532 lines
54 KiB
Plaintext
532 lines
54 KiB
Plaintext
\id EZR
|
|
\ide UTF-8
|
|
\h ዕዝራ
|
|
\toc1 ዕዝራ
|
|
\toc2 ዕዝራ
|
|
\toc3 ezr
|
|
\mt ዕዝራ
|
|
|
|
\s5
|
|
\c 1
|
|
\p
|
|
\v 1 የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ በነገሠበት የመጀመሪያው ዓመት እግዚአብሔር በኤርምያስ አፍ የተነገረውን ቃሉን ፈጸመና የቂሮስን መንፈስ አነሣሣ። የቂሮስ ድምጽ በመንግሥቱ ሁሉ ላይ ተሰማ። የተነገረውና የተጻፈው እንዲህ የሚል ነው፤
|
|
\v 2 "የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ እንዲህ ይላል፤ የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር የምድር መንግሥታትን ሁሉ ሰጥቶኛል፥ በይሁዳ ባለች በኢየሩሳሌም ቤት እንድሠራለት አዞኛል።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 3 ማንም ከሕዝቡ ጋር የሚመጣ ቢኖር አምላኩ ከእርሱ ጋር ይሁን፥ ወደ ኢየሩሳሌም ይውጣና የኢየሩሳሌም አምላክ ለሆነው ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ቤት ይሥራ።
|
|
\v 4 የሚቀሩት በሚኖሩባቸው በመንግሥቱ በየትኛውም አካባቢ የሚገኙ ሰዎች ብርና ወርቅ፥ ንብረትና እንስሳ በተጨማሪም በኢየሩሳሌም ላለው የእግዚአብሔር ቤት የበጎ ፈቃድ ቁርባን ይስጡ"።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 5 ከዚያም የይሁዳና የብንያም ነገድ የቤተሰብ አለቆች፥ ካህናቱ፥ ሌዋውያኑና እንዲሄዱና ቤቱን እንዲሠሩለት እግዚአብሔር መንፈሳቸውን ያነሣሣ ሁሉ ተነሡ።
|
|
\v 6 በዙሪያቸው ያሉትም ሥራቸውን በብርና ወርቅ ዕቃ፥ በቁሳቁስ፥ በእንስሳ፥ በጠቃሚ ዕቃዎችና በበጎ ፈቃዳቸው በሰጡት መባ አገዟቸው።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 7 ደግሞም ናቡከደነፆር ከኢየሩሳሌም አምጥቶ በአማልክቶቹ ቤቶች ያኖራቸውን የእግዚአብሔርን ቤት ዕቃዎች ንጉሡ ቂሮስ አወጣቸው።
|
|
\v 8 ቂሮስ በግምጃ ቤቱ ኃላፊ በሚትሪዳጡ እጅ ሰጠ፥ እርሱም ለይሁዳው አለቃ ለሰሳብሳር ቆጥሮ አስረከበው።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 9 ብዛታቸው እንደሚከተለው ነበር፤ ሠላሳ የወርቅ ሳሕን፥ አንድ ሺህ የብር ሳሕን፥ ሃያ ዘጠኝ ሌሎች ሳሕኖች።
|
|
\v 10 ሠላሳ ጎድጓዳ የወርቅ ሳሕን፥ 410 ትናንሽ ጎድጓዳ የብር ሳሕኖችና ሌሎች አንድ ሺህ ዕቃዎች ነበርሩ። በአጠቃላይ 5400 የብርና የወርቅ ዕቃዎች ነበሩ።
|
|
\v 11 ምርኮኞቹ ከባቢሎን ወደ ኢየሩሳሌም በሄዱ ጊዜ እነዚህን ሁሉ ሰሳብሳር አመጣቸው።
|
|
|
|
\s5
|
|
\c 2
|
|
\p
|
|
\v 1 ንጉሡ ናቡከደነፆር ማርኮ ወደ ባቢሎን ካፈለሳቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና በይሁዳ ወዳሉ ወደየከተሞቻቸው የተመለሱት እነዚህ ናችው፤
|
|
\v 2 እነርሱም ከዘሩባቤል፥ ከኢያሱ፥ ከነህምያ፥ ከሠራያ፥ ከረዕላያ፥ ከመርዶክዮስ፥ ከበላሳን፥ ከመሴፋር፥ ከበጉዋይ፥ ከሬሁምና ከበዓና ጋር መጡ። የሚከተለው የእስራኤል ሰዎች የወንዶቹ ዝርዝር ነው፤
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 3 የፋሮስ ተወላጆች 2172።
|
|
\v 4 የሰፋጥያስ ተወላጆች 372።
|
|
\v 5 የኤራ ተወላጆች 775።
|
|
\v 6 በኢያሱና በኢዮአብ በኩል የፊሐት ሞዓብ ተወላጆች 2812።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 7 የኤላም ተወላጆች 1254።
|
|
\v 8 የዛቱዕ ተወላጆች 945።
|
|
\v 9 የዘካይ ተወላጆች 760።
|
|
\v 10 የባኒ ተወላጆች 642።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 11 የቤባይ ተወላጆች 623።
|
|
\v 12 የዓዝጋድ ተወላጆች 1222።
|
|
\v 13 የአዶኒቃም ተወላጆች 666።
|
|
\v 14 የበጉዋይ ተወላጆች 2056።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 15 የዓዲን ተወላጆች 454።
|
|
\v 16 በሕዝቅያስ በኩል የአጤር ሰዎች 98።
|
|
\v 17 የቤሳይ ተወላጆች 323።
|
|
\v 18 የዮራ ተወላጆች 112።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 19 የሐሱም ሰዎች 223።
|
|
\v 20 የጋቤር ሰዎች 95።
|
|
\v 21 የቤተልሔም ሰዎች 123።
|
|
\v 22 የነቶፋ ሰዎች 56።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 23 የዓናቶት ሰዎች 128።
|
|
\v 24 የዓዝሞት ሰዎች 42።
|
|
\v 25 የቂርያት ይዓሪም፥ የከፊራና የብኤሮት ሰዎች 743።
|
|
\v 26 የራማና የጌባ ሰዎች 621።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 27 የማክማስ ሰዎች 122።
|
|
\v 28 የቤቴልና የጋይ ሰዎች 223።
|
|
\v 29 የናባው ሰዎች 52።
|
|
\v 30 የመጌብስ ሰዎች 156።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 31 የሌላው ኤላም ሰዎች 1254።
|
|
\v 32 የካሪም ሰዎች 320።
|
|
\v 33 የሎድ፥ የሐዲድና የኦኖም ሰዎች 725።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 34 የኢያሪኮ ሰዎች 345።
|
|
\v 35 የሴናዓ ሰዎች 3630።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 36 ካህናቱ፤ ከኢያሱ ቤተሰብ የዮዳኤ ተወላጆች 973።
|
|
\v 37 የኢሜር ተወላጆች 1052።
|
|
\v 38 የፋስኮር ተወላጆች 1247።
|
|
\v 39 የካሪም ተወላጆች 1017።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 40 ሌዋውያኑ፤ በሆዳይዋ በኩል የኢያሱና የቀድምኤል ተወላጆች 74።
|
|
\v 41 የቤተ መቅደሱ መዘምራን፤ የአሳፍ ተወላጆች 128።
|
|
\v 42 የበረኞቹ ተወላጆች፤ የሴሎም፥ የአጤር፥ የጤልሞን፥ የዓቁብ፥ የሐጢጣና የሶባይ ተወላጆች በአጠቃላይ 139።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 43 በቤተ መቅደስ ውስጥ እንዲያገለግሉ ተመድበው የነበሩት፤ የሲሐ፥ ሐሡፋ፥ ጠብዖት፥
|
|
\v 44 ኬራስ፥ ሲዓ፥ ፋዶን፥
|
|
\v 45 ልባና፥ አጋባ፥ ዓቁብ፥
|
|
\v 46 አጋብ፥ ሰምላይና ሐናን ተወላጆች፤
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 47 የጌዴል፥ ጋሐር፥ ራያ፥
|
|
\v 48 ረአሶን፥ ኔቆዳ፥ ጋሴም፥
|
|
\v 49 ዖዛ፥ ፋሴሐ፥ ቤሳይ፥
|
|
\v 50 አስና፥ ምዑናውያንና ንፉሰሲም ተወላጆች፤
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 51 የበቅቡቅ፥ ሐቁፋ፥ ሐርሑር፥
|
|
\v 52 በስሎት፥ ምሒዳ፥ ሐርሳ፥
|
|
\v 53 በርቆስ፥ ሲሣራ፥ ቴማ፥
|
|
\v 54 ንስያና ሐጢፋ ተወላጆች።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 55 የሰለሞን አገልጋዮች ተወላጆች፤ የሶጣይ፥ ሶፌሬት፥ ፍሩዳ፥
|
|
\v 56 የዕላ፥ ደርቆን፥ ጌዴል፥
|
|
\v 57 ሰፋጥያስ፥ ሐጢል፥ ፈክራት፥ ሐፂቦይምና አሚ ተወላጆች።
|
|
\v 58 በቤተ መቅደስ እንዲያገለግሉ የተመደቡት ተወላጆችና የሰለሞን አገልጋዮች ተወላጆች በድምሩ 392 ነበሩ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 59 ቴልሜላን፥ ቴላሬሳን፥ ክሩብን፥ አዳንና ኢሜርን ትተው የመጡ፥ ነገር ግን አባቶቻቸው እስራኤላውያን ስለመሆናቸው ማስረዳት ያልቻሉ
|
|
\v 60 652 የዳላያ፥ የጦብያና የኔቆዳ ተወላጆች ተካተቱ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 61 የካህናቱ ተወላጆችም፤ የኤብያ፥ የአቆስና የቤርዜሊ (እርሱም ከገለዓዳዊው ከቤርዜሊ ሴቶች ሚስት በማግባቱ በስማቸው የተጠራው ነው) ተወላጆች።
|
|
\v 62 እነዚህ በመዝገቡ ውስጥ የትውልዳቸውን ሐረግ ቢፈልጉም ለማግኘት ስላልቻሉ ከክህነት አገልግሎት ታገዱ።
|
|
\v 63 በኡሪምና በቱሚም የሚዳኝ ካህን እስኪገኝ ድረስ ከማንኛውም የተቀደሰ መሥዋዕት እንዳይበሉ አስተዳዳሪው አዘዛቸው።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 64 ጠቅላላ ሕዝቡ7337
|
|
\v 65 ወንድና ሴት አገልጋዮቻቸውን እኔዲሁም 200 ወንድና ሴት የቤተ መቅደስ መዘምራኖቻቸውን ሳይጨምር 42360 ነበር።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 66 736 ፈረሶች፥ 245 በቅሎዎች፥
|
|
\v 67 435 ግመሎችና 6720 አህዮች ነበሯቸው።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 68 በኢየሩሳሌም ወዳለው የእግዚአብሔር ቤት በሄዱ ጊዜ የአባቶች አለቆች ለቤቱ መሥሪያ የበጎ ፈቃድ ስጦታዎቻቸውን ሰጡ።
|
|
\v 69 ለሥራው የሚያስፈልገውን እንደ ችሎታቸው መጠን ሰጡ፤ የሰጡትም ስልሳ አንድ ሺህ የወርቅ ዳሪክ፥ አምስት ሺህ ምናን ብርና አንድ መቶ የክህነት ልብስ ነበር።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 70 ካንናቱና ሌዋውያኑ፥ ሕዝቡ፥ የቤተ መቅደስ መዘምራን፥ በረኞቹና በቤተ መቅደስ እንዲያገለግሉ የተመደቡት በየከተሞቻቸው ተቀመጡ። የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ በከተምቻቸው ነበሩ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\c 3
|
|
\p
|
|
\v 1 የእስራኤል ሕዝብ በኢየሩሳሌም እንደ አንድ ሰው ሆነው በሚሰበሰቡበት ጊዜ ወደ ከተሞቻቸው ከመጡ ሰባት ወር ሆኗቸው ነበር።
|
|
\v 2 የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱና ካህናት ወንድሞቹ፥ የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤልና ወንድሞቹ ተነሥተው በእግዚአብሔር ሰው በሙሴ ሕግ እንደታዘዘው የሚቃጠለው መሥዋዕት የሚቀርብበትን የእስራኤልን አምላክ መሠዊያ ሠሩ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 3 ከዚያም በምድሪቱ ከሚኖሩ ሰዎች የተነሣ ሥጋት ስለነበረባቸው መሠዊያውን በሥፍራው አቆሙት። የሚቃጠለውንም መሥዋዕት በጠዋትና በማታ ለእግዚአብሔር አቀረቡ።
|
|
\v 4 ደግሞም የዳሱን በዓል እንደተጻፈው አከበሩ፥ ለየዕለቱ እንደታዘዘው የሚቃጠለውን መሥዋዕት ዕለት በዕለት አቀረቡ።
|
|
\v 5 እንዲሁም በበጎ ፈቃድ ከሚቀርበው መባ ሁሉ ጋር ለዕለት፥ ለወርና ለተደነገጉት የእግዚአብሔር በዓላት ሁሉ መሥዋዕት ይቀርብ ነበር።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 6 የቤተ መቅደሱ መሠረት ባይጣልም በሰባተኛው ወር የመጀመሪያ ቀን የሚቃጠለውን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ማቅረብ ጀመሩ።
|
|
\v 7 እንዲሁም ለድንጋይ ጠራቢዎችና ለአናጺዎች ብር ሰጧቸው፤ የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ እንዳዘዘላቸው የዝግባ ዛፎችን ከሊባኖስ በባህር ወደ ኢዮጴ እንዲልኩላቸው ለጢሮስና ለሲዶና ሰዎች ምግብ፥ መጠጥና ዘይት ሰጧቸው።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 8 ከዚያም ዘሩባቤል፥ የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱ፥ የቀሩት ካህናቱ፥ ሌዋውያኑና ከምርኮ ወደ ኢየሩሳሌም የተመለሱት በኢየሩሳሌም ወዳለው ወደ እግዚአብሔር ቤት በመጡ በሁለተኛው ዓመት በሁለተኛው ወር ሥራውን ጀመሩ። ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ የሆኑትን ሌዋውያን የእግዚአብሔርን ቤት ሥራ እንዲቆጣጠሩ መደቧቸው።
|
|
\v 9 ኢያሱም ወንዶች ልጆቹንና ወንድሞቹን፥ ቀድምኤልና ወንዶች ልጆቹን፥ እንዲሁም የይሁዳን ተወላጆች የእግዚአብሔርን ቤት የሚሠሩትን ሰዎች ላእንዲቆጣጠሩ ደለደላቸው። ከእነርሱም ጋር የኤንሐዳድ ተወላጆች፥ ደግሞም ተወላጆቻቸውና ባልደረቦቻቸው ሌዋውያን ነበሩ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 10 ግንበኞቹ የእግዚአብሔርን ቤት መሠረት ጣሉ። ይህ ካህናቱ ልብሰ ተክህኗቸውን ለብሰውና መለከቶችን ይዘው እንዲቆሙና ሌዋውያኑ የአሳፍ ወንዶች ልጆች በእስራኤል ንጉሥ በዳዊት እጅ እንደታዘዘው በጸናጽል እግዚአብሔርን ለማመስገን አስቻላቸው።
|
|
\v 11 እነርሱም፥ "ቸር ነው! ለእስራኤልም የቃል ኪዳን ታማኝነቱ ለዘላለም ነው" እያሉ በምስጋናና በውዳሴ ለእግዚአብሔር ዘመሩ። የቤተ መቅደሱ መሠረት ስለተጣለ ሕዝቡ ሁሉ እግዚአብሔርን እያመሰገኑ በታላቅ የደስታ ድምጽ እልል አሉ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 12 ነገር ግን በርካታ ካህናት፥ ሌዋውያን፥ የአባቶች አለቆችና የመጀመሪያውን ቤት ያዩ አዛውንቶች የዚህኛው ቤት መሠረት ሲጣል ባዩ ጊዜ በታላቅ ድምጽ አለቀሱ። ብዙዎቹ ግን የመደነቅና የደስታ ጩኸት ይጮሁ ነበር።
|
|
\v 13 ሰዎች የደስታውንና የሐሴቱን ድምጽ ክሕዝቡ የልቅሶ ድምጽ ለመለየት አልቻሉም፥ ሕዝቡ በታላቅ ደስታ ይጮኹ ስለነበር ድምጻቸው ከሩቅ ተሰማ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\c 4
|
|
\p
|
|
\v 1 አንዳንድ የይሁዳና የብንያም ጠላቶች ከምርኮ የተመለሱት ሰዎች ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በመሥራት ላይ መሆናቸውን ሰሙ።
|
|
\v 2 እነርሱም ወደ ዘሩባቤልና ወደ አባቶቻቸው የነገድ አለቆች መጡ። እነርሱም፥ "እንደናንተው አምላካችሁን እንፈልገዋለንና የአሶር ንጉሥ አስራዶን ወደዚህ ስፍራ ካመጣን ጊዜ ጀምሮም ስንሠዋለት ነበርና አብረናችሁ እንሥራ"አሏቸው።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 3 ዘሩባቤል፥ ኢያሱና የአባቶቻቸው የነገድ አለቆች ግን፥ "የአምላካችንን ቤት መሥራት የሚገባን እኛ እንጂ እናንተ አይደላችሁም፥ የፋርስ ንጉሥ እንዳዘዘው ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር የምንሠራው እኛ ነን" አሏቸው።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 4 ስለዚህ የምድሩ ሕዝብ የይሁዳን ሰዎች እጅ አደከሙ፤ እንዳይሠሩም የይሁዳን ሰዎች አስፈራሩ።
|
|
\v 5 ደግሞም ዕቅዳቸውን ለማጨናገፍ ለአማካሪዎች ጉቦ ሰጡ። ይህንንም በቂሮስ ዘመን ሁሉና እስከ ፋርስ ንጉሥ ዳርዮስ እስከ ነገሠበት ጊዜ ድረስ አደረጉ።
|
|
\v 6 ከዚያም አርጤክስስ መንገሥ በጀመረበት ዘመን በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ነዋሪዎች ላይ ክስ ጻፉባቸው።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 7 በአርጤክስስ ዘመን ቢሽላም፥ ሚትሪዳጡ፥ ጣብኤልና ተባባሪዎቻቸው ነበር ለአርጤክስስ የጻፉት። ደብዳቤውም በአረማይስጥ ቋንቋ ተጽፎ የተተረጎመ ነበር።
|
|
\v 8 አዛዡ ሬሁምና ጸሐፊው ሲምሳይ ስለ ኢየሩሳሌም ለአርጤክስስ እንዲህ ብለው ጻፉ፤
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 9 ከዚያም ዳኞች የነበሩት ሬሁም፥ ሲምሳይና ተባባሪዎቻቸው እንዲሁም በአርክ፥ በባቢሎንና በኤላሙ ሱሳ የነበሩ ሌሎች የመንግሥት ኃላፊዎች ደብዳቤውን ጻፉ -
|
|
\v 10 እነርሱንም ታላቁና ኃያሉ አሹርባኒጳል በወንዙ ማዶ ባለው አውራጃ ከቀሩት ከሌሎቹ ጋር በሰማርያ እንዲሰፍሩ ያስገደዷቸው ሰዎች ደገፏቸው።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 11 ለአርጤክስስ የላኩት የደብዳቤው ግልባጭ ይህ ነው፤ "ይህንን የሚጽፉት ከወንዙ ማዶ ያሉት ሰዎች፥ አገልጋዮችህ ናቸው፤
|
|
\v 12 ካንተ ዘንድ የወጡት አይሁድ እኛን በመቃወም አመጸኛይቱን ከተማ በኢየሩሳሌም ውስጥ ለመሥራት መጀመራቸውን ንጉሡ ይወቅ። እነርሱም ቅጥሮቹን ጨርሰው መሠረቶቹን አድሰዋል።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 13 ይህቺ ከተማ ከተሠራችና ቅጥሯም ከተጠናቀቀ ምንም ዓይነት እጅ መንሻና ቀረጥ እንደማይሰጡና ንጉሡን እንደሚጎዱት ንጉሡ ይወቅ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 14 በርግጥ የቤተመንግሥቱን ጨው ስለ በላን በንጉሡ ላይ ማናቸውም ዓይነት ውርደት ሲደርስበት ማየት አይገባንም።
|
|
\v 15 ለዚህም ነው የአባትህን መዛግብት እንድትመረምርና ነገሥታትንና አውራጃዎችን የምትጎዳ አመጸኛ ከተማ መሆኗን እንድታረጋግጥ ለንጉሡ ያስታወቅነው። በነገሥታትና በአውራጃዎች ላይ ብዙ ችግር የፈጠረች ነች። ከብዙ ዘመን ጀምሮም የአመጽ ማዕከል ነች። ከተማይቱ ተደምስሳ የነበረችውም በዚሁ ምክንያት ነበር።
|
|
\v 16 ይህቺ ከተማ ከቅጥሯ ጋር ከተሠራች ከዚህ በኋላ ከታላቁ ከኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ ምንም የሚቀርልህ ነገር እንደማይኖር ለንጉሡ እናስታውቃለን"።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 17 ስለዚህ ንጉሡ ለሬሁም፥ ሲምሳይ፥ በሰማሪያ ላሉ ተባባሪዎቻቸውና ከወንዙ ማዶ ላሉት ለቀሩት ምላሽ ላከ፤ "ሰላም ይሁንላችሁ።
|
|
\v 18 የላካችሁልኝ ደብዳቤ ተተርጉሞ ተነቦልኛል።
|
|
\v 19 በመሆኑም ምርመራ እንዲደረግ አዘዝኩኝና ባለፉት ዘመናት በነገሥታት ላይ ስታምጽ የኖረች አመጸኛ መሆኗ ታውቋል።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 20 በኢየሩሳሌም ላይ ኃያላን ነገሥታት ገዝተዋል፥ ከወንዙ ማዶ ባለው ሁሉ ላይም ሥልጣን ነበራቸው። እጅ መንሻና ቀረጥም ይሰጣቸው ነበር።
|
|
\v 21 አሁንም እነዚህ ሰዎች ሥራውን እንዲያቆሙና እኔ እስከማዝዝ ድረስ ይህቺን ከተማ እንዳይሠሩ ትዕዛዝ ስጡ።
|
|
\v 22 ይህንን ማድረጉን ቸል እንዳትሉ ተጠንቀቁ። ነገሥታቱን የሚጎዳው ጥፋት ለምን ይጨምራል?"
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 23 የንጉሡ የአርጤክስስ ትዕዛዝ በሬሁም፥ በሲምሳይና በተባባሪዎቻቸው ፊት በተነበበ ጊዜ በፍጥነት ወደ ኢየሩሳሌም ሄዱና አይሁድ ሥራውን እንዲያቆሙ አስገደዷቸው።
|
|
\v 24 ስለዚህ በኢየሩሳሌም ያለው የእግዚአብሔር ቤት ሥራ የፋርስ ንጉሥ ዳርዮስ እስከ ነገሠበት እስከ ሁለተኛው ዓመት ድረስ ተቋረጠ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\c 5
|
|
\p
|
|
\v 1 ከዚያም ነቢዩ ሐጌና የአዶ ልጅ ንቢዩ ዘካርያስ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ አይሁድ በእስራኤል አምላክ ስም ትንቢት ተናገሩ።
|
|
\v 2 የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤልና የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱ ካደፋፈሯቸው ነቢያት ጋር በመሆን በኢየሩሳሌም ያለውን የእግዚአብሔር ቤት መሥራት ጀመሩ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 3 ከወንዙ ማዶ ያለው አውራጃ አስተዳዳሪ ተንትናይ፥ ሰተር ቡዝናይና ተባባሪዎቻቸው መጥተው፥ "በማን ትዕዛዝ ነው ይህንን ቤት የምትሠሩትና የቅጥሮቹን ጥገና እየጨረሳችሁ ያላችሁት?" አሏቸው።
|
|
\v 4 ደግሞም፥ "ይህን ሕንፃ የሚሠሩት ሰዎች ስም ማን ማን ነው?" አሏቸው።
|
|
\v 5 ነገር ግን የእግዚአብሔር ዓይን በአይሁድ አለቆች ላይ ነበር፥ ጠላቶቻቸውም አላስቆሟቸውም። እነርሱም በዚህ ጉዳይ ለንጉሡ ደብዳቤ ለመጻፍና ትዕዛዝ እስኪመጣላቸው ይጠብቁ ነበር።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 6 ተንትናይ፥ ሰተር ቡዝናይና ተባባሪዎቻቸው የሆኑት አለቆች ለንጉሡ ለዳርዮስ የጻፉት ደብዳቤ ይህ ነበር፤
|
|
\v 7 እንዲህ ሲሉ ለንጉሡ ዳርዮስ ጻፉለት፤ "ሙሉ ሰላም ለአንተ ይሁን።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 8 ወደ ይሁዳ ወደ ታላቁ አምላክ ቤት ሄደን እንደነበረ ንጉሡ ይወቅ። እርሱም በታላላቅ ድንጋዮች እየተሠራና በቅጥሮቹም መሐል እንጨቶችን እያስገቡበት ነው። ሥራው በትጋት እየተሠራና በእጆቻቸው ላይ በመከናወን ላይ ይገኛል።
|
|
\v 9 አለቆቹንም፥ "ይህንን ቤትና ቅጥሮቹን እንድትሠሩ የፈቀደላችሁ ማነው?" ብለን ጠየቅናቸው።
|
|
\v 10 ደግሞም የሚመሯቸውን ሰዎች የእያንዳንዳቸውን ስም ታውቅ ዘንድ ስሞቻቸውን እንዲነግሩን ጠየቅናቸው።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 11 እነርሱም መልሰው፤ "እኛ የሰማይና የምድር አምላክ አገልጋዮች ነን፥ ከብዙ ዓመታት በፊት ታላቁ የእስራኤል ንጉሥ የሠራውንና የጨረሰውን ይህንን ቤት በማደስ ላይ ነን።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 12 ይሁንና አባቶቻችን የሰማይን አምላክ ባስቆጡት ጊዜ ይህንን ቤት ባፈረሰውና ሕዝቡን ማርኮ ወደ ባቢሎን በወሰዳቸው በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ አሳልፎ ሰጣቸው።
|
|
\v 13 ሆኖም ቂሮስ በባቢሎን ላይ በነገሠ ጊዜ በመጀመሪያው ዓመት የእግዚአብሔር ቤት እንዲሠራ ትዕዛዝ ሰጠ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 14 ደግሞም ንጉሥ ቂሮስ ናቡከደነፆር ከኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ በባቢሎን ወደሚገኘው መቅደስ ያመጣቸውን የእግዚአብሔር ቤት መገልገያ የሆኑትን የወርቁንና የብሩን ዕቃዎች መለሰ። አስተዳዳሪ እንዲሆን ለሾመው ለሰሳብሳር አስረከበው።
|
|
\v 15 እርሱንም፥ "እነዚህን ዕቃዎች ውሰድ። ሂድና በኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ውስጥ አኑራቸው። በዚያም የእግዚአብሔር ቤት ይሠራ" አለው።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 16 ከዚያም ይህ ሰሳብሳር ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ የእግዚአብሔርን ቤት መሠረት ጣለ፤ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በመሠራት ላይ ነው፥ ይሁን እንጂ እስካሁን አላለቀም።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 17 አሁንም ንጉሡ መልካም መስሎ ከታየው በኢየሩሳሌም የእግዚአብሔር ቤት እንዲሠራ ንጉሥ ቂሮስ ያዘዘው ትዕዛዝ በባቢሎን መዝገብ ቤት ይገኝ እንደሆን ይመርመር፤ ከዚያም ንጉሡ ውሳኔውን ይላክልን።
|
|
|
|
\s5
|
|
\c 6
|
|
\p
|
|
\v 1 ስለዚህ ንጉሥ ዳርዮስ በባቢሎን ባሉት ቤተ መዛግብት ምርመራ እንዲደረግ አዘዘ።
|
|
\v 2 በሜዶን አገር ቅጥር ባላት ኤክባታና ከተማ አንድ የመጽሐፍ ጥቅልል ተገኝ፥ ጽሑፉም የሚለው እንዲህ ነበር፤
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 3 "ንጉሡ ቂሮስ በነገሠ በመጀመሪያው ዓምት በኢየሩሳሌም ስላለው የእግዚአብሔር ቤት ቂሮስ እንዲህ የሚል ትዕዛዝ ሰጥቷል፤ የመሥዋዕቱ ቤት ይሠራ። ቅጥሩም ስልሳ ክንድ ከፍታ፥ ስልሳ ክንድ ወርድ ተደርጎ
|
|
\v 4 በሦስት ዙር ትላልቅ ድንጋዮችና በአንድ ዙር አዲስ እንጨት ይሠራ። ወጪውም በንጉሡ ቤት ይሸፈን።
|
|
\v 5 ደግሞም ናቡከደነፆር ከኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ወደ ባቢሎን ቤተ መቅደስ ያመጣቸውን የእግዚአብሔር ቤት የወርቅና የብር ዕቃዎች መልሱላቸው። በኢየሩሳሌም ወዳለው ቤተ መቅደስ ላኩና በዚያ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ይቀመጥ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 6 አሁንም በወንዙ ማዶ ያላችሁት ተንትናይ፥ ሰተር ቡዝናይና ተባባሪዎቻችሁ ከእነርሱ ራቁ።
|
|
\v 7 ይህንን የእግዚአብሔር ቤት ሥራ ለእነርሱ ብቻ ተዉሏቸው። ይህንን የእግዚአብሔር ቤት አስተዳዳሪውና የአይሁድ አለቆች በዚያው ሥፍራ ላይ ይሠሩታል።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 8 ለእነዚህ የእግዚአብሔርን ቤት ለሚሠሩት ይህንን እንድታደርጉላቸው አዝዣለሁ፤ ሥራቸውን እንዳያስተጓጉሉ በወንዙ ማዶ ካሉት ለንጉሡ ከሚሰበሰበው ገቢ ላይ ወጪ እየተደረገ ይከፈላቸው።
|
|
\v 9 ለሰማይ አምላክ ለሚቃጠለው መሥዋዕት የሚፈለገው ሁሉ ወይፈኖችን፥ አውራ በጎችን ወይም ጠቦቶችን እንዲሁም በኢየሩሳሌም ባሉት ካህናት ትዕዛዝ መሠረት ስንዴ፥ ጨው፥ ወይን ወይም ዘይት እነዚህን ነገሮች ሳታቋርጡ በየዕለቱ ስጧቸው።
|
|
\v 10 ለሰማይ አምላክ መሥዋዕት እንዲያቀርቡና ለእኔ ለንጉሡና ለልጆቼም እንዲጸልዩ ይህንን አድርጉላቸው።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 11 ይህንን ትዕዛዜን የሚተላለፍ ማንም ቢሆን የቤቱ ምሶሶ ተነቅሎ እርሱ እንዲሰቀልበት አዝዣለሁ። በዚህ ምክንያት መኖሪያ ቤቱ የቆሻሻ መጣያ ይሁን።
|
|
\v 12 በኢየሩሳሌም የሚገኘውን የእግዚአብሔር ቤት ለማፍረስ የሚነሳውን ንጉሥና ሕዝብ በዚያ የሚኖረው አምላክ ያጥፋው። እኔ ዳርዮስ ይህንን አዝዣለሁ። ሙሉ በሙሉ ይፈጸም።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 13 ከዚያም ተንትናይ፥ ሰተር ቡዝናይና ተባባሪዎቻቸው ንጉሡ ዳርዮስ ያዘዘውን ሁሉ ፈጸሙ።
|
|
\v 14 ስለዚህ የአይሁድ አለቆች ሐጌና ዘካርያስ በትንቢት በነገሯቸው መሠረት ሥራውን ሠሩ። እነርሱም በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር እና በፋርስ ነገሥታት በቂሮስ፥ በዳርዮስና በአርጤክስስ ትዕዛዝ መሠረት ሠሩ።
|
|
\v 15 ቤቱም ንጉሡ ዳርዮስ በነገሠ በስድስተኛው ዓመት አዳር በሚባለው ወር በሦስተኛው ቀን ተጠናቀቀ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 16 የእስራኤል ሕዝብ፥ ካህናቱ፥ ሌዋውያኑና የቀሩት ምርኮኞች የዚህን የእግዚአብሔር ቤት ምረቃ በደስታ አከበሩ።
|
|
\v 17 እነርሱም ለእግዚአብሔር ቤት ምረቃ አንድ መቶ ወይፈኖችን፥ ሁለት መቶ አውራ በጎችንና አራት መቶ ጠቦቶችን አቀረቡ። ለእያንዳንዱ የእስራኤል ነገድ አንድ፥ ለእስራኤል ሁሉ የኃጢአት መሥዋዕት አሥራ ሁለት ወንድ ፍየሎች ቀረቡ።
|
|
\v 18 ደግምም ካህናቱና ሌዋውያኑ በሙሴ ሕግ እንደተጻፈው በኢየሩሳሌም ያለውን የእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት በየተራቸው እንዲፈጽሙ ተመደቡ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 19 እንዲሁም በምርኮ የነበሩት በመጀመሪያው ወር በአሥራ አራተኛው ቀን የፋሲካን በዓል አከበሩ።
|
|
\v 20 ካህናቱና ሌዋውያኑ ሁሉ ራሳቸውን አነጹና እራሳቸውን ጨምሮ በምርኮ ለነበሩት ሁሉ የፋሲካውን መሥዋዕቶች አረዱ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 21 የፋሲካውን ሥጋ ከበሉት እስራኤላውያን ውስጥ አንዳንዶቹ ከምርኮ የተመለሱና ራሳቸውን ከሚኖሩበት ምድር ሰዎች እርኩሰት በመለየት የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን የሚፈልጉ ነበሩ።
|
|
\v 22 እግዚአብሔር ደስታን ስለ ሰጣቸውና በቤቱ፥ በእስራኤል አምላክ ቤት ሥራ ላይ እጆቻቸውን እንዲያበረቱ የአሶር ነገሥታትን ልብ መልሶላቸው ስለነበረ የቂጣውን በዓል ለሰባት ቀናት በደስታ አከበሩ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\c 7
|
|
\p
|
|
\v 1 ከእነዚህ ነገሮች በኋላ በንጉሡ በአርጤክስስ ዘመነ መንግሥት በትውልዱ የሠራያ፥ ዓዛርያስ፥ ኬልቅያስ፥
|
|
\v 2 ሰሎም፥ ሳዶቅ፥ አኪጦብ፥
|
|
\v 3 አማርያ፥ ዓዛርያስ፥ መራዮት፥
|
|
\v 4 ዘራአያ፥ ኦዚ፥ ቡቂ፥
|
|
\v 5 አቢሱ፥ ፊንሐስ፥ አልዓዛር ከዚያም የታላቁ ካህን የአሮን ልጅ የሆነው ዕዝራ -
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 6 ዕዝራ ባቢሎንን ለቆ ወጣ። እርሱም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለሙሴ በሰጠው ሕግ በሚገባ የተካነ ጸሐፊ ነበር። የእግዚአብሔር እጅ ከእርሱ ጋር ስለነበረ የጠየቀውን ሁሉ ንጉሡ ሰጠው።
|
|
\v 7 ደግሞም በንጉሥ አርጤክስስ በሰባተኛው ዓመት አንዳንድ የእስራኤል ተወላጆችና ካህናቱ፥ ሌዋውያን፥ የቤተ መቅደስ መዘምራን፥ በር ጠባቂዎችና በቤተ መቅደስ እንዲያገለግሉ የተመደቡት ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 8 እርሱም በዚያው ዓመት በአምስተኛው ወር ኢየሩሳሌም ደረሰ።
|
|
\v 9 በመጀመሪያው ወር በመጀመሪያው ቀን ባቢሎንን ለቀቀ። መልካሚቱ የእግዚአብሔር እጅ ከእርሱ ጋር ስለነበረ ኢየሩሳሌም የደረሰው በአምስተኛው ወር የመጀመሪያ ቀን ነበር።
|
|
\v 10 ዕዝራም የእግዚአብሔርን ሕግ ለማጥናት፥ ለመተግበርና ሥርዓትና ትዕዛዙን ለማስተማር ልቡን አዘጋጅቶ ነበር።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 11 ንጉሡ አርጤክስስ ለካህኑና እግዚአብሔር ለእስራኤል በሰጠው ትዕዛዝና ሥርዓት ጸሐፊና ለሆነው ለዕዝራ የሰጠው ትዕዛዝ ይህ ነበር፤
|
|
\v 12 ከንጉሠ ነገሥት አርጤክስስ፥ የሰማይ አምላክ ሕግ ጸሐፊ ለሆነው ለካህኑ ዕዝራ፤
|
|
\v 13 በመንግሥቴ ውስጥ እስራኤላዊ የሆነ ማንም ቢሆን ከካህናቶቻቸውና ከሌዋውያኖቻቸው ጋር ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ የሚወዱ ካንተ ጋር እንዲሄዱ አዝዣለሁ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 14 ይሁዳና ኢየሩሳሌምን በሚመለከት በምታውቀው በእግዚአብሔር ሕግ እንድትመረምር፥
|
|
\v 15 ለእስራኤል አምላክ በፈቃዳቸው ያቀረቡትን ብርና ወርቅ ወደ ኢየሩሳሌም ወደ ቤቱ እንድትወስድ እኔ ንጉሡና ሰባቱ አማካሪዎቼ ልከንሃል።
|
|
\v 16 ሕዝቡና ካህናቱ በኢየሩሳሌም ለሚገኘው የእግዚአብሔር ቤት በፈቃዳቸው ካቀረቡት በተጨማሪ ባቢሎናዊያን በሙሉ የሰጡትን ወርቅና ብር ሁሉ በነጻ ስጥ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 17 ስለዚህ በሬዎችን፥ አውራ በጎችንና ጠቦቶችን፥ ስንዴና የመጠጥ ቁርባኑን በርከት አድርገህ ግዛ። በኢየሩሳሌም በሚገኘው በአምላክህ ቤት መሠዊያ ላይ ሠዋቸው።
|
|
\v 18 በቀረው ብርና ወርቅ አምላክህን ለማስደሰት አንተና ወንድሞችህ መልካም መስሎ የታያችሁን ሁሉ አድርጉበት።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 19 በፈቃደኝነት የተሰጡህን ዕቃዎች በኢየሩሳሌም በሚገኘው በአምላክህ ቤት ለአገልግሎት እንዲሆን በፊቱ አስቀምጥ።
|
|
\v 20 ለአምላክህ ቤት ያስፈልጋል ብለህ ለምትጠይቀው ለየትኛውም ተጨማሪ ወጪ ገንዘቡን ከግምጃ ቤቴ ውሰድ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 21 እኔ ንጉሥ አርጤክስስ በወንዙ ማዶ ላላችሁት የግምጃ ቤት ኃላፊዎች በሙሉ፥ ዕዝራ የሚጠይቃችሁን ማናቸውንም ነገር በዛ አድርጋችሁ እንድትሰጡት አዝዣለሁ፥
|
|
\v 22 እስከ አንድ መቶ መክሊት ብር፥ አንድ መቶ ቆሮስ ስንዴ፥ አንድ መቶ የባዶስ መስፈሪያ ወይንና አንድ መቶ የባዶስ መስፈሪያ ዘይት፥ ደግሞም ያለ መጠን የሆነ ጨው ስጡአቸው።
|
|
\v 23 ከሰማይ አምላክ የሚመጣውን ማንኛውንም ነገር ለቤቱ በትጋት አድርጉት። በእኔና በልጆቼ መንግሥት ላይ ቁጣው ለምን ይምጣብን?
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 24 በካህናቱ፥ በሌዋውያኑ፥ በሙዚቀኞቹ፥ በበር ጠባቂዎቹ ወይም ለቤተ መቅደሱ አገልግሎት በተመደቡት ሰዎችና የዚህ አምላክ ቤት አገልጋዮች በሆኑት ላይ ምንም ዓይነት እጅ መንሻም ሆነ ቀረጥ እንዳይጥሉ ስለ እናንተ እናስታውቃቸዋለን።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 25 አንተም ዕዝራ፥ እግዚአብሔር በሰጠህ ጥበብ መሠረት በወንዙ ማዶ ያሉትን ሰዎች ሁሉ እና የአምላክህን ሕግ የሚያውቀውን ማንኛውንም ሰው እንዲያገለግሏቸው ፈራጆችንና አስተዋዮችን ሰዎች መሾም አለብህ። አንተ ደግሞ እነዚያን ሕጉን የማያውቁትን ሰዎች አስተምራቸው።
|
|
\v 26 የእግዚአብሔርን ሕግ ወይም የንጉሡን ሕግ ሙሉ በሙሉ የማይፈጽመውን ማንኛውንም ሰው በሞት፥ በስደት፥ ንብረቱን በመውረስ ወይም በእስራት ቅጣው።"
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 27 ዕዝራም አለ፥ "በኢየሩሳሌም ያለውን የእግዚአብሔርን ቤት ለማስዋብ ይህንን ሁሉ በንጉሡ ልብ ያኖረና ደግሞም በንጉሡ፥
|
|
\v 28 በአማካሪዎቹና በኃያላን አለቆቹ ሁሉ ፊት የቃል ኪዳን ታማኝነቱን በእኔ ላይ ያበዛ የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን። በአምላኬ በእግዚአብሔር እጅ በረታሁኝ፥ ከእኔ ጋር እንዲሄዱም የእስራኤልን አለቆች ሰበሰብሁ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\c 8
|
|
\p
|
|
\v 1 በንጉሡ አርጤክስስ የንግሥና ዘመን ከእኔ ጋር ከባቢሎን የወጡት የአባቶች ቤት አለቆች እነዚህ ናቸው፤
|
|
\v 2 ከፊንሐስ ተወላጆች ጌርሶን። ከኢታምር ተወላጆች ዳንኤል። ከዳዊት ተወላጆች ሐጡስ።
|
|
\v 3 ከሴኬንያ ተወላጆች፥ ከፋሮስ ተወላጆች ዘካርያስ። ከእርሱ ጋር የተመዘገቡት ወንዶች 150 ነበሩ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 4 ከፋሐት ሞዓብ ተወላጆች የዘራእያ ልጅ ኤሊሆዔናይ። ከእርሱ ጋር የተመዘገቡት ሁለት መቶ ወንዶች ነበሩ።
|
|
\v 5 ከሴኬንያ ተወላጆች የየሕዚኤል ልጅ። ከእርሱ ጋር የተመዘገቡት ሦስት መቶ ወንዶች ነበሩ።
|
|
\v 6 ከዓዲን ተወላጆች የዮናታን ልጅ ዔቤድ። ከእርሱ ጋር የተመዘገቡት ሃምሳ ወንዶች ነበሩ።
|
|
\v 7 ከኤላም ተወላጆች የጎቶልያ ልጅ የሻያ። ከእርሱ ጋር የተመዘገቡት ሰባ ወንዶች ነበሩ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 8 ከሰፋጥያስ ተወላጆች የሚካኤል ልጅ ዝባድያ። ከእርሱ ጋር የተመዘገቡት ሰማንያ ወንዶች ነበሩ።
|
|
\v 9 ከኢዮአብ ተወላጆች የይሒኤል ልጅ አብድዩ። ክእርሱ ጋር የተመዘገቡት218 ወንዶች ነበሩ።
|
|
\v 10 ከሰሎሚት ተወላጆች የዮሲፍያ ልጅ። ከእርሱ ጋር የተመዘገቡት 160 ወንዶች ነበሩ።
|
|
\v 11 ከቤባይ ተወላጆች የቤባይ ልጅ ዘካርያስ። ከእርሱ ጋር የተመዘገቡት ሃያ ስምንት ወንዶች ነበሩ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 12 ከዓዝጋድ ተወላጆች የሃቃጣን ልጅ ዮሐናን። ከእርሱ ጋር የተመዘገቡት 110 ወንዶች ነበሩ።
|
|
\v 13 የአዶኒቃም ተወላጆች ዘግይተው መጡ። ስማቸው እንደሚከተለው ነው፤ ኤሊፋላት፥ ይዑኤል፥ ሸማያ። ከእነርሱ ጋር ስልሳ ወንዶች መጡ።
|
|
\v 14 ከበጉዋይ ተወላጆች ዑታይና ዘቡድ። ከእነርሱ ጋር የተመዘገቡት ሰባ ወንዶች ነበሩ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 15 ዕዝራም አለ፥ "መንገደኞቹን ወደ አኅዋ በሚወርደው ወንዝ አጠገብ ሰበሰብኋቸው፥ በዚያም ሦስት ቀን ቆየን። ሕዝቡንና ካህናቱን ተመለከትኩ፥ ከሌዊ ተወላጆች ግን በዚያ አንድም አላገኘሁኝም።
|
|
\v 16 እኔም አለቆች ወደነበሩት ወደ አልዓዛር፥ አርኤል፥ ሸማያ፥ ኤልናታን፥ ያሪብ፥ ኤልናታን፥ ናታን፥ ዘካርያስ፥ ሜሱላምና አስተማሪዎች ወደነበሩት ዮያሪብና ኤልናታን መልዕክት ላክሁ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 17 በመቀጠልም በካሲፍያ አለቃ ወደ ሆነው ወደ አዶ ላክኋቸው። ለአዶ፥ ለወንድሞቹና በካሲፍያ ለሚኖሩ የቤተ መቅደስ አገልጋዮች ምን ማለት እንዳለባቸው አስታወቅኋቸው፤ ይኸውም ለእግዚአብሔር ቤት አገልጋዮችን እንዲልኩልን ነበር።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 18 ስለዚህ በመልካሚቱ በእግዚአብሔር እጅ ምክንያት ሰራብያ ተብሎ የሚጠራውን አስተዋይ ሰው ላኩልን። እርሱም ከእስራኤል ልጅ፥ ከሌዊ ልጅ፥ ከሞሖሊ ተወላጆች አንዱ ነበር። እርሱም ከአሥራ ስምንት ወንዶች ልጆቹና ወንድሞቹ ጋር መጣ።
|
|
\v 19 ሐሸብያም ከእርሱ ጋር መጣ። ደግሞም ከሜራሪ ወንዶች ልጆች አንዱ የሆነው የሻያን ከወንድሞቹና ከወንዶች ልጆቹ ጋር በድምሩ ሃያ ወንዶች ነበሩ።
|
|
\v 20 በቤተ መቅደስ ውስጥ እንዲያገለግሉ ከተመደቡት ውስጥ ዳዊትና ሹማምንቱ ሌዋውያኑን ለማገልገል የሰጡት 220 ነበሩ፥ እያንዳንዳቸው በየስማቸው ተመደቡ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 21 ራሳችንን በእግዚአብሔር ፊት ለማዋረድ፥ ለእኛ፥ ለታናናሽ ልጆቻችንና ለንብረታችን ሁሉ መንገዳችንን እንዲያቃናልን በአኅዋ ወንዝ አጠገብ ጾም አወጅኩ።
|
|
\v 22 ንጉሡን፥ 'የአምላካችን እጅ ለመልካም በሚፈልጉት ሁሉ ላይ ናት፥ ቁጣውና ኃይሉ ግን እርሱን በሚተዉት ሁሉ ላይ ነው' ብለን ስለነበር በመንገድ ላይ ከጠላቶቻችን የሚጠብቁንን ሠራዊት ወይም ፈረሰኞችን እንዲሰጠን ንጉሡን ለመጠየቅ አፈርኩኝ።
|
|
\v 23 ስለዚህ በእግዚአብሔ ፊት ጾምንና ጸለይን፥ ስለዚህም ጉዳይ ለመንነው።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 24 ከዚያም ከካህናቱ ዋና ዋናዎቹን ሰራብያን፥ ሐሸቢያንና አሥር ወንድሞቻቸውን፥ አሥራ ሁለት ሰዎች መረጥኩ።
|
|
\v 25 ንጉሡ፥ አማካሪዎቹ፥ አለቆቹና በዚያ የነበሩ እስራኤል ሁሉ ለእግዚአብሔር ቤት በፈቃዳቸው ያቀረቡትን ብር፥ ወርቅ፥ ቁሳቁስና መባ መዝኜ ሰጠዃቸው።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 26 ስለዚህ 650 መክሊት ብር፥ አንድ መቶ መክሊት የብር ዕቃዎች፥ አንድ መቶ መክሊት ወርቅ፥ አንድ ሺህ ዳሪክ የሚያወጡ
|
|
\v 27 ሃያ ጎድጓዳ የወርቅ ሳሕኖች፥ የወርቅ ያህል የከበሩ ሁለት አብረቅራቂ የነሐስ ዕቃዎች መዝኜ በእጃቸው ሰጠኋቸው።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 28 ከዚያም እንዲህ አልኳቸው፥ 'እናንተና እነዚህ ዕቃዎች ለእግዚአብሔር ተቀድሳችኋል። ይህ ብርና ወርቅ ለአባቶቻችሁ አምላክ ለእግዚአብሔር በፈቃደኝነት የቀረበ መባ ነው።
|
|
\v 29 በካህናቱ ኃላፊዎች፥ በሌዋውያኑና በእስራኤል የነገድ አለቆች ፊት በኢየሩሳሌም በእግዚአብሔር ቤት ክፍሎች ውስጥ እስክትመዝኑት ድረስ በጥንቃቄ ጠብቁት።
|
|
\v 30 ካህናቱና ሌዋውያኑ የተመዘነውን ብር፥ ወርቅና ቁሳቁስ ወደ ኢየሩሳሌም ወደ አምላካችን ቤት ለመውሰድ ተረከቡት።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 31 በመጀመሪያው ወር በአሥራ ሁለተኛው ቀን ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ ከአኅዋ ወንዝ አጠገብ ተነሣን። የአምላካችን እጅ በእኛ ላይ ነበረች፤ እርሱም ከጠላቶቻችን እጅና በመንገድ ላይ አድፍጠው ሊያጠቁን ከፈለጉት አዳነን።
|
|
\v 32 ወደ ኢየሩሳሌም ደርስንና ሦስት ቀን በዚያ ቆየን።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 33 ከዚያም በአራተኛው ቀን ብሩ፥ ወርቁና ቁሳቁሱ በአምላካችን ቤት ውስጥ በካህኑ በኦርዮ ልጅ በሜሪሞት እጅ ተመዝነው ተሰጡ። የፊንሐስ ልጅ አልዓዛር፥ ሌዋውያኑ የኢያሱ ልጅ ዮዛባትና የቢንዊ ልጅ ኖዓድያ ከእርሱ ጋር ነበሩ።
|
|
\v 34 የሁሉም ነገር ቁጥሩና ክብደቱ ታወቀ፤ በዚያኑ ጊዜም ጠቅላላ የክብደቱ መጠን ተጻፈ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 35 ተማርከው የነበሩት፥ ከምርኮም የተመለሱት ለእስራኤል አምላክ የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረቡ፤ ለእስራኤል ሁሉ አሥራ ሁለት ወይፈኖችን፥ ዘጠና ስድስት አውራ በጎችን፥ ሰባ ሰባት ጠቦቶችንና ለኃጢአት መሥዋዕት አሥራ ሁለት አውራ ፍየሎችን አቀረቡ። ሁሉም ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ነበር።
|
|
\v 36 ከዚያም የንጉሡን ትዕዛዝ በወንዙ ማዶ ላሉት የንጉሡ ሹማምንትና አስተዳዳሪዎች ሰጧቸው፥ እነርሱም ሕዝቡንና የእግዚአብሔርን ቤት አገዙ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\c 9
|
|
\p
|
|
\v 1 "እነዚህ ነገሮች በተደረጉ ጊዜ አለቆቹ ወደ እኔ መጥተው፥ 'የእስራአል ሕዝብ፥ ካህናቱና ሌዋውያኑ ራሳቸውን ከሌላው ምድር ሕዝብ፤ ከከነዓናውያን፥ ኬጢያውያን፥ ፌርዛውያን፥ ኢያቡሳውያን፥ አሞናውያን፥ ሞዓባውያን፥ ግብፃውያንና አሞራውያን እና ከርኩሰቶቻቸው አልለዩም።
|
|
\v 2 ከወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸው ጋር በመጋባት ቅዱሱን ሕዝብ ከሌላው ምድር ሕዝብ ጋር ደባልቀዋል። በዚህ እምነት የለሽነት ቀዳሚዎቹ ሹማምንቱና አለቆቹ ናቸው።'
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 3 ይህንን በሰማሁ ጊዜ፥ ልብሴንና ካባዬን ቀደድሁ፥ ከራሴና ከፂሜም ላይ ፀጉሬን ነጨሁ። አፍሬም ተቀመጥኩ።
|
|
\v 4 ከእስራኤል አምላክ ከእግዚአብሔር ቃል የተነሣ ስለዚህ እምነት የለሽነት በፍርሃት የተንቀጠቀጡ ሁሉ እስከ ምሽቱ መሥዋዕት ማቅረቢያ ጊዜ ድረስ በእፍረት ተቀምጬ ሳለሁ ወደ እኔ መጡ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 5 የምሽት መሥዋዕት በማቅረቢያ ጊዜ ግን የተቀደደ ልብሴንና ካባዬን ለብሼ በእፍረት ከተቀመጥኩበት ተነሣሁ፥ ተንበርክኬም እጆቼን ወደ አምላኬ ወደ እግዚአብሔር ዘረጋሁ።
|
|
\v 6 እንዲህም አልኩ፥ 'አምላኬ ሆይ፥ ኃጢአታችን በራሳችን ላይ በዝቷል፥ በደላችንም እስከ ሰማያት ደርሷልና ፊቴን ወደ አንተ ለማቅናት እፈራለሁ፥ እጅግም አፍራለሁ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 7 ከአባቶቻችን ዘመን ጀምሮ እስካሁን ድረስ በታላቅ በደል ውስጥ አለን። ዛሬ እንደሆነብን ሁሉ በበደላችን ምክንያት ነገሥታቶቻችንና ካህናቶቻችን በዚህ ዓለም መንግሥታት እጅ ለሰይፍ፥ ለምርኮ፥ ለመበዝበዝና ለእፍረት ፊት ተሰጡ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 8 አሁንም ገና ለጥቂት ጊዜ የተረፍነው እኛ ጥቂቶቹ በሕይወት እንድንኖርና በዚህም ቅዱስ ሥፍራ የእግር መቆናጠጫ ሊሰጠን ከእግዚአብሔር ከአምላካችን ቸርነት መጥቶልናል። ዓይኖቻችንን ለማብራትና በባርነት እያለን ጥቂት እረፍት ሊሰጠን ይህ የአምላካችን ሥራ ነበር።
|
|
\v 9 ባሪያዎች ነንና፥ አምላካችን ግን የቃል ኪዳን ታማኝነቱን ለእኛም አስረዘመልን እንጂ አልረሳንም። ፍርስራሹን እንድናነሣና የአምላካችንን ቤት እንደገና መሥራት እንድንችል አዲስ ጉልበት ሊሰጠን በፋርስ ንጉሥ ፊት ይህንን አድርጓል። በኢየሩሳሌምና በይሁዳ የመከላከያ ቅጥር ሊሰጠን ይህንን አደረገ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 10 አሁን ግን አምላካችን ሆይ፥ ከዚህ በኋላ ምን ማለት እንችላለን? ትዕዛዝህን እረስተናል፥
|
|
\v 11 የረሳነውም፤ "ልትወርሷት የምትገቡባት ይህቺ ምድር የረከሰች ምድር ናት። በምድሪቱ በሚኖሩት ሰዎች እርኩሰት ረክሳለች። ከአንደኛው ጫፍ እስከ ሌላኛው ጫፍ ድረስ በእርኩሰታቸው ሞልተዋታል።
|
|
\v 12 አሁንም፥ እንድትበረቱና የምድሪቱን ፍሬ እንድትበሉ፥ ለልጆቻችሁም ለዘላለም እንድታወርሷቸው ሴቶች ልጆቻችሁን ለወንዶች ልጆቻቸው አትስጡ፤ ለወንዶች ልጆቻችሁም ሴቶች ልጆቻቸውን አትውሰዱ፥ ሰላምና ደኅንነታቸው እንዲቀጥልም አትፈልጉ ብለህ ለአገልጋዮችህ ለነቢያት የሰጠኸውን ትዕዛዝ ነው።"
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 13 ይሁን እንጂ በክፉ ሥራችንና በብዙ በደላችን ምክንያት ከደረሱብን ነገሮች በኋላ አንተ አምላካችን ለኃጢአታችን የሚገባውን ተውክልንና የተረፍነውን በሕይወት እንድንኖር ፈቀድክ።
|
|
\v 14 ታዲያ እንደገና ትዕዛዝህን መጣስና ከእነዚህ ከረከሱ ሕዝቦች ጋር በጋብቻ መደባለቅ ነበረብን? አንተስ አንድም የሚቀር ወይም የሚያመልጥ እስከማይኖር ድረስ ታጠፋን ዘንድ ልትቆጣን አይገባህምን?
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 15 የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ አንተ ጻድቅ ነህ፥ እኛም ጥቂቶች ተርፈን በሕይወት አለን። እነሆ፥ ከበደላችን ጋር በፊትህ ነን፥ ከዚህ የተነሣ በፊትህ ለመቆም የሚችል ማንም የለም።"
|
|
|
|
\s5
|
|
\c 10
|
|
\p
|
|
\v 1 ዕዝራ እየጸለየና እየተናዘዘ በእግዚአብሔር ቤት ፊት ተደፍቶ አለቀሰ። ወንዶች፥ ሴቶችና ልጆች ያሉበት እጅግ ታላቅ የእስራኤል ጉባዔ በዙሪያው ተሰበሰቡ፥ ሕዝቡም ታላቅ ልቅሶ አለቀሱ።
|
|
\v 2 የኤላም ተወላጅ የይሒኤል ልጅ ሴኬንያ ዕዝራን እንዲህ አለው፥ "እኛ ራሳችን በአምላካችን ላይ ክህደት ፈጽመናል፥ ከሌላ ምድር ሰዎችም ሚስቶችን አግብተናል። ይሁን እንጂ በዚህ ጉዳይ ላይ አሁንም ለእስራኤል ተስፋ አለ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 3 አሁንም ጌታዬና የአምላካችንን ትዕዛዝ የሚፈሩት በምትሰጡን መመሪያ መሠረት ሴቶቹን ሁሉ ከልጆቻቸው ጋር ለማሰናበት ከአምላካችን ጋር ቃል ኪዳን እናድርግ፥ ይህም በሕጉ መሠረት ይፈጸም።
|
|
\v 4 ይህ አንተ ልታደርገው የሚገባህ ጉዳይ ነውና ተነሥ፥ እኛም አብረንህ ነን። በርታና አድርገው።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 5 ዕዝራ ተነሣና የካህናቱን ዋነኞች፥ ሌዋውያኑንና እስራኤላውያኑን በሙሉ በዚሁ መሠረት ተግባራዊ እንዲያደርጉ ቃል አስገባቸው። እነርሱም ቃል ገቡ።
|
|
\v 6 ከዚያም ዕዝራ ከእግዚአብሔር ቤት ፊት ተነሥቶ ወደ ኤልያሴብ ልጅ ወደ ዮሐናን ክፍል ገባ። በምርኮ የነበሩት እምነት የለሽ ስለመሆናቸው ያለቅስ ነበርና ምንም ዓይነት ምግብ አልተመገበም አንዳች ውሃም አልጠጣም ነበር።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 7 በይሁዳና በኢየሩሳሌም የሚገኙ ከምርኮ የተመለሱት ሰዎች ሁሉ በኢየሩሳሌም እንዲሰበሰቡ መልዕክት ላኩ።
|
|
\v 8 በሦስት ቀን ውስጥ የማይመጣ ማንም ቢኖር በሹማምንቱና በሽማግሌዎቹ ውሳኔ መሠረት ንብረቱ ይወረሳል፥ እርሱም ከምርኮ ከተመለስው ታላቅ የሕዝብ ጉባዔ ይለያል።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 9 ስለዚህ የይሁዳና የብንያም ሰዎች በሙሉ በሦስት ቀናት ውስጥ በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ። ይህም የሆነው በዘጠነኛው ወር ከወሩም በሃያኛው ቀን ነበር። ሕዝቡ ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት ፊት ባለው አደባባይ ላይ ቆመው ነበር፥ ከሚሰሙት ቃልና ከዝናቡ የተነሣም ይንቀጠቀጡ ነበር።
|
|
\v 10 ካህኑ ዕዝራም ተነሥቶ እንዲህ አለ፥"እናንተ ራሳችሁ ክህደት ፈጽማችኋል። የእስራኤልን በደል ለማብዛት ባዕዳን ሴቶችን አግብታችኋል።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 11 አሁን ግን ለአባቶቻችሁ አምላክ ክብርን ስጡ፥ ፈቃዱንም አድርጉ። ከምድሩ ሰዎችና ከባዕዳን ሴቶች ተለዩ።"
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 12 ጉባዔውም ሁሉ በታላቅ ድምጽ፥ "እንደ ተናገርከው እናደርጋለን።
|
|
\v 13 ይሁንና ሕዝቡ ብዙ ነው፥ ወቅቱም የዝናብ ጊዜ ነው። እንዲህ ሜዳው ላይ ለመቆም አቅም የለንም፥ በዚህ ጉዳይ እጅግ ተላልፈናልና ሥራው የአንድ ወይም የሁለት ቀን ብቻ አይደለም።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 14 ስለዚህ ሹማምንቶቻችን ጉባዔውን በሙሉ ይወክሉ። የአምላካችን ብርቱ ቁጣ ከእኛ እስኪመለስ ድረስ ባዕዳን ሴቶች በከተሞቻችን እንዲኖሩ የፈቀዱ ሁሉ የከተማው ሽማግሌዎችና የከተማው ዳኞች በሚወስኑት ቀን ይምጡ።"
|
|
\v 15 የአሣሄል ልጅ ዮናታንና የቴቁዋ ልጅ የሕዝያ ይህንን ሃሳብ ተቃወሙ፥ ሌዋውያኑ ሜሱላምና ሳባታይም ደገፉአቸው።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 16 ስለዚህ ከምርኮ የተመለሱት ሰዎች እንዲህ አደረጉ። ካህኑ ዕዝራም ከነገድ አባቶችና ከቤተሰቡ መሪዎች የሚሆኑ ሰዎችን ሁሉንም በየስማቸው መረጠ፥ እነርሱም በዘጠነኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ጉዳዩን መመልከት ጀመሩ።
|
|
\v 17 በመጀመሪያው ወር የመጀመሪያው ቀን ባዕዳን ሴቶችን ያገቡት እነማን እንደሆኑ ምርመራቸውን ጨረሱ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 18 ከካህናቱ ወገን ባዕዳን ሴቶችን ያገቡ ነበሩ። ከኢዮሴዴቅ ልጅ ከኢያሱና ከወንድሞቹ ተወላጆች መካከል መዕሤያ፥ አልዓዛር፥ ያሪብና ጎዶልያስ። እነዚህ ሚስቶቻቸውን ለመፍታት ወሰኑ።
|
|
\v 19 በደለኞች ነበሩና ከመንጋዎቻቸው ስለ በደል መሥዋዕት አንዳንድ አውራ በግ አቀረቡ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 20 ከኢሜር ተወላጆች አናኒና ዝባድያ።
|
|
\v 21 ከካሪም ተወላጆች መዕሤያ፥ ኤልያስ፥ ሸማያ፥ ይሒኤልና ዖዝያ።
|
|
\v 22 ከፋስኩር ተወላጆች ኤልዮዔናይ፥ መዕሤያ፥ ይስማኤል፥ ናትናኤል፥ ዮዛባትና ኤልዓሣ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 23 ከሌዋውያኑ መካከል፤ ዮዛባት፥ ሰሜኢ፥ ቆሊጣስ የሚባለው ቆልያ፥ ፈታያ፥ ይሁዳና አልዓዛር።
|
|
\v 24 ከመዘምራኑ መካከል፤ ኤልያሴብ። በር ከሚጠብቁት መካከል፤ ሰሎም፥ ጤሌምና ኡሪ።
|
|
\v 25 ከተቀሩት እስራኤላውያን መካከል፤ ከፋሮስ ተወላጆች መካከል፥ ራምያ፥ ይዝያ፥ መልክያ፥ ሚያሚን፥ አልዓዛር፥ መልክያና በናያስ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 26 ከኤላም ተወላጆች መካከል፤ ሙታንያ፥ ዘካርያስ፥ ይሒኤል፥ አብዲ፥ ይሬሞትና ኤልያ።
|
|
\v 27 ከዛቱዕ ተወላጆች መካከል ዔሊዮዔናይ፥ ኢልያሴብ፥ ሙታንያ፥ ይሬሞት፥ ዛባድና ዓዚዛ።
|
|
\v 28 ከቤባይ ተወላጆች መካከል፤ ይሆሐናን፥ ሐናንያ፥ ዘባይና አጥላይ።
|
|
\v 29 ከባኒ ተወላጆች መካከል፤ ሜሱላም፥ መሉክ፥ ዓዳያ፥ ያሱብና ሸዓል ራሞት።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 30 ከፈሐት ሞዓብ ተወላጆች መካከል፤ ዓድና፥ ክላል፥ በናያስ፥ መዕሤያ፥ ሙታንያ፥ ባስልኤል፥ ቢንዊና ምናሴ።
|
|
\v 31 ከካሪም ተወላጆች መካከል፤ አልዓዛር፥ ይሺያ፥ መልክያ፥ ሸማያ፥ ስምዖን፥
|
|
\v 32 ብንያም፥ መሉክና ሰማራያ።
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 33 ከሐሱም ተወላጆች መካከል መትናይ፥ መተታ፥ ዛባድ፥ ኤሊፋላት፥ ይሬማይ፥ ምናሴና ሰሜኢ።
|
|
\v 34 ከባኒ ተወላጆች መካከል፤ መዕዳይ፥ ዓምራም፥ ኡኤል፥
|
|
\v 35 በናያስ፥ ቤድያ፥ ኬልቅያ፥
|
|
\v 36 ወንያ፥ ሜሪሞት፥ ኤሌያሴብ፥
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 37 መታንያ፥ መትናይ፥ የዕሡ፥
|
|
\v 38 ባኒ፥ ቢንዊ፥ ሰሜኢ፥
|
|
\v 39 ሰሌምያ፥ ናታን፥ ዓዳያ፥
|
|
\v 40 መክነድባይ፥ ሴሴይ፥ ሸራይ፥
|
|
|
|
\s5
|
|
\v 41 ኤዝርኤል፥ ሰምምያ፥ ሰማራያ፥
|
|
\v 42 ሰሎም፥ አማርያና ዮሴፍ።
|
|
\v 43 ከናባው ተወላጆች መካከል፤ ይዔኤል፥ መቲትያ፥ ዛባድ፥ ዘቢና፥ ያዳይ፥ ኢዮኤልና በናያስ።
|
|
\v 44 እነዚህ ሁሉ ባዕዳን ሴቶችን ያገቡና አንዳንዶቹም ከእነርሱ የወለዱ ነበሩ።
|