am_ulb/06-JOS.usfm

1329 lines
145 KiB
Plaintext

\id JOS
\ide UTF-8
\h ኢያሱ
\toc1 ኢያሱ
\toc2 ኢያሱ
\toc3 jos
\mt ኢያሱ
\s5
\c 1
\p
\v 1 እንዲህም ሆነ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ከሞተ በኋላ እግዚአብሔር የሙሴ ዋና ረዳት የሆነውን የነዌ ልጅ ኢያሱን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦
\v 2 አገልጋዬ ሙሴ ሞቶአል። ስለዚህም ለእስራኤል ልጆች ወደምሰጣቸው ምድር አንተና ይህ ሕዝብ ሁሉ ተነሥታችሁ ይህን ዮርዳኖስ ተሻገሩ።
\v 3 የእግራችሁ ጫማ የሚረግጥውን ቦታ ሁሉ ለእናንተ ሰጥቼአለሁ።ለሙሴም ተስፋ እንደ ሰጠሁት ሰጥቻችኋለሁ።
\s5
\v 4 ከምድረ በዳው ከዚህም ከሊባኖስ ጀምሮ እስከ ታላቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ድረስ፤ የኪጢያውያን ምድር ሁሉ እስከ ፀሐይ መግቢያ እስከ ታላቁ ባሕር ድረስ ዳርቻእሁ ይሆናል።
\v 5 በሕይወትህ ዘመን ሁሉ ማንም ሊቋቋምህ አይችልም። ከሙሴ ጋር እንደ ነበርሁ እንዲሁ ከአንተ ጋር እሆናለሁ። አልጥልህም አልትውህም።
\s5
\v 6 ለአባቶቻቸው፦እሰጣችኋለሁ ብዬ ተስፋ የሰጠ'ኋችሁውን ምድር ይህ ሕዝብ እንዲወርስ ታደርጋለህና ጽና አይዞህ።
\v 7 ስለዚህም ጽና እጅግ በርታ። አገልጋዬ ሙሴ ያዘዘህን ሕግን ሁሉ ትጠብቀው ዘንድ ተጠንቀቅ። በምትሄድበትም ሁሉ እንዲከናወንልህ ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ አትበል።
\s5
\v 8 ስለዚህ ሕግ መጽሐፍ ሁልጊዜ ተናገር። የተጻፈበትንም ሁሉ ትጠብቅ ዘንድ በቀንና በሌሊትም አሰላስለው። የዚያን ጊዜም የተከናወነልህና የተሳከልህ ትሆናለህ።
\v 9 በምትሄድበት ሁሉ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና፦ "ጽና፥ አይዞህ፥ አትፍራ፥ ተስፋ አትቁረጥ ብዬ አላዘዝሁህምን?"
\s5
\v 10 ኢያሱም የሕዝቡን አለቆች እንዲህ ብሎ አዘዘ፦
\v 11 "በሰፈሩ መካከል እለፉ፤ ሕዝቡንም፦ ለራሳችሁ ስንቃችሁን አዘጋጁ ብላችሁ እዘዙአቸው። እግዚአብሔር አምላካችሁ እንዲትወርሱ ወደሚሰጣችሁ ምድር በሦስት ቀናት ውስጥ ይህን ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ ትወርሳላችሁ።
\s5
\v 12 ኢያሱም የሮቤልን ልጆች የጋድንም ልጆች የምናሴንም ነገድ እኩሌታ እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦
\v 13 የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ እንዲህ ብሎ ያዘዛቸውን ቃል አስቡ፦አምላካችሁ እግዚአብሔር እረፍት ይሰጣችኋል፤ይህንንም ምድር ይሰጣችኋል።
\s5
\v 14 ሚስቶቻችሁ፥ ልጆቻችሁና ከብቶቻችሁ ሙሴ በዮርዳኖስ ማዶ በሰጣችሁ ምድር ይቀመጣሉ። ነገር ግን ተዋጊ የሆኑ ሰዎቻችሁ እግዚአብሔር ለእናንተ እንደሰጣችሁ
\v 15 ወንድሞቻችሁን እረፍት እስኪሰጥ ድረስ ከወንድሞቻችሁ ፊት በመሆን እነርሱንም ለመርዳት ይሄዳሉ ። እነርሱም ደግሞ አምላካችሁ እግዚአብሔር የሚሰጣቸውን ምድር ይወርሳሉ። ከዚያም በኋላ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ብዮርዳኖሴ ማዶ በፀሐይ መውጫ ወደሰጣችሁ ወደ ርስታችሁ ትመለሳላችሁ፤ ትወርሳላችሁም።
\s5
\v 16 እነርሱም ለኢያሱ እንዲህ ብለው መለሰለት፦ያዘዝኸንን ነገር ሁሉ እናደርጋለን፤ ወደምትልከንም ስፍራ ሁሉ እንሄዳለን።
\v 17 ለሙሴ እንደ ታዘዝን ለአንተ ደግሞ እንታዘዛለን። ከሙሴ ጋር እንደ ነበረ እግዚአብሔር አምላክህ ብቻ ከአንተጋር ይሁን።
\v 18 በትእዛዝህ ላይ የሚያምፅና ቃልህን የማይታዘዝ ማንም ቢሆን ይገደል። ብቻ ጽና፥ በርታ።
\s5
\c 2
\p
\v 1 የነዌም ልጅ ኢያሱ፦ "ሄዳችሁ ምድሪቱን፥ በተለይም ኢያሪኮን ሰልሉ ብሎ ከሰጢም ሁለት ሰዎች በስውር ላከ። እነርሱም ሄደው ረዓብ ወደምትባል ሴተኛ አዳሪ ቤት ገቡ፥ በዚያም አደሩ።
\v 2 ለኢያሪኮም ንጉሥ፦ እነሆ የእስራኤል ሰዎች አገሩን ሊሰልሉ ወደዚህ ገብተዋል ብለው ነገሩት።
\v 3 የኢያሪኮም ንጉሥ፡-አገሩን ሁሉ ሊሰልሉ ወደ አንቺ የመጡትንና ወደ ቤትሽ የገቡትን ሰዎች አውጪ ብሎ ወደ ረዓብ መልእክት ላከ።
\s5
\v 4 ነገር ግን ሴቲቱም ሁለቱን ሰዎች ወስዳ ሽሸገቻቸው። እርስዋም፦አዎን ሰዎቹ ወደ እኔ መጥተዋል፥ ነገር ግን ከወዴት እንደ ሆኑ አላወቅሁም፤
\v 5 የከተማውም በር የሚዘጋበት ጊዜ ላይ ሰዎቹ ወጡ፤ ወዴት እንደ ሄዱ አላውቅም፤ፈጥናችሁ ከተከተላችሁ ምናልባት ልትይዙአቸው ትችላላችሁ አለች።
\s5
\v 6 እርስዋ ግን ወደ ሰገንቱ አውጥታቸው፤ በዚያም በጣሪያ ውስጥ ባዘጋጀችው በተልባ እግር ውስጥ ሸሸጋቸው።
\v 7 ሰዎቹ ወደ ዮርዳኖስ መሻገሪያ በሚወስደው መንገድ አሳደዱአቸው። አሳዳጆችም እንደወጡ በሮቹ ተቆለፉ።
\s5
\v 8 ሰዎቹም ሳይተኙ ሴቲቱ ወደ እነርሱ ወደ ሰገነቱ ወጣች።
\v 9 ሰዎቹንም እንዲህ አለቻቸው፦እግዚአብሔር ምድሪቱን አሳልፎ እንደሰጣችሁ እናንተንም መፍራት በላያችን እንደ ወደቀ፤ በምድሪቱም በሚኖሩት ሁሉ ከፊታችሁ እንደ ቀለጡ አውቃለሁ።
\s5
\v 10 ከግብፅ ምድር በወጣችሁ ጊዜ እግዚአብሔር የኤርትራን ባሕር በፊታችሁ እንዳደረቀ፤ በዮርዳኖስም ማዶ በነበሩት እናንተም ፈጽማችሁ ባጠፋችኋቸው በሁለቱ በአሞራውያን ነገሥታት፥በሴዎንና በዐግ ያደረጋችሁትን ሰምተናል።
\v 11 ይህን በሰማን ጊዜ ልባችን ቀለጠ፤ አምላካችሁም እግዚአብሔር በላይ በሰማይ በታችም በምድር እርሱ አምላክ ነውና ከእናንተ የተንሣ ከዚያ ወዲያ ለማንም ነፍስ አልቀርለትም።
\s5
\v 12 እሁንም እባካችሁ እኔ ለእናንተ ቸርነት እንዳደረግሁ እናንተ
\v 13 ደግሞ ለአባቴ ቤት ቸርነት እንድታደርጉ፥ አባቴንና እናቴን፥ ወንድሞቼንና እኅቶቼንና ቤተ ሰቦቻቸውን ሁሉ እንድታድኑ፤ እንዲሁም ከሞት እንድታድኑን በእግዚአብሔር ማሉልኝ እውነተኛ ምልክትም ስጡኝ።
\s5
\v 14 ሰዎቹ፦ "ይህን ነገራችንን ባትገልጪ ነፍሳችን በነፍሳችሁ ፋንታ እስከሞት እንኳ ይሆናል፤ እግዚአብሔርም ምድሪቱን በሰጠን ጊዜ ምሕረትን እናደርጋለን እንዲሁም ታማኝ ሆነን እንገኛለን፤" አሉአት።
\s5
\v 15 ቤትዋም በከተማ ቅጥር የተጠጋ ስለነበረ በመስኮቱ በገመድ አወረደቻቸው።
\v 16 እርስዋም፦አሳዳጆቹ እንዳያገኙአችሁ ወደ ተራራው ሂዱ አሳዳጆቹም እስኪመለሱ ድረስ በዚያ ሦስት ቀን ተሰውራችሁ ተቀመጡ ኋላም መንገዳችሁን ትሄዳላችሁ አለቻቸው።
\v 17 ሰዎቹም አሉአት፦ይህን የምንልሽን ካላደረግሽ እኛም ከዚህ ካማልሽን መሐላ የተነሣ የሰጠንሽን ተስፋ ከመጠበቅ ነፃ እንሆናለን።
\s5
\v 18 እነሆ እኛ ወደ አገሩ በገባን ጊዜ ይህን ቀይ ክር እኛን ባወረድሽበት መስኮት በኩል እሰሪው ፤አባትሽንም እናትሽንም ወንድሞችሽንም የእባትሽንም ቤተ ሰብ ሁሉ ወደ አንቺ ቤት ሰብስቢ።
\v 19 ከቤትሽም ደጅ ወደ ሜዳ የሚወጣ ሁሉ ደሙ በራሱ ላይ ይሆንበታል፤ እኛም ንጹሐን እንሆናለን። ነገር ግን ከአንቺ ጋር በቤቱ ውስጥ ያለውን አንድ ሰው ቢነካው ደሙ በእኛ ራስ ላይ ይሆናል።
\s5
\v 20 ነገር ግን ይህንን ጉዳያችንን ብትገልጪ እኛም ከዚህ ካማልሽን መሐላ የተነሣ የሰጠንሽን ተስፋ ከመጠበቅ ነፃ እንሆናለን።
\v 21 እርስዋም፦ እንደቃላችሁ ይሁን አለች። ሰደደቻቸውም እነርሱም ሄዱ፤ ቀዩንም ክር በመስኮቱ በኩል አንጠለጠልችው።
\s5
\v 22 እነርሱም ሄደው ወደ ተራራው ደረሱ፥ አሳዳጆቹም እስኪመለሱ ድረስ እዚያ ለሦስት ቀናት ቆዩ። በመንገዱ ሁሉ ፈልገው አላገኙአቸውም።
\s5
\v 23 ሁለቱም ሰዎች ተመለሱ፤ ከተራራውም ወርደው ተሻገሩ ወደ ነዌም ልጅ ወደ ኢያሱ መጡ፤ የደረሰባቸውንም ሁሉ ነገሩት።
\v 24 ለኢያሱም እንዲህ አሉት፦ በእውነት እግዚአብሔር ይህን አገር ሁሉ በእጃችን አሳልፎ ሰጥቶናል፤ በአገሩም ውስጥ ያሉ ሰዎች ሁሉ ከእኛ የተነሣ እየቀለጡ አሉት።
\s5
\c 3
\p
\v 1 ኢያሱም በጠዋት ተነሣ፥ እነርሱም ከሰጢም ተነሥተው ወደ ዮርዳኖስ መጡ፤ እርሱና የእስራኤልም ልጆች ሁሉ ሳይሻገሩም በዚም ሰፈሩ።
\s5
\v 2 ከሦስት ቀንም በኋላ አለቆች በሰፈሩ መካከል ሄዱ።
\v 3 ሕዝቡንም እንዲህ ብለው አዘዙ፦የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ሌዋውያን ካህናት ተሸክመውት ባያችሁ ጊዜ ከሰፈራችሁ ተነሥታችሁ መከትል አለባችሁ።
\v 4 በእናንተና በታቦቱ መካከል ያለው ርቀት ሁለት ሺህ ክንድ ያህል ይሁን። በዚህ መንገድ በከዚሄ በፊት አልሄዳችሁበትምና የምትሄዱበትን መንገድ እንድታውቁ ወደ ታቦቱ አትቅረቡ።
\s5
\v 5 ኢያሱም ለሕዝቡ እንዲህ አለ፦ እግዚእአብሔር በመካከላችሁ ድንቅ ነገር ያደርጋልና ነገ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር ቀድሱ።
\v 6 ከዚያም ኢያሱ ካህናቱን እንዲህ አለ፦ የቃል ኪዳኑን ታቦት ተሸክማችሁ በሕዝቡ ፊት እለፉ። ስለዚህ የቃል ኪዳኑን ታቦት ተሸክመው በሕዝቡ ፊት አለፉ።
\s5
\v 7 እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለ፦ በዚህ ቀን በእስራኤል ሁሉ ፊት ከፍ ከፍ አደርጋለሁ። ከሙሴ ጋር እንደ ነበርሁ እንዲሁ ከእንተ ጋር መሆኔን ያውቃሉ።
\v 8 አንተም የቃል ኪዳኑን ታቦት የሚሸከሙትን ካህናት፦ በዮርዳኖስ ውኃ ዳር ስትደርሱ በዮርዳኖስ ውስጥ ቁሙ ብለህ ታዛቸዋለህ።
\s5
\v 9 ከዚያም ኢያሱ ለእስራኤል ሕዝብ እንዲህ አለ፦ ወደዚህ ቀርባችሁ የእግዚአብሔርን የአምላካችሁን ቃል ስሙ አለ።
\v 10 ሕያው አምላክ በመካከላችሁ እንደ ሆነና እርሱም ኤዊያዊውንም ፈርዛዊውንም ጌርጌሳዊውንም አሞራዊውንም ኢያቡሳዊውንም ከፊታችሁ ፈጽሞ እንደሚያወጣ በዚህ ታውቃላችሁ።
\v 11 እነሆ የምድር ሁሉ ጌታ የቃል ኪዳን ታቦት በፊታችሁ በዮርዳኖስ ውስጥ ያልፋል።
\s5
\v 12 አሁምን ከእስራኤል ነገዶች አሥራ ሁለት ሰዎችን ምረጡ፤ ከየነገዱ አንድ አንድ ሰው ይሁን።
\v 13 እንዲህም ይሆናል የምድርም ሁሉ ጌታ የእግዚአብሔርን ታቦት የተሸከሙ ካህናት የእግራቸው ጫማ በዮርዳኖስ ውኃ ሲቆም የዮርዳኖስም ውኃ ይቆማል፤ ከላይ የሚፈሰው ውኃ ሳይቀር መፍሰሱን ያቆማል፤ እንደ ክምርም ሆኖ ይቆማል።
\s5
\v 14 ሕዝቡም ዮርዳኖስን ለመሻገር ከድንኳናቸው በወጡ ጊዜ የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙ ካህናት በሕዝቡ ፊት ቀድመው ሄዱ።
\v 15 የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙ ወደ ዮርዳኖስ እንደመጡ፤ እግራቸውም የውኃውን ጫፍ በጠለቁ ጊዜ (በመከር ወራት ሁሉ ዮርዳኖስ እጅግ ሞልቶ እንደሚፈስ)
\v 16 ከላይ የሚወርደው ውኃ ቆመ፤ በጻርታን አጠገብ ባለችው አዳም በምትባል ከተማ በሩቅ ቆሞ እንደ ክምርም ሆነ፤ ወደ ዓረባ ባሕር ወደ ጨው ባሕር የሚወርደውም ውኃ ፈጽሞ ተቋረጠ፤ ሕዝቡም በኢያሪኮ አጠገብ ተሻገሩ።
\s5
\v 17 የእስራኤልም ሕዝቡ ሁሉ ዮርዳኖስን ፈጽመው አስኪሻሩ ድረስ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት የተሸከሙ ካህናት በዮርዳኖስ መካክል በደረቅ መሬት ጸንተው ቆመው ነበር።
\s5
\c 4
\p
\v 1 ሕዝቡ ሁሉ ዮርዳኖስን ፈጽመው በተሻገሩ ጊዜ እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለ፦
\v 2 "ከሕዝቡ ከየነገዱ አንድ አንድ ሰው፥ አሥራ ሁለት ሰዎች ምረጥ።
\v 3 እንዲህ ብለህ ትእዛዝ ስጣቸው፦"በዮርዳኖስ መካከል የካህናት እግር ከቆመበት ስፍራ አሥራ ሁለት ድንጋዮችን አንሡ፤ ተሸክማችሁም በዚህ ሌሊት በምታድሩበት ስፍራ አኑሩአቸው።"
\s5
\v 4 ከዚያም ኢያሱ ከእያንዳንዱ የእስራኤል ነገድ አንድ አንድ ሰው የመረጣቸውን አሥራ ሁለት ሰዎች ጠራቸው።
\v 5 ኢያሱም አላቸው፦"በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ታቦት ፊት በዮርዳኖስ መካከል፤ እያንዳንዱም ሰው በጫንቃው ከአንዳንድ ድንጋይ ጋር በእስራኤል ልጆች ሁሉ ነገድ ቁጥር አሥራ ሁለት ድንጋዮችን ተሸክመው ይለፉ።
\s5
\v 6 ፤ልጆቻችሁም በሚመጣው ዘመን፦ እነዚህ ድንጋዮች ለእናንተ ምን ትርጉም አላቸው? ብለው በሚጠይቁበት ጊዜ ይህ በመካከላችሁ ምልክት ይሆናል።
\v 7 በዚያን ጊዜ እናንተም እንዲህ ብላችሁ ትመልሳላችሁ፦ "በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት ፊት የዮርዳኖስ ውኃ ስለተቋረጠ ነው። በተሻገሩም ጊዜ የዮርዳኖስ ውኃ ቆመ፤ እነዚህም ድንጋዮች ለእስራኤል ልጆች ለዘላለም መታሰቢያ ይሆናሉ።"
\s5
\v 8 የእስራኤልም ልጆች ኢያሱ እንዳዘዛቸው አደረጉ፤ እግዚአብሔርም ኢያሱን እንደ ተናገረው በእስራኤል ነገድ ቁጥር ከዮርዳኖስ መካከል እንደ እስራኤል ነገድ ቁጥር አሥራ ሁለት ድንጋዮች አንሥተው ወደሚያድሩበት ስፍራ ወሰዱ። በዚያም በሚያድሩበት ስፍራ አኖሩአቸው።
\v 9 ኢያሱም የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙ ካህናት እግሮች በቆሙበት ስፍራ በዮርዳኖስ መካከል ሌሎችን አሥራ ሁለት ድንጋዮች ተከለ። እስከ ዛሬም ድረስ መታሰቢያ ሆነው በዚያ አሉ።
\s5
\v 10 ሙሴም ኢያሱን እንዳዘዘው ሁሉ እግዚአብሔር ኢያሱን ለሕዝቡ እንዲነገር ያዘዘው ነገር ሁሉ እስክፈጸም ድረስ ታቦቱን የተሸከሙ ካህናት በዮርዳኖስ መካከል ቆመው ነበር። ሕዝቡም ፈጥነው ተሻገሩ።
\v 11 ሕዝቡም ሁሉ ፈጽመው መሻገራቸውን በጨረሱ ጊዜ የእግዚአብሔር ታቦትና ካህናቱ በሕዝቡ ፊት ተሻገሩ።
\s5
\v 12 ሙሴም እንዳዘዘቸው የሮቤል ልጆች፥ የጋድም ልጆች፥ የምናሴም ነገድ እኩሌታ ተሰልፈው በእስራኤል ልጆች ፊት ተሻገሩ።
\v 13 አርባ ሺህ ያህል ሰዎች ጋሻና ጦራቸውን ይዘው ለጦርነት በእግዚእብሔር ፊት ወደ ኢያሪኮ ሜዳ ተሻገሩ።
\v 14 በዚያም ቀን እግዚአብሔር ኢያሱን በእስራኤል ሁሉ ፊት ከፍ አደረገው። ሕዝቡም ሙሴን እንዳከበሩት በዕድሜው ሁሉ አከበሩት።
\s5
\v 15 እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦
\v 16 "የምስክርን ታቦት የሚሸከሙትን ካህናት ከዮርዳኖስ እንዲወጡ እዘዝ።"
\s5
\v 17 ኢያሱም ካህናቱን፦ ከዮርዳኖስ ውጡ ብሎ አዘዛቸው።
\v 18 የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙ ካህናት ከዮርዳኖስ መካከል በወጡ ጊዜና የካህናቱም እግር ጫማ ደረቅ መሬት መርገጥ በጀመረ ጊዜ የዮርዳኖስ ውኃ ወደ ስፍራው ተመለሰ፤ ቀድሞም ከአራት ቀናት በፊት እንደ ነበረ በዳሩርቻው ሁሉ መፍሰስ ጀመረ።
\s5
\v 19 ሕዝቡም በመጀመሪያው ወር በአሥረኛው ቀን ከዮርዳኖስ ወጡ። ከኢያሪኮ በስተ ምሥራቅ በኩል በጌልገላ ሰፈሩ።
\v 20 ከዮርዳኖስም ውስጥ የወሰዱአቸውን አሥራ ሁለቱን ድንጋዮች ኢያሱ በጌልገላ አቆማቸው።
\v 21 ለእስራኤልም ልጆች እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ "በሚመጣው ዘመን ልጆቻችሁ አባቶቻቸውን፦ እነዚህ ድንጋዮች ምንድን ናቸው? ብለው ሲጠይቁ፥
\s5
\v 22 ለልጆቻችሁ እንዲህ ብላችሁ ታስታውቃላችሁ፦ እስራኤል ይህን ዮርዳኖስን በደረቅ ተሻገረ።
\v 23 እስክንሻገር ድረስ አምላካችሁ የኤርትራን ባሕር ከፊታችን እንዳደረቀ እንዲሁ እስክትሻገሩ ድረስ አምላካችሁ እግዚአብሔር የዮርዳኖስን ውኃ ከፊታችሁ አደረቀ።
\v 24 የእግዚአብሔርም እጅ ጠንካራ እንደ ሆነች የምድር አሕዛብ ሁሉ እንዲያውቁ አምላካችሁንም እግዚአብሔርን ለዘላለሙ እንድታከብሩ ነው።
\s5
\c 5
\p
\v 1 በዮርዳኖስ ማዶ በምዕራብ በኩል የነበሩ የአሞራውያን ነገሥታት ሁሉ፥ በታላቁም ባሕር አጠገብ የነበሩ የከነዓናውያን ነገሥታት ሁሉ፥ የእስራኤል ሕዝብ እስኪሻገሩ ድረስ የዮርዳኖስን ውኃ እግዚአብሔር እንዳደረቀ በሰሙ ጊዜ ልባቸው ቀለጠ፤ ከእስራኤልም ሕዝብ የተነሣ የአንድም ሕዝብ ነፍስ አልቀረላቸውም።
\s5
\v 2 በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር ኢያሱን እንዲህ አለው፦"የባልጩት ድንጋይ ስለት ሠርተህ የእስራኤልን ሕዝብ እንደገና ግርዛቸው።"
\v 3 ኢያሱም የባልጩት ድንጋይ ስለት ሠርቶ ግብት ሃራሎት (ትርጉሙም የግርዛት ኮረብታ) በተባለ ስፍራ የእስራኤልን ወንዶች ሁሉ ገረዛቸው።
\s5
\v 4 ኢያሱም የገረዘበት ምክንያት ይህ ነው፤ ከግብፅ የወጡት ወንዶች ሁሉ ጦረኞችን ሁሉ ጭምር ከግብፅ ከወጡ በኋላ በመንገድ ላይ በምድረ በዳ ሞቱ።
\v 5 የወጡት ሕዝብ ሁሉ ተገርዘው ነበር፤ ነገር ግን ከግብፅ በወጡበት መንገድ በምድረ በዳ የተወለዱት ሕዝብ ሁሉ አልተገረዙም ነበር።
\s5
\v 6 ከግብፅ የወጡ የእስራኤል ሕዝብና ጦረኞች ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ባለመስማታቸው እስኪሞቱ ድረስ አርባ ዓመት በምድረ በዳ ይጓዙ ነበር ። እግዚአብሔርም ወተትና ማር የምታፈስሰውን ምድር ለእኛ ይሰጠን ዘንድ ለአባቶቻቸው የማለላቸውን ምድር እንደማያሳያቸው ማለላቸው።
\v 7 እግዚአብሔር በእነርሱ ፋንታ ያስነሳቸው በመንገድ ሳሉ ሳይገረዙ የነበሩ ኢያሱም ገረዛቸው እነዚህን ልጆቻቸው ነበሩ።
\s5
\v 8 ሕዝቡም ሁሉ በተገዙ ጊዜ እስኪድኑ ድረስ በሰፈር ውስጥ በየስፍራቸው ነበሩ።
\v 9 እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለ፦ ዛሬ የግብፅን ነውር ከእናንተ ላይ አንከባልያለሁ አለው፤ ስለዚህ የዚያ ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ ጌልገላ ተብሎ ይጠራል።
\s5
\v 10 የእስራኤልም ሕዝብ በጌልገላ ሰፈሩ። ከወሩም በአሥራ አራተኛው ቀን በመሸ ጊዜ በኢያሪኮ ሜዳ ፋሲካ አደረጉ።
\v 11 ከፋሲካውም በዓል ቀን በኋላ በዚያው ዕለት የምድሪቱን ፍሬ ቂጣና ቆሎ በሉ።.
\s5
\v 12 ከምድሪቱም ፍሬ ከበሉበት ቀን በኋላ መና ተቋረጠ። ከዚያም ጊዜ ጀምሮ ለእስራኤል ልጆች መና አልነበራቸውም፤ ነገር ግን በዚያ ዓመት የከነዓንን ምድር ፍሬ በሉ።
\s5
\v 13 ኢያሱ ወደ ኢያሪኮ አጠገብ በነበረ ጊዜ ዓይኖቹን አንሥቶ ተመለከተ፥ እነሆም ሰይፍ በእጁ የያዘ ሰው በፊቱ ቆሞ ነበር፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ፦ ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህን? አለው።
\s5
\v 14 እርሱም፦ አይደለሁም እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ እዚህ መጥቼአለሁ አለ። ኢያሱም ወደ ምድር በግምባሩ ተደፍቶ ሰገደና፦ ጌታዬ ለአገልጋዩ የሚነግረው ምንድን ነው? አለው።
\v 15 የእግዚአብሔርም ሠራዊት አለቃ ኢያሱን፦ አንተ የቆምህበት ስፍራ የተቀደሰ ነውና ጫማህን ከእግህ አውልቅ አለው። ኢያሱም እንዲሁ አደረገ።
\s5
\c 6
\p
\v 1 ከእስራኤልም ሠራዊት የተነሣ የኢያሪኮ በሮች መጽሞ ተዘግተው ነበር። ወደ እርስዋም የሚገባና የሚወጣ ማንም አልነበረም።
\v 2 እግዚአብሔርም ኢያሱን አለው፦ ተመልከት፥ ኢያሪኮንና ንጉሥዋን የሠለጠኑ ወታደሮችዋንም በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼአለሁ።
\s5
\v 3 ሠራዊቶኞቻችሁ ሁሉ ከተማይቱን አንድ ጊዜ መዞር አለባቸው። ይህንንም ለስድስት ቀናት አድርጉት።
\v 4 ሰባትም ካህናት ሰባት ቀንደ መለከት በታቦቱ ፊት ይሸከሙ፤ በሰባተኛውም ቀን ከተማይቱን ሰባት ጊዜ ይዙሩ፥ ካህናቱም ቀንደ መለከቱን ይንፉ።
\s5
\v 5 ቀንደ መለከቱም ባለማቋረጥ ሲነፋ የመለከቱንም ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ታላቅ ጩኸት ይጩኽ፥ የከተማይቱም ቅጥር ይወድቃል። እያንዳንዱ ወታደር ወደፊት በመሄድ ማጥቃት አለባቸው።
\s5
\v 6 ከዚያም የነዌ ልጅ ኢያሱ ካህናቱን ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ የቃል ኪዳኑን ታቦት ተሸከሙ፥ ሰባትም ካህናት ሰባት ቀንደ መለከት ወስደው በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ይሂዱ አላቸው።
\v 7 ሕዝቡንም፦ ሂዱ፥ ከተማይቱንም ዙሩ፥ሠራዊቱም በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ይሂዱ አለ።
\s5
\v 8 ኢያሱም ለሕዝቡ እንደተናገረው ሰባቱ ካህናት ሰባቱን ቀንደ መለከት በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ይዘው ወደፊት እያለፉ ቀንደ መለከቱንም ይነፉ ነበር። የእግዚአብሔርም ቃል ኪዳን ታቦት ከኋቸው ይከተላቸው ነበር።
\v 9 ሠራዊቱም በካህናቱ ፊት ቀንደ መለከታቸውን እየነፉ ይሄዱ ነበር፤ ከዚያም ከቃል ኪዳን ታቦት ኋላ ደጀን ጦር ይሄድ ነበር፤እንዲሁም ካህናቱ ቀንደ መለከታቸውን ያለማቋረጥ ይነፉ ነበር።
\s5
\v 10 ኢያሱ ግን ሕዝቡን እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፦ እኔ ጩኹ እስከምልበት ቀን ድረስ አትጩኹ፥ ከአፋችሁም ድምፅ አይውጣ፤ በዚያን ጊዜ ብቻ ትጮኻላችሁ።
\v 11 ስለዚህ እግዚአብሔር የዚያን ቀን የቃል ኪዳን ታቦት አንድ ጊዜ ከተማይቱን እንዲዞር አደረገው፤ ከዚያም ወደ ማደሪያቸው ገቡ፤ ሌሊቱንም እዚያው አደሩ።
\s5
\v 12 ከዚያም ኢያሱ ማለዳ ተነሣ ካህናቱም የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ተሸከሙ።
\v 13 ሰባቱም ካህናት ሰባት ቀንደ መለከት ይዘው በእግዚአብሔር ታቦት ፊት በቀስታ እየሄዱ ቀንደ መለከቱንም ይነፉ ነበር። ሠራዊቱም በፊታቸው ይሄዱ ነበር። የደጀን ጦር ከእግዚአብሔር ታቦት ኋላ በሚድበት ጊዜ የቀንደ መለከት ድምፅ ያልማቋረጥ ይሰማ ነበር።
\v 14 በሁለተኛውም ቀን ከተማይቱን አንድ ጊዜ ዞረው ወደ ሰፈር ተመለሱ፤ ስድስት ቀንም እንዲሁ አደረጉ።
\s5
\v 15 በሰባተኛውም ቀን ሲነጋ ማልደው ተነሡ፥ ከዚህ በፊት በተለመደው ሁኔታ ከተማይቱን ሰባት ጊዜ ዞሩ፤ ከተማይቱን ሰባት ጊዜ የዞሩት በዚያ ቀን ነው።
\v 16 በሰባተኛውም ቀን ካህናቱ ቀንደ መለከቱን ሲነፉ ኢያሱ ሕዝቡን አዘዘ፦ እግዚአብሔር ከተማይቱን ሰጥቶአችኋልና ጩኹ።
\s5
\v 17 ከተማይቱና በእርስዋም ያለው ሁሉ ለእግዚአብሔር የተለየና ለጥፋት ይሆናሉ። የላክናቸውን መልክተኞች ስለ ሸሸገች ሴተኛ አዳሪዋ ረዓብ ብቻና ከእርስዋም ጋር በቤትዋ ውስጥ ያሉት ሁሉ በሕይወት ይኖራሉ።
\v 18 እናንተ ግን ለጥፋት የተለዩ ነገሮችን ከለያችሁት በኋላ አንዳች እንዳትወስዱ ራሳችሁን ጠብቁ። ለጥፋትም ከሆነው ነገር አንዳች የወሰዳችሁ እንደ ሆነ የእስራኤልን ሰፈር እንዲጠፋ ታደርጉታላችሁ፥ ችግርም ታመጣላችህ።
\v 19 ብር፥ ወርቅ፥ ናስና ከብረት የተሠሩ ዕቃዎች ሁሉ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ይሁን። ወደ እግዚአብሔርም ግምጃ ቤት ይግባ።
\s5
\v 20 ሕዝቡም ጮኹ፥ ካህናቱም ቀንደ መለከቱን ነፉ። ሕዝቡም የቀንደ መለከቱን ድምፅ በሰሙ ጊዜ ታልቅ ጩኸት ጮኹ፥ ቅጥሩም ሲወድቅ፤ ሕዝቡም እያንዳንዱ አቅንቶ ወደ ፊቱ ወደ ከተማይቱ ወጣ፤ ከተማይቱንም ያዙ።
\v 21 በከተማይቱም የነበሩትን ሁሉ ወንዱንና ሴቱን፥ ሕፃኑንና ሽማግሌውን፥ በሬውንም ፥በጉንና አህያውን በሰይፍ ስለት ፈጽመው አጠፉ።
\s5
\v 22 ኢያሱም ምድሪቱን የሰለሉትን ሁለቱን ሰዎች እንዲህ አላቸው፦ ወደ ሴተኛ አዳሪዋ ቤት ግቡ ከዚያም ሴቲቱንና ከእርስዋ ጋር ያሉትን ሁሉ እንደ ማላችሁላት አውጡ።
\s5
\v 23 ሰላዮቹም ወጣቶች ሄደው ረዓብን አውጧአት፤ አባትዋንና እናትዋን፥ ወንድሞችዋንም፥ አብሯት የነበሩ ቤተ ዘምዶችዋንም ሁሉ አወጡ። ከእስራኤልም ሰፈር ውጭ ወዳለው ስፍራ አመጦአቸው።
\v 24 ከተማይቱንም በእርስዋም የነበረውን ሁሉ በእሳት አቃጠሉ። ብሩ፥ ወርቅ፥የናሱና የብረት ዕቃዎች ብቻ በእግዚአብሔር ግምጃ ቤት አስቀመጡአቸው።
\s5
\v 25 ነገር ግን ኢያሪኮን ሊሰልሉ ኢያሱ የሰደዳቸውን መልክተኞች የሸሸገች ሴተኛ አዳሪዋን ረዓብን፥ የአባትዋንም ቤተ ሰብ፥አብሯት የነበሩትንም ሁሉ ኢያሱ በሕይወት እንዲሆሩ ፈቀደላቸው። እርስዋም ኢያሱ ኢያሪኮን እንዲሰልሉ የላካቸውን ሰዎች ስለሸሸገች በእስራኤል መካከል እስከ ዛሬ ድረስ ትኖራለች።
\s5
\v 26 በዚያን ጊዜም ኢያሱ እንዲህ ሲል አዘዛቸው፦ ይህችን ኢያሪኮ ከተማን ለመሥራት የሚነሣ ሰው በእግዚአብሔር ፊት የተረገመ ይሁን። መሠረትዋን ሲጀምር በኩር ልጁ ይሙት፥ እርዋንም ሲያቆም ታናሹ ልጁ ይሙት፥ ብሎ ማለ።
\v 27 እግዚአብሔርም ከኢያሱ ጋር ነበር፤ ዝናውም በምድር ሁሉ ላይ ወጣ።
\s5
\c 7
\p
\v 1 የእስራኤል ሕዝብ ግን እንዲጠፉ ከተለዩ ነገሮች በመውሰድ ታማኝነትን አጎደሉ። ከይሁዳ ነገድ የሆነ አካን፥ እርሱም የከርሚ ልጅ፥ የዘንበሪ ልጅ፥ የዛራ ልጅ፥ እንዲጠፉ ከተለዩት ነገሮች ወስደ፤ የእግዚአብሔርም ቁጣ በእስራኤል ሕዝብ ላይ ነደደ።
\s5
\v 2 ኢያሱም ከቤቴል በምሥራቅ በኩል በቤት አዌን አጠገብ ወዳለችው ወደ ጋይ ከኢያሪኮ ሰዎችን ላከ። እርሱም፦ ውጡ ምድሪቱንም ሰልሉ ብሎ ተናገራቸው። ሰዎቹም ወጡ፥ ጋይንም ሰለሉ።
\v 3 እነርሱም ወደ ኢያሱ ተመልሰው፡- ሕዝብን ሁሉ ወደ ጋይ አትላክ። ጋይን እንዲመቱ ሁለት ወይም ሦስት ሺህ ያህል ሰዎች ብቻ ይላክ። የጋይ ሰዎች በቁጥር ጥቂቶች ስለሆኑ ሕዝብ ሁሉ በውጊያ እንዲደክም አታድርግ።
\s5
\v 4 ከሠራዊቱ ሦስት ሺህ ያህል ሰዎች ብቻ ወደዚያ ወጡ፤ እነርሱም ከጋይ ሰዎች ፊት ሸሹ።
\v 5 የጋይም ሰዎች ከእነርሱ ሠላሳ ስድስት ያህል ሰዎችን መቱ፥ ከበሩ እስከ ሸባሪም ድረስ አባረሩአቸው፤ በቁልቁለቱም መቱአቸው። የሕዝቡም ልብ ፈራ፤ ድፍረትንም አጡ።
\s5
\v 6 ኢያሱም ልብሱን ቀደደ። እርሱና የእስራኤልም ሽማግሌዎች በእግዚአብሔር ታቦት ፊት እስከ ማታ ድርስ በግምባራቸው ተደፉ፤ በራሳቸውም ላይ ትቢያ ነሰነሱ።
\v 7 ኢያሱም አለ፦ ወዮ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፦ ይህን ሕዝብ ቀድሞኑ ዮርዳኖስን ለምን አሻገርኸው? እንዲያጠፉን በአሞራውያን እጅ ለምን አሳልፈህ ሰጠሃን? ከዚህ የተለየ ምርጫ ማድረግ በቻልንና በዮርዳኖስም ማዶ በተመቀመጥን ይሻለን ነበር።
\s5
\v 8 ጌታ ሆይ የእስራኤል ሕዝብ በጠላቶቻቸው ፊት ከሸሹ በኋላ ምን ማለት እችላለሁ?
\v 9 ይህንን ከነዓናውያንና በምድሪቱም የሚኖሩ ሁሉ ይሰማሉ። እነርሱም ይከብቡናል፥ በምድር ያሉትም ሕዝብ ስማችን እንዲረሳ ያደርጋሉ። ለታላቁ ስምህስ የምታደርገው ምንድን ነው?
\s5
\v 10 እግዚአብሔርም ኢያሱን አለው፦ተነስተህ ቁም! ለምን በግምባርህ ተደፍተሃል?
\v 11 እስራኤል ኃጢአትን አድርጎአል። ያዘዝኋቸውንም ቃል ኪዳኔን አፍርሰዋል። ለጥፋት ከተለዩት ነገሮችን ሰርቀዋል፤ ሰርቀው የወሰዱትንም ኃጢአት በዕቃቸውም ውስጥ ሸሸጉት።
\v 12 በዚህም ምክንያት የእስራኤል ሕዝብ በጠላቶቻቸው ፊት መቆም አይችሉም። ራሳቸው ለጥፋት የተለዩ ሆነው በጠላቶቻቸው ፊት ሸሹ። በመካከላችሁ እስካሁን ያለውን መወገድ ያለበትን እርም ከመካከላችሁ ካላጠፋችሁ ከዚህ በኃላ ከእናንተ ጋር አልሆንም።
\s5
\v 13 ተነሣና ሕዝቡን ቀድስልኝ፤ እንዲህም በላቸው፦ራሳችሁን ለነገ ለእግዚአብሔር ቀድሱ ይላል የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር፤ እስራኤል ሆይ ፥ሊጠፉ የሚገቡ ነገሮች እስካሁን በመካከላችሁ አለ። መጥፋት ያልባቸው ነገሮች ከመካከላችሁ እስክታጠፉ ድረስ በጠላቶቻችሁ ፊት መቆም አትችሉም።
\s5
\v 14 ነገም ራሳችሁን በየነገዳችሁ ታቀርባላችሁ፤ እግዚአብሔርም በዕጣ የሚለየው ነገድ በየወገኖቹ ይቀርባል። እግዚአብሔርም የሚለየው ወገን በየቤተ ሰቦቹ ይቀርባል። እግዚአብሔርም የሚለየው ቤተ ሰብ አንድ በአንድ ይቀርባል።
\v 15 ለጥፋትም የተለየ ነገር የተገኘበት ሰው የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን በማፍረሱና በእስራኤልም ላይ ክፉ ነገር እንዲመጣ በማድረጉ እርሱና ለእርሱም ያለው ነገር ሁሉ በእሳት ይቃጠላል።
\s5
\v 16 ኢያሱም ማልዶ ተነሣ፥ እስራኤልንም በየነገዶቻቸው አቀረበ፤ የይሁዳም ነገድ ተለየ።
\v 17 የይሁዳንም ወገን አቀረበ፥የዛራም ወገን ለየ። የዛራንም ወገን እያንዳንዱን አቀረበ፤ ዘንበሪም ተለየ።
\v 18 የቤተ ሰቡንም እያንዳንዱን አቀረበ፤ ከይሁዳም ነገድ የሆነ የከርሚ ልጅ የዘንበሪ ልጅ የዛራ ልጅ አካን ተለየ።
\s5
\v 19 ከዚያ ኢያሱ አካንን አለው፦ ልጄ ሆይ፥ በእስራኤልም አምላክ ፊት እውነቱን ተናገር፥ ለእርሱም ተናዘዝ። ያደረግኸውንም ንገረኝ፤ ከእኔም አትሸሽግ።
\v 20 አካንም መልሶ ኢያሱን እንዲህ አለ፦ በእውነት የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን በድያለሁ። ያደረግሁትም ይህንን ነው፦
\v 21 በዘረፋ መካከል አንድ የሚያምር የባቢሎን ኮት፥ ሁለት መቶም ሰቅል ብር፥ ሚዛኑም አምሳ ሰቅል የሆነ ወርቅ አይቼ ተመኘኋቸው፥ ወሰድኋቸውም። እነሆም፥ በድንኳኔ ውስጥ በመሬት ተሸሽገዋል፥ ብሩም ከሁሉ በታች ነው አለው።
\s5
\v 22 ኢያሱም መልእክተኞችን ሰደደ፥ ወደ ድንኳኑም ሮጡ፤ ዕቃዎቹም ነበሩ። በድንኳኑም ውስጥ ተሸሽጎ አገኙት ብሩም ከበታች ነበረ።
\v 23 ከድንኳኑም መካከል ዕቃዎቹን ወስደው ወደ ኢያሱና ወደ እስራኤል ሕዝብ ሁሉ አመጡት። በእግዚአብሔርም ፊት አኖሩት።
\s5
\v 24 ኢያሱና እስራኤል ሁሉ የዛራን ልጅ አካንን፥ ብሩንም፥ ኮቱንም፥ ወርቁንም፥ ወንዶችንና ሴቶች ልጆቹንም፥ በሬዎቹንም፥ አህያውዎቹንም፥ በጎቹንም፥ ድንኳኑንም፥ ያለውንም ሁሉ ወስደው ወደ አኮር ሸለቆ አመጡአቸው።
\s5
\v 25 ኢያሱም እንዲህ አለው፦ ለምን አስጨነቅኸን? እግዚአብሔርም ዛሬ ያስጨንቅሃል። እስራኤልም ሁሉ በድንጋይ ወገሩት፤ሁሉንም በእሳትም አቃጠሉአቸው፥ በድንጋይም ወገሩአቸው።
\v 26 በላዩም እስከ ዛሬ ድረስ ያለ ታላቅ የድንጋይ ክምር ሆነ። እግዚአብሔርም ከቁጣው ትኩሳት ተመለሰ። ስለዚህም የዚያ ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ የአኮር ሸለቆ ነው።
\s5
\c 8
\p
\v 1 እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለ፦ አትፍራ አትደንግጥ። ጦረኞችንም ሁሉ ከአንተ ጋር ውሰድ ተነሥተህም ወደ ጋይ ውጣ። ተመልከት፥ የጋይን ንጉሥ፥ ሕዝቡን፥ ከተማውንና ምድሩን በእጅህ ሰጥቼሃለሁ።
\v 2 በኢያሪኮና በንጉሥዋም እንዳደረግህ እንዲሁ በጋይና በንጉሥዋ ታደርጋለህ፤ ምርኮውንና ከብቱን ግን ለራሳችሁ ትወስዳላችሁ። ከከተማይቱም በስተ ኋላ ድብቅ ጦር አዘጋዝጅ አለው።
\s5
\v 3 ኢያሱም ተነሣና ጦረኞቹንም ሁሉ ወደ ጋይ ወሰዳቸው። ኢያሱም ጽኑዓን ኃያላን የሆኑትን ሠላሳ ሺህ ሰዎች መርጦ በሌሊትም ሰደዳቸው።
\v 4 እንዲህም ብሎ አዘዘቸው፦ እነሆ፥ከከተማይቱ በስተ ኋላ ተደበቁ። ከከተማይቱ በጣም ርቃችሁ አትሂዱ፤ነገር ግን ሁላችሁም ተዘጋጁ።
\s5
\v 5 እኔና ከእኔም ጋር ያለው ሕዝብ ሁሉ ወደ ከተማይቱ እንቀርባለን። እንደ በፊቱ ሊያጠቁን በሚመጡበት ጊዜ ከፊታቸው እንሸሻለን።
\v 6 አስቀድመን እንደ ሸሸን፥ የምንሸሸ ይመስላቸዋል፥ ከከተማይቱ እስክናርቃቸው ድረስ ወጥተው ይከተሉናል። እንዲህም ይላሉ፦ባለፈው እንዳደረጉት ከፊታችን እየሸሹ ነው። እኛም ከእነርሱ እንሸሻለን።
\v 7 እናንተም ከተደበቃችሁበት ስፍራ መጥታችሁ ከተማዋን ትይዛላችሁ። እግዚአብሔር አምላካችሁም እርስዋን በእጃችሁ አሳልፎ ይሰጣችኋል።
\s5
\v 8 ከተማይቱንም በያዛችኋት ጊዜ በእሳት አቃጥሉአት። በእግዚአብሔርም ቃል እንደታዘዛሁ ታደርጋላችሁ። እነሆ፥ አዝዣችኋለሁ።
\v 9 ኢያሱም ሰደዳቸው፤ እነርሱም ወደሚደበቁበት ስፍራ ሄደው፥ በጋይና በቤቴል መካከልም ከጋይ በስተምዕራብ ተደበቁ። ኢያሱ ግን በዚያች ሌሊት በሕዝቡ መካከል አደረ።
\s5
\v 10 ኢያሱም ማልዶ ተነሣና ሕዝቡን አሰለፈ፤እርሱና የእስራኤልም ሽማግሌዎች የጋይን ሕዝብ አጠቁ ።
\v 11 ከእርሱም ጋር የነበሩ ጦረኞች ሁሉ ሄደው፥ ወደ ከተማይቱ ደረሱ። ወደ ከተማይቱ አጠገብ መጡና በሰሜን በኩል በጋይ ሰፈሩ። በእነርሱና በጋይ መካከል ሸለቆ ነበረ።
\v 12 አምስት ሺህ ያህል ሰዎችንም ወስዶ በቤቴልና በጋይ መካከል በከተማይቱም በምዕራብ በኩል በድብቅ አስቀመጣቸው።
\s5
\v 13 በከተማይቱ የነበሩትን ሠራዊት ሁሉ፤ በከተማይቱ ሰሜን በኩል ዋና ጦርና በከተማይቱ ምዕራብ በኩል ደጀን ጦር ጠባቂዎችን አኖሩ። ኢያሱም በዚያች ሌሊት በሸለቆው አደረ።
\v 14 የጋይም ንጉሥ ባየ ጊዜ ይህ ስለታወቀ፥እርሱና ሠራዊቱ በማለዳ ተነስተው እስራኤልን ለማጥቃት ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ሸለቆ ወዳለው ሰፍራ ቸኮሉ። ከከተማይቱ በስተ ኋላ ግን ድብቅ ጦር ለማጥቃት እንዳለ አያውቅም ነበር።
\s5
\v 15 ኢያሱና እስራኤል ሁሉ ራሳቸው በፊታቸው ድል የተነሡ መስለው ወደ ምድረ በዳው መንገድ ሸሹ።
\v 16 በከተማይቱም የነበሩ ሰዎች ሁሉ በአንድነት ከኋላቸው እንዲሄዱ ተጠሩ፤ ኢያሱንም አሳደዱት፥ ከከተማይቱም ርቀው ወጡ።
\v 17 በጋይና በቤቴልም ውስጥ እስራኤልን ለማሳደድ ያልወጣ ሰው አልነበረም። ከተማይቱንም ክፍት አድርገው፥ እስራኤልን አሳደዱ።
\s5
\v 18 እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለ፦ በእጅህ ያለውን ጦር በጋይ አነጣጥር፤ ጋይንም በእጅህ አሳልፌ እሰጥሃለሁ። ኢያሱም በእጁ ያለውን ጦር በከተማይቱ ላይ ዘረጋ።
\v 19 የተደበቁትም ሠራዊት ፈጥነው ከስፍራቸው ወጥተው ኢያሱም እጁን እንደ ዘረጋ ሮጡ። ወደ ከተማይቱም ሮጡ፤ ገብተውም ያዙአት። ፈጥነውም ከተማይቱን በእሳት አቃጠሉአት።
\s5
\v 20 የጋይም ሰዎች ወደ ኋላቸው ዞረው ተመለከቱ። ከከተማይቱ ወደ ሰማይ የሚወጣውን ጢስ አዩ፤ ወዲህ ወይም ወዲያም መንገድ ማምለጥ አልቻሉም። ወደ ምድረ በዳ ሸሽተው የነበሩ የእስራኤላውያን ጦር ሠራዊት ያሳድዱአቸው የነበሩትን ለመግጠም ተመለሱ።
\v 21 ኢያሱና እስራኤል ሁሉ ድብቅ ጦር ከተማይቱን እንደ ያዙ ወደ ላይ ከሚወጣ ጢስ ጋር ባዩ ጊዜ፥ ወደ ኋላ ተመልሰው የጋይን ሰዎች ገደሉ።
\s5
\v 22 ሌሎቹም ወደ ከተማይቱ ሄደው የነበሩ የእስራኤል ሠራዊት ለማጥቃት ወጡ። ስለዚህም የጋይ ሰዎች በእስራኤል ሠራዊት መካከል ሌሎቹ በዚህ በኩልና ሌሎቹ በዚያ በኩል ተያዙ። እስራኤልም የጋይን ሰዎች አጠቁአቸው፤ አንዳቸውም አልተረፉም፤ አላመለጡምም።
\v 23 በሕይወት የያዙትን የጋይንም ንጉሥ ማርከው ወደ ኢያሱ አመጡት።
\s5
\v 24 እንዲህም ሆነ፤ የጋይን ሰዎች ሁሉ በሜዳና በምድረ በዳ አጠገብ እስራኤልን ሲያሳድዱ በነበሩበት ቦታ ሁሉም የመጨረሻ በሰይፍ ስለት እስኪ ወድቁ ድረስ ጨርሰው ከገደሉአቸው በኋላ፥ እስራኤል ሁሉ ወደ ጋይ ተመለሱ። በሰይፍም ስለት መቱአቸው።
\v 25 በዚያም ቀን በሰይፍ ስለት የወደቁት ወንዶችና ሴቶች የጋይ ሰዎች ሁሉ አሥራ ሁለት ሺህ ነበሩ።
\v 26 ኢያሱም የጋይን ሰዎች ሁሉ ፈጽሞ እስኪያጠፋ ድረስ ጦር የዘረጋባትን እጁን አላጠፈም።
\s5
\v 27 እስራኤላውያንም እግዚአብሔር ኢያሱን እንዳዘዘው የዚያችን ከተማ ከብትና ምርኮ ለራሳቸው ወሰዱ።
\v 28 ኢያሱም ጋይን አቃጠላት፥ ለዘላለም የፍርስራሽ ክምር እንዲሆን አደረጋት። እስከ ዛሬም ድረስ ባዶ ስፍራ ሆነች።
\s5
\v 29 የጋይንም ንጉሥ እስከ ማታ ድረስ በዛፍ ላይ ሰቀለው። ኢያሱም ፀሐይ በገባች ጊዜ የንጉሡን አስክሬን ከዛፍ አወርደው፥ በከተማይቱ በር አደባባይ እንዲጥሉት አዘዘ። በላዩም ታላቅ የድንጋይ ክምር አደረጉት። እስከ ዛሬ ድረስም ይህ የድንጋይ ክምር አለ።
\s5
\v 30 ከዚያም ኢያሱ በጌበል ተራራ ላይ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር መሠዊያን ሠራ።
\v 31 የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ የእስራኤልን ሕዝብ እንዳዘዘ፦ በሙሴም ሕግ መጽሐፍ እንደተጻፈው፥ መሠዊያው ካልተወቀረ ድንጋይና ብረት ካልነካው ነበረ። በእርሱም ላይ ለእግዚአብሔር የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቀረቡ፥ የደኅንነትንም መሥዋዕት ሠዉ።
\v 32 የእስራኤልም ሰዎች ፊት በድንጋዮቹ ላይ የሙሴን ሕግ ቅጂ ጻፈባቸው።
\s5
\v 33 እስራኤል ሁሉ፥ ሽማግሌዎቻቸውም፥ አለቆቻቸውም፥ ፈራጆቻቸውም፥ በመጻተኞችና በአገሩ ልጆች ፥እኩሌቶቹ በገሪዛን ተራራ ፊት ለፊት እኩሌቶቹም በጌባል ተራራ ፊት ሆነው የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት በተሸከሙት በካህናትና በሌዋውያን ፊት ለፊት፥ በታቦቱም ፊት በወዲህና በወዲያ ቆመው ነበር። የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ እንዳዘዘ፥የእስራኤልን ሕዝብ አስቀድሞ ባረኩ።
\s5
\v 34 ከዚህም በኋላ ኢያሱ በሕጉ መጽሐፍ እንደ ተጻፉ የሕጉን ቃሎች ሁሉ በረከቱንና እርግማኑን አነበብ።
\v 35 ኢያሱም በእስራኤል ጉባኤ ሁሉ ፊት በሴቶቹም፥ በሕፃናቱም፥ በመካከላቸውም በሚኖሩት መጻተኞች ፊት ሙሴ ካዘዘው አንዲት ቃል ሳያስቀር ሁሉን አነበበ ።
\s5
\c 9
\p
\v 1 ከዚያም በዮርዳኖስ ማዶ በተራራማውና በቆላማው በታላቁ ባሕር ዳርቻ በሊባኖስም ፊት ለፊት የነበሩ ነገሥታት ሁሉ፥ ኬጢያዊ አሞራዊም ከነዓናዊም ፌርዛዊም ኤዊያዊም ኢያቡሳዊም
\v 2 ኢያሱንና እስራኤልን ሊወጉ አንድ ሆነው ተሰበሰቡ።
\s5
\v 3 የገባዖን ሰዎችም ኢያሱ በኢያሪኮና በጋይ ያደረገውን በሰሙ ጊዜ፥
\v 4 እነርሱ ደግሞ የማታለል ዕቅድ አደረጉ። ራሳችውን እንደ መልእክተኛ አድርገው ቀረቡ። ያረጀና የተቀደደ ጆኒያ ወስደው በአህዮቻቸውም ላይ ጫኑ። ደግሞም ያረጀ፥የተቀደደና የተሰፋ አሮጌ ወይን ጠጅ አቁማዳ ጫኑ።
\v 5 ያረጀ የተሰፋም ጫማ በእግራቸው አደረጉ፤ አሮጌምና የተቀደድ ልብስም ለበሱ። ለስንቅም የያዙት እንጀራ ሁሉ የደረቀና የሻገተ ነበረ።
\s5
\v 6 ኢያሱም ወደ ሰፈረበት ወደ ጌልገላ ሄደው ለእርሱና ለእስራኤል ሕዝብ፦በጣም ሩቅ አገር ከሆነ ተጉዘን የመጠን ነን፥ ከእኛ ጋር ኪዳን አድርጉ አሉ።
\v 7 የእስራኤልም ሰዎች ኤዊያውያንን፦ ምናልባት በመካከላችን የምትቀመጡ ትሆናላችሁ። እንዴትስ ከእናንተ ጋር ቃል ኪዳን እናደርጋለን? አሉአቸው።
\v 8 እነርሱም እንዲህ አሉት፦ እኛ የእናንተ አገልጋዮች ነን። ኢያሱም እንዲህ አላቸው፦ እናንተ እነማን ናችሁ? ከወዴትስ መጣችሁ?
\s5
\v 9 እነርሱም ለኢያሱ እንዲህ አሉት፦ እኛ አገልጋዮችህ ከእግዚአብሔር ከአምላክህ ስም የተነሣ እጅግ ከራቀ አገር እዚህ መጥተናል። ዝናውንም በግብፅም ያደረገውን ሁሉ፥
\v 10 በዮርዳኖስ ማዶም በነበሩት በሁለቱ በአሞራውያን ነገሥታት በሐሴቦን በንጉሥ በሴዎን በአስታሮትም በነበረው በባሳን ንጉሥ በዐግ ያደረገውን ሁሉ ሰምተናል።
\s5
\v 11 ሽማግሌዎቻችንና በአገራችን የሚኖሩት ሁሉ፦ ለጉዞአችሁም ስንቅ በእጃችሁ ያዙ። ልትገናኙአቸውም ሂዱና እንዲህ በሉአቸው፦ እኛ አገልጋዮቻችሁ ነን፤ ከእኛም ጋር ቃል ኪዳን አድርጉ።
\v 12 ወደ እናንተ ለመምጣት በተነሣንበት ቀን ይህን እንጀራ ትኩስን ለስንቅ ከቤታችን የወሰደነው ነው። ነገር ግን ተመልከቱ፥ አሁንም ደረቅና የሻግብተ ነው።
\v 13 እነዚህም የጠጅ አቁማዳዎች ስንሞላቸው አዲስ ነበሩ፤ እነሆም፥ ተቀድደዋል። ጉዞአችንም እጅግ ሩቅ ስለ ነበረ ልብሶቻችንና ጫማዎቻችን አርጅተዋል።
\s5
\v 14 እስራኤላውያንም ከስንቃቸው ወሰዱ፥ ነገር ግን ከእግዚአብሔርም ምክርን አልጠይቁም ነበር።
\v 15 ኢያሱም ከእነርሱ ጋር ስምምነት አደረገ፥ በሕይወት እንዲተዋቸውም ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ። የማኅበሩም አለቆች ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደረጉ።
\s5
\v 16 የእስራኤላውያንም ከገባዖን ሰዎች ጋር ቃል ኪዳኑን ካደረጉ ከሦስት ቀን በኋላ፥ ሰዎቹ እዚያው አጠገባቸው የሚኖሩ ጎረቤቶቻቸው መሆናቸውን ዐወቁ።
\v 17 ከዚያም እስራኤላውያን ተዘጋጅተው በሦስተኛው ቀን ወደ ከተሞቻቸው መጡ። የከተሞቻቸውም ስም ገባዖን፥ ክፈራ፥ ብኤሮትና ቂርያትይዓይሪም ናቸው።
\s5
\v 18 የሕዝቡም አለቆች በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ስም ቃል ኪዳን አድርገው ስለነበረ እስራኤላውያንም ጥቃት አልደረሱባቸውም። የእስራኤልም ሕዝብ ሁሉ በመሪዎቹ ላይ አጉረመረሙ፥
\v 19 ነገር ግን መሪዎቹ ሁሉ ለማኅበሩ እንዲህ አሉ፦ በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ስም ቃል ኪዳን ስለገባንላቸው አሁን ጉዳት ልናደርስባቸው አንችልም፥
\s5
\v 20 የምናደርግላቸው ነገር ቢኖር ይህ ነው፦ የገባንላቸውን የቃል ኪዳን ማሐላ ብናፈርስ ቁጣ እንዳይደርስብን በሕይወት እንዲኖሩ ማድረግ ነው። የሕዝቡም አለቆች ለሕዝባቸው እንዲህ አሉ፦ በሕይወት ይኑሩ።
\v 21 ስለዚህም የእስራኤል አለቆች ስለእነርሱ እንደ ተናገሩት ገባዖናውያን ለእስራኤላውያን ሁሉ እንጨት ሰባሪና ውኃ ቀጂ ሆኑ።
\s5
\v 22 ከዚያም ኢያሱ የገባዖንን ሰዎች ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ እናንተ እዚሁ በመካከላችን እየኖራችሁ፥ ከእናንተ ሩቅ ስፍራ ነው የመጠነው፥ ብላችሁ ያታለላችሁን ለምንድን ነው?
\v 23 ስለዚህ በዚህ ምክንያት እናንተ የተረገማችሁ ናችሁ፥ አንዳንዶቻችሁም ለአምላኬ ቤት ሁል ጊዜ እንጨት ሰባሪና ውኋ ቀጂ አገልጋዮች ትሆናላችሁ።
\s5
\v 24 እነርሱም ለኢያሱ እንዲህ ብለው መለሱለት፥ እግዚአብሔር አምላክህ አገልጋዩን ሙሴን እንዳዘዘው፥ ምድሪቱን በሙሉ ለእናንተ እንደሚሰጣችሁና ነዋሪዎቿንም ከፊታችሁ እንደሚያጠፋቸው በእርግጥ ለእኛ አገልጋዮችህ ተነግሮናል፥ ስለዚህ ከእናንተ የተነሣ ለሕይውታችን በመሥጋት ይህን አድርገናል።
\v 25 እነሆ አሁን በእጅህ ነን፥ መልካምና ትክክል መስሎ የታየህን ነገር ሁሉ አድርግብን።
\s5
\v 26 ስለዚህ ኢያሱ የገባዖንን ሰዎች ከእስራኤል ሰዎች እጅ አዳናቸ እስራኤላውያንም አልገደሏቸውም።
\v 27 በዚያም ዕለት ኢያሱ የገባዖንን ሰዎች ለማኅበረ ሰቡና እግዚአብሔር በመረጠው ስፍራ ለሚቆመው የእግዚአብሔር መሠዊያ እስከ ዛሬ ድረስ እንጨት ሰባሪችና ውኃ ቀጂዎች አደረጋቸው።
\s5
\c 10
\p
\v 1 የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶነጼዴቅ ኢያሱ ጋይን ይዞ ፈጽሞ እንደ ደመሰሳት፤ እንደዚሁም በኢያሪኮና በንጉሥዋ ላይ ያደረገውን ሁሉ ሰማ። እንዲሁም የገባዖን ሰዎች ከእስራኤል ጋር እንዴት የሰላም ውል አድርገው በመካከላቸው መኖራቸውን ሰማ።
\v 2 የኢየሩሳሌም ሕዝብ ፈሩ፥ ምክንያቱም ገባዖን እንደ ነገሥታቱ ከተማ ሁሉ ታላቅ ከተማ ነች። ገባዖንም ከጋይ ይልቅ ትልቅና ሰዎቿም ብርቱ ተዋጊዎች ነበሩ።
\s5
\v 3 ስለዚህ የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶኒጼዴቅ፥ ወደ የኬብሮን ንገሥ ሆነም፥ ወደ የያርሙት ንጉሥ ጲርአም ፥ ወደ የለኪሶ ንጉሥ ያፈዓና ወደ የዔግሎን ንጉሥ ዳቤር ላከ።
\v 4 ወደዚህ መጥታችሁ አግዙኝ። ገባዖን ከኢያሱና ከእስራኤላውያን ጋር የሰላም ስምምነት ስላደረጉ ገባዖንን እንምታ።
\s5
\v 5 ከዚያም አምስቱ የአሞራውያን ነገሥታት ማለት የኢየሩሳሌም ንጉሥ፥ የኬብሮን ንጉሥ፥ የያርሙት ንጉሥ፥ የለኪሶ ንጉሥና የዔግሎን ንጉሥ ያላቸውን ሠራዊታቸውን ሁሉ አስተባብረው፥ ገባዖንን ወጓት።
\s5
\v 6 የገባዖንም ሰዎች ወደ ኢያሱና ወደ ጌልገላ ሠራዊት መልእክት ላኩ። እንዲህም አሉ፦ ከአገልጋዮቻችሁ እጃችሁን አታውጡ ፍጠኑ። በፍጥነት መጥታችሁ አድኑን። በተራራማው አገር የሚኖሩ የአሞራውያን ነገሥታት ሁሉ ኃይላቸውን አስተባብረው እኛን ለማጥቃት ተሰልፈውብናልና እርዱን። እኛን ባሮችህን አትተወን ርዳን ፈጥነህ በመድረስም አድነን ብለው ላኩበት።
\v 7 ስለዚህ ኢያሱ እርሱና ተዋጊዎች ሰዎች ሁሉ ከእርሱ ጋር ጨምሮ ከጌልገላ ወጣ።
\s5
\v 8 እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለ፦ አትፍራቸው። በእጅህ አሳልፌ ሰጥቻለሁ፤ ማንም ሊቋቋሙህ አይችልም።
\s5
\v 9 ኢያሱም ከጌልገላ ሌሊቱን ሁሉ ሲገሠግሥ አድሮ ድንገት ደረሰባቸው።
\v 10 እግዚአብሔም የጠላትን ሠራዊት በእስራኤል ፊት ግራ አጋባቸው። እጅግ መታቸው። በገባዖንም ወደ ቤት ሖሮን በሚያስወጣው መንገድ እስከ ዓዜቅ መንገድ እስከ መቄዳም ድረስ ተከትሎአቸው አሳድዶ መታቸው።
\s5
\v 11 ከቤት ሖሮን ወደ ዓዜቃ ቁልቁል በሚወስደው መንገድ ላይ ከእስራኤላውያን ፊት በሚሽሹበት ጊዜ እግዚአብሔር ከሰማይ ትልልቅ ድንጋዮች ወረወረባቸው ሞቱም። በእስራኤል ሰዎች ሰይፍ ከሞቱት ይልቅ በወረደው የበረዶ ድንጋዮች የሞቱት የበለጡ ነበሩ።
\s5
\v 12 ከዚያም እግዚአብሔር ለእስራኤል በአሞራውያን ላይ ድል በሰጠበት ዕለት ኢያሱ እግዚአብሔርን ተናገረ። ኢያሱም በእስራኤል ፊት እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፦ "ፀሐይ፥ በኤሎን ሸለቆ በገባዖን ላይ ይቁም።"
\s5
\v 13 ሕዝቡ ጠላቶቹን እስኪ በቀል ድረስ፤ ፀሐይ ባለችበት ቆመች፥ ጨረቃም አልተንቀሳቀሰችም። ይህም በያሻር መጽሐፍ ላይ የተጻፈ አይደለምን? ፀሐይ በሰማዩ መካከል ቆመች፥ ለሙሉ ቀን ያህል አልተንቀሳቀሰችም ነበር።
\v 14 እግዚአብሔር የሰውን ቃል እንደዚያ የሰማበት ዕለት ከዚያ በፊት ወይም ከዚያ በኋላ አልነበረም። እግዚእአብሔር ለእስራኤል ይዋጋ ነበር።
\s5
\v 15 ኢያሱና መላው እስራኤል ወደ ጌልገላ ሰፈር ተመለሱ።
\v 16 በዚህ ጊዜ አምስቱ የአሞራውያን ገሥታት ሸሽተው በመቄዳ ዋሻ ራሳቸውን ደብቀው ነበር።
\v 17 ኢያሱም አምስቱ ነገሥታት በመቄዳ ዋሻ ውስጥ ተደብቀው መገኘታቸውን ሰማ፤
\s5
\v 18 ኢያሱም እንዲህ አለ፦ ትልልቅ ድንጋዮች ወደ ዋሻው አፍ አንከባልሉ፤ወታደሮችንም እንዲጠብቁአቸው በዚያ አቁሙ። ቸልም አትበሉ።
\v 19 ጠላቶቻችሁን አሳዱአቸው፤ ከበስተ ኋላ ሆናችሁም ጥቃት አድርሱባቸው። እግዚአብሔር አምላካችሁ በእጃችሁ አሳልፎ ስለሰጣችሁ ወደ ከተሞቻቸው እንዳይገቡ አድርጉአቸው።
\s5
\v 20 ኢያሱና እስራኤል ልጆች ፈጽሞ እስኪያጠፉ ድረስ ከታላቅ ጭፍጨፋ ጋር ጨረሱ። የተረፉት ጥቂቶቹ ብቻ ወደ ተመሸጉት ከተሞቻቸው ደረሱ።
\v 21 ከዚያም ሠራዊቱ በሙሉ በደኅና ተመልሶ ኢያሱ ወደ ሰፈረበት ወደ መቄዳ ተመለሰ። በእስራኤላውያንም ላይ አንድት ቃል ለመናገር ማንም ሰው የደፈረ አልነበረም።
\s5
\v 22 ኢያሱም እንዲህ አላቸው፦ የዋሻውንም አፍ ክፈቱና ከዋሻው እነዚህን አምስቱን ነገሥታት አምጡልኝ።
\v 23 እነርሱም እንዳለው አደረጉ። እነዚህንም አምስቱን ነገሥታት፦ የኢየሩሳሌምን ንጉሥ፥ የኬብሮንን ንጉሥ፥ የያርሙትን ንጉሥ የለኪሶን ንጉሥና የዔግሎንን ንጉሥ አውጥተው አመጡለት።
\s5
\v 24 እነዚህን ነገሥታት ወደ ኢያሱ ባማጡበት ጊዜ፥ እርሱም እያንዳንዱን የእስራኤል ሰዎች ጠራቸው፤ እንዲሁም ከእርሱ ጋር ወደ ጦርነት ሄደው የነበሩትን የጦር አዛዦችን እንዲህ አላቸው፦ እግሮቻችሁን በእነዚህ ነገሥታት አንገት ላይ አድርጉ። እነርሱም ወደ ፊት ቀርበው እግሮቻቸውን በነገሥታቱ አንገት ላይ አሳረፉ።
\v 25 ኢያሱም እንዲህ አላቸው፦ አትፍሩ፥ አትደንግጡም። በርቱ፥ ጽኑም። እግዚአብሔር አምላካችሁ በምትዋጉበት ጊዜ በጠላቶቻችሁ ሁሉ ላይ እንዲህ ያደርጋል።
\s5
\v 26 ከዚያም ኢያሱ ነገሥታቱን መትቶ ገደላቸው። በአምስትም ዛፎች ላይ ሰቀላቸው። አስክሬናቸውም እስኪመሽ ድረስ ተሰቅለው ነበር።
\v 27 የፀሐይ መጥለቂያ በሆነ ጊዜ ኢያሱ ትእዛዝ ሰጠ፦ ከዚያም የነገሥታቱን አስክሬኖች ከዛፎቹ ላይ እንዲያወርዱ ቀድሞ ራሳቸውን ደብቀው ወደነበሩበት ዋሻ ውስጥ እንዲጥሉአቸው አዘዛቸው። በዋሻውም አፍ ላይ ትልልቅ ድንጋዮች አኖሩ። እነዚያ ድንጋዮች እስከ ዛሬ ድረስ በዚያ ይገኛሉ።
\s5
\v 28 በዚህ መንገድ በዚያች ዕለት ኢያሱ መቄዳን ያዘ፤ ከንጉሥዋም ጭምር ሁሉንም በሰይፍ ገደለ። በሕይወት ያሉትንም ፍጥረት ሁሉ ምንም ሳያስቀር ፈጽሞ አጠፋቸው። በኢያሪኮ ንጉሥ ላይ ያደረገውንም ሁሉ፥ በመቄዳ ንጉሥ ላይ አደረገ።
\s5
\v 29 ኢያሱና እስራኤላውያን ከመቄዳ ወደ ልብና አለፉ። ወጓትም።
\v 30 እንደገናም ከልብና ጋር ጦርነት ገጠሙ። እግዚአብሔርም ከተማይቱንና ንጉሥዋን በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጣቸው። ኢያሱም በተከማዪቱንና በውስጧ ያለውን ሕይወት ያለውን ፍጥረት ሁሉ በሰይፍ ስለት አጠፋ። ሕይወት ያለውን ምንም አላስቀረም። በኢያሪኮ ንጉሥ ላይ ያደረገውንም በልብና ንጉሥ ላይ አደረገ።
\s5
\v 31 ከዚያም ኢያሱና እስራኤላውያን ከእርሱ ጋር ከልብና ወደ ለኪሶ አለፉ። በእርስዋም ሰፈሩ፤ ጦርነትም አደረጉ።
\v 32 እግዚአብሔርም ለኪሶን በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጠው። ኢያሱም በሁለተኛው ቀን ያዛት። በልብና እንዳደርገው በሕይወት ያለውን ፍጥረት ሁሉ በሰይፍ ስለት አጠፋ።
\s5
\v 33 ከዚያ የጌዝር ንጉሥ ሆራም ለኪሶን ለመርዳት መጣ። ኢያሱ ግን አንድ እንኳ ሳያስተርፍ እርሱንና ሕዝቡን መታቸው።
\s5
\v 34 ከዚያም ኢያሱና እስራኤላውያን በሙሉ ከለኪሶን ወደ ዔግሎን አለፉ። እዚያም ሰፈሩ፤ ወጓትም፤
\v 35 በዚያኑ ዕለት ከተማዋንም ያዟት። ኢያሱም በለኪሶ እንዳደረገ ከተማይቱንና በውስጧ የሚገኙትን ፈጽመው በሰይፍ ስለት አጠፏት።
\s5
\v 36 ከዚያም ኢያሱና እስራኤላውያን ከዔግሎን ወደ ኬብሮን አለፉ። በከተማይቱም ጦርነት አደረጉ።
\v 37 ከተማዪቱንም ከንጉሥዋ ከመንደሮቿና በውስጧ ካሉት ጭምር ሁሉ አንድም ሰው ሳያስቀሩ በሰይፍ ስለት አጠፉአቸው። በዔግሎን እንዳደርጉት ሁሉ ከተማዪቱንና በውስጧ ያለውን ሁሉ ፈጽመው ደመሰሱ። ማንኛውንም ሕይወት ያለውን ፍጥረት ሁሉ አጠፋ።
\s5
\v 38 ከዚያ ኢያሱና እስራኤል ሠራዊት ከእርሱ ጋር ወደ ኋላ ተመልሰው በደቤርን አለፉ፤ ጦርነቱንም አደረጉ።
\v 39 ከተማዪቱን ንጉሥዋንና በአካባቢ ያሉ መንደሮቿን ሁሉ ያዙ። ከተማይቱንና በውስጧ ያለውንም ሁሉ አንድም ሰው ሳያስቀሩ፥ በሰይፍ ስለት አጠፉአቸው። ኢያሱ በኬብሮን ያደረጉትን ሁሉ በዳቤርና በንጉሥዋ ላይ አደረጉት።
\s5
\v 40 ኢያሱ ተራራማውን አገር ኔጌቭን ቆላና የተራራውን ሸንተረሮች ጨምሮ ምድሪቱን በሙሉ ከነገሥታቷ ጋር አሸነፈ። ከነገሥታቱንም ያስቀረው ማንም የለም። የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረትሕይወት ያላቸውን ሁሉ ፈጽሞ አጠፋቸው።
\v 41 ኢያሱም ከቃዴስ በርኔ እስከ ጋዛ፥ የጎሶምን ምድር ሁሉ እስከ ገባዖን ድረስ በሙሉ አጠፋ።
\s5
\v 42 ኢያሱ እነዚህን ሁሉ ነገሥታትና ምድራቸውን የያዘው በአንድ ጊዜ፥ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ስለተዋጋ ነው።
\v 43 ኢያሱ ከመላው እስራኤላውያን ጋር ጌልገላ ወዳለው ሰፈር ተመለሰ።
\s5
\c 11
\p
\v 1 የአሦርም ንጉሥ ኢያቢስ ይህን በሰማ ጊዜ፥ ወደ ዮባብ ንጉሥ፥ ወደ ማዶን ንጉሥ፥ ወደ ሺምሮን ንጉሥና ወደ አዚፍ ንጉሥ መልእክት ላከ።
\v 2 ደግሞም በሰሜናዊ በተራራማው አገር፥ በየርዳኖስ ወንዝ ሸለቆ ከኪኔሬት በስተ ደቡብ ፥ በምዕራቡ ቆላማ አገሮችና ከኮር ኮረብታማ በስተ ምዕራብ ወዳሉት ነገሥታት ላከ።
\v 3 በምሥራቅና በምዕራብ ወደሚገኙት ወደ ከነዓናውያንም፥ ወደ አሞራውያን፥ ወደ ኬጢያውያን፥ ወደ ፌርዛውያንና በኮረብታማው አገር ወደሚኖሩት ወደ ኢያቡሳውያን እንዲሁም በምጽጳ ምድር በአርሞንዔም ተራራ ወዳሉት ወደ ኤዊያውያን ነገሥታት መልእክት ላከ።
\s5
\v 4 እንዚህም ሠራዊቶቻቸው ሁሉ በቁጥርም በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ እጅግ ከብዙ ወታደሮች ጋር መጡ። ታላቅም ቁጥር ፈረሶችና ሠረገሎች ነበሩአቸው።
\v 5 እነዚህ ሁሉ ነገሥታት እስራኤልን ለመውጋት ኃይላቸውን አስተባብረው በማሮን ውሃ አጠገብ በተቀጠረው ጊዜ ሰፈሩ።
\s5
\v 6 እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለው፦ እነዚህን ሁሉ ነገ በዚች ሰዓት እንደ ሙት አድርጌ በእስራኤል እጅ አሳልፌ ስለምሰጣቸው አትፍራቸው። የፈረሶቻቸውንም ቋንጃ ትቆርጣለህ፥ ሠረገሎቻቸውንም ታቃጥላለህ።
\v 7 ኢያሱና ሠራዊቱ ሁሉ መጡ። በድንገትም ወደ ማሮን ውሃ መጥተው ጠላቶቻቸውን አጠቁኣቸው።
\s5
\v 8 እግዚአብሔርም ጠላትን በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጣቸው። በሰይፍም ስለት አጠቁአቸው፥ ወደ ሲዶና፥ወደ ማስሮን፥ ምጽጳ ሸለቆ ድረስ በስተምሥራቅ አሳደዷቸው። ከእነርሱም በሕይወት አንድንም ሰው ሳያስቀሩ በሰይፍ ስለት አጠፉአቸው።
\v 9 ኢያሱም እግዚአብሔር እንዳዘዘው በእነርሱ ላይ አደረጉ። የፈረሶቻቸውንም ቋንጃ ቆረጠ፥ ሠረገሎቻቸውንም አቃጠለ።
\s5
\v 10 በዚያን ጊዜም ኢያሱ ወደ ኋላ ተመልሶ አጾርን ያዘ። ንጉሥዋንም በሰይፍ ገደለው። (አጾርም የእነዚህ መንግሥታት ሁሉ የበላይነት ነበራች።)
\v 11 በውስጧ ያሉትን ሁሉ በሰይፍ ስለት ገደሉ፥ በሕይወት ካለው ፍጡር አንድ እንኳ ሳያስቀሩ ሁሉንም ደመሰሱ። አሦርንም በእሳት አቃጠሏት።
\s5
\v 12 ኢያሱም የእነዚህን ነገሥታት ከተሞች በሙሉ ያዘ። ነገሥታታቸውን ሁሉ ማረካቸው፥ በሰይፍም ስለት አጠፋቸው። የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ እንዳዘዘው በሰይፍ ስለት አጠፋቸው።
\v 13 እስራኤልም በተራራው ላይ ከተሠሩ ከተሞች ከአጾር በስተቀር ሌሎችን አላቃጠሉም። ኢያሱ ይህችን ለብቻዋ አቃጠላት።
\s5
\v 14 እስራኤላውያንም ምርኮውን በሙሉ ከእነዚህም ከተሞች የተገኙትን እንስሳት ለራሳቸው ወሰዱ። ሕዝቡን በሙሉ ሁሉም ሙት እስኪሆኑ ድረስ በሰይፍ ስለት ገደሉአቸው። በሕይወት ካለው ፍጡር አንድም አልቀሩም።
\v 15 እግዚአብሔር አገልጋዩን ሙሴን እንዳዘዘው ሁሉ ሙሴም ኢያሱን አዘዘው። ኢያሱም እግዚአብሔር ሙሴን ካዘዘው ሁሉ እርሱ ያልፈጸመው አንዳች ነገር አልነበረም።
\s5
\v 16 ኢያሱም ማለት ተራራማውን አገር፥ ኔጌቭን ሁሉ፥ የጎሶምን ምድር በሙሉ፥ የኮረብታ ግርጌ። የዮርዳኖስ ወንዝ ሸለቆ፥ የእስራኤልም ኮረብታማ አገርና ቆላማውን የምዕራቡን ቆላዎችን ሁሉ፥ያንን ምድር በሙሉ ወሰደ።
\v 17 እንዲሁም እስከ ሴይር በሚደርሰው ከሐላቅ ተራራ አንሥቶ ከአርሞንዔም ተራራ በታች በሊባኖስ ሸለቆ ውስጥ እስካለው እስከ በዓል ጋድ ድረስ ያለውን ምድር በሙሉ ያዘ። ነገሥታታቸውንም ሁሉ ያዘ፥ መትቶም ገደላቸው።
\s5
\v 18 ኢያሱ ከእነዚህ ነገሥታት ጋር ረጅም ጊዜ ጦርነት አደረገ።
\v 19 በገባዖን ከሚኖሩ ከኤዊያውያን በስተቀር ከእስራኤላውያን ጋር የሰላም ስምምነት ያደረገ አንድም ከተማ አልነበረም። እስራኤል ሁሉንም ከተሞች የያዙት በጦርነት ነበር።
\v 20 እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ያለ አንዳች ርኅራኄ ፈጽሞ ይደመስሳቸው ዘንድ እስራኤልን እንዲወጉ ልባቸውን ያደነደናቸው ራሱ እግዚአብሔር ነበር።
\s5
\v 21 በዚያንም ጊዜ ኢያሱ መጥቶ ዔናቅን አጠፋ። ይህንንም በተራራማው አገር በኬብሮን፥ በዳቤርና በአናብ እንዲሁም በመላው ይሁዳና የእስራኤል ተራራማ አገሮች ያሉትን ላይ አደረገ። እርሱም እነርሱንና ከተሞቻቸውን በሙሉ አጠፋቸው።
\v 22 ከእነዚህም ጥቂቶቹ ብቻ በጋዛ፥ በጌትና በአሽዶድ ከቀሩት በስተቀር በእስራኤል አገር ከዓናቅ የቀሩት አልነበሩም።
\s5
\v 23 ስለዚህ ኢያሱ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ምድሪቱን በሙሉ ያዘ። ኢያሱም እንደ ነገዳቸው አከፋፈል በመመደብም ርስት አድርጎ ለእስራእላውያን ሰጣቸው። ከዚያም ምድሪቱ ከጦርነት ዐረፈች።
\s5
\c 12
\p
\v 1 የእስራኤልም ሰዎች ድል ያደረጉአቸው ነገሥታት እነዚህ ነበሩ። እስራኤላውያንም ከአዮርዳኖንም ሸለቆ በስተ ምሥራቅ ጀምሮ እስከ ፀሐይ መውጫ ድረስ፥ ከአርሞን ወንዝ ሸለቆ ወደ አርሞንዔም ተራራ ድረስ በምሥራቅ ያለውን ዓረባ ሁሉ ወሰዱ። የአሞራውያን ንጉሥ ሴዎን በሐሴቦን ተቀመጠ።
\v 2 በአርኖንም ሸለቆ አጠገብ ካለችው ከአሮዔር ከሸለቆውም መካከል ጀምሮ የገለዓድን እኩሌታ እስከ ያቦቅ ወንዝ፥ እስከ አሞን ልጆች ዳርቻ ድረስ ገዛ።
\s5
\v 3 ሴዎንም በምሥራቅም በኩል ያለውን ዓርባ እስከ ኪኔሬት ባሕር ድረስ፥በቤት የሺሞት መንገድ አጠገብ እስካለው እስከ ዓረባ ባሕር (እስከ ጨው ባሕር) ወደ ምሥራቅ ድረስ በደቡብም በኩል ከፍስጋ ተራራ አፋፍ በታች ያለውን ምድር ገዛ።
\v 4 የባሳን ንጉሥ ዐግ ከራፋይምም ወገን የቀረ፥ በአስታሮትና በኤድራይ ተቀመጠ።
\v 5 እርሱም የአርሞንዔምንም ተራራ፥ ስልካንና ባሳንንም ሁሉ እስከ ጌሹራውያንና እስከ ማዕካታውያን ዳርቻ፥ የገለዓድንም እኩሌታ፥ እስከ ንጉሥ ሀሴቦን ድረስ ገዛው ።
\s5
\v 6 የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴና የእስራኤል ልጆች አሸነፉአቸው፤ የእግዚአብሔርም አገልጋይ ሙሴ ርስት አድርጎ ለሮቤል ልጆች፤ ለጋድም ልጆች ለምናሴም ነገድ እኩሌታ ምድሪቱን ሰጣቸው።
\s5
\v 7 ኢያሱና የእስራኤል ሕዝብ ያሸነፉአቸ ነገሥታትና አገሮች እነዚህ ናቸው፡- በዮርዳኖስም ማዶ በምዕራብ በኩል፥ በሊባኖስ ሸለቆ አጠገብ ወደ ኤዶን አጠገብ ሃላክ ተራራ ድረስ ነው። ኢያሱም ለእስራኤል ነገዶች ሁሉ ምድሪቱን ርስት አድርጎ ሰጣቸው።
\v 8 ተራራማውን አገር፥ በቆላውንም፥ በዓረባንም፥ የተራሮችን ቁልቁለት፥ ምድረ በዳውንም፥ የደቡቡም ያሉትን ኬጢያውያን፥ አሞራውያንም፥ ከነዓናውያንም፥ ፌርዛውያንም፥ ኤዊያውያንም፥ ኢያቡሳውያንም ሰጣቸው።
\s5
\v 9 የኢያሪኮ ንጉሥ ጨምሮ፦ በቤቴል አጠገብ ያለው የጋይ ንጉሥ፥
\v 10 የኢየሩሳሌም ንጉሥ፥ የኬብሮን ንጉሥ፥
\v 11 የያርሙት ንጉሥ፥ የለኪሶ ንጉሥ፥
\v 12 የአግሎን ንጉሥ፥ የጌዝር ንጉሥ፥
\s5
\v 13 የዳቤር ንጉሥ፥ የጌድር ንጉሥ፥
\v 14 የሔርማ ንጉሥ፥ የዓራድ ንጉሥ፥
\v 15 የልብና ንጉሥ፥ የአዶላም ንጉሥ፥
\v 16 የመቄዳ ንጉሥ፥ የቤቴል ንጉሥ፥
\s5
\v 17 የታጱዋ ንጉሥ፥ ይአፌር ንጉሥ፥
\v 18 የአፌቅ ንጉሥ፥ የሽሮን ንጉሥ፥
\v 19 የማዶ ንንጉሥ፥የአሶር ንጉሥ፥
\v 20 የሺምሮን፥ ሚሮን ንጉሥ፥ የአዚፍ ንጉሥ፥
\s5
\v 21 የታዕናክ ንጉሥ፥የመጊዶ ንጉሥ፥
\v 22 የቃዴስ ንጉሥ፥ በቀርሜሎስ የነበረ የዮቅንዕም ንጉሥ፥
\v 23 በዶር ኮረብታ የነበረ የዶር ንጉሥ፥ የጌልገላ አሕዛብ ንጉሥ፥
\v 24 የቲርሳ ንጉሥ፥ ነገሥታቱ ሁሉ ሠላሳ አንድ ናቸው።
\s5
\c 13
\p
\v 1 ኢያሱም ሸመገለ በዕድሜም አረጀ፤ እግዚአብሔርም አለው፦ አንተ ሸመገልህ፥ በዕድሜህም አረጀህ ያልተወረሰ እጅግ ብዙ ምድር ገና ቀርቶአል።
\s5
\v 2 የቀረውም ምድር ይህ ነው፤ የፍልስጥኤማውያንና የጌሹራውያን አገር ሁሉ፥
\v 3 (በግብፅ ፊት ካለው ከሺሖር ወንዝ ጀምሮ በሰሜን በኩል አስካለው የከነዓናውያን ንብረት ሆኖ ተቆጠረው እስከ አቃሮን ዳርቻ ድረስ፥ የጋዛ፥ የአዛጦን የአስቀሎና፥የጌትና የአቃሮን አምስቱ የፍልስጥኤማውያን መኳንንት።)
\s5
\v 4 በደቡብም በኩል የከነዓናውያንም ምድር ሁሉ፥ ለሲዶናውያንም የምትሆን መዓራ እስከ አሞራውያን ዳርቻ እስከ አፌቅ ድረስ፥
\v 5 የጌባላውያንም ምድር፥ በፀሐይ መውጫ በኩል ሊባኖስ ሁሉ፥ ከኣል ጋድ ከአርሞንዔም ተራራ በታች እስከ ሐማት ድረስ ያለው ።
\s5
\v 6 በተራራማውም አገር የሚኖሩትን ሁሉ ከሊባኖስ ጀምሮ እስከ ማሴሮን ድረስ ሲዶናውያን ሁሉ። እነዚህን ከእስራኤል ፊት አባርራቸዋለሁ። እንዳዘዝሁም፤ምድራቸውን ለእስራኤል ርስት አድርገህ ለመመደብ እርግጠኛ ሁን።
\v 7 አሁንም ይህን ምድር ለዘጠኙ ነገድ ለምናሴም ነገድ እኩሌታ ርስት አድርገህ አከፋፍል።
\s5
\v 8 የእግዚእብሔር አገልጋይ ሙሴም እንደ ሰጣቸው ከሌላ እኩሌታ የምናሴ ነገድ ጋር የሮብልና የጋድ ሰዎች በምሥራቅ በኩል በዮርዳኖስ ማዶ ሙሴ አዞአቸው የነበረውን ርስታቸውን ተቀበሉ።
\v 9 በአርኖን ወንዝ ሸለቆ ዳር ካለው ከአሮዔር፥ (በሸለቆውም መካከል ካለው ከተማ ጀምሮ) የሜድባን ሜዳ ሁሉ እስከ ዲቦን ድረስ፥
\s5
\v 10 በሐሴቦንም የአሞርውያን ንጉሥ የሴዎን ከተሞች ሁሉ እስከ አሞራውያን ዳርቻ ድረስ፥
\v 11 ገለዓድንም፥ የጌሹራውያንና የማዕካታውያንን አካባቢ ሁሉ፥ የአርሞንዔምንም ተራራ ሁሉ፥ባሳንንም ሁሉ እስከ ሰልካ ድረስ፥
\v 12 በባሳን የነበረውን በአስታሮትና በኤድራይ የነገሠውን የዐግን መንግሥት ሁሉ፥ እነርሱም ከራፋይም የቀረ ነበረ፤ እነዚህንም ሙሴ መታቸው አወጣቸውም።
\s5
\v 13 ነገር ግን የእስራኤል ሰዎች ጌሹራውያንን ወይም ማዕካታውያንን አላወጡም ነበር። በዚህ ፈንታ ጌሹርና ማዕካት እስከ ዛሬም ድረስ በእስራኤል መካከል ይኖራሉ።
\s5
\v 14 ሙሴም ለሌዊ ነገድ ለብቻ ርስት አልሰጠም። እግዚአብሔር ለሙሴ እንደ ተናገረው ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር የሚቀረበው፥ በእሳት የተደረገ መሥዋዕት ርስታቸው ነው።
\s5
\v 15 ሙሴም ለሮቤል ልጆች ነገድ በየወገናቸው ርስትን ሰጥጣቸው።
\v 16 ድንበራቸውም በአርኖን ሸለቆ ዳር ካለችው ከአሮዔር ጀሞሮ በሸለቆው መካከል ያለችው ከተማ፥
\s5
\v 17 ሐሴቦንና በሜዳውም ያሉት ከተሞችዋ ሁሉ፥ዲቦን፥ ባሞት በኣል፥ ቤት በኣልምዖን፥
\v 18 ያሀጽና ቅዴሞት፥ ሜፍዓት፥
\v 19 ቂርያታይም፥ ሴባማ፥ ጼሬትሻሐና በሸለቆውም ተራራ ያለውና ሁሉ ሮቢን ተቀበለ።
\s5
\v 20 ሮቤም ቤተ ፌጎርን፥ ከፈስጋ ተራራ በታች ያለው ምድርን፥ ቤት የሺሞትን፥
\v 21 የሜዳውም ከተሞች ሁሉ፥ የአሞራውያን ንጉሥ የሴዎን መንግሥት፥ በሐሴቦንም የነገሠው፥ ሙሴም እርሱንና በምድሪቱ የተቀመጡትን የምድያምን አለቆች፥ ኤዊን፥ ሮቆምን፥ ሱርን፥ ሑርንና ሪባን፥ የሴዎን መሳፍንት፥ መታቸው።
\s5
\v 22 የእስራኤል ሰዎች ከገደሉአቸውም ሰዎች ጋር ምዋርተኛውን የቢዖርን ልጅ በለዓምን በሰይፍ ገደሉ። የሮቤልም ልጆች ድንበር የዮርዳኖስ ወንዝና ዳርቻው ነበረ።
\v 23 የሮቤል ነገድ ድንበር የዮርዳኖስ ወንዝ ነው፥ ይህም ድንበራቸው ነው። ይህም ከከተሞቻቸውና መንደሮቻቸው በየወገኖቻቸው ለሮቤል ነገድ የተሰጣቸው ርስት ነበረ።
\s5
\v 24 ይህም መሴ ለጋድ ነገድ በየውገኖቻቸው ርስት አድርጎ የሰጣቸው ነው።
\v 25 ድንበራቸውም ኢያዜርና የገለዓድ ከተሞች ሁሉ፥ የአሞራውያንም ምድር እኩሌታ፥
\v 26 ከረባት በስተምሥራቅ፥ አስካለው እስከ አሮዔር ድረስ፥ ከሐሴቦን ጀምሮ እስከ ራማት ምጽጴ፥ እስከ ብጦኒም ድረስ፥ ከመሃናይም ጀምሮ እስከ ዳቤር ዳርቻ ድረስ ነበር።
\s5
\v 27 ሙሴም ቤትሀራምን፥ ቤትኒምራ፥ ሱኮትና ጻፎን፥ የቀሩትንም የሐሴቦን ንጉሥ የሴዎን መንግሥት ከዮርዳኖስን እንደ ድንበር በምሥራቅ በኩል ባለው በዩርዳኖስ ማዶ የኪኔሬት ባሕር ወዲያኛው ዳርቻ ሰጣቸው።
\v 28 ይህም የጋድ ነገድ ከከተሞቻቸውና ከመንደሮቻቸው ጋር በየወገኖቻቸው ርስት ነበረ።
\s5
\v 29 ሙሴም ለምናሴ እኩሌታ ነገድ ርስትን ሰጣቸው። ለምናሴም ነገድ እኩሌታ በየወገኖቻቸው መሠረት የተመመደበ ነበረ።
\v 30 ድንበራቸውም ባሳን ሁሉ፥ ከመሃናይም ጀምሮ የባሳን ንጉሥ የዐግ መንግሥት፥ በባሳንም ያሉት የኢያፅር መንደሮች ሁሉ ስድሳው ከተሞች፤
\v 31 የገለዓድም እኩሌታ፥ አስታሮትና ኤድራይ ነበር፤ (የ'ዐግ በባሳን ያሉ የመንግሥት ከተሞች) ። እነዚህም ለምናሴ ልጅ ለማኪር ልጆች ሆኑ፤ ለማኪር ሰዎች እኩሌታ በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ።
\s5
\v 32 ይህም ሙሴ በምሥራቅ በኩል በኢያሪኮ አንጻር በዮርዳኖስ ማዶ በሞዓብ ሜዳ ሳለ፥ የከፈለው ርስት ነው።
\v 33 ሙሴም ለሌዊ ነገድ ርስት አልሰጣም ነበር። የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንደ ተናገራቸው ርስታቸው ነው።
\s5
\c 14
\p
\v 1 የእስራኤልም ሕዝብ በካነዓን ምድር የወረሱት ካህኑ አልዓዛርና የነዌ ልጅ ኢያሱ በእስራኤልም ነገድ መካከል የአባቶቻቸው አለቆች ያካፈሉአቸው ርስት ይህ ነው፤
\s5
\v 2 እግዚአብሔር በሙሴ እጅ እንዳዘዘ ለዘጠኙ ነገዶችና ለእኩሌታው በየርስታቸው በዕጣ አካፈሉአቸው፤
\v 3 ለሁለቱ ነገድና ለእኩሌታው ነገድ በዮዳኖስ ማዶ ሙሴ ርስት ሰጥቶ ነበር፤ ነገር ግን በመካከላቸው ለሌዋውያን ርስት አልሰጣቸውም።
\v 4 የዮሴፍ ነገድ፥ ምናሴና ኤፍሬም ሁለት ነገዶች ነበሩ። ለሌዋውያንም ከሚቀመጡባቸው ከተወሰኑ ከተሞች፥ ለእንስሶቻቸውና ለከብቶቻቸውም ከሚሆን መሰምርያቸው በቀር በምድሩ ውስጥ ድርሻ አልሰጡአቸውም።
\v 5 እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው የእስራኤል ሕዝብ አደረጉ፥ ምድሩንም ተካፈሉ።
\s5
\v 6 የይሁዳም ነገድ በጌልገላ ወደ ኢያሱ ቀረቡ። ቄኔዛዊውም የዮፎኒ ልጅ ካሌብ እንዲህ አለው፦ ለእግዚአብሔር ሰው ለሙሴ ስለ እኔና ስለ አንተ እግዚአብሔር በቃዴስ በርኔ የተናገረውን ነገር ታውቃለህ።
\v 7 የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ምድርን እሰልል ዘንድ ከቃዴስ በርኔ በላከኝ ጊዜ እኔ የአርባ ዓመት ሰው ነበርሁ፤ እኔም በልቤ እንደ ነበረ መረጃ አመጠሁለት።
\s5
\v 8 ነገር ግን ከእኔ ጋር የሄዱ ወንድሞቼ የሕዝቡን ልብ በፍርሃት አቀለጡ። እኔ ግን አምላኬን እግዚአብሔርን ፈጽሜ ተከተልሁ።
\v 9 ሙሴም በዚያ ቀን፦ አምላኬን እግዚአብሔርን ፈጽመህ ተከትለሃልና እግርህ የረገጠው ምድር ለአንተና ለልጆችህ ለዘላለም በእርግጥ ርስት ይሆናል ብሎ ማለ።
\s5
\v 10 አሁንም፥ እነሆ፥ እግዚአብሔር ለሙሴ ይህን ቃል ከተናገር በኋላ፥ እስራኤል በምድረ በዳ ሲጓዙ፥ እርሱ እንደ ተናገረኝ እግዚአብሔር እነዚህን አርባ አምስት ዓመት በሕይወት አኖረኝ። እነሆ፥ ለእኔ ዛሬ ሰማንያ አምስት ዓመት ሆነኝ።
\v 11 ሙሴም በላከኝ ጊዜ እንደ ነበርሁ፥ ዛሬ ጉልበታም ነኝ፥ ጉልበቴም በዚያን ጊዜ እንደ ነበር፥ እንዲሁ ዛሬ ለመዋጋት፥ ለመውጣትና ለመግባትም ጉልበቴ ያው ነው።
\s5
\v 12 እንግዲህ በዚያን ቀን እግዚአብሔር የተናገረውን ይህን ተራራማ አገር ስጠኝ። አንተም በዚያ ቀን ታላላቅና በተመሸጉ ከተሞቻቸው ጋር ዔናቃውያን በዚያ እንደ ነበሩ ሰምተህ ነበር። እግዚአብሔርም እንደ ተናገረ እግዚአብሔርም ከእኔ ጋር ይሆናል፥ አሳድዳቸዋለሁ።
\s5
\v 13 ኢያሱም ባረከው፤ ለዮፎኒም ልጅ ለካሌብ ኬብሮንን ርስት አድርጎ ሰጠው።
\v 14 ስለዚህም የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን ፈጽሞ ስለ ተከተለ ኬብሮን እስከ ዛሬ ለቄኔዛዊው ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ ርስት ሆንች።
\v 15 የኬብሮንም ስም አስቀድሞ ቂርያት አርባቅ ትባል ነበር። (አርባቅም በዔናቅ ሰዎች መካከል ከፍ ያለ ነበረ።) ምድሪቱም ከጦርነት ዐረፈች።
\s5
\c 15
\p
\v 1 ለይሁዳም ልጆች ነገድ በየወገናቸው መሬትን ማከፋፈል እስከ ጺን ምድረ በዳ እስከ ደቡብም መጨረሻ እስከ ኤዶምያስ ዳርቻ ድረስ ዕጣ ሆነላቸው።
\v 2 በደቡብም በኩል ያለው ድንበራቸው እስከ ጨው ባሕር መጨረሻ ወደ ደቡብ እስከሚያይ እስከ ባሕረ ልሳን ነበረ።
\s5
\v 3 ከዚያም ቀጥሎ ከኮረብታ በስተደቡብ በኩል ወደ ጺንም አለፈ፤በቃዴስ በርኔ ወደ ደቡብ በኩል ይዘልቃል፤ በሐጽሮንም በኩል አልፎ ወደ አዳርም ደረሰ፥ ወደ ቀርቃ ዞረ፥
\v 4 ወደ አጽሞንም አለፈ፥ በግብፅም ወንዝ በኩል ወጣ፥ የድንባሩም መውጫ በባሕሩ አጠገብ ነበር፤ በደቡብ በኩል ያለው ድንበራቸው ይህ ነው።
\s5
\v 5 በምሥራቅም በኩል ያለው ድንበር እስከ ጨው ባሕር እስከ ዮርዳኖስም መጨረሻ ነበረ። በሰሜንም በኩል ያለው ድንበር በዩርዳኖስ መጨረሻ እስካለው እስከ ባሕሩ ልሳን ድረስ ነበር።
\v 6 ከዚያም ድንበሩ ወደ ቤት ሖግላ ወጣ፥ በቤት ዓርባ በሰሜን በኩል አለፈ። (ወደ ሮቤልም ልጅ ወደ ቦሀን) ድንጋይ ወጣ።
\s5
\v 7 ድንበሩም ከአኮር ሸለቆ ወደ ዳቤር ወጣ፥ በሰሜን በኩል በአዱሚም ኮረብታ ፊት ለፊት፥በወንዙም በደቡብ በኩል ወዳለችው ወደ ጌልገላ ዞረ። ከዚያም ድንበሩ ወደ ቤት ሳሚስ ውኃ አለፈ፥ መውጫውም በዓይን ሮጌል አጠገብ ነበረ።
\v 8 ከዚያ ድንበሩም በሄኖም ልጅ ሸለቆ አጠገብ (ኢየሩሳሌም) ወደምትባለው ወደ ኢያቡሳዊው ወደ ደቡብ ወገን ወጣ፤ ድንበሩም በራፋይም ሸለቆ ዳር በሰሜን በኩል ባለው በሄኖም ሸለቆ ፊት ለፊት በምዕራብ ወገን ወዳለው ተራራ ራስ ላይ ወጣ።
\s5
\v 9 ድንበሩም ከተራራው ራስ ወደ ኔፍቶ ውኃ ምንጭ ደረሰ፥ ወደ ዔፍሮንም ተራራ ከተሞች ወጣ። ቂርያትይዓሪም ወደምትበል ወደ በኣላ ደረሰ። (ከዚያም ድንበሩ በባኣላ ዙሪያ እንደ ቂርያት በተመሳሳይ ታጠፈ) ።
\v 10 ድንበሩም ከባአላ በምዕራብ በኩል ወደ ሴይር ተራራ ዞረ፤ክሳሎን ወደምትባል ወደ ይዓሪም ተራራ ወገን በሰሜን በኩል አለፈ፤ ወደ ቤት ሳሚስ ወረድ፥ በተምና በኩልም አለፈ።
\s5
\v 11 ድንበሩም ወደ አቃሮን ወደ ሰሜን ወገን ወጣ፤ወደ ሽክሮን ደረሰ ወደ በኣላ ተራራ አለፈ፥ በየብኒኤል በኩልም ወጣ፤ የድንበሩም መውጫ በባሕሩ አጠገብ ነበረ።
\v 12 በምዕራቡም በኩል ያለው ድንበር እስከ ታላቁ ባሕርና እስከ ዳርቻው ድረስ ነበረ።ለይሁዳ ልጆች በየወገናቸው በዙሪያው ያለ ድንበራቸው ይህ ነው።
\s5
\v 13 እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዳዘዘው ለዮፎኒ ልጅ ካሌብ በይሁዳ ልጆች መካከል ቂርያት አርበቅ የምትባለውን ከተማ ድርሻ አድርጎ ሰጠው፤ እርስዋም ኬብሮን ናት፥ ይህም ዘርባቅ የዔናቅ አባት ነበረ።
\v 14 ካሌብም ሦስቱን የዔናቅን ልጆች ሴስን፥ አኪመንንና ተላሚን ከዚያ አሳደደ።
\v 15 ከዚምም በዳቤር ሰዎች ላይ ወጣ፤ የዳቤርም ስም አስቀድሞ ቂርያት ሤፍር ትባል ነበር።
\s5
\v 16 ካሌብም እንዲህ አለ፦ ቂርያት ሤፍርን ለሚመታ ለሚይዛትም ልጄን ዓክሳን አጋባዋለሁ አለ።
\v 17 የካሌብ ወንድም የቄኔዝ ልጅ ጎቶንያል ያዛት። ስለዚህም ካሌብ ልጁን ዓክሳን አጋባው።
\s5
\v 18 ዓክሳም ወደ እርሱ በመጣች ጊዜ ከአባትዋ እርሻ ለመለምን ገፋፈችው፤ እርስዋም ከአህያዋ ወረደች፤ካሌብም፦ ምን ፈለግሽ? አላት።
\s5
\v 19 እርስዋም፦ ስጦታ ስጠኝ፤ የኔጌቭ ምድር ሰጥተኸኛል፥ አሁን ደግሞ የውኃውን ምንጭ ስጠኝ አለችው። እርሱም የላይኛውንና የታችኛውን ምንጭ ሰጣት።
\s5
\v 20 በየወገኖቻቸውም የይሁዳ ልጆች ነገድ የተሰጠ ርስት ይህ ነው።
\s5
\v 21 በድቡብም በኩል በምድራቸው ዳርቻ አጠገብ እስከ ኤዶምያስ ድንበር ያሉትን የይሁዳ ልጆች ነገድ ከተሞች እነዚህ ነበሩ ቀብስኤል፥ ዓዴር፥ ያጉር፥
\v 22 ቂና፥ ዲሞና፥ ዓድዓዳ፥
\v 23 ቃዴስ፥ ሐጾር፥ ዪትናን
\v 24 ዚፍ፥ጠሌም፥በዓሎት።
\s5
\v 25 ሐጾርሐ ዳታ፥ ሐጾር የምትባለውም ቂርታይሐጾር፥
\v 26 አማም ሽማዕ፥ ሞላዳ፥
\v 27 ሐጸርጋዳ፥ሐሽሞን፥ ቤትጳሌጥ፥
\v 28 ሐጸርሹዓል፥ ቤርሳቤህ፥ ቢዝዮትያ፥
\s5
\v 29 በኣላ፥ ዒዮም፥ ዓጼም፥
\v 30 ኤልቶላድ፥ ኪሲል፥ ሔርማ፥
\v 31 ጺቅላግ፥ ማድማና፥ ሳንሳና፥
\v 32 ልባዎት፥ ሺልሂም፥ ዓይን፥ ሪሞም፤ ሀያ ዘጠኝ ከተሞችና መንደሮቻቸው።
\s5
\v 33 በቆላው ኤሽታኦል፥ ጾርዓ፥ አሽና፥
\v 34 ዛኖዋ፥ ጫይንገኒም፥ ያጱዋ፥ ዓይናም፥
\v 35 የሩት፥ ዓዶላም፥ ሰኮት፥ ዓዜቃ፥
\v 36 ሽዓራይም፥ ዓዲታይም፥ ግርራ፥ ግርሮታይም፤ አሥራ አራት ከተሞችና መንደሮቻቸው።
\s5
\v 37 ጽናን፥ ሐዳሻ፥ ሚግዳልጋድ፥
\v 38 ዲልዓን፥ ምጽጳ፥ ዮቅትኤል፥
\v 39 ለኪሶ፥ በጽቃት፥ አግሎን
\s5
\v 40 አዶላም፥ ከቦን፥ ለሕማስ፥ ኪትሊሽ፥
\v 41 ግዴሮት፥ ቤት ዳጎን፥ ናዕማ፥ መቄዳ፤አሥራ ስድስት ከተሞችና ቁጥር ስፍር የሌላቸው መንደሮቻቸው።
\s5
\v 42 ልብና፥ ዔቴር፥ ዓሻን፥
\v 43 ይፍታሕ፥ አሽና፥ንጺብ፥
\v 44 ቅዒላ፥ አክዚብ፥ መሪሳ፤ ዘጠኝ ከተሞችና ቁጥር ስፍር የሌላቸው መንደሮቻቸው።
\s5
\v 45 አቃሮን፥ ከተመሸጉና ካልተመሸጉ ከተሞችና መንደሮችዋ ጋር፤
\v 46 ከአቃሮንም ጀምሮ እስከ ባሕር ድረስ በአዛጦን አጠገብ ያሉት ሁሉ ከመንደሮቻቸው ጋር።
\v 47 በአዛጦን የተመሸጉና መንደሮችዋም፥ ጋዛና የተመሸጉ ከተሞችና መንደሮችዋ፥ እስከ ግብፅ ወንዝና እስከ ታላቁ ባሕር ካርቻ ክረስ።
\s5
\v 48 በተራራማውም አገር ሳምር፥ የቲር፥ ሶኮ፥
\v 49 ደና፥ ዳቤር የምትባለው ቂርያትሰና፥
\v 50 ዓባብ፥ኤሽትሞዓ፥ ዓኒም፥
\v 51 ጎሶም፥ ሖሎን፥ ጊሎ፤ አሥራ አንድ ከተሞችና ቁጥር ስፍር የሌላቸው መንደሮቻቸው።
\s5
\v 52 አራብ፥ ዱማ፥ ኤሽዓን፥
\v 53 ያንም፥ ቤትታጱዋ፥ አፌቃ፥
\v 54 ሑምጣ፥ ኬብሮን የምትባል ቂርያትአርባቅ፥ ጺዖር ፤ ዘጠኝ ከተሞችና ቁጥር ስፍር የሌላቸው መንደሮቻቸው።
\s5
\v 55 ማዖን፥ ቀርሜሎስ፥ ዚፍ፥ ዩጣም
\v 56 ኢይዝራሴል፥ ዮቅድዓም፥ ዛኖዋሕ፥
\v 57 ቃይን፥ ጊብዓ፥ ተምና፤ አሥር ከተሞና ቁጥር ስፍር የሌላቸው መንደሮቻቸው።
\s5
\v 58 ሐልሑል፥ ቤት ጹር፥ ጌዶር፥
\v 59 ማዕራት፥ ቤትዓኖት፥ ኤልትቆን፤ስድስት ከተሞችና ቁጥር ስፍር የሌላቸው መንደሮቻቸው።
\s5
\v 60 ቂርያትይዓሪም የምትባለው ቂርያት በኣል፥ ረባት፤ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው።
\v 61 በምድረ በዳ ቤትዓረባ፥ ሚዲን፥ ስካካ፥
\v 62 ኒብሻን፥ የጨው ከተማ፥ ዓይንጋዲ፤ ስድስት ከተሞችና ቁጥር ስፍር የሌላቸው መንደሮቻቸው።
\s5
\v 63 በኢየሩሳሌም የተቀመጡትን ኢያቡሳውያንን ግን የይሁዳ ልጆች ሊያሳድዱአቸው አልተቻላቸውም፤ ኢያቡሳውያንም እስከ ዛሬ በይሁዳ ልጆች መካከል በኢየሩሳሌም ውስጥ ተቀምጠዋል።
\s5
\c 16
\p
\v 1 የዮሴፍም ልጆች የመሬት ድልድል በኢያሪኮ አጠገብ በምሥራቁ በኩል ካለው ከዮርዳኖስ አንሥቶ በምድረ በዳውና በተራራማው በኩል ከኢያሪኮ ወደ ቤቴል ወጣ።
\v 2 ከቤቴል ወደ ሎዛ ወጣ፥ በአርካውያንም ዳርቻ በኩል ወደ አጣሮት አለፈ።
\s5
\v 3 ወደ ምዕራብም እስከ የፍርሌጣውያን ዳርቻ እስከ ታችኛው ቤት ሖሮን ዳርቻ እስከ ጌዝር ድረስ ዘልቆ፥ መጨራሻውም በባሕሩ አጠገብ ነበር።
\v 4 የዮሴፍም ነገድ ምናሴና ኤፍሬም ርስታቸውን የተቀበሉት በዚህ መንገድ ነበር።
\s5
\v 5 የኤፍሬምም ነገድ ድንበር በየወገኖቻቸው እንደዚህ ነበረ፦ በምሥራቅ በኩል የርስታቸው ድንበር አጣሮት አዳር እስከ ላይኛው ቤት ሖሮን ድረስ ነበረ፤
\v 6 ከዚያ ወደ ባሕሩ ቀጠለ። ድንበሩም ወደ ምዕራብ ወደ ሚክምታት በሰሜን በኩል ወደ ምሥራቅ ወደ ተአናት ሴሎ ዞረ፥ ከዚያም ወደ ኢያኖክ በምሥራቅ በኩል አለፈ።
\v 7 ከኢያኖክም ወደ አጣሮትና ወደ ነዓራት ወረደ፤ ወደ ኢያሪኮም ደረሰ፥ ወደ ዮርዳኖስም ወጣ።
\s5
\v 8 ድንበሩም ካታጱዋ ወደ ምዕራብ እስከ ቃና ወንዝ ድረስ አለፈ፥ መውጫውም በባሕሩ መጨራሻ ነበረ። የኤፍሬም ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ፤
\v 9 ይኸውም፥ በምናሴ ነገድ ርስት መካከል ለኤፍሬምም ልጆች ከተለዩ ከተሞች ጋር፥ ከተሞች ሁሉ ከመንደሮቻቸው ጋር ነው።
\s5
\v 10 በጌዝርም የተቀመጡትን ከነዓናውያንን አላሳደዱአቸውም ነበር፤እስከ ዛሬም ድረስ ከነዓናውያን በኤፍሬም መካከል ተቀምጠዋል፤ሆኖም እነዚህ ሰዎች የጉልበት ሥራ እንዲሠሩ ተደርገው ነበር።
\s5
\c 17
\p
\v 1 ለምናሴ ነገድ የተመደበው ይህ ነበር፤ እርሱም የዮሴፍ በኩር ነበር። የምናሴም በኩር የገለዓድ አባት ማኪር ራሱም የገለዓድ አባት ነበር። የማኪርም ወገኖች የገለዓድና የባሳን ምድር ተሰጣቸው ምክንያቱም ማኪር የጦር ሰው ነበርና።
\v 2 ለቀሩት ለምናሴ ልጆች በየወገኖቻቸው ለአቢዔዝር ልጆች፥ለኬሴግ ልጆች ለአሥሪኤል ልጆች፥ ለሴኬም ልጆች፥ ለአፌር ልጆች፥ልሸሚዳ ልጆች ተሰጣቸው። የዮሴፍ ልጅ የምናሴ ወንዶች ልጆች በየወገኖቻቸው የተሰጣቸው እነዚህ ናቸው።
\s5
\v 3 ለምናሴ ልጅ፥ ለማኪር ልጅ፥ ለገለዓድ ልጅ፤ ለኦፌር ልጅ፥ ለሰለጰዓድግን ሴቶች ልጆች እንጂ ወንዶች ልጆች አልነበሩአቸውም የሴቶች ልጆቹም ስም ማህለህ፥ ኑዓ፥ ዔግላ፥ ሚልካ፥ ቲርጻ ነበረ።
\v 4 እነርሱም ወደ ካህኑ ወደ አልዓዛር፥ ወደ ነዌ ልጅ ወደ ኢያሱና ወደ አለቆች ቀርበው እንዲህ አሉ፦ እግዚአብሔርም ሙሴን ከወንድሞቻችን ጋር ርስት እንዲሰጠን አዝዞ ነበር። ስለዚህ ትእዛዙን በመከተል በአባታቸው ወንድሞች መካከል ለእነዚያ ሴቶች ርስት ሰጣቸው።
\s5
\v 5 በዮርዳኖስ ማዶ ካለው በገለዓድና በባሳን ምድር ለምናሴ አሥር የመሬት መደቦች ተመድቦ ነበር፤
\v 6 ምክንያቱም የምናሴ ሴቶች ልጆች ከወንዶቹ ጋር ርስት ተቀብለዋል። የገለዓድም ምድር ለቀሩት ለምናሴ ነገድ ተመደበ።
\s5
\v 7 የምናሴም የድንበር ክልል ከአሴር ጀምሮ በሴኬም ፊት ለፊት እስካለው እስከ ሚክምታት ድረስ ደረሰ። ድንበሩም በምዕራብ በኩል ወደ ታጱዋ ምንጭ አጠገብ ወደሚኖሩ ሰዎች አለፈ።
\v 8 (የታጱዋ ምድር ለምናሴ ነበረ፤ በምናሴ ዳርቻ ያለው ታጱዋ ከተማ ግን ለኤፍሬም ነገድ ሆነ።)
\s5
\v 9 ድንበሩም ወደ ቃና በኩል ወደ ታች ወረደ። እነዚህ ከወንዙ በስተደቡብ ያሉ ከተሞች በምናሴም ከተሞች መካከል ለኤፍሬም ሆኑ። የምናሴም ድንበር በወንዙ በስተሰሜን በኩል ሆኖ በባሕሩ መጨራሻ ነበረ።
\v 10 በደቡብ በኩል ያለው ለኤፍሬም ነበረ፥ በሰሜንም በኩል ያለው ለምናሴ የነበረው ድንበሩ ባሕር ነበረ። በሰሜን በኩል ወደ አሴር፥ በምሥራቅ ም በኩል ወደ ይሳኮር ደረሰ።
\s5
\v 11 በይሳኮርና በአሴር መካከል ቤት ሳንና መንደሮችዋን፥ ይብልዓምንና መንደሮችዋን፥ ዶር ሰዎችንና መንደሮችዋን ፥ የዓይንዶር ሰዎችንና መንደሮችዋን፥ የታዕናክ ሰዎችንና መንደሮችዋን ፥ የመጊዶ ሰዎችንና መደሮችዋን ፥ ሦስቱ ኮረብቶች ምናሴ ወረሳቸው።
\v 12 ሆኖም የምናሴ ነገድ ግን እነዚህን ከተሞች ርስት አድርጎ ሊወስዳቸው አልቻሉም፤ ምክንያቱም ከነዓናውያን በዚያ ምድር መኖራቸውን ቀጥለው ነበር።
\s5
\v 13 የእስራኤልም ሕዝብ እየጠነከሩ በመጡ ጊዜ ከነዓናውያንን የጉልበት ሥራ እንዲሠሩ አደረጉአቸው፤ ነገር ግን ሙሉ በሙሉ ከምካከላቸው እንዲወጡ አላደረጉም ነበር።
\s5
\v 14 ከዚያም የዮሴፍ ልጆች ኢያሱን እንዲህ ብለው ተናገሩ፦ እኛ ብዙ ሕዝብ ሆነን ሳለን፥ እግዚአብሔርም ባርኮን እያለ ለምን አንድ ክፍል፥ አንድም ዕጣ ብቻ ርስት አድርገህ ሰጠኸን? አሉት።
\v 15 ኢያሱም እንዲህ አላቸው፦ በቁጥር ብዙ ሕዝብ ከሆናችሁ፥ ወደ ዱር ወጥታችሁ በፌርዛውያንና በራፋይም ምድር ለራሳችሁ መንጥሩ። ተራራማውም የኤፍሬም አገር ጠብቦአችሁ እንደ ሆነ ይህንን አድርጉ።
\s5
\v 16 የዮሴፍም ልጆች እንዲህ አሉ፦ '"ተራራማውም አገር አይበቃንም። ነገር ግን በሸለቆውም ውስጥ ለሚኖሩት፥ በቤት ሳንና በመንደሮችዋ በኢይዝራኤልም ሸለቆ ለሚኖሩት ከነዓናውያን የብረት ሰርገሎች አላቸው።"
\v 17 ከዚያም ኢያሱ ለዮሴፍ ልጆች መለሰላቸው፦ ለመሆኑ ለኤፍሬምና ለምናሴ እናንተ ብዙ ሕዝብ ናችሁ፥ ጽኑም ኃይልም አላችሁ። አንድ ክፍል መሬት ብቻ ሊኖራችሁ አይገባም።
\v 18 ተራራማውም አገር ለእናንተ ይሆናል። ዱር እንኳ ቢሆንም ትመነጥሩአቸዋላችሁ፥ ለእናንተም እንዲሆኑ ታደርጋላችሁ። ከነዓናውያንም የብረት ሰረገሎች ያሉአቸውና ኃይለኞች ቢሆኑም ልታስለቅቁአቸው ትችላላችሁ። ታሳድዳቸዋላችሁ አላቸው።
\s5
\c 18
\p
\v 1 የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ በሴሎ ተሰበሰቡ። በዚያም የመገናኛውን ድንኳን ተከሉ፤ ምድሩም ጸጥ ብሎ ተገዛላቸው።
\v 2 ከእስራኤልም ልጆች መካከል ያልተካፈሉ ሰባት ነገዶች ቀርተው ነበር።
\s5
\v 3 ኢያሱም ለእስራኤል ሰዎች አላቸው፦ የአባቶቻቸሁ እግዚአብሔር አምላክ የሰጣችሁን ምድር ትወርሱ ዘንድ እስከ መቼ ድረስ ቸል ትላላችሁ?
\v 4 ከየነገዱም ሦስት ሦስት ሰዎች ምረጡ፥ እኔም እልካቸዋለሁ። ተነሥተውም የምድሪቱን ላይና ታች ይለካሉ። እንደ ርስታቸውም መጠን ይጽፉታል፤ ወደ እኔም ይመለሳሉ።
\s5
\v 5 በሰባትም ክፍል ይከፍሉታል። ይሁዳም በደቡብ ድንበር ባሉበት ይጸናሉ፤ የዮሴፍ ወገኖች በሰሜን በኩል በዳርቻው ውስጥ ይቀጥላሉ።
\v 6 እናንተም ምድሪቱን በሰባት ክፍል ትጽፋላችሁ፥ የጻፋችሁትንም ወደ እኔ ታመጣላችሁ፤ በአምላካችንም በእግዚአብሔር ፊት ዕጣ አጣጥላችኋለሁ።
\s5
\v 7 ለሌዋውያንም ርስት የላቸውም፤ የእግዚአብሔር ክህነት ርስታቸው ነውና። የጋድም፥ የሮቤልም፥ የምናሴም ነገድ እኩሌታ ከዮርዳኖስ ማዶ ተቀበሉ።ይህም የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ የሰጣቸው ርስታቸው ይህ ነው።
\s5
\v 8 ሰዎችም ተነሥተው ሄዱ፤ ኢያሱም ምድሩን ሊጽፉ የሄዱትን እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፦ ሂዱ፥ በምድሩም ላይና ታች ዞራችሁ ጻፉት፥ ከዚያም ወደ እኔ ተመለሱ። በዚህም በሴሎ በእግዚአብሔር ፊት ዕጣ አጣጥላችኋለሁ።
\v 9 ሰዎቹም ሄደው ምድሩን ላይና ታች ዞሩ። እንደ ከተሞችም በሰባት ክፍል ከፈሉት፥ ዝርዝራቸውንም ጻፉት። ከዚያም ኢያሱ ወደ ሰፈረበት ወደ ሴሎ ተመለሱ።
\s5
\v 10 ኢያሱም በእግዚአብሔር ፊት በሴሎ ዕጣ አጣጠላቸው። በዚያም ኢያሱ ለእስራኤል ልጆች እንደ ክፍሎቻቸው ምድሩን አካፈላቸው።
\s5
\v 11 የምድሩም ዕጣ ለብንያምም ነገድ በየወገኖቻቸው ተሰጠ። የዕጣቸውም ዳርቻ በይሁዳ ልጆችና በዮሴፍ ልጆች መካከል ነበረ።
\v 12 በሰሜን በኩል ድንብራቸው ከዮርዳኖስ ይጀራል። ድንበሩም ወደ ኢያሪኮ ወደ ሰሜን በኩል፥በተራራማው አገር ወደ ምዕራብ ደረሰ። መውጫውም በቤት አዌን ምድረ በዳ ነብረ።
\s5
\v 13 ድንበሩም ከዚያ በደቡብ በኩል ቤቴል ወደምትባል ወደ ሎዛ አለፈ። ድንበሩም በታችኛው ቤት ሖሮን በደቡብ በኩል ባለው ተራራ ወደ አጣሮት አዳር ወረደ።
\v 14 ድንበሩም ወደ ምዕራብ ዘለቀ፥ በቤⶆሮንም ፊት ለፊት ካለው ተራራ ወደ ደቡብ ይዞራል፤ መውጫውም ቂርታትይዓሪም በትባል በይሁዳ ልጆች ከተማ በቂርያት በኣል ነበረ፤ ይህ የምዕራቡ ዳርቻ ነበረ።
\s5
\v 15 የደቡብም ዳርቻ ከቂርያት ይዓሪም ውጪ ይጀምራል። ድንበሩም በምዕራብ በኩል ወደ ነፍቶ ውኃ ምንጭ ሄደ።
\v 16 ድንበሩም በበን ሄኖም ሸለቆ ፊት ለፊት ወዳለው ተራራ መጨረሻ ወረደ፥ እርሱም በራፋይም ሸለቆ በሰንን በኩል ነው፤ ወደ ሄኖም ሸለቆ ወደ ኢያቡስ ዳር በደቡብ በኩል ወረደ፥ ወደ ዓይን ሮጌልም ወረደ።
\s5
\v 17 ወደ ሰሜንም ዞረ፤ በኢን ሳሚስ አቅጣጫ በአዱሚም ዐቀበት ፊት ለፊት ወዳለው ወደ ጌሊሎትወጣ፤ ከዚያሜ ወደ ሮቤ ልጅ ወደ ቦሀን ድንጋይ ወረደ፤
\v 18 በሰሜንም ወገን ወደ ዓረባ አጠገብ አለፈ፥ ወደ ዓረባም ወረደ።
\s5
\v 19 ድንበሩም ወደ ቤት ሖግላ ወደ ሰሜን በኩል አለፈ። መውጫውም በዮርዳንስ መጨረሻ በደቡብ በኩል ባለው በጨው ባሕር ልሳን አጠገብ ነበር፥ ይህም የደቡቡ ዳርቻ ነበረ።
\v 20 በምሥራቅም በኩል ድንበሩ ዮርዳኖስ ነበረ። ይህ በዙሪያቸው ዳርቻ በየወገኖቻቸው የብንያም ልጆች ርስት ነበረ።
\s5
\v 21 የብንያምም ልጆች ነገድ ከተሞች በየወገኖቻችቸው እነዚህ ነበሩ፦ ኢያሪኮ፥ ቤት ሖግላ፥ ዓመቀጺጽ፥
\v 22 ቤት ዓረባ፥ ዘማራይም፥ ቤቴል፥
\v 23 ዓዊም፥ ፋራ፥ ኤፍራታ፥
\v 24 ክፊርዓሞናይ፥ ዖፍኒ፣ ጋባ፤ አሥራ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው።
\s5
\v 25 ገባዖን፥ ራማ፥ ብኤሮት፥
\v 26 ምጽጳ፥ ከፊራ፥አሞቂ፥
\v 27 ፍርቄም፥ይርጵኤል፥ ተርአላ፥
\v 28 ዼላ፥ ኤሌፍ፥ ኢየሩሳሌም የምትባልየኢያቡስ ከተማ፥ ቂርያትጊብዓት፤ አሥራ ሦስት ከትሞችና መንደሮቸችው። የብንያም ልጆች ርስት በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ።
\s5
\c 19
\p
\v 1 ሁለተኛውም ዕጣ ለስምዖን ልጆች ነገድ በየወገኖቻቸው ወጣ። ርስታቸውም በይሁዳ ልጆች ርስት መካከል ነበረ።
\s5
\v 2 እነርዚህም ርስታቸው ሆኑላቸው፤ ቤርሳቤህም ሤባ፥ሞላዳ፥
\v 3 ሐጸርሹዕል፥ ባለ፥ዔጼም፥
\v 4 ኤልቶላድ፥ በቱል፥ ሔርማ፥ ጺቅላግ፥
\s5
\v 5 ቤትማርካቦት፥ ሐጸርሱሳ፥
\v 6 ቤተ ለባኦት፥ ሻሩሔን፤ አሥራ ሦስት ከተሞችና መንደሮቻቸው።
\v 7 ዓይን፥ ሪሞን፥ ዔቴር፥ ዓሻን፤ አራት ከተሞችና መንደሮቻቸው፤
\s5
\v 8 እስከ ባዕላት ብኤርና እስከ ደቡቡ ራማት ድረስ በእነዚህ ከተሞችና ዙሪያ ያሉ መንደሮች ሁሉ። የስምዖን ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ።
\v 9 ከይሁዳ ልጆች ክፍል የስምዖን ልጆች ርስት ሆነ። የይሁዳም ልጆች ዕድል ፈንታ ስለ በዛባቸው የስምዖን ልጆች በርስታቸ መካከል ወረሱ።
\s5
\v 10 ሦስተኛውም ዕጣ ለዛብሎን ልጆች በየወገኖቻቸው ወጣ። የርስታቸውም ድንበር ወደ ሣሪድ ደረሰ።
\v 11 ድንበራቸውም በምዕራብ በኩል ወደ መርዓላ ወጣ፥ እስከ ደባሼትም ደረሰ፤ በዮቅንዓም ፊት ለፊት ወዳለው ወንዝ ደረሰ።
\s5
\v 12 ከሣሪድም ወደ ፀሐይ መውጫ ወደ ምሥራቅ ወደ ኪስሎት ታቦር ዳርቻ ዞረ። ወደ ዳብራትም ወጣ፥ ወደ ያፊዓም ደረሰ።
\v 13 ከዚያም በምሥራቅ በኩል ወደ ጋትሔፍርና ወደ ዒታቃጺን አለፈ፥ ወደ ሪምንና ወደ ኒዓ ወጣ።
\s5
\v 14 ድንበሩም በሰሜን በኩል ወደ ሐናቶን ዞረ፥ መውጫውም በይፍታሕኤል ሸለቆ ነበረ።
\v 15 ቀጣት፥ ነህላል፥ ሺምሮን፥ ይዳላ፥ ቤተ ልሔም፤ አሥራ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው።
\v 16 የዛብሎን ልጆች ርስት በየወገኖቻቸው እነዚህ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።
\s5
\v 17 አራተኛውም ዕጣ ለይሳኮር ልጆች በየወገኖቻቸው ወጣ።
\v 18 ድንበራቸውም ወደ ኢይዝራኤል፥ወደ ከስሎት፥ወደ ሱነም፥
\v 19 ወደ ሐፍራይም፥ ወደ ሺአን፥ ወደ አናሐራት፥
\s5
\v 20 ወደ ረቢት፥ ወደ ቂሶን፥ ወደ አቤጽ፥
\v 21 ሬሜት፥ ወደ ዓይንጋቢም፥ ወደ ዓይንሐዳ፥ ወደ ቤት ጳጼጽ ደረሰ፤ ድንበሩም ወደ ብቦርና ወደ ሻሕጽይማ፥ ወደ ቤት ሳሚስ ደረሰ።
\v 22 የድንበራቸውም መውጫ ዮርዳኖስ ነበረ፤ አሥራ ስድስት ከተሞችና መንደሮቻቸው።
\s5
\v 23 የይሳኮር ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው እነዚህ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።
\s5
\v 24 አምስተኛውም ዕጣ ለአሴር ልጆች ነገድ በየወገኖቻቸው ወጣ።
\v 25 ድንበራቸውም ሔልቃት፥ ሐሊ፥ ቤጤን፥ አዚፍ፥ አላሜሌክ፥ ዓምዓድ፥ ሚሽአል ነበረ፤
\v 26 በምዕራብ በኩል ወደ ቀርሜሎስና ወደ ሺሖርሊብናት ደረሰ።
\s5
\v 27 ወደ ፀሐይም መውጫ ወደ ቤት ዳጎን ዞረ፥ወደ ዛብሎንም ወደ ይፍታሕኤል ሸለቆ፥ በሰሜን በኩል ወደ ቤት ዓሜቅና ወደ ንዒኤልም ደረሰ፤ በስተ ግራ ቡልም ወደ ካቡል ወጣ።
\v 28 ከዚያም ወደ ዔብሮን፥ ወደ ረአብ፥ ወደ ሐሞን፥ ወደ ቃና እስከ ታላቁ ሲኖናም ደረሰ።
\s5
\v 29 ድንበርም ወደ ራማ፥ ወደ ተመሸገውም ከተማ ወደ ጢሮስ ዞረ፤ ድንበሩም ወደ ሖሳ ዞረ፤ መውጫውም በአክዚብ በኩል ወደ ባሕሩ ነበረ፤
\v 30 ዑማ፥ አፌቅ፥ ረአብ ደግሞ ነበሩ። እነዚህም ሀያ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው።
\s5
\v 31 የአሴር ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።
\s5
\v 32 ስድስተኛውም ዕጣ ለንፍታሌም ልጆች በየወገኖቻቸው ወጣ።
\v 33 ድንበራቸውም ከሔሌፍ፥ ከጸዕነኒም ዛፍ፥ ከአዳሚኔቄብ፥ ከየብኒኤል እስከ ለቁም ድረስ ነበረ፤ መውጫውም በዮርዳኖስ ነበረ።
\v 34 ድንበሩም ወደ ምዕራብ ወደ አዝኖት ታቦር ዞረ፥ ከዚያም ወደ ሑቆቅ ወጣ፤ከዚያም በደቡም በኩል ወደ ዛብሎን፥ በምዕራብ በኩል ወደ አሴር፥ በዮርዳስም ወንዝ በፀሐይ መውጫ ወደ ይሁዳ ደረሰ።
\s5
\v 35 የተመሸጉትም ከትሞች እነዚህ፦ ነበሩ ጺዲም፥ ጼር፥ ሐማት፥ ረቃት፥ ኬኔሬት፥
\v 36 አዳማ፥ ራማ፥ አሶር፥
\v 37 ቃዴስ፥ኤድራይ፥ ዓይንሐጽር፥ ይርአን፥
\s5
\v 38 ሚግዳልኤል፥ ሖሬም፥ ቤት ዓናት፥ ቤት ሳሚስ፤ አሥራ ዘጠኝ ከተሞችና መንደሮቻቸው ያልተቆጠሩ።
\v 39 የንፍታሌም ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው እነዚህ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።
\s5
\v 40 ሰባተኛውም ዕጣ ለዳን ልጆች ነገድ በየወገኖቻቸው ወጣ።
\v 41 የርስታቸውም ዳርቻ ይህ ነበረ፤ ጾርዓ፥ ኤሽታኦል፥ ዒርሼሜሽ፥
\v 42 ሸዕለቢን፥ ኤሎን፥ ይትላ፥ ኤሎን፥
\s5
\v 43 ተምና፥አቃሮን፥
\v 44 ኢልተቄ። ገባቶን።ባዕላት፥ ይሁድ፥
\v 45 ብኔንርቅ፥ ጋትሪሞ፥
\v 46 ሜያርቆን፥ በኢዮጴ ፊት ለፊት ካለው ዳርቻ ጋር ራቆን።
\s5
\v 47 የዳንም ልጆች ዳርቻ አልበቃቸውም፥ የዳንም ልጆች ከሌሼም ጋር ሊዋጉ ወጡ፥ ያዙአትም፥ በሰይፍም ስለመቱአት፥ ወረሱአትም፥ ተቀመጡባትም። ስምዋንም በአባቶታቸው በዳን ስም ዳን ብለው ጠርአት።
\v 48 የዳን ነገድ ርስት በየወገኖቻቸ እነዚህ ከትሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።
\s5
\v 49 ምድሩንም ሁሉ በየድንበሩ ርስት እንዲሆን ከፍለው ከጨረሱ በኋላ፥ የእስራኤል ልጆች ለነዌ ልጅ ለኢያሱ በመካከላቸው ርስት ሰጡት።
\v 50 በኤፍሬም ተራራማ አገር ያለችውን ተምናሴራ የምትባለውን የፈለጋትን ከተማ እንደ እግዚአብሔር ትእዛዝ ሰጡት። ከተማውንም እንደ ገና ሠርቶ ተቀመጠበት።
\s5
\v 51 ካህኑ አልዓዛር፥ የነዌም ልጅ ኢያሱ፥ የእስራኤልም ነገዶችና የአባቶች አለቆች በእግዚአብሔር ፊት በሴሎ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አጠገብ በዕጣ የተካፈሉት ርስት ይህ ነው። የምርሪቱንም ማከፋፈል ሥራ ጨረሱ።
\s5
\c 20
\p
\v 1 ከዚያም እግዚአብሔር ኢያሱን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦
\v 2 ለእስራኤልም ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገራቸው፡
\v 3 ሳያውቅም ሰውን የገደለ እንዲሸሽባቸው በሙሴ እጅ የነገርኋችሁን የመማፀኛ ከተሞችን ለዩ። እነዚህም ከተሞች ከተገደለበት ከማንኛውም ከደም ተበቃይ የሚሸሹበት ቦታ ይሆኑላችኋል።
\s5
\v 4 ከእነዚህም ከተሞች ወደ አንዲቱ ይሸሻል፥ በከተማይቱም በር አደባባይ ቆሞ ለከተማይቱ ሽማግሌዎች ጉዳዩን ያስረዳል። እነርሱም ወደ ከተማይቱ ይቀበሉታል፥ የሚኖርበትንም ስፍራ ይሰጡታል።
\s5
\v 5 ሰው የሞተበትም ደም ተበቃዩ መጥቶ ለመበቀል ቢሞክር፥ የከተማውም ሰዎች ሰውየውን ለከተማው ባለሥልጣናት አሳልፈው መስጠት አይኖርባቸውም። ይህን ማድረግ የማይገባቸው እርሱ የገደለው ከዚህ በፊት ጥላቻ ሳይኖርና ሆነ ብሎ ባለመሆኑ ነው።
\v 6 በማኅበሩ ፊት ለፍርድ እስኪቆም ድረስ፥ በዚያን ጊዜ ያለው በሊቀ ካህንነት የሚያገለግለው እስኪሞት ድረስ በዚያች ከተማ ይቀመጥ። ከዚያም ወዲያ ነፍሰ ገዳዩ ፥ ሸሽቶ ከነበረበት ከተማ ወደ ከተማውና ወደ ቤቱ ይመለሳል።
\s5
\v 7 በንፍታሌም ባለው በተራራማው አገር በገሊላ ቃዴስን፥ በኤፍሬምም ባለው በተራራማው አገር ኬብሮን የምትባለውን ቂርያትአርባቅን ለዩ።
\v 8 ከዮርዳኖስም ማዶ ከኢያሪኮ ወደ ምሥራቅ ከሮቤል ነገድ በምድረ በዳው በደልዳላው ስፍራ ቦሶርን፣ ከጋድም ነገድ በገለዓድ ራሞትን፥ ከምናሴም ነገድ በባሳን ቶላንን ለዩ።
\s5
\v 9 ማንም ሰው ሳያውቅ ሰውን የገደለ ወደዚያ እንዲሸሽና በመካከላቸውም ለሚቀመጥ መጻተኛ ለእስራኤል ልጆች ሁሉ የተመረጡ ከተሞች እነዚህ ናቸው። ይህም ሰው በማኅብሩ ፊት ለፍርድ እስኪቆም ድረስ በደም ተበቃዩ እጅ እንዳይሞት ነው።
\s5
\c 21
\p
\v 1 ከዚያም የሌዋውያን ወገኖች አለቆች ወደ ካህኑ አልዓዘር፥ ወደ ነዌ ልጅ ኢያሱና ወደ እስራኤል ነገዶች አለቆች ቀርቡ።
\v 2 እነርሱም በከነዓን ምድር ባለችው በሴሎ እንዲህ አሉአቸው፡- እግዚአብሔር በሙሴ እጅ የምንቀመጥባቸውንና ለከብቶቻችንም መሰማሪያ የሚሆኑ ከተሞች እንድትሰጡን አዞአችኋል።
\s5
\v 3 ስለዚህም የእስራኤልም ሕዝብ በእግዚአብሔር ትእዛዝ የሚከተሉትን ከተሞች ለከብቶቻቸውም መሰማሪያ ጭምር እንዲሆኑ ርስታቸውን ለሌዋውያን ሰጡአቸው።
\s5
\v 4 ለቀዓትም ወገኖች የዕጣው ውጤት እንዲህ ሆነ፦ ሌዋውያንም ለነበሩ ለካህኑ ለአሮን ልጆች፥ ከይሁዳ ነገድ ከስምዖንም ነገድ ከብንያምም ነገድ አሥራ ሦስት ከተሞች ተሰጣቸው።
\v 5 ለቀሩትም ለቀዓት ልጆች ከኤፍሬም ነገድ፥ ከዳንም ነገድና ከምናሴ ነገድ እክኩሌታ አሥር ከተሞች በዕጣ ተቀበሉ።
\s5
\v 6 ለጌድሶንም ልጆች ከይሳኮር ነገድ፥ ከአሴር ነገድ፥ ከንፍታሌምም ነገድ፥ በባሳን ካለው ከምናሴ ነገድ እኩሌታ አሥራ ሦስት ከተሞች በዕጣ ተሰጣቸው።
\v 7 ለሜራሪም ልጅች በየወገኖቻቸው ከሮቤል ነገድ፥ከጋድ ነገድና ከዛብሎን ነገድአሥራ ሁለት ከተሞ ተቀበሉ።
\s5
\v 8 እግዚአብሔርም በሙሴ እጅ እንዳዘዛቸው የእስራኤል ልጆች እነዚህን ከተሞችና መሰማሪያቸውን ለሌዋውያን በዕጣ ሰጡ።
\v 9 ከይሁዳም ልጆች ነገድ ከስምዖንም ልጆች ነገድ በስማቸው እነዚህን ከተሞች ሰጡ።
\v 10 እነዚህ ከተሞች ከሌዊ ልጆች ነገድ የቀዓት ወገን ለሆኑ ለአሮን ልጆች ተሰጥቶአቸው ነበር። የመጀመሪያው ዕጣ ለእነርሱ ወጥቶላቸው ነበር።
\s5
\v 11 እንደ ኬብሮን ተመሳሳይ ቦታ በይሁዳ ተራራማ አገር ያለችውን ቂርያት አርባቅ (ይህም አርባቅ የዔናቅ አባት ነበረ) የምትባለውን ከተማ በዙሪያዋም ያለውን የከብቶች መሰማሪያዋን ሰጡአቸው።
\v 12 የከተማይቱንም እርሻ ግን መንደሮችዋንም ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ ርስት አድርገው ሰጡት።
\s5
\v 13 ለካህኑም ለአሮን ልጆች ሳያውቁ ነፍሰ ገዳይ ለሆኑት መማፀኛ ከተማ የሆነችውን ኬብሮንንና መሰማሪያዋን፥ ልብናን ከመሰማሪያዋን ጋር ሰጡ፤
\v 14 የቲርንና መሰማሪያዋን፥ ኤሽት ሞዓንና መሰማሪያዋን፥
\v 15 ሖሎንንና መሰማሪያዋን፥ ዳቤርንና መሰማሪያዋን፥
\v 16 ዓይንንና መሰማሪያዋን፥ ዮጣንና መሰማሪያዋን፥ ቤት ሳሚስንና መሰማሪያዋን ሰጡ። ከእነዚህ ከሁለቱ ነገዶች ዘጠኝ ከተሞችን ነበሩ።
\s5
\v 17 ከብንያምም ነገድ ገባዖንንና መሰማሪያዋን፥ ናሲብንና መሰማሪያዋን፥
\v 18 ዓናቶትንና መሰማሪያዋን፥ አልሞንንና መሰማሪያዋን፤አራት ከተሞችን ሰጡ።
\v 19 ለአሮን ልጆች ለካህናት የተሰጡ ከተሞች ከመሰማሪያቸው ባጠቃላይ አሥራ ሦስት ከተሞች ናቸው።
\s5
\v 20 ለቀሩትም ለቀዓት ልጆች ወገኖች ሌዋውያን የተሰጣቸ ከተሞች ከኤፍሬም ነገድ ዕጣ ወጥቶላቸው ነበር።
\v 21 ለእነርሱም በኤፍሬም ተራራማ አገር ሳያውቁ ነፍሰ ገዳይ ለሆኑት መማፀኛ ከተማ የሆነችውን ሴኬምንና መሰማሪያዋን፥ ጌዝርንና መሰማሪያዋን፥
\v 22 ቂብጻይምንና መስማሪያዋን፥ ቤት ሖሮንንና መሰማሪያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡአቸው።
\s5
\v 23 ከዳንም ነገድ ኤልተቄንና መሰማሪያዋን፥ ገባቶንንና መሰማሪያዋን፥
\v 24 ኤሎንንና መሰማሪያዋን፥ ጋትሪሞንንና መሰማሪያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡአቸው።
\s5
\v 25 ከምናሴም ነገድ እኩሌታ ታዕናክንና መሰማሪያዋን፥ ጋትሪሞንንና መሰማሪያዋን፤ ሁለቱን ከተሞች ሰጡአቸው።
\v 26 ለቀሩት የቀዓት ልጆች ወገኖች የተሰጡ ከተሞች ሁሉ ከመሰማሪያቸውን ጋር አሥር ከተሞችናቸው።
\s5
\v 27 ለሌሎች ሌዋውያንም ወገኖች ለጌድሶን ልጆች ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ሳያውቁ ነፍሰ ገዳይ ለሆኑት መማፀኛ ከተማ በባሳን ውስጥ የሆነችውን ጎላንንና መሰማሪያዋን፥ በኤሽትራንና መሰማይያዋን ሁለቱን ከተሞች ሰጡአቸው።
\s5
\v 28 ከይሳኮርም ነገድ ቂሶንንና መሰማሪያዋን፥ ዳብራትንና መሰማሪያዋን፥
\v 29 የያርሙትንና መሰማሪያዋን፥ ዓይንጋኒምንና መሰማሪያዋን፤ አራቱን ከተሞች ለጋሪሶን ነገድ ሰጡአቸው።
\v 30 ከአሴርም ነገድ ሚሽአልንና መሰማሪያዋን፥ ዓብዶንና መሰማሪያዋን፥
\v 31 ሔልቃትንና መሰማሪያዋን፥ ረአብንና መሰማሪያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡአቸው።
\s5
\v 32 ከንፍታሌምም ነገድ ሳያውቁ ነፍሰ ገዳይ ለሆኑት መማፀኛ ከተማ የሆነችውን በገሊላ ውስጥ ቃዴስንና መሰማሪያዋን፥ ሐሞትዶርንና መሰማሪያዋን፥ ቀርታንንና መሰማሪያዋን፤ ሦስቱን ከተሞች ለጌድሶን ነገድ ሰጡአቸው።
\v 33 የጌድሶን ልጆች ከተሞች ሁሉ በየወገኖቻቸው ከመሰማሪያቸው ጋር አሥራ ሦስት ከተሞች ናቸው።
\s5
\v 34 ከሌዋውያንም ለቀሩት ለሜራሪ ልጆች ወገን ከዛብሎን ነገድ ዮቅንዓምንና መሰማሪያዋን፥ ቀርታንና መሰማሪያዋን፥
\v 35 ዲሞናንና መሰማሪያዋን፥ ነህላልንና መሰማሪያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡ።
\s5
\v 36 ለሜራሪ ነገድ ከሮቤልም ነገድ ቦሶርንና መሰማሪያዋን፥ ያሀጽንና መሰምሪያዋን፥
\v 37 ቅዴሞትንና መሰማሪያዋን፥ ሜፍዓትንና መሰማሪያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡ።
\v 38 ሳያውቁ ነፍሰ ገዳይ ለሆኑት መማፀኛ ከተማ የሆነችውን ከጋድም ነገድ በገለዓድ ውስጥ ራሞትንና መሰማሪያዋን፥ መሃናይምንማ መሰማሪያዋን ሰጡ።
\s5
\v 39 ሐሴቦንንና መሰማሪያዋን፥ ኢያዜርንና መሰማሪያዋን ሜራሪ ነገድ ደግሞ የተሰጡ ባጠቃላይ አራት ከተሞች ናቸው።
\v 40 ከሌዋውያን ወገኖች የቀሩት የሜራሪ ልጆች ከተሞች ሁሉ በየወገኖቻቸው እነዚህ ነበሩ፤ ዕጣቸውም ባጠቃላይ አሥራ ሁለት ከተሞች ነበሩ።
\s5
\v 41 በእስራኤል ልጆች ርስት መካከል የነበሩት የሌዋውያን ከተሞች ሁሉ አርባ ስምንት ከተሞችና መሰማሪያቸው ነበሩ።
\v 42 እነዚህም ከተሞች እያንዳንዳቸው ከመሰማሪያቸው ጋር ነበሩ፤ እነዚህም ከተሞች ሁሉ በዚህ ዓይነት መንገድ ነበሩ።
\s5
\v 43 እግዚአብሔርም ይሰጣቸው ዘንድ ለአባቶቻቸው የማለላቸውን ምድር ሁሉ ለእስራኤል ሰጠ። ወረሱአትም፥ ተቀመጡባትም።
\v 44 እግዚአብሔርም ለአባቶቻቸው እንደ ማለላቸው በዙሪያቸው ካሉት አሳረፋቸው። ከጠላቶቻቸውም ሁሉ ይቋቋማቸው ዘንድ ማንም ሰው አልቻለም፤ እግዚአብሔርም ጠላቶቻቸውን ሁሉ በእጃቸው አሳልፎ ሰጣቸው።
\v 45 እግዚአብሔር ለእስራኤል ቤት ከተናገረው መልካም ነገር ሁሉ ተፈጸመ እንጂ ምንም አልቀረም።
\s5
\c 22
\p
\v 1 በዚያን ጊዜም ኢያሱ የሮቤል ልጆችንና የጋድ ልጆችን የምናሴንም ነገድ እኩሌታ ጠራቸው።
\v 2 እንዲህም አላቸው፦ የእግዚእአብሔር አገልጋይ ሙሴ ያዘዛችሁን ሁሉ ጠብቃችኋል፥ እኔም ላዘዝኋችሁ ነገር ሁሉ ታዝዛችኋል።
\v 3 ይህንም ያህል ብዙ ጊዜ እስከ ዛሬ ድረስ ወንድሞቻችሁን አልተዋችሁም፥ የአምላካችሁንም የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ጠብቃችኋል።
\s5
\v 4 አሁንም እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ተናገራቸው ወድሞቻችሁን አሳርፎአቸዋል። አሁን እንግዲህ ተመለሱ፥ ወደ ቤታችሁና የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ በዮርዳኖስ ማዶ ወደ ሰጣችሁ ወደ ርስታችሁ ምድር ሂዱ።
\v 5 የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ያዘዛችሁን ትእዛዙንና ሕጉን ታደርጉ ዘንድ እግዚአብሔር አምላካችሁን ትወድዱ ዘንድ መንገዱንም ሁሉ ትሄዱ ዘንድ፥ ትእዛዙንም ትጠብቁ ዘንድ፥ ወደ እርሱም ትጠጉ ዘንድ፥ በፍጹምም ልባችሁ በፍጹምም ነፍሳችሁ ታመልኩ ዘንድ ብቻ እጅግ ተጠንቀቁ።
\v 6 ኢያሱም መረቃቸው፥ ሰደዳቸውም፤ ወደ ቤታቸውም ሄዱ።
\s5
\v 7 ለምናሴም ነገድ እኩሌታ ሙሴ በባሳን ውስጥ ርስት ሰጥቶአቸው ነበር፤ ለቀረው እኩሌታው ግን ኢያሱ በዮርዳኖስ ማዶ በምዕብብ ወንን በወንድሞቻቸው መካከል ርስት ሰጣቸው። ኢያሱም ወደ ቤታቸው በሰደዳቸው ጊዜ
\v 8 እንዲህ ብሎ መረቃቸው፦ በብዙ ብልጥግና በእጅግም ብዙ ከብት፥ በብርም፥ በወርቅም፥ በናስም፥ በብረትም፥ በእጅግም ብዙ ልብስ ወደ ቤታችሁ ተመለሱ፤ የጠላቶቻችሁንም ምርኮ ከወንድሞቻችሁ ጋር ተካፈሉ።
\s5
\v 9 የሮቤልም ልጆች የጋድም ልጆች የምናሴም ነገድ እኩሌታ የእስራኤል ሕዝብ በከነዓን በሴሎ ትተው ወደ ቤታቸው ተመለሱ። በሙሴም እጅ በተሰጠ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ወደ ተቀበሉአት ወደ ርስታቸው ወደ ገለዓድ ምድር ይገቡ ዘንድ ሄዱ።
\s5
\v 10 በከነዓን ምድር ወዳለው ወደ ዮርዳኖስ አቅራቢያም በመጡ ጊዜ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች የምናሴም ነገድ እኩሌታ በዚያ በዩርዳኖስ አጠገብ ታላቅ መሠዊያ ሠሩ።
\v 11 ለእስራኤልም ልጆች፦ እነሆ፥ በከነዓን ምድር ዳርቻ በዮርዳኖስ አጠገብ ባለው ግዛት፥ የእስራኤል ልጆች ባሉበት ወገን፥ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች የምናሴም ነገድ እኩሌታ መሠዊያ ሠርውዋል፤ የሚል ወሬ ደረሰላቸው።
\s5
\v 12 የእስራኤል ሕዝብ ይህን በሰሙ ጊዜ የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ ወጥተው እነርሱን ሊዋጉ በሴሎ ተሰበስቡ።
\s5
\v 13 የእስራኤልም ልጆች በገለዓድ ምድር ወዳሉት ወደ ሮቤል ልጆችና ወደ ጋድ ልጆች ወደ ምናሴም ነገድ እኩሌታ መልእክት ላኩ። የካህኑን የአልዓዛርን ልጅ ፊንሐስን ደግሞ ላኩ፥
\v 14 ከእርሱም ጋር አሥር አለቆች ነበሩ፥ ከእስራኤል ከነገዱ ሁሉ አንድ አንድ የአባቶች ቤት አለቃ እያንዳንዱም በእስራኤል አእላፋት መካከል የእየአባቶቻቸው ቤት አለቃ ነበሩ።
\s5
\v 15 በገለዓድም ምድር ወዳሉት ወደ ሮቤል ልጆችና ወደ ግድ ልጆች ወደ ምናሴም ነገድ እኩሌታ መጡ፥ እንዲህም ብለው ተናገሩአቸው፦
\v 16 የእግዚአብሔር ማኅበር ሁሉ የሚለው ይህ ነው፦ ይህ በእስራኤል አምላክ ላይ ያደረጋችሁት ኃጢአት ምንድን ነው? ዛሬ እግዚእአብሔርን ከመከተል ተመልሳችኋል ዛሬም በራሳችሁ መሠዊያ በመሥራታችሁ በእግዚአብሔር ላይ ዐምፃችኋል።
\s5
\v 17 በፌጎር ያደረገነው ኃጢአታችን አይበቃምን? እስከ ዛሬም ድረስ ከዚያ ኃጢአት ራሳችንን አላነጸንበትም። ከዚያም ኃጢአት የተነሣ በእግዚአብሔር ማኅበር ላይ መቅሠፍት ወረደ።
\v 18 እናንተ ዛሬ እግዚአብሔርን ከመከተል መመለስ ይገባችኋልን? ዛሬ በእግዚአሔር ላይ ብታምፁ ነገ በእስራኤል ማኅበር ሁሉ ላይ ይቆጣል።
\s5
\v 19 የርስታችሁም ምድር የረከሰ ቢመስላችሁ የእግዚአብሔር ማደሪያ ወደ ሚቀመጥበት ወደ እግዚአብሔር ርስት ምድር አልፋችሁ በመካከላችን ውረሱ። ከአምላካችንም ከእግዚአብሔር መሠዊያ ሌላ ለእናንተ መሠዊያ በመሥራታችሁ በእግዚአብሔርና በእኛ ላይ አታምፁ።
\v 20 የዛራ ልጅ አካን እርም ነገር በመውሰድ ኃጢአትን ስለ ሠራ በእስራኤል ማኅበር ሁሉ ላይ ቁጣ አልወረደምን? እርሱም በኃጢአት ብቻውን አልሞተም።
\s5
\v 21 ከዚያም የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች የምናሴም ነገድ እኩሌታ ለእስራኤል አለቆች እንዲህ ብለው መለሱላቸው፦
\v 22 ሁሉን የሚችል አምላክ እግዚአብሔር ታላቁ አምላክ እግዚአብሔር እርሱ ያውቃል፥ እስራኤልም እንዲያውቅ ያደርጋል! በእግዚአብሔር ላይ ዐምፀንና ተላልፈን እንደ ሆነ ዛሬ አታድነን እግዚአሔርን ከመከተል እንድንመለስ፥ የሚቃጠለውን
\v 23 መሥዋዕትና የእህልን ቁርባን እንድናሳርግበት፥ የደኅነትትንም መሥዋዕት እንድናቀርብበት ብለን መሠዊያ ሠርተን እንደ ሆነ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ ይበቀለን።
\s5
\v 24 ይልቁንም ከልባችን ፍርሃት የተነሣ፦ በሚመጣው ዘመን ልጆቻችንን፦ እናንተ የሮቤልና የጋድ ልጆች፥ ከእስራኤል አምላክ ከእግዚአብሔር ጋር ምን አላችሁ?
\s5
\v 25 እግዚአብሔር በእኛና በእናንተ መካከል ዮርዳኖስን ድንበር አድርጎአል። እናንተ የሮቤልና የጋድ ልጆች በእግዚአብሔር ዘንድ እድል ፈንታ የላችሁም ይሉአቸዋል ብለን ይህን አደረግን። በዚህም ልጆቻችሁ ልጆቻችንን እግዚአብሔርን ከመፍራት ያስተዋቸዋል።
\s5
\v 26 ስለዚህ፦ መሠዊያ እንሥራ አልን፤ ነገር ግን ለሚቃጠል መሥዋዕት ወይም ለሌላ መሥዋዕት አይደለም፤
\v 27 ነገር ግን በእኛና በእናንተ መካከል ከእኛም በኋላ በትውልዳችንና በትውልዳችሁ መካከል በሚቃጠል መሥዋዕትና በቁርባን በደኅንነትም መሥዋዕታችን እግዚአብሔርን እናመልክ ዘንድ በሚመጣውም ዘመን ልጆቻችሁ ልጆቻችንን፦በእግዚአብሔር ዘንድ እድል ፈንት የላችሁም እንዳይሉ ምስክር ይሆናል።
\s5
\v 28 ስለዚህም አልን፦ በሚመጣው ዘመን ለእኛ ወይም ለትውልዳችን፥ ይህን እንላለን እኛ፦ እነሆም አባቶቻችን ያደረጉትን የእግዚአብሔርን መሠዊያ ምሳሌ እዪ በእኛና በእናንተ መካከል ምስክር ነው እንጂ ስለሚቃጠል መሥዋዕታችን ስለሌላ መሥዋዕት አይደለም። በማደሪያው ፊት ካለው ከአምላካችን
\v 29 ከእግዚአብሔር መሠዊያ ሌላ ለሚቃጠል መሥዋዕትና ለእህል ቁርባን ለሌላ መሥዋዕትም የሚሆን መሠዊያን የሠራነው በእግዚአብሔር ላይ በማመፅ እግዚአብሔርንም ዛሬ መከተልን ለመተው በማለት እንደ ሆነ ይህ ከእኛ ይራቅ።
\s5
\v 30 ካህኑ ፊንሐና የማኅበሩ አለቆች፥ ከእርሱ ጋር ከነበሩት የእስራኤል አለቆች፥ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች የምናሴም ልጆች የተናገሩትን ቃል በሰሙ ጊዜ ነገሩ እጅግ ደስ አሰኛቸው።
\v 31 የካህኑም በአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ ለሮቤል ልጆችና ለጋድ ልጆች ለምናሴም ልጆች፦ ይህን መተላለፍ በእግዚአብሔር ላይ አላደረጋችሁምና እግዚአብሔር በመካከላችን እንዳለ ዛሬ እናውቃለን፤ አሁን የእስራኤልን ልጆች ከእግዚአብሔር እጅ አድናችኋል አላቸው።
\s5
\v 32 የካህኑም የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስና አለቆቹ ከሮቤል ልጆችና ከጋድ ልጆች ዘንድ ከገለዓድ አገር ወደ ከነዓን አገር ወደ እስራኤል ልጆች ተመለሱ፥ ወሬም አመጡላቸው።
\v 33 ነገሩም የእስራኤል ልጆችን ደስ አሰኘ፤ የእስራኤልም ልጆች እግዚአብሔርን አመሰገኑ፥ ከዚያም ወዲያ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች የተቀመጡባትን ምድር ያጠፉ ዘንድ ወጥተው አንዲወጉአቸው አልተናገሩም።
\s5
\v 34 የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች፦ እግዚአብሔር አምላክ እንደ ሆነ ይህ በመካከላችን ምስክር ነው ሲሉ መሠዊያውን ምስክር ብለው ጠሩት።
\s5
\c 23
\p
\v 1 ከብዙ ቀናት በኋላ፥እግዚአብሔርም እስራኤልን በዙሪያቸው ካሉት ጠላቶቻቸው ሁሉ ካሳረፈ፥ ኢያሱ ሸምግሎ ነበር።
\v 2 ኢያሱም እስራኤልን ሁሉ ሽማግሌዎቻቸውን፥ አለቆቻቸውን፥ ፈራጆቻቸውንና ሹማምቶቻቸውን ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ እኔ በጣም ሸምግያለሁ።
\v 3 እናንተም አምላካችሁ እግዚአብሔር በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ ስለ እናንተ ያደረገውን ሁሉ አይታችኋል፤ ስለ እናንተ የተዋጋ እርሱ አምላካችሁ እግዚአብሔር ነው።
\s5
\v 4 ተመልከቱ! እኔ ካጠፋኋቸው አሕዛብ ሁሉ ጋር ከዮርዳኖስ ጀምሮ እስካለው እስከ ታላቁ ባሕር ድረስ ለነገዶቻችሁ ርስት እንዲሆኑ መድቤላችኋለሁ።
\v 5 እግዚአሔር አምላካችሁም እርሱ ከፊታችሁ በብርቱ ይበትናቸዋል፥ ከፊታችሁም ያሳድዳቸዋል። እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ተናገራችሁም ምድራቸውን ትወርሳላችሁ።
\s5
\v 6 ስለዚህም በሙሴ ሕግ መጽሐፍ የተጻፈውን ሁሉ ለመጠበቅና ለማድረግ በጣም በርቱ፥ ከእርሱም ወደ ቀኝም ወደ ግራም ፈቀቅ አትበሉ።
\v 7 በእናንተ መካከል ወደ ቀሩት ወደ እነዚህ አሕዛብ አትግቡ፤ የአማልክታቸውንም ስም አትጥሩ፥ አትማሉባቸውም፥ አታምልኩአቸውም፥ አትስገዱላቸውም።
\v 8 እስከ ዛሬ ድረስ እንዳደረጋችሁት በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ተጣበቁ።
\s5
\v 9 እግዚአብሔርም ታላላቆችንና ኃይለኞችን መንግሥታት ከፊታችሁ አስወጣላችሁ። እስከ ዛሬም ድረስ ማንም ሊቋቋማችሁ አልቻለም።
\v 10 እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ተጋገራችሁ ስለ እናንተ የሚዋጋ እርሱ ነውና፥ ከእናንተ አንድ ሰው ሺህ ሰውን ያሳድዳል።
\v 11 እግዚእብሔር አምላካችሁን ትወድዱት ዘንድ ትኩረት አድርጉ።
\s5
\v 12 እናንተ ግን ተመልሳችሁ በመካከላችሁ ከቀሩት ከእነዚህ አሕዛብ ጋር ብትጣበቁ፥ወይም ከእነርሱም ጋር ብትጋቡ፥ ወይም እናንተ ወደ እነርሱም ወደ እናንተ ኅብረት ብታደርጉ፥
\v 13 ከዚያም እግዚአብሔር አምላካችሁ ከመካከላችሁ እነዚህን ሰዎች እንደማያስወጣችሁ በርግጥ እወቁ። በዚህ ፈንታ ከዚህች እግዚአብሔር ከሰጣችሁ ከመልካሚቱ ምድር እስክትጠፉ ድረስ ለእናንተም መውደቂያና ወጥመድ፥ በጎናችሁም መግረፊያ፥ በዓይናችሁም እሾህ ይሆኑባችኋል።
\s5
\v 14 እነሆም ዛሬ የምድርን መንገድ ሁሉ እሄዳለሁ፤ እናንተም እግዚአብሔር ስለ እናንተ ከተናገረው ከመልካም ነገር ሁሉ አንድ ነገር እንዳልቀረ በልባችሁ ሁሉ በነፍሳችሁም ሁሉ እወቁ፥ ሁሉ ደርሶላችኋል፤ ከእርሱም አንድ ነገር አልቀረም።
\v 15 እግዚአብሔ አምላካችሁ የተናገረው መልካም ነገር ሁሉ እንደ ደረሰላችሁ፥ እግዚአብሔር አምላካችሁ ከሰጣችሁ ከዚህች ከመልካሚቱ ምድር እናንተን እስኪያጠፋችሁ ድረስ እግዚአብሔር እንዲሁ ክፉን ነገር ሁሉ ያመጣባችኋል።
\s5
\v 16 የእግዚአብሔር አምላካችሁን ቃል ኪዳን ብታፈርሱ፥ ሄዳችሁም ሌሎችን አማልክት ብታመልኩ፥ ብትሰግዱላቸውም፥ በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔር ቁጣ ይነድድባችኋል፥ ከሰጣትችሁም ከመልካሚቱ ምድር ፈጥናችሁ ትጠፋላችሁ።
\s5
\c 24
\p
\v 1 ኢያሱም የእስራኤልን ነገድ ሁሉ ወደ ሴኬም ሰበስበ፥ የእስራኤልንም ሽማግሌዎችን፥ አለቆቻቸውን፥ ፈራጆቻቸውንና ሹማምቶቻቸውን ጠራቸው፤ እነርሱም በእግዚአብሔር ፊት ቆሙ።
\v 2 ኢያሱም ለሕዝቡ ሁሉ እንዲህ አለ፦ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ አባቶቻችሁ፥ የአብርሃምና የናኮር አባት ታራ፥ አስቀድመው በወንዝ ማዶ ተቀመጡ፤ ሌሎችንም አማልክት አመለኩ።
\s5
\v 3 አባታችሁንም አብርሃምን ከኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ ወስጄ በከነዓን ምድር ሁሉ መራሁት፤ ዘሩንም በልጁ በይስሐቅ በኩል እንዲበዛ ሰጠሁት።
\v 4 ለይስሐቅም ያዕቆብንና ዔሳውን ሰጠሁት። ለዔሳውም የሴይርን ተራራ ርስት አድርጌ ሰጠሁት፥ ነገር ግን ያዕቆብና ልጂቹ ወደ ግብፅ ወረዱ።
\s5
\v 5 ሙሴንና አሮንንም ላክሁ፥ ግብፃውያንን በመቅሠፍት መታሁ። ከዚያም በኋላ አወጣኋችሁ።
\v 6 አባቶቻችሁንም ከግብፅ አወጣኋችው፤ ወደ ባሕሩም መጣችሁ። ግብፃውያንም አባቶቻችሁን በሰረገሎችና በፈረሰኞች እስከ ኤርትራ ባሕር ድረስ አሳደዱአቸው።
\s5
\v 7 አባቶቻችሁም ወደ እግዚአብሔር በጮኹ ጊዜ በእናንተና በግብፃውያን መካከል ጨለማ አደረገ። ባሕሩንም በእነርሱ ላይ መለሰባቸው፥ አሰጠማቸውም። ዓናኖቻችሁም በግብፃውያን ላይ ያደረግሁትን አይታችኋል። ለረጅም ጊዜም በምድረ በዳ ተቀመጣችሁ።
\s5
\v 8 እኔም በዮርዳኖስ ማዶ ወደ ተቀመጡበት ወደ አሞራውያን ምድር አመጣኋችሁ። ከእናንም ጋር ተዋጉ፥ በእጃችሁ አሳልፌ ሰጠኋችሁ። ምድራቸውንም ወረሳችሁ፤ ከፊታችሁም አጠፋኋቸው።
\s5
\v 9-10 የሞዓብም ንጉሥ የሴፎር ልጅ ባላቅ ተንሥቶ ከእስራኤል ጋር ተዋጋ እንዲረግማችሁም የቢዖርን ልጅ በለዓምን ልኮ አስጠራው።እኔ ግን በለዓምን አልሰማሁትም። እርሱም በዚህ ፈንታ ባረካችሁ፥ እኔም ከእጁ አዳንኋችሁ።
\s5
\v 11 ዮርዳኖስንም ተሻግራችሁ፥ ወደ ኢያሪኮም መጣችሁ። የኢያሪኮም ሰዎች፥ ከአሞራዊውያን፥ ከፌርዛዊውያን፥ ከከነዓናዊውያን፥ ከኬጢያዊውያን፥ ከጌርጌሳዊውያን፥ ከኤዊያዊውያንና ከኢያቡሳዊውያን፥ ጋር ተዋጉአችሁ። በእነርሱም ላይ ድልን ሰጠኋችሁ፤አሳልፌም በእጃችሁ ሰጠኋችሁ።
\v 12 በፊታችሁ ያሉትን ሁለቱን የአሞራውያንን ነገሥታት እንዲያስወጡአቸው በፊታችሁም ተርብን ሰደድሁባቸው። ይህም በእናንተ ሰይፍና ቀሥት አይደለም።
\s5
\v 13 ያልደከማችሁበትንም ምድር፥ ያልሠራችኋቸውንም ዛሬ የተቀመጣችሁባቸውን ከተሞች ሰጠኋችሁ። ያልተከላችኋቸውን ወይንና ወይራ በላችሁ።
\s5
\v 14 አሁንም እግዚአብሔርን ፍሩ፥ በፍጹም ቅንነትና ታማኝነት አምልኩት፤ አባቶቻችሁም በኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ በግብፅም ያመለኩአቸውን አማልክት ከእናንተ አርቁ፤ እግዚአብሔርንም አምልኩ።
\v 15 እግዚአብሔርንም ማምለክ ክፉ መስሎ ቢታያችሁ፥ እባቶቻችሁ በኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ ሳሉ ያመለኩአቸውን አማልክት ወይም በምድራቸው ያላችሁባቸውን የአሞራውያንን አማልክት ታመልኩ እንደ ሆነ፥ የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ። እኔና ቤተ ሰቦቼ ግን እግዚአብሔርን እናመካለን።
\s5
\v 16 ሕዝቡም መልሰው እንዲህ አሉ፦ እግዚአብሔርን ትተን ሌሎች አማልክትን ማምለክ ከእኛ ይራቅ፥
\v 17 እኛንና አባቶቻችንን ከባርነት ቤት ከግብፅ ምድር ያወጣን፥ በዓይናችንም ፊት እነዚያን ታላላቅ ተአምራት ያደረገ፥ በሄድንባትም መንገድ ሁሉ ባለፍንባችውም አሕዛብ ሁሉ መካከል የጠበቀን፥ እርሱ አምላካችን እግዚአብሔር ነው።
\v 18 እግዚአብሔር አሕዛብን ሁሉ በምድሪቱም የተቀመጡትን አሞራውያን ከፊታችን አስወጣ። ስለዚህ እርሱ አምላካችን ነውና፤ እግዚአብሔርን እናመልካለን።
\s5
\v 19 ኢያሱም ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፦ እርሱ ቅዱስና፥ ቀናተኛ አምላክ ነውና፥ እግዚአብሔርን ማምለክ አትችሉም፤ መተላለፋችሁንና ኃጢአታችሁን ይቅር አይልም።
\v 20 እግዚአብሔርን ትታችሁ እንግዶችን አማልክት ብታመልኩ፥ ተመልሶ ክፉ ነገር ያደርግባችኋል፥ መልካም ካደረገላችሁ በኋላ ያጠፋችኋል።
\s5
\v 21 ሕዝቡም ኢያሱን፦ እንዲህ አይሁን እግዚአብሔርን እናመልካለን አሉት።
\v 22 ከዚያም ኢያሱ ሕዝቡን፦ እግዚአብሔርን እንድታመኩት እንደመረጣችሁ በራሳችሁ ላይ ምስክሮች ናችሁ አላቸው። እነርሱም፦ ምስክሮች ነን አሉ።
\v 23 እርሱም፦ አሁን እንግዲህ በመካከላችሁ ያሉትን እንግዶችን አማልክት አርቁ፥ ልባችሁንም ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር አዘንብሉ አላቸው።
\s5
\v 24 ሕዝቡም ኢያሱን፦ አምላካችንን እግዚአብሔርን እናመልካለን፥ ድምፁንም እንሰማለን፥ አሉ።
\v 25 በዚያን ቀን ኢያሱ ከሕዝቡ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ። በሴምም አዋጅንና ሕግን አደረገላቸው።
\v 26 ኢያሱም እነዚህን ቃላት ሁሉ በእግዚአብሔር ሕግ መጽሐፍ ጻፈ። ታላቁንም ድንጋይ ወስዶ በእግዚአብሔር መቅደስ አጠገብ ከነበረችው ከአድባሩ ዛፍ በታች አቆመው።
\s5
\v 27 ኢያሱም ለሕዝቡ፦ ተመልከቱ፥ የተናገረነውን ይህ ድንጋይ ይመሰክርብናል። እግዚአብሔር የተናገርነውን ሁሉ ሰምቶአል። እንግዲህ አምላካችሁን እንዳትክዱ ይህ ምስክር ይሆንባችኋል አላቸው።
\v 28 ስለዚህም ኢያሱ ሕዝቡን ወደ እያንዳንዱ ርስት እንዲሄዱ አደረገ።
\s5
\v 29 ከዚህ ነገር በኋላ የእግዚአብሔር አገልጋይ የነዌ ልጅ ኢያሱ ዕድሜው መቶ አሥር ዓመት ሞልቶት ሞተ።
\v 30 በተራራማውም በኤፍሬም አገር በገዓስ ተራራ በሰሜን ባለችው በራሱ ርስት በተምና ሴራ ቀበሩት።
\s5
\v 31 ኢያሱ በነረበት ዘመን ሁሉ፤ከኢያሱም በኋላ በነበሩት ለእስራኤልም ያደረገውን የእግዚአብሔርን ሥራ ሁሉ ባወቁት በሽማግሌዎች ዘመን ሁሉ እስራኤላውያን እግዚአብሔርን አመለኩ።
\s5
\v 32 የእስራኤልም ልጆች ከግብፅ የወጡት የዮሴፍን አጥንት ያዕቆብ ከሴም አባት ከኤሞር ልጆች በገዛው እርሻ በሴኬም ቀበሩት። እርሱም በአንድ መቶ ብር ገዛው፤እርሻውም ለዮሴፍ ልጆች ርስት ሆነ።
\v 33 የአሮንም ልጅ አልዓዛር ሞተ፤ በተራራውም በኤፍሬም አገር ለልጁ ለፊንሐስ በተሰጠችው በጊብዓ መሬት ቀበሩት።