am_ulb/09-1SA.usfm

1672 lines
198 KiB
Plaintext

\id 1SA
\ide UTF-8
\h 1ኛ ሳሙኤል
\toc1 1ኛ ሳሙኤል
\toc2 1ኛ ሳሙኤል
\toc3 1sa
\mt 1ኛ ሳሙኤል
\s5
\c 1
\p
\v 1 በተራራማው በኤፍሬም አገር በራማ መሴፋ የሚኖር አንድ ሰው ነበር፤ ስሙ ሕልቃና ይባላል፥ እርሱም የኤፍሬማዊው የናሲብ ልጅ፥ የቶሑ ልጅ፥ የኤሊዮ ልጅ፥ የኢያርምኤል ልጅ ነበር።
\v 2 እርሱም ሁለት ሚስቶች ነበሩት፤ ስማቸውም የአንደኛዋ ሐና፥ የሁለተኛዋም ፍናና ነበር። ፍናና ልጆች ነበሯት፣ ሐና ግን አንድም ልጅ አልነበራትም።
\s5
\v 3 ይህም ሰው በየዓመቱ ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር ለመስገድና መሥዋዕት ለማቅረብ ወደ ሴሎ ይሄድ ነበር። የእግዚአብሔር ካህናት የሆኑት ሁለቱ የኤሊ ወንዶች ልጆች አፍኒንና ፊንሐስ በዚያ ነበሩ።
\v 4 በየዓመቱ ሕልቃና የሚሠዋበት ጊዜ ሲደርስ፥ ለሚስቱ ፍናና፥ ለወንዶችና ሴቶች ልጆችዋ በሙሉ ሁልጊዜ ከመሥዋዕቱ ሥጋ ድርሻቸውን ይሰጣቸው ነበር።
\s5
\v 5 ነገር ግን ሐናን ይወዳት ስለነበር ሁልጊዜም ድርሻዋን ሁለት ዕጥፍ አድርጎ ይሰጣት ነበር፤ እግዚአብሔር ግን ማኅፀንዋን ዘግቶት ነበር።
\v 6 እግዚአብሔር ማኅፀንዋን ዘግቶት ስለነበር ጣውንቷ እርስዋን ለማስመረር ክፉኛ ታስቆጣት ነበር።
\s5
\v 7 ስለዚህ በየዓመቱ ወደ እግዚአብሔር ቤት ከቤተሰብዋ ጋር በምትወጣበት ጊዜ ጣውንቷ ሁልጊዜ ታበሳጫት ነበር። በዚህ ምክንያት ታለቅስ ነበር፤ ምግብም አትበላም ነበር።
\v 8 ባሏ ሕልቃና ሁልጊዜ "ሐና ሆይ፥ ለምንድነው የምታለቅሽው? ምግብስ የማትበዪው ለምንድነው? ልብሽ የሚያዝነውስ ለምንድነው? ከዐሥር ወንዶች ልጆች ይልቅ ላንቺ እኔ አልሻልም?" ይላት ነበር።
\s5
\v 9 ከእነዚህ ወቅቶች በአንዱ፥ በሴሎ መብላታቸውንና መጠጣታቸውን ከጨረሱ በኋላ ሐና ተነሣች። ካህኑ ዔሊ በእግዚአብሔር ቤት መግቢያ በራፍ በወንበሩ ላይ ተቀምጦ ነበር።
\v 10 እርሷም እጅግ አዝና ነበር፤ ወደ እግዚአብሔር ጸለየች፥ አምርራም አለቀሰች።
\s5
\v 11 እንዲህ ስትልም ስዕለት ተሳለች፣ "የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ የአገልጋይህን ጉስቁልና ብትመለከትና ብታስበኝ፥ አገልጋይህን ባትረሳኝ፥ ነገር ግን ወንድ ልጅን ብትሰጠኝ፥ እኔም የሕይወት ዘመኑን ሁሉ ለእግዚአብሔር እሰጠዋለሁ፥ መቼም ቢሆን ጸጉሩ አይላጭም"።
\s5
\v 12 በእግዚአሔር ፊት ጸሎቷን ቀጥላ እያለች ዔሊ አፏን ይመለከት ነበር።
\v 13 ሐና በልቧ ትናገር ነበር። ከንፈሮችዋ ይንቀሳቀሱ ነበር፥ ድምፅዋ ግን አይሰማም ነበር። ስለዚህ ዔሊ ሰክራለች ብሎ አሰበ።
\v 14 ዔሊም "ስካርሽ የሚቆየው እስከ መቼ ነው? ወይንሽን ከአንቺ አርቂው" አላት።
\s5
\v 15 ሐናም፣ "ጌታዬ ሆይ፥ አይደለም፥ እኔ ልቤ በሐዘን የተጎዳብኝ ሴት ነኝ። ወይን ወይም የሚያሰክር መጠጥ አልጠጣሁም፥ ነገር ግን ነፍሴን በእግዚአብሔር ፊት እያፈሰስኩ ነው።
\v 16 አገልጋይህን እንደ ኃፍረተ ቢስ ሴት አትቁጠረኝ፤ ይህን ያህል ጊዜ የተናገርኩት እጅግ ከበዛው ሐዘኔና ጭንቀቴ የተነሣ ነው" በማለት መለሰችለት።
\s5
\v 17 ከዚያም ዔሊ፣ "በሰላም ሂጂ፤ የእስራኤል አምላክ የለመንሽውን ልመና ይስጥሽ" ብሎ መለሰላት።
\v 18 እርሷም፣ "አገልጋይህ በዐይንህ ፊት ሞገስን ላግኝ" አለችው። ከዚያም መንገዷን ሄደች፥ በላችም፤ ከዚያም በኋላ ፊቷ ሐዘንተኛ አልሆነም።
\s5
\v 19 እነርሱም ማልደው ተነሥተው በእግዚአብሔር ፊት ሰገዱ፥ ከዚያም ወደ መኖሪያቸው ወደ አርማቴም ተመለሱ። ሕልቃና ከሚስቱ ከሐና ጋር ተኛ፥ እግዚአብሔርም አሰባት።
\v 20 ጊዜው ሲደርስም ሐና አረገዘችና ወንድ ልጅ ወለደች። "ከእግዚአብሔር ስለ እርሱ ለምኜ ነበር" ስትል ስሙን ሳሙኤል ብላ ጠራችው።
\s5
\v 21 ሕልቃናና ቤተ ሰቡ በሙሉ ለእግዚአብሔር ዓመታዊውን መሥዋዕት ለማቅረብና ስዕለታቸውን ለመፈጸም ዳግመኛ ወደ ሴሎ ወጡ።
\v 22 ሐና ባሏን "ልጁ ጡት መጥባት እስኪያቆም እኔ አልሄድም፤ ከዚያም በእግዚአብሔር ፊት እንዲታይና ለዘላለም በዚያ እንዲኖር አመጣዋለሁ" ብላው ስለነበረ አልሄደችም።
\v 23 ባሏም ሕልቃና፥ "መልካም መስሎ የታየሽን አድርጊ። ጡት መጥባቱን እስኪያቆም ቆዪ፥ ብቻ እግዚአብሔር ቃሉን ያጽና" አላት። ስለዚህ ልጇ ጡት መጥባቱን እስኪያቆም ድረስ በቤት በመቆየት ተንከባከበችው።
\s5
\v 24 ጡት መጥባቱን ባስቆመችው ጊዜ፥ እርሱን ከሦስት አመት ወይፈን፥ አንድ ኢፍ ዱቄትና አንድ ጠርሙስ ወይን ጋር በሴሎ ወደሚገኘው ወደ እግዚአብሔር ቤት ወሰደችው። ልጁ ገና ሕፃን ነበር።
\v 25 ወይፈኑን አረዱት፤ ልጁንም ወደ ዔሊ አመጡት።
\s5
\v 26 እርሷም፥ "ጌታዬ ሆይ፥ ሕያው እንደመሆንህ፥ እዚህ አጠገብህ ቆማ ወደ እግዚአብሔር የጸለየችው ሴት እኔ ነኝ።
\v 27 ስለዚህ ልጅ ጸለይኩኝ፥ እግዚአብሔርም የለመንኩትን ልመና ሰጥቶኛል።
\v 28 ለእግዚአብሔር ሰጥቼዋለሁ፤ በሕይወት በሚኖርበት ዘመን ሁሉ ለእግዚአብሔር የተሰጠ ይሆናል"። እነርሱም በዚያ ለእግዚአብሔር ሰገዱ።
\s5
\c 2
\p
\v 1 ሐናም እንዲህ በማለት ጸለየች፥ “ልቤ በእግዚአሔር በደስታ ተሞላ። ቀንዴም በእግዚአብሔር ከፍ አለ። በማዳንህ ደስ ብሎኛልና አፌ በጠላቶቼ ላይ ተከፈተ።
\s5
\v 2 አንተን የሚመስልህ የለምና፥ እንደ እግዚአብሔር ቅዱስ የለም፤ እንደ አምላካችን ያለም ዐለት የለም።
\s5
\v 3 ከእንግዲህ አትታበዩ፤ አንዳች የዕብሪት ንግግር ከአፋችሁ አይውጣ። እግዚአብሔር ዐዋቂ አምላክ ነውና፤ ሥራዎች ሁሉ በእርሱ ይመዘናሉ።
\v 4 የኃያላን ሰዎች ቀስት ተሰብሯል፥ የተሰናከሉት ግን ኃይልን ታጥቀዋል።
\s5
\v 5 ጠግበው የነበሩት እንጀራ ለማግኘት ሲሉ ለሥራ ተቀጠሩ፤ ተርበው የነበሩት ረሃብተኝነታቸው አብቅቷል። መካኒቱ እንኳን ሰባት ወልዳለች፥ ብዙ ልጆች የነበሯት ሴት ግን ጠውልጋለች።
\s5
\v 6 እግዚአብሔር ይገድላል፥ ያድናልም። ወደ ሲዖል ያወርዳል፥ ያነሣልም።
\v 7 እግዚአብሔር ድሃ ያደርጋል፥ ባለጸጋም ያደርጋል። እርሱ ያዋርዳል፥ ደግሞም ከፍ ያደርጋል።
\s5
\v 8 እርሱ ድሃውን ከመሬት ያነሣዋል። ምስኪኖችን ከልዑላን ጋር ሊያስቀምጣቸውና የክብርን ወንበር ሊያወርሳቸው ከአመድ ክምር ላይ ብድግ ያደርጋቸዋል። የምድር መሠረቶች የእግዚአብሔር ናቸውና ዓለምን በእነርሱ ላይ አድርጓል።
\s5
\v 9 የታመኑ ሰዎችን እግር ይጠብቃል፥ ማንም በኃይሉ አያሸንፍም፤ ክፉዎች ግን በጨለማ ውስጥ ወዳለው ጸጥታ ይጣላሉ።
\s5
\v 10 እግዚአብሔርን የሚቃወሙ ይደቅቃሉ፤ እርሱ ከሰማይ ያንጎደጉድባቸዋል። እግዚአብሔር በምድር ዳርቻዎች ላይ ይፈርዳል፤ የእርሱ ለሆነው ንጉሥ ኃይልን ይሰጠዋል፥ ለቀባውም ቀንዱን ከፍ ያደርግለታል።”
\s5
\v 11 ከዚያም ሕልቃና በራማ ወደሚገኘው ቤቱ ሄደ። ልጁም በካህኑ በዔሊ ፊት እግዚአብሔርን ያገለግል ነበር።
\s5
\v 12 የዔሊ ወንዶች ልጆች ምንም የማይረቡ ነበሩ። እግዚአብሔርን አያውቁም ነበር።
\v 13 የካህናቱ ልማድ ከሕዝቡ ጋር እንደዚያ ነበርና፥ ማንኛውም ሰው መሥዋዕት ሲያቀርብ፥ ሥጋው እየተቀቀለ እያለ የካህኑ አገልጋይ ሦስት ጣት ያለው ሜንጦ ይዞ ይመጣ ነበር።
\v 14 እርሱም ወደ ድስቱ፥ ወይም ወደ አፍላሉ፥ ወይም ወደ ምንቸቱ ውስጥ ያጠልቀው ነበር። ሜንጦው ያወጣውንም ሁሉ ካህኑ ለራሱ ይወስደው ነበር። ይህንን ወደዚያ ወደ ሴሎ በሚመጡት እስራኤላውያን ሁሉ ላይ ያደርጉ ነበር።
\s5
\v 15 ይልቁንም ስቡን ከማቃጠላቸው በፊት የካህኑ አገልጋይ ይመጣና የሚሠዋውን ሰው፥ “ጥሬውን ብቻ እንጂ የተቀቀለውን ሥጋ ከአንተ አይቀበልምና ለካህኑ እንድጠብስለት ሥጋ ስጠኝ" ይለው ነበር።
\v 16 ሰውየው፥ "መጀመሪያ ስቡን ማቃጠል አለባቸው፥ ከዚያም የፈለከውን ያህል መውሰድ ትችላለህ" ካለው ያ ሰው መልሶ፥ "አይደለም፥ አሁኑኑ ስጠኝ፤ እምቢ ካልክም በግድ እወስደዋለሁ" ይለው ነበር።
\v 17 የእግዚአብሔርን መስዋዕት ንቀዋልና የእነዚህ ወጣቶች ኃጢአት በእግዚአብሔር ፊት እጅግ ታላቅ ነበር።
\s5
\v 18 ትንሹ ልጅ ሳሙኤል ግን ከተልባ እግር ጨርቅ የተሠራ ኤፉድ ለብሶ እግዚአብሔርን ያገለግል ነበር።
\v 19 እናቱም ዓመታዊውን መሥዋዕት ለማቅረብ ከባሏ ጋር በምትመጣበት ጊዜ በየዓመቱ አነስተኛ መደረቢያ ልብስ እየሠራች ታመጣለት ነበር።
\s5
\v 20 ዔሊም ሕልቃናን እና ሚስቱን እንዲህ በማለት ባረካቸው፥”ከእግዚአብሔር በለመነችው ልመና ምክንያት እግዚአብሔር ከዚህች ሴት ተጨማሪ ልጆችን ይስጥህ።“ ከዚያም ወደ ራሳቸው መኖሪያ ተመለሱ።
\v 21 እግዚአብሔር እንደገና ሐናን ረዳት፥ እንደገናም አረገዘች። እርሷም ሦስት ወንዶችና ሁለት ሴት ልጆችን ወለደች። እንዲሁም ትንሹ ልጅ ሳሙኤል በእግዚአብሔር ፊት አደገ።
\s5
\v 22 ዔሊ በጣም አርጅቶ ነበር፤ ልጆቹ በእስራኤላውያን ሁሉ ላይ እያደረጉ ያሉትን በሙሉ እና በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ከሚያገለግሉት ሴቶች ጋር እንደ ተኙ ሰማ።
\v 23 እርሱም እንዲህ አላቸው፥”ስለ ክፉ ሥራችሁ ከዚህ ሕዝብ ሁሉ ሰምቻለሁና እንደዚህ ያሉትን ነገሮች የምትፈጽሙት ለምንድነው?
\v 24 ልጆቼ ሆይ፥ የምሰማው መልካም ወሬ አይደለምና ልክ አይደላችሁም። የእግዚአብሔር ሕዝብ እንዲያምጽ ታደርጉታላችሁ።
\s5
\v 25 አንድ ሰው ሌላውን ቢበድል፥ እግዚአብሔር በእርሱ ላይ ይፈርዳል፤ አንድ ሰው ግን በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአትን ቢሠራ ስለ እርሱ የሚናገር ማን ነው?" እነርሱ ግን እግዚአሔር ሊገድላቸው ፈልጓልና የአባታቸውን ቃል አልሰሙም።
\v 26 ትንሹም ልጅ ሳሙኤል አደገ፥ በእግዚአብሔርና በሰዎችም ፊት ደግሞ በሞገስ እያደገ ሄደ።
\s5
\v 27 አንድ የእግዚአብሔር ሰው ወደ ዔሊ መጥቶ እንዲህ አለው፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ 'በግብፅ አገር፥ በፈርዖን ቤት ባሪያዎች በነበሩ ጊዜ ለአባትህ ቤት ራሴን ገለጥኩኝ፤
\v 28 ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ ካህን እንዲሆነኝ፥ ወደ መሠዊያዬ እንዲወጣ፥ ዕጣን እንዲያጥንልኝ፥ በፊቴም ኤፉድ እንዲለብስ መረጥኩት። የእስራኤል ሕዝብ በእሳት የሚያቀርበውን መባ ሁሉ ለአባትህ ቤት ሰጠሁ።
\s5
\v 29 ታዲያ በማደሪያዬ ያዘዝኩትን መሥዋዕትና መባ የምትንቁት ለምንድነው? በሕዝቤ በእስራኤል ከሚቀርበው መስዋዕት ሁሉ በተመረጠው እየወፈራችሁ ልጆችህን ከእኔ በላይ ያከበርከው ለምንድነው?'
\v 30 የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ 'ቤትህና የአባትህ ቤት ለዘላለም በፊቴ እንዲመላለስ ተስፋ ሰጥቼ ነበር'። አሁን ግን እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ 'ይህንን ማድረግ ከእኔ ይራቅ፥ የሚያከብሩኝን አከብራለሁና የሚንቁኝ ግን ፈጽሞ ይናቃሉ።
\s5
\v 31 ተመልከት፥ ከእንግዲህ በቤትህ ሽማግሌ የሚሆን አንድም ሰው እንዳይኖር ያንተን ኃይልና የአባትህን ቤት ኃይል የምቆርጥበት ቀን ቀርቧል።
\v 32 በማድርበት ስፍራም መከራን ታያለህ። ለእስራኤል መልካም ነገር ቢሰጥም ከእንግዲህ በቤትህ ሽማግሌ የሚሆን አንድ ሰው አይኖርም።
\v 33 ያንተ የሆኑትና ከመሠዊያዬ የማልቆርጣቸው ማናቸውም ዐይኖችህን እንዲያፈዝዙና ሕይወትህን በሐዘን እንዲሞሉት አደርጋቸዋለሁ። በቤተ ሰብህ ውስጥ የተወለዱ ወንዶች ሁሉ ይሞታሉ።
\s5
\v 34 በሁለቱ ወንዶች ልጆችህ በአፍኒን እና በፊንሐስ የሚደርስባቸው ምልክት ይሆንሃል፤ ሁለቱም በአንድ ቀን ይሞታሉ።
\v 35 በልቤና በነፍሴ ውስጥ ያለውን የሚፈጽም ታማኝ ካህን ለራሴ አስነሣለሁ። የማያጠራጥር ቤት እሠራለታለሁ፤ ለዘላለምም በቀባሁት ንጉሥ ፊት ይሄዳል።
\s5
\v 36 ከቤተ ሰብህ የተረፈ ሁሉ ጥቂት ጥሬ ብርና ቁራሽ እንጀራ እንዲሰጠው ለመለመን በዚያ ሰው ፊት መጥቶ ይሰግዳል፥ 'ቁራሽ እንጀራ መብላት እንድችል እባክህ ከካህናቱ ኃላፊነቶች በአንዱ ስፍራ መድበኝ'" ይለዋል።
\s5
\c 3
\p
\v 1 ትንሹ ልጅ ሳሙኤል በዔሊ ሥር ሆኖ እግዚአብሔርን ያገለግል ነበር።
\v 2 በእነዚያ ቀናት የእግዚአብሔር ቃል እምብዛም አይገኝም ነበር፤ ትንቢታዊ ራዕይም አይዘወተርም ነበር። በዚያን ጊዜ፥ ዔሊ ዐይኖቹ ከመፍዘዛቸው የተነሣ አጥርቶ ማየት ባቃተው ጊዜ፥ በአልጋው ላይ ተኝቶ እያለ፥
\v 3 የእግዚአብሔር መብራት ገና አልጠፋም ነበር፥ ሳሙኤል የእግዚአብሔር ታቦት ባለበት በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ተኝቶ ነበር።
\v 4 እግዚአብሔር ሳሙኤልን ጠራው፥ እርሱም፥ “አቤት!” አለው።
\s5
\v 5 ሳሙኤል ወደ ዔሊ ሮጠና፥ “ጠርተኸኛልና ይኸው መጥቻለሁ” አለው፤ ዔሊም፥ “እኔ አልጠራሁህም፤ ተመልሰህ ተኛ” አለው። ስለዚህ ሳሙኤል ሄደና ተኛ።
\v 6 እግዚአብሔር እንደገና፥ “ሳሙኤል” ብሎ ተጣራ። ሳሙኤልም እንደገና ተነሥቶ ወደ ዔሊ ሄደና፥ “ጠርተኸኛልና ይኸው መጥቻለሁ” አለው። ዔሊም፥ "ልጄ ሆይ፥ እኔ አልጠራሁህም፤ ተመልሰህ ተኛ" ብሎ መለሰለት።
\s5
\v 7 ሳሙኤል እግዚአብሔርን ገና አላወቀም ነበር፥ ከእግዚአብሔር ምንም ዓይነት መልዕክት ገና አልተገለጠለትም ነበር።
\v 8 እግዚአብሔር ሳሙኤልን እንደገና ለሦስተኛ ጊዜ ጠራው። ሳሙኤልም እንደገና ተነሥቶ ወደ ዔሊ ሄደና፥ “ጠርተኸኛልና ይኸው መጥቻለሁ” አለው። ከዚያም ልጁን እግዚአብሔር እንደ ጠራው ዔሊ አስተዋለ።
\s5
\v 9 ዔሊም ሳሙኤልን፥ "ሂድና ተመልሰህ ተኛ፤ ደግሞ ከጠራህም፥ 'እግዚአብሔር ሆይ፥ አገልጋይህ እየሰማህ ነውና ተናገር' ማለት አለብህ" አለው። ስለዚህ ሳሙኤል እንደገና ወደ ስፍራው ተመልሶ ተኛ።
\s5
\v 10 እግዚአብሔርም መጥቶ ቆመ፤ እንደ ቀድሞው ሁሉ፥ "ሳሙኤል፥ ሳሙኤል" ብሎ ጠራው። ከዚያም ሳሙኤል፥ "አገልጋይህ እየሰማህ ነውና ተናገር" አለው።
\v 11 እግዚአብሔርም ሳሙኤልን እንዲህ አለው፥ "ተመልከት፥ የሚሰማውን ሁሉ ጆሮውን ጭው የሚያደርግ አንድ ነገር በእስራኤል ላይ አደርጋለሁ።
\s5
\v 12 በዚያም ቀን፥ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ስለ ቤቱ የተናገርኩትን ሁሉ በዔሊ ላይ አመጣበታለሁ።
\v 13 ልጆቹ በራሳቸው ላይ እርግማንን ስላመጡና እርሱም ስላልከለከላቸው፥ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እርሱ ስለሚያውቀው ኃጢአት በቤቱ ላይ እንደምፈርድ ነግሬዋለሁ።
\v 14 በዚህ ምክንያት የቤቱ ኃጢአት በመሥዋዕት ወይም በመባ ይቅር እንዳይባል ለዔሊ ቤት ምያለሁ።"
\s5
\v 15 ሳሙኤል እስኪነጋ ተኛ፤ ከዚያም የእግዚአብሔርን ቤት በሮች ከፈተ። ሳሙኤል ግን ስላየው ራዕይ ለዔሊ ለመንገር ፈራ።
\v 16 ከዚያም ዔሊ ሳሙኤልን ጠርቶ፥ "ልጄ ሳሙኤል ሆይ" አለው። ሳሙኤልም፥ "አቤት!" ብሎ መለሰለት።
\s5
\v 17 እርሱም፥ "የነገረህ ቃል ምንድነው? እባክህ አትደብቀኝ። ከነገረህ ቃል ሁሉ አንዱን ብትደብቀኝ እግዚአብሔር ይህን ያድርግብህ፤ ከዚያም የባሰውን ጨምሮ ያድርግብህ" አለው።
\v 18 ሳሙኤል ሁሉንም ነገር ነገረው፤ ከእርሱም ምንም አልደበቀም። ዔሊም፥ "እርሱ እግዚአብሔር ነው። መልካም መስሎ የታየውን ያድርግ" አለ።
\s5
\v 19 ሳሙኤል አደገ፥ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነበር፥ ከትንቢታዊ ቃሉ ሳይፈጸም የቀረ አንድም አልነበረም።
\v 20 ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ያሉት እስራኤላውያን በሙሉ ሳሙኤል የእግዚአብሔር ነቢይ እንዲሆን መመረጡን ዐወቁ።
\v 21 እግዚአብሔር እንደገና በሴሎ ተገለጠ፥ እርሱም በቃሉ አማካይነት በሴሎ ራሱን ለሳሙኤል ገለጠለት።
\s5
\c 4
\p
\v 1 የሳሙኤልም ቃል ወደ እስራኤላውያን ሁሉ መጣ። በዚህ ወቅት እስራኤላውያን ከፍልስጥኤማውያን ጋር ለመዋጋት ሄዱ። የጦር ሰፈራቸውንም በአቤንኤዘር አደረጉ፥ ፍልስጥኤማውያንም የጦር ሰፈራቸውን በአፌቅ አደረጉ።
\v 2 ፍልስጥኤማውያንም ከእስራኤላውያን ጋር ለመዋጋት ተሰለፉ። ውጊያው በተፋፋመ ጊዜ እስራኤላውያን አራት ሺህ ሰዎቻቸው በውጊያው ሜዳ በመገደላቸው በፍልስጥኤማውያን ተሸነፉ።
\s5
\v 3 ሕዝቡ ወደ ጦር ሰፈሩ በመጣ ጊዜ፥ የእስራኤል ሽማግሌዎች፥ "እግዚአብሔር ዛሬ በፍልስጥኤማውያን ፊት እንድንሸነፍ ያደርገን ለምንድነው? ከእኛ ጋር እንዲሆንና ከጠላቶቻችን ኃይል እንዲያድነን የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት ከሴሎ እናምጣው" አሉ።
\v 4 ስለዚህ ሕዝቡ ወደ ሴሎ ሰዎችን ላኩ። ከዚያ በኪሩቤል ላይ የሚቀመጠውን የሠራዊቱን ጌታ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት አመጡ። ሁለቱ የዔሊ ልጆች አፍኒንና ፊንሐስ ከእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት ጋር በዚያ ነበሩ።
\s5
\v 5 የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት ወደ ጦር ሰፈሩ በመጣ ጊዜ፥ የእስራኤል ሕዝብ በሙሉ በታላቅ ዕልልታ ጮኹ፥ ምድሪቱም አስተጋባች።
\v 6 ፍልስጥኤማውያን የዕልልታውን ድምፅ በሰሙ ጊዜ፥ “ይህ በዕብራውያኑ የጦር ሰፈር የሚሰማው የዕልልታ ድምፅ ምን ማለት ይሆን? አሉ። ከዚያም የእግዚአብሔር ታቦት ወደ ጦር ሰፈሩ እንደ መጣ ተገነዘቡ።
\s5
\v 7 ፍልስጥኤማውያኑ ፈሩ፤ እነርሱም፥”እግዚአብሔር ወደ ጦር ሰፈሩ መጥቷል" አሉ።
\v 8 እነርሱም፥ "ወዮልን! እንደዚህ ያለ ነገር ከአሁን በፊት አልሆነም! ወዮልን! ከዚህ ኃያል አምላክ ክንድ ማን ያድነናል? ይህ በምድረ በዳ ግብፃውያንን በልዩ ልዩ ዓይነት መቅሠፍት የመታቸው አምላክ ነው።
\v 9 እናንተ ፍልስጥኤማውያን በርቱ፥ ወንድነታችሁንም አሳዩ፥ ካልሆነ እነርሱ ባሪያዎቻችሁ እንደነበሩ ባሪያዎቻቸው ትሆናላችሁ። ወንድነታችሁ ይታይ፥ ተዋጉም" አሏቸው።
\s5
\v 10 ፍልስጥኤማውያኑ ተዋጉ፥ እስራኤላውያንም ተሸነፉ። እያንዳንዱ ወደ ቤቱ ሸሸ፥ የተገደሉትም እጅግ ብዙ ነበሩ፤ ከእስራኤል ሠላሳ ሺህ እግረኛ ወታደር ወደቀ።
\v 11 የእግዚአብሔር ታቦት ተወሰደ፥ ሁለቱ የዔሊ ልጆች አፍኒንና ፊንሐስም ሞቱ።
\s5
\v 12 በዚያው ቀን አንድ ብንያማዊ ከውጊያው መስመር ወደ ሴሎ በሩጫ መጣ፥ በደረሰ ጊዜ ልብሱን ቀድዶና በራሱ ላይ አፈር ነስንሶ ነበር።
\v 13 እርሱ በደረሰ ጊዜ፥ ዔሊ ስለ እግዚአብሔር ታቦት በመስጋት ልቡ ታውኮበት ስለነበረ በመንገዱ ዳር ወንበሩ ላይ ተቀምጦ ነበር። ሰውየው ወደ ከተማ ገብቶ ወሬውን በነገራቸው ጊዜ፥ ከተማው በሙሉ አለቀሱ።
\s5
\v 14 ዔሊ የልቅሶውን ድምፅ በሰማ ጊዜ፥ “የዚህ ሁካታ ትርጉሙ ምንድነው?” አለ። ሰውየው ፈጥኖ መጣና ለዔሊ ነገረው።
\v 15 በዚህ ጊዜ ዔሊ የዘጠና ስምንት ዓመት ሽማግሌ ነበር፤ ዓይኖቹ አጥርተው አያዩም ነበር፥ ማየትም አይችልም ነበር።
\s5
\v 16 ሰውየውም ዔሊን፥ “ከውጊያው መስመር የመጣሁት እኔ ነኝ። ዛሬ ከውጊያው ሸሽቼ መጣሁ” አለው። ዔሊም፥ “ልጄ ሆይ፥ ነገሩ እንዴት እየሆነ ነው?” አለው።
\v 17 ወሬውን ያመጣው ያ ሰው መልሶ፥ “እስራኤላውያን ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ። ደግሞም በሕዝቡ መካከል ታላቅ ዕልቂት ሆኗል። ሁለቱ ወንዶች ልጆችህ፥ አፍኒን እና ፊንሐስ ሞተዋል፥ የእግዚአብሔር ታቦትም ተወስዷል” አለው።
\s5
\v 18 እርሱም የእግዚአብሔርን ታቦት ጠቅሶ በተናገረ ጊዜ፥ ዔሊ በመግቢያው በር አጠገብ ከተቀመጠበት ወንበር ላይ ወደ ኋላው ወደቀ። ስላረጀና ውፍረት ስለነበረው አንገቱ ተሰብሮ ሞተ። እርሱም በእስራኤላውያን ላይ ለአርባ ዓመታት ፈርዶ ነበር።
\s5
\v 19 በዚህ ጊዜ ምራቱ የፊንሐስ ሚስት አርግዛ የመውለጃ ሰዓቷ ደርሶ ነበር። የእግዚአብሔር ታቦት መማረኩን፥ ዐማቷና ባሏ መሞታቸውን በሰማች ጊዜ ተንበርክካ ወለደች፥ ነገር ግን ምጡ አስጨነቃት።
\v 20 ለመሞት በምታጣጥርበት ጊዜ ያዋልዷት የነበሩ ሴቶች፥ "ወንድ ልጅ ወልደሻልና አትፍሪ“ አሏት። እርሷ ግን አልመለሰችላቸውም ወይም የነገሯትን በልቧ አላኖረችውም።
\s5
\v 21 እርሷም የእግዚአብሔር ታቦት ስለተማረከና ስለ ዐማቷና ስለ ባልዋ "ክብር ከእስራኤል ተለየ!" ስትል ልጁን ኤካቦድ ብላ ጠራችው።
\v 22 እርሷም፥”የእግዚአብሔር ታቦት ስለተማረከ ክብር ከእስራኤል ተለየ!" አለች።
\s5
\c 5
\p
\v 1 ፍልስጥኤማውያንም የእግዚአብሔርን ታቦት በመማረክ ከአቤንኤዘር ወደ አሽዶድ አመጡት።
\v 2 እነርሱም የእግዚአብሔርን ታቦት ማርከው ወደ ዳጎን ቤት ወስደው በዳጎን አጠገብ አቆሙት።
\v 3 የአሽዶድ ሰዎች በቀጣዩ ቀን ማልደው በተነሡ ጊዜ፥ ዳጎን በእግዚአብሔር ታቦት ፊት በምድር ላይ በግምባሩ ተደፍቶ አዩ። ስለዚህ ዳጎንን አንሥተው በስፍራው መልሰው አቆሙት።
\s5
\v 4 ነገር ግን በማግስቱ ማልደው በተነሡ ጊዜ፥ ዳጎን በእግዚአብሔር ታቦት ፊት በምድር ላይ በግምባሩ ተደፍቶ አዩ። በደጁ መግቢያ ውስጥ የዳጎን ራሱና እጆቹ ተሰብረው ወድቀው ነበር። የቀረው የዳጎን ሌላው የአካል ክፍሉ ብቻ ነበር።
\v 5 ለዚህ ነው እስካሁን እንኳን የዳጎን ካህናትና ሌላ ማንኛውም ሰው በአሽዶድ ወደሚገኘው ወደ ዳጎን ቤት በሚመጣበት ጊዜ የዳጎንን ደጅ መግቢያ ሳይረግጥ የሚያልፈው።
\s5
\v 6 የእግዚአብሔር እጅ በአሽዶድ ሰዎች ላይ ከብዶ ነበር። በአሽዶድና በዙሪያው ባሉት ላይ ጥፋትን በማምጣት በእባጭ መታቸው።
\v 7 የአሽዶድ ሰዎች የሆነባቸውን ባስተዋሉ ጊዜ፥ “እጁ በእኛና በአምላካችን በዳጎን ላይ ከብዳለችና የእስራኤል አምላክ ታቦት ከእኛ ጋር መቆየት የለበትም” አሉ።
\s5
\v 8 ስለዚህ ወደ ፍልስጥኤማውያን ገዢዎች ልከው በአንድ ላይ ሰበሰቧቸው፤ እነርሱም፥ "በእስራኤል አምላክ ታቦት ላይ ምን እናድርግ?" አሏቸው። እነርሱም፥ “የእስራኤል አምላክ ታቦት ወደ ጌት ይምጣ” ብለው መለሱላቸው። የእስራኤልን አምላክ ታቦት ወደዚያ ወሰዱት።
\v 9 ነገር ግን ወደዚያ ካመጡት በኋላ የእግዚአብሔር እጅ በከተማዪቱ ላይ ሆነ፥ ታላቅ መደናገርንም አደረገባቸው። ልጅና ዐዋቂውን፥ የከተማውን ሰዎች አስጨነቀ፤ ሰውነታቸውም በእባጭ ተወረረ።
\s5
\v 10 ስለዚህ የእግዚአብሔርን ታቦት ወደ አቃሮን ላኩት። ነገር ግን የእግዚአብሔር ታቦት ወደ አቃሮን እንደ መጣ፥ አቃሮናውያን፥ "እኛንና ሕዝባችንን እንዲገድል የእስራኤልን አምላክ ታቦት ወደ እኛ አምጥተዋል" በማለት ጮኹ።
\s5
\v 11 ስለዚህ ወደ ፍልስጥኤማውያን ገዢዎች በመላክ ሁሉንም በአንድ ላይ ሰበሰቧቸው፤ እነርሱም፥ “እኛንና ሕዝባችንን እንዳይገድል የእስራኤልን አምላክ ታቦት ላኩት፥ ወደ ስፍራውም ይመለስ" አሏቸው። በዚያ የእግዚአብሔር እጅ እጅግ ስለበረታባቸው በከተማው ሁሉ የሞት ድንጋጤ ነበረ።
\v 12 ከሞት የተረፉት ሰዎች በእባጮቹ ይሠቃዩ ስለነበር የከተማዪቱ ጩኸት ወደ ሰማያት ወጣ።
\s5
\c 6
\p
\v 1 የእግዚአብሔር ታቦት በፍልስጥኤማውያን አገር ከተቀመጠ ሰባት ወር ሆነው።
\v 2 ከዚያም የፍልስጥኤም ሰዎች ካህናትንና ጠንቋዮችን ጠርተው፥ “የእግዚአብሔርን ታቦት ምን እናድርገው? ወደ አገሩ እንዴት አድርገን መመለስ እንዳለብን ንገሩን” አሉአቸው።
\s5
\v 3 ካህናቱና ጠንቋዮቹም፥ "የእስራኤልን አምላክ ታቦት መልሳችሁ የምትልኩ ከሆነ ያለስጦታ አትላኩት፤ በተቻለ መጠን የበደል መስዋዕትም ላኩለት። ከዚያም ትፈወሳላችሁ፥ እናንተም እስካሁን ድረስ እጁን ከላያችሁ ላይ ያላነሣው ለምን እንደሆነ ታውቃላችሁ"።
\v 4 ሕዝቡም፥ “የምንመልሰው የበደል መስዋዕት ምን መሆን አለበት?”አሏቸው። እነርሱም እንዲህ በማለት መለሱላቸው፥ "አምስት የወርቅ እባጮችንና አምስት የወርቅ አይጦችን፥ በቁጥር አምስት መሆኑም የፍልስጥኤማውያንን ገዢዎች ቁጥር የሚወክል ነው። እናንተንና ገዢዎቻችሁን የመታው ተመሳሳይ መቅሰፍት ነውና።
\s5
\v 5 ስለዚህ ምድራችንን ባጠፋው በእባጮቻችሁና በአይጦቻችሁ አምሳል ማድረግ አለባችሁ፥ ለእስራኤል አምላክም ክብርን ስጡ። ምናልባት እጁን ከእናንተ፥ ከአማልክቶቻችሁና ከምድሪቱ ላይ ያነሣ ይሆናል።
\v 6 ግብፃውያንና ፈርዖን ልባቸውን እንዳደነደኑ ለምን ልባችሁን ታደነድናላችሁ? ያን ጊዜ ነበር የእስራኤል አምላክ ክፉን ያደረገባቸው፤ ታዲያ ግብፃውያኑ ሕዝቡን አልለቀቋቸውም?እነርሱስ ከዚያ አልወጡም?
\s5
\v 7 እንግዲህ አዲስ ሠረገላና እስካሁን ቀንበር ያልተጫነባቸውን ሁለት የሚያጠቡ ላሞች አዘጋጁ። ላሞቹን በሠረገላው ጥመዷቸው፥ እምቦሳዎቻቸውን ግን ከእነርሱ ለይታችሁ በቤት አስቀሩአቸው።
\v 8 ከዚያም የእግዚአብሔርን ታቦት ወስዳችሁ በሠረገላው ላይ አኑሩት። የበደል መስዋዕት አድርጋችሁ የምትመልሱለትን የወርቁን አምሳያዎች በሳጥን ውስጥ አድርጋችሁ በአንደኛው ጎኑ አስቀምጡ። ከዚያም ልቀቁትና በራሱ መንገድ እንዲሄድ ተዉት።
\v 9 ከዚያም ተመልከቱ፥ ወደ ራሱ ምድር፥ ወደ ቤት ሳሚስ በመንገዱ ከሄደ፥ ይህንን ታላቅ ጥፋት ያመጣው እግዚአብሔር ነው ማለት ነው። ካልሆነ ግን፥ ይህ በአጋጣሚ የደረሰብን እንጂ የመታን የእርሱ እጅ እንዳልሆነ እናውቃለን"።
\s5
\v 10 ሰዎቹም እንደተነገራቸው አደረጉ፤ ሁለት የሚያጠቡ ላሞችን ወሰዱና በሠረገላው ጠመዷቸው፥ እምቦሳዎቻቸውንም ከቤት እንዳይወጡ አደረጉ።
\v 11 የወርቁን አይጥና የእባጮቻቸው ምሳሌ የሆነውን ከያዘው ሳጥን ጋር የእግዚአብሔርን ታቦት በሠረገላው ላይ አደረጉት።
\v 12 ላሞቹም በቤት ሳሚስ አቅጣጫ ቀጥ ብለው ሄዱ። እነርሱም በዚያው ጎዳና፥ ወደ ግራም ወደ ቀኝም ሳይሉ ቁልቁል ሄዱ። የፍልስጥኤማውያን ገዢዎችም እስከ ቤት ሳሚስ ዳርቻ ድረስ ከበስተኋላቸው ተከተሏቸው።
\s5
\v 13 በዚህ ጊዜ የቤት ሳሚስ ሰዎች በሸለቆው ውስጥ ስንዴአቸውን በማጨድ ላይ ነበሩ። ቀና ብለው ባዩ ጊዜ ታቦቱን ተመለከቱ፥ ደስም አላቸው።
\s5
\v 14 ሠረገላው የቤት ሳሚስ ሰው ወደሆነው ወደ ኢያሱ እርሻ መጥቶ በዚያ ቆመ። በዚያም ትልቅ ቋጥኝ ነበር፥ የሠረገላውን እንጨት በመፍለጥ ላሞቹን ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገው አቀረቡ።
\v 15 ሌዋውያኑ የእግዚአብሔርን ታቦትና አብሮት የነበረውን፥ የወርቁ ምስሎች የነበሩበትን ሳጥን፥ ከሠረገላው አውርደው በትልቁ ቋጥኝ ላይ አስቀመጡት። በዚያው ቀን የቤት ሳሚስ ሰዎች ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት አቀርቡ፥ መሥዋዕቶችንም ሠዉ።
\s5
\v 16 አምስቱ የፍልስጥኤማውያን ገዢዎች ይህንን ባዩ ጊዜ በዚያው ቀን ወደ አቃሮን ተመለሱ።
\s5
\v 17 የፍልስጥኤም ሰዎች ለእግዚአብሔር የበደል መስዋዕት አድርገው የመለሷቸው የወርቅ እባጮች እነዚህ ናቸው፤ አንዱ ስለ አሽዶድ፥ አንዱ ስለ ጋዛ፥ አንዱ ስለ አስቀሎና፥ አንዱ ስለ ጌት እና አንዱ ስለ አቃሮን ነበር።
\v 18 የወርቁ አይጥ አምስቱ ገዢዎች ከሚገዟቸው የተመሸጉ የፍልስጥኤማውያን ከተሞችና መንደሮች ቁጥር ሁሉ ጋር ቁጥሩ ተመሳሳይ ነበር። የእግዚአብሔርን ታቦት ያስቀመጡበት ያ ታላቅ ቋጥኝ በቤት ሳሚስ በኢያሱ እርሻ ውስጥ እስከ ዛሬ ድረስ ምስክር ሆኖ ይኖራል።
\s5
\v 19 ወደ ታቦቱ ውስጥ ተመልክተዋልና እግዚአብሔር ከቤት ሳሚስ ሰዎች ጥቂቶቹን መታቸው። እርሱም ሰባ ሰዎችን ገደለ። እግዚአብሔር ሕዝቡን ክፉኛ ስለመታቸው ሕዝቡ አለቀሱ።
\v 20 የቤት ሳሚስ ሰዎችም፥ “በዚህ ቅዱስ አምላክ በእግዚአብሔር ፊት መቆም የሚችል ማነው? ከእኛስ ወደ ማን ይሄዳል?” አሉ።
\s5
\v 21 በቂርያትይዓሪም ወደሚኖሩት መልዕክተኞች ልከው፥ “ፍልስጥኤማውያን የእግዚአብሔርን ታቦት መልሰዋል፤ ወደዚህ ውረዱና ውሰዱት” አሏቸው።
\s5
\c 7
\p
\v 1 የቂርያትይዓሪም ሰዎች መጥተው የእግዚአብሔርን ታቦት ወሰዱ፥ በኮረብታው ላይ ወዳለው ወደ አሚናዳብ ቤት አስገቡት። የእግዚአብሔርን ታቦት እንዲጠብቅ ልጁን አልዓዛርን ለዚህ አገልግሎት ለዩት።
\v 2 ታቦቱ በቂርያትይዓሪም ከተቀመጠ ብዙ ዓመት አለፈው፥ ሃያ ዓመትም ሆነው። የእስራኤል ቤት ሁሉ አዘኑ፥ ወደ እግዚአብሔር ለመመለስም ፈለጉ።
\s5
\v 3 ሳሙኤል የእስራኤልን ሕዝብ በሙሉ እንዲህ አላቸው፥ "በሙሉ ልባችሁ ወደ እግዚአብሔር የምትመለሱ ከሆነ እንግዶቹን አማልክትና አስታሮትን ከመካከላችሁ አስወግዱ፥ ልባችሁን ወደ እግዚአብሔር መልሱ፥ እርሱንም ብቻ አምልኩት፥ ያን ጊዜ ከፍልስጥኤማውያን እጅ ያድናችኋል"።
\v 4 ከዚያም የእስራኤል ሕዝብ በኣልንና አስታሮትን አስወገዱ፥ እግዚአብሔርን ብቻም አመለኩ።
\s5
\v 5 ከዚያም ሳሙኤል፥ "እስራኤልን በሙሉ ምጽጳ ላይ ሰብስቡ፥ እኔም ስለ እናንተ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ“ አላቸው።
\v 6 እነርሱም በምጽጳ ተሰበሰቡ፥ ውሃም ቀድተው በእግዚአብሔር ፊት አፈሰሱ። በዚያም ቀን ጾሙ፥”በእግዚአብሔር ላይም ኃጢአትን አድርገናል“ አሉ። ሳሙኤል በእስራኤል ሕዝብ ላይ የፈረደውና ሕዝቡን የመራው በዚያ ነበር።
\s5
\v 7 የእስራኤል ሕዝብ በምጽጳ መሰብሰባቸውን ፍልስጥኤማውያን በሰሙ ጊዜ፥ የፍልስጥኤማውያን ገዢዎች እስራኤልን ለማጥቃት መጡ። የእስራኤል ሰዎች ይህንን በሰሙ ጊዜ ፍልስጥኤማውያንን ፈሩ።
\v 8 ከዚያም የእስራኤል ሕዝብ ሳሙኤልን፥”ከፍልስጥኤማውያን እጅ እንዲያድነን፥ ስለ እኛ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር መጣራትህን አታቁም“ አሉት።
\s5
\v 9 ሳሙኤል የሚጠባ ግልገል ወስዶ ለእግዚአብሔር ሙሉውን የሚቃጠል መስዋዕት አድርጎ ሠዋው። ከዚያም ሳሙኤል ስለ እስራኤል ወደ እግዚአብሔር ጮኸ፥ እግዚአብሔርም መለሰለት።
\s5
\v 10 ሳሙኤል የሚቃጠለውን መስዋዕት በማቅረብ ላይ እያለ ፍልስጥኤማውያን እስራኤልን ለማጥቃት ቀረቡ። ነገር ግን በዚያን ቀን እግዚአብሔር በፍልስጥኤማውያን ላይ በታላቅ ድምፅ አንጎደጎደባቸው፥ አሸበራቸውም፥ በእስራኤልም ፊት ተሸንፈው ሸሹ።
\v 11 የእስራኤል ሰዎችም ከምጽጳ ተነሥተው ፍልስጥኤማውያንን አሳደዱ፥ ከቤትካር በታች እስካለው ቦታ ድረስ ተከትለው ገደሏቸው።
\s5
\v 12 ከዚያም ሳሙኤል አንድ ድንጋይ አንሥቶ በምጽጳና በሼን መካከል አቆመው።”እስካሁን ድረስ እግዚአብሔር ረድቶናል“ በማለት አቤንኤዘር ብሎ ጠራው።
\s5
\v 13 ስለዚህ ፍልስጥኤማውያን ተሸነፉ፥ የእስራኤልን ድንበርም አልፈው አልገቡም። በሳሙኤል የሕይወት ዘመን ሁሉ የእግዚአብሔር እጅ በፍልስጥኤማውያን ላይ ከብዳ ነበር።
\v 14 ፍልስጥኤማውያን ከእስራኤል የወሰዷቸው ከአቃሮን እስከ ጌት ያሉ መንደሮች ለእስራኤል ተመለሱላቸው፤ እስራኤላውያን ድንበሮቻቸውን ከፍልስጥኤማውያን አስመለሱ። በዚያን ጊዜ በእስራኤላውያንና በአሞራውያን መካከል ሰላም ነበረ።
\s5
\v 15 ሳሙኤል በሕይወት ዘመኑ ሁሉ በእስራኤል ላይ ፈረደ።
\v 16 በየዓመቱ ወደ ቤቴል፥ ወደ ጌልገላና ወደ ምጽጳ ይዘዋወር ነበር። በእነዚህ ስፍራዎች ሁሉ በእስራኤላውያን መካከል ባሉ አለመግባባቶች ላይ ይፈርድ ነበር።
\v 17 ከዚያም መኖሪያው በዚያ ነበርና ወደ ራማ ይመለስ ነበር፤ በዚያም ደግሞ በእስራኤላውያን አለመግባባት ላይ ይፈርድ ነበር። በዚያም ደግሞ ለእግዚአብሔር መሠዊያን ሠራ።
\s5
\c 8
\p
\v 1 ሳሙኤል በሸመገለ ጊዜ ልጆቹን በእስራኤል ላይ ፈራጆች አድርጎ ሾማቸው።
\v 2 የመጀመሪያ ልጁ ስም ኢዮኤል፥ የሁለተኛው ስም አብያ ነበር። እነርሱም በቤርሳቤህ ፈራጆች ነበሩ።
\v 3 ነገር ግን ልጆቹ ነውረኛ ጥቅም ፈላጊዎች ሆኑ እንጂ በእርሱ መንገድ አልሄዱም። ጉቦ እየተቀበሉ ፍትሕን አዛቡ።
\s5
\v 4 ከዚያም የእስራኤል ሽማግሌዎች በአንድነት ተሰብስበው በራማ ወደሚኖረው ወደ ሳሙኤል መጡ።
\v 5 እነርሱም፥ "ተመልከት፥ አንተ ሸምግለሃል፥ ልጆችህም በመንገድህ አይሄዱም። እንደ ሌሎች ሕዝቦች ሁሉ እንዲፈርድልን ንጉሥ አንግሥልን" አሉት።
\s5
\v 6 ነገር ግን፥ “እንዲፈርድልን ንጉሥ ስጠን” ባሉት ጊዜ ነገሩ ሳሙኤልን ቅር አሰኘው። ስለዚህ ሳሙኤል ወደ እግዚአብሔር ጸለየ።
\v 7 እግዚአብሔርም ሳሙኤልን እንዲህ አለው፥ “በላያቸው ላይ ንጉሥ እንዳልሆን የተቃወሙት እኔን እንጂ አንተን አይደለምና በሚሉህ ነገር ሁሉ የሕዝቡን ቃል ታዘዝ።
\s5
\v 8 ከግብፅ ካወጣዃቸው ጊዜ ጀምሮ እኔን ትተው ሌሎች አማልክቶችን በማምለክ ሲያደርጉት የነበረውን ያንኑ አሁን እያደረጉ ነው፤ በአንተም ላይ የሚያደርጉት እንደዚሁ ነው።
\v 9 አሁንም የሚሉህን ስማቸው፤ ነገር ግን በላያቸው የሚገዛው ንጉሥ የሚያደርግባቸውን እንዲያውቁ አጥብቀህ አስጠንቅቃቸው"።
\s5
\v 10 ስለዚህ ሳሙኤል ንጉሥ ለጠየቀው ሕዝብ የእግዚአብሔርን ቃል በሙሉ ነገራቸው።
\v 11 እርሱም እንዲህ አላቸው፥ "ንጉሡ በላያችሁ ላይ የሚገዛው እንዲህ ነው። ወንዶች ልጆቻችሁን ወስዶ ፈረሰኞች እንዲሆኑና በሠረገላዎቹ ፊት እንዲሮጡ በሠረገላዎቹ ላይ ይሾማቸዋል።
\v 12 እርሱም ለራሱ ሻለቃዎችንና ሃምሳ አለቃዎችን ይሾማል። አንዳንዶቹ መሬቱን እንዲያርሱ፥ ሌሎቹም እህሉን እንዲያጭዱ፥ አንዳንዶቹ የጦር መሳሪያዎችንና ሌሎቹም የሠረገላ ዕቃዎችን እንዲሠሩለት ያደርጋቸዋል።
\s5
\v 13 ሴቶች ልጆቻችሁን ደግሞ ሽቶ ቀማሚዎች፥ ወጥ ሠሪዎችና እንጀራ ጋጋሪዎች እንዲሆኑ ይወስዳቸዋል።
\v 14 በጣም ምርጥ የሆነውን መሬታችሁን፥ የወይን ቦታችሁንና የወይራ ዛፋችሁን ወስዶ ለአገልጋዮቹ ይሰጣቸዋል።
\v 15 ከእህላችሁና ከወይናችሁ አንድ ዐሥረኛውን ወስዶ ለሹማምንቱና ለአገልጋዮቹ ይሰጣቸዋል።
\s5
\v 16 ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮቻችሁን፥ ከወጣት ልጆቻችሁና ከአህዮቻችሁ የተመረጡትን ይወስዳል፤ ሁሉንም ለእርሱ እንዲሠሩ ያደርጋቸዋል።
\v 17 ከበግና ከፍየል መንጋዎቻችሁ አንድ ዐሥረኛውን ይወስዳል፥ እናንተም አገልጋዮቹ ትሆናላችሁ።
\v 18 በዚያም ቀን ለራሳችሁ ስለመረጣችሁት ንጉሥ ታለቅሳላችሁ፤ ነገር ግን በዚያን ቀን እግዚአብሔር አይመልስላችሁም”።
\s5
\v 19 ሕዝቡ ግን ሳሙኤልን ለመስማት እምቢ አሉ፤
\v 20 ሳሙኤልንም፥ “አይሆንም፥ ንጉሣችን እንዲፈርድልን፥ በፊታችን እንዲሄድና ጦርነቶቻችንን እንዲዋጋልን፥ እንደ ሌሎች ሕዝቦች ሁሉ ለእኛም ንጉሥ ሊሆንልን ይገባል” አሉት።
\s5
\v 21 ሳሙኤል የሕዝቡን ቃል ሁሉ በሰማ ጊዜ እርሱም በእግዚአብሔር ጆሮ ደግሞ ተናገረው።
\v 22 እግዚአብሔርም ሳሙኤልን፥ “ቃላቸውን ታዘዝና ንጉሥ አድርግላቸው” አለው። ስለዚህ ሳሙኤል የእስራኤልን ሰዎች፥ “እያንዳንዱ ወደገዛ ከተማው ይሂድ” አላቸው።
\s5
\c 9
\p
\v 1 ከብንያም ወገን ጽኑ ኃያል የሆነ አንድ ሰው ነበር። ስሙ ቂስ ሲሆን እርሱም የአቢኤል ልጅ፥ የጽሮር ልጅ፥ የብኮራት ልጅ፥ የብንያማዊው የአፌቅ ልጅ ነበር።
\v 2 እርሱም ሳኦል የሚባል መልከ መልካም ወጣት ልጅ ነበረው። ከእርሱ የሚበልጥ መልከ መልካም ሰው በእስራኤል ሕዝብ መካከል አልነበረም። ከሕዝቡ ሁሉ ይልቅ ቁመቱ ረጅም ነበር።
\s5
\v 3 የሳኦል አባት የቂስ ሴት አህዮች ጠፍተው ነበር። ስለዚህ ቂስ ልጁን ሳኦልን፥ “ከአገልጋዮቻችን አንዱን ውሰድ፤ ተነሥናም አህዮቹን ፈልግ” አለው።
\v 4 ስለዚህ ሳኦል በኮረብታማው በኤፍሬም አገር በኩል አልፎ ወደ ሻሊሻ ምድር ሄደ፥ ነገር ግን አላገኟቸውም። ከዚያም በሻዕሊም ምድር በኩል አለፉ፥ ነገር ግን በዚያ አልነበሩም። ከዚያም በብንያማውያን ምድር በኩል አለፉ፥ ነገር ግን አላገኟቸውም።
\s5
\v 5 ወደ ጹፍ ምድር በመጡ ጊዜ፥ ሳኦል ከእርሱ ጋር የነበረውን አገልጋዩን፥ "ና እንመለስ፥ አለበለዚያ አባቴ ስለ አህዮቹ ማሰቡን ትቶ ስለ እኛ መጨነቅ ይጀምራል" አለው።
\v 6 ነገር ግን አገልጋዩ እንዲህ አለው፥ “ስማኝ፥ በዚህ ከተማ ውስጥ አንድ የእግዚአብሔር ሰው አለ። እርሱም የተከበረ ሰው ነው፤ የሚናገረው ነገር ሁሉ ይፈጸማል። ወደዚያ እንሂድ፤ በየትኛው አቅጣጫ መሄድ እንዳለብን ሊነግረን ይችል ይሆናል"።
\s5
\v 7 ከዚያም ሳኦል አገልጋዩን፥ "ታዲያ ወደ እርሱ የምንሄድ ከሆነ ለዚያ ሰው ምን ልንሰጠው እንችላለን? እንጀራው ከከረጢታችን አልቋል፥ ለእግዚአብሔር ሰው የምናቀርበው ምንም ስጦታ የለንም። ምን አለን?"አለው።
\v 8 አገልጋዩም ለሳኦል፥ "ይኸውና፥ የሰቅል ጥሬ ብር አንድ አራተኛው አለኝ፥ በየትኛው አቅጣጫ መሄድ እንዳለብን እንዲነግረን ለእግዚአብሔር ሰው እሰጠዋለሁ" ሲል መለሰለት።
\s5
\v 9 (ቀደም ሲል በእስራኤል ውስጥ፥ አንድ ሰው የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመጠየቅ በሚሄድበት ጊዜ፥ "ኑ፥ ወደ ባለ ራዕዩ እንሂድ" ይል ነበር። የዛሬው ነቢይ ቀደም ሲል ባለ ራዕይ ተብሎ ይጠራ
\v 10 ነበር።)ከዚያም ሳኦል አገልጋዩን፥”መልካም ብለሃል። ና፥ እንሂድ“ አለው። ስለዚህ የእግዚአብሔር ሰው ወደነበረበት ከተማ ሄዱ።
\v 11 ኮረብታው ላይ ወዳለው ከተማ በመውጣት ላይ እያሉ ወጣት ሴቶች ውሃ ለመቅዳት ሲወጡ አገኟቸው፤ ሳኦልና አገልጋዩም፥”ባለ ራዕዩ በዚህ አለ? “ በማለት ጠየቋቸው።
\s5
\v 12 እነርሱም እንዲህ በማለት መለሱላቸው፥ "አዎን፤ ተመልከቱ፥ እንዲያውም ከፊታችሁ እየቀደመ ነው። ዛሬ ሕዝቡ በኮረብታው ራስ ላይ ስለሚሠዉ ወደ ከተማው ይመጣልና ፍጠኑ።
\v 13 ወደ ከተማው እንደገባችሁ ለመብላት ወደ ኮረብታው ራስ ከመውጣቱ በፊት ታገኙታላችሁ። መሥዋዕቱን የሚባርከው እርሱ ስለሆነ፥ እርሱ ከመምጣቱ በፊት ሕዝቡ አይበሉም፤ ከዚያ በኋላም የተጋበዙት ይበላሉ። ወዲያውኑ ታገኙታላችሁና አሁን ወደ ላይ ውጡ።”
\s5
\v 14 ስለዚህ ወደ ላይ ወደ ከተማው ወጡ። ወደ ከተማይቱ በመግባት ላይ እያሉም ሳሙኤል ወደ ኮረብታው ራስ ለመውጣት በእነርሱ አቅጣጫ ሲመጣ አዩት።
\s5
\v 15 ሳኦል ከመምጣቱ ከአንድ ቀን በፊት እግዚአብሔር ለሳሙኤል እንዲህ ሲል ገልጦለት ነበር፥
\v 16 “ነገ በዚህ ሰዓት ከብንያም ምድር አንድ ሰው እልክልሃለሁ፥ በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መስፍን እንዲሆን ትቀባዋለህ። እርሱም ሕዝቤን ከፍልስጥኤማውያን እጅ ያድናቸዋል። እርዳታ በመፈለግ መጮኻቸው ወደ እኔ ደርሷልና ሕዝቤን በርኅራኄ ተመልክቻለሁ።”
\s5
\v 17 ሳሙኤል ሳኦልን ባየው ጊዜ፥ እግዚአብሔር እንዲህ አለው፥”ስለ እርሱ የነገርኩህ ሰው ይህ ነው! ሕዝቤን የሚገዛው ሰው እርሱ ነው።“
\v 18 ከዚያም ሳኦል በበሩ አጠገብ ወደ ሳሙኤል ቀረብ ብሎ፥”የባለ ራዕዩ ቤት የት እንደሆነ ንገረኝ“ አለው።
\v 19 ሳሙኤልም ለሳኦል እንዲህ በማለት መለሰለት፥”ባለ ራዕዩ እኔ ነኝ። ከእኔ በፊት ቀድማችሁ ወደ ኮረብታው ራስ ውጡ፥ ዛሬ ከእኔ ጋር ትበላላችሁና። ነገ ጠዋት በአዕምሮህ ያለውን ነገር ሁሉ እነግርህና አሰናብትሃለሁ።
\s5
\v 20 ከሦስት ቀን በፊት ጠፍተው የነበሩት አህዮች ተገኝተዋልና ስለ እነርሱ አታስብ። የእስራኤል ሁሉ ምኞት የተቀመጠው በማን ላይ ነው? በአንተና በአባትህ ቤት ሁሉ ላይ አይደለም? “
\v 21 ሳኦልም፥ "ከእስራኤል ነገዶች ትንሹ የሆነው ብንያማዊ አይደለሁም? ጎሳዬስ ከብንያም ነገድ ጎሳዎች ሁሉ የመጨረሻው አይደለም? ታዲያ እንዲህ ባለ ሁኔታ ለምን ትናገረኛለህ?"ሲል መለሰለት።
\s5
\v 22 ከዚያም ሳሙኤል ሳኦልንና አገልጋዩን ወደ አዳራሹ አስገብቶ ሠላሳ ከሚያህሉ ከተጋበዙት ሰዎች ከፍ ባለው ስፍራ ላይ አስቀመጣቸው።
\s5
\v 23 ሳሙኤልም ወጥ ሠሪውን፥ "'ለብቻ አስቀምጠው' ብዬ የሰጠሁህን ድርሻ አምጣው" አለው።
\v 24 ወጥ ሠሪውም በመሥዋዕቱ ጊዜ ያነሣውን ጭኑንና ከእርሱ ጋር ያለውን አምጥቶ በሳኦል ፊት አኖረው። ከዚያም ሳሙኤል፥ "የተቀመጠልህን ተመልከት! ለአንተ እስከተወሰነው ሰዓት ድረስ የቆየልህ ነውና ብላው። አሁን 'ሕዝቡን ጋብዣለሁ' ማለት ትችላለህ" አለው። ስለዚህ በዚያን ቀን ሳኦል ከሳሙኤል ጋር በላ።
\s5
\v 25 ከኮረብታው ራስ ወደ ከተማው በወረዱ ጊዜ፥ በቤቱ የጣሪያ ወለል ላይ ሳሙኤል ከሳኦል ጋር ተነጋገረ።
\v 26 ከዚያም በነጋ ጊዜ ሳሙኤል በጣሪያው ወለል ላይ ሳኦልን ተጣርቶ፥ "መንገድህን እንድትሄድ አሰናብትህ ዘንድ ተነሥ" አለው። ስለዚህ ሳኦል ተነሣ፥ እርሱና ሳሙኤል ሁለቱም ወደ ጎዳናው ሄዱ።
\s5
\v 27 ወደ ከተማው ዳርቻ በመሄድ ላይ እያሉ፥ ሳሙኤል ሳኦልን፥ "አገልጋዩ ከፊታችን ቀድሞ እንዲሄድ ንገረው፥ (እርሱም ቀድሞ ሄደ) አንተ ግን የእግዚአብሔርን መልዕክት እንዳስታውቅህ እዚህ ጥቂት መቆየት አለብህ" አለው።
\s5
\c 10
\p
\v 1 ከዚያም ሳሙኤል የዘይቱን ጠርሙስ ወስዶ በሳኦል ራስ ላይ አፈሰሰው፤ ሳመውም። እርሱም እንዲህ አለው፥ "በርስቱ ላይ ገዢ እንድትሆን እግዚአብሔር ቀብቶሃል፤
\v 2 ዛሬ ከእኔ ተለይተህ ስትሄድ፥ የብንያም ወሰን በሆነው በጼልጻህ፥ በራሔል መቃብር አጠገብ ሁለት ሰዎች ታገኛለህ። እነርሱም፥ 'ስትፈልጋቸው የነበሩት አህዮች ተገኝተዋል። አሁን አባትህ ስለ አህዮቹ ማሰቡን ትቶ፥ "ስለ ልጄ ምን ባደርግ ይሻለኛል?" በማለት ተጨንቋል“ ይሉሃል።
\s5
\v 3 ከዚያ አልፈህ ትሄድና በታቦር ወደሚገኘው ወደ በሉጥ ዛፍ ትመጣለህ። ወደ ቤቴል፥ ወደ እግዚአብሔር የሚሄዱ አንደኛው ሦስት የፍየል ጠቦቶች ይዞ፥ ሌላኛው ሦስት ዳቦ ተሸክሞ፥ ሌላኛው ደግሞ ወይን ጠጅ የተሞላ አንድ አቁማዳ ተሸክሞ ሦስት ሰዎች ይገናኙሃል።
\v 4 ሰላምታ ከሰጡህ በኋላ ሁለት ዳቦ ይሰጡሃል፥ ከእጃቸውም ትቀበላቸዋለህ።
\s5
\v 5 ከዚህ በኋላ የፍልስጥኤም የጦር ሠፈር ወዳለበት ወደ እግዚአብሔር ኮረብታ ትመጣለህ። ወደ ከተማው በምትደርስበት ጊዜ፥ አንድ የነቢያት ቡድን በፊታቸው መሰንቆ፥ ከበሮ፥ እምቢልታና በገና ይዘው ከተራራው ሲወርዱ ትገናኛቸዋለህ፤ እነርሱም ትንቢት ይናገራሉ።
\v 6 የእግዚአብሔር መንፈስ በኃይል ይመጣብሃል፥ አንተም ከእነርሱ ጋር ትንቢት ትናገራለህ፥ እንደ ሌላ ሰው ሆነህም ትለወጣለህ።
\s5
\v 7 እነዚህ ምልክቶች በሚፈጸሙልህ ጊዜ፥ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና እጅህ ያገኘውን ሁሉ አድርግ።
\v 8 ቀድመኸኝ ወደ ጌልገላ ውረድ። ከዚያም የሚቃጠለውን መባ ለማቅረብና የሰላሙን መባ ለመሠዋት ወደ አንተ እወርዳለሁ። ወደ አንተ እስክመጣና ልታደርገው የሚገባህን እስከማሳይህ ድረስ ሰባት ቀን ቆይ።”
\s5
\v 9 ሳኦል ከሳሙኤል ተለይቶ ለመሄድ ፊቱን ባዞረ ጊዜ እግዚአብሔር ሌላ ልብ ሰጠው። እነዚህ ምልክቶች ሁሉ በዚያው ቀን ተፈጸሙ።
\v 10 እነርሱም ወደ ኮረብታው በመጡ ጊዜ፥ የነቢያት ቡድን ተገናኙት፥ የእግዚአብሔርም መንፈስ በኃይል መጣበት፥ ከእነርሱም ጋር ትንቢት ተናገረ።
\s5
\v 11 ቀድሞ ያውቁት የነበሩት ሁሉ እርሱም ከነቢያት ጋር ትንቢት ሲናገር ባዩት ጊዜ፥ እርስ በእርሳቸው፥ “የቂስን ልጅ ምን ነካው? አሁን ሳኦል ከነቢያት አንዱ መሆኑ ነው?” ተባባሉ።
\v 12 በዚያው ስፍራ የነበረ አንድ ሰው፥ “አባታቸው ማነው?” ሲል መለሰ። በዚህ ምክንያት፥ “ሳኦልም ከነቢያት አንዱ ነው?” የሚል ምሳሌአዊ አባባል የተለመደ ሆነ።
\v 13 ትንቢት መናገሩን በጨረሰ ጊዜ ወደ ተራራው ራስ መጣ።
\s5
\v 14 ከዚያም የሳኦል አጎት፥ እርሱንና አገልጋዩን፥ “የት ነበር የሄዳችሁት?” አላቸው። እርሱም፥ “አህዮቹን ለመፈለግ ነበር፤ ልናገኛቸው እንዳልቻልን ባየን ጊዜ ወደ ሳሙኤል ሄድን” ብሎ መለሰለት።
\v 15 የሳኦልም አጎት፥ “ሳሙኤል የነገረህን እባክህ ንገረኝ" አለው።
\v 16 ሳኦልም አጎቱን፥ "አህዮቹ መገኘታቸውን በግልጽ ነገረን" ብሎ መለሰለት። ሳሙኤል ነግሮት የነበረውን የንግሥና ጉዳይ ግን አልነገረውም።
\s5
\v 17 ሳሙኤል ሕዝቡን በአንድነት በእግዚአብሔር ፊት ወደ ምጽጳ ጠራቸው።
\v 18 እርሱም የእስራኤልን ሕዝብ እንዲህ አላቸው፥”የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የሚለው ይህንን ነው፥ 'እስራኤልን ከግብፅ አወጣሁት፥ ከግብፃውያን እጅና ካስጨነቋችሁ መንግሥታት ሁሉ እጅ አዳንኋችሁ'።
\v 19 ነገር ግን ዛሬ እናንተ ከመከራና ከጭንቃችሁ ሁሉ የሚያድናችሁን አምላካችሁን ተቃውማችኋል፤ እርሱንም፥ 'በላያችን ላይ ንጉሥ አንግሥልን' ብላችሁታል። አሁን በየነገዳችሁና በየጎሣችሁ ራሳችሁን በእግዚአብሔር ፊት አቅርቡ"።
\s5
\v 20 ስለዚህ ሳሙኤል የእስራኤልን ነገዶች በሙሉ አቀረበ፥ የብንያም ነገድም ተመረጠ።
\v 21 ከዚያም የብንያምን ነገድ በየጎሣቸው አቀረበ፤ የማጥሪ ጎሣም ተመረጠ፤ የቂስ ልጅ ሳኦልም ተመረጠ። ነገር ግን በፈለጉት ጊዜ ሊያገኙት አልቻሉም።
\s5
\v 22 ከዚያም ሕዝቡ”ገና የሚመጣ ሌላ ሰው አለ? “ በማለት እግዚአብሔርን ተጨማሪ ጥያቄዎች ለመጠየቅ ፈለጉ። እግዚአብሔርም፥”ራሱን በዕቃዎቹ መካከል ደብቋል" በማለት መለሰላቸው።
\v 23 ከዚያም ሮጠው ሄዱና ሳኦልን ከዚያ አመጡት። በሕዝቡ መካከል በቆመ ጊዜ፥ ከሕዝቡ ሁሉ ይልቅ ቁመቱ ረጅም ነበር።
\s5
\v 24 ሳሙኤልም ሕዝቡን፥ "እግዚአብሔር የመረጠውን ይህንን ሰው ታዩታላችሁ? በሕዝቡ ሁሉ መካከል እንደ እርሱ ያለ የለም! “ አላቸው። ሕዝቡም ሁሉ፥”ንጉሥ ለዘላለም ይኑር! “ በማለት ጮኹ።
\s5
\v 25 ከዚያም ሳሙኤል የንግሥናን ደንብና ልማዶች ለሕዝቡ ነገራቸው፥ በመጽሐፍ ጽፎም በእግዚአብሔር ፊት አስቀመጣቸው። ከዚያም ሳሙኤል እያንዳንዱ ወደ ገዛ መኖሪያው እንዲሄድ ሕዝቡን ሁሉ አሰናበተ።
\s5
\v 26 ሳኦልም ደግሞ በጊብዓ ወደሚገኘው መኖሪያው ሄደ፥ እግዚአብሔር ልባቸውን የነካቸው አንዳንድ ኃያላን ሰዎችም ከእርሱ ጋር ሄዱ።
\v 27 አንዳንድ የማይረቡ ሰዎች ግን፥”ይህ ሰው ሊያድነን እንዴት ይችላል? “ አሉ። እነዚህ ሰዎች ሳኦልን ናቁት፥ ምንም ዓይነት ስጦታዎችንም አላመጡለትም። ሳኦል ግን ዝም አለ።
\s5
\c 11
\p
\v 1 አሞናዊው ናዖስ ሄዶ ኢያቢስ ገለዓድን ከበባት። የኢያቢስ ሰዎች ሁሉ ናዖስን፥ "ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን አድርግ፥ እኛም እናገለግልሃለን" አሉት።
\v 2 አሞናዊው ናዖስም፥ "የሁላችሁንም ቀኝ ዐይኖቻችሁን በማውጣት በመላው እስራኤል ላይ ኃፍረትን አመጣለሁ፥ በዚህ ቅድመ ሁኔታ ከእናንተ ጋር ቃል ኪዳን አደርጋለሁ" ብሎ መለሰላቸው።
\s5
\v 3 የኢያቢስ ሽማግሌዎችም፥ "ወደ እስራኤል ወገኖች ሁሉ መልዕክተኞችን እንድንልክ ለሰባት ቀናት ታገሰን። ከዚያም የሚያድነን አንድም ባይኖር ለአንተ እንገዛለን" በማለት መለሱለት።
\s5
\v 4 መልዕክተኞቹም ሳኦል ወደሚኖርበት ወደ ጊብዓ መጥተው የሆነውን ነገር ለሕዝቡ ነገሯቸው። ሕዝቡም ሁሉ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ።
\v 5 በዚህ ጊዜ ሳኦል ከእርሻ በሬዎቹን እየነዳ መጣ። ሳኦልም፥ "ሕዝቡ ምን ሆኖ ነው የሚያለቅሰው?" አለ። እነርሱም የኢያቢስ ሰዎች ያሉትን ለሳኦል ነገሩት።
\s5
\v 6 ሳኦል የነገሩትን በሰማ ጊዜ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ በኃይል መጣበት፥ እጅግም ተቆጣ።
\v 7 የበሬዎቹን ቀንበር ወስዶ ፈለጣቸውና ወደ እስራኤል ወሰኖች ሁሉ በመልዕክተኞች እጅ ላከው። እርሱም፥ "ሳኦልንና ሳሙኤልን ተከትሎ በማይመጣው ሁሉ በበሬዎቹ ላይ እንዲህ ይደረግበታል" አለ። ከዚያም ከእግዚአብሔር ታላቅ ፍርሃት በሕዝቡ ላይ ወደቀ፥ እንደ አንድ ሰው ሆነው ተሰብስበው መጡ።
\v 8 ቤዜቅ በተባለ ስፍራ በሰበሰባቸው ጊዜ፥ የእስራኤል ሰዎች ሦስት መቶ ሺህ፥ የይሁዳም ሰዎች ሠላሳ ሺህ ነበሩ።
\s5
\v 9 እነርሱም ለመጡት መልዕክተኞች፥ "ለኢያቢስ ገለዓድ ሰዎች፥ 'ነገ ፀሐይ ሞቅ በሚልበት ሰዓት እንታደጋችኋለን' ብላችሁ ንገሯቸው" አሏቸው። መልዕክተኞቹ ሄደው ለኢያቢስ ሰዎች ነገሯቸው፥ እነርሱም እጅግ ደስ አላቸው።
\v 10 ከዚያም የኢያቢስ ሰዎች ናዖስን፥”ነገ እንገዛልሃለን፥ አንተም ደስ የሚያሰኝህን ልታደርግብን ትችላለህ“ አሉት።
\s5
\v 11 በቀጣዩ ቀን ሳኦል ሕዝቡን በሦስት ቡድን ከፈላቸው። ሊነጋጋ ሲል ወደ ጦር ሠፈሩ መካከል መጡ፥ አሞናውያንንም አጠቁ፥ ቀኑ እስኪሞቅ ድረስም አሸነፏቸው። በሕይወት የተረፉትም ከእነርሱ ሁለቱ አንድ ላይ ሆነው እስከማይታዩ ድረስ ተበታተኑ።
\s5
\v 12 በዚያን ጊዜ ሕዝቡ ሳሙኤልን፥ "'ሳኦል በእኛ ላይ እንዴት ይነግሣል?' ያለው ማን ነበር? እንድንገድላቸው ሰዎቹ ይምጡልን" አሉት።
\v 13 ነገር ግን ሳኦል፥ "ዛሬ እግዚአብሔር እስራኤልን ታድጎታልና በዚህ ቀን ማንም መገደል የለበትም" አላቸው።
\s5
\v 14 ሳሙኤልም ሕዝቡን፥ "ኑ፥ ወደ ጌልገላ እንሂድና በዚያ መንግሥቱን እናድስ" አላቸው።
\v 15 ስለዚህ ሕዝቡ ሁሉ ወደ ጌልገላ ሄደው በእግዚአብሔር ፊት በጌልገላ ሳኦልን አነገሡት። በዚያም በእግዚአብሔር ፊት የሰላምን መባ ሠዉ፥ ሳኦልና የእስራኤል ሰዎችም ሁሉ እጅግ ደስ አላቸው።
\s5
\c 12
\p
\v 1 ሳሙኤል እስራኤላውያንን በሙሉ እንዲህ አላቸው፥”የነገራችሁኝን በሙሉ ሰምቻችኋለሁ፥ ንጉሥንም በላያችሁ ላይ አንግሼላችኋለሁ።
\v 2 አሁንም፥ በፊታችሁ የሚሄድላችሁ ንጉሥ ይኸውላችሁ፤ እኔ አርጅቻለሁ፥ ጸጉሬም ሸብቷል፤ ልጆቼም ከእናንተ ጋር ናቸው። ከልጅነቴ ጀምሮ እስካሁን ድረስ በፊታችሁ ኖሬአለሁ።
\s5
\v 3 ይኸው በፊታችሁ ነኝ፤ በእግዚአብሔርና እርሱ በቀባው ፊት መስክሩብኝ። የማንን በሬ ወስጃለሁ? የማንንስ አህያ ወስጃለሁ? ማንን አታለልሁ? በማንስ ላይ ግፍ ሠራሁ? ዓይኖቼን ለማሳወር ከማን እጅ ጉቦ ተቀበልሁ? መስክሩብኝና እመልስላችኋለሁ።“
\s5
\v 4 እነርሱም፥”አላታለልከንም፥ ግፍም አልሠራህብንም ወይም ከማንም እጅ ምንም ነገር አልሰረቅህም“ አሉ።
\v 5 እርሱም፥”በእጄ ላይ ምንም እንዳላገኛችሁ ዛሬ እግዚአብሔር በእናንተ ላይ ምስክር ነው፥ እርሱ የቀባውም ምስክር ነው“ አላቸው። እነርሱም፥”እግዚአብሔር ምስክር ነው“ ብለው መለሱ።
\s5
\v 6 ሳሙኤልም ሕዝቡን፥”ሙሴንና አሮንን የመረጣቸው፥ አባቶቻችሁንም ከግብፅ ምድር ያወጣቸው እግዚአብሔር ነው።
\v 7 አሁን እንግዲህ፥ እግዚአብሔር ለእናንተና ለአባቶቻችሁ ስለ ሠራላችሁ የጽድቅ ሥራ ሁሉ እንድሟገታችሁ በእግዚአብሔር ፊት ራሳችሁን አቅርቡ።
\s5
\v 8 ያዕቆብ ወደ ግብፅ በመጣ ጊዜ አባቶቻችሁ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ። እግዚአብሔር፥ ከግብፅ ምድር እየመሩ አውጥተው በዚህ ስፍራ እንዲቀመጡ ያደረጓቸውን ሙሴንና አሮንን ላከ።
\v 9 እነርሱ ግን አምላካቸውን እግዚአብሔርን ረሱ፤ እርሱም የሐጾር ሠራዊት አዛዥ በሆነው በሲሣራ እጅ፥ በፍልስጥኤማውያን እጅና በሞአብ ንጉሥ እጅ ሸጣቸው፤ እነዚህ ሁሉ አባቶቻችሁን ተዋጓቸው።
\s5
\v 10 እነርሱም ወደ እግዚአብሔር በመጮህ፥ "እግዚአብሔርን ትተን በኣልንና አስታሮትን በማገልገላችን ኃጢአት አድርገናል። አሁን ግን ከጠላቶቻችን እጅ አድነን፥ እኛም እናገለግልሃለን' አሉት።
\v 11 ስለዚህ እግዚአብሔር ይሩበኣልን፥ ባርቅን፥ ዮፍታሔንና ሳሙኤልን ልኮ በሰላም እንድትኖሩ በዙሪያችሁ ባሉ ጠላቶቻችሁ ሁሉ ላይ ድልን ሰጣችሁ።
\s5
\v 12 እናንተም የአሞን ሕዝብ ንጉሥ ናዖስ እንደመጣባችሁ ባያችሁ ጊዜ፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር ንጉሣችሁ ሆኖ እያለ፥ 'አይሆንም፥ ይልቁን በላያችን ላይ ንጉሥ መንገሥ አለበት' አላችሁኝ።
\v 13 አሁንም እናንተ የመረጣችሁት፥ እንዲሆንላችሁ የጠየቃችሁትና እግዚአብሔርም በእናንተ ላይ ንጉሥ እንዲሆን የመረጠው ንጉሥ ይኸውላችሁ።
\s5
\v 14 እናንተም እግዚአብሔርን ብትፈሩት፥ ብታገለግሉት፥ ድምፁንም ብትታዘዙና በእግዚአብሔር ትዕዛዝ ላይ ባታምጹ ያን ጊዜ እናንተና በላያችሁ የሚገዛው ንጉሣችሁ የአምላካችሁ የእግዚአብሔር ተከታዮች ትሆናላችሁ።
\v 15 የእግዚአብሔርን ድምፅ ባትታዘዙ፥ ነገር ግን በእግዚአብሔር ትዕዛዝ ላይ ብታምጹ፥ ያን ጊዜ በአባቶቻችሁ ላይ እንደነበረ የእግዚአብሔር እጅ በእናንተ ላይ ይሆናል።
\s5
\v 16 አሁንም፥ ራሳችሁን አቅርቡና እግዚአብሔር በዓይናችሁ ፊት የሚያደርገውን ይህንን ታላቅ ነገር ተመልከቱ።
\v 17 ዛሬ የስንዴ መከር ነው አይደል? ነጎድጓድና ዝናብን እንዲልክ እግዚአብሔርን እጠራለሁ። ከዚያም ለራሳችሁ ንጉሥ በመጠየቃችሁ በእግዚአብሔር ፊት ያደረጋችሁት ክፋት ታላቅ እንደሆነ ታውቃላችሁ፥ ታያላችሁም“።
\v 18 ስለዚህ ሳሙኤል እግዚአብሔርን ጠራ፤ በዚያው ቀን እግዚአብሔር ነጎድጓድንና ዝናብን ላከ። ሕዝቡም ሁሉ እግዚአብሔርንና ሳሙኤልን በጣም ፈሩ።
\s5
\v 19 ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ ሳሙኤልን፥ "እንዳንሞት፥ ስለ አገልጋዮችህ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይ። ለራሳችን ንጉሥ በመጠየቃችን በኃጢአታችን ሁሉ ላይ ይህንን ክፋት ጨምረናልና” አሉት።
\v 20 ሳሙኤል እንዲህ ሲል መለሰላቸው፥ “አትፍሩ። ይህንን ሁሉ ክፋት አድርጋችኋል፥ ነገር ግን እግዚአብሔርን በሙሉ ልባችሁ አገልግሉት እንጂ ከእግዚአብሔር ፊታችሁን አትመልሱ።
\v 21 የማይጠቅሙ ናቸውና ሊረዷችሁ ወይም ሊረቧችሁ የማይችሉትን ከንቱ ነገሮች አትከተሉ።
\s5
\v 22 እግዚአብሔር የራሱ ሕዝብ ሊያደርጋችሁ ስለ ወደደ፥ ስለ ታላቅ ስሙ ሲል ሕዝቡን አይጥላቸውም።
\v 23 ስለ እናንተ መጸለይን በመተው በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአትን ማድረግ ከእኔ ይራቅ። ይልቁንም፥ መልካሙንና ትክክለኛውን መንገድ አስተምራችኋለሁ።
\s5
\v 24 ብቻ እግዚአብሔርን ፍሩት፥ በሙሉ ልባችሁም በእውነት አገልግሉት። ያደረገላችሁን ታላላቅ ነገሮች አስቡ።
\v 25 ክፉ በማድረግ ብትጸኑ ግን እናንተና ንጉሣችሁ ትጠፋላችሁ”።
\s5
\c 13
\p
\v 1 ሳኦል መንገሥ በጀመረ ጊዜ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበር፤ በእስራኤል ላይ አርባ ዓመት በነገሠ ጊዜ፥
\v 2 ከእስራኤል ሦስት ሺህ ሰዎች መረጠ። አንዱ ሺህ ከዮናታን ጋር በብንያም ጊብዓ ሲሆኑ ሁለቱ ሺህ በኮረብታማው አገር በቤቴልና በማክማስ ከእርሱ ጋር ነበሩ። የቀሩትን ወታደሮች ወደየቤታቸው፥ እያንዳንዱንም ወደ ድንኳኑ አሰናበታቸው።
\s5
\v 3 ዮናታን በጊብዓ የነበረውን የፍልስጥኤማውያን ጦር ድል አደረገ፥ ፍልስጥኤማውያንም ይህንን ሰሙ። ከዚያም ሳኦል፥ “ዕብራውያን ይስሙ” በማለት በምድሪቱ ሁሉ ላይ መለከት አስነፋ።
\v 4 ሳኦል የፍልስጥኤማውያንን ጦር እንዳሸነፈ፥ ደግሞም እስራኤላውያን በፍልስጥኤማውያን እንደ ግም መቆጠራቸውን እስራኤላውያን በሙሉ ሰሙ። ከዚያም ወታደሮቹ በጌልገላ ሳኦልን ለመከተል በአንድ ላይ ተሰበሰቡ።
\s5
\v 5 ፍልስጥኤማውያንም ከእስራኤል ጋር ለመዋጋት በአንድ ላይ ተሰበሰቡ፤ ሦስት ሺህ ሠረገሎች፥ ስድስት ሺህ ሠረገላ ነጂዎችና የሠራዊቱም ቁጥር በባህር ዳርቻ እንዳለ አሸዋ ነበሩ። እነርሱም መጥተው ከቤትአዌን በስተምሥራቅ ማክማስ ላይ ሰፈሩ።
\s5
\v 6 የእስራኤል ሰዎች ችግር ውስጥ መግባታቸውንና ሕዝቡም መጨነቁን ባዩ ጊዜ፥ ሕዝቡ በዋሻዎች፥ በየቁጥቋጦ ሥር፥ በዐለቶች፥ በገደሎችና በጉድጓዶች ውስጥ ተደበቁ።
\v 7 አንዳንድ ዕብራውያንም የዮርዳኖስን ወንዝ በመሻገር ወደ ጋድና ገለዓድ ምድር ሄዱ። ሳኦል ግን ገና በጌልገላ ነበር፥ የተከተለው ሕዝብ በሙሉ በፍርሃት ይንቀጠቀጥ ነበር።
\s5
\v 8 እርሱም ሳሙኤል በሰጠው ቀጠሮ መሠረት ሰባት ቀን ቆየ። ነገር ግን ሳሙኤል ወደ ጌልገላ አልመጣም ነበር፥ ሕዝቡም ከሳኦል ተለይቶ መበታተን ጀምሮ ነበር።
\v 9 ሳኦልም፥ "የሚቃጠለውን መባና የሰላሙን መባዎች አምጡልኝ" አለ። ከዚያም የሚቃጠለውን መባ አቀረበ።
\v 10 የሚቃጠለውን መባ ማቅረቡን እንደ ጨረሰ ሳሙኤል ወደዚያ ደረሰ። ሳኦልም ሊገናኘውና ሰላምታ ሊሰጠው ሄደ።
\s5
\v 11 ከዚያም ሳሙኤል፥ "ያደረግከው ምንድነው?" አለው። ሳኦልም፥ "ሕዝቡ ትተውኝ እየሄዱ እንዳሉ፥ አንተም በቀጠሮው ሰዓት አለመምጣትህን፥ ፍልስጥኤማውያንም በማክማስ መሰብሰባቸውን ባየሁ ጊዜ፥
\v 12 'አሁን ፍልስጥኤማውያን ወደ ጌልገላ በእኔ ላይ ሊወርዱብኝ ነው፥ እኔም የእግዚአብሔርን ሞገስ አልለመንኩም' ብዬ አሰብኩኝ። ስለዚህ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ለማቅረብ ግድ ሆነብኝ“ ብሎ መለሰለት።
\s5
\v 13 ሳሙኤልም ሳኦልን፥”ያደረግከው ስንፍና ነው። አምላክህ እግዚአብሔር የሰጠህን ትዕዛዝ አልጠበቅክም። በዚህ ቀን እግዚአብሔር መንግሥትህን በእስራኤል ላይ ለዘላለም ሊያጸናልህ ነበር።
\v 14 አሁን ግን አገዛዝህ አይቀጥልም። እግዚአብሔር ያዘዘህን አልታዘዝክምና እርሱ እንደ ልቡ የሚሆንለትን ሰው ፈልጓል፥ እግዚአብሔርም በሕዝቡ ላይ መስፍን እንዲሆን መርጦታል" አለው።
\s5
\v 15 ከዚያም ሳሙኤል ከጌልገላ ተነሥቶ ወደ ብንያም ጊብዓ ወጣ። ሳኦል ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሰዎች ቆጠራቸው፥ ስድስት መቶ የሚያክሉ ነበሩ።
\v 16 ሳኦል፥ ልጁ ዮናታንና ከእነርሱ ጋር የነበሩት ሰዎች በብንያም ጊብዓ ቆዩ። ፍልስጥኤማውያን ግን በማክማስ ሰፍረው ነበር።
\s5
\v 17 ከፍልስጥኤም ጦር ሰፈር ወራሪዎች በሦስት ቡድን ተከፍለው መጡ። አንደኛው ቡድን ወደ ሦጋል ምድር ወደ ዖፍራ ታጠፈ።
\v 18 ሌላኛው ቡድን በቤትሖሮን አቅጣጫ ታጠፈ፥ ሌላኛውም ቡድን በምድረ በዳው አቅጣጫ ወደ ስቦይም ሸለቆ ቁልቁል ወደሚያሳየው ወሰን ዞረ።
\s5
\v 19 ፍልስጥኤማውያን፥ “ዕብራውያን ለራሳቸው ሰይፍ ወይም ጦር እንዳይሠሩ" ብለው ስለነበረ፥ በመላው እስራኤል ብረት ሠሪ አልተገኘም።
\v 20 ነገር ግን የእስራኤል ወንዶች ሁሉ፥ እያንዳንዱ የማረሻውን ጫፍ፥ ዶማውን፥ ጠገራውንና ማጭዱን ለማሳል ወደ ፍልስጥኤማውያን ይወርድ ነበር።
\v 21 የክፍያው ዋጋ ለማረሻው ጫፍና ለዶማው የሰቅል ሁለት ሦስተኛ፥ ጠገራ ለማሳልና መውጊያውን ለማቃናት የሰቅል አንድ ሦስተኛ ነበር።
\s5
\v 22 ስለዚህ በጦርነቱ ቀን ሰይፍና ጦር በሳኦልና በዮናታን እጅ ብቻ እንጂ ከእነርሱ ጋር ከነበሩት ወታደሮች በአንዱም እጅ ሰይፍ ወይም ጦር አልነበረም።
\v 23 የፍልስጥኤማውያን ሠራዊት ወደ ማክማስ መተላለፊያ ወጣ።
\s5
\c 14
\p
\v 1 አንድ ቀን የሳኦል ልጅ ዮናታን ወጣቱን ጋሻ ጃግሬውን፥”ና፥ በፍልስጥኤማውያን ሠራዊት ላይ በሌላ አቅጣጫ እንሂድባቸው“ አለው። ለአባቱ ግን አልነገረውም።
\s5
\v 2 ሳኦል መጌዶን በሚባል በጊብዓ ዳርቻ በሮማኑ ዛፍ ሥር ሰፍሮ ነበር።
\v 3 እርሱም በሴሎ የእግዚአብሔር ካህን የነበረው የዔሊ ልጅ፥ የፊንሐስ ልጅ፥ የኢካቦድ ወንድም የአኪጦብ ልጅ የሆነው፥ ኤፉድ ይለብስ የነበረውን አኪያን ጨምሮ ስድስት መቶ ያህል ሰዎች ከእርሱ ጋር ነበሩ። ዮናታን መሄዱን ሕዝቡ አላወቀም ነበር።
\s5
\v 4 ዮናታን ወደ ፍልስጥኤማውያኑ ጦር ሰፈር አቋርጦ ለመሄድ ባሰበባቸው በመተላለፊያዎቹ መካከል በግራና በቀኙ በኩል ሾጣጣ ድንጋዮች ነበሩ። የአንደኛው ሾጣጣ ድንጋይ ስም ቦጼጽ ሲሆን የሁለተኛው ስም ሴኔ ነበር።
\v 5 አንደኛው ቀጥ ያለው ድንጋይ የቆመው በስተሰሜን በሚክማስ ፊት ለፊት ሲሆን ሌላኛው በጊብዓ ፊት ለፊት በስተደቡብ ነበር።
\s5
\v 6 ዮናታንም ወጣት ጋሻ ጃግሬውን፥ "ና፥ ወደእነዚህ ወዳልተገረዙት ጦር ሰፈር እንሻገር። እግዚአብሔር በብዙ ወይም በጥቂት ሰዎች ከማዳን ሊከለክለው የሚችል ነገር የለምና፥ ምናልባት እግዚአብሔር ይሠራልን ይሆናል" አለው።
\v 7 ጋሻ ጃግሬውም፥ "በልብህ ያለውን ሁሉ አድርግ። ወደፊት ቀጥል፥ ተመልከት፥ የምታዝዘኝን ሁሉ ለመፈጸም ከአንተ ጋር ነኝ" ብሎ መለሰለት።
\s5
\v 8 ከዚያም ዮናታን እንዲህ አለው፥ "ወደ እነርሱ ተሻግረን እንታያቸዋለን።
\v 9 እነርሱም፥ 'ወደ እናንተ እስክንመጣ እዚያው ቆዩ' ካሉን በስፍራችን እንቆያለን፥ ወደ እነርሱም አንሻገርም።
\v 10 ነገር ግን፥ 'ወደ እኛ ውጡ' ብለው ቢመልሱልን እግዚአብሔር በእጃችን አሳልፎ ሰጥቶናልና ወደ እነርሱ እንሻገራለን።”
\s5
\v 11 ስለዚህ ሁለቱም ራሳቸውን ለፍልስጥኤማውያን ጦር ገለጡ። ፍልስጥኤማውያኑም፥ “ተመልከቱ፥ ዕብራውያኑ ከተደበቁባቸው ጉድጓዶች ወጥተው እየመጡ ነው" ተባባሉ።
\v 12 ከዚያም የጦር ሰፈሩ ሰዎች ወደ ዮናታንና ጋሻ ጃግሬው በመጣራት፥”ወደ እኛ ውጡ፥ አንድ ነገርም እናሳያችኋለን" አሏቸው። ዮናታን ጋሻ ጃግሬውን፥ “እግዚአብሔር በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጥቷቸዋልና ተከተለኝ" አለው።
\s5
\v 13 ዮናታን በእጁና በእግሩ ተንጠላጥሎ ወጣ፥ ጋሻ ጃግሬውም ከኋላው ተከተለው። ፍልስጥኤማውያኑ በዮናታን ተገደሉ፥ ጋሻ ጃግሬውም ከኋላው ተከትሎ ጥቂቶቹን ገደለ።
\v 14 ዮናታንና ጋሻ ጃግሬው በፈጸሙት በዚያ የመጀመሪያ ጥቃት አንድ ጥማድ በሬ ሊያርሰው በሚችለው የመሬት ስፋት ላይ ሃያ ያህል ሰዎችን ገደሉ።
\s5
\v 15 በጦር ሰፈሩ፥ በእርሻውና በሕዝቡ መካከል ሽብር ሆነ። የጦር ሰፈሩና ወራሪዎቹም እንኳን ተሸበሩ። ምድሪቱ ተንቀጠቀጠች፥ ታላቅ ሽብርም ሆነ።
\s5
\v 16 በብንያም ጊብዓ የነበሩ የሳኦል ጠባቂዎች፥ የፍልስጥኤም ወታደሮች ሲበተኑና ወዲያና ወዲህ ሲራወጡ ተመለከቱ።
\v 17 ከዚያም ሳኦል ከእርሱ ጋር ለነበሩት ሰዎች፥”ቁጠሩና ከእኛ የጎደለ ማን እንደሆነ ዕወቁ“ አላቸው። በቆጠሩ ጊዜም ዮናታንና ጋሻ ጃግሬው ታጡ።
\s5
\v 18 ሳኦልም አኪያን፥ "የእግዚአብሔርን ኤፉድ ወደዚህ አምጣው" አለው። በዚያ ቀን አኪያ ኤፉድ ለብሶ ከእስራኤል ወታደሮች ጋር ነበር።
\v 19 ሳኦል ከካህኑ ጋር በመነጋገር ላይ እያለ በፍልስጥኤማውያን የጦር ሰፈር የነበረው ሁከት መጨመሩን ቀጠለ። ሳኦልም ካህኑን፥ "እጅህን መልስ" አለው።
\s5
\v 20 ሳኦልና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሰዎች ሁሉ በሩጫ ወደ ጦርነቱ ሄዱ። የእያንዳንዱ ፍልስጥኤማዊ ሰይፍ በራሱ ዜጋ ላይ ነበር፥ ታላቅ ግራ መጋባት ውስጥ ነበሩ።
\v 21 ቀድሞ ከፍልስጥኤማውያን ጋር የነበሩና አብረዋቸው ወደ ጦር ሰፈሩ የገቡት ዕብራውያን እነርሱም እንኳን አሁን ከሳኦልና ከዮናታን ጋር ከነበሩት እስራኤላውያን ጋር ተባበሩ።
\s5
\v 22 በኤፍሬም አቅራቢያ በኮረብታዎቹ ውስጥ የተደበቁ የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ፍልስጥኤማውያን መሸሻቸውን በሰሙ ጊዜ እነርሱም እንኳን ለውጊያ በኋላቸው አሳደዷቸው።
\v 23 ስለዚህ እግዚአብሔር በዚያን ቀን እስራኤልን አዳነ፥ ውጊያውም ቤትአዌንን አልፎ ሄደ።
\s5
\v 24 ሳኦል፥”ጠላቶቼን እስከምበቀልበት እስከ ምሽት ድረስ የትኛውንም ዓይነት መብል የሚበላ ቢኖር የተረገመ ይሁን“ ብሎ ሕዝቡን አምሎ ስለነበረ በዚያን ቀን የእስራኤል ሰዎች ተጨነቁ። ስለዚህ ከሠራዊቱ አንዱም ምግብ አልቀመሰም።
\v 25 ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ ወደ ጫካ ውስጥ ገባ፥ ማርም በምድሩ ላይ ነበር።
\v 26 ሕዝቡ ወደ ጫካ በገባ ጊዜ ማሩ ይፈስስ ነበር፥ ነገር ግን ሕዝቡ መሓላውን ስለፈራ በእጁ ጠቅሶ ወደ አፉ ያደረገ አንድም አልነበረም።
\s5
\v 27 ዮናታን ግን አባቱ ሕዝቡን በመሓላ ማሰሩን አልሰማም ነበር። በእጁ ላይ የነበረውን በትር ጫፉን በማሩ እንጀራ ውስጥ አጠቀሰው። እጁን አንሥቶ ወደ አፉ አደረገው፥ ዐይኖቹም በሩለት።
\v 28 ከዚያም ከሰዎቹ አንዱ፥”ሕዝቡ በረሃብ ቢደክምም እንኳን አባትህ፥ 'በዚህ ቀን ምግብ የሚበላ የተረገመ ይሁን' ብሎ ሕዝቡን ከመሓላ ጋር አጥብቆ አዝዞአል" ብሎ መለሰለት።
\s5
\v 29 ከዚያም ዮናታን፥ "አባቴ በምድሪቱ ላይ ችግር ፈጥሯል። ከዚህ ማር ጥቂት በመቅመሴ ዐይኖቼ እንዴት እንደበሩ ተመልከቱ።
\v 30 ሕዝቡ ከጠላቶቻቸው ከበዘበዙት ላይ ዛሬ በነጻነት በልተው ቢሆን ኖሮ ምንኛ በተሻለ ነበር? ምክንያቱም አሁን በፍልስጥኤማውያን መካከል የተገደሉት ያን ያህል ብዙ አይደሉም“ አለ።
\s5
\v 31 እነርሱም በዚያን ቀን ፍልስጥኤማውያንን ከሚክማስ ጀምሮ እስከ ኤሎን ድረስ መቱአቸው። ሕዝቡም እጅግ ደከሙ።
\v 32 ሕዝቡም ተስገብግበው ወደ ብዝበዛው ተጣደፉ፥ በጎችን፥ በሬዎችንና ጥጆችንም በመሬት ላይ አረዱ። ሕዝቡም ከነደሙ በሉ።
\s5
\v 33 ከዚያም ለሳኦል፥ "ተመልከት፥ ሕዝቡ ከነደሙ በመብላታቸው በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት በመሥራት ላይ ናቸው" አሉት። ሳኦልም፥ "ተላልፋችኋል፥ አሁንም ትልቅ ድንጋይ አንከባልላችሁ አምጡልኝ“ አለ።
\v 34 በመቀጠልም፥ "ወደ ሕዝቡ ሂዱና፥ 'እያንዳንዱ ሰው በሬውንና በጉን እዚህ አምጥቶ በማረድ ይብላ። ከነደሙ በመብላት በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአትን አታድርጉ' ብላችሁ ንገሯቸው" አለ። ስለዚህ በዚያ ምሽት እያንዳንዱ በሬውን እያመጣ በዚያ ዐረደው።
\s5
\v 35 ሳኦል ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፥ ይኸውም ለእግዚአብሔር የሠራው የመጀመሪያው መሠዊያ ነበር።
\s5
\v 36 ከዚያም ሳኦል፥ "ሌሊቱን ፍልስጥኤማውያንን እናሳድ፥ እስኪነጋም ድረስ ሀብታቸውን እንበዝብዝ፤ ከእነርሱም አንድ በሕይወት አናስቀር“ አለ። እነርሱም፥”መልካም መስሎ የታየህን ሁሉ አድርግ“ ብለው መለሱለት። ካህኑ ግን፥”እዚሁ እግዚአብሔርን እንጠይቅ“ አለ።
\v 37 ሳኦልም እግዚአብሔርን እንዲህ ሲል ጠየቀ፥”ፍልስጥኤማውያንን ላሳድዳቸው? በእስራኤል እጅ አሳልፈህ ትሰጣቸዋለህ? “። ነገር ግን በዚያን ቀን እግዚአብሔር አልመለሰለትም።
\s5
\v 38 ከዚያም ሳኦል፥”የሕዝቡ አለቆች የሆናችሁ ሁሉ ወደዚህ ቅረቡ፤ ዛሬ ይህ ኃጢአት እንዴት እንደመጣብን መርምሩና ዕወቁ።
\v 39 እስራኤልን ያዳነ ሕያው እግዚአብሔርን! ልጄ ዮናታን ቢሆን እንኳን በእርግጥ እርሱ ይሞታል" አለ። ነገር ግን ከሕዝቡ ሁሉ አንዱም እንኳን አልመለሰለትም።
\s5
\v 40 እርሱም እስራኤልን በሙሉ፥ “እናንተ በአንድ በኩል ቁሙ፥ እኔና ልጄ ዮናታን በሌላው በኩል እንቆማለን” አላቸው። ሕዝቡም ሳኦልን፥ “መልካም መስሎ የታየህን አድርግ” አሉት።
\v 41 ስለዚህ ሳኦል የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔርን፥ “በቱሚም አሳየኝ” አለው። ዮናታንና ሳኦል በዕጣ ተያዙ፥ ሕዝቡ ግን የተመረጠ ሆነና አመለጠ።
\v 42 ከዚያም ሳኦል፥ “በእኔና በልጄ በዮናታን መክከል ዕጣ ጣሉ” አለ። ዮናታንም በዕጣ ተያዘ።
\s5
\v 43 ሳኦልም ዮናታንን፥ “ያደረግኸውን ንገረኝ” አለው። ዮናታንም፥ “በእጄ በነበረው በትር ጫፍ ጥቂት ማር ቀምሻለሁ። ይኸው ለመሞት ዝግጁ ነኝ” አለ።
\v 44 ሳኦልም፥ “ዮናታን ሆይ፥ ባትሞት እግዚአብሔር በእኔ ላይ እንዲሁ ያድርግ፥ ይጨምርም” አለ።
\s5
\v 45 ሕዝቡም ሳኦልን፥ “ለእስራኤል ይህንን ታላቅ ድል ያመጣ ዮናታን መሞት ይገባዋል? ይህ ከእርሱ ይራቅ! እርሱ ዛሬ ከእግዚአብሔር ጋር ሠርቷልና ሕያው እግዚአብሔርን! ከራስ ጸጉሩ አንድ በምድር ላይ አይወድቅም" አሉት። ስለዚህ ሕዝቡ ዮናታንን ከመሞት አዳነው።
\v 46 ከዚያም ሳኦል ፍልስጥኤማውያንን ማሳደዱን አቆመ፥ ፍልስጥኤማውያንም ወደ ስፍራቸው ሄዱ።
\s5
\v 47 ሳኦል እስራኤልን መግዛት በጀመረ ጊዜ፥ በየአቅጣጫው ከነበሩ ጠላቶቹ ሁሉ ጋር ተዋጋ። እርሱም ከሞዓብ፥ ከአሞን ሰዎች፥ ከኤዶም፥ ከሱባ ነገሥታትና ከፍልስጥኤማውያን ጋር ተዋጋ። በደረሰበት ሁሉ በቅጣት ያሰቃያቸው ነበር።
\v 48 ከአማሌቃውያን ጋር በጀግንነት ተዋግቶ ድል አደረጋቸው። እስራኤላውያንንም ከዘራፊዎቻቸው እጅ አዳናቸው።
\s5
\v 49 የሳኦል ወንዶች ልጆች ዮናታን፥ የሱዊና ሜልኪሳ ነበሩ። የሁለቱ ሴቶች ልጆቹ ስም፥ የመጀመሪያ ልጁ ሜሮብና ታናሿ ሜልኮል ይባሉ ነበሩ።
\v 50 የሳኦል ሚስት ስም አኪናሆም ነበር፥ እርሷም የአኪማአስ ልጅ ነበረች። የሠራዊቱ አዛዥ ስም፥ የሳኦል አጎት የኔር ልጅ አበኔር ነበር።
\v 51 ቂስ የሳኦል አባት ነበር፤ የአበኔር አባት ኔርም የአቢኤል ልጅ ነበር።
\s5
\v 52 በሳኦል ዘመን ሁሉ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ከባድ ጦርነት ይካሄድ ነበር። ሳኦል ኃያል ወይም ብርቱ የሆነ ሰው ባየ ጊዜ ሁሉ ያንን ወደ ራሱ ይሰበስብ ነበር።
\s5
\c 15
\p
\v 1 ሳሙኤልም ሳኦልን እንዲህ አለው፥”እግዚአብሔር በሕዝቡ በእስራኤል ላይ ንጉሥ ትሆን ዘንድ እንድቀባህ ላከኝ። አሁንም የእግዚአብሔርን ቃል ስማ።
\v 2 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሚለው እንዲህ ነው፥ 'እስራኤል ከግብፅ በወጣ ጊዜ አማሌቅ እየተቃወመ በመንገዱ ላይ ያደረገበትን አስታውሻለሁ።
\v 3 አሁንም ሂድና አማሌቅን ምታ፥ ያላቸውን ሁሉ ፈጽመህ ደምስስ። አትራራላቸው፥ ወንድና ሴቱን፥ ልጅና ሕፃኑን፥ በሬና በጉን፥ ግመልና አህያውን ግደል።"
\s5
\v 4 ሳኦል ሕዝቡን በጥላኢም ከተማ ሰብስቦ ቆጠራቸው፤ እነርሱም ሁለት መቶ ሺህ እግረኞችና ዐሥር ሺህ የይሁዳ ሰዎች ነበሩ።
\v 5 ከዚያም ሳኦል ወደ አማሌቅ ከተማ መጥቶ በሸለቆው ውስጥ አደፈጠ።
\s5
\v 6 ከዚያም ሳኦል ቄናውያንን፥ "ከግብፅ በመጡ ጊዜ ለእስራኤል ሕዝብ በሙሉ ደግነትን አሳይታችኋልና ከእነርሱ ጋር እንዳላጠፋችሁ፥ ከአማሌቃውያን መካከል ተለይታችሁ ውጡና ሂዱ" አላቸው። ስለዚህ ቄናውያን ከአማሌቃውያን ተለይተው ሄዱ።
\v 7 ሳኦልም አማሌቃውያንን ከኤውላጥ ጀምሮ ከግብፅ በስተምሥራቅ እስካለችው እስከ ሱር ድረስ መታቸው።
\s5
\v 8 የአማሌቃውያኑን ንጉሥ አጋግን ከነሕይወቱ ያዘው፤ ሕዝቡን ሁሉ በሰይፍ ስለት ፈጽሞ አጠፋቸው።
\v 9 ነገር ግን ሳኦልና ሕዝቡ አጋግን፥ እንዲሁም ምርጥ የሆኑትን በጎች፥ በሬዎች፥ የሰቡትን ጥጆችና የበግ ጠቦቶች በሕይወት ተዉአቸው። መልካም የሆነውን ሁሉ አላጠፉም። የተናቀውንና ዋጋ ቢስ የሆነውን ነገር ሁሉ ግን ፈጽመው ደመሰሱ።
\s5
\v 10 ከዚያም የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ ሳሙኤል መጣ፥
\v 11 "እኔን ከመከተል ስለተመለሰና ያዘዝኩትንም ስላልፈጸመ ሳኦልን በማንገሤ ተጸጽቻለሁ"። ሳሙኤልም ተቆጣ፤ ሌሊቱን በሙሉ ወደ እግዚአብሔር ሲጮህ አደረ።
\s5
\v 12 ሳሙኤልም ሳኦልን በጠዋት ለመገናኘት ማልዶ ተነሣ። ለሳሙኤልም፥ "ሳኦል ወደ ቀርሜሎስ መጥቶ ለራሱ ሐውልት አቆመ፥ ከዚያም ተመልሶ ወደ ጌልገላ ወረደ" ብለው ነገሩት።
\v 13 ከዚያም ሳሙኤል ወደ ሳኦል መጣ፥ ሳኦልም፥ "አንተ በእግዚአብሔር የተባረክህ ነህ! የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ፈጽሜአለሁ" አለው።
\s5
\v 14 ሳሙኤልም፥ "ታዲያ ይህ በጆሮዬ የምሰማው የበጎች ድምፅና የበሬዎች ግሣት ምንድነው?" አለው።
\v 15 ሳኦልም፥ "ከአማሌቃውያኑ ያመጧቸው ናቸው። ሕዝቡ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ለመሠዋት ምርጥ የሆኑትን በጎችና በሬዎች በሕይወት አስቀሯቸው። የቀሩትን ፈጽመን አጥፍተናል" ብሎ መለሰለት።
\v 16 ከዚያም ሳሙኤል ሳኦልን፥ "አድምጠኝ፥ በዛሬው ሌሊት እግዚአብሔር የነገረኝን እነግርሃለሁ" አለው። ሳኦልም፥ "ተናገር!" አለው።
\s5
\v 17 ሳሙኤልም እንዲህ አለው፥ "በራስህ ግምት ታናሽ ብትሆንም በእስራኤል ነገዶች ላይ አለቃ ተደረግህ። እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ንጉሥ አድርጎ ቀባህ፤
\v 18 እግዚአብሔርም፥ 'ሂድና ኃጢአተኞቹን አማሌቃውያንን ፈጽመህ አጥፋቸው፥ እስኪጠፉም ድረስ ተዋጋቸው' ብሎ በመንገድህ ልኮህ ነበር።
\v 19 ታዲያ የእግዚአብሔርን ድምፅ ያልታዘዝከው ለምንድነው? ከዚያ ይልቅ ግን ከምርኮው በመውሰድ በእግዚአብሔር ፊት ክፋትን አደረግህ።"
\s5
\v 20 ሳኦልም ሳሙኤልን፥ "የእግዚአብሔርን ድምፅ በትክክል ታዝዣለሁ፥ እግዚአብሔር በላከኝም መንገድ ሄጃለሁ። የአማሌቅን ንጉሥ አጋግን ማርኬዋለሁ፥ አማሌቃውያንንም በሙሉ ፈጽሜ ደምስሻለሁ።
\v 21 ሕዝቡ ግን ከምርኮው ላይ ጥቂት በጎችንና በሬዎችን፥ ሊጠፉም የነበሩ ምርጥ ነገሮችን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር በጌልገላ ሊሠዉአቸው ወሰዱ" አለው።
\s5
\v 22 ሳሙኤልም፥ "የእግዚአብሔርን ድምፅ ከመታዘዝ የበለጠ በሚቃጠል መባና መሥዋዕት እግዚአብሔር ደስ ይሰኛል? ከመሥዋዕት መታዘዝ ይሻላል፥ ከአውራ በግ ስብም መስማት ይሻላል።
\v 23 እምቢተኝነት እንደ ምዋርተኝነት ኃጢአት ነው፥ እልኸኝነትም እንደ አመጸኝነትና እንደ ክፋት ነው። የእግዚአብሔርን ቃል ንቀሃልና እርሱም ደግሞ ንጉሥ እንዳትሆን ንቆሃል“ አለው።
\s5
\v 24 ከዚያም ሳኦል ሳሙኤልን፥”ኃጢአትን ሠርቻለሁ፤ ሕዝቡን ስለፈራሁና ቃላቸውን ስለታዘዝኩ የእግዚአብሔርን ትዕዛዝና የአንተን ቃል ተላልፌአለሁ።
\v 25 አሁንም እባክህን ኃጢአቴን ይቅር በለኝ፥ ለእግዚአብሔር እንድሰግድም ከእኔ ጋር ተመለስ“ አለው።
\s5
\v 26 ሳሙኤልም ሳኦልን፥”ከአንተ ጋር አልመለስም፤ የእግዚአብሔርን ቃል ንቀሃልና አንተም በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንዳትሆን እግዚአብሔር ንቆሃል" አለው።
\v 27 ሳሙኤል ለመሄድ ዘወር ባለ ጊዜ፥ ሳኦል የልብሱን ጫፍ ያዘ፥ እርሱም ተቀደደ።
\s5
\v 28 ሳሙኤልም፥ "እግዚአብሔር ዛሬ የእስራኤልን መንግሥት ከአንተ ቀደደው፥ ከአንተ ለሚሻለው ለጎረቤትህም አሳልፎ ሰጠው።
\v 29 ደግሞም የእስራኤል ኃይል አይዋሽም፥ አሳቡንም አይለውጥም፥ እርሱ አሳቡን መለወጥ ይችል ዘንድ ሰው አይደለምና“ አለው።
\s5
\v 30 ከዚያም ሳኦል፥”ኃጢአትን አድርጌአለሁ። አሁን ግን እባክህ በሕዝቤ ሽማግሌዎችና በእስራኤል ፊት አክብረኝ። ለአምላክህ ለእግዚአብሔር እንድሰግድ ከእኔ ጋር ተመለስ“ አለው።
\v 31 ስለዚህ ሳሙኤል ከሳኦል ኋላ ተመለሰ፥ ሳኦልም ለእግዚአብሔር ሰገደ።
\s5
\v 32 ከዚያም ሳሙኤል፥”የአማሌቃውያንን ንጉሥ አጋግን አምጡልኝ“ አለ። አጋግ በሠንሠለት አንደታሠረ ወደ እርሱ መጣና፥”ለካስ ሞት እንዲህ መራራ ነው“ አለ።
\v 33 ሳሙኤልም፥”ሰይፍህ እናቶችን ልጅ ዐልባ እንዳደረጋቸው አሁን እናትህ በሴቶች መካከል ልጅ ዐልባ ትሆናለች“ ብሎ መለሰለት። ከዚያም ሳሙኤል አጋግን በእግዚአብሔር ፊት በጌልገላ ቆራረጠው።
\s5
\v 34 ሳሙኤል ወደ ራማ ሄደ፥ ሳኦልም ወደ ቤቱ ወደ ሳኦል ጊብዓ ሄደ።
\v 35 ሳሙኤል እስከሞተበት ጊዜ ድረስ ሳኦልን አላየውም፥ ለሳኦልም አለቀሰለት። እግዚአብሔርም ሳኦልን በእስራኤል ላይ በማንገሡ አዘነ።
\s5
\c 16
\p
\v 1 እግዚአብሔርም ሳሙኤልን፥ “በእስራኤል ንጉሥ እንዳይሆን ለናቅኩት ለሳኦል የምታለቅስለት እስከ መቼ ነው? በወንዶች ልጆቹ መካከል ለራሴ ንጉሥ የሚሆነውን መርጫለሁና ወደ ቤተ ልሔማዊው ወደ እሴይ እልክሃለሁ። የዘይት መያዣ ቀንድህን በዘይት ሞልተህ ሂድ” አለው።
\s5
\v 2 ሳሙኤልም፥ “እንዴት መሄድ እችላለሁ? ሳኦል ከሰማ ይገድለኛል” አለ። እግዚአብሔርም፥ “አንዲት ጊደር ይዘህ ሂድና፥ 'ለእግዚአብሔር ልሠዋ መጥቻለሁ' በል።
\v 3 እሴይንም ወደ መሥዋዕቱ ጥራው፥ እኔም የምታደርገውን አሳይሃለሁ። የምነግርህንም እርሱን ትቀባልኛለህ” አለው።
\s5
\v 4 ሳሙኤልም እግዚአብሔር እንደተናገረው አደረገ፥ ወደ ቤተ ልሔምም ሄደ። የከተማይቱም ሽማግሌዎች እየተንቀጠቀጡ ሊገናኙት መጡና፥ “በሰላም ነው የመጣኸው?” አሉት።
\v 5 እርሱም፥ “በሰላም ነው። ለእግዚአብሔር ልሠዋ መጥቻለሁ። ራሳችሁን ለእግዚአብሔር ቀድሱና ከእኔ ጋር ወደ መሥዋዕቱ ኑ”አላቸው። እሴይንና ወንዶች ልጆቹንም ቀደሳቸው፥ ወደ መሥዋዕቱም ጠራቸው።
\s5
\v 6 እነርሱ በመጡ ጊዜም፥ ወደ ኤልያብ ተመልክቶ እግዚአብሔር የሚቀባው በእርግጥ በፊቱ ቆሟል ብሎ በልቡ አሰበ።
\v 7 ነገር ግን እግዚአብሔር ሳሙኤልን፥ "እኔ ንቄዋለሁና ውጫዊ ገጽታውን ወይም የቁመቱን ዘለግታ አትመልከት። እግዚአብሔር ሰው እንደሚያይ አያይምና፤ ሰው ውጫዊ ገጽታን ያያል፥ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል" አለው።
\s5
\v 8 ከዚያም እሴይ አሚናዳብን ጠርቶ በሳሙኤል ፊት እንዲያልፍ አደረገው። ሳሙኤልም፥ "እግዚአብሔር ይኸኛውንም አልመረጠውም“ አለ።
\v 9 ከዚያም እሴይ ሳማን አሳለፈው። ሳሙኤልም፥ "እግዚአብሔር ይኸኛውንም አልመረጠውም“ አለ።
\v 10 እሴይ ሰባቱን ወንዶች ልጆቹን በሳሙኤል ፊት እንዲያልፉ አደረጋቸው። ሳሙኤልም እሴይን፥”እግዚአብሔር ከእነዚህ አንዳቸውንም አልመረጠም“ አለው።
\s5
\v 11 ሳሙኤልም እሴይን፥”ወንዶቹ ልጆችህ እነዚህ ብቻ ናቸው? “ አለው። እርሱም፥”የሁሉ ታናሽ የሆነው ገና ቀርቷል፥ እርሱ ግን በጎች እየጠበቀ ነው" ብሎ መለሰ። ሳሙኤልም እሴይን፥ "ልከህ አስመጣው፤ እርሱ እዚህ እስኪመጣ ድረስ አንቀመጥምና" አለው።
\v 12 እሴይም ልኮ አስመጣው። በመጣ ጊዜም ልጁ ቀይ፥ ዐይኖቹ የተዋቡና መልከ መልካም ገጽታ ነበረው። እግዚአብሔርም፥ "ያ ሰው እርሱ ነውና ተነሣ፤ ቀባውም" አለው።
\s5
\v 13 ሳሙኤልም የዘይቱን ቀንድ አንሥቶ በወንድሞቹ መካከል እርሱን ቀባው። ከዚያን ቀን ጀምሮ የእግዚአብሔር መንፈስ በእርሱ ላይ በኃይል መጣበት። ሳሙኤልም ተነሥቶ ወደ አርማቴም ሄደ።
\s5
\v 14 የእግዚአብሔር መንፈስ ከሳኦል ተለየ፥ በምትኩም ከእግዚአብሔር የታዘዘ ክፉ መንፈስ አሠቃየው።
\v 15 የሳኦል አገልጋዮችም፥ "ተመልከት፥ ክፉ መንፈስ ከእግዚአብሔር ዘንድ እያሠቃየህ ነው።
\v 16 ደህና አድርጎ በገና መደርደር የሚችል ሰው እንዲፈልጉ ጌታችን በፊቱ ያሉትን አገልጋዮቹን ይዘዝ። ከዚያም ከእግዚአብሔር ዘንድ ክፉ መንፈስ በሆነብህ ጊዜ እርሱ ይጫወትልሃል፥ አንተም ደኅና ትሆናለህ" አሉት።
\s5
\v 17 ሳኦልም አገልጋዮቹን፥ "በገና በደንብ መደርደር የሚችል ሰው ፈልጋችሁ አምጡልኝ" አላቸው።
\v 18 ከዚያም ከወጣቶቹ አንዱ እንዲህ ሲል መለሰ፥ "ደኅና አድርጎ በገና መደርደር የሚችለውን፥ ጽኑ፥ ኃያል፥ ተዋጊ፥ በንግግሩ ጠንቃቃና መልከ መልካም የሆነውን የቤተ ልሔማዊውን የእሴይን ልጅ አይቻለሁ፥ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነው።"
\v 19 ስለዚህ ሳኦል መልዕክተኞችን ወደ እሴይ ልኮ፥ "ከበጎች ጋር ያለውን ልጅህን ዳዊትን ላክልኝ" አለው።
\s5
\v 20 እሴይም እንጀራና ወይን ጠጅ የተሞላ አቁማዳ የተጫነበትን አህያ፥ ከፍየል ጠቦት ጋር አስይዞ ልጁን ዳዊትን ወደ ሳኦል ላከው።
\v 21 ከዚያም ዳዊት ወደ ሳኦል መጣና አገልግሎቱን መስጠት ጀመረ። ሳኦል እጅግ ወደደው፥ ዳዊትም ጋሻ ጃግሬው ሆነ።
\s5
\v 22 ሳኦልም፥ "በዐይኔ ፊት ሞገስን አግኝቷልና ዳዊት በፊቴ እንዲቆም ፈቃድህ ይሁን“ ብሎ ወደ እሴይ ላከ።
\v 23 በሳኦል ላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ክፉ መንፈስ በሚሆንበት ጊዜ ሁሉ ዳዊት በገና አንሥቶ ይደረድርለት ነበር። ስለዚህ ሳኦል ይታደስና ደኅና ይሆን ነበር፥ ክፉውም መንፈስ ከእርሱ ይርቅ ነበር።
\s5
\c 17
\p
\v 1 ፍልስጥኤማውያን ሠራዊታቸውን ለውጊያ አዘጋጁ። እነርሱም የይሁዳ በሆነችው በሰኮት ተሰበሰቡ። በሰኮትና በዓዜቃ መካከል በምትገኘው በኤፌስደሚምም ሰፈሩ።
\s5
\v 2 ሳኦልና የእስራኤል ሰዎችም ተሰብስበው በኤላ ሸለቆ ሰፈሩ፥ ፍልስጥኤማውያንን ለመግጠምም ስፍራቸውን ያዙ።
\v 3 ፍልስጥኤማውያን በአንደኛው ወገን ተራራ ላይ ቆሙ፥ በዚህኛው ወገን ባለው ተራራ ላይ እስራኤላውያኑ ቆሙ፥ በመካከላቸውም ሸለቆ ነበር።
\s5
\v 4 የጌት ሰው ጎልያድ የሚባል አንድ ጀግና ከፍልስጥኤማውያን የጦር ሰፈር ወጣ፥ ቁመቱም ስድስት ክንድ ከስንዝር ነበር።
\v 5 በራሱ ላይ ከነሐስ የተሠራ የራስ ቁር ደፍቶ፥ ጥሩርም ለብሶ ነበር። ጥሩሩም አምስት ሺህ የነሐስ ሰቅል ይመዝን ነበር።
\s5
\v 6 በእግሮቹ ላይ የነሐስ ገምባሌዎች አድርጎ ነበር፥ በትከሻዎቹም መሓል ቀለል ያለ የነሐስ ጦር ነበር።
\v 7 የጦሩ ዘንግ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ ወፍራም ነበር። የጦሩ ጫፍ ስድስት መቶ የብረት ሰቅል ይመዝን ነበር። ጋሻ ጃግሬው በፊቱ ሄደ።
\s5
\v 8 እርሱም ተነሥቶ በእስራኤል ሠልፈኞች ላይ እንዲህ በማለት ጮኸ፥ “ለውጊያ የተሰለፋችሁት ለምንድነው? እኔ ፍልስጥኤማዊ፥ እናንተ የሳኦል አገልጋዮች አይደላችሁም? ለራሳችሁ አንድ ሰው ምረጡና ወደ እኔ ይውረድ።
\v 9 እርሱ ሊዋጋኝ ቢችልና ቢገድለኝ እኛ አገልጋዮቻችሁ እንሆናለን። ነገር ግን ባሸንፈውና ብገድለው እናንተ አገልጋዮቻችን በመሆን ታገለግሉናላችሁ።”
\s5
\v 10 ፍልስጥኤማዊው ደገመና፥ “ዛሬ የእስራኤልን ሰልፈኞች እገዳደራቸዋለሁ። እንድንዋጋ አንድ ሰው ስጡኝ" አለ።
\v 11 ፍልስጥኤማዊው የተናገረውን ሳኦልና እስራኤላውያን ሁሉ በሰሙ ጊዜ እጅግ ፈሩ፥ ተስፋም ቆረጡ።
\s5
\v 12 ዳዊት በይሁዳ የሚኖረው የቤተ ልሔም ኤፍራታዊው የእሴይ ልጅ ነበር። እሴይ ስምንት ወንዶች ልጆች ነበሩት። በሳኦል ዘመን እሴይ በዕድሜው ያረጀና ከወንዶቹ ሁሉ በዕድሜ የገፋ ሰው ነበር።
\v 13 የእሴይ ሦስቱ ታላላቅ ልጆች ሳኦልን ተከትለው ወደ ጦርነቱ ሄደው ነበር። ወደ ጦርነት የሄዱት የሦስቱ ወንዶች ልጆች ስም፥ የመጀመሪያው ልጅ ኤልያብ፥ ተከታዩ አሚናዳብና ሦስተኛው ሣማ ይባሉ ነበር።
\s5
\v 14 ዳዊት የሁሉም ታናሽ ነበር። ትልልቆቹ ሦስቱ ሳኦልን ተከተሉት።
\v 15 ዳዊት በሳኦል ሠራዊትና በቤተ ልሔም የሚገኙትን የአባቱን በጎች በመጠበቅ ተግባር ወዲያና ወዲህ ይመላለስ ናበር።
\v 16 ፍልስጥኤማዊው ኃያል ሰው ለአርባ ቀናት በየጠዋቱና በየምሽቱ ለጦርነት ዝግጁ መሆኑን ለማሳየት ይቀርብ ነበር።
\s5
\v 17 ከዚያም እሴይ ልጁን ዳዊትን እንዲህ አለው፥”ከዚህ ከተጠበሰው እሸት ዐሥር ኪሎና እነዚህን ዐሥር ዳቦዎች በጦር ሰፈሩ ውስጥ ላሉት ወንድሞችህ ፈጥነህ ውሰድላቸው።
\v 18 በተጨማሪም እነዚህን ዐሥር የአይብ ጥፍጥፎች ለሻለቃቸው ስጠው። ወንድሞችህ ያሉበትን ሁኔታ ተመልከትና ደኅና ስለመሆናቸው ማረጋገጫ አምጣልኝ።
\s5
\v 19 ወንድሞችህ ከሳኦልና ከእስራኤል ሰዎች ሁሉ ጋር ፍልስጥኤማውያንን እየተዋጉ በኤላ ሸለቆ ናቸው።“
\v 20 ዳዊት ማልዶ ተነሣና በጎቹን ለእረኛ ዐደራ ሰጠ። እርሱም እሴይ እንዳዘዘው የወንድሞቹን ስንቅ ይዞ ሄደ። ሠራዊቱ ወደ ውጊያው ግምባር እየፎከረ በመውጣት ላይ እያለ ዳዊት ወደ ጦር ሰፈሩ ደረሰ።
\v 21 እስራኤላውያንና ፍልስጥኤማውያን፥ ሠራዊት በሠራዊት ላይ ለውጊያ ተሰለፉ።
\s5
\v 22 ዳዊት የያዘውን ዕቃ ለስንቅ ጠባቂው ዐደራ ሰጥቶ ወደ ሠራዊቱ በመሮጥ ለወንድሞቹ ሰላምታ አቀረበ።
\v 23 ከእነርሱ ጋር እየተነጋገረ እያለ ጎልያድ ተብሎ የሚጠራው፥ ከጌት የመጣው ፍልስጥኤማዊ ከሰልፈኞች መካከል ወጥቶ የቀድሞውን የሚመስል ቃል ተናገረ። ዳዊትም ሰማቸው።
\v 24 የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ሰውዬውን ባዩት ጊዜ፥ ከእርሱ ሸሹ፥ እጅግም ፈርተውት ነበር።
\s5
\v 25 የእስራኤልም ሰዎች፥ "ይህን የሚወጣውን ሰው አያችሁት? እስራኤልን ለመገዳደር ነው የመጣው። እርሱን የሚገድለውን ሰው ንጉሡ እጅግ ያበለጽገዋል፥ ልጁን ይድርለታል፥ የአባቱንም ቤት በእስራኤል ውስጥ ከግብር ነጻ ያደርጋቸዋል" ይባባሉ ነበር።
\s5
\v 26 ዳዊትም በአጠገቡ የቆሙትን ሰዎች፥ "ይህንን ፍልስጥኤማዊ ለሚገድልና ከእስራኤል ኀፍረትን ለሚያስወግድ ሰው ምን ይደረግለታል? የሕያው እግዚአብሔርን ሠራዊት ሊንቅ ይህ ያልተገረዘ ፍልስጥኤማዊ ማን ሆነና ነው?" አላቸው።
\v 27 ከዚያም ሰዎቹ ቀደም ሲል የተናገሩትን ደግመው፥ "ስለዚህ እርሱን ለሚገድለው የሚደረግለት ይህ ነው" አሉት።
\s5
\v 28 ዳዊት ከሰዎቹ ጋር ሲነጋገር የሁሉ ታላቅ የሆነው ወንድምየው ኤልያብ ሰማው። ኤልያብም በዳዊት ላይ ቁጣው ነድዶ፥ "ወደዚህ የወረድከው ለምንድነው? እነዚያንስ ጥቂት በጎች በምድረ በዳ ውስጥ ለማን ተውካቸው? እኔ ትዕቢትህንና የልብህን ክፋት አውቃለሁ፤ ወደዚህ የወረድከው ውጊያውን ለማየት ነውና" አለው።
\v 29 ዳዊትም፥ "አሁን እኔ ምን አደረኩ? እንዲያው መጠየቄ ብቻ አልነበረም?" አለው።
\v 30 ከእርሱ ወደ ሌላው ዞር ብሎ በተመሳሳይ መንገድ ተናገረ። ሰዎቹም የቀድሞውን የሚመስል መልስ ሰጡት።
\s5
\v 31 ዳዊት የተናገረው ቃል በተሰማ ጊዜ፥ ወታደሮች ቃሉን ለሳኦል ነገሩት፥ እርሱም ዳዊትን አስጠራው።
\v 32 ከዚያም ዳዊት ሳኦልን፥ "በዚያ ፍልስጥኤማዊ ምክንያት የማንም ልብ አይውደቅ፤ አገልጋይህ ሄዶ ከፍልስጥኤማዊው ጋር ይዋጋል" አለው።
\v 33 ሳኦልም ዳዊትን፥ "አንተ ከዚህ ፍልስጥኤማዊ ጋር ለመዋጋት መሄድ አትችልም፤ አንተ ገና ልጅ ነህ፥ እርሱ ደግሞ ከወጣትነቱ ጀምሮ ተዋጊ ነው" አለው።
\s5
\v 34 ዳዊት ግን ሳኦልን፥ "አገልጋይህ የአባቴን በጎች እጠብቅ ነበር። አንበሳ ወይም ድብ መጥቶ ከመንጋው ጠቦት በሚወስድበት ጊዜ
\v 35 በኋላው ተከትዬ እመታውና ከአፉ አስጠለው ነበር። ሊያጠቃኝ በተነሣብኝ ጊዜም ጉሮሮውን ይዤ እመታውና እገድለው ነበር።
\s5
\v 36 አገልጋይህ አንበሳና ድብ ገድያለሁ። የሕያው እግዚአብሔርን ሠራዊት ስለተገዳደረ ይህም ያልተገረዘ ፍልስጥኤማዊ ከእነርሱ እንደ አንዱ ይሆናል" አለው።
\s5
\v 37 ዳዊትም፥ "እግዚአብሔር ከአንበሳና ከድብ መዳፍ አድኖኛል። ከዚህም ፍልስጥኤማዊ እጅ ያድነኛል" አለው።
\v 38 ከዚያም ሳኦል ዳዊትን፥ "ሂድ፥ እግዚአብሔርም ከአንተ ጋር ይሁን" አለው። ሳኦል የራሱን የጦር መሣሪያ ለዳዊት አስታጠቀው። በራሱ ላይ የነሐስ ቁር ደፋለት፥ ጥሩርም አለበሰው።
\s5
\v 39 ዳዊትም ሰይፉን በጦር ልብሱ ላይ ታጠቀው። ነገር ግን አልተለማመደውምና ለመራመድ አቃተው። ከዚያም ዳዊት ሳኦልን፥ "አልተለማመድኳቸውምና በእነዚህ መዋጋት አልችልም" አለው። ስለዚህ ዳዊት ከላዩ ላይ አወለቃቸው።
\v 40 በትሩን በእጁ ያዘ፥ ከጅረቱም አምስት ድቡልቡል ድንጋዮች መርጦ በእረኛ ኮሮጆው ውስጥ ጨመራቸው። ፍልስጥኤማዊውን በሚቀርብበት ጊዜ ወንጭፉን ይዞ ነበር።
\s5
\v 41 ፍልስጥኤማዊውም በፊት ለፊቱ ከሚሄደው ጋሻ ጃግሬው ጋር መጥቶ ወደ ዳዊት ቀረበ።
\v 42 ፍልስጥኤማዊው ዙሪያውን ሲመለከት ዳዊትን ባየው ጊዜ ቀይ፥ መልከ መልካም ገጽታ ያለው ትንሽ ልጅ ብቻ ስለነበረ ናቀው።
\v 43 ፍልስጥኤማዊው ዳዊትን፥ "በትር ይዘህ የምትመጣብኝ እኔ ውሻ ነኝ?" አለው። ፍልስጥኤማዊውም በአማልክቶቹ ስም ዳዊትን ረገመው።
\s5
\v 44 ፍልስጥኤማዊውም ዳዊትን፥ "ወደ እኔ ና፥ እኔም ሥጋህን ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት እሰጣለሁ" አለው።
\v 45 ዳዊትም ለፍልስጥኤማዊው እንዲህ ሲል መለሰለት፥ "አንተ ሰይፍ፥ ጦርና ጭሬ ይዘህ ትመጣብኛለህ። እኔ ግን አንተ ባቃለልከው፥ የእስራኤል ሠራዊት አምላክ በሆነው፥ በእግዚአብሔር ስም እመጣብሃለሁ።
\s5
\v 46 ዛሬ እግዚአብሔር በአንተ ላይ ድልን ይሰጠኛል፥ እገድልሃለሁ፥ ራስህንም ከሰውነትህ ላይ አነሣዋለሁ። ዛሬ የፍልስጥኤምን ሠራዊት ሬሳ ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት እሰጣለሁ፥ ይኸውም ምድር ሁሉ በእስራኤል አምላክ እንዳለ እንዲያውቅና
\v 47 በዚህ የተሰበሰበው ሁሉ እግዚአብሔር በሰይፍ ወይም በጦር ድልን እንደማይሰጥ እንዲያውቁ ነው። ጦርነቱ የእግዚአብሔር ነውና እናንተንም በእጃችን ላይ አሳልፎ ይሰጣችኋል።"
\s5
\v 48 ፍልስጥኤማዊው ተነሥቶ ዳዊትን በቀረበው ጊዜ ዳዊት ሊገናኘው ወደ ጠላት ጦር በፍጥነት ሮጠ።
\v 49 ዳዊት እጁን ወደ ኮሮጆው አስገብቶ አንድ ድንጋይ ከዚያ ወሰደ፥ ወነጨፈውና የፍልስጥኤማዊውን ግንባር መታው። ድንጋዩም በፍልስጥኤማዊው ግንባር ውስጥ ጠልቆ ገባ፥ እርሱም በግንባሩ በምድር ላይ ተደፋ።
\s5
\v 50 ዳዊት ፍልስጥኤማዊውን በወንጭፍና በድንጋይ አሸነፈው። ፍልስጥኤማዊውንም መትቶ ገደለው። በዳዊት እጅ ሰይፍ አልነበረም።
\v 51 ከዚያም ዳዊት ሮጠና በፍልስጥኤማዊው ላይ ቆመ፥ ከእርሱም ሰይፉን ወሰደ፥ ከሰገባው አወጣና ገደለው፥ በእርሱም ራሱን ቆርጦ አነሣው። ፍልስጥኤማውያን ጀግናቸው መሞቱን ባዩ ጊዜ ሸሹ።
\s5
\v 52 ከዚያም የእስራኤልና የይሁዳ ሰዎች እልል እያሉ ተነሥተው ፍልስጥኤማውያንን እስከ ሸለቆውና እስከ ኤቅሮን መግቢያ ድረስ አሳደዷቸው። የፍልስጥኤማውያኑ ሬሳ ከሸዓራይም እስከ ጌትና ዔቅሮን ድረስ በየመንገዱ ወድቆ ነበር።
\v 53 የእስራኤል ሰዎች ፍልስጥኤማውያንን ከማሳደድ ተመለሱና የጦር ሰፈራቸውን በዘበዙ።
\v 54 ዳዊት የፍልስጥኤማዊውን ራስ ወስደ፥ ወደ ኢየሩሳሌምም አመጣው፥ የጦር መሣሪያውን ግን በድንኳኑ ውስጥ አኖረው።
\s5
\v 55 ዳዊት ፍልስጥኤማዊውን ለመጋጠም ሲሄድ ሳኦል ባየው ጊዜ፥ የሰራዊቱን አዛዥ አበኔርን፥ "አንተ አበኔር፥ ይህ ወጣት የማን ልጅ ነው?" አለው። አበኔርም፥ "ንጉሥ ሆይ፥ በሕያውነትህ እምላለሁ፥ አላውቅም" አለው።
\v 56 ንጉሡም፥ "የማን ልጅ እንደሆነ ምናልባት ሊያውቁት የሚችሉትን ጠይቅ" አለው።
\s5
\v 57 ዳዊት ፍልስጥኤማዊውን ገድሎ በተመለሰ ጊዜ፥ አበኔር ወሰደው፥ የፍልስጥኤማዊውን ራስ በእጁ እንደያዘ ወደ ሳኦል አመጣው።
\v 58 ሳኦልም፥ "አንተ ወጣት፥ የማን ልጅ ነህ?" አለው። ዳዊትም፥ "እኔ የቤተ ልሔማዊው የአገልጋይህ የእሴይ ልጅ ነኝ" ብሎ መለሰለት።
\s5
\c 18
\p
\v 1 ለሳኦል መናገሩን በጨረሰ ጊዜ የዮናታን ነፍስ በዳዊት ነፍስ ታሰረች፥ ዮናታንም እንደ ራሱ ነፍስ አድርጎ ወደደው።
\v 2 በዚያ ቀን ሳኦል ዳዊትን ወደ ራሱ አገልግሎት ወሰደው፤ ወደ አባቱ ቤት እንዲመለስ አላሰናበተውም።
\s5
\v 3 ዮናታን ዳዊትን እንደ ራሱ ነፍስ አድርጎ ስለወደደው በመካከላቸው የወዳጅነት ቃል ኪዳን አደረጉ።
\v 4 ዮናታን የለበሰውን ካባ አውልቆ ከጦር ልብሱ ጋር፥ እንዲሁም ሰይፉን፥ ቀስቱንና መታጠቂያውን ለዳዊት ሰጠው።
\s5
\v 5 ዳዊት ሳኦል ወደሚልከው ቦታ ሁሉ ይሄድ ነበር፥ ይከናወንለትም ነበር። ሳኦልም በተዋጊዎቹ ላይ ሾመው። ይህም በሕዝቡ ዓይን ሁሉ ደግሞም በሳኦል አገልጋዮች ፊት ደስ የሚያሰኝ ሆነ።
\s5
\v 6 ፍልስጥኤማውያንን ድል አድርገው ወደ መኖሪያቸው በመመለስ ላይ እያሉ ከእስራኤል ከተሞች ሁሉ ንጉሥ ሳኦልን ለመገናኘት፥ ሴቶች በከበሮና በሙዚቃ መሳሪያዎች በደስታ እየዘመሩና እየጨፈሩ መጡ።
\v 7 ሴቶቹም ሲጫወቱ እየተቀባበሉ ይዘምሩ ነበር፤ እነርሱም፥ "ሳኦል ሺዎችን ገደል፥ ዳዊትም ዐሥር ሺዎችን ገደለ" እያሉ ዘመሩ።
\s5
\v 8 ሳኦል እጅግ ተቆጣ፥ ይህም መዝሙር አስከፋው። እርሱም፥ "ለዳዊት ዐሥር ሺዎች አሉ፥ ለእኔ ግን ሺዎችን ብቻ። ታዲያ ከመንግሥት በቀር ምን ቀረው?" አለ።
\v 9 ሳኦል ከዚያን ቀን ጀምሮ ዳዊትን በጥርጣሬ ዐይን ተመለከተው።
\s5
\v 10 በቀጣዩ ቀን በሳኦል ላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ክፉ መንፈስ መጣበት። እርሱም በቤት ውስጥ እንደ ዕብድ ይለፈልፍ ነበር። ስለዚህ ዳዊት በየቀኑ ያደርግ እንደነበረው በገናውን ይደረድር ነበር። ሳኦልም በእጁ ጦር ይዞ ነበር።
\v 11 ሳኦል፥ "ዳዊትን ከግድግዳው ጋር አጣብቀዋለሁ" ብሎ በማሰብ ጦሩን ወረወረበት። ነገር ግን ዳዊት ከሳኦል ፊት ሁለት ጊዜ እንዲህ ባለ መንገድ አመለጠ።
\v 12 እግዚአብሔር ከዳዊት ጋር እንጂ ከእርሱ ጋር ስላልነበረ ሳኦል ዳዊትን ፈራው።
\s5
\v 13 ስለዚህ ሳኦል ከፊቱ አራቀው፥ ሻለቃም አድርጎ ሾመው። በዚህ ሁኔታ ዳዊት በሕዝቡ ፊት ይወጣና ይገባ ነበር።
\v 14 እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ስለነበረ ዳዊት የሚሠራው ሁሉ ይከናወንለት ነበር።
\s5
\v 15 እንደ ተከናወነለት ሳኦል ባየ ጊዜ እጅግ ፈራው።
\v 16 ነገር ግን በፊታቸው ይወጣና ይገባ ስለነበረ እስራኤልና ይሁዳ ሁሉ ዳዊትን ወደዱት።
\s5
\v 17 ከዚያም ሳኦል ዳዊትን፥ "ትልቋ ልጄ ሜሮብ ይቹት። እርሷን እድርልሃለሁ። ብቻ ጎብዝልኝ፥ የእግዚአብሔርን ጦርነቶችም ተዋጋ" አለው። ሳኦል፥ "እጄ በእርሱ ላይ አይሁን፥ ነገር ግን የፍልስጥኤማውያን እጅ በእርሱ ላይ ይሁን" ብሎ አስቦአልና።
\v 18 ዳዊትም ሳኦልን፥ "የንጉሥ አማች ለመሆን እኔ ማነኝ? ሕይወቴ ወይም የአባቴ ቤተ ሰብ በእስራኤል ውስጥ ምንድነው?" አለው።
\s5
\v 19 ነገር ግን የሳኦል ልጅ ሜሮብ ለዳዊት የምትዳርበት ጊዜ ሲደርስ ለመሓላታዊው ለኤድሪኤል ተዳረች።
\s5
\v 20 ነገር ግን የሳኦል ልጅ ሜልኮል ዳዊትን ወደደችው። ለሳኦል ነገሩት፥ ይህም እርሱን ደስ አሰኘው።
\v 21 ከዚያም ሳኦል፥ "ወጥመድ እንድትሆነውና የፍልስጥኤማውያን እጅ በእርሱ ላይ እንድትሆን እርሷን እድርለታለሁ" ብሎ አሰበ። ስለዚህ ሳኦል ዳዊትን ለሁለተኛ ጊዜ፥ "አማቼ ትሆናለህ" አለው።
\s5
\v 22 ሳኦል አገልጋዮቹን እንዲህ ሲል አዘዛቸው፥ "ዳዊትን በምስጢር እንዲህ በሉት፥ 'አስተውል፥ ንጉሡ በአንተ ደስ ብሎታል፥ አገልጋዮቹም ሁሉ ይወዱሃል። እንግዲያው የንጉሡ አማች ሁን'"
\s5
\v 23 ስለዚህ የሳኦል አገልጋዮች ይህንን ቃል ለዳዊት ነገሩት። ዳዊትም፥ "እኔ ድሃና ብዙም የማልታወቅ ሰው ሆኜ እያለሁ የንጉሥ አማች እንድሆን ማሰባችሁ ጉዳዩ እንዴት ቀልሎ ታያችሁ?" አላቸው።
\v 24 የሳኦል አገልጋዮችም ዳዊት የተናገረውን ቃል ነገሩት።
\s5
\v 25 ሳኦልም፥ "ለዳዊት እንዲህ ትሉታላችሁ፥ 'የንጉሡን ጠላቶች ለመበቀል ከአንድ መቶ የፍልስጥኤማውያን ሸለፈት ብቻ በቀር ንጉሡ ምንም ጥሎሽ አይፈልግም"። ዳዊት በፍልስጥኤማውያን እጅ እንዲወድቅ ለማድረግ ሳኦል አሰበ።
\v 26 አገልጋዮቹ ይህንን ቃል ለዳዊት በነገሩት ጊዜ የንጉሡ አማች መሆን ዳዊትን ደስ አሰኘው።
\s5
\v 27 እነዚያ ቀናት ከማብቃታቸው በፊት፥ ዳዊት ከሰዎቹ ጋር ሄዶ ሁለት መቶ ፍልስጥኤማውያንን ገደለ። ዳዊት የንጉሡ አማች ይሆን ዘንድ ሸለፈቶቹን አመጣ፥ ለንጉሡም ሙሉውን ቁጥር አስረከቡ። ስለዚህ ሳኦል ልጁን ሜልኮልን ዳረለት።
\v 28 እግዚአብሔር ከዳዊት ጋር እንደነበረ ሳኦል አየ፥ ዐወቀም። የሳኦል ልጅ ሜልኮልም ወደደችው።
\v 29 ሳኦልም ዳዊትን የበለጠ ፈራው። ሳኦል የዳዊት ጠላቱ እንደሆነ ቀጠለ።
\s5
\v 30 ከዚያም የፍልስጥኤም ልዑላን ብዙ ጊዜ ያደርጉት እንደነበረው ለጦርነት መጡ፥ ዳዊት ከሳኦል አገልጋዮች ሁሉ በበለጠ ሁኔታ የተሳካለት ሆነ፥ በመሆኑም ስሙ እጅግ የተከበረ ሆነ።
\s5
\c 19
\p
\v 1 ሳኦል ልጁን ዮናታንን እና አገልጋዮቹን በሙሉ ዳዊትን እንዲገድሉት ነገራቸው። የሳኦል ልጅ ዮናታን ግን ዳዊትን እጅግ ይወድደው ነበር።
\v 2 ስለዚህ ዮናታን ዳዊትን፥ "አባቴ ሳኦል ሊገድልህ ይፈልጋል። በመሆኑም ለራስህ ጥንቃቄ አድርግ፥ በነገውም ቀን በምስጢራዊ ቦታ ተደበቅ።
\v 3 አንተ ባለህበት አካባቢ ሄጄ በአባቴ አጠገብ እቆማለሁ፥ ስለ አንተም አነጋግረዋለሁ። አንዳች ነገር ካገኘሁኝም እነግርሃለሁ“ አለው።
\s5
\v 4 ዮናታንም ለአባቱ ለሳኦል ስለ ዳዊት መልካምን ነገር ተናገረ፥ እንዲህም አለው፥”ንጉሡ በአገልጋዩ በዳዊት ላይ ክፉ ነገር አያድርግ። እርሱ ክፉ አላደረገብህም፥ እርሱ የሠራው ሥራ ለአንተ መልካም ሆኖልሃልና።
\v 5 ነፍሱን በእጁ ላይ ጥሎ ፍልስጥኤማዊውን ገደለ። እግዚአብሔርም ለእስራኤል በሙሉ ታላቅ ድልን ሰጠ። አንተም አይተህ ደስ ብሎህ ነበር። ያለምንም ምክንያት ዳዊትን በመግደልህ በንጹህ ደም ላይ ለምን ኃጢአት ትሠራለህ?“
\s5
\v 6 ሳኦልም ዮናታንን ሰማው። ሳኦልም፥”ሕያው እግዚአብሔርን! ዳዊት አይገደልም“ ብሎ ማለ።
\v 7 ከዚያም ዮናታን ዳዊትን ጠራው፥ ዮናታንም ይህንን ነገር ሁሉ ነገረው። ዮናታንም ዳዊትን ወደ ሳኦል አመጣው፥ እርሱም እንደቀድሞው በፊቱ ነበረ።
\s5
\v 8 እንደገናም ጦርነት ሆነ። ዳዊት ወጥቶ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ተዋጋ፥ በታላቅ አገዳደልም ድል አደረጋቸው። እነርሱም ከፊቱ ሸሹ።
\v 9 ሳኦል በእጁ ጦሩን እንደያዘ በቤቱ ተቀምጦ እያለ ክፉ መንፈስ ከእግዚአብሔር ዘንድ በሳኦል ላይ መጣበት፥ ዳዊትም በገና ይደረድር ነበር።
\s5
\v 10 ሳኦል በጦሩ ዳዊትን ከግድግዳው ጋር ለማጣበቅ ሞከረ፥ ዳዊት ግን ከሳኦል ፊት ዘወር አለ፥ ስለዚህ የሳኦል ጦር በግድግዳው ላይ ተሰካ። በዚያ ምሽት ዳዊት ሸሽቶ አመለጠ።
\v 11 ሳኦልም በማግስቱ ይገድለው ዘንድ ከብበው እንዲጠብቁት ወደ ዳዊት ቤት መልዕክተኞች ላከ። የዳዊት ሚስት ሜልኮልም፥”በዚህ ሌሊት ሕይወትህን ካላዳንክ ነገ መገደልህ ነው“ አለችው።
\s5
\v 12 ስለዚህ ሜልኮል ዳዊትን በመስኮት እንዲወርድ አደረገችው። እርሱም ሄደ፥ ሸሽቶም አመለጠ።
\v 13 ሜልኮልም የቤተሰቡን የጣዖት ምስል ወስዳ በአልጋው ውስጥ አጋደመችው። በራስጌው ከፍየል ጸጉር የተሠራ ትራስ አስቀመጠች፥ በልብስም ሸፈነችው።
\s5
\v 14 ሳኦል ዳዊትን የሚወስዱ መልዕክተኞች በላከ ጊዜ እርሷ፥ "አሞታል" አለቻቸው።
\v 15 ከዚያም ሳኦል ዳዊትን እንዲያዩት መልዕክተኞች ላከ፥ እርሱም፥ "እንድገድለው ከነዐልጋው አምጡልኝ" አላቸው።
\s5
\v 16 መልዕክተኞቹ ወደ ቤት በገቡ ጊዜ፥ በዐልጋው ውስጥ የቤተሰቡ የጣዖት ምስል፥ በራስጌውም ከፍየል ጸጉር የተሠራው ትራስ ነበር።
\v 17 ሳኦል ሜልኮልን፥ "ጠላቴ እንዲሄድና እንዲያመልጥ በማድረግ ለምን አታለልሽኝ?" አላት። ሜልኮልም ለሳኦል፥ "'ልሂድ፥ አለበለዚያ እገድልሻለሁ' ስላለኝ ነው" ብላ መለሰችለት።
\s5
\v 18 ዳዊትም ሸሽቶ አመለጠ፥ ሳሙኤል ወዳለበት ወደ ራማም ሄደ፥ ሳኦል ያደረገበትንም ሁሉ ነገረው። ከዚያም እርሱና ሳሙኤል ሄዱ፥ በነዋትም ተቀመጡ።
\v 19 ለሳኦልም፥ "ዕወቀው፥ ዳዊት በራማ ነዋት ነው" ተብሎ ተነገረው።
\v 20 ሳኦልም ዳዊትን እንዲይዙት መልዕክተኞችን ላከ። እነርሱም ትንቢት የሚናገሩ የነቢያትን ጉባዔ፥ ሳሙኤልንም መሪያቸው ሆኖ ባዩ ጊዜ በሳኦል መልዕክተኞች ላይ የእግዚአብሔር መንፈስ መጣባቸው፥ እነርሱም ደግሞ ትንቢት ተናገሩ።
\s5
\v 21 ይህ ሁኔታ ለሳኦል በተነገረው ጊዜ፥ ሌሎች መልዕክተኞችን ላከ፥ እነርሱም ደግሞ ትንቢት ተናገሩ። ስለዚህ ሳኦል እንደገና ለሦስተኛ ጊዜ ሌሎች መልዕክተኞችን ላከ፥ እነርሱም ደግሞ ትንቢት ተናገሩ።
\v 22 ከዚያም እርሱ ደግሞ ወደ አርማቴም ሄደ፥ በሤኩ ወዳለው ጥልቅ የውሃ ጉድጓድም መጣ። እርሱም፥”ሳሙኤልና ዳዊት የት ነው ያሉት? “ ብሎ ጠየቀ። አንደኛው ሰው፥”በራማ ነዋት ናቸው“ ብሎ መለሰለት።
\s5
\v 23 ሳኦልም በራማ ወዳለው ነዋት ሄደ። የእግዚአብሔር መንፈስ በእርሱም ላይ መጣ፥ በራማም ወደሚገኘው ወደ ነዋት እስኪደርስ ድረስ በመንገድ ላይ ትንቢት ይናገር ነበር።
\v 24 እርሱም ደግሞ ልብሶቹን አወለቀ፥ በሳሙኤል ፊት እርሱም ደግሞ ትንቢት ተናገረ፥ ያን ቀንና ሌሊቱን ሁሉ ራቁቱን ተጋደመ። እነርሱም፥”ሳኦል ከነቢያት አንዱ ሆነ እንዴ? “ ያሉት በዚህ ምክንያት ነው።
\s5
\c 20
\p
\v 1 ከዚያም ዳዊት በራማ ካለው ከነዋት ሸሽቶ መጣና ዮናታንን፥”ምን አድርጌአለሁ? ጥፋቴስ ምንድነው? በአባትህ ፊት ኃጢአቴ ምን ቢሆን ነው ሕይወቴን ለማጥፋት የሚፈልገው? “ አለው።
\v 2 ዮናታንም ዳዊትን፥”ይህ ከአንተ ይራቅ፥ አትሞትም። ነገሩ ትልቅም ይሁን ትንሽ ሳይነግረኝ አባቴ ምንም አያደርግም። አባቴ ይህንን ነገር ለምን ይደብቀኛል? ነገሩ እንዲህ አይደለም።
\s5
\v 3 ዳዊት ግን እንደገና ማለና፥ “በፊትህ ሞገስ ማግኘቴን አባትህ ያውቃል። እርሱም፥ 'ይህንን ዮናታን አይወቅ፥ ካልሆነ ያዝናል' ይላል። በሕያው እግዚአብሔር ስም፥ በሕያው ነፍስህም እምላለሁ፥ በእኔና በሞት መካከል የቀረው አንድ እርምጃ ነው" አለው።
\s5
\v 4 ዮናታን ዳዊትን፥ "የምትጠይቀኝን ሁሉ አደርግልሃለሁ" አለው።
\v 5 ዳዊትም ዮናታንን፥ "ነገ አዲስ ጨረቃ የምትታይበት ቀን ነው፥ ከንጉሡ ጋር ለመብላት መቀመጥ ይኖርብኛል። እስከ ሦስተኛው ቀን ምሽት ድረስ በመስኩ ውስጥ ሄጄ እንድደበቅ ፍቀድልኝ" አለው።
\s5
\v 6 አባትህ እኔን በማጣቱ ከጠየቀህ፥ "ዳዊት፥ መላው ቤተ ሰቡ ዓመታዊ መሥዋዕት ስለሚያቀርቡ ወደ ቤተ ልሔም ይሄድ ዘንድ እንድፈቅድለት አጥብቆ ለመነኝ' በለው።
\v 7 እርሱም፥ 'መልካም ነው' ካለህ ነገሩ ለአገልጋይህ ሰላም ሆኗል ማለት ነው። ነገር ግን እርሱ እጅግ ከተቆጣ ክፉ ሊያደርግብኝ እንደወሰነ በዚህ ታውቃለህ።
\s5
\v 8 እንግዲህ አገልጋይህን በርኅራኄ ተመልከተኝ። በእግዚአብሔር ፊት ከአገልጋይህ ጋር ቃል ኪዳን አድርገሃልና። ኃጢአት ቢገኝብኝ ግን አንተው ግደለኝ፤ ለምንስ ወደ አባትህ ትወስደኛለህ?" አለው።
\v 9 ዮናታንም፥ "ይህ ከአንተ ይራቅ! አባቴ ክፉ ሊያደርግብህ መወሰኑን ባውቅ አልነግርህም?"
\s5
\v 10 ዳዊትም ዮናታንን፥ "አባትህ አንደ አጋጣሚ በቁጣ ቢመልስልህ ማን ይነግረኛል?" አለው።
\v 11 ዮናታንም ዳዊትን፥ "ና፥ ወደ መስኩ እንሂድ" አለው። ሁለቱም ወደ መስኩ ሄዱ።
\s5
\v 12 ዮናታንም ዳዊትን እንዲህ አለው፥ "የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ምስክር ይሁን። ነገ ወይም በሦስተኛው ቀን እንደዚህ ባለው ሰዓት አባቴን በምጠይቀው ጊዜ፥ ስለ ዳዊት በጎ አሳብ ካለው ልኬብህ አላሳውቅህም?
\v 13 አባቴ በአንተ ላይ ክፉ ማድረጉ የሚያስደስተው ከሆነ በሰላም እንድትሄድ ባላሳውቅህና ባላሰናብትህ እግዚአብሔር በዮናታን ላይ ይህንን እና ከዚህም የከፋውን ያድርግበት። ከአባቴ ጋር እንደነበረ እግዚአብሔር ከአንተም ጋር ይሁን።
\s5
\v 14 አንተስ በሕይወት በምኖርበት ዘመን እንዳልሞት የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታማኝነት አታሳየኝም?
\v 15 እግዚአብሔር የዳዊትን ጠላቶች፥ እያንዳንዳቸውን ከምድር ላይ በሚያጠፋበት ጊዜ የቃል ኪዳን ታማኝነትህን ከቤቴ አታጥፋ"።
\v 16 ሰለዚህ ዮናታን ከዳዊት ቤት ጋር ቃል ኪዳን አደረገና”እግዚአብሔር ከዳዊት ጠላቶች እጅ ይጠይቀው“ አለ።
\s5
\v 17 ዮናታን ነፍሱን እንደሚወዳት ዳዊትን ይወደው ስለነበረ፥ ለእርሱ ከነበረው ፍቅር የተነሣ ዳዊት እንደገና እንዲምልለት አደረገ።
\v 18 ከዚያም ዮናታን እንዲህ አለው፥”ነገ አዲስ ጨረቃ የምትታይበት የወር መጀመሪያ ቀን ነው። ወንበርህ ባዶ ስለሚሆን ላትኖር ነው።
\v 19 ለሦስት ቀናት ከቆየህ በኋላ፥ ፈጥነህ ውረድና በዚህ ጉዳይ ካሁን በፊት ወደተደበቅህበት ስፍራ መጥተህ በኤዜል ድንጋይ አጠገብ ቆይ።
\s5
\v 20 በዒላማ ላይ የምወረውር መስዬ ሦስት ፍላጻዎችን ወደዚያ አቅራቢያ እወረውራለሁ።
\v 21 ከእኔ ጋር ያለውን ታዳጊ ወጣት እልከውና፥ 'ሂድ ፍላጻዎቹን ፈልግ' እለዋለሁ። ታዳጊውን ልጅ፥ 'ተመልከት፥ ፍላጻዎቹ አጠገብህ ናቸው፤ ውሰዳቸው' ካልኩት ሕያው እግዚአብሔርን! ለአንተ ደኅንነት እንጂ ጉዳት አይሆንብህምና ትመጣለህ።
\s5
\v 22 ነገር ግን ታዳጊውን ወጣት፥ 'ተመልከት፥ ፍላጻዎቹ ከአንተ በላይ ናቸው' ካልኩት እግዚአብሔር አሰናብቶሃልና መንገድህን ሂድ።
\v 23 እኔና አንተ ያደረግነውን ስምምነት በሚመለከት እግዚአብሔር በእኔና በአንተ መካከል ለዘላለም ምስክር ነው።"
\s5
\v 24 ስለዚህ ዳዊት በመስኩ ውስጥ ተደበቀ። አዲስ ጨረቃ በሆነ ጊዜ ንጉሡ ምግብ ለመብላት ተቀመጠ።
\v 25 ንጉሡ እንደተለመደው በግድግዳው አጠገብ በነበረው በመቀመጫው ላይ ተቀመጠ። ዮናታን ተነሣ፥ አበኔርም በሳኦል አጠገብ ተቀምጦ ነበር። የዳዊት ቦታ ግን ባዶ ነበር።
\s5
\v 26 በዚያን ቀን ሳኦል ገና ምንም አልተናገረም፥ ምክንያቱም፥ "አንድ ነገር ደርሶበት ይሆናል፥ ወይም በሕጉ መሰረት አልነጻም ይሆናል፤ በርግጥ ባይነጻ ነው" ብሎ ሳላሰበ ነው።
\v 27 ነገር ግን አዲስ ጨረቃ በታየችበት ማግስት፥ በሁለተኛው ቀን የዳዊት ስፍራ ባዶ ነበር። ሳኦል ልጁን ዮናታንን፥ "የእሴይ ልጅ ዳዊት ትላንትም ይሁን ዛሬ ወደ ማዕድ ያልመጣው ለምንድነው?" አለው።
\s5
\v 28 ዮናታንም ለሳኦል እንዲህ በማለት መለሰለት፥ "ዳዊት ወደ ቤተ ልሔም ለመሄድ እንድፈቅድለት አጥብቆ ለመነኝ።
\v 29 እርሱም፥ 'እባክህን እንድሄድ ፍቀድልኝ። በዚያ ከተማ ቤተሰባችን የሚያቀርበው መሥዋዕት አለ፥ እኔም በዚያ እንድገኝ ወንድሜ አዞኛል። አሁንም በፊትህ ሞገስን ካገኘሁ፥ ወንድሞቼን አያቸው ዘንድ እንድሄድ እባክህን ፍቀድልኝ' አለኝ። ወደ ንጉሡ ማዕድ ያልመጣው በዚህ ምክንያት ነው።"
\s5
\v 30 ከዚያም የሳኦል ቁጣ በዮናታን ላይ ነደደ፥ እርሱም እንዲህ አለው፥ "አንተ የጠማማና አመጸኛ ሴት ልጅ! ለራስህ ኃፍረትና ለእናትህ የዕርቃንነት ኃፍረት የእሴይን ልጅ እንደ መረጥክ የማላውቅ መሰለህ?
\v 31 የእሴይ ልጅ በምድር ላይ እስካለ ድረስ አንተም ሆንክ መንግሥትህ አትጸኑም። አሁንም በእርግጥ መሞት የሚገባው ነውና ልከህ አስመጣልኝ።“
\s5
\v 32 ዮናታንም አባቱን ሳኦልን፥”የሚገደለው በምን ምክንያት ነው? ያደረገውስ ምንድነው? “ ሲል መለሰለት።
\v 33 በዚያን ጊዜ ሳኦል ሊገድለው ጦሩን ወረወረበት። ስለዚህ አባቱ ዳዊትን ለመግደል መወሰኑን ዮናታን ተረዳ።
\v 34 ዮናታን እጅግ ተቆጥቶ ከማዕድ ተነሣ፥ አባቱ ስላዋረደው ስለ ዳዊት አዝኖ ነበርና በወሩ በሁለተኛው ቀን ምንም ምግብ አልበላም።
\s5
\v 35 በማግስቱ ዮናታን ከዳዊት ጋር ወደተቀጣጠሩበት መስክ ሄደ፥ አንድ ታዳጊ ወጣትም አብሮት ነበር።
\v 36 እርሱም ታዳጊውን ወጣት፥”ሩጥ፥ የምወረውራቸውን ፍላጻዎች ሰብስብ“ አለው። ታዳጊው ወጣት በሚሮጥበት ጊዜ ፍላጻውን ከበላዩ ላይ ወረወረው።
\v 37 ታዳጊው ወጣት ዮናታን የወረወረው ፍላጻ ወደ ወደቀበት ስፍራ በደረሰ ጊዜ፥ ዮናታን ታዳጊውን ተጣርቶ፥ "ፍላጻው ከአንተ በላይ ነው" አለው።
\s5
\v 38 ዮናታንም ታዳጊውን፥ "ቶሎ በል፥ ፍጠን፥ አትዘግይ!" አለው። ስለዚህ የዮናታኑ ታዳጊ ወጣት ፍላጻዎቹን ሰብስቦ ወደ ጌታው መጣ።
\v 39 ታዳጊው ወጣት ግን አንዳች የሚያውቀው አልነበረም። ጉዳዩን የሚያውቁት ዮናታንና ዳዊት ብቻ ነበሩ።
\v 40 ዮናታን የጦር መሣሪያዎቹን ለታዳጊው ወጣት ሰጥቶ፥ "ሂድ፥ ወደ ከተማ ውሰዳቸው" አለው።
\s5
\v 41 ታዳጊው ወጣት እንደ ሄደ፥ ዳዊት ከጉብታው ኋላ ተነሣ፥ ወደ ምድርም ተጎንብሶ ሦስት ጊዜ ሰገደ። እርስ በእርሳቸው ተሳሳሙ፥ ተላቀሱም፥ ዳዊትም አብዝቶ አለቀሰ።
\v 42 ዮናታንም ዳዊትን፥”'እግዚአብሔር፥ በእኔና በአንተ፥ በዘሬና በዘርህ መካከል ለዘላለም ይሁን' ተባብለን በእግዚአብሔር ስም ተማምለናልና በሰላም ሂድ” አለው። ከዚያም ዳዊት ተነሥቶ ሄደ፥ ዮናታንም ወደ ከተማ ተመለሰ።
\s5
\c 21
\p
\v 1 ከዚያም ዳዊት ካህኑን አቢሜሌክን ለማግኘት ወደ ኖብ መጣ። አቢሜሌክም ዳዊትን ለመገናኘት እየተንቀጠቀጠ መጣና፥ “አንድም ሰው አብሮህ ያልሆነውና ብቻህን የሆንከው ለምንደነው?” አለው።
\v 2 ዳዊትም ካህኑን አቢሜሌክን፥ “ንጉሡ ለአንድ ጉዳይ ልኮኛል። እርሱም፥ 'ስለምልክህ ጉዳይና ያዘዝኩህን ነገር ማንም እንዳያውቅ'ብሎኛል። ወጣቶቹንም የሆነ ቦታ ላይ እንዲጠብቁኝ ነግሬአቸዋለሁ።
\s5
\v 3 ታዲያ አሁን እጅህ ላይ ምን አለ? አምስት እንጀራ ወይም ያለውን ነገር ስጠኝ” አለው።
\v 4 ካህኑም ለዳዊት መልሶ፥ “ማንኛውም ሰው የሚበላው እንጀራ የለኝም፥ ነገር ግን ታዳጊ ወጣቶቹ ራሳቸውን ከሴቶች ጠብቀው ከሆነ የተቀደሰ እንጀራ አለ” አለው።
\s5
\v 5 ዳዊትም ለካህኑ እንዲህ ሲል መለሰለት፥ “በእርግጥ በእነዚህ ሦስት ቀናት ከሴቶች ተጠብቀናል። ለተራ ተልዕኮ በሚወጡበት ጊዜ ራሳቸውን ካነጹ ለዚህ ተልዕኮማ ከእኔ ጋር ያሉት ወጣቶች ሰውነት ለእግዚአብሔር እንዴት የበለጠ የተቀደሰ አይሆንም?”
\v 6 ስለዚህ ከተነሣ በኋላ በስፍራው ትኩስ እንጀራ ይደረግ ዘንድ፥ ከእግዚአብሔር ፊት ከተነሣው፥ ከገጸ ሕብስቱ በስተቀር ሌላ እንጀራ በዚያ አልነበረምና፥ ካህኑ ለእግዚአብሔር የተቀደሰውን እንጀራ ሰጠው።
\s5
\v 7 በዚያም ቀን ከሳኦል አገልጋዮች አንዱ በእግዚአብሔር ፊት በእዚያ ቆይቶ ነበር፤ ስሙ ዶይቅ የሚባል ኤዶማዊ፥ የሳኦል የእረኞቹ አለቃ ነበር።
\s5
\v 8 ዳዊት አቢሜሌክን፥ "እዚህ ጦር ወይም ሰይፍ ይኖርሃል? የንጉሡ ጉዳይ አስቸኳይ ስለነበረ ሰይፌንም ሆነ መሣሪያዬን ይዤ አልመጣሁም“ አለው።
\v 9 ካህኑም፥”በዔላ ሸለቆ የገደልከው የፍልስጥኤማዊው የጎልያድ ሰይፍ በጨርቅ ተጠቅልሎ እዚህ ከኤፉዱ ኋላ አለ። ሌላ የጦር መሣሪያ በዚህ የለምና እርሱን ልትወስደው ብትፈልግ ውሰደው።" ዳዊትም፥ "እንደ እርሱ ያለ ሌላ ሰይፍ የለም፤ እርሱን ስጠኝ" አለው።
\s5
\v 10 በዚያን ቀን ዳዊት ተነሥቶ ከሳኦል ፊት ሸሸ፥ ወደ ጌት ንጉሥ ወደ አንኩስም ሄደ።
\v 11 የአንኩስ አገልጋዮችም ንጉሡን፥ "ይህ የምድሪቱ ንጉሥ የሆነው ዳዊት አይደለም? 'ሳኦል ሺዎችን ገደለ፥ ዳዊት ዐሥር ሺዎችን ገደለ' እያሉ ስለ እርሱ በዘፈን እየተቀባበሉ ዘምረውለት አልነበረም? አሉት።
\s5
\v 12 ዳዊት ይህንን ቃል በልቡ አኖረው፥ የጌትን ንጉሥ አንኩስንም እጅግ ፈራው።
\v 13 በፊታቸውም አዕምሮውን ለወጠ፥ በያዙት ጊዜም እንደ ዕብድ ሆነ፤ የቅጥሩን በር እየቧጨረም ለሃጩን በጺሙ ላይ አዝረከረከ።
\s5
\v 14 አንኩስም አገልጋዮቹን፥ “ተመልከቱ፥ ሰውዬው ዕብድ እንደሆነ ታያላችሁ።
\v 15 ወደ እኔ ለምን አመጣችሁት? ይህንን ሰው በፊቴ እንዲያብድ ወደ እኔ ያመጣችሁት ያበዱ ሰዎችን ስላጣሁኝ ነው? በእርግጥ እንዲህ ያለው ሰው ወደ ቤቴ ይገባል?” አላቸው።
\s5
\c 22
\p
\v 1 ስለዚህ ዳዊት ያንን ትቶ ወደ ዓዶላም ዋሻ አመለጠ። ወንድሞቹና የአባቱ ቤተሰብ በሙሉ ይህንን በሰሙ ጊዜ ወደዚያ ወደ እርሱ ወረዱ።
\v 2 የተጨነቁ፥ ዕዳ ያለባቸውና የተከፉ ሁሉ ወደ እርሱ ተሰበሰቡ። ዳዊትም አዛዣቸው ሆነ። ከእርሱም ጋር ወደ አራት መቶ የሚጠጉ ሰዎች ነበሩ።
\s5
\v 3 ዳዊት ከዚያ በሞዓብ ወዳለችው ወደ ምጽጳ ሄደ። እርሱም የሞዓብን ንጉሥ፥ “እግዚአብሔር የሚያደርግልኝን እስካውቅ ድረስ እባክህን አባቴና እናቴ አንተጋ እንዲኖሩ ፈቃድህ ይሁን” አለው።
\v 4 እነርሱንም በሞዓብ ንጉሥ ዘንድ ተዋቸው። ዳዊት በጠንካራው ምሽግ ውስጥ በነበረበት ጊዜ ሁሉ አባቱና እናቱ ከንጉሡ ጋር ኖሩ።
\v 5 ከዚያም ነቢዩ ጋድ ዳዊትን፥ “በጠንካራው ምሽግ ውስጥ አትቆይ። እርሱን ትተህ ወደ ይሁዳ ምድር ሂድ” አለው። ስለዚህ ዳዊት ያንን ትቶ ወደ ሔሬት ጫካ ሄደ።
\s5
\v 6 ዳዊት ከእርሱ ጋር ከነበሩት ሰዎች ጋር መገኘቱን ሳኦል ሰማ። ሳኦል በጊብዓ ከአጣጥ ዛፍ ስር በእጁ ጦሩን እንደያዘ ተቀምጦ ነበር፥ አገልጋዮቹም ሁሉ በዙሪያው ቆመው ነበር።
\s5
\v 7 ሳኦል በዙሪያው የቆሙትን አገልጋዮቹን እንዲህ አላቸው፥ “እናንተ የብንያም ሰዎች ሆይ፥ አሁን ስሙ! የእሴይ ልጅ ለእያንዳንዳችሁ እርሻና የወይን ቦታ ይሰጣችኋል? ሁላችሁም በእኔ ላይ ስላደማችሁበት ምትክ ሻለቆችና መቶ አለቆችስ አድርጎ ይሾማችኋል?
\v 8 ልጄ ከእሴይ ልጅ ጋር ቃል ኪዳን ባደረገ ጊዜ ከእናንተ አንዱም አልነገረኝም። አንዳችሁም ስለ እኔ አላዘናችሁም። ልጄ አገልጋዬን ዳዊትን በእኔ ላይ ሲያነሣሣው ከእናንተ ማንም አልነገረኝም። ዛሬ ተደብቋል፥ እኔን ለማጥቃትም ይጠባበቃል።"
\s5
\v 9 ከዚያም በሳኦል አገልጋዮች መካከል ቆሞ የነበረው ኤዶማዊው ዶይቅ፥ "የእሴይን ልጅ ወደ ኖብ፥ ወደ አኪጦብ ልጅ ወደ አቢሜሌክ መጥቶ አይቼዋለሁ።
\v 10 አቤሜሌክም እግዚአብሔር ዳዊትን እንዲረዳው ጸለየለት፥ እርሱም ስንቅና የፍልስጥኤማዊውን የጎልያድን ሰይፍ ሰጠው" አለው።
\s5
\v 11 ንጉሡም የአኪጦብን ልጅ ካህኑን አቢሜሌክንና የአባቱን ቤተሰብ በሙሉ፥ እንዲሁም በኖብ ይኖሩ የነበሩትን ካህናት እንዲጠራ መልዕክተኛ ላከ። ሁሉም ወደ ንጉሡ መጡ።
\v 12 ሳኦልም፥ "የአኪጦብ ልጅ ሆይ፥ አሁን ስማ!" አለው። እርሱም፥ "ጌታዬ ሆይ፥ ይኸው አለሁ” ብሎ መለሰለት።
\v 13 ሳኦልም እንዲህ አለው፥ “አንተና የእሴይ ልጅ በእኔ ላይ ያሤራችሁት ለምንድነው? ዛሬ እንደሚያደርገው ሁሉ በእኔ ላይ እንዲነሣና በምስጢራዊ ቦታ እንዲደበቅ እንጀራና ሰይፍ ሰጠኸው፥ ይረዳው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር የጸለይክለት ለምንድነው?”
\s5
\v 14 አቢሜሌክም ለንጉሡ፥ “የንጉሡ አማችና በጠባቂዎቹ ላይ የበላይ የሆነ፥ በቤትህም የተከበረ፥ በአገልጋዮችህ ሁሉ መካከል እንደ ዳዊት የታመነ ማነው?
\v 15 እግዚአብሔር እንዲረዳው ስጸልይለት የዛሬው የመጀመሪያዬ ነውን? ይህ ከእኔ ይራቅ! ንጉሡ ምንም ነገር በአገልጋይህ ወይም በአባቴ ቤት ሁሉ ላይ አያኑር። አገልጋይህ ከዚህ ሁሉ ነገር አንዱንም አላውቅምና" ብሎ መለሰለት።
\s5
\v 16 ንጉሡም፥ "አቢሜሌክ ሆይ፥ አንተና የአባትህ ቤት በሙሉ በእርግጥ ትሞታላችሁ" ብሎ መለሰለት።
\v 17 ንጉሡም በዙሪያው የቆሙትን ጠባቂዎች፥ "መሸሹን እያወቁ አላስታወቁኝምና፥ እጃቸውም ከዳዊት ጋር ነውና፥ ዙሩና የእግዚአብሔርን ካህናት ግደሏቸው” አላቸው። የንጉሡ አገልጋዮች ግን የእግዚአብሔርን ካህናት ለመግደል እጆቻቸውን አላነሡም።
\s5
\v 18 ከዚያም ንጉሡ ዶይቅን፥ "ዙርና ካህናቱን ግደላቸው" አለው። ስለዚህ ኤዶማዊው ዶይቅ ዞረና መታቸው፤ በዚያም ቀን ከተልባ እግር የተሠራ ኤፉድ የለበሱ ሰማንያ አምስት ሰዎችን ገደለ።
\v 19 እርሱም የካህናቱን ከተማ ኖብን፥ ወንዶችንና ሴቶችን፥ ልጆችንና ሕፃናትን፥ በሬዎችን፥ አህዮችንና በጎችን በሰይፍ ስለት መታቸው። ሁሉንም በሰይፍ ስለት ገደላቸው።
\s5
\v 20 ነገር ግን አብያታር የተባለው የአኪጦብ ልጅ፥ የአቢሜሌክ ልጅ አመለጠ፥ ወደ ዳዊትም ሸሸ።
\v 21 አብያታርም ሳኦል የእግዚአብሔርን ካህናት እንደ ገደለ ለዳዊት ነገረው።
\s5
\v 22 ዳዊትም አብያታርን፥ “ኤዶማዊው ዶይቅ በዚያ በነበረ ጊዜ በእርግጥ ለሳኦል እንደሚነግረው በዚያን ቀን ዐውቄ ነበር። ለአባትህ ቤተ ሰብ ሁሉ መሞት ተጠያቂው እኔ ነኝ! ።
\v 23 ከእኔ ጋር ተቀመጥ፥ አትፍራ። ያንተን ነፍስ የሚፈልግ የእኔንም ነፍስ የሚፈልግ ነው። ከእኔ ጋር በሰላም ትኖራለህ” አለው።
\s5
\c 23
\p
\v 1 ለዳዊትም፥ "ፍልስጥኤማውያን ቅዒላን በመውጋት ላይ ናቸው፥ ዐውድማውንም እየዘረፉ ነው“ ብለው ነገሩት።
\v 2 ስለዚህ ዳዊት እግዚአብሔር እንዲረዳው ጸለየ፥ እርሱም፥”እነዚህን ፍልስጥኤማውያን ሄጄ ልምታቸው? “ ብሎ ጠየቀ። እግዚአብሔርም ዳዊትን፥”ሂድና ፍልስጥኤማውያንን ምታ፥ ቅዒላንም አድን“ አለው።
\s5
\v 3 የዳዊት ሰዎችም፥”ተመልከት፥ እዚሁ በይሁዳ ሆነን እየፈራን ነው። በፍልስጥኤማውያን ላይ ወደ ቅዒላ ለመውጣትማ ይልቁን እንዴት አስፈሪ አይሆንብንም? “ አሉት።
\v 4 ከዚያም ዳዊት እግዚአብሔር እንዲረዳው እንደገና ጸለየ። እግዚአብሔርም፥”ተነሥ፥ ወደ ቅዒላ ውረድ። በፍልስጥኤማውያን ላይ ድልን እሰጥሃለሁ“ ብሎ መለሰለት።
\s5
\v 5 ዳዊትና ሰዎቹም ሄደው ከፍልስጥኤማውያን ጋር ተዋጉ። የቀንድ ከብቶቻቸውን ወሰዱ፥ እነርሱንም በታላቅ አገዳደል መቷቸው። ስለዚህ ዳዊት የቅዒላን ነዋሪዎች አዳናቸው።
\v 6 የአቢሜሌክ ልጅ አብያታር ወደ ቅዒላ ወደ ዳዊት በሸሸ ጊዜ ኤፉዱን ይዞ ወርዶ ነበር።
\s5
\v 7 ዳዊት ወደ ቅዒላ መሄዱ ለሳኦል ተነገረው። ሳኦልም፥ "በሮችና መቀርቀሪያዎች ወዳሏት ከተማ በመግባቱ በራሱ ላይ ዘግቷልና እግዚአብሔር በእጄ ላይ ጥሎታል" አለ።
\v 8 ሳኦልም ወደ ቅዒላ ወርደው ዳዊትንና ሰዎቹን እንዲከቡ ሠራዊቱን ሁሉ ለጦርነት ጠራቸው።
\v 9 ዳዊትም ሳኦል ክፉ ሊያደርግበት እንዳቀደ ዐወቀ። እርሱም ካህኑን አብያታርን፥ "ኤፉዱን ወደዚህ አምጣው" አለው።
\s5
\v 10 ዳዊትም፥ "የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ ሳኦል በእኔ ምክንያት ከተማይቱን ለማጥፋት ወደ ቅዒላ ለመምጣት እንደሚፈልግ አገልጋይህ በእርግጥ ሰምቷል።
\v 11 አገልጋይህ እንደ ሰማው፥ ሳኦል ወደዚህ ይወርዳል? የቅዒላ ሰዎችስ በእጁ አሳልፈው ይሰጡኝ ይሆን? የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ እባክህን ለአገልጋይህ እንድትነግረኝ እለምንሃለሁ” አለ። እግዚአብሔርም፥ “አዎን፥ ወደዚህ ይወርዳል” አለው።
\s5
\v 12 ዳዊትም፥ “የቅዒላ ሰዎች እኔንና ሰዎቼን በሳኦል እጅ አሳልፈው ይሰጡናልን?” ብሎ ጠየቀው። እግዚአብሔርም፥ “አሳልፈው ይሰጧችኋል" አለ።
\s5
\v 13 ከዚያም ዳዊትና ወደ ስድስት መቶ የሚደርሱ ሰዎቹ ተነሡ፥ ከቅዒላም ወጥተው ሄዱ፥ ከቦታ ቦታም እየተዘዋወሩ ሄዱ። ዳዊት ከቅዒላ መሸሹ ለሳኦል ተነገረው፥ እርሱም ማሳደዱን አቆመ።
\v 14 ዳዊትም በዚፍ ምድረ በዳ ውስጥ ባለው በኮረብታማው አገር፥ በምድረ በዳው ባለ ምሽግ ውስጥ ኖረ። ሳኦል በየቀኑ ይፈልገው ነበር፥ እግዚአብሔር ግን በእጁ ላይ አልጣለውም።
\s5
\v 15 ዳዊት በዚፍ ምድረ በዳ ሖሬሽ በተባለ ቦታ ነበር፤ ሳኦልም የእርሱን ሕይወት ለማጥፋት እንደ ወጣ አየ።
\v 16 ከዚያም የሳኦል ልጅ ዮናታን ተነሥቶ በሖሬሽ ወደሚገኘው ወደ ዳዊት ሄደ፥ በእግዚአብሔር ስም አበረታታው።
\s5
\v 17 እንዲህም አለው፥ "የአባቴ የሳኦል እጅ አያገኝህምና አትፍራ። አንተ በእስራኤል ላይ ንጉሥ ትሆናለህ፥ እኔም ምክትልህ እሆናለሁ። አባቴ ሳኦልም ደግሞ ይህንን ያውቃል።"
\v 18 እነርሱም በእግዚአብሔር ፊት ቃል ኪዳን አደረጉ። ዳዊት በሖሬሽ ቆየ፥ ዮናታንም ወደ ቤቱ ተመለሰ።
\s5
\v 19 ዚፋውያንም በጊብዓ ወዳለው ወደ ሳኦል መጥተው፥ "ዳዊት ከየሴሞን በስተደቡብ በሚገኘው በኤኬላ ኮረብታ ላይ፥ በሖሬሽ ምሽጎች ውስጥ በመካከላችን ተደብቋል፤
\v 20 አሁንም ንጉሥ ሆይ! ወደዚህ ውረድ፥ ደስ ባለህ ጊዜ ወደዚህ ውረድ! በንጉሡ እጅ አሳልፎ የመስጠቱ ድርሻ የእኛ ይሆናል” አሉት።
\s5
\v 21 ሳኦልም፥ “ስለ እኔ ተቆርቁራችኋልና እግዚአብሔር ይባርካችሁ።
\v 22 ሂዱና በይበልጥ እርግጠኛ ሁኑ። የት እንደ ተደበቀና በዚያ ማን እንዳየው መርምሩና ዕወቁ። እጅግ ተንኮለኛ ስለመሆኑ ተነግሮኛል።
\v 23 ስለዚህ ልብ በሉ፥ ራሱን የሚደብቅባቸውን ቦታዎች በሙሉ መርምሩ። የተረጋገጠ መረጃ ይዛችሁልኝ ተመለሱ፥ ከዚያ በኋላ እኔም ከእናንተ ጋር እሄዳለሁ። በምድሪቱ ላይ ካለ፥ በይሁዳ ሺዎች ሁሉ መካከል እፈልገዋለሁ” አላቸው።
\s5
\v 24 እነርሱም ተነሡ፥ ሳኦልንም ቀድመው ወደ ዚፍ ሄዱ። ዳዊትና ሰዎቹ ከየሴሞን በስተደቡብ በዓረባ በምትገኘው በማዖን ምድረ በዳ ውስጥ ነበሩ።
\v 25 ሳኦልና ሰዎቹም እርሱን ሊፈልጉት ሄዱ። ይህም ለዳዊት ተነገረው፥ ስለዚህ ወደ ዐለታማው ኮረብታ ወርዶ በማዖን ምድረ በዳ ውስጥ ኖረ። ሳኦል በሰማ ጊዜ ዳዊትን በማዖን ምድረ በዳ አሳደደው።
\s5
\v 26 ሳኦል በተራራው በአንዱ ወገን ሄደ፥ ዳዊትና ሰዎቹም በተራራው በወዲያኛው ወገን ይሄዱ ነበር። ዳዊት ከሳኦል ለማምለጥ ተቻኮለ። ሳኦልና ሰዎቹ ዳዊትንና ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሰዎች ለመያዝ እየከበቧቸው በነበሩበት ጊዜ
\v 27 አንድ መልዕክተኛ ወደ ሳኦል መጥቶ፥ “ፍልስጥኤማውያን ምድሪቱን ወረዋታልና ፈጥነህ ና" አለው።
\s5
\v 28 ስለዚህ ሳኦል ዳዊትን ከማሳደድ ተመልሶ ፍልስጥኤማውያንን ለመዋጋት ሄደ። በዚህ ምክንያት ያ ስፍራ የማምለጫ ዐለት ተብሎ ተጠራ።
\v 29 ዳዊት ከዚያ ወጥቶ በዓይንጋዲ ባሉ ምሽጎች ውስጥ ኖረ።
\s5
\c 24
\p
\v 1 ሳኦል ፍልስጥኤማውያንን ከማሳደድ በተመለሰ ጊዜ፥ "ዳዊት በዓይንጋዲ ምድረ በዳ ውስጥ ነው" ተብሎ ተነገረው።
\v 2 ከዚያም ሳኦል ከእስራኤል ሁሉ የተመረጡትን ሦስት ሺህ ሰዎች ይዞ ዳዊትንና ሰዎቹን ለመፈለግ ወደ ዓይንጋዲ ሄደ።
\s5
\v 3 እርሱም በመንገዱ በበጎች ማደሪያ አቅራቢያ ወደነበረ ዋሻ መጣ። ሳኦልም ለመጸዳዳት ወደዚያ ገባ። ዳዊትና ሰዎቹ በዋሻው ውስጥ ከኋላ ጥጉጋ ተቀምጠው ነበር።
\v 4 የዳዊት ሰዎችም፥ "'ደስ ያሰኘህን እንድታደርግበት ጠላትህን በእጅህ ላይ አሳልፌ እሰጥሃለሁ' ባለህ ጊዜ እግዚአብሔር የተናገረው ስለዚህ ቀን ነው” አሉት። ከዚያም ዳዊት ተነሥቶ በጸጥታ በደረቱ እየተሳበ ወደ ፊት በመሄድ የሳኦልን የካባውን ጫፍ ቆረጠው።
\s5
\v 5 ከዚህ በኋላ የሳኦልን የካባውን ጫፍ ስለ ቆረጠ ዳዊትን ኅሊናው ወቀሰው።
\v 6 እርሱም ሰዎቹን፥ "እግዚአብሔር በቀባው በጌታዬ ላይ እጄን በማንሣት እንዲህ ያለውን ነገር ማድረግን እግዚአብሔር ከእኔ ያርቀው" አላቸው።
\v 7 ስለዚህ ዳዊት የእርሱን ሰዎች በዚህ ቃል ገሰጻቸው፥ በሳኦል ላይ አደጋ እንዲጥሉበት አልፈቀደላቸውም። ሳኦል ተነሥቶ ከዋሻው ወጣና መንገዱን ቀጠለ።
\s5
\v 8 ከዚህ በኋላ ዳዊት ተነሥቶ ከዋሻው በመውጣት ሳኦልን፥ "ጌታዬ፥ ንጉሥ ሆይ!" በማለት ተጣራ። ሳኦል ወደ ኋላው ዘወር ብሎ በተመለከተ ጊዜ፥ ዳዊት በመስገድ አክብሮትን አሳየው።
\v 9 ዳዊትም ሳኦልን፥ “ 'ዳዊት ሊጎዳህ ይፈልጋል' የሚሉህን ሰዎች ለምን ትሰማቸዋለህ?
\s5
\v 10 በዋሻው በነበርን ጊዜ እግዚአብሔር ዛሬ እጄ ላይ ጥሎህ እንደነበረ ዓይኖችህ አይተዋል። አንዳንዶቹ እንድገድልህ ነግረውኝ ነበር፥ እኔ ግን ራራሁልህ። እኔም፥ 'በእግዚአብሔር የተቀባ ስለሆነ፥ በጌታዬ ላይ እጄን አላነሣም' አልኩኝ።
\v 11 አባቴ ሆይ ተመልከት፥ በእጄ ላይ ያለውን የካባህን ቁራጭ ተመልከት። የካባህን ጫፍ ቆረጥኩኝ እንጂ አልገደልኩህም፥ በመሆኑም በእጄ ላይ ክፋትና ክህደት እንደሌለ ዕወቅ፤ ምንም እንኳን ሕይወቴን ለማጥፋት ብታሳድደኝም፥ እኔ አልበደልኩህም።
\s5
\v 12 እግዚአብሔር በእኔና በአንተ መካከል ይፍረድ፥ እግዚአብሔር ይበቀልልኝ፥ እጄ ግን ባንተ ላይ አትሆንም።
\v 13 የጥንቱ ምሳሌ፥ 'ከክፉ ሰው ክፋት ይወጣል' ይላል። እጄ ግን ባንተ ላይ አትሆንም።
\s5
\v 14 የእስራኤል ንጉሥ የወጣው በማን ላይ ነው? የምታሳድደው ማንን ነው? የሞተን ውሻ! ቁንጫን!
\v 15 እግዚአብሔር ፈራጅ ይሁን፥ በእኔና በአንተ መካከል ይመልከት፥ ይፍረድም፥ ጉዳዬን ተመልክቶም ከእጅህ እንዳመልጥ ይርዳኝ።”
\s5
\v 16 ዳዊት ይህንን ቃል ለሳኦል ተናግሮ በጨረሰ ጊዜ፥ ሳኦል፥ “ልጄ ዳዊት! ይህ ድምፅህ ነው?” አለው። ሳኦልም ድምፁን አሰምቶ አለቀሰ።
\s5
\v 17 እርሱም ዳዊትን እንዲህ አለው፥ "በክፋት ስመልስልህ በደግነት መልሰህልኛልና ከእኔ ይልቅ አንተ ጻድቅ ነህ።
\v 18 እግዚአብሔር በእጅህ ላይ በጣለኝ ጊዜ አልገደልከኝምና በጎነትን እንዳደረግህልኝ ዛሬ አሳይተሃል።
\s5
\v 19 አንድ ሰው ጠላቱን ቢያገኘው በሰላም ያሰናብተዋል? ዛሬ ስላደረግህልኝ ነገር እግዚአብሔር ቸርነትን ያድርግልህ።
\v 20 አሁንም፥ በእርግጥ ንጉሥ እንደምትሆንና የእስራኤል መንግሥት በእጅህ እንደሚጸና ዐውቃለሁ።
\s5
\v 21 ከእኔ በኋላ ዘሮቼን እንደማታጠፋና ስሜንም ከአባቴ ቤት እንደማትደመስሰው በእግዚአብሔር ማልልኝ።"
\v 22 ስለዚህ ዳዊት ለሳኦል ማለለት። ከዚያም ሳኦል ወደ ቤቱ ሄደ፥ ዳዊትና ሰዎቹ ግን ወደ አምባው ወጡ።
\s5
\c 25
\p
\v 1 ሳሙኤል ሞተ። እስራኤላውያን ሁሉ ተሰብስበው አለቀሱለት፥ በራማም በቤቱ ቀበሩት። ከዚያም ዳዊት ተነሥቶ ወደ ፋራን ምድረ በዳ ወረደ።
\s5
\v 2 በማዖን አንድ ሰው ነበር፥ ንብረቱም በቀርሜሎስ ይኖር ነበር። ሰውዬው እጅግ ባለጸጋ ነበር። እርሱም ሦስት ሺህ በጎችና አንድ ሺህ ፍየሎች ነበሩት። በቀርሜሎስም በጎቹን ይሸልት ነበር።
\v 3 የሰውየው ስም ናባል፥ የሚስቱም ስም አቢግያ ነበር። ሴቲቱ ብልህና መልኳም የተዋበ ነበረች። ሰውየው ግን አስቸጋሪና በምግባሩ ክፉ ነበር። እርሱም የካሌብ ቤተ ሰብ ተወላጅ ነበር።
\s5
\v 4 ዳዊት በምድረ በዳ ውስጥ ሳለ ናባል በጎቹን እንደሚሸልት ሰማ።
\v 5 ስለዚህ ዳዊት ዐሥር ወጣቶችን ላከ። ዳዊትም ወጣቶቹን እንዲህ አላቸው፥ “ወደ ቀርሜሎስ ውጡ፥ ወደ ናባልም ሂዱና በስሜ ሰላምታ አቅርቡለት።
\v 6 እርሱንም እንዲህ በሉት፥ 'በብልጽግና ኑር፥ ሰላም ላንተ፥ ለቤትህና ያንተ ለሆነው ሁሉ ይሁን።
\s5
\v 7 ሸላቾች እንዳሉህ ሰምቻለሁ። እረኞችህ ከእኛ ጋር ነበሩ፥ ምንም ጉዳት አላደረስንባቸውም፥ በቀርሜሎስ በነበሩበት ጊዜ ሁሉ አንድም አላጡም።
\v 8 ወጣቶችህን ጠይቃቸው፥ እነርሱም ይነግሩሃል። አሁንም በግብዣህ ቀን መጥተናልና ወጣቶቼ በዓይንህ ፊት ሞገስ ያግኙ። በእጅህ ያለውን ማንኛውንም ነገር ለአገልጋዮችህና ለልጅህ ለዳዊት እባክህን ስጠው።"
\s5
\v 9 የዳዊት ወጣቶች በደረሱ ጊዜ፥ በዳዊት ስም ይህንን ሁሉ ለናባል ነገሩትና ምላሹን ጠበቁ።
\v 10 ናባልም ለዳዊት አገልጋዮች፥ "ዳዊት ማነው? የእሴይስ ልጅ ማነው? በእነዚህ ቀናት ከጌቶቻቸው የሚኮበልሉ ብዙ አገልጋዮች አሉ።
\v 11 ታዲያ እንጀራዬን፥ ውሃዬንና ለሸላቾቼ ያረድኩትን ሥጋ ወስጄ ከየት እንደ መጡ ለማላውቃቸው ሰዎች መስጠት ይኖርብኛል?" ሲል መለሰላቸው።
\s5
\v 12 ስለዚህ የዳዊት ወጣቶች ዞረው በመመለስ የተባለውን ሁሉ ነገሩት።
\v 13 ዳዊትም ሰዎቹን፥ "ሁሉም ሰው ሰይፉን ይታጠቅ" አለ። ስለዚህ ሁሉም ሰይፎቻቸውን ታጠቁ። ዳዊትም ደግሞ ሰይፉን ታጠቀ። አራት መቶ የሚያህሉ ሰዎች ዳዊትን ተከተሉት፥ ሁለት መቶዎቹም ከስንቅና ትጥቃቸው ጋር ቆዩ።
\s5
\v 14 ነገር ግን ከወጣቶቹ አንዱ፥ ለናባል ሚስት ለአቢግያ እንዲህ ሲል ነገራት፥”ዳዊት ከምድረ በዳ ለጌታችን ሰላምታ ለማቅረብ መልዕክተኞች ላከ፥ ጌታችን ግን ሰደባቸው።
\v 15 ሰዎቹ ግን ለእኛ በጣም ጥሩዎች ነበሩ። በመስኩ ላይ እያለን ከእነርሱ ጋር በሄድንበት ጊዜ ሁሉ አንድም አልጎደለብንም፥ እነርሱም አልጎዱንም።
\s5
\v 16 በጎቹን እየጠበቅን ከእነርሱ ጋር በቆየንበት ጊዜ ሁሉ ቀንና ሌሊት አጥር ሆነውልን ነበር።
\v 17 በጌታችንና በቤተሰቡ ሁሉ ላይ ክፉ ታስቦአልና ይህንን ዕወቂ፥ ምን ማድረግ እንዳለብሽም አስቢበት። እርሱ የሚረባ ሰው አይደለምና ማንም ሊያነጋግረው አይችልም“።
\s5
\v 18 አቢግያም ፈጥና ሁለት መቶ እንጀራ፥ ሁለት ጠርሙስ የወይን ጠጅ፥ ቀደም ብሎ የተዘጋጀ አምስት በግ፥ አምስት መስፈሪያ የተጠበሰ እሸት፥ አንድ መቶ የወይን ዘለላና ሁለት መቶ የበለስ ፍሬ ጥፍጥፍ ወስዳ በአህዮች ላይ ጫነች።
\v 19 ከእርሷ ጋር የነበሩትንም ወጣቶች፥ "በፊቴ ቅደሙ፥ እኔም እከተላችኋለሁ" አለቻቸው። ለባልዋ ለናባል ግን አልነገረችውም።
\s5
\v 20 እርሷም በአህያዋ ላይ በመቀመጥ ተራራውን ተከልላ በመውረድ ላይ እያለች ዳዊትና ሰዎቹ ወደ እርሷ ወረዱ፥ እርሷም አገኘቻቸው።
\s5
\v 21 ዳዊትም፥”የእርሱ ከሆነው ሁሉ አንድ እንኳን እንዳይጠፋበት፥ ይህ ሰው የነበረውን ሁሉ በምድረ በዳ መጠበቄ በእርግጥም በከንቱ ነበር፥ ስላደረግሁት በጎነት ክፋትን መልሶልኛልና።
\v 22 ነገ ጠዋት የእርሱ ከሆነው ሁሉ አንድ ወንድ እንኳን ባስቀርለት እግዚአብሔር በእኔ በዳዊት ላይ ይህንኑ ያድርግብኝ፥ ደግሞም ይጨምርብኝ" ብሎ ነበር።
\s5
\v 23 አቢግያ ዳዊትን ባየችው ጊዜ፥ ከአህያዋ ላይ ፈጥና ወረደች፥ በዳዊትም ፊት አጎንብሳ ወደ ምድር ሰገደች።
\v 24 በእግሩ ላይ ወድቃም እንዲህ አለችው፥ "ጌታዬ ሆይ፥ በደሉ በእኔ ላይ ብቻ ይሁን። እባክህን አገልጋይህ እንድናገርህ ፍቀድልኝ፥ የአገልጋይህንም ቃል ስማ።
\s5
\v 25 ጌታዬ ለዚህ ለማይረባው ናባል ትኩረት አይስጥ፥ እርሱ እንደ ስሙ ነው። ስሙ ናባል ነውና ጅልነትም ከእርሱ ጋር ነው። እኔ አገልጋይህ ግን የላካቸውን የጌታዬን ወጣቶች አላየሁም።
\v 26 አሁንም ጌታዬ ሆይ፥ በሕያው እግዚአብሔር ስም፥ በሕያው ነፍስህም እምላለሁ፤ ደም ከማፍሰስና በራስህ እጅ ከመበቀል እግዚአብሔር አግዶሃልና፥ አሁንም ጠላቶችህና በጌታዬ ላይ ክፉ ለማድረግ የሚፈልጉ እንደ ናባል ይሁኑ።
\s5
\v 27 አሁንም አገልጋይህ ወደ ጌታዬ ያመጣሁት ይህ ስጦታ ጌታዬን ለሚከተሉ ወጣቶች ይሰጥ።
\v 28 እባክህን የአገልጋይህን መተላለፍ ይቅር በል፥ አንተ ጌታዬ፥ የእግዚአብሔርን ጦርነት በመዋጋት ላይ ስላለህ፥ እግዚአብሔር በርግጥ ለጌታዬ እውነተኛ የሆነን ቤት ይሠራል፥ በሕይወት ዘመንህም ሁሉ ክፋት አይገኝብህም።
\s5
\v 29 ሰዎች ተነሥተው ሕይወትህን ለማጥፋት ቢያሳድዱህም የጌታዬ ሕይወት በአምላክህ በእግዚአብሔር በሕያዋን አንድነት የታሰረች ትሆናለች፤ እርሱም የጠላቶችህን ሕይወት ከወንጭፍ ኪስ እንደሚወረወር፥ በወንጭፍ ይወረውራል።
\s5
\v 30 ይህ በሆነ ጊዜ፥ እግዚአብሔር ተስፋ የሰጠህን መልካም ነገር ሁሉ ለጌታዬ በፈጸመ ጊዜ፥ በእስራኤልም ላይ መሪ ባደረገህ ጊዜ፥
\v 31 ይህ ጉዳይ ሐዘን አይሆንብህም፥ ለጌታዬም የልብ ጸጸት አይሆንም፥ ያለ ምክንያት ደም ያፈሰስክ፥ በራስህም እጅ የተበቀልክ አትሆንም። እግዚአብሔር ለጌታዬ ስኬትን ባመጣልህ ጊዜ አገልጋይህን አስበኝ።"
\s5
\v 32 ዳዊትም አቢግያን፥ "ዛሬ እንድታገኚኝ የላከሽ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ቡሩክ ይሁን።
\v 33 ደም በማፍሰስ ከሚሆን በደልና በራሴ እጅ ስለ ራሴ ከመበቀል ጠብቀሽኛልና ጥበብሽ የተባረከ ነው፥ አንቺም የተባረክሽ ነሽ።
\s5
\v 34 በእውነት፥ አንቺን ከመጉዳት የጠበቀኝ የእስራኤል አምላክ ሕያው እግዚአብሔርን፥ እኔን ለመገናኘት ፈጥነሽ ባትመጪ ኖሮ፥ ያለምንም ጥርጥር ነገ ጠዋት ለናባል አንድ ወንድ ሕፃን ልጅ አይቀርለትም ነበር“ አላት።
\v 35 ስለዚህ ዳዊት ያመጣችለትን ከእጇ ተቀበላት፤ እርሱም፥ "ወደ ቤትሽ በሰላም ሂጂ፤ ይኸው ቃልሽን ሰማሁ፥ ተቀበልኩሽም" አላት።
\s5
\v 36 አቢግያም ተመልሳ ወደ ናባል ሄደች፤ እርሱም የንጉሥ ግብዣን የመሰለ ግብዣ በቤቱ ያደርግ ነበር፤ ናባልም በጣም ሰከሮ፥ ልቡም ደስ ብሎት ነበር። ስለዚህ እስኪነጋ ድረስ ምንም ነገር አልነገረችውም።
\s5
\v 37 ከነጋ በኋላ፥ የናባል ስካር በበረደ ጊዜ፥ ሚስቱ እነዚህን ነገሮች ነገረችው፤ ልቡ ቀጥ አለ፥ እርሱም እንደ ድንጋይ ሆነ።
\v 38 ዐሥር ቀን ካለፈ በኋላ እግዚአብሔር ናባልን ስለመታው ሞተ።
\s5
\v 39 ናባል መሞቱን ዳዊት በሰማ ጊዜ፥”የመሰደቤን ምክንያት ከናባል እጅ የተቀበለና አገልጋዩን ከክፉ የጠበቀ ጌታ እግዚአብሔር ቡሩክ ይሁን። እርሱም የናባልን ክፉ ሥራ በራሱ ላይ መለሰበት“ አለ። ከዚያም ዳዊት ወደ አቢግያ መልዕክተኛ ልኮ ሚስት አድርጎ ሊወስዳት አናገራት።
\v 40 የዳዊት አገልጋዮች ወደ ቀርሜሎስ፥ ወደ አቢግያ በመጡ ጊዜ፥ "ሚስቱ እንድትሆኚው ልንወስድሽ ዳዊት ወዳንቺ ልኮናል" አሏት።
\s5
\v 41 እርሷም ተነሣች፥ በግምባርዋ ወደ ምድር ሰግዳ፥ "ይኸው፥ ሴት አገልጋይህ፥ የጌታዬን አገልጋዮች እግር የማጥብ አገልጋይ ነኝ" አለች።
\v 42 አቢግያም ፈጥና ተነሣች፥ ከተከተሏት ከአምስት ሴት አገልጋዮቿ ጋር በአህያ ተቀመጠች፥ የዳዊትን መልዕክተኞች ተከትላ ሄደች፥ ሚስትም ሆነችው።
\s5
\v 43 በተጨማሪም ዳዊት ኢይዝራኤላዊቱን አኪናሆምን ሚስት እንድትሆነው ወሰዳት፥ ሁለቱም ሚስቶቹ ሆኑ።
\v 44 ሳኦል የዳዊት ሚስት የነበረችውን ልጁን ሜልኮልን፥ በጋሊም ለሚኖረው ለሌሳ ልጅ ለፈልጢ ሰጥቶ ነበር።
\s5
\c 26
\p
\v 1 ዚፋውያን ወደ ሳኦል ወደ ጊብዓ መጥተው፥ “ዳዊት በምድረ በዳው ፊት ለፊት በኤኬላ ኮረብታ ላይ ተደብቋል?” አሉት።
\v 2 ከዚያም ሳኦል ተነሣ፥ ከእስራኤል የተመረጡትን ሦስት ሺህ ሰዎች ይዞ ዳዊትን ለመፈለግ ወደ ዚፍ ምድረ በዳ ወረደ።
\s5
\v 3 ሳኦልም በምድረ በዳው ፊት ለፊት ባለው በኤኬላ ኮረብታ ላይ፥ በመንገዱ ዳር ሰፈረ። ዳዊት ግን በምድረ በዳው ቆይቶ ነበር፥ ሳኦል በምድረ በዳው ከበስተኋላው እንደመጣ አየ።
\v 4 ስለዚህ ዳዊት ሰላዮችን ላከና በርግጥም ሳኦል በመምጣት ላይ መሆኑን ዐወቀ።
\s5
\v 5 ዳዊት ተነሥቶ ሳኦል ወደ ሰፈረበት ስፍራ ሄደ፤ ሳኦልና የሰራዊቱ አዛዥ የኔር ልጅ አበኔር የተኙበትን ስፍራ አየ፤ ሳኦል በሰፈሩ ውስጥ ተኝቶ ነበር፥ ሕዝቡም በዙሪያው ሰፍሮ ነበር፥ ሁሉም እንቅልፍ ወስዷቸው ነበር።
\s5
\v 6 ከዚያም ዳዊት ኬጢያዊውን አቢሜሌክንና የኢዮአብን ወንድም የጽሩያን ልጅ አቢሳን፥ "ወደ ሳኦል ወደ ጦር ሰፈሩ ውስጥ ከእኔ ጋር የሚወርድ ማነው?" አላቸው። አቢሳም፥ "እኔ ከአንተ ጋር እወርዳለሁ" አለው።
\v 7 ስለዚህ ዳዊትና አቢሳ በሌሊት ወደ ሰራዊቱ ሄዱ። ሳኦል በሰፈሩ መካከል ተኝቶ፥ ጦሩም ከራስጌው በምድር ላይ ተተክሎ ነበር። አበኔርና ወታደሮቹ በዙሪያው ተኝተው ነበር።
\v 8 አቢሳም ዳዊትን፥ "እግዚአብሔር ዛሬ ጠላትህን በእጅህ ላይ ጣለው። አሁንም፥ በአንድ ምት ብቻ በጦር ከምድር ጋር እንዳጣብቀው ፍቀድልኝ፥ ሁለተኛ መምታትም አያስፈልገኝም" አለው።
\s5
\v 9 ዳዊትም አቢሳን እንዲህ አለው፥ "አትግደለው፤ እግዚአብሔር በቀባው ላይ እጁን ዘርግቶ ከበደል መንጻት የሚችል ማነው?
\v 10 ሕያው እግዚአብሔርን! እግዚአብሔር ራሱ ይገድለዋል፥ ወይም ቀኑ ደርሶ ይሞታል፥ ወይም ወደ ጦርነት ሄዶ ይሞታል።
\s5
\v 11 እርሱ በቀባው ላይ እጄን ማንሣትን እግዚአብሔር ከእኔ ያርቀው፤ አሁን ግን፥ በራስጌው ያለውን ጦርና የውሃውን ኮዳ ይዘህ እንድንሄድ እለምንሃለሁ።"
\v 12 ስለዚህ ዳዊት በሳኦል ራስጌ የነበረውን ጦርና የውሃ ኮዳ ወሰደና ሄዱ። ከእግዚአብሔር ከባድ እንቅልፍ ስለወደቀባቸው ሁሉም አንቀላፍተው ነበርና አንድም የነቃ፥ ያየ ወይም ያወቀ አልነበረም።
\s5
\v 13 ከዚያም ዳዊት በሌላኛው ወገን ወጣ፥ በተራራው ጫፍ ላይም ርቆ ቆመ፤ በመካከላቸው ሰፊ ርቀት ነበረ።
\v 14 ዳዊትም ወደ ኔር ልጅ ወደ አበኔርና ወደ ሕዝቡ ጮኾ፥ "አበኔር ሆይ፥ አትመልስምን?" አለው። አበኔርም፥ "በንጉሡ ላይ የምትጮኸው አንተ ማነህ?" ብሎ መለሰለት።
\s5
\v 15 ዳዊትም አበኔርን፥ "አንተ ጀግና አይደለህም? በእስራኤልስ አንተን የሚመስልህ ማነው? ታዲያ ጌታህን ንጉሡን ያልጠበቅኸው ለምንድነው? አንድ ሰው ጌታህን ንጉሡን ለመግደል መጥቶ ነበርና።
\v 16 ይህ ያደረግኸው ነገር መልካም አይደለም። ሕያው እግዚአብሔርን! ሞት የሚገባህ ነህ፥ ምክንያቱም እግዚአብሔር የቀባውን ጌታህን አልጠበቅኸውም። አሁንም፥ የንጉሡ ጦርና በራስጌው የነበረው የውሃ ኮዳ የት እንዳለ ተመልከት" አለው።
\s5
\v 17 ሳኦልም የዳዊት ድምፅ መሆኑን ለየና፥ "ልጄ ዳዊት፥ ይህ ድምፅህ ነው?" አለው። ዳዊትም፥ "ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ድምፄ ነው" አለው።
\v 18 እርሱም እንዲህ አለው፥ "ጌታዬ አገልጋዩን የሚያሳድደው ለምንድነው? ምን አድርጌአለሁ? በእጄስ ያለው ክፋት ምንድነው?
\s5
\v 19 አሁንም ጌታዬ ንጉሡ የአገልጋይህን ቃል እንድትሰማ እለምንሃለሁ። በእኔ ላይ ያነሣሣህ እግዚአብሔር ከሆነ መስዋዕትን ይቀበል፤ ሰዎች ከሆኑ ግን በእግዚአብሔር ፊት የተረገሙ ይሁኑ፥ 'ሄደህ ሌሎች አማልክቶችን አምልክ' ብለው የእግዚአብሔርን ርስት አጥብቄ እንዳልይዝ ዛሬ አባረውኛልና።
\v 20 ስለዚህ፥ አንድ ሰው በተራሮች ላይ ቆቅን እንደሚያድን፥ የእስራኤል ንጉሥ ቁንጫን ለመፈለግ መጥቷልና ደሜ ከእግዚአብሔር ፊት ርቆ በምድር ላይ እንዲፈስ አታድርግ።“
\s5
\v 21 ከዚያም ሳኦል፥”ኃጢአትን አድርጌአለሁ። ልጄ ዳዊት፥ ተመለስ፤ ዛሬ ሕይወቴ በዐይንህ ፊት ከብራለችና ከእንግዲህ ወዲህ ክፉ አላደርግብህም። ስንፍናን አድርጌአለሁ፥ እጅግም ተሳስቻለሁ“ አለው።
\s5
\v 22 ዳዊትም እንዲህ ሲል መለሰለት፥”ንጉሥ ሆይ ተመልከት! ጦርህ ያለው እዚህ ነው፥ ከወጣቶቹ አንዱ ይምጣና ይውሰድልህ።
\v 23 ዛሬ እግዚአብሔር በእጄ ላይ ጥሎህ እያለ በእርሱ የተቀባውን አልመታሁትምና እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ እንደ ጽድቁና ታማኝነቱ ይክፈለው።
\s5
\v 24 ተመልከት፥ ዛሬ ሕይወትህ በዐይኔ ፊት እንደ ከበረች የእኔም ሕይወት በእግዚአብሔር ዐይን አብልጣ የከበረች ትሁን፥ ከመከራዬም ሁሉ ያድነኝ።“
\v 25 ከዚያም ሳኦል ዳዊትን፥”ልጄ ዳዊት፥ በርግጥ ታላላቅ ነገሮችን እንድታደርግና እንዲከናወንልህ የተባረክህ ሁን“ አለው። ስለዚህ ዳዊት መንገዱን ሄደ፥ ሳኦልም ወደ ስፍራው ተመለሰ።
\s5
\c 27
\p
\v 1 ዳዊትም፥”አሁንም አንድ ቀን በሳኦል እጅ እሞታለሁ፤ ወደ ፍልስጥኤማውያን ምድር ከመሸሽ የሚሻል አማራጭ የለኝም፤ ያን ጊዜ ሳኦል በእስራኤል ወሰኖች ሁሉ ውስጥ እኔን መፈለጉን ያቆማል፤ በዚህ መንገድ ከእጁ አመልጣለሁ" ብሎ በልቡ አሰበ።
\s5
\v 2 ዳዊትም ተነሣ፥ እርሱና ከእርሱ ጋር የነበሩት ስድስት መቶ ሰዎች ወደ ጌት ንጉሥ ወደ አሜህ ልጅ ወደ አንኩስ ተሻገሩ።
\v 3 ዳዊትና ሰዎቹ እያንዳንዱ ከቤተሰቡ ጋር፥ እርሱም ከሁለቱ ሚስቶቹ፥ ከኢይዝራኤላዊቱ ከአኪናሆምና የናባል ሚስት ከነበረችው ከቀርሜሎሳዊቷ ከአቢግያ ጋር በጌት ከአንኩስ ጋር ኖሩ።
\v 4 ዳዊት ወደ ጌት መሸሹን ሳኦል ሰማ፥ ስለዚህ ከዚህ በኋላ አልፈለገውም።
\s5
\v 5 ዳዊትም አንኩስን፥ "በዐይንህ ፊት ሞገስ አግኝቼ ከሆነ፥ በዚያ እኖር ዘንድ በአገሪቱ ካሉት ከተሞች በአንዲቱ ስፍራ ይስጡኝ፤ አገልጋይህ በንጉሣዊ ከተማ ከአንተ ጋር ለምን ይኖራል?" አለው።
\v 6 ስለዚህ በዚያን ቀን አንኩስ ጺቅላግን ሰጠው፤ እስከዛሬ ድረስ ጺቅላግ የይሁዳ ነገሥታት የሆነችው ለዚህ ነው።
\v 7 ዳዊት በፍልስጥኤም ምድር የኖረበት ቀን ሲቆጠር አንድ ዓመት ከአራት ወር ሆነው።
\s5
\v 8 ዳዊትና ሰዎቹ ጌሹራውያንን፥ ጌርዛውያንን እና አማሌቃውያንን በመውረር የተለያዩ ቦታዎችን አጠቁ፤ እነዚህ ሕዝቦች እስከ ሱርና እስከ ግብፅ ምድር ድረስ ባለው አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ናቸው። እነርሱም ከጥንት ጀምሮ በዚያ ምድር ይኖሩ ነበር።
\v 9 ዳዊትም ምድሪቱን መታ፥ ወንዱንም ሆነ ሴቱን በሕይወት አልተወም፤ በጎችን፥ በሬዎችን፥ አህዮችን፥ ግመሎችን እና ልብሶችን ወሰደ፤ ተመልሶም እንደገና ወደ አንኩስ መጣ።
\s5
\v 10 አንኩስ፥ "ዛሬ በማን ላይ ወረራ ፈጸማችሁ?" ብሎ ይጠይቅ ነበር፥ ዳዊትም፥ "በይሁዳ ደቡብ ላይ" ወይም "በደቡብ ይረሕምኤላውያን ላይ" ወይም "በደቡብ ቄናውያን ላይ" ብሎ ይመልስለት ነበር።
\s5
\v 11 "ስለዚህ ስለ እኛ፥ 'ዳዊት እንዲህና እንዲህ አደረገ' ለማለት እንዳይችሉ" ብሎ ነበርና ዳዊት ወደ ጌት ይዞ ለመምጣት በማሰብ ወንድ ወይም ሴት በሕይወት አያስቀርም ነበር። በፍልስጥኤም አገር በኖረበት ጊዜ ሁሉ ያደረገው እንደዚህ ነበር።
\v 12 አንኩስም፥ "የራሱ የሆነው የእስራኤል ሕዝብ አምርሮ እንዲጠላው አድርጓል፤ ስለዚህ ለዘላለም አገልጋዬ ይሆናል“ ብሎ ስላሰበ ዳዊትን አመነው።
\s5
\c 28
\p
\v 1 በዚያም ዘመን ፍልስጥኤማውያን ከእስራኤል ጋር ለመዋጋት ሠራዊታቸውን ሁሉ በአንድ ላይ ሰበሰቡ። አንኩስም ዳዊትን፥ “አንተና ሰዎችህ ያለ ጥርጥር ከእኔ ጋር ወደ ጦርነቱ እንደምትወጡ ዕወቅ” አለው።
\v 2 ዳዊትም አንኩስን፥ “ስለዚህ አገልጋይህ ምን ሊያደርግ እንደሚችል ታያለህ” አለው። አንኩስም ዳዊትን፥ “ስለዚህ እኔም በቋሚነት የግል ጠባቂዬ አደርግሃለሁ" አለው።
\s5
\v 3 ሳሙኤል ሞቶ ነበር፤ እስራኤል ሁሉ አልቅሰውለት በከተማው በራማም ቀብረውት ነበር። ሳኦል ከሙታንና ከመናፍስት ጋር የሚነጋገሩትን ከምድሪቱ አጥፍቶ ነበር።
\v 4 ፍልስጥኤማውያን በአንድነት ተሰባስበው በመምጣት ሱነም ላይ ሰፈሩ፤ ሳኦልም እስራኤልን በሙሉ በአንድነት ሰብስቦ ጊልቦዓ ላይ ሰፈረ።
\s5
\v 5 ሳኦል የፍልስጥኤማውያንን ሰራዊት ባየ ጊዜ ፈራ፥ ልቡም እጅግ ተንቀጠቀጠ።
\v 6 ይረዳው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር በጸለየ ጊዜም እግዚአብሔር በህልም፥ ወይም በኡሪም፥ ወይም በነቢያት አልመለሰለትም።
\v 7 ከዚያም ሳኦል አገልጋዮቹን፥ "ወደ እርሷ ሄጄ ምክሯን እንድጠይቅ ከሞተ ጋር መነጋገር እችላለሁ የምትል ሴት ካለች ፈልጉልኝ" አላቸው። አገልጋዮቹም፥ "ከሞተ ጋር መነጋገር እችላለሁ የምትል ሴት በዓይንዶር አለች" አሉት።
\s5
\v 8 ሳኦል ሌላ ልብስ በመልበስ ራሱን ቀይሮ ከሁለት ሰዎች ጋር ሄደ፤ እነርሱም በሌሊት ወደ ሴቲቱ ሄዱ። እርሱም፥ "የምነግርሽን ሰው አስነሥተሽ ከሞተው ጋር በመነጋገር እንድትጠነቁይልኝ እለምንሻለሁ" አላት።
\v 9 ሴቲቱም፥ "ሳኦል ከሙታንና ከመናፍስት ጋር የሚነጋገሩትን ከምድሪቱ በማጥፋት ያደረገውን ታውቃለህ። ታዲያ እንድሞት ለሕይወቴ ወጥመድ የምታዘጋጀው ለምንድነው?" አለችው።
\v 10 ሳኦልም በእግዚአብሔር ስም ምሎላት፥ "ሕያው እግዚአብሔርን! በዚህ ጉዳይ ምንም ቅጣት አይደርስብሽም” አላት።
\s5
\v 11 ሴቲቱም፥ “ማንን ላስነሣልህ?” አለችው። ሳኦልም፥ “ ሳሙኤልን አስነሽልኝ” አላት።
\v 12 ሴቲቱም ሳሙኤልን ባየችው ጊዜ በታላቅ ድምፅ ጮኻ ሳኦልን፥ "አንተ ራስህ ሳኦል ሆንህ ሳለ ለምን አታለልከኝ?" አለችው።
\s5
\v 13 ንጉሡም፥ "አትፍሪ፤ ምንድነው ያየሽው?" አላት። ሴቲቱም ሳኦልን፥ "አንድ መንፈስ ከምድር ሲወጣ አያለሁ" አለችው።
\v 14 እርሱም፥ “ምን ይመስላል?” አላት። እርሷም፥ "አንድ ካባ የለበሰ ሽማግሌ እየመጣ ነው" አለችው። ሳኦልም ሳሙኤል እንደሆነ ዐወቀ፥ አክብሮቱን ለማሳየትም በምድር ላይ ሰገደለት።
\s5
\v 15 ሳሙኤልም ሳኦልን፥ "እኔን በማስነሣት የምታስቸግረኝ ለምንድነው?" አለው። ሳኦልም፥ "በጣም ተጨንቄአለሁ፥ ፍልስጥኤማውያን ጦርነት ዐውጀውብኛል፥ እግዚአብሔር ትቶኛል፥ በሕልምም ሆነ በነቢያት አይመልስልኝም። ምን ማድረግ እንዳለብኝ እንድታስታውቀኝ ለዚህ ነው የጠራሁህ" ብሎ መለሰለት።
\s5
\v 16 ሳሙኤልም እንዲህ አለው፥ "ታዲያ እግዚአብሔር ከተወህና ጠላት ከሆነህ የምትጠይቀኝ ምንድነው?
\v 17 እግዚአብሔር አደርገዋለሁ ብሎ የነገረህን እርሱን ነው ያደረገብህ። እግዚአብሔር መንግሥትን ከእጅህ ቀዶ ለሌላ ሰው፥ ለዳዊት ሰጥቶታል።
\s5
\v 18 የእግዚአብሔርን ድምፅ ስላልታዘዝክና ጽኑ ቁጣውን በአማሌቅ ላይ ስላልፈጸምክ ዛሬ ይህንን አድርጎብሃል።
\v 19 በተጨማሪም እግዚአብሔር አንተንና እስራኤልን በፍልስጥኤማውያን እጅ አሳልፎ ይሰጣል። አንተና ልጆችህ ነገ ከእኔ ጋር ትሆናላችሁ። በተጨማሪም እግዚአብሔር የእስራኤልን ሰራዊት በፍልስጥኤማውያን እጅ አሳልፎ ይሰጣል።“
\s5
\v 20 ከዚያም ሳኦል በሳሙኤል ቃል ምክንያት እጅግ ስለፈራ ወዲያውኑ በቁመቱ ሙሉ በምድር ላይ ወደቀ። በዚያ ቀንና ሌሊት ምግብ ስላልበላ ምንም አቅም አልነበረውም።
\v 21 ሴቲቱም ወደ ሳኦል መጥታ እጅግ መጨነቁን አየች፥ እርሷም እንዲህ አለችው፥ "እኔ አገልጋይህ ቃልህን ሰምቻለሁ፤ ሕይወቴን በእጄ ላይ ጥዬ የነገርከኝን ቃል ሰምቻለሁ።
\s5
\v 22 አሁንም እንግዲህ አንተም ደግሞ የእኔን የአገልጋይህን ቃል እንድትሰማና ጥቂት ምግብ እንዳቀርብልህ እለምንሃለሁ። መንገድህን ለመሄድ ዐቅም እንድታገኝ ብላ።
\v 23 ሳኦል ግን፥ "አልበላም" በማለት እንቢ አለ። ነገር ግን አገልጋዮቹ ከሴቲቱ ጋር በመሆን ለመኑት፥ እርሱም ቃላቸውን ሰማ። ስለዚህ ከምድር ላይ ተነሥቶ ዐልጋ ላይ ተቀመጠ።
\s5
\v 24 ሴቲቱም በቤቷ የደለበ ጥጃ ነበራት፤ ፈጥና አረደችው፤ ዱቄትም ወስዳ ለወሰችው፤ ቂጣ አድርጋም ጋገረችው።
\v 25 እርሷም በሳኦልና በአገልጋዮቹ ፊት አቀረበችላቸው፥ እነርሱም በሉ። ከዚያም በዚያው ሌሊት ተነሥተው ሄዱ።
\s5
\c 29
\p
\v 1 ፍልስጥኤማውያንም ሰራዊታቸውን ሁሉ አፌቅ ላይ ሰበሰቡ፤ እስራኤላውያንም በኢይዝራኤል ምንጭ አጠገብ ሰፈሩ።
\v 2 የፍልስጥኤማውያኑ መሳፍንት በመቶዎችና በሺዎች እየሆኑ አለፉ፤ ዳዊትና ሰዎቹም ከአንኩስ ጋር በደጀንነት አለፉ።
\s5
\v 3 ከዚያም የፍልስጥኤም መሳፍንት፥ "እነዚህ ዕብራውያን እዚህ ምን ይሠራሉ?" አሉ። አንኩስም ለሌሎቹ የፍልስጥኤም መሳፍንት፥ "ይህ በእነዚህ ቀናት ሁሉ ከእኔ ጋር የነበረው፥ የእስራኤል ንጉሥ የሳኦል አገልጋይ ዳዊት አይደለምን? ደግሞም በእነዚህ ዓመታት ሁሉ ወደ እኔ ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ምንም ስህተት አላገኘሁበትም” አላቸው።
\s5
\v 4 ነገር ግን የፍልስጥኤም መሳፍንት በእርሱ ላይ ተቆጥተው፥ “ያንን ሰው ወደ ሰጠኸው ወደ ስፍራው እንዲመለስ አሰናብተው፥ በውጊያው ውስጥ ጠላት እንዳይሆንብን ከእኛ ጋር ወደ ጦርነት አትላከው። ይህ ሰው ከጌታው ጋር ሰላምን የሚፈጥረው በምንድነው? የሰዎቻችንን አንገት በመቁረጥ አይደለምን?
\s5
\v 5 ይህ በዘፈን እየተቀባበሉ፥ 'ሳኦል ሺዎችን ገደለ፥ ዳዊት ዐሥር ሺዎችን ገደለ" ያሉለት ዳዊት አይደለምን?" አሉት።
\s5
\v 6 ከዚያም አንኩስ ዳዊትን ጠርቶ፥ "ሕያው እግዚአብሔርን! አንተ ጥሩ ሰው ነህ፥ በእኔ አመለካከት በሰራዊቱ ውስጥ መውጣትህና መግባትህ መልካም ነው፤ ወደ እኔ ከመጣህበት ጊዜ ጀምሮ እስከዛሬው ቀን ድረስ ምንም ስህተት አላገኘሁብህም። ይሁን እንጂ መሳፍንቱ አልደገፉህም።
\v 7 ስለዚህ አሁን የፍልስጥኤም መሳፍንት ቅር እንዳይሰኙ ተመለስና በሰላም ሂድ" አለው።
\s5
\v 8 ዳዊትም አንኩስን፥ “ግን ምን አድርጌአለሁ፥ እንዳልሄድና ከጌታዬ ከንጉሡ ጠላቶች ጋር እንዳልዋጋ በእነዚህ በፊትህ በኖርኩባቸው ቀናት በአገልጋይህ ላይ ምን አግኝተህብኛል?” አለው።
\v 9 አንኩስም ለዳዊት፥ “አንተ በእኔ ዕይታ ነቀፌታ እንደማይገኝበት እንደ እግዚአብሔር መልአክ ነህ፤ ይሁንና የፍልስጥኤም መሳፍንት፥ 'ከእኛ ጋር ወደ ጦርነት አይሄድም' ብለዋል።
\s5
\v 10 ስለዚህ ከአንተ ጋር ከመጡት ከጌታህ አገልጋዮች ጋር ማልዳችሁ ተነሡ፤ ማልዳችሁ ተነሡና ሲነጋላችሁ ሂዱ" ብሎ መለሰለት።
\v 11 ስለዚህ ዳዊትና ሰዎቹ በጠዋት ለመሄድ፥ ወደ ፍልስጥኤማውያንም ምድር ለመመለስ ማልደው ተነሡ። ፍልስጥኤማውያን ግን ወደ ኢይዝራኤል ወጡ።
\s5
\c 30
\p
\v 1 እንዲህም ሆነ፥ ዳዊትና ሰዎቹ በሦስተኛው ቀን ወደ ጺቅላግ በመጡ ጊዜ አማሌቃውያን በኔጌቭና በጺቅላግ ላይ ወረራ ፈጽመው ነበር። እነርሱም ጺቅላግን መቱ፥ አቃጠሏትም፥
\v 2 ሴቶችንና በውስጧ የነበረውን ትንሽና ትልቅ ሁሉ ማረኩ። ይዘዋቸው መንገዳቸውን ሄዱ እንጂ አንዱንም አልገደሉም።
\s5
\v 3 ዳዊትና ሰዎቹ ወደ ከተማይቱ በመጡ ጊዜ ከተማይቱ በእሳት ተቃጥላ፥ ሚስቶቻቸው፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸው ተማርከው ተወስደው ነበር።
\v 4 ከዚያም ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሰዎች ለማልቀስ ኃይል እስከማይኖራቸው ድረስ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ።
\s5
\v 5 ሁለቱ የዳዊት ሚስቶች፥ ኢይዝራኤላዊቱ አኪናሆምና የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት የነበረችው አቢግያ ተማርከው ነበር።
\v 6 የሕዝቡም ሁሉ መንፈስ፥ እያንዳንዱም ስለ ወንዶችና ሴቶች ልጆቹ ስላዘነ በድንጋይ ሊወግሩት ይነጋገሩ ስለነበር ዳዊት እጅግ ተጨነቀ፤ ዳዊት ግን በአምላኩ በእግዚአብሔር ራሱን አበረታ።
\s5
\v 7 ዳዊትም የአቢሜሌክን ልጅ ካህኑን አብያታርን፥ "ኤፉዱን ወደዚህ እንድታመጣልኝ እለምንሃለሁ" አለው። አብያታር ኤፉዱን ለዳዊት አመጣለት።
\v 8 ዳዊትም ምሪት ለማግኘት ወደ እግዚአብሔር፥ "ይህንን ወራሪ ብከተል እደርስበታለሁ?" ብሎ ጸለየ። እግዚአብሔርም፥ "ተከተላቸው፥ ያለጥርጥር ትደርስባቸዋለህ፥ ሁሉንም ነገር ታስመልሳለህ" ብሎ መለሰለት።
\s5
\v 9 ስለዚህ ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩት ስድስት መቶ ሰዎች ሄዱ፤ ከእነርሱ ወደ ኋላ የቀሩት ወደሚቆዩበት ወደ ባሦር ወንዝ መጡ።
\v 10 ነገር ግን ዳዊት ከአራት መቶ ሰዎች ጋር መከታተሉን ቀጠለ፤ ሁለት መቶዎቹ በጣም ስለ ደከሙ የባሦርን ወንዝ መሻገር አልቻሉምና ወደ ኋላ ቀሩ።
\s5
\v 11 እነርሱም በሜዳው ላይ አንድ ግብፃዊ አገኙና ወደ ዳዊት አመጡት፤ ምግብ ሰጡትና በላ፥ እንዲጠጣም ውሃ ሰጡት፤
\v 12 ደግሞም ከበለስ ጥፍጥፍ ቁራጭና ሁለት የወይን ዘለላ ሰጡት። ለሦስት ቀንና ሌሊት ምንም ምግብ አልበላም፥ ውሃም አልጠጣም ነበርና በበላ ጊዜ እንደገና ብርታት አገኘ።
\s5
\v 13 ዳዊትም፥ "አንተ የማን ነህ? ከየትስ ነው የመጣኸው?" አለው። እርሱም፥ "እኔ የአማሌቃዊ አገልጋይ፥ ግብፃዊ ወጣት ነኝ፤ ከሦስት ቀናት በፊት ታምሜ ስለነበር ጌታዬ ትቶኝ ሄደ።
\v 14 እኛም በከሊታውያን ኔጌቭ፥ የይሁዳ በሆነው ምድርና በካሌብ ኔጌቭ ላይ ወረራ ፈጸምን፥ ጺቅላግንም አቃጠልናት“ አለው።
\s5
\v 15 ዳዊትም፥”ወደዚህ ወራሪ አካል መርተህ ልታወርደኝ ትፈቅዳለህ? “ አለው። ግብፃዊውም፥”እንዳትገድለኝ ወይም በጌታዬ እጅ ላይ አሳልፈህ እንዳትሰጠኝ በእግዚአብሔር ማልልኝ እንጂ ወደ ወራሪው አካል መርቼ አወርድሃለሁ“ አለው።
\s5
\v 16 ግብፃዊው ዳዊትን እየመራው ወደ ታች ባወረደው ጊዜ፥ ወራሪዎቹ ከፍልስጥኤማውያን ምድርና ከይሁዳ ምድር ከወሰዱት ምርኮ ሁሉ የተነሣ እየበሉና እየጠጡ፥ እየጨፈሩም በምድሩ ሁሉ ተበትነው ነበር።
\v 17 ዳዊትም ደንገዝገዝ ሲል ጀምሮ እስከ ማግስቱ ምሽት ድረስ መታቸው። በግመሎች ተቀምጠው ከሸሹት ከአራት መቶ ወጣቶች በስተቀር አንድም ሰው አላመለጠም።
\s5
\v 18 ዳዊት አማሌቃውያን ወስደዋቸው የነበሩትን ሁሉ አስመለሰ፤ ሁለቱን ሚስቶቹንም አዳነ።
\v 19 ትንሽ ይሁን ትልቅ፥ ወንዶች ልጆች ይሁኑ ሴቶች ልጆች፥ ምርኮም ይሁን ወራሪዎቹ ለራሳቸው ከወሰዱት ማንኛውም ነገር አንዱም አልጠፋም። ዳዊት ሁሉን ነገር አስመለሰ።
\v 20 ዳዊትም ሰዎቹ ከሌሎች ከብቶች ፊት ይነዷቸው የነበሩትን የበጉን፥ የፍየሉንና የላሙን መንጋ ሁሉ ወሰደ። እነርሱም፥ "ይህ የዳዊት ምርኮ ነው" አሉ።
\s5
\v 21 ዳዊት ሊከተሉት እጅግ ደክሟቸው በባሦር ወንዝ አጠገብ እንዲቆዩ ወደተደረጉት ወደ ሁለት መቶዎቹ ሰዎች መጣ። እነዚህ ሰዎች ዳዊትንና ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሰዎች ለመገናኘት ወጡ። ዳዊት ወደ እነዚህ ሰዎች በመጣ ጊዜ ሰላምታ ሰጣቸው።
\v 22 ከዚያም ከዳዊት ጋር ሄደው በነበሩት ሰዎች መካከል ክፉዎችና የማይረቡት ሁሉ፥”እያንዳንዱ ሚስቱንና ልጆቹን ይዞ ከመሄድ በስተቀር እነዚህ ሰዎች ከእኛ ጋር ስላልሄዱ፥ ካስመለስነው ምርኮ ምንም አንሰጣቸውም“ አሉ።
\s5
\v 23 ከዚያም ዳዊት፥”ወንድሞቼ ሆይ፥ እግዚአብሔር በሰጠን ነገር እንዲህ ልታደርጉ አይገባም። እርሱ ጠበቀን፥ በእኛ ላይ የመጡትንም ወራሪዎች በእጃችን ላይ አሳልፎ ሰጠን።
\v 24 በዚህ ጉዳይ ማን ይሰማችኋል? ወደ ጦርነት የሄደው የየትኛውም ሰው ድርሻ ስንቅና ትጥቅ ከጠበቀ ከየትኛውም ሰው ድርሻ ጋር እኩል ይሆናል፤ ሁሉም እኩል ይካፈላሉ" አላቸው።
\v 25 ዳዊት ለእስራኤል ደንብና ሥርዓት ስላደረገው፥ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስከዚህ ቀን ድረስ እንደዚሁ ሆነ።
\s5
\v 26 ዳዊት ወደ ጺቅላግ በመጣ ጊዜ፥ ከምርኮው ጥቂቱን፥ "ይህ ከእግዚአብሔር ጠላቶች ካገኘነው ምርኮ ለእናንተ የተላከ ስጦታ ነው“ብሎ ለይሁዳ ሽማግሌዎችና ለወዳጆቹ ላከላቸው።
\v 27 የላከውም፥ በቤቴል፥ በደቡብ ራሞት፥ በየቲር፥
\v 28 በአሮኤር፥ በሢፍሞት፥ በኤሽትሞዓ ለነበሩ ሽማግሌዎች ነበር።
\s5
\v 29 እንዲሁም በራካል፥ በይረሕምኤላውያንና በቄናውያን ከተሞች፥
\v 30 በሔርማ፥ በቦራሣን፥ በዓታክ፥
\v 31 በኬብሮን፥ እንዲሁም ዳዊት ራሱና ሰዎቹ አዘውትረው ይሄዱባቸው በነበሩ ስፍራዎች ሁሉ ለሚኖሩ ሽማግሌዎች ላከላቸው።
\s5
\c 31
\p
\v 1 ፍልስጥኤማውያን ከእስራኤል ጋር ተዋጉ። የእስራኤል ሰዎች ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ፥ በጊልቦዓ ተራራ ላይም ተገድለው ወደቁ።
\v 2 ፍልስጥኤማውያንም ሳኦልንና ልጆቹን በቅርብ ርቀት ተከተሏቸው። ፍልስጥኤማውያንም ልጆቹን ዮናታንን፥ አሚናዳብንና ሜልኪሳን ገደሏቸው።
\v 3 ውጊያው በሳኦል ላይ በረታበት፥ ቀስተኞችም አገኙት። በእነርሱም ምክንያት በጽኑ ሕመም ላይ ነበር።
\s5
\v 4 ሳኦልም ጋሻ ጃግሬውን፥”ሰይፍህን ምዘዝና ውጋኝ። አለበለዚያ፥ እነዚህ ያልተገረዙ መጥተው ይሳለቁብኛል“ አለው።
\v 5 ጋሻ ጃግሬው ግን እጅግ ፈርቶ ስለነበረ እምቢ እለ። ስለዚህ ሳኦል የራሱን ሰይፍ ወስዶ በላዩ ላይ ወደቀበት። ጋሻ ጃግሬው ሳኦል መሞቱን ባየ ጊዜ እርሱም ደግሞ ሰይፉ ላይ ወድቆ አብሮት ሞተ።
\v 6 ስለዚህ ሳኦል፥ ሦስቱ ወንዶች ልጆቹና ጋሻ ጃግሬው ሞቱ፤ እነዚህ ሰዎች ሁሉ በአንድ ቀን ሞቱ።
\s5
\v 7 ከሸለቆው በወዲያኛው ወገን የነበሩትና ከዮርዳኖስ በላይ የነበሩት የእስራኤል ሰዎች፥ የእስራኤል ሰዎች መሸሻቸውን፥ ሳኦልና ልጆቹ መሞታቸውን ባዩ ጊዜ ከተሞቻቸውን ትተው ሸሹ፥ ፍልስጥኤማውያንም መጥተው ተቀመጡባቸው።
\v 8 በማግስቱ እንዲህ ሆነ፥ ፍልስጥኤማውያን የሞቱትን ሰዎች ትጥቅ ለመግፈፍ በመጡ ጊዜ ሳኦልና ሦስቱ ልጆቹ በጊልቦዓ ተራራ ላይ ወድቀው አገኟቸው።
\s5
\v 9 እነርሱም ራሱን ቆረጡት፥ የጦር መሣሪያውንም ገፈፉት፥ ወደ ፍልስጥኤማውያን ምድር ሁሉ ለጣዖት መቅደሶቻቸውና ለሕዝቡ ወሬውን እንዲያደርሱ መልዕክተኞችን ላኩ።
\v 10 የጦር መሣሪያውን በአስታሮት መቅደስ ውስጥ አስቀመጡት፥ ሬሳውንም በቤትሳን ከተማ የግንብ አጥር ላይ አንጠለጠሉት።
\s5
\v 11 የኢያቢስ ገለዓድ ሰዎች ፍልስጥኤማውያን በሳኦል ላይ ያደረጉትን በሰሙ ጊዜ
\v 12 ተዋጊ የሆኑ ሰዎች ሁሉ ተነሥተው ሌሊቱን ሁሉ ተጉዘው የሳኦልንና የልጆቹን ሬሳ ከአጥሩ ላይ ወሰዱ። ወደ ኢያቢስ ሄዱ፥ በዚያም አቃጠሏቸው።
\v 13 ከዚያም አጥንቶቻቸውን በመውሰድ በኢያቢስ ባለው የአጣጥ ዛፍ ሥር ቀበሯቸው፥ ሰባት ቀንም ጾሙ።