am_ulb/16-NEH.usfm

770 lines
107 KiB
Plaintext

\id NEH
\ide UTF-8
\h ነህምያ
\toc1 ነህምያ
\toc2 ነህምያ
\toc3 neh
\mt ነህምያ
\s5
\c 1
\p
\v 1 እኔ የሐካልያ ልጅ ነህምያ ነኝ፡፡ ንጉስ አርጤክስስ የፋርስን መንግስት መግዛት በጀመረበት በሃያኛው አመት፣ ካሴሉ በተባለው ወር፤ ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሼ ያደረግሁትን ይህን ነገር ጻፍሁ፡፡ እኔም በፋርስ ዋና ከተማ በሱሳ ነበርሁ፡፡
\v 2 ወንድሜ አናኒ እኔን ለማየት መጣ፡፡ እርሱና ሌሎች ጥቂት ሰዎች ከይሁዳ መጥተው ነበር፡፡ ከባቢሎን ምርኮ ስላመለጡ ጥቂት አይሁዶች፣ እና ስለ ኢየሩሳሌም ከተማ ጥያቄዎችን ጠየቅኳቸው፡፡
\s5
\v 3 እነርሱም እንዲህ አሉኝ፣ “ከምርኮ ያመለጡት አይሁዶች በዚያ በታላቅ መከራ እና ውርደት እየኖሩ ይገኛሉ፡፡ የከተማዋ ቅጥሮች በብዙ ስፍራዎች ተገፍተው ስለወደቁ ጠላት በቀላሉ ይገባባታል፣ ይህም ብቻ ሳይሆን፣ ነገር ግን የከተማዋ በሮች ሙሉ በሙሉ በእሳት ተቃጥለዋል፡፡”
\s5
\v 4 ይህንን በሰማሁ ጊዜ፣ ተቀምጬ አለቀስኩ፡፡ ለብዙ ቀናት በሰማይ ወዳለው አምላክ በለቅሶ ጾምኩ ጸለይኩ፡፡
\v 5 እንዲህ ስል ጸለይኩ፣ “ያህዌ፣ አንተ በሰማይ ያለህ አምላክ ነህ፡፡ አንተ ታላቅና አስደናቂ አምላክ ነህ፣ ለሚወዱህና ህግጋትህንና ትዕዛዛትህን ለሚጠብቁ ሁሉ የተቀደሰውን አብሮነትህንና ቃልኪዳንህን ትጠብቃለህ፡፡
\s5
\v 6 እባክህ አሁን ወደ እኔ ተመልከት ወደ ጸሎቴም አድምጥ፡፡ በቀንና በለሊት ለህዝብህ ለእስራኤል እጸልያለሁ፡፡ ኃጢአት መስራታችንን እናዘዛለሁ፡፡ እኔና ቤተሰቤ ጭምር አንተን በድለናል፡፡
\v 7 በጣም ክፉ አድርገናል፡፡ ከብዙ አመታት አስቀድሞ ባሪያህ ሙሴ አንተ እናደርገው ዘንድ ያዘዝከውን ህግጋትና ስርዓቶች ሰጥቶናል፣ እኛ ግን ህግጋትህን አልጠበቅንም፡፡
\s5
\v 8 እባክህ ለአገልጋይህ ለሙሴ የተናገርከውን አስብ፡፡ እንዲህ ብለሃል፣ ‘በፊቴ በታማኝነት እና በመታዘዝ ባትመላለሱ በአገራት መሃል እበትናችኋለሁ፡፡
\v 9 ነገር ግን ወደ እኔ ብትመለሱ እና ትዕዛዞቼን ብትጠብቁ፣ ወደ ሩቅ ሥፍራዎች ብትጋዙም እንኳን፣ ሁላችሁንም ሰብስቤ የእኔን ታላቅነትና ክብር ወደማሳያችሁ ወደዚህ ስፍራ እመልሳችኋለሁ፡፡
\s5
\v 10 እኛ የአንተ አገልጋዮች ነን፡፡ በታላቁ ሀይልህ ከባርነት ነጻ ያወጣኸን ህዝብ ነን፡፡ አንተ ያንን ያደረግከው ማድረግ የምትፈልገውን ሁሉ ማድረግ ስለምትችል ነው፡፡
\v 11 ያህዌ፣እባክህ የእኔን የአገልጋይህን ፀሎት ስማ፡፡ እባክህ በማንነትህና በስራህ አንተን ሲያከብሩ፣ ታላቅ ሀሴት የሚያደርጉትን የህዝብህን ሁሉ ጸሎት ስማ፡፡ ወደ ንጉሱ ፊት ስቀርብ መከናወንን እንድትሰጠኝ እጸልያለሁ፤ ለንጉሱ ጥያቄዬን ሳቀርብ ህይወቴ አደጋ ላይ እንዳትወድቅ ጠብቃት፡፡ ምህረትህ ይከተለኝ፡፡” እኔ ለንጉሱ እጅግ ከታመኑት አገልጋዮች አንዱ ሆኜ አገለግል ነበር፡፡
\s5
\c 2
\p
\v 1 በንጉስ አርጤክስ፣ አገዛዝ ሃያኛ ዓመት፣ ኒሳን ተብሎ በሚጠራው ወር፣ በክብረ በዓሉ ለንጉሱ ወይን ጠጅ የሚቀርብበት ሰዓት ነበር፡፡ ወይን ወስጄ ለንጉሱ አቀረብኩ፡፡ ከዚያ አስቀድሞ በንጉሱ ፊት እንዲህ አዝኜ ቀርቤ አላውቅም ነበር፡፡
\v 2 በዚያን ቀን ግን፣ ንጉሱ እኔን ተመልክቶ እንዲህ አለኝ፣ “ለምን እንዲህ እጅግ አዘንህ? የታመምክ አትመስልም፡፡ ምናልባት መንፈስህ ታውኮ ይሆንን?” እኔም በጣም ፈርቼ ነበር፡፡
\s5
\v 3 እንዲህ ስል መለስኩ፣ “ንጉስ ሆይ፣ ለዘለዓለም ንገስ! ያዘንኩት ያለ ምክንያት አይደለም፣ አባቶቼ የተቀበሩባት ከተማ ፍርስራሽ ሆናለች፣ በከተማዋ ዙሪያ ያሉ በሮቿ በሙሉ ተቃጥለው አመድ ሆነዋል፡፡”
\s5
\v 4 ንጉሱ እንዲህ ሲል መለሰልኝ፣ “ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ?” እናም ለእርሱ መልስ ከመስጠቴ አስቀድሞ፣ በሰማይ ወዳለው አምላክ ጸለይኩ፡፡
\v 5 ከዚያ እንዲህ ሲል ምላሽ ሰጠሁ፣ “ታደርገው ዘንድ ፈቃድህ ከሆነ፣ እኔም አንተን ደስ አሰኝቼ ከሆነ፣ አባቶቼ የተቀበሩባትን ከተማ ኢየሩሳሌምን መልሼ እንድገነባ ወደዚያ እንድሄድ ፈቀድልኝ፡፡”
\v 6 ንጉሱ (ንገስቲቱ አጠገቡ ተቀምጣ ሳለ) እንደህ ሲል ጠየቀኝ፣ “እንድትሄድ ብፈቅድልህ፣ ለስንት ጊዜ በዚያ ትቆያለህ? ደግሞስ መቼ ትመለሳለህ?” እርሱም፣ ወደዚያ የምሄድበትንና ተመልሼ የምመጣበትን ቀን እንዳሳወቅሁት፣ ወዲያውኑ እንድሄድ ፈቃድ ሰጠኝ፡፡
\s5
\v 7 ደግሞም ለንጉሱ እንዲህ አልኩት፣ “ለአንተ ለሰጠሁት ታማኝ አገልግሎቴ እንደ ሽልማት አድርገህ፣ ከአፍራጦስ ወንዝ ባሻገር ለሚያስተዳድሩ ገዥዎች ደብዳቤ ስጠኝ፡፡ ወደ ይሁዳ ስገባና ስወጣ በግዛቶቻቸው በደህንነት መጓዝ እችል ዘንድ እንዲፈቅዱልኝ እባክህን ትዕዛዝ ስጣቸው፡፡
\v 8 እንዲሁም፣ እባክህን ደኖችህን ለሚያስተዳድረው ለአሳፍ ደብዳቤ ፃፍልኝ፣ ደግሞም በቤተ መቅደሱ አጠገብ የሚገኘውን ግንብ በሮች አምዶቹን ለማበጀት፣ የከተማዋን ቅሮች ለመጠገን፣ እና የምኖርበትን ቤት እንዲሰጠኝ ፃፍለት፡፡” እግዚአብሔር ለዚህ ስራ የሚያስፈልገኝን እንዳገኝ እየረዳኝ ስለነበር፣ ንጉሱ እንዲያደርግ የጠየቅኩትን አደረገልኝ ፡፡
\s5
\v 9 ወደ ይሁዳ ለመሄድ ተነሳሁ፡፡ ንጉሱ፣ እኔን እንዲያጅቡኝና እንዲጠብቁኝ አንዳንድ ፈረሰኛ የጦር መኮንኖችንና ወታደሮችን ላከ ፡፡ ገዥዎቹ ወደሚያስተዳድሩት ግዛት ስንደርስ፣ ከንጉሱ ዘንድ የተላከውን ደብዳቤ ሰጠኋቸው፡፡
\v 10 ነገር ግን ሁለቱ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ሖሮናዊው ሰንበላጥና አሞራዊው አገልጋይ ጦቢያ፣ እኔ መድረሴን ሲሰሙ የእስራኤልን ህዝብ የሚረዳ በመምጣቱ በጣም ተቆጡ፡፡
\s5
\v 11 ስለዚህም እኔ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቼ በዚያ ለሶስት ቀናት ቆየሁ፡፡
\v 12 በምሽት ከከተማ ወጣሁ፣ ከእኔ ጋርም ጥቂት ሰዎች ነበሩ፡፡ እኛ የነበረን እኔ የተቀመጥኩበት አንድ እንስሳ ብቻ ነበር፡፡ በኢየሩሳሌም አደርገው ዘንድ እግዚአብሔር በልቤ ስላስቀመጠው ነገር ለማንም ሰው ምንም አልተናገርኩም፡፡
\s5
\v 13 በሸለቆው መግቢያ አለፍኩና ከከተማው ቅጥር ውጭ ሄድኩ፡፡ ከዚያ በከተማዋ ዙሪያ ተዟዙሬ የቀበሮዎች ጉድጓድ በሚባለው ጉድጓድ በኩል አለፍኩ፡፡ ከዚያ ወደ ፋንድያ መድፊያ በር አለፍኩ፡፡ በኢየሩሳሌም ዙሪያ የሚገኙ ቅጥሮችን ሁሉ ዞሬ ተመለከትኩ፣ እናም ሁሉም በሮች ተሰባብረው ቅጥሮቹ ክፍት መሆናቸውን አየሁ፣ ደግሞም በቅጥሩ ዙሪያ የነበሩ የእንጨት በሮች ሁሉ አመድ እስኪሆኑ ተቃጥለው ነበር፡፡
\v 14 ከዚያ ወደ ፏፏቴ በር እና የንጉስ ገንዳ ወደሚባለው ገንዳ ሄድኩ፣ ነገር ግን የተቀመጥኩበት አህያ በጠባቡ መተላለፊያ ማለፍ አልቻለችም፡፡
\s5
\v 15 ስለዚህ ወደ ኋላ ዞሬ ወደ በቄድሮን ሸለቆ አጠገብ እያለፍኩ ወደ ኋላ ከመመለሴና ወደ ሸለቆው በር ወደ ከተማዋ ከመግባቴ አስቀድሞ በዚያ የነበሩ ቅጥሮችን ተመለከትኩ፡፡
\v 16 የከተማዋ ባለስልጣናት እኔ ወዴት እንደሄድኩ ወይም ምን እንዳደረግኩ አላወቁም ነበር፡፡ ለአይሁድ መሪዎች ወይም ለባለስልጣናቱ ወይም ለካህናቱ ወይም በእድሳቱ ስራ ለሚሳተፉ ለማናቸው ሌሎች ሰዎች ስለዚህ ምንም ነገር አልተናገርኩም፡፡
\s5
\v 17 እንዲህ አልኩ፣ “በከተማችን ላይ የደረሰውን መጥፎ ነገሮች ሁሉ ሁላችሁም በሚገባ ታውቃላችሁ፡፡ ከተማዋ ፍርስራሽ ሆናለች፣ ሌላው ቀርቶ በሮቿ ተቃጥለው ወድቀዋል፡፡ ኑ፣ የኢየሩሳሌምን ቅጥር እንደገና ለመገንባት ስራውን እንጀምር፡፡ እኛ ያንን ብናደርግ፣ ከዚህ በኋላ በከተማችን አናፍርም፡፡”
\v 18 ከዚያ ከንጉሱ ጋር በተነጋገርኩ ጊዜ እግዚአብሔር እንዴት በመልካምነቱ እንዲረዳንና ንጉሱ ምን እንዳለኝ ነገርኳቸው፡፡ እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱ፣ “ተነስተን የእድሳቱን ስራ እንጀምር!” ስለዚህም ይህን መልካም ሥራ ለመስራት ተነሱ፡፡
\s5
\v 19 ነገር ግን ሰንበላጥ፣ አሞናዊው አገልጋይ ጦቢያ፣ እና አረባዊው ጌሻም፣ እኛ ለመስራት ያቀድነውን ሰሙ፡፡ በእኛ ላይ ቀለዱ አፌዙብንም፡፤ እንዲህም አሉ፣ “ይህ እናንተ የምትሰሩት ስራ ምንድን ነው? በንጉሱ ላይ እያመጻችሁ ነውን?”
\v 20 እኔ ግን እንዲህ አልኳቸው፣ “በሰማይ ያለው አምላክ ስኬት ይሰጠናል፡፡ እናንተ ግን በዚህ ከተማ ላይ መብት የላችሁም፣ ተሳትፎ የላችም፣ በዚህ ላይ ህጋዊ መብት የላችሁም፣ በኢየሩሳሌም ከተማ ላይ ምንም ታሪካዊ መታሰቢያ የላችሁም፡፡”
\s5
\c 3
\p
\v 1 ከዚያ የእስራኤል ሊቀ ካህን የሆነው ኤልያብ፣ ከሌሎች ካህናት ጋር የበጎች በር የተባለውን እንደገና ሰሩ፡፡ ይህንንም ለያህዌ ክብር ለዩት፣ እናም የመግቢያውን በሮች በስፍራው አቆሙ ቀጥሎ ቅጥሩን የመቶ ማማ እስከሚባለው ድረስ መልሰው ገነቡ፣ እናም ያህዌን ለማክበር ለዩት፡፡ እንዲሁም የሐንኤልን ማማ መልሰው ገነቡ፡፡
\v 2 ከእነርሱ ቀጥሎ፣ የኢያሪኮ ሰዎች መልሰው ይገነቡ ነበር፡፡ ከእነርሱ ቀጥሎ፣ የአምሪ ልጅ ዘኩር መልሶ ይገነባ ነበር፡፡
\s5
\v 3 የአሳ በር የሚባለውን የሃስና ልጆች ገነቡት፡፡ እነርሱ የእንጨት አምዶቹን ከመግቢያዎቹ በላይ አጋደሙ፣ ደግሞም በሮቹን በስፍራቸው አኖሩ፡፡ ከዚያ ጠንካራ ቁልፍ እንዲኖር መቀርቀሪያ እና መወርወሪያዎችን አበጁ፡፡
\v 4 ከእነርሱ ቀጥሎ፣ የአቆስ የልጅ ልጅ፣ የአርዮ ልጅ የሆነው ሜርሞት ቅጥሮቹን ለማጠናከር ጠገናቸው፡፡ ከእርሱ ቀጥሎ፣ የሜሴዜቤል የልጅ ልጅ፣ የበራክየ ልጅ የሆነው ሜሱላም የቅጥሩን ከፊል ጠገነ፡፡ ከእርሱ ቀጥሎ፣ የበዓና ልጅ ሳዶቅ የቅጥሩን ከፊል ጠገነ፡፡
\v 5 ከእርሱ ቀጥሎ፣ የተቁሖ ሰዎች ቅጥሩን በከፊል ጠገኑ፣ ነገር ግን የቴቁ መሪዎች አሰሪዎቻቸው እንዲሰሩ የሰጣቸውን ለመስራት አልፈለጉም፡፡
\s5
\v 6 የፋሴሐ ልጅ ዮዳሄ እና የበሶድያ ልጅ ሜሱላም አሮጌውን መግቢያ ጠገኑ፡፡ ከመግቢያው በላይ ያሉትን አምዶችም በስፍራቸው አደረጉ፣ እንዲሁም መቀርቀሪያዎችንና መወርወሪያዎችን መግቢያውን ለመቆለፍ አስገቡ፡፡
\v 7 ከእነርሱ ቀጥሎ፣ የገባኦንና ከምጽጳ ሰዎች የሆኑት ገባኦናዊው መልጥያ እና ሜሮኖታዊው ያዶን፣ ከባህሩ ማዶ የሚገኘው አውራጃ ገዢ የሚኖርበትን ክፍል ጠገኑ፡፡
\s5
\v 8 ከእርሱ ቀጥሎ፣ የሖርሃያ ልጅ ዑዝኤል፣ እና ሐናንያ ነበሩ፣ ነገር ግን እነርሱ እስከ ሰፊው ቅጥር ድረስ ያለውን ክፍል ሰሩ፡፡ ሐርሃያ ወርቅ አንጥረኛ፣ ሐናንያ ደግሞ ሽቶ ቀማሚ ነበሩ፡፡
\v 9 ከእርሱ ቀጥሎ፣ የኢየሩሳሌምን ከፊል አውራጃ የሚገዛው የሆር ልጅ ረፋ የቅጥሩን ከፊል መልሶ ሰራ፡፡
\v 10 ከእርሱ ቀጥሎ፣ የኤርማፍ ልጅ ይዳያ ከቤቱ አጠገብ የሚገኘውን ቅጥር ከፊሉን መልሶ ሰራ፡፡ ከእርሱ ቀጥሎ የአሰቦንያ ልጅ ሐጡስ የቅጥሩን ከፊል መልሶ ሰራ፡፡
\s5
\v 11 የሃሪም ልጅ መልክያ፣ እና የፈሐት ሞዓብ ልጅ አሱብ የቅጥሩን ከፊል ጠገነ፣ እንዲሁም የእቶን ማማ የተባለውን መልሶ ሰራ፡፡
\v 12 ከእርሱ ቀጥሎ፣ ሌላውን የኢየሩሳሌም ከፊል አውራጃ የሚገዛው የአጦሎኤስ ልጅ ሰሎም የቅጥሩን ከፊል መልሶ ሰራ፡፡ ሴት ልጆቹ በስራው ረዱት፡፡
\s5
\v 13 ሐኖንና የዛኖ ከተማ ሰዎች የሸለቆ መግቢያ ተብሎ የሚጠራውን መልሰው ሰሩ፡፡ እነርሱም መግቢያዎቹን መልሰው በስፍራቸው አቆሙ፣ ደግሞም መወርወሪያዎቹንና መቀርቀሪያዎቹን በሮቹን ለመቆለፊያ አበጁ፡፡ ቅጥሩን የቆሻሻ መጣያ በር እስከሚባለው ድረስ 460 ሜትር መልሰው ሰሩ፡፡
\s5
\v 14 የበት ሐካሪም አውራጃ ገዢ የሆነው የረካብ ልጅ መልክያ የቆሻሻ መጣያ በር ተብሎ የሚጠራውን መልሶ ሰራ፡፡ መግቢያውን ለመቆለፊያ መወርወሪያዎቹንና ፍርግርጎቹን መልሶ ሰራ፡፡
\v 15 የምጽጳ አውራጃን የሚገዛው የኮልሐዜ ልጅ ሰሎም የፏፏቴ በር ተብሎ የሚጠራውን መግቢያ መልሶ ሰራ፡፡ ከመግቢያው በላይ ጣራ አበጀ፣ በሩን ለመቆለፍ መግቢያዎቹንና መቀርቀሪያዎቹን እንዲሁም ፍርግርጎቹን አበጀ፡፡ ከዳዊት ከተማ ተነስቶ ቁልቁል እስከ ሼላን ገንዳ አጠገብ ከንጉሱ መናፈሻ ቀጥሎ ቅጥሩን ገነባ፡፡
\s5
\v 16 ከእርሱ ቀጥሎ፣ የቤት ዱር አውራጃን በከፊል የሚገዛው የዓዝቡቅ ልጅ ነህምያ፣ በዳዊት ከተማ ውስጥ እስከ መቃብር ስፍራ ያለውን ቅጽር፣ ሰው ሰራሽ እስከ ሆነው መዋኛ እና እስከ ፈረስ ቤቶች ድረስ መልሶ ሰራ፡፡
\v 17 ከእርሱ ቀጥሎ፣ ካህናቱን የረዱት ብዙ የሌዊ ትውልዶች የቅጥሩን ክፍሎች መልሰው ሰሩ፡፡ የባኒ ልጅ ሬሁ አንዱን ክፍል መልሶ ሰራ፡፡ የቅኢላን ግማሽ አውራጃ የሚገዛው ሐሽብያ የአውራጃውን ህዝብ ወክሎ ቀጣዩን ክፍል መልሶ ሰራ፡፡
\s5
\v 18 የቅዒሊን ቀሪውን ግማሽ አውራጃ የሚገዛው የኤንሐዳድ ልጅ በዋይና ከሌሎች የሌዊ ትውልዶች ጋር ቀጣዩን ክፍል መልሶ ሰራ፡፡
\v 19 ከእርሱ ቀጥሎ፣ የምጽጳ ከተማን የሚገዛው የኢያሱ ልጅ ኤጽር እስከ ጦር መሣሪያ ግምጃ ቤት ደጃፍ፣ መአዘን ላይ እስከ ሚገኘው የቅጥሩ ቅስት ድረስ ያለውን ሌላውን ክፍል መልሶ ሰራ፡፡
\s5
\v 20 ከእርሱ ቀጥሎ፣ የዘባይ ልጅ ባሮክ የቀረውን የቅጥሩን ክፍል በታላቅ ትጋት መልሶ ሰራው፡፡ ከሊቀ ካህኑ ከኤልያሴብ ቤት በር እስከ ራሱ እስከ ባሮክ ቤት መጨረሻ ድረስ ያለውን ክፍል መልሶ ሰራ፡፡
\v 21 ከእርሱ ቀጥሎ፣ የአቆስ የልጅ ልጅ፣ የኦርዮ ልጅ የሆነው ሜሪሞት ከኤልያሴብ ቤት በር እስከ ራሱ እስከ ሜሪምት ቤት መጨረሻ ያለውን ክፍል መልሶ ሰራ፡፡
\s5
\v 22 ከእርሱ ቀጥሎ፣ ብዙ ካህናት የቅጽሩን ክፍሎች መልሰው ሰሩ፡፡ በኢየሩሳሌም አቅራቢያ ያሉ ካህናት አንድ ክፍል መልሰው ሰሩ፡፡
\v 23 ከእነርሱ ቀጥሎ፣ ብንያምና አሱብ ከቤታቸው ፊት ለፊት ያለውን አንድ ክፍል መልሰው ሰሩ፡፡ የሖናንያ የልጅ ልጅ፣ የመፅሤያ ልጅ የሆነው ዓዛርያስ ቀጣዩን ክፍል መልሶ ሰራ፡፡
\v 24 ከእርሱ ቀጥሎ፣ ከዓዛርያስ ቤት ቅጽሩ በጥቂቱ ዞር እስከሚልበት ድረስ ያለውን አንዱን ክፍል የኤንሐዳድ ልጅ ቢንዊ መልሶ ሰራ፡፡
\s5
\v 25 ከእርሱ ቀጥሎ፣ ቅጥሩ ከሚዞርበትና የመጠበቂያ ማማው ከላይኛው ቤተ መንግስት ከፍ ብሎ እስከሚታይበት ድረስ ያለውን አንድ ክፍል የኡዛይ ልጅ ፉላል መልሶ ሰራ፡፡ መጠበቂያ ማማው ጠባቂዎቹ ከሚኖሩበት አደባባይ አጠገብ ይገኛል፡፡ ከፉላል ቀጥሎ፣ የፋሮስ ልጅ ፈዳ ቅጥሩን መልሶ ሰራ፡፡
\v 26 ከእርሱ ቀጥሎ የቤተ መቅደስ አገልጋዮች በትልቁ ማማ ምስራቅ አቅጣጫ ፊቱን ወደ ውሃ በር ያደረገውን አንድ ክፍል መልሰው ጠገኑ፡፡
\v 27 ከእርሱ ቀጥሎ፣ የተቁሐ ሰዎች ከትልቁ ማማ ፊት ለፊት እስከ ኦፌል ቅጥር ድረስ ያለውን ሁለተኛውን ክፍል መልሰው ሰሩ፡፡
\s5
\v 28 ከፈረስ መግቢያ ሰሜን አንስቶ ያለውን ቅጽር አንድ የካህናት ቡድን መልሶ ሰራው፡፡ እያንዳንዱ ካህን ከቤቱ ፊት ለፊት ያለውን ክፍል መልሶ ሰራ፡፡
\v 29 ከእነርሱ ቀጥሎ፣ የኢሜር ልጅ ሳዶቅ ከቤቱ ፊት ለፊት ያለውን ክፍል መልሶ ሰራ፡፡ ከእርሱ ቀጥሎ፣ በስተምስራቅ የሚገኘው በር ጠባቂ የነበረው የሴኬንያ ልጅ ሸማያ ቀጣዩን ክፍል መልሶ ሰራ፡፡
\v 30 ከእርሱ ቀጥሎ፣ የሰሌምያ ልጅ ሐናንያ፣ እና የሴሌፍ ስድስተኛ ልጅ አንድ ክፍል መልሰው ሰሩ፡፡ ያም እነርሱ መልሰው የጠገኑት ሁለተኛው ክፍል ነበር፡፡ ከእርሱ በኋላ የበራክያ ልጅ ሜሱላም እርሱ ይኖርበት በነበረው ቤት ፊት ለፊት የሚገኙትን ቅጥሮች ክፍል መልሶ ሰራ፡፡
\s5
\v 31 ከእነርሱ ቀጥሎ፣ ወርቅ አንጣሪው መልክያ ከቀጠሮ በር ማዕዘን ላይ እስከሚገኘው የላይኛው መኖሪያዎች የሚገኙትን የቤተ መቅደስ አገልጋዮችና ነጋዴዎች እስከ ሚገለገሉባቸው ህንጻዎች ድረስ ያለውን ክፍል መልሶ ሰራ፡፡
\v 32 ሌሎች ወርቅ አንጥረኞች፣ ከነጋዴዎች ጋር ሆነው የቅጥሩን የመጨረሻ ክፍያ እስከ በጎች በር ድረስ መልሰው ሰሩ፡፡
\s5
\c 4
\p
\v 1 ሰንበላጥ የከተማዋን ቅጥር እንደገና እየሰራን መሆኑን በሰማ ጊዜ፣ እኛ ኢየሩሳሌምን እንደ ገና መገንባታችን በውስጡ እንደ እሳት አቃጠለው፣ እናም በጣም ተቆጥቶ በአይሁዶች ላይ በጥላቻ ተሞልቶ ተናገረ፡፡
\v 2 ከሰማርያ በመጡት አማካሪዎቹና የጦር አለቆቹ ፊት እንዲህ አለ፣ “እነዚህ አይሁዶች ራሳቸውን ችለው መቆም አይችሉም፣ ምን እያደረጉ ያሉ መስሏቸዋል? ከተማዋን እንደገና ገንብተው ራሳቸው ሊኖሩባት ነውን? ቤተ መቅደሱን እንደገና ገንብተው ካህናቱ ለያህዌ የሚያቀርቡትን መስዋእት ሁሉ ሊያቀርቡ ነውን? በአንዲት ቀን እንዲህ ያለውን ታላቅ ሥራ ይጨርሳሉን? እነዚህን የተቃጠሉና ከጥቅም ውጭ የሆኑ ድንጋዮች ቅጥሩን እንደገና ለመገንባት ሊጠቀሙበትና ለከተማዋ ዳግም ሕይወት ሊሰጧት ይችላሉን?
\v 3 ጦቢያ ከሰንበላጥ አጠገብ ቆሞ ነበር፡፡ እርሱም እንዲህ አለ፣ “ያ እነርሱ የሚገነቡት ቅጥር እጅግ ደካማ ነው፤ ትንሽ ቀበሮዎች ቢወጡበት እንኳን ይፈርሳል፤ የእነርሱ የድንጋይ ቅጥር ቀበሮ ቢወጣበት ይፈርሳል!”
\s5
\v 4 ከዚያ እኔ እንዲህ ስል ጸለይኩ፣ “አምላካችን ሆይ፣ ስማን፣ እነርሱ እየቀለዱብን ነው! የስድባቸውን ቃል ወደ ራሳቸው እንዲመለስ አድርግ! ጠላቶቻቸው እንዲመጡባቸውና እንዲይዟቸው ወደ ባዕድ ምድርም እንዲያሳድዷቸው አድርግ!
\v 5 እነርሱ በደለኞች ናቸው፡፡ በደላቸውን ከእነርሱ አታርቅ በፊትህ ለሰሩት ኃጢአት ዋጋ ይክፈሉ፡፡ በስድቦቻቸው፣ ቅጥሩን መልሰው የሚገነቡትን በጣም አስቆጥተዋል!”
\v 6 ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን፣ ሰራተኞቹ ከጠቅላላው በከተማይቱ ዙሪያ ከሚገኘው የቅጥሩ ከፍታ ግማሽ ያህሉን ሰሩ፡፡ ይህን ማከናወን የቻሉት ሊሰሩ የሚችሉትን በሙሉ ልባቸው ለመስራት ስለፈለጉ ነበር፡፡
\s5
\v 7 ነገር ግን ሰንበላጥ፣ ጦብያ፣ ዐረቦች፣ አሞናዊያን፣ እና አሽዶዳዊያን የቅጥሩ ስራ መሰራቱ እንደ ቀጠለና የፈረሰውን ቅጥር እየጠገንን መሆኑን ሲሰሙ በጣም ተቆጡ፡፡
\v 8 እነርሱም መጥተው የኢየሩሳሌምን ሰዎች ለመውጋት እና በከተማይቱ ውስጥ ሀብት ለመፍጠር በአንድነት ዕቅድ አወጡ፡፡
\v 9 እኛ ግን ቅጥሩን መልሰን በመገንባታችን እጅግ በተቆጡት በእነዚህ ሰዎች ምክንያት ወደ አምላካችን ጸለይን፣ ደግሞም ከተማዋን ቀንና ሌሊት ይጠብቁ ዘንድ ወንዶችን በቅጥሮቹ ዙሪያ አቆምን፡፡
\s5
\v 10 ከዚያ የይሁዳ ሰዎች እንዲህ ማለት ጀመሩ፣ “ቅጥሩን የሚሰሩት ወንዶች መላ አቅማቸውን እየተጠቀሙ ነው፡፡ ልናነሳው የሚገባ እጅግ ብዙ ፍርስራሽ አለ፤ እኛ ይህን ስራ መጨረስ አልቻልንም ስራው እጅግ በዝቶብናል፡፡
\v 11 ከዚህም ባሻገር፣ ጠላቶቻችን እንዲህ እያሉ ነው! ‘አይሁዶች እኛን ከማየታቸው አስቀድሞ፣ በእነርሱ ላይ እንውጣባቸውና እንግደላቸው፣ የቅጥሩን ስራቸውንም እናስቁማቸው!”
\s5
\v 12 በጠላቶች አቅራቢያ ይኖሩ የነበሩ አይሁዶች ብዙ ጊዜ ወደ እኛ እየመጡ ጠላቶቻችን በእኛ ላይ ሊፈጽሙ የሚያስቡትን ክፉ እቅድ ይነግሩን ነበር፡፡
\v 13 ስለዚህ ከእያንዳንዱ ቤተሰብ ቅጥሩን እንዲጠብቁ ሰዎችን አቆምኩ፡፡ እነዚህ ሰዎች ቅጥሩን በቀላሉ መሻገር በሚቻልባቸው በቅጥሩ ዝቅተኛ ስፍራዎች እንዲቆሙ ተደረገ፡፡ እነርሱም ሰይፎቻቸውን ጦሮቻቸውን፣ እና ደጋኖቻቸውንና ቀስቶቻቸውን ይዘው ይጠብቁ ነበር፡፡
\v 14 ከዚያ እያንዳንዳቸውን ከተመለከትኩ በኋላ፣ መሪዎችንና ሌሎች ሹማምንቶችን እንዲሁም ሌሎች ብዙ ሰዎችን ሰብስቤ እንዲህ አልኳቸው፣ “ጠላቶቻችንን አትፍሯቸው! እግዚአብሔር ታላቅና በክብር የተሞላ እንደሆነ አስቡ! እናም ቤተሰባችሁን፣ ወንድና ሴቶች ልጆቻችሁን፣ ሚስቶቻችሁን እና ቤቶቻችሁን ለመጠበቅ ተዋጉ!”
\s5
\v 15 ጠላቶቻችን፣ ዕቅዶቻቸውን እንደሰማን አወቁ፣ እግዚአብሔርም ስራችንን ለማስቆም ያወጡትን ዕቅድ ከንቱ አደረገባቸው፡፡ ስለዚህ እኛ ሁላችንም ወደ ፊት እንሰራበት ወደነበረው ወደዚያው ስፍራ ቅጥሩን ለመገንባት ተመለስን፡፡
\v 16 ነገር ግን ከዚያ በኋላ፣ በዚያ ከነበሩት ወንዶች ግማሾቹ ብቻ የቅጥሩን ሥራ ይሰሩ ነበር፡፡ ሌሎቹ ጦሮቻቸውን፣ ጋሻዎቻቸውን፣ ደጋኖቻቸውንና ቀስቶቻቸውን ይዘውና የጦር ልብሶቻቸውን ለብሰው ይጠብቁ ነበር፡፡ መሪዎቹ የይሁዳን ሕዝብ ይጠብቁ ነበር፡፡
\s5
\v 17 መሪዎች ቅጥሩን የሚሰሩትንና የጉልበት ሥራ የሚሰሩትን ይጠብቁ ነበር፡፡ እያንዳንዱ ሰው በአንድ እጁ ቅጥሩን ሲገነባ በሌላው እጁ መሳሪያ ይይዛል፡፡
\v 18 ቅጥሩን የሚገነባ ሁሉ በወገቡ ሰይፍ ይታጠቃል፡፡ ጠላቶቻችን ቢመጡ መለከት የሚነፋው ሰው ከእኔ አጠገብ ይሆናል፡፡
\s5
\v 19 ከዚያ ለባለስልጣናቱ፣ ለሌሎች ታላላቅ ሰዎች፣ እና ለሌሎች ሰዎች እንዲህ አልኳቸው፣ “ይህ ሥራ ታላቅ ነው፣ እኛ በቅጥሩ ዙሪያ የምንገኝ አንዳችን ከሌላችን ተራርቀን እንገኛለን፡፡
\v 20 የመለከት ድምጽ ስትሰሙ፣ መለከቱ በሚነፋበት ስፍራ ተሰብስቡ፡፡ አምላካችን ለእኛ ይዋጋልናል!”
\s5
\v 21 ስለዚህም ስራችንን መስራት ቀጠልን፡፡ ከህዝቡ እኩሌታው ቀኑን ሙሉ ጦሩን ይዞ፣ ጠዋት ጸሀይ ስትወጣ አንስቶ ምሽት ከዋክብት እስኪታዩ ድረስ ጥበቃ ያደርጋል፡፡
\v 22 በዚያን ጊዜ፣ እኔ ለህዝቡ፣ “ለእያንዳንዱ ሰራተኛ እና ለረዳቱ በምሽት ኢየሩሳሌም ውስጥ እንዲቆዩ ይነገራቸው፡፡ ያንን በማድረግ፣ በምሽት እኛን መጠበቅና በቀን ቅጥሩን መገንባት ይችላሉ” በማለት እናገራሁ፡፡
\v 23 በእነዚያ ጊዜያት፣ ልብሴን አላወልቅም፣ የጦር መሳሪያዬንም ሁልጊዜ እይዛለሁ፡፡ ወንድሞቼ፣ አገልጋዮቼ እና እኔን የሚከተሉ ወንዶች እና ዘብ ሆነው የሚያገለግሉ ሁሉ ይህንኑ ያደርጋሉ፡፡ ሁላችንም ውሃ ለመጠጣት ስንሄድ እንኳን የጦር መሳሪያዎችንን እንደያዝን ነበር፡፡
\s5
\c 5
\p
\v 1 ቆይቶ፣ ሌሎቹ አንዳንድ አይሁዶች በሚያደርጉት ብዙዎቹ ወንዶችና ሚስቶቻቸው ፍትህ ለማግኘት ጮኹ፡፡
\v 2 አንዳንዶቹ እንዲህ አሉ፣ “እኛ ብዙ ልጆች አሉን፡፡ በልተን ለማደርና በህይወት ለመቆየት እንኳን ብዙ እህል ያስፈልገናል፡፡”
\v 3 ሌሎቹ ደግሞ እንዲህ አሉ፣ “በዚህ የረሃብ ወቅት የምንበላው እህል ለማግኘት የእርሻ መሬታችንን፣ የወይን ተክላችንንና ቤቶቻችንን ማስያዝ ግድ ሆኖብናል፡፡
\s5
\v 4 ሌሎቹም እንዲህ አሉ፣ “ለእርሻ መሬቶቻችንና ለወይን ተክላችን ለንጉሱ ግብር ለመክፈል ገንዘብ መበደር የግድ ሆኖብናል፡፡
\v 5 እኛም እንደ ሌሎቹ አይሁዶች አይሁዳውያን ነን፡፡ የእነርሱ ልጆች ለእነርሱ ጠቃሚ እንደሆኑ ሁሉ፤ የእኛም ልጆች ለእኛ እንደዚያው ናቸው፡፡ ነገር ግን መክፈል የሚገባንን ለመክፈል ስንል ልጆቻችንን ለባርነት ለመሸጥ ተገደናል፡፡ አንዳንድ ሴት ልጆቻችንን አሁን ለባርነት ሸጠናል፡፡ የእርሻ መሬቶቻችንና የወይን ተክሎቻችን ከእኛ ተወስደዋል፣ ስለዚህም መክፈል ያለብንን ገንዘብ ለመክፈል ገንዘቡ የለንም፡፡”
\s5
\v 6 እነዚህን እነርሱ የተጨነቁባቸውን ነገሮች በሰማሁ ጊዜ በጣም ተቆጣሁ፡፡
\v 7 ስለዚህም ማድረግ ያለብኝን ነገር አሰብ፡፡ ለመሪዎችና ለሹማምንቱ እንዲህ አልኳቸው፣ “ገንዘብ ሲበደሯችሁ የገዛ ዘመዶቻችሁን ወለድ ታስከፍላላችሁ፡፡ ይህ ልክ እንዳልሆነ ታውቃላችሁ!” ከዚያም ክስ እንዲያቀርቡባችሁ ብዙ ሰዎችን በእነርሱ ላይ ሰብስቤ ጠራሁ፡፡
\v 8 እንዲህም አልኳቸው፣ “አንዳንድ አይሁዳዊ ወገኖቻችን የአህዛብ ባሪያዎች ለመሆን ራሳቸውን ለመሸጥ ተገደው ነበር፡፡ የቻልነውን ያህል፣ መልሰን ገዝተናቸው ነበር፡፡ ነገር ግን አሁን እናንተ የገዛ ወገኖችሁን እንኳን እየሸጣችሁ ነው፤ ይኸውም የገዛ ወገኖቻቸው ወደ ሆኑ አይሁዶች ተመልሰው ይሸጡ ዘንድ ነው!” ይህን ስናገራቸው፣ ምላሽ አልሰጡም፡፡ አንዲት ቃል እንኳን አልመለሱም፡፡
\s5
\v 9 ከዚያ እንዲህ አልኳቸው፣ “የምታደርጉት ነገር ክፉ ነው፡፡ እግዚአብሔርን ልትታዘዙና ትክክል የሆነውን ልታደርጉ አይገባችሁምን? ይህን ብታደርጉ፣ ጠላቶቻችን በንቀት እንዳያዩን ማድረግ ትችላላችሁ፡፡
\v 10 እኔና አይሁዳዊ ወገኖቼ እንዲሁም አገልጋዮቼ ለህዝቡ ገንዘብና እህል አበደርን፡፡ ነገር ግን ሁላችንም ከእነዚህ ብድሮች በአንዱም ወለድ መቀበል እናቁም፡፡
\v 11 እንደዚሁም፣ የወሰዳችሁባቸውን የእርሻ መሬቶቻቸውን፣ የወይን ስፍራቸውን፣ የወይራ ዛፍ ቦታቸውን እንዲሁም ቤቶቻቸውን ልትመልሱላቸው ይገባል፡፡ እንደዚሁም ገንዘብ፣ እህል፣ ወይን፣ እና የወይራ ዘይት ሲበደሯችሁ ያስከፈላችኋቸውን ወለዶች ልትመልሱላቸው ይገባል፡፡ ይህን ዛሬውን ልታደርጉ ይገባል!”
\s5
\v 12 መሪዎች እንዲህ ሲሉ መለሱ፣ “ያልከንን እናደርጋለን፡፡ እንዲሰጡን ያስገደድናቸውን ነገር ሁሉ እንመልስላቸዋለን፣ ደግም ሌላ ተጨማሪ ነገር እንዲሰጡን አንጠይቅም፡፡” ከዚያ ካህናቱን ሰበሰብኩ፣ እናም ቃል የገቡትን እንዲያደርጉት አስማልኳቸው፡፡
\v 13 የክህነት ልብሴን እጥፋት አራግፌ እንዲህ አልኳቸው፣ “ልታደርጉት አሁን ቃል የገባችሁትን ባታደርጉ፣ እኔ ልብሴን እንዳራገፍኩ እግዚአብሔር ያራግፋችኋል፡፡” እነርሱም “አሜን እንዳልከው ይሁን!” ሲሉ መለሱ፤ ደግሞም ያህዌን አወደሱ፡፡ ከዚያ ለማድረግ ቃል የገቡትን አደረጉ፡፡
\s5
\v 14 አርጤክስስ የፋርስ ንጉስ በነበረበት በሀያኛው ዓመት የይሁዳ ገዥ ሆኜ ተሹሜ ነበር፡፡ ከዚያን ጊዜ አንስቶ እስከ ሰላሳ ሁለተኛው የንግስናው አመት ድረስ እኔም ሆንኩ የእኔ ሹማምንት ገዥ በመሆኔ ለቀለብ የተፈቀደልኝን ገንዘብ አልተቀበልንም፡፡
\v 15 ከእኔ አስቀድሞ ገዥ የነበሩ ሰዎች በየቀኑ አርባ የብር ሳንቲሞች ለምግብና ለወይን በመጠየቅ በህዝቡ ላይ ሸክም አክብደውበት ነበር፡፡ አገልጋዮቻቸው ጭምር ህዝቡን ይጨቁኑ ነበር፡፡ እኔ ግን ያን አላደረግኩም፣ ምክንያቱም ለእግዚአብሔር ክብር መስጠት እፈልግ ነበር፡፡
\s5
\v 16 በዚህ ቅጥር ላይ መስራቴንም ቀጠልኩ፣ እኛም ከህዝቡ ምንም መሬት አልገዛንም፡፡ ለእኔ የሚሰሩት ሁሉ በቅጥሩ ስራ ተባበሩን፡፡
\v 17 እንዲሁም፣ በየዕለቱ ከገበታችን አይሁዶችንና ሹማምንቱን፣ አንድ መቶ ሀምሳ ሰዎችን፣ እና በዙሪያችን ካሉ አገሮች የመጡ ጎብኚዎችን እንመግብ ነበር፡፡
\s5
\v 18 በየቀኑ አገልጋዮቼ አንድ በሬ፣ ስድስት ሙክቶች እና የዶሮዎች ስጋ እንዲያቀርቡ አደርግ ነበር፡፡ በየአስሩ ቀን ብዙ የሆነ አዲስ ወይን ጠጅ አቀርብላቸው ነበር፡፡ ነገር ግን ህዝቡ እጅግ ብዙ ግብር በመክፈል ጫና እንደሚበዛበት አውቅ ነበር፣ ስለዚህም እንደ አገረ ገዥ የተፈቀደልኝን ገንዘብ እንኳን አልቀበልም ነበር፡፡
\v 19 አምላኬ፣ አስበኝ፣ እናም ለዚህ ህዝብ ላደረግኩት ሽልማት ስጠኝ፡፡
\s5
\c 6
\p
\v 1 ምንም እንኳን እስከ አሁን በሮቹን በመግቢያዎቹ ላይ ገና ባንገጥምም፣ የቅጥሩን ሥራ መጨረሳችንንና ያልተጠገነ የፈረሰ ስፍራ አለመኖሩን ሰንበላጥ፣ ጦቢያ፣ ጌሳምና ሌሎች ጠላቶቻችን ሰሙ፡፡
\v 2 ስለዚህ ሰንበላጥና ጌሳም እንዲህ የሚል መልዕክት ወደ እኔ ላኩ፣ “ከኢየሩሳሌም በስተሰሜን በሚገኘው ኦኖ በሚባለው ሜዳ መጥተህ እንነጋገር፡፡” ነገር ግን ይህን ያሉት እኔን ለመጉዳት አስበው እንደነበር ግልጽ ነው፡፡
\s5
\v 3 ስለዚህም እንዲህ ብለው እንዲነግሯቸው መልዕክተኞችን ላክሁ፣ “ከፍ ያለ ስራ እየሰራሁ ነው፣ እናም ወደዚያ ልሄድ አልችልም፡፡ እኔ ከእናንተ ጋር ለመነጋገር ወደዚያ በመሄድ ይህ ስራ መስተጓጎል አይኖርበትም፡፡
\v 4 እነርሱ ይህንኑ መልዕክት አራት ጊዜ ወደ እኔ ላኩ፣ እኔም በእያንዳንዱ ወቅት ተመሳሳይ መልስ ሰጠኋቸው፡፡
\s5
\v 5 ከዚያም ሰንበላጥ አምስተኛውን መልዕክት አስይዞ አንዱን አገልጋዩን ወደ እኔ ላከ፡፡ ይህኛው መልዕክት በጽሁፍ ነበር፣ በእርግጥ ማህተም ያልተደረገበትና ያልታሸገ ደብዳቤ ነበር፡፡
\v 6 በመልዕክቱ የተጻፈው ይህ ነበር፡ “በባቢሎን ንጉስ ላይ አመጽ ለማስነሳትና አንተም የእስራኤል ንጉስ ለመሆን አቅደህ አንተና ሌሎች አይሁዶች ቅጥሩን እንደገና እየገነባችሁ እንደሆነ በአቅራቢያ ባሉ አገሮች ያሉ አንዳንድ ሰዎች ወሬ ሰምተዋል፡፡ እውነቱ ይህ መሆኑን ጌሳም ነግሮናል፡፡
\s5
\v 7 ደግሞም ሰዎች፣ አንተ ነህምያ፣ አሁን የአይሁድ ንጉስ መሆንህን እንዲያውጁ ነቢያትን መሾምህን እየተናሩ ነው፡፡ ንጉስ አርጤክስስ በእርግጥ ይህን ወሬ መስማቱ አይቀርም፣ ያን ጊዜ ትልቅ ችግር ላይ ትወድቃለህ፡፡ ስለዚህ ተገናኝተን በዚህ ጉዳይ ላይ መነጋገር እንደሚኖርብን አሳስባለሁ፡፡”
\s5
\v 8 ያን መልዕክት ካነበብኩ በኋላ መልዕክተኛው ወደ ሰንበላጥ ይህን መልዕክት መልሶ እንዲያደርስ ላክሁ፣ “ከምትናገረው ውስጥ አንዱም እውነት አይደለም፡፡ ይህን የምትለው ከገዛ ልብህ ፈጥረህ ነው፡፡”
\v 9 ይህንን የምለው እነርሱ እኛን ለማስፈራራት እየሞከሩ እንደነበር ስለማወቅ ነው፣ ስለዚህም እንዲህ ብለው ያስባሉ፣ “ከዚህ በኋላ ቅጥሩን ለመስራት ፍጹም ተስፋ ይቆርጣሉ፣ ስራውም በፍጹም ከፍጻሜ አይደርስም፡፡” ስለዚህም እኔ፣ “አምላኬ ሆይ፣ ብርታትን ስጠኝ፡፡” ስል ጸለይኩ፡፡
\s5
\v 10 አንድ ዕለት የመሔጣብኤል የልጅ ልጅ፣ የድልያ ልጅ፣ ከሆነው ከሸማያ ጋር ለመነጋገር ሄድኩ፡፡ ከእርሱ ጋር ለመነጋገር ወደ ቤቱ ሄድኩ፡፡ ከቤቱ እንዳይወጣ ትዕዛዝ ተሰጥቶት ነበር፡፡ እርሱም እንዲህ አለኝ፣ “አንተና እኔ ከቤተ መቅደሱ ውስጠኛ ክፍሎች ወደ አንዱ መግባትና በሮቹን መቆለፍ አለብን፡፡ ዛሬ ምሽት ሊገድሉህ ይመጣሉ፡፡”
\v 11 እኔም እንዲህ ስል መለስኩለት፣ “እኔ እንዲያ ያለ ሰው አይደለሁም! ህይወቴን ለማትረፍ ራሴን ቤተመቅደስ ውስጥ ሸሽቼ ገብቼ አልደብቅም! አይ፣ ያንን አላደርግም!”
\s5
\v 12 የተናገረውን አሰላሰልኩ፣ ሸማያ እግዚአብሔር ያላለውን እንደነገረኝ አወቅሁ፡፡ ጦቢያ እና ሰንበላጥ ቀጥረውት ነበር፡፡
\v 13 እንዲያስፈራራኝ እነርሱ ቀጥረውት ነበር፡፡ እነርሱ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት እንዳልጠብቅ በመቅደስ ውስጥ በመደበቅ እንድበድል ይፈልጉ ነበር፡፡ ያንን ባደርግ፣ ስሜን ያጠፉና ከዚያም ያዋርዱኛል፡፡
\v 14 ስለዚህም እንዲህ ስል ጸለይኩ “አምላኬ ሆይ፣ ጦቢያና ሰንበላጥ ያደረጉትን አትርሳ፡፡ ነቢይቱ ኖዓድያ እና ሌሎች ነቢያት ሊያስፈራሩን የሞከሩትን አትርሳ፡፡”
\s5
\v 15 በኤሉል ወር በወሩ ሃያ አምስተኛው ቀን የቅጥሩን ጥገና አጠናቀቅን፡፡ ጠቅላላውን ስራ በሀምሳ ሁለት ቀናት አጠናቀቅን፡፡
\v 16 በአቅራቢያችን በሚገኙ አገሮች የሚኖሩ ጠላቶቻችን ይህንን ሲሰሙ፣ በጣም ፈሩ፣ ዕፍረትም ተሰማቸው ምክንያቱም ይህን ሥራ እንድናጠናቅቅ የረዳን እግዚአብሔር እንደሆነ አውቀው ነበር፡፡
\s5
\v 17 በዚህ ጊዜ ውስጥ፣ የአይሁድ መሪዎች ብዙ መልዕክቶችን ወደ ጦቢያ ይልኩ ነበር፣ ጦቢያም መልሶ መልዕክቶችን ወደ እነርሱ ይልክ ነበር፡፡
\v 18 በይሁዳ ያሉ ብዙ ሰዎች ታማኝታቸውን በመሀላ ለጦቢያ አረጋግጠውለት ነበር፡፡ እርሱም የኤራ ልጅ የሴኬንያ አማት ሲሆን፣ የጦቢያ ወንድ ልጅ የቤሪክያን ልጅ የሆሐና የሚሹ ሀላምን ሴት ልጅ አግብቶ ነበር፡፡
\v 19 ሰዎች ብዙ ጊዜ እኔ ባለሁበት ጦቢያ ስለ ሰራቸው መልካም ስራዎች ይናገሩና፣ ከዚያ እኔ የተናገርኩትን እያንዳንዱን ነገር ይነግሩታል፡፡ ስለዚህም ጦቢያ እኔን ለማስፈረራት በርካታ ደብዳቤዎችን ወደ እኔ ይልክልኝ ነበር፡፡
\s5
\c 7
\p
\v 1 ቅጥሩ ተሰርቶ ከተጠናቀቀና በሮቹም በስፍራቸው ከቆሙ በኋላ፣ የቤተ መቅደሱ ጠባቂዎችና የዝማሬ አባላቱ እንዲሁም የተቀሩት የሌዊ ትውልዶች በየስራ መደባቸው ተመደቡ፡፡
\v 2 ወንድሜን አናኒን የኢየሩሳሌም ገዥ አድርጌ ሾምኩት፡፡ እርሱ ከብዙ ሌሎች ሰዎች ይልቅ ታማኝና እግዚአብሔርን የሚፈራና የሚያከብር ሰው ነበር፡፡ በተጨማሪም ሐናንያ በኢየሩሳሌም ለሚገኘው የከተማይ ግንብ አዛዥ ሆኖ ተሾሙ፡፡
\s5
\v 3 እነርሱን እንዲህ አልኳቸው፣ “ፀሀይ ሞቅ እስክትል የኢየሩሳሌምን መግቢያ በሮች አትክፈቱ፡፡ በሮችን የምትቆልፉትና የበሮችን መቀርቀሪያዎች የምትዘጉት በር ጠባቂዎች መግቢያዎችን እየጠበቁ ሳለ ነው፡፡” አንዳንድ በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ሰዎችን ዘቦችና በከተማዋ ዙሪያ ያሉ ማረፊያዎችን ጠባቂዎች እንዲያደረጓቸው፤ እንዲሁም አንዳንዶችን ከራሳቸው ቤቶች አቅራቢያ ጠባቂ እንዲያደረጓቸው ነገርኳቸው፡፡
\v 4 የኢየሩሳሌም ከተማ ሰፊ ናት፣ ነገር ግን በዚያን ጊዜ በከተማዋ ብዙ ህዝብ አይኖርም ነበር፣ እንዲሁም ከቤቶቹ አንዱንም እንደገና አልገነቡም ነበር፡፡
\s5
\v 5 እግዚአብሔር መሪዎችንና ሹማምንቱን እንዲሁም ሌሎች ሰዎችን እንድሰበስብ እና በየቤተሰባቸው መዛግብት እንድጽፍ አሳብ በልቤ አኖረ፡፡ እንደዚሁም ወደ ኢየሩሳሌም የተመለሱትን የመጀመሪያዎቹን ተመላሾች ዝርዝር አገኘሁ፡፡ በእዚያ መዛግብት ተጽፎ ያገኘሁት ይህንን ነው፡፡
\s5
\v 6 ”ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ሌሎች ስፍራዎች የተመለሱ ሰዎች ዝርዝር ይህ ነው፡፡ እነርሱ ባቢሎን ውስጥ ይኖሩ ነበር፡፡ ናቡከደነጾር ወደዚያ ወስዷቸው ነበር፡፡ እነርሱ ወደ ኢየሩሳሌምና ይሁዳ ተመለሱ፡፡ እያንዳንዱ ተመላሽ አባት ከልደት በፊት ይኖርበት ወደነበረበት ወደ ራሱ ከተማ ተመልሶ ሄደ፡፡
\v 7 እነርሱ ከዘሩባቤል፣ ከኢያሱ፣ ከነህምያ፣ ከአዛርያስ፣ ከረዓምያ፣ ከነሐማኒ፣ ከመርዶክዮስ፣ ከላሶን፣ ከሚስጴሬት፣ ከጉዋይ፣ ከነሑም፣ እና ከዓና ጋር ተመልሰው መጡ፡፡ ከህዝቡ የተመለሱት የወንዶች ቁጥር ዝርዝር እንደሚከተለው ነበር፡
\s5
\v 8 ከፋሮስ ትውልዶች 2172
\v 9 ከሰፋጥያስ ትውልዶች 372
\v 10 ከኤራ ትውልዶች፣ 652
\s5
\v 11 ሞዓብ ትውልዶች፣ የኢያሱና ኢዮብአብ ትውልዶች 2818
\v 12 ከኤላም ትውልዶች 1254፣
\v 13 ከዛቱዕ ትውልዶች፣ 845፣
\v 14 ከዘካይ ትውልዶች፣ 845፣
\s5
\v 15 ትውልዶች፣ 648፣
\v 16 ከቤባይ ትውልዶች፣ 628፣
\v 17 ከዓዝጋድ ትውልዶች፣ 2322፣
\v 18 ከአዶኒቃም ትውልዶች፣ 667፣
\s5
\v 19 ከበጉዋይ ትውልዶች፣ 2067፣
\v 20 ከዓዲን ትውልዶች፣ 655፣
\v 21 ከአጤር ትውልዶች ሌላ ስማቸው ሕዝቅያስ ከሚባለው፣ 98፣
\v 22 ከሐሱም ትውልዶች፣ 328
\s5
\v 23 ከቤሳይ ትውልዶች፣ 324፣
\v 24 ከሐሪፍ ትውልዶች፣ ሌላ ስማቸው ጆራህ ከሚባለው፣ 112
\v 25 ከገባዖን ትውልዶች 95
\v 26 አባቶቻቸው በእነዚህ ከተሞች የኖሩ ወንዶችም ደግሞ ተመለሱ ከቤተልሔምና ከነጦፉ የመጡ ወንዶች፣ 188፡፡
\s5
\v 27 ከዓናቶት የመጡ ወንዶች፣ 128 ነበሩ
\v 28 ከቤት አዛምት የመጡ ወንዶች 42፣
\v 29 ከቂርያት ይዓሪም ከከፈሪና ከብኤሮት 743 ወንዶች
\v 30 ኮራማና ከጌባ 621 ወንዶች
\s5
\v 31 122 ወንዶች ነበሩ
\v 32 ከቤቴልና ከጋይ፣ 123 ወንዶች
\v 33 ከናባው፣ 52 ወንዶች
\v 34 ከኤላም፣ 1254 ወንዶች
\s5
\v 35 ከካሪም 320 ወንዶች ነበሩ
\v 36 ከኢያሪኮ፣ 345 ወንዶች
\v 37 ከሎድ፣ ሐዲድና አኖ 721 ወንዶች ነበሩ እነዚህ ካህናትም ደግሞ ተመልሰዋል
\v 38 ከሴናዓ ትውልድ 3930 ነበሩ
\s5
\v 39 የኢያሱ ቤተሰብ የሆኑ፣ የዮዳኤ ትውልዶች፣ 973
\v 40 ከኢሜር ትውልዶች 1052፣
\v 41 ከፋስኮር ትውልዶች፣ 1247፣
\v 42 ከካሪም ትውልዶች፣ 1017
\s5
\v 43 ከሌዋውያን ትውልዶች የተመለሱት እነዚህ ነበሩ፣ የኢያሱ፣ ቀደምኤል፣ ቤትኢ እና የሆዳይዋ ትውልዶች 74 ናቸው
\v 44 ከመዘምራኑ ትውልዶች የተመለሱት እነዚህ ነበሩ ከኤሳፍ ትውልድ 148
\v 45 እንዲሁም ከሰሎም፣ አጤር፣ ጤልሞን፣ ዓቁብ፣ ሐጢጣ፣ እና ሶባይ ትውልዶች የተመለሱ 138 የቤተ መቅደሱ በር ጠባቂዎች ናቸው፡፡
\s5
\v 46 የተመለሱት የቤተ መቅደሱ ሰራተኞች የእነዚህ ሰዎች ትውልዶች ነበሩ የሲሐ፣ ሐሡፋ፣ ጠብዖት
\v 47 የኬረስ፣ ሲዓዓ ሩዶን
\v 48 የልባና አገባ፣ ሰሞላይ
\v 49 የሐናን ጌዱል፣ ጋሐር፣
\s5
\v 50 ራያ፣ ራአሰን፣ ኔቆዳ
\v 51 ጋሴም፣ አዛ፣ ፋሴሐ
\v 52 ቤሳይ፣ ምዑኒም፣ ንፉሰሊም፣ እነዚህ ንፉሰሲም ተብለውም ይጠራሉ
\s5
\v 53 በቅቡቅ፣ ሐቀፋ፣ ሐርሑር፣
\v 54 በሰሎት፣ እነዚህ በሰሉት ተብለውም ይጠራሉ ምሒዳ፣ ሐርሻ
\v 55 ቦርቆስ፣ ሲሣራ፣ ቴማ
\v 56 ንስያ፣ ሐጢፋ
\s5
\v 57 ከንጉስ ዳዊት አገልጋዮች ትውልዶች የተመለሱት እነዚህ ነበሩ፣ ሶጣይ፣ ሶፌሬት፣ ፍሩዳ
\v 58 የዕላ፣ ደርቆን፣ ጊዴል
\v 59 ሰፋጥያስ፣ ሐጢል፣ ፈከራት፣ ሐፂቦይምና አሞን
\v 60 በአጠቃላይ፣ 392 የቤተ መቅደስ ሰራተኞችና የሰለሞን ትውልዶች አገልጋዮች ተመላሾች ነበሩ፡፡
\s5
\v 61 ከዳላያ፣ ጦብያ እና ኔቆዳ ጎሣዎች
\v 62 ሰዎች ያሉት ሌላ ቡድን ከቴልሜላ ቴላሬሳ፣ ከክሩብ፣ አዳን፣ በባቢሎን አዳን እና ኢሜር ተብሎም ይታወቃል፤ ከእነዚህ ከተሞች ይመለሳሉ፡፡ ነገር ግን እነርሱ እስራኤላዊያን መሆናቸውን ማረጋገጥ አልቻሉም፡፡
\v 63 የኤብያ፣ አቆስ፣ እና ቤርዜሊ ትውልድ የሆኑ ካህናትም ደግሞ ተመለሱ፡፡ ቤርዜሊ ከገለዓድ አካባቢ የቤርዜሊ ትውልድ የሆነችን አንዲት ሴት አገባ፤ እርሱም የሚስቱን ቤተሰቦች ስም መጠሪያው አድርጎ ወሰደ፡፡
\s5
\v 64 እነዚህ የአባቶችን ስሞች በያዙ መዛግብቶች ውስጥ የትውልድ ሀረጋቸውን ፍለጋ አደረጉ፣ ነገር ግን የቤተሰቦቻቸውን ስሞች ማግኘት አልቻሉም፤ ስለዚህ ካህናት ያሏቸውን መብቶችና ግዴታዎች ማግኘት አልተፈቀደላቸውም፡፡ በመሆኑም ንጹህ እንዳልሆኑ ስተቆጠረ ካህናት ለመሆን አልበቁም ምክንያቱም የትውልድ ሀረጋቸውን ማመላከት አልቻሉም፡፡
\v 65 ስለዚህ አገረ ገዥው በኡሪምና ቱሚም የሚያገለግል ከህን እስኪነሳ ድረስ ከመስዋዕቱ ከተወሰደው እጅግ ከተቀደሰው ከካህናቱ ድርሻ ምግብ እንዳይበሉ አዘዛቸው፡፡
\s5
\v 66 በአጠቃላይ፣ ከይሁዳ የተመለሱት ሰዎች 42360 ነበሩ፡፡
\v 67 እንደዚሁም 7337 አገልጋዮቻቸውና 245ዘማሪዎች ከወንዶችም ከሴቶችም በአንድነት ተቆጠሩ፡፡
\s5
\v 68 እስራኤላዊያኑ ከባቢሎን 736 ፈረሶችና 245 በቅሎዎች፣
\v 69 አራት መቶ ሰላሳ አምስት ግመሎችና 6720 አህዮችንም ጭምር ይዘው ተመለሱ፡፡
\s5
\v 70 አንዳንዶቹ የጎሣው መሪዎች ለመቅደሱ ግንባታ ሠራተኞች ስጦታዎችን ሰጡ፡፡ አገረ ገዥው 8. 5 ኪሎግራም ወርቅ ለመቅደስ አገልግሎት ሀምሳ ጎድጓዳ ሳህኖች፣ እና 530 የክህነት ልብሶችን ለካህናቱ ሰጠ፡፡
\v 71 ሌሎቹ መሪዎች ለግምጃ ቤት ሀላፊው 170 ኪሎግራም ወርቅ ሰጡ፣ የጎሣው መሪዎች በአጠቃላይ 1. 2 ሜትሪክ ቶን ብር ሰጡ፡፡
\v 72 ሌላው ህዝብ 170 ኪሎግራም ወርቅ፣ እና 1. 1 ሜትሪክ ቶን ብር እንዲሁም 67 የክህነት ልብስ ለካህናቱ ሰጡ፡፡
\s5
\v 73 ስለዚህም ካህናቱ፣ ካህናቱን የሚረዱ ሌዋውያን፣ የቤተመቅደሱ ጠባቂዎች፣ ዘማሪዎቹ፣ የቤተ መቅደሱ ሰራተኞች፣ እና በርካታው ተራ ህዝብ እንዲሁም እስራኤላዊ የሆኑ ሁሉ አባቶቻቸው ይኖሩባቸው በነበሩ በይሁዳ ከተሞች መኖር ጀመሩ፡፡
\s5
\c 8
\p
\v 1 ህዝቡ ሁሉ በውሃ በር አጠገብ በሚገኘው አደባባይ በአንድነት ተሰበሰቡ፡፡ የሚነገረውን መረዳት የሚችሉ ወንዶችና ሴቶች እንዲሁም ልጆች በአንድነት ተሰበሰቡ፡፡ እነርሱም ህግጋቱንና ትዕዛዛቱን ይጠብቁ ዘንድ፣ ያህዌ ለእስራኤል ህዝብ መመሪያ አድርጎ የሰጠውን ሙሴ የፃፈውን የህግ ጥቅልል መጽሐፍ እንዲመያጣ ዕዝራን ጠየቁት፡፡
\v 2 በቤተ መቅደስ መስዋዕቶችን በማቅረብ እግዚአብሔርን የሚያገለግለው ዕዝራ፣ ለወንዶችና ለሴቶች እንዲሁም ለማናቸውም የሚነበበውን መረዳት ለሚችሉ ህጉን አውጥቶ በህዝቡ ሁሉ ፊት አነበበ፡፡ ይህንን በዚያ አመት በሰባተኛው ወር በወሩ በመጀመሪያው ቀን አደረገ፡፡
\v 3 ስለዚህም መጽሐፉን አውጥቶ ለህዝቡ አነበበ፡፡ ጠዋት ከማለዳ አንስቶ እስከ እኩለ ቀን ድረስ የህጉን መጽሐፍ አነበበ፡፡ ወንዶና ሴቶች እንዲሁም የሚያነበውን መረዳት የሚችሉ ሁሉ ሰሙት፡፡ ዕዝራ ከህጉ መጽሐፍ የሚያነበውን፣ ህዝቡ በታላቅ ፍላጎት አደመጠ፡፡
\s5
\v 4 ዕዝራ ለዚህ ተግባር በህዝቡ በተዘጋጀ ከፍ ያ የእንጨት መድረክ ላይ ቆመ፡፡ ከእርሱ በስተቀኝ መቲትያ፣ ሽማዕ፣ ዓናያ፣ ኦርዮ፣ ኬልቅያስ እና መዕሤያ ቆመው ነበር፡፡ በስተግራው በኩል ደግሞ ፈዳያ፣ ሚሳኤል፣ መልክያ፣ ሐሱም፣ ሐሽበዳ፣ ዘካርያስና ሜሱላም ቆመው ነበር፡፡
\v 5 ዕዝራ በመድረኩ ላይ ሁሉም ሰዎች ሊያዩት በሚችሉት ቦታ ቆሞ ጥቅልሉን ተረተረው፣ እርሱ መጽሐፉን ሲከፍት ህዝቡ ሁሉ ተነስቶ ቆመ፡፡
\s5
\v 6 ከዚያም ዕዝራ ታላቁን አምላክ ያህዌን አመሰገነ፣ ህዝቡም ሁሉ እጆቻቸውን አንስተው፣ “አሜን! አሜን!” አሉ፡፡ ከዚያም ሁሉም በግምባራቸው ወደ ምድር እየሰገዱ ያህዌን አመለኩ፡፡
\v 7 ኢያሱ፣ ባኒ፣ ሰራብያ፣ ያሚን፣ ዓቁብ፣ ሳባታይ፣ ሆዲያ፣ መዕሤያ፣ ቆሊጣስ፣ ዓዛርያስ፣ ዮዛባት፣ ሐናን እና ፌልያ ሁሉም ሌዋውያን ነበሩ፡፡ እነርሱም የሙሴን ህግጋት ትርጉም በዚያ ቆመው ለነበሩ ህዝቦች አብራሩ፡፡
\v 8 እንደዚሁም እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠውን ህግ ከመጽሐፉ ጥቅልሎች አነበቡ፣ ደግም ወደ አረማይክ ቋንቋ እየተረጎሙ ህዝቡ ሊረዱት እንዲችሉ ትርጉሙን ግልጽ አደረጉ፡፡
\s5
\v 9 ከዚያ አገረ ገዥው ነህምያ እና ጸሓፊውና ካህኑ ዕዝራ፣ እንዲሁም የተነበበውን ለህዝቡ ይተረጉሙ የነበሩ ሌዋውያን፣ እንዲህ አሏቸው፣ “ያህዌ አምላካችሁ ይህን ቀን ከሌሎች ቀናት ለይቶታል፡፡ ስለዚህ በዚህ ቀን አትዘኑ ወይም አታልቅሱ!” ይህን የተናገሩት፣ ዕዝራ ህጉን ሲያነብ፤ የሚሰሙት ሁሉ ያለቅሱ ስለነበር ነው፡፡
\v 10 ከዚያም ነህምያ እንደዚህ አላቸው፣ “አሁን ወደየቤታችሁ ሄዳችሁ መልካም ምግብ ተመገቡ ደስ የሚያሰኝ ጣፋጭ መጠጥም ጠጡ፡፡ ከምትበሉትና ከምትጠጡት የሚበሉትና የሚጠጡት ለሌላቸው አካፍሉ፡፡ ይህ ቀን፣ ጌታችንን ለማምለክ የተለየ ቀን ነው፡፡ ሀዘን አይሙላባችሁ! ያህዌ የሚሰጣችሁ ደስታ ብርቱ ያደርጋችኋል፡፡”
\s5
\v 11 ሌዋውያኑም ህዝቡን “ዝም በሉ አታልቅሱ፣ ይህ ቀን ለያህዌ የተለየ ቀን ነው፡፡ አትዘኑ!” በማለት ፀጥ አሰኙ፡፡
\v 12 ስለዚህም ህዝቡ ተነስቶ ሄደ፤ በሉም ጠጡም፣ እንዲሁም ምንም ለሌላቸው ከምግባቸው አካፈሉ፡፡ የተነበባላቸውን ቃላት ትርጉሙን ስለተረዱ በጣም ደስተኞች ነበሩ፡፡
\s5
\v 13 በማግስቱ፣ የየቤተሰቡ አባወራዎች እና ካህናቱ እንዲሁም ሌዋውያኑ የህጉን ቃላት ይበልጥ ለመረዳት በአንድነት ወደ ዕዝራ መጡ፡፡
\v 14 አያቶቻቸው በበረሃ ሲጓዙ በዳሶች ውስጥ እንደኖሩ ያስታውሱ ዘንድ፣ በእነዚያ ወራት ሁሉ የእስራኤል ህዝብ እንዴት በጊዜያዊ ዳሶች ውስጥ መኖር እንደሚገባቸው ያህዌ ለሙሴ የሰጠውን ተዕዛዝ በህጉ ውስጥ ተጽፎ አገኙ፡፡
\v 15 እንደዚሁም ህዝቡ ወደ ኮረብቶች ሄዶ፤ ከወይራ ዛፎች ቅርንጫፎችን፣ ከበረሃ ወይራ ዛፎችና ከባርሰነት ዛፎች፣ ከዘንባባ ዛፎችና ሰፊ ጥላ ከሚሰጡ ዛፎች ዝንጣፊዎችን እየቆረጡ እንዲያመጡና በኢየሩሳሌምና በሌሎች ከተሞች ማወጅ እንዳለባቸው ተረድተዋል፡፡ ሙሴ እንደፃፈው፣ በበዓላቱ ወቅቶች ለመኖሪያነት የሚገለገሉባቸውን እነዚህን ዳሶች ከእነዚህ ዛፎች ቅርንጫፎች ማበጀት አለባቸው፡፡
\s5
\v 16 ስለዚህም ህዝቡ ከከተማ ወጥቶ ቅርንጫፎችን ቆርጦ ዳሶችን ለመስራት ተጠቀመባቸው፡፡ ዳሶችንም በየቤቶቻቸው ሰገነቶችች በየአደባባዮቻቸው፣ በቤተ መቅደስ አደባባዮች፣ እና በውሃ በር አጠገብ በሚገኘው አደባባይና በኤፍሬም መግቢያ ሰሩ፡፡
\v 17 ከባቢሎን የተመለሱ እስራኤላዊያን ሁሉ ዳሶችን ገንብተው ለአንድ ሳምንት ኖሩባቸው፡፡ እስራኤላዊያን ያንን በዓል ከኢያሱ ዘመን አንስቶ እስከዚያ ጊዜ ድረስ እንዲህ አላከበሩም፡፡ ህዝቡ በጣም ተደስቶ ነበር፡፡
\s5
\v 18 ዕዝራ በዚያን ሳምንት በየዕለቱ ከእግዚአብሔር ህግ ለህዝቡ ያነብ ነበር፡፡ ከዚያ በስምንተኛው ቀን፣ ድንጋጌውን ተከትለው ህዝቡ እንዲሰበሰብ አደረጉ፣ ይህም የበዓሉ ፍጻሜ ነበር፡፡
\s5
\c 9
\p
\v 1 በዚያው ወር በሃያ አራተኛው ቀን፣ ህዝቡ በአንድነት ተሰበሰበ፡፡ ለጥቂት ጊዜ አልበሉም፣ ሰንዴና ሌላ እህል ለመያዣ የተዘጋጁ ጆንያዎችን ልብስ አደርገው ለበሱ፣ በራሳቸው ላይ የምድር ትቢያ ነሰነሱ፡፡
\v 2 የእስራኤል ትውልዶች ራሳቸውን ከሌሎች መጻተኞች ሁሉ ለዩ፡፡ በዚያ ቆመው የራሳቸውን ኃጢአትና አባቶቸው የሰሯቸውን ክፉ ነገሮች ተናዘዙ፡፡
\s5
\v 3 ቆመው ለሶስት ሰዓቶች ከያህዌ ህግ አነበቡ፣ ደግሞም ለሌላ ሶስት ሰዓቶች በያህዌ ፊት ኃጢአቶቻቸውን ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ተናገሩ፣ ከዚያ በመሬት ላይ ተደፍተው እርሱን አመለኩ፡፡
\v 4 ሌዋውያኑ በደረጃው ላይ ቆመው ነበር፡፡ እነርሱም ኢያሱ፣ ባኒ፣ ቀድምኤል፣ ሰበንያ፣ ቡኒ፣ ሰራብያ፣ ባኒ፣ እና ከናኒ ነበሩ፡፡
\s5
\v 5 ከዚያ የሌዋውያኑ መሪዎች በህዝቡ ፊት ተሰየሙ፡፡ እነርሱም ኢያሱ፣ ባኒ፣ አሰበንያ፣ ሰራብያ፣ ሆዲያ፣ ሰበንያና ፈታያ ነበሩ፡፡ እነርሱም እንዲህ አሉ፣ “ቁሙና ከዘለዓም እስከ ዘለዓለም ለነበረውና ለሚኖረው ለአምላካችሁ ለያህዌ ምስጋና አቅርቡ! ያህዌ፣ የከበረውን ስምህን እናወድሳለን! መልካምና ድንቅ ከሆነው ነገር ሁሉ ስምህ የበለጠ ጠቃሚ ነው!
\v 6 አንተ ያህዌ ነህ፣ ሌላ ማንም ዘለዓለማዊና በራሱ ህልውና ያለው የለም፡፡ አንተ ሰማይንና ሰማያትን ከሁሉም በላይ ሰራህ፣ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚፈጽሙትን መላዕክት ሁሉ ፈጠርህ፡፡ ምድርንና በላይዋ ያሉትን አንተ አበጀህ፣ ባህሮችንና በውስጣቸው የሚገኙትን ሰራህ፡፡ አንተ ለሁሉም ነገር ህይወት ሰጠህ፡፡ በሰማይ ያሉ የመላዕክት ሰራዊት ሁሉ አንተን ያመልኩሃል፡፡
\s5
\v 7 ያህዌ፣ አንተ እግዚአብሔር ነህ፡፡ አንተ አብራምን መርጠህ ከኡር ከከለዓድ አወጣኸው፡፡ አብርሃም የሚል ስም ሰጠኸው፡፡
\v 8 አንተ የእርሱን ልብ አየህ፣ የታመነ ሰው እንደነበረ ታውቅ ነበር፡፡ ከዚያ ከእርሱ ጋር በደም ቃል ኪዳን አደረግህ፣ የከነዓናዊያንን፣ የኬጢያውያንን፣ የአሞራውያንን፣ የፌርዛውያንን፣ የኢያቡሳውያንንና የጌርሳውያንን ምድር ለትውልዶች እንደምትሰጠው ቃል ገባህለት፡፡ እና አንተ ያህዌ፣ ቃል የገባኸውን ፈጸምክ፣ ምክንያቱም አንተ ሁልጊዜም ትክክል የሆነውን ታደርጋለህ፡፡
\s5
\v 9 አባቶቻችን በግብጽ ምን ያህል ይሰቃዩ እንደ ነበር አንተ አይተሃል፡፡ ቀይ ባህር አጠገብ በነበሩ ጊዜ ወደ አንተ ለእርዳታ ሲጮኹ ሰማሃቸው፡፡
\v 10 ንጉሱ፣ አገልጋዮቹና የእርሱ ህዝቦች ሁሉ እንዲጨነቁ የሚያደርግ ብዙ አይነት ተአምራቶችን አደረግህ፡፡ በዚህም፣ አንተ፣ ያህዌ፣ ለራስህ ስም አደረግህ፣ እናም ዛሬም ድረስ ስምህ ታላቅ መሆኑ ይታወቃል!
\s5
\v 11 ለሁለት ክፍል ከፈልህ፣ እናም ህዝብህ በደረቅ ምድር በመሀሉ ተራመደ፡፡ አንተ የግብጽን ወታደሮች በውሃዎች ስር አሰመጥክ፣ ድንጋይ በጥልቅ ውሃ እንደሚሰምጥ ሰመጡ!
\s5
\v 12 በቀን ደመና እንደ አምድ እየተከተላቸው መራሃቸው፣ በምሽት ወዴት እንደሚሄዱ ልታሳያቸው የእሳት አምድ ብርሃን ሰጠሃቸው፡፡
\v 13 አንተ ከሰማይ ወርደህ በሲና ተራራ ላይ አናገርካቸው፡፡ የታመኑና እውነተኛ የሆኑ ብዙ ድንጋጌዎችንና ደንቦችን ሰጠሃቸው፣ መልካም የሆኑ ትዕዛዛትንና ህግጋትንም ሰጠሃቸው፡፡
\s5
\v 14 ስለ ቅዱሱ ሰንበትህ አስተማርካቸው፣ ትዕዛዛትንና ህግጋትን እንዲሁም ይፈጽሟቸው ዘንድ የህግጋት አይቶችን በአገልጋይህ በሙሴ በኩል ሰጠሃቸው፡፡ እርሱ ለህዝቡ ይነግራቸዋል፡፡
\v 15 በተራቡ ጊዜ፣ ከሰማይ እንጀራ ሰጠሃቸው፡፡ በተጠሙ ጊዜ፣ ከአለት ውሃ አጠጣሃቸው፡፡ ትሰጣቸው ዘንድ በመሀላ ቃል የገባህላቸውን ምድር ሄደው እንዲወርሱ ነገርካቸው፡፡
\s5
\v 16 ነገር ግን አባቶቻችን በጣም ኩራተኞችና ግትሮች ነበሩ፡፡ እንዲያደርጉት ያዘዝካቸውን ለማስማት እንኳን ተቃወሙ፡፡
\v 17 አንተን ለመስማት አልወደዱም፡፡ ለእነርሱ ያደረግከውን ተአምራቶች ሁሉ ረሱ፡፡ ደንዳኖች ሆኑ፣ በአንተ ላይ ስላመጹ፣ ዳግም ባሪያዎች ወደሚሆኑበት! ወደ ግብጽ የሚመልሳቸውን መሪ መረጡ፡፡ ነገር ግን አንተ ደግመህ ደጋግመህ ይቅር የምትል አምላክ ነህ፡፡ ለመቆጣት አትቸኩልም፣ ለእነርሱ ያለህ ፍቅርም በፍጹም የማያልቅና ታላቅ ነው፡፡ እነርሱን አልተውካቸውም፡፡
\s5
\v 18 ስለዚህ፣ ምንም እንኳን የከበሩ ማዕድናትን አቅልጠው ጥጃ የሚመስል ጣኦት ቢቀርጹም ሙሉ ለሙሉ አልተወካቸውም፡፡ እግዚአብሔርን በመራገምና እርሱ የከለከለውን በማድረግ፣ ይህን ጥጃ ወደ ህዝቡ አቅርበው፣ ‘ይህ እናንተን ከግብጽ ያወጣችሁ አምላካችሁ ነው’ አሉ፡፡
\v 19 አንተ ሁልጊዜም መሃሪ ነህ፣ በበረሃ በነበሩ ጊዜም አልተውካቸውም፡፡ እንደ ታላቅ አምድ የሆነው ብሩህ ደመና በቀን ይመራቸው ነበር፣ የእሳት ደመናው በምሽት የሚሄዱበትን ይመራቸው ነበር፡፡
\s5
\v 20 መልካሙን መንፈስህን እንዲመራቸው ላክህላቸው፡፡ በተራቡ ጊዜ መናውን አልከለከልካቸውም፣ በተጠሙ ጊዜ ውሃ ሰጠሃቸው፡፡
\v 21 ለአርባ አመታት በበረሃ ተጠነቀቅክላቸው፡፡ በነዚያ ጊዜያት ሁሉ፣ የአንዳች ነገር ጉድለት አልነበረባቸውም፡፡ ልብሳቸው አላረጀም፣ እግሮቻቸው አላበጡም፡፡
\s5
\v 22 የአህዛብን ነገስታትና መንግስታት ሰጠሃቸው፡፡ በዚህ ምድር እጅግ ሩቅ የሆነውን ስፍራ እንኳን ርስት አድርገው ወሰዱ፡፡ ንጉስ ሴዎን የሚገዛውን ምድር ከሐሴቦን ወሰዱ እንዲሁም የንጉስ ዐግን ግዛት ባሳንን ወረሱ፡፡
\s5
\v 23 አባቶቻችንን በሰማይ እንዳሉ ከዋክብት እንዲበዙ ረዳሃቸው፣ አባቶቻቸው ይገቡባትና ይኖሩባት ዘንድ ወደ ነገርካቸው ወደዚህ ምድር አመጣሃቸው፡፡
\v 24 የእስራኤል ህዝቦች ገብተው በዚያ ከሚኖሩ ህዝቦች ምድሪቱን ወሰዱ፡፡ አንተ ከነአናዊያንንና ነገስታቶቻውን እንዲያሸንፉ ረዳሃቸው፣ አንተም በዚይ ምድር ህዝቦች ላይ ገዛህ፡፡ በእነዚያ ህዝቦች ላይ ማድረግ የሚፈልጉትን ሁሉ እንዲያደርጉ አንተ ረዳሃቸው፡፡
\s5
\v 25 አባቶቻችን ዙሪያቸው የተቀጠሩትን ከተሞች ያዙ፡፡ የለምለሚቱን ምድር ሀብት ወረሱ፡፡ በመልካም ነገሮች የተሞሉትን ቤቶችና የተቆፈሩ የውሃ ጉድጓዶችን ወረሱ፡፡ የወይን እርሻዎችን፣ የወይራ ዛፎችን እና የፍራፍሬ ዛፎችን ወረሱ፡፡ የፈለጉትን ሁሉ በልተው ረኩ፡፡ አንተ በሰጠሃቸው ብዙ ስጦታዎች ራሳቸውን ደስ አሰኙ፡፡
\s5
\v 26 ነገር ግን አልታዘዙህም በአንተ ላይም አመጹ፡፡ በህግጋትህ ላይ ጀርባቸውን ሰጡ፡፡ ወደ አንተ መመለስ እንዳለባቸው ያስጠነቀቋቸውን ነቢያት ገደሉ፡፡ ስምህን ተራገሙ፡፡
\v 27 ስለዚህም ያሸንፏቸው ዘንድ ለጠላቶቻቸው አሳልፈህ ሰጠሃቸው፡፡ ነገር ግን ጠላቶቻቸው ባሰቃይዋቸው ጊዜ፣ ወደ አንተ ጮኹ፡፡ አንተ ከሰማይ ጩኸታቸውን ሰማህ፣ አንተ እጅግ መሃሪ ስለሆንክ ከጠላቶቻቸው ነጻ የሚያወጧቸውን ሁሉ ላክህላቸው፡፡ እነርሱም ነፃ አወጧቸው፡፡
\s5
\v 28 ነገር ግን እንደገና የሰላም ጊዜ ከሆነ በኋላ፣ አባቶቻችን ዳግም አንተ የምትጠላውን ክፉ ነገሮች አደረጉ፡፡ ስለዚሀ ጠላቶቻቸው እንዲያሸንፏቸውና እንዲገዟቸው ፈቀድህ፡፡ ነገር ግን እንደገና እንድትረዳቸው በጮኹ ጊዜ ሁሉ አንተ ከሰማይ ሆነህ ትሰማቸዋለህ፣ አንተ በምህረት የተሞላህ ስለሆንክ ትታደጋቸዋለህ፡፡
\v 29 አንተ እንደገና ህግጋትህን እንዲታዘዙ ታስጠነቅቃቸዋለህ፣ ነገር ግን እነርሱ ኩራተኞችና ግትሮች ይሆናሉ፣ ድንጋጌዎችህንም ይጥሳሉ፡፡ እንዲያደርጉ ያዘዝካቸውን ሳይታዘዙ ይቀራሉ፡፡ ለትዕዛዛትህ አንዳች ትኩረት አይሰጡም፡፡ አንተን መስማትን በግትርነት ይቃወማሉ፡፡
\s5
\v 30 አንተ ለብዙ አመታት ታግሰሃቸው ነበር፡፡ መንፈስህ ለነቢያት በሚሰጣቸው መልዕክት አማካይነት ታስጠነቅቃቸዋለህ፡፡ ነገር ግን እነርሱን እነዚያን መልዕክቶች አይሰሙም፡፡ ስለዚህ እንደገና በአጠገባቸው ያሉ የአህዛብ ነገስታት እንዲያሸንፏቸው ትፈቅዳለህ፡፡
\v 31 ነገር ግን አንተ በይቅርታ ስለተሞላህ ሙሉ ለሙሉ አታጠፋቸውም ወይም ለዘለዓለም አትተዋቸውም አንተ መሀሪና ይቅር ባይ አምላክ ነህ!
\s5
\v 32 አምላካችን ሆይ፣ አንተ ታላቅ ነህ! አንተ ሃያል ነህ! አንተ አስደናቂ ነህ! አንተ እንደምታደርግልን በኪዳንህ ቃል እንደ ገባህልን በታማኝነት ትወደናለህ! ነገር ግን እኛ በእነዚህ ነገሮች ሁሉ ታላቅ ችግሮች አሉብን፡፡ መከራችን በፊትህ እንደ ቀላል አይታይ! ይህ በእኛ ነገስታት ልዑላን፣ ካህናት፣ ነቢያት፣ አባቶች እና በመላው ህዝብህ ላይ ከአሶር ነገስታት ዘመን አንስቶ እስከ ዛሬ ደርሷል፡፡
\v 33 በቀጣኸን ጊዜ ሁሉ በጥፋታችን እንደተቀጣን እናውቃለን፡፡ እጅግ በድለናል፣ አንተ ግን በምህረትህ አይተኸናል እኛ ክፉ አድርገናል፡፡
\v 34 ንጉሶቻችን እና ሌሎች መሪዎች፣ ካህኖቻችን እና የእኛ አባቶች ህግህን አልጠበቁም፡፡ እነርሱ ትዕዛዛትን ወይም የሰጠኃቸውን ማስጠንቀቂያዎች አልሰሙም፡፡
\s5
\v 35 የራሳቸው ነገስታት በኖራቸው ጊዜ እንኳን፣ በዚህ በሰጠሃቸው ሰፊና ለም ምድር ለእነርሱ ባደረግካለቸው መልካም ነገሮች በተደሰቱ ጊዜ እንኳን፣ አንተን አላገለገሉህም ደግሞም ክፉ ማድረጋቸውን አላቆሙም፡፡
\s5
\v 36 ስለዚህ አሁን ምድሪቱ በምታበቅለው መልካም ነገሮች ሁሉ ደስ እንዲሰኙ ለአባቶቻችን በሰጠሃቸው በዚህች ምድር ባሮች ነን፡፡ እነሆ ዛሬም በዚህ ባሮች ነን!
\v 37 ስለበደልን ምድሪቱ የምታበቅለውን ነገሮች መብላት አልቻልንም፡፡ አሁን እኛን የሚገዙ ነገስታት በዚህ በሚበቅሉ ነገሮች ደስ እየተሰኙ ነው፡፡ እነርሱ ይገዙናል ከብቶቻችንንም ይወስዳሉ፡፡ እኛ እነርሱን የማገልገልና ደስ የሚያሰኛቸውን ነገሮች የማድረግ ግዴታ አለብን፡፡ በታላቅ ጉስቁልና ውስጥ እንገኛለን፡፡
\s5
\v 38 ከዚህ ሁሉ የተነሳ፣ እኛ የእስራኤል ሰዎች በጥቅልል ጽሁፍ ታላቅ ስምምነት እናደርጋለን፡፡ በጥቅልሉ ላይ የመሪዎቻችንን፣ የሌዋውያንን፣ የካህናትን ስሞች እንጽፍና ማህተም እናደርግበታለን፡፡”
\s5
\c 10
\p
\v 1 በስምምቱ ላይ የፈረሙት የስማቸው ዝርዝር ይህ ነው፡
\v 2 በጽሁፉ ላይ የፈረሙ ካህናት እነዚህ ናቸው፡ ሠራያ፣ ዓዛርያስ፣ ኤርምያስ
\v 3 ፉስኮር፣ አማርያ፣ መልክያ፣
\s5
\v 4 ሐጡስ፣ ሰበንያ፣ መሉክ
\v 5 ካሪም፣ ሜሪምት፣ አብድዩ
\v 6 ዳንኤል፣ ጌንቶን፣ ባሮክ
\v 7 ሜሱላም፣ አብያ፣ ሚያሚን፣
\v 8 መዓዝያ፣ ቤልጋይ፣ ሸማያ እነዚህ ካህናት ነበሩ፡፡
\s5
\v 9 የፈረሙት ሌዋውያን ትውልዶች እነዚህ ነበሩ፡ የአዛንያ ልጅ ኢያሱ፣ ቤንዊ፣ ከኤንሐዳድ፣ ቀድምኤል፣
\v 10 ሰባንያ፣ ሆዲያ፣ ቆሊጣስ፣ ፌልያ፣ ሐናን
\v 11 ሚካ፣ ሪአብ፣ ሐሽብያ፣
\v 12 ዘኩርር ሰራብያ፣ ሰበንያ፣
\v 13 ሆዲያ፣ ባኒ፣ ብኒኑ፡፡
\v 14 በመጽሐፍ ጥቅሉ ላይ የፈረሙት የእስራኤል መሪዎች እነዚህ ነበሩ፡ ፋሮስ፣ ፈሐት፣ ሞዓብ፣ ኤላም፣ ዛቱዕ፣ ባኒ፡፡
\s5
\v 15 ቡኒ፣ ዓዝጋድ፣ ቤባይ፣
\v 16 አዶንያስ፣ በጉዋይ፣ ዓዲን
\v 17 አጤር፣ ሕዝቅያስ፣ ዓዙር፣
\v 18 ሆዲያ፣ ሐሱም፣ ቤሳይ
\v 19 ሐሪፍ፣ ዓናቶት፣ ኖባይ፣
\v 20 መግጲዓስ፣ ሜሱላም፣ ኤዘር
\v 21 ሜሴዜቤል፣ ሳዶቅ፣ ያጹአ፣
\s5
\v 22 ፈላጥያ፣ ሐናን፣ ዓናያ፣
\v 23 ሆሴዕ፣ ሐናንያ፣ አሱብ፣
\v 24 አሎኤስ፣ ፈልሃ፣ ሶቤቅ
\v 25 ሬሁም፣ ሐሰብና፣ መዕሤያ፣
\v 26 አኪያ፣ ሐናን፣ ዓናን፣
\v 27 ሙሉክ፣ ካሪምና በዓና፡፡
\s5
\v 28 ካህናቱን በር ጠባቂዎቹን፣ ዘማሪዎቹን እና የመቅደስ ሰራተኞቹን ጨምሮ የቀረው ሕዝብ የከበረ ስምምነት አደረጉ፡፡ እንደዚሁም አገራቸውን ለቀው የወጡትንና በእስራኤል ይኖሩ የነበሩትን ጎረቤቶቻቸው ከሆኑ ከሌሎች ህዝቦች ወንዶችን ሁሉ ጨመሩ፡፡ እነዚህ ወንዶች ከሚስቶቻቸውና የሚያደርጉትን ለይተው ከሚያውቁ ከፍ ካሉ ወንድና ሴት ልጆቻቸው ጋር ሆነው የእግዚአብሔርን ህግ እንደሚጠበቁ ቃል ገቡ፡፡
\v 29 ይህን የከበረ ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ ሁሉም ከመሪዎቻቸው ጋር ተባበሩ፡፡ እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠውን ህግጋት ሁሉ ለመታዘዝ ተስማሙ፡፡ ያህዌ አምላካችን ያዘዘውን፣ ድንጋጌዎቹንና ትዕዛዛቱን ሁሉ ለመከተልና ለመፈፀም ተስማሙ፡፡ ተከታዩን ለማድረግ ቃል ገቡ፡፡
\s5
\v 30 “ሴቶች ልጆቻችን ያህዌን የማያመልኩትን የዚህ ምድር ሰዎች እንዲያገቡ አንሰጥም፣ ወንድ ልጆቻችን ሴት ልጆቻቸውን እንዲያገቡም አንፈቅድም፡፡
\v 31 ምድር የሚኖሩ የሌላ አገር ሰዎች በሰንበት ወይም በሌላ በተቀደሰ ቀን እህል ወይም ሌሎች ነገሮችን ሊሸጡልን ቢያመጡ፣ አንዳች ነገር አንገዛቸውም፡፡ እናም በየሰባት አመቱ አንዴ ለምድሪቱ እረፍት እንሰጣለን፤ በዚያን አንድ አመት ምንም አይነት እህል አንዘራም፤ እንዲሁም ለሌሎች አይሁዶች እዳቸውን ሁሉ እንሰርዛለን፡፡
\s5
\v 32 እንዲሁም እያንዳንዳችን ቤተ መቅደሱን ለሚያገለግሉና ለሚንከባከቡ በየአመቱ 5 ግራም ብር ለመክፈል ቃል ገባን፡፡
\v 33 በዚያ ገንዘብ እነዚህን ነገሮች መግዛት ይችላሉ፡ በእግዚአብሔር ፊት በገበታው ላይ የሚቀርብ ዳቦ፣ በእያንዳንዱ ቀን በመሰዊያው ላይ የሚቀርብ የእህል ቁርባን፣ በመሰዊያ ላይ ታርደው ሙሉ ለሙሉ የሚቃጠሉ እንስሳት፣ ለእግዚአብሔር በሰንበት የሚርቡ የተቀደሱ መስዋዕቶች እና የአዲስ ጨረቃ በዓልን ለማክበርና ለሌሎች በዓላት መስዋዕቶች፣ ለእስራኤል ህዝቦች ኃጢአት መስዋዕት የሚሆኑ እንስሳት፣ እና ማናቸውም የቤተመቅደሱን ሥራ ለመንከባከብ የሚያስፈልጉ ሌሎች ነገሮች መግዛት ይችላሉ፡፡
\s5
\v 34 በየአመቱ ካህናቱ፣ ካህናቱን የሚረዱ የሌዊ ትውልዶች እና የተቀረነው በእግዚአብሔር ሕግ እንደተፃፈው በዚያ አመት ከሌዋውያን መሃል የትኛው ቤተሰብ በአምካላችን በእግዚአብሔር ቤት መስዋዕቶቹን ለማቅረብ በመሰዊያው ላይ የሚነደውን እንጨት እንደሚያቀርቡ ለመወሰን እጣዎችን እንጥላለን፡፡
\v 35 በእያንዳንዱ አመት እያንዳንዱ ቤተሰብ በእርሻችን ካበቀልነውና ለምግብ ካጨድነው እንዲሁም በዚያ አመት ከፍራፍሬ ዛፎች የተገኘውን በኩራት መስዋዕት አድረገን ወደ ቤተ መቅደስ ለማምጣት ቃል እንገባለን፡፡
\v 36 የበኩር ወንድ ልጆችንና የላም፣ የበግና የፍየል በኩሮችን ለእግዚአብሔር መታሰበያ አድርገን ወደ እግዚአብሔር ቤት እናመጣለን፡፡ ማድረግ የሚገባን፣ በእግዚአብሔር ሕግጋት የተፃፈው ይህ ነው፡፡
\s5
\v 37 በየአመቱ ካመረትነው እህል ከበኩራቱ የተዘጋጀ ዱቄት ለካህናቱ ወደ ቤተ መቅደስ እናመጣለን፣ እንዲሁም ሌሎች የወይን፣ የወይራ ዘይትና የፍራፍሬ መስዋዕቶችንም ከበኩራቱ እናመጣለን፡፡ ካህናቱን ለሚረዱ የሌዊ ትውልዶች አስራቶችንም እናመጣለን፡፡
\v 38 የአሮን ትውልድ የሆነ አንድ ካህን፣ ከሌዋውያን ጋር ሆኖ አስራቶችን ሲሰበስቡ አብሮ ይገኛል፡፡ ከዚያ የሌዊ ትውልዶች ድርሻቸውን ይወስዳሉ፤ ህዝቡ ካመጣው ነገሮች አንድ አስረኛውን ይወስዱና በቤተ መቅደስ በግምጃ ቤት ያስቀምጣሉ፡፡
\s5
\v 39 የሌዊ ትወልዶችና አንዳንድ የእስራኤል ሰዎች በቤተ መቅደስ ለሚያገለግሉ የእህል፣ የወይን፣ እና የወይራ ዘይት ስጦታዎችን የተለያዩ መገልገያዎች ወደ ሚከማቹበት ግምጃ ቤቶች መውሰድ አለባቸው፡፡ በዚያን ጊዜ የሚያገለግሉ ካህናት፣ በር ጠባቂዎች፣ እና በቤተ መቅደስ የሚዘምሩ የዝማሬ ቡድን የሚኖሩበት ስፍራ ይህ ነው፡፡ “የአምላካችንን ቤተ መቅደስ ከመጠበቅ ቸል እንደማንል ቃል እንገባለን፡፡”
\s5
\c 11
\p
\v 1 የእስራኤል መሪዎችና ቤተሰቦቻቸው በኢየሩሳሌም ተቀመጡ፡፡ ለእግዚአብሔር በተለየችው ከተማ የሚኖሩትን ከአስሩ ቤተሰብ አንዱን ለመለየት የተቀሩት ሰዎች እጣ ተጣጣሉ፡፡
\v 2 በኢየሩሳሌም ለመኖር ፈቃደኛ የሆኑትን ሰዎች እግዚአብሔር እንዲባርካቸው ጸለዩላቸው፡፡
\s5
\v 3 እነዚህ ቢየሩሳሌም ለመኖር የመጡት የአውራጃው ባለስልጣናት ናቸው፡፡ ነገር ግን በይሁዳ ከተሞች እያንዳንዱ በየራሱ ቤተሰብ ንብረት በየራሱ ከተማ ኖረ፡፡ አንዳንዶች ካህናት፣ ሌዋውያን፣ የቤተመቅደስ አገልጋዮች እና የሰለሞን አገልጋዮች ትውልዶች የሆኑ እስራኤላውያን በኢየሩሳሌም ውስጥ ለመኖር መጡ፡፡
\v 4 ነገር ግን አንዳንድ የይሁዳ ሰዎች እና የብንያም ሰዎች በኢየሩሳሌም ቆዩ በዚያም ኖሩ፡፡ እነዚህ ከይሁዳ ወገን ናቸው፡፡ የፋሬስ ትውልድ፣ የመላልኤል ልጅ፣ የሶፋጥያስ ልጅ፣ የአማርያ ልጅ፣ የዘካርያስ ልጅ፣ የኦዝያ ልጅ አታያ ናቸው፡፡
\s5
\v 5 እና የይሁዳ ልጅ ሴሎ ትውልድ የሆነው የዘካርያስ ልጅ፣ የዮያሪብ ልጅ፣ የዓዳያ ልጅ፣ የኦዛያ ልጅ፣ የኮልሖዜ ልጅ የባሮክ ልጅ መዕሤያ ነበር፡፡
\v 6 በኢየሩሳሌም የተቀመጡት የፋሬስ ትውልዶች 468 ወንዶች ነበሩ፡፡
\s5
\v 7 ከብንያም ትውልድ በኢየሩሳሌም ለመኖር ከወሰነው ጎሳ ሰዎች መሀል አንዱ የየሻያ ልጅ፣ የኢቲኤል ልጅ የመዕሤያ ልጅ፣ የቆላያ ልጅ፣ የፈዳያ ልጅ፣ የዮእድ ልጅ፣ የሜሱላም ልጅ ሰሉ ነው፡፡
\v 8 የሳሉ ሁለቱ ቤተ ዘመዶች ጌቤ እና ሳላይም በኢየሩሳሌም ተቀመጡ፡፡ በአጠቃላይ ከብንያም ጎሣ 928 ሰዎች በኢየሩሳሌም ተቀመጡ፡፡
\v 9 መሪያቸው ዝክሪ ነበር፡፡ በኢየሩሳሌም በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ሹም ሐስኑአ ነበር፡፡
\s5
\v 10 በኢየሩሳሌም የተቀመጡት ካህናት የዮያሪብ ልጅ ዮዳኤ፣
\v 11 አስቀድሞ የካህናቱ ሁሉ መሪ የነበረው የአኪጦብ ልጅ የመራዮት ልጅ፣ የሳዶቅ ልጅ የሜሱላም ልጅ የኪልቅያስ ልጅ ሠራያ ነበር፡፡
\v 12 በአጠቃላይ ከዚያ ነገድ የቤተ መቅደሱ ሠራተኞች 822 ሰዎች ናቸው፡፡ በኢየሩሳሌም የተቀመጠ ሌላው ካህን የመልክያ ልጅ፣ የፋስኮር ልጅ፣ የዘካርያስ ልጅ የአማሲ ልጅ፣ የፈላልያ ልጅ የይሮሐም ልጅ ዓዳያ ነበር፡፡
\s5
\v 13 በኢየሩሳሌም የተቀመጡ የዚያ ነገድ መሪዎች በጠቅላላው 242 አባላት ነበሩ፡፡ በኢየሩሳሌም የተቀመጠው ሌላው ካህን የኢሜር ልጅ፣ የምሺሌሞት ልጅ፣ የአሕዛይ ልጅ፣ የኤዝርኤል ልጅ፣ አማስያ ነበር፡፡
\v 14 ከዚያ ነገድ ደፋር የሆኑ 128 ወታደሮች በኢየሩሳሌም ተቀመጡ፡፡ የእነርሱ መሪ የሐግዶሊም ልጅ ዘብድኤል ነበር፡፡
\s5
\v 15 በኢየሩሳሌም የተቀመጠው ሌላው የሌዊ ትውልድ የቡኒ ልጅ የአሳብያ ልጅ፣ የዓዝሪቃም ልጅ፣ የአሱብ ልጅ ሻማያ ነበር፡፡
\v 16 ከቤ ተመቅደሱ ውጭ ያለውን ሥራ የሚከታተሉ ሁለቱ ሌዋውያን ታላላቅ ሰዎች ሳባታይ እና ዮዛባት ነበሩ፡፡
\s5
\v 17 ሌላው የአሳፍ ልጅ፣ የዘብዲ ልጅ፣ የሚካ ልጅ መታንያ ነበር፡፡ መታንያ የቤተ መቅደሱ የመዘምራን ቡድን እግዚአብሔርን ለማመስገን ዝማሬ ሲያቀርብ ቡድኑን ይመራ ነበር፡፡ ረዳቱ በቅበቃር ነበር፡፡ ሌላው በኢየሩሳሌም የተቀመጠው የኤዶታም ልጅ፣ የጋላል ልጅ፣ የሳሙኤል ልጅ አብድያ ነበር፡፡
\v 18 በጠቅላላው፣ ለእግዚአብሔር በተለየችው ከተማ 284 ሌዋውያን ነበሩ፡፡
\s5
\v 19 በኢየሩሳሌም የተቀመጡት በር ጠባቂዎች ዓቁብ እና ጤልሞን ነበሩ፡፡ እነርሱና በአጠቃላይ በኢየሩሳሌም የተቀመጡ ቤተሰቦቸው 172 ነበሩ፡፡
\v 20 ሌሎቹ የእስራኤል ትውልዶች የሌዊና ካህናትን ትውልዶች ጨምሮ በገዛ ይዞታቸውና በሌሎች ከተሞችና በይሁዳ ከተማዎች ተቀመጡ፡፡
\v 21 የቤተ መቅደሱ ሰራተኞች ግን በኦፌል ኮረብታ ኢየሩሳሌም ውስጥ ተቀመጡ፡፡ እነርሱን የሚያዙት ሲሐ እና ጊሽጳ ነበሩ፡፡
\s5
\v 22 በኢየሩሳሌም የሚኖሩት የሌዊ ትውልዶች አለቃ የሚካ ልጅ፣ የመታንያ ልጅ፣ የሐሻብ ልጅ፣ የባኒ ልጅ ኦዚ ነበር፡፡ ኦዚ የአሳፍ ነገድ፣ በቤተ መቅደስ የዝማሬ ክፍሉ ሀላፊ ወገን ነበር፡፡
\v 23 የፋርስ ንጉስ እያንዳንዱ ነገድ በእያንዳንዱ ቀን በቤተ መቅደስ በሚቀርበው ዝማሬ እያንዳንዱ ነገድ የሚሰራውን ነገዶቹ እንዲወስኑ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡
\v 24 የይሁዳ ትውልድ የዛራ ነገድ የሆነው የሜሴዜቤል ልጅ ፈታያ በፋርስ መንግስት የእስራኤል አምባሳደር ነበር፡፡
\s5
\v 25 በኢየሩሳሌም ያልተቀመጡት አንዳንድ ሰዎች በእርሻቸው አቅራቢያ በሚገኙ መንደሮች ይኖሩ ነበር፡፡ ከይሁዳ ነገድ የሆኑ አንዳንዶች በቂርያት አርባቅ፣ በዲቦን፣ እና በይቀብጽኤል አጠገብ በሚገኙ መንደሮች ኖሩ፡፡
\v 26 አንዳንዶቹ በኢያሱ፣ በምላዳ፣ በቤትጳሌጥ፣
\v 27 በሐጸርሹዓል እና በቤርሳቤህ እንዲሁም በአቀራቢያው ባሉ መንደሮች ኖሩ፡፡
\s5
\v 28 ሌሎቹ በጺቅላግ፣ በምኮና እና በአካባቢው ባሉ መንደሮች፣
\v 29 በዓይንሪሞን፣ በጸርዓ፣ በየርሙት፣
\v 30 በዛኖዋ፣ በዓዶላም፣ እና በእነዚያ ከተሞች አቅራቢያ ተቀመጡ፡፡ አንዳንዶቹ በለኪሶ እና በአካባቢ ባሉ መንደሮች፣ እንዲሁም አንዳንዶች በዓዜቃና በአካባቢዋ ባሉ መንደሮች ተቀመጡ፡፡ እነዚህ ሁሉ ህዝቦች በደቡብ በቤርሳቤህ መሀል ባሉ ስፍራዎች እና በሰሜን ቦኖም ሸለቆ በኢየሩሳሌም ዳርቻ በይሁዳ ተቀመጡ፡፡
\s5
\v 31 የብንያም ጎሣ ሰዎች በጌባ፣ ማክማስ፣ በጋያ ይህ አይ ቤቴል ተብሎም ይታወቃል፣ እና በአካባቢው ባሉ መንደሮች፣
\v 32 በዓናቶች፣ በኖብ፣ በሐናንያ፣
\v 33 በሐጾር፣ በራማ፣ በጊቴም፣
\v 34 በሐዲድ፣ በስቦይም፣ በንቦላት፣
\v 35 በሎድ፣ በአኖ፣ እና የእጅ ጥበብ ባለሙያዎች ሸለቆ በሚባሉ ቦታዎች ተቀመጡ፡፡
\v 36 በይሁዳ የኖሩ አንዳንድ ሌዋውያን ከብንያም ሰዎች ጋር ለመኖር ሄዱ፡፡
\s5
\c 12
\p
\v 1 ብዙ ካህናትና የሌዊ ትውልዶች ከዘሩባቤል እና ከኢያሱ ጋር ከባቢሎን ተመለሱ፡፡ እነዚህም፡ ሠራያ፣ ኤርምያስ፣ ዕዝራ፣
\v 2 አማርያ፣ ሙሉክ፣ ሐጡስ፣
\v 3 ሴኬንያ፣ ሬሁም፣ ሜሪሞት፣
\s5
\v 4 አዶ፣ ጌንቶን፣ አብያ፣
\v 5 ሚያሚን፣ መዓድያ፣ ቢልጋ፣
\v 6 ሸማያ፣ ዮያሪብ፣ ዮዳኤ፣
\v 7 ሰሉ፣ ዓሞቅ፣ ኬልቅያስና ዮዳኤ ነበሩ፡፡ እነዚህ በኢያሱ ዘመን የካህናቱና የወንድሞቸው አለቆች ነበሩ፡፡
\s5
\v 8 የተመለሱት የሌዊ ትውልዶች ዝርዝር ይህ ነው፡፡ እነርሱም ኢያሱ፣ ቢንዊ፣ ቀድምኤል፣ ሰራብያ፣ ይሁዳ እና መታንየ ነበሩ፡፡ የእነዚሀ ሀላፊነት ለእግዚአብሔር የምስጋና ዝማሬ ማቅረብ ነበር፡፡
\v 9 በቅቡቅያ፣ ዑኒም እና ሌሎች የሌዊ ትውልዶች በዝማሬ ወቅት በትይዩ የሚቆሙ የዝማሬ ቡድን አበጁ፡፡
\s5
\v 10 ከብዙ አመታት አስቀድሞ አያሱ ሊቀ ካህን ነበር፡፡ ኢያሱ የዩአቂም አባት ነበረ፣ ዮአቄም የኤልያሴብ አባት ነበረ፣ ኤልያሴብ የዩአዳን አባት ነበረ፣
\v 11 ዩአዳ የዮናታን አባት ነበረ፣ ዮናታን የያዱአን አባት ነበረ፡፡
\s5
\v 12 ዮአቂም የካህናቱ ሁሉ መሪ ነበረ፡፡ የካህናቱ ቤተሰቦች መሪዎች እነዚህ ነበሩ፡ የሠራያ ቤተሰብ መሪ ምራያ፣ የኤርምያስ ቤተሰብ መሪ ሐናንያ፣
\v 13 የዕዝራ ቤተሰብ መሪ ሜሱላም፣ የአማርያ ቤተሰብ መሪ ይሆሐናን
\v 14 የሙሊኪ ቤተሰብ መሪ ዮናታን፣ የሰብንያ ቤተሰብ መሪ ዮሴፍ
\s5
\v 15 ከካሪም ቤተሰብ ብዙዎቹ መሪዎች ዓድና ነበሩ፣ ከመራዮት ቤተሰብ ሔልቃይ
\v 16 ከአዶ ቤተሰብ ዘካርያስ ከጌንቶን ቤተሰብ ሜሱላም
\v 17 ከአብያ ቤተሰብ ዝክሪ መሪዎች ነበሩ፡፡ ከሚያሚን ቤተሰብም አንድ መሪ ነበር፡፡ ከሞዓድያ ቤተሰብ ፈልጣይ ነበር፡፡
\v 18 ከቢልጋ ቤተሰብ ሳሙስ፣ ከሸማያ ቤተሰብ ዮናታን
\v 19 ከዮያሪብ ቤተሰብ መትናይ፣ ከዮዳኤ ቤተሰብ ኦዚ፣
\v 20 ከሳላይ ቤተሰብ ቃላይ፣ ከዓምቅ ቤተሰብ ዔቤር፣
\v 21 ከኬልቅያስ ቤተሰብ ሐሽብያ፣
\s5
\v 22 ኤሊያሴብ ሌዋውያንን በሚመራበት ወቅት፣ የእነርሱ ሁሉ ዝርዝር ይህ ነው፡ ኤሊያሴብ፣ ዮአዳ፣ ዮሐና እና ያዱአ የካህናቱ ሁሉ መሪዎች ነበሩ፡፡ እነርሱ የሌዊ ትውልድ የሆኑትን ቤተሰቦች ስሞች መዘገቡ፡፡ዳርዮስ የፋርስ ንጉስ በነበረበት ዘመን የየቤተሰቡን መሪዎች የመመዝገቡ ሀላፊነት የካህናቱ ነበር፡፡
\v 23 የሌዊ ትውልድ የሆኑ የቤተሰብ መሪዎችን ስሞች ዝርዝር በታሪክ መጽሐፍ ጽፈው ነበር፡፡ የኤልያሴብ የልጅ ልጅ የሆነው ዮሐና የካህናት ሁሉ መሪ እስከ ሆነበት ጊዜ ድረስ ያሉትን ክንዋኔዎች መዝግበው ነበር፡፡
\s5
\v 24 እነዚህ የሌዋውያን መሪዎች ነበሩ፡ ሐሽብያ፣ ሰራብያ፣ የቀድመኤል ልጅ ኢያሱ፣ እና ለእግዚአብሔር ውዳሴና ምስጋና ለማቅረብ ከእነርሱ ፊት ለፊት የቆሙ ወንድሞቸው፡፡ ይህንንም የእግዚአብሔር አገልጋይ የሆነው ንጉስ ዳዊት እንዳዘዛቸው እንደዚያው አደረጉ፡፡
\v 25 በር ጠባቀዎቹ፣ መታንያ፣ በቅቡቅያ፣ አብድዩ፣ ሜሱላም ጤልሞንና ዓቁብ ነበሩ፡፡
\v 26 አገረ ገዢው ነህምያ እና ካህኑ ዕዝራ በነበሩበት ወቅት፣ በኢዮሴዴቅ የልጅ ልጅ በኢያሱ ልጅ በዮቂም ዘመን ይህንን ሥራ ሰሩ፡፡ ዕዝራ የአይሁድን ህግጋትም በሚገባ ያውቅ ነበር፡፡
\s5
\v 27 የኢየሩሳሌምን ቅጥር ስንመርቅ፣ የሌዊን ትወልዶች ከሚኖሩባቸው የእስራኤል አካባቢዎች የቅጥሩን ምርቃት ያከብሩ ዘንድ ጠራናቸው፡፡ እነርሱም እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ብዙዎቹም በጽናጽልና፣ በበገና፣ በክራርና በሌሎች የክር ሙዚቃ መሳሪያዎች በመጫወት ይዘምሩ ነበር፡፡
\v 28 በህብረት ያለማቋረጥ የሚዘምሩትን የሌዊ ወገኖች ሰበሰብን፡፡ ከሰፈሩበት ከኢየሩሳሌም ዙሪያ ከነጦፋውያን መንደሮችና ከደቡብ ምስራቅ ኢየሩሳሌም ወደ መሃል ኢየሩሳሌም መጡ፡፡
\s5
\v 29 ከሰሜን ምስራቅ የኢየሩሳሌም ሶስት ቦታዎችም ከቤት ጌልገላ፣ ከጌባ አካባቢና ከዓዝሞት አካባቢ መጡ፡፡ መዘምራኑ ኢየሩሳሌም አቅራቢያ መንደሮችን መሰረቱ፡፡
\v 30 ካህናቱና የሌዊ ወገኖች ራሳቸውን በእግዚአብሔር ፊት የመንጻት ሥርዓት አደረጉ፣ ለህዝቡም ይህንኑ ስርዓት አደረጉ፣ ለከተማዋ መግቢያዎችና በመጨረሻም ለቅጥሩ ጭምር ስርዓቱን ፈጸሙ፡፡
\s5
\v 31 ከዚያ በቅጥሩ ጫፍ የይሁዳ መሪዎችን በአንድነት ሰበሰብኩ፣ እግዚአብሔርን እያገገኑ በቅጥሩ ላይ በከተማዋ ዙሪያ በሰልፍ እንዲዞሩ ሁለት ትላልቅ ቡድኖችን እዲመሩ ሾምኳቸው፡፡ በከተማይቱ ትይዩ ሲሆኑ፣ አንዱ ቡድን ወደ ቀኝ የቆሻሻ መጣያው በር ወደሚባለው ሄደ፡፡
\s5
\v 32 ከመሪዎቻቸው በኋላ ሆሻያና የይሁዳ እኩሌቶቹ መሪዎች ተሰለፉ፡፡
\v 33 ከእነርሱ በኋላ የተከተሏቸው ዓዛርያስ፣ ዕዝራ፣ ሜሱላም፣
\v 34 ይዳ፣ ብንያም፣ ሸማያ፣ ኤርምያስ፣
\v 35 እና መለከት የሚጫወቱ አንዳንድ የክህናቱ ወንዶች ልጆች ናቸው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ የአሳፍ ትውልድ የሆኑት የዘኩር ልጅ፣ የሚካያ ልጅ፣ የመታንያ ልጅ፣ የሸማያ ልጅ፣ የዮናታን ልጅ ዘካርያስ ይገኙበታል፡፡
\s5
\v 36 ከእነዚህ በኋላ የሚገዙት የዘካርያስ ቤተሰቦች ሌሎች አባላት ነበሩ፡፡ ከእነዚህም ሸማያ፣ ኤዝርኤል፣ ሚላላይ፣ ጊላላይ፣ መዓይ፣ ናትናኤል፣ ይሁዳ፣ እና አናኒምን ያካትታል፡፡ ሁሉም ንጉስ ዳዊት ከብዙ አመታት አስቀድሞ ይጫወትበት የነበሩ እነዚያኑ አይነት የሙዚቃ መሳሪያዎችን ይጫወቱ ነበር፡፡ የአይሁድን ህግጋት በሚገባ የሚያውቀው ሰው ዕዝራ፣ ከዚህ ቡድን ፊት ሰልፉን ይመራ ነበር፡፡
\v 37 የፋፏቴ በር ሲደርሱ፣ ወደ ዳዊት ከተማ ደረጃዎችን ወጡ፣ የዳዊትን ቤተ መንግስት አልፈው፣ ከዚያ ውሃ በር አጠገብ ወደሚገኘው ቅጥር በከተማዋ ምስራቅ አቅጣጫ ሄዱ፡፡
\s5
\v 38 ለያህዌ ይዘምርና ያመሰግን የነበረው ሌላው የዝማሬ ቡድን በቅጥሩ ላይ በግራ በኩል በሰልፍ አለፈ፡፡ እኔ ከህዝቡ ከፊሉን ይዤ ተከተልኳቸው፡፡ እኛ የእቶን ግንቡን አልፈን ወደ ሰፊው ቅጥር አለፍን፡፡
\v 39 ከዚያ ተነስተን የኤፍሬምን በር፣ የጄቫናን በር፣ የአሣን በር፣ የሐናንኤልን ግንብ፣ የመቶ ወታደሮችን በር አልፈን ወደ በጎች በር ተጓዝን፡፡ ወደ ቤተ መቅደሱ በር ስንቃረብ ሰልፋችንን ጨረስን፡፡
\s5
\v 40 ሁለቱም ቡድኖች እየዘመሩና እርሱን እያመሰገኑ ወደ እግዚአብሔር ቤት ደረሱ፡፡ በዚያም በየስፍራቸው ቆሙ፡፡ እኔና ከእኔ ጋር የነበሩ መሪዎችም በስፍራችን ቆምን፡፡
\v 41 የእኔ ቡድን መለከት የሚነፉትን እነዚህን ካህናት ያጠቃልላል፡ ኤልያቄም፣ መዕሤያ፣ ሚንያሚን፣ ሚካያ፣ ኤልዮዔናይ፣ ዘካርያስ እና ሐናንያ፣
\v 42 ሌሎቹም መዕሤያ፣ ሸማያ፣ አልዓዛር፣ ኦዚ፣ ይሆሐናን፣ መልክያ፣ ኤላም እና ኤድር ናቸው፡፡ መሪያቸው ይዝራሕያ የሆነው መዘምራኑ ድምቸውን ከፍ አድርገው ዘመሩ፡፡
\s5
\v 43 ከቤተ መቅደሱ ውጭ ከሄድን በኋላ ብዙ መስዋዕቶችን አቀረብን፡፡ እኛ ወንዶች ሁላችን እግዚብሔር በጣም ደስተኞች ስላደረገን ደስ አለን፡፡ ሴቶቹና ልጆችም እንደዚሁ ደስ አላቸው፤ በሩቅ ያሉ ሰዎች እኛ በኢሩሳሌም ውስጥ ሆነን የምናሰማውን ድምጽ መስማት ይችሉ ነበር፡፡
\s5
\v 44 በዚያን ቀን ህዝቡ ለቤተ መቅደስ የሰጠውን ገንዘብ ለሚያስቀምጡበት ግምጃ ቤት ሀላፊ የሚሆኑ ወንዶች ተሾሙ፡፡ እነዚህ ሰዎች ለአስራትና በየአመቱ ለሚሰበሰበው እህልና ፍራፍሬ በኩራቶችም ሀላፊዎች ነበሩ፡፡ እነዚሁ ሰዎች ወደ ግምጃ ቤቶቹ ከእርሻዎች ምርት ለካህናቱና ለሌዊ ትውልዶች ያመጡ ነበር፡፡ ይህ የተደረገው የይሁዳ ሰዎች በያህዌ ቤት የሚያገለግሉ አገልጋዮች እንዲኖር ይፈልጉ ስለነበር ነው፡፡
\v 45 ካህናቱና ሌዋውያኑ ነገሮችን ለማንጻት፣ በማንጻት ስርዓቱ ያህዌን ያገለግሉ ነበር፤ መዘምራኑ በቤተ መቅደስ፣ እንዲሁም በር ጠባቂዎቹ ንጉስ ዳዊትና ልጁ ሰለሞን እንዲደረግ እንደ ደነገጉት ስራቸውን ያከናውኑ ነበር፡፡
\s5
\v 46 ከዳዊትና ከአሳፍ ዘመን አንስቶ፣ የዘማሪዎች መሪዎች ነበሩ፤ መዘምራኑም እግዚአብሔርን ለማወደስና ለማመስገን ይዘምሩ ነበር፡፡
\v 47 ዘሩባቤል በነበረበት አመታትና በአገረ ገዥው ነህምያ ዘመን፣ ዘማርያኑና የቤተ መቅደስ በር ጠባቂዎች በየዕለቱ የሚያስፈልጋቸውን ምግብ መላው እስራኤል ያወጣ ነበር፡፡ ህዝቡ ለሌዋውያን ኑሮ የሚያስፈልገውን ያስቀምጡላቸውና ሌዋውያኑ ደግሞ ከካህናቱ ቀዳሚ መሪ ለሆኑት ለአሮን ትውልዶች የሚያስፈልገውን ያስቀምጡላቸው ነበር፡፡
\s5
\c 13
\p
\v 1 በዚያን ቀን እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠውን አሞናዊያን ወይም ሞአባዊያን የእግዚአብሔር ህዝቦች ወደሚያመልኩበት ስፍራ አይግቡ የሚለውን የህጉን ክፍል ካህናቱ ለህዝቡ አነበቡ፤ ህዝቡም አደመጠ፡፡
\v 2 ይህ የሆነው የአሞንና የሞአብ ሰዎች እስራኤላዊያን ከግብጽ ወጥተው ወደሚገቡበት አገር ሲጓዙ ምንም ምግብ ወይም ውሃ ስላልሰጧቸው ነበር፡፡ ይልቁንም፣ የአሞንና የሞብ ሰዎች በለዓም እስራኤላዊያንን እንዲረግም ገንዘብ ከፈሉት፡፡ እግዚአብሔር ግን እስራኤልን ለመርገም የተደረገውን ያን ጥረት ወደ በረከት ለወጠው፡፡
\v 3 ስለዚህም ህዝቡ እነዚያ ህጎች ሲነበቡላቸው በሰሙ ጊዜ፣ አባቶቻቸው ከሌሎች አገሮች የሆኑትን ሰዎች ሁሉ አስወጡ፡፡
\s5
\v 4 አስቀድሞ፣ ካህኑ ኤልያሴብ በቤተ መቅደሱ የግምጃ ቤቱ ኃላፊ ሆኖ ተሹሞ ነበር፡፡ እርሱም የጦቢያ ቤተዘመድ ነበር፡፡ እነርሱም የእህል ቁርባኖቹንና እጣኑን በዚያ ስፍራ አከማቹ፡፡
\v 5 ለቤተ መቅደስ የሚያገለግሉ ዕቃዎችን በዚያ አስቀመጡ፡፡ ህዝቡ ለሌዋውያን የሰጠውን ስጦታዎች በግምጃ ቤት አስቀመጡ፡፡ እግዚአብሔር ለሌዋውያኑ፣ ለዘማሪዎቹና ለበር ጠባቂዎች እንዲሰጡ ያዘዘውን የእህል፣ የወይንና የወይራ ዘይት አስራት አመጡ፡፡ ሌሎች ካህናትን ለመደገፍም ስጦታዎቹን አመጡ፡፡
\s5
\v 6 በዚያን ጊዜ እኔ ኢየሩሳሌም ውስጥ አልነበርኩም፡፡ አርጤክስስ የባቢሎን ንጉስ በነበረበት በሰላሳ ሁለተኛው አመት ያከናወንኩትን ለንጉሱ ለመናገር ተመለስኩ፡፡ ለጥቂት ጊዜ በዚያ ከቆየሁ በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም እንድመለስ እንዲፈቅደልኝ ንጉሱን ጠየቅሁት፡፡
\v 7 ስመለስ፣ ኤልያሴብ ያደረገውን ክፉ ነገር አወቅሁ፡፡ ጦቢያ ለእግዚአብሔር የተለየውን አንድ ክፍል ቤት ለገዛ ጥቅሙ እንዲያውለው ትቶለት ነበር፡፡
\s5
\v 8 እኔም በጣም ተቆጣሁ፡፡ ወደዚያ ክፍል ገብቼ የጦቢያ የሆኑትን ነገሮች ሁሉ አውጥቼ ጣልኩ፡፡
\v 9 ከዚያ ያንን ክፍል እንደገና ለማንጻት የማንጻት ሥርኣት እንዲደረግ አዘዝኩ፡፡ እንደዚሁም ደግሞ ለቤተ መቅደሱ አገልግሎት የሚውሉ ማናቸውም ዕቃዎችና የእህል ቁርባኖችን እንዲሁም እጣኑ ወደነበሩበት ወደዚያ ክፍል እንዲመለሱ አዘዝኩ፡፡
\s5
\v 10 የእስራኤል ሰዎች የሚያስፈልጋቸውን ቀለብ ወደ ግምጃ ቤት ስላላመጡአቸው፣ የቤተ መቅደሱ ዘማሪዎችና ሌሎች ሌዋውያን ኢየሩሳሌምን ለቀው ወደ እርሻዎቻቸው መመለሳቸውን ተረዳሁ፡፡
\v 11 ስለዚህ ሹማምንቱን እንዲህ ስል ገሰጽኳቸው፣ “በቤተ መቅደስ ለሚካሄደው አገልግሎት ጥንቃቄ ያላደረጋችሁት ለምንድን ነው?” ስለዚህም እነርሱን በአንድነት ሰብስቤ ወደ መጀመሪያ ስፍራቸው መለስኳቸው፡፡
\s5
\v 12 ከዚያ የይሁዳ ሰዎች በሙሉ የእህል፣ የወይንና የወይራ ዘይት አስራታቸውን ወደ ቤተ መቅደሱ ግምጃ ቤት ዳግም ማምጣት ጀመሩ፡፡
\v 13 እኔም እነዚህን ሰዎች የግምጃ ቤቶቹ ሀላፊዎች አድርጌ ሾምኳቸው፡፡ እነርሱም ካህኑ ሰሌምያ፣ የአይሁድ ህግ አዋቂው ሳዶቅ፣ እና ከሌዊ ወገን የሆነው ፈዳያ ናቸው፡፡ እነርሱን እንዲረዳ የመታንያን የልጅ ልጅ የዘኩርን ልጅ ሐናን ሾምኩት፡፡ እነዚያ ሰዎች ለሠራተኞቹ ወገኖቸው ስጦታዎችን በትክክል እንደሚያከፋፍሉ ልተማመንባቸው እንደምችል አውቅ ነበር፡፡
\v 14 አምላኬ ሆይ፣ ለአንተ ቤተ መቅደስ የሰራኋቸውን እነዚህን መልካም ሥራዎችና እዚህ ለተሰራው ሰራ ሁሉ ያደረኩትን አትርሳ!
\s5
\v 15 በእነዚያ ጊዜያት፣ ይሁዳ ውስጥ አንዳንዶች በሰንበት ቀን ሲሰሩ አየሁ፡፡ አንዳንዶች ወይን ለመጥመቅ የወይን ፍሬ ይረግጡ ነበር፡፡ ሌሎች እህል፣ የወይን አቁማዳዎች፣ የወይን ፍሬ የሞሉ ቅርንጫቶች፣ በለስ፣ እና ሌሎች ብዙ ነገሮች በአህዮቻቸው ጭነው ወደ ኢየሩሳሌም ይወስዱ ነበር፡፡ በሰንበት ለይሁዳ ሰዎች ምንም ነገር እንዳይሸጡ አስጠነቀቅኳቸው፡፡
\s5
\v 16 ደግሞም በኢየሩሳሌም የሚኖሩ አንዳንድ የጢሮስ ሰዎች በሰንበት ቀን አሳና ሌሎች ነገሮችን ለአይሁድ ሰዎች ለመሸጥ ወደ ኢየረሳሌም ሲያመጡ አይሁ፡፡
\v 17 ስለዚህ የአይሁድን መሪዎች በመገሰጽ እንዲህ አልኳቸው፣ “ይህ የምታደርጉት በጣም ክፉ ነገር ነው! በሰንበት ቀን እግዚአብሔር በፍጹም እንዲሆን የማይወደውን ነገር እያደረጋችሁት ነው፡፡
\v 18 አባቶችሁ እንደዚህ ያለ ነገሮችን አደረጉ፣ ስለዚህም እግዚአብሔር ቀጣቸው፡፡ በእነርሱ ኃጢአት ምክንያት ይህች ከተማ እንድትጠፋ ፈቅዶ ነበር! እና አሁን የሰንበት ቀን ህግጋትን በመተላፍ እግዚአብሔር በእኛ ላይ እንዲቆጣ ምክንያት እየሆናችሁ ነው፣ እናም የከፋ ቅጣት ይቀጣናል!”
\s5
\v 19 ቀኑ ሲመሽ በኢየሩሳሌም መግቢያ ላይ አንዳንድ የራሴን ሰዎች አቆምኩ፣ ስለዚህ እነዚህ ሰዎች በዚያን ቀን ምንም አይነት የሚሸጥ ዕቃ ማንም ሰው ወደ ከተማይቱ እንዳያስገባ ያደርጋሉ፡፡
\v 20 ነጋዴዎችና ሻጮች የተለያዩ አይነት ዕቃዎችና ሸቀጦች እንዲሁም አንዳንድ ነገሮችን በማግስቱ ለመሸጥ ተስፋ አድርገው ሰንበት ከሚጀምርበት ከአርብ ምሽት አንስቶ ከኢየሩሳሌም ውጭ ለጥቂት ጊዜ ይሰፍራሉ፡፡
\s5
\v 21 እኔም እንዲህ ስል አስጠነቀቅኳቸው፣ “ዓርብ ምሽት ከቅጥሩ ውጭ በዚህ ማደራችሁ አይጠቅማችሁም! ይህን ደግማችሁ ብታደርጉ፣ እኔ ራሴ አስወጣችሁና አባርራችኋለሁ!” ስለዚህ ከዚያ በኋላ፣ ዳግመኛ በሰንበት ቀናት ተመልሰው አልመጡም፡፡
\v 22 እንደዚሁም ደግሞ የሌዊ ትውልዶች፤ ራሳቸውን ለማንጻት የማንጻት ሥርዓቱን እንዲፈጽሙና የከተማዋን በሮች ለመጠበቅ ስፍራቸውን እንዲይዙ፣ በዚያ የተቀደሰ ቀን ነጋዴዎች እንዳይገቡ በመከልከል ሰንበት ቅዱስ ሆኖ መጠበቁን እንዲያረጋግጡ አዘዝኳቸው፡፡ አምላኬ ሆይ፣ ስለዚህም ደግሞ አሰበኝ! እንደ ታላቅ ፍቅርህ መጠን ምህረትህን አድርግልኝ፡፡
\s5
\v 23 በዚያን ጊዜ ብዙዎቹ የአይሁድ ወንዶች ከአሽዶድ፣ አሞንና ሞዓብ ሴቶች ጋር መጋባታቸውን አወቅሁ፡፡
\v 24 ከልጆቻቸው እኩሌቶቹ የኖሩበትን ህዝብ የአሽዶድ ሰዎችን ቋንቋ ወይም ሌላ ቋንቋ ይናገሩ እንጂ የአይድን ቋንቋ መናገር አይችሉም ነበር፡፡
\s5
\v 25 ስለዚህም እነዚያን ሰዎች ገስጽኳቸው፣ እግዚአብሔር የተረገሙ እንዲያደርጋቸው ጠየቅኩት፤ አንዳንዶቹን በቡጢ መታኋቸው፤ የአንዳንዶቹንም ጸጉር ነጨሁ! ከዚያ እግዚአብሔር እንደሚሰማ በማወቅ ዳግመኛ ባዕዳንን እንዳያገቡና ልጆቻቸውም ከባዕዳን ጋር እንዲጋቡ እንዳይፈቅዱ ጥብቅ ቃል ኪዳን እንዲገቡ አስገደድኳቸው፡፡
\v 26 እንዲህ አልኳቸው፣ “የእስራኤል ንጉስ፣ ሰለሞን፣ ከባዕድ ሴቶች ጋር በመጋባቱ ምክንያት ኃጢአት ሰራ፡፡ እርሱ ከሌሎች መንግስታት ነገስታት ሁሉ ታላቅ ነበር፡፡ እግዘአብሔር ወዶት በመላው የእስራኤል ህዝብ ላይ ንጉስ አደረገው፡፡ ነገር ግን ባዕዳን የሆኑት ሚስቶቹ ኃጢአት እንዲሰራ ምክንያት ሆኑ፡፡
\v 27 እናንተ ስህተት መሆኑን እያወቃችሁ ባዕድ ሚስቶችን እንዳገባችሁና ጣኦት አምላኪ የሆኑ ባዕድ ሴቶችን በማግባት በአምላካችሁ ላይ ታላቅ ኃጢአት እንደፈፀማችሁ እኛም ያንን ማድረግ ያለብን ይመስላችኋልን?”
\s5
\v 28 ከዮአዳ ልጆች አንዱ፣ የሊቀ ካህኑ የአልያሴብ ልጅ የሰንበላጥን ልጅ አገባ፡፡ ስለዚህ የዮአዳን ልጅ ከኢየሩሳሌም አባረርኩት፡፡
\v 29 አምላኬ ሆይ በክህነት ማዕረግ ላይ ዕፍረት ያስተሉትን አስብ፣ እናም በስራቸው የክህነትንና የሌዋዊነትን ቃል ኪዳን ተላልፈዋል!
\s5
\v 30 ከሌሎች አገሮችና ሀይማኖቶች ካመጧቸው ማናቸውም ነገር አነፃኋቸው፣ እንደዚሁም ለካህናቱና ለሌዊ ወገኖች ደንቦችን ሰጠሁ፣ ስለዚህም እያንዳንዳቸው ማድረግ የለባቸውን ያውቃሉ፡፡
\v 31 በተወሰነው ጊዜና ቀናት በመሰዊያው ላይ የሚነድ ማገዶ ስለመኖሩ አረጋገጥሁ፡፡ ህዝቡ ከምርቱ በኩራቱን ወደ ግምጃ ቤት እንዲያመጣ መመሪያ ሰጠሁ፡፡ አምላኬ ሆይ፣ እዚህን ሁሉ ነገሮች ማድረጌን አትርሳ፣ እነዚህን በማድረጌም ባርከኝ፡፡