am_ulb/21-ECC.usfm

484 lines
46 KiB
Plaintext

\id ECC
\ide UTF-8
\h መክብብ
\toc1 መክብብ
\toc2 መክብብ
\toc3 ecc
\mt መክብብ
\s5
\c 1
\p
\v 1 ይህ በኢየሩሳሌም የነገሠውና የዳዊት ልጅ የሆነው የአስተማሪው ቃል ነው።
\v 2 አስተማሪው እንዲህ ይላል፥ "እንደ እንፋሎት ትነት፥ በደመናም ውስጥ እንዳለ እስትንፋስ፥ ሁሉም ነገር ይጠፋል፥ በርካታ ጥያቄዎችን ትቶ።
\v 3 ከፀሐይ በታች በሚደክሙበት ሥራ ሁሉ የሰው ልጆች ምን ትርፍ ያገኙበት ይሆን?
\s5
\v 4 አንደኛው ትውልድ ይሄዳል፥ ሌላኛው ትውልድ ይመጣል፥ ምድር ግን ለዘላለም ትኖራለች።
\v 5 ፀሐይ ትወጣለች፥ ትጠልቃለችም፥ ዳግም ወደምትወጣበት ሥፍራ ለመመለስም ትቸኩላለች።
\v 6 ነፋስ ወደ ደቡብ ይነፍሳል፥ ወደ ሰሜንም ያከብባል፥ ሁሌም በመንገዱ ይሄዳል፥ እንደገናም ይመለሳል።
\s5
\v 7 ወንዞች ሁሉ ወደ ባህር ይፈስሳሉ፥ ባህሩ ግን መቼም ቢሆን አይሞላም። ወንዞቹ ወደሚሄዱበት ሥፍራ፥ ወደዚያው ሥፍራ እንደገና ይሄዳሉ።
\v 8 ሁሉም ነገር አድካሚ ነው፥ ሊያስረዳ የሚችልም የለም። ዓይን በሚያየው አይረካም፥ ጆሮም በሚሰማው አይሞላም።
\s5
\v 9 የሆነው ሁሉ ወደፊትም የሚሆን ነው፥ የተደረገውም ሁሉ ወደፊት የሚደረግ ነው። ከፀሐይ በታች አንድም አዲስ ነገር የለም።
\v 10 'ተመልከት፥ ይህ አዲስ ነው' ሊባልለት የሚችል አንዳች ነገር አለ? አሁን ያለው ሁሉ ለብዙ ዘመናት አስቀድሞ የነበረ ነው፥ ወደ እኛ ከመምጣቱ በፊት በዘመናት መካከል።
\v 11 በቀድሞ ዘመን የሆኑትን ነገሮች የሚያስታውስ ያለ አይመስልም። እጅግ ዘግይተው የሆኑትን ነገሮችና ወደፊት ሊሆኑ ያሉት ሁለቱም የሚታወሱ አይመስሉም።
\s5
\v 12 እኔ አስተማሪ ነኝ፥ በእስራኤልም ላይ በኢየሩሳሌም ንጉሥ ነበርኩ።
\v 13 ከሰማይ በታች የተደረገውን ነገር ሁሉ በጥበብ ለማጥናትና ለመመርመር አዕምሮዬን አሠራሁት። ይህ ምርምር እግዚአብሔር የሰው ልጆች በሥራ እንዲጠመዱ የሰጣቸው አድካሚ ተግባር ነው።
\v 14 ከሰማይ በታች የተሠሩትን ሥራዎች ሁሉ አየሁ፥ ተመልከቱ፥ ሁሉም የሚተንና ነፋስን ለማገድ መሞከር ነው።
\v 15 የተጣመመ መቃናት አይችልም! የጠፋው መቆጠር አይችልም!
\s5
\v 16 ለልቤ እንዲህ ስል ተናገርኩ፥ "ተመልከት፥ ከእኔ በፊት በኢየሩሳሌም ከነበሩት ሁሉ ይልቅ ጥበብን አከማችቻለሁ። አዕምሮዬ ትልቅ ጥበብንና እውቀትን አይቷል።"
\v 17 ስለዚህ ጥበብን ለማወቅ ልቤን አሠራሁት፥ ደግሞም ዕብደትንና ሞኝነትን። ይህም ደግሞ ነፋስን ለማገድ እንደ መሞከር መሆኑን አስተዋልኩኝ።
\v 18 ጥበብን በማብዛት ውስጥ ብዙ ተስፋ መቁረጥ አለ፥ እውቀትንም የሚያበዛ ሐዘንን ያበዛል።
\s5
\c 2
\p
\v 1 እኔም በልቤ፥ "ና እንግዲህ፥ በደስታ እፈትንሃለሁ። ስለዚህ እንዳሻህ ተደሰት" አልኩ። ግን ተመልከት፥ ይህም ደግሞ ልክ የአፍታ እስትንፋስ ነበር።
\v 2 ስለ ሣቅ "እርሱ ዕብደት ነው"፥ ስለ ደስታም "ምን ይጠቅማል?" አልኩ።
\s5
\v 3 በወይን ጠጅ ራሴን እንዴት እንደማስደስተው በልቤ መረመርሁ። እስካሁን ሞኝነትን ብይዛትም አዕምሮዬ በጥበብ እንዲመራ ተውኩት። ሰዎች በሕይወት ዘመናቸው ከሰማይ በታች ሊያደርጉት የሚገባቸውን መልካም ነገር ለማግኘት ፈለግሁ።
\s5
\v 4 ታላላቅ ነገሮችን አከናወንኩ። ለራሴ ቤቶችን ሠራሁ፥ ወይንንም ተከልሁ።
\v 5 የአትክልትና የመዝናኛ ቦታዎችን ለራሴ ሠራሁ፤ በእነርሱም ላይ ሁሉንም ዓይነት የፍሬ ዛፎች ተከልሁባቸው።
\v 6 ዛፎች የሚያድጉበትን ዱር የሚያጠጡ የውሃ ገንዳዎችን አበጀሁ።
\s5
\v 7 ወንድና ሴት ባሪያዎችን ገዛሁ፤ በቤተ መንግሥቴ የተወለዱ ባሪያዎችም ነበሩኝ። ከእኔ በፊት በኢየሩሳሌም ከነገሡት ሁሉ እጅግ የሚበልጥ የከብት መንጋና የቤት እንስሶች ነበሩኝ።
\v 8 ብርና ወርቅን፥ የነገሥታቱንና የአውራጃዎቹንም ሃብት ለራሴ አከማቸሁ። ለእኔ ለራሴ ወንድና ሴት አዝማሪዎች ነበሩኝ፤ እጅግ በበዙት ሚስቶቼና ቁባቶቼም በምድር ማንኛውንም ሰው ሊያስደስተው የሚችለውን ነገር አደረግሁ።
\s5
\v 9 ከእኔ በፊት በኢየሩሳሌም ከነበሩት ሁሉ ይልቅ ታላቅና ባለጸጋ ሆንኩ፥ ጥበቤም ከእኔው ጋር ቆየች።
\v 10 ዓይኖቼ የፈለጉትን ማናቸውንም ነገር አልከለከልኳቸውም። በምሠራው ሁሉ ልቤ ስለ ተደሰተና ደስታ የሠራሁት ሥራ ሁሉ ብድራት ስለ ነበረ ከየትኛውም ደስታ ልቤን አልከለከልኩትም።
\s5
\v 11 ከዚያም እጆቼ ያከናወኗቸውን ተግባራት ሁሉ፥ እኔም የሠራኋቸውን ሥራዎች ተመለከትኩ፥ ነገር ግን ሁሉም እንፋሎትና ነፋስን ለማገድ መሞከር ነበር። በእርሱ ውስጥ ከፀሐይ በታች አንድም ትርፍ አልነበረበትም።
\v 12 ከዚያም ጥበብን፥ ደግሞም ዕብደትንና ሞኝነትን ለመመርመር ራሴን መለስኩ። አስቀድሞ ከተደረገው በቀር ከዚህኛው ንጉሥ በኋላ የሚመጣው ንጉሥ ምን ለማድረግ ይችላል?
\s5
\v 13 ከዚያም ልክ ብርሃን ከጨለማ እንደሚሻል ጥበብም ከሞኝነት የሚሻል መሆኑን መረዳት ጀመርሁ።
\v 14 ጥበበኛ ሰው የሚሄድበትን እንዲያውቅ ዓይኖቹን በራሱ ላይ አድርጎ ይጠቀምባቸዋል፥ ሞኙ ግን በጨለማ ይሄዳል፥ ቢሆንም ለእያንዳንዱ የተዘጋጀለት ፍጻሜ ተመሳሳይ መሆኑን አውቃለሁ።
\s5
\v 15 እኔም በልቤ፥ "በሞኙ ላይ የሚደርሰው በእኔም ላይ ይደርሳል። ስለዚህ በጣም ጥበበኛ ብሆን ምን ልዩነት ያመጣል?" አልኩ። "ይህም ደግሞ እንፋሎት ብቻ ነው" ብዬ በልቤ ደመደምኩኝ።
\v 16 ምክንያቱም ጠቢቡም እንደ ሞኙ ለዘላለም አይታሰብም። በሚመጣው ዘመን ሁሉም ነገር የተረሳ ይሆናል። ልክ ሞኙ እንደሚሞት ጠቢቡም ሰው ይሞታል።
\s5
\v 17 ከፀሐይ በታች የሚሠራው ሥራ ሁሉ ክፉ ስለሆነብኝ ሕይወትን ጠላሁ። ይህም የሆነው ሁሉም ነገር እንፋሎትና ነፋስን ለማገድ መሞከር ስለሆነ ነው።
\v 18 ከፀሐይ በታች በሥራ የደከምኩበትን ሁሉ ጠላሁ፥ ከእኔ በኋላ ለሚመጣው ሰው ልተውለት የግድ ነውና።
\s5
\v 19 እርሱ ጥበበኛ ወይም ሞኝ ይሆን እንደሆነ ማን ያውቃል? ሆኖም ከሰማይ በታች በጥበቤ በሠራሁት ሁሉ ላይ አዛዥ ይሆናል። ይህም ደግሞ እንፋሎት ነው።
\v 20 ከዚህ የተነሣ ከፀሐይ በታች በሠራሁት ሥራ ሁሉ ላይ ልቤ ተስፋ መቁረጥ ጀመረ።
\s5
\v 21 ምክንያቱም አንዱ በጥበብ፥ በእውቀትና በብልሃት ይሠራ ይሆናል፥ ነገር ግን የነበረውን ነገር ሁሉ አንድም ላልለፋበት ሰው ይተውለታል።
\v 22 ይህም ደግሞ እንፋሎትና እጅግ የሚያሳዝን ነው። ከፀሐይ በታች ሰው ተግቶ በመሥራቱና ሥራውን ሁሉ ለማጠናቀቅ በልቡ በመሞከሩ ምን ያተርፋል?
\v 23 የየዕለት ሥራው በስቃይና በውጥረት የተሞላ ነው፥ ስለዚህ ነፍሱ በሌሊት እረፍት አታገኝም። ይህም ደግሞ እንፋሎት ነው።
\s5
\v 24 ለማንኛውም ሰው ከመብላት፥ መጠጣትና ከሥራው መልካም በሆነው ከመርካት የሚበልጥበት ምንም ነገር የለም። ይህ እውነት የሚመጣው ከእግዚአብሔር እጅ እንደሆነም አየሁ።
\v 25 ከእግዚአብሔር ካልሆነ በስተቀር ማን ሊበላ ይችላል? ወይም የትኛውንም ዓይነት ደስታ ማን ሊደሰት ይችላል?
\s5
\v 26 እርሱን ደስ ለሚያሰኝ እግዚአብሔር ጥበብን፥ እውቀትንና ደስታን ይሰጠዋል። እንዲሁም ለኃጢአተኛው የመሰብሰብንና የማከማቸትን ሥራ ይሰጠዋል፥ እግዚአብሔርን ደስ ለሚያሰኘው ሰው ይሰጠው ዘንድ። ይህም ደግሞ እንፋሎትን ማብዛትና ነፋስን ለማገድ መሞከር ነው።
\s5
\c 3
\p
\v 1 ለሁሉም ነገር የተቀጠረለት ጊዜ አለው፥ ከምድር በታች ለሚሆነውም ወቅት አለው።
\v 2 ለመወለድ ጊዜ አለው፥ ለመሞት ጊዜ አለው፥ ለመትከል ጊዜ አለው፥ ለመንቀል ጊዜ አለው፥
\v 3 ለመግደል ጊዜ አለው፥ ለመፈወስ ጊዜ አለው፥ ለማፍረስ ጊዜ አለው፥ ለመገንባት ጊዜ አለው፥
\s5
\v 4 ለማልቀስ ጊዜ አለው፥ ለመሣቅ ጊዜ አለው፥ ለማዘን ጊዜ አለው፥ ለመጨፈር ጊዜ አለው፥
\v 5 ድንጋይ ለመወርወር ጊዜ አለው፥ ድንጋይ ለመሰብሰብ ጊዜ አለው፥ ለመተቃቀፍ ጊዜ አለው፥ ከመተቃቀፍ ለመራቅ ጊዜ አለው፥
\s5
\v 6 ለመፈለግ ጊዜ አለው፥ ፍለጋን ለማቆም ጊዜ አለው፥ ነገሮችን ለመጠበቅ ጊዜ አለው፥ ነገሮችን ወርውሮ ለመጣል ጊዜ አለው፥
\v 7 ልብስ ለመቅደድ ጊዜ አለው፥ ለመስፋት ጊዜ አለው፥ ዝም ለማለት ጊዜ አለው፥ ለመናገር ጊዜ አለው፥
\s5
\v 8 ለመውደድ ጊዜ አለው፥ ለመጥላት ጊዜ አለው፥ ለጦርነት ጊዜ አለው፥ ለሰላም ጊዜ አለው።
\v 9 ሠራተኛው ከጥረቱ የሚያተርፈው ምንድነው?
\v 10 እግዚአብሔር እንዲፈጽሙት ለሰው ልጆች የሰጣቸውን ሥራ አይቻለሁ።
\s5
\v 11 እግዚአብሔር ሁሉን ነገር በጊዜው ተስማሚ አድርጎ ሠራው። ደግሞም በልባቸው ውስጥ ዘላለማዊነትን አስቀመጠ። ነገር ግን የሰው ልጆች ከጅማሬአቸው እስከ ፍጻሜአቸው ድረስ እግዚአብሔር የሠራውን ሥራ ሊያስተውሉት አይችሉም።
\s5
\v 12 ለሰው በሕይወት ዘመኑ ከመደሰትና መልካም ከማድረግ በቀር የሚሻል ምንም ነገር እንደሌለ አውቃለሁ።
\v 13 ደግሞም ሰው ሁሉ ሊበላና ሊጠጣ፥ ከሥራውም ሁሉ በሚመጣ መልካም እንዴት መደሰት እንዳለበት ሊያውቅ። ይህ የእግዚአብሔር ሥጦታ ነው።
\s5
\v 14 እግዚአብሔር የሠራው ሁሉ ለዘላለም እንደሚኖር አውቃለሁ። በዚህ ላይ መጨመርም ሆነ መቀነስ አይቻልም። ምክንያቱም ሰዎች በአክብሮት እንዲቀርቡት ይህንን ያደረገው እግዚአብሔር ነው።
\v 15 አሁን ያለው ሁሉ ቀደም ሲል የነበረ ነው፤ ወደ ፊት የሚኖረውም ሁሉ ቀደም ሲል የነበረ ነው። እግዚአብሔር ሰዎችን የተደበቁ ነገሮችን እንዲፈልጉ ያደርጋቸዋል።
\s5
\v 16 ከፀሐይ በታች ፍትሕ ሊኖር በሚገባበት ግፍ መኖሩን አየሁ፥ ጽድቅ ሊኖር በሚገባበትም ሥፍራ ብዙ ጊዜ የሚገኘው ግፍ ነው።
\v 17 እኔም በልቤ፥ "ስለ እያንዳንዱ ጉዳይና ስለ እያንዳንዱ ሥራ በጻድቁና በአመጸኛው ላይ በትክክለኛው ጊዜ እግዚአብሔር ይፈርዳል" አልሁ።
\s5
\v 18 እኔም በልቤ፥ "የሰው ልጆች እንደ እንስሳ መሆናቸውን ለማሳየት እግዚአብሔር ይፈትናቸዋል" አልሁ።
\s5
\v 19 በእንስሳት ላይ የሚደርሰው ያው ዕድል ፈንታ በሰው ልጆች ላይ ይደርሳልና። እንደ እንስሳቱ፥ ሰዎች ሁሉ ይሞታሉ። ያንኑ አየር ሁሉም ይተነፍሱታል፥ ስለዚህ በዚህ መንገድ ሰው ከእንስሳ ብልጫ የለውም። ሁሉም ነገር ፈጥኖ የሚጠፋ እስትንፋስ አይደለም?
\v 20 ሁሉም ወደ አንድ ሥፍራ ይሄዳሉ። ሁሉም ነገር ከአፈር ይመጣል፥ ሁሉም ነገር ደግሞ ወደ አፈር ይመለሳል።
\s5
\v 21 የሰው መንፈስ ወደ ላይ፥ የእንስሳ መንፈስም ወደ ታች ወደ ምድር ውስጥ ይሄድ እንደሆነ የሚያውቅ ማን ነው?
\v 22 ስለዚህ ማንም ሰው በሥራው ከመደሰት የሚበልጥ የተሻለ ነገር እንደሌለ እንደገና አስተዋልሁ፥ ያ ዕድል ፈንታው ነውና። ከእርሱ በኋላ የሚሆነውን እንዲያይ ማን መልሶ ሊያመጣው ይችላል?
\s5
\c 4
\p
\v 1 እንደገና ከፀሐይ በታች ስለሚደረገው ግፍ ሁሉ አሰብሁ። የሚጨቆኑትን ሰዎች ዕንባ ተመልከቱ። የሚያጽናናቸውም የለም። በጨቋኞቻቸው እጅ ኃይል አለ፥ ነገር ግን የተጨቆኑት ሰዎች አጽናኝ የላቸውም።
\s5
\v 2 ስለዚህ ካሉት የሞቱት፥ እስካሁን በሕይወት ካሉት ቀደም ሲል የሞቱት ይሻላሉ አልሁ።
\v 3 ሆኖም ከሁለቱ የሚሻለው ያልኖረው፥ ከፀሐይ በታች የሚደረገውን ክፉ ድርጊት ያላየው ነው።
\s5
\v 4 ከዚያም የትኛውም ጥረትና የጥበብ ሥራ ባልንጀራውን ለቅንዓት እንደሚያነሣሣው አየሁ። ይህም ደግሞ እንፋሎትና ንፋስን ለማገድ መሞከር ነው።
\s5
\v 5 ሞኝ ሰው እጁን አጣምሮ ይቀመጣል፥ አይሠራምም፥ ስለዚህ የራሱ ሥጋ ምግቡ ነው።
\v 6 ንፋስን ለማገድ በመሞከር ከሚገኝ ሁለት እፍኝ ይልቅ በጥሞና የተሠራ አንድ እፍኝ ይሻላል።
\s5
\v 7 ከዚያም እንደገና ስለሚበልጠው ከንቱነት፥ ከፀሐይ በታች በይበልጥ ተንኖ ስለሚጠፋው እንፋሎት አሰብሁ።
\v 8 ብቻውን የሆነ አንድ ሰው አለ። ወንድ ልጅም ሆነ አባት አንድም የለውም። ለሚሠራው ሁሉ ማለቂያ የለውም፥ ዓይኖቹም ባገኘው ብልጽግና አይረኩም። እርሱም፥ "የምለፋው ለማን ነው? ራሴንስ ከደስታ የማርቀው ለምንድነው?" ብሎ ይደነቃል። ይህ የከፋ ሁኔታ ደግሞም እንፋሎት ነው።
\s5
\v 9 ከአንድ ሰው ይልቅ ሁለቱ የተሻለ ሥራ ይሠራሉ፤ በጋራ ለሥራቸው የተሻለ ገቢ ማግኘት ይችላሉ።
\v 10 አንደኛው ቢወድቅ ሌላኛው ጓደኛውን ሊያነሣው ይችላልና። በመሆኑም በወደቀ ጊዜ የሚያነሣው ካልኖረ ብቸኛውን ሰው ሀዘን ይከተለዋል።
\v 11 ሁለቱ አብረው ቢተኙ ሊሞቃቸው ይችላል፥ ብቻውን ቢሆን ግን እንዴት ሊሞቀው ይችላል?
\s5
\v 12 አንድ ሰው ብቻውን ሊሸነፍ ይችላል፥ ሁለቱ ግን ጥቃቱን መመከት ይችላሉ። በሦስት የተገመደ ገመድ ቶሎ አይበጠስም።
\s5
\v 13 ማስጠንቀቂያዎችን እንዴት መስማት እንዳለበት ከማያውቅ ሞኝ ሽማግሌ ንጉሥ ይልቅ ድሃ፥ ነገር ግን ጥበበኛ የሆነ ወጣት ይሻላል።
\v 14 ወጣቱ ከወህኒ ወጥቶ ቢነግሥ ወይም በሀገሩ በድህነት ተወልዶ ቢያድግም ይህ አውነት ነው።
\s5
\v 15 ይሁንና ከፀሐይ በታች ሕያው የሆነና የሚንቀሳቀሰው ሁሉ ራሳቸውን ንጉሥ ሆኖ ለተነሣው ለሌላው ወጣት ሲያስገዙ አየሁ።
\v 16 አዲሱን ንጉሥ መታዘዝ ለሚፈልገው ሕዝብ ሁሉ መጨረሻ የለውም፥ በኋላ ላይ ግን ብዙዎቹ አያመሰግኑትም። በርግጥ ይህ ሁኔታ እንፋሎት፥ ንፋስንም ለማገድ መሞከር ነው።
\s5
\c 5
\p
\v 1 ወደ እግዚአብሔር ቤት በምትሄድበት ጊዜ ጠባይህን ተቆጣጠር። ለመስማት ወደዚያ ሂድ። ሞኞች ክፉ መሥራታቸውን ሳያውቁ ከሚያቀርቡት መሥዋዕት ይልቅ መስማት ይበልጣል።
\s5
\v 2 ለመናገር እጅግ አትፍጠን፥ በእግዚአብሔር ፊት የትኛውንም ጉዳይ ለማቅረብ ልብህ እጅግ አይፍጠን። እግዚአብሔር በሰማይ ነው፥ አንተ ግን በምድር፤ ስለዚህ ቃልህ ጥቂት ይሁን።
\v 3 የምትሠራው ከበዛና ሃሳብ ከሆነብህ፥ ክፉ ህልም ሊገጥምህ ይችላል። ቃልህ ብዙ ሲሆን ብዙ የሞኝነት ነገርም ትናገራለህ።
\s5
\v 4 ለእግዚአብሔር በምትሳልበት ጊዜ ከመፈጸም አትዘግይ፥ እግዚአብሔር በሞኞች ደስ አይለውምና።
\v 5 የተሳልከውን ፈጽመው። የተሳሉትን ካለመፈጸም ያለመሳል ይሻላል።
\s5
\v 6 አንደበትህ ሰውነትህን ለኃጢአት እንዲያነሣሣው አትፍቀድለት። ለካህኑ መልዕክተኛ፥ "ያ ስዕለት ስሕተት ነበረ" አትበል። በሐሰት በመሳል እግዚአብሔርን ለምን ታስቆጣዋለህ፥ የእጅህንስ ሥራ እንዲያጠፋ እግዚአብሔርን ለምን ታነሣሣዋለህ?
\v 7 በብዙ ሕልም ውስጥ፥ በብዙም ቃል ውስጥ እንፋሎት የሆነ ከንቱነት አለ። ስለዚህ እግዚአብሔርን ፍራ።
\s5
\v 8 በግዛትህ ውስጥ ድሃው ሲበደል፥ ፍትህንና መብቱን ሲነጠቅ በምታይበት ጊዜ፥ ማንም አላወቀም ብለህ አትደነቅ፥ ምክንያቱም ከሥራቸው ያሉትን የሚቆጣጠሩ አለቆች አሉ፥ በእነርሱም ላይ እንኳን የበላይ አለቆች አሉ።
\v 9 በአጠቃላይ የምድሪቱ ምርት ለሁሉም ነው፥ ንጉሡ ራሱም ምርቱን ከእርሻ ይወስዳል።
\s5
\v 10 ማንም ብርን የሚወድ በብር አይረካም፥ ማንም ብልጽግናን የሚወድ ሁልጊዜ ተጨማሪውን ይፈልጋል። ይህም ደግሞ እንፋሎት ነው።
\v 11 ሀብት ሲበዛ በእርሱ የሚጠቀሙ ደግሞ ይበዛሉ። ባለቤቱ በዓይኖቹ ከማየቱ በስተቀር ሀብቱ ምን ይጠቅመዋል?
\s5
\v 12 ብዙም ሆነ ጥቂት ቢበላ፥ የሚሠራ ሰው እንቅልፉ ጣፋጭ ናት፥ የባለጸጋው ሀብት ግን እንቅልፉን ይነሳዋል።
\s5
\v 13 ከፀሐይ በታች ያየሁት እጅግ የከፋ ነገር አለ፡ ይኸውም በባለሌቱ የተከማቸው ሀብት መጥፊያው ሲሆን ነው።
\v 14 ባለጸጋው በክፉ አጋጣሚ ሀብቱን በሚያጣበት ጊዜ ለልጁ፥ እርሱ ላሳደገው፥ በእጁ የሚተውለት አይኖረውም።
\s5
\v 15 ሰው ከእናቱ ማኅፀን ራቁቱን እንደ ተወለደ፥ ራቁቱን ደግሞ የምድሩን ሕይወት ይሰናበታል። ከሥራው አንዱን በእጁ መውሰድ አይችልም።
\v 16 ሌላው እጅግ ክፉ ነገር፥ ሰው እንደ መጣ እንዲሁ ደግሞ መሄዱ ነው። ስለዚህ ለንፋስ በመሥራት ሰው የሚያገኘው ትርፍ ምንድነው?
\v 17 በዘመኑ ሁሉ በጨለማ ይበላል፥ በህመምና በቁጣ በብዙ ይበሳጫል።
\s5
\v 18 ተመልከቱ! እኔ እግዚአብሔር በሰጠን በምድር ሕይወታችን ከፀሐይ በታች በምንደክምበት፥ መልካምና ተስማሚ ሆኖ ያገኘሁት፥ መብላት፥ መጠጣትና ባገኘነው በሥራችን ውጤት ሁሉ መደሰትን ነው። ይህ የሰው ዕድል ፈንታው ነው።
\s5
\v 19 እግዚአብሔር ለማንኛውም ሰው ሀብትንና ባለጸግነትን፥ ድርሻውን የሚያገኝበትን ችሎታና በሥራው መደሰትን መስጠቱ ይህ የእግዚአብሔር ሥጦታ ነው።
\v 20 ለመሥራት በሚያስደስተው ነገር እግዚአብሔር ባተሌ ስለሚያደርገው፥ የሕይወት ዘመኑን እምብዛም አያስባቸውም።
\s5
\c 6
\p
\v 1 ከፀሐይ በታች ያየሁት ክፉ ነገር አለ፥ እርሱም ለሰዎች ከባድ ነው።
\v 2 ለራሱ የሚመኘውን አንዳች ላያጣ እግዚአብሔር ሀብትን፥ ባለጠግነትንና ክብርን ይሰጠዋል፥ የሚደሰትበትን ችሎታ ግን አይሰጠውም። ይልቁንም እነዚህን ነገሮች ሌላው ሰው ይጠቀምባቸዋል። ይህ እንፋሎት፥ ክፉ ስቃይም ነው።
\s5
\v 3 ሰው አንድ መቶ ልጆች ቢወልድና ብዙ ዘመን ቢኖር፥ የዕድሜው ዘመን ቢረዝም፥፥ ልቡ ግን በመልካም ነገር ባይረካ፥ በክብርም ባይቀበር፥ ከዚህ ሰው ይልቅ ሞቶ የተወለደ ሕጻን ይሻላል አልሁ።
\v 4 እንዲህ ያለው ሕጻን እንኳን በከንቱ ይወለዳል በጨለማም ይሄዳል፥ ስሙም አይታሰብም።
\s5
\v 5 ይህ ሕጸን ፀሐይን ባያይ ወይም ምንም ባያውቅ፥ ያኛው ባይኖረውም ለዚህኛው ዕረፍት አለው።
\v 6 ሰው ሁለት ሺህ ዓመት ያህል እንኳን ቢኖር በመልካም ነገሮች ግን መደሰትን ባያውቅ፥ እንደ ሌላው ሁሉ ወደዚያው ስፍራ ይሄዳል።
\s5
\v 7 የሰው ሁሉ ሥራ አፉን ለመሙላት ነው፥ ፍላጎቱ ግን አይሞላም።
\v 8 በርግጥ ከሞኙ ይልቅ የጠቢብ ሰው ብልጫው ምንድነው? ድሃ በሌሎች ሰዎች ፊት እንዴት መመላለስ እንዳለበት ቢያውቅ ምን ብልጫ አለው?
\s5
\v 9 በምኞት ከመቅበዝበዝ በዓይን አይቶ መርካት ይሻላል፥ ይህም ደግሞ እንፋሎትና ንፋስን ለማገድ መሞከር ነው።
\v 10 ለነበረው ሁሉ ቀደም ሲል ስያሜ ተሰጥቶታል፥ ሰው ምን እንደሚመስልም አስቀድሞ ታውቋል። ስለዚህ በሁሉ ላይ ብርቱ ፈራጅ ከሆነው ጋር መከራከር አይረባም።
\s5
\v 11 የሚነገር ቃል ሲበዛ ከንቱነትም ይበዛል፥ ታዲያ ይህ ለሰው ምን ይጠቅመዋል?
\v 12 እንደ ጥላ በሚያልፍበት ከንቱና የተቆጠረ የሕይወት ዘመኑ ለሰው በሕይወቱ መልካም የሆነውን የሚያውቅ ማን ነው? እርሱ ካለፈ በኋላ ከፀሐይ በታች ምን ሊሆን እንዳለ ማን ሊነግረው ይችላል?
\s5
\c 7
\p
\v 1 ከውድ ሽቶ መልካም ስም ይሻላል፥ ከልደት ቀንም የሞት ቀን ይሻላል።
\v 2 ወደ ግብዣ ቤት ከመሄድ ወደ ሀዘን ቤት መሄድ ይሻላል፥ በሕይወቱ መጨረሻ ሰው ሁሉ ሀዘን ይገጥመዋልና፥ ስለዚህ ሕያዋን የሆኑ ሰዎች ይህንን ልብ ማለት አለባቸው።
\s5
\v 3 ከሣቅ ጥልቅ ሐዘን ይሻላል፥ ከፊት ሐዘን በኋላ የልብ ደስታ ይመጣልና።
\v 4 የጠቢብ ልቡ ሐዘን ቤት ውስጥ ነው፥ የሞኞች ልብ ግን በግብዣ ቤት ውስጥ ነው።
\s5
\v 5 የሞኞችን መዝሙር ከመስማት የጠቢብን ተግሳጽ መስማት ይሻላል።
\v 6 ከድስጥ ሥር የሚነድ እሾህ እንደሚንጣጣ የሞኞች ሣቅ ደግሞ እንደዚሁ ነው። ይህም ደግሞ እንፋሎት ነው።
\s5
\v 7 ቀማኛነት ጠቢቡን ሰው ያለጥርጥር ሞኝ ያደርገዋል፥ ጉቦም ልቡን ያበላሸዋል።
\s5
\v 8 የአንድ ነገር መጨረሻ ከጅማሬው ይሻላል፤ በመንፈሳቸው ትዕግስተኞች የሆኑ ሰዎች በመንፈሳቸው ከሚታበዩት ይሻላሉ።
\v 9 በመንፈስህ ለመቆጣት አትቸኩል፥ ቁጣ በሞኞች ልብ ያድራልና።
\s5
\v 10 "ከእነዚህ ይልቅ ያለፉት ዘመናት ለምን ተሻሉ?" አትበል፥ ይህንን የምትጠይቀው ጥበበኛ ስለሆንክ አይደለምና።
\s5
\v 11 ጥበብ ከአባቶቻችን የምንወርሳቸውን ጠቃሚ ነገሮች ያህል መልካም ነው። እርሱ ፀሐይን ለሚያዩ ለእነዚያ ትርፍ ያስገኝላቸዋል።
\v 12 ገንዘብ ጥበቃ ሊሰጥ እንደሚችል ጥበብም ጥበቃን ይሰጣል፥ የዕውቀት ብልጫው ግን ጥበብ ላገኟት ሕይወት መስጠቷ ነው።
\s5
\v 13 የእግዚአብሔርን ሥራ ተመልከት፡ እርሱ ያጣመመውን የትኛውንም ነገር ማን ሊያቃናው ይችላል?
\s5
\v 14 ጊዜው መልካም ሲሆን በደስታ ኑርበት፥ ቀኑ ሲከፋ ግን ይህን አስብ፡ ሁለቱም አጠገብ ለአጠገብ እንዲኖሩ እግዚአብሔር ፈቅዶላቸዋል። በዚህ ምክንያት ማንም ሰው ከእርሱ በኋላ የሚሆነውን የትኛውንም ነገር አያውቅም።
\s5
\v 15 ከንቱ በሆነው የሕይወት ዘመኔ ብዙ ነገሮችን ተመልክቻለሁ። ጻድቃን ቢሆኑም የሚጠፉ ጻድቅ ሰዎች አሉ፥ ክፋትን ቢያደርጉም ረጅም ዘመን የሚኖሩ አመጸኞችም አሉ።
\v 16 ራስህን አታጽድቅ፥ በራስህም ግምት ጠቢብ አትሁን። ለምን ራስህን ታጠፋለህ?
\s5
\v 17 እጅግ አመጸኛ ወይም ሞኝ አትሁን። ለምን ከቀንህ በፊት ትሞታለህ?
\v 18 ይህንን ጥበብ ብትይዝ መልካም ነው፥ ጽድቅንም ከማድረግ እጅህን ባትመልስ። እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ኃላፊነቱን ሁሉ ይወጣልና።
\s5
\v 19 በአንድ ከተማ ውስጥ ካሉ አሥር አስተዳዳሪዎች ይልቅ በጥበበኛ ሰው ውስጥ ያለች ጥበብ ተጽዕኖዋ ትልቅ ነው።
\v 20 መልካምን የሚያደርግና ፈጽሞ ኃጢአትን የማይሠራ አንድም ጻድቅ በምድር ላይ የለም።
\s5
\v 21 የሚነገረውን ቃል ሁሉ አታድምጥ፥ ምናልባት አገልጋይህ ሲረግምህ ትሰማው ይሆናልና።
\v 22 በተመሳሳይ፥ ሌሎችን በልብህ ብዙ ጊዜ እንደረገምካቸው አንተ ራስህ ታውቃለህ።
\s5
\v 23 ይህንን ሁሉ በጥበብ አረጋገጥሁ። እኔም፥ "ጠቢብ እሆናለሁ" አልሁ፥ እርሱ ግን መሆን ከምችለው በላይ ነው።
\v 24 ጥበብ ሩቅና ጥልቅ ናት። ማን ሊያገኛት ይችላል?
\v 25 ለመማርና ለመፈተን፥ ጥበብንና የእውነታን ማብራሪያ ለመፈለግና ክፋት የማይረባ፥ ሞኝነትም ዕብደት መሆኑን ለመረዳት ልቤን መለስሁ።
\s5
\v 26 ልቧ በወጥመድና በመረብ የተሞላ፥ እጆቿም የእግር ብረት የሆኑ የትኛዋም ሴት ከሞት ይልቅ መራራ ናት። እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ማንም ቢሆን ከእርሷ ያመልጣል፥ ኃጢአተኛው ግን በእርሷ ይወሰዳል።
\s5
\v 27 "መርምሬ ያገኘሁትን ተመልከቱ" ይላል አስተማሪው። የእውነታን ፍቺ ለማግኘት በአንደኛው ምርምር ላይ ሌላውን እጨምር ነበር።
\v 28 እስካሁን የምፈልገው ይህንን ነው፥ ነገር ግን አላገኘሁትም። በሺህ ሰዎች መካከል አንድ ጻድቅ አገኘሁ፥ በእነዚያ ሁሉ መካከል ግን አንዲት ሴት አላገኘሁም።
\s5
\v 29 እግዚአብሔር ሰዎችን ቅን አድርጎ እንደ ፈጠራቸው፥ እነርሱ ግን ብዙ ችግሮችን እየፈለጉ ርቀው እንደ ሄዱ ይህንን ብቻ አገኘሁ።
\s5
\c 8
\p
\v 1 ጥበበኛ የሆነ ሰው ማን ነው? በሕይወት ውስጥ የሚያጋጥሙ ሁነቶችን ትርጉም የሚያውቅ ማን ነው? በሰው ውስጥ ያለች ጥበብ ፊቱን ታበራለች፥ የፊቱም ክባዴ ይለወጣል።
\s5
\v 2 እግዚአብሔር ሊጠብቀው ምሎለታልና የንጉሡን ትዕዛዝ እንድትፈጽም እመክርሃለሁ።
\v 3 ንጉሡ ደስ ያለውን ያደርጋልና ከፊቱ በችኮላ አትውጣ፥ ትክክል ላልሆነውም ነገር ድጋፍህን አትስጥ።
\v 4 የንጉሥ ቃል ይገዛል፥ ስለዚህ፥ "ምን እያደረግህ ነው?" ማን ይለዋል?
\s5
\v 5 የንጉሡን ትዕዛዝ የሚጠብቅ ጉዳትን ያርቃል። የጠቢብ ልብ የመተግበሪያ ጊዜንና ተገቢ አካሄድን ያስተውላል።
\v 6 የሰው መከራው ብዙ ነውና ለእያንዳንዱ ጉዳይ ትክክለኛ ምላሽና ምላሹን የሚሰጥበት ጊዜ አለ።
\v 7 ቀጥሎ የሚሆነውን ማንም አያውቅም። ሊመጣ ያለውን ማን ሊነግረው ይችላል?
\s5
\v 8 መተንፈስን ለማቆም በሕይወት እስትንፋስ ላይ ሥልጣን ያለው ማንም የለም፥
\v 9 ደግሞም በሞቱ ቀን ላይ ሥልጣን ያለው ማንም የለም። በጦርነት ጊዜ ከሠራዊቱ የሚሰናበት ማንም የለም፥ አመጻም ባሪያ የሆኑለትን አይታደጋቸውም። ይህንን ሁሉ አስተዋልሁ፤ ከፀሐይ በታች ለሚሠራው ለሁሉም ዓይነት ሥራ ልቤን ሰጠሁ። አንድ ሰው በሌሎች ላይ ክፉ ለማድረግ አቅም የሚያገኝበት ጊዜ አለ።
\s5
\v 10 ስለዚህ አመጸኞች በይፋ ሲቀበሩ አየሁ። ከተቀደሰው አካባቢ ተወስደው ተቀበሩ፥ የአመጽ ሥራቸውን ይሠሩበት የነበረ ከተማ ሰዎችም አመሰገኗቸው። ይህ ደግሞ ከንቱነት ነው።
\v 11 በክፉ ወንጀል ላይ ፍርድ ፈጥኖ በማይሰጥበት ጊዜ፥ ክፋትን እንዲያደርጉ የሰው ልጆችን ልብ ያነሣሣል።
\s5
\v 12 አንድ ኃጢአተኛ መቶ ጊዜ ክፋትን ቢያደርግና ረጅም ዘመን ቢኖር እንኳን እግዚአብሔርን ለሚያከብሩት፥ አብሯቸው መሆኑን ለሚያከብሩ በጎነት እንደሚሆንላቸው አውቃለሁ።
\v 13 ለክፉ ሰው ግን በጎነት አይሆንለትም፤ ሕይወቱም አይረዝምም። እግዚአብሔርን አያከብርምና ዘመኑ ፈጥኖ እንደሚያልፍ ጥላ ነው።
\s5
\v 14 በምድር ላይ የተደረገ ሌላ ከንቱ እንፋሎት አለ። በክፉ ሰዎች ላይ የሚደርሰው በጻድቃኑም ላይ ይደርሳል፥ ለጻድቃኑ የሚደርሰውም ለክፉዎች ሰዎችም ይደርሳል። እኔም፥ ይህ ደግሞ ክፉ እንፋሎት ነው አልሁ።
\v 15 ለሰው ከፀሐይ በታች ከመብላት፥ መጠጣትና መደሰት የሚሻል ነገር ስለሌለው ደስታ ይሻላል እላለሁ። ከፀሐይ በታች እግዚአብሔር በሰጠው የሕይወት ዘመኑ ሁሉ በሚደክምበት ነገር ደስታ አብሮት ይሆናል።
\s5
\v 16 ጥበብን ለማወቅና በምድር ላይ የሚሠራውን ሥራ ለማስተዋል ልቤን በሰጠሁ ጊዜ ብዙ ጊዜ በቀንም ሆነ በሌሊት ያለ እንቅልፍ በሚሠራው ሥራ
\v 17 ከዚያም የእግዚአብሔርን ሥራ ሁሉ ተመለከትሁ ከፀሐይ በታች የሚሠራውን ሥራ ሰው ሊያስተውለው አይችልም። አንድ ሰው መልሶቹን ለማግኘት ምንም ያህል ቢጥር አያገኛቸውም። ጠቢብ ሰው እንድሚያውቅ ቢያምንም እንኳን በርግጥ አያውቅም።
\s5
\c 9
\p
\v 1 ስለ ጻድቃንና ስለ ጥበበኛ ሰዎች፥ ስለ ሥራቸውም፥ ስለ እነዚህ ሁሉ ለመገንዘብ በልቤ አሰብሁ። ሁሉም በእግዚአብሔር እጅ ውስጥ ናቸው። አንድ ሰው ፍቅር ወይም ጥላቻ ይገጥመው እንደሆነ ማንም አያውቅም።
\s5
\v 2 ሁሉም ሰው ተመሳሳይ ዕጣ ፈንታ አለው። ጻድቃንን እና አመጸኞችን፥ መልካምና ክፉ ሰዎችን፥ ንጹሕ የሆኑትንና ያልሆኑትን፥ መሥዋዕት የሚያቀርበውንና የማያቀርበውን ተመሳሳይ ዕጣ ፈንታ ይጠብቃቸዋል። መልካም ሰዎች እንደሚሞቱ ኃጢአተኞችም ደግሞ እንዲሁ ናቸው። የሚምለው ሰው እንደሚሞተው ሁሉ ለመማል የሚፈራው ሰውም ይሞታል።
\s5
\v 3 ከፀሐይ በታች ለተደረገው ሁሉ ክፉ ዕጣ ፈንታ አለው፥ ለሁሉም አንድ መጨረሻ። የሰዎች ልብ በክፋት የተሞላ ነው፥ በሕይወት እያሉም ዕብደት በልባቸው አለ። ከዚያ በኋላ ወደ ሙታን ይሄዳሉ።
\s5
\v 4 ከሞተ አንበሳ በሕይወት ያለ ውሻ እንደሚሻል በሕይወት ላለ ሰውም አሁንም ተስፋ አለው።
\v 5 ሕያዋን ሰዎች እንደሚሞቱ ያውቃሉ፥ ሙታን ግን ምንም አያውቁም። መታሰቢያቸው ተረስቷልና ምንም ብድራት አይኖራቸውም።
\s5
\v 6 ፍቅራቸው፥ ጥላቻቸውና ቅናታቸው ከብዙ ጊዜ በፊት ጠፍቷል። ከፀሐይ በታች በተደረገ በማንኛውም ነገር ዳግም ስፍራ አይኖራቸውም።
\v 7 መንገድህን ሂድ፥ ምግብህን በደስታ ተመገብ፥ በደስተኛ ልብ ወይንህን ጠጣ፥ መልካሙን ሥራህን እግዚአብሔር ተቀብሎታልና።
\v 8 ልብሶችህ ሁልጊዜ ነጭ ይሁኑ፥ ራስህንም በዘይት ተቀባ።
\s5
\v 9 ከፀሐይ በታች እግዚአብሔር በሰጠህ በከንቱ ዘመንህ፥ ከንቱ በሆነው የሕይወት ዘመንህ ሁሉ ከምትወዳት ሚስትህ ጋር በደስታ ኑር። ከፀሐይ በታች ለሆነው ሥራህ ይህ ብድራት ነው። እጅህ ለመሥራት የሚያገኘውን ሁሉ በሙሉ ኃይልህ ሥራ፥
\v 10 በምትሄድበት በመቃብር ስፍራ ሥራ ወይም ገለጻ ወይም እውቀት ወይም ጥበብ በዚያ የለምና።
\s5
\v 11 ከፀሐይ በታች አንዳንድ የሚያስደስቱ ነገሮችን አየሁ፡ ሩጫ ለፈጣኖች አይሆንም። ውጊያ ለብርቱ ሰዎች አይሆንም። እንጀራ ለጥበበኞች ሰዎች አይሆንም። ሀብት ለአስተዋይ ሰዎች አይሆንም። ሞገስ እውቀት ላላቸው ሰዎች አይሆንም። ከዚህ ይልቅ ጊዜና ዕድል በሁሉ ላይ ተጽዕኖ ያደርጋል።
\v 12 ዓሳ በሚሞትበት መረብ እንደሚጠመድ ወይም ወፎች በወጥመድ እንደሚያዙ ማንም ሰው የሚሞትበትን ጊዜ አያውቅም። የሰው ልጆችም ልክ እንደ እንስሳ ድንገት በሚወድቅባቸው ክፉ ጊዜ ይታሰራሉ።
\s5
\v 13 ደግሞም ከፀሐይ በታች ያስገረመኝን ጥበብ አየሁ።
\v 14 ጥቂት ሰዎች ብቻ የሚኖሩባት አንዲት ከተማ ነበረች፥ አንድ ታላቅ ንጉሥ መጣባት፥ ከበባት፥ በዙሪያዋም ታላቅ ምሽግ ገነባባት።
\v 15 በከተማው ውስጥ አንድ ድሃ ጠቢብ ሰው ተገኘ፥ በጥበቡም ከተማይቱን አዳነ። በኋላ ላይ ያንን ድሃ ሰው ማንም አላሰበውም።
\s5
\v 16 እኔም፥ "ጥበብ ከኃይል ይሻላል፥ ነገር ግን የድሃው ጥበብ ተንቋል፥ ቃሎቹም አልተሰሙም" ብዬ ደመደምኩ።
\s5
\v 17 በሞኞች መካከል ከሚጮህ ማንኛውም ገዥ ይልቅ በዝግታ የሚነገሩ የጥበበኞች ሰዎች ቃል ይደመጣል።
\v 18 ከጦር መሣሪያዎች ጥበብ ትሻላለች፥ ነገር ግን አንድ ኃጢአተኛ ብዙ መልካም ነገሮችን ሊያበላሽ ይችላል።
\s5
\c 10
\p
\v 1 የሞቱ ዝንቦች ሽቶን ያገሙታል፥ ትንሽ ሞኝነትም ጥበብና ክብርን ሊጎዳ ይችላል።
\v 2 የጠቢብ ልብ ወደ ቀኝ ያዘነብላል፥ የሞኝ ልብ ግን ወደ ግራው።
\v 3 ሞኝ መንገድ ላይ በሚሄድበት ጊዜ ማስተዋሉ ያነሰ ነው፥ ሞኝነቱን ለሁሉ ያሳውቃል።
\s5
\v 4 አለቃ በቁጣ ቢነሣብህ ሥራህን አትልቀቅ። ትዕግስት ታላቁን ቁጣ ጸጥ ማድረግ ይችላል።
\s5
\v 5 ከፀሐይ በታች ያየሁት ክፉ አለ፥ ያም ከገዝ የሚመጣ ስህተት ነው፡
\v 6 ውጤታማ ሰዎች ዝቅተኛ የሥራ መደብ ሲሰጣቸው ሞኞች የመሪነት ሥራ ተሰጣቸው።
\v 7 ባሪያዎች በፈረስ ተቀምጠው፥ ስኬታማ ሰዎች አንደ ባሪያ በእግራቸው ሲሄዱ አየሁ።
\s5
\v 8 ጉድጓድ የሚቆፍር በዚያ ውስጥ ሊወድቅ ይችላል፥ ካብ የሚያፈርሰውንም እባብ ሊነድፈው ይችላል።
\v 9 ድንጋዮችን የሚፈነቅል በእነርሱ ሊጎዳ ይችላል፥ ግንድ የሚጠርብም አደጋ ይደርስበታል።
\s5
\v 10 የብረቱ መቁረጫ ጫፉ ቢደንዝና ሰው ባይስለው ብዙ ኃይል ሊያወጣበት የግድ ነው፥ ጥበብ ግን ውጤታማ የሚሆንበትን መንገድ ያዘጋጅለታል።
\v 11 ድግምቱ ከመደገሙ በፊት እባብ ቢነድፍ ደጋሚው ምንም አይጠቀምም።
\s5
\v 12 ከጠቢብ ሰው አፍ የሚወጣ ቃል ሞገስ አለው፥ የሞኝ ከንፈር ግን ራሱን ያጠፋዋል።
\s5
\v 13 ከሞኝ አፍ ቃል መውጣት ሲጀምር ሞኝነት አብሮ ይወጣል፥ በመጨረሻም ከአፉ ክፉ ዕብደት ይወጣል።
\v 14 ሞኝ ቃሉን ያበዛል፥ የሚመጣው ምን እንደሆነ ግን ማንም አያውቅም። ከእርሱ በኋላ የሚሆነውን ማን ያውቃል?
\s5
\v 15 ወደ ከተማ የሚወስደውን መንገድ እንኳን እስከማያውቁ ድረስ ሞኞችን ሥራቸው ያደክማቸዋል።
\s5
\v 16 ንጉሣችሁ ወጣት ከሆነና መሪዎቻችሁም ግብዣቸውን በማለዳ የሚጀምሩ ከሆኑ በዚያች ምድር መከራ ይሆናል።
\v 17 ነገር ግን ንጉሣችሁ ከተከበረው ቤተሰብ የተወለደ፥ መሪዎቻችሁ ለመስከር ሳይሆን ለመበርታት በተገቢው ጊዜ ሲመገቡ ምድሪቱ ደስ ይላታል።
\s5
\v 18 በስንፍና ምክንያት ጣሪያ ይዘብጣል፥ በእጅ ሥራ መፍታትም ቤት ያንጠባጥባል።
\v 19 ሰዎች ምግብን ለሣቅ ያዘጋጃሉ፥ ወይን ሕይወትን ደስ ያሰኛል፥ ገንዘብም ፍላጎትን ሁሉ ያሟላል።
\s5
\v 20 በልብህም ቢሆን ንጉሡን አትርገመው፥ በመኝታህም ላይ ባለጸጎችን አትርገም። በሰማይ የሚበር ወፍ ቃልህን ይወስድ ይሆናልና ክንፍ ያለውም ሁሉ ጉዳዩን ሊያሰራጨው ይችላል።
\s5
\c 11
\p
\v 1 እንጀራህን በውሃ ላይ ጣል፥ ከብዙ ቀናት በኋላ መልሰህ ታገኘዋለህ።
\v 2 ከሰባት እንዲያውም ከስምንት ሰዎች ጋር ተካፈለው፥ በምድር ላይ የሚመጣውን ጥፋት አታውቅምና።
\v 3 ደመና ዝናብን ከተሞላ በምድር ላይ ይለቀዋል፥ አንድ ዛፍ ወደ ደቡብ አቅጣጫ ወይም ወደ ሰሜን ቢወድቅ፥ ዛፉ በወደቀበት በዚያው ይኖራል።
\s5
\v 4 ማንም ንፋስን የሚጠባበቅ አይተክልም፥ ደመናንም የሚጠብቅ መከሩን አይሰበስብም።
\v 5 ንፋስ ከየት አቅጣጫ እንደሚመጣ፥ እንዲሁም የሕጻኑ አጥንቶች በእናቱ ማኅፀን ውስጥ እንዴት እንደሚያድግ እንደማታውቅ ሁሉን የፈጠረውን የእግዚአብሔር አሠራር ደግሞ ለማወቅ አትችልም።
\s5
\v 6 በጠዋት ዘርህን ዝራ፤ እስከ ምሽትም ድረስ፥ የሚያስፈልገውን ያህል በእጆችህ ሥራ፤ የትኛው እንደሚበቅል፥ የጠዋቱ ወይም የምሽቱ፥ ይህ ወይም ያኛው፥ ወይም ሁለቱም መልካም ይሆኑ እንደኾነ አታውቅምና።
\v 7 በእውነት ብርሃን ጣፋጭ ነው፥ ፀሐይን ማየትም ለዓይን የሚያስደስት ነገር ነው።
\v 8 ሰው ረጅም ዘመን ቢኖር በእነዚያ ሁሉ ደስ ይበለው፥ ነገር ግን ብዙዎች ናቸውና ሊመጡ ያሉትን ጨለማ ቀናት ያስብ። የሚመጣውም ሁሉ እንደ እንፋሎት ጠፊ ነው።
\s5
\v 9 አንተ ወጣት፥ በወጣትነትህ ደስ ይበልህ፥ በወጣትነትህም ዘመን ልብህን ደስታ ይሙላው። የልብህን መልካም ምኞትና ዓይንህ የሚያየውን ሁሉ ተከተል። ይሁን እንጂ ስለ እነዚህ ነገሮች ሁሉ እግዚአብሔር ወደ ፍርድ እንደሚያመጣህ እወቅ።
\v 10 ከልብህ ቁጣን አስወግድ፥ የትኛውንም በሰውነትህ ያለውን ሕመም ቸል በለው፥ ወጣትነትና ብርታቱ እንፋሎት ነውና።
\s5
\c 12
\p
\v 1 አስቸጋሪዎቹ ቀናት ሳይመጡ፥ "ደስ አያሰኙኝም" የምትላቸው ዓመታትም ሳይደርሱ፥
\v 2 የፀሐይ፥ የጨረቃና የከዋክብት ብርሃን ሳይጨልም፥ የጠቆረው ደመና ከዝናብ ኋላ ሳይመለስ፥ በወጣትነት ዘመንህ ፈጣሪህን አስብ።
\s5
\v 3 ያ ጊዜ የቤተ መንግሥት ጠባቂዎች የሚርበደበዱበት፥ ብርቱዎች የሚጎብጡበት፥ ጥቂቶች በመሆናቸው የሚፈጩት ሥራቸውን የሚያቆሙበት፥ በመስኮት ወደ ውጪ የሚመለከቱ አጥርተው የማያዩበት፥ ይሆናል።
\s5
\v 4 ያ ጊዜ በጎዳናው ላይ በሮች የሚዘጉበትና የወፍጮ ድምጽ የሚቆምበት፥ ከወፍ ድምጽ የተነሣ ሰዎች የሚደነግጡበትና የሚዘምሩ ልጃገረዶች ድምጻቸው ዝግ የሚልበት ይሆናል።
\s5
\v 5 ያ ጊዜ ሰዎች ከፍታዎችንና በመንገድ ላይ የሚገጥማቸውን አደጋ በማሰብ የሚፈሩበት፥ የለውዝ ዛፍ ሲያብብ፥ አንበጣዎች ተከታትለው ሲሳቡ፥ ተፈጥሯዊ ፍላጎት የሚጠፋበት ጊዜ ነው። ሰው ወደ ዘላለም ቤቱ ይሄዳል፥ አልቃሾችም በጎዳናዎቹ ላይ ይወርዳሉ።
\s5
\v 6 የብር ሰንሰለት ሳይበጠስ ወይም ጎድጓዳው የወርቅ ሳሕን ሳይሰበር ወይም እንስራው በምንጩ አጠገብ ብትንትኑ ሳይወጣ ወይም የውሃ ማውጫው ጉድጓዱ ውስጥ ሳይበጠስ፥
\v 7 አፈር ወደ መጣበት መሬት ሳይመለስና መንፈስም ወደ ሰጪው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ ፈጣሪህን አስብ።
\s5
\v 8 አስተማሪው፥ "የሚተን እንፋሎት፥ ሁሉም ነገር የሚጠፋ እንፋሎት ነው" ይላል።
\v 9 አስተማሪው ጠቢብ ነበር፥ ለሕዝቡም እውቀትን አስተማረ። ብዙ ምሳሌዎችን መረመረና አጠና፥ በስርዓትም አስቀመጣቸው።
\s5
\v 10 አስተማሪው ግልጽና ቅን የእውነት ቃላትን በመጠቀም ለመጻፍ ፈለገ።
\v 11 የጠቢባን ቃል አንደ ከብት መንጃ አርጩሜ ነው። ጠልቀው እንደ ገቡ ሚስማሮች አንድ እረኛ ያስተማራቸውና አስተማሪዎች የሰበሰቧቸው ምሳሌዎችም እንዲሁ ናቸው።
\s5
\v 12 ልጄ ሆይ፥ በይበልጥ አንድ ነገር ተጠንቀቅ፡ ብዙ መጻሕፍት መጻፍ ማለቂያ የለውም። ብዙ ማጥናትም ሰውነትን ያደክማል።
\s5
\v 13 ሁሉም ነገር ከተሰማ በኋላ የጉዳዩ መጨረሻ እግዚአብሔርን እንድትፈራውና ትዕዛዙን እንድትጠብቅ ነው፥ ይህ የሰው ሙሉ ተግባሩ ነውና።
\v 14 መልካምም ይሁን ክፉ፥ የተደረገውን ሁሉ፥ ከተሰወረው ነገር ሁሉ ጋር፥ እግዚአብሔር ወደ ፍርድ ያመጣዋልና።