am_ulb/03-LEV.usfm

1665 lines
188 KiB
Plaintext

\id LEV
\ide UTF-8
\h ኦሪት ዘሌዋውያን
\toc1 ኦሪት ዘሌዋውያን
\toc2 ኦሪት ዘሌዋውያን
\toc3 lev
\mt ኦሪት ዘሌዋውያን
\s5
\c 1
\p
\v 1 ያህዌ ከመገናኛው ድንኳን ሆኖ ሙሴን ጠርቶ እንዲህ አለው፣
\v 2 “ለእስራኤላዊያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፣ ‘ከእናንተ መሃል ማንም ሰው ለያህዌ መባ በሚያቀርብበት ጊዜ ከከብቶቻችሁ ወይም ከመንጋው እንስሳት መሃል አንዱን ያቅርብ፡፡
\s5
\v 3 መባው ከመንጋው መሃል የሚቃጠል መስዋዕት ከሆነ፣ ነውር የሌለበት ወንድ መስዋዕት ያቅርብ፡፡ መስዋዕቱ በያህዌ ፊት ተቀባይነት ያለው ይሆን ዘንድ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ያቅርበው፡፡
\v 4 በሚቃጠለው መስዋዕት ራስ ላይ እጁን ይጭናል፣ ይህም በእርሱ ምነትክ ያስተሰርይለት ዘንድ ተቀባይነት ያገኛል፡፡
\s5
\v 5 ከዚያ በያህዌ ፊት ወይፈኑን ይረድ፡፡ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ካህናቱ የአሮን ልጆች ደሙን ያቀርቡና በመሰዊያው ላይ ይረጩታል፡፡
\v 6 ከዚያም ካህኑ የመስዋዕቱን ከብት ቆዳ መግፈፍና ብልቶችንም ማውጣት ይኖርበታል፡፡
\s5
\v 7 ከዚያም ካህናቱ የአሮን ልጆች በመሰዊያው ላይ ዕሳት ይለኩሱና እንጨት ይጨምሩበታል፡፡
\v 8 ካህናቱ የአሮን ልጆች የስጋውን ብልቶች፣ የከብቱን ጭንቅላትና ስቡን በመስዋዕቱ ምድጃ ላይ በሚገኘው እንጨት ላይ በስርዓት ይደረድሩታል፡፡
\v 9 ነገር ግን ካህኑ የመስዋዕቱን ሆድቃና እግሮቹን በውሃ ማጠብ ይኖርበታል፡፡ በመስዋዕቱ ላይ የሚገኘውን ሁሉ የሚቃጠል መስዋዕት አብርጎ ያቃጥለዋል፡፡ ይህም ለእኔ ጣፋጭ ሽታ ይሆናል፤ ይህም ለእኔ በዕሳት የቀረበ መስዋዕት ይሆናል፡፡
\s5
\v 10 ለመስዋዕት የሚያቀርበው የሚቃጠል መስዋዕት ከመንጋው ከሆነ፣ ከበጎች ወይም ከፍየሎች መሃል ነውር የሌለበት ተባዕት መስዋዕት ማቅረብ አለበት፡፡
\v 11 በያህዌ ፊት መስዋዕቱን ከመሰዊያው በስተቀኝ በኩል ይረደው፡፡ ካህናቱ የአሮን ልጆች የመስዋዕቱን ከብት ደም በመሰዊያው ዙሪያ ሁሉ ይርጩት፡፡
\s5
\v 12 ከዚያ ካህኑ የመስዋዕቱን ከብት ጭንቅላቱንና ስቡን እንዲሁም ብልቶቹን ይቆራርጥ፡፡ ከዚያም በመሰዊያው በሚገኘው የሚነድ እንጨት ላይ በስርዓት ይደርድረው፡፡
\v 13 ነገር ግን የመስዋዕቱን ሆድቃና እግሮቹን በውሃ ይጠብ፡፡ ከዚያ ካህኑ መባውን በሙሉ ያቅርብና በመሰዊያው ላይ ያቃጥለው፡፡ ይህም የሚቃጠል መስዋዕት ነው፣ ለያህዌ ጣፋጭ መዓዛ ይሆናል፤ ለእርሱ በዕሳት የተዘጋጀ መስዋዕት ይሆናል፡፡
\s5
\v 14 “ካህኑ ለያህዌ የሚያቀርበው የሚቃጠል የወፎች መስዋዕት ከሆነ፣አንድ ወፍ ወይም ዕርግብ ማቅረብ አለበት፡፡
\v 15 ካህኑ መስዋዕቱን ወደ መሰዊያው ያመጣና አንገቱን ይቆለምመዋል፣ ከዚያም በመሰዊያው ላይ ያቃጥለዋል፡፡ ደሙም በመሰዊያው ጎን ተንጠፍጥፎ ይፈሳል፡፡
\s5
\v 16 የወፉን ማንቁርትና በውስጡ ያሉትን ያስወግድ፣ ከዚያም አመድ በሚደፉበት ከመሰዊያው በስተ ምስራቅ ይወርውረው፡፡
\v 17 ክንፎቹን ይዞ ይሰንጥቀው፣ ነገር ግን ለሁለት አይክፈለው፡፡ ከዚያ ካህኑ በዕሳቱ ላይ ባለው እንጨት መሰዊያው ላይ ያቃጥለው፡፡ ይህ የሚቃጠል መስዋዕት ይሆናል፣ እናም ለያህዌ ጣፋጭ ማዕዛ ይሆናል፣ ይህ ለእርሱ በዕሳት የተዘጋጀ መስዋዕት ይሆናል፡፡”
\s5
\c 2
\p
\v 1 ማንኛውም ሰው ለያህዌ የእህል ቁርባን ሲያቀርብ፣ መባው መልካም ዱቄት ይሁን፣ ዘይት ያፈስበታል ደግሞም ዕጣን ያድርግበት፡፡
\v 2 ቁርባኑን ወደ ካህናቱ ወደ አሮን ልጆች ይወስደዋል፣ ካህኑ ከዘይቱና በላዩ ካለው ዕጣን ጋር ከመልካሙ ዱቄት እፍኝ ይወስዳል፡፡ ከዚየም ካህኑ የያህዌን በጎነት ለማሰብ መስዋዕቱን በመሰዊያው ላይ ያቃጥለዋል፡፡ ይህም ለያህዌ ጣፋጭ መዓዛ ነው፣ ለእርሱ በዕሳት የቀረበ መስዋዕት ይሆናል፡፡
\v 3 ከእህል መስዋዕቱ የተረፈው ሁሉ ለአሮንና ለልጆቹ ይሆናል፡፡ ይህ ሙሉ ለሙሉ ለያህዌ በዕሳት ከተዘጋጀው መስዋዕት ለእርሱ የተለየ ነው፡፡
\s5
\v 4 በምድጃ የተጋገረ እርሾ የሌለበት የእህል ቁርባን ስታቀርብ፣ በዘይት የተለወሰ ከመልካም ዱቄት የተዘጋጀ ለስላሳ ዳቦ መሆን አለበት፣ ወይም እርሾ የሌለበት በዘይት የተቀባ ቂጣ መሆን አለበት፡፡
\v 5 የእህል ቁርባንህ በመጥበሻ ላይ የተጋገረ ከሆነ፣ እርሾ ያልገባበት በዘይት የተለወሰ ከመልካም ዱቄት የተዘጋጀ ይሁን፡፡
\s5
\v 6 ቆራርሰህ በላዩ ዘይት ጨምርበት፡፡ ይህ የእህል ቁርባን ነው፡፡
\v 7 የእህል ቁርባንህ በመጥበሻ የሚዘጋጅ ከሆነ ከመለካም ዱቄትና ዘይት ይዘጋጅ፡፡
\s5
\v 8 ከእነዚህ ነገሮች የተዘጋጀውን የእህል ቁርባን ወደ ያህዌ ማቅረብ አለብህ፣ እናም ይህ ወደ መሰዊያው ወደሚያመጣው ወደ ካህኑ ይቅረብ፡፡
\v 9 ከዚያም የያህዌን በጎነት ለማሰብ ካህኑ ከእህል ቁርባኑ ጥቂት ይወስዳል፣ ቀጥሎም በመሰዊያው ላይ ያቃጥለዋል፡፡ ይህ በዕሳት የተዘጋጀ መስዋዕት ይሆናል፣ እናም ለያህዌ ጣፋጭ መዓዛ ይሆናል፡፡
\v 10 ከእህል ቁርባኑ የሚተርፈው ለአሮንና ለልጆቹ ይሆናል፡፡ ይህ ለያህዌ በዕሳት ከሚዘጋጀው ቁርባን ሙሉ ለሙሉ ለእርሱ የተለየ ነው፡፡
\s5
\v 11 ለያህዌ በምታቀርቡት የእህል ቁርባን ውስጥ እርሾ አይግባበት፣ ለያህዌ በዕሳት በምታዘጋጁት ቁርባን ውስጥ ምንም እርሾ፣ ወይም ማር አታቃጥሉ፡፡
\v 12 እነዚህን እንደ በኩራት ፍሬዎች ለያህዌ ታቀርባላችሁ፣ ነገር ግን በመሰዊያው ላይ መልካም መዓዛ ለመስጠት አታቀርቧቸውም፡፡
\v 13 የእህል ቁርባንህን ሁሉ በጨው አጣፍጠው፡፡ ከእህል ቁርባንህ በፍጽም የአምላክህ የቃል ኪዳን ጨው አይታጣ፡፡ በመስዋዕቶችህ ሁሉ ጨው ማቅረብ አለብህ፡፡
\s5
\v 14 ለያህዌ ከፍሬህ በኩራት የእህል ቁርባን ስታቀርብ ከእሸቱ በእሳት የተጠበሰውንና የተፈተገውን አቅርብ፡፡
\v 15 ከዚያ በላዩ ላይ ዘይትና እጣን ጨምርበት፡፡ ይህ የእህል ቁርባን ነው፡፡
\v 16 ከዚያ ካህኑ የተፈተገውን እህል እና ዘይት እንዲሁም ዕጣን የያህዌን በጎነት በአንክሮ ለማሰብ ከፊሉን ያቃጥለዋል፡፡ ይህም ለያህዌ የሚቀርብ የዕሳት መስዋዕት ነው፡፡
\s5
\c 3
\p
\v 1 ማንኛውም ሰው ከመንጋው መሃል ወንድም ሆነ ሴት እንስሳ የህብረት መስዋዕት እንስሳ ቢያቀርብ፣በያህዌ ፊት ነውር የሌለበት እንስሳ ያቅርብ፡፡
\v 2 እጁን በመስዋዕቱ እንስሳ ራስ ላይ ይጭናል፣ ከዚያም በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ ያርደዋል፡፡ ከዚያ ካህናቱ የአሮን ልጆች በመሰዊያው ዙሪያ ደሙን ይረጩታል፡፡
\s5
\v 3 የህብረት መስዋዕቱን ለያህዌ በዕሳት ያቀርባል፡፡ ሆድቃውን የሸፈነውን ወይም ከዚያ ጋር የተያያዘውን ስብ፣
\v 4 እና ሁለቱን ኩላሊቶች እንዲሁም በጎድኑ አጠገብ የሚገኘውን ስብ፣ እና የጉበቱን መረብ ከኩላሊቶቹ ጋር እነዚህን ሁሉ አውጥቶ ያቀርባል፡፡
\v 5 የአሮን ልጆች ከሚቃጠለው መስዋዕት ጋር እነዚህን በዕሳቱ ላይ በሚገኘው እንጨት በመሰዊያው ላይ ያቃጥሉታል፡፡ ይህም ለያህዌ ጣፋጭ ማዕዛ ይሆናል፣ ይህ በእሳት ለያህዌ የሚቀርብ መስዋዕት ይሆናል፡፡
\s5
\v 6 ለያህዌ የሚያቀርበው የህብረት መስዋዕት ወንድም ይሁን ሴት እንስሳ ነውር የሌለበት ይሁን፡፡
\v 7 መስዋዕቱ የበግ ጠቦት ከሆነ፣ በያህዌ ፊት ያቅርበው፡፡
\v 8 እጁን በመስዋዕቱ ራስ ላይ ይጫንና በመገናኛው ድንኳን ፊት ለፊት ይረደው፡፡ ከዚያ አሮን ልጆች በመሰዊያው ጎንና ጎኖች ደሙን ይረጩታል፡፡
\s5
\v 9 የህብረት መስዋዕቱን በእሳት እንደሚቀርብ መስዋዕት አድርጎ ለያህዌ ያቀርባል፡፡ ስቡን፣ላቱን እስከ ጀርባ አጥንቱ ድረስ፣እንዲሁም የሆድ እቃውን የሸፈነውን ስብ ሁሉ፣በሆድ እቃው ዙሪያ የሚገኘውን ስብ ሁሉ፣
\v 10 እና ሁለቱን ኩላሊቶችና ከእነዚህ ጋር ያለውን ስብ፣ በጎድኑ አጠገብ የሚገኘውን እና የጉበቱን መሸፈኛ ከኩላሊቶቹ ጋር እነዚህን ሁሉ አውጥቶ ያቀርባል፡፡
\v 11 ከዚያም ካህኑ ሁሉንም ለያህዌ በመሰዊያው ላይ በእሳት የመበል ቁርባን አድርጎ ያቃጥላል፡፡
\s5
\v 12 የሚያቀርበው መስዋዕት ፍየል ከሆነ፣በያህዌ ፊት ያቅርበው፡፡
\v 13 እጁን በፍየሉ ራስ ላይ መጫንና በመገናኛው ድንኳን ፊት ለፊት ማረድ ይኖርበታል፡፡ ከዚያ አሮን ልጆች በመሰዊያው ጎንና ጎኖች ደሙን ይረጩታል፡፡
\v 14 በእሳት የተዘጋጀውን መስዋእቱን ለያህዌ ያቀርባል፡፡ የሆድ እቃውን የሸፈነውንና በሆድ እቃው ዙሪያ የሚገኘውን ስብ ሁሉ አውጥቶ ያቀርባል፡፡
\s5
\v 15 እንዲሁም ሁለቱን ኩላሊቶችና ከእነዚህ ጋር የሚገኘውን ስብ፣ በጎድኖች እና ከኩላሊቶቹ ጋር በጉበቱን መሸፈኛው ላይ የሚገኘውን ስብ እነዚህን ሁሉ አውጥቶ ያቀርባል፡፡
\v 16 ካህኑ እነዚህን ሁሉ በመሰዊያው ላይ መልካም መዓዛ እንዲሆን እንደ መብል መስዋዕት አድርጎ ሁሉንም ያቃጥለዋል፡፡ ስቡ ሁሉ የያህዌ ነው፡፡
\v 17 “‘ይህ ለእናንተ ከትውልድ እስከ ትውልድ በምትኖሩበት ስፍራ ሁሉ ቀዋሚ መታሰቢያ ነው፣ እናንተ ስብ ወይም ደም አትብሉ፡፡’”
\s5
\c 4
\p
\v 1 ያህዌ ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፣
\v 2 “ለእስራኤል ህዝብ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፣ ‘ማንም ሰው ያህዌ እንዳይደረግ ያዘዘውን ማናቸውንም ነገር በማድረግ ኃጢአት መስራት ሳይፈልግ ኃጢአት ቢሰራ፣ ደግሞም የተከለከለ አንዳች ነገር ቢያደርግ፣ እንዲህ ይደረግ፡፡
\v 3 ኃጢአት የሰራው ሊቀ ካህኑ ቢሆንና በህዝቡ ላይ በደል የሚያስከትል ኃጢአት ቢሰራ ስለ ሰራው ኃጢአት ለያህዌ ነውር የሌለበት ወይፈን የኃጢአት መስዋእት አድርጎ ያቅርብ፡፡
\s5
\v 4 ወይፈኑን በያህዌ ፊት ወደ መገናኛው ድንኳን ያምጣ፤ ካህኑ እጆቹን በወይፈኑ ራስ ላይ ይጫንና በያህዌ ፊት ይረደው፡፡
\v 5 የተቀባው ካህን ከወይፈኑ ጥቂት ደም ይውድና ወደ መገናኛው ድንኳን ያምጣው፡፡
\s5
\v 6 ካህኑ ጣቱን ደሙ ውስጥ እየነከረ ሰባት ጊዜ በቅድስተ ቅዱሳኑ መጋረጃ ላይ ከደሙ ጥቂት በያህዌ ፊት ይረጫል፡፡
\v 7 ደግሞም ካህኑ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በያህዌ ፊት ከደሙ ጥቂት ወስዶ መልካም መዓዛ ያለውን ዕጣን በመሰዊያው ቀንዶች ይጨምራል፤ የቀረውን ወይፈኑን ደም ሁሉ በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ላይ ለሚቃጠል መስዋዕት በመሰዊያው ስር ያፈሰዋል፡፡
\s5
\v 8 የሆድ ዕቃውን የሸፈነውንና ከሆድ ዕቃው ጋር የተያያዘውን የበደል መስዋዕቱን የሆነውን ወይፈን ስብ ሁሉ አውጥቶ ያቀርባል፡፡
\v 9 (ቁጥር 9?)
\v 10 ለህብረት መስዋዕት ከሚቀርበው ወይፈን አውጥቶ እንዳቀረበ ሁሉ ይንንም አውጥቶ ያቀርባል፡፡ ከዚያም ካህኑ እነዚህን ክፍሎች ለሚቃጠል መስዋዕት በመሰዊያው ላይ ያቃጥላል፡፡
\s5
\v 11 የወይፈኑን ቆዳና ማንኛውንም ስጋ ከጭንቅላቱና ከእግሮቹ እንዲሁም ከሆድዕቃው ክፍሎችና ከፈርሱ ጋር፣
\v 12 የቀረውን የወይፈኑን ክፍሎች ሁሉ ከእነዚህ ክፍሎች ሁሉ ከመንደር ተሸክሞ አመዱን ወደ ደፉበት ለእኔ ወደሚነጹበት ስፍራ ወስዶ እነዚያን ክፍሎች በእንጨት ላይ ያቃጥላቸው፡፡ እነዚያን የከብቱን ክፍሎች አመዱን በደፉበት ስፍራ ያቃጥለው፡፡
\s5
\v 13 መላው የእስራኤል ጉባኤ ኃጢአት መስራት ሳይፈልግ ኃጢአት ቢሰራ፣ ጉባኤውም ኃጢአት መስራቱን ባያውቅና ያህዌ እንዳይደረግ ያዘዘውን ማናቸውንም ነገር ፈጽሞ ቢገኝና በደለኛ ቢሆን፣
\v 14 ከዚያም፣ የፈጸሙት በደል በታወቀ ጊዜ፣ ጉባኤው ለኃጢአት መስዋዕት ወይፈን ይሰዋና ወደ መገናኛው ድንኳን ፊት ያምጣው፡፡
\v 15 የጉባኤው ሽማግሌዎች በያህዌ ፊት በወይፈኑ ላይ እጃቸውን ይጫኑና በያህዌ ፊት ይረዱት፡፡
\s5
\v 16 የተቀባው ካህን ከወይፈኑ ደም ወደ መገናኛው ድንኳን ያመጣል፣
\v 17 ከዚያ ካህኑ ጣቱን በደሙ ውስጥ ነክሮ በመጋረጃው ላይ በያህዌ ፊት ሰባት ጊዜ ይረጨዋል፡፡
\s5
\v 18 በመገናኛው ድንኳን ውስጥ፣በያህዌ ፊት በመሰዊያው ቀንዶች ውስጥ ከደሙ ጥቂት ይጨምርበታል፤ ደግሞም ለሚቃጠል መስዋዕት በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ላይ በመሰዊያው ታች ደሙን በሙሉ ያፈሳል፡፡
\v 19 ስቡን ሁሉ ከእንስሳው ቆርጦ ያወጣና በመሰዊያው ላይ ያቃጥላል፡፡
\s5
\v 20 ወይፈኑን በዚህ መልክ ለመስዋዕት ያቀርባል፡፡ ለኃጢአት መስዋዕት እንዳቀረበው ወይፈን ሁሉ፣ በዚህኛውም ወይፈን ይህንኑ ያደርጋል፣ እናም ካህኑ ለህዝቡ ማስተስረያ ያደርጋል፣ እናም ጉባኤው ይቅር ይባላል፡፡
\v 21 ካህኑ ወይፈኑን ከመንደር ያወጣና የመጀመሪያውን ወይፈን እንዳቃጠለ ይህኛውንም ያቃጥለዋል፡፡ ይህ ለጉባኤው የኃጢአት መስዋዕት ነው፡፡
\s5
\v 22 የህዝቡ መሪ ኃጢአት ለመስራት ሳያስብ ኃጢአት ቢሰራ፣ አምላኩ ያህዌ እንዳይደረግ ካዘዘው ማናቸውም ነገሮች አንዱን አድርጎ ቢገኝና በደለኛ ቢሆን፣
\v 23 ከዚያም የሰራው ኃጢአት ቢታወቀው፣ ነውር የሌለበት ተባዕት ፍየል ለመስዋዕት ያቀርባል፡፡
\s5
\v 24 እጁን በፍየሉ ራስ ላይ ይጭንና የሚቃጠል መስዋዕት በሚያርዱበት ስፍራ በያህዌ ፊት ይረደው፡፡ ይህ የኃጢአት መስዋዕት ነው፡፡
\v 25 ካህኑ ያኃጢአት መስዋዕቱን ደም በጣቱ ይውሰድና ለሚቃጠል መስዋዕት በመሰዊያው ቀንዶች ውስጥ ይጨምረው፣ ደግሞም ደሙን ለሚቃጠል መስዋዕት በመሰዊያው ስር ያፍስሰው፡፡
\s5
\v 26 ልክ እንደ ሰላም መስዋዕት ሁሉ ስቡን በሙሉ በመሰዊያው ላይ ያቃጥለው፡፡ ካህኑ የህዝቡ መሪ ለሰራው ኃጢአት ማስተስረያ ያድርግለታል፣ መሪውም ይቅር ይባላል፡፡
\s5
\v 27 ከተራው ህዝብ መሃል አንድ ሰው ኃጢአት ለማድረግ ሳያስብ ኃጢአት ቢሰራ፣ያህዌ እንዳይደረግ ካዘዘው ከእነዚህ ነገሮች መሃል አንዱን ቢፈጽም፣ እናም በደለኛ ሆኖ ቢገኝ፣
\v 28 ከዚያም የፈጸመው በደል ቢታወቀው፣ ለበደሉ መስዋዕት ነውር የሌለበት ሴት ፍየል ያቅርብ፡፡
\s5
\v 29 በኃጢአት መስዋዕቱ ራስ ላይ እጁን ይጭናል ከዚያም በሚቃጠል መስዋዕቱ ስፍራ የኃጢአት መስዋዕቱን ያርዳል፡፡
\v 30 ካህኑ በጣቱ ጥቂት ደም ወስዶ ለሚቃጠል መስዋዕት በመሰዊያው ቀንዶች ውስጥ ይጨምረዋል፡፡ የተቀረውን ደም ሁሉ በመሰዊያው ስር ያፈሰዋል፡፡
\s5
\v 31 መስዋዕቱ በተወሰደበት ሁኔታ ከዚህኛውም ሁሉንም ስብ ይወስዳል፡፡ ካህኑ ለያህዌ ጣፋጭ መዓዛ ለማቅረብ በመሰዊያው ላይ ያቃጥለዋል፣የሰውየውንም ኃጢአት ያስተሰርያል፡፡
\s5
\v 32 ለኃጢአት መስዋዕቱ የበግ ጠቦት ቢያቀርብ ነውር የሌለባት ሴት ጠቦት ያምጣ፡፡
\v 33 በኃጢአት መስዋዕቱ ራስ ላይ እጁን ይጫንና የሚቃጠል መስዋዕት በሚያርድበት ስፍራ ለኃጢአት መስዋዕት ያርዳል፡፡
\s5
\v 34 ካህኑ ከኃጢአት መስዋዕቱ ጥቂት ደም ይወስድና ለሚቃጠል መስዋዕት በመሰዊያው ቀንዶች ውስጥ ይጨምረዋል፡፡ ከዚያም በመሰዊያው ስር ደሙን ሁሉ ያፈሰዋል፡፡
\v 35 ከሰላም መስዋዕቱ የጠቦቱ ስብ በወጣበት ሁኔታ፣ከዚህኛውም ሁሉንም ስብ ይወስዳል፣ከዚያ ካህኑ በያህዌ መስዋዕቶች ላይ በእሳት በሚቀርበው መሰዊያ ላይ ያቃጥለዋል፡፡ ካህኑ መስዋእት አቅራቢው የሰራውን ኃጢአት ያስተሰርይለታል፣ እናም ሰውየው ይቅር ይባላል፡፡
\s5
\c 5
\p
\v 1 ማንም ሰው ያየውንም ሆነ የሰማውን አንዳች ነገር መምስከር ሲገባው ባለመመስከር ኃጢአት ቢሰራ፣ ይጠየቅበታል፡፡
\v 2 ወይም ማንም ሰው እግዚአብሔር ንጹህ አይደለም ያለውን ማናቸውንም ነገር ቢነካ፣ ይህ ንጹህ ያልሆነ ነገር የዱር እንስሳ ስጋ ወይም የሞተ የቤት እንስሳ ቢሆን፣ ወይም ማናቸውንም ያልነጻ ሰው ቢነካ፣ ደግሞም ይህን ማድረጉን ባያውቅ፣ ስለ ነገሩ ባወቀ ጊዜ ኃጢአጠኛ ይሆናል፡፡
\s5
\v 3 ቁጥር 3 (?)
\v 4 ወይም ማንም ሰው በችኮላ ክፉ ወይም በጎ ለማድረግ በከንፈሮቹ ቢምል፣በችኮላ የማለው መሀላ ምንም አይነት ይሁን፣ ስለ ነገሩ ባያውቅ እንኳን፣ ነገሩን ባወቀ ጊዜ ከእነዚህ በማናቸውም ነገር ኃጢአተኛ ይሆናል፡፡
\s5
\v 5 አንድ ሰው ከእነዚህ ነገሮች በማንኛውም በደለኛ ሆኖ ሲገኝ፣የሰራውን ማንኛውንም ኃጢአት መናዘዝ አለበት፡፡
\v 6 ከዚያም ለሰራው ኃጢአት የበደል መስዋዕቱን ወደ ያህዌ ማምጣት አለበት፣ ለኃጢአት መስዋዕት ሴት ጠቦት በግ ወይም ሴት ፍየል ያቀርባል፤ ካህኑም ስለ ሰራው ኃጢአት ያስተሰርይለታል፡፡
\s5
\v 7 ጠቦት መግዛት ካልቻለ፣ ለኃጢአቱ የበደል መስዋዕት ለያህዌ ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት እርግቦች ማምጣት ይችላል፤ አንዱ ለኃጢአት መስዋዕት እና ሌላኛው ለሚቃጠል መስዋዕት ያመጣል፡፡
\v 8 እነዚህን ወደ ካህኑ ያመጣል፣ እርሱም በመጀመሪያ አንዱን ለኃጢአት መስዋዕት ያቀርባል - እርሱም የመስዋዕቱን ራስ ከአንገቱ ይቆለምማል ነገር ግን ሙሉ ለሙሉ አይለያየውም፡፡
\v 9 ከዚያ ከኃጢአት መስዋዕቱ ጥቂት ደም ወስዶ በመሰዊያው ጎን ይረጫል፣ ከዚያ የቀረውን ደም በመሰዊያው ስር ደሙን ያንጠፈጥፈዋል፡፡ ይህ የኃጢአት መስዋዕት ነው፡፡
\s5
\v 10 ከዚያ ሁለተኛውን ወፍ በህጉ መሰረት የሚቃጠል መስዋዕት አድርጎ ያቀርበዋል፣ እናም ካህኑ ሰውየው ለሰራው ኃጢአት ማስተስረያ ያደርገዋል፤ ይቅር ይባላል፡፡
\s5
\v 11 “ነገር ግን ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት እርግቦች መግዛት ሳይችል ቢቀር፣ ለሰራው ኃጢአት የኢፍ መስፈሪያ አንድ አስረኛ መልካም ዱቄት መስዋዕት ያቅርብ፡፡ ያኃጢአት መስዋዕት ስለሆነ ዘይት ወይም ዕጣን አይጨምርበት፡፡
\s5
\v 12 መስዋዕቱን ወደ ካህኑ ያቅርበው፣ካህኑም ለያህዌ በጎነት ምስጋና ለማቅረብ ከዱቄቱ እፍኝ ይወስዳል፣ ከዚያም በመሰዊያው ላይ ለያህዌ በመስዋዕቱ ላይ በእሳት ያቃጥለዋል፡፡ ይህ የኃጢአት መስዋዕት ነው፡፡
\v 13 ካህኑ ሰውየው የሰራውን ማንኛውንም ኃጢአት ያስተሰርይለታል፤ይቅር ይባላል፡፡ ከመስዋዕት የተረፈው እንደ እህል ቁርባኑ ሁሉ የካህኑ ይሆናል፡፡’”
\s5
\v 14 ከዚያም ያህዌ እንዲህ ሲል ሙሴን ተናገረው፣
\v 15 “ማንም ሰው የያህዌን ትዕዛዝ በመጣስ እርሱ ካለው ውጭ ሆኖ ኃጢአት ቢሰራ፣ ነገር ግን ይህንን ሁን ብሎ ባያደርግ ለያህዌ የበደል መስዋዕት ያቅርብ፡፡ ይህ መስዋዕት ከመንጋው ውስጥ ነውር የሌለበት ዋጋውም ለኃጢአት መስዋዕት በቤተ መቅድስ ገንዘብ በጥሬ ብር መገመት አለበት፡፡
\v 16 ቅዱስ ከሆነው በማጉደል ለሰራው በደል ዕዳውን በመክፈል ያህዌን ደስ ማሰኘት አለበት፣ እናም አንድ አምስተኛውን በዚህ ላይ ጨምሮ ለካህኑ ይስጥ፡፡ ከዚያ ካህኑ ከበደል መስዋዕቱ ጠቦት ጋር ያስተሰርይለታል፤ እናም ይቅር ይባላል፡፡
\s5
\v 17 ማንም ሰው ኃጢአት ቢሰራና ያህዌ እንዳይደረግ ያዘዘውን ማናቸውንም ነገር ቢያደርግ፣ ምንም እንኳን ነገሩን ሳያውቅ ቢያደርገውም በደለኛ ነው፤ ስለዚህም በበደሉ ጥፋተኛ ነው፡፡
\v 18 ከመንጋው ውስጥ ነውር የሌለበት ጠቦት ያቅርብ ለካህኑ ለበደል መስዋዕት ተመጣጣኝ ዋጋ ያምጣ፡፡ ከዚያም ካህኑ ሳያውቅ ከሰራው ኃጢአት ያስተሰርይለታል፤ ይቅር ይባላል፡፡
\v 19 ይህ የበደል መስዋዕት ነው፣ በያህዌ ፊት በእርግጥ ኃጢአተኛ ነው፡፡”
\s5
\c 6
\p
\v 1 ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፣
\v 2 “ ማንም ሰው ኃጢአት ቢሰራና የያህዌን ትዕዛዝ ቢተላለፍ፣ ታማኝነቱን አፍርሶ ሃሰተኛ ቢሆን፣ ወይም ጎረቤቱ በአደራ የሰጠውን ቢክድ፣ ወይም ቢያታልል ወይም ቢሰርቀው፣ወይም ጎረቤቱን ቢበድል
\v 3 ወይም ከጎረቤቱ የጠፋ ነገር አግኝቶ ቢዋሽ፣ እናም በሃሰት ቢምል፣ ወይም እነዚህን በመሰሉ ሰዎች በሚበድሉባቸው ጉዳዮች ኃጢአት ቢሰራና፣
\v 4 በደለኛ ሆኖ ቢገኝ፣ በስርቆት የወሰደውን ይመልስ ወይም የበደለውን ይካስ፣ ወይም ታማኝነቱን አጉድሎ የወሰደውን ጠፍቶ ያገኘውን ነገር ይመልስ፡፡
\s5
\v 5 ወይም በማንኛውም ጉዳይ ላይ ቢዋሽ፣ ሙሉ ለሙሉ ይመልስ፤ እንዲሁም ጥፋተኛ ሆኖ በተገኘ ጊዜ ለባለንብረቱ አንድ አምስተኛውን ጨምሮ ይክፈል፡፡
\v 6 ከዚያም የበደል መስዋዕቱን ዋጋው ተመጣጣኝ የሆነ ነውር የሌለበት ጠቦት ከመንጋው የኃጢአት መስዋእት ለያህዌ ወደ ካህኑ ያምጣ፡፡
\v 7 ካህኑ የኃጢአት ማስተስረያ በያህዌ ፊት ያቀርባል፣ እናም በዳዩ ለሰራው በደል ሁሉ ይቅር ይባላል፡፡”
\s5
\v 8 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
\v 9 “አሮንን እና ልጆቹን እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፣ ‘የሚቃጠል መስዋዕት ህግ ይህ ነው፡ የሚቃጠለው መስዋዕት በመሰዊያው ምድጃ ላይ ሌሊቱን ሁሉ እስከ ማለዳ ይገኝ፣ ደግሞም የመሰዊያው እሳት ሳያቋርጥ ይንደድ፡፡
\s5
\v 10 ካህኑ የበፍታ ልብሱን ይልበስ፣ እንዲሁም የበፍታ ቀሚን ይልበስ፡፡ እሳቱ በመሰዊያው ላይ ያለውን የሚቃጠለውን መስዋዕት ከበላ በኋላ አመዱን ይፈስ፣ ከዚያም አመዱን ከመሰዊያው ጎን ይድፋው፡፡
\v 11 አመዱን ከሰፈር ውጭ ንጹህ ወደ ሆነ ስፍራ ለመውሰድ የለበሰውን አውልቆ ሌላ ልብስ ይልበስ፡፡
\s5
\v 12 በመሰዊው ላይ ያለው እሳት ሳያቋርጥ ይንደድ፡፡ መጥፋት የለበትም፣ እናም ካህኑ በየማለዳው እንጨት ይጨምርበት፡፡ እንደ አስፈላጊነቱ በላዩ የሚቃጠል መስዋዕት ያድርግበታል፣ ደግሞም የሰላም መስዋዕት ስብ በላዩ ያቃጥልበታል፡፡
\v 13 እሳቱ ሳያቋርጥ በመሰዊያው ላይ ይንደድ፤መጥፋት የለበትም፡፡
\s5
\v 14 የእህል ቁርባን ህግ ይህ ነው፡፡ የአሮን ልጆች ከያህዌ ፊት በመሰዊያው ላይ ያቀርቡታል፡፡
\v 15 ካህኑ የእህል ቁርባን አድርጎ እፍኝ መልካም የእህል ዱቄትና ዘይት እንዲሁም ዕጣን ለመስዋዕት ይውሰድና የያህዌን በጎነት ምስጋና ለማቅረብ በመሰዊያው ላይ ያቃጥለው፡፡
\s5
\v 16 አሮንና ልጆቹ ከመስዋዕቱ የቀረውን ይመገቡት፡፡ ይህም እርሾ ሳይገባበት በተቀደሰው ስፍራ ይብላ፡፡ በመገናኛው ድንኳን ቅጽረ ግቢ ይመገቡት፡፡
\v 17 በእርሾ መጋገር የለበትም፡፡ እኔ በእሳት የተዘጋጀ ድርሻ አድርጌ ሰጥቻቸዋለሁ፡፡ የኃጢአት መስዋዕትና የበደል መስዋዕት እጅግ የተቀደሰ ነው፡፡
\v 18 ለሚመጣው ተውልድ ሁሉ ለዘመናት ሁሉ ወንድ የሆነ የአሮን ትውልድ ድርሻው አድርጎ ከያህዌ ከሚቀርበው የእሳት ቁርባን ሊበላው ይችላል፡፡ ማናቸውም እርሱን የሚነካ ቅዱስ ይሆናል፡፡”
\s5
\v 19 ያህዌ ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፣
\v 20 “ይህ አሮንና ልጆቹ የሚያቀርቡት መስዋዕት ነው፣ እያንዳንዳቸው የአሮን ልጆች በሚቀቡበት ቀን ለያህዌ የሚያቀርቡት መስዋዕት ነው፡፡ እንደ ተለመደው የእህል ቁርባን የኢፍ አንድ አስረኛ ክፍል መልካም ዱቄት፤ በጠዋት ግማሹን የተቀረውን ግማሽ ደግሞ ምሽት ያቀርቡታል፡፡
\s5
\v 21 በመጥበሻ ላይ በዘይት ይጋገራል፡፡ በእርጥቡ ሳለ፣ለያህዌ ጣፋጭ መዓዛ እንዲሆን ታቀርበዋለህ፡፡ የእህል ቁርባኑን ለያህዌ ጣፋጭ መዓዛ እንዲሆን ቆራርሰህ ታቀርበዋለህ፡፡
\v 22 ከሊቀ ካህኑ ልጆች መሃል ተተኪ ካህን የሚሆነው ወንድ ልጅ መስዋዕቱን ያቀርባል፡፡ ለዘለዓለም እንደታዘዘው፣ መስዋዕቱ በሙሉ ለያህዌ ይቃጠላል፡፡
\v 23 ካህኑ የሚያቀርበው እያንዳንዱ የእህል ቁርባን ሙሉ ለሙሉ ይቃጠላል፤አይበላም፡፡”
\s5
\v 24 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
\v 25 “አሮንና ወንዶች ልጆቹን እንዲህ በላቸው፣ ‘የኃጢአት መስዋዕት ህግ ይህ ነው፡ የኃጢአት መስዋዕት የሚታረደው የሚቃጠል መስዋዕት በሚታረድበት ስፍራ ያህዌ ፊት ነው፡፡ እጅግ ቅዱስ ነው፡፡
\v 26 የኃጢአት መስዋዕት የሚያቀርበው ካህን ይመገበዋል፡፡ በመገናኛው ድንኳን ቅጽረግቢ በተቀደሰው ስፍራ ይበላ፡፡
\s5
\v 27 የመስዋዕቱን ስጋ የሚነካ ሁሉ ይቀደሳል፣ደሙ በየትኛውም ልብስ ላይ ቢረጭ ደሙ የነካውን የጨርቁን ስፍራ በተቀደሰ ቦታ እጠበው፡፡
\v 28 የተቀቀለበት የሸክላ ማሰሮ ግን ይሰበር፡፡
\s5
\v 29 ከካህናቱ መሀል ማናቸውም ወንድ ከዚህ መብላት ይችላል ምክንያቱም እጅግ ቅዱስ ነው፡፡
\v 30 በተቀደሰው ስፍራ ወደ መገናኛው ድንኳን ለማስተስረይ ደሙ ከቀረበው የኃጢአት መስዋዕት ምንም አይበላ፡፡
\s5
\c 7
\p
\v 1 የበደል መስዋዕት ህግ ይህ ነው፡፡ እጅግ ቅዱስ ነው፡፡
\v 2 የበደል መስዋዕቱን በሚታረድበት ስፍራ የበደሉንም መስዋዕ ይረዱት፣ ደሙን በመሰዊያው እያንዳንዱ ጎን ይርጩት፡፡
\v 3 በመስዋዕቱ ከብት ውስጥ ያለው ስብ ሁሉ ይቃጠል፤ ላቱ፣የሆድ ዕቃውን ክፍሎች የሸፈነው ስብ በመሁሉ፣
\v 4 በጎድኑ አጠገብ ያለው ስብ፣ ሁለቱ ኩላሊቶችና በላያቸው ያለው ስብ፣ ጉበቱን የሸፈነው ስብ፣ ከኩላሊቶቹ ጋር - እነዚህ ሁሉ ይቅረቡ፡፡
\s5
\v 5 ካህኑ እነዚህን ክፍሎች በእሳት የተዘጋጀ መስዋዕት አድርጎ በመሰዊያው ላይ ለያህዌ ያቃጥል፡፡ ይህ የበደል መስዋዕት ነው፡፡
\v 6 እያንዳንዱ ካህን ከዚህ መስዋዕት መብላት ይችላል፡፡ በተቀደሰ ስፍራ ይበላ ምክንያቱም እጅግ ቅዱስ ነው፡፡
\s5
\v 7 የኃጢአት መስዋዕት ልክ እንደ በደል መስዋዕት ነው፡፡ የሁለቱም ህግ ተመሳሳይ ነው፡፡ እነዚህ ህጎች የማስተስረይ አገልግሎት ለሚሰጡ ካህናት ያገለግላሉ፡፡
\v 8 የየትኛውንም ሰው የሚቃጠል መስዋዕት የሚያቀርብ ካህን የመስዋዕቱን ቆዳ መውሰድ ይችላል፡፡
\s5
\v 9 በምድጃ የሚዘጋጅ እያንዳንዱ የእህል ቁርባን፣ እና በመጥበሻ የሚዘጋጅ እንዲህ ያለው እያንዳንዱ መስዋዕት ወይም በመጋገሪያ መጥበሻ ላይ የሚዘጋጅን መስዋዕት፣ መስዋዕቱን የሚያሳርገው ካህን ይወስደዋል፡፡
\v 10 ደረቅም ሆነ በዘይት የተለወሰ እያንዳንዱ የእህል ቁርባን ለአሮን ትውልዶች እኩል የእነርሱ ነው፡፡
\s5
\v 11 ይህ ሰዎች ለያህዌ የሚያቀርቡት የሰላም መስዋዕት ህግ ነው፡፡
\v 12 ማንም ሰው ምስጋና ለማቅረብ ይህን ቢያደርግ፣ እርሾ የሌለበት መስዋዕት አድርጎ ያቅርበው፣ ነገር ግን ቂጣውን በዘይት ይለውሰው፣ ቂጣው በመልካም ዱቄት የተዘጋጀ በዘይት የተለወሰ ይሁን፡፡
\s5
\v 13 ደግሞም ምስጋና ለማቅረብ፣ ከሰላም መስዋዕቱ ጋር በእርሾ የተዘጋጀ ህብስት ያቅርብ፡፡
\v 14 ከእነዚህ መስዋዕቶች ከእያንዳንዳቸው አንድ አይነት መስዋዕት ለያህዌ ያቅርብ፡፡ ይህ የሰላም መስዋዕቱን ደም በመሰዊያው ላይ ለሚረጩት ካህናት ይሰጥ፡፤
\s5
\v 15 ምስጋና ለማቅረብ የሰላም መስዋዕት የሚያቀርበው ሰው መስዋዕቱ በሚቀርብበት ዕለት የመስዋዕቱን ስጋ ይብላ፡፡ ከስጋው እስከ ማግስቱ አይደር፡፡
\v 16 ነገር ግን መስዋዕቱ የሚያቀርበው ለስዕለት ከሆነ፣ ወይም በበጎ ፈቃድ የሚቀርብ መስዋዕት ከሆነ ስጋው መስዋዕቱን ባቀረበበት ዕለት ባያልቅ በማግስቱ ሊበላ ይችላል፡፡
\s5
\v 17 ሆኖም፣ ከመስዋዕቱ የተረው ስጋ በሶስተኛው ቀን ይቃጠል፡፡
\v 18 አንድ ሰው ካቀረበው የበጎ ፈቃድ መስዋዕት አንዳች ስጋ በሶስተኛው ቀን ቢበላ ይህ ተቀባይነት የለውም፤ መስዋዕቱን ላቀረበውም ዋጋ የለውም፡፡ ደስ የማያሰኝ ነገር ይሆናል፣ ስጋውን ለሚበላውም ሰው የበደል ዕዳ ይሆንበታል፡፡
\s5
\v 19 ንጹህ ያልሆነ ነገር የነካ ከዚህ ስጋ አይበላም፡፡ ስጋው መቃጠል ይኖርበታል፡፡ የተረውን ስጋ፣ ማንኛውም ንጹህ የሆነ ሰው ሊበላው ይችላል፡፡
\v 20 ሆኖም፣ ለያህዌ የሚቀርበውን የሰላም መስዋዕት ስጋ የበላ ንጹህ ያልሆነ ሰው ከህዝቡ ተለይቶ ይወገድ፡፡
\s5
\v 21 ማንኛውም ሰው ንጹህ ያልሆነ ነገር ቢነካ - ንጹህ ያልሆነን ሰው፣ ወይም ንጹህ ያልሆነን አውሬ፣ ወይም ንጹህ ያልሆነ እና ደስ የማያሰኝ ነገር ቢነካ፣ እና ከዚያም ለያህዌ ከቀረበው የሰላም መስዋዕት ስጋ ቢበላ ያሰው ከህዝቡ ተለይቶ ይወገድ፡፡
\s5
\v 22 ቀጥሎም ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
\v 23 “የእስራኤልን ሰዎች እንዲህ በላቸው፣ ‘የበሬ ወይም የበግ ወይም የፍየል ስብ አትብሉ፡፡
\v 24 ሳይታረድ ሞቶ የተገኘ እንስሳ ስብ፣ ወይም በዱር አውሬ የተገደለ እንስሳ ስብ ለሌላ ተግባር ሊውል ይችላል፣ ነገር ግን የዚያን እንስሳ ስብ በፍጹም አትብሉ፡፡
\s5
\v 25 ሰዎች በእሳት ለያህዌ መስዋዕት አድርገው ሊያቀርቡ የሚችሉትን እንስሳ ስብ የሚላ ማንኛውም ሰው፣ ከህዝቡ ተለይቶ ይወገድ፡፡
\v 26 በቤቶቻችሁ የወፍም ሆነ የእንስሳ ማናቸውም ዐይነት ደም አትብሉ፡፡
\v 27 ማናቸውንም ደም የበላ ማንም ሰው፣ ከህዝቡ ተለይቶ ይጥፋ፡፡’”
\s5
\v 28 ደግሞም ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
\v 29 “የእስራኤልን ሰዎች እንዲህ በላቸው፣ ‘ለያህዌ የሰላም መስዋዕት የሚያቀርብ ከመስዋዕቱ ላይ ወስዶ ለያህዌ ያቅርብ፡፡
\v 30 ለያህዌ በእሳት የሚዘጋጀውን መስዋዕት፣ በእርሱ በራሱ እጅ ያቅረበው፡፡ ስቡን ከፍርምባው ጋር ያቅርበው፣ ስለዚህ ፍርምባውን በያህዌ ፊት ለመስዋዕት ያቅርበው፡፡
\s5
\v 31 ካህኑ ስቡን በመሰዊያ ላይ ያቃጥለው፣ ነገር ግን ፍርምባው የአሮንና የትውልዱ ነው፡፡
\v 32 የቀኙን ወርች ከሳለም መስዋዕታችሁ የቀረበ ስጦታ አድርጋችሁ ለካህኑ ስጡት፡፡
\s5
\v 33 የሰላም መስዋዕቱንና ስቡን ደም የሚያቀርበው ከአሮን ትውልድ ውስጥ የሆነው ካህን ከመስዋዕቱ ውስጥ የቀኝ ወርቹ የእርሱ ድርሻ ነው፡፡
\v 34 ለእኔ የተወዘወዘውንና የቀረበውን የፍርምባውንና የወርቹን መስዋዕት እኔ ስለ ወሰድኩ፣ እነዚህን ሊቀካህን ለሆነው ለአሮንና ለዘሩ ሰጥቻለሁ፣ ይህ ሁልጊዜም በእስራኤል ህዝብ ከሚዘጋጀው የሰላም መስዋዕት ድርሻቸው ይሆናል፡፡
\s5
\v 35 ሙሴ በካህናት አገልግሎት ያህዌን እንዲያገለግሉ እነርሱን ባቀረበ ቀን ይህ ለአሮንና ለዘሮቹ በእሳት ለያህዌ ከሚቀርበው መስዋዕት ድርሻቸው ነው፡፡
\v 36 እርሱ ካህናትን በቀባ ቀን ያህዌ ከእስራኤል ህዝብ ድርሻቸው ሆኖ ለእነርሱ እንዲሰጥ ያዘዘው ይህ ነው፡፡ ይህ ሁልጊዜም በትውልዶች ሁሉ ድርሻቸው ይሆናል፡፡
\s5
\v 37 ይህ የሚቃጠል መስዋዕት፣ የእህል ቁርባን፣ የኃጢአት መስዋዕት፣ በደል መስዋዕት፣ የክህነት ሹመት መስዋዕት እና የሰላም መስዋዕት ስርዓት ነው፤
\v 38 ይህ ያህዌ ለሙሴ በሲና ተራራ ላይ የእስራኤል ህዝብ መስዋዕታቸውን በሲና ምድረበዳ የሚያቀርቡበትን ህግጋት ለሙሴ በሰጠበት ቀን የተሰጠ ስርዓት ነው፡፡
\s5
\c 8
\p
\v 1 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
\v 2 “አሮንንና ልጆቹን፣ የክህነት ልብሶቹን፣ የቅባት ዘይቱን፣የኃጢአት መስዋዕቱን ወይፈኖች፣ ሁለቱን ጠቦቶች፣ እርሾ የሌለበትን ህብስት መሶብ ከእርሱ ጋር ውሰድ፡፡
\v 3 በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ላይ ሁሉንም ጉባኤ ሰብስብ፡፡”
\s5
\v 4 ስለዚህም ሙሴ ያህዌ እንዳዘዘው አደረገ፣ ጉባኤውም በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ላይ ተሰበሰበ፡፡
\v 5 ከዚያም ሙሴ ለጉባኤው እንዲህ አለ፣ “ያህዌ እንዲደረግ ያዘዘው ይህ ነው፡፡”
\s5
\v 6 ሙሴ አሮንንና ልጆቹን አቀረበና በውሃ አጠባቸው፡፡
\v 7 አሮንን እጀ ጠባብ አለበሰውና በወገቡ ዙሪያ መቀነት አስታጠቀው፣ ቀሚ አጠለቀለትና ኤፉድ ደረበለት፣ ከዚያም ኤፉዱን በጥበብ በተጠለፈ መቀነት አስታጠቀው፡፡
\s5
\v 8 በቀሚሱ ላይ ደረት ኪስ አደረገለት፣ በደረት ኪሱ ውስጥ ኡሪምና ቱሚም አደረገበት፡፡
\v 9 ሙሴ ያህዌ እንዳዘዘው በራሱ ላይ ጥምጥሙን ጠመጠመለት፣ በጥምጥሙ ላይ ከፊት በኩል ወርቃማ ቅብና ቅዱስ አክሊል አደረገለት፡፡
\s5
\v 10 ሙሴ የቅባቱን ዘይት ወሰደ፣ ማደሪያ ድንኳኑንና በውስጡ ያለውን ሁሉ ቀባው፤ እናም ለያህዌ ቀደሳቸው፡፡
\v 11 በመሰዊያው ላይ ዘይቱን ሰባት ጊዜ ረጨው፣ እናም መሰዊያውንና መገልገያዎቹን ሁሉ ቀባቸው፣ እንዲሁም የመታጠቢያ ሳህኑንና ማስቀመጫውን፣ ለያህዌ ቀደሳቸው፡፡
\s5
\v 12 አሮንን ያህዌ ለመለየት ከቅባቱ ዘይት ጥቂቱን በአሮን ራስ ላይ አፈሰሰው፡፡
\v 13 ሙሴ ያህዌ እንዳዘዘው የአሮንን ወንድ ልጆች አቅርቦ እጀጠባብ አለበሳቸው፣ በወገባቸው ዙሪያ መታጠቂያ አሰረላቸው፣ በራሳቸው ላይ በፍታ ጨርቅ ጠቀለለላቸው፡፡
\s5
\v 14 ሙሴ ለኃጢአት መስዋዕት በሬ አመጣ፣ አሮንና ልጆቹ ለኃጢአት መስዋዕት ባመጡት በሬ ላይ እጆቻቸውን ጫኑ፡፡
\v 15 በሬውን አርዶ ደሙን በመሰዊያው ቀንዶች ውስጥ በጣቱ ጨመረ፣ በመሰዊያው ስር ደሙን አፈሰሰ፣ ለማስተስረይ ለእግዚአብሔር ለየው፡፡
\s5
\v 16 በመስዋዕቱ ሆድ ዕቃ ውስጥ ያለውን ስብ ሁሉ አወጣ፣ በጉበቱ መሸፈኛና በሁለቱ ኩላሊቶች ላይ ያለውን ስብ ወስዶ በመሰዊያው ላይ ሁሉንም አቃጠለው፤
\v 17 ነገር ግን በሬውን፣ ቆዳውን፣ ስጋውን እና ፈርሱን ያህዌ እንዳዘዘው ከሰፈር አውጥቶ አቃጠለው፡፡
\s5
\v 18 ሙሴ ለሚቃጠል መስዋዕት ጠቦቱን አቀረበ፣ አሮንና ልጆቹ በጠቦቱ ራስ ላይ እጃቸውን ጫኑ፡፡
\v 19 ሙሴም ጠቦቱን አርዶ በመሰዊያው ዙሪያ ደሙን ረጨ፡፡
\s5
\v 20 ጠቦቱን ቆራርጦ ራሱንና ቁርጥራጩን እንዲሁም ስቡን አቃጠለ፡፡
\v 21 የሆድ ዕቃውን ክፍሎችና እግሮቹን በውሃ አጠበ፣ ከዚያም ጠቦቱን በሙሉ በመሰዊያው ላይ አቃጠለ፡፡ ያህዌ ሙሴን እንዳዘዘው ይህ የሚቃጠል መስዋዕት ነው፤ ደግሞም ለያህዌ በእሳት የተዘጋጀ ጣፋጭ መዓዛ ነው፡፡
\s5
\v 22 ከዚያም ሙሴ ሌላውን ጠቦት ያቀርባል፣ ይህም የክህነት ሹመት መስዋዕት ነው፣ እናም አሮንና ልጆቹ በጠቦቱ ራስ ላይ እጃቸውን ይጭናሉ፡፡
\v 23 አሮን ጠቦቱን ያርዳል፣ ሙሴም ከደሙ ጥቂት ወስዶ በአሮን ቀኝ ጆሮ ጫፍ ላይ፣ በቀኝ እጁ አውራ ጣት እና በቀኝ እግሩ አውራ ጣት ላይ ያደርጋል፡፡
\v 24 የአሮንን ልጆች አቅርቦ፣ በቀኝ ጆሯቸው ጫፍ ላይ፣ በቀኝ እጃቸው አውራ ጣት ላይ እና በቀኛ እግራቸው አውራ ጣት ላይ ከደሙ ጥቂት ወስዶ ያደርጋል፡፡ ከዚያ ሙሴ የበጉን ደም በመሰዊያው ጎኖች ሁሉ ይረጫል፡፡
\s5
\v 25 ስቡን፣ ላቱን፣ በሆድ ዕቃ ክፍሎች ውስጥ ሁሉ የሚገኘውን ስብ፣ የጉበቱን መሸፈኛ፣ ሁለቱን ኩላሊቶች እና በላያቸው የሚገነውን ስብ እንዲሁም ቀኝ ወርቹን ወሰደ፡፡
\v 26 በያህዌ ፊት ከነበረው መሶብ እርሾ የሌለበት አንድ ህብስት ይወስዳል፣ደግሞም በዘይት ተለውሶ ከተሰራው ዳቦ አንዱን እና አንድ ስስ ቂጣ ይውሰድና በስቡና በቀኝ ወርች ላይ ያኖረዋል፡፡
\v 27 ሁሉንም በአሮን እጆችና በአሮን ወንድ ልጆች እጆች ላይ ያስቀምጠዋል፣ ይህንንም ለሚወዘወዝ መስዋዕት በያህዌ ት ያቀርባሉ፡፡
\s5
\v 28 ከዚያም ሙሴ ከእጃቸው ይወስድና የሚቃጠል መስዋዕት አድርጎ ያቀርበው፡፡ እነዚህ የክህነት ሹመት መስዋዕት ናቸው፤ ጣፋጭ መዓዛ ሆነው ይቀርባሉ፡፡ ይህ በእሳት ለያህዌ የሚቀርብ መስዋዕት ነው፡፡
\v 29 ሙሴ ፍርምባውን ወስዶ ለያህዌ መስዋዕት አድርጎ ይወዝውዘው፡፡ ያህዌ እንዳዘዘው ይህ ከጠቦቱ የክህነት ሹመት የሙሴ ድርሻ ነው፡፡
\s5
\v 30 ሙሴ በመሰዊያው ላይ ካለው ከቅባት ዘይቱና ከደሙ ጥቂት ወስዶ እነዚህን በአሮን ላይ፣ በልብሶ ላይ፣ በወንድ ልጆቹ ላይ እና ከእርሱ ጋር በልጆቹ ልብሶች ላይ ይረጫል፡፡ በዚህ መንገድ አሮንና የክህነት ልብሱን እንዲሁም ልጆቹንና ልብሳቸውን ለያህዌ ይቀድሳል፡፡
\s5
\v 31 ደግሞም ሙሴ ለአሮንና ለልጆቹ እንዲህ አለ፣ “በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ ስጋውን ቀቅሉት፣ በዚያም ስፍራ በሹመት መስጫው መሶብ ውስጥ ያለውን ህብስትም ‘አሮንና ልጆቹ ይብሉት’ ብዬ እንዳዘዝኩት ብሉት፡፡
\v 32 ከስጋውና ከህብስቱ የተረፈውን በሙሉ አቃጥሉት፡፡
\v 33 የሹመት ስርዓቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ ለሰባት ቀናት ከመገናኛው ከመገናኛው ድንኳን መግቢያ አትለፉ፡፡ ያህዌ በሰባት ቀናት ውስጥ ይሾማችኋል፡፡
\s5
\v 34 በዚህ ቀን የሚሆነው እናንተን ለማስተረይ ያህዌ እንዲደረግ ያዘዘው ነው፡፡
\v 35 ለሰባት ቀናት ቀንም ሆነ ሌሊት በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ ትቆያላችሁ፣ ደግሞም የያህዌን ትዕዛዝ ትጠብቃላችሁ፣ ይህን ካደረጋችሁ አትሞቱም፣ ምክንያቱም የታዘዝኩት ይህንን ነው፡፡”
\v 36 ስለዚህም አሮንና ልጆቹ ያህዌ በሙሴ በኩል እንዲያደርጉት ያዘዛቸውን ሁሉንም ነገር አደረጉ፡፡
\s5
\c 9
\p
\v 1 በስምንተኛው ቀን ሙሴ አሮንንና ልጆቹን እንዲሁም የእስራኤልን ሽማግሌዎች ጠራ፡፡
\v 2 አሮንን እንዲህ አለው፣ “ለኃጢአት መስዋዕት ከመንጋው እምቦሳ እና ነውር የሌለበትን አውራ በግ ወስደህ በያህዌ ፊት ሰዋቸው፡፡
\s5
\v 3 እስራኤል ሰዎች እንዲህ ባላቸው፣ ‘ለኃጢአት መስዋዕት ወንድ ፍየል ውሰድ እንደዚሁም ነውር የሌለባቸው የአንድ አመት እምቦሳና ጠቦት ለሚቃጠል መስዋዓት ውሰድ፤
\v 4 እንዲሁም በያህዌ ፊት የሰላም መስዋት ለመስዋዕት አንድ በሬና አንድ አውራ በግ ውሰድ፣ በዘይት የተለወሰ የእህል ቁርባንም አቅርብ፣ ምክንያቱም ዛሬ ያህዌ ይገለጥላችኋል፡፡”
\v 5 ስለዚህም ሙሴ ያዘዘውን ሁሉ ወደ መገናኛው ድንኳን አመጡ፣ የእስራኤል ጉባኤም ሁሉ ቀርበው በያህዌ ፊት ቆሙ፡፡
\s5
\v 6 ከዚያም ሙሴ እንዲህ አለ፣ “ያህዌ እንድታደርጉት ያዘዘው ይህንን ነው፣ስለዚህም ክብሩ ይገለጥላችኋል፡፡”
\v 7 ሙሴ አሮንን እንዲህ አለው፣ “ወደ መዊያው ቀርበህ የኃጢአት መስዋዕትህንና የሚቃጠል መስዋዕትህን አቅርብ፣ ደግሞም ያህዌ እንዳዘዘው ለራስህና ለህዝቡ አስተስርይ፣ ለህዝቡ ማስተስረያ ለማቅረብ መስዋዕቱን ሰዋ፡፡” 8ስለዚህም አሮን ወደ መሰዊያው ቀርቦ ለራሱ የሆነውን መስዋዕት ለኃጢአት መስዋዕት እምቦሳውን አረደ፡፡
\s5
\v 8 ስለዚህም አሮን ወደ መሰዊያው ቀርቦ ለራሱ የሆነውን መስዋዕት ለኃጢአት መስዋዕት እምቦሳውን አረደ፡፡
\v 9 የአሮን ልጆቸ ደሙን አቀረቡለት፣ እርሱም ጣቱን ደሙ ውስጥ እየነከረ በመሰዊያው ቀንዶች ውስጥ ጨመረ፤ ከዚያም በመሰዊያው ስር ደሙን አፈሰሰ፡፡
\s5
\v 10 ሆኖም ያህዌ ሙሴን እንዳዘዘው ስቡን፣ ኩላሊቶቹን እና በመሰዊያው ላይ የጉበቱን ሽፋን የኃጢአት መስዋዕት አድርጎ አቃጠላቸው፡፡
\v 11 ስጋውንና ቆዳውን ከሰፈር ውጭ አቃጠለው፡፡
\s5
\v 12 አሮን የሚቃጠለውን መስዋዕት አረደ፣ ልጆቹ በመሰዊያው ዙሪያ የሚረጨውን ደም ሰጡት፡፡
\v 13 ከዚያ የሚቃጠለውን መስዋዕት ከከብቱ ራስ ጋር እየቆራረጡ ሰጡት፣ እርሱም በመሰዊያው ላይ አቃጠለው፡፡
\v 14 የሆድ ዕቃዎቹንና እግሮቹን አጥቦ በመሰዊያው ላይ በሚቃጠል መስዋዕቱ ላይ አቃጠላቸው፡፡
\s5
\v 15 አሮን አንድ ፍየል የህዝቡን መስዋዕት አቀረበ፣ ከዚያ ለኃጢአታቸው መስዋዕት አድርጎ አረደው፤ በመጀመሪያው ፍየል ላይ እንዳደረገው ሁሉ ለኃጢአት መስዋዕትነት ሰዋው፡፡
\v 16 ያህዌ እንዳዘዘው የሚቃጠል መስዋዕቱን አቅርቦ ሰዋው፡፡
\v 17 የእህል ቁርባኑን፣ ከእህል ቁርባኑ እፍኝ ሙሉ ወስዶ ከማለዳው የሚቃጠል መስዋዕት ጋር በመሰዊያው ላይ አቃጠለው፡
\s5
\v 18 እንዲሁም ለህዝቡ የሰላም መስዋዕት የሆነውን መስዋዕት በሬውንና አውራ በጉን አረደ፡፡ የአሮን ልጆች በመሰዊያው ዙሪያ የሚረጨውን ደሙን ሰጡት፡፡
\v 19 ሆኖም፣ የበሬውንና የአውራ በጉን ስብ፣ ላቱን፣ ሆድ ዕቃውን ክፍሎች የሸፈነውን ስብ፣ ኩላሊቶቹን፣ የጉበቱን ሽፋን
\s5
\v 20 እነዚህን በፍርምባው ላይ አደረጉ፣ ከዚያም አሮን ሙሴ ባዘዘው መሰረት ስቡን በመሰዊያው ላይ አቃጠለው፡፡
\v 21 አሮን ፍርምባውንና የቀኝ ወርቹን መስዋዕት አድርጎ በያህዌ ፊት ይወዝስዘውና እነዚህን ለያህዌ ያቅርብ፡፡
\s5
\v 22 ከዚያ አሮን አጆቹን ወደ ህዝቡ አንስቶ ይባርካቸው፤ ቀጥሎ የኃጢአት መስዋዕቱን፣ የሚቃጠል መስዋዕቱንና የሰላም መስዋዕቱን አቅርቦ ይወርዳል፡፡
\v 23 ሙሴና አሮን ወደ መገናኛው ድንኳን ይሂዱ፣ ከዚያ ተመልሰው ይውጡና ህዝቡን ይባርኩ፣ እናም የያህዌ ክብር ለህዝቡ ሁሉ ይገለጣል፡፡
\v 24 ከያህዌ ዘንድ እሳት ወጥቶ የሚቃጠል መስዋዕቱንና በመሰዊያው ላይ ያለውን ስብ ሁሉ በላ፡፡ ህዝቡ ሁሉ ይህንን ባዩ ጊዜ ጮኸው በፊታቸው ተደፉ፡፡
\s5
\c 10
\p
\v 1 የአሮን ልጆች ናዳብና አብዩድ እያንዳንዳቸው ጥናዎቻቸውን ወስደው እሳት አደረጉበት ከዚያም ዕጣን ጨመሩበት፡፡ ከዚያ በያህዌ ፊት እርሱ እንዲያቀርቡ ያላዘዛቸውን ያልተፈቀደ ዕሳት አቀረቡ፡፡
\v 2 ስለዚህም ከያህዌ ዘንድ እሳት ወጥታ በላቻቸው፣ እነርሱም በያህዌ ፊት ሞቱ፡፡
\s5
\v 3 ከዚያም ሙሴ አሮንን፣ “ያህዌ ‘ወደ እኔ በሚቀርቡ ላይ ቅድስናዬን እገልጻለሁ፡፡ በሰዎች ሁሉ ፊት እከብራለሁ’ ሲል ይህን ማለቱ ነው” አለው፡፡ አሮንም ምንም አልመለሰም፡፡
\v 4 ሙሴ የአሮን አጎት የሆነውን የዑዝኤልን ልጆች ሚሳኤልንና ኤልጻፋንን ጠርቶ እንዲህ አላቸው፣ “ወደዚህ ኑና ከመቅደሱ ደጃፍ ወንድሞቻችሁን ተሸክማችሁ ከሰፈር አውጣቸው፡፡”
\s5
\v 5 ስለዚህም ሙሴ እንዳዘዘው ቀርበው የክህነት ቀሚሳቸውን እንደለበሱ ተሸክመው ከሰፈር አወጧቸው፡፡
\v 6 ከዚያም ሙሴ ለአሮንና ለልጆቹ ለአልአዛርና ለኢታምር እንዲህ አላቸው፣ “እንዳትቀሰፉ ፀጉራችሁን አትንጩ፣ ልብሳችሁንም አትቅደዱ፣ ያህዌ በህዝቡ ላይ ሁሉ እንዳይቆጣ ተጠንቀቁ፡፡ ነገር ግን ቤተዘመዶቻችሁና መላው የእስራኤል ቤት የያህዌ እሳት ለበላቻቸው ያልቅሱ፡፡
\v 7 እናንተ ግን ከመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አትለፉ፣ የያህዌ የቅባት ዘይት በእናንተ ላይ ነውና ትሞታላችሁ፡፡ ስለዚህም ሙሴ እንዳዘዘው አደረጉ፡፡
\s5
\v 8 ያህዌ አሮንን እንዲህ አለው፣
\v 9 “አንተ፣ ወይም ከአንተ ጋር የሚሆኑ ልጆችህ ወደ መገናኛው ድንኳን ስትገቡ እንዳትሞቱ ወይን ጠጅ ወይም የሚያሰክር መጠጥ አትጠጡ፡፡ ይህ በትውልዳችሁ ሁሉ ቋሚ ስርዓት ይሆናል፣
\v 10 ቅዱስ በሆነውና ተራ በሆነው መሃል ለመለየት፣ ንጹህ በሆነውና ንጹህ ባልሆነው መሃል ለመለየት፣
\v 11 ለእስራኤል ህዝብ ሁሉ በሙሴ በኩል ያህዌ ያዘዘውን ስርዓት ሁሉ አስተምሩ፡፡”
\s5
\v 12 ሙሴ ለአሮንና ለተረፉት ልጆቹ ለአልአዛርና ለኢታምርን እንዲህ አላቸው፣ “በእሳት ለያህዌ ከቀረበው የእህል ቁርባን የተረፈውን መስዋዕት ውሰድ፣ እጅግ ቅዱስ ነውና እርሾ ሳይገባበት ከመሰዊያው አጠገብ ብሉት፡፡
\v 13 በተቀደሰው ስፍራ ብሉት፣ ምክንያቱም በእሳት ለያህዌ ከቀረበው መስዋዕት ይህ የአንተና የልጆችህ ድርሻ ነው፣ እንድነግርህ የታዘዝኩት ይህንን ነው፡፡
\s5
\v 14 ለመስዋዕት የተወዘወዘውን ፍርምባና ለያህዌ የቀረበውን ወርች እግዚአብሔር ደስ በሚሰኝበት በተቀደሰው ስፍራ ብሉት፡፡ እነዚህን ድርዎቻችሁን አንተ፣ እንዲሁም ወንዶችና ሴቶች ልጆች ብሉት፣ እነዚህ የእስራኤል ህዝብ ከሚያቀርበው የህብረት መስዋዕት የአንተና የልጆችህ ድርሻ ሆነው ተሰጥተዋል፡፡
\v 15 ለያህዌ መስዋዕት ሆኖ የቀረበውን ወርች እና መስዋዕት ሆኖ የተወዘወዘውን ፍርምባ በእሳት ከተዘጋጀው የስብ መስዋዕቶች ጋር ከፍ አድርገው ለመወዘወዝና ለያህዌ መስዋዕት ለማድረግ በአንድነት ያቅርቧቸው፡፡ ይህም ያህዌ እንዳዘዘው ለዘለዓለም የአንተና የልጆችህ ድርሻ ይሆናል፡፡”
\s5
\v 16 ከዚያ ሙሴ ለኃጢአት መስዋዕት ስለሚሆነው ፍየል ጠየቀ፣እናም በእሳት እንደተቃጠለ አወቀ፡፡ ስለዚህም በአልአዛርና በኢታምር በተቀሩትም የአሮን ልጆች ላይ ተቆጣ፤ እንዲህም አላቸው፣
\v 17 “ይህ የኃጢአት መስዋዕት እጅግ የተቀደሰ ሆኖ ሳለና የጉባኤውን በደል በእረሱ ፊት እንድታስወግዱበትና ኃጢአታቸውንም እንድታስተረዩላቸው ሰጥቷችሁ ሳለ ስለምን በቤተ አምልኮው ስፍራ አልበላችሁትም?
\v 18 ተመልከቱ፣ ደሙ ወደ ቤተመቅደስ ውስጥ አልመጣም፤ እንዳዘዝኳችሁ በቤተ መቅደሱ አካባቢ ለትበሉት ይገባ ነበር፡፡”
\s5
\v 19 ከዚያም አሮን ለሙሴ እንደህ ሲል መለሰለት፣ “እነሆ፣ ዛሬ የኃጢአት መስዋዕታቸውን እና የሚቃጠል መስዋዕታቸውን በያህዌ ፊት አቀርቡ፣ እናም ይህ ነገር በእኔ ላይ ደርሷል፡፡ ዛሬ እኔ የኃጢአት መስዋዕቱን ብበላ ኖሮ ይህ በያህዌ ፊት ደስ ያሰኝ ነበርን?”
\v 20 ሙሴ ያንን ሲሰማ መልሱ አረካው፡፡
\s5
\c 11
\p
\v 1 ያህዌ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፣
\v 2 “ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ በሏቸው፣ ‘በምድር ላይ ከሚገኙ እንስሳት ሁሉ የምትመገቧቸው ህያዋን ነገሮች እነዚህ ናቸው፡፡
\s5
\v 3 የተሰነጠቀ ሰኮና ያላቸውንና የሚያመሰኩትን ትመገባላችሁ፡፡
\v 4 ሆኖም፣ የሚያመሰኩ ቢሆኑም ነገር ግን የተሰነጠቀ ሰኮና የሌላቸውን እንደ ግመል ያሉትን አትብሉ፤ምክንያቱም ያመሰኳሉ ነገር ግን ሰኮናው አልተሰነጠቀም፡፡ ስለዚህ ግመል ለእናንተ ንጹህ አይደለም፡፡
\s5
\v 5 እንዲሁም ሽኮኮ ያመሰኳል ነገር ግን የተሰነጠቀ ሰኮና የለውም፣ ይህም ለእናንተ ንጹህ አይደለም፡፡
\v 6 ጥንቸል ቢያመሰኳም የተሰነጠቀ ሰኮና ስለሌለው ለእናንተ ንጹህ አይደለም፡፡
\v 7 አሳማ የተሰነጠቀ ሰኮና ቢኖረውም፣ አያመሰኳም ስለዚህ ለእናንተ ንጹህ አይደለም፡፡
\v 8 የእነዚህን ስጋ ፈጽሞ አትብሉ፣ ጥንባቸውንም አትንኩ፡፡ እነርሱ ለእናንተ ንጹህ አይደሉም፡፡
\s5
\v 9 በውቂያኖስም ሆነ በባህር በውሃ ውስጥ ከሚኖሩ እንስሳት የምትበሏቸው ክንፍና ቅርፊት ያላቸው ናቸው፡፡
\v 10 ነገር ግን በውቂያኖስ ወይም በባህር የሚኖሩ ክንፍና ቅርፊት የሌላቸው ህያዋን ፍጥረታት ሁሉ፣በውሃ ውስጥ የሚንቀሳቀሱትን ጨምሮ እንዲሁም በውሃ ውስጥ ያሉት እንዲህ ያሉ ህያዋን ፍጥረታት በሙሉ በእናንተ ዘንድ ጸያፍ ናቸው፡፡
\s5
\v 11 ጸያፍ ሊሆኑ ስለሚገባቸውም፣ ስጋቸውን ልትበሉ አይገባም፣ እንደዚሁም በድናቸውም ጸያፍ ነው፡፡
\v 12 በውሃ ውስጥ የሚኖሩ ቅርፊት የሌላቸው እንስሳት ሁሉ፣በእናንተ ዘንድ ጸያፍ ናቸው፡፡
\s5
\v 13 ልትጸየፏቸው የሚገቡና የማትበሏቸው ወፎች እነዚህ ናቸው፤ ንስር፣ ጥንብ አንሳ፣
\v 14 ጭላት፣ ማንኛውም አይነት የሎስ
\v 15 ማንኛውም አይነት ቁራ፣
\v 16 የተለያ አይነት ጉጉት፣ የባህር ወፍ እና ማንኛውም ዐይነት ጭልፊት፡፡
\s5
\v 17 ትናንሽና ትላልቅ ጉጉቶችን ትጸየፋላችሁ፣ርኩምና ጋጋኖ፣
\v 18 የተለያዩ ጉጉቶች፣ ይብራ፣
\v 19 ሽመላ፣ ማናቸውም ዐይነት የውሃ ወፍ፣ ሳቢሳ፣ ጅንጁላቲ ወፍና የለሊት ወፍ፡፡
\s5
\v 20 በእግራቸው የሚራዱ ክንፍ ያላቸው በራሪ ነፍሳት በሙሉ በእናንተ ዘንድ አስጸያፊ ናቸው፡፡
\v 21 ሆኖም ግን ከእግራቸው በላይ በምድር ላይ የሚፈናጠሩበት አንጓ ያላቸውን ማናቸውንም የሚበሩ ነፍሳት መብላት ትችላላችሁ፡፡
\v 22 እንደዚሁም ደግሞ ማናቸውንም ዐይነት አንበጣ፣ ትልቅ የአንበጣ ዝርያ፣ ፌንጣና ዝንቢት መብላት ትችላላችሁ፡፡
\v 23 ነገር ግን አራት እግር ያላቸው የሚበሩ ነፍሳት ሁሉ በእናንተ ዘንድ የተጠሉ ናቸው፡፡
\s5
\v 24 ከእነዚህ እንስሳት ውስጥ የአንዱን በድን ብትነኩ እስከ ማታ ድረስ የረደሳችሁ ናችሁ፡፡
\v 25 ከእነዚህ የአንዱን በድን ያነሳ ማንም ሰው ልብሱን ይጠብ፣ እስከ ማታ ድረስ እርኩስ ነው፡፡
\s5
\v 26 ማንኛውም ሙሉ ለሙሉ ያልተሰነጠቀ ሰኮና ያለው እንስሳ ወይም የማያመሰኳ እንስሳ በእናንተ ዘንድ ጸያፍ ነው፡፡ እነዚህን የነካ ሁሉ ይረክሳል፡፡
\v 27 በአራት እግሩ ከሚራመድ እንስሳ መሃል በመዳፋቸው የሚሄዱ ሁሉ በእናንተ ዘንድ እርሱስ ናቸው፡፡ እንደነዚህ ያሉትን በድናቸውን የነካ እስከ ማታ እርኩስ ነው፡፡
\v 28 እንደነዚህ ያሉትን በድናቸውን ያነሳ ልብሱን ይጠብ እስከ ማታ ድረስ እርኩስ ይሆናል፡፡ እነዚህ እንስሳት በእናንተ ዘንድ እርኩስ ናቸው፡፡
\s5
\v 29 በምድር ላይ ከሚሳቡ እንስሳት መሃል፣ በእናንተ ዘንድ እርኩስ የሆኑት እነዚህ ናቸው፡ አቁስጣ፣ አይጥ፣ ማናቸውም አይነት እንሽላሊት
\v 30 ትንሽ የቤት ላይ እንሽላሊት እና እስስት
\s5
\v 31 ከሚሳቡ እንስሳት በእናንተ ዘንድ እርኩስ የሆኑት እነዚህ ናቸው፡፡ ከእነዚህ የሞቱትን አንዳቸውን የነካ ሰው እስከ ምሽት እርሱስ ይሆናል፡፡
\v 32 ከእነዚህ መሃል አንዱ ሞቶ በማናቸውም ከእንጨት፣ ከጨርቅ፣ ከቆዳ ወይም ከበርኖስ በተሰራ ነገር ላይ ቢወድቀቅ ያዕቃ እርኩስ ይሆናል፡፡ ዕቃው ምንም ይሁን ለምንም አይነት ተግባር ይዋል ውሃ ውስጥ ይነከር እስከ ምሽት ድረስ እርኩስ ነው፡፡ ከዚያ ንጹህ ይሆናል፡፡
\v 33 ንጹህ ያልሆነ እንስሳ የገባበት ወይም የነካው የሸክላ ማሰሮ እንዲሁም በውስጡ ያለው ነገር ሁሉ እርኩስ ይሆናል፤ ያንን ማሰሮ ሰባብረው፡፡
\s5
\v 34 ማናቸውም ለመበላት የተፈቀደ ምግብ፣ ንጹህ ካልሆነ ማሰሮ ውሃ ቢገባበት እርኩስ ይሆኖል፡፡ እንዲህ ካለው ማሰሮ ማንኛውም ነገር ቢጠጣ ያረክሳል፡፡
\v 35 እርኩስ ከሆነ እንስሳ በድን ማናቸውም አካሉ የወደቀበት ምድጃም ሆነ የማብሰያ ሸክላ እንዲሁም ማንኛውም ነገር ይረክሳል፡፡ ይሰባበር፡፡ እርኩስ ነው፣ በእናንተም ዘንድ የተጠላ ይሁን፡፡
\s5
\v 36 የመጠጥ ውሃ የሚገኝበት ምንጭ ወይም የውሃ ጉድጓድ እንዲህ ያሉ እንስሳት ቢገኙበትም ንጹህ ነው፡፡ ነገር ግን ማንም ሰው በውሃው ውስጥ የሚገኘውን እርኩስ የሆነውን በድን ቢነካ እርኩስ ይሆናል፡፡
\v 37 ንጹህ ያልሆነ እንስሳ በድን በዘር ላይ ቢወድቅ፣ እነዚያ ዘሮች የረከሱ ይሆናሉ፡፡
\v 38 ነገር ግን በዘሮቹ ላይ ውሃ ቢፈስ ንጹህ ያልሆነው እንስሳ በድን ማንኛውም አካል የተክል ዘሩ ላይ ቢወድቅ ዘሩ በእናንተ ዘንድ እርኩስ ይሆናል፡፡
\s5
\v 39 ለመበላት ከተፈቀደው እንስሳ አንዱ ቢሞት፣ በድኑን የነካው ሰው እስከ ምሽት እርኩስ ይሆናል፡፡
\v 40 ደግሞም እንዲህ ያለውን በድን ያነሳ ሰው ልብሱን ያጥባል፣ እስከ ምሽት ድረስ እርኩስ ይሆናል፡፡
\s5
\v 41 ማንኛውም በምድር ላይ የሚሳብ እንስሳ ጸያፍ ነው፤ አይበላም፡፡
\v 42 በሆዱ የሚሳብ እንስሳ ሁሉ፣ እና በአራቱም እግሮቹ የሚራመድ፣ወይም ማንኛውም ብዙ እግሮች ያሉት - በምድር የሚሳብ እንስሳን ሁሉ፣ አትብሉ፤ እነዚህ ጸያፍ ናቸው፡፡
\s5
\v 43 በደረቱ በሚሳብ ማናቸውም ህያው ፍጥረት ራሳችሁን አታርክሱ፤ እነዚህ እናንተን ያረክሳሉ፡፡
\v 44 እኔ አምላካችሁ ያህዌ ነኝ፡፡ በምድር በሚንቀሳቀስ በማናቸውም አይነት እንስሳ ራሳችሁን አታርክሱ፡፡
\v 45 እኔ አምላካችሁ እሆን ዘንድ ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ ያህዌ ነኝ፡፡ ስለዚህ እኔ ቅዱስ እንደሆንኩ እናንተም ቅዱስ መሆን አለባችሁ፡፡
\s5
\v 46 ስለ እንስሳት፣ ስለ ወፎች፣ በውሃ ውስጥ ስለሚንቀሳቀሱ ማናቸውም ህያዋን ፍጥረታት፣ እንዲሁም በምድር ላይ ስለሚሳቡ ፍጥረታት ህጉ ይህ ነው፤
\v 47 ንጹህ ባልሆኑና ንጹህ በሆኑት መካከል ልዩነት ለመፍጠር፣ እና በሚበሉ ህያዋን ነገሮችና በማይበሉ ህያዋን ነገሮች መሃል ለመለየት ህጉ ይህ ነው፡፡’”
\s5
\c 12
\p
\v 1 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
\v 2 “ለእስራኤል ሰዎች እንደህ በላቸው፣ ‘አንዲት ሴት ብታረግዝና ወንድ ልጅ ብትወልድ፣ ልክ እንደ ወር አበባዋ ወቅት ለሰባት ቀናት ንጹህ አይደለችም፡፡
\v 3 በስምንተኛው ቀን ህጻኑ ልጅ መገረዝ አለበት፡፡
\s5
\v 4 ከዚያ የእናቲቱ ከደሟ መንጻት ለሰላሳ ሶስት ቀናት ይቆያል፡፡ ምንም አይነት የተቀደሰ ነገር መንካት የለባትም ወይም የመንጻቷ ቀናት እስኪፈጸም ድረስ ወደ ቤተመቅደስ አትምጣ፡፡
\v 5 ሴት ልጅ ከወለደች፣ በወር አበባዋ ወቅት እንደነበረችው ለሁለት ሳምንታት ንጹህ አትሆንም፡፡ ከዚያ የእናትየው የመንጻት ስርዓት ለስድስት ቀናት ይቀጥላል፡፡
\s5
\v 6 ወንድ ልጅም ሆነ ሴት ልጅ ከወለደች በኋላ የመንጻቷ ቀናት ሲያበቃ ለካህኑ በመገናኛው ድንኳን መግቢያ የአንድ አመት ጠቦት ለሚቃጠል መስዋዕት እንዲሁም ለኃጢአት መስዋዕት ዋኖስ ወይም ዕርግብ ታቅርብ፡፡
\s5
\v 7 ከዚያ ካህኑ መስዋዕቱን በያህዌ ፊት ይሰዋና ያስተሰርይላታል፣ እናም ከደሟ መፍሰስ ንጹህ ትሆናለች፡፡ ወንድም ይሁን ሴት ልጅ ለወለደች ሴት ህጉ ይህ ነው፡፡
\v 8 ጠቦት ማቅረብ ባትችል፣ ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት ርግቦች ትውሰድ፣ አንዱን ለሚቀጠል መስዋዕት ሌላውን ለኃጢአት መስዋዕት ታቅርብ እናም ካህኑ ያስተሰርይላታል፣ ከዚያም ንጹህ ትሆናለች፡፡’”
\s5
\c 13
\p
\v 1 ያህዌ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፣
\v 2 “ማንኛውም ሰው በሰውነቱ ቆዳ ላይ እባጭ ወይም ችፍታ ወይም ቋቁቻ ቢወጣና ቢቆስል በሰውነቱ ላይ የቆዳ በሽታ ይሆናል፣ በዚህ ጊዜ ወደ ሊቀካህኑ አሮን ይምጣ፣ አሊያም ካህናት ከሆኑት ልጆቹ ወደ አንዱ ይምጣ፡፡
\s5
\v 3 ከዚያ በሰውነቱ ቆዳ ላይ ያለውን በሽታ ካህኑ ይመረምረዋል፡፡ በበሽታው ዙሪያ ያለው ጸጉር ወደ ነጭነት ከተለወጠ፣ እና በሽታው በቆዳው ላይ ከሚታየው ይልቅ የከፋ ሆኖ ከተገኘ ተላላፊ በሽታ ነው፡፡ ካህኑ ከመረመረው በኋላ፣ ንጹህ አለመሆኑን ያሳውቅ፡፡
\v 4 በቆዳው ላይ የታየው ቋቁቻ ነጭ ከሆነ፣ እና ወደ ቆዳው ዘልቆ የገባ ካልሆነ፣ እንዲሁም በህመሙ አካባቢ የሚገኘው ጸጉር ወደ ነጭነት ካልተለወጠ፣ ካህኑ በሽታው ያለበትን ሰው ለሰባት ቀናት ያገልግለው፡፡
\s5
\v 5 በሰባተኛው ቀን፣ ካህኑ በእርሱ እይታ በሽታው አየከፋ በቆዳው ላይ እየሰፋ አለመሄዱን ለማየት ይመርምረው፡፡ በሽታው ለውጥ ካላሳየ፣ ካህኑ ለተጨማሪ ሰባት ቀናት ሰውየውን አግልሎ ያቆየው፡፡
\v 6 በሰባተኛው ቀን በሽታው እየተሻለው እንደሆነና በቆዳው ላይ እየሰፋ እንደላሆነ ለማየት ካህኑ ሰውየውን ደግሞ ይመረምረዋል፡፡ በሽታው ለውጥ ካለው፣ ካህኑ ሰውየው ንጹህ መሆነኑን ይገልጻል፡፡ ይህ ሽፍታ ነው፡፡ ሰውየው ልብሱን ይጠብ፣ እናም ከዚህ በኋላ ንጹህ ነው፡፡
\s5
\v 7 ነገር ግን ሰውየው ራሱን ለካህን ካሳየ በኋላ ሽፍታው በቆዳው ላይ ከተስፋፋ፣ እንደገና ራሱን ለካህን ያሳይ፡፡
\v 8 ሽፍታው ይበልጥ በሰውየው ቆዳ ላይ እየሰፋ መሆኑን ለማየት ካህኑ ይመረምረዋል፡፡ ከተስፋፋ፣ ከዚያ ካህኑ ሰውየው ንጹህ አይደለም ይላል፡፡ ይህ ተላላፊ የቆዳ በሽታ ነው፡፡
\s5
\v 9 ተላላፊ የቆዳ በሽታ በአንድ ሰው ላይ ሲገኝ፣ ይህ ሰው ወደ ካህን ይምጣ፡፡
\v 10 ካህኑ በሰውየው ቆዳ ላይ ነጭ ዕብጠት መኖሩን ለማየት ይመረምረዋል፣ ጸጉሩ ወደ ነጭነት መቀየሩን፣ ወይም በዕብጠቱ ላይ የስጋ መላጥ መኖሩን ይመልከት፡፡
\v 11 እንዲህ ያለ ነገር ካለ፣ ይህ ጽኑ የቆዳ ህመም ነው፣ እናም ካህኑ ሰውየው ንጹህ አለመሆኑን ይግለጽ፡፡ ሰውየውን አያገለውም፣ ምክንያቱም ቀድሞውኑም ንጹህ አይደለም፡፡
\s5
\v 12 በሽታው በቆዳው ላይ በሰፊው ጎልቶ ከታየና የሰውየውን ቆዳ ከአናቱ እስከ እግሩ ከሸፈና፣ ካህኑ ይህ እስከ ታየው ድረስ፣ በሽታው የሰውየውን አካል ሸፍኖት እንደሆነ ለማየት ይመርምረው፡፡
\v 13 እንዲህ ሆኖ ከተገኘ፣ በሽታው ያለበት ሰው ንጹህ አለመሆኑን ካህኑ ይግለጽ፡፡ ሁሉም ወደ ንጣት ተለውጦ ከሆነ ንጹህ ነው፡፡
\v 14 ነገር ግን የስጋ መላጥ ከታየበት፣ ሰውየው ንጹህ አይደለም፡፡
\s5
\v 15 ካህኑ የስጋውን መላጥ ማየትና ንጹህ አለመሆኑን ይግለጽ፣ ምክንያቱም የተላጠ ስጋ ንጹህ አይደለም፡፡ ይህ ተላላፊ በሽታ ነው፡፡
\v 16 ነገር ግን የተላጠው ስጋ መለልሶ ነጭ ቢሆን፣ ሰውየው ወደ ካህኑ ይሂድ፡፡
\v 17 ካህኑ ስጋው ወደ ነጭነት ተመልሶ እንደሆነ ይመረምረዋል፡፡ እንዲህ ከሆነ ካህኑ ሰውየው ንጹህ መሆኑን ይገልጻል፡፡
\s5
\v 18 አንድ ሰው በቆዳው ላይ እባጭ ወጥቶ ሲድን፣
\v 19 እና በዕባጩ ስፍራ እብጠት ወይም ቋቁቻ፣ ቀላ ያለ ንጣት፣ ሲኖር ይህን ካህኑ ሊያየው ይገባል፡፡
\v 20 ካህኑ ይህ ወደ ታማሚው ቆዳ ዘልቆ የገባ መሆኑን እና በዚያ ዙሪያ ያለው ጸጉር ወደ ነጭነት መለወጡን ለማየት ይመረምራል፡፡ እንዲያ ከሆነ፣ ካህኑ ታማሚው ንጹህ አለመሆኑን ያሳውቃል፡፡ እብጠቱ በነበረበት ስፍራ እየሰፋ ከሄደ ይህ ተላላፊ በሽታ ነው፡፡
\s5
\v 21 ነገር ግን ካህኑ ይህንን መርምሮ በውስጡ ነጭ ጸጉር አለመኖሩን ከተመለከተ፣ እና ይህም ከቆዳው ስር ካልሆነ ሆኖም ከደበዘዘ ካህኑ ታማሚውን ለሰባት ቀናት ያግልለው፡፡
\v 22 በቆዳው ላይ በሰፊው ከተስፋፋ፣ ካህኑ ታማሚው ንጹህ አይደለም ይበል፡፡ ይህ የሚተላለፍ በሽታ ነው፡፡
\v 23 ነገር ግን ቋቁቻው በቦታው ከሆነና ካልተስፋፋ፣ ይህ የእባጩ ጠባሳ ነው፣ እናም ካህኑ ንጹህ ነው ብሎ ያስታውቅ፡፡
\s5
\v 24 አንድ ሰው ቆዳው ቃጠሎ ሲኖርበትና የስጋው መላጥ ቀላ ያለ ንጣት ወይም ነጭ ጠባሳ ሲሆን፣
\v 25 ካህኑ ያጠባሳ ስፍራ ወደ ንጣት መለወጡን እና ወደ ቆዳው ዘልቆ መግባቱን ለማየት ይመረምራል፡፡ እንደዚህ ከሆነ፣ ተላላፊ በሽታ ነው፡፡ ከቃጠሎው አልፎ ከውስጥ የመጣ ነው፣ እናም ካህኑ ሰውየው ንጹህ አለመሆኑን ያሳውቅ፡፡ ተላላፊ በሽታ ነው፡፡
\s5
\v 26 ነገር ግን ካህኑ በሚመረምርበት ጊዜ በስፍራው ነጭ ጸጉር አለመኖሩን ቢደርስበትና ቁስሉ ከቆዳው ስር ሳይሆን ቢቀር እየከሰመ ቢመጣ ካህኑ ታማሚውን ለሰባት ቀናት ያግልለው፡፡
\v 27 ከዚያም ካህኑ በሰባተኛው ቀን ይመርምረው፡፡ ምልክቱ በሰፊው በቆዳው ላይ ቢስፋፋ፣ ካህኑ ንጹህ አይደለም ብሎ ያሳውቅ፡፡ ይህ ተላላፊ በሽታ ነው፡፡
\v 28 ምልክቱ በስፍራው ከቆየና በቆዳው ላይ እየሰፋ ካልሄደ ነገር ግን ከከሰመ ይህ በቃጠሎው የመጣ እብጠት ነው፣ እናም ካህኑ ሰውየው ንጹህ መሆኑን ያሳውቅ፣ ይህ ከቃጠሎው የመጣ ጠባሳ እንጂ ሌላ ነገር አይደለም፡፡
\s5
\v 29 በአንድ ወንድ ወይም ሴት ራስ ወይም አገጭ ላይ ተላላፊ በሽታ ቢኖር፣
\v 30 ችግሩ ከቆዳው ስር የዘለቀ መሆኑና በላዩ ቢጫ ስስ ጸጉር እንዳለ ለማየት ካህኑ ካህኑ የተላላፊ በሽታ ምርመራ ያድርግለት፡፡ ይህ ከተገኘ፣ ካህኑ ሰውየው ንጹህ አለመሆኑን ያሳውቅ፡፡ ይህ የሚያሳክክ በሽታ ነው፣ በራስ ወይም አገጭ ላይ የወጣ ተላላፊ በሽታ ነው፡፡
\s5
\v 31 የሚያሳክከውን በሽታ መርምሮ ከቆዳ ስር ያልዘለቀ መሆኑን ቢያይ፣ ደግሞም በውስጡ ጥቁር ጸጉር ባይኖር፣ ካህኑ ሰውየውን በሚያሳክክ በሽታው ምክንያት ለሰባት ቀናት ያግልለው፡፡
\s5
\v 32 በሰባተኛው ቀን በሽታው ተስፋፍቶ እንደሆነ ለማየት ካህኑ ይመረምረዋል፡፡ ቢጫ ጸጉር ከሌለና፣ በሽታው ላይ ላዩን ብቻ ከታየ፣
\v 33 ሰውየው ይላጭ፣ ነገር ግን በሽታው የሚገኝበት ዙሪያ መላጨት የለበትም፣ እናም ካህኑ የሚያሳክክ በሽታ ያለበትን ሰው ለሰባት ቀናት ያግልለው፡፡
\s5
\v 34 በሰባተኛው ቀን በሽታው በቆዳው ላይ መስፋፋቱን ማቆሙን ለማየት ካህኑ ምርመራ ያደርጋል፡፡ በሽታው ቆዳውን ዘልቆ የገባ ካልሆነ፣ ካህኑ የሰውየውን ንጹህ መሆን ያሳውቅ፡፡ ሰውየው ልብሱን ይጠብ፣ እናም ከዚያ ንጹህ ይሆናል፡፡
\s5
\v 35 ነገር ግን ካህኑ ንጹህ መሆኑን ካሳወቀ በኋላ የሚያሳክከው በሽታ እየሰፋ ከሄደ ፣
\v 36 ካህኑ ዳግም ይመርምረው፡፡ በሽታው በሰውየው ቆዳ ላይ እየሰፋ ከሄደ፣ካህኑ ቢጫ ጸጉር መኖሩን መፈለግ አይኖርበትም፡፡ ሰውየው ንጹህ አይደለም፡፡
\v 37 ነገር ግን ካህኑ ሰውየውን የሚያሳክከው በሽታ እየሰፋ መሄዱን እንዳቆመ ከተመለከተ ንጹህ መሆኑን ያሳውቅ፡፡
\s5
\v 38 አንድ ወንድ ወይም አንዲት ሴት በቆዳቸው ላይ ነጭ ምልክቶች ቢወጣ
\v 39 ምልክቱ ዳለቻ መልክ ያለው በቆዳ ላይ የወጣ ሽፍታ ብቻ መሆኑን ለማየት ካህኑ ምርመራ ያድርግ፡፡ ሰውየው ንጹህ ነው፡፡
\s5
\v 40 የሰውየው ጸጉር ከራሱ ላይ ካለቀ፣መላጣ ነው፣ ነገር ግን ንጹህ ነው፡፡
\v 41 ደግሞም ከፊት ለፊት ጸጉሩ ተመልጦ ራሰ በራ ቢሆንም ንጹህ ነው፡፡
\s5
\v 42 ነገር ግን በህመም ምክንያት ፈዘዝ ያለ ቅላት በተመለጠው ራሱ ላይ ወይም በግምባሩ ላይ ቢኖር፣ ይህ በተላላፊ በሽታ ምክንያት የመጣ ነው፡፡
\v 43 በቆዳ ላይ ተላላፊ በሽታ ሲኖር እንደሚታየው በመላጣው ወይም በበራው ላይ በህመሙ ዙሪያ ፈዘዝ ያለ ቅላት መኖሩን ለማየት ካህኑ ምርመራ ያድርግለት፡፡
\v 44 ይህ ከሆነ፣ ተላላፊ በሽታ አለበት እናም ንጹህ አይደለም፡፡ በእርግጥ ካህኑ ሰውየው በራሱ ላይ ካለበት በሽታ የተነሳ ንጹህ እንደልሆነ ያስታውቅ፡፡
\s5
\v 45 ተላላፊ በሽታ ያለበት ሰው የተቀደደ ልብስ ይልበስ፣ ጸጉሩን በከፊል ይሸፍን፣ እስከ አፍንጫው ይከናነብና ‘እርኩስ ነኝ፣ እርኩስ ነኝ’ እያለ ይጩህ፡፡
\v 46 ተላላፊው በሽታ ባለበት ቀናት ሁሉ እርኩስ ነው፡፡ እየሰፋ ሊሄድ በሚችል በሽታ ምክንያት ንጹህ ስላልሆነ፣ ለብቻው ይኑር፡፡ ከሰፈር ውጭ ይኑር፡፡
\s5
\v 47 በማናቸውም ነገር የተበከለ የሱፍም ሆነ የተልባ ዕግር ጨርቅ፣
\v 48 ወይም ከሱፍም ሆነ ከተልባ ዕግር ጨርቅ የተፈተለ፣ ወይም ቆዳም ሆነ ከቆዳ በተሰራ ልብስ -
\v 49 በልብሱ ላይ አረንጓዴ ወይም ቀላ ያለ ብክለት ቢገኝበት፤ በቆዳው፣ በተጠለፈው ወይም በተሰፋው ነገር፣ ወይም ማናቸውም ከቆዳ በተሰራው ነገር ለይ ብክለቱ እየሰፋ ቢሄድ ካህኑ ይህን ይመልከት፡፡
\s5
\v 50 ካህኑ የሚበከለውን ዕቃ ይመርምር፣ የተበከለውን ማናቸውንም ነገር ለሰባት ቀናት ይለየው፡፡
\v 51 በሰባተኛው ቀን እንደገና ብክለቱን ይመርምር፡፡ በልብሱ ወይም ከሱፍ ወይም ከተልባ ዕግር ጨርቅ በተሸመነው ወይም በተጠለፈው ማናቸውም ልብስ ላይ ብክለቱ እየሰፋ ቢሄድ ወይም በቆዳ ወይም ከቆዳ በተሰራ ማናቸውም ነገር ላይ ብክለቱ ቢሰፋ ጎጁ ነው፣ እናም ዕቃው ንጹህ አይደለም፡፡
\v 52 ካህኑ ያንን ልብስ ያቃጥል፣ ወይም ማናቸውም ከሱፍ ወይም ከተልባ ዕግር ጨርቅ የተፈተለ ወይም ቆዳ ወይም ከቆዳ የተሰራ ነገር፣ ማናቸውም ጎጂ ብክለት የተገኘበት ነገር በሽታ ያመጣልና ያቃጥለው፡፡ ዕቃው ሙሉ ለሙሉ ይቃጠል፡፡
\s5
\v 53 ካህኑ ዕቃውን መርምሮ ብክለቱ በልብ ወይም በተሸመነው ወይም በተለጠፈው ልብስ ወይም በቆዳ ዕቃዎቹ ላይ እየሰፋ የሚሄድ አለመሆኑን ካወቀ፣
\v 54 ብክለቱ የተገኘባቸውን ዕቃዎች እንዲያጥቡ ያዛቸዋል፤ ደግሞም ዕቃውን ለሰባት ቀናት ያግልል፡፡
\v 55 ከዚያ ካህኑ የተበከለውን ዕቃ ከታጠበ ከሰባት ቀናት በኋላ ይመረምረዋል፡፡ ብክለቱ ቀለሙን ካልቀየረውና እየሰፋ ባይሄድ እንኳን ንጹህ አይደለም፡፡ ብክለቱ የትም ላይ ይሁን ዕቃዎቹን አቃጥሏቸው፡፡
\s5
\v 56 ካህኑ ዕቃውን ከመረመረና ልብሱ ከታጠበ በኋላ ብክለቱ እየለቀቀ ከሄደ፣ ከተበከለው የልብሱ ወይም የቆዳው ክፍል ወይም ከተሸመነው ወይም ከተጠለፈው ዕቃ ቀድዶ ያውጣው፡፡
\v 57 እንዲህም ሆኖ ብክለቱ አሁንም በተሸመነው ወይም በተጠለፈው፣ ወይም በማናቸውም ከቆዳ በተሰራው ነገር ላይ ከተገኘ እየሰፋ በመሄድ ላይ ነው፡፡ ብክለት ያለበትን ማናቸውንም ነገር አቃጥለው፡፡
\v 58 ከሱፍ ወይም ከተልባ ዕግር ጨርቅ የተሰራ ወይም የተለጠፈ ልብስ ወይም ማናቸውም ነገር፣ ወይም ቆዳ ወይም ከቆዳ የተሰራ ማናቸውም ነገር - ስታጥበው ብክለቱ እየለቀቀ ከሄደ፣ ዕቃው ዳግመኛ ይታጠብ እናም ንጹህ ይሆናል፡፡
\s5
\v 59 ከሱፍ ወይም ከተልባ ዕግር ጨርቅ ለተሸመነ ወይም ለተጠለፈ፣ከሱፍ ወይም ከተልባ ዕግር ጨርቅ ወይም ቆዳ ወይም ከቆዳ ለተሰራ ማናቸውም ነገር ብክለት ህጉ ይህ ነው፣ ስለዚህ ንጹህ ነው ወይም እርኩስ ነው ብለህ ማሳወቅ ትችላለህ፡፡”
\s5
\c 14
\p
\v 1 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
\v 2 “የታመመ ሰው በሚነጻበት ቀን ህጉ ይህ ነው፡፡ ወደ ካህኑ ይቅረብ፡፡
\s5
\v 3 ካህኑ የሰውየው ተላላፊ የቆዳ በሽታ መዳኑን ለመመርመር ከሰፈር ይወጣል፡፡
\v 4 ከዚያም ካህኑ የሚነጻው ሰው ህይወት ያላቸው ሁለት ንጹህ ወፎችን፣ የጥድ ዕንጨት፣ ደማቅ ቀይ ድርና ሂሶጵ እንዲያመጣ ያዘዋል፡፡
\v 5 ካህኑ የታመመው ሰው ከወፎቹ አንዱን አርዶ በሸክላ ማሰሮ ውስጥ እንዲጨምር ያደርጋል፡፡
\s5
\v 6 ከዚያ ካህኑ ህይወት ያለውን ወፍ፣የጥዱን እንጨትና፣ ደማቁን ቀይ ድርና ሂሶጵ ይቀበለውና ህይወት ያለውን ወፍ ጨምሮ እነዚህን ነገሮች በሙሉ ቀደም ሲል በታረደው ወፍ ደምና ንጹህ ውሃ ውስጥ ይከታቸዋል፡፡
\v 7 ከዚያ ካህኑ ይህንን ውሃ ከበሽታው በሚነጻው ሰው ላይ ሰባት ጊዜ ይረጫል፣ ከዚያ በኋላ ካህኑ ሰውየው ንጹህ መሆኑን ያሳውቃል፡፡ ከዚያ ካህኑ ህይወት ያለውን ወፍ ወደ ሜዳ ይለቀዋል፡፡
\s5
\v 8 የነጻው ሰው ልብሱን ያጥባል፣ ፀጉሩን በሙሉ ይላጫል፣ገላውንም ይታጠባል፤ ከዚህ በኋላ ንጹህ ይሆናል፡፡ ከዚያ በኋላ ወደ ሰፈር ይመለስ፣ ነገር ግን ከድንኳኑ ውጭ ለሰባት ቀናት ይቆያል፡፡
\v 9 በሰባተኛው ቀን የራሱን ፀጉር በሙሉ ይላጭ፣ ልብሶቹን ይጠብ፣ ገላውን በውሃ ይታጠብ፤ ከዚህ በኋላ ንጹህ ይሆናል፡፡
\s5
\v 10 በስምንተኛው ቀን ነውር የሌለባቸው ሁለት ወንድ የበግ ጠቦቶች፣አንድ ነውር የሌለበት የአንድ አመት የበግ ጠቦት ያምጣ፣ በዘይት የተለወሰ የኢፍ ሶስት አስረኛ የላመ ዱቄት እና አንድ ሊትር ዘይት ለእህል ቁርባን ያቅርብ፡፡
\v 11 የመንጻት ስርዓቱን የሚያስፈጽመው ካህን የሚነጻውን ሰው ከእነዚህ ነገሮች ጋር ይዞ፣ በያህዌ ፊት በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ ይቆማል፡፡
\s5
\v 12 ካህኑ ወንዱን ጠቦት ወስዶ ለኃጢአት መስዋዕት ከአንዱ ሊትር ዘይት ጋር ያቀርባል፤ እነዚህንም በያህዌ ፊት ለመስዋዕት ይወዘውዘዋል፤ ለእርሱም ያቀርበዋል፡፡
\v 13 ወንዱን ጠቦት የኃጢአት መስዋዕቱንና የሚቃጠል መስዋዕቱን ባቀረቡበት ስፍራ በቤተ መቅደስ ያርደዋል፤ እንደ በደል መስዋዕቱ ሁሉ የኃጢአት መስዋዕቱም ለካህኑ ይሰጥ፣ ምክንያቱም ይህ እጅግ ቅዱስ ነው፡፡
\s5
\v 14 ካህኑ ከበደል መስዋዕቱ ጥቂት ደም ወስዶ በሚነጻው ሰው ቀኝ ጆሮ ጫፍ፣ በቀኝ እጁ አውራ ጣት ላይ እና በቀኝ እግሩ አውራ ጣት ላይ ይቀባ፡፡
\v 15 ከዚያ ካህኑ ከዘይቱ ወስዶ በእርሱ በራሱ ግራ እጅ መዳፍ ላይ ያፈሳል፣
\v 16 ከዚያም በግራ እጁ መዳፍ ላይ በፈሰሰው ዘይት ውስጥ የቀኝ እጁን ጣት ያጠልቃል፣ በጣቱ ላይ ካለው ዘይት በያህዌ ፊት ሰባት ጊዜ ይረጫል፡፡
\s5
\v 17 ካህኑ በእጁ ላይ የቀረውን ዘይት በሚነጻው ሰው ቀኝ ጆሮ ጫፍ፣ በቀኝ እጁ አውራ ጣት፣ እና በቀኝ እግሩ አውራ ጣት ላይ ይቀባል፡፡ ይህንን ዘይት በበደል መስዋዕቱ ደም ላይ ያድርገው፡፡
\v 18 ካህኑ በእጁ የቀረውን ዘይት፣ በሚነጻው ሰው ራስ ላይ ያፍስስ፣ እናም ካህኑ በያህዌ ፊት የሚነጻውን ሰው ያሰርይለታል፡፡
\s5
\v 19 ከዚያ ካህኑ የኃጢአት መስዋዕቱን ይሰዋል፤ ደግሞም ንጹህ ባለመሆኑ ምክንያት መንጻት ላለበት ሰው ያሰርይለታል፣ እናም ከዚህ በኋላ የሚቃጠል መስዋዕቱን ይሰዋል፡፡
\v 20 ካህኑ የሚቃጠለውን መስዋዕትና የእህል ቁርባኑን በመሰዊያ ላይ ያቀርባል፡፡ ካሁኑ ለሰውየው ማስተስረያ ያቀርብለታል፡፡ ከዚያ ንጹህ ይሆናል፡፡
\s5
\v 21 ሆኖም ሰውየው ደሃ ከሆነና እነዚህን መስዋዕቶች ማቅረብ ካልቻለ ለኃጢአቱ ማስተስረያ የበደል መስዋዕት አንድ ወንድ ጠቦት፣ በዘይት የተለወሰ የኢፍ አንድ አስረኛ መልካም ዱቄትና አንድ ሊትር ዘይት ያቅርብ፣
\v 22 ሰውየው በአቅሙ ከሁለት ርግቦች ወይም ሁለት ዋኖሶች ጋር፣ አንደኛውን ወፍ የኃጢአት መስዋዕት ሌላኛው ደግሞ የሚቃጠል መስዋዕት ያቀርባል፡፡
\v 23 በስምንተኛው ቀን ስለ መንጻቱ ወደ መገናኛው ድንኳን በያህዌ ፊት ያምጣቸው፡፡
\s5
\v 24 ከዚያ ካህኑ ጠቦቱን ለበደል መስዋዕት ደግሞም አንዱን ሊትር ዘይት፣ይወስድና ለያህዌ የበደል መስዋዕት ይወዘውዛል፣ እናም ለእርሱ እነዚህን ያቀርባቸዋል፡፡
\v 25 ለበደል መስዋዕት ጠቦቱን ያርዳል፣ እናም ከበደል መስዋዕቱ ጥቂት ደም ይወስድና በሚነጻው ሰው ቀኝ ጆሮ ጫፍ፣ በቀኝ እጁ አውራ ጣት ላይና በቀኝ እግሩ አውራ ጣት ላይ ይቀባል፡፡
\s5
\v 26 ከዚያ ካህኑ ከዘይቱ ጥቂቱን በገዛ ራሱ ግራ እጅ መዳፍ ላይ ያፈሳል፣
\v 27 በቀኝ ጣቱ ከዘይቱ በግራ እጁ በያህዌ ፊት ሰባት ጊዜ ይረጫል፡፡
\s5
\v 28 ከዚያ ካህኑ በእጁ ካለው ዘይት ጥቂቱን በሚነጻው ሰው ቀኝ ጆሮ ጫፍ ላይ፣ በቀኝ እጁ አውራ ጣት ላይና በቀኝ እግሩ አውራ ጣት ላይ የበደል መስዋዕቱን ደም ባደረገበት ተመሳሳይ ስፍራዎች ይቀባል፡፡
\v 29 የተረፈውን በእጁ ያለውን ዘይት ያስተሰርይለት ዘንድ በያህዌ ፊት በሚነጻው ሰው ራስ ላይ ያፈሳል፡፡
\s5
\v 30 ሰውየው በአቅሙ ካቀረበው ከእርግቦቹ ወይም ከዋኖሶቹ አንዱን ይሰዋ -
\v 31 ከእህል ቁርባኑ ጋር፣ አንዱን ለኃጢአት መስዋዕት ሌላውን ለሚቃጠል መስዋዕት ያቅርብ፡፡ ከዚያም ካህኑ ለሚነጻው ሰው በያህዌ ፊት ያስተሰርይለታል፡፡
\v 32 ለመንጻት ዋናውን መስዋዕት ማቅረብ ለማይችል ተላላፊ የቆዳ በሽታ ላለበት ሰው የመንጻት ህጉ ይህ ነው፡፡”
\s5
\v 33 ያህዌ ሙሴንና አሮንን እንዲህ ሲል ተናገራቸው፣
\v 34 “ርስት አድርጌ ወደሰጠኋችሁ ወደ ከነዓን ምድር ስትመጡ፣ ርስት በሆናችሁ ምድር በቤታችሁ እየሰፋ የሚሄድ ብክለት ባደርግባችሁ፣
\v 35 የቤቱ ባለቤት ወደ ካህኑ መጥቶ ይናገር፡፡ እንዲህም ይበል፣ “በቤቴ ብክለት ያለ ይመስለኛል፡፡’
\s5
\v 36 ከዚያ ካህኑ በቤቱ ውስጥ የሚገኝ ማናቸውም ነገር እርኩስ እንዳይሆን ብክለት መኖሩን ለማየት ወደዚያ ቤት ከመግባቱ አስቀድሞ ቤቱን ባዶ እንዲያደርጉ ያዛል፣ ከዚህ አስቀድሞ ካህኑ ያንን ቤት ለማየት ይገባል፡፡
\v 37 ሻጋታው በቤቱ ግድግዳዎች ላይ መኖሩን፣ ደግሞም አረንጓዴ ሆኖ ወይም ቀላ ብሎ በግርግዳዎቹ ላይ መታየቱን ይመርምር፡፡
\v 38 ቤቱ ሻጋታ ካለው፣ ካህኑ ከዚያ ቤት ይወጣና ለሰባት ቀናት በሩን ይዘጋዋል፡፡
\s5
\v 39 በሰባተኛው ቀን ካህኑ ተመልሶ ይመጣና ሻጋታው በቤቱ ግድግዳዎች ላይ መስፋፋቱን ለማየት ይመረምራል፡፡
\v 40 እንዲያ ከሆነ፣ ካህኑ ሻጋታ የተገኘባቸውን ድንጋዮች ከግድግዳው ላይ እየፈነቀሉ እንዲያወጡና ከከተማ ውጭ ቆሻሻ ስፍራ መጣያ እንዲጥሏቸው ያዛል፡፡
\s5
\v 41 የቤቱ የውስጥ ግድግዳዎች ሁሉ እንደዲፋቁ ይጠይቃል፣ እነርሱም እየተፋቁ የተነሱትን የተበከሉትን ቁሶች ከከተማ አውጥተው በቆሻሻ መጣያ ስፍራ ይጥላሉ፡፡
\v 42 ባስወገዷቸው ድንጋዮች ስፍራ ሌሎች ድንጋዮች ወስደው ያስቀምጡ፣ ቤቱን ለመምረግ አዲስ ጭቃ ይጠቀሙ፡፡
\s5
\v 43 ድንጋዮቹ ተነስተውና ግርግዳው ተፍቆ እንዲሁም ተለስኖ ዳግም ብክለቱ ከወጣና ከታየ፣
\v 44 ካህኑ ብክለቱ መስፋፋቱን ለመመልከት ቤቱን ይመርምር፡፡ እንዲያ ከሆነ፣ ይህ ጎጂ ብክለት ነው፤ ቤቱ ንጹህ አይደለም፡፡
\s5
\v 45 ቤቱ ይፍረስ፡፡ የቤቱ ድንጋዮች፣ በሮች፣ እና ፍርስራሾች ከከተማ ውስጥ በቆሻሻ መጣያ ይጣል፡፡
\v 46 በተጨማሪም፣ ቤቱ በተዘጋባቸው ጊዜያት ወደዚያ ቤት የሄደ ሁሉ እስከ ምሽት ድረስ እርኩስ ነው፡፡
\v 47 ማንም በዚያ ቤት ውስጥ የተኛ ሰው ልብሱን ይጠብ፣ እንዲሁም በዚህ ቤት ውስጥ የተመገበ ሰው ልብሱን ይጠብ፡፡
\s5
\v 48 ቤቱ ከተለሰነ በኋላ ብክለቱ ወዴት እንደተስፋፋ ለመመርመር ካህኑ ወደዚያ ቤት ቢገባ፣ እናም ብክለቱ ተወግዶ ቢሆን ቤቱ ንጹህ መሆኑን ያሳውቃል፡፡
\s5
\v 49 ከዚያ ካህኑ ቤቱን ለማንጻት ሁለት ወፎች፣ የጥድ እንጨት፣ ደማቅ ቀይ ድር እና ሂሶጵ ይውሰድ፡፡
\v 50 ከወፎቹ አንዱ ንጹህ ውሃ በያዘ በሸክላ ዕቃ ውስጥ ያርደዋል፡፡
\v 51 የጥድ እንጨት፣ሂሶጵደማቅ ቀይ ድር እና በህይወት ያለ ወፍ ይውድና በታረደው ወፍ ደም ውስጥ እና በንጹህ ውሃ ውስት ይነክራቸዋል፣ከዚያም ቤቱን ሰባት ጊዜ ይርጨው፡፡
\s5
\v 52 ቤቱን በወፉ ደምና በንጹህ ውሃ፣ በህይወት በሚገኘው ወፍ፣ በጥድ እንጨት፣በሂሶጵና በደማቅ ቀይ ድር ያነጻዋል፡፡
\v 53 በህይወት የሚገኘውን ወፍ ግን ከከተማ ውጭ ወደ ሜዳ ይለቀዋል፡፡ በዚህ መንገድ ቤቱን ያስተሰርያል፣ ቤቱም ንጹህ ይሆናል፡፡
\s5
\v 54 ለሁሉም አይነት ተላላፊ የቆዳ በሽታና እንዲህ ያለውን በሽታ ለሚያመጡ ነገሮች፣ እንዲሁም ለሚያሳክክ ህመም፣
\v 55 እንዲሁም ለልብስና ለቤት ብክለት፣
\v 56 ለእብጠት፣ ለሚያሳክክ ህመም፣ እና ለቋቁቻ፣
\v 57 በእነዚህ ሁኔታዎች እርኩስና ንጹህ የሚሆነውን ለመለየት ህጉ ይህ ነው፡፡”
\s5
\c 15
\p
\v 1 ያህዌ ሙሴንና አሮንን እንዲህ ሲል ተናገራቸው፣
\v 2 ‹ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ ብላችሁ ንገረቸው፣ ‹ማንም ሰው ከሰውነቱ የሚወጣ የሚመረቅዝ ፈሳሽ ሲኖርበት፣ ንጹኅ አይደለም፡፡
\v 3 ንጹኅ የማይሆነ ከሚመረቅዝ ፈሳሽ የተነሳ ነው፡፡ ከሰውነቱ የሚወጣ ፈሳሽ ቢቀጥል ወይም ቢቆም ንጹህ አይደለም፡፡
\s5
\v 4 የሚተኛበት አልጋ ሁሉ ንጹኅ አይሆንም፣ የሚቀመጥበት ነገር ሁሉ ንጹኅ አይሆንም፡፡
\v 5 አልጋን የነካ ሁሉ ልብሱን ይጠብ ሰውየውም በውሃ ይታጠብ፣ እስከ ምሽት ድረስ ንጹኅ አይደለም፡፡
\s5
\v 6 የሚመረቅዝ ፈሳሽ ያለበት ሰው በተቀመጠበት ማናቸውም ነገር ላይ የተቀመጠ ማንኛውም ሰው ልብሱን ይጠብ፣ እርሱም በውሃ ይታጠብ፣ እስከ ምሽት ንጹህ አይደለም፡፡
\v 7 የሚመረቅዝ ፈሳሽ ያለበትን ሰው አካል የነካ ማንኛውም ሰው ልብሱን ይጠብ፣ እርሱም በውሃ ይታጠብ፡፡ እስከ ምሽት ንጹህ አይደለም፡፡
\s5
\v 8 እንዲህ ያለ ፈሳሽ ያለበት ሰው ንጹኅ በሆነ ሰው ላይ ንጹኅ በሆነ ሰው ላይ ቢተፋ፣ ያ ሰው ልብሱን ማጠብና እርሱም በውሃ መታጠብ አለበት፣ እስከ ምሽት ንጹኅ አይደለም፡፡
\v 9 ፈሳሽ ያለበት ሰው የተቀመጠበት ማንኛውም ኮርቻ ንጹኅ አይደለም፡፡
\s5
\v 10 ከዚያ ሰው በታች ያለን ማንኛውንም ነገር የነካ እስከ ምሽት ንጹኅ አይደለም፣ እነዚያን ነገሮች የተሸከመ ማንም ሰው ልብሱን ይጠብ እርሱም በውሃ ይታጠብ፤ እስከ ምሽት ንጹኅ አይደለም፡፡
\v 11 እንዲህ ያለ ፈሳሽ ያለበት ማንም ቢሆን አስቀድሞ እጆቹን በውሃ ሳያጠራ ቢነካ፣ የተነካው ሰው ልብሱን ይጠብ እርሱም በውሃ ይታጠብ፣ እስከ ምሽት ንጹኅ አይደለም፡፡
\v 12 እንዲህ ያለ ፈሳሽ ያለበትን ሰው የነካ ማናቸውም አይነት የሸክላ ዕቃ ይሰበር፣ የእንጨት የተሰራ ማጠራቀሚያ ሁሉ በውሃ ይንጻ፡፡
\s5
\v 13 ፈሳሽ ያለበት ሰው ከፈሳሹ ሲነጻ ለመንጻቱ ለእራሱ ሰባት ቀናትን ይቁጠር፤ ከዚያ ልብሶቹን ይጠብ ሰውነቱን በምንጭ ውሃ ይታጠብ፡፡ ከዚያ ንጹህ ይሆናል፡፡
\v 14 በስምንተኛው ቀን ሁለት ርግቦች ወይም ሁለት ኖሶች ይውሰድና ወደ መገናኛ ድንኳን ያህዌ ፊት ይቅረብ፣ በዚያ ወፎቹን ለካህኑ ይስጥ፡፡
\v 15 ካህኑ አንዱን ለሀጢአት መስዋዕት እና ሌላውን የሚቃጠል መስዋዕት ያቅርባቸው፣ እናም ካህኑ ለሰውዬው ስለ ፈሳሹ ማስተሰርያ ያድርግ፡፡
\s5
\v 16 የማንንም ሰው የዘር ፈሳሽ ሳይታሰብ በድንገት ከእርሱ ቢወጣ፣ መላ ሰውነቱን በውሃ ይታጠብ፣ እስከ ምሽት ድረስ ንጹህ አይደለም፡፡
\v 17 ማናቸውም የዘር ፈሳሽ የነካ ልብስ ወይም ሌጦ በውሃ ይታጠብ፤ እስከ ምሽት ንጹኅ አይደለም፡፡
\v 18 አንዲት ሴትና አንድ ወንድ አብረ ቢተኙና ወደ እርሷ የዘር ፈሳሽ ቢተላለፍ ሁለቱም በውሃ ይታጠቡ፣ እስከ ምሽት ንጹኅ አይደሉም፡፡
\s5
\v 19 አንዲት ሴት የወር አበባ ሲፈሳት፣ ያለመንጻቷ ለሰባት ቀናት ይቀጥላል፣ እርሷን የነካ ሁሉ እስከ ምሽት ንጹህ አይደለም፡፡
\v 20 በወር አበባ ወቅት የምትተኛበት ማንኛውም ነገር ንጹህ አይደለም፤ እንደዚሁም የምትቀመጥበት ነገር ሁሉ ንጹኅ አይደለም፡፡
\s5
\v 21 አልጋውን የነካ ማንኛም ሰው ልብሱን ይጠብ እርሱም በውሃ ይታጠብ፣ ያሰው እስከ ምሽት ንጹህ አይደለም፡፡
\v 22 የተቀመጠችበትን ማናቸውንም ነገር የነካ ሁሉ ልብሱን ይጠብ እርሱም በውሃ ይታጠብ ያ ሰው እስከ ምሽት ንጹህ አይደለም፡፡
\v 23 በአልጋም ይሁን በማንኛም ነገር ላይ ብትቀመጥ የተቀመጠችበትን ነገር የነካ ሰው እስከ ምሽት ንጹህ አይደለም፡፡
\s5
\v 24 ከእርሷ ጋር የተኛ ንጹህ ያልሆነ ፈሳሽ ቢነካ፣ ለሰባት ቀናት ንጹህ አይደለም፡፡ የሚተኛበትም አልጋ ንጹህ አይደለም፡፡
\s5
\v 25 አንዲት ሴት ከወር አበባ ቀናት በኋላ ለብዙ ቀናት ደም መፍሰሱን ቢቀጥል፣ ይህም ከወር አበባ ጊዜያት በኋላ ፈሳሽ ቢኖርባት፣ ንጹኅ ባልሆነችባቸው ፈሳሽ ባለባት ጊዜያት ሁሉ፣ በወር አበባ ወቅት ላይ እንዳለች ሁሉ እርኩስ ይሆናል ንጹህ አይደለችም፡፡
\v 26 ደሟ በሚፈስባቸው ጊዜያት የምትተኛበት አልጋ ሁሉ በወር አበባ ወቅት እንደምትተኛበት እርኩስ ይሆናል፣ የምትቀመጥበት ነገር ሁሉ ልክ በወር አበባ ወቅት እንደሚሆነ ንጹህ አይደለም፡፡
\v 27 ደግሞም ከእነዚህ ነገሮች ማናቸንም የነካ ሁሉ ንጹህ አይደለም፤ ልብሶቹን ይጠብ እርሱም በውሃ ይታጠብ፤ እስከ ምሽት ድረስ ንጹህ አይደለም፡፡
\s5
\v 28 ነገር ግን ከደም መፍሰሳ ብትነጻ፣ ለራስዋ ሰባት ቀናትን ትቆጥራለች፣ እናም ከዚያ በኋላ ንጹኅ ናት፡፡
\v 29 በስምንተኛው ቀን ሁለት ርግቦች ወይም ሁለት ዋኖሶች ትወሰድና ወደ መገናኛው ድንኳን መግቢያ ለካህኑ ትስጥ፡፡
\v 30 ካህኑ አንዱን ወፍ ለሀጢአት መስዋእት ሌላውን ለሚቃጠል መስዋዕት ያቅርብ፣ ስለ ፈሳሽም እርኩሰት በያህዌ ፊት ያስተሰርይላታል፡፡
\s5
\v 31 የእስራኤል ሰዎች ከእርኩሰታቸው የምትይች እንደዚህ ነ፣ ይህ ከሆነ በመካከላቸ የምኖርበትን ቤተ መቅደሴን በማርከስ በእርኩሰታቸ አይሞቱም፡፡
\s5
\v 32 ከሰነቱ ፈሳሽ ለሚጣ፣ የዘረ ፈሳሹ ከእርሱ ለሚጣና ለሚያረክሰ ማንኛም ሰ ህግጋቱ እነዚህ ናቸ፡፡
\v 33 ለማንኛም በር አበባ ላይ ላለች ሴት፣ ከሰነቱ ፈሳሽ ለሚፈሰ ሰ ሁሉ፣ ንድም ይሁን ሴት፣ እንዲሁም ንጹህ ካልሆነች ሴት ጋር ለሚተኛ ንድ ህጉ ይህ ነ፡፡”
\s5
\c 16
\p
\v 1 ያህ እንዲህ ሲል ሙሴን ተናገረ፡ - ይህ የሆነ የአሮን ሁለቱ ልጆች ¨ደ ያህ«ከቀረቡና ከሞቱ በሀላ ነበር፡፡
\v 2 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለ፣ “ለ¨ንድምህ ለአሮን እንዲህ ብለህ ተናገረ፣ በፈለገ¬ ጊዜ ሁሉ በመጋረጃ ¬ስጠኛ ¨ዳለ ¨ደ ቅድስተ ቅዱሳኑ፣ በታቦቱ ላይ ወዳለ ወደ ማስተሰርያ ክዳን ፊት እንዳይቀርብ ንገረው፡፡ ይህንን ካደረገ፣ ይሞታል፣ ምክንያቱም እኔ በደመና በማስተሰርያ ክዳን ፊት እንዳይቀርብ ንገረው፡፡ ይህንን ካደረገ፣ ይሞታል፣ ምክንያቱም እኔ በደመና በማስተሰርያ ክዳን ላይ እገለጣለሁ፡፡
\s5
\v 3 ስለዚህም አሮን ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ መቅረብ ያለበት እንደዚህ ነው፡፡ ለሀጢአት መስዋዕት ወይፈን፣ ለሚቃጠል መስዋዕት አ¬ራ በግ ይዞ መግባት አለበት፡፡
\v 4 ቅዱሱን በፍታ ቀሚስ ይልበስ፣ እንዲሁም የበፍታ የስጥ ሱሪ ይልበስ፣ ደግሞም የበፍታ መጠምጠሚያ የበፍታ ቀሚስ ይልበስ፡፡ ቅዱሳኑ አልባሳት እነዚህ ናቸው፡፡ ሰውነቱን በውሃ ይታጠብና እነዚህን ልብሶች ይልበስ፡፡
\v 5 ከእስራኤል ሰዎች ጉባኤ ሁለት ወንድ ፍየሎችን ለሀጢአት መስዋዕት እንዲሁም አንድ አ¬ራ በግ ለሚቃጠል መስዋዕት ይውሰድ፡፡
\s5
\v 6 ከዚያም አሮን ለእራሱ ኮርማ¬ን ለኃጢአት መስዋዕት ያቅርብ፣ ይህም ለራሱና ለቤተሰቡ ማስተሰርያ ነው፡፡
\v 7 ቀጥሎም ሁለቱም ፍየሎች ወስዶ በመገናኛ¬ ድንኳን መግቢያ ላይ በያህዌ ፊት ያቁማቸው፡፡
\s5
\v 8 ከዚያ አሮን በሁለቱ ፍየሎች ላይ ዕጣ ይጣል፣ አንዱን ዕጣ ለያህዌ ሌላ¬ን ዕጣ ለሚለቀቀው ፍየል ይጣል፡፡
\v 9 ከዚያም አሮን ዕጣ ለያህ«የ¨ጣለትን ፍየል ያቀርባል፣ ያንን ፍየልም ለኃጢአት መስªዕት ያቀርበªል፡፡
\v 10 ለመለቀቅ ዕጣ የጣትን ፍየል ግን ወደ ምድረበዳ በመልቀቅ ለስርየት ከነህይ¨ት ለያህዌ መቅረብ አለበት፡፡
\s5
\v 11 ከዚያም አሮን ለእራሱ ኮርማን ለሀጢአት መስዋዕት ያቀርባል፡፡ ለራሱና ለቤተሰቡ ማስተሰርያ ማድረግ አለበት፣ ስለዚህ ኮርማን ለራሱ የሀጢአት መስዋዕት አድርጎ ይረዳ፡፡
\s5
\v 12 አሮን በያህዌ ፊት ከመሰዊያ የከሰል እሳት የሞላውን ማጠንት ይውሰድ፣ በእጆቹ ሙሉ የላመ ጣፋጭ ዕጣን ይያዝና እዚህንም ነገሮች ¨ደ መጋረጃ ¬ስጥ ይዞ ይግባ፡፡
\v 13 በዚያም በያህ«ፊት ዕጣኑን በእሳቱ ላይ ይጨምር፣ ከእጣኑ የሚ¨ጣ ጢስ በምስክሩ ላይ ያለ የማስተሰርያን ክዳን ይሸፍናል፡፡ እንዳይሞት ይህንን ያድርግ፡፡
\s5
\v 14 ከዚያም ከወይፈኑ ጥቂት ደም ይውሰድና በጣቱ በማስተሰርያ ክዳን ፊት ይርጭ ከደሙ ጥቂት ¨ስዶ በጣቱ ሰባት ጊዜ በማስተሰርያ ክዳን ፊት ይርጭ፡፡
\s5
\v 15 ከዚያም ለህዝቡ ኃጢአት የኃጢአት መስªዕት ፍየሉን ይረድና ደሙን ¨ደ መጋረጃ ¬ስጥ ይዞ ይግባ፡፡ በዚያም በኮርማ ደም እንዳደረገ ሁሉ ያድርግ በማስተሰርያ¬ ክዳን ላይ ደሙን ይርጭ ከዚያም በማስተሰርያ¬ ክዳን ፊት ይርጭ፡፡
\v 16 በእስራኤል ህዝብ ያልተቀደሱ ተግባራት፣ በአመጻቸ¬ና በኃጢአቶቻቸ¬ ሁሉ ምክንያት ለተቀደሰ ስፍራ ማስተሰርያ ያድርግ፡፡ ንጹህ ያልሆኑ ተግባሮቻቸ¬ በታዩ ጊዜያት፣ ያህ በመካከላቸ¬ ለሚያድርበት ለመገናኛ¬ ድንኳንም ይህን ያድርግ፡፡
\s5
\v 17 አሮን ለማስተሰርይ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን በሚገባበት ሰዓትና እንዲሁም ለእርሱ፣ ለቤተሰቡና ለእስራኤል ጉባኤ ሁሉ ማስተሰርዩን እስከሚጨርስ ድረስ ማንም ሰው በመገናኛው ድንኳን ውስጥ አይገኝም፡፡
\v 18 በያህ«ፊት ወዳለ መሰዊያ ይሂድና መሰዊያን ያስተሰርይ፣ ከኮርማ ደም ጥቂት እንዲሁም ከፍየሉ ደም ጥቂት ይ¬ስድና በመሰዊያ ዙሪያ ባሉ ቀንዶች ሁሉ ¬ስጥ ያስነካ፡፡
\v 19 መሰዊያዉን ንጹህ ካልሆነ የእስራኤል ሰዎች ድርጊቶች ለማንጻትና ለያህዌ ለመለየት በላዩ ካለ ጥቂት ደም ወስዶ በጣቱ ሰባት ጊዜ ይርጭ፡፡
\s5
\v 20 ቅድስተ ቅዱሳኑን፣ የመገናኛን ድንኳንና መሰዊያን ማስተሰርያ¬ን ሲጨርስ በህይወት የሚገኘ¬ን ፍየል ያቅርብ፡፡
\v 21 አሮን ህይወት ባለው ፍየል ላይ ሁለቱንም እጆቹን ይጫንና የእስራኤልን ህዝብ በደልን ሁሉ፣ አመጻቸውን ሁሉ፣ እና ሀጢአታቸውን ሁሉ በላዩ ላይ ይናዘዝበት፡፡ ከዚያም ያንን ሃጢአተኛነት በፍየሉ ራስ ላይ አድርጎ ፍየሉን ወደ በረሃ ለመስደድ ኃላፊነት ባለበት ሰው አማካይነት ወደ በረሃ ያባው፡፡
\v 22 ፍየሉ የሰ­ቹን በደል ሁሉ ይሸከምና ገለልተኛ ¨ደ ሆነ ስፍራ ይሄዳል፡፡ በበረሃ ስፍራም፣ ሰ¬ዬ¬ ፍየሉን ይለቀªል፡፡
\s5
\v 23 ከዚያም አሮን ወደ መገናኛ ድንኳን ይመለስና ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ ከመሄዱ አስቀድሞ የለበሰን የበፍታ ልብሶች ያወልቃል፣ እነዚያን ልብሶችም በዚያ ስፍራ ያስቀምጣቸዋል፡፡
\v 24 በተቀደሰ ስፍራ ሰውነቱን በውሃ ይታጠብ፣ ከዚያም የዘወትር ልብሱን ይልበስ፣ ከዚያም ወጥቶ የራሱን የሚቃጠል መስዋዕቱን የህዝቡን የሚቃጠል መስዋዕት ያቅርብ፤ በዚህ መንገድ ለራሱና ለህዝቡ ማስተሰርያ ያቀርባል፡፡
\s5
\v 25 በመሰዊያ ላይ የኃጢአት መስዋዕቱን ስብ ያቃጥል፡፡
\v 26 የሚሰደደውን ፍየል የለቀቀው ሰው ልብሶቹንና ሰውነቱን ይታጠብ፣ ከዚያ በኋላ ወደ ሰፈር መመለስ ይችላል፡፡
\s5
\v 27 በተቀደሰው ስፍራ ለማስተሰርያው ደማቸው የቀረበው የኃጢአት መስªዕቱ ኮርማ እና የኃጢአት መስªዕቱ ፍየል ከሰፈር ውጭ ይውስዳቸው። በዚያም ቆዳቸውን፣ ስጋቸውንና ፈርሳቸውን ያቃጥላFቸው፡፡
\v 28 እነዚህን የእንስሳውን ክፍሎች የሚያቃጥለው ሰው ልብሶቹንና ሰውነቱን በውሃ ይታጠብ፣ ከዚያ በኋላ፣ ወደ ሰፈር መመለስ ይችላል፡፡
\s5
\v 29 በሰባተኛው ወር፣ በወሩ በአስረኛው ቀን ራሳችሁን ትሁት ታደርጋላችሁ ስራም አትሰሩበትም ለእናንተም ሆነ ለመጻተኛው ይህ ሁልጊዜም መታሰቢያ ይሆናል፡፡
\v 30 ይህ የሚሆነው በዚህ ዕለት በያህዌ ፊት ቅዱስ ትሆኑ ዘንድ ከኃጢአቶቻችሁ ሁሉ እንድትነጹ ማስተሰርያ ስለሚደረግላችሁ ነው፡፡
\v 31 ይህ ለእናንተ ክቡር ሰንበት ዕረፍት ነው፣ ራሳችሁን ትሁት ማድረግ አለባችሁ ምንም ስራ አትስሩበት፡፡ይህ በእናንተ መሀል ሁልጊዜም መታሰቢያ ነው
\s5
\v 32 ሊቀ ካህኑ፣ በአባቱ ስፍራ ሊቀካህን ሊሆን የሚቀባውና የሚሾመው፣ ይህን ማስተሰርያ ማስፈጸምና ቅዱስ የሆነውን የበፍታ ልብሶች መልበስ አለበት፡፡
\v 33 ለቅድስተ ቅዱሳኑ፣ ለመገናኛው ድንኳንና ለመስዋዕቱ፣ ማስተሰርያ ያደርጋል፤ እንደዚሁም ለካህናቱና ለጉባኤው ሰዎች በሙሉ ማስተሰርያ ያደርጋል፡፡
\s5
\v 34 "ይህ ለእናንተ ሁልጊዜም መታሰቢያ ይሆናል፣ ለእስራኤል ሰዎች ለኃጢአቶቻቸው ሁሉ ማስተሰርያ ለማቅረብ ይህ በየአመት አንድ ጊዜ ይደረግ፡፡” ያህዌ ሙሴን እንዳዘዘው እንዲሁ ተደረገ፡፡
\s5
\c 17
\p
\v 1 እንዲህ ሲል ሙሴን ተናገረው፣
\v 2 አሮንና ልጆቹን እንዲሁም የእስራኤል ህዝብ ሁሉ እንዲህ በላቸው፡፡ ያህዌ ያዘዘውን ንገራቸው፡፡
\v 3 “ከእስራኤል ሰዎች መሀል ማንም ለመስዋዕት በሰፈር ውስጥ ወይም ከሰፈር ውጭ በሬ፣ በግ፣ ወይም ፍየል ያረደ ሰው፣
\v 4 ወደ መገናኛው ድንኳን መግቢያ በመቅደሱ ፊት ለያህዌ መስዋዕት ለማድረግ ባመጣው ውሃ ያ ሰው ስላፈሰሰው ደም በደለኛ ነው” ደም አፍስሷልና ያ ሰው ከህዝቡ መሃል ተለይቶ ይጥፋ፡፡
\s5
\v 5 የዚህ ትእዛዝ ዓላማ የእስራኤል ሰዎች ለያህዌ በሜዳ ላይ የሚያቀርቧቸውን መስዋዕቶች ወደ ካህናት ለያህዌ የህብረት መስዋዕት አድርገው በመገናኛው ድንኳን መግቢያ እንዲያቀርቡ ነው፡፡
\v 6 ካህኑ የመስዋዕቱን ደም በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ላይ በያህዌ መሰዊያ ላይ ይረጫል፤ ስቡን ለያህዌ ጣፋጭ ማዕዛ አድርጎ ያቃጥለዋል፡፡
\s5
\v 7 ሕዝቡ ከእንግዲህ መስዋዕቱን ለጣኦት አይሰዋ፣ እንዲህ ያለው ተግባር ምንዝርና ነው፡፡ ይህ በትወልዶቻቸው ሁሉ ቋሚ መታሰቢያ ይሆናል፡፡
\s5
\v 8 እንዲህ በላቸው፣ “ማንኛውም እስራኤላዊ፣ ወይም ማንኛውም በእነርሱ መሀል የሚኖር መጻተኛ፣ የሚቃጠል መስዋዕት የሚሰዋ ወይም መስዋዕት የሚያቀርብ
\v 9 እና ለያህዌ ለመሰዋት ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ የማያመጣው ያ ሰው ከህዝቡ ተለይቶ ይጥፋ፡፡
\s5
\v 10 ደግሞም ከእስራኤል አንዱ፣ ወይም በእነርሱ መሀል ከሚኖር መጻተኛ አንዱ፣ ደም ቢበላ፣ ፊቴን ከዚያ ሰው አስቆጣለሁ፣ ማንንም ደም የሚበላን ሰው ከህዝቡ መሃል አጠፋዋለሁ፡፡
\v 11 የእንስሳ ህይወቱ በደሙ ውስጥ ነው፡፡ በመሰዊያ ላይ ማስተሰርያ ይሁናችሁ ዘንድ ደሙን ለሕይወታችሁ ሰትቻችኋለሁ፣ ምክንያቱም ማስተሰርያ የሚሆነው ደም ነው፣ ለሕይወት ስርየት የሚያስገኘው ደም ነው፡፡
\s5
\v 12 ስለዚህም ለእስራኤላውያን ከመሀላችሁ ማንም ደም አይብላ እላለሁ፣ በመሀላችሁ የሚኖር ማንም ሙያተኛም ቢሆን ደም አይብላ፡፡
\v 13 ከእስራኤል ሰዎች መሀል ማንም ቢሆን፣ ወይም በእነርሱ መሃል የሚኖር ማንኛውም መጻተኛ፣ የሚበላ እንስሳ ቢያርድ ወይም ወፍ ቢያጠምድ ደሙን ያፍስና በአፈር ይሸፍነው፡፡
\s5
\v 14 የእያንዳንዱ ፍጥረት ነፍስ ደሙ ነውና፡፡ ስለዚህም ነው ለእስራኤላውያን፣ የማንኛውም ፍጥረት ደም አትብሉ፣ የእያንዳንዱ ሕያው ፍጥረት ሕይወት ደሙ ነው፡፡ ማንም ይህን የሚበላ ተቆርጦ ይጥፋ” ብዬ የተናገርኩት፡፡
\s5
\v 15 እያንዳንዱ የሞተ፣ ወይም በዱር አውሬ የተዘነጠለ እንስሳ የበላ ሰው የአገር ተወላጅ ይሁን በመሀላችሁ የሚኖ መጻተኛ ልብሶቹን ይጠብ፣ እርሱም በውሃ ይታጠብ፣ እስ ምሽት ድረስ ንጹህ አይሆንም፡፡ ከዚያ ንጹህ ይሆናል፡፡
\v 16 ነገር ግን ልብሱን ባያጥብ ወይም ሰውነቱን ባይታጠብ፣ በበደሉ ተጠያቂ ነው፡፡
\s5
\c 18
\p
\v 1 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
\v 2 “ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፣ “እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡
\v 3 እኔ በማስገባችሁ ምድር፤ ቀድሞ ትኖሩበት በነበረው በግብጽ የነበሩ ሰዎች ያደርጓቸው የነበሩ ነገሮችን አታድርጉ፣ ደግሞም በከነአን ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ያደርጓቸው የነበሩ ነገሮችን አታድርጉ፡፡ የእነርሱን ልምዶች አትከተሉ፡፡
\s5
\v 4 እናንተ መፈጸም ያለባችሁ የእኔን ህጎች ነው መጠበቅ ያለባችሁ የእኔን ትዕዛዛት ነው፣ ስለዚህም በእነርሱ ትኖራላችሁ፣ ምክንያቱም እኔ አምላካችሁ ያህዌ ነኝ፡፡
\v 5 ስለዚህም እኔን ትዕዛዛትና ህጎች ትጠብቀላችሁ፡፡ አንድ ሰው እነዚህን ቢጠብቅ፣ በእነርሱ ምክንያት በህይወት ይኖራል፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡
\s5
\v 6 ማንም ሰው ከቅርብ ዘመዱ ጋር አይተኛ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡
\v 7 ከእናትህ ጋር በመተኛት አባትህን አታዋርድ፡፡ እርሷ እናትህ ናት! እርሷን ማዋረድ የለብህም፡፡
\v 8 ከአባትህ ሚስት ከየትኛዋም ጋር አትተኛ፤ አባትህን በዚያን አይነት ማዋረድ የለብህም፡፡
\s5
\v 9 የአባትህ ልጅ ወይም የእናትህ ልጅ ብትሆን በቤት ውስጥ አብራህ ብታድግ ወይም ርቃ ብታድግም ከየትኛዋም እህትህ ጋር አትተኛ፡፡
\v 10 ከወንድ ልጅህ ሴት ልጅ ጋር ወይም ከሴት ልጅህ ሴት ልጅ ጋር አትተኛ፡፡ ይህ እፍረት ይሆንብሃል፡፡
\v 11 ከአባትህ ከተወለደች ከእንጀራ እናትህ ሴት ልጅ ጋር አትተኛ፡፡ እህትህ ናት፣ እናም ከእርሷ ጋር መተኛት የለብህም፡፡
\s5
\v 12 ከአባትህ እህት ጋር አትተኛ፡፡ ለአባትህ የቅርብ ዘመድ ናት፡፡
\v 13 ከእናትህ እህት ጋር አትተኛ፡፡ ለእናትህ የቅርብ ዘመድ ናት፡፡
\v 14 ወንድም ከሚስቱ ጋር በመተኛት አታዋርደው” ለዚያ ተግባር ወደ እርሷ አትቅረብ፣ አክስትህ ናት፡፡
\s5
\v 15 ከምራትህ ጋር አትተኛ፡፡ የወንድ ልጅህ ሚስት ናት፣ ከእርሷ ጋር አትተኛ፡፡
\v 16 ከወንድምህ ሚስት ጋር አትተኛ፣ በዚህ መንገድ አታዋርደው፡፡
\s5
\v 17 ከአንዲት ሴትና ከልጇ ጋር ወይም ከወንድ ልጇ ሴት ልጅ ጋር ወይም ከሴት ልጇ ሴት ልጅ ጋር አትተኛ፡፡ እነርሱ ለእርሷ የቅርብ ዘመዶች ናቸው፣ እናም ከእነርሱ ጋር መተኛት ጸያፍ ነው፡፡
\v 18 የሚስትህን እህት ሁለተኛ ሚስት አድርገህ አታግባ፤ ሚስትህ በህይወት ሳለች ከእህቷ ጋር አትተኛ፡፡
\s5
\v 19 አንዲት ሴት በወር አበባዋ ወቅት ላይ ሳለች አብረሃት አትተኛ፡፡ በዚያን ጊዜ ንጹኅ አይደለም፡፡
\v 20 ከጎረቤትህ ሚስት ጋር አትተኛ፣ በዚህ መንገድ ራስህን አታርክስ፡፡
\s5
\v 21 ከልጆችህ አንዳቸውንም በእሳት ውስጥ እንዲያልፉ አትስጥ፣ በዚህ ድርጊት ለሞሎክ መስዋዕት አድርህ ትሰጣቸዋለህ፣ የአምላክህን ስም ማቃለል የለብህም፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡
\s5
\v 22 ከወንዶች ጋር ከሴት ጋር እንደምትተኛው አትተኛ፡፡ ይህ ጻያፍ ነው፡፡
\v 23 ከማናቸውም እንስሳ ጋር አትተኛ ራስህን አታርክስ፡፡ ማንም ሴት ከማናቸውም እንስሳ ጋር መተኛት የለባትም፡፡ ይህ አስጸያፊ ወሲብ ነው፡፡
\s5
\v 24 ከእነዚህ መንገዶች በየትኛውም ራስህን አታርክስ፣ ከአንተ አስቀድሞ ያባረርኳቸው ህዝቦች በእነዚህ ሁሉ መንገዶች ረክሰዋል፡፡
\v 25 ምድሪቱ ረከሰች፣ ስለዚህም በኃጢአታቸው ቀጣኋቸው፣ ምድሪቱም በላይዋ የሚኖሩትን ተፋቻቸው፡፡
\s5
\v 26 ስለዚህ እናንተ የእኔን ትዕዛዛትና ህግጋቴን መጠበቅ አለባችሁ፣ እናንተ ተወላጅ እስራኤላዊያንም ሆናችሁ በእንተ መሀል የሚኖሩ እንግዶች ከእነዚህ ያልተገቡ ነገሮች የትኞቹንም ማድረግ የለባችሁም፡፡
\v 27 ከእናንተ አስቀድሞ በዚህ ምድር የኖሩ ሰዎች የሰሩት ጸያፍነት ይህ ነው፣ እናም አሁን ምድሪቱ ረከሰች፡፡
\v 28 ስለዚህም ምድሪቱ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ሰዎች እንደተፋች እናንተንም ካረከሳችኋት በኋላ እንዳትተፋችሁ ተጠንቀቁ፡፡
\s5
\v 29 ከእነዚህ አስነዋሪ ነገሮች መሀል የትኛውንም ነገር ያደረገ፣ እንዲህ ያለ ነገሮችን ያደረገው ሰው ከህዝቡ መሀል ተለይቶ ይጠፋል፡፡
\v 30 ስለዚህ በእነዚህ ነገሮች እንዳታረክሱ ከእናንተ አስቀድሞ በዚህ ስፍራ ይፈፀሙ የነበሩትን ጸያፍ ልምዶች ባለማድረግ ትዕዛዛቴን መጠበቅ አለባችሁ፡፡ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ።
\s5
\c 19
\p
\v 1 ሙሴን እንዲህ አለው
\v 2 “ለእስራኤል ሰዎች ጉባኤ ሁሉ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፣ “እኔ ያህዌ አምላካችሁ ቅዱስ እንደሆንኩ እናተም ቅዱሳን ሁኑ፡፡
\v 3 እያንዳንዱ እናቱንና አባቱን ያክብር፣ እናንተም ሰንበቴን ጠብቁ፡፡ እኔ አምላካች ያህዌ ነኝ፡፡
\v 4 ጥቅም ወደሌላቸው ጣኦታት ዘወር አትበሉ፣ ከቀለጠ ብረት ለራሳችሁ አማልዕክትን አታብጁ፡፡ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡
\s5
\v 5 ለያህዌ የህብረት መስዋእቶችን ስታቀርቡ፣ ተቀባይነት ልታገኙ በምትችሉበት መንገድ አቅርቡ፡፡
\v 6 መስዋዕቱ ባቀረባችሁበት ቀን አሊያም በማግስቱ ይበላ፡፡ አንዳች ነገር እስ ሶተኛው ቀን ቢተርፍመ ይቃጠል፡፡
\v 7 በሶስተኛው ቀን ቢበላ የረከሰ ነው፡፡ ተቀባይነት አያገኝም፣
\v 8 ነገር ግን የበላው ሁሉ በበደለኛነቱ ይጠየቅበታል ምክንያቱም ለያህዌ የተለየውን አርክሷል፡፡ ያ ሰው ከህዝቡ ተለይቶ ይጥፋ፡፡
\s5
\v 9 የምድራችሁን ሰብል በምትሰበስቡበት ጊዜ፤ የእርሻችሁን ቀርጢያ ሁሉ አትልቀሙ፣ አሊያም የአዝመራችን ምርት ሁሉ አትሰብስቡ፡፡
\v 10 ከወይን ተክልህ እያንዳንዱን ወይን ፍሬ አትሰብስብ፣ አሊያም በወይን ስፍራ የወዳደቁትን የወይን ፍሬዎች አትልቀም፡፡ ለድሆችና ለመጻተኞች እነዚህን ተዉላቸው፡፡ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡
\s5
\v 11 አትስረቁ፡፡ አትዋሹ፡፡ አንዳችሁ ሌላችሁን አታታሉ፡፡
\v 12 በሃሰት በስሜ አትማሉ የአምላካችን ስም አታርክሱ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡
\s5
\v 13 ጎረቤትህን አትበድል ወይም አትዝረፈው፡፡ የቀን ሰራተኛውን ክፍያ በአንተ ዘንድ አታሳድር፡፡
\v 14 መስማት የተሳነውን ሰው አትርገመው ወይም ከእውሩ ፊት ማሰናከያ ድንጋይ አታስቀምጥ ይልቁንም አምላክህን ፍራ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡
\s5
\v 15 ፍትህን አታጣም፡፡ አንድ ሰው ድሃ ስለሆነ ልታደላለት አይገባም፣ እንደዚሁም አንድ ሰው ባለጸጋ ስለሆነ አታዳላለት፡፡ ይልቁንም ለጎረቤትህ በጽድቅ ፍረድ 16በሰዎች መሃል በሀሳት ሃሜትን አታሰራጭ
\v 16 በሰዎች መሃል ሀሜትን እያሰራጨህ አትዙር፣ ይልቁንም የጎረቤትህን ሕይወት አቅና፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡
\s5
\v 17 በልብህ ወንድምህን አትጥላ፡፡ በእርሱ ምክንያት የኃጢአቱ ተካፋይ እንዳትሆን ጎረቤትህን በቅንነት ገስጸው፡፡
\v 18 ከህዝብህ ማንንም አትቀበል ወይም በማንም ላይ ቂም አይኑርህ፣ ነገር ግን በዚህ ፈንታ ጎረቤትህን እንደራስህ ውደድ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡
\s5
\v 19 ትዕዛዛቴን መጠበቅ አለብህ፡፡ እንስሳትህን ከሌሎች ልዩ ዝርያ ካላቸው እንስሳት ጋር አታዳቅል፡፡ በእርሻህ ላይ ስትዘራ የተለያየ የዘር ዐይነቶችን አትደባልቅ፡፡ ከሁለት የተለያዩ አይነት ነገሮች ተደባልቆ የተሰራ ልብስ አትልበስ፡፡
\s5
\v 20 ቤዛ ካልተከፈለላት ወይም ነጻ ካልወጣች ለባል ከታጨት ባሪያ ከሆነች ልጃገረድ የተኛ ሁሉ ይቀጡ፡፡ ሊገደሉ ግን አይገባም ምክንያቱም ነጻ አልወጣችም፡፡
\v 21 ሰውዬው ወደ መገናኛው ድንኳን መግቢያ ለበደል መስዋዕት ለያህዌ አውራ በግ ያምጣ፡፡
\v 22 ከዚያ ካህኑ በያህዌ ፊት ሰውዬው ለሰራው ኃጢአት የበደል መስዋዕት አውራ በግ በማቅረብ ያስተሰርይለታል፡፡ ከዚያ የሠራው ኃጢአት ይቅር ይባልለታል፡፡
\s5
\v 23 ወደምድሪቱ ስትገቡና ለምግብ የሚሆን ሁሉንም ዐይነት ዛፎች ስትተክሉ፣ ዛፎቹ ያፈሩትን ፍሬ ለመብላት እንደተከለከለ ቁጠሩት፡፡ ፍሬው ለእናንተ ለሶስት ዓመታት የተከለከለ ነው፡፡ አይበላም፡፡
\v 24 ነገር ግን በአራተኛው አመት ፍሬው ሁሉ ለያህዌ ለምስጋና የሚሰዋ ቅዱስ ይሆናል፡፡
\v 25 አመት ፍሬውን መብላት ትችላላችሁ፡፡ በመጠበቃችሁ ዛፎቹ ብዙ ያፈራሉ፡፡ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡
\s5
\v 26 ደሙ በውስጡ ያለበትን ስጋ አትብሉ፡፡ ስለ ወደፊቱ መናፍስትን አታማክሩ፣ ደግም ከተፈጥሮ በላይ በሆኑ ኃይላት ሌሎችን ለመቆጣጠር አትፈልጉ፤፡፡
\v 27 እንደ ጣኦት አምላኪዎች የጸጉራችሁን ዙሪያ አትላጩ ወይም የጺማችሁን ዙሪያ አትቆረጡ፡፡
\v 28 ለሙታን ሰውነታችሁን በስለት አትቁረጡ ወይም በሰውነታችሁ ላይ ንቅሳት አታድርጉ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡
\s5
\v 29 ሴት ልጅህን ሴተኛ አዳሪ በማድረግ አታወርዳት፣ በዚህ ነገር አገረ ወደ ግልሙትና ትገባለች ምድሪቱም በእርኩሰት ትሞላለች፡፡
\v 30 ጠብቁ የቤተመቅደሴን ቅድስና አክብሩ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡
\s5
\v 31 ወደ ሙታን ጠሪዎችና መናፍስትን ወደሚያነጋግሩ ዘወር አትበሉ፡፡ እነዚህን አትፈልጉ፣ ካልሆነ ያረክሷችኋል፡፡ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡
\s5
\v 32 ፀጉሩ ለሸበተ ሰው ተነስለት ደግሞም በዕድሜ የገፋውን ሰው አክብር፡፡ አምላክህን ፍራ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡
\s5
\v 33 በምድርህ በመካከልህ መጻተኛ ቢኖር፣ አትግፋው፡፡
\v 34 በመካከላችሁ የሚኖረው መጻተኛ እንደ ተወላጅ እስራኤላዊ ወገናችሁ ቁጠሩት ደግሞም እንደ ራሳችሁ ውደዱት፣ ምክንያቱም እናንተም በግብጽ ምድር መጻተኞች ነበራችሁ፡፡ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡
\s5
\v 35 ርዝመትን፣ ክብደትን፣ ወይም ብዛትን ስትለኩ፡፡ ሀሰተኛ መለኪያ አትጠቀሙ፡፡
\v 36 ትክክለኛ መስፈሪያን፣ ትክክለኛ ሚዛኖችን፣ ትክክለኛ የኢፍ እና የኢን መለኪያዎችን ተጠቀሙ፡፡ ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡
\v 37 ትዕዛዛቴንና ህግጋቴን ሁሉ ጠብቁ፣ አድርጓቸውም፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡”
\s5
\c 20
\p
\v 1 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
\v 2 “ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ በላቸው፣ ‹ከእስራኤል ሰዎች መሃል ማንም ሰው፣ ወይም ማንኛውም በእስራኤል የሚኖር መጻተኛ ከልጆቹ መሃል አንዱን ለሞሎክ ቢሰጥ በዕርግጥ ይገደል፡፡ በምድሪቱ የሚኖሩ ሰዎች በድንጋይ ይውገሩት፡፡
\s5
\v 3 እኔም በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አዞርበታለሁ፣ ከህዝቡም መሃል እቆርጠዋለሁ ምክንያቱም የተቀደሰውን ስፍራዬን ለማርከስና ቅዱሱን ስሜን ለማቃለል ልጁን ለሞሎክ ሰጥቷል፡፡
\v 4 ያ ሰው ከልጆቹ አንዱን ለሞሎክ ሲሰጥ ዚያች ምድር ሰዎች እንዳላዩ ቢሆን፣ ባይገድሉት፣
\v 5 እኔ ራሴ በዚያ ሰውና በቤቱ ላይ ፊቴን አዞራለሁ፣ እኔ ቆርጬ እጥለዋለሁ እንደዚሁም ከሞሎክ ጋር በሚያመነዝረው በማንኛውም ላይ ይህን አደርጋለሁ፡፡
\s5
\v 6 ወደ ሙታን ጠሪዎች ዘወር የሚል፣ ወይም ከመናፍስት ጋር ከሚነጋገሩ ጋር የሚመነዝርን ሰው ፊቴን አዞርበታለሁ፤ ከህዝቡም መሃል አጠፋዋለሁ፡፡
\v 7 ስለዚህ ራሳችሁን ለያህዌ ስጡ ተቀደሱም፣ ምክንያቱም እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡
\s5
\v 8 ትዕዛዛቴን ጠብቁ አድርጓቸውም፡፡ ለራሴ የመረጥኳችሁ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡
\v 9 ወይም እናቱን የሚረግም ሁሉ ይገደል፡፡ አባቱን ወይም እናቱን ረግሟልና በደለኛ ነው ሞት ይገባዋል፡፡
\s5
\v 10 ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ዝሙት የፈጸመ ሰው፣ ከጎረቤቱ ሚስት፣ ጋር ያመነዘረ ይገደል አመንዝራውና አመንዝራይቱም ሁለቱም ይገደሉ፡፡
\v 11 ከአባቱ ሚስት ጋር ሊተኛት የወደቀ የገባ አባቱን ያዋርዳል፡፡ ልጅየውም የአባቱ ሚስትም ሁለቱም ይገደሉ፡፡ በደለኞች ናቸው ሞት ይገባቸዋል፡፡
\v 12 አንድ ሰው ከልጁ ሚስት ጋር ቢተኛ፣ ሁለቱም ሊገደሉ ይገባል ያልገባ ፍትወት ፈጽመዋል በደለኞች ናቸው ሞት ይገባቸዋል፡፡
\s5
\v 13 አንድ ወንድ ከሴት ጋር እንደሚተኛ ከሌላ ወንድ ጋር ቢተኛ፣ ሁለቱም ጸያፍ ነገር አድርገዋል፡፡ በእርግጥ ሞት ይገባቸዋል፡፡ ይገደሉ፡፡ በደለኞች ናቸው ሞት ይገባቸዋል፡፡
\v 14 አንድ ሰው አንዲትን ሴትና እናቲቱንም ቢያገባ፣ ይህ አሳፋሪ ነው፡፡ እርሱና ሴቲቱ ሁለቱም በእሳት ይቃጠሉ፣ ይህ ሲደረግ በመሀላችሁ ክፋት አይኖርም፡፡
\s5
\v 15 አንድ ሰው ከእንስሳ ጋር ቢተኛ፣ በእርግጥ ይገደል፣ እንስሳይቱንም ግደሏት፡፡
\v 16 አንዲት ሴት ለመገናኘት ወደ ማንኛውም አይነት እንስሳ ብተቀርብ ሴትየዋንም እንስሳውንም ግደሏቸው፡፡ በእርግጥ ሊገደሉ ይገባል፡፡ በደለኞች ናቸው ሞት ይገባቸዋል፡፡
\s5
\v 17 አንድ ሰው የአባቱ ልጅ ከሆነችውም ሆነ የእናቱ ልጅ ከሆነች እህቱ ጋር ቢተገኛ እህትም ከእርሱ ጋር ብትተኛ ይህ አሳፋሪ ነገር ነው፡፡ ከህዝባቸው መሃል ተለይተው ይውጡ፤ ምክንያቱም ከእህቱ ጋር ተኝቷል፡፡ በደሉን ይሸከማል፡፡
\v 18 አንድ ሰው አንዲትን ሴት በወር አበባዋ ወቅት አብሯት ቢተኛና ቢገናኛት፣ የደሟ ምንጭ የሆነውን የደም መፍሰሷን ገልጧል፡፡ ወንዱም ሴቷም ሁለቱም ከህዝባቸው መሃል ተለይተው ይውጡ፡፡
\s5
\v 19 ከእናትህ ወይም ከአባትህ እህት ጋር አትተኛ፣ ምከንያቱም የቅርብ ቤተ ዘመድህን ታዋርዳለህ፡፡ በደልህን ልትሸከም ይገባሃል፡፡
\v 20 አንድ ሰው ከአጎቱ ሚስት ጋር ቢተኛ አጎቱን አዋርዷል፡፡ በደላቸውን ሊሸከሙ ይገባል ያለ ልጅ ይቀራሉ፡፡
\v 21 አንድ ሰው የወንድሙን ሚስት ቢያገባ ይህ እርኩስ ነው ምክንያቱም ዘመዱ ሆኖ ሳለ የወንድሙን ትዳር አፍርሷል፣ ልጅ አልባ ይሆናሉ፡፡
\s5
\v 22 ስለዚህም ስርአቶቼንና ህግጋቶቼን ሁሉ መጠበቅ አለባችሁ፤ እንድትኖርባት ያመጣኋቸው ምድር እንዳትተፋችሁ ህግጋቴንና ሥርዓቶቼን ጠብቁ፡፡
\v 23 ከፊታችሁ በማባርራቸው ህዝቦች ልምዶች አትመላለሱ፣ እነርሱ እነዚህን ነገሮች ሁሉ አድርገዋል፣ እኔም እነርሱን ጠላሁ፡፡
\s5
\v 24 እኔ እንዲህ እላችኋለሁ፣ “ምድራቸውን ትወርሳላችሁ፣ ምድሪቱን እንድትወርሷት ለእናንተ እሰጣችኋለሁ፣ ወተትና ማር የምታፈስ ምድር ናት፡፡ ከሌላው ህዝብ የለየኋችሁ፣ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ”
\v 25 ስለዚህ እናንተ ንጹህ በሆኑና ንጹኅ በሆኑ እንስሳት መሃል፣ ንጹኅ በሆኑና ንጹህ ባልሆኑ ወፎች መሃል ልዩነት አድርጉ፡፡ ለእናንተ ርኩስ ናቸው ብዬ በለየኋቸው ንጹኅ ባልሆኑ እንስሳት ወይም ወፎች ወይም በማንኛውም በምድር ላይ በሚሳብ ፍጥረት ራሳችሁን አታርክሱ፡፡
\s5
\v 26 እኔ ያህዌ ቅዱስ እንደሆንኩ፣ ደግሞም ለእኔ ትሆኑ ዘንድ ከሌሎች ህዝቦች እንደለየኋችሁ ቅዱሳን ሁኑ፡፡
\s5
\v 27 ከሙታን ጋር የሚነጋገር አንድ ወንድ ወይም አንዲት ሴት ወይም ከመናፍስት ጋር የሚነጋገር በእርግጥ ይገደል፡፡ ህዝቡ በድንጋይ ወግፎ ይግደላቸው በደለኞች ናቸውና ሞት ይገባቸዋል፡፡
\s5
\c 21
\p
\v 1 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው “ለካህናቱ፣ ለአሮን ልጆች እንዲህ በላቸው፣ ‹ከእናንተ መሃል ማንም በመካከላችሁ በሞተ ሰው አይርከስ፣
\v 2 ለቅርብ ዘመድ ካልሆነ በስተቀር ማንም አይርከስ ለእናቱ እና አባቱ፣ ለወንድ ልጁና ለሴት ልጁ፣ ወይም ለወንድሙ
\v 3 ወይም በቤቱ ከምትኖር ባል ካላገባች ልጃገረድ እህቱ በስተቀር አይርከስ፡፡ ለእርሷ ግን ራሱን ንጹህ ላያርግ ይችላል፡፡
\s5
\v 4 ለሌሎች ዘመዶቹ ግን እስኪረክስ ድረስ ራሱን ማርከስ የለበትም፡፡
\v 5 ካህናት ራሳቸውን አይላጩ ወይም የጺማቸውን ዳርቻ አይላጩ፣ አሊያም ሰውነታቸውን በስለት አይቁረጡ፡፡
\v 6 እነርሱ ለአምላካቸው የተለዩ ይሆኑ፣ የአምላካቸውን ስም አያቃሉ፣ ምክንያቱም ካህናቱ የአምላካቸውን “ምግብ” መስዋዕቱን ለያህዌ በእሳት ያቀርባሉ፡፡ ስለዚህም እነርሱ የተለዩ ይሁኑ፡፡
\s5
\v 7 ለአምላካቸው የተለዩ ስለሆኑ ማናቸውንም ጋለሞታ እና የረከሰች ሴት እንደዚሁም ከባሏ የተፋታችን ሴት ማግባት የለባቸውም፡፡
\v 8 የአምላክህን “ምግብ” የሚያቀርብ ነውና እርሱን መለየት አለብህ፡፡ በፊትህ ቅዱስ መሆን አለበት፣ ምክንያቱም ለራሴ የለየሁህ እኔ፣ ያህዌ ቅዱስ ነኝ፡፡
\v 9 ማንኛዋም የማንኛውም ካህን ሴት ልጅ ጋለሞታ ብትሆን አባቷን ታሳፍራለች፡፡ በእሳት ትቃጠል፡፡
\s5
\v 10 ከወንድሞቹ መሃል ሊቀ ካህን የሆነው፣ የሹመቱ ዘይት በራሱ ላይ የፈሰሰበት፣ ደግሞም የሊቀ ካህኑን ልዩ ልብሶች ለመልበስ የተጾመ ጸጉሩን ይሸፍን ልብሱን አይቅደድ፡፡
\v 11 ለአባቱ ወይም ለእናቱም ቢሆን እንኳን የሞተ ሰው በሚገኝበትና ራሱን በሚያረክስበት ማናቸውም ስፍራ አይሂድ፡፡
\v 12 ሊቀካህኑ የቤተ መቅደሱን የተቀደሰ ስፍራ ትቶ አይሂድ ወይም የአምላኩን ቅድስና አያቃል፣ ምክንያቱም በአምላኩ የቅባት ዘይት ሊቀ ካህን ሆኖ ተሾሞ ነበርና፡፡እኔ ያህዌ ነኝ፡፡
\s5
\v 13 ካህኑ ድንግሊቱን ሚስቱ አድርጎ ያግባት፡፡
\v 14 ባሏ የሞተባትን ሴት፣ የተፋታችን ሴት፣ ወይም ጋለሞታን ሴት አያግባ፡፤ እንዲያ ካሉት ሴቶች መሃል አያግባ፡፡ ከራሱ ህዝብ መሃል ድንግሊቱን ብቻ ማግባት ይችላል፡፡
\v 15 እነዚህን ህጎች ይጠብቅ፣ በህዝቡ መሃል ልጆቹን እንዳያረክስ ህግጋቱን ይጠብቅ፣ እርሱን ለራሴ የለየሁት እኔ ያህዌ ነኝ፡፡
\s5
\v 16 ያህዌ እንደህ ሲል ሙሴን ተናገረው፣
\v 17 “አሮንን እንዲህ ብለህ ንገረው፣ ማናቸውም ከወገንህ መሀል በትወልዳቸው ውስጥ አካላዊ ጉድለት ያለበት፣ የአምላኩን ‹ምግብ› ለመሰዋት መቅረብ የለበትም፡፡
\s5
\v 18 ማናቸውም አካላዊ እንከን ያለበት ሰው ወደ ያህዌ መቅረብ የለበትም፣ እንደ ዐይነ ስውር፣ ሽባ የሆነ ሰው፣ አካሉ የጎደለ ወይም አካሉ የተወላገደ፣
\v 19 እጆቹ ወይም እግሮቹ ሽባ የሆነ፣
\v 20 መጻጉ ወይም ድንክ ሰው፣ ወይም በዐይኖቹ ላይ እንከን ያለበት ሰው፣ ወይም በሽታ የያዘው፣ ሞጭሟጫ፣ እከክ ያለበት ወይም ጃንደረባ ወደ ያህዌ አይቅረብ፡፡
\v 21 ከካህኑ ከአሮን መሃል ምንም አካላዊ ጉድለት ያለበት ሰው ለያህዌ የእሳት መስዋዕቶች ለመሰዋት አይቅረብ፡፡ አካላዊ ጉድለት ያለበት እንዲህ ያለው ሰው የአምላኩን ‹ምግብ ለማቅረብ መቅረብ የለበትም፡፡
\s5
\v 22 ከቅድስተ ቅዱሳኑም ሆነ ከቅዱሱ የአምላኩ ምግብ ሊበላ ግን ይችል፣
\v 23 ሆኖም፣ ወደ መጋረጃው መግባት የለበትም ወይም ወደ መሰዊያው አይቅረብ፣ ምክንያቱም አካላዊ ጉድለት ያለበት፣ ስለዚህም ቅዱሱን ስፍራዬን አያርክስ፣ ለራሴ የለየኋቸው እኔ ያህዌ ነኝ፡፡”
\v 24 ሙሴ እነዚህን ቃላት ለአሮን፣ ለልጆቹ፣ እና ለእስራኤል ሰዎች ሁሉ ተናገረ፡፡
\s5
\c 22
\p
\v 1 ያህዌ ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፣
\v 2 “ለአሮንና ለልጆቹ እንዲህ በላቸው፣ የእስራኤል ሕዝብ ለእኔ ከለይዋቸው የተቀደሱ ነገሮች እንዲጠበቁ ንገራቸው፡፡ የተቀደሰው ስሜን አያርክሱ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡
\v 3 እንዲህ በላቸው፣ በዘመን ሁሉ ከትውልዳችሁ መሀል ማንም ንጹህ ያልሆነ ሰው የእስራኤል ህዝብ ለያህዌ ወደ ለየው ቅዱስ ነገሮች ቢቀርብ፣ ያ ሰው እኔ ፊት ከመቅረብ የተከለከለ ነወ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡
\s5
\v 4 ከአሮን ትውልድ ውስጥ ተላላፊ የቆዳ በሽታ ያለበት፣ ወይም ከሰውቱ ፈሳሽ የሚወጣ ንጹኅ እስኪሆን ድረስ ለያህዌ ከሚቀርብ መስዋዕት አይብላ፡፡ማንም ከሞተ ጋር በመነካካት ንጹህ ያልሆነውን ማንኛውንም ነገር የነካ፣ ወይም የዘር ፈሳሽ ካለበት ሰው ጋር በመነካካት፣
\v 5 ወይም የሚያረክሰውን ማናቸውንም በሆዱ የሚሳብ እንስሳ የነካ፣ ወይም ማናቸውንም የሚያረክሰውን ሰው የነካ፣ ማንኛውም አይነት እርኩሰት የሚያስከትል ነገር የነካ
\v 6 ማናቸውንም እርኩስ ነገር የነካ ካህን እስከ ምሽት ንጹህ አይደለም፡፡ ሰውነቱን በውሃ ካልታጠበ በቀር ከተቀደሱት ነገሮች አንዳች አይብላ፡፡
\s5
\v 7 ፀሐይ ስትጠልቅ፣ በዚያን ሰዓት ንጹህ ይሆናል፡፡ ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ከተቀደሱት ነገሮች መብላት ይችላል፣ ምክንያቱም ለእርሱ የተፈቀዱ ምግብ ናቸው፡፡
\v 8 ሞቶ የተገኘን ማናቸውም ነገር አይብላ ወይም እርሱን የሚያረክሰውን በዱር እንስሳ የተገደለውን አይብላ፡፡
\v 9 ካህናት ትእዛዛቴን ይጠብቁ፣ ይህን ካላደረጉ በኃጢአት በደለኛ ይሆናሉ ደግም ስሜን በማቃለል ይሞታሉ፡፡ ለራሴ የለየኋቸው እኔ ያህዌ ነኝ፣
\s5
\v 10 ማንም የካህኑ ቤተሰብ ያልሆነ ሰው፣ የካህኑን እንግዶች ጨምሮ፣ ወይም ቅጥር አገልጋዮቹ ጭምር ቅዱስ ከሆነው አንዳች አይብሉ፡፡
\v 11 ነገር ግን ካህኑ በገንዘቡ ባሪያ ቢገዛ ያ ባሪያ ለያህዌ ከተለዩ ነገሮች መብላት ይችላል፡፡ የካህኑ ቤተሰብ አባላት እና በቤቱ የተወለዱ ባሪያዎች ከእርሱ ጋር ከእነዚህ የተቀደሱ ነገሮች መብላት ይችላሉ፡፡
\s5
\v 12 የካህኑ ሴት ልጅ ካህን ያልሆነ ሰው ብታገባ ለመስዋዕት ከመጣው ውስጥ አንዳች አትበላም፡፡
\v 13 ነገር ግን የካህኑ ሴት ልጅ ባሏ የሞተባት ከሆነች፣ ወይም ከባሏ ከተፋታች፣ እና ልጅ ያልወለደች ከሆነች እንደ ልጅነቷ ዘመን ለመኖር ወደ አባቷ ቤት ብትመለስ ከአባቷ ምግብ መብላት ትችላለች፡፡ ነገር ግን ማንም የካህን ቤተሰብ ያልሆነ ከካህናት ምግብ መብላት አይችልም፡፡
\s5
\v 14 አንድ ሰው ሳያውቅ ቅዱሱን ምግብ ቢበላ፣ ከወሰደው አንድ አምስተኛ ጨምሮ ለካህኑ ይመልስ፡፡
\v 15 የእስራኤል ህዝብ ለያህዌ የወዘወዙትንና ያቀረቡትን ቅዱስ ነገሮች ማቃለል የለባቸውም፣
\v 16 ያልተፈቀደላቸውን ቅዱሱን ምግብ በመብላት ራሳቸውን በደለኛ የሚያደርጋቸውን ኃጢአት እንዲሸከሙ ማድረግ የለባቸውም እነርሱን ለራሴ የለየሁት እኔ ያህዌ ነኝ”
\s5
\v 17 ያህዌ እንዲህ አለው፣
\v 18 “ለአሮንና ልጆቹ እንዲሁም ለእስራኤል ሰዎች ሁሉ እንዲህ በላቸው፣ ‹ማንኛውም እስራኤላዊ፣ ወይም በእስራኤል የሚኖር ባይተዋር፣ ለስዕለትም ይሁን፣ ወይም ለበጎ ፈቃድ መስዋዕት ሲያቀርቡ፣ ወይም ለያህዌ የሚቃጠል መስዋዕት ሲያቀርቡ፣
\v 19 ተቀባይነትን እንዲያገኝ ከቀንድ ከብታቸው፣ ከበግ ወይም ፍየሎች ውስጥ ነውር የሌለበትን ተባዕት እንስሳ ያቅርቡ፡፡
\s5
\v 20 ነውር ያለበትን ግን አታቅርቡ፡፡ ይህን እኔ አልቀበልም፡፡
\v 21 ከከብቱ ወይም ከመንጋው ለስዕለት የህብረት መስዋዕት ለያህዌ የሚሰዋ ሁሉ፣ ወይም የበጎ ፍቃድ መስዋዕት የሚያቀርብ ተቀባይነት ያገኝ ዘንድ ነውር የሌለበትን መስዋዕት ያቅርብ፡፡ በእንስሳው ላይ እንከን አይኑርበት፡፡
\s5
\v 22 ዕውር፣ አንካሳ ወይም ሰንካላ፣ ወይም ኪንታሮት፣ ህመም፣ ወይም ቁስል ያለበትን እንስሳ አትሰዉ፡፡ እዚህን በእሳት መስዋዕት አድርጋችሁ በመሰዊያ ላይ ለያህዌ አታቅርቡ፡፡
\v 23 የበጎ ፈቃድ መስዋዕት አድርጋችሁ ጎደሎ ወይም ትንሽ በሬ ወይም በግ ማቅረብ ትችላላችሁ፣ እንዲህ ያለው መስዋዕት ግን ለስዕለት ተቀባይነት የለውም፣
\s5
\v 24 ለያህዌ ሰንበር ያለበት፣ የተሰበረ፣ የተዘነጠለ፣ ወይም የዘር ፍሬው የተቀጠቀጠ እንስሳ አታቅርቡ፡፡ እነዚህን በምድራችሁ አታቅርቡ፣
\v 25 ለእግዚአብሔር ለምግብ የሚቀርብ አድርጋችሁ ከመጻተኛው እጅ አትቀበሉ፣ ምክንያቱም በእነዚህ ላይ ጉድለቶች ወይም ነውሮች አሉባቸው እነዚህን ከእናንተ አልቀበለም፡፡›”
\s5
\v 26 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
\v 27 “አንድ ጥጃ ወይም አንድ የበግ ወይም የፍየል ግልገል ሲወለድ፣ ከእናቱ ጋር ሰባት ቀናት ይቆይ፡፡ ከዚያም ከስምንተኛው ቀን አንስቶ፣ ለያህዌ በእሳት መስዋዕት ሆኖ መቅረብ ይችላል፡፡
\s5
\v 28 አንዲትን ላም ወይም ሴት በግ ከጥጃዋ ወይም ከግልገሏ ጋር በአንድ ቀን አትረዱ፡፡
\v 29 ለያህዌ የምስጋና መስዋዕት ስታቀርቡ፣ ተቀባይነት ባለው መንገድ አቅርቡ፡፡
\v 30 መስዋዕቱ በቀረበበት ቀን ይበላ፡፡ እስከ ማለዳው አንዳች አታስቀሩ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡
\s5
\v 31 ትዕዛዛቴን ጠብቁ አድርጓቸውም፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡
\v 32 ቅዱስ ስሜን አታቃሉ፡፡ በቅድስናዬ በእስራኤል ህዝብ መታወቅ አለብኝ፡፡ እናንተን ለራሴ የለየሁት እኔ ያህዌ ነኝ፣
\v 33 አምላካችሁ እሆን ዘንድ ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡”
\s5
\c 23
\p
\v 1 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
\v 2 “ለእስራኤል ህዝብ እንዲህ በላቸው፣ ‹ለያህዌ የተለዩ የተቀደሱ ባዕሎቻችሁ፣ እንደ ቅዱስ ጉባኤዎቻችሁ የምታውጇቸው፣ የእኔ መደበኛ በዓላት ናቸው፡፡
\s5
\v 3 ስድስት ቀናት ትሰራላችሁ፣ ሰባተኛው ቀን ግን ሙሉ እረፍት የሚደረግበት ሰንበት ነው፣ የተቀደሰ ጉባኤ ዕለት ነው በምትኖሩበት ስፍራ ሁሉ ለያህዌ ሰንበት ስለሆነ ምንም ስራ አትስሩበት፡፡
\s5
\v 4 እነዚህ ለያህዌ የተመረጡ በዓላት ብላችሁ በተወሰነላቸው ጊዜ የምታውጇቸው የተቀደሱ ስብሰባዎች ናቸው፡፡
\v 5 በመጀመሪያው ወር በወሩ በአስራ አራተኛው ቀን ጸሀይ ስትጠልቅ የያህዌ ፋሲካ ነው፡፡
\v 6 በዚያው ወር በአስራ አምስተኛው ቀን የያህዌ የቂጣ በዓል ነው፡፡ ለሰባት ቀናት እርሾ ያልገባበት ቂጣ ትበላላችሁ፡፡
\s5
\v 7 በመጀመሪያው ቀን ለያህዌ የተለየ ጉባኤ ይኖራችኋል፣ የተለመደ ተግባራችሁን አትሰሩበትም፡፡
\v 8 ለሰባት ቀናት በእሳት የሚቀርብ መስዋዕት ለያህዌ ታቀርባላችሁ ሰባተኛው ቀን የተለመደ ተግባራችሁን የማታከናውኑበት ለያህዌ የተለየ ጉባኤ የሚደረግበት ነው›”
\s5
\v 9 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
\v 10 ”ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ ብለህ ንገራቸው ‹ወደምሰጣችሁ ምድር ስትገቡ፣ እና የመጀመሪያውን አዝመራ ስትሰበስቡ፣ ከበኩራቱ ፍሬዎች ለካህኑ አንድ ነዶ ታመጣላችሁ፡፡
\v 11 ነዶው ተቀባይነትን እንዲያገኝ ካህኑ በያህዌ ፊት ይወዘውዘውና ለእርሱ ያቀርበዋል፡፡ ካህኑ ነዶውን የሚወዘውዘውና ለእኔ የሚያቀርበው በሰንበት ቀን ማግስት ነው፡፡
\s5
\v 12 ነዶውን በምትወዘውዙበትና ለእኔ በምታቀርቡበት ቀን ለያህዌ ነውር የሌለበት የአንድ አመት ወንድ ጠቦት የሚቃጠል መስዋዕት ታቀርባላችሁ፡፡
\v 13 የእህል ቁርባን ለያህዌ መልካም መዓዛ የሚሆን በዘይት የተለወሰ የኢፍ ሁለት አስረኛ መልካም ዱቄት፣ በእሳት የተዘጋጀ መስዋዕት፣ እና ከነዚህም ጋር የኢን አንድ አራተኛ ወይን የመጠጥ ቁርባን መቅረብ አለበት፡፡
\v 14 ለአምላካችሁ ይህን መስዋዕት እስከምታቀርቡበት ቀን ድረስ ምንም ዓይነት ዳቦ፣ አሊያም የተጠበሰ እሸት ወይም ለምለሙን እሸት አትብሉ፡፡ ይህ ለትወልዳችሁ ሁሉ በምትኖሩበት ስፍራ ሁሉ ቋሚ መታሰቢያ ይሆናል፡፡
\s5
\v 15 ከዚያ ሰንበት ቀን ማግስት አንስቶ ነዶውን ለመወዝወዝና ለያህዌ ለማቅረብ ካመጣችሁት ቀን ጀምራችሁ ሰባት ሙሉ ሳምንታት፣ ሰባት ሰንበት ትቆጥራላችሁ፣
\v 16 እስከ ሰባተኛው ሰንበት ማግስት ድረስ ትቆጥራላሁ፡፡ ያም ማለት ሀምሳ ቀናት ትቆጥራላችሁ፡፡ ከዚያ ለያህዌ የአዲስ አዝመራ መስዋዕት ታቀርባላችሁ፡፡
\s5
\v 17 ከየቤቶቻችሁ ከኢፍ ሁለት አስረኛ የተጋገሩ ሁለት ዳቦዎች ታመጣላችሁ፡፡ ከመልካም ዱቄት የሚዘጋጅና በእርሾ የተጋገሩ ይሁኑ፤ ከበኩራት ፍሬዎች የሚቀርቡ የሚወዘወዙና ለያህዌ የሚቀርቡ መስዋዕቶች ይሆናሉ፡፡
\v 18 ከዳቦው ጋር ነውር የሌለባቸው የአንድ ዓመት እድሜ ያላቸው ሰባት ጠቦቶች፣ አንድ ወይፈን በሬ፣ እና ሁለት አውራ በጎች ታቀርባላችሁ፡፡ እነርሱም ለያህዌ የሚቃጠል መስዋዕት ይሆናሉ፣ ከእህል ቁርባን ከመጠጥ ቁርባን ጋር፣ በእሳት የተዘጋጀ መስዋዕት እና ለያህዌ መልካም መዓዛ ያለው መስዋዕት ይሆናሉ፡፡
\s5
\v 19 ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ታቀርባላሁ፣ እንዲሁም ለህብረት መስዋዕት የአንድ አመት ዕድሜ ያላቸው ሁለት ወንድ ጠቦቶች ለመስዋዕት ታቀርባላችሁ፡፡
\v 20 ካህኑ ከበኩራት ፍሬዎች ዳቦ ጋር በያህዌ ፊት ይወዘወዛቸው፣ እነርሱንም መስዋዕት አድርጎ ለእርሱ ከሁለት ጠቦቶች ጋር ያቅርብ፡፡ ለያህዌ ቅዱስ መስዋዕቶች ሲሆኑ የካህኑ ድርሻ ናቸው፡፡
\v 21 በዚያው ቀን ማወጅ አለባችሁ፡፡ የተቀደሰ ጉባኤ ይኖራል፣ እናም የተለመደ ስራችሁን አትሰሩም፡፤ ይህ የህዝባችሁ በትውልዶች ሁሉ በምትኖሩበት ሥፍራ ሁሉ ቋሚ መታሰቢያ ይሆናል፡፡
\s5
\v 22 የምድራችሁን ፍሬ ስትሰበስቡ፣ የእርሻችሁን ጥግጋት ሁሉ ሙሉ ለሙሉ አትሰብስቡ፣ የሰብላችን ቃርሚያ ሁሉ አትሰብስቡ፡፡ እነዚህን ለድሆችና ለመጻተኛው ተዉላቸው፡፡ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡”
\s5
\v 23 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
\v 24 ”ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ በላቸው፣ ‹በሰባተኛው ወር፣ የወሩ የመጀመሪያው ቀን ለእናንተ ታላቅ እረፍት ይሆናል፣ በመለኮት ድምጽ መታሰቢያ የሚደረግበት፣ እና የተቀደሰ ጉባኤ ይሆናል፡፡
\v 25 የተለመደ ሥራ አትሰሩበትም፣ ለያህዌ የእሳት መስዋዕት አቅርቡበት፡፡›”
\s5
\v 26 ከዚያ ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
\v 27 “አሁን የዚህ የሰባተኛው ወር አስረኛ ቀን የስርየት ቀን ይሆናል፡፡ ለያህዌ የተለየ ጉባኤ መሆን አለበት፣ ራሳችሁን ማዋረድና ለያህዌ በእሳት መስዋዕት መሰዋት አለባችሁ፡፡
\s5
\v 28 በዚያን ቀን ምንም ሥራ አትስሩ ምክንያቱም በአምላካችሁ በያዌ ፊት ለራሳች ማስታሰርያ የምታቀርቡበት የስርየት ቀን ነው፡፡
\v 29 በዚያን ቀን ራሱን የማያዋርድ ማንም ቢሆን ከህዝቡ ተለይቶ ይጥፋ፡፡
\s5
\v 30 በዚያን ቀን ማናቸውንም ሥራ የሚሰራውን ማንንም ቢሆን፣ እኔ ያህዌ ከህዝቡ መሀል አጠፋዋለሁ፡፡
\v 31 በዚያ ቀን ማናቸውንም ዐይነት ሥራ አትሰሩም፡፡ ይህ በህዝባችሁና ትውልዶቻችሁ ሁሉ በምትኖሩባቸው ስፍራዎች ሁሉ ቋሚ መታሰቢያ ይሆናል፡፡
\v 32 ይህ ቀን ለእናንተ የከበረ የሰንበት ዕረፍት ይሁንላችሁ፣ እናንተም በወሩ በዘጠነኛው ቀን ራሳችን አዋርዱ፡፡ ከምሽት እስከ ምሽት ሰንበትን ጠብቁ፡፡”
\s5
\v 33 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
\v 34 “ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ በላቸው፣ ‹በሰባተኛው ወር አስራ አምስተኛው ቀን ለያህዌ የዳስ በዓል ይሆናል፡፡ ይህም ሰባት ቀናት ይወስዳል፡፡
\s5
\v 35 በመጀመሪያው ቀን ቅዱስ ጉባኤ ይኖራል፡፡ የተለመደውን ሥራ አትስሩበት፡፡
\v 36 ለሰባት ቀናት ለያህዌ የሚቃጠል መስዋዕት አቅርቡበት፡፡ በስምንተኛው ቀን ቅዱስ ጉባኤ ይሁን፣ እናንተም ለያህዌ የሚቃጠል መስዋዕት አቅርቡ፡፡ ይህ ክቡር ጉባኤ ነው፣ እናም አንዳች የተለመደ ሥራ አትስሩበት፡፡
\s5
\v 37 እነዚህ ለያህዌ የተለዩ በአላት ናቸው፣ ለያህዌ የሚቃጠል መስዋዕት ለማቅረብ ቅዱስ ጉባኤ የምታውጁበት፣ የሚቃጠል መስዋዕትና የእህል ቁርባን፣ የመስዋዕቶችና የመጠጥ ቁርባች እያንዳንዱን በየራሱ ቀን ለይታችሁ ለእግዚአብሔር የምታውጁባቸው በዓላት ናቸው፡፡
\v 38 እነዚህ በአላት ከያህዌ ሰንበታትና ከእናንተ ስጦታዎች ተጨማሪ ናቸው፣ ስጦቻችሁ ሁሉ፣ እና ለያህዌ የምትሰጧቸው የበጎ ፈቃድ መስዋዕቶቻችሁ ሁሉ ናቸው፡፡
\s5
\v 39 የዳስ በዓልን በሚመለከት፣ በሰባተኛው ወር በአስራ አምስተኛው ቀን፣ እናንተ የምድሪቱን ፍሬዎች ስትሰበስቡ ይህን የያህዌ በዓል ለሰባት ቀናት ማክበር አለባችሁ፡፡ የመጀመሪያው ቀን የፍፁም ዕረፍት ቀን ይሆናል፣ ስምንተኛው ቀንም እንደዚሁ የፍጹም ዕረፍት ቀን ይሆናል፡፡
\s5
\v 40 በመጀመሪያው ቀን ከዛፎቹ መልካሞቹን ፍሬዎች ውሰዱ፣ የዘንባባ ዛፎች ዝንጣፊዎች፣ እና የለምለሙ ዛፎች ቅርንጫፎች፣ ከወንዝ ዳርቻ ለምለም ዛፎች ቅርንጫፎች ወስዳችሁ በአምላካችሁ በያህዌ ፊት ለሰባት ቀናት ሃሴት ታደርጋላችሁ፡፡
\v 41 በየአመቱ ለሰባት ቀናት፣ ይህን በዓል ለያህዌ ታከብራላችሁ፡፡ ይህ በትውልዳችሁ ሁሉ በምትኖሩባቸው ስፍራዎች ሁሉ ቋሚ መታሰቢያ ይሆናል፡፡ ይህን በዓል በሰባተኛው ወር አክብሩ፡፡
\s5
\v 42 ለሰባት ቀናት በትንንሽ ዳሶች ውስጥ ትኖራላችሁ፡፡ እስራኤላዊ የሆነ ሁሉ ለሰባት ቀናት በትንንሽ ዳሶች ውስጥ ይቀመጥ፣
\v 43 ከእናንተ በኋላ የሚመጣው ትውልድ፣ የልጅ ልጆቻችሁ፣ እስራኤላውያንን ከግብጽ ምድር ሳወጣ በእንደዚህ ዐይነት ዳሶች ውስጥ እንዴት እንዲኖሩ እንዳደረግኩ ያውቃሉ፡፡ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡›”
\v 44 በዚህ መንገድ፣ ሙሴ ለእስራኤል ህዝብ ለያህዌ የተለዩትን በዓላት አስታወቁ፡፡
\s5
\c 24
\p
\v 1 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
\v 2 “የእስራኤል ሰዎች መቅረዞች ሁልጊዜም እንዲነዱና ብርሃን እንዲሰጡ ከወይራ ፍሬ የተጠመቀ ንጹኅ ዘይት ለመቅረዞችህ ወደ አንተ እንዲያመጡ እዘዛቸው፡፡
\s5
\v 3 አሮን ያለማቋረጥ ከምሽት እስከ ማለዳ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ከመጋረጃው ውጭ በቃልኪዳኔ ድንጋጌ ፊት መቅረዙን በያህዌ ፊት ያለማቋረጥ ያብራ፡፡ ይህ በትወልዳች ሁሉ ቋሚ ስርዓት ይሆናል፡፡
\v 4 ሊቀ ካህኑ በንጹኅ ወርቅ በተሰራው የመቅረዝ መያዣ ላይ መቅረዞቹ ሁልጊዜም በያህዌ ፊት እንዲበሩ ያደርጋል፡፡
\s5
\v 5 መልካም ዱቄት ወስደህ አስራ ሁለት ዳቦዎች ጋግር፡፡ ለእያንዳንዱ ዳቦ የኢፍ ሁለት እስረኛ መጠን ተጠቀም፡፡
\v 6 ከዚያ በሁለት ረድፍ ደርድራቸው፣ በአንዱ መስመር ስድስቱን በንጹኅ ወርቅ በተሰራ ጠረጴዛ ላይ በያህዌ ፊት ደርድር፡፡
\s5
\v 7 በእያንዳንዱ የዳቦዎቹ ረድፍ እንደ ዳቦዎቹ ምልክት ንጹኅ ዕጣን አድርግበት፡፡ ይህ ዕጣን ለያህዌ በእሳት የሚቀርብ መስዋእት ይሆናል፡፡
\v 8 በእያንዳንዱ የሰንበት ዕለት ሊቀ ካህኑ የእስራኤልን ህዝብ ወክሎ የዘላለም ቃልኪዳን ምልክት አድርጎ ህብስቱን በመደበኛነት ለያህዌ ያቀርባል፡፡
\v 9 ይህ መስዋዕት የአሮንና የልጆቹ ድርሻ ይሆናል፡፡ ሙሉ ለሙሉ ለእርሱ የተለየና ለያህዌ በእሳት ከሚቀርበው መስዋዕት የተወሰደ ስለሆነ ቅዱስ በሆነው ስፍራ ይብሉት፡፡”
\s5
\v 10 እናቱ እስራኤላዊ የሆነች እና አባቱ ግብፃዊ የሆነ ልጅ በእስራኤል ህዝብ መሀል ወጣ፡፡ ይህ እስራኤላዊት ሴት ልጅ በሰፈር ውስጥ ከእስራኤላዊ ሰው ጋር ተጣላ፡፡
\v 11 የእስራኤላዊቷ ሴት ልጅ የያህዌን ስም ሰደበ እግዚአበሔርንም ረገመ፣ ስለዚህም ህዝቡ ወደ ሙሴ አመጡት፡፡ የእናቱ ስም ሰሎሚት ነበር፣ የደብራይ ልጅ ስትሆን ከዳን ወገን ነበረች፡፡
\v 12 ያህዌ ራሱ ፈቃዱን እስኪገልጽላቸው ድረስ በጥበቃ ስር አቆዩት፡፡
\s5
\v 13 ከዚያ ያህዌ ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፣
\v 14 “እግዚአብሔርን የተሳደበውን ሰው ከሰፈር አውጡት የሰሙት ሁሉ እጆቻቸውን በላዩ ይጫኑ፣ ከዚያም መላው ጉባኤ በድንጋይ ይውገረው፡፡
\s5
\v 15 ለእስራኤል ሰዎች ብለህ ግለጽላቸው፣ ‹አምላኩን የተሳደበ ማንኛውም ሰው በደሉን ይሸከም፡፡
\v 16 ተወላጅ የሆነ እስራኤላዊም ቢሆን ወይም መጻተኛ የያህዌን ስም በስድብ ያቃለለ መላው ጉባኤ በድንጋይ ይውገሩትና ይገደል፡፡ ማንም ሰው የያህዌን ስም ቢሳደብ፣ ይገደል፡፡
\s5
\v 17 ሌላ ሰው የገደለ ይገደል፡፡
\v 18 የሌላውን ሰው እንስሳ የገደለ በገደለው ፈንታ ይክፈል፣ ህይወት ስለ ህይወት ነው፡፡
\s5
\v 19 አንድ ሰው ጎረቤቱን ቢጎዳ፣ እርሱ በጎረቤቱ ላይ ያደረገው ነገር ይደረግበት፡፡
\v 20 ስብራት ስለ ስብራት፣ አይን ስለ አይን፣ ጥርስ ስለ ጥርስ፡፡ በአንድ ሰው ላይ ጉዳት እንዳደረሰ፣ በእርሱም ላይ እንደዚያው ይደረግበት፡፡
\v 21 ማንም እንስሳ የገደለ ሰው መልሶ ይክፈል ማንም ሰው የገደለ ይገደል፡፡
\s5
\v 22 ለመጻተኛውም ይሁን ለተወላጅ እስራኤላዊው አንድ አይነት ህግ ይኑራችሁ፣ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝና፡፡”
\v 23 ሙሴ ለእስራኤል ሰዎች ይህን ነገራቸው፣ ሰዎቹም ያህዌን የተሳደበውን ሰው ከሰፈር ውጭ አመጡት፡፡ በድንጋይ ወገሩት፡፡ የእስራኤል ሰዎች የያህዌን ትዕዛዝ ሙሴ ባዘዘው መሠረት ፈጸሙ፡፡
\s5
\c 25
\p
\v 1 ያህዌ በሲና ተራራ ላይ ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፣
\v 2 “ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፣ ‹እኔ ወደሰጠኋችሁ ምድር ስትገቡ፣ ምድሪቱ ለያህዌ የሰንበት ዕረፍት ታክብር፡፡
\s5
\v 3 እርሻህን ለስድስት አመታት ታርሳለህ፣ ለስድስት አመታት የወይን ተክልህን እየገረዝህ ምርቱን ትሰበስባህ፡፡
\v 4 በሰባተኛው አመት ግን፣ ለምድሪቱ የከበረ የሰንበት ረፍት ይሁንላት፣ ለያህዌ ሰንበት ነው፡፡ እርሻህን አታርስም፡፡ ወይም የወይን ተክልህን አትገርዝም፡፡
\s5
\v 5 ሳትዘራው የበቀለውን አትጨደው፣ ያልገረዝከውን የወይን ተክል ፍሬ አትለቅመውም፡፡ ይህ ለምድሪቱ የከበረ የእረፍት አመት ነው፡፡
\v 6 ያልሰራህበት ምድር በሰባተኛው ዓመት ያፈራችው ሁሉ ለአንተ ምግብ ይሆናል፡፡ አንተ፣ ወንድና ሴት ባሮችህ፣ ለቅጥረኛ አገልጋዮችህ እና ከአንተ ጋር ለሚኖሩ መጻተኞች ምግብ ይሁን፡፡
\v 7 ምድሪቱ ያፈራችውን ሁሉ የቤት እንስሳትህና የዱር እንስሳት ይመገቡት፡፡
\s5
\v 8 ሰባት የሰንበት አመታትን ቁጠር፣ ይህም ማለት፣ ሰባት ጊዜ ሰባት አመታት ነው፣ ስለዚሀ ሰባት የሰንበት አመታት ይሆናሉ፣ ድምሩ አርባ ዘጠኝ አመታት ነው፡፡
\v 9 በሰባተኛው ወር በአስረኛው ቀን ከፍ ያለ የመለከት ድምጽ በሁሉም ስፍራ ንፉ፡፡ በማስተሰርያ ቀን በምድራችሁ ላይ ሁሉ መለከት ንፉ፡፡
\s5
\v 10 አምሳኛውን አመት ለያህዌ ለዩና በምድሪቱ ላይ ለሚኖሩ ነዋሪዎች ሁሉ ነጻነትን አውጁ፡፡ ይህ ለእናንተ ንብረትና ባሮች ወደየቤተሰቦቻቸው የሚመለሱበት ኢዩቤልዩ ይሆንላችኋል፡፡
\s5
\v 11 አምሳኛው አመት ለእናንተ ኢዮቤልዮ ይሆናል፡፡ አትተክሉም ወይም አዝመራ አትሰበስቡም፡፡ ሳትዘሩ የበቀለውን ብሉ፣ ሳትገርዙት ወይናችሁ ያፈራውን ፍሬ ሰብስቡ፡፡
\v 12 ኢዮቤልዩ ነውና፣ ለእናንተ ቅዱስ ይሆናል፡፡ በሜዳ ሳትዘሩት የበቀለውን ምርት ብሉ፡፡
\s5
\v 13 በዚህ የኢዮቤልዩ አመት የእያንዳንዱን ሰው ንብረት መልሱለት፡፡
\v 14 ለጎረቤትህ ማናቸውንም መሬት ሸጠህለት ቢሆን ወይም ከጎረቤትህ ማንኛውንም መሬት ገዝተህ ቢሆን አንዱ ሌላውን አያታል ወይም እርስ በእርሱ ያልተገባ ነገር አታድርጉ።
\s5
\v 15 ከጎረቤትህ መሬት ብትገዛ፣ እስከ መጪው ኢዮቤልዩ ድረስ ያሉትን አመታት እና ሊሰበሰብ የሚችለውን ሰብል ከግምት አስገባ፡፡ መሬቱን የሚሸጠው ጎረቤትህም እነዚህን ነገሮች ከግምት ያስገባል፡፡
\v 16 እስከ መጪው ኢዮቤልዩ ለመድረስ ብዙ አመታት የሚቀር ከሆነ ይህ የመሬቱን ዋጋ ከፍ ያደርገዋል፣ እስከ መጪው ኢዮቤልዩ ለመድረስ ጥቂት አመታት የሚቀር ከሆነ ይህ የመሬቱን ዋጋ ዝቅ ያደርገዋል፣ ምክንያቱም ለአዲሱ የመሬቱ ባለቤት መሬቱ የሚሰጠው አዝመራ መጠን ለሚቀጥለው ኢዮቤልዩ ለመድረስ ከቀረው አመታት ቁጥር ጋር የተያያዘ ነው፡፡
\v 17 አንዳችሁ ሌላችሁን አታታሉ ወይም አንዳች ሌላችሁን አታሳስቱ፤ ይልቁንም አምላካችን አክብሩ፣ እኔ አምላካች ያህዌ ነኝ፡፡
\s5
\v 18 ስለዚህ ትዕዛዛቴን ጠብቁ፣ ህግጋቴን ፈጽሙ እናም አድርጓቸው፡፡ ይህን ካደረጋችሁ በምድሪቱ ላይ በሰላም ትቀመጣላችሁ፡፡
\v 19 ምድሪቱ ምርቷን ትሰጣለች፣ እናንተም ትጠግባላችሁ በዚያም በሰላም ትኖራላችሁ፡፡
\s5
\v 20 እንዲህ ልትሉ ትችላላችሁ “በሰባተኛው አመት ምን እንበላለን አንዘራም፣ ምርታችንንም አንሰበስብምና፡፡”
\v 21 በስድስተኛው አመት በረከቴ እንዲሆንላችሁ በእናንተ ላይ አዛለሁ፣ ምድሪቱ ለሶስት አመታት የሚሆን ምርት ትሰጣለች፡፡
\v 22 በስምንተኛው አመት ትተክላላችሁ፣ በቀደሙት አመታት ካመረታችሁትና ከሰበሰባችሁት ምግብ መብላት ትቀጥላላችሁ፡፡
\s5
\v 23 መሬት ለአዲስ ጊዜያዊ ባለቤቶች አይሸጥ፣ ምክንያቱም መሬቷ የእኔ ናት፡፡ እናንተ ሁላችሁም በምድሬ ላይ እንግዶችና ጊዜያዊ ነዋሪዎች ናችሁ፡፡
\v 24 የያዛችሁትን ምድር ሁሉ የመቤዠት መብት እንዳላችሁ ማስተዋል አለባችሁ፤ በገዛችሁት ቤተሰብ መሬቱ ተመልሶ እንዲገዛ መፍቀድ አለባችሁ፡፡
\v 25 እስራኤላዊ ወገናችሁ ደሃ ቢሆንና በዚህም ምክንያት ከንብረቱ ቢሸጥ፣ የቅርብ ዘመዱ ለአንተ የሸጠልህን ንብረት መልሶ ይግዛ፡፡
\s5
\v 26 ሰውዬው ንብረቱን የሚቤዥለት ምንም ዘመድ ባይኖረው፣ ነገር ግን ሀብት ቢያፈራና ንብረቱን መልሶ መቤዠት ቢችል፣
\v 27 መሬቱ ከተሸጠበት ጊዜ አንስቶ ያሉትን አመታት ያሰላና ለሸጠለት ሰው ቀሪ ሂሳቡን ይክፈል፡፡ ከዚያ ወደ ራሱ ንብረት ይመለስ፡፡
\v 28 ነገር ግን መሬቱን ለራሱ ማስመለስ ባይችል፣ የሸጠው መሬት እስከ ኢዮቤልዩ አመት ድረስ በገዛው ሰው ባለቤትነት ስር ይቆያል፡፡ በኢዮቤልዩ አመት፣ መሬቱ ለሸጠው ሰው ይመለስለታል፣ ከመሰረቱ ባለቤት የነበረው ወደ ንብረቱ ይመለሳል፡፡
\s5
\v 29 አንድ ሰው በተቀጠረ ከተማ ውስጥ የሚገኝ ቤቱን ቢሸጥ፣ በተሸጠበት በአመት ጊዜ ውስጥ መልሶ ሊገዛው ይችላል፡፡
\v 30 ለአንድ ሙሉ አመት ውስጥ ካልተቤዠ፣ በተቀጠረ ከተማ ውስጥ የሚገኘው ቤት፣ የገዛው ሰው ትውልድ የልጅ ልጅ ቋሚ ንብረት ይሆናል፡፡ ያ ቤት በኢዮቤልዩ ተመላሽ አይሆንም፡፡
\s5
\v 31 ነገር ግን በዙሪያቸው ቅጥር የሌላቸው መንደሮች ቤቶች ከአገሩ የእርሻ መሬት ጋር የሚታዩ ንብረቶች ይሆናሉ፡፡ ተመልሰው ሊዋጁ ይችላሉ፣ በኢዮቤልዩ ተመላሽ ይሆናሉ፡፡
\v 32 ሆኖም፣ የሌዋውያን ንብረት የሆኑ ቤቶች በማንኛውም ጊዜ ሊዋጁ ይችላሉ፡፡
\s5
\v 33 ከሌዋዊያን አንዱ የሸጠውን ቤት መልሶ ባይቤዥ፣ በከተማ ውስጥ የሚኘው የተሸጠው ቤት በኢዮቤልዩ ተመላሽ ይሆናል፣ በከተማ የሚገኝ የሌዋዊ ቤቶች በእስራኤል ሰዎች መሀል የእነርሱ ንብረት ነው፡፡
\v 34 በከተማዎቻቸው ዙሪያ የሚገኙ እርሻዎች ግን አይሸጡም ምክንያቱም እነዚህ የሌዋዊያን ቋሚ ንብረት ናቸው፡፡
\s5
\v 35 የአገራቸው ሰው ወገናችሁ ደሃ ቢሆን፣ ስለዚህም ራሱን መቻል ቢያቅተው፣ መጻተኛውን እንደምትረዱ እርዱት ወይም በመሀከላችሁ የሚኖርን ባዕድ እንደምትረዱ ዕርዱት፡፡
\v 36 ወለድ አታስከፍሉት ወይም በማናቸውም መንገድ ከእርሱ ትርፍ ለማግኘት አትሞክሩ፣ ነገር ግን እግዚአብሔርን አክብሩ በመሆኑም ወንድማችሁ ከእናንተ ጋር አብሮ መኖር ይችላል፡፡
\v 37 በወለድ ገንዘብ አታበድሩት፣ ወለድም አታስከፍሉት፣ ትርፍ ለማግኘት ምግባችሁን አትሽጡለት፡፡
\v 38 የከነዓንን ምድር እሰጣችሁና አምላካችሁ እሆን ዘንድ ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡
\s5
\v 39 የአገርህ ሰው ወገንህ ደሃ ቢሆንና ራሱን ለአንተ ቢሸጥ፣ እንደ ባሪያ አታሰራው፡፡
\v 40 እንደ ተቀጣሪ አገልጋይ አስተናግደው፡፡ ከአንተ ጋር በጊዜያዊነት እንደሚኖር ሰው ይሁን፡፡ እስከ ኢዮቤልዩ አመት ድረስ በአንተ ዘንድ ያገለግል፡፡
\v 41 ከዚያ ከአንተ ዘንድ ይሄዳል፣ እርሱና ከእርሱ ጋር ያሉ ልጆቹ፣ ወደ ራሱ ቤተሰቦችና ወደ አባቱ ይዞታ ይመለሳሉ፡፡
\s5
\v 42 እነርሱ ከግብፅ ምድር ያወጣኋቸው አገልጋዮቼ ናቸውና፡፤ እንደ ባሪያዎች አይሸጡም፡፡
\v 43 በጭካኔ ልትገዛቸው አይገባም፣ ነገር ግን አምላክህን አክብር፡፡
\v 44 በዙሪያህ ከሚኖሩ ህዝቦች ወንድና ሴት ባሪያዎችን ከእነርሱ መሀል መግዛት ትችላለህ፡፡
\s5
\v 45 በመሀልህ ከሚኖሩ መጻተኞችም ባሪያዎችን መግዛት ትችላለህ፣ ይህም ማለት፣ ከአንተ ጋር ካሉ ቤተሰቦቻቸው፣ በምድርህ ከተወለዱ ልጆች ባሪያዎችን መግዛት ትችላለህ፡፡ እነርሱ የአንተ ሀብት ይሆናሉ፡፡
\v 46 እንዲህ ያሉትን ባሪያዎች ንብረት አድርገው እንዳይዟቸው ከአንተ በኋላ ለልጆችህ ውርስ አድርገህ መስጠት ትችላለህ፡፡ ከእነርሱ ሁልጊዜም ባሪያዎችህን መግዛት ትችላለህ ነገር ግን ከእስራኤላዊያን መሀል በወንድሞችህ ላይ በጭካኔ መግዛት የለብህም፡፡
\s5
\v 47 መጻተኛው ወይም ከአንተ ጋር በጊዜያዊነት ከሚኖረው እንግዳ መሃል አንዱ ባለጸጋ ቢሆንና ከእስራኤላዊ ወገንህ መሃል አንዱ ደሃ ቢሆን፣ ለራሱም ለዚያ ባዕድ ቢሸጥ፣ ወይም ከባዕዳን ቤተሰብ መሃል ለአንዱ ቢሸት፣
\v 48 እስራኤላዊ ወገንህ ከተገዛ በኋላ ተመልሶ ይገዛ፡፡ ከቤተሰቡ መሃል አንዱ ይቤዠው፡፡
\s5
\v 49 የሚቤዠው አጎቱ፣ የአጎቱ ልጅ፣ ሊሆን ይችላል፣ ወይም ከቤተሰቡ ውስጥ ማንኛውም የቅርብ ዘመዱ ሊቤዠው ይችላል፡፡ ወይም፣ እርሱ ራሱ ባለፀጋ ቢሆን፣ ራሱን መቤዠት ይችላል፡፡
\v 50 ከገዛው ሰው ጋር ይደራደር፣ ለገዛው ሰው ራሱን ከሸጠበት አመት ጀምረው እስከ ኢዮቤልዩ አመት ድረስ ይቁጠሩ፡፡ የመቤዣው ዋጋ ለገዛው ሰው መስራቱን መቀጠል በሚኖርበት አመታት ቁጥር ለተቀጣሪ አገልጋይ በሚከፍለው ክፍያ ይሰላል፡፡
\s5
\v 51 እስከ ኢዮቤልዩ ለመድረስ ብዙ አመታት የሚኖር ከሆነ፣ ለቤዣው መልሶ የሚከፍለው የገንዘብ መጠን ከእነዚያ ቀሪ አመታት ጋር የተመጣጠነ ይሁን፡፡
\v 52 ለኢዮቤልዩ አመት የቀሩት አመታት ጥቂት ከሆኑ፣ ከገዛው ሰው ጋር ለኢዮቤልዩ በቀሩት አመታት ልክ ይደራደር፣ ለመቤዣው በቀሩት አመታት ውስጥ ይክፈለው፡፡
\s5
\v 53 በየዓመቱ እንደ ቅጥር ሰው ይኑር፡፡ በግፍ አለመስተናገዱን ማረጋገጥ ይገባሃል፡፡
\v 54 በእነዚህ መንገዶች ካልተዋጀ፣ እስከ ኢዮቤልዩ አመት ድረስ እርሱና ከእርሱ ጋር ልጆቹም አብረው ያገልግሉ፡፡
\v 55 እስራኤላውያን የእኔ አገልጋዮቼ ናቸው፡፡ ከግብጽ ምድር ያወጣኋቸው አገልጋዮቼ ናቸው፡፡ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡”
\s5
\c 26
\p
\v 1 “እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፤ ጣኦታትን አታብጁ፣ የተቀረጸ ምስልንም አታቁሙ፣ ወይም ለአምልኮ የድንጋይ አምዶችን አታቁሙ፣ እንደዚሁም ልትሰግዱላቸው ማናቸውንም የቀረፀ የድንጋይ ምስል በምድራችሁ አታድርጉ፡፡
\v 2 ሰንበቴን ጠብቁ የተቀደሰውን ስፍራዬን አክብሩ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡
\s5
\v 3 በህጌ ብትኖሩና ትዕዛዛቴን ብትጠብቁ ብትታዘዟቸውም፣
\v 4 ዝናብን በወቅቱ እሰጣችኋለሁ፤ ምድር ምርቷን ትሰጣችኋለች፣ የሜዳ ዛፎችም ፍሬያቸውን ይሰጧችኋል፡፡
\s5
\v 5 የወቃችሁት እስከ ወይን አዝመራችሁ ድረስ ይቆያል፣ የወይን ፍሬ አዝመራችሁም እስከምትዘሩበት ወቅት ድረስ ይቆያል፡፡ እንጀራችሁን በምድሪቱ ቤታችን በሰራችሁበት ጠግባችሁ ትበላላችሁ በእረፍት ትኖራላችሁ፡፡
\v 6 በምድሪቱ ሰላምን እሰጣለሁ፣ ምንም ነገር ሳያስፈራችሁ ተዘልላችሁ ትቀመጣላችሁ፡፡ ከምድሪቱ አደገኛ እንስሳትን አስወጣለሁ፣ በምድራች ሰይፍ አያልፍም፡፡
\s5
\v 7 ጠላቶቻችሁን ታሳድዳላችሁ፣ እነርሱም በፊታችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ፡፡
\v 8 ከእናንተ አምስታችሁ መቶውን ታሳድዳላችሁ፣ ከእናንተ መቶው አስር ሺኅ ያሳድዳል፤ ጠላቶቻች በፊታችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ፡፡
\s5
\v 9 ወደ እናንተ በሞገስ እመለከታለሁ፣ ፍሬያማም አደርጋችኋለሁ፣ አበዛችሁማለሁ፤ ከእናንተ ጋር ቃል ኪዳኔን አደርጋለሁ፡፡
\v 10 ለረጅም ጊዜ የተከማቸ እህል ትበላላችሁ፡፡ ለአዲሱ ምርታችሁ ስፍራ ስለሚያስፈልጋችሁ የተከማቸውን እህል ታወጣላችሁ፡፡
\s5
\v 11 ማደሪያዬን በመካከላችሁ አደርጋለሁ፣ እኔም እናንተን አልጣላችሁም፡፡
\v 12 በመካከላችሁ እሆናለሁ አምላካችሁም እሆናለሁ፣ እናንተም የእኔ ህዝብ ትሆናላችሁ፡፡
\v 13 ከግብጽ ምድር ያወጣኋቸው፣ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፣ ስለዚህም የእነርሱ ባሮች አትሆኑም፡፡ የቀንበራችሁን ብረት ሰብሬያሁ፣ ቀና ብላችሁ እንድትሄዱ አድርጌያለሁ፡፡
\s5
\v 14 ነገር ግን እኔን ባትሰሙኝ፣ እነዚህን ትዕዛዛቴን ሁሉ ባትጠብቁ፣
\v 15 ትዕዛዛቴን ብትተዉና ህግጋቴን ብትጠሉ፣ እናም ትዕዛዞቼን ሁሉ ሳትፈጽሙ ብትቀሩ፣ ነገር ግን ቃልኪዳኔን ብታፈርሱ
\s5
\v 16 እነዚህን ነገሮች ብታደርጉ፣ እኔም ይህን አደርግባችኋለሁ፡ ፍርሃትን እሰድባችኋለሁ፣ ዐይኖችንና ሕይወታችሁን የሚያጠፋ በሽታና ትሳት አደርስባችኋለሁ፡፡ በከንቱ ትዘራላችሁ፣ ምክንያቱም ፍሬያቸውን ጠላቶቻችሁ ይበሉታል፡፡
\v 17 ፊቴን በጠላትነት ወደ እናንተ እመልሳለሁ፣ ከጠላቶቻችሁ ሀይል በታች ትወድቃላችሁ፡፡ የሚጠሏችሁ ሰዎች ይገዙዋችኋል፣ ማንም ሳያሳድዳችሁ እንኳን ትሸሻላችሁ፡፡
\s5
\v 18 ትዕዛዛቴን ባትሰሙ፣ ከዚህ በኋላ ስለ ሀጢአታችሁ ሰባት እጥፍ እቀጣችኋለሁ፡፡
\v 19 የትእቢታችሁን ኃይል እሰብራለሁ፡፡ ሰማይን በላያችሁ እንደ ብረት ምድራችሁንም እንደ ናስ አደርጋለሁ፡፡
\v 20 ብርታታችሁ ለአንዳች ነገር አይጠቅምም፣ ምክንያቱም ምድራችሁ አዝመራዋን አትሰጥም፣ በምድራችሁ ዛፎቻችሁ ፍሬያቸውን አይሰጡም፡፡
\s5
\v 21 በእኔ ላይ ጠላት ሆናችሁ ብትመላለሱና ከኃጢአታችሁ በላይ እኔን ባትሰሙኝ፣ በእናንተ ላይ ሰባት ዕጥፍ ድንጋጤ አመጣለሁ፡፡
\v 22 ልጆቻችን የሚነጥቁ፣ ከብቶቻችሁን የሚያጠፉ፣ እናንተን በቁጥር ጥቂት የሚያደርጉ አደገኛ አውሬዎችን እሰድባችኋሉሁ፡፡ ስለዚህም ጎዳናዎቻችሁ በረሃ ይሆናሉ፡፡
\s5
\v 23 በእነዚህ ሁሉ ነገሮች ትምህርቶቼን ባትሰሙ ነገር ግን በእኔ ላይ ጠላት ሆናችሁ መመላለሳችሁን ብትቀጥሉ፣
\v 24 እኔም በእናንተ ላይ ጠላት እሆናለሁ፡፡ እኔ ራሴ በሀጢአቶቻችሁ ሰባት እጥፍ እቀጣችኋለሁ፡፡
\s5
\v 25 ቃልኪዳን በማፍረሳችሁ በእናንተ ላይ የበቀል ሰይፍ አመጣለሁ፡፡ በከተሞቻችሁ ውስጥ በአንድነት ትሰበሰባላችሁ፣ በዚያም በማህላችሁ በሽታን እልካለሁ፣ እናንተም በጠላቶቻችሁ ሀይል ትሸነፋላችሁ፡፡
\v 26 የምግብ አቅርቦታችሁን ስቆርጥ፣ አስር ሴቶች በአንድ ምድጃ እንጀራችሁን ይጋግራሉ፣ እንጀራችሁንም በሚዛን ያካፍሏችኋል፡፡ ትበላላችሁ ነገር ግን አትጠግቡም፡፡
\s5
\v 27 እነዚህ ነገሮች ሁሉ ሆነው ባትሰሙት፣ ነገር ግን በእኔ ላይ በጠላትነት መመላሳችሁን ብትቀጥሉ፣
\v 28 እኔ በቁጣ እመጣባችኋለሁ፣ በኃጢአቶቻችሁ ሰባት እጥፍ እቀጣችኋለሁ፡፡
\s5
\v 29 ወንድ ልጆቻችሁን ስጋና የሴት ልጆቻችሁን ስጋ ትበላላችሁ፡፡
\v 30 የአምልኮ ሥፍራችሁን አጠፋለሁ፣ የእጣን መሰዊያዎቻችሁን እቆርጣለሁ፣ በድኖቻችሁን በድን በሆኑ በጣኦቶቻችሁ ላይ እጥላለሁ፣ ደግሞም እኔ ራሴ እጸየፋችኋለሁ፡፡
\s5
\v 31 ከተሞቻችሁን ፍርስራሽ አደርጋለሁ የተቀደሱ ቦታዎቻችሁን አጠፋለሁ፡፡ በመስዋዕቶቻችሁ መዓዛ ደስ አልሰንም፡፡
\v 32 ምድሪቱን አጠፋለሁ፡፡ በዚያ የሚኖሩ ጠላቶቻችሁ በጥፋቱ ይደነግጣሉ፡፡
\v 33 በአገራት መሃል እበትናችኋለሁ፣ ሰይፌን መዝዤ አሳድዳችኋለሁ፡፡ ምድራችሁ ባድማ ትሆናለች፣ ከተሞቻችሁም ፍርስራሽ ይሆናሉ፡፡
\s5
\v 34 ከዚያም ምድሪቱ ባድማ ሆኖ እስከቆየች ድረስና እናንተ በጠላቶቻችሁ ምድር እስከቆያችሁ ድረስ የሰንበት ዕረፍቷን ታገኛለች፡፡ በነዚያ ጊዜያት፣ ምድሪቱ ታርፋለች ሰንበቶቿንም ታገኛለች፡፡
\v 35 ፍርስራሽ ሆና እስከቆየች ድረስስ እረፍት ይሆንላታል፣ እናንተ በውስጧ ስትኖሩ በሰንበቶቻችሁ ያላገኘችውን ዕረፍት ታገኛች፡፡
\v 36 እናንተ በጠላቶቻችሁ ምድር በቀራችሁት ላይ በልቦቻችሁ ውስጥ ፍርሃት እሰዳለሁ፣ ስለዚህም የቅጠል ኮሰሽታ እንኳን ያስደነግጣችኋል፣ ከሰይፍ እንደሚሸሽ ትሆናላች፡፡ ማንም ሳያሳድዳችሁ ትወድቃላች፡፡
\s5
\v 37 ማንም ባያሳድዳችሁም እንኳን ከሰይፍ እንደሚሸሽ ሰው አንዳችሁ በሌላችሁ ላይ ትደነቃቀፋላችሁ፡፡ በጠላቶቻችሁ ፊት ለመቆም ምንም ሀይል አይኖራችሁም፡፡
\v 38 ከአገራት መሀል ተለይታችሁ ትጠፋላችሁ፣ የጠላቶቻችሁ ምድር ራሱ በፍርሃት ይሞላችኋል፡፡
\v 39 ከእናንተ መሃል የቀሩት በዚያ በጠላቶቻችሁ ምድር በሀጢአቶቻቸው ይጠፋሉ፣ እንዲሁም በአባቶቻቸው ሀጢአቶች ምክንያት ይጠፋሉ፡፡
\s5
\v 40 ሆኖም የእነርሱንና የአባቶቻቸውን ሀጢአቶች ቢናዘዙ፣ ለእኔ ታማኝ ካልሆኑበት ክህደታቸው ቢመለሱ፣ ከእኔ ጋር ተላት ከሆኑበት አካሄዳቸው ቢመለሱ
\v 41 እኔ በእነርሱ ላይ እንድነሳ ካደረገንና ለጠላቶቸው ምድር አሳልፌ እንድሰጣቸው ካደረገ አካሄዳቸው ቢመለሱ ያልተገረዙ ልቦቻቸው ዝቅ ቢሉ፣ እናም በሀጢአቶቻቸው የደረሰባቸውን ቅጣታቸውን ቢቀበሉ፣
\v 42 ከያዕቆብ ጋር የገባሁትን ኪዳኔን አስባለሁ፤ እንዲሁም፣ ምድሪቱን አስባለሁ፡፡
\s5
\v 43 ምድሪቱ ለቀዋት ስለሄዱ ባዶ ትቀራለች፣ ስለዚህ ካለእነርሱ በተተወችበት ጊዜ በሰንበቶቿ ታርፋለች፡፡ እነርሱ በሀጢአታቸው ቅጣታቸውን ይቀበላሉ ምክንያቱም እነርሱ ራሳቸው ስርአቴን ትተዋል ህግጋቴንም ጠልተዋል፡፡
\s5
\v 44 ሆኖም ከዚህ ሁሉ ባሻገር፣ በጠላቶቸው ምድር ውስጥ ሲሆኑ፣ እኔ አልተዋቸውም ሙሉ በሙሉ እስካጠፋቸውም ድረስ አልጠላቸውም፣ ደግሞም ከእነርሱ ጋር የገባሁትን ኪዳኔን አልረሳም፣ እኔ አምላካቸው ነኝ፡፡
\v 45 ነገር ግን ስለ እነርሱ ስል አምላካቸው እሆን ዘንድ አሕዛብ እያዩ ከግብጽ ምድር ካወጣኋቸው ከአባቶቻቸው ጋር የገባሁትን ኪዳኔን አስባሁ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡”
\s5
\v 46 በሙሴ በኩል ያህዌ በሲና ተራራ ላይ በራሱና በእስራኤል ህዝብ መሃል ያደረጋቸው ትዕዛዛት፣ ደንቦችና ህጎች እነዚህ ናቸው፡፡
\s5
\c 27
\p
\v 1 ያህዌ ሙሴን ተናገረው እንዲህም አለ፣
\v 2 “ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፣ ‹አንድ ሰው ለያህዌ ሰውን ለመስጠት የተለየ ስዕለት ቢሳል ተመጣጣን ዋጋ ለመክፈል ተከታዮን ዋጋዎች ተጠቀም፡፡
\s5
\v 3 ከዚያ እስከ ስልሳ አመት ዕድሜ ላለው ወንድ መደበኛው ዋጋ በቤ መቅደሱ ሰቅል መለኪያ ሃምሳ የብር ሰቅሎች ይሁን፡፡
\v 4 ለተመሳሳይ ዕድሜ ክልል ለሴቷ መደበኛው ዋጋ ሰላሳ ሰቅሎች ይሁን፡፡
\s5
\v 5 ከአምስት አመት እስከ ሀያ አመት ዕድሜ ለወንድ መደበኛው ዋጋ ሀያ ሰቅሎች ይሁን፣ ለሴቷ አስር ሰቅሎች ነው፡፡
\v 6 ከአንድ ወር ዕድሜ እስከ አምስት አመት ለወንድ መደበኛው ዋጋ አምስት የብር ሰቅሎች ይሁን፣ ለሴት ሶስት የብር ሰቅሎች ነው፡፡
\s5
\v 7 ከስልሳ አመት በላይ ለወንድ መደበኛው ዋጋ አስራ አምስት ሰቅሎች፣ ለሴት አስር ሰቅሎች ይሁን፡፡
\v 8 ነገር ግን ስዕለቱን የገባው ሰው መደበኛውን ዋጋ መክፈል ባይችል፣ በስለት የተሰጠው ሰው ወደ ካህኑ ይቅረብ፣ ካህኑም ያንን ሰው የተሳለው ሰው ሊከፍል በሚችል ዋጋ ይተምነዋል።
\s5
\v 9 አንድ ሰው ለያህዌ እንስሳ መሰዋት ቢፈልግ፣ ያህዌ ያንን ቢቀበል፣ ከዚያ ያ እንስሳ ለእርሱ ይለያል፡፡
\v 10 ሰውዬው እንዲህ ያለውን እንስሳ መለወጥ ወይም መቀየር የለበትም፣ መልካሙን በመጥፎው ወይም መጥፎውን በመልካሙ አይቀይርም፡፡ አንዱን እንስሳ በሌላው ቢለውጥ፣ ያ እንስሳና የተለወጠው ሁለቱም ንጹህ ይሆናሉ፡፡
\s5
\v 11 ሆኖም፣ ሰውዬው ለያህዌ ሊሰጥ የተሳለው ንጹህ ካልሆነ ስለዚህ ምክንያት ያህዌ ያንን አይቀበልም፣ ከዚያ ሰውዬው እንስሳውን ወደ ካህኑ ማምጣት አለበት፡፡
\v 12 ካህኑ በገበያው የእንስሳ ዋጋ ይተምነዋል፡፡ ማናቸውም ካህኑ ለእንስሳው የሰጠው ዋጋ፣ ያ የእንስሳው ዋጋ ይሆናል፡፡
\v 13 እናም ባለቤቱ እንስሳውን ሊዋጅ ቢፈልግ፣ በሚዋጅበት ዋጋ ላይ አንድ አምስተኛውን ጨምሮ ይዋጀው፡፡
\s5
\v 14 አንድ ሰው ቤቱን ለያህዌ መቀደስ ሲፈልግ፣ ካህኑ የቤቱን ዋጋ ይተምናል፡፡ ማናቸውም ካህኑ የተመነው ዋጋ ያ የዚያ ቤት ዋጋ ነው፡፡
\v 15 ነገር ግን ባለቤቱ ቤቱን ቢለይና በኋላ ሊዋጀው ቢፈልግግ በሚዋጅበት ዋጋ ላይ አንድ አመስተና ይጨመር፣ እናም ከዚያ እንደገና የእርሱ ይሆናል፡፡
\s5
\v 16 አንድ ሰው ከመሬቱ ለያህዌ ለመለየት ቢፈልግ፣ የመሬቱ ዋጋ ግምት ለመዝራት በሚያስፈልገው ፍሬ መጠን ይተመናል፡፡ አንድ ሆሜር መስፈሪያ ገብስ ሃምሳ የብር ሰቅሎች ያወጣል፡፡
\s5
\v 17 እርሻውን በኢዮቤልዩ አመት ቢለይ፣ የተገመተው ዋጋ ይፀናል፡፡
\v 18 እርሻውን ከኢዮቤልዩ በኋላ ቢለይ ግን፣ ካህኑ የእርሻ መሬቱን ዋጋ እስከ ቀጣዩ የኢዮቤልዩ አመት ድረስ ባሉ አመታት ቁጥር ያሰላና የተገመተው ዋጋ ይቀነሳል፡፡
\s5
\v 19 እርሻውን የለየው ሰው ሊዋጀው ቢፈልግ፣ በተገመተው ዋጋ ላይ አንድ አምስተኛ ይጨምራ፣ እናም መሬቱ ተመልሶ የእርሱ ይሆናል፡፡
\v 20 እርሻውን ካልዋጀ ወይም ለሌላ ሰው ሸጦት ከሆነ፣ ከዚያ በኋላ ተመልሶ ሊዋጅ አይችልም፡፡
\v 21 ይልቁንም፣ እርሾው፣ በኢዮቤልዩ ተመልሶ ሲለቀቅ ሙሉ ለሙሉ ለያህዌ እንደተሰተ እርሻ ሁሉ ለያህዌ ቅዱስ ስጦታ ይሆናል፡፡ የካህናቱ ንብረት ይሆናል፡፡
\s5
\v 22 አንድ ሰው የገዛውን መሬት ለያዌ ቢለይ፣ ነገር ግን መሬቱ ከሰውዬው ቤተሰቦች መሬት ውስጥ ባይሆን፣
\v 23 ካህኑ የእርሻውን ዋጋ እስ ኢዮቤልዩ አመት ድረስ ባለው ጊዜ መተን ይተምናል፣ ሰውዬውም ዋጋውን በዚያ ቀን ለያህዌ ቅዱስ ስጦታ አድርጎ ይከፍላል፡፡
\s5
\v 24 በኢዮቤልዮ አመት፣ እርሻው ከገዛው ሰው ተወስዶ ወደ መሬቱ የቀድሞ ባለቤት ይመለሳል፡፡
\v 25 የሚተመኑ ዋጋዎች ሁሉ በመቅደሱ ሰቅል ዋጋ ሊተመኑ ይገባል፡፤ ሃያ ጌራ ከአንድ ሰቅል ጋር እኩል ነው፡፡
\s5
\v 26 ከእንስሳት በመጀመሪያ የሚወለደው ግን አስቀድሞም ቢሆነ የያህዌ ነው፣ ማንም ሰው ሊቀድሰው አይችልም በሬም ይሁን በግ የያህዌ ነው፣ ማንም ሰው ሊቀድሰው አይችልም በሬም ይሁን በግ የያህዌ ነው
\v 27 ንጹህ ያልሆነ እንስሳ ከሆነ፣ ባለቤቱ በተመገተው ዋጋ መልሶ ይግዛውው ደግሞም ከዋጋው በላይ አንድ አምስተኛ ይጨምርበት፡፡ እንስሳው ካልተዋጀ፣ በተተመነው ዋጋ ይሸጥ፡፡
\s5
\v 28 ሆኖም፣ አንድ ሰው ለያህዌ ከለየው ሰውም ሆነ ወይም እንስሳ፣ ወይም የቤተሰቡ ርዕስት ምንም ነገር አይሽጥ ወይም አይዋጅ ማናቸውም የተለየ ነገር ለያህዌ ቅዱስ ነው፡፡
\v 29 እንዲጠፋ ለተለየ ሰው ምንም መዋጃ አይከፈልለትም፡፡ ያ ሰው መገደል አለበት፡፡
\s5
\v 30 አስራት ሁሉ፣ በምድሪቱ ላይ የበቀለ ሰብልም ሆነ ወይም የዛፍ ፍሬ የያህዌ ነው፡፡ ለያህዌ የተቀደሰ ነው፡፡
\v 31 አንድ ሰው ከአስራቱ አንዳች ቢዋጅ፣ በዋጋው ላይ አንድ አምስተኛ ይቸምር፡፡
\s5
\v 32 ከመንጋ ወይም ከከብት አስራት ሁሉ፣ ከእረኛው በትር ስር የሚያልፍ ሁሉ፣ ከአስር አንዱ ለያህዌ ይለይ፡፡
\v 33 እረኛው የተሸለውን ወይም የከፋውን እንስሳ አይፈልግም፣ ደግሞም አንዱን በሌላው አይተካ፡፡ ቢለውጠው እኗን፣ የተለወጠውና የሚለወጠው ሁለቱም የተቀደሱ ይሆናሉ፡፡ ሊዋጅ አይችልም፡፡”
\s5
\v 34 ያህዌ በሲና ተራራ ለሙሴ የሰጣቸው ለእስራኤላውያን የተሰጡ ትእዛዛት እነዚህ ናቸው፡፡