am_ulb/08-RUT.usfm

177 lines
21 KiB
Plaintext

\id RUT
\ide UTF-8
\h ሩት
\toc1 ሩት
\toc2 ሩት
\toc3 rut
\mt ሩት
\s5
\c 1
\p
\v 1 መሳፍንት ይገዙ በነበረበት ዘመን በምድሪቱ ላይ ራብ ነበረ። አንድ ከበተልሔም ይሁዳ የሆነ ሰው ከሚስቱና ከሁለቱ ልጆቹ ጋር ወደ ሞአብ አገር ሄደ፡፡
\v 2 የሰውዮው ስም አቤሜሌክ ይባል ነበር፣ የሚስቱም ስም ኑኃሚን ይባላል፡፡ የሁለቱም ወንዶች ልጆቹ ስም መሐሎንና ኬሌዎን፣ የይሁዳ ቤተልሔም ኤፍራታውያን ነበሩ፡፡ እነርሱም ወደ ሞዓብም አገር ደረሱና በዚያ ተቀመጡ፡፡
\s5
\v 3 የኑኃሚንም ባል አቤሜሌክ ሞተ እርስዋም ከሁለቱ ወንዶች ልጆችዋ ጋር ቀረች፡፡
\v 4 እነዚህ ወንዶች ልጆች ከሞዓባውያን ሴቶች ሚስቶችን ወሰዱ፤ የአንዷ ስም ዖርፋ ነበር፣ የሌላኛዋ ስም ደግሞ ሩት ነበረ። በዚያም ለአሥር ዓመታት ያህል ተቀመጡ፡፡
\v 5 ከዚያም መሐሎንና ኬሌዎን ሁለቱም ሞቱ፣ ኑኃሚንም ያለ ባልዋና ያለ ሁለቱ ልጆችዋ ብቻዋን ተለይታ ቀረች፡፡
\s5
\v 6 በዚያን ጊዜ ኑኃሚን ከሁለቱ ምራቶችዋ ጋር ሞአብን ለመልቀቅና ወደ ይሁዳ ለመመለስ ወሰነች፡፡ እርስዋም በሞዓብ ምድር ሳለች እግዚአብሔር የተቸገሩትን ሕዝቡን እንደረዳቸውና መብልን እንደ ሰጣቸው ሰማች፡፡
\v 7 ስለዚህ እርስዋ ከሁለቱ ምራቶችዋ ጋር ከነበረችበት ስፍራ ለቀቀች፣ ከዚያም ወደ ይሁዳ ምድር ለመመለስ መንገዱን ይዘው ወደታች ሄዱ፡፡
\s5
\v 8 ኑኃሚን ለምራቶችዋ “ሂዱ፣ እያንዳንዳችሁ ወደ እናታችሁ ቤት ተመለሱ፡፡ ለሞቱትና ለእኔ ታማኝነት እንዳሳያችሁን ሁሉ፣ እግዚአብሔር ለእናንተ ታማኝነቱን ያሳያችሁ፡፡
\v 9 ጌታ እያንዳንዳችሁን በሌላ ባል ቤት ዕረፍት ይስጣችሁ” አለቻቸው፡፡ ከዚያም ሳመቻቸው፣ እነርሱም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ፡፡
\v 10 እነርሱም “አይሆንም! ከአንቺ ጋር ወደ ሕዝብሽ እንመለሳለን” አሉአት፡፡
\s5
\v 11 ኑኃሚን ግን “ልጆቼ ሆይ፣ ተመለሱ! ለምን ከእኔ ጋር ትሄዳላችሁ? ባሎቻችሁ ይሆኑ ዘንድ ለእናንተ የሚሆኑ ወንዶች ልጆች በማሕጸኔ አሁን አሉን?
\v 12 ልጆቼ ሆይ፣ ተመለሱ፣ በራሳችሁ መንገድ ሂዱ፤ ባል ለማግባት በጣም አርጅቻለሁና፡፡ ዛሬ ማታ ባል አገኛለሁ ብየ እንኳ ተስፋ ባደርግና ወንዶች ልጆችን ብወልድ፣
\v 13 እነርሱ እስኪያድጉ ድረስ ትጠብቃላችሁን? እየጠበቃችሁ አሁን ባል ሳታገቡ ትቀራላችሁን? አይሆንም፣ ልጆቼ ሆይ! ከእናንተ ይልቅ ሁኔታው እኔን እጅግ በጣም ያስመርረኛል፣ ምክንያቱም የእግዚአብሔር እጅ በእኔ ላይ ወጥቶአልና፡፡
\s5
\v 14 በዚያን ጊዜ ምራቶችዋ ድምፃቸውንም ከፍ አደረጉና እንደገና አለቀሱ፡፡ ዖርፋም አማትዋን ሳመቻትና ተሰናበተቻት፣ ሩት ግን ተጠግታ ያዘቻት፡፡
\v 15 ኑኃሚንም “አድምጪኝ፣ እነሆ የባልሽ ወንድም ሚስት ወደ ሕዝብዋና ወደ አማልክትዋ ተመልሳለች፡፡ ከባልሽ ወንድም ሚስት ጋር አንቺም ተመለሽ” አለቻት፡፡
\s5
\v 16 ነገር ግን ሩት “ከአንቺ ርቄ እንድሄድ አታድርጊኝ፣ ወደምትሄጅበት እሄዳለሁና፤ በምትቆይበትም እቆያለሁና፤ ሕዝብሽ ሕዝቤ ይሆናል፣ አምላክሽም አምላኬ ይሆናል፡፡
\v 17 በምትሞችበትም እሞታለሁ፣ በዚያም እቀበራለሁ፡፡ ከሞት በቀር እኛን አንድም ነገር ቢለየን እግዚአብሔር ይቅጣኝ፣ ከዚህም በላይ ያድርግብኝ” አለቻት፡፡
\v 18 ኑኃሚን ሩት ከእርስዋ ጋር ለመሄድ እንደ ወሰነች ባየች ጊዜ፣ ከእርስዋ ጋር መከራከር አቆመች፡፡
\s5
\v 19 ስለዚህ ሁለቱም ወደ ቤተ ልሔም ከተማ እስኪመጡ ድረስ ተጓዙ፡፡ ወደ ቤተ ልሔምም በደረሱ ጊዜ፣ ከተማው በሙሉ ስለ እነርሱ እጅግ በጣም ተደነቁ፡፡ ሴቶችም “ይህች ኑኃሚን ናትን?” አሉ፡፡
\v 20 እርስዋ ግን “ኑኃሚን ብላችሁ አትጥሩኝ፡፡ ሁሉን የሚችል አምላክ ሕይወቴን መራራ አድርጎታልና፣ ማራ በሉኝ” አለቻቸው፡፡
\v 21 በሙላት ሄድሁ፣ ነገር ግን እግዚአብሔር ወደ ቤቴ ባዶዬን እንደገና መለሰኝ፡፡ ታዲያ እግዚአብሔር አዋርዶኝ፣ ሁሉንም የሚችል አምላክ አስጨንቆኝ እያያችሁ ለምን ኑኃሚን ትሉኛላችሁ?” አለቻቸው፡፡
\s5
\v 22 ስለዚህ ኑኃሚንና ምራትዋ ሞአባዊት ሩት ከሞዓብ አገር ተመለሱ፡፡ እነርሱ የገብስ መከር በተጀመረ ጊዜ ወደ ቤተልሔም መጡ፡፡
\s5
\c 2
\p
\v 1 የኑኃሚን ባል አቤሜሌክ፣ በጣም ባለጠጋና ኃያል ሰው የሆነ ቦዔዝ የሚባል ዘመድ ነበረው፡፡
\v 2 ሞዓባዊቱ ሩት ኑኃሚንን “አሁን ልሂድና ወደ እርሻዎች ገብቼ እህል ልቃርም፡፡ በፊቱ ሞገስ የማገኘውን ሰው እከተላለሁ” አለቻት፡፡ ኑኃሚንም “ልጄ ሆይ፣ ሂጂ” አለቻት፡፡
\s5
\v 3 ሩት ሄደችና ከአጫጆችም በኋላ በእርሻ ውስጥ ቃረመች፡፡ እርስዋም የአቤሜሌክ ዘመድ ወደሆነው ወደ ቦዔዝ እርሻ እንደ አጋጣሚ ሆኖ ደረሰች።
\v 4 እነሆም፣ ቦዔዝ ከቤተ ልሔም መጣና ለአጫጆቹ “እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን” አላቸው፡፡ እነርሱም “እግዚአብሔር ይባርክህ” ብለው መለሱለት፡፡
\s5
\v 5 ከዚያም ቦዔዝ በአጫጆቹ ላይ ተቆጣጣሪ የነበረውን አገልጋዩን “ይህች ወጣት ሴት የማን ናት?” አለው፡፡
\v 6 አጫጆቹንም የሚቆጣጠረው አገልጋይ “ይህች ወጣት ሞዓባዊት ከሞዓብ ምድር ከኑኃሚን ጋር የመጣች ናት” አለው፡፡
\v 7 እርስዋም ‘ከአጫጆቹ በኋላ እየተከተልሁ የእህል ቃርሚያ እንድቃርምና እንድለቅም እባክህ ፍቀድልኝ አለች’ አለው፡፡ ስለዚህ እርስዋም ወደዚህ መጣች፣ በቤት ጥቂት ከማረፍዋ በስተቀር፣ ከጠዋት ጀምራ እስከ አሁን ድረስ መቃረም ቀጥላለች፡፡”
\s5
\v 8 የዚያን ጊዜ ቦዔዝ ሩትን “ልጄ ሆይ፣ እኔን እያዳመጥሽኝ ነውን? ወደ ሌላ እርሻ ሄደሽ አትቃርሚ፤ ከእርሻየ አትሂጂ፣ ይልቁንም በዚህ ቆዪና ከወጠት ሴቶች ሰራተኞቼ ጋር አብረሽ ስሪ፡፡
\v 9 ዓይኖችሽ ሰዎቹ ወደሚያጭዱበት ስፍራ ብቻ ይመልከቱ፣ ሌሎቹንም ሴቶች ተከተያቸው፡፡ ሰዎቹን እንዳይነኩሽ አላዘዝኋቸውምን? ሲጠማሽ ወደ ውኃ ማሰሮዎቹ ሄደሽ ወንዶቹ ከቀዱት ውኃ መጠጣት ትችያለሽ” አላት፡፡
\s5
\v 10 ከዚያም በግንባርዋ መሬቱን በመንካት በቦዔዝ ፊት ሰገደች፡፡ እርስዋም “እኔ እንግዳ የሆንሁት ታስበኝ ዘንድ በአንተ ፊት ሞገስ ያገኘሁት ለምንድን ነው?” አለችው፡፡
\v 11 ቦዔዝም ለእርስዋ “ባልሽ ከሞተበት ጊዜ ጀምሮ የሰራሽው ስራ ሁሉ ለእኔ ተነግሮኛል፡፡ አማትሽን ለመከተልና ወደ ማታውቂው ሕዝብ ለመምጣት አባትሽንና እናትሽን የተወለድሽባትንም ምድር ትተሻል፡፡
\v 12 ስለ ስራሽ እግዚአብሔር ይክፈልሽ፡፡ ከክንፉ በታች መጠጊያ ካገኘሽበት ከእስራኤል አምላክ ከእግዚአብሔር ሙሉ ደመወዝሽን ተቀበይ” አላት፡፡
\s5
\v 13 እርስዋም “ጌታዬ ሆይ፣ ምንም እንኳ እኔ ከሴት አገልጋዮችህ እንደ አንዲቱ ባልሆንም አጽናንተኸኛልና፣ እኔን በደግነት አናግረኸኛልና በፊትህ ሞገስን ላግኝ” አለቸው፡፡
\s5
\v 14 በምሳም ጊዜ ቦዔዝ ለሩት እንዲህ አላት፡- “ወደዚህ ነይ፣ እንጀራም ብዪ፣ ጉርሻሽንም በሆምጣጤው ወይን አጥቅሺው፡፡” በአጫጆቹም አጠገብ ተቀመጠች፣ እርሱም የተጠበሰ እህል ሰጣት፣ እርስዋም እስክትጠግብ ድረስ በላች፣ የቀረውንም አተረፈች፡፡
\s5
\v 15 ለመቃረም ስትነሳ፣ ቦዔዝ ወጣት አገልጋዮቹን “በነዶው መካከልም እንድትቃርም ፍቀዱላት፣ ምንም መጥፎ ነገር ለእርስዋ አትናገሩአት፡፡
\v 16 ደግሞም ከነዶው ዘለላዎች አስቀርታችሁ በእርግጠኝነት ልተተዉላት ይገባል፣ እንድትቃርም ለእርስዋ ተዉላት፡፡ እርስዋንም አትውቀሱአት” ብሎ አዘዛቸው፡፡
\s5
\v 17 ስለዚህ በእርሻው ውስጥ እስከ ማታ ድረስ ቃረመች፡፡ ከዚያም የቃረመችውን እህል ወቃችው፣ የወቃችውም እህል አንድ የኢፍ መስፈሪያ ያህል ገብስ ሆነ፡፡
\v 18 እርስዋም ተሸክማው ወደ ከተማ ሄደች፡፡ አማትዋም የቃረመችውን አየች፡፡ ሩትም በልታ ከጠገበች በኋላ የተረፋትን የተጠበሰ እህል አውጥታ ለእርስዋ ሰጠቻት፡፡
\s5
\v 19 አማትዋም ለእርስዋ እንዲህ አለቻት፡-“ዛሬ የቃረምሽው ወዴት ነው? ለመስራትስ ወዴት ሄድሽ? የረዳሽ ሰው የተባረከ ይሁን፡፡” ከዚያም ሩት ለአማትዋ የቃረመችበት እርሻ ባለቤት ስለሆነው ሰው ነገረቻት፡፡ እርስዋም “ዛሬ ቃርሚያ የቃረምሁበት እርሻ ባለቤት ስሙ ቦዔዝ ይባላል” አለቻት፡፡
\v 20 ኑኃሚንም ለምራትዋ “ታማኝነቱን በሕያዋንና በሙታን ላይ ባልተወው በእግዚአብሔር የተባረከ ይሁን” አለቻት፡፡ ኑኃሚንም ደግሞ “ይህ ሰው ለእኛ የቅርብ ዘመዳችን ነው፣ ከሚቤዡን አንዱ ነው” አለቻት፡፡
\s5
\v 21 ሞዓባዊቱ ሩትም “በእርግጥም፣ እንዲህ አለኝ፣ ‘መከሬን ሁሉ እስኪጨርሱ ድረስ ከወጣት ወንዶች ሰራተኞቼ አትራቂ፡፡’”
\v 22 ኑኃሚንም ለምራትዋ ለሩት “ልጄ ሆይ፣ ከወጣት ሴቶች ሰራተኞቹ ጋር ብትወጪ መልካም ነው፣ በሌላ በየትኛውም እርሻ ጉዳት እንዳያገኝሽ” አለቻት፡፡
\s5
\v 23 ስለዚህም እርስዋ እስከ ገብሱና ስንዴው መከር መጨረሻ ድረስ ልትቃርም ወደ ቦዔዝ ሴቶች ሰራተኞች ተጠግታ ቆየች፡፡ እርስዋም ከአማትዋ ጋር ትኖር ነበር፡፡
\s5
\c 3
\p
\v 1 አማትዋም ኑኃሚን ለእርስዋ “ልጄ ሆይ፣ ታርፊ ዘንድ፣ ነገሮችም ለአንቺ መልካም ይሆኑልሽ ዘንድ፣ የምታርፊበትን ስፍራ አልፈግልሽምን?” አለቻት፡፡
\v 2 አሁንም ቦዔዝ፣ ከወጣት ሴቶች ሰራተኞቹ ጋር የነበርሽበት ሰው፣ ዘመዳችን አይደለምን? ተመልከቺ፣ እርሱ ዛሬ ማታ በአውድማው ላይ ገብሱን በመንሽ ይበትናል፡፡
\s5
\v 3 ስለዚህ፣ ታጠቢ፣ ሽቶሽን ተቀቢ፣ ልብስሽን ቀይሪ፣ ወደ አውድማውም ውረጂ፡፡ ነገር ግን መብላትና መጠጣት እስኪጨርስ ድረስ ለሰውዮው አትታወቂ፡፡
\v 4 በተኛም ጊዜ፣ ወደ እርሱ መሄድ እንድትችይ እርሱ የተኛበትን ስፍራ ማስታወስሽን እርግጠኛ ሁኚ፣ እግሩን ግለጪ፣ በዚያም ተጋደሚ፡፡ ከዚያም የምታደርጊውን እርሱ ይነግርሻል፡፡
\v 5 ሩትም ለኑኃሚን “የተናገርሽኝን ሁሉ አደርጋለሁ” አለቻት፡፡
\s5
\v 6 ስለዚህ ወደ አውድማውም ወረደች፣ እርስዋም አማትዋ የሰጠቻትን ትዕዛዝ ተከተለች፡፡
\v 7 ቦዔዝም በበላና በጠጣ ጊዜ፣ ልቡም ደስ ባለው ጊዜ፣ በእህሉ ክምር ጫፍ ሊተኛ ሄደ፡፡ ከዚያም ሩት በቀስታ መጣች፣ እግሩንም ገለጠች፣ ተኛችም፡፡
\s5
\v 8 እኩለ ሌሊት በሆነ ጊዜ ሰውዮው ደነገጠ፡፡ እርሱም ዘወር አለ፣ አንዲትም ሴት እዚያው እግርጌው ተኝታ ነበረች፡፡
\v 9 እርሱም “ማን ነሽ? አለ፡፡ እርስዋም “እኔ ሴት አገልጋይህ ሩት ነኝ” አለችው፡፡ አንተ የቅርብ ዘመዴ ነህና ልብስህን በሴት አገልጋይህ ላይ ዘርጋ አለችው፡፡
\s5
\v 10 ቦዔዝም፣ “ልጄ ሆይ፣ በእግዚአብሔር የተባረክሽ ሁኚ፡፡ ከመጀመርያው ይልቅ በመጨረሻ ብዙ ደግነት አሳይተሻል፣ ምክንያቱም ድሃም ይሁን ባለጠጋ ከወጣት ወንዶች ከአንዳቸውም ጋር አልሄድሽምና” አላት፡፡
\v 11 አሁንም፣ ልጄ ሆይ፣ አትፍሪ! ያልሽውን ሁሉ አደርግልሻለሁ፣ ምክንያቱም በከተማየ ያሉ ሕዝብ ሁሉ ምግባረ መልካም ሴት እንደ ሆንሽ ያውቃሉ፡፡
\s5
\v 12 አሁን እኔ የቅርብ ዘመድ መሆኔ እውነት ነው፤ ይሁን እንጂ ከእኔ የበለጠ የሚቀርብ ዘመድ አለ፡፡
\v 13 ዛሬ ሌሊት እዚህ ቆዪ፣ ነገም ጠዋት የዋርሳነትን ግዴታ እርሱ የሚፈጽም ከሆነ፣ መልካም ነው፣ የዋርሳነትን ግዴታ ይፈጽም፡፡ ነገር ግን እርሱ ለአንቺ የዋርሳነትን ግዴታ ባይፈጽም፣ ሕያው እግዚአብሔርን እኔ አደርገዋለሁ፡፡ እስከ ማለዳ ድረስ ተኚ፡፡
\s5
\v 14 ስለዚህ እስከ ማለዳ ድረስ በእግርጌው ተኛች፡፡ ነገር ግን አንዱ ሌላውን ማወቅ ከመቻሉ በፊት ተነሳች፡፡ ቦዔዝ “ሴት ወደ አውድማው መምጣትዋን ማንም እንዳያውቅ” ብሎ ነበርና፡፡
\v 15 ከዚያም ቦኤዝ “የለበስሽውን ልብስ አምጭና ያዢው” አላት፡፡ በያዘችም ጊዜ ስድስት ትልቅ መስፈሪያ ገብስ በልብሷ ላይ ሰፍሮ አሸከማት፡፡ የዚያን ጊዜ እርሱ ወደ ከተማ ሄደ፡፡
\s5
\v 16 ሩት ወደ አማትዋ በመጣች ጊዜ “ልጄ ሆይ፣ እንዴት ነሽ?” አለቻት፡፡ ሩትም ሰውዮው ለእርስዋ ያደረገውን ሁሉ ነገረቻት፡፡
\v 17 እርስዋም “እነዚህ ስድስት መስፈሪያ ገብስ እርሱ የሰጠኝ ናቸው፣ ‘ወደ አማትሽ ባዶ እጅሽን አትሂጂ’” ብሏልና፡፡
\v 18 ኑኃሚንም “ልጄ ሆይ፣ ይህ ጉዳይ እንዴት እንደሚሆን እስከምታውቂ ድረስ በዚህ ቆዪ፣ ሰውዮው ይህን ነገር ዛሬ እስኪጨርስ ድረስ አያርፍምና” አለች፡፡
\s5
\c 4
\p
\v 1 ቦዔዝም ወደ ከተማይቱ በር ሄደና በዚያ ተቀመጠ፡፡ ወዲያውኑ ቦዔዝ ሲናገርለት የነበረው የቅርብ ዘመድ መጣ፡፡ ቦዔዝም ለእርሱ “ወዳጄ ሆይ፣ ና በዚህም ተቀመጥ” አለው፡፡ ሰውየውም መጣና ተቀመጠ፡፡
\v 2 ቦዔዝም ከከተማይቱ ሽማግሌዎች አሥር ሰዎች ወሰደ፣ “በዚህ ተቀመጡ” አላቸው፡፡ እነርሱም ተቀመጡ፡፡
\s5
\v 3 ቦዔዝም የቅርብ ዘመድ ለሆነው፣ “ከሞዓብ ምድር የተመለሰችው ኑኃሚን የወንድማችንን የአቤሜሌክን ቁራሽ መሬት ትሸጣለች፡፡
\v 4 እኔም ለአንተ አስታውቅህ ዘንድ አሰብሁ እንዲህም አልሁ፡- ‘ይህንን መሬት በዚህ በተቀመጡት በሕዝቤ ሽማግሌዎች ፊት ግዛው፡፡’ መቤዠት ብትፈልግ ተቤዠው፡፡ ነገር ግን መቤዠት የማትፈልግ ከሆነ ግን ከአንተ በቀር ሌላ የሚቤዥ የለምና፣ እኔም ከእአንተ በኋላ ነኝና እንዳውቀው ንገረኝ” አለው፡፡ የዚያን ጊዜ ሌላኛው ሰው “እቤዠዋለሁ” አለው፡፡
\s5
\v 5 ቦዔዝም “ከኑኃሚን እጅ እርሻውን በምትገዛበት ቀን፣ የሞተውን ሰው ስም በርስቱ ላይ እንድታስነሣለት የምዋቹን ሰው ሚስት ሞዓባዊቱን ሩትን ደግሞ መውሰድ አለብህ” አለ፡፡
\v 6 የቅርብ ዘመድ የሆነውም “የራሴን ርስት ሳልጎዳ እርሻውን ለራሴ መቤዠት አልችልም፡፡ እኔ ልቤዠው አልችልምና የእኔን የመቤዠት መብት ለራስህ ውሰድ” አለ፡፡
\s5
\v 7 በጥንት ዘመን መቤዠትና የሸቀጦች መለዋወጥ በተመለከተ በእስራኤል ዘንድ አንድ ልማድ ነበረ፡፡ ሁሉንም ነገር ለማጽናት ሰው ጫማውን ያወልቅና ለባልንጀራው ይሰጠዋል፤ በእስራኤል ውስጥ ሕጋዊ ስምምነት የሚኖረው በዚህ ሁኔታ ነበር፡፡
\v 8 ስለዚህ የቅርብ ዘመዱ ቦዔዝ፣ “አንተ ለራስህ ግዛው” አለው፡፡ እርሱም ጫማውን አወለቀ፡፡
\s5
\v 9 ቦዔዝም ለሽማግሌዎቹና ለሕዝቡ ሁሉ፣ “ለአቤሜሌክ የነበረውን ሁሉ እንደዚሁም ለኬሌዎንና ለመሐሎንም የነበረውን ሁሉ ከኑኃሚን እጅ እኔ መግዛቴን እናንተ ዛሬ ምስክሮች ናችሁ፡፡
\v 10 ከዚህም በላይ ስለ መሐሎን ሚስት ስለ ሞዓባዊቷ ሩት፡- የምዋቹን ሰው ስም በርስቱ ላይ እንዳስነሣ፣ ስሙ ከወንድሞቹ መካከልና ከአገሩም ደጅ እንዳይጠፋ፣ እኔ ደግሞ እርስዋ ሚስቴ እንድትሆን ወስጃታለሁ፡፡ እናንተም ዛሬ ምስክሮች ናችሁ” አላቸው፡፡
\s5
\v 11 በበሩ የነበሩ ሕዝብ ሁሉና ሽማግሌዎቹም እንዲህ አሉ፡- “እኛ ምስክሮች ነን፡፡ እግዚአብሔር ወደ ቤትህ የመጣችውን ሴት የእስራኤልን ቤት እንደ ገነቡት እንደ ሁለቱ እንደ ራሔልና ልያ ያድርጋት፡፡ አንተም በኤፍራታ ባለጠጋ ሁን፣ በቤተ ልሔምም እንደገና የታወቅህ ሁን፡፡
\v 12 ቤትህ እግዚአብሔር ከዚህች ወጣት ሴት በሚሰጥህ ዘር በኩል ትዕማር ለይሁዳ እንደወለደችለት እንደ ፋሬስ ቤት ይሁን” አሉት፡፡
\s5
\v 13 ስለዚህ ቦዔዝ ሩትን ወሰደ፣ ሚስቱም ሆነች፡፡ እርሱም ከእርስዋ ጋር ተኛ፣ እግዚአብሔርም ልጅ እንድትፀንስ ፈቀደላት፣ እርዋም ወንድ ልጅ ወለደች፡፡
\v 14 ሴቶችም ለኑኃሚን፣ “ዛሬ የሚቤዥ የቅርብ ዘመድ ያላሳጣሽ እግዚአብሔር ይባረክ፡፡ ይህ ሕጻን ስሙ በእስራኤል ውስጥ የገነነ ይሁን፡፡
\v 15 ይህ ልጅ ለአንቺ ሕይወትሽን የሚያድስ እርጅናሽንም የሚመግብ ይሁን፣ የምትወድሽ፣ ከሰባትም ወንዶች ልጆች ይልቅ ለአንቺ የምትሻል፣ ምራትሽ ይህን ልጅ ወልዳለችና፡፡
\s5
\v 16 ኑኃሚንም ሕፃኑን ወሰደችው፣ በእቅፍዋም አስቀመጠችው፣ እርሱንም ተንከባከበችው፡፡
\v 17 ጎረቤቶቿ የሆኑት ሴቶችም “ለኑኃሚን ወንድ ልጅ ተወለደላት” እያሉ ስም ሰጡት፡፡እነርሱም ስሙን ኢዮቤድ ብለው ጠሩት፡፡ እርሱም የዳዊት አባት የሆነው፣ የእሴይ አባት ሆነ፡፡
\s5
\v 18 አሁንም እነዚህ የፋሬስ ትውልድ ነበሩ፡- ፋሬስ የኤስሮም አባት ሆነ፣
\v 19 ኤስሮምም የአራም አባት ሆነ፣ አራምም የአሚናዳብ አባት ሆነ፣
\v 20 አሚናዳብም የነአሶን አባት ሆነ፣ ነአሶንም የሰልሞን አባት ሆነ፣
\v 21 ሰልሞንም የቦዔዝ አባት ሆነ፣ ቦዔዝም የኢዮቤድ አባት ሆነ፣
\v 22 ኢዮቤድ የእሴይ አባት ሆነ፣ እሴይም የዳዊት አባት ሆነ፡፡