am_ulb/07-JDG.usfm

1429 lines
164 KiB
Plaintext
Raw Permalink Blame History

This file contains ambiguous Unicode characters

This file contains Unicode characters that might be confused with other characters. If you think that this is intentional, you can safely ignore this warning. Use the Escape button to reveal them.

\id JDG
\ide UTF-8
\h መሳፍንት
\toc1 መሳፍንት
\toc2 መሳፍንት
\toc3 jdg
\mt መሳፍንት
\s5
\c 1
\p
\v 1
ከኢያሱ ሞት በኋላ፣ የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔርን እንዲህ ብለው ጠየቁ፡- “ከነዓናውያንን ለመዋጋት ወደላይ ስንሄድ ማን ይመራናል?”
\v 2 እግዚአብሔርም አላቸው፡- “ይሁዳ ይመራችኋል፡፡ ተመልከቱ፣ ምድሪቱን ለእነርሱ አሳልፌ ሰጥቻለሁ፡፡”
\v 3 የይሁዳም ሰዎች ለወንድሞቻቸው ለስምዖን ሰዎች እንዲህ አሏቸው፡- “ከነዓናውያንን አብረን እንወጋቸው ዘንድ ከእኛ ጋር ለእኛ ወደተሰጠው ክልል ኑ፡፡ እኛም እንዲሁ ለእናንተ ወደተሰጠው ክልል እንመጣለን፡፡” ስለዚህም የስምዖን ነገድ ከእነርሱ ጋር ሄዱ፡፡
\s5
\v 4 የይሁዳ ሰዎችም ወደ ላይ ወጡ፣ እግዚአብሔርም በከነዓናውያንና በፌርዛውያን ላይ ድልን ሰጣቸው፡፡ በቤዜቅም ከእነርሱ አስር ሺህ ሰዎችን ገደሉ፡፡
\v 5 አዶኒ ቤዜቅን በቤዜቅ አገኙት፣ ከእርሱም ጋር ተዋግተው ከነዓናውያንና ፌርዛውያንን አሸነፉ፡፡
\s5
\v 6 አዶኒ ቤዜቅ ግን ሸሸ፣ ተከታትለውም አገኙትና ያዙት፣ የእጁንና የእግሩን አውራጣቶች ቆረጡ፡፡
\v 7 አዶኒ ቤዜቅም እንዲህ አለ፡- “የእግርና የእጅ አውራ ጣቶቻቸው የተቆረጠባቸው ሰባ ነገስታት ከእኔ ማዕድ ስር መብላቸውን ሰበሰቡ፡፡ እኔ እንዳደረግሁት፣ እግዚአብሔር በእኔ ላይ አደረገብኝ፡፡” እርሱንም ወደ ኢየሩሳሌም አመጡት፣ በዚያም ሞተ፡፡
\s5
\v 8 የይሁዳ ሰዎች ከኢየሩሳሌም ከተማ ጋር ተዋግተው ተቆጣጠሯት፡፡ በሰይፍ ስለት ወጓት፣ ከተማዋንም አቃጠሏት፡፡
\v 9 ከዚያም በኋላ የይሁዳ ሰዎች በኮረብታማው አገር ይኖሩ የነበሩትን ከነዓናውያንን ለመዋጋት፣ወደ ኔጌብና ወደ ምዕራቡ ኮረብታ ግርጌ ወረዱ፡፡
\v 10 ይሁዳም በኬብሮን (የኬብሮን ስም ቀድሞ ቂርያት አርባቅ ትባል ነበር) የሚኖሩትን ከነዓናውያንን ለመውጋት ሄደ፣ ሴሲን፣ አክመንና ቴላሚንም ድል አደረጉ፡፡
\s5
\v 11 ከዚያም የይሁዳ ሰዎች ወደ ዴብር (የዴብር ስም ቀድሞ ቅርያት ሤፍር ተብላ ትጠራ ነበር) ሄዱ፡፡
\v 12 ካሌብም አለ፣ “ቅርያት ሤፍርን የሚዋጋና የሚቆጣጠራትን ሰው፣ ሴት ልጄን ዓክሳን ሚስት ትሆነው ዘንድ እሰጠዋለሁ፡፡”
\v 13 የካሌብ ታናሽ ወንድም የቄናዝ ልጅ ጎቶንያልም ዴብርን ተቆጣጠረ፣ ስለዚህ ካሌብ ሴት ልጁን ዓክሳን ሚስት ትሆነው ዘንድ ሰጠው፡፡
\s5
\v 14
ዓክሳም ወዲያውኑ ወደ ጎቶንያል መጣች፣ ለእርሱም አባቷ እርሻ እንዲሰጣት እንዲለምነው ጠየቀችው፡፡ ከአሕያዋም በወረደች ጊዜ፣ ካሌብ እንዲህ ብሎ ጠየቃት፣ “ምን እንዳደርግልሽ ትፈልጊያለሽ?”
\v 15 እርሷም እንዲህ አለችው፣ “በረከትን ስጠኝ፡፡ በኔጌብ ምድር ያለውን መሬት ሰጥተኸኛልና፣ የውሃ ምንጭንም ስጠኝ፡፡” ካሌብም የላይኛውንና የታችኛውን ምንጭ ሰጣት፡፡
\s5
\v 16 የቄናዊው የሙሴ አማት ዘሮችም ከባለ ዘንባባዋ ከተማ ለቀው ከይሁዳ ሰዎች ጋር በኔጌብ ወዳለችው ወደ ይሁዳ ምድረ በዳ ከይሁዳ ሰዎች ጋር በዓራድ አጠገብ ለመኖር ሄዱ፡፡
\v 17 የይሁዳ ሰዎችም ከወንድሞቻቸው ከስምዖን ሰዎች ጋር ሄዱና በጽፋት ይኖሩ የነበሩትን ከነዓናውያንን ወጓቸው፣ፈጽሞም አጠፏት፡፡ የከተማይቱም ስም ሔርማ ይባል ነበር፡፡
\s5
\v 18 በተጨማሪ የይሁዳ ሰዎች ጋዛንና በዙርያዋ ያለውን አገር፣ አስቀሎናንና በዙርያዋ ያለውን አገር እንደዚሁም አቃሮንንና በዙርያዋ ያለውን አገር ሁሉ ተቆጣጠሩ፡፡
\v 19 እግዚአብሔርም ከይሁዳ ሰዎች ጋር ነበር፣ የኮረብታማውንም አገር ተቆጣጠሩ፣ ነገር ግን በረባዳው ምድር የሚኖሩትን ሰዎች ማስወጣት አልቻሉም ነበር ምክንያቱም ነዋሪዎቹ የብረት ሰረገሎች ነበሯቸው፡፡
\s5
\v 20
ሙሴም እንደተናገረ ኬብሮንን ለካሌብ ሰጡት፣ እርሱም የዔናቅን ሶስት ልጆች ከዚያ አስወጣቸው፡፡
\v 21 ነገር ግን የቢንያም ሰዎች በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ኢያቡሳውያንን አላስወጧቸውም፡፡ ስለዚህ ኢያቡሳውያን እስከዛሬ ድረስ ከቢንያም ሰዎች ጋር በኢየሩሳሌም ይኖራሉ፡፡
\s5
\v 22
የዮሴፍ ወገንም ቤቴልን ለመውጋት ተዘጋጁ፣ እግዚአብሔርም ከእነርሱ ጋር ነበር፡፡
\v 23 ቀድሞ ሎዛ ተብላ ትጠራ የነበረችውን ቤቴልን ለመሰለል ሰዎችን ላኩ፡፡
\v 24 ሰላዮቹም ከከተማው አንድ ሰው ሲወጣ አዩ፣ እንዲህም አሉት፣ “ወደ ከተማው እንዴት መግባት እንደምንችል እባክህ አሳየን፣ ለአንተም ቸርነት እናደርግልሃለን፡፡”
\s5
\v 25 እርሱም ወደ ከተማው መግቢያውን መንገድ አሳያቸው፡፡ እነርሱም በሰይፍ ስለት ከተማውን ወጉ፣ ያንን ሰውና ቤተሰቦቹንም እንዲያመልጡ አደረጓቻው፡፡
\v 26 ሰውየውም ወደ ኬጢያውያን ሐገር ሄደና ከተማ ገነባ ስሙንም ሎዛ አለው፣ የዚያ ቦታ ስምም እስከዛሬ ሎዛ ነው፡፡
\s5
\v 27 የምናሴ ሰዎች በቤትሳንና በመንደሮቿ፣ በታዕናክና በመንደሮቿ፣ በዶርና በመንደሮቿ፣ በይብለዓምና በመንደሮቿ፣ በመጊዶና በመንደሮቿ ይኖሩ የነበሩትን ሰዎች አላስወጡአቸውም፣ ምክንቱም ከነዓናውያን በዚያ ለመቀመጥ ወስነው ስለነበር ነው፡፡
\v 28 እስራኤልም በበረታ ጊዜ፣ ከነዓናውያንን የጉልበት ስራ እየሰሩ እንዲያገለግሉአቸው አስገደዷቸው፣ ነገር ግን ሙሉ በሙሉ አላስወጧቸውም፡፡
\s5
\v 29
ኤፍሬም በጌዝር ይኖሩ የነበሩትን ከነዓናውያን አላስወጣቸውም፣ ስለዚህ ከነዓናውያን በእነርሱ መካከል በጌዝር መኖር ቀጠሉ፡፡
\s5
\v 30 ዛብሎንም በቂድሮን የሚኖሩትን ሰዎች ወይም በነህሎል ይኖሩ የነበሩትንም ሰዎች አላስወጣቸውም፣ ስለዚህ ከነዓናውያን በእነርሱ መካከል መኖር ቀጠሉ፣ ነገር ግን ዛብሎን ከነዓናውያን የጉልበት ስራ እየሰሩ እንዲያገለግሉአቸው ያስገድዳቸው ነበር፡፡
\s5
\v 31 አሴር በዓኮ፣ በሲዶን፣ በአሕላብ፣ በአክዚብ፣ በሒልባን፣ በአፌቅ፣ በረአብም የሚኖሩትን ሰዎች አላስወጣቸውም፡፡
\v 32 ስለዚህ የአሴር ነገድ በምድሪቱ በሚኖሩት በከነዓናውያን መካከል ኖሩ፣ ምክንያቱም አላስወጧቸውም ነበር፡፡
\s5
\v 33 የንፍታሌም ነገድ በቤት ሳሚስና በቤት ዓናት ይኖሩ የነበሩትን ሰዎችን አላስወጧቸውም፡፡ ስለዚህ የንፍታሌም ነገድ በምድራቸው ይኖሩ በነበሩ በነዓናውያን ሰዎች መካከል አብረው ኖሩ፡፡ ይሁን እንጂ የቤት ሳሚስና የቤት ዓናት ነዋሪዎች ለንፍታሌም ሰዎች የጉልበት ስራ እንዲሰሩ ይገደዱ ነበር፡፡
\s5
\v 34 አሞራውያንም የዳን ነገድ በኮረብታማው አገር እንዲኖሩ አስገደዷቸው፣ ወደ ሜዳማ ስፍራ ወርደው እንዲኖሩ አልፈቀዱላቸውም ነበር፡፡
\v 35 ስለዚህ አሞራውያን በሔሬስ ተራራ፣ በኤሎን፣ በሸዓልቢምም ኖሩ፣ ነገር ግን የዮሴፍ ቤት ወታደራዊ ኃይል በእነርሱ ላይ በረቱባቸው፣ ከዚህ የተነሳ ከባድ የጉልበት ስራ እየሰሩ
\v 36 የአሞራውያንም ድንበር በሴላ ካለው ከአቅረቢም ኮረብታ ጀምሮ እስከ ኮረብታማው አገር ድረስ ነው፡፡
\s5
\c 2
\p
\v 1 የእግዚአብሔር መልዓክም ከጌልጌላ ወደ ቦኪም ወጣ፣ እንዲህም አለ፣ “ከግብጽ አወጣኋችሁ፣ ለአባቶቻችሁ ወደማልሁላቸው ምድር አመጣኋችሁ፡፡ እንዲህም አልሁ፣ ‘ከእናንተ ጋር ያለኝን ቃል ኪዳን አላፈርስም፡፡
\v 2 በዚህ ምድር ከሚኖሩ ሰዎች ጋር ቃል ኪዳን አትግቡ፡፡ መሰዊያቸውን ማፍረስ አለባችሁ፡፡’ እናንተ ግን ቃሌን አልሰማችሁም፡፡ ይህ ያደረጋችሁት ምንድን ነው?
\s5
\v 3
አሁንም እላለሁ፣ ‘ከነዓናውያንን ከእናንተ ፊት አላወጣም፣ ነገር ግን እነርሱ የጎን እሾህ ይሆኑባችኋል፣ ጣዖቶቻቸውም ለእናንተ ወጥመድ ይሆናሉ፡፡’”
\v 4 የእግዚአብሔር መልዓክም እነዚህን ቃሎች ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ በተናገረ ጊዜ ሕዝቡ ጮሁ አለቀሱም፡፡
\v 5 ያንንም ቦታ ቦኪም ብለው ጠሩት፡፡ በዚያም ለእግዚአብሔር መስዋዕትን አቀረቡ፡፡
\s5
\v 6
ኢያሱም ሰዎችን ወደ መንገዳቸው በላካቸው ጊዜ፣ የእስራኤል ሕዝብ ምድሩን ለመውሰድና የራሳቸው ለማድረግ ለእንዳንዳቸው ወደተመደበላቸው ቦታ ሄዱ፡፡
\v 7 ኢያሱ በሕይወት በነበረበት ዘመን፣ የእግዚአብሔርን ታላቅ ስራንና ለእስራኤል ምን እንዳደረገም ያዩ ከእርሱ በኋላም በኖሩ ሽማግሌዎች ዘመን ሁሉ ሕዝቡ እግዚአብሔርን አገለገለ፡፡
\v 8 የእግዚአብሔር አገልጋይ፣ የነዌ ልጅ ኢያሱ፣ በመቶ አስር ዓመቱ ሞተ፡፡
\s5
\v 9 እነርሱም በኤፍሬም ኮረብታማው አገር በሰሜናዊው ገአስ ተራራ በምድሪቱ ድንበር በተዘጋጀለት ቦታ በተምናሔሬስ ቀበሩት፡፡
\v 10 ያ ሁሉ ትውልድም ወደ አባቶቻቸው ተሰበሰቡ፡፡ ከእነርሱም በኃላ እግዚአብሔርንና እርሱ ለእስራኤል ያደረገውን ነገር የማያውቅ ሌላ ትውልድ ተነሳ፡፡
\s5
\v 11
የእስራኤል ሕዝብም በእግዚአብሔር ዓይን ክፉ የሆነውን ነገር አደረጉ፣ የበኣል አማልክትንም አመለኩ፡፡
\v 12 ከግብጽ ምድር ያወጣቸውን የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ተዉ፡፡ ሌሎች አማልክትን፣ በዙርያቸው የነበሩ ሕዝቦች አማልክትን ተከተሉ፣ ለእነርሱም ሰገዱ፡፡ እግዚአብሔርንም አስቆጡት ምከንያቱም
\v 13 እግዚአብሔርን ትተዋልና፣ በኣልንና አስታሮትንም አምልከዋልና፡፡
\s5
\v 14
የእግዚአብሔርም ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፣ ንብረታቸውን ለሰረቋቸው ወራሪዎች አሳልፎ ሰጣቸው፡፡ ከእንግዲህ ወዲህ ራሳቸውን ከጠላታቸው መከላከል እንዳይችሉ፣ በዙርያቸው በጠላቶቻቸው ብርታት ተይዘው እንደ ነበሩት ባርያዎች አሳልፎ ሸጣቸው፡፡
\v 15 እስራኤል ለውጊያ በምትሄዱበት ስፍራ ሁሉ፣ ለእነርሱ እንደማለላቸው ይሸነፉ ዘንድ የእግዚአብሔር እጅ በእነርሱ ላይ ይከፋ ነበር፡፡ ከዚህ የተነሳ እነርሱም በጣም ተጨነቁ፡፡
\s5
\v 16 ያን ጊዜ ንብረታቸውን ከሚሰርቋቸው ሰዎች ኃይል ያድናቸው ዘንድ እግዚአብሔር መሳፍንትን አስነሳላቸው፡፡
\v 17 ይሁን እንጂ እነርሱ መሳፍንቶቻቸውን ሊሰሟቸው አልቻሉም፡፡ ለእግዚአብሔር አልታመኑም፣ ራሳቸውንም እንደ አመንዝራዎች ለሌሎች አማልክት ሰጡ፣ አመለኳቸውም፡፡ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ይከተሉ ከነበሩት ከአባቶቻቸው መንገድ ወዲያውኑ ዘወር አሉ፣ እነርሱ ራሳቸው እንደ አባቶቻቸው አላደረጉም፡፡
\s5
\v 18 እግዚአብሔር ለእነርሱ መሳፍንትን ባስነሳላቸው ጊዜ፣ መሳፍንቱ በኖሩበት ዘመን ሁሉ እግዚአብሔር መሳፍንቱን ረዳቸው፣ ከጠላቶቻቸውም ጉልበት ሁሉ አዳናቸው፡፡ በጨቆኗቸውና መከራ ባሳዩአቸው ሰዎች ምክንያት ወደ እርሱ በጮኹ ጊዜ እግዚአብሔር ለእነርሱ አዘነላቸው፡፡
\v 19 ነገር ግን መስፍኑ በሞተ ጊዜ፣ ተመልሰው አባቶቻው ያደርጉ ከነበረውም እጅግ የከፋ ነገር አደረጉ፡፡ ሌሎች አማልክትን በመከተል እነርሱን ያገለግሉና ያመልኩ ነበር፡፡ ክፉ ድርጊታቸውንና እልኸኛ መንገዳቸውንም ለመተው ፈቃደኛ አልነበሩም፡፡
\s5
\v 20 የእግዚአብሔርም ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፣ እንዲህም አለ፣ “ይህ ሕዝብ ለአባቶቻቸው የገባሁትን ቃል ኪዳኔን ስላፈረሱ፣ ድምጼንም ስላልሰሙ
\v 21 ከአሁን በኋላ ኢያሱ ሲሞት ሳያወጣቸው የተዋቸውን አሕዛብ ከፊታቸው አላወጣቸውም፡፡
\v 22 ይህን የማደርገው እስራኤል አባቶቻቸው እንዳደረጉት የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁና በዚያም ይሄዱ እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ እፈትናቸው ዘንድ ነው፡፡”
\v 23 እግዚአብሔርም እነዚያን አሕዛብ የተዋቸው፣ በፍጥነትም ያላስወጣቸው፣ ኢያሱም እንዲያሸንፋቸው ያልፈቀደለት ለዚህ ነው፡፡
\s5
\c 3
\p
\v 1 እግዚአብሔር እነዚህን ሕዝቦች ሳያስወጣ ያስቀራቸው እስራኤልን ይልቁንም ደግሞ በከነዓን በተደረጉት ጦርነቶች ያልተዋጉትን በእስራኤል የሚገኙትን እያንዳንዱ ሰው ይፈትን ዘንድ ነው፡፡
\v 2 (ይህንን ያደረገው ውጊያ የማያውቁትን አዲሱ የእስራኤል ትውልድ ውጊያን ለማስተማር ነው) ፡-
\v 3 አምስቱ የፍልስጤማውያን ነገስታት፣ ከነዓናውያንም ሁሉ፣ ሲዶናውያን እና ከበዓልኤርሞንየም ተራራ እስከ ሐማት መግቢያ ድረስ በሊባኖስ ተራራዎች ይኖሩ የነበሩትም ኤውያውያን ነበሩ፡፡
\s5
\v 4
እነዚህ ሕዝቦች ሳይወጡ እንዲቀሩ የተደረጉት እግዚአብሔር እስራኤልን መፈተኛ እንዲሆኑ ነው፣ እነርሱ ለአባቶቻቸው በሙሴ በኩል የሰጣቸውን ሕግ ይታዘዙና አይታዘዙ እንደሆነ ለማረጋገጥ ነው፡፡
\v 5 ስለዚህ የእስራኤል ሕዝብ በከነዓናውያን፣ ከኬጢያውያን፣ ከአሞራውያን፣ ከፌርዛውያን ከኤውያውያንና ከኢያቡሳውያን ጋር አብረው ኖሩ፡፡
\v 6 ሴት ልጆቻቸውንም ሚስት እንዲሆኗቸው ወሰዷቸው፣ የራሳቸውን ሴት ልጆችም ለወንድ ልጆቻቸው ሰጧቸው፣ አማልክቶቻቸውንም አመለኩ፡፡
\s5
\v 7
የእስራኤል ሕዝብ በእግዚአብሔር ዓይን ጸያፍ የነበረውን ነገር ፈጸሙ፣ አምላካቸው እግዚአብሔርንም ረሱ፡፡ የኣልንና የአስታሮትን አማልክት አመለኩ፡፡
\v 8 ስለዚህም የእግዚአብሔር ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፣ ለመስጶጣምያ ንጉስ ለኩሰርሰቴም እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፡፡ የእስራኤል ሕዝብም ኩሰርሰቴን ለስምንት አመታት አገለገሉ፡፡
\s5
\v 9 የእስራኤል ሕዝብ ወደ እግዚአብሔር በጮሁ ጊዜ፣ እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ ለመርዳት የሚመጣና ካሉበት ሁኔታም የሚያድናቸው ሰው አስነሳ፡- ይህም ሰው የካሌብ ታናሽ ወንድም የቄኔዝ ልጅ ጎቶንያል ነበር፡፡
\v 10 የእግዚአብሔር መንፈስም አበረታው፣ እስራኤላውያን ላይም ይፈርድ ነበር፣ ወደ ውጊያም ይወጣ ነበር፡፡ እግዚአብሔርም በመስጶጣምያ ንጉስ በኩሰርሰቴ ላይ ድልን ሰጠው፡፡ ኩሰርሰቴንም ያሸነፈው የጎቶንያል እጅ ነበር፡፡
\v 11 ምድሪም ለአርባ ዓመት ሰላም አገኘች፡፡ የቄኔዝ ልጅ ጎቶንያልም ሞተ፡፡
\s5
\v 12 የእስራኤልም ሕዝብ ክፉ ነገሮችን በማድረግ ደግመው እግዚአብሔርን ሳይታዘዙ ቀሩ፣ እርሱም ምን እንዳደረጉ ተመለከተ፡፡ ስለዚህ እስራኤል ክፉ ነገሮችን ስላደረጉና፣ እግዚአብሔርም ስላያቸው የሞኣብ ንጉስ ኤግሎም እስራኤልን ለመውጋት በመጣ ጊዜ እግዚአብሔር ብርታትን ሰጠው፡፡
\v 13 ኤግሎምም ከአሞንና ከአማሌቃውያን ጋር ተባበረ፣ እነርሱም ሄዱ እስራኤልንም አሸነፉ፣ ከዚያም የዘንባባ ከተማን ተቆጣጠሩ፡፡
\v 14 የእስራኤልም ሕዝብ የሞኣብን ንጉስ ኤግሎምን ለአስራ ስምንት አመታት አገለገሉ፡፡
\s5
\v 15 ነገር ግን የእስራኤል ሕዝብ ወደ እግዚአብሔር በጮሁ ጊዜ፣ እግዚአብሔር የሚረዳቸውን ሰው አስነሳ፣ ይህም ግራኝ የነበረው ብንያማዊው የጌራን ልጅ ናኦድ ነው፡፡ የእስራኤልም ሕዝብ እርሱን ወደ ሞኣብ ንጉስ ወደ ኤግሎም የሚከፍሉትን ግብር አስይዘው ላኩት፡፡
\s5
\v 16 ናኦድ በሁለት በኩል የተሳለ ርዝመቱ አንድ ክንድ የሆነ ሰይፍን ሰራ፤ ከልብሱም በታች በቀኝ ጭኑ አሰረው፡፡
\v 17 ግብሩንም ለሞኣብ ንጉስ ለኤግሎም ሰጠው፡፡ (ኤግሎም በዚያን ጊዜ እጅግ ወፍራም ሰው ነበር፡፡)
\v 18 ናኦድም የግብሩን ክፍያ ካቀረበ በኋላ፣ ግብሩን ተሸክመው ገብተው ከነበሩ ሰዎች ጋር ወጣ፡፡
\s5
\v 19 ይሁን እንጂ ናኦድ በጌልጌላ አጠገብ የተቀረጹ ምስሎች ተሰርተውበት ወደነበረው ስፍራ ሲደርስ ተመልሶ ሄደና እንዲህ አለ፡- “ንጉስ ሆይ፣ ለአንተ የሚስጥር መልዕክት አለኝ፡፡” ኤግሎምም እንዲህ አለ፡- “ጸጥታ!” ስለዚህም አገልጋዮቹ ሁሉ ክፍሉን ትተው ወጡ፡፡
\v 20 ናኦድም ወደ እርሱ መጣ፡፡ ንጉሱም ቀዝቃዛ በሆነው ሰገነት ላይ ብቻውን ተቀምጦ ነበር፡፡ናኦድም እንዲህ አለ፣ “ለአንተ ከእግዚአብሔር የመጣ መልዕክት አለኝ፡፡” ንጉሱም ከመቀመጫው ተነሳ፡፡
\s5
\v 21 ናኦድም ግራ እጁን ዘረጋና ሰይፉን ከቀኝ ጭኑ አወጣ፣ ሰይፉንም በንጉሱ ሰውነት ውስጥ ሰካው፡፡
\v 22 የሰይፉም እጀታ ከስለቱ ጋር ወደ ሰውነቱ ገባ፣ ጫፉም በጀርባው ወጣ፣ ሞራም ስለቱን ሸፈነው፣ ናኦድም ሰይፉን ከንጉሱ ሰውነት አላወጣውም፡፡
\v 23 ከዚያም ናዖድ ወደ በረንዳው ወጣና የሰገነቱን በር በንጉሱ ላይ ዘግቶ ቈለፈው፡፡
\s5
\v 24 ናዖድም ከሄደ በኋላ፣ የንጉሱ ባሪያዎች መጡ፤ የሰገነቱም ደጅ ተቈልፎ አዩ፣ ስለዚህ እንዲህ ሲሉ አሰቡ፣ “ምናልባት በቀዝቃዛው ሰገነት ውስጥ እየተጸዳዳ ይሆናል፡፡”
\v 25 ንጉሱ የሰገነቱን በር ሳይከፍት በቆየም ጊዜ ስራቸውን ችላ እንዳሉ እስኪሰማቸው ድረስ ስጋት እያደረባቸው ጠበቁ፡፡ ስለዚህ ቁልፉን ወሰዱና በሮቹን ከፈቱ፣ እነሆም ጌታቸው ተጋድሞ፣ በወለሉም ላይ ወድቆ፣ ሞቶም አገኙት፡፡
\s5
\v 26 ባርያዎቹ ምን ማድረግ እንዳለባቸው እያሰቡ ሲጠባበቁ፣ ናዖድ አመለጠ፣ የጣኦታት ምስል በተቀረጸበት ስፍራ በኩል አለፈ፣ ወደ ቤይሮታም አመለጠ፡፡
\v 27 በደረሰም ጊዜ፣ በኮረብታማው በኤፍሬም አገር ቀንደ መለከት ነፋ፡፡ ከዚያም የእስራኤል ሕዝብ ከእርሱ ጋር ከኮረብታማው አገር ወረዱ፣ እርሱም ይመራቸው ነበር፡፡
\s5
\v 28
እርሱም እንዲህ አላቸው፣ “ተከተሉኝ፣ እግዚአብሔር ጠላቶቻችሁን፣ ሞዓባውያንን በእጃችሁ አሳልፎ ሰጥቶአልና፡፡” እነርሱም ተከትለውት ወረዱና የዮርዳኖስን መሻገርያ ከሞዓባውያን ቀምተው ያዙ፣ እነርሱም ማንም ሰው ወንዙን እንዳይሻገር ከለከሉ፡፡
\v 29 በዚያን ጊዜም ከሞዓብ አሥር ሺህ የሚሆኑ ሰዎችን ገደሉ፣ የተገደሉትም ሁሉ ጠንካራና ኃይለኛ ሰዎች ነበሩ፡፡ አንድም እንኳ አላመለጠም፡፡
\v 30 በዚያም ቀን ሞዓብ በእስራኤል ብርታት ድል ሆነች፡፡ ምድሪቱም ለሰማንያ ዓመት ዐረፈች፡፡
\s5
\v 31 ከናኦድ በኋላ የተነሳው መስፍን ስድስት መቶ የፍልስጥኤም ሰዎችን በበሬ መንጃ የገደለው የዓናት ልጅ ሰሜጋር ነበር፡፡ እርሱም ደግሞ እስራኤልን ከአደጋ አዳነ፡፡
\s5
\c 4
\p
\v 1 ናዖድም ከሞተ በኋላ፣ የእስራኤል ሕዝብ ክፉ ነገሮችን በመስራት እንደገና እግዚአብሔርን አልታዘዙም፣ እርሱም ምን እንዳደረጉ ተመለከተ፡፡
\v 2 እግዚአብሔርም በሐጾር ሆኖ ይገዛ በነበረው፣ በከነዓን ንጉሥ በኢያቢስ እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፡፡ የሠራዊቱም አለቃ ሲሣራ ተብሎ ይጠራ ነበር፣ እርሱም የአሕዛብ በሆነችው በአሪሶት ኖረ፡፡
\v 3 የእስራኤልም ሕዝብ ለእርዳታ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፣ ምክንያቱም ሲሳራ ዘጠኝ መቶ የብረት ሰረገሎች ነበሩት፣ እርሱም የእስራኤልን ሕዝብ ለሀያ ዓመት በኃይል አስጨንቆ ገዛቸው፡፡
\s5
\v 4 በዚያ ጊዜ ነቢይቱ የለፊዶት ሚስት ዲቦራ፣ በእስራኤል ላይ ዋነኛ ፈራጅ ነበረች፡፡
\v 5 እርስዋም በኮረብታማው በኤፍሬም አገር በራማና በቤቴል መካከል ካለው የዲቦራ ዘንባባ ዛፍ ስር ትቀመጥ ነበር፣ የእስራኤልም ሕዝብ ለክርክራቸው መፍትሔ ለማግኘት ወደ እርስዋ ይመጡ ነበር፡፡
\s5
\v 6 እርስዋም በንፍታሌም ውስጥ ካለው ከቃዴስ የአቢኒኤምን ልጅ ባርቅን ጠራች፡፡ እንዲህም አለችው፣ “የእስራኤል አምላክ፣ እግዚአብሔር፣ እንዲህ ይልሃል፣ ‘ወደ ታቦር ተራራ ሂድ፣ ከንፍታሌምና ከዛብሎን አሥር ሺህ ሰዎች ከአንተ ጋር ውሰድ፡፡
\v 7 እኔ የኢያቢስን ሠራዊት አዛዥ ሲሣራን በቂሶን ወንዝ አቅራቢያ ከሰረገሎቹና ከሰራዊቱ ጋር እንዲያገኝህ አስወጣዋለሁ፣ እኔም በእርሱ ላይ ድልን እሰጥሃለሁ፡፡’”
\s5
\v 8-9 ባርቅም እንዲህ አላት፣ “አንቺ ከእኔ ጋር ከሄድሽ እኔም እሄዳለሁ፣ ነገር ግን አንቺ ከእኔ ጋር ካልሄድሽ እኔም አልሄድም፡፡” እርስዋም እንዲህ አለች፣ “በእውነት ከአንተ ጋር እሄዳለሁ፡፡ ይሁን እንጂ፣ አንተ የምትሄድበት መንገድ ወደ ክብር አያደርስህም፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር ሲሣራን በጥንካሬዋ ድል ታደርገው ዘንድ ለሴት አሳልፎ ይሰጣልና፡፡” ከዚያም ዲቦራ ተነሥታ ከባርቅ ጋር ወደ ቃዴስ ሄደች፡፡
\s5
\v 10
ባርቅም የዛብሎንና የንፍታሌም ሰዎች በአንድነት ወደ ቃዴስ እንዲመጡ ጠራቸው፡፡ አሥር ሺህም ሰዎች ተከተሉት፣ ዲቦራም ከእርሱ ጋር ሄደች፡፡
\s5
\v 11
ቄናዊው ሔቤርም ከቄናውያን ራሱን ለየ፣ እነርሱም የሙሴ አማት የኦባብ ልጆች ነበሩ፣ እርሱም በቃዴስ አጠገብ በጻዕናይም በነበረው በበሉጥ ዛፍ ጥግ ድንኳኑን ተከለ፡፡
\s5
\v 12 ለሲሳራም የአቢኔኤም ልጅ ባርቅ ወደ ታቦር ተራራ እንደወጣ በነገሩት ጊዜ፣
\v 13 ሲሣራም ሰረገሎቹን ሁሉ፣ ዘጠኝ መቶ የብረት ሰረገሎች፣ ከእርሱም ጋር የነበሩትን ወታደሮቹን ሁሉ፣ የአሕዛብ ከሆነችው ከአሪሶት ወደ ቂሶን ወንዝ ሰበሰባቸው፡፡
\s5
\v 14 ዲቦራም ባርቅን እንዲህ አለችው፣ “ሂድ! ዛሬ እግዚአብሔር በሲሣራ ላይ ድል እንድታደርግ በእጅህ አሳልፎ የሚሰጥበት ቀን ነውና፡፡ እነሆ እግዚአብሔር ከፊትህ አልወጣምን?” ስለዚህ ባርቅ ከታቦር ተራራ አብረውት ከነበሩት አስር ሺህ ሰዎች ጋር ወረደ፡፡
\s5
\v 15 እግዚአብሔርም የሲሣራን ሰራዊት ግራ አጋባ፣ ሰረገሎቹንም ሁሉ፣ ሠራዊቱንም ሁሉ፣ የባርቅም ሰዎች የሲሳራን ሰዎች አጠቋቸው፣ ሲሳራም ከሰረገላው ወርዶ በእግሩ ሸሸ፡፡
\v 16 ባርቅ ግን ሰረገሎችንና ሠራዊቱን እስከ አሪሶት ድረስ አባረራቸው፣ የሲሣራም ሠራዊት ሁሉ በሰይፍ ስለት ተገደሉ፣ አንድ ሰው እንኳ አልቀረም፡፡
\s5
\v 17 ሲሳራ ግን በእግሩ ወደ ቄናዊው ሔቤር ሚስት፣ ወደ ኢያዔል ድንኳን ሸሸ፣ ምክንያቱም በሐሶር ንጉስ በኢያቢስና፣ በቄናዊው በሔቤር ቤት መካከል ሰላም ስለነበር ነው፡፡
\v 18 ኢያዔልም ሲሣራን ለመገናኘት ወጣች እንዲህም አለችው፣ “ግባ፣ ጌታዬ ሆይ፤ ወደ እኔ ግባ አትፍራም፡፡” እርሱም ወደ እርስዋ ወደ ድንኳንዋ ገባ፣ በብርድ ልብስም ሸፈነችው፡፡
\s5
\v 19 እርሱም እንዲህ አላት፣ “ጠምቶኛልና፣ እባክሽ የምጠጣው ጥቂት ውኃ ስጭኝ፡፡” እርስዋም ከቆዳ የተሰራ የወተቱን ማስቀመጫ ከፍታ የሚጠጣ ሰጠችው፣ ከዚያም እንደገና ሸፈነችው፡፡
\v 20 እርሱም አላት፣ “በድንኳኑ በር ላይ ቁሚ፡፡ ሰውም ቢመጣና ‘በዚህ ሰው አለን? ብሎ ቢጠይቅሽ ‘የለም’ በይ፡፡”
\s5
\v 21
ከዚያም የሔቤር ሚስት ኢያዔል የድንኳን ካስማ ወሰደች በእጅዋም መዶሻ ያዘች በቀስታ ወደ እርሱ ሄደች፣ እርሱም በከባድ እንቅልፍ ላይ ነበር፣ እርስዋም ካስማውን በጆሮ ግንዱ ላይ ሰካችው፣ ካስማውም ሰውነቱን ወግቶ አለፈና ወደ መሬት ጠለቀ፡፡ እርሱም ሞተ፡፡
\v 22 ባርቅም ሲሣራን ሲያባርር፣ ኢያዔል ልታገኘው ወጣችና እንዲህ አለችው፣ “ና፣ የምትፈልገውንም ሰው አሳይሃለሁ፡፡” እርሱም ወደ ውስጥ ከእርስዋ ጋር ገባ፣ እነሆም በዚያ ሲሣራ ሞቶ ተጋድሞ ነበር፣ ካስማውም በጆሮ ግንዱ ውስጥ ተሰክቶ አገኘው፡፡”
\s5
\v 23 ስለዚህ በዚያ ቀን እግዚአብሔር የከነዓንን ንገሥ ኢያቢስን በእስራኤል ሕዝብ ፊት አሸነፈው፡፡
\v 24 የእስራኤል ሕዝብ ጉልበት የከነዓን ንጉሥ ኢያቢስን እስከሚያጠፉ ድረስ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየበረታ መጣ፡፡
\s5
\c 5
\p
\v 1 በዚያም ቀን ዲቦራና የአቢኒኤም ልጅ ባርቅ ይህንን መዝሙር ዘመሩ፡-
\v 2 “በእስራኤል ውስጥ መሪዎች የመሪነት ስፍራውን ሲይዙ፣ ሕዝቡም በደስታና በፈቃዳቸው ለጦርነት ሲወጡ፣ እግዚአብሔርን እናመሰግናለን!
\s5
\v 3
ስሙ፣ እናንተ ነገሥታት! አድምጡ፣ እናንተም መኳንንት! እኔ፣ እኔ ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ፤ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ምስጋናን እዘምራለሁ፡፡
\v 4 እግዚአብሔር ሆይ፣ ከሴይር በወጣህ ጊዜ፣ ከኤዶምያስም በተነሳህ ጊዜ፣ ምድር ተናወጠች፣ ሰማያት ደግሞ ተንቀጠቀጡ፤ ደመናትም ደግሞ ውኃን አንጠባጠቡ፡፡
\s5
\v 5 ተራሮች በእግዚአብሔር ፊት ተንቀጠቀጡ፤ ሲና ተራራም እንኳ በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ፊት ተንቀጠቀጠ፡፡
\v 6 በዓናት ልጅ በሰሜጋር ዘመን፣ በኢያዔል ዘመን፣ መንገዶች ተተዉ፣ መንገደኞችም በጠመዝማዛ መንገድ ብቻ ይጠቀሙ ነበር፡፡
\s5
\v 7 እኔ ዲቦራ አለቃ እስከሆንሁበት ጊዜ ድረስ፣ ለእስራኤል እናት ሆኜ አለቅነትን እስከወሰድሁበት ጊዜ ድረስ፣ በእስራኤል ውስጥ ገበሬዎች አልነበሩም፡፡
\v 8 አዲስ አማልክትን መረጡ፣ በከተማዋ ደጆች ጦርነት ነበረ፤ በእስራኤል ውስጥ በአርባ ሺህ መካከል ጋሻ ወይም ጦር አልታየም፡፡
\s5
\v 9 ልቤ ወደ እስራኤል አለቆች ሄደ፣ በሕዝቡ መካከል ራሳቸውን በደስታ ስለ ሰጡትም እግዚአብሔርን እናመሰግናለን፡፡
\v 10 እናንተ በነጫጭ አህዮች ላይ ትንሽ የምንጣፍ ኮርቻ ላይ ተቀምጣችሁ የምትጓዙ፣ በመንገድም የምትሄዱ እናንተ ስለዚህ ነገር አስቡ፡፡
\s5
\v 11 በማጠጫው ስፍራ መካከል ሆነው በጎችን የሚከፋፍሉትን ሰዎች ድምጽ ስሙ፡፡ የእግዚአብሔርን የጽድቅ ድርጊትና ተዋጊዎቹ በእስራኤል ውስጥ የሰሩትን የጽድቅ ተግባር በዚያ እንደገና እየተናገሩ ነው፡፡ ያን ጊዜ የእግዚአብሔር ሕዝብ ወደ ከተማው በሮች ወረዱ፡፡
\s5
\v 12
ንቂ፣ ንቂ፣ ዲቦራ ሆይ! ንቂ፣ ንቂ፣ መዝሙርን ዘምሪ! ባርቅ ሆይ፣ ተነሣ፣ የአቢኒኤም ልጅ ሆይ፣ ምርኮኞችህን ማርከህ ውሰድ፡፡
\v 13 የዚያን ጊዜ የተረፉት ወደ ኃያላኑ መጡ፣ ከተዋጊዎቹም መካከል የእግዚአብሔር ሕዝብ ወደ እኔ መጡ፡፡
\s5
\v 14
መሰረታቸው ከአማሌቅ ወገን የሆኑ ከኤፍሬም መጡ፤ የብንያም ሕዝብም ተከተሉህ፡፡ ከማኪርም አዛዦች ወረዱ፣ የስልጣን በትር የያዙ ከዛብሎን ወረዱ፡፡
\s5
\v 15
የይሳኮርም መሳፍንት ከዲቦራ ጋር ነበሩ፤ ይሳኮርም ከባርቅ ጋር በትዕዛዙ መሰረት ከኋላው እየተከተለ ወደ ሸለቆው ሄደ፡፡ በሮቤል ጎሳ መካከል ታላቅ የልብ ምርምር ነበረ፡፡
\s5
\v 16 የበጎች እረኞች ለመንጎቻቸው በፉጨት ሲጫወቱ እያዳመጥህ በእሳት ማንደጃ መካከል ለምን ተቀመጥህ? በሮቤል ጎሳ መካከል ታላቅ የልብ ምርምር ነበረ፡፡
\s5
\v 17
ገለዓድ በዮርዳኖስ ማዶ ተቀመጠ፤ ዳን ለምን በመርከብ ውስጥ ቀረ? አሴርም በባሕሩ ዳርቻ ቀረ፣ በወንዞቹም ዳርቻ ኖረ፡፡
\v 18 ዛብሎን ነፍሱን ወደ ሞት አሳልፎ የሚሰጥ ሕዝብ ነው፣ ንፍታሌምም በውጊያ ሜዳ ላይ ነው፡፡
\s5
\v 19
ነገሥታት መጡ ተዋጉም፣ የዚያን ጊዜ የከነዓን ነገስታትም በመጊዶ ውኆች አጠገብ በታዕናክ ተዋጉ፡፡ ምንም የብር ምርኮ አልወሰዱም፡፡
\v 20 ከሰማይ ከዋክብት ተዋጉ፣ በሰማያት ላይ በአካሄዳቸውም ሲሣራን ተዋጉት፡፡
\s5
\v 21 ከዱሮ ጀምሮ የታወቀው፣ የቂሶን ወንዝም፣ ጠርጎ ወሰዳቸው፡፡ ነፍሴ ሆይ ገስግሺ፣ በርቺ!
\v 22 የፈረሶች የግልብያ ኮቴዎች ድምጽ፣ የኃያላኑ ግልቢያ ድምጽም፡፡
\s5
\v 23 የእግዚአብሔር መልአክ “ሜሮዝን እርገሙ!” ይላል፡፡ ‘ነዋሪዎቿን ፈጽማችሁ እርገሙ! ምክንያቱም እግዚአብሔርን ለመርዳት አልመጡም፣ ከኃያላን ጦረኞች ጋር በተደረገው ውጊያ እግዚአብሔርን ለመርዳት አልመጡምና፡፡'
\s5
\v 24 የቄናዊው የሔቤር ሚስት፣ ኢያዔል፣ ከሴቶች ሁሉ ይልቅ የተባረከች ናት፣ በድንኳን ውስጥ ከሚኖሩ ሴቶች ሁሉ ይልቅ የተባረከች ናት፡፡
\v 25 ሰውየው ውኃ ለመናት፣ እርስዋም ወተት ሰጠችው፤ ለመሳፍንት በሚሆን በተከበረ ሳህን ቅቤ አመጣችለት፡፡
\s5
\v 26 እጅዋን ወደ ድንኳን ካስማ፣ ቀኝ እጅዋንም ወደ ሠራተኛ መዶሻ አደረገች፤ በመዶሻውም ሲሣራን መታች፣ ራሱንም ቀጠቀጠች፡፡ ጆሮ ግንዱን በወጋችው ጊዜ ጭንቅላቱንም ፈረከሰችው፡፡
\v 27 በእግሮችዋ መካከል ተደፋ፣ ወደቀ ተኛም፡፡ በእግሮችዋ አጠገብ ተሰብሮ ወደቀ፡፡ የተደፋበት ስፍራ በክፉ ሁኔታ የሞተበት ነው፡፡
\s5
\v 28 ከመስኮት ሆና ወደ ውጭ ተመለከተች፣ የሲሣራ እናት በርብራብ በኩል በኃዘን ወደ ውጭ ጮኸች፣ ‘ወደዚህ ለመምጣት ሰረገላው ረዥም ጊዜ ለምን ወሰደበት? ለምንስ ሰረገላዎቹን የሚጎትቱት የፈረሶቹ ኮቴዎች ዘገየ?
\s5
\v 29 ብልሃተኞች ልዕልቶቿም መለሱላት፣ ለራስዋም ተመሳሳይ መልስ መለሰች፡-
\v 30 ምርኮውን አግኝተው ተካፍለው የለምን? ለእያንዳንዱ ሰው ምርኮ አንዲት ወይም ሁለት ልጃገረድ፤ ለሲሣራ ምርኮ ልዩ ልዩ ቀለም ያለው ልብስ፣ የተጠለፈ ባለቀለም ጨርቅ ምርኮ፣ ለማረኩ ሰዎች ለአንገታቸው የሚሆን በሁለት እጥፍ የተጠለፈ ባለቀለም ጨርቆች ምርኮን አላገኙምን?
\s5
\v 31
ስለዚህ፣ እግዚአብሔር ሆይ፣ ጠላቶችህ ሁሉ እንዲሁ ይጥፉ! ነገር ግን እርሱን የሚወዱት በኃይል እንደሚወጣ ጸሐይ ይሁኑ፡፡” ምድሪቱም ለአርባ ዓመት ያህል ዐረፈች፡፡
\s5
\c 6
\p
\v 1 የእስራኤልም ሕዝብ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ የሆነውን ሥራ ሠሩ፤ እርሱም በምድያም ቁጥጥር ስር እንዲሆኑ ለሰባት ዓመት አሳልፎ ሰጣቸው፡፡
\v 2 የምድያምም ኃይል በእስራኤል ላይ በረታ፡፡ ከምድያምም የተነሣ የእስራኤል ሕዝብ በኮረብታዎች ላይ ጕድጓድ፣ ዋሻና ምሽግም ለራሳቸው መሸሸጊያ አበጁ።
\s5
\v 3 እንዲህም ሆነ፣ እስራኤል ዘር በዘሩ ጊዜ ምድያማውያን፣ አማሌቃውያንና ከምሥራቅም የመጡ ሰዎች እስራኤላውያንን ያጠቁ ነበር፡፡
\v 4 ሰራዊታቸውን በምድሪቱ ላይ ያሰፍሩና እስከ ጋዛ ድረስ ያለውን ሰብል ያጠፉ ነበር፡፡ በእስራኤልም ምንም መብል፣ በጎች፣ ከብቶችና አህያዎች አይተዉም ነበር፡፡
\s5
\v 5
እነርሱ እንስሶቻቸውንና ድንኳኖቻቸውን ይዘው ሲመጡ እንደ አንበጣ መንጋ ሆነው ይመጡ ነበር፤ እነርሱንና ግመሎቻቸውንም መቁጠር አይቻልም ነበር፡፡ ምድሪቱንም ያጠፉ ዘንድ ይወርሩአት ነበር፡፡
\v 6 ምድያም እስራኤልን ክፉኛ ከማዳከማቸው የተነሣ የእስራኤል ሕዝብ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፡፡
\s5
\v 7 የእስራኤል ሕዝብ በምድያም ምክንያት ወደ እግዚአብሔር በጮኹ ጊዜ፣
\v 8 እግዚአብሔር ወደ እስራኤል ልጆች ነቢይ ላከ፡፡ ነቢዩም እንዲህ አለ፡- “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡- ‘እኔ ከግብፅ ምድር አወጣኋችሁ፤ ከባርነትም ቤት አወጣኋችሁ፡፡
\s5
\v 9 ከግብፃውያንም እጅ እንደዚሁም ይጨቁኑአችሁ ከነበሩ ኃይላት ሁሉ አዳንኋችሁ፡፡ ከፊታችሁም አሳድጄ አወጣኋቸው፣ ምድራቸውንም ሰጠኋችሁ፡፡
\v 10 ለእናንተንም እንዲህ አልኋችሁ፣ “እኔ አምላካችሁ እግዚአብሔር ነኝ፤ በምድራቸው የተቀመጣችሁባቸውን፣ የአሞራያውያንን አማልክት እንዳታመልኩ አዘዝኋችሁ፡፡ ነገር ግን እናንተ ድምጼን አልታዘዛችሁም፡፡
\s5
\v 11 የእግዚአብሔርም መልአክ መጣና በዖፍራ ባለችው ለአቢዔዝራዊው ለኢዮአስ በነበረችው ከበሉጥ ዛፍ በታች ተቀመጠ፤ የኢዮአስም ልጅ ጌዴዎን ከምድያማውያን ለመሸሸግ በወይን መጥመቂያው ውስጥ ስንዴ ይወቃ ነበር፡፡
\v 12 የእግዚአብሔርም መልአክ ለእርሱ ተገልጠለትና እንዲህ አለው፣ “አንተ ብርቱ ተዋጊ ሰው፣ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው አለው!”
\s5
\v 13 ጌዴዎንም ለእርሱ እንዲህ አለው፣ “ጌታዬ ሆይ፣ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ፣ ይህ ነገር ሁሉ ለምን በእኛ ላይ ደረሰብን? አባቶቻችንስ የነገሩን እርሱ የሰራቸው አስደናቂ ነገሮች ወዴት አሉ፣ እንዲህ ብለው የነገሩን፣ ‘እግዚአብሔር ከግብፅ አላወጣንምን? አሁን ግን እግዚአብሔር ትቶናል፣ ለምድያማውያንም ብርታት አሳልፎ ሰጥቶናል፡፡
\s5
\v 14
እግዚአብሔርም ወደ እርሱ ተመለከተና እንዲህ አለው፣ “በዚህ ባለህ ብርታት ሂድ፡፡ እስራኤልንም ከምድያም ኃይል አድን፤ እነሆ እኔ አልላክሁህምን?”
\v 15 ጌዴዎንም እንዲህ አለው፣ “ጌታ ሆይ፣ እባክህ፣ እኔ እስራኤልን እንዴት ማዳን እችላለሁ? ተመልከት፣ የእኔ ቤተሰብ ከምናሴ ነገድ ከሁሉ ይልቅ ደካማ ነው፣ እኔም በአባቴ ቤት ውስጥ የመጨረሻ ነኝ፡፡
\s5
\v 16
እግዚአብሔርም፣ “እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፣ አንተም የምድያምን ሰራዊት በሙሉ ታሸንፋለህ” አለው፡፡
\v 17 ጌዴዎንም እንዲህ አለው፣ “በእኔ ደስተኛ ከሆንህ፣ የምትናገረኝ አንተ እንደሆንህ እርግጠኛ እሆን ዘንድ ምልከትን ስጠኝ፡፡
\v 18 ወደ አንተ እስክመጣና መስዋእቴን አምጥቼ በፊትህ እስካቀርብ ድረስ እባክህ ከዚህ አትሂድ፡፡” እግዚአብሔርም “እስክትመለስ ድረስ እቆያለሁ” አለ፡፡
\s5
\v 19
ጌዴዎን ሄደ የፍየሉንም ጠቦት አረደ፣ የኢፍ መስፈሪያም ዱቄት ወስዶ ያልቦካ ቂጣ አዘጋጀ፡፡ ሥጋውን በቅርጫት አኖረ፣ መረቁንም በምንቸት ውስጥ አኖረ፣ ሁሉንም ይዞ በበሉጥ ዛፍ በታች አቀረበለት፡፡
\v 20 የእግዚአብሔርም መልአክ እንዲህ አለው፣ “ሥጋውንና ያልቦካውን ቂጣ ውሰድና በዚህ ድንጋይ ላይ አኑረው፣ መረቁንም በላዩ ላይ አፍስሰው፡፡” ጌዴዎንም እንዲሁ አደረገ፡፡
\s5
\v 21
የእግዚአብሔርም መልአክ በእጁ የያዘውን የበትሩን ጫፍ ወደዚያ ዘረጋ፡፡ በበትሩም ሥጋውንና ያልቦካውን ቂጣ ነካው፤ እሳትም ከድንጋዩ ውስጥ ወጥቶ ሥጋውንና ያልቦካውን ቂጣ በላ፡፡ የእግዚአብሔርም መልአክ ሄደ፣ ጌዴዎንም ሊያየው አልቻለም፡፡
\s5
\v 22
ጌዴዎንም የእግዚአብሔር መልአክ እንደ ሆነ አወቀ፡፡ ጌዴዎንም፣ “አምላኬ እግዚአብሔር ሆይ፣ ወዮልኝ! የእግዚአብሔርን መልአክ ፊት ለፊት አይቻለሁና” አለ፡፡
\v 23 እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፣ “ሰላም ለአንተ ይሁን! አትፍራ፣ አትሞትም፡፡”
\v 24 ስለዚህ ጌዴዎን በዚያ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፡፡ ስሙንም፣ እግዚአብሔር ሰላም ብሎ ጠራው፡፡ እስከ ዛሬ ድረስ በአቢዔዝራውያን ጎሳ በምትሆነው በዖፍራ አለ፡፡
\s5
\v 25 እግዚአብሔርም በዚያች ሌሊት እንዲህ አለው፣ “የአባትህን በሬ፣ ሰባት ዓመት የሆነውን ሁለተኛውንም በሬ ውሰድ፣ የአባትህ የሆነውን የበኣል መሠዊያ አፍርስና በአጠገቡ ያለውን አሼራን ሰባብረው፡፡
\v 26 በዚህ መሸሸጊያ ስፍራ ጫፍ ላይ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሥራ፣ በትክክለኛው መንገድም ስራው፡፡ ከአሼራ ሰባብረህ በጣልኸው እንጨት ሁለተኛውን በሬ የሚቃጠል መስዋእት አድርገህ አቅርበው፡፡”
\s5
\v 27
ስለዚህ ጌዴዎን ከባሪያዎቹ አሥር ሰዎችን ወሰደና እግዚአብሔር እንደነገረው አደረገ፡፡ ነገር ግን በቀን ለማድረግ የአባቱን ቤተ ሰቦችና የከተማውንም ሰዎች እጅግ በጣም ስለፈራ፣ በሌሊት አደረገው፡፡
\s5
\v 28 በማለዳ የከተማው ሰዎች በተነሱ ጊዜ፣ የበኣል መሠዊያ ፈርሶ ነበር፣ በአጠገቡ የነበረውም አሼራ ተሰባብሮ ነበር፣ ሁለተኛውም በሬ አዲስ በተሰራው መሠዊያ ላይ ተሠውቶ ነበር፡፡
\v 29 የከተማውም ሰዎች እርስ በርሳቸው፣ “ይህን ያደረገው ማን ነው?” ተባባሉ፡፡ ከሌሎች ጋር ሲነጋገሩና መልስ ሲፈልጉ ሳሉ፣ “ይህን ያደረገው የኢዮአስ ልጅ ጌዴዎን ነው” አሉ፡፡
\s5
\v 30 የዚያን ጊዜ የከተማው ሰዎች ኢዮአስን እንዲህ አሉት፣ “የበኣልን መሠዊያ አፍርሶአልና፣ በአጠገቡ የነበረውንም አሼራ ሰባብሮታልና እንዲሞት ልጅህን አውጣ፡፡”
\s5
\v 31
ኢዮአስም ለተቃወሙት በሙሉ እንዲህ አላቸው፣ “ለበኣል ትምዋገቱለታላችሁን? እርሱን ታድኑታላችሁን? ለእርሱ የሚምዋገትለት ሁሉ እስከ ነገ ጠዋት ይገደል፡፡ በኣል አምላክ ከሆነ፣ መሠዊያውን ሲያፈርሱበት ራሱን ይከላከል፡፡
\v 32 ስለዚህም በዚያ ቀን ጌዴዎን “ይሩበኣል” የሚል ስም ተሰጠው፣ ምክንያቱም እርሱ “በኣል ራሱን ይከላከል” ብሏልና፣ ጌዴዎን መሠዊያውን አፍርሶአልና፡፡
\s5
\v 33
ምድያማውያንና አማሌቃውያን ሁሉ፣ የምሥራቅም ሰዎች አንድ ላይ ተሰበሰቡ፡፡ ዮርዳኖስን ተሻግረው በኢይዝራኤል ሸለቆ ውስጥ ሰፈሩ፡፡
\s5
\v 34
ነገር ግን የእግዚአብሔር መንፈስ ጌዴዎንን ሊረዳው በእርሱ ላይ ወረደ፡፡ ጌዴዎንም ቀንደ መለከት ነፋ፣ የአቢዔዝር ጎሳ ሰዎች ይከተሉት ዘንድ ጠራቸው፡፡
\v 35 እርሱም ወደ ምናሴ ነገድ ሁሉ መልክተኞችን ሰደደ፣ እነርሱም ደግሞ እንዲከተሉት ተጠርተው ነበር፡፡ መልክተኞችንም ወደ አሴር፣ ዛብሎንና ንፍታሌምም ላከ፣ እነርሱም እርሱን ሊየገኙት ሄዱ፡፡
\s5
\v 36
ጌዴዎንም እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፣ “እንደ ተናገርኸው እስራኤልን ለማዳን እኔን የምትጠቀምብኝ ከሆነ
\v 37 ተመልከት፣ በአውድማው ላይ የበግ ጠጕር ባዘቶ አኖራለሁ፡፡ በጠጕሩ ብቻ ላይ ጠል ቢሆንና በምድሩም ሁሉ ደረቅ ቢሆን፣ የዚያን ጊዜ እንደተናገርኸው አንተ እስራኤልን ለማዳን እንደምትጠቀምብኝ አውቃለሁ፡፡”
\s5
\v 38
እንዲሁም ሆነ፣ ጌዴዎን በነጋው ማልዶ ተነሣ፣ ጠጕሩንም በአንድ ላይ ጨመቀው፣ ከጠጕሩም የተጨመቀው ጠል አንድ ቆሬ ለመሙላት በቂ ሆነ፡፡
\s5
\v 39 ጌዴዎንም እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፣ “አትቈጣኝ፣ አንድ ጊዜ እንደገና እናገራለሁ፡፡ እባክህ፣ የጠጉሩ ባዘቶ በመጠቀም አንድ ተጨማሪ ሙከራ እንዳደርግ ፍቀድልኝ፡፡ በዚህ ጊዜ ጠጕሩ ብቻ ደረቅ ይሁን፣ በምድሩና በዙርያውም ሁሉ ላይ ደግሞ ጠል ይሁን፡፡”
\v 40 እግዚአብሔርም በዚያ ሌሊት የጠየቀውን አደረገ፡፡ ጠጕሩ ደረቅ ነበረ፣ በምድሩም ሁሉ ላይ ጠል ነበረ፡፡
\s5
\c 7
\p
\v 1
ከዚያም ጌዴዎን የተባለው ይሩበኣልና ከእርሱም ጋር የነበሩ ሕዝብ ሁሉ በጠዋት ተነሡ፣ በሐሮድ ምንጭ አጠገብም ሰፈሩ፡፡ የምድያምም ሰፈር ከእነርሱ ወደ ሰሜን በኩል በሞሬ ኮረብታ አጠገብ በሸለቆው ውስጥ ነበረ፡፡
\s5
\v 2 እግዚአብሔርም ጌዴዎንን እንዲህ አለው፣ “ምድያማውያንን እንድታሸንፍ የሚያደርጉህ እጅግ በጣም ብዙ ወታደሮች አሉኝ፡፡ ‘የራሳችን ኃይል አዳነን’ ብለው እስራኤል እንዳይታበዩብኝ እርግጠኛ ሁን፡፡
\v 3 ስለዚህም አሁን፣ በሕዝቡ ጆሮዎች እንዲህ ብለህ ተናገር፣ “ማንም የፈራ ቢኖር፣ ማንም የደነገጠ ቢኖር፣ የገለዓድን ተራራ ትቶ ይመለስ፡፡” ስለዚህ 22, 000 ሰዎች ተመለሱ፣ 10, 000 ሰዎችም ቀሩ፡፡
\s5
\v 4
እግዚአብሔርም ጌዴዎንን እንዲህ አለው፣ “ሕዝቡ አሁንም ገና ብዙ ነው፡፡ ሕዝቡን ወደ ውኃ ውሰዳቸው፣ በዚያም ቁጥራቸውን ጥቂት አደርግልሃለሁ፡፡ እኔ ‘ይህ ከአንተ ጋር ይሄዳል’ ካልሁህ እርሱ ከአንተ ጋር ይሄዳል፤ ነገር ግን እኔ ‘ይህ ከአንተ ጋር አይሄድም’ ካልሁህ እርሱ ከአንተ ጋር አይሄድም፡፡”
\s5
\v 5
ስለዚህ ጌዴዎን ሕዝቡን ወደ ውኃ ወሰዳቸው፣ እግዚአብሔርም ጌዴዎንን እንዲህ አለው፣ “ውሻ እንደሚጠጣ ውኃ የሚጠጣውን ሁሉ፣ ውኃ ለመጠጣት በጕልበታቸው ከሚንበረከኩት ሰዎች መካከል ለይ፡፡”
\v 6 ሦስት መቶ ሰዎች ውኃ እንደ ውሻ ጠጡ፡፡ የቀሩት ሰዎች ግን ውኃ ለጠጡ በጉልበታቸው ተንበረከኩ፡፡
\s5
\v 7
እግዚአብሔርም ጌዴዎንን እንዲህ አለው፣ “ውኃን እንደ ውሻ በጠጡት በሦስት መቶ ሰዎች ከምድያማውያን አድንሃለሁ፣ በእነርሱም ላይ ድል እሰጥሃለሁ፡፡ ሌሎቹ ሰዎች በሙሉ ወደ ስፍራቸው ይመለሱ፡፡”
\v 8 ስለዚህ የተመረጡት ሰዎች ስንቃቸውንና ቀንደ መለከታቸውን ወሰዱ፡፡ ጌዴዎን የእስራኤልን ሰዎች ሁሉ፣ እያንዳንዱን ሰው ወደ ድንኳናቸው ሰደዳቸው፣ ነገር ግን ሦስቱን መቶ ሰዎች በእርሱ ዘንድ አቆያቸው፡፡ የምድያምም ሰፈር ከእርሱ በታች በሸለቆው ውስጥ ነበረ፡፡
\s5
\v 9
በዚያም ሌሊት እግዚአብሔር ለእርሱ እንዲህ አለው፣ “ተነስ! ሰፈራቸውን ምታ፣ በእነርሱ ላይ እኔ ድል እሰጥሃለሁና፡፡
\v 10 ነገር ግን አንተ ወደ ለመውረድ ከፈራህ፣ ከአገልጋይህ ከፉራ ጋር ወደ ሰፈሩ ውረድ፣
\v 11 የሚናገሩትንም አድምጥ፣ ከዚያም በኋላ ሰፈሩን ለመውጋት ድፍረት ታገኛለህ፡፡” ስለዚህ ጌዴዎን ከአገልጋዩ ከፉራ ጋር በሰፈሩ ወደ ነበሩት ጠባቂዎች ወረዱ፡፡
\s5
\v 12 ብዛታቸውም እንደ አንበጣ መንጋ የሆነ ምድያማውያን፣ አማሌቃውያንና የምሥራቅም ሰዎች ሁሉ በሸለቆው ውስጥ ሰፍረው ነበር፡፡ የግመሎቻቸውም ብዛት መቁጠር አይቻልም ነበር፤ ቁጥራቸው በባህር ዳርቻ ካለው አሸዋ ይልቅ የሚበልጥ ነበር፡፡
\s5
\v 13
ጌዴዎን በዚያ በደረሰ ጊዜ አንድ ሰው ሕልምን ለጓደኛው ሲነግረው ነበር፡፡ ሰውየውም እንዲህ አለ፣ “ተመልከት! ሕልም አለምሁ፣ አንዲት ክብ የገብስ ቂጣ ወደ ምድያም ሰፈር ተንከባልላ ስትወርድ አየሁ፡፡ ወደ ድንኳኑም ደረሰች፣ እስኪወድቅ ድረስም በጣም መታችው ከዚህ የተነሳ ወደቀ፣ ደግሞም ተገለበጠ፣ ስለዚህም ድንኳኑ ተጋደመ፡፡”
\v 14 ሌላኛውም ሰው እንዲህ አለ፣ “ይህ ነገር ከእስራኤል ሰው ከኢዮአስ ልጅ ከጌዴዎን ሰይፍ በቀር ሌላ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር በምድያምና በሠራዊቱ ሁሉ ላይ ድል ሰጥቶታል፡፡”
\s5
\v 15
ጌዴዎን የሕልሙን ዝርዝርና ትርጓሜውን በሰማ ጊዜ በጸሎት ተደፍቶ ሰገደ፡፡ እርሱም ወደ እስራኤል ሰፈር ሄደና እንዲህ አለ፣ “ተነሱ! እግዚአብሔር በምድያም ሠራዊት ላይ ድል ሰጥተአችኋል፡፡”
\v 16 እርሱም ሦስቱን መቶ ሰዎች በሦስት ቡድን ከፈላቸው፣ ለሁሉም ሰዎች ቀንደ መለከትና ባዶ ማሰሮ፣ በማሰሮውም ውስጥ ችቦ ሰጣቸው፡፡
\s5
\v 17
እርሱም እንዲህ አላቸው፣ “እኔን ተመልከቱ፣ የማደርገውንም አድርጉ፡፡ አስተውሉ! ወደ ሰፈሩ ዳርቻ በመጣሁ ጊዜ፣ እኔ የማደርገውን እናንተም ታደርጋላችሁ፡፡
\v 18 እኔና ከእኔም ጋር ያሉት ሁሉ ቀንደ መለከት ስንነፋ፣ እናንተ ደግሞ በሰፈሩ በሁሉም አቅጣጫ ቀንደ መለከታችሁን ንፉና “ለእግዚአብሔርና ለጌዴዎን” ብላችሁ ጩኹ፡፡
\s5
\v 19 ስለዚህ ጌዴዎንና ከእርሱ ጋር የነበሩት መቶ ሰዎች የመካከለኛው የጥበቃ ሰዓት በተጀመረ ጊዜ ወደ ሰፈሩ ዳርቻ መጡ፡፡ ምድያማውያን የጥበቃ ሰዎችን በሚቀይሩበት ጊዜ፣ ቀንደ መለከቶቹን ነፉ፣ በእጃቸውም የነበሩትንም ማሰሮች ሰባበሩ፡፡
\s5
\v 20
ሦስቱም ቡድኖች ቀንደ መለከቶቹን ነፉ፣ ማሰሮችንም ሰበሩ፡፡ በግራ እጃቸው ችቦችን ያዙ፣ በቀኝ እጃቸው ደግሞ ቀንደ መለከቶችን ይዘው ለመንፋት ተዘጋጁ፡፡ እነርሱም “የእግዚአብሔርና የጌዴዎን ሰይፍ” ብለው ጮኹ፡፡
\v 21 ሁሉም ሰው በሰፈሩ ዙሪያ በየቦታው ቆመ፣ የምድያማውያን ሠራዊት ሁሉ ሮጡ፡፡ እነርሱም ጮኹና ሸሹ፡፡
\s5
\v 22
ሦስት መቶውንም ቀንደ መለከቶች በነፉ ጊዜ፣ እግዚአብሔር የእያንዳንዱን ምድያማዊ ሰው ሰይፍ በጓደኛውና በራሳቸው ሰራዊት ሁሉ ላይ አዘጋጀ፡፡ ሠራዊቱም በጽሬራ በኩል እስከ ቤትሺጣ፣ በጠባት አጠገብ እስካለው እስከ አቤልምሖላ ዳርቻ ድረስ ሸሸ፡፡
\v 23 የእስራኤል ሰዎች ከንፍታሌም፣ ከአሴርና ከምናሴም ሁሉ ተሰብስበው ምድያምን ከኋላ እየተከተሉ አሳደዱ፡፡
\s5
\v 24 ጌዴዎን መልክተኞችን በኤፍሬም ወዳለው ኮረብታማ አገር ሁሉ በመስደድ እንዲህ አለ፣ “ምድያምን ለመዋጋት ውረዱና እነርሱን ለማስቆም የዮርዳኖስን ወንዝ እስከ ቤትባራም ድረስ ተቆጣጠሩ፡፡” ስለዚህ የኤፍሬም ሰዎች ሁሉ በአንድ ላይ ተሰብስበው እስከ ቤትባራና ዮርዳኖስ ወንዝ ድረስ ውኃውን ተቆጣጠሩ፡፡
\v 25 የምድያምን ሁለቱን መሪዎች ሔሬብንና ዜብን ያዙ፡፡ ሔሬብንም በሔሬብ ዓለት ገደሉት፣ ዜብንም በዜብ ወይን መጥመቂያ ላይ ገደሉት፡፡ ምድያማውያንንም አሳደዱ፣ የሔሬብንና የዜብንም ራስ ይዘው በዮርዳኖስ ማዶ ወደነበረው ወደ ጌዴዎን አመጡ፡፡
\s5
\c 8
\p
\v 1 የኤፍሬም ሰዎች ለጌዴዎን እንዲህ አሉት፣ “ይህ በእኛ ላይ ያደረግኸው ምንድር ነው? ምድያምን ለመዋጋት በሄድህ ጊዜ እኛን አልጠራኸንም?” ከእርሱም ጋር በኃይል ተጣሉ።
\s5
\v 2 እርሱም እንዲህ አላቸው፣ “ከእናንተ ጋር ሲነጻጸር አሁን እኔ ያደረግት ምንድን ነው? ከኤፍሬም የወይን ቃርሚያ ይልቅ የአቢዔዝር ሙሉ የወይን መከር አይሻልምን?
\v 3 እግዚአብሔር በምድያም መሪዎች በሔሬብና በዜብ ላይ ድልን ሰጥቶአችኋል! ከእናንተ ጋር ሲነጻጸር እኑ ምን ፈጸምሁ?” ይህን በተናገረ ጊዜ ቍጣቸው በረደ።
\s5
\v 4
ጌዴዎን ከእርሱ ጋር ከነበሩት ከሦስቱ መቶ ሰዎች ጋር ወደ ዮርዳኖስ መጣና ተሻገረ፡፡ እጅግ በጣም ደክመው ነበር፣ ይሁን እንጂ ያሳድዱ ነበር።
\v 5 እርሱም ለሱኮት ሰዎች እንዲህ አላቸው፣ “ደክመዋልና እባካችሁ ለተከተሉኝ ሰዎች እንጀራ ስጡአቸው፣ እኔም የምድያምን ነገሥታት ዛብሄልንና ስልማናን እያሳደድሁ ነው፡፡”
\s5
\v 6
የሱኮትም መሪዎች እንዲህ አሉ፣ “ዛብሄልንና ስልማናን በጉልበትህ አሸነፍኃቸውን?” እኛ ለሠራዊትህ እንጀራ ለምን እንደምንሰጥ አናውቅም?
\v 7 ጌዴዎንም እንዲህ አለ፣ “እግዚአብሔር በዛብሄልና በስልማና ላይ ድል በሰጠኝ ጊዜ፣ እኔ በምድረ በዳ እሾህና በኵርንችት ሥጋችሁን እቦጫጭቀዋለሁ፡፡”
\s5
\v 8
ከዚያም ወደ ጵኒኤል ወጣና በተመሳሳይ መንገድ በዚያ ለሚገኙ ሰዎች ተናገራቸው፣ ነገር ግን የጵንኤልም ሰዎች የሱኮት ሰዎች እንደ መለሱ መለሱለት።
\v 9 እርሱም የጵኒኤልን ሰዎች ደግሞ እንዲህ አላቸው፣ “በሰላም በተመለስሁ ጊዜ፣ ይህን ግንብ አፈርሰዋለሁ፡፡
\s5
\v 10 ዛብሄልና ስልማናም ከሠራዊቶቻቸው ጋር፣ ከምሥራቅም ሰዎች ሠራዊት ሁሉ የቀሩ 15, 000 ያህል ሰዎች በቀርቀር ነበሩ፡፡ በሰይፍ ለመዋጋት ስልጠና የወሰዱ መቶ ሀያ ሺህ ሰዎች ወድቀው ነበርና፡፡
\s5
\v 11 ጌዴዎንም ዘላኖች ባሉበት መንገድ በኖባህና በዮግብሃ አልፎ ወደ ጠላት ሰፈር ሄደ፡፡ እርሱም የጠላትን ሰራዊት አሸነፈ፣ ምክንያቱም እንዲህ ዓይነት አደጋ ይገጥመናል ብለው አላሰቡም ነበርና፡፡
\v 12 ዛብሄልና ስልማናም ሸሹ፣ ጌዴዎንም ባሳደዳቸው ጊዜ ሁለቱንም የምድያም ነገሥታት ዛብሄልንና ስልማናን ያዛቸው፣ ሠራዊታቸውንም ሁሉ ድንጋጤ ላይ ጣላቸው፡፡
\s5
\v 13
የኢዮአስ ልጅ ጌዴዎንም በሔሬስ ዳገት በኩል በማለፍ ከጦርነት ተመለሰ፡፡
\v 14 እርሱም ከሱኮት ሰዎች አንድ ወጣት ይዞ ጠየቀውና ከእርሱ ምክር ፈለገ፡፡ ወጣቱም የሱኮትን መሪዎችና ሽማግሌዎች ሰባ ሰባት ሰዎች እነማን እንደሆኑ ገለጸለት።
\s5
\v 15
ጌዴዎንም ወደ ሱኮት ሰዎች መጣና እንዲህ አላቸው፣ “‘ዛብሄልንና ስልማናን በጉልበትህ አሸነፍኃቸውን? እኛ ለሠራዊትህ እንጀራ መስጠት እንዳለብን አናውቅም? ብላችሁ ያላገጣችሁብኝ ዛብሄልና ስልማና ተመልከቱአቸው፡፡”
\v 16 ጌዴዎንም የከተማይቱን ሽማግሌዎች ያዛቸው፣ የሱኮትንም ሰዎች በምድረ በዳ እሾህና በኵርንችት ገረፋቸው፡፡
\v 17 የጵኒኤልንም ግንብ አፈረሰ፣ የዚያችን ከተማ ሰዎችን ገደለ፡፡
\s5
\v 18
ጌዴዎንም ለዛብሄልና ለስልማና እንዲህ አላቸው፣ “በታቦር የገደላችኋቸው ሰዎች ምን ዓይነት ሰዎች ነበሩ?” እነርሱም፣ “እንደ አንተ ያሉ ነበሩ፡፡ እያንዳንዳቸው የንጉሥ ልጅ ይመስላሉ” አሉት፡፡
\v 19 ጌዴዎንም “እነርሱ የእናቴ ልጆች ወንድሞቼ ነበሩ፡፡ በሕይወት እንዲኖሩ አድናችኋቸው ቢሆን ኖሮ፣ ሕያው እግዚአብሔርን፣ እኔ አልገድላችሁም ነበር” አለ፡፡
\s5
\v 20
ለበኵር ልጁ ለዬቴር እንዲህ አለው፣ “ተነሳና ግደላቸው!” ነገር ግን ወጣቱ ልጅ ስለፈራ ሰይፉን አልመዘዘም፣ ምክንያቱም ገና ወጣት ልጅ ነበረና፡፡
\v 21 የዚያን ጊዜ ዛብሄልና ስልማና እንዲህ አሉ፣ “አንተ ተነሳና ግደለን! የሰው ኃይሉ እንደ ሰውነቱ ነውና፡፡” ጌዴዎንም ተነሥቶ ዛብሄልንና ስልማናን ገደላቸው፡፡ በግመሎቻቸውም አንገት ላይ የነበሩትን ጌጦች ወሰደ፡፡
\s5
\v 22
የእስራኤልም ሰዎች ጌዴዎንን “አንተ ግዛን፣ አንተ፣ የአንተ ልጅና የልጅ ልጆችህ ግዙን፣ ምክንያቱም አንተ ከምድያም ብርታት አድነኸናልና፡፡”
\v 23 ጌዴዎንም ለእነርሱ እንዲህ አላቸው፣ “እኔ በእናንተ ላይ አልገዛም፣ ልጄም በእናንተ ላይ አይገዛም፣ እግዚአብሔር ይገዛችኋል አላቸው፡፡
\s5
\v 24
ጌዴዎን ለእነርሱ እንዲህ አላቸው፣ “አንድ የምጠይቃችሁ ነገር አለኝ፡- እያንዳንዳችሁ ከምርኮአችሁ ጕትቻችሁን እንድትሰጡኝ እለምናችኋለሁ፡፡” (ምድያማውያን የወርቅ ጕትቻ ነበራቸው ምክንያቱም እነርሱ እስማኤላውያንም ነበሩና፡፡)
\v 25 እነርሱም፣ “ለአንተ ልንሰጥህ ደስተኞች ነን” አሉት፡፡ እነርሱም ልብስ አነጠፉና ሁሉም ሰው የምርኮውን ጕትቻ በዚያ ላይ ጣለ፡፡
\s5
\v 26
እርሱ የጠየቀው የወርቅ ጕትቻ ክብደት 1, 700 ሰቅል ወርቅ ነበር፡፡ ይህም ምርኮ ከጌጣ ጌጦቹ ሌላ የአንገት ጌጥ፣ የምድያምም ነገሥታት ከሚለብሱት ሐምራዊ ልብስ፣ እንደዚሁም በግመሎቻቸውም አንገት ከነበሩት ጌጦች ሌላ ነበረ፡፡
\s5
\v 27
ጌዴዎንም ከጉትቻዎቹ ባገኘው ወርቅ ኤፉድ ሠራና በከተማው፣ በዖፍራ አኖረው፣ እስራኤልም ሁሉ እርሱን በማምለክ አመነዘረበት፡፡ ለጌዴዎንና በቤቱም ላሉት ወጥመድ ሆነባቸው፡፡
\v 28 ስለዚህም ምድያም በእስራኤል ሕዝብ ፊት ተዋረደ፣ ራሳቸውንም እንደገና አላነሡም፡፡ በጌዴዎንም ዘመን ምድሪቱ ለአርባ ዓመት ሰላም ሆነች።
\s5
\v 29
የኢዮአስም ልጅ ይሩበኣል ሄደና በራሱ ቤት ተቀመጠ።
\v 30 ጌዴዎንም ብዙ ሚስቶች ነበሩትና ሰባ ወንዶች ልጆች ነበሩት፡፡
\v 31 በሴኬም የነበረችው ቁባቱም ወንድ ልጅ ወለደችለት፣ ጌዴዎንም ስሙን አቤሜሌክ ብሎ ጠራው፡፡
\s5
\v 32
የኢዮአስ ልጅ ጌዴዎን በመልካም የሽምግልና ዕድሜ ሞተ፣ በአቢዔዝራውያን ጎሳ በሆነው በዖፍራ በነበረው በአባቱ በኢዮአስ መቃብር ተቀበረ፡፡
\v 33 ጌዴዎን ከሞተ በኋላ ብዙ ሳይቆይ እንዲህ ሆነ፣ የእስራኤል ሕዝብ እንደገና ተመለሱ፣ የበኣልን አማልክት በማምለክ አመነዘሩ፡፡ በኣልብሪትንም አምላካቸው አደረጉ፡፡
\s5
\v 34 የእስራኤልም ሕዝብ በተለያዩ አቅጣጫዎች ከነበሩት ከጠላቶቻቸው ኃይል ያዳናቸውን አምላካቸውን እግዚአብሔርን አላሰቡትም፡፡
\v 35 እነርሱም ለእስራኤል ስላደረገው በጎ ነገር አስበው ለይሩበኣል (የጌዴዎን ሌላኛው ስም ነው) ውለታ ለመመለስ ቃል ኪዳናቸውን አልጠበቁም፡፡
\s5
\c 9
\p
\v 1
የይሩበኣል ልጅ አቤሜሌክ ወደ እናቱ ዘመዶች ወደ ሴኬም ሄደና ለእነርሱና ለእናቱ ቤተሰብ ጎሳ በሙሉ እንዲህ አላቸው፣
\v 2 “በሴኬም የሚገኙ መሪዎች በሙሉ ይሰሙ ዘንድ ይህን ተናገሩ፣ ‘ለእናንተ የሚሻለው የትኛው ነው? የይሩበኣል ሰባ ልጆች ሁሉ ቢገዙአችሁ ወይስ አንድ ሰው ቢገዛችሁ? እኔ የአጥንታችሁ ፍላጭ የሥጋችሁ ቍራጭ እንደ ሆንሁ አስቡ፡፡”
\s5
\v 3
የእናቱም ዘመዶች ስለ እርሱ ለሴኬም መሪዎች ተናገሩ፣ እነርሱም አቤሜሌክን ለመከተል ተስማሙ፣ “እርሱ ወንድማችን ነው” ብለዋልና፡፡
\v 4 እነርሱም ከበኣልብሪትም ቤት ሰባ ብር ሰጡት፣ አቤሜሌክም እርሱን የተከተሉትን ስርዓት አልበኞችንና ወሮበሎችን ለመቅጠር ተጠቀበመት፡፡
\s5
\v 5
እርሱም ወደ አባቱ ቤት ወደ ዖፍራ ሄደ፣ የይሩበኣልን ልጆች ሰባ ወንድሞቹን በአንድ ድንጋይ ላይ አረዳቸው፡፡ ትንሹ የይሩበኣል ልጅ ኢዮአታም ግን ተሸሽጎ ስለነበር እርሱ ብቻ ተረፈ፡፡
\v 6 የሴኬምና የቤትሚሎ መሪዎች ሁሉ በአንድ ላይ ተሰበሰቡ፣ እነርሱም ሄደው በሴኬም በዓምዱ አጠገብ ባለው በበሉጥ ዛፍ ስር አቤሜሌክን አነገሡት፡፡
\s5
\v 7
ለኢዮአታም ይህን ነገር በነገሩት ጊዜ፣ በገሪዛን ተራራ ራስ ላይ ሄደና ቆመ፡፡ ድምፁንም ከፍ አድርጎ ጮኸና እንዲህ አላቸው፣ “እናንተ የሴኬም መሪዎች፣ እግዚአብሔርም እናንተን ይሰማ ዘንድ፣ እኔን ስሙኝ፡፡
\v 8 አንድ ጊዜ ዛፎች በእነርሱ ላይ የሚያነግሱት ለመቀባት ሄዱ፡፡ እነርሱም ለወይራ ዛፍ ‘በእኛ ላይ ንገሥ’ አሉት፡፡
\s5
\v 9 የወይራ ዛፍ ግን ለእነርሱ እንዲህ አላቸው፣ ‘እግዚአብሔርና ሰዎችን ለማክበር የሚጠቅመውን ቅባቴን ትቼ ተመልሼ በሌሎች ዛፎች ላይ ለመወዛወዝ ልሂድን?
\v 10 ዛፎቹም ለበለስ ዛፍ እንዲህ አሉት፣ ‘መጥተህ በእኛ ላይ ንገሥ፡፡’
\v 11 ነገር ግን የበለሱ ዛፍ፣ ጣፋጭነቴንና መልካሙን ፍሬዬን ትቼ ተመልሼ በሌሎች ዛፎች ላይ ለመወዛወዝ ልሂድን? አላቸው፡፡
\s5
\v 12
ዛፎችም ለወይኑ፣ ‘መጥተህ በእኛ ላይ ንገሥ’ አሉት፡፡
\v 13 ወይኑም፣ እግዚአብሔርንና ሰውን ደስ የሚያሰኘውን አዲስ የወይን ጠጄን ትቼ ተመልሼ በዛፎች ላይ ለመወዛወዝ ልሂድን? አላቸው፡፡
\v 14 ከዚያም ዛፎች ሁሉ የእሾህ ቁጥቋጦን፣ ‘መጥተህ በእኛ ላይ ንገሥ’ አሉት፡፡
\s5
\v 15 የእሾህ ቁጥቋጦውም ዛፎቹን፣ ‘በእውነት እኔን በእናንተ ላይ እንድነግስ ልትቀቡኝ የምትፈልጉ ከሆነ፣ ኑና በጥላዬ ስር ተጠለሉ፡፡ እንዲህ ካልሆነ ግን እሳት ከእሾህ ቁጥቋጦ ይውጣና የሊባኖስንም ዝግባ ያቃጥል’ አላቸው፡፡
\v 16 አሁን እንግዲህ፣ አቤሜሌክን ባነገሳችሁት ጊዜ በእውነትና በቅንነት አድርጋችሁ ከሆነ፣ ለይሩበኣልና ለቤቱም በጎነት አስባችሁ አድርጋችሁ ከሆነ፣ እንዳደረገውም መጠን ለእርሱ የተገባውን ቀጥታችሁት ከሆነ
\s5
\v 17
አባቴ ስለ እናንተ ተዋግቶ እንደነበር፣ ሕይወቱን አሳልፎ በመስጠት፣ ከምድያምም እጅ እናንተን እንዳዳናችሁ አሰባችሁ ማለት ነው
\v 18 ነገር ግን ዛሬ እናንተ በአባቴ ቤት ላይ ተነሥታችኋል፣ በአንድ ድንጋይ ላይ ልጆቹን፣ ሰባ ሰዎችን፣ አረዳችኋቸው፡፡ ከዚያም የሴት አገልጋዩን ልጅ አቤሜሌክን ዘመዳችሁ ስለ ሆነ በሴኬም መሪዎች ላይ እንዲነግስ አደረጋችሁት፡፡
\s5
\v 19
ያንጊዜ ለይሩበኣልና ለቤቱ በእውነትና በቅንነትን አድርጋችሁ ከሆነ፣ እንግዲያው እናንተ በአቤሜሌክ ደስ ሊላችሁ ይገባል፣ እርሱም በእናንተ ደስ ይበለው፡፡
\v 20 ነገር ግን እንዲህ ባይሆን፣ ከአቤሜሌክ እሳት ይውጣና የሴኬምንም ሰዎችና የቤትሚሎን ቤት ያቃጥል፡፡ ከሴኬምም ሰዎችና ከቤትሚሎ እሳት ይውጣና አቤሜሌክን ያቃጥል፡፡
\v 21 ኢዮአታምም ሸሽቶ አመለጠ፣ ከዚያም ወደ ብኤር ሄደ፡፡ እርሱም በዚያ ተቀመጠ ምክንያቱም ከአቤሜሌክ ከወንድሙ በጣም ሩቅ ነበረ፡፡
\s5
\v 22
አቤሜሌክም በእስራኤል ላይ ለሦስት ዓመት ገዛ፡፡
\v 23 እግዚአብሔር በአቤሜሌክና በሴኬም መሪዎች መካከል ክፉን መንፈስ ሰደደ፡፡ የሴኬም መሪዎችም በአቤሜሌክ ላይ የነበራቸውን እምነት ጥለው ከዱት፡፡
\v 24 እግዚአብሔር ይህንን ያደረገው በሰባዎቹ የይሩበኣል ልጆች ላይ የተደረገውን ዓመፅ ለመበቀል ነው፣ ወንድማቸው አቤሜሌክም እነርሱን በመግደሉ ተጠያቂ እንዲሆን ለማድረግ ነው፤ የሴኬም ሰዎችም እርሱ ወንድሞቹን እንዲገድላቸው ስለተባበሩት ተጠያቂ እንዲሆኑ ለማድረግ ነው፡፡
\s5
\v 25 ስለዚህ የሴኬም መሪዎች በኮረብቶች ራስ ላይ እርሱን አድፍጠው የሚጠብቁ ሰዎች መደቡ፣ እነርሱም በዚያ መንገድ በአጠገባቸው ያለፉትን ሰዎች በሙሉ ዘረፉ፡፡ ይህም ወሬ ለአቤሜሌክ ደረሰው፡፡
\s5
\v 26 የአቤድም ልጅ ገዓል ከዘመዶቹ ጋር መጣና ወደ ሴኬም ሄዱ፡፡ የሴኬም መሪዎች በእርሱ ተማመኑበት፡፡
\v 27 እነርሱም ወደ እርሻው ወጥተው ሄዱና ከወይን አትክልት ቦታ ወይን ለቅመው ጨመቁት፡፡ በአምላካቸው ቤት የደስታ በዓል አደረጉ፣ በሉም ጠጡም፣ አቤሜሌክንም ሰደቡ፡፡
\s5
\v 28
የአቤድም ልጅ ገዓል እንዲህ አለ፣ “እናገለግለው ዘንድ አቤሜሌክ ማን ነው? ሴኬምስ ማን ነው? እርሱ የይሩብኣል ልጅ አይደለምን? ዜቡልስ የእርሱ ሹም አይደለምን? ለኤሞር ሰዎች፣ ለሴኬም አባት አገልግሉ! ለምን እርሱን እናገለግላለን?
\v 29 ይህ ሕዝብ በእኔ አዛዥነት ስር ቢሆን እመኝ ነበር! የዚያን ጊዜ አቤሜሌክን አስወግደው ነበር፡፡ ለአቤሜሌክም ‘ሠራዊትህን ሁሉ ጥራ’ እለው ነበር፡፡”
\s5
\v 30 የከተማይቱ ሹም፣ ዜቡል የአቤድን ልጅ የገዓልን ቃል በሰማ ጊዜ ቁጣው ነደደ፡፡
\v 31 ወደ አቤሜሌክም ያታልለው ዘንድ እንዲህ ብሎ መልክተኞች ላከ፣ “ተመልከት፣ የአቤድ ልጅ ገዓልና ዘመዶቹ ወደ ሴኬም እየመጡ ነው፣ ከተማይቱን በአንተ ላይ እንድትሸፍት አነሳስተዋል፡፡
\s5
\v 32 አሁንም አንተና ከአንተ ጋር ያሉት ወታደሮች በሌሊት ተነሡ፣ ሜዳውም ላይ አድፍጡ፡፡
\v 33 ከዚያም በጠዋት ፀሐይ በወጣች ጊዜ ማልደህ ተነሣና በከተማይቱ ላይ ድንገተኛ ጥቃት ፈጽምባት፡፡ እርሱና ከእርሱ ጋር ያሉት ሕዝብ በአንተ ላይ በመጡ ጊዜ በእነርሱ ላይ ልታደርግ የምትችለውን ማንኛውንም ነገር አድርግባቸው፡፡”
\s5
\v 34 ስለዚህ አቤሜሌክ በሌሊት ተነሳ፣ እርሱና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሰዎች በሙሉ፣ በአራት ወገን ተከፋፍለው በሴኬም ላይ አደፈጡ፡፡
\v 35 የአቤድ ልጅ ገዓል ወጥቶ በከተማይቱ በር መግቢያ ቆመ፡፡ አቤሜሌክና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሰዎችም ከተደበቁበት ስፍራ ወጥተው መጡ፡፡
\s5
\v 36
ገዓልም ሰዎቹን ባየ ጊዜ ዜቡልን፣ “ተመልከት፣ ሰዎች ከኮረብቶች ራስ ወርደው እየመጡ ነው!” አለው፡፡ ዜቡልም እንዲህ አለው፣ “አንተ የምታየው ሰዎች የሚመስለውን የኮረብቶች ጥላ ነው፡፡”
\v 37 ገዓልም እንደገና እንዲህ ሲል ተናገረ፣ “ተመልከት፣ በምድር መካከል ሰዎች ወርደው እየመጡ ነው፣ አንድም ወገን በቃላተኞች የበሉጥ ዛፍ መንገድ እየመጣ ነው፡፡
\s5
\v 38 የዚያን ጊዜ ዜቡል እንዲህ አለው፣ “‘እናገለግለው ዘንድ አቤሜሌክ ማን ነው? ብለህ የተናገርሃቸው እነዚያ የትዕቢት ቃላቶችህ አሁን የት አሉ? እነዚህ ሰዎች አንተ የናቅሃቸው አይደሉምን? አሁን ውጣና ከእነርሱ ጋር ተዋጋ፡፡”
\v 39 ገዓል ወጣና የሴኬም ሰዎችን ይመራ ነበር፣ ከአቤሜሌክም ጋር ተዋጋ፡፡
\v 40 አቤሜሌክም አሳደደው፣ ገዓልም በፊቱ ሸሸ፡፡ ብዙዎቹም በከተማይቱ በር መግቢያ ፊት ለፊት በከባድ ሁኔታ ቆስለው ወደቁ፡፡
\s5
\v 41 አቤሜሌክም በአሩማ ተቀመጠ፡፡ ዜቡልም ገዓልንና ዘመዶቹን ከሴኬም እንዲወጡ አስገደዳቸው፡፡
\v 42 በሚቀጥለው ቀን የሴኬም ሕዝብ ወደ እርሻ ሄዱ፣ ይህም ወሬ ለአቤሜሌክ ደረሰው፡፡
\v 43 ሕዝቡንም ወሰደ፣ በሦስት ወገንም ከፈላቸውና በእርሻዎቹ ውስጥ አደፈጡ፡፡ እርሱም ተመለከተ፣ ሕዝቡ ከከተማ ወጥተው ሲመጡ አየ፡፡ እርሱም ተዋጋቸውና ገደላቸው፡፡
\s5
\v 44 አቤሜሌክና ከእርሱም ጋር የነበሩት ወገኖች ተዋጉና የከተማይቱን በር መግቢያ ዘጉ፡፡ ሌሎቹ ሁለት ወገኖች ደግሞ በእርሻው ውስጥ የነበሩትን ሁሉ ወጓቸውና ገደሉአቸው፡፡
\v 45 አቤሜሌክም ቀኑን ሙሉ ከከተማይቱ ጋር ተዋጋ፡፡ ከተማይቱንም ተቆጣጠረና በውስጧ የነበሩትን ሕዝብ ገደላቸው፡፡ የከተማይቱንም ቅጥር አፈራረሰው፣ በላይዋም ጨው በተነባት፡፡
\s5
\v 46 የሴኬም ግንብ መሪዎች በሙሉ ይህንን ወሬ በሰሙ ጊዜ፣ ወደ ኤልብሪት ቤት ምሽግ ውስጥ ገቡ፡፡
\v 47 አቤሜሌክም መሪዎቹ በሙሉ በሴኬም ግንብ ውስጥ በአንድ ላይ እንደተሰበሰቡ ተነገረው፡፡
\s5
\v 48 አቤሜሌክ ወደ ሰልሞን ተራራ ወጣ፣ እርሱና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሰዎች ሁሉ፡፡አቤሜሌክም በእጁ መጥረቢያ ወሰደና የዛፉን ቅርንጫፎች ቆረጠ፡፡ እርሱም አንሥቶ በትከሻው ላይ አደረገውና ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሰዎች እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፣ “እኔ ሳደርግ ያያችሁትን፣ ፈጥናችሁ እኔ እንዳደረግሁ አድርጉ፡፡”
\v 49 ስለዚህ እያንዳንዱ ሰው የዛፉን ቅርንጫፎች ቈረጠና አቤሜሌክን ተከተሉት፡፡ እነርሱም ቅርንጫፎቹን በምሽጉ ላይ ከመሩአቸው፣ በላዩም ላይ እሳት አቀጣጠሉበት፣ ከዚህ የተነሳ የሴኬም ግንብ ሰዎች ሁሉ፣ አንድ ሺህ የሚያህሉ ወንድና ሴት ሞቱ፡፡
\s5
\v 50 ከዚያ በኋላ አቤሜሌክ ወደ ቴቤስ ሄደ፣ ቴቤስንም ከበባትና ተቆጣጠራት፡፡
\v 51 ነገር ግን በከተማይቱ ጠንካራ ግንብ ነበረ፣ የከተማይቱም ሰዎች ሁሉ፣ ወንዶችና ሴቶች ሁሉ፣ የከተማይቱም መሪዎች ሁሉ ወደዚያ ሸሹና በውስጥ ሆነው ደጁን ዘጉት፡፡ ከዚያም እስከ ግንቡ ሰገነት ድረስ ወደ ላይ ወጡ፡፡
\s5
\v 52
አቤሜሌክም ወደ ግንቡ መጣና ተዋጋ፣ በእሳትም ሊያቃጥለው ወደ ግንቡ በር አጠገብ መጣ፡፡
\v 53 ነገር ግን አንዲት ሴት በአቤሜሌክ ራስ ላይ የወፍጮ መጅ ጣለችበት፣ መጁም ጭንቅላቱን ሰባበረው፡፡
\v 54 ከዚያም እርሱ በአስቸኳይ ጋሻ ጃግሬውን ጠርቶ፣ “አንድም ሰው እኔን ‘ሴት ገደለችው’ እንዳይል ሰይፍህን መዝዘህ ግደለኝ” አለው፡፡ ስለዚህ ወጣቱ ሰው ወጋውና ሞተ፡፡
\s5
\v 55 የእስራኤልም ሰዎች አቤሜሌክ እንደ ሞተ ባዩ ጊዜ ወደ ቤታቸው ተመለሱ፡፡
\v 56 እግዚአብሔርም ሰባ ወንድሞቹን በመግደል አቤሜሌክ በአባቱ ላይ ያደረገውን ክፋት ተበቀለው፡፡
\v 57 እግዚአብሔርም የሴኬምን ሰዎች ክፋት ሁሉ በራሳቸው ላይ መለሰባቸው፣ የይሩበኣልም ልጅ የኢዮአታም እርግማን በእነርሱ ላይ መጣባቸው፡፡
\s5
\c 10
\p
\v 1
ከአቤሜሌክ በኋላ ከይሳኮር ነገድ የሆነውና በኮረብታማውም በኤፍሬም አገር ባለችው በሳምር ይኖር የነበረው የዱዲ ልጅ የፎሖ ልጅ ቶላ እስራኤልን ለማዳን ተነሣ፡፡
\v 2 እርሱም በእስራኤል ላይ ሀያ ሦስት ዓመት ፈረደ፡፡ እርሱም ሞተ፣ በሳምርም ተቀበረ፡፡
\s5
\v 3
ከእርሱም በኋላ ገለዓዳዊው ኢያዕር ተነሣ፡፡ በእስራኤልም ላይ ሀያ ሁለት ዓመት ፈረደ፡፡
\v 4 በሠላሳ አህያዎች የሚጋልቡ ሠላሳ ልጆች ነበሩት፣ እነርሱም በገለዓድ ምድር ያሉ እስከ ዛሬ ድረስ የኢያዕር መንደሮች ተብለው የሚጠሩ ሠላሳ ከተሞች ነበሩአቸው፡፡
\v 5 ኢያዕርም ሞተ፣ በቃሞንም ተቀበረ፡፡
\s5
\v 6
የእስራኤል ሕዝብ ከዚህ በፊት ከሰሩት በላይ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ስራ ጨምረው ሠሩ፣ በኣልን፣ አስታሮትን፣ እንደዚሁም የሶርያን አማልክት፣ የሲዶናን አማልክት፣ የሞዓብን አማልክት፣ የአሞንን ሕዝብ አማልክት፣ የፍልስጥኤማውያንን አማልክት አመለኩ፡፡እግዚአብሔርን ተዉ፣ እርሱንም አላመለኩትም፡፡
\v 7 የእግዚአብሔርም ቍጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፣ እርሱም ፍልስጥኤማውያንና አሞናውያን ያሸንፉአቸው ዘንድ ለእነርሱ አሳልፎ ሰጣቸው፡፡
\s5
\v 8
እነርሱም በዚያን ዓመት የእስራኤልን ሕዝብ አደቀቋቸው፣ አስጨነቋቸው፣ ለአሥራ ስምንት ዓመት በዮርዳኖስ ማዶ በአሞራውያን ምድር በገለዓድ ውስጥ የነበሩትን የእስራኤልን ሕዝብ ሁሉ አስጨነቋቸው፡፡
\v 9 የአሞንም ሰዎች ከይሁዳ፣ ከብንያምና ከኤፍሬም ቤት ጋር ለመዋጋት ዮርዳኖስን ተሻገሩ፣ ከዚህ የተነሳ እስራኤል እጅግ በጣም ተጨነቁ፡፡
\s5
\v 10 የዚያን ጊዜ የእስራኤልም ሕዝብ ወደ እግዚአብሔር ጮሁ፣ እንዲህ በማለት፣ “በአንተ ላይ በድለናል፣ ምክንያቱም አምላካችንን ትተን የበኣል አማልክትን አምልከናልና፡፡”
\v 11 እግዚአብሔርም ለእስራኤል ልጆች እንዲህ አላቸው፣ “ከግብፃውያን፣ ከአሞራውያንም፣ ከአሞናውያን፣ ከፍልስጤማውያንና
\v 12 ከሲዶናውያን አላዳንኋችሁምን? አማሌቃውያንና ማዖናውያን አስጨነቋችሁ፤ ወደ እኔም ጮኻችሁ፣ እኔም ከእነርሱ ኃይል አዳንኋችሁ፡፡
\s5
\v 13 ይሁን እንጂ እናንተ እንደገና ተዋችሁኝና ሌሎችን አማልክት አመለካችሁ፡፡ ስለዚህ፣ እኔም ከእንግዲህ ወዲህ አላድናችሁም፡፡
\v 14 ሂዱና ወደምታመልኳቸው አማልክት ጩኹ፡፡ በመከራችሁ ጊዜ እነርሱ ያድኑአችሁ፡፡
\s5
\v 15
የእስራኤልም ሕዝብ እግዚአብሔርን እንዲህ አሉት፣ “እኛ ኃጢአትን ሠርተናል፡፡ ለአንተ ደስ የሚያሰኝህን ማንኛውንም ነገር በእኛ ላይ አድርግብን፡፡ እባክህ፣ የዛሬን ብቻ አድነን፡፡”
\v 16 እነርሱም በመካከላቸው ካሉት ባዕዳን አማልክት ዘወር አሉ፣ እግዚአብሔርንም አመለኩ፡፡እርሱም የእስራኤልን ጕስቍልና ሊታገሰው የማይቻለው ሆነ፡፡
\s5
\v 17 ከዚያም አሞናውያን በአንድ ላይ ተሰበሰቡና በገለዓድ ሰፈሩ፡፡ እስራኤላውያንም በአንድ ላይ ተሰበሰቡና ሰፈራቸውን በምጽጳ ላይ አደረጉ፡፡
\v 18 የገለዓድ ሕዝብ መሪዎችም እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፣ “አሞናውያንን ለመዋጋት የሚጀምር ሰው ማን ነው? እርሱ በገለዓድ በሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ላይ መሪ ይሆናል፡፡”
\s5
\c 11
\p
\v 1
ገለዓዳዊውም ዮፍታሔ ኃያል ተዋጊ ነበር፣ ነገር ግን የጋለሞታ ሴት ልጅ ነበረ፡፡ አባቱም ገለዓድ ነበረ፡፡
\v 2 የገለዓድም ሚስት ደግሞ ሌሎች ወንዶች ልጆችን ወለደችለት፡፡ የሚስቱ ልጆች ባደጉ ጊዜ፣ ዮፍታሔን ቤቱን ለቅቆ እንዲወጣ አስገደዱት፣ እንዲህም አሉት፡- “አንተ ከቤተሰባችን ምንም ነገር አትወርስም፡፡ አንተ የሌላ ሴት ልጅ ነህ፡፡”
\v 3 ስለዚህ ዮፍታሔ ከወንድሞቹ ፊት ሸሸና በጦብ ምድር ተቀመጠ፡፡ ስርዓት አልበኛ ሰዎችም ተከተሉት፣ ተሰብስበውም ከእርሱ ጋር ሄዱ፡፡
\s5
\v 4
ከጥቂት ቀናት በኋላ፣ የአሞን ሰዎች ከእስራኤል ጋር ውጊያ አደረጉ፡፡
\v 5 የአሞንም ሰዎች ከእስራኤል ጋር ውጊያ ባደረጉ ጊዜ፣ የገለዓድ ሽማግሌዎች ዮፍታሔን ከጦብ ምድር ለማምጣት ሄዱ፡፡
\v 6 ዮፍታሔንም፣ “ና፣ ከአሞን ሰዎች ጋር እንድንዋጋ አለቃችን ሁን” አሉት፡፡
\s5
\v 7 ዮፍታሔም ለገለዓድ ሽማግሌዎች እንዲህ አላቸው፣ “እናንተ ጠልታችሁኛል፣ የአባቴንም ቤት ትቼ እንድሄድ አስገድዳችሁኛል፡፡ አሁን በተቸገራችሁ ጊዜ ለምን ወደ እኔ መጣችሁ?”
\v 8 የገለዓድም ሽማግሌዎችም ለዮፍታሔ፣ “አሁን ወደ አንተ የተመለስነው ለዚህ ነው፤ ከእኛ ጋር ና፣ ከአሞንም ሰዎች ጋር ተዋጋ፣ ከዚያም በኋላ በገለዓድ በሚኖሩት ሰዎች ሁሉ ላይ መሪ ትሆናለህ” አሉት፡፡
\s5
\v 9
ዮፍታሔም ለገለዓድ ሽማግሌዎች፣ “ከአሞን ሰዎች ጋር እንድዋጋ እንደገና ወደ ቤቴ ከመለሳችሁኝ፣ እግዚአብሔርም በእነርሱ ላይ ድል ከሰጠን መሪያችሁ እሆናለሁ” አላቸው፡፡
\v 10 የገለዓድ ሽማግሌዎችም ለዮፍታሔ፣ “እንደተናገርነው የማናደርግ ከሆነ እግዚአብሔር በእኛ መካከል ምስክር ይሁን” አሉት፡፡
\v 11 ስለዚህ ዮፍታሔ ከገለዓድ ሽማግሌዎች ጋር ሄደ፣ ሕዝቡም በላያቸው ላይ መሪና የጦር አዛዥ አደረጉት፡፡ እርሱ በምጽጳ በእግዚአብሔር ፊት በነበረ ጊዜ፣ ዮፍታሔ የገባውን ቃል ኪዳን ሁሉ ደገመው፡፡
\s5
\v 12
ዮፍታሔም ወደ አሞን ሰዎች ንጉሥ እንዲህ በማለት መልእክተኞችን ላከ፡- “በእኛ መካከል ያለው ጠብ ምንድን ነው? ምድራችንን ለመውሰድ በጦር ለምን መጣህ?”
\v 13 የአሞንም ሰዎች ንጉሥም ለዮፍታሔ መልክተኞች “እስራኤል ከግብፅ በወጣ ጊዜ ከአርኖን ጀምሮ እስከ ያቦቅና እስከ ዮርዳኖስ ድረስ ምድሬን ወስደዋል፡፡ አሁን እነዚህን መሬቶች በሰላም መልሱልኝ” ብሎ መለሰላቸው፡፡
\s5
\v 14 ዮፍታሔም ወደ አሞን ሰዎች ንጉሥ መልክተኞችን እንደ ገና ላከ፣
\v 15 እንዲህም አለው፣ “ዮፍታሔ የሚለው ይህንን ነው፡- እስራኤል የሞዓብን ምድር የአሞንንም ሰዎች ምድር አልወሰደም፣
\v 16 ነገር ግን ከግብፅ በወጡ ጊዜ፣ እስራኤል በምድረ በዳ በኩል ወደ ቀይ ባሕር ከዚያም ወደ ቃዴስ ሄዱ፣
\s5
\v 17
እስራኤል ወደ ኤዶምያስ ንጉሥ እንዲህ በማለት መልእክተኞችን ላኩ፣ ‘በምድርህ እንድናልፍ እባክህ ፍቀድልን፣’ ነገር ግን የኤዶምያስ ንጉሥ አልሰማም፡፡ እንዲሁም ወደ ሞዓብ ንጉሥ መልእክተኞች ላኩ፣ እርሱም አልፈቀደም፡፡ ስለዚህ እስራኤል በቃዴስ ተቀመጠ፡፡
\v 18 እነርሱም በምድረ በዳ በኩል ሄዱና ከኤዶምያስና ከሞዓብ ምድር ተመለሱ፣ በሞዓብም ምድር በምሥራቅ በኩል ሄዱ፣ በአርኖንም ማዶ ሰፈሩ፡፡ ነገር ግን ወደ ሞዓብ ክልል ውስጥ አልገቡም፣ አርኖን የሞዓብ ድንበር ነበረና፡፡
\s5
\v 19
እስራኤልም በሐሴቦን ውስጥ ገዥ ወደነበረው ወደ አሞራውያን ንጉሥ ወደ ሴዎን መልክተኞችን ላከ፤ እስራኤልም ‘እባክህ፣ በምድርህ በኩል ወደ ስፍራችን እንድናልፍ ፍቀድልን’ አለው፡፡
\v 20 ነገር ግን ሴዎን እስራኤል በድንበሩ እንዲያልፍ አላመነውም፡፡ ስለዚህ ሴዎን ሰራዊቱን ሁሉ ሰበሰበና ወደ ያሀጽ ተንቀሳቀሰ፣ በዚያም ከእስራኤል ጋር ተዋጋ፡፡
\s5
\v 21
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔርም ለእስራኤል በሴዎን ላይ ድል ሰጠውና ሕዝቡን ሁሉ በቁጥጥራቸው ስር እንዲሆኑ አሳልፎ ሰጣቸው፡፡ ስለዚህም እስራኤል በዚያች አገር ተቀምጠው የነበሩትን የአሞራውያንን አገር ሁሉ ወሰዱ፡፡
\v 22 በአሞራውያን ክልል ውስጥ የነበረውን ሁሉንም ነገር ወሰዱ፣ ከአርኖንም እስከ ያቦቅ ድረስ፣ ከምድረ በዳውም እስከ ዮርዳኖስ ድረስ፡፡
\s5
\v 23
ያንጊዜ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር አሞራውያንን ከሕዝቡ ከእስራኤል ፊት አስወጣቸው፣ ታዲያ አንተ አሁን ምድራቸውን ልትወስድ ይገባልን?
\v 24 አምላክህ ካሞሽ የሚሰጥህን ምድር አትወስድምን? ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካችን የሰጠንን ምድር ሁሉ እንወስዳለን፡፡
\v 25 አሁን አንተ ከሞዓብ ንጉሥ ከሴፎር ልጅ ከባላቅ በእውነት ትሻላለህን? እርሱ ከእስራኤል ጋር ከቶ ክርክር ነበረውን? ከእነርሱ ጋር ጦርነት አካሂዷልን?
\s5
\v 26
እስራኤል በሐሴቦንና በቀበሌዎችዋ፣ በአሮዔርና በቀበሌዎችዋ፣ በአርኖንም ዳርቻ ባሉት ከተሞች ሁሉ ለሦስት መቶ ዓመት ሲኖር በነበረበት ጊዜ፣ ለምን ታዲያ በዚያን ጊዜ መልሳችሁ አልወሰዳችኋቸውም ነበር?
\v 27 እኔ አልበደልሁህም ነገር ግን አንተ እኔን በመውጋት እየበደልከኝ ነው፡፡ ፈራጅ የሆነው እግዚአብሔር በእስራኤል ሰዎችና በአሞን ሰዎች መካከል ዛሬ ይፈርዳል፡፡
\v 28 ነገር ግን የአሞን ሰዎች ንጉሥ ዮፍታሔ የላከበትን ማስጠንቀቂያ አልተቀበለም፡፡
\s5
\v 29
ያን ጊዜ የእግዚአብሔር መንፈስ በዮፍታሔ ላይ መጣ፣ እርሱም በገለዓድና በምናሴ አለፈ፣ በገለዓድ ባለው ምጽጳም አለፈ፣ ከዚያም በገለዓድ ካለው ምጽጳ ወደ አሞን ሰዎች አለፈ፡፡
\v 30 ዮፍታሔም ለእግዚብሔር እንዲህ ሲል ስእለት ተሳለ፡- “በአሞንን ሰዎች ላይ ድልን ብትሰጠኝ፣
\v 31 ከአሞን ሰዎች በሰላም በተመለስሁ ጊዜ እኔን ሊያገኘኝ ከቤቴ በር የሚወጣው ማንኛውም ለእግዚአብሔር ይሆናል፣ እርሱንም ለሚቃጠል መሥዋዕት አቀርበዋለሁ፡፡
\s5
\v 32
ስለዚህ ዮፍታሔ እነርሱን ለመውጋት ወደ አሞን ሰዎች አለፈ፣ እግዚአብሔርም በእነርሱ ላይ ድል ሰጠው፡፡
\v 33 እርሱም ከአሮዔርም እስከ ሚኒት፣ እንደዚሁም እስከ አቤልክራሚም ድረስ ያሉ ሀያ ከተሞችን ወጋቸው፣ ታላቅ እልቂትም አደረሰባቸው፡፡ ስለዚህ የአሞን ሰዎች በእስራኤል ሰዎች ቁጥጥር ስር ሆኑ፡፡
\s5
\v 34
ዮፍታሄ ምጽጳ ወዳለው ቤቱ መጣ፣ በዚያም የእርሱ ልጅ ከበሮ ይዛ እያሸበሸበች ልታገኘው ወጣች፡፡ እርስዋም ብቸኛ ልጁ ነበረች፣ ከእርስዋ ሌላ ወንድ ልጅም ይሁን ሴት ልጅ አልነበረውም፡፡
\v 35 እርስዋንም ባየ ጊዜ፣ ልብሱን ቀደደ እንዲህም አለ፡- “ወይኔ! ልጄ ሆይ! በኀዘን አደቀቅሽኝ፣ በእኔ ላይ ጭንቅ ያመጣብኝ ሰው ሆንሽብኝ! ለእግዚአብሔር ስእለት ተስያለሁና፣ ቃሌን ማጠፍ በፍጹም አልችልም፡፡”
\s5
\v 36
እርስዋም እንዲህ አለችው፡- “አባቴ ሆይ፣ ለእግዚአብሔር ስእለት ተስለሃል፣ ቃል የገባኸውን ሁሉ በእኔ ላይ አድርግብኝ፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር በጠላቶችህ በአሞናውያን ላይ ተበቅሎልሃልና፡፡”
\v 37 አርስዋም ለአባትዋ እንዲህ አለች፡- “ይህ ቃል ለእኔ ይደረግልኝ፡፡ ይህንን አካባቢ እንድለቅና ወደ ታች ወደ ኮረብታዎቹ እንድወርድ፣ ከጓደኞቼም ጋር ስለ ድንግልናየ እንዳለቅስ ለሁለት ወራቶች ያህል ብቻየን እንድሆን ፍቀድልኝ፡፡
\s5
\v 38
እርሱም፣ “ሂጂ” አለ፡፡ ለሁለት ወራትም አሰናበታት፡፡ እርስዋም ትታው ሄደች፣ ከባልንጀሮችዋም ጋር ስለ ድንግልናዋ በኮረብታዎቹ ላይ አለቀሱ፡፡
\v 39 በሁለት ወር መጨረሻ ላይ ወደ አባትዋ ተመለሰች፣ እርሱም ቃል እንደገባው እንደ ስእለቱ አደረገባት፡፡ እርስዋም ከወንድ ጋር ተኝታ አታውቅም፣ ይህም በእስራኤል ዘንድ ልማድ ሆነ፣
\v 40 የእስራኤል ሴቶች ልጆች በየዓመቱ፣ ለአራት ቀናት፣ የገለዓዳዊውን የዮፍታሔን ሴት ልጅ ታሪክ እየተናገሩ ያስቡአታል፡፡
\s5
\c 12
\p
\v 1 ወደ ኤፍሬም ሰዎችም ጥሪ ደረሰ፤ በጻፎን በኩል ተሻግረው ዮፍታሔን፣ “ከአሞን ሕዝብ ጋር ለመዋጋት ስታልፍ ከአንተ ጋር እንድንሄድ ያልጠራኸን ለምድን ነው? ቤትህን በአንተ ላይ እናቃጥለዋለን” አሉት፡፡
\v 2 ዮፍታሔም እንዲህ አላቸው፣ “እኔና ሕዝቤ ከአሞን ሕዝብ ጋር በታላቅ ጦርነት ውስጥ ነበርን፡፡ በጠራኋችሁም ጊዜ ከእነርሱ አላዳናችሁኝም፡፡
\s5
\v 3
እናንተም እንዳላዳናችሁኝ ባየሁ ጊዜ፣ ሕይወቴን በራሴ ብርታት አስቀምጬ በአሞን ሕዝብ ላይ ለመዋጋት አለፍሁ፣ እግዚአብሔርም በእነርሱ ላይ ድል ሰጠኝ፡፡ ዛሬ እኔን ለመውጋት ለምን መጣችሁ?
\v 4 ዮፍታሔም የገለዓድን ሰዎች ሁሉ ሰበሰበና ከኤፍሬምም ጋር ተዋጋ፡፡ የገለዓድም ሰዎች የኤፍሬምን ሰዎች ወጓቸው ምክንቱም፣ “እናንተ ገለዓዳውያን በኤፍሬም ውስጥ ሸሽታችሁ የተጠጋችሁ፣ በኤፍሬምና በምናሴ ውስጥ ጥገኞች የሆናችሁ ናችሁ” ይሏቸው ነበርና፡፡
\s5
\v 5
ገለዓዳውያንም ወደ ኤፍሬም የሚወስደውን የዮርዳኖስን መሻገሪያ ያዙባቸው፡፡ አምልጦ የሚሸሽ የኤፍሬም ሰው፣ “ወንዙን ተሻግሬ ልለፍ” ባለ ጊዜ፣ የገለዓድ ሰዎች ደግሞ እንዲህ ይሉታል፣ “አንተ ኤፍሬማዊ ነህን?” እርሱም፣ “አይደለሁም” ቢል፣
\v 6 እነርሱም “ሺቦሌት በል” ይሉታል፡፡ እርሱም “ሲቦሌት” ብሎ ከተናገረ (ምክንያቱም እርሱ ቃሉን አጥርቶ መናገር አይችልምና) ፣ ገለዓዳውያን እርሱን ይዘው በዮርዳኖስ መሻገሪያ ላይ ይገድሉታል፡፡ በዚያም ጊዜ አርባ ሁለት ሺህ ኤፍሬማውያን ተገደሉ፡፡
\s5
\v 7
ዮፍታሔም በእስራኤል ላይ ለስድስት ዓመት እንደ ፈራጅ አገለገለ፡፡ ከዚያም ገለዓዳዊውም ዮፍታሔ ሞተ፣ ከገለዓድ ከተሞችም በአንዱ ተቀበረ።
\s5
\v 8
ከእርሱም በኋላ የቤተ ልሔሙ ኢብጻን በእስራኤል ላይ እንደ ፈራጅ አገለገለ፡፡
\v 9 እርሱም ሠላሳ ወንዶች ልጆች ነበሩት፡፡ ሠላሳ ሴቶች ልጆችንም ወደ ውጭ በትዳር ለሌሎች ሰጠ፣ ሠላሳ ሴቶች ልጆችን ደግሞ ከሌሎች ሰዎች በትዳር ለወንድ ልጆቹ አመጣ። በእስራኤልም ላይ ለሰባት ዓመት ፈረደ።
\s5
\v 10
ኢብጻንም ሞተ፣ በቤተ ልሔምም ተቀበረ፡፡
\v 11 ከእርሱም በኋላ ዛብሎናዊው ኤሎም በእስራኤል ላይ እንደ ፈራጅ አገለገለ፡፡ እርሱም በእስራኤል ላይ ለአሥር ዓመት ፈረደ፡፡
\v 12 ዛብሎናዊውም ኤሎም ሞተ፣ በዛብሎንም ምድር ባለችው በኤሎም ተቀበረ፡፡
\s5
\v 13
ከእርሱም በኋላ የጲርዓቶናዊው የሂሌል ልጅ ዓብዶን በእስራኤል ላይ እንደ ፈራጅ አገለገለ፡፡
\v 14 እርሱም አርባ ወንዶች ልጆችና ሠላሳ ወንዶች የልጅ ልጆች ነበሩት፡፡ በሰባ አህያዎች ላይ ይጋልቡ ነበር፣ እርሱም በእስራኤል ላይ ለስምንት ዓመት ፈረደ፡፡
\v 15 የጲርዓቶናዊውም የሂሌል ልጅ ዓብዶን ሞተ፣ በተራራማውም በአማሌቃውያን አገር በኮረብታማው በኤፍሬም አገር ውስጥ ባለችው በጲርዓቶን ውስጥ ተቀበረ፡፡
\s5
\c 13
\p
\v 1
የእስራኤልም ሕዝብ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ የሆነውን ስራ እንደ ገና ሠሩ፣ እርሱም ፍልስጥኤማውያን በእነርሱ ላይ ለአርባ ዓመት እንዲገዙ ፈቀደላቸው፡፡
\v 2 ከዳን ቤተሰብ የሆነ ስሙም ማኑሄ የሚባል አንድ የጾርዓ ሰው ነበረ፡፡ ሚስቱም መካን ስለነበረች ልጅ አልወለደችም፡፡
\s5
\v 3 የእግዚአብሔርም መልአክ ለሴቲቱ ተገልጦ እንዲህ አላት፣ “ተመልከቺ፣ አንቺ መካን ነበርሽ፣ ልጅም አልወለድሽም፣ ነገር ግን ትፀንሻለሽ፣ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፡፡
\v 4 አሁንም የወይን ጠጅ ወይም የሚያሰክር ጠንካራ መጠጥ እንዳትጠጪ ተጠንቀቂ፣ ሕጉ ርኩስ እንደሆነ የገለጸውን ማንኛውንም ምግብ አትብዪ፡፡
\v 5 ተመልከቺ፣ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፡፡ ልጁ ከአንቺ ማኅፀን ጀምሮ ለእግዚአብሔር የተለየ ናዝራዊ ስለሚሆን በራሱ ላይ ምላጭ አይድረስበት፡፡ እርሱም እስራኤልን ከፍልስጥኤማውያን ጉልበት ማዳን ይጀምራል፡፡
\s5
\v 6 የዚያን ጊዜ ሴቲቱ ወደ ባልዋ መጥታ እንዲህ ብላ ነገረችው፣ “አንድ የእግዚአብሔር ሰው ወደ እኔ መጣ፣ መልኩም እንደ እግዚአብሔር መልአክ የሚመስል ነበረ፣ በጣምም አስደነገጠኝ፡፡ ከወዴት እንደ መጣ አልጠየቅሁትም፣ እርሱም ስሙን አልነገረኝም፡፡
\v 7 እርሱም እንዲህ አለኝ፣ ‘ተመልከቺ! ትፀንሻለሽ፣ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፡፡ ስለዚህ ልጁ ከአንቺ ማኅፀን ጀምሮ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ ለእግዚአብሔር የተለየ ናዝራዊ ስለሚሆን የወይን ጠጅ ወይም የሚያሰክር ጠንካራ መጠጥ እንዳትጠጪ፣ ሕጉ ርኩስ እንደሆነ የገለጸውን ማንኛውንም ምግብ አትብዪ፡፡’”
\s5
\v 8
ከዚያም ማኑሄ ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ጸለየ፣ “ጌታ ሆይ፣ አሁን በቅርቡ ለሚወለደው ልጅ ምን ማድረግ እንዳለብን እንዲያስተምረን እባክህ የላክኸው የእግዚአብሔር ሰው እንደገና ወደ እኛ ይምጣ፡፡”
\v 9 እግዚአብሔርም የማኑሄን ጸሎት መለሰ፣ የእግዚአብሔርም መልአክ እንደ ገና ወደ ሴቲቱ በእርሻ ውስጥ ተቀምጣ ሳለች መጣ፡፡ ነገር ግን ባልዋ ማኑሄ ከእርስዋ ጋር አልነበረም፡፡
\s5
\v 10 ስለዚህ ሴቲቱም ፈጥና ሮጠችና ለባልዋ ነገረችው፣ “ተመልከት! በሌላኛው ቀን ወደ እኔ የመጣው ሰው እንደገና ተገለጠልኝ፡፡”
\v 11 ማኑሄም ተነሳና ሚስቱን ተከተላት፡፡ ወደ ሰውዮውም በመጣ ጊዜ እንዲህ አለው፣ “ከሚስቴ ጋር የተነጋገርህ ሰው አንተ ነህን?” ሰውየውም፣ “እኔ ነኝ” አለው፡፡
\s5
\v 12 ስለዚህ ማኑሄ እንዲህ አለ፣ “አሁንም ቃሎችህ እውነት ይሁኑ፡፡ ነገር ግን ልጁ የሚመራው በምንድን ነው፣ እኛስ ለእርሱ የምንሰራው ምንድን ነው?”
\v 13 የእግዚአብሔርም መልአክ ለማኑሄ እንዲህ አለው፣ “እርስዋ የነገርኋትን ነገር ሁሉ በጥንቃቄ ማድረግ አለባት፡፡
\v 14 ከወይን ከሚወጣው ማንኛውንም ነገር አትብላ፣ የወይን ጠጅ ወይም የሚያሰክር ሌላ ጠንካራ መጠጥ አትጠጣ፤ ሕጉ ርኩስ ነው ብሎ የገለጸውን ማንኛውንም ምግብ አትብላ፡፡ እኔ እንድታደርገው ያዘዝኋትን ማንኛውንም ነገር መታዘዝ አለባት፡፡
\s5
\v 15 ማኑሄም ለእግዚአብሔር መልአክ እንዲህ አለው፣ “ለአንተ የፍየል ጠቦት ለማዘጋጀት ጊዜ እናገኝ ዘንድ፣ እባክህ ለአጭር ጊዜ ቆይ፡፡”
\v 16 የእግዚአብሔርም መልአክ ለማኑሄ እንዲህ አለው፣ “ብቆይም እንኳ፣ መብልህን አልበላም፡፡ነገር ግን የሚቃጠል መሥዋዕት የምታዘጋጅ ከሆነ፣ ያንን ለእግዚአብሔር አቅርበው፡፡” ማኑሄ የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን አላወቀም ነበር፡፡
\s5
\v 17
ማኑሄም ለእግዚአብሔር መልአክ እንዲህ አለው፣ “የተናገርሃቸው ቃሎች እውነት በሆኑ ጊዜ እናከብርህ ዘንድ ስምህ ማን ነው?”
\v 18 የእግዚአብሔርም መልአክ እንዲህ አለው፣ “ስሜን ለምን ትጠይቃለህ? ስሜ ድንቅ ነው!”
\s5
\v 19
ስለዚህ ማኑሄም የፍየሉን ጠቦት ከእህል ቍርባን ጋር ወሰደና በድንጋይ ላይ ለእግዚአብሔር አቀረበው፡፡ ማኑሄና ሚስቱ እያዩ እርሱ አስደናቂ ነገር አደረገ፡፡
\v 20 ነበልባሉም ከመሠዊያው ላይ ወደ ሰማይ በወጣ ጊዜ፣ የእግዚአብሔር መልአክ በመሠዊያው ነበልባል ውስጥ ወደ ላይ ዐረገ፡፡ ማኑሄና ሚስቱም ይህን ተመለከቱና በግምባራቸው ምድር ላይ ተደፉ፡፡
\s5
\v 21 የእግዚአብሔርም መልአክ ላማኑሄ ወይም ለሚስቱ እንደገና አልተገለጠም፡፡ ያን ጊዜም ማኑሄ የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን አወቀ፡፡
\v 22 ማኑሄም ለሚስቱ እንዲህ አላት፣ “እግዚአብሔርን ስላየን በእርግጠኝነት እንሞታለን፡፡”
\s5
\v 23 ነገር ግን ሚስቱ እንዲህ አለችው፣ “እግዚአብሔር ሊገድለን ቢፈልግ ኖሮ፣ ለእርሱ ያቀረብነውን የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን ባልተቀበለን ነበር፡፡ ይህንም ነገር ሁሉ ባላሳየን ነበር፣ በዚህ ጊዜ እንዲህ ያሉ ነገሮችንም እንድንሰማ ባላደረገን ነበር፡፡”
\s5
\v 24 ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ሴቲቱ ወንድ ልጅ ወለደች፣ ስሙንም ሳምሶን ብላ ጠራችው፡፡ ልጁም አደገ እግዚአብሔርም ባረከው፡፡
\v 25 የእግዚአብሔርም መንፈስ እርሱን በጾርዓና በኤሽታኦል መካከል ባለው በዳን ሰፈር ውስጥ ያነቃቃው ጀመር፡፡
\s5
\c 14
\p
\v 1
ሳምሶንም ወደ ተምና ወረደ፣ በዚያም ከፍልስጥኤማውያን ሴቶች ልጆች አንዲት ሴት አየ፡፡
\v 2 ከዚያ በተመለሰ ጊዜ፣ ለአባቱና ለእናቱ እንዲህ ሲል ነገራቸው፣ “በተምና ከፍልስጥኤማውያን ሴቶች ልጆች መካከል አንዲት ሴት አየሁ፡፡ ሚስቴ እንድትሆነኝ አሁን እርስዋን አምጡልኝና አጋቡኝ፡፡
\s5
\v 3
ነገር ግን እንዲህ አሉት፣ “ከዘመዶችህ ሴቶች ልጆች ወይም ከሕዝባችን ሁሉ መካከል ሴት የለምን? ካልተገረዙት ከፍልስጥኤማውያን ሚስት ለመውሰድ ትሄሄዳለህን?” ሳምሶንም ለአባቱ እንዲህ አለው፣ “እርስዋን አምጣልኝ፣ እርስዋን ባየኋት ጊዜ ደስ አሰኝታኛለችና፡፡”
\v 4 ነገር ግን አባቱና እናቱ ይህ ነገር የመጣው ከእግዚአብሔር እንደሆነ አላወቁም፣ እርሱ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ግጭት ለመፍጠር ይፈልግ ነበርና፡፡ በዚያን ጊዜ ፍልስጥኤማውያን እስራኤልን ይገዙ ነበርና፡፡
\s5
\v 5 ከዚያም ሳምሶን ከአባቱና ከእናቱ ጋር ወደ ተምና ወረዱ፣ እነርሱም በተምና ወዳለው ወደ ወይኑ አትክልት ስፍራ መጡ፡፡ ከዚያም ከአንበሳ ደቦሎች መካከል አንዱ ተነስቶ መጣና በእርሱ ላይ አገሳበት፡፡
\v 6 የእግዚአብሔር መንፈስ በድንገት በእርሱ ላይ ወረደ፣ ትንሽ የፍየል ጠቦት እንደሚቆራርጥ እንዲሁ አንበሳውን በቀላሉ ቈራረጠው፣ በእጁም ምንም ነገር አልያዘም ነበር፡፡ ነገር ግን ያደረገውን ነገር ለአባቱ ወይም ለእናቱ አልነገራቸውም፡፡
\s5
\v 7
እርሱም ሄደና ከሴቲቱ ጋር ተነጋገረ፣ እርስዋንም ባያት ጊዜ ሳምሶንን ደስ አሰኘችው፡፡
\v 8 ከጥቂትም ቀን በኋላ ሊያገባት ተመለሰ፣ የአንበሳውንም በድን ያይ ዘንድ ከመንገድ ዘወር አለ፡፡ በአንበሳ በድን ትራፊ ውስጥ የንብ መንጋ ሰፍሮበት ነበር፣ ማርም ነበረበት፡፡
\v 9 ማሩንም በእጁ ወስዶ መንገድ ለመንገድ እየበላ ሄደ፡፡ ወደ አባቱና ወደ እናቱ በመጣ ጊዜ፣ ለእነርሱም ሰጣቸውና እነርሱም በሉ፡፡ ነገር ግን ማሩን የወሰደው ከአንበሳ በድን ትራፊ ውስጥ እንደ ሆነ አልነገራቸውም፡፡
\s5
\v 10 የሳምሶን አባትም ሴቲቱ ወደ ነበረችበት ወረደ፣ ሳምሶንም በዚያ ግብዣ አደረገ፣ ይህን ማድረግ የወጣት ወንዶች ወግ ነበርና፡፡
\v 11 የእርስዋ ዘመዶች ባዩት ጊዜ፣ ከእርሱ ጋር ይሆኑ ዘንድ ሌሎች ሠላሳ ጓደኞች አመጡለት፡፡
\s5
\v 12 ሳምሶንም ለእነርሱ እንዲህ አላቸው፣ “አሁን እንቆቅልሽ ልንገራችሁ፡፡ ከእናንተ ውስጥ አንዱ ሰው እንቆቅልሹን ማግኘት ቢችልና በሰባቱ የግብዣ ቀኖች ውስጥ መልሱን ቢነግረኝ፣ ሠላሳ የቀጭን በፍታ ቀሚስና ሠላሳ የክት ልብስ እሰጠዋለሁ፡፡
\v 13 ነገር ግን እናንተ መልሱን ልትነግሩኝ ካልቻላችሁ፣ ሠላሳ የቀጭን በፍታ ቀሚስና ሠላሳ የክት ልብስ ትሰጡኛላችሁ፡፡” እነርሱም እንዲህ አሉት፣ “እንሰማው ዘንድ እንቆቅልሽህን ንገረን፡፡”
\s5
\v 14 እርሱም እንዲህ አላቸው፣ “ከበላተኛው ውስጥ መብል ወጣ፤ ከብርቱም ውስጥ ጣፋጭ ወጣ፡፡” ነገር ግን የእርሱ እንግዶች በሦስት ቀን ውስጥ መልሱን ሊያገኙት አልቻሉም፡፡
\s5
\v 15 በአራተኛውም ቀን ለሳምሶን ሚስት እንዲህ አሏት፣ “የእንቈቅልሹን መልስ እንዲነግረን ባልሽን አግባቢልን፣ አለዚያ ግን እንቺንና የአባትሽን ቤት በእሳት እናቃጥላለን፡፡ ወደዚህ የጠራችሁን ድሃ ልታደርጉን ነውን፡፡”
\s5
\v 16
የሳምሶን ሚስት በፊቱ ማልቀስ ጀመረች፤ እንዲህም አለችው፣ “ይህን ሁሉ ያደረግኸው እኔን ስለምትጠላኝ ነው! አንተ አትወደኝም፡፡ ከሕዝቤ ውስጥ ለአንዳንዶቹ እንቈቅልሽ ነግረሃቸዋል፣ ነገር ግን መልሱን ለእኔ አልነገርኸኝም፡፡” ሳምሶንም እንዲህ አላት፣ “ወደዚህ ተመልከቺ፣ ለአባቴና ለእናቴ ካልነገርኋቸው፣ ለአንቺ ልነግርሽ ይገባልን?”
\v 17 ግብዣቸው በሚቆይበት በሰባቱም ቀናት ውስጥ በፊቱ አለቀሰች፡፡ መልሱንም በሰባተኛው ቀን ነገራት ምክንቱም እጅግ በጣም አጥብቃ ስለነዘነዘችው ነው፡፡ መልሱንም ለሕዝቧ ዘመዶች ነገረቻቸው፡፡
\s5
\v 18 በሰባተኛው ቀን ፀሐይ ከመግባትዋ በፊት የከተማይቱ ሰዎች እንዲህ አሉት፣ “ከማር የበለጠ የሚጣፍጥ ምንድን ነው? ከአንበሳስ የበለጠ የሚበረታ ምንድን ነው?” ሳምሶንም እንዲህ አላቸው፣ “በጊደሬ ባታርሱ ኖሮ፣ ለእንቈቅልሼ መልስ ባላገኛችሁ ነበር፡፡”
\s5
\v 19 በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔር መንፈስ በድንገት በሳምሶን ላይ በኃይል ወረደ፡፡ ሳምሶንም ወደ አስቀሎና ወረደና ከሕዝቡ መካከል ሠላሳ ሰዎችን ገደለ፡፡ እርሱም የለበሱትን ሁሉ ከገፈፈ በኋላ ልብሳቸውን በሙሉ ወስዶ እንቈቅልሹን ለመለሱለት ሰዎች ሰጣቸው፡፡ እርሱም በጣም ተናደደና ወደ አባቱ ቤት ወጣ፡፡
\v 20 የሳምሶን ሚስት ግን በጣም ቅርብ ለሆነው ጓደኛው ተሰጠች፡፡
\s5
\c 15
\p
\v 1 ከጥቂት ቀናትም በኋላ በስንዴ መከር ጊዜ፣ ሳምሶን የፍየል ጠቦት ይዞ ሚስቱን ሊጠይቅ ሄደ፡፡ ለራሱም እንዲህ አለ፣ “ወደ ሚስቴ ወደ ጫጉላው ቤት ልግባ፡፡” ነገር ግን አባትዋ ወደ ውስጥ እንዳይገባ ከለከለው፡፡
\v 2 አባትዋም እንዲህ አለ፣ “እኔ በእርግጠኝነት የጠላሃት መሰለኝ፣ ስለዚህም ለጓደኛህ ሰጠኋት፡፡የእርስዋ ታናሽ እኅት ከርስዋ የበለጠች ቆንጆ ናት፣ አይደለችም እንዴ? በእርስዋ ፋንታ ታናሽዋን ውሰዳት፡፡”
\s5
\v 3
ሳምሶንም ለእነርሱ እንዲህ አላቸው፣ “ከእንግዲህ ወዲህ በፍልስጥኤማውያን ላይ ጉዳት ባደረስሁባቸው ጊዜ እኔ ንጹሕ ነኝ፡፡”
\v 4 ሳምሶንም ሄደና ሦስት መቶ ቀበሮዎች ያዘ፣ ሁለት ሁለቱንም ቀበሮዎች በአንድ ላይ በጅራታቸው አሰራቸው፡፡ ከዚያም ችቦዎችን ወስዶ በእያንዳንዱ ጥንድ በሁለቱም ጅራቶች መካከል አሰራቸው፡፡
\s5
\v 5
ችቦውንም በእሳት ባቀጣጠለው ጊዜ፣ ቀበሮዎቹን በቆመው በፍልስጥኤማውያን እህል መካከል እንዲሄዱ አደረጋቸው፣ የእህሉን ነዶና በእርሻ ውስጥ የቆመውንም እህል፣ ከወይኑ አትክልት ስፍራና ከወይራውም ተክል ጋር አቃጠሉት፡፡
\v 6 ፍልስጥኤማውያንም እንዲህ በማለት ጠየቁ፣ “ይህን ያደረገው ማን ነው?” እነርሱም “ይህን ያደረገው የተምናዊው አማች ሳምሶን ነው፣ ምክንያቱም ተምናዊው የሳምሶንን ሚስት ወስዶ ለጓደኛው ሰጥቶአታልና” አሉ፡፡ ፍልስጥኤማያንም ሄደው እርስዋንና አባትዋን በእሳት አቃጠሉ፡፡
\s5
\v 7 ሳምሶንም “እናንተ ይህንን ካደረጋችሁ፣ እኔ እበቀላችኋለሁ፣ እኔ የማርፈው ይህን ካደረግሁ በኋላ ነው” አላቸው፡፡
\v 8 እርሱም ዳሌአቸውንና ጭናቸውን ቆራረጣቸውና በታላቅ አገዳደል ገደላቸው፡፡ ከዚያም ወርዶ በኤጣም ዓለት ባለው ዋሻ ውስጥ ተቀመጠ፡፡
\s5
\v 9 የዚያን ጊዜ ፍልስጥኤማውያን ወጡና በይሁዳ ጦርነት ለማካሄድ ተዘጋጁ፣ ሰራዊታቸውንም በሌሒ ውስጥ አሰፈሩ፡፡
\v 10 የይሁዳም ሰዎች እንዲህ አሉ፣ “እኛን ለመውጋት የመጣችሁት ለምንድን ነው?” እነርሱም እንዲህ አሉ፣ “የምንወጋችሁ ሳምሶንን ለመያዝ ነው፣ እርሱ በእኛ ላይ እንዳደረገው እኛም በእርሱ ላይ ልናደርግበት ነው፡፡”
\s5
\v 11 ሦስት ሺህ የይሁዳ ሰዎችም በኤጣም ዓለት ወዳለው ዋሻ ወረዱና፣ ለሳምሶን እንዲህ አሉት፣ “ፍልስጥኤማውያን በእኛ ላይ ገዢዎች እንደሆኑ አታውቅምን? ይህ በእኛ ላይ ያደረግኸው ነገር ምንድን ነው?” ሳምሶንም ለእነርሱ እንዲህ አላቸው፣ “እነርሱ በእኔ ላይ አደረጉብኝ፣ እኔም በእነርሱ ላይ አደረግሁባቸው፡፡”
\s5
\v 12
እነርሱም ለሳምሶን እንዲህ አሉት፣ “አንተን አስረን ለፍልስጥኤማውያን እጅ አሳልፈን ልንሰጥህ መጥተናል፡፡” ሳምሶንም እንዲህ አላቸው፣ “እናንተ ራሳችሁ እንደማትገድሉኝ ማሉልኝ፡፡”
\v 13 እነርሱም እንዲህ አሉት፣ “አንገድልህም፣ በገመድ አስረን ብቻ ለእነርሱ አሳልፈን እንሰጥሃለን፡፡ እንደማንገድልህ ቃል እንገባልሃለን፡፡” ከዚያም በሁለት አዲስ ገመዶች አሰሩትና ከዓለቱ ውስጥ አወጡት፡፡
\s5
\v 14 ወደ ሌሒ በመጣ ጊዜ፣ ፍልስጥኤማውያን እየጮሁ መጡ፣ አገኙትም፡፡ የዚያን ጊዜ የእግዚአብሔር መንፈስ በእርሱ ላይ በኃይል ወረደበት፡፡ ክንዶቹ የታሰሩበት ገመዶችም በእሳት እንደ ተቃጠለ የተልባ እግር ፈትል ከእጆቹ ላይ ወደቁ፡፡
\s5
\v 15 ሳምሶንም አዲስ የአህያ መንጋጋ አገኘ፣ እጁንም ዘርግቶ አነሳውና በእርሱ አንድ ሺህ ሰዎች ገደለ፡፡
\v 16 ሳምሶንም እንዲህ አለ፣ “በአህያ መንጋጋ ክምር በክምር ላይ አድርጌአቸዋለሁ፣ በአህያ መንጋጋ አንድ ሺህ ሰዎች ገድያለሁ፡፡”
\s5
\v 17 ሳምሶንም መናገሩን በፈጸመ ጊዜ፣ የአህያ መንጋጋውን ከእጁ ጣለው፣ ያም ስፍራ ራማትሌሒ ተብሎ ተጠራ፡፡
\v 18 ሳምሶን በጣም ተጠምቶ ነበርና ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ጮኸ፣ “አንተ ይህን ታላቅ ድል ለአገልጋይህ ሰጥተሃል፣ ነገር ግን አሁን በጥም እሞታለሁ፣ ባልተገረዙትም ሰዎች እጅ እወድቃለሁ፡፡”
\s5
\v 19 እግዚአብሔርም በሌሒ ያለውን ክፍት ስፍራ ሰንጥቆ ከፈተው፣ ከእርሱም ውኃ ወጣ፡፡እርሱም በጠጣ ጊዜ፣ ብርታቱ ተመለሰና ተጠናከረ፡፡ ስለዚህ የዚያ ቦታ ስም ዓይንሀቆሬ ተብሎ ተጠራ፣ እስከ ዛሬ ድረስ በሌሒ ይገኛል፡፡
\v 20 ሳምሶን በፍልስጥኤማውያን ዘመን በእስራኤል ላይ ለሀያ ዓመት ፈረደ፡፡
\s5
\c 16
\p
\v 1
ሳምሶን ወደ ጋዛ ሄደና በዚያ ዝሙት አዳሪ ሴት አየ፣ ከእርስዋም ጋር ወደ አልጋ ሄደ፡፡
\v 2 የጋዛ ሰዎችም “ሳምሶን ወደዚህ መጥቶአል” የሚል ወሬ ሰሙ፡፡ የጋዛ ሰዎች ስፍራውን ከበቡትና ሌሊቱን ሁሉ ተደብቀው በከተማይቱ በር ጠበቁት፡፡ ሌሊቱን ሁሉ ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ አላደረጉም፡፡ እንዲህ ብለዋልና፣ “እስኪነጋ ድረስ እንጠብቀው፣ ከዚያም እንገድለዋለን፡፡”
\s5
\v 3 ሳምሶንም እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ በአልጋ ላይ ተኛ፡፡ እኩለ ሌሊትም በሆነ ጊዜ ተነሳና የከተማይቱን በር መዝጊያና ሁለቱን መቃኖች ያዘ፡፡ እነርሱንም ከመወርወሪያው ጋር ከመሬት ነቀላቸው፣ በትከሻውም ላይ አደረጋቸው፣ በኬብሮንም ፊት ለፊት ወዳለው ኮረብታ ራስ ላይ ተሸክሞት ወጣ፡፡
\s5
\v 4
ከዚህ በኋላ ሳምሶን በሶሬቅ ሸለቆ የምትኖር አንዲት ሴት ወደደ፡፡ ስምዋም ደሊላ ይባል ነበር፡፡
\v 5 የፍልስጥኤማውያንም አለቆች ወደ እርስዋ መጡና እንዲህ አሏት፣ “እርሱን ለማዋረድ እናስረው ዘንድ በእርሱ ያለው ታላቅ ኃይል የት እንደሆነና በምን መንገድ እርሱን ማሸነፍ እንደምንችል እንዲያሳይሽ ሳምሶንን አባብዪው፡፡ ይህንን አድርጊልን፣ እኛም እያንዳንዳችን 1, 100 ብር እንሰጥሻለን፡፡
\s5
\v 6
ደሊላም ለሳምሶን እንዲህ አለችው፣ “እባክህ፣ እንዲህ በጣም ብርቱ የሆንከው እንዴት እንደሆነ ንገረኝ፣ በቁጥጥር ስር መዋል እንድትችል ሰው ሊያስርህ የሚችለው እንዴት ነው?
\v 7 ሳምሶንም እንዲህ አላት፣ “ባልደረቁ ሰባት እርጥብ ጠፍሮች ቢያስሩኝ፣ እደክማለሁ፣ እንደ ማንኛውም ሰውም እሆናለሁ፡፡”
\s5
\v 8 የፍልስጥኤማውያን አለቆችም ያልደረቁ ሰባት እርጥብ ጠፍሮች አመጡላት፣ እርስዋም ሳምሶንን በእነርሱ አሰረችው፡፡
\v 9 በዚህን ጊዜ በጓዳዋ ውስጥ ሰዎች በምስጢር ተደብቀው ይጠብቁ ነበር፡፡ እርስዋም፣ “ሳምሶን፣ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ” አለችው፡፡ ነገር ግን የተልባ እግር ፈትል እሳት በነካው ጊዜ እንደሚበጣጠስ ጠፍሩን በጣጠሰው፡፡ እነርሱም የብርታቱ ምስጢር ምን እንደሆነ አላወቁም፡፡
\s5
\v 10
ከዚያም ደሊላ ሳምሶንን እንዲህ አለችው፣ “አንተ እኔን እንዴት እንዳታለልኸኝ ግልጽ ሆኗል፣ ሐሰትንም ነገርኸኝ፡፡ እባክህ፣ እንዴት እንደምትታሰር ንገረኝ፡፡”
\v 11 እርሱም እንዲህ አላት፣ “ለሥራ ጥቅም ላይ ፈጽሞ ባልዋሉ በአዲስ ገመዶች ቢያስሩኝ፣ እደክማለሁ፣ እንደ ማንኛውም ሰው እሆናለሁ፡፡”
\v 12 ስለዚህ ደሊላ አዲስ ገመዶች ወሰደችና በእነርሱ አሰረችው፣ እንዲህም አለችው፣ “ሳምሶን፣ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ፡፡” ተደብቀው ሲጠብቁ የነበሩት ሰዎች በጓዳዋ ነበሩ፡፡ ነገር ግን ሳምሶን ገመዶቹን እንደ ፈትል ክር ከክንዶቹ በጣጠሰው፡፡
\s5
\v 13
ደሊላም ሳምሶንን እንዲህ አለችው፣ “እስከ አሁን ድረስ አታልለኸኛልና የነገርኸኝም ውሸት ነው፡፡ አንተን ማሰር የሚቻለው እንዴት እንደሆነ ንገረኝ፡፡” ሳምሶንም እንዲህ አላት፣ “የራሴን ጠጕር ሰባቱን ጕንጕን ከድር ጋር ጎንጉነሽ በችካል ብትቸክዪው፣ እንደ ሌላ ሰው እሆናለሁ፡፡”
\v 14 እርሱም በተኛ ጊዜ፣ ደሊላ የራሱን ጠጕር ሰባቱን ጕንጕን ከድሩ ጋር ጐነጐነችው፣ በችካልም ቸከለችውና፣ እንዲህ አለችው፣ “ሳምሶን፣ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ!” እርሱም ከእንቅልፉ ነቃና ችካሉን ከነቆንዳላውና ከነድሩ ነቀለው፡፡
\s5
\v 15
እርስዋም እንዲህ አለችው፣ “ምስጢርህን ለእኔ ሳትነግረኝ ‘እወድሻለሁ’ ልትለኝ እንዴት ትችላለህ? ሦስት ጊዜ ቀለድህብኝ፣ እንዲህ ዓይነቱን ታላቅ ኃይል እንዴት ሊኖርህ እንደቻለ አልነገርኸኝም፡፡”
\v 16 ሞት እስኪመኝ ድረስ ዕለት ዕለት በቃሎችዋ እጅግ በጣም ጨቀጨቀችው፣ ከመጠን በላይም ጫና አደረገችበት፡፡
\s5
\v 17
ስለዚህ ሳምሶን ሁሉንም ነገር ነገራትና እንዲህ አላት፣ “ከእናቴ ማኅፀን ጀምሬ ለእግዚአብሔር ናዝራዊ ሆኜ ስለተለየሁ በራሴ ላይ ምላጭ ደርሶና ጸጉሬን ተላጭቼ አላውቅም፡፡ የራሴን ጸጕር ብላጭ ኃይሌ ከእኔ ይሄዳል፣ እደክማለሁም እንደ ማንኛውም ሰው እሆናለሁ፡፡”
\s5
\v 18
ደሊላም ስለ ሁሉ ነገር እውነቱን እንደነገራት ባየች ጊዜ፣ ሰዎች ላከችና የፍልስጥኤማውያንን አለቆች ጠራች፣ እንዲህም አለቻቸው፣ “ሁሉንም ነገር ነግሮኛልና እንደገና ኑ፡፡” የዚያን ጊዜ የፍልስጥኤማውያን አለቆች ብሩን በእጃቸው ይዘው ወደ እርስዋ ሄዱ፡፡
\v 19 እርስዋም በጭኗ ላይ እንዲተኛ አደረገችው፡፡ ሰባቱን የራሱን ጕንጕን እንዲላጨው አንድ ሰው ጠራች፣ ኃይሉ ስለተለየው እርስዋ በቁጥጥሯ ስር ልታደርገው ጀመረች፡፡
\s5
\v 20
እርስዋም፣ “ሳምሶን፣ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ!” አለችው፡፡ እርሱም ከእንቅልፉ ነቅቶ እንዲህ አለ፣ “እንደ ሌላው ጊዜ እወጣለሁ፣ ራሴንም ነጻ አወጣለሁ፡፡” ነገር ግን እግዚአብሔር እንደ ተወው አላወቀም፡፡
\v 21 ፍልስጥኤማውያንም ያዙትና ዓይኖቹን አወጡት፡፡ ወደ ጋዛም ወሰዱትና በናስ ሰንሰለት አሰሩት፡፡ በእስር ቤትም ውስጥ ሆኖ እህል ይፈጭ ነበር፡፡
\v 22 ነገር ግን ከተላጨ በኋላ የራሱ ጠጕር እንደገና ያድግ ጀመር፡፡
\s5
\v 23
የፍልስጥኤማውያንም አለቆች ለአምላካቸው ለዳጎን ታላቅ መሥዋዕት ያቀርቡ ዘንድ፣ ደስም ይላቸው ዘንድ በአንድ ላይ ተሰበሰቡ፡፡ እነርሱ “አምላካችን ጠላታችንን ሳምሶንን አሸንፏል፣ በእጃችን አሳልፎ ሰጥቶናል” ብለዋልና፡፡
\v 24 ሕዝቡም እርሱን ባዩት ጊዜ አምላካቸውን አመሰገኑ፣ እንዲህ ብለዋልና፣ “አገራችንን ያጠፋውን፣ ከእኛም ብዙ ሰው የገደለውን ጠላታችንን አምላካችን አሸነፈው፣ በእጃችንም አሳልፎ ሰጠው፡፡”
\s5
\v 25
እጅግ ደስ ባላቸው ጊዜ፣ እንዲህ አሉ፣ “እንዲያስቀን ሳምሶንን ጥሩት፡፡” ሳምሶንን ከእስር ቤት ጠሩትና እንዲስቁ አደረጋቸው፡፡ በምሰሶና በምሰሶ መካከል እንዲቆም አደረጉት፡፡
\v 26 ሳምሶንም እጁን የያዘውን ልጅ፣ “እደገፍባቸው ዘንድ ሕንጻውን የደገፉትን ምሰሶዎች እንድነካቸው አስጠጋኝ” አለው፡፡
\s5
\v 27
በዚያን ጊዜ ቤቱ በወንዶችና በሴቶች ተሞልቶ ነበር፡፡ የፍልስጥኤም አለቆች ሁሉ በዚያ ነበሩ፡፡ ሳምሶን እነርሱን ሲያዝናናቸው ይመለከቱ የነበሩ ሦስት ሺህ የሚያህሉ ወንዶችና ሴቶች በጣራው ላይ ነበሩ፡፡
\s5
\v 28
ሳምሶንም ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ጮኸ፣ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፣ እንደገና አስበኝ! አምላኬ ሆይ፣ ሁለት ዓይኖቼን ስላወጡ ፍልስጥኤማውያንን አሁን በአንድ ምት እንድበቀል፣ እባክህ፣ ይህን አንድ ጊዜ ብቻ አበርታኝ፡፡”
\v 29 ሳምሶንም ሕንጻው ተደግፎባቸው የነበሩትን ሁለቱን መካከለኞች ምሰሶዎች ጠምጥሞ ያዘ፣ አንዱን ምሰሶ በቀኝ እጁ ሌላውን ደግሞ በግራ እጁ ይዞ በእነርሱ ላይ ተደገፈ፡፡
\s5
\v 30
ሳምሶንም እንዲህ አለ፣ “ከፍልስጥኤማውያን ጋር ልሙት!” በሙሉ ኃይሉ ገፋው፣ ሕንጻውም በውስጡ በነበሩት አለቆችና በሕዝቡም ሁሉ ላይ ወደቀ፡፡ ስለዚህ እርሱ በሞተ ጊዜ የገደላቸው ሰዎች በሕይወት ሳለ ከገደላቸው ይልቅ የበለጡ ነበሩ፡፡
\v 31 የዚያን ጊዜ ወንድሞቹና የአባቱ ቤተ ሰቦች በሙሉ ወረዱ፣ እርሱንም ይዘው ወሰዱት፣ መልሰው አመጡትና በጾርዓና በኤሽታኦል መካከል ባለው በአባቱ በማኑሄ መቃብር ውስጥ ቀበሩት፡፡ ሳምሶን በእስራኤል ላይ ለሀያ ዓመት ፈረደ፡፡
\s5
\c 17
\p
\v 1 በኮረብታማውም በኤፍሬም አገር አንድ ሰው ነበር፣ ስሙም ሚካ ይባላል፡፡
\v 2 ለእናቱም እንዲህ አላት፣ “ከአንቺ ዘንድ ተወስዶ የነበረው 1, 100 ብር፣ የእርግማን ንግግር የተናገርሽበትና እኔም የሰማሁት እነሆ እዚህ አለ! ብሩ በእኔ ዘንድ አለ፡፡ እኔ ሰርቄዋለሁ!” እናቱም እንዲህ አለች፣ “ልጄ ሆይ፣ እግዚአብሔር ይባርክህ!”
\s5
\v 3 እርሱም 1, 100 ብር ለእናቱ መለሰላት፣ እናቱም እንዲህ አለችው፣ “ስለ ልጄ የተቀረጸ የእንጨት ምስልና ቀልጦ የተሠራ ምስል ለማድረግ ይህን ብር ለእግዚአብሔር ለይቼዋለሁ፡፡ ስለዚህ አሁን፣ ለአንተ መልሼዋለሁ፡፡”
\v 4 ለእናቱም ገንዘቡን በመለሰላት ጊዜ፣ እናቱ ሁለቱን መቶ ብር ወሰደችና የተቀረጸ የእንጨት ምስልና ቀልጦ የተሠራ ምስል አድርጎ ለሰራው ለብረት ሰራተኛ ሰጠችው፡፡ ያም በሚካ ቤት ተቀመጠ፡፡
\s5
\v 5
ሚካ የተባለውም ሰው የጣዖታት አምልኮ ቤት ነበረውና አንድ ኤፉድና ተራፊም ሰራ፣ ከልጆቹም አንዱ ካህን ሆኖ እንዲያገለግለው አደረገ፡፡
\v 6 በዚያን ዘመን በእስራኤል ዘንድ ንጉሥ አልነበረም፣ ሰውም ሁሉ በዓይኖቹ ፊት ትክክል መስሎ የታየውን ያደርግ ነበር፡፡
\s5
\v 7 አሁን በቤተ ልሔም ይሁዳ ከይሁዳ ወገን የሆነ አንድ ሌዋዊ ወጣት ሰው ነበረ፡፡ እርሱም ተግባሩን ለመፈጸም በዚያም ይቀመጥ ነበር፡፡
\v 8 ይህ ሰው የሚቀመጥበትን ስፍራ ለመፈለግ ቤተ ልሔም ይሁዳን ለቅቆ ሄደ፡፡ ሲጓዝም ወደ ኮረብታማው የኤፍሬም አገር ወደ ሚካ ቤት መጣ፡፡
\v 9 ሚካም ለእርሱ እንዲህ አለው፣ “ከወዴት መጣህ?” እርሱም እንዲህ አለው፣ “እኔ ከቤተ ልሔም ይሁዳ የመጣሁ ሌዋዊ ነኝ፣ የምኖርበትን ስፍራ ለማግኘት እየተጓዝሁ ነው፡፡”
\s5
\v 10 ሚካም እንዲህ አለው፣ “ከእኔ ጋር ተቀመጥ፣ ለእኔም አማካሪና ካህን ሁነኝ፡፡ እኔም በየዓመቱ አሥር ብር፣ እንደዚሁም ልብሶችንና ምግብህን እሰጥሃለሁ፡፡” ስለዚህ ሌዋዊው ወደ ቤቱ ገባ፡፡
\v 11 ሌዋዊውም ከሰውዮው ጋር ለመቀመጥ ፈቃደኛ ሆነ፣ ወጣቱም ሰው ለሚካ ከልጆቹ እንደ አንዱ ሆነለት፡፡
\s5
\v 12
ሚካም ሌዋዊውን ለተቀደሰ ሃላፊነት ቀደሰው፣ ወጣቱም ሰው ካህኑ ሆነለት፣ በሚካም ቤት ነበረ፡፡
\v 13 ከዚያም ሚካ እንዲህ አለ፣ “አሁን እግዚአብሔር ለእኔ መልካም እንደሚሰራልኝ አውቄአለሁ፣ ምክንያቱም ይህ ሌዋዊ ካህን ሆኖልኛል፡፡”
\s5
\c 18
\p
\v 1 በዚያን ዘመን በእስራኤል ውስጥ ንጉሥ አልነበረም፡፡ የዳን ነገድ ተወላጆች የሚቀመጡበትን ርስት ይፈልጉ ነበር፣ እስከዚያ ቀን ድረስ በእስራኤል ነገዶች መካከል ርስት አልተቀበሉም ነበርና፡፡
\v 2 የዳን ሰዎች ከአጠቃላይ ወገናቸው በሙሉ ከጾርዓ ጀምሮ እስከ ኤሽታኦል ድረስ በጦርነት ልምድ ያላቸውን አምስት ሰዎች በእግራቸው ሄደው ምድሪቱን እንዲሰልሉና እንዲያዩ ላኩ፡፡ ለእነርሱም እንዲህ አሉአቸው፣ “ሂዱና ምድሪቱን ሰልሉ፡፡” እነርሱም ወደ ኮረብታማው ወደ ኤፍሬም አገር ወደ ሚካ ቤት መጡና ሌሊቱን በዚያ አሳለፉ፡፡
\s5
\v 3 በሚካ ቤት አጠገብ በነበሩ ጊዜ፣ የአንድ ወጣት ሌዋዊ ንግግር አወቁ፡፡ ስለዚህ አስቆሙትና እንዲህ ብለው ጠየቁት፣ “ወደዚህ ማን አመጣህ? በዚህ ስፍራ ምን ታደርጋለህ? ለምን ወደዚህ መጣህ?”
\v 4 እርሱም እንዲህ አላቸው፣ “ሚካ ለእኔ ያደረገው ነገር ይህ ነው፡- የእርሱ ካህን እንድሆን ቀጠረኝ፡፡”
\s5
\v 5 እነርሱም እንዲህ አሉት፣ “የምንሄድበት መንገድ መቃናቱን ወይም አለመቃናቱን እናውቅ ዘንድ፣ እባክህ፣ የእግዚአብሔርን ምክር ጠይቅልን፡፡”
\v 6 ካህኑም ለእነርሱ እንዲህ አላቸው፣ “በሰላም ሂዱ፡፡ ልትሄዱ በሚገባችሁ መንገድ እግዚአብሔር ይመራችኋል፡፡”
\s5
\v 7
የዚያን ጊዜ አምስቱ ሰዎች ሄዱና ወደ ላይሽ መጡ፣ ሲዶናውያን በጸጥታ ያለስጋት ይኖሩ እንደነበረ ሁሉ፣ በዚያም ተዘልለው ይኖሩ የነበሩትን ሕዝብ አዩ፡፡ በምድሪቱም በየትኛውም መልኩ የገዛቸው፣ ወይም ያስቸገራቸው አልነበረም፡፡ ከሲዶናውያን በጣም ርቀው ይኖሩ ነበር፣ ከማንኛውም ሕዝብ ጋር ምንም ግንኙነት አልነበራቸውም፡፡
\v 8 በጾርዓና በኤሽታኦል ውስጥ ወደነበሩት ወንድሞቻቸው ተመለሱ፡፡ ዘመዶቻቸውም እንዲህ ብለው ጠየቁአቸው፣ “ምን ወሬ ይዛችኋል?”
\s5
\v 9 እነርሱም እንዲህ አሉ፣ “ኑ! እንውጋቸው! ምድሪቱን አይተናታል፣ በጣም ጥሩ ናት፡፡ እናንተ ዝም ትላላችሁን? ምድሪቱን ከመውጋትና ከመውረስ አትዘግዩ፡፡
\v 10 በሄዳችሁ ጊዜ፣ ያለ ስጋት እንደሚኖሩ ወደሚያስቡ ሕዝብ ትደርሳላችሁ፣ ምድሪቱም ሰፊ ናት! እግዚአብሔርም ለእናንተ ሰጥቶአችኋል፣ በምድር ካለው ነገር ሁሉ አንዳች የማይጎድልባት ስፍራ ናት፡፡
\s5
\v 11 ከዳን ወገን የሆኑና የጦር መሳርያ የታጠቁ ስድስት መቶ ሰዎች ከጾርዓና ከኤሽታኦል ተነሥተው ሄዱ፡፡
\v 12 እነርሱም ሄዱና በይሁዳ ባለችው በቂርያትይዓሪም ሰፈሩ፡፡ እስከ ዛሬ ድረስ የዚያ ስፍራ ስም የዳን ሰፈር ብለው የሚጠሩት ለዚህ ነው፤ እርሱም ከቂርያትይዓሪም በምዕራብ በኩል ነው፡፡
\s5
\v 13
እነርሱም ከዚያ ተነስተው ወደ ኮረብታማው የኤፍሬም አገር አልፈው ሄዱ፣ ወደ ሚካም ቤት መጡ፡፡
\v 14 ከዚያም የላይሽን አገር ሊሰልሉ ሄደው የነበሩት አምስቱ ሰዎች ለዘመዶቻቸው እንዲህ አሉአቸው፣ “በእነዚህ ቤቶች ውስጥ ኤፉድና ተራፊም፣ የተቀረጸ ምስልና ቀልጦ የተሠራ ምስል እንዳሉ ታውቃላችሁን? ምን እንደምታደርጉ አሁን ወስኑ፡፡”
\s5
\v 15 ስለዚህ ከዚያ ዘወር አሉና ወጣቱ ሌዋዊ ይኖርበት ወደነበረው ወደ ሚካ ቤት መጡ፤ ሰላምታም አቀረቡለት፡፡
\v 16 በዚያን ጊዜ የጦር መሳርያ የታጠቁት ስድስት መቶ ዳናውያን በበሩ መግቢያ ቆሙ፡፡
\s5
\v 17
ካህኑ የጦር መሳርያ ከታጠቁት ከስድስት መቶ ሰዎች ጋር በበሩ አካባቢ ቆሞ በነበረበት ጊዜ፣ ምድሪቱንም ሊሰልሉ ሄደው የነበሩት አምስቱ ሰዎች ወደዚያ ሄዱና የተቀረጸውን ምስል፣ ኤፉዱን፣ ተራፊሙንና ቀልጦ የተሠራውን ምስል ወሰዱ፡፡
\v 18 እነዚህ ወደ ሚካ ቤት ገብተው የተቀረጸውን ምስል፣ ኤፉዱን፣ ተራፊሙንና ቀልጦ የተሠራውን ምስል በወሰዱ ጊዜ፣ ካህኑ ለእነርሱ እንዲህ አላቸው፣ “ምን ታደርጋላችሁ?”
\s5
\v 19 እነርሱም እንዲህ አሉት፣ “ዝም በል! እጅህን በአፍህ ላይ ጫንና ከእኛ ጋር ና፣ ለእኛም አባትና ካህን ሁንልን፡፡ ለአንተስ ለአንድ ሰው ቤት ካህን መሆን ወይስ በእስራኤል ውስጥ ላለው ነገድና ወገን ሁሉ ካህን መሆን ይሻልሃል?”
\v 20 የካህኑም ልብ ደስ አለው፡፡ ኤፉዱን፣ ተራፊሙንና የተቀረጸውንም ምስል ወሰደና ከሕዝቡ ጋር ሄደ፡፡
\s5
\v 21
ስለዚህ እነርሱ ዞሩና ሄዱ፡፡ ሕፃናቶችን፣ ከብቶችንና ንብረታቸውን በፊታቸው አስቀደሙ፡፡
\v 22 ከሚካም ቤት ጥቂት በራቁ ጊዜ፣ በሚካ ቤት አጠገብ በነበሩት ቤቶች ውስጥ የነበሩ ሰዎች ተጠራርተው ተሰበሰቡ፣ የዳን ሰዎችንም ተከትለው ደረሱባቸው፡፡
\v 23 ወደ ዳንም ሰዎች ጮኹ፣ ዘወር ብለው ለሚካም እንዲህ አሉት፣ “ተሰብስባችሁ በአንድ ላይ የመጣችሁት ለምንድን ነው?”
\s5
\v 24 እርሱም፣ “የሠራኋቸውን አማልክቴን ሰረቃችሁ፣ ካህኔንም ይዛችሁ ሄዳችሁ፡፡ ሌላ ምን የቀረኝ ነገር አለ? ‘ያስጨነቀህ ምንድን ነው? ብላችሁ እንዴት ልትጠይቁኝ ትችላላችሁ፡፡”
\v 25 የዳን ሰዎችም እንዲህ አሉት፣ “ምንም ዓይነት ንግግር ስትናገር እንድንሰማ አታድርገን፣ አለዚያ አንዳንድ የተቈጡ ሰዎች ይጎዱሃል፣ አንተና ቤተሰቦችህም ትሞታላችሁ፡፡”
\v 26 የዚያን ጊዜ የዳን ሰዎች መንገዳቸውን ሄዱ፡፡ ሚካ ከእርሱ ይልቅ እነርሱ እጅግ በጣም የበረቱ እንደሆኑ ባየ ጊዜ፣ ተመልሶ ወደ ቤቱ ሄደ፡፡
\s5
\v 27
የዳን ሰዎችም ሚካ የሠራውን ጣዖትና ካህኑን ወሰዱና ወደ ላይሽ መጡ፣ በሰላምና ያለ ስጋት ተዘልሎም ወደ ተቀመጠው ሕዝብ መጥተው በሰይፍ ስለት ገደሉአቸው፣ ከተማይቱንም በእሳት አቃጠሉአት፡፡
\v 28 እነርሱን የሚያድን አንድም ሰው አልነበረም ምክንያቱም ከተማይቱ ከሲዶና በጣም ራቅ ያለች ነበረች፣ እነርሱም ከሌሎች ሰዎች ጋር ምንም ግንኙነት አልነበራቸውም፡፡ እርስዋም በቤትሮዖብ አጠገብ ባለው ሸለቆ ውስጥ ነበረች፡፡ የዳን ሰዎችም ከተማይቱን እንደገና ሠሩና ተቀመጡባት፡፡
\v 29 ከተማይቱንም ከእስራኤል ወንዶች ልጆች አንዱ በሆነው በአባታቸው በዳን ስም ዳን ብለው ጠሩአት፡፡ ነገር ግን አስቀድሞ የከተማይቱ ስም ላይሽ ነበረ፡፡
\s5
\v 30 የዳን ሰዎችም ለራሳቸው የተቀረጸ ምስል አቆሙ፣ የሙሴ ልጅ የጌርሳም ልጅ ዮናታን፣ እርሱና ወንዶች ልጆቹ ምድሪቱ እስከምትያዝበት ቀን ድረስ ለዳን ሰዎች ካህናት ነበሩ፡፡
\v 31 ስለዚህ የእግዚአብሔር ቤት በሴሎ በነበረበት ጊዜ ሁሉ፣ ሚካ የሰራውን የተቀረጸ ምስል አመለኩ፡፡
\s5
\c 19
\p
\v 1
በዚያም ዘመን፣ በእስራኤል ውስጥ ንጉሥ ባልነበረበት ጊዜ፣ በኮረብታማው የኤፍሬም አገር እጅግ በጣም ሩቅ በሆነ አካባቢ ለአጭር ጊዜ የኖረ አንድ ሌዋዊ ሰው ነበረ፡፡ እርሱም አንዲትን ሴት ቁባት አድርጎ ወሰዳት፡፡
\v 2 ነገር ግን ቁባቱ ለእርሱ ታማኝ አልነበረችም፤ እርሱን ተወችውና ተመልሳ ወደ አባትዋ ቤት ወደ ቤተ ልሔም ይሁዳ ሄደች፡፡ እርስዋም በዚያ አራት ወር ቆየች፡፡
\s5
\v 3
የዚያን ጊዜ ባልዋ ተነሣና ተመልሳ ወደ እርሱ እንድትመጣ ለማባበል ተከትሏት ሄደ፡፡ የእርሱ አገልጋይና ሁለት አህዮች ከእርሱ ጋር ነበሩ፡፡ እርስዋም ወደ አባትዋ ቤት አስገባችው፡፡የልጅቱ አባት ባየው ጊዜ ደስ አለው፡፡
\v 4 የልጂቱ አባት፣ አማቱም በቤቱ ለሦስት ቀን እንዲቆይ ለመነው፡፡ እነርሱም በሉ፣ ጠጡ፣ ሌሊቱንም በዚያ አሳለፉ፡፡
\s5
\v 5
በአራተኛው ቀን ማልደው ተነሡ፣ እርሱም ለመሄድ ተዘጋጀ፣ ነገር ግን የልጂቱ አባት አማቹን እንዲህ አለው፣ “እንድትበረታ እንጀራ ብላ፣ ከዚያ መሄድ ትችላለህ፡፡”
\v 6 ስለዚህ ሁለቱም በአንድ ላይ ለመብላትና ለመጠጣት ተቀመጡ፡፡ ከዚያም የልጂቱ አባት እንዲህ አለ፣ “እባክህ ሌሊቱን ደግሞ እዚህ ለማሳለፍ ፈቃደኛ ሁን፣ መልካም ጊዜም ይሁንልህ፡፡”
\s5
\v 7
ሌዋዊው ለመሄድ በማለዳ በተነሳ ጊዜ፣ የወጣቷ ሴት አባት እንዲቆይ ለመነው፣ ከዚህ የተነሳ እቅዱን ለወጠና ሌሊቱን በዚያ አሳለፈ፡፡
\v 8 በአምስተኛው ቀን ለመሄድ ማልዶ ተነሣ፣ ነገር ግን የልጂቱ አባት እንዲህ አለ፣ “ሰውነትህን አበርታ፣ እስከ ማምሻ ድረስ ቆይ አለው፡፡ ስለዚህ ሁለቱም አብረው በሉ፡፡
\s5
\v 9
ሌዋዊው፣ ቁባቱና አገልጋዮቹ ለመሄድ በተነሱ ጊዜ፣ የልጂቱ አባት አማቱ እንዲህ አለው፣ “ተመልከት፣ አሁን ቀኑ እየመሸ ነው፡፡ እባክህ ሌላ ሌሊት በዚህ ቆዩ፣ መልካም ጊዜም ይሁንልህ፡፡ ነገ በማለዳ ተነስታችሁ ወደ ቤታችሁ ተመልሳችሁ መሄድ ትችላላችሁ፡፡”
\s5
\v 10
ነገር ግን ሌዋዊው ሌሊቱን በዚያ ለማሳለፍ ፈቃደኛ አልነበረም፡፡ ተነሳና ሄደ፡፡ ኢየሩሳሌምም ወደ ተባለችው ወደ ኢያቡስ ሄደ፡፡ ሁለት የተጫኑ አህዮች ነበሩት፣ ቁባቱም ከእርሱ ጋር ነበረች፡፡
\v 11 ወደ ኢያቡስም በቀረቡ ጊዜ መሸባቸው፣ አገልጋዩም ለጌታው እንዲህ አለው፣ “ና፣ ወደ ኢያቡሳውያን ከተማ እንሂድና ሌሊቱን በዚያ እናሳልፍ፡፡”
\s5
\v 12
ጌታውም፣ “የእስራኤል ሕዝብ ወገን ወዳልሆነ ወደ እንግዳ ሕዝብ ከተማ ውስጥ አንገባም፡፡ እኛ ወደ ጊብዓ እንሄዳለን፡፡”
\v 13 ሌዋዊውም ለወጣቱ ሰው እንዲህ አለው፣ “ና፣ ከእነዚህ ስፍራዎች ወደ አንዱ እንሂድ፣ ሌሊቱንም በጊብዓ ወይም በራማ እናሳልፍ፡፡”
\s5
\v 14 ስለዚህ መንገዳቸውን ቀጠሉ፣ የብንያም ነገድ ወደምትሆነው ወደ ጊብዓ ግዛት ሲቀርቡ ፀሐይ ገባችባቸው፡፡
\v 15 እነርሱም ሌሊቱን በጊብዓ ለማሳለፍ ወደዚያ አቀኑ፡፡ እርሱም ወደ ውስጥ ገባና በከተማው አደባባይ ተቀመጠ፣ ሌሊቱን በዚያ ያሳልፉ ዘንድ ወደ ቤቱ የወሰዳቸው ማንም ሰው አልነበረምና፡፡
\s5
\v 16 ነገር ግን በዚያን ጊዜ አንድ ሽማግሌ ሰው ከእርሻ ሥራው በምሽት እየመጣ ነበር፡፡ እርሱም ከኮረብታማው ከኤፍሬም አገር ነበረ፣ እርሱም በጊብዓ በእንግድነት ተቀምጦ ነበር፡፡ ነገር ግን በዚያ ስፍራ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ብንያማውያን ነበሩ፡፡
\v 17 እርሱም ዓይኑን አነሳና መንገደኛውን በከተማው አደባባይ አየው፡፡ ሽማግሌውም እንዲህ አለ፣ “ወዴት ትሄዳለህ? ከወዴትስ መጣህ?”
\s5
\v 18 ሌዋዊውም እንዲህ አለው፣ “እኛ ከቤተ ልሔም ይሁዳ በጣም ሩቅ ወደሆነው ወደ ኮረብታማው ወደ ኤፍሬም አገር እንሄዳለን፣ እኔም የመጣሁት ከዚያ ነው፡፡ ወደ ቤተ ልሔም ይሁዳ ሄጄ ነበር፣ አሁን ወደ እግዚአብሔር ቤት እየሄድሁ ነው፣ ነገር ግን ወደ ቤቱ የሚወስደኝ ማንም ሰው የለም፡፡
\v 19 ለአህዮቻችን ገለባና ገፈራ አለን፣ ለእኔና እዚህ ላለችው ለሴት አገልጋይህ፣ ከአገልጋዮችህም ጋር ላለው ለዚህ ወጣት ሰው እንጀራና የወይን ጠጅ አለን፡፡ አንዳችም አላጣንም፡፡”
\s5
\v 20 ሽማግሌውም ሰላምታ አቀረበላቸው፣ “ሰላም ለእናንተ ይሁን! የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ እኔ እሰጣችኋለሁ፡፡ በአደባባይ ግን ሌሊቱን አትደሩ” አለው፡፡
\v 21 ስለዚህም ሰውየው ሌዋዊውን ወደ ቤቱ ወሰደው፣ ለአህዮቹም ገፈራ ሰጣቸው፡፡ እግራቸውን ታጠቡ፣ በሉም ጠጡም፡፡
\s5
\v 22
እነርሱም መልካም ጊዜ ነበራቸው፣ ክፉ የሆኑ የከተማይቱ ሰዎች ያደሩበትን ቤት ከበቡ፣ በሩንም ይደበድቡ ነበር፡፡ የቤቱ ባለቤት ለሆነው ለሽማግሌው እንዲህ አሉት፣ “ከእርሱ ጋር መተኛት እንድንችል ወደ ቤትህ የገባውን ሰው አምጣው፡፡”
\v 23 ሰውየውም፣ የቤቱ ባለቤት፣ ወደ እነርሱ ሄደና እንዲህ አላቸው፣ “አይሆንም፣ ወንድሞቼ ሆይ፣ ይህን ክፉ ነገር እባካችሁ አታድርጉ! ይህ ሰው ወደ ቤቴ የገባ እንግዳ ስለሆነ፣ ይህን ክፉ ነገር አትሥሩ፡፡
\s5
\v 24
ተመልከቱ፣ ድንግል ልጄና የእርሱም ቁባት እዚህ አሉ፡፡ አሁን ሄጄ ላምጣቸው፡፡ አስነውሩአቸው፣ የፈለጋችሁትንም አድርጉባቸው፡፡ ነገር ግን በዚህ ሰው ላይ እንደዚህ ያለ ክፉ ነገር አታድርጉበት!”
\v 25 ነገር ግን ሰዎቹ እርሱን አልሰሙትም፣ ስለዚህ ሰውዮው ቁባቱን ያዛትና ወደ ውጭ አወጣላቸው፡፡ እነርሱም ያዟትና ከእርሷ ጋር ተኙ፣ ሌሊቱን በሙሉ አመነዘሩባት፣ ጎህም ሲቀድ ለቀቁአት፡፡
\v 26 ሴቲቱም በማለዳ መጣችና ጌታዋ ባለበት በሰውዮው ቤት በር ወደቀች፣ ጸሐይ እስኪወጣ ድረስ እዚያው ተዘረረች፡፡
\s5
\v 27
ጌታዋም በማለዳ ተነሣና የቤቱን በር ከፈተ፣ መንገዱንም ለመሄድ ወጣ፡፡ እርሱም ቁባቱ እጅዋን በመድረኩ ላይ ዘርግታ በበሩ ተዘርራ አያት፡፡
\v 28 ሌዋዊውም እንዲህ አላት፣ “ተነሺ፡፡ እንሂድ፡፡” ነገር ግን ምንም መልስ አልነበረም፡፡ እርሱም በአህያው ላይ ጫናት፣ ተነሥቶም ወደ ቤቱ ሄደ፡፡
\s5
\v 29
ሌዋዊውም ወደ ቤቱ በመጣ ጊዜ፣ ቢላዋ ወሰደ፣ ቁባቱንም ይዞ ቆራረጣት፣ ብልት በብልት ለአሥራ ሁለት ቈራርጦ ቁራጮቹን ወደ እስራኤል አገር ሁሉ ላከው፡፡
\v 30 ይህንን ያየ ሁሉ እንዲህ አለ፣ “የእስራኤል ሕዝብ ከግብፅ ምድር ከወጡ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እንዲህ ያለ ነገር ከቶ አልተደረገም ወይም አልታየም፡፡ ስለ ነገሩ አስቡበት! ምክር ስጡን! ምን ማድረግ እንዳለብን ንገሩን!”
\s5
\c 20
\p
\v 1
የዚያን ጊዜ የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ እንደ አንድ ሰው ሆነው ወጡ፣ ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ድረስ፣ የገለዓድ አገር ሰዎችንም ጨምሮ፣ በእግዚአብሔር ፊት በምጽጳ ተሰበሰቡ፡፡
\v 2 የሕዝቡም ሁሉ መሪዎች፣ የእስራኤል ነገዶች ሁሉ፣ እግረኞች ሆነው በሰይፍ የሚዋጉ 400, 000 ሰዎች በእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ ውስጥ ስፍራቸውን ያዙ፡፡
\s5
\v 3 በዚህ ጊዜ የእስራኤል ሕዝብ እስከ ምጽጳ ድረስ እንደ ሄዱ የብንያም ሕዝብ ሰሙ፡፡ የእስራኤልም ሕዝብ እንዲህ አሉ፣ “ይህ ክፉ ነገር እንዴት እንደ ተደረገ ንገሩን?”
\v 4 ሌዋዊውም፣ የተገደለችው ሴት ባል፣ እንዲህ ብሎ መለሰ፣ “እኔና ቁባቴ ሌሊቱን በዚያ ለማሳለፍ የብንያም ግዛት ወደሆነችው ወደ ጊብዓ መጣን፡፡
\s5
\v 5 በዚያ ሌሊት የጊብዓ ሰዎች በእኔ ላይ ተነሱ፣ ሊገድሉኝም አስበው ቤቱን ከበቡት፡፡ ቁባቴንም ያዙና ከእርስዋ ጋር ተኙ፣ እርስዋም ሞተች፡፡
\v 6 እኔም ቁባቴን ወሰድሁና ሰውነቷን ቆራረኋጥኋት፣ ቁርጥራጩንም በእስራኤል ርስት ወደሚገኝ ወደ እያንዳንዱ ክልል ላክሁት፣ ምክንያቱም እንዲህ ዓይነቱን ክፋትና መአት በእስራኤል ላይ ፈጽመዋልና፡፡
\v 7 አሁንም፣ እናንተ እስራኤላውያን ሁላችሁም ተነጋገሩ፣ ምክራችሁንም ስጡ፣ ለዚህ ነገርም ፍርዳችሁን ስጡ!”
\s5
\v 8 ሕዝቡም ሁሉ እንደ አንድ ሰው ሆነው በአንድ ላይ ተነሱ፣ እንዲህም አሉ፣ “ከእኛ ዘንድ ማንም ሰው ወደ ድንኳኑ አይሄድም፣ ማንም ሰው ወደ ቤቱ አይመለስም!
\v 9 ነገር ግን አሁንም በጊብዓ ላይ ማድረግ ያለብን ነገር ይህ ነው፡- ዕጣው እንደሚመራን እንወጋታለን፡፡
\s5
\v 10
ከእስራኤል ነገዶች በሙሉ ለሕዝቡ ስንቅ እንዲይዙ ከመቶው አስር ሰው፣ ከሺህ መቶ ሰው፣ ከአስር ሺህ አንድ ሺህ ሰው እንወስዳለን፣ ይህም ሕዝቡ ወደ ብንያም ጊብዓ በሚመጣበት ጊዜ እነርሱ በእስራኤል ላይ ለፈጸሙት ክፋት ይቀጧቸው ዘንድ ነው፡፡”
\v 11 ስለዚህም የእስራኤል ወታደሮች በሙሉ በአንድ ዓላማ በመስማማት በከተማይቱ ላይ ለመዝመት ተሰበሰቡ፡፡
\s5
\v 12
የእስራኤልም ነገዶች ወደ ብንያም ነገድ ሁሉ እንዲህ ብለው ሰዎችን ላኩ፣ “በእናንተ መካከል የተደረገው ይህ ክፉ ነገር ምንድር ነው?
\v 13 ስለዚህ እንድንገድላቸውና ይህንን ክፋት ከእስራኤል ሙሉ ለሙሉ ለማስወገድ በጊብዓ ውስጥ ያሉትን እነዚህን ክፉ ሰዎች አውጥታችሁ ስጡን፡፡” ነገር ግን ብንያማውያን የወንድሞቻቸውን የእስራኤልን ሕዝብ ቃል አልሰሙም፡፡
\v 14 የዚያን ጊዜ የብንያም ሕዝብ ከእስራኤል ሕዝብ ጋር ለመዋጋት ዝግጅት ያደርጉ ዘንድ ከየከተማው ወጥተው ወደ ጊብዓ ተሰበሰቡ፡፡
\s5
\v 15
የብንያም ሕዝብ ከየከተማው በአንድ ላይ ለመዋጋት መጡ፣ በዚያም ቀን በሰይፍ ስለት ለመዋጋት የሰለጠኑ 26, 000 ወታደሮች ነበሩ፤ ከዚህ በተጨማሪ ከጊብዓ ነዋሪዎች ሰባት መቶ የተመረጡ ሰዎች ተቈጠሩ፡፡
\v 16 ከእነዚህ ወታደሮች መካከል ሰባት መቶ የተመረጡ ግራኝ ሰዎች ነበሩ፤ እያንዳንዳቸውም ድንጋይ ወንጭፈው አንዲት ጠጕርስ እንኳ አይስቱም፡፡
\s5
\v 17
የእስራኤል ወታደሮች፣ ከብንያም ወገን የሆኑትን ሳይጨምር፣ በሰይፍ ስለት ለመዋጋት የሰለጠኑ አራት መቶ ሺህ ሰዎች ተቆጠሩ፡፡ እነዚህ በሙሉ የጦር ሰዎች ነበሩ፡፡
\v 18 የእስራኤልም ሕዝብ ተነሱ፣ ወደ ቤቴል ወጡ፣ ከእግዚአብሔርም ምክር ጠየቁ፡፡ እንዲህም ብለው ጠየቁ፣ “የብንያምን ልጆች ለመውጋት ለእኛ መጀመርያ ማን ይውጣልን?” እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፣ “ይሁዳ በመጀመርያ ይዋጋል፡፡”
\s5
\v 19
የእስራኤልም ሕዝብ በማለዳ ተነሱና በጊብዓ ፊት ለውጊያ ተዘጋጁ፡፡
\v 20 የእስራኤልም ወታደሮች ከብንያም ጋር ለመዋጋት ወጡ፡፡ እነርሱም በጊብዓ ከእነርሱ ጋር ለመዋጋት ቦታ ቦታቸውን ይዘው ተሰለፉ፡፡
\v 21 የብንያም ወታደሮች ከጊብዓ ወጥተው መጡ፣ በዚያም ቀን ከእስራኤላውያን ሰራዊት 22, 000 ሰዎች ገደሉ፡፡
\s5
\v 22
ነገር ግን የእስራኤል ወታደሮች ራሳቸውን አበረቱ፣ በመጀመርያው ቀን ተሰልፈው በነበረበት ስፍራ ላይ እንደገና ቦታ ቦታቸውን በመያዝ የውጊያውን መስመር አዘጋጁ፡፡
\v 23 የእስራኤልም ሕዝብ ወደ ላይ ወጡና እስከ ማታ ድረስ በእግዚአብሔር ፊት አለቀሱ፡፡ከእግዚአብሔርም ምሪትን ፈለጉ እንዲህም ብለው ጠየቁ፣ “ከወንድሞቻችን ከብንያም ሕዝብ ጋር ለመዋጋት እንደገና ወደዚያ መቅረብ ይገባናልን?” እግዚአብሔርም “በእነርሱ ላይ ውጡና ግጠሟቸው” አለ፡፡
\s5
\v 24 ስለዚህም በሁለተኛው ቀን የእስራኤል ወታደሮች የብንያምን ወታደሮች ለመዋጋት ሄዱ፡፡
\v 25 በሁለተኛው ቀን የብንያም ወታደሮች ከጊብዓ እነርሱን ሊወጉ ወጡና ከእስራኤል ወታደሮች 18, 000 ሰዎች ገደሉ፡፡ እነዚህም ሰዎች ሁሉ በሰይፍ ለመዋጋት የሰለጠኑ ነበሩ፡፡
\s5
\v 26
የዚያን ጊዜ የእስራኤል ወታደሮች ሁሉ፣ ሕዝቡም ሁሉ ወደ ቤቴል ወጡና አለቀሱ፣ በዚያም በእግዚአብሔር ፊት ተቀመጡ፣ እነርሱም በዚያ ቀን እስከ ምሽት ድረስ ጾሙ፣ በእግዚአብሔር ፊት የሚቃጠል መሥዋዕትና የሰላም መሥዋዕት አቀረቡ፡፡
\s5
\v 27
የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔርን ጠየቁ፣ በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት በዚያ ነበረ፣
\v 28 በእነዚህ ጊዜያቶች የአሮን ልጅ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ በታቦቱ ፊት ያገለግል ነበር፣ “ከወንድሞቻችን ከብንያም ሕዝብ ጋር አንድ ጊዜ ለመዋጋት እንደገና እንሂድ ወይስ እንቅር?” እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፣ “ጥቃት ፈጽሙባቸው፣ ነገ እነርሱን እንድታሸንፉ እረዳችኋለሁና፡፡”
\s5
\v 29
ስለዚህ እስራኤል በጊብዓ ዙሪያ በምስጢራዊ ስፍራዎች የተደበቁ ሰዎች አኖሩ፡፡
\v 30 የእስራኤል ወታደሮች ከብንያም ወታደሮች ጋር ለሦስተኛ ቀን ተዋጉ፣ ከዚህ በፊት እንዳደረጉት በጊብዓ ላይ የውጊያ መስመራቸውን ዘርግተው ተሰለፉ፡፡
\s5
\v 31
የብንያምም ሕዝብ ሄዱና ሕዝቡን ተዋጉ፣ ከከተማይቱም እንዲወጡ ተደረጉ፡፡ ከሕዝቡም አንዳንዶቹን መግደል ጀመሩ፡፡ ከእስራኤልም ወገን የሞቱ ሠላሳ የሚያህሉ ሰዎች በእርሻዎቹና በመንገዶቹ ነበሩ፣ ከመንገዶቹ አንዱ ወደ ቤቴል የሚወስድ ነው፣ ሌላኛው ደግሞ ወደ ጊብዓ የሚወስድ ነው፡፡
\s5
\v 32
የዚን ጊዜ የብንያምም ሕዝብ እንዲህ አሉ፣ “እንደ በፊቱ ተሸንፈዋል፣ ከእኛ እየሸሹ ነው፡፡” ነገር ግን የእስራኤል ወታደሮች እንዲህ አሉ፣ “እንሽሽ፣ ከከተማይቱ እንዲወጡና ወደ መንገዶቹ እንዲሄዱ እናድርጋቸው፡፡”
\v 33 የእስራኤልም ወታደሮች በሙሉ ከስፍራቸው ተነሱና በበኣልታማር ለውጊያ ራሳቸውን አዘጋጅተው ተሰለፉ፡፡ በምስጢራዊ ስፍራ ተደብቀው የነበሩት የእስራኤል ወታደሮችም ከነበሩበት ስፍራ ከጊብዓ ወጥተው ሮጡ፡፡
\s5
\v 34
ከእስራኤልም ሁሉ 10, 000 የተመረጡ ሰዎች በጊብዓ ላይ መጡ፣ ጦርነቱም በርትቶ ነበር፣ ነገር ግን ብንያማውያን ጥፋት ወደ እነርሱ ቀርቦ እንደነበር አላወቁም፡፡
\v 35 እግዚአብሔርም ብንያምን በእስራኤል ፊት ድል አደረገ፡፡ በዚያም ቀን የእስራኤል ወታደሮች 25, 100 የብንያም ሰዎችን ገደሉ፡፡ የሞቱት ሰዎች በሙሉ በሰይፍ ለመዋጋት ስልጠና የወሰዱ ነበሩ፡፡
\s5
\v 36
ስለዚህ የብንያም ወታደሮች እንደ ተሸነፉ አዩ፡፡ የእስራኤልም ሰዎች ለብንያም ስፍራ ለቀቁላቸው፣ ምክንያቱም ከጊብዓ ውጭ በድብቅ ስፍራዎች ባስቀመጡአቸው ሰዎች ላይ ተማምነው ነበርና፡፡
\v 37 የዚያን ጊዜ ተደብቀው የነበሩት ሰዎች ተነሱና ፈጥነው ወደ ጊብዓ ሮጡ፣ በከተማይቱም ውስጥ የሚኖረውን ሰው በሙሉ በሰይፋቸው ገደሉ፡፡
\v 38 በእስራኤል ወታደሮችና በምስጢር በተደበቁት ሰዎች መካከል ከከተማው የታላቅ ጢስ ደመና በምልክትነት እንዲያስነሡ ስምምነት ተደርጎ ነበር፡፡
\s5
\v 39 የእስራኤልም ወታደሮች በውጊያው ጊዜ ከጦርነቱ ርቀው እንዲያፈገፍጉ ነበር፡፡ የዚያን ጊዜ ብንያማውያን ማጥቃት ጀመሩ ሠላሳ የእስራኤልንም ሰዎች ገደሉ፣ እነርሱም እንዲህ አሉ፣ “እንደ መጀመርያው የጦርነት ጊዜ በእኛ ፊት መሸነፋቸው እርግጠኛ ነው፡፡”
\s5
\v 40
ነገር ግን የጢሱ ዓምድ ከከተማው ወደ ላይ መውጣት በጀመረ ጊዜ፣ ብንያማውያን ወደ ኋላቸው ሲመለከቱ ጢሱ ከከተማዋ በሙሉ ወደ ሰማይ ሲወጣ አዩ፡፡
\v 41 የዚያን ጊዜ የእስራኤል ወታደሮች ዞረው አጠቋቸው፡፡ የብንያም ሰዎችም ደነገጡ፣ በእነርሱ ላይ ጥፋት እንደመጣባቸው አይተዋልና፡፡
\s5
\v 42
ስለዚህ ከእስራኤል ወታደሮች ተመልሰው ወደ ምድረ በዳው መንገድ ሸሹ፡፡ ነገር ግን ውጊያው ተከታትሎ ደረሰባቸው፡፡ የእስራኤልም ወታደሮች ከከተማዎቹ ወጡና በቆሙበት ስፍራ ገደሉአቸው፡፡
\s5
\v 43
እነርሱም ብንያማውያንን ከበቡና ተከትለዋቸው ሄዱ፤ በመኑሔም አሸነፉአቸው፣ ከጊብዓ በስተ ምሥራቅ በኩል እስካለው ስፍራ ድረስ አሳደዱአቸው፡፡
\v 44 ከብንያም ነገድም 18, 000 ወታደሮች ሞቱ፣ እነዚህ ሰዎች በሙሉ በጦርነት ምርጥ ተዋጊዎች ነበሩ፡፡
\s5
\v 45
እነርሱም ተመልሰው በምድረ በዳ ወዳለው ወደ ሬሞን ዓለት ሸሹ፡፡ እስራኤላውያንም ከእነርሱ ተጨማሪ አምስት ሺህ ሰዎችን በየመንገዱ ገደሉ፡፡ እነርሱም ተከታተሉአቸው፣ ወደ ጊድአምም በቅርብ እየተከታተሉአቸው ተጨማሪ ሁለት ሺህ ሰዎችን ገደሉ፡፡
\v 46 በዚያ ቀን የሞቱት የቢኒያም ወታደሮች በሙሉ 25, 000 በሰይፍ ለመዋጋት ልዩ ስልጠና የወሰዱ ሰዎች ነበሩ፤ እነዚህ በሙሉ በጦርነት ምርጥ ተዋጊዎች ነበሩ፡፡
\s5
\v 47 ነገር ግን ስድስት መቶ ሰዎች ተመልሰው በምድረ በዳ ወዳለው ወደ ሬሞን ዓለት ሸሹ፡፡ ለአራት ወራት ያህል በሬሞን ዓለት ተቀመጡ፡፡
\v 48 የእስራኤልም ወታደሮች በብንያም ሕዝብ ላይ እንደገና ተመለሱ፣ ሞላውን ከተማ፣ ከብቶችንና ያገኙትንም ሁሉ አጠቁ ደግሞም ገደሉ፡፡ በመንገዳቸው ያገኙትን ማንኛውንም ከተማ ሁሉ በእሳት አቃጠሉ፡፡
\s5
\c 21
\p
\v 1 በዚያን ጊዜ የእስራኤል ወታደሮች በምጽጳ “ከእኛ ማንም ሰው ሴት ልጁን በጋብቻ ለብንያማውያን መዳር የለበትም” በማለት ቃል ገብተው ነበር፡፡
\v 2 ከዚያም ሕዝቡ ወደ ቤቴል ሄዱና በዚያ በእግዚአብሔር ፊት እስከ ምሽቱ ድረስ ተቀመጡ፣ ድምፃቸውንም ከፍ በማድረግ አምርረው አለቀሱ፡፡
\v 3 እነርሱም እንዲህ ሲሉ ጮኹ፣ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፣ ይህ በእስራኤል ለምን ሆነ? ዛሬ ከእኛ አንዱ ነገድ መታጣቱ ለምንድን ነው?”
\s5
\v 4 በሚቀጥለውም ቀን ሕዝቡ በጠዋት ተነሡና በዚያ መሠዊያ ሠሩ፣ የሚቃጠልና የሰላም መሥዋዕትንም አቀረቡ፡፡
\v 5 የእስራኤልም ሕዝብ እንዲህ አሉ፣ “ከእስራኤል ነገዶች በሙሉ ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ ያልመጣ የትኛው ነው?” በምጽጳ ወደ እግዚአብሔር ፊት ስላልመጣ ማንም ሰው በጣም ወሳኝ የሆነ ቃል ኪዳን አድርገው ነበርና፡፡ እነርሱም እንዲህ አሉ፣ “እርሱ ፈጽሞ ሊገደል ይገባዋል፡፡”
\s5
\v 6 የእስራኤልም ሕዝብ ስለ ወንድማቸው ስለ ብንያም አዘኑ፡፡ አነርሱም እንዲህ አሉ፣ “ዛሬ ከእስራኤል ነገድ አንዱ ተቆርጧል፡፡
\v 7 ሴቶች ልጆቻችንን ከእነርሱ ለአንዳቸውም ቢሆን በጋብቻ ላንሰጥ ለእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ስለገባን ለተረፉት ሚስቶችን የሚሰጣቸው ማን ነው?”
\s5
\v 8 እነርሱም አሉ፣ “ከእስራኤል ነገድ በምጽጳ ወደ እግዚአብሔር ያልመጣ የትኛው ነው?” ከኢያቢስ ገለዓድ ወደ ጉባኤው አንድም ሰው አለመምጣቱን አወቁ፡፡
\v 9 ሕዝቡም በቅደም ተከተል ተሰልፈው እንዲቆጠሩ በተደረገ ጊዜ፣ እነሆ፣ ከኢያቢስ ገለዓድ ነዋሪዎች ማንም ሰው በዚያ አልነበረም፡፡
\v 10 ጉባኤውም 12, 000 ኃያላን ሰዎችን ወደ ኢያቢስ ገለዓድ ልከው በዚያ ያሉትን ሰዎች ሴቶችንና ሕፃናትንም ጭምር ጥቃት እንዲያደርሱባቸውና እንዲገድሏቸው አዘዙአቸው፡፡
\s5
\v 11 “እንግዲህ የምታደርጉት ይህ ነው፡- ወንዱን በሙሉ እንዲሁም ከወንድ ጋር የተኛችውንም ሴት በሙሉ ግደሉ፡፡”
\v 12 ሰዎቹም በኢያቢስ ገለዓድ ከሚኖሩት መካከል ከወንድ ጋር ተኝተው የማያውቁ አራት መቶ ወጣት ሴቶች አገኙ፣ እነርሱንም በከነዓን ወዳለው በሴሎ ወደሚገኘው ሰፈር ወሰዷቸው፡፡
\s5
\v 13
ጉባኤውም በሙሉ መልክት ላኩ፣ በሬሞን ዓለት ለነበሩት ለብንያም ሕዝብ የሰላም ጥሪ እንዳቀረቡላቸውም ነገሩአቸው፡፡
\v 14 ሲለዚህ በዚያን ጊዜ ብንያማውያን ተመለሱ፣ የኢያቢስ ገለዓድንም ሴቶች ሰጧቸው፡፡ ነገር ግን ለሁሉም የሚበቁ ሴቶች አልነበሩም፡፡
\v 15 ሕዝቡም በብንያም ላይ በሆነው ገር አዘኑ፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር በእስራኤል ነገዶች መካከል ስብራት አድርጓልና፡፡
\s5
\v 16
የዚያን ጊዜ የጉባኤው መሪዎች እንዲህ አሉ፣ “የብንያም ሴቶች ተገድለዋልና፣ ለተረፉት ብንያማውያን ሚስቶችን እንዴት እናግኝላቸው?”
\v 17 እንዲህም አሉ፣ “ከእስራኤል አንድ ነገድ እንዳይጠፋ ከብንያም አሁን በሕይወት ላሉት ሰዎች ርስት ሊኖራቸው ይገባል፡፡
\s5
\v 18
ከሴቶች ልጆቻችን ሚስቶች ልንሰጣቸው አንችልም፡፡ የእስራኤል ሕዝብ፣ ‘ለብንያም ሚስት የሚሰጥ ርጉም ይሁን’ የሚል ቃል ኪዳን ገብተው ነበርና፡፡”
\v 19 ስለዚህ እንዲህ አሉ፣ “በቤቴል በሰሜን በኩል፣ ከቤቴልም ወደ ሴኬም በሚወስደው መንገድ በምሥራቅ በኩል፣ በለቦና በደቡብ በኩል ባለችው በሴሎ በየዓመቱ የእግዚአብሔር በዓል እንዳለ ታውቃላችሁ፡፡”
\s5
\v 20 እነርሱም ለብንያም ሰዎች እንዲህ ብለው አዘዙአቸው፣ “ሂዱና በምስጢር ተሸሸጉ፣ በወይኑ ስፍራም ተደበቁ፡፡
\v 21 የሴሎ ልጃገረዶች ለመጨፈር የሚወጡበትን ጊዜ ተመለክቱ፣ የዚያን ጊዜ ከወይኑ ስፍራ ፈጥናችሁ ውጡና እያንዳንዳችሁ ከሴሎ ልጃገረዶች ለየራሳችሁ ሚስት ውሰዱ፣ ከዚያም ወደ ብንያም ምድር ተመለሱ፡፡
\s5
\v 22 አባቶቻቸው ወይም ወንድሞቻቸው ሊጣሉን በመጡ ጊዜ፣ እንዲህ እንላቸዋለን፣ ‘ምህረት አድርጉልን! ባልና ሚስት ሆነው ይጽኑ ምክንያቱም በጦርነቱ ጊዜ እኛ ለያንዳንዳቸው ሚስት አላገኘንላቸውም፡፡ እናተ ደግሞ ሴቶች ልጆቻችሁን ለእነርሱ ስላልሰጣችሁ፣ ቃል ኪዳኑን በተመለከተ በደለኞች አይደላችሁም፡፡’”
\s5
\v 23
የብንያምም ሕዝብ እንዲሁ አደረጉ፣ በቍጥራቸው መጠን የሚያስፈልጋቸውን ያህል ሚስቶች ይጨፍሩ ከነበሩት ልጃገረዶች ወሰዱ፣ ሚስትም ይሆኗቸው ዘንድ ይዘዋቸው ሄዱ፡፡ እነርሱም ወደ ርስታቸው ስፍራ ተመልሰው ሄዱ፤ ከተሞችንም እንደገና ሠሩ፣ በውስጣቸውም ኖሩ፡፡
\v 24 በዚያን ጊዜ የእስራኤል ሕዝብ ያን ስፍራ ለቀቁና ወደ ቤታቸው ሄዱ፣ እያንዳንዱም ወደ ነገዱና ወደ ወገኑ ሄደ፣ እያንዳንዱም ወደ ርስቱ ተመለሰ፡፡
\s5
\v 25 በዚያም ዘመን በእስራኤል ውስጥ ንጉሥ አልነበረም፡፡ እያንዳንዱ ሰው በዓይኖቹ ፊት መልካም መስሎ የታየውን ያደርግ ነበር፡፡