግዚአብሔር እስትንፋስ ይነፍስበታልና ሣሩ ይደርቃል አበባውም ይረግፋል፤ በእውነት ሕዝቡ ሣር ነው።
\v 8 ሣሩ ይደርቃል፣ አበባውም ይረግፋል፣ የአምላካችን ቃል ግን ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች።"
\s5
\v 9 የምስራች የምትነግሪ ጽዮን ሆይ፣ ከፍ ወዳለው ተራራ ውጪ፣ የምስራች የምትነግሪ ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ድምፅሽን በኃይል አንሺ፣ አንሺ፣ አትፍሪ፤ ለይሁዳም ከተሞች፣ "እነሆ፣ አምላካችሁ!" ብለሽ ንገሪ።
\v 10 ተመልከቱ፣ ጌታ እግዚአብሔር እንደ ኃያል ይመጣል። ክንዱም ስለ እርሱ ይገዛል፤ እነሆ፣ ዋጋው ከእርሱ ጋር ደመወዙም በፊቱ ነው።
\s5
\v 11 መንጋውን እንደ እረኛ ያሰማራል፣ ጠቦቶቹን በክንዱ ሰብስቦ በብብቱ ይሸከማል፣ የሚያጠቡትንም በቀስታ ይመራል።
\s5
\v 12 ውኆችን በእፍኙ የሰፈረ፣ ሰማይንም በስንዝር የለካ፣ የምድርንም አፈር በመስፈሪያ ሰብስቦ የያዘ፣ ተራሮችን በሚዛን ኮረብቶችንም በሚዛኖች የመዘነ ማን ነው?
\s5
\v 13 የእግዚአብሔርን መንፈስ ያዘዘ፣ ወይስ አማካሪ ሆኖ ያስተማረው ማን ነው?
\v 14 ወይስ ከማን ጋር ተመካከረ? ወይስ ማን መከረው? የፍርድንም መንገድ ማን አስተማረው? እውቀትንስ ማን አስተማረው? የማስተዋልንስ መንገድ ማን አሳየው?
\s5
\v 15 ተመልከቱ፣ አሕዛብ በገንቦ እንዳለች ጠብታ ናቸው፣ በሚዛንም እንዳለ ትንሽ ትቢያ ተቈጥረዋል፤ ተመልከቱ፣ ደሴቶችን እንደ ቀላል ነገር ያነሣል።
\v 16 ሊባኖስ ለማንደጃ፣ እንስሶችዋም ለሚቃጠል መሥዋዕት አይበቁም።
\v 17 አሕዛብ ሁሉ በፊቱ እንዳልነበሩ ናቸው፤ ከምናምን እንደሚያንሱ፣ እንደ ከንቱ ነገርም ይቈጥራቸዋል።
\s5
\v 18 እንግዲህ እግዚአብሔርን በማን ትመስሉታላችሁ? ወይስ በምን ምሳሌ ታስተያዩታላችሁ?
\v 19 የተቀረጸውንስ ምስል! ሠራተኛ ሠርቶታል፤ አንጥረኛም በወርቅ ለብጦታል፣ የብሩንም ሰንሠለት አፍስሶለታል።
\v 20 ለዚህ መባዕ ገንዘቡ ያልበቃው ድሀ የማይነቅዘውን እንጨት ይመርጣል፤ ምስሉም እንዳይናወጥ ያቆመው ዘንድ ብልህ ሠራተኛን ይፈልጋል።
\s5
\v 21 አላወቃችሁምን? ወይስ አልሰማችሁምን? ከጥንትስ አልተወራላችሁምን? ወይስ ምድር ከተመሠረተች ጀምሮ አላስተዋላችሁምን?
\v 22 እርሱ በምድር ክበብ ላይ ይቀምጣል፣ በእርስዋም የሚኖሩት እንደ አንበጣ ናቸው፤ ሰማያትን እንደ መጋረጃ የሚዘረጋቸው እንደ ድንኳንም ለመኖርያ የሚዘረጋቸው፥
\s5
\v 23 አለቆችንም እንዳልነበሩ፣ የምድርንም ፈራጆች እንደ ከንቱ ነገር የሚያሳንሳቸው እርሱ ነው።
\v 24 ተመልከቱ፣ ገና እንደ ተተከሉና እንደ ተዘሩ፣ በምድርም ሥር ገና እንደ ሰደዱ ወዲያውኑ ነፈሰባቸው፣ እነርሱም ደረቁ፣ ዐውሎ ነፋስም እንደ እብቅ ጠረጋቸው።
\s5
\v 25 "እንግዲህ እተካከለው ዘንድ በማን መሰላችሁኝ?" ይላል ቅዱሱ።
\v 26 ዓይናችሁን ወደ ላይ አንሥታችሁ ተመልከቱ፤ እነዚህን የፈጠረ ማን ነው? ሠራዊታቸውን በቍጥር የሚያወጣ እርሱ ነው፣ ሁሉንም በየስማቸው ይጠራቸዋል፤ በኃይሉ ብዛትና በችሎቱ ብርታት አንድስ እንኳ አይታጣውም።
\s5
\v 27 ያዕቆብ ሆይ፣ እስራኤልም ሆይ፣ "መንገዴ ከእግዚአብሔር ተሰውራለች፣ ፍርዴም ከአምላኬ አልፋለች" ለምን ትላለህ? ለምንስ እንዲህ ትናገራለህ?
\v 28 አላወቅህምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፣ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው፤ አይደክምም፣ አይታክትም፣ ማስተዋሉም ወሰን የለውም።
\s5
\v 29 ለደካማ ኃይልን ይሰጣል፤ ጕልበት ለሌለውም ብርታትን ይጨምራል።
\v 30 ብላቴኖች ይደክማሉ፣ ይታክቱማል፣ ጐበዛዝቱም ፈጽሞ ይወድቃሉ፤
\v 31 እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፣ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፣ አይደክሙም።
\s5
\c 41
\p
\v 1 "ደሴቶች ሆይ በፊቴ ዝም ብላችሁ አድምጡ፣ አሕዛብም ኃይላቸውን ያድሱ፤ ይቅረቡም በዚያን ጊዜም ይናገሩ፤ ለፍርድ ለአንድነት እንቅረብ።
\v 2 ከምሥራቅ አንዱን ያስነሣ፣ በጽድቅም ወደ አገልግሎቱ የተጠራው ማን ነው? አሕዛብንም አሳልፎ በፊቱ ሰጠው፣ ነገሥታትንም አስገዛለት፤ ለሰይፉ እንደ ትቢያ ለቀስቱም እንደ ተጠረገ እብቅ አድርጎ ሰጣቸው።
\s5
\v 3 አሳደዳቸው፣ እግሮቹም አስቀድመው ባልሄዱባት ፈጣን መንገድ በደኅነት አለፈ።
\v 4 ይህን የሠራና ያደረገ፣ ትውልድንም ከጥንት የጠራ ማን ነው? እኔ፣ እግዚአብሔር፣ ፊተኛው በኋላኞችም ዘንድ የምኖር እኔ ነኝ።
\s5
\v 5 ደሴቶች አይተው ፈሩ፣ የምድርም ዳርቾች ተንቀጠቀጡ፤ ቀረቡም ደረሱም።
\v 6 ሁሉም እያንዳንዱ ባልንጀራውን ይረዳው ነበር፣ ወንድሙንም፣ 'አይዞህ' ይለው ነበር።
\v 7 አናጢውም አንጥረኛውን፣ በመዶሻም የሚያሳሳውን መስፍ መችውን አጽናና፣ ስለ ብየዳ ሥራውም፣ 'መልካም ነው' አለ፤ እንዳይንቀሳቀስም በችንካር አጋጠመው።
\s5
\v 8 አንተ ግን፣ ባሪያዬ እስራኤል፣ የመረጥሁህ ያዕቆብ፣ የወዳጄ የአብርሃም ዘር ሆይ፣
\v 9 አንተ ከምድር ዳርቻ የያዝሁህ፣ ከማዕዘንዋም የጠራሁህና፣ 'አንተ ባሪያዬ ነህ፤' መርጬሃለሁ አልጥልህም ያልሁህ ሆይ።
\s5
\v 10 እኔ ከአንተ ጋር ነኝና፣ አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፣ እረዳህማለሁ፣ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ።
\s5
\v 11 ተመልከት፣ እነሆ የሚቆጡህ ሁሉ ያፍራሉ፣ ይዋረዱማል፤ የሚከራከሩህም እንዳልነበሩ ይሆናሉ፣ ይጠፉማል።
\s5
\v 12 የሚያጣሉህንም ትሻቸዋለህ አታገኛቸውምም፣ የሚዋጉህም እንዳልነበሩና እንደ ምናምን ይሆናሉ።
\v 13 እኔ አምላክህ እግዚአብሔር፣ 'አትፍራ፣ እረዳሃለሁ' ብዬ ቀኝህን እይዛለሁና።
\s5
\v 14 አንተ፣ ትል ያዕቆብ፣ የእስራኤልም ሰዎች ሆይ፣ አትፍሩ፤ እረዳሃለሁ፤" ይላል እግዚአብሔር፣ የሚቤዥህም የእስራኤል ቅዱስ ነው።
\v 15 "ተመልከቱ፣ እንደ ተሳለች እንደ አዲስ ባለ ሁለት ጎን ጥርስ ማሄጃ አድርጌሃለሁ፤ ተራሮችንም ታሄዳለህ ታደቅቃቸውማለህ፣ ኮረብቶችንም እንደ ገለባ ታደርጋቸዋለህ።
\s5
\v 16 ታበጥራቸዋለህ፣ ነፋስም ይጠርጋቸዋል፣ ዐውሎ ነፋስም ይበትናቸዋል። አንተም በእግዚአብሔር ደስ ይልሃል፣ በእስራኤልም ቅዱስ ትመካለህ።
\s5
\v 17 ድሆችና ምስኪኖችም ውኃ ይሻሉ አያገኙምም፣ ምላሳቸውም በጥማት ደርቋል፤ እኔ እግዚአብሔር እሰማቸዋለሁ፣ የእስራኤል አምላክ እኔ አልተዋቸውም።
\v 18 በወናዎቹ ኮረብቶች ላይ ወንዞችን፣ በሸለቆችም መካከል ምንጮችን እከፍታለሁ፤ ምድረ በዳውን ለውኃ መቆሚያ፣ የጥማትንም ምድር ለውኃ መፍለቂያ አደርጋለሁ።
\s5
\v 19 የእግዚአብሔር እጅ ይህን እንደ ሠራች፣ የእስራኤልም ቅዱስ እንደ ፈጠረው ያዩ ዘንድ ያውቁም ዘንድ ያስቡም ዘንድ በአንድነትም ያስተውሉ ዘንድ፣
\v 20 በምድረ በዳ ዝግባውንና ግራሩን ባርሰነቱንና የዘይቱን ዛፍ አበቅላለሁ፣ በበረሀውም ጥዱንና አስታውን ወይራውንም በአንድነት አኖራለሁ።
\s5
\v 21 ክርክራችሁን አቅርቡ፣" ይላል እግዚአብሔር፤ "ማስረጃችሁን አምጡ፣" ይላል የያዕቆብ ንጉሥ።
\v 22 የገዛ ራሳቸውን ሙግት ያምጡ፣ የሚሆነውንም ይንገሩን፤ ልብም እናደርግ ዘንድ ፍጻሜአቸውንም እናውቅ ዘንድ፣ የቀደሙት ነገሮች ምን እንደ ሆኑ ተናገሩ፣ የሚመጡትንም አሳዩን።
\s5
\v 23 አማልክትም መሆናችሁን እናውቅ ዘንድ፣ በኋላ የሚመጡትን ተናገሩ፤ እንደነግጥም ዘንድ በአንድነትም እናይ ዘንድ መልካሙን ወይም ክፉውን አድርጉ።
\v 24 ተመልከቱ፣ እንዳልነበረ ናችሁ፣ ሥራችሁም ከንቱ ነው፤ የሚመርጣችሁም አስጻያፊ ነው።
\s5
\v 25 አንዱን ከሰሜን አነሣሁ፣ እርሱም መጥቶአል፤ አንዱም ከፀሐይ መውጫ ስሜን የሚጠራ ይመጣል፤ በጭቃ ላይ እንደሚመጣ ሰው አፈርም እንደሚረግጥ ሸክለኛ በአለቆች ላይ ይመጣል።
\v 26 እናውቅ ዘንድ ከጥንት የተናገረው። "እውነት ነው" እንልም ዘንድ ቀድሞ የተናገረው ማን ነው? የሚናገር የለም፣ የሚገልጥም የለም፣ ቃላችሁንም የሚሰማ የለም።
\s5
\v 27 በመጀመሪያ ለጽዮን፣ "ተመልከቱ እዚህ ናቸው፤" እላለሁ፤ ለኢየሩሳሌምም የምስራች ነጋሪን እሰጣለሁ።
\v 28 ብመለከት፣ ማንም አልነበረም፤ ብጠይቃቸውም የሚመልስልኝ አማካሪ በመካከላቸው የለም።
\v 29 ተመልከቱ፣ እነርሱ ሁሉ ከንቱዎች ናቸው፣ ሥራቸውም ምንምን ናት፤ ቀልጠው የተሠሩት ምስሎቻቸውም ነፋስና ኢምንት ናቸው።
\s5
\c 42
\p
\v 1 እነሆ፣ ደግፌ የያዝሁት ባሪያዬ፤ ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ምርጤ፤ በእርሱ ላይ መንፈሴን አድርጌአለሁ። እርሱም ለአሕዛብ ፍርድን ያወጣል።
\v 2 አይጮኽም ቃሉንም አያነሣም፣ ድምፁንም በጎዳናዎች አያሰማም።
\s5
\v 3 የተቀጠቀጠን ሸምበቆ አይሰብርም፣ የሚጤስንም ክር አያጠፋም፤ በእውነት ፍርድን ያወጣል።
\v 4 በምድርም ፍትሕን እስኪያደርግ ድረስ ይበራል እንጂ አይጠፋም፤ አሕዛብም ሕጉን ይጠብቃሉ።
\s5
\v 5 ሰማያትን የፈጠረ የዘረጋቸውም፣ ምድርንና በውስጥዋ ያለውን ያጸና፣ በእርስዋ ላይ ለሚኖሩ ሕዝብ እስትንፋስን፣ ለሚሄዱባትም መንፈስን የሚሰጥ አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣
\v 6 "እኔ፣ እግዚአብሔር በጽድቅ ጠርቼሃለሁ፣ እጅህንም እይዛለሁ እጠብቅህማለሁ። እጠብቅሃለሁ፣ ለአሕዛብ ብርሃን እንደሆንክ ሁሉ፣ ለሕዝቡም እንደ ኪዳን አደርግሃለሁ።
\s5
\v 7 የዕውሩንም ዓይን ትከፍት ዘንድ፣ የተጋዘውንም ከግዞት ቤት በጨለማም የተቀመጡትን ከወህኒ ቤት ታወጣ ዘንድ ለሕዝብ ቃል ኪዳን ለአሕዛብም ብርሃን አድርጌ እሰጥሃለሁ።
\s5
\v 8 እኔ እግዚአብሔር ነኝ፣ ስሜ ይህ ነው፤ ክብሬን ለሌላ፣ ምስጋናዬንም ለተቀረጹ ምስሎች አልሰጥም።
\v 9 ተመልከቱ፣ የቀድሞው ነገር ተፈጸመ፣ አዲስ ክስተቶችንም እናገራለሁ። አስቀድሞም ሳይከሰት ስለ እነርሱ አስታውቃችኋለሁ።"
\s5
\v 10 ወደ ባሕር የምትወርዱ በእርስዋም ውስጥ ያላችሁ ሁሉ፣ ደሴቶችና በእነርሱም ላይ የምትኖሩ ሆይ፣ ለእግዚአብሔር አዲስ መዝሙር፣ ከምድርም ዳርቻ ምስጋናውን ዘምሩ።
\v 11 ምድረ በዳውና ከተሞቹ የቄዳርም ሰዎች የሚቀመጡባቸው መንደሮች ድምፃቸውን በደስታ ያንሡ! በሴላ የሚኖሩ እልል ይበሉ፤ በተራሮችም ራስ ላይ ሆነው ይጩኹ።
\s5
\v 12 ለእግዚአብሔር ክብርን ይስጡ፣ ምስጋናውንም በደሴቶች ይናገሩ።
\v 13 እግዚአብሔር እንደ ኃያል ይወጣል፤ እንደ ሰልፈኛም ቅንዓትን ያስነሣል፤ ይጮኻል ድምፁንም ያሰማል፣ በጠላቶቹም ላይ ኃይሉን ያሳያል።
\s5
\v 14 ከድሮ ዘመን ጀምሮ ዝም ብያለሁ፤ ዝም ብዬም ታግሻለሁ፤ አሁን ምጥ እንደ ያዛት ሴት እጮኻለሁ፤ አጠፋለሁ በአንድነትም እጨርሳለሁ።
\v 15 ተራሮችንና ኮረብቶችን አፈርሳለሁ፣ ቡቃያዎቻቸውንም ሁሉ አደርቃለሁ፤ ወንዞችንም ደሴቶች አደርጋለሁ፣ ኵሬዎችንም አደርቃለሁ።
\s5
\v 16 ዕውሮችንም በማያውቋት መንገድ አመጣቸዋለሁ፤ በማያውቋትም ጎዳና እመራቸዋለሁ፤ በፊታቸውም ጨለማውን ብርሃን አደርጋለሁ፣ ጠማማውንም አቀናለሁ። ይህን አደርግላቸዋለሁ፣ አልተዋቸውምም።
\s5
\v 17 በተቀረጹትም ምስሎች የሚታመኑ፣ ቀልጠው የተሠሩትንም ምስሎች፣ "አምላኮቻችን ናችሁ" የሚሉ ወደ ኋላቸው ይመለሳሉ ፈጽመውም ያፍራሉ።
\s5
\v 18 እናንተ ደንቆሮች፣ ስሙ፤ እናንተም ዕውሮች፣ ታዩ ዘንድ ተመልከቱ።
\v 19 ከባሪያዬ በቀር ዕውር ማን ነው? እንደምልከው መልእክተኛዬስ በቀር ደንቆሮ የሆነ ማን ነው? እንደ ፍጹሙ ወይስ እንደ እግዚአብሔር ባሪያ ዕውር የሆነ ማን ነው?
\s5
\v 20 ብዙ ነገርን ታያላችሁ ነገር ግን አትገነዘቡትም፤ ጆሮአችሁም ተከፍተዋል፣ ነገር ግን አትሰሙም።
\v 21 እግዚአብሔር ስለ ጽድቁ ሕጉን ታላቅ ያደርግና ያከብር ዘንድ ወደደ።
\s5
\v 22 ይህ ግን የተበዘበዘና የተዘረፈ ሕዝብ ነው፤ ሁላቸው በዋሻ ውስጥ ተጠምደዋል፣ በግዞት ቤትም ተሸሽገዋል፤ ብዝበዛ ሆነዋል የሚያድንም የለም፣ ምርኮም ሆነዋል፣ ማንም፣ "መልሷቸው!" የሚል የለም።
\s5
\v 23 ከመካከላችሁ ይህን የሚያደምጥ፣ ለሚመጣውም ጊዜ የሚያደምጥና የሚሰማ ማን ነው?
\v 24 ያዕቆብን ለማረኩ እስራኤልንም ለበዘበዙ ሰዎች የሰጠ ማን ነው? እኛ የበደልነው፥ እነርሱም በመንገዱ ይሄዱ ዘንድ ያልወደዱት ለሕጉም ያልታዘዙለት እግዚአብሔር እርሱ አይደለምን?
\s5
\v 25 ስለዚህ፣ የቍጣውን መዓትና የሰልፉን ጽናት አፈሰሰበት። በዙሪያም አነደደው እርሱ ግን አላወቀም፣ አቃጠለውም እርሱ ግን ልብ አላደረገም።
\s5
\c 43
\p
\v 1 አሁንም ያዕቆብ ሆይ፣ የፈጠረህ፣ እስራኤልም ሆይ፣ የሠራህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ተቤዥቼሃለሁና አትፍራ፤ በስምህም ጠርቼሃለሁ፣ አንተ የእኔ ነህ።
\s5
\v 2 በውኃ ውስጥ ባለፍህ ጊዜ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፣ በወንዞችም ውስጥ ባለፍህ ጊዜ አያሰጥሙህም፤ በእሳትም ውስጥ በሄድህ ጊዜ አትቃጠልም፥ ነበልባሉም አይፈጅህም።
\v 3 እኔ የእስራኤል ቅዱስ አምላክህ እግዚአብሔር መድኃኒትህ ነኝ፤ ግብጽን ለአንተ ቤዛ አድርጌ፣ ኢትዮጵያንና ሳባንም ለአንተ ፋንታ ሰጥቻለሁ።
\s5
\v 4 በዓይኔ ፊት የከበርህና የተመሰገንህ ነህና፣ እኔም ወድጄሃለሁና ስለዚህ ሰዎችን ለአንተ አሕዛብንም ለነፍስህ እሰጣለሁ።
\v 5 እኔ ከአንተ ጋር ነኝና፣ አትፍራ፤ ዘርህንም ከምሥራቅ አመጣዋለሁ፣ ከምዕራብም እሰበስብሃለሁ።
\s5
\v 6 ሰሜንን፣ 'መልሰህ አምጣ፣' ደቡብንም፣ 'ማናቸውንም አትከልክል፤' ወንዶች ልጆቼን ከሩቅ፣ ሴቶች ልጆቼንም ከምድር ዳርቻ፣
\v 7 በስሜ የተጠራውን ለክብሬም የፈጠርሁትን፣ የሠራሁትንና ያደረግሁትን ሁሉ አምጣ እለዋለሁ።
\s5
\v 8 ዓይኖች ያሉአቸውን ዕውሮችን ሕዝብ፣ ጆሮችም ያሉአቸውን ደንቆሮቹን አውጣ።
\v 9 አሕዛብ ሁሉ በአንድነት ይሰብሰቡ፣ ወገኖችም ይከማቹ። ከመካከላቸው፤ ይህን የሚናገር፣ የቀድሞዎቹንስ ክስተቶች የሚያሳየን ማን ነው? ይጸድቁ ዘንድ ምስክሮቻቸውን ያምጡ፣ ሰምተውም 'እውነት ነው' ይበሉ።
\s5
\v 10 "ታውቁና ታምኑብኝ ዘንድ፣ እኔም እንደሆንሁ ታስተውሉ ዘንድ፣ እናንተ የመረጥሁትም ባሪያዬ ምስክሮቼ ናችሁ" ይላል እግዚአብሔር። ከእኔ በፊት አምላክ አልተሠራም ከእኔም በኋላ አይሆንም።
\v 11 እኔ፣ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፣ ከእኔ ሌላም የሚያድን የለም።
\s5
\v 12 ተናግሬአለሁ፣ አድኜማለሁ፣ አውጄማለሁ፥ በእናንተም ዘንድ ባዕድ አምላክ አልነበረም። ስለዚህ እናንተ ምስክሮቼ ናችሁ፣" ይላል እግዚአብሔር። "እኔም አምላክ ነኝ።"
\v 13 ከጥንት ጀምሮ እኔ ነኝ፣ ከእጄም የሚያመልጥ የለም፤ እሠራለሁ፣ የሚከለክልስ ማን ነው?"
\s5
\v 14 የእስራኤል ቅዱስ፣ የሚቤዣችሁ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ "ስለ እናንተ ወደ ባቢሎን ሰድጃለሁ፣ ከለዳውያንንም ሁሉ ስደተኞች አድርጌ በሚመኩባቸው መርከቦች አዋርዳቸዋለሁ።
\v 15 ቅዱሳችሁ፣ የእስራኤል ፈጣሪ፣ ንጉሣችሁ፣ እግዚአብሔር እኔ ነኝ።"
\s5
\v 16 እግዚአብሔር የሚለው ይህንን ነው (በባሕር ውስጥ መንገድን በኃይለኛም ውኃ ውስጥ መተላለፊያን ያደርጋል፤
\v 17 እግዚአብሔር ሠረገላውንና ፈረሱን፣ ሠራዊቱንና አርበኛውን ያወጣል። እነርሱ ግን በአንድነት ተኝተዋል፤ መቼም አይነሡም፤ ቀርተዋል፣ እንደ ጥዋፍ ኩስታሪም ጠፍተዋል።)
\s5
\v 18 "የፊተኛውን ነገር አታስተውሉ፣ የጥንቱንም ነገር አታስቡ።
\v 19 ተመልከቱ፣ አዲስ ነገርን አደርጋለሁ፤ እርሱም አሁን ይበቅላል፣ አታዩትምን? በምድረ በዳም መንገድን በበረሀም ወንዞችን አደርጋለሁ።
\s5
\v 20 የምድረ በዳ አራዊት፥ ቀበሮችና ሰጎኖች፥ ያከብሩኛል።
\v 21 ምስጋናዬን እንዲናገሩ ለእኔ የፈጠርሁት ሕዝብ፣ የመረጥሁትን ሕዝቤን አጠጣ ዘንድ በምድረ በዳ ውኃን በበረሀም ወንዞችን ሰጥቻለሁና።
\s5
\v 22 ያዕቆብ ሆይ፣ አንተ ግን አልጠራኸኝም፣ አንተም እስራኤል ሆይ፣ በእኔ ዘንድ ደክመሃል።
\v 23 ለሚቃጠል መሥዋዕት በጎችህን አላቀረብህልኝም፣ በሌላም መሥዋዕትህ አላከበርኸኝም፤ በእህልም ቍርባን አላስቸገርሁህም፣ በዕጣንም አላደከምሁህም።
\s5
\v 24 ጣፋጭ መዐዛ ያለው ዕጣን በገንዘብ አልገዛህልኝም፣ በመሥዋዕትህም ስብ አላጠገብኸኝም፤ ነገር ግን በኃጢአትህ አስቸገርኸኝ፣ በበደልህም አደከምኸኝ።
\s5
\v 25 አዎን፣ መተላለፍህን፣ ስለ እኔ ስል የምደመስስ እኔ ነኝ፤ ኃጢአትህንም ከእንግዲህ አላስብም።
\v 26 የተከሰተውን አሳስበኝ። በአንድነትም ሆነን እንከራከር፤ ስለ ንጹህነትህ እንድትጸድቅ ነገርህን ተናገር።
\s5
\v 27 የመጀመሪያው አባትህ ኃጢአት ሠርቶአል፣ መምህሮችህም በድለውኛል።
\v 28 ስለዚህ የመቅደሱን ቅዱሳን አለቆች አረከስሁ፣ ያዕቆብንም እርግማን፣ እስራኤልንም ስድብ አደረግሁ።"
\s5
\c 44
\p
\v 1 አሁንም ባሪያዬ ያዕቆብ፣ የመረጥሁህም እስራኤል ሆይ፣ ስማ።
\v 2 የፈጠረህ፣ ከማኅፀንም የሠራህ፣ የሚረዳህም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ባሪያዬ ያዕቆብ የመረጥሁህም ይሹሩን ሆይ፣ አትፍራ።
\s5
\v 3 በተጠማ ላይ ውኃን፣ በደረቅም መሬት ላይ ፈሳሾችን አፈስሳለሁና፤ መንፈሴን በዘርህ ላይ፣ በረከቴንም በልጆችህ ላይ አፈስሳለሁ፥
\v 4 በፈሳሾችም አጠገብ እንደሚበቅሉ እንደ አኻያ ዛፎች በሣር መካከል ይበቅላሉ።
\s5
\v 5 ይህ፣ 'እኔ የእግዚአብሔር ነኝ' ይላል፤ ሌላኛውም በያዕቆብ ስም ይጠራል፤ ይህም፣ 'እኔ የእግዚአብሔር ነኝ' ብሎ በእጁ ይጽፋል፣ በእስራኤልም ስም ይጠራል።"
\s5
\v 6 የእስራኤል ንጉሥ እግዚአብሔር የሚለው እንዲህ ነው - የሚቤዥም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "እኔ ፊተኛ ነኝ፣ እኔም ኋለኛ ነኝ፣ ከእኔ ሌላም አምላክ የለም።
\s5
\v 7 እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ይነሣና ይጥራ ይናገርም፤ ከጥንት የፈጠርሁትን ሕዝብ ያዘጋጅልኝ፣ የሚመጣውም ነገር ሳይደርስ ይንገሩኝ።
\s5
\v 8 አትፍሩ አትደንግጡም። ከጥንቱ ጀምሬ አልነገርኋችሁምን? ወይስ አላሳየኋችሁምን? እናንተ ምስክሮቼ ናችሁ፦ ከእኔ ሌላ አምላክ አለን? ሌላ ዐለት የለም፤ ማንንም አላውቅም።"
\s5
\v 9 የተቀረጸውን ምስል የሚሠሩ ሁሉ ከንቱዎች ናቸው፤ የወደዱትም ነገር አይረባቸውም፤ ምስክሮቻቸውም አያዩምና አያውቁም፤ ስለዚህ እንዲያፍሩ ይደረጋሉ።
\v 10 አምላክን የሠራ ወይስ ለምንም የማይረባ ምስልን የቀረጸ ማን ነው?
\s5
\v 11 ተመልከቱ፣ ባልንጀሮቹ ሁሉ ያፍራሉ፤ ሠራተኞቹም ከሰዎች ወገን ብቻ ናቸው። ሁላቸው ተሰብስበው ይቁሙ፤ ይፈራሉ በአንድነትም ያፍራሉ።
\s5
\v 12 ብረት ሠሪ መጥረቢያውን ይሠራል፣ በፍምም ውስጥ ያደርገዋል፣ በመዶሻም መትቶ ቅርጽ ይሰጠዋል። በክንዱም ኃይል ይሠራዋል፣ እርሱም ይራባል፣ ይደክምማል፣ ውኃም አይጠጣም ይታክትማል።
\s5
\v 13 አናጢውም ገመድ ዘርግቶ በበረቅ ይለካዋል፣ በመቅረጫም ይቀርጸዋል። በመለኪያም ይለካዋል። በቤትም ውስጥ ይቀመጥ ዘንድ በሰው አምሳልና በሚስብ የሰው ውበት ያስመስለዋል።
\s5
\v 14 የዝግባን ዛፎች ይቈርጣል፣ የዞጲንና የኮምቦልን ዛፍ ይመርጣል። ከዱር ዛፎችም መካከል ይጠነክር ዘንድ ይተወዋል፤ የጥድንም ዛፍ ይተክላል ዝናብም ያበቅለዋል።
\s5
\v 15 ለሰውም ማገዶ ይሆናል፤ ከእርሱም ወስዶ ይሞቃል፣ አዎን፣ አንድዶ እንጀራ ይጋግርበታል። ከእርሱም አምላክ አበጅቶ ይሰግድለታል፣ የተቀረጸውንም ምስል ሠርቶ በእርሱ ፊት ይንበረከካል።
\v 16 ግማሹን በእሳት ያቃጥላል፣ በዚያ በግማሹ ሥጋ ይበላል። ሥጋም ይጠብስበትና ይጠግባል። ራሱን ያሞቅና፣ "እሰይ ሞቅሁ፣ እሳቱን አይቻለሁ" ይላል።
\s5
\v 17 የቀረውንም እንጨት አምላክ አድርጎ ምስል ይቀርጽበታል፤ በፊቱም ተጐንብሶ ይሰግዳል ወደ እርሱም እየጸለየ፣ "አምላኬ ነህና፣ አድነኝ" ይላል።
\s5
\v 18 አያውቁም፣ አያስቡም፣ እንዳያዩ ዓይኖቻቸውን፣ እንዳያስተውሉ ልቦቻቸውን ታውረዋል።
\s5
\v 19 በልቡም ማንም አያስብም፣ "ግማሽዋን በእሳት አቃጥያለሁ፣ በፍምዋም ላይ እንጀራን ጋግሬአለሁ፣ ሥጋም ጠብሼ በልቻለሁ። የቀረውንም አስጸያፊ ነገር አደርጋለሁን? ለዛፍስ ግንድ እሰግዳለሁን? እንዲልም እውቀትና ማስተዋል የለውም።"
\s5
\v 20 አመድ ይበላል፤ የተታለለ ልብ አስቶታል። ነፍሱን ለማዳን አይችልም፣ ወይም፣ በቀኝ እጄ ሐሰት አለ" አይልም።
\s5
\v 21 ስለ እነዚህ ነገሮች አስብ፣ ያዕቆብ ሆይ፣ አንተም እስራኤል፣ ባሪያዬ ነህና ይህን አስብ፤ እኔ ሠርቼሃለሁ፤ አንተም ባሪያዬ ነህ፤ እስራኤል ሆይ፣ በእኔ ዘንድ ያልተረሳ ትሆናለህ።
\v 22 መተላለፍህን እንደ ደመና፣ ኃጢአትህንም እንደ ጭጋግ ደምስሼአለሁ፤ ተቤዥቼሃለሁና ወደ እኔ ተመለስ።
\s5
\v 23 ሰማያት ሆይ፣ እግዚአብሔር አድርጎታልና ዘምሩ፤ እግዚአብሔር ያዕቆብን ተቤዥቶአልና፣ በእስራኤልም ዘንድ ይከበራልና አንተ የምድር ጥልቅ ሆይ፣ ጩኽ፤ እናንተም ተራሮች፣ አንተም ዱር በአንተም ያለ ዛፍ ሁሉ፣ እልል በሉ።
\s5
\v 24 ከማኅፀን የሠራህ፣ የሚቤዥህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ሁሉን የፈጠርሁ፣ ሰማያትን ለብቻዬ የዘረጋሁ ምድርንም ያጸናሁ እግዚአብሔር እኔ ነኝ፤ ከእኔ ጋር ማን ነበረ?
\v 25 የሐሰተኞችን ምልክት ከንቱ አደርጋለሁ፣ ምዋርተኞችንም አሳብዳለሁ፣ ጥበበኞቹንም ወደ ኋላ እመልሳለሁ፣ እውቀታቸውንም ስንፍና አደርጋለሁ፤
\s5
\v 26 እኔ፣ እግዚአብሔር! የባሪያዬን ቃል አጸናለሁ፣ የመልእክተኞቼንም ምክር እፈጽማለሁ፤ ኢየሩሳሌምን፣ 'የሰው መኖሪያ ትሆኛለሽ፣' የይሁዳንም ከተሞች፣ 'ድጋሚ ትታነጻላችሁ፣ ፍራሾቻችሁንም አቆማለሁ' እላለሁ፤
\v 27 ቀላዩንም፣ 'ደረቅ ሁን፣ ፈሳሾችህንም አደርቃለሁ' እላለሁ፤
\s5
\v 28 ቂሮስንም፣ 'እርሱ እረኛዬ ነው፤ እርሱም ኢየሩሳሌምን፣ - 'ትታነጺያለሽ፣ ቤተ መቅደስም ይመሠረታል' ብሎ ፈቃዴን ሁሉ ይፈጽማል" እላለሁ።
\s5
\c 45
\p
\v 1 እግዚአብሔር ለቀባሁት፣ አሕዛብንም በፊቱ አስገዛ ዘንድ የነገሥታትንም ወገብ እፈታ ዘንድ፣ በሮቹም እንዳይዘጉ መዝጊያዎቹን በፊቱ እከፍት ዘንድ፣ ቀኝ እጁን ለያዝሁት ለቂሮስ እንዲህ ይላል፦
\s5
\v 2 "በፊትህ እሄዳለሁ ተራሮችንም ትክክል አደርጋለሁ፤ የናሱንም ደጆች እሰብራለሁ የብረቱንም መወርወሪያዎች እቈርጣለሁ፤
\v 3 በስምህም የምጠራህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እኔ እንደ ሆንሁ ታውቅ ዘንድ፣ በጨለማ የነበረችውን መዝገብ በስውርም የተደበቀችውን ሀብት እሰጥሃለሁ።
\s5
\v 4 ስለ ባሪያዬ ስለ ያዕቆብ፣ ስለ መረጥሁትም ስለ እስራኤል ብዬ በስምህ ጠርቼሃለሁ፤ በቍልምጫ ስምህ ጠራሁህ፤ አንተ ግን አላወቅኸኝም።
\v 5 እኔ እግዚአብሔር ነኝ፣ ከእኔም ሌላ ማንም የለም፤ ከእኔም በቀር አምላክ የለም፤
\v 6 በፀሐይ መውጫና በምዕራብ ያሉ ከእኔ በቀር ማንም ሌላ እንደሌለ ያውቁ ዘንድ አስታጠቅሁህ፥ አንተ ግን አላወቅኸኝም፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፣ ከእኔም ሌላ ማንም የለም።
\s5
\v 7 ብርሃንን ሠራሁ፣ ጨለማውንም ፈጠርሁ፤ ደኅንነትን እሠራለሁ፣ ክፋትንም እፈጥራለሁ፤ እነዚህን ሁሉ ያደረግሁ እግዚአብሔር እኔ ነኝ።
\v 8 እናንተ ሰማያት ከላይ አንጠባጥቡ፣ ደመናትም ጽድቅን ያዝንቡ! ምድርም ትከፈት መድኃኒትንም ታብቅል፣ ጽድቅም በአንድነት ይብቀል። እኔ እግዚአብሔር ፈጥሬዋለሁ።
\s5
\v 9 ከሠሪው ጋር ለሚከራከር ወዮለት! በምድር ሸክላዎች መካከል ያለ ሸክላ ነው! ጭቃ የሚሠራውን፣ 'ምን ትሠራለህ?' ወይስ 'ሥራህ - እጅ የለውም' ይላልን?
\s5
\v 10 አባቱን፣ 'ምን ወልደሃል?' ወይም ሴትን፣ 'ምን አማጥሽ?' ለሚል ወዮ!
\s5
\v 11 የእስራኤል ቅዱስ፣ ሠሪውም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ስለሚመጣው ነገር ጠይቁኝ፣ ስለ ልጆቼና ስለ እጄ ሥራም እዘዙኝ።'
\s5
\v 12 'እኔ ምድርን ሠርቻለሁ ሰውንም በእርስዋ ላይ ፈጥሬአለሁ። እኔ በእጄ ሰማያትን ዘርግቼአለሁ፣ ሠራዊታቸውንም ሁሉ አዝዣለሁ።
\s5
\v 13 እኔ ቂሮስን በጽድቅ አስነሥቼዋለሁ፣ መንገዱንም ሁሉ አቀናለሁ። እርሱ ከተማዬን ይገነባል፣ በዋጋም ወይም በደመወዝ ሳይሆን ምርኮኞቼን ያወጣል፣" ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
\s5
\v 14 እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፣ "የግብጽ ድካምና የኢትዮጵያ ንግድ ቁመተ ረጅሞችም የሳባ ሰዎች ወደ አንተ ያልፋሉ፤ ለአንተም ይሆናሉ። እጆቻቸውም ታስረው ይከተሉሃል፤ በፊትህም ያልፋሉ፣ ለአንተም እየሰገዱ። 'በእውነት እግዚአብሔር በአንተ አለ፣ ከእርሱም ሌላ አምላክ የለም' ብለው ይለምኑሃል።"
\v 15 የእስራኤል አምላክ መድኃኒት ሆይ፣ በእውነት አንተ ራስህን የምትሰውር አምላክ ነህ።
\s5
\v 16 ሁሉም ያፍራሉ ይዋረዱማል፤ ጣዖታትንም የሚሠሩ በአንድነት ወደ ውርደት ይሄዳሉ።
\v 17 እግዚአብሔር ግን እስራኤልን በዘላለማዊ መድኃኒት ያድነዋል፤ እናንተም ለዘላለም አታፍሩምና አትዋረዱም።
\s5
\v 18 ሰማያትን የፈጠረ እግዚአብሔር፣ እርሱም ምድርን የሠራና ያደረገ ያጸናትም፣ መኖሪያም ልትሆን እንጂ ለከንቱ እንድትሆን ያልፈጠራት አምላክ፣ እንዲህ ይላል፣ "እኔ እግዚአብሔር ነኝ፣ ከእኔም በቀር ሌላ የለም።
\s5
\v 19 በስውር ወይም በጨለማ ምድር ስፍራ አልተናገርሁም፤ ለያዕቆብ ዘር፣ 'በከንቱ ፈልጉኝ አላልሁም!' እኔ እግዚአብሔር ጽድቅን እናገራለሁ፣ ቅንንም አወራለሁ።
\s5
\v 20 እናንተ ከአሕዛብ ወገን ሆናችሁ ያመለጣችሁ ኑ! ተሰብስባችሁ ኑ፣ በአንድነትም ቅረቡ! የተቀረጸውን የምስላቸውን እንጨት የሚሸከሙና ያድን ዘንድ ወደማይችል አምላክ የሚጸልዩ እውቀት የላቸውም።
\s5
\v 21 ይናገሩ ይቅረቡም በአንድነትም ይማከሩ! ከጥንቱ ይህን ያሳየ ከቀድሞስ የተናገረ ማን ነው? ያሳየሁም የተናገርሁም እኔ እግዚአብሔር አይደለሁምን? ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ እኔ ጻድቅ አምላክና መድኃኒት ነኝ፣ ከእኔም በቀር ማንም የለም።
\s5
\v 22 እናንተ የምድር ዳርቻ ሁሉ፣ እኔ አምላክ ነኝና፤ ከእኔም በቀር ሌላ የለምና ወደ እኔ ዘወር በሉ ትድኑማላችሁ።
\v 23 'ቃሌ ከአፌ በጽድቅ ወጥታለች፣ አትመለስም። ጕልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል፣ ምላስም ሁሉ በእኔ ይምላል ብዬ በራሴ ምያለሁ።
\s5
\v 24 ስለ እኔም፣ "በእግዚአብሔር ዘንድ ብቻ ጽድቅና ኃይል አለ፣ ወደ እርሱም ሰዎች ይመጣሉ።" በእርሱም ላይ የተቈጡ ሁሉ ያፍራሉ።
\v 25 የእስራኤልም ዘር ሁሉ በእግዚአብሔር ይጸድቃሉ፤ ይመካሉም ይባላል።
\s5
\c 46
\p
\v 1 ቤል ተዋረደ፣ ናባው ተሰባበረ፤ ጣዖቶቻቸው በእንስሳና በከብት ላይ ተጭነዋል። ሸክሞቻችሁ ለደካማ እንስሳ ከባድ ጭነት ሆነዋል።
\v 2 ተጐነበሱ በአንድነትም ተዋረዱ፤ ሸክሙን ለማዳን አልቻሉም፣ ራሳቸው ግን ተማረኩ።
\s5
\v 3 እናንተ የያዕቆብ ቤት ሆይ፣ የእስራኤልም ቤት ቅሬታ ሁሉ፣ ከሆድ ያነሣኋችሁ ከማኅፀንም የተሸከምኋችሁ፣ ስሙኝ።
\v 4 እስከ ሽምግልና ድረስ እኔ ነኝ፣ እስከ ሽበትም ድረስ እሸከማችኋለሁ፤ እኔ ሠርቻለሁ እኔም አነሣለሁ፤ እኔ እሸከማለሁ እኔም አድናለሁ።
\s5
\v 5 በማን ትመስሉኛላችሁ? ከማንስ ጋር ታስተካክሉኛላችሁ? እንመሳሰል ዘንድ ከማን ጋር ታስተያዩኛላችሁ?
\v 6 ወርቁን ከኮረጆ የሚያፈስሱ ብሩንም በሚዛን የሚመዝኑ እነርሱ አንጥረኛውን ይቀጥራሉ፣ እርሱም አምላክ አድርጎ ይሠራ ዋል፤ ለዚያም ይጐነበሱለታል ይሰግዱለትማል።
\s5
\v 7 በጫንቃቸው ላይ አንሥተው ይሸከሙታል፤ በስፍራውም ያደርጉታል፣ በዚያም ይቆማል፣ ከስፍራውም ፈቀቅ አይልም፤ ሰውም ወደ እርሱ ቢጮኽ አይሰማውም ከመከራውም አያድነውም።
\s5
\v 8 ስለእነዚህ ነገሮች አስቡና አልቅሱ፤ ተላላፊዎች ሆይ፣ ንስሐ ግቡ! ልባችሁንም መልሱ።
\v 9 እኔ አምላክ ነኝና፣ ሌላም የለምና የቀድሞውን የጥንቱን ነገር አስቡ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ እንደ እኔም ያለ ማንም የለም።
\s5
\v 10 በመጀመሪያ መጨረሻውን፣ ከጥንትም ያልተደረገውን ሳይሆን በፊት እነግራለሁ፤ "ምክሬ ትጸናለች፣ ፈቃዴንም ሁሉ እፈጽማለሁ፤" እላለሁ።
\v 11 ከምሥራቅ ነጣቂ ወፍን፣ ከሩቅም አገር ምክሬን የሚያደርገውን ሰው እጠራዋለሁ፤ ተናግሬአለሁ፤ እፈጽማለሁ፤ አስቤአለሁ አደርግማለሁ።
\s5
\v 12 እናንተ ጽድቅን ከማድረግ የራቃችሁ፣ እልከኞች፣ ስሙኝ።
\v 13 ጽድቄን አቀርባለሁ፤ አይርቅም መድኃኒቴም አይዘገይም፤ ከጽዮን ለክብር እንዲሆን መድኃኒትን ለእስራኤል ሰጥቻለሁ።
\s5
\c 47
\p
\v 1 አንቺ ድንግል የባቢሎን ልጅ ሆይ፣ ውረጂ በመሬት ትቢያም ላይ ያለ ዙፋን ተቀመጪ፤ የከለዳውያን ሴት ልጅ ሆይ፤ ከዚህ በኋላ ቅልጣናምና ቅምጥል አትባይምና።
\v 2 ወፍጮ ወስደሽ ዱቄትን ፍጪ፤ መሸፈኛሽን አውጪ፣ ረጅሙንም ልብስሽን አውልቀሽ ጣዪው፤ ባትሽን ግለጪ፣ ወንዙን ተሻገሪ።
\s5
\v 3 ኀፍረተ ሥጋሽ ይገለጣል እፍረትሽም ይታያል፤ አዎን፣ እኔ እበቀላለሁ፥ ለማንም አልራራም።
\v 4 ታዳጊያችን፣ ስሙ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ የእስራኤል ቅዱስ ነው።
\v 5 የከለዳውያን ሴት ልጅ ሆይ፣ ከዚህ በኋላ፣ የመንግሥታት እመቤት አትባይምና ዝም ብለሽ ተቀመጪ ወደ ጨለማም ውስጥ ግቢ።
\s5
\v 6 በሕዝቤ ላይ ተቈጥቼ ነበር፤ ርስቴንም አረከስሁ፣ በእጅሽም አሳልፌ ሰጠኋቸው፤ ለእነርሱ ምንም ምሕረት አላደረግሽም፣ በሽማግሌዎቻቸው ላይ ቀንበርሽን እጅግ አክብደሻል።
\v 7 አንቺም፣ "እኔ ለዘላለም እመቤት እሆናለሁ" ብለሻል፤ ይህንም በልብሽ አላደረግሽም ፍጻሜውንም አላሰብሽም።
\s5
\v 8 አሁንም አንቺ ቅምጥል ተዘልለሽ የምትቀመጪ፣ በልብሽም፣ "እኔ እኖራለሁ፣ ከእኔም በቀር ሌላ የለም፤ መበለትም ሆኜ አልኖርም የወላድ መካንነትንም አላውቅም" የምትዪ ይህን ስሚ፤
\v 9 አሁን ግን በአንድ ቀን እነዚህ ሁለት ነገሮች፦ የወላድ መካንነትና መበለትነት፣ በድንገት ይመጡብሻል፤ ስለ መተቶችሽ ብዛትና ስለ አስማቶችሽ ጽናት ፈጽመው ይመጡብሻል።
\s5
\v 10 በክፋትሽ ታምነሻል፤ "የሚያየኝ የለም" ብለሻል፤ ጥበብሽና እውቀትሽ አታልለውሻል፣ ነገር ግን በልብሽ፣ "እኔ እኖራለሁ፣ ከእኔም በቀር ሌላ የለም።" ብለሻል።
\v 11 ስለዚህ ምክንያት ክፉ ነገር ይመጣብሻል፤ በምዋርትሽም እንዴት እንደምታርቂው አታውቂም። ጉዳት ይውድቅብሻል ታስወግጅውም ዘንድ አይቻልሽም፤ የማትውቂያትም ጕስቍልና ድንገት ትመጣብሻለች።
\s5
\v 12 ምናልባትም መጠቀም ትችዪ ወይም ታስደነግጪ እንደ ሆነ፣ ከአስማቶችሽና ከሕፃንነትሽ ጀምረሽ ከደከምሽበት ከመተቶችሽ ብዛት ጋር ቁሚ።
\v 13 በምክርሽ ብዛት ደክመሻል፤ አሁንም የሰማይን ከዋክብት የሚቈጥሩ፣ ከዋክብትንም የሚመለከቱ፣ በየመባቻውም የሚመጣውን ነገር የሚናገሩ ተነሥተው ከሚመጣብሽ ነገር ያድኑሽ።
\s5
\v 14 ተመልከቱ፣ እንደ እብቅ ይሆናሉ። እሳትም ያቃጥላቸዋል። ሰውነታቸውንም ከነበልባል ኃይል አያድኑም። እርሱም ሰው እንደሚሞቀው ፍም፣ ወይም በፊቱ ሰው እንደሚቀመጥበት እሳት ያለ አይደለም!
\v 15 የደከምሽባቸው ነገሮች እንዲህ ይሆኑብሻል፤ ከሕፃንነትሽ ጀምረው ከአንቺ ጋር ይነግዱ የነበሩ እያንዳንዳቸው ወደ ስፍራቸው ይሄዳሉ፣ የሚያድንሽም የለም።
\s5
\c 48
\p
\v 1 እናንተ በእስራኤል ስም የተጠራችሁ፣ ከይሁዳም ዘር የወጣችሁ፣ በእግዚአብሔር ስም የምትምሉ፣ በእውነት ሳይሆን በጽድቅም ሳይሆን የእስራኤልን አምላክ የምትጠሩ።
\v 2 በቅድስት ከተማ ስም የተጠራችሁ፣ ስሙም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በሚባል በእስራኤል አምላክ የምትደገፉ፤ የያዕቆብ ቤት ሆይ፣ ይህን ስሙ።
\s5
\v 3 የቀድሞውን ነገር ከጥንት ተናግሬአለሁ፣ ከአፌም ወጥቶአል፣ አሳይቼውማለሁ፤ ድንገት አድርጌዋለሁ ተፈጽሞማል።
\v 4 አንተ እልከኛ፣ አንገትህም የብረት ጅማት፣ ግምባርህም ናስ እንደሆነ አውቄአለሁ፤
\v 5 ስለዚህ፣ አንተ፣ 'ጣዖቴ ይህን አድርጎአል፣ የተቀረጸው ምስሌና ቀልጦ የተሠራው ምስሌ ይህን አዘዙኝ' እንዳትል፣ አስቀድሜ ነግሬህ ነበር ሳይሆንም አሳይቼህ ነበር።
\s5
\v 6 ስለ እነዚህ ነገሮች ሰምተሃል፤ ይህን ሁሉ ማረጋገጫ ተመልከት፤ እናንተም የምትናገሩት አይደላችሁምን? የተሰወሩትን ያላወቅሃቸውንም አዲሶች ነገሮችን ከዚህ ጀምሬ አሳይቼሃለሁ።
\v 7 እነርሱም አሁን እንጂ ከጥንት አልተፈጠሩም፤ አንተም፣ እነሆ፣ 'አውቄአቸዋለሁ' እንዳትል ከዛሬ በፊት አልሰማሃቸውም።
\s5
\v 8 አልሰማህም፣ አላወቅህም፣ ጆሮህ ከጥንት አልተከፈተችም። አንተ ፈጽሞ ወንጀለኛ እንደ ሆንህ ከማኅፀንም ጀምረህ ተላላፊ ተብለህ እንደተጠራህ አውቄአለሁና።
\s5
\v 9 ስለ ስሜ ቍጣዬን አዘገያለሁ፣ እንዳላጠፋህም ስለ ምስጋናዬ እታገሣለሁ።
\v 10 ተመልከት፣ አንጥሬሃለሁ፣ ነገር ግን እንደ ብር አይደለም፤ በመከራም እቶን ፈትኜሃለሁ።
\v 11 ስለ እኔ፣ ስለ ራሴ አደርገዋለሁ፣ ስሜ እንዲነቀፍ የምፈቅደው እንዴት ነው? ክብሬንም ለሌላ አልሰጥም።
\s5
\v 12 ያዕቆብ ሆይ፣ የጠራሁህም እስራኤል ሆይ፣ ስማኝ፤ እኔ ነኝ፤ እኔ ፊተኛው ነኝ፣ እኔም ኋለኛው ነኝ።
\v 13 አዎን፣ እጄ ምድርን መሥርታለች፣ ቀኜም ሰማያትን ዘርግታለች፤ በጠራኋቸው ጊዜ በአንድነት ይቆማሉ።
\s5
\v 14 እናንተ ሁሉ፣ በአንድነት ተሰብስባችሁ ስሙ፤ ከእነርሱ ይህን የተናገረ ማን ነው? እግዚአብሔር የወደደው ፈቃዱን በባቢሎን ላይ ያደርጋል፣ ክንዱም በከለዳውያን ላይ ይሆናል።
\v 15 እኔ፣ እኔ ራሴ ተናግሬአለሁ፤ እኔ ጠርቼዋለሁ፤ አምጥቼዋለሁ፥ መንገዱም ትሳካለታለች።
\s5
\v 16 ወደ እኔ ቅረቡ፣ ይህንም ስሙ፤ እኔ ከጥንት ጀምሬ በስውር አልተናገርሁም፤ ከሆነበት ዘመን ጀምሮ እኔ በዚያ ነበርሁ፣ አሁንም ጌታ እግዚአብሔርና መንፈሱ" ልከውኛል።
\s5
\v 17 ታዳጊህ፣ የእስራኤል ቅዱስ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። "እኔ የሚረባህን ነገር የማስተምርህ፣ በምትሄድባትም መንገድ የምመራህ፣ አምላክህ እግዚአብሔር ነኝ።"
\v 18 ትእዛዜን ብትፈጽም ኖሮ፣ ሰላምህ እንደ ወንዝ ጽድቅህም እንደ ባሕር ሞገድ በሆነ ነበር፤
\s5
\v 19 ዘርህም እንደ አሸዋ፣ የሆድህም ትውልድ እንደ ምድር ትቢያ በሆነ ነበር፣ ስሙም ከፊቴ ባልጠፋና ባልፈረሰ ነበር።
\s5
\v 20 ከባቢሎን ውጡ! ከከለዳውያንም ኰብልሉ! በእልልታ ድምፅ ተናገሩ፣ ይህንም ንገሩ፣ እስከ ምድርም ዳርቻ ድረስ አውሩና፣ 'እግዚአብሔር ባሪያውን ያዕቆብን ታድጎታል' በሉ።
\s5
\v 21 በምድረ በዳ በኩል በመራቸው ጊዜ አልተጠሙም፤ ውኃንም ከዓለቱ ውስጥ አፈለቀላቸው፣ ዓለቱንም ሰነጠቀ ውኃውም ፈሰሰ።
\v 22 ለክፉዎች ሰላም የላቸውም" ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\c 49
\p
\v 1 ደሴቶች ሆይ፣ ስሙኝ! እናንተም በሩቅ ያላችሁ አሕዛብ፣ አድምጡ፤ እግዚአብሔር ከማኅፀን በስም ጠርቶኛል፣ ከእናቴም ሆድ ጀምሮ ።
\v 2 አፌንም እንደ ተሳለ ሰይፍ አድርጎአል፣ በእጁ ጥላ ሰውሮኛል፤ እንደ ተሳለ ፍላጻም አድርጎኛል፣ በሰገባውም ውስጥ ሽጎኛል።
\s5
\v 3 እርሱም፣ "እስራኤል ሆይ፣ አንተ ባሪያዬ ነህ፣ በአንተም እከበራለሁ" አለኝ።
\v 4 እኔ ግን፣ በከንቱ ደከምሁ፣ ምንም ጥቅም ለሌለውና ለከንቱ ጕልበቴን ፈጀሁ፤ ፍርዴ ግን በእግዚአብሔር ዘንድ፣ ዋጋዬም በአምላኬ ዘንድ ነው አልሁ።
\s5
\v 5 አሁንም በእግዚአብሔር ዓይን ከብሬአለሁና፣ አምላኬም ጕልበት ሆኖኛልና ያዕቆብን ወደ እርሱ እንድመልስ እስራኤልንም ወደ እርሱ እንድሰበስብ፣ ባሪያ እሆነው ዘንድ ከማኅፀን ጀምሮ የሠራኝ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል።
\v 6 እርሱ እንዲህ ይላል፣ "የያዕቆብን ነገዶች እንድታስነሣ፣ ከእስራኤልም የዳኑትን እንድትመስል፣ ባሪያዬ ትሆን ዘንድ እጅግ ቀላል ነገር ነውና እስከ ምድር ዳር ድረስ መድኃኒት ትሆን ዘንድ ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌ ሰጥቼሃለሁ" ይላል።
\s5
\v 7 የእስራኤል ታዳጊ ቅዱሱም፣ እግዚአብሔር፣ ሰዎች ለሚንቁት ሕዝብም ለሚጠላው ለገዥዎች ባሪያ እንዲህ ይላል፣ "ስለ ታማኙ ስለ እግዚአብሔር፣ ስለ መረጠህም ስለ እስራኤል ቅዱስ ነገሥታት አይተው ይነሣሉ፣ መሳፍንትም አይተው ይሰግዳሉ።"
\s5
\v 8 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "በተወደደ ጊዜ ሰምቼሃለሁ፣ በመዳንም ቀን እረዳሃለሁ፤ እጠብቅህማለሁ፣ ምድርንም ታቀና ዘንድ፣ ውድማ የሆኑትንም ርስቶች ታወርስ ዘንድ፥
\s5
\v 9 የተጋዙትንም፣ 'ውጡ፤' በጨለማም የተቀመጡትን፣ 'ራሳችሁን ግለጡ' ትል ዘንድ ቃል ኪዳን አድርጌ ለሕዝቡ ሰጥቼሃለሁ። በመንገድም ላይ ይሰማራሉ፣ ማሰማርያቸውም በወና ኮረብታ ሁሉ ላይ ይሆናል።
\s5
\v 10 የሚራራላቸውም ይመራቸዋልና፣ በውኃም ምንጮች በኩል ይነዳቸዋልና አይራቡም፣ አይጠሙም፣ ትኩሳት ወይም ፀሐይ አይጐዳቸውም።
\v 11 ተራሮቼንም ሁሉ መንገድ አደርጋለሁ፣ ጎዳኖቼም ከፍ ከፍ ይላሉ።"
\s5
\v 12 ተመልከቱ፣ እነዚህ ከሩቅ፣ አንዳንዶቹም፣ ከሰሜንንና ከምዕራብ፣ እነዚህም፣ ከሲኒም አገር ይመጣሉ።
\v 13 እግዚአብሔር ሕዝቡን አጽናንቶአልና፣ ለችግረኞቹም ራርቶአልና ሰማያት ሆይ፣ ዘምሩ፣ ምድር ሆይ፣ ደስ ይበልሽ ተራሮችም ሆይ፣ እልል በሉ።
\s5
\v 14 ጽዮን ግን፣ "እግዚአብሔር ትቶኛል፣ ጌታም ረስቶኛል" አለች።
\v 15 "በውኑ ሴት ከማኅፀንዋ ለተወለደው ልጅ እስከማትራራ ድረስ ሕፃንዋን ትረሳ ዘንድ ትችላለችን? አዎን፣ እርስዋ ትረሳ ይሆናል፣ እኔ ግን አልረሳሽም።
\s5
\v 16 ተመልከቱ፣ እኔ በእጄ መጻፍ ቀርጬሻለሁ፤ ቅጥሮችሽም ሁልጊዜ በፊቴ አሉ።
\v 17 ልጆችሽ ተመልሰው ይፈጥናሉ፤ ያፈረሱሽና ያወደሙሽ ከአንቺ ዘንድ ይወጣሉ።
\v 18 ዓይንሽን አንሥተሽ ዙሪያሽን ተመልከቺ፤ እነዚህ ሁሉ ተሰብስበው ወደ አንቺ ይመጣሉ። እኔ ሕያው ነኝና እነዚህን ሁሉ እንደ ጌጥ ትለብሻቸዋለሽ፣ እንደ ሙሽራም ትጐናጸፊአቸዋለሽ፣ ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 19 ባድማሽና ውድማሽ ወናም የሆነው ምድርሽ ከሚኖሩብሽ የተሣ ዛሬ ጠባብ ትሆናለችና፣ የዋጡሽም ይርቃሉና።
\v 20 የወላድ መካን ከሆንሽ በኋላ የተወለዱልሽ ልጆችሽ በጆሮሽ፣ 'ስፍራ ጠብቦናልና፣ እንቀመጥ ዘንድ ቦታ አስፊልን' ይላሉ።
\s5
\v 21 አንቺም በልብሽ፣ 'የወላድ መካን ሆኛለሁና፣ እኔም ብቻዬን ተሰድጄአለሁና ተቅበዝበዤ አለሁምና እነዚህን ልጆች ማን ወለደልኝ? እነዚህንስ ማን አሳደጋቸው? እነሆ፣ ብቻዬን ቀርቼ ነበር፤ እነዚህስ ከወዴት መጡ?" ትያለሽ።
\s5
\v 22 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ተመልከቺ፣ እጄን ወደ አሕዛብ አነሣለሁ፣ ዓላማዬንም ወደ ወገኖች አቆማለሁ፤ ወንዶች ልጆችሽንም በብብታቸው ያመጡአቸዋል። ሴቶች ልጆችሽንም በጫንቃቸው ላይ ይሸከሙአቸዋል።
\s5
\v 23 ነገሥታትም አሳዳጊ አባቶችሽ ይሆናሉ፣ እቴጌዎቻቸውም ሞግዚቶችሽ ይሆናሉ፤ ግምባራቸውንም ወደ ምድር ዝቅ አድርገው ይሰግዱልሻል፥ የእግርሽንም ትቢያ ይልሳሉ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ፤ እኔንም በመተማመን የሚጠባበቁ አያፍሩም።"
\s5
\v 24 በውኑ ብዝበዛ ከኃያል እጅ ይወሰዳልን፣ ወይስ የጨካኙ ምርኮኞች ያመልጣሉን?
\v 25 እግዚአብሔር ግን እንዲህ ይላል፣ "አዎን፣ በኃያላን የተማረኩ ይወሰዳሉ፣ የጨካኞችም ብዝበዛ ያመልጣል፤ ከአንቺ ጋር የሚጣሉትን እጣላቸዋለሁ፣ ልጆችሽንም አድናለሁ።
\s5
\v 26 አስጨናቂዎችሽንም ሥጋቸውን አስበላቸዋለሁ፣ እንደ ጣፋጭም ወይን ጠጅ ደማቸውን ጠጥተው ይሰክራሉ፤ ሥጋ ለባሹም ሁሉ እኔ እግዚአብሔር መድኃኒትሽና ታዳጊሽ፣ የያዕቆብ ኃያል እንደ ሆንሁ ያውቃል።"
\s5
\c 50
\p
\v 1 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "እናታችሁን የፈታሁበት የፍችዋ ጽሕፈት የት አለ? ወይስ እናንተን የሸጥሁ ከአበዳሪዎች ለየትኛው ነው? እነሆ፣ ስለ ኃጢአታችሁ ተሽጣችኋል፥ ስለ በደላችሁም እናታችሁ ተፈትታለች።
\s5
\v 2 እኔ በመጣሁ ጊዜ ሰው ስለ ምን አልነበረም? በጠራሁስ ጊዜ የሚመልስ ስለ ምን አልነበረም? መታደግ እንዳትችል እጄ አጭር ሆናለችን? ወይስ ለማዳን ኃይል የለኝምን? እነሆ፣ በገሠጽሁ ጊዜ ባሕርን አደርቃለሁ፤ ወንዞችንም ምድረ በዳ አደርጋቸዋለሁ፤ ውኃም በማጣት ዓሦቻቸው ይገማሉ በጥማትም ይሞታሉ።
\v 3 ሰማያትን ጥቍረት አለብሳቸዋለሁ፣ መጋረጃቸውንም ማቅ አደርጋለሁ።"
\s5
\v 4 የደከመውን በቃል እንዴት እንደምደግፍ አውቅ ዘንድ ጌታ እግዚአብሔር የተማሩትን ምላስ ሰጥቶኛል ማለዳ ማለዳ ያነቃኛል፣ እንደ ተማሪዎችም ትሰማ ዘንድ ጆሮዬን ያነቃቃል።
\s5
\v 5 ጌታ እግዚአብሔር ጆሮዬን ከፍቶአል፣ እኔም ዓመፀኛ አልነበርሁም ወደ ኋላዬም አልተመለስሁም።
\v 6 ጀርባዬን ለገራፊዎች፣ ጕንጬንም ለጠጕር ነጪዎች ሰጠሁ፣ ፊቴንም ከውርደትና ከትፋት አልመለስሁም።
\s5
\v 7 ጌታ እግዚአብሔር ይረዳኛልና፣ ስለዚህ አልተዋረድሁም፤ ስለዚህም ፊቴን እንደ ባልጩት ድንጋይ አድርጌዋለሁ፣ እንዳላፍርም አውቃለሁ።
\s5
\v 8 የሚያጸድቀኝ ቅርብ ነው። ከእኔስ ጋር የሚከራከር ማን ነው? በአንድነት እንቁም፤ የሚከስሰኝ ማን ነው? ወደ እኔ ይቅረብ።
\v 9 ተመልከቱ፣ ጌታ እግዚአብሔር ይረዳኛል። ማን ይፈርድብኛል? ተመልከቱ፣ ሁሉ እንደ ልብስ ያረጃሉ ብልም ይበላቸዋል።
\s5
\v 10 ከእናንተ እግዚአብሔርን የሚፈራ፣ የባሪያውንም ቃል የሚሰማ፣ በጨለማም የሚሄድ፣ ብርሃንም የሌለው፣ ነገር ግን በእግዚአብሔር ስም የሚታመን፣ በአምላኩም የሚደገፍ ማን ነው?
\s5
\v 11 ተመልከቱ፣ እሳት የምታነድዱ የእሳትንም ወላፈን የምትታጠቁ ሁላችሁ፥ በእሳታችሁ ነበልባል ባነደዳችሁትም ወላፈን ሂዱ፤ ይህ ከእጄ ይሆንባችኋል፦ በኀዘን ትተኛላችሁ።
\s5
\c 51
\p
\v 1 እናንተ ጽድቅን የምትከተሉ እግዚአብሔርንም የምትሹ፣ ስሙኝ፤ ከእርሱ የተቈረጣችሁበትን ድንጋይ ከእርሱም የተቈፈራችሁበትን ጕድጓድ ተመልከቱ።
\s5
\v 2 ወደ አባታችሁ ወደ አብርሃም፣ ወደ ወለደቻችሁም ወደ ሳራ ተመልከቱ፤ አንድ ብቻውን በሆነ ጊዜ ጠራሁት፣ ባረክሁትም አበዛሁትም።
\s5
\v 3 አዎን፣ እግዚአብሔር ጽዮንን ያጽናናል፤ በእርስዋም ባድማ የሆነውን ሁሉ ያጽናናል፤ ምድረ በዳዋንም እንደ ዔደን፣ በረሀዋንም እንደ እግዚአብሔር ገነት ያደርጋል፤ ደስታና ተድላ ምስጋናና የዝማሬ ድምፅ ይገኝበታል።
\s5
\v 4 ወገኔ ሆይ፣ አድምጠኝ፤ ሕዝቤ ሆይ፣ ስማኝ! ሕግ ከእኔ ይወጣልና፣ ፍርዴም ለአሕዛብ ብርሃን ይሆናልና።
\v 5 ጽድቄ ፈጥኖ ቀርቦአል፣ ማዳኔም ወጥቶአል፣ ክንዴም በአሕዛብ ላይ ይፈርዳል፤ ደሴቶች እኔን በመተማመን ይጠባበቃሉ፣ በክንዴም ይታመናሉ።
\s5
\v 6 ዓይናችሁን ወደ ሰማይ አንሡ፣ ወደ ታችም ወደ ምድር ተመልከቱ፤ ሰማያት እንደ ጢስ በንነው ይጠፋሉ፣ ምድርም እንደ ልብስ ታረጃለች፣ የሚኖሩባትም እንዲሁ ይሞታሉ። ማዳኔ ግን ለዘላለም ይሆናል፣ ጽድቄም አይፈርስም።
\s5
\v 7 ጽድቅን የምታውቁ ሕጌም በልባችሁ ያለ ሕዝብ ሆይ፣ ስሙኝ፤ የሰውን ተግዳሮት አትፍሩ፣ በስድባቸውም አትደንግጡ።
\v 8 እንደ ልብስም ብል ይበላቸዋል፣ እንደ በግ ጠጕርም ትል ይበላቸዋል፤ ጽድቄ ግን ለዘላለም ማዳኔም ለትውልድ ሁሉ ይሆናል።"
\s5
\v 9 የእግዚአብሔር ክንድ ሆይ፣ ተነሥ፣ ተነሥ፣ ኃይልንም ልበስ። በቀድሞው ወራትና በጥንቱ ዘመን በነበረው ትውልድ እንደ ሆነው ተነሥ። ረዓብን የቈራረጥህ ዘንዶውንም የወጋህ አንተ አይደለህምን?
\v 10 ባሕሩንና የታላቁን ጥልቅ ውኃ ያደረቅኸው፣ የዳኑትም ይሻገሩ ዘንድ ጠሊቁን ባሕር መንገድ ያደረግህ አንተ አይደለህምን?
\s5
\v 11 እግዚአብሔርም የተቤዣቸው ይመለሳሉ ወደ ጽዮንም ይመጣሉ፤ የዘላለምም ደስታ በራሳቸው ላይ ይሆናል፤ ደስታንና ተድላን ያገኛሉ፣ ኀዘንና ልቅሶም ይሸሻል።
\s5
\v 12 "እኔ፣ የማጽናናችሁ እኔ ነኝ፣ እኔ ነኝ፤ የሚሞተውን ሰው እንደ ሣርም የሚጠወልገውን የሰው ልጅ ትፈራ ዘንድ አንተ ማን ነህ?
\s5
\v 13 ሰማያትንም የዘረጋው ምድርንም የመሠረተውን ፈጣሪህን እግዚአብሔርን ረስተሃል፤ ያጠፋ ዘንድ ባዘጋጀ ጊዜ ከአስጨናቂው ቍጣ የተነሣ ሁልጊዜ ቀኑን ሁሉ ፈርተሃል፤ የጨቋኙ ቍጣ የት አለ?
\s5
\v 14 ምርኮኛ ፈጥኖ ይፈታል፣ አይሞትም ወደ ጕድጓድም አይወርድም፣ እንጀራም አይጐድልበትም።
\v 15 ሞገዱም እንዲተምም ባሕርን የማናውጥ አምላክህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ፣ ስሜም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው።
\s5
\v 16 ሰማያትን እዘረጋ ዘንድ ምድርንም እመሠርት ዘንድ፣ ጽዮንንም፣ 'አንቺ ሕዝቤ ነሽ' እል ዘንድ ቃሌን በአፍህ አድርጌአለሁ፣ በእጄም ጥላ ጋርጄሃለሁ።"
\s5
\v 17 ከእግዚአብሔር እጅ የቍጣውን ጽዋ የጠጣሽ ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ንቂ፣ ንቂ፣ ቁሚ፤ የሚያንገደግድን ዋንጫ ጠጥተሻል፣ ጨልጠሽውማል።
\v 18 ከወለደቻቸው ልጆች ሁሉ የሚመራት የለም፣ ካሳደገቻቸውም ልጆች ሁሉ እጅዋን የሚይዝ የለም።
\s5
\v 19 እነዚህ ሁለት ነገሮች ሆነውብሻል፣ ማንስ ያስተዛዝንሻል? መፈታትና ጥፋት ራብና ሰይፍ ናቸው፤ እንዴትስ አድርጌ አጽናናሻለሁ?
\v 20 ልጆችሽ ዝለዋል፤ በወጥመድ እንደተያዘ ሚዳቋ በአደባባይ ሁሉ ራስ ላይ ተኝተዋል፤ በእግዚአብሔር ቍጣና በአምላክሽ ተግሣጽ ተሞልተዋል።
\s5
\v 21 አሁን ግን ይህንን ስሚ፣ ያለ ወይን ጠጅ የሰከርሽ አንቺ የተጨቆንሽ።
\v 22 ስለ ወገኑ የሚምዋገት አምላክሽ ጌታሽ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ተመልከቺ፣ የሚያንገደግድን ጽዋ የቍጣዬንም ዋንጫ ከእጅሽ ወስጃለሁ፤ ደግመሽም ከእንግዲህ ወዲህ አትጠጪውም።
\s5
\v 23 ነፍስሽንም፣ 'እንሻገር ዘንድ ዝቅ በዪ፣ በሚሉአት በአስጨናቂዎችሽ እጅ አኖረዋለሁ፤' ጀርባሽንም ለሚሻገሩት እንደ መሬትና እንደ መንገድ አደረግሽላቸው።"
\s5
\c 52
\p
\v 1 ጽዮን ሆይ፣ ተነሺ፣ ተነሺ፣ ኃይልሽን ልበሺ፤ ቅድስቲቱ ከተማ ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ያልተገረዘና ርኩስ ከእንግዲህ ወዲህ አይገባብሽምና ጌጠኛ ልብስሽን ልበሺ።
\s5
\v 2 ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ትቢያን አራግፊ፤ ተነሺና ተቀመጪ፤ ምርኮኛይቱ የጽዮን ልጅ ሆይ፣ የአንገትሽን እስራት ፍቺ።
\v 3 እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፣ "በከንቱ ተሽጣችሁ ነበር፣ ያለ ገንዘብም ትቤዣላችሁ።"
\s5
\v 4 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ወገኔ በዚያ እንግዳ ሆኖ ይቀመጥ ዘንድ አስቀድሞ ወደ ግብጽ ወረደ፣ አሦርም ቅርብ ጊዜ ላይ ያለ ምክንያት በደለው።
\s5
\v 5 ወገኔ በከንቱ ተወስዶአልና አሁን ከዚህ ምን አለኝ? ይላል እግዚአብሔር፤ የሚገዙአቸው ይጮኻሉ፣ ይላል እግዚአብሔር፣ ስሜም ሁልጊዜ ቀኑን ሁሉ ይሰደባል።
\v 6 ስለዚህ ወገኔ ስሜን ያውቃል፤ ስለዚህም የምናገር እኔ እንደ ሆንሁ በዚያ ቀን ያውቃሉ፤ አዎን፣ እኔ ነኝ!"
\s5
\v 7 የምስራች የሚናገር፣ ሰላምንም የሚያወራ፣ የመልካምንም ወሬ የምስራች የሚናገር፣ መድኃኒትንም የሚያወራ፣ ጽዮንንም፣ "አምላክሽ ነግሦአል!" የሚል ሰው እግሩ በተራሮች ላይ እጅግ ያማረ ነው።
\v 8 አድምጪ፣ ጕበኞችሽ ጮኸዋል፤ እግዚአብሔር ወደ ጽዮን በተመለሰ ጊዜ ዓይን በዓይን ይተያያሉና ድምፃቸውን ያነሣሉ፣ በአንድነትም ይዘምራሉ።
\s5
\v 9 እናንተ የኢየሩሳሌም ፍርስራሾች ሆይ፣ እግዚአብሔር ሕዝቡን አጽናንቶአልና፤ ኢየሩሳሌምንም ታድጎአልና ደስ ይበላችሁ፣ በአንድነትም ዘምሩ።
\v 10 እግዚአብሔር የተቀደሰውን ክንዱን በአሕዛብ ሁሉ ፊት ገልጦአል፤ በምድር ዳርቻ የሚኖሩትም ሁሉ የአምላካችንን መድኃኒት ያያሉ።
\s5
\v 11 እናንተ የእግዚአብሔር ዕቃ የምትሸከሙ ሆይ፣ ትታችሁ ውጡ፣ ትታችሁ ውጡ፤ ከዚያ ውጡ፣ ርኩስን ነገር አትንኩ፣ ከመካከልዋ ውጡ፣ ንጽሐን ሁኑ።
\v 12 እግዚአብሔር ይቀድማችኋልና፣ የእስራኤልም አምላክ ይከተላችኋልና በችኰላ አትወጡም በመኰብለልም አትሄዱም።
\s5
\v 13 ተመልከቱ፣ ባሪያዬ በማስተዋል ያደርጋል፤ ይከብራል ከፍ ከፍም ይላል፣ እጅግ ታላቅም ይሆናል።
\v 14 ፊቱ ከሰዎች ሁሉ ይልቅ፣ መልኩም ከሰዎች ልጆች ይልቅ ተጐሳቍሎአልና ብዙ ሰዎች ስለ አንተ እንደ ተደነቁ፣ እንዲሁ ብዙ አሕዛብን ያስደንቃል፤
\s5
\v 15 ያልተነገረላቸውንም ያያሉና፣ ያልሰሙትንም ያስተውላሉና ነገሥታት ስለ እርሱ አፋቸውን ይዘጋሉ።
\s5
\c 53
\p
\v 1 የሰማነውን ነገር ማን አምኖአል? የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገልጦአል?
\v 2 በፊቱ እንደ ቡቃያ፣ ከደረቅም መሬት እንደ ሥር አድጎአል። መልክና ውበት የለውም፣ ባየነውም ጊዜ እንወድደው ዘንድ ደም ግባት የለውም።
\s5
\v 3 የተናቀ ከሰውም የተጠላ፣ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው። ሰውም ፊቱን እንደሚሰውርበት የተናቀ ነው፣ እኛም አላከበርነውም።
\s5
\v 4 በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል፤ እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው።
\s5
\v 5 እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፣ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፣ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።
\s5
\v 6 እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ።
\s5
\v 7 ተጨቆነ፣ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም፤ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፣ በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፣ እንዲሁ አፉን አልከፈተም።
\s5
\v 8 በማስጨነቅና በፍርድ ተወሰደ፤ ስለ ሕዝቤ ኃጢአት ተመትቶ ከሕያዋን ምድር እንደ ተወገደ ከትውልዱ ማን አስተዋለ?
\v 9 ከክፉዎችም ጋር መቃብሩን አደረጉ፣ ከባለጠጎችም ጋር በሞቱ ሆኖም ግፍን አላደረገም ነበር፣ በአፉም ተንኮል አልተገንበትም ነበር።
\s5
\v 10 እግዚአብሔርም በደዌ ያደቅቀው ዘንድ ፈቀደ፤ ነፍሱን ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ካደረገ በኋላ ዘሩን ያያል፣ ዕድሜውም ይረዝማል፣ የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል።
\v 11 ከነፍሱ መከራ በኋላ፣ ብርሃን ያያል ደስም ይለዋል፤ ጻድቅ ባሪያዬም በእውቀቱ ብዙ ሰዎችን ያጸድቃል፣ ኃጢአታቸውን ይሸከማል።
\s5
\v 12 ስለዚህም እርሱ ብዙዎችን ይወርሳል፣ ከብዙ ኃያላንም ጋር ምርኮን ይከፋፈላል፤ ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰጥቶአልና፣ ከዓመፀኞችም ጋር ተቈጥሮአልና፤ እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ፣ ስለ ዓመፀኞችም ማለደ።
\s5
\c 54
\p
\v 1 "አንቺ ያልወለድሽ መካን ሆይ፣ ዘምሪ፤ አንቺ ያላማጥሽ ሆይ፣ እልል በዪ፣ ጩኺም፤ ባል ካላት ይልቅ ፈት የሆነቺቱ ልጆች በዝተዋልና፣" ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 2 የድንኳንሽን ስፍራ አስፊ፣ መጋረጃዎችሽንም ይዘርጉ፤ አትቈጥቢ፤ አውታሮችሽን አስረዝሚ ካስሞችሽንም አጽኚ።
\v 3 በቀኝና በግራ ትሰፋፊያለሽና፣ ዘርሽም አሕዛብን ይወርሳልና፣ የፈረሱትንም ከተሞች መኖሪያ ያደርጋልና።
\s5
\v 4 አታፍሪምና አትፍሪ፤ አተዋረጂምና አትደንግጪ፤ የሕፃንነትሽንም እፍረት ትረሺዋለሽ፣ የመበለትነትሽንም ስድብ ከእንግዲህ ወዲህ አታስቢም።
\s5
\v 5 ፈጣሪሽ ባልሽ ነው፣ ስሙም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው፤ የእስራኤልም ቅዱስ ታዲጊሽ ነው፣ እርሱም የምድር ሁሉ አምላክ ይባላል።
\v 6 እግዚአብሔር እንደ ተተወችና እንደ ተበሳጨች በልጅነትዋም እንደ ተጣለች ሚስት ጠርቶሻል፣ ይላል አምላክሽ።
\s5
\v 7 "ለጥቂት ጊዜ ተውሁሽ፣ በታላቅም ምሕረት እሰበስብሻለሁ።
\v 8 በጥቂት ቍጣ ለቅጽበት ዓይን ፊቴን ከአንቺ ሰወርሁ፣ በዘላለምም ቸርነት እምርሻለሁ፣ ይላል ታዳጊሽ እግዚአብሔር።
\s5
\v 9 ይህ ለእኔ እንደ ኖኅ ውኃ ነው፤ የኖኅ ውኃ ደግሞ በምድር ላይ እንዳያልፍ እንደ ማልሁ፣ እንዲሁ አንቺን እንዳልቈጣ እንዳልገሥጽሽም ምያለሁ።
\v 10 ተራሮች ይፈልሳሉ፣ ኮረብቶችም ይወገዳሉ፤ ቸርነቴ ግን ከአንቺ ዘንድ አይፈልስም የሰላሜም ቃል ኪዳን አይወገድም፣ ይላል መሐሪሽ እግዚአብሔር።
\s5
\v 11 አንቺ የተቸገርሽ በዐውሎ ነፋስም የተናወጥሽ ያልተጽናናሽም፣ ተመልከቺ፣ ድንጋዮችሽን ሸላልሜ እገነባለሁ፣ በሰንፔርም እመሠርትሻለሁ።
\v 12 የግንብሽንም ጕልላት በቀይ ዕንቍ፣ በሮችሽንም በሚያብረቀርቅ ዕንቍ፣ ዳርቻሽንም ሁሉ በከበሩ ድንጋዮች እሠራለሁ።
\s5
\v 13 ልጆችሽም ሁሉ ከእግዚአብሔር የተማሩ ይሆናሉ፣ የልጆችሽም ሰላም ብዙ ይሆናል።
\v 14 በጽድቅ ትታነጺያለሽ፤ ከግፍ ራቂ፣ አትፈሪምም፣ ድንጋጤም ወደ አንቺ አትቀርብም።
\s5
\v 15 ተመልከቺ፣ ይሰበሰባሉ፣ ነገር ግን ከእኔ ዘንድ አይሆንም፤ በአንቺም ላይ ችግር የሚፈጥሩ ሁሉ ይሸነፋሉ።
\v 16 ተመልከቺ፣ ፍሙን በወናፍ የሚያናፋ ለሥራውም መሣሪያ የሚያወጣ ብረት ሠሪን እኔ ፈጥሬአለሁ፤ የሚያፈርሰውንም እንዲያጠፋ ፈጥሬአለሁ።
\s5
\v 17 በአንቺ ላይ የተሠራ መሣሪያ ሁሉ አይከናወንም፤ በፍርድም በሚነሣብሽ ምላስ ሁሉ ትፈርጂበታለሽ። የእግዚአብሔር ባሪያዎች ርስት ይህ ነው፣ ጽድቃቸውም ከእኔ ዘንድ ነው፣" ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\c 55
\p
\v 1 "እናንተ የተጠማችሁ ሁሉ፣ ወደ ውኃ ኑ፣ ገንዘብም የሌላችሁ ኑና ግዙ ብሉም፤ ኑ ያለ ገንዘብም ያለ ዋጋም የወይን ጠጅና ወተት ግዙ።
\s5
\v 2 ገንዘብን እንጀራ ላይደለ፣ የድካማችሁንም ዋጋ ለማያጠግብ ነገር ለምን ትመዝናላችሁ? በጥንቃቄ አድምጡኝ በረከትንም ብሉ፣ ሰውነታችሁም በጮማ ደስ ይበለው።
\s5
\v 3 ጆሮአችሁን አዘንብሉ ወደ እኔም ቅረቡ! ስሙ፣ ሰውነታችሁም በሕይወት ትኖራለች! የታመነችይቱን የዳዊትን ምሕረት፣ የዘላለምን ቃል ኪዳን ከእናንተ ጋር አደርጋለሁ።
\v 4 ተመልከቱ፣ ለአሕዛብ ምስክር፣ ለወገኖችም አለቃና አዛዥ እንዲሆን ሰጥቼዋለሁ።
\s5
\v 5 ተመልከቱ፣ የማታውቀውን ሕዝብ ትጠራለህ፤ የእስራኤልም ቅዱስ አክብሮሃልና ስለ አምላክህ ስለ እግዚአብሔር የማያውቁህ ሕዝብ ወደ አንተ ይሮጣሉ።"
\s5
\v 6 እግዚአብሔር በሚገኝበት ጊዜ ፈልጉት፣ ቀርቦም ሳለ ጥሩት፤
\v 7 ክፉ ሰው መንገዱን በደለኛም አሳቡን ይተው፤ ወደ እግዚአብሔርም ይመለስ እርሱም ይምረዋል፣ ይቅርታውም ብዙ ነውና ወደ አምላካችን ይመለስ።
\s5
\v 8 አሳቤ እንደ አሳባችሁ፣ መንገዳችሁም እንደ መንገዴ፣ አይደለምና ይላል እግዚአብሔር።
\v 9 ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፣ እንዲሁ መንገዴ ከመንገዳችሁ አሳቤም ከአሳባችሁ ከፍ ያለ ነው።
\s5
\v 10 ዝናብና በረዶ ከሰማይ እንደሚወርድ፣ ምድርን እንደሚያረካት፣ ታበቅልና ታፈራም ዘንድ እንደሚያደርጋት፣ ዘርንም ለሚዘራ እንጀራንም ለሚበላ እንደሚሰጥ እንጂ ወደ ሰማይ እንደማይመለስ፣
\v 11 ከአፌ የሚወጣ ቃሌ እንዲሁ ይሆናል፤ የምሻውን ያደርጋል የላክሁትንም ይፈጽማል እንጂ ወደ እኔ በከንቱ አይመለስም።
\s5
\v 12 እናንተም በደስታ ትወጣላችሁ በሰላምም ትሸኛላችሁ፤ ተራሮችና ኮረብቶች በፊታችሁ እልልታ ያደርጋሉ፣ የሜዳም ዛፎች ሁሉ ያጨበጭባሉ።
\v 13 በእሾህም ፋንታ ጥድ፣ በኩርንችትም ፋንታ ባርሰነት፣ ይበቅላል፤ ለእግዚአብሔርም መታሰቢያን ለዘላለምም የማይጠፋ፣ ምልክት ይሆናል።"
\s5
\c 56
\p
\v 1 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ማዳኔ ሊመጣ፣ ጽድቄም ሊገለጥ ቀርቦአልና ፍርድን ጠብቁ ጽድቅንም አድርጉ።
\v 2 ይህን የሚያደርግ ሰው ይህንንም የሚይዝ የሰው ልጅ፣ እንዳያረክሰው ሰንበትንም የሚጠብቅ እጁንም ክፋት ከማድረግ የሚጠብቅ ብፁዕ ነው።"
\s5
\v 3 ወደ እግዚአብሔርም የተጠጋ መጻተኛ፣ "በእውነት እግዚአብሔር ከሕዝቡ ይለየኛል" አይበል፤ ጃንደረባም፣ "ተመልከቱ፣ እኔ ደረቅ ዛፍ ነኝ አይበል።"
\s5
\v 4 እግዚአብሔር ሰንበቴን ስለሚጠብቁ ደስ የሚያሰኘኝንም ነገር ስለሚመርጡ ቃል ኪዳኔንም ስለሚይዙ ጃንደረቦች እንዲህ ይላልና፣
\v 5 "በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ፤ የማይጠፋም የዘላለም ስም እሰጣቸዋለሁ።"
\s5
\v 6 ያገለግሉት ዘንድ የእግዚአብሔርንም ስም ይወድዱ ዘንድ ባሪያዎቹም ይሆኑ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር የሚጠጉትንም መጻተኞች፣ እንዳያረክሱት ሰንበትን የሚጠብቁትን ቃል ኪዳኔንም የሚይዙትን ሁሉ፣
\v 7 "ወደ ተቀደሰ ተራራዬ አመጣቸዋለሁ፣ በጸሎቴም ቤት ደስ አሰኛቸዋለሁ፤ ቤቴ ለአሕዛብ ሁሉ የሚሆን የጸሎት ቤት ይባላልና የሚቃጠለውን መሥዋዕታቸውንና ሌላ መሥዋዕታቸውን በመሠዊያዬ ላይ እቀበላለሁ።
\s5
\v 8 ከእስራኤል የተበተኑትን የሚሰበስብ ጌታ እግዚአብሔር፣ ወደ ተሰበሰቡት ዘንድ ሌሎችን እሰበስብለታለሁ" ይላል።
\s5
\v 9 እናንተ የምድረ በዳ አራዊት ሁሉ፣ እናንተም የዱር አራዊት ሁሉ፣ ትበሉ ዘንድ ቅረቡ!
\v 10 ጕበኞቹ ዕውሮች ናቸው፣ ሁሉ ያለ እውቀት ናቸው፤ ሁሉም ዲዳ የሆኑ ውሾች ናቸው ይጮኹም ዘንድ አይችሉም፤ ሕልምን ያልማሉ፤ ይተኛሉ፤ ማንቀላፋትንም ይወድዳሉ።
\s5
\v 11 መብል ወዳጆች ከቶ የማይጠግቡ ውሾች ናቸው፤ እነርሱም ያስተውሉ ዘንድ የማይችሉ እረኞች ናቸው፤ ሁሉ ወደ መንገዳቸው፣ ከፊተኛው እስከ ኋለኛው ድረስ ሁሉ፣ እያንዳንዳቸው ወደ ጥቅማቸው ዘወር ብለዋል።
\v 12 "ኑ፣ የወይን ጠጅ እንውሰድ፣ በሚያሰክርም መጠጥ እንርካ፤ ዛሬም እንደ ሆነ እንዲሁ ነገ ይሆናል፣ ከዛሬም ይልቅ እጅግ ይበልጣል" ይላሉ።
\s5
\c 57
\p
\v 1 ጻድቅ ይጠፋል፣ በልቡም ነገሩን የሚያኖር የለም፤ ምሕረተኞችም ይወገዳሉ፣ ጽድቅም ከክፋት ፊት እንደ ተወገደ ማንም አያስተውልም።
\v 2 ወደ ሰላም ይገባል፤ በቅንነት የሄደ በአልጋው ላይ ያርፋል።
\s5
\v 3 እናንተ የአስማተኛይቱ ልጆች፣ የአመንዝራውና የጋለሞታይቱ ዘር፣ ወደዚህ ቅረቡ።
\v 4 በማን ታላግጣላችሁ? በማንስ ላይ አፋችሁን ታላቅቃላችሁ? ምላሳችሁንስ በማን ላይ ታስረዝማላችሁ?
\s5
\v 5 እናንተ በአድባር ዛፎች መካከል በለመለመም ዛፍ ሁሉ በታች በፍትወት የምትቃጠሉ፣ እናንተም በሸለቆች ውስጥ በዓለትም ስንጣቂዎች በታች ሕፃናትን የምታርዱ፣ የዓመፅ ልጆችና የሐሰት ዘር አይደላችሁምን?
\s5
\v 6 በሸለቆው ውስጥ ያሉ የለዘቡ ድንጋዮች እድል ፈንታሽ ናቸው፣ እነርሱም ዕጣሽ ናቸው፤ ለእነርሱም የመጠጥ ቍርባን አፍስሰሻል፣ የእህልንም ቍርባን አቅርበሻል። እንግዲህ በዚህ ነገር አልቈጣምን?
\s5
\v 7 ከፍ ባለውም በረዘመውም ተራራ ላይ መኝታሽን አደረግሽ፣ መሥዋዕትንም ትሠዊ ዘንድ ወደዚያ ወጣሽ።
\v 8 ከመዝጊያውና ከመቃኑ በኋላ መታሰቢያሽን አደረግሽ፤ እኔን ትተሽ ለሌላ ተገልጠሻል፣ ወጥተሽ መኝታሽን አስፍተሻል፤ ቃል ኪዳንም ተጋባሻቸው፣ ባየሽበትም ስፍራ ሁሉ መኝታቸውን ወደድሽ።
\s5
\v 9 ዘይትም ይዘሽ ወደ ንጉሡ ሄድሽ፣ ሽቱሽንም አበዛሽ፣ መልእክተኞችሽንም ወደ ሩቅ ላክሽ፣ እስከ ሲኦልም ድረስ ተዋረድሽ።
\v 10 በመንገድሽም ብዛት ደከምሽ፣ ነገር ግን፣ "ተስፋ የለም" አላልሽም፤ የጕልበትን መታደስ አገኘሽ፣ ስለዚህም አልዛልሽም።
\s5
\v 11 "ሐሰትን የተናገርሺው እኔንም ያላሰብሺው በልብሽም ነገሩን ያላኖርሺው ማንን ሰግተሽ ነው? ማንንስ ፈርተሽ ነው? እኔ ብዙ ጊዜ ዝም አልሁ፣ አንቺም አልፈራሽም።
\v 12 እኔ ጽድቅሽን እናገራለሁ፣ ሥራሽም አይረባሽም።
\s5
\v 13 ወደ አንቺ የሰበሰብሻቸው በጮኽሽ ጊዜ ይታደጉሽ፤ ንፋስ ግን ይወስዳቸዋል ሽውሽውታም ሁሉን ያስወግዳቸዋል። በእኔ የታመነ ግን ምድሪቱን ይገዛል፣ የተቀደሰውንም ተራራዬን ይወርሳል።
\s5
\v 14 እርሱም፣ 'ጥረጉ፣ መንገድን አዘጋጁ! ከሕዝቤም መንገድ ዕንቅፋትን አውጡ!" ይላል።
\v 15 ለዘላለም የሚኖር ስሙም ቅዱስ የሆነ፣ ከፍ ያለው ልዑል እንዲህ ይላል፣ "የተዋረዱትን ሰዎች መንፈስ ሕያው አደርግ ዘንድ፣ የተቀጠቀጠውንም ልብ ሕያው አደርግ ዘንድ፣ የተቀጠቀጠና የተዋረደ መንፈስ ካለው ጋር በከፍታና በተቀደሰ ስፍራ እቀመጣለሁ።
\s5
\v 16 መንፈስም የፈጠርሁትም ነፍስ ከፊቴ እንዳይዝል ለዘላለም አልጣላም፣ ሁልጊዜም አልቈጣም።
\v 17 ስለ ኃጢአቱ ጥቂት ጊዜ ተቈጥቼ ቀሠፍሁት፣ ፊቴን ሰውሬ ተቈጣሁ፤ እርሱም በልቡ መንገድ እያፈገፈገ ሄደ።
\s5
\v 18 መንገዱን አይቻለሁ እፈውሰውማለሁ፣ እመራውማለሁ፣ ለእርሱና ስለ እርሱም ለሚያለቅሱ መጽናናትን እመልሳለሁ።
\v 19 የከንፈሮችን ፍሬ እፈጥራለሁ። በሩቅም በቅርብም ላለው ሰላም ሰላም ይሁን፣ እፈውሰውማለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 20 ክፉዎች ግን እንደሚንቀሳቀስ ባሕር ናቸው፤ ጸጥ ይል ዘንድ አይችልምና፣ ውኆቹም ጭቃና ጕድፍ ያወጣሉና።
\v 21 ለክፉዎች ሰላም የላቸውም" ይላል አምላኬ።
\s5
\c 58
\p
\v 1 "በኃይልህ ጩኽ፣ አትቈጥብ፣ ድምፅህን እንደ መለከት አንሣ፣ ለሕዝቤ መተላለፋቸውን ለያዕቆብ ቤትም ኃጢአታቸውን ንገር።
\v 2 ነገር ግን ዕለት ዕለት ይሹኛል መንገዴንም ያውቁ ዘንድ ይወድዳሉ፤ ጽድቅን እንዳደረጉ የአምላካቸውንም ፍርድ እንዳልተዉ ሕዝብ እውነተኛውን ፍርድ ይለምኑኛል። ወደ እግዚአብሔርም ለመቅረብ ይወድዳሉ።
\s5
\v 3 'ስለ ምን ጾምን፣' አንተም 'አልተመለከትኸንም? ሰውነታችንንስ ስለ ምን አዋረድን፣ አንተም አላወቅህም?' ይላሉ። ተመልከቱ፣ በጾማችሁ ቀን ፈቃዳችሁን ታደርጋላችሁ፣ ሠራተኞቻችሁንም ሁሉ ታስጨንቃላችሁ።
\s5
\v 4 ተመልከቱ፣ ለጥልና ለክርክር ትጾማላችሁ በግፍ ጡጫም ትማታላችሁ፤ ድምፃችሁንም ወደ ላይ ታሰሙ ዘንድ ዛሬ እንደምትጾሙት አትጾሙም።
\v 5 እኔ የመረጥሁት ጾም ይህ ነውን? ሰውስ ነፍሱን የሚያዋርደው እንደዚህ ባለ ቀን ነውን? በውኑ ራሱን እንደ እንግጫ ዝቅ ያደርግ ዘንድ ማቅንና አመድንም በበታቹ ያነጥፍ ዘንድ ነውን? በውኑ ይህን ጾም፣ በእግዚአብሔርም ዘንድ የተወደደ ቀን ትለዋለህን?
\s5
\v 6 እኔስ የመረጥሁት ጾም ይህ አይደለምን? የክፋት በደልን እስራት ትፈቱ ዘንድ፣ የቀንበርንስ ጠፍር ትለቅቁ ዘንድ፣ የተገፉትንስ አርነት ትሰድዱ ዘንድ፣ ቀንበሩንስ ሁሉ ትሰብሩ ዘንድ አይደለምን?
\v 7 እንጀራህንስ ለተራበ ትቈርስ ዘንድ፣ ስደተኞቹን ድሆች ወደ ቤትህ ታገባ ዘንድ፣ የተራቈተውንስ ብታይ ታለብሰው ዘንድ፣ ከሥጋ ዘምድህ እንዳትሸሽግ አይደለምን?
\s5
\v 8 የዚያን ጊዜ ብርሃንህ እንደ ንጋት ይበራል፣ ፈውስህም ፈጥኖ ይበቅላል፣ ጽድቅህም በፊትህ ይሄዳል፣ የእግዚአብሔርም ክብር በኋላህ ሆኖ ይጠብቅሃል።
\s5
\v 9 የዚያን ጊዜ ትጠራለህ፣ እግዚአብሔርም ይሰማሃል፤ ትጮኻለህ እርሱም፣ "እነሆኝ" ይላል። ከመካከልህ ቀንበርን ብታርቅ፣ ጣትህንም መጥቀስ ብትተው፣
\v 10 ባታንጐራጕርም፣ ነፍስህንም ለተራበ ብታፈስስ፣ የተጨነቀውንም ነፍስ ብታጠግብ፣ ብርሃንህ በጨለማ ይወጣል ጨለማህም እንደ ቀትር ይሆናል።
\s5
\v 11 እግዚአብሔርም ሁልጊዜ ይመራሃል፤ ነፍስህንም በመልካም ነገር ያጠግባል አጥንትህንም ያጠናል። አንተም እንደሚጠጣ ገነት፣ ውኃውም እንደማያቋርጥ ምንጭ ትሆናለህ።
\s5
\v 12 ከዱሮ ዘመን የፈረሱት ስፍራዎች ይሠራሉ፣ የብዙ ትውልድም መሠረት ይታነጻል፤ አንተም፣ "ቅጥሩን ጠጋኝ፣" "የመኖሪያ መንገድን አዳሽ" ትባላለህ።
\s5
\v 13 ፈቃድህን በተቀደሰው ቀኔ ከማድረግ እግርህን ከሰንበት ብትመልስ፣ ሰንበትንም ደስታ፣ እግዚአብሔርም የቀደሰውን ክቡር ብትለው፣ የገዛ መንገድህንም ከማድረግ ፈቃድህንም ከማግኘት ከንቱ ነገርንም ከመናገር ተከልክለህ ብታከብረው።
\s5
\v 14 "በዚያን ጊዜ በእግዚአብሔር ደስ ይልሃል፤ በምድርም ከፍታዎች ላይ አወጣሃለሁ፤ የአባትህንም የያዕቆብን ርስት አበላሃለሁ፤ የእግዚአብሔር አፍ ተናግሮአልና።"
\s5
\c 59
\p
\v 1 ተመልከቱ፣ የእግዚአብሔር እጅ ከማዳን አላጠረችም፣ ጆሮውም ከመስማት አልደነቈረችም፤
\v 2 ነገር ግን፣ በደላችሁ በእናንተና በአምላካችሁ መካከል ለይታለች፣ እንዳይሰማም ኃጢአታችሁ ፊቱን ከእናንተ ሰውሮታል።
\s5
\v 3 እጃችሁ በደም ጣታችሁም በበደል ረክሳለች፣ ከንፈራችሁም ሐሰትን ተናግሮአል፣ ምላሳችሁም ኃጢአትን አሰምቶአል።
\v 4 በጽድቅ የሚጠራ በእውነትም የሚፈርድ የለም፤ በምናምንቴ ነገር ታምነዋል ሐሰትንም ተናግረዋል፤ ጕዳትን ፀንሰዋል በደልንም ወልደዋል።
\s5
\v 5 የእባብን እንቍላል ቀፈቀፉ፣ የሸረሪትንም ድር አደሩ። እንቍላላቸውንም የሚበላ ሰው ይሞታል፣ እንቍላሉም ሲሰበር እፉኝት ይወጣል።
\v 6 ድሮቻቸውም ልብስ አይሆኑላቸውም፣ በሥራቸውም አይሸፈኑም፤ ሥራቸውም የበደል ሥራ ነው፣ የግፍም ሥራ በእጃቸው ነው።
\s5
\v 7 እግሮቻቸው ወደ ክፋት ይሮጣሉ፣ ንጹሑን ደም ለማፍሰስ ይፈጥናሉ፤ አሳባቸው የኃጢአት አሳብ ነው። ጕስቍልናና ቅጥቃጤ በመንገዳቸው አለ።
\v 8 የሰላምን መንገድ አያውቁም፣ በአካሄዳቸውም ፍርድ የለም፤ መንገዳቸውን አጣምመዋል፣ የሚሄድባትም ሁሉ ሰላምን አያውቅም።
\s5
\v 9 ስለዚህ ፍርድ ከእኛ ዘንድ ርቆአል፣ ጽድቅም አላገኘንም፤ ብርሃንን በተስፋ እንጠባበቅ ነበር። እነሆም፣ ጨለማ ሆነ፤ ጸዳልን በተስፋ እንጠባበቅ ነበር፣ ነገር ግን በጨለማ ሄድን።
\v 10 እንደ ዕውሮች ወደ ቅጥሩ ተርመሰመስን፣ ዓይን እንደሌላቸው ተርመሰመስን፤ በቀትር ጊዜ በድግዝግዝታ እንዳለ ሰው ተሰናከልን፣ እንደ ሙታን በጨለማ ስፍራ ነን።
\s5
\v 11 ሁላችን እንደ ድቦች እንጮኻለን፤ እንደ ርግብ እንለቃቀሳለን፤ ፍርድን በተስፋ እንጠባበቅ ነበር። እርሱም የለም፤ መዳንም ከእኛ ዘንድ ርቆአል።
\s5
\v 12 ዓመፃችን በአንተ ፊት በዝቶአልና፣ ኃጢአታችን መስክሮብናልና፣ ዓመፃችን ከእኛ ጋር ነውና፣ በደላችንን እናውቃለንና።
\v 13 ዐምፀናል፣ ሐሰትን ተናግረናል፣ አምላካችንንም ከመከተል ተመልሰናል፤ ግፍንና ዓመፅንም ተናግረናል፣ የኃጢአት ቃልንም ፀንሰን ከልብ አውጥተናል።
\s5
\v 14 ፍርድም ወደ ኋላ ተመልሶአል፣ ጽድቅም በሩቅ ቆሞአል፤ እውነትም በአደባባይ ላይ ወድቆአልና፣ ቅንነትም ሊገባ አልቻለምና።
\v 15 እውነትም ታጥቶአል፣ ከክፋትም የራቀ ሰው ለብዝበዛ ሆኖአል። እግዚአብሔርም አየ፣ ፍርድም ስለሌለ ተከፋ።
\s5
\v 16 ሰውም እንደሌለ አየ፣ ወደ እርሱ የሚማልድ እንደሌለ ተረዳ ተደነቀም፤ ስለዚህ የገዛ ክንዱ መድኃኒት አመጣለት፣ ጽድቁም አገዘው።
\s5
\v 17 ጽድቅንም እንደ ጥሩር ለበሰ፣ በራሱም ላይ የማዳንን ራስ ቍር አደረገ፤ የበቀልንም ልብስ ለበሰ፣ በቅንዓትም መጐናጸፊያ ተጐናጸፈ።
\v 18 እንደ ሥራቸው መጠን እንዲሁ ቍጣን ለባላጋራዎቹ፣ ፍዳንም ለጠላቶቹ ይከፍላል፤ ለደሴቶችም ፍዳቸውን ይከፍላል።
\s5
\v 19 እርሱ የእግዚአብሔር ነፋስ እንደሚነዳው እንደ ጐርፍ ፈሳሽ ይመጣልና በምዕራብ ያሉት የእግዚአብሔርን ስም፣ በፀሐይ መውጫም ያሉት ክብሩን ይፈራሉ።
\v 20 "ለጽዮን ታዳጊ ይመጣል፣ በያዕቆብም ዘንድ ከኃጢአት ለሚርቁ፣ ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 21 ከእርሱ ጋር ያለው ቃል ኪዳኔ ይህ ነው ይላል እግዚአብሔር፣ በአንተ ላይ ያለው መንፈሴ በአፍህም ውስጥ ያደረግሁት ቃሌ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም ድረስ ከአፍህ ከዘርህም አፍ ከዘር ዘርህም አፍ አያልፍም፣" ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\c 60
\p
\v 1 ብርሃንሽ መጥቶአልና፣ የእግዚአብሔርም ክብር ወጥቶልሻልና ተነሺ፣ አብሪ።
\s5
\v 2 እነሆ፣ ጨለማ ምድርን ድቅድቅ ጨለማም አሕዛብን ይሸፍናል፤ ነገር ግን በአንቺ ላይ እግዚአብሔር ይወጣል፣ ክብሩም በአንቺ ላይ ይታያል፤
\v 3 አሕዛብም ወደ ብርሃንሽ ነገሥታትም ወደ መውጫሽ ጸዳል ይመጣሉ።
\s5
\v 4 ዓይኖችሽን አንሥተሽ በዙሪያሽ ተመልከቺ። እነዚህ ሁሉ ተሰብስበው ወደ አንቺ ይመጣሉ። ወንዶች ልጆችሽ ከሩቅ ይመጣሉ፣ ሴቶች ልጆችሽንም በጫንቃ ላይ ይሸከሙአቸዋል።
\v 5 በዚያን ጊዜ የባሕሩ በረከት ወደ አንቺ ስለሚመለስ፣ የአሕዛብም ብልጥግና ወደ አንቺ ስለሚመጣ፣ አይተሽ ደስ ይልሻል፣ ልብሽም ይደነቃል ይሰፋማል።
\s5
\v 6 የግመሎች ብዛት፣ የምድያምና የጌፌር ግመሎች፣ ይሸፍኑሻል፤ ሁሉ ከሳባ ይመጣሉ፣ ወርቅንና ዕጣንን ያመጣሉ የእግዚአብሔርንም ምስጋና ያወራሉ።
\v 7 የቄዳር መንጎች ሁሉ ወደ አንቺ ይሰበሰባሉ፣ የነባዮትም አውራ በጎች ያገለግሉሻል፤ እኔን ደስ ሊያሰኙ በመሠዊያዬ ላይ ይወጣሉ፣ የክብሬንም ቤት አከብራለሁ።
\s5
\v 8 ርግቦች ወደ ቤታቸው እንደሚበርሩ፣ እነዚህ እንደ ደመና የሚበርሩ እነማን ናቸው?
\v 9 እርሱ አክብሮሻልና ለአምላክሽ ለእግዚአብሔር ስምና ለእስራኤል ቅዱስ ልጆችሽን ከሩቅ ከእነርሱ ጋርም ብራቸውንና ወርቃቸውን ያመጡ ዘንድ ደሴቶች የተርሴስ መርከቦችም አስቀድመው ይጠባበቁኛል።
\s5
\v 10 በቍጣዬ ቀሥፌ በፍቅሬ ምሬሻለሁና መጻተኞች ቅጥርሽን ይሠራሉ፣ ነገሥታቶቻቸውም ያገለግሉሻል።
\v 11 በሮችሽም ሁልጊዜ ይከፈታሉ፤ ሰዎች የአሕዛብን ብልጥግና የተማረኩትንም ነገሥታቶቻቸውን ወደ አንቺ ያመጡ ዘንድ ሌሊትና ቀን አይዘጉም።
\s5
\v 12 ለአንቺም የማይገዛ ሕዝብና መንግሥት ይጠፋል፣ እነዚያ አሕዛብም ፈጽመው ይጠፋሉ።
\v 13 የመቅደሴንም ስፍራ ያስጌጡ ዘንድ የሊባኖስ ክብር፣ ጥዱና አስታው ባርሰነቱም፣ ወደ አንቺ ይመጣሉ፣ የእግሬንም ስፍራ አከብራለሁ።
\s5
\v 14 የአስጨናቂዎችሽም ልጆች አንገታቸውን ደፍተው ወደ አንቺ ይመጣሉ፣ የናቁሽም ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ፤ የእግዚአብሔርም ከተማ፣ የእስራኤል ቅዱስ የሆንሽ ጽዮን ይሉሻል።
\s5
\v 15 ከሰውም ማንም እስከማያልፍብሽ ድረስ የተተውሽና የተጠላሽ ነበርሽ፤ ነገር ግን የዘላለም ትምክሕትና የልጅ ልጅ ደስታ አደርግሻለሁ።
\v 16 የአሕዛብንም ወተት ትጠጫለሽ፣ የነገሥታትንም ጡት ትጠቢያለሽ፤ እኔም እግዚአብሔር የያዕቆብ ኃይል፣ መድኃኒትሽና ታዳጊሽ እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ።
\s5
\v 17 በናስ ፋንታ ወርቅን፣ በብረትም ፋንታ ብርን፣ በእንጨትም ፋንታ ናስን፣ በድንጋይም ፋንታ ብረትን አመጣለሁ። አለቆችሽንም ሰላም፣ የበላይ ገዢዎችሽንም ጽድቅ አደርጋለሁ፤
\v 18 ከዚያ በኋላ በምድርሽ ውስጥ ግፍ፣ በዳርቻሽም ውስጥ ጕስቍልናና ቅጥቃጤ አይሰማም፤ ቅጥርሽን መዳን በሮችሽንም ምስጋና ብለሽ ትጠሪያለሽ
\s5
\v 19 ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር የዘላለም ብርሃንሽ፣ አምላክሽም ክብርሽ ይሆናልና ፀሐይ በቀን ብርሃን አይሆንልሽም፣ የጨረቃም ብርሃን በሌሊት አይበራልሽም።
\v 20 እግዚአብሔር የዘላለም ብርሃንሽ ይሆናልና፣ የልቅሶሽም ወራት ታልቃለችና ፀሐይሽ ከዚያ በኋላ አትጠልቅም ጨረቃሽም አይቋረጥም።
\s5
\v 21 ሕዝብሽም ሁሉ ጻድቃን ይሆናሉ፤ እኔም እከብር ዘንድ የአታክልቴን ቡቃያ፣ የእጄ ሥራ የምትሆን ምድሪቱንም ለዘላለም ይወርሳሉ።
\v 22 ታናሹ ለሺህ የሁሉም ታናሹ ለብርቱ ሕዝብ ይሆናል፤ እኔ እግዚአብሔር በዘመኑ ይህን አፋጥነዋለሁ።
\s5
\c 61
\p
\v 1 የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፣ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና፤ ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፣ ለተማረኩትም ነጻነትን ለታሰሩትም መፈታትን እናገር ዘንድ ልኮኛል።
\s5
\v 2 የተወደደችውን የእግዚአብሔርን ዓመት አምላካችንም የሚበቀልበትን ቀን እናገር ዘንድ፣ የሚያለቅሱትንም ሁሉ አጽናና ዘንድ፤
\s5
\v 3 እግዚአብሔር ለክብሩ የተከላቸው የጽድቅ ዛፎች እንዲባሉ ለጽዮን አልቃሾች አደርግላቸው ዘንድ፣ በአመድ ፋንታ አክሊልን፣ በልቅሶም ፋንታ የደስታን ዘይት፣ በኀዘንም መንፈስ ፋንታ የምስጋናን መጐናጸፊያ እሰጣቸው ዘንድ ልኮኛል።
\s5
\v 4 ከጥንትም ጀምሮ ባድማ የነበሩትን ይሠራሉ፤ ከቀድሞ የፈረሱትንም ያቆማሉ። ባድማ የነበሩትንና ከብዙ ትውልድ በፊት የፈረሱትን ከተሞች እንደ ገና ይሠራሉ።
\v 5 መጻተኞችም ቆመው በጎቻችሁን ያሰማራሉ፣ ሌሎች ወገኖችም አራሾችና ወይም ጠባቂዎች ይሆኑላችኋል።
\s5
\v 6 እናንተ ግን የእግዚአብሔር ካህናት ትባላላችሁ፣ ሰዎቹም የአምላካችን አገልጋዮች ብለው ይጠሩአችኋል፤ የአሕዛብን ሀብት ትበላላችሁ፣ በክብራቸውም ትመካላችሁ።
\v 7 በእፍረታችሁ ፋንታ ሁለት እጥፍ ይሆንላችኋል፣ በውርደታችሁም ፋንታ ዕድል ፈንታችሁ ደስ ይላቸዋል፤ ስለዚህ በምድራቸው ሁሉ እጥፍ ይገዛሉ፣ የዘላለምም ደስታ ይሆንላቸዋል።
\s5
\v 8 እኔ እግዚአብሔር ፍርድን የምወድድ፣ ስርቆትንና በደልን የምጠላ ነኝ፤ ፍዳቸውንም በእውነት እሰጣቸዋለሁ፣ ከእነርሱም ጋር የዘላለም ቃል ኪዳን አደርጋለሁ።
\v 9 ዘራቸውም በአሕዛብ መካከል፣ ልጆቻቸውም በወገኖች መካከል የታወቁ ይሆናሉ፤ ያያቸው ሁሉ እግዚአብሔር የባረካቸው ዘር እንደ ሆኑ ይገነዘባል።
\s5
\v 10 አክሊልን እንደ ለበሰ ሙሽራ፣ በጌጥ ሽልማትዋም እንዳጌጠች ሙሽራ፣ የማዳንን ልብስ አልብሶኛልና፣ የጽድቅንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛልና በእግዚአብሔር እጅግ ደስ ይለኛል፣ ነፍሴም በአምላኬ ሐሤት ታደርጋለች።
\v 11 ምድርም ቡቃያዋን እንደምታወጣ፣ ገነትም ዘሩን እንደሚያበቅል፣ እንዲሁ ጌታ እግዚአብሔር ጽድቅንና ምስጋናን በአሕዛብ ሁሉ ፊት ያበቅላል።
\s5
\c 62
\p
\v 1 ስለ ጽዮን ዝም አልልም፣ ስለ ኢየሩሳሌምም ጸጥ አልልም፣ ጽድቅዋ እንደ ጸዳል መዳንዋም እንደሚበራ ፋና እስኪወጣ ድረስ።
\v 2 አሕዛብም ጽድቅሽን ነገሥታትም ሁሉ ክብርሽን ያያሉ፤ የእግዚአብሔርም አፍ በሚጠራበት በአዲሱ ስም ትጠሪያለሽ።
\s5
\v 3 በእግዚአብሔር እጅ የክብር አክሊል፣ በአምላክሽም እጅ የመንግሥት ዘውድ ትሆኛለሽ።
\v 4 ከእንግዲህ ወዲህ፣ "የተተወች" አትባዪም፤ ምድርሽም ከእንግዲህ ወዲህ፣ "ውድማ" አትባልም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር በአንቺ ደስ ብሎታልና፣ ምድርሽም ባል ታገባለችና አንቺ፣ "ደስታዬ የሚኖርባት" ትባያለሽ ምድርሽም፣ "ባል ያገባች" ትባላለች።
\s5
\v 5 ጕልማሳም ድንግሊቱን እንደሚያገባ፣ እንዲሁ ልጆችሽ ያገቡሻል። ሙሽራም በሙሽራይቱ ደስ እንደሚለው፣ እንዲሁ አምላክሽ በአንቺ ደስ ይለዋል።
\s5
\v 6 ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ጕበኞችን በቅጥርሽ ላይ አቁሜአለሁ፤ ቀንና ሌሊት ከቶ ዝም አይሉም፤ እናንተ እግዚአብሔርን የምታሳስቡ፣
\v 7 ኢየሩሳሌምን እስኪያጸና በምድርም ላይ ምስጋና እስኪያደርጋት ድረስ አትረፉ ለእርሱም ዕረፍት አትስጡ።
\s5
\v 8 እግዚአብሔር፣ "ከእንግዲህ ወዲህ በእርግጥ ለጠላቶችሽ መብል ይሆን ዘንድ እህልሽን አልሰጥም፣ መጻተኞችም የደከምሽበትን ወይንሽን አይጠጡም።
\v 9 ነገር ግን የሰበሰቡት ይበሉታል፣ እግዚአብሔርንም ያመሰግናሉ፣ ያከማቹትም በመቅደሴ አደባባይ ላይ ይጠጡታል" ብሎ በቀኙና በኃይሉ ክንድ ምሎአል።
\s5
\v 10 እለፉ፣ በበሮች በኩል እለፉ! የሕዝቡንም መንገድ ጥረጉ፤ አዘጋጁ፣ ጐዳናውን አዘጋጁ፣ ድንጋዮቹንም አስወግዱ፤ ለአሕዛብም ዓለማ አንሡ!
\s5
\v 11 ተመልከቱ፣ እግዚአብሔር ለምድር ዳርቻ አዋጅ እንዲህ ብሎ ነግሮአል፣ "ለጽዮን ልጅ፣ እነሆ፥ መድኃኒትሽ ይመጣል፤ እነሆ፣ ዋጋው ከእርሱ ጋር ሥራውም በፊቱ አለ" በሉአት።
\v 12 እግዚአብሔር፣ "የተቤዣቸው፣ የተቀደሰ ሕዝብ" ብለው ይጠሩአቸዋል፤ አንቺም፣ "የተፈለገች ያልተተወችም" ከተማ ትባያለሽ።
\s5
\c 63
\p
\v 1 ይህ ከኤዶምያስ፣ ልብሱም የቀላ ከባሶራ የሚመጣ፣ አለባበሱ ያማረ፣ በጕልበቱ ጽናት በራስ መተማመን የሚራመድ ማን ነው? በጽድቅ የምናገር ለማዳንም የምበረታ እኔ ነኝ።
\v 2 ቀሚስህ ስለ ምን ቀላ፣ ልብስህስ በወይን መጥመቂያ እንደሚረግጥ ሰው ልብስ ስለ ምን መሰለ?
\s5
\v 3 መጥመቂያውን ብቻዬን ረግጫለሁ፣ ከአሕዛብም አንድ ሰው ከእኔ ጋር አልነበረም፤ በቍጣዬ ረገጥኋቸው በመዓቴም ቀጠቀጥኋቸው፤ ደማቸውም በልብሴ ላይ ተረጭቶአል፣ ልብሴንም ሁሉ አስድፌአለሁ።
\v 4 የምበቀልበት ቀን በልቤ ነውና፣ የምቤዥበትም ዓመት ደርሶአልና።
\s5
\v 5 ተመለከትሁ፣ የሚረዳም አልተገኘም፤ የሚያግዝም አልነበረምና ተደነቅሁ፤ ስለዚህ የገዛ ክንዴ መድኃኒት አመጣልኝ፣ ቍጣዬም እርሱ አገዘኝ።
\v 6 በቍጣዬም አሕዛብን ረገጥሁ በመዓቴም ቀጠቀጥኋቸው፣ ደማቸውንም ወደ ምድር አፈሰስሁት።
\s5
\v 7 እግዚአብሔር እንደ ሰጠን ሁሉ፣ የእግዚአብሔርን ቸርነትና የእግዚአብሔርን ምስጋና፣ እንደ ምሕረቱና እንደ ቸርነቱም ብዛት ለእስራኤል ቤት የሰጠውን ትልቅ በጎነት አሳስባለሁ።
\v 8 እርሱም፣ "በእውነት ሕዝቤ፣ ሐሰትን የማያደርጉ ልጆች ናቸው" አለ፤ መድኃኒትም ሆነላቸው።
\s5
\v 9 በጭንቃቸው ሁሉ እርሱ ተጨነቀ፣ የፊቱም መልአክ አዳናቸው፤ በፍቅሩና በርኅራኄውም ተቤዣቸው፣ በቀደመውም ዘመን ሁሉ አንሥቶ ተሸከማቸው።
\s5
\v 10 እነርሱ ግን ዐመፁ ቅዱስ መንፈሱንም አስመረሩ። ስለዚህ ተመልሶ ጠላት ሆነባቸው፣ እርሱም ተዋጋቸው።
\s5
\v 11 እርሱም እንዲህ ብሎ የቀደመውን ዘመን አሰበ። "የበጎቹን እረኛ ከባሕሩ ያወጣው ወዴት ነው ያለ? ቅዱስ መንፈሱንም በመካከላቸው ያኖረ ወዴት ነው ያለ?
\s5
\v 12 የከበረውንም ክንድ በሙሴ ቀኝ ያስሄደ፣ ለራሱም የዘላለምን ስም ያደርግ ዘንድ ውኃውን በፊታቸው የከፈለ፣
\v 13 በምድረ በዳም እንደሚያልፍ ፈረስ፣ በቀላይ ውስጥ ያለ ዕንቅፋት ያሳለፋቸው ወዴት ነው ያለ?
\s5
\v 14 ወደ ሸለቆ እንደሚወርዱ ከብቶች፣ እንዲሁ የእግዚአብሔር መንፈስ ወደ ዕረፍት አመጣቸው። እንዲሁም ለራስህ የከበረ ስም ታደርግ ዘንድ ሕዝብን መራህ።
\s5
\v 15 ከሰማይ ቁልቊል ተመልከት፣ ከቅዱስነትህና ከክብርህም ማደሪያ ጐብኝ፤ ቅንዓትህና ኃይልህስ ወዴት ነው? ለእኔም የሆነው የልብህ ናፍቆትና ርኅራኄህ ተከለከለ።
\v 16 አብርሃም ባያውቀን እስራኤልም ባይገነዘበን፣ አንተ አባታችን ነህ፤ 'አቤቱ፣ አንተ አባታችን ነህ፣' ስምህም ከዘላለም ታዳጊያችን ነው።
\s5
\v 17 አቤቱ፣ ከመንገድህ ለምን አሳትኸን? እንዳንፈራህም ልባችንን ለምን አጸናህብን? ስለ ባሪያዎችህ ስለ ርስትህ ነገዶች ተመለስ።
\s5
\v 18 የተቀደሰው ሕዝብህ መቅደስህን ጥቂት ጊዜ ወረሱት፤ ጠላቶቻችንም ረግጠውታል።
\v 19 ከዘላለም እንዳልገዛኸን በስምህም እንዳልተጠራን ሆነናል።
\s5
\c 64
\p
\v 1 "ሰማዮችን ቀድደህ ምነው ብትወርድ! ተራሮችም ምነው ቢናወጡ!
\v 2 እሳት ጭራሮውን እንደሚያቃጥል፥ እሳትም ውኃውን እንደሚያፈላ፥ ስምህ ለጠላቶችህ ይገለጥ ዘንድ፥ አሕዛብም በፊትህ ይንቀጠቀጡ ዘንድ!
\s5
\v 3 ያልተጠባበቅነውን የክብርህን ሥራ ባደረግህ ጊዜ፣ ወረድህ ተራሮችም በፊትህ ተንቀጠቀጡ።
\v 4 ሰዎች ከጥንት ጀምሮ ለሚጠብቁህ ከምትሠራላቸው ከአንተ በቀር ሌላ አምላክን አልሰሙም በጆሮአቸውም አልተቀበሉም ዓይንም አላየችም።
\s5
\v 5 ጽድቅን የሚያደርገውን በመንገዶችህም የሚያስቡህን ትገናኛቸዋለህ። እነሆ፣ እነተ ተቈጣህ እኛም ኃጢአት ሠራን፤ ስለዚህም ተሳሳትን።
\s5
\v 6 ሁላችን እንደ ርኩስ ሰው ሆነናል፣ ጽድቃችንም ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ ሁላችንም እንደ ቅጠል ረግፈናል፣ በደላችንም እንደ ነፋስ ወስዶናል።
\v 7 ስምህንም የሚጠራ፣ አንተንም ሊይዝ የሚያስብ የለም፤ ፊትህንም ከእኛ ሰውረሃል፣ በኃጢአታችንም አጥፍተኸናል።
\s5
\v 8 አሁን ግን፣ አቤቱ፣ አንተ አባታችን ነህ፤ እኛ ጭቃ ነን አንተም ሠሪያችን ነህ፣ እኛም ሁላችን የእጅህ ሥራ ነን።
\v 9 አቤቱ፣ እጅግ አትቈጣ፣ ለዘላለምም ኃጢአትን አታስብ፤ እነሆ፣ እባክህ፣ ተመልከት፣ እኛ ሁላችን ሕዝብህ ነን።
\s5
\v 10 የተቀደሱ ከተሞችህ ምድረ በዳ ሆነዋል፤ ጽዮን ምድረ በዳ ኢየሩሳሌምም ውድማ ሆናለች።
\v 11 አባቶቻችን አንተን ያመሰገኑበት የተቀደሰና የተዋበ ቤታችን በእሳት ተቃጥሎአል፣ ያማረውም ስፍራችን ሁሉ ፈርሶአል።
\v 12 አቤቱ፣ በውኑ በዚህ ነገር ትታገሣለህን? ዝምስ ትላለህን? አጥብቀህስ ታስጨንቀናለህን?
\s5
\c 65
\p
\v 1 ላልጠየቁኝ ተገለጥሁ፣ ላልፈለጉኝም ተገኘሁ፤ በስሜም ያልተጠራውን ሕዝብ፣ 'እነሆኝ! እነሆኝ!' አልሁት።
\v 2 መልካም ባልሆነው መንገድ፣ አሳባቸውን እየተከተሉ፣ ወደሚሄዱ ወደ ዓመፀኛ ሕዝብ ቀኑን ሁሉ እጆቼን ዘረጋሁ!
\s5
\v 3 ይህ ሕዝብ ዘወትር የሚያስቈጡኝ ናቸው፤ እነርሱ በአትክልት ውስጥ የሚሠዉ በጡብም ላይ የሚያጥኑ፣
\v 4 በመቃብርም መካከል የሚቀመጡ፣ በስውርም ስፍራ የሚያድሩ፣ የእሪያ ሥጋም የሚበሉ ናቸው። የረከሰው መረቅ በዕቃቸው ውስጥ አለ።
\s5
\v 5 እነርሱም፣ 'ርቀህ ቁም፣ እኔ ከአንተ ይልቅ ቅዱስ ነኝና ወደ እኔ አትቅረብ' ይላሉ፤ እነዚህ በአፍንጫዬ ዘንድ ጢስ ቀኑንም ሁሉ የምትነድድ እሳት ናቸው።
\s5
\v 6 እነሆ፣ በፊቴ ተጽፎአል። ኃጢአታችሁና የአባቶቻችሁን ኃጢአት በአንድ ላይ ወደ ብብታቸው ፍዳ አድርጌ አመልሳለሁ እንጂ ዝም አልልም፣" ይላል እግዚአብሔር፤
\v 7 "በተራሮችም ላይ ስላጠኑ፣ በኮረብቶችም ላይ ስለ ሰደቡኝ፣ ስለዚህ አስቀድመው የሠሩትን ሥራቸውን በብብታቸው እሰፍራለሁ።"
\s5
\v 8 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ወይን በዘለላው በተገኘች ጊዜ፣ በረከት በእርስዋ ላይ አለና አታጥፉት" እንደሚባለው፣ ሁሉን እንዳላጠፉ ስለባሪያዎቼ እንዲሁ አደርጋለሁ።'
\s5
\v 9 ከያዕቆብ ዘርን ከይሁዳም ተራሮቼን የሚወርሰውን አወጣለሁ፤ እኔም የመረጥኋቸው ይወርሱአታል፣ ባሪያዎቼም በዚያ ይኖራሉ።
\v 10 ሳሮንም የበጎች ማሰማርያ፣ የአኮርም ሸለቆ የላሞች መመሰግያ ለፈልጉኝ ሕዝቤ ይሆናል።
\s5
\v 11 እናንተን ግን እግዚአብሔርን የተዋችሁትን፣ ቅዱሱንም ተራራዬን የረሳችሁትን፣ ጉድ ለተባለ ጣዖትም ማዕድ ያዘጋጃችሁትን፣ እድል ለተባለ ጣዖትም የወይን ጠጅ ለመጠጥ ቍርባን የቀዳችሁትን -
\s5
\v 12 እድላችሁን ለሰይፍ አደርገዋለሁ፣ ሁላችሁም ለመታረድ ትጐነበሳላችሁ፤ በፊቴም ክፉ ነገርን አደረጋችሁ፣ ያልወደድሁትንም መረጣችሁ እንጂ በጠራሁ ጊዜ አልመለሳችሁልኝምና፣ በተናገርሁም ጊዜ አልሰማችሁኝምና።"
\s5
\v 13 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ተመልከቱ፣ ባሪያዎቼ ይበላሉ እናንተ ግን ትራባላችሁ፤ ተመልከቱ፣ ባሪያዎቼ ይጠጣሉ እናንተ ግን ትጠማላችሁ፤ ተመልከቱ፣ ባሪያዎቼ ደስ ይላቸዋል እናንተ ግን ታፍራላችሁ፤
\v 14 ተመልከቱ፣ ባሪያዎቼ ከልባቸው ደስታ የተነሣ ይዘምራሉ፣ እናንተ ግን ከልባችሁ ኀዘን የተነሣ ትጮኻላችሁ፣ መንፈሳችሁም ስለ ተሰበረ ወዮ ትላላችሁ።
\s5
\v 15 ስማችሁንም ለተመረጡት ሕዝቤ እርግማን አድርጋችሁ ትተዋላችሁ፣ ጌታ እግዚአብሔርም ይገድላችኋል፣ ባሪያዎቹንም በሌላ ስም ይጠራቸዋል።
\v 16 እንዲሁም በምድር ላይ የተባረከ በእውነት አምላክ ይባረካል፣ በምድርም ላይ የማለ በእውነት አምላክ ይምላል፤ የቀድሞው ጭንቀት ተረስቶአልና፣ ከዓይኔም ተሰውሮአልና።
\s5
\v 17 ተመልከቱ፣ አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር እፈጥራለሁና፤ የቀደሙትም አይታሰቡም፣ ወደ ልብም አይገቡም።
\v 18 ነገር ግን በፈጠርሁት ደስ ይበላችሁ፣ ለዘላለምም ሐሤት አድርጉ፤ ተመልከቱ፣ ኢየሩሳሌምን ለሐሤት፣ ሕዝብዋንም ለደስታ እፈጥራለሁና።
\v 19 እኔም በኢየሩሳሌም ሐሤት አደርጋለሁ በሕዝቤም ደስ ይለኛል፤ ከዚያም ወዲያ የልቅሶ ድምፅና የዋይታ ድምፅ አይሰማባትም።
\s5
\v 20 ከዚያም ወዲያ ጥቂት ዘመን ብቻ የሚኖር ሕፃን, ወይም ዕድሜውን ያልፈጸመ ሽማግሌ አይገኝም፤ ጕልማሳው የመቶ ዓመት ሆኖት ይሞታልና, ኃጢአተኛውም የመቶ ዓመት ሆኖት የተረገመ ይሆናልና።
\v 21 ቤቶችንም ይሠራሉ ይቀመጡባቸውማል፤ ወይኑንም ይተክላሉ ፍሬውንም ይበላሉ።
\s5
\v 22 ሌላ እንዲቀመጥበት አይሠሩም፣ ሌላም እንዲበላው አይተከሉም፤ የሕዝቤ ዕድሜ እንደ ዛፍ ዕድሜ ይሆናልና፣ እኔም የመረጥኋቸው በእጃቸው ሥራ ረጅም ዘመን ደስ ይላቸዋልና።
\v 23 እነርሱ ከነልጆቻቸው የእግዚአብሔር ቡሩካን ዘር ናቸውና በከንቱ አይደክሙም ለጥፋትም አይወልዱም።
\s5
\v 24 እንዲህም ይሆናል፤ ሳይጠሩ አመልስላቸዋለሁ፣ ገናም ሲናገሩ እሰማለሁ።
\v 25 ተኵላና ጠቦት በአንድነት ይሰማራሉ፣ አንበሳም እንደ በሬ ገለባ ይበላል፣ የእባብም መብል ትቢያ ይሆናል። በተቀደሰው ተራራዬ ሁሉ አይጐዱም፣ አያጠፉምም፣" ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\c 66
\p
\v 1 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ሰማይ ዙፋኔ ነው፣ ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ የምትሠሩልኝ ቤት ምን ዓይነት ነው? የማርፍበትስ ስፍራ ምንድር ነው?
\s5
\v 2 እነዚህን ሁሉ እጄ ሠርታለችና እነዚህ ሁሉ የእኔ ናቸው ይላል እግዚአብሔር፤ ነገር ግን ወደዚህ ወደ ትሑት፣ መንፈሱም ወደ ተሰበረ፣ በቃሌም ወደሚንቀጠቀጥ ሰው እመለከታለሁ።
\s5
\v 3 በሬን የሚያርድልኝ ሰውን እንደሚገድል ነው፤ ጠቦትንም የሚሠዋ የውሻውን አንገት እንደሚሰብር ነው፤ የእህልን ቍርባን የሚያቀርብ የእርያን ደም እንደሚያቀርብ ነው፤ ዕጣንን የሚያጥን ጣዖትን እንደሚባርክ ነው። እነዚህ የገዛ መንገዳቸውን መረጡ፤ ነፍሳቸውም በርኵሰታቸው ደስ ይላታል፤
\s5
\v 4 እኔ ደግሞ የተሳለቀባቸውን እመርጣለሁ፣ የፈሩትንም ነገር አመጣባቸዋለሁ፤ በፊቴ ክፉ ነገርን አደረጉ፣ ያልወደድሁትንም መረጡ እንጂ በጠራሁ ጊዜ አልመለሱልኝምና፣ በተናገርሁም ጊዜ አልሰሙኝምና።"
\s5
\v 5 በቃሉ የምትንቀጠቀጡ ሆይ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፣ "የጠሉአችሁ ስለ ስሜም ያባረሩአችሁ ወንድሞቻችሁ፣ ደስታችሁን እናይ ዘንድ እግዚአብሔር ይክበር' ብለዋል፤ ነገር ግን ያፍራሉ።
\s5
\v 6 የጩኸት ድምፅ ከከተማ፣ ድምፅም ከመቅደስ፣ በጠላቶቹ ላይ ፍዳን የሚያመጣ የእግዚአብሔር ድምፅ ተሰምቶአል።
\s5
\v 7 ሳታምጥ ወለደች፤ ምጥም ሳያገኛት ወንድ ልጅን ወለደች።
\v 8 ከቶ እንዲህ ያለ ነገር ማን ሰምቶአል? እንዲህስ ያለ ነገር ማን አይቶአል? በውኑ አገር በአንድ ቀን ታምጣለችን? ወይስ በአንድ ጊዜ ሕዝብ ይወለዳልን? ጽዮን እንዳማጠች ወዲያው ልጆችዋን ወልዳለችና።
\s5
\v 9 በውኑ ወደ መውለድ የማደርስ እኔ አላስወልድምን? ይላል እግዚአብሔር፤ የማስወልድስ ማኅፀንን እኔ እዘጋለሁን?" ይላል አምላክሽ።
\s5
\v 10 እናንተ የምትወድዱአት ሁሉ፣ ከኢየሩሳሌም ጋር ሐሤትን አድርጉ፣ ስለ እርስዋም ደስ ይበላችሁ፤ እናንተም የምታለቅሱላት ሁሉ፣ ከእርስዋ ጋር በደስታ ሐሤትን አድርጉ፣
\v 11 ትጠቡ ዘንድ ከማጽናናትዋም ጡት ትጠግቡ ዘንድ፤ እጅግ ጠጥታችሁ በክብርዋ ሙላት ደስ ይላችሁ ዘንድ።
\s5
\v 12 እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፣ "እነሆ፣ ሰላምን እንደ ወንዝ፣ የአሕዛብንም ክብር እንደሚጐርፍ ፈሳሽ እመልስላታለሁ፤ ከዚያም ትጠባላችሁ፣ በጫንቃ ላይ ይሸከሙአችኋል በጕልበትም ላይ እያስቀመጡ ያቀማጥሉአችኋል።
\v 13 እናት ልጅዋን እንደምታጽናና እንዲሁ አጽናናችኋለሁ፣ በኢየሩሳሌምም ውስጥ ትጽናናላችሁ።"
\s5
\v 14 ታያላችሁ፣ ልባችሁም ሐሤት ታደርጋለች፣ አጥንታችሁም እንደ ለምለም ሣር ትበቅላለች፤ የእግዚአብሔርም እጅ ለሚፈሩት ትታወቃለች፣ በጠላቶቹም ላይ ይቈጣል።
\s5
\v 15 ተመልከቱ፣ እግዚአብሔር መዓቱን በቍጣ፣ ዘለፋውንም በእሳት ነበልባል ይመልስ ዘንድ ከእሳት ጋር ይመጣል፣ ሰረገሎቹም እንደ ዐውሎ ነፋስ ይሆናሉ።
\v 16 እግዚአብሔርም በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ በእሳትና በሰይፉ ይፈርዳል፤ በእግዚአብሔርም ተወግተው የሞቱት ይበዛሉ።
\s5
\v 17 በመካከላቸው ያለውን አንዱን ተከትለው ወደ ገነቱ ይገቡ ዘንድ ሰውነታቸውን የሚቀድሱና የሚያነጹ፣ የእሪያንም ሥጋ አስጸያፊ ነገርንም አይጥንም የሚበሉ በአንድነት ይጠፋሉ፣ ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 18 ሥራቸውንና አሳባቸውን አውቄአለሁና፤ አሕዛብንና ልሳናትን ሁሉ የምሰበስብበት ጊዜ ይደርሳል፣ እነርሱም ይመጣሉ ክብሬንም ያያሉ።
\v 19 በመካከላቸውም ምልክት አደርጋለሁ፣ ከእነርሱም የዳኑትን ዝናዬን ወዳልሰሙ፣ ክብሬንም ወዳላዩ ወደ አሕዛብ ወደ ተርሴስ ወደ ፉጥ ወደ ሉድ ወደ ሞሳሕ ወደ ቶቤል ወደ ያዋን በሩቅ ወዳሉ ደሴቶች እልካቸዋለሁ፣ በአሕዛብም መካከል ክብሬንም ይናገራሉ።
\s5
\v 20 የእስራኤል ልጆች ቍርባናቸውን በጥሩ ዕቃ አድርገው ወደ እግዚአብሔር ቤት እንደሚያመጡ፣ እንዲሁ ለእግዚአብሔር ቍርባን ይሆን ዘንድ ወንድሞቻችሁን ሁሉ፣ በፈረሶችና በሰረገሎች፣ በአልጋዎችና በበቅሎች በጠያር ግመሎችም ላይ አድርገው፣ ከአሕዛብ ሁሉ ወደ ተቀደሰው ተራራዬ ወደ ኢየሩሳሌም ያመጡአቸዋል፣ ይላል እግዚአብሔር።
\v 21 ካህናትና ሌዋውያን እንዲሆኑ ከእነርሱ እወስዳለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 22 እኔ የምሠራቸው አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ከፊቴ ጸንተው እንደሚኖሩ፣ እንዲሁ ዘራችሁና ስማችሁ ጸንተው ይኖራሉ፣ ይላል እግዚአብሔር።
\v 23 እንዲህ ይሆናል፤ በየመባቻውና በየሰንበቱ ሥጋ ለባሽ ሁሉ በፊቴ ይሰግድ ዘንድ ዘወትር ይመጣል፣ ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 24 ወጥተውም በእኔ ያመፁብኝን ሰዎች ሬሳቸውን ያያሉ፤ ትላቸው አይሞትምና፣ እሳታቸውም አይጠፋምና፤ ለሥጋ ለባሽም ሁሉ አስጸያፊ ነገር ይሆናሉ።"