am_ulb/10-2SA.usfm

1365 lines
169 KiB
Plaintext
Raw Permalink Blame History

This file contains ambiguous Unicode characters

This file contains Unicode characters that might be confused with other characters. If you think that this is intentional, you can safely ignore this warning. Use the Escape button to reveal them.

\id 2SA
\ide UTF-8
\h 2ኛ ሳሙኤል
\toc1 2ኛ ሳሙኤል
\toc2 2ኛ ሳሙኤል
\toc3 2sa
\mt 2ኛ ሳሙኤል
\s5
\c 1
\p
\v 1 ሳዖል ከሞተ በኋላ፣ ዳዊት በአማሌቃውያን ላይ ጥቃት ከማድረስ በመመለስ በጺቅላግ ሁለት ቀን ቆየ፡፡
\v 2 በሦስተኛው ቀን የተቀዳደደ ልብስ የለበሰ፣ በራሱም ላይ ትቢያ የነሰነሰ አንድ ሰው ከሳኦል ሰፈር መጣ፡፡ ወደ ዳዊት እንደ ደረሰም ወደ መሬት ለጥ ብሎ ሰገደለት፡፡
\s5
\v 3 ዳዊትም “ከወዴት መጣህ?” ሲል ጠየቀው፡፡ እርሱም፣ “ከእስራኤላውያን ሰፈር አምልጬ የመጣሁ ነኝ” ሲል መለሰ፡፡
\v 4 ዳዊትም፣ “እስቲ የሆነውን ሁሉ ንገረኝ” አለው፡፡ እርሱም “ሰዎቹ ከጦርነት ሸሽተዋል፤ ብዙዎቹ ወድቀዋል ደግሞም ሞተዋል፤ ሳዖልና ልጁ ዮናታንም ሞተዋል” አለ፡፡
\v 5 ዳዊትም ለወጣቱ፤ “ሳኦልና ልጁ ዮናታን መሞታቸውን እንዴት አወቅህ?” ሲል ጠየቀው፡፡
\s5
\v 6 ወጣቱም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ድንገት ወደ ጊልቦዓ ተራራ ወጥቼ ነበር፤ እዚያም ሳኦል ጦሩን ተደግፎ ሳለ፣ ሠረገሎችና ፈረሰኞች ተከታትለው ደረሱበት፤
\v 7 ወደ ኋላውም ዞር ሲል እኔን ስላየ ጠራኝ፤ እኔም ‘እነሆኝ አለሁ’ አልኩት፡፡
\s5
\v 8 እርሱም፣ ‘አንተ ማን ነህ? ሲል ጠየቀኝ፡፡ አኔም፣ ‘አማሌቃዊ ነኝ’ ብዬ መለስሁለት፡፡
\v 9 እርሱም አለኝ ‘እኔ በታላቅ ስቃይ ውስጥ እገኛለሁ፤ ነፍሴ ግን አልወጣችም፤ እባክህ በላዬ ቆመህ ግደለኝ’ አለኝ፡፡
\v 10 ስለሆነም፣ ከወደቀ በኋላ እንደማይተርፍ ስላወቅሁ፤ በላዩ ቆሜ ገደልሁት፤ በራሱ ላይ የነበረውን ዘውድና የክንዱን አንባር ወስጄ እነሆ፣ ለጌታዬ አምጥቻለሁ፡፡” አለው፡፡
\s5
\v 11 ከዚያም ዳዊት ልብሱን ቀደደ፤ ከእርሱም ጋር የነበሩት ሁሉ እንደዚሁ አደረጉ፡፡
\v 12 የወደቁት በሰይፍ ነበርና ለሳኦል ለልጁ ለዮናታንና ለእግዚአብሔር ሕዝብ አዘኑ፤ አለቀሱ፤ እስከ ማታም ድረስ ጾ፡፡
\v 13 ዳዊትም ወጣቱን ሰውዬ፣ “የየት አገር ሰው ነህ?” ሲል ጠየቀው፡፡ እርሱም፣ “በአገሪቱ ውስጥ በመጻተኛነት የሚኖር አማሌቃዊ ልጅ ነኝ” ብሎ መለሰ፡፡
\s5
\v 14 ዳዊትም፣ “እግዚአብሔር የቀባውን ንጉሥ በገዛ እጅህ ስትገድል ለምን አልፈራህም?” ሲል ጠየቀው፡፡
\v 15 ዳዊትም ከጎልማሶቹ አንዱን ጠርቶ፣ “ግደለው” አለው፤ ጎልማሳው ሰው ሄዶ መታው፣ አማሌቃዊውም ሞተ፡፡
\v 16 ከዚያም ዳዊት ለሞተው አማሌቃዊ፣ “‘እግዚአብሔር የቀባውን ገድያለሁ’ ስትል አፍህ መስክሮብሃልና ደምህ በራስህ ላይ ነው” አለው፡፡
\s5
\v 17 ከዚያም ዳዊት ለሳዖልና ለልጁ ለዮናታን የሚከተለውን የሐዘን እንጉርጉሮ አንጎራጎረ፡፡
\v 18 እንዲሁም የቀስት እንጉርጉሮ የተባለውን ለይሁዳ ሕዝብ እንዲያስተምሩ አዘዘ፤ ይህም በያሸር መጽሐፍ ተጽፎአል፡፡
\v 19 “እስራኤል ሆይ፣ ክብርህ ሞቶአል፣ በተራሮችህ ላይ ተገድሎአል! ኃያላኑ እንዴት ወደቁ!
\v 20 የፍልስጥኤም ሴቶች ልጆች እንዳይደሰቱ፣ ያልተገረዙት ሴት ልጆች ፌሽታ እንዳያደርጉ ይህን በጌት አትናገሩ፣ በአስቆሎናም መንገዶች አታውጁት፡፡
\s5
\v 21 እናንት የጊልቦዓ ተራሮች ሆይ ጠል አያረስርሳችሁ፣ ዝናብም አይውረድባችሁ፤ የቁርባን እህል የሚያበቅሉም እርሻዎች በዚያ አይኑሩ፤ በዚያ የኃያሉ ሰው ጋሻ ረክሶአልና፣ የሳዖል ጋሻ ከእንግዲህ በዘይት አይወለወልም፡፡
\v 22 ከሞቱት ሰዎች ደም፣ ከኃያላኑም ገላ የዮናታን ቀስት ተመልሶ አልመጣም፤ የሳዖልም ሰይፍ በከንቱ አልተመለሰም፡፡
\s5
\v 23 ሳዖልና ዮናታን በሕይወት እያሉ የሚዋደዱና ግርማ ያላቸው ነበሩ፤ ሲሞቱም አልተለያዩም፤ከንስርም ይልቅ ፈጣኖች ከአንበሳም ይልቅ ብርቱዎች ነበሩ፡፡
\v 24 እናንተ የእስራኤል ቆነጃጅት ሆይ፤ ሐምራዊ ቀሚስና ቀጭን ፈትል ላለበሳችሁ ፤ ልብሶቻችሁንም በወርቀ-ዘቦ ላስጌጠላችሁ ለሳዖል አልቅሱለት፡፡
\s5
\v 25 ኃያላን እንዴት እንዲህ በጦርነት መካከል ወደቁ! ዮናታን ከፍ ባሉ ስፍራዎቻችሁ ላይ ሞቶአል፡፡
\v 26 ወንድሜ ዮናታን ሆይ፤ እኔ ስለ አንተ አዘንሁ፤ አንተ ለእኔ እጅግ ውድ ነበርህ፤ ፍቅርህ ለእኔ ድንቅ ነበር፤ ከሴት ፍቅርም የላቀ ነበር፡፡
\v 27 ኃያላን እንዴት ወደቁ፤ የጦር መሣሪዎቹስ እንዴት ከንቱ ሆኑ!”
\s5
\c 2
\p
\v 1 ከዚህ በኋላ ዳዊት፤ “ከይሁዳ ከተሞች ወደ አንዲቱ ልውጣን?” ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ፣ እግዚአብሔርም፣ “ወደ ኬብሮን” ብሎ መለሰለት፡፡
\v 2 ስለዚህ ዳዊት ከሁለቱ ሚስቶቹ ከኢይዝራኤላዊቷ ከአኪናሆምና የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት ከነበረችው ከአቢግያ ጋር ሄደ፡፡ ጠየቀ፡፡ እግዚአብሔርም፣ “ውጣ” ብሎ መለሰለት፡፡ ዳዊትም፣ “ወደ የትኛው ከተማ ልሂድ?” ብሎ ጠየቀ፡፡
\v 3 ዳዊት ቤተ ሰቦቻቸውን ይዘው የመጡትን ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሰዎች ወደሚኖሩበት ወደ ኬብሮን ይዟቸው መጣ፡፡
\s5
\v 4 ከዚያ በኋላም የይሁዳ ሰዎች ወደ ኬብሮን መጥተው ዳዊትን በይሁዳ ቤት ላይ ንጉሥ አድርገው ቀቡት፡፡ የኢያቢስ ገለዓድ ሰዎች ሳኦልን እንደቀበሩት ለዳዊት ነገሩት፡፡
\v 5 ስለዚህ ወደ ኢያቢስ ገለዓድ ሰዎች መልእክተኞች ልኮ እንደዚህ አላቸው፣ “ጌታችሁን ሳኦልን በመቅበር ይህንን በጎነት ስላሳያችሁ በእግዚአብሔር የተባረካችሁ ናችሁ፡፡
\s5
\v 6 አሁንም እግዚአብሔር ጽኑ ፍቅሩንና ታማኝነቱን ይገለጥላችሁ፤ እናንተ ይህን ስላደረጋችሁ እኔም እንደዚሁ በጎ ነገር አደርግላችኋለሁ፡፡
\v 7 እንግዲህ እጆቻችሁ ይጠንክሩ፣ በርቱ፤ ጌታችሁ ሳኦል ሞቶአልና፣ የይሁዳ ቤትም እኔን ቀብተው በላያቸው አንግሠውኛል፡፡”
\s5
\v 8 የሳኦል ሠራዊት አዛዥ፣ የኔር ልጅ አብኔር ግን የሳዖልን ልጅ ኢያቡስቴን ወስዶ ወደ መሃናይም አሻገረው፤
\v 9 ኢያቡስቴንም በገለዓድ፣ በአሴር፣ በኢይዝራኤል፣ በኤፍሬምና በብንያም እንዲሁም በእስራኤል ሁሉ ላይ አነገሠው፡፡
\s5
\v 10 የሳኦል ልጅ ኢያቡስቴ በእስራኤል ላይ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው አርባ ዓመት ነበረ፣ ሁለት ዓመትም ገዛ፡፡ የይሁዳ ቤት ግን ዳዊትን ተከተለ፡፡
\v 11 ዳዊት በኬብሮን በይሁዳ ቤት ላይ ንጉሥ የሆነበት ዘመን ሰባት ዓመት ከስድስት ወር ነበር፡፡
\s5
\v 12 የኔር ልጅ አብኔርና የሳኦል ልጅ የኢያቡስቴ አገልጋዮች ከመሃናይም ተነሥተው ወደ ገባዖን ሄዱ፡፡
\v 13 እነርሱንም የጽሩይ ልጅ ኢዮአብና የዳዊት ሰዎች በገባዖን ኩሬ አጠገብ ተገናኟቸው፤ በዚያም አንዱ ወገን በኩሬው ወዲህ ማዶ፣ ሌላው ወገን ደግሞ በኩሬው ወዲያ ማዶ ተቀመጠ፡፡
\s5
\v 14 አበኔርም ለኢዮአብ፣ “ጎልማሶች ይነሡና እርስ በርሳቸው ይጋጠሙ” አለው፡፡ ኢዮአብም፣ “እሺ፣ ይነሡ” አለ፡፡
\v 15 ከዚያ በኋላም ከብንያምና ከሳኦል ልጅ ከኢየቡስቴ ወገን አሥራ ሁለት፣ የዳዊት አገልጋዮች ከሆኑት ደግሞ አሥራ ሁለት ጎልማሶች ተነሥተው በአንድነት ተሰባሰቡ፡፡
\s5
\v 16 እያንደንዱም ሰው የባላጋራውን ራስ በመያዝ ሰይፉን በጎኑ እየሻጠበት ተያይዘው ወደቁ፡፡ ስለዚህ በገባዖን ያለው ያ ስፍራ በዕብራይስጥ ‘ሐልቃት አዙሪም’ ወይም ‘የሰይፍ ምድር’ ተባለ፡፡
\v 17 በዚያን ዕለት ጦርነቱ እጅግ ከባድ ነበር፣ አበኔርና የእስራኤል ሰዎች በዳዊት አገልጋዮች ድል ሆኑ፡፡
\s5
\v 18 ሦስቱ የጽሩይ ወንዶች ልጆች ኢዮአብ፣ አቢሳና አሣሄል እዚያው ነበሩ፡፡ አሣሄል እንደ ዱር ሚዳቋ በሩጫ ፈጣን ነበር፤
\v 19 አሣሄል በየትኛውም አቅጣጫ ዞር ሳይል አበኔርን በቅርበት ተከታተለው፡፡
\s5
\v 20 አበኔርም ወደ ኋላው ዞር ብሎ በመመልከት፣ “አሣሄል አንተ ነህን?” አለው፡፡ እርሱም፣ “እኔ ነኝ” ሲል መለሰለት፡፡
\v 21 አበኔርም፣ “ወደ ቀኝህ ወይም ወደ ግራህ ዘወር በልና አንዱን ጎልማሳ ይዘህ መሣሪያውን ንጠቀው” አለው፤ አሣሄል ግን እርሱን መከታተሉን አልተወም ነበር።
\s5
\v 22 እንደገናም አቤኔር “እኔን መከታተል ብትተው ይሻልሃል፤ እኔስ ለምን ከመሬት ጋር ላጣብቅህ? ከዚያስ የወንድምህን የኢዮአብን ፊት ቀና ብዬ እንዴት አያለሁ?” አለው።
\v 23 አሣሄል ግን ዘወር ለማለት እምቢ አለ፤ ስለዚህ አብኔር በጦሩ ጫፍ አከላቱን ወጋው፤ ጦሩም በአካሉ በሌላው ወገን ዘልቆ ወጣ፤ አሣሄልም ወደቀ፣ በዚያ ስፍራም ሞተ፡፡ ስለሆነም አሣሄል ወደ ወደቀበት ይመጣ የነበረ እያንዳንዱ ሰው በዚያ ስፍራ ሲደርስ ይቆም ነበር፡፡
\s5
\v 24 ኢዮአብና አቢሳ ግን አበኔርን አሳደዱት፤ ፀሐይም በምትጠልቅበት ጊዜ ወደ ገባዖን ምድረ በዳ በሚወስደው መንገድ ከጋይ አጠገብ ወዳለው ወደ አማ ኮረብታ ደረሱ፡፡
\v 25 የብንያም ሰዎችም ከአበኔር በስተኋላ ተሰብስበው በተራራው ጫፍ ላይ ቆሙ፡፡
\s5
\v 26 ከዚያ በኋላም አበኔር ኢዮአብን ጠርቶ፣ “ሰይፍ ለዘላለም ማጥፋት አለበትን? ውጤቱ በመጨረሻ መራራ መሆኑን አንተ አታውቅምን? ሰዎችህ ወንድሞቻቸውን ማሳደድ እንዲያቆሙ የማትነግራቸውስ እስከ መቼ ድረስ ነው?” አለው፡፡
\v 27 ኢዮአብም ፣ “ሕያው እግዚአብሔርን፣ ይህን ባትናገር ኖሮ፣ ወታደሮቼ እስኪነጋ ድረስ ወንድሞቻቸውን ባሳደዱ ነበር” ብሎ መለሰ፡፡
\s5
\v 28 ስለዚህ ኢዮአብ ቀንደ መለከቱን ነፋ፤ ሰዎቹም ሁሉ ቆሙ፤ ከዚያ በኋላም እስራኤልን አላሳደዱም፣ መዋጋታቸውንም አልቀጠሉም፡፡
\v 29 አበኔርና ሰዎቹም ሌሊቱን ሁሉ በዓረባ በኩል አለፉ፤ ዮርዳኖስን ተሻግረው በማግሥቱ ጥዋት ሲጓዙ ቆይተው ከዚያ በኋላ ወደ መሃናይም ደረሱ፡፡
\s5
\v 30 ኢዮአብም አበኔር ከማሳደድ ተመለሰ፡፡ አሣሄልና ከዳዊት ወታደሮች አሥራ ዘጠኙ የጎደሉባቸውን ሰዎቹን ሁሉ ሰበሰበ፡፡
\v 31 የዳዊት ሰዎች ግን ከአበኔር ጋር ከነበሩት ሦስት መቶ ሥልሳ ብንያማውያንን ገድለዋል፡፡
\v 32 ከዚያ በኋላም አሣሄልን ከወደቀበት አንሥተው ቤተ ልሔም በነበረው በአባቱ መቃብር ቀበሩት፡፡ ኢዮአብና ሰዎቹ ሌሊቱን ሁሉ ገሥግሠው ኬብሮን ሲደርሱ ሌሊቱ ነጋላቸው፡፡
\s5
\c 3
\p
\v 1 በሳዖል ቤትና በዳዊት ቤት መካከል ለረጅም ጊዜ የቆየ ጦርነት ነበረ፡፡ ዳዊት እየበረታ ሲሄድ የሳዖል ቤት ግን እየደከመ ሄደ፡፡
\s5
\v 2 በኬብሮን ለዳዊት ወንዶች ልጆች ተወለዱለት፡፡ የበኩር ልጁ፣ ከኢይዝራኤላዊቷ ከአኪናሆም የተወለደው አምኖን ነበር፡፡
\v 3 ሁለተኛው፣ የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት ከነበረችው ከአቢግያ የተወለደው ኪልአብ ነበር፡፡ ሦስተኛ የነበረው፣ አቤሴሎም የጌሹር ንጉሥ ከነበረው ከተልማይ ልጅ ከመዓካ የተወለደው ነበር፡፡
\s5
\v 4 አራተኛው፣ ልጁ ከአጊት የተወለደው አዶንያስ፣ አምስተኛው፣ ከአቢጣል የተወለደው ሰፋጥያ፣
\v 5 ስድስተኛው፣ ከዳዊት ሚስት ከዔግላ የተወለደው ይትርኃም ነበር፤ እነዚህ ወንዶች ልጆች ለዳዊት በኬብሮን የተወለዱለት ነበሩ፡፡
\s5
\v 6 የሳኦል ቤትና የዳዊት ቤት በጦርነት ላይ በነበሩበት ጊዜ አበኔር በሳዖል ቤት ራሱን ጠንካራ አድርጎ ነበር፡፡
\v 7 ሳኦል የኢዮሄል ልጅ ሪጽፋ የተባለች ቁባት ነበረችው፤ ኢያቡስቴም አበኔርን፣ “ለምንድን ነው ከአባቴ ቁባት ጋር የተኛኸው?” አለው፡፡
\s5
\v 8 አብኔርም በዚያን ጊዜ በኢያቡስቴ ንግግር እጅግ ስለተቆጣ እንዲህ አለ፣ “እኔ ለይሁዳ የተሰጠሁ የውሻ ራስ ነኝን? አንተን ለዳዊት አሳልፌ ባለመስጠቴ እኔ ዛሬ ለአባትህ ለሳኦል ቤት ለወንድሞቹና ለወዳጆቹ ታማኝነቴን አሳይቻለሁ፤ ይህም ሆኖ ሳለ አንተ ከዚህች ሴት ጋር በፈጸምሁት ነገር ትከሰኛለህን?
\s5
\v 9 እግዚአብሔር ለዳዊት መንግሥትን ከሳዖል ቤት አውጥቶ
\v 10 ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ባለው በእስራኤልና በይሁዳ ዙፋኑን እንደሚያጸና በመሐላ የገባለት ተስፋ እንዲፈጸም ባለደርግ እግዚአብሔር በእኔ በአበኔር ላይ ክፉ ያድርግብኝ ከዚያ የባሰም ያምጣብኝ፡፡”
\v 11 ኢያቡስቴም አበኔርን ፈርቶት ስለነበረ አንዲት ቃል ስንኳ ሊመልስለት አልቻለም፡፡
\s5
\v 12 ከዚያም አበኔር ለዳዊት፣ “ይህች ምድር የማን ናት? ከእኔ ጋር ቃል ኪዳን አድርግ፣ እነሆ፣ እስራኤል ሁሉ ወደ አንተ እንዲመለሱ ለማድረግ እጄ ከአንተ ጋር እንደሆነ ትመለከታለህ” ብለው እንዲነግሩለት መልእክተኞችን ላከ፡፡
\v 13 ዳዊትም፣ “መልካም ከአንተ ጋር ቃል ኪዳን እገባለሁ፤ ነገር ግን ከአንተ የምሻው አንድ ነገር፤ ወደ እኔ በምትመጣበት ጊዜ የሳዖልን ሴት ልጅ ሜልኮልን ይዘህልኝ ካልመጣህ ፊቴን ማየት እንደማትችል እንድታውቅ ነው፡፡” አለው፡፡
\s5
\v 14 ከዚያም ዳዊት፣ “የመቶ ፍልስጥኤማውያን ሸለፈት ማጫ የከፈልሁባትን ሚስቴን ሜልኮልን ስጠኝ” ብሎ ወደ ሳኦል ልጅ ወደ ኢያቡስቴ መልእክተኞች ላከበት፡፡
\v 15 ስለዚህም ኢያቡስቴ መልእክተኛ ልኮ፣ ሜልኮልን ከባሏ ከሌሳ ልጅ ከፍልጢኤል ወሰዳት፡፡
\v 16 ባሏም እስከ ብራቂም ከተማ ድረስ እያለቀሰ ተከትሎአት ሄደ፤ ከዚያም አበኔር፣ “አሁን፣ ወደ ቤትህ ተመለስ” አለው፡፡ ስለዚህም ተመለሰ፡፡
\s5
\v 17 አበኔር ከእስራኤል ሽማግሌዎች ጋር እንደዚህ በማለት ተመካከረ፤ “ባለፈው ጊዜ ዳዊትን በላያችሁ ለማንገሥ ሞክራችሁ ነበር፤
\v 18 እግዚአብሔር ለዳዊት፣ ‘በባሪያዬ በዳዊት ሕዝቤን እስራኤልን ከፍልስጥኤማውያን እጅና ከጠላቶቻቸው ሁሉ እጅ እታደጋቸዋለሁ’ ብሎ ስለተናገረው፣ ይህን አሁኑኑ አድርጉት፡፡”
\s5
\v 19 አበኔርም ራሱ ሄዶ ለብንያማውያን ይህንን ነገራቸው፤ ከዚያም በኋላ አበኔር እስራኤልና መላው የብንያም ቤት ለማድረግ የፈለገውን ሁሉ በመግለጽ ለዳዊት ለመንገር ወደ ኬብሮን ሄደ፡፡
\v 20 ከሃያ ሰዎች ጋር አበኔር በዳዊት ፊት ለመቅረብ ወደ ኬብሮን በመጡ ጊዜ ዳዊት ግብዣ አደረገላቸው፡፡
\s5
\v 21 አበኔርም ለዳዊት፣ “ከአንተ ጋር ቃል ኪዳን እንዲያደርጉና በፈለግኸውም ሁሉ ላይ እንድትገዛ ተነሥቼ እስራኤልን ሁሉ ወደ አንተ እሰበስባለሁ” በማለት ገለጸለት፡፡ ዳዊትም አሰናበተው፤ አበኔርም በሰላም ሄደ፡፡
\s5
\v 22 ከዚያ በኋላ የዳዊትና የኢዮአብ ወታደሮች ከዘመቻ ሲመለሱ ብዙ ምርኮ ይዘው መጡ፡፡ ዳዊት አሰናብቶት ስለነበረና እርሱም በሰላም ስለሄደ አበኔር በኬብሮን ከዳዊት ጋር አልነበረም፡፡
\v 23 ኢዮአብና አብሮት የነበረው ሠራዊት ሁሉ እዚያ እንደ ደረሱ፣ “የኔር ልጅ አበኔር ወደ ንጉሡ መጣ ንጉሡም አሰናበተው እርሱም በሰላም ሄደ” ብለው ለኢዮአብ ነገሩት፡፡
\s5
\v 24 ስለዚህ ኢዮአብ ወደ ንጉሡ ገብቶ እንዲህ አለ፣ “ምን ማድረግህ ነው? እነሆ አበኔር መጥቶልህ ለምን ይሄድ ዘንድ አሰናበትኸው?
\v 25 የኔር ልጅ አበኔር የመጣው አንተን ሊያታልልህ፣ ዕቅድህን ለማወቅና የምታደርገውን ማንኛውንም ነገር ለማጥናት እንደሆነ አታውቅምን?”
\v 26 ኢዮአብ ከዳዊት ዘንድ በወጣ ጊዜ አበኔር ዘንድ መልእክተኞችን ላከ እነርሱም ከሴይር የውሃ ጉድጓድ አጠገብ መለሱት፡፡ ዳዊት ግን ይህን አላወቀም ነበር፡፡
\s5
\v 27 አበኔር ወደ ኬብሮን በተመለሰ ጊዜ ኢዮአብ በቆይታ ለማነጋገር ወደ ቅጥሩ ዞር አደረገው በዚያም ሆዱን ወግቶ ገደለው፤ በዚህም ዓይነት መንገድ የወንድሙን የአሣሄልን ደም ተበቀለ፡፡
\s5
\v 28 ዳዊት ይህንን በሰማ ጊዜ እንዲህ አለ፣ “እኔም ሆንሁ መንግሥቴ ከኔር ልጅ ከአብኔር ደም በእግዚአብሔር ፊት ለዘላለም ንጹሕ ነን፤
\v 29 ደሙ በኢዮአብ ራስና በአባቱ ቤት ሁሉ ላይ ይሁን፤ ፈሳሽ ነገር የሚወጣው ወይም አሠቃቂ የቆዳ በሽታ ያለበት፣ በምርኩዝ የሚሄድ አንካሳ፣ ወይም በሰይፍ የሚገደል ወይም ምግብ አጥቶ የሚራብ ሰው ከኢዮአብ ቤት አይታጣ፡፡”
\v 30 ስለዚህ ወንድማቸውን አሣሄልን በገባዖን በተደረገው ጦርነት ገድሎባቸው ነበርና፣ ኢዮአብና ወንድሙ አቢሳ አበኔርን ገደሉት፡፡
\s5
\v 31 ዳዊት ለኢዮአብና አብሮት ለነበረው ሕዝብ ሁሉ፣ “ልብሳችሁን ቀዳችሁ፣ ማቅ ለብሳችሁ በአበኔር አስከሬን ፊት አልቅሱ” አላቸው፤ ንጉሥ ዳዊትም አስከሬኑን ከሚያጅበው ሕዝብ ጋር አብሮ ይሄድ ነበር፡፡
\v 32 አበኔርንም በኬብሮን ቀበሩት፤ ንጉሡም በአበኔር መቃብር ላይ ጮኾ አለቀሰ፤ ሕዝቡም ሁሉ እንደዚሁ አለቀሱ፡፡
\s5
\v 33 ንጉሡም በሐዘን እንጉርጉሮ ለአበኔር አለቀሰ፣ “አበኔር እንደ ተራ ሰው ሊሞት ይገባው ነበር?
\v 34 እጆችህ አልታሰሩም፤ እግሮችህ በእግር ብረት አልገቡም፤ ሰዎች በግፈኞች ፊት እንደሚወድቁ አንተም እንደዚሀ ወደቅህ፡፡” ሕዝቡም ሁሉ እንደገና አለቀሱለት፡፡
\s5
\v 35 ገና ቀን ሳለ ምግብ እንዲበላ ለማድረግ ሕዝቡ ሁሉ ወደ ዳዊት መጡ፤ ዳዊት ግን፣ “ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት እንጀራ ወይም ማንኛውንም ነገር ብቀምስ እግዚአብሔር ክፉ ያድርግብኝ ከዚያም የባሰ ያምጣብኝ” ብሎ ማለ፡፡
\v 36 ሕዝቡም ሁሉ የዳዊትን ሐዘን ተመለከቱ፤ ንጉሡ የሚያደርገው ሁሉ በእርግጥ ደስ ያሰኛቸው ስለነበረ፣ በዚህም ደስ አላቸው፡፡
\s5
\v 37 ስለዚህ የኔር ልጅ አበኔር ይገደል ዘንድ የንጉሡ ፍላጎት እንዳልነበረ ሕዝቡ ሁሉና እስራኤል በሙሉ በዚያን ዕለት ዐወቁ፡፡
\v 38 ንጉሡ ለአገልጋዮቹ እንደዚህ አላቸው፣ “በዛሬይቱ ዕለት በእስራኤል መስፍንና ታላቅ ሰው መውደቁን አላወቃችሁምን?
\v 39 ምንም እንኳን የተቀባሁ ንጉሥ ብሆንም እኔ ደካማ ነኝ፤ እነዚህ የጽሩይ ልጆች እጅግ ጨካኞች ሆነውብኛል፡፡ እንደ ክፋቱ በመቅጣት እግዚአብሔር ለክፉ አድራጊው እንደ እጁ ሥራ መጠን ይክፈለው፡፡”
\s5
\c 4
\p
\v 1 አበኔር በኬብሮን መሞቱን የሳኦል ልጅ ኢያቡስቴ በሰማ ጊዜ እጆቹ ዛሉ፣ መላው እስራኤልም ተጨነቀ፡፡
\v 2 በዚህ ጊዜ የሳኦል ልጅ የወታደር ጭፍራ መሪዎች የነበሩ ሁለት ሰዎች ነበሩት፤ የአንደኛው ስም በዓና ሲሆን የሌላኛው ስም ደግሞ ሬካብ ይባሉ ነበር፡፡ እነርሱም ከብንያም ነገድ የብኤሮት ተወላጅ የሆነው የሬሞን ልጆች ነበሩ (ብኤሮት ከብንያም ክፍል እንደ አንዱ ትቆጠር ነበር፤
\v 3 የብኤሮት ሕዝብ ወደ ጌቴም በመሸሽ እስከ ዛሬ በዚያ ይኖራሉ) ፡፡
\s5
\v 4 የሳኦል ልጅ ዮናታን ሁለት እግሮቹ ሽባ የሆኑ አንድ ልጅ ነበረው፡፡ እርሱም የሳዖልና የዮናታን ወሬ ከኢይዝራኤል በመጣ ጊዜ የአምስት ዓመት ልጅ ነበር፡፡ በዚህን ጊዜ ሞግዚቱ ይዛው ለመሸሽ አነሣችው፣ ነገር ግን ይዛው በምትሮጥበት ጊዜ የዮናታን ልጅ ወደቀና ሽባ ሆነ፡፡ ስሙም ሜምፊቦስቴ ይባል ነበር፡፡
\s5
\v 5 በዚህ ጊዜ የብኤሮታዊው የሬሞን ልጆች ሬካብና በዓና ሞቃት በነበረበት በቀትሩ ሰዓት እርሱ ዕረፍት እያደረገ ሳለ ወደ ኢያቡስቴ ቤት ሄዱ፡፡
\v 6 ትጠብቅ የነበረችው ሴት ስንዴ በምታበጥርበት ጊዜ እንቅልፍ ወስዷት ነበርና ሬካብና በዓና በቀስታ አልፈዋት ገቡ፡፡
\v 7 ስለዚህ ወደ ቤት ከገቡ በኋላ በክፍሉ ተኝቶ ሳለ አጠቁት ገደሉትም፡፡ ከዚያ በኋላ ራሱን ቆርጠው በመውሰድ ሌሊቱን ሁሉ በዓረባ መንገድ ተጓዙ፡፡
\s5
\v 8 የኢያቤስቴንም ራስ ወደ ኬብሮን ወደ ዳዊት ዘንድ አምጥተው፣ “አንተን ሊገድል ይፈልግ የነበረው የጠላትህ የሳዖል ልጅ የኢያቡስቴ ራስ ይኸውልህ፤ እነሆ እግዚአብሔር በዛሬው ቀን ስለ ጌታዬ ስለ ንጉሡ ሳዖልንና ዘሩን ተበቅሎአል፡፡” አሉት፡፡
\v 9 ዳዊትም ለብኤሮታዊው ለሬሞን ልጆች ለሬካብና ለወንድሙ ለበዓና ምላሽ በመስጠት እንዲህ አላቸው፣ “ከመከራ ሁሉ ያዳነኝ ሕያው እግዚአብሔርን፣
\v 10 የምሥራች ያመጣልኝ መስሎት ‘እነሆ ሳኦል ሞተ’ ብሎ የነገረኝን ሰው ይዤ ጺቅላግ ላይ ገደልሁት፤ እንግዲህ ወሬውን ላመጣው ለዚያ ሰው የሸለምሁት ይህንን ነበር፡፡
\s5
\v 11 ታዲያ በገዛ ዐልጋው ላይ ዐርፎ የተኛውን ንጹሕ ሰው ክፉ ሰዎች የገደሉት ከሆነ እንዴት ይልቅ ደሙን ከእጃችሁ አልፈልግ፣ ከዚህ ምድርስ አልደመስሳችሁ?”
\v 12 ስለዚህም ዳዊት ጎልማሶቹን አዘዘ፤ እነርሱም ገደሏቸው፤ እጅና እግራቸውንም ቆርጠው በኬብሮን ካለው ኩሬ አጠገብ ሰቀሏቸው፡፡ ነገር ግን የኢያቡስቴን ራስ ወስደው ኬብሮን በሚገኘው በአብኔር መቃብር ውስጥ ቀበሩት፡፡
\s5
\c 5
\p
\v 1 የእስራኤል ነገዶች በሙሉ ወደ ኬብሮን ወደ ዳዊት መጥተው እንዲህ አሉ፣ “እነሆ እኛ የዐጥንትህ ፍላጭ የሥጋህ ቁራጭ ነን፤
\v 2 ሳኦል በእኛ ላይ ነግሦ በነበረበት ባለፈው ጊዜ የእስራኤልን ሠራዊት የምትመራ አንተ ነበርህ፤ እግዚአብሔርም፣ ‘ሕዝቤን እስራኤልን ትጠብቃለህ፣ በእስራኤልም ላይ ገዥ ትሆናለህ’ ብሎህ ነበር፡፡”
\s5
\v 3 ስለዚህም የእስራኤል ሽማግሌዎች በሙሉ ወደ ንጉሡ ወደ ኬብሮን መጡ፤ ንጉሥ ዳዊትም ኬብሮን ላይ በእግዚአብሔር ፊት ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ፤ እነርሱም ዳዊትን ቀብተው በእስራኤል ላይ አነገሡት፡፡
\v 4 ዳዊት በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበረr፤ አርባ ዓመትም ገዛ፡፡
\v 5 በኬብሮን በይሁዳ ላይ ለሰባት ዓመት ከስድስት ወር፣ ኢየሩሳሌም ሆኖም በመላው እስራኤልና በይሁዳ ላይ ሠላሳ ሦስት ዓመት ነገሠ፡፡
\s5
\v 6 ንጉሡና ሰዎቹ የምድሪቱ ነዋሪዎች በሆኑት በኢያቡሳውያን ላይ ለመዝመት ወደ ኢየሩሳሌም ሄዱ፡፡ እነርሱም ለዳዊት፣ “በዕውሮችና በአንካሶች ልትመለስ ካልሆነ በስተቀር አንተ ወደዚህ አትገባም፤ ዳዊት እዚህ መምጣት አይችልም” አሉት፡፡
\v 7 ይሁን እንጂ ዳዊት የጽዮንን አምባ ያዘ፤ ይህችም አሁን የዳዊት ከተማ የሆነችው ነች፡፡
\s5
\v 8 በዚያን ጊዜ ዳዊት እንደዚህ አለ፣ “ኢያቡሳውያንን የሚያጠቃ በውሃ መተላለፊያው ሽቅብ መውጣት አለበት፤ በዚያም ዳዊትን የሚጠሉትን ዕውሮችንና አንካሶችን ያገኛል፡፡” እንግዲህ ሰዎች፣ “አንካሶችና ዕውሮች ወደ ቤተ መንግሥት መግባት አይችሉም” ያሉት ከዚህ የተነሣ ነው፡፡
\v 9 በመሆኑም ዳዊት በአምባይቱ ኖረ፤ የዳዊት ከተማም ብሎ ጠራት፡፡ ከሸንተረሩ አንሥቶ ወደ ውስጥ ዙሪያዋን ምሽግ ገነባባት፡፡
\v 10 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ስለነበረ፣ ዳዊት እጅግ እየበረታ ሄደ፡፡
\s5
\v 11 በዚህ ጊዜ የጢሮስ ንጉሥ ኪራም መልእክተኞችን፣ የዝግባ እንጨት፣ አናጢዎችንና ድንጋይ ጠራቢዎችን ወደ ዳዊት ላከ፤ እነርሱም ለዳዊት ቤት ሠሩለት፡፡
\v 12 እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ ንጉሥ አድርጎ እንዳጸናውና ስለ ሕዝቡም ስለ እስራኤል ሲል መንግሥቱን ከፍ እንዳደረገለት ዳዊት አወቀ፡፡
\s5
\v 13 ኬብሮንን ትቶ ወደ ኢየሩሳሌም ከመጣ በኋላ ዳዊት በኢየሩሳሌም ተጨማሪ ቁባቶችን አስቀመጠ ሚስቶችንም አገባ፤ ተጨማሪ ወንዶችና ሴቶች ልጆችም በኢየሩሳሌም ተወለዱለት፡፡
\v 14 በኢየሩሳሌም የተወለዱለትም ልጆች ስም፣ ሳሙስ፣ ሶባብ፣ ናታን፣ ሰሎሞን፣
\v 15 ኢያቤሔር፣ ኤሊሱዔ፣ ናፌቅ፣ ናፍያ፣
\v 16 ኤሊሳማ፣ ኤሊዳሄ፣ ኤሊፋላት ይባሉ ነበር፡፡
\s5
\v 17 ዳዊት በእስራኤል ላይ ንጉሥ ሆኖ መቀባቱን ፍልስጥኤማውያን በሰሙ ጊዜ፣ እርሱን ለመፈለግ በሙሉ ኃይላቸው ወጡ፤ ዳዊት ግን ይህን ሰምቶ ወደ ምሽጉ ወረደ፡፡
\v 18 በዚህ ጊዜ ፍልስጥኤማውያን መጥተው በራፋይም ሸለቆ ተበታትነው ሰፈሩ፡፡
\s5
\v 19 ዳዊትም ከእግዚአብሔር ዘንድ እንዲህ ሲል ዕርዳታ ጠየቀ፣ “ፍልስጥኤማውያንን ወጥቼ ልውጋቸውን? በእነርሱስ ላይ ድል ትሰጠኛለህ?” እግዚአብሔርም ለዳዊት፣ “በፍልስጥኤማውያን ላይ በእርግጥ ድል እሰጥሃለሁና ውጋቸው” አለው፡፡
\v 20 ስለዚህ ዳዊት በበአልፐራሲም ወጋቸው በዚያም ድል አደረጋቸው፡፡ እርሱም፣ “የጎርፍ ውሃ ጥሶ በመውጣት እንደሚያፈራርስ እግዚአብሔርም ጠላቶቼን በፊቴ አፈራረሳቸው” በማለት ስሜቱን ገለጸ፡፡ ከዚህ የተነሣም የዚያ ቦታ ስም በአልፐራሲም ተባለ፡፡
\v 21 ፍልስጥኤማውያን ጣዖቶቻቸውን እዚያ ትተው ስለነበር ዳዊትንና ሰዎቹን ወሰዷቸው፡፡
\s5
\v 22 ፍልስጥኤማውያን እንደ ገና መጥተው በራፋይም ሸለቆ በድጋሚ ተበታትነው ሰፈሩ፡፡
\v 23 ስለዚህ ዳዊት እንደገና ከእግዚአብሔር ዕርዳታ ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም፣ “በፊት ለፊት በኩል አትውጋቸው፤ ይልቁኑ በስተኋላቸው በኩል በመክበብ በበለሳኑ ዛፎች ፊት ለፊት ግጠማቸው፡፡
\s5
\v 24 በበለሳኑ ዛፎች ጫፍ ላይ የሰልፍ ጉዞ ድምፅ ስትሰማ የፍልስጥኤማውያንን ሠራዊት ለመምታት እግዚአብሔር ቀድሞ ወጥቶአልና በዚያን ጊዜ በኃይል አጥቃ” አለው፡፡
\v 25 ስለዚህም ዳዊት እግዚአብሔር እንዳዘዘው ፍልስጥኤማውያንን ከገባዖን እስከ ጌዘር ድረስ ገደላቸው፡፡
\s5
\c 6
\p
\v 1 ዳዊት እንደ ገና ከእስራኤል የተመረጡትን ሠላሳ ሺህ ሰዎች ሰበሰበ፡፡
\v 2 ዳዊትና አብረውት ያሉት ሰዎች ሁሉ በኪሩቤል ላይ በዙፋኑ በተቀመጠው በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ስም የተጠራውን የእግዚአብሔርን ታቦት ለማምጣት በይሁዳ ወዳለው ወደ በአል ሄዱ፡፡
\s5
\v 3 የእግዚአብሔርን ታቦት በአዲስ ሠረገላ ላይ አኑረው በኮረብታ ላይ ካለው ከአሚናዳብ ቤት አውጥተው አመጡ፡፡ ልጆቹ ዖዛና አሒዩ አዲሱን ሠረገላ ይመሩ ነበር፡፡
\v 4 የእግዚአብሔርን ታቦት በላዩ ላይ አኑረው ሠረገላውን በኮረብታ ላይ ካለው ከአሚናዳብ ቤት አውጥተው አመጡ፤ አሒዩ ከታቦቱ ፊት ለፊት ይሄድ ነበር፡፡
\v 5 ዳዊትና የእስራኤል ቤት በሙሉ በጥድ እንጨት በተሠሩ የሙዚቃ መሣሪያዎች ማለትም በበገና፣ በመሰንቆ፣ በከበሮ፣ በጸናጽልና በቃጭል መጫወትና ደስታቸውን መግለጽ ጀመሩ፡፡
\s5
\v 6 ወደ ናኮን ዐውድማ ሲደርሱም በሬዎቹ ስለተደናቀፉ፤ ዖዛ የእግዚአብሔርን ታቦት ለመያዝ እጁን ዘረጋ በእጁም ያዘው፡፡
\v 7 ከዚያ በኋላ የእግዚአብሔር ቁጣ በዖዛ ላይ ነደደ፤ በዚያም ስፈራ እግዚአብሔር ስለ ኃጢአቱ መታው፡፡ ዖዛም በዚያ በእግዚአብሔር ታቦት አጠገብ ሞተ፡፡
\s5
\v 8 እግዚአብሔር ዖዛን ስለመታው ዳዊት ተቆጣ፤ የዚያን ቦታም ስም ፔሬዝ ዖዛ ብሎ ጠራው፡፡ ያም ቦታ እስከ ዛሬ ድረስ ፔሬዝ ዖዛ ተብሎ ይጠራል፡፡
\v 9 ዳዊት በዚያን ቀን እግዚአብሔርን ስለ ፈራ፣ “የእግዚአብሔር ታቦት ወደ እኔ እንዴት ሊመጣ ይችላል?” ብሎ ጠየቀ፡፡
\s5
\v 10 ስለዚህ ዳዊት የእግዚአብሔርን ታቦት ከእርሱ ጋር ወደ ዳዊት ከተማ ይዞት ለመሄድ አልፈቀደም፤ በዚህ ፋንታ አቅጣጫ ለውጦ የጌት ሰው ወደ ሆነው ወደ አቢዳራ ቤት ወሰደው፡፡
\v 11 የእግዚአብሔርም ታቦት የጌት ሰው በሆነው በአቢዳራ ቤት ሦስት ወር ተቀመጠ፤ እርሱንና ቤተሰቡንም ሁሉ እግዚአብሔር ባረካቸው፡፡
\s5
\v 12 በዚህ ጊዜ፣ “በእግዚአብሔር ታቦት ምክንያት የአቢዳራን ቤተሰብና ያለውን ሁሉ እግዚአብሔር ባረከለት” ብለው ለዳዊት ነገሩት፡፡ ስለዚህ ዳዊት ወደዚያ ሄዶ የእግዚአብሔርን ታቦት ከኦቤድ ኤዶም ቤት ወደ ዳዊት ከተማ በደስታ አመጣው፡፡
\v 13 የእግዚአብሔርን ታቦት ተሸክመው የነበሩት ሰዎች ስድስት እርምጃ በሄዱ ቁጥር አንድ በሬና አንድ የሰባ ጥጃ ይሠዋ ነበር፡፡
\s5
\v 14 ዳዊትም የበፍታ ኤፉድ ብቻ በወገቡ ታጥቆ በሙሉ ኃይሉ በእግዚአብሔር ፊት ይጨፍር ነበር፡፡
\v 15 ስለዚህ ዳዊትና መላው የእስራኤል ቤት እልል እያሉና ቀንደ መለከት እየነፉ የእግዚአብሔርን ታቦት ይዘውት መጡ፡፡
\s5
\v 16 የእግዚአብሔር ታቦት ወደ ዳዊት ከተማ እየገባ ሳለ የሳዖል ልጅ ሜልኮል በመስኮት ሆና ተመለከተች፤ ንጉሥ ዳዊትም በእግዚአብሔር ፊት ሲዘልና ሲጨፍር አየችው፤ ከዚያ በኋላም በልቧ ናቀችው፡፡
\v 17 ከዚያም የእግዚአብሔርን ታቦት አምጥተው ዳዊት በተከለለት ድንኳን በተዘጋጀለት በማዕከላዊ ስፍራ አኖሩት፡፡ ከዚያ በኋላም ዳዊት የሚቃጠል መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት በእግዚአብሔር ፊት አቀረበ፡፡
\s5
\v 18 ዳዊት የሚቃጠል መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት ማቅረብ በፈጸመ ጊዜ ሕዝቡን በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ስም ባረከ፡፡
\v 19 ከዚያ በኋላ ለመላው እስራኤል፣ ለሕዝቡ ሁሉ ለወንዱም ለሴቱም ለእያንዳንዱ ሰው አንዳንድ እንጀራ፣ አንዳንድ ሙዳ ሥጋና አንዳንድ የዘቢብ ጥፍጥፍ አከፋፈለ፡፡ ከዚያ በኋላ ሕዝቡ ሁሉ እያንዳንዱ ወደየቤቱ ሄደ፡፡
\s5
\v 20 ከዚያ በኋላ ቤተሰቡን ለመባረክ ተመለሰ፡፡ የሳዖል ልጅ ሜልኮልም ዳዊትን ልትቀበለው መጣችና እንደዚህ አለች፣ “ራሳቸውን ከሚያራቁቱ ባለጌዎች እንደ አንዱ ዛሬ የእስራኤል ንጉሥ በአገልጋዮቹ መካከል በነበሩት ገረዶች ፊት ራሱን በማራቆቱ ምን ያህል የተከበረ ነበር!”
\s5
\v 21 ዳዊትም ለሜልኮል እንዲህ ሲል መለሰላት፣ “እኔን ከአባትሽና ከቤተሰቡ ሁሉ በላይ በመረጠኝና በእግዚአብሔር ሕዝብ በእስራኤል ላይ መሪ አድርጎ በሾመኝ በእግዚአብሔር ፊት ያንን አድርጌአለሁ፡፡ በእግዚአብሔር ፊት ሐሴት አደርጋለሁ!
\v 22 እንዲያውም ከዚህም የበለጠ ራሴን ዝቅ አደርጋለሁ፣ ከዚህም የባሰ የተናቅሁ እሆናለሁ፤ ነገር ግን በጠቀስሻቸው ገረዶች ፊት እከብራለሁ፡፡”
\v 23 ስለዚህም የሳኦል ልጅ ሜልኮል እስከምትሞተችበት ጊዜ ድረስ ልጅ አልወለደችም ነበር፡፡
\s5
\c 7
\p
\v 1 ንጉሡ በቤቱ ተደላድሎ ከተቀመጠና እግዚአብሔርም በዙሪያው ካሉት ጠላቶቹ ሁሉ ካሳረፈው በኋላ፣
\v 2 ለነቢዩ ለናታን ንጉሡ እንደዚህ አለው፣ “እነሆ፤ እኔ ከዝግባ በተሠራ ቤተ መንግሥት ውስጥ እኖራለሁ፤ የእግዚአብሔር ታቦት ግን በድንኳን ውስጥ ይኖራል” አለው፡፡
\s5
\v 3 ከዚያ በኋላ ናታን ለንጉሡ፣ “እግዚአብሔር ካንተ ጋር ስለሆነ ያሰብኸውን ሁሉ አድርግ” አለው፡፡
\v 4 ነገር ግን በዚያች ሌሊት እንደዚህ የሚል የእግዚአብሔር ቃል ወደ ናታን መጣ፣
\v 5 “ሂድና ለባሪያዬ ለዳዊት እንደዚህ በለው፣ ‘እግዚአብሔር የሚልህ እንደዚህ ነው፣ የምኖርበትን ቤት አንተ ትሠራልኛለህን?
\s5
\v 6 የእስራኤልን ሕዝብ ከግብፅ ካወጣሁበት ጊዜ አንሥቶ እስከ ዛሬ ድረስ በድንኳን ማደሪያ ውስጥ ሆኜ እንቀሳቀስ ነበር እንጂ በቤት ውስጥ ኖሬ አላውቅምና፤
\v 7 በመላው የእስራኤል ሕዝብ መካከል በተመላለስሁባቸው በሁሉም ስፈራዎች ሕዝቤን እስራኤልን እንዲጠብቁ ከሾምኋቸው መሪዎች ለአንዱ ስንኳ፣ ‘ከዝግባ እንጨት ለምን ቤት አልሠራህልኝም? ብያለሁን?
\s5
\v 8 እንግዲህ አሁን ለባሪያዬ ለዳዊት እንደዚህ በለው፣ ‘የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሚለው ይህንን ነው፣ በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ገዥ ትሆን ዘንድ ከመስክ በጎችን ትከተል ከነበርህበት ስፍራ ወሰድሁህ፤
\v 9 በሄድህበት ሁሉ እኔ ከአንተ ጋር ነበርሁ፤ ጠላቶችህንም ሁሉ ከፊትህ አጠፋሁልህ’፤ በምድር ላይ ስማቸው ታላቅ እንደሆነው እንደ አንዱ ለአንተ ታላቅ ስም አደርግልሃለሁ፡፡
\s5
\v 10 ከእንግዲህ ወዲያ በራሳቸው መኖሪያ እንዲኖሩ እንጂ እንዳይናወጡ ለሕዝቤ ለእስራኤል ቦታ እሰጣቸዋለሁ፣ በዚያም እተክላቸዋለሁ፡፡ ከዚህ በፊት እንደሆነውም ከእንግዲህ ወዲህ ክፉ ሕዝብ አይጨቁናቸውም፤
\v 11 መሳፍንትን በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ባዘዝሁበት ጊዜ እንዳደረጉባቸው ከእንግዲህ ወዲህ አያደርጉባቸውም፤ ከጠላቶችህም ሁሉ አሳርፍሃለሁ፡፡ ከዚህም ባሻገር፣ እኔ እግዚአብሔር ቤት እንደምሠራልህ እነግርሃለሁ፡፡
\s5
\v 12 ዕድሜህ በሚጠናቀቅበት ጊዜና ከአባቶችህ ጋር በምታርፍበት ጊዜ ከአብራክህ የሚወጣ ዝርያ አስነሳልሃለሁ፣ መንግሥቱንም አጸናለሁ፡፡
\v 13 እርሱ ለእኔ ቤት ይሠራልኛል፤ እኔም የመንግሥቱን ዙፋን ለዘላለም አጸናለሁ፡፡
\v 14 እኔ አባት እሆነዋለሁ፣ እርሱም ልጄ ይሆናል፡፡ ኃጢአት በሚያደርግበት ጊዜ በሰዎች በትር እቀጣዋለሁ፣ የሰው ልጆች በሚገረፉበትም ግርፋት እገርፈዋለሁ፤
\s5
\v 15 ከፊትህ ካስወገድሁት ከሳኦል ላይ እንደወሰድሁ ኪዳናዊ ታማኝነቴ ከእርሱ አይርቅም፡፡
\v 16 ቤትህና መንግሥትህ በፊትህ ለዘላለም የጸና ይሆናል፤ ዙፋንህም ለዘላለም የጸና ይሆናል፡፡”
\v 17 ናታን ለዳዊት እንደዚህ ተናገረ፣ ይህንንም ሁሉ ነገር ነገረው፤ ጠቅላላውንም ራእይ ገለጸለት፡፡
\s5
\v 18 ከዚያም ንጉሥ ዳዊት ገባና በእግዚአብሔር ፊት ተቀመጠና እንደዚህ አለ፣ “እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፣ እኔ ማን ነኝ? እስከዚህ ደረጃስ ታደርሰኝ ዘንድ ቤተሰቤስ ምንድን ነው?
\v 19 ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፣ ይህ በፊትህ ታናሽ ነገር ነው፡፡ ስለ ባሪያህ ቤተሰብ እንኳን ለረጅም ጊዜ የሚሆነውን ተናገርህ፣ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ ከዚህ በኋላ የሚኖረውንም ትውልዴን አሳየኸኝ!
\v 20 እኔ ዳዊት ከዚህ በላይ ለአንተ ምን እላለሁ? ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ ባሪያህን አክብረኸዋል፡፡
\s5
\v 21 ስለ ቃልህ ብለህ፣ ዓላማህንም ትፈጽም ዘንድ ይህን ታላቅ ነገር አድርገሃል፤ ለባሪያህም ገልጸህለታል፡፡
\v 22 ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ ታላቅ ነህና እንደ አንተ ያለም የለም፤ በገዛ ጆሮቻችንም እንደ ሰማን ከአንተም በቀር አምላክ የለም፡፡
\v 23 አንተ እግዚአብሔር መጥተህ ለራስህ እንዳዳንከው በምድር ላይ እንዳለው እንደ ሕዝብህ ያለ በምድር ላይ ምን ሕዝብ አለ? ይህንን ያደረግኸው ለራስህ ሕዝብን ታስነሳ ዘንድ፣ ለራስህም ስምህን ታስጠራ ዘንድና ታላቅና አስፈሪ ነገር በምድርህ ታደርግ ዘንድ ነው፡፡ ከግብፅ ከዋጀኸው ከሕዝብህ ፊት አሕዛብንና ጣዖቶቻቸውን አባረርህ፡፡
\s5
\v 24 እስራኤልን ሕዝብህ አድርገህ ለዘላለም አጸናህ፣ አንተም፣ እግዚአብሔር ሆይ አምላክ ሆንህላቸው፡፡
\v 25 አሁንም ባሪያህንና ቤተሰቡን በሚመለከት የሰጠኸውን ተስፋ ለዘላለም አጽናለት፤ እንደተናገርኸውም አድርግለት፡፡
\v 26 የእኔ፣ የባሪያህ የዳዊት ቤት በፊትህ በሚጸናበት ጊዜ ሕዝቦች፣ ‘የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የእስራኤል አምላክ ነው’ ይሉ ዘንድ ስምህ ለዘላለም ታላቅ ይሁን፡፡
\s5
\v 27 አንተ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ የእስራኤል አምላክ ለባሪያህ ቤት እንደምትሠራለት ገልጸህለታልና፤ ለዚህ ነው እኔ ባሪያህ ወደ አንተ ለመጸለይ ድፍረት ያገኘሁት፡፡
\v 28 አሁን፣ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ አምላክ ነህ፣ ቃሎችህም የታመኑ ናቸው፤ ይህንን መልካም የተስፋ ቃል ለባሪያህ ገብተህለታል፡፡
\v 29 በፊትህ ለዘላለም የሚቀጥል ይሆን ዘንድ፣ እንግዲህ አሁን የባሪያህን ቤት መባረክ አንተን ደስ ያሰኝህ፡፡ አንተ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፣ እነዚህን ነገሮች ተናግረሃልና በበረከትህ የባሪያህ ቤት ለዘላለም የተባረከ ይሆናል፡፡”
\s5
\c 8
\p
\v 1 ከዚህ በኋላ ዳዊት ፍልስጥኤማውያንን ወጋቸው ድልም አደረጋቸው፡፡ ስለዚህ ዳዊት ጋትና መንደሮችዋን ከፍልስጥኤማውያን ቁጥጥር ነጻ አወጣት፡፡
\s5
\v 2 ከዚያ በኋላም ዳዊት ሞዓባውያንን ድል አደረገ፤ በመሬት ላይ አጋድሞ በገመድ ለካቸው፤ በገመድ ከተለኩትም ሁለት እጅ ሲገድል፣ አንድ እጅ ግን በሕይወት ይተው ነበር፡፡ ስለዚህ ሞዓባውያን የዳዊት አገልጋዮች ሆኑ፣ ግብርም ገበሩለት፡፡
\s5
\v 3 ከዚህ በኋላ ደዊት በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ ያለውን ግዛቱን ለማስመለስ ይጓዝ በነበረበት ጊዜ የሱባን ንጉሥ የረአብን ልጅ አድርአዛርን ድል አደረገው፡፡
\v 4 ዳዊትም ከእርሱ ላይ 1700 ሠረገሎችና 20, 000 እግረኞች ማረከ፡፡ ለመቶ ሠረገሎች የሚሆኑትን አስቀርቶ ዳዊት የሠረገሎቹን ፈረሶች ሁሉ ቋንጃዎች ቆረጠ፡፡
\s5
\v 5 ከደማስቆ አራማውያን የሱባን ንጉሥ አድርአዛርን ለመርዳት በመጡ ጊዜ ሃያ ሁለት ሺህ አራማውያን ሰዎችን ገደለ፡፡
\v 6 ከዚያም የደማስቆ ክፍል በሆነው በአራም የጦር ሰፈሮችን አቋቋመ፤ አራማውያንም ለእርሱ አገልጋዮች ሆነው ተገዙለት፣ ግብርም ገበሩለት፡፡ ዳዊት በሄደበት ሁሉ እግዚአብሔር ድልን ሰጠው፡፡
\s5
\v 7 የአድርአዛር አገልጋዮች ይዘዋቸው የነበሩትን የወርቅ ጋሻዎች ዳዊት ወሰዳቸው ወደ ኢየሩሳሌምም አመጣቸው፡፡
\v 8 ቤጣህና ቤሮታይ ከተባሉ ከአድርአዛር ከተሞችም ዳዊት እጅግ ብዙ ናስ ወሰደ፡፡
\s5
\v 9 የሐማት ንጉሥ ቶዑ ዳዊት መላውን የአድርአዛርን ሠራዊት ድል ማድረጉን በሰማ ጊዜ፣
\v 10 ዳዊት ከአድርአዛር ጋር ስለ ተዋጋና ድል ስላደረገው ደግሞም አድርአዛር ከቶዑ ጋር ተዋግቶ ስለ ነበረ፣ ቶዑ ልጁን ዮራምን ሰላምታ ይሰጠው ዘንድና ይባርከው ዘንድ ወደ ዳዊት ላከው፡፡ ዮራምም ከእርሱ ጋር የብር፣ የወርቅና የናስ ዕቃዎች ይዞ መጣ፡፡
\s5
\v 11 ንጉሥ ዳዊትም ድል ካደረጋቸው መንግሥታት ሁሉ ማለትም
\v 12 ከአራም፣ ከሞዓብ፣ የአሞን ሕዝብ፣ ከፍልስጥኤማውያን ከአማሌቅ እንዲሁም ከሱባ ንጉሥ ከረአብ ልጅ ከአድርአዛር ከበዘበዛቸው ዕቃዎችና ካገኛቸው ብርና ወርቅ ጋር እነዚህን ለእግዚአብሔር ቀደሰ፡፡
\s5
\v 13 ዳዊት የጨው ሸለቆ በተባለው ስፍራ ከአሥራ ስምንት ሺህ ሰዎቻቸው ጋር የነበሩትን አራማውያንን ድል አድርጎ ከተመለሰ በኋላ ስሙ ገነነ፡፡
\v 14 በመላው ኤዶም የጦር ሰፈሮችን አቋቋመ፤ ኤዶማውያን ሁሉ የዳዊት አገልጋዮች ሆኑ፤ እግዚአብሔርም ዳዊት በሄደበት ስፈራ ሁሉ ድልን ሰጠው፡፡
\s5
\v 15 ዳዊት በመላው እስራኤል ላይ ነገሠ፤ ሕዝቡንም ሁሉ በፍትሐዊነትና በጽድቅ አስተዳደረ፡፡
\v 16 የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ የሠራዊቱ አለቃ ሲሆን፣ የአሒሉድ ልጅ ኢዮሣፍጥም ታሪክ ጸሐፊ ነበረ፡፡
\v 17 የአኪጦብ ልጅ ሳዶቅና የአብያታር ልጅ አቢሜሌክ ካህናት ሲሆኑ፣ ሠራያ ጸሐፊ ነበር፡፡
\v 18 የዮዳሔ ልጅ በናያስ የከሊታውያንና የፈሊታውያን አለቃ ሲሆን፣ የዳዊት ወንዶች ልጆች ደግሞ የንጉሡ ተቀዳሚ አማካሪዎች ነበሩ፡፡
\s5
\c 9
\p
\v 1 ዳዊትም፣ “ስለ ዮናታን ስል ቸርነት አደርግለት ዘንድ ከሳዖል ቤት የቀረ ሰው ይኖር ይሆን?” በማለት ጠየቀ፡፡
\v 2 በሳኦል ቤተሰብ ውስጥ ሲባ የሚባል አንድ አገልጋይ ነበረ፤ እነርሱም ወደ ዳዊት እንዲሄድ ነገሩት፡፡ ንጉሡም፣ “አንተ ሲባ ነህን?” ብሎ ጠየቀው፡፡ ሲባም፣ “አዎን፣ እኔ አገልጋይህ ነኝ” ብሎ መለሰ፡፡
\s5
\v 3 ንጉሡም፣ “የእግዚአብሔርን ቸርነት እንዳደርግለት ከሳኦል ቤት የቀረ ሰው የለምን?” በማለት ጠየቀው፡፡ ሲባም ለንጉሡ፣ “ዮናታን እግሩ ሽባ የሆነ አንድ ልጅ አለው” ብሎ መለሰ፡፡
\v 4 ንጉሡም፣ “ወዴት ነው ያለው?” አለው፡፡ ሲባም ለንጉሡ፣ “ሎዶባር በተባለ ስፍራ በዓሚኤል ልጅ በማኪር ቤት ይገኛል” ብሎ መለሰለት፡፡
\s5
\v 5 በዚህን ጊዜ ንጉሥ ዳዊት ሎደባር ወደሚገኘው ወደ ዓሚኤል ልኮ ከማኪር ቤት ሜምፊቦስቴን አስመጣው፡፡
\v 6 የሳኦል ልጅ፣ የዮናታን ልጅ ሜምፊቦስቴ ወደ ዳዊት መጥቶ ለጥ ብሎ እጅ በመንሣት ለዳዊት አክብሮቱን ገለጠ፡፡ ዳዊትም፣ “ሜምፊቦስቴ” ብሎ ጠራው፡፡ እርሱም፣ “እነሆ፣ አገልጋይህ” አለ፡፡
\s5
\v 7 ዳዊትም፣ “አትፍራ፤ ስለ አባትህ ስለ ዮናታን ስል በእርግጥ ቸርነት አደርግልሃለሁና፡፡ የአያትህንም የሳኦልን ምድር በሙሉ እመልስልሃለሁ፤ ዘወትርም ከገበታዬ ትበላለህ፡፡” አለው፡፡
\v 8 ሜምፊቦስቴም ለጥ ብሎ እጅ ነሣና፣ “እንደ ሞተ ውሻ የሆንኩትን እኔ አገልጋይህን በሞገስ ትመለከተኝ ዘንድ እኔ ማን ነኝ?”
\s5
\v 9 ከዚያም ንጉሡ የሳኦልን አገልጋይ ሲባን ጠርቶ እንዲህ አለው፤ “የሳኦልና የቤተሰቡ የሆነውን ሁሉ ለጌታህ ልጅ ሰጥቼዋለሁ፡፡
\v 10 አንተ፤ ልጆችህና አገልጋዮችህ የጌታችሁ የልጅ ልጅ የሚበላውን እንዲያገኝ መሬቱን እረሱለት፣ ምርቱንም አግቡለት፡፡ የጌታህ የልጅ ልጅ ሜምፊቦስቴ ግን ምን ጊዜም ከገበታዬ ይበላል፡፡” በዚያን ጊዜ ሲባ ዐሥራ አምስት ልጆችና ሃያ አገልጋዮች ነበሩት፡፡
\s5
\v 11 ከዚያም ሲባ ንጉሡን፣ “ጌታዬ ንጉሥ፣ አገልጋዩን ያዘዘውን ሁሉ፣ አገልጋይህ ይፈጽመዋል” አለው፡፡ ንጉሡም በተጨማሪ፣ “ሜምፊቦስቴ በበኩሉ ከንጉሡ ልጆች እንደ አንዱ ከገበታዬ የሚበላ ይሆናል” አለ፡፡
\v 12 ሜምፊቦስቴ ሚካ የተባለ አንድ ትንሽ ልጅ ነበረው፤ የሲባ ቤተሰቦች በሙሉ የሜምፊቦስቴ አገልጋዮች ነበሩ፡፡
\v 13 ስለዚህ ሜምፊቦስቴ ይኖር የነበረው በኢየሩሳሌም ነበር፣ ሁለት እግሮቹም ሽባ ቢሆኑም ሁልጊዜ ከንጉሡ ገበታ ይበላ ነበር፡፡
\s5
\c 10
\p
\v 1 ከዚህ በኋላ የአሞናውያን ንጉሥ ሞተ፣ ልጁ ሐኖንም በእርሱ ምትክ ንጉሥ ሆነ፡፡
\v 2 ዳዊትም፣ “አባቱ ቸርነትን እንዳደረገልኝ ሁሉ እኔን ለናዖስ ልጅ ለሐኖን ቸርነትን አደርግለታለሁ፡፡” አለ፡፡ ስለዚህ በአባቱ ምክንያት ከደረሰበት ኃዘን ያጽናኑት ዘንድ ዳዊት አገልጋዮቹን ላከ፡፡ አገልጋዮቹም ወደ አሞን ምድር ገቡ፡፡
\v 3 የአሞን ሕዝብ መሪዎች ግን ለጌታቸው ለሐኖን እንደዚህ አሉት፣ “አንተን እንዲያጽናኑ ሰዎቹን በመላኩ ዳዊት በእርግጥ አባትህን በማክበር ነው ብለህ ታስባለህን? ዳዊት ሰዎቹን የላከው ከተማይቱን እንዲመለከቱና ያጠፏትም ዘንድ እንዲሰልሏት አይደለምን?”
\s5
\v 4 ስለዚህ ሐኖን የዳዊትን ሰዎች ይዞ፤ የእያንዳንዳቸውን ጢም በከፊል ላጨ፣ ልብሳቸውንም እስከ ቂጣቸው ድረስ አሳጥሮ በመቁረጥ መልሶ ሰደዳቸው፡፡
\v 5 ይህንን ለዳዊት በገለጹለት ጊዜ፣ ሰዎቹ እጅግ አፍረው ነበርና መልእክተኞችን ወደ እነርሱ ላከ፡፡ ንጉሡም፣ “ጢማችሁ እስኪያድግ በኢያሪኮ ቆዩና ከዚያ በኋላ ተመለሱ” አላቸው፡፡
\s5
\v 6 የአሞን ሰዎች ለዳዊት መጥፎ ጠረን እንዳላቸው ሰዎች እንደሆኑበት ባወቁ ጊዜ የአሞን ሰዎች መልእክተኞችን ልከው ከቤትሮዖብና ከሱባ ሃያ ሺህ አራማውያን እግረኛ ወታደሮችን፣ ከንጉሥ መዓካ አንድ ሺህ ሰዎችን ደግሞም ከጦብ ዐሥራ ሁለት ሺህ ሰዎችን ቀጠሩ፡፡
\v 7 ዳዊት ይህን በሰማ ጊዜ ኢዮአብን ከመላው ተዋጊ ሠራዊት ጋር ላከው፡፡
\v 8 አሞናውያን ወጥተው በከተማቸው መግቢያ በር ላይ ሲሰለፉ፤ የሱባና የረአብ አራማውያን ሰዎች ለብቻቸው ሜዳው ላይ ቆሙ፡፡
\s5
\v 9 ኢዮአብም ከፊትና ከኋላው ጦር እንደ ከበበው ባየ ጊዜ፣ በእስራኤል በጀግንነታቸው ከታወቁት ጥቂቶቹን መርጦ በአራማውያን ግንባር አሰለፋቸው፡፡
\v 10 የቀሩትን ሰዎች ደግሞ በወንድሙ በአቢሳ ሥር መድቦ በአሞናውያን ሠራዊት ግንባር አሰለፋቸው፡፡
\s5
\v 11 ኢዮአብም እንዲህ አለ፤ “አራማውያን የሚያይሉብኝ ከሆነ አንተ መጥተህ ትረዳኛለህ፤ አሞናውያን የሚያይሉብህ ከሆነ እኔ መጥቼ እረዳሃለሁ፡፡
\v 12 እንግዲህ በርታ ለሕዝባችንና ለአምላካችን ከተሞች ጠንካሮች መሆናችንን እናስመስክር፤ እግዚአብሔርም ለዓላማው መልካም መስሎ የታየውን ያደርጋል፡፡”
\s5
\v 13 ከዚያም ኢዮአብና አብሮት የነበረው ሠራዊት ከእስራኤል ሠራዊት ፊት እንዲሸሹ ወደ ተገደዱት ወደ አራማውያን በመገሥገሥ ወደ ጦርነቱ ሄዱ፡፡
\v 14 አራማውያን መሸሻቸውን አሞናውያን ባዩ ጊዜ፣ እነርሱም ከአቢሳ ፊት ሸሽተው ወደ ከተማይቱ ውስጥ ገቡ፡፡ ከዚህ በኋላ ኢዮአብ ከአሞናውያን ሕዝብ ተመልሶ ወደ ኢየሩሳሌም ሄደ፡፡
\s5
\v 15 አራማውያን በእስራኤላውያን እየተሸነፉ እንደሆኑ ባዩ ጊዜ እንደ ገና ተሰባሰቡ፡፡
\v 16 አድርአዛር ከኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ ወደነበሩት ወደ አራማውያን ሠራዊት መልእክተኞችን ላከ፤ እነርሱም በአድርአዛር ሠራዊት አዛዥ በሶባክ መሪነት ወደ ዔላም መጡ፡፡
\s5
\v 17 ይሄ ነገር ለዳዊት በተነገረው ጊዜ መላውን እስራኤልን ሰበሰበ፤ ከዚያም ዮርዳኖስን ተሻግሮ ወደ ዔላም ሄደ፡፡ አራማውያን ለጦርነት ተሰልፈው ዳዊትን ገጠሙት ተዋጉትም፡፡
\v 18 አራማውያን ከእስራኤል ፊት ሸሹ፤ ዳዊትም ሰባት መቶ ሠረገለኞችንና አርባ ሺህ ፈረሰኞችን ገደለ፡፡ የሠራዊቱ አዛዥ ሶባክም ቆስሎ በዚያ ሞተ፡፡
\v 19 የአድርአዛር አገልጋዮች የነበሩት ነገሥታት ሁሉ በእስራኤል መሸነፋቸውን ባዩ ጊዜ ከእስራኤላውያን ጋር ሰላም መሠረቱ ተገዙላቸውም፡፡ ስለዚህም ሶርያውያን ከዚያ በኋላ አሞናውያንን መርዳት ፈሩ፡፡
\s5
\c 11
\p
\v 1 ነገሥታት ወደ ጦርነት መውጣታቸው የተለመደ በነበረበት በፀደይ ወራት ዳዊት ኢዮአብን፣ አገልጋዮቹንና መላውን የእስራኤል ሠራዊት ወደ ዘመቻ ላካቸው፤ እነርሱም አሞናውያንን አጠፉ፤ ረባትንም ከበቡአት፡፡ ዳዊት ግን በኢየሩሳሌም ቀረ፡፡
\s5
\v 2 ከዚህም የተነሣ በአንድ የምሽት ወቅት ዳዊት ከዐልጋው ተነስቶ በቤተ መንግሥቱ ሰገነት ወዲያና ወዲህ ይመላለስ ነበር፤ በዚያም ስፍራ ሆኖ አንዲት ሴት ገላዋን ስትታጠብ አየ፤ ሴቲቱም እጅግ በጣም ውብ ነበረች፡፡
\v 3 ዳዊትም ሰው ልኮ ስለ ሴቲቱ የሚያውቁ ሰዎችን አጠያየቀ፡፡ አንድ ሰውም፣ “ይህች የኤልያብ ልጅ፣ የኬጢያዊው የኦርዮን ሚስት አይደለችምን?”
\s5
\v 4 ከዚያም ዳዊት መልእክተኞች ልኮ አስመጣት፤ ወደ እርሱም ገባች፣ (ከወር አበባ ጊዜዋ የነጻችበት ወቅት ነበርና) አብሮአት ተኛ፡፡ ከዚያም ተመልሳ ወደ ቤቷ ሄደች፡፡
\v 5 ሴቲቱ ፀነሰች፣ “አርግዣለሁ” ብላም ወደ ዳዊት መልእክት ላከችበት፡፡
\s5
\v 6 ከዚያ በኋላም ዳዊት ለኢዮአብ፣ “ኬጢያዊውን ኦርዮንን ወደ እኔ ላክልኝ” ብሎ መልእክት ላከበት፡፡ ስለዚህም ኢዮአብ ኦርዮንን ወደ ዳዊት ላከው፡፡
\v 7 ኦርዮን በደረሰ ጊዜ ኢዮአብና ሠራዊቱ በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ እንዲሁም ጦርነቱ እንዴት እየተካሄደ እንዳለ ጠየቀው፡፡
\v 8 ዳዊትም ለኦርዮን፣ “ወደ ቤትህ ሄደህ እግርህን ተታጠብ” አለው፡፡ ኦርዮንም ከቤተ መንግሥቱ ወጣ፣ ንጉሡም ኦርዮን ከወጣ በኋላ ስጦታ አስከትሎ ላከለት፡፡
\s5
\v 9 ኦርዮን ግን ከጌታው አገልጋዮች ጋር በቤተ መንግሥቱ ቅጥር በር ተኛ እንጂ ወደ ቤቱ አልወረደም ነበር፡፡
\v 10 ለዳዊት “ኦርዮ ወደ ቤቱ አልሄደም” ብለው በነገሩት ጊዜ፣ ዳዊት ኦርዮንን፣ “ከመንገድ መግባትህ አይደለምን? ለምን ወደ ቤትህ ያልሄድኸው ለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው፡፡
\v 11 ኦርዮም ዳዊትን፣ “ታቦቱ፣ እስራኤልና ይሁዳ በድንኳን ሆነው፣ ጌታዬ ኢዮአብና የጌታዬም አገልጋዮች ገላጣ ሜዳ ላይ ሰፍረው፤ ለመብላትና ለመጠጣት እንዲሁም ከሚስቴ ጋር ለመተኛት እንዴት ወደ ቤቴ እሄዳለሁ? እንዲህ ያለውን ነገር እንደማላደርገው በነፍስህ እምላለሁ፡፡” አለው፡፡
\s5
\v 12 ከዚህም የተነሣ ዳዊት ለኦርዮ፣ “ዛሬ ደግሞ በዚህ እደርና ነገ አሰናብትሃለሁ” አለው፡፡ ስለዚህ ኦርዮ በዚያ ዕለትና በማግሥቱ እዚያው ኢየሩሳሌም ቆየ፡፡
\v 13 ዳዊትም ባስጠራው ጊዜ በእርሱ ፊት በላ ደግሞም ጠጣ፣ ዳዊትም እንዲሰክር አደረገው፤ ሲመሽም ኦርዮን በአልጋው ላይ ለመተኛት የጌታው አገልጋዮች ወዳሉበት ሄደ፣ ወደ ቤቱ ግን አልሄደም፡፡
\s5
\v 14 ስለዚህ በማግስቱ ሲነጋ ዳዊት ለኢዮአብ ደብዳቤ ጽፎ በኦርዮን እጅ ላከለት፡፡
\v 15 በደብዳቤውም ውስጥ ዳዊት፣ “ኦርዮንን ውጊያው በተፋፋመበት ግንባር መድበው፤ ከዚያም እንዲመታና እንዲሞት ከኋላው አፈግፍጉ” ብሎ ጻፈ፡፡
\s5
\v 16 ስለዚህ ኢዮአብ የከተማይቱን መከበብ እየተመለከተ ሳለ ጠንካሮቹ የጠላት ሠራዊት እየተዋጉ እንዳሉ በሚያውቅበት ግንባር ኦርዮንን መደበው፡፡
\v 17 የከተማይቱ ሰዎች ወጥተው ከኢዮአብ ጋር ጦርነት በገጠሙበት ጊዜ ከዳዊት ወታደሮች ጥቂቶቹ ሞቱ፣ እንዲሁም ኬጢያዊው ኦርዮንም በዚያ ሞተ፡፡
\s5
\v 18 ኢዮአብም በጦርነቱ የሆነውን ሁሉ ለዳዊት በላከበት ጊዜ፣
\v 19 መልእክተኛውን እንዲህ ብሎ አዘዘው፣ “ጦርነቱን በሚመለከት ሁሉንም ነገር ለንጉሡ ከጨረስክ በኋላ፣
\v 20 ምናልባት ንጉሡ ይቆጣና፣ ‘ለመዋጋት ስትሉ ወደ ከተማይቱ ይህን ያህል የተጠጋችሁት ስለምንድን ነው? በግንቡ ቅጥር ላይ ሆነው ፍላፃ እንደሚወርውሩባችሁ አታውቁም ኖሮአል?
\s5
\v 21 የይሩቤሼትን ልጅ አቤሜሌክን የገደለው ማነው? በቴቤስ እንዲሞት ያደረገችው አንዲት ሴት ከግንቡ ላይ የወፍጮ መጅ ስለለቀቀችበት አይደለምን? ወደ ግንቡ ቅጥር ይህን ያህል የተጠጋችሁት ለምንድን ነው?’ይልህ ይሆናል፡፡ በዚያን ጊዜ፣ ‘አገልጋይህ ኬጢያዊው ኦርዮም ሞቶአል’ ብለህ ንገረው፡፡”
\s5
\v 22 ስለዚህ መልእክተኛው ተነሥቶ ወደ ዳዊት ዘንድ ሄደ፣ ኢዮአብ እንዲናገር የላከውን ማንኛውንም ነገር ነገረው፡፡
\v 23 መልእክተኛውም ለዳዊት እንዲህ አለው፣ “እኛ በመጀመሪያ ከነበረው ይልቅ ጠላት በርትቶ ነበር ወደ ሜዳው ወደ እኛ ዘንድ መጡ፤ እኛም እስከ ቅጥሩ መግቢያ በር ድረስ አሳድደን መለስናቸው፡፡
\s5
\v 24 የእነርሱም ባለ ፍላጻዎች ከግንቡ ላይ ሆነው በወታደሮችህ ላይ ቀስት ወረወሩ፣ ከንጉሡ አገልጋዮችም ጥቂቶችን ገደሉ፤ አገልጋይህ ኬጢያዊው ኦርዮም ሞተ፡፡”
\v 25 ከዚያ በኋላ ዳዊት ለመልእክተኛው፣ “ለኢዮአብ፣ ‘መቼም ሰይፍ አንድ ጊዜ ይህን፣ ሌላ ጊዜም ሌላውን ይበላልና ይህ አያሳዝንህ፡፡ በከተማይቱ ላይ ውጊያህን አጠናክረህ አፍርሳት፡፡’ በለው፣ ኢዮአብን አበረታታው፡፡”
\s5
\v 26 ስለዚህ የኦርዮ ሚስት ባሏ መሞቱን በሰማች ጊዜ አምርራ አለቀሰችለት፡፡
\v 27 የሐዘኗም ጊዜ ካበቃ በኋላ ዳዊት ልኮ ቤርሳቤህን ወደ ቤቱ ወሰዳት፣ ሚስቱም ሆነች፣ ወንድ ልጅም ወለደችለት፤ ነገር ግን ዳዊት ያደረገው ነገር እግዚአብሔርን አሳዘነው፡፡
\s5
\c 12
\p
\v 1 እግዚአብሔር ናታንን ወደ ዳዊት ላከው፤ እርሱም ወደ ዳዊት መጥቶ እንዲህ አለው፣ “በአንድ ከተማ ሁለት ሰዎች ነበሩ፤ ከእነርሱም አንዱ ባለጠጋ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ድኻ ነበረ፡፡
\v 2 ባለጠጋው እጅግ ብዙ መንጋዎችና የቀንድ ከብቶች ነበሩት፤
\v 3 ድኻው ግን ከገዛትን ካሳደጋት ከአንዲት መሲና በግ በስተቀር ሌላ አልነበረውም፡፡ ይህች በግ ከእርሱ ጋር ኖረች ከልጆቹም ጋር አደገች፡፡ በጊቱ እንዲያውም ከእርሱ ጋር ትበላ፣ ከጽዋውም ትጠጣ ነበር፤ በእቅፉም ትተኛ ነበር፣ ለእርሱም እንደ ሴት ልጁ ነበረች፡፡
\s5
\v 4 አንድ ቀን አንድ እንግዳ ወደ ባለጠጋው ቤት መጣ፤ ባለጠጋው ግን ለእንግዳው ምግብ ለማቅረብ ከራሱ መንጋ ወይም ከቀንድ ከብቶቹ አንድ እንሰሳ ለመውሰድ ፈቃደኛ አልነበረም፡፡ ከዚያ ይልቅ የድኻውን መሲና ጠቦት ወስዶ ለእንግዳው ምግብ አድርጎ አዘጋጀለት፡፡”
\v 5 ዳዊትም በባለጠጋው ላይ ቁጣው ነደደ፣ በንዴትም ለናታን፣ “ሕያው እግዚአብሔርን ይህን ያደረገው ሰው ሞት ይገባዋል!
\v 6 እንዲህ ያለውን ነገር በማድረጉና ለደኻውም ባለመራራቱ ስለ በጊቱ አራት ዕጥፍ መክፈል አለበት፡፡”
\s5
\v 7 ከዚያ በኋላም ናታን ለዳዊት፣ “ያ ሰው አንተ ነህ፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንደዚህ ይላል፣ ‘በእስራኤል ላይ ንጉሥ ትሆን ዘንድ ቀባሁህ ከሳኦልም እጅ ታደግሁህ፤
\v 8 የጌታህን ቤት ሰጠሁህ፣ የጌታህንም ሚስቶች በብትህ አስታቀፍሁህ፤ የእስራኤልና የይሁዳን ቤት ሰጠሁህ፤ ይህም ሁሉ አንሶህ ቢሆን ብዙ ሌሎች ነገሮችንም ጨምሬ በሰጠሁህ ነበር፡፡
\s5
\v 9 ስለዚህ በእርሱ ፊት ክፉ የሆነውን ታደርግ ዘንድ የእግዚአብሔርን ሕግ ለምን አቃለልህ? ኬጢያዊውን ኦርዮንን በሰይፍ ገደለህ፣ ሚስቱንም ወስደህ የራስህ ሚስት አደረግኸት፡፡ ኦርዮንን በአሞናውያን ሠራዊት ሰይፍ ገደልኸው፡፡
\v 10 እኔን አቃለኸኛልና የኬጢያዊውንም የኦርዮንን ሚስት ሚስትህ አድርገህ ወስደሃልና ሰይፍ ከቤትህ በፍጹም አይርቅም፡፡’
\s5
\v 11 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ ‘ከራስህ ቤት ጥፋት አስነሳብሃለሁ፤ ዓይንህ እያየም ሚስቶችህን ወስጄ ለጎረቤትህ እሰጠዋለሁ፣ እርሱም በቀን ብርሃን ከሚስቶችህ ጋር ይተኛል፡፡
\v 12 አንተ ኃጢአትህን በስውር እኔ ግን ይህንን ነገር በቀን ብርሃን በእስራኤል ሁሉ ፊት እገልጠዋለሁ፡፡’”
\v 13 ከዚያም ዳዊት ለናታን፣ “እግዚአብሔርን በድያለሁ” አለው፡፡ ናታንም ለዳዊት መለሰለት፣ “እግዚአብሔር ኃጢአትህን አስወግዶልሃል፡፡ አንተ አትሞትም፤
\s5
\v 14 ይሁን እንጂ በዚህ ድርጊትህ እግዚአብሔርን ስላቃለልህ የተወለደልህ ልጅ በእርግጥ ይሞታል፡፡”
\v 15 ከዚያ በኋላ ናታን ወጥቶ ወደ ቤቱ ሄደ፡፡ እግዚአብሔርም የኦርዮን ሚስት ለዳዊት የወለደችለትን ልጅ እግዚአብሔር አስጨነቀው እጅግም ታመመ፡፡
\s5
\v 16 ዳዊት ስለ ልጁ እግዚአብሔርን ለመነ፤ ጾመም ከዚያም ወደ ክፍሉ ገብቶ ሌሊቱን ወለሉ ላይ ተኝቶ አደረ፡፡
\v 17 የቤተሰቡ ሽማግሌዎችም ከወለሉ ላይ ያነሱት ዘንድ በአጠገቡ ቆሙ፣ እርሱ ግን አልተነሳም፣ ከእነርሱም ጋር አልበላም፡፡
\v 18 በሰባተኛውም ቀን ልጁ ሞተ፡፡ “እነሆ፣ ልጁ ገና በሕይወት ሳለ ስናነጋግረው ድምፃችንን አልሰማንም፣ ታዲያ፣ ልጁ ሞቶአል ብንለው በራሱ ላይ ምን ያደርግ ይሆን?!” ብለው ስለነበረ፣ የዳዊት አገልጋዮች ልጁ እንደ ሞተ ለመንገር ፈርተው ነበር፡፡
\s5
\v 19 ነገር ግን እርስ በርሳቸው ሲንሾካሾኩ ዳዊት በተመለከተ ጊዜ፣ ልጁ እንደ ሞተ ዳዊት ተገነዘበ፤ ለአገልጋዮቹም፣ “ልጁ ሞተ?” ብሎ ጠየቃቸው፡፡ እነርሱም፣ “ሞቶአል” ብለው መለሱለት፡፡
\v 20 ከዚያም ዳዊት ከወለሉ ላይ ተነስቶ ታጠበ፣ ቅባት ተቀባ ደግሞም ልብሱን ለወጠ፤ ወደ እግዚአብሔር ቤትም ሄዶ አምልኮ አቀረበ፣ ከዚያ በኋላም ወደ ራሱ ቤተ መንግሥት ተመለሰ፡፡ ምግብ እንዲያቀርቡለት በጠየቀ ጊዜ አቀረቡለት፣ እርሱም በላ፡፡
\s5
\v 21 ከዚያ በኋላ አገልጋዮቹ፣ “እንደዚህ ያደረግኸው ለምንድን ነው? ልጁ በሕይወት እያለ ጾምህ አለቀስህም፤ ልጁ ከሞተ በኋላ ግን ተነሥተህ በላህ” አሉት፡፡
\v 22 ዳዊትም፣ “ልጁ ገና በሕይወት ሳለ ጾምሁ አለቀስሁም፤ ‘ልጁ በሕይወት ይኖር ዘንድ እግዚአብሔር ቸርነት ያደርግልኝ እንደሆነ ማን ያውቃል’ ብዬ ነበር፡፡
\v 23 አሁን ግን፣ እርሱ ሞቶአልና ለምን እጾማለሁ? መልሼ ላመጣው እችላለሁን? እኔ ወደ እርሱ እሄዳለሁ እንጂ እርሱ ወደ እኔ አይመለስም፡፡”
\s5
\v 24 ከዚያም ዳዊት ሚስቱን ቤርሳቤህን አጽናናት፤ ወደ እርሷም ገብቶ አብሮአት ተኛ፡፡ ከዚህም የተነሣ ወንድ ልጅ ወለደች፣ ልጁም ሰሎሞን የሚል ስም ተሰጠው፤ እግዚአብሔርም ወደደው፡፡
\v 25 ስለሆነም እግዚአብሔር ስለወደደው ይዲድያ ተብሎ እንዲጠራ በነቢዩ በናታን በኩል ቃል ላከ፡፡
\s5
\v 26 በዚያን ጊዜም ኢዮአብ የአሞናውያን የንጉሥ ከተማ የነበረችውን ረባትን ወግቶ ምሽጉን ያዘ፡፡
\v 27 ስለሆነም ኢዮአብ ወደ ዳዊት መልእክተኞችን በመላክ እንዲህ አለው፣ “ረባትን ወግቼ የከተማይቱን የውሃ ማከፋፈያ ይዤአለሁ፡፡
\v 28 እንግዲህ አሁን፣ የቀረውን ሠራዊት አሰባስበህ በከተማይቱ ዙሪያ ሠፍረህ ያዛት፤ ምክንያቱም እኔ ከተማይቱን ከያዝኳት በስሜ መጠራቷ ነው፡፡”
\s5
\v 29 ስለዚህ ዳዊት መላውን ሠራዊት አሰባስቦ ወደ ረባት ሄዶ ከተማይቱን ወግቶ ያዛት፡፡
\v 30 ዳዊት ከሞሎክ ራስ ላይ ዘውዱን ወሰደ፤ የዘውዱም ክብደት አንድ መክሊት ወርቅ ሲሆን የከበረ ዕንቁም በላዩ ላይ ነበረበት፡፡ ዘውዱም በዳዊት ራስ ላይ ተጫነ፡፡ ከዚያም እጅግ ብዙ የከተማይቱን ምርኮ አመጣ፡፡
\s5
\v 31 በከተማይቱ የነበሩትንም ሰዎች አውጥቶ በመጋዝ፣ በብረት መቆፈሪያና በመጥረቢያ እንዲሠሩ አስገደዳቸው፤ የሸክላ ጡብም እንዲሠሩ አደረጋቸው፡፡ ዳዊት የአሞን ሕዝብ ከተሞች ሁሉ ይህንኑ ተግባር እንዲፈጽሙ አደረጋቸው፡፡ ከዚያም ዳዊትና ሠራዊቱ በሙሉ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፡፡
\s5
\c 13
\p
\v 1 ከዚህ በኋላ የዳዊት ልጅ አምኖን የዳዊት ሌላ ልጅ የአቤሴሎም ሙሉ እኅት በነበረችው በውቧ ግማሽ እህቱ በትዕማር እጅግ ተማረከ፡፡
\v 2 በእኅቱ በትዕማር ምክንያት እስኪታመም ድረስ አምኖን እጅግ ተጨነቀ፡፡ ድንግል ስለነበረች በእርሷ ላይ ምንም ነገር ማድረግ ለአምኖን የማይቻል መሰለው፡፡
\s5
\v 3 አምኖን ግን የዳዊት ወንድም የሳምዕ ልጅ ኢዮናዳብ የተባለ ወዳጅ ነበረው፡፡ ኢዮናዳብ እጅግ ተንኮለኛ ሰው ነበር፡፡
\v 4 ኢዮናዳብም ለአምኖን፣ “የንጉሥ ልጅ ሆይ፣ በየጥዋቱ ጭንቀት የሚሰማህ ለምንድን ነው? አትነግረኝምን?” ብሎ ጠየቀው፡፡ አምኖንም፣ “የወንድሜን የአቤሴሎምን እህት ትዕማርን አፍቅሬ ነው” ብሎ መለሰለት፡፡
\s5
\v 5 በዚህን ጊዜ ኢዮናዳብ፣ “የታመምህ መስለህ አልጋህ ላይ ተኛ፣ አባትህ ሊጠይቅህ ሲመጣም፣ ‘እህቴ ትዕማር የምበላውን ምግብ ታቀርብልኝ ዘንድ እባክህ ላክልኝ፤ ምግቡንም ዓይኔ እያየ ከእጇ እንድጎርስ እዚሁ መጥታ ታዘጋጅልኝ’ ብለህ ጠይቀው፡፡”
\v 6 ስለዚህ አምኖን የታመመ ሰው መስሎ ተኛ፤ ንጉሡም ሊጠይቀው በመጣ ጊዜ አምኖን ለንጉሡ፣ “ለሕመሜ የሚሆን ጥቂት ምግብ በፊቴ እንድታዘጋጅልኝና ከእጇም እንድበላ እባክህ እህቴን ትዕማርን ላክልኝ” ብሎ ጠየቀው፡፡
\s5
\v 7 ከዚያም ዳዊት፣ “አሁን ሂጂና ለወንድምሽ ለአምኖን ምግብ አዘጋጂለት” በማለት በቤተ መንግሥቱ ወደ ነበረችው ትዕማር መልእክት ላከባት፡፡
\v 8 ስለዚህም ትዕማር ወንድሟ አምኖን ወደተኛበት ቤት ሄደች፤ ጥቂት ሊጥ ወስዳ ካቦካችው በኋላ ቂጣ አደረገችው፣ ጋገረችውም፡፡
\v 9 ከዚያም መጋገሪያውን አውጥታ ቂጣውን አቀረበችለት፣ እርሱ ግን መብላት አልፈለገም፡፡ ስለዚህ አምኖን በዘያ ለነበሩት ለሌሎቹ፣ “ማንኛውንም ሰው ከዚህ ከእኔ ዘንድ አስወጡልኝ” አላቸው፤ ስለዚህ ሰው ሁሉ ከእርሱ ዘንድ ወጣ፡፡
\s5
\v 10 ከዚያም አምኖን ትዕማርን፣ “ምግቡን ከእጅሽ እበላ ዘንድ ወደዚህ ወደ ክፍሌ አምጭልኝ” አላት፡፡
\v 11 ምግቡን ባመጣችለት ጊዜ አምኖን እጇን ያዛትና፣ “እህቴ ሆይ፣ ነይ ከእኔ ጋር ተኚ” አላት፡፡
\v 12 እርሷም፣ “አይሆንም፣ ወንድሜ ሆይ፣ አታስገድደኝ፤ ይህን የመሰለ ነገር በእስራኤል ሊደረግ አይገባውምና፡፡ ይህን አሳፋሪ ነገር አታድርግ፡፡
\s5
\v 13 ይሄ ነገር ከሚያስከትልብኝ ዕፍረት ለማምለጥስ ወዴት መሄድ እችላለሁ? ይህም ድርጊት አንተን በመላው እስራኤል ኀፍረተ-ቢስ ጅል አድርጎ ያስቆጥርሃል፡፡ እባክህ፣ ለንጉሡ እንድትነግረው እጠይቅህሃለሁ፤ እንድታገባኝ ይፈቅድልሃል፡፡”
\v 14 ይሁን እንጂ አምኖን አልሰማትም፡፡ ከትዕማር ይልቅ ብርቱ ስለ ነበረ ይዟት ከእርሷ ጋር ተኛ፡፡
\s5
\v 15 ከዚያም አምኖን ትዕማርን ከመጠን በላይ ጠላት፤ አፍቅሯት ከነበረውም ይልቅ ጠላት፡፡ አምኖንም፣ “ተነሺ፣ ውጭልኝ” አላት፡፡
\v 16 እርሷ ግን፣ “አይሆንም፣ ምክንያቱም እኔን በማስወጣት የምታደርገው ይህ ክፉ ነገር ቀድመህ ካደረግኸው ይልቅ የከፋ ነው፡፡” አምኖን ግን እርሷን አልሰማትም፡፡
\v 17 ከዚያ ይልቅ የግል አገልጋዩን ጠርቶ፣ “ይህችን ሴት ከእኔ ዘንድ አስወጥተህ፣ በሩን ቀርቅረው” አለው፡፡
\s5
\v 18 ከዚህ በኋላ አገልጋዩ አስወጣትና በሩን ከበስተኋላዋ ቀረቀረባት፡፡ ድንግል የሆኑት የንጉሡ ሴት ልጆች እንደዚያ ይለብሱ ነበርና፣ ትዕማር በጣም ያጌጠ ቀሚስ ለብሳ ነበር፡፡
\v 19 ትዕማር በራሷ ላይ ማቅ ነሰነሰች፣ ቀሚሷንም ቀደደች፡፡ እጇንም በራሷ ላይ አድርጋ ሄደች፣ በምትሄድበትም ወቅት ድምፅዋን ከፍ አድርጋ አለቀሰች፡፡
\s5
\v 20 ወንድሟ አቤሴሎምም፣ “ወንድምሽ አምኖን ካንቺ ጋር ነበርን? ሆኖም፣ እህቴ ሆይ፣ አሁን ዝም በይ፡፡ ወንድምሽ ስለሆነ ነገሩን በልብሽ አትያዢው፡፡” ስለሆነም ትዕማር በወንድሟ በአቤሴሎም ቤት ብቸኛ ሆና ኖረች፡፡
\v 21 ነገር ግን ንጉሥ ዳዊት ይህንን ሁሉ በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ፤
\v 22 አቤሴሎም ለአምኖን ምንም አልተናገረውም፤ ስላደረገባት ነገር እህቱንም ትዕማርን ስላስነወራት ጠልቶት ነበርና፡፡
\s5
\v 23 ከሁለት ሙሉ ዓመት በኋላ አቤሴሎም በጎቹን በኤፍሬም አጠገብ በነበረው በቤላሶር ከተማ በጎችን የሚሸልቱ ሰዎች አስመጥቶ ነበር፤ አቤሴሎምም የንጉሡን ልጆች ወደዚያ ስፍራ ጋበዛቸው፡፡
\v 24 አቤሴሎም ወደ ንጉሡ ሄዶ፣ “እነሆ፣ ባሪያህ በጎችን የሚሸልቱ አስመጥቷል፣ንጉሡና አገልጋዮቹ እባክህን ከባሪያህ ጋር ይምጡ” አለው፡፡
\s5
\v 25 ንጉሡም ለአቤሴሎም፣ “ልጄ ሆይ፣ ሁላችንም መሄድ የለብንም፤ ሸክም እንሆንብሃለን” ብሎ መለሰለት፡፡ አቤሴሎም ንጉሡን አደፋፈረው፣ እርሱ ግን መሄድ ባይፈልግም አቤሴሎምን ባረከው፡፡
\v 26 ከዚህ በኋላ አቤሴሎም፣ “ይሄ ካልሆነ፣ እባክህ ወንድሜ አምኖን ከእኛ ጋር ይሂድ” አለው፡፡ ስለዚህ ንጉሡ አቤሴሎምን፣ “አምኖን አብሮአችሁ የሚሄደው ለምንድን ነው?” ብሎ ጠየቀው፡፡
\s5
\v 27 አቤሴሎም አጥብቆ ስለለመነው፣ አምኖንና የንጉሡ ልጆች አብረውት እንዲሄዱ ፈቀደ፡፡
\v 28 አቤሴሎም አገልጋዮቹን፣ “ልብ ብላችሁ አድምጡ፣ አምኖን ወይን ጠጅ ጠጥቶ መስከር ሲጀምርና እኔ ‘አምኖንን ምቱት’ ስላችሁ፣ በዚያን ጊዜ ግደሉት፤ አትፍሩ፡፡ ያዘዝኋችሁ እኔ ነኝና በርቱ፣ ጠንክሩ፡፡” ብሎ አዘዛቸው፡፡
\v 29 ስለዚህ የአቤሴሎም አገልጋዮች እንዳዘዛቸው በአምኖን ላይ አደረጉበት፡፡ ከዚያ በኋላም የንጉሡ ልጆች በየበቅሎአቸው ላይ ተቀምጠው ሸሹ፡፡
\s5
\v 30 እነርሱም እየሄዱ በመንገድ ላይ ሳሉ፣ “አቤሴሎም የንጉሡን ልጆች ሁሉ ገደለ፣ አንድም የተረፈ የለም” የሚል ዜና ለዳዊት ደረሰው፡፡
\v 31 ከዚያ በኋላ ንጉሡ ተነሥቶ ልብሱን ቀደደ፣ በወለሉም ላይ ተጋደመ፣ አገልጋዮቹም ልብሳቸውን ቀደው በአጠገቡ ቆሙ፡፡
\s5
\v 32 የዳዊት ወንድም የሳምዓ ልጅ ኢዮናዳብ ግን፣ “የሞተው አምኖን ብቻ ነውና የንጉሡ ልጆች የሆኑትን ጎልማሶች ሁሉ ገድለዋቸዋል ብሎ ጌታዬ አይመን፡፡ አምኖን እህቱን ትዕማርን ከደፈራት ቀን አንስቶ አቤሴሎም ይህንን ሲያቅድ ነበር፤
\v 33 ስለሆነም የሞተው አምኖን ብቻ ነውና፣ የንጉሡ ልጆች ሁሉ ሞተዋል ብሎ እስከሚያምን ድረስ ጌታዬ ንጉሡ የሚለውን ዜና ወደ ልቡ አያስገባው፡፡”
\s5
\v 34 አቤሴሎም ሸሸ፡፡ ለጥበቃ የቆመውም አገልጋይ ቀና ብሎ ሲመለከት ከእርሱ በስተምዕራብ ካለው ኮረብታ ጥግ ባለው መንገድ ብዙ ሰዎች ሲመጡ አየ፡፡
\v 35 በዚያን ጊዜ ኢዮናዳብ ለንጉሡ፣ “እነሆ፣ የንጉሡ ልጆች እየመጡ ነው፤ ልክ ባሪያህ እንዳለው ነው፡፡”
\v 36 ስለሆነም ተናግሮ እንደጨረሰ፣ የንጉሡ ልጆች ደረሱ፣ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው አለቀሱ፡፡ ንጉሡና አገልጋዮቹም ሁሉ አምርረው አለቀሱ፡፡
\s5
\v 37 አቤሴሎም ኮብልሎ የጌሹር ንጉሥ ወደ ሆነው ወደ ዓሚሁድ ልጅ ወደ ተልማይ ሄደ፡፡ ዳዊትም ስለ ሞተው ልጁ ዘወትር ያለቅስ ነበር፡፡
\v 38 አቤሴሎም ለሶስት ዓመታት ወደ ቆየበት ወደ ጌሹር ሸሽቶ ሄደ፡፡
\v 39 በልጁ በአምኖን ሞት ከደረሰበት ሐዘን ተጽናንቶ ስለነበረ ንጉሥ ዳዊት በሃሳቡ ወደ አቤሴሎም የመሄድ ናፍቆት አደረበት፡፡
\s5
\c 14
\p
\v 1 የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ የንጉሡ ልብ አቤሴሎምን እንደ ናፈቀ ተረዳ፡፡
\v 2 ስለዚህም ኢዮአብ ወደ ቴቁሔ ልኮ አንዲት ብልኅ የሆነች ሴት አስመጥቶ፣ “ሐዘንተኛ በመምሰል የሐዘን ልብስ ልበሺ፣ እባክሽን ዘይት አትቀቢ ነገር ግን ለብዙ ጊዜ እንዳዘነች መስለሽ ታዪ፡፡
\v 3 ከዚያም ወደ ንጉሡ ሄደሽ እኔ የምገልጽልሽን ንገሪው፡፡” ስለዚህ ኢዮአብ ለንጉሡ የምትናገረውን ነገር ነገራት፡፡
\s5
\v 4 ከቴቁሔ የመጣችውም ሴት ለንጉሡ ለመንገር በገባችበት ጊዜ በንጉሡ ፊት ለጥ ብላ እጅ በመንሣት፣ “ንጉሥ ሆይ፣ እርዳኝ” አለች፡፡
\v 5 ንጉሡም፣ “ችግርሽ ምንድን ነው?” አላት፡፡ ሴቲቱም፣ “እኔ በእውነቱ ባሏ የሞተባት ባልቴት ነኝ፡፡
\v 6 እኔ ባሪያህ ሁለት ልጆች ነበሩኝ፣ እነርሱም ሜዳ ላይ እርስ በርሳቸው ተጣሉ፣ የሚገላግላቸውም ሰው አልነበረም፡፡ አንደኛውም ሌላኛውን መታውና ገደለው፡፡
\s5
\v 7 መላው ቤተሰብም አሁን በባሪያህ ላይ ተነሥቶ፣’ስለገደለው ስለ ወንድሙ ዋጋ እንዲከፍልና እኛም እንድንገድለው ወንድሙን የገደለውን ሰው አውጥተሸ ስጪን’ አሉኝ፤ ወራሽ የሆነውንም ያጠፉ ዘንድ ይፈልጋሉ፡፡ በዚህም ዓይነት የቀረኝን አንድ የጋለ ፍም አጥፍተው፣ ባሌን በምድር ላይ ያለ ስምና ያለ ዘር ሊያስቀሩት ነው፡፡”
\s5
\v 8 ስለዚህ ንጉሡ ለሴቲቱ፣ “አንቺ ወደ ቤትሽ ሂጂ፣ አንድ ነገር እንዲደረግልሽ እኔ ትዕዛዝ እሰጣለሁ” አላት፡፡
\v 9 የቴቁሔዪቱም ሴት ለንጉሡ፣ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፣ በደሉ በእኔና በአባቴ ቤተሰብ ላይ ይሁን፤ ንጉሡና ዙፋኑ ከበደል የነጹ ይሁኑ” አለች፡፡
\s5
\v 10 ንጉሡም፣ “ማንም ሰው ቢናገርሽ ወደ እኔ ዘንድ አምጪው ከዚያ በኋላም አያስቸግርሽም” በማለት መለሰላት፡፡
\v 11 ከዚያ በኋላ ሴቲቱ፣ “ደም ተበቃዩ ሌላ ሰው እንዳያጠፋና ልጄንም እንዳያጠፉት፣ እባክህን ንጉሥ እግዚአብሔር አምላክህን አሳስብልኝ” አለችው፡፡ ንጉሡም፣ “ሕያው እግዚአብሔርን ከልጅሽ ራስ አንዲት ፀጉር እንኳ አትወድቅም” ብሎ መለሰላት፡፡
\s5
\v 12 ከዚያ በኋላም ሴቲቱ፣ “ባሪያህ ለጌታዬ ለንጉሡ ተጨማሪ ቃል እንድናገር እባክህ ፍቀድልኝ” አለችው፡፡ ንጉሡም፣ “ተናገሪ” አላት፡፡
\v 13 ስለዚህ ሴቲቱ፣ “ታዲያ፣ እንዲሀ ያለውን ነገር በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ያሰብኸው ለምንድን ነው? ምክንያቱም ይህንን በመናገሩ ንጉሡ ራሱን በደለኛ እንደሚያደርግ ሰው ነው፣ የኮበለለውን ልጁን ንጉሡ ወደ ቤቱ አልመለሰውምና፡፡
\v 14 ሁላችንም እንሞት ዘንድ ይገባናልና፣ እንደገናም ሊሰበሰብ እንደማይችል እንደ ፈሰሰ ውሃ ነንና፡፡ እግዚአብሔር ግን የሰውን ሕይወት አይወስድም ይልቁንም ከፊቱ ራሱን ያስኮበለለውን ሰው ወደ ራሱ የሚመልስበት መንገድ ይፈልጋል እንጂ፡፡
\s5
\v 15 እንግዲህ አሁን ለጌታዬ ለንገሡ ይህንን ልናገር የመጣሁት ሕዝቡ እንድፈራ ስላደረጉኝ ነው፡፡ ከዚህም የተነሣ ባሪያህ ለራሷ፣ ‘አሁን ለንጉሡ እናገራለሁ፣ ምናልባትም ንጉሡ የባሪያውን ጥያቄ ይቀበል ያደርግላት ይሆናል፡፡
\v 16 እኔንና ልጄን ከእግዚአብሔር ርስት ሊያጠፋን ካለው ሰው እጅ ያድን ዘንድ ባሪያውን ያወጣ ዘንድ ንጉሡ ይሰማኛልና፣’ አለች፡፡
\v 17 ከዚያ በኋላም ባሪያህ፣ ‘እግዚአብሔር ሆይ፣ የጌታዬ የንጉሡ ቃል እፎይታን የሚሰጠኝ ይሁን፣ ምክንያቱም መልካሙን ከክፉው በመለየት ጌታዬ ንጉሡ እንደ እግዚአብሔር መልአክ ነውና’ እግዚአብሔር አምላክህ ከአንተ ጋር ይሁን፡፡”
\s5
\v 18 ከዚያ በኋላም ንጉሡ ለሴቲቱ፣ “እኔ ለምጠይቅሽ ጥያቄ እባክሽ ምንም ነገር አትደብቂኝ” አላት፡፡
\v 19 ንጉሡም፣ “በዚህ ሁሉ የኢዮአብ እጅ ከአንቺ ጋር የለም?” ሴቲቱም፣ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፣ በሕያው ነፍስህ እምላለሁ፤ ጌታዬ ንጉሡ ከተናገረው አንዳችም ነገር ማንም ሰው ወደ ቀኝም ወደ ግራም ማምለጥ አይችልም፡፡ ያዘዘኝና ባሪያህም የተናገረችውን እነዚህን ነገሮች እንድናገር የነገረኝ ባሪያህ ኢዮአብ ነው፡፡
\v 20 ባሪያህ ኢዮአብ ይህንን ያደረገው ነገሮች እየሄዱበት ያለውን አቅጣጫ ለመለወጥ ነው፡፡ እንደ እግዚአብሔር መልአክ ጥበብ ጌታዬ ጠቢብ ነው፤ በምድሪቱም የሚሆነውን ማንኛውንም ነገር ያውቃል፡፡”
\s5
\v 21 ስለዚህ ንጉሡ ለኢዮአብ፣ “እነሆ፣ እኔ አሁን ይህንን አደርጋለሁ፡፡ እንግዲህ ሂድና ወጣቱን አቤሴሎምን አምጣው” አለው፡፡
\v 22 ስለዚህ ኢዮአብ ለንጉሡ አክብሮቱንና ምስጋናውን ለመግለጽ ጎንበስ ብሎ እጅ ነሳ፡፡ ኢዮአብም፣ “ዛሬ ባሪያህ በጌታዬ በንጉሡ ፊት ሞገስ እንዳገኘ አወቅሁ፣ ንጉሡ የባሪያውን ጥያቄ ፈጽሞለታልና”
\s5
\v 23 ስለዚህ ኢዮአብ ተነሥቶ ወደ ጌሹር ሄደ፣ አቤሴሎምንም ይዞ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ፡፡
\v 24 ንጉሡም፣ “ወደ ራሱ ቤት መመለስ ይችላል፣ ነገር ግን ፊቴን አያይም” ስለዚህ አቤሴሎም ወደ ቤቱ ተመለሰ፣ የንጉሡን ፊት ግን አላየም፡፡
\s5
\v 25 በመላው እስራኤል ከአቤሴሎም ይልቅ በመልከ መልካምነቱ የተመሰገነ ማንም አልነበረም፡፡ ከእግር ተረከዙ ጀምሮ እስከ አናቱ ድረስ ምንም እንከን አልነበረበትም፡፡
\v 26 ይከብደው ስለ ነበረ የራሱን ፀጉር በሚቆረጥበት ጊዜ ፀጉሩን ይመዝነው ነበር፣ በንጉሡም የመመዘኛ ልክ ሁለት መቶ ሰቅል ይመዝን ነበር፡፡
\v 27 አቤሴሎምም ሦስት ወንዶች ልጆችና ትዕማር የምትባል አንድ ሴት ልጅ ነበሩት፡፡ ሴት ልጁም ውብ ነበረች፡፡
\s5
\v 28 አቤሴሎምም የንጉሡን ፊት ሳያይ ሁለት ሙሉ ዓመት በኢየሩሳሌም ኖረ፡፡
\v 29 ከዚህ በኋላ ወደ ንጉሡ ይወስደው ዘንድ አቤሴሎም ወደ ኢዮአብ መልእክት ላከ፣ ኢዮአብ ግን ሊመጣ አልፈለገም፡፡ ስለዚህ አቤሴሎም ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ኢዮአብ መልእክት ላከ፣ ኢዮአብ ግን አሁንም አልመጣም፡፡
\s5
\v 30 ስለዚህ አቤሴሎም ለአገልጋዮቹ፣ “ኢዮአብ በእኔ እርሻ አጠገብ እርሻ አለው፣ በዚያም ገብስ አለው፤ ሂዱና በገብሱ ላይ እሳት ልቀቁበት” አላቸው፡፡ ስለዚህ የአቤሴሎም አገልጋዮች በእርሻው ላይ እሳት ለቀቁበት፡፡
\v 31 ከዚያም ኢዮአብ ተነስቶ ወደ አቤሴሎም ቤት መጣና፣ “አገልጋዮችህ በእርሻዬ ላይ እሳት የለቀቁበት ለምንድን ነው?” አለው፡፡
\s5
\v 32 አቤሴሎምም ለኢዮአብ፣ “እነሆ፣ ወደ አንተ ዘንድ፣ ‘ወደ ንጉሡ እልክህ ዘንድ ወደ እኔ ዘንድ መጥተህ ለንጉሡ፣ ከጌሹር ለምን መጣሁ? እዚያው ብቆይ ይሻለኝ ነበር’ ብለህ እንድትነግርልኝ መልእክት ልኬብህ ነበር፡፡ ስለዚህ አሁን የንጉሡን ፊት ልይ፣ በደለኛ ከሆንኩም ይግደለኝ” አለው፡፡
\v 33 ስለዚህ ኢዮአብ ወደ ንጉሡ ዘንድ ሄዶ ነገረው፡፡ ንጉሡም አቤሴሎምን ባስጠራው ጊዜ አቤሴሎም በንጉሡ ፊት ለጥ ብሎ እጅ ነሣ፣ ንጉሡም አቤሴሎምን ሳመው፡፡
\s5
\c 15
\p
\v 1 ከዚህ በኋላ አቤሴሎም ሠረገላና ፈረሶች እንዲሁም ፊት ፊቱ የሚሮጡ ሃምሳ ሰዎች ለራሱ አዘጋጀ፡፡
\v 2 አቤሴሎም በማለዳ ተነሥቶ ወደ ከተማይቱ መግቢያ በር በሚወስደው መንገድ ዳር ይቆማል፡፡ ሙግት ያለበት ማንኛውም ሰው ዳኝነት ለማግኘት ወደ ንጉሡ ሲመጣ፣ በዚያን ጊዜ አቤሴሎም ወደ እርሱ ይጠራውና፣ “ከየትኛው ከተማ ነው የመጣኸው?” ይለው ነበር፡፡ ሰውዬውም፣ “አገልጋይህ ከእስራኤል ነገዶች ከአንዱ ነው?” ይለው ነበር፡፡
\s5
\v 3 ከዚህም የተነሣ አቤሴሎም፣ “ተመልከት፣ ጉዳይህማ ትክክልና ተገቢም ነው፤ ነገር ግን ጉዳይህን ለመመልከት ከንጉሡ ሥልጣን የተሰጠው ማንም ሰው የለም፡፡” ይለው ነበር፡፡
\v 4 ከዚህ ጋር በማያያዝ አቤሴሎም፣ “ሙግት ወይም ጉዳይ ያለው ማንኛውም ሰው ወደ እኔ እንዲመጣና እኔም ፍትሕ እንድሰጠው በምድሪቱ ዳኛ ሆኜ መሾም እመኛለሁ” ይል ነበር፡፡
\s5
\v 5 ስለዚህ ክብርን ሊሰጠው ማንኛውም ሰው ወደ አቤሴሎም በሚመጣበት ጊዜ አቤሴሎም እጁን ዘርግቶ ይይዘውና ይስመው ነበር፡፡
\v 6 ከንጉሡ ፍትሕ ለማግኘት በሚመጡ እስራኤላውያን ሁሉ አቤሴሎም እንደዚህ ያደርግ ነበር፡፡ በዚህም ሁኔታ አቤሴሎም የእስራኤላውያንን ልብ ሰረቀ፡፡
\s5
\v 7 በአራተኛው ዓመት ፍጻሜ አቤሴሎም ለንጉሡ፣ “ለእግዚአብሔር የተሳልሁትን ስእለት ለማድረስ ወደ ኬብሮን እንድሄድ እባክህን ፍቀድልኝ፡፡
\v 8 ባሪያህ በአራም በጌሹር በነበርኩበት ጊዜ፣ ‘እግዚአብሔር በእርግጥ ወደ ኢየሩሳሌም ዳግመኛ የመለሰኝ እንደሆነ በኬብሮን እሰግዳለሁ’ ብዬ ተስዬ ነበር፡፡”
\s5
\v 9 ንጉሡም፣ “በሰላም ሂድ” አለው፤ ስለዚህ አቤሴሎም ወደ ኬብሮን ሄደ፡፡
\v 10 አቤሴሎም ግን ወደ መላው የእስራኤል ነገዶች፣ “የመለከትን ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ ‘አቤሴሎም በኬብሮን ነገሠ’ ማለት ይገባችኋል” የሚሉ ሰላዮችን ላከ፡፡
\s5
\v 11 ከአቤሴሎምም ጋር ሁለት መቶ የተጋበዙ ሰዎች ወደ ኢየሩሳሌም ሄዱ፡፡ አቤሴሎም ምን እንዳቀደ ምንም ነገር ሳያውቁ በየዋህነት ነበረ የሄዱት፡፡
\v 12 አቤሴሎም መሥዋዕት በሚያቀርብበት ጊዜ የዳዊት አማካሪ ለሆነው ለአኪጦፌል ወደሚኖርበት ወደ ጊሎ መልእክት ላከበት፡፡ አቤሴሎምን ይከተለው የነበረው ሕዝብ እየጨመረ ስለነበረ የአቤሴሎም ሤራ ጠንካራ ነበር፡፡
\s5
\v 13 “የእስራኤል ሰዎች ልብ አቤሴሎምን እየተከተለ ነው፡፡” የሚል መልእክተኛ ወደ ዳዊት መጣ፡፡
\v 14 ስለዚህ ዳዊት በኢየሩሳሌም ለነበሩት አገልጋዮቹ ሁሉ፣ “ተነሡ እንሽሽ፤ ያለበለዚያ አንዳችንም ከአቤሴሎም እጅ ማምለጥ አንችልም፤ አሁኑኑ ለመውጣት ተዘጋጁ አለዚያ እርሱ መጥቶ ይይዘናል በእኛም ላይ ጥፋት ያደርስብናል፣ ከተማይቱንም በሰይፍ ይመታታል፡፡” አላቸው፡፡
\v 15 የንጉሡም አገልጋዮች፣ “እነሆ፣ ጌታችን የወሰነውን ማንኛውንም ለማድረግ አገልጋዮችሀ ዝግጁ ነን” በማለት ለንጉሡ ነገሩት፡፡
\s5
\v 16 ንጉሡ ከእርሱም ጋር መላው ቤተሰቡ ሄዱ፣ ነገር ግን ቤተ መንግሥቱን ይጠብቁ ዘንድ ቁባቶች የነበሩ አሥር ሴቶችን እንዲቀሩ አደረገ፡፡
\v 17 ንጉሡና እርሱን ተከትሎ መላው ሕዝብ ከሄደ በኋላ ከመጨረሻው ቤተ ሲደርሱ ቆሙ፡፡
\v 18 ሠራዊቱ ሁሉ ከእርሱ ጋር ተጓዙ፣ ከሊታውያን፣ ፈሊታውያን እንዲሁም ከጌት አብረውት የመጡት ስድስት መቶ ጌታውያን በንጉሡ ፊት አለፉ፡፡
\s5
\v 19 ከዚያም ንጉሡ ጌታዊውን ኢታይን፣ “አንተ ደግሞ ከእኛ ጋር የመጣኸው ለምንድን ነው? እንግዳና ስደተኛ ነህና ተመልሰህ ሄደህ ከአቤሴሎም ጋር ቆይ፤ ወደ ራስህ አገር ሂድ፡፡
\v 20 የወጣኸው ገና ትላንት ስለሆነ፣ ከእኔ ጋር በየቦታው ለምን እንድትንከራተት ላድርግህ? ወዴት እንደምሄድ እንኳን አላውቅም፡፡ ስለዚህ ተመለስ የአገርህንም ሰዎች መልሳቸው፤ በጎነትና ታማኝነት ከአንተ ጋር ይሁን፡፡” አለው፡፡
\s5
\v 21 ኢታይ ግን ለንጉሡ፣ “ሕያው እግዚአብሔርን እንዲሁም በጌታዬ በንጉሡ እምላለሁ፤ ሕይወትም ይሁን ሞት ንጉሡ ወደሚሄድበት ወደየትኛውም ቦታ አገልጋይህም ይሄዳል፡፡” ብሎ መለሰለት፡፡
\v 22 ስለዚህ ዳዊት ለኢታይ፣ “እንግዲያውስ፣ ከእኛ ጋር መሄድህን ቀጥል” አለው፡፡ ከእርሱ ጋር ከነበሩት ሰዎች ሁሉና አብረውት ከነበሩት ቤተሰቦቹ ሁሉ ጋር ጌታዊው ኢታይ ከንጉሡ ጋር ተጓዘ፡፡
\v 23 ሕዝቡ ሁሉ ንጉሡም ራሱ የቄድሮንን ወንዝ ሲሻገሩ የአገሩ ሕዝብ ድምፁን ከፍ አድርጎ አለቀሰ፡፡ ሕዝቡ ሁሉ ወደ ምድረ-በዳ በሚወስደው መንገድ ተጓዘ፡፡
\s5
\v 24 ሳዶቅም እንኳን የእግዚአብሔርን የኪዳን ታቦት ከተሸከሙት ሌዋውያን ጋር በዚያ ነበር፡፡ የእግዚአብሔርን ታቦት አስቀመጡትና አብያታር ከእነርሱ ጋር ሆነ፤ እነርሱም ሕዝቡ ሁሉ ከከተማይቱ እስኪወጡ ድረስ ጠበቁ፡፡
\v 25 ንጉሡም ሳዶቅን፣ “ታቦቱን ወደ ከተማይቱ ይዘህ ተመለስ፣ በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ ካገኘሁ ወደዚህ መልሶ ያመጣኛል፣ ታቦቱንና እርሱም የሚኖርበትን ስፍራ እንደገና ያሳየኛል፡፡
\v 26 ነገር ግን እርሱ፣ ‘በአንተ አልተደሰትሁም’ ካለኝ፣ እነሆ፣ በፊቱ አለሁ፣ መልካም መስሎ የታየውን ያድርግብኝ፡፡”
\s5
\v 27 ንጉሡ ለካህኑ ለሳዶቅ፣ “አንተ ነቢይ አይደለህምን? አንተ ከሁለቱ ልጆችህ፣ ከልጅህ አኪማአስና ከአብያታር ልጅ ከዮናታን ጋር ሆናችሁ በሰላም ወደ ከተማይቱ ተመለሱ፡፡
\v 28 ከአንተ ዘንድ መልእክት እስካገኝ ድረስ፣ እነሆ፣ እኔ በአረባ በሚገኘው በወንዙ መሻገሪያ እቆያለሁ፡፡”
\v 29 ስለዚህ ሳዶቅና አብያታር የእግዚአብሔርን ታቦት ይዘው ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሰው እዚያው ቆዩ፡፡
\s5
\v 30 ዳዊት ግን እያለቀሰ በባዶ እግሩ የደብረ ዘይትን ተራራ ሽቅብ ወጣ፣ ራሱንም ተከናንቦ ነበር፡፡ ከእርሱ ጋር የነበረውም እያንዳንዱ ሰው ራሱን ተከናንቦ ነበር፤ እየሄዱም ሳሉ ያለቅሱ ነበር፡፡
\v 31 አንድ ሰውም ለዳዊት፣ “በሤራው ውስጥ ከአቤሴሎም ጋር ካሉት አንደኛው አኪጦፌል ነው” ብሎ ነገረው፡፡ ስለዚህ ዳዊት፣ “እባክህ፣ እግዚአብሔር ሆይ፣ የአኪጦፌልን ምክር ወደ ሞኝነት ለውጠው” ብሎ ጸለየ፡፡
\s5
\v 32 ዳዊት እግዚአብሔር ወደሚመለክበት ወደ መንገዱ ጫፍ በደረሰ ጊዜ፣ አርካዊው ኩሲ መጎናጸፊያውን ቀድዶ ትቢያ በራሱ ላይ ነስንሶ ሊገናኘው መጣ፡፡
\v 33 ዳዊትም ለእርሱ፣ “አብረኸኝ ብትሄድ ሸክም ትህንብኛለህ፤
\v 34 ነገር ግን ወደ ከተማይቱ ተመልሰህ አቤሴሎምን ‘ንጉሥ ሆይ፣ አገልጋይህ እሆናለሁ፣ ቀድሞ የአባትህ አገልጋይ እንደ ነበርሁ ሁሉ አሁን ደግሞ የአንተ አገልጋይ እሆናለሁ’ ብትለው የአኪጦፌልን ምክር በማደናገር ትረዳኛለህ፡፡
\s5
\v 35 ካህናቱ ሳዶቅና አብያታር እዚያው ከአንተ ጋር አሉልህ አይደለምን? በንጉሡ ቤተ መንግሥት የምትሰማውን ማንኛውንም ነገር ለካህናቱ ለሳዶቅና ለአብያታር መንገር አለብህ፡፡
\v 36 የሳዶቅ ልጅ አኪማአስና የአብያታር ልጅ ዮናታን ሁለቱ ወንዶች ልጆች በዚያ አብረዋቸው መሆናቸውን አረጋግጥ፡፡ የምትሰማውን ማንኛውንም ነገር በእነርሱ በኩል ላክልኝ፡፡”
\v 37 ስለዚህ የዳዊት ወዳጅ ኩሲ አቤሴሎም ኢየሩሳሌም በገባበት በዚያው ወቅት ወደ ከተማይቱ መጣ፡፡
\s5
\c 16
\p
\v 1 ዳዊት ከተራራው ጫፍ ባሻገር ጥቂት እልፍ ብሎ እንደሄደ ሲባ የተባለው የሜምፊቦስቴ አገልጋይ፣ ሁለት መቶ እንጀራ አንድ ሙሉ ጥፍጥፍ ዘቢብ አንድ መቶ ጥፍጥፍ በለስና አንድ አቁማዳ የወይን ጠጅ የተጫኑ ሁለት አህዮች ይዞ ተገናኘው፡፡
\v 2 ንጉሡም ሲባን፣ “ይህን ሁሉ ያመጣኸው ለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው፡፡ ሲባም፣ “አህዮቹን የንጉሡ ቤተ ሰቦች እንዲቀመጡባቸው፣ እንጀራውንና በለሱን ከአንተ ጋር ያሉት ሰዎች እንዲበሉት፣ የወይን ጠጁ ደግሞ በምድረ-በዳ የደከመ ማንኛውም ሰው እንዲጠጣው ነው” አለው፡፡
\s5
\v 3 ንጉሡም፣ “የጌታህ የልጅ ልጅ የት ነው?” አለው፡፡ ሲባም ለንጉሡ፣ “’ዛሬ የእስራኤል ቤት የአባቴን መንግሥት ለእኔ ይመልስልኛል’ እያለ ስለነበረ፣ እነሆ፣ በኢየሩሳሌም ተቀምጦአል” ብሎ መለሰለት፡፡
\v 4 ከዚያም ንጉሡ ሲባን፣ “የሜምፊቦስቴ የነበረው ሁሉ ከእንግዲህ፣ እነሆ፣ የአንተ ሆኖአል” አለው፡፡ ሲባም፣ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ በትሕትና በፊትህ እጅ እነሣለሁ፣ በፊትህ ሞገስ ላግኝ” አለው፡፡
\s5
\v 5 ንጉሥ ዳዊት ወደ ብራቂም ሲደርስ ከሳዖል ቤተሰብ ነገድ የሆነ የጌራ ልጅ ሳሚ ብቅ አለ፡ እርሱም እየመጣ ሳለ ይራገም ነበር፡፡
\v 6 የንጉሡ ወታደሮችና የክብር ዘቦቹ ሁሉ በዳዊትና ግራና ቀኝ ቢኖሩም እንኳን፣ በዳዊትና በሹማምንቱ ላይ ድንጋይ ይወረውርባቸው ነበር፡፡
\s5
\v 7 ሳሚም እንደዚህ ብሎ ተራገመ፣ “ውጣ፣ ከዚህ ውጣ፣ አንተ ወሮበላ፣ አንተ የደም ሰው፤
\v 8 በእርሱ ምትክ የነገሥህበትን የሳዖልን ቤተሰብ ደም ብድራት ሁሉ እግዚአብሔር እየከፈለህ ነው፡፡ እግዚአብሔር መንግሥቱን በልጅህ በአቤሴሎም እጅ አሳልፎ ሰጥቷል፡፡ አሁንም አንተ የደም ሰው ስለሆንክ ጥፋት ደርሶብሃል፡፡”
\s5
\v 9 ከዚህ በኋላ የጽሩይ ልጅ አቢሳ፣ “ይህ የሞተ ውሻ ንጉሡ ጌታዬን ለምን ይራገማል? እባክህ፣ ተሻግሬ ልሂድና ራሱን ልቁረጠው” አለ፡፡
\v 10 ንጉሡ ግን፣ “እናንተ የጽሩያ ልጆች፣ እኔ ከእናንተ ጋር ምን አለኝ? እርሱ የሚረግመኝ ምናልባት እግዚአብሔር፣ ‘ዳዊትን ርገመው’ ብሎት ይሆናል፡፡ ታዲያ እርሱን፣ ‘ንጉሡን ለምን ትረግማለህ? ሊለው የሚችለው ማን ነው?”
\s5
\v 11 ስለዚህ ዳዊት ለአቢሳና ለአገልጋዮቹ ሁሉ፣ “ከአብራኬ የወጣው ልጄ ነፍሴን ሊያጠፋት ከፈለገ፣ ይህ ብንያማዊ ምን ያህል ጥፋቴን አይፈልግ? እግዚአብሔር እንዲራገም አዞት ይሆናልና፣ ተዉት፣ ይራገም፡፡
\v 12 ምናልባት የተሰነዘረብኝን ውርደት እግዚአብሔር ተመልክቶ ስለ ዛሬው እርግማኑ በጎ ያደርግልኝ ይሆናል፡፡”
\s5
\v 13 ስለዚህም ዳዊትና ሰዎቹ በመንገዱ ጉዟቸውን ቀጠሉ፣ ሳሚም በኮረብታው ጥግ ጥግ እየሄደ ድንጋይ ይወረውር አቧራም ይበትንበት ነበር፡፡
\v 14 ከዚህ በኋላ ንጉሡና ከእርሱ ጋር የነበሩት የእስራኤል ሰዎች ደከሙ፣ እነርሱም ለምሽቱ በሚቆሙበት ጊዜ እርሱ ዕረፍቱ አደረገ፡፡
\s5
\v 15 አቤሴሎምና ከእነርሱ ጋር የነበሩት የእስራኤል ሰዎች ሁሉ በበኩላቸው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፣ አኪጦፌልም ከእርሱ ጋር ነበረ፡፡
\v 16 የዳዊት ወዳጅ፣ አርካዊው ኩሲም ወደ አቤሴሎም በመጣ ጊዜ፣ “ንጉሥ ሆይ፣ ለዘላለም ንገሥ! ንጉሥ ሆይ፣ ለዘላለም ንገሥ!” አለው፡፡
\s5
\v 17 አቤሴሎምም ኩሲን፣ “ለወዳጅህ ያለህ ታማኝነት ይሄ ነው? ለምን ከእርሱ ጋር አልሄድህም?” አለው፡፡
\v 18 ኩሲም አቤሴሎምን፣ “አይሆንም፣ ይልቁኑ እግዚአብሔርና ይህ ሕዝብ እንዲሁም የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ከመረጡት ከእርሱ ጋር ነው እኔ የምሆነው፣ ከእርሱም ጋር እቆያለሁ፡፡
\s5
\v 19 ላገለግለው የሚገባኝ ሰው ማን ነው? በልጁስ ፊት ላገለግል አይገባኝምን? በአባትህ ፊት እንዳገለገልሁ በአንተም ፊት አገለግላለሁ፡፡”
\s5
\v 20 ከዚያ በኋላ አቤሴሎም ለአኪጦፌል፣ “ምን ማድረግ እንደሚገባን ምክርህን ስጠን” አለው፡፡
\v 21 አኪጦፌልም ለአቤሴሎም፣ “ቤተ መንግሥቱን እንዲጠብቁ አባትህ ከተዋቸው ቁባቶቹ ጋር ግባና ተኛ፣ ከዚያም አንተ ለአባትህ መጥፎ ጠረን እንዳለው ሰው እንደሆንክበት እስራኤል ሁሉ ይሰማል፤ ከዚያም ከአንተ ጋር ያሉት ሰዎች ሁሉ እጅ ይበረታል፡፡”
\s5
\v 22 ስለዚህ በቤተ መንግሥቱ ሰገነት ላይ ለአቤሴሎም ድንኳን ተከሉለት፤ አቤሴሎምም መላው እስራኤል እያየው ከአባቱ ቁባቶች ጋር ተኛ፡፡
\v 23 በዚያን ጊዜ አኪጦፌል ይሰጠው የነበረው ምክር ከእግዚአብሔር ከራሱ አፍ እንደ መስማት ያለ ነበር፡፡ ዳዊትም ሆነ አቤሴሎም ለአኪጦፌል ምክር የነበራቸው ግምት እንደዚህ ነበር፡፡
\s5
\c 17
\p
\v 1 ከዚህ በኋላ አኪጦፌል ለአቤሴሎም፣ “አሥራ ሁለት ሺህ ሰው መርጬ በዛሬይቱ ሌሊት አባትህን አሳድደዋለሁ፤
\v 2 በደከመውና ዐቅም ባነሰው ጊዜ ድንገት ደርሼ በማስፈራት አስደንቀዋለሁ፤ አብሮት ያለው ሕዝብም ይሸሻል፣ በንጉሡ ላይ ብቻ ጥቃት አደርስበታለሁ፡፡
\v 3 ሙሽራ ወደ ባሏ እንደምትመጣ ሕዝቡን ሁሉ ወደ አንተ እመልሳለሁ፤ ሕዝቡም ሁሉ በአንተ ሥር በሰላም ይሆናል፡፡”
\v 4 አኪጦፌል የተናገረውም አቤሴሎምንና የእስራኤልን ሽማግሌዎች ሁሉ ደስ አሰኛቸው፡፡
\s5
\v 5 ከዚያ በኋላ አቤሴሎም፣ “አርካዊውን ኩሲን አሁን ጥሩትና እስቲ፣ እርሱ ደግሞ የሚለውን እንስማ” አለ፡፡
\v 6 ኩሲ ወደ አቤሴሎም በመጣ ጊዜ፣ አኪጦፌል ያለውን ከገለጸለት በኋላ፣ ኩሲን፣ “አኪጦፌል ያለውን እናድርግ? ካልሆነም የምትመክረንን አንተ ንገረን፡፡”
\v 7 ስለዚህ ኩሱ ለአቤሴሎም፣ “አኪጠፌል በዚህን ጊዜ የሰጠው ምክር መልካም አይደለም፡፡” ካለ በኋላ፣
\s5
\v 8 ኩሲ በመቀጠል፣ “አባትህና ሰዎቹ ብርቱ ተዋጊዎችና ግልገሎቿ በሜዳ እንደተነጠቁባት ድብ መራሮች እንደሆኑ አንተ ታውቃለህ፡፡ አባትህ የጦር ሰው ነው፣ በዛሬው ሌሊት ከሠራዊቱ ጋር አይተኛም፡፡
\v 9 እነሆ፣ አሁን እንኳ በአንዱ ዋሻ ወይም በሌላ ቦታ ተደብቆ ይሆናል፡፡ በውጊያው መጀመሪያ ላይ ከአንተ ሰዎች ጥቂቶቹ ቢሞቱ፣ ያንን የሰማ ማንኛውም ሰው፣ ‘አቤሴሎምን ይከተሉ በነበሩት ላይ እልቂት ተፈጽሟል’ ይላል፡፡
\v 10 ከዚያ በኋላ አባትህ ኃያል ሰው ስለሆነና ከእርሱም ጋር ያሉት በጣም ብርቱዎች መሆናቸውን መላው እስራኤል ስለሚያውቅ ልባቸው እንደ አንበሳ ልብ የሆነው እጅግ ጀግና የሆኑት እንኳን ይፈራሉ፡፡
\s5
\v 11 ስለዚህ እኔ የምመክርህ በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ ብዙ የሆነው ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ያለው መላው የእስራኤል ሕዝብ ወደ አንተ ይሰብሰብ፣ አንተም በግልህ ወደ ጦርነቱ ግባ፡፡
\v 12 ከዚያ በኋላ እርሱ በየትኛውም ቦታ ቢሆን እንመጣበታለን፣ ጤዛም ምድርን እንደሚሸፍን በላዩ ላይ እንወድቅበታለን፡፡ ከእርሱ ማንኛውንም ሰው ወይም እርሱን ራሱንም እንኳን ቢሆን በሕይወት አንተውም፡፡
\s5
\v 13 ወደ አንዲት ከተማ የሚያፈገፍግ እንኳ ቢሆን፣ እስራኤል ሁሉ ገመድ አምጥቶ አንድ እንኳ እስከማይቀር ድረስ ከተማይቱን ወደ ወንዝ ውስጥ ስበን እንከታታለን፡፡”
\v 14 ከዚያም አቤሴሎምና የእስራኤል ሽማግሌዎች ሁሉ፣ “የአርካዊው ኩሲ ምክር ከአኪጦፌል ምክር ይልቅ የተሻለች ነች” አሉ፡፡ በአቤሴሎም ላይ ጥፋት ይመጣ ዘንድ እግዚአብሔር የአኪጦፌል መልካም ምክር ተቀባይነት እንዳያገኝ አደረገ፡፡
\s5
\v 15 ከዚያም ኩሲ ለካህናቱ ለሳዶቅና ለአብያታር፣ “አኪጦፌል አቤሴሎምንና የእስራኤልን ሽማግሌዎች ምን ምን ማድረግ እንዳለባቸው መክሮአቸው ነበር፣ እኔ ግን የተለየ ምክር ሰጠኋቸው፡፡
\v 16 እንግዲህ እናንተ ፈጥናችሁ ወደ ዳዊት ዘንድ ሂዱና ፣ ‘በአረባ ባለው የወንዙ መሻገሪያ እንዳታድር፣ ነገር ግን እንደ ምንም ብለህ ተሻገር፤ አለበለዚያ ንጉሡና አብሮት ያለው ሕዝብ በሙሉ ትዋጣላችሁ’ በሉት፡፡”
\s5
\v 17 በዚህ ጊዜ፣ ዮናታንና አኪማአስ በዓይንሮጌል ባለችው ምንጭ ይጠብቁ ነበር፣ ወደ ከተማ ሲገቡ እንዳይታዩ አንዲት ሴት አገልጋይ ወደ እነርሱ እየሄደች መልእከቶችን ታቀብላቸው ነበር፤ እነርሱም በዚያን ጊዜ ለዳዊት ሄደው ይነግሩት ነበር፡፡
\v 18 በዚህን ጊዜ ግን አንድ ወጣት አያቸውና ለአቤሴሎም ሄዶ ነገረ፡፡ ስለዚህ ዮናታንና አኪማአስ ፈጥነው በግቢው ውስጥ የውሃ ጉድጓድ ወደነበረው በብራቂም ወደ ነበረ ሰው ቤት መጡ፡፡
\s5
\v 19 የሰውዬው ሚስት የውሃ ጉድጓዱን መሸፈኛ ወስዳ በጉድጓዱ አፍ ላይ ዘረጋችው ከዚያ በኋላም ዮናታንና አኪማአስ በውሃ ጉድጓድ ዘንድ እንዳሉ ማንም እንዳያውቅ በላዩ ላይ እህል አሰጣችበት፡፡
\v 20 የአቤሴሎም ሰዎች በቤት ወደነበረችው ሴትዮ መጡና፣ “አኪማአስና ዮናታን ወዴት አሉ?” አሏት፤ እርሷም፣ “ወንዙን ተሻግረው ሄደዋል” አለቻቸው፡፡ ስለዚህ ፈልገው ሊያገኟቸው ስላልቻሉ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፡፡
\s5
\v 21 እነርሱ ከሄዱ በኋላ አኪማአስና ዮናታን ከጉድጓዱ ወጡ፤ ወደ ዳዊትም ዘንድ ሄደው፣ “ተነሣና ፈጥነህ ወንዙን ተሻገር፣ ምክንያቱም አኪጦፌል አንተን በሚመለከት እንደዚህና እንደዚያ ብሎ ምክር ሰጥቶአል፡፡”
\v 22 ከዚያ በኋላ ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበረው ሕዝብ ተነሡ፣ የዮርዳኖስንም ወንዝ ተሻግረው ሄዱ፤ ሲነጋም ዮርዳኖስን መሻገር አቅቶት የቀረ አንድም ሰው አልነበረም፡፡
\s5
\v 23 አኪጦፌልም ምክሩን እንዳልተቀበሉት ባየ ጊዜ አህያውን ጭኖ ቤቱ ወዳለበት ወደ መኖሪያ ከተማው ሄደ፣ ጉዳዩንም መልክ ካስያዘ በኋላ በገዛ እጁ ታንቆ ሞተ፡፡ በዚህ አኳኋን ሞተና በአባቱ መቃብር ተቀበረ፡፡
\s5
\v 24 ከዚያ በኋላ ዳዊት ወደ መሃናይም መጣ፤ አቤሴሎምም ከእርሱ ጋር ከነበሩት ከመላው የእስራኤል ሰዎች ጋር ዮርዳኖስን ተሻገረ፡፡
\v 25 ከዚህ በኋላም አቤሴሎም በኢዮአብ ምትክ አሜሳይን በሠራዊቱ ላይ ሾመ፤ አሜሳይ የእስራኤላዊው የዮቴር ልጅ ነበር፡፡ ዮቴር ከኢዮአብ እናት ከጽሩያ እህት ከናዖስ ልጅ ከአቢግያ ጋር ተኝቶ የነበረ ነው፡፡
\v 26 ከዚህ በኋላ እስራኤላውያንና አቤሴሎም ከበገለዓድ ምድር ሰፈሩ፡፡
\s5
\v 27 ዳዊት ወደ መሃናይም በመጣ ጊዜ ከአሞናውያን ከተማ ከራባ የመጣው፣ የናዖስ ልጅ ሾቢ፣ ከሎዶባር የመጣው የዓሚኤል ልጅ ማኪርና ከሮግሊም የመጣው ገለዓዳዊው ቤርዜሊ፣
\v 28 መተኛ ምንጣፎችና ብርድ ልብሶች፣ ጎድጓዳ ሳህኖችና ድስቶች እንዲሁም ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሰዎች ይበሉ ዘንድ ስንዴ፣ የገብስ ዱቄት፣ የተጠበሰ እሸት፣ ባቄላ፣ ምስር፣
\v 29 ማር፣ ቅቤ፣ በግና እርጎ አመጡ፡፡ እነዚህ ሰዎች፣ “ሕዝቡ በምድረ-በዳ ተርቦአል፣ ደክሞአል ደግሞም ተጠምቶአል” ብለው ነበር፡፡
\s5
\c 18
\p
\v 1 ዳዊት አብሮት የነበሩትን ወታደሮች ቆጠረ፤ በእነርሱም ላይ የሻለቆችንና የመቶ አለቆችን ሾመላቸው፡፡
\v 2 ከዚህ በኋላ ዳዊት ሠራዊቱን ሲሦውን በኢዮአብ፣ ሲሦውን በኢዮአብ ወንድም በጽሩይ ልጅ በአቢሳ፣ ሲሦውን ደግሞ በጌታዊው በኢታይ አዛዥነት ሥር ላካቸው፡፡ ንጉሡም ለሠራዊቱ፣ “እኔ ራሴም አብሬአችሁ በእርግጥ እወጣለሁ” አላቸው፡፡
\s5
\v 3 ሰዎቹ ግን፣ “አንተ መውጣት የለብህም፤ እንድንሸሽ ብንገደድ፣ ሰዎቹ ስለ እኛ ግድ አይኖራቸውም ወይም ከእኛ ግማሻችን እንኳን ብንሞት ደንታም የላቸውም፡፡ አንተ ግን ከእኛ አሥር ሺሁ ያህል ነህ፤ ስለዚህ በከተማ ሆነህ ልትረዳን ዝግጁ ብትሆን የተሻለ ነው፡፡” አሉት፡፡
\v 4 ስለዚህ ንጉሡ፣ “መልካም መስሎ የታያችሁን ሁሉ አደርጋለሁ” አላቸው፡፡ ስለዚህ ሠራዊቱ ሁሉ በመቶና በሺህ እየሆነ ተሰልፎ ሲወጣ ንጉሡ በከተማይቱ ቅጥር በር ቆሞ ነበር፡፡
\s5
\v 5 ንጉሡ ኢዮአብን፣ አቢሳንና ኢታይን፣ “ለእኔ ስትሉ ለወጣቱ ለአቤሴሎም ራሩለት” ብሎ አዘዛቸው፡፡ ሕዝቡ ሁሉ አቤሴሎምን በሚመለከት ንጉሡ ይህንን ትዕዛዝ ለአዛዦቹ ሲሰጣቸው ሰሙ፡፡
\s5
\v 6 ስለዚህ እስራኤልን ይወጋ ዘንድ ሠራዊቱ ከከተማ ወጣ፤ ውጊያውም እስከ ኤፍሬም ደን ተስፋፋ፡፡
\v 7 በዚያ የእስራኤል ሠራዊት በዳዊት ወታደሮች ድል ሆነ፤ በዚያ ሃያ ሺህ ሰው የሞተበት ታላቅ እልቂት በዚያ ቀን ነበረ፡፡
\v 8 ውጊያው በገጠሩ ሁሉ ተስፋፋ፣ በሰይፍ ካለቀውም ይልቅ ጫካ ውጦ ያስቀረበው ሰው በለጠ፡፡
\s5
\v 9 አቤሴሎም ከዳዊት ሰዎች ከጥቂቶቹ ጋር ተገናኘ፡፡ አቤሴሎምም በበቅሎው እየጋለበ ነበር፤ በቅሎውም ጥቅጥቅ ያሉ ቅርንጫፎች በነበሩት የወርካ ዛፍ ሥር ያልፍ ነበርና ራሱ በዛፉ ቅርንጫፎች ተያዘ፡፡ የተቀመጠበት በቅሎ ከሥሩ አልፎ ሲሄድ እርሱ በሰማይና በምድር ተንጠልጥሎ ቀረ፡፡
\v 10 አንድ ሰው ይህንን ተመልክቶ፣ “እነሆ፣ አቤሴሎም በወርካ ዛፍ ላይ ተንጥልጥሎ አየሁት” ብሎ ለኢዮአብ ነገረው፡፡
\v 11 ኢዮአብም ስለ አቤሴሎም ለነገረው ሰው፣ “እነሆ፣ አንተ አየኸው፣ ታዲያ መትተህ ለምን ወደ መሬት አልጣልከውም? እኔ አሥር የብር ሰቅልና ቀበቶ በሸለምኩህ ነበር፡፡”
\s5
\v 12 ሰውዬውም ለኢዮአብ፣ “አሥር ሺህ ሰቅል የምቀበል ብሆንም እንኳን እጄን ዘርግቼ የንጉሡን ልጅ ባልነካሁም ነበር፤ ምክንያቱም አንተን፣ አቢሳንና ኢታይን ንጉሡ፣ ‘አንድም ሰው ወጣቱን አቤሴሎምን እንዳይነካው’ ብሎ ሲያዛችሁ ሁላችንም ሰምተናል፡፡
\v 13 ውሸት በመናገር ሕይወቴን አደጋ ላይ ብጥል እንኳን (ከንጉሡ የሚደበቅ ምንም ነገር አይኖርምና) አንተ ታጋልጠኝ ነበር፡፡” አለው፡፡
\s5
\v 14 ከዚህ በኋላ ኢዮአብ፣ “እኔ አንተን አልጠብቅም” አለ፡፡ ስለዚህ ኢዮአብ ሦስት ጦር ወስዶ ገና በሕይወት እያለና በወርካው ዛፍ ላይ ተንጠልጥሎ ሳለ በአቤሴሎም ልብ ላይ ተከላቸው፡፡
\v 15 ከዚያ በኋላም ከኢዮአብ ጋሻ ጃግሬዎች አሥሩ አቤሴሎምን በመክበብ ወግተው ገደሉት፡፡
\s5
\v 16 ከዚያም ኢዮአብ ቀንደ-መለከቱን ነፋ፣ ኢዮአብም ከልክሏቸው ስለነበረ ሠራዊቱ እስራኤልን ከማሳደድ ተመለሰ፡፡
\v 17 አቤሴሎምን ወስደው በጫካ ውስጥ ወደነበረ አንድ ትልቅ ጉድጓድ ውስጥ ጣሉት፤ እስራኤልም ሁሉ እያንዳንዱ ሰው ወደ ቤቱ በሚሸሽበት ጊዜ በአስከሬኑ ላይ ታላቅ የድንጋይ ክምር ከመሩበት፡፡
\s5
\v 18 አቤሴሎም፣ “የስሜን መታሰቢያ የሚያስጠራ ልጅ የለኝምና” በማለት ገና በሕይወቱ ሳለ ለራሱ አንድ ትልቅ የድንጋይ ሐውልት በንጉሡ ሸለቆ አቁሞ ነበር፡፡ ሐውልቱንም በስሙ ጠርቶት ስለነበረ፣ እስከዚህ ቀን ድረስ ‘የአቤሴሎም ሐውልት’ ተብሎ ይጠራል፡፡
\s5
\v 19 በዚህ ጊዜ የሳዶቅ ልጅ አኪማአስ እግዚአብሔር ከጠላቶቹ እንዳዳነው ሄጄ ለንጉሡ የምሥራች ልንገረው አለ፡፡
\v 20 ኢዮአብም፣ “ዛሬ የምሥራቹን የምታደርስለት አንተ አይደለህም፣ ሌላ ጊዜ ታደርስለታለህ፤ የንጉሡ ልጅ ስለሞተ ምንም የምሥራች አታደርስም፡፡”
\s5
\v 21 ከዚያም ኢዮአብ ለአንድ ኩሻዊ፣ “ሂድና ለንጉሡ ያየኸውን ተናገር” አለው፡፡ ኩሻዊውም ኢዮአብን እጅ ነሥቶ እየሮጠ ሄደ፡፡
\v 22 የሳዶቅ ልጅ አኪማአስም እንደገና ለኢዮአብ፣ “ምንም ዓይነት ነገር ይሁን፣ እባክህ፣ ኩሻዊውን ተከትዬው ልሩጥ” አለው፡፡ ኢዮአብም፣ “ለየምሥራቹ ምንም ብድራት እንደማታገኝ እያወቅህ፣ ልጄ ሆይ፣ ለምን ትሮጣለህ?” ብሎ መለሰለት፡፡
\v 23 “የሆነው ይሁን፣ እሮጣለሁ” አለ፣ አኪማአስ፡፡ ስለዚህ ኢዮአብ ፣ “እንግዲያውስ፣ ሩጥ” ብሎ መለሰለት፡፡ ከዚያም አኪማአስ በሜዳው መንገድ በኩል ሮጠ፣ ኩሻዊውንም ቀደመው፡፡
\s5
\v 24 ዳዊት በውስጠኛውና በውጭኛው በሮች መካከል ተቀምጦ ነበር፡፡ ጠባቂው ቅጥሩ ላይ ወዳለው ወደ በሩ ሰገነት ጣራ ወጥቶ ወደ ውጭ ዓይኑን አንስቶ ሲመለከት አንድ ብቻውን የሚሮጥ ሰው እየተቃረበ ነበር፡፡
\v 25 ጠባቂው ተጣራና ለንጉሡ ነገረው፤ ከዚያም ንጉሡ፣ “ብቻውን ከሆነ መልካም ዜና በአንደበቱ አለ” አለ፡፡ ሯጩ እየተጠጋ መጥቶ ወደ ከተማይቱ ቀረበ፡፡
\s5
\v 26 ከዚያም ጠባቂው ሌላ የሚሮጥ ሰው አስተዋለ፤ ጠባቂውም ዘበኛውን ጠራና፣ “እነሆ፣ ብቻውን የሚሮጥ ሌላ ሰው አለ” አለው፡፡ ንጉሡም፣ “እርሱም መልካም ዜና አለው” አለ፡፡
\v 27 ስለዚህ ጠባቂው፣ “ከፊት እየሮጠ ያለው ሰው አሯሯጥ የሳዶቅን ልጅ የአኪማአስን ሩጫ ይመስለኛል” አለ፡፡ ንጉሡም፣ “እርሱ ጥሩ ሰው ነው፣ እርሱም የሚመጣው የምሥራች ይዞ ነው” አለ፡፡
\s5
\v 28 ከዚያ በኋላ አኪማአስ ተጣርቶ ለንጉሡ፣ “ሁሉም ደኅና ነው” አለና በንጉሡ ፊት ለጥ ብሎ እጅ ነሥቶ፣ ወደ መሬት እያቀረቀረ፣ “በጌታዬ በንጉሡ ላይ እጃቸውን ያነሡትን ሰዎች አሳልፎ የሰጠህ እግዚአብሔር አምላክህ የተባረከ ይሁን” አለው፡፡
\v 29 ንጉሡም፣ “ወጣቱ አቤሴሎም ደህና ነውን? ሲል ጠየቀ፡፡ አኪማአስም፣ “ኢዮአብ እኔን የንጉሡን አገልጋይ በላከኝ ጊዜ ትልቅ ሁካታ ነበር፣ ምን እንደሆነ ግን እኔ አላወቅሁም” አለው፡፡
\v 30 ከዚያ በኋላ ንጉሡ፣ “እልፍ በልና ቁም” አለው፡፡ ስለዚህ አኪማአስ እልፍ ብሎ ዝም ብሎ ቆመ፡፡
\s5
\v 31 ከዚያ በኋላ ወዲያውኑ ኩሻዊው ደረሰና፣ “ለጌታዬ ለንጉሡ የምሥራች አለኝ፣ እግዚአብሔር በንጉሡ ላይ የተነሡብህን ሁሉ ዛሬ ተበቅሎልሃልና” አለው፡፡
\v 32 ንጉሡም ኩሻዊውን፣ “ወጣቱ አቤሴሎም ደህና ነውን?” አለው፡፡ ኩሻዊውም፣ “የጌታዬ የንጉሡ ጠላቶች እንዲሁም በእርሱ ላይ ጉዳት ለማድረስ በአንተ ላይ የሚነሡብህ ሁሉ እንደዚያ ወጣት ይሁኑ” ብሎ መለሰለት፡፡
\v 33 በዚያን ጊዜ ንጉሡ ጥልቅ የሆነ ሐዘን አዘነ፤ በቅጥሩ በር ዐናት ላይ ወዳለችው ቤት ገብቶም አለቀሰ፡፡ እየሄደም ሳለ፣ “ልጄ አቤሴሎም ሆይ! ልጄ አቤሴሎም! በአንተ ፈንታ ምነው እኔ በሞትሁ ኖሮ! አቤሴሎም ልጄ፣ ልጄ!” እያለ ያለቅስ ነበር፡፡
\s5
\c 19
\p
\v 1 “እነሆ፣ ንጉሡ ለልጁ ለአቤሴሎም እያለቀሰ ነው” ተብሎ ለኢዮአብ ተነገረው፡፡
\v 2 “ንጉሡ ለልጁ እያለቀሰ ነው” የሚለውን ሠራዊቱ በዚያን ቀን ሰምቶ ስለነበረ፣ የዚያን ቀኑ ድል ለሠራዊቱ ወደ ኃዘን ቀንነት ተለወጠ፡፡
\s5
\v 3 ከጦርነት ሸሽተው የሚመጡ በኀፍረት ሹልክ ብለው እንደሚገቡ በዚያን ቀን ወታደሮቹ ሹልክ ብለው ወደ ከተማ ይገቡ ነበር፡፡
\v 4 ንጉሡ ፊቱን ሸፍኖና ድምፁን ከፍ አድርጎ፣ “ልጄ አቤሴሎም ሆይ፣ አቤሴሎም፣ ልጄ፣ ልጄ!” እያለ አለቀሰ፡፡
\s5
\v 5 ከዚያም ኢዮአብ ወደ ቤት ወደ ንጉሡ ዘንድ ገብቶ፣ “የሚወዱህን ትጠላለህና የሚጠሉህንም ትወዳለህና ዛሬ ሕይወትህን፣ የወንዶችና የሴቶች ልጆችህን ሕይወት፣ የሚስቶችህን ሕይወት እንዲሁም የቁባቶችህን ሕይወት ያዳኑትን የወታደሮችህን ሁሉ ፊት አሳፍረሃል፡፡
\v 6 የሚጠሉህን ትወዳለህ የሚወዱህን ትጠላለህ፤ የጦር አዛዦችና ወታደሮች ለአንተ ምንም እንዳይደሉ ዛሬ አሳይተሃልና፡፡ ዛሬ አቤሴሎም በሕይወት በኖረና እኛ ሁላችንም ብንሞት፣ ያ ደስ ያሰኝህ እንደነበረ አምናለሁ፡፡
\s5
\v 7 ስለዚህ አሁንም ተነሥተህ ውጣና ለወታደሮችህ በትሕትና ተናገራቸው፣ ባትሄድ ግን፣ በእግዚአብሔር ስም እምላለሁ፣ በዛሬው ሌሊት አንድም ሰው ከአንተ ጋር አይቀርም፡፡ ይሄ ደግሞ ከልጅነትህ ጀምሮ እስካሁን ከደረሰብህ መከራ ሁሉ የከፋ ይሆንብሃል፡፡”
\v 8 ስለዚህ ንጉሡ ተነሥቶ በከተማይቱ በር አጠገብ ተቀመጠ፣ ለሰዎችም ሁሉ፣ “እነሆ፣ ንጉሡ በበሩ ተቀምጦአል” ተብሎ ተነገራቸው፡፡ ከዚያ በኋላም ሰዎች ሁሉ በንጉሡ ፊት መጡ፡፡ በዚህን ጊዜ በእስራኤል ሰው ሁሉ ወደየቤቱ ሸሽቶ ነበር፡፡
\s5
\v 9 በመላው እስራኤል በየነገዱ ያሉ ሰዎች ሁሉ እርስ በርሳቸው፣ “ንጉሡ ከጠላቶቻችን እጅ አስጥሎናል፤ ከፍልስጥኤማውያንም እጅ አድኖናል፤ አሁን ደግሞ ከአቤሴሎም ሸሽቶ ከአገር ወጥቷል፡፡
\v 10 በላያችን ላይ የቀባነውም አቤሴሎም በጦርነቱ ተገድሏል፡፡ ስለዚህ ንጉሡን መልሰን ስለማምጣት ለምን አንነጋገርም?” እያሉ ይነጋገሩ ነበር፡፡
\s5
\v 11 ንጉሥ ዳዊት ወደ ካህናቱ ወደ ሳዶቅና ወደ አብያታር ልኮ፣ “ለይሁዳ ሽማግሌዎች፣ ‘ወደ ቤተ መንግሥቱ ይመልሰው ዘንድ የመላው የእስራኤል ልብ ለንጉሡ ድጋፍ የሚሰጥ ነውና፣ ንጉሡን ወደ ቤተ መንግሥቱ ለመመለስ እናንተ የመጨረሻዎቹ የምትሆኑት ለምንድን ነው?
\v 12 እናንተ የሥጋዬ ቁራጭ የአጥንቴ ፍላጭ ናችሁ፡፡ ታዲያ፣ ንጉሡን ለመመለስ እናንተ የመጨረሻዎቹ የሆናችሁት ለምንድን ነው?
\s5
\v 13 ለአሜስያም፣ ‘አንተስ የሥጋዬ ቁራጭ የአጥንቴ ፍላጭ አይደለህምን? ከአሁን ጀምሮ በኢዮአብ ምትክ የሠራዊቴ አዛዥ ባለደርግህ እግዚአብሔር ይህንን ያድርግብኝ፣ ከዚህም የባሰ ይጨምርብኝ’” በሉ ብሎ መልእክት ላከ፡፡
\v 14 “አንተና ሰዎችህ ሁሉ ተመለሱ” ብለው ወደ ንጉሡ መልእከት እስኪልኩ ድረስ የአንድ ሰው ልብ እንደነበራቸው ያህል የይሁዳን ሁሉ ልብ ማረከ፡፡
\v 15 ስለዚህ ንጉሡ ተመልሶ ወደ ዮርዳኖስ መጣ፡፡ የይሁዳም ሰዎች ዮርዳኖስን ሲሻገር ለማጀብ፣ ንጉሡን ለመገናኘት ወደ ጌልጌላ መጡ፡፡”
\s5
\v 16 ከብራቂም የሆነው የጌራ ልጅ ሳሚ ንጉሥ ዳዊትን ለመቀበል ከይሁዳ ሰዎች ጋር ፈጥኖ ወረደ፡፡
\v 17 ከእርሱ ጋር ከብንያም አንድ ሺህ ሰዎች ነበሩ፤ ደግሞም ከሲባ ከሳዖል አገልጋይ ጋር አሥራ አምስት ልጆቹና ሃያ አገልጋዮቹ ነበሩ፡፡ በንጉሡ ፊት ዮርዳኖስን አቋረጠው ተሻገሩ፡፡
\v 18 የተሻገሩት የንጉሡን ቤተሰብ ለማምጣትና እርሱ መልካም ነው ያለውን ለማድረግ ነበር፡፡
\s5
\v 19 ሳሚ ለንጉሡ፣ “ጌታዬ እኔን በደለኛ አድርጎ አይቁጠረኝ ወይም ጌታዬ ንጉሡ ከኢየሩሳሌም በወጣበት ቀን ባሪያህ በግትረኛነት ያደረገውን ትኩረት አይስጠው፡፡ ንጉሥ ሆይ፣ እባክህ ይህንን በልብህ አታኑረው፡፡
\v 20 ባሪያህ ኃጢአት ማድረጌን አውቃለሁ፡፡ ከመላው የዮሴፍ ቤት ጌታዬ ንጉሡን ለመቀበል የመጀመሪያ ሆኜ ዛሬ የመጣሁት እነሆ፣ ለዚህ ነው፡፡” አለ፡፡
\s5
\v 21 ነገር ግን የጽሩይ ልጅ አቢሳ፣ “እግዚአብሔር የቀባውን ተራግሟልና ስለዚህ ጉዳይ ሳሚ ሊገደል አይገባውምን?”
\v 22 ከዚያ በኋላ ዳዊት፣ “ዛሬ ለእኔ ጠላቶች ትሆኑኝ ዘንድ እናንተ የጽሩያ ልጆች ከእናንተ ጋር ምን አለኝ? ዛሬ በእስራኤል አንድ ሰው ሊገደል ይገባዋል? በእስራኤል ላይ ንጉሥ መሆኔን ያወቅሁት በዛሬው ቀን አይደለምን?”
\v 23 ስለዚህ ንጉሡ ለሳሚ፣ “አትሞትም” አለው፡፡ ስለዚህ ንጉሡ በመሐላ ቃል ገባለት፡፡
\s5
\v 24 ከዚያ በኋላ የሳዖል ልጅ ሜምፊቦስቴ ንጉሡን ለመቀበል መጣ፡፡ ንጉሡ ከሄደበት ቀን ጀምሮ በሰላም ወደ ቤቱ እስከተመለሰበት ቀን ድረስ በእግሩ ሱሪ አላስገባም፣ ጢሙን አልተላጨም ወይም ልብሱን አላጠበም፡፡
\v 25 ስለዚህም ንጉሡን ለመቀበል ወደ ኢየሩሳሌም በመጣ ጊዜ፣ ንጉሡ፣ “ሜምፊቦስቴ ከእኔ ጋር ለምን አልሄድክም?” አለው፡፡
\s5
\v 26 እርሱም፣ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፣ አገልጋዬ አታለለኝ፣ ምክንያቱም፣ ‘እኔ ባሪያህ ሽባ ስለሆንኩኝ እንድቀመጥበትና ከንጉሡ ጋር እንድሄድ አህያዬን እጭናለሁ’ ብዬ ነበርና፡፡
\v 27 አገልጋዬ ሲባ እኔን ባሪያህን ለጌታዬ ለንጉሡ አማ፤ ጌታዬ ንጉሡ ግን እንደ እግዚአብሔር መልአክ ነው፡፡ ስለዚህ በዓይንህ ፊት መልካም መስሎ የታየህን አድርግብኝ፡፡
\v 28 የአባቴ ቤት ሰዎች ሁሉ በጌታዬ በንጉሡ ዘንድ የሞት ሰዎች ነበሩና፤ ነገር ግን ባሪያህን በገበታህ ከሚበሉት አንዱ አድርገህ አስቀመጥኸኝ፡፡ ስለዚህ አሁንም በንጉሡ ፊት ልቅሶዬን ለመቀጠል እኔ ምን መብት አለኝ?”
\s5
\v 29 ከዚያ በኋላም ንጉሡ፣ “ከዚህ በላይ መግለጫ መስጠት ምን ያስፈልጋል? እርሻውን አንተና ሲባ እንድትካፈሉት ወስኛለሁ፡፡”
\v 30 ስለዚህ ሜምፊቦስቴ ለንጉሡ፣ “ጌታዬ ንጉሡ ወደ ራሱ ቤት በሰላም ስለመጣ፣ ግድ የለም፣ እርሱ ሁሉንም ይውሰደው” አለው፡፡
\s5
\v 31 ከዚያም ገለዓዳዊው ቤርዜሊ ከንጉሡ ጋር ዮርዳኖስን ለመሻገር ከሮግሊም መጣ፣ ንጉሡም ዮርዳኖስን ሲሻገር አጀበው፡፡
\v 32 ቤርዜሊ ሰማንያ ዓመት የሆነው ሽማግሌ ሰው ነበር፡፡ እጅግ ባለጠጋ ሰው ስለነበረ፣ ንጉሡ በመሃናይም በቆየበት ጊዜ ስንቅ አምጥቶለት ነበር፡፡
\v 33 ንጉሡም ለቤርዜሊ፣ “ከእኔ ጋር ና፣ እኔ በኢየሩሳሌም የምትመገበውን አቀርብልሃለሁ” አለው፡፡
\s5
\v 34 ቤርዜሊም ለንጉሡ፣ “ከንጉሡ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም እሄድ ዘንድ ከሕይወት ዘመኔ ምን ያህል ቢቀር ነው?
\v 35 እኔ ሰማንያ ዓመቴ ነው፤ መልካሙንና ክፉውን መለየት እችላለሁን? ባሪያህ የሚበላውንስ ሆነ የሚጠጣውን ጣዕም መለየት ይችላልን? የሚዘፍኑ ወንዶችንና የሚዘፍኑ ሴቶችን ከእንግዲህ መስማት እችላለሁን? ስለዚህ ባሪያህ በጌታዬ በንጉሡ ላይ ለምን ሸክም ይሆናል?
\v 36 ባሪያህ የሚፈልገው ከንጉሡ ጋር ዮርዳኖስን መሻገር ብቻ ነው፡፡ ንጉሡ ለባሪያው ይህንን ያህል ብድራት ለምን ይከፍለኛል?
\s5
\v 37 በአገሬ እሞት ዘንድ፣ በአባቴና በእናቴ መቃብር አጠገብ እቀበር ዘንድ፣ እባክህ ወደ አገሬ እንድመለስ ፍቀድልኝ፡፡ ነገር ግን አገልጋይህ ከመዓም ከዚህ አለ፣ እርሱ ከአንተ ጋር ይሻገር፣ የመሰለህን መልካም ነገር አድርግለት፡፡”
\s5
\v 38 ንጉሡም፣ “ከመዓም ከእኔ ጋር ይሻገራል፣ ለአንተም መልካም መስሎ የታየህን አደርግለታለሁ፤ ከእኔም የምትፈልገውን ማንኛውንም ነገር እኔ አደርግልሃለሁ፡፡”
\v 39 ከዚያም ሰዎቹ ሁሉ ዮርዳኖስን ተሻገሩ፤ ከዚያም ንጉሡ ተሻገረ፣ ንጉሡም ቤርዜሊን ሳመው ባረከውም፡፡ ከዚህ በኋላ ቤርዜሊ ወደ ራሱ አገር ተመለሰ፡፡
\s5
\v 40 ስለዚህ ንጉሡ ወደ ጌልጌላ ተሻገረ፣ ከመዓምም ከእርሱ ጋር ተሻገረ፡፡ የይሁዳ ሠራዊት ንጉሡንና የእስራኤልን ግማሽ ሠራዊት ይዞ ተመለሰ፡፡
\v 41 ወዲያውም የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ወደ ንጉሡ መጥተው ለንጉሡ፣ “ወንድሞቻችን የይሁዳ ሰዎች አንተን ዳዊትንና ቤተሰቡን እንዲሁም የዳዊትን ሰዎች ሰርቀው ዮርዳኖስን አሻግረው ለምን አመጧቸው?”
\s5
\v 42 ስለዚህ የይሁዳ ሰዎች ለእስራኤል ሰዎች፣ “ይህንን ያደረግነው ንጉሡ የቅርብ ዘመዳችን ስለሆነ ነው፡፡ ታዲያ እናንተ በዚህ ለምን ትቆጣላችሁ? እኛ የበላነውና ንጉሡ መክፈል ያለበት አንዳች ነገር አለ? ለእኛስ አንዳች ስጦታ ሰጥቶናል?”
\v 43 የእስራኤል ሰዎች ለይሁዳ ሰዎች፣ “እኛ ከዳዊት ጋር የሚዛመዱ አሥር ነገዶች አሉን፣ ስለዚህ እኛ ከእናንተ ይልቅ በዳዊት ዘንድ መብት አለን፡፡ ታዲያ እናንተ እኛን ለምን ትንቁናላችሁ? ንጉሡን ለማምጣት ያቀረብነው ሃሳብ በመጀመሪያ ሊሰማ የሚገባው አልነበረምን? ነገር ግን የይሁዳ ሰዎች የሰጡት መልስ የእስራኤል ሰዎች ከሰጡት መልስ ይልቅ እጅግ የከረረ ነበር፡፡”
\s5
\c 20
\p
\v 1 በዚህ ጊዜ በዚሁ ስፍራ የቢክሪ ልጅ ስሙ ሳቤዔ የተባለ አንድ ችግር ፈጣሪ ብንያማዊ ነበር፡፡ እርሱም መለከት ነፍቶ፣ “እኛ ከዳዊት ጋር ድርሻ የለንም፣ ከእሴይ ልጅም ጋር ርስት የለንም፤ እስራኤል ሆይ፣ እያንዳንዱ ሰው ወደ ቤቱ ይመለስ” አለ፡፡
\v 2 ስለዚህ የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ዳዊትን ከድተው የቢክሪን ልጅ ሳቤዔን ተከተሉ፡፡ የይሁዳ ሰዎች ግን ከዮርዳኖስ አንስተው እስከ ኢየሩሳሌም ድረስ ንጉሣቸውን አጥብቀው ተከተሉ፡፡
\s5
\v 3 ዳዊት በኢየሩሳሌም ወዳለው ቤተ መንግሥቱ በመጣ ጊዜ ቤተ መንግሥቱን እንዲጠብቁ ትቶአቸው የነበሩትን ዐሥሩን ቁባቶች በአንድ ቤት ውስጥ አስገብቷቸው በአንድ ዘበኛ እንዲጠበቁ አደረገ፡፡ የሚያስፈልጋቸውን አቀረበላቸው፣ ነገር ግን ከዚያ በኋላ ከእነርሱ ጋር አልተኛም፡፡
\s5
\v 4 እስከ ዕለተ ሞታቸው ድረስ ተዘግቶባቸው እንደ መበለት ይኖሩ ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ ንጉሡ ለአሜሳይ፣ “በሦስት ቀን ውስጥ የይሁዳ ሰዎች ሁሉ እንዲሰባሰቡ ጥራቸው፣ አንተም እዚህ መገኘት አለብህ” አለው፡፡
\v 5 ስለዚህ አሜሳይ የይሁዳ ሰዎች እንዲሰባሰቡ ለመጥራት ሄደ፣ ነገር ግን ንጉሡ ካዘዘው ቀነ-ገደብ በላይ ቆየ፡፡
\s5
\v 6 ስለዚህ ዳዊት ለአቢሳ፣ “አሁን የቤክሪ ልጅ ሳቤዔ አቤሴሎም ካደረሰው ይልቅ የባሰ ጉዳት ያደርስብናል፡፡ የጌታህን አገልጋዮች ወታደሮቼን ያዝና አሳደው፣ አለበለዚያ የተመሸጉ ከተሞችን ያገኝና ከዓይናችን ይሰወራል፡፡” አለው፡፡
\v 7 በዚያን ጊዜ የኢዮአብ ሰዎች ከከሊታውያን ከፈሊታውያን እንዲሁም ከሌሎች ኃያላን ጦረኞች ጋር ተከትለውት ወጡ፡፡ የቤክሪን ልጅ ሳቤዔን ያሳድዱ ዘንድ ከኢየሩሳሌም ወጡ፡፡
\s5
\v 8 ገባዖን ከሚገኘው ታላቅ ዐለት በደረሱ ጊዜ አሜሳይ ሊገናኛቸው መጣ፣ ኢዮአብ በሰገባው ውስጥ የገባ ሰይፍ በወገቡ የታጠቀበትን ቀበቶ የሚያካትት የጦር ሜዳ ልብሱን ለብሶ ነበር፡፡ ወደፊት እየተራመደ ሳለም ሰይፉ ወደቀ፡፡
\s5
\v 9 ኢዮአብም አሜሳይን፣ “ወንድሜ ሆይ፣ ደህና ነህን?” አለው፡፡ ኢዮአብም አሜሳይን እንደሚያፈቅረው አድርጎ ለመሳም ጢሙን ይዞ ሳበው፡፡
\v 10 አሜሳይ ኢዮአብ በግራ እጁ ይዞት የነበረውን ጩቤ አላስተዋለም፡፡ ኢዮአብ አሜሳይን ሆዱን ወጋው፣ ሆድ-ዕቃውም በምድር ላይ ተዘረገፈ፡፡ ኢዮአብ እንደገና አልወጋውም፣ አሜሳይም ሞተ፡፡ ስለዚህ ኢዮአብና ወንድሙ አቢሳ የቤክሪን ልጅ ሳቤዔን አሳደዱ፡፡
\s5
\v 11 ከዚያ በኋላ ከኢዮአብ ሰዎች አንዱ በአሜሳይ አጠገብ ቆመና፣ “ኢዮአብን የሚደግፍና የዳዊት የሆነ ኢዮአብን ይከተል” አለ፡፡
\v 12 በዚህን ጊዜ አሜሳይ በደም ተጨማልቆ በመንገዱ መካከል ወድቆ ነበር፡፡ ሰዎች ሁሉ ቆመው እንደቀሩ ሰውዬው ተመልክቶ የአሜሳይን ሬሳ ከመንገድ ጎትቶ ወደ እርሻ ውስጥ አስገባው፡፡ ወደ አጠገቡ የደረሰ ማንኛውም ሰው ቆሞ ይቀር እንደነበረ ተመልክቶ ልብስ በላዩ ጣል አደረገበት፡፡
\v 13 አሜሳይ ከመንገድ ዞር ከተደረገ በኋላ የቤክሪ ልጅ ሳቤዔን ለማሳደድ ሰዎች ሁሉ ኢዮአብን ተከተሉ፡፡
\s5
\v 14 ሳቤዔአም በእስራኤል ነገዶች ሁሉ መካከል አልፎ ወደ አቤል ቤትማዓካና ተሰባስበው ሳቤዔን ያሳድዱ ወደነበሩት ወደ መላው የቤክሪያውያን ግዛት መጣ፡፡
\v 15 ደረሱበትና አቤል ቤትመዓካ ላይ ከበቡት፡፡ በከተማይቱም ላይ ግድግዳውን አስጠግተው የአፈር ድልድል ሠሩበት፡፡ ከኢዮአብ ጋር የነበረውም ሠራዊት ግንቡን ለመናድ ደበደበው፡፡
\v 16 ከዚያ በኋላ አንድ ብልህ ሴት ከከተማ ውስጥ ተጣራችና፣ “ስማኝ፣ እባክህን ስማኝ ኢዮአብ፤ እንዳነጋግርህ ወደዚህ ጠጋ በል” አለችው፡፡
\s5
\v 17 ስለዚህ ኢዮአብ ጠጋ አለ፣ ሴቲቱም፣ “አንተ ኢዮአብ ነህን?” አለችው፡፡ እርሱም፣ “አዎን፣ ነኝ” አለ፡፡ እርሷም ከዚያ በኋላ ለእርሱ፣ “የባሪያህን ቃል ስማ” አለችው፡፡ እርሱም፣ “እየሰማሁ ነው” ብሎ መለሰላት፡፡
\v 18 ከዚያ በኋላም እርሷ፣ “በቀደሙት ጊዜያት ‘በእርግጥ ምክርን ከአቤል ጠይቅ ምክሩም ችግሮችን ይፈታል’ ይሉ ነበር፡፡
\v 19 እኛ በእስራኤል ውስጥ እጅግ ሰላማዊና ታማኝ ከሆኑት ከተሞች አንዱ ነን፡፡ በእስራኤል ውስጥ እናት የሆነችውን ከተማ ለማጥፋት እየሞከርክ ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ርስት ለምን ለመዋጥ ትፈልጋለህ?”
\s5
\v 20 ስለዚህ ኢዮአብ፣ “መዋጥ ወይም ማጥፋት ከእኔ የራቀ ይሁን፣
\v 21 ያ እውነት አይደለም፡፡ ነገር ግን ከኮረብታማው ከኤፍሬም አገር የሆነ ሳቤዔ የተባለ የቤክሪ ልጅ እጁን በንጉሡ ላይ ፣ በዳዊት ላይ አንስቷል፤ እርሱን ብቻ አሳልፋችሁ ስጡኝ፣ ከተማውን ለቅቄ እወጣለሁ” ብሎ መለሰላት፡፡ ሴቲቱም ለኢዮአብ፣ “ራሱ በቅጥሩ ላይ ይወረወርልሃል” አለችው፡፡
\v 22 ከዚያም ሴቲቱ በጥበብዋ ወደ ሕዝቡ ሁሉ ሄደች፡፡ የቤክሪን ልጅ የሳቤዔን ራስ ቆርጠው በቅጥሩ ላይ ለኢዮአብ ወረወሩለት፡፡ እርሱም ቀንደ-መለከቱን ነፋ፣ የኢዮአብም ሰዎች ከተማይቱን ለቀው እያንዳንዱ ሰው ወደየቤቱ ሄደ፡፡
\s5
\v 23 በዚህን ጊዜ ኢዮአብ በሠራዊቱ ሁሉ ላይ የበላይ ነበር፣ የዮዳሄ ልጅ በናያስ ደግሞ በከሊታውያንና በፈሊያታውያን ላይ አለቃ ሆነ፡፡
\v 24 አዶኒራም በግዳጅ ሥራ ላይ ለተሰማሩት አለቃ ሆነ፣ የአሒሉድ ልጅ ኢዮሣፍጥ ደግሞ ታሪክ ጸሐፊ ሆነ፤
\v 25 ሱሳ ጸሐፊ፣ ሳዶቅና አብያታር ካህናት ነበሩ፤
\v 26 እንዲሁም የኢያዕር ሰው ዒራስ የዳዊት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነ፡፡
\s5
\c 21
\p
\v 1 በዳዊት ዘመን ለሶስት ተከታታይ ዓመታት ራብ ሆነ፣ ዳዊትም የእግዚአብሔርን ፊት ፈለገ፡፡ስለዚህ እግዚአብሔር፣ “ሳዖልና ገዳይ ቤተሰቡ ገባዖናውያንን እንዲሞቱ ስላደረገ ይህ ረሃብ በአንተ ላይ ነው” አለ፡፡
\s5
\v 2 እንግዲህ ገባዖናውያን ከአሞራውያን የተረፉ እንጂ የእስራኤል ሕዝብ ወገን አልነበሩም፡፡ የእስራኤል ሕዝብ እንደማይገድሏቸው ምለውላቸው ነበር፣ ሳዖል ግን ለእስራኤልና ለይሁዳ ሕዝብ ከነበረው ቅናት የተነሣ እንዲሁ ሁሉንም የመግደል ሙከራ አድርጎ ነበር፡፡
\v 3 ስለዚህ ዳዊት ገባዖናውያንን በአንድነት ጠራቸውና፣ “ምን ላደርግላችሁ? የእርሱን በጎነትና ተስፋ ቃሉን የሚወርሱትን የእግዚአብሔርን ሕዝብ ትባርኩ ዘንድ ስርየትን እንዴት ማድረግ እችላለሁ?” አላቸው፡፡
\s5
\v 4 ገባዖናውያንም፣ “በእኛና በሳዖል ወይም በቤተሰቡ መካከል ያለው የብርና የወርቅ ጉዳይ አይደለም፡፡ በእስራኤልም ውስጥ ማንም ሰው እንየዲገደል የምናደርግ እኛ አይደለንም፡፡” ብለው መለሱለት፡፡ ዳዊትም፣ “የምትጠይቁትን ማንኛውንም ነገር ቢሆን እኔ ያንን አደርግላችኋለሁ” አላቸው፡፡
\s5
\v 5 እነርሱም ለንጉሡ፣ “እንድንጠፋና በእስራኤል ክልል ውስጥ ምንም ስፍራ እንዳይኖረን ሁላችንንም ለመግደል ሙከራ ካደረገውና በእኛ ላይ ሤራ ካውጠነጠነው
\v 6 ከእርሱ ዝርያዎች ሰባት ሰዎች ለእኛ ተላልፈው ይሰጡን እኛም በእግዚአብሔር በተመረጠው በሳዖል አገር በጊብዓ በእግዚአብሔር ፊት እንሰቅላቸዋለን” አሉት፡፡ ስለዚህ ንጉሡ፣ “እነርሱን እሰጣችኋለሁ” አላቸው፡፡
\s5
\v 7 ንጉሡ ግን በእርሱና በሳዖል ልጅ በዮናታን ስለነበረው የእግዚአብሔር መሐላ የሳዖልን ልጅ የዮናታንን ልጅ ሜምፊቦስቴን አዳነው፡፡
\v 8 ነገር ግን ንጉሡ የኢዩሄል ልጅ ሪጽፋ ለሳዖል የወለደቻቸውን ሁለቱን ወንዶች ልጆች ሄርሞንንና ሜምፊቦስቴን ወሰዳቸው፣ በተጨማሪም ዳዊት የሳዖል ልጅ ሜልኮል ለመሓላታዊው ለቤርዜሊ ልጅ ለኤስድሪኤል የወለደቻቸውን አምስት ወንዶች ልጆች ወሰዳቸው፣
\v 9 በገባዖናውያንም እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፡፡ እነርሱም በተራራው ላይ በእግዚአብሔር ፊት ሰቀሏቸው፣ ሰባቱም አንድ ላይ ሞቱ፡፡ የተገደሉት በመከራ ወቅት፣ የገብስ መከር በሚሰበሰብባቸው የመጀመሪያዎቹ አምስት ቀናት ነበረ፡፡
\s5
\v 10 ከዚያ በኋላ የኢዩሄል ልጅ ሪጽፋ ከመከር መሰብሰብ ጊዜ ጀምሮ ዝናብ በእነርሱ ላይ እስኪወርድባቸው ድረስ በአስከሬኖቹ አጠገብ ባለው ተራራ ለራሷ ማቅ ወስዳ ዘረጋች፡፡ የሰማይ ወፎች በቀን፣ የዱር አራዊት በማታ እንዲነኳቸው አልፈቀደችም፡፡
\v 11 የሳዖል ቁባት የኢዩሄል ልጅ ሪጽፋ ያደረገችው ለዳዊት ተነገረው፡፡
\s5
\v 12 ስለዚህ የሳዖልንና የልጁን የዮናታንን አጥንት ሳዖልን በጊልቦዓ ከገደሉት በኋላ ሰቅለውት ከነበረበት ከቤትሻን አደባባይ ከሰረቁት ከኢያቢስ ገለዓድ ሰዎች ዘንድ ዳዊት ሄዶ አመጣ፡፡
\v 13 ዳዊት ከዚያ ስፍራ የሳዖልንና የልጁን የዮናታንን አጥንት እንዲሁም በዚያ የተሰቀሉትን የሰባት ሰዎች አጥንትም ሰብስቦ ወሰደ፡፡
\s5
\v 14 የሳዖልንና የልጁን የዮናታንን አጥንት በብንያም አገር በጼላ በአባቱ በቂስ መቃብር ቀበሩአቸው፡፡ ንጉሡም ያዘዘውን ነገር ሁሉ አከናወኑ፡፡ ከዚያ በኋላ ለምድሪቱ የተደረገውን ጸሎት እግዚአብሔር መለሰ፡፡
\s5
\v 15 ከዚያ በኋላ ፍልስጥኤማውያን ከእስራኤል ጋር እንደገና ውጊያ ገጠሙ፡፡ ስለዚህ ዳዊት ከሠራዊቱ ጋር ወርዶ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ተዋጋ፡፡ ዳዊት በጦርነቱ የሰውነት መዛል አጋጠመው፡፡
\v 16 የኃላኑ ዝርያ የነበረውና የናስ ጦሩ ሦስት መቶ ሰቅል የሚመዝነው እንዲሁም አዲስ ሰይፍ የታጠቀው ይሽቢብኖብ ዳዊትን ለመግደል አቀደ፡፡
\v 17 ነገር ግን የጽሩይ ልጅ አቢሳ ፍልስጥኤማዊውን ወግቶ በመግደል ዳዊትንም ታደገው፡፡ ከዚያ በኋላም የዳዊት ሰዎች፣ “የእስራኤል መብራት እንዳታጠፋ ከእንግዲህ አንተ ከእኛ ጋር መውጣት የለብህም” ብለው ማሉለት፡፡
\s5
\v 18 ከዚህ በኋላ ጎብ በተባለ ስፍራ የራፋይም ዝርያ የነበረው ኩስታዊው ሴቦካይ ሳፋንን የገደለበት ጦርነት ከፍልስጥኤማውያን ጋር እንደገና ተደረገ፡፡
\v 19 ጎብ ላይ ከፍልስጥኤማውያን ጋር በተደረገ ጦርነት የቤተልሔሙ የየዓሬዓርጊም ልጅ ኤልያናን የጦሩ ዘንግ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የሆነውን የጌት ሰው ጎልያድን ገደለ፡፡
\s5
\v 20 ጋዛ ላይ በተደረገ ሌላ ጦርነት በእጆቹ ላይ ስድስት ስድስት ጣቶች በእግሮቹም ላይ ስድስት ጣቶች ባጠቃላይ ሃያ አራት ጣቶች የነበሩት ታላቅ ቁመት የነበረው ሰው ነበር፡፡ እርሱም የራፋይም ዝርያ ነበር፡፡
\v 21 እርሱም በእስራኤል ላይ ባፌዘ ጊዜ የዳዊት ወንድም የሣማ ልጅ ዮናታን ገደለው፡፡
\v 22 እነዚህ የጋዛዋ ራፋይም ዝርያዎች ነበሩ፣ እነርሱም በዳዊት እጅና በወታደሮቹ እጅ ተገደሉ፡፡
\s5
\c 22
\p
\v 1 እግዚአብሔር ከጠላቶቹ ሁሉና ከሳዖል እጅ በታደገው ጊዜ፣ ዳዊት በዚህ መዝሙር ያሉትን የቅኔ ቃላት ለእግዚአብሔር ዘመረ፡፡
\v 2 እንዲህም እያለ ጸለየ፣ “እግዚአብሔር ዐለቴ፣ አምባዬና ታዳጊዬ ነው፡፡
\s5
\v 3 እግዚአብሔር የምጠጋበት ዐለቴ፣ ጋሻዬና የድነቴ ቀንድ ነው፡፡ እርሱም ጠንካራ ምሽጌ፣ መጠጊዬና ከግፍ የሚያድነኝ ነው፡፡
\v 4 ሊመሰገን የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ፤ ከጠላቶቼም እድናለሁ፡፡
\s5
\v 5 የሞት ማዕበል ከበበኝ፤ የከንቱነት ጎርፍም አጥለቀለቀኝ፡፡
\v 6 የሲዖል ገመድ ተጠመጠመብኝ፣ የሞትም ወጥመድ አጥምዶ ያዘኝ፡፡
\s5
\v 7 በጨነቀኝ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ተጣራሁ፣ አምላኬን ጠራሁት፣ ከመቅደሱ ድምፄን ሰማኝ፤ ለረድኤት ያደረግሁት ጥሪም ወደ ጆሮው ደረሰ፡፡
\s5
\v 8 በዚያን ጊዜ ምድር ተንቀጠቀጠች እግዚአብሔር ተቆጥቶ ነበረና የሰማይ መሠረቶች ተናወጡ ተንቀጠቀጡም፡፡
\v 9 ከአፍንጫው ጢስ፣ ከአፉም ፍሙን የሚያግል የሚንበለበል እሳት፡፡
\s5
\v 10 ሰማይን ከፍቶ ወረደ፣ ድቅድቅ ጨለማም ከእግሩ በታች ነበር፡፡
\v 11 በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ፣ በንፋስም ክንፍ ተቀምጦ ሲበር ታየ፡፡
\v 12 በሰማይ ላይ ያሉ ከባድ የዝናብ ደመናዎችን በማሰባሰብ ጨለማን እንደ ድንኳን እንዲከበው አደረገ፡፡
\s5
\v 13 በፊቱ ካለው ነጎድጓድ የእሳት ፍም ወረደ፡፡
\v 14 እግዚአብሔር ከሰማይ አንጎደጎደ፣ የልዑልም ድምፅ አስተጋባ፡፡
\v 15 ፍላፃውን ወረወረ ጠላቶቹንም በተነ - መብረቁ እንዲበርቅ አደረገ፣ በታተናቸውም፡፡
\s5
\v 16 በዚያን ጊዜ የውሃ መውረጃዎች ታዩ፣ እግዚአብሔር ባስተጋባው የክተት ድምፅ፣ ከአፍንጫው በሚወጣ የእስትንፋስ ግፊት የምድር መሠረቶች ተጋለጡ፡፡
\s5
\v 17 ከላይ እጁን ዘርግቶ ያዘኝ፣ እየተንዶለዶለ ካለውም ውሃ አወጣኝ፡፡
\v 18 ብርቱ ከሆነው ጠላቴ፣ ከሚጠሉኝም ታደገኝ፣ በእኔ ላይ እጅግ በርትተውብኝ ነበርና፡፡
\s5
\v 19 በጭንቀቴ ጊዜ መጡብኝ፣ እግዚአብሔር ግን ድጋፍ ሆነኝ፡፡
\v 20 እርሱም ሰፋ ወዳለ ስፍራ አወጣኝ፡፡ በእኔ ደስ ተሰኝቶ ነበርና አዳነኝ፡፡
\v 21 እግዚአብሔር እንደ ጽድቄ መጠን ብድራትን ከፍሎኛል፣ እንደ እጄም ንጽሕና መጠን ወደ ስፍራዬ መልሶኛል፡፡
\s5
\v 22 የእግዚአብሔርን መንገድ ጠብቄአለሁና፣ ከአምላኬም ዞር በማለት ክፋትን አላደረግሁም፡፡
\v 23 የጽድቅ ሥርዓቱ በፊቴ ናቸውና፣ ከድንጋጌም ፈቀቅ አላልሁም፡፡
\s5
\v 24 ቅንነቴን በፊቱ ጠብቄ ነበርና፣ ራሴንም ከኃጢአት አርቄ ነበር፡፡
\v 25 ስለዚህ እግዚአብሔር ወደ ጽድቅ ደረጃዬ፣ በፊቱ ካለኝ የንፅሕና አቋሜ መልሶኛል፡፡
\s5
\v 26 ታማኝ ለሆነው ታማኝነትህን ታሳያለህ፣ ነቀፋ ለሌለበትም ሰው ነቀፋ የሌለብህ መሆንህን ታሳያለህ፡፡
\v 27 ከንጹሖች ጋር ንጹሕ መሆንህን ስታሳይ ለተጣመሙት ግን ጠማማ ነህ፡፡
\s5
\v 28 የተጎሳቆሉትን ታድናለህ፣ ዐይኖችህ ግን በትዕቢተኞች ላይ ነው፣ ታዋርዳቸውማለህ፡፡
\v 29 እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ መብራቴ ነህና፣ እግዚአብሔር ጨለማዬን ያበራል፡፡
\s5
\v 30 በአንተ መሰናክሉን ጥሼ አልፋለሁ፣ በአምላኬ ቅጥሩን እዘላለሁ፡፡
\v 31 የእግዚአብሔር መንገድማ ፍጹም ነው፣ የእግዚአብሔር ቃል ንፁሕ ነው፡፡ ወደ እርሱ ለሚጠጋ ለማንኛውም ሰው ጋሻ ነው፡፡
\s5
\v 32 ከእግዚአብሔር በቀር አምላክ ማን ነው? ከአምላካችንስ በቀር አምባ ማን ነው?
\v 33 እግዚአብሔር መጠጊያዬ ነው፣ ነቀፋ የሌለበትንም ሰው በመንገዱ ይመራዋል፡፡
\s5
\v 34 እንደ ዋላ እግሮች እግሮቼን ፈጣን ያደርጋቸዋል፣ በተራራም ላይ ያቆመኛል፡፡
\v 35 እጆቼን ለውጊያ፣ ክንዴንም የናስ ቀስት ለመለጠጥ ያሠለጥናቸዋል፡፡
\s5
\v 36 የድነትን ጋሻ ሰጥተኸኛል፣ ሞገስህም ታላቅ አድርጎኛል፡፡
\v 37 በእግሮቼ ሥር ያለውን ስፍራ ሰፊ አድርገህልኛል፣ ስለዚህ እግሮቼ አልተንሸራተቱም፡፡
\s5
\v 38 ጠላቶቼን አሳደድኋቸው፣ አጠፋኋቸውም፡፡ እስካጠፋቸውም ድረስ አልተመለስሁም፡፡
\v 39 ፈጽሜ አጠፋኋቸው፣ አደቀቅኋቸውም፣ ተመልሰው መነሣት አይችሉም፡፡ በእግሬ ሥር ወድቀዋል፡፡
\s5
\v 40 እንደ ጦር መታጠቂያ ኃይልን በእኔ ላይ አደረግህ፣ በላዬ ላይ የተነሡትንም ከእኔ በታች አደረግኸቸው፡፡
\v 41 የጠላቶቼን ማጅራት ሰጠኸኝ፣ የሚጠሉኝንም አፈራረስኳቸው፡፡
\s5
\v 42 ዕርዳታ ለማግኘት ተጣሩ ነገር ግን ማንም አላዳነቸውም፣ ወደ እግዚአብሔር ተጣሩ እርሱ ግን አልመለሰላቸውም፡፡
\v 43 እንደ አቧራ መሬት ላይ ፈጨኋቸው፣ በመንገድ ላይ እንዳለ ጭቃም ረገጥኋቸው፡፡
\s5
\v 44 ከራሴ ሕዝብ ክርክር አድነኸኛል፣ የሕዝቦችም ራስ አድርገህ አጽንተኸኛል፣ የማላውቀው ሕዝብ ያገለግለኛል፡፡
\v 45 ባዕድ ሕዝቦች ለእኔ ለመስገድ ተገደዱ፣ ስለ እኔ እንደሰሙ ወዲያውኑ ታዘዙኝ፡፡
\v 46 ባዕዳን ከምሽጋቸው እየተንቀጠቀጡ ወጡ፡፡
\s5
\v 47 እግዚአብሔር ሕያው ነው! ዐለቴ የተመሰገነ ይሁን፣ የድነቴ ዐለት እግዚአብሔር ከፍ ይበል፡፡
\v 48 በቀልን የሚበቀልልኝ፣ ሕዝብንም ከእኔ ሥር የሚያደርግልኝ አምላክ ይሄ ነው፡፡
\v 49 ከጠላቶቼ ነፃ ያወጣኛል፡፡ እንዲያውም በእኔ ላይ ከተነሡት በላይ አውጥተኸኛል፡፡ ከግፍኞች ታድገኸኛል፡፡
\s5
\v 50 ስለዚህ እግዚብሔር ሆይ፣ በሕዝቦች መካከል ለአንተ ምስጋና አቀርባለሁ፣ ለስምህም ምስጋና መዝሙር እዘምራለሁ፡፡
\v 51 እግዚአብሔር ለንጉሡ ታላቅ ድልን ይሰጠዋል፣ ኪዳናዊ ታማኝነቱን እርሱ ለቀባው፣ ለዳዊትና ለዘሮቹ ለዘላለም ያሳየዋል፡፡”
\s5
\c 23
\p
\v 1 እነዚህ ተወዳጁ የእስራኤል ዘማሪ፣ በያዕቆብ አምላክ የተቀባው፣ እጅግ የተከበረው፣ የእሴይ ልጅ የዳዊት የመጨረሻ ቃሎች ናቸው፡፡
\v 2 የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ተናገረ፣ ቃሉም በምላሴ ላይ ነበረ፡፡
\s5
\v 3 የእስራኤል አምላክ ተናገረ፣ የእስራኤልም ዐለት እንደዚህ አለኝ፣ “ሰዎችን በጽድቅ የሚገዛ፣ በፈሪሀ-እግዚአብሔር የሚያስተዳድር፣
\v 4 እርሱ ከዝናብ በኋላ ብሩሕ በሆነው የፀሐይ ብርሃን ከምድር እንደሚበቅል ለምለም ሣር፣ ደመና የሌለባት ፀሐይ ጥዋት ስትወጣ እንደሚፈነጠቅ የማለዳ ብርሃን ነው፡፡
\s5
\v 5 በእርግጥ የእኔ ቤተሰብ በእግዚአብሔር ፊት እንደዚህ አይደለምን? ከእኔስ ጋር ሥርዓት ያለውና በሁሉም መንገድ እርግጠኛ የሆነ የዘላለም ቃል ኪዳን አልገባምን? ድነቴን ከፍ ከፍ አድርጎ፣ ማንኛውንም ፍላጎቴን አይፈጽምልኝምን?
\s5
\v 6 ነገር ግን በእጅ ሊሰበሰቡ ስለማይችሉ ሁላቸውም እንደሚጣሉ እሾሆች ከንቱዎች ናቸው፡፡
\v 7 እነርሱን የሚነካ የብረት መሣሪያ መጠቀም ወይም የጦር ዘንግ መያዝ ስላለበት ባሉበት መቃጠል ይገባቸዋል፡፡”
\s5
\v 8 የዳዊት ምርጥ ወታደሮች ስም የሚከተለው ነው፡- የታህክሞን ሰው ዮሴብ የሦስቱ አለቆች አለቃና በአንድ ውጊያ ላይ ስምንት መቶ ሰዎችን የገደለ ነው፡፡
\s5
\v 9 ከእርሱ ቀጥሎ የአሆሃዊው የዱዲ ልጅ ኤልዔዘር ነበረ፣ እርሱም ከሶስቱ ኃያላን ሰዎች አንዱ ነበር፡፡ እርሱም ጦርነት ለመግጠም የተሰባሰቡ ፍልስጥኤማውያን በተገዳደሩ ጊዜና የእስራኤልም ሰዎች በፈገፈጉ ጊዜ በዚያ ነበር፡፡
\v 10 ኤልኤዘር እስኪዝልና እጁ ከሰይፉ ጋር ተጣብቆ እስኪቀር ድረስ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ቆሞ ተዋጋ፡፡ የዚያን ቀን እግዚአብሔር ታላቅ ድል አስገኘ፡፡ ከኤልኤዘር በኋላ ሠራዊቱ የተመለሰው አስከሬኖቹን ለመግፈፍ ብቻ ነበር፡፡
\s5
\v 11 ከእርሱም በኋላ የአሮዳዊው የአጌ ልጅ ሣማ ነበር፡፡ ፍልስጥኤማውያኑ የምስር እርሻ በነበረበት ተሰብስበው ሳሉ ሠራዊቱ ከ እነርሱ ሸሸ፡፡
\v 12 ሣማ ግን በእርሻው መካከል ቆሞ ተቋቋማቸው ፍልስጥኤማዊውንም ገደለው እግዚአብሔርም ታላቅ ድል ሰጣቸው፡፡
\s5
\v 13 ከሰላሳዎቹ ወታደሮች ሶስቱ በመከር ጊዜ ወደ አዶላም ዋሻ ወደ ዳዊት ዘንድ ሄዱ፡፡ የፍልስጥኤም ሠራዊት በራፋይም ሸለቆ ሰፍረው ነበር፡፡
\v 14 በዚያን ጊዜ ዳዊት በአንድ ዋሻ በምሽጉ ውስጥ ሲሆን ፍልስጥኤማውያን ግን በቤተልሔም ተደራጅተው ነበር፡፡
\s5
\v 15 ዳዊትም ውሃ ተጠምቶ፣ “በበሩ አጠገብ ካለችው ጉድጓድ የምጠጣውን ውሃ ምነው አንድ ሰው በሰጠኝ!” አለ፡፡
\v 16 ስለዚህ እነዚህ ሶስቱ ኃያላን ፍልስጥኤማውያንን ጥሰው አልፈው በበሩ አጠገብ ካለችው ከቤተልሔም ጉድጓድ ውሃ ቀዱ፡፡ ውሃውንም ይዘው ለዳዊት አመጡለት፣ እርሱ ግን ሊጠጣው ስላልፈቀደ በእግዚአብሔር ፊት አፈሰሰው፡፡
\v 17 ከዚያ በኋላም፣ “እግዚአብሔር ሆይ፣ ይህንን እጠጣው ዘንድ ከእኔ ይራቅ፤ ሕይወታቸውን አደጋ ላይ የጣሉ ሰዎችን ደም ልጠጣ ይገባኛልን?” ከዚህም የተነሣ ሊጠጣው አልፈቀደም፡፡ ሶስቱ ኃያላን ያደረጓቸው ነገሮች እነዚህ ናቸው፡፡
\s5
\v 18 የኢዮአብ ወንድምና የጽሩያ ልጅ አቢሳ የሶስቱ አለቃ ነበር፡፡ በአንድ ወቅት ከሶስት መቶዎቹ ጋር በጦሩ ተዋግቶ ገደላቸው፡፡ ከሶስቱ ወታደሮች ጋር በተያያዘ ብዙውን ጊዜ ስሙ ይጠቀሳል፡፡
\v 19 እርሱ ከእነርሱም ይልቅ ዝነኛ አልነበረምን? እርሱ የሶስቱ አለቃ ሆኖ ተሾመ፡፡ ይሁን እንጂ የእርሱም ዝና ከሶስቱ እጅግ ዝነኛ ከነበሩት ወታደሮች ጋር የሚስተካከል አልነበረም፡፡
\s5
\v 20 የቀብጽኤል አገር ሰው የሆነው የዮዳሄ ልጅ በናያስ ታላቅ ጀብዱ የሠራ ጠንካራ ሰው ነበረ፡፡ እርሱም ሁለቱን የአርኤል ልጆች ገደለ፡፡ በረዶ በጣለበትም ወቅት በጉድጓድ ውስጥ ገብቶ አንበሳ ገድሎአል፡፡
\v 21 ደግሞም አንድ ግዙፍ ግብፃዊም ገድሎአል፡፡ ግብፃዊው በእጁ ጦር የያዘ ቢሆንም በናያስ በትር ብቻ ይዞ ገጠመው፡፡ ጦሩን ከግብፃዊው እጅ ቀምቶ በራሱ ጦር ገደለው፡፡
\s5
\v 22 በናያስ እነዚህን ጀብዱዎች ፈጸመ ከሶስቱም ኃያላን ጋርም ስሙ የተጠራ ሆነ፡፡
\v 23 በአጠቃላይ ከነበሩት ሰላሳ ወታደሮች ይልቅ ከፍ ያለ ግምት የተሰጠው ነበረ፣ ሆኖም የሶስቱ እጅግ ምርጥ ወታደሮችን ያህል ታላቅ ግምት የተሰጠው አልነበረም፡፡ ሆኖም ዳዊት የክቡር ዘበኞቹ አለቃ አደረገው፡፡
\s5
\v 24 ሰላሳዎቹ የሚከተሉትን ያካተተ ነበር፣ የኢዮአብ ወንድም አሣሄል፣ የቤተልሔሙ ሰው የዱዲ ልጅ ኤልያናን፣
\v 25 አሮዳዊው ሣማ፣ አሮዳዊው ኤሊቃ፣
\v 26 ፈሊጣዊው ሴሌስ፣ የቴቁሐዊው የዒስካ ልጅ ዒራስ፣
\v 27 ዓኖቶታዊው አቢዔዜር፣ ኩስታዊው ምቡናይ ፣
\v 28 አሆሃዊው ጸልሞን፣ ነጦፋዊው ማህራይ፣
\s5
\v 29 የነጦፋዊው የበዓና ልጅ ሔሌብ፣ ከብንያም ወገን የጊብዓ ሰው የሆነው የሪባይ ልጅ ኢታይ፣
\v 30 ጲርዓቶናዊው በናያስ፣ የገዓስ ሸለቆ ሰው ሂዳይ፣
\v 31 ዓረባዊው አቢዔልቦን፣ በርሑማዊው ዓዝሞት፣
\v 32 ሸዓልቦናዊው ኤሊያሕባ፣ የአሳን ልጆች፤ ዮናታን የተባለው፣
\s5
\v 33 የአሮዳዊው የሣማ ልጅ፣ የአሮዳዊው የሻራር ልጅ አሒአም፣
\v 34 የማዕካታዊው የአሐሰባይ ልጅ ኤልፋላት፣ የጊሎናዊው የአኪጦፌል ልጅ ኤሊኦም፣
\v 35 ቀርሜሎሳዊው ሐጽሮ፣ አርባዊው ፈዓራይ፣
\v 36 የሱባ ሰው የሆነው የናታን ልጅ ይግዓል፣
\s5
\v 37 አሞናዊው ጻሌቅ፣ የጽሩያ ልጅ የኢዮአብ ጦር መሣሪያ ያዥ የነበረው ብኤሮታዊው ነሃራይ፣
\v 38 ይትራዊው ዔራስ ፣ ይትራዊው ጋሬብ፣
\v 39 እንዲሁም ኬጢያዊው ኦርዮ፤ በጠቅላላው ሠላሳ ሰባት ነበሩ፡፡
\s5
\c 24
\p
\v 1 እንደገናም እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ እጅግ ተቆጣ፤ ዳዊትንም በእነርሱ ላይ በማስነሳት፣ “ሂድ እስራኤልንና ይሁዳን ቁጠር” አለው፡፡
\v 2 ንጉሡ አብሮት ለነበረው ለኢዮአብ፣ “ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ወደ እስራኤል ነገዶች ሁሉ ሂዱ፣ ለጦርነት ብቁ የሆኑትንም ጠቅላላ ብዛት ማወቅ እችል ዘንድ ሕዝቡን ሁሉ ቁጠሩ፡፡” አለው፡፡
\s5
\v 3 ኢዮአብም ለንጉሡ፣ “እግዚአብሔር አምላክህ የሕዝቡ ቁጥር መቶ እጥፍ ያብዛ፣ የጌታዬ የንጉሡ ዓይንም ይህንን ለማየት ያብቃው፡፡ ነገር ግን ጌታዬ ይህንን ለማድረግ ለምን ፈለገ?”
\v 4 ይሁን እንጂ የንጉሡ ቃል የኢዮአብንና የሠራዊት አለቆችን ቃል የሚሽር የመጨረሻ ቃል ነበር፡፡ ስለዚህ የእስራኤልን ሕዝብ ይቆጥሩ ዘንድ ኢዮአብና የሠራዊቱ አለቆች ከንጉሡ ፊት ወጡ፡፡
\s5
\v 5 ዮርዳኖስን ተሻገሩና ከከተማው በስተደቡብ በሸለቆው ዘንድ ባለው በአሮዔር አጠገብ ሠፈሩ፡፡ ከዚያም በጋድ በኩል አድርገው ወደ ኢያዜር ተጓዙ፡፡
\v 6 ወደ ገለዓድና ወደ ተባሶን አደሰይ፣ ቀጥሎም ወደ ዳንየዓን ከዚያም ዞረው ወደ ሲዶና ሄዱ፡፡
\v 7 ወደ ጢሮስ ምሽግና ወደ ኤዊያውያንና ወደ ከነዓናውያን ከተሞች ደረሱ፡፡ ከዚያም በይሁዳ ቤርሳቤህ ወዳለችው ወደ ኔጌቭ ወጡ፡፡
\s5
\v 8 በመላው ምድሪቱ ከተዘዋወሩ በኋላ ከዘጠኝ ወር ከሃያ ቀናት በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፡፡
\v 9 ከዚያም ኢዮአብ ለንጉሡ የተዋጊ ወንዶችን ጠቅላላ ቁጥር ዘገባ አቀረበ፡፡ በእስራኤል ሰይፍን መምዘዝ የሚችሉ ስምንት መቶ ሺህ ጀግኖች ሲኖሩ በይሁዳ ደግሞ አምስት መቶ ሺህ ሰዎች ነበሩ፡፡
\s5
\v 10 ሰዎቹን ከቆጠረ በኋላ ዳዊት በልቡ ተጨነቀ፡፡ ስለዚህ ለእግዚአብሔር፣ “ይህንን በማድረጌ ታላቅ ኃጢአት ሠርቻለሁ፡፡ የሠራሁት እጅግ የስንፍና ሥራ ነውና፣ እግዚአብሔር ሆይ፣ የባሪያህ በደል አስወግድ፡፡”
\s5
\v 11 ዳዊት ጠዋት ከመኝታው ሲነሣ፣ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ዳዊት ባለ ራእይ ወደ ነቢዩ ጋድ እንዲህ ሲል መጣ፣
\v 12 “ሂድና ለዳዊት፣ ‘እግዚአብሔር የሚለው ይህንን ነው፣ ሶስት ምርጫ እሰጥሃለሁ፣ አንዱን ምረጥ’”
\s5
\v 13 ስለዚህ ጋድ ወደ ዳዊት ሄደና፣ “የሦስት ዓመት ረሃብ ወደ ምድርህ ይምጣን? ወይስ እነርሱ እያሳደዱህ ከጠላቶችህ ለሶስት ወራት ብትሸሽ ይሻልሃል? ወይስ በአገርህ የሶስት ቀን ቸነፈር ይምጣብህ? ለላከኝ ምን መልስ እንደምሰጥ አሁን ወስን” አለው፡፡
\v 14 ዳዊትም ጋድን፣ “እጅግ ተጨንቄአለሁ፤ ምሕረታዊ አደራረጉ እጅግ ታላቅ ስለሆነ በእግዚአብሔር እጅ እንውደቅ እንጂ በሰው እጅ አንውደቅ” አለው፡፡
\s5
\v 15 ስለዚህ እግዚአብሔር ህከጥዋት እስከ ተወሰነ ጊዜ ቸነፈሩን በእስራኤል ላይ ላከ፣ ከዳን እስከ ቤርሳቤህም ሰባ ሺህ ሰዎች ሞቱ፡፡
\v 16 መልአኩ ኢየሩሳሌምን ለማጥፋት እጁን በዘረጋ ጊዜ፣ እግዚአብሔር ስለደረሰው ጉዳት ተፀፀቶ ሕዝቡን እያጠፋ የነበረውን መልአክ፣ “ይበቃል፣ እጅህን ሰብስብ” አለው፡፡ በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ በኢያቡሳዊው በኦርና ዐውድማ አጠገብ ቆሞ ነበር፡፡
\s5
\v 17 ሕዝቡን እየቀሠፈ የነበረውን መልአክ ባየ ጊዜ ዳዊት ለእግዚአብሔር፣ “ኃጢአት ሠርቻለሁ፣ የማይገባም ነገር አድርጌአለሁ፡፡ ነገር ግን እነዚህ በጎች ምን ያደረጉት ነገር አለ? እባክህን የአንተ እጅ እኔንና የአባቴን ቤተሰብ ይቅጣ፡፡” ብሎ ለእግዚአብሔር ተናገረ፡፡
\s5
\v 18 ከዚያ በኋላ ጋድ በዚያን ቀን ወደ ዳዊት መጣና፣ “ውጣና በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሥራ” አለው፡፡
\v 19 ስለዚህ ዳዊት ጋድ እንደ ነገረውና እግዚአብሔር እንዳዘዘው ወጣ፡፡
\v 20 ኦርና ሲመለከት ንጉሡና አገልጋዮቹ ሲደርሱ አየ፡፡ ስለዚህ ኦርና ወጣ ብሎ በንጉሡ ፊት ለጥ ብሎ እጅ ነሣ፡፡
\s5
\v 21 ከዚያ በኋላም ኦርና፣ “ጌታዬ ንጉሡ ወደ ባሪያው ዘንድ ለምን መጣ?” ዳዊትም መለሰ፣ “ቸነፈሩ ከሕዝቡ ይወገድ ዘንድ ለእግዚአብሔር መሠዊያ የምሠራበትን የአንተን ዐውድማ እገዛ ዘንድ ነው፡፡”
\v 22 ኦርናም ለዳዊት፣ “ጌታዬ ንጉሡ የራስህ አድርገህ ውሰደው፡፡ በፊትህ ደስ ያሰኘህንም አድርግበት፡፡ እነሆ፣ ለሚቃጠል መሥዋዕት በሬዎች፣ ለማገዶም የሚሆን የመውቂያ ዕቃና ቀንበር በዚህ አለ፡፡
\v 23 ይህንን ሁሉ ንጉሤ ሆይ፣ እኔ ኦርና ለአንተ እሰጣለሁ” አለና ከዚያ በኋላ፣ “እግዚአብሔር አምላክህ ይቀበልህ” አለው፡፡
\s5
\v 24 ንጉሡም ለኦርና፣ “አይሆንም፣ ይህንን በዋጋ መግዛት ይኖርብኛል፡፡ ምንም ነገር ያላወጣሁበትን አንድም ነገር ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጌ አላቀርብም” አለው፡፡ ስለዚህ ዳዊት ዐውድማውንና በሬዎቹን በሃምሳ የብር ሰቅል ገዛ፡፡
\v 25 ዳዊት በዚያ ላይ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራና የሚቃጠል መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት አቀረበ፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር ስለ ምድሪቱ ተለመነው፣ በእስራኤል የነበረውም ቸነፈር ቆመ፡፡