am_ulb/18-JOB.usfm

2028 lines
155 KiB
Plaintext

\id JOB
\ide UTF-8
\h ኢዮብ
\toc1 ኢዮብ
\toc2 ኢዮብ
\toc3 job
\mt ኢዮብ
\s5
\c 1
\p
\v 1 ዖጽ በሚባል ምድር ኢዮብ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤ ኢዮብም በደል የማይገኝበት፤ ትክክለኛ፤ እግዚአብሄርን የሚፈራና ከክፋት የራቀ ሰው ነበረ።
\v 2 ለእርሱም ሰባት ወንዶችና ሶስት ሴቶች ልጆች ተወልደውለት ነበር።
\v 3 ሰባት ሺህ በጎች፤ ሶስት ሺህ ግመሎች፤ አምስት ሺህ ጥንድ በሬዎችና አምስት ሺህ አህዮች እንዲሁም እጅግ ብዙ ሰራተኞች ነበሩት። ይህም ሰው በምስራቅ ካሉ ሰዎች ሁሉ ይልቅ ታላቅ ሰው ነበር።
\s5
\v 4 ወንዶች ልጆቹም በየተመደበላቸው ተራ በያንዳንዳቸው ቤት ግብዣ ያደርጉ ነበር፤ ሦስቱ እኅቶቻቸውም ከእነርሱ ጋር እንዲበሉና እንዲጠጡ ልከው ይጠሩአቸው ነበር።
\v 5 የግብዣቸውም ቀናቶች ሲያበቁ ኢዮብ፦ ያስጠራቸውና ለእግዚአብሔር መልሶ ይቀድሳቸው ነበር።ማልዶ በጠዋት ተነስቶ “ምናልባት ልጆቼ በድለው፥ እግዚአብሔርንም በልባቸው ረግመው ይሆናል” ብሎ ፤ ለልጆቹ ለእያንዳንዳቸው የሚቃጠል መሥዋዕት ያቀርባል። ይህንንም ኢዮብ ሁልጊዜ ያደርግ ነበር።
\s5
\v 6 በኋላም የእግዚአብሔር ልጆች በያህዌ ፊት ራሳቸውን የሚያቀርቡበት ቀን ነበረ ፥ ሰይጣንም ደግሞ ከእነርሱ ጋር መጣ።
\v 7 እግዚአብሔርም ሰይጣንን፦“ ከወዴት እየመጣህ ነው?” አለው። ሰይጣንም ለእግዚአብሔር ሲመልስ፦ “ምድርን ሁሉ ዞርሁ፥ በእርስዋም ላይ ወዲህና ወዲያ ተመላልሼ መጣሁ” አለ።
\v 8 እግዚአብሔርም ሰይጣንን፦”በውኑ ባሪያዬን ኢዮብንስ ተመለከትኸውን? በምድር ላይ እንደ እርሱ ያለ በደል የማይገኝበት ትክክለኛ ሰው ፥ እግዚአብሔርንም የሚፈራ፥ ከክፋትም የራቀ ሰው የለም“ አለው።
\s5
\v 9 ሰይጣንም ለእግዚአብሔር ሲመልስ እንዲህ አለ፦ “ኢዮብ እግዚአብሔርን የሚፈራው እንዲሁ ነውን?
\v 10 በእርሱና በቤቱ ባለውም ነገር ሁሉ ዙሪያ በየአቅጣጫው አጥር አላደረግህለትምን? የእጁን ሥራ ባርከህለታል፥ ሐብቱም በምድር ላይ በዝቶአል።
\v 11 ነገር ግን አሁን እጅህን ዘርግተህ ያለውን ሀብት ሁሉ አውድም ፤ ፊትለፊት ይክድሃል።”
\v 12 እግዚአብሔርም ሰይጣንን፦ “እነሆ እርሱ ያለው ነገር ሁሉ በስልጣንህ ስር ነው፥ በእርሱ ላይ ግን ጉዳት እንዳታደርስ” አለው። ሰይጣንም ከእግዚአብሔር ፊት ወጥቶ ሄደ።
\s5
\v 13 ወንዶችና ሴቶች ልጆቹ በታላቅ ወንድማቸው ቤት በሚበሉበትና የወይን ጠጅ በሚጠጡበት ቀን እንዲህ ሆነ፤
\v 14 መልክተኛ ወደ ኢዮብ መጥቶ፦”በሬዎች እርሻ እያረሱ፥ በአጠገባቸውም አህዮች ተሰማርተው ነበር፤
\v 15 የሳባም ሰዎች አደጋ አድርሰው ወሰዱአቸው፥ ሰራተኞቹንም በሰይፍ ስለት ገደሉ፤ እኔም እንድነግርህ ብቻዬን አመለጥሁ“ አለው።
\s5
\v 16 እርሱም ገና እየተናገረ ሳለ ሌላ መጥቶ፦“ የእግዚአብሔር እሳት ከሰማይ ወደቀ፥ በጎቹንና ጠባቂዎችን አቃጥሎ በላቸው፤ እኔም እንድነግርህ ብቻዬን አመለጥሁ“ አለው።
\v 17 እርሱም ገና እየተናገረ ሳለ ሌላ መጥቶ፦”ከለዳውያን በሦስት ቡድን ተከፍለው በግመሎች ላይ አደጋ ጥለው ወሰዱአቸው ፥ ሰራተኞቹንም በሰይፍ ስለት ገደሉ፤ እኔም እንድነግርህ ብቻዬን አመለጥሁ“ አለው።
\s5
\v 18 እርሱም ገና እየተናገረ ሳለ ሌላ መጥቶ፦ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ በታላቅ ወንድማቸው ቤት እየበሉና የወይን ጠጅ እየጠጡ ነበር፤
\v 19 ታላቅ ነፋስ ከምድረ በዳ መጥቶ የቤቱን አራቱን ማዕዘን መታውና በልጆቹ ላይ ወደቀ፥ እነርሱም ሞቱ፤ እኔም እንድነግርህ ብቻዬን አመለጥሁ“ አለው።
\s5
\v 20 ኢዮብም ተነሣ ልብሱንም ቀደደ፥ ራሱንም ተላጨ፥ በምድርም ላይ በፊቱ ተደፍቶ እግዚአብሔርን አመለከ፤
\v 21 እንዲህም አለ፦”ከእናቴ ማኅፀን ራቁቴን ወጥቻለሁ፥ ራቁቴንም ወደዚያ እመለሳለሁ፤ እግዚአብሔር ሰጠ፥ እግዚአብሔርም ወሰደ፤ የእግዚአብሔር ስም የተባረከ ይሁን።“
\v 22 በእነዚህ ነገሮች ሁሉ ኢዮብ ሐጢያት አላደረገም፥ በስንፍናም እግዚአብሔርን አልከሰሰም።
\s5
\c 2
\p
\v 1 በድጋሚ የእግዚአብሔር ልጆች በያህዌ ፊት ራሳቸውን በሚያቀርቡበት ቀን ፥ ሰይጣንም ደግሞ አብሮ መጣ።
\v 2 እግዚአብሔርም ሰይጣንን፦“ ከወዴት እየመጣህ ነው?” አለው። ሰይጣንም ለእግዚአብሔር ሲመልስ፦ “ምድርን ሁሉ ዞርሁ፥ በእርስዋም ላይ ወዲህና ወዲያ ተመላልሼ መጣሁ” ብሎ አለ።
\s5
\v 3 እግዚአብሔርም ሰይጣንን፦”በውኑ ባሪያዬን ኢዮብንስ ተመለከትኸውን? በምድር ላይ እንደ እርሱ ያለ በደል የማይገኝበት ትክክለኛ፥ እግዚአብሔርንም የሚፈራ፥ ከክፋትም የራቀ ሰው የለም። ምንም እንኳ ያለምክንያት በእርሱ ላይ በከንቱም ጥፋት እንዲመጣበት ግፊት ብታደርግብኝም ፥ እርሱ ግን እስከ አሁን በታማኝነቱ ጸንቷል“ አለው።
\s5
\v 4 ሰይጣንም መልሶ እግዚአብሔርን፦ “ቆዳ በርግጥ ስለ ቆዳ ነው፤ ሰው ያለውን ነገር ሁሉ ሕይወቱን ለማዳን ሲል ይሰጣል” አለው።
\v 5 ነገር ግን አሁን እጅህን ዘርግተህ አጥንቱንና ሰውነቱ ላይ ጉዳት ብታደርስ ፊተ ለፊት ይክድሃል” አለው።
\v 6 እግዚአብሔም ሰይጣንን፦” ሕይወቱን ብቻ ተው፤ እነሆ፥ እርሱ በእጅህ ነው“ አለው።
\s5
\v 7 እናም ሰይጣን ከእግዚአብሔር ፊት ወጥቶ ሄደ። ኢዮብንም ከውስጥ እግሩ እስከ ራስ ጸጉሩ ድረስ በሚያሰቃይ ቍስል መታው።
\v 8 ኢዮብም ሰውነቱን ለመፋቅ የሸክላ ስባሪ ወሰዶ በአመድ ላይ ተቀመጠ።
\s5
\v 9 በኋላም ሚስቱ ፦”እስከ አሁን በታማኝነት ጸንተሃል እንዴ? እግዚአብሔርን እርገምና ሙት“ አለችው።
\v 10 እርሱ ግን መልሶ”አንቺ እንደ ሰነፍ ሴቶች ተናገርሽ፤ ከእግዚአብሔር እጅ መልካሙን ብቻ እንጂ ክፉን አንቀበልም ብለሽ ነው የምታስቢው? “ አላት። በእነዚህ ነገሮች ሁሉ ኢዮብ በአፉ ቃል ሐጢያት አላደረገም።
\s5
\v 11 ይህን የደረሰበትን ክፉ ነገር ሁሉ በሰሙ ጊዜ ሦስቱ የኢዮብ ወዳጆች ከየስፍራቸው መጡ፤ እነርሱም ቴማናዊው ኤልፋዝ፥ ሹሐዊው በልዳዶስ፥ ነዕማታዊው ሶፋር ነበሩ። እነርሱም ከኢዮብ ጋረ ሊያለቅሱና ሊያጽናኑት በአንድነት ጊዜ አመቻችተው መጡ።
\s5
\v 12 ከሩቅ ዓይናቸውን አማትረው ሲመለከቱ በትክክል ሊለዩት አልቻሉም፤ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው አለቀሱ፤ እያንዳንዳቸውም ልብሳቸውን ቀደዱ፥ አቧራ ወደ ላይ እየበተኑ ራሳቸው ላይ ነሰነሱ።
\v 13 ሰባት ቀንና ሰባት ሌሊት ከእርሱ ጋር መሬት ላይ ተቀመጡ፤ ሕመሙም እጅግ ከባድ እንደነበረ ስላዩ ከእርሱ ጋር አንድ ቃል ለመናገር የደፈረ አልነበረም።
\s5
\c 3
\p
\v 1 ከዚህም በኋላ ኢዮብ አፉን ከፍቶ የተወለደበትን ቀን ረገመ።
\v 2 እንዲህም አለ፦
\v 3 “ያ የተወለድሁበት ቀን ፤ 'ወንድ ልጅም ተፀነሰ' የተባለበት ሌሊት ይጥፋ”
\s5
\v 4 ያ ቀን ጨለማ ይሁን እግዚአብሔርም ከላይ አያስበው ፤ የጸሀይ ብርሀንም አያግኝው።
\v 5 ጨለማና የሞት ጥላ የራሳቸው እንደሆነ ይቁጠሩ፤ ዳመናም ይኑርበት፤ ቀኑን የሚያጨልሙ ነገሮች ሁሉ በርግጥ ያስደንግጡት።
\s5
\v 6 ያንን ሌሊት ድቅድቅ ጨለማ ይያዘው፤ በዓመቱ ካሉት ቀኖች ጋር ደስ አይበለው፤ በወራት ውስጥ ገብቶ አይቈጠር።
\v 7 ያቺ ምሽት መካን ትሁን፤ ወደ እርሷም የደስታ ድምጽ አይግባበት።
\s5
\v 8 ሌዋታንን እንዴት ማንቃት እንዳለባቸው የሚያውቁ ያንን ቀን ይርገሙት።
\v 9 አጥቢያ ኮከቦች ይጨልሙ፤ ያ ቀን ብርሃንን ሲጠባበቅ አያግኝ፥ የንጋትንም ወገግታ አይመልከት፤
\v 10 ምክንያቱም የእናቴን ማኅፀን ደጅ አልዘጋምና፥ መከራንም ከዓይኔ አልሰወረምና።
\s5
\v 11 ከማኅፀን ስወጣ ስለ ምን አልሞትሁም? እናቴ ስትወልደኝስ ስለምን አልጠፋሁም?
\v 12 ጕልበቶቿ ስለ ምን ተቀበሉኝ? ጡቶቿስ እንድጠባ ስለ ምን ተቀበሉኝ?
\s5
\v 13 ይሄኔ በጸጥታ በተጋደምሁ፤
\v 14 አሁን ፈርሶ ያለውን መቃብር ለራሳቸው ከገነቡት የምድር ነገሥታትና አማካሪዎች ጋር፥ አንቀላፍቼም ባረፍሁ ነበር፤
\s5
\v 15 ወይም ባንድ ወቅት ቤታቸውን በብር ከሞሉ ወርቅም ከነበራቸው መኳንንት ጋር በተጋደምሁ ነበር፥
\v 16 ወይም ያለጊዜያቸው እንደተወለዱ፥ ብርሃንንም አይተው እንደማያውቁ ሕፃናት በሆንሁ ነበር።
\s5
\v 17 በዚያ ክፉዎች ረብሻቸውን ያቆማሉ፤ የደከሙትም በዚያ ያርፋሉ።
\v 18 በዚያ እስረኞች አርፈው በአንድነት ይቀመጣሉ፤ የአስጨናቂውን ጠባቂ ድምፅ አይሰሙም።
\v 19 ታናናሽና ታላላቅ ሰዎች በዚያ አሉ፤ በዚያም ባሪያ ከጌታው ነጻ ወጥቶአል።
\s5
\v 20 በመከራ ላለ ሰው ብርሃን ፤ ነፍሳቸው መራራ ለሆነችባቸውስ ህይወት፤
\v 21 የተሰወረን ሀብት ከሚፈልጉ ይልቅ ሞትን እየተመኙ ላልመጣላቸው ህይወት ለምን ተሰጠ?
\v 22 መቀበሪያቸውን ባገኙ ጊዜ እጅግ ደስ ለሚላቸው፥ ሐሤትንም ለሚያደርጉ ሕይወት ለምን ተሰጠ?
\s5
\v 23 መንገዱ ለጠፋበት ሰው፥ እግዚአብሔርም አጥር ላጠረበት ሰው ብርሃን ለምን ተሰጠ?
\v 24 በመመገብ ምትክ ሲቃዬ ፈጥኖ ይመጣልና፥ መቃተቴም እንደ ውኃ ፈስሶአል።
\s5
\v 25 የፈራሁት ነገር መጥቶብኛልና፥ የደነገጥሁበትም ደርሶብኛል።
\v 26 በእርጋታና በጸጥታ አልተቀመጥሁም፥ አላረፍሁም ይልቅ መከራና ችግር መጣብኝ።
\s5
\c 4
\p
\v 1 ቴማናዊውም ኤልፋዝ እንዲህ ሲል መለሰ ፦
\v 2 አንድ ሰው ከአንተ ጋር ለመነጋገር ቢሞክር ታዝናለህን? ነገር ግን ከመናገር ራሱን ሊገታ የሚችል ማን ነው?
\v 3 እነሆ፥ አንተ ብዙዎችን ታስተምር ነበር፥ የደከሙትንም እጆች ታበረታ ነበር፥
\s5
\v 4 ቃልህ ሊወድቅ የተሰናከለውን ያስነሣ ነበር፥ አንተም የሚብረከረከውን ጕልበት ታጸና ነበር።
\v 5 አሁን ግን ጥፋት በአንተ ላይ መጥቶአል፥ አንተም ደከመህ፤ በርግጥ ደረሰብህ፥ አንተም ታወክህ።
\v 6 እግዚአብሔርን መፍራትህ ድፍረትን፥ ያካሄድህስ ቀናነት ተስፋን አይሰጥህምን?
\s5
\v 7 እባክህ ይህን እንድታስብ እለምንሃለሁ፥ ንጹሕ ሆኖ የጠፋ ማን አለ? ልበ ቅንስ ሆኖ የተደመሰሰ ማን ነው?
\v 8 እኔ እንዳየሁ፥ ኃጢአትን የሚያርሱ፥ ሁከትንም የሚዘሩ መልሰው ያንኑ ያጭዳሉ።
\v 9 በእግዚአብሔር እስትንፋስ ይጠፋሉ፥ በቍጣውም ንዳድ ያልቃሉ።
\s5
\v 10 የአንበሳ ግሳት፥ የቁጡ አንበሳ ድምፅ፥ የደቦል አንበሳ ጥርስ ተሰባብረዋል።
\v 11 ያረጀ አንበሳ አደን አጥቶ ይሞታል፥ የአንበሳይቱም ግልገሎች የትም ይበተናሉ።
\s5
\v 12 ለእኔም ነገሩ በምሥጢር መጣልኝ፥ ጆሮዬም ስለነገሩ ሹክሹክታን ሰማች።
\v 13 ከባድ እንቅልፍ በሰው ላይ በሚሆንበት ጊዜ፥ በሃሳብ ብዛት በሌሊት ሕልም ሲመጣ፥
\s5
\v 14 ድንጋጤና መንቀጥቀጥ መጡብኝ አጥንቶቼም ሁሉ ተንቀጠቀጡ
\v 15 በፊቴም መንፈስ አለፈ የሰውነቴም ጠጕር ቆመ።
\s5
\v 16 መንፈሱም ቆመ፥ መልኩን ግን ለመለየት አልቻልሁም፥ ቅርጹ በዓይኔ ፊት ነበረ፤ ጸጥታም ሆነ እንዲህም የሚል ድምፅ ሰማሁ፤
\v 17 “በውኑ ሥጋ የለበሰ ሰው ከእግዚአብሔር ይልቅ ጻድቅ ሊሆን ይችላልን?ሰውስ ከፈጣሪው ይልቅ ንጹህ ሊሆን ይችላልን?”
\s5
\v 18 እነሆ፥ እግዚአብሔር በአገልጋዮቹ ካልተማመነ፤ መላእክቱንም በስህተት ከወቀሳቸዋል፤
\v 19 ይልቁንስ በሸክላ ቤቶች ውስጥ በሚኖሩ፥ መሠረታቸውም በትቢያ ውስጥ ለሆነ፥ ከብል ቀድመው በሚጠፉት ዘንድ ይህ እንዴት እውነት ይሆን?
\s5
\v 20 በጥዋትና በማታ መካከል ይጠፋሉ፤ ማንም ሳያውቀው እስከ ወዲያኛው ይጠፋሉ።
\v 21 የድንኳናቸው ገመድ ከመካከላቸው የተነቀለ አይደለምን? ይሞታሉ፦ ያለጥበብም ይሞታሉ።
\s5
\c 5
\p
\v 1 አሁን እስቲ ተጣራ፤ የሚመልስ አንድ እንኳ አለ? ከቅዱሳንስ ወደየትኛው ትዞራለህ?
\v 2 ሰነፍን ሰው ቍጣ ይገድለዋል፥ ሞኙንም ቅንዓት ያጠፋዋል።
\v 3 ቂል ሰው ሥር ሲሰድድ አየሁ፥ ነገር ግን በድንገት ቤቱን ረገምሁት።
\s5
\v 4 ልጆቹም ከደኅንነት ከለላ ውጪ ናቸው፥ በከተማም አደባባይ የተረገጡ ናቸው፥ አንድም የሚያድናቸው የለም።
\v 5 የተሰበሰበውን ሰብል በተራቡ በሌሎች ተበላ፥ ከእሾህ ውስጥ እንኳ የወጡ ሰዎች ወሰዱት፤ ያለውም ሁሉ ሀብትን በተጠሙ ሰዎች ተዋጠ።
\s5
\v 6 ችግር እንዲሁ ከአፈር አይመጣም፥ መከራም ከመሬት አይመነጭም፤
\v 7 ነገር ግን የእሳት ፍንጣሪዎች ወደ ላይ እንደሚበርሩ፥ እንዲሁ ሰው መከራን በራሱ ላይ ያመጣል።
\s5
\v 8 እኔ ግን እግዚአብሔርን ወደራሱ፥ ጉዳዬን ወደ ማቀርብለት ወደ እግዚአብሔር እመለስ ነበር።
\v 9 እርሱ ታላቅና የማይመረመሩ ዋና ነገሮችንና የማይቈጠሩ አስደናቂ ነገሮችን ያደርጋል።
\v 10 በምድር ላይ ዝናብን ይሰጣል፥ በእርሻም ላይ ውኃ ይልካል።
\s5
\v 11 የተዋረዱትን በከፍታ ሊያኖር ፥ ኀዘንተኞችንም ለደኅንነት ከፍ ለማድረግ ይህንን ያደርጋል።
\v 12 እጃቸው እቅዳቸውን እንዳይፈጽም የተንኰለኞችን ወጥመድ ከንቱ ያደርጋል።
\v 13 ጠቢባንን በተንኰላቸው ይይዛቸዋል የተንኮለኞችንም ዕቅድ ያጠፋል።
\s5
\v 14 በቀን ከጨለማ ጋር ይጋጠማሉ፥ በዕኩለቀንም በሌሊት እንዳሉ ያክል በዳበሳ ይሄዳሉ።
\v 15 ነገር ግን ድሀውን ከአፋቸው ሰይፍ፤ ችግረኛውንም ከኃያላን እጅ ያድነዋል።
\v 16 ስለዚህ ድሀው ተስፋ አለው፤ ፍትህ አልባነት ግን አፍዋን ትዘጋለች።
\s5
\v 17 እነሆ፥ እግዚአብሔር የሚያርመው ሰው ምስጉን ነው፤ ስለዚህ ሁሉን የሚችለውን አምላክንተግሣጽ አትናቅ።
\v 18 ምክንያቱም እርሱ ይሰብራል፥ ይጠግናል ያቈስላል በኋላም በእጆቹ ይፈውሳል።
\v 19 እርሱ ከስድስት ክፉ ነገሮች ውስጥ ያወጣሃል፥ በርግጥ በሰባተኛው ክፋት አይነካህም።
\s5
\v 20 በራብ ጊዜ ከሞት፥ በጦርነትም ከሰይፍ ስለት ያድንሃል።
\v 21 ከምላስ ጅራፍ ትሰወራለህ፤ ጥፋትም ሲመጣ አትፈራም።
\v 22 በጥፋትና በራብ ላይ ትስቃለህ፤ የምድር አውሬዎችንም አትፈራም፤
\s5
\v 23 ከምድርህ ድንጋይ ጋር ኪዳን ይኖርሃል ከምድር አራዊትም ጋር በሰላም ትሆናለህ።
\v 24 ድንኳንህም በደህንነት እንዳለ ታውቃለህ፤ በረትህን ትጐበኛለህ አንድም አይጠፋብህም።
\v 25 ዘሮችህም ታላቅ እንደሚሆኑ፥ ትውልድህም እንደ ምድር ሣር እንደሚበዙ ታውቃለህ።
\s5
\v 26 የእህሉ ነዶ ደርሶ በወቅቱ ወደ አውድማ እንደሚገባ፥ ዕድሜን ጠግበህ ወደ መቃብር ትሄዳለህ።
\v 27 እነሆ፥ ይህንን ነገር መረመርን፥ ነገሩ እውነት ነው፤ ልብ በለው፤ የራስህም እውቀት አድርገው።
\s5
\c 6
\p
\v 1 ኢዮብም ሲመልስ እንዲህም አለ፦
\v 2 ኦ ስቃዬ ምነው በተመዘነ ኖሮ! መከራዬም ሁሉ ምነው በሚዛን ላይ በተደረገ ኖሮ!
\v 3 ከባሕር አሸዋ ይልቅ ይከብድ ነበርና ለዚህ ነው ቃሎቼ የድፍረት ቃላት የሆኑት።
\s5
\v 4 ሁሉን የሚችል አምላክ ቀስት በውስጤ ነው፥ መርዙንም ነፍሴ ትጠጣለች፤ የእግዚአብሔር ማስደንገጥ በእኔ ላይ ተሰልፎአል።
\v 5 በውኑ የሜዳ አህያ ሣር እያለው በዝለት ያናፋልን? በሬስ ገለባ እያለው በረሀብ ይጮኻልን?
\v 6 ጣዕም የሌለው ነገርስ ያለ ጨው ይበላልን? ወይስ በእንቁላል ውኃ ውስጥ ጣዕም አለን?
\s5
\v 7 ለመንካት ሰውነቴ እምቢ አላቸው፤ እንደሚያስጸይፍ ምግብ ሆኑብኝ።
\v 8 ምነው ልመናዬ በደረሰልኝ! እግዚአብሔርም መሻቴን ምነው በሰጠኝ!
\v 9 እግዚአብሔርም አንድ ጊዜ እኔን ማጥፋት ደስ ቢያሰኘው እጁንም ዘርግቶ ከዚህ ሀይወት ቢያስወግደኝ!
\s5
\v 10 ይህም መጽናናት ይሆንልኛል፤ በማይበርድ ሕመም ውስጥ ብሆንም፥ የቅዱሱን ቃል አልክድምና።
\v 11 እድጠብቅ አቅሜ ምንድን ነው? የምታገሰውስ የህይወቴ ፍጻሜ ምን ስለሆነ ነው?
\s5
\v 12 ጕልበቴ የድንጋይ ጕልበት ነውን? ወይስ ሥጋዬ የተሰራው ከናስ ነውን?
\v 13 በእኔ ውስጥ ሊረዳኝ የሚችልነገር እንደሌለ ጥበብም ከእኔ እንደ ተባረረ እውነት አይደለምን?
\s5
\v 14 ሁሉን የሚችል አምላክን መፍራት የተወ ሰው፥ በዝለት ሊወድቅ ለቀረበ ስንኳ ታማኝነት ከወዳጁ ሊሆንለት ይገባል።
\v 15 ነገር ግን ወንድሞቼ ጥቂት ቆይቶ ውሃ እንደማይኖረው r እንደ በረሃ ወንዝ የማይታመኑ ሆኑብኝ።
\v 16 ከበረዶ የተነሣ ፥በውስጡም ከተሰወረው አመዳይ፤ ወንዙ ደፍርሶ ይጠቁራል፥
\v 17 ሙቀትበመጣ ጊዜ ይደርቃሉ፤ በበጋም ወቅት ከስፍራቸው ይጠፋሉ።
\s5
\v 18 ተጔዥ ነጋዴዎች ውሃ ፍለጋ መንገዳቸውን ሲቀይሩ፤ ወደ በረሃ ገብተው ተቅበዝብዘው ይጠፋሉ።
\v 19 የቴማን ነጋዴዎች በዚያ ተመለከቱ፥ የሳባ መንገደኞችም ተስፋ አደረጉ።
\v 20 ውሃ እንደሚያገኙ ተማምነው ነበርና አፈሩ፤ ወደዚያ ደረሱ፥ ነገር ግን ተታልለው ነበር።
\s5
\v 21 አሁንም እናንተ እንዲሁ ደረቅ ሆናችሁብኝ መከራዬን አይታችሁ ለራሳችሁ ፈራችሁ።
\v 22 በውኑ እኔ፦”አንዳች ነገር ስጡልኝ? ፤ ከሃብታችሁ ስጦታ አቅርቡልኝ?
\v 23 ወይስ፦ ከጠላቴ እጅ አድኑኝ? ከአስጨናቂዎቼ እጅ ተቤዡኝ“ ብያችኋለሁን?
\s5
\v 24 አስተምሩኝ፥ እኔም ዝም እላለሁ፤ ምን ጋር እንደተሳሳትሁ አስረዱኝ።
\v 25 የእውነት ቃል እንዴት ያማል! ነገር ግን የእናንተ ሙግት እንዴት እኔን ይገሥጻል?
\s5
\v 26 ተስፋ እንደ ሌለው ሰው ንግግር ቃሌን እንደ ነፋስ ችላ ለማለት ታስባላችሁን?
\v 27 በርግጥ አባት አልባ በሆኑ ልጆች ላይ ዕጣ ትጣጣላላችሁ፤ ለወዳጆቻችሁም ጕድጓድ ትቈፍራላችሁ።
\s5
\v 28 አሁንም፥ እባካችሁ፥ ወደ እኔ ተመልከቱ፤ በእርግጥ በፊታችሁ አልዋሽም።
\v 29 እባካችሁ፥ ተመለሱ፤ ፍትህ አልባነት በእናንተ መካከል አይሁን፤ በርግጥ ምክንያቴ ጽድቅ ነውና መለስ በሉ።
\v 30 በውኑ በምላሴ ክፋት አለን? አፌስ ተንኰልን መለየት አይችልምን?
\s5
\c 7
\p
\v 1 ለእያንዳንዱ ሰው ህይወት በምድር ብርቱ ልፋት አይደለምን?ቀኖቹስ እንደ ተቀጣሪ ሰራተኛ ቀኖች አይደሉምን?
\v 2 የምሽት ጥላን እንደሚመኝ አገልጋይ፤ደመወዙንም በጽኑ እንደሚፈልግ ቅጥረኛ፤
\v 3 እንዲሁ የጉስቁልና ወራትና፤ መከራ የተሞሉ ለሊቶችን በጽናት እንዳልፍ ተሰጡኝ።
\s5
\v 4 በተኛሁ ጊዜ፦ መቼ እነሣለሁ? ሌሊቱስ መቼ ያልፋል እላለሁ። እስኪነጋ ድረስም ወዲያና ወዲህ እገላበጣለሁ።
\v 5 ሥጋዬ ትልና የአመድ ቅርፊት ለብሶአል፤ ደርቆ የነበረው የቆዳዬም ቁስል እንደ ገና ያመረቅዛል።
\s5
\v 6 ቀኖቼ ከሸማኔ መወርወርያ ይልቅ ፈጣን ናቸው፥ ያለ ተስፋም ያልፋሉ።
\v 7 ሕይወቴ አንድ ትንፋሽ እንደ ሆነ፤ ዓይኔም መልካም ነገርን ከእንግዲህ አንደማያይ አሳሰበኝ።
\s5
\v 8 የሚያየኝ የእግዚአብሔር ዓይን ከእንግዲህ ወዲህ አያየኝም፤ ዓይኖችህ በእኔ ላይ ይሆናል፥ እኔ ግን አልገኝም።
\v 9 ደመና ተበትኖ እንደሚጠፋ፥ እንደዚሁ ወደ ሲኦል የሚወርድ ተመልሶ አይወጣም።
\v 10 ወደ ቤቱ ዳግመኛ አይመለስም፥ የነበረበት ስፍራውም ዳግመኛ አያውቀውም።
\s5
\v 11 ስለዚህም አፌን አልገድበውም፤ በመንፈሴ ስቃይ ሆኜ እናገራለሁ፤ በነፍሴ ምሬት በኀዘን አቤቱታዬን አቀርባለሁ።
\v 12 ጠባቂ በላዬ ትቀጥርብኝ ዘንድ፥ እኔ ባሕር ወይስ የባህር አውሬ ነኝን?
\s5
\v 13 እኔም፦ "አልጋዬ ያጽናናኛል፥ መቀመጫዬም የኀዘን እንጕርጕሮዬን ያቀልልኛል" ባልሁ ጊዜ፥
\v 14 አንተ በሕልም ታስፈራራኛለህ፥ በራእይም ታስደነግጠኛለህ፤
\v 15 ስለዚህም እኔ አጥንቴን ከምታገስ ይልቅ መታነቅንና ሞትን እመርጣለሁ።
\s5
\v 16 ለዘላለም መኖርን እንዳልመኝ፤ ሕይወቴን ናቅኋት። ቀኖቼ ዋጋ ቢስ ናቸውና እባካችሁ ተዉኝ።
\v 17 ትኩረት ትሰጠው ዘንድ ፥ልብህንስ ትጥልበት ዘንድ ሰው ምንድር ነው፥
\v 18 ማለዳ ማለዳስ ትጐበኘው ዘንድ፥ በየጊዜውስ ትፈትነው ዘንድ?
\s5
\v 19 የማትተወኝ እስከ መቼ ነው? ምራቄንስ እስክውጥ ድረስ የማትለቅቀኝ እስከ መቼ ነው?
\v 20 ሰውን የምትጠብቅ ሆይ፥ ኅጢያትንስ አድርጌ እንደ ሆነ ይህ ላንተ ምንድን ነው? ሸክም እ ሆንብህ ዘንድ? ስለ ምን የኢላማሀ ግብ አደረግኸኝ?
\s5
\v 21 መተላለፌን ይቅር ብለህ ስለ ምን ጉስቁልናዬን አታስወግድልኝም? አሁን በምድር ውስጥ እተኛለሁ፤ በጥንቃቄም ትፈልገኛለህ፥ አታገኘኝም።
\s5
\c 8
\p
\v 1 ሹሐዊውም በልዳዶስ መለሰ እንዲህም አለ፦
\v 2 እስከ መቼ እነዚህን ነገሮች ትናገራለህ? የአፍህስ ቃል እስከ መቼ እንደ ብርቱ ነፋስ ይሆናል?
\v 3 በውኑ እግዚአብሔር ፍትህን ያቃውሳልን? ሁሉንም የሚችል አምላክ ጽድቅን ያጣምማልን?
\s5
\v 4 ልጆችህ በድለውት እንደ ሆነ፥ እርሱም በበደላቸው እጅ አሳልፎ እንደሰጣቸው እናውቃለን።
\v 5 ነገር ግን እግዚአብሔርን በትጋት ብትፈልገውና፥ ሁሉንም ለሚችለው አምላክ ልመናህን ብታቀርብ፥
\s5
\v 6 ንጹሕና ቅን ብትሆን፥ በእውነት እርሱ ስለ አንተ ይቆማል፥ በርግጥ የታመነ መኖሪያ ያደርግልሃል።
\v 7 ጅማሬህ ትንሽ ቢሆንም እንኳ ፍጻሜህ እጅግ ታላቅ ይሆናል።
\s5
\v 8 ስለ ቀደመው ዘመን ትውልድ ትጠይቅ ዘንድ እለምንሃለሁ፥ አባቶቻቸውም ከመረመሩና ካገኙት ነገር ለመማር ትጋ፤
\v 9 (ዘመናችን በምድር ላይ እንደ ጥላ ስለሆነ እኛ ትናንት ተወለድን፤ ምንም አናውቅም) ፤
\v 10 እነዚህ የሚነግሩህና የሚያስተምሩህ አይደሉምን? ቃልንም ከልባቸው የሚያወጡ አይደሉምን?
\s5
\v 11 በውኑ ረግረግ በሌለበት ደንገል ሳር ይበቅላልን? ወይስ ቄጠማ ውኃ በሌለበት ቦታ ይለመልማልን?
\v 12 ገና ለምለም አረንጓዴ ሆኖ ሳይቈረጥ፥ ከአትክልት ሁሉ በፊት ይጠወልጋል።
\s5
\v 13 እግዚአብሔርን የሚረሱ ሁሉ የመንገዳቸው ፍጻሜ እንዲሁ ነው፤ አምላክ የሌለው ሰው ተስፋም ይጠፋል።
\v 14 መታመኛቸው እንደሚናድባቸው፥ እምነቱም የሸረሪት ድር አይነት የሆነበት።
\v 15 እዲህ አይነት ሰው ቤቱን ይደገፋል፥ነገር ግን አይቆምለትም፤ደግፎም ይይዘዋል፥ አይጸናለትም።
\s5
\v 16 ፀሐይም እንደወጣች ይለመልማል፥ ጫፉም በአትክልቱ ቦታ ጎልቶ ይወጣል።
\v 17 ሥሮቹ በድንጋይ ክምር ላይ ይጠመጠማሉ፤ በድንጋዮቹም መካከል መልካም ቦታን ይፈልጋሉ።
\v 18 ነገር ግን ይህ ሰው ከቦታው ቢጠፋ፦ ስፍውም "ፈጽሞ አቼህ አላውቅም" ብሎ ይክደዋል።
\s5
\v 19 እነሆ፥ የደስእንደዚህ አይነትሰው ደስታ ይህ ነው፤ ሌሎች ተክሎች ከዚያው አፈር በፋንታው ይበቅላሉ።
\v 20 እነሆ፥ እግዚአብሔር ንጹሁን ሰው አይጥለውም፥ የክፉ አድራጊውንም እጅ አያበረታም።
\s5
\v 21 አፍህን እንደ ገና ሳቅ፥ ከንፈሮችህንም በደስታ ጩኊት ይሞላል።
\v 22 የሚጠሉህ እፍረትን ይለብሳሉ፤ የአመጸኞችም ድንኳን አይገኝም።
\s5
\c 9
\p
\v 1 ኢዮብም ሲመልስ እንዲህም አለ፦
\v 2 “ እንዲህ እንደ ሆነ በእውነት አውቃለሁ፤ ነገር ግን ሰው በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ መሆን እንዴት ይችላል?
\v 3 ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ለመከራከር ቢፈልግ፥ ከሺህ ነገር አንዱን እንኳ መመለስ አይችልም።
\s5
\v 4 እግዚአብሔር በልቡ ጠቢብ ነው፥ ኃይሉም ታላቅ ነው፤ እርሱን ተዳፍሮ በደኅና የተሳካለት ማን ነው?
\v 5 በቍጣው ተራሮችን ሲገለብጣቸው፤ ተራሮችን ሲነቅላልቸው ለማን አስቀድሞ ተናገረ።
\v 6 ምድርን ከስፍራዋ ያሚያናውጣት እርሱ፥ ምሰሶዎችዋንም ያንቀጠቅጣቸዋል።
\s5
\v 7 ይኸው እግዚአብሔር ፀሐይን እንዳትወጣ ያዝዛታል፥ አትወጣምም፤ ከዋክብትንም ይከልላቸዋል።
\v 8 ሰማያትን በራሱ ይዘረጋል፥ የባሕሩን ማዕበል የሚገዛ በላዩም ይራመዳል።
\v 9 ድብና ኦሪዮን የሚባሉትን ኮከቦች፥ ሰባቱንም ከዋክብት፥ በደቡብም በኩል ያሉትን የከዋክብት ስብስቦች ሠርቶአል።
\s5
\v 10 ይኸው እግዚአብሔር የማይመረመሩ ታላላቅ ነገሮችን፥ በርግጥ የማይቈጠሩ ተአምራቶችን ያደርጋል።
\v 11 እነሆ፥ ወደ እኔ ቢመጣ አላየውም፤፤ በአጠገቤም ቢያልፍ አላውቀውም።
\v 12 እነሆ አንድን ሰው ነጥቆ ቢወስድ የሚከለክለው ማን ነው? ምን እያደረግህ ነው? የሚለውስ ማን ነው?
\s5
\v 13 እግዚአብሔር ቍጣውን አይመልስም፤ የረዓብ ረዳቶች ከእርሱ በታች ይሰግዳሉ።
\v 14 ይልቁንስ መልስ ልመልስለት፥ ከእርሱ ጋርስ ለክርክር ቃልን እመርጥ ዘንድ እኔ ማን ነኝ?
\v 15 ጻድቅ ብሆን ኖሮ እንኳ ልመልስለት አልችልም፤ የምችለው ዳኛዬን ምህረት መለመን ብቻ ነው ።
\s5
\v 16 ብጠራውና እርሱ ቢመልስልኝ ም ኖሮ፥ ድምጼን ይሰማ እንደ ነበር አላምንም ።
\v 17 በዐውሎ ነፋስ ይሰብረኛል፥ ቍስሌንም ያለ ምክንያት ያበዛዋል።
\v 18 ትንፋሽ እድወስድ እንኳ ፋታ አልሰጠኝም፥ ይልቅ በመራራነት አጠገበኝ።
\s5
\v 19 ስለ ኃይል ከተናገርን እንደ እርሱ ኃያል ማን ነው፤ የፍርትህ ነገር ከተነሳ፦”የሚጠይቀኝ ማን ነው? “ ይላል።
\v 20 ጻድቅ ብሆን እንኳ አንደበቴ ይወቅሰኛል፤ ሰበብ ባይገኝብኝ እንኳ ጥፋተኛ ያደርገኛል።
\s5
\v 21 ያለነቀፋ ብሆንም ከእንግዲህ ለራሴ ግድ የለኝም፤ ሕይወቴንም እንቃታለሁ።
\v 22 ልዩነት የለውም፤ እርሱ “ጻድቁንና ሃጥኡን ባንድነት ያጠፋል" የምለው ለዚህ ነው።
\v 23 መቅሠፍ በድንገት ቢገድል፥ በንጹሐን ሰዎች ችግር ይስቃል።
\v 24 ምድር ለኃጥአን እጅ ታልፋ ተሰጥታለች፤ እግዚአብሔርም የዳኞችዋን ፊት ሸፍኖአል፤ ይህን ያረገው እርሱ ካልሆነ ታድያ ማን ነው?
\s5
\v 25 ዘመኔ ከመልክተኛ ሰው ሩጫ ይልቅ ይፈጥናል፤ ቀኖቼ፥ መልካምን ሳያዩ ይከንፋሉ።
\v 26 የደንገል ጀልባ እንደሚፈጥን፥ ንስርም ወደሚነጥቀው ግዳይ እንደሚበርር ፈጣን ናቸው።
\s5
\v 27 “አቤቱታዬን እረሳለሁ፤ ሐዘንተኛ ፊቴን ትቼ ደስተኛ እሆናለሁ” ብዬ ብል፥
\v 28 ንጹሕ አድርገህ እንደማትቆጥረኝ ስላወቅሁ መከራዬን ሁሉ እፈራዋለሁ።
\v 29 ጥፋተኛ ሆኜ መቀጣቴ ላይቀር፤ ለምን በከንቱ እደክማለሁ?
\s5
\v 30 ራሴን በአመዳይ ውሃ ባጥብና እጆቼንም እጅግ ባነጻቸው፥
\v 31 የገዛ ልብሴ እስኪጸየፈኝ ድረስ እግዚአብሔር በአዘቅት ውስጥ ይመልሰኛል።
\s5
\v 32 መልስ እድሰጠው ፥ አብረን ወደ ፍርድ ችሎት እንዳንገባ፥ እርሱ እንደ እኔ ሰው አይደለም።
\v 33 እጁን በሁለታችንም ላይ የሚያኖር ፈራጅ፤ በመካከላችንም የሚዳኝ የለም!
\s5
\v 34 የእርሱን በትሩ ከእኔ ላይ የሚያነሳ፥ ማስደንገጡንም ከኔ የሚያርቅ ሌላ ፈራጅ የለምን?
\v 35 በሚገባ በተናገርሁ፥ ባልፈራሁም ነበር፤ ነገር ግን አሁን ነገሮች እንዲህ ባሉበት አልችልም።
\s5
\c 10
\p
\v 1 በራሴ ሕይወት ዝያለሁ፤ አቤቱታዬን ያለመቆጠብ እገልጻለሁ፤ በነፍሴም ምሬት እናገራለሁ።
\v 2 እግዚአብሔርን እንዲህ እለዋለሁ፦ ለምን እንደ ከሰስከኝ ንገረኝ እንጂ እንዲያው አትፍረድብኝ።
\v 3 የእጅህን ሥራ መናቅ፤እኔንስ ማስጨነቅ የኃጥአንን እቅድ ግን በፈገግታ ስትተወው ይህ በአንተ ዘንድ መልካም ነውን?
\s5
\v 4 በውኑ አይኖችህ የሥጋ ለባሽ ዓይኖች ናቸውን? ሰውስ እንደሚያይ ታያለህን?
\v 5 በደሌን ትከታተል ዘንድ፥ ኃጢአቴንም ትመረምር ዘንድ፥
\v 6 ቀኖችህ እንደ ሰው ቀኖች ናቸውን? ዓመታትህስ እንደ ሰው ዓመታት ናቸውን?
\v 7 በደለኛ እንዳልሆንሁ ብታውቅም እንኳ፥ ከእጅህ ሊያድነኝ የሚችል የለም።
\s5
\v 8 እጆቸህ አበጃጁኝ አሳምረህም ሠራኸኝ፤ መልሰህ ግን እያታጠፋኸኝ እኮ ነው።
\v 9 እለምንሃለሁ፤ እንደ ሸክላ አበጃጅተህ እንደ ሰራኸኝ አስብ፤ እንደገናስ ወደ ትቢያ ትመልሰኛለህን?
\s5
\v 10 እንደ ወተት አላፈሰስኸኝምን? እንደ እርጎስ አላረጋኸኝምን?
\v 11 ስጋን አደረክልኝ ቁርበትንም አለበስኸኝ፥ በአጥንትና በጅማትም አቀናብረህ አጠነከርኸኝ።
\s5
\v 12 ሕይወትና የታመነ ኪዳን ሰጠኸኝ፤ እርዳታህም መንፈሴን ጠበቀ።
\v 13 ነገር ግን እነዚህንም ነገሮች በልብህ ሰወርህ፤ ይህንንም ታስብ እንደነበር አውቃለሁ።
\v 14 ኃጢአትም ባደርግ አንተ ታውቀዋለህ፤ ከአመጻዬም ነጻ አትለቀኝም።
\s5
\v 15 በደለኛ ብሆን ወዮልኝ፤ ጻድቅ ብሆንም ራሴን ቀና አላደርግም፤ በሃፍረት ተሞልቼአለሁና፥ መከራዬንም እያየሁ ነውና።
\v 16 ራሴንም ቀና ባደርግ እንደ አንበሳ ታድነኛለህ፤ እንደገና ሃያል መሆንህን ታሳየኛለህ፤
\s5
\v 17 አዲስ ምስክሮችህን ታቆምብኛለህ ቍጣህንም በላዬ ታበዛብኛለህ፤ በአዲስ ሰራዊትም ታጠቃኛለህ።
\s5
\v 18 ታዲያ ለምን ከማኅፀን አወጣኸኝ? ምነው ያኔ ነፍሴ በጠፋችና የሰው ዓይን ባላየኝ።
\v 19 ኖሮ እንደማያውቅ በሆንሁና፤ ከማኅፀን ቀጥታ ወደ መቃብር በወሰዱኝ።
\s5
\v 20 የቀሩኝ ቀናቶች ጥቂት አይደሉምን? ታዲያ ጥቂት እንዳርፍ ተወት አድርገኝ፤
\v 21 ወደማልመለስበት ከመሄዴ በፊት፥ ወደ ጨለማና ወደ ሞት ጥላ ምድር፥
\v 22 እንደ እኩለ ለሊት ወደ ጨለመች ምድር፥ ሥርዓትም ወደሌለበት ወደ ሞት ጥላ፥ ብርሃንዋም እንደ ጨለማ ወደ ሆነ ምድር ሳልሄድ፥ ጥቂት እጽናና ዘንድ ተወኝ።
\s5
\c 11
\p
\v 1 ነዕማታዊውም ሶፋር እንዲህ በሎ መለሰ፦
\v 2 ለዚህ ሁሉ ቃል መልስ መስጠት አይገባምን? በንግግር የተማላው ይህ ሰው እንዲያው ይታመናልን?
\v 3 ትምክህትህስ ሌሎችን ሁሉ ዝም ያሰኛቸዋልን? ትምህርታችንን ስትሳለቅበት፤ የሚያሳፍርህ ማንም የለምን?
\s5
\v 4 ለእግዚአብሔር ስትናገር “ትምህርቴ የተጣራ ነው፥በዓይንህም ፊት ነቀፋ የለብኝም” ትላለህ።
\v 5 ምነው እግዚአብሔር ቢናገርህ! በአንተም ላይ ከንፈሩን ቢከፍት!
\v 6 በማስተዋሉ ታላቅ ነውና፤ የጥበቡን ምሥጢር ምነው ገልጦ ቢያሳይህ! እግዚአብሔር ለበደልህ ከሚገባው አሳንሶ እንደሚያስከፍልህ ታውቅ ነበር።
\s5
\v 7 እግዚአብሔርን መርምረህ ልትረዳው ትችላለህን? ሁሉን የሚችል አምላክን በሙላት ልታውቀው ትችላለህን?
\v 8 ነገሩ እንደ ሰማይ ከፍ ይላል፤ ምን ልታደርግ ትችላለህ? ከሲኦልም ይልቅ ይጠልቃል፤ ምን ልታውቅ ትችላለህ?
\v 9 ርዝመቱ ከምድር ይልቅ ይረዝማል፥ ከባሕርም ይልቅ ይሰፋል።
\s5
\v 10 እርሱ በመካከልህ ቢያልፍ፥ የፈለገውን በግዞት ቢዘጋ፥ ለፍርድ የወደደውን ቢጠራ፥ የሚከለክለው ማን ነው?
\v 11 እርሱ ሃሰተኛ ሰዎችን ያውቃልና፥ አመጻንም ሲመለከት እንዳላየ ያልፋልን?
\v 12 የሜዳ አህያ ሰው በወለደ ጊዜ ካልሆነ በቀር፥ ሞኞች ሊረዱት አይችሉም።
\s5
\v 13 ነገር ግን ልብህን በትክክል ብታቀና፤ እጅህንም ወደ እግዚአብሔር ብትዘረጋ፥
\v 14 በደልንም ከእጅህ እጅግ ብታርቀው፤ በድንኳንህም ኃጢአት ባይኖር፤
\s5
\v 15 ያን ጊዜ በእርግጥ ያለ እፍረት ቀና ትላለህ፤ ጠንክረህም ትቆማለህ፥ አትፈራምም።
\v 16 መከራህንም ትረሳዋለህ፤ እንዳለፎ እንደሔደም ውኃ ታስበዋለህ።
\v 17 ሕይወትህ ከቀትር ይልቅ ይበራል፤ ጨለማም ቢኖር እንኳ እንደ ጥዋት ይሆናል።
\s5
\v 18 ተስፋ ስላለህ ተማምነህ ትቀመጣለህ፤ በዙሪያህ ሁሉ ደኅንነትን ታያለህ፥ በእረፍትም ትቀመጣለህ።
\v 19 ለማረፍ ትተኛለህ፥ የሚያስፈራህም የለም፤ ብዙዎችም ያንተን እርዳታ ይሻሉ።
\s5
\v 20 ነገር ግን የክፉዎች ዓይን ግን ትጨልማለች፤ የሚያመልጡበትም መንገድ የላቸውም፥ ያላቸው ተስፋም የመጨረሻ ትንፋሻቸውን መስጠት ብቻ ነው።
\s5
\c 12
\p
\v 1 በመቀጠልም ኢዮብ መለሰ እንዲህም አለ፦
\v 2 በእርግጥ እናንተ አዋቂ ሰዎች ናቸሁ፤ ጥበብ ከእናንተ ጋር ትሞታለች።
\v 3 ነገር ግን እኔ እንደ እናንተው ማስተዋል አለኝ፤ ከእናንተም የማንስ አይደለሁም፤ በእርግጥ እንደ እነዚህ ያሉትን ነገሮች የማያውቅ ማን ነው?
\s5
\v 4 እግዚአብሔርን ሲጠራ የሚመልስለት ሰው የነበርሁ እኔ አሁን ለጎረቤቶቼ መሳለቅያ ሆኛለሁ፤ ጻድቅና ነቀፋ የሌለበት የነበርሁ እኔ አሁን ማሾፊያ ሆኛለሁ።
\v 5 በደላው ሰው ሃሳብ ውስጥ መከራ የተናቀ ነው፤ እግሩ ለሚሸራተት ሰው ችግሩን ሊጨምርበት ያስባል።
\v 6 የዘራፊዎች ድንኳን ይበለጥጋል፥ እግዚአብሔርንም የሚያስቈጡ በደህና ተቀምጠዋል፤ የገዛ እጃቸውን አምላካቸው አድርገዋል።
\s5
\v 7 አሁን ግን እንስሶችን ጠይቁ፥ ያስተምሯችኋል፤ የሰማይንም ወፎች ጠይቁ፥ ይነግሯችኋል።
\v 8 ወይም ለምድር ተናገሩ፥ እርስዋም ታስተምራችኋለች፤ የባሕርም ዓሣዎች በግልጥ ይነግሯችኋል።
\s5
\v 9 ከእነዚህ ሁሉ እንስሳት የእግዚአብሔር እጅ ይህን እንዳደረገ፤ የሕያዋን ሁሉ ህይወት፤
\v 10 የሰው ልጆችንም ሁሉ እስትንፋስ በእጁ እንደያዘ የማያውቅ ማን ነው?።
\s5
\v 11 ምላስ የምግብን ጣዕም እንደሚቀምስ፥ ጆሮ ቃላትን አይለይምን?
\v 12 እድሜ በገፉት ዘንድ ጥበብ፥ በዘመን ርዝማኔም ማስተዋል ይገኛል።
\s5
\v 13 በእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ኃይል አለ ምክርና ማስተዋልም በእርሱ ዘንድ ይገኛሉ።
\v 14 እነሆ፥ እርሱ ያፈርሳል፥ ተመልሶም አይሠራም፤ አንድን ሰው ቢያስር ሊፈታው የሚችል የለም።
\v 15 እነሆ፥ ውኆቹን ቢከለክል፥ እነርሱ ይደርቃሉ፤ እንደ ገናም ቢለቃቸው፥ ምድርን ያጥለቀልቃሉ።
\s5
\v 16 ብርታትና ጥበብ በእርሱ ዘንድ ናቸው፤ የሚስተውና የሚያስተው በእርሱ ስልጣን ስር ናቸው።
\v 17 መካሪዎችንም ባዶአቸውን በሃዘን ይሰዳቸዋል፥ ፈራጆችንም አላዋቂ ያደርጋቸዋል።
\v 18 የነገሥታትንም የስልጣን ሰንሰለት ይፈታል፥ ወገባቸውንም በመታጠቂያ ልብስ ያስርላቸዋል።
\s5
\v 19 ይሽራል ባዶአቸውንምይሰዳቸዋል፥ ኃያላንንም ይገለብጣቸዋል።
\v 20 የታመኑ ሰዎችንም ንግግረ ያስወግዳል፥ የሽማግሌዎችንም ማስተዋል ይወስድባቸዋል።
\v 21 በአለቆች ላይ ንቀትን ያፈሳል፥ የብርቱ ሰዎችንም ቀበቶ ይፈታል።
\s5
\v 22 ከጨለማ ውስጥ ጥልቅ ነገሮችን ይገልጣል፥ ከሙታንም ሰፈር የመታየትን ጥላ ወደ ብርሃን ያወጣል።
\v 23 ህዝቦችን ብርቱ ያደርጋል፥ ደግሞም ያጠፋቸዋል፤ ህዝቦችንም ያበዛል፥ ደግሞም ወደ ግዞት ይልካቸዋል።
\s5
\v 24 ከምድር ሕዝብ አለቆች ማስተዋልን ይወስዳል፥ መንገድም በሌለበት ምድረበዳ ያቅበዘብዛቸዋል።
\v 25 ብርሃን በሌለበት በጨለማ ይዳክራሉ፤ እንደ ሰካራምም ይንገዳገዳሉ።
\s5
\c 13
\p
\v 1 እነሆ፥ ይህን ሁሉ ዓይኔ አይቷል፤ ጆሮዬም ሰምቶ አስተውያለሁ።
\v 2 እናንተ የምታውቁትን እኔም ደግሞ አውቀዋለሁ ከእናንተ የማንስ አይደለሁም።
\s5
\v 3 ቢሆንም ግን ሁሉን ከሚችል አምላክ ጋር መነጋገር እመርጣለሁ፥ ከእግዚአብሔርም ጋር መዋቀስ እፈልጋለሁ።
\v 4 እናንተ ግን እውነትን በሐሰት ለባጮች ናችሁ፤ ሁላችሁ ዋጋ የሌላችሁ ሃኪሞች ናችሁ።
\v 5 ምነው ሁላችሁ ዝም ብትሉ! ይህም ጥበብ ይሆንላችሁ ነበር።
\s5
\v 6 እንግዲህ ክርክሬን ስሙ፥ የከንፈሬንም ሙግት አዳምጡ።
\v 7 ለእግዚአብሔር ጽድቅ የሌለበትን ነገር ትናገሩለታላችሁን? ለእርሱስ በማታለል ታወሩለታላችሁን?
\v 8 ቸርነትንስ ታደርጉለታላችሁን? ለእግዚአብሔርስ በሸንጎ ጠበቃ ትሆኑለታላችሁን?
\s5
\v 9 እንደ ዳኛ ወደ እናንተ ቢዞርና ቢመረምራችሁ ይህ መልካም ይመስላችኋልን? ወይስ አንዱ ሌላውን ሰው እንደሚያታልል፣ በሸንጎ ትሳለቁበታላችሁን?
\v 10 በስውር ወደ እርሱ ብታደሉ እንኳ፤ እርሱ በእርግጥ ይገስጻችኋል።
\s5
\v 11 ግርማዊነቱ አያስፈራችሁምን? ማስደንገጡስ በላያችሁ አይወድቅምን?
\v 12 አስገራሚ ንግግራችሁ ከአመድ የተሰሩ ምሳሌዎች ናቸው፤ ምላሻችሁም ከሸክላ የተሰሩ መመከቻዎች ናቸው።
\s5
\v 13 ዝም በሉ፥ እኔም እንድናገር ተዉኝ፤ የሚመጣው ነገር ይምጣብኝ።
\v 14 ሥጋዬን በጥርሴ እይዛለሁ፥ ሕይወቴንም በእጆቼ አኖራታለሁ።
\v 15 እነሆ ቢገድለኝ የሚቀርልኝ ተስፋ የለኝም፤ ቢሆንም ስለ መንገዴ በፊቱ እሟገታለሁ።
\s5
\v 16 አምላክ እንደሌለው ሰው ወደ ፊቱ አልቀረብኩምና፤ለደህንነቴ ይሆንልኛል።
\v 17 አምላኬ፡ንግግሬን በሚገባ አድምጥ፥ አስረግጬ የምለውም ለጆሮህ ይድረስ።
\s5
\v 18 እነሆ አሁን፥ ሙግቴን አሰናድቻለሁ፤ ነጻ እንደምወጣም አውቃለሁ።
\v 19 በሸንጎስ ቆሞ የሚከራከረኝ ማን ነው? ጥፋተኛ ሆኜ ከተገኘሁ፤ በዝምታ ህይወቴን ለሞት እሰጣለሁ።
\s5
\v 20 አማላኬ ሁለት ነገር ብቻ አድርግልኝ፤ እኔም ራሴን ከፊትህ አልሸሽግም፤
\v 21 ጠንካራ እጅህን ከእኔ አርቅ፤ በማስደንገጥህም አታስፈራኝ።
\v 22 ከዚያም ጥራኝ፥ እኔም እመልስልሃለሁ። ወይም እኔ ልናገር፥ አንተም መልስልኝ።
\s5
\v 23 በደሌና ኃጢአቴ ምን ያህል ሆነ? መተላለፌንና ኃጢአቴን አስታውቀኝ።
\v 24 ፊትህን ከእኔ ለምን ትሰውራለህ፥ እንደ ጠላትህስ ለምን ታደርገኛለህ?
\v 25 የረገፈን ቅጠል ታሳድደዋለህን? ወይስ የደረቀን ገለባ ትከታተለዋለህ?
\s5
\v 26 የመረረ ነገር ስለጻፍህብኝ፤ የወጣትነቴን ኃጢአት ታወርሰኛለህ።
\v 27 እግሬንም በእግር ግንድ አስገባኸው፥ መንገዶቼን ሁሉ በቅርበት አየኻቸው፤ የእግሬ መርገጫ የተራመደበትን መሬት ሁሉ መረመርህ።
\v 28 ምንምእንኳ እኔ እንደሚጣል ብስባሽ፥ ብልም እንደበላው ልብስ ብሆንም።
\s5
\c 14
\p
\v 1 ከሴት የተወለደ ሰው ጥቂት ቀናት ቢኖርም፥ በመከራ የተሞሉ ሆኑ።
\v 2 እንደ አበባ ከመሬት ይወጣል፥ ይረግፋልም፤ እንደ ጥላም ይፈጥናል፥ ነገር ግን አይቆይም።
\v 3 እንደዚህ ያለውን ሰው ትመለከታለህን? ከአንተስ ጋር እኔን ወደ ፍርድ ታመጣኛለህን?
\s5
\v 4 ከርኩስ ነገር ንጹሕን ማውጣት ማን ይችላል? ማንም የለም።
\v 5 የሰው ዕድሜ የተወሰነ ነው፥ የወራቶቹም ቍጥር በአንተ እጅ ነው፥ እርሱም ሊያልፈው የማይችለውን ገደብ ቀጠርህለት።
\v 6 እንደ ተቀጣሪ ሰው የቀሩትን ቀኖች እዲደሰትባቸው፤ እዲያርፍም ከእርሱ ዘወር በል።
\s5
\v 7 ዛፍ ቢቈረጥ ደግሞ ሊያቈጠቍጥ፥ ቅርንጫፉም ማደግ እንዳያቆም ተስፋ ሊኖረው ይችላል።
\v 8 ምንምእንኳ ሥሩ በምድር ውስጥ ቢያረጅ፥ ግንዱም በመሬት ውስጥ ቢሞት፥
\v 9 የውኃ ሽታ ሲያገኝ ዳግም ያቈጠቍጣል እንደ አትክልትም ቅርንጫፍ ያወጣል።
\s5
\v 10 ሰው ግን ይሞታል፤ ይደክማል፤ በርግጥ ሰው እስትንፋሱን ይሰጣል፥ እርሱስ ወዴት አለ?
\v 11 ውኃ ከሐይቅ እንደሚያልቅ፤ ወንዙም እንደሚቀንስና እንደሚደርቅ፤
\v 12 እንዲሁ ሰዎች ይተኛሉ ዳግም አይነሱም፤ ሰማይ እስኪያልፍ ድረስ አይነቁም፥ ከእንቅልፉቸውም አይነሱም።
\s5
\v 13 በሲኦል ውስጥ ምነው በሰወርኸኝ ኖሮ! ቍጣህ እስኪያልፍ ድረስ በሸሸግኸኝ ኖሮ! ቀጠሮም አድርገህ ምነው ባሰብኸኝ ኖሮ!
\v 14 በውኑ ሰው ከሞተ ተመልሶ ሕያው ይሆናልን? መለወጤ እስኪመጣ ድረስ፥ የሰልፌን ዘመን ሁሉ በትዕግሥት በተጠባበቅሁ ነበር።
\s5
\v 15 በጠራኸኝና በመለስሁልህ ነበር፤ የእጅህንም ሥራ በተመኘኸው ነበር።
\v 16 ለእርምጃዬ ጥንቃቄንና ገደብን ታደርግለታለህ፤ ኃጢአቴንም አትቆጣጠርብኝም።
\v 17 መተላልፌን በከረጢት ውስጥ ታትመዋለህ፥ ኃጢአቴንም ትሸፍንልኛለህ።
\s5
\v 18 ነገር ግን ተራራ እንኳ ይወድቃል ይጠፋልም፥ ዓለቶችም እንዲሁ ከስፍራቸው ይለቃሉ፤
\v 19 ውኆች በድንጋዮቹ ላይ ይወርዳሉ፤ ጎርፎቹም የምድሩን አፈር ይወስዳሉ፤ እንዲሁ የሰውን ተስፋ ታጠፋዋለህ።
\s5
\v 20 ሁልጊዜ ታሸንፈዋለህ፥ እርሱም ያልፋል፤ፊቱን ትለውጣለህ፥ እርሱንም ወደ ሞት ትሰድደዋለህ።
\v 21 ልጆቹ ወደ ክብር ቢመጡም አያውቅም፤ ቢዋረዱም ይህ ሲሆን አያይም።
\v 22 ነገር ግን የራሱ ሰውነት ሕመም ብቻ ይሰማዋል፥ ለራሱም በሃዘን ያለቅሳል።
\s5
\c 15
\p
\v 1 ቀጥሎም ቴማናዊውም ኤልፋዝ መለሰ እንዲህም አለ፦
\v 2 በውኑ ጠቢብ ሰው ከንቱ በሆነ እውቀት ይመልሳልን? ራሱንስ በምሥራቅ ነፋስ ይሞላልን?
\v 3 ትርፍ በሌለው ወሬ ወይም በማይጠቅም ንግግር ይሟገታልን?
\s5
\v 4 በእርግጥ አንተ የእግዚአብሔርን አክብሮት ታሳንሳለህ፤ ለእግዚአብሔር ያለህን መሰጠት ታስቀራለህ።
\v 5 ሃጢያትህ አፍህን ያስተምረዋል፥ የተንኰለኛ አንደበት ቢኖርህ ትመርጣለህ።
\v 6 የሚፈርድብህ የራስህ አፍ እንጂ እኔ አይደለሁም፤ በርግጥም የራስህ ከንፈሮች ይመሰክሩብሃል።
\s5
\v 7 ከተወለዱት ሁሉ አንተ የመጀመሪያ ሰው ነህን? ወይስ ከኮረብቶች በፊት አንተ ነበርህ?
\v 8 የእግዚአብሔርን ምሥጢራዊ እውቀት ሰምተሃልን? ጥበብንስ ለራስህ ብቻ ገደብሃትን?
\v 9 እኛ የማናውቀው አንተ የምታውቀው ምንድር ነው? በእኛ ዘንድ የሌለ አንተ ብቻ የተረዳኸው ምን አለ?
\s5
\v 10 ከአባትህ በዕድሜ የሚበልጡ ሽበትም ያላቸው ሽማግሌዎችም ከእኛ ጋር አሉ።
\v 11 በውኑ የእግዚአብሔር ማጽናናት፥ በየውሃነት የቀረበልህ ቃልስ ጥቂት ሆነብህን?
\s5
\v 12 የነፍስህ ስሜት ለምን ይወስድሃል? ዓይኖችህስ ለምን በቁጣ ያፈጣሉ?
\v 13 መንፈስህ በእግዚአብሔር ላይ ተነስቷል፤ እንዲህ ያለ ቃል ከአፍህ እስከ ማውጣት ደረስህ።
\v 14 ንጹሕ ሆኖ ሊገኝ ሰው ማን ነው? ጻድቅ ሊሆን ከሴት የተወለደ እርሱ ማን ነው?
\s5
\v 15 እነሆ እግዚአብሄር በቅዱሳኑ እንኳ አይታመንም፤ በእርግጥ ሰማያትም በእርሱ አይን ንጹሕ አይደሉም።
\v 16 ይልቁንስ ኃጢአትን እንደ ውኃ የሚጠጣ ፥ አመጸኛና የተበላሸው የሰው ልጅ ምንኛ ያንስ?
\s5
\v 17 ስማኝ፥አሳይሃለሁ፤ያየሁትንም አሳውቅሃለሁ፤ በመካከላቸውም እንግዳ ያልገባባቸው ጠቢባን
\v 18 ጠቢባን ከአባቶቻቸው ተቀብለው ያስተላለፉትን ፤ የእነርሱ ቀደምት ትውልድ ያልሸሸጉትን ነገር እገልጥልሃለሁ።
\s5
\v 19 ለአባቶቻቸውም ፥ ምድሪቱ ለእነርሱ ብቻ ተሰጥታ ነበረ፥ በመካከላቸው እንግዶች አልፈው አያውቁም
\v 20 ክፉ ሰው ዕድሜውን ሙሉ በሕመም ይሰቃያል፥ ግፈኛም በፊቱ ያሉት ዓመታት ለስቃይ ይሆኑበታል።
\v 21 የሽብር ድምፅ በጆሮው ውስጥ ነው፤ በብልጽግናው እያለ አጥፊው ይመጣበታል።
\s5
\v 22 ከጨለማ ተመልሶ እንደሚወጣ አያስብም፥ ሰይፍም አሸምቆ ይጠብቀዋል።
\v 23 ወዴት አለ? እያለ እንጀራ ፍለጋ ብዙ ስፍራ ይዞራል፤ የጨለማ ቀን እንደ ደረሰበትም ያውቃል።
\v 24 ጭንቀትና ስቃይ ያስፈራሩታል፤ ለጦርነት ዝግጁ እንደ ሆነ ንጉሥ ይበረቱበታል።
\s5
\v 25 ምክንያቱም እጁን በእግዚአብሔር ላይ አንስቶአል፥ ሁሉንም በሚችል አምላክ ፊት በትዕቢት ሔዷልና፥
\v 26 በደንዳና አንገቱና በወፍራም ጋሻው ሆኖ፥ ይህ አመጸኛ ሰው በእግዚአብሔር ላይ ይመጣልና፥
\s5
\v 27 ይህ እውነት ነው፥ምንም እንኳ በስብ ፊቱን ቢከድንም፥ ስቡንም በወገቡ ላይ ቢያጠራቅም፥
\v 28 በፈረሱ ከተሞች ውስጥ፥ ሰውም በማይኖርበትና፥ ክምር ለመሆን በተመደቡ ቤቶች ውስጥ ይኖራልና፤
\s5
\v 29 ባለጠጋ አይሆንም፥ ሀብቱም አይጸናም፤ ጥላው እንኳ በምድር ላይ አይቆይም፤
\v 30 ከጨለማ ተለይቶ አይወጣም፤ ነበልባልም ቅርንጫፎቹን ያደርቃቸዋል፥ በእግዚአብሔር አፍ እስትንፋስም ይጠፋል።
\s5
\v 31 ዋጋው ከንቱነት እንዳይሆን፥ ራሱን እያሳተ በከንቱ ነገር አይታመን።
\v 32 ቀኑ ሳይደርስ የፍጻሜው ሰዓት ይመጣል፥ ቅርንጫፉም አይለመልምም።
\v 33 እንደ ወይን ያልደረሰውን ዘለላ ይጥላል፤ እንደ ወይራ ዛፍም አበባውን ያረግፋል።
\s5
\v 34 አምላክ የሌለው ህዝብ ጉባኤ ሁሉ ይመክናል፥ የሙሰኞችንም ድንኳን እሳት ትበላለች።
\v 35 ተንኰልን ይፀንሳሉ፥ በደልንም ይወልዳሉ፥ ማህጸናቸውም ማታለልን ያዘጋጃል።
\s5
\c 16
\p
\v 1 ኢዮብም ሲመል እንዲህ አለ፦
\v 2 እንደዚህ ያለ ብዙ ነገር ሰምቻለሁ፤ ሁላችሁም የማትጠቅሙ አጽናኞች ናችሁ።
\v 3 ከንቱ ቃሎች መጨረሻ የላቸውምን? እንደዚህ ለመመለስ የቻላችሁት ምን ነክቷችሁ ነው?
\s5
\v 4 እናንተ በእኔ ቦታ ብትሆኑ፤ እንደ እናንተ መናገር እችል ነበር፤ እኔም ቃላቶችን ሰብስቤ እያቀናበረሁ፥ በማሾፍም በእናንተ ላይ ራሴን መነቅነቅ እችል ነበር።
\v 5 ኦ! በአፌም እንዴት አድርጌ ባበረታታኋችሁ! የከንፈሬም ማጽናናት እንዴት ሃዘናችሁን ባቀለለ ነበር!
\s5
\v 6 ብናገር ሰቆቃዬ አይቀንስም፤ ከመናገር ዝም ብል እንዴት እገዛ ላገኝ እችላለሁ።
\v 7 አሁን ግን እግዚአብሔር አድክመኸኛል፤ ቤተሰቤን ሁሉ አፈራርሰሃል።
\v 8 አድርቀኸኛል ይኸውም በላዬ ይመሰክርብኛል፤ የሰውነቴም መጨማተር ምስክር ነው፤ ክሳቴም ተነሥቶ፤በፊቴ ላይ ይመሰክራል።
\s5
\v 9 እግዚአብሔር በቍጣው ቀደደኝ፥ አሳደደኝም፤ ጥርሶቹንም አፋጨብኝ፤ ይህም ሲሆን ጠላቴ ዓይኑን አፈጠጠብኝ፤
\v 10 ሰዎችም በግርምት አፋቸውን ከፈቱ፤ እያላገጡም ጕንጬን ጠፈጠፉኝ፤ በአንድነትም በእኔ ላይ ተሰበሰቡ።
\s5
\v 11 እግዚአብሔር አመጸኛ ሰዎች አሳልፎ ሰጠኝ፥ በክፉዎችም እጅ ጣለኝ።
\v 12 በሰላም ተቀምጬ ነበር፥ እርሱም ሰባበረኝ፤ በርግጥም አንገቴን ይዞ አደቀቀኝ፤ ኢላማው አድርጎም አቆመኝ።
\s5
\v 13 ቀስተኞቹ ከበቡኝ፤ ኵላሊቶቼንም ወጋቸው፥ አላስተረፈኝምም፤ ሐሞቴንም በምድር ላይ አፈሰሰ።
\v 14 ከግድግዳዬም ጋር ደጋግሞ አጋጨኝ፤ እንደ ጦረኛ በላዬ ሮጠብኝ።
\s5
\v 15 በሰውነቴ ላይ ማቅ ሰፋሁ፥ ቀንዴንም በመሬት ላይ ጣልሁት።
\v 16 ፊቴ ከልቅሶ የተነሣ ቀላ፤ በዓይኖቼ ቆብ ላይም የሞት ጥላ አለ፤
\v 17 ቢሆንም ግን በእጄ ዓመፅ የለም፤ ጸሎቴም ንጹሕ ነው።
\s5
\v 18 ምድር ሆይ፥ ደሜን አትሸፍኚ፥ ለቅሶዬም ማረፊያ ቦታ አይኑረው።
\v 19 አሁንም ቢሆን፥ ምስክሬ በሰማይ አለ፥ ለእኔም የሚሟገትልኝ በአርያም ነው።
\s5
\v 20 ጓደኞቼ ተሳለቁብኝ ነገር ግን አይኖቼ በእግዚአብሔር ፊት እንባን ያፈሳሉ።
\v 21 የሰው ልጅ ከባልንጀራው ጋር እንደሚምዋገት፥ ያ በሰማይ ያለው ምስክሬ በእግዚአብሔር ፊት እንዲምዋገትልኝ እጠይቃለሁ!
\v 22 ምክንያቱም ጥቂት ዓመታት ካለፉ በኋላ እኔም ወደማልመለስበት ስፍራ እሄዳለሁ።
\s5
\c 17
\p
\v 1 መንፈሴ ተጨረሰ፥ ቀኖቼም አለቁ፥ መቃብርም ተዘጋጅቶልኛል።
\v 2 በርግጥ አላጋጮች ከእኔ ጋር አሉ፥ ዓይኔም ይህን ማላገጣቸውን ሁልጊዜ ያያል።
\v 3 አሁንም መያዣን ለራስህ ሰጥተህ ዋስ ሁነኝ፤ ከአንተ ሌላ የሚረዳኝ ማን አለ?
\s5
\v 4 እግዚአብሔር አንተ ልባቸው እንዳያስተውል አድርገሃል፤ በላዬም ከፍ እንዲሉ አታደርጋቸውም።
\v 5 ለጥቅም ብሎ ጓደኞቹን አሳልፎ የሚሰጥ ሰው፥ የልጆቹ ዓይን ይታወራል።
\s5
\v 6 ነገር ግን እርሱ ለሰዎች መተረቻ አደረገኝ፤ በፊቴም ላይ ተፉብኝ።
\v 7 ዓይኔ ከኀዘን የተነሣ ፈዘዘ፥ የሰውነቴ ክፍሎች በሙሉ እንደ ጥላ ቀጠኑ።
\v 8 ጻድቅ ሰዎችም በዚህ ነገር ይደነቃሉ፥ ንጹሑም ሰው በዐመጸኞች ላይ ይበሳጫል።
\s5
\v 9 ጻድቅ ግን መንገዱን ያጸናል፥ ንጹሕ እጆች ያሉትም ሰው ብርታትን እየጨመረ ይሄዳል።
\v 10 እናንተ ሁላችሁ ግን እስቲ ወደ እኔ ኑ፤ ከመካከላችሁ አንድም ጠቢብ አላገኝም።
\s5
\v 11 ቀኖቼ አለቁ፤ እቅዶቼ አበቃላቸው፥የልቤም ምኞት ሳይቀር ከንቱ ሆነ።
\v 12 እነዚህ አሿፊ ሰዎች ሌሊቱን ወደ ቀን ይለውጣሉ፤ ብርሃንም የሚሉተ ወደ ጨለማ የቀረበውን ነው።
\s5
\v 13 ሲኦልን እንደ ቤቴ ካየሁ፤ መቀመጫዬንም በጨለማ ከዘረጋሁ፤
\v 14 ለጉድጓድም፦ “አንተ አባቴ ነህ” ፤ ለትልም፦ “አንቺ እናቴ እኅቴም ነሽ” ብዬ ካልሁ።
\v 15 ታዲያ ተስፋዬ ወዴት ነው? ተስፋዬንስ የሚያይልኝ ማን ነው?
\v 16 ተስፋስ ወደ አፈር ስንወርድ፥ አብሮኝ ወደ ሲኦል ይወርዳልን?
\s5
\c 18
\p
\v 1 ሹሐዊው በልዳዶስ ሲመልስ እንዲህ አለ፦
\v 2 ወሬህን የምታቆመው መቼ ነው? እስቲ አስብ፥ ከዚያም እኛ እንናገራለን።
\s5
\v 3 ለምን እንደ እንስሶች ቆጠርኸን? ለምን በአንተ ፊት እንደ ቆሻሻ ሆንን?
\v 4 አንተ በራስህ ቍጣ ተወርሰሃል፤ ምድር ለአንተ ሲባል ባድማ ትሆናለችን? ወይስ ዓለቶች ከስፍራው መወገድ አለባቸው?
\s5
\v 5 በእርግጥ የኃጢአተኛ መብራት ይጠፋል፥ የእሳቱም ነበልባል አያበራም።
\v 6 ብርሃን በድንኳኑ ውስጥ ጨለማ ይሆናል፥ በላዩ ያለው መብራትም ይጠፋል።
\s5
\v 7 የብርታቱም እርምጃ ያጥራሉ፥ የራሱ እቅዶች ወደታች ይጥሉታል።
\v 8 በገዛ እግሩ ወደ ወጥመድ ይገባል፥ ወደ ጉድጓድም ውስጥ ይገባል።
\s5
\v 9 ወጥመድ ተረከዙን ይይዘዋል፥ ወስፈንጠርም በላዩላይ ይሆናል።
\v 10 በመሬትም ላይ የሸምቀቆ ገመድ፥ በመንገዱም ላይ ወጥመድ ለእርሱ ተሰውሯል።
\v 11 ድንጋጤ በሁሉ አቅጣጫ ያስፈራዋል፥ ከኋላውም ሆነው ያሳድዱታል።
\s5
\v 12 ብልጥግናው ወደ ራብ ይለወጣል፥ መቅሠፍትም ካጠገቡ ተዘጋጅቶለታል።
\v 13 የሰውነቱም ክፍሎች ፈጽመው ይጠፋሉ፤ የሞትም በኵር ልጅም አካል ክፍሎቹን ይበላል።
\s5
\v 14 ከሚታመንበት ቤት፤ ከተቀመጠበትም ድንኳን ይነቀላል፤ የድንጋጤ ንጉሥ ወደሆነው ወደ ሞት ያመጡታል።
\v 15 ዲን በመኖሪያው እንደተበተነ ይመለከታሉ፤ የራሱያልሆኑ ሰዎችም በድንኳኑ ውስጥ ይኖራሉ።
\s5
\v 16 ሥሩ ከበታቹ ይደርቃል፥ ቅርንጫፉም ከላዩ ይወድቃል።
\v 17 መታሰቢያው ከምድር ላይ ይጠፋል፥ በመንገድም ላይ ስሙ አይነሳም።
\s5
\v 18 ከብርሃን ወደ ጨለማ ይወስዱታል፥ ከዚህም ዓለም ያሳድዱታል።
\v 19 በሕዝቡ መካከል ልጅ የልጅ ልጅም አይኖረውም፤ ጥቂት የሚቆይበትም ዘመድ እንኳ አያገኝም።
\v 20 በአንድ ቀን የሆነበትን ሲያዩ የምዕራብ ሰዎች 、ይደነግጣሉ፥ በምስራቅ የሚኖሩ ሰዎችም ይፈራሉ ።
\s5
\v 21 በርግጥ የኃጥዕ ቤቶች እንዲህ ናቸው፥ እግዚአብሔርንም የማያውቁ ሰዎች ስፍራ ይህ ነው።
\s5
\c 19
\p
\v 1 ኢዮብም ሲመልስ እንዲህ አለ፦
\v 2 በቃላቶቻችሁ የምታሰቃዩኝና፥ የምትሰባብሩኝ እስከ መቼ ነው?
\s5
\v 3 አሥር ጊዜ ዘለፋችሁኝ፤ በጭካኔ ስትበድሉኝም አላፈራችሁም።
\v 4 በርግጥ ተሳስቼ ቢሆን እንኳ፥ ስሕተቱ የእኔ ጉዳይ ይሆናል።
\s5
\v 5 በእርግጥ ራሳችሁን በላዬ ከፍ ብታደርጉ፥ እኔንም እንደተላላፊ ለሁሉ ብታስቆጥሩኝም፥
\v 6 ግን ደግሞ እግዚአብሔር እንደ በደለኝ፥ በመረቡም እንደ ያዘኝ ማወቅ ነበረባችሁ።
\s5
\v 7 ስለ መበደሌ ልናገር ብጮኽም አልሰማም፤ እርዳታ ለማግኝት ብጠራም ፍትህ የለም።
\v 8 እንዳላልፍ መንገዴን አጥሮታል፥ በመንገዴም ላይ ጨለማ አኑሮበታል።
\v 9 ክብሬን ከላዬ ገፈፈ፥ ዘውዴንም ከራሴ ላይ አነሳ።
\s5
\v 10 እስክጠፋ ድረስ፥ በየአቅጣጫው ሰበረኝ፤ ተስፋዬንም እንደ ዛፍ ነቀለው፤
\v 11 ቍጣውንም በላዬ አነደደው፥ ከጠላቶቹም እንደ አንዱ አድርጎ ቈጠረኝ።
\v 12 ሠራዊቱ በአንድነት መጡብኝ፥ መወጣጫም በእኔ ላይ አዘጋጁ፥ በድንኳኔም ዙሪያ ሰፈሩ።
\s5
\v 13 ወንድሞቼን ከእኔ አራቃቸው፥ የሚያውቁኝም ፈጽመው ተለዩኝ።
\v 14 ዘመዶቼ ተዉኝ፥ የቅርብ ጓደኞቼም ረሱኝ።
\s5
\v 15 አንድ ወቅት በቤቴ በእንግድነት የተቀመጡ፥ ሴቶች ሰራተኞቼም እንደ መጻተኛ ቈጠሩኝ፤ በፊታቸውም እንደ ባዕድ ሆንሁ።
\v 16 አገልጋዬን ተጣራሁ፥ በአፌም ለመንሁት ነገር ግን መልስ አልሰጠኝም።
\s5
\v 17 ትንፋሼም ለሚስቴ የሚያስጠላት ሆነ፥ ልመናዬም በገዛ ወንድሞቼና እህቶቼ ተጠላ።
\v 18 ሕፃናቶች እንኳ አንቋሸሹኝ፤ ለመናገር ብነሣም መልሰው ይናገሩኛል።
\v 19 የሚያማክሩኝ ጓደኞቼ ሁሉ ተጸየፉኝ፤ የምወድዳቸው በእኔ ላይ ተነሱ።
\s5
\v 20 አጥንቴ ከሥጋዬና ከቆዳዬ ጋር ተጣበቀ በድድ ብቻ ቀርቶልኝ አመለጥሁ።
\v 21 ጓደኞቼ ሆይ፥ እዘኑልኝ የእግዚአብሔር እጅ መትታኛለችና እዘኑልኝ።
\v 22 እግዚአብሔር እንደሆናችሁ ያክል ለምን ታሳድዱኛላችሁ? ሥጋዬን ማጥፋታችሁ ስለ ምን አይበቃችሁም?
\s5
\v 23 ኦ ምነው ቃሎቼ ቢጻፍ! ምነው በመጽሐፍ ቢታተሙ!
\v 24 ምነው በብረት ብዕርና በእርሳስ ተጽፎ፥ በዓለት ላይ ለዘላለም ቢቀረጽ!
\s5
\v 25 እኔ ግን የሚቤዠኝ ሕያው እንደ ሆነ፥ በመጨረሻም በምድር ላይ እንዲቆም አውቃለሁ፥
\v 26 ይህ ቆዳዬ ማለትም ሰውነቴ ከጠፋ በኋላ፥ በአካሌ እግዚአብሔርን እንዳይ አውቃለሁ።
\v 27 አየዋለሁ፥ እኔ ራሴ በአጠገቤ አየዋለሁ፥ ዓይኖቼ ይመለከቱታል፥ እንግዳም አይሆንብኝም። ልቤ በመናፈቅ ዝሎአል።
\s5
\v 28 “ 'እንዴት እናሳድደዋለን! የችግሩ ሥር በእርሱ ውስጥ ነው' ብትሉ፥
\v 29 ቍጣ የሰይፍን ቅጣት ያስከትላልና፣ ሰይፍን ፍሩ፤ ፍርድ እንዳለም ታውቃላችሁ።”
\s5
\c 20
\p
\v 1 ናዕማታዊውም ሶፋር ሲመልስ እንዲህ አለ፦
\v 2 ከውስጤ ጭንቀት የተነሳ አሳቤ መልስ እንድሰጥ አስቸኮለኝ።
\v 3 የሚያሳፍረኝን ተግሣጽ ከአንተ ሰምቻለሁ፥ ነገር ግን ከመረዳቴ የሚያልፍ መንፈስ ይመልስልኛል።
\s5
\v 4 እግዚአብሔር ሰውን በምድር ላይ ካኖረበት፥ ከጥንት ጀምሮ እንዴት እንደ ነበር አታውቅም?
\v 5 የኃጢአተኛ መፈንጨት አጭር ፣ የአመጸኛም ደስታ ለቅጽበት መሆኑን አታውቅምን?
\s5
\v 6 ቁመቱ እስከ ሰማይ ቢደርስ፥ ራሱም እስከ ደመና ቢሆን፥
\v 7 እንዲህ ያለ ሰው እንደ ምናምን ፈጽሞይጠፋል፤ አይተውት የነበሩም፦ ወዴት ነው? ይላሉ።
\s5
\v 8 እንደ ሕልም ይበርራል፥ እርሱም አይገኝም፤ በርግጥ እንደ ሌሊት ራእይ በርሮ ይጠፋል።
\v 9 ያየውም ዓይን ዳግመኛ አያየውም፤ የነበረበት ስፍራም እንደገና አይመለከተውም።
\s5
\v 10 ልጆቹ ድሆችን ይቅርታ ይላሉ፤ እጆቹም ሀብቱን መመለስ ይገባቸዋል።
\v 11 አጥንቶቹ በወጣትነት ጉልበት ተሞልተዋል፤ ነገር ግን ከእርሱ ጋር በአፈር ውስጥ ይተኛል።
\s5
\v 12 ክፋት በአፉ ውስጥ ቢጣፍጥ፥ ከምላሱም በታች ቢደብቀው፥
\v 13 ምንም እንኳ እዚያው ቢያቆየው ባይለቅቀውም፥ በአፉ ውስጥ ቢይዘው፥
\v 14 ምግቡ በአንጀቱ ውስጥ ወደ መራራነት ይለወጣል፤ በውስጡ እንደ እባብ መርዝ ይሆንበታል።
\s5
\v 15 የዋጠውን ሀብት መልሶ ይተፋል፤ እግዚአብሔርም ከሆዱ ያስወጣዋል።
\v 16 የእባብን መርዝ ይመጣል፤ የእፉኝትም ምላስ ይገድለዋል።
\s5
\v 17 በማርና በቅቤ ፈሳሾች፥ በወንዞችም ተደስቶ አይኖርም።
\v 18 የደከመበትንም ሳይበላው መልሶ ይሰጣል፤ ባገኝውም ሃብት ደስ አይለውም።
\v 19 ድሆችን አስጨንቆአልና፥ ትቷቸዋልም፤ ያልሠራውንም ቤት በጉልበት ነጥቋል።
\s5
\v 20 በራሱ እርካታን ስለማያውቅ፤ የሚደሰትበትን አንድ ነገር ሊያስቀምጥ አይችልም።
\v 21 ሳያጠፋ የሚያስቀረው ነገር ስለማይኖር የሚዘልቅ ብልጽግና አይኖረውም።
\v 22 በሃብት ጠግቦ እያለ ይቸገራል፤ በድህነት ያሉ እጆች ሁሉ ይነሱበታል።
\s5
\v 23 ሆዱን ሊሞላ ሲዘጋጅ እግዚአብሔር ብርቱ ቍጣውን ይሰድበታል፥ እየበላም ሳለ ያዘንብበታል።
\v 24 ከብረት መሣርያ ይሸሻል፥ የናስ ቀስት ግን ይወጋዋል።
\v 25 በርግጥ ቀስቱም ከኋላ ይወጋዋል፤ የጫፉም ብልጭታ በጉበቱ በኩል ይወጣል፤ ፍርሃትም ይመጣበታል።
\s5
\v 26 ለከበረ ዕቃው ፍጹም ጥፋት ተዘጋጅቶለታል፤ ያልተራገበ እሳት ይበላዋል፤ በድንኳኑም የተረፈውን ይጨርሰዋል።
\v 27 ሰማያት ኃጢአቱን ይገልጡበታል፥ ምድርም ምስክር ሆና ትነሣበታለች።
\s5
\v 28 የቤቱም ባለጠግነት ይጠፋል፤ በእግዚአብሔር ቍጣ ቀን የቤቱን ዕቃ ጎርፍ ይወስድበታል።
\v 29 ይህም ከእግዚአብሔር ዘንድ የበደለኛ ሰው እድል ፈንታ፥ ከእግዚአብሔርም የተመደበለት ርስቱ ይህ ነው።
\s5
\c 21
\p
\v 1 ቀጥሎም ኢዮብ ሲመልስ እንዲህ አለ፦
\v 2 ንግግሬን በጥንቃቄ ስሙ፤ የምታጽናኑኝም እንደዚህ ይሁን።
\v 3 እንድናገር ፍቀዱልኝ፤ ከተናገርሁም በኋላ ተሳለቁ።
\s5
\v 4 ቅሬታዬን የማሰማው ሰው ላይ ነውን? ትዕግስት ባጣስ፤ አይገባኝምን?
\v 5 እስቲ ተመልከቱኝና ተደነቁ፤ አፋችሁንም በእጃችሁ ያዙ።
\v 6 እኔ ስቃዬን ባሰብሁ ቍጥር እጨነቃለሁ፥ በፍርሃትምሥጋዬ ይንቀጠቀጣል።
\s5
\v 7 ለምን ኃጢአተኞች በሕይወት እስከ እርጅና ይኖራሉ? ለምን በሃይልስ ይበረታሉ?
\v 8 ዘራቸው ከእነርሱ ጋር ተደላድለዋል፥ ልጆቻቸውም በአይናቸው ፊት ጸንተው ይኖራሉ።
\v 9 ቤቶቻቸው ያለስጋት ናቸው፥ የእግዚአብሔርም በትር በላያቸው የለም።
\s5
\v 10 ኮርማቸው ይወልዳል፥ ዘሩም በከንቱ አይወድቅም፤ ላማቸውም አትጨነግፍም በጊዜዋ ትወልዳለች፥ ።
\v 11 ሕፃናቶቻቸውን እንደ መንጋ ያሰማራሉ፥ ልጆቻቸውም ይቦርቃሉ።
\v 12 በከበሮና በክራር ይዘምራሉ፥ በእምቢልታም ሙዚቃ ይደሰታሉ።
\s5
\v 13 ዕድሜያቸውንም በብልጥግና ይፈጽማሉ፤ በጸጥታም ወደ ሲኦል ይወርዳሉ።
\v 14 እግዚአብሔርንም፦" ከእኛ ራቅ፤ የመንገድህን እውቀት አንፈልግም' ይሉታል።
\v 15 እናመልከው ዘንድ ሁሉን የሚችል አምላክ ማን ነው? ወደ እርሱ በመጸለይስ ምን ጥቅም ይገኛል? ይላሉ።
\s5
\v 16 እነሆ፥ ሀብታቸው በእጃቸው ውስጥ አይደለምን? ከኃጥአን ምክር ጋር ምንም አይነት ህብረት የለኝም። የኃጥአን መብራት የጠፋው፥
\v 17 መቅሠፍትም በላያቸው የመጣባቸው ስንት ጊዜ ነው ፥ እግዚአብሔርም በቍጣው መከራ የከፈላቸው መቼ ነው፥
\v 18 በነፋስ ፊት እንደ ገለባ፥ በዐውሎ ነፋስም እንደ ተወሰደ ትቢያ የሆኑ ስንት ጊዜ ነው?
\s5
\v 19 እናንተ፦ 'እግዚአብሔር የበደለኛውን ቅጣት ለልጆቹ ይጠብቃል' ብላችኋል። ጥፋቱን እንዲያው ቅጣቱን ራሱ ይክፈል።
\v 20 የገዛ ዓይኖቹ ጥፋቱን ይዩ፥ ሁሉን የሚችል አምላክን ቍጣ ራሱ ይጠጣ።
\v 21 ወራቶቹስ ካለቁ በኋላ፥ ከራሱ ሌላ ስለቤተሰቦቹ ምን ገዶት?
\s5
\v 22 በከፍታ ያሉትን ለሚፈርድ ለእግዚአብሔር ማን እውቀትን ሊያስተምረው ይችላል?
\v 23 አንድ ሰው በፍጹም ሰላምና ጤና ሲቀመጥ በሙሉ ብርታቱ ሳለ ይሞታል።
\v 24 በሰውነቱ ወተት ሞልቶአል፥ የአጥንቶቹም መቅን እርጥብና በጤንነት ናቸው።
\s5
\v 25 ሌላው ሰው ደግሞ መልካምን ነገር ፈጽሞ ሳይቀምስ፤ በተመረረች ነፍስ ይሞታል።
\v 26 በአፈር ውስጥ በአንድ ላይ ይጋደማሉ፥ ሁለቱንም ትል ይጨርሳቸዋል።
\s5
\v 27 አሳባችሁን፥ያሴራችሁብኝንም ክፉ ምክር አውቄዋለሁ።
\v 28 እናንተ፦ 'የልኡሉ ቤት የት አለ? ኃጢአተኛውም ሰው ይኖርበት የነበረ ድንኳን የት ነው?" ብላችኋል።
\s5
\v 29 መንገድ ተጓዦችን አልጠየቃችሁምን? ሊናገሩ የሚችሉትን ማስረጃ አታውቁምን?
\v 30 ኃጢአተኛው ከመቅሠፍት ቀን እንደ ተጠበቀ፥ ከቍጣው ቀን ዘወር እንደተደረገ።
\s5
\v 31 የሃጥያተኛውን መንገድ ፊት ለፊትl የሚቃወም ማን ነው? በሠራው ስራ የሚቀጣው ማን ነው?
\v 32 እርሱን ግን ወደ መቃብር ይሸከሙታል፥ ሰዎቹም መቃብሩን ይጠብቃሉ።
\v 33 የተቀበረበት አፈር እንኳ ይጣፍጥለታል፤ ሰዎች ሁሉ ይከተሉታል፥ እጅግ ብዙ ሕዝብም ከፊቱ ይሄዳል።
\s5
\v 34 መልሳችሁ ከውሸት በቀር ምንም ስለሌለበት፤ በከንቱ ነገር እንዴት ልታጽናኑኝ ትችላላችሁ?
\s5
\c 22
\p
\v 1 ቴማናዊውም ኤልፋዝ ሲመልስ እንዲህ አለ፦
\v 2 ሰው እግዚአብሔርን መጥቀም ይችላልን? ጥበበኛ ቢሆን እንኳ ይጠቅመዋልን?
\v 3 ጻድቅ መሆንህስ ሁሉን ለሚችለው አምላክ የሚጨምረው ደስታ አለን? መንገድህ ፍጹም ቀና ቢሆን የሚጠቅመው ነገር አለን?
\s5
\v 4 የሚገስጽህና ወደ ፍርድስ ስፍራ የሚያመጣ፥ እርሱን ስለፈራህ ነውን?
\v 5 በደልህ እጅግ የበዛ፣ ኃጢአትህም ፍጻሜ የሌለው አይደለምን?
\s5
\v 6 ያለምክንያት ከወንድሞችህን መያዣን ወስደሃል፥ ሰዎችን ልብሳቸውን ገፈህ እርቃናቸውን አስቀረሃቸው።
\v 7 ለዛሉም ሰዎች ውኃ አልሰጠሃቸውም፥ ከራብተኛ ሰዎችም እንጀራን ከልክለሃል።
\v 8 ምድርን የገዛህ ሃያል፤ ክቡር ሰው ብትሆንም።
\s5
\v 9 መበለቶን ባዶአቸውን ሰድደሃቸዋል አባት የሌላቸው ልጆችም ክንድ ተሰብሮአል።
\v 10 ስለዚህ ወጥመድ በዙሪያህ አለ፥ ድንገተኛ ፍርሃት ያናውጥሃል።
\v 11 እንዳታይም ጨለማ ሆነብህ፥ የጎርፍ ውሃም አሰጠመህ።
\s5
\v 12 እግዚአብሔር በሰማያት ከፍታ ላይ አይልምን? የዋክብትን ከፍታ ተመልከት ምን ያህል ከፍ ይላሉ!
\v 13 አንተም፦ 'እግዚአብሔር ምን ያውቃል? በድቅድቅ ጨለማ ሆኖ ሊፈርድ ይችላልን?
\v 14 እንዳያየን ጥቅጥቅ ደመና ጋርዶታል፤ በሰማይም ክበብ ላይ ይራመዳል' አልህ።
\s5
\v 15 እነዚያ ኃጢአተኞች የሄዱበትን፥ የቀድሞውን መንገድ አንተ ደግሞ ትደግመዋለህን?
\v 16 ጊዜያቸው ሳይደርስ ተነጠቁ፤ መሠረታቸውም እንደ ወንዝ ፈሳሽ ተወሰደ።
\v 17 እግዚአብሔርንም፦ “ከእኛ ዘንድ ራቅ ሁሉንም የሚችል አምላክ ምን ሊያደርግልን ይችላል?” አሉት።
\s5
\v 18 ነገር ግን እርሱ ቤታቸውን በመልካም ነገር ሞላ፤ የኃጥአን ምክር ከእኔ ይራቅ።
\v 19 ጻድቃን የነዚህን ፍጻሜ ያያሉ፥ ደስም ይላቸዋል፤ ንጹሐንም በንቀት እዲህ በማለት ይስቁባቸዋል።
\v 20 'በእርግጥ በእኛ ላይ የተነሱ ጠፍተዋል፥ ሃብታቸውንም እሳት በልቶታል።'
\s5
\v 21 አሁን ከእግዚአብሔር ጋር ተስማማ፥ ሰላምም ይኑርህ፤ በዚያም መንገድ መልካም ነገር ያገኝሃል።
\v 22 እለምንሃለሁ፥ ከእርሱ አፉ መመሪያ ተቀበል፥ በልብህም ቃሉን አኑር፤
\s5
\v 23 ሁሉን ወደሚችል አምላክ ብትመለስ፥ እንደገና ትሰራለህ፥ ኃጢአትንም ከድንኳንህ አርቀህ ብትጥል፥
\v 24 የከበረ ሃብትህን በአፈር ውስጥ፥ የኦፊርንም ወርቅ በጅረት ድንጋይ መካከል ብትጥል፥
\v 25 ሁሉን የሚችል አምላክ የከበረ ሃብትና የተመረጠ ብር ይሆንልሃል።
\s5
\v 26 በዚያን ጊዜ ሁሉን በሚችል አምላክ ደስ ይልሃል፥ ፊትህንም ወደ እግዚአብሔር ታነሣለህ።
\v 27 ወደ እርሱ ትጸልያለህ፥ እርሱም ይሰማሃል፤ ስእለትህንም ለእርሱ ትሰጣለህ።
\v 28 በማናቸውም ነገር አዋጅ ትናገራለህ፥ እርሱም ይጸናልሃል፤ ብርሃንም በመንገድህ ላይ ይበራል።
\s5
\v 29 እግዚአብሔር ትዕቢተኛን ሰው ያዋርዳል፤ ትሑቱንም ሰው ያድነዋል።
\v 30 ንጹሕ ያልሆነውን ሰው እንኳ፤ በእጅህ ንጽሕና በኩል ይታደገዋል።
\s5
\c 23
\p
\v 1 ኢዮብም ሲመልስ እንዲህ አለ፦
\v 2 ዛሬም ቢሆን የኅዘን አቤቱታዬ መራራ ነው፤ መከራዬም ማቃሰት ከምችለው በላይ ይከብዳል።
\s5
\v 3 ኦ! እርሱን ወዴት እንደማገኘው ምነው ባውቅ! እርሱ ወዳለበት ስፍራ በሔድሁ!
\v 4 ጉዳዬን በፊቱ በተገቢ ሁኔታ ባቀረብሁ፥ አፌንም ለሙግት ሞልቼ አዘጋጅ ነበር።
\v 5 የሚመልስልኝን ቃሎች አውቅ ነበር፥ የሚለኝንም በተረዳሁ ነበር።
\s5
\v 6 በኃይሉ ብዛት ከእኔ ጋር ይምዋገት ነበርን? እንኳን! ያደምጠኝ ነበር።
\v 7 ጻድቅ ሰው ከእርሱ ጋር በዚያ ይዋቀሳል፤ እንደዚህም በዳኛዬ በእርሱ ለዘላለም ነጻ እወጣ ነበር።
\s5
\v 8 ነገር ግን፥ ወደ ምስራቅ ብሄድ፥ በዚያ የለም፤ ወደ ምዕራብም ብሔድ ላየው አልቻልኩም፤
\v 9 ወደሚሠራበት ወደ ሰሜን ብሄድ አላየሁትም፤ ራሱን ወደሚሰውርበት በደቡብም፥ላየው አልቻልኩም፤
\s5
\v 10 ነገር ግን የምሄድበትን መንገድ ያውቃል፤ ከፈተነኝም በኋላ እንደ ወርቅ እወጣለሁ።
\v 11 እግሮቼ እርምጃውን በጽናት ተከተሉ፤ ውልፍት ሳልል መንገዱን ጠብቄአለሁ።
\v 12 ከከንፈሩም ትእዛዝ አላፈገፈግሁም፤ የአፉን ቃል በልቤ ሰውሬአለሁ።
\s5
\v 13 እርሱ ግን በአይነቱ ብቸኛ ነው፤ እርሱንስ ማን ሊመልሰው ይችላል? እርሱ የወደደውን ነገር ያደርጋል።
\v 14 በእኔ ላይ የተወሰነብኝን ይፈጽማል፤ እንደነዚህም አይነት ብዙ አለ።
\s5
\v 15 ስለዚህ በእርሱ ፊት ደነገጥሁ፤ ስለእርሱም ባሰብሁ ጊዜ እፈራዋለሁ።
\v 16 እግዚአብሔር ልቤን አድክሞታል፥ ሁሉንም የሚችል አምላክ አስደንግጦኛል።
\v 17 እንጂ ጨለማ ወይም ድቅድቁ ጨለማ ፊቴን ከመክደኑ የተነሣ አልጠፋሁም።
\s5
\c 24
\p
\v 1 ሁሉን ከሚችል አምላክ ሃጢያተኛ የሚፈረድበት ጊዜ ለምን አልተወሰነም? ለእርሱስ ታማኝ የሆኑት የፍርዱ ቀን እንደመጣ ለምን አያዩም?
\s5
\v 2 የድንበር ምልክትን የሚያፈርሱ ኅጢያተኛ ሰዎች አሉ፤ የሌሎችን መንጋ በግፍ ወስደው የሚያሰማሩ አመጸኞች አሉ።
\v 3 የድሀ አደጎችን አህያ ቀምተው ይነዳሉ ፤ የመበለቲቱንም በሬ በመያዣ ይወስዳሉ።
\v 4 ድሆችን ከመንገዳቸው ያስወጣሉ፤ የምድርም ችግረኞች ሁሉ ከእነርሱ ይሸሸጋሉ።
\s5
\v 5 እነዚህ ችግረኞች፥ በምድረ በዳ እንዳሉ የሜዳ አህዮች ወደ ስራቸው ይወጣሉ፥ ምግብን ፍለጋ በጥንቃቄ ይሄዳሉ፤ ምንአልባት ምድረ በዳው ለልጆቻቸው መብልን ይሰጣቸዋል።
\v 6 ድሆቹም በሌሎች ሰዎች በእርሻ ውስጥ በምሽት ያጭዳሉ፤ ከበደለኞችም መከር ወይንን ይቃርማሉ።
\v 7 ራቁታቸውን ያለ ልብስ ምሽቱን ሁሉ ይተኛሉ፥ በብርድም ጊዜ መጐናጸፊያ የላቸውም።
\s5
\v 8 ከተራሮች በሚወርድ ዝናብ ይረጥባሉ፤ መጠለያም ስለሌላቸው ከቋጥኝ ስር ይጋደማሉ።
\v 9 ድሀ አደጉን ህጻን ከእናቱ ጡት የሚነጥሉ ኅጢያተኞች አሉ፤ በደለኞችም ልጆችን በመያዣነት ይወስዳሉ።
\v 10 ነገር ግን ድሃዎቹ ያለ ልብስ ራቁታቸውን ይሄዳሉ፤ ተርበውም ቢሆን የሌሎችን እህል ነዶ ይሸከማሉ፤
\s5
\v 11 ድሃ ሰዎች በኁጢኣን አጥር ውስጥ ዘይት ይሰራሉ፤ ወይንም ይጠምቃሉ፥ ነገር ግን እነርሱ በጥም ይሰቃያሉ።
\v 12 በከተማ ውስጥ ሰዎች ያቃስታሉ ፤ የቆሰሉም ለእርዳታ ይጮኻሉ፤ እግዚአብሔር ግን ልመናቸውን አይመለከትም።
\s5
\v 13 እነዚህ ኅጢያተኞች በብርሃን ላይ ያምጻሉ፤ መንገዱን አያውቁም፥ በጎዳናውም አይጸኑም።
\v 14 ነፍሰ ገዳዩም ማልዶ ይነሣል፤ ችግረኞችንና ድሆችን ይገድላል፤ በሌሊትም እንደ ሌባ ነው።
\s5
\v 15 የአመንዝራም ዓይን ድግዝግዝታን ይጠብቃል። "የማንም ዓይን አያየኝም" ይላል፥ ፊቱንም እንደሌላ ይለውጣል።
\v 16 አመጸኞች ቤቶችን በጨለማ ይሰረስራሉ፤ በቀን ግን ይሸሸጋሉ፤ ለብርሃንም ግድ የላቸውም።
\v 17 ለእነርሱ ጥዋት እንደ ድቅድቅ ጨለማ ነውና፤ ከድቅድቅ ጨለማ ሽብር ጋርም ተወዳጅተዋል።
\s5
\v 18 ይሁን እንጂ በውኃ ላይ እንዳለ አረፋ በርረው ይጠፋሉ፤ የርስት እድል ፈንታቸውም የተረገመ ነው፤ በወይን ቦታቸውም ላይ ለመስራት ማንም አይሄድም።
\v 19 ድርቅና ሙቀት በረዶውን እንደሚያቀልጥ፤ እንዲሁ ሲኦል ሃጢያተኞችን ታጠፋለች።
\s5
\v 20 የተሸከመችው ማኅፀን ትረሳዋለች፤ ትልም በደስታ ይበላዋል፤ ዳግመኛም አይታሰብም፤ በዚህ ሁኔታ ዓመጸኝነት እንደ ዛፍ ይሰበራል።
\v 21 የማትወልደውን መካኒቱን ሃጥያተኛው ይጎዳታል፤ ለመበለቲቱም ምንም አይነት በጎነት አያደርግም።
\s5
\v 22 ነገር ግን እግዚአብሔር በኃይሉ ኃያላንን ጎትቶ ይጥላል፤ እርሱም ይቆማል በሕይወቱ ግን አይጠነክርም።
\v 23 እግዚአብሔር በደኅንነት እንዳሉ እንዲያስቡ ይፈቅዳል፥ በዚያም ደስ ይላቸዋል፤ ነገር ግን ዓይኖቹ በመንገዳቸው ላይ ናቸው።
\s5
\v 24 እነዚህ ሰዎች ለጥቂት ጊዜ ከፍ ከፍ ይላሉ፤ በርግጥ ግን፥ ይዋረዳሉ፤ እንደ ሌሎች ሁሉ ተሰብስበው፤ እንደ እሸት ራስ ጫፍ ይቈረጣሉ።
\v 25 እንደዚህስ ባይሆን ሐሰተኛ የሚያደርገኝ፥ ንግግሬንም ከንቱ የሚያደርግ ማን ነው?
\s5
\c 25
\p
\v 1 ሹሐዊው በልዳዶስ ሲመልስ እንዲህ አለ፦
\v 2 ገዢነትና መፈራት የእርሱ ናቸው፤ በሰማይ ከፍታውም ስርአትን ያደርጋል።
\v 3 በውኑ ለሠራዊቶቹ ቍጥር ፍጻሜ አላቸውን? ብርሃኑስ የማይወጣው በማን ላይ ነው?
\s5
\v 4 እንግዲህ ሰው በእግዚአብሔር ፊት እንዴት ጻድቅ ይሆናል፥ ከሴትስ የተወለደ እንዴት ንጹሕና በእርሱ ዘንድ ተቀባይነት ይኖረዋል?
\v 5 ጨረቃ እንኳ ለእርሱ ብሩህ አይደለም፥ ከዋክብትም በፊቱ ንጹሐን አይደሉም።
\v 6 ይልቁንስ ትል የሆነ ሰው፥ የሰው ልጅ ምንኛ ያንስ!
\s5
\c 26
\p
\v 1 ኢዮብም ሲመልስ እንዲህ አለ፦
\v 2 ኃይል የሌለውን እንዴት ረዳኸው! ብርታት የሌለውን ክንድ ምንኛ አዳንኸው!
\v 3 ጥበብስ የሌለውን እንዴት መከርኸው! መልካም እውቀትንስ ምንኛ ገለጥህለት!
\v 4 እነዚህን ቃሎች በማን እርዳታ ተናገርህ? ስትናገርስ ከአንተ የወጣው መንፈስ የማን ይሆን?
\s5
\v 5 በልዳዶ ስ መለሰ “ሙታን ሰዎች ከውሃዎች በታች የሚኖሩ፥ጥላዎ ቻቸውም ይንቀጠቀጣሉ።
\v 6 ሲኦል በእግዚአብሔር ፊቱ ራቁትዋን ናት፥ ጥፋትም ቢሆን ራሱን መሸፈኛ የለውም።
\s5
\v 7 ሰሜንን በባዶ ሕዋ ውስጥ ዘረጋው፥ ምድርንም እንዲያው ባዶ ላይ አንጠለጠላት።
\v 8 ውሃዎችን በደመናዎች ውስጥ ያስራል፥ ደመናውም ከታች አልተቀደደችም።
\s5
\v 9 የጨረቃን ፊት ይጋርዳል፥ ደመናውንም በላይዋ ይዘረጋበታል።
\v 10 በብርሃንና በጨለማ መካከል እንዳለ መስመር፥ በውሃዎች ላይ ድንበርን አደረገ።
\s5
\v 11 የሰማይ አዕማድ ተንቀጠቀጡ፥ ከተግሣጹም የተነሣ ደነገጡ።
\v 12 በኃይሉ ባሕርን ጸጥ አደረገ፥ በማስተዋሉም ረዓብን መታ።
\s5
\v 13 በእስትንፋሱ የሰማያትን ማዕበል ያነጻል፤ ሰማያትም ውበትን አገኙ፥ እጁም በራሪይቱን እባብ ወጋች።
\v 14 እነዚህም ገና የመንገዱ መጀመሪያ ብቻ ናቸው፤ ከእርሱ የሰማነው ይህ ነገር ምንኛ ጥቂት ነው! የኃይሉን ነጐድጓድ ሊረዳ የሚችል ማን ነው?
\s5
\c 27
\p
\v 1 ኢዮብም መናገሩን ቀጠለ እንዲህም አለ፦
\v 2 ፍርዴን ያስወገደ ሕያው እግዚአብሔርን! ነፍሴንም መራራ ያደረገ ሁሉን የሚችል አምላክን!
\v 3 ነፍሴ በእኔ ውስጥ፥ የእግዚአብሔርም እስትንፋስ በአፍንጫዬ እስካለ ድረስ፥
\s5
\v 4 በርግጥ ከንፈሬ ኃጢአትን አይናገርም፥ ምላሴም ሽንገላን አያወራም።
\v 5 እናንተን ትክክል አድርጎ መቀበል ከእኔ ይራቅ፤ እስክሞት ድረስ ትክክለኛነቴን በፍጹም አልጥልም።
\s5
\v 6 ጽድቄን አጥብቄ እይዛለሁ እርሱንም አለቅም፤ ከኖርኩባቸው ቀኖቼ ስለ አንዱም ህሊናዬ አይወቅሰኝም።
\v 7 ጠላቴ እንደ በደለኛ ሰው ይሁን፥ በእኔ ላይም የሚነሣ እንደ ኃጢአተኛ ይሁን።
\s5
\v 8 እግዚአብሔር ባጠፋውና ነፍሱን በለየ ጊዜ፥ አምላክ የሌለው ሰው ተስፋው ምንድር ነው?
\v 9 መከራ በመጣበት ጊዜ፥ እግዚአብሔር ጩኸቱን ይሰማልን?
\v 10 ሁሉንስ በሚችል አምላክ ደስ ይለዋልን? እግዚአብሔርንስ ሁልጊዜ ይጠራልን?
\s5
\v 11 ስለ እግዚአብሔር እጅ አስተምራችኋለሁ፤ የሁሉን ቻይ አምላክን ሃሳብ አልሸሽግም።
\v 12 እናንተ ሁላችሁ ይህንን አይታችሁ፤ ለምን ይህን ሁሉ ከንቱ ነገር ተናገራችሁ?
\s5
\v 13 ይህ እግዚአብሔር ለክፉ ሰው ያቆየው እድል ፈንታ፥ ግፈኛም ሁሉን ከሚችል አምላክ የሚቀበለው ርስት ነው፤
\v 14 ልጆቹ ቢበዙ ለሰይፍ ይዳረጋሉ፤ ዘሩም በቂ እንጀራን አያገኝም።
\s5
\v 15 የተረፉለትም በመቅሰፍት ምክንያት ይቀበራሉ፤ መበለቶቻቸውም አያለቅሱላቸውም።
\v 16 አመጸኛ ሰው ብርን እንደ አፈር ቢከምር፥ ልብስንም እንደ ሸክላ ቢያከማች፥
\v 17 እርሱ ያከማቸውን ልብስ፥ ጻድቃን ይለብሱታል፤ ብሩንም ንጹሐን ሰዎች ይከፋፈሉታል።
\s5
\v 18 ቤቱን እንደ ሸረሪት ይሠራል፥ ጠባቂም እንደሚቀልሰው ጎጆ ይመስላል።
\v 19 ባለጠጋ ሆኖ ይተኛል፥ ነገር ግን አይዘልቅበትም፤ ዓይኑን በከፈተ ጊዜ፥ ሃብቱ ሁሉ የለም።
\s5
\v 20 ድንጋጤ እንደ ጐርፍ ያገኘዋል፤ ማዕበልም በሌሊት ይወስደዋል።
\v 21 የምሥራቅ ነፋስ ይወስደዋል፥ እርሱም ይለቃል፤ ከስፍራውም ይጠርገዋል።
\s5
\v 22 ከነፋሱ ሊያመልጥ ይሞክራል፥ ነገርግን ሳያቋርጥ እየተወረወረ ይደርስበታል።
\v 23 በመሳለቅም እጁን ያጨበጭብበታል፤ በፉጨትም ከስፍራው ያስወጣዋል።
\s5
\c 28
\p
\v 1 በእርግጥ ብር የሚወጣበት፥ ወርቅም የሚነጠርበት ስፍራ አለ።
\v 2 ብረት ከመሬት ውስጥ ይወሰዳል፥ መዳብም ከድንጋይ ቀልጦ ይወጣል።
\s5
\v 3 ሰው የጨለማ መጨረሻ ድረስ ይወርዳል፤ በጨለማና ባስፈሪ ስፍራ ውድ ድንጋይ ይፈላልጋል።
\v 4 ሰው ከሚኖርበት ርቆ መውረጃ ይቈፍራሉ፤ ከሁሉ እግር በተረሳ ስፍራ፥ ከሰዎችም ሩቅ ሆኖ እየተንጠላጠለ ይወዛወዛል።
\s5
\v 5 ከምድር እንጀራ ቢገኝም፤ ከታችኛው ክፍል ግን እሳት ይገላበጣል።
\v 6 ድንጋይዋ ሰንፔር የሚገኝበት ስፍራ ነው፥ አፈሯም ወርቅን ይዟል።
\s5
\v 7 ያን መንገድ ጭልፊት አያውቀውም፥ የአሞራም ዓይን አላየውም።
\v 8 ኲሩ እንስሶች ይህን መንገድ አልሄዱበትም፥ አስፈሪው አንበሳም በዚያ አላለፈም።
\s5
\v 9 ሰው ቡላድ ድንጋይ ላይ እጁን ይጭናል፥ ተራራዎችንም ከሥራቸው ይገለብጣል።
\v 10 በድንጋይ ውስጥ መንዶልዶያን ፈልፍሎ ይሰራል፤ በዚያም ዓይኑ የከበሩ ነገሮችን ሁሉ ያያል።
\v 11 ፈሳሹም እንዳያልፉ ይገድባል፤ በዚያም የተሰወሩትን ወደ ብርሃን ያወጣቸዋል።
\s5
\v 12 ጥበብ ግን የት ትገኛለች? የማስተዋልስ ስፍራ ወዴት ነው?
\v 13 ሰው ዋጋዋን አላወቀም በሕያዋንም ምድር አትገኝም።
\v 14 ከምድር ጥልቅ ያለ ውሃ፦ "በእኔ ውስጥ የለችም' አለ፤ ባሕርም፦ "እኔ ጋር የለችም" አለ።
\s5
\v 15 ወርቅ ሊገዛት አይችልም፥ ዋጋዋም በብር አይመዘንም።
\v 16 በኦፊር ወርቅ፥ በከበረም መረግድና በሰንፔር አትገመትም።
\v 17 ወርቅና ብርሌ አይተካከሉአትም፥ በነጠረ ወርቅ ጌጥም አትለወጥም።
\s5
\v 18 ዛጐልና አልማዝ ከቁጥር አይገቡም። በርግጥ የጥበብ ዋጋ ከቀይ ዕንቍ ይበልጣል።
\v 19 የኢትዮጵያ ቶጳዝዮን አይስተካከላትም፥ በንጹህ ወርቅም አትገመትም።
\s5
\v 20 ታዲያ ጥበብ ከወዴት ትመጣለች? የማስተዋልስ ስፍራ የት ነው?
\v 21 ጥበብ ሕይወት ካላቸው ነገሮች ሁሉ ዓይን ተሰውራለች፥ ከሰማይ ወፎችም ተሸሽጋለች።
\v 22 ጥፋትና ሞት፦ “ወሬዋን ብቻ በጆሮቻችን ሰምተናል” አሉ።
\s5
\v 23 እግዚአብሔር ወደ እርሷ የሚወስደውን መንገድ ያስተውላል፥ስፍራዋንም ያውቃል።
\v 24 ምክንያቱም እርሱ የምድርን ዳርቻ፥ ከሰማይም በታች ያለውን ሁሉ ያያል።
\v 25 እርሱ አስቀድሞ ለነፋስ ሃይል መጠንን አደረገ፥ ውኆችንም በስፍር ሰፈረ፥
\s5
\v 26 እርሱ ለዝናብ ሥርዓትን፥ ለነጐድጓድ መብረቅም መንገድን አደረገ፥
\v 27 በዚያን ጊዜ ጥበብን አያት፥ ገለጣትም አጸናት፥ በርግጥም መረመራት።
\v 28 ለሰዎችም፦ እነሆ፥ “እግዚአብሔርን መፍራት ጥበብ ነው፤ ከክፋትም መራቅ ማስተዋል ነው” አለ።
\s5
\c 29
\p
\v 1 ኢዮብም መናገሩን ቀጠለ፥ እንዲህም አለ፦
\v 2 እግዚአብሔር ይጠብቀኝ እንደ ነበረው ጊዜ፥ እንዳለፉት ወራት ምነው በሆንሁ!
\v 3 መብራቱ በራሴ ላይ እንደበራበት ወቅት፥ በጨለማ ውስጥ በብርሃኑ አልፌ እንደሄድሁበት ጊዜ፥
\s5
\v 4 ቀኖቼ ወደ ሙላታቸው በደረሱ ጊዜ፥ የእግዚአብሔር ወዳጅነት በድንኳኔ በነበረ ጊዜ፥
\v 5 ሁሉን የሚችል አምላክ ገና ከእኔ ጋር በነበረ ጊዜ፥ ልጆቼም በዙሪያዬ እያሉ፥
\v 6 መንገዴ በቅቤ ይታጠብ በነበረ ጊዜ፥ ድንጋዩ የዘይት ፈሳሽ ያፈስስልኝ በነበረ ጊዜ።
\s5
\v 7 ወደ ከተማው በር በወጣሁ ጊዜ፥ በአደባባዩ መሃል ወንበሬ ላይ በተቀመጥሁ ጊዜ፥
\v 8 ወጣቶች አይተው በአክብሮት ገለል አሉ፥ ሽማግሌዎችም ተነሥተው ቆሙ።
\s5
\v 9 በመጣሁ ጊዜ ልኡላን ከመናገር ይቆጠባሉ፥ እጃቸውንም በአፋቸው ላይ ይጭኑ ነበር።
\v 10 የብልሆች ድምፅ ጸጥ ይል፤ ምላሳቸውም በላንቃቸው ተጣበቀች።
\s5
\v 11 በጆሮአቸው ከሰሙኝ በኋላ ይባርኩኝ ነበር፥` በአይናቸው ዓይተው ያሞግሱኝና ይመሰክሩልኝ ነበር፤
\v 12 ምክንያቱም የሚጮኸውን ችግረኛ፥ ድሀ አደጉንና ረዳት የሌላቸውን አድን ነበረና።
\v 13 ሊጠፋ የቀረበ በረከት ወደ እኔ ይመጣል፤ ባል የሞተባትንም ሴት ልብ በደስታ እንድትዘምር አደርግ ነበርና።
\s5
\v 14 ጽድቅን ለበስሁ እርስዋም ለበሰችኝ፤ ፍትሃዊነቴም እንደ መጐናጸፊያዬና ጥምጣሜ ነበረ።
\v 15 ለአይነ ስውራን ዓይናቸው፥ መራመድ ለማይችሉም ሰዎች እግር ነበርሁ።
\v 16 ለችግረኞች አባት ነበርሁ፤ የማላውቀውንም ሰው ሙግት እመረምር ነበር።
\s5
\v 17 የኃጢአተኛውን መንጋጋ ሰበርሁ፥ የያዘውንም ከጥርሱ ውስጥ አስጣልሁ።
\v 18 እንዲህም አልሁ፦ “በጎጆዬ ሆኜ እሞታለሁ፥ ቀኖቼን እንደ አሸዋ አበዛለሁ፤
\v 19 ሥሮቼ ወደ ውኃ ይሰራጫሉ፥ ጠልም ምሽቱን ሁሉ በቅርንጫፎቼ ላይ ያድራል፤
\s5
\v 20 በእኔ ዘንድ ያለው ክብር ሁልጊዜ ትኩስ ነው፥ በእጄ ያለው የብርታቴ ቀስት አዲስ ነው።
\v 21 ሰዎች እኔን ለመስማት በትዕግሥት ተጠባበቁ፥ ምክሬንም ለማዳመጥ በጸጥታ ተቀመጡ።
\v 22 ንግግሬንም ከጨረስኩ በኋላ መልሰው አልተናገሩም፤ ቃሎቼም በላያቸው እንደ ውሃ ተንጠባጠበ።
\s5
\v 23 ዝናብን እንደሚጠብቁ ሁልጊዜ ይጠብቁኛል፤ የበልግ ዝናብን እንደሚሹት፥ ከቃሎቼ ለመጠጣት አፋቸውን ከፈቱ ።
\v 24 እነርሱ ባልጠበቁተ ጊዜ ሳቅሁላቸው፤ የፊቴንም ብርሃን ቸል አላሉትም።
\s5
\v 25 መንገድን እመርጥላቸውና አለቃቸው ሆኜ እቀመጣለሁ፤ ኅዘነተኞችን በቀብር ጊዜ እንደሚያጽናና ሰው፥ በሠራዊቱም መካከል እንዳለ ንጉሥ በመካከላቸው ኖርሁ።
\s5
\c 30
\p
\v 1 አሁን ግን በዕድሜ ከእኔ የሚያንሱ፥ አባቶቻቸውን ከመንጋዬ ጠባቂ ውሾች ጎን እንዳይሰሩ ልከለክላቸው የምችል የነበሩ እነዚህ ወጣቶች፥ በእኔ ላይ ተሳለቁብኝ።
\v 2 በርግጥ የአባቶቻቸው ክንድ ጥንካሬ ምን ሊፈይድልኝ ይችል ነበር? የጉልምስናቸው ጥንካሬ ጠፍቶባቸው ነበርና።
\v 3 በድህነትና በራብ የመነመኑ ናቸው፤ በደረቅ መሬት በምድረ በዳ ጨለማና ጥፋት ይሰቃያሉ።
\s5
\v 4 ከቍጥቋጦ አጠገብ ያለውን ጨው ጨው የሚሉትን ቅጠሎች ይለቅማሉ፤ የክትክታ ሥራሥር ምግባቸው ነበር።
\v 5 ሌባን እየተከታተሉ እንደሚጮኹበት፤ ከሚጮኹባቸው ሰዎች ተለይተው ተሰደዱ።
\v 6 በወንዝ ሸለቆ በምድር ጕድጓድና በድንጋይም ዋሻ ውስጥ ይኖራሩ ነበር።
\s5
\v 7 በቍጥቋጦ መካከል እንደ አህያ ይጮኻሉ፤ ከቁጥቋጦ በታች በጋራ ተሰብስበዋል።
\v 8 በርግጥ የሰነፎችና ዋጋ የሌላቸው ሰዎች ልጆች ናቸው፤ እየተገረፉ ከምድሪቱ ተባረዋል።
\s5
\v 9 አሁን ግን ለልጆቻቸው የስላቅ ዘፈን ሆንኩላቸው፤ በርግጥም የነሱ መቀለጃ ሆኛለሁ።
\v 10 ተጸየፉኝ፥ ከእኔም ርቀው ይቆማሉ፤ ፊቴም ላይ መትፋትን አያቆሙም።
\v 11 እግዚአብሔር የቀስቴን መወጠሪያ አላልቶብኛል፥ መከራም አሳይቶኛል፤ እነርሱም በፊቴ ይሉኝታ የላቸውም።
\s5
\v 12 በቀኜ በኩል ዱርዬዎች ተነሥተዋል፥ ያሳድዱኛል፤ ለእግሬም የጥፋትን ወጥመድ ያደርጋሉ።
\v 13 መንገዴን ያበላሻሉ፤ ከልካይ እንደሌላቸው ሰዎች ጥፋትን ገፍተው ያመጡብኛል።
\s5
\v 14 በሰፊ ፍራሽ ቀዳዳ እንደሚመጣ ሰራዊት ይመጡብኛል፤ በጥፋት ላይ ተንከባልለው መጡብኝ።
\v 15 ድንጋጤ በላዬ መጥቶብኛል፥ ክብሬም በነፋስ ያሳደዱት ያክል በነነ፤ ብልጥግናዬም እንደ ደመና ተበተፈ።
\s5
\v 16 አሁንም ነፍሴ በውስጤ ፈሰሰች፤ የብዙ ቀናት መከራም ያዘኝ።
\v 17 በሌሊት አጥንቶቼ በውስጤ ተወጉ፥ የሚያሰቃየኝ ህመም ፋታ አይሰጠኝም።
\s5
\v 18 ከእግዚአብሔር ታላቅ ኃይል የተነሣ ልብሴ ተያዘ፥ እንደ ቀሚስ መቀነት ተጠቀለለብኝ።
\v 19 እርሱ ጭቃ ውስጥ ወረወረኝ፥ አፈርና አመድም መሰልሁ።
\s5
\v 20 ወደ አንተ ጮኽሁ እግዚአብሔር፥ አንተም አልመለስህልኝም ቆምሁኝ፥ አልተመለከትኸኝም።
\v 21 ተለወጥህብኝ ፤ ጨካኝም ሆንህብኝ፤ በእጅህም ሃይል አሳደድኸኝ።
\s5
\v 22 በነፋስ አነሣኸኝ፥ በላዩም አስቀምጠኸ ወሰድኸኝም፤ በማእበልም ውስጥ አቀለጥኸኝ።
\v 23 ለሕያዋን ሁሉ ወደተወሰነው ቤት፤ ወደ ሞት እንደምትወስደኝ አውቄአለሁ።
\s5
\v 24 ነገር ግን ሰው ሲወድቅ እጁን እርዳታ ፍለጋ አይዘረጋምን? በችግር ውስጥ ያለ ማንም ለእርዳታ አይጮኽምን?
\v 25 በችግር ላለ ሰው አላለቀስሁምን? ለድሆችስ ነፍሴ አላዘነችምን?
\v 26 መልካምን በተጠባበቅሁ ጊዜ ክፉ መጣብኝ፤ ብርሃንን ስጠባበቅ፥ ጨለማ መጣ።
\s5
\v 27 ልቤ ታወከ፥ እረፍትም አላገኘም የስቃይም ቀናቶች መጡብኝ።
\v 28 ያለ ፀሐይ በጨለመ ሰማይ በትካዜ ሄድሁ፤ በጉባኤም መካከል ቆሜ ለእርዳታ እጮኻለሁ።
\v 29 ለቀበሮ ወንድም፥ ለሰጐንም ጓደኛ ሆንሁ።
\s5
\v 30 ቆዳዬ ጠቈረ፥ ከላዬም ተቀርፎ ወደቀ፤ አጥንቶቼም በትኵሳት ተቃጠሉ።
\v 31 ስለዚህ በገናዬ ለኀዘን እንጉርጉሮ ፥ እምቢልታዬም ለለቅሶ ጩኸት ተቃኙ።
\s5
\c 31
\p
\v 1 ከዓይኔ ጋር ቃል ኪዳን ስለገባሁ፤ እንዴት ድንግሊቱን በምኞት እመለከታለሁ?
\v 2 ከላይ ከእግዚአብሔር የሆነው እድል ፈንታ ፥ ሁሉንም የሚችል አምላክስ ርስት ከአርያም ምንድን ነው?
\s5
\v 3 መዓት ለኃጢአተኛ፥ ጥፋትም ክፋትን ለሚያደርጉ ነው ብዬ አስብ ነበር።
\v 4 እግዚአብሔር መንገዴን አያይምን? እርምጃዬንስ ሁሉ አይቈጥርምን?
\s5
\v 5 በሐሰት ሄጄ እንደ ሆነ እግሬም ለሽንገላ ቸኵሎ እንደ ሆነ፥
\v 6 በእውነተኛ ሚዛን ልመዘን፥ እግዚአብሔርም ትክክለኛቴን ይወቅ።
\s5
\v 7 እርምጃዬ ከትክክለኛው መንገድ ፈቀቅ ብሎ፥ ልቤም የዓይኔን ምኞት ተከትሎ፥ ነውርም በእጄ ላይ ተጣብቆ እንደ ሆነ፥
\v 8 እኔ ልዝራ፥ ሌላ ሰውም ይብላው፤ መከሩም ከእርሻዬ ላይ ይነቀል።
\s5
\v 9 ልቤ ወደ ሌላይቱ ሴት ጐምጅቶ እንደ ሆነ፥ የጎረቤቴን ሚስት ለማየት ደጃፉ አድብቼ እንደ ሆነ፥
\v 10 ሚስቴ ለሌላ ሰው እህል ታዘጋጅ፥ ሌሎችም ከእርስዋ ጋር ይተኙ።
\s5
\v 11 ይህ ክፉ ወንጀል ነውና፥ በፈራጆችም ሊቀጣ የሚገባው በደል ነውና፤
\v 12 ይህ እስከ ሲኦል ድረስ የሚበላ እሳት፥ ያመረትኩትን ሁሉ የሚያቃጥል ነውና።
\s5
\v 13 ወንድ ወይም ሴት ባሪያዎቼ ከእኔ ጋር በተምዋገቱ ጊዜ፥ ሙግታቸውን በትክክል ሳላይ ቀርቼ እንደ ሆነ፥
\v 14 እግዚአብሔር ሊከሰኝ በተነሣ ጊዜ ምን አደርጋለሁ? ሊፈርደኝም በመጣ ጊዜ እንዴት እመልስለታለሁ?
\v 15 እኔን በማኅፀን የሰራኝ እነርሱንስ የፈጠረ አይደለምን? በማኅፀንስ ውስጥ ሁላችንን የሠራን አንድ አይደለምን?
\s5
\v 16 ድሀዎችን ከፍላጎታቸው ከልክዬ፥ የመበለቲቱንም ዓይን በለቅሶ አጨልሜ እንደ ሆነ፥
\v 17 እንጀራዬን ለብቻዬ በልቼ እንደ ሆነ፥ አባት የሌላቸውንም ከእርሱ እንዳይበሉ ከልክዬ እንደ ሆነ፤
\v 18 ይልቁን እርሱ ከታናሽነቴ ጀምሬ እንደ አባቱ ሆኜ ከእኔ ጋር አሳድጌው ነበር፥ እናቱንም ከእናቴ ማኅፀን ጀምሬ መራኋት፤
\s5
\v 19 አንድ ሰው የሚለብሰው አጥቶ ሲጠፋ፥ ወይም ድሀ ያለ ልብስ ሲሆን እንዲያው አይቼ እንደ ሆነ፥
\v 20 በበጎቼም ጠጕር ያልሞቀና፥ በልቡ ያልባረከኝ እንደ ሆነ፤
\v 21 በከተማው በር ረዳት ስላለኝ፥ አባት በሌላቸው ላይ እጄን አንሥቼ እንደ ሆነ፥
\s5
\v 22 ትከሻዬ ከመጋጠሚያው ይውደቅ፥ ክንዴም ከመገናኛው ይሰበር።
\v 23 ከእግዚአብሔር የሆነ ቁጣ ለእኔ አስደንጋጭ ነውና ከግርማውም የተነሳ እነዚህን ነገሮች ማድረግ አልችልም።
\s5
\v 24 ወርቅን ተስፋዬ አድርጌ፥ ጥሩውንም ወርቅ”በአንተ እታመናለሁ“ ብዬ እንደ ሆነ፤
\v 25 ሀብቴ ስለ በዛ፥ እጄም ብዙ ስላከማቸ ደስ ብሎኝ እንደ ሆነ፤
\s5
\v 26 ፀሐይ ሲበራ ተመልክቼ፥ ጨረቃ በድምቀት ስትሄድ አይቼ፥
\v 27 ልቤ እነርሱን ለማምለክ በስውር ተስቦ፥ አፌም እጄን ስሞ እንደ ሆነ፤
\v 28 በላይ ያለውን እግዚአብሔርን መካድ ነውና ይህም ዳኞች ሊቀጡት የሚገባ ወንጀል በሆነ ነበር።
\s5
\v 29 በሚጠላኝ በማንም መጥፋት ደስ ብሎኝ ወይም ክፉ ነገር በሆነበት ጊዜ ራሴን አስደስቼው እንደ ሆነ፤
\v 30 ለነፍሱ እርግማንን በመናገር፥ አንደበቴ ኃጢአት እንዲሰራ በርግጥ አልፈቀድኩለትም፤
\s5
\v 31 በድንኳኔ የሚኖሩ ሰዎች፦ “ከኢዪብ ማዕድ ያልጠገበ ማን ይገኛል?” ብለው ካልተናገሩ፤
\v 32 መጻተኛው በከተማ ጎዳና እንዳያድርም፥ ሁልጊዜ ደጄን ለመንገደኛ እከፍት ነበር፤
\s5
\v 33 በደሌንም በብብቴ በመሸሸግ ኃጢአቴን እንደ ሰዉ ሁሉ ደብቄ እንደ ሆነ፤
\v 34 የሕዝብን ብዛት ከመፍራቴ የተነሳ፥ የዘመዶቼም ንቀት አስደንግጦኝ፥ ዝም ብዬ ከቤቴ ሳልወጣ ቀርቼ እንደ ሆነ፤
\s5
\v 35 ኦ የሚያዳምጠኝ አንድ ሰው ምነው በኖረኝ! ይኸው የእጄ ፊርማ ምልክት፤ ሁሉን የሚችል አምላክ ይመልስልኝ! ባላጋራዬ የጻፈው የክስ ጽሑፍ ምነው በተገኘልኝ!
\v 36 በግልጽ ትከሻዬ ላይ አድርጌ እሸከመው ነበር፥ እንደ አክሊልም ራሴ ላይ አስቀምጠው ነበር።
\v 37 የእርምጃዎቼን ቍጥር በግልጽ አስታውቀው፥ እንደ ተማመነ አለቃም ፊትለፊቱ እወጣ ነበር።
\s5
\v 38 የእርሻዬ መሬት በእኔ ላይ ጮሆ እንደ ሆነ፥ ትልሞቹም አብረው አልቅሰው እንደ ሆነ፤
\v 39 የምርቱን ዋጋ ሳልከፍል በልቼ፥ የባለቤቶቹንም ነፍስ አሳዝኜ እንደ ሆነ፥
\v 40 በስንዴ ፋንታ እሾኸ፥ በገብስም ፋንታ አረም ይብቀልበት።“ የኢዮብም ንግግር ተፈጸመ።
\s5
\c 32
\p
\v 1 ኢዮብም ራሱን ጻድቅ አድርጎ ስላስቀመጠ እነዚያ ሦስቱ ሰዎች ምላሽ መስጠት አለብህ።
\v 2 ከራም ቤተሰብ የሆነ የቡዛዊው የባርክኤል ልጅ ኤሊሁ እጅግ ተቆጣ፤ ከእግዚአብሔር ይልቅ ራሱን ስላጸደቀ ኢዮብን ተቈጣው።
\s5
\v 3 ደግሞም በኢዮብ ፈረዱበት እንጂ የሚገባ መልስ ስላልሰጡት በሦስቱ ጓደኞቹ ላይ ተቈጣ።
\v 4 ከእርሱ ይልቅ ሰዎቹ ሽማግሌዎች ስለነበሩ ኤሊሁ ከኢዮብ ጋር ለመነጋገር ተራውን ይጠብቅ ነበር።
\v 5 ቢሆንም ግን ኤሊሁም በእነዚህ በሦስቱ ሰዎች አፍ መልስ እንደሌለ ሲያይ በጣም ተቆጣ።
\s5
\v 6 ቡዛዊውም የባርክኤል ልጅ ኤሊሁ መናገር ሲጀምር እንዲህም አለ፦ እኔ በዕድሜ ወጣት ነኝ፥ እናንተም ሽማግሌዎች ናችሁ፤ ስለዚህም ሰጋሁ፤ እውቀቴን እንዳልናገር ራሴን ገታሁ።
\v 7 እንደዚህም አልሁ፦ የቀናት ርዝመት ንግግርን፥ የዓመታትም ብዛት ጥበብን ሊያስተማሩ ይገባ ነበር።
\s5
\v 8 ነገር ግን በሰው ውስጥ መንፈስ አለ፤ የሁሉን ቻዩ እስትንፋስ ማስተዋልን ይሰጠዋል።
\v 9 ታላላቅ ሰዎች በመሆናቸው ብቻ ጥበበኞች አይደሉም፣ በእድሜ የገፉ ስለሆኑ ብቻም ፍትሕን አያስተውሉም።
\v 10 ስለዚህ እንዲህ እላችኋለሁ፥ 'አድምጡኝ፤ እኔም ደግሞ የማውቀውን እነግራችኋለሁ'።
\s5
\v 11 ተመልከቱ፥ እስክትናገሩ ጠበቅኋችሁ፥ ምን መናገር እንዳለባችሁ በማሰብ ላይ እያላችሁም ክርክራችሁን አዳመጥኩኝ።
\v 12 በርግጥ ትኩረቴን ሰጠዃችሁ፥ ነገር ግን፥ ተመልከቱ፥ አንዳችሁም ኢዮብን ማስረዳት ወይም ለቃሎቹ ምላሽ መስጠት አልቻላችሁም።
\s5
\v 13 'ጥበብን አግኝተናል!' እንዳትሉ ተጠንቀቁ ኢዮብን ማሸነፍ ያለበት እግዚአብሔር ነው፤ ተራ ሰው ይህንን ለማድረግ አይችልም።
\v 14 ኢዮብ እኔን በመቃወም አልተናገረምና እኔም የእናንተን በሚመስል ቃል አልመልስለትም።
\s5
\v 15 እነዚህ ሦስት ሰዎች ዲዳ ሆነዋል፤ ከዚህ በኋላ ለኢዮብ ሊመልሱለት አይችሉም፤ ቀጥለው የሚናገሩት አንድም ቃል የላቸውም።
\v 16 እዚያ በዝምታ ስለቆሙና ከእንግዲህ ስለማይመልሱ፥ ስለማይናገሩም፥ መጠበቅ አለብኝ?
\s5
\v 17 አይሆንም፥ እኔም ደግሞ የበኩሌን እመልሳለሁ፤ እኔም ደግሞ ዕውቀቴን እነግራቸዋለሁ። ቃል
\v 18 ተሞልቻለሁና፤ በውስጤ ያለው መንፈስም ይገፋፋኛል።
\v 19 ተመልከቱ፥ ውስጤ ተከድኖ እንደሚብላላ ወይን ነው፤ ሊፈነዳ እንደተቃረበ አዲስ የወይን ጠጅ አቁማዳም ነው።
\s5
\v 20 አርፍ ዘንድ እናገራለሁ፤ አፌንም ከፍቼ መልስ እሰጣለሁ።
\v 21 አድልዎ አላደርግም፤ የትኛውንም ሰው አላቆላምጥም።
\v 22 እንዴት እንደማቆላምጥ አላውቅምና፤ እንዲህ ባደርግ ኖሮ ፈጣሪዬ ፈጥኖ ያስወግደኝ ነበር።
\s5
\c 33
\p
\v 1 አሁንም ኢዮብ ሆይ፥ ቃሎቼን እንድትሰማ፥ ንግግሬንም እንድታደምጥ እለምንሃለሁ።
\v 2 ይኸው አሁን አፌን ከፍቻለሁ፤ ምላሴም በአፌ ውስጥ ተናግሯል።
\v 3 ቃሎቼ የልቤን ቅንነት ይናገራሉ፤ ከንፈሮቼ የሚያውቁትን በታማኝነት ይናገራሉ።
\s5
\v 4 የእግዚአብሔር መንፈስ ፈጠረኝ፤ የሁሉን ቻዩ እስትንፋስ ሕይወትን ሰጠኝ።
\v 5 ከቻልክ መልስልኝ፤ በፊቴም ቃሎችህን በቅደም ተከተል አዘጋጅና ቁም።
\s5
\v 6 ተመልከት፥ በእግዚአብሔር ፊት አንተ እንደሆንከው እንዲሁም እኔም ነኝ፤ እኔም ደግሞ ከጭቃ ተሠርቻለሁ።
\v 7 ተመልከት፥ ማስፈራራቴ አያስፈራህም፤ ተጽዕኖዬም ቢሆን አይከብድብህም።
\s5
\v 8 በእርግጥ በጆሮዬ ተናግረሃል፤ እንዲህ የሚለውንም የቃልህን ድምፅ ሰምቻለሁ፥
\v 9 ንጹሕ ነኝ መተላለፍም የለብኝም፤ አልበደልኩም፥ ኃጢአትም የለብኝም።
\s5
\v 10 ይኸው፥ እግዚአብሔር ሊያጠቃኝ አጋጣሚ ይፈልጋል፤ እንደ ጠላቱ አድርጎ ይቆጥረኛል።
\v 11 እግሮቼን በግንድ ውስጥ ያስገባቸዋል፤ መንገዶቼንም ሁሉ ይመለከታል።
\v 12 እግዚአብሔር ከሰው ይበልጣልና እንደዚህ መናገርህ ትክክል አይደለም ብዬ እመልስልሃለሁ።
\s5
\v 13 ለየትኛውም ሥራው ትኩረት አይሰጠውም በማለት ከእርሱ ጋር ለምን ትታገላለህ?
\v 14 ሰው ባያስተውለውም እግዚአብሔር አንድ ጊዜ፥ አዎን፥ ሁለት ጊዜ ይናገራል።
\v 15 ሰዎች አልጋቸው ላይ ተኝተው ከባድ እንቅልፍ በሚወድቅባቸው ጊዜ በህልም፥ በሌሊት ራዕይ ይናገራቸዋል።
\s5
\v 16 በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር የሰዎችን ጆሮ ይከፍትና በማስጠንቀቂያው ያስፈራራቸዋል፤
\v 17 ይህንን የሚያደርገውም ሰውን ከኃጢአታዊ ዓላማው ሊመልሰውና ከትዕቢት ሊጠብቀው ነው።
\v 18 እግዚአብሔር የሰውን ሕይወት ከጉድጓድ ይጠብቃል፥ ሕይወቱንም ወደ ሞት ከመውረድ።
\s5
\v 19 ደግሞም ሰው በአልጋው ላይ በሕመም ይቀጣል፥ በአጥንቶቹም ውስጥ በማያቋርጥ ስቃይ፤
\v 20 ሕይወቱ ምግብን፥ ነፍሱም ጣፋጩን መብል እስክትጠላ ድረስ።
\s5
\v 21 ሥጋው ሊታይ እስከማይችል ድረስ ጠፍቷል፥ የማይታዩ የነበሩት አጥንቶቹም አሁን ገጠው ወጥተዋል።
\v 22 በርግጥ ነፍሱ ወደ ጉድጓድ ቀርባለች፥ ሕይወቱም ሊያጠፏት ወደሚፈልጉት።
\s5
\v 23 ነገር ግን መካከለኛ ሊሆንለት የሚችል አንድ መልአክ ቢኖር፥ የትኛውን መልካም ነገር ማድረግ እንዳለበት የሚያሳየው፥ መካከለኛ የሚሆንለት ከሺህ መላእክት አንድ ቢገኝለት፥
\v 24 መልአኩም ለእርሱ ደግ ቢሆንና እግዚአብሔርን፥ 'ቤዛ የሚሆንለት አግኝቻለሁና ይህንን ሰው ወደ ጉድጓድ ከመውረድ አድነው' ቢለው
\s5
\v 25 በዚያን ጊዜ ሥጋው ከሕፃን ገላ ይልቅ ይታደሳል፤ ወደ ወጣትነት የብርታቱ ዘመንም ይመለሳል።
\v 26 እርሱ ወደ እግዚአብሔር ይጸልያል፥ እግዚአብሔርም ይራራለታል፥ እርሱም የእግዚአብሔርን ፊት በደስታ ያያል። እግዚአብሔርም ለሰውየው ድልን ይሰጠዋል።
\s5
\v 27 ከዚያም ያ ሰው በሌሎች ሰዎች ፊት እንዲህ ሲል ይዘምራል፥ 'ኃጢአትን ሠርቻለሁ፥ ትክክለኛ የሆነውንም አጣምሜአለሁ፥ ይሁን እንጂ ስለኃጢአቴ አልተቀጣሁም።
\v 28 እግዚአብሔር ነፍሴን ወደ ጉድጓድ ከመውረድ አዳናት፤ ሕይወቴም ብርሃን ማየቷን ትቀጥላለች"።
\s5
\v 29 ተመልከቱ፥ እግዚአብሔር እነዚህን ነገሮች ሁሉ በሰው ሕይወት ሁለት ጊዜ፥ አዎን፥ እንዲያውም ሦስት ጊዜ ያደርጋቸዋል፤
\v 30 ይኸውም የሕይወት ብርሃን ይበራለት ዘንድ ነፍሱን ከጉድጓድ ለመመለስ ነው።
\s5
\v 31 ኢዮብ ሆይ አስተውለህ ስማኝ፤ ዝም በል፥ እኔም እናገራለሁ።
\v 32 የምትናገረው ነገር ካለህ መልስልኝ፤ ትክክለኛ መሆንህን ለማረጋገጥ እፈልጋለሁና ተናገር።
\v 33 ካልሆነ ግን ጸጥ ብለህ ስማኝ፤ እኔም ጥበብን አስተምርሃለሁ“።
\s5
\c 34
\p
\v 1 ኤሊሁም በመቀጠል እንዲህ አለ፥
\v 2 ”እናንተ ጥበበኞች፥ ቃሎቼን አድምጡ፤ እውቀት ያላችሁ እናንተ ስሙኝ።
\v 3 ምላስ ምግብን እንደሚያጣጥም ጆሮም ቃላትን ያመዛዝናል።
\s5
\v 4 ትክክለኛ የሆነውን ለራሳችን እንምረጥ፤ መልካም የሆነውንም በመካከላችን እንፈልገው።
\v 5 ኢዮብ 'እኔ ጻድቅ ነኝ እግዚአብሔር ግን መብቴን ነፍጎኛል። መብት ቢኖረኝም እንደ ሐሰተኛ ተቆጥሬአለሁ።
\v 6 ምንም እንኳን ኃጢአት ባይኖርብኝም ቁስሌ የማይፈወስ ነው' ብሏልና።
\s5
\v 7 ስድብን እንደ ውሃ የሚጠጣ፥
\v 8 ክፋትን ከሚያደርጉት ጋር እንደሚወዳጅ፥ ከአመጸኞችም ጋር እንደሚመላለስ እንደ ኢዮብ ያለ ማነው?
\v 9 እርሱ፥ 'ሰው እግዚአብሔር የሚፈልገውን በማድረግ መደሰቱ ምንም አይጠቅምም' ብሏልና።
\s5
\v 10 ስለዚህ እናንተ አዋቂዎች ስሙኝ፤ አመጻን ማድረግ ከእግዚአብሔር ይራቅ፤ ኃጢአትን ማድረግም ሁሉን ቻይ ከሆነው ይራቅ።
\v 11 ለሰው እንደ ሥራው ይከፍለዋልና፤ እያንዳንዱም በየራሱ መንገድ ወደ ብድራቱ እንዲመጣ ያደርገዋል።
\v 12 በእርግጥ እግዚአብሔር አንዳችም አመጻን አያደርግም፥ ደግሞም ሁሉን ቻዩ ከቶም ፍትሕን አያዛባም።
\s5
\v 13 በምድር ላይ እርሱን ፈራጅ ያደረገው ማነው? ዓለሙንስ በሙሉ ከእርሱ በታች ያደረገው ማነው?
\v 14 እርሱ ፍላጎቱን በራሱ ላይ ብቻ ቢያደርግና መንፈሱንና እስትንፋሱን ወደ ራሱ ቢመልስ ኖሮ
\v 15 ያን ጊዜ ሥጋን የለበሰ ሁሉ በጠፋ፥ ሰውም እንደገና ወደ ዐፈር በተመለሰ ነበር።
\s5
\v 16 አሁን እንግዲህ ማስተዋል ካለህ ይህንን ስማ፤ የቃሌንም ድምፅ አድምጥ።
\v 17 ፍትሕን የሚጠላ ማስተዳደር ይችላል? ጻድቅና ሁሉን ቻይ የሆነውን አምላክ ትኮንነዋለህ?
\s5
\v 18 እግዚአብሔር ንጉሡን፥ 'በደለኛ ነህ' ወይም ባለስልጣኖችን፥ 'አመጸኞች ናችሁ' አይልምን?
\v 19 እግዚአብሔር ለመሪዎች አያዳላም፤ ባለጸጋዎችንም ከድኾች አስበልጦ አይመለከታቸውም፤ ሁሉም የእጁ ሥራዎች ናቸውና።
\v 20 በቅጽበት ይሞታሉ፤ እኩለ ሌሊት ላይ ሰዎች ይንቀጠቀጣሉ፥ ይሞታሉም፤ ኃያላን ሰዎች ይወሰዳሉ፥ በሰው እጅ ግን አይደለም።
\s5
\v 21 የእግዚአብሔር ዐይኖች በሰው አካሄድ ላይ ናቸው፤ እርምጃዎቹንም ሁሉ ያያቸዋል።
\v 22 ክፉ አድራጊዎች የሚደበቁበት ጨለማ ወይም ድቅድቅ ጭጋግ የለም።
\v 23 እግዚአብሔር ከዚህ በላይ ሰውን መመርመር አይፈልግም፥ የትኛውም ሰው በእርሱ ፊት ቆሞ መሟገት አያስፈልገውም።
\s5
\v 24 ስለ አካሄዳቸው ተጨማሪ ምርመራ እንዳያስፈልጋቸው ኃያላኑን ሰዎች ይሰባብራቸዋል፤ በስፍራቸውም ሌሎችን ይሾማል።
\v 25 እንዲህ ባለ መንገድ ሥራቸውን ያውቃል፤ እነዚህን ሰዎች በጨለማ ይጥላቸዋል፤ እነርሱም ይጠፋሉ።
\s5
\v 26 በሌሎች ፊት፥ በአደባባይ ስለ ክፉ ሥራቸው እንደ ወንጀለኛ ይገድላቸዋል፥
\v 27 እርሱን ከመከተል ተመልሰዋልና፥ ከመንገዶቹም የትኛውንም ለመቀበል ፈቃደኞች አልሆኑምና።
\v 28 እንዲህ ባለ መንገድ የድኾች ጩኸት በፊቱ እንዲወጣ አደረጉ፤ እርሱም የተጨነቁትን ሰዎች ጩኸት ሰማ።
\s5
\v 29 በዝምታ በሚቆይበት ጊዜ ማን ሊወቅሰው ይችላል? ፊቱንስ ቢሰውር ማን ሊገነዘበው ይችላል?
\v 30 አመጸኛው ሰው ገዢ እንዳይሆን፥ በሕዝቡም ላይ ወጥመድን የሚያደርግ እንዳይገኝ እርሱ በሀገሮችና በግለሰቦች ላይ ይገዛል።
\s5
\v 31 አንድ ሰው እግዚአብሔርን እንዲህ እንደሚለው ገምቱ፥ 'በርግጥ በድያለሁ፥
\v 32 ከዚህ በኋላ ግን ከቶ ኃጢአትን አላደርግም፤ ላየው የማልችለውን አስተምረኝ፤ ኃጢአትን ሠርቻለሁ፥ ከእንግዲህ ግን አላደርግም'።
\v 33 እግዚአብሔር የሚያደርገውን የምትጠላ ሰው ብትሆንም፥ እግዚአብሔር የዚያን ሰው ኃጢአት የሚቀጣ ይመስልሃል? እኔ ሳልሆን አንተው መምረጥ አለብህ። ስለዚህ ትክክል ነው ብለህ የምታውቀውን ተናገር።
\s5
\v 34 ዐዋቂዎች ሰዎችም እንዲህ ይሉኛል፥ በእርግጥ የሚሰማኝ ጥበበኛ ሰው ሁሉ የሚለው እንዲህ ነው፥
\v 35 'ኢዮብ የሚናገረው የማያውቀውን ነው፤ ቃሎቹም ጥበብ የለባቸውም'።
\s5
\v 36 እንደ አመጸኞች ሰዎች ተናግሯልና ምነው ኢዮብ ብቻውን ከጉዳዮቹ ስለ ጥቂቶቹ በዝርዝር በተመረመረ።
\v 37 በኃጢአቱ ላይ አመጽን ጨምሯልና፤ በመካከላችን እጆቹን እያጨበጨበ ተሳድቧልና፤ እግዚአብሔርን በመቃወምም ብዙ ቃል ተናግሯል።"
\s5
\c 35
\p
\v 1 ኤሊሁ እንዲህ ሲል ንግግሩን ቀጠለ፥
\v 2 “ንጹሕ ነኝ ብለህ ታስባለህ? 'ከእግዚአብሔር ይልቅ ጻድቅ ነኝ' ብለህስ ታስባለህ?
\v 3 ጻድቅ መሆኔ ምን ይጠቅማል? ኃጢአት አድርጌ ቢሆን ኖሮ ከዚህ የሚበልጥ ምን ያገኘኝ ነበር?' ብለሃልና።
\s5
\v 4 ለአንተና ለወዳጆችህ ምላሽ እሰጣለሁ።
\v 5 ወደ ሰማይ ቀና በሉና ተመልከቱት፤ ከእናንተ ከፍ የሚለውን ሰማይ ተመልከቱ።
\s5
\v 6 ኃጢአትን ብታደርግ እግዚአብሔርን ምን ትጎዳዋለህ? መተላለፍህ እጅግ የበዛ ቢሆን ለእርሱ ምኑ ነው?
\v 7 ጻድቅ ብትሆንስ ምን ልትሰጠው ትችላለህ? ከእጅህስ ምን ይቀበላል?
\v 8 አንተም ሰው ነህና ክፋትህ ሌላውን ይጎዳ ይሆናል፤ ጽድቅህም ሌላውን የሰው ልጅ ይጠቅመው ይሆናል።
\s5
\v 9 በብዙ በደል ምክንያት ሰዎች ይጮኻሉ፤ ከኃያላኑ እጅ የሚያድናቸውን ፍለጋ ይጣራሉ።
\v 10 ነገር ግን 'በሌሊት ዝማሬን የሚሰጥ፥
\v 11 የምድር አራዊትን ከሚያስተምርበት በበለጠ የሚያስተምረን፥ ከሰማይ አዕዋፍም ይልቅ ጥበበኞች የሚያደርገን ፈጣሪያችን እግዚአብሔር የት አለ?' ማንም አላለም።
\s5
\v 12 በዚያን ጊዜ ይጮኻሉ፥ ነገር ግን በክፉ ሰዎች ትዕቢት ምክንያት እግዚአብሔር ምንም ምላሽ አይሰጣቸውም።
\v 13 ያለጥርጥር እግዚአብሔር የሞኞችን ጩኸት አይሰማም፤ ሁሉን ቻዩም ትኩረት አይሰጠውም።
\v 14 ጉዳይህን በፊቱ አቅርበህ እየተጠባበቅኸው እያለህ እንዳላየኸው ከተናገርክ እንዴት አድርጎ መልስ ይሰጥሃል!
\s5
\v 15 ማንንም ተቆጥቶ አይቀጣም፥ በሰዎች ትዕቢት እምብዛም ግድ አይለውም ካልክ እንዴት አድርጎ መልስ ይሰጥሃል?
\v 16 ስለዚህ ኢዮብ አፉን የሚከፍተው ስንፍናን ለመናገር ብቻ ነው፤ ዕውቀት የሌለበትን ቃል መናገርንም ያበዛል"።
\s5
\c 36
\p
\v 1 ኤሊሁ እንዲህ በማለት ንግግሩን ቀጠለ፥
\v 2 "ትንሽ ጨምሬ እንድናገር ፍቀድልኝ፥ እግዚአብሔርን በመወገን ትንሽ አክዬ የምናገረው አለኝና ጥቂት ነገሮችን አሳይሃለሁ።
\v 3 ዕውቀቴን ከሩቅ አመጣለሁ፤ ጽድቅ የፈጣሪዬ ነው እላለሁ።
\s5
\v 4 በርግጥ ቃሎቼ ሐሰት አይደሉም፤ አንድ በዕውቀት የበሰለም ከአንተ ጋር ነው።
\v 5 ተመልከት፥ እግዚአብሔር ኃያል ነው፥ ማንንም አይንቅም፤ እርሱ በማስተዋል ብርታቱም ኃያል ነው።
\s5
\v 6 እርሱ የአመጸኞች ሰዎችን ሕይወት አይጠብቅም ነገር ግን ከዚያ ይልቅ መከራ ለሚቀበሉት ትክክል የሆነውን ነገር ያደርግላቸዋል።
\v 7 ፊቱን ከጻድቃን አይመልስም ነገር ግን ከዚያ ይልቅ እንደ ነገሥታት በዙፋኖች ላይ ያስቀምጣቸዋል፥ እነርሱም ይከብራሉ።
\s5
\v 8 ይሁንና፥ በሰንሰለት ቢገቡ፥ በመከራም ገመድ ቢታሰሩ
\v 9 ያን ጊዜ ያደረጉትን መተላለፋቸውንና በግፍ እንደተመላለሱ ይገልጥላቸዋል።
\s5
\v 10 ደግሞም እርሱ ጆሮዎቻቸውን ለትምህርቱ ይከፍታቸዋል፥ ከክፋታቸው እንዲመለሱም ያዛቸዋል።
\v 11 ቢሰሙትና ቢያመልኩት ቀኖቻቸውን በብልጽግና ዓመቶቻቸውንም በእርካታ ያሳልፋሉ።
\v 12 ይሁን እንጂ፥ ባይሰሙት በሰይፍ ይጠፋሉ፤ ዕውቀት ስለሌላቸው ይሞታሉ።
\s5
\v 13 ልባቸው ከእግዚአብሔር የራቀ እነዚያ ቁጣቸውን ያከማቻሉ፤ እግዚአብሔር በሚያስራቸው ጊዜ እንኳን ለዕርዳታ አይጮኹም።
\v 14 በወጣትነታቸው ይሞታሉ፤ ሕይወታቸውም በቤተ ጣዖት ዝሙት አዳሪዎች መካከል ይጠፋል።
\s5
\v 15 የሚሰቃዩትን ሰዎች በስቃያቸው አማካይነት ያድናቸዋል፤ በመከራቸው አማካይነትም ጆሮዎቻቸውን ይከፍታል።
\v 16 በእርግጥ እርሱ ከጭንቀት አውጥቶ የሰባ ምግብ የሞላበት ጠረጴዛ በፊትህ ወደሚቀመጥበትና ስቃይ ወደሌለበት ሰፊ ስፍራ ሊያወጣህ ይፈልጋል።
\s5
\v 17 ነገር ግን አንተ በክፉ ሰዎች ፍርድ ተሞልተሃል፤ ፍርድና ፍትሕም ይዘውሃል።
\v 18 ብልጽግና ወደ መታለል እንዲስብህ እትፍቀድለት፤ መጠኑ የበዛ ጉቦም ፍትሕን እንድታዛባ እንዲያደርግህ አትፍቀድለት።
\s5
\v 19 ብልጽግናህ ከሐዘን ሊያርቅህ ይችላል? ወይም የኃይልህ ብርታት ሁሉ ሊረዳህ ይችላል?
\v 20 ሰዎች በየስፍራቸው በሚወገዱበት ጊዜ በሌሎች ላይ ኃጢአትን ለመሥራት ጨለማን አትመኝ።
\v 21 ኃጢአትን ከማድረግ ትርቅ ዘንድ በመከራ ተፈትነሃልና ወደ ኃጢአት እንዳትመለስ ተጠንቀቅ።
\s5
\v 22 ተመልከት፥ እግዚአብሔር በኃይሉ ከፍ ያለ ነው፤ እንደ እርሱስ ያለ አስተማሪ ማነው?
\v 23 ስለ መንገዱ ከቶ ማን አስተምሮታል? 'በደለኛ ነህ' ሊለውስ ከቶ ማን ይችላል?
\v 24 ሰዎች የዘመሩለትን ሥራዎቹን ለማወደስ አስታውስ።
\s5
\v 25 እነዚያን ሥራዎች ሰዎች ሁሉ አይተዋል፥ ነገር ግን እነዚያን ሥራዎች የሚያዩት ከርቀት ብቻ ነው።
\v 26 ተመልከት፥ እግዚአብሔር ትልቅ ነው፤ እኛም በሚገባ አናውቀውም፤ ዘመኖቹም አይቆጠሩም።
\s5
\v 27 እርሱ እንፋሎቱ ዝናብ ሆኖ ይወርድ ዘንድ የውሃ ነጠብጣቦችን ወደ ላይ ስቦ ያከማቻል፥
\v 28 ደመናዎች ወደ ታች ያፈስሱታል፥ በሰዎች ላይም በብዙ ያንጠባጥቡታል።
\v 29 በርግጥ የደመናዎቹን መዘርጋትና ከድንኳኑ የሚወጣውን መብረቅ ሊያስተውል የሚችል አለ?
\s5
\v 30 ተመልከት፥ መብረቁን በዙሪያው ይበትናል፤ ባህሩን በጨለማ ይከድነዋል።
\v 31 በዚህ መንገድ ሰዎችን ይመግባቸዋል፥ ብዙ ምግብንም ይሰጣቸዋል።
\s5
\v 32 ዒላማቸውን እንዲመቱ እስኪያዛቸው ድረስ እጆቹን በመብረቅ ነጓድጓድ ይሸፍናቸዋል።
\v 33 ዐውሎ ነፋስ እንደሚመጣ ድምፁ ለሰዎች ይነግራቸዋል፤ መቃረቡንም እንስሶች ደግሞ ያውቃሉ።
\s5
\c 37
\p
\v 1 በርግጥ በዚህ ጉዳይ ልቤ ተናውጧል፤ ስፍራውንም ለቋል።
\v 2 ኦ እስቲ አድምጡ፤ የድምፁን ሁካታ፥ ከአፉም የሚወጣውን ድምፅ አድምጡ።
\v 3 እርሱ ድምፁን ከሰማይ በታች ወዳለ ስፍራ ሁሉ ይልካል፥ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስም መብረቁን ይልካል።
\s5
\v 4 ከእርሱ በኋላ ድምፅ ይጮኻል፤ በግርማዊ ድምፁም ያንጎደጉዳል፤ ድምፁ በሚሰማበት ጊዜ የመብረቁን ብልጭታ አይከለክልም።
\v 5 እግዚአብሔር በድምፁ በሚያስደንቅ ሁኔታ ያንጎደጉዳል፤ ልናስተውላቸው የማንችላቸውን ታላላቅ ነገሮችንም ያደርጋል።
\v 6 በረዶውን፥ 'በምድር ላይ ውደቅ'፤ እንዲሁም ዝናቡን፥ 'ብርቱ ዝናብ ሆነህ ውረድ' ይለዋል።
\s5
\v 7 ሰዎች ሁሉ ያደረገውን ሥራውን እንዲያዩ የእያንዳንዱን ሰው እጅ ከመሥራት ይከለክላል።
\v 8 ከዚያም አራዊት ወደ መደበቂያቸው ይሄዳሉ፥ በዋሻዎቻቸውም ውስጥ ይቆያሉ።
\v 9 ዐውሎ ነፋስ ከደቡብ መኖሪያው ይመጣል፤ ቅዝቃዜም በሰሜን ከተበተነው ነፋስ።
\s5
\v 10 በእግዚአብሔር እስትንፋስ በረዶ ይገኛል፤ የውኆቹም ስፋት እንደ ብረት ይቀዘቅዛል።
\v 11 በርግጥ ጥቅጥቁን ደመና በሙቀት ይበትነዋል፤ መብረቆቹን በደመናዎች መካከል ይበትናቸዋል።
\s5
\v 12 በመላው ዓለም ላይ ፈቃዱን ያደርጉ ዘንድ በአመራሩ ደመናትን ያሽከረክራቸዋል።
\v 13 እነዚህ ሁሉ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል፤ ይህንን የሚያደርገው አንዳንድ ጊዜ ለማቅናት፥ አንዳንዴም ምድሩን ለማጠጣት፥ አንዳንዴም የቃል ኪዳን ታማኝነቱን ለማሳየት ነው።
\s5
\v 14 ኢዮብ ሆይ፥ ይህንን ስማ፤ ቆም በልና የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራዎች አስብ።
\v 15 እግዚአብሔር እንዴት ፈቃዱን በደመናት ላይ እንደሚፈጽም፥ የመብረቁንም ብልጭታ በእነርሱ ውስጥ እንዲበራ እንደሚያደርግ ታውቃለህ?
\s5
\v 16 በዕውቀቱ ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራዎች፥ የደመናትንም መንሳፈፍ ታስተውላለህ?
\v 17 ከደቡብ በሚመጣው ነፋስ ምክንያት ምድር ጸጥ በምትልበት ጊዜ ልብስህ እንዴት እንደሚሞቅ ታስተውላለህ?
\s5
\v 18 ከብረት የተሠራ ጠንካራ መስታወት የሚመስለውን ሰማይ እንደ እርሱ መዘርጋት ትችላለህ?
\v 19 አዕምሮአችን ከመጨለሙ የተነሣ ክርክራችንን በሥርዓት ማቅረብ አልቻልንምና ምን እንደምንመልስለት አስተምረን።
\v 20 ላነጋግረው እንደምፈልግ ይነገረው ዘንድ ይገባል? አንድ ሰው እንዲዋጥ ይፈልጋል?
\s5
\v 21 እነሆ፥ ነፋስ በውስጡ ካለፈና ደመናውን ካጠራው በኋላ በሰማይ ላይ የሚያበራውን ፀሐይ ሰዎች ለማየት አይችሉም።
\v 22 እንደ ወርቅ የሚያብረቀርቅ ብርሃን ከሰሜን ይመጣል- በእግዚአብሔር ዘንድ አስፈሪ ግርማ አለ።
\s5
\v 23 ሁሉን ቻዩን በሚመለከት እኛ ልናገኘው አንችልም፤ እርሱ በጽድቁና በኃይሉ ታላቅ ነው። ሰዎችን አያስጨንቅም።
\v 24 ስለዚህ፥ ሰዎች ይፈሩታል። ጥበበኞች ነን ብለው የሚያስቡትን አይመለከታቸውም"።
\s5
\c 38
\p
\v 1 ያን ጊዜ እግዚአብሔር ከብርቱ ዐውሎ ነፋስ ውስጥ ኢዮብን ጠራውና እንዲህ አለው፥
\v 2 "ዕውቀት በጎደለው ቃል ዕቅዴን የሚያጨልም ይህ ማነው?
\v 3 ጥያቄዎችን እጠይቅሃለሁና አሁን እንደ ሰው ወገብህን ታጠቅ፥ አንተም ልትመልስልኝ ይገባሃል።
\s5
\v 4 የምድርን መሠረቶች ባቆምኩ ጊዜ አንተ የት ነበርክ? ከፍ ያለ ማስተዋል ካለህ ነገረኝ።
\v 5 መጠኑን የወሰነው ማነው? የምታውቅ ከሆነ ንገረኝ። በላዩ ላይስ የመለኪያ ገመድ የዘረጋ ማነው?
\s5
\v 6 መሠረቶቹስ የቆሙት በምን ላይ ነው?
\v 7 የንጋት ከዋክብት በአንድነት በዘመሩና የእግዚአብሔር ልጆች ሁሉ በደስታ በዘመሩ ጊዜ የማዕዘኑን ድንጋይ ያስቀመጠ ማን ነበር?
\s5
\v 8 ደመናትን ልብሱ፥ ድቅድቁንም ጨለማ መጠቅለያው ባደረግሁ ጊዜ
\v 9 ከማኅፀን የሚወጣ ይመስል ፈንድቶ በወጣ ጊዜ የባህሩን መዝጊያ የዘጋ ማነው?
\s5
\v 10 ያን ጊዜ ነበር ለባህሩ ገደብን ያደረግሁለት፥ በሮችንና መወርወሪያዎችን ባደረግሁለት ጊዜ፥
\v 11 እንዲህም ባልኩት ጊዜ፥ 'እስከዚህ ድረስ መምጣት ትችል ይሆናል፥ ከዚህ ግን አትለፍ፤ ለሞገድህ ትዕቢት ገደብ የማደርግለት እዚህጋ ነው'።
\s5
\v 12 ከተወለድክበት ጊዜ ጀምሮ ንጋት እንዲጀምር ከቶ ትዕዛዝ ሰጥተኸዋል? ወጋገኑስ በነገሮች መካከል ስፍራውን እንዲያውቅ አድርገኸዋል?
\v 13 የምድርን ማዕዘናት በመያዝ ክፉዎች ሰዎች ከእርሱ ላይ እንዲራገፉ አድርገሃል?
\s5
\v 14 ጭቃው ከማኅተም በታች እንደሚለወጥ የምድርም መልክ ተለውጧል፤ በእርሱ ላይ ያለው ነገር ሁሉ በግልጽ እንደ ቁራጭ ጨርቅ ተጠቅልሎ ቆሟል።
\v 15 ከክፉ ሰዎች 'ብርሃናቸው' ተወስዷል፤ ወደ ላይ የተነሣው ክንዳቸውም ተሰብሯል።
\s5
\v 16 ወደ ባህሩ መገኛ ሄደህ ታውቃለህ? ዝቅ ወዳለው ጥልቅ ስፍራስ ወርደህ ታውቃለህ?
\v 17 የሞት በሮች ተገልጠውልሃል? የሞት ጥላ በሮችንስ አይተኻቸዋል?
\v 18 ምድርን በስፋቱ ታውቀዋለህ? ይህንን ሁሉ የምታውቅ ከሆነ ንገረኝ።
\s5
\v 19 ብርሃን የሚያርፍበት ስፍራ መንገዱ የት ነው? የጨለማውስ ስፍራው የት ነው?
\v 20 ብርሃንና ጨለማን ወደ ሥራቸው ስፍራ ልትመራቸው ትችላለህ? ወደ መኖሪያቸው የሚመለሱበትን መንገድስ ልትፈልግላቸው ትችላለህ?
\v 21 ያን ጊዜ ተወልደህ ስለነበርና የዕድሜህም ቁጥር ታላቅ ስለሆነ ያለጥርጥር ታውቃለህ!
\s5
\v 22 ወደ በረዶው መጋዘን ገብተሃል? ወይም የአመዳዩን ማከማቻ አይተሃል?
\v 23 እነዚህን ነገሮች ለመከራ ጊዜ፥ ለጦርነትና ለውጊያ ቀናት ያስቀመጥኳቸው ናቸው።
\v 24 የመብረቅ ብልጭታ የሚሰራጭበት መንገድ የትኛው ነው? ወይም ነፋሳት ከምስራቅ በምድር ላይ የሚበተኑበት መንገድ የቱ ነው?
\s5
\v 25 ለዶፍ ዝናብ መውረጃን ያበጀለት ወይም ለመብረቅ ብልጭታ መንገድ ያዘጋጀለት ማነው?
\v 26 ሰው በሌለበት ምድር፥ ማንም በሌለበት ምድረ በዳ ላይ እንዲዘንብ ያደረገ ማነው?
\v 27 ሰው የሌለበትንና የባድማውን አካባቢ ፍላጎት የሚያረካ፥ ሣር እንዲበቅልበትስ የሚያደርግ ማነው?
\s5
\v 28 ዝናብ አባት አለው? የጤዛን ጠብታ የወለደው ማነው?
\v 29 በረዶስ የመጣው ከማን ማኅፀን ነው? የሰማዩን አመዳይ ማን ወለደው?
\v 30 ውኆች ራሳቸውን ይደብቁና እንደ ድንጋይ ይጠነክራሉ፤ የጥልቁም ገጽታ ግግር ይሆናል።
\s5
\v 31 ፕልያዲስ የተባለውን ኮከብ በሠንሰለት ልታስረው ወይም የኦሪዮንን እስራት ልትፈታ ትችላለህ?
\v 32 የከዋክብት ክምችት በተገቢው ጊዜአቸው እንዲታዩ ልትመራቸው ትችላለህ? ድብ የተባለውን ከነልጆቹ ልትመራቸው ትችላለህ?
\v 33 የሰማይን ሥርዓት ታውቃለህ? የሰማይን ሥርዓት በምድር ላይ መተግበር ትችላለህ?
\s5
\v 34 ብዙ የዝናብ ውሃ እንዲያጥለቀልቅህ ድምፅህን ወደ ደመናት ማሰማት ትችላለህ?
\v 35 'ይኸው እዚህ አለን' ብለው ይላኩህ ዘንድ የመብረቅ ብልጭታዎችን ልትልካቸው ትችላለህ?
\s5
\v 36 በደመናት ውስጥ ጥበብን ያኖረ ወይም ለእርጥበት ዕውቀትን የሰጠ ማነው?
\v 37 በጥበቡ ደመናትን ለመቁጠር የሚችል ማነው?
\v 38 ብናኙ ዐፈር ተበጥብጦ ጠንካራ ጓል በሚሆንበትና ጭቃው አፈር በአንድ ላይ በሚጣበቅበት ጊዜ የሰማይን የውሃ መያዣ አዘንብሎ ማፍሰስ የሚችል ማነው?
\s5
\v 39 በዋሻዎቻቸው በሚያደቡበትና በመኖሪያቸው ተጋድመው በሚጠባበቁበት ጊዜ
\v 40 ለአንበሳዪቱ አደን ልታድንላት ወይም ግልገሎቿን ልታጠግብላት ትችላለህ?
\s5
\v 41 ጫጩቶቻቸው ወደ እግዚአብሔር በሚጮኹበትና ምግብ በማጣት በሚንከራተቱበት ጊዜ ለቁራዎች ምግብ የሚሰጣቸው ማነው?
\s5
\c 39
\p
\v 1 የበረሃ ፍየሎች በዐለቶች መካከል የሚወልዱበትን ጊዜ ታውቃለህ? አጋዘኖችስ ግልገሎቻቸውን በሚወልዱበት ጊዜ ልታያቸው ትችላለህ?
\v 2 የእርግዝናቸውንስ ወራት ለመቁጠር ትችላለህ? የሚወልዱበትንስ ጊዜ ታውቃለህ?
\s5
\v 3 ይንበረከኩና ግልገሎቻቸውን ይወልዳሉ፤ የምጣቸውንም ሕመም ያበቃሉ።
\v 4 ግልገሎቻቸው ይጠነክራሉ፥ በገላጣው መስክ ላይም ያድጋሉ፤ ርቀው ይሄዳሉ፥ ወደ ወለዷቸውም አይመለሱም።
\s5
\v 5 የሜዳ አህያው በነጻነት እንዲሄድ የፈቀደለት ማነው?
\v 6 አራባህን ቤቱ፥ የጨውንም ምድር መኖሪያው ያደረግሁለትን የፈጣኑንስ አህያ እስራት የፈታ ማነው?
\s5
\v 7 በከተማ ባለው ሁካታ በንቀት ይስቃል፤ የነጂውንም ጩኸት አይሰማም።
\v 8 በመሰማሪያዎቹ በተራሮች ላይ ይንከራተታል፤ በዚያም የሚመገበውን የለመለመ ሣር ሁሉ ይፈልጋል።
\s5
\v 9 ጎሽ ሊያገለግልህ ይፈቅዳል? በበረትህስ አጠገብ ለማደር ይስማማል?
\v 10 ጎሽ ትልሞችህን እንዲያርስልህ በገመድ ልትቆጣጠረው ትችላለህ? ጓሉንስ ይከሰክስልሃል?
\s5
\v 11 ጉልበቱ ብርቱ ስለሆነ ትታመነዋለህ? እርሱ እንዲያከናውንልህ ተግባርህን ትተውለታለህ?
\v 12 ምርትህን ዐውድማ ላይ እንዲያከማችልህ፥ እህልህንም ወደ ቤት እንዲያገባልህ ትተማመነዋለህ?
\s5
\v 13 የሰጎን ክንፎች በደስታ ይራገባሉ፤ ነገር ግን እነርሱ የፍቅር ክንፎችና ላባዎች ናቸው?
\v 14 እንቁላሎቿን በአፈር ውስጥ ትጥላለች፥ እንዲሞቃቸውም በትቢያ ውስጥ ትተዋቸዋለች።
\v 15 እግር እንዲረግጣቸው ወይም የዱር አውሬ እንዲጨፈልቃቸው ትረሳቸዋለች።
\s5
\v 16 የእርስዋ ያልሆኑ ይመስል በጫጩቶቿ ትጨክናለች፤ ድካሟ ሁሉ ከንቱ እንደሚሆን በማሰብ አትፈራም፤
\v 17 እግዚአብሔር ጥበብን ነፍጓታልና አንዳች ማስተዋልንም አልሰጣትም።
\v 18 በፍጥነት በምትሮጥበት ጊዜ በፈረሱና በጋላቢው ላይ በንቀት ትሥቃለች።
\s5
\v 19 ለፈረስ ኃይሉን ሰጥተኸዋል? አንገቱንስ በጋማው አልብሰኸዋል?
\v 20 እንደ አንበጣ እንዲዘል አድርገኸዋል? የማንኮራፋቱ ገናናነት አስፈሪ ነው።
\s5
\v 21 በኃይል ይጎደፍራል፥ በብርታቱም ደስ ይለዋል፤ የጦር መሳሪያዎችን ለመገናኘት ይፈጥናል።
\v 22 በፍርሃት ላይ ይሳለቃል፥ አይደነግጥምም፤ ከሰይፍም ወደ ኋላ አይመለስም።
\v 23 ከሚብለጨለጨው ፍላጻና ጦር ጋር የፍላጻዎች መያዣ ጎኑ ላይ ይንኳኳል።
\s5
\v 24 በቁጣና በጭካኔ መሬትን ይውጣል፤ የመለከት ድምፅ ሲሰማ ይቁነጠነጣል።
\v 25 የመለከት ድምፅ በሚሰማበት ጊዜ ሁሉ 'አሃ!' ይላል፤ ጦርነትን፥ የአዛዦችን የሚንጎደጎድ ጩኸትና ሁካታ ከሩቅ ያሸታል።
\s5
\v 26 ጭልፊት ርቆ የሚመጥቀው፥ ክንፎቹንም ወደ ደቡብ የሚዘረጋው ባንተ ጥበብ ነው?
\s5
\v 27 ንስር ወደ ላይ የሚበረውና ጎጆውን ከፍ ባሉ ስፍራዎች የሚሠራው ባንተ ትዕዛዝ ነው?
\v 28 በገደል ላይ ይኖራል፥ መኖሪያ ምሽጉንም በገደሉ ጫፍ ላይ ያደርጋል።
\s5
\v 29 እዚያ ላይ ሆኖ የሚነጥቀውን ይቃኛል፤ ዐይኖቹም ከርቀት ይመለከቱለታል።
\v 30 ጫጩቶቹ ደግሞ ደም ይጠጣሉ፤ በድን ባለበት እርሱም በዚያ አለ"።
\s5
\c 40
\p
\v 1 እግዚአብሔር ኢዮብን እንዲህ ሲል መናገሩን ቀጠለ፥
\v 2 "ማንም መተቸት የሚፈልግ ሁሉን ቻዩን አምላክ ማረም አለበት? ከእግዚአብሔር ጋር የሚከራከር እርሱ ምላሹን ይስጥ"።
\s5
\v 3 ኢዮብም ለእግዚአብሔር እንዲህ ሲል መለሰ፥
\v 4 "ተመልከት፥ እኔ ከምንም የማልቆጠር ነኝ፤ እንዴትስ መልስ ልሰጥህ እችላለሁ? እጄን በአፌ ላይ እጭናለሁ።
\v 5 አንድ ጊዜ ተናገርኩ፥ መልስ መስጠትም አልችልም፤ በእርግጥ ሁለተኛ ተናግሬ ይሆናል፥ ከዚህ በኋላ ግን አልቀጥልም"።
\s5
\v 6 ከዚያም እግዚአብሔር ከኃይለኛ ዐውሎ ነፋስ ውስጥ ሆኖ ኢዮብን እንዲህ ሲል ተናገረው፥
\v 7 "እንግዲህ እንደ ወንድ ወገብህን ታጠቅ፥ እጠይቅሃለሁና አንተም ልትመልስልኝ ይገባል።
\s5
\v 8 ፍትሐዊ ስላለመሆኔ ትናገራለህ? ራስህን ትክክለኛ አድርገህ ለመቁጠር እኔን ትኮንናለህ?
\v 9 የእግዚአብሔርን የሚያክል ክንድ አለህ? እንደ እርሱስ ድምፅህን ልታንጎደጉድ ትችላለህ?
\s5
\v 10 አሁንም ክብርንና ልዕልናን ልበስ፤ ክብርንና ግርማንም ታጠቅ።
\v 11 የቁጣህን ብዛት በዙሪያህ አፍስስ፤ ትዕቢተኛ የሆነውን ሁሉ ተመልከተውና አዋርደው።
\s5
\v 12 ትዕቢተኛ የሆነውን ሁሉ ተመልከተውና ዝቅ አድርገው፤ ክፉዎችንም ሰዎች በቆሙበት ስፍራ አድቅቃቸው።
\v 13 አንድ ላይ ዐፈር ውስጥ ቅበራቸው፤ በተሰወረ ስፍራም ፊታቸውን ደብቀው።
\v 14 ያን ጊዜ እኔ ደግሞ የገዛ ክንድህ ሊያድንህ እንደቻለ ዐውቃለሁ።
\s5
\v 15 አሁንም አንተን እንደፈጠርኩህ የፈጠርኩትን ጉማሬ ተመልከት፤ እርሱ እንደ በሬ ሣር ይበላል።
\v 16 ተመልከት፥ ኃይሉ በወገቡ፥ ብርታቱም በሆዱ ጡንቻ ውስጥ ነው።
\s5
\v 17 ጭራውን እንደ ጥድ ያወዛውዛል፤ የወርቹ ጅማቶችም እርስ በእርሳቸው የተገጣጠሙ ናቸው።
\v 18 አጥንቶቹ እንደ ነሐስ ቱቦ ናቸው፤ እግሮቹም እንደ ብረት ዘንግ ናቸው።
\s5
\v 19 እርሱ እግዚአብሔር ከፈጠራቸው ፍጥረታት ዋነኛው ነው። እርሱን የፈጠረው እግዚአብሔር ብቻ ሊያሸንፈው ይችላል።
\v 20 ኮረብታዎች ምግቡን ያዘጋጁለታልና፤ በመስክ ላይ ያሉት አራዊትም በአቅራቢያው ይጫወታሉ።
\v 21 በረግረጉ ስፍራ ከደንገል ተክሎች ስር ይተኛል።
\s5
\v 22 በውሃ ዳር የሚበቅሉ ዛፎች በጥላዎቻቸው ይሸፍኑታል፤ የአኻያውም ዛፍ ሁሉ በዙሪያው ነው።
\v 23 ተመልከት፥ ወንዙ ቢጎርፍም እርሱ አይፈራም፤ የዮርዳኖስ ወንዝ እስከ አፉ ቢሞላም እርሱ ተማምኖ ይኖራል።
\v 24 በወጥመድ ሊይዘው ወይስ አፍንጫውን በወጥመድ ሊበሳው የሚችል አለ?
\s5
\c 41
\p
\v 1 ሌዋታንን በዓሳ መንጠቆ ልትይዘው ትችላለህ? ወይስ መንጋጋዎቹን በገመድ ታስራለህ?
\v 2 በአፍንጫው ገመድ ልታስገባ ወይም አገጩን በችካል ልትበሳው ትችላለህ?
\v 3 አብዝቶስ ይለምንሃል? በለሰለሱ ቃላትስ ያናግርሃል?
\s5
\v 4 የሁልጊዜ አገልጋይህ ለመሆን እንድትወስደው ከአንተ ጋር ስምምነት ያደርጋል?
\v 5 ከወፍ ጋር እንደምትጫወት ከእርሱ ጋር ትጫወታለህ? ሴት አገልጋዮችህ እንዲጫወቱበት ታስርላቸዋለህ?
\v 6 ዓሳ አጥማጆችስ በእርሱ ላይ ይደራደራሉ? ለነጋዴዎችስ ያከፋፍሉታል?
\s5
\v 7 ቆዳውን በአንካሴ ወይም ራሱን በዓሳ መውጊያ ጦር ልትበሳው ትችላለህ? አንድ ጊዜ ብቻ
\v 8 እጅህን በላዩ ላይ አድርግ፥ ያን ጊዜ ግብግቡን አትረሳውም፥ እንዲህ ያለውን ተግባርም አትደግመውም።
\v 9 ተመልከት፥ ማንም ይህንን ለማድረግ ተስፋ ቢያደርግ ሐሰተኛ ነው፤ እርሱን በማየቱ ብቻ በድንጋጤ የማይወድቅ ማነው?
\s5
\v 10 ሌዋታንን ለመቀስቀስ የሚደፍር የለም፤ ማንስ በፊቱ ሊቆም ይችላል?
\v 11 እንድመልስለት ማንኛውንም ነገር አስቀድሞ ለእኔ የሰጠኝ ማነው? ከሰማይ በታች ያለው ሁሉ የእኔ ነው።
\v 12 ስለ ሌዋታን እግሮች፥ ስለ ብርታቱና ስለተዋበው ቅርጹ ከመናገር ዝም አልልም።
\s5
\v 13 ቆዳውን ማን ሊገፈው ይችላል? ድርብ መከላከያውንስ ማን ሊበሳው ይችላል?
\v 14 አስፈሪ ጥርሶቹ የተገጠገጡበትን የፊቱን ደጆች ማን ሊከፍት ይችላል?
\v 15 ጀርባው ተቀራርበው ከተጣበቁ ንብርብር ጋሻዎች የተሠራ ነው።
\s5
\v 16 አንደኛው ከሌላኛው ጋር እጅግ ከመቀራረቡ የተነሣ በመካከላቸው ነፋስ አያስገባም።
\v 17 እርስ በእርስ ተገናኝተዋል፥ ሊነቅሏቸው እስከማይቻልም ድረስ በአንድነት ተጣብቀዋል።
\v 18 ከእንጥሽታው የብርሃን ብልጭታ ይወጣል፤ ዓይኖቹ እንደ ንጋት ጮራ ያበራሉ።
\s5
\v 19 የሚነድ ፍም፥ የእሳትም ትንታግ ከአፉ ይወጣል።
\v 20 በእሳት ላይ ተጥዶ በኃይል እንደሚንተከተክ ድስት ከአፍንጫው ጢስ ይወጣል።
\v 21 እስትንፋሱ ከሰሉን እንዲቀጣጠል ያደርገዋል፤ ከአፉም እሳት ይወጣል።
\s5
\v 22 ብርታት በአንገቱ ውስጥ አለ፥ ሽብርም በፊት ለፊቱ ይጨፍራል።
\v 23 የሥጋው እጥፋቶች እርስ በእርሳቸው የተገጠገጡ ናቸው፤ በእርሱ ላይ ጸንተዋል፤ ሊያነቃንቋቸውም አይቻልም።
\v 24 ልቡ እንደ ድንጋይ የጠነከረ ነው፤ በእርግጥም እንደ ወፍጮ መጅ ጠንካራ ነው።
\s5
\v 25 ቀና በሚልበት ጊዜ አማልክት እንኳ ይፈራሉ፤ ከፍርሃታቸውም የተነሣ ወደኋላቸው ይመለሳሉ።
\v 26 ሰይፍ ቢቆርጠው አንዳች አይሰማውም፤ ጦር፥ ቀስት፥ ወይም የትኛውም የጦር መሣሪያ ቢነጣጠርበት አይሰጋም።
\v 27 ብረትን እንደ አገዳ፥ ናስንም እንደ ነቀዘ እንጨት ይቆጥረዋል።
\s5
\v 28 ቀስት እንዲሸሽ አያደርገውም፥ የወንጭፍ ድንጋይም ለእርሱ እንደ ገለባ ነው።
\v 29 ዱላ እንደ አገዳ ተቆጥሯል፤ በሚወረወርበት ጦር ላይም ይስቃል።
\v 30 የሆዱ ስር እንደ ገል ስብርባሪ የሾለ ነው፤ የእህል መውቂያ መሣሪያ ይመስል በጭቃው ላይ ምልክት ትቶ ያልፋል።
\s5
\v 31 በድስጥ ውስጥ ያለ ውሃ እንደሚፈላ የጥልቁን ውሃ ያናውጠዋል፤ ባህሩንም እንደ ሽቶ ቢልቃጥ ያደርገዋል።
\v 32 የሄደበት መንገድ ከበስተኋላው እንዲያበራ ያደርጋል፤ ይህንን ያየም ጥልቁን ነጭ ነው ብሎ ያስባል።
\s5
\v 33 ያለ ፍርሃት እንዲኖር የተፈጠረ በምድር ላይ እርሱን የሚያክል የለም።
\v 34 ኩሩ የሆነውን ሁሉ ያያል፤ እርሱ በትዕቢት ልጆች ሁሉ ላይ ንጉሥ ነው።"
\s5
\c 42
\p
\v 1 ኢዮብም ለእግዚአብሔር እንዲህ ሲል መለሰ፥
\v 2 "ሁሉን ለማድረግ እንደምትችል፥ ዓላማህ ሊደናቀፍ እንደማይችል አውቃለሁ።
\v 3 'ያለዕውቀት ዕቅዴን የሚያጨልም ይህ ማነው?' ብለህ ጠይቀኸኛል። ስለዚህ የማላውቀውን፥ ያልተረዳሁትን፥ ለማወቅም እጅግ አስቸጋሪ የሆነውን ነገር ተናግሬአለሁ።
\s5
\v 4 አንተም፥ 'አሁንም፥ አድምጥ፥ እኔ እናገራለሁ፤ አንዳንድ ነገሮችን እጠይቅሃለሁ፥ አንተም ትነግረኛለህ' አልከኝ።
\v 5 ስለአንተ መስማትን በጆሮዬ ሰምቼ ነበር፥ አሁን ግን ዓይኖቼ አዩህ።
\v 6 ስለዚህ ራሴን እንቃለሁ፤ በአመድና በትቢያ ላይ ተቀምጬ ንስሓ እገባለሁ"።
\s5
\v 7 እግዚአብሔር ኢዮብን ይህን ቃል ከተናገረው በኋላ ቴማናዊውን ኤልፋዝን እንዲህ አለው፥ "አንተና ሁለቱ ጓደኞችህ አገልጋዬ ኢዮብ እንዳደረገው ስለ እኔ ትክክለኛውን ነገር አለተናገራችሁምና ቁጣዬ በእናንተ ላይ ነዶባችኋል።
\v 8 አሁን እንግዲህ ሰባት ወይፈኖችንና ሰባት አውራ በጎችን ለራሳችሁ ይዛችሁ ወደ አገልጋዬ ኢዮብ ሂዱ፤ ለራሳችሁም የሚቃጠል ምስዋዕት አድርጋችሁ አቅርቡ። እኔም እንደ ስንፍናችሁ እንዳላደርግባችሁ አገልጋዬ ኢዮብ ይጸልይላችኋል፤ እኔም ጸሎቱን እቀበላለሁ። አገልጋዬ ኢዮብ እንዳደረገው ስለ እኔ ትክክለኛውን ነገር አልተናገራችሁምና።"
\v 9 ስለዚህ ቴማናዊው ኤልፋዝ፥ ሹሐዊው በልዳዶስና ናዕማታዊው ሶፋር እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው ሄደው አደረጉ፤ እግዚአብሔርም ኢዮብን ተቀበለው።
\s5
\v 10 ኢዮብ ስለ ጓደኞቹ በጸለየ ጊዜ እግዚአብሔር እንደገና አበለጸገው። ቀድሞ ከነበረው በላይ እግዚአብሔር ዕጥፍ አድርጎ ሰጠው።
\v 11 ከዚያም የኢዮብ ወንድሞቹና እህቶቹ ሁሉ፥ ቀድሞ ያውቁት የነበሩትም ሁሉ እርሱ ወደነበረበት መጡ፤ ከእርሱም ጋር ምግብ በሉ። እነርሱም ሐዘኑን ተጋሩት፤ እግዚአብሔር አምጥቶበት ስለነበረው መከራ ሁሉ አጽናኑት። እያንዳንዳቸውም ለኢዮብ ጥሬ ብርና የወርቅ ቀለበት ሰጡት።
\s5
\v 12 እግዚአብሔር ከመጀመሪያው ይልቅ የኢዮብን የኋለኛውን ዘመን ባረከለት፤ እርሱም ዐሥራ አራት ሺህ በጎች፥ ስድስት ሺህ ግመሎች፥ አንድ ሺህ ጥማድ በሬዎች፥ አንድ ሺህም ሴት አህዮች ነበሩት።
\v 13 ደግሞም ሰባት ወንዶችና ሦስት ሴቶች ልጆች ነበሩት።
\v 14 የመጀመሪያ ሴት ልጁን ይሚማ፥ ሁለተኛዋን ቃሥያ፥ ሦስተኛዋን አማልቶያስ ቂራስ ብሎ ሰየማቸው።
\s5
\v 15 በሀገሩ ሁሉ እንደ ኢዮብ ሴቶች ልጆች የተዋቡ ሴቶች አልተገኙም። አባታቸውም ከወንድሞቻቸው እኩል ርስትን ሰጣቸው።
\v 16 ከዚህ በኋላ ኢዮብ 140 አመት ኖረ፤ እርሱም ወንዶች ልጆችን፥ የወንዶች ልጆቹን ወንዶች ልጆች እስከ አራት ትውልድ ድረስ አየ።
\v 17 ከዚያም ኢዮብ አርጅቶ፥ ዕድሜንም ጠግቦ ሞተ።