am_ulb/13-1CH.usfm

1787 lines
166 KiB
Plaintext

\id 1CH
\ide UTF-8
\h 1ኛ ዜና
\toc1 1ኛ ዜና
\toc2 1ኛ ዜና
\toc3 1ch
\mt 1ኛ ዜና
\s5
\c 1
\p
\v 1 አዳም፣ ሴት፣ ሄኖስ፣
\v 2 ቃይናን፣ መላልኤል፣ ያሬድ፣
\v 3 ሄኖክ፣ ማቱሳላ፣ ላሜሕ፣ኖኅ።
\v 4 የኖኅ ወንዶች ልጆች፤ ሴም፣ካምናያፌት።
\s5
\v 5 የያፌት ወንዶች ልጆች፤ ጋሜር፣ማጎግ፣ማዴ፣ያዋን፣ቶቤል፣ሞሳሕ፣ቴራስ።
\v 6 የጋሜር ወንዶች ልጆች፤ አስከናዝ፣ሪፋት፣ቴርጋማ።
\v 7 የያዋን ወንዶች ልጆች፤ ኤሊሳ፣ተርሴስ፣ኪቲም፣ሪድኢ።
\s5
\v 8 የካም ወንዶች ልጆች፤ ኪሽ፣ ምፅራይም፣ ፋጥናከነዓን።
\v 9 የኩሽ ወንዶች ልጆች፤ ሳባ፣ ኤውላጥ፣ ሰብታ፣ ራዕማናሰብቃታ። ያራዕማ ወንዶች ልጆች፤ ሳባናድዳን ነበሩ።
\v 10 ኩሽ ናምሩድን ወለደ፤ እርሱም በምድር ላይ የመጀመሪያው ኅያል ጦረኛ ሆነ።
\s5
\v 11 ምፅራይም የሉዲማውያን፣ የዐናማውያን፣ የላህባማውያን፣ የነፍተሂማውያን፣
\v 12 የፈትሩሲማውያን፣ የፍልስጥኤማውያን ቅድመ አባቶች የሆኑት የከስሉሂማውያንና የከፍቶሪማውያን ነገዶች አባት ነው።
\s5
\v 13 ከነዓን የበኩር ልጁ የሆነው የሶዶን እንዲሁም የከጢያውያን፣
\v 14 የኢያቡሳውያን፣
\v 15 የኤዊውያን፣ የዐርካውያን፣
\v 16 የሲኒውያን፣ የአራዴዎውያን፣ የሰማርያውያን፣ የአማቲያውያን አባት ነው።
\s5
\v 17 የሴም ወንዶች ልጆች፤ ኤላም፣ አሦር፣ አርፋክስድ፣ ሉድ፣ አራም። የአራም ወንዶች ልጆች፤ ዑፅ፣ ሁል፣ ጌቴር፣ ሞሳሕ።
\v 18 አርፋክስድ ሳላን ወለደ።
\v 19 ዔርቦ ወንዶች ልጆች ወለደ፤ በዘመኑ ምድር ስለተከፈለች፣ የአንደኛው ስም ፋሌቅ ተብሎ ተጠራ፣
\s5
\v 20 ዮቅጣንም፡ አልሞዳድን፣ ሣሌፍን፣ ሐስረሞትን፣ ያራሕን፣
\v 21 ሀዶራምን፣አውዛልን፣ደቅላን፣
\v 22 ዖባልን፣ አቢማኤልን፣ ሳባን፣
\v 23 ኦፋርን፣ ኤውላጥን፣ ዮባብን ወለደ፤ እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ወንዶች ልጆች ናቸው።
\s5
\v 24 ሴም፣ አርፋክስድ፣ ሳለ፣
\v 25 ዔቦር፣ ፋሌቅ፣ ራግው፣
\v 26 ሴሮህ፣ ናኮር፣ ታራ፣
\v 27 እንዲሁም በኋላ አብርሃም የተባለ አብራም።
\s5
\v 28 የአብርሃም ወንዶች ልጆች፤ይስሐቅና እስማኤልሲሆኑ።
\v 29 የእነዚህ ዘሮች የሚከተሉት ናቸው፤ የእስማኤል በኩር ልጅ ነባዮት፣ ቄዳር፣ ነብ፣ ዳኤል፣ መብሳም፣
\v 30 ማስማዕ፣ ዱማ፣ ማሣ፣ ኩዳን፣ ቴማን፣
\v 31 ኢጡር፣ ናፌስ፣ ቄድማ፣ እነዚህ የእስማኤል ወንዶች ልጆች ናቸው።
\s5
\v 32 የአብርሃም ቁባት ኬጡራ የወለደቻቸው ወንዶች ልጆች ዘምራን፣ ዮቅሳን፣ ሜዳን፣ ምድያም፣ የስቦቅና፣ ስዌሕ ናቸው። የዮቅሳን ወንዶች ልጆች፤ ሳባ፣ ድዳን፣
\v 33 የምድያም ወንዶች ልጆች፤ ጌፈር፣ ዔፌር፣ ሄኖኅ፣ አቢዳዕ፣ ኤልዳዓ፣ እነዚህ ሁሉ የኬጡራ ዘሮች ናቸው።
\s5
\v 34 አብርሃም ይስሐቅን ወለደ። የይስሐቅ ወንዶች ልጆች፤ ዔሳው፣ እስራኤል።
\v 35 የዔሳው ወንዶች ልጆች፤ ኤልፋዝ፣ ራጉኤል፣ የዑስ፣ የዕላም፣ ቆሬ።
\v 36 የኤልፋዝ ወንዶች ልጆች ቴማር፣ ኦማር፣ ሰፎ፣ ጎቶም፣ ቄኔዝ፣ ቲምናዕ፣ አማሌቅ።
\v 37 የራጉኤል ወንዶች ልጆች፤ ናሖት፣ ዛራ፣ ሣማ፣ ሚዛህ።
\s5
\v 38 የሴይር ወንዶች ልጆች፤ ሎጣን፣ ሦባል፣ ጽብዖን፣ ዓና፣ ዲሶን፣ ኤጽር፣ ዲሳን።
\v 39 የሎጣን ወንዶች ልጆች፤ ሖሪ፣ ሄማም፣ ቲሞናዕ፣ የሎጣን፣ እኅት ነበረች።
\v 40 የሦባል ወንዶች ልጆች፤ ዓልዋን፣ ማኔሐት፣ ዔናል፣ ስፎ፣ አውናም። የጽብዖን ወንዶች ልጆች፤ አያ፣ ዓና።
\s5
\v 41 የዓና ወንድ ልጅ፤ ዲሶን። የዲሶን ወንዶች ልጆች፤ ሔምዳን፣ ኤስባን፣ ይትራን፣ ክራን።
\v 42 የኤጽር ወንዶች ልጆች፤ ቢልሐን፣ ዛዕዋን፣ ዓቃን። የዲሳን ወንዶች ልጆች፤ ዑፅ፣ አራን።
\s5
\v 43 በእስራኤል አንድም ንጉሥ ገና ሳይነግሥ በኤዶም ምድር የነገሡ ነገሥታት እነዚህ ናቸው። የቢዖር ልጅ ባላቅ፤ ከተማይቱም ዲንሃባ ትባል ነበር።
\v 44 ባላቅ ሲሞትም የባሳራ ሰው የሆነው የዛራ ልጅ ኢዮባብ በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።
\v 45 ኢዮባብ ሲሞት የቴማን አገር ሰው የሆነው ሑሳም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።
\s5
\v 46 ሑሳም ሲሞት በሞዓብ ምድር ምድያ ምን ድል ያደረገው የባዳድ ልጅ በእግሩ ተተክቶ ነገሠ። የከተማይቱም ስም ዓዊት ተባለ።
\v 47 ሃዳድም ሲሞት የመሥሬቃ ሰው የሆነው ሠምላ በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።
\v 48 ሠምላም ሲሞት በወንዙ አጠገብ ያለችው የረኆቦት ሰው የሆነው ሳኡል በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።
\s5
\v 49 ሳኡልም ሲሞት የዓክቦል ልጅ የሆነው በኣልሕናንም ሲሞት በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።
\v 50 በኣልሐናን ሲሞት ሀዳድ በእግሩ ተተክቶ ነገሠ። ከተማው ፋዑ ትባል ነበር፤ ሚስቱ መሄጣብኤል ትባልላለች፤ እርሷም የሜዛሃብ ልጅ የመጥሬድ ልጅ ነበረች።
\s5
\v 51 ሀዳድም ሞተ። ዋና ዋናዎቹ የኤዶም ሕዝብ አለቆች እነዚህ ነበሩ፤ ቲምናዕ፣ ዓልዋ፣ የቴት፣
\v 52 አህሊባማ፣ ኤላ፣ ፊኖን፣ ቄኔዝ፣ ቴማን፣ ሚብሳር፣
\v 53 ቄኔዝ፣ ቴማን፣ ሚብሳር፣
\v 54 መግዲኤል፣ ዒራም። እነዚህ የኤዶም አለቆች ነበሩ።
\s5
\c 2
\p
\v 1 የእስራኤል ወንዶች ልጆች እነዚህ ነበሩ፤ ሮቤል፣ ስምዖን፣ ሌዊ፣ ይሁዳ፣ ይሳኮር፣ ዛብሎን፣
\v 2 ዳን፣ ዮሴፍ፣ ብንያም፣ ንፍታሌም፣ ጋድ፣ እሴር።
\s5
\v 3 የይሁዳ ወንዶች ልጆች፤ ዔር፣ አውናን፣ ሴሎም፣ እነዚህን ጆስቱን ከከነዓን ሚስቱ ከሴዋ ወለደ። የበኩር ልጁ ዔር በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሰው ሆነ፤ እግዚአብሔር ቀፈፈው።
\v 4 የልጁም ሚስት የነበረችው ትዕማር ፋሬስንና ዛራን ወለደችለት፤ ይሁዳም ባጠቃላይ አምስት ወንዶች ልጆች ነበሩት።
\s5
\v 5 የፋሬስ ወንዶች ልጆች፤ ኤስሮም፣ ሐሙል።
\v 6 የዛራ ወንዶች ልጆች፤ ዘምሪ፣ ኤታን፣ ሄማን፣ ከልኮል፣ ዳራ፣ ባጠቃላይ አምስት ናቸው።
\v 7 የከሚር ወንድ ልጅ አካን፤ እርሱም ፈፅሞ መደምሰስ የነበረበት ነገር ሰርቆ በእስራኤል ላይ ጥፋት እንዲመጣ ያደረገ ነው።
\v 8 የኤታን ወንድ ልጅ፤ አዛርያ።
\s5
\v 9 የኤስሮን ወንዶች ልጆች፤ ይረሕምል፣አራም፣ካሌብ።
\v 10 አራም አሚናዳብን ወለደ፤አሚናዳብም የይሁዳ ሕዝብ መሪ የሆነውን ነአሶንን ወለደ፤
\v 11 ነአሶን ሰልሞንን ወለደ፤ሰልሞን ቦዔንን ወለደ።
\v 12 ቦዔዝ ኢዮቤድን ወለደ፤ኢዮብይድ እሴይን ወለደ።
\s5
\v 13 የእሴይ ወንዶች ልጆች፤ የብኩር ልጁ ኤልያብ፣ ሁለተኛ ልጁ አሚናዳብ፣ ሦስተኛ ልጁ ሣማ፣
\v 14 አራተኛው ልጁ ናትናኤል፣ አምስተኛ ልጁ ራዳይ፣
\v 15 ስድስተኛ ልጁ አሳም፣ ሰባተኛ ልጁ ዳዊት።
\s5
\v 16 እኅቶቻቸውም ጽሩያና አቢግያ ነበሩ። የጹሩያ ሦስት ወንዶች ልጆች አቢሳ፣ ኢዮአብና አሣኤል ነበሩ።
\v 17 አቢግያ አሜሳይን ወለደች፣ አባቱም ዬቴር የተባለ እስማኤላዊ ነበረ።
\s5
\v 18 የኤስሮም ልጅ ካሌብ ከሚስቱ ከዓዙባና እንዲሁም ከይሪዖት ወንዶች ልጆች ወለደ፥ ከዓዜባ የተወለዱት ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው። ያሳብ፣ ሶባብ፣ አርዶን፣
\v 19 ዓዙባ ስትሞት፣ ካሌብ ኤፍራታን አገባ፤ እርሷም ሆርን ወለደችለት።
\v 20 ሆርኡሪን ወለደ፤ ኡሪም ባስልኤልን ወለደ።
\s5
\v 21 ከዚህም በኋላ ኤስሮም ሥልሳ ዓመት ሲሆነው የገለዓድን አባት የማኪርን ልጅ አገባ፤ እርሷም ሠጉብን ወለደችለት።
\v 22 ሠጉብም ኢያዕርን ወለድደ፤ እርሱም በገለዓድ ምድር ሃያ ሦስት አተሞች ያስተዳድር ነበር።
\s5
\v 23 ይሁን እንጂ ጌሹና አራም፣ ቄናትንና በዙሪያዋ የሚገኑትን ሥልሳ መነደሮች ጨምሮ የኢያዕርን ከተሞች ነጠቁት። እነዚህ ሁሉ የገለዓድ አባትየማኪር ዘሮች ነበሩ።
\v 24 ኤስሮም በካሌብ ኤፍራታ ከሞተ በኋላ፣ ሚስቱ አቢያ የቴቁሔን አባት አሽሑርን ወለደችለት።
\s5
\v 25 የኤስሮም የበኩር ልጅ የይረሕምኤል ወንዶች ልጆች፤ የበኩር ልጁ ራም፣ ቡናህ፣ ኦሬን፣ ኦጼን፣ አኪያ።
\v 26 ይረሕምኤል ዓጣራ የተባለች ሌላ ሚስት ነበረችው፤ እርሷም የኦናምን እናት ነበረች።
\v 27 የይረሕምኤል የበኩር ልጁ የራም ወንዶች፤ መዓስ፣ ያሚን፣ ዔቄር።
\v 28 የኦናም ወንዶች ልጆች፤ ሸማይና ያዳ። የሸማይ ወንዶች ልጆች፤ ናዳብና አቢሱር።
\s5
\v 29 የአቢሱር ሚስት አቢካኢል ትባላለች፤ እርሷም አሕባንንና ሞሊድ የተባሉ ልጆች ወለደችለት።
\v 30 የናባድ ወንዶች ልጆች፤ ሴሌድ፣አፋይም፣ሴሌድ፣ወንድ ልጅ ሳይወልድ ሞተ።
\v 31 የአፋይም ወንድ ልጅ፤ይሸዒ።ይሽዒም ሶሳን ወለደ።ሶሳን አሕልይን ወለደ።
\v 32 የሸማይ ወንድም የያዳ ወንዶች ልጆች፤ዬቴር፣ዮናታን፣ዬቴርም ልጅ ሳይወልድ ሞተ።
\v 33 የዮናታን ወንዶች ልጆች፤ፌሌት፣ዛዛ። እነዚህ የይረሕምኤል ዘሮች ነበሩ።
\s5
\v 34 ሶሳን ሴቶች እንጂ ወንዶች ልጆች አልነበሩትም። እርሱም ኢዮሄል የተባለ ግብፃዊ አገልጋይ ነበርረው።
\v 35 ሶሳን ልጁን ለአገልጋዩ ለኢዮሄል ሚስት ትሆነው ዘንድ ሰጠው፤ እርሷም ዓይታ የተባለ ወንድ ልጅ ወለደችለት።
\s5
\v 36 ዓታይ ናታንን ወለደ፣ናታንም ዛባድን ወለደ፣
\v 37 ዛባድ ኤፍላን ወለደ፤ ኤፍላል ዖቤድን ወለደ፤
\v 38 ዖቤድ ኢዩን ወለደ፤ ኢዩ ዓዛርያስን ወለደ፤
\s5
\v 39 ዓዛርያስ ኬሌስን ወለደ፤ ኬሌስ ኤልዓሣ ወለደ፤
\v 40 ኤልዓሣ ሲስማይን ወለደ፤ ሲስማይ ሰሎምን ወለደ፤
\v 41 ሰሎም የቃምያን ወለደ፤ የቃምያም ኤሊሳማን ወለደ።
\s5
\v 42 የይረሕምኤል ወንድም የካሌብ ወንዶች ልጆች፤ የበኩር ልጁ ሞሳ ሲሆን፤ እርሱም ዚፍን ወለደ፤ ዚፍም መሪሳን ወለደ፤ መሪ ሳም ኬብሮንን ወለደ።
\v 43 የኬብሮን ወንዶች ልጆች፤ ቆሬ፣ ተፋዋ፣ ሬቄም፣ ሽማዕ።
\v 44 ሽማዕ ርችሐምን ወለደ፤ ረሐምም ዮርቅዓምን ወለደ። ሬቄም ሽማይን ወለደ፤
\s5
\v 45 ሽማይም ማዖንን ወለደ፤ ማዖንም ቤት ጹርን ወለደ።
\v 46 የካሌብ ቁባት ዔፋ ሐራንን፣ ሞዳን፣ ጋዜዝን ወለደች። ሐራንም ጋዜዝን ወለደ።
\v 47 የያህዳይ ወንዶች ልጆች፤ ሬጌም፣ ኢዮታም፣ ጌሻን፣ ፋሌጥ፣ ዔፋ፣ ሸዓፍ።
\s5
\v 48 የካሌብ ቁባት ማዕካ ሼቤርን፣ ቲርሐናን ወለደለችለት።
\v 49 እንዲሁም የመድማናን አባት ሸዓፍን፣ የመክቢናንና የጊብዓን አባት ሱሳን ወለደች። ካሌብ ዓክሳ የተባለች ልጅ ነበረችው።
\v 50 የኤፍራታ የበኩር ልጅ የሑር ወንዶች ልጆች ሦባል የቂርያት ይዓሪም አባት፤
\s5
\v 51 ሰልሞን የቤተልሔም አባት፤ ሐሬፍ የቤት ጋዴር አባት።
\s5
\v 52 የቂርያትይዓሪም አባት የሦባል ዘሮች፤ የመናሕታውያን ነዋሪዎች እኩሌታ፣ ሀሮኤ፤
\v 53 እንዲሁም የቂርያትይዓሪም ጎሣዎች፤ ይትራውያን፤ ፋታውያን፣ ሹማታውያን፣ ሚሽራውያን፤ ጾርዓውያንና ኤሽታኦውያን ከእነዚህ የመጡ ጎሣዎች ነበሩ።
\s5
\v 54 የሰልሞን ዘሮች፤ ቤተልሔም፣ ነጦፋውያን፣ ዓጣሮት ቤት ዮአብ፣ የመናሕታውያን እኩሌታ፣ ጾርዓውያን።
\v 55 በያቤጽ የሚኖሩ የጸሐፍት ጎሣዎች ቲርዓውያን፣ ሺምዓታውያን፣ ሡካታውያን። እነዚህ ከሬካብ ቤት አባት ከሐማት የመጡ ቄናውያን ናቸው።
\s5
\c 3
\p
\v 1 ዳዊት በኬብሮን ሳለ የወለዳቸው ወንዶች ልጆች እነዚህ ነበሩ፤ ከኢይዝራኤላዊቷ ከአኪናሆም የተወለደው የብኩር ልጁ አምኖን፣ሁለተኛው ከቀርሜሎሳዊቷ ከአቢግያ የተወለደው ዳንኤል፣
\v 2 ሦስተኛው ከጌሹር ንጉሥ ከተማይ ልጅ ከመዓካ የተወለደው አቤሴሎም፣አራተኛው የአጊት ልጅ አዶንያስ፣
\v 3 አምስተኛው ከሚስቱ ከዔግላ የተወለደው ይትረኃም።
\s5
\v 4 እነዚህ ስድስቱ የተወለዱት ዳዊት በኬብሮን ሆኖ ሰባት ዓመት ተኩል በገዛበት ጊዜ ነበር። ዳዊት በኢየሩሳሌም ሠላሳ ሦስት ዓመት ነገሠ፤
\v 5 በዚያም የወለዳቸው ልጆች እነዚህ ነበሩ፤ ሳሙስ፣ ሶባብ፣ ናታን፣ ሰለሞን፣ እነዚህ አራት ወንዶች ልጆች ከዓሚኤል ልጅ ከቤርሳቤህ የተወለዱ ናቸው።
\s5
\v 6 እንዲሁም ሌሎች ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ ስማቸውም ኢያቤሐር፣ ኤሊሱዔ፣ ኤሊፋላት፣
\v 7 ኖጋ፣ ናፌቅ፣ ያፍያ፣
\v 8 ኤሊሳማ፣ ኤሊዳሄ፣ ኤሊፋላት ይባላል፤ ባጠቃላይ ዘጠነኛ ነበሩ።
\v 9 ከቁባቶቹ ከወለዳቸው ወንዶች ልጆች ሌላ እነዚህ ሁሉ ልጆቹ ነበሩ፤ እነዚህም ትዕማር የምትባል እኅት ነበረቻቸው።
\s5
\v 10 የሰሎሞን ልጅ ሮብዓም ነበረ፤ የሮብዓም ልጅ አቢያ፣ የአቢያ ልጅ አሳ፣ የአሳ ልጅ ኢዮሣፍጥ፣
\v 11 የኢዮሣፍጥ ልጅ ኢዮራም፣ የኢዮራም ልጅ አካዝያስ፣ የአካዝያስ ልጅ ኢዮአስ፣
\v 12 የኢዮአስ ልጅ አሜስያስ፣ የአሜስያስ ልጅ ዓዛርያስ፣ የዓዛርያስ ልጅ ኢዮአታም፣
\s5
\v 13 የኢዮአታም ልጅ አካዝ፣ የአካዝዝ ልጅ ሕዝቅያስ፣ የሕዝቅያስ ልጅ ማናሴ፣
\v 14 የምናሴ ልጅ አሞጽ፣ የአሞጽ፣ የአሞጽ ልጅ ኢዮስያስ፣
\s5
\v 15 የኢዮስያስ ወንዶች ልጆች፣ በኩሩ ዮሐናን በኩሩ ዮሐናን፣ ሁለተኛ ልጁ ኢዮአቄም፣ ሦስተኛ ልጁ ሴዴቅያስ፣ አራተኛ ልጁ ሰሎም።
\v 16 የኢዮአቄም ዘሮች፤ ልጁ ኢኮንያ፣ ልጁ ሴዴቅያስ።
\s5
\v 17 የምርኮኛው የኢኮንያን ዘሮች፣ ልጁ ሰላትያል፣
\v 18 መልኪራም፣ ፈዳያ፣ ሼናጻር፣ ይቃምያ፣ ሆሻማ፣ ነዳብያ።
\s5
\v 19 የፈዳያ ወንዶች ልጆች፤ ዘሩባቤል ወንዶች ልጆች፥ ሜሱላም፣ ሐናንያ፣ እኅታቸው ሰሎሚት ትባላለች።
\v 20 ሌሎችም አምስት ልጆች ነበሩ፤ እነርሱም ሐሹባ፣ ኦሄል፣ በራክያ፣ ሐሳድያ፣ ዮሻብሒሴድ።
\v 21 የሐናንያ ዘሮች፤ ፈላጥን፣ የአብድዩና የሴኬንያ ወንዶች።
\s5
\v 22 የሴኬንያ ዘሮች፤ ሸማያና ወንዶች ልጆቹ፤ ሐሙስ፣ ይግአል፣ ባሪያሕ፣ ነዓርያ፣ ሻፋጥ፣ ባጠቃላይ ስድስት ነበሩ።
\v 23 የነዓርያ ወንዶች ልጆች፤ ኤልዩዔናይም
\v 24 ወንዶች ልጆች፤ ሆዳይዋ፣ ኤልያሴብ፣ ፌልያ፣ ዓቁብ፣ ዮሐናን፣ ደላያ፣ ዓናኒ፤ ባጠቃላይ ሰባት ናቸው።
\s5
\c 4
\p
\v 1 የይሁዳ ዘሮች፤ ፋሬስ፣ ኤስሮም፣ ከርሚ፣ ሆር፣ ሦባል።
\v 2 የሦባል ልጅ ራያ ኢኤትን ወለደ፤ ኢኤትደግሞ አሑማይንና ላሃድን ወለደ፤ እነዝዝዚህ የጾርዓውያን ጎሣዎች ናቸው።
\s5
\v 3 የኤጣም ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ኢይዝራኤል፣ ይሽማ፣ ይደባሽ። እኅታቸው ሃጽሌልፎኒ ትባላለች።
\v 4 ፋኑኤል ጌዶርን ወለደ፤ ኤጽር ደግሞ ሑሻ ምን ወለደ። እነዚህ የኤፍራታ የበኩር ልጅና የቤተልሔም አባት የሆነው የሆር ዘሮች ናቸው።
\s5
\v 5 የቴቁሔ አባት አሽሑር፣ ሔላና ነዕራ የተባሉ ሁለቱ ሚስቶች ነበሩት።
\v 6 ነዕራም አሑዛምን፣ ኦፌርን፣ ቴምኒን፣ አሐሽታሪን ወለደችለት፤ የነዕራ ዘሮች እነዚህ ነበሩ።
\v 7 የሔላ ወንዶች ልጆች፤ ዴሬት፣ ይጽሐር፣ ኤትናን ናቸው።
\v 8 የቆጽ ወንዶች ልጆች ደግሞም ዓኑብ፣ ጾቤባና፣ የሃሩም ናቸው።
\s5
\v 9 ያቤጽ ከወንድሞቹ ይልቅ የተከበረ ሰው ነበረ፤ እናቱም "በጣር የወለድድኩት" ስትል ስሙን ያቤጽ አለችው።
\v 10 ያቤጽም፣ "አቤቱ፤ እንድትባርከኝ፣ ግዛቴንም እንድታሰፋልኝ እለምንሃለሁ፣ እጅህ ከእኔ ጋር ትሁን፣ ከሥቃይና ከጉዳትም ጠብቀኝ" በማለት ወደ እስራኤል አምላክ ጮኸ።እግዚአብሔርም የለመነውን ሰጠው።
\s5
\v 11 የሹሐ ወንድም ክሉብ ምሒርን ወለደ፤ ምሒርን ወለደ፤ ምሒርም ኤሽቶን ወለደ፤
\v 12 ኤሽቶን ቤትራፋንና ፋሴሐን ወለደ፤ የዒርናሐሽን ከተሞች የቁረቁረ እርሱ ነው። እነዚህ የሬካ ሰዎች ናቸው።
\s5
\v 13 የቄኔዝ ወንዶች ልጆች፤ ሐታት፣ መዖኖታይ።
\v 14 መዖታይ ደግሞ ዖፍራን ወለደ። ሠራያ የኢዮአብ አባት ሲሆን፣ ኢዮአብ ጌሐራሺምን ወለደ፤ የእደ ጥበብ ባለ ሙያዎች ስለ ነበሩ ይህ ስም ተሰጣቸው።
\v 15 የዮፎኔ ልጅ የካሌብ ወንዶች ልጆች፤ ዒሩ፣ ኤላ፣ ነዓም። የኤላ ልጅ ቄኔዝ።
\v 16 የይሃልኤል ወንዶች ልጆች፤ ዚፍ፣ ዚፋ፣ ቲርያ፣አሣርኤል።
\s5
\v 17 የዕዝራ ሜሬድ፣ዔፌር፣ያሎን። ከሜሬድ ሚስቶች እንዲቱ ማርያምን፣ ሽማይንና የኤሽትምዓን አባት ፅሽባን ወለደች።
\v 18 አይሁዳዊት ሚስቱም የጌዶርን አባት ዮሬድን፣ የጆኮን አባት ሔቤርን፣ የዛኖዋን አባት ይቁቲኤልን ወለደች፤ እነዚህም ሜሬድ ያገባት የፈርዖን ልጅ የቢትያ ልጆች ናቸው።
\s5
\v 19 የሆዲያ ሚስት የነሐም እኅት ወንዶች ልጆች፤ የገርሚው የቅዒላ አባት፣ ማዕካታዊው ኤሽትሞዓ።
\v 20 የሺሞን ወንዶች ልጆች፤ አምኖን፣ ሪና፣ ቤንሐናን፣ ቲሎን። የይሺዒ ዘሮች፤ ዞሔትና ቤንዞሔት።
\s5
\v 21 የይሁዳ ልጅ የሴሎም ወንዶች ልጆች፤ የሌካ አባት ዔር፣ የመሪሳና በቤት አሽቤዓ የበፍታ ጨርቅ ሠሪ የሆኑት ጎሣዎች አባት ለዓዳ፣
\v 22 ዮቂም፣ የኮዜባ ሰዎች፣ ኢዮአስ፣ ሞዓብን የገዛ ሣራፍና ያሹቢሌሔም። ታሪካቸውም ጥንታዊነት ያለው ነው።
\v 23 ሰዎቹ ነበጣዒምና በጋዴራ የሚቀመጡ ሸክላ ሠሪዎች ነበሩ፤ በዚያም በመቀመጥ ለንጉሡ ሸክላ ይሠሩ ነበር።
\s5
\v 24 የስምዖን ዘሮች፤ ነሙኤል፣ ያሚን፣ ያሪን፣ ዛራ፣ ሳኡል፣
\v 25 ሰሎም የሳኡል ልጅ ነው፤ መብሳም የሰሎም ልጅ ነው፤ ማስማዕ ደግሞ የመብሳም ልጅ ነው።
\v 26 የማስማዕ ዘሮች ልጁ ሃሙኤል፣ ልጁ ዘኩር፣ ልጁ ሰሜኢ።
\s5
\v 27 ሰሚኤ ዐሥራ ስድስት ወንዶችና ስድስት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ ወንድሞቹ ግን ብዙ ልጆች አልነበሯቸው፤ ስለዚህ ጎሣቸው በሙሉ እንደ ይሁዳ ሕዝብ ብዙ አልነበረም።
\v 28 የኖረባችውም ቦታዎች እነዚህ ናቸው። ቤርሳቤህ፣ ሞላደ፣ ሐጻርሹዓል፣
\s5
\v 29 ቢልሃ፣ ዔጼም፣ ቶላድ፣
\v 30 ቤቱኤል፣ ሔርማ፣ ፊቅላግ፣
\v 31 ቤትማርካቦት፣ ሐጸርሲሲም፣ ቤትቢሪ፣ ሽዓራይም፣ እስከ ዳዊት ዘመነ መንግስት ድረስ የኖሩት በእነዚህ ከተሞች ነው።
\s5
\v 32 በአካባቢያቸው የሚገኙት ወንደሮች ደግሞ ኤጣም፣ ዓይን፣ ሬሞን፣ ቶኬን፣ ዓሻን የተባሉ አምስት ከተሞች ናቸው፤
\v 33 በእነዚህ ከተሞች ዙሪያ በአል የሚዝችልቁ መንደሮች ነበሩ፤ መኖሪያቸው በዚሁ ሲሆን፤ የትውልድ መዝገብም አላቸው።
\s5
\v 34 ሞሾብብ፣ የምሌክ፣ የአሜስያስ ልጅ ኢዮስያስ፣
\v 35 ኢዮኤል፣ የዮሺብያ ልጅ፣ የሠራያ የዓጂኤል ልጅ ኢዩ
\v 36 እንዲሁም ኤልዩዔናይ፣ ያዕቆብ፣ ፅሾሐያ፣ ዓሣያ፣ ዓሲዔል፣ ዩሲምኤል፣ በናያስ፣
\v 37 የሺፊ ልጅ ዚዛ፣ የአሎን ልጅ፣ የይዳያ ልጅ፣ የሺምሪ ልጅ፤ የሸማያ ልጅ፤
\v 38 እነዚህ ስማቸው ከላይ የተዘረዘረው ሰዎች የየጎሣቸው መሪዎች ነበሩ፤ የቤተሰባቸው ብዛት እጅግ በጣም እየጨመረ ሄደ፤
\s5
\v 39 እነርሱም ለከብቶቻቸው ግጦሽ ፍለጋ ከሸለቆው በስተምስራቅ እስካለው እስከ ጌደር መግቢያ ድረስ ዘልቀው ሄዱ።
\v 40 በዚያም ለምለምና ያማረ የግጦሽ ቦታ አገኙ፤ ምድሪቱም ሰፊ፤ ሰላምና ጸጥታ የሰፈነበት ነበረች። በቀድሞ ቀመን በዚህ ምድር ይኖሩ የነበሩት አንዳንድ የካም ዘሮቼ ናቸው።
\v 41 እነዚህ ስማቸው ከላይ የተዘረዘሩው ወደዚሁ ቦታ የመቱት በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ዘመን ነበረ፤ እነርሱም በድንኳኖቻቸው ውስጥ በነበሩበት በካም ወገኖችና በምዑናውያን ላይ አደጋ በመጣል ፈፅመው አላጠፋአቸው፤ ይህም እስከ ዛሬ ድረስ በግልጽ ይታያል። ለመንጎቻቸው በቂ ግጦሽ ቦታ ስላላገኙ፣ በዚያ መኖር ጀመሩ።
\s5
\v 42 ከእነዚሁ አምስት መቶ የሚሆኑ የስምዖን ወገኖች በይሽዒ ልጆች በፈላጥያ፣ በነዓርያ፣ በረፋያና በዑዝኤል ተመርተው የሴይርን ኩረብታማ አገር ወረሩ።
\v 43 አምልጠው የቀሩትን አማሌቅውያን ፈጅተው እስከ ዛሬ በዚያው ይኖራሉ።
\s5
\c 5
\p
\v 1 የእስራኤሌ በኩር ልጅ የሮቤል ልጆች፤ ሮቤል የበኩር ልጅ ቢሆንም፤ የአባቱን መኝታ ስላረከሰ፤ የበኩርናው መብቱ ለእስራኤል ልጅ ለዮሴፍ ልጆች ተሰጥቶአል። ከዚህም የተነሣ ትውልዱ የበኩርነቱን ተራ ይዞ ሊቁጥል አልቻለም።
\v 2 ይሁዳ ከወንድሞቹ ይልቅ ብርቱ ነበረ፤ ገዥ የወጣው ከእርሱ ቢሆንም፣ የበኩርነት መብቱ የተላለፈው ለዮሴፍ ነበረ።
\v 3 የእስራኤል የበኩር ልጅ የሮቤል ወንዶች ልጆች፤ ሄኖኅ፣ ፋሉሶ፣ አስሮን፣ ከርሚ ነበሩ።
\s5
\v 4 የኢዮኤል ዘሮች ልጁ ሽማያ፣ ልጁ ጎግ፣ ልጁ ስሜኢ፣
\v 5 ልጁ ሚካ፣ ልጁ ራያ፣ ልጁ ቢኤል፣
\v 6 የአጆር ንጉስ ቴልጌል ቴልፌልሶር ማኮር የወሰደው ልጅ ብኤራ ነበሩ።
\s5
\v 7 የቤተሰቡ የዘር ትውልድ በየጎሣ በየጎሣው ሲቁጠር እንደሚከተለው ነው፤ የጎሣ አለቃ የሆነው ኢዮኤል፣ ዘካርያስ፣
\v 8 የኢዮኤል ልጅ፣ እነዚህ ከአሮዔር እስከ ናባውና እስከ በኣልሜዎን ድረስ በሚገኘው ምድር ላይ ሰፈሩ።
\v 9 ከብቶቻቸው በገለዓድ ምድር በዝተው ስለነበር በምስራቅ በኩል ወደ ኤፍራጥስ ወንዝ እስከ ምድረ በዳው ዳርቻ ድረስ የሚገኘውን ምድር ያዙ።
\s5
\v 10 በሳኦልም ዘመነ መንግሥት በእጃቸው ተመትተው ድል ከተደረጉት አጋራውያን ጋር ተዋጉ፤ በመላው የገለዓድ ምሥራቃዊ ክፍል የሚገኙትን መኖሪያዎቻቸውን ያዙ።
\s5
\v 11 የጋድ ነገድ ደግሞ ከእነርሱ ቀጥሎ እስከ ሰልካ ድረስ በሚገኘው በባሳን ምድር ኖሩ፤
\v 12 አለቃው ኢዮኤል፣ ሁለተኛው ሳፋም ከዚህም ያናይና ሰፋጥ ሆነው በባሳን ተቀመጡ።
\v 13 ቤተ ዘመዶቻቸውም በየቤተሰቡ እነዚህ ነበሩ፤ ሚካኤል፣ ሜሱላም፣ ሳባ፣ ዮራይ፣ ያካን፣ ዙኤ፣ ኦቤድ፣ ባጠቃላይ ስባት ነበሩ።
\s5
\v 14 እነዚህ ደግሞ የቢዝ ልጅ፣ የዬዳይ ልጆች፣ ኦቤድ፣ የኢዬሳይ ልጅ፣ የሚካኤል ልጅ፣ የገለዓድ ልጅ፣ የኢዳይ ልጅ፣ የዑሪ ልጅ፣ የሑሪ ልጅ፣ የአቢካኢል ልጆች ናቸው።
\v 15 የቤተሰባቸው አለቃ የኑጊ ልጅ፣ የአብዲኤል ልጅ አሒ ነበረ።
\s5
\v 16 እነዚህም በገለኣድ፣ በባሳንና እስከ ዳርቻዋ በሚገኙት መንደሮች እንዲሁም በሳሮን በሚገኙ የግጦሽ ስፍራዎች ሁሉና ከዚያም ወዲያ አልፈው ተቀመጡ።
\v 17 እነዚህ ሁሉ ትውልድ በመዝገብ የሰፈሩት በይሁዳ ንጉሥ በኢዮአታምና በእስራኤል ንጉሥ በኢዮርብዓም ዘመነ መንግሥት ነው።
\s5
\v 18 የሮቤል፣ የጋድና፣ የምናሴ ነገድ እኩሌታ አርባ አራት ሺህ ብቁ የጦር ሰዎች ነበሩአቸው። እነርሱም ጋሻ መያዝ፣ ሰልፍ መምዘዝና ቀስት መሳብ የሚችሉ ጠንካራና በውጊያ የሠለጠኑ ናቸው።
\v 19 እነዚህም በአጋራውያን፣ በኢጡር፣ በናፌስ፣ በናዳብ ላይ ዘመቱ።
\s5
\v 20 በጦርነቱም ላይ ወደ እግዚአብሔር ጮኸው ስለ ነበር፣ በውጊያው ረዳቸው፣ አጋራው ያንንና የጦር አጋሮቻቸውን ሁሉ አሳልፎ ሰጣቸው፤ ስለ ታመኑበትም ፀሎታቸውን ሰማ።
\v 21 የአጋራውያንንም እንስሶች ማረኩ፤ እነዚህም አምሳ ሺህ ግመሎች፣ 250 000 በጎችና ሁለት ሺህ አህዮች ነበሩ። እንዲሁም 100 000 ሰው ማረኩ።
\v 22 ውጊያው የእግዚአብሔር ስለነበር ሌሎችም ብዙ ሰዎች ተገደሉ። እስከ ምርኮ ጊዜ ምድሪቱ በእጃቸው ነበረች።
\s5
\v 23 የምናሴ ነገድ እኩሌታ ህዝብ ቁጥር ብዙ ነበረ፣ እነርሱም ከባሳን ጀምሮ እስከ በኣልአርሞንዔም ድረስ ባለው ምድር ሰፈሩ፤ ይህም እስከ ሳኔር አርሞንዔም ተራራ ድረስ ማለት ነው።
\v 24 የየቤተሰቡ አለቆች እነዚህ ነበሩ፤ ዔፌር፤ ይሽዒ፣ ኤሊኤል፣ ዓዝርኤል፣ ኤርምያ፣ ሆዳይዋ፣ ኢየድኤ፤ እነዚህ ጀግና ተዋጊዎች የታወቁ ሰዎችና የየቤተሰባቸው አለቆች ነበሩ።
\s5
\v 25 ይሁን እንጂ ለአባቶቻቸው አምላክ ታማኞች አልሆኑም፤ እግዚአብሔር ከፊታቸው ያጠፋቸው የምድሪቱን ከሕዝብ አማልክት በማምለክ አመነዘሩ
\v 26 ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የአሦርን ንጉሥ የፎሐት መንፈስ ይኸውም የቴልጌል ቴፌልሶርን መንፈስ አነሣሥቶ የሮቤልን፣ የጋድንና፣ የምናሴን ነገድ እኩሌታ ማርኮ እንዲወሰድ አደረገ። እነዚህንም ወደ ጎዛን ወንዝ ዳርቻ አፈለሳቸው፤ እነርሱም እስከ ዛሬ ድረስ በዚያ ይገኛሉ።
\s5
\c 6
\p
\v 1 የሌዊ ወንዶች ልጆች፤ ጌድሶን፣ቀዓት፣ሜራሪ፣
\v 2 የቀዓት ወንዶች ልጆች፤እንበረም፣ ይሰዓር፣ኬብሮን፣ዑዝኤል።
\v 3 የእምበረም ልጆች፤ አሮን፣ሙሴ፣ማርያም። የአሮን ወንዶች ልጆች፤ናዳብ፣አብዮድ፣አልዓዛር፣ኢታምር።
\s5
\v 4 አልዓዘር ፊንሐስን ወለደ፤ ፊንሐስ አቡሲን ወለደ፤
\v 5 አቢሲ ኦዚን ወለደ፤
\v 6 ኦዚ ዘራእያን ወለደ፤ዘራእያ መራዮትን ወለደ፤
\s5
\v 7 መራዮት አማርያን ወለደ፤አማርያ አኪጦብን ወለደ፤
\v 8 አኪጦብ ሳዶቅን ወለደ፤
\v 9 ሳዶቅ አኪማአስን ወለደ፤አኪማአስ ዓዛርያስን ወለደ፤ዓዛርያስ ዮሐናን ወለደ፤
\s5
\v 10 ዮሐናን ዓዛርያስ ወለደ፤እርሱም ሰለሞን በኢየሩሳሌም ባሠራው ቤተ መቅደስ በክህነት ያገለግል ነበር፤
\v 11 ዓዛርያስ አማርን ወለደ፤አማርያም አኪጦብን ወለደ፤
\v 12 አኪጦብ ስሳዶቅን ወለደ፤ሳዶቅ ሰሎምን ወለደ፤
\s5
\v 13 ሰሎም ኬሌቅያስን ወለደ፤ኬሌቅያስ ዓዛርያስ ሠራያን ወለደ፤
\v 14 ዓዛርያስ ሠራያን ወለደ፤ሠራያ ኢዮሴዴቅን ወለደ፤
\v 15 እግዚአብሔር የይሁዳና የእየሩሳሌም ሕዝብ በናቡከደነፆር እጅ ተማርከው እንዲወሰዱ ባደረገ ጊዜ ኢዮሴዴቅም አብሮ ተማርኮ ሄደ።
\s5
\v 16 የሌዊ ወንዶች ልጆች፤ ጌድሶን፣ቀዓት፣ሜራሪ።
\v 17 የጌድሶን ወንዶች ልጆች፤ሎቢኒ፣ሰሜኢ።
\v 18 የቀሃት ወንዶች ልጆች፤እምበረም፣ይስዓር፣ኬቤሮን፣ዑዝኤል።
\s5
\v 19 የሜራሪ ወንዶች ልጆች፤ሞሖሊ፣ሙሲ። በየአባቶቻቸው ቤተሰብ የተቁጠሩ የሌዊ ጎሣዎች የሚከተሉት ናቸው፤
\v 20 ከጌርሶን፤ ልጁ ሎቢኒ፣ልጅ ኢኤት፣ልጁ ዛማት፣
\v 21 ልጁ ዮአክ፣ልጁ አዶ፣ልጁ ዛራ፣ልጁ ያትራይ።
\s5
\v 22 የቀዓት ዘሮች፤ ልጁ አሚናዳብ፣ልጁ ቆሬ፣ልጁ አሴር፣
\v 23 ልጁ ህልቃና፣ልጁ አቢሳፍ፣ልጁ አሴር፣
\v 24 ልጁ ኢኢት፣ልጁ ኡርኤል፣ልጁ ዖዝያ፣ልጁ ሳውል።
\s5
\v 25 የሕልቃና ዘሮች፤ አማሢ፣አኪሞት።
\v 26 ልጁ ሕልቃና፣ልጁ ሱፊ፣ልጁ ናሐት፣
\v 27 ልጁ ኤልያብ፣ልጁ ይሮሐም፣ልጁ ሕልቃና፣ልጁ ሳሙኤል።
\s5
\v 28 የሳሙኤል ወንዶች ልጆች፤የበኩር ልጁ ኢዮኤል፣ሁለተኛው ልጁ አብያ።
\v 29 የሜራሪ ዘሮች፤ ሞሖሊ፣ልጁ ሎቤኒ፣ልጁ ሰሜኢ፣ልጁ ዖዛ፣
\v 30 ልጁ ሳምን፣ልጁ ሐግያ፣ልጁ ዓሣያ።
\s5
\v 31 ታቦቱ ከገባ በኋላ፣ዳዊት የመዘምራን አለቃ አድርጎ በእግዚአብሄር ቤት የሾማቸው ሰዎች እነዚህ ናቸው፤
\v 32 እርሱም ሰሎሞን የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በኢየሩሳሌም እስኪሠራ ድረስ፣በማደሪያው ይኸውም በመገናኛ ድንኳን ፊት ሆነው እየዘመሩ ያገለግሉ ነበር፣አገልግሎታቸውንም የሚያከናውኑት በወጣላቸው ደንብ መሠረት ነው።
\s5
\v 33 ከወንዶች ልጆቻቸው ጋር ሆነው ያገለገሉ ሰዎች እነዚህ ናቸው፤ከቀዓታዊያን ልጆች፤ሙዚቃ ተጫዋቹ ኤማን፣የኢዮኤል ልጅ፣የሳሙኤል ልጅ፤
\v 34 ሳሙኤል የሕልቃና ልጅ ነበረ፤ ሕልቃና ፣የይሮሐም ልጅ፣ይብኤሊኤል ልጅ፣የቶዋ ልጅ፣
\v 35 የሱፍ ልጅ፣የሥልቃና ልጅ፣የመሐት ልጅ፣የአማሢ ልጅ፣
\s5
\v 36 የሕልቃና ልጅ፣የኢዮኤል ልጅ፣የዓዛርይስስ ልጅ፣የሶፎንያስ ልጅ፣
\v 37 የታሐት ልጅ፣የአሴር ልጅ፣የአብያሳፍ ልጅ፣የቆሬ ልጅ፣
\v 38 የይስዓር ልጅ፣የቃዓት ልጅ፣የሌዊ ልጅ፣የእስራኤል ልጅ።
\s5
\v 39 እንዲሁም የሔማን ወንድም አሳፍ በስተቀኙ ሆኖ ያገለግል ነበር፤ አሳፍ የበራክያ ልጅ፤የሳምዓ ልጅ፤
\v 40 የሚካኤል ልጅ፣
\v 41 የኤትኒ ልጅ፣የዛራ ልጅ፣የዓዳያ ልጅ፣
\v 42 የኤታን ልጅ፣የዛማት ልጅ፣የሰሜኢ ልጅ፣
\v 43 የኢኤት ልጅ፣የጌድሶን ልጅ፣የሌዊ ልጅ፣
\s5
\v 44 በስተግራቸው በኩል አብረዋቸው ያሉት የሜራሪ ልጂች፣የቂሳ ልጅ ኤታን፣የአብዲ ልጅ፣የማሎክ ልጅ፣
\v 45 የሐሸብያ ልጅ፣የአሰያሰ ልጅ፣የኬልቅያስ ልጅ፣
\v 46 የአማሲ ልጅ፣የባኒ ልጅ፣የሰሜር ልጅ፣
\v 47 የሞሖሊ ልጅ፣የሙሲ ልጅ፣የሜራሪ ልጅ፣የሌዊ ልጅ፣
\s5
\v 48 ሌዋውያን ወንድሞቻቸው ግን የእግዚአብሔር ቤት የማደሪያ ድንኳን ተግባር እንዲያከናውኑ ተመድበው ነበር።
\s5
\v 49 አሮንና ልጆቹ የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ ባዘዝው ምሠረት ስለእስራኤል ማስተሰሪያ በቅድስት ቅዱሳኑ ውስጥ የሚያከናውነውን ተግባር ሁሉ፣በመሠዊያ ላይ የሚቃጠል መሥቃዕትና በዕጣኑ መሠዊያ ላይ የሚቀርበውም መሥዋዕት የሚቀርቡት ግን አሮንና ዘሮቹ ብቻ ነበሩ።
\s5
\v 50 የአሮን ዝርያዎች እነዚህ ነበሩ፤ ልጁ አልዓዛር፣ልጅ ፊንሐስ፣ልጁ አቢሹ፣
\v 51 ልጁ ቡቂ፣ልጁኦዚ፣ልጁ ዘራአያ፣
\v 52 ልጁ መራዮት፣ልጁ አማርያ፣ልጁ አኪጦብ፣
\v 53 ልጁ ሳዶቅ፣ልጁ አኪማአስ።
\s5
\v 54 መኖሪያዎቻቸው እንዲሆኑ የተመደቡላቸው ቦታቸው እነዚህ ናቸው፤የመጀመሪያ ዕጣ የእነርሱ ስለ ሆነ፣ከቀዓት ጎሣ ለሆኑት ለአሮን ዘሮች የተመደቡላቸው መኖሪያቸው እነዚህ ነበሩ።
\v 55 ለእነርሱም በይሁዳ ምድር የሚገኘው ኬብሮንና በዙሪያዋ ያለው የግጦሽ ቦታ ተሰጠ፣
\v 56 በኬብሮን ዙሪያ የሚገኙት የዕርሻ ቦታዎችና መንደሮች ግን ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ ተሰጡ።
\s5
\v 57 ለአሮን ዘሮች የመማፀኛ ከተሞች የሆኑትን ኬብሮንን፣ልብናን፣የቲርን፣ኤሽትሞዓን፣
\v 58 ሖሎንን፣ዳቤርን፣ከነመሰማሪዎቻቸው።
\s5
\v 59 ዓሳንን፣ዮታን፣ቤትሳኒስን ከነመሰማሪዎቻቸው ሰጡ።
\v 60 ከብንያም ነገድ ድርሻ ላይ ገባዖንን፣ጌባን፣ጋሌማን፣ዓናቶትን ከነመሰማሪያዋቻቸው ሰጡ። ለቀዓት ዘሮች የተከፋፈሉ እነዚህ ከተሞች ባጠቃላይ ዐሥራ ሦስት ናቸው።
\s5
\v 61 ለቀሩት የቀዓት ዘሮች ደግሞ ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ድርሻ በዕጣ ዐሥር ከተሞች ተሰጧቸው።
\v 62 ለጌድሶን ነገድ በየጎሣቸው ከይሳኮር፣ከአሴር፣ከንፍታሌምና በባሳን ከሚገኘው ከምናሴ ነገድ ድርሻ ላይ ዐሥራ ሦስት ከተሞች ተመደቡላቸው።
\s5
\v 63 ለሜራሪ ዘሮች በየጎሣቸው ከሮቤል፣ከጋድና ከዛብሎን ድርሻ ላይ ዐሥራ ሁለት ከተሞች በዕጣ ተመደቡላቸው።
\v 64 እስራኤላዊያን ከተሞቹን በዚሁ ሁኔታ መድበው ከነመሰማሪያዎቻቸው ለሌዋውያኑ ሰጧቸው።
\v 65 ቀደም ብለው የተጠቀሱትንም ከተሞች ከይሁዳ ከስምዖንና ከብንያም ነገድ ላይ ወስደው በዕጣ መደቡላቸው።
\s5
\v 66 ለአንዳንድ የቀዓት ጎሣዎችም ከኤፍሬም ነገድ ድርሻ ላይ ከተሞች ተሰጣቸው።
\v 67 በኮረብታማው በኤፍሬም ምድር የሚገኙትን ሴኬምን(የማማፀኛ ከተማ) ፣ኔዝርን፣
\v 68 ዮቅምዓምን፣ቤትሖሮን፣
\v 69 ኤሎንንና ጋትሪሞን ከነመሰማሪዎቻቸው ሰጧቸው።
\s5
\v 70 እንዲሁም እስራኤላውያን ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ድርሻ ላይ ዓኔርና ቢልዓም የተባሉትን ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው ወስደው ለሩት የቀዓት ጎሣዎች ሰጧቸው።
\s5
\v 71 ለጌድሶናውያን ከምናሴ ነገድ እኩሌታ፣ በባሳን የሚገኘውን ጎላንና አስታሮትን ከነመሰማሪያዎቻቸው ተሰጠ፤
\v 72 ከይሳኮር ነገድ፤ ቃዴስን፣ዳብራትን
\v 73 ራሞትንና ዓኔምናን ከነመሰማሪያዎቻቸው ወሰዱ፤
\s5
\v 74 ከአሴር ነገድ መዓሳልን፣ዓብዶን፣
\v 75 ሑቆቅንና፣ረአብን ከነመሰማሪያዎቻቸው ወሰዱ፤
\v 76 ከንፍታሌም ነገድ በገሊላ የሚገኘውን ቃዴስን፣ሐሞንንና፣ቂርያታይምን ከነመሰማሪያዎቻቸው ወሰዱ።
\s5
\v 77 ከሌዋውያን የቀሩት የሜራሪ ጎሣዎች ደግሞ ከዚህ የሚከተለው ወሰዱ፤ከዛቢሎን ነገድ ዮቅኒዓምን፣ቀርታህን፣ሬሞንና፣ታቦርን፣ከነመሰማሪዮቻቸው ወሰዱ።
\v 78 ከዮርዳኖስ ወንዝ ማዶ ኪኢያሪኮ በስተምስራቅ ከሚገኘውን ቦሶርን፣ያሳን፣
\v 79 ቅዴሞትንና ሜፍዓትን ከነመሰማሮያዎቻችው ወሰዱ፤
\s5
\v 80 ከጋድ ነገድ በገለዓድ የምትገኘውን ሬማትን፣መሃናይምን፣
\v 81 ሐሴቦንና ኢያዜርን ከነመሰማሪያዎቻቸው ወሰዱ።
\s5
\c 7
\p
\v 1 የይሳኮር ወንዶች ልጆች፤ ቶላ፣ፋዋ፣ያሱብ፣ሺምሮን፣ባጠቃላይ አራት ናቸው።
\v 2 የቶላ ወንዶች ልጆች፤ኦዚ፣ርረፋያ፣ይሪኤል፣የሕማይ፣ይብሣም፣ሽሚኤል፣እነዚህ የየቤተሰባቸው አለቆች ናቸው።በዳዊት ዘመነመንግሥት ከቶላ ዘሮች በየትውልድ ሀረጋቸው የተቁጠሩ የቶላ ዘሮች ብርቱ ተዋጊዎች ነበሩ፤ቁጥራቸው ሃያ ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ነበረ።
\v 3 የኦዚ ወንድ ልጅ፤ይዝረሕያ። የይዝረሐያ ወንዶች ልጆች፤ሚካኤል፣አብድዩ፣ይሺያ፣አምስቱም አለቆች ነበሩ።
\s5
\v 4 ብዙ ሚስቶችና ልጆች ስለ ነበሩአቸው፣ከነቤተሰባቸው የትውልድ ሐረግ ለውጊያ ብቁ የሆኑ 36000 ሰዎች ነበሩአቸው።
\v 5 ከይስኮር ጎሣዎች ሁሉ የተመዘገቡት ተዋጊዎች የቤተሰቦቹ ትውልድ ቁጥር ባጠቃላይ 87000 ነበሩ።
\s5
\v 6 ሦስቱ የብንያም ወንዶች ልጆች፤ ቤላ፣ቤኬብ፣ይዲኤል።
\v 7 የቤላ ወንዶች ልጆች፤ ኤሴቦንም፣ኦዚ፣ዑዝኤል፣ኢያሪሙት፣ዒሪ፣ባጠቃላይ አምስት ሲሆኑ፣ የቤተ ሰብ አለቆች ናቸው፤በትውልድ ሐረግ መዝገባቸው 22034 ተዋጊ ሰዎች ተመዝገበዋል።
\s5
\v 8 የቤኬር ወንዶች ልጆች፤ዝሚራ፣ኢዮአስ፣አልዓዛር፣ኤልዮዔናይ፣ዖምሪ፣ ኢያሪሙት፣አብያ፣ዓናቶት፣ዔሌሜት፣እነዚህ ሁሉ የቤኬር ልጆች ነበሩ።
\v 9 በትውልድ ሐረግ መዝገባቸውም ውስጥ የየቤተ ሰባቸው አለቆችና ሃያ ሺህ ሁለት መቶ ተዋጊዎች ተመዝግበዋል።
\v 10 የይዲኤል ልጅ፤ ቢልሐን።የቢልሐን ወንዶች ልጆች፤ የዑስ፣አሲሳኦር፣
\s5
\v 11 እነዚህ ሁሉ የይዲኤል ልጆች የየቤተሰቡ አለቆች ነበሩ፤እነርሱም ለውጊያ ብቁ የሆኑ 17200 ተዋጊዎች ነበሯቸው።
\v 12 (ሳፈንና ሁፊም የዒር ዘሮች ሲሆኑ ሑሺም ደግሞ የአሐር ዘር ነው።)
\s5
\v 13 የንፍታሌም ወንዶች ልጆች፤ ያህጽሔል፣ጉኒ፣ዬጽር፣ሺሌም፤እነዚህ የባላ የልጅ ልጆች ናቸው።
\s5
\v 14 የምናሴ ዘሮች፤ ሶርያዊት ቁባቱ የወለደችለት ልጁ አሥርኤል ነው።እርሷም የገለዓድን አባት ማኪርያ የወለደች ናት፤
\v 15 ማኪርም ከሑፊምና ከሳፊም ወገኖች ሚስት አገባ።እኅቱም መዓካ ትባል ነበር።ሌላው ዘሩ ሰለጸዓድ ሲሆን፣እርሱም ሴቶች ልጆች ብቻ ነበሩት።
\v 16 የሚከር ሚስት መዓካ ወንድ ልጅ ወለደች፣ስሙንም ፋሬስ አለችው።የወንድሙም ስም ሱሮስ ይባላል፤ወንዶች ልጆቹም ኡላምና ራቄም ነበሩ።
\s5
\v 17 የኡላም ወንድ ልጅ፤ባዳን፣እነዚህ የምናሴ ልጅ፣የማኪር ልጅ፣የገለዓድ ወንዶች ልጆች ናቸው፤፤
\v 18 እኅቱ መለኬት ኢሱድን፣አቢዔዝርንና መሐላን ወለድች።
\v 19 የሽሚዳ ወንዶች ልጆች ደግሞ እነዚህ ነበሩ፤ አሒያንምምሴኬም፣ሊቅሒ፣አኒዓም።
\s5
\v 20 የኤፍሬም ዘሮች፤ ሹቱላ፣ልጁ ባሬድምምልጁ ታሐት፣ልጁ ኤልዓዳ፣ልጁ ታሐት፣
\v 21 ልጁ ዛባድ፣ልጁ ሹቱላ።ኤድርና ኤልዓድ ከብቶች ለመስረቅ በወረዱ ጊዜ፣የአገሩ ተወለጆች በሆኑት በጌት ሰዎች ተገደሉ።
\v 22 አባታቸውም ኤፍሬም ብዙ ቀን አለቀሰላቸው፤ዘመዶቹም መጥተው አፅናኑት።
\s5
\v 23 ከዚያም ወደ ሚስቱ ገብቶ ተኛ፤እርሷም ፀነሰች፤ወንድ ልጅም ወለደች፤በቤተሰቡ ላይ ከደረሰው መከራ የተነሣ ስሙን በሪያ አለው።
\v 24 ሴት ልጁ ስሟ ሲኢራ ይባላል፤እርሷም የታችኛውና የላይኛውን ቤት ሖሮንንና ኡዜን ሼራን የተባሉትን ከተሞች የቁረቁረች ናት።
\s5
\v 25 ልጁ ፋፌ፣ልጁ ሬሴፍ፣ልጁ ቴላ፣ልጁ ታሐን፣
\v 26 ልጁ ለአዳን፣ልጁ ዓሚሁድ ልጁ ኤሊሳማ፣
\v 27 ልጁ ነዌ፣ልጁ ኢያሱ።
\s5
\v 28 በምድራቸውና መኖሪያቸው ቤቴልንና በዙሪያዋ የሚገኙት ከተሞች በስተምሥራቅ ነዓራን፣በስተ ምዕራብ ጌዝርንና መንደሮቿን በሙሉ ታጠቃልል ነበር።
\v 29 በምናሴ ወሰን ላይ ቤትሳን፣ታዕናክ፣መጊዶና ዶና ከነመንደሮቻቸው ነበሩ።በእነዚህም መንደሮች የእስራኤል ልጅ የዮሴፍ ዘሮች ነበር።
\s5
\v 30 የአሴር ወንዶች ልጆች፤ዩምና፣የሱዋ፣የሱዊ፣በሪዓ፣እኅታቸውም ሤራሕ ትባል ነበር።
\v 31 የበሪዓ ወንዶች ልጆች፤ሐቤርም የቢርዛዊት አባት መልኪኤል።
\v 32 ሔቤርም ያፍሌጥን፣ሳሜርን፣ኮታምንና እኅታቸውን ሶላን ወለደ።
\s5
\v 33 የያፍሌጥ ወንዶች ልጆች፤ ፋሴክ፣ቢምሃል፣ዓሲት፣የያፍሌጥ ወንዶች ልጆች እነዚህ ነበሩ ።
\v 34 የስሜር ወንዶች ልጆች፤ አ፣፥ሮኦጋ፣ይሑባ፣አራም።
\v 35 የወንድሙ የኤላም ወንዶች ልጆች፤ጾፋ ይምና፣ሰሌስ፣ዓማል።
\s5
\v 36 የጻፋ ወንዶች ልጆች፤ ሱዋ፣ሐርኔፍር፣ሦጋል፣ቤሪ፣ይምራ፣
\v 37 ቤጼር፣ሆድ፣ሳማ፣ ሰሊሳ፣ይትራን፣ብኤራ።
\v 38 የዬቴር ወንዶች ልጆች፤ዮሮኒ፣ፊስጻ፣አራ።
\s5
\v 39 የዑላ ወንዶች ልጆች፤ኤራ፣ሐኒኤል፣ሪጽያ።
\v 40 እነዚህ ሁሉ የአሴር ዜሮች ናቸው።እነርሱም የቤተ ሰብ አለቆች፣ምርጥ ሰዎች፣ብርቱ ተዋጊዎችና ድንቅ መሪዎች ነበሩ።ለውጊያ ብቁ የሆኑት ወንዶች ቁጥር 26000 ነበር።
39የዑላ ወንዶች ልጆች፤ኤራ፣ሐኒኤል፣ሪጽያ። 40እነዚህ ሁሉ የአሴር ዜሮች ናቸው።እነርሱም የቤተ ሰብ አለቆች፣ምርጥ ሰዎች፣ብርቱ ተዋጊዎችና ድንቅ መሪዎች ነበሩ።ለውጊያ ብቁ የሆኑት ወንዶች ቁጥር 26000 ነበር።
\s5
\c 8
\p
\v 1 የብንያም አምስት ወንድ ልጆች የነበሩት የብኩር ልጅን ቤላን ፤ አስቤልን፣ አሐራን፣
\v 2 ኖሐን፣ ራፋን ወለደ።
\s5
\v 3 የቤላ ወንዶች ልጆች እነዚህ ነበሩ፤አዳር ጌራ፣አቢሁድ፣አቡሁድ፣
\v 4 አቢሱ፣ናዕማን፣ኦሖዋ፣
\v 5 ጌራ፣ሰፋፋ፣ሒራም።
\s5
\v 6 በጌባ ይኑሩ የነበሩትና በኋላም በምርኮ ወደ መናሐት የተወሰዱት የኤሁድ ዘሮች እነዚህ ናቸው።
\v 7 ናዕማን፣አኪያ፣ጌራ፣በምርኮ ጊዜ እየመራ የወሰዳቸው የዖዛና የኢሒሑድ አባት ጌራ ነበረ።
\s5
\v 8 ሽሐራይም ሚስቶቹን ሑሺምንና በዕራን ከፍታ በኋላ በሞዓብ ምድር ወንዶች ልጆች ወለደ።
\v 9 ከሚስቱ ከሖዴሽ ዮባብን፣ዲብያን፣ማሴን፣ማልካምን፣
\v 10 ይዑጽን፣ሻክያንና ሚርማን ወለደ፤እነዚህም የቤተ ሰብ አለቆች የነበሩ ልጆቹ ናቸው።
\v 11 ሑሺም ከተባለች ሚስቱ አቢጡብና ኤልፍዓል የተባሉ ወንዶች ልጆች።
\s5
\v 12 የኤልፍዓል ወንዶች ልጆች፤ ዔቤር፣ሚሻም፣እንዲሁም ኦኖንና ሎድ የተባሉ ከተሞች ከነመንደሮቻቸው የቁረቁረ ሻሜድ፣
\v 13 በኤሌን ይኖሩ ለነበሩ ቤተሰቦች አለቆችና የጋት ነዋሪዎችን አስወጥተው ያሳደዱ በሪዓና ሽማዕ።
\s5
\v 14 አሒዮ፣ሻሻቅ፣ይሬምት፣
\v 15 ዝባድያ፣ዓራያ፣ዔድር፣
\v 16 ሚካኤል፣ይሽጻናዮሐ የበሪያ ወንዶች ልጆች ነበሩ።
\v 17 ዝባድያ፣ሜሱላም፣ህዝቂ፣ሔቤር፣
\v 18 ይሽምራይ፣ ይዝሊያና፣ዮባብ፣የኤልፍዓል ወንዶች ልጆች ነበሩ።
\s5
\v 19-21 ሺሜኢ እነዚህ ወንዶች ልጆች ያቃም፣ዝክሪ፣ዘብዲ፣ኤሊዔናይ፣ጺልታይ፣ኤሊኤል ፣ዓዳያ፣ብራያና፣ሺምራት ነበሩት።
\s5
\v 22 ይሽጻን፣ዔቤር፣ኤሊኤል፣
\v 23 ዓብዶን፣ዝክሪ፣ሐናን፣
\v 24 ሐናንያ፣ኤላም፣ዓንቶትንያ
\v 25 ይፍዴያና ፋኑኤል የሶሴቅ ወንዶች ልጆች ነበሩ።
\s5
\v 26 ሽምሽራይ፣ሽሃሪያ፣ጎቶልያ፣
\v 27 ያሬሽያ፣ኤልያስና፣ዝክሪ የይሮሐም ወንዶች ልጆች ነበሩ።
\v 28 እነዚህ ሁሉ በየትውልድ ሐርረጋቸው የተቁጠሩ አለቆችና የቤተ ሰብ መሪዎች ሲሆኑ፣የሚኖሩትም በኢየሩሳሌም ነበረ።
\s5
\v 29 የገባዖን አባት ይዒኤል በገባዖን ኖረ፣ሚስቱ መዓካ ትባል ነበር።
\v 30 የበኩር ልጁም አብዶን ይባል ነበር፣የእርሱም ተከታታዮች ዱር፣ቂስ፣በኣል፣ኔር፣ናዳብ፣
\v 31 ጌዶር፣አሂዮ፣ዛኩርና፣
\s5
\v 32 የሺምዓ አባት ሚቅሎት ነበሩ።እነዚህም ከሥጋ ዘመዶቻቸው ጋር በኢየሩሳሌም ከተማ አቅራቢያ ይኖሩ ነበር።
\v 33 ኔር ቂስን ወለደ፣ቂስ ሳኦልንወለደ፣ሳኦልም ዮናታንን፣ሜልኪሳን፣አሚናዳብን፣አስበኣልን ወለደ።
\v 34 የዮናትን ወንድ ልጅ መሪበኣልን፣እርሱም ሚካን ወለደ።
\s5
\v 35 የሚካ ወንዶች ልጆች ፒቶን፣ ሜሌክ፣ ታሬዓ፣ አካዝ ነበሩ።
\v 36 አካዝ ይሆዓዳን ወለደ፤ ይሆዓዳም ዔሌሜትን፣ ዓዝሞትን፣ ዘምሪን ወለደ፤ ዘምሪም ሞዳን ወለደ።
\v 37 ሞጻ ቢንዓን ወለደ፤ ቢንዓ ረፋያን ወለደ፤ ረፋያ ኤልዓሣን ወለደ። ኤልዓሣም ኤሴልን ወለደ።
\s5
\v 38 ኤሴል ስድስት ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም ዓዝሪቃም፣ ቦክሩ፣ እስማኤል፣ ሽዓርያ፣ አብድዩ፣ ሐናን ናቸው። እነዚህ ሁሉ የኤሴል ልጆች ነበሩ።
\v 39 የእርሱ ወንድም የኤሴቅ ወንዶች ልጆች የበኩር ልጁ ኡላም፣ ሁለተኛው ልጁ ኢያስ፣ ሦስተኛው ልጁ ኤላፋላት ናቸው።
\v 40 የኡላም ልጆች ጦረኞችና ቀስተኞች ነበሩ። ብዙ ልጆችና የልጅ ልጆች ነበሩዋቸው፤ ጠቅላላ ቁጥራቸው አንድ መቶ ሃምሳ ነበር። እነዚህ ሁሉ የብንያም ዘሮች ናቸው።
\s5
\c 9
\p
\v 1 እስራኤል ሁሉ በየትውልድ ሐረጋቸው ተቁጥረው ስማቸው በእስራኤል ነገሥታት መዝገብ ላይ ሰፈረ።የይሁዳ ሕዝብ ከፈፀሙት በደል የተነሣ ተማርከው ወደ ባቢሎን ተወሰዱ።
\v 2 በመጀመሪያ በየርስታቸውና በየከተሞቻቸው ተመልሰው የሰፈሩት ጥቂት እስራኤላውያን፣ካህናት፣ሌዋውያንና ቤተመቅደሱ ውስጥ የጉልበት ሥራ የሚሠሩ አገልጋዮች ነበሩ።
\v 3 በእየሩሳሌም ይኖሩ የነበሩ የይሁዳ፣የብንያም፣የኤፍሬምና ምናሴ ነገዶች የሚከተሉት ናቸው፤
\s5
\v 4 ከሰፋሪዎችም መካከል ይሁዳ ልጅ፣ከፋሬስ ዘሮች፣የባኒ ልጅ፣የአምሪ ልጅ፣የዖምሪ ልጅ፣የዓሚሁድ ልጅ ዑታይ።
\v 5 ከሴሎናውያን፦የበኩር ልጁ ዓሣያና ወንዶች ልጆቹ።
\v 6 ከዛራውያን ዝርያዎች መካከል ይዑኤል፤ የሕዝቡ ቁጥር 690 ነበረ።
\s5
\v 7 ከብንያማዊን፦የሐስኑኤ ልጅ፣የሆዳይዋ ልጅ፣የሜሱላ ልጅ ስሉ።
\v 8 የይሮሐም ልጅ ብኔያ፣የሚክሪ ልጅ፣የኦዚ ልጅ ኤላ፣የይብንያ ልጅ፣የራጉኤል ልጅ፣የሰፋ ጥያ ልጅ ሜሱላም።
\v 9 በትውልድ ሐረግ መዝገቡ ላይ በተጻፈው መሠረት ከብንያም ነገድ የሕዝቡ ቁጥር ዘጠኝ መቶ ሃምሳ ስድስት ነበረ፤እነዚህ ሁሉ ወንዶች የቤተሰብ አለቆች ነበሩ።
\s5
\v 10 ከካህናቱ፦ ዮዳኤ፣ዮአሪብ፣ያኪን፣
\v 11 የእግዚአብሔር ቤት አለቃ የሆነው የአኪጦብ ልጅ፣የጳስኮር ልጅ፣የይሮሐም ልጅ፣የሜሱላም ልጅ፣የኬልቅያስ ልጅ ዓዛርያስ።
\s5
\v 12 የመልክያ ልጅ፣የጳስኮር ልጅ፣የሳዶቅ ልጅ፣ዓዳያ፣የኢሜር ልጅ፣የምሺላሚት ልጅ፣የሜሴላም ልጅ፣የየሕዜራ ልጅ፣የዓዲኤል ልጅ መዕሣይ።
\v 13 የቤተሰብ አለቃ የነበሩ ካህናት ቁጥር አንድ ሺህ ሰባት መቶ ሥልሳ ነበረ፤እነዚህም በእግዚአብሔር ብት ለሚከናወነው አገልግሎት ብቁ ሰዎች ነበሩ።
\s5
\v 14 ከሌዋውያን ወገን፦ ከሜራሪ ዘሮች የአሳብያ ልጅ፣የዓዝሪቃም ልጅ፣የአሱብ ልጅ፣ሽማያ፣
\v 15 በቅበቃር፣ኤሬስ፣ጋላልና የአሳፍ ልጅ የዝክሪ፣የሚካ ልጅ፣መታንያ።
\v 16 የኤዶም ልጅ፣የጋላል ልጅ፣ይችሰሙስ ልጅ፣አብድያ።እንዲሁም በነጦፋውያን ከተሞች የኖረው የሕልቅና ልጅ፣የአሳ ልጅ በራክያ።
\s5
\v 17 የቤተ መቅደስ በር ጠባቂዎች፦ሰሎም፣ዓቁብ፣ጡልሞን፣አሂማንና ወንድሞቻቸው፣አለቃቸው ሰሎም ነበረ፤
\v 18 እነርሱም በስተ ምስራቅ በሚገኝው በንጉስ በር እካሁን ድረስ ተመድቦአል።እነዚህ የሌዋያኑ ሰፈር በር ጠባቂዎች ነበሩ።
\v 19 የቆሬ የአብያሳፍ ልጅ፣የቆሬ ልጅ ሰሎምና ክእነሱም ቤተሰብ የሆኑት ቆሬያውያን ወደ እግዚአብሔር ማደሪያ የሚያስገባውን በር ይጠብቁ እንደ ነበር ሁሉ፣እነዚህም ወደ ቤተ መቅደሱ የሚያስገባውን በር ይጠብቁ ነበር።
\s5
\v 20 በቀድሞ ጊዜ የበር ጠባቂዎቹ አለቃ የአላዓዛር ልጅ ፊንሐስ ነበረ፥እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረ።
\v 21 ወደ መገኛው ድንኳን የምያስገባው በር የሚጠብቀው ደግሞ የሜሱላም ልጅ ዘካሪያስ ነበረ።
\s5
\v 22 መግቢያ በሮቹን እንዲጠብቁ የተመረጡ ባጠቃላይ ሁለት መቶ ዐሥራ ሁለት ነበሩ።እነርሱም በትውልድ ሐረጋቸው መሠረት በሚኖሩባቸው መንደሮች ተቁጥረው ተመዘገቡ፤በር ጠባቂዎቹን በዚያ ቦታ ላይ የመደቡላቸው ዳዊትና ባለ ራእዩ ሳሙኤል ነበሩ።
\v 23 የማደሪያውን ድንኳን ምማለትም የእግዚአብሔርን ቤት የሚጠብቁትንም እነርሱና ዘሮቻቸው ነበሩ።
\v 24 በር ጠባቂዎቹም በምሥራቅ፣በምዕራብ፣በሰሜንና፣በደቡብ በሚገኙት በአራቱም ማዕዘኖች ላይ ነበሩ።
\s5
\v 25 ወንድሞቻቸውም በየመንደሮቻቸው ሆነው በየጊዜው እየወጡ የጥበቃውን ሥራ ሰባት ሰባት ቀን ያግዙአቸው ነበር።
\v 26 ሌዋውያን የነበሩት አራቱ የበር ጠባቂ አለቆች ግን በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ የሚገኙትን ክፍሎችና ግምጃ ቤቶች በኃላፊነት ይጠብቁ ነበር።
\v 27 የጥበቃውን ሥራ የሚያከናውኑት እነርሱ በመሆናቸው የሚያድሩትም በዚያው በእግዚአብሔር ቤት አካባቢ ነበረ፤ጠዋት ጠዋትም ደጆቹን የሚከፋፍቱት እነርሱ ነበሩ።
\s5
\v 28 ከእነርሱም አንዳንዶቹ ለብቤተመቅደሱ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በኃላፊነት ይጠብቁ ነበር፤ዕቃዎቹም በሚገቡበትና በሚወቱበት ጊዜ ሁሉ ይቁትሩ ነበር፤
\v 29 ሌሎቹ ሌዋውያን ደግሞ ዕቃዎቹንና የቤተ መውደሱን ንዋያት ቅድሳት፣ዱቄቱን፣የወይን ጠጁን፣የወይራ ዘይቱን፣ዕጣኑን የሽቱውን ቅመማ ቅመም እንዲጠብቁ ተምመድበው ነበር።
\s5
\v 30 ከካህናቱም አንዳንዶቹ የሽቱውን ቅመማ ቅመም ይለውሱ ያዘጋጁ ነበር።
\v 31 የቆሬያዊው የሰሎም በኩር ልጅ ሌዋዊው ማቲትያ የቁርባኑን እንጀራ የመጋገር ኅላፊነት ተሰጥቶት ነበር።
\v 32 በየሰንበቱ የተሰጠው ከቀዓታውያን ወንድሞቻቸው መካከል ለአንዳንዶቹ ነበር።
\s5
\v 33 የሌዋውያን ቤተ ሰብ አለቆች የነበሩት መዘምራኑ ደግሞ በብይተ መቅደሱ ክፍሎች ውስጥ እንዲኖሩና ከሌላው ሥራ ሁሉ ነፃ ሌሊት የሚሠሩት ሥራ ነበራቸው።
\v 34 እነዚሁ ሁሉ የሌዋውያን ቤተ ሰብ አለቆች ሲሆኑ፣በትውልድ ሐረጋቸ መሠረት ተመዘገቡ፤የሚኖሩትም በኢየሩሳሌም ነበረ።
\s5
\v 35 የገባዖን አባት ይዒኤል የሚኖረው በገባዖን ነበረ፤የሚስቱም ስም መዓካ ይባላል።
\v 36 የበኩር ልጁ ዓብዶን ሲሆን፣የእርሱም ተከታዮች ዱር፣ቂስ፣በኣል፣ኔር፣ናዳብ፣
\v 37 ጌዶር፣አሒዮ፣ዛኩር፣ሚቅሎት ነበሩ።
\s5
\v 38 ሚቅሎት ሳምአን ወለደ፣እርሱም ከዘመዶቻቸው ጋር በኢየሩሳሌም አቅራቢያ ይኖሩ ነበር።
\v 39 ኔር ቂስን ወለደ፤ቂስ ሳኦልን ወለደ፤ሳኦል ዮናታን፣ሜልኪሳን፣አሚናዳብን፣አስበኣልን ወለደ።
\v 40 የዮናታ ወንድ ልጅ፤ መሪበኣል ነው፤መሪበኣል ሚካን ወለደ
\s5
\v 41 የሚካ ወንዶች ልጆች፤ፒቶን፣ሜሌክ፣ታሬዓ፣አካዝ።
\v 42 አካዝ የዕራን ወለደ፤ዘምንሪን ሞፃን ወለደ።
\v 43 ሞፃም ቢንዓን ወለደ፤ልጁ ረፋያ ነበረ፤ልጁ ኤልዓሣ፣ልጁ ኤሴል።
\v 44 ኤሴል ስድስት ወንዶች ልጆች ነበሩ፤ስማቸውም፦ ዓዝሪቃም፣ቦክሩ፣እስማኤል፣ሸዓርያ፣አብድዩ ሐናን እነዚህ የኤሴል ወንዶች ልጆች ናቸው።
\s5
\c 10
\p
\v 1 ከዚህ በኋላ ፍልስጥኤማውያን ራኤላውያንም ከፊታቸ ሸሹ፤ብዙዎች በጊቦልቦን ተራራ ላይ ሞቱ።
\v 2 ፍልስጥኤማውያን ሳኦልንና ልጆቹን ይበልጥ አሳደዱአቸው የሳኦልም ልጆች ዮናታን፣አሚናዳብንና ሜልካሳን ገደሉ፤
\v 3 ሳኦል በተሰለፈበት ግንባር ውጊያው በረታ፤ቀስተኞችም አግኝተው አቁሰሉት።
\s5
\v 4 ሳኦል ጋሻ ጃግሬውን፣"እነዚህ ሸለፈታምፕች መሳለቂያ እንዳያደርጉኝ ሰልፍህን መዝዘህ ውጋኝ"አለው።ጋሻ ጃግሬው ግን እጅግ ፈርቶ ሰለ ነበር አልደፍርም፤ስለዚህ ሳኦል በገዛ ሰይፉ ላይ ወድቆ ሞተ።
\s5
\v 5 ጋሻ ጃግሬውም ሳኦል መሞቱን ሲያይ፤እርሱም በሰይፉ ላይ ወድቆ ሞተ።
\v 6 ስለዚህ ሳዖልና ሦስት ልጆቹ ሞቱ፤ቤተ ሰዎቹም ሁሉ አብረው ሞቱ።
\s5
\v 7 በሸለቆው ውስጥ የነበሩት እስራኤላዊያን ሁሉ ሰራዊቱ እንደ ሸሽ፣ሳኢልና ልጆቹም እንደ ሞቱ ባዩ ጊዜ ከተሞቻቸውን ለቀው ሸሹ፤ፍልስጥኤማውያንመጥተው ከተሞቹን ያዙ።
\v 8 በማግሥቱ ፍልስጥኤማውያን የሞቱትን ለመግፈፍ ሲመጡ፣ሳኦልና ልጆቹ በጊልቦዓ ተራራ ላይ ወድቀው አገኙአቸው።
\s5
\v 9 ሳኦልን ከገፈፉ፣ረሱን ከቁረጡና መሣሪያውንም ከወሰዱ በኋላ፣ለአማልክቶቻቸውና ለሕዝቡ የምሥራቹን እንዲነግሩ ወደ መላው የፍልስጥኤም ምድር መልክዕተኞች ላኩ።
\v 10 ከዚህም መሣሪያውን በአማልክቶቻቸው ቤተ ጣዖት አኖሩ፤ራሱንም በዳጎን ቤተ ጣዖት ውስጥ አንጠለጠሉት።
\s5
\v 11 የኢያቢስ ገለዓድ ነዋሪዎች ሁሉ ፍልስጥኤማውያን በሳኦል ላይ ያደረጉትን በሰሙ ጊዜ፤
\v 12 ብርቱ የሆኑ ሰዎች ሄደው የሳኦልንና የልጆቹን ሬሳ አንሥተው ወደ ኢያቢስ አመጡ፤ዐጽማቸውንም ኢያቢስ ውስጥ በሚገኘው ትልቁ ዛፍ ሥር ቀበሩ፤ከዚህያም ሰባት ቀን ጾሙ።
\s5
\v 13 ሳኦል እግዚአብሔር ስላታዘዘ ሞተ፤የእግዚአብሔር ቃል አልጠበቀም፤ይልቁንም ከሙታን ጠሪ ምክርን ጠየቀ፤
\v 14 ይህን ከእግዚአብሔር አልጠየቀም፤ስስለዚህ እግዚአብሔር ገደለው፤መንግሥቱንም ወደ እሴይ ልጅ ወደ ዳዊት እንዲተላለፍ አደረገ።
\s5
\c 11
\p
\v 1 እስራኤል ሁሉ በኬብሮን ወደ እነሆ፤እኛ የገዛ ሥጋህና ደምህ ነን፤
\v 2-3 በቀደመው ዘመን ሳኦል ንጉሥ ሆኖ ሳለ እስራኤልን ወደ ጦርነት የምትመራ አንተ ነበርህ፤እግዚአብሔር አምላክም፣ሕዝቤን እስራኤልን የምትጠብቅ አንተ ነህ፤ንጉሥ ዳዊት ወዳለበት ወደ ኬብሮን መጡ፤ዳዊትም በኬብሮን በእግዚአብሔር ፊት ከእነሱ ጋር ቃል ኪዳን ገባ።እግዚአብሔር በሳሙኤል አማካይነት በሰጠው ተስፋ መሠረት ዳዊትን ቀብተው በእስራኤል ላይ አነገሡት።
\s5
\v 4 ዳዊትና እስራኤላዊያን ሁሉ ኢያቡስ ወደምትባለው ወደ ኢየሩሳሌም ሄዱ።በዚያም የሚኖሩ ኢያቡሳዊያን፤
\v 5 ዳዊትን "ወደዚያ ፈፅሞ አትገባም"አሉት፤ዳዊትግን የጽዮንን ምሽግ ያዘ፤እርሷም የዳዊት ከተማ ናት።
\v 6 ዳዊትና "ኢያቡሳዊያንን ቀድሞ የሚወጋ ሰው የሰራዊቱ አዛዥ ይሆናል"አለ፤ስለዚህ የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ በመጀመሪያ ወጣ፤እርሱም አዛዥ ለመሆን በቃ።
\s5
\v 7 ከዚያም ዳዊት መኖሪያውን በዐባምዩቱ ውስጥ አደረገ፤ከዚያም የተነሣ የዳዊት ከተማ ተባለች።
\v 8 ዳዊትም ከሚሎ ጀምሮ የከተማይቱን ዙሪያ ቅጥር ሠራ፤ኢዮአብ ደግሞ የቀረውን የከተማይቱን ክፍል መልሶ ሠራ።
\v 9 እግዚአብሔር ጸባኦት ከእርሱ ጋር ሰለ ነበር ዳዊት በየጊዜው እየበረታ ሄደ።
\s5
\v 10 የዳዊት ኅያላን ሰዎች አለቆች እነዚህ ናቸው፤እነርሱም እግዚአብሔር በሰጠው ተስፋ መሠረት መንግሥቱን በምድሪቱ ሁሉ ትስፋ ዘንድ ከሌሎች እስራኤላዊያን ጋር ሆነው ለመንግሥቱ ብርቱ ድጋፍ ሰጡ።
\v 11 ዳዊት ኅያላን ሰዎች ስም ዜርዜር ይህ ነው፤ ሐክሞናዊው ያሶብዓም የጦር መኮንኖች አለቃ ነበረ፤እነርሱም ጦሩን አንጅቶ በአንድ ጊዜ ሦስት መቶ ሰው ገደለ።
\s5
\v 12 ከእርሱም ቀጥሎ ከሦስቱ ኅያላን አንዱ የሆነው የአሆሃዊው የዱዲ ልጅ አልዓዘር ነው፤
\v 13 እርሱም ፍልስጥኤማዊያን ለጦርነት በተሰበሰቡ ጊዜ በፈስደሚም ከዳዊት ጋር አብሮ ነበረ፤ገብስ በሞላበት የእርሻ ቦታ ወታደሮቹ ከፍልስትኤማውያን ፊት ሸሹ፤
\v 14 ይሁን እንጂ በእርሻው መካከል ቦታ ይዘው ስለ ነበረ ፍልስጥኤማውያንን ገደሉ፤እግዚአብሔር ታላቅ ድል ሰጣቸው።
\s5
\v 15 ከፍልስጥኤማውያን ሰራዊት ጥቂቱ በራፋይም ሸለቆ ሰፍሮ ሳለ፣ከሠላሳዎቹ አለቆች ጆስቱ ዳዊትን ለመገናኘት በዓዶላም ዋሻ አጠገብ ወደሚገኘው ወደ ዐለቱ ወረዱ።
\v 16 በዚያን ጊዜ ዳዊት በምሽጉ ውስጥ ነበረ፤የፍልስጥኤማዊያን ሰራዊት ደግሞ በቤተልሕም ነበረ።
\v 17 ዳዊትም ውሃ ፈልጎ ነበርና፣"ከቤተ ልሔም በር አቅራቢያ ከሚገኘው ጉድጓድ የምጠጣው ውሃ ማን ባመጣልኝ!" አለ።
\s5
\v 18 በዚህ ጊዜ ጆስቱ የፍልስጥኤማውያንን ሰራዊት ጥሰው በማለፍ በቤተ ልሔም በር አጠገብ ከሚገኘው ጉድጓድ ውሃ ቀድተው ለዳዊት አመጡለት፤እርሱ ግን ሊጠጣው ስላልፈለገ በእግዚአብሔር ፊት አፈሰሰው፤
\v 19 ከዚያም "ይህን ከማድረግ እግዚአብሔር የጠብቀኝ፤ይህ በሕይወታችን ቁርጠው የሄዱትን የእነዚህን ሰዎች ደም እንደ መጠጣት አይደለምን?"አለ።ይህን ለማምጣት በሕይወታቸው ቁርጠው ስለ ነበር፣ዳዊት ሊጠጣው አልፈለገም።
\s5
\v 20 የኢዮአብ ወንድም አቢሳ የጆስቱ አለቃ ነበረ። እርሱም ጦሩን አንሥቶ ሦስት መቶ ሰዎች ገደለ፤ከዚህም የተነሣ እንደ ሦስቱ ሁሉ ዝነኛ ሆነ፤
\v 21 ከጆስቱ አንዱ ሆኖ ባይቁጠርም እንኳን፣እጥፍ ክብር አገኘ፤አዛዣቸውም ሆነ።
\s5
\v 22 ከቀብስኤል የወጣውና ታላቅ ጀብዱ የሠውው የዮዳሄ ልጅ በናያስ ብርቱ ተዋጊ ነበረ።እርሱም እጅግ ያታወቁ ሁለት የሞአብ ሰዎች ገደለ።እንዲያውም አንድ ጊዜ በረዶ ምድርን በሰፈነበት ቀን ወደ አንድ ጉድጓድ ወርዶ አንበሳ ወደለ።
\v 23 ደግሞም ቁመቱ አምስት ክንድ የሆነ አንድ ግብፃዊው የሸማኔ መጥቅለያ የመሰለ ቶር በእጁ ይዞ ገጠመው፤ክችግብፃዊው ጋር እጅ ጦሩ ነጥቆ በገዛ ጦሩ ገደለው።
\s5
\v 24 የዮሄዳ ልጅ በናያስ የፈፀመው ጀብዱ ይህ ነበር፤እርሱም እንደ ሦስቱ ኅያላን ዝነኛ ሆነ።
\v 25 ከሠላሳዎቹም ይልቅ የበለጠ አንዱ አልነበረመ፤ዳዊትም የክብር ዘቡ አዛዥ አደረገው።
\s5
\v 26 ኅያላኑ ወንድም አሣሄል፤የቤተ ልሔም የዱዲ ልጅ ኤልያናን፤
\v 27 ሃሮራዊው ሳሞት፣ፊሎናዊው ሴሌዴ፣
\v 28 የቴቁሔ ሰው የሆነው የዓስካ ልጅ፣ዒራስ፣የዓናቶቱ ሰው፣አቢዔዜር፣
\v 29 ኩሳዊው ሴቤካይ፣ኦሆሃዊው ዔላይ፣
\s5
\v 30 ነቶፋዊው ማህራይ፣የነቶፋዊው የበዓና ልጅ ሔሌድ፣
\v 31 ከብንያም ወገን የጊብዓ ሰው የሆነው የሪባይ ልጅ ኤታል፣ጲርዓቶናዊው በናያስ፣
\v 32 የገዓስ ሸለቆዎች ሰው የሆነው ኡሪ፣ዓረባዊው አቢኤል፣
\v 33 ባሕሩማዊው ዓዝሞት፣ሰዓልቦዊው ኤልያሕባ፣
\s5
\v 34 የጊዞናዊው የአሳን ልጆች፣የሃራራዊው የሻጌ ልጅ ዮናታን፣
\v 35 የሃራራዊው የሳኮር ልጅ አሒአም፣የኡር ልጅ ኤሊፋል፣
\v 36 ምኬራታዊው ኦፌር፣ፍሎናዊው አኪያ፣
\v 37 ቀርሜሎሳዊው ሐጽሮ፣የኤዝባይ ልጅ ነዕራይ፤
\s5
\v 38 የናታን ወንድም ኢዮኤል፣የሃግሪ ልጅ ሚብሐር፣
\v 39 አሞናዊ ጼሌቅ፣የጽሩያ ልጅ የኢዮአብ ጋሻ ጃግሬ ቤሮ ታዊው ነሃራይ፣
\v 40 ይትራዊው ዒራስ፣ይትራዊው ጋሬብ፣
\v 41 ኬጤያዊው ኦርዮ፣የአህላይ ልጅ ዛባድ፣
\s5
\v 42 የሮቤላዊው የሺዛ ልጅ ዓዲና፣እርሱም የሮቤላዊያንና አብረውት ለነበሩት የሠላሳ ሰዎች አለቃ ነበረ።
\v 43 የማዕካ ልጅ ሐናን፣ሚትናዊው ኢዮሣፍጥ፣
\v 44 አስታሮዊው ዖዝያ፣የአሮዔራዊው የኮታም ልጆች ሻማና ይዒኤል፣
\s5
\v 45 የሺምሪ ልጅ ይዲኤል፣ወንድሙም ቴዳዊው ዮሐ፣
\v 46 መሐዋዊው ኤሊኤል፣የኤልነዓም ልጆች ይባሪይና ዮሻውያ፣ሞዓባዊው ይትማ፣
\v 47 ኤሊኤል፣ዖቤድና ምጾባዊው የዕሢኤል።
\s5
\c 12
\p
\v 1 ዳዊት ከቂስ ልጅ ከሳኦል ፊት ሸሽቶ በጺቅላግ ሳለ ወደ እርሱ የመጡት ሰዎች እነዚህ ናቸው፤እነርሱም በጦርነቱ ላይ ከረዱት ተዋጊዎች መካከል ነበሩ።
\v 2 ሰዎቹ ቀስተኞች ሲሆኑ፣በቀኝም ሆነ በግራ እጃቸው ፍላጻ መወርወርና ድንጋይ መወንጨፍ የሚችሉ ነበሩ፤እነርሱም ከብንያም ነገድ የሆነው የሳኦል ሥጋ ዘመዶች ነበሩ፤
\s5
\v 3 አለቃቸው አሐዔዝር ነበረ፥ከእርሱም በኋላ ኢዮአስ ነበረ፤ሁለቱም የጊብዓዊው የሸማዓ ልጆች ነበሩ፤የዓዝሞት ልጆች ይዝኤልና ፋሌጥ፣በራኪያ፣ዓናቶታዊው ኢዩ፣
\v 4 ገባናዊው ሰማያስ ከሠላሳዎቹም መሪ ነበረ፤ርርሚያስ፣የሕዚኤል ዮሐንስ፣ገድሮታዊው ዮዛባት፣
\s5
\v 5 ኤሊዛይ፣ኢያሪሙት፣በዓልያ፣ሰማራያ፤ሐሩፋዊው ሰፋትያስ፣
\v 6 ቆሬያውያኑ ሕልቃና፣ይሺያ፣ዓዘኤል፣ዮዛር፣ያሻብዓም፣
\v 7 የጌዶር ሰው ከሆነው ደግሞ የይሮሐም ልጆች ዮዔላና ዝባድያ።
\s5
\v 8 ዳዊት በምድረ በዳ በሚገኘው ምሽጉ ውስጥ ሳለ፣ከጋድ ነገድ የሆኑ ሰዎች መጥተውው የእርሱን ሰራዊት ተቀላቀሉ፤ከእነሱም ለውጊያ የተዘጋጁ ጋሻና ጦር ለመያዝ የሚችሉ ብርቱ ተዋጊዎች ነበሩ፤ፊታቸው እንደ አንበሳ እንደሚይዝ ሚዳቋ ፈጣኖች ነበሩ ።
\s5
\v 9 የእነዚህም አለቃ ዔፌር ነበረ፤ሁለተኛ አዛዥ አብድዩ፣ሦስተኛው ኤልያብ፣
\v 10 አራተኛ መስመና፣አምስተኛው ኤርሚያስ፤
\v 11 ስድስተኛው ዓታይ፣ሰባተኛው ኢሊኤል፣
\v 12 ስምንተኛው ዮሐናን፣ዘጠነኛው ኤልዛባድ፣
\v 13 ዐሥረኛው ኤርሚያስ፣ዐሥራ አንድኛው መክበናይ።
\s5
\v 14 እነዚህ ጋዳውያን የጦር አዛዦች ነበሩ፣ከእነሱም ታናሽ የሆነው እንደ መቶ፣ታላቅ የሆነው ደግሞ እንደ ሺህ አለቃ ይቁጠር ነበር።
\v 15 በመጀመሪያው ወር የዮርዳኖስ ወንዝ ከአፍ እስከ ሞልቶ ሳለ፣ወንዙን ተሻግረው በስተ ምሥራቅና በስተ ምዕራብ ሸለቆዎች ይኖሩ የነበሩትን ሁሉ ከዚያ ያባረሩት እነዚህ ሰዎች ነበሩ።
\s5
\v 16 ሌሎች ከብንያምና ከይሁዳም ወገን የሆኑ ሰዎች ዳዊት ወደሚገኝበት ምሽግ መጡ።
\v 17 ዳዊትም እነዚህን ሰዎች ሊቀበል ወጥቶ እንዲህ አላቸው፤የመጣችሁት ልትረዱኝና በሰላም ከሆነ፤ከእኔ ጋር እንድትሰለፉ ልቀበላችሁ ዝግጁ ነኝ፤ነገር ግን እጄ ከበደል ንጹሕ ሆኖ ሳለ፤ለጠላቶቼ አሳልፋችሁ ልትሰጡኝ ከሆነ፤የአባቶቻችን አምላክ ይመልከተው፤ይፍረድውም።
\s5
\v 18 ከዚያም እግዚአብሔር መንፈስ በሠላሳዎቹ አለቃ በዓማሣይ ላይ ወረደ፤እርሱም እንዲህ አለ፤"ዳዊት፤እኛ ክችአንተ ጋር ነን፤ሰላም ፍፁም ሰላም ለአንተ ይሁን፤አንተን ለሚረዱም ሁሉ ሰላም ይሁን፤አምላክህ ይረዳሃል"።ስለዚህ ዳዊት ተቀበላቸው፤የሰራዊቱም አለቃ አደረረጋቸው።
\s5
\v 19 ዳዊት ከፍልስጥኤማዊያን ጋር ተባብሮ ሳኦልን ለመውጋት በሄደ ጊዜ፤ከምናሴ ነገድ የሆኑ ጥቂት ሰዎች ከድተው ከዳዊት ሰራዊት ጋር ተቀላቀሉ።እርሱ ግን ርዳታ አላደረገላቸውም፤ምክንዩም የፍልስትኤማዊያን ገዦች ምክር ካደረጉ በኋላ እንዲህ ሲሉ ልከውት ነበር፤"ከድቶ ወደ ጌታው ውደ ሳኦል ቢሄድ እኛን ያስጨርሰናል።
\v 20 ዳዊት ወደ ጺውላግ በሄደ ጊዝዜ ከድተው ወደ እርሱ የተቀላቀሉ የምናሴ ነገድ ሰዎች እነዚህ ነበሩ፤ዓድና፣ዮዛባት፣ይዲኤል፣ሚካኤል፣ዮዛባት፣ኤሊሁ፣ ጺልታይ፤እነዚህ በምናሴ ግዛት ሳሉ የሸለቆች ነበሩ።
\s5
\v 21 ሁሉ ብርቱ ተዋጊዎችና በዳዊትም ሰራዊት ውስጥ አዛዦች ሰለ ነበሩ፣አደጋ ጣዮችን በመውጋት ረዱት።
\v 22 ሰራዊቱም እንደ እግዚአብሔር ሰራዊት እስኪሆን ድረስ፤፣ዳዊትን ለመርዳት በየዕለቱ ብዙ ሰዎች ይጎርፉ ነበር።
\s5
\v 23 እግዚአብሔር ለዳዊት በገባለት ቃል ኪዳን መሠረት የሳኦል መንግሥት አንሥተው ለእርሱ ለመስጠት ዳዊት ወደ ሚገኝበት ወደ ኬቤሮን የመጡት ሰዎች ቁጥር ይህ ነው፤
\v 24 ጋሻና ጦር አንግበው ለጦርነት የተዘጋጁት የይሁዳ ሰዎች ስድስት ሺህ ስምንት መቶ።
\v 25 ከስምዖን ነገድ ለጦርነት ዝግጁ የሆኑ ሰባት ሺህ አንድ መቶ።
\s5
\v 26 ከሌዊ ነገድ አራት ሺህ ስድስት መቶ፤
\v 27 የአሮን ቤተ ሰብ መሪ የሆነውን ዮዳሄን ጨምሮ ሦስት ሺህ ሰባት መቶ ሰዎች፤
\v 28 ወጣቱ ብርቱ ተዋጊ ጻዶቅና ከቤተ ሰቡ ሃያ ሁለት የጦር አለቆች፤
\s5
\v 29 የሳኦል ሥጋ ዘመድ የሆኑ የብንያም ሰዎች ሦስት ሺህ፤ከነዚህም አብዛኞቹ እስከዛያች ጊዜ ድረስ ለሳኦል ቤት ታማኝ ነበሩ፤
\v 30 ከኤፍሬም ሰዎች በጎሣዎቻቸው ዘንድ ታዋቂ የሆኑ ብርቱ ተዋጊዎች ሃያ ሺህ ስምንት መቶ፤
\v 31 ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ዐሥራ ስምንት ሺህ ሰዎች፤እነርሱም ዳዊትን ለማንገሥ በየስማቸው ተጽፈው የመጡ ነበሩ።
\s5
\v 32 ዘመኑን የተረዱና እስራኤላዊያንም ምን ማድረግ እንደሚገባቸው የተገነዘቡ የይሳኮር ሰዎች ሁለት መቶ አለቆች፤በእነሱም ሥር ሆነው የሚታዘዙ ዘመዶቻቸው።
\v 33 ልምድ ያላቸው፤በሁለቱም ዐይነት መሣሪያ ለመዋጋት የተዘጋጁትና ዳዊትን ለመርዳት የመጡት መንታ ልብ የሌላቸው የዛቢሎን ሰዎች ሃምሳ ሺህ፤
\s5
\v 34 ከንፍታሌም ሰዎች አንድ ሺህ የጦር አለቆች፤ከእነርሱም ጋር ጋሻና ጦር የያዙ ሠላሳ ሰባት ሺህ ሰዎች፤
\v 35 ከዳን ሰዎች ለጦርነት የተዘጋጁ ሀያ ስምንት ሺህ ስድስት መቶ፤
\s5
\v 36 ከአሴር ሰዎች ልምድ ያላቸውና ከጦርነት የተዘጋጁ ወታደሮች አርባ ሺህ፤
\v 37 ከምስራቅ ዮርዳኖስ ከሮቤል፣ከጋድና ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ልዩ ልዩ ዐይነት መሣሪያ የታጠቁ አንድ መቶ ሃያ ሺህ ሰዎች።
\s5
\v 38 እነዚህ ሁሉ በሰራዊቱ ውስጥ ለማገልገል ፈቃደኞች የሆኑ ተዋጊዎች ናቸው፤ወደ ኬብሮን የመጡትንም ዳዊትም በእስራኤል ሁሉ ላይ ለማንገሥ ወስነው ስለ ነበር ነው።የቀሩትም እስራኤላዊያን ሁሉ ዳዊትን ለማንገሥ በአንድ ሐሳብ ጸኑ።
\v 39 የሚያስፈልጋቸውን ቤተ ሰቦቻቸው አዘጋጅተውላቸው ሰለ ነበር፣ሰዎቹ እየበሉና እየጠቱ ከዳዊት ጋር ሦስት ቀን ቁዩ።
\v 40 እንዲሁም ሩቅ ከሆነው ከይሳኮር፣ከዛቢሎንና ከንፍታሌም አገር ሳይቀር ጎረቤቶቻቸው በአህያ፣በግመል፣በበቅሎና በበሬ ጭነው ምግብ አመጡላቸው፤በእስራኤል ታላቅ ደስታ ሰለ ሆነ ዱቄት፣የበለስና የዘቢብ ጥፍጥፍ፣የወይን ጠጅ፣የወይራ ዘይት፣የቀንድ ከብትና በጎች በገፍ ቀርበው ነበር።
\s5
\c 13
\p
\v 1 ዳዊትም ሻለቆችና መቶ አለቆች ከሆኑት የጦር ሹማምቱ ሁሉ ጋር ተማከረ።
\v 2 ከዚያም ለመላምው የእስራኤል ማኅበር እንዲህ አለ፤"እንግዲህ ነገሩ መልካም መስሎ ከታያችሁ የአምላካችን የእግዚአብሔር ፍቃድ ከሆነ፤በእስራኤል ግዛት ሁሉ ለሚኖሩ በሩቅም ሆነ በቅርብ ላሉት ለቀሩትም ሆነ በቅርብ ላሉት ለቀሩት ወንድሞቻችን እንዲሁም በየራሳቸው ከተሞና መሰማሪያዎች የሚኖሩ ካህናትና ሌዋውያን መጥተው ከእኛ ጋር እንዲሰባሰቡ እንላክላቸው።
\v 3 በሳኦል ዘምን መንግሥት ሳንፈልገው የነበረውን የአምላካችንን ታቦት መልሰን ወደ እኛ እናምጣ።
\v 4 በገሩም በሕዝቡ ሁሉ ዘንድ ተቀባይነት ስላገኘ መላው ማኅበር ይህንኑ ለማድረግ ተስማማ።
\s5
\v 5 ስለዚህ ዳዊ የእግዚአብሔር ታቦት ከቂርያትይዓሪም ለማምጣት ከግብፅ ወንዝ ከሺሖር ጀምሮ እስከ ሐማት መተላለፊያ ድረስ የሰፈሩትን እስራኤላውያን ሁሉ ሰበሰበ።
\v 6 ዳዊትና እስራኤላዊያን ሁሉ በኩሩብና በኪሩብ መካከል የተቀመጠውን፣የእግዚአብሔር በይሁዳ ወዳለችው ቂርያትይዓሪም ወደ ተባለችው ወደ በኣላ ሄዱ።
\s5
\v 7 የእግዚአብሔርም ታቦት ከአሚናዳብ ቤት በእዲስ ሠረገላ ላይ እድርገው አመጡ፤ሠረገላውን ይነዱየነበሩትም ዖዛና አሒዮ ነበሩ።
\v 8 ዳዊትና እስራኤላዊያን ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ሆነው በቅኔና በበገና፣በመሰንቆ በከበሮ፣በጽናጽልና በመለከት በሙሉ ኅይላቸው በዓሉን በደስታ ያከብሩ ነበር።
\s5
\v 9 ወደ ኪዶን ዐውድማ በደረሱ ጊዜ በሬዎቹ አደናቅፏቸው ሰለ ነበር፣ዖዛ ታቦቱን ለመደገፍ እጁን ዘረጋ።
\v 10 ታቦቱን በእጁ ሰለ ነካ፣የእግዚአብሔር ቁጣ ዖዛን ላይ ነደደ፤ስለዚህም በዚያው በእግዚአብሔር ፊት ሞተ።
\v 11 የእግዚአብሔር ቁጣ ዖዛን በድንገት ስለ ቀሠፈው ዳዊት አዘነ፤ያም ቦታ እስከ ዛሬ ድረስ የዖዛ ስብራት ተብሎ ይጠራል።
\s5
\v 12 ዳዊት በዚያን ዕለት የእግዚአብሔር ታቦት ወደ እኔ እንዴት ማምጣት እንችላለሁ?"አለ።
\v 13-14 ስለዚህ ታቦቱን ወደ ዳዊት ከተማ በመውሰድ ፈንታ የጋት ሰው ወደ ሆነው ወደ አቢዳራ ቤት ከቤተ ሰቡ ጋር ሦስት ወር ተቀመጠ፤እግዚአብሔርም ቤተ ሰቡንና ያለውንም ሁሉ ባረከ።
\s5
\c 14
\p
\v 1 በዚህ ጊዜ የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ለዳዊት ቤተ መንግሥት እንዲሠሩ መልክተኞችን፣ድንጋይ ጠራቦዎችንና አናጢዎችም ከዝግባ ዕንጨት ጋር ላከ።
\v 2 ዳዊትም እግዚአብሄር በእስራኤል ላይ አንግሦ እንዳጽናውና ስለ ሕዝቡም ስለ እስራኤል ሲል መንግጅቱን ከፍ ከፍ እንዳደረገለት አስተዋለ።
\s5
\v 3 ዳዊትም በኢየሩሳሌም ብዙ ሚስቶች አገባ፤ከእነሱም ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ።
\v 4 በዚያ ሳለ የወለዳቸው የልጆች ስም ይህ ነው፤ሳሙስ፣ሶባብ፣ናታን፣ሰለሞን፣
\v 5 ኢያቤሐር፣ኤሊሱዔ፣ ኤሊፋላት፣
\v 6 ኖጋ፣ናፌቅ፣ያፍያ፣
\v 7 ኤሊሳማ፣ኤሊዳሄ፣ኤሊፋላት።
\s5
\v 8 ዳዊት በእስራኤል ሁሉ ላይ ተቀብቶ መንገሡን ፍልስጥኤማውያን በሰሙ ጊዜ፣እርሱን ፍለጋ በሙሉ ኅይላቸው ወቱ፤ዳዊት ይህን ሰምቶ ሰለ ነበር ሊገጥማቸውው ወጣ።
\v 9 በዚህ ጊዜ ፍልስጥኤማውያን ውጥተው የራፋይምን ሸለቆ ወረሩ።
\s5
\v 10 ስለዚህ ዳዊት፣"ወጥቼ በፍልስጥኤማዊያን ላይ አደጋ ልጣልን? አንተስ በእጄ አሳልፈህ ትሰጣቸዋለህን? ሲል እግዚአብሔር ጠየቀ።እግዚአብሔር "አዎን ውጣ! በእጅህ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ"ብሎ መለሰለት።
\v 11 ስለዚህ ዳዊትና ሰዎቹ ወደ በኣልፐራሲም ወጡ፤በዚያም ድል አደረጋቸው።ዳዊትም "ውሃ ነድሎ እንደሚውጣ ሁሉ እግዚአብሄርም ጠላቶችይን በእጄ አፈርሳቸው"አለ፤ከዚህ የተነሳ ያን ቦታ "በኣልፐራሲም"ብለው ሰየሙት።
\v 12 ፍልስጥኤማውያን አማልዕክቶቻቸውን በዚያው ጥለዋቸው ስለ ነበር፣ዳዊትት በእሳት እንዲያቃጥሏቸው አዘዘ።
\s5
\v 13 ፍልስጥኤማውያን ሸለቆውን እንደ ገና ወረሩ፣
\v 14 ዳዊትም እንደገና እግዚአብሔር ጠየቀ።እግዚአብሔር እንዲህ ሲል መለሰለት "ዙሪያውን ከበህ በሾላው ዛፍ ፊት ለፊት አደጋ ጣልባቸው እንጂ በቀጥታ ወደ ላይ አትውጣ፤
\s5
\v 15 በሾላው ዐናት ላይ የሰልፍ ድምፅ ስትሰማ ወዲያኑ ለጦርነት ውጣ፤ይህም የፍልስጥኤማውያንን ስራዊት ለመምታት እግዚአብሔር በፊትህ ወጥቶአል ማለት ነውና።
\v 16 ዝዝዚህ ዳዊት እግዚአብሔር እንዳለው አደረገ፤ከገባዖን ጀምሮ እስከ ጌዝር ድረስ ፍልስጥኤማውያንን መቷቸው።
\v 17 ከዚህም የተነሳ የዳዊት ዝና በየአገሩ ሁሉ ተሰማ፤እግዚአብሔርም መንግሥታት ሁሉ እንዲፈሩት አደረገ።
\s5
\c 15
\p
\v 1 ዳዊት በስሙ በተጠራችው ከተማ ለራሱ ብይቶችን ሠራ፤በእግዚአብሔር ታቦት ቦታ አዝጋጅቶ ድንኳን ተከለ።
\v 2 ከዚያም ዳዊት፣"የእግዚአብሔርን ታቦት እንዲሸከሙና ለዘላለም በፊቱ እንዲያገለግሉ እግዚአብሔር ከመረጣቸው ከሌዋውያን በቀር፣የእግዚአብሔርን ታቦት ማንም አይሸከምም ሲል አዘዘ።
\v 3 ዳዊት የእግዚያብሔር ታቦት ወዳዘጋጀለት ስፍራ እንዲያወጡ እስራኤላዊያን ሁሉ በኢየሩሳሌም ሰበስበ።
\s5
\v 4 የአሮንን ዘሮችና ሌዋዊያውያንኑም በአንድነት ሰበሰበ፤
\v 5 ከቀዓት ዘሮች፣አለቃውን ኡርኤልንና አንድ መቶ ሃያ የሥጋ ዘመዶቹን፤
\v 6 ከሜራሪ ዘሮች፤አለቃው ዓሣያንና ሁለት መቶ ሃያ የሥጋ ዘመዶቹን፤
\s5
\v 7 ከጌድሶን ዘሮች፤ አልቃው ኤሊኤልንና አንድ መቶ ሠላሳ የሥጋ ዘመዶቹን፤
\v 8 ከኤሊጻፍን ዘሮች፤አለቃውን ሽማያንና ሁለት መቶ የሥጋ ዘመዶቹን፤
\v 9 ከኬብሮን ዘሮች፤ አለቃው ኤሊኤልንና ሰማንያ የሥጋ ዘመዶቹ፤
\v 10 ከዑዝኤል ዘሮች፤አለቃውን አሚናሳብንና አንድ መቶ ዐሥራ ሁለት የሥጋ ዘመዶቹን።
\s5
\v 11 ከዚያም ዳዊት ከህናቱን ሳዶቅንና አብያታርን፣ሌዋውያኑን ኡርኤልን፣ዓሣያን፣ኢዩኤልን፣ሽማያን፣ኤሊኤልንና አሚናዳብን ጠርቶ፣
\v 12 እንዲህ አልቸው፤"እንግዲህ እናንተ የሌዋውያን ቤተ ሰብ አለቆች ሰለ ሆናችሁ፣እናንተና ወንድሞቻችሁ ሌዋውያን ራሳችሁን ቀድሱ፤ከዚያም የእስራኤል አምላክ የእግዚአብሔርን ታቦት ወደአዘጋጀሁለት ቦታ አምጡ።
\s5
\v 13 የአምላካችን የእግዚአብሔር ቁጣ በላያችን ላይ እንዲህ የነደደው እናንተ ሌዋውያኑ ቀድሞም ስላላመጣችሁት ነው፤እኛም ብንሆን ምን ማድረግ እንዳለብን በታዘዘው መሠረት አልጠየቅነውም።
\v 14 ስለዚህ ካህናቱና ሌዋውያኑ የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔር ታቦት ለማምጣት ራሳቸውን ቀደሱ።
\v 15 ሙሴ በእግዚአብሔር ቃል እንዳዘዘው፣ሌዋውያኑ የእግዚአብሔር ታቦት በትከሻቸው ላይ በሙሎጊያዎች አድርግገው ተሸከሙ።
\s5
\v 16 ዳዊትም በዜማ መሣሪያ ማለትም በመሰንቆ፣በበገና፣በፅናፅል እየታጀቡ የደስታ ዜማዎችን እያዜሙ መዘመራንን ከወንድሞቻቸው መካከል እንዲሾሙ ሌዋውያኑ መሪዎች ነገራቸው።
\v 17 ስለዚህ ሌዋውያኑ የኢዮኤልን ልጅ ኤማንን ሾሙ፤ከወንድሞቹም የበራክያን ልጅ አሳፍን፣ከወንድሞቻቸው ከሜራራ ዘሮች የቂሳን ልጅ ኤታንን ሾሙ፤
\v 18 ከእነሱም ጋር ወንድሞቻቸውን በደረጃ ተሾሙ፤እነሱም ዘካሪያስ፣ያዝኤል፣ሰሚራ ሞት፣ይሒኤል፣ዑኒን፣ኤልያብ፣በናያስ፣መዕሤያን፣መቲትያ፣ ኤሊፍሌሁ፣ሚቅኔያ፣ደግሞም በር ጠባቂዎቹ ዖቤድ ኤዶምና ይዒኤል ነበሩ።
\s5
\v 19 መዘመራኑ ኤማን፣አሳፍ ኤታን በናስ ጸናጽል ድምፁን ከፍ እድርገው እንዲያሰሙ ተሾሙ፤
\v 20 ዘካሪያስ፣ዓዝኤል፣መዕሤያና በናያስ ደግሞ በአላሞት ቅኝት መሰንቆ ይገርፉ ነበር።
\v 21 እንዲሁም መቲትያ፣ኤሊፍሌሁ፣ሚቅኔያ፣ዖብድኤዶም፣ይዒረድኤ፣ ዓዛዝያ፣በሺሚኒት ቅኝት በገና ይደረድሩ ነበር።
\s5
\v 22 የዝማሬው ኅላፊ ሌዋዊው አለቃ ክንያን ነበረ፤ይህን ኅላፊነት የወሰደው በዝማሬ የተካነ ስለ ነበር ነው።
\v 23 በራክያና ሕልቃና ያታቦቱ በር ጠባቂዎች ነበሩ፤
\v 24 ካህናቱ ሰበኒያ፤ኢዮሣፍጥ፣ናትናኤል፣ዓማሣይ፣ዘካሪያስ፣በናያስና አልዓዛር በእግዚአብሔር ታቦት ፊት መለከት ይነፋ ነበር።ዖቤድኤዶምና ይሒያ ደግሞ ያታቦቱ በር ጠባቂዎች ነበሩ።
\s5
\v 25 ስለዚህ ዳዊት የእስራኤል ሽማግሌዎችና የሻለቃው አዛዦች የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳኑን ታቦት ከዖቤድኤዶም ቤት በደስታ ለማምጣት ሄዱ።
\v 26 የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት የተሸከሙትን ሌዋውያን እግዚአብሔር ረድቶአቸው ስለ ነበር፣ሰባት ኮርማዎችና ሰባት አውራ በጎች ሠው።
\s5
\v 27 ታቦቱን የተሸከሙት ሌዋውያን ሁሉ፣መዘመራኑና የመዘመራኑ አለቃ ክናንያ የለበሱትና ዐይነት ከቀጭን በፍታ የተሠራ ልብስ ዳዊትም ለብሶ ነበር፤እንዲሁም በከፍታ የተሠራ ኤፋድ ለብሶ ነበር።
\v 28 በዚህ ሁኔታ መላው የእስራኤል ህዝብ በሆታ ቀንደ መለከትና እምቢልታ እየነፉ፣ጽናጽል እየጸነጸሉ፣መሰንቆና በገና እየደረደሩ የእግዚአብሔር የኪዳኑን ታቦት አመጡ።
\s5
\v 29 የእግዚአብሔር የኪዳኑ ታቦት ወደ ዳዊት ከተማ ሲገባ የሳኦል ልጅ ሚልኮል በመስኮት ሆና ተመለከተች ፤ንጉሥ ዳዊት ደስ ብሎት ሲያሸበሽብ አይታ በልቧ ናቀችው።
\s5
\c 16
\p
\v 1 ከዚያም የእግዚአብሔር ታቦት አምጥተው ዳዊት በተከለለት ድንኳን ውስጥ አኖሩት፤የሚዋጠል መሥዕዋትና የኅብረት መሥዕዋትም በእግዚአብሔር ፊት አቀረቡ።
\v 2 ዳዊት የሚቃጠለውን መሥዕዋትና የኅብረቱ መሥዕዋት ከሠዋ በኋላ፣ህዝቡን በእግዚአብሔር ስም ባረከ።
\v 3 ከዚያም ለእስራኤል ሁሉ ለወንዱም ልችሴቱም አንዳንድ ሙልሙል ዳቦ፣አንዳንድ ጥፍጥፍ ዘቢብ ሰጠ።
\s5
\v 4 በእግዚአብሔር ታቦት ፊት እንዲያገለግሉና ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ልመና፣ምስጋናና ውዳሴ እንዲቀርቡ ከሌዋውያን ሰዎች ሾሙ፤
\v 5 አለቃው አሳፍ ነበረ፤ከእርሱ ቀጥሎ ዘካሪያስ ሁለተኛ ሆኖ ተሾመ፤ከዚያም ይዒኤል፣ሰሚራሞት፣ይሒኤል፣መቲትያ፣ኤልያብ፣በናያስ፣ ዖቤድኤዶም፣ይዒኤል ተሾሙ፤እነሱም በመሰንቆና በበገና ይዘምሩ ነበር፤አሳፍ ደግሞ ጽናጽል የሚጸነጽል ሆኖ ተመደበ።
\v 6 እንዲሁም ካህናቱ በናያስና የሕዚኤል ዘውትር በእግዚአብሔር የኪዳኑ ታቦቱ ፊት መለከት እንዲነፉ ተመደቡ።
\s5
\v 7 በዚያም ቀን ዳዊት በመጀመሪያ ለአሳፍና ለሥራ ጓደኞቹ ይህን የእግዚአብሔር ምስጋና መዝሙር ሰጠ፤
\v 8 ለእግዚአብሔር ምስጋና አቅርቡ፤ስሙንም ጥሩ፤ለአሕዛብ ያደረገውን ሁሉ ንገሩ፤
\v 9 ዘምሩለት፤ውዳሴም አቅርቡለት፤ድንቅ ሥራውን ሁሉ ንገሩ፤
\s5
\v 10 በቅዱስ ስሙ ተጓደዱ፤እግዚአብሔር የሚፈልግ ሁሉ፤ልባቸው ሐሤት ያድርግ፤
\v 11 ወደ እግዚአብሔር ወደ ኅይሉ ተምልከቱ፤ዘውትር ፊቱን ፈልጉ፤
\s5
\v 12 ይደረጋቸውን ድንቅ ሥራዎች፣ታምራቱንና የሰጠውንም ፍርድ አስታውሱ፤
\v 13 እናንተ የባሪያው የእስራኤል ዘሮች፣እናንተ የተመረጣችሁ የያዕቆብ ልጆች።
\v 14 እርሱ እግዚአብሔር አምልካችን ነው፤ፍርዱም በምድር ሁሉ ላዬ ነው፤
\s5
\v 15 ኪዳኑን እስከ ዘላለም፣ይያዘዘውንም ቃል እስከ ሺህ ትውልድ ያስባል፤
\v 16 ከአብርሃም ጋር የገባውን ቃል ኪዳን፣ለይስሐቅ የማለውን መሐላ።
\v 17 ይህንንም ለያዕቆብ ሥርዐት አድርጎ አጸና፤ለእስራኤልም የዘላለም ኪዳን አደረገ፤
\v 18 እንዲህ ሱል "የምትወርሰው ርስት እንዲሆን፣የከነዓንን ምድር ለአንተ እሰታለሁ።"
\s5
\v 19 ቁጥራቸው ገና ጥቂት ሳለ፤በርግጥ ጥቂትና መጻተኞች ሳሉ፤
\v 20 ከአንዱ ሕዝብ ወደ ሌላው ሕዝብ ከአንዱም መንግሥት ወደ ሌላው መንግሥት ተንከራተቱ።
\v 21 ማንም እንዲጨቁናቸው አልፈቅድም፤ስለ እነርሱም ነገሥታትን ገሠጸ፤
\v 22 እንዲህ ሲል፤"የቀባኋቸውን አትንኩ፤በነብያቴ ላይ ክፉ አታድርጉ።"
\s5
\v 23 ምድር ሁሉ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ማዳኑንም ዕለት ዕለት ዐውጁ።
\v 24 ክብሩን ለአሕዛብ ተናገሩ፤ድንቅ ሥራዎቹን ለሕዝቦች ሁሉ ንገሩ።
\s5
\v 25 እግዚአብሔር ታላቅ ነው፤ምስጋናውም ብዙ ነው፤ከአማልዕክትም ሁሉ በላይ ሊፈራ የሚገባው ነው።
\v 26 የአሕዛብ ሁሉ አማልክት ጣዖታት ናቸው፤እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ሠራ።
\v 27 በፊቱ ክብርና ሞገስ አለ፤ ብርታትና ደስታም በማድሪያው ስፍራ።
\s5
\v 28 የአሕዛብ ወገኖች ለእግዚአብሔር ስጡ፤ክብርና ኅይልን ለእግዚአብሔር አምጡ።
\v 29 ለስሙ የሚገባውን ክብር ለእግዚአብሔር ሰጡ፤መባ ይዛችሁ በፊቱ ቅረቡ፤በቅድስናውም ክብር ለእግዚአብሔር ሰገዱ።
\s5
\v 30 ምድር ሁሉ በፊቱ ትንቀጥቀጥ፤ዓለም በጽኑ ተመሥርታለች፤አትናወጥምም።
\v 31 ሰማያት ደስ ይባላቸው፤ምድር ሐሤት ታድርግ፤በአሕዛብ መካከል፣"እግዚአብሔር ነገሠ!"ይበሉ።
\s5
\v 32 ባሕርና በውስጧ ያለው ሁሉ ይናውጥ፤ሜዳዎችና በእርሷ ላይ ያሉ ሁሉ ሐሤት ያድርጉ።
\v 33 ያን ጊዜ የዱር ዛፎች በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይበላቸው፤በደስታ ይዘምራሉ፤በምድር ላይ ሊፈርዱ ይመጣልና።
\s5
\v 34 ቸር ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ፍቅሩንም ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።
\v 35 «አዳኛችን እግዚአብሔር ሆይ፤ታደገን፤ለቅዱስ ስምህ ምስጋና እንድናቀርብ፣በምስጋናም እንድንከብር ስብሰበን"ብላችሁ ጩኹ።
\s5
\v 36 ከዘላለም እስከ ዘላለም፣ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን።ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ፣"አሜን፤እግዚአብሔር ይመስገን"አለ።
\s5
\v 37 ዳዊትም ለእያንዳንዱ ቀን በተመደበው መሠረት ዘውትር እንዲያገለግሉ አሳፍና የሥራ ባልደረቦቹን በዚያው በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት ፊት ተዋቸው።
\v 38 እንዲሁም ዖቡድኤዶምና ሥልሳ ስምንቱ የሥራ ባልደረቦቹ አብረዋቸው እንዲያገለግሉ በዚያው ተዋቸው።የኤዶታም ልጅ ዖቤድኤዶምና ሖላ የቅጥሩ በር ጠባቂዎች ሆኑ።
\v 39 ዳዊት ካህኑን ሳዶቅንና የሥራ ባልደረቦቹን ካህናት በገባዖን ከፍተኛ ቦታ ላይ በሚገኘው በእግዚአብሔር ድንኳን ፊት ተዋቸው፤
\s5
\v 40 የተዋቸውም ለእስራኤል በተሰጠው ትእዛዝ መሠረት በእግዚአብሔር ሕግ እንደ ተጻፈው ሁሉ በመሠዊያው ላይ የሚቀርበውን የሚቃጠል መሥዕዋት ላይ የሚቀርበውን የሚቃጠል መሥዋዕት ጧትና ማታ በየጊዜው እንዲያቀርቡ ነው።
\v 41 ደግሞም፤"ፍቅሩ ለዘላለም ነውና"እያሉ ምስጋና እንዲያቀርቡ ኤማንና ኤዶታም እንዲሁም ተመርጠውና ስማቸው ተመዝግቦ የተመደቡ ሌሎችም አብረዋቸው ነበሩ።
\s5
\v 42 ድምፅ መለከቱንና ጽናጽሉን ለማሰማት፤ደግሞም መንፈሳዊ መዝሙር ሲዘመር ሊጠቀሙባቸው ሌሎች መሣሪያዎች ኅላፊዎች ኤማንና ኤዶታም ነበሩ፤የኤዶታምም ልጆች በሩን እንዲጠብቁ ተመድበው ነበር።
\v 43 ከዚያም ህዝቡ ተነሣ፤እያንዳንዱም ወደየቤቱ ሄደ።ዳዊትም ቤተ ሰቡን ለመባረክ ወደ ቤቱ ተመለሰ።
\s5
\c 17
\p
\v 1 ዳዊት በቤተ መንግሥቱ ተደላድሎ በተቀመጠበት ጊዜ፤ነቢዩ ናታንን"እነሆ እኔ ከዝግባ በተሠራ ቤት ውስጥ እኖራለሁ፤የእግዚአብሔር የኮዳኑ ታቦት ግን በድንኳን ውስጥ ይኖራል"አለው።
\v 2 ናታንም ለዳዊት፣"እግግዚአብሔር ከአንተ ጋር ስለሆነ፣ያሰብከውን ሁሉ እድርግ"ሲል መለሰለት።
\s5
\v 3 በዚያም ሌሊት የእግዚአብሔር ቃል ወደ ናታን መጥቶ እንዲህ አለው፤
\v 4 "ሂድና ለባርያዬ ለዳዊት እንዲህ ብለህ ንገረው፤እግዚአብሔር የሚለውን ይህን ነው፤እኔ የምኖርበትን ቤት የምትሠራልኝ አንንተ አይደለህም።
\v 5 እስራኤልን ከግብፅ ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ፤ከአንዱ ድንኳን ወደ ሌላው ማደሪያ እሄድ ነበር እንጂ፣በቤት ውስጥ አልኖርሁም።
\v 6 ከእስራኤላዊያን ጋር በሄድኩባቸው ቦታዎች ሁሉ፣ሕዝቤን እንዲጠብቁ ላዘዝኋቸው መሮዎቻቸው ከቶ፣"ለምን ከዝግባ ዕንጨት ቤት አልሰራችሁልኝምያልሁበት ጊዜ አለን?፤
\s5
\v 7 "ከእንግዲህ አሁንም ለባሪያዬ ለዳዊት እንዲህ ብለህ ንገረው፤የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሚለው ይህን ነው፤የሕዝቤ ይእስራኤል ገዥ እንድትሆን በጎችን ከመጠበቅና ከመከትተል አንሥቶ ወሰድሁህ።
\v 8 በሄድህበት ሁሉ ከአንተ አልተለየሁህም፤ጠላቶችህም ስምህን እንደ ምድር ታላላቅ ሰዎች ስም ገናና አደርገዋለሁ።
\s5
\v 9 ለሕዝቤ ለእስራኤል መኖሪያ ስፍራ እሰጥተዋለሁ፤የራሳቸውም መኖሪያ ስፍራ እንዲኖራቸው ከእንግዲህም በኋላ እንዳይናወጡ አደርጋቸዋለሁ።ክፉ ሰዎች በመጀመሪያ እንዳደረጉት ሁሉ፤ከእንግዲህ አይጨቁናቸውም፤
\v 10 ከዚህ ቀደም በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መሪዎች በሾምሁ ጊዜ ጨቋኞቹ ያደረጉትን ዛሬ አያደርጉትም፤ጠላቶቻችሁም ሁሉ አዋርዳቸዋለሁ።"እግዚአብሄር ቤት እንደሚሠራልህ በግልፅ እነግርሃለሁ፤
\s5
\v 11 ዘመንህን ጨርሰህ ወደ አባቶችህ በምትሄድበት ጊዜ፤ከአብራክህ ከተከፈሉት ልጆችህ አንዱ በእግርህ እንዲተካ አደረጋለሁ፤መንግሥቱንም አፅናለሁ፤
\v 12 ቤት የሚሠራልኝ እርሱ ነው፤እኔም ዙፋኑን ለዘላለም አፀናለሁ።
\s5
\v 13 አባት እሆነዋለሁ፤እርሱም ልጅ ይሆነኛል፤ፅኑ ፍቅሬን ከአንተ በፊት ከነበረው ላይ እንደወሰድሁ፣ከእርሱ ላይ ከቶ አልወስድም።
\v 14 በቤቴና በመንግሥቴ ላይ ለዘላለም እኖረዋለሁ፤ዙፋኑም ለዘላለም ይፀናል።"
\v 15 ናታንም የዚህን ሁሉ ራእይ ቃል ለዳዊት ነገረው።
\s5
\v 16 ከዚያም ንጉሥ ዳዊት ገባ፤በእግዚአብሔር ፊት ተቀምጦ እንዲህ አለ፤ "እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፤ለመሆኑ እስከዚህ ያደረሰኸኝ እኔ ማን ነኝ? ቤተ ሰብይስ ምንድን ነው?
\v 17 አምላክ ሆይ፤ይህ በፊትህ በቂ እንዳልሆነ ቁጥረህ ስለ ወደፊቱ የባሪያህ ቤት ተናገረ።እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፤እኔንም ከሰዎች ሁሉ እጅግ የከበርረ ሰው አድርገህ ተመለከትኸኝ።
\v 18 ባሪያህን ስላከበትኸው፣ዳዊት ከዚህ በላይ ምን ማለት ይችላል? ባሪያህ እኮ ታውቀቃለህ፤
\s5
\v 19 እግዚአብሔር ሆይ፤ስለ ባሪያህ ብለህና እንደ ፈቃድህም መሠረት ይህን ታላቅ ነገር አድርግሃል፤እነዚህም ታላላቅ ተስፋዎች ሁሉ እንዲታወቁ አደረግህ።
\v 20 አቤቱ፤እንደ አንተ ያለ የለም፤በጆሮአቸን አንደ ሰማነው ሁሉ ከአንተ በቀር አምላክ የለም
\v 21 ከግብፅ ተቤዠተህ እንዳወጣኸው እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ያለ ማን አለ? እነርሱ እግዚአብሔር ለራሱ ሊቤዣቸው ናቸው፤በሕዝብህም ፊት ታላቅና አስፈሪ ነገሮችን በማድረግ መንግሥታትን በፊታቸው አሳደድህ።
\s5
\v 22 ሕዝብህንም እስራኤልን ለዘላለም የራስህ ሕዝብ አደረግኸው፤እግዚአብሔር ሆይ፤አንተም አምላክ ሆንህለት።
\v 23 እግዚአብሔር ሆይ፤አሁንም ስለባሪያህ ስለ ቤቱ የሰጠኸው ተስፋ ለዘላለም የጸና ይሁን፤የሰጠኸውንም ትተስፋ ፈፅም፤
\v 24 ይህም ስምህ ጸንቶ እንዲኖርና ለዘላለም ታላቅ እንዲሆን ነው።ከዚያም ሰዎች "የእስራኤል አምላክ ጌታ እግዚአብሔር በእውነት የእስራኤል አምላክ ነው!"ይላሉ፤የባሪያህ የዳዊትም ቤት በፊትህ የጸና ይሆናል።
\s5
\v 25 አምላክ ሆይ፤ቤት እንደምትሠራለት ለባሪያህ ገልጸህለታል፤ስለዚህ ባሪያህ ወደ አንተ ለመጸለይ ድፍረት አገኘ።
\v 26 እግዚአብሄር ሆይ፤በእውነት አንተ አምላክ ነህ፤ይህንንም መልካም ተስፋ ለባሪያህ ስጥተሃል።
\v 27 በፊትህ ለዘላለም እንዲኖር አሁንም የባሪያህን ቤት ልትባርክ ወደሃል፤እግዚአብሔር ሆዩ፤የባረክኸውን አንተ ስለ ሆንህ፣ለዘላለም የተባረከ ይሆናል።
\s5
\c 18
\p
\v 1 ከዚህ በኋላ ዳዊት ፍልስጥኤማዊያንን ድል መትቶ ተገዢ አደረጋቸው፤ጌትንና በዙሪያዋም የሚገኙትን መንደሮች ከፍልስጥኤማዊያን እጅ ወስደ።
\v 2 እንዲሁም ዳዊት ሞዓባዊያንድል አደረጋቸው፤እነሱም ገባሮቹ ሆኑ፤ግብርም አመጡለት።
\s5
\v 3 ከዚያም በላይ ዳዊት በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ የነበረው ግዛት ለመቁጣጠር በሄደ ጊዜ፣የሱባን ንጉሥ አድርአዛርን እስከ ሐማት ድረስ ዘልቆ ወጋው።
\v 4 ዳዊትም አንድ ሺህ ሠረገላ. ሰባት ሺህ ፈረሰኛና ሃያ ሺህ እግረኛ ወታደር ማረከ፤አንድ መቶ የሠረገላ ፈረሳች ብቻ አስቀርቶ የቀሩትን ቋንጃቸውን ቁረጠ።
\s5
\v 5 ሶርያውያንም የሱባን ንጉሥ እድርአዛርን ለመርዳት ከደማስቆ በመጡ ጊዜ፣ከእነሱ ሃያ ሁለት ሺህ ሰው ገደለ።
\v 6 ከዚያም በሶርያ ግዛት ውስጥ ባለችው ወደማስቆ የጦር ሰፈር ፤አቋቋመ፤ሶርያውያን ገባሮቹ ሆኑ፤ግብርም አመጡለት።እግዚአብሔርም ዳዊትን በሄደበት ሁሉ ድል አጎናፀፈው።
\s5
\v 7 ዳዊትም የአድርአዘር ጦር አለቆች ያነገቡትን የወርቅ ጋሻ ወሰደ፤ወደ ኢየሩሳሌም አመጣው።
\v 8 ዳዊት ከአድርአዛር ከተሞች ከጢብሐትና ከኩን እጅግ ብዙ ናስ ወስደ፤ሰለሞን የናሱን ባሕር፤ዐምዶቹንና ልዩ ልዩ የናስ ዕቃዎቹን የሠራው በዚሁ ነበር።
\s5
\v 9 የሐማት ንጉሥ ቶዑ ዳዊት የሱባን ንጉሥ የአድርአዛርን ሰራዊት ሁሉ ድል እንደመታ ሲሰማ፣
\v 10 እጅ እንዲነሳውና ደስታውንም እንዲገልጥለት ልጁን አዳራምን ወደ ንጉሥ ዳዊት ላከው፤ቶዑ ከአድርአዛር ጋር ብዙ ጊዜ ጦርነት ገጥሞ ነበር።አዶራምም ከወርቅ፣ከብርና ከነስ የተጀሩ ልዩ ልዩ ዕቃዎች አመጣለት።
\v 11 ንጉሥ ዳዊት ከሞዓብ፣ከአሞናዊያን፣ከፍልስጥኤማውያንና ከአማሌቃውያን ከእነዚህ ሁሉ መንግሥትታት የማረከውን ወርቅና ብር ከዚህ ቀደም እንዳደረገው ሁሉ፤እነዚህንም ዕቃዎች ለእግዚአብሔር ቀደሰ።
\s5
\v 12 የጹሩያ ልጅ አቢሳ በጨው ሸለቆ ዐሥራ ስምንት ሺህ ኤዶማውያን ገደለ።
\v 13 እርሱም በኤዶም የጦር ሰፈሮች አቋቋም፤ኤዶማውያንም ሁሉ ለንጉሥ ዳዊት ገባሮች ሆኑ።እግዚአብሔር ዳዊትን በሄደበት ሁሉ ድል አጎናጸፈው።
\s5
\v 14 ዳዊት በመላው እስራኤል ላይ ነገሠ፤ለሕዝቡም ሁሉ ፍትሕና ጽድቅን አሰፈናላቸው።
\v 15 የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ የሰራዊት አዛዥ ነበረ፤የአሒሉድ ልጅ ኢዮሣፍጥ ደግሞ የቤተ መዛግብቱ ኃላፊ ነበረ።
\v 16 የአኪጦብ ልጅ ሳዶቅና የአቤምሜሌክ ልጅ አብያታር ካህናት ነበሩ፤ሱሳ ደግሞ ጸሓፊ ነበረ።
\v 17 የዮሄድ ልጅ በናያስ የከሊታውያንና የፊልታውያን አዛዥ ነበረ።የዳዊት ወንዶች ልጆች ከንጉሥ ቀጥሎ የበላይ ሹማምት ነበሩ።
\s5
\c 19
\p
\v 1 ከዚህ በኋላ የአሞናውያን ንጉሥ ናዖስ ሞተ. ልጁም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።
\v 2 ዳዊትም "አባቱ ለእኔ በጎ ነገር እንዳደረገልኝ እስቲ እኔም ለናዖስ ልጅ ለሐኖን በጎ ነገር ላድርግለት"ብሎ አስብ።ስለዚህ ዳዊት ስለ አባቱ ሞት ሐዘኑን ለመግለጽ ወደ ሐኖን መልክተኞችን ላከ።የዳዊት ሰዎች ሐናቸውን ለመግለጽ ሐኖን ወደሞኖርበት ወደ አሞናውያን ምድር በመጡ ጊዜ፣
\v 3 የአሞናውያን መኳንንት ለሐኖን "ዳዊት ሀዘኑን ለመግለጽ ሰዎችን ወደ አንተ የላከው አባትህን አክብሮ ይመስልሃን? ሰዎች ወደ አንተ የመቱት አገሩቱን ለመመርመር፣ለመሰለልና ለመያዝ አይደለምን? አሉት።
\s5
\v 4 ስለዚህ ሐኖን የዳዊትን ሰዎች ይዞ ላጫቸውል ልብሳቸውንም እስከ መቀመጫቸው ድረስ መኻል ለመኻል ቀዶ ሰደዳቸው።
\v 5 በሰዎቹ ላይ የደረሰባቸውን ዳዊት በሰማ ጊዜ እጅግ ዐፍረው ስለ ነበር፣ወደ እነርሱ መልክተኞችን ላከ፤ንጉሥም፣"ጢማችሁ እስኪያድግ ድረስ በኢያኮር ቁዩና ከዚያ በኋላ ትመጣላችሁ"አለ።
\s5
\v 6 አሞናውያን በዳዊት ዘንድ እንደ ተጠሉባወቁ ጊዜ፣ሐኖንና አሞናውያን ከመሰጴጦምያ፣ከአራምመዓካና ከሱባ ሠረገሎችንና ፈረሶችን ለመከራየት አንድ ሺህ መክሊት ብር ላኩ፤
\v 7 ከዚያም ሠላሳ ሁለት ሺህ ሠረገሎችንና ፈረሶኞችን እንዲሁም የመካዓን ንጉሥና ወታደሮች በገንዘብ ቀጠሩ፤እነርሱም መጥተው በሜድባ አጠገብ ሲሰፍሩ፣አሞናውያን ደግሞ ከየከተሞቻቸው ተሰብስበው ለጦርነት ወጡ።
\s5
\v 8 ዳዊት ይህን ሲሰማ ኢዮአብንና መላውን ተዋጊ ሰራዊት ላከ።
\v 9 አሞናውያንም መጥተው ወደ ከተማቸው በሚያስገባው በር ላይ ለጦርነት ተሰለፉ፤የመጡት ነገሥታት ደግሞ ብቻቸውን በሜዳው ላይ ነበሩ።
\s5
\v 10 ኢዮአብም ከፊቱና ከኋላው ጦር መኖሩንና አየ፤ስለዚህ በእስራኤል የታወቁትን ጀግኖች መርጦ ሶርያውያንን እንዲገጥሙ አሰለፋቸው።
\v 11 የቀሩትም ሰዎች በወንድሙ በአቢሳ ሥጋ ሆነው አሞናውያንን እንዲገጥሙ አስለፋቸው።
\s5
\v 12 ኢዮአብም እንዲህ አለ፤"ሶርያውያን ከበረቱብኝ አንተ ትረዳኛለህ"አሞናውያን ከበረቱብህ ደግሞ እኔ እረዳሃለሁ።
\v 13 እንግዲህ በርቱ፤ስለ ሕዝባችንና ስለ አምላካችን ከተሞች ብለን በጀግንነት እንዋጋ፤እግዚአብሔር ደስ ያሰኘውን ያድርግ።"
\s5
\v 14 ከዚያም ኢዮአብና አብረውት ያሉት ወታደሮች ሶርያውያን ለመዋጋት ወደ ፊት ገሠገሠ፤ሶርያውያንም ከፊታቸው ሸሹ።
\v 15 አሞናውያንም ሶርያውያን መሸሻቸውን ሲያዩ፣እርሱም ከውንድሙ ከአቢሳ ፊት ሸሽተው ወደ ከተማይቱ ገቡ፤ስለዚህ ኢዮአብ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ።
\s5
\v 16 ሶርያውያን በእስራኤል መሸነፋቸውን ሲያዩ፣መልክተኞችን ልከው ከኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ ያሉትን ሶርያዊያን አስመጡ፤እነዚህንም የሚመራቸው የአድርአዛር ስራዊት አዛዥ ሾፋክ ነበረ።
\v 17 ዳዊት ይህን ሲሰማ፣እስራኤልን ሁሉ ሰብስቦ ዮርዳኖስን ተሻገረ፤ወደፊት በመገሥገሥም ከፊት ለፊታቸው የውጊያ መሥመሩን ያዘ።ዳዊትም ሶርያውያንን ጦርነት ለመግጠም ወታደሮቹን አሰለፈ፤እነርሱም ተዋጉት።
\s5
\v 18 ይሁን እንጂ ከእስራኤል ፊት ሸሹ።ዳዊትም ሰባት ሺህ ሠረገለኞችና አርባ ሺህ እግረኛ ወታደሮች ገደለ።የሠራዊታቸው አዛዥ ሾፋክም በጦርነት ላይ ሞተ።
\v 19 የአድርአዛርም ሹማምት በእስራኤል መሸነፋቸውን ሲያዩ፣ከዳዊት ጋር ታረቁ፤ገባሮቹም ሆኑ።ስለዚህ ሶርያውያን ከዚህ ጊዜ ጀምሮ አሞናውያንን ለመርዳት ፍቃደኞች አልሆኑም።
\s5
\c 20
\p
\v 1 ነገሥታት ለጦርነት በሚሄዱበት በፈደይ ወራት፣ኢዮአብ የጦር ሰራዊቱን እየመራ ሄዶ የአሞናውያንን አገር አጠፋ፤ወደ ራባትም ሄዶ የአሞናውያንን አገር አጠፋ፤ወደ ራባትም ሄዶ ከበባት፤ዳዊት ግን ኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር።ኢዮአብም ራባትን ወግቶ አፈራረሳት፤
\s5
\v 2 ዳዊት የንጉሣቸውን ዘውድ ከራሱ ላይ ወሰደ፤ክብደቱም አንድ መክሊት ወርቅ ነበረ፤ይህንንም በዳዊት ራስ ላይ ጫኑለት፤እንዲሁም ከከተማይቱ እጅግ ብዙ ምርኮ ወሰደ።
\v 3 በዚያ የነበረውን ሕዝብ አውጥቶ መጋዝ፣ዶማና መጥረቢያ ይዘው እንዲሠሩ አደረጋቸው።ዳዊት በሌሎቹም የአሞን ከተሞች ሁሉ ይህንኑ አደረጉ።ከዚያም ዳዊትና መላው ሰራዊቱ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።
\s5
\v 4 ከዚያም በኋላ ከፍልስጥኤማዊያን ጋር በጌዝር ጦርነት ተደረገ፤በዚያ ጊዜ ኩሳታዊው ሴቦካይ የራፋይም ዘር የሆነውን ሲፋይን ገደለ፤ፍልስጥኤማውያንም ድል ተመቱ።
\v 5 ከፍልስጥኤማውያን ጋር ሌላ ጦርነት ተደረገ፤የያዒር ልጅ ኤልያናን የጦሩ የቦውፍረቱ እንደ ሽማኔ መጠቅለያ የሚያህለውን የጌት ተወላጅ የሆነውን የጎልያድን ወንድም ላሕሚን ገደለ።
\s5
\v 6 ደግሞም ጌት ላይ በተደረገ ሌላ ጦርነት፣በእጆቹና በእግሮቹ ላይ ስድስት ስድስት ጣት በድምሩ ሃያ አራት ጣት የነበሩት አንድ ግዙፍ ሰው ነበረ፤ይህም እንደዚሁከራፋይም ዘር ነበረ።
\v 7 እርሱም እስራኤልን በተገዳደረ ጊዜ የዳዊት ወንድም የሳምዓ ልጅ ዮናታን ገደለው።
\v 8 በጌት የነበሩ የራፋይም ዘሮች እነዚህ ናቸው፤እነሱም በዳዊትና ሰዎቹ እጅ ወደቁ።
\s5
\c 21
\p
\v 1 ሰይጣን በእስራኤል ላይ ተነሥቶ ዳዊት የእስራኤልን ሕዝብ እንዲቁጥር አነሣሣው።
\v 2 ዳዊትም ኢዮአብንና የሰራዊቱን አዛዦች፤"ሄዳችሁ ከቤርሳቤህ እስከ ዳን ያሉትን እስራኤላዊያን ቁጠሩ፤ከዚያም ምን ያህል እንደ ሆኑ ዐውቅ ዘንድ ንገሩኝ አላቸው።
\v 3 ኢዮአብ ግን፣እግዚአብሔር የእስራኤል ሰራዊት አሁን ካለው በላይ በመቶ ዕጥፍ ያብዛው፤ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፤ሁልስ ቢሆኑ የጌታዬ ተገዢዎች አይደሉምን? ታዲያ ጌታዬ ይህን ማድረግ ለምን አስፈለገው? ለምንስ በእስራኤል ላይ በደል ያመጣል?"አለ።
\s5
\v 4 ይሁን እንጂ የንጉሥ ቃል ኢዮአብን አሸነፈው፤ስለዚህ ኢዮአብ ወጣ፤በመላው እስራኤል ከተዘዋወረ በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ።
\v 5 ኢዮአብም የተዋጊዎቹን ሰዎች ቁጥር ለዳዊት አቀረበ፤እነዚህም በመላው እስራኤል አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ሺህ፣በይሁዳ ደግሞ አራት መቶ ሰባ ሺህ ሲሆኑ፣ሁሉም ሰይፍ መምዘዝ የሚችሉ ነበሩ።
\s5
\v 6 ነገር ግን የንጉሡ ትእዛዝ በእርሱ ዘንድ አስጸያፊ ነበረና፣ኢዮአብ የሌዊንና የብንያም ነገድ ጨምሮ አልቁጠረም።
\v 7 ይህ ትእዛዝ በእግዚአብሄር ዘንድ የተጠላ ነበር፤ስለዚህ እግዙአብሔርን ቀጣ።
\v 8 ከዚያም ዳዊት እግዚአብሔርን፣"ይህን በማድረጌ እጅግ በድያለሁ፤የፈጸምኩትም የስንፍና ሥራ ስለሆነ፣የባሪያህን በደል እንድታስወግድ እለምንሃለሁ"አለ።
\s5
\v 9 እግዚአብሔር የዳዊት ባለ ራእይ የሆነውን ጋድን እንዲህ አለው፤
\v 10 ሂድና ለዳዊት እንዲህ ብለህ ንገረው፤እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፤እነሆ፣ሦስት ምርጫ ሰጥሃለሁ፤በአንተ ላይ እንዳደርስብህ እንዱን ምረጥ።"
\s5
\v 11 ስለዚህ ጋድ ዳዊት ሄዶ እንዲህ አለው፤"እግዚአብሔር የሚለው ይህን ነው፤አንዱን ምረጥ፤
\v 12 የሦስት ዓመት ራብ ወይስ የጠላቶችህን ሰይፍ ለሦስት ወር አይሎብህ ተሰዶ መጥፋት ወይስ ሦስት ቀን የእግዚአብሔር ስይፍ መቅሠፍት በምድሪቱ ላይ ወርዶ የእግዚአብሔር መልአክ እስራኤልን ሁሉ ያጥፋ? እንዲህ ላልከኝ ምን እንደምመልስ ቁርጡን ነገረኝ።
\s5
\v 13 ዳዊትም ጋድን፣"ችጅግ ተጨንቅይአለሁ፤ምሕረቱ ታላቅ ስለሆነ በእግዚአብሔር እጅ መውደቅ ይሻለኛል፤በሰው እጅስ አልወድቅ"አለ።
\v 14 እለዚህ እግዚአብሔር በእስራኤል ሰባ ሺህ ሰው ዐለቀ።
\v 15 እንዲሁም እግዚአብሔር እየሩሳሌምን እንዲያጠፋ መልአክ ላከ፤መልአኩም ሊያጠፋት ሲል እግዚአብሔር አይቶ ስለሚያደርሰው ጥፋት ዐዘን፤ህዝቡን የሚያጠፋውንም መልአክ፣"እጅህን መልስ"አለው።የእግዚአብሔር መልአክ በኢያቡሳዊያ በኦርና ዐውድማ አጠገብ ቆሞ ነበር።
\s5
\v 16 ዳዊት ቀና ብሎ ሲመለከት፣የእግዚአብሔር መልአክ በሰማይና በምድር መካከል ቆሞ አየ፤መልአኩም በኢየሩሳሌም ላይ የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ ይዞ ነበር፤ከዚያም ዳዊትና ሽማግሌዎች ማቅ እንደሚለብሱ በግንባራቸው ተደፉ።
\v 17 ዳዊት እግዚአብሔር "ተዋጊዎቹ እንዲቁጠሩ ያዘዝሁ እኔ እይደለሁም? ኅጢአት የሠራሁበትም ሆነ የበደልሁት እኔ ነኝ፤እነዚህ እኮ በጎች ናቸው፤ታዲያ እነርሱ ምን አደረጉ? እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤እጅህ በእኔና በአባቴ ቤት ላይ ትሁን እንጂ፣መቅሠፍት በሕዝብህ ላይ አይውረድ"አለ።
\s5
\v 18 ከዚያም እግዚአብሔር መልአክ ዳዊት ወጥቶ በአቡሳዊያን በኦርና ዐውድማ ላይ ልችእግዚአብሔር መሠዊያ ይሠራ ዘንድ እንዲነግረው ጋድን አዘዘው።
\v 19 ዳዊትም ጋድ በእግዚአብሔር ስም በነገረው ቃል መሠረት ለመፈፀም ውጣ።
\v 20 ኦርና ስንዴ በመውቃት ላይ ሳለዘወር ሲል መለአኩን አየ፤አብረውት የነበሩት አራት ወንዶች ልጆችም ተሸሸጉ።
\s5
\v 21 ዳዊት ወደ እርሱ እየቀረበ መጣ፤ኦርናቀና ብሎ ሲመለከት፣ዳዊትን አየው፤ከዐውድማውም ወጥቶ መሬት ላይ በግንባሩ ተደፍቶ ዳዊትን እጅ ነሣ።
\v 22 ዳዊትም፣"በሕዝቡ ላይ የወረደው መቅሠፍት እንዲወገድ ለእግዚአብሔር መሠዊያ እሠራ ዘንድ ዐውድማህን ልውሰደው፤ሙሉውን ዋጋ እከፍልሃለሁ"አለው።
\s5
\v 23 ኦርናም ዳዊትም፣"እንዲሁ ወስደው፤ጌታዬ ንጉጅ ደስ ያለውን ያድርግ፤እነሆ ለሚቃጠል መሥዋዕት በሬዎቹን፣መውቂያ በትሮቹን ለማቀጣጠያ ዕንጨት፣ስንዴው ደግሞ ለእህል ቁርባን እንዲሆን እሰጣለሁ፤ሁሉንም እኔ እሰጣለሁ።አለ።
\v 24 ንጉሥ ዳዊት ግን ለኦርና "አይደረግም፤ሙሉውን ዋጋ እኔ እከፍላለሁ፤የአንተ የሆነውን ለእግዚአብሔር ለማውረብ አልፈልግም፤ዋጋ ያልከፈልኩበትም የሚቃጠል መሥዋዕት እድርጌ አላቀርብም" ሲል መለሰለት።
\s5
\v 25 ስለዚህ ዳዊት ለኦርና የቦታውን ዋጋ ስድስት መቶ ስቅል ወርቅ ከፈለ።
\v 26 ዳዊትም በዚያ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠርቶ የሚቃጠል መሥዕዋትና የኅብረት መሥዋዕት አቀረበ።እግዚአብሔርም ጠራ፤እግዚአብሔርም የሚቃጠል መሥዕዋት በሚቀርብበት መሠዊያ ላይ ከሰማይ በእሳት መለሰለት።
\v 27 ከዚያም እግዚአብሔር ለመልአኩ ተናገረ፤መልአኩም ሰይፉን ወደ አፎቱ መለሰ።
\s5
\v 28 በዚያን ጊዜ ዳዊት፤እግዚያብሔር በኢያቡሳዊው በኦርና ዐውድማ ላይ እንደ መለሰለት ሲያይ፤በዚያው ቦታ መሥዕዋት ማቅረብ ጀመረ።
\v 29 ሙሴ በምድረ በዳ የሠራው የእግዚአብሔር ማደሪያ ድንኳንና የሚቃጠል መሥዕዋት የሚቀርብበት መሠዊያ በዚያ ጊዜ በገባዖን ኮረብታ ላይ ነበረ።
\v 30 ዳዊት የእግዚአብሔር መልአክ ሰይፍ ሰለፈራ ወዲያ ሄዶ እግዚአብሔር ለመጠየቅ አልቻለም።
\s5
\c 22
\p
\v 1 ከዚያም ዳዊት፣"ከእንግዲህ የእግዚአብሔር አምላክ ቤት በዚህ ይሆናል፤እንዲሁም ስለ እስራኤል የሚቃጠል መሥዕዋት የሚቀርብበት መሠዊያ በዚሁ ይቆማል"አለ።
\v 2 ስለዚህ ዳዊት በእስራኤል የሞኖሩ መጻተኞች እንዲሰበሰቡ አዘዘ፤ከመካከላቸም እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የሚሠራበትን ጥጋብ ድንጋይ እንዲያዘጋጁ ጠራቢዎች መደበ።
\s5
\v 3 ለቅጥር በሮች ምስማርና ማጠፊያ የሚሆን ብዙ ብረትና ከብዛቱ የተነሣ ሊመዘን የማይችል ናስ አዘጋጀ።
\v 4 እንዲሁም ሲዶናውያንና ጢሮሳውያን በብዛት አውጥተውለት ስለ ነበር፣ስፍር ቁጥር የሌለው የዝግባ ዕንጨት አሰናዳ።
\v 5 ዳዊትም፣"ልጅ ሰሎሞን ወጣት ነው፤ልምዱም የለውም፤ለእግዚአብሔር የሚሠራው ቤተ መቅደስ ደግሞ እጅግ የሚያምር፣በአሕዛብም ሁሉ ዘንድ አለበት፤ስለዚህ ሁሉንም እኔ አዘጋጃለሁ"እንዳለው ዳዊት ከመሞቱ በፊት በብዛት አዘጋጀ።
\s5
\v 6 ከዚያም ልጁን ሰሎሞንን ጠርቶ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚያብሔር ቤት እንዲሥራ አዘዘው።
\v 7 ዳዊትም ሰሎሞን እንዲህ አለ፤"ልጄ ሆይ ለአምላክህ እግዚአብሔር ስም ቤት ለመሥራት በልቤ አሰብ ነበር፤
\v 8 ነገር ግን ከእግዚአብሔር እንዲህ የሚል ቃል መጣልኝ፤"አንተ ብዙ ደም አፍስሰሃል፤በፊቴ በምድር ላይ ብዙ ደም ያፈሰስህ ስለሆነ አንተ ለስሜ ቤት አትሠራልኝም፤
\s5
\v 9 ነገር ግን የሰላምና የዕረፍት ሰው የሆነ ልጅ ትወልዳለህ፤ በየአቅጣጫው ካሉ ጠላቶቹ ዐሳርፈዋለሁ፤ ስሙም ሰሎሞን ይባላል። በዘመኑም ለእስራኤል ሰላምና ጸጥታን እሰጣለሁ።
\v 10 ለስሜ ቤት የሚሰራልኝ እርሱ ነው። እርሱ ልጅ ይሆነኛል 'እኔም አባት እሆነዋለሁ። ዙፋንም በእስራኤል ላይ ለዘላለም አጸናለሁ።
\s5
\v 11 አሁንም ልጅ ሆይ፤ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን፤ እንድትፈጽሙ በተናገረውም መሠረት፣ ተሳክቶልህ የአምላክን የእግዚአብሔር ቤት ለመሥራት ያብቃህ።
\v 12 በእስራኤል ላይ አለቃ ባደረገህ ጊዜ የአምላክህ እግዚአብሔርን ትእዛዝ ትፈጽም ዘንድ እግዚአብሔር ጥበብንና ማስተዋል ይስጥህ።
\v 13 ችግዚአብሔር በሙሴ አማካኝነት ለእስራኤል የሰጠውን ሕጉንና ሥርዐቱን ተጠንቅቀን ብትጠብቅ ይሳካልሃል፤ አይዞህ ጠንክር፤ በርትስ፤ ተስፋም አትቁረጥ።
\s5
\v 14 "ለእግዚአብሔር ቤት እንዲሆንም አንድ ሺህ መክሊት ወርቅ፣ አንድ ሚሊዮን መክሊት፣ ብር፣ ከብዛቱ የተነሣ ሊመዘን የማይቻል ናስና ብረት ለማዘጋጅ በተቻለኝ ሁሉ ጥሬአለሁ። ደግሞም እንጨትና ድንጋዮች አዘጋጀሁ፤ በተረፈ አንተ ጨምርበት።
\s5
\v 15 ድንጋይ ጠራቢዎች፣ግን በኞች አናጢዎች የሆኑ ልዩ ሙያ የተጠበቡ ሰዎች አሉህ፤
\v 16 አነዚህ ቁጥራቸው እጅግ የበዛ የውርቅ፣የብር፣የናስና የብረት ሠራተኞች ናቸው።በል ሥራህን ጀምር፤እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን።"
\s5
\v 17 ከዚያም ዳዊት የእስራኤል መሪዎች ሁሉ ልጁን ሰሎሞንን እንዲረዱት አዘዘ፤
\v 18 እንዲህም አለ፤"እግዚአብሔር አምላካችን እስካሁን ከእናንተ ጋር አይደለምን? በየአቅጣጫውስ ዕረፍትን ስጥቷችሁ የለምን? የምድሪቱንም ነዋሪዎች በእጄ አሳልፎ ሰጥቶኛል፤ምድሪቱም ለእግዚአብሔር ለሕዝቡ ተገዝታለች።
\v 19 አሁንም እግዚአብሔር የኪዳኑን ታቦትና ንዋያት ቅዱሳቱን ለእግዚአብሔር ስም ወደሚሠራው ቤተ መቅደስ አምጥታችሁ የአምላክ የእግዚአብሔር መቅድደስ ሥሩ።
\s5
\c 23
\p
\v 1 ዳዊት በሽመገለና ዕድሜው በገፋ ጊዜ፤ልጁን ሰሎሞንን በእራኤል ላይ አነገጀው።
\v 2 እንዲሁም መላውን የእስራኤል መሪዎች፣ካህናቱ ሌዋውያኑን ሁሉ በአንድነት ሰበሰበ።
\v 3 ዕድሜውቸው ሥላሳና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ተቁጠሩ፤ቁጥራቸውም በጠቅላላው ሠላሳ ስምንት ሺህ ነበረ
\s5
\v 4 ዳዊትም እንዲህ አለ፤ "ከእነዚህ መካከል ሃያ አራቱ ሺህ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ሥራ ይቁጣጠሩ፤ ስድስቱ ሺህ ደግሞ ሹሞችና ዳኞች ይሁኑ፤
\v 5 አራቱ ሺህ የቅጥሩ በር ጠባቂዎች ይሁኑ፤ አራት ሺህ ደግሞ ለዚሁ ብዬ ባዘጋጀሁት የዜማ መሣሪያ እግዚአብሔር ያመስግኑ"።
\v 6 ዳዊትም ሌዋውያኑን በሌዊ ልጆች በጌድሶን፣ በቀነዓና በሜራሪ በየጎሣቸው መደባቸው።
\s5
\v 7 ከጌድሳናውያን ወገን፤ ለአዳን፣ሰሜኢ።
\v 8 የለእአዳን ወንዶች ልጆች፤ የመጀመሪያው ይሒኤል፣ ዜቶም፣ ኢዮኤል፣ባጠቃላይ ሦስት ናቸው።
\v 9 የስማኢ ወንዶች ልጆች፤ ሰሎሚት፣ ሀዝዝኤል፣ ሐራን፣ ባጠቃላይ ሦስት ናቸው። እነዚህ የለአዳን ቤተሰብ አለቆች ናቸው።
\s5
\v 10 የስማኢ ወንዶች ልጆች፤ ኢኢት፣ ዚዛ፣ የዑስ፣ በሪዓ፣ እነዚህ አራቱ የስሚኤ ልጆች ናቸው።
\v 11 የመጀመሪያው ኢኢት፣ ሁለተኛው ደግሞ ዚዛ፣ ነበረ የዑስና በሪዓ ግን ብዙ ወንዶች ልጆች አልነበሯቸውም፤ ስለዚህ የተቁጥዐሩት በሥራ መደብ እንደ ቤተሰብ ሆነው ነው።
\s5
\v 12 የቀነዓት ወንዶች ልጆች፤ እንበረም፣ ይስዓር፣ ኬብሮን፣ ዑዝኤል፣ ባጠቃላይ አራት ናቸው።
\v 13 የእንበረት ወንዶች ልጆች፤ አሮን፣ ሙሴ። አሮን የተቀደሰ እንዲሆን ተለየ፤ እርሱና ዘሮቹ ለዘላለም ቅዱስ የሆኑትን ነገሮች እንዲቀደሱ፣ እግዚአብሔር ፊት መሥዕዋት እንዲያቀርቡ፤ በፊቱ እንዲያገለግሉና በስሙም ለዘላለም እንዲባረኩ ተለዩ።
\v 14 እግዚአብሔር ሰው የሙሴ ወንዶች ልጆችም እንደ ሌዊ ነገድ ሆነው ተቁጠሩ።
\s5
\v 15 የሙሴ ወንዶች ልጆች፤ ጌርሳም፣ አልዓዛር።
\v 16 የጌሳም ዘሮች፤ ሱባኤል።
\v 17 የአልዓዛር ዘሮች፤ የመጀመሪያው ረዓብያ ነበረ።አልዓዛር ሌሎች ወንዶች ልጆች ግን እጅግ ብዙ ነበሩ።
\v 18 የይስዓር ዶዶችች ልጆች፤ የመጀመሪያው ሰሎሚት።
\s5
\v 19 የኬብሮን ወንዶች ልጆች፤ የመጀመሪያው ዬሪያ፣ ሁለተኛው አማርያ፣ ሦስተኛው የሕዚኤል፣ አራተኛ ይቅምዓም ነበሩ።
\v 20 የዑዝኤል ወንዶች ልጆች፤ የመጀመሪያው ሚካ፣ ሁለተኛው ይሺያ ነበሩ።
\s5
\v 21 የሜራሪ ወንዶች ልጆች፤ ሚሖሊ፣ ሙሲ፣ የሞሐሊ ወንዶች ልጆች አልዓዛር ቂስ ነበሩ።
\v 22 አልዓዛር ወንድ ልጅ ሳይወልድ ሞተ፤ ልጆቹ ሴቶች ብቻ ነበሩ፤ እርሱንም የአጎታቸው የቂስ ልጆች አገቡአቸው።
\v 23 የሙሲ ወንዶች ልጆች፤ ሞሖሊ፣ ዔደር፣ ኢያሪሙት ባጠቃላይ ሦስት ናቸው።
\s5
\v 24 እንግዲህ እነዚህ የቤተሰብ አለቆች ሆነው እያንዳንዳቸው በየስማቸው ተመዝግበው የተቁጠሩት የሌዊ ዘሮች ናቸው፤ ዕድሜአቸው ሃያና ከዚያ በላይ የሆናቸው በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስት የሚያገለግሉ ነበሩ።
\v 25 ዳዊት እንዲህ ብሎ ነበርና፣ "የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ዕረፍት ሰጥቷል፤ በእየሩሳሌምም ለዘላለም ለመኖር መጥቷል፤
\v 26 ሌዋውያን ከእንግዲህ ወዲህ ድንኳኑን ወይም የመገልገያ ዕቃውን ሁሉ መሸከም የለባቸውም።"
\s5
\v 27 ዳዊት በሰጠው የመጨረሻ መመሪያ መሠረት የተቁጠሩት ሌዋውያን ዕድሜያቸው ሃያና ከዚያ በላይ ነበረ።
\v 28 የሌዋውያኑ ተግባር በእግዚአብሔር ቤተ መቅደሱን ቅጥር ግቢና ክፍሎች መንከባከብ፣ የተቀደሱ ዕቃዎች ሁሉ ማጻትና በእግዚአብሔር ቤት ያሉትን ሌሎች ተግባሮች ማከናውን ነበር።
\v 29 እንዲሁም መባ ሆኖ የሚቀረውን ኅብስት ገፅ፣ የእህል ቁርባኑን ዱቄት፣ ያለ እርሾ የሚጋገረውን ቂጣ የሚጋግሩ፣ የሚያቦኩና የሚሰፍረውንም ሆነ የሚለካውን ሁሉ በኅላፊነት የሚቁጣጠሩ እኔሩ ነበር።
\s5
\v 30 በየለዕቱ እግዚአብሔርን ለማመስገንና ለመወደስ ጠዋት ጠዋት ይቆኑ ነበር፤ይህንንም ማታ ማታ፣
\v 31 እንዲሁም በየሰንበቱ፣ በወር መባቻ በዓልና በተደነገጉት በዓላት ሁሉ፣ የሚቃጠል መሥዕዋት ለእግዚአብሔር በሚቀርብበት ጊዜ ሁሉ ይፈፅሙ ነበር። በተወሰነላቸው ቁጥርና በተሰጠው መመሪያ መሠረት ዘውትር በእግዚአብሔር ፊት ያገለግሉ ነበር።
\s5
\v 32 ስለዚህ ሌዋውያኑ ለመገናኘት ድንኳንና ለመቅደሱ እንዲሁም በወንድሞቻቸው በአሮን ዘሮች ሥር ሆነው ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ያለባቸውን ኅላፊነት ያከናውኑ ነበር።
\s5
\c 24
\p
\v 1 የአሮን ልጆች አመዳደብ እንደ ሚከተለው ነበረ፤ የኦ ልጆች ናዳብ፣ አብድዩ፣ አልዓዛር፣ ኢታምር፣ ነበሩ።
\v 2 ናዳብና አብድዩ ግን ዘር ሳይተኩ ከአባታቸው በፊት ሞቱ፤ ስለዚህ አልዓዛርና ኢታምር ካህናት ሆነው ያገለግሉ ነበር።
\v 3 ዳዊትም የአላዓዛር ዘር የሆነው ሳዶቅና የኢታምር ዘር ሆነው አቢሜሌክ እየረዱ እንደየአገልግሎታቸው ሥርዓት እየለየ መደባቸው።
\s5
\v 4 ከኢታምር ይልቅ በአልዓዛር ዘሮች መካከል ብዙ መሪዎች ተገኙ፤ አከፋፈላቸውም እንደሚከተለው ነበር፤ ከአልዓዛር ዘሮች ዐሥራ ስድስት የቤተሰብ አለቆች።
\v 5 ከአልዓዛርና ከኢታምር ዘሮች መካከል የመቅደሱ ሹማምትና የእግዚአብሔር ሹማምት ስለ ነበሩ፣ ያለ አድልዎ በዕጣ ለዩአቸው።
\s5
\v 6 የሌዋውያ የናትናኤል ልጅ ጻሓፊው ሸማያ በንጉሥና በሹማምቱ፣ በካህኑ በሳዶቅ፣ በአብያታር ልጅ በአሜሌክ እንዲሁም በካህናቱና በሌዋውያኑ ቤተሰብ አለቆች ፊት ስማቸውን ጻፊ፤ የጻፈውም አንዱን ቤተሰብ ከአልዓዛር ሌላውን ደግሞ ከኢታምር በመወሰድ ነው፤
\s5
\v 7 የመጀመሪያው ዕጣ ለዮአሩብ፣ ሁለተኛውም ዕጣ ለዮዳሄ ወጣ።
\v 8 ሦስተኛው ለካሪም፣ አራተኛው ለሥዖሪም፣
\v 9 አምስተኛው ለመልክያ፣ ስድስተኛው፤
\v 10 ሰባተኛው ለአቆስ፣ ስምንተኛው ለአብያ፣
\s5
\v 11 ዘጠናኝው ለኢያሱ፣ ዐሥረኛ ለሴኬንያ፣
\v 12 ዐሥራ አንደኛው ልች ኤሊያሴብምም ዐሥራ ሁለተኛው ለያቂም፣
\v 13 ዐሥራ ሦስተኛው ለኦፓ፣ዐሣር አራተኛው ለየሼብአብ፣
\v 14 ዐሥራ ሰባተኛው ለቢልጋ፣ ዐሥራ ስድስተኛው ለኢሜር፤
\s5
\v 15 ዐሥራ ሰባተኛው ለኤዚር፣ ዐሥራ ስምንተኛው ለሃፊጼጽ፣
\v 16 ዐሥራ ዘጠነኛው ለፈታያ፣ ሃያኛው ለኤዜቄል፣
\v 17 ሃያ አንደኛው ለያኪያ፣ ሃያ ሁለተኛው ለጋሙል፣
\v 18 ሃያ ሦስተኛው ለድላያ፣ ሃያ አራተኛ ለመዓዝያ ውጣ።
\s5
\v 19 የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ባዘዘውና ከቀድሞ አባታቸው ከአሮን በተሰጣቸው መመሪያ መጠረት ወደ እግዞአብሔር ቤተ መቅደስ በሚገቡበት ጊዜ፣ የተወሰነላቸው ሥርዐት ይህ ነበር።
\s5
\v 20 የቀሩት የሌዊ ዘሮች አግሚ፦ከእንበረም ወንዶች ልጆች፤ ሱባኤል፤ ከሱባኤል ወንዶች ልጆች፤ ዬሕድያ።
\v 21 ከረዓብያ ወንዶች ልጆች፤ አለቃው ይሺው።
\v 22 ከይስዓራውያን ወገን፤ ሰሎሚት ከሰሎሚት ወንዶች ልጆች፤ ያሐት።
\s5
\v 23 የኬብሮን ወንዶች ልጆች፤ የመጀመሪያው ይሪያ፣ ሁለተኛው አማርያ፣ ሦስተኛው የሕዚኤል፣ አራተኛው ይቀምዓም።
\v 24 የዑዝኤል ልጅ፤ ሚካ። የሚካ ወንዶች ልጆች ሻሚር።
\v 25 የሚካ ወንድም ይሺያ፤ ከይሺያ ወንዶች ልጆች ዘካርያስ።
\s5
\v 26 የሜራሪ ወንዶች ልጆች፤ሞሖሊምም ሙሲ።የያዝያ ወንድ ልጅ በኖ፤
\v 27 የሜራሪ ወንዶች ልጆች፤ ከያዝያ በኖ፣ ሾሃም፣ ዘኩር፣ ዔብሪ።
\v 28 ከሞሒሊ፤ አልዓዛር፤ ይህ ሰው ወንዶች ልጆች አልነበሩትም።
\s5
\v 29 ከቂስ፣ የቂስ ወንድ ልጅ፤ ይረሕምኤል።
\v 30 የሙሲ ወንዶች ልጆች፤ ሞሖሊ፣ ዔዳር፣ ኢያሪሙት። እነዚህ እንግዲህ እንደቤተሰባቸው የተቁጠሩ ሌዋውያን ነበሩ።
\v 31 ወንድሞቻቸው የአሮን እንዳደረጉት ሁሉ፣ እነዚህም በንጉሥ ዳዊት፣ በሳዶቅ፣ በአቢሜሌክ እንዲሁም የካህናቱ የሌዋውያኑ ቤተሰብ አለቆች ባሉበት ዕጣ ተጣጣሉ፤ የበኩሩም ቤተሰቦች እንደ ትንሹ ወንድም ቤተሰብ እኩል ዕጣ ተጣለላቸው።
\s5
\c 25
\p
\v 1 ዳዊት ከሰራዊቱ አለቆች ጋር ሆኖ በመሰንቆ፣ በበገና በጽናጽል ድምፅ እየታጀቡ ትንቢት የሚናገሩትን ከአሳፍ፣ ከኤማንና ከኤዶም ቤተሰብ መካከል መርጦ መደብ፤ ይህን አገልግሎት የሚያከናውኑትም ሰዎች ዝርዝር እንደ ሚከተለው ነው፤
\v 2 ከአሳፍ ወንዶ ልጆች፤ ዘኩር፣ ዮሴፍ፣ ነታንያ፣ አሼርኤላ። እአሳፍ ልጆች በአሳፍ አመራር ሥር ነበሩ፤ አሳፍም በንጉሥ አመራር ሥር ነበረ።
\v 3 ከኤዶምወንዶች ልጆች፤ ዶልያስ፣ ጽሪ፣ የሻያ፣ ሰሜኢ፣ ሐሸብያ፣ መቲትያ። እነዚህ ስድስቱ በመሰንቆ እግዚአብሔርን እያመሰገነና እየወደሰ ትንቢት በተናገረው አባታቸው በኤዶታም አመራር ሥር ነበሩ።
\s5
\v 4 ከኤማን ወንዶች ልጆች፤ ቡቅያ፣ መንታያ፣ ዓዛርዔል፣ ሱባኤል፣ ኢያሪሙት፣ ሐናንያ፣ ናኒ፣ ኤልያታ፣ ጊዶልቲ፣ ሮማንቲዔዘር፣ ዮሽብቃሻ፣ መሎቲ፣ ሆቲር፣ መሐዝዮት።
\v 5 እነዚህም ሁሉ የንጉሡ ባለራእይ የኤማን ልጆች ነበሩ። እርሱን ከፍ ከፍ እንዲያደርጉትም እግዚአብሔር በገባለት ቃል መሠረት ተሰጡት፤ እግዚአብሔር ለኤማን ዐሥራ አራት ወንድሞችና ሦስት ሴቶች ልጆች ሰጠው።
\s5
\v 6 እነዚህ ሁሉ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በጽናጽል፣ በመሰንቆ በበገና አገልግሎት በአባቶቻቸው አመራር ሥር ነበሩ። አሳፍ፣ ኤዶታምና ኤማን ደግሞ በንጉሥ የበላይ አመራር ሥር ነበሩ።
\v 7 እነዚህም ከቤተዘመዶቻቸው ጋር በመሆን ሁሉም ወደ እግዚአብሔር በሚቀርበው ዜማ የሠለጠኑ የተካኑ ነበሩ፤ ቁጥራቸውም ሁለት መቶ ሰማንያ ስምንት ነበረ።
\v 8 የሥራ ድርሻቸውንም ለመወሰን ወጣት፣ ሽማግሌ፣ መምህርም ሆነ ደቀ መዝሙር ሳይባል እኩል ዕጣ ተጣጣሉ።
\s5
\v 9 የመጀመሪያው ዕጣ ከአሳፍ ወገን ለሆነው ዮሴፍ ወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸው12 ሁለተኛው ለጎዶልያስ ወጣ፤ እነሱን ጨምሮ ለቤተ ዘመዶቹና ለወንዶች ልጆቹ፤ ቁጥራቸውም12
\v 10 ሦስተኛው ለዛኩር፣ ወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም12
\v 11 አራተኛው ላይጽሪ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12
\v 12 አምስተኛው ለነታንያ ለወንዶቹ ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ ቁጥራቸውም 12
\s5
\v 13 ስድስተኛው ለቡቃያ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12
\v 14 ሰባተኛው ለይሽርኤል፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12
\v 15 ስምንተኛው ለየሻያ፤ ለወንዶች ልጆቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12
\v 16 ዘጠነኛው ለመታንያ፣ ወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ቁጥራቸውም 12
\s5
\v 17 ዐሥረኛው ለሰሜኢ፣ ወጣ ወንዶች ልጆችና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ ቁጥራቸውም 12
\v 18 ዐሥራ አንደኛው ለዓዛርኤል፣ ወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12
\v 19 ዐሥራ ሁለተኛው ለሐሻብያ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12
\v 20 ዐሥራ ሦስተኛው ለሱባኤል፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ ቁጥራቸውም 12
\s5
\v 21 ዐሥራ አራተኛው ለመቲትያ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12
\v 22 ዐሥራ አምስተኛው ለኢያሪሙት፣ ለወንዶች ልጆቹና ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12
\v 23 ዐሥራ ስድስተኛው ለሐናንያ፣ ለወንዶች ልጆቹና ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12
\v 24 ዐሥራ ሰባተኛ ለዮሽብቃሻ፣ ለወንዶች ልጆቹና ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12
\s5
\v 25 ዐሥራ ስምንተኛው ለሐናኒ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12
\v 26 ዐሥራ ዘጠነኛ ለመሎቲ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጧ፤ ቁትራቸውም 12
\v 27 ሃያኛው ለኤልያታ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12
\v 28 ሃያ አንድኛው ለሆቲር፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸው 12
\s5
\v 29 ሃያ ሁለተኛው ለጊዶልቲ፣ ወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12
\v 30 ሃያ ሦስተኛው ለመሐዝዮት፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12
\v 31 ሃያ አራተኛውም ለሮማንቲዔዘር፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12
\s5
\c 26
\p
\v 1 6 የቤተ መውደሱ በር ተባቂዎች አመዳደብ፤ ከቆሬያውያን ወገን፤ ከአሳፍ ወንዶች ልጆች አንዱ የሆነው የቆሬ ወንድ ልጅ ሜሱላም።
\v 2 ሜሱላም ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ የመጀመሪያው ዘካሪያስ ሁለተኛው ይዲኤል፣ ሦስተኛው ዮዛባት፣ አራተኛው የትኒኤል፣
\v 3 አምስተኛው ኤላም፣ ስድስተኛው ይሆሐናን፣ ሰባተኛው ኤሊሆዔናይ።
\s5
\v 4 ዖቤድኤዶምም እንደዚሁም ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ የመጀመሪያው ሽማያ፣ ሁለተኛው ዮዛባት፣ ሦስተኛው ኢዮአስ፣ አራተኛው ሣካር፣ አምስተኛው ናትናኤል፣
\v 5 ስድስተኛው ዓሚኤል፣ ሰባተኛው ይሳኮር፣ ስምንተኛው ፒላቲ፤ እግዚአብሔር ዖቤድኤዶምን ባርኮታልና።
\v 6 እንዲሁም ልጁ ሽማያ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ እነሱም በቂ ችሎታ ስለነበራቸው የአባታቸው ቤት መሪዎችች ሆኔ ነበር።
\s5
\v 7 የሽማያ ወንዶች ልጆች፤ ዖትኒ፣ ራፋቼል፣ ዖቤድ፣ ኤልዛባድ፣ ዘመዶቹ ኤሊሁና ስማክያም እንደዚሁ በቂ ችሎታ ነበራቸው።
\v 8 እነዚሁ ሁሉ የዖቤድኤዶም ዘሮች ሲሆኑ፣ እነሱም ሆኑ ወንዶች ልጆቻቸውና ቤተ ዘመዶቻቸው ሥራውን ለመጅርት በቂ ችሎታ ነበራቸው። የዖቤድኤዶም ዘሮች ባጠቃላይ ሥልሳ ሁለት ነበሩ።
\v 9 ሜሱላም በቂ ችሎታ ያላቸው ወንዶች ልጆችና ቤተ ዘመዶች ነበሩ፤ ቁጥራቸውም ባጠቃላይ ዐሥራ ሁለት ነበሩ።
\s5
\v 10 ከሜራሪ ወገን የሆነው ሖሳ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ የመጀመሪያው ሽምሪ ነበረ፤ የበኩር ልጅ ባይሆንም እንኳን አባቱ ቀዳሚ አድርጎ ነበር።
\v 11 ሁለተኛው ኬልቅያስ፣ ሦስተኛው ጥበልያ፣ አራተኛው ዘካሪያስ፤ የሖሳ ወንዶች ልጆች ቤተ ዘመዶቹ ባጠቃላይ ዐሥራ ሦስት ነበሩ።
\s5
\v 12 የቤተ መቅደሱም ጠባቂዎች በአለቆቻቸው ሥር ተመድበው ልክ እንደ በተ ዘመዶቻቸው ሁሉ እግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ሥራ ለማከናውን ምድብ ተራ ነበራቸው።
\v 13 ለእያንዳንዱም በር ወጣት ሽማግሌ ሳይባል ለሁሉም እኩል ዕጣ ተጣለ።
\v 14 የምስራቁ በር ዕጣ ለሴሌምያ ወጣ።ከዚያም ምክር ዕዋቂ ለሆነው ለልጁ ለዘካሪያስ ዕጣ ጣሉ፤እርሱም የሰሜኑ በር ደረሰው።
\s5
\v 15 የደቡብ በር ዕጣ ለዖቤኤዶም ሲወጣ፤ የግምጃ ቤቱ ዕጣ ደግሞ ለልጆቹ ወጣ።
\v 16 የምዕራቡ በርና በላይኛው መንገድ ላይ የሚገኘው የሸሌኬት በር ዕጣዎችች ለሰፊንና ለሖሳ ወጣ።
\s5
\v 17 በአንዱ ዘብ ጥበቃ ትይዩ ሌላ ዘብ ትበቃ ነበረ፣ በየቀኑም በምሥራቅ በኩል ስድስት፤ በሰሜን በኩል አራት፣ በደቡብ በኩል አራት፣፣ በዕቃ ቤቱ በኩል በአንድ ሂዜ ሁለት ሌዋውያን ይጠብቁ ነበር።
\v 18 በምዕራቡ በኩል የሚገኘው አደባባዩ ደግሞ ሁለት ሆነው ይጠብቁ ነበር።
\v 19 እንዲህ የቆየና የሜራሪ ዘሮች የሆኑት በር ጠባቂዎች ድልድይ ይህ ነበር።
\s5
\v 20 ከሌዋውያን መካከል አኪያ የእግዚአብሔር ቤት ግምጃ ቤትና የተቀደሱት ዕቃዎች የሚቀመጡበት ግምጃ ቤት ኅላፊ ነበረ።
\v 21 የለአዳን ዘሮች፣ በለኣዳን በኩል ጌድሶናውያን የሆኑትና ለጌድሶዊው ለለአዳን ቤተሰቦች አለቆች የሆኑት ለለአዳን ዘሮች እነዚህ ነበሩ፤ ይሒኤሊ፣
\v 22 የይሒኤሊ ወንዶች ልጆች፣ ዜቶምና ወንድሙ ኢዩኤል። እነዚህም እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ግምጃ ቤት ኅላፊዎች ነበሩ።
\s5
\v 23 ከእንበረማውያን፣ ከይስዓራውያን፣ ከኬብሮናውያን፣ ለዑዝኤላውያን፤
\v 24 የሙሴ ልጅ የግርሳም ዘር የሆነው ሱባኤል የግምጃ ቤቱ የበላይ ኅላፊ ነበረ።
\v 25 በአልዓዛር በኩል የሚዛመዱት፤ ልጁ ረዓብያ፣ ልጁ የሻያ፣ ልጁ ኢዮራም ልጁ ዝክሪ፣ ልጁ ሰሎሚት።
\s5
\v 26 ሰሎሚትና የሥጋ ዘመዶቹ ንጉሥ ዳዊት፣ የቤተሰቡ ኅላፊዎች፣ የሻለቆችና የመቶ አለቆች እንዲሁም ሌሎች የሰራዊቱ አዦች ቀድሰው ላቀረቧቸው ንዋያት ቅድሳት ኅላፊዎች ነበሩ።
\v 27 በጦርነቱ ከተገኘውም ምርኮ ከፊሉን ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ማደሻ እንዲሆን ቀደሱት።
\v 28 ባለ ራእይ ሳሙኤል፣ የቂስ ልጅ ሳኦል፣ የኔር ልጅ አቤኔር፣ ቅድሳት ሰሎሚናትና ቤተ ዘመዶቹ ይጠብቁ ነበር።
\s5
\v 29 ከይስዓራውያን፤ ከናንያና ወንዶች ልጆቹ ከቤተ መቅደሱ ውጭ ባለው ሥራ በእስራኤል ላይ ሹማምትና ዳኞች ሆነው ተመደቡ።
\v 30 ከኬብሮናውያን፤ ሐሽብያ፣ ጠንካራና ጎበዝ የሆኑ ሺህ ሰባት መቶ ሰዎች ከዮርዳኖስ በሰተ ምዕራብ በሚገኘው የእስራኤል ምድር ላለው የእግዚአብሔር ሥራና ለንጉሥም አገልግሎት ኅላዎች ሆነው ተመደቡ።
\s5
\v 31 በኬብሮናውያን በኩል በቤተሰቦቻቸው የትውልድ መዝገብ መሠረት ይሪያ አለቃቸው ነበረ። በዳዊት ዘመነ መንግሥት በአርባኛው ዓመት መዛግብቱ ተመርምረው ስለ ነበር፣ በገለዓድ ውስጥ ኢያዜ በተባለ ቦታ ከኬብሮናውያን መካከል ጠንካራ ሰዎች ሊገኙ ችለዋል።
\v 32 ይሪያም ጠንካሮችና የቤተሰባቸው አለቆች የሆኑ ሁለ ሺህ ሰባት መቶ ሥጋ ዘመዶች ነበሩት። ንጉሥ ዳዊትም እነዚህን የእግዚአብሔር ለሆነውና የንጉሥም በሆነው ጎዳይ ላይ ሮቤልን፣ ጋድንና የምናሴ ነገድ እኩሌታ ኅላፊ አድርጎ ሾማቸው።
\s5
\c 27
\p
\v 1 የእስራኤል የቤተሰብ አለቆች፣ የሻልለቆች፣ መቶ አለቆች እንዲሁም ዓመቱን ሙሉ በየወሩ አለቆች እንዲሁም ዓመቱን ሙሉ በየወሩ የሚመደቡትና ዋና ዋና ክፍሎች በተመለከተ ንጉሡን ያገለገሉ አለቆቻቸው ዜርዜር ይህ ነው። እያንዳንዱ ዋና ክፍል ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረው።
\v 2 በመጀመሪያው ወር የመጀመሪያው ዋና ክፍል የበላይ የዘብድኤል ልጅ ያሾብዓም ሲሆን፣ በሥሩ የሚታዘዙ ሃያ አራት ሺህ ሰዎች ነበሩ።
\v 3 እርሱም የፋሬስ ዘር ሲሆን፣ በመጀመሪያው ወር የሰራዊቱ ሹማምት ሁሉ የበላይ ነበር።
\s5
\v 4 በሁለተኛው ወር የክፍለ ጦሩ የበላይ አዛዥ ኢሆሃዊው ዱዲ ሲሆን፣ የዚሁ ክፍል መሪ ደግሞ ሚቅሎት ነው፤ በጅሩም ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረ።
\v 5 በሦስተኛውም ወር የሦስተኛው ክፍለ ጦር የበላይ አዛዥ የካህኑ የዮዳሄ ልጅ በናያስ ነበረ፤ ዋናው እርሱ ሲሆን፤ በሥሩ ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረ።
\v 6 ይህም ከሠላሳዎቹ ይልቅ ኅያል ሲሆን፤ የሠላሳዎቹ የበላይ ነበረ፤ ልጁ ዒሚዛባድም የክፍሉ ሰራዊ አዛዥ ነበረ።
\s5
\v 7 በአራተኛው ወር አራተኛው የበላይ አዛዥ የኢዮአብ ወንድም አሣሣል ሲሆን፤ በእግሩ የተተካውም ልጁ ዝባድያ ነው፤ በሥሩም ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረ።
\v 8 በእብምስተኛው ወር አምስተኛው የበላይ አዛዥ ይዝራዊው ሸምሁት ሲሆን፤ በሥሩም ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረ።
\v 9 በስድስተኛው ወር ስድስተኛው የበላይ አዛዥ የቴቁሐዊው የዒስካ ልጅ ዒራስ ሲሆን፣ በሥሩም ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረ።
\s5
\v 10 በሰባተኛው ወር ሰባተኛው የበላይ አዛ የኤፍሬም ወገን የሆነው ፍሎናዊው ሴሌስ ሲሆን፣ በሥሩም ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረ።
\v 11 በስምንተኛው ወር ስምንተኛው የበላይ አዛዥ ከካዛራውያን ወገን የሆነው ኩሳታዊ ሲቦካይ ሲሆን፣ በሥሩም ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረ።
\v 12 በዘጠነኛው ወር ዘጠነኛው የበላይ አዛዥ ከብንያም ወገን የሆነው ዓናቶታዊው አቢዔዘር ሲሆን፣በሥሩም ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረ።
\s5
\v 13 በዐሥረኛው ወር ዐሥረኛው የበላይ አዛዥ ከከዛራውያን ወገን የሆነው ነጦፋዊው ኖኤሬ ሲሆን፣ በሥሩም ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረ።
\v 14 በዐሥራ አንደኛው ወር እስራ አንደኛው የበላይ አዛዥ ከኤፌሬም ነገድ የሆነው ጲርዓቶናዊው በናያስ ሲሆን፣ በሥሩም ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረ።
\v 15 በዐሥራ ሁለተኛው ወር ዐሥራ ሁለተኛ የበላይ አዛዥ ከጎቶንያል ቤተሰብ የሆነው ነጦፋዊው ሔልዳይ ነበረ፤ በጅሩም ሃያ አራት ሰው ነበረ።
\s5
\v 16 የየነገዱ የእስራኤል የጦር ሹማምት፤ በሮቤል ነገድ ላይ የተሾመው፣ የዝክሪ ልጅ አልዓዛር፤ በስምዖን ነገድ ላይ የተሶመው፣ የመዓካ ልጅ ሰፍጢያስ።
\v 17 በሌዊ የተሾመው የቀሙኤል ልክ ሐሸቡያ፤ በእሮን ነገድ ላይ የተሾመው፣ ሳዶቅ።
\v 18 በይሁዳ ነገድ ላይ የተሾመው፣ የዳዊት ወንድም ኤሊሁ፤ በይሳኮር ነገድ ላይ የተሾመው፣ የሚካኤል ልጅ ዖምሪ።
\s5
\v 19 በዛቢሎን ነገድ ላይ የተሾመው፣ የአብዱዩ ልጅ ይሽማያ፤ በንፍታሌም ነገድ ላይ የተሾመው፣ የዓዝሪኤል ልጅ ኢያሪሙት።
\v 20 በኤፍሬም ነገድ ላይ የተሾመው፣ የዓዝያ ልጅ ሆሴዕ፤ በምናሴ ነገድ እኩሌታ ላይ የተሾው፣ የፈዳያ ልጅ ኢዩኤል።
\v 21 በገለዓድ ባለው የምናሴ ነገድ እኩሌታ ላይ የተሾመው፣ የዛካርያስ ልጅ አዶ፣ በብንያም ነገድ ላይ የተሾመው፣ የአቤኔር ልጅ የዕሢኤል።
\v 22 በዳን ነገር ላይ የተሶመው፣ የይህሮም ልጅ ዓዛርኤል፤ እንግዲህ የእዝራኤል ነገድ እነዚሁ ነበሩ።
\s5
\v 23 እግዚአብሔር እስራኤልን እንደ ሰማይ ክዋክብት እንደሚያዛቸው ሃያና ከዚያ በታች ይየሆነው አልቁጠረም ነበር።
\v 24 የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ መቁጠር ጀመረ፤ ሆኖም አልፈፀመውም፤ መቁጠራቸው በእስራኤል ላይ ቁጣ ስላመጣ፣ የተቁጠረውም በንጉሥ ዳዊት መዝገብ አልገባም።
\s5
\v 25 የዓዲኤል ልጅ ዓዝሞት የቤተ መንግሥቱ ዕቃ ኅላፊ ነበረ፤
\v 26 የክሉብ ልጅ ዔዝሪ ምድሪቱም ለሚያርሱት ገበሬዎች ኅላፊ ነበረ።
\v 27 ራማታዊው ስሜኢ የውይን ተክል ቦታዎች ኅላፊ ነበረ፤ ሽፋማዊው ዘብዲ የወይን ጠጅ ዕቃ ኅላፊ ነበረ።
\s5
\v 28 ጌድራዊው በአሐናን በምራባዊው ኩረብታዎች ግርጌ ለሚገኙት የወይንና የወርካ ዛፎች ጥበቃ ኅላፊ ነበረ፤ ኢዮአስ የዘይት ቤቱ ኅላፊ ነበረ።
\v 29 ሳሮናዊው ሰጥራይ በሳሮን ለሚሰሩት የከብት መንጋዎች ኅላፊ ነበረ። የዓድላይ ልጅ ሻፋጥ በሸለቆው ውስጥ ላሉት የከብት መንጋዎች ኅላፊ ነበረ።
\s5
\v 30 እስማኤላዊው ኡቢያስ የግመሎች ኅላፊ ነበረ። ሜሮታዊው ዬሕድያ የአህዮች ኅላፊ ነበረ።
\v 31 አረጋዊው ያዚዝ የበግና የፍየል መንጋዎች ኅላፊ ነበረ።
\s5
\v 32 አስተዋይ የሆነው አጎት ዮናታን አማካሪና ጸሐፊ ነበረ፤ የሐክሞኒም ልጅ ይሒኤል ደግሞ የንጉሥ ልጆች ሞግዚት ነበረ።
\v 33 አኪጦፌል የንጉሥ አማካሪ ሲሆን፣ አርካዊው ኩሲ ደግሞ የንጉሥ ልጆች ሞግዚት ነበረ። አኪጦፌል የንጉሥ አማካሪ ሲሆን፣ አርካዊው ኩሲ ደግሞ የንጉሥ ወዳጅ ነበረ።
\v 34 የበናያስ ልጅ ዮዳሄና አብያታር በአኪጦፌል እእግር ተተኩ። ኢዮአብም የንጉሥ የክብር ዘብ አዛዥ ሆነ።
\s5
\c 28
\p
\v 1 ዳዊት በኢየሩሳሌም እንዲሰበሰቡ የነገዱን የጦር አለቆች፣ ንጉሡን የሚያገለግሉትን የክፍለ ጦር አዛዦች፣ የሻለቆቹን፣ የመቶ አለቆቹን፣ የንጉሥና የልጆቹ ንብረትና ከብት ሁሉ ኅላፊ የሆኑትን፣ እንዲሁም የቤተ መንግሥቱን ሹማምት፣ ኅያላንና ጀግና ተዋጊዎቹን፣ በአጠቃላይ የእስራኤልን ሹማምት ሁሉ ጠራ።
\s5
\v 2 ከዚያም ንጉሥ ዳዊት በእግሩ ቆሞ እንዲህ አላቸው፤ "ወንድሞቼንና ወገኖቼ ሆይ፤ እስቲ አድምጡኝ፤ እግዚአብሔር ለቃል ኪዳኑ ታቦት ማደሪያና ለአምላካችን እግር ማረፊያ የሚሆን ኔት ለመሥራት ዐስቤ ዕቅድ አውጥቼ ነበር።
\v 3 እግዚአብሔር ግን እንዲህ አለኝ፤ ጦረኛ ለስሜ ቤት አትሠራም።
\s5
\v 4 ነገር ግን የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ ለዘላለም እንድነግሥ ከቤተሰቤ ሁሉ እኔን አረጠ፤ መሪ እንድሆንም ይሁዳን መረጠ፤ ከአባቴ ልጆች መካከል ደግሞ በመላው እስራኤል ላይ እንድነግሥ ፈዋዱ ሆነ።
\v 5 እግዚአብሔር ብዙ ልጆች ሰጥቶኛል፤ ከወንዶቹ ልጆቼ ሁሉ በእግዚአብሔር መንግሥት ዙፋን ላይ ተቀምጦ በእስራኤል ሁሉ ላይ እንዲነግሥ ደግሞ ልጄን ሰሎሞንን መርጦታል።
\s5
\v 6 እንዲህም አለኝ፤ ቤቴንና አደባባዮቼን የሚሠራልኝ ልጅህ ሰሎሞን ነው፤ ምክንያቱም ልጄ እንዲሆን መርጩዋለሁ፤ እኔም አባት እሆነዋለሁ።
\v 7 አሁን እንደሚያድርገው ሁሉ፤ ትህዛዛቶቼንና ሕጎቼን ምንጊዜም ሳያውላውል የሚፈጽም ከሆነ መንግሥቱም ለዘላለም አጸናታለሁ።
\s5
\v 8 እንግዲህ አሁንም ይህቺን መልካሚቱን ምድር እንድትወርሱና ለልጆቻችሁም የዘላለም ርስት አድርጋችሁ እንድታወርስይአቸው፣ የእግዚአብሔርም ትእዛዝ ሁሉ ፊት፣ በእግዚአብሔር ጉባኤና እግዚአብሔር እየሰማ አዛችኋለሁ።
\s5
\v 9 "አንተም ልጄ ሰሎሞን ሆይ! እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ስለሚመረምርና ሐሳብን ሁሉ ስለሚያውቅ፣ የአባትህን አምላክ ዕወቅ፤ በፍጹም ልብና በበጎ ፍቃድ አገግለው።
\v 10 ለመቅደስ የሚሆን ቤት እንድትሠራ እግዚአብሔር የመረጠህ መሆኑን አሁንም ዕስብ፤ በትርተህም ሥራ።
\s5
\v 11 ከዚያም ዳዊት የቤተ መቅደሱን መመላለሻ፣ የሕንጻውን፣ የዕቃ ቤቶቹን፣
\v 12 የፎቁንና የውስጥ ክፍሎቹን እንዲሁም የማስተሰሪያውን ቦታ ንድፍ ለልጁ መንፈስ ቅዱስ በልቡ ያሳደረውን የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አደባባይ፤ በዙሪያው ውያሉትን ክፍሎች ሁሉ፣ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ዕቃ ቤቶችና የንዋይ ቅድሳቱን ግምጃ ቤቶች ንድፍ ሁሉ ሰጠው፤
\s5
\v 13 እንዲሁም የካህናቱንና የሌዋውያኑን አመዳደብ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አገልግሎት ሥራና ለአገልግሎቱ ስለሚጠቀምባቸው ዕቃዎች ሁሉ መመሪያ ሰጠው።
\v 14 ልዩ ልዩ አገልግሎት የሚውሉትን የወርቅ ዕቃዎች ሁሉ መጠን፤ ልዩ ልዩ አገልግሎት የሚውሉትን የብር ዕቃዎች ሁሉ መጠን አሳወቀው፤
\v 15 እንደሚቀዞችና ለቀንዲሎቻቸው የሞሆነው የእያንዳንዳቸውን የውርቅ መጠን፤ ለብሩ መቅረዞችና ለቀንዲሎቻቸው የሚያድፈልገውን የእያንዳንዳቸውን የብር መጠን፤
\s5
\v 16 ለያንዳንዱ ኅብስት ገጽ ጠረጼዛ የሚያስፈልገውን የወርቅ መጠን፣ ለእያንዳንዱ የብር መጠን፣
\v 17 ለሹካዎቹ፣ ለጎዳጓዳ ሳሕኖቹ፣ ለማንቆርቆሪያዎች የሚያስፈልገውን ንጹሕ የውርቅ መጠን፤ ለእያንዳንዱ የብር መጠን፣
\s5
\v 18 ለዕጣኑ መሠዊያ የሞሆነውን የጠራ ውርቅ መጠን እንዲሁም ክንፎቻቸውን ዘርግተው የእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑን ታቦት የሚሸፍኑት ከወርቅ የተሠሩትን የኪሩቤል ጀረገላዎች ንድፍ ሰጠው።
\v 19 ዳዊትም "ይህ ሁሉ፣በእኔ ላይ ባለው በእግዚአብሔር እጅ በጽሑፍ ተገለተልኝ፤ የንድፋንም ዝርዝር እንድረዳ ማስተዋልን ስጠን"አለ።
\s5
\v 20 ደግሞም ዳዊት ልጁን ሰሎሞንን እንዲህ አለው፤ "እንግዲህ በል በርታ፤ ጠንክር፤ ሥራውንም ጀመር። አትርፍ፤ ተስፋም አትቁረጥ፤ እግዚአብሔር አምላኬ ከአንተ ጋር ነውና፤ እርሱም የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አገልግሎት ሥራ እስኪፈጸም ድረስ አይተውህም፤ አይጥልህም።
\v 21 ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሥራ ሁሉ የሚያስፈልጉትን ካህናትና ሌዋዋን ምድብም ዝግጁ ነው።በሁሉም የእጅ በሥራው ሁሉ ይረዱሃል። ሹማምቱና ሕዝቡ ሁሉ ትእዛዝህን ይፍፈጽማሉ።
\s5
\c 29
\p
\v 1 ከዚያም ንጉሥ ዳዊት ለመላው ጉባኤ እንዲህ አለ፤ "እግዚአብሔር የመረጠው ልጄ ሰሎሞን ገና ወጣትና ልምድም የሌለው ነውው። ይህ ታላቅ ሕንጻ የሚሠራውን ለሰው ሳይሆን ለእግዚአብሔ አምላክ በምሆን፣ ጅራው ከባድ ነው።
\v 2 እኔም ያለኝን ሀብት ለአምላኬ ቤተ መቅደስ ለወርቁ ሥራ ወርቁን ለብሩ ሥራ ብሩን፣ ለናስ ሥራ ናሱን፣ ለብረቱ ሥራ ብረቱን፣ ለዕንጨቱ ጅራ ዕንጨቱን እንዲሁም ለፈርጥ የሞሆነው መረግድ፣ ኬልቄዶን፣ ልዩ ልዩ ኅብር ያላቸውን ዐይነት የሚያምር ድንጋይና ዕብነበረድ፣ ይህን ሁሉ በብዛት አዘጋጅቻለሁ።
\s5
\v 3 ከዚህም በቀር ለአምላኬ ቤት ካለን ፍቅር የተነሣ ለዚህ ለተቀደሰ ቤት ከዚህ በፊት ከሰጠሁት በተጨማሪ ለዚሁ ለእግዚአብሔር ቤተ ምቅደስ የግል ሀብቴ የሆነውን ወርቅና ብር እሰጣለሁ፤
\v 4 ይህም ሦስት ሺህ መክሊት ንጹሕ ብር ለቤተ መቅደሱ የግድግዳ ግንብ ማስጌጫ
\v 5 እንዲሁም ለወርቁ ሥራ፣ ለብሩ ሥራ፣ በባለሞያዎች ለሚሠራው ሥራ ሁሉ የሚሆን ነው። ታዲያ ዛሬ ራሱን ለእግዚአብሔር ለመቀደስ ፍቃደኛ የሚሆን ማን ነው?።
\s5
\v 6 ከዚያም የቤተሰቡ አሪዎች፣ የነገዱ የእስራኤል ሹማምት፣ የሻለቆችና የመቶ አለቆች እንዲሁም በንጉሥ ሥራ ላይ የተመደቡ ሹማምት፣ በፍቃዳቸው ሰጡ፤
\v 7 ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሥራ የሰጡትም አምስት ሺህ መክሊት ወርቅ፣ ዐሥር ሺህ ዳሪክ ወርቅ፣ ዐሥር ሺህ መክሊት ናስ አንድ መቶ ሺህ መክሊት ብረት ነው።
\s5
\v 8 የከበሩ ድንጋዮች ያለውም ሁሉ፣ በጌድሶናዊው በይሒኤል አማካኝነት ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ግምጃ ቤት አስገባ።
\v 9 ስጦታው በገዛ ፈቃደና በፍጹም ልብ የቀረበ በመሆኑ፣ አለቆች ስላደረጉት የብበጎ ፈቃድ ስጦታ ሕዝቡ ደስ አለው፤ ንጉሥ ዳዊትም እንደዚሁ እጅግ ደስ አለው።
\s5
\v 10 ዳዊትም በመላው ጉባኤ ፊት እግዚአብሔር እንዲህ ሲል አመሰገነ፤ "የአባታችን የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ ከዘላለም እስከ ዘላለም ለአንተ ምስጋና ትሁን።
\v 11 እግዚአብሔር ሆይ፤ በሰማይና በምድር ያለው ሁሉ ለአንተ ነውና፤ ታላቅነት፣ ኅይል ክብርና ግርማ የአንተ ነው። እግዚአብሄር ሆይ፤ መንግሥትህም የአንተ ነው፤ አንተም እንደ ራስ ከሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያልህ ነህ።
\s5
\v 12 ባለጠግነት ክብር የሚገኘው ከአንተ ነው፤ አንተም የሁሉ ገዢ ነህ፤ ከፍ ከፍ ለማድረግ፣ ለሁሉም በርታትን ለመስጠት፣ ብርታትና ኅይል በእጅህ ነው።
\v 13 አምላካችሁ ሆይ፤ አሁንም እናመሰግንሃለን፤ ለከበረው ስምህም ውዳሴ እናቀርባለን።
\s5
\v 14 "ሁሉ የተገኘው ከአንተ ነው፤ ለአንተም የሰጠንህ ከእጅህ የተቀበልነው ብቻ ነው። ታዲያ እንዲህ ያለ ቸርነት እናድርግ ዘንድ እኔ ማነኝ? ሕዝቤስ ማንኝ?
\v 15 እኛም እንደ ቀድሞ አባቶቻችን በፊትህ መጻተኞችና እንግዶች ነን፤ ዘመናችንም በምድር ላይ እንደ ጥላ ነው፤ ተስፋ ሲስም ነው።
\s5
\v 16 እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ፤ ለተቀደሰው ስምህ ቤተ መቅደስ እንሠራለን ዘንድ ይህ በብዛት ያዘጋጀውን ሁሉ፤ ከእጅህ የተገኘውና ሁሉም ለአንተ ነው።
\v 17 አምልኬ ሆይ፤ ልብን እንደምትመረምርና ቅንነትን እንደምትወድ ዐውቃለሁ፤ እኔም ይህን ሁሉ የሰጠሁት በበጎ ፈቃደና በቀና መንፈስ ነው። አሁንም በዚህ ያለው ሕዝብህ በበጎ ፈቃዱ እንዴት እንደ ሰጠ አይቻለሁ።
\s5
\v 18 የአባታቸው የአብርሃም፣ የይስሐቅ፣ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህን ዐሳብ ለዘላለም በሕዝብህ ልብ ጠብቀው፤ ልባቸውንም ለአንተ ታማኝ አድርገው።
\v 19 ትእዛዞችህን፣ እኔ ባዘጋጀሁለት ነገሮች ታላቅ ህንጻ ለመጅራት እንዲችል፣ ለልጄ ለሰሎሞ ፍጹም ፈቃደኛነት ሰጠው።
\s5
\v 20 ከዚያም ዳዊት ለመላው ጉባኤ፣ "አምላካችሁን እግዚአብሔር ወሰዱት" አላቸው። ስለዚህ የአባታቻችን አምላክ እግዚአብሔር ወደሱ፤ በእግዚአብሔር በንጉሡም ፊት ተደፍተው ሰገዱ።
\v 21 በማግስቱም ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ሠው፤ የሚቃጠል መስሥዕዋትም አቀረቡ፤ ይህም አንንድ ሺህ ወይፈን፣ አንድ ሺህ አውራ በግ፣ አንድ ሺህ የበግ ጠቦት ሲሆን፤ ከመጠጥ ቁርባኖቻቸውና ከሌሎች መሥዕዋቶች ጋር ስለ እስራኤል ሁሉ በብዛት አቀረቡ።
\s5
\v 22 በዚህችም ዕለት በእግዚአብሔር ፊት በታላቅ ደስታ በሉ፤ ጠጡም። ከዚያም የዳዊት ልጅ ሰሎሞን ንጉሥ መሆኑን ሁለተኛ ጊዜ በይፋ ዐወቁ፤ ገዥ እንዲሆንም በእግዚአብሔር ፊት ቀቡት፤
\v 23 ሰለሞንም ነግሦ በአባቱ በዳዊት ምትክ በእግዚአብሔር ዙፋን ላይ ተቀመጠ፤ ተከናወነለት፤ እስራኤልም ሁሉ ታዘዙለት።
\s5
\v 24 የጦር አለቆችና ኅያላኑ ሁሉ እንዲሁም የንጉሥ የዳዊት ወንዶች ልጆች በሙሉ ታማኝነታቸውን ለንጉሥ ሰሎሞን አረጋ ገጡለት።
\v 25 እግዚአብሔር ሰሎሞንን በእስራኤል ሕዝብ ዘንድ ሁሉ እጅግ ከፍ ከፍ አደረገው፤ ከእነሱ በፊት ለነበሩት የእስራኤል ነገሥታት ያላጎናጸፋቸውን ንጉሣዊ ክብር ሁሉ ሰጠው።
\s5
\v 26 የእሴይ ልጅ ዳዊት በእስራኤል ሁሉ ላይ ነግሦ ነበር።
\v 27 እርሱም በኬብሮን ሰባት ዓመት፤ በእየሩሳሌም ሠላሳ ሦስት ዓመት፣ በአጠቃላይ አርባ ዓመት ነገሠ።
\v 28 ብዙ ዘመን ባለጠግነትና ክብር ሳይጎድልበት ዕድሜ ጠግቦ ሞተ፤ ጅጁ ልምሞን በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።
\s5
\v 29 በንጉሥ ዳዊት ዘመነ መንግሥት ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻ የተከናወነው ድርጊት በባለ ራእዩ በሳሙኤል የታሪክ መጽሐፍ፣ በነብዩ በናታን የታሪክ መጽሐፍ ተጽፎአል።
\v 30 የተጻፈውም በሥልጣን ላይ በነበረበት ጊዜ ከፈጸማቸው ዝርዝር ጉዳዮችና በዙሪያው ከከበቡት፤ ከእስራኤልና ከሌሎች አገር መንግሥታት ታሪክ ጋር ነው።