am_ulb/20-PRO.usfm

1867 lines
132 KiB
Plaintext

\id PRO
\ide UTF-8
\h ምሳሌ
\toc1 ምሳሌ
\toc2 ምሳሌ
\toc3 pro
\mt ምሳሌ
\s5
\c 1
\p
\v 1 የእስራኤል ንጉስ፣ የዳዊት ልጅ የሰለሞን ምሳሌዎች፡፡
\v 2 እነዚህ ምሳሌዎች የተጻፉት ጥበብንና ተግሳጽን፣ አርቆ ለማስተዋል የሚያስችሉ ቃላትን፣
\v 3 እርማትን በመቀበል ጽድቅ፣ ፍትሕና ሚዛናዊ የሆነ ብያኔን በማድረግ እንድትኖር ለማስተማር ነው፡፡
\s5
\v 4 ከዚህ በተጨማሪ እነዚህ ምሳሌዎች የተጻፉት ላልተማሩ ጥበብን፣ ለወጣቶች ደግሞ እውቀትንና ልባምነትን ለመስጠት ነው፡፡
\v 5 ጥበበኞች ያድምጡና ትምህርታቸውን ያዳብሩ፣ አስተዋዮች ደግሞ ምሪትን ያግኙበት፣
\v 6 ይህ ደግሞ የጠቢባንን ምሳሌዎች፣ አባባሎችና ቃላቶች እንደዚሁም እንቆቅልሾቻቸውን እንዲረዱ ነው፡፡
\s5
\v 7 እግዚአብሔርን መፍራት የጥበብ መጀመርያ ነው፣ ሞኞች ግን ጥበብንና ተግሳጽን ይንቃሉ፡፡
\v 8 ልጄ ሆይ፣ የአባትህን ምክር ስማ፣ የእናትህንም ሕግ አትተው፤
\v 9 ለራስህ የሞገስ አክሊል፣ ለአንገትህ ደግሞ ውበት የሚሰጥ ጌጥ ይሆኑልሃል፡፡
\s5
\v 10 ልጄ ሆይ፣ ኃጢአተኞች በኃጢአታቸው እንድትሳተፍ ሊያባብሉህ ቢሞክሩ፣ እሺ አትበላቸው፡፡
\v 11 “ከእኛ ጋር ና፣ ነፍስ ለመግደል ተደብቀን እንጠብቅ፣ ንጹሐን ሰዎችን ያለ ምንም ምክንያት ለማትፋት እንሸምቅበት፡፡
\s5
\v 12 ሲኦል ጤናማ ሰዎችን እንደሚውጣቸው፣ ወደ ጉድጓድ እንደሚወርዱ፣ እንዲሁ በሕይወት እያሉ እንዋጣቸው፡፡
\v 13 ሁሉም አይነት ውድ የሆኑ ነገሮች እናገኛለን፤ ከሌሎች ሰዎች በሰረቅናቸው ነገሮች ቤቶቻችንን እንሞላለን፡፡
\v 14 ከእኛ ጋር ዕጣህን ጣል፤ ሁላችንም አንድ የጋራ ቦርሳ ይኖረናል፡፡” ቢሉህ፣
\s5
\v 15 ልጄ ሆይ፣ ከእነርሱ ጋር በዚያ መንገድ አትሂድ፤ እነርሱ በሚሄዱበት መንገድ እግርህ አይርገጥ፤
\v 16 እግሮቻቸው ወደ ክፋት ይሮጣሉ፣ ደም ለማፍሰስም ይቸኩላሉ፡፡
\v 17 ወፍ ፊት ለፊት እያየች ወፍን ለመያዝ ወጥመድ መዘርጋት ጥቅም የለውም፡፡
\s5
\v 18 እነዚህ ሰዎች ራሳቸውን ለመግደል ተደብቀው ይጠብቃሉ፣ በራሳቸው ላይ ወጥመድን ይዘረጋሉ፡፡
\v 19 ፍትሃዊ ባልሆነ መንገድ ሀብትን ያከማቹ ሰዎች መንገዳቸው እንደዚህ ነው፣ ፍትሃዊ ባልሆነ መንገድ የተከማቸ ሃብት የባለቤቱን ሕይወት ያጠፋል፡፡
\s5
\v 20 ጥበብ በጎዳና ላይ ጮኻ ትጣራለች፣ በአደባባይም ድምጿን ከፍ ታደርጋለች፤
\v 21 ጩኸት በበዛባቸው ጎዳናዎች ላይ ትጣራለች፣ በከተማ መግቢያ በሮች ላይ እንዲህ በማለት ትናገራለች፣
\v 22 እናንተ ጥበብ የሌላችሁ አላዋቂነትን የምትወዱት እስከ መቼ ነው? እናንተ ፌዘኞች በፌዝ የምትደሰቱት እስከ መቼ ነው? እናንተ ሞኞች እውቀትን የምትጠሉት እስከ መቼ ነው?
\s5
\v 23 ለዘለፋየ ትኩረት ስጡ፤ ሃሳቤን ሁሉ ለእናንተ አፈስሳለሁ፤ ቃሎቼን አሳውቃችኋለሁ፡፡
\v 24 ጠራኋችሁ፣ እናንተ ግን ለመስማት እምቢ አላችሁ፤ እጄን ለእናንተ ዘረጋሁ፣ ነገር ግን አንድም ሰው ትኩረት አልሰጠውም፡፡
\v 25 ነገር ግን እናንተ ተግሳጼን በሙሉ ችላ አላችሁ፣ ለዘለፋየ ደግሞ ትኩረት አልሰጣችሁም፡፡
\s5
\v 26 እኔ ደግሞ በመከራችሁ እስቃለሁ፣ ሽብር በመጣባችሁ ጊዜ አላግጥባችኋለሁ፣
\v 27 አስፈሪ ድንጋጤ እንደ ማዕበል በእናንተ ላይ ሲመጣባችሁ፣ ጥፋት እንደ አውሎ ነፋስ እናንተን ሲጠራርጋችሁ፣ ጭንቅና ችግር በእናንተ ላይ በመጣ ጊዜ፡፡
\s5
\v 28 በዚያን ጊዜ ይጠሩኛል፣ እኔም አልመልስላቸውም፤ አጥብቀው ይፈልጉኛል፣ ነገር ግን አያገኙኝም፡፡
\v 29 እውቀትን ስለ ጠሉ፣ እግዚአብሔርን መፍራት ስላልመረጡ፣
\v 30 ምክሬን አልተከተሉምና፣ ዘለፋየንም ሁሉ ናቁ፡፡
\s5
\v 31 የመንገዳቸውን ፍሬ ይበላሉ፣ በእቅዳቸው ፍሬ ይጠግባሉ፡፡
\v 32 እነዚህ ያልተማሩ ሰዎች ከእውቀት መራቃቸው ይገድላቸዋል፣ ሞኞችንም ቸልተኝነታቸው ያጠፋቸዋል፡፡
\v 33 ነገር ግን የሚያደምጠኝ ሁሉ በሰላም ይኖራል፣ ከመከራም ስጋት ያርፋል፡፡
\s5
\c 2
\p
\v 1 ልጄ ሆይ፣ ቃሎቼን ብትቀበልና ትእዛዛቴን በአንተ ዘንድ ብታኖር፣
\v 2 ጥበብን ብታደምጥና ልብህን ወደ እውቀት ብትመልስ፡፡
\s5
\v 3 እውቀትን ለማግኘት ብትጣራና ድምጽህን ከፍ አድርገህ ለማስተዋል ብትጮህ፣
\v 4 ብርን አጥብቀህ እንደምትፈልግ እርስዋንም ብትፈልጋት፣ የተሰወረ ሃብትን እንደምትፈልግ እንደዚሁ ማስተዋልን ብትሻት፣
\v 5 በዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን መፍራት ታውቃለህ፣ የአምላክንም እውቀት ታገኛለህ፡፡
\s5
\v 6 እግዚአብሔር ጥበብን ይሰጣልና፣ እውቀትና ማስተዋል ከአንደበቱ ይወጣሉ፡፡
\v 7 እርሱ ደስ ለሚያሰኙት ጥልቅ ጥበብን ያከማቻል፣ ያለ ነቀፋ ለሚሄዱ ጋሻ ነው፣
\v 8 የፍትህን መንገድ ይጠብቃል፣ ለእርሱ ታማኞች ለሆኑት ደግሞ መንገዳቸውን ያጸናል፡፡
\s5
\v 9 በዚያን ጊዜ ጽድቅን፣ ፍትህንና ሚዛናዊነትን እንደዚሁም ማንኛውንም መልካም መንገድ ትገነዘባለህ፡፡
\v 10 ጥበብ ወደ ልብህ ትመጣለችና፣ እውቀትም ነፍስህን ደስ ታሰኛለች፡፡
\s5
\v 11 የመለየት ችሎታ ይጠብቅሃል፣ ማስተዋል ይጋርድሃል፡፡
\v 12 እነዚህ ከክፋት መንገድ፣ ጠማማ ንግግር ከሚናገሩ ሰዎች፣
\v 13 ትክክለኛውን መንገድ ከተዉና በጨለማ መንገድ ከሚሄዱ ይጠብቁሃል፡፡
\s5
\v 14 እነዚህ ክፋትን ሲያደርጉ ደስ ይላቸዋል፣ በጠማማነት ሃሴት ያደርጋሉ፡፡
\v 15 ጠማማ መንገድን ይከተላሉ፣ አካሄዳቸውን ደግሞ በአታላይነታቸው ይደብቃሉ፡፡
\s5
\v 16 ጥበብና ልባምነት ከአመንዝራ፣ ከጀብደኛና በንግግሯ ከምታታልል ሴት ያድኑሃል፡፡
\v 17 ይህች ሴት የወጣትነት በልዋን የተወችና የአምላክዋን ቃል ኪዳን የረሳች ናት፡፡
\s5
\v 18 ቤቷ ወደ ሞት ያዘነበለ ስለሆነ አካሄዷ በመቃብር ወዳሉት ሙታን ይመራሃል፡፡
\v 19 ወደ እርስዋ የሚገቡ ሁሉ እንደገና አይመለሱም፣ የሕይወትንም መንገድ አያገኙም፡፡
\s5
\v 20 ስለዚህ አንተም በመልካም ሰዎች መንገድ ትሄዳለህ፣ የጻድቃንን መንገድ ትከተላለህ፡፡
\v 21 ጻድቃን ቤታቸውን በምድሪቱ ይሰራሉና፣ እነዚህ ነቀፋ የሌለባቸው ደግሞ በእርሷ ጸንተው ይኖራሉና፡፡
\v 22 ክፉዎች ግን ከምድሪቱ ይቆረጣሉ፣ ታማኝነት የሌላቸውም ከእርሷ ይወገዳሉ፡፡
\s5
\c 3
\p
\v 1 ልጄ ሆይ፣ ትእዛዛቴን አትርሳ፣ ትምህርቴንም በልብህ ጠብቅ፣
\v 2 በሕይወትህ ብዙ ቀኖችንና ዓመቶችን እንደዚሁም ሰላምን ይጨምሩልሃል፡፡
\s5
\v 3 በኪዳን የተመሰረተ ታማኝነትና እውነተኛነት አይለዩህ፣ በአንገትህ ዙርያ በአንድ ላይ እሰራቸው፣ በልብህም ጽላት ላይ ጻፋቸው፡፡
\v 4 በዚያን ጊዜ ሞገስና መልካም ስም በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ታገኛለህ፡፡
\s5
\v 5 በሙሉ ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፣ በራስህም ማስተዋል ላይ አትደገፍ፤
\v 6 በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፣ እርሱም መንገድህን ቀና ያደርገዋል፡፡
\s5
\v 7 በራስህ አስተያየት ጥበበኛ አትሁን፤ እግዚብሔርን ፍራ፣ ከክፉም ራቅ፡፡
\v 8 ይህም ለስጋህ ፈውስ፣ ለሰውነትህም መታደስ ይሆንልሃል፡፡
\s5
\v 9 እግዚአብሔርን በሀብትህና በምርትህ ሁሉ በኩራት አክብረው፣
\v 10 ጎተራህ ሙሉ ይሆናል፣ ገንዳህ ደግሞ በአዲስ ወይን ጠጅ ተትረፍርፎ ይሞላል፡፡
\s5
\v 11 ልጄ ሆይ፣ የእግዚአብሔርን ቅጣት አትናቅ፣ ተግሳጹንም አትጥላ፣
\v 12 አባት ደስ የሚሰኝበትን ልጁን እንደሚቀጣ እንደዚሁ እግዚአብሔርም የሚወዳቸውን ይቀጣልና፡፡
\s5
\v 13 ጥበብን የሚያገኛት ሰው ደስተኛ ነው፣ እውቀትንም ያገኛል፡፡
\v 14 ከጥበብ የምታገኘው ጥቅም ብር ከሚሰጥህ ትርፍ ይልቅ እጅግ ይበልጣል፣ የጥበብ ትርፍ ከወርቅም ይበልጣል፡፡
\s5
\v 15 ጥበብ ከከበረ ዕንቁ ይልቅ እጅግ ውድ ናት፣ አንተ ከምትመኘው ነገር ሁሉ እርሷን የሚተካከላት ምንም ነገር የለም፡፡
\v 16 በቀኝ እጇ ረጅም ዕድሜ አለ፤ በግራ እጇ ደግሞ ባለጠግነትንና ክብርን ይዛለች፡፡
\s5
\v 17 መንገዷ የደግነት መንገድ ነው፣ ጎዳናዋም ሰላም ነው፡፡
\v 18 እርሷ አጥብቀው ለሚይዟት የሕይወት ዛፍ ናት፣ የሚደገፉባትም ደስተኞች ናቸው፡፡
\s5
\v 19 እግዚአብሔር በጥበብ ምድርን መሰረተ፣ ሰማያትን ደግሞ በማስተዋል አጸና፡፡
\v 20 በእወቀቱ ጥልቆች ተሰንጥቀው ተከፈቱ፣ ደመናትም ጠልን አንጠበጠቡ፡፡
\s5
\v 21 ልጄ ሆይ፣ ትክክለኛ ፍርድንና ነገሮችን በሚገባ መለየትን ጠብቅ፣ እነዚህ ከእይታህ አይራቁ፡፡
\v 22 እነዚህ ለነፍስህ ሕይወት፣ በአንገትህ ዙርያ የምታስራቸው የሞገስ ጌጥ ይሆናሉ፡፡
\s5
\v 23 በዚያን ጊዜ በመንገድህ ተማምነህ በሰላም ትራመዳለህ፣ እግርህም አይሰናከልም፤
\v 24 በምትተኛበት ጊዜ አትፈራም፤ ስትተኛ እንቅልፍህ ጣፋጭ ይሆናል፡፡
\s5
\v 25 በድንገተኛ ሽብርና በክፉዎች አማካይነት በሚደርስ ጥፋት አትፍራ፣
\v 26 እግዚአብሔር በአጠገብህ ይሆናልና፣ እግርህም በወጥመድ እንዳያያዝ ይጠብቅሃልና፡፡
\s5
\v 27 ልታደርግ የሚቻልህ ሲሆን፣ ለሚገባቸው ሰዎች መልካምን ነገር ከማድረግ አትከልክል፡፡
\v 28 አሁን በእጅህ ገንዘብ እያለ ለጎረቤትህ “አሁን ሂድ፣ እንደገና ተመልሰህ ና፣ ነገ እሰጥሃለሁ” አትበለው፡፡
\s5
\v 29 በአጠገብህ የሚኖረውንና በአንተ የሚተማመነውን ጎረቤትህን ለመጉዳት አትምከርበት፡፡
\v 30 አንድ ሰው አንተን ለመጉዳት ክፉ ካልሰራብህ ያለ በቂ ምክንያት ከዚህ ሰው ጋር አትከራከር፡፡
\s5
\v 31 በክፉ ሰው አትቅና፣ የትኛውንም መንገዱን አትምረጥ፡፡
\v 32 ጠማማ ሰው በእግዚብሔር ፊት የተጠላ ነውና፣ ቅን ሰውን ግን ወዳጁ ያደርገዋል፡፡
\s5
\v 33 የእግዚአብሔር እርግማን በክፉ ሰዎች ቤት ላይ ነው፣ የጻድቃንን ቤት ግን ይባርካል፡፡
\v 34 እርሱ በፌዘኞች ላይ ያፌዛል፣ ለትሁታን ግን ሞገሱን ይሰጣቸዋል፡፡
\s5
\v 35 ጥበበኞች ክብርን ይወርሳሉ፣ የሞኞች ከፍታ ግን ውርደታቸው ነው፡፡
\s5
\c 4
\p
\v 1 ልጆች ሆይ፣ የአባትን ተግሳጽ አድምጡ፣ ማስተዋል ምን እንደሆነ እንድታውቁ ልብ በሉ፡፡
\v 2 እኔ መልካም ትምህርት እሰጣችኋለሁ፣ ትምህርቴን አትተዉ፡፡
\s5
\v 3 የአባቴ ልጅ ሳለሁ፣ ለእናቴም ተወዳጅና ብቸኛ ልጅ ሳለሁ፣
\v 4 አባቴ አስተማረኝ፣ እንዲህም አለኝ፡- “ቃሎቼን ሁሉ በልብህ ያዝ፤ ሕግጋቴን ጠብቅ በሕይወትም ኑር፡፡”
\s5
\v 5 ጥበብንና ማስተዋልን አግኝ፤ የአፌን ቃላቶች አትርሳ፣ እነርሱንም አትተው፤
\v 6 ጥበብን አትተዋት፣ እርሷ ከለላ ትሆንሃለች፤ ውደዳት፣ ትጠብቅሃለች፡፡
\s5
\v 7 ጥበብ እጅግ በጣም ጠቃሚ ናት፣ ስለዚህ ጥበብን አግኛት፣ ያለህን ሀብት ሁሉ ከፍለህ ማስተዋልን የራስህ አድርጋት፡፡
\v 8 ለጥበብ ከፍተኛ ስፍራ ስጣት፣ እርሷም ከፍ ከፍ ታደርግሃለች፤ እርሷን አጥብቀህ ስትይዛት ታከብርሃለች፡፡
\v 9 በራስህ ላይ የክብር አክሊል ታስቀምጥልሃለች፤ ውብ የሆነ ዘውድም ትሰጥሃለች፡፡
\s5
\v 10 ልጄ ሆይ፣ አድምጠኝ፣ ለቃሎቼም ትኩረት ስጥ፣ በሕይወት ዘመንህም ብዙ አመታት ይጨመሩልሃል፡፡
\v 11 በጥበብ ጎዳና አስተምርሃለሁ፤ በቀጥተኛ መንገዶችም እመራሃለሁ፡፡
\v 12 በምትራመድበት ጊዜ ማንም በመንገድህ ላይ አይቆምም፣ በሮጥህ ጊዜ አትሰናከልም፡፡
\s5
\v 13 ምክርን ያዝ፣ አትልቀቀው፤ ጠብቀው፣ እርሱ ሕይወትህ ነውና፡፡
\v 14 የክፉዎችን መንገድ አትከተል፣ ክፋትን በሚያደርጉ ሰዎች መንገድ አትሂድ፡፡
\v 15 ከእርሷ ራቅ፣ በዚያ አትሂድ፤ ከዚያ ተመለስ፣ በሌላ መንገድ ሂድ፡፡
\s5
\v 16 ክፋትን እስኪፈጽሙ ድረስ መተኛት አይችሉምና፣ አንድ ሰው እስኪያሰናክሉ ድረስ እንቅልፋቸው አይመጣምና፡፡
\v 17 የክፋትን እንጀራ ይበላሉና፣ የአመጽንም ወይን ጠጅ ይጠጣሉና፡፡
\s5
\v 18 ጽድቅን የሚያደርግ ሰው መንገድ ግን እየፈካ እንደሚሔድ የንጋት ብርሃን ነው፤ ሙሉ ቀን እስከሚሆን ድረስ ብርሃኑ የበለጠ እየጨመረ ይሄዳል፡፡
\v 19 የክፉዎች መንገድ ግን እንደ ጨለማ ነው፣ምን እንደሚያሰናክላቸው በፍጹም አያውቁም፡፡
\s5
\v 20 ልጄ ሆይ፣ ቃሎቼን ልብ በል፣ ንግግሮቼን አድምጥ፡፡
\v 21 ከአይኖችህ አይራቁ፣ በልብህ ውስጥ ጠብቃቸው፡፡
\s5
\v 22 ቃሎቼ ለሚያገኘኟቸው ሰዎች ሕይወት፣ ለመላው ሰውነታቸውም ፈውስ ናቸውና፡፡
\v 23 ልብህን በጥንቃቄ ጠብቅ፣ በትጋትም ከልለው፣ የሕይወት ምንጭ የሚፈልቀው ከእርሱ ነውና፡፡
\s5
\v 24 ጠማማ ንግግርን ከአንተ አስወግድ፣ ብልሹ ወሬ ከአንተ አርቅ፡፡
\v 25 ዓይኖችህ ወደ ፊት በቀጥታ ይመልከቱ፣ በቀጥታ ፊት ለፊት አተኩረህ እይ፡፡
\s5
\v 26 ለእግርህ ደልዳላ ጎዳና አበጅለት፤ ከዚያ በኋላ መንገድህ በሙሉ አስተማማኝ ይሆናል፡፡
\v 27 ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ አትበል፤ እግርህን ከክፉ መልስ፡፡
\s5
\c 5
\p
\v 1 ልጄ ሆይ፣ ለጥበቤ ትኩረት ስጥ፤ የማስተዋል ቃሌንም በጥንቃቄ አድምጥ፡፡
\v 2 ይህም ልባምነትን ትማር ዘንድ፣ ከንፈሮችህም እውቀትን ይጠብቁ ዘንድ ነው፡፡
\s5
\v 3 የአመንዝራ ሴት ከንፈር ማርን ያንጠባጥባልና፣ አንደበቷም ከዘይት ይልቅ የለሰለሰ ነውና፣
\v 4 ነገር ግን ፍጻሜዋ እንደ እሬት መራራ ናት፣ እንደ ስለታም ሰይፍ የምትቆርጥ ናት፡፡
\s5
\v 5 እግሮቿ ወደ ሞት ይወርዳሉ፣ እርምጃዎቿም ወደ ሲኦል መንገድ ይሄዳሉ፡፡
\v 6 ስለ ሕይወት መንገድ ምንም አታስብም፡፡ አረማመዷ የተቅበዘበዘ ነው፣ ወዴት እንደምትሄድም አታውቅም፡፡
\s5
\v 7 አሁንም ልጆቼ ሆይ፣ አድምጡኝ፣ የአፌን ቃል ከማድመጥ ፈቀቅ አትበሉ፡፡
\v 8 መንገድህን ከእርሷ አርቅ፣ ወደ ቤቷም በር አትቅረብ፡፡
\s5
\v 9 እንዲህ ካደረግህ ክብርህን ለሌሎች ሰዎች፣ የሕይወት ዘመንህንም ለጨካኝ ሰው አሳልፈህ አትሰጥም፤
\v 10 ባዕዳን በሀብትህ አይፈነጥዙም፣ የደከምክበት ነገር ወደ ባዕዳን ቤት አይገባም፡፡
\s5
\v 11 በሕይወትህ መጨረሻ ስጋህና ሰውነትህ ሲጠፋ ታቃስታለህ፡፡
\v 12 እንዲህም ትላለህ፡- “ተግሳጽን እንዴት ጠላሁ፣ መታረምን ልቤ ናቀ!
\s5
\v 13 አስተማሪዎቼን አልታዘዝሁም፣ አሰልጣኞቼንም አላደመጥሁም፡፡
\v 14 በጉባኤና ሰዎች በተሰበሰቡበት መካከል ሙሉ በሙሉ ወደ ጥፋት ተቃርቤ ነበር፡፡”
\s5
\v 15 ከማጠራቀሚያህ ውሃ ጠጣ፣ ከጉድጓድህም የሚፈልቀውን ውሃ ጠጣ፡፡
\v 16 ምንጮችህ በሁሉም ቦታ ያለገደብ ሊፈስሱ፣ ወንዞችህስ በአደባባዩ ሁሉ ሊጎርፉ ይገባልን?
\v 17 እነርሱ ለአንተ ብቻ ይሁኑ፣ ከአንተ ጋር ላሉ ባዕዳን አይሁኑ፡፡
\s5
\v 18 ምንጭህ የተባረከ ይሁን፣ በወጣትነት ሚስትህም ደስ ይበልህ፡፡
\v 19 ምክንያቱም እርሷ በፍቅር እንደተሞላች ዋላ፣ ግርማ ሞገስ እንዳላትም ሚዳቋ ናት፡፡ ጡቷም ሁልጊዜ ያስደስትህ፣ ሁልጊዜም በፍቅሯ ተማረክ፡፡
\s5
\v 20 ልጄ ሆይ፣ ስለምን በጋለሞታ ሴት ትማረካለህ፤ የሌላይቱንስ ሴት ሰውነት ለምን ታቅፋለህ?
\v 21 እግዚአብሔር ሰው የሚሰራውን በሙሉ ያያል፣ የሚሄድበትንም መንገድ ሁሉ ይመለከታል፡፡
\s5
\v 22 ክፉ ሰው በራሱ ኃጢአት ይጠመዳል፤ የኃጢአቱም ገመድ አጥብቆ ይይዘዋል፡፡
\v 23 አልተቀጣምና ይሞታል፤ ከሞኝነቱም ብዛት የተነሳ መንገድ ይስታል፡፡
\s5
\c 6
\p
\v 1 ልጄ ሆይ፣ ጎረቤትህ ለወሰደው ብድር ዋስ ብትሆንና ገንዘብህን ለዋስትና ብታስይዝ፣ የማታውቀው ሰው ለወሰደው ብድር መተማመኛ ሰጥተህ ከሆነ፣
\v 2 የዚያን ጊዜ በቃልህ ምክንያት በራስህ ላይ ወጥመድ ዘርግተሃል፣ በአፍህም ቃል ተጠምደህ ተይዘሃል፡፡
\s5
\v 3 ልጄ ሆይ፣ ይህን አድርግ፣ ራስህንም አድን፣ አንተ በጎረቤትህ ምህረት ስር ነህና፡፡ ሂድ፣ ጎረቤትህም እንዲተውህ ሄደህ በትህትና ለምነው፡፡
\s5
\v 4 ለአይንህ እንቅልፍን ለሽፋሽፍቶችህም እንጉልቻን አትስጥ፡፡
\v 5 የሜዳ ፍየል ከአዳኝ እጅ፣ ወፍም ከአጥማጅ እጅ እንደምታመልጥ እንዲሁ ራስህን አድን፡፡
\s5
\v 6 አንተ ሰነፍ ሰው፣ ወደ ጉንዳን ተመልከት፣ መንገዷን አስተውል፣ ጥበበኛም ሁን፡፡
\v 7 አዛዥ፣ አለቃ ወይም ገዥ የላትም፣
\v 8 ይሁን እንጂ ምግቧን በበጋ ታዘጋጃለች፣ በመኸር ደግሞ የምትበላውን ታከማቻለች፡፡
\s5
\v 9 አንተ ሰነፍ፣ የምትተኛው እስከ መቼ ነው? ከእንቅልፍህስ የምትነሣው መቼ ነው?
\v 10 “ጥቂት ማንቀላፋት፣ ጥቂት ማንጎላቸት፣ ጥቂት እጅን አጣጥፎ ማረፍ”
\v 11 ድህነትህ እንደ ወንበዴ፣ ችግርህም መሳርያ እንደ ታጠቀ ወታደር ይመጣብሃል፡፡
\s5
\v 12 የማይረባ፣ ክፉ ሰው፣ በጠማማ ንግግሩ ይኖራል፣
\v 13 በዓይኑ ይጠቅሳል፣ በእግሩም ምልክት ያስቀምጣል፣ በጣቶቹም ይጠቁማል፡፡
\s5
\v 14 በልቡ ውስጥ ባለው አጭበርባሪነት ክፋትን ይዶልታል፣ ግጭትንም ሁልጊዜ ይጭራል፡፡
\v 15 ስለዚህ ጥፋቱ ሳይታሰብ በቅጽበት ይደርስበታል፤ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደማይድን ሆኖ ይሰበራል፡፡
\s5
\v 16 እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች አሉ፣ የሚጸየፋቸውም ሰባት ናቸው፡-
\s5
\v 17 የትዕቢተኛ ሰው አይን፣ ሐሰትን የሚናገር ምላስ፣ የንጹሃን ሰዎችን ደም የሚያፈስስ እጅ፣
\v 18 ክፋትን የሚፈጥር ልብ፣ ክፋት ለማድረግ በፍጥነት የሚሮጥ እግር፣
\v 19 ውሸትን የሚለፈልፍ ምስክር፣ በወንድማማቾች መካከል ብጥብጥ የሚዘራ ሰው፡፡
\s5
\v 20 ልጄ ሆይ፣ የአባትህን ትዕዛዝ ፈጽም፣ የእናትህንም ትምህርት አትተው፡፡
\v 21 ሁልጊዜ በልብህ አኑራቸው፣ በአንገትህም ዙርያ እሰራቸው፡፡
\s5
\v 22 ስትሄድ፣ ይመሩሃል፤ በተኛህ ጊዜ ይጠብቁሃል፤ በነቃህም ጊዜ ያስተምሩሃል፡፡
\v 23 ትዕዛዛቱ መብራት ናቸው፣ ትምህርቱም ብርሃን ነው፤ የተግሳጽም ዘለፋዎች የሕይወት መንገድ ናቸውና፡፡
\s5
\v 24 ከምግባረ ብልሹ ሴት፣ ከአመንዝራ ሴትም ጣፋጭ ቃላት ይጠብቅሃል፡፡
\v 25 በልብህ ውበቷን አትመኝ፣ በሽፋሽፍትዋም አትጠመድ፡፡
\s5
\v 26 ከጋለሞታ ሴት ጋር መተኛት የአንድ ቁራሽ ዳቦ ዋጋ ያሳጣሃል፤ ከሌላ ሰው ሚስት ጋር መተኛት ግን ሕይወትህን ያሳጣሃል፡፡
\v 27 አንድ ሰው ልብሱ ሳይቃጠል በደረቱ እሳት መያዝ ይችላልን?
\s5
\v 28 አንድ ሰው እግሩ ሳይቃጠል በፍም ላይ መራመድ ይችላልን?
\v 29 ከጎረቤቱ ሚስት ጋር የሚተኛም ሰው እንዲሁ ነው፤ ከእርሷ ጋር የሚተኛም ሳይቀጣ አይቀርም፡፡
\s5
\v 30 ሌባ በተራበ ጊዜ ፍላጎቱን ለማሟላት ቢሰርቅ ሰዎች አይንቁትም፡፡
\v 31 ሆኖም ሌባው ሲሰርቅ ከተያዘ፣ የሰረቀውን ሰባት እጥፍ ይመልሳል፤ በቤቱም ያለውን ንብረት ሁሉ መስጠት አለበት፡፡
\s5
\v 32 የሚያመነዝር ሰው አእምሮው አያመዛዝንም፤ እንዲህ የሚያደርግ ራሱን ያጠፋል፡፡
\v 33 ቁስልና ውርደት ይገባዋል፣ ውርደቱም አይደመሰስለትም፡፡
\s5
\v 34 ቅናት ሰውን ቁጡ ያደርገዋልና፤ በሚበቀልበት ጊዜ ምህረትን አያደርግም፡፡
\v 35 እርሱ ምንም ዓይነት ካሳ አይቀበልም፣ ብዙ ስጦታዎችን ብታቀርብለትም እሺ አይልም፡፡
\s5
\c 7
\p
\v 1 ልጄ ሆይ፣ ቃሎቼን ጠብቅ፣ ትእዛዜንም በአንተ ውስጥ አኑር፡፡
\v 2 ትእዛዜን ጠብቅ በሕይወትም ኑር፣ ሕጌንም እንደ ዓይንህ ብሌን ጠብቅ፡፡
\v 3 በጣቶችህም ላይ እሰራቸው፤ በልብህም ጽላት ጻፋቸው፡፡
\s5
\v 4 ጥበብ “አንቺ እህቴ ነሽ” በላት፣ ማስተዋልን ደግሞ ዘመዴ ብለህ ጥራው፣
\v 5 ከአመንዝራ ሴት፣ ቃሏንም ከምታለዝብ ከዘማዊም ሴት ትጠብቅህ ዘንድ፡፡
\s5
\v 6 በቤቴ መስኮት ላይ ሆኜ ወደ ውጭ ተመለከትሁ፣
\v 7 ብዙ እውቀት አልባ ወጣቶች ተመለከትሁ፡፡ ከመካከላቸው አንድ የማያስተውል ወጣት ተመለከትሁ፡፡
\s5
\v 8 ያ ወጣት በቤቷ ማዕዘን አጠገብ ባለው መንገድ አለፈ፣ ከዚያም ወደ ቤቷ አቅጣጫ ሄደ
\v 9 ብርሃን ደንገዝገዝ፣ ቀኑ መሸትሸት ብሎ ነበር፣ በምሽትና በሌሌት ጨለማ፡፡
\s5
\v 10 በዚያ አንዲት ሴት አገኘችው፣ እንደ ሴተኛ አዳሪ የለበሰች፣ እዚያ ለምን እንደ መጣች በሚገባ ታውቃለች፡፡
\v 11 ጯኺና እምቢተኛ ናት፣ እግሮቿ በቤት አይቀመጡም
\v 12 አንዴ በመንገድ፣ አንዴ በገበያ፣ በየማዕዘኑም ተጋድማ ታደባለች፡፡
\s5
\v 13 ስለዚህም ትይዘዋለች፣ ትስመውማለች፣ ፊቷም እፍረት ሳይታይበት እንዲህ አለችው፣
\v 14 ዛሬ የሰላም መስዋዕቴን አቅርቤአለሁ፣ ስእለቴንም ፈጽሜአለሁ፣
\v 15 ስለዚህ አንተን ለማግኘት፣ ፊትህን ለመፈለግ ወጣሁ፣ አግኝቼሃለሁም፡፡
\s5
\v 16 በአልጋየ ላይ መሸፈኛ ዘርግቼበታለሁ፣ ከግብጽ የመጣ ባለቀለም የአልጋ ልብስ አንጥፌበታለሁ፡፡
\v 17 አልጋየን ከርቤ፣ አልሙንና ቀረፋ ረጭቼበታለሁ፡፡
\v 18 ና፣ እስኪነጋ ድረስ በፍቅር እንርካ፤ ፍቅራችንን በምንገልጥባቸው የተለያዩ መንገዶች በታላቅ ደስታ እንፈንድቅ፡፡
\s5
\v 19 ባሌ በቤት የለም፤ ወደ ሩቅ መንገድ ሄዷል፡፡
\v 20 በገንዘብ የተሞላ ቦርሳ ወስዷል፤ ሙሉ ጨረቃ በወጣበት ቀን ይመለሳል፡፡”
\v 21 በሚያባብል ንግግሯ ታሳስተዋለች፣ በለሰለሰ ንግሯም ታታልለዋለች፡፡
\s5
\v 22 ለመታረድ እንደሚነዳ በሬ፣ ፍላጻ ጉበቱን እስኪወጋው ድረስ በወጥመድ እንደተያዘ አጋዘን፣
\v 23 ወደ ወጥመድ በርራ እንደምትገባ ወፍ፣ ሕይወቱን እንደሚያሳጣው ሳያውቅ እርሷን ይከተላታል፡፡
\s5
\v 24 አሁን፣ ልጆቼ ሆይ፣ አድምጡኝ፤ የምናገረውንም ልብ ብላችሁ ስሙኝ፡፡
\v 25 ልባችሁ ወደ መንገዷ እንዲያዘነብል አትፍቀዱ፤ በጎዳናዋም አትሳቱ፡፡
\s5
\v 26 ብዙ ተጎጂዎችን አጥምዳ ጥላለች፤ ቁጥራቸውም እጅግ ብዙ ነው፡፡
\v 27 ቤቷ ወደ ሲኦል በሚወስደው መንገድ ነው፤ ወደ ሞት ማደርያም የሚያወርድ ነው፡፡
\s5
\c 8
\p
\v 1 ጥበብ እየጮኸች አይደለምን? ማስተዋልስ ድምጿን ከፍ አላደረገችምን?
\v 2 ከመንገድ አጠገብ ባሉት ኮረብታዎች ጫፍ ላይ፣ መንገዶች በሚገናኙበት ቦታ፣ ጥበብ ትቆማለች፡፡
\v 3 ወደ ከተማይቱ በሚያስገቡት በሮች አጠገብ፣ በከተማይቱ መግቢያ አጠገብ፣ ትጣራለች፡፡
\s5
\v 4 እናተ ሰዎች፣ ወደ እናንተ እጣራለሁ፣ ድምጼንም ከፍ አድርጌ ወደ ሰው ልጆች እጮኸለሁ፡፡
\v 5 እናንተ ትምህርት ያላገኛችሁ፣ ጠንቃቃነትን ተማሩ፣ እናንተ እውቀትን የምትጠሉ፣ የሚያስተውል ልብ ይኑራችሁ፡፡
\s5
\v 6 የከበሩ ነገሮችን እናገራለሁና አድምጡኝ፣ ከንፈሮቼ ሲከፈቱ ቀና የሆነውን ነገር እናገራለሁ
\v 7 አንደበቴ እውነትን ይናራልና፣ ከንፈሮቼም ክፋትን ይጠላሉና፡፡
\s5
\v 8 ከአንደበቴ የሚወጡ ቃሎች ሁሉ ጽድቅ ናቸው፤ በእነርሱ ውስጥ ጠማማ ወይም አሳሳች ነገር የለውም፡፡
\v 9 ለሚያስተውል ሰው ቃሎቼ በሙሉ ቀና ናቸው፤ እውቀትን ለሚያገኙ ቃሎቼ ትክክለኛ ናቸው፡፡
\s5
\v 10 ከብር ይልቅ ተግሳጼን ምረጡ፣ ከንጹህ ወርቅም ይልቅ እውቀትን ምረጡ፡፡
\v 11 እኔ ጥበብ፣ ከከበረ ዕንቁ እበልጣለሁና፤ ከምትመኙት ነገር በሙሉ ከእኔ ጋር የሚስተካከል የለም፡፡
\s5
\v 12 እኔ ጥበብ፣ ከጥንቃቄ ጋር እኖራለሁ፣ እውቀትና ነገሮችን ለይቶ ውሳኔ የመስጠት ኃይልም አለኝ፡፡
\v 13 እግዚአብሔርን መፍራት ክፋትን ይጠላል፤ ትዕቢት፣ እብሪት፣ ክፉ መንገድና ጠማማ ንግግር እጠላለሁ፣ ፈጽሞም እጠላቸዋለሁ፡፡
\s5
\v 14 እኔ መልካም ምክርና እውነተኛ ጥበብ አለኝ፤ ማስተዋል አለኝ፣ ብርታትም የእኔ ነው፡፡
\v 15 ነገስታት፣ የከበሩ ሰዎችና በፍትሃዊነት ሕዝብን የሚመሩ ሁሉ በእኔ ያስተዳድራሉ፡፡
\v 16 መሳፍንቶች፣ የከበሩ ሰዎችና በፍትህ ሕዝብን የሚመሩ ሁሉ በእኔ ያስተዳድራሉ፡፡
\s5
\v 17 የሚወዱኝን እወዳቸዋለሁ፣ ተግተው የሚፈልጉኝም ያገኙኛል፡፡
\v 18 ባለጠግነትና ክብር፣ ዘላቂነት ያለው ሃብትና ጽድቅም በእኔ ዘንድ አሉ፡፡
\s5
\v 19 ፍሬየ ከወርቅ ይበልጣል፣ ከነጠረ ወርቅም ይበልጣል፤ ስጦታየም ከንጹህ ብር ይበልጣል፡፡
\v 20 እኔ በጽድቅ መንገድ እሄዳለሁ፣ ወደ ፍትህ በሚወስድ ጎዳና እጓዛለሁ፣
\v 21 ስለዚህ ለሚወዱኝ ሀብትን እሰጣቸዋለሁ፣ ግምጃ ቤታቸውንም እሞላለሁ፡፡
\s5
\v 22 እግዚአብሄር ከመጀመርያ ፈጠረኝ፣ በቀድሞ ዘመን የስራው መጀመርያ ነኝ፡፡
\v 23 ከመጀመርያ፣ ምድር ከመፈጠሯ በፊት፣ ከረጅም ዘመናት ጀምሮ ተሾምሁ፡፡
\s5
\v 24 ውቅያኖሶች ሳይኖሩ፣ የውኃ ምንጮች ሳይፈልቁ በፊት፣ እኔ ተወልጄ ነበር፣
\v 25 ተራሮች ገና ሳይመሰረቱ፣ ከኮረብቶችም በፊት፣ እኔ ተወለድሁ፡፡
\s5
\v 26 እግዚአብሔር ምድርንና ሜዳዎቿን፣ የመጀመርያውን የዓለም አፈር እንኳ ከመፍጠሩ በፊት እኔ ተወለድሁ፡፡
\v 27 እርሱ ሰማያትን ሲመሰርት፣ በውቅያኖስ ገጽ የአድማስን ምልክት ባደረገ ጊዜ እኔ እዚያ ነበርሁ፡፡
\s5
\v 28 እርሱ በላይ ያሉትን ደመናት ባጸና ጊዜ፣ የውቅያኖስን ምንጮች በመሰረተ ጊዜ እኔ እዚያ ነበርሁ፡፡
\v 29 ውሆች የእርሱን ትዕዛዝ አልፈው እንዳያጥለቀልቁ እርሱ ለባህር ድንበርን ባበጀለት ጊዜ፣ የምድርም መሰረት የት መሆን እንዳለበት በወሰነበት ጊዜ እኔ እዚያ ነበርሁ፡፡
\s5
\v 30 እኔ ዋና ሰራተኛ ሆኜ በአጠገቡ ነበርሁ፣ እኔ ዕለት በዕለት እርሱን ደስ አሰኘው ነበርሁ፣ ሁልጊዜ በፊቱ ደስ ይለኝ ነበር፡፡
\v 31 የእርሱ በሆነው በመላው ዓለም ደስ ይለኝ ነበር፣ ደስታየም በሰው ልጅ ነበር፡፡
\s5
\v 32 አሁንም፣ ልጆቼ ሆይ፣ አድምጡኝ፣ መንገዴን የሚጠብቁ ሁሉ ደስተኞች ይሆናሉና፡፡
\v 33 ምክሬን አድምጡ፣ ጥበበኞችም ሁኑ፤ ቸልም አትበሉት፡፡
\v 34 እኔን የሚያደምጠኝ ደስተኛ ይሆናል፣ ዕለት በዕለት በመግቢያየ የሚተጋ፣ በቤቴም በሮች አጠገብ የሚጠብቀኝ፡፡
\s5
\v 35 እኔን ያገኘ ሕይወትን ያገኛልና፣ የእግዚአብሔርንም ሞገስ ያገኛል፡፡
\v 36 እኔን ያጣ ግን ራሱን ይጎዳል፤ እኔን የሚጠሉኝ በሙሉ ሞትን ይወድዳሉ፡፡
\s5
\c 9
\p
\v 1 ጥበብ ቤቷን ሰራች፤ ሰባት ምሰሶዎችን ከድንጋይ ጠርባ አቆመች፡፡
\v 2 ለእራት እንስሳዎቿን አረደች፤ የወይን ጠጇንም ደባለቀች፤ ማዕዷንም አዘጋጀች፡፡
\s5
\v 3 በሴት ሰራተኞቿ በኩል የጥሪ ወረቀት ላከች፣ ከከተማይቱ ከፍተኛ ቦታ ተጣራች፡፡
\v 4 እርሷም አእምሮ ለጎደላቸው “እውቀትን ያላገኙ ሁሉ ወደዚህ ይምጡ!” አለች፡፡
\s5
\v 5 “ኑ፣ ምግቤን ተመገቡ፣ የደባለቅሁትንም የወይን ጠጄን ጠጡ፡፡
\v 6 የአላዋቂነት መንገዳችሁን ወደኋላ በመተው በሕይወት ኑሩ፤ በማስተዋል መንገድ ተመላለሱ፡፡
\s5
\v 7 ፌዘኛን የሚገስጽ ሰው በራሱ ላይ ስድብን ያመጣል፣ ክፉን ሰው የሚገስጽ ደግሞ ይጎዳል፡፡
\v 8 ፌዘኛን ሰው አትገስጽ፣ ይጠላሃል፤ ጥበበኛን ሰው ገስጽ፣ ይወድድሃል፡፡
\v 9 ለጥበበኛ ሰው ትምህርትን ስጠው፣ ይበልጥ ጥበበኛ ይሆናል፤ ጻድቅን ሰው አስተምረው፣ እርሱም ይበልጥ እውቀትን ይጨምራል፡፡
\s5
\v 10 የጥበብ መጀመርያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፣ ቅዱሱንም ማወቅ ማስተዋል ነው፡፡
\v 11 በእኔ ዘመንህ ይበዛልና፣ በሕይወትህም ዓመታት ይጨመሩልሃል፡፡
\v 12 ጥበበኛ ከሆንህ፣ ጥበበኛ የምትሆነው ለራስህ ነው፣ ነገር ግን የምታፌዝ ከሆንህ፣ ፌዘኛነትህን ለብቻህ ትሸከመዋለህ፡፡”
\s5
\v 13 ሞኝ ሴት ለፍላፊ ናት፣ ትምህርት የሌላትና ምንም የማታውቅ ናት፡፡
\v 14 በከተማዋ ከፍተኛ ስፍራ በቤቷ በር በመቀመጫ ላይ ትቀመጣለች፡፡
\v 15 እርሷ በመንገድ የሚያልፉትን፣ በመንገዳቸውም ቀጥ ብለው የሚሄዱትን ሰዎች ትጣራለች፡፡
\s5
\v 16 እርሷም አእምሮ ለጎደላቸው “እነዚህ ትምህርት የሌላቸው ሰዎች ወደዚህ ይምጡ!” አለች፡፡
\v 17 “የተሰረቀ ውኃ ጣፋጭ ነው፣ በምስጢር የበሉት እንጀራም አስደሳች ነው፡፡”
\v 18 ነገር ግን እርሱ ሙታን በዚያ እንዳሉ አያወቅም፣ ተጋባዦቿ በሲዖል ጥልቀት ውስጥ እንዳሉ አያውቅም፡፡
\s5
\c 10
\p
\v 1 የሰሎሞን ምሳሌዎች፡፡ ጥበበኛ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል፣ ሞኝ ልጅ ግን ለእናቱ ሃዘንን ያመጣል፡፡
\v 2 በክፋት የተከማቸ ሃብት ምንም ጥቅም የለውም፣ ጽድቅ ግን ከሞት ያድናል፡፡
\v 3 እግዚአብሔር በጽድቅ የሚሄዱትን እንዲራቡ አያደርግም፣ የክፉዎችን ምኞት ግን ያከሽፋል፡፡
\s5
\v 4 የሰነፍ እጅ ድሃ ታደርጋለች፣ የትጉ እጅ ግን ብልጽግናን ታመጣለች፡፡
\v 5 ጥበበኛ ልጅ በበጋ ምርትን ይሰበስባል፣ በመከር መተኛት ግን ለእርሱ ውርደት ነው፡፡
\s5
\v 6 የእግዚአብሔር ስጦታ በጻድቃን ራስ ላይ ነው፣ የክፉ ሰው አፍ ግን ጥፋት ይከድነዋል፡፡
\v 7 ጻድቅ ሰው ስለ እርሱ ስናስብ ደስ እንድንሰኝ ያደርገናል፣ የክፉ ሰው ስም ግን ይጠፋል፡፡
\s5
\v 8 አዋቂዎች ትእዛዛትን ይቀበላሉ፣ ለፍላፊ ሞኝ ግን ወደ ጥፋት ይሄዳል፡፡
\v 9 በሀቀኝነት የሚሄድ ሰው ተማምኖ ይሄዳል፣ መንገዱን የሚያጣምም ግን ይጋለጣል፡፡
\s5
\v 10 በዓይኑ የሚጠቅስ መከራን ያመጣል፣ ለፍላፊ ሞኝ ግን ወደ ይጠፋል፡፡
\v 11 ጽድቅን የሚያደርግ ሰው አፍ የሕይወት ምንጭ ነው፣ የክፉ ሰው አፍ ግን ጥፋትን ይደብቃል፡፡
\s5
\v 12 ጥላቻ ጠብን ያነሳሳል፣ ፍቅር ግን ስህተትን ሁሉ ይሸፍናል፡፡
\v 13 በአስተዋይ ሰው ከንፈር ጥበብ ትገኛለች፣ በትር ግን አእምሮ ለጎደለው ሰው ጀርባ ነው፡፡
\s5
\v 14 ጥበበኛ ሰዎች እውቀትን ይሰበስባሉ፣ የሞኝ አፍ ግን ጥፋትን ያመጣል፡፡
\v 15 የባለጠጋ ሰው ሀብት የተመሸገ ከተማው ነው፤ የድሆች ድህነት ግን መጥፊያቸው ነው፡፡
\s5
\v 16 የጻድቅ ሰው ደመወዝ ወደ ሕይወት ይመራል፤ የክፉዎች ትርፍ ግን ወደ ኃጢአት ይመራቸዋል፡፡
\v 17 እርምትን ለሚከተል ሰው ወደ ሕይወት የምትመራ ጎዳና አለች፣ ተግሳጽን የማይቀበል ሰው ግን ይስታል፡፡
\s5
\v 18 ጥላቻን የሚደብቅ ሰው ሐሰተኛ ከንፈሮች አሉት፣ ሐሜትን የሚያስፋፋ ሞኝ ነው፡፡
\v 19 በብዙ ቃላቶች ውስጥ ኃጢአት ሳይኖር አይቀርም፣ ለሚናገረው ነገር ጥንቃቄ የሚደርግ ሰው ግን ጥበበኛ ነው፡፡
\s5
\v 20 የጻድቅ ሰው ምላስ የነጠረ ብር ነው፤ የክፉ ሰው ልብ ግን ዋጋ የለውም፡፡
\v 21 የጻድቅ ሰው ከንፈሮች ብዙ ሰዎችን ያንጻሉ፣ ሞኞች ግን ባለማማዛዘናቸው ምክንያት ይሞታሉ፡፡
\s5
\v 22 የእግዚአብሔር መልካም ስጦታዎች ሃብትን ያመጣሉ፣ መከራንም አያክልበትም፡፡
\v 23 ክፋት የሞኞች ጨዋታ ነው፣ ጥበብ ግን ለአስተዋይ ሰው ደስታ ነው፡፡
\s5
\v 24 የክፉ ሰው ፍርሃት ድንገት ይደርስበታል፣ የጻድቅ ሰው ምኞት ግን ይፈጸማል፡፡
\v 25 ክፉ ሰዎች እንደሚያልፍ አውሎ ነፋስ ናቸው፣ ከዚያም በኋላ አይገኙም፣ ጽድቅን የሚያደርጉ ግን ለዘላለም የሚኖሩ መሰረት ናቸው፡፡
\s5
\v 26 በጥርስ ላይ ያለ ሆምጣጤ፣ በዓይንም ውስጥ ያለ ጢስ እንደሚጎዳ፣ ሰነፍ ሰው ለሚልኩት እንዲሁ ነው፡፡
\v 27 እግዚአብሔርን መፍራት ዕድሜን ያረዝማል፣ የክፉዎች ዕድሜ ግን አጭር ይሆናል፡፡
\s5
\v 28 ጽድቅን የሚያደርጉ ሰዎች ተስፋ ደስታቸው ነው፣ የክፉዎች ዕድሜ ግን አጭር ይሆናል፡፡
\v 29 የእግዚአብሔር መንገድ ሃቀኞችን ይጠብቃቸዋል፣ ለክፉዎች ግን መጥፊያቸው ነው፡፡
\v 30 ጽድቅን የሚያደርጉ ፈጽሞ አይወድቁም፣ ክፉዎች ግን በምድሪቱ አይቀሩም፡፡
\s5
\v 31 ከጻድቃን አፍ የጥበብ ፍሬ ይወጣል፣ ጠማማ ምላስ ግን ይቆረጣል፡፡
\v 32 የጻድቃን ከንፈሮች ተገቢ የሆነውን ነገር ያውቃሉ፣ የክፉዎች አፍ ግን የሚያውቀው ጠማማ የሆነውን ነገር ብቻ ነው፡፡
\s5
\c 11
\p
\v 1 እግዚአብሔር ትክክለኛ ያልሆነ ሚዛን ይጠላል፣ በትክክለኛ ሚዝን ግን ሚዛን ደስ ይለዋል፡፡
\v 2 ትዕቢት ከመጣች ውርደት ትመጣለች፣ ከትህትና ጋር ግን ጥበብ ትመጣለች፡፡
\s5
\v 3 የቅኖች ሀቀኝነታቸው ይመራቸዋል፣ የከዳተኞች ጠማማ መንገድ ግን ራሳቸውን ያጠፋቸዋል፡፡
\v 4 በቁጣ ቀን ሀብት ዋጋ ቢስ ነው፣ ጽድቅ ግን ከሞት ታድንሃለች፡፡
\s5
\v 5 ነቀፋ የሌለበት ሰው ጽድቅ መንገዱን ያቀናለተል፣ ክፉዎች ግን በክፋታቸው ይወድቃሉ፡፡
\v 6 እግዚብሔርን ደስ የሚያሰኙ ሰዎች ጽድቃቸው ትታደጋቸዋለች፣ ከዳተኞች ግን በክፉ ምኞታቸው ይጠመዳሉ፡፡
\s5
\v 7 ክፉ ሰው ሲሞት ተስፋው ይጠፋል፣ በብርታቱ የተመካበት ተስፋም ከንቱ ይሆናል፡፡
\v 8 ጽድቅን የሚያደርግ ከመከራ ይድናል፣ ይልቁንም መከራው በክፉው ይመጣበታል፡፡
\s5
\v 9 አምላክ የለሽ ሰው በአንደበቱ ጎረቤቱን ያጠፋል፣ ጽድቅን የሚያደርጉ ግን በእወቀት ይድናሉ፡፡
\v 10 ጽድቅን የሚያደርጉ ሰዎች ሲበለጽጉ ከተማ ትደሰታለች፤ ክፉዎች ሲጠፉ የደስታ ጩኸት ይሆናል፡፡
\v 11 እግዚአብሔርን ደስ በሚያሰኙ ሰዎች መልካም ስጦታ ከተማ ታላቅ ትሆናለች፤ በክፉዎች አንደበት ግን ከተማ ትፈርሳለች፡፡
\s5
\v 12 ጓደኛውን የሚንቅ ሰው አእምሮ የጎደለው ነው፣ አስተዋይ ሰው ግን ዝም ይላል፡፡
\v 13 ለሐሜት የሚሄድ ሰው ምስጢርን ይገልጣል፣ ታማኝ ሰው ግን ምስጢርን ይሰውራል፡፡
\s5
\v 14 በጥበብ አልባ አመራር ሕዝብ ይወድቃል፣ የመካሮች ብዛት ባለበት ግን ድል ይመጣል፡፡
\s5
\v 15 ለማይታወቅ ሰው ዋስ የሚሆን መከራን ይቀበላል፣ በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ ዋስ ለመሆን የሚጠላ ሰው ግን ይድናል፡፡
\v 16 ሞገስ ያላት ሴት ክብር ታገኛለች፣ ጨካኝ ሰዎች ግን ሀብትን ብቻ ያገኛሉ፡፡
\s5
\v 17 ደግ ሰው ራሱን ይጠቅማል፣ ጨካኝ ሰው ግን ራሱን ይጎዳል፡፡
\v 18 ክፉ ሰው ደመወዙን ለማግኘት ይዋሻል፣ ጽድቅን የሚዘራ ግን የእውነትን ደመወዝ ይሰበስባል፡፡
\s5
\v 19 ጽድቅን የሚያደርግ ታማኝ ሰው በሕይወት ይኖራል፣ ክፋትን የሚያደርግ ግን ይሞታል፡፡
\v 20 እግዚአብሔር ጠማማ ልብ ያላቸውን ይጠላል፣ በመንገዳቸው ነቀፋ በሌለባቸው ሰዎች ግን ደስ ይሰኛል፡፡
\s5
\v 21 ክፉ ሰዎች ሳይቀጡ እንደማይቀሩ ይህን እርግጠኛ ሁን፣ ጽድቅን የሚያደርጉ ሰዎች ዘሮች ግን ይድናሉ፡፡
\v 22 በአሳማ አፍንጫ እንደተሰካ የወርቅ ቀለበት፣ ማስተዋል የሌላትም ቆንጆ ሴት እንዲሁ ናት፡፡
\s5
\v 23 ጽድቅን የሚያደርጉ ሰዎች ምኞት መልካም ውጤት ያመጣል፣ ክፉ ሰዎች ግን ተስፋ ሊያደርጉት የሚችሉት መቅሰፍት ብቻ ነው፡፡
\v 24 ዘርን የሚዘራ አንድ ሰው አለ፣ እርሱ ይበልጥ ይሰበስባል፤ ሌላ ደግሞ የማይዘራ አለ፣ እርሱ ይደኸያል፡፡
\s5
\v 25 ለጋስ ሰው ይበለጽጋል፣ ለሌሎች ውኃ የሚሰጥ ደግሞ ለራሱም ውኃ ያገኛል፡፡
\v 26 እህል ለመሸጥ ፈቃደኛ ያልሆነ ሰው ሕዝብ ይረግመዋል፣ በሚሸጠው ግን መልካም ስጦታዎችን በራሱ ላይ እንደ አክሊል ይጎናጸፋል፡፡
\s5
\v 27 መልካምን ነገር ተግቶ የሚፈልግ ሞገስን ይፈልጋል፣ ክፉን የሚፈልግ ግን ክፉ በራሱ ላይ ይመጣበታል፡፡
\v 28 በባለጠግነታቸው ላይ የሚታመኑ ሰዎች ይወድቃሉ፣ ጽድቅን የሚያደርጉ ግን እንደ ቅጠል ይለመልማሉ፡፡
\s5
\v 29 በቤተሰቡ ላይ ሁከትን የሚያመጣ ሰው ነፋስን ይወርሳል፣ ሞኝም ሰው በልቡ ጥበበኛ ለሆነው ሰው አገልጋይ ይሆናል፡፡
\s5
\v 30 ጽድቅን የሚያደርጉ ሰዎች እንደ ሕይወት ዛፍ ይሆናሉ፣ ሁከት ግን ሕይወትን ያጠፋል፡፡
\v 31 ጽድቅን የሚደርጉ ሰዎች ለሰሩት ስራ የሚገባቸውን የሚቀበሉ ከሆነ፣ ይልቁንስ ክፉዎችና ኃጢአተኞች እንዴት አይቀበሉ!
\s5
\c 12
\p
\v 1 ተግሳጽን የሚወድ እውቀትን ይወዳል፣ እርምትን የሚጠላ ግን ደነዝ ነው፡፡
\v 2 እግዚአብሔር ለመልካም ሰው ሞገስን ይሰጠዋል፣ ክፉ እቅድ ለሚያወጣ ሰው ግን ይፈርድበታል፡፡
\s5
\v 3 ሰው በክፋት ላይ ተመስርቶ ጸንቶ ሊቆም አይችልም፣ ጽድቅን የሚያደርጉ ግን ከመሰረታቸው አይነቀሉም፡፡
\v 4 መልካም ሴት ለበሏ ዘውድ ናት፣ አሳፋሪ ሴት ግን አጥንቱን እንደሚያበሰብስ በሽታ ናት፡፡
\s5
\v 5 ጽድቅን የሚያደርጉ ሰዎች እቅድ ጽድቅ ነው፣ የክፉዎች ምክር ግን ተንኮል ነው፡፡
\v 6 የክፉ ሰዎች ቃል ድንገት ለመግደል አድፍጦ ያደባል፣ የቅኖች ቃል ግን ይታደጋቸዋል፡፡
\s5
\v 7 ክፉ ሰዎች ይገለበጣሉ፣ አይገኙምም፣ ጽድቅን የሚያደርጉ ሰዎች ቤት ግን ጸንቶ ይቆማል፡፡
\v 8 ሰው በጥበቡ ብዛት ይመሰገናል፣ ጠማማ ምርጫዎች የሚያደርግ ግን ይናቃል፡፡
\s5
\v 9 የሚበላው ምግብ ሳይኖረው ከሚኩራራ ሰው ይልቅ ራሱን ዝቅ አድርጎ አገልጋይ መሆን ይሻላል፡፡
\v 10 ጽድቅን የሚያደርግ ሰው እንስሳቱ ስለሚያስፈልጋቸው ነገር ግድ ይለዋል፣ ክፉ ሰው ግን ርህራሄ አደረገ ቢባል እንኳ ስራው ጭካኔ የተሞላ ነው፡፡
\s5
\v 11 መሬቱን በሚገባ የሚያርስ የተትረፈረፈ ምግብ ያገኛል፣ ዋጋ ቢስ ስራዎችን የሚያሳድድ ሰው ግን አእምሮ አልባ ነው፡፡
\v 12 ኃጢአተኞች ክፉ ሰዎች ከሌሎች የሰረቁትን ይመኛሉ፣ ጽድቅን የሚያደርጉ ሰዎች ፍሬ ግን ከገዛ ራሳቸው ይመጣል፡፡
\s5
\v 13 ክፉ ሰው በክፉ ንግግሩ ይጠመዳል፣ ጽድቅን የሚያደርጉ ሰዎች ግን ከመከራ ያመልጣሉ፡፡
\v 14 ሰው ከቃሎቹ ፍሬ የተነሳ መልካም ነገርን ይጠግባል፣ እንደ እጁ ስራም ዋጋውን ይቀበላል፡፡
\s5
\v 15 የሞኝ መንገድ ለራሱ ትክክል መስሎ ይታየዋል፣ ጥበበኛ ሰው ግን ምክርን ይሰማል፡፡
\v 16 ሞኝ ቁጣውን በቶሎ ይገልጣል፣ ስድብን ንቆ የሚተው ግን አስተዋይ ነው፡፡
\s5
\v 17 እወነትን የሚናገር ትክክለኛውን ነገር ይናራል፣ ሐሰተኛ ምስክር ግን ውሸትን ይናገራል፡፡
\v 18 የለፍላፊ ሰው ቃሎች እንደሚዋጋ ሰይፍ ነው፣ የጥበበኛ አንደበት ግን ፈውስን ያመጣል፡፡
\s5
\v 19 እውነተኛ ከንፈሮች ለዘላለም ይኖራሉ፣ ሀሰተኛ ከንፈር ግን ለቅጽበት ብቻ ነው፡፡
\v 20 ክፋትን ለማድረግ በሚያቅዱ ሰዎች ልብ ውስጥ ተንኮል አለ፣ ሰላምን ለሚመክሩ ሰዎች ግን ደስታ ይመጣል፡፡
\s5
\v 21 ጽድቅን የሚያደርጉ ሰዎች በሽታ አያገኛቸውም፣ ክፉ ሰዎች ግን በመከራ የተሞሉ ናቸው፡፡
\v 22 እግዚአብሔር ሀሰተኛ ከንፈሮችን ይጠላል፣ በእውነተኛነት በሚኖሩ ሰዎች ግን ደስ ይለዋል፡፡
\s5
\v 23 አስተዋይ ሰው እወቀቱን ይሰውራል፣ የሞኞች ልብ ግን ከንቱነትን ያወራል፡፡
\v 24 የትጉ ሰዎች እጅ ይገዛል፣ ሰነፍ ሰዎች ግን ለጉልበት ስራተኝነት ታልፈው ይሰጣሉ፡፡
\s5
\v 25 በሰው ልብ ውስጥ የሚገኝ ጭንቀት ያዋርደዋል፣ መልካም ቃል ግን ደስ ያሰኘዋል፡፡
\v 26 ጽድቅን የሚያደርግ ሰው ለጓደኛው መንገድን ያሳያል፣ የክፉ መንገድ ግን ታስታቸዋለች፡፡
\s5
\v 27 ሰነፍ ሰዎች አድነው ያመጡትን እንስሳ እንኳ አይጠብሱም፣ ትጉ ሰው ግን የከበረ ሀብት ያገኛል፡፡
\v 28 በጽድቅ መንገድ የሚሄዱ ሰዎች ሕይወትን ያገኛሉ፣ በጎዳናዋም ሞት የለም፡፡
\s5
\c 13
\p
\v 1 ጥበበኛ ልጅ የአባቱን ምክር ይሰማል፣ ፌዘኛ ግን ተግሳጽን አያዳምጥም፡፡
\v 2 ሰው ከአፉ ፍሬ መልካምን ነገር ይጠግባል፣ ጠማማ ሰው ግን ዓመጽን ይመኛል፡፡
\s5
\v 3 አፉን የሚጠብቅ ሕይወቱን ይጠብቃል፣ ከንፈሮቹን ያለ ልክ የሚከፍት ግን ይጠፋል፡፡
\v 4 ሰነፍ ሰው ይመኛል ነገር ግን አንዳችም አያገኝም፣ የትጉ ሰው ምኞት ግን በሙላት ይረካል፡፡
\s5
\v 5 ጽድቅን የሚያደርግ ሰው ውሸትን ይጠላል፣ ክፉ ሰው ግን ራሱ ጥላቻን ይፈጥራል፣ አሳፋሪ ተግባርንም ይፈጽማል፡፡
\v 6 በመንገዳቸው ያለ ነቀፋ የሚሄዱትን ጽድቅ ትጠብቃቸዋለች፣ ክፋት ግን ኃጢአተኞችን ትጥላቸዋለች፡፡
\s5
\v 7 ራሱን ባለጠጋ የሚያስመስል ሰው አለ፣ ነገር ግን አንዳች የለውም፣ ምንም እንደሌለው መስሎ የሚታይ ሰው ደግሞ አለ፣ ይሁን እንጂ እጅግ ባለጠጋ ነው፡፡
\v 8 ባለጠጋ ሰው ሀብቱን ለሕይወቱ ቤዛ አድርጎ ያቀርብ ይሆናል፣ ድሀ ግን እንዲህ ዓይነት ሥጋት በፍጹም የለበትም፡፡
\s5
\v 9 ጽድቅን የሚያደርግ ሰው ብርሃን ደምቆ ይበራል፣ የክፉዎች መብራት ግን ይጠፋል፡፡
\v 10 ትዕቢት ጠብን ብቻ ያስፋፋል፣ መልካም ምክርን ለሚያደምጡ ግን ጥበብ አለ፡፡
\s5
\v 11 ብዙ ከንቱነት ሲኖር ሀብት እየመነመነ ያልቃል፣ በእጁ እየሰራ ገንዘብ የሚያከማች ሰው ግን ገንዘቡ እየጨመረ እንዲሄድ ያደርጋል፡፡
\v 12 ተስፋ ሲዘገይ ልብን ይሰብራል፣ የተሳካ ምኞት ግን የሕይወት ዛፍ ነው፡፡
\s5
\v 13 ትእዛዝን የሚንቅ በትእዛዝ ይቀጣል፣ ትእዛዝን የሚያከብር ግን ወሮታን ያገኛል፡፡
\v 14 የጥበበኛ ሰው ትምህርት የሕይወት ምንጭ ነው፣ ከሞት ወጥመድ እንድታመልጥ ያደርግሃል፡፡
\s5
\v 15 መልካም እውቀት ሞገስ ያስገኛል፣ የከዳተኛ ሰው መንገድ ግን አያልቅም፡፡
\v 16 ጥንቃቄ የተሞሉ ሰዎች ማንኛውንም ውሳኔ የሚያደርጉት በጥበብ ነው፣ ሞኝ ግን ከንቱነቱን ይገልጣል፡፡
\s5
\v 17 ክፉ መልእክተኛ መከራ ውስጥ ይገባል፣ ታማኝ መልእክተኛ ግን እርቅን ያመጣል፡፡
\v 18 ተግሳጽን የሚንቅ ድህነትና ኃፍረት ይመጣበታል፣ ከእርምት የሚማር ግን ክብር ወደ እርሱ ይመጣል፡፡
\s5
\v 19 ምኞት ሲፈጸም የውስጥ ፍላጎትን ደስ ያሰኛል፣ ሞኞች ግን ከክፋት መመለስን ይጠላሉ፡፡
\v 20 ከጥበበኞች ጋር ሂድ አንተም ጥበበኛ ትሆናለህ፣ የሞኞች ባልንጀራ ግን እጅግ ይጎዳል፡፡
\s5
\v 21 መቅሰፍት ኃጢአተኞችን ይከታተላቸዋል፣ ጽድቅን የሚያደርጉ ግን መልካምን ነገር ይቀበላሉ፡፡
\v 22 መልካም ሰው ለልጅ ልጆቹ የሚያወርሰውን ይተዋል፣ የኃጢአተኛ ሀብት ግን ጽድቅን ለሚያደርጉ ይከማቻል፡፡
\s5
\v 23 የድሆች እርሻ ያልታረሰም ቢሆን ብዙ ምግብ ሊያመርት ይችላል፣ ነገር ግን በፍትህ መጓደል ምክንያት ተጠራርጎ ይወሰዳል፡፡
\v 24 ልጁን የማይቀጣ ይጠላዋል፣ ልጁን የሚወድ ግን በጥንቃቄ ይቀጣዋል፡፡
\s5
\v 25 ጽድቅን የሚያደርግ ሰው ፍላጎቱን እስከሚያረካ ድረስ ጠግቦ ይበላል፣ የክፉዎች ሆድ ግን ሁልጊዜ እንደተራበ ነው፡፡
\s5
\c 14
\p
\v 1 ጥበበኛ ሴት ቤቷን ትሰራለች፣ ሞኝ ሴት ግን በገዛ እጇ ታፈርሰዋለች፡፡
\v 2 በጽድቅ የሚሄድ ሰው እግዚአብሔርን ይፈራል፣ በመንገዱ ታማኝ ያልሆነ ግን ይንቀዋል፡፡
\s5
\v 3 ከሞኝ አፍ የትዕቢት በትር ይወጣል፣ የጥበበኛ ከንፈሮች ግን ይጠብቋቸዋል፡፡
\v 4 ከብቶች በሌሉበት የመመገቢያ ገንዳ ባዶ ይሆናል፣ በበሬ ጉልበት ግን ብዙ ምርት ይገኛል፡፡
\s5
\v 5 እውነተኛ ምስክር አይዋሽም፣ ሐሰተኛ ምስክር ግን ውሸትን ይለፈልፋል፡፡
\v 6 ፌዘኛ ጥበብን ይፈልጋል ሆኖም አያገኛትም፣ እውቀት ግን ወደ አስተዋይ ሰው በቀላሉ ትመጣለች፡፡
\s5
\v 7 ከሞኝ ሰው ራቅ፣ ከከንፈሮቹ እውቀትን አታገኝምና፡፡
\v 8 የጠንቃቃ ሰው ጥበብ መንገዱን ማስተዋል ነው፣ የሞኞች ከንቱነት ግን ማታለል ነው፡፡
\s5
\v 9 ሞኞች የኃጢአት መስዋዕት በሚቀርብበት ጊዜ ያፌዛሉ፣ በጻድቃን መካከል ግን ቸርነት ይገኛል፡፡
\v 10 ልብ የራሱን ምሬት ያውቃል፣ ደስታውንም ሌላ ሰው አይጋራውም፡፡
\s5
\v 11 የክፉ ሰዎች ቤት ይጠፋል፣ የጻድቃን ድንኳን ግን ይስፋፋል፡፡
\v 12 ለሰው ቅን የምትመስል መንገድ አለች፣ ፍጻሜዋ ግን ወደ ሞት ይመራል፡፡
\s5
\v 13 ልብ በሐዘን ውስጥ ሆኖ ሊስቅ ይችላል፣ የደስታም ፍጻሜ ሐዘን ሊሆን ይችላል፡፡
\v 14 ታማኝ ያልሆነ ሰው ለመንገዱ የሚገባውን ዋጋ ያገኛል፣ መልካም ሰው ግን የራሱ የሆነውን ያገኛል፡፡
\s5
\v 15 እውቀት አልባ ሰው ሁሉንም ነገር ያምናል፣ አስተዋይ ሰው ግን አካሄዱን ያስተውላል፡፡
\v 16 ጥበበኛ ሰው ይፈራል ከክፉም ይርቃል፣ ሞኝ ግን ራሱን ታምኖ ማስጠንቀቂያን ችላ ይላል፡፡
\s5
\v 17 ለቁጣ የሚቸኩል ሰው ከንቱ ነገሮችን ይፈጽማል፣ ክፋትን የሚያሴር ሰው ደግሞ ይጠላል፡፡
\v 18 እውቀት አልባ ሰዎች ሞኝነትን ይወርሳሉ፣ አስተዋይ ሰዎች ግን በእውቀት ይከበባሉ፡፡
\s5
\v 19 ክፉዎች በመልካም ሰዎች ፊት ይሰግዳሉ፣ ኃጢአተኞች ደግሞ በጻድቃን ደጅ ይሰግዳሉ፡፡
\v 20 ድሃ ሰው በራሱ ባልንጀሮችም ጭምር ይጠላል፣ ባለጠጋ ሰዎች ግን ብዙ ወዳጆች አሏቸው፡፡
\s5
\v 21 ለጎረቤቱ ንቀትን የሚያሳይ ኃጢአትን ያደርጋል፣ ለድሃ በጎነትን የሚያሳይ ግን ደስተኛ ነው፡፡
\v 22 ክፋትን የሚያሴሩ አይስቱምን? መልካምን ለማድረግ የሚያቅዱ ግን በኪዳን የተመሰረተ ታማኝነትና እውነተኛነት ይቀበላሉ፡፡
\s5
\v 23 በብዙ ድካም ትርፍ ይገኛል፣ ወሬ ግን ወደ ድህነት ይመራል፡፡
\v 24 የጥበበኞች ዘውድ ባለጠግነታቸው ነው፣ የሞኞች ሞኝነት ግን ተጨማሪ ከንቱነትን ያመጣባቸዋል፡፡
\s5
\v 25 እውነተኛ ምስክር ሕይወት ያድናል፣ ሐሰተኛ ምስክር ግን ውሸትን ይለፈልፋል፡፡
\s5
\v 26 ሰው እግዚአብሔርን ሲፈራ፣ በእርሱ ይታመናል፤ እነዚህ ነገሮች ደግሞ ለልጆቹ እንደ ብርቱ መጠጊያ ስፍራ ይሆኗቸዋል፡፡
\v 27 እግዚአብሔርን መፍራት የሕይወት ምንጭ ነው፣ ሰውን ከሞት ወጥመድ እንዲያመልጥ ያደርገዋል፡፡
\s5
\v 28 የንጉስ ክብር የሚገኘው ከሕዝቡ ብዛት ነው፣ ሕዝብ በሌለበት ግን ልዑል ይጠፋል፡፡
\v 29 ትዕግስተኛ ሰው ታላቅ ማስተዋል አለው፣ ለቁጣ የሚቸኩል ሰው ግን ሞኝነትን ከፍ ከፍ ያደርጋል፡፡
\s5
\v 30 በሰላም የተሞላ ልብ ለሰውነት ሕይወት ነው፣ ቅናት ግን አጥንትን ያበሰብሳል፡፡
\v 31 ድሀን የሚያስጨንቅ ሰው ፈጣሪውን ይሰድባል፣ ለድሀ ቸርነትን የሚያሳይ ግን ፈጣሪውን ያከብራል፡፡
\s5
\v 32 ክፉ ሰው በክፉ ስራው ይወድቃል፣ ጻድቅ ግን በሞት ጊዜ እንኳ መጠጊያ አለው፡፡
\v 33 ጥበብ በአስተዋይ ሰው ዘንድ ትኖራለች፣ በሞኞች መካከል እንኳ ራሷን ታሳውቃለች፡፡
\s5
\v 34 ጽድቅን ማድረግ ህዝብን ከፍ ከፍ ያደርጋል፣ ኃጢአት ግን ለማንኛውም ሕዝብ ውርደት ነው፡፡
\v 35 የንጉስ ሞገስ ተግተው በሚሰሩ አገልጋዮቹ ላይ ነው፣ ቁጣው ግን በአሳፋሪ አገልጋይ ላይ ነው፡፡
\s5
\c 15
\p
\v 1 የለዘበ መልስ ቁጣን ይመልሳል፣ መጥፎ ቃል ግን ቁጣን ያስነሳል፡፡
\v 2 የጥበበኛ ሰዎች ምላስ እውቀትን የተላበሰ ነው፣ የሞኞች አፍ ግን ሞኝነትን ያንቆረቁራል፡፡
\s5
\v 3 የእግዚአብሔር ዓይኖች በሁሉም ስፍራ ናቸው፣ ክፉውንና መልካሙን ሁሉ ነቅተው ይመለከታሉ፡፡
\v 4 ፈዋሽ ምላስ የሕይወት ዛፍ ነው፣ አታላይ ምላስ ግን መንፈስን ይሰብራል፡፡
\s5
\v 5 ሞኝ የአባቱን ተግሳጽ ይንቃል፣ ከእርምት የሚማር ግን አስተዋይ ነው፡፡
\v 6 ጽድቅን በሚያደርጉ ሰዎች ቤት ብዙ ሀብት አለ፣ ክፉ ሰዎች የሚያገኙት ገቢ ግን መከራ ያመጣባቸዋል፡፡
\s5
\v 7 የጥበበኛ ሰዎች ከንፈሮች እውቀትን ያስፋፋሉ፣ የሞኞች ልብ ግን እንዲህ አይደለም፡፡
\v 8 እግዚአብሔር የክፉዎችን መስዋዕት ይጠላል፣ የቅኖች ጸሎት ግን ደስ ያሰኘዋል፡፡
\s5
\v 9 እግዚአብሔር የክፉዎችን መንገድ ይጠላል፣ ጽድቅን የሚከታተለውን ግን ይወደዋል፡፡
\v 10 ከመንገድ የሚወጣ ሰው ከባድ ቅጣት ይጠብቀዋል፣ እርምትን የሚጠላም ይሞታል፡፡
\s5
\v 11 ሲኦልና ጥፋት በእግዚአብሔር ፊት የተገለጡ ናቸው፤ የሰው ልጆች ልብማ ምንኛ የተገለጠ ይሆን?
\v 12 ፌዘኛ እርምትን ይንቃል፤ ወደ ጥበበኛም አይሄድም፡፡
\s5
\v 13 ደስተኛ ልብ ፊትን ያፈካል፣ የልብ ሐዘን ግን መንፈስን ይሰብራል፡፡
\v 14 የአስተዋይ ልብ እውቀትን ይፈልጋል፣ የሞኞች አፍ ግን ከንቱነትን ይመገባል፡፡
\s5
\v 15 የተጨቆኑ ሰዎች ቀናት በሙሉ አሰቃቂ ናቸው፣ ደስተኛ ልብ ግን የማይቋረጥ ግብዣ አለው፡፡
\v 16 እግዚአብሔርን ከመፍራት ጋር ያለ ጥቂት ነገር ከሁከት ጋር ካለ ትልቅ ሃብት ይሻላል፡፡
\s5
\v 17 ፍቅር ባለበት የአትክልት ምግብ መብላት ጥላቻ ባለበት የሰባ ጥጃ ከመብላት ይሻላል፡
\v 18 ቁጡ ሰው ጭቅጭቅን ያነሳሳል፣ ለቁጣ የዘገየ ሰው ግን ጠብን ጸጥ ያሰኛል፡፡
\s5
\v 19 የታካች ሰው መንገድ በእሾህ እንደ ታጠረ ስፍራ ነው፣ የቅን መንገድ ግን በሚገባ የተገነባ አውራ ጎዳና ነው፡፡
\v 20 ጥበበኛ ልጅ ለአባቱ ደስታን ያመጣለታል፣ ሞኝ ሰው ግን እናቱን ይንቃል፡፡
\s5
\v 21 ከንቱ ነገር አእምሮ ለጎደለው ሰው ደስ ያሰኛል፣ አስተዋይ ሰው ግን በቅን መንገድ ይሄዳል፡፡
\v 22 ምክር በሌለበት እቅድ ይበላሻል፣ በአማካሪዎች ብዛት ግን ይከናወናል፡፡
\s5
\v 23 ሰው ተገቢ የሆነ መልስ ሲሰጥ ደስታን ያገኛል፤ የጊዜው ቃል ምንኛ መልካም ነው!
\v 24 የሕይወት መንገድ አስተዋይ ሰዎችን ወደ ላይ ይመራቸዋል፣ በታች ካለው ከሲኦል ያመልጥ ዘንድ፡፡
\s5
\v 25 እግዚአብሔር የትዕቢተኛውን ውርስ ያፈራርሳል፣ የመበለቲቱን ንብረት ግን ይጠብቃል፡፡
\v 26 እግዚአብሔር የክፉ ሰዎችን ሐሳብ ይጠላል፣ የርኅራኄ ቃሎች ግን ንጹሐን ናቸው፡፡
\s5
\v 27 ዘራፊ ለቤተሰቡ መከራን ያመጣል፣ ጉቦን የሚጠላ ግን በሕይወት ይኖራል፡፡
\v 28 ጽድቅን የሚያደርግ ሰው ልብ መልስ ከመስጠቱ በፊት አጥብቆ ያስባል፣ የክፉ ሰዎች አፍ ግን ክፋትን ሁሉ ያጎርፋል፡፡
\s5
\v 29 እግዚአብሔር ከክፉ ሰዎች እጅግ ሩቅ ነው፣ ጽድቅን የሚያደርጉ ሰዎችን ጸሎት ግን ይሰማል፡፡
\v 30 የዓይን ብርሃን ለልብ ደስታን ያመጣል፣ መልካም ወሬ ደግሞ ለሰውነት ጤና ነው፡፡
\s5
\v 31 አንድ ሰው እንዴት መኖር እንዳለብህ እርምትን ሲሰጥህ ትኩረት ሰጥተህ የምትሰማ ከሆንህ፣ በጥበበኛ ሰዎች መካከል ትቆያለህ፡፡
\v 32 ተግሳጽን የማይቀበል ራሱን ይንቃል፣ እርምትን የሚያደምጥ ግን ማስተዋልን ያገኛል፡፡
\s5
\v 33 የእግዚአብሔር ፍርሃት ጥበብን ያስተምራል፣ ትህትናም ከክብር በፊት ትመጣለች፡፡
\s5
\c 16
\p
\v 1 የልብ እቅድ የሰው ነው፣ መልስ ግን ከእግዚአብሔር አንደበት ይመጣል፡፡
\v 2 የአንድ ሰው መንገዶች ሁሉ ለእርሱ ንጹህ ሆኖ ይታየዋል፣ እግዚአብሔር ግን መንፈስን ይመዝናል፡፡
\s5
\v 3 ስራህን ለእግዚአብሔር አስረክብ፣ እቅድህም ይሳካልሃል፡፡
\v 4 እግዚአብሔር ሁሉን ነገር ለራሱ ዓላማ ፈጠረ፣ ሃጢአተኛውንም እንኳ ለክፉ ቀን፡፡
\s5
\v 5 እግዚአብሔር እምቢተኛ ልብ ያለውን ሁሉ ይጠላል፣ ተባብረው ቢቆሙም ከቅጣት አያመልጡም፡፡
\v 6 በኪዳን በተመሰረተ ታማኝነትና እውነተኛነት ኃጢአት ስርየት ያገኛል፣ እግዚአብሔርን በመፍራትም ሰዎች ከክፋት ይርቃሉ፡፡
\s5
\v 7 የሰው መንገዶቹ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኙ ሲሆኑ፣ እግዚአብሔር የዚያን ሰው ጠላቶች እንኳ ከእርሱ ጋር በሰላም እንዲኖሩ ያደርጋል፡፡
\v 8 ፍትህ በጎደለው መንገድ ከተገኘ በርካታ ገቢ ይልቅ፣ በጽድቅ የተገኘ ጥቂት ገቢ ይሻላል፡፡
\s5
\v 9 ሰው በልቡ መንገዱን ያቅዳል፣ እግዚአብሔር ግን እርምጃውን ያቀናለታል፡፡
\v 10 ውሳኔ በንጉስ ከንፈሮች ላይ አለ፣ በፍርድም ጊዜ አፉ በማታለል አይናገርም፡፡
\s5
\v 11 እውነተኛ ሚዛን ከእግዚአብሔር ይመጣል፤ በከረጢትም ውስጥ ያሉት መመዘኛዎች ሁሉ የእርሱ ስራዎች ናቸው፡፡
\v 12 ነገስታት ክፋትን ሲሰሩ፣ እርሱ አጸያፊ ነገር ነው፣ ዙፋን የሚጸናው ጽድቅን በማድረግ ነውና፡፡
\s5
\v 13 ንጉስ እውነትን በሚናገሩ ከንፈሮች ደስ ይለዋል፣ በግልጽነት የሚናገረውንም ሰው ይወደዋል፡፡
\v 14 የንጉስ ቁጣ የሞት መልእክተኛ ነው፣ ጥበበኛ ሰው ግን የንጉሱን ቁጣ ያበርዳል፡፡
\s5
\v 15 የንጉስ ፊት ሲያበራ ሕይወት አለ፣ መልካም ፈቃዱም የጸደይን ዝናብ እንደሚያመጣ ደመና ነው፡፡
\v 16 ከወርቅ ይልቅ ጥበብን ማግኘት ምንኛ ይበልጣል፡፡ ከብርም ይልቅ ማስተዋል ይመረጣል፡፡
\s5
\v 17 የጻድቃን መንገድ ከክፋት ትርቃለች፤ ሕይወቱን የሚጠብቅም መንገዱን ይጠብቃል፡፡
\v 18 ትዕቢት ከጥፋት በፊት ትመጣለች፣ ኩሩ መንፈስም ከውድቀት በፊት፡፡
\s5
\v 19 ከትዕቢተኞች ጋር ዝርፊያን ከመካፈል ይልቅ ከድሆች ጋር ራስን ዝቅ ማድረግ ይሻላል፡፡
\v 20 የተማሩትን የሚያሰላስሉ ሰዎች መልካምን ነገር ያገኛሉ፣ በእግዚአብሔር የሚታመኑም ደስተኛ ይሆናሉ፡፡
\s5
\v 21 በልቡ ጥበበኛ የሆነ ሰው አስተዋይ ይባላል፣ ጣፋጭ ንግግርም የማስተማር ችሎታን ያዳብራል፡፡
\v 22 ገንዘብ ላደረገው ማስተዋል የሕይወት ምንጭ ነው፣ የሞኞች ቅጣት ግን ሞኝነታቸው ነው፡፡
\s5
\v 23 የጥበበኛ ሰው ልብ ለአፉ ትምህርትን ይሰጠዋል፣ ለከንፈሮቹም ትምህርትን ይጨምራል፡፡
\v 24 ደስ የሚያሰኙ ቃላት የማር ወለላ ናቸው፣ ለነፍስ የሚጣፍጡ አጥንትንም የሚፈውሱ ናቸው፡፡
\s5
\v 25 ለሰው ትክክል የሚመስል መንገድ አለ፣ ፍጻሜው ግን ወደ ሞት የሚወስድ ነው፡፡
\v 26 የሰራተኛ ረሃብ ለእርሱ ይሰራል፤ ረሃቡም ያነሳሳዋል፡፡
\s5
\v 27 የማይረባ ሰው ክፋትን ይቆፍራል፣ ንግግሩም እንደሚያቃጥል እሳት ነው፡፡
\v 28 ጠማማ ሰው ጥልን ያነሳሳል፣ ሐሜትም የቅርብ ወዳጆችን ያለያያል፡፡
\s5
\v 29 በጥባጭ ሰው ጎረቤቱን ይዋሻል፣ መልካም ወዳልሆነ መንገድም ይመራዋል፡፡
\v 30 በዓይኑ የሚጠቅስ ሰው ጠማማ ነገሮችን ያስባል፤ ከንፈሮቻቸውን የሚነክሱም ክፋትን ይጎትታሉ፡፡
\s5
\v 31 ሽበት የክብር ዘውድ ነው፤ በጽድቅ መንገድ በመኖር ይገኛል፡፡
\v 32 ጦረኛ ከመሆን ይልቅ ትዕግስተኛ መሆን ይሻላል፣ መንፈሱን የሚገዛም ከተማን ከሚቆጣጠር ይልቅ ይበረታል፡፡
\s5
\v 33 እጣ በጉያ ይጣላል፣ ውሳኔው ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው፡፡
\s5
\c 17
\p
\v 1 ጥል ባለበት ግብዛ ከሞላበት ቤት ይልቅ ሰላም ባለበት ደረቅ ቁራሽ ዳቦ ይሻላል፡፡
\v 2 ጥበበኛ ባርያ አስነዋሪ ስራ የሚሰራውን ልጅ ይገዛል፣ ከወንድማማቾችም መካከል እንደ አንዱ ውርስን ይካፈላል፡፡
\s5
\v 3 ማቅለጫ ለብር ነው እቶንም ለወርቅ ነው፣ እግዚአብሔር ግን ልብን ያነጥራል፡፡
\v 4 ክፋትን የሚያደርግ ሰው ክፋትን የሚናገሩ ሰዎች ምክር ይሰማል፤ ውሸታምም ክፉ ነገሮች የሚያወሩ ሰዎችን ያዳምጣል፡፡
\s5
\v 5 በድሃ የሚቀልድ ሰው ፈጣሪውን ይሰድባል፣ በጥፋትም የሚደሰት ከቅጣት አያመልጥም፡፡
\v 6 የልጅ ልጆች ለሽማግሌዎች ዘውድ ናቸው፣ ወላጆችም ለልጆቻቸው ክብር ናቸው፡፡
\s5
\v 7 መልካም ንግግር ለሞኝ ሰው አይስማማውም፤ ውሸታም ከንፈሮችም ለንጉሳውያን አይመቹም፡፡
\v 8 ጉቦ ለሰጪው እንደ አስማት ድንጋይ ነው፤ በሄደበት ስፍራ ሁሉ ስኬትን ያገኛል፡፡
\s5
\v 9 በደልን የሚሸፍን ፍቅርን ይፈልጋል፣ ነገርን የሚደጋግም ግን የቅርብ ወዳጆችን ይለያያል፡፡
\v 10 መቶ ግርፋት ወደ ሞኝ ጠልቆ ከሚገባ ይልቅ ተግሳጽ ወደ አስተዋይ ሰው ጠልቆ ይገባል፡፡
\s5
\v 11 ክፉ ሰው አመጽን ይፈልጋል፣ ጨካኝ መልዕክተኛም ወደ እርሱ ይላክበታል፡፡
\v 12 ሞኝን በሞኝነቱ ከመገናኘት ይልቅ ግልገሎቿ የተነጠቀችን ድብ መገናኘት ይሻላል፡፡
\s5
\v 13 አንድ ሰው በበጎ ፈንታ ክፋትን ሲመልስ፣ ክፋት ከቤቱ ፈጽሞ አይርቅም፡፡
\v 14 የጠብ መጀመርያ በሁሉም ስፍራ ውኃ እንደሚለቅ ሰው ነው፣ ስለዚህ ከመበርታቱ በፊት ከግጭት ራቅ፡፡
\s5
\v 15 ክፉ ሰዎችን ነጻ የሚለቅም ሆነ ጽድቅን የሚያደርጉትን ደግሞ የሚኮንን ማንኛውም ሰው፣ ሁለቱም በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠሉ ናቸው፡፡
\v 16 ሞኝ ጥበብን ለመማር የማይችል ሆኖ ሳለ፣ ጥበብን ለመማር ለምን ገንዘብ ይከፍላል?
\s5
\v 17 ጓደኛ በዘመኑ ሁሉ ወዳጅ ነው፣ ወንድምም ለክፉ ቀን ይወለዳል፡፡
\v 18 አእምሮ የጎደለው ሰው ቃል በመግባት ግዴታ ውስጥ ይገባል፣ ለጎረቤቱም ብድር ዋስ ይሆናል፡፡
\s5
\v 19 ጠብ የሚወድ ኃጢአትን ይወዳል፤ መግቢያ በሩን እጅግ ከፍ አድርጎ የሚሰራ አጥንቶች እንዲሰበሩ ያደርጋል፡፡
\v 20 ጠማማ ልብ ያለው ሰው አንዳችም መልካም ነገር አያገኝም፤ ጠማማ ምላስ ያለውም ወደ መከራ ይወድቃል፡፡
\s5
\v 21 ሞኝን የወለደ ሐዘንን ወደራሱ ያመጣል፣ የሞኝም አባት ደስታን አያገኝም፡፡
\v 22 ደስተኛ ልብ ጥሩ መድሃኒት ነው፣ የተሰበረ መንፈስ ግን አጥንትን ያደርቃል፡፡
\s5
\v 23 ክፉ ሰው የፍትህን መንገድ ለማጣመም በሚስጥር ጉቦን ይቀበላል፡፡
\v 24 አስተዋይ ሰው ፊቱን ወደ ጥበብ ያዘነብላል፣ የሞኝ አይኖች ግን ወደ ምድር ዳርቻ ያዘነብላሉ፡፡
\s5
\v 25 ሞኝ ልጅ ለአባቱ ሐዘን ነው፣ ለወለደችውም እናቱ ምሬትን ያመጣል፡፡
\v 26 ጽድቅ የሚያደርግን ሰው መቅጣት በፍጹም መልካም አይደለም፤ በሐቀኝነት የሚሄዱትን የተከበሩ ሰዎችን መግረፍም መልካም አይደለም፡፡
\s5
\v 27 እውቀት ያለው ሰው ጥቂት ቃላትን ይናገራል፣ አስተዋይ ሰውም ለቁጣ የዘገየ ነው፡፡
\v 28 ሞኝ እንኳ ዝም ሲል ጥበበኛ እንደሆነ ይታሰባል፤ አፉንም ዘግቶ ዝም ሲል፣ እንደ ምሁር ይቆጠራል፡፡
\s5
\c 18
\p
\v 1 ራሱን ከሰው የሚለይ የራሱን ምኞት ይፈልጋል፣ ትክክለኛውንም ፍርድ ሁሉ ይቃወማል፡፡
\v 2 ሞኝ ሰው በማስተዋል ደስታን አያገኝም፣ በራሱ ልብ ውስጥ ያለውን ነገር በመግለጥ እንጂ፡፡
\s5
\v 3 ክፉ ሰው ሲመጣ፣ ንቀት ከእፍረትና ከስድብ ጋር አብረውት ይመጣሉ፡፡
\v 4 ከሰው አፍ የሚወጡ ቃላት ጥልቅ ውሃ ናቸው፤ የጥበብ ምንጭም የሚፈስ ወንዝ ነው፡፡
\s5
\v 5 ለክፉው ማድላት፣ ጽድቅን ለሚያደርጉም ፍትህን ማጉደል መልካም አይደለም፡፡
\v 6 የሞኝ ከንፈሮች ጥልን ያመጡበታል፣ አፉም በትርን ትጠራለች፡፡
\s5
\v 7 የሞኝ አፍ መጥፊያው ነው፣ በከንፈሮቹም ራሱን ወጥመድ ውስጥ ይጥላል፡፡
\v 8 የሐሜት ቃላት እንደ ጣፋጭ ጉርሻ ናቸው፣ ወደ ሰውነት ውስጣዊ ክፍሎች ጠልቀው ይገባሉ፡፡
\s5
\v 9 በስራው ችላ የሚልም ብዙውን የአጥፊ ሰው ወንድም ነው፡፡
\v 10 የእግዚአብሔር ስም ጽኑ ግንብ ነው፤ ጽድቅን የሚያደርግ ሰው ወደ እርሱ ሮጦ ይድናል፡፡
\s5
\v 11 የባለጸጋ ሐብት የእርሱ የተመሸገ ከተማ ነው፣ ሃሳቡም እንደ ረዥም ግንብ ነው፡፡
\v 12 ከውድቀቱ በፊት የሰው ልብ ትዕቢተኛ ይሆናል፣ ትህትና ግን ክብርን ቀድሞ ይመጣል፡፡
\s5
\v 13 ከማድመጡ በፊት የሚመልስ ሰው ሞኝነትና ዕፍረት ይሆንበታል፡፡
\v 14 የሰው መንፈስ ሕመምን ትታገሳለች፣ የተሰበረን መንፈስ ግን ማን ሊሸከም ይችላል?
\s5
\v 15 የአስተዋይ ሰው ልብ እውቀትን ያገኛል፣ የጠቢብም ጆሮ ይፈልገዋል፡፡
\v 16 የሰው ስጦታ መንገዱን ትከፍትለታለች በተከበሩም ሰዎች ፊት ታቆመዋለች፡፡
\s5
\v 17 ወደ ፍርድ ቀድሞ በመምጣት ጉዳዩን የሚያሰማ ጻድቅ ይመስላል፣ ይህ ግን የሚሆነው ተቀናቃኙ መጥቶ እስከሚጠይቀው ድረስ ነው፡፡
\v 18 እጣ ማውጣት ክርክርን ያቆማል፣ ሃይለኛ ጠላቶችንም ትለያለች፡፡
\s5
\v 19 የተበደለ ወንድምን መርታት ጠንካራ ከተማን ከማሸነፍ ይልቅ በጣም የከበደ ነው፣ ጠብም እንደ ግንብ ብረት ነው፡፡
\v 20 የሰው ሆድ ከአፉ ፍሬ ይሞላል፤ በንፈሮቹም ምርት ይረካል፡፡
\s5
\v 21 ሞትና ሕይወት በምላስ ላይ ናቸው፣ የሚወዱትም ፍሬዋን ይበላሉ፡፡
\v 22 ሚስትን ያገኘ መልካምን ነገር አግኝቷል፣ ከእግዚአብሔርም ዘንድ ሞገስን አግኝቷል፡፡
\s5
\v 23 ድሃ ሰው ምህረትን ይለምናል፣ ሃብታም ግን በማመናጨቅ ይመልሳል፡፡
\v 24 ብዙ ጓደኞች ያለው ሰው በእነርሱ አማካኝነት ወደ ጥፋት ይመጣል፣ ከወንድም የቀረበ ጓደኛ ግን አለ፡፡
\s5
\c 19
\p
\v 1 በንግግሩ ጠማማ ከሆነና ከሞኝ ሰው ይልቅ በሃቀኝነት የሚራመድ ድሃ ሰው ይሻላል፡፡
\v 2 ደግሞም ያለ እውቀት አንድን ነገር መመኘት መልካም አይደለም፣ በችኮላ የሚሮጥም መንገዱን ይስታል፡፡
\s5
\v 3 የሰው ጅልነት ሕይወቱን ያበላሸዋል፣ ልቡም በእግዚአብሔር ላይ ይቆጣል፡፡
\v 4 ሐብት ብዙ ጓደኞችን ይጨምራል፣ ድሃ ሰው ግን ከወዳጆቹ የተለየ ነው፡፡
\s5
\v 5 ሐሰተኛ ምስክር ሳይቀጣ አይታለፍም፣ ውሸትንም የሚያሰራጭ አያመልጥም፡፡
\v 6 ብዙዎች ከቸር ሰው ውለታን ይጠይቃሉ፣ ስጦታን ለሚሰጥም ሁሉ ጓደኛ ይሆነዋል፡፡
\s5
\v 7 ድሃ ሰው ወንድሞቹ ሁሉ ይጠሉታል፤ ከእርሱ ብዙ ርቀው የሚገኙ ጓደኞቹማ ምንኛ ይጠሉት! ወደ እነርሱ ይጣራል፣ እነርሱ ግን አይገኙም፡፡
\v 8 ጥበብን የሚያገኝ ሕይወቱን ይወዳል፤ ማስተዋልንም ገንዘቡ ያደረገ መልካም ነገር ያገኛል፡፡
\s5
\v 9 ሐሰተኛ ምስክር ሳይቀጣ አይቀርም፣ ውሸትን የሚያሰራጭ ግን ይጠፋል፡፡
\v 10 ለሞኝ በቅንጦት መኖር አይገባውም፣ ባርያ መሳፍንትን ሲገዛ ደግሞ ምንኛ የከፋ ይሆን፡፡
\s5
\v 11 ጠቢብ አእምሮ ሰውን ታጋሽ ያደርገዋል፣ በደልንም መተው ክብር ይሆንለታል፡፡
\v 12 የንጉስ ቁጣ እንደ ጎረምሳ አንበሳ ግሳት ነው፣ በፊቱ ሞገስ ማግኘት ግን ሳር ላይ እንዳለ ጤዛ ነው፡፡
\s5
\v 13 ሞኝ ልጅ ለአባቱ መጥፊያ ነው፣ ጨቅጫቃ ሚስትም እንደማያቋርጥ የውኃ ነጠብጣብ ናት፡፡
\v 14 ቤትና ሐብት ከወላጆች ይወረሳል፣ ጠንቃቃ ሚስት ግን ከእግዚአብሔር ናት፡፡
\s5
\v 15 ስንፍና ሰውን ወደ እንቅልፍ ይጥለዋል፣ ለመስራት የማይፈቅድ ግን ይራባል፡፡
\v 16 ትእዛዛትን የሚያከብር ሕይወቱን ይጠብቃል፣ ስለ መንገዶቹ የማያስብ ሰው ግን ይሞታል፡፡
\s5
\v 17 ለድሃ ቸር የሆነ ሰው ለእግዚአብሔር ያበድራል፣ ለሰራውም ቸርነት መልሶ ይከፍለዋል፡፡
\v 18 ተስፋ ሳለ ልጅህን ስርዓት አስይዘው፣ ሞቱንም እየተመኘህ ዝም ብለህ አትየው፡፡
\s5
\v 19 ንዴቱን መቆጣጠር የማይችል ሰው ቅጣቱን ማግኘት አለበት፤ ብታድነውም ለሁለተኛ ጊዜ ማድረግህ አይቀርም፡፡
\v 20 ምክርን ስማ ተግሳጽንም ተቀበል፣ በሕይወትህ መጨረሻ ጥበበኛ እንድትሆን፡፡
\s5
\v 21 በሰው ልብ ብዙ እቅዶች አሉ፣ የሚፈጸመው ግን የእግዚአብሔር ሃሳብ ነው፡፡
\v 22 ሰው የሚመኘው ታማኝ ሆኖ መገኘት ነው፣ ድሃም ሰው ከውሸታም ይሻላል፡፡
\s5
\v 23 እግዚአብሔርን ማክበር ሰዎችን ወደ ሕይወት ይመራል፤ እንዲህ ያለውም ሰው ይረካል በመከራም አይጎዳም፡፡
\v 24 ሰነፍ ሰው እጁን በሳህን ውስጥ ያጠልቃል፤ ወደ አፉም እንኳ እንደገና መልሶ አያመጣውም፡፡
\s5
\v 25 ፌዘኛን ብትመታው፣ ያልተማረው ጠንቃቃ ይሆናል፤ አስተዋዩን ብታርመው እውቀትን ያገኛል፡፡
\s5
\v 26 ከአባቱ የሚሰርቅ እናቱንም የሚያሳድድ ዕፍረትና ውርደት የሚያመጣ ልጅ ነው፡፡
\v 27 ልጄ ሆይ፣ ተግሳጽን አልሰማ ብትል፣ ከእውቀት ቃሎች ትስታለህ፡፡
\s5
\v 28 ምግባረ ብልሹ ምስክር በፍትህ ላይ ያፌዛል፣ የክፉ ሰው አፍም በደልን ይውጣል፡፡
\v 29 ለፌዘኞች ፍርድ፣ ለሞኞች ጀርባም ጅራፍ ተዘጋጅቶላቸዋል፡፡
\s5
\c 20
\p
\v 1 ወይን ጠጅ ፌዘኛ፣ ብርቱ መጠጥም ጠበኛ ያደርጋል፤ በመጠጥ የሳተ ሁሉ ጠቢብ አይደለም፡፡
\v 2 የንጉስ ቁጣ እንደሚያገሳ ደቦል አንበሳ ቁጣ ነው፤ የሚያስቆጣውም ሰው ሕይወቱን ይከፍላል፡፡
\s5
\v 3 ጥልን መራቅ ለማንም ሰው ቢሆን ክብር ነው፣ ሞኝ ሰው ግን ወደ ጭቅጭቅ ይገባል፡፡
\v 4 ሰነፍ ሰው በመከር ወቅት አያርስም፤ በምርት ጊዜ እህል ይለምናል ነገር ግን ምንም አያገኝም፡፡
\s5
\v 5 በሰው ልብ ውስጥ ያለ አሳብ እንደ ጥልቅ ውሃ ነው፣ አስተዋይ ሰው ግን ከዚያ ቀድቶ ያወጣዋል፡፡
\v 6 ብዙ ሰው ታማኝ እንደሆነ ይናገራል፣ ታማኝ የሆነውን ግን ማን ሊያገኘው ይችላል?
\s5
\v 7 ጽድቅን የሚያደርግ ሰው በሐቀኝነቱ ይራመዳል፣ ፍለጋውን የሚከተሉ ልጆቹም ደስተኞች ናቸው፡፡
\v 8 የዳኛን ተግባር በማከናወን በዙፋኑ ላይ የተቀመጠ ንጉስ በፊቱ ያለውን ክፋት ሁሉ በዓይኖቹ አበጥሮ ይለያል፡፡
\s5
\v 9 “ልቤን በንጽህና ጠብቄያለሁ፤ ከኃጢአቴ ንጹህ ነኝ” ብሎ መናገር የሚችል ማን ነው?
\v 10 1የተለያዩ ሚዛኖችና እኩል ያልሆኑ መስፈሪያዎች፣ ሁለቱንም እግዚአብሔር ይጠላቸዋል፡፡
\s5
\v 11 ወጣት እንኳ ባህርዩ ንጹህና ቅን መሆኑ በስራው ይታወቃል፡፡
\v 12 የሚሰሙ ጆሮዎችና የሚያዩ ዓይኖች፣ ሁለቱንም እግዚአብሔር ሰራቸው፡፡
\s5
\v 13 እንቅልፍን አትውደድ ወደ ድህነት ትመጣለህና፤ ዓይኖችህን ክፈት፣ የተትረፈረፈ መብል ይኖርሃል፡፡
\v 14 ዕቃ የሚገዛ ሰው “መጥፎ ነው! መጥፎ ነው!” ይላል፣ በሄደ ጊዜ ግን ይኩራራል፡፡
\s5
\v 15 ወርቅና ብዙ ውድ ድንጋዮች አሉ፣ የእውቀት ከንፈሮች ግን የከበረ ጌጥ ናቸው፡፡
\v 16 ለማይታወቅ ሰው ብድር በዋስትና ገንዘብ ያስያዘውን ሰው ልብስ ውሰድበት፣ ዝሙት ለምትፈጽም ሴት ዋስትና አስይዞ ከሆነ ውሰድበት፡፡
\s5
\v 17 በማጭበርበር የተገኘ ዳቦ ይጣፍጣል፣ ከዚያ በኋላ ግን አፉ ጠጠር ይሞላል፡፡
\v 18 እቅዶች በምክር ይጸናሉ፣ በጠቢብ ምክርም ብቻ ጦርነት አድርግ፡፡
\s5
\v 19 ሐሜት ሚስጥርን ያባክናል፣ ስለዚህ ወሬን ከሚያበዙ ሰዎች ጋር አንድነት አትፍጠር፡፡
\v 20 አንድ ሰው አባቱን ወይም እናቱን ከሰደበ፣ መብራቱ በድቅድቅ ጨለማ መካከል ይጠፋል፡፡
\s5
\v 21 በመጀመርያ በጥድፊያ የተገኘ ሀብት በመጨረሻ ላይ በረከት አይኖረውም፡፡
\v 22 “ለፈጸምክብኝ በደል ብድራትህን እመልስልሃለሁ” አትበል! እግዚአብሔርን ጠብቅ እርሱም ያድንሃል፡፡
\s5
\v 23 እኩል ያልሆኑ ሚዛኖችን እግዚአብሔር ይጠላል፣ ሐሰተኛ መስፈሪያም መልካም አይደለም፡፡
\v 24 የሰው አካሄድ በእግዚአብሔር ይመራል፤ ታዲያ ሰው የራሱን መንገድ እንዴት ሊያስተውል ይችላል?
\s5
\v 25 ሰው በችኮላ “ይህ ነገር የተቀደሰ ነው” ቢሎ ስእለት ቢሳል፣ ከተሳለም በኋላ ስለ ነገሩ ምንነት ማሰላሰል ቢጀምርና ቢጸጸት ወጥመድ ይሆንበታል፡፡
\v 26 ጥበበኛ ንጉስ ክፉውን አበጥሮ ያወጣል፣ ከዚያም የመውቂያ ጋሪውን በላያቸው ላይ ይነዳል፡፡
\s5
\v 27 የሰው መንፈስ የእግዚአብሔር መብራት ነው፣ ውስጣዊ ማንነቱንም ይመረምራል፡፡
\v 28 በኪዳን የተመሰረተ ታማኝነትና እውነተኛነት ንጉስን ይጠብቁታል፤ ዙፋኑም በፍቅር ይጸናል፡፡
\s5
\v 29 የወጣት ወንዶች ክብር ጥንካሬያቸው ነው፣ የሽማግሌዎችም ውበት ሽበታቸው ነው፡፡
\v 30 የሚያቆስል ምት ክፋትን ያስወግዳል፣ ግርፋትም ውስጣዊ የሰውነት ክፍሎችን ያነጻል፡፡
\s5
\c 21
\p
\v 1 የንጉስ ልብ በእግዚአብሔር እጅ እንዳለ የውኃ ፈሳሽ ነው፤ እርሱ ደስ ወዳሰኘው ይመራዋል፡፡
\v 2 ለሰው መንገዱ በራሱ ዓይን ፊት ቀና ሊመስለው ይችላል፣ ልብን የሚመዝን ግን እግዚአብሔር ነው፡፡
\s5
\v 3 ከመስዋዕት ይልቅ ጽድቅንና ፍትሕን ማድረግ በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት አለው፡፡
\v 4 ትቢተኛ ዓይንና ኩሩ ልብ፣ የክፉ ሰውም መብራት፣ ኃጢአት ናቸው፡፡
\s5
\v 5 የትጉ ሰው እቅዶች ወደ ብልጽግና ይመራሉ፣ በችኮላ የሚያደርግ ሰው ሁሉ ግን ወደ ድህነት ይመጣል፡፡
\v 6 በሐሰተኛ ምላስ ሀብትን ማግኘት በኖ የሚጠፋ ተን፣ የሚገድልም ወጥመድ ነው፡፡
\s5
\v 7 የክፉዎች አመጽ ራሳቸውን ይጠራርጋቸዋል፣ ፍትሕን ማድረግ አይፈቅዱምና፡፡
\v 8 የበደለኛ ሰው መንገድ ጠማማ ነው፣ ንጹሕ ሰው ግን ጽድቅን ያደርጋል፡፡
\s5
\v 9 ከጠበኛ ሚስት ጋር በአንድ ቤት ከመኖር በጣራ ማእዘን ላይ ተጠግቶ መኖር ይሻላል፡፡
\v 10 የክፉ ሰው ምኞት ክፋትን አጥብቆ ይመኛል፤ ጎረቤቱም በዓይኖቹ ውስጥ ምንም ደግነት አያይም፡፡
\s5
\v 11 ፌዘኛ ሲቀጣ ፣ እውቀት አልባ ሰው ጥበበኛ ይሆናል፣ ጥበበኛ ሰው ሲገሰጽ፣ እውቀትን ይጨምራል፡፡
\v 12 ጽድቅን የሚያደርግ ሰው የክፉውን ቤት ልብ ብሎ ይመለከታል፤ እርሱ ክፉውን ወደ ጥፋት ያወርደዋል፡፡
\s5
\v 13 የድሆችን ጩኸት የማይሰማ ሰው፣ እርሱም ሲጮህ ማንም አይሰማውም፡፡
\v 14 በምስጢር የተደረገ ስጦታ ቁጣን ያበርዳል፣ የተሸሸገ ስጦታም ታላቅ ቁጣን ያጠፋል፡፡
\s5
\v 15 ፍትሕ በተደረገ ጊዜ ጽድቅን ላደረገው ሰው ደስታን ያመጣለታል፣ ለክፉ አድራጊዎች ግን ሽብር ያመጣባቸዋል፡፡
\v 16 ከማስተዋል መንገድ የሳተ ሰው፣ በሙታን ጉባኤ ውስጥ ያርፋል፡፡
\s5
\v 17 ቅንጦት የሚወድ ሰው ድሃ ይሆናል፤ የወይን ጠጅና ዘይት የሚወድ ደግሞ ባለጠጋ አይሆንም፡፡
\v 18 ክፉ ሰው ጽድቅን ለሚያደርግ ሰው ቤዛ ይሆናል፣ ከዳተኛ ሰው ደግሞ ለጻድቅ ቤዛ ነው፡፡
\s5
\v 19 ጠብ ከምታነሳሳና ያለማቋረጥ ከምታማርር ሴት ጋር ከመኖር በምድረ በዳ መኖር ይሻላል፡፡
\v 20 የከበረ ሀብትና ዘይት በጥበበኛ ቤት ይገኛሉ፣ ሞኝ ሰው ግን ያባክናቸዋል፡፡
\s5
\v 21 ጽድቅን የሚያደርግና ደግ ሰው፣ ይህ ሰው ሕይወትን፣ ጽድቅንና ክብርን ያገኛል፡፡
\v 22 ጥበበኛ ሰው ወደ ኃያላን ከተማ ይገባል፣ የምትታመንበት ምሽጓንም ያፈርሳል፡፡
\s5
\v 23 አፉንና ምላሱን የሚጠብቅ ሰው ራሱን ከመከራ ይጠብቃል፡፡
\v 24 ኩሩና ትዕቢተኛ ሰው ስሙ “ሞኝ” ይባላል፣ እርሱም በእብሪትና በትዕቢት ያደርጋል፡፡
\s5
\v 25 የሰነፍ ምኞት ራሱን ይገድለዋል፣ እጆቹ ለመስራት አይፈቅዱምና፡፡
\v 26 እርሱ ቀኑን በሙሉ ይመኛል፣ ተጨማሪ ይመኛል፣ ጽድቅን የሚያደርግ ግን ይሰጣል፣ አይሰስትምም፡፡
\s5
\v 27 የክፉዎች መስዋዕት አስጸያፊ ነው፤ በክፉ ሃሳብ ሲያቀርበው ደግሞ የበለጠ አስጸያፊ ነው፡፡
\v 28 ሐሰተኛ ምስክር ይጠፋል፣ የሚያዳምጥ ሰው ግን ለሁልጊዜ የሚሆን ይናገራል፡፡
\s5
\v 29 ክፉ ሰው ራሱን ጠንካራ አስመስሎ ያቀርባል፣ ጻድቅ ሰው ግን ስለ ድርጊቶቹ ይጠነቀቃል፡፡
\s5
\v 30 እግዚአብሔርን ሊቋቋም የሚችል ጥበብ፣ ማስተዋል ወይም ምክር የለም፡፡
\v 31 ፈረስ ለጦርነት ቀን ይዘጋጃል፣ ድል ግን የእግዚአብሔር ነው፡፡
\s5
\c 22
\p
\v 1 ከብዙ ሐብት ይልቅ ጥሩ ስም ይመረጣል፣ ሞገስም ከብርና ከወርቅ ይበልጣል፡፡
\v 2 ሃብታምና ድሃ ሰዎች የሚጋሩት አንድ ነገር አለ፤ ይህም እግዚአብሔር የሁሉም ፈጣሪ መሆኑ ነው፡
\s5
\v 3 ጠንቃቃ ሰው ችግር ሲያይ ራሱን ይሸሽጋል፣ አላዋቂዎች ግን በዚያው ገፍተው ይሄዳሉ በሱም ምክንያት ይጎዳሉ፡፡
\v 4 የትህትናና እግዚአብሔርን የመፍራት ሽልማት ባለጠግነት፣ ክብርና ሕይወት ነው፡፡
\s5
\v 5 እሾህና አሜኬላ በጠማማ ሰው መንገድ ላይ ይገኛሉ፤ ሕይወቱን የሚጠብቅም ከእነርሱ ይርቃል፡፡
\v 6 ልጅን የሚሄድበትን መንገድ አስተምረው፣ በሸመገለም ጊዜ ከነገርከው መንገድ ፈቀቅ አይልም፡፡
\s5
\v 7 ባለጠጎች ድሆችን ይገዛሉ፣ ተበዳሪም ለአበዳሪው ባርያ ነው፡፡
\v 8 ክፋትን የሚዘራ መከራን ያጭዳል፣ የቁጣውም በትር አይጠቅመውም፡፡
\s5
\v 9 ቸር አይኖች ያሉት ሰው ይባረካል፣ እንጀራውን ከድሆች ጋር ይካፈላልና፡፡
\v 10 ፌዘኛን ከአንተ አርቀው፣ ጠብም ከአንተ ይርቃል፤ ግጭትና ስድብም ይቆማሉ፡፡
\s5
\v 11 ንጹህ ልብ የሚወድድና ንግግሩም ሞገስ ያለው ሰው፣ ንጉስ ጓደኛው ይሆናል፡፡
\v 12 የእግዚአብሔር ዓይኖች እውቀትን ይከታተላሉ፣ የከዳተኞችን ቃሎች ግን ይገለብጣል፡፡
\s5
\v 13 ሰነፍ ሰው “አንበሳ በመንገድ ላይ አለ! በውጪ ላይ እገደላለሁ” ይላል፡፡
\v 14 የአመንዝራ ሴት አፍ ጥልቅ ጉድጓድ ነው፤ ወደ እርሱም በሚወድቅ ሰው ሁሉ የእግዚአብሔር ቁጣ በእርሱ ላይ ይሆናል፡፡
\s5
\v 15 ሞኝነት በሕጻን ልብ ላይ ታስሯል፣ የስርዓት በትር ግን ከእርሱ ያርቀዋል፡፡
\v 16 ሀብቱን ለማካበት ወይም ለሀብታሞች ለመስጠት ሲል ድሆችን የሚያስጨንቅ፣ ወደ ድህነት ይመጣል፡፡
\s5
\v 17 የጠቢብን ቃላት ልብ በል አስተውለህም ስማ፣ ልብህንም ወደ ከእውቀቴ አዘንብል፣
\v 18 በውስጥህ ብትጠብቃቸውና ሁሉም በከንፈሮችህ ላይ ዝግጁ ቢሆኑ ለአንተ ደስ ያሰኙሃልና፡፡
\v 19 እምነትህ በእግዚአብሔር ላይ ይሆን ዘንድ፣ እነዚህን ለአንተ ዛሬ አስተምርሃለሁ፣ ለአንተም ቢሆን አስተምርሃለሁ፡፡
\s5
\v 20 ሰላሳ የተግሳጽና የእውቀት ቃሎችን ለአንተ አልጻፍኩልህምን፣
\v 21 በእነዚህ ታማኝ ቃሎች እውነትን አስተምርህ ዘንድ፣ አንተም ለላኩህ ታማኝ መልስ ትሰጥ ዘንድ?
\s5
\v 22 ድሃ በመሆኑ ምክንያት ድሃ ሰው አትዝረፍ፣ ችግረኛውንም በበር ላይ አትግፋው፣
\v 23 እግዚአብሔር ለእነርሱ ይፈርድላቸዋልና፣ የዘረፏቸውንም ሰዎች ሕይወት እርሱ ይነጥቃል፡፡
\s5
\v 24 ግልፍተኛ ሰውን ጓደኛ አታድርግ፣ ቁጣም ካለበት ሰው ጋር አብረህ አትሂድ፣
\v 25 አለበለዚያ መንገዱን ትማራለህ፣ ራስህንም በወጥመድ ታጠላልፋለህ፡፡
\s5
\v 26 ገንዘብን በተመለከተ ግዴታ የሚያስገባ ውል የምትሰጥ አትሁን፣ ለሌሎችም ብድር ዋስ አትሁን፡፡
\v 27 መክፈል ካልቻልህ፣ ያንን ሰው አልጋህን ከስርህ ከመውሰድ ሊያቆመው የሚችል ምን ነገር አለ?
\s5
\v 28 አባቶችህ ያስቀመጡትን የጥንቱን የድንበር የምልክት ድንጋይ አታንሳ፡፡
\v 29 በስራው ስልጡን የሆነውን ሰው አይተሃልን? በነገስታት ፊት ይቆማል፤ በተራ ሰዎች ፊትም አይቆምም፡፡
\s5
\c 23
\p
\v 1 ከገዢ ጋር ለመብላት ስትቀመጥ፣ በፊት ያለውን በጥንቃቄ አስተውል፣
\v 2 ከመጠን ያለፈ ምግብ መብላት የምትወድ ዓይነት ሰው ከሆንህ በጉሮሮህ ላይ ካራ አድርግ፡፡
\v 3 የእርሱ ጣፋጭ ምግቦች አያስጎምጁህ፣ በውሸት የመጣ ምግብ ነውና፡፡
\s5
\v 4 ባለጠጋ ትሆን ዘንድ ከመጠን በላይ አትልፋ፤ መቼ ማቆም እንዳለብህም ታውቅ ዘንድ ብልህ ሁን፡፡
\v 5 አይንህን በገንዘብ ላይ በጣልክ ጊዜ፣ እርሱ ይጠፋል፣ በድንገት ክንፍ ያወጣል እንደ ንስርም ወደ ሰማይ እየበረረ ይሄዳል፡፡፤
\s5
\v 6 የክፉ ሰውን፣ እጅግ በጣም ከርቀት በምግብህ ላይ በቅናት የሚመለከተውን ሰው ምግብ አትብላ፣ ጣፋጭ መብሎቹንም አትጎምጅ፣
\v 7 እርሱ የምግቡን ዋጋ የሚቆጥር ሰው ነውና፡፡ “ብላ፣ ጠጣ!” ይልሃል፣ ልቡ ግን ከአንተ ጋር አይደለም፡፡
\v 8 ትንሽ የበላኸው ያስታውክሃል፣ የምስጋና ቃልህንም ከንቱ ታደርጋለህ፡፡
\s5
\v 9 ሞኝ ሰው ባለበት ንግግር አታድርግ፣ እርሱ የቃሎችህን ጥበብ ያንኳስሳልና፡፡
\v 10 የጥንቱን የድንበር የምልክት ድንጋይ አታንሳ፣ ወላጅ የሌላቸውን ልጆች እርሻ አትግፋ፣
\v 11 ታዳጊያቸው ብርቱ ነውና፣ እርሱ ጉዳያቸውን ከአንተ ጋር ይፋረዳል፡፡
\s5
\v 12 ልብህን ለተግሳጽ ጆሮህንም ለእውቀት ቃሎች ስጥ፡፡
\s5
\v 13 ልጅን ከመቅጣት ወደ ኋላ አትበል፣ በበትር ብትመታው አይሞትምና፡፡
\v 14 በበትር ብትመታው ነፍሱን ከሲኦል ታድናታለህ፡፡
\s5
\v 15 ልጄ ሆይ፣ ልብህ ጥበበኛ ቢሆን፣ ያኔ ልቤ ደግሞ ደስተኛ ይሆናል፤
\v 16 ከንፈሮችህ ትክክለኛ የሆነውን በሚናገሩበት ጊዜ ውስጣዊ ሰውነቴ ሁሉ ደስ ይለዋል፡፡
\s5
\v 17 ልብህ በኃጢአተኞች እንዲቀና አትፍቀድ፣ ነገር ግን ቀኑን ሙሉ እግዚአብሔርን በመፍራት ተመላለስ፡፡
\v 18 ለወደፊት እርግጠኛ አለኝታ አለህ፣ ተስፋህም አይጠፋም፡፡
\s5
\v 19 ልጄ ሆይ፣ ስማኝ፣ ጥበበኛ ሁን ልብህንም በትክክለኛው መንገድ ላይ አዘንብል፡፡
\v 20 ከሰካራሞች ወይም በሆዳምነት ስጋ ከሚበሉ ጋር አትተባበር፣
\v 21 ሰካራሞችና ሆዳሞች ድሃ ይሆናሉ፣ እንቅልፋምነትም ቁራጭ ጨርቅ ያስለብሳቸዋል፡፡
\s5
\v 22 የወለደህን አባትህን ስማ እናትህም ባረጀች ጊዜ አትናቃት፡፡
\v 23 እውነትን የራስህ አድርጋት፣ አትሽጣትም፤ ጥበብን፣ ስርዓትንና ማስተዋልንም ገንዘብህ አድርግ፡፡
\s5
\v 24 የጻድቅ አባት በደስታ ይሞላል፣ ጥበበኛ ልጅንም የወለደ በልጁ ይደሰታል፡፡
\v 25 አባትህና እናትህን ደስ አሰኛቸው፣ የወለደችህ እናትህም ሐሴት ታድርግ፡፡
\s5
\v 26 ልጄ ሆይ፣ ልብህን ስጠኝ፣ አይኖችህም የእኔን መንገድ ያስተውሉ፡፡
\v 27 ዝሙት አዳሪ ሴት ጥልቅ ጉድጓድ፣ የሌላ ሰውም ሚስት ጠባብ ጉድጓድ ናትና፡፡
\v 28 እንደ ሌባ አድፍጣ ጥጠብቃለች፣ በሰዎችም መካከል የከዳተኞችን ቁጥር ታበዛለች፡፡
\s5
\v 29 ዋይታ የማን ነው? ሃዘን የማን ነው? ጠብስ የማን ነው? ማጉረምረም የማን ነው? ያለ ምክንያት መቁሰል የማን ነው? የዓይን መቅላት የማን ነው?
\v 30 ወይን ጠጅ በመጠጣት የሚቆዩ፣ ድብልቅ ወይን ጠጅ የሚቀምሱ ሰዎች ነው፡፡
\s5
\v 31 በቀላ ጊዜ ወደ ወይን ጠጅ አትመልከት፣ በብርጭቆ ውስጥ መልኩ ባንጸባረቀ ጊዜ የሚያንጸባርቅ በሆነ ጊዜ፣ ስትጠጣውም ያለ ምንም ችግር በገባ ጊዜ፡፡
\v 32 በመጨረሻ እንደ እባብ ይናከሳል፣ እንደ እፉኝትም ይናደፋል፡፡
\v 33 አይኖችህ አዲስ ነገሮችን ያያሉ፣ ልብህም ጠማማ ነገሮችን ይናገራል፡፡
\s5
\v 34 በባህር ከፍታ ላይ እንደተኛ፣ በመርከብ ምሰሶ ጫፍ ላይ እንደተጋደመ ሰው ትሆናለህ፡፡
\v 35 “መቱኝ!” “ነገር ግን አልተጎዳሁም፡፡ ደበደቡኝ፣ ነገር ግን አልተሰማኝም፡፡ መቼ ይሆን የምነቃው? ሌላ መጠጥ እፈልጋለሁ፡፡” ትላለህ፡፡
\s5
\c 24
\p
\v 1 ክፉ በሆኑ ሰዎች አትቅና፣ ከእነርሱም ጋር ለመተባበር አትፈልግ፣
\v 2 ምክንያቱም ልባቸው ግጭትን ያሴራል፣ ከንፈራቸውም ችግርን ያወራል፡፡
\s5
\v 3 ቤት በጥበብ ይሰራል፣ በማስተዋልም ይጸናል፡፡
\v 4 በእውቀትም ውድና ባማሩ እቃዎች ክፍሎቹ ይሞላሉ፡፡
\s5
\v 5 ጥበበኛ ሰው ብርቱ መሆኑን ያረጋግጣል፣ እውቀት ያለውም ሰው ከጠንካራ ሰው ይልቅ ይሻላል፣
\v 6 በጥበበኛ ምክር ጦርነትህን መዋጋት ትችላለህ፣ በብዙ አማካሪዎችም ድል ይገኛልና፡፡
\s5
\v 7 ለሞኝ ሰው ጥበብ እጅግ ትርቃለች፤ በበርም አፉን አይከፍትም፡፡
\s5
\v 8 ክፋትን ለማድረግ የሚያስብ አንድ ሰው አለ፣ ሰዎችም የተንኮል አለቃ ብለው ይጠሩታል፡፡
\v 9 የስንፍና እቅድ ኃጢአት ነው፣ ሰዎችም ፌዘኛን ይንቁታል፡፡
\s5
\v 10 በችግር ጊዜ ፍርሃትህን ካሳየህ፣ እንግዲያው አቅምህ ትንሽ ነው፡፡
\s5
\v 11 ወደ ሞት የሚወሰዱትን አድናቸው፣ እየተጎተቱ ለመታረድ የሚነዱትንም ይዘህ መልሳቸው፡፡
\v 12 አንተም “እዚያ! ስለዚህ ነገር ምንም አናውቅም” ብትል ልብን የሚመረምረው እርሱ ንግግርህን አያስተውለውምን? ሕይወትህን የሚጠብቀው እርሱ አያውቅምን? ለእያንዳንዱ እንደ ስራው መጠን እግዚአብሔር አይሰጠውምን?
\s5
\v 13 ልጄ ሆይ፣ መልካም ነውና ማር ብላ፣ የማር ወለላ ጠብታዎች ለጣዕምህ ጣፋጭ ናቸው፡፡
\v 14 ጥበብም ለነፍስህ እንዲህ ነው፣ ካገኘኸውም፣ ወደፊት ዋስትና ይኖርሃል፣ ተስፋህም አይጠፋም፡፡
\s5
\v 15 ጽድቅን የሚያደርጉ ሰዎችን ቤት እንደሚዘርፉ ክፉ ሰዎች አድፍጠህ አትጠብቅ፡፡ የጻድቁንም ቤት አታፍርስ፡፡
\v 16 ጽድቅን የሚያደርግ ሰው ሰባት ጊዜ ቢወድቅ፣ እንደገና ከወደቀበት ይነሳልና፣ ክፉዎች ግን ይቀሰፋሉ፡፡
\s5
\v 17 ጠላትህ በወደቀ ጊዜ ደስ አይበልህ፣ በተሰናከለም ጊዜ ልብህ ደስ አይበለው፣
\v 18 እግዚአብሔር ያያል፣ ተመልሶም ቁጣውን ከእርሱ ይመልሳልና፡፡
\s5
\v 19 ክፋትን በሚያደርጉ ሰዎች አትጨነቅ፣ በክፉዎችም አትቅና፣
\v 20 ክፉ ሰው ተስፋ የለውምና፣ የክፉ ሰውም መብራት ይጠፋልና፡፡
\s5
\v 21 እግዚአብሔርን ፍራ፣ ንጉስንም ፍራ፣ ልጄ ሆይ፤ በእነርሱ ላይ ከሚያምጹ ሰዎችም ጋር አትተባበር፣
\v 22 ጥፋታቸው በድንገት ይመጣልና፣ ከሁለቱም የሚመጣባቸውን ጥፋት ምን ያህል እንደሆነ ማን ያውቃል?
\s5
\v 23 እነዚህ ደግሞ የጥበበኛ ሰው ንግግር ናቸው፡፡ በዳኝነት አድልዎ ማድረግ መልካም አይደለም፡፡
\s5
\v 24 ወንጀለኛውን “ጻድቅ ነህ” የሚለው በሕዝብ ዘንድ ይረገማል፣ በመንግስታትም ዘንድ ይጠላል፡፡
\v 25 ነገር ግን በደለኛውን የሚገስጹ ደስታ ይሆንላቸዋል፣ የደግነት ስጦታዎችም ወደ እነርሱ ይመጣሉ፡፡
\s5
\v 26 እውነተኛ መልስ የሚሰጥ ሰው ከንፈሮችን ይስማል፡፡
\v 27 የውጪ ስራህን አዘጋጅ፣ በመስክም ሁሉንም ነገር ለራስህ ዝግጁ አድርግ፣ ከዚያም በኋላ ቤትህን ስራ፡፡
\s5
\v 28 ያለ ምክንያት በጎረቤትህ ላይ አትመስክር፣ በከንፈሮችህም አታታልል፡፡
\v 29 “እርሱ በእኔ ላይ ያደረገውን እኔም በእርሱ ላይ አደርግበታለሁ፤ በእኔ ላይ ላደረገው ነገር ዋጋውን እከፍለዋለሁ” አትበል፡፡
\s5
\v 30 በሰነፍ ሰው እርሻ በኩል ሄድሁ፣ አእምሮ በሌለውም ሰው የወይን እርሻ አለፍሁ፡፡
\v 31 እሾህም በየቦታው በቅሎ ነበር፣ መሬቱም በሳማ ተሸፍኖ ነበር፣ የድንጋይ ካቡም ፈርሶ ነበር፡፡
\s5
\v 32 ከዚያም አየሁና አሰብኩኝ፤ ተመለከትሁና ተግሳጽን ተቀበልሁ፡፡
\v 33 ጥቂት መተኛት፣ ጥቂት እንቅልፍ፣ ጥቂት ለማረፍ እጅን ማጣጠፍ፣
\v 34 ድህነት እንደ ሌባ በአንተ ላይ ይመጣል፣ ችግርህም መሳርያ እንደታጠቀ ወታደር ይመጣብሃል፡፡
\s5
\c 25
\p
\v 1 እነዚህ የይሁዳ ንጉስ፣ የሕዝቅያስ ሰዎች የቀዷቸው ተጨማሪ የሰለሞን ምሳሌዎች ናቸው፡፡
\v 2 ነገርን መሰወር የእግዚአብሔር ክብር ነው፣ የነገስታት ክብር ግን ነገርን መርምሮ ማውጣት ነው፡፡
\v 3 ሰማያት ከፍ ያሉ እንደሆኑ፣ ምድርም ጥልቅ እንደሆነች ሁሉ፣ የነገስታት ልብም አይመረመርም፡፡
\s5
\v 4 ቆሻሻውን ከብር አስወግድ፣ የብረት ሰራተኛውም ብሩን ለእጅ ሙያው ሊጠቀምበት ይችላል፡፡
\v 5 እንደዚሁ ክፉ ሰዎችን ከንጉስ ፊት አርቃቸው፣ ዙፋኑ ጽድቅን በማድረግ ይጸናል፡፡
\s5
\v 6 በንጉስ ፊት ራስህን ከፍ ከፍ አታድርግ፣ ለታላቅ ሰዎች መቆሚያ በተዘጋጀም ስፍራ ላይ አትቁም፡፡
\s5
\v 7 በተከበሩ ሰዎች ፊት ከምትዋረድ ይልቅ፣ እርሱ “ወደዚህ ና” ቢልህ ይሻላል፡፡ ያየኸውን ነገርም፣
\v 8 ወደ ፍርድ ፈጥነህ አታምጣው፡፡ ጎረቤትህ ባሳፈረህ ጊዜ በመጨረሻ ምን ታርጋለህ?
\s5
\v 9 ጉዳይህን በአንተና በጎረቤትህ መካከል ተከራከር፣ የሌላ ሰው ምስጢር ግን አታውጣ፣
\v 10 አለበለዚያ ግን አንተን የሰማ ሰው በአንተ ላይ ሃፍረትን ያመጣብሃል፣ ስለ አንተም ልትመልሰው የማትችለው መጥፎ ወሬ ይወራብሃል፡፡
\s5
\v 11 በጥንቃቄ የተመረጠ ቃል መናገር፣ በብር ላይ እንደተቀረጻ የወርቅ ንድፍ ነው፡፡
\v 12 ለሚሰማ ጆሮ የጥበበኛ ተግሳጽ እንደ ወርቅ ቀለበት፣ ከንጹህ ወርቅም እንደተሰራ ጌጥ ነው፡፡
\s5
\v 13 በምርት መሰብሰቢያ ወቅት እንዳለ የበረዶ ቅዝቃዜ ታማኝ መልዕክተኛ ለላኩት ሰዎች እንዲሁ ነው፤ የጌቶቹን ሕይወት ይመልሳል፡፡
\v 14 የማይሰጠውን ስጦታ እሰጣለሁ ብሎ የሚመካ ሰው ዝናብ እንደሌለው ደመናና ንፋስ ነው፡፡
\s5
\v 15 በትዕግስት ገዢን እንዲለዝብ ማድረግ ይቻላል፣ መልካም ምላስም አጥንትን ትሰብራለች፡፡
\s5
\v 16 ማር ካገኘህ፣ ለአንተ በቂ የሆነውን ብላ፣ አለበለዚያ ግን ከመጠን በላይ ከበላህ ትተፋዋለህ፡፡
\v 17 ወደ ጎረቤትህ ቤት እግር አታብዛ፣ ሊሰለችህና ሊጠላህ ይችላልና፡፡
\s5
\v 18 በጎረቤቱ ላይ በሐሰት የሚመሰክር ሰው በጦርነት ላይ ጥቅም ላይ እንደሚውል ዱላ፣ ሰይፍ ወይም የተሳለ ቀስት ነው፡፡
\v 19 በችግር ጊዜ የታመንከው ወስላታ ሰው እንደ ተበላሸ ጥርስ ወይም እንደሚያነክስ እግር ነው፡፡
\s5
\v 20 ላዘነ ልብ መዝሙር የሚዘምር፣ በብርድ ጊዜ ልብሱን እንደሚያወልቅ ወይም በሶዳ ላይ ኮምጣጤ እንደሚጨምር ነው፡፡
\s5
\v 21 ጠላትህ ቢራብ እንዲበላ ምግብ ስጠው፣ ቢጠማም እንዲጠጣ ውኃ ስጠው፣
\v 22 በራሱ ላይ ፍም ትከምራለህና፣ እግዚአብሔርም ዋጋህን ይከፍልሃልና፡፡
\s5
\v 23 የሰሜን ንፋስ በእርግጠኝነት ዝናብን ይዞ እንደሚመጣ፣ ሚስጥርን የሚያባክን ሰው ሰዎችን ያስቆጣል፡፡
\v 24 ከጠበኛ ሴት ጋር በአንድ ቤት ከመኖር በጣራ ማእዘን ላይ ተጠግቶ መኖር ይሻላል፡፡
\s5
\v 25 ለተጠማ ሰው ቀዝቃዛ ውሃ እንደሚያረካው ሁሉ፣ ከሩቅ አገር የመጣ የምስራችም እንዲሁ ነው፡፡
\v 26 በክፉ ሰዎች ፊት የሚንበረከክ መልካም ሰው፣ እንደ ተበከለ ፈሳሽና እንደተበላሸ ምንጭ ነው፡፡
\s5
\v 27 እጅግ በጣም ብዙ ማር መብላት ጥሩ አይደለም፤ በክብር ላይ ክብር እንደመፈለግ ነው፡፡
\v 28 ራሱን መግዛት የማይችል ሰው እንደፈረሰችና ቅጥር እንደሌላት ከተማ ነው፡፡
\s5
\c 26
\p
\v 1 በበጋ ጊዜ እንደሚወርድ በረዶና በመከር ጊዜ እንደሚዘንብ ዝናብ፣ ክብርም ለሞኝ ሰው አይገባውም፡፡
\v 2 ድንቢጥ ከቦታ ቦታ እንደምትበርር፣ ጨረባም እንደምትሸመጥጥ፣ ያልተገባ እርግማን ማንም ላይ አይደርስም፡፡
\s5
\v 3 ጅራፍ ለፈረስ፣ ልጓምም ለአህያ እንደሆነ፣ በትርም ለሞኞች ጀርባ ነው፡፡
\v 4 ለሞኝ መልስ አትስጠው፣ በሞኝነቱም አትተባበር፣ አለዚያ እንደ እርሱ ትሆናለህ፡፡
\s5
\v 5 ሞኝን እንደ ሞኝነቱ መልስለት፣ በሞኝነቱም ተባበረው፣ አለዚያ በዓይኖቹ ጥበበኛ የሆነ ይመስለዋል፡፡
\v 6 በሞኝ ሰው እጅ መልዕክትን የሚልክ ሁሉ የራሱን እግር ይቆርጣል ሁከትንም ይጠጣል፡፡
\s5
\v 7 የሰለሉ የሽባ እግሮች በሞኝ አፍ እንዳለ ምሳሌ ናቸው፡፡
\v 8 ለሞኝ ክብር መስጠት ድንጋይን በወንጭፍ እንደ ማሰር ነው፡፡
\s5
\v 9 በሰካራም እጅ ላይ ያለ እሾህ በሞኞች አፍ እንዳለ ምሳሌ ነው፡፡
\v 10 ሁሉንም ሰው የሚያቆስል ቀስተኛ፣ ሞኝን ወይም አላፊ አግዳሚውን እንደሚቀጥር ሰው ነው፡፡
\s5
\v 11 ውሻ ወደ ትውከቱ እንደሚመለስ፣ ሞኝነቱን የሚደጋግም ሞኝም እንዲሁ ነው፡፡
\v 12 በራሱ ዓይን ጥበበኛ እንደሆነ የሚያስብን ሰው አይተሃልን? ከእርሱ ይልቅ ለሞኝ የተሻለ ተስፋ አለው፡፡
\s5
\v 13 ሰነፍ ሰው እንዲህ ይላል፣ “አንበሳ በመንገድ አለ! በውጭ በአውራ ጎዳና አንበሳ አለ፡፡”
\v 14 በር በማጠፊያው ላይ እንደሚዞር፣ ሰነፍም በአልጋው ላይ ይዟዟራል፡፡
\s5
\v 15 ሰነፍ ሰው እጁን ወደ ሳህኑ ያስገባል፣ ነገር ግን እጁን ወደ አፉ ለመመለስ ጉልበት የለውም፡፡
\v 16 ሰነፍ ሰው ማስተዋል ካላቸው ከሰባት ሰዎች የበለጠ ጥበበኛ እንደሆነ በራሱ ዓይን ያስባል፡፡
\s5
\v 17 የውሻን ጆሮ እንደሚይዝ ሰው፣ የራሱ ባልሆነ ጥል ላይ የሚገባ መንገድ አላፊ ሰውም እንዲሁ ነው፡፡
\s5
\v 18 ተቀጣጣይ ቀስት እንደሚወራወር እብድ ሰው፣
\v 19 “የተናገርሁት እኮ ቀልዴን ነበር?” በማለት ጎረቤቱን የሚያታልል ሰው እንዲሁ ነው፡፡
\s5
\v 20 በእንጨት እጦት እሳት ይጠፋል፣ ሐሜት በሌለበትም ጥል ያቆማል፡፡
\v 21 ከሰል ፍምን እንጨትም እሳትን እንደሚያቀጣጥል፣ ጠበኛ ሰውም ሁከትን ያቀጣጥላል፡፡
\s5
\v 22 የሐሜት ቃላቶች እንደ ጣፋጭ ጉርሻ ናቸው፤ ወደ ውስጣዊ የሰውነት ክፍሎችም ይወርዳሉ፡፡
\v 23 እንሚያቃጥሉ ከንፈሮችና እንደ ክፉ ልብ በብር ፈሳሽ የተለበጠ የሸክላ ድስት እንዲሁ ነው፡፡
\s5
\v 24 ሌሎችን የሚጠላ ሰው ስሜቱን በከንፈሮቹ ይሸነግላል፣ ተንኮሉን ግን በውስጡ ያኖራል፡፡
\v 25 ማራኪ የሆነ ንግግር ይናገራል፣ ነገር ግን አትመነው፣ በልቡ ውስጥ ሰባት ርኩሰቶች አሉና፡፡
\v 26 ምንም እንኳ ጥላቻው በሽንገላ የተሸፈነ ቢሆንም፣ ክፋቱ ግን በጉባኤ ይገለጣል፡፡
\s5
\v 27 ጉድጓድን የሚቆፍር ሰው እርሱ ይገባበታል፣ ድንጋይንም የሚያንከባልል ተመልሶ በላዩ ላይ ይገለበጥበታል፡፡
\v 28 ውሸታም ምላስ የጎዳቸውን ሰዎች ይጠላል፣ ሸንጋይ አፍም ጥፋትን ያመጣል፡፡
\s5
\c 27
\p
\v 1 ነገ በሚሆነው አትመካ፣ ቀኑ የሚያመጣው ምን እንደሆነ አታውቅምና፡፡
\v 2 ሌላ ያመስግንህ እንጂ በራስህ አፍ ራስህን አታመስግን፤ የማያውቅህ ሰው እንጂ የራስህ ከንፈሮች አያመስግኑህ፡፡
\s5
\v 3 የድንጋይን ክብደትና የአሸዋንም ክብደት አስብ፣ የሞኝ ሰው ትንኮሳ ግን ከሁለቱም እጅግ የከበደ ነው፡፡
\v 4 የንዴት ጨካኝነትና የቁጣ ጎርፍ አለ፣ በቅናት ፊት መቆም የሚችል ግን ማን ነው?
\s5
\v 5 ከተሰወረ ፍቅር ይልቅ የተገለጠ ተግሳጽ ይሻላል፡፡
\v 6 የጓደኛ ማቁሰል የታመኑ ናቸው፣ ጠላት ግን ከመጠን በላይ ይስማል፡፡
\s5
\v 7 በጣም ጠግቦ የበላ ሰው የማር ወለላንም አይቀበልም፣ ለራበው ሰው ግን ማንኛውም መራራ ነገር እንኳ ጣፋጭ ነው፡፡
\v 8 ከጎጆዋ ወጥታ የምትንከራተት ወፍ ከመኖሪያው አካባቢ ወጥቶ እንደሚባዝን ሰው ናት፡፡
\s5
\v 9 ሽቶና እጣን ልብን ደስ ያሰኛሉ፣ የጓደኛ ጣፋጭነት ግን ከምክሩ ይበልጣል፡፡
\v 10 በችግርህ ጊዜ ጓደኛህንና የጓደኛህን አባት ትተህ ወደ ወንድምህ ቤት አትሂድ፡፡ በቅርብ ያለ ወዳጅ በሩቅ ካለ ወንድም ይሻላልና፡፡
\s5
\v 11 ልጄ ሆይ፣ ጥበበኛ ሁን፣ ልቤንም ደስ አሰኛት፤ በዚያን ጊዜ ለሚያፌዝብኝ ሰው እኔ መልስ እሰጣለሁ፡፡
\v 12 ጥንቁቅ ሰው ችግር ሲያይ ራሱን ይሸሽጋል፣ አላዋቂዎች ግን ቀድመው ሄደው በችግሩ ምክንያት ይጎዳሉ፡፡
\s5
\v 13 ለማይታወቅ ሰው ብድር በዋስትና ገንዘብ ያስያዘውን ሰው ልብስ ውሰድበት፤ ዝሙት ለምትፈጽም ሴት ዋስትና አስይዞ ከሆነ ውሰድበት፡፡
\v 14 ጎረቤቱን በማለዳ ድምጹን በጣም ከፍ አድርጎ የሚባርክ ሰው፣ ባርኮቱ እንደ እርግማን ይቆጠራል!
\s5
\v 15 ጠበኛ ሚስት በዝናብ ቀን እንደማያቋርጥ ነጠብጣብ ናት፤
\v 16 እሷን ማቆም ንፋስን እንደማቆም ወይም ዘይትን በቀኝ እጅህ ለመጨበጥ እንደ መሞከር ነው፡፡
\s5
\v 17 ብረት ብረትን ይስለዋል፤ በተመሳሳይ መንገድ ሰው ጓደኛውን ይስለዋል፡፡
\v 18 የበለስ ዛፍ የሚጠብቅ ፍሬውን ይበላል፣ ጌታውንም የሚጠብቅ ይከብራል፡፡
\s5
\v 19 ውኃ የሰውን ፊት እንደሚያሳይ፣ የሰው ልብ ሰውየውን ያሳያል፡፡
\v 20 ሲዖልና የሙታን ዓለም መቼም እንደማይጠግቡ፣ የሰውም ዓይኖች መቼም አይጠግቡም፡፡
\s5
\v 21 ማቅለጫ ለብር ከውርም ለወርቅ ነው፣ ሰውም በሚመሰገንበት ጊዜ ይፈተናል፡፡
\v 22 ሰነፍን ከእህል ጋር በዘነዘና ብትወቅጠውም፣ ሞኝነቱ ግን እርሱን አይለቀውም፡፡
\s5
\v 23 የመንጋህን ሁኔታ በእርግጠኝነት እወቅ፣ ስለ ከብቶችህም ግድ ይበልህ፣
\v 24 ሐብት ለዘላለም አይኖርምና፡፡ ዘውድ ለትውልድ ሁሉ ይጸናልን?
\v 25 የነበረው ሳር ጠፍቶ፣ አዲሱ ቡቃያ አድጎ ሲታይ፣ በተራሮች ደግሞ ለከብቶች የሚሆን መብል ተሰብስቦ ይገባል፡፡
\s5
\v 26 ለልብስህ የሚሆን ከበጎች ታገኛለህ፣ ለእርሻህ ዋጋ የሚሆን ደግሞ ከፍየሎችህ ታገኛለህ፡፡
\v 27 ለአንተና ለቤተሰብህ መብል፣ ሴት አገልጋዮችህንም ለመመገብ የሚበቃ የፍየሎች ወተት ይኖራል፡፡
\s5
\c 28
\p
\v 1 ኃጢአተኛ ማንም ሳያባርረው ይሸሻል፣ ጽድቅን የሚያደርጉ ግን እንደ አንበሳ ደፋር ናቸው፡፡
\v 2 በአገር አመጽ ምክንያት ብዙ ገዢዎች አሏት፣ ማስተዋልና እውቀት ባለው ሰው ግን፣ አገር ለረዥም ዘመን ትቆያለች፡፡
\s5
\v 3 ድሃ ሆኖ ሌሎች ድሆችን የሚያስጨንቅ ሰው፣ ሰብልን እንሚያጠፋ ዶፍ ዝናብ ነው፡፡
\v 4 ሕግን የሚተዉ ሰዎች ክፉዎችን ያመሰግናሉ፣ ሕግን የሚጠብቁ ግን ከእነርሱ ጋር ይዋጋሉ፡፡
\s5
\v 5 ክፉ ሰዎች ፍትህን አያውቁም፣ እግዚአብሔርን የሚፈልጉ ግን ሁሉን ነገር ያውቃሉ፡፡
\v 6 በመንገዱ ጠማማ ከሆነ ባለጠጋ ይልቅ፣ በሐቀኝነቱ የሚራመድ ድሃ ሰው ይሻላል፡፡
\s5
\v 7 ሕግን የሚጠብቅ ማስተዋል ያለው ልጅ ነው፣ የሆዳሞች ጓደኛ ግን አባቱን ያሳፍራል፡፡
\v 8 ከፍተኛ ወለድ በመሰብሰብ ሀብቱን የሚያከማች ለድሀዎች ለሚራራ ለሌላ ሰው ሀብቱን ይሰበሰብለታል፡፡
\s5
\v 9 አንድ ሰው ሕግን ከማድመጥ ጆሮውን የሚያዞር ከሆነ፣ ጸሎቱ እንኳ የተጠላ ነው፡፡
\v 10 ቅኑን ሰው ወደ ክፋት መንገድ የሚመራ ሁሉ ራሱ በቆፈረው ጉድጓድ ይገባል፣ ንጹሐን ግን መልካምን ነገር ይወርሳሉ፡፡
\s5
\v 11 ባለጠጋ ሰው በራሱ ዓይኖች ጥበበኛ ሊሆን ይችላል፣ አስተዋይ የሆነ ድሃ ሰው ግን እርሱን ይመረምረዋል፡፡
\v 12 ጽድቅን የሚያደርጉ ድል በሚያገኙበት ጊዜ፣ ታላቅ ክብር አለ፣ ክፉዎች በሚነሱበት ጊዜ ግን ሰዎች ራሳቸውን ይሸሽጋሉ፡፡
\s5
\v 13 ኃጢአቱን የሚሸሽግ አይሳካለትም፣ የሚናዘዝና የሚተወው ግን ምህረትን ያገኛል፡፡
\v 14 ዘወትር እግዚአብሔርን እየፈራ የሚኖር ሰው ደስተኛ ነው፣ ልቡን የሚያደነድን ግን ወደ መከራ ይወድቃል፡፡
\s5
\v 15 እንደሚያገሳ አንበሳ ወይም እንደ ተቆጣ ድብ በድሆች ላይ የሚገዛ ክፉ ገዥም እንዲሁ ነው፡፡
\v 16 ማስተዋል የሌለው ገዥ በጭካኔ የሚያስጨንቅ ነው፣ ማታለልን የሚጠላ ግን እድሜውን ያረዝማል፡፡
\s5
\v 17 አንድ ሰው የሌላውን ደም በማፍሰሱ ምክንያት በደለኛ ከሆነ፣ እስከ ሞቱ ቀን ድረስ ኮብላይ ይሆናል፣ ማንም ሰው አይረዳውም፡፡
\v 18 በሐቀኝነት የሚራመድ ሰው በደህና ይጠበቃል፣ መንገዱ በጠማማነት የተሞላ ግን በድንገት ይወድቃል፡፡
\s5
\v 19 መሬቱን የሚያርስ ሰው ብዙ መብል ይኖረዋል፣ የማይጠቅም ሞያ የሚከተል ግን እጅግ በጣም ይደኸያል፡፡
\v 20 ታማኝ ሰው ታላቅ በረከት ያገኛል፣ በጥድፊያ ሃብታም የሆነ ግን ሳይቀጣ አይቀርም፡፡
\s5
\v 21 አድልዎን ማሳየት መልካም አይደለም፣ ነገር ግን ለቁራጭ ዳቦ ሲል ሰው ስህተትን ይሰራል፡፡
\v 22 ስስታም ሰው ሐብትን ያሳድዳል፣ ድህነት በላዩ ላይ እንደሚመጣ ግን አያውቅም፡፡
\s5
\v 23 ሰውን በምላሱ ከሚያሞግስ ይልቅ የሚገስጽ ሰው በኋላ ውሎ አድሮ ከገሰጸው ሰው ብዙ ሞገስ ያገኛል፡፡
\v 24 አባቱንና እናቱን ሰርቆ “ኃጢአት አይደለም” የሚል ሰው የአጥፊ ተባባሪ ነው፡፡
\s5
\v 25 ስግብግብ ሰው ግጭትን ያነሳሳል፣ በእግዚአብሔር የሚታመን ግን ይባረካል፡፡
\v 26 በራሱ ልብ የሚታመን ሰው ሞኝ ነው፣ በጥበብ የሚራመድ ግን ከአደጋ ይርቃል፡፡
\s5
\v 27 ለድሃ የሚሰጥ ምንም ነገር አይጎድልበትም፣ በድሆች ላይ ዓይኖቹን የሚከድን ሰው ግን ብዙ እርግማን ይቀበላል፡፡
\v 28 ክፉ ሰዎች ሲነሱ፣ ሰዎች ራሳቸውን ይሸሽጋሉ፣ ክፉ ሰዎች ሲጠፉ ግን፣ ጽድቅን የሚያደርጉ ይበዛሉ፡፡
\s5
\c 29
\p
\v 1 ብዙ ተግሳጽን ተቀብሎ አንገቱን ያደነደነ ሰው እንደማይድን ሆኖ በቅጽበት ይሰበራል፡፡
\v 2 ጽድቅን የሚያደርጉ ሰዎች ሲበዙ፣ ሕዝብ ደስ ይለዋል፣ ክፉ ሰው ገዢ ሲሆን ግን ሕዝብ ያቃስታል፡፡
\s5
\v 3 ጥበብን የሚወድ ሁሉ አባቱን ደስ ያሰኛል፣ አመንዝራዎች ወዳጅ ግን ሀብቱን ያጠፋል፡፡
\v 4 ንጉስ አገሩን በፍትህ ያጸናል፣ ጉቦን የሚፈልግ ግን ያፈራርሳታል፡፡
\s5
\v 5 ጎረቤቱን የሚሸነግል ሰው ለገዛ እግሩ መረብ እየዘረጋ ነው፡፡
\v 6 ክፉ ሰው በራሱ ኃጢአት በወጥመድ ይያዛል፣ ጽድቅን የሚያደርግ ግን ይዘምራል፣ ይደሰታልም፡፡
\s5
\v 7 ጽድቅን የሚያደርግ ሰው ለድሆች ፍትሕ ይጨነቃል፤ ክፉ ሰው ግን እንዲህ ዓይነት እውቀት የለውም፡፡
\v 8 ፌዘኞች ከተማን ያቃጥላሉ፣ ጥበበኞች ግን ቁጣን ይመልሳሉ፡፡
\s5
\v 9 ጥበበኛ ሰው ከሞኝ ጋር በሚከራከርበት ጊዜ፣ ሞኝ ይቆጣል ይስቃልም፣ እረፍትም አይኖርም፡፡
\v 10 ደም የተጠማ ሰው ንጹሐንን ይጠላሉ፣ ቅን የሆነውንም ሕይወት ለማጥፋት ይፈልጋሉ፡፡
\s5
\v 11 ሞኝ ቁጣውን ሁሉ ይገልጣል፣ ጥበበኛ ሰው ግን ቁጣውን ይቆጣጠራል፣ ራሱንም ያረጋጋል፡፡
\v 12 ገዢ ለሐሰተኛ ወሬ ትኩረት የሚሰጥ ከሆነ፣ ሹማምንቶቹ ሁሉ ክፉ ይሆናሉ፡፡
\s5
\v 13 ድሃና ጨቋኝን አንድ የሚያደርጋቸው አለ፣ እግዚአብሔር ለሁለቱም የዓይን ብርሃንን ሰጥቷቸዋልና፡፡
\v 14 ንጉስ ለድሃ በእውነት ከፈረደ፣ ዙፋኑ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል፡፡
\s5
\v 15 በትርና ተግሳጽ ጥበብን ይሰጣሉ፣ ያልተቀጣ ልጅ ግን እናቱን ያሳፍራል፡፡
\v 16 ክፉ ሰዎች ስልጣን ሲይዙ፣ አመጸኝነት ይጨምራል፣ ጽድቅን የሚያደርጉ ግን የክፉዎችን ውድቀት ያያሉ፡፡
\s5
\v 17 ልጅህን ቅጣው እረፍትም ይሰጥሃል፤ ለሕይወትህም ደስታን ያመጣል፡፡
\v 18 ትንቢታዊ ራዕይ በሌለበት ሕዝብ መረን ይሆናል፣ ሕግን የሚጠብቅ ግን የተባረከ ነው፡፡
\s5
\v 19 አገልጋይ በቃል አይታረምም፣ ቢገባውም ምላሽ አይሰጥም፡፡
\v 20 በቃሎቹ የሚቸኩለውን ሰው ተመልክተሃል? ከእርሱ ይልቅ ለሞኝ የበለጠ ተስፋ አለው፡፡
\s5
\v 21 አገልጋዩን ከወጣትነቱ ጀምሮ የሚያሞላቅቅ፣ በመጨረሻ ችግር ይገጥመዋል፡፡
\v 22 ቁጡ ሰው ሁከትን ያነሳሳል፣ ቁጣ የሞላበትም ሰው ብዙ ኃጢአቶችን ይሰራል፡፡
\s5
\v 23 የሰው ትዕቢት ያዋርደዋል፣ ትሁት መንፈስ ያለው ግን ይከበራል፡፡
\v 24 ከሌባ ጋር የሚካፈል ሰው ሕይወቱን ይጠላል፤ እርግማንን ይሰማል መልስ ግን አይሰጥም፡፡
\s5
\v 25 ሰውን መፍራት ወጥመድ ውስጥ ይከትታል፣ በእግዚአብሔር የሚታመን ግን ይጠበቃል፡፡
\v 26 ብዙዎች የገዢን ፊት ይሻሉ፣ ፍትህ ለሰው የሚመጣው ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው፡፡
\s5
\v 27 ፍትህን የሚያጓድል ሰው ጽድቅን በሚያደርጉ ሰዎች ፊት የተጠላ ነው፣ መንገዱ ቅን የሆነ ሰው ግን በክፉዎች የተጠላ ነው፡፡
\s5
\c 30
\p
\v 1 የያቄ ልጅ የአጉር ቃል፡- ይህ ሰው ለኢቲኤል፣ ለኢቲኤልና ለኡካል ተናገረ፡-
\v 2 በእርግጠኝነት እኔ ከሰው ሁሉ ይልቅ እንደ እንስሳ ሞኝ ነኝ፣ የሰው ልጅ ማስተዋልም የለኝም፡፡
\v 3 ጥበብን አልተማርሁም፣ ስለ ቅዱሱም እውቀት የለኝም፡፡
\s5
\v 4 ወደ ሰማይ ከፍ ብሎ የሄደና ወደታች የተመለሰ ማን ነው? ነፋሳትን በእጁ መዳፍ ሰብስቦ የያዘ ማን ነው? ውሆችንስ በካባው ላይ የሰበሰበ ማን ነው? የምድርን ዳርቻ ሁሉ ያጸና ማን ነው? ስሙ ማን ነው፣ የልጁስ ስም ማን ነው? አንተ በእርግጠኝነት ታውቃለህ!
\s5
\v 5 የእግዚአብሔር ቃል ሁሉ ተፈትኗል፣ በእርሱ ለሚታመኑ ጋሻ ነው፡፡
\v 6 በቃሉ ላይ ምንም አትጨምር፣ አለዚያ ይገስጽሃልና፣ ሐሰተኛም ትሆናለህ፡፡
\s5
\v 7 ሁለት ነገር እጠይቅሃለሁ፣ ከመሞቴም በፊት እነዚህን ነገሮች አትከልክለኝ፡
\v 8 ከንቱነትንና ውሸትን ከእኔ አርቅ፡፡ ድህነትንም ብልጽግናንም አትስጠኝ፣ የሚያስፈልገኝን መብል ብቻ ስጠኝ፡፡
\v 9 ብዙ ሃብት ካለኝ፣ አንተን ከድቼ “እግዚአብሔርን ማን ነው?” እላለሁና፣ ድሃ ከሆንኩኝ ደግሞ እሰርቃለሁ፣ የአምላኬንም ስም አሰድባለሁና፡፡
\s5
\v 10 አገልጋዩን በጌታው ፊት ስሙን አታጥፋ፣ ይረግምሃል አንተም በደለኛ ሆነህ ትገኛለህና፡፡
\s5
\v 11 አባቱን የሚረግም፣ እናቱንም የማይባርክ ትውልድ፣
\v 12 ይህ ትውልድ ራሱን ንጹህ አድርጎ የሚያይ፣ ነገር ግን ከእድፉ ያልጸዳ ትውልድ ነው፡፡
\s5
\v 13 ይህ ትውልድ ዓይናቸው ምንኛ ትዕቢተኛ ነው፣ ሽፋሽፍቶቻቸውም ምንኛ ወደ ላይ ከፍ ያሉ ናቸው!
\v 14 ጥርሳቸው ሰይፍ የሆነ፣ መንጋጋቸውም ካራ የሆነ ትውልድ ናቸው፣ ድሆችን ከምድር፣ ችግረኞችንም ከሰው ልጆች መካከል ያጠፉ ዘንድ፡፡
\s5
\v 15 አልቅት “ስጡን፣ ስጡን” እያሉ የሚጮሁ ሁለት ሴቶች ልጆች አሉት፡፡ ፈጽሞ የማይጠግቡ ሦስት ነገሮች አሉ፣ ፈጽሞ “በቃኝ” የማይሉ አራት፤
\v 16 እነርሱም ሲኦል፣ የማትወልድ ማህጸን፣ ውሃ የተጠማች መሬትና፣ “በቃኝ” የማትል እሳት ናቸው፡፡
\v 17 በአባት ላይ የሚያፌዝ ለእናት መታዘዝን የሚንቅ ዓይን፣ ዓይኑ በሸለቆ አሞራዎች ይጎጠጉጡአታል፣ በአሞራዎችም ይበላል፡፡
\s5
\v 18 እጅግ የሚያስደንቁኝ ሦስት ነገሮች አሉ፣ አራት ደግሞ ፈጽሞ የማላስተውለው፡-
\v 19 የንስር መንገድ በሰማይ ውስጥ፤ የእባብ መንገድ በቋጥኝ ላይ፤ የመርከብ መንገድ በባህር ልብ ውስጥ፤ የሰውም መንገድ ከወጣት ሴት ጋር ናቸው፡፡
\s5
\v 20 ይህም የአመንዝራ ሴት መንገድ ነው፣ ትበላለች አፏንም ትጠርጋለች፣ “ምንም ስህተት አልሰራሁም” ትላለች፡፡
\s5
\v 21 በሶስት ነገሮች ምድር ትናወጣለች፣ አራተኛውንም መቋቋም አትችልም፡-
\v 22 ባርያ ንጉስ ሲሆን፤ ሞኝ በመብል በጠገበ ጊዜ፤
\v 23 የተጠላች ሴት ትዳር ስትይዝና፤ የቤት ሰራተኛ የእመቤቷን ቦታ ስትወስድ፡፡
\s5
\v 24 በምድር ላይ አራት ነገሮች ትንሽ ናቸው፣ ሆኖም እጅግ ጥበበኞች ናቸው፡-
\v 25 ጉንዳኖች ጠንካራ ያልሆኑ ፍጡራን ናቸው፣ ነገር ግን ምግባቸውን በበጋ ያዘጋጃሉ፤
\v 26 ሽኮኮዎች ብርቱ ያልሆኑ ፍጡሮች ናቸው፣ ነገር ግን ቤታቸውን በአለት ውስጥ ይሰራሉ፡፡
\s5
\v 27 አንበጣዎች ንጉስ የላቸውም፣ ነገር ግን ሁሉም በሰልፍ ይሄዳሉ፡፡
\v 28 እንሽላሊቶችም በሁለት እጅህ ልትይዛቸው ትችላለህ፣ ይሁን እንጂ በነገስታት ቤተ መንግስታት ውስጥ ይገኛሉ፡፡
\s5
\v 29 ግርማ ሞገስ ያለው አረማመድ ያላቸው ሶስት ነገሮች አሉ፣ በአካሄዳቸው ግርማ ሞገስ ያላቸው አራት አሉ፡-
\v 30 አንበሳ፣ ከዱር እንስሳት ሁሉ ብርቱ የሆነና ከምንም ነገር ወደኋላ የማይመለስ ነው፤
\v 31 እየተንጎራደደ የሚሄድ አውራ ዶሮ፤ ፍየል፤ እና በወታደሮቹ የታጀበ ንጉስ ናቸው፡፡
\s5
\v 32 ሞኝ ከሆንህ፣ ራስህንም ከፍ ከፍ የምታደርግ ከሆነ ወይም ክፉ ሃሳብን እያሰብክ ከሆነ፣ እጅህን በአፍህ ላይ አድርግ፡፡
\v 33 የተናጠ ወተት ቅቤ እንደሚወጣው፣ በጣም የታሸ አፍንጫም ደም እንደሚወጣው፣ በቁጣ የሚፈጸሙ ድርጊቶችም ጠብን ያመጣሉ፡፡
\s5
\c 31
\p
\v 1 እናቱ ያስተማረችው የንጉስ ልሙኤል ቃሎች፣
\v 2 ልጄ ሆይ፣ ምንድን ነው? የማሕጸኔ ልጅ ሆይ ምንድን ነው? የስእለቴ ልጅ ሆይ ምንድን ነው?
\v 3 ብርታትህን ለሴቶች አትስጥ፣ ነገስታትን ለሚያጠፉም መንገድህን፡፡
\s5
\v 4 ለነገስታት አይደለም፣ ልሙኤል ሆይ፣ የወይን ጠጅ መጠጣት ለነገስታት አይደለም፣ “ብርቱ መጠጥ የት ነው” ብለው ይጠይቁ ዘንድ ለገዢዎችም አይደለም፡፡
\v 5 ምክንያቱም እነርሱ መጠጥ ከጠጡ የተደነገገውን ሕጉን ይረሳሉ፣ የተጨቆኑ ሰዎችንም መብት ያጣምማሉ፡፡
\s5
\v 6 እየጠፉ ላሉ ሰዎች ብርቱ መጠጥ ስጧቸው፣ መራራ ችግር ውስጥ ላሉትም ወይን ስጧቸው፡፡
\v 7 ይጠጣል ድህነቱንም ይረሳል፣ ችግሩንም አያስታውስም፡፡
\s5
\v 8 መናገር ለማይችሉ ተናገርላቸው፣ እየጠፉም ላሉት ሁሉ ስለ ጉዳያቸው ተናገር፡፡
\v 9 ትክክል ስለሆነው ነገር ጮህ ብለህ ተናገር፣ ፍርድም ስጥ፣ ስለ ድሆችና ስለ ተቸገሩም ሰዎች ጉዳይ መልስ ስጥ፡፡
\s5
\v 10 ችሎታ ያላትን ሴት ማን ሊያገኛት ይችላል? የእርሷ ዋጋ ከእንቁ የበለጠ ነው፡፡
\v 11 የባሏ ልብ በእርሷ ይተማመናል፣ ድሃም አይሆንም፡፡
\v 12 በሕይወት ዘመኗ ሁሉ ለእርሱ መልካም ነገር ታደርግለታለች፣ ክፋትንም አታደርግበትም፡፡
\s5
\v 13 የበግ ጠጉርና የተልባ ትመርጣለች፣ በእጆቿም ደስ ብሏት ትሰራለች፡፡
\v 14 እርሷ እንደ ነጋዴ መርከብ ናት፤ መብሏን ከሩቅ ታመጣለች፡፡
\v 15 በሌሊት ተነስታ ለቤተሰቧ መብልን ታቀርባለች፣ ስራዋንም ለሴት አገልጋዮቿ ታከፋፍላለች፡፡
\s5
\v 16 እርሻን ተመልክታ ትገዛለች፣ በእጆቿም ፍሬ የወይን ተክል ትተክላለች፡፡
\v 17 ራሷን በብርታት ታለብሳለች፣ ክንዶቿንም ታጠነክራለች፡፡
\s5
\v 18 ለእርሷ ጥሩ ትርፍ የሚያመጣላትን ታውቃለች፤ ሌሊቱንም ሙሉ መብራቷ አይጠፋም፡፡
\v 19 እጆቿን በእንዝርቱ ላይ ታስቀምጣለች፣ የሚሽከረከረውንም ክር ትይዛለች፡፡
\s5
\v 20 እጇን ለድሆች ትዘረጋለች፤ ለተቸገሩትም እጆቿን ትዘረጋለች፡፡
\v 21 በረዶም ቢዘንብ ስለ ቤተሰቧ አትፈራም፣ ቤተሰቧ ሁሉ ቀይ ልብስ ለብሰዋልና፡፡
\s5
\v 22 ለመኝታዋ የአልጋ ልብስ ትሰራለች፣ ቀጭን ሐምራዊ ልብስም ትለብሳለች፡፡
\v 23 ባለቤቷም ከአገሩ ሽማግሌዎች ጋር ሲቀመጥ በበሮቹ የታወቀ ይሆናል፣ ፡፡
\s5
\v 24 የሊኖ ልብሶችን ትሰራለች፣ ትሸጣለችም፣ ለነጋዴዎችም መቀነቶችን ታስረክባለች፡፡
\v 25 ጥንካሬንና ክብርን ተላብሳለች፣ ወደፊት የሚመጣውን ጊዜ እያሰበች ትስቃለች፡፡
\s5
\v 26 አፏን በጥበብ ትከፍታለች፣ የደግነት ሕግም በምላሷ ላይ አለ፡፡
\v 27 የቤተሰቦቿን መንገዶች ትመለከታለች፣ የስንፍናንም እንጀራ አትበላም፡፡
\s5
\v 28 ልጆቿም አድገው የተባረክሽ ነሽ ይሏታል፤ ባለቤቷም እንዲህ ብሎ ያመሰግናታል፣
\v 29 “ብዙ ሴቶች መልካምን አድርገዋል፣ አንቺ ግን ከሁሉ ትበልጫለሽ፡፡”
\s5
\v 30 ቁንጅና አሳሳች ነው፣ ውበትም ጠፊ ነው፣ እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን እርሷ ትመሰገናለች፡፡
\v 31 የእጆቿን ፍሬ ስጧት፣ ስራዋቿም በአደባባዮች ያስመሰግኗት፡፡