am_ulb/14-2CH.usfm

1650 lines
215 KiB
Plaintext

\id 2CH
\ide UTF-8
\h ሁለተኛ ዜና
\toc1 ሁለተኛ ዜና
\toc2 ሁለተኛ ዜና
\toc3 2ch
\mt ሁለተኛ ዜና
\s5
\c 1
\p
\v 1 የዳዊት ልጅ ሰለሞንም በመንግሥቱ በረታ፤ አምላኩም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበር፤ እጅግም ብርቱ ንጉሥ አደረገው።
\s5
\v 2 ሰለሞንም ለእስራኤል ሁሉ፥ ለሻለቆች፥ ለመቶ አለቆችም፥ ለዳኞችም፥ በመላው እስራኤልም ሁሉ ለነበሩ መሳፍንት ሁሉ፥ ለአባቶች ቤቶች አለቆች ተናገረ፤
\v 3 የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ በምድረ በዳ የሠራው የእግዚአብሔር መገናኛ ድንኳን በገባኦን ስለነበር ሰለሞንና ጉባኤው ሁሉ እዚያ ወደነበረው የአምልኮ ሥፍራ ሄዱ።
\v 4 ዳዊት ግን ለእግዚአብሔር ታቦት በኢየሩሳሌም ድንኳን ተክሎለት ስለነበር ከቂርያት ይዓሪም ወዳዘጋጀለት ሥፍራ አምጥቶት ነበር።
\v 5 በተጨማሪም በሆር ልጅ በኡሪ ልጅ በባስልኤል የተሠራው የናስ መሠዊያ በዚያ በእግዚአብሔር ማደሪያ ድንኳን ፊት ነበረ፤ ሰለሞንና ጉባኤውም ወደ እርሱ ሄዱ።
\s5
\v 6 ሰለሞንም በእግዚአብሔር ፊት በመገናኛው ድንኳን ዘንድ ወደነበረው ወደ ናሱ መሰዊያ ወጣ። በዚያም አንድ ሺህ የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረበ።
\v 7 በዚያም ሌሊት እግዚአብሔር ለሰለሞን ተገልጦ ፦ እንድሰጥህ የምትፈልገውን ማንኛውንም ነገር ለምነኝ አለው።
\s5
\v 8 ሰለሞንም እግዚአብሔርን፦ ለአባቴ ለዳዊት ታላቅ የቃል ኪዳን ታማኝነት አሳይተሃል፤ እኔንም በእርሱ ምትክ ንጉሥ አድርገኸኛል፤
\v 9 አሁንም እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፦ ቁጥራቸው እንደ ምድር ትቢያ በሆነው ሕዝብ ላይ አንግሠኸኛልና ለአባቴ ለዳዊት የሰጠኸው የተስፋ ቃል ይፈጸም።
\v 10 አሁንም እንደዚህ ቁጥራቸው በበዛ ሕዝብህ ላይ ሊፈርድ የሚችል ማንም ስለሌለ ይህንን ሕዝብ እመራ ዘንድ ጥበብና እውቀት ስጠኝ አለው፡፡
\v 11 እግዚአብሔርም ሰለሞንን፡- በልብህ የነበረው ይህ ስለነበር ባለጠግነትን፥ ሀብትን፥ ወይም ክብርን ወይም የሚጠሉህን ሰዎች ነፍስ ወይም ለራስህ ረጅም እድሜ ስላልጠየቅህ ነገር ግን ባነገሥሁህ በህዝቤ ላይ ለመፍረድ ትችል ዘንድ ለራስህ ጥበብንና እውቀትን ስለጠየቅህ
\s5
\v 12 አሁን ጥበብና እውቀት ተሰጥተውሃል፤ ከአንተ በፊት የነበሩት ከነበራቸው እና ከአንተም በኋላ የሚመጡት ከሚኖራቸው ከየትኛውም ነገሥታት ይበልጥ ባለጠግነት፥ ሀብት፥ ክብርም እሰጥሃለሁ አለው፡፡
\v 13 ስለሆነም በገባኦን ከመገናኛው ድንኳን ፊት ከነበረው ከኮረብታው መስገጃ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፡፡ እዚያም በእስራኤል ላይ ነገሠ፡፡
\s5
\v 14 ሰለሞን ሰረገሎችን እና ፈረሰኞችን ሰበሰበ፡፡ በሰረገሎች ከተማዎችና ከራሱ ከንጉሡ ጋር በኢየሩሳሌም ያኖራቸው አንድ ሺህ አራት መቶ ሰረገሎች እና አሥራ ሁለት ሺህም ፈረሰኞች ነበሩት፡፡
\v 15 ንጉሡም ብርና ወርቅ በኢየሩሳሌም እንደ ድንጋይ እንዲበዛ አደረገው፤ የዝግባም እንጨት በቆላ እንዳሉት የሾላ ዛፎች እንዲበዛ አደረገው፡፡
\s5
\v 16 ከግብጽና ከቀዌ ለሰለሞን ፈረሶችን ስለ ማስመጣት የእርሱ ነጋዴዎች በገንዘብ እየገዙ ያመጡአቸው ነበር፡፡
\v 17 ከግብጽ አንዱን ሰረገላ በስድስት መቶ ሰቅል ብር፥ አንዱን ፈረስ በመቶ ሃምሳ ሰቅል ብር ዋጋ ያስመጡ ነበር፡፡ ለኬጢያውያንና ለሶርያ ነገሥታትም ልከው ይሸጡአቸው ነበር፡፡
\s5
\c 2
\p
\v 1 በዚህ ጊዜ ሰለሞን ለእግዚአብሔር ስም ቤት እንዲገነባ እና ለመንግሥቱ ቤተ መንግሥት እንዲገነባ አዘዘ፡፡
\v 2 ጭነት የሚሸከሙ ሰባ ሺህ ሰዎች እና ከተራሮች እንጨት የሚቆርጡትን ሰማንያ ሺህ ሰዎች እነርሱንም የሚቆጣጠሩ ሦስት ሺህ ስድስት መቶ ሰዎች መደበ፡፡
\v 3 ሰለሞንም ወደ ጢሮስ ንጉሥ ወደ ኪራም ፦የሚኖርበትን ቤት እንዲሠራ የዝግባ እንጨት በመላክ ከአባቴ ከዳዊት ጋር እንዳደረግህ ለእኔም እንደዚሁ አድርግልኝ፡፡
\s5
\v 4 እነሆ በእግዚአብሔር ፊት የጣፋጩን ቅመም ሽታ ለማጠን፥ የመገኘቱን ኅብስት ዘወትር ለማኖር፥ በጠዋትና በማታ፥ በሰንበታቱም ፥ በመባቻዎቹና ለአምላካችን ለእግዚአብሔር በተመደቡት ልዩ በዓላት የሚቃጠለውን መሥዋዕት ለማቅረብ ለአምላኬ ለእግዚአብሔር ስም ቤት ልገነባና ልቀድሰው ነው፡፡ ይህ ለእስራኤል ለሁልጊዜ ሕግ ነው፡፡
\v 5 አምላካችን ከአማልክት ሁሉ በላይ ታላቅ ስለሆነ የምሠራው ቤት እጅግ ታላቅ ይሆናል፡፡
\s5
\v 6 ነገር ግን መላው አጽናፈ ዓለምና ሰማይ ራሱ ሳይቀር ሊይዘው ለማይችለው ለእርሱ ለእግዚአብሔር ቤት ይሠራ ዘንድ የሚችል ማን ነው? በፊቱ መሥዋዕት ከማቅረብ በስተቀር ለእርሱ ቤት እሰራ ዘንድ እኔ ማን ነኝ?
\v 7 በመሆኑም በወርቅ፥ በብር፥ በናስ፥ በብረት፥ እንዲሁም ሐምራዊውን፥ ቀዩን፥ ሰማያዊውን ግምጃ በመሥራት የተካነ ሰው፥ የእንጨት ቅርጻ ቅርጽ ዓይነቶችን ሁሉ መሥራት የሚያውቅ ሰው ላክልኝ፡፡ እርሱም አባቴ ዳዊት ካዘጋጃቸው በእኔ ዘንድ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ካሉት የተካኑ ሰዎች ጋር ይሆናል፡፡
\s5
\v 8 አገልጋዮችህ እንጨት ከሊባኖስ መቁረጥ እንደሚያውቁ ስለማውቅ ከሊባኖስ የዝግባ እንጨቶች፥ የጥድ እንጨቶች፥ የሰንደልም እንጨቶች ላክልኝ፡፡ እነሆ ባሪያዎችህ ከባሪያዎቼ ጋር ይሆናሉ፡፡
\v 9 ልሠራ ያሰብኩት ቤት ታላቅና ድንቅ ይሆናልና የተትረፈረፈ ሳንቃ እንጨት እንዲያዘጋጁልኝ ነው፡፡
\v 10 እነሆ እንጨቱን ለሚቆርጡ ሰዎች ሀያ ሺህ የቆሮስ መስፈሪያ የተፈጨ ስንዴ፥ ሀያ ሺህ የቆሮስ መስፈሪያ ገብስ፥ ሀያ ሺህ የባዶስ መስፈሪያ የወይን ጠጅ፥ ሀያ ሺህ የባዶስ መስፈሪያ ዘይት ለባሪያዎችህ እሰጣለሁ፡፡
\s5
\v 11 ንጉሥ ኪራም፦ እግዚአብሔር ሕዝቡን ስለሚወዳቸው በላያቸው አንግሦሃል ብሎ መልሶ ወደ ሰለሞን መልእክት ላከ፡፡
\v 12 በተጨማሪም ኪራም፦ ሰማይንን ምድርን የፈጠረ፥ ለእግዚአብሔር ቤት እና ለመንግሥቱ ቤት የሚሠራ ጥበበኛና ብልሃተኛ አስተዋይም ልጅ ለንጉሡ ለዳዊት የሰጠ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የተባረከ ይሁን አለ፡፡
\s5
\v 13 አሁንም ማስተዋል የተሰጠውን የተካነውን ባለሙያዬን ሁራምን ልኬልሃለሁ፡፡
\v 14 ከዳን ሴት ልጆች የአንዲቱ ልጅ ነው፡፡ አባቱ የጢሮስ ሰው ነበር፡፡ ወርቁን፥ ብሩን፥ ናሱን፥ ብረቱን፥ ድንጋዩን እንዲሁም እንጨቱን፥ ሐምራዊውን፥ ሰማያዊንና ቀዩን ግምጃ ጥሩ በፍታውንም በመሥራት የተካነ ነው፡፡ የትኛውንም ዓይነት ቅርጽ በመሥራት እና የትኛውንም ዓይነት ንድፍ በማውጣትም የተካነ ነው፡፡ በተካኑት ሠራተኞችህ መካከል እና ከጌታዬ ከአባትህ ከዳዊት ብልሃተኞች ጋር ይሆን ዘንድ ስፍራ ይዘጋጅለት፡፡
\s5
\v 15 አሁንም ጌታዬ የተናገረውን ስንዴውንና ገብሱን ዘይቱንና የወይን ጠጁን እነዚህን ነገሮች ወደ አገልጋዮቹ ይላክ፡፡
\v 16 እኛም የሚያስፈልግህን ያህል እንጨት ከሊባኖስ እንጨት እንቆርጣለን፡፡ እንደ ታንኳ በባሕር ላይ ወደ ኢዮጴ እንወስድልሃለን፤ አንተም እስከ ኢየሩሳሌም ድረስ ታጓጉዘዋለህ፡፡
\s5
\v 17 ሰለሞንም ኣባቱ ዳዊት በእስራኤል ምድር የነበሩትን የውጪ አገር ዜጎች ሁሉ እንደቆጠረ እርሱ ያደረገበትን ዘዴ ተከትሎ ቆጠራቸው፡፡ እነርሱም አንድ መቶ ሃምሳ ሦስት ሺህ ስድስት መቶ ሆነው ተገኙ፡፡
\v 18 ሰባ ሺህው ጭነት እንዲሸከሙ ሰማንያ ሺህው በተራሮችም ላይ እንጨት እንዲቆርጡ እና ሦስት ሺህ ስድስት መቶው ደግሞ ሕዝቡን ለሥራ የሚያሰማሩ ተቆጣጣሪዎች እንዲሆኑ መደባቸው፡፡
\s5
\c 3
\p
\v 1 ከዚህ በኋላ ሰለሞን እግዚአብሔር ለአባቱ ለዳዊት በተገለጠለት በሞሪያ ተራራ ላይ በኢየሩሳሌም የእግዚአብሔር ቤት መሥራት ጀመረ፡፡ ዳዊት እንዳቀደለት በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ ሥፍራውን አዘጋጀ፡፡
\v 2 በነገሠ በአራተኛው ዓመት በሁለተኛው ወር በሁለተኛው ቀን መሥራት ጀመረ፡፡
\v 3 ሰለሞንም ለእግዚአብሔር ቤት የጣለው መሠረት ስፍሮች እነዚህ ናቸው፡፡ ርዝመቱ በድሮው መለኪያ ስልሳ ክንድ ወርዱም ሃያ ክንድ ነበር፡፡
\s5
\v 4 በቤቱም ፊት የነበረው በረንዳ ርዝመቱ ከቤቱ ወርድ ተመሳሳይ ሆኖ ሃያ ክንድ ነበር፡፡ ቁመቱም ሃያ ክንድ ነበረ፡፡ ሰለሞንም ውስጡን በንጹህ ወርቅ ለበጠው፡፡
\v 5 የዋናውን ቤት ጣሪያ በጥድ እንጨት ሠራው፡፡ በንጹህ ወርቅም ለበጠው፡፡ የዘንባባ ዛፎችንና የሰንሰለቶችን አምሳል ቀረጸበት፡፡
\s5
\v 6 ቤቱንም በከበሩ ድንጋዮች አስጌጠው፤ ወርቁም የምሥራቅ ፈርዋይም ወርቅ ነበር፡፡
\v 7 አውታሮቹን፥ ሰረገሎቹን፥ ግድግዳዎቹንና በሮቹንም በወርቅ ለበጣቸው፡፡ በግድግዳዎቹም ላይ ኪሩቤልን ቀረፀ፡፡
\s5
\v 8 ቅድስተ ቅዱሳኑንም ሠራ፤ ርዝመቱም ከቤቱ ወርድ ጋር ተመሳሳይ ሆኖ ሃያ ክንድ ነበር፤ ወርዱም ሃያ ክንድ ነበር፡፡ ስድስት መቶ መክሊት በሚያህል በጥሩ ወርቅም ለበጠው፡፡
\v 9 የሚስማሮቹም ክብደት ሃምሳ ሰቅል ወርቅ ነበር፡፡ ከፍ ያሉ ገጽታዎቹን/ሰሌዳዎቹን በወርቅ ለበጣቸው፡፡
\s5
\v 10 ለቅድስተ ቅዱሳን ሁለት የኪሩቤል አምሳያዎችን ሠራ፤ ባለሙያዎችም በወርቅ ለበጡዋቸው፡፡
\v 11 ክንፎቹ በአጠቃላይ ከዳር እስከ ዳር ሃያ ክንድ ይረዝሙ ነበር፡፡ የአንዱ ኪሩብ ክንፍ ክፍሉ ግድግዳ ድረስ የሚደርስ አምስት ክንድ ይረዝም ነበር፤ ሌላኛው ክንፍ እንደዚሁ እስከ ሌላኛው ኪሩብ ክንፍ ድረስ የሚደርስ አምስት ክንድ ነበር፡፡
\v 12 የሌላኛው ኪሩብ ክንፍም ክፍሉ ግድግዳ ድረስ የሚደርስ አምስት ክንድ ይረዝም ነበር፤ ሌላኛው ክንፉም እንደዚሁ የመጀመሪያውን ኪሩብ ክንፍ የሚነካ አምስት ክንድ ነበር፡፡
\s5
\v 13 የእነዚህም ኪሩቤሎች ክንፎች በአጠቃላይ ሃያ ክንድ ያህል ተዘርግተው ነበር፡፡ ኪሩቤልም ፊቶቻቸው ወደ ዋናው ቤት እየተመለከቱ በእግሮቻቸው ቆመው ነበር፡፡
\v 14 ከሰማያዊም፥ ከሐምራዊም፥ ከቀዩም፥ ሐር እና ከጥሩ በፍታ መጋረጃውን ሠራ፤ የኪሩቤሎችንም ቅርፅ ሠራባቸው፡፡
\s5
\v 15 ሰለሞንም ለቤቱ ፊት ለፊት እያንዳንዳቸው ሠላሳ አምስት ክንድ ከፍታ ያላቸውን ሁለት ምሰሶዎች ሠራ፡፡ በእያንዳንዳቸውም ጫፍ ላይ የነበሩት ርዕሰ አእማድ አምስት ክንድ ከፍታ ያላቸው ነበሩ፡፡
\v 16 ለምሰሶዎቹም ሰንሰለቶችን አድርጎ በጫፋቸው ላይ አኖራቸው፡፡ መቶም ሮማኖች ሠርቶ ከሰንሰለቶቹ ጋር አገናኛቸው፡፡
\v 17 ምሰሶዎቹንም በቤት መቅደሱ ፊት ለፊት አንደኛውን በቀኝ ሌላኛውንም በግራ አቆማቸው፤ በስተቀኝ የነበረውን ምሰሶ የሚያቆም/ያኪን፥ የበስተግራውንም ምሰሶ የሚያበረታ/ቦኤዝ ብሎ ሰየመው፡፡
\s5
\c 4
\p
\v 1 በተጨማሪም የናሱን መሠዊያ ሠራ፤ ርዝመቱ ሃያ ክንድ ነበር፤ ወርዱም ሃያ ክንድ ነበር፤ ቁመቱም አሥር ክንድ ነበር፡፡
\v 2 ክፈፉ ከጫፍ እስከ ጫፉ አሥር ክንድ የሆነ ከቀለጠ ብረት ትልቅ ክብ ውሃ መያዣ ኩሬም ሠራ፡፡ ቁመቱም አምስት ክንድ ነበር፤ ዙሪያውም ሰላሳ ክንድ ነበር፡፡
\v 3 ውሃ መያዣው ቀልጦ ሲሰራ ከአርሱ ጋር አብረው የተሠሩ ከውሃ መያዣው ዙሪያ ከክፈፉ በታች በእያንዳንዱ ክንድ ርቀት አሥር ኮርማዎች ነበሩበት፡፡
\s5
\v 4 ውሃ መያዣው ሦስቱ ወደ ሰሜን በሚመለከቱ፥ ሦስቱ ወደ ምዕራብ በሚመለከቱ፥ ሦስቱ ወደ ደቡብ በሚመለከቱ፥ ሦስቱ ወደ ምሥራቅ በሚመለከቱ በአሥራ ሁለት በሬዎች ላይ ተቀምጦ ነበር፡፡ ውሃ መያዣው በላያቸው ላይ ሆኖ የጀርባ የሠውነት ክፍላቸው በስተ ውስጥ ነበር፡፡
\v 5 ውፍረቱም አንድ ጋት ያህል ነበር፡፡ የአፉ ክፈፍም እንደ ጽዋ ከንፈር እንደ ፈነዳ የሱፍ አበባ ሆኖ ተሠርቶ ነበር፡፡ ሦስት ሺህም የባዶስ መስፈሪያ ውሃ ይይዝ ነበር፡፡
\v 6 ደግሞም የተለያዩ ነገሮችን ማጠቢያ አሥር ጎድጓዳ ሳህኖች ሠራ፤ አምስቱን በስተግራ አምስቱንም በስተቀኝ አኖራቸው፤ የሚቃጠለውም መሥዋዕት ለማቅረብ ጥቅም የሚሰጡ ነገሮች በውስጣቸው ይታጠቡባቸው ነበር፡፡ የውሃ መያዣው ኩሬ ግን ለካህናቱ መታጠቢያ ነበር፡፡
\s5
\v 7 ለንድፋቸው በተሰጠው መመሪያ መሠረት አሥሩን የወርቅ መቅረዞች ሠራ፤ በቤተ መቅደሱ ውስጥ አምስቱን በስተግራ አምስቱን በስተቀኝ አኖራቸው፡፡
\v 8 አሥሩንም ገበታዎች ሠርቶ በቤተ መቅደሱ ውስጥ አምስቱን በስተግራ አምስቱን በስተቀኝ አኖራቸው፡፡ አንድ መቶ የወርቅ ጎድጓዳ ሳህኖች ሠራ፡፡
\s5
\v 9 በተጨማሪም የካህናቱን አደባባይ እና ታላቁንም አደባባይ የአደባባዮቹንም በሮች ሠራ፤ በሮቻቸውንም በናስ ለበጠ፡፡
\v 10 የውሃ መያዣውንም ኩሬ በቤቱ በስተቀኝ በስተምስራቅ ፊቱን ወደ ደቡብ አዙሮ አኖረው፡፡
\s5
\v 11 ኪራምም ምንቸቶቹን፥ መጫሪያዎቹንና መሠዊያውን መርጪያ ጎድጓዳ ሳህኖች ሠራ፡፡ ኪራምም እንደዚህ ለንጉሥ ሰለሞን በእግዚአብሔር ቤት የሠራውን ሥራ ሁሉ -
\v 12 ሁለቱን አዕማድ፥ በሁለቱ አዕማድ ጫፍ ላይ የነበሩትን ጉልላቶች፥ በሁለቱ አዕማድ ጫፍ ላይ የነበሩትን ጉልላቶች የሚሸፍኑትን ሁለቱን ጌጠኛ ቅርፃ ቅርፆች ጨረሰ፡፡
\v 13 በአዕማዱ ጫፍ ላይ የነበሩትን ጉልላቶች ለሚሸፍኑት ሁለቱ ጌጠኛ ቅርፃ ቅርፆች ለእያንዳንዳቸው ሁለት ተርታ ሮማኖች አድርጎ ለሁለቱ ጌጠኛ ቅርፃ ቅርፆች አራት መቶ ሮማኖች ሠራ፡፡
\s5
\v 14 ማቆሚያዎቹንና በማቆሚያዎቹ ላይ የሚቀመጡትን የመታጠቢያ ሰሃኖችንም ሠራ፤
\v 15 አንድ የውሃ መያዣ ኩሬ እና ከስሩ የሚሆኑትን አስራ ሁለት ኮርማዎች፥
\v 16 እንዲሁም ምንቸቶቹን፥ መጫሪያዎቹን፥ ሜንጦዎቹን እና ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ቁሳቁሶችን ሁሉ ሠራ፤ ኪራም ለንጉሥ ሰለሞን ለእግዚአብሔር ቤት ከአንፀባራቂ ናስ ሠራቸው፡፡
\s5
\v 17 ንጉሡም በዮርዳኖስ ሜዳ በሱኮትና ዛሬታን መካከል በሸክላው መሬት ውስጥ ብረታ ብረቱ እንዲቀልጥ አስደረገ፡፡
\v 18 ሰለሞንም እነዚህን እቃዎች ሁሉ በብዛት እንዲሰሩ አስደረገ፤ በእርግጥም የናሱ ክብደት ሊታወቅ አይችልም ነበር፡፡
\s5
\v 19 ሰለሞን በእግዚአብሔር ቤት የነበሩትን የቤት ዕቃዎች፥ የወርቁን መሠዊያ፥ የመገኘቱ ሕብስት የሚቀመጥባቸውን ገበታዎች፥
\v 20 በቅድስተ ቅዱሳን ፊት ያበሩ ዘንድ የታቀዱትን መቅረዞችን ከቀንዲሎቹ ጋር ሠራ፡፡እነዚህ ከንጹሕ ወርቅ የተሰሩ ነበሩ፡፡
\v 21 አበባዎቹም፥ ቀንዲሎቹና መኮስተሪያዎቹም የጥሩ ወርቅ ነበሩ፡፡
\s5
\v 22 ጉጠቶቹም፥ ጎድጓዳ ሳህኖቹም፥ ማንኪያዎቹም ፥ እጣን ማጨሻዎቹም ሁሉ ከንጹህ ወርቅ የተሰሩ ነበሩ፡፡ ወደ ቤቱ ውስጥ መግቢያዎቹን በተመለከተ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን የሚያስገቡት የውስጥ በሮች እና የቤቱ ማለትም የቤተ መቅደሱ በሮች ከወርቅ የተሠሩ ነበሩ፡፡
\s5
\c 5
\p
\v 1 ሰለሞንም እንደዚህ ለእግዚአብሔር ቤት የሠራው ሥራ ሁሉ ተጠናቀቀ፡፡ ሰለሞንም አባቱ ዳዊት የቀደሳቸውን እቃዎች ብሩን፥ ወርቁንና የቤት እቃዎችን ሁሉ ጨምሮ አምጥቶ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ በነበሩት ግምጃ ቤቶች ውስጥ አስቀመጣቸው፡፡
\s5
\v 2 ከዚያም ሰለሞን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ከዳዊት ከተማ ማለትም ከጽዮን እንዲያመጡ የእስራኤልን ሽማግሌዎች ፥ የነገድ አለቆችን ሁሉ እና የእስራኤልን ሕዝብ ቤተሰብ መሪዎች ሰበሰበ፡፡
\v 3 የእስራኤልም ሰዎች ሁሉ በሰባተኛው ወር በበዓሉ ወቅት በንጉሡ ፊት ተሰበሰቡ፡፡
\s5
\v 4 የእስራኤልም ሽማግሌዎች ሁሉ መጡ፤ ሌዋውያንም ታቦቱን አነሱ፡፡
\v 5 ታቦቱንም፥ የመገናኛውንም ድንኳን፥ በድንኳኑም ውስጥ የነበሩትን ቅዱሳት ዕቃዎች በሙሉ አመጡ፡፡ ከሌዊ ነገድ የነበሩት ካህናት እነዚህን ነገሮች ሁሉ አመጡ፡፡
\v 6 ንጉሥ ሰለሞንና የእስራኤል ማህበር ሁሉ ሊቆጠሩ የማይችሉትን በጎችና በሬዎች እየሰዉ በታቦቱ ፊት ተሰበሰቡ፡፡
\s5
\v 7 ካህናቱም የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ወደ ቤቱ ውስጠኛ ክፍል ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ከኪሩቤል ክንፍ በታች ወደ ቦታው አመጡት፡፡
\v 8 ኪሩቤልም በታቦቱ ስፍራ ላይ ክንፎቻቸውን ዘርግተው ነበር፤ ኪሩቤልም ታቦቱንና መሸከሚያዎቹን ምሶሶዎችም ይሸፍኑ ነበር፡፡
\s5
\v 9 መሸከሚያዎቹ ምሶሶዎችም እጅግ ረጅም ከመሆናቸው የተነሳ ጫፎቻቸው ከውስጠኛው ክፍል ፊት ለፊት ከቅዱሱ ሥፍራ ይታዩ ነበር፤ ነገር ግን ክውጪ መታየት አይችሉም ነበር፡፡ እስከዚህች ቀንም ድረስ በዚያ ይገኛሉ፡፡
\v 10 በታቦቱም ውስጥ የእስራኤል ሰዎች ከግብጽ ምድር በወጡ ጊዜ እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን ባደረገ ጊዜ ሙሴ በኮሬብ ካስቀመጣቸው ከሁለቱ ጽላቶች በስተቀር ምንም ነገር አልነበረባቸውም፡፡
\s5
\v 11 ካህናቱም ከቤተ መቅደሱ ቅዱስ ስፍራ ወጡ፡፡ በዚያ የነበሩትም ካህናት በተመደቡበት ክፍል ላይ ሳያተኩሩ ሁሉም ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ቀድሰው ነበር፡፡
\v 12 መዘምራን የነበሩትም ሌዋውያንም አሳፍን፥ ኤማንን፥ ኤዶታምን ልጆቻቸውንና ወንድሞቻቸውን ጨምሮ ሁሉም ጥሩ በፍታ ለብሰው ጸናጽል፥ በገና እና መሰንቆ/ክራር እየመቱ በመሠዊያው አጠገብ በስተምሥራቅ ቆመው ነበር፡፡ ከእነርሱም ጋር መቶ ሃያ መለከት የሚነፉ ካህናት ነበሩ፡፡
\s5
\v 13 መለከቱን የሚነፉትና መዘምራኑም ከመቅደሱ ሲወጡ በአንድነት ሆነው እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እያወደሱ በአንድ ቃል ድምጻቸውን ያሰሙ ነበር፡፡ ከመለከቶቹና ከጸናጽሎቹ ከሌሎቹም መሳሪያዎች ጋር ድምጻቸውን ከፍ አድርገው እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር፡፡" ቸር ነውና የቃል ኪዳን ታማኝነቱ ለዘላለም የሚጸና ነውና" ብለው ዘመሩ፡፡ በዚያን ጊዜ ቤቱ የእግዚአብሔር ቤት በደመና ተሞላ፡፡
\v 14 የእግዚአብሔር ክብር ቤቱን ሞልቶት ስለነበር ከደመናው የተነሳ ካህናቱ ለማገልገል መቆም አልቻሉም ነበር፡፡
\s5
\c 6
\p
\v 1 ሰለሞንም፦"እግዚአብሔር በድቅድቅ ጨለማ እንደሚኖር ተናግሯል፤
\v 2 እኔ ግን ለዘላለም እንድትኖርበት የላቀ መኖሪያ ቤት ሠራሁልህ" አለ፡፡
\v 3 ከዚያም የእስራኤል ጉባኤ ቆመው በነበሩበት ንጉሡ ፊቱን ዘወር አድርጎ የእስራኤልን ጉባኤ ሁሉ ባረከ፡፡
\s5
\v 4 እርሱም ፦ "ለአባቴ ለዳዊት የተናገረ እና በገዛ እጆቹ የፈጸመ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ፤
\v 5 "ሕዝቤን እስራኤልን ከግብጽ ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ ስሜ በዚያ የሚሆንበት ቤት በዚያ ይሠራልኝ ብዬ ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ ማንኛውንም ከተማ አልመረጥኩም፤ በሕዝቤም በእስራኤል ላይ አለቃ ይሆን ዘንድ አንድም ሰው አልመረጥኩም፤
\v 6 ነገር ግን ስሜ በዚያ እንዲሆንባት ኢየሩሳሌምን መርጫለሁ፤ በሕዝቤም በእስራኤል ላይ እንዲሆን ዳዊትን መርጫለሁ" ብሎአል፡፡
\s5
\v 7 አሁንም ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ቤት መስራት በአባቴ በዳዊት ልብ ነበር፡፡
\v 8 ነገር ግን እግዚአብሔር ለአባቴ ለዳዊት፦ "ለስሜ ቤት ትሠራ ዘንድ በልብህ ነበረ፤ ያ በልብህ የነበረ መሆኑ መልካም አደረግህ፡፡
\v 9 ነገር ግን ቤቱን አንተ ልትገነባው አይገባም፤ ይልቁንም ከወገብህ የሚወጣው ልጅህ እርሱ ለስሜ ቤትን ይሠራልኛል" አለው፡፡
\s5
\v 10 እግዚአብሔር ተስፋ እንደ ሰጠ በአባቴ በዳዊት ፈንታ ስለተነሳሁ በእስራኤልም ዙፋን ላይ ስለተቀመጥሁ እግዚአብሔር የተናገረውን ቃል ፈጽሞአል፡፡ ለእስራኤል አምላክም ለእግዚአብሔር ስም ቤት ሠራሁ፡፡
\v 11 ከእስራኤል ሕዝብ ጋር ያደረገው የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ያለበትን ታቦቱን በዚያ ውስጥ አኖርሁ፡፡
\s5
\v 12 ሰለሞን የእስራኤል ጉባኤ ሁሉ ባሉበት በእግዚአብሔር መሠዊያ ፊት እጆቹን ዘርግቶ ቆመ፡፡
\v 13 ርዝመቱ አምስት ክንድ፥ ወርዱ አምስት ክንድ፥ ቁመቱም ሦስት ክንድ የሆነ የናስ መድረክ ሰርቶ ነበር፡፡ በአደባባዩም መሃል ላይ አድርጎት ነበር፡፡ በእርሱም ላይ በመቆም በመላው የእስራኤል ጉባኤ ፊት ተንበርክኮ እጆቹን ወደ ሰማይ ዘረጋ፡፡
\s5
\v 14 እንዲህም አለ፦ "የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ በፍጹም ልባቸው በፊትህ ከሚሄዱ ባሪያዎችህ ጋር ኪዳንንና የቃል ኪዳን ታማኝነትን የምትጠብቅ በሰማይም ሆነ በምድር እንዳንተ ያለ አምላክ የለም፤ ለባሪያህ
\v 15 ለአባቴ ለዳዊት የሰጠኸውን ተስፋ የጠበቅህ አንተ፥ አዎ በአፍህ የተናገርኸውን ዛሬም እንደሆነው በእጅህ ፈጽመኸዋል፡፡
\s5
\v 16 አሁንም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ ለባሪያህ ለአባቴ ለዳዊት፦ "'አንተ በፊቴ እንደተመላለስህ ልጆችህ በሕጌ ይሄዱ ዘንድ ቢጠነቀቁ በእስራኤል ዙፋን የሚቀመጥ ሰው በፊቴ አታጣም' በማለት የሰጠኸውን ተስፋ ፈጽምለት፡፡
\v 17 እንግዲህ የእስራኤል አምላክ ሆይ ለባሪያህ ለዳዊት የሰጠኸው የተስፋ ቃል ይፈጸም፡፡
\s5
\v 18 በውኑ እግዚአብሔር ከሰው ጋር በምድር ላይ ይኖራልን? እነሆ መላው አጽናፈ ዓለም እና ሰማየ ሰማያት ራሱ ሊይዝህ አይችልም - ይልቁንም እኔ የሠራሁት ቤት ምንኛ ያነሰ ይችላል!
\v 19 ነገር ግን እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ የባሪያህን ይህንን ጸሎትና ልመናውን እባክህን ተቀበል፤ ባሪያህ በፊትህ የሚጸልየውን ጩኸትና ጸሎት ስማ፡፡
\v 20 ባሪያህ ወደዚህ ስፍራ የሚጸልየውን ጸሎት ትሰማ ዘንድ ስምህን እንደምታደርበት ወደተናገርከው ወደዚህ ስፍራ ዓይኖችህ ወደዚህ ቤተ መቅደስ በቀንና በሌሊት የተገለጡ ይሁኑ፡፡
\s5
\v 21 ባሪያህና ሕዝብህ እስራኤል ወደዚህ ስፍራ በሚጸልዩበት ጊዜ ልመናዎቻቸውን ስማ፤ ከማደሪያህ ስፍራ ከሰማያት ስማ፤ ሰምተህም ይቅር በል፡፡
\s5
\v 22 አንድ ሰው ባልንጀራውን ቢበድልና እንዲምል ቢጠየቅ እርሱም መጥቶ በዚህ ቤት ውስጥ በመሠዊያህ ፊት ቢምል
\v 23 ከሰማያት ሆነህ ስማ፤ አድርግም፤ በደሉን በራሱ ላይ በማድረግ በደለኛውን መልሰህ በመክፈል በባሪያዎችህ መካከል ፍረድ፡፡ ለጽድቁ ብድራትን ለመስጠት ጻድቁ ንጹህ መሆኑንም አስታውቅለት፡፡
\s5
\v 24 ሕዝብህ እስራኤል አንተን ከመበደላቸው የተነሳ በጠላት ድል ሲነሱ ወደ አንተ ቢመለሱ፥ በዚህም ቤተ መቅደስ ውስጥ በፊትህ ስምህን ቢጠሩ፥ ቢጸልዩና ምህረትን ቢለምኑ
\v 25 እባክህን ከሰማያት ስማና የሕዝብህን የእስራኤልን ኃጢአት ይቅር በል፤ ለእነርሱና ለአባቶቻቸውም ወደ ሰጠሃቸው ምድር መልሳቸው፡፡
\s5
\v 26 አንተን ከመበደላቸው የተነሳ ሰማያት ቢዘጉና ምንም ዝናብ በማይኖርበት ጊዜ ወደዚህ ስፍራ ቢጸልዩ፥ ስምህን ቢጠሩና ስታስጨንቃቸው ከኃጢአታቸው ቢመለሱ
\v 27 ከሰማይ ስማ፤ ሊመላለሱበት ወደሚገባቸው መልካሙ መንገድ ስትመራቸው የባሪያዎችህንና የሕዝብህን የእስራኤልን ኃጢአት ይቅር በል፡፡ ለሕዝብህ ርስት አድርገህ በሰጠሃት በምድርህ ላይ ዝናብን ላክ፡፡
\s5
\v 28 በምድሪቱ ላይ ርሃብ ቢኖር ወይም ቸነፈር ወይም ዋግ ወይም አረማሞ ወይም አንበጣ ወይም ኩብኩባ ቢኖር ወይም ጠላቶች በምድራቸው ውስጥ የከተማ በሮችን ቢያጠቁ ወይም ማናቸውም መቅሰፍት ወይም ደዌ ቢኖር
\v 29 አንድም ሰው ወይም ሕዝብህ እስራኤል ሁሉ እያንዳንዱ መቅሰፍቱንና ሐዘኑን በልቡ አውቆ ወደዚህ ቤተ መቅደስ እጆቹን ዘርግቶ ጸሎትና ልመና ቢያቀርብ
\v 30 በሰማይ በምትኖርበት ሆነህ ስማ፤ ይቅርም በል፤ የሰውን ሁሉ ልብ የምታውቅ አንተ ብቻ ስለሆንክ ልቡን ታውቃለህ፤ ለእያንዳንዱ እንደ መንገዱ ሁሉ ብድራትን ስጠው፡፡
\v 31 ለአባቶቻችን በሰጠሃቸው ምድር ላይ በሚኖሩበት ጊዜ ሁሉ አንተን እንዲፈሩህ በመንገድህም ይሄዱ ዘንድ ይህንን አድርግ፡፡
\s5
\v 32 ከሕዝብህ ከእስራኤል ወገን ያልሆነ ባእድ ሰው ደግሞ ከታላቁ ስምህ ፥ ከኃያሉ እጅህና ከተዘረጋችው ክንድህ የተነሳ ከሩቅ አገር ሲመጣ፥ ወደዚህ ቤተ መቅደስ መጥተው በሚጸልዩበት ጊዜ
\v 33 በሰማይ በምትኖርበት ስፍራ ሆነህ ስማ፤ በምድር ላይ ያሉ ሕዝቦች ሁሉ ስምህን እንዲያውቁ፥ እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል እንዲፈሩህ እና ይህ የሠራሁት ቤት በስምህ የሚጠራ መሆኑን እንዲያውቁ ባእዱ ሰው የሚለምንህን ሁሉ አድርግ፡፡
\s5
\v 34 ሕዝብህ አንተ በምትልካቸው በምንም መንገድ ከጠላቶቻቸው ጋር ለመዋጋት ቢወጡ ፥ አንተ ወደመረጥካት ወደዚች ከተማና ለስምህ ወደሠራሁት ወደዚህ ቤት ቢጸልዩ
\v 35 ከሰማያት ጸሎታቸውንና ልመናቸውን ስማና በጉዳያቸው አግዛቸው፡፡
\s5
\v 36 ኃጢአት የማይሰራ ማንም የለምና አንተን በበደሉህ ጊዜ ተቆጥተሃቸውም ለጠላት አሳልፈህ ብትሰጣቸው ጠላት ወደ ቅርብም ሆነ ሩቅ አገር ቢያግዛቸውና እንደ ምርኮኛ ወደ ምድራቸው ቢወስዳቸው
\v 37 በግዞት አገር ውስጥ መሆናቸውን ቢገነዘቡ፥ ንስሃ ቢገቡና በተማረኩበት ምድር ሞገስን ካንተ ቢፈልጉ፥ 'ጠማማን ነገር አድርገናል፤ በድለናል፤ እኩይ ምግባር ፈጽመናል፤' ቢሉ
\v 38 ምርኮኛ ተደርገው በተወሰዱባት በተማረኩባት ምድር በሙሉ ልባቸውና በሙሉ ነፍሳቸው ወዳንተ ቢመለሱና ለአባቶቻቸው ወደሰጠሃቸው ምድር፥ ወደ መረጥካት ከተማና ለስምህ ወደሠራሁት ቤት ቢጸልዩ
\v 39 በሰማያት በምትኖርበት ስፍራ ጸሎታቸውንና ልመናቸውን ስማና በጉዳያቸው አግዛቸው፡፡ የበደሉህን የሕዝብህን ኃጢአት ይቅር በል፡፡
\s5
\v 40 አሁንም አምላኬ ሆይ በዚህ ስፍራ ወደሚደረገው ጸሎት ዓይኖችህ የተገለጡና ጆሮዎችህ የሚያተኩሩ እንዲሆኑ እለምንሃለሁ፡፡
\v 41 አሁንም እግዚአብሔር አምላክ ሆይ አንተና የኃይልህ ታቦት ወደ ማረፊያህ ስፍራ ተነስ፤ እግዚአብሔር አምላክ ሆይ ካህናትህ ደህንነትን ይልበሱ፤ ቅዱሳንህም በመልካምነትህ ደስ ይበላቸው፡፡
\v 42 እግዚአብሔር አምላክ ሆይ የቀባኸውን ሰው ፊት ካንተ አትመልሰው፡፡ ለባሪያህም ለዳዊት ያደረግህለትን የቃል ኪዳን ታማኝነት አስብ፡፡
\s5
\c 7
\p
\v 1 ሰለሞን ጸሎቱን በፈጸመ ጊዜ እሳት ከሰማይ ወርዶ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና መሥዋዕቶችን በላ፤ የእግዚአብሔርም ክብር ቤቱን ሞላ፡፡
\v 2 የእርሱ ክብር ቤቱን ሞልቶት ስለነበር ካህናቱ ወደ እግዚአብሔር ቤት መግባት አልቻሉም፡፡
\v 3 የእስራኤልም ሕዝብ ሁሉ እሳቱ ሲወርድና የእግዚአብሔር ክብር በቤቱ ላይ እንደነበር ያዩ ነበር፡፡ በድንጋዩ ወለል ንጣፍ ላይ በግንባራቸው ተደፍተው ሰገዱ፤ ለእግዚአብሔርም ምስጋና አቀረቡ፡፡ "መልካም ነውና የቃል ኪዳን ታማኝነቱም ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና" አሉ፡፡
\s5
\v 4 ንጉሡና ሕዝቡ ሁሉ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አቀረቡ፡፡
\v 5 ንጉሥ ሰለሞንም ሃያ ሁለት ሺህ በሬዎችና መቶ ሃያ ሺህ በጎች በጎችና ፍየሎች ሰዋ፡፡ እንደዚህ ንጉሡና ሕዝቡ ሁሉ የእግዚአብሔርን ቤት ቀደሱ፡፡
\v 6 ካህናቱም እያንዳንዳቸው በሚያገለግሉበት ቦታ ቆመው ሌዋውያኑም "የቃል ኪዳን ታማኝነቱ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና" በሚለው መዝሙር እግዚአብሔርን እንዲያመሰግኑ ንጉሥ ዳዊት ያዘጋጀውን የእግዚአብሔር የዜማ መሳሪያዎች ይዘው ቆመው ነበር፡፡ ካህናቱ ሁሉ በፊታቸው መለከቶቻቸውን ሲነፉ እስራኤላውያን ሁሉ ቆሙ፡፡
\s5
\v 7 ሰለሞን በእግዚአብሔር ቤት ፊት ለፊት የነበረውን የአደባባዩን መካከል ቀደሰ፡፡ በዚያም የሠራው የናስ መሠዊያ የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ የእህሉን ቁርባንና ስቡን መያዝ ስላልቻለ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የሕብረት መሥዋዕቱን ስብ በዚያ አቀረበ፡፡
\s5
\v 8 በዚያን ጊዜ ሰለሞን ከእርሱም ጋር እስራኤል ሁሉ ከሐማት መግቢያ እስከ ግብጽ ወንዝ ድረስ የመጡ እጅግ ታላቅ ጉባኤ ለሰባት ቀናት ለሰባት ቀናት በዓል አደረጉ፡፡
\v 9 መሠዊያውን ለሰባት ቀናት ቀድሰው እና በዓሉን ለሰባት ቀናት ጠብቀው ስለነበር በስምንተኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ አደረጉ፡፡
\v 10 ሰለሞንም በሰባተኛው ወር በሃያ ሦስተኛው ቀን እግዚአብሔር ለዳዊት፥ ለሰለሞንና ለሕዝቡ ለእስራኤል ካሳየው በጎነት የተነሳ በደስታና በሐሴት ልብ ወደ የቤታቸው እንዲሄዱ ሕዝቡን አሰናበተ፡፡
\s5
\v 11 በመሆኑም ሰለሞን የእግዚአብሔርን ቤትና የገዛ ራሱን ቤት ጨረሰ፡፡ ለእግዚአብሔር ቤትና ለገዛ ራሱ ቤት ሰለሞን በልቡ ያሰበውን ማናቸውንም ነገር በስኬት አከናወነ፡፡
\v 12 እግዚአብሔርም በሌሊት ለሰለሞን ተገልጦ፦" ጸሎትህን ሰምቻለሁ፤ ይህንንም ስፍራ ለራሴ የመስዋዕት ቤት እንዲሆን መርጫለሁ" አለው፡፡
\s5
\v 13 ዝናብ እንዳይኖር ሰማያትን ብዘጋ ወይም ምድሪቱን እንዲበላ አንበጣን ባዝዘው ወይም በሕዝቡ መካከል ቸነፈርን ብሰድድ
\v 14 በስሜ የተጠሩት ህዝቤ ራሳቸውን ቢያዋርዱ፥ ቢጸልዩ፥ ፊቴን ቢፈልጉና ከክፉ መንገዳቸው ቢመለሱ ከሰማይ ሆኜ እሰማለሁ፤ ኃጢአታቸውን ይቅር እላለሁ፤ ምድራቸውንም እፈውሳለሁ፡፡
\v 15 አሁንም በዚህ ስፍራ ለሚደረግ ጸሎት ዓይኖቼ ክፍት ይሆናሉ፤ ጆሮዎቼም ያደምጣሉ፡፡
\s5
\v 16 አሁንም ስሜ ለዘላለም በዚያ ይኖር ዘንድ ይህንን ቤት መርጫለሁ፤ ቀድሻለሁም፤ ዓይኖቼና ልቤም ዘወትር በዚያ ይሆናሉ፡፡
\v 17 አንተ ደግሞ ያዘዝሁህን ሁሉ በመፈጸም እና ሥርዓቶቼንና ሕግጋቴን በመጠበቅ አባትህ ዳዊት እንደሄደ በፊቴ ብትሄድ፥
\v 18 ከአባትህ ከዳዊት ጋር በገባሁት በቃል ኪዳን "ከዘርህ በእስራኤል ላይ አለቃ የሚሆን አይታጣም" እንዳልኩት የመንግሥትህን ዙፋን አጸናለሁ፡፡
\s5
\v 19 ነገር ግን እኔን ከመከተል ብትመለሱና በፊታችሁ ያኖርኳቸውን ሥርዓቶቼንና ትዕዛዛቶቼን ብትተዉ፥ ሄዳችሁ ሌሎችንም አማልክት ብታመልኩ ብትሰግዱላቸውም፥
\v 20 ያን ጊዜ ከሰጠኋችሁ ምድሬ እነቅላቸዋለሁ፤ ለስሜ የቀደስኩትን ይህንን ቤት ከፊቴ እጥለዋለሁ፡፡ በሕዝቦችም ሁሉ መካከል ምሳሌና መቀለጃ አደርገዋለሁ፡፡
\s5
\v 21 ምንም እንኳን ይህ ቤተ መቅደስ እጅግ የላቀ ቢሆንም በአጠገቡ የሚያልፉ ሰዎች ይደነግጣሉ፤ በጥላቻ ይነጋገራሉ፡፡ "እግዚአብሔር በዚህ ምድርና በዚህ ቤት ላይ ይህንን እንዲህ ያደረገው ለምንድን ነው?" ብለው ይጠይቃሉ፡፡
\v 22 ሌሎችም፦ "ከግብጽ ምድር ያወጣቸውን አምላካቸውን እግዚአብሔርን ትተው ሌሎችን አማልክትን የሙጥኝ ከማለታቸው የተነሳ ፥ ስለሰገዱላቸው ስላመለኳቸው ነው፡፡ ለዚህ ነው እግዚአብሔር ይህንን ሁሉ አደጋ ያመጣባቸው" ብለው ይመልሳሉ፡፡
\s5
\c 8
\p
\v 1 ሰለሞን የእግዚአብሔርን ቤትና የራሱን ቤት የሠራበትን ሃያው ዓመት መጠናቀቂያ ላይ
\v 2 ሰለሞን ኪራም የሰጠውን ከተሞች እንደገና ሠርቶ የእስራኤል ሰዎች እንዲኖሩባቸው አደረገ፡፡
\s5
\v 3 ሰለሞን ሐማትሱባን አጥቅቶ አሸነፋት፡፡
\v 4 በምድረ በዳም የነበረችውን ታድሞርን እና በሐማትም የሠራቸውን የዕቃ ቤቱን ከተሞች ሁሉ ሠራ፡፡
\s5
\v 5 በቅጥሮች፥ በበሮችና በመዝጊያዎች የተመሸጉትን የላይኛውን ቤትሆሮንን እና የታችኛዋን ቤትሆሮንን ከተሞች ሠራ፡፡
\v 6 የባዕላትንም ከተማ፥ ሰለሞንም የነበሩትን የዕቃ ቤት ከተሞች ሁሉ፥ የሰረገላዎቹንም ከተሞች፥ የፈረሰኞቹንም ከተሞች እንዲሁም በኢየሩሳሌም፥ በሊባኖስ እና በግዛቱ ሥር በነበሩት ስፍራዎች ሊሠራ የተደሰተባቸውን ነገሮች ሁሉ ሠራ፡፡
\s5
\v 7 ከኬጢያውያን፥ ከአሞራውያን፥ ከፌርዜያውያን፥ ከኤዊያውያን እና ከኢያቡሳውያን የቀሩትን የእስራኤል ወገን ያልሆኑትን ሕዝብ ሁሉ፥
\v 8 የእስራኤል ሕዝብ ያላጠፉአቸውን በምድሪቱ ላይ ከእነርሱ በኋላ የቀሩትን ዝርያዎቻቸውን ሰለሞን እስከ ዛሬ ድረስ የግዳጅ የጉልበት ሠራተኞች አደረጋቸው፡፡
\s5
\v 9 ነገር ግን ሰለሞን የእስራኤል ሰዎችን አንድም የግዳጅ የጉልበት ሠራተኞች አላደረጋቸውም፤ ይልቁንም ወታደሮቹ፥ አዛዦቹ፥ ሹማምንቶቹ እና የሠረገሎቹና የፈረሰኞቹ አዛዦች አደረጋቸው፡፡
\v 10 እነዚህ ሁለት መቶ ሃምሳው፥ ሥራውን የሚሰሩትን ሰዎች የሚቆጣጠሩ የንጉሥ ሰለሞን ዋና ተቆጣጣሪዎችን የሚያስተዳድሩ ዋና ሹማምንቶችም ነበሩ፡፡
\s5
\v 11 ሰለሞንም፦ "የእግዚአብሔር ታቦት የደረሰበት ቦታ ሁሉ ቅዱስ ስለሚሆን ሚስቴ በእስራኤል ንጉሥ በዳዊት ቤት መኖር አይገባትም" በማለቱ ምክንያት የፈርኦንን ልጅ ከዳዊት ከተማ ውጪ ለእርሷ ወደ ሰራላት ቤት አመጣት፡፡
\s5
\v 12 ከዚያም ሰለሞን በመተላለፊያው ፊት ለፊት በሠራው በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረበ፡፡
\v 13 ዕለታዊው መርሀ ግብር በሚጠይቀው መሰረት መሥዋዕቶች አቀረበ፤ በሙሴ ትዕዛዝ የሚገኙትን መመሪያዎች በመከተል በሰንበታቱ ቀናት፥ በየመባቻዎቹ እና በተደነገጉት በዓላት በየዓመቱ ሦስት ጊዜ በየቂጣው በዓል፥ በየሰባቱ ሱባኤ በዓል እና በየዳሱም በዓል አቀረባቸው፡፡
\s5
\v 14 ሰለሞን የአባቱን የዳዊትን ትዕዛዝ በመከተል ካህናቱን በየክፍላቸው፥ ሌዋውያንንም ዕለታዊው መርሀ ግብር እንደሚጠብቅባቸው እግዚአብሔርን ለማወደስና በካህናቱ ፊት ለማገልገል በየሥራቸው መደባቸው፡፡ የእግዚአብሔር ሰው ዳዊት ይህንንም አዝዞ ስለነበር ደጅ ጠባቂዎችን ደግሞ በእያንዳንዱ በር በየክፍላቸው መደባቸው፡፡
\v 15 እነዚህ ሰዎች ንጉሡ ለካህናቱና ለሌዋውያኑ ማናቸውንም ጉዳይ ወይም መጋዘኖቹን በተመለከተ ከሰጠው ትዕዛዛቱ አላፈነገጡም፡፡
\s5
\v 16 እዚህ ላይ የእግዚአብሔር ቤት መሠረት ከተጣለበት ቀን አንስቶ እስከ ማጠናቀቂያው ድረስ የሰለሞን ሥራ ተከናወነ፡፡ በዚህ ሁኔታ የእግዚአብሔር ቤት ተጠናቅቆ ጥቅም ላይ ዋለ ፡፡
\s5
\v 17 ከዚህ በኋላ ሰለሞን በኤዶምያስ ምድር የባሕር ዳርቻ ወዳሉት ወደ ዔጽዮንጋብር እና ኤላት ሄደ፡፡
\v 18 ኪራምም የባህርን ነገር በሚገነዘቡ መርከበኞች የሚታዘዙ መርከቦችን ላከለት፡፡እነርሱም ከሰለሞን አገልጋዮች ጋር ወደ ኦፊር ሄዱ፡፡ ከዚያም አራት መቶ ሃምሳ መክሊት ወርቅ ለንጉሥ ሰለሞን አመጡ፡፡
\s5
\c 9
\p
\v 1 የሳባም ንግሥት የሰለሞንን ዝና በሰማች ጊዜ በከባባድ ጥያቄዎች ልትፈትነው ወደ ኢየሩሳሌም መጣች፡፡ ቅመማ ቅመሞች፥ ብዙ ወርቆች እና በርካታ የከበሩ ማዕድናት ከተጫኑ ግመሎች ጋር ከብዙ ጓዝ ጋር መጣች፡፡ ወደ ሰለሞን በመጣች ጊዜ በልብዋ የነበረውን ሁሉ አጫወተችው፡፡
\v 2 ሰለሞንም ጥያቄዎችዋን ሁሉ መለሰላት፤ ለሰለሞንም የከበደው ምንም ነገር አልነበረም፡፡ ያልመለሰውም ምንም ጥያቄ አልነበረም፡፡
\s5
\v 3 የሳባም ንግሥት የሰለሞንን ጥበብ፥ ሠርቶትም የነበረውን ቤተ መንግሥት፥
\v 4 በጠረጴዛው ላይ የነበረውን ምግብ፥ የአገልጋዮቹን አቀማመጥ፥ የሎሌዎቹንም ሥራ እና አለባበሳቸውን፥ አስተናጋጆቹንና አለባበሳቸውንም፥ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥም መስዋዕት የሚያቀርብበትን ሁኔታ ባየች ጊዜ አንዳች መንፈስ አልቀረላትም፡፡
\s5
\v 5 ንጉሡንም ፦ "ስለምትናገረው ነገርና ስለ ጥበብህ በገዛ አገሬ የሰማሁት ዘገባ እውነት ነው፤
\v 6 እዚህ እስክመጣ ድረስ ግን የሰማሁትን አላመንኩም ነበር፤ አሁን ዓይኖቼ አይተውታል፡፡ ስለ ጥበብህና ሃብትህ ግማሹ እንኳን አልተነገረኝም ነበር! ከሰማሁት ዝና ትበልጣለህ፡፡" አለችው፡፡
\s5
\v 7 "ጥበብህን ስለሚሰሙ ህዝብህ ምንኛ የተባረኩ፥ ዘወትር በፊትህ የሚቆሙ አገልጋዮችህም ምንኛ የተባረኩ ናቸው፡፡
\v 8 ለአምላክህ እግዚአብሔር ንጉሥ ትሆን ዘንድ ባንተ ደስ የተሰኘ እና በዙፋን ላይ ያስቀመጠህ አምላክህ እግዚአብሔር ብሩክ ይሁን፡፡ አምላክህ እስራኤልን ለዘላለም ያፀናቸው ዘንድ ስለወደደ ፍትህንና ጽድቅን እንድታደርግላቸው በላያቸው ላይ አነገሠህ" አለችው፡፡
\s5
\v 9 ለንጉሡም መቶ ሃያ መክሊት ወርቅ እና ከፍተኛ መጠን ያላቸው ቅመሞችንና የከበሩ ድንጋዮችን ሰጠችው፡፡ የሳባም ንግሥት ለንጉሡ ለሰለሞን ከሰጠችው ከእደነዚህ የሚበልጥ መጠን ያላቸው ቅመሞች እንደገና ተሰጥቶት አያውቅም፡፡
\s5
\v 10 ከኦፊር ወርቅ ያመጡት የኪራም አገልጋዮችና የሰለሞን አገልጋዮች የሰንደል እንጨትና የከበሩ ድንጋዮችን አመጡ፡፡
\v 11 ንጉሡም ከሰንደሉ እንጨት ለእግዚአብሔር ቤትና ለራሱ ቤት ደረጃዎችን እንዲሁም ለሙዚቀኞቹ በገናዎችንና መሰንቆዎችን/ክራሮችን አስደረገ፡፡ እንደዚህ ያለ እንጨት ከዚያ በፊት በይሁዳ ምድር ታይቶ አይታወቅም ነበር፡፡
\v 12 የሳባም ንግሥት ወደ ንጉሡ ካመጣችው የበለጠ ንጉሥ ሰለሞን የተመኘችውን ሁሉ፥ የለመነችውንም ሁሉ ሰጣት፡፡ እርስዋም ተመልሳ ከአገልጋዮችዋ ጋር ወደ ራሷ ምድር ሄደች፡፡
\s5
\v 13 በአንድ ዓመት ለሰለሞን የመጣለት ወርቅ ክብደት ስድስት መቶ ስልሳ ስድስት መክሊት ወርቅ ነበር፡፡
\v 14 ይህም ነጋድራሶችና ነጋዴዎች ካመጡት ወርቅ በተጨማሪ ነው፡፡ የዓረብም ነገሥታት ሁሉ እና የአገሪቱ ሹማምንት ለሰለሞን ወርቅና ብር ያመጡ ነበር፡፡
\s5
\v 15 ንጉሡም ሰለሞን በጥፍጥፍ ወርቅ ሁለት መቶ ትልልቅ ጋሻዎችን ሠራ፡፡ በእያንዳንዳቸውም ውስጥ ስድስት መቶ ሰቅል ጥፍጥፍ ወርቅ ገብቶባቸው ነበር፡፡
\v 16 ከጥፍጥፍ ወርቅም ሦስት መቶ ጋሻዎችን ሠራ፡፡ በእያንዳንዱም ጋሻ ውስጥ ሦስት ምናን ወርቅ ገብቶበት ነበር፡፡ ንጉሡም በሊባኖስ ዱር ቤተ መንግሥት ውስጥ አስቀመጣቸው፡፡
\s5
\v 17 ከዚያም ንጉሡ ከዝሆን ጥርስ ታላቅ ዙፋን አሠርቶ ከሁሉ በበለጠ ወርቅ አስለበጠው፡፡
\v 18 ወደ ዙፋኑ የሚያደርሱ ስድስት ደረጃዎች ነበሩት፤ የዙፋኑም የላይኛው ክፍል ከጀርባው ክብ ነበር፡፡ በመቀመጫው በእያንዳንዱ ጎን በኩል የክንድ መደገፊያዎች እና ከመደገፊያዎቹም አጠገብ ሁለት አንበሶች ቆመው ነበር፡፡
\s5
\v 19 በስድስቱም ደረጃዎች በእያንዳንዱ ላይ በእያንዳንዱ ጎን በኩል አንድ አንበሳ አስራ ሁለት አንበሶች ቆመው ነበር፡፡ በሌላ በየትኛውም መንግሥት እንደ እርሱ ያለ ዙፋን አልነበረም፡፡
\v 20 ንጉሥ ሰለሞን የሚጠጣባቸው ዕቃዎች በሙሉ የወርቅ ነበሩ፤ በሊባኖስ ዱር ቤተ መንግሥት ውስጥ የነበሩትም የሚጠጣባቸው ዕቃዎች በሙሉ ከንፁህ ወርቅ የተሠሩ ነበሩ፡፡ በሰለሞን ዘመን ብር ዋጋ እንዳለው የማይቆጠር ስለነበር አንዳቸውም ብር አልነበሩም፡፡
\v 21 ከኪራም መርከቦች ጋር በመሆን በባሕር ላይ የሚሄዱ ብዙ መርከቦች ነበሩት፡፡ በየሦስት ዓመቱም አንድ ጊዜ መርከቦቹ ወርቅ፥ ብር እና የዝሆን ጥርስ እንዲሁም ጦጣዎችና ዝንጀሮዎች ይዘው ይመጡ ነበር፡፡
\s5
\v 22 በመሆኑም ንጉሥ ሰለሞን ከዓለም ነገሥታት ሁሉ በባለጠግነትና በጥበብ በለጠ፡፡
\v 23 ምድር ሁሉ እግዚአብሔር በልቡ ያኖረውን ጥበቡን ይሰሙ ዘንድ የሰለሞንን መገኘት ይፈልጉ ነበር፡፡
\v 24 ከዓመት ዓመት የሚጎበኙትም ግብር፥ የብርና የወርቅ ዕቃዎች፥ አልባሳት፥ የጦር መሣሪያዎች እና ቅመማ ቅመሞች እንዲሁም ፈረሶችና በቅሎዎችን ያመጡ ነበር፡፡
\s5
\v 25 ሰለሞንም በሰረገሎች ከተሞችና ከራሱ ጋር በኢየሩሳሌም በተመደበላቸው ሥፍራ ለሚያኖራቸው ለፈረሶችና ለሰረገላዎች አራት ሺህ ጋጣዎች አስራ ሁለት ሺህም ፈረሰኞች ነበሩት፡፡
\v 26 ከኤፍራጥስ ወንዝ ጀምሮ እስከ ፍልስጤም ምድርና እስከ ግብፅ ዳርቻ ድረስ ባሉ ነገሥታት ሁሉ ላይ ይገዛ ነበር፡፡
\s5
\v 27 ንጉሡም በምድር ላይ እንዳለ ድንጋይ ያህል የበዛ ብር በኢየሩሳሌም ነበረው፡፡ የዝግባውንም እንጨት በቆላ እንዳሉት የሾላ ዛፎች የተትረፈረፈ እንዲሆን አደረገው፡፡
\v 28 ለሰለሞንም ከግብፅና ከየአገሩ ሁሉ ፈረሶችን ያመጡለት ነበር፡፡
\s5
\v 29 ሰለሞንን የሚመለከቱ ሌሎች ነገሮች የመጀመሪያውና የመጨረሻው በነቢዩ በናታን ታሪክ፥ በሴሎናዊውም በአሒያ ትንቢት፥ ስለ ናባጥም ልጅ ስለ ኢዮርብዓም ባየው በባለ ራዕዩ በአዶ የተፃፉ አይደለምን?
\v 30 ሰለሞንም በኢየሩሳሌም በእስራኤል ሁሉ ላይ አርባ ዓመት ነገሠ፡፡
\v 31 ከአባቶቹም ጋር አንቀላፋ፤ ሕዝቡም በአባቱ በዳዊት ከተማ ቀበሩት፤ ልጁም ሮብዓም በእርሱ ቦታ ነገሠ፡፡
\s5
\c 10
\p
\v 1 እስራኤልም ሁሉ ሊያነግሡት ወደ ሴኬም እየመጡ ስለነበር ሮብዓም ወደ ሴኬም ሄደ፡፡
\v 2 የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም ይህንን ሰማ (ከንጉሡ ከሰለሞን ፊት ሸሽቶ በግብፅ ይኖር ነበር፤ ነገር ግን ኢዮርብዓም ከግብፅ ተመለሰ)
\s5
\v 3 ልከውም አስጠሩት፤ ኢዮርብዓም እና እስራኤልም ሁሉ መጡ፤ ሮብዓምንም ተናገሩት፤
\v 4 "አባትህ ቀንበራችንን ከባድ አድርጎት ነበር፤ ስለዚህ አሁን አንተ ጽኑውን የአባትህን ሥራ ቀሊል፥ በእኛ ላይ ያደረገውንም ከባድ ቀንበር የማያስቸግር አድርግልን፤ እኛም እንገዛልሃለን" አሉት፡፡
\v 5 ሮብዓምም ፦ "ከሦስት ቀናት በኋላ ወደ እኔ ተመልሳችሁ ኑ" አላቸው፤ ሕዝቡም ሄዱ፡፡
\s5
\v 6 ንጉሥ ሮብዓም፦ "ለእነዚህ ሰዎች መልስ እንድሰጣቸው እንዴት ትመክሩኛላችሁ?" ብሎ አባቱ ሰለሞን በሕይወት እያለ በፊቱ ይቆሙ የነበሩትን ሽማግሌዎች አማከራቸው፡፡
\v 7 እነርሱም ፦ "ለዚህ ሕዝብ መልካም ብታደርግላቸውና ብታስደስታቸው፥ በመልካም ቃል ብታናግራቸው ሁልጊዜ አገልጋዮችህ ይሆኑልሃል፤" ብለው ተናገሩት፡፡
\s5
\v 8 ሮብዓም ግን ሽማግሌዎቹ የመከሩትን ምክር ችላ ብሎ ከእርሱ ጋር ያደጉትን በፊቱም የሚቆሙትን ወጣቶች አማከራቸው፡፡
\v 9 "'አባትህ በእኛ ላይ ያደረገውን ቀንበር አቅልልልን' ላሉኝ ሰዎች መልስ እንድሰጣቸው ምን ምክር ትሰጡኛላችሁ?" አላቸው፡፡
\s5
\v 10 ከሮብዓም ጋር ያደጉት ወጣቶች ተናገሩት፦ "'አባትህ ሰለሞን ቀንበራችንን አከበደብን፤ አንተ ግን ልታቀልልን ይገባል' ብለው ለነገሩህ ሰዎች፦ 'ትንሿ ጣቴ ክአባቴ ወገብ ትወፍራለች' ልትላቸው ይገባል፡፡
\v 11 "በመሆኑም አሁን ምንም እንኳን አባቴ ቀንበር አክብዶባችሁ የነበረ ቢሆንም እኔ ቀንበራችሁ ላይ እጨምራለሁ፤ አባቴ በአለንጋ ገርፏችሁ ነበር፤ ነገር ግን እኔ በጊንጥ እገርፋችኋለሁ" አላቸው፡፡
\s5
\v 12 በመሆኑም ንጉሡ፦ "በሦስተኛው ቀን ወደ እኔ ተመልሳችሁ ኑ" ባላቸው መሠረት ኢዮርብዓምና ሕዝቡ ሁሉ በሦስተኛው ቀን ወደ ሮብዓም መጡ፡፡
\v 13 ንጉሡም በጽኑ ምላሽ መለሰላቸው፤ ንጉሡም ሮብዓም የሽማግሌዎችን ምክር ቸል አለ፡፡
\v 14 የወጣቶቹን ምክር ተከትሎ ተናገራቸው፤ "ቀንበራችሁን ይበልጥ አከብድባችኋለሁ፤ እጨምርባችኋለሁ፡፡ አባቴ በአለንጋ ገርፏችሁ ነበር፤ ነገር ግን እኔ በጊንጥ እገርፋችኋለሁ" አላቸው፡፡
\s5
\v 15 በመሆኑም ንጉሡ ሕዝቡን አልሰማም፤ እግዚአብሔር በሴሎናዊው በአሒያ ለናባጥ ልጅ ለኢዮርብአም የተናገረውን ቃሉን ይፈጽም ዘንድ በእግዚአብሔር የተደረገ ክስተት ነበር፡፡
\s5
\v 16 እስራኤል ሁሉ ንጉሡ እንዳልሰማቸው ሲያዩ ሕዝቡ ፦ "ከዳዊት ምን ድርሻ አለን? ከእሴይም ልጅ ምንም ርስት የለንም! እስራኤል ሆይ እያንዳንዳችሁ ወደየድንኳኖቻችሁ ተመለሱ፡፡ ዳዊት ሆይ የገዛ ራስህን ቤት ተመልከት" ብለው መለሱለት፡፡ በመሆኑም እስራኤል ሁሉ ወደየድንኳኖቻቸው ተመለሱ፡፡
\s5
\v 17 በይሁዳ ከተሞች በሚኖሩት በእስራኤል ሕዝብ ላይ ግን ሮብዓም ነገሠባቸው፡፡
\v 18 ከዚያም ንጉሡ ሮብዓም አስገባሪውን አዶኒራምን ላከው፤ ነገር ግን የእስራኤል ሕዝብ በድንጋይ ወግረው ገደሉት፡፡ ንጉሥ ሮብዓም ፈጥኖ በሰረገላው ወደ ኢየሩሳሌም ሸሸ፡፡
\v 19 በመሆኑም እስራኤል እስከ ዛሬ ድረስ በዳዊት ቤት ላይ አመጸ፡፡
\s5
\c 11
\p
\v 1 ሮብዓም ኢየሩሳሌም ሲደርስ ከእስራኤል ጋር ተዋግተው መንግሥቱን ወደ ሮብዓም ለመመለስ ወታደሮች የሆኑ መቶ ሰማንያ ሺህ የተመረጡ ሰዎች ከይሁዳና ከቢንያም ቤት ሰበሰበ፡፡
\s5
\v 2 ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል ወደ እግዚአብሔር ሰው ወደ ሸማያ እንዲህ ሲል መጣ፤
\v 3 "ለይሁዳ ንጉሥ ለሰለሞን ልጅ ለሮብዓም በይሁዳና በቢንያምም ላሉት ለእስራኤል ሁሉ ተናገር፦
\v 4 እግዚአብሔር ይህንን ይላል፦ "ወንድሞቻችሁን ማጥቃት ወይም መዋጋት አይገባችሁም፡፡ ይህ ነገር በእኔ እንዲሆን የተፈቀደ ስለሆነ እያንዳንዱ ሰው ወደ ቤቱ መመለስ ይገባዋል፡፡" በመሆኑም የእግዚአብሔርን ቃል ሰሙ፤ በኢዮርብዓምም ላይ ለማጥቃት ከመውጣት ተመለሱ፡፡
\s5
\v 5 ሮብዓም በኢየሩሳሌም ይኖር ነበር፤ በይሁዳም ለምሽግነት ከተሞችን ገነባ፡፡
\v 6 ቤቴልሔምን፥ ኤጣምን፥ ቴቁሔን፥
\v 7 ቤትጹርን፥ ሦኮን፥ ዓዶላምን፥
\v 8 ጌትን፥ መሪሳን፥ ዚፍን፥
\v 9 አዶራይምን፥ ለኪሶን፥ ዓዜቃን፥
\v 10 ጾርዓን፥ ኤሎንን፥ ኬብሮንን ሠራ፡፡ እነዚህ በይሁዳና በብንያም ያሉት የተመሸጉት ከተሞች ናቸው፡፡
\s5
\v 11 ምሽጎቹንም አጠናክሮ ምግቡንም፥ ዘይቱንም፥ እና ከወይን ጠጁም መጋዘኖች ጋር አለቆቹንም አኖረባቸው፡፡
\v 12 በከተሞቹ ሁሉ ጋሻዎችና ጦሮችም አኖረባቸው፤ ከተሞቹንም እጅግ ጠንካራ አደረጋቸው፡፡ ይሁዳና ብንያምም የእርሱ ወገን ነበሩ፡፡
\s5
\v 13 በመላው እስራኤል የነበሩት ካህናትና ሌዋውያን ከነበሩባቸው ድንበሮች ወደ እርሱ መጡ፡፡
\v 14 ለእግዚአብሔር የክህነት ግዴታቸውን ከዚያ በኋላ መወጣት እንዳይችሉ ኢዮርብዓምና ልጆቹ አስለቅቀዋቸው ነበርና ሌዋውያንም ወደ ይሁዳና ወደ ኢየሩሳሌም ለመምጣት መሠማሪያቸውንና ቦታቸውን ትተው ነበር፡፡
\v 15 ኢዮርብዓም ለመስገጃዎቹና ለሠራቸው የጥጆችና የፍየሎች ጣኦታት ለራሱ ካህናትን ሾመ፡፡
\s5
\v 16 የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን ለመፈለግ ልባቸው የቆረጠ ሰዎች ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ ተከትለዋቸው መጡ፤ ለአባቶቻቸው አምላክ ለእግዚአብሔር ለመሰዋት ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፡፡
\v 17 በመሆኑም ለሦስት ዓመታት በዳዊትና በሰለሞን መንገድ ስለሄዱ በሦስቱ ዓመታት ውስጥ የይሁዳን መንግሥት አበረቱ፤ የሰለሞንንም ልጅ ሮብዓምን ጠንካራ አደረጉ፡፡
\s5
\v 18 ሮብዓም የዳዊትን ልጅ የኢያሪሙትን እና የእሴይን ልጅ የኤልያብን ሴት ልጅ የአቢካኢልን ሴት ልጅ መሐላትን ለራሱ ሚስት አድርጎ ወሰደ፤
\v 19 እርስዋም ወንዶች ልጆችን የዑስን፥ ሰማራያን፥ እና ዘሃምን ወለደችለት፡፡
\s5
\v 20 ከመሐላት በኋላ ሮብዓም የአቤሴሎምን ሴት ልጅ መዓካን ወሰደ፤ እርስዋም አብያን፥ ዓታይን፥ ዚዛን እና ሰሎሚትን ወለደችለት፡፡
\v 21 ሮብዓምም ከሌሎቹ ሚስቶቹና ቁባቶቹ ሁሉ ይልቅ የአቤሴሎምን ሴት ልጅ መዓካን ወደደ፤ (አስራ ስምንት ሚስቶችና ስልሳ ቁባቶች ወስዶ የሃያ ስምንት ወንዶች ልጆችና የስልሳ ሴቶች የልጅ ልጆች አባት ሆኖ ነበር፡፡)
\s5
\v 22 ሮብዓምም ንጉሥ ሊያደርገው ስላሰበ የመዓካን ልጅ አብያን በወንድሞቹ መካከል መሪ እንዲሆን አለቃ አድርጎ ሾመው፡፡
\v 23 ሮብዓም በጥበብ ያስተዳድር ነበር፤ ልጆቹንም ሁሉ ወደ ይሁዳና ቢንያም ምድር ሁሉ ወደ ተመሸጉት ከተሞች ሁሉ በተናቸው፡፡ የተትረፈረፈም ምግብ ሰጣቸው፤ ብዙ ሚስቶችንም ፈለገላቸው፡፡
\s5
\c 12
\p
\v 1 እንዲህም ሆነ፤ የሮብዓም መንግሥት በጸናች ጊዜና እርሱም በበረታበት በዚያን ጊዜ እርሱና እስራኤል ሁሉ የእግዚአብሔርን ሕግ ተዉ፡፡
\s5
\v 2 ሕዝቡ ለእግዚአብሔር ታማኞች ባለመሆናቸው ንጉሥ ሮብዓም በነገሠ በአምስተኛው ዓመት የግብጽ ንጉሥ ሺሻቅ ኢየሩሳሌምን ሊያጠቃ መጣባት፡፡
\v 3 ከአንድ ሺህ ሁለት መቶ ሰረገሎችና ከስልሳ ሺህ ፈረሰኞች ጋር መጠባት፡፡ ከእርሱም ጋር ሊቆጠሩ የማይችሉ ወታደሮች ሊቢያውያን፥ ሱካውያን እና ኢትዮጵያውያን መጡ፡፡
\v 4 የይሁዳ ይዞታ የነበሩትን የተመሸጉ ከተሞች ወሰደና ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፡፡
\s5
\v 5 ይሄኔ ነቢዩ ሸማያ ወደ ሮብዓምና ከሺሻቅ የተነሳ ወደ ኢየሩሳሌም በአንድነት ወደተሰበሰቡት መሪዎች መጣ፡፡ ሸማያ እንዲህ አላቸው፦ "እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔን ትታችሁኛል፤ ስለዚህ እኔ ደግሞ ለሺሻቅ እጅ አሳልፌ ሰጠኋችሁ፡፡"
\v 6 በዚያን ጊዜ የእስራኤል መሳፍንትና ንጉሡ ራሳቸውን አዋረዱ፤ "እግዚአብሔር ጻድቅ ነው" አሉ፡፡
\s5
\v 7 እግዚአብሔርም ራሳቸውን እንዳዋረዱ ባየ ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ሽማያ መጣ፦ "ሰውነታቸውን አዋርደዋል፡፡ አላጠፋቸውም፤ በተወሰነ ደረጃ አድናቸዋለሁ፡፡ ቁጣዬም በሺሻቅ እጅ በኢየሩሳሌም ላይ አይፈስስም፡፡
\v 8 ነገር ግን እኔን ማገልገል እና የሌሎች አገራትን ገዢዎች ማገልገል ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንዲገባቸው አገልጋዮቹ ይሆናሉ" አለ፡፡
\s5
\v 9 ስለሆነም የግብጽ ንጉሥ ሺሻቅ ኢየሩሳሌምን ሊያጠቃ መጥቶ የእግዚአብሔርን ቤት የከበሩ መዝገቦችና የንጉሡን ቤት የከበሩ መዝገቦች ወሰደ፡፡ ሁሉንም ነገር ወሰደ፤ ሰለሞን የሠራቸውን የወርቁን ጋሻዎችም ጭምር ወሰደ፡፡
\v 10 ንጉሥ ሮብዓም በእነርሱ ምትክ የናስ ጋሻዎች ሠርቶ የንጉሡን ቤት በሮች በሚጠብቁት ዘበኞች አለቃዎች እጅ አስቀመጣቸው፡፡
\s5
\v 11 ከዚያ በኋላ ንጉሡ ወደ እግዚአብሔር ቤት በገባ ቁጥር ዘበኞቹ ይሸከሙአቸው ነበር፤ ከዚያም ወደ ዘበኞቹ ቤት ይመልሷቸው ነበር፡፡
\v 12 ሮብዓም ሰውነቱን ባዋረደ ጊዜ ሙሉ በሙሉ እንዳያጠፋው የእግዚአብሔር ቁጣ ከእርሱ ተመለሰ፤ ደግሞም በይሁዳ የተወሰነ መልካምነት ገና ይገኝ ነበር፡፡
\s5
\v 13 ንጉሡም ሮብዓም ንግሥናውን በኢየሩሳሌም አጠናከረ፤ በዚህ ሁኔታም ገዛ፡፡ ሮብዓም መንገሥ ሲጀምር አርባ አንድ ዓመቱ ነበር፤ እግዚአብሔር ስሙን ያኖርባት ዘንድ ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ በመረጣት በኢየሩሳሌም ከተማ አስራ ሰባት ዓመታት ነገሠ፡፡ የአሞናዊቷ እናቱም ስም ናዕማ ነበር፡፡
\v 14 እግዚአብሔርን ይፈልግ ዘንድ ልቡን አላዘጋጀም ነበርና ክፉውን ነገር አደረገ፡፡
\s5
\v 15 ሮብዓምን የሚመለከቱ ሌሎች ነገሮች የመጀመሪያውና የመጨረሻው የትውልዶች ስም ዝርዝርና በሮብዓምና በኢዮርብዓም መካከል የነበሩት ያልተቋረጡ ጦርነቶች በተመዘገቡበት በነቢዩ ሸማያና በባለ ራዕዩ በአዶ ጽሑፎች ውስጥ የተጻፉ አይደለምን?
\v 16 ሮብዓምም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊትም ከተማ ተቀበረ፤ ልጁም አብያ በእርሱ ቦታ ነገሠ፡፡
\s5
\c 13
\p
\v 1 ንጉሥ ኢዮርብዓም በነገሠ በአሥራ ስምንተኛው ዓመት አብያ በይሁዳ ላይ መንገሥ ጀመረ፡፡
\v 2 በኢየሩሳሌም ለሦስት ዓመታት ገዛ፤ የገብዓው ሰው የኡርኤል ልጅ የነበረችው የእናቱ ስም ሚካያ ነበር፡፡ በአብያና በኢዮርብዓም መካከል ጦርነት ነበረ፡፡
\v 3 አብያም ከአራት መቶ ሺህ የተመረጡ ጠንካራ፥ ደፋር ሰዎች ሠራዊት ጋር ወደ ጦርነት ሄደ፡፡ ኢዮርብዓምም ከተመረጡት ስምንት መቶ ሺህ የተመረጡ ጠንካራ፥ ደፋር ወታደሮች ጋር ሊጋጠመው ተሰለፈ፡፡
\s5
\v 4 አብያም በተራራማው በኤፍሬም አገር ባለው በጽማራይም ተራራ ላይ ቆሞ፦ "ኢዮርብዓምና እስራኤል ሁሉ ስሙኝ!
\v 5 የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ መንግሥት ለዳዊት ለዘላለም ለልጆቹ በደንብ በተጠበቀ ቃል ኪዳን እንዲገዙ እንደሰጠ አታውቁምን?" አለ፡፡
\s5
\v 6 የዳዊት ልጅ የሰለሞን ባሪያ የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም ግን ተነሳና በጌታው ላይ ዐመፀ፡፡
\v 7 የማይረቡ ሰዎችም ጸያፍ ሰዎችም ወደ እርሱ ተሰበሰቡ፡፡ የሰለሞን ልጅ ሮብዓም ወጣትና ልምድ የለሽ በነበረበትና ሊቋቋማቸው በማይችልበት ጊዜ በሮብዓም ላይ ተነሱበት፡፡
\s5
\v 8 አሁንም በዳዊት ዝርያዎች እጅ ውስጥ የሆነውን የእግዚአብሔር አገዛዝ ኃይል ልትቋቋሙ እንደምትችሉ ትናገራላችሁ፡፡ እናንተም ታላቅ ሠራዊት ናችሁ፤ ኢዮርብዓም አማልክት አድርጎ የሠራላችሁ የወርቅ ጥጃዎች ከእናንተ ጋር አሉ፡፡
\v 9 የአሮንን ትውልዶች የእግዚአብሔርን ካህናትና ሌዋውያን አላባረራችሁምን? እንደ ሌሎች ምድር ሕዝቦች ልማድ ለራሳችሁ ካህናት አላደረጋችሁምን? ከአንድ ወይፈንና ሰባት አውራ በጎች ጋር ራሱን ሊቀድስ የሚመጣው ሁሉ አማልክት ላልሆኑ ነገሮች ካህን ይሆናል፡፡
\s5
\v 10 ለእኛ ግን እግዚአብሔር አምላካችን ነው፤ እኛም አልተውነውም፡፡ የአሮን ዝርያዎች የሆኑት እግዚአብሔርን የሚያገለግሉ ካህናትና በሥራቸው ላይ የተሰማሩ ሌዋውያን አሉን፡፡
\v 11 በየማለዳውና በየምሽቱ ለእግዚአብሔር የሚቃጠለውን መሥዋዕትና ጣፋጩን ዕጣን ያቃጥላሉ፤ የመገኘቱንም ሕብስት በንጹህ ገበታ ላይ ያዘጋጃሉ፤ በየምሽቱ እንዲያበሩ የወርቁን መቅረዝ ከቀንዲሎቹ ጋር ይንከባከባሉ/ይጠብቃሉ፡፡ እኛም የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ እንጠብቃለን፤ እናንተ ግን ትታችሁታል፡፡
\s5
\v 12 እነሆ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር እንደ አለቃችን ነው፤ በእናንተ ላይ መለከቶቹን ለመንፋት የእርሱ ካህናትም እዚህ ይገኛሉ፡፡ የእስራኤል ሕዝብ ሆይ ስለማይሳካላችሁ ከአባቶቻችሁ አምላክ ከእግዚአብሔር ጋር አትዋጉ፡፡
\s5
\v 13 ኢዮርብዓም ግን ክጀርባቸው ድብቅ ጦር አዘጋጅቶ ነበር፤ የእርሱ ሠራዊት ከይሁዳ ፊት ለፊት ሆኖ ድብቁ ጦር ግን ክጀርባቸው ነበር፡፡
\v 14 ይሁዳ ከወደ ኋላ ሲመለከቱ እነሆ ውጊያው ከፊታቸውና ከኋላቸውም ነበር፡፡ ወደ እግዚአብሔርም ጮኹ፤ ካህናቱም መለከቶቹን ነፉ፡፡
\v 15 የይሁዳም ሰዎች ጮኹ፤ በጮኹም ጊዜ እግዚአብሔር ኢዮርብዓምንና እስራኤልን ሁሉ በአብያና በይሁዳ ፊት መታቸው፡፡
\s5
\v 16 የእስራኤል ሕዝብ ከይሁዳ ፊት ሸሹ፤ እግዚአብሔርም በይሁዳ እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፡፡
\v 17 አብያና ሠራዊቱ በታላቅ አገዳደል ገደሏቸው፤ አምስት መቶ ሺህ የተመረጡ የእስራኤል ሰዎች ተገድለው ወደቁ፡፡
\v 18 በዚህ መንገድ በዚያን ጊዜ የእስራኤል ሕዝብ ተሸነፉ፤ የይሁዳ ሕዝብ በአባቶቻቸው አምላክ በእግዚአብሔር ታምነው ስለነበር አሸነፉ፡፡
\s5
\v 19 አብያ ኢዮርብዓምን አሳደደ፤ ከእርሱም ከተሞችን ወሰደ፤ ቤቴልንና መንደሮችዋን፥ ይሻናንና መንደሮችዋን፥ እንዲሁም ዔፍሮንንና መንደሮችዋን ወሰደ፤
\v 20 ኢዮርብዓምም በአብያ ዘመን እንደገና ኃይሉ ከቶም አላገገመም፡፡ እግዚአብሔርም ቀሰፈው፤ እርሱም ሞተ፡፡
\v 21 አብያ ግን በረታ፤ ለራሱ አስራ አራት ሚስቶችን ወሰደ፤ ሃያ ሁለት ወንዶች ልጆችንና አስራ ስድስት ሴቶች ልጆችን ወለደ፡፡
\v 22 የተቀሩት የአቢያ ድርጊቶችና ባሕርዩ የተናገራቸው ነገሮችም በነቢዩ አዶ ትርጓሜ/አንድምታ ተጽፈዋል፡፡
\s5
\c 14
\p
\v 1 አብያም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊት ከተማ ቀበሩት፡፡ ልጁም አሳ በእርሱ ቦታ ነገሠ፡፡ በእርሱም ዘመን በምድሪቱ ላይ ለአሥር ዓመታት ፀጥታ ነበር፡፡
\v 2 አሳ በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት መልካምና ትክክለኛውን ነገር አደረገ፤
\v 3 የእንግዶቹን አማልክት መሠዊያ እና መስገጃዎቹን አስወገደ፤ የተቀደሱትን የድንጋይ ሐውልቶች ሰባበረ፤ የማምለኪያ ዐፀዶቹንም ቆራረጠ፡፡
\v 4 የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ይሹ ዘንድ እና ሕጉንና ትዕዛዛቱን ይፈጽሙ ዘንድ ይሁዳን አዘዘ፡፡
\s5
\v 5 ከይሁዳም ከተሞች ሁሉ መስገጃዎቹንና ዕጣን የሚጨስባቸውን መሠዊያዎች አስወገደ፡፡ መንግሥቱም በእርሱ ሥር በሰላም ተቀመጠች፡፡
\v 6 በምድሪቱ ላይ ጸጥታ ስለነበርና እግዚአብሔርም ሰላም ስለሰጠው በእነዚያ ዓመታት ምንም ጦርነት ስላልነበረበት በይሁዳ የተመሸጉ ከተሞችን ሠራ፡፡
\s5
\v 7 አሳም ይሁዳን፡-"እነዚህን ከተሞች እንገንባ፤ በዙሪያቸው ቅጥር ፥ ማማዎች፥ መዝጊያዎች፥ እና መወርወሪያዎች እንሥራ፤ አምላካችንን እግዚአብሔርን ስለፈለግነው ምድሪቱ እስከ አሁንም የእኛ ናት፡፡ እኛም ፈልገነዋል እርሱም በሁሉም በኩል እረፍት ሰጥቶናል፡፡" አላቸው፡፡ እነርሱም ገነቡ፤ ተሰካላቸውም፡፡
\v 8 ለአሳም ጋሻና ጦር የሚይዙ ከይሁዳ ሦስት መቶ ሺህ ሰዎች፥ ጋሻ የሚይዙና ቀስት የሚስቡ ደግሞ ከቢኒያም ሁለት መቶ ሰማንያ ሺህ ሰዎች የያዘ ሠራዊት ነበረው፡፡
\s5
\v 9 ኢትዮጵያዊው ዝሪ አንድ ሚሊዮን ወታደሮችና ሦስት መቶ ሰረገሎች ያሉት ሠራዊት ይዞ ሊያጠቃቸው መጣባቸው፤ ወደ መሪሳም መጣ፡፡
\v 10 አሳም ሊጋጠመው ወጣ፤ በመሪሳም በጽፋታ ሸለቆ ውስጥ በጦርነቱ ግንባር ተሰለፉ፡፡
\v 11 አሳም ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር ፦ "እግዚአብሔር ሆይ ምንም ጉልበት የሌለው ሰው ብዙዎችን በሚጋፈጥበት ጊዜ ካንተ በቀር ማንም የሚረዳው የለም፡፡ አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ በአንተ ላይ ተማምነናልና እርዳን፤ ይህንን የመጣብንን ብዙ ቁጥር ያለው ሠራዊት በስምህ እንመጣባቸዋለን፡፡ እግዚአብሔር ሆይ አንተ አምላካችን ነህ፤ ሰውም አያሸንፍህ" ብሎ ጮኸ፡፡
\s5
\v 12 እግዚአብሔርም በአሳና በይሁዳ ፊት ኢትዮጵያውያንን መታ፤ ኢትዮጵያውያንም ሸሹ፡፡
\v 13 አሳና ወታደሮቹም እስከ ጌራራ ድረስ አሳደዱአቸው፡፡ ስለዚህ በእግዚአብሔርና በሠራዊቱ ፊት ሙሉ በሙሉ ስለተደመሰሱ ማገገም እስከማይችሉ ድረስ በርካታ ኢትዮጵያውያን ወደቁ፡፡ሠራዊቱም እጅግ ብዙ ምርኮ ወሰዱ፡፡
\s5
\v 14 የእግዚአብሔር ድንጋጤ በነዋሪዎቹ ላይ ስለመጣባቸው ሠራዊቱ በጌራራ ዙሪያ ያሉ መንደሮችን ሁሉ ደመሰሱ፡፡ በውስጣቸውም እጅግ ብዙ ምርኮ ስለነበር ሠራዊቱ መንደሮቹን ሁሉ በዘበዙ፡፡
\v 15 የከብት አርቢ ዘላኖቹን የድንኳን ሰፈራዎችም ደመሰሱ፤ ከመጠን በላይ በጎችን እንዲሁም ግመሎችን ወስደው ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፡፡
\s5
\c 15
\p
\v 1 የእግዚአብሔር መንፈስ በዖዴድ ልጅ በዓዛርያስ ላይ መጣ፡፡
\v 2 አሳንም ሊገናኘው ወጣ፤ እንዲህም አለው፦ "አሳ፥ ይሁዳ ሁሉና ቢኒያም ሆይ ስሙኝ፤ እናንተ ከእግዚአብሔር ጋር ስትሆኑ እርሱ ከእናንተ ጋር ይሆናል፡፡ ብትፈልጉትም ይገኝላችኋል፤ ብትተዉት ግን ይተዋችኋል፡፡
\s5
\v 3 እስራኤል ለረጅም ጊዜ ያለ እውነተኛ አምላክ፥ ያለ አስተማሪ ካህን እና ያለ ሕግ ይኖሩ ነበር፡፡
\v 4 በጭንቃቸው ጊዜ ግን ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር ተመልሰው ሲፈልጉት ይገኝላቸው ነበር፡፡
\v 5 በዚያን ዘመን ርቆ ለሚሄደውና ወደዚህ ቅርብ ለሚመጣው ሰላም አልነበረም፤ ይልቁንም በምድሪቱ በሚኖሩ ሁሉ ላይ ታላቅ ጭንቅ ነበር፡፡
\s5
\v 6 እግዚአብሔር በሁሉም ዓይነት መከራዎች ያስጨንቃቸው ስለነበር ፍርስርሳቸው ወጥቶ ነበር፤ ህዝብ ከህዝብ ጋር፥ ከተማም ከከተማ ጋር ይዋጋ ነበር፡፡
\v 7 እናንተ ግን ሥራችሁ ብድራት ስለአለው በርቱ እጃችሁም እንዲደክም አትፍቀዱ፡፡"
\s5
\v 8 ይህንን ቃል፥ የነቢዩን የዖዴድን ትንቢት በሰማ ጊዜ ብርታት አግኝቶ ከይሁዳና ከቢኒያም ምድር ሁሉ፥ ከተራራማው የኤፍሬም አገር ከያዛቸው ከተሞች ጸያፉን ነገር አስወገደ፤ በእግዚአብሔርም ቤት መተላለፊያ ፊት ለፊት የነበረውን የእግዚአብሔር መሠዊያ እንደገና ሠራ፡፡
\v 9 ይሁዳንና ቢኒያምን ሁሉ ፥ ከኤፍሬምና ከምናሴም ከስምዖንም ወገን የሆኑትን ከእርሱም ጋር የዘለቁትን ሰበሰበ፡፡ እግዚአብሔር አምላኩ ከእርሱ ጋር እንደነበር ሲያዩ ከእስራኤል ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ወደ እርሱ መጡ፡፡
\s5
\v 10 በመሆኑም አሳ በነገሠ በአስራ አምስተኛው ዓመት በሦስተኛው ወር በኢየሩሳሌም በአንድ ላይ ተሰበሰቡ፡፡
\v 11 በዚያም ቀን ካመጡት ምርኮ የተወሰነውን ሰባት መቶ በሬዎችና ሰባት ሺህ በጎችና ፍየሎች ለእግዚአብሔር ሠዉ፡፡
\s5
\v 12 የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን በሙሉ ልባቸውና በሙሉ ነፍሳቸው ሊፈልጉት ቃል ኪዳን አደረጉ፡፡
\v 13 የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን የማይፈልግ ማንም ቢኖር ሰውየው ታናሽ ይሁን ታላቅ፥ ወንድ ወይም ሴት ሊገደል እንደሚገባው ተስማሙ፡፡
\s5
\v 14 በታላቅ ድምጽና በጩኸት፥ በእምቢልታና በቀንደ መለከት ለእግዚአብሔር ማሉ፡፡
\v 15 በሙሉ ልባቸው መሐላውን ስለፈጸሙ፥ እግዚአብሔርንም በሙሉ ፍላጎታቸው ስለፈለጉት እርሱም ተገኝቶላቸው ስለነበር ይሁዳ ሁሉ በመሐላው ደስ አላቸው፡፡ እግዚአብሔር በዙሪያቸው ሁሉ ሰላምን ሰጣቸው፡፡
\s5
\v 16 ንጉሡም አሳ ሴት አያቱ መዓካ ከማምለኪያ አጸድ አስጸያፊ ምስል/ጣኦት ስላበጀች ከንግሥትነትዋ አስወገዳት፡፡ አሳም አስጸያፊ ምስሏን/ጣኦቷን ቆርጦ አቧራ አድርጎ ፈጨው፤ በቄድሮንም ወንዝ አጠገብ አቃጠለው፡፡
\v 17 መስገጃዎቹ ግን ከእስራኤል አልራቁም ነበር፡፡ ይሁን እንጂ የአሳ ልብ በዘመኑ ሁሉ ፍጹም ታማኝና ታዛዥ ነበር፡፡
\s5
\v 18 የእግዚአብሔር የሆኑትን የአባቱን ነገሮችና የገዛ ራሱን ነገሮች፥ የብርና የወርቅ ዕቃዎች ወደ እግዚአብሔር ቤት ውስጥ አስገባቸው፡፡
\v 19 አሳም እስከነገሠበት እስከ ሠላሳ አምስተኛው ዓመት ድረስ ከዚያ ወዲያ ጦርነት አልነበረም፡፡
\s5
\c 16
\p
\v 1 አሳ በነገሠ በሠላሳ ስድስተኛው ዓመት የእስራኤል ንጉሥ ባኦስ በይሁዳ ላይ የጠብ ጫሪነት ድርጊት ፈጸመ፡፡ ወደ ይሁዳም ንጉሥ ወደ አሳ ምድር ማንም መውጣትና መግባት እንዳይፈቀድለት ራማን ዙሪያዋን ሠራ፡፡
\s5
\v 2 አሳም ከእግዚአብሔር ቤት እና ከንጉሡ ቤት መጋዘኖች ብርና ወርቅ አውጥቶ በደማስቆ ይኖር ወደ ነበረው ወደ አራም ንጉሥ ወደ ቤንሃዳድ ላከው፡፡
\v 3 "በአባትህና በአባቴ መካከል እንደነበረው በእኔና በአንተ መካከል የሰላም ስምምነት ይኑር፡፡ እነሆ ብርና ወርቅ ሰድጄልሃለሁ፤ ከእኔ ርቆ እንዲተወኝ ከእስራኤል ንጉሥ ከባኦስ ጋር ያደረግኸውን የሰላም ስምምነት አፍርስ" አለው፡፡
\s5
\v 4 ቤንሃዳድም ንጉሡን አሳን ሰማው፤ የእስራኤልን ከተሞች እንዲያጠቁም የሠራዊቱን አለቆች ላከ፡፡ እነርሱም ኦዮንን፥ ዳንን፥ አቤልማይምንና የንፍታሌምን የዕቃ ቤት ከተሞች ሁሉ መቱ፡፡
\v 5 ባኦስም ይህንን ሲሰማ የራማን ዙሪያዋን መሥራቱን አቆመ፤ ሥራውንም አቋረጠ፡፡
\v 6 በዚያን ጊዜ ንጉሡ አሳ ይሁዳን ሁሉ ሰበሰበ፤ ባኦስ ከተማይቱን ይሠራበት የነበረውን የራማን ድንጋዮችና ጣውላዎች ወሰዱ፡፡ ከዚያም ንጉሡ አሳ ያንን የግንባታ ዕቃ ጌባንና ምጽጳን ለመሥራት ተጠቀመበት፡፡
\s5
\v 7 በዚያን ጊዜ ባለ ራዕዩ አናኒ ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ አሳ ሄዶ፦ "በአራም ንጉሥ ስለታመንህና በአምላክህ በእግዚአብሔር ስላልታመንህ የአራም ንጉሥ ሠራዊት ከእጅህ አምልጦአል፡፡
\v 8 እጅግ ብዙ ሰረገሎችና ፈረሰኞች የነበሯቸው ኢትዮጵያውያንና ሊቢያውያን ታላቅ ሠራዊት አልነበሩምን? ነገር ግን በእግዚአብሔር ስለታመንህ በእነርሱ ላይ ድልን ሰጠህ፡፡
\s5
\v 9 ልቡ በእርሱ ዘንድ ፍጹም የተሰጠ የሆነውን ሰው በኃይሉ ያበረታ ዘንድ የእግዚአብሔር ዓይኖች በምድር ሁሉ ላይ ይዘዋወራሉ፡፡ ነገር ግን አንተ በዚህ ጉዳይ ስንፍና አድርገሃል፡፡ ከአሁን ጊዜ ጀምሮ ጦርነት ይሆንብሃል" አለው፡፡
\v 10 በዚያን ጊዜ ንጉሡ አሳ በባለ ራዕዩ ላይ ተቆጣ፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ተቆጥቶ ስለነበር እስር ቤት ውስጥ አኖረው፡፡ በዚያው ጊዜ አሳ ከሕዝቡ የተወሰኑትን አስጨነቀ፡፡
\s5
\v 11 እነሆ የአሳ ድርጊቶች ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው እነሆ በይሁዳና በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፈዋል፡፡
\v 12 አሳ በነገሠ በሠላሳ ዘጠኝ ዓመቱ እግሩን ታመመ፤ ሕመሙም እጅግ ጽኑ ነበር፡፡ እንዲህም ሆኖ ከባለ መድኃኒቶች ብቻ እንጂ ከእግዚአብሔር እርዳታ አልፈለገም፡፡
\s5
\v 13 አሳ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በነገሠም በአርባ አንደኛው ዓመት ሞተ፡፡
\v 14 በዳዊት ከተማ ለእርሱ ለራሱ በቆፈረው በራሱ መቃብር ቀበሩት፡፡ በተካኑ ቀማሚዎች በተሰናዳ ልዩ ልዩ የቅመም ዓይነቶች በጣፋጭ መዓዛ በተሞላ ቃሬዛ ላይ አኖሩት፡፡ ለክብሩም እጅግም ታላቅ የሆነ እሳት ለኮሱለት፡፡
\s5
\c 17
\p
\v 1 ልጁ ኢዮሳፍጥ በእርሱ ቦታ ነገሠ፤ በእስራኤልም ላይ ራሱን አጠነከረ፡፡
\v 2 በተመሸጉትም በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ወታደሮችን አስቀመጠ፤ በይሁዳም ምድር እና አባቱ አሳ በያዛቸው የኤፍሬም ከተሞች ውስጥ የጦር ሠፈር አደራጀ፡፡
\s5
\v 3 በአባቱ በዳዊት በፊተኛይቱ መንገድ ስለሄደና በአሊምንም ስላልፈለገ እግዚአብሔር ከኢዮሣፍጥ ጋር ነበረ፡፡
\v 4 በዚያ ፈንታ በአባቱ አምላክ ላይ ተደገፈ፤ እንደ እስራኤል ባህርይ ሳይሆን በአምላኩ ትዕዛዛት መሠረት ሄደ፡፡
\s5
\v 5 በመሆኑም እግዚአብሔር መንግሥቱን በእጁ አጸናለት፤ ይሁዳ ሁሉ ለኢዮሣፍጥ ግብር ያመጡለት ነበር፡፡ የተትረፈረፈ ባለጠግነትና ክብርም ነበረው፡፡
\v 6 ልቡም በእግዚአብሔር መንገድ የጸና ነበረ፡፡ መስገጃዎቹንና የማምለኪያ ዐፀዶቹንም ከይሁዳ አስወገደ፡፡
\s5
\v 7 በነገሠም በሦስተኛው ዓመት ያስተምሩ ዘንድ ባለሥልጣናቱን ቤንኃይልን፥ አብድያስን፥ ዘካርያስን፥ ናትናኤልንና ሚኪያስን ወደ ይሁዳ ከተሞች ላካቸው፡፡
\v 8 ከእነርሱም ጋር ሌዋውያኑ ሸማያ፥ነታንያ፥ ዝባድያ፥ አሣኤል፥ ሰሚራሞት፥ዮናትን፥ አዶንያስ፥ ጦብያ እና ጠባዶንያ ነበሩ፡፡ ከእነርሱም ጋር ካህናቱ ኤሊሳማና ኢዮራም ነበሩ፡፡
\v 9 እነርሱም የእግዚአብሔር የሕግ መጽሐፍ ከእነርሱ ጋር ስለነበር በይሁዳ አስተማሩ፡፡በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ተዘዋውረው በሕዝቡ መካከል አስተማሩ፡፡
\s5
\v 10 በይሁዳ ዙሪያ በነበሩት አገራት ነገሥታት ላይ የእግዚአብሔር ድንጋጤ ስለወደቀባቸው ከኢዮሣፍጥ ጋር ምንም ጦርነት አላደረጉም፡፡
\v 11 የተወሰኑት ፍልስጤማውያን ለኢዮሳፍጥ ስጦታዎችና ብር እንደ ግብር ያመጡለት ነበር፡፡ አረቦችም ሰባት ሺህ ሰባት መቶ የአውራ በጎችና ሰባት ሺህ ሰባት መቶ የፍየሎች መንጋዎችን አመጡለት፡፡
\s5
\v 12 ኢዮሣፍጥም እጅግ ብርቱ ሆነ፤ በይሁዳም ትልልቅ ምሽጎችንና የመጋዘን ከተሞችን ሠራ፡፡
\v 13 በይሁዳም ከተሞች በርካታ አቅርቦት እና በኢየሩሳሌምም ጠንካራና ደፋር ሰዎች - ወታደሮች ነበሩት፡፡
\s5
\v 14 በአባቶቻቸው ቤቶች ስም ቅደም ተከተል ዝርዝራቸው ይህ ነው፤ ከይሁዳ የሺዎች አዣዦች፥ አዣዡ ዓድና ከእርሱም ጋር ሦስት መቶ ሺህ ተዋጊ ሰዎች፤
\v 15 ከእርሱም ቀጥሎ አለቃው ይሆሐናን፥ ከእርሱም ጋር ሁለት መቶ ሰማንያ ሺህ ሰዎች ነበሩ፤
\v 16 ከእርሱም ቀጥሎ ራሱን በፈቃዱ እግዚአብሔርን ለማገልገል ያቀረበ የዝክሪ ልጅ ዓማስያ ከእርሱም ጋር ሁለት መቶ ሺህ ተዋጊ ሰዎች ነበሩ፤
\s5
\v 17 ከቢኒያም ኃይለኛ ደፋር ሰው የነበረው ኤሊዳሄ ከእርሱም ጋር ቀስትና ጋሻ የሚይዙ ሁለት መቶ ሺህ ተዋጊ ሰዎች ነበሩ፤
\v 18 ከእርሱም ቀጥሎ ዮዛባት ከእርሱም ጋር ለጦርነት የተዘጋጁ መቶ ሰማንያ ሺህ ሰዎች ነበሩ፤
\v 19 ንጉሡ በተመሸጉት የይሁዳ ከተሞች ሁሉ ካስቀመጣቸው በተጨማሪ እነዚህ ንጉሡን የሚያገለግሉ ነበሩ፡፡
\s5
\c 18
\p
\v 1 ኢዮሣፍጥ ታላቅ ባለጠግነትና ክብር ነበረው፡፡ ከቤተሰቦቹ አንዱ ሴት ልጁን እንዲያገባ በማድረግ ከአክዓብ ጋር ራሱን አዛመደ፡፡
\v 2 ከተወሰኑ ዓመታት በኋላም ወደ አክዓብ ወደ ሰማርያ ወረደ፡፡ አክዓብም ለእርሱና ከእርሱ ጋር ለነበሩት ሕዝብ በርካታ በጎችንና በሬዎችን አረደላቸው፡፡ ከእርሱም ጋር ሬማት ዘገለአድን ለማጥቃት ይሄድ ዘንድም አክዓብ አሳመነው፡፡
\v 3 የእስራኤል ንጉሥ አክዓብ የይሁዳን ንጉሥ ኢዮሣፍጥን ፦ "ከእኔ ጋር ወደ ሬማት ዘገለአድ ትሄዳለህን?" አለው፡፡ ኢዮሣፍጥም ፦"እኔ እንደ አንተ ነኝ፤ ሕዝቤም እንደ ሕዝብህ ናቸው፤ በጦርነቱ ውስጥ ካንተ ጋር አብረን እንሆናለን" ብሎ መለሰለት፡፡
\s5
\v 4 ኢዮሣፍጥም የእስራኤልን ንጉሥ ፦ "እባክህን ለመልስህ በመጀመሪያ የእግዚአብሔርን ቃል ጠይቅ" አለው፡፡
\v 5 ከዚያም የእስራኤል ንጉሥ ነቢያቱን አራት መቶ ሰዎች በአንድነት ሰብስቦ፦ "ወደ ሬማት ዘገለአድ ለጦርነት መሄድ ይገባናል ወይስ መሄድ አይገባኝም?" አላቸው፡፡ እነርሱም ፦" እግዚአብሔር ለንጉሡ ድል ይሰጠዋልና አጥቃት!" አሉት፡፡
\s5
\v 6 ኢዮሣፍጥ ግን፦ "ምክር የምንጠይቀው አሁንም ሌላ የእግዚአብሔር ነቢይ የሆነ ሰው በእዚህ የለምን?" አለ፡፡
\v 7 የእስራኤልም ንጉሥ ኢዮሣፍጥን ፦" የእግዚአብሔርን ምክር የምንጠይቅበት አሁንም አንድ ሰው የይምላ ልጅ ሚክያስ አለ፤ ነገር ግን ችግር ብቻ እንጂ ስለእኔ ምንም ነገር መልካም ትንቢት ከቶም ተናግሮልኝ ስለማያውቅ እጠላዋለሁ" አለው፡፡ኢዮሣፍጥ ግን ፦ "ንጉሥ እንደዚያ አይበል" አለ፡፡
\v 8 ከዚያም የእስራኤል ንጉሥ አንድ ሹም ጠርቶ ፦"የይምላን ልጅ ሚክያስን በፍጥነት አምጣው" ሲል አዘዘው፡፡
\s5
\v 9 የእስራኤል ንጉሥ አክዓብና የአስራኤል ንጉሥ ኢዮሳፍጥ መጎናጸፊያቸውን እንደለበሱ እያንዳንዳቸው በዙፋን ላይ በሰማርያ በር መግቢያ በግልጽ ሥፍራ ላይ ተቀምጠው ነቢያቱም ሁሉ በፊታቸው ትንቢት እየተናገሩ ነበር፡፡
\v 10 የክንዓና ልጅ ሴዴቅያስም ለራሱ የብረት ቀንዶች ሠርቶ፦ "እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ 'በእነዚህ ቀንዶች አርመናውያን እስኪያልቁ ድረስ ትወጋቸዋለህ'" አለ፡፡
\v 11 ነቢያቱም ሁሉ፦" እግዚአብሔር በንጉሡ እጅ አሳልፎ ስለሚሰጣት ሬማት ዘገለዓድን አጥቃና አሸንፍ" እያሉ ተመሳሳይ ትንቢት ይናገሩ ነበር፡፡
\s5
\v 12 ሚክያስን ሊጠራ የሄደው መልዕክተኛ ፦" እነሆ የነቢያቱ ቃላት በአንድ አፍ ለንጉሡ መልካም ነገሮች ያውጃሉ፡፡ እባክህን ያንተም ቃል ከእነርሱ የአንዱን ቃል ዓይነት ይሁንና መልካም ነገሮች ተናገር" ሲል ተናገረው፡፡
\v 13 ሚክያስም፦"ሕያው እግዚአብሔርን የምናገረው አምላኬ እርሱ የሚለውን ነው" ብሎ መለሰ፡፡
\v 14 ወደ ንጉሡም በመጣ ጊዜ ንጉሡ፦" ሚክያስ ሆይ ወደ ሬማት ዘገለዓድ ለጦርነት መሄድ ይገባናል ወይስ መቅረት?"አለው፡፡ ሚክያስም፦" አጥቃና አሸንፍ! ታላቅ ድል ይሆንልሃልና!" ብሎ መለሰለት፡፡
\s5
\v 15 ከዚያም ንጉሡ ፦" በእግዚአብሔር ስም ከእውነቱ በቀር ሌላ ምንም ነገር እንዳትነግረኝ ስንት ጊዜ እንድትምል ላደርግህ ይገባኛል?" አለው፡፡
\v 16 ሚክያስም፦" እስራኤል ሁሉ እረኛ እንደሌላቸው በጎች በተራሮች ላይ ተበትነው አየኋቸው፤ እግዚአብሔርም፦ 'እነዚህ እረኛ የላቸውም፡፡ እያንዳንዱ ሰው በሰላም ወደ ቤቱ ይመለስ' አለ" ብሎ ተናገረ፡፡
\s5
\v 17 በመሆኑም የእስራኤል ንጉሥ ለኢዮሳፍጥ ፦" እኔን በተመለከተ ጥፋት ብቻ እንጂ መልካም ትንቢት እንደማይናገርልኝ አልነገርኩምን?" አለው፡፡
\v 18 ከዚያም ሚክያስ፦" እንግዲህ ሁላችሁም የእግዚአብሔርን ቃል መስማት ይገባችኋል፤ እግዚአብሔር በዙፋኑ ተቀምጦ የሰማይም ሰራዊት ሁሉ በቀኙና በግራው ቆመው እንደነበር አየሁ፡፡
\s5
\v 19 እግዚአብሔርም ፦" የእስራኤል ንጉሥ አክዓብ ወደ ሬማት ዘገለዓድ እንዲወጣና እንዲወድቅ የሚያታልለው ማነው?" አለ፡፡ አንዱ በእዚህ መንገድ ብሎ ሲመልስ ሌላውም በዚያ መንገድ ብሎ መለሰ፡፡
\s5
\v 20 ከዚያም አንድ መንፈስ መጥቶ በእግዚአብሔር ፊት ቆሞ፦" እኔ አታልለዋለሁ" አለ፡፡ እግዚአብሔርም ፦"እንዴት?" አለው፡፡
\v 21 መንፈሱም፡-" ወጥቼ በነቢያቱ ሁሉ አፍ ሐሰተኛ መንፈስ እሆናለሁ" አለ፡፡ እግዚአብሔርም፦" ታታልለዋለህ፤ ይሳካልሃልም፤ አሁንም ሂድና እንደዚሁ አድርግ" ብሎ መለሰ፡፡
\s5
\v 22 አሁንም እነሆ እግዚአብሔር በእነዚህ ነቢያትህ አፍ ሐሰተኛ መንፈስ አስቀምጧል፤ እግዚአብሔርም ጥፋት እንዲመጣብህ ተናግሯል፡፡
\s5
\v 23 የክንዓና ልጅ ሴዴቅያስም ቀረብ ብሎ ሚክያስን በጥፊ መታውና ፦"የእግዚአብሔር መንፈስ ለአንተ ሊናገር በየትኛው መንገድ ከእኔ ሄደ?" አለው፡፡
\v 24 ሚክያስም፦" እነሆ በዚያ ቀን ልትሸሸግ ወደ አንድ የውስጥ ክፍል ስትሸሽ ታውቀዋለህ" አለው፡፡
\s5
\v 25 የእስራኤል ንጉሥም ለአገልጋዮቹ ፦" እናንተ ሰዎች ሚክያስን ያዙና ወደ ከተማይቱ አስተዳዳሪ ወደ አሞንና ወደ ልጄ ወደ ኢዮአስ ውሰዱት፤"
\v 26 ንጉሡ፦' በደህና እስከምመለስ ድረስ ይህንን ሰው እስር ቤት ውስጥ አኑሩት፤ ጥቂት ምግብ ብቻ እና ጥቂት ውሃ ብቻ መግቡት' ይላል በሉት" አላቸው፡፡
\v 27 ሚክያስም፦" አንተ በደህና ከተመለስህ በእኔ የተናገረው እግዚአብሔር አይደለም" አለ፡፡ ጨምሮም፦"እናንተ ሕዝብ ሁሉ ይህንን ስሙ" አለ፡፡
\s5
\v 28 በመሆኑም የእስራኤል ንጉሥ አክዓብና የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሳፍጥ ሬማት ዘገለዓድን ሊዋጉ ወጡ፡፡
\v 29 የእስራኤል ንጉሥ ኢዮሳፍጥን፡-"እኔ እንዳልታወቅ አለባበሴን ለውጬ ወደ ጦርነቱ እገባለሁ፤ አንተ ግን ንጉሣዊ መጎናፊያህን ልበስ" አለው፡፡ በመሆኑም የእስራኤል ንጉሥ በአለባበሱ እንዳይታወቅ ራሱን ለውጦ ወደ ጦርነቱ ሄዱ፡፡
\v 30 የአራምም ንጉሥ የሰረገሎቹን አዛዦች፦ "ከፍተኛ ወይም ዝቅተኛ ወታደሮችን እንዳታጠቁ፤ ይልቁንም የእስራኤል ንጉሥን ብቻ አጥቁ" በማለት አዝዟቸው ነበር፡፡
\s5
\v 31 የሰረገሎቹ አለቆች ኢዮሳፍጥን ባዩ ጊዜ፦"የእስራኤል ንጉሥ ያ ነው ፤" አሉ፡፡ ሊያጠቁትም ወደ እርሱ ዞሩበት፤ ነገር ግን ኢዮሳፍጥ ሲጮህ እግዚአብሔር ረዳው፡፡ እግዚአብሔርም ከእርሱ ዞር አደረጋቸው፡፡
\v 32 የሰረገሎቹም አለቆች የእስራኤል ንጉሥ እንዳልነበረ ባዩ ጊዜ እርሱን ከመከታተል ተመለሱ፡፡
\s5
\v 33 አንድ ሰው ግን በዘፈቀደ ቀስቱን ሲስበው የእስራኤል ንጉሥን በጥሩር መገጣጠሚያዎቹ መካከል ወጋው፡፡ ያን ጊዜ አክዓብ የሰረገላውን ነጂ፦" ክፉኛ ተወግቻለሁና አቅጣጫህን ቀይርና ከጦርነቱ ውስጥ አውጣኝ፡፡
\v 34 በዚያን ጊዜ ጦርነቱ እጅግ የከፋ ሆነ፤ የእስራኤልም ንጉሥ አርመናውያንን እየተመለከተ እስኪመሽ ድረስ ሰረገላውን እንደተደገፈ ነበር፡፡ ፀሐይ በምታዘቀዝቅበት ጊዜ አካባቢ ሞተ፡፡
\s5
\c 19
\p
\v 1 የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሳፍጥም ወደ ቤቱ ወደ ኢየሩሳሌም በደህና ተመለሰ፡፡
\v 2 ያኔ የባለ ራዕዩ የአናኒ ልጅ ኢዩ ሊገናኘው ወጣ፤ ንጉሡንም ኢዮሳፍጥን፦"ክፉውን ልትረዳ ይገባሃልን? እግዚአብሔርን የሚጠሉትን ልትወድ ይገባሃልን? ለዚህ ድርጊትህ ከእግዚአብሔር ዘንድ ቁጣ ሆኖብሃል፡፡
\v 3 ነገር ግን የማምለኪያ አፀዶቹን ከምድሪቱ ላይ አስወግደሃልና እግዚአብሔርን ለመፈለግ ቆርጠህ ልብህን አዘጋጅተሃልና በአንተ ዘንድ መልካምነት ተገኝቶብሃል" አለው፡፡
\s5
\v 4 ኢዮሳፍጥ በኢየሩሳሌም ተቀመጠ፤ ከቤርሳቤህ እስከ ተራራማው የኤፍሬም አገር ድረስ እንደገና በሕዝቡ መካከል ወጥቶ ወደ አባቶቻቸው አምላክ መለሳቸው፡፡
\v 5 በምድሪቱ ላይ በተመሸጉት በይሁዳ ከተሞች ሁሉ በእያንዳንዱ ከተማ ውስጥ ፈራጆችን አስቀመጠ፡፡
\s5
\v 6 ፈራጆቹንም፦"የምትፈርዱት ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው ስላልሆነ ምን ማድረግ እንደሚገባችሁ አጢኑ፤ በፍርድ ነገር እርሱ ከእናንተ ጋር ነው፤
\v 7 አሁንም የእግዚአብሔር ፍርሃት በእናንተ ላይ ይሁን፡፡ በአምላካችን በእግዚአብሔር ዘንድ ምንም በደል የለምና፤ ለሰው ፊት ማድላት ወይም መማለጃ መውሰድ የለምና በምትፈርዱበት ጊዜ ተጠንቀቁ" አላቸው፡፡
\s5
\v 8 በተጨማሪም ኢዮሳፍጥ በኢየሩሳሌም ከሌዋውያኑንና ከካህናቱ የተወሰኑትንና ከእስራኤል የአባቶች ቤቶች መሪዎች የተወሰኑትን የእግዚአብሔርን ፍርድ እንዲያስፈጽሙና ጠቦችን እንዲፈቱ ሾማቸው፡፡ እነርሱም በኢየሩሳሌም ተቀመጡ፡፡
\v 9 "እግዚአብሔርን በመፍራት፥ በታማኝነትና በፍጹም ልብ የምታደርጉት ይህ ነው፤
\s5
\v 10 በደም መፍሰስ ጉዳይ ቢሆን፥ በሕግና በትእዛዝ፥ በሥርዓት ወይም በድንጋጌ ጉዳዮች ቢሆን በከተሞቻቸው ከተቀመጡት ከወንድሞቻችሁ ምንም ኣይነት ጠብ ወደ እናንተ ቢመጣ እግዚአብሔርን እንዳይበድሉ፥ ቁጣ በእናንተና በወንድሞቻችሁ ላይ እንዳይወርድ ልታስጠነቅቋቸው ይገባል፡፡ እንደዚህ ብታደርጉ በኃጢአት በደለኛ አትሆኑም፡፡
\s5
\v 11 እነሆ ለእግዚአብሔር በሚሆኑት ነገሮች ሁሉ ላይ ሊቀ ካህናቱ አማርያ፥ በንጉሡ ጉዳዮች ሁሉ ላይ የተሾመው የይሁዳ ቤት መሪ የእስማኤል ልጅ ዝባድያ አለቆች ናቸው፡፡ ሌዋውያኑም ደግሞ የሚያገለግሏችሁ ባለሥልጣናት ይሆናሉ፡፡ በድፍረት አድርጉ፤ እግዚአብሔርም መልካም ከሆኑት ጋር ይሁን፡፡
\s5
\c 20
\p
\v 1 ከዚህ ጊዜ በኋላ የሞዓብና የአሞን ሕዝቦች ከእነርሱም ጋር ምዑናውያን ኢዮሳፍጥን ሊዋጉት መጡ፡፡
\v 2 አንዳንድ ሰዎች መጥተው፦"ከባሕሩ ማዶ ከሶሪያ ታላቅ ሠራዊት መጥቶብሃል፤ እነሆም ዓይንጋዲ በተባለች በሐሴሶን ታማር ናቸው" ብለው ነገሩት፡፡
\s5
\v 3 ኢዮሳፍጥም ፈራ፤ እግዚአብሔርንም ሊፈልግ ራሱን አቀና፤ በመላው ይሁዳ ፆምን አወጀ፡፡
\v 4 ይሁዳም እግዚአብሔርን ይፈልግ ዘንድ በአንድነት ተሰበሰበ፤ ከመላው የይሁዳ ከተሞች ሁሉ እግዚአብሔርን ይፈልጉ ዘንድ መጡ፡፡
\s5
\v 5 ኢዮሳፍጥም በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ጉባዔ በአዲሱ አደባባይ ፊት ቆመ፡፡
\v 6 "የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ሆይ አንተ በሰማይ ያለህ አምላክ አይደለህምን? በሕዝቦች ነገሥታት ሁሉ ላይ ገዢ አይደለህምን? ኃይልና ብርታት በእጅህ ናቸው፤ በመሆኑም ማንም ሊቋቋምህ የሚችል የለም፡፡
\v 7 አምላካችን ሆይ በዚህ ምድር ላይ የነበሩትን ነዋሪዎች ከሕዝብህ ከእስራኤል ፊት አሳድደህ ለዘላለም ለአብርሃም ዝርያዎች አልሰጠሃትምን?" አለ፡፡
\s5
\v 8 እነርሱም በውስጧ ኖሩባት፤
\v 9 "አደጋ/መቅሰፍት ቢመጣብን - ሰይፍ፥ ፍርድ፥ ወይም በሽታ፥ ወይም ረሃብ - (ስምህ በዚህ ቤት ስላለ) በዚህ ቤት ፊትና በፊትህ እንቆምና በመከራችን ወደ አንተ እንጮሃለን፤ አንተም ሰምተህ ታድነናለህ" በማለት ለስምህም ቅዱስ ሥፍራ በውስጥዋ ሠሩ፡፡
\s5
\v 10 አሁንም እነሆ እስራኤል ከግብጽ ምድር በሚወጡበት ጊዜ እንዲወሩዋቸው ያልፈቀድክላቸው ይልቁንም ዞር ብለው ያላጠፏቸው የአሞን፥ የሞዓብና የሴይር ተራራ ሕዝቦች እዚህ ናቸው፤
\v 11 እነሆ ለወረታችን እንዴት እንደሚመልሱልን ተመልከት፤ እንድንወርሰው ከሰጠኸን ከምድርህ ሊያስወጡን መጥተዋል፡፡
\s5
\v 12 አምላካችን ሆይ አትፈርድባቸውምን? ይህንን ሊያጠቃን የመጣብንን ታላቅ ሠራዊት እንቋቋም ዘንድ ምንም ኃይል የለንም፡፡ የምናደርገውንም አናውቅም፤ ነገር ግን ዓይኖቻችን በአንተ ላይ ናቸው" አለ፡፡
\v 13 ይሁዳ ሁሉ ከሕጻናቶቻቸው፥ ከሚስቶቻቸውና ከልጆቻቸው ጋር በእግዚአብሔር ፊት ቆመው ነበር፡፡
\s5
\v 14 በጉባዔው መካከል የእግዚአብሔር መንፈስ ከአሳፍ ልጆች አንዱ በነበረው በሌዋዊው በማታንያ ልጅ በይዒኤል ልጅ በበናያስ ልጅ በዘካርያስ ልጅ በየሕዚኤል ላይ መጣ፡፡
\v 15 የሕዚኤልም፦" ይሁዳ ሁሉ የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች እና ንጉሥ ኢዮሳፍጥ ስሙ፤ እግዚአብሔር የሚላችሁ ይህ ነው፦"ከዚህ ታላቅ ሠራዊት የተነሳ አትፍሩ፤ አትደንግጡም፤ ምክንያቱም ጦርነቱ የእግዚአብሔር እንጂ የእናንተ አይደለም፡፡
\s5
\v 16 ነገ በእነርሱ ላይ ለጦርነት ልትወጡ ይገባል፤ እነሆ በጺጽ መተላለፊያ መንገድ ይመጣሉ፡፡ በይሩኤል ምድረ በዳ ፊት ለፊት በሸለቆው መጨረሻ ታገኙዋቸዋላችሁ፡፡
\v 17 በዚህ ጦርነት እናንተ መዋጋት የሚያስፈልጋችሁ አይደላችሁም፡፡ ይሁዳና ኢየሩሳሌም ሆይ በቦታችሁ ቁሙ፤ ዝም ብላችሁ ቁሙ፤ እግዚአብሔር ለእናንተ የሚያደርገውን ማዳን ተመልከቱ፡፡ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ስለሆነ አትፍሩ፤ አትደንግጡም፤ ነገ ለጦርነት ውጡባቸው" አለ፡፡
\s5
\v 18 ኢዮሳፍጥም በምድር ላይ በፊቱ ተደፋ፤ ይሁዳ ሁሉና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች እግዚአብሔርን በማምለክ በፊቱ ወደቁ፡፡
\v 19 የቀዓትና የቆሬ ዝርያዎች ሌዋውያን የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን በታላቅ ድምጽ ለማወደስ ቆመው ነበር፡፡
\s5
\v 20 ጥዋት በማለዳ ተነስተው ወደ ቴቁሔ ምድረ በዳ ሄዱ፡፡ እየሄዱም እያለ ኢዮሳፍጥ ቆሞ፦" ይሁዳና እናንተ የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ስሙኝ! በአምላካችሁ በእግዚአብሔር እመኑ፤ ድጋፍ ታገኛላችሁ፡፡ በነቢያቱም እመኑ፤ ይቃናላችኋልም" አለ፡፡
\v 21 ከሕዝቡ ጋር ከተማከረ በኋላም ከሠራዊቱ ፊት ቀድመው እየሄዱ "የቃል ኪዳን ታማኝነቱ ለዘላለም የሚኖር ስለሆነ ለእግዚአብሔር ምሥጋናን ስጡ" በማለት ለእግዚአብሔር የሚዘምሩትንና ለቅዱስ ክብሩ ውዳሴ የሚሰጡትን ሾመ፡፡
\s5
\v 22 መዘመርና ማወደስ ሲጀምሩ ይሁዳን ሊዋጉ በመጡት በአሞን፥ በሞዓብና በሴይር ተራራ ሰዎች ላይ እግዚአብሔር ድብቅ ጦር አስነስቶ በድንገት እንዲያጠቋቸው አደረገ፡፡ እነርሱም ተሸነፉ፡፡
\v 23 የአሞንና የሞዓብ ሰዎች የሴይርን ተራራ ነዋሪዎች ሙሉ በሙሉ እስኪገድሉዋቸውና እስኪያጠፏቸው ድረስ ሊዋጉዋቸው ተነስተው ነበር፡፡ የሴይርን ተራራ ነዋሪዎች በጨረሷቸው ጊዜ ሁሉም እርስ በእርስ ለመጠፋፋት ተረዳዱ፡፡
\s5
\v 24 ይሁዳ ምድረ በዳውን ወደሚመለከቱበት ቦታ ሲመጡ ሠራዊቱን ተመለከቱ፡፡ እነሆ ሞተው በምድሩም ላይ ወድቀው ነበር፤ አንድም ያመለጠ ሰው አልነበረም፡፡
\s5
\v 25 ኢዮሳፍጥና ሕዝቡም ምርኮ ለመውሰድ በመጡ ጊዜ ሊሸከሙት ከሚችሉት በላይ የተትረፈረፈ ባለጸግነትና የከበሩ ጌጦች አገኙ፤ ለራሳቸውም በዘበዙ፡፡ እጅግ ብዙ ስለነበርም ምርኮውን ለመውሰድ ሦስት ቀናት ፈጀባቸው፡፡
\v 26 በአራተኛው ቀን በበረከት ሸለቆ ውስጥ ተሰበሰቡ፡፡ በዚያም እግዚአብሔርን አወደሱ፤ ስለዚህም የዚያ ሥፍራ ስም እስከዛሬ ድረስ "የበረከት ሸለቆ" ነው፡፡
\s5
\v 27 የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሰዎች ሁሉ እግዚአብሔር በጠላቶቻቸው ላይ ደስ አሰኝቷቸዋልና በደስታ እንደገና ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ ኢዮሳፍጥ እየመራቸው ተመለሱ፡፡
\v 28 በበገናና በመሰንቆ በመለከትም ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ እግዚአብሔር ቤት መጡ፡፡
\s5
\v 29 እግዚአብሔር የእስራኤልን ጠላቶች እንደተዋጋ በሰሙ ጊዜ በሕዝቦች ነገሥታት ሁሉ ላይ የእግዚአብሔር ፍርሃት ሆነ፡፡
\v 30 በመሆኑም አምላኩ በዙሪያው ሁሉ ሰላም ስለሰጠው የኢዮሳፍጥ መንግሥት ጸጥታ ሰፈነባት፡፡
\s5
\v 31 ኢዮሳፍጥ በይሁዳ ላይ ነገሠ፡፡ መንገሥ በጀመረ ጊዜ ሠላሳ አምስት ዓመቱ ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ለሃያ አምስት ዓመታት ነገሠ፡፡ የእናቱ የሺልሒ ሴት ልጅ ስም ዓዙባ ነበር፡፡
\v 32 በአባቱም በዓሳ መንገዶች ሄደ፤ ከእነርሱም ፈቀቅ አላለም፤ በእግዚአብሔር ፊት ቅን የነበረውን ነገር አደረገ፡፡
\v 33 ነገር ግን የኮረብታው መስገጃዎች ገና አልተወገዱም ነበር፡፡ ሕዝቡም ልባቸውን ወደ አባቶቻቸው አምላክ ገና አላቀኑም ነበር፡፡
\s5
\v 34 ኢዮሳፍጥን በተመለከተ ሌሎቹ ጉዳዮች የመጀመሪያውና የመጨረሻው በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ እንደተመዘገበው በአናኒ ልጅ በኢዩ ታሪክ ውስጥ ተጽፈዋል፡፡
\s5
\v 35 ከዚህ በኋላ የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሳፍጥ እጅግ ክፋት ከፈጸመው ከእስራኤል ንጉሥ ከአካዝያስ ጋር ራሱን አዛመደ፡፡
\v 36 በባህር ላይ የሚሄዱ መርከቦችን ለመገንባት ከእርሱ ጋር ተባበረ፡፡ መርከቦቹንም በዔጽዮንጋብር ገነቡ፡፡
\v 37 የመሪሳም ሰው የዶዳያ ልጅ አልዓዛር ፦" ከአካዝያስ ጋር ተባብረሃልና እግዚአብሔር ሥራዎችህን አፍርሷል፤" ብሎ በኢዮሳፍጥ ላይ ትንቢት ተናገረበት፡፡ መርከቦቹም ተሰባበሩ፤ ጉዞ ለማድረግም አልቻሉም፡፡
\s5
\c 21
\p
\v 1 ኢዮሳፍጥም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊትም ከተማ ከእነርሱ ጋር ተቀበረ፤ ልጁም ኢዮራም በእርሱ ቦታ ነገሠ፡፡
\v 2 ኢዮራም የኢዮሳፍጥ ልጆች የሆኑ ወንድሞች ዓዛርያስ፥ ይሒኤል፥ ዘካርያስ፥ ዔዛርያስ፥ ሚካኤልና ሰፋጥያስ ነበሩት፡፡ እነዚህ ሁሉ የይሁዳ ንጉሥ የኢዮሳፍጥ ልጆች ነበሩ፡፡
\v 3 አባታቸው ብዙ የብር፥ የወርቅ እና የሌሎች የከበሩ ነገሮች እንዲሁም በይሁዳም የተመሸጉ ከተሞችን ሰጣቸው፤ ዙፋኑን ግን የመጀመሪያ ልጁ ስለነበር ለኢዮራም ሰጠው፡፡
\s5
\v 4 ኢዮራም በአባቱ መንግሥት ላይ በወጣና ራሱን እንደ ንጉሥ አጽንቶ በመሠረተ ጊዜ ወንድሞቹን ሁሉና የተለያዩ የእስራኤል ሌሎች መሪዎችን ጭምር በሰይፍ ገደላቸው፡፡
\v 5 ኢዮራምም መንገሥ በጀመረ ጊዜ ሠላሳ ሁለት ዓመቱ ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ስምንት ዓመት ነገሠ፡፡
\s5
\v 6 የአክዓብን ሴት ልጅ አግብቶ ስለነበር የአክዓብ ቤት ያደርግ እንደነበር በእስራኤል ነገሥታት መንገድ ሄደ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ የነበረውን ነገር አደረገ፡፡
\v 7 ነገር ግን እግዚአብሔር ከዳዊት ጋር ካደረገው ቃል ኪዳን የተነሳ የዳዊትን ቤት ለማጥፋት አልፈለገም፤ ለአርሱና ለዝርያዎቹ ሁልጊዜ ሕይወት እንደሚሰጣቸው ቃል ገብቶላቸው ነበር፡፡
\s5
\v 8 በኢዮራም ዘመን ኤዶምያስ በይሁዳ ኃይል ላይ ዐመፀ፤ በራሳቸውም ላይ ንጉሥ ሾሙ፡፡
\v 9 በዚያን ጊዜ ኢዮራም ከአዛዦቹና ከሠረገላዎቹ ሁሉ ጋር ተሻገረ፤ በሌሊትም ተነስቶ እርሱንና የሠረገላዎቹን አዛዦች ከብበው የነበሩትን ኤዶማውያንን መታ፡፡
\v 10 በመሆኑም እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ ኤዶምያስ በይሁዳ ኃይል ላይ እንዳመፀ ነው፡፡ ኢዮራም የአባቶቹን አምላክ እግዚአብሔርን ስለተወ የልብና ከተማ ጭምር በዚያው ጊዜ በኃይሉ ላይ ዐመጸ፡፡
\s5
\v 11 በተጨማሪም ኢዮራም በይሁዳ ተራራዎች ላይ መስገጃዎችን ሠርቶ ነበር፤ የኢየሩሳሌምን ነዋሪዎችም እንደ አመንዝራ ሌሎች አማልክትን እንዲከተሉ አደረጋቸው፡፡ በዚህ መንገድ ይሁዳን ከትክክለኛው መስመር አስወጣቸው፡፡
\s5
\v 12 ከነቢዩም ከኤልያስ አንድ ደብዳቤ ወደ ኢዮራም መጣለት፤ የአባትህ የዳዊት አምላክ እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፦" በአባትህ በኢዮሳፍጥ መንገድ ወይም በይሁዳ ንጉሥ በአሳ መንገድ ስላልሄድህ
\v 13 ነገር ግን በእስራኤል ነገሥታት መንገድ ስለሄድህ ይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ነዋሪዎች የአክዓብ ቤት እንዳደረገ እንደ አመንዝራ ሌሎች አማልክትን እንዲከተሉ ስላደረግሃቸው፤ በአባትህ ቤተሰብም ውስጥ ከአንተ የሚሻሉ የነበሩትን ወንድሞችህን በሰይፍ ስለገደልካቸው
\v 14 እነሆ እግዚአብሔር ሕዝብህን፥ ልጆችህን፥ ሚስቶችህን እና ሀብትህንም ሁሉ በታላቅ መቅሰፍት ይመታል፡፡
\v 15 አንተም ራስህ ከበሽታው የተነሳ ከቀን ወደ ቀን አንጀትህ እስኪወጣ ድረስ በአንጀትህ ሕመም እጅግ ትታመማለህ፡፡"
\s5
\v 16 እግዚአብሔርም የፍልስጤማውያንን እና በኢትዮጵያውያን አጠገብ ይኖሩ የነበሩትን የዓረባውያንን መንፈስ በኢዮራም ላይ አስነሳበት፡፡
\v 17 እነርሱም ይሁዳን አጠቁ፤ ወረሩአትም፤ በንጉሡ ቤት ውስጥ የተገኘውን ሀብት ሁሉ ወሰዱ፤ ወንዶች ልጆቹንና ሚስቶቹንም ወሰዱ፡፡ ከታናሹ ልጁ ከአካዝያስ በስተቀር ምንም ልጅ አልቀረለትም፡፡
\s5
\v 18 ከዚህ ሁሉ በኋላ እግዚአብሔር ሊድን በማይችል በሽታ አንጀቱን መታው፤
\v 19 በተገቢው ጊዜ በሁለቱ ዓመት መጨረሻ ከሕመሙ የተነሳ አንጀቱ ወጣ፤ በብርቱ በሽታም ሞተ፡፡ ሕዝቡም ለእርሱ አባቶች እንዳደረገው ለክብሩ ምንም ችቦ አላበራም፡፡
\v 20 በሠላሳ ሁለት ዓመቱ ላይ መንገሥ ጀምሮ ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ስምንት ዓመት ነገሠ፤ ማንም ሳያዝንለት ሞተ፡፡ በነገሥታቱ መቃብር ሳይሆን በዳዊት ከተማ ቀበሩት፡፡
\s5
\c 22
\p
\v 1 የኢየሩሳሌም ነዋሪዎችም የኢዮራምን ታናሽ ልጅ አካዝያስን በእርሱ ቦታ አነገሡት፤ ምክንያቱም ከአረቢያኖቹ ጋር ወደ ካምፑ የመጡባቸው የሽፍቶች ቡድን የእርሱን ታላላቆች ሁሉ ገድለዋቸው ስለነበር ነው፡፡ በመሆኑም የይሁዳ ንጉሥ የኢዮራም ልጅ አካዝያስ ነገሠ፡፡
\v 2 አካዝያስ መንገሥ በጀመረ ጊዜ አርባ ሁለት ዓመቱ ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሁለት ዓመት ነገሠ፡፡ የእናቱ ስም ጎቶልያ ነበረ፤ እሷም የዖምሪ ልጅ ነበረች፡፡
\v 3 እናቱ ክፉ ነገሮችን ለማድረግ መካሪው ስለነበረች እርሱም በአክዓብ ቤት መንገድ ሄደ፡፡
\s5
\v 4 ከአባቱ ሞት በኋላ ለገዛ ራሱ ጉዳት እስኪሆን የአክዓብ ቤት መካሪዎቹ ስለነበሩ የአክዓብ ቤት እንዳደረገ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አደረገ፡፡
\v 5 ምክራቸውንም ተከተለ፤ የአራምን ንጉሥ አዛሄልን በሬማት ዘገለዓድ ሊዋጋ ከእስራኤል ንጉሥ ከአክዓብ ልጅ ከኢዮራም ጋር ሄደ፡፡ አርመናውያንም ኢዮራምን አቆሰሉት፡፡
\s5
\v 6 ኢዮራምም የአራምን ንጉሥ አዛሄልን በራማ በተዋጋ ጊዜ ካቆሰሉት ቁስል ይፈወስ ዘንድ ወደ ኢይዝራኤል ተመለሰ፡፡ ኢዮራም ቆስሎ ስለነበር የይሁዳ ንጉሥ የኢዮራም ልጅ አካዝያስ የአክዓብን ልጅ ኢዮራምን ሊያየው ወደ ኢይዝራኤል ወረደ፡፡
\s5
\v 7 አካዝያስ ኢዮራምን በመጎብኘቱ አማካይነት እንዲጠፋ እግዚአብሔር ፈቅዶ ነበር፡፡ በመጣ ጊዜ የአክዓብን ቤት እንዲያጠፋ እግዚአብሔር የመረጠውን የናሚሴን ልጅ ኢዩን ለማጥቃት ከኢዮራም ጋር ሄደ፡፡
\v 8 ኢዩም የእግዚአብሔርን ፍርድ በአክዓብ ቤት ላይ እየፈጸመ በነበረበት ጊዜ የይሁዳን መሪዎችና አካዝያስን የሚያገለግሉትን የአካዝያስን ወንድሞች ልጆች አገኛቸው፡፡ ኢዩም ገደላቸው፡፡
\s5
\v 9 ኢዩ አካዝያስን ፈለገው፤ በሰማርያም ተሸሽጎ አገኙት፤ ወደ ኢዩም አመጡት፤ እርሱም ገደለው፡፡ ከዚያም "እግዚአብሔርን በፍጹም ልቡ የፈለገው የኢዮሳፍጥ ልጅ ነው" ብለው ቀበሩት፡፡ በመሆኑም የአካዝያስ ቤት መንግሥቱን ለመምራት ምንም የቀረ ኃይል አልነበረውም፡፡
\s5
\v 10 የአካዝያስ እናት ጎቶልያ ልጇ መሞቱን ባየች ጊዜ ተነስታ በይሁዳ ቤት ውስጥ የነገሥታቱን ዝርያ ልጆች ሁሉ ገደለች፡፡
\v 11 ነገር ግን የንጉሡ ልጅ ዮሳቤት የአካዝያስ ልጅ ኢዮአስን ከተገደሉት ከንጉሡ ልጆች መካከል ሰርቃ ወሰደችው፤ እርሱንና ሞግዚቱን በመኝታ ክፍል ውስጥ አስቀመጠቻቸው፡፡ ስለዚህ የንጉሡ የኢዮራም ልጅ የካህኑ የዮዳሄ ሚስት ዮሳቤት (የአካዝያስ እኅት ስለነበረች) ጎቶልያ እንዳትገድለው ከጎቶልያ ሸሸገችው፡፡
\v 12 ጎቶልያ በምድሪቱ ላይ ስትገዛ ሳለ እርሱ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ለስድስት ዓመታት ተሸሽጎ ከእነርሱ ጋር ነበረ፡፡
\s5
\c 23
\p
\v 1 በሰባተኛውም ዓመት ዮዳሄ ውጤት ያለው ነገር አደረገ፡፡ የመቶ አለቆቹን የይሮሐምን ልጅ ዓዛርያስን፥ የይሆሐናንን ልጅ ይስማኤልን፥ የዖቤድን ልጅ ዓዛሪያስን፥ የዓዳያንም ልጅ መዕሴያን፥ የዝክሪንም ልጅ ኤሊሳፋጥን ወስዶ ከእርሱ ጋር ቃል ኪዳን እንዲገቡ አደረገ፡፡
\v 2 በይሁዳ ሁሉ ዞረውም ከይሁዳ ከተሞች ሁሉ ሌዋውያንንና የእስራኤልን ቤቶች አባቶች መሪዎች ሰብስበው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፡፡
\v 3 ጉባኤውም ሁሉ ከንጉሡ ጋር በእግዚአብሔር ቤት ቃል ኪዳን አደረጉ፡፡ ዮዳሄም፦ "እነሆ እግዚአብሔር ስለ ዳዊት ዝርያዎች እንደተናገረው የንጉሡ ልጅ ይነግሣል" አላቸው፡፡
\s5
\v 4 "ማድረግ የሚገባችሁ ይህ ነው፤ በሰንበት ቀን ለማገልገል ከምትመጡት ከእናንተ ከካህናትና ከሌዋውያን አንድ ሦስተኛው በበሮቹ ላይ ጠባቂዎች ትሆናላችሁ፡፡
\v 5 አንድ ሦስተኛችሁ ደግሞ በንጉሡ ቤት ትሆናላችሁ፤ ሌላው አንድ ሦስተኛ በመሠረቱ በር ላይ ይሁኑ፤ ሕዝቡም ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ ላይ ይሁኑ፡፡
\s5
\v 6 ከካህናቱና ከሚያገለግሉት ሌዋውያን በስተቀር ማንም ወደ እግዚአብሔር ቤት እንዲገባ አትፍቀዱ፤ እነርሱ ለዛሬው ሥራቸው ተለይተው ተመድበዋልና መግባት ይገባቸዋል፡፡ ሁሉም የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት መጠበቅ ይገባቸዋል፡፡
\v 7 ሁሉም ሰው የጦር መሣሪያውን በእጁ ይዞ ሌዋውያኑ ንጉሡን በሁሉም በኩል ሊከቡት ይገባቸዋል፡፡ ማንም ወደ ቤቱ ውስጥ ቢገባ ይገደል፡፡ ንጉሡም በሚገባበትና በሚወጣበት ጊዜ ሁሉ ከእርሱ ጋር ሁኑ፡፡
\s5
\v 8 በመሆኑም ሌዋውያኑና ይሁዳ ሁሉ በሁሉም መንገድ ካህኑ ዮዳሄ ባዘዘው መሠረት አገለገሉ፡፡ እያንዳንዱ ሰው የየራሱን በሰንበት ለማገልገል የሚገቡትንና በሰንበትም ከአገልግሎት ይወጡ የነበሩትን ሰዎች ወሰደ፤ ምክንያቱም ካህኑ ዮዳሄ የትኞቹንም የሥራ ክፍሎች አላሰናበተም ነበር፡፡
\v 9 ከዚያም ካህኑ ዮዳሄ በእግዚአብሔር ቤት የነበሩትን የንጉሡን የዳዊትን ጦሮች፥ ትንንሽና ትልልቅ ጋሻዎች ለአለቆቹ አመጣላቸው፡፡
\s5
\v 10 ዮዳሄ እያንዳንዱ ሰው የጦር መሣሪያውን እንደያዘ ከቤተ መቅደሱ ቀኝ በኩል እስከ ቤተ መቅደሱ ግራ በኩል በመሠዊያውና በቤተ መቅደሱ አጠገብ ንጉሡን እንዲከቡ ሁሉንም ወታደሮች በቦታቸው አቆማቸው፡፡
\v 11 ከዚያም የንጉሡን ልጅ አውጥተው፥ ዘውዱን በላዩ ላይ ደፍተው የቃል ኪዳኑ ሕግጋት የተጸፈበትን ጥቅልል ሰጡት፡፡ ከዚያም አነገሡት፤ ዮዳሄና ልጆቹም ቀቡት፡፡ ከዚያም ፦" ንጉሡ ረጅም ዘመን ይኑር!" ብለው ጮኹ፡፡
\s5
\v 12 ጎቶልያ የህዝቡን መሯሯጥና ንጉሡን ማወደስ ጫጫታ ስትሰማ ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ሕዝቡ መጣች፡፡
\v 13 እነሆም ንጉሡ መግቢያው ላይ በራሱ ምሰሶ አጠገብ ቆሞ እንደነበርና አዛዦቹና መለከት ነፊዎቹ ከንጉሡ አጠገብ ቆመው እንደነበር አየች፡፡ የአገሩ ህዝብ ሁሉ ደስ እያላቸውና መለከት እየነፉ ነበር፡፡ ዘማሪዎቹም የሙዚቃ መሣሪያዎች እየተጫወቱ የውዳሴ መዝሙሮችን ይዘምሩ ነበር፡፡ ጎቶልያ ልብሷን ቀድዳ፦" አገር ከመክዳት የሚቆጠር ዓመፅ ነው! ዓመፅ ነው!" ብላ ጮኸች፡፡
\s5
\v 14 ካህኑ ዮዳሄ በሠራዊቱ ውስጥ መሪዎች የነበሩትን የመቶ አለቆች አውጥቶ፦ "ወደ ወታደሮቹ መካከል አውጡአት፤ የሚከተላትም በሰይፍ ይገደል" አላቸው፡፡ ካህኑ ፦"በእግዚአብሔር ቤት አትግደሉአት" ብሎ ነበር፡፡
\v 15 በመሆኑም ገለል ብለው ሲያሳልፏት ወደ ንጉሡ ቤት ፈረሱ በር በሚወስደው መንገድ ሄደች፤ እዚያም ገደሏት፡፡
\s5
\v 16 ከዚያም ዮዳሄ የእግዚአብሔር ሕዝብ ይሆኑ ዘንድ በእርሱ፥ በሕዝቡና በንጉሡ መካከል ቃል ኪዳን አደረገ፡፡
\v 17 ሕዝቡም ሁሉ ወደ በኣል ቤት ሄደው አፈረሱት፡፡ የበኣል መሠዊያዎቹንና ምስሎቹን አደቀቁ፤ የበኣል ካህንን ማታንን በእነዚያ መሠዊያዎች ፊት ገደሉት፡፡
\s5
\v 18 ዮዳሄም በሙሴ ሕግ ተጽፎ እንደነበረው በእግዚአብሔር ቤት ከደስታና ከመዝሙር ጋር የሚቃጠለውን መሥዋዕት እንዲያቀርቡ፥ ዳዊት በእግዚአብሔር ቤት ላይ የሾማቸው ሌዋውያን ዳዊት በሰጠው መመሪያ መሠረት ከካህናቱ እጅ በታች እንዲያገለግሉ ለእግዚአብሔር ቤት ኃላፊዎችን ሾመ፡፡
\v 19 ርኩስ የሆነ ማንም በማናቸውም መንገድ ወደ እግዚአብሔር ቤት እንዳይገባ በበሮቹ ላይ ጠባቂዎችን አኖረ፡፡
\s5
\v 20 ዮዳሄ ከእርሱ ጋር የመቶ አለቆቹን፥ ባላባቶቹን ፥ የሕዝቡን አስተዳዳሪዎችና የአገሩንም ሕዝብ ሁሉ ወሰደ፡፡ ንጉሡንም በኮረብታ ላይ ከነበረው ከእግዚአብሔር ቤት አወረደው፡፡ ሕዝቡም በላይኛው በር በኩል ወደ ንጉሡ ቤት መጥተው ንጉሡን በመንግሥቱ ዙፋን ላይ አስቀመጡት፡፡
\v 21 የአገሩም ሕዝብ ሁሉ ደስ አላቸው፤ ከተማይቱም ጸጥ አለች፡፡ ጎቶልያንም በሰይፍ ገድለዋት ነበር፡፡
\s5
\c 24
\p
\v 1 ኢዮስያስ መንገሥ በጀመረ ጊዜ ሰባት ዓመቱ ነበር፤ በኢየሩሳሌምም አርባ ዓመት ነገሠ፡፡ የቤርሳቤዋ እናቱ ስም ሳብያ ነበር፡፡
\v 2 ኢዮስያስ ካህኑ ዮዳሄ በነበረበት ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ትክክል የሆነውን ነገር አደረገ፡፡
\v 3 ዮዳሄ ለኢዮስያስ ሁለት ሚስቶችን አጋባው፤ የወንዶችና የሴቶች ልጆች አባት ሆነ፡፡
\s5
\v 4 ከዚህም በኋላ ኢዮስያስ የእግዚአብሔርን ቤት ለመጠገን ወሰነ፡፡
\v 5 ካህናቱንና ሌዋውያኑን በአንድነት ሰብስቦ ፦"በየዓመቱ ወደ ይሁዳ ከተሞች ውጡና የአምላካችሁን ለማደስ ከእስራኤል ሁሉ ገንዘብን ሰብስቡ፡፡ በፍጥነት መጀመራችሁን እርግጠኛ ሁኑ" አላቸው፡፡ ሌዋውያኑ በመጀመሪያ ምንም አላደረጉም፡፡
\s5
\v 6 በመሆኑም ንጉሡ ሊቀ ካህናቱን ጠርቶ፦"ሌዋውያኑ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ለቃል ኪዳኑ ድንኳን ድንጋጌ የእስራኤል ጉባኤ የተጣለባቸውን ግብር ከይሁዳና ከኢየሩሳሌም እንዲያስመጡ ለምን አላደረግሃቸውም?" አለው፡፡
\v 7 የዚያች ክፉ ሴት የጎቶልያ ልጆች የእግዚአብሔርን ቤት አፍርሰው እና የእግዚአብሔርንም ቤት የተቀደሱ ነገሮች ሁሉ ለበኣል ሰጥተው ነበር፡፡
\s5
\v 8 በመሆኑም ንጉሡ ስለአዘዘ የገንዘብ ሳጥን ሰርተው በእግዚአብሔር ቤት መግቢያ በስተውጪ አስቀመጡት፡፡
\v 9 የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ በምድረ በዳ በእስራኤል ላይ የጣለባቸውን ግብር ለእግዚአብሔር እንዲያመጡ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ሁሉ አዋጅ ነገሩ፡፡
\v 10 መሪዎቹ ሁሉና ሕዝቡ ሁሉ ደስ ብሎአቸው ገንዘብ አመጡ፤ እስኪሞሉትም ድረስ በገንዘብ ሳጥኑ ውስጥ አስቀመጡት፡፡
\s5
\v 11 የገንዘብ ሳጥኑ በሌዋውያኑ እጅ ወደ ንጉሡ ሹማምንት በሚመጣበት ጊዜ ሁሉና ብዙ ገንዘብ እንዳለበት ባዩ ጊዜ ሁሉ የንጉሡ ጸሐፊና የሊቀ ካህናቱ ሹም መጥተው ከገንዘብ ሳጥኑ ገንዘቡን አውጥተው በመውሰድ ሳጥኑን ወደ ሥፍራው ይመልሱት ነበር፡፡ ከፍ ያለ መጠን ያለው ገንዘብ በመሰብሰብ ይህንንም ዕለት ዕለት ያደርጉት ነበር፡፡
\v 12 ንጉሡና ዮዳሄ በእግዚአብሔር ቤት የማገልገል ሥራ ለሚሠሩት ሰዎች ገንዘቡን ይሰጡ ነበር፡፡ እነዚህ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቤት ለሚያድሱት ድንጋይ ጠራቢዎችና አናጢዎች እንዲሁም የብረትና የነሃስ ሥራ የሚሠሩትን ቀጥረው ያሠሩበት ነበር፡፡
\s5
\v 13 በመሆኑም ሠራተኞቹ አብዝተው ሠሩ፤ የጥገናውም ሥራ በእጃቸው ተከናወነ፤ የእግዚአብሔርንም ቤት በመጀመሪያ ንድፉ አቁመው አጠናከሩት፡፡
\v 14 በጨረሱም ጊዜ የተረፈውን ገንዘብ ወደ ንጉሡና ዮዳሄ አመጡት፡፡ ይህ ገንዘብ የእግዚአብሔርን ቤት ዕቃ ፥ ለአገልግሎትና መሥዋዕት ለማቅረብ የሚሆኑ ማንኪያዎችንና የወርቅና የብር ዕቃዎች ለማሟላት ጥቅም ላይ ዋለ፡፡ በዮዳሄ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ የሚቃጠል መሥዋዕት ባለማቋረጥ ያቀርቡ ነበር፡፡
\s5
\v 15 ዮዳሄም ሸመገለ፤ ዕድሜም ጠግቦ ሞተ፡፡ በሚሞትበት ጊዜ ዕድሜው መቶ ሠላሳ ዓመት ነበር፡፡
\v 16 በእስራኤልም ለእግዚአብሔርና ለእግዚአብሔር ቤት መልካም ስላደረገ በነገሥታቱ መካከል በዳዊት ከተማ ቀበሩት፡፡
\s5
\v 17 ዮዳሄ ከሞተ በኋላ የይሁዳ መሪዎች መጥተው ለንጉሡ ክብርን ሰጡት፡፡ ንጉሡም አዳመጣቸው፡፡
\v 18 የአባቶቻቸውን አምላክ የእግዚአብሔርን ቤት ትተው የማምለኪያ ዐፀዶችንና ጣዖታቱን አመለኩ፡፡በዚህም ኃጢአታቸው ምክንያት የእግዚአብሔር ቁጣ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ መጣ፡፡
\v 19 ሆኖም ግን ወደ እግዚአብሔር ወደ ራሱ እንደገና እንዲያመጧቸው ነቢያትን ይልክላቸው ነበር፤ ነቢያቱም በሕዝቡ ላይ ይመሰክሩባቸው ነበር፤ እነርሱ ግን ለመስማት እምቢ አሉ፡፡
\s5
\v 20 የእግዚአብሔር መንፈስ በካህኑ በዮዳሄ ልጅ በዘካርያስ ላይ መጣ፤ እርሱም ከሕዝቡ በላይ ቆሞ፦"እግዚአብሔር ይህንን ይላል፤ 'የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ለምን ትተላለፋላችሁ? መልካም ነገር ሊሆንላችሁ አይችልም፡፡ እግዚአብሔርን ስለተዋችሁ እርሱም ትቶአችኋል'" አላቸው፡፡
\v 21 እነርሱ ግን አሴሩበት፤ በንጉሡ ትዕዛዝም በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ ውስጥ በድንጋይ ወገሩት፡፡
\v 22 በዚህ ሁኔታ ንጉሡ ኢዮአስ የዘካርያስ አባት ዮዳሄ ያደረገለትን ቸርነት ችላ አለ፡፡ ይልቁንም የዮዳሄን ልጅ ገደለ፡፡ ዘካርያስም በሚሞትበት ጊዜ፦" እግዚአብሔር ይህንን ይየው፤ ይጠይቃችሁም" አለ፡፡
\s5
\v 23 በዓመቱ መጨረሻም የአራም ሠራዊት ሊያጠቁት በኢዮአስ ላይ መጡበት፡፡ ወደ ይሁዳና ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፤ የሕዝቡን መሪዎች ሁሉ ገደሉ፤ ከእነርሱ የወሰዱትንም ምርኮ ሁሉ ወደ ደማስቆ ንጉሥ ላኩ፡፡
\v 24 የሶርያውያንም ሠራዊት የመጡት ከትንሽ ሠራዊት ጋር ነበር፤ ነገር ግን ይሁዳ የአባቶቻቸውን አምላክ ከመተዋቸው የተነሳ እግዚአብሔር እጅግ ታላቅ በነበረው ሠራዊት ላይ ድልን ሰጣቸው፡፡ በዚህ መንገድ የሶርያውያን ሠራዊት በኢዮአስ ላይ ፍርድን አመጡበት፡፡
\s5
\v 25 ሶርያውያን ከሄዱ በኋላ ኢዮአስ ክፉኛ ቆስሎ ነበር፡፡ ከካህኑ ከዮዳሄ ልጆች ግድያ የተነሳ የገዛ አገልጋዮቹ አሲረውበት ነበር፡፡ በአልጋው ላይ ገደሉት፤ እርሱም ሞተ፤ በነገሥታቱ መቃብር ሳይሆን በዳዊት ከተማ ቀበሩት፡፡
\v 26 ያሴሩበትም ሰዎች የአሞናዊቷ የሰምዓት ልጅ ዛባድ፥ የሞዓባዊቷ የሰማሪት ልጅ ዮዛባት ነበሩ፡፡
\s5
\v 27 የልጆቹ ነገርና ስለ እርሱ የተነገሩት ዋና ዋና ትንቢቶች እንዲሁም የእግዚአብሔርን ቤት እንደገና መገንባቱ እነሆ በነገሥታቱ መጽሐፍ ማብራሪያ ተጽፈዋል፡፡ ልጁም አሜስያስ በእርሱ ቦታ ነገሠ፡፡
\s5
\c 25
\p
\v 1 አሜስያስ መንገሥ በጀመረ ጊዜ ሃያ አምስት ዓመቱ ነበር፤ በኢየሩሳሌም ሃያ ዘጠኝ ዓመት ነገሠ፡፡ የኢየሩሳሌሟ እናቱ ስም ዮዓዳን ነበር፡፡
\v 2 በእግዚአብሔር ፊት ትክክለኛውን ነገር አደረገ፤ ነገር ግን በፍጹምና በተሰጠ ልብ አይደለም፡፡
\s5
\v 3 መንግሥቱ በሚገባ በጸናለት ጊዜ አባቱን ንጉሡን የገደሉትን አገልጋዮቹን ገደላቸው፡፡
\v 4 በሙሴ ሕግ መጽሐፍ በተጻፈው መሠረት፦"አባቶች ስለ ልጆች መሞት አይገባቸውም፤ ልጆችም ስለ አባቶች መሞት አይገባቸውም፡፡ ይልቁንም ማንኛውን ሰው ለራሱ ኃጢአት መሞት ይገባዋል" በማለት እግዚአብሔር እንዳዘዘው በማድረግ የገዳዮቹን ልጆች አልገደለም፡፡
\s5
\v 5 በተጨማሪም አሜስያስ ይሁዳን በአንድነት ሰበሰበ፤ ይሁዳንና ቢንያምን ሁሉ በየአባቶቻቸው ቤቶች ከሺህ አለቆችና ከመቶ አለቆች በታች መዘገባቸው፡፡ ከሃያ ዓመትና ከዚያ በላይ ያሉትን ቆጠረ፤ ወደ ጦርነት ሊሄዱ የሚችሉ፥ ጋሻና ጦርም ሊይዙ የሚችሉ ሦስት መቶ ሺህ የተመረጡ ሰዎች አገኘ፡፡
\v 6 ከእስራኤልም መቶ ሺህ ጦረኛ ሰዎች በመቶ መክሊት ብር ቀጠረ፡፡
\s5
\v 7 ነገር ግን አንድ የእግዚአብሔር ሰው ወደ እርሱ መጥቶ፦"ንጉሥ ሆይ እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር፥ ከኤፍሬምም ሰዎች ከአንዳቸውም ጋር አይደለምና የእስራኤል ሠራዊት ከአንተ ጋር አይሂዱ፡፡
\v 8 ነገር ግን ብትሄድ በጦርነትም ደፋርና ብርቱ ብትሆን እግዚአብሔር በጠላት ፊት ይጥልሃል፤ ምክንያቱም የመርዳት ኃይል እና የመጣል ኃይል ያለው እግዚአብሔር ነው" አለው፡፡
\s5
\v 9 አሜስያስም ለእግዚአብሔር ሰው፦" ለእስራኤል ሠራዊት ስለሰጠሁት መቶ መክሊትስ ምን እናደርጋለን?" አለው፡፡ የእግዚአብሔር ሰውም፦ "እግዚአብሔር ከዚያ እጅግ የበለጠ ሊሰጥህ ይችላል" ብሎ መለሰለት፡፡
\v 10 በመሆኑም አሜስያስ ከኤፍሬም ወደርሱ የመጡትን ሠራዊት ለይቶአቸው እንደገና ወደ ቤት ላካቸው፡፡ ስለዚህም በይሁዳ ላይ ቁጣቸው እጅግ ነደደ፤ ወደ ቤትም በጋለ ቁጣ ተመለሱ፡፡
\s5
\v 11 አሜስያስም በርትቶ ሕዝቡን አውጥቶ ወደ ጨው ሸለቆ መራቸው፤ በዚያም አሥር ሺህ የሴይርን ሰዎች ድል ነሳቸው፡፡
\v 12 የይሁዳም ሠራዊት አሥር ሺህ ሰዎች ከነሕይወታቸው ማርከው ወሰዱ፡፡ ወደ ኮረብታው ጫፍ ላይ ወሰዱአቸውና ሁሉም እስኪንኮታኮቱ ድረስ ከዚያ ወደ ታች ወረወሩአቸው፡፡
\s5
\v 13 ነገር ግን አሜስያስ ከእርሱ ጋር ወደ ጦርነት እንዳይሄዱ ያስመለሳቸው የሠራዊት ሰዎች ከሰማርያ እስከ ቤትሖሮን በይሁዳ ከተሞች ላይ ጥቃት አደረሱ፤ ከሕዝቡም ሦስት ሺህ ሰዎች መትተው እጅግ ብዙ ምርኮ ወሰዱ፡፡
\s5
\v 14 አሜስያስ የኤዶምያስን ሰዎች ገድሎ ከተመለሰ በኋላ የሴይርን ሰዎች ጣኦታት አምጥቶ የገዛ ራሱ አማልክት እንዲሆኑ አቆማቸው፡፡ በፊታቸውም ሰገደ፤ እጣንም አጠነላቸው፡፡
\v 15 ስለዚህም የእግዚአብሔር ቁጣ በአሜስያስ ላይ ነደደ፡፡ አንድ ነቢይ ልኮ፦"የገዛ ሕዝባቸውን እንኳን ከአንተ እጅ ያላዳኑትን የአሕዛብን አማልክት ለምን ፈለግሃቸው?" አለው፡፡
\s5
\v 16 ነቢዩም ከእርሱ ጋር እየተነጋገረ እያለ ንጉሡ፦"የንጉሡ አማካሪ እንድትሆን አድርገንሃል? አቁም! ለምን መገደል ይገባሃል?" አለው፡፡ ነቢዩም ንግግሩን አቁሞ፦"ይህንን ድርጊት በመፈጸምህና ምክሬን ባለመስማትህ እግዚአብሔር ሊያጠፋህ እንደወሰነ አውቃለሁ" አለ፡፡
\s5
\v 17 ከዚያም የይሁዳ ንጉሥ አሜስያስ ከአማካሪዎቹ ጋር ተማክሮ፦" ና በጦርነት ፊት ለፊት እንጋጠም" ብሎ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ ኢዩ ልጅ ወደ ኢዮአካዝ ልጅ ወደ ኢዮአስ ላከ፡፡
\s5
\v 18 የእስራኤልም ንጉሥ ኢዮአስ መልዕክተኞችን ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ አሜስያስ መልሶ ላከና፦"በሊባኖስ የነበረ አንድ ኩርንችት፦ 'ልጅህን ለልጄ ሚስት አድርገህ ስጠው' ብሎ ወደ ሊባኖስ ዝግባ መልዕክት ላከ፤ ነገር ግን አንድ የሊባኖስ አውሬ መንገድ ሲያልፍ ኩርንችቱን ረገጠው፡፡
\v 19 አንተም ፦'እነሆ ኤዶምያስን መትቻለሁ' ብለህ ልብህ ከፍ ከፍ ብሏል፡፡ በድልህ ኩራ፤ ነገር ግን በቤትህ ተቀመጥ፤ አንተና ካንተ ጋር ይሁዳ ሁሉ ለምን በራስህ ላይ ችግር ፈጥረህ ትወድቃለህ?" አለው፡፡
\s5
\v 20 የይሁዳ ሰዎች ከኤዶምያስ አማልክት ምክር ከመፈለጋቸው የተነሳ የይሁዳን ሰዎች ለጠላቶቻቸው አሳልፎ ይሰጣቸው ዘንድ ይህ ከእግዚአብሔር ታስቦ ነበርና አሜስያስ ሊሰማ አልፈለገም፡፡
\v 21 ስለዚህ የእስራኤል ንጉሥ ኢዮአስ ጥቃት አደረሰ፤ እርሱና የይሁዳ ንጉሥ አሜስያስ የይሁዳ በነበረችው በቤትሳሚስ ፊት ለፊት ተጋጠሙ፡፡
\v 22 ይሁዳም በእስራኤል ፊት ተመታ፤ እያንዳንዱም ሰው ወደ ቤቱ ሸሸ፡፡
\s5
\v 23 የእስራኤል ንጉሥ ኢዮአስ የይሁዳን ንጉሥ የአካዝያስን ልጅ አሜስያስን በቤትሳሚስ ማረከው፡፡ ወደ ኢየሩሳሌምም ይዞት መጣና ከኤፍሬም በር እስከ ማዕዘኑ በር ድረስ የኢየሩሳሌምን ቅጥር አራት መቶ ክንድ ርቀት ያህል አፈረሰው፡፡
\v 24 ወርቁንና ብሩን ሁሉ፥ በእግዚአብሔርም ቤት ከዖቤድኤዶም ጋር የነበሩትን ዕቃዎች በሙሉ እንዲሁም በንጉሡ ቤት የነበሩትን ዋጋ ያላቸውን ነገሮች ከታገቱት ጋር ወስዶ ወደ ሰማርያ ተመለሰ፡፡
\s5
\v 25 የይሁዳ ንጉሥ የኢዮአስ ልጅ አሜስያስ፥ ከእስራኤል ንጉሥ ከኢዮአካዝ ልጅ ከኢዮአስ ሞት በኋላ አሥራ አምስት ዓመት ኖረ፡፡
\v 26 አሜስያስን በተመለከተ ሌሎቹ ነገሮች የመጀመሪያውና የመጨረሻው እነሆ በይሁዳና በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ የተጻፉ አይደለምን?
\s5
\v 27 አሜስያስም እግዚአብሔርን ከመከተል ከራቀበት ጊዜ አንስቶ በኢየሩሳሌም ሴራ ያሴሩበት ጀመር፡፡ ወደ ለኪሶም ሸሸ፤ ነገር ግን ከበስተኋላው ሰዎች ላኩበት፤ እነርሱም በዚያ ገደሉት፡፡
\v 28 በፈረስም ጭነው መልሰው አመጡት፤ በይሁዳም ከተማ ከአባቶቹ ጋር ቀበሩት፡፡
\s5
\c 26
\p
\v 1 የይሁዳም ሕዝብ ሁሉ አሥራ ስድስት ዓመት የነበረውን ዖዝያንን ወስደው በአባቱ በአሜስያስ ቦታ አነገሡት፡፡
\v 2 ኤላትን እንደገና የገነባትና ወደ ይሁዳ ወደቀድሞ ይዞታዋ የመለሳት እርሱ ነው፡፡ ከዚያ በኋላ ንጉሡ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፡፡
\v 3 ዖዝያን መንገሥ በጀመረ ጊዜ አሥራ ስድስት ዓመቱ ነበር፡፡ በኢየሩሳሌምም ሃምሳ ሁለት ዓመት ነገሠ፡፡ የእናቱም ስም ይኮልያ ነበር፤ የኢየሩሳሌም ሴት ነበረች፡፡
\s5
\v 4 በሁሉም ነገር የአባቱን የአሜስያስ ምሳሌነት በመከተል በእግዚአብሔር ፊት ትክክለኛውን ነገር አደረገ፡፡
\v 5 እግዚአብሔርን መታዘዝ ባስተማረው በዘካርያስ ዘመን እግዚአብሔርን ለመፈለግ በልቡ ቆርጦ ነበር፡፡ እግዚአብሔርን በፈለገ ጊዜ እግዚአብሔር የተሳካለት አደረገው፡፡
\s5
\v 6 ዖዝያን ወጥቶ ከፍልስጤማውያን ጋር ተዋጋ፡፡ የጌትንና የየብናንና የአዛጦንን የከተማ ቅጥሮች አፈረሰ፤ በአዛጦን አገርና በፍልስጤማውያን መካከል ከተሞችን ገነባ፡፡
\v 7 እግዚአብሔርም በፍልስጤማውያን ላይ፥ በጉርበኣል በሚኖሩ ዓረባውያን ላይና በምዑናውያን ላይ ረዳው።
\v 8 አሞናውያንም ለዖዝያን ግብር ይከፍሉ ነበር፤ እጅግ ኃይለኛ ከመሆኑ የተነሳ ዝናውም እስከ ግብጽ መግቢያ ድረስ ወደ ሌሎች አገሮች ተሰራጨ።
\s5
\v 9 በተጨማሪም ዖዝያን በኢየሩሳሌም በማዕዘኑ በር፥ በሸለቆው በርና በቅጥሩ መዞሪያ ላይ ረጃጅም ማማዎችን ገንብቶ መሸጋቸው።
\v 10 በቆላው እንዲሁም በደጋው እጅግ ብዙ ከብቶች ስለነበሩት በምድረ በዳው የመጠባበቂያ ማማዎችን ሠራ፤ በርካታ ጉድጓዶችንም ቆፈረ። እርሻ ይወድ ስለነበርም በኮረብታማው አገርና በፍሬያማው መስክ ውስጥ ገበሬዎችና የወይን አትክልተኞች ነበሩት።
\s5
\v 11 በተጨማሪም ዖዝያን በጸሐፊው በይዒኤልና ከንጉሡ አለቆች በአንዱ በሐናንያ ሥልጣን ስር በነበረው በመዕሤያ በሚቆጠሩበት ቁጥር መሰረት የተደራጁ በቡድን ወደ ጦርነት ይሄዱ የነበሩ የተዋጊ ሰዎች ሠራዊት ነበሩት።
\v 12 የአባቶቻቸውም ቤቶች አለቆች የተዋጊ ሰዎች አጠቃላይ ቁጥር ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ነበር።
\v 13 ከበታቻቸውም ንጉሡን ከጠላቱ ለመጠበቅ የሚረዳ በብርቱ ኃይል የሚዋጋ የሦስት መቶ ሰባት ሺህ እምስት መቶ ሰዎች ሠራዊት ነበር።
\s5
\v 14 ዖዝያንም ለሠራዊቱ ሁሉ ጋሻዎች፥ ጦሮች፥ የራስ ቁሮች፥ ጥሩሮች፥ ቀስቶችና የሚወነጭፉአቸውን ድንጋዮች አዘጋጅቶላቸው ነበር።
\v 15 በኢየሩሳሌምም ፍላጻዎችንና ትልልቅ ድንጋዮችን ለመወርወር በግንብና በመታኮሻ ቅጥር ላይ እንዲሆኑ የተካኑ ባለሙያዎች የፈለሰፏቸውን ማንቀሳቀሻ ሞተሮች ገነባ። እጅግ እስኪበረታም ድረስ እግዚአብሔር በብዙ ረድቶታልና ዝናው እስከ ሩቅ ቦታዎች ተሰራጨ።
\s5
\v 16 ነገር ግን ዖዝያን በበረታ ጊዜ እስኪበላሽ ድረስ ልቡ ታበየ፤ ወደ እግዚአብሔር ቤት ገብቶ በዕጣን መሠዊያው ላይ ዕጣን በማጠኑ አምላኩን እግዚአብሔርን በደለ።
\v 17 ካህኑም ዓዛርያስ ከእርሱም ጋር ደፋር ሰዎች የነበሩ ሰማንያ የእግዚአብሔር ካህናት ተከትለውት ገቡ።
\v 18 ንጉሡንም ዖዝያንን ተቃውመው፦"ዖዝያን ሆይ፦ ለእግዚአብሔር ዕጣን ማጠን ለእግዚአብሔር ለተቀደሱት ለካህናቱ ለአሮን ልጆች የተሰጠ እንጂ ዕጣን ማጠን ለአንተ አይደለም። ተላልፈሃልና ከቅዱሱ ቦታ ውጣ። በዚህ ነገር ከእግዚአብሔር ዘንድ ላንተ ምንም ክብር አይሆንልህም" አሉት።
\s5
\v 19 ዖዝያንም ተቆጣ። ዕጣን የሚያጥንበትን ጥና በእጁ ይዞ ነበር። በካህናቱ ላይ በተቆጣ ጊዜ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ በዕጣኑ መሠዊያ አጠገብ በካህናቱ ፊት ግንባሩ ላይ ለምጽ ወጣበት።
\v 20 ዋናው ካህንና ካህናቱ ሁሉ ተመለከቱት፤ እነሆ ግንባሩ ላይ ለምጻም ሆኖ ነበር። በፍጥነትም ከዚያ ቦታ አስወጡት። በእርግጥም እግዚአብሔር በለምጽ መትቶት ስለነበር እርሱም ለመውጣት ቸኮለ።
\s5
\v 21 ንጉሡም ዖዝያን እስከሚሞትበት ቀን ድረስ ለምጻም ነበረ፤ ለምጻም በመሆኑም ከእግዚአብሔር ቤት ተገልሎ ስለነበር ከሰዎች ርቆ በተለየ ቤት ይኖር ነበር። ልጁም ኢዮአታም በንጉሡ ቤት ላይ የበላይ ሆኖ የምድሩን ሕዝብ ይገዛ ነበር።
\s5
\v 22 ዖዝያንን በተመለከተ ሌሎቹ ነገሮች የመጀመሪያውና የመጨረሻው የአሞጽ ልጅ ነቢዩ ኢሳይያስ በጻፈው ውስጥ ይገኛሉ።
\v 23 ዖዝያንም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ "ለምጻም ነው" ብለውም ከአባቶቹ ጋር በነገሥታቱ መቃብር ሥፍራ ቀበሩት።
\s5
\c 27
\p
\v 1 ኢዮአታምም መንገሥ በጀመረ ጊዜ ሃያ አምስት ዓመቱ ነበር፤ በኢየሩሳሌምም አሥራ ስድስት ዓመት ነገሠ። የእናቱም ስም ኢየሩሳ ነበር፤ እርሷም የሳዶቅ ልጅ ነበረች።
\v 2 በሁሉም ነገር የአባቱን የዖዝያንን ምሳሌ ተከትሎ በእግዚአብሔር ፊት ትክክለኛውን ነገር አደረገ። ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ከመግባትም ተቆጠበ። ሕዝቡ ግን ገና በክፉ መንገድ ይሄዱ ነበር።
\s5
\v 3 የእግዚአብሔርን ቤት የላይኛውን በር ሠራ፤ በዖፌልም ኮረብታ ላይ እጅግ ብዙ የግንባታ ሥራዎችን ሠራ።
\v 4 በተጨማሪም በኮረብታማው የይሁዳ አገር ላይ ከተሞችን፥ በደኖቹ ውስጥ ደግሞ አምባዎችንና ማማዎችን ገነባ።
\s5
\v 5 ከአሞንም ሕዝብ ንጉሥ ጋር ተዋግቶ አሸነፋቸው። በዚያው ዓመት የአሞን ልጆች አንድ መቶ መክሊት ብር፥ አሥር ሺህ መስፈሪያ ስንዴ፥ አሥር ሺህ መስፈሪያ ገብስ ሰጡት። የአሞን ሕዝብ በሁለተኛውና በሦስተኛውም ዓመት ተመሳሳዩን ያህል ሰጡት።
\s5
\v 6 በመሆኑም ኢዮአታም በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት በጽናት ስለተራመደ ብርቱ ሆነ።
\v 7 ኢዮአታምን በተመለከተ ሌሎቹ ነገሮች ጦርነቶቹ ሁሉና መንገዱ እነሆ በእስራኤልና በይሁዳ ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፈዋል።
\s5
\v 8 ኢዮአታም መንገሥ በጀመረ ጊዜ ሃያ አምስት ዓመቱ ነበር፤ በኢየሩሳሌም ለአሥራ ስድስት ዓመታት ነገሠ።
\v 9 ኢዮአታምም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊትም ከተማ ቀበሩት። ልጁም አካዝ በእርሱ ቦታ ነገሠ።
\s5
\c 28
\p
\v 1 አካዝ መንገሥ በጀመረ ጊዜ ሃያ ዓመቱ ነበረ፤ በኢየሩሳሌም አሥራ ስድስት ዓመት ነገሠ። ዝርያው ዳዊት እንዳደረገው በእግዚአብሔር ፊት ትክክለኛውን ነገር አላደረገም።
\v 2 ይልቁንም በእስራኤል ነገሥታት መንገድ ሄደ፤ ለበኣሊምም ከብረት ቀልጠው የተሠሩ ምስሎችን ሠራ።
\s5
\v 3 በተጨማሪም በሄኖም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ዕጣን ዐጠነ፤ እግዚአብሔር ከእስራኤል ሕዝብ ፊት ያሳደዳቸውን ሕዝቦች ክፉ ልማድ ተከትሎ ልጆቹን እንደሚቃጠል መሥዋዕት በእሳት ውስጥ አሳለፋቸው።
\v 4 በኮረብታው መስገጃዎች፥ በኮረብቶች ላይ እና በለመለመው ዛፍ ሁሉ በታች መስዋዕት ይሰዋና ዕጣን ያጥን ነበር።
\s5
\v 5 ስለዚህ የአካዝ አምላክ እግዚአብሔር ለሶርያ ንጉሥ እጅ አሳልፎ ሰጠው። ሶርያውያንም ድል አደረጉት፤ የብዙ እስረኞችን ስብስብ ከእርሱ ወስደው ወደ ደማስቆ አመጡአቸው። አካዝ ለእስራኤልም ንጉሥ እጅ ተላልፎ ተሰጥቶ ነበር፤ እርሱም በታላቅ ግድያ አሸነፈው።
\v 6 የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ከመተዋቸው የተነሳ የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ በአንድ ቀን ከይሁዳ ሁሉም ደፋር የሆኑ አንድ መቶ ሃያ ሺህ ወታደሮችን ገደለ።
\s5
\v 7 ኤፍሬማዊው ኃይለኛ ሰው ዝክሪ የንጉሡን ልጅ መዕሤያንና የቤተ መንግሥቱን ባለሥልጣን ዓዝሪቃምን ለንጉሡ በማዕረግ ሁለተኛ የነበረውን ሕልቃናን ገደለ።
\v 8 የእስራኤል ሠራዊት ከዘመዶቻቸው ሁለት መቶ ሺህ ሚስቶች፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆች ምርኮ አድርገው ወሰዱ። ወደ ሰማሪያም ተሸክመው ያመጡትን እጅግ ብዙ ምርኮም ወሰዱ።
\s5
\v 9 ነገር ግን አንድ የእግዚአብሔር ነቢይ በዚያ ነበረ፤ ስሙም ዖዴድ ነበር። ወደ ሰማርያም የሚመጣውን ሠራዊት ለመገናኘት ወጣ።" የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር በይሁዳ ላይ ስለተቆጣ በእጃችሁ አሳልፎ ሰጣቸው። እናንተ ግን ወደ ሰማይ በሚደርስ ቁጣ ገደላችኋቸው።
\v 10 አሁንም የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ወንዶችና ሴቶች እንደ ባሪያዎቻችሁ አድርጋችሁ ልትይዟቸው ታስባላችሁ። በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ላይ በገዛ ራሳችሁ ኃጢአት በደለኞች አይደላችሁምን?
\v 11 እንግዲያውስ አሁን ስሙኝ፤ የእግዚአብሔር የጋለ ቁጣ በእናንተ ላይ ስለሆነ ከገዛ ወንድሞቻችሁ የወሰዳችኋቸውን እስረኞች መልሳችሁ ስደዱ" አላቸው።
\s5
\v 12 ከዚያም የተወሰኑ የኤፍሬም ሰዎች መሪዎች የዮሐናን ልጅ ዓዛርያስ፥ የምሺሌሞትም ልጅ በራክያ፥ የስሎምም ልጅ ይሒዝቅያ፥ የሐድላይም ልጅ ዓሜሳይ ከጦርነቱ ተመልሰው የመጡትን ተቃወሙአቸው።
\v 13 "መተላለፋችን ታላቅ ስለሆነና በእስራኤል ላይ የጋለ ቁጣ ስላለባት በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት የሚሆንብንን ነገር ልታመጡብን፥ ኃጢአታችንንና መተላለፋችንን ልትጨምሩብን ስላሰባቸሁ እስረኞቹን እዚህ ልታመጧቸው አይገባችሁም" አሏቸው።
\s5
\v 14 የታጠቁት ሰዎችም እስረኞቹንንና ምርኮውን በመሪዎቹና በጉባኤው ሁሉ ፊት ተዉአቸው።
\v 15 በስማቸው የተመደቡትም ሰዎች ተነስተው እስረኞቹን ወስደው ከመካከላቸው እርቃናቸውን የነበሩትን ሁሉ ከተማረከው ልብስ አለበሷቸው። አጎናጸፉአቸው፤ ጫማም አደረጉላቸው። የሚበሉትን ምግብና የሚጠጡትን ሰጡአቸው። ቁስላቸውን አከሙላቸው፤ የደከሙትንም በአህዮች ላይ አስቀመጧቸው። የዘንባባ ከተማ ተብላ በምትጠራዋ ኢያሪኮ ወዳሉት ቤተሰቦቻቸው መልሰው ወሰዷቸው። ከዚያም ወደ ሰማርያ ተመለሱ።
\s5
\v 16 በዚያን ጊዜ ንጉሥ አካዝ እንዲረዱት እንዲጠይቋቸው ወደ አሦርያ ነገሥታት መልዕክተኞችን ላከ።
\v 17 የኤዶምያስ ሰዎች አንድ ጊዜ ደግመው መጥተው ይሁዳን በማጥቃት እስረኞችን ይዘው ወስደው ነበር።
\v 18 ፍልስጤማውያንም የቆላውን ከተሞች እና የይሁዳን ደቡባዊ ክልሎች ወርረው ነበር። ቤት ሳሚስንና ኤሎንን ፥ ግዴሮትንም፥ ሦኮን ከነመንደርዎቿ፥ ተምናን ከነመንደርዎቿ እና ጊምዞን ከነመንደርዎቿ ወስደው ነበር። በእነዚያ ቦታዎችም ውስጥ ለመኖር ሄደው ነበር።
\s5
\v 19 በይሁዳ ክፉ ስላደረገና እግዚአብሔርንም እጅግ በጣም ስለበደለ ከእስራኤል ንጉሥ ከአካዝ የተነሳ እግዚአብሔር ይሁዳን ዝቅ ዝቅ አድርጎ ነበር።
\v 20 የአሦርም ንጉሥ ቴልጌልፌልሶር አካዝን በማበርታት ፈንታ መጥቶ አስጨንቆት ነበር።
\v 21 ለሦርያ ነገሥታት የከበሩትን ነገሮች ለመስጠት አካዝ የእግዚአብሔርን ቤት እና የንጉሡንና የመሪዎቹን ቤቶች ዘርፎ ነበር፤ ነገር ግን ይህ አልጠቀመውም።
\s5
\v 22 ይኸው ንጉሥ አካዝ በመከራው ጊዜ በእግዚአብሔር ላይ ይበልጥ ኃጢአት ሠራ።
\v 23 ድል ላደረጉት አማልክት ለደማስቆ አማልክት መስዋዕት አቀረበ። "የሦርያ ነገሥታት አማልክት እነርሱን ስለረዷቸው መስዋዕት ባቀርብላቸው እኔንም ይረዱኝ ይሆናል" አለ። ነገር ግን ለእርሱና ለእስራኤል ሁሉ ውድመት ሆኑ።
\s5
\v 24 አካዝም የእግዚአብሔርን ቤት እቃዎች ሁሉ በአንድ ላይ ሰብስቦ ሰባበራቸው። የእግዚአብሔርን ቤት በሮች ዘጋ፤ ለራሱም በኢየሩሳሌም በየማዕዘኑ ሁሉ መሰዊያዎችን ሠራ።
\v 25 በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ለሌሎች አማልክት መሥዋዕት የሚቃጠልባቸው መስገጃዎችን ሠራ፤ በዚህ መንገድ የአባቶቹን አምላክ እግዚአብሔርን ለቁጣ ቀሰቀሰ።
\s5
\v 26 የአካዝ የተቀሩት ድርጊቶቹና መንገዶቹ ሁሉ የመጀመሪያውና የመጨረሻው እነሆ በይሁዳና በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፎአል።
\v 27 አካዝም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በከተማይቱ በኢየሩሳሌምም ቀበሩት፤ ነገር ግን ወደ እስራኤል ነገሥታት መቃብር አላስገቡትም። ልጁ ሕዝቅያስ በእርሱ ቦታ ነገሠ።
\s5
\c 29
\p
\v 1 ሕዝቅያስ መንገሥ በጀመረ ጊዜ ሃያ አምስት ዓመቱ ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሃያ ዘጠኝ ዓመት ነገሠ። የእናቱ ስም አቡ ነበር፤ የዘካርያስ ልጅ ነበረች።
\v 2 በማንኛውም ነገር የዝርያውን የዳዊትን ምሳሌ ተከትሎ በእግዚአብሔር ፊት ትክክለኛውን ነገር አደረገ።
\s5
\v 3 በነገሠም በመጀመሪያው ዓመት በመጀመሪያው ወር የእግዚአብሔርን ቤት በሮች ከፈተ፤ አደሳቸውም።
\v 4 ካህናቱንና ሌዋውያኑን አምጥቶ በምሥራቅ በኩል ባለው አደባባይ ላይ በአንድነት ሰበሰባቸው።
\v 5 "እናንተ ሌዋውያን ሆይ ስሙኝ! ራሳችሁን ለእግዚአብሔር ቀድሱ፤ የአባቶቻችሁን አምላክ የእግዚአብሔርንም ቤት ቀድሱ፤ ከተቀደሰው ሥፍራም ርኩሱን ነገር ሁሉ አስወግዱ" አላቸው።
\s5
\v 6 አባቶቻችን ሕጉን ስለተላለፉና በአምላካችን በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር ስላደረጉ፥ እርሱንም ትተውታል፤ ፊታቸውንም እግዚአብሔር ከሚኖርበት ሥፍራ መልሰዋል፤ ጀርባቸውንም ሰጥተውታል።
\v 7 የበሮቹንም በረንዳዎች ዘግተዋል፤ መብራቶቹንም አጥፍተዋል። ለእስራኤል አምላክ በተቀደሰው ሥፍራ እጣን አላጠኑም ወይም የሚቃጠለውንም መስዋዕት አላቀረቡም።
\s5
\v 8 ስለዚህ የእግዚአብሔር ቁጣ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ ወረደ፤ በገዛ ራሳችሁ ዓይኖች ማየት እንደምትችሉት ለሽብር፥ ለድንጋጤና ለመዘበቻም ማረፊያ አደረጋቸው።
\v 9 ለዚህ ነው አባቶቻችን በሰይፍ የወደቁት፤ ለዚህም ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችን ሚስቶቻችንም በምርኮ ውስጥ አሉ።
\s5
\v 10 አሁንም የጋለ ቁጣው ከእኛ እንዲመለስ ከእስራኤል አምላክ ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን ለማድረግ በልቤ አስቤአለሁ።
\v 11 ልጆቼ እግዚአብሔር በፊቱ ትቆሙ፥ ታመልኩትና፥ አገልጋዮቹ ልትሆኑና ዕጣንን ልታጥኑለት ስለመረጣችሁ አሁን ታካች አትሁኑ።
\s5
\v 12 ከዚያም ሌዋውያኑ የቀዓት ሰዎች የአሚሳ ልጅ መሐትና የዓዛርያስ ልጅ ኢዮኤል፥ የሜራሪ ሰዎች የአብዲ ልጅ ቂስና የይሃሌልኤል ልጅ ዓዛርያስ፥ የጌድሶን ሰዎች የዛማት ልጅ ዮአክና የዮአክ ልጅ ዔድን፥
\v 13 የኤሊጸፋንም ልጆች ሺምሪና ይዒኤል፥ የአሳፍም ልጆች ዘካርያስና መታንያ፥
\v 14 የኤማንም ልጆች ይሒኤልና ሰሜኢ፥ የኤዶታምም ልጆች ሸማያና ዑዝኤል ተነሡ።
\s5
\v 15 ወንድሞቻቸውን ሰብስበው ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ቀደሱ፤ የእግዚአብሔርን ቃል በመከተል ንጉሡ እንዳዘዘው የእግዚአብሔርን ቤት ለማንጻት ወደ ውስጥ ገቡ።
\v 16 ካህናቱም የእግዚአብሔርን ቤት ለማንጻት ወደ ውስጠኛው ክፍል ገቡ፤ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ ያገኙትን ቆሻሻ ነገር ሁሉ ወደ ቤቱ አደባባይ አወጡት። ሌዋውያንም ወደ ቄድሮን ዥረት ተሸክመው ሊወስዱት አወጡት።
\v 17 ቤቱን ለእግዚአብሔር መቀደስን በመጀመሪያው ወር በመጀመሪያው ቀን ጀምረው በወሩ በስምንተኛው ቀን ወደ እግዚአብሔር በረንዳ ደረሱ። የእግዚአብሔርን ቤት በስምንት ቀናት ቀደሱ። በመጀመሪያው ወር በአሥራ ስድስተኛው ቀን ጨረሱ።
\s5
\v 18 ከዚያም ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝቅያስ ቤተ መንግሥት ውስጥ ገብተው፦" የእግዚአብሔርን ቤት፥ የሚቃጠል መስዋዕት የሚቀርብበትን መሠውያ ከዕቃዎቹ ሁሉ ጋር እና የመገኘቱን ሕብስት ገበታ ከዕቃዎቹ ሁሉ ጋር አንጽተናል።
\v 19 በተጨማሪም ንጉሥ አካዝ ነግሦ በነበረበት ጊዜ በመተላለፍ የወረወራቸውን ዕቃዎች ሁሉ አዘጋጅተን ለእግዚአብሔር ቀድሰናል። እነሆ በእግዚአብሔር መሠዊያ ፊት ለፊት ይገኛሉ" አሉት።
\s5
\v 20 ከዚያም ንጉሡ ሕዝቅያስ በማለዳ ተነስቶ የከተማዋን መሪዎች ሁሉ ሰበሰበ፤ ወደ እግዚአብሔርም ቤት ወጣ።
\v 21 ለመንግሥቱ፥ ለቤተ መቅደሱና ለይሁዳ የኃጢአት መስዋዕት አድርገው ሰባት ወይፈኖች፥ ሰባት አውራ በጎችና ሰባት የበግ ጠቦቶችና ሰባት ወንድ ፍየሎች አመጡ። ካህናቱን የአሮንን ልጆች በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ እንዲያቀርቧቸው አዘዛቸው።
\s5
\v 22 በመሆኑም ወይፈኖቹን አረዷቸውና ካህናቱ ደሙን ተቀብለው በመሠዊያው ላይ ረጩት። አውራ በጎቹንም አረዱ፤ ደሙንም በመሠዊያው ላይ ረጩት፤ የበግ ጠቦቶቹንም አረዱ፤ ደሙንም በመሠዊያው ላይ ረጩት።
\v 23 ለኃጢአት መስዋዕት ወንድ ፍየሎቹን በንጉሡና በጉባዔው ፊት አመጧቸው፤ እጃቸውንም ጫኑባቸው።
\v 24 ካህናቱም አረዷቸው፤ ንጉሡም ለእስራኤል ሁሉ የሚቃጠል መስዋዕትና የኃጢአት መስዋዕት ሊደረግ እንደሚገባው አዝዞ ስለነበር ለእስራኤል ሁሉ ለማስተሰረይ በመሠዊያው ላይ ደማቸውን የኃጢአት መስዋዕት አደረጉት።
\s5
\v 25 ሕዝቅያስ ትዕዛዙ በነቢያቱ አማካይነት ከእግዚአብሔር ስለ ነበር በዳዊትና በንጉሡ ባለ ራዕይ በጋድ፥ በነቢዩ ናታንም ትዕዛዝ ሌዋውያኑን ከጽናጽል፥ ከበገናና ከመሰንቆ ጋር በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ አደራጅቶ አስቀመጣቸው።
\v 26 ሌዋውያኑም ከዳዊት የሙዚቃ መሣሪያዎች ጋርና ካህናቱ ከመለከቶች ጋር ቆሙ።
\s5
\v 27 ሕዝቅያስም የሚቃጠለውን መሥዋዕት በመሠዊያው ላይ እንዲያቀርቡ አዘዛቸው። የሚቃጠለውን መሥዋዕት ማቅረብ ሲጀመር የእግዚአብሔር መዝሙርም በመለከቶችና በእስራኤል ንጉሥ በዳዊት የሙዚቃ መሣሪያዎች ተጀመረ።
\v 28 ጉባዔውም ሁሉ አመለኩ፤ መዘምራኑም ዘመሩ፤ መለከቶቹም ተነፉ፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ማቅረብ እስኪፈጸም ድረስ ይህ ሁሉ ቀጠለ።
\s5
\v 29 መስዋዕት ማቅረቡን በፈጸሙ ጊዜ ንጉሡና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሁሉ አጎነበሱ፤ ሰገዱም።
\v 30 በተጨማሪም ንጉሡ ሕዝቅያስና መሪዎቹ ሌዋውያኑ በዳዊትና በባለራዕዩ በአሳፍ ቃል ለእግዚአብሔር ውዳሴ እንዲዘምሩ አዘዙ። በደስታም ውዳሴዎችን ዘመሩ፤ አጎነበሱ፤ ሰገዱም።
\s5
\v 31 ከዚያም ሕዝቅያስ፦"አሁን ራሳችሁን ለእግዚአብሔር ቀድሳችኋል። ወደዚህ መጥታችሁ ለእግዚአብሔር ቤት መሥዋዕቱንና የምስጋና መሥዋዕቱን አቅርቡ" አላቸው። ጉባዔውም መሥዋዕቱንና የምስጋና መሥዋዕቱን አቀረቡ፤ ፈቃደኛ ልብ የነበራቸውም ሁሉ የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረቡ።
\s5
\v 32 ጉባዔው ያቀረቡት የሚቃጠል መሥዋዕት ቁጥር ሰባ ወይፈን፥ አንድ መቶ አውራ በጎችና ሁለት መቶ ወንድ ጠቦቶች ነበሩ። እነዚህ ሁሉ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ነበሩ።
\v 33 ለእግዚአብሔር የተቀደሱት እንስሳት ስድስት መቶ በሬዎችና ሦስት ሺህ በጎች ነበሩ።
\s5
\v 34 ነገር ግን ካህናቱ የሚቃጠሉትን መሥዋዕት ሁሉ ለመግፈፍ እጅግ ጥቂት ነበሩ፤ በመሆኑም ወንድሞቻቸው ሌዋውያኑ ሥራው እስኪጠናቀቅ ድረስ፥ ሌዋውያኑም ከካህናቱ ይልቅ ራሳቸውን ለመቀደስ ይበልጥ ጥንቁቅ ስለ ነበሩ ካህናቱ ራሳቸውን ለእግዚአብሔር እስኪቀድሱ ድረስ ረዷቸው።
\s5
\v 35 በተጨማሪም እጅግ ብዙ የሚቃጠሉ መሥዋዕቶች ነበሩ፤ ከሕብረት መሥዋዕት ስብ ጋር ይከናወኑም ነበር፤ ለእያንዳንዱም የሚቃጠል መሥዋዕት የመጠጥ መሥዋዕትም ነበር። በመሆኑም የእግዚአብሔር አገልግሎት በደንብ ተደራጅቶ ነበር።
\v 36 እግዚአብሔር ለሕዝቡ ካዘጋጀው ነገር የተነሳ ሥራው በፍጥነት በመከናወኑ ሕዝቅያስ ሕዝቡም ሁሉ ደስ አላቸው።
\s5
\c 30
\p
\v 1 ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር የፋሲካን በዓል ለማክበር ወደ ኢየሩሳሌም ወደ እግዚአብሔር ቤት እንዲመጡ ሕዝቅያስ ወደ እስራኤልና ይሁዳ ሁሉ መልዕክተኞችን ላከ፤ ወደ ኤፍሬምና ምናሴም ደብዳቤዎችን ጻፈ።
\v 2 ንጉሡ፥ መሪዎቹና የኢየሩሳሌሙ ጉባዔ ሁሉ በአንድነት ከተመካከሩ በኋላ ፋሲካውን በሁለተኛው ወር ለማክበር እየወሰኑ ነበር።
\v 3 ካህናቱ በበቂ ቁጥር ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ስላልቀደሱና ሕዝቡም ገና ወደ ኢየሩሳሌም በአንድነት ስላልተሰበሰበ ወዲያውኑ በዓሉን ሊያከብሩ አልቻሉም ነበር።
\s5
\v 4 ይህ እቅድ በንጉሡና በጉባዔው ሁሉ ፊት መልካም ሆኖ ታይቶ ነበር።
\v 5 በመሆኑም በመላው እስራኤል ከቤርሳቤህ እስከ ዳን የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን ፋሲካ በዓል በኢየሩሳሌም ለማክበር ሕዝቡ እንዲመጡ አዋጅ እንዲነገር ድንጋጌ አወጡ። በእርግጥም በጽሑፍ እንደታዘዘው በብዙ ቁጥር አላከበሩትም ነበር።
\s5
\v 6 በንጉሡ ትእዛዝ መልዕክተኞች ወደ መላው ይሁዳና እስራኤል ሁሉ የንጉሡንና የመሪዎቹን ደብዳቤ ይዘው ሄዱ። "እናንተ የእስራኤል ሰዎች ከአሦር ነገሥታት እጅ ወዳመለጠው ቅሬታችሁ እንዲመለስ ወደ አብርሃም፥ ይስሐቅና እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ።
\s5
\v 7 እንደምታዩት ለጥፋት አሳልፎ እስኪሰጣቸው ድረስ በአባቶቻቸው አምላክ በእግዚአብሔር ላይ እንደተላለፉት እንደ አባቶቻችሁ ወይም ወንድሞቻችሁ አትምሰሉ።
\v 8 አሁንም አባቶቻችሁ እንደነበሩት እናንተም አንገተ ደንዳና አትሁኑ። ይልቁንም ራሳችሁን ለእግዚአብሔር ስጡና የጋለ ቁጣው ከእናንተ እንዲመለስ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ለማምለክ ለዘላለም ለእግዚአብሔር ወደ ተሰጠው ቅዱስ ሥፍራው ኑ!
\v 9 አምላካችሁ እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ ስለሆነ ወደ እርሱ ብትመለሱ ፊቱን ከእናንተ ስለማይመልስ ወደ እግዚአብሔር ብትመለሱ ወንድሞቻችሁና ልጆቻችሁ እንደ እስረኛ በወሰዷቸው ሰዎች ፊት ሃዘኔታ ያገኛሉ። ወደዚህችም ምድር ይመለሳሉ።
\s5
\v 10 በመሆኑም መልዕክተኞቹ እስከ ዛብሎን ድረስ በመላው የኤፍሬምና የምናሴ ክልሎች ሁሉ ከከተማ ወደ ከተማ አለፉ፤ ሕዝቡ ግን ሳቁባቸው፤ አፌዙባቸውም።
\v 11 ነገር ግን የተወሰኑ የአሴርና የምናሴ የዛብሎንም ሰዎች ራሳቸውን አዋርደው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።
\v 12 በእግዚአብሔር ቃል የንጉሡንና የመሪዎቹን ትዕዛዝ ለመፈጸም አንድ ልብ ሊሰጣቸው የእግዚአብሔር እጅ በይሁዳ ላይም መጣ።
\s5
\v 13 በሁለተኛው ወር የቂጣውን በዓል ለማክበር ብዙ ሰዎች፥ እጅግ ታላቅ ጉባዔ ለማክበር በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ።
\v 14 ተነስተው በኢየሩሳሌም የነበሩትን መሠዊያዎችና ለጣዖታት የሚያጥኑበትን ማጠኛዎች ሁሉ አስወገዱ፤ ወደ ቄድሮን ወንዝም ጣሉአቸው።
\v 15 ከዚያም በሁለተኛው ወር በአሥራ አራተኛው ቀን የፋሲካውን ጠቦቶቹን አረዱ። ካህናቱና ሌዋውያኑ አፍረው ነበርና ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ሰጡ። ወደ እግዚአብሔርም ቤት የሚቃጠል መሥዋዕት አመጡ።
\s5
\v 16 በእግዚአብሔር ሰው በሙሴ ሕግ የተሰጠውን መመሪያ በመከተል በየሥራ ክፍላቸው በቦታቸው ቆሙ፤ ካህናቱም ከሌዋውያኑ እጅ የተቀበሉትን ደም ይረጩ ነበር።
\v 17 በጉባዔው ውስጥ ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ያልሰጡ እጅግ ብዙ ነበሩ፤ ስለዚህ ሌዋውያን ለእግዚአብሔር ጠቦቶቹን ለእግዚአብሔር ለመቀደስ ነጽተው ላልነበሩት ሰዎች ሁሉ የፋሲካውን ጠቦቶች የማረዱ ኃላፊነት የእነርሱ ነበር።
\s5
\v 18 እጅግ ብዙ ሰዎች ብዙዎቹም ከኤፍሬምና ከምናሴ፥ ከይሳኮርና ከዛብሎን በሕጉ መሠረት ራሳቸውን አላነጹም ነበር፤ ነገር ግን እንደ ተጻፈው ትዕዛዝ ባይሆንም የፋሲካውን ምግብ በሉ፤ ሕዝቅያስም ፦" ምንም እንኳን እንደ ቅዱሱ ሥፍራ የመንጻት መለኪያ መሠረት የነጻ ባይሆንም
\v 19 የአባቶቹን አምላክ እግዚአብሔር አምላክን ለመፈለግ በልቡ የቆረጠውን ሰው ሁሉ ቸሩ እግዚአብሔር ይቅር ይበለው" በማለት ፀልዮላቸው ነበር።
\v 20 እግዚአብሔርም ሕዝቅያስን ሰማው፤ ሕዝቡንም ፈወሰ።
\s5
\v 21 በኢየሩሳሌምም ተገኝተው የነበሩ የእስራኤል ሰዎች በታላቅ ደስታ የቂጣውን በዓል ለሰባት ቀናት አከበሩ። ሌዋውያኑና ካህናቱም ድምጹ በጎላ የሙዚቃ መሣሪያ ለእግዚአብሔር በመዘመር ከእለት ወደ እለት እግዚአብሔርን ያወድሱ ነበር።
\v 22 ሕዝቅያስም ለእግዚአብሔር የሚሰጠውን አገልግሎት ያስተዋሉትን ሌዋውያን ሁሉ በማበረታታት ተናገራቸው። በመሆኑም የሕብረት ሥጦታ መሥዋዕት እያቀረቡና ለአባቶቻቸው አምላክ ለእግዚአብሔር እየተናዘዙ በሰባቱ ቀናት በዓል ሁሉ ይመገቡ ነበር።
\s5
\v 23 ከዚያም መላው ጉባዔ ለሌላ ሰባት ቀናት በዓሉን ለማክበር ወሰኑ፤ እንደዚህም በደስታ አደረጉ።
\v 24 የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስ ለጉባዔው እንደ ሥጦታ ሰጥቶ ነበር፤ መሪዎቹም ለጉባዔው አንድ ሺህ ወይፈኖችና አሥር ሺህ በጎችና ፍየሎች ሰጡ። ብዙ ቁጥር ያላቸው ካህናትም ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ሰጥተው ነበር።
\s5
\v 25 የይሁዳ ጉባዔ ሁሉ ከካህናቱና ከሌዋውያኑ ጋር፥ ከእስራኤል በአንድነት የመጡት ሕዝብ ሁሉ፥ እንዲሁም ከእስራኤል ምድር እና በይሁዳ ይኖሩ ከነበሩት የመጡት እንግዶች ሁሉም ደስ አላቸው።
\v 26 በመሆኑም በኢየሩሳሌም ታላቅ ደስታ ነበር፤ ከእስራኤል ንጉሥ ከዳዊት ልጅ ከሰለሞን ጊዜ አንስቶ እንደዚህ ያለ ነገር በኢየሩሳሌም ምንም አልነበረም።
\v 27 ከዚያም ካህናቱ፥ ሌዋውያኑ ተነስተው ሕዝቡን ባረኩ፤ ድምጻቸውም ተሰማ፤ ፀሎታቸውም ወደ እግዚአብሔር ማደሪያ ቅዱስ ሥፍራ ወደ ሰማይ አረገ።
\s5
\c 31
\p
\v 1 ሁሉም ነገር ከተጠናቀቀ በኋላ እዚያ የተገኙት የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ወደ ይሁዳ ከተሞች ወጥተው የአምልኮ ድንጋይ ምሶሶዎችን ሰባበሩ፤ የማምለኪያ ዐፀዶቹን ቆረጡ፤ በይሁዳና በብንያም ሁሉ መስገጃዎችንና መሠዊያዎችን ሰባበሩ፤ ሁሉንም እስኪያጠፉ ድረስ ይህንኑ በኤፍሬምና በምናሴም ጭምር አደረጉት። ከዚያም የእስራኤል ሰዎች ሁሉ እያንዳንዱ ወደ ገዛ ምድሩና ወደ ገዛ ከተማው ተመለሰ።
\s5
\v 2 ሕዝቅያስም ካህናቱንና ሌዋውያኑን በየሥራ ክፍል በማደራጀት ለካህናቱና ለሌዋውያኑ ለእያንዳንዱ ሥራ በመስጠት በየአገልግሎታቸው መደባቸው። የሚቃጠል መሥዋዕትና የሕብረት መሥዋዕት እንዲያቀርቡ፥ እንዲያገለግሉ፥ እንዲያመሰግኑና በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በሮች እንዲያወድሱ መደባቸው።
\v 3 በእግዚአብሔር ሕግ ተጽፎ እንደነበረውም ለሚቃጠል መሥዋዕት ማለትም ለጠዋትና ለማታ የሚቃጠል መሥዋዕት፥ ለሰንበት ቀናት፥ ለመባቻዎቹና ለመደበኛ በዓላትም የሚቃጠል መሥዋዕት ከንጉሡ ከገዛ ራሱ ሃብት ድርሻውን መደበ።
\s5
\v 4 በተጨማሪም ካህናቱና ሌዋውያኑ የእግዚአብሔርን ሕግ በመታዘዝ ላይ እንዲያተኩሩ በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ሰዎች ለካህናቱና ሌዋውያኑ ድርሻቸውን እንዲሰጡ አዘዘ።
\v 5 ትእዛዙ እንደወጣም የእስራኤል ሕዝብ የእህሉን፥ የአዲሱን ወይን፥ የዘይቱን፥ የማሩን እንዲሁም ከእርሻው መከር ሁሉ በኩራት አትረፍርፈው ሰጡ፤ የሁሉንም ነገር አሥራትም አትረፍርፈው አመጡ።
\s5
\v 6 በይሁዳ ከተሞች የሚኖሩ የእስራኤልና የይሁዳ ሕዝብ የበሬዎቹንና በጎቹን አሥራት፥ ለአምላካቸው ለእግዚአብሔር የተሰጡ ነገሮችን ጭምር አሥራት አምጥተው ከምረው አስቀመጡት።
\v 7 በሦስተኛው ወር መከመር ጀምረው በሰባተኛው ወር ጨረሱ።
\v 8 ሕዝቅያስና መሪዎቹ መጥተው ክምሮቹን ሲያዩ እግዚአብሔርንና ሕዝቡን እስራኤልን ባረኩ።
\s5
\v 9 ሕዝቅያስም ካህናቱንና ሌዋውያኑን ስለ ክምሩ ጠየቀ።
\v 10 የሳዶቅም ቤት የሆነው ሊቀ ካህን ዓዛርያስ፦" ሕዝቡ ሥጦታዎቻቸውን ወደ እግዚአብሔር ቤት ማምጣት ከጀመሩ አንስቶ በልተናል፤ ጠግበናልም፤ እግዚአብሔርም ሕዝቡን ስለባረከ ብዙ ተርፎአል። የተረፈውም ነገር ይህ እዚህ ያለው ታላቅ መጠን ነው" ብሎ መልስ ሰጠ።
\s5
\v 11 ከዚያም ሕዝቅያስ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ መጋዘኖች እንዲዘጋጁ አዘዘ፤ እነርሱም አዘጋጇቸው።
\v 12 ሥጦታዎቹን፥ አሥራቱንና የእግዚአብሔር የሆኑትን ነገሮች በታማኝነት አመጡ። ሌዋዊው ኮናንያ የበላያቸው አስተዳዳሪ ነበር፤ ወንድሙም ሰሜኢ በደረጃ ከእርሱ ቀጥሎ ሁለተኛ ነበረ። በንጉሡም በሕዝቅያስና በእግዚአብሔር ቤት ላይ ባለ ሥልጣን በነበረው በዓዛርያስ የተሾሙ፥ ከኮናንያና ከወንድሙ ከሰሜኢ እጅ በታች
\v 13 ይሒዒል፥ ዓዛዝያ፥ ናሖት፥ አሣኤል፥ ይሬሞት፥ ዮዛባት፥ ኤሊኤል፥ ሰማኪያ፥ መሐት፥ በናያስ አስተዳዳሪዎች ነበሩ።
\s5
\v 14 ሌዋዊው የይምና ልጅ የምሥራቁ በር ጠባቂ ቆሬ ለእግዚአብሔር የተቀደሱትን ሥጦታዎችና በእግዚአብሔር የበጎ ፈቃድ ሥጦታዎች ላይ የበላይ ሆኖ ለእግዚአብሔር የቀረቡ ሥጦታዎችን ለማከፋፈል አዛዥ ነበር።
\v 15 ከበታቹም በካህናቱ ከተሞች ውስጥ ዔድን፥ ሚንያሚን፥ ኢያሱ፥ ሽማያ፥ አማርያና ሴኬንያ ነበሩ። እነዚህን ሥጦታዎች ለታላላቆቹና ለታናናሾቹ ወንድሞቻቸው እንደየሥራ ክፍላቸው ለመስጠት በመታመን ሥልጣን ተሰጣቸው።
\s5
\v 16 በዕለታዊ የጊዜ ሰሌዳ እንደሚጠበቅባቸው ወደ እግዚአብሔር ቤት የሚገቡ ሁሉ በቦታቸው ሆነው በየሥራ ክፍላቸው ሥራቸውን ለመሥራት በዘር ሐረጋቸው ተቆጥረው የነበሩ ሦስት ዓመትና ከዚያ በላይ ለሆኑ ወንዶችም ሰጡ።
\s5
\v 17 በቦታቸው ሆነው በየሥራ ክፍላቸው ሥራቸውን ለመሥራት በአባቶቻቸው ቤቶች በዘር ሐረጋቸው ተቆጥረው የነበሩ ሌዋውያን ሃያ ዓመትና ከዚያ በላይ ለሆኑትም ሰጡ።
\v 18 በዘር ሐረጋቸው ተቆጥረው ለነበሩ ለሕፃናቱ፥ ለሚስቶቻቸው፥ ለወንዶችና ለሴቶች ልጆቻቸው ሁሉ በመላው ሕዝብ መካከል በተቀደሰ ሁኔታ በአመኔታ ለተሰጣቸው ሥልጣን ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ስለቀደሱ ለእነርሱም ሰጡ።
\v 19 በየከተማቸው ወይም በከተሞቹ ሁሉ ባሉ መንደሮች መስኮች ላይ ለነበሩ ለአሮን ዝርያዎች በካህናቱ መካከል ለሁሉም ወንዶች በስማቸው ድርሻቸውን ለመስጠትና በሌዋውያን መካከል እንደሆኑ በትውልድ ሐረጋቸው ለተቆጠሩ ሁሉ የተመደቡላቸው ሰዎች ነበሩ።
\s5
\v 20 ሕዝቅያስም ይህንን በይሁዳ ሁሉ አደረገ። በእግዚአብሔር በአምላኩ ፊት መልካም፥ ትክክለኛና ታማኝ ነገርን አከናወነ።
\v 21 በእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት በጀመረው በየትኛውም ሥራ በሕጉና በትዕዛዛቱ አምላኩን ለመፈለግ በሙሉ ልቡ አከናወነው፤ እርሱም ተሳካለት።
\s5
\c 32
\p
\v 1 ከእነዚህ ነገሮችና ከእነዚህ የታማኝነት ድርጊቶች በኋላ የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም መጥቶ ወደ ይሁዳ ገባ፤ ለራሱ ሊይዛቸው ያሰባቸውን የተከበቡ ከተሞች ሊያጠቃ ሰፈረ።
\s5
\v 2 ሕዝቅያስም ሰናክሬም እንደ መጣ ኢየሩሳሌምንም ሊዋጋ እንዳሰበ ባየ ጊዜ
\v 3 ከከተማው በስተውጪ የነበሩትን የምንጭ ውሃዎች ለመድፈን ከመሪዎቹና ከኃያላን ሰዎቹ ጋር ተመካከረ፤ እነርሱም እንደዚህ ለማድረግ ረዱት።
\v 4 በመሆኑም በርካታ ሰዎች በአንድነት ተሰብስበው ምንጮቹን ሁሉና በምድሪቱ መካከል አልፎ ይፈስ የነበረውን ጅረት አስቆሙ። እነርሱም "የአሦር ነገሥታት መጥተው ለምን ብዙ ውሃ ያገኛሉ?" አሉ።
\s5
\v 5 ሕዝቅያስም ተደፋፈረና የፈረሰውን ቅጥር ሁሉ ጠገነ፤ እስከ ማማዎቹ ድረስ ሠራው፤ በስተውጪ ሌላ ግንብም ሠራ። በዳዊትም ከተማ ውስጥ የነበረችውን ሚሎንም አጠነከረ፤ ከፍተኛ መጠን ያላቸውን የጦር መሣርያዎችንና ጋሻዎችንም ሠራ።
\s5
\v 6 በሕዝቡ ላይም የጦር አዛዦችን አስቀመጠ። በአንድነትም በከተማይቱም በር በሰፊ ቦታ ወደራሱ ሰብስቦአቸው በማበረታታት ተናገራቸው።
\v 7 "በርቱ አይዞአችሁ። ከእርሱ ጋር ካሉት ከእኛ ጋር ያለው እርሱ እግዚአብሔር የሚበልጥ ስለሆነ ከአሦር ንጉሥና ከእርሱ ጋር ካለው ሠራዊት የተነሳ እንዳትፈሩ ወይም እንዳትደነግጡ።
\v 8 ከእርሱ ጋር ያለው የሥጋ ክንድ ብቻ ነው፤ ከእኛ ጋር ግን ሊረዳንና ጦርነታችንን ሊዋጋልን ያለው አምላካችን እግዚአብሔር ነው" አላቸው። ሕዝቡም በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ቃል ራሳቸውን አጽናኑ።
\s5
\v 9 ከዚህ በኋላ የሦርያ ንጉሥ ሰናክሬም (በዚህ ጊዜ በለኪሶ ፊት ለፊት ነበረ፤ ሠራዊቱም ሁሉ ከእርሱ ጋር ነበሩ) አገልጋዮቹን ወደ ኢየሩሳሌም ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ሕዝቅያስና በኢየሩሳሌም ወደነበሩት ወደ ይሁዳ ሁሉ ላከ፤
\v 10 "የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም የሚለው ይህንን ነው፦'በኢየሩሳሌም የተከበባችሁበትን ለመቋቋም የምትደገፉት በምን ላይ ነው?
\s5
\v 11 ሕዝቅያስ፦ 'አምላካችን እግዚአብሔር ከአሦር ንጉሥ እጅ ይታደገናል' ብሎ ሲነግራችሁ በረሃብና በጥማት እንድትሞቱ አሳልፎ ሊሰጣችሁ እያሳሳታችሁ አይደለምን?
\v 12 የኮረብታ መስገጃዎቹንና መሠዊያዎቹን ያስወገደና 'በአንድ መሠዊያ ላይ ታመልካላችሁ፤ በእርሱም ላይ መሥዋዕታችሁን ታቃጥላላችሁ' ብሎ ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን ያዘዘው ይኸው ሕዝቅያስ አይደለምን?
\s5
\v 13 እኔና አባቶቼ በሌሎች ምድሮች ሕዝቦች ሁሉ ላይ ያደረግነው ምን እንደሆነ አላወቃችሁምን? የእነዚህ ምድሮች ሕዝቦች አማልክት በየትኛውም መንገድ ምድራቸውን ከኃይሌ ሊታደጉ ችለው ነበርን?
\v 14 አባቶቼ ሙሉ በሙሉ ካጠፏቸው ከእነዚያ ሕዝቦች አማልክት ሁሉ መካከል ሕዝቡን ከእጄ መታደግ የቻለ አምላክ ነበርን? አምላካችሁስ እናንተን ከኃይሌ ሊታደጋችሁ እንዴት ይችላል?
\v 15 አሁንም ሕዝቅያስ በዚህ መንገድ አያታልልላችሁ ወይም አያሳምናችሁ። የየትኛውም ሕዝብ ወይም መንግሥት አማልክት ሕዝቡን ከእጄ ወይም ከአባቶቼ እጅ ሊታደግ ስላልቻለ አትመኑት። ይልቁንም አምላካችሁ ከእጄ እንዴት ሊያድናችሁ ይችላል?" አለ።
\s5
\v 16 የሰናክሬም አገልጋዮችም እግዚአብሔር አምላክና አገልጋዩ ሕዝቅያስ ላይ ይበልጥ የተቃውሞ ነገር ተናገሩ።
\v 17 ሰናክሬም በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ላይ ለማፌዝና እርሱንም በመቃወም ለመናገር ደብዳቤዎችንም ጻፈ። "የምድሪቱ ሕዝቦች አማልክት ሕዝባቸውን ከእጄ እንዳልታደጉ እንደዚሁ የሕዝቅያስም አምላክ ሕዝቡን ከእጄ አይታደግም" አለ።
\s5
\v 18 ከተማይቱን ለመያዝም በቅጥሩ ላይ የነበሩትን የኢየሩሳሌም ሰዎች ለማስፈራራትና ለማስጨነቅ በአይሁድ ቋንቋ በጎላ ድምጽ ይጮሁ ነበር።
\v 19 የሰዎች የእጅ ሥራ ብቻ በነበሩት በምድር ሌሎች ሕዝቦች አማልክት ላይ እንደተናገሩት በኢየሩሳሌም አምላክም ላይ ተናገሩ።
\s5
\v 20 ንጉሡ ሕዝቅያስና የአሞጽ ልጅ ነቢዩ ኢሳይያስ ከዚህ ጉዳይ የተነሳ ፀለዩ፤ ወደ ሰማይም ጮኹ።
\v 21 እግዚአብሔርም መልአክን ላከ፤ እርሱም ተዋጊዎቹን ሰዎች፥ አዛዦቹንና የንጉሡን ባለሥልጣናት በሰፈሩበት ቦታ ገደላቸው። በመሆኑም ሰናክሬም አፍሮ ወደ ገዛ ምድሩ ተመለሰ። ወደ አምላኩ ቤት በገባ ጊዜ እዚያ ከገዛ ራሱ ልጆች አንዳንዱ በሰይፍ ገደሉት።
\s5
\v 22 በዚህ መንገድ እግዚአብሔር ሕዝቅያስንና የኢየሩሳሌምን ነዋሪዎች ከአሦር ንጉሥ ከሰናክሬም እጅና ከሌሎች ሁሉ እጅ አዳናቸው፤ በሁሉም መንገድም መራቸው።
\v 23 በርካቶችም ለእግዚአብሔር ሥጦታዎችን፥ የከበሩ ነገሮችንም ለይሁዳ ንጉሥ ለሕዝቅያስ ወደ ኢየሩሳሌም ያመጡ ነበር። እርሱም ከዚያን ጊዜ አንስቶ በሕዝቦች ሁሉ ፊት ከፍ ከፍ አለ።
\s5
\v 24 በዚያን ወቅት ሕዝቅያስ ለመሞት እስኪቀርብ ድረስ ታምሞ ነበር። ወደ እግዚአብሔርም ፀለየ፤ እርሱም ተናገረው፤ እንደሚፈወስም ምልክትን ሰጠው።
\v 25 ሕዝቅያስ ግን ልቡ ታብዮ ስለ ነበር እግዚአብሔር ለሰጠው እርዳታ ውለታ ቢስ ሆነ። በመሆኑም በእርሱ፥ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ ቁጣ መጣባቸው።
\v 26 ቢሆንም ግን በኋላ ላይ ሕዝቅያስ ስለ ልቡ ትዕቢት እርሱና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ሁለቱም ራሳቸውን አዋረዱ። የእግዚአብሔርም ቁጣ በሕዝቅያስ ዘመን አልመጣባቸውም።
\s5
\v 27 ሕዝቅያስ እጅግ ብዙ ባለጠግነትና ብዙ ክብር ነበረው። ለራሱም ለብር፥ ለወርቅ፥ ለከበሩ ድንጋዮችና ለቅመማ ቅመሞች እንዲሁም ለጋሻዎችና ዋጋ ላላቸው ነገሮች ሁሉ መጋዘኖችን ሠራ።
\v 28 ለእህል፥ ለአዲስ ወይንና ዘይት መጋዘኖች፥ ለሁሉም ዓይነት እንስሳት ጋጣዎችም ነበሩት። በጋጣቸውም መንጋዎችም ነበሩት።
\v 29 በተጨማሪም እግዚአብሔር እጅግ ብዙ ሃብት ስለሰጠው ለራሱ ከተሞችን፥ የተትረፈረፉ የበጎችና የከብቶች መንጋዎች ንብረት አዘጋጀ።
\s5
\v 30 የግዮንን የላይኛውን ውሃ ምንጮች የደፈነና በዳዊትም ከተማ በምዕራብ በኩል በቀጥታ ቁልቁል እንዲመጡ ያደረጋቸው ይኸው ሕዝቅያስ ነው። ሕዝቅያስም በሠራው ሥራ ሁሉ ተሳካለት።
\v 31 ነገር ግን በምድሪቱ ስለተደረገው ተዓምራዊ ምልክት የሚያውቁ ሰዎችን ጥያቄ ለመጠየቅ የተላኩትን የባቢሎን መሳፍንት መልዕክተኞችን በተመለከተ ጉዳይ እግዚአብሔር ሊፈትነውና በልቡ ያለውን ለማወቅ ለራሱ ተወው።
\s5
\v 32 ሕዝቅያስን በተመለከተ ሌሎቹ ጉዳዮች የቃል ኪዳን ታማኝነት ድርጊቶቹን ጨምሮ በአሞጽ ልጅ በነቢዩ በኢሳይያስ ራዕይና በይሁዳና በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ መጻፋቸውን መመልከት ትችላላችሁ።
\v 33 ሕዝቅያስ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊትም ዝርያዎች መቃብር በኮረብታው ላይ ቀበሩት። የይሁዳና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ሁሉ በሞቱ ጊዜ አከበሩት። ልጁ ምናሴ በእርሱ ቦታ ነገሠ።
\s5
\c 33
\p
\v 1 ምናሴ መንገሥ በጀመረ ጊዜ አሥራ ሁለት ዓመቱ ነበር፤ በኢየሩሳሌም ሃምሳ አምስት ዓመት ነገሠ።
\v 2 እግዚአብሔር ከእስራኤል ሕዝብ ፊት እንዳስወጣቸው ሕዝቦች ዓይነት አስጸያፊ ነገር በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር አደረገ።
\v 3 አባቱም ሕዝቅያስ ያፈረሳቸውን የኮረብታውን መስገጃዎች እንደገና ገነባ፤ ለበኣልም መሠዊያዎችን ሠራ፤ የማምለኪያ ዐፀዶችንም አቆመ፤ ለሰማይም ከዋክብት ሁሉ ሰገደ፤ አመለካቸውም።
\s5
\v 4 ምንም እንኳን እግዚአብሔር፦ "ስሜ ለዘላለም የሚኖረው በኢየሩሳሌም ነው" ብሎ ያዘዘ ቢሆንም በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ለጣዖታት መሠዊያዎችን ገነባ።
\v 5 በእግዚአብሔር ቤት ሁለቱ አደባባዮች ውስጥ ለሰማይ ከዋክብት ሁሉ መሠዊያዎችን ሠራ።
\v 6 በሄኖም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ልጆቹን በእሳት ውስጥ እንደሚቃጠል መሥዋዕት አቀረበ፤ ሞራ ገላጭ ሆነ፤ አስማት አደረገ፤ መተተኛም ነበረ፤ ከሙታን ጋር ከሚነጋገሩና ከመናፍስት ጋር ከሚነጋገሩ ጋር ይማከር ነበር። በእግዚአብሔር ፊት እጅግ ክፋት በመለማመድ እግዚአብሔርን ለቁጣ አነሳሳ።
\s5
\v 7 የአሼራን የተቀረጸ ምስል ሠርቶ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ አኖረው፤ እግዚአብሔር ለዳዊትና ለልጁ ለሰለሞን ሲናገር፦" ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ ስሜ ለዘላለም እንዲኖርበት የመረጥኩት በዚህ ቤትና በኢየሩሳሌም ነው" ብሎ የነበረው ስለዚህ ቤት ነበር።
\v 8 በሙሴ አማካይነት የሰጠኋቸው ሕግ፥ ደንቦችና ድንጋጌዎች በመከተል ያዘዝኳቸውን ሁሉ ለመጠበቅ ቢጠነቀቁ ለአባቶቻቸው ከመደብኩላቸው ምድር የእስራኤልን ሕዝብ ከዚህ በኋላ አላወጣም" ብሎ ነበር።
\v 9 ምናሴም የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ነዋሪዎች እግዚአብሔር ከእስራኤል ሕዝብ ፊት ካጠፋቸው ሕዝቦች የበለጠ ክፋትን እንዲያደርጉ መራቸው።
\s5
\v 10 እግዚአብሔርም ምናሴንና ሕዝቡን ተናገራቸው፤ ነገር ግን አልሰሙትም።
\v 11 በመሆኑም የአሦርን ንጉሥ ሠራዊት አዛዦች አመጣባቸው፤ ምናሴንም በእግር ብረት ያዙት፤ በሰንሰለት አሰሩት፤ ወደ ባቢሎንም ወሰዱት።
\s5
\v 12 ምናሴ በተጨነቀ ጊዜ አምላኩን እግዚአብሔርን ተማፀነ፤ በአባቶቹም አምላክ ፊት ራሱን እጅግ አዋረደ።
\v 13 ወደ እርሱም ፀለየ፤ እግዚአብሔርም ተለመነው። እግዚአብሔር ልመናውን ሰምቶ ወደ ኢየሩሳሌም ወደ ንግሥናው መለሰው። ምናሴም እግዚአብሔር እርሱ አምላክ እንደሆነ አወቀ።
\s5
\v 14 ከዚህ በኋላ ምናሴ በዳዊት ከተማ በግዮን ምዕራብ በኩል በሸለቆው ውስጥ እስከ ዓሣው በር መግቢያ ድረስ የውጫዊውን ግንብ ገነባ። የኦፊልንም ኮረብታ በእርሱ ከበበው። ግንቡንም እጅግ ታላቅ ከፍታ ድረስ አነሳው። በተመሸጉት በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ደፋር አዛዦችን አኖረ።
\v 15 የባዕድ አማልክትን ጣዖቱንም ከእግዚአብሔር ቤት አስወገደ፤ በእግዚአብሔር ቤት ተራራ ላይና በኢየሩሳሌም ውስጥ የገነባቸውን መሠዊያዎች ከከተማው ውጪ ወረወራቸው።
\s5
\v 16 የእግዚአብሔርም መሠዊያ አደሰ፤ የሕብረት መሥዋዕትና የምሥጋናን መሥዋዕት ሥጦታዎች አቀረበበት፤ የይሁዳ ሕዝብ የእስራኤልን አምላክ እንዲያገለግሉ አዘዘ።
\v 17 ነገር ግን ሕዝቡ እስከ አሁንም በኮረብታው መስገጃዎች ላይ ይሰዋ ነበር፤ ነገር ግን ለአምላካቸው ለእግዚአብሔር ብቻ ነበር።
\s5
\v 18 ምናሴን የሚመለከቱት ሌሎች ነገሮች ወደ አምላኩ የፀለየው ፀሎትና በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ስም የተናገሩት የነቢያት ቃል እነሆ በእስራኤል ነገሥታት ድርጊቶች መካከል ተጽፈዋል።
\v 19 ፀሎቱም እግዚአብሔርም እንዴት እንደተለመነው፥ ኃጢአቱና መተላለፉ ሁሉ ራሱንም ከማዋረዱ በፊት የኮረብታ መስገጃዎች የገነባባቸው፥ የማምለኪያ አጸዶችንና የተቀረጹትን ምስሎች ያቆመባቸው ቦታዎች በባለ ራዕዮቹ ታሪክ መጽሐፍ ተጽፎአል።
\v 20 ምናሴም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በገዛ ራሱ ቤት ውስጥ ቀበሩት። ልጁም አሞጽ በእርሱ ቦታ ነገሠ።
\s5
\v 21 አሞጽ መንገሥ በጀመረ ጊዜ እድሜው ሃያ ሁለት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ሁለት ዓመት ነገሠ።
\v 22 አባቱ ምናሴ እንዳደረገ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር አደረገ። አሞጽ አባቱ ምናሴ ለሠራቸው ለተቀረጹ ምስሎች ሁሉ ሠዋ፤ አመለካቸውም።
\v 23 አባቱ ምናሴ እንዳደረገ በእግዚአብሔር ፊት ራሱን አላዋረደም። ይልቁንም ይኸው አሞጽ መተላለፉን ይበልጥ ጨመረው።
\s5
\v 24 አገልጋዮቹ በእርሱ ላይ አሲረው በገዛ ቤቱ ውስጥ ገደሉት።
\v 25 የምድሪቱ ሕዝብ ግን በንጉሡ በአሞጽ ላይ ያሴሩበትን ሰዎች ሁሉ ገደሉ፤ ልጁንም ኢዮስያስን በእርሱ ቦታ አነገሡት።
\s5
\c 34
\p
\v 1 ኢዮስያስ መንገሥ በጀመረ ጊዜ እድሜው ስምንት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ሠላሳ አንድ ዓመት ነገሠ።
\v 2 በእግዚአብሔር ፊት ትክክለኛውን ነገር አደረገ፤ በአባቱም በዳዊት መንገድ ሄደ፤ ከእርሱም ወደ ቀኝም ወደ ግራም አላለም።
\v 3 በነገሠም በስምንተኛው ዓመት ገና ወጣት እያለ የአባቱን የዳዊትን አምላክ መፈለግ ጀመረ። በአሥራ ሁለተኛው ዓመትም ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን ከኮረብታው መስገጃዎች፥ ከማምለኪያ ዐፀዶቹ፥ ከተቀረጹት ምስሎችና ቀልጠው ከተሠሩት ምስሎች ማጽዳት ጀመረ።
\s5
\v 4 ሕዝቡ የበኣሊምን መሠዊያዎች በእርሱ ፊት አፈረሱ፤ እርሱ ከበላያቸው የነበሩትን የዕጣን መሠዊያዎች ሰባበረ። የማምለኪያ ዐፀዶቹንም ሰባበረ፤ የተቀረጹትን ምስሎች፥ ቀልጠው የተሠሩትንም ምስሎች አፈር እስኪሆኑ ድረስ አደቀቃቸው። ትቢያውንም መሥዋዕት ይሰዉላቸው በነበሩ ሰዎች መቃብር ላይ በተነው።
\v 5 የካህናቶቻቸውንም አጥንቶች በመሠዊያቸው ላይ አቃጠለ። በዚህ መንገድ ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን አጸዳ።
\s5
\v 6 በምናሴ፥ በኤፍሬም፥ በስምዖን ከተሞችም እስከ ንፍታሌም ድረስና በዙሪያቸው ባሉት ፍርስራሾች ሁሉ ተመሳሳይ ነገር አደረገ።
\v 7 መሠዊያዎቹን አፈረሰ፤ የማምለኪያ ዐፀዶቹንና የተቀረጹትን ምስሎች አደቀቃቸው፤ በእስራኤል ምድር ሁሉ የዕጣን መሠዊያዎችን ሁሉ ቆራረጠ፤ ከዚያም ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ።
\s5
\v 8 ኢዮስያስ ምድሪቱንና ቤተ መቅደሱን ካጸዳ በኋላ በነገሠ በአሥራ ስምንተኛው ዓመት የኤዜልያስን ልጅ ሳፋን፥የከተማይቱንም ገዢ መፅሤያ፥ የታሪክ ጸሐፊውንም የኢዮአካዝን ልጅ ኢዮአክን የአምላኩን የእግዚአብሔርን ቤት እንዲያድሱ ላካቸው።
\v 9 እነርሱም ወደ ሊቀ ካህኑ ወደ ኬልቅያስ ሄደው ሌዋውያኑ፥ የበሮቹ ጠባቂዎች ከምናሴና ከኤፍሬም፥ ከእስራኤል ቅሬታዎች ሁሉ፥ ከይሁዳና ከብንያም ሁሉ፥ ከኢየሩሳሌምም ነዋሪዎች የሰበሰቡትን ወደ እግዚአብሔር ቤት የመጣውን ገንዘብ አደራ ሰጡት።
\s5
\v 10 ገንዘቡን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ሥራ በበላይነት ለሚቆጣጠሩት ሰዎች ሰጧቸው። እነዚህ ሰዎች ቤተ መቅደሱን ለሚጠግኑና ለሚያድሱ ሠራተኞች ከፈሏቸው።
\v 11 የተጠረበውን ድንጋይ፥ ለማጋጠሚያ ጣውላ እንጨትና አንዳንድ የይሁዳ ነገሥታት እንዲፈርስ ለተዉት መዋቅር ወራጆች እንዲገዙ ለአናጢዎቹና ግንበኞቹ ከፈሏቸው።
\s5
\v 12 ሰዎቹም ሥራውን በታማኝነት ሠሩ። ሥራውን በበላይነት የሚቆጣጠሯቸው ሌዋውያኑ ከሜራሪ ልጆች ኢኤትና አብድዩ፥ ከቀዓትም ልጆች ዘካርያስና ሜሱላም ነበሩ። ሁሉም መልካም የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዋቾች የነበሩ ሌሎች ሌዋውያንም ሠራተኞቹን በቅርበት አቅጣጫ ይመሯቸው ነበር።
\v 13 እነዚህ ሌዋውያን የግንባታ ዕቃ የሚሸከሙትንና በሌላም መንገድ የሚሠሩትን ሌሎች ሰዎች ሁሉ ይቆጣጠሩ ነበር። ጸሐፊዎች፥ አስተዳዳሪዎችና የበር ጠባቂዎች የነበሩ ሌሎች ሌዋውያንም ነበሩ።
\s5
\v 14 ወደ እግዚአብሔር ቤት የመጣውን ገንዘብ ወደ ውጪ ሲያመጡት ካህኑ ኬልቅያስ በሙሴ በኩል የተሰጠውን የእግዚአብሔርን ሕግ መጽሐፍ አገኘ።
\v 15 ኬልቂያስም ጸሐፊውን ሳፋንን፦" በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ የሕጉን መጽሐፍ አግኝቼአለሁ" አለው። ኬልቅያስም መጽሐፉን ወደ ሳፋን አመጣው።
\v 16 ሳፋንም መጽሐፉን ወደ ንጉሡ ወስዶ፦"አገልጋዮችህ በኃላፊነት የተሰጣቸው ማናቸውንም ነገር እያደረጉ ናቸው።
\s5
\v 17 በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ የተገኘውን ገንዘብ ወደ ውጪ አውጥተው ለተቆጣጣሪዎቹና ለሠራተኞቹ አደራ ሰጥተዋል" በማለት ነገረው።
\v 18 ጸሐፊውም ሳፋን ለንጉሡ ፦"ካህኑ ኬልቅያስ አንድ መጽሐፍ ሰጥቶኛል" ብሎ ነገረው። ከዚያም ለንጉሡ አነበበለት።
\v 19 ንጉሡ የሕጉን ቃላት በሰማ ጊዜ ልብሱን ቀደደ።
\s5
\v 20 ንጉሡም ኬልቅያስን፥ የሳፋንንም ልጅ አኪቃምን፥ የሚክያስንም ልጅ ዓብዶንን፥ ጸሐፊውንም ሳፋንን የራሱንም አገልጋይ ዓሳያን፦
\v 21 "ሄዳችሁ ከተገኘው መጽሐፍ ቃል የተነሳ ለእኔና በእስራኤልና በይሁዳ ለተረፉት ሰዎች የእግዚአብሔርን ፈቃድ ጠይቁ። በእኛ ላይ የፈሰሰው የእግዚአብሔር ቁጣ ታላቅ ስለሆነ፥ በውስጡ የተጻፈውን ሁሉ ለመታዘዝ አባቶቻችን የዚህን መጽሐፍ ቃላት ስላልሰሙ ቁጣው ታላቅ ነው።
\s5
\v 22 በመሆኑም ኬልቅያስና ንጉሡ ያዘዛቸው ሰዎች (በኢየሩሳሌም በሁለተኛው ክፍል ትኖር ወደ ነበረችው) ወደ ልብሰ ተክህኖ ጠባቂው ወደ ሐስራ ልጅ፥ ወደ ቲቁዋ ልጅ፥ ወደ ሴሌም ሚስት ወደ ነቢይቱ ወደ ሕልዳና ሄዱ፤ እንዲህም ብለው አናገሯት።
\s5
\v 23 እርሷም፦"የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የሚለው ይህንን ነው፦ወደ እኔ ለላካችሁ ሰው ንገሩት፥
\v 24 "እግዚአብሔር የሚለው ይህንን ነው፦ 'እነሆ በይሁዳ ንጉሥ ፊት ባነበቡት መጽሐፍ ውስጥ የተጻፉትን እርግማን ሁሉ በዚህ ቦታና በነዋሪዎቹ ላይ ጥፋትን ላመጣ ነው።
\v 25 ባደረጓቸው ተግባራት ሁሉ ለቁጣ ሊያነሳሱኝ እኔን ትተው ለሌሎች አማልክት ዕጣንን ከማጠናቸው የተነሳ ስለዚህ ቁጣዬ በዚህ ሥፍራ ላይ ይነድዳል፤ ምንም ነገርም አያቆመውም'" አለቻቸው።
\s5
\v 26 ነገር ግን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመጠየቅ ለላካችሁ ለይሁዳ ንጉሥ የምትሉት ይህ ነው፦" የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ስለ ሰማኸው ቃል፦
\v 27 ' ልብህ ለስላሳ ስለ ነበርና በዚህ ቦታና በነዋሪዎቹ ላይ እንደሚመጣ የተነገረውን ቃሉን ስትሰማ በእግዚአብሔር ፊት ራስህን ስላዋረድህ፥ ራስህንም በፊቴ አዋርደህ ልብስህንም ቀድደህ በፊቴ ስላለቀስህ እኔም ሰምቼሃለሁ' እግዚአብሔር የሚናገረው ይህ ነው፤
\v 28 'እነሆ ወደ ዝርያዎችህ እሰበስብሃለሁ፤ በሰላምም ወደ መቃብርህ ትሰበሰባለህ፤ በዚህ ቦታና በነዋሪዎቹ ላይ የማመጣውን የትኛውንም ጥፋት ዓይኖችህ አያዩም'" በመሆኑም ሰዎቹ ይህንን መልዕክት ለንጉሡ መልሰው ወሰዱለት።
\s5
\v 29 ከዚያም ንጉሡ መልዕክተኞችን ልኮ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ሽማግሌዎች ሁሉ በአንድነት ሰበሰበ።
\v 30 ንጉሡም የይሁዳ ወንዶችና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ሁሉ፥ ካህናቱም፥ ሌዋውያኑና ከትልቅ እስከ ትንሽ ሕዝቡ ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ቤት ወጡ። በእግዚአብሔርም ቤት የተገኘውን የቃል ኪዳኑን መጽሐፍ ቃል ሁሉ እየሰሙት አነበበላቸው።
\s5
\v 31 ንጉሡም በቦታው ቆሞ እግዚአብሔርን ተከትሎ ለመሄድ፥ ትዕዛዛቱን፥ የቃል ኪዳን ድንጋጌዎቹንና ደንቦቹን ለመጠበቅ፥ በሙሉ ልቡና በሙሉ ነፍሱ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የተጻፉትን የቃል ኪዳኑን ቃላት ለመታዘዝ በእግዚአብሔር ፊት ቃል ኪዳን አደረገ።
\v 32 በኢየሩሳሌምና በብንያም የሚገኙትን ሁሉ በቃል ኪዳኑ እንዲቆሙ አደረጋቸው። የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ለአባቶቻቸው አምላክ ለእግዚአብሔር ቃል ኪዳን በመታዘዝ አደረጉ።
\s5
\v 33 ኢዮስያስም የእስራኤል ሕዝብ ከነበረው ምድር ላይ አስጸያፊውን ነገር ሁሉ አስወገደ። በእስራኤልም የነበሩት ሰዎች ሁሉ አምላካቸው እግዚአብሔርን እንዲያመልኩ አደረጋቸው። በእርሱ ዘመን ሁሉ የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ከመከተል ዘወር አላሉም።
\s5
\c 35
\p
\v 1 ኢዮስያስ በኢየሩሳሌም ለእግዚአብሔር የፋሲካን በዓል አከበረ፤ በመጀመሪያው ወር በአሥራ አራተኛው ቀን የፋሲካ ጠቦቶቹን አረዱ።
\v 2 ካህናቱን በየሥራ ቦታቸው አድርጎ በእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት አበረታታቸው።
\s5
\v 3 እስራኤልንም ሁሉ ያስተምሩ ለነበሩት ለእግዚአብሔር ለተሰጡት ሌዋውያን ፦ "ቅዱሱን ታቦት የእስራኤል ንጉሥ የዳዊት ልጅ ሰለሞን በገነባው ቤት ውስጥ አስቀምጡት። ከዚህ በኋላ በትከሻችሁ እየተሸከማችሁ አታዟዙሩት፤ አሁንም አምላካችሁን እግዚአብሔርን አምልኩ፤ ሕዝቡንም እስራኤልን አገልግሉ።
\v 4 በእስራኤል ንጉሥ ዳዊት የተጻፈና በልጁም በሰለሞን ጭምር የተሰጠውን መመሪያ በመከተል በየአባቶቻችሁ ቤቶችና በየሥራ ክፍላችሁ ስም ራሳችሁን አደራጁ።
\s5
\v 5 በሕዝቡ ዝርያዎች በወንድሞቻችሁ የአባቶች ቤቶች ውስጥ በየሥራ ክፍላችሁ የኃላፊነት ቦታችሁን በመያዝና በሌዋውያን አባቶች ቤቶች ውስጥ በየሥራ ክፍላችሁ ቦታችሁን በመያዝ በተቀደሰው ሥፍራ ቁሙ።
\v 6 የፋሲካውን ጠቦቶች እረዱ፤ እናንተም ራሳችሁን ለእግዚአብሔር ስጡ። ለወንድሞቻችሁ ለእስራኤል ጠቦቶቹን ዝግጁ አድርጉላቸው፤ በሙሴ አማካይነት ለተሰጠው ለእግዚአብሔር ቃል በመታዘዝ አድርጉት።
\s5
\v 7 ኢዮስያስ ለፋሲካው መሥዋዕት እንዲሆን እዚያ ለነበሩት ሕዝብ ሁሉ ከመንጋው ሠላሳ ሺህ የበግና የፍየል ጠቦቶች ሰጠ። ሦስት ሺህ ወይፈኖችንም ሰጠ፤ እነዚህም የንጉሡ ኃብት ከነበሩት ነበሩ።
\v 8 መሪዎቹም ለህዝቡ፥ ለካህናቱና ለሌዋውያኑ የበጎ ፈቃድ ሥጦታዎችን ሰጡ። በእግዚአብሔር ቤት ባለሥልጣናት የነበሩት ኬልቅያስ፥ ዘካርያስና ይሒኤል ለፋሲካው መሥዋዕት እንዲሆን ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ትንንሽ ከብቶችና ሦስት መቶ በሬዎች ለካህናቱ ሰጡ።
\v 9 የሌዋውያኑ አለቆች ኮናንያ፥ ወንድሞቹም ሸማያና ናትናኤል፥ ሐሸቢያ፥ ይዒኤልና ዮዛባት ለፋሲካው መሥዋዕት አምስት ሺህ ትንንሽ ከብቶችና አምስት መቶ በሬዎች ለሌዋውያኑ ሰጡ።
\s5
\v 10 በመሆኑም አገልግሎቱ ዝግጁ ነበረ፤ ካህናቱም ለንጉሡ ትዕዛዝ ምላሽ በመስጠት በየሥራ ክፍላቸው ከሆኑት ከሌዋውያኑ ጋር በየቦታቸው ቆመው ነበር።
\v 11 የፋሲካ ጠቦቶቹንም አረዱ፤ ካህናቱም ከሌዋውያኑ እጅ የተቀበሉትን ደም ረጩ፤ ሌዋውያኑም የጠቦቶቹን ቆዳቸውን ገፈፉ።
\v 12 በሙሴ መጽሐፍ እንደተጻፈ ለእግዚአብሔር ለማቅረብና በሕዝቡ የአባቶች ቤቶች መሠረት በየሥራ ክፍላቸው ሊያድሏቸው የሚቃጠለውን መሥዋዕት ለይተው አስቀመጡ። በወይፈኖቹም ላይ እንደዚሁ አደረጉ።
\s5
\v 13 መመሪያዎቹን በመከተል የፋሲካውን ጠቦቶች በእሳት ጠበሷቸው። የተቀደሱትን ሥጦታዎች በምንቸቶች፥ በሰታቴዎችና በመጥበሻዎች ቀቀሏቸው፤ ለሕዝቡም ሁሉ በፍጥነት አዳረሷቸው።
\v 14 ከዚያም በኋላ ለራሳቸውና ለካህናቱም መሥዋዕቱን አዘጋጁ፤ የአሮን ልጆች ካህናቱ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና ስቡን በማቅረብ እስከ ምሽት ድረስ በሥራ ተጠምደው ስለነበር ሌዋውያኑ ለራሳቸውና ለአሮን ልጆች ለካህናቱ መሥዋዕቱን አዘጋጁ።
\s5
\v 15 ዳዊት፥ አሳፍ፥ ኤማንና የንጉሡ ባለ ራዕይ ኤዶታም በሰጡት መመሪያ መሠረት የአሳፍም ዝርያዎች መዘምራኑ በሥፍራቸው ቆመው ነበር። ጠባቂዎቹም በየበሮቹ ላይ ነበሩ፤ ወንድሞቻቸው ሌዋውያን መሥዋዕቱን ያዘጋጁላቸው ስለነበር የሥራ ቦታቸውን መልቀቅ አያስፈልጋቸውም ነበር።
\s5
\v 16 ስለዚህ ንጉሡ ኢዮስያስ ባዘዘው መሠረት በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ለማቅረብ፥ በዚያን ጊዜ መላው የእግዚአብሔር አገልግሎት የፋሲካን በዓል ለማክበር ተፈፀመ።
\v 17 በዚያን ቦታ ተገኝተው የነበሩ የእስራኤል ሕዝብ በዚያን ጊዜ ፋሲካውንና ከዚያም ለሰባት ቀናት የቂጣ በዓልን አከበሩ።
\s5
\v 18 ከነቢዩ ከሳሙኤል ዘመን ጀምሮ እንደዚህ ያለ የፋሲካ በዓል በእስራኤል ተከብሮ አያውቅም፤ ከእስራኤልም ሌሎች ነገሥታት ሁሉ የትኛውም ኢዮስያስ ከካህናቱ፥ ከሌዋውያኑና ከይሁዳና እዚያ ከነበሩ ከእስራኤል ሕዝብና ከኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ሁሉ ጋር እንዳደረገው ያለ ፋሲካ አክብሮ አያውቅም።
\v 19 ይህ ፋሲካ የተከበረው ኢዮስያስ በነገሠ በአሥራ ስምንተኛው ዓመት ነበር።
\s5
\v 20 ከዚህ ሁሉ በኋላ ኢዮስያስ ቤተ መቅደሱን ካስተካከለ በኋላ የግብጽ ንጉሥ ኒካዑ በኤፍራጥስ ወንዝ ከርከሚሽን ሊዋጋ ወጣ፤ ኢዮስያስም ሊዋጋው ሄደ።
\v 21 ኒካዑ ግን ወደ እርሱ ፦" የይሁዳ ንጉሥ ሆይ ካንተ ጋር ምን አለኝ? ጦርነት የምዋጋው በሌላ ቤት ላይ ነው እንጂ በአንተ ላይ ዛሬ ለጦርነት አልመጣሁብህም። እግዚአብሔር እንድፈጥን አዝዞኛል፤ ስለዚህ ከእኔ ጋር በሆነው በእግዚአብሔር ላይ ጣልቃ አትግባ፤ አለበለዚያ ያጠፋሃል" በማለት መልዕክተኞችን ላከበት።
\s5
\v 22 ነገር ግን ኢዮስያስ ከእርሱ መመለስን እምቢ አለ። ከእርሱ ጋር ለመዋጋት ራሱን በሌላ መልክ ሸፈነ። ከእግዚአብሔር አፍ የመጣውን የኒካዑን ቃል አልሰማም፤ ስለሆነም በመጊዶ ሸለቆ ውስጥ ሊዋጋ ሄደ።
\s5
\v 23 ቀስተኞችም ንጉሥ ኢዮስያስን ወጉት፤ ንጉሡም ለአገልጋዮቹ፦" ክፉኛ ቆስያለሁና ወደዚያ ውሰዱኝ" አላቸው።
\v 24 ስለዚህ አገልጋዮቹ ከሰረገላው አውርደው በሌላኛው ተጨማሪ ሰረገላ ውስጥ አስቀመጡት። ወደ ኢየሩሳሌምም ወሰዱት፤ በዚያም ሞተ። በአባቶቹም መቃብር ተቀበረ። ይሁዳና ኢየሩሳሌም ሁሉ ለኢዮስያስ አለቀሱለት።
\s5
\v 25 ኤርምያስም ለኢዮስያስ የሐዘን እንጉርጉሮ አወጣለት፤ እስከ ዛሬም ድረስ ውንዶችና ሴቶች መዘምራን ሁሉ ስለ ኢዮስያስ የሐዘን እንጉርጉሮ ያወጣሉ። እነዚህ መዝሙሮች በእስራኤል ልማድ ሆኑ፤ እነሆ በሐዘን እንጉርጉሮ መዝሙር ውስጥ ተጽፈዋል።
\s5
\v 26 ኢዮስያስን በተመለከተ ሌሎቹ ጉዳዮችና በእግዚአብሔር ሕግ ለተጻፈው ነገር በመታዘዝ ያደረጋቸው መልካም ድርጊቶች፥
\v 27 የእርሱ ድርጊቶች ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ በይሁዳና በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፈዋል።
\s5
\c 36
\p
\v 1 የምድሪቱም ሰዎች የኢዮስያስን ልጅ ኢዮአክስን ወስደው በአባቱ ቦታ በኢየሩሳሌም አነገሡት።
\v 2 ኢዮአክስም መንገሥ በጀመረ ጊዜ ሃያ ሦስት ዓመቱ ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሦስት ወር ነገሠ።
\s5
\v 3 የግብጽ ንጉሥ ከኢየሩሳሌም ከመንግሥቱ አስወገደው፤ ምድሩንም አንድ መቶ መክሊት ብርና አንድ መቶ መክሊት ወርቅ ቅጣት ጣለባት።
\v 4 የግብጽ ንጉሥ ወንድሙን ኤልያቄምን በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ ንጉሥ አደረገው፤ ስሙንም ኢዮአቄም ብሎ ለወጠው። የኤልያቄምን ወንድሙን ኢዮአክስን ወሰደና ወደ ግብጽ አመጣው።
\s5
\v 5 ኢዮአቄም መንገሥ በጀመረ ጊዜ ሃያ አምስት ዓመቱ ነበር፤ በኢየሩሳሌምም አሥራ አንድ ዓመት ነገሠ። በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት ክፉውን ነገር አደረገ።
\v 6 ከዚያም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ጦርነት ከፍቶበት በሰንሰለት አስሮ ወደ ባቢሎን ወሰደው።
\v 7 ናቡከደነፆር ከእግዚአብሔር ቤት ዕቃዎችም አንዳንዶቹን ወደ ባቢሎን ወሰደ፤ በባቢሎንም በቤተ መንግሥቱ ውስጥ አስቀመጣቸው።
\s5
\v 8 ኢዮአቄምን በተመለከተ ሌሎቹ ጉዳዮችና ያደረጋቸው አስጸያፊ ድርጊቶች፥ በእርሱ ላይ በክፉነት የተያዙበት ድርጊቶች እነሆ በይሁዳና በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፈዋል። ልጁም ዮአኪን በእርሱ ቦታ ነገሠ።
\s5
\v 9 ዮአኪን መንገሥ በጀመረ ጊዜ ስምንት ዓመቱ ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሦስት ወርና አሥር ቀን ነገሠ። በእግዚአብሔር ፊት ክፉውን ነገር አደረገ።
\v 10 በፀደይ ወራት ንጉሥ ናቡከደነፆር ሰዎችን ልኮ ከእግዚአብሔር ቤት ከተወሰዱ የከበሩ ነገሮች ጋር ወደ ባቢሎን አመጣው፤ ዘመዱንም ሴዴቅያስን በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ አነገሠው።
\s5
\v 11 ሴዴቅያስ መንገሥ በጀመረ ጊዜ ሃያ አንድ ዓመቱ ነበር፤ በኢየሩሳሌምም አሥራ አንድ ዓመት ነገሠ።
\v 12 በእግዚአብሔር በአምላኩ ፊት ክፉውን ነገር አደረገ። ከእግዚአብሔርም አፍ በተናገረው በነቢዩ በኤርምያስ ፊት ራሱን አላዋረደም።
\s5
\v 13 ሴዴቅያስም ታማኝ እንዲሆንለት በእግዚአብሔር እንዲምል ባደረገው በንጉሡ በናቡከደነፆር ላይ አመፀ። ሴዴቅያስ ግን ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር ላለመመለስ አንገቱን አደነደነ፤ ልቡንም አጠነከረ።
\v 14 በተጨማሪም የካህናቱ መሪዎችና ሕዝቡ የሌሎችን ሕዝቦች አስፀያፊ ነገሮች ምሳሌነት በመከተል እጅግ በጣም መተላለፍ አበዙ። እግዚአብሔር ለራሱ በኢየሩሳሌም የቀደሰውን የእግዚአብሔርን ቤት በከሉት።
\s5
\v 15 የአባቶቻቸው አምላክ እግዚአብሔር ለሕዝቡና ለማደሪያው ሥፍራ ከመራራቱ የተነሳ ደግሞ ደጋግሞ በመልዕክተኞቹ በኩል ቃል ይልክላቸው ነበር።
\v 16 እነርሱ ግን የእግዚአብሔር ቁጣ በሕዝቡ ላይ እስኪነሳ ድረስ፥ መሸሻ መንገድ እስከማይኖር ድረስ የእግዚአብሔርን መልዕክተኞች ይሳለቁባቸው፥ ቃሉንም ያቃልሉና በነቢያቱም ላይ ያፌዙ ነበር።
\s5
\v 17 ስለዚህም እግዚአብሔር የከለዳውያንን ንጉሥ አመጣባቸው፤ እርሱም በቤተ መቅደሱ ውስጥ ወጣቶቻቸውን በሰይፍ ገደላቸው፤ ለወጣቶቻቸው ወይም ለደናግልቱ፥ ለሽማግሌዎች ወይም ለሸበቶዎች አልራራም። እግዚአብሔር ሁሉንም በእጁ አሳልፎ ሰጠው።
\s5
\v 18 የእግዚአብሔርንም ቤት እቃዎች ሁሉ ትልልቁንም ትንንሹንም የእግዚአብሔርንም ቤት ሃብትና የንጉሡንና የመሪዎቹን ሃብት እነዚህን ሁሉ ወደ ባቢሎን ወሰደ።
\v 19 የእግዚአብሔርን ቤት አቃጠሉ፤ የኢየሩሳሌምን አጥር አፈረሱ፤ ቤተ መንግሥቶቹን ሁሉ አቃጠሉ፤ በውስጧ ያሉትን ውብ ነገሮች ሁሉ አጠፉ።
\s5
\v 20 ከሰይፍም ያመለጡትን ንጉሡ ወደ ባቢሎን አጋዛቸው። የፋርስ መንግሥት አገዛዝ እስኪደርስ ድረስ ለእርሱና ለልጆቹ አገልጋዮች ሆኑ።
\v 21 ይህ የሆነው ምድሪቱ የሰንበት እረፍትዋን እስክታገኝ ድረስ በነቢዩ በኤርምያስ አፍ የተነገረውን የእግዚአብሔር ቃል እንዲፈፀም ነው። በዚህ መንገድ ሰባ ዓመት በማሳለፍ ተትታ በነበረበት ጊዜ ሁሉ ሰንበቷን አከበረች።
\s5
\v 22 በኤርምያስ አፍ የተነገረው የእግዚአብሔር ቃል እንዲፈፀም በፋርስ ንጉሥ በቂሮስ በመጀመሪያው ዓመት እግዚአብሔር የፋርስን ንጉሥ የቂሮስን መንፈስ አነሳሳ። እርሱም በመንግሥቱ ሁሉ አዋጅ አስነገረ፤ በጽሑፍም አደረገው።
\v 23 "የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ የሚለው ይህ ነው፦ 'የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር የምድርን መንግሥታት ሁሉ ሰጥቶኛል፤ በይሁዳም ባለችው በኢየሩሳሌም ለእርሱ ቤት እንድሠራለት አዝዞኛል። በመካከላችሁ ከእርሱ ሕዝብ መካከል ማንም ቢሆን አምላካችሁ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ይሁን፤ እርሱም ወደ ምድሪቱ ይውጣ" አለ።