am_ulb/01-GEN.usfm

2909 lines
301 KiB
Plaintext
Raw Permalink Blame History

This file contains ambiguous Unicode characters

This file contains Unicode characters that might be confused with other characters. If you think that this is intentional, you can safely ignore this warning. Use the Escape button to reveal them.

\id GEN
\ide UTF-8
\h ኦሪት ዘፍጥረት
\toc1 ኦሪት ዘፍጥረት
\toc2 ኦሪት ዘፍጥረት
\toc3 gen
\mt ኦሪት ዘፍጥረት
\s5
\c 1
\p
\v 1 እግዚአብሔር በመጀመሪያ ሰማይንና ምድርን ፈጠረ።
\v 2 ምድርም ቅርፅ የሌላትና ባዶ ነበረች። ጥልቅ የሆነው ስፍራዋም በጨለማ ተውጦ ነበር። የእግዚአብሔርም መንፈስ በውሃው ላይ ሰፍፎ ነበር።
\s5
\v 3 እግዚአብሔርም፦ “ብርሃን ይሁን” አለ፤ ብርሃንም ሆነ።
\v 4 እግዚአብሔርም ብርሃኑ መልካም እንደሆነ አየ፤ ብርሃንኑም ከጨለማ ለየው።
\v 5 እግዚአብሔርም ብርሃኑን ‘ቀን’ ጨለማውን ደግሞ ‘ሌሊት’ ብሎ ጠራው። ቀኑ መሸ ሌሊቱም ነጋ አንድ ቀን ሆነ።
\s5
\v 6 እግዚአብሔርም፦ “በውሆች መካከል ጠፈር ይሁን፣ ውሆችንም ይለያዩ” አለ።
\v 7 እግዚአብሔር ጠፈርን አደረገና ከጠፈር በላይና ከጠፈር በታች ያሉትን ውሆች ለየ። እንደዚያም ሆነ።
\v 8 እግዚአብሔር ጠፈሩን ‘ሰማይ’ብሎ ጠራው። ቀኑ መሸ ሌሊቱም ነጋ ሁለተኛ ቀን።
\s5
\v 9 እግዚአብሔር፦ “ከሰማይ በታች ያለው ውሃ ወደ አንድ ስፍራ ይሰብሰብ፣ ምድሩም ይገለጥ” አለ። እንደዚያም ሆነ።
\v 10 እግዚአብሔርም ምድሩን ‘የብስ’፣ ወደአንድ ስፍራ የተሰበሰበውንም ውሃ ‘ባሕር’ ብሎ ጠራው። ይህም መልካም መሆኑን ተመለከተ።
\s5
\v 11 እግዚአብሔር፦ እንደ ዓይነታቸው ዘርን የሚያፈሩ ተክሎችን፣ በውስጣቸው ዘርን ያዘሉ የፍራፍሬ ዛፎችን እንደዓይነታቸው የሚያፈሩ አዝርዕትን ታብቅል” አለ። እንደዚያም ሆነ።
\v 12 ምድር እንደአይነታቸው የሚያፈሩ አዝርዕትን አበቀለች። ይህም መልካም እንደሆነ እግዚአብሔር ተመለከተ።
\v 13 ቀኑ መሸ፣ ሌሊቱም ነጋ ሶስተኛ ቀን ሆነ።
\s5
\v 14 እግዚአብሔር፦ “ቀኑን ከሌሊቱ ይለዩ ዘንድ በሰማይ ብርሃናት ይሁኑ። እነዚህ ብርሃናት የዓመት ወቅቶችን፣ ቀናትንና ዓመታትን የሚለዩ ምልክቶች ይሁኑ።
\v 15 ለምድርም ብርሃን ይሰጡ ዘንድ በሰማይ ላይ የሚገኙ ብርሃናት ይሁኑ” አለ። እንደዚያም ሆነ።
\s5
\v 16 እግዚአብሔር ታላቁ ብርሃን በቀን፣ ታናሹ ብርሃን በሌሊት ይሠለጥኑ ዘንድ ሁለት ታላላቅ ብርሃናትን አደረገ። ከዋክብትንም ደግሞ አደረገ።
\v 17 ለምድርም ብርሃን ይሰጡ ዘንድና
\v 18 በቀንና በሌሊት ላይ እንዲሠለጥኑ እንደዚሁም ብርሃንን ከጨለማ እንዲለዩ በሰማይ አኖራቸው። እግዚአብሔር ይህ መልካም እንደሆነ ተመለከተ።
\v 19 ቀኑ መሸ፣ ሌሊቱም ነጋ አራተኛ ቀን ሆነ።
\s5
\v 20 እግዚአብሔር፦ “ውሆች በሕያዋን ፍጡራን የተሞሉ ይሁኑ፣ ወፎችም ከምድር በላይ ባለው በሰማይ ጠፈር ይብረሩ” አለ።
\v 21 እግዚአብሔር ታላላቅ የባሕር ፍጥረታትን እንደዚሁም በምድር የሚንቀሳቀሱ፣ በውሆች ውስጥ የሚርመሰመሱና በክንፎቻቸው የሚበሩ ወፎችን እንደዓይነታቸው ፈጠረ። እግዚአብሔር ይህ መልካም እንደሆነ ተመለከተ።
\s5
\v 22 እግዚአብሔርም፦ “ብዙ ተባዙ የባሕርን ውሆች ሙሉአቸው፣ ወፎችም በምድር ላይ ይብዙ” ብሎ ባረካቸው።
\v 23 ቀኑ መሸ፣ ሌሊቱም ነጋ አምስተኛ ቀን ሆነ።
\s5
\v 24 እግዚአብሔርም፦ “ምድር እንደወገናቸው ሕያው ፍጥረታትን ማለትም ከብቶችን፣ በምድር ላይ የሚሳቡትንና የምድር አራዊትን ታስገኝ” አለ። እንደዚያም ሆነ።
\v 25 እግዚአብሔር በየዓይነታቸው የምድር አራዊትን፣ በየዓይነታቸው ማናቸውንም በምድር የሚሳቡትን ፈጠረ።
\s5
\v 26 እግዚአብሔርም፦ “ሰውን በመልካችን እንደ አምሳላችን እንፍጠር፣ ሰዎችም በባሕር ዓሣዎች፣ በሰማይ በሚበሩ ወፎችና በምድር ላይ በሚሳቡ ማናቸውም ተሳቢ ፍጥረቶች ላይ ሥልጣን ይኑራቸው” አለ።
\v 27 እግዚአብሔር ሰውን በራሱ መልክ፣ በራሱም አምሳል ፈጠረው። ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።
\s5
\v 28 እግዚአብሔር ባረካቸው እንደዚህም አላቸው፦ “ብዙ ተባዙ፣ ምድርንም ሙሉአት ግዟትም። በባሕር ውስጥ ባሉት ዓሣዎች፣ በሰማይ ላይ በሚበሩት ወፎችና በምድር ላይ በሚንቀሳቀሱት ማናቸውም ሕያዋን ፍጥረቶች ሁሉ ላይ ሥልጣን ይኑራችሁ”
\v 29 እግዚአብሔርም፦ “እነሆ፣ ምግብ ይሆኑላችሁ ዘንድ በምድር ሁሉ ላይ በውስጣቸው ዘርን ያዘሉ ማናቸውንም ተክሎችና በውስጣቸው ፍሬ ያላቸውን ማናቸውንም የፍራፍሬ ዛፎች ሰጥቻችኋለሁ።
\s5
\v 30 በምድር ላይ ለሚገኙ እንስሳት ሁሉ፣ በሰማይ ለሚበሩ ወፎች ሁሉ፣ እንዲሁም በምድር ላይ ለሚሳቡ ፍጥረታት ሁሉ ማለትም የሕይወት እስትንፋስ ላለበት ማንኛውም ፍጡር ማንኛውም ለምለም ተክል ምግብ እንዲሆናቸው ሰጥቻለሁ። እንደዚሁም ሆነ።
\v 31 እግዚአብሔር የፈጠረውን ማንኛውንም ነገር ተመለከተ። እነሆ፣ እጅግ መልካም ነበረ። ቀኑ መሸ፣ ሌሊቱም ነጋ ስድስተኛ ቀን ሆነ።
\s5
\c 2
\p
\v 1 የምድር በውስጣቸው ያሉትም ሕያዋን ፍጡራን አፈጣጠር በዚህ ሁኔታ ተከናወነ።
\v 2 እግዚአብሔር ይሠራ የነበረውን ሥራ በሰባተኛው ቀን ፈጽሞ በዚሁ ቀን ከሥራው ሁሉ አረፈ።
\v 3 እግዚአብሔር የመፍጠር ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ ያረፈው በዚህ ቀን ስለሆነ ሰባተኛውን ቀን ባረከው ቀደሰውም።
\s5
\v 4 እግዚአብሔር አምላክ ሰማይንና ምድርን በፈጠረበት ወቅት የሰማይና የምድር የአፈጣጠራቸው ታሪክ እንደዚህ ነበር።
\v 5 እግዚአብሔር አምላክ በምድር ላይ ዝናብ እንዲዘንብ ስላደረገና ምድርንም የሚያለማ ሰው ባለመኖሩ በምድር ላይ ምንም ቡቃያ አልነበረም፣ በምድር ላይ የሚበቅል ተክልም ገና አልበቀለም።
\v 6 ነገር ግን ውሃ ከመሬት እየመነጨ የምድርን ገጽ ያረሰርስ ነበር።
\s5
\v 7 እግዚአብሔር አምላክም ከምድር አፈር ሰውን አበጀው፤ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስ እፍ አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።
\v 8 እግዚአብሔር አምላክም በስተምሥራቅ በኩል በዔደን የአትክልት ስፍራ አዘጋጀ፣ የአበጀውንም ሰው በዚያ አኖረው።
\s5
\v 9 ከምድር ውስጥም እግዚአብሔር አምላክ ለዓይን የሚያስደስቱና ለምግብነት የሚጠቅሙ ልዩ ልዩ ዛፎች እንዲበቅሉ አደረገ። በአትክልት ስፍራው መካከልም የሕይወት ዛፍ ነበር፣ መልካሙንና ክፉውን የሚያሳውቀውም ዛፍ በዚያ ነበር።
\v 10 የአትክልት ስፍራውንም የሚያጠጣ ወንዝ ከኤደን ይፈስ ነበር። ወንዙም ከኤደን ከወጣ በኋላ አራት ወንዞች ሆኖ ይከፋፈል ነበር።
\s5
\v 11 የመጀመሪያው ፊሶን የተባለው ወንዝ ነበር፣ ይህም ወርቅ ይገኝበት የነበረውን መላውን የሐዊላ ምድር አቋርጦ የሚፈስው ወንዝ ነበር።
\v 12 የዚያ አገር ወርቅ የጠራ ወርቅ ነበር፤ በተጨማሪም በዚያ አገር ሽቶና የከበሩ ድንጋዮች ነበሩ።
\s5
\v 13 የሁለተኛው ወንዝ ስም ግዮን ይባል ነበር፣ እርሱም መላውን የኢትዮጵያ ምድር አቋርጦ ይፈስ ነበር።
\v 14 የሶስተኛው ወንዝ ስም ጤግሮስ ይባል ነበር፣ እርሱም በአሦር በስተምሥራቅ ይፈሳል። አራተኛው ወንዝ ኤፍራጥስ ነበር።
\s5
\v 15 እግዚአብሔር አምላክም የኤደንን የአትክልት ስፍራ ያለማና ይንከባከብ ዘንድ ሰውን ወስዶ በዚያ አኖረው።
\v 16 እግዚአብሔር አምላክም እንዲህ በማለት አዘዘው፣ “በአትክልቱ ስፍራ ካለው ከማንኛውም የፍሬ ዛፍ መብላት ትችላልህ።
\v 17 ነገር ግን መልካሙንና ክፉውን ከሚያሳውቀው ዛፍ አትብላ፣ ምክንያቱም ከእርሱ በበላህ ቀን በእርግጥ ትሞታለህ።”
\s5
\v 18 ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ፦ “ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም። ስለዚህ የምትመቸውን ረዳት እፈጥርለታለሁ” አለ።
\v 19 እግዚአብሔር አምላክም ከምድር አፈር የምድር እንስሶችንና የሰማይ ወፎችን አበጀ። ምን ስም እንደሚያወጣላቸው ይመለከት ዘንድ ወደ አዳም አመጣቸው። ለእያንዳንዱ ሕያው ፍጡር አዳም ያወጣለት ስም ያ ስሙ ሆነ።
\v 20 አዳም ለሁሉም ከብቶች፣ ለሁሉም የሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት ሁሉ ስም አወጣላቸው። ነገር ግን ለአዳም ለራሱ የምትመች ረዳት አልተገኘለትም።
\s5
\v 21 እግዚአብሔር አምላክ በአዳም ላይ ከባድ እንቅልፍ እንዲወስደው አደረገ፣ ስለሆነም አዳም አንቀላፋ። እግዚአብሔር አምላክ አዳም አንቀላፍቶ ሳለ ከጎድን አጥንቶቹ አንዱን ወስዶ አጥንቱን የወሰደበትን ስፍራ በሥጋ ዘጋው።
\v 22 እግዚአብሔር አምላክ ከአዳም ከወሰደው የጎድን አጥንት ሴት አድርጎ ሠራት። ወደ አዳምም አመጣት።
\v 23 አዳምም፦ “አሁን ይህቺ ከአጥንቴ የተገኘች አጥንት ከሥጋዬ የተገኘች ሥጋ ናት። ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል” አለ።
\s5
\v 24 ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይጣመራል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።
\v 25 አዳምና ሚስቱ ሁለቱም ራቁታቸውን ነበሩ፤ ይሁን እንጂ አይተፋፈሩም ነበር።
\s5
\c 3
\p
\v 1 እግዚአብሔር በምድር ላይ ከፈጠራቸው ማናቸውም ሌሎች አራዊቶች ሁሉ ይልቅ እባብ ተንኮለኛ ነበር። እርሱም ሴቲቱን፦ “በእርግጥ እግዚአብሔር ‘በአትክልቱ ስፍራ ካለው ከማንኛውም ዛፍ አትብሉ’ ብሎአልን?” ብሎ ጠየቃት።
\v 2 ሴቲቱም ለእባቡ፦ “በአትክልቱ ስፍራ ካሉት የዛፎች ፍሬዎች መብላት እንችላለን፤
\v 3 ነገር ግን በአትክልቱ ስፍራ መካከል ስለሚገኘው ዛፍ እግዚአብሔር “እንዳትሞቱ ከእርሱ አትብሉ አትንኩትም” ብሎአል።
\s5
\v 4 እባብም ለሴቲቱ፦ “በፍጹም አትሞቱም።
\v 5 ከእርሱ በበላችሁ ቀን ዓይኖቻችሁ እንደሚከፈቱ እንደ እግዚአብሔርም መልካሙንና ክፉውን የምታውቁ እንደምትሆኑ እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ነው አላት።”
\v 6 ሴቲቱም ዛፉ ለመብላት መልካም፣ ሲያዩት ደስ የሚያሰኝና ጥበብንም ለማግኘት የሚያጓጓ እንደሆነ ተመልክታ ከፍሬው ወስዳ በላች፤ ከእርሷ ጋር ለነበረውም ለባሏ ከፍሬው ሰጠችው፣ እርሱም በላ።
\s5
\v 7 የሁለቱም ዓይኖች ተከፈቱ፣ ራቁታቸውን እንደነበሩም አወቁ። የበለስ ቅጠሎችንም በማጋጠም ከሰፉ በኋላ ለራሳቸው መሸፈኛ ግልድም ሠሩ።
\v 8 ቀኑ ወደ ምሽት ሲቃረብ በአትክልት ስፍራው ሲመላለስ የእግዚአብሔር አምላክን ድምፅ ሰሙ፤ ስለዚህ አዳምና ሚስቱ ከእግዚአብሔር አምላክ ፊት በመሸሽ በአትክልቱ ስፍራ በነበሩት ዛፎች መካከል ተሸሸጉ።
\s5
\v 9 እግዚአብሔር አምላክ አዳምን ጠራውና፣ “የት ነህ?” አለው።
\v 10 አዳምም፣ “በአትክልቱ ስፍራ ውስጥ ድምፅህን ሰማሁና ራቁቴን ስለነበርሁ ፈራሁ፤ በዚህም ምክንያት ተሸሸግሁ።”
\v 11 እግዚአብሔርም፦ “ራቁትህን እንደሆንክ ማን ነገረህ? ከእርሱ እንዳትበላ ብዬ ካዘዝኩህ ከዛፉ ፍሬ በላህን?” አለው።
\s5
\v 12 አዳምም፦ “አብራኝ እንድትሆን የሰጠኸኝ ሴት ከዛፉ ፍሬ ሰጠችኝ፣ እኔም በላሁት” አለ።
\v 13 እግዚአብሔር አምላክም ሴቲቱን፦ “ምንድነው ያደረግሽው?” አላት። ሴቲቱም፦ “እባቡ አታለለኝና በላሁ” አለች።
\s5
\v 14 እግዚአብሔር አምላክም ለእባቡ፦ “ይህንን በማድረግህ ከእንስሳት ሁሉና ከምድር አራዊት ሁሉ ተለይተህ የተረገምህ ትሆናለህ። በደረትህ እየተሳብክ ትሄዳለህ፣ በሕይወት ዘመንህም ሁሉ አፈር ትበላለህ።
\v 15 በአንተና በሴቲቱ፣ በዘርህና በዘሯ መካካል ጠላትነትን አደርጋለሁ። የእርሷ ዘር ራስህን ይቀጠቅጣል፣ አንተም ተረከዙን ትነክሳለህ” አለው።
\s5
\v 16 ለሴቲቱም እንዲህ አላት፦ “በምጥ ጊዜ ጭንቅሽን አበዛለሁ፤ በስቃይም ትወልጃለሽ። ፈቃድሽ ወደ ባልሽ ይሆናል፣ እርሱም ገዢሽ ይሆናል።”
\s5
\v 17 ለአዳምም እንደዚህ አለው፦ “የሚስትህን ቃል ሰምተህ ‘ከእርሱ እንዳትበላ’ ብዬ ካዘዝሁህ ከዛፉ ፍሬ ስለበላህ ከአንተ የተነሳ ምድር የተረገመች ትሁን፤ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ በከባድ ድካም ምግብህን ከእርሷ ታገኛለህ።
\v 18 ምድር እሾህና አሜኬላ ታበቅልብሃለች፤ የምድርንም ቡቃያ ትበላለህ።
\v 19 ከተገኘህበት አፈር እስክትመለስ ድረስ በላብህ እንጀራን ትበላለህ። አፈር ነህና ወደ አፈር ተመልሰህ ትሄዳለህ”።
\s5
\v 20 የሕያዋን ሁሉ እናት በመሆኗ አዳም ለሚስቱ ‘ሔዋን’ የሚል ስም አወጣላት።
\v 21 እግዚአብሔር አምላክ ከቆዳ ልብስ አዘጋጅቶ አዳምንና ሚስቱን አለበሳቸው።
\s5
\v 22 እግዚአብሔር አምላክ፦ “መልካምንና ክፉውን ለይቶ በማውቅ ረገድ አሁን ሰው ከእኛ እንደ አንዱ ሆኖአል። ስለዚህ አሁን እጁን ዘርግቶ ከሕይወት ዛፍ ፍሬ ቀጥፎ እንዳይበላ ለዘላለምም እንዳይኖር ሊፈቀድለት አይገባም” አለ።
\v 23 በዚህም ምክንያት የተገኘባትን ምድር እንዲያለማ እግዚአብሔር አዳምን ከኤደን የአትክልት ስፍራ አስወጣው።
\v 24 ስለዚህ እግዚአብሔር አዳምን ከአትክልት ስፍራው አባረረው፣ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውንም መንገድ ይጠብቁ ዘንድ ከኤደን የአትክልት ስፍራ በስተቀኝ በኩል ኪሩቤልን እንደዚሁም በየአቅጣጫው የምትገለባበጥ ነበልባላዊ ሰይፍ አኖረ።
\s5
\c 4
\p
\v 1 አዳምም ከሚስቱ ከሔዋን ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት ፈጸመ። እርሷም ፀነሰች። ቃየንንም ወለደች። “በእግዚአብሔር ዕርዳታ ወንድ ልጅ ወለድሁ” አለች።
\v 2 ከዚያ በኋላም ወንድሙን አቤልን ወለደች። አቤል የበግ እረኛ ሲሆን ቃየን ግን ገበሬ ሆነ።
\s5
\v 3 ከዕለታት አንድ ቀን ቃየን ከምድር ፍሬ ለእግዚአብሔር መባ አቀረበ።
\v 4 አቤል ደግሞ መጀመሪያ ከተወለዱ በጎች መካከል ስባቸውን መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ። እግዚአብሔር በአቤልና በመሥዋዕቱ ደስ ተሰኘ፣
\v 5 በቃየንና በመሥዋዕቱ ግን ደስ አልተሰኘም። ስለዚህ ቃየን በጣም ተቆጣ፣ ፊቱም ተኮሳተረ።
\s5
\v 6 እግዚአብሔር አምላክ ቃየንን፦ “ለምን ተቆጣህ፣ ፊትህስ ለምን ተኮሳተረ?
\v 7 መልካም ብታደርግ ፊትህ ያበራ አልነበረምን? ያደረግኸው መልካም ካልሆን ግን ኃጢአት በደጅህ እያደባች ናት፣ ልትቆጣጠርህም ትፈልጋለች፣ አንተ ግን በቁጥጥርህ ሥር አድርጋት” አለው።
\s5
\v 8 ቃየን ወንድሙን አቤልን፦ “ወደ ሜዳ እንውጣ” አለው፣ በዚያም ቃየን በወንድሙ በአቤል ላይ በቁጣ ተነሳበት፣ ገደለውም።
\v 9 ከዚያ በኋላም እግዚአብሔር ቃየንን፦ “ወንድምህ አቤል ወዴት ነው?” አለው። እርሱም፦ “አላውቅም፣ እኔ የወንድሜ ጠባቂ ነኝን?” አለ።
\s5
\v 10 እግዚአብሔርም፦ “ያደረግኸው ምንድን ነው? የወንድምህ ደም ከምድር ወደ እኔ ይጮኻል” አለው።
\v 11 “አሁንም የወንድምህን ደም ከእጅህ ለመቀበል አፍዋን በከፈተች በምድር ላይ አንተ የተረገምህ ነህ።
\v 12 ምድርንም በምታርስበት ጊዜ ፍሬዋን በሙላት አትሰጥህም። በምድር ላይ ኮብላይና ተንከራታች ትሆናለህ” አለው።
\s5
\v 13 ቃየንም ለእግዚአብሔር፦ ቅጣቴ ከምችለው በላይ ነው።
\v 14 በእርግጥም ዛሬ ከምድሪቱ አባርረኸኛል፣ እኔም ከፊትህ እሸሸጋለሁ። በምድር ላይ ኮብላይና ተንከራታች እሆናለሁ፣ የሚያገኘኝም ሁሉ ይገድለኛል” አለው።
\v 15 እግዚአብሔርም፦ “ቃየንን የሚገድል ማንኛውም ሰው ሰባት እጥፍ የበቀል እርምጃ ይወሰድበታል” አለ። ከዚያ በኋላም የሚያገኘው ማንኛውም ሰው እንዳይገድለው እግዚአብሔር በቃየን ላይ ምልክት አደረገበት።
\s5
\v 16 ቃየንም ከእግዚአብሔር ፊት ወጥቶ ሄደ፣ ከኤደን በስተምሥራቅ በነበረው ኖድ በተባለው ምድር ኖረ።
\v 17 ቃየንም ከሚስቱ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት ፈጸመ፣ እርሷም ፀነሰች፣ ሄኖክንም ወለደች። ቃየን ከተማን መሠረተ፣ የመሠረታትንም ከተማ በልጁ ስም ሄኖክ ብሎ ጠራት።
\s5
\v 18 ሄኖክም አራድን ወለደ። አራድም መሑያኤልን ወለደ። መሑያኤልም መቱሳኤልን ወለደ። መቱሳኤልም ላሜክን ወለደ።
\v 19 ላሜክም ዓዳና ጺላ የተባሉ ሁለት ሚስቶችን አገባ።
\s5
\v 20 ዓዳ ያባልን ወለደች፣ እርሱም በድንኳን ለሚኖሩ ለከብት አርቢዎች አባት ነበር።
\v 21 የእርሱ ወንድም ዩባልም የበገና ደርዳሪዎችና የዋሽንት ነፊዎች አባት ነበር።
\v 22 ጺላም ከነሐስና ከብረት መሣሪያዎችን የሚሠራውን ቱባልቃይንን ወለደች። የቱባልቃይንም እህት ናዕማ ትባል ነበር።
\s5
\v 23 ላሜክ ለሚስቶቹ፦ “አዳና ጺላ ስሙኝ፣ እናንተ የላሜክ ሚስቶች የምላችሁን ስሙኝ ስለጎዳኝና ስላቆሰለኝ አንድ ሰው ገድያለሁ።
\v 24 ቃየንን የሚገድል ሰባት እጥፍ የበቀል እርምጃ የሚወሰድበት ከሆነ የላሜክ ገዳይማ ሰባ ሰባት እጥፍ የበቀል እርምጃ ይወሰድበታል” አላቸው።
\s5
\v 25 አዳም ከሚስቱ ጋር እንደገና የግብረ ሥጋ ግንኙነት ፈጸመ፣ እርሷም ወንድ ልጅ ወለደች። “ቃየን በገደለው በአቤል ፈንታ እግዚአብሔር ምትክ ሰጠኝ” በማለት ስሙን ሤት ብላ ጠራችው።
\v 26 ለሤትም ወንድ ልጅ ተወለደለት፣ ስሙንም ሄኖስ አለው። በዚያም ዘመን ሰዎች የእግዚአብሔርን ስም መጥራት ጀመሩ።
\s5
\c 5
\p
\v 1 የአዳም የትውልድ ሐረግ እንደሚከተለው ነው። እግዚአብሔር ሰውን በፈጠረው ጊዜ በራሱ አምሳያ ፈጠራቸው፤
\v 2 ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፣ ባረካቸውም። በተፈጠሩም ጊዜ ‘ሰው’ ብሎ ጠራቸው።
\s5
\v 3 አዳም ዕድሜው 130 ዓመት በሆነ ጊዜ፣ እርሱን የሚመስል ወንድ ልጅ ወለደ፣ ስሙንም ‘ሤት’ ብሎ ጠራው።
\v 4 አዳም ሤትን ከወለደ በኋላ 800 ዓመታት ኖረ። ሌሎችን ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ፤
\v 5 930 ዓመት ሲሆነውም ሞተ።
\s5
\v 6 ሤት ዕድሜው 105 ሲሆን ሄኖስን ወለደ።
\v 7 ሄኖስን ከወለደ በኋላ ሤት 807 ዓመት ኖረ። ሌሎች ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ።
\v 8 ሤት 912 ዓመታት ከኖረ በኋላ ሞተ።
\s5
\v 9 ሄኖስ 90 ዓመት ሲሆነው ቃይናንን ወለደ።
\v 10 ሄኖስ ቃይናንን ከወለደ በኋላ 815 ዓመታት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ።
\v 11 ሄኖስ 905 ዓመታት ከኖረ በኋላ ሞተ።
\s5
\v 12 ቃይናን 70 ዓመት ሲሆነው መላልኤልን ወለደ።
\v 13 ቃይናን መላልኤልን ከወለደ በኋላ 840 ዓመታት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ።
\v 14 ቃይናን 910 ዓመታት ከኖረ በኋላ ሞተ።
\s5
\v 15 መላልኤል 65 ዓመት ሲሆነው ያሬድን ወለደ።
\v 16 መላልኤል ያሬድን ከወለደ በኋላ 800 ዓመታት ኖረ። ሌሎች ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ።
\v 17 መላልኤል 895 ዓመታት ከኖረ በኋላ ሞተ።
\s5
\v 18 ያሬድ 162 ዓመት ሲሆነው ሄሮክን ወለደ።
\v 19 ያሬድ ሄኖክን ከወለደ በኋላ 800 ዓመታት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ።
\v 20 ያሬድ 962 ዓመታት ከኖረ በኋላ ሞተ።
\s5
\v 21 ሄኖክ 65 ዓመት ሲሆነው ማቱሳላን ወለደ።
\v 22 ሄኖክ ማቱሳላን ከወለደ በኋላ የእግዚአብሔርን መንገድ በመከተል 300 ዓመታት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ።
\v 23 ሄኖክ 365 ዓመታት ኖረ።
\v 24 ሄኖክ የእግዚአብሔርን መንገድ በመከተል ኖረ፣ ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር ስለወሰደው አልተገኘም።
\s5
\v 25 ማቱሳላ 187 ዓመት ሲሆነው ላሜሕን ወለደ።
\v 26 ማቱሳላ ላሜሕን ከወለደ በኋላ 782 ዓመታት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ።
\v 27 ማቱሳላ 969 ዓመታት ከኖረ በኋላ ሞተ።
\s5
\v 28 ላሜሕ 182 ዓመት ሲሆነው አንድ ወንድ ልጅ ወለደ።
\v 29 “ይህ ልጅ እግዚአብሔር በረገማት ምድር ከልፋታችንና ከብርቱ ሥራችን ያሳርፈናል” ሲል ስሙን ‘ኖህ’ ብሎ ጠራው።
\s5
\v 30 ላሜሕ ኖህን ከወለደ በኋላ 595 ዓመታት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ።
\v 31 ላሜሕ 777 ዓመታት ከኖረ በኋላ ሞተ።
\s5
\v 32 ኖህ 500 ዓመታት ሲሆነው ሴም፣ ካምንና ያፌትን ወለደ።
\s5
\c 6
\p
\v 1 የሰው ልጆች በምድር ላይ እየበዙ ሲሄዱ ሴቶች ልጆች ተወለዱላቸው።
\v 2 የእግዚአብሔር ልጆችም የሰዎች ሴቶች ልጆች የሚስብ ውበት እንዳላቸው ተመለከቱ። ከእነርሱ መካከልም የመረጧቸውን ሚስቶች አድርገው ወሰዱ።
\v 3 እግዚአብሔርም፦ “እርሱ ሥጋ ስለሆነ መንፈሴ በሰው ላይ ለዘላለም አይኖርም፤ ዕድሜውም 120 ዓመት ይሆናል” አለ።
\s5
\v 4 የእግዚአብሔር ልጆች ከሰዎች ሴቶች ልጆች ጋብቻ በፈጸሙና ልጆችን በወለዱበት በዚያን ጊዜ ከዚያም በኋላ ኔፊሊም የተባሉ ግዙፍ ሰዎች በምድር ላይ ነበሩ። እነርሱም በጥንት ዘመን ዝናን ያተረፉ ኅያላን ነበሩ።
\s5
\v 5 እግዚአብሔር የሰው ልጆች ክፋት በምድር ላይ እየበዛ እንደሆነና የልቡም ሃሳብ ዘወትር ወደ ክፋት ብቻ ያዘነበለ መሆኑን ተመለከተ።
\v 6 እግዚአብሔር የሰው ልጆችን በምድር ላይ በመፍጠሩ ተጸጸተ ልቡም አዘነ።
\s5
\v 7 በዚህም ምክንያት እግዚአብሔር፦ “የፈጠርሁትን የሰው ልጅ ከምድር ገጽ አጠፋለሁ፤ ስለፈጠርኋቸው ተጸጽቻለሁና ከእነርሱም ጋር እንስሳትን፣ በደረታቸው የሚሳቡትን ፍጥረታትና የሰማይ ወፎችን ሁሉ አጠፋለሁ” አለ።
\v 8 ኖኅ ግን በእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስ አገኘ።
\s5
\v 9 የኖኅ ታሪክ እንደሚከተለው ነው። ኖኅ በዘመኑ ከነበሩት ሰዎች ሁሉ ይልቅ ጻድቅና ከበደል የራቀ ሰው ነበር፤ የእግዚአብሔርንም መንገድ የሚከተል ሰው ነበር።
\v 10 ኖኅ ሴም፣ ካምና ያፌት የተባሉትን ሶስት ወንዶች ልጆች ወለደ።
\s5
\v 11 በእግዚአብሔር ፊት በክፉ ሥራ ረከሰች በዓመፅም ተሞላች።
\v 12 እግዚአብሔር ምድርን ተመለከተ፣ የተበላሸች እንደሆነችና በምድር የሚኖሩትም ሰዎች ሁሉ በክፋት እንደሚኖሩ አየ።
\s5
\v 13 እግዚአብሔርም ኖኅን፦ “ሥጋን የለበሰ ሁሉ ፍጻሜ ደርሶአል፣ ከእነርሱ የተነሳ ምድር በግፍ ተሞልታለችና። እኔም በእርግጥ ከምድር ጋር አጠፋቸዋለሁ።
\v 14 አንተ ግን ከጥሩ እንጨት መርከብ ሥራ፤ መርከቧም ክፍሎች እንዲኖራት አድርግ፤ ውስጧንና ውጭዋንም በቅጥራን ለቅልቀው።
\v 15 እንደዚህ አድርገህ ሥራት፦ ርዝመቷ 140 ሜትር፣ ወርዷ 23 ሜትር፣ ከፍታዋ 13. 5 ሜትር ይሁን።
\s5
\v 16 ለመርከቧ ጣራ አብጅላት፣ ጣራና ግድግዳው በሚጋጠምበት ቦታ ግማሽ ሜትር ክፍተት ተው፤ ከጎኗ በር አውጣላት፤ ባለ ሦስት ፎቅ አድርገህ ሥራት።
\v 17 እኔም ከሰማይ በታች የሕይወት እስትንፋስ ያለባችውን ፍጡራን ሁሉ ለማጥፋት እነሆ በምድር ላይ የጥፋት ውሃ አወርዳለሁ፤ በምድር ላይ ያለ ሁሉ ይጠፋል።
\s5
\v 18 ከአንተ ጋር ግን ቃል ኪዳን እገባለሁ፤ አንተና ሚስትህ፣ ልጆችህና የልጆችህ ሚስቶች ከአንተ ጋር ወደ መርከቧ ትገባላችሁ።
\v 19 ከአንተ ጋር በሕይወት እንዲቆዩ ከሕያዋን ፍጡራን ሁሉ ወንድና ሴት እያደረግህ ሁለት ሁለቱን ወደ መርከቧ ታስገባለህ።
\s5
\v 20 ከእያንዳንዱ የወፍ ወገን፣ ከእያንዳንዱ የእንስሳ ወገን፣ በምድር ላይ ከሚሳቡ ፍጥረት ሁሉ በየወገናቸው በሕይወት ይቆዩ ዘንድ ወደ አንተ ይምጡ።
\v 21 ለአንተና ለእነዚህ ፍጥረቶች ሁሉ የሚበቃ ልዩ ልዩ ዓይነት ምግብ በመርከቡ ውስጥ አከማች።”
\v 22 ኖኅም እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ አደረገ።
\s5
\c 7
\p
\v 1 እግዚአብሔር ኖኅን እንዲህ አለው፦ “በዚህ ትውልድ መካከል አንተን ጻድቅ ሆነህ አግኝቼሃለሁና ቤተሰብህን በሙሉ ይዘህ ወደ መርከቧ ግባ።
\v 2 ከንፁህ እንስሳት ሁሉ ሰባት ሰባት ወንድና ሴት፣ ንፁሕ ካልሆኑት እንስሳት ደግሞ ሁለት ሁለት ወንድና ሴት ከአንተ ጋር አስገባ።
\v 3 እንዲሁም ከሰማይ ወፎች ወገን ሰባት ወንዶችና ሰባት ሴቶች በምድር ላይ ለዘር እንዲተርፉ ከአንተ ጋር ታስገባለህ።
\s5
\v 4 ከሰባት ቀን በኋላ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በመድር ላይ ዝናብ አዘንባለሁ፤ የፈጠርሁትንም ሕያው ፍጡር ሁሉ ከምድር ላይ አጠፋለሁ።”
\v 5 ኖኅም እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ አደረገ።
\s5
\v 6 የጥፋት ውሃ በምድር ላይ በወረደ ጊዜ ኖኅ የ600 ዓመት ሰው ነበር።
\v 7 ኖኅና ወንዶች ልጆቹ ሚስቱና የልጆቹ ሚስቶች ከጥፋት ውሃ ለማምለጥ ወደ መርከቡ ገቡ።
\s5
\v 8 ንፁሕ ከሆኑትና ንፁሕ ካልሆኑት እንስሳት ከወፎችና በምድር ላይ ከሚሳቡ ፍጡራን ሁሉ
\v 9 ጥንድ ጥንድ ወንድና ሴት ሆነው ወደ ኖኅ መጡ፤ እግዚአብሄር ኖኅን ባዘዘው መሠረትም ወደ መርከቧ ገቡ።
\v 10 ከሰባት ቀንም በኋላ የጠፋት ውሃ በምድር ላይ መጣ።
\s5
\v 11 ኖኅ በተወለደ በ600ኛው ዓመት በሁለተኛው ወር ከወሩም በአሥራ ሰባተኛው ቀን የታላቁ ጥልቅ ምንጮች በሙሉ ተነደሉ፤ የሰማይ መስኮቶችም ተከፈቱ።
\v 12 ዝናቡም መዝነብ ጀመረ፣ አርባ ቀንና አርባ ሌሊትም ባለማቋረጥ በምድር ላይ ዘነበ።
\s5
\v 13 ዝናቡ መዝነብ በጀመረበት ቀን ኖኅና ሚስቱ ከልጆቻቸው ጋር ከሴም ከካም ከያፌትና ከሶስቱም ልጆቻቸው ሚስቶች ጋር ወደ መርከቡ ገቡ።
\v 14 ከአራዊት ከእንስሳት በደረታቸው እየተሳቡ ከሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶችና በሰማይ ከሚበሩ ወፎች ከእያንዳንዱ ዓይነት አብረዋቸው ገቡ።
\s5
\v 15 የሕይወት እስትንፋስ ያለባቸው ፍጡራን በሙሉ ጥንድ ጥንድ እየሆኑ ከኖኅ ጋር ወደ መርከቡ ገቡ።
\v 16 ከሕያዋንም ፍጡራን ሁሉ እግዚአብሔር ኖኅን ባዘዘው መሠረት ወንድና ሴት እየሆኑ ገቡ፤ ከዚያም እግዚአብሔር የመርከቡን በር ከውጭ ዘጋ።
\s5
\v 17 የጥፋት ውሃም ለአርባ ቀናት ያለመቋረጥ በምድር ላይ ዘነበ ውሃው እየጨመረ በሄድ መጠን መርከቧን ከምድር ወደ ላይ አነሳት።
\v 18 ውሃው በምድር ላይ በጣም እየጨመረና ከፍ እያለ ሲሄድ፣ መርከቧ በውሃ ላይ ተንሳፈፈች።
\s5
\v 19 ውሃው በጣም ከፍ በማለቱ፣ ከሰማይ በታች ያሉትን ታላላቅ ተራሮች ሁሉ ሸፈናቸው።
\v 20 ውሃው ከተራሮች ጫፍ በላይ 7ሜትር ያህል ከፍ አለ።
\s5
\v 21 በምድር ላይ የነበሩ ሕያዋን ፍጡራን ሁሉ፦ ወፎች፣ የቤት እንስሳት፣ አራዊት፣ በምድር የሚርመሰመሱ ፍጡራን ሰዎችም በሙሉ ጠፉ።
\v 22 የሕይወት እስትንፋስ ያላቸው በምድር የነበሩ ፍጡራን ሁሉ ሞቱ።
\s5
\v 23 ሕይወት ያላቸው ፍጡራን ሁሉ ከሰዎች ጀምሮ እንስሳት፣ በምድር ላይ የሚሳቡ ፍጡራንና የሰማይ ወፎች ሁሉም ከምድር ገጽ ጠፉ። ኖኅና ከእርሱ ጋር በመርከቧ ውስጥ የነበሩት ብቻ ተረፉ።
\v 24 ውሃውም ምድርን ሸፍኖ መቶ አምሳ ቀን ቆየ።
\s5
\c 8
\p
\v 1 እግዚአብሔር ኖኅንና ከእርሱ ጋር በመርከቧ ውስጥ የነበሩትን አራዊትና እንስሳት ሁሉ አሰበ። በምድር ላይ ነፋስ እንዲነፍስ አደረገ ውሃውም ጎደለ።
\v 2 የጥልቁ ምንጮችና የሰማይ መስኮቶች ተዘጉ፣ ዝናቡም መዝነቡን አቆመ።
\v 3 ውሃው ከምድር ላይ ቀስ በቀስ እየቀነሰ መጣ፤ ከመቶ ሃምሳ ቀን በኋላም የውሃው ከፍታ እጅግ ቀነሰ።
\s5
\v 4 በሰባተኛው ወር፤ በአሥራ ሰባተኛው ቀን መርከቧ በአራራት ተራሮች ላይ አረፈች።
\v 5 ውሃው እስከ አሥረኛው ወር ድረስ ቀስ በቀስ እየጎደለ ሄደ። በአሥረኛው ወር መጀመሪያው ቀን የተራሮች ጫፎች ታዩ።
\s5
\v 6 ከአርባ ቀን በኋላ ኖኅ የሠራውን የመርከቧን መስኮት ከፍቶ፣
\v 7 ቁራን ወደ ውጭ ላከ፤ ቁራውም ውሃው ከምድር ላይ እስኪደርቅ ድረስ ወዲያና ወዲህ ይበር ነበር።
\s5
\v 8 ከዚያም በኋላ ኖኅ ውሃው ከምድር ላይ ገጽ ጎድሎ እንደሆነ ለማወቅ ርግብን ላከ፤
\v 9 ነገር ግን ውሃው ገና ምድርን ሁሉ ሸፍኖ ስለነበር ርግቢቱ የምታርፍበት ቦታ አላገኘችም፤ ስለዚህ ኖኅ ወዳለበት መርከብ ተመልሳ መጣች፤ ኖኅም እጁን ዘርግቶ ወደ መርከቡ ውስጥ አስገባት።
\s5
\v 10 ሰባት ቀን ከቆየ በኋላ ኖኅ ርግቧን እንደገና ላካት።
\v 11 እርሷም ወደ ማታ ተመለሰች፤ እነሆም የለመለመ የወይራ ቅጠል በአፏ ይዛ ነበር፤ ከዚህም የተነሣ ኖኅ ውሃው ከምድር ላይ መጉደሉን አወቀ።
\v 12 ደግሞም ሰባት ቀን ከቆየ በኋላ ኖኅ ርግቢቱን እንደገና አውጥቶ ላካት፤ በዚህ ጊዜ ግን ርግቢቱ ወደ እርሱ አልተመለሰችም።
\s5
\v 13 ኖኅ በተወለደ 601ኛው ዓመት፣ በመጀመሪያው ወር፣ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ውሃው ከምድር ላይ ደረቀ። ኖኅ የመርከቡን ክዳን አንሥቶ ዙሪያውን ተመለከተ፣ ምድሪቱም እንደደረቀች አየ።
\v 14 በሁለተኛው ወር፣ በሃያ ሰባተኛው ቀን ምድሪቱ ሙሉ በሙሉ ደረቀች።
\s5
\v 15 ከዚያም እግዚአብሔር ኖኅን እንዲህ አለው።
\v 16 “አንተና ሚስትህ፣ ልጆችህና የልጆችህ ሚስቶች ከመርከቧ ውጡ።
\v 17 እንዲዋለዱ፣ እንዲራቡና በምድር ላይ እንዲበዙ ከአንተ ጋር ያሉትን ወፎች፣ እንስሳትና በምድር ላይ የሚሳቡ ሕያዋን ፍጡራንን ሁሉ ይዘሃቸው ውጣ።”
\s5
\v 18 ስለዚህ ኖኅ ከልጆቹ፣ ከሚስቱና ከልጆቹ ሚስቶች ጋር ወጣ።
\v 19 እንስሳቱ ሁሉ፣ ወፎችም፣ በምድር የሚሳቡት፣ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱ ሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ በየወገናቸው ከመርከቧ ወጡ።
\s5
\v 20 ኖኅም ለእግዚአብሔር መሠዊያን ሠራ። ንፁሕ ከሆኑት እንስሳትና ንፁሕ ከሆኑት ወፎች አንዳንዶቹን ወስዶ የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረበ።
\v 21 እግዚአብሔርም ደስ የሚያሰኘውን መዓዛ አሸተተ፣ በልቡም እንዲህ አለ፦ “ምንም እንኳ ሰው ገና ከልጅነቱ ጀምሮ ሐሳቡ ወደ ክፋት ያዘነበለ ቢሆንም በእርሱ ምክንያት ሁለተኛ ምድርን አልረግማትም፤ አሁን እንዳደረግሁት ሕያዋን ፍጡራንን ዳግመኛ አላጠፋም።
\v 22 ምድር እስካለች ድረስ የዘር ወቅትና መከር፣ ሙቀትና ቅዝቃዜ፣ በጋና ክረምት፣ ቀንና ሌሊት አይቋረጡም።”
\s5
\c 9
\p
\v 1 ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር ኖኅንና ልጆቹን እንዲህ ሲል ባረካቸው፦ “ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሏት፤
\v 2 አስፈሪነታችሁና አስደንጋጭነታችሁ በእንስሳት፣ በሰማይ ወፎች፣ በደረት በሚሳቡ ተንቀሳቃሽ ፍጡሮችና በባሕር ዓሦች፣ በምድር ላይ በሚገኙ ሕያዋን ፍጡራን ሁሉ ላይ ይሁን። ሁሉም በሥልጣናችሁ ሥር ይሁኑ።
\s5
\v 3 ሕያውና ተንቀሳቃሽ ፍጡር ሁሉ ምግብ ይሁናችሁ፣ ለምለሙን ዕፅዋት እንደሰጠኋችሁ፣ አሁን ደግሞ ሁሉን ሰጠኋችሁ።
\v 4 ነገር ግን ሕይወቱ ማለት ደሙ ገና በውስጡ ያለበትን ሥጋ አትብሉ።
\s5
\v 5 ሰውን የገደለ ሁሉ ስለሟቹ ደም ተጠያቂ ነው፤ የሟቹን ሰው ደም ከገዳዩ ከእንስሳም ይሁን ከሰው እሻለሁ።
\v 6 የሰውን ደም የሚያፈስ ሁሉ ደሙ በሰው እጅ ይፈሳል፤ በእግዚአብሔር አምሳል እግዚአብሔር ሰውን ሠርቶታልና።
\v 7 እናንተ ግን ብዙ ተባዙ፣ ዘራችሁ በምድር ላይ ይብዛ ይንሠራፋም።”
\s5
\v 8 ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ለኖኅና ለልጆቹ እንዲህ አላቸው፦
\v 9 “እነሆ ከእናንተና ከእናንተ በኋላ ከሚመጣው ዘራችሁ ጋር ኪዳኔን እመሠርታለሁ፤
\v 10 እንዲሁም ከእናንተ ጋር ከነበሩት ሕያዋን ፍጡራን ሁሉ ከወፎች፣ ከእንስሳት ከእናንተ ጋር ከመርከቧ ከወጡት በምድር ላይ ካሉት ሕያዋን ፍጡራን ሁሉ ጋር ኪዳን እገባለሁ።
\s5
\v 11 ከእንግዲህ ሕይወት ያለው ፍጡር ሁሉ በጥፋት ውሃ እንደማይጠፋ፣ ዳግመኛም ምድርን የሚያጠፋ ውሃ ከቶ እንደማይመጣ ከእናንተ ጋር ኪዳን እገባለሁ።”
\v 12 እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፦ “በእኔና በእናንተ መካከል ከእናንተም ጋር ካሉ ሕያዋን ፍጡራን ሁሉ፣ ከሚመጣው ትውልድ ሁሉ ጋር፣ የማደርገው የኪዳኑ ምልክት ይህ ነው፤
\v 13 ቀስተ ደመናዬን በደመና ላይ አድርጋለሁ፤ ይህም በእኔና በምድር መካከል ለገባሁት ኪዳን ምልክት ይሆናል።
\s5
\v 14 ደመናን በምድር ላይ በጋረድሁና ቀስቴም በደመና ላይ በሚታይበት ጊዜ ሁሉ
\v 15 ከእናንተና ከሕያዋን ፍጡራን ሁሉ ጋር የገባሁትን ኪዳን አስባለሁ፤ ሕይወት ያለውንም ሁሉ ያጠፋ ዘንድ፣ ከእንግዲህ የጥፋት ውሃ ከቶ አይመጣም።
\s5
\v 16 ቀስቱ በደመና ላይ ተገልጦ በማይበት ጊዜ ሁሉ በእኔና በምድር ላይ ባሉ ሕያዋን ፍጡራን መካከል ያለውን ዘላለማዊ ኪዳን አስባለሁ።”
\v 17 ከዚያ በኋላም እግዚአብሔር ለኖኅ፦ “ይህ በእኔና በምድር ላይ በሚኖሩ ሕያዋን ሁሉ መካከል የገባሁት ኪዳን ምልክት ነው።” አለው።
\s5
\v 18 ከመርከቧ የወጡትም የኖኅ ልጆች ሴም፣ ካምና ያፌት ነበር፤ ካም የከነዓን አባት ነው።
\v 19 እነዚህ ሶስቱ የኖኅ ልጆች ሲሆኑ፣ በምድር ላይ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ የተገኙት ከነዚሁ ነው።
\s5
\v 20 ኖኅ ገበሬ መሆን ጀመረ፣ ወይንንም ተከለ።
\v 21 ከወይኑም ጠጅ ጠጥቶ ሰከረና በድንኳኑ ውስጥ እርቃኑን ተኛ።
\s5
\v 22 የከንዓን አባት ካም የአባቱን ዕርቃነ ሥጋ አየ፤ ወደ ውጭም ወጥቶ ለሁለቱ ወንድሞቹ ነገራቸው።
\v 23 ሴምና ያፌት ግን ልብስ ወስደው በትከሻቸው ላይ አደረጉና የአባታቸውን ዕርቃነ ሥጋ እንዳያዩ ፊታቸውን አዙረው የኋሊት በመሄድ የአባታቸውን ዕርቃነ ሥጋ ሸፈኑ።
\s5
\v 24 ኖኅ ከወይን ጠጁ ስካር ሲነቃ ታናሽ ልጁ ያደረገበትን አወቀ።
\v 25 ከዚህም የተነሣ፦ “ከነዓን የተረገመ ይሁን፤ ለወንድሞቹም አገልጋይ ይሁን።” አለ።
\s5
\v 26 ደግሞም፦ “የሴም አምላክ የሆነው እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፣ ከነዓንም የሴም አገልጋይ ይሁን።
\v 27 እግዚአብሔር የያፌትን ግዛት ያስፋ፤ ያፌት በሴም ድንኳኖች ይኑር፤ ከነዓን የያፌት አገልጋይ ይሁን።” አለ።
\s5
\v 28 ኖኅ ከጥፋት ውሃ በኋላ 350 ዓመት ኖረ።
\v 29 ኖኅ በአጠቃላይ 950 ዓመት ኖሮ ሞተ።
\s5
\c 10
\p
\v 1 የኖኅ ልጆች የሴም፣ የካምና የያፌት ዝርያዎች የሚከተሉት ናቸው። ከጥፋት ውሃም በኋላ ልጆች ተወለዱላቸው።
\s5
\v 2 የያፌት ልጆች፦ ጋሜር፣ ማጎግ፣ ማዴ፣ ያዋን፣ ቶቤል፣ ሞሳሕና ቴራስ ነበሩ።
\v 3 የጋሜር ልጆች፦ አስከናዝ፣ ሪፋትና ቴርጋማ ነበሩ።
\v 4 የያዋን ልጆች፦ ኤሊሳ፣ ተርሴስ፣ ኪቲምና ሮዳኢ ነበሩ።
\v 5 ከእነዚህም በየነገዳቸው በየጎሳቸውና በየቋንቋቸው ተከፋፍለው በባሕር ዳርና በደሴቶች በየምድራቸው የሚኖሩ ሕዝቦች ወጡ።
\s5
\v 6 የካም ልጆች፦ ኩሽ፣ ምጽራይም፣ ፉጥና ከነዓን ነበሩ።
\v 7 የኩሽ ልጆች፦ ሳባ፣ ኤውላጥ፣ ሰብታ፣ ራዕማና ሰበቀታ ነበሩ። የራዕማ ልጆች፦ ሳባና ድዳን ነበሩ።
\s5
\v 8 ኩሽ በምድር ላይ የመጀመሪያው ታላቅ ጦረኛ የነበረው የናምሩድ አባት ነበር።
\v 9 እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ብርቱ አዳኝ ነበር። ስለዚህም፣ “በእግዚአብሔር ፊት እንደ ናምሩድ ብርቱ አዳኝ” ይባል ነበር።
\v 10 የግዛቱም የመጀመሪያ ከተሞች በሰናዖር ምድር የነበሩት፡- ባቢሎን፣ አሬክ፣ አርካድና ካልኔ ነበሩ።
\s5
\v 11 ከዚያም ወደ አሦር ምድር ሄደና ነነዌን፣ ርሆቦትን፣ ካላሕን
\v 12 እንዲሁም በነነዌና በካላሕ መካከል የነበረውን ታላቅ ከተማ ሬሴን የተባሉትን ከተሞች መሠረተ።
\v 13 ምጽራይም የሎዳማውያን፣የዐናሚማውያን፣ የላህሚማውያን፣ የነፍታሌማውያን፣
\v 14 የፈተሩሲማውያንና ፍልስጥኤማውያን የተገኙባቸው የካስሎሂማውያንና የቀፍቶርማውያን አባት ነበር።
\s5
\v 15 የከነዓንም የበኩር ልጅ ሲዶን ተከታዩም ሔት ይባሉ ነበር።
\v 16 ሌሎቹም የከነዓን ዝርያዎች ኢያቡሳውያን፣ አሞራውያን፣ ጌርጌሳውያን፣
\v 17 ኤውያውያንን፣ ዓርቃውያን፣ ሲናውያን፣
\v 18 ኤርዋዳውያን፣ አርዋዳውያን፣ ደማራውያን፣ ሐማታውያን የሚባሉ ነበሩ። ከጊዜ በኋላ የከነዓን ጎሣዎች በየስፍራው ተሠራጩ።
\s5
\v 19 የከነዓን ወሰን ከሲዶና አንሥቶ በጌራራ በኩል ገሞራን አዳማንና ሰቦይን ይዞ እስከ ላሣ ይዘልቃል።
\v 20 እነዚህም በየጎሣቸውና በየቋንቋቸው በየምድራቸውና በየነገዳቸው ይኖሩ የነበሩ የካም ዝርያዎች ነበሩ።
\s5
\v 21 ለያፌት ታላቅ ወንድም ለሴም ደግሞ ወንዶች ልጆች ተወለዱለት፤ እርሱም የዔቦር ልጆች ሁሉ ቅድመ አያት ነበር።
\v 22 የሴም ልጆች ኤላም፣ አሦር፣ አርፋክስድ፣ ሉድ፣ አራም ነበሩ።
\v 23 የአራም ልጆች ዑፅ፣ ሁል፣ ጌቴር፣ ሞሶሕ ነበሩ።
\s5
\v 24 አርፋክስድ ሳላን ወለደ፤ ሳላም ኤቦርን ወለደ።
\v 25 ዔቦርም ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ። በዘመኑ ምድር ተከፍላ ስለነበር የአንደኛው ልጅ ስም ፍሌቅ ተባለ፤ ወንድሙም ዮቅጣን ተባለ።
\s5
\v 26 ዮቅጣንም የአልሞዳድ፣ የሼሌፍ፥ የሐጸርማዌት፣ የዮራሕ፣
\v 27 የዐዶራም፣ የኢዛል፣ የዲቅላ፣
\v 28 የዖባል፣ የአቢማኤል፣ የሳባ፣
\v 29 የኦፊር፣ የሐዊላና የዮባብ አባት ነበር። እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ዝርያዎች ነበሩ።
\s5
\v 30 መኖርያ ስፍራቸውም በስተምሥራቅ ባለው በተራራማው አገር ከሜሻ እስከ ስፋር ይደርስ ነበር።
\v 31 እነዚህም በየጎሣቸውና በየቋንቋቸው በየምድራቸውና በየነገዳቸው ይኖሩ የነበሩ የሴም ዝርያዎች ነበሩ።
\s5
\v 32 የኖኅ ወንዶች ልጆች ጎሣዎች እንደ ትውልዳቸው በየነገዳቸው እነዚህ ነበሩ። ከጥፋት ውሃ በኋላ ሕዝቦች በምድር ላይ የተሠራጩት ከእነዚሁ ነበር።
\s5
\c 11
\p
\v 1 በዚያ ዘመን መላው ዓለም የሚናገረውና የሚግባባው በአንድ ቋንቋ ነበር።
\v 2 ወደ ምሥራቅ ሲጓዙ፣ በሰናዖር አንድ ሜዳማ ቦታ አግኝተው በዚያ ሰፈሩ።
\s5
\v 3 እርስ በርሳቸውም፣ “ኑ፣ ጡብ እንሥራና እስከበቃው ድረስ በእሳት እንተኩሰው” ተባባሉ። በድንጋይ ፈንታ ጡብ ተጠቀሙ፤ ጡቡን እርስ በርስ ለማያያዝም ቅጥራን ተጠቀሙ።
\v 4 ከዚያም፣ “ለስማችን መጠሪያ እንዲሆን ጫፉ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንሥራ። ያንን ካላደረግን በምድር ሁሉ ፊት መበታተናችን ነው” አሉ።
\s5
\v 5 የአዳም ልጆች የሠሩትን ለማየት ያህዌ ወደ ከተማውና ወደ ግንቡ ወረደ።
\v 6 ያህዌም፣ “አንድ ቋንቋ የሚናገሩ አንድ ሕዝብ በመሆናቸው ይህን ማድረግ ችለዋል! ከእንግዲህ ማድረግ የፈለጉትን ለማድረግ ምንም የሚያቅታቸው አይኖርም።
\v 7 ኑ እንውረድ፤ አርስ በርስ እንዳይግባቡም ቋንቋቸውን እንደበላልቀው” አለ።
\s5
\v 8 ስለዚህ ያህዌ ከዚያ ቦታ ወደ መላው ዓለም በታተናቸው፣ እነርሱም ከተማዋን መሥራት አቋረጡ።
\v 9 በዚያ የዓለምን ቋንቋ ስለ ደበላለቀ የከተማዋ ስም ባቤል ተባለ። ከዚያም ያህዌ በመላው ዓለም በተናቸው።
\s5
\v 10 የሴም ትውልድ ይህ ነው። የጥፋት ውሃ ከመጣ ሁለት ዓመት በኋላ ሴም መቶ ዓመት ሲሆነው አርፋድሰድን ወለደ።
\v 11 አርፋድሰድን ከወለደ በኋላ ሴም አምስት መቶ ዓመት ኖረ። ሌሎች ወንዶች እና ሴቶች ልጆችንም ወለደ።
\s5
\v 12 አርፋክሰድ በሰለሣ አምስት ዓመቱ ሰላን ወለደ፤
\v 13 ሰላን ከወለደ በኋላ አርፋክሰድ አራት መቶ ሦስት ዓመት ኖረ፤ እርሱም ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ።
\s5
\v 14 ሳላ ሰላሣ ዓመት ሲሆነው ዔቦርን ወለደ፤
\v 15 ዔቦርን ከወለደ በኋላ ሳላ አራት መቶ ሦስት ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ።
\s5
\v 16 ዔቦር አራት ዓመት ሲሆነው ፋሌቅን ወለደ፤
\v 17 ፋሌቅን ከወለደ በኋላ ዔቦር አራት መቶ ሰላሣ ዓመት ኖረ፤ እርሱም እንዲሁ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ።
\s5
\v 18 ፋሌቅ ሰለሣ ዓመት ሲሆነው፣ ራግውን ወለደ፤
\v 19 ራግውን ከወለደ በኋላ ፋሌቅ ሁለት መቶ ዘጠኝ ዓመት ኖረ፤ እርሱም እንዲሁ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ።
\s5
\v 20 ራግው ሰለሣ ሁለት ዓመት ሲሆነው፣ ሴሮሕን ወለደ፤
\v 21 ሴሮሕን ከወለደ በኋላ ራግው ሁለት ሞት ሰባት ዓመት ኖረ፤ እርሱም እንዲሁ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ።
\s5
\v 22 ሴሮሕ ሰለሣ ዓመት ሲሆነው፣ ናኮርን ወለደ፤
\v 23 ናኮርን ከወለደ በኋላ ሴሮሕ ሁለት መቶ ዓመት ኖረ፤ እርሱም እንዲሁ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ።
\s5
\v 24 ናኮር ሃያ ዘጠኝ ዓመት ሲሆነው ታራን ወለደ፤
\v 25 ታራን ከወለደ በኋላ ናኮር አንድ መቶ አሥራ ዘጠኝ ዓመት ኖረ፤ እርሱም እንዲሁ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆች ወለደ።
\v 26 ታራ ሰባ ዓመት ሲሆነው አብራምን፣ ናኮርንና ሐራንን ወለደ።
\s5
\v 27 የታራ ትውልድ ይህ ነው። ታራ፣ አብራምን፣ ናኮርንና ሐራን ወለደ። ሐራን ሎጥን ወለደ።
\v 28 ሐራን አባቱ ታራ በሕይወት እያለ በተወለደበት ከተማ በከለዳውያን ዑር ሞተ።
\s5
\v 29 አብራምና ናኮር ሁለቱም ሚስት አገቡ። የአብራም ሚስት ሦራ ስትባል፣ የናኮር ሚስት ደግሞ ሚልካ ትባል ነበር፤ ሚልካ የሐራን ልጅ ስትሆን፣ ሐራን የሚልካና የዮሳካ አባት ነበር።
\v 30 ሦራ ምንም ልጅ ያልነበራት መካን ነበረች።
\s5
\v 31 ታራ ልጁ አብራምን፣ የልጅ ልጁን ሎጥንና የአብራምን ሚስት ምራቱን ሦራን ይዞ ወደ ከነዓን ለመሄድ በከለዳውያን ምድር ከምትገኘው ዑር አብረው ወጡ። ሆኖም፣ ካራን በደረሱ ጊዜ በዚያ ተቀመጡ።
\v 32 ታራ ሁለት መቶ አምስት ዓመት ኖሮ በካራን ሞተ።
\s5
\c 12
\p
\v 1 በዚህ ጊዜ ያህዌ አብራምን እንዲህ አለው፤ “አገርህን፣ ወገንህንና የአባትህን ቤተ ሰብ ትተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ሂድ፤
\v 2 ታላቅ ሕዝብ አደርግሃለሁ፤ እባርክሃለሁ፤ ስምህን ገናና አደርገዋለሁ፤ ለሌሎችም በረከት አደርግሃለሁ።
\v 3 የሚባርኩህን እባርካለሁ፤ የሚረግሙህንና የሚያዋርዱህን እረግማለሁ። በአንተ አማካይነት በምድር የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ይባረካሉ።”
\s5
\v 4 ስለዚህ አብራም ያህዌ እንዳዘዘው ወጣ፤ ሎጥም አብሮት ሄደ። አብራም ከካራን ተነሥቶ ሲሄድ፣ የሰባ አምስት ዓመት ሰው ነበር።
\v 5 አብራም ሚስቱ ሦራን፣ የውንድሙ ልጅ ሎጥን አስከትሎ በካራን ያፈሩትን ሀብትና የነበራቸውን አገልጋዮች ይዞ በመጓዝ፣ ከነዓን ምድር ገቡ።
\s5
\v 6 አብራም በሞሬ ያለው ግዙፍ የወርካ ዛፍ እስካለበት እስከ ሴኬም ዘልቆ ሄደ። በዚያ ዘመን ከነሻናውያን በዚህ ምድር ይኖሩ ነበር።
\v 7 ያህዌ ለአብራም ተገልጦ፣ “ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ” አለው። ስለዚህ አብራም ለተገለጠለት ለያህዌ በዚያ መሠዊያ ሠራ።
\s5
\v 8 ከዚያ በመነሣት ከቤቴል በስተ ምሥራቅ ወዳለው ተራራማ አገር ሄደ፤ ቤቴል በስተ ምዕራብ፣ ጋይ በስተ ምዕራብ ባለችበት ቦታ ድንኳኑን ተከለ። እዚያ ለያህዌ መሠዊያ ሠራ፤ የያህዌንም ስም ጠርቶ ጸለየ።
\v 9 አብራም ከዚያ ተነሥቶ ወደ ኔጌብ መጓዙን ቀጠለ።
\s5
\v 10 በዚያ ምድር ጽኑ ራብ ስለ ነበር አብራም እዚያ ጥቂት ጊዜ ለመቆየት ወደ ግብፅ ሄደ።
\v 11 ግብፅ በመግባት ላይ እያለ አብራም ሚስቱ ሦራን እንዲህ አላት፤ “መቼም አንቺ ቆንጆ ሴት መሆንሽን አውቃለሁ።
\v 12 ግብፃውያን ሲያዩሽ ‘ይህች ሚስቱ ናት’ ይላሉ፤ እኔን ይገድሉኛል፤ አንቺን ግን ይተዉሻል።
\v 13 ስለዚህ በአንቺ ምክንያት ለእኔ መልካም እንዲሆልኝ ሕይወቴም እንዲተርፍ እኅቱ ነኝ’ በዪ አላት።
\s5
\v 14 አብራም ወደ ግብፅ ሲገባ፣ ሦራ ምን ያህል ቆንጆ እንደ ሆነች ግብፃውያኑ አዩ።
\v 15 የፈርሾን ሹማምንት ባዩአት ጊዜ እርሷን እያደነቁ ለፈርዖን ነገሩት፤ ወደ ቤተ መንግሥትም ተወሰደች።
\v 16 በእርሷ ምክንያት ፈርኦን አብራምን በክብር አስተናገደው፤ በጎች፣ በሬዎች፣ ወንድ አህዮች ወንድና ሴት ባሪያዎች፣ ሴት አህዮችና ግመሎች ሰጠው።
\s5
\v 17 በአብራም ሚስት በሦራ ምክንያት ያህዌ ፈርዖንና ቤተ ሰቡን በታላቅ መቅሠፍት መታ።
\v 18 ፈርዖን አብራምን አስጠርቶ እንዲህ አለው፤ “ለመሆኑ ምን እያደረግህብኝ ነው? ሚስትህ መሆንዋን ለምን አልነገርከኝም?
\v 19 ለምን እኅቴ ናት አልከኝ? እኅቴ ናት ስላልከኝ ሚስቴ ላደርጋት ነበር። አሁንም ሚስትህ እቻት፤ ይዘሃት ሂድ”
\v 20 ከዚያም ፈርዖን አብራምን በተመለከተ ለባለሟሎቹ ትእዛዝ ሰጠ፤ እነርሱም አብራምን ከሚስቱና ከንብረቱ ሁሉ ጋር አሰናበቱት።
\s5
\c 13
\p
\v 1 ስለዚህ አብራም ሚስቱንና ያለውን ንብረት ሁሉ ይዞ ከግብፅ ወደ ኔጌብ ሄደ። ሎጥም ከእነርሱ ጋር ነበረ።
\v 2 በዚህ ጊዜ አብራም በከብት፣ በብርና በወርቅ በልጽጎ ነበር።
\s5
\v 3 ከኔጌብ ተነሥቶ እስከ ቤቴል ተጓዘ፤ ቀድሞ ድንኳን ተክሎበት ወደ ነበረው በቤቴልና በጋይ መካከል ወደ ነበረው ቦታ ደረሰ።
\v 4 ይህ ቀድሞ መሠዊያ የሠራበት ቦታ ሲሆን በዚያ ያህዌን ጠራ።
\s5
\v 5 ከአብራም ጋር ይጓዝ የነበረው ሎጥ የራሱ በጎች፣ ከብቶችና ድንኳኖች ነበሩት።
\v 6 ሁለቱ አንድ ላይ ይኖሩ ስለ ነበር ስፍራው አልበቃቸውም፤ በዚህ ላይ ንብረታቸውም በጣም ብዙ ስለ ነበር አብረው መኖር አልቻሉም።
\v 7 ይህም በመሆኑ በአብራምና በሎጥ እረኞች መካከል ጠብ ተፈጠረ። በዚያ ዘመን ከነኣናውያንና ፌርዛውያን በዚያው አገር ይኖሩ ነበር።
\s5
\v 8 አብራም ሎጥን እንዲህ አልው፤ “በእኔና በአንተ፣ በእኔ እረኞችና በአንተ እረኞች መካከል ግጭት መኖር የለበትም፤ በዚህ ላይ ደግሞ ቤተ ሰብ ነን።
\v 9 ይኸው እንደምታየው ምድሩ ሰፊ ነው፤ ብንለያይ ይሻላል። አንተ ግራውን ብትመርጥ፣ እኔ ወደ ቀኝ እሄዳለሁ፤ ወይም አንተ ቀኙን ብትመርጥ እኔ ወደ ግራ እሄዳለሁ።
\s5
\v 10 ስለዚህ ሎጥ ዙሪያውን ሲመለከት እስከ ዞዓር ድረስ ያለው የዮርዳኖስ ረባዳ ሜዳ ሁሉ እንደ ያህዌ ገነት እንደ የግብፅ ምድር በጣም ለም ሆኖ አገኘው። እንዲህ የነበረው እግዚአብሔር ሰዶምና ገሞራን ከማጥፋቱ በፊት ነበር።
\v 11 ሎጥ የዮርዳኖስን ረባዳ ሜዳ ሁሉ መርቶ ወደ ምሥራቅ ተጓዘ፤ በዚህ ሁኔታ ዘመዳሞቹ ተለያዩ።
\s5
\v 12 አብራም መኖሪያውን በከነዓን ምድር አደረገ፤ ሎጥ ግን በረባዳው ሜዳ ባሉት ከተሞች መካከል ኖረ። እስከ ሰዶም ድረስ ባለው ቦታ ድንኳኖቹን ተከለ።
\v 13 የሰዶም ሰዎች በጣም ዐመፀኞችና በያህዌም ፊት እጅግ ኀጢአተኞች ነበሩ።
\s5
\v 14 ሎጥ ከእርሱ ከተለየው በኋላ ያህዌ አብራምን እንዲህ አለው፤ “ካለህበት ቦታ ወደ ሰሜን፣ ወደ ደቡብ፣ ወደ ምሥራቅና ምዕራብ ተመልከት።
\v 15 ይህን የምታየውን ምድር ሁሉ ለአንተና ለዘርህ ለዘላለም እሰጣለሁ።
\s5
\v 16 ዘርህን እንደ ምድር ትቢያ አበዛዋለሁ፤ የምድር ትቢያ ሊቆጠር እንደማይቻል ሁሉ የአንተም ዘር ሊቆጠር አይችልም።
\v 17 እንግዲህ ምድሪቱን ስለምስጥህ ተነሣና በርዝመትና በስፋቱ ተመላለሰባት።”
\v 18 ስለዚህ አብራም ድንኳኑን ነቀለና በኬብሮን ወዳሉት የመምሬ ወርካ ዛፎች መጥቶ ኖረ፤ እዚያም ለያህዌ መሠዊያ ሠራ።
\s5
\c 14
\p
\v 1 አምራፌል የሰናዖር ንጉሥ፣ አርዮክ የአላሳር ንጉሥ፣ ከሎደጎምር የኤላም ንጉሥ፣ ተድዓል የጎይም ንጉሥ፣
\v 2 በነበሩበት ዘመን፤ ከሰዶም ንጉሥ በላ፣ ከጎሞራ ንጉሥ ከብርሳ፣ ከአዳማ ንጉሥ ከሰነአብ፣ ከሰቦይ ንጉሥ ከሰሜበር፣ እንዲሁም ዞዓር ከተባለች ከቤላ ንጉሥ ጋር ለመዋጋት ወጡ።
\s5
\v 3 እነዚህ የኋለኞቹ አምስት ነገሥታት የጨው ባሕር እየተባለች በምትጠራው በሲዶም ሸለቆ ተሰበሰቡ።
\v 4 እነርሱም አሥራ ሁለት ዓመት ለኮሎዶጎምር ተገዙ፤ በአሥራ ሦስተኛው ዓመት ግን ዐመፁ።
\v 5 በአሥራ አራተኛው ዓመት ከሎዶጎምርና ከእርሱም ጋር የነበሩት ነገሥታት መጥተው ራፋይምን፣ በአስታሮት ቃርናይምን፣ በካም ዙዚምን፣ በሴዊ ኑሚምን፣ በሸቮት ኢምንን፣
\v 6 የሖር ሰዎችንም በተራራማው አገር በሴይ በረሐማ አጠገብ እስካለው እስከ አልፋራን ድረስ ድል አደረጋቸው።
\s5
\v 7 ከዚያም ተመልሰው ዓይንሚስፓጥ ወደሚባለው ወደ ቃዴስ መጡ፤ የአማሌዋውያንና በሐሴስ ታማር ይኖሩ የነበሩትን የአሞራውያን ግዛት በሙሉ ድል አድርገው ያዙ።
\v 8 ከዚያም የሶዶም፣ የገሞራ፣ የአዳማ፣ የሰቦይ እንዲሁም ዞዓር የተባለችው የቤላ ነገሥታት ወደ ሲዶም ሸለቆ ሄደው ለጦርነት ተዘጋጁ።
\v 9 እነዚህ አምስቱ በኤላም ንጉሥ በኮሎዶጎምር፣ በጎይም ንጉስ በቲድዓል፣ በሰናዖር ንጉሥ በአምራፌል፣ በአላሶር ንጉሥ በአርዮክ በእነዚህ ላይ ዘመቱባቸው።
\s5
\v 10 በሲዲም ሸለቆ ብዙ የቅጥራን ጉድጓዶች ነበሩ፤ የሰዶምና የጎመራ ነገሥታት ሲሸሹ ከሰዎቻቸው አንዳንዶቹ በእነዚህ ጉድጓዶች ውስጥ ወደቁ። የተረፉትም ወደ ተራሮች ሸሹ።
\v 11 አራቱ ነገሥታትም በሰዶምና በጎሞራ ያገኙትን ሀብትና ምግብ ሁሉ ዘርፈው ሄዱ።
\v 12 በሰዶም ይኖር የነበረውን የአብርሃምን ወንድም ልጅ ሎጥንና የነበረውን ንብረት ሁሉ ይዘው ሄዱ።
\s5
\v 13 ከዚያ ያመለጠ አንድ ሰው መጥቶ ለዕብራዊው ለአብራም ነገረው። በዚያ ጊዜ ይኖር የነበረው የአስኮና የእውናን ወንድም በነበረው በአሞራዊው መምሬ ዋርካ ዛፎች አጠገብ ነበር፤ እነዚህ ሁሉ የአብራም አጋሮች ነበር።
\v 14 ጠላት ዘመዶቹን ማርኮ መውሰዱን አብራም ሲሰማ በቤቱ ተወልደው ያደጉ ሦስት መቶ አሥራ ስምንት ሰዎች ይዞ እስከ ዳን ድረስ ተከታተሏቸው።
\s5
\v 15 አብራም ጠላቶቹን ለማጥቃት ሰራዊቱን ሌሊቱን በቡድን በቡድን ከፋፍሎ ከደማስቆ በስተ ሰሜን እስከሚገኘው እስከ ሖባ ድረስ አሳደዳቸው።
\v 16 ጠላት የማረከውን በሙሉ አስጣለ፤ ዘመዱ ሎጥንና ንብረቱን፣ እንዲሁም ሴቶቹንና ሌሎች ሰዎችን አስመለሰ።
\s5
\v 17 አብራም የኮሎዶጎምርንና ከእርሱ ጋር የነበሩ ነገሥታትን ድል አድርጎ ሲመለስ የሰዶም ንጉሥ የንጉሥ ሸለቆ ተብሎ በሚጠራው በሴዊ ሸለቆ ሊቀበለው ወጣ።
\v 18 የሰሌም ንጉሥ መልከጼዴቅ እንጀራና ወይን ጠጅ ይዞ መጣ። እርሱ የልዑል አምላክ ካህን ነበር።
\s5
\v 19 አብራምም እንዲህ በማለት ባረከው፣ “ሰማይና ምድርን የፈጠረ ልዑል እግዚአብሔር አብራምን ይባርክ።
\v 20 ጠላቶችህን በእጅህ አሳልፎ የሰጠ ልዑል እግዚአብሔር ይባረክ።” አብራምም ይዞት ከነበረው ሁሉ አንድ አሥረኛውን ሰጠው።
\s5
\v 21 የሰዶም ንጉሥ አብራምን፣ “ሰዎቹን ለእኔ ስጠኝ፤ ንብረቱን ግን ለራስህ አስቀር” አለው።
\v 22 አብራምም ለሰዶም ንጉሥ እንዲህ አለው፤ “ከአንተ ብጣሽ ክርም ሆነ የጫማ ማሰሪያ እንኳ ቢሆን፣
\v 23 ደግሞም ‘አብራምን ባለጸጋ አደረግሁት’ እንዳትል የአንተ ከሆነ ምንም ነገር እንዳልወስድ ሰማይና ምድርን ወደ ፈጠረ አምላክ ወደ ያህዌ እጄን አንሥቻለሁ።
\v 24 አብረውኝ ያሉት ሰዎች ከበሉትና የእነርሱ ድርሻ ከሆነው በቀር ምንም ነገር አልወስድም። አውናን፣ ኤስኩልና መምሬ ድርሻቸውን ይውሰዱ።”
\s5
\c 15
\p
\v 1 ከዚህ በኋላ የያህዌ ቃል እንዲህ ሲል ወደ አብራም መጣ፤ “አብራም ሆይ፣ አትፍራ፤ እኔ ለአንተ ጋሻህ ነኝ፤ ታላቅ ሽልማትህም እኔው ነን።”
\v 2 አብራምም፣ “ጌታ ያህዌ ሆይ፣ እኔ ልጅ የለኝም፤ የቤት ወራሽ የሚሆነው የደማስቆው ሰው ኤሊዔዘር ነው፤ ታዲያ አንተ ለእኔ የምትሰጠኝ ምንድን ነው?” አለ።
\v 3 በመቀጠልም አብራም “አንተ ልጅ እስካልሰጠኸኝ ድረስ፣ ከቤቴ አገልጋይ አንዱ ወራሼ መሆኑ አይቀርም” አለ።
\s5
\v 4 በዚህ ጊዜ የያህዌ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እርሱ መጣ፤ “ይህ ሰው ወራሽህ አይሆንም፤ ይልቁንም ወራሽህ የሚሆነው ከአብራክህ የሚከፈል የራስህ ልጅ ይሆናል።”
\v 5 ከዚያም ወደ ውጭ አወጣውና እንዲህ አለው፤ “ቀና ብለህ ወደ ሰማይ ተመልከት፤ መቍጠር ከቻልህ ከዋክብቱን ቍጠር። ዘርህም እንዲሁ ይበዛል።”
\s5
\v 6 አብራም ያህዌን አመነ፤ እርሱም ጽድቅ አድርጎ ቆጠረለት።
\v 7 እንዲህም አለው፤ “ይህችን ምድር እንድትወርስ ልሰጥህ ከከለዳውያን ምድር ከዑር ያወጣሁህ እኔ ያህዌ ነኝ።”
\v 8 አብራምም፣ “ጌታ ያህዌ ሆይ፣ ይህችን ምድር እንደምወርስ እንዴት አውቃለሁ?” አለ።
\s5
\v 9 በዚህ ጊዜ፣ “እያንዳንዳቸው ሦስት ዓመት የሆናቸው አንዲት ጊደር፣ አንዲት ፍየልና አንድ በግ እንዲሁም ዋኖስና አንድ ርግብ አቅርብልኝ” አለው።
\v 10 እርሱም እነዚህን ሁሉ አቀረበለት፤ ቆርጦም ሁለት ቦታ ከከፈላቸው በኋላ እያንዳንዱን ክፍል በሌላው ወገን ትይዩ አስቀመጣቸው፤ ወፎቹን ግን አልከፈላቸውም።
\v 11 አሞሮች ሥጋውን ለመብላት ወረዱ፤ አብራምም አባረራቸው።
\s5
\v 12 ፀሓይ ልትጠልቅ ስትል አብራም ከባድ እንቅልፍ ወሰደው፤ የሚያስፈራም ድቅድቅ ጨለማም መጣበት።
\v 13 በዚህ ጊዜ ያህዌ አብራምን እንዲህ አለው፤ “ዘሮችህ የራሳቸው ባልሆነ ምድር ባዕድ እንደሚሆኑና እዚያ ለአራቶ መቶ ዓመት በባርነት እንደሚኖሩ በእርግጥ ዕወቅ።
\s5
\v 14 እኔም ባሪያዎች ባደረጓቸው ሕዝብ እፈርዳለሁ፤ በኋላም ብዙ ሀብት ይዘው ይወጣሉ።
\v 15 አንተ ግን በሰላም ወደ አባቶችህ ትሄዳለህ፤ ዕድሜም ጠግበህ ትቀበራለህ።
\v 16 በአራተኛውም ትውልድ እንደ ገና ወደዚህ ይመጣሉ፤ ምክንያቱም የአሞራውያን ኀጢአት ጽዋው ገና አልሞላም።”
\s5
\v 17 ፀሓይ ገብታ ከጨለመ በኋላ የምድጃ ጢስና የሚንበለበል ፋና በተቆራረጡት ሥጋዎች መካከል አለፈ።
\v 18 በዚያን ቀን ያህዌ እንዲህ በማለት ከአብራም ጋር ኪዳን አደረገ፤ “ከግብፅ ወንዝ ጀምሮ እስከ ታላቁ ወንዝ ኤፍራጥስ ድረስ ያለውን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ፤
\v 19 የምሰጣቸውም የቄናውያንን፣ የቄንፌዛውያንን፣ የቃድሞናውያንን፣
\v 20 የኬጢያውያንን፣ የፌርዛውያንን፣ የራፋይምን፣
\v 21 የአሞራውያንን፣ የከነዓናውያን፣ የጌርሳውያንንና የኢያቡሳውያን ምድር ነው።”
\s5
\c 16
\p
\v 1 የአብራም ሚስት ሦራ ልጅ አልወለደችለትም ነበር፤ ነገር ግን አጋር የምትባል ግብፃዊት አገልጋይ ነበረቻት።
\v 2 አብራምንም፣ "ያህዌ ልጅ እንዳልወደልድ አድርጎኛል። ምናልባት በእርሷ በኩል ልጅ አገኝ ይሆናልና ክአገልጋዬ ጋር ተኛ" አለችው። አብራም ሦራ በነገረችው ተስማማ።
\v 3 የአብራም ሚስት ሦራ ግብፃዊት አገልጋይዋ ሚስት እንድትሆነው ለአብራም የሰጠችው አብራም በከነዓን ምድር አሥር ዓመት ከኖረ በኋላ ነበር።
\v 4 አብራም ክአጋር ግን'ኡንት አደረገ እርሷም ፀነሰች። አጋር መፅነሷን ባወቀች ጊዜ እመቤቷን በንቀት ማየት ጀመረች።
\s5
\v 5 በዚህ ጊዜ ሦራ አብራምን፣ "ይህ በደል የደረሰብኝ በአንተ ምክንያት ነው። ኅቅፍህ ውስጥ እንድትሆን አገልጋዬን ሰጠሁ፤ እርሷ ግን መፅነሷን ስታውቅ እኔን መናቅ ጀመረች። ያህዌ በእኔና በአንተ መካከ ይፍረድ" አለችው።
\v 6 አብራምም መልሶ ሦራን፣ "አገልጋይሽ እኮ በእጅሽ ውስጥ ናት እርሷ ላይ የፈለግሽውን ማድረግ ትችያልለሽ" አላት። ስለዚህ ሦራ ስላሠቃየቻት፣ አጋር ከቤት ጠፍታ ሄደች።
\s5
\v 7 የያህዌ መልአክ አጋርን ምድረ በዳ ውስጥ በነበረ አንድ ምንጭ አጠገብ አገኛት፤ ያ ምንጭ ወደ ሱር በሚወስደው መንገድ ላይ ነበር።
\v 8 መልአኩም፣ "የሦራ አገልጋይ አጋር ሆይ፣ ከየት መጣሽ ወዴትስ እየሄድሽ ነው?" አላት። እርሷም፣ "ከእመቤቴ ከሦራ ኮብልዬ እየሄድሁ ነው" አለችው።
\s5
\v 9 የያህዌ መልአክ፣ "ወደ እመቤትሽ ተመለዒ፤ ራስሽንም ለሥልጣንዋ አስገዢ" አላት።
\v 10 ከዚያም የያህዌ መልአክ፣ "ዘርሽን እጅግ አበዛዋለሁ፤ ከበምዛቱም የተነሣ ሊቆጠር አይቻልም" አላት።
\s5
\v 11 የያህዌም መልአክ በተጨማሪ እንዲህ አላት፤ "እነሆ ፀንሰሻል ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ያህዌ ችግርሽን ሰምቷልና ስሙን እስማኤል ትዪዋለሽ።
\v 12 እርሱ እንደ ዱር አህያ ይሆናል። ከሰው ሁሉ ጋር ይጣላል፤ ሰው ሁሉም ከእርሱ ጋር ይጣላል፤ ከወንድሞቹ ሁሉ ተነጥሎ ይኖራል።"
\s5
\v 13 እርሷም ይሚያናግራትን ያህዌን፣ "አንተኮ እኔን የምታይ አምላክ ነህ"በማለት ጠራችው፤ ምክንያቱም፥ "እርሱ እኔን እንዳየ ሁሉ እኔም እርሱን አየው ይሆን?" ብላ ነበር።
\v 14 ስለዚህ ያ ምንጭ ብኤርልያህሮኢ ተባለ፤ የሚገኘው በቃዴስና በባሬድ መካከ ልነው።
\s5
\v 15 አጋር ለአብራም ወድን ልጅ ወለደችለው፤ አብራምም አጋር የወለደችለትን ልጅ እስማኤል ብሎ ጠራው።
\v 16 አጋር እስማኤልን በወለደች ጊዜ አብራም ሰማንያ ስድስት ዓመት ሆኖት ነበር።
\s5
\c 17
\p
\v 1 አብራም የዘጠና ዘጠኝ ዓመት ሰው እያለ ያህዌ ተገለጠለትና እንዲህ አለው፤ "እኔ ሁሉን ቻይ አምላክ ነኝ፤ በፊቴ ተመላለስ ነቀፋም አይኑርብህ።
\v 2 በእኔና በአንተ መካከል የተደረገውን ኪዳን አጸናለሁ፤ አንተንም እጅግ አበዛሃለሁ።"
\s5
\v 3 አብራም በግንባሩ መሬት ላይ ተደፋ፤ እግዚአበሔርም እንዲ አለው፤
\v 4 "እነሆ ኪዳኔ ክአንተ ጋር ነው። የብዙ ሕዝብ አባት አደርግሃለሁ።
\v 5 ከእንግዲህ ስምህ አብራም መባል የለበትም፤ ስምህ አብርሃም መባል እለበት፤ ምክንያቱም የብዙ ሕዝብ አባት አድርጌሃለሁ።
\v 6 እጅግ አበዛሃለሁ፣ ሕዝቦች ክአንተ ይገኛሉ፤ ነገሥታትም ክአንተ ይወጣሉ።
\s5
\v 7 በእኔና በአንተ፣ ክአንተም በኋላ ከዘርህ ጋር ኪዳኔን እመሠርታለሁ፤ ለአንተ ከአንተም በኋላ ለዘርህ በዘላለም ኪዳን አምላክ እሆናችኋለሁ።
\v 8 ለአንተና ከአንተም በኋላ ለዘርህ ይህች አሁን የምትኖርባትን የከነዓንን ምድር በሙሉ ለዘላለም ርስት አድርጌ እሰጣላለሁ፤ አምላካቸውም እሆናለሁ።"
\s5
\v 9 ከዚያም እግዚአብሔር አብርሃምን፣ "በአንተም በኩል፣ አንተና ከአንተ በኋላ የሚመጣው ዘርህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ኪዳኔን መጠበቅ አለባችሁ።
\v 10 በእኔና በአንተ መካከል ከአንተም በኋላ በእኔና በዘርህ መካከል መጠበቅ ያለባችሁ ኪዳኔ ይህ ነው፤ በመካከላችሁ ያለ ወንድ ሁሉ ይገረዝ።
\v 11 እናንተ ሸለፈታችሁን ትገረዛላችሁ፤ ይህም በእናንተ መካከል ያለው ኪዳን ምልክት ይሆናል።
\s5
\v 12 በመካከላችሁ ያለው ማንኛውም ስምንት ዓመት የሞላው ወንድ የሚመጣው ትውልድ ሁሉ ይገረዝ። ይህ በቤትህ የተወለደውን በገንዘብህ የተገዛውን ሁሉ ይጨምራል።
\v 13 ቤትህ ውስጥ የተወለደና በገንዘብህ የገዛኸው መገረዝ አለባቸው። ስለሆነም ኪዳኔ በዘላለም ኪዳን ሥጋችሁ ላይ ይሆናል።
\v 14 ሸለፈቱን ያልተገረዘ ማንኛውም ወንድ ኪዳኔን አፍርሷልና ከወገኖቹ ይወገድ።"
\s5
\v 15 እግዚአብሔር አብርሃምን እንዲህ አለው፤ "ሚስትህ ሦራን ክአንግዲህ ሥራ እንጂ ሦራ ብለህ አትጥራት።
\v 16 እባርክሃለሁ፤ ከእርሷ ወንድ ልጅ እሰጥሃለሁ። እባርካታለሁ። እርሷም የብዙ ሕዝብ እናት ትሆናልች፤ የሕዝቦችም ነገሥታት ክአርሷ ይወጣሉ።
\s5
\v 17 በዚህ ጊዜ አብርሃም በግንባሩ መሬት ላይ ተደፍቶ እየሳቀ በሉ እንዲህ አለ፤ "ለመሆኑ የመቶ ዓመት ሽማግሌ ልጅ መውልደድ ይችላል? የዘጠና ዓመቷ አሮጊት ሥራስ ብትሆን ልጅ መውለድ ይሆንላታል?"
\v 18 አብርሃም እግዚአብሔርን፣ "ይልቅ፣ እስማኤልን ብቻ ባኖርህልኝ!" አለ።
\s5
\v 19 እግዚአብሔርም፣ "እንደዚያ አይደለም፤ ሚስትህ ሥራ ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ይስሐቅ ብለህ ትጠራዋለህ። የዘላለም ኪዳኔን ከእርሱ ጋር፣ ከእርሱም በኋላ ከዘሩ ጋር እመጸርታለሁ።
\v 20 እስማኤልን በተመለከተም ልምናህን ሰምቻለሁ። እነሆ እርሱንም እባርከዋለሁ፤ ፍሬያማም አደርገዋለሁ፤ እጅግም አበዛዋለሁ። የአሥራ ሁለት ነገዶች አባት ይሆናል፤ ታላቅ ሕዝብ እንዲሆንም አደርጋለሁ።
\v 21 ኪዳኔን ግን፣ የዛሬ ዓመት በዚህ ጊዜ ሣራ ከምትወልድህል ከይስሐቅ ጋር እመሠርታለሁ።"
\s5
\v 22 ከእርሱ ጋር መነጋገሩን ከጨረሰ በኋላ እግዚአብሔር ወደ ላይ ወጣ።
\v 23 በዚያኑ ዕለት አብርሃም ልጁ ይስሐቅን፣ በቤቱ ውስጥ የተወለዱትን በሙሉ፣ በገንዘቡ የገዛቸውን ሁሉ፣ ቤቱ ውስጥ ያለ ማንኛውንም ወንድ ሁሉ እግዚአብሔር በነገረው መሠረት ገረዛቸው።
\s5
\v 24 አብርሃም በተገረዘ ጊዜ እድሜው ዘጠና ዘጠኝ ዓመት ነበር።
\v 25 ልጁም እስማኤል በተገረዘ ጊዜ እድሜው አሥራ ሦስት ነበር።
\v 26 በዚያው ቀን አብርሃምና ልጁ እስማኤልም ተገረዙ።
\v 27 ቤቱ ውስጥ የተወለዱትን፣ ከውጭ በገንዘብ የተገዙትን ጨምሮ ቤቱ ውስጥ የነበሩ ወንዶች ሁሉ ከእርሱ ጋር ተገረዙ።
\s5
\c 18
\p
\v 1 ቀኑ በጣም ሞቃት በሆነ ጊዜ አብርሃም በመምሬ ወርካ ዛፎች አቅራቢይ ኣድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ እያለ ያህዌ ተገለጥለት።
\v 2 እርሱም ቀና ብሎ ሦስት ሰዎች ፊት ለፊቱ ቆመው አየ። ባያቸውም ጊዜ ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ ፈጥኖ ወደ እነርሱ ሄዶ፣ ወደ መሬት ዝቅ ብሎም እጅ ነሣ።
\s5
\v 3 አብርሃም እንዲህ አለ፤ "ጌታዬ፣ በፊትህ ሞገስ አግኝቼ ከሆነ፣ ባሪያህን አልፈህ አትሂድ።
\v 4 ጥቂት ውሃ ትምጣላችሁና እግራችሁን ታጠቡ፤ ከዚያም ዛፉ ሥር ዐረፍ በሉ።
\v 5 ወደ እኔ ወዳገልጋያችሁ ከመጣችሁ የደከመ ሰውነታችሁ እንዲበረታ እስቲ ጥቂት እህል ላምጣላችሁና ብሉ፤ ከዚያ ጕዞአችሁን ትቀጥላላችሁ።" እነርሱም. "እንዳልኸው አድርግ" አሉት።
\s5
\v 6 ያኔውኑ አብርሃም በፍጥነት ሣራ ወደ ነበረችበት ድንኳን ገብቶ፣ "ቶሎ ብለሽ ሦስት መስፈሪያ ስልቅ ዱቄት አቡኪና ቂጣ ጋግሪ" አላት።
\v 7 ከዚያም ወደ መንጋው በፍጥነት ሄዶ አንድ ፍርጥም ያለ ሥጋው ግን ገር የሆነ ጥጃ መረጠና ለአገልጋዩ ሰጠው፤ እርሱም በአስቸኳይ አደረሰው።
\v 8 አብርሃምም እግሮ፣ ወተትና የተዘጋጀውን የጥጃ ሥጋ አቀበላቸው፤ እነርሱ እየበሉ እያለ እርሱ ዛፉ ሥር አጠገባቸው ቆሞ ነበር።
\s5
\v 9 እነርሱም እንዲህ አሉት፤ "ሚስትህ ሥራ የታለች?" እርሱም፣ "ድንኳን ውስጥ ናት" አለ።
\v 10 እነርሱም፣ "የዛሬ ዓመት በፀደይ ወቅት ልክ በዚሁ ጊዜ በእርግጥ ተመልሼ እመጣለሁ፤ ሚስትህ ሥራ ልጅ ትወልዳለች" አለ። ሥራ ከጀርባ በነበረው ድንኳን ደጃፍ ሆና ታዳምጥ ነበር።
\s5
\v 11 በዚህ ጊዜ አብርሃምና ሥራ በጣም አርጅተው ነበር፤ ሥራማ ልጅ የመውለጃ ጊዜ አልፎባት ነበር።
\v 12 ስለዚህ ሣራ በልቧ፣ "ይህን ያህል ካረጀሁና ጌታዬም ከደከመ በኋላ በዚህ ነገር መደሰት ይሆንልኛልን?" ብላ ሳቀች።
\s5
\v 13 ያህዌ አብርሃምን እንዲህ አለው፤ "ካረጀሁ በኋላ እንዴት አድርጌ ልጅ እወልዳለሁ ስትል ሣራ የሳቀችው ለምንድን ነው?
\v 14 ለመሆኑ ለያህዌ የሚሳነው ነገር አለ? እኔ በወሰንሁት የፀደይ ወቅት ወደ እናንተ እመለሳለህ፤ በሚመጣው ዓመት በዚህ ጊዜ ሥራ ወንድ ልጅ ትወልዳለች።"
\v 15 ሣራ ግን ፈርታ ስል ነበር፣ "ኧረ እልሳቅሁም" በማለት ካደች። እርሱም፣ "የለም፤ ስቀሻል እንጂ" አላት።
\s5
\v 16 ሰዎቹ ለመሄድ ሲነሡ ቁልቁል ወደ ሰዶም ተመለከቱ። አብርሃምም ሊሸኛቸው ከእነርሱ ጋር ሄደ።
\v 17 በዚህ ጊዜ ያህዌ እንዲህ አለ፤ "እኔ የማደርገውን ክአብርሃም መደበቅ አለብኝን?
\v 18 አብርሃም በእርግጥ ታላቅና ብርቱ ሕዝብ ይህሆናል፤ የምድር ሕዝቦችም ሁሉ በእርሱ ይባረካሉ።
\v 19 ትክክለኛና ቀና የሆነውን በማድረግ የያህዌን መንገድ እንዲጠብቁ ልጆቹንና ከእርሱ በኋላ ቤተ ሰቡን እንዲያስተምር እኔ አብርሃምን መርጬዋለሁ፤ ይኸውም ለአብርሃም የነገረውን ሁሉ ያህዌ እንዲፈጽምለት ነው።"
\s5
\v 20 ደግሞም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ "በሰዶምና በገሞራ ላይ የሚሰማው ክስ በጣም ስለ በዛ፣ ኀጢአታቸውም በጣም ትልቅ ስል ሆነ፤
\v 21 ወደ እኔ የመጡ ክሶች ምን ያህል እውነት መሆናቸውን ለማየት ወደዚያ እወርዳለሁ፤ እንደዚይ ካልሆነም አውቃለሁ።"
\s5
\v 22 ሰዎቹም ፊታቸውን ወደ ሰዶም አቅንተው ሄዱ፤ አብርሃም ግን ያህዌ ፊት እንደ ቆመ ነበር።
\v 23 አብርሃም ወደ እርሱ ቀረብ ብሎ፣ "በእርግጥ ጻድቁን ከኀጢአተኛው ጋር ታጠፋለህን?
\s5
\v 24 ምናልባት በከተማዋ ሃምሳ ጻድቃን ቢገኙስ? እዚያ ባሉ ጻድቃን ስትል ከተማዋን ሳታድን ታጠፋታለህን?
\v 25 ጻድቁን ከኀጢአተኛው ጋር በመግደል፣ ኀጢአተኛ ላይ የደረሰው በእርሱም እንዲደርስ ማድረግን የመሰለ ንገር ከአንተ ይራቅ! እንዲህ ያለው ከአንተ ይራቅ! የምድር ሁሉ ዳኛ እውነተኛ ጻድቅ የሆነውን አያደርግምን?
\v 26 ያህዌም እንዲህ አለ፤ "በሰዶም ከተማ ውስጥ ሃምሳ ጻድቃን ካገኘሁ ፣ ለእነርሱ ስል ያንን ቦታ እምራለሁ።"
\s5
\v 27 አብርሃምም መልሶ እንዲህ አለ፤ "እኔ ትቢያና ዐመድ ሆኜ ሳለሁ ከጌታዬ ጋር ለመናገር አንዴ ደፍሬአለሁ፤
\v 28 ለመሆኑ ከአምሳዎቹ ጻድቃን አምስት ቢጎድሉ፣ በጎደሉት አምስቱ ምክንያት ከተማዋን በሙሉ ታጠፋለህን?" እርሱም፣ "እዚያ አርባ አምስ ጻድቃንካገኘሁ አላጠፋትም" አለ።
\s5
\v 29 አብርሃምም እንደ ገና፣ "ምናልባት አርባ ጻድቃን ቢገኙስ?" እለ፤ እርሱም፣ "ለአርባዎቹ ስል አላደርገውም" እለ።
\v 30 አብርሃምም፣ "እባክህን ጌታዬ ይህን ያህል በመናገሬ አትቆጣኝ። እንደው ምናልባት ሰለሣ ቢገኙስ" አለ። እርሱም መልሶ፣ "ሰላሣ ጻድቃን ካገኘሁ አላደርገውም" በማለት መለሰ።
\v 31 አብርሃምም፣ "መቼም አንዴ ከጌታዬ ጋር መናገር ጀምሬአለሁ! እንደው ምናልባት ሃያ ቢገኙስ" አለ። እርሱም መልሶ፥ "ለሃያዎቹ ስል አላደርገውም" አለ።
\s5
\v 32 በመጨረሻም እንዲህ አለ፤ "እባክህ ጌታዬ አትቆጣኝ፤ አንዴ ብቻ ልናገር፤ ምናልባት አሥር ቢገኙስ። እርሱም፣ "ለአሥሩ፣ ሲል አላጠፋትም" አለ።
\v 33 ከአብርሃም ጋር መነጋገሩን እንደ ጨረሰ ያህዌ ሄደ፤ አብርሃምም ወደ ቤቱ ተመለሰ።
\s5
\c 19
\p
\v 1 ሁለቱ መላእክት ምሽት ላይ ወደ ሰዶም መጡ፤ በሰዶም ከተማ መግቢያበር ላይ ተቀምጦ ነበር። ሎጥ ሲያያቸው ሊቀበላቸው ተነሣ፤ በግንባሩም መሬት ላይ ተደፋ።
\v 2 እርሱም፣ "እባካችሁ ጌቶቼ ወደ እኔ ወደ ባሪያችሁ ቤት ጎራ በሉ፤ እግራችሁን ታጠቡ፤ ሌሊቱንም ከእኛ ጋር አሳልፉ፤ ከዚያ ጧት በማለዳ ተነሥታችሁ ጕዞአችሁን ትቀጥላላችሁ።" እነርሱም፣ "የለም፤ እዚሁ አደባባዩ ላይ እናድራለን" አሉት።
\v 3 ሎጥ ግን አጥብቆ ስለ ለመናቸው እርሱ ቤት ለማደር አብረውት ገቡ። ከዚያም ቂጣ ጋግሮ አቀረበላቸው፤ እነርሱም በሉ።
\s5
\v 4 ሆኖም፣ ገና ከመተኛታቸው በፊት የሰዶም ከተማ ነዋሪዎች የሆኑ ወጣቶችና ሽማግሌዎች ከየአካባቢው መጥተው ቤቱን ከበቡት።
\v 5 ሎጥን በመጣራት፣ "በዚህ ምሽት ወደ ቤትህ የመጡ ሰዎች የታሉ? ሩካቤ ሥጋ እንድንፈጽምባቸው ወደ ውጭ አውጣልን" አሉት።
\s5
\v 6 ሎጥ ሊያነጋግራቸው ወደ ውጭ ወጣ መዝጊያውን ከበስተ ኋላው ዘጋ።
\v 7 እንዲህም አለ፤ "ወንድሞቼ እንዲህ ያለ ክፉ ነገር እንዳታደርጉ እለምናችሏለሁ።
\v 8 ከወንድ ጋር ተኝተው የማያውቁ ሁለት ሴቶች ልጆች አሉኝ፤ እነርሱን ላውጣላችሁና የወደዳችሁትን አድርጉባቸው። በእነዚህ ሰዎች ላይ ግን ምንም ነገር አታድርጉባቸው፤ እኔን ብለው ወደ ቤቴ ተብተዋልና።"
\s5
\v 9 እነርሱ ግን፣ "ዞር በል!" ይኸ ሰውዬ ስደተኛ ሆኖ እዚህ ለመኖር መጣ፤ ደግሞ ዳኛ ሆነብን! ይልቁ በእነርሱ ላይ ካሰብነው የከፋ እንዳይደርስብህ ዘወር በልልን" አሉት ሎጥንም እየገፈታተሩ የበሩን መዝጊያ ለመስበር ተቃርበው ነበር።
\s5
\v 10 ሰዎቹ እጃቸውን ዘርግተው ሎጥን ወደ ቤት አስገቡትና በሩን ዘጉ።
\v 11 ከቤቱ ውጪ የነበሩትን ውጣቶችንም ሆን ሽማግሌዎችን ግን የሎጥ እንግዶች ዐይናቸውን አሳወሩአቸው፤ እነርሱም በሩን ለማግኘት ይደነባበሩ ጀመር።
\s5
\v 12 ከዚያም ሰዎቹ ሎጥን እንዲህ አሉት፤ "በከተማዋ የሚኖሩ የአንተ የሆኑ ሰዎች አሉህ? ወንዶችና ሴቶች ልጆችህን፣ የወንዶች ልጆችህን ሚስቶች፣ የሴቶች ልጆችህን ባሎችና ሌሎች ዘመዶችህን ሁሉ ከዚህ አውጣ።
\v 13 ምክንያቱም ይህን ቦታ ልናጠፋ ነው፤ በያህዌ ፊት ከተማዋ ላይ የሚቀርቡ ክሶች በጣም እየጮኹ በመሆናቸው እንድናጠፋት እርሱ ልኮናል።"
\s5
\v 14 ሎጥ ከቤቱ ወጥቶ የሴት ልጆቹን ባሎች፣ የሴት ልጆቹን እጮኞች፣ "ቶሎ ከዚህ ቦታ ውጡ፤ ያህዌ ከተማዋን ሊያጠፋ ነው" አላቸው። የሴት ልጆቹ ባሎች ግን የሚቀልድ መሰላቸው።
\v 15 ሲነጋጋም መላእክቱ ሎጥኝ፣ "ከተተማዋ ላይ በሚመጣው ቅጣት አብራችሁ እንዳትጠፉ ሚስትህንና ሁለቱ ሴት ልጆችህን ይዘህ ከዚህ ቦታ በፍጥነት ውጣ" እያሉ አቻኮሉት።
\s5
\v 16 ሎጥ አመነታ፤ ያህዌ ምሕረት ስላደረገላቸው ሰዎቹ የእርሱ፣ የሚስቱንና የሁለት ሴት ልጆቹን እጅ ይዘው ከከተማዋ አወጣቸው።
\v 17 ከከተማው ካወጧቸው በኋላ ከሰዎቹ አንዱ፣ "ሕይወታችሁን ለማዳን ሩጡ! ወደ ኋላችሁ አትመልከቱ፤ ወይም ረባዳው ስፍራ ላይ አትቆዩ። ወደ ተራሮች ሽሹ፤ አለበለዚያ ትጠፋላችሁ።"
\s5
\v 18 ሎጥም እንዲህ አላቸው፤ "ጌቶቼ ሆይ፣
\v 19 እኔ ባሪያችሁ በፊታችሁ ሞገስ አግኝቻለሁ፤ ሕይወቴን ለማዳን ታላቅ ርኅራኄ አድርጋችሁልኛል፤ እኔ እንደ ሆንኩ ወደ ተራሮቹ ሸሽቼ ማምለጥ ስለማልችል የሚወርደው መዓት ደርሶ ያጠፋኛል።
\v 20 ወደዚያ ሸሽቶ ለማምለጥ ቅርብ ቦታ ያለች ትንሽ ከተማ አለች ሸሽቼ ወደዚያ ብሄድ ሕይወቴን ማዳን እችላለሁ።"
\s5
\v 21 እርሱም፣ "ይሁን እሺ፤ ልመናህን ተቀብብያለሁ፤ ያክካትንም ከተማ አላጠፋትም።
\v 22 አንተ እዚያ እስክትደርስ ምንም ማድረግ ስለማልችል በል ቶሎ ፍጠንና ወደዚያ ሽሽ" አለው። ስለዚህ ያቺ ከተማ ዞዓር ተባለች።
\s5
\v 23 ሎጥ ዞዓር ሲደርስ ፀሓይ በምድሩ ወጥታ ነበር።
\v 24 ከዚያ ያህዌ ሰዶምና ጎሞራ ላይ ድኝና እሳት አዘነበ።
\v 25 እነዚያን ከተሞችና ረባዳ ቦታዎቹን፣ የከተሞቹ ነዋሪዎችንና እዚይ ኣያሉ ለምለም ነገሮችን ሁሉ አጠፋ።
\s5
\v 26 ከኋላው የነበረችው የሎጥሚስት ግን ወደ ኋላዋ ስለ ተመለከተች የጨው ዐምድ ሆና ቀረች።
\v 27 አብርሃም ጠዋት ማለዳ ተነሥቶ ያህዌ ፊት ቆሞ ወደ ነበረበት ቦታ ሄደ።
\v 28 ቁልቁል ሰዶምና ጎሞራን፣ እንዲሁም በረባዳው ስፍራ የነበረውን ምድር ተመለከተ። ከምድጃ የሚወጣ የመሰለ ጢስ ከምድሩ እየወጣ ነበር።
\s5
\v 29 እግዚአብሔር በረባዳው ቦታ የነበሩ ከተሞችን ባጠፋ ጊዜ አብርሃምን አሰበው። ሎጥ የነበረበትን ከተሞች ቢያጠፋም፣ እርሱ ግን ከጥፋት መሐል አወጣው።
\s5
\v 30 ሎጥ ግን በዞዓር መኖር ስለ ፈራ ከሁለት ሴቶች ልጆቹ ጋር ተራሮቹ ላይ ለመኖር ከዞዓር ወደ ላይ ወጣ። ስለዚህ እርሱና ሁለት ሴቶች ልጆቹ ዋሻ ውስጥኖሩ።
\s5
\v 31 ታላቋ ልጅ ታናሿን እንዲህ አለቻት፣ "አባታችን አርጅቷል፤ በምድር ሁሉ እንደሚኖሩ ሰዎች ወግ ከእኛ ጋር የሚተኛ ወንድ በአካባቢያችን የለም።
\v 32 ስለዚህ አባታችንን የወይን ጠጅ እናጠጣውና ከእርሱ ጋር እንተኛ፤ የትውልድ ሐረጋችን እንዳይቋረጥ ከአባታችን ዘር እናትርፍ።"
\v 33 ስለዚህ በዚያ ምሽት አባታቸውን የወይን ጠጅ አጠጡት። ታላቂቱ ልጅ ሄዳ ክአባቷ ጋር ተኛች፤ እርሷ ስትተኛም ሆነ ስትነሣ አላወቅም።
\s5
\v 34 በሚቀጥለው ቀን ታላቂቱ ታናሺቱን እንዲህ አለቻት፤ "ትናንት ሌሊት እኔ ከእባቴ ጋር ተኛሁ። ዛሬም እንደ ገና የወይን ጠጅ እናጠጣው፣ ከዚያ አንቺ ሄደሽ ከእርሱ ጋር ትተኛለሽ፣ የአባታችንንም ዘር እናተርፋለን።"
\v 35 ስለዚህ በዚያም ምሽት አባታቸውን ወይን ጠጅ አጠጡት፤ ታናሺቱ ልጅ ሄዳ ከእርሱ ጋር ተኛች፤ እርሷ ስትተኛም ሆነ ስትነሣ አላወቀም።
\s5
\v 36 ሁለቱ የሎጥ ልጆች ክአባታቸው አረገዙ።
\v 37 ታላቂቱ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ሞዓብ አለችው። እርሱም ዛሬ ያሉት ሞዓባውያን አባት ሆነ።
\v 38 ታናሺቱም እንዲሁ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ቤንአሚ አለችው። እርሱም ዛሬ ያሉት አሞናውያን አባት ሆነ።
\s5
\c 20
\p
\v 1 አብርሃም ከዚያ ተነሥቶ ወደ ኔጌብ አካብቢ ሄደ፤ በቃዴስና በሱር መካከልም መኖር ጀመረ። ለጥቂት ጊዜ በጌራራ ተቀመጠ።
\v 2 አብርሃም ሚስቱ ሥራራን፣ "እኅቴ ናት" ይል ነበር፤ ስለዚህ ይጌራራ ንጉሥ አቢሜሌክ ሰዎች ልኮ ሣራን ወሰዳት።
\v 3 እግዚአብሔር ግን በሕልም ወደ እቢሜሌክ መጥቶ፣ "እነሆ በወሰድካት ሴት ምክንያት አንተ ምውት ነህ፤ ምክንያቱም እርሷ ባለ ባል ናት" አለው።
\s5
\v 4 አቢሜሌክ ገና አልሰረሰባትም ነበርና እንዲህ አለ፤ "ጌታ ሆይ፣ በደል ያልተገኘበትን ሕዝብ ልታጠፋ ነውን?
\v 5 'እኅቴ ናት' ያለኝ እርሱ ራሱ አይደለምን? እርሷም ብትሆን 'ወንድሜ ነው' ብላኛለች። እኔ እንዲህ ያደረግሁት በቅን ልቦናና በንጹሕ እጅ ነው።"
\s5
\v 6 በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር በሕልም እንዲህ አለው፤ "አዎን፣ ይህን ያደረግኸው በልብ ቅንነት እንደ ነበር እኔም አውቃለሁ፤ እኔ ላይ ኀጢአት እንዳትፈጽም የጠበቅሁህና እንዳትነካትም ያደረግሁት በዚህ ምክንያት ነው፤
\v 7 ስለዚህ የሰውየውን ሚስት መልስለት፤ እርሱ ነቢይ ስለ ሆነ ይጸልይልሃል አንትም ትድናለህ። እርሷን ካልመለስህ፣ እንተና የአንተ የሆነው ሁሉ በእርግጥ እንደምትጠፉ ዐውቃለሁ።"
\s5
\v 8 አቤሜሊክ ጧት በማለዳ ተነሥቶ ሹማምንቶቹን ሁሉ ጠራ። የሆነውን ሁሉ ሲነግራቸው በጣም ፈሩ።
\v 9 ከዚያም አቤሜሌ አብርሃምን አስጠርቶ፣ "ለመሆኑ፣ ምን እያደረግህብን ነው? በእኔና በግዛቴ ላይ እንዲህ ያለውን ትልቅ መዘዝ ያመጣህብኝ ምን ብበድልህ ነው? መደረግ ያልነበረትን አድርገህብኛል" አለው።
\s5
\v 10 በመቀጠልም፣ አብርሃምን፣ "እንዲህ እንድታደርግ ያነሣሣህ ምንድን ነው?" ሲል ጠየቀው።
\v 11 አብርሃምም፣ "በዚህ ቦታ እግዚአብሔርን መፍራት የለም፤ ለሚስቴ ሲሉ ይገድሉኛል በማለት ስላሰብሁ ነው።
\v 12 በዚህ ላይ ደግሞ ከእናቴ ባትወለድም የአባቴ ልጅ እኅቴ ናት፤ በኋላም ሚስቴ ሆነች።
\s5
\v 13 የአባቴን ቤት ትቼ በየአገሩ እንድዞር እግዚአብሔር ሲያዝዘኝ፣ "ለእኔ ለባልሽ ያለሽን ታማኝነት በዚህ አሳዪኝ፤ በምንሄድበት ቦታ ሁሉ 'ወንድሜ ነው' በዪ አልኳት።"
\v 14 ከዚያ አቤሜሊክ በጎችና በሬዎች፣ ወንዶችና ሴቶች ባሪያዎች ለአብርሃም ሰጠው። ሚስቱ ሣራንም ለአብርሃም መለሰለት።
\s5
\v 15 አቤሜሌክ እንዲህ አለ፤ "አገሬ አገርህ ነው፤ ደስ በሚያሰኝህ ቦታ ተቀመጥ።"
\v 16 ሣራንም፣ "ለወንድምሽ አንድ ሺህ ጥሬ ብር እሰጠዋለሁ። ይህም፣ በአንቺ ላይ ለተፈጸመው በደል ካሣ እንዲሆንና አብረውሽ ያሉ ሁሉ አንቺ ንጹሕ ሴት መሆንሽን እንዲያውቁ ነው።"
\s5
\v 17 ከዚያም አብርሃም ለአቤሜሌክ ጸለየ፤ እግዚአብሔርም አቤሜሌክን፣ ሚስቱንና ሴት አገልጋዮቹን ፈወሳቸው፤ ልጅ ለመውለድም በቁ።
\v 18 ከአብርሃም ሚስት ከሣራ የተነሣ በአቢሜሌክ ቤት የሚገኙ ሴቶችን ሁሉ ያህዌ ማኅፀናቸውን ዘግቶ ነበር።
\s5
\c 21
\p
\v 1 ለአብርሃም በሰጠው የተስፋ ቃል መሰረት እግዚአብሔር ሳራን አሰባት፤ እንደገባላት የተስፋ ቃልም አደረገ ፤
\v 2 ስለዚህም ሳራ አርግዛ በእርጅናው ጊዜ ለአብርሃም ወንድ ልጅ ወለደችለት፤ ልጁም የተወለደው «በዚህ ጊዜ ይወለዳል» ብሎ እግዚአብሔር በተናገረበት ጊዜ ነው።
\v 3 አብርሃም ሚስቱ ሳራ የወለደችለትን ልጅ «ይስሐቅ» ብሎ ስም አወጣለት።
\v 4 ይስሐቅ ከተወለደ ከስምንት ቀን በኋላ እግዚአብሔር ባዘዘው መሰረት አብርሃም ገረዘው።
\s5
\v 5 ልጁ ይስሐቅ በተወለደለት ጊዜ አብርሃም መቶ ዓመት ሆኖት ነበር።
\v 6 ሳራም «እግዚአብሔር ሳቅ አደረገልኝ ስለዚህ ይህንን ነገር የሚሰማ ሁሉ ከእኔ ጋር ይስቃል»አለች።
\v 7 ቀጥላም «ሳራ ለአብርሃም ልጆችን ወልዳ ታጠባለች» ብሎ የሚናገር ከቶ ማን ነበር አሁን ግን እነሆ በእርጅናው ዘመን ወንድ ልጅ ወለድሁለት» አለች።
\s5
\v 8 ልጇም አድጎ ጡት መጥባት ተወ፤ ጡት ባስጣሉበትም ቀን አብርሃም ታላቅ ግብዣ አደረገ።
\v 9 ግብጻዊትዋ አጋር ለአብርሃም የወለደችለት እስማኤል ከዕለታት አንድ ቀን በሳራ ልጅ በይስሐቅ ላይ ሲያሾፍበት ሳራ አየች።
\s5
\v 10 ስለዚህ ሳራ አብርሃምን«ይህችን አገልጋይ ከነ ልጅዋ ወዲያ አባርልኝ የዚህች አገልጋይ ልጅ ከልጄ ከይስሐቅ ጋር አብሮ መውረስ አይገባውም» አለችው።
\v 11 እስማኤልም ልጁ ስለሆነ ይህ ጉዳይ አብርሃምን በብርቱ አስጨነቀው
\s5
\v 12 እግዚአብሔር ግን አብርሃምን «ስለ ልጁና ስለ አገልጋይቱ ስለ አጋር አትጨነቅ። ዘር የሚወጣልህ በይስሃቅ በኩል ስለሆን እርሳ የምትልህን ሁሉ አድርግ።
\v 13 የአገልጋይቱም ልጅ የአንተ ዘርያ ስልሆን ታላቅ ሕዝብ አደርገዋለሁ» አለው
\s5
\v 14 አብርሃም በማለዳ ተነሳ ጥቂት ምግብ ውሃም በአቁማዳ ለአጋር በትከሻዋ አደረገላት። ልጁንም በጀርባዋ አሳዝሎ ከቤት አስወጣት፤ እርስዋም በቤርሳቤህ በረሃ ትንከራተት ጀመር።
\v 15 በአቁማዳ የነበረው ውሃ ባለቀ ጊዜ ልጁን በቁጥቋጦ ስር አስቀምችጠችው።
\v 16 እርስዋም «ልጄ ሲሞት ማየት አልፈልግም» በማለት ጥቂት ከልጅዋ ርቃ ተቀመጠች፤ እዚያም ሆና ድምጻን ከፍ አድርጋ ታለቅስ ጀመር።
\s5
\v 17 እግዚአብሔሬም ልሉ ምርር ብሎ ሲያለቅስ ሰማ የእግዚአብሔርም መልአክ ከሰማይ አጋርን «አጋር ሆይ የምትጨነቂበት ነገር ምንድር ነው? እግዚአብሔር የልጂን ለቅሶ ሰምቶአልና አትፍሪ።
\v 18 ተነሺ ሂንና ልጁን አንስተስ አባብይው፤ የእርሱንም ዘር አበዛለሁ ታላቅ ሕዝብም አደርገዋለሁ።
\s5
\v 19 በዚህም ጊዜ እግዚአብሔር ዓይኖችዋን ከፈተላትና አንድ የውኃ ጉድጋድ አየች፤ ሄዳም በአቁማዳ ውሃ ሞላች ለልጅዋም አጠጣችው።
\v 20 ልጁ እያደገ በሚሄድበት ጊዜ ሁሉ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበር።
\v 21 በፋራንም በረሓ ኖረ፤ ቀስት በመወርወርም የታወቀ አዳኝ ሆነ። እናቱም ከአንዲት ግብጻዊት ጋር አጋባችው።
\s5
\v 22 በዚያን ጊዜ አቤሜሌክ ከሰራዊቱ አለቃ ከፊኮል ጋር ሄደና አብርሃምን «በምታደርገው ሁሉ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው፤
\v 23 እኔንም ሆነ ልጆቼን ወይም ዝርያዎቼን እንዳትዋሸኝ አሁን በእግዚአብሔር ስም ማልልኝ። እኔ ለአንተ ታማኝነትን አሳይቻለሁ፤ አንተም ለእኔና ለዚህች ለምትኖርባትአገር ታማኝንትን እንደምታሳይ ማልልኝ» አለው።
\v 24 አብርሃምም «እሺ እምላለሁ» አለ።
\s5
\v 25 አብርሃም የአቢሜሌክ አገልጋዮች ስለ ወሰዱበት የውሃ ጉድጋድ ለአቤሜሌክ አቤቱታ አቀረበ፤
\v 26 አቤሜሌክም «ይህን ያደረገ ማን እንደሆን አላውቅም። አንተም አልነገርኸኝም ይህንን ነገር ገና ዛሬ መስማቴ ነው» አለው።
\v 27 ከዚህ በኋላ አብርሃም ብዙ በጎችና ከብቶች አምጥቶ ለአቢሜሌክ ሰጠው፤ በዚያን ቀን ሁለቱም የስምምነት መሀላ አደረጉ።
\s5
\v 28 በዚያን ጊዜ አብርሃም ሰባት እንስት የበግ ጠቦቶችን ከመንጋው ለየ፤
\v 29 አቤሜሌክም «እንዚህን ሰባት ጠቦቶች ለይተህ ያቆምሃቸው ለምንድር ነው?» አለው።
\v 30 አብርሃምም «እነዚህን ሰባት እንስት ጠቦቶች ተቀበለኝ እነርሱን ከተቀበልከኝ ይህን ጉድጋድ የቆፈርሁ እኔ መሆኔን ምስክር እንዲሆን ነው» አለው፤
\s5
\v 31 ሁለቱ ተማምለው የተስማሙበት ስፍራ በመሆኑ የዚያ ቦታ ስም ቤርሳቤህ ተባል፤
\v 32 ይህን ስምምንት በቤርሳቤህ ተስማምተው ካደረጉ በኋላ አቤሜሌክና የሰራዊቱ አለቃ ፊኮል ወደ ፍልስጥኤም ምድር ተመለሱ
\s5
\v 33 ከዚህ ብኃላ አብርሃም በቤርሳቤህ የታማሪስክ ዛፍ ተከልና የዘላለም አምላክ ለሆነው ሰገደ፤
\v 34 አብርሃም በፍልስጥኤም ምድር በእንግድነት ለረዥም ጊዜ ኖረ።
\s5
\c 22
\p
\v 1 ሁሉ ነገር በኋላ እግዚአብሔር አብርሃምን ፈተነው፤ እግዚአብሔርም «አብርሃም»ብሎ ጠራው፤ «እነሆ አለሁኝ» ብሎ መለሰ።
\v 2 እግዚአብሔርም «የምትወደውን አንድ ልጅህን ወደ ሞሪያ ምድር ሂድ። እዚያ በማሳይህ አንድ ኮረብታ ላይ እርሱን የሚቃጠል መስዋዕት አድርገህ አቅርብልኝ» አለው፤
\v 3 አብርሃም በማለዳ ተነስቶ ለመስዋዕት የሚሆን እንጨት ቆረጠና በአህያው ላይ ጫነው፤ከእርሱ ጋር ልጁን ይስሐቅን ና ሁለት ወጣት ሰዎችን ይዞ እግዚአብሔር ወደ ነገረው ቦታ ለመሄድ ጉዞ ጀመረ።
\s5
\v 4 በሦስተኛው ቀን አብርሃም ቀና ብሎ ሲመለከት ቦታውን በሩቅ አየ።
\v 5 ከዚህ በኃላ አብርሃም የርሱን ወጣቶች «እናንተ ከአህያው ጋር በዚህ ቆዩ እኔና ልጄ ወደዚያ ሄደን ከሰገድን በኃላ እንመለሳለን፤
\v 6 አብርሃምም የሚቃጠለውን መስዋዕቱን ማቃጠያ እንጨት አንስቶ ለልጁ ለይስአቅ አሸከመው፤ እርሱ ግን ቢላዋውንና እሳቱን ያዘ ሁለቱም አብረው ሄዱ።
\s5
\v 7 ይስሐቅ አብርሃምን «አባባ» አለው፤ እርሱም «እነሆ አለሁ ልጄ» አለው፤ ይስሐቅም «እነሆ እሳትና እንጨት ይዘናል ታዲያ ለመስዋዕት የሚሆነው በግ የት አለ?» በማለት አብርሃምን ጠየቀው።
\v 8 አብርሃምም «ልጄ ሆይ ለመስዋዕት የሚሆነውን በግ እግዚአብሔር እራሱ ያዘጋጃል» አለው። ሁለቱም አብረው መንገዳቸውን ቀጠሉ።
\s5
\v 9 እግዚአብሔር ነገረው ቦታ በደረሱ ጊዜ አብርሃም መሰዊያ ሰርቶ እንጨቱን ረበረበው፤ ልጁን ይስሐቅንም አስሮ ከእንጨቱ በላይ በመሰዊያው ላይ አጋደመው።
\v 10 ልጁን ለማረድ ቢላዋ አንስቶ እጁን ዘረጋ።
\s5
\v 11 ነገር ግን የእግዚአብሔር መልአክ ከሰማይ «አብርሃም! አብርሃም!» ብሎ ጠራው። እርሱም «እነሆኝ አለሁኝ» አለ።
\v 12 እርሱም «በልጁ ላይ እጅህን አትጫንበት፣ ምንም ዓይነት ጉዳትም አታድርስበት፣ እነሆ እግዚአብሔርን የምትፈራ መሆንህን ተረድቻለሁ፤ አንድ ልጅህን እንኳ ለእኔ ከመስጠት አልተቆጠብህም» አለው።
\s5
\v 13 አብርሃም ዙሪያውን በተመለከት ጊዜ ከበስተጀርባው ቀንዶቹ በቁጥቋጥ ዛፍ የተያዙ አንድ በግ አየ፤ አብርሃምም ሄዶ በጉን አመጣና በልጁ ፋንታ የሚቃጠል መስዋዕት አድርጎ አቀረበው።
\v 14 አብርሃምም ያን ቦታ «እግዚአብሔር ያዘጋጃል» ብሎ ጠራው። ዛሬም ቢሆን ሠዎች «እግዚአብሔር በተራራው ላይ ያዘጋጃል» ይላሉ።
\s5
\v 15 የእግዚአብሔር መልአክ ለሁለተኛ ጊዜ አብርሃምን ከሰማይ ጠራውና፤
\v 16 እንዲህ አለው፤ «እግዚአብሔር ብዙ በረከት እንድምሰጥህ በራሴ ስም እምላለሁ» ይላል፤ ይህን ስላደረግህና አንድ ልጅህንም ለእኔ ለመስጠት ስላልተቆጠብህ፤
\v 17 እኔም ዘርህን እንደ ሰማይ ከዋክብትና እንደ ባህር ዳር አሸዋ አበዛዋለሁ፤ ዝርያዎችህም ጠላቶቻቸውን ድል ነስተው፤ ከተሞቻቸውን ይይዛሉ።
\s5
\v 18 ትዕዛዜን ስለ ፈጸምህ የዓለም ህዝቦች ሁሉ በዘርህ ይባረካሉ»፤
\v 19 ከዚህ በኋላ አብርሃም ወደ ወጣቶችሁ ተመለሰና በአንድነት ሆነው ወደ ቤርሳቤህ ሄዱ፤ አብርሃምም በቤርሳቤህ ተቀመጠ።
\s5
\v 20 ከዚህ ሁሉ በኋላ እንዲህ ተብሎ ለአብርሃም ተነገረው «ሚልካ ልጆችን ለወንድምህ ለናኮር ወልዳለች፤
\v 21 እነርሱም የመጀመሪያው ልጅ ዑፅ ወንድሙም ቡዝ የአራም አባት ቀሙኤል፤
\v 22 ኬሰድ፣ ሐዞ፣ ፊልዳሽ፤ ይድላፍና በቱኤል ናቸው።
\s5
\v 23 በቱኤል ርብቃን ወለደ። ሚልካ እነዚህን ስምንት ልጆች ለአብርሃም ወንድም ለንኮር ወለደችለት፤
\v 24 ረኡማ የተባለች የናኮር ቁባት ደግሞ ጤባሕን፣ ገሐምን፣ ተሐሽና ማዕካን ወለደችለት።
\s5
\c 23
\p
\v 1 ሣራ መቶ ሃያ ሰባት ዓመት ኖረች። እነዚህን ዓመታት ነበር ሳራ የኖረችው።
\v 2 በከነዓን ምድር ባለችው ቂርያት አርባ ተብላ በምትጠራው በኬብሮን ከተማ ሞተች፤ አብርሃም በሣራ ሞት ምክንያት እጅግ ሃዘነ አለቀሰም።
\s5
\v 3 ከዚያም አብርሃም ከተቀመጠበት ከሚስቱ ሬሳ አጠገብ ተነሳ፣ ኬጢያውያንን እንዲህ አላቸው፤
\v 4 «እኔ በመካከላችሁ በእንግድነት የምኖር ነኝ። እባካችሁ የመቃብር ቦታ ስጡኝ፤ የሚስቴንም ሬሳ ልቅበርበት።»
\s5
\v 5 የኬጢ ልጆችም ለአብርሃም እንዲህ ሲሉ መለሱለት፤
\v 6 «ጌታ ሆይ ስማን፣ አንተ በእኛ መካከል ከእግዚአብሔር አለቃ ነህ። ከመቃብር ቦታችን በመረጥከው ስፍራ ሬሳህን መቅበር ትችላለህ፣ ማናችንም ብንሆን የሞተብህን ሰው እንዳትቀብርበት የምቃብር ቦታችንን አንከለክልህም።»
\s5
\v 7 አብርሃም ተነሣ በኬጢያውያን ልጆች ፊት እጅ ነስቶ እንዲህ አለ።
\v 8 የሚስቴን አስከሬን እዚህ እንድቀብር ከፈቀዳችሁልኝ የጾሐር ልጅ ዔፍሮምን ስለ እኔ ሆናችሁ ልምኑልኝ፤
\v 9 በእርሻው ዳር ያለችውን መክፈል የተባለችውን ዋሻውን እንዲሸጥልኝ ጠይቁልኝ፣ ይህ ስፍራ የመቃብር ቦታ እንዲሆንልኝ በእናንት ፊት ሙሉ ዋጋ ከፍዬ እንድገዛው አድርጉልኝ።»
\s5
\v 10 ኤፍሮንም በኬጢ ልጆች መካከል ተቀምጦ ነበር፤ የኬጢም ሰው ኤፍሮንም የኪጥ ልጆችና ወደ ከተማ የሚገቡ ሲስሙ ለአብርሃም እንዲህ ሲል መለሰለት፤
\v 11 «አይደለም ጌታዬ፣ ስማኝ። እርሻውን፣ በርሱም ዳር ያለውን ዋሻ፤ በወገኔ ልጆች ፊት ሰጥቼአለሁ። ሬሳህን ቅበር።»
\s5
\v 12 አብርሃምም በአገሩ ሰዎች ፊት ሰገደ።
\v 13 የአገሩ ሰዎችም እየሰሙ ለኤፍሮን እንዲህ ሲል ተናገረ፤ «እባክህ ፈቃደኛ ብትሆን አድምጠኝ፤ የእርሻውን ዋጋ እሰጥሃለሁ። አንተም ከእኔ ዘንድ ውሰድ፤ ሬሳዬንም በዚያ እቀብራለሁ
\s5
\v 14 ኤፍሮንም ለአብርሃም እንዲህ ሲል መለሰለት፤
\v 15 «ጌታዬ ሆይ እኔን ስማኝ፤ የመሬቱ ዋጋ እራት መቶ ሰቅል ቢሆን ነው፤ ታዲያ ይሄ በእኔና በአንተ መካከል ምንድር ነው? ሬሳህንም ቅበር»
\v 16 አብርሃምም የኤፍሮንን ነገር ሰማ፤ አብርሃምም በኬት ልጆች ፊት የነገረውን አራት መቶ ሰቅል መዝኖ ለኤፍሮን ሰጠው፤ ብሩንም በወቅቱ የንግድ መለኪያ መሰረት መዘነለት።
\s5
\v 17 በዚህም ሁኔታ በመምሬ አጠገብ በመክፈላ ያለውን የኤፍሮንን እርሻ ቦታ ከነዋሻው በከልሉ ካሉት ዛፎች ሁሉ ጭምር ለአብርሃም በርስትነት ተላለፈ፤
\v 18 እርሻው በእርሱ ያለውን ዋሻው በእርሻውም ውስጥ በዙሪያውም ያለው እንጨት ሁሉ በኬጢ ልጆችና በከተማይቱ በር በሚገቡ ሁሉ ፊት ለአብርሃም ርስቱ ሆነ።
\s5
\v 19 ከዚያም በኋላ ኬብሮን በምትባል በምምሬ ፊት በከነአን ፊት ባለው እርሻ ባለ ድርብ ክፍሌ በሆነው ዋሻ ውስጥ ሚስቱን ሳራን ቀበረ።
\v 20 እርሻውና በርሱ ያለው ዋሻው በኪጥ ልጆች ዘንድ ለአብርሃም የመቃብር ርስት ሆኖ ጸና።
\s5
\c 24
\p
\v 1 በዚህ ጊዜ አብርሃም ሸመገለ፤ ዕድሜውም ገፋ፤ እግዚአብሔርም አብርሃምን በሁሉ ነገር ባረከው።
\v 2 አብርሃምም የንብረቱ ሁሉ ኀላፊ የቤቱ ሁሉ አዛዥ የሆነውን አገልጋይ እንዲህ አለው፤ እጅህን ከጭኔ በታች አድርግ
\v 3 እኔም በመካከላቸው ከምኖረው ከከነዓናዊያን ለልጄ ሚስት እንዳታጭለት በሰማይና በምድር አምላክ እግዚአብሔር አስምልሃለሁ።
\v 4 ነገር ግን ወደ ገዛ ሀገሬ እና ወደ ወገኖቼ ሄደህ ለልጄ ለይስሐቅ ሚስትን ታጭለታለህ።
\s5
\v 5 አገልጋዩም «ምናልባት የምመርጥለት እጮኛ ከእንይ ጋሬ ወደዚህ አገር ለመምጣት እምቢ ብትልስ? ልጅህን ቀድሞ አንተ ወደ ነበርክበት አገር እንዲመለስ ላድርገው?» ብሎ ጠየቀ።
\v 6 አብርሃም ግን እንዲህ አለው፤ «በምንም ዓይነት ምክንያት ቢሆን ልጄን ወደዚያ አገር መልሰህ እንዳትወስድ ተጠንቀቅ፤
\v 7 የሰማይ አምክክ እግዚአብሔር ከአባቴ ቤትና ከትውልድ አገሬ አውጥቶ አምጥቶኛል፤ ይህንንም ምድር ለዝርያዎቼ እንደሚሰጥ በመሃላ ቃል ገብቶልኛል፤ ከዚያ ለልጄ ሚስት ማግኘት እንድትችል እግዚአብሔር መልአኩን በፊትህ ይልካል።
\s5
\v 8 ልጅትዋ ከአንተ ጋር ለመምጣት ፈቃደኛ ባትሆንከዚህ መሓላ ነፃ ትሆናለህ፤ ልጄን ግን በምንም ዓይነት ሁኔታ ወደዚያ አትመልሰው።»
\v 9 ከዚህ በኋላ አገልጋዩ እጁን በጌታው በአብርሃም ጉልበት ላይ አድርጎ አብርሃም ያዘዘውን ሁሉ እንደሚፈፅም በመሐላ ቃል ገባ።
\s5
\v 10 የአብርሃም ንብረት ኀላፊ የነበረው መጋቢ ከጌታው ቤት ምርጥ የሆኑ የስጦታ ዕቃዎችን በዕሥር ግመሎች ጭኖ በሰሜን መስጴጦምያ ናኮር ወደሚኖርበት ከተማ ሄደ።
\v 11 እዚያ በደረሰ ጊዜ ከከተማው ውጭ ባለ የውሃ ጉድጓድ አጠገብ ግመሎቹ ተንበርክከው እንዲያርፉ አደረገ፤ ሰዓቱም ሊመሽ ተቃርቦ፣ ሴቶች ውሃ ለመቅዳት የሚወጡበትን ጊዜ ነበር፤
\s5
\v 12 አገልጋዩ እንዲህ ብሎ ጸለየ፣ "የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! ዛሬ የእኔን አሳብ በመፈፀም ለጌታዬ ለአብርሃም ዘላለምዊ ፍቅርህን ግለጥ።
\v 13 እነሆ፣ እኔ በዚህ የውሃ ጉድጓድ አጠገብ ቆሜአለሁ፤ የከተማይቱም ልጃገረዶች ውሃ ሊቀዱ ወደዚህ ይመጣሉ፤
\v 14 ከእነሱም አንድዋ ልጃገረድ 'እንስራሽን ዘንበል አድርገሽ ውሃ አጠጪኝ' እላታለሁ፤ 'አንተም ጠጣ፤ ግመሎችህም እንዲጠጡ ውጃ ቀድቼ አመጣለሁ' ካለችኝ ለአገልጋይህ ለይስሐቅ ፍቅርህን እንዳሳየኸው ዐውቃለሁ።"
\s5
\v 15 ገና ጸሎቱን ሳፅቸርስ ርብቃ እንስራ ተሸክማ መጣች፤ የዚህችም ልጅ አባት ባቱኤል ይባል ነበር፤ እርሱም የአብርሃም ወንድም ናኮር ከሚስቱ ከሚልካ የወለደው ነው።
\v 16 ርብቃ ገና ወንድ ያልደረሰባት በጣም ቆንጆ ልጃገረድ ነበረች፤ እርስዋ ወደ ውሃው ጉድጓድ ወርዳ በእንስራዋ ውሃ ከቀዳች በኋላ ተመለሰች።
\s5
\v 17 አገልጋዩም ወደ እርስዋ ሮጦ ሄዳና "እባክሽ ከእንስራሽ ከእንስራሽ ጥቂት ውሃ አጠጪኝ"አላት።
\v 18 እርስዋም "እሺ ጌታዬ ጠጣ" አለችና እንስራዋን ከትከሻዋ አውርዳ ዘንበል አድርጋ ያዘችለት።
\s5
\v 19 ጠጥቶም ከረካ በኋላ "ለግመሎችህም ውሃ እቀዳላቸዋለሁ፤ እስኪበቃቸውም ድረስ ይጠጡ" አለችው።
\v 20 ወዲያውኑ፤ በእንስራዋ የያዘችውን ውሃ ግመሎቹ በሚጠጡበት ገዳን ላይ ገልብጣ ግመሎቹ ሁሉ ጠጥተው እስከሚረኩ ድረስ እየተጣደፈች ከጉድጓድ ውሃ መቅዳት ቀጠለች።
\s5
\v 21 ሰውየውም እግዚአብሔር የሄደበትን ተልእኮ አቃንቶለት እንደሆን ለማረጋገጥ የምታደርገውን ሁሉ ዝም ብሎ ይመለከት ነበር።
\v 22 ግመሎቹ ጠጥተው በኋላ ሰውየው አምስት ግራም ያህል የሚመዝን የወርቅ ጎታቻ አውጥቶ በጆሮዋ ላይ አደረገላት፤ መቶ ዐሥር ግራም ያህል የሚመዝን ሁለት የወርቅ አምባሮችንም አውጥቶ በእጆችዋ ላይ አደረገላትና፤
\v 23 "የማን ልጅ ነሽ? እስቲ እባክሽ ንገሪኝ፤ ለእኔና አብረውኝ ቤት ይገኛልን?" ብሎ ጠየቃት።
\s5
\v 24 እርስዋም "የባቱኤል ልጅ ነኝ፤ የባቱኤል አባት ናኮር፣ እናቱም ሚልካ ይባላሉ፤
\v 25 በቤታችን ብዙ ገለባና ድርቆሽ አለ፤ ለእናንተም ማደሪያ ቦታ ይገኛል" አለችው።
\s5
\v 26 ሰውየምውም በመንበርከክ ለእግዚአብሔር ሰግዶ፣
\v 27 "ለጌታዬ የገባውን ቃል ኪዳንና ዘላለማዊ ፍቅሩን የጠበቀ የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን፤ በቀጥታ መርቶ ወደ ጌታዬ ወንድሞች ቤት ያመጣኝ እርሱ ነው" አለ።
\s5
\v 28 ልጅትዋ ወደ ቤት ሮጣ ሄደችና የሆነውን ሁሉ ለእናትዋና ለእርስዋ ጋር ላሉት ሁሉ ነገረቻቸው።
\v 29 ርብቃ ላባ የተባለ ወንድም ነበራት፤ እርሱ የአብርሃም አገልጋይ ወዳለበት ውሃ ጉድጓድ እየሮጠ ሄደ።
\v 30 ላባ ወደ ሰውየው የሄደው እኅቱ በጆሮዋ ላይ ያደረገችውን ጉትቻና በእጆችዋ ላይ ያደረገቻቸውን አንባሮች ስላየና ርብቃ ሰውየው ጉድጓድ አጠገብ ከግመሎቹ ጋር ቆሞ አገኘው።
\s5
\v 31 ስለዚህ ላባ "አንተ እግዚአብሔር የባረከህ ሰው! ና ወደ ቤት እንሂድ፤ በውጭ የቆምኸው ለምንድን ነው? በቤታችን ለአንተ ማደሪያ የተዘጋጀ ቦታ አለ" አለው።
\v 32 ከዚህ በኋላ ሰውየው ወደ ቤት ሄደ፤ ላባም በግመሎቹ ላይ የነበረውን ጭነት አረግፎ ገለባና ድርቆሽ አቀረበላቸው፤ ቀጥሎም የአብርሃም አገልጋይና አብረውት የነበሩት ሰዎች እግራቸውን የሚታጠቡበትን አመጣላቸው።
\s5
\v 33 ገበታ በቀረበው ጊዜ ጊዜ ሰውየው "የተላክሁበትን ጎዳይ ከመናገሬ በፊት እህል አልቀምስም" አለ። ላባም "ይሁን ተናገር" አለው።
\v 34 እርሱም "እኔ የአብርሃም አገልጋይ ነን፤
\v 35 እግዚአብሔር ጌታዬ እጅግ ባርኮል፤ ባለጸጋም አድርጎታል፤ ብዙ የበግ፣ የፍየልና የከብት መንጋ፣ ብርና ወርቅ፣ ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮች ግመሎችና አህዮች ሰጥቶታል።
\s5
\v 36 የጌታዬ ሚስት ሣራ በእርጅናዋ ዘምን ወንድ ልጅ ወልዳለታለች፤ ጌታዬም ያለውን ሀብት ሁሉ ለዚሁ ልጅ አውርሶታል።
\v 37 ጌታዬ አብርሃም 'እኔ በመካከላቸው ከምኖረው ከከነዓናዊያን ሴቶች ልጆች መካከል ለልጄ ሚስት እንዳላጭለት፤
\v 38 ነገር ግን ወደ አባቴ ቤተሰብና ወደ ዘመዶቼ ሄደህ ለልጄ ሚስት እጭለት' ሲል በመሐላ ቃል ኪዳን አስገብቶኛል።'
\s5
\v 39 እኔም ጌታዬን 'ልጅቷ ከእኔ ጋር ለመምጣት ፈቃደኛ ባትሆንስ ምን ላድርግ?' ብዬ ጠየኩት።
\v 40 እርሱም እንዲህ አለኝ 'ዘውትር የማገለግለው እግዚአብሔር መልአኩን ከአንተ ጋር ይልካል፤ ጉዞህም የተቃና እንዲሆን ያደርጋል፤ በዚህ ሁኔታ አንተም ከአባትቴ ቤተሰብና ከዘመዶቼ መካከል ለልጄ ሚስት ልታጭለት ትችላለህ፤
\v 41 ከመሐላህ ነፃ የምትሆነው ወደ ዘመዶቼ ሄደህ እነርሱ ልጅትዋን አንሰጥም ብለው የከለከሉህ እንደሆነ ብቻ ነው።'
\s5
\v 42 "ከዚያም በኋላ ዛሬ ወደ ውሃው ጉድጓድ ስመጣ እንዲህ ብዬ ጸለይሁ 'የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! እባክህ የመጣሁበት ጉዳይ እንዲቃና አድርግልኝ፣
\v 43 እነሆ በዚህ ውሃ ጉድጓድ አጠገብ ቆሜአለሁ፤ አንዲት ልጃገረድን ውሃ ልትቀዳ ስትመጣ፣ 'እባክሽ ከእንስራሽ ጥቂት ውሃ አጠጪኝ' ብዬ እጠይቃታለሁ፤
\v 44 እርስዋም 'እሺ ጠጣ፤ ለግመሎችህም እቀዳቸዋለሁ'የምትለኝ ብትሆን፣ ለጌታዬ ልጅ ሚስት እንድትሆን አንተ የመረጥሃት እርስዋ ትሁን።
\s5
\v 45 የኅሊና ጸሎትን ገና ሳልጨርስ ርብቃ እንስራ ተሸክማ ብቅ አለች፤ ወደ ጉድጓዱም ሄዳ ውሃ ቀዳች፤ እኔም 'እባክሽ ጥቂት ውሃ አጠጪኝ አልኋት።
\v 46 እርስዋም እንስራዋን በፍጥነት ከጀርባዋ አወረደችና ዘንበል አድርጋ 'እሺ ጠጣ፤ ግመሎችህንም አጠጣልሃለሁ' አለችኝ፤ ስለዚህ እኔም ጠጣሁ፤ ግመሎቼንም አጠጣችልኝ።
\s5
\v 47 እኔም 'የማን ልጅ ነሽ?' ብዬ ጠየቅኋት። እርስዋም 'የባቱኤል ልጅ ነኝ፤ የባቱኤል አባት ናኮር እናቱም ሚልካ ይባላሉ' አለችኝ። ከዚህ በኋላ ጉትቻ በጆሮዋ ላይ፣ አንባሮቹንም በእጅዎችዋ ላይ አደረግሁላት፤
\v 48 ከዚህ በኋላ በጉልበቴ ተንበርክኬ ለእግዚአብሔር ሰገድሁ፤ የጌታዬን የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር አመሰገንሁ፤ ምክንያቱም ለጌታዬ ልጅ ሚስት የምትሆነዋን ሴት ወዳገኘሁበት ወደ ጌታዬ ወንድም ቤት በቀና መንገድ የመራኝ እርሱ ነው።
\s5
\v 49 እንግዲህ የጌታዬን ዐደራ በእውነት ተቀብላችሁ እርሱን ደስ ለማሰኘት የምትፈቅዱ እንደሆነ ንገሩኝ፤ የማትፈቅዱም እንደሆነ ቁርጡን ነገሩኝ፤ እኔም እግዚአብሔር ወደሚመራኝ እሄዳለሁ።"
\s5
\v 50 ላባና ባቱኤልም "ይህ ነገር ከእግዚአብሔር የመጣ ስለሆነ፣ መከልከል አልችልም፤
\v 51 ርብቃ ይችውልህ፤ እነሆ ይዘሃት ሂድ፤ እግዚአብሔር ራሱ እንደተናገረው ለጌታዬ ልጅ ሚስት ትሁን" አሉት።
\s5
\v 52 የአብርሃም አገልጋይ ይህን በሰማ ጊዜ በጉልበቱ ተንበርክኮ ለእግዚአብሔር ሰገደ፤
\v 53 ከውርቅና ከብር የተሠሩ ጌጣጌጦችን፣ እንዲሁም ልብስ አውጥቶ ለርብቃ ሰጣት፤ ለወንድምዋና ለእናትዋም በጣም ውድ የሆኑ ስጦታዎችን አውጥቶ ሰጣቸው።
\s5
\v 54 ከዚህ በኋላ የአብርሃም አገልጋይና አብረውት የነበሩ ሰዎች በልተው ጠጥተው እዚያው አደሩ፤ ጠዋት በተነሡ ጊዜ የአብርሃም አገልጋይ "እንግዲህ ወደ ጌታዬ እንድመለስ ፍቀዱልኝ" አለ።
\v 55 ነገር ግን የርብቃ ወንድምና እናትዋ "ልጅትዋ ዐሥር ቀን ያህል ከእኛ ጋር ትቆይ፤ ከዚህ በኋላ ከአንተ ጋር ልትሄድ ትችላለች" አሉት።
\s5
\v 56 እርሱ ግን "እባካችሁ አታቆዩኝ፤ እግዚአብሔር የመጣሁበትን ጉዳይ ስላቃናልኝ ቶሎ ብፄ ወደ ጌታዬ ልመለስ" አላቸው።
\v 57 እነርሱም "እስቲ ልጅቷን እንጥራትና እርስዋ የምትለውን እንስማ" አሉ።
\v 58 ስለዚህ ርብቃን ጠሩና "ከዚህ ሰው ጋር መሄድ ትፈልጊያለሽ?" ብለው ጠየቅዋት። እርስዋም "አዎ እሄዳለሁ"አለች።
\s5
\v 59 ስለዚህ ርብቃ ሞግዚትዋን አስከትላ፣ ከአብርሃም አገልጋይና ከእርሱ ሰዎች ጋር እንድትሄድ ፈቀዱላት።
\v 60 "አንቺ እኅታችን የብዙ ሺ ሕዝብ እናት ሁኚ፤ ዝርያዎችሽም የጠላቶችሽን ከተሞች ይውረሱ" ብለው ርብቃን መረቁአት።
\s5
\v 61 ከዚህ በኋላ ርብቃ ከተከታዮችዋ ጋር ለመሄድ ተነሣች፤ በግመሎቹ ላይ ተቀምጠው ከአብርሃም አገልጋይ ጋር ለመሄድ ተዘጋጁ። በዚህ ዐይነት የአብርሃም አገልጋይ ርብቃን ይዞ ሄደ።
\v 62 በዚህ ጊዜ ይስሐቅ "ብኤር ላሐይ ሮኤ ወይም የሚያየኝን ሕያው አምላክ"የተባለው ኩሬ ወዳለበት በረሓ መጥቶ በኔጌብ ተቀምጦ ነበር።
\s5
\v 63 ከለዕታት አንድ ቀን ወደ ማታ ጊዜ እያሰላሰለ በመስክ ውስጥ ሲዘዋወር ሳለ ግመሎች ሲመጡ በሩቅ አየ።
\v 64 ርብቃ ይስሐቅ ባየች ጊዜ ከግመሏ ወረደችና፣
\v 65 "ያ በመስክ ውስጥ ወደ እኛ የሚመጣው ሰው ማን ነው?" ስትል የአብርሃምን አገልጋይ ጠየቀችው። አገልጋዩም "እርሱ ጌታዬ ነው!" አላት። ስለዚህ በጥፍነት በሻሽ ፊትዋን ሸፈነች።
\s5
\v 66 አገልጋዩም ያደረገውም ነግር ሁሉ ለይስሐቅ ነገረው።
\v 67 ከዚህ በኋላ ይስሐቅ እናቱ ሣራ ትኖርበት ወደነበረው ድንኳን ርብቃን ይዞአት ገባ፤ ሚስትም ሆነችው፤ ይስሐቅ ርብቃን ወደዳት፤ በእናቱ ሞት ምክንያት ከደረሰበትም ሐዘን በዚህ ሁኔታ ተጽናና።
\s5
\c 25
\p
\v 1 አብርሃም ቀጡራ የምትባል ሌላ ሚስት አገባ፤
\v 2 እርስዋም ዚምራንን፣ ዮቅሻንን፣ መዳንን፣ ምድያምን፣ ዩሽባቅንና ሹሐን ወለደችለት።
\v 3 ዮቅሻንም ሳባንና ደዳንን ወለደ፤ የዳደንም ዝርያዎች አሹራውያን፣ ሌጡሻውያንና ሌአማውያን ናቸው።
\v 4 የምድያም ልጆች ዔፋ፣ ዔፈር፣ ሐኖክ፣ አቢዳዕና ኤልዳዓ ናቸው፤ እነዚሁ ሁሉ የቁጠራ ዝርያዎች ናቸው።
\s5
\v 5 አብርሃም ያለው ሀብት ሁሉ ለይስሐቅ አወረሰው፤
\v 6 ከሌሎች ሴቶች ለተወለዱትም ልጆች ገና በሕይወት ሳለ ስጦታ ሰጣቸው፤ ከዚህ በኋላ እነዚህ ሌሎች ልጆች ከይስሐቅ ርቀው ወደ ምሥራቅ አገር እንዲሄዱ አደረጋቸው።
\s5
\v 7 የአብርሃም ዕድሜ በአጠቃላይ መቶ ሰባ አምስት ዓመት ነበር፤
\v 8 በዚህም ዐይነት አብርሃም በቂ ዕድሜ አግኝቶ ካረጀ በኋላ ሞተ፤
\s5
\v 9 ልጆቹ ይሰሐቅና እስማኤል ማክጴላ በተባለ ዋሻ ቀበሩት፤ ይህም ዋሻ ከመምሬ በስተምሥራቅ በሒታዊ በጶሐር ልጅ በዔፍሮን እርሻ ውስጥ የሚገኘው ነው።
\v 10 እነሱም አብርሃም ከሒታዊያን ላይ የገዛው የመቃብር ቦታ ነው፤ በዚህ ዐይነት አብርሃም ሚስቱ ሣራ በተቀበረችበት ዋሻ ተቀበረ።
\v 11 አብርሃም ከሞተ በኋላ ልጁን ይስሐቅን እግዚአብሔር ባረከው፤ ይስሐቅ "ብኤርላሐይሮኢ ወይም የሚያየኝ ሕያው አምላክ" ተብሎ በመጠራት ኩሬ አጠገብ ይኖር ነበር።
\s5
\v 12 የሣራ አገልጋይ ግብፃዊትዋ አጋር ለአብርሃም የወለደችለትን እስማኤል፤
\s5
\v 13 ከዚህ በታች በዕድሜአቸው ቅደም ተከተል ተራ የተዘረዘሩትን ልጆች ወለደ፤ እነርሱም፦ ነባዮት፣ ቄዳር፣ አድብኤል፣ ሚብሣም፣
\v 14 ሚሽማዕ፣ ዱማ፣ ማሣ፣
\v 15 ሐዳድ፣ ቴማ፣ ይጡር፣ ናፊሽና ቄድማ ናቸው።
\v 16 እነዚህ የእስማኤል ልጆች ለአሥራ ሁለት ነገዶች ቅድመ አያቶች ነበሩ፤ ስማቸውም በኖሩባቸው ከተሞችና ስፍራዎች ሲጠራ ይኖራል።
\s5
\v 17 እስማኤል መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ሲሆነው ሞተ።
\v 18 የእስማኤል ዝርያዎች ከግብፅ በስተምጅራቅ ወደ አሦር በምትወስደው መንገድ በሐዊላና በሹር መካከል ይኖሩ ነበር። የኖሩበትም ከሌሎቹ የአብርሃም ዝርያዎች ጋር በጥላቻ ተራርቀው ነበር።
\s5
\v 19 የአብርሃም ልጅ ይስሐቅ ታሪክ ይህ ነው። አብርሃም ይስሐቅን ወለደ።
\v 20 ይስሐቅ የባቱኤልን ልጅ ርብቃን ሲያገባ አርባ ዓመት ሆኖት ነበር፤ የርብቃ አባት ባቱኤልና ወንድምዋ ላባ በመስጴጦምያ የሞኖሩ ሶሪያውያን ነበሩ።
\s5
\v 21 ርብቃ መኻን ስለ ነበረች ይስሐቅ ስለ እርስዋ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ እግዚአብሔርም ጸሎቱን ስለ ሰማ ርብቃ ፀነሰች፤
\v 22 የተፀነሱትም መንትያዎች ስለነበሩ እርስ በርሳቸው በማሕፀንዋ ውስጥ ይገፋ ነበር፤ እርስዋም "ይህን ዐይነት በገር ለምን ደረሰብኝ?" በማለት ወደ እግዚአብሔር ለመጸለይ ተነሣሣች።
\s5
\v 23 እግዚአብሔርም ያሉት ሁለት ሕዝቦች ናቸው፤ እርስ በርሳቸው የማይስማሙ ሁለት ወገኖች ትወልጃለሽ፤ አንዱም ከሌላው የበረታ ይሆናል፤ ታላቁም ታናሹ አገልጋይ ይሆናል" አላት።
\s5
\v 24 የመውለጃዋም ሰዓት በደረሰ ጊዜ ሁለት ወንዶች ልጆች ወለደ።
\v 25 የመጀመሪያው ልጅ መልኩ ቀይ፣ ሰውነቱ ጠጉራም ነበር፤ ስለዚህ ዔሳው ተባለ።
\v 26 ሁለተኛው ልጅ ሲወለድ የዔሳውን ተገረዝ ይዞ በመውጣቱ ያዕቆብ ተባለ፤ ልጆቹ በተወለዱ ጊዜ ይስሐቅ ስልሳ ዓመት ሆኖት ነበር።
\s5
\v 27 ሁለቱም ልጆች አደጉ፤ ዔሳው በዱር መዋል የሚወደ ብልኅ አዳኝ ሆነ፤ ያዕቆብ ግን በቤት መዋል የሚወድ ጭምት ሰው ነበር።
\v 28 ይስሐቅ ዔሳውን ይወድ ነበር። ምክንያቱም ዔሳው እያደነ ሥጋ ያበላው ነበር።ርብቃ ግን ያዕቆብን ትንን ነበር።
\s5
\v 29 ለዕለታት አንድ ቀን ያዕቆብ ቀይ የምስር ወጥ በመሥራት ላይ እንዳለ ዔሳው ከአደን መጣ፤ በጣም እርቦት ነበር፤
\v 30 ስለዚህም ያዕቆብ "ከዚህ ከቀይ ወጥ ሰጠኝ" አለው። ኤዶም የተባለውም ነዚሁ ምክንያት ነበር።
\s5
\v 31 ያዕቆብም "በመጀመሪያ ብኩርናህን ሽጥልኝ" አለው።
\v 32 ዔሳውም "እኔ በረሀብ መሞቴ ነው፤ ታዲያ ብኩርና ምን ያደርግልኛል?" አለው።
\v 33 ያዕቆብም "እንግዲያውስ ብኩርናህን እንደምትሸጥልኝ መጀመሪያ ማልልኝ" አለው። ስለዚህ ዔሳው ምሎ ብኩርናውን ለያዕቆብ ሸጠ።
\v 34 ከዚህ በኋላ ያዕቆብ የምስሩን ወጥ በእንጀራ አድርጎ ሰጠው፤ ዔሳውም ከበላና ከጠጣ በኋላ ተነሥቶ ሄደ፤ በዚህ ዐይነት ዔሳው ብኩርናውን በመናቅ አቃለላት።
\s5
\c 26
\p
\v 1 በአብርሃም ዘመን ከደረሰው ረሀብ ሌላ ዳግመኛ ረሀብ በምድር ላይ መጣ፤ በዚህ ምክንያት ይስሐቅ የፍልስጥኤማዋን ንጉሥ አቢሜሌክ ወዳለበት ወደ ገራር ሄደ፤
\s5
\v 2 በዚህም እግዚአብሔር ለይስሐቅ ተገለጠለትና እንዲህ አለው፣ "ወደ ግብፅ አገር አትሂድ፤ እንድትኖርበትም በምነግርህ በዚህ ምድር ተቀመጥ፤
\v 3 እዚሁ ኑር፤ እኔም ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ እባርክሃለሁ፤ ይህም ምድር ለአንተና ለዝርይዎችህ እሰጣለሁ፤ በዚህ ዐይነት ለአባትህ ለአብርሃም የገባሁትን ቃል ኪዳን እፈፅማለሁ፤
\s5
\v 4 ዘርህን አንደ ሰማይ ክዋክብት አበዛዋልለሁ፤ ይህንንም ሁሉ ምድር አወርሳቸዋለሁ፤ ይህንንም ሁሉ በዘርህ ይባረካሉ።
\v 5 አንተን የምባርክበትንም ምክንያት አባትህ አብርሃም ለእኔ ታዛዥ በመሆን የሰጠሁት ሕግና ሥርዓት ሁሉ ስለ ጠበወ ነው።
\s5
\v 6 ስለዚህ ይስሐቅ መኖሪያውን በገራር አደረገ፤
\v 7 በዚያ አገር ስሰዎችም ስለ ርብቃ "ምንህናት" ብለው በጠየቁት ጊዜ "እኅቴ ናት" አላቸው፤ ይህንንም ያለበት ምክንያት ርብቃ በጣም ቆንጆ ስለ ነበረች የዚያ አገር ሰዎች በእርስዋ ሰበብ እንዳይገድሉት በመፍራት ነው።
\v 8 ይስሐቅ እዚያ አገር ብዙ ጊዜ ከቆያ በኋላ የፍልስጥኤም ንጉሥ አቢሜሌክ በመስኮት ወደ ውጪ ሲመለከት ይስሐቅና ርብቃ እንደባልና ሚስት በመዳራት ሲጫወቱ አየ።
\s5
\v 9 ስለዚህ አቢሜሌክ ይስሐቅን አስጠርቶ "ለካስ ርብቃ ሚስትህ ናት! ታዲያ "እኅቴ ናት' ያልከው ለምንድን ነው?" ሲል ጠየቀው። እርሱም "ሚስቴ ነች ያልኩ እንደሆን ሰዎች ይገድሉኝል ብዬ አስፈራሁ ነው" ብሎ መለሰ።
\v 10 አቢሜሌክ "ይህ በእኛ ላይ ያደረግኸው ነገር ምንድን ነው? ከእኛ ሰዎች አንዱ በቀላሉ ሚስትህን ለመድፈር በቻለ ነበር፤"
\v 11 ቀጥሎም አቢሜሌክ "ይህን ሰው ወይም ሚስቱን የሚነካ ሰው በሞቱ ይቀጣል"የሚል ማስጠንቀቂያ ለሕዝቡ ሰጠ።
\s5
\v 12 ይስሐቅ በዚያች ምድር ዘርን ዘራ፤ እግዚአብሔር ስለባረከውም በዚያኑ ዓመት መቶ እጥፍ አመረተ፤
\v 13 ሀብት በሀብት ላይ እየተጨመረበት ዘመን የእርሱ አገልጋዮች ቁፍረዋቸው የነበሩትን የውሃ ጉድጓዶች ሁሉ ዐፈር ሞልተው ደፈኑአቸው።
\v 14 ብዙ የበግና የከብት መንጋ፤ እንዲሁም ብዙ አገልጋዮች ስለ ነበሩት ፍልስጥኤማውያን ቀኑበት።
\s5
\v 15 ስለዚህ የይስሐቅ አባት አብርሃም በሕይወት በነበረበት ዘመን የእሱን አገልጋዮች ቁፍረዋቸው የነበሩትን ውሃ ጉድጓዶች ሁሉ ዐፈር ሞልተው ደፈኑአቸው።
\v 16 በዚያን ጊዜ አቢሜሌክ ይስሐቅን "ኅይልህ ከእኛ ይልቅ እየበረታ ስለሄደ፤ አገራችንን ለቀህ ውጣ" አለው።
\v 17 በዚህ ምክንያት ይስሐቅ ያንን ቦታ ለቆ በገራር ሸለቆ ውስጥ ሰፈረ፤ እዚያም ተቀመጠ።
\s5
\v 18 አብርሃም በሕይወት ሳለ አስቆፍሮአቸው የነበሩትን አብርሃም ከሞተ በኋላ ግን ፍልስጥኤማውያን የደፈኑአቸውን የውሃ ጉድጓዶች ይስሐቅ እንደገና እንዲቆፍሩ አደረገ፤ አባቱ ባወጣላቸ ስሞችም ጠራቸው።
\s5
\v 19 የይስሐቅ አገልጋዮች በሸለቆው ውስጥ የውሃ ጉድጓድ ቁፍሩና ጥሩ የምንጭ ውሃ አገኙ፤
\v 20 የገራር እረኞች ግን "ይህ ውሃ የእኛ ነው" በማለት ከይስሐቅ እረኞች ጋር ተጣሉ።በዚህ ምክንያት ይስሐቅ ጉድጓዱን "ዔሤቅ" ብሎ ሰየመው።
\s5
\v 21 የይስሐቅ አገልጋዮች ሌላ የውሃ ጉድጓድ ቁፈሩ፤ በዚህኛውም ጉድጓድ ምክንያት ሌላ ጠብ ተነሣ፤ ስለዚህ ይስሐቅ ይህን ጉድጓድ "ስጥና" ብሎ ሰየመው።
\v 22 ከዚያም እልፍ ብሎ ሌላ የውሃ ጉድጓድ ምክንያት ምንም ጠብ ስላልተናሳ "እነሆ አሁን እግዚአብሔር ሰፊ ቦታ ሰጠን፤ በምድር ላይም እንበዛለን ሲል ያንን ቦታ 'ረሖቦት" ብሎ ሰየመው።
\s5
\v 23 ከዚያ በኋላ ይስሐቅ ወደ ቤርሳቤህ ወጣ፤
\v 24 በዚያን ሌሊት እግዚአብሔር ተገለጠለትና "እኔ የአባትህ አምላክ ነኝ፤እኔ ከአንተ ጋር ስለሆንኩ አትፍራ! ለአገልጋዬ ለአብርሃም በገባሁት ቃል ኪዳን መሠረት እባርክሃለሁ፤ ዘርህንም አበዛዋለሁ" አለው።
\v 25 ይስሐቅ በዚያ መሠዊያ መሠዊያ ሠራና ለእግዚአብሔር ሰገደ፤ መኖሪያውንም እዚያ አደረገ፤ አገልጋዮቹም ሌላ ጉድጓድ ቆፈሩ።
\s5
\v 26 አቢሜሌክ ከአማካሪው ከአሑዘትና ከሠራዊቱ ኣዥ ኮፊኮል ጋር ይስሐቅን ለመጎብኘት ከገራር ወት፤
\v 27 ስለዚህ ይስሐቅ "ከዚህ በፊት ጠልታችሁን አገራችሁ እንድወጣ አድርጋችሁኛል፤ ታዲያ አሁን ልትጎበኝ የመጣችሁት ለምንድን ነው?" አላቸው።
\s5
\v 28 እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱለት፣ "እግዚአብሔር ከአንተ ጋር መሆኑን በግልጥ ዐውቀናል፤ ስለዚህ በእኛና በአንተ መካከል በሰላም ለመኖር የሚያስችል ስምምነት በመሐላ ለመፈፀም አስበናል፤ በዚህም መጀረት ቃል ኮዳን እንድትገባልን የሚንፈለገው፣
\v 29 በእኛ ላይ ምንም ዐይነት በደል እንዳታደርስብን ነው፤ ምክንያቱም እኛ በአንተ ላይ ምንም ግፍ አልሠራንም፤ ዘውትር መልካም ነገር አደረግንልህ እንጂ ክፉ አላደረግብህም፤ ከአገራችንም የወጣኸው በሰላም ነው፤ አሁንም እግዚአብሔር ባርኮሃል።"
\s5
\v 30 ከዚህ በኋላ፣ ይስሐቅ ግብዣ አደረገላቸው፤ እነሱም በሉ፣ ጠጡ።
\v 31 በማግሥቱ ጠዋት በማለዳ ተነሡና ተማማሉ፤ ይስሐቅ ካሰናበታቸው በኋላም በሰላም ሄዱ።
\s5
\v 32 ከዚያኑ ቀን የይስሐቅ አገልጋዮች መጥተው ስለ ቁፈሩት ጉድጓድ ለይስሐቅ ነገሩት፤ "ውሃ አገኘን" ብለውም አበሠሩት።
\v 33 እርሱም የውሃን ጉድጓድ "ሳቤህ"ብሎ ጠራው፤ ስለዚህም የከተማይቱ ስም እስከ ዛሬ "ቤርሳቤህ" እየተባለ ይጠራል።
\s5
\v 34 ዔሳው አርባ ዓመት ሲሆንው የብኤሪን ልጅ ዮዲትንና የኤሎንን ልጅ ባሴማትን አገባ፤ ሁለቱም ሒታውያን ነበሩ።
\v 35 ይህም ጋብቻ ይስሐቅንና ርብቃን ሲያዝናቸው ይኖር ነበር።
\s5
\c 27
\p
\v 1 ይስሐቅ አርጅቶ ዐይኖቹም ታውረው ነበር፤ ታላቁ ልጁን ዔሳውን፤ "ልጄ ሆይ!" ብሎ ጠራው፤ ልጁም "እነሆ አለሁ" አለ።
\v 2 ይስሐቅም እንዲህ አለው፣ "እንደምታየኝ አርጅቻለሁ፤ የምሞትበትንም ቀን አላውቅም፤
\s5
\v 3 ስለዚህ የምታድንበትን ቀስትና ፍላጻ ያዝ፤ ወደ ዱር ሂድና አውሬ አድነህ ሥጋ አምጣልኝ፤
\v 4 ልክ እንደምወደው አድርገህ ምግብ ሥራልኝ ከበላሁም በኋላ ከመሞቴ በፊት የመጨረሻ ምርቃቴን እሰጥሃለሁ።"
\s5
\v 5 ይስሐቅ ለልጁ ለዔሳው ወደ አደን ከሄደ በኋላ፣
\v 6 ርብቃ ልጅዋን ያዕቆብን "አባትህ ዔሳውን እንዲህ ሲለው ሰማሁ፣
\v 7 አውሬ አድነህ ሥጋ አምጣልኝ፤ ልክ እንደምወደው አድርገህ የጣፈጠ ምግብ ሥራልኝ፤ ሳልሞትም በእግዚአብሔር ፊት እነርቅሃለሁ፤
\s5
\v 8 አሁንም ልጄ ሆይ! የምነግርህን አድምጥ፤ የማዝህንም አድርግ፤
\v 9 አባትህ እንደሚወደው አጣፋጩ ጥሩ ምግብ እንድሠራለት፣ ወደ መንጋዎች ሂድና ሁለት የሰቡ የፍየል ጥቦቶች አምጣልኝ፤
\v 10 አንተም ያዘጋጀሁትን ምግብ እንዲበላ ለአባትህ ወስደህ ታቀርብለታለህ፤ በዚህ ዐይነት አባትህ ከመሞቱ በፊት ይመርቅሃል።"
\s5
\v 11 ያዕቆብ ግን እናቱን ርብቃን "የወንድሜ የዔሳው ገላ ጠጉራም ነው፤ የ እኔ ገላ ግን ምንም ጠጉር የሌለው ለስላሳ ነው፤
\v 12 ምናልባት አባቴ ቢዳስሰኝና እንዳታለልኩህ ቢያውቅ በምርቃት ፈንታ እርግማን እንደማተርፍ ታውቂ የለምን?" አላት።
\s5
\v 13 እናቱም "ልጄ ሆይ! የአንተ እርግማን በእኔ ላይ ይሁን፤ አሁንም እንደነገርሁህ አድርግ፤ ሄድህ ጥቦቶቹን አምጣልኝ" አለችው።
\v 14 ስለዚህ ሄዶ ጥቦቶቹን አመጣለት እርስዋም ልክ አባቱ እንደሚወደው እድርጋ ጥሩ ወጥ ሠራች፤
\s5
\v 15 የታላቁ ልጅዋን የዔሳውን የክት ልብስ ከተቀመጠበት ቦታ አውጥታ ለያዕቆብ አለበሰችው።
\v 16 የፍየሎቹንም ቆዳ በክንዶቹ ላይና ጠጉር በሌለበት በአንገቱ ላይ አለበሰችው።
\v 17 ያዘጋጀውንም ጥሩ ወጥ ከጋገረችው እንጀራ ጋር ልልጅዋ ለያዕቆብ ሰጠችው።
\s5
\v 18 ያዕቆብ ወደ አባቱ ሄደና "አባባ!" አለው፤ እርሱም "እነሆ አለሁ! ለመሆኑ አንተ የትኛው ልጄ ነህ!" አለ።
\v 19 ያዕቆብም "የበኩር ልጅህ ዔሳው ነኝ፤ እነሆ እንዳዘዝከኝ አድርጌአለሁ፤ እንድትመርቀኝ እስቲ ቀና በልና ያመጣሁልህን የአደን ሥጋ ተመገብ" አለው።
\s5
\v 20 ይስሐቅም "ልጄ ሆይ! እንዴት ቶሎ ልታገኝ ቻልህ?" አለው። ያዕቆብም "አምላክህ እግዚአብሔር ስለረዳኝ በቶሎ ለማግኘት ቻልሁ" አለው።
\v 21 ይስሕቅም "እስቲ ወደ እኔ ቀረብ በልና ልዳብስህ፤ በእርግጥ አንተ ዔሳው ነህን?" አለው።
\s5
\v 22 ያዕቆብም ወደ አባቱ ተጠጋ፤ አባቱም ዳሰሰውና "ድምፅህ የያዕቆብ ድምፅ ይመስላል፤ ክንድህ ግን የዔሳውን ክንድ ይመስላል" አለው።
\v 23 ክንዶቹ እንደ ዔሳው ክንዶች ጠጉራም ስለ ነበሩ ይስሐቅ ያዕቆብን ለይቶ ማውቅ አልቻለም፤ ሊመርቀው ከዝዘጋጀ በኋላ፣
\s5
\v 24 "እርግጥ አንተ ልጄ ዔሳው ነህን?" ሲል እንደገና ጠየቀው፤ እርሱም "አዎ ነን" አለ።
\v 25 ይስሐቅም "ልጄ! በል ከአደንከው ሥጋ አቅርብልኝ፤ ከበላሁም በኋላ እመርቅህለሁ" አለው። ያዕቆብም ምግቡን አቀረበለት፤ የወይን ጠጅም እንዲጠጣ አመጣለት።
\s5
\v 26 ከዚህ በኋላ አባቱ ይስሐቅ "ልጄ ሆይ! ቀረብ በልና ሳመኝ" አለው፤
\v 27 ያዕቆብም ቀርቦ ሳመው። ይስሐቅ የያዕቆብ ልብስ ባሸተተ ጊዜ እንዲህ ሲል መረቀው፣ "እነሆ የልጄ መልካም ሽታ እግዚአብሔር እንደባረከው የእርሻ ሽታ ነው፤
\s5
\v 28 እግዚአብሔር ከሰማይ የሚያረሰርሰው ተል ይስጥህ፤ ምድርህን ያለምልምልህ፤ እህልንና የወይን ጠጅህን ያብዛልህ፤
\s5
\v 29 መንግሥታት ይገዙልህ፤ ሕዝቦችህም ያገልግሉህ፤ በወንድሞችህ ሁሉ ላይ አለቃ ሁን፤ የእናትህም ልጆች ይስገዱልህ፤ የሚረግሙህ የተረገሙ ይሁኑ፤ የሚመርቁህ የተመረቁ ይሁኑ።"
\s5
\v 30 ይስሐቅ ያዕቆብን መርቆ እንዳበቃና ያዕቆብም አባቱን ፊት እንደወጣ ወዲያውኑ ዔሳው ከአደን ተመልሶ መጣ።
\v 31 እርሱም በበኩሉ የጣፈጠ ወጥ ሠርቶ ለአባቱ አቀረበለትና "አባቴ ሆይ እንድትመርቀኝ፣ እስቲ ቀና ብለህ ካመጣሁልህ የአደን ሥጋ ብላ" አለው።
\s5
\v 32 ይስሐቅም 'አንተ ማን ነህ?" አለው፤ እርሱም "እኔ የበኩር ልጅ ዔሳው ነኝ" አለ።
\v 33 ይስሐቅም እጅግ ደንግጦ እየተነቀጠቀጠ "ታዲያ አውሬ አድኖ ያመጣልኝ ማን ነበረ? ልክ አንተ ከመምጣትህ በፊት ተመገብሁ የመጨረሻ ምርቃቴንም ሰጠሁት፤ ምርቃቱም ተእርሱ ሆኖ ይኖራል"አለው።
\s5
\v 34 ዔሳው ይህን በሰማ ጊዜ ድምፁን ከፍ በማድረግ ምርር ብሎ እያለቀሰ "አባቴ ሆይ! እኔንም መርቀኝ!" አለ።
\v 35 ይስሐቅም "ወንድምህ መጥቶ እኔን በማታለል የአንተን ምርቃት ወስዶብሃል"አለው።
\s5
\v 36 ዔሳውም "እርሱ እኔን ሲያሰናክለኝ ይህ ሁለተኛው ነው፤ ያዕቆብ መባሉ ተገቢ ነው፤ ከዚህ በፊት ብኩርናዬን ወሰደብኝ፤ አሁን ደግሞ ምርቃቴን ቀማኝ፤ ታዲያ ለእኔ ያስቀረከው ምንም ምርቃት የለምን? አለው።
\v 37 ይስሐቅም "ቀድሞ ብዬ እርሱን የአንተ ጌታ አድርጌዋለሁ፤ ወንድሞቹ ሁሉ የእርሱ አገልጋዮች እንዲሆኑ አድርጌአለሁ፤ እህልና የወይን ጠጅ እንዲበዛለት አድርጌአለሁ፤ ልጄ ሆይ! እንግዲህ ለአንተ ምን ላደርግልህ እችላለሁ?" አለው።
\s5
\v 38 ዔሳውም "አባቴ ሆይ! ምርቃትህ እንዲት ብቻ ናትን? እባክህ እኔንም መርቀኝ" እያለ ለማልቀስ አባቱን ነዘነዘው።
\s5
\v 39 ይስሐቅም አንዲህ አለው። "በረከት ከሞላበት ለምለም ምድር ርቀህ ትኖራለህ፤ የሰማይ ጠልም አታገኝም፤
\v 40 በሰይፍም ኅይል ትኖራለህ፤ የወንድምህም አገልጋይ ትሆናለህ፤ በተቃወምከውም ጊዜ ግን ከእርሱ ጭቁና ትላቀቃለህ።"
\s5
\v 41 አባቱ ስለመረቀው ዔሳው ያዕቆብን አጥብቆ ጠላው፤ በልቡም "አባቴ በቅርብ ቀን ይሞታል፤ ከዚህ በኋላ ወንድሜን ያዕቆብን እገድለዋለሁ"ብሎ አሰበ።
\v 42 ነገር ግን ርብቃ የዔሳውን ዕቅድ ስለ ሰማች፣ ያዕቆብን ጠርታ እንዲህ አለችው፣ "አድምጠኝ፤ ወንድምህ ዔሳው አንተን በመግደል ሊበቀልህ አስቦአል፤
\s5
\v 43 አሁንም ልጄ ሆይ! የምልህን አድርግ፤ ተነሥተህ በካራን ወደሚገኘው ወደ ወንድሜ ወደ ላባ ሽሽ፤
\v 44 የወንድምህ ቁጣ እስኪበርድ ድረስ ለጥቂት ጊዜ እዚያው ቆይ፤
\v 45 ቁጣውም ሲበርድ ያደረግህበትን ነገር ይረሳል፤ ከዚያ በኋላ ሰው ልኬ አስመጣሃለሁ፤ ሁለታችሁም በአንድ ቀን ማጣት አልፈልግም።
\s5
\v 46 ርብቃ ይስሐቅን "ዔሳው ባገባቸው በእነዚህ በሖታውያን ሴቶች ምክንያት መኖሬን ጠላሁት፤ ያዕቆብ ደግሞ ከነዚህ ከሒታውያን ሴቶች አንዲቱ ከገባ ለመኖር ይልቅ ሞቴን እመርጣለሁ"አለችው።
\s5
\c 28
\p
\v 1 ይስሐቅ ያዕቆብን ጠርቶ መረቀው፤ እንዲህም ሲል አዘዘው፣ "ከነዓናዊት ሴት እንድታገባ፤
\v 2 ይልቅስ ተነሥተህ በመስጴጦምያ ወዳለው ወደ እናትህ አባት ወደ ባቱኤል ቤት ሂድ፤ እዚያም ከአጎትህ ከገባ ሴቶች ልጆች አንዷን አግባ፤
\s5
\v 3 ሁሉን የሚችል እግዚአብሔር ይባርክህ፤ ብዙ ልጆችም ይስጥህ፤ የብዙ ሕዝቦችም አባት ያድርግህ፤
\v 4 አብርሃምን እንደባረከ አንተንና ዘርህን ይባርክ፤ ይህንንም ለአብርሃም ሰጥቶት የነበረውንና አንተም ደስተኛ ሆነህ የኖርክበት ምድር ርስት አድርጎ ይስጥህ።"
\s5
\v 5 በዚህ ሁኔታ ይስሐቅ ያዕቆብን አሰናበተው፤ ያዕቆብም በመስጴጦምያ ወደሚያኖረው ወደ ላባ ሄደ፤ ላባ የያዕቆብና የዔሳው እናት የርብቃ ወንድም ነበረ፤ አባቱም ሶርያዊው ባቱኤል
\s5
\v 6 ይስሐቅ ያዕቆብን እንደመረቀና ሚስት እንደሚፈልግ ወደ መስጴጦምያ እንደላከው ዔሳው ተረዳ፤ ይስሐቅ ያዕቆብን ሲመርቀው "ከነዓናዊት ሴት እንዳታገባ" ብሎ ያዘዘው መሆኑንም ሰማ፤
\v 7 ያዕቆብ ለአባቱና ለእናቱ በመታዘዝ ወደ መስጴቶምያ መሄዱንም ተረዳ፤
\s5
\v 8 በዚህም አባቱ ይስሐቅ የከነዓንያውያንን ሴቶች እንደማይወድ ዔሳው ተገነዘበ፤
\v 9 ስለዚህ ከዚህ በፊት ከገባቸው ሌላ በተጨማሪ ወደ አብርሃም ልጅ ወደ እስማኤል ሄዶ ልጁን ማሕላትን አገባ፤ እርስዋም የነባዮት እኅት ናት።
\s5
\v 10 ያዕቆብ ቤርሳቤህን ትቶ ወደ ካራን ለመሄድ ተነሣ፤
\v 11 ፀሐይ በጠለቀች ጊዜ ወደ አንድ ስፍራ መጥቶ ዐፈር፤ በዚያም አንድ ድንጋይ ተንተርሶ ተኛ፤
\s5
\v 12 በሕልሙም ከመሬት እስከ ሰማይ የሚደርሰው መሰላል አየ፤ በመሰላሉም የእግዚአብሔር መላእክት ወደ ላይ ይውጡና ወደ ታች ይውረዱ ነበር።
\v 13 እግዚአብሔር በአጠገቡ ቆሞ እንዲህ አለው፣ "እኔ የአባትህ የአብርሃምና የይስሐቅ አምላክ እግዚአብሔር ነኝ፤ ለአንተና ለዝርያዎችህ እንዲሆን ይህን የተገኘበት ምድር እሰጥሃለሁ።
\s5
\v 14 ዘርህን እንደ ምድር አሸዋ አበዛዋለሁ፤ እነርሱ በሁሉ አቅጣጫ ይዞታቸውን ያስፋፋሉ፤ በአንተና በዘርህ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ ይባረካሉ።
\v 15 አይዞህ! እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፤ በምትሄድበት ስፍራ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፤ ወደዚያም ምድር በደህና እመልስሃለሁ፤ የገባሁልህን ቃል ኪዳን ሁሉ እፈፅምልሃለሁ፤ ከቶም አልተውህም።"
\s5
\v 16 ያዕቆብም ከእንቅልፉ ነቃና "በእርግጥ እግዚአብሔር በዚህ ስፍራ አለ፤ እኔ ግን ይህን አላወቅሁም ነበር"አለ።
\v 17 በጣም ፈርቶም ስለነበር "ይህ እንዴት የሚያስፈራ ቦታ ነው፤ ይህ የእግዚአብሔር ቤት መሆን አለበት፤ ወደ ሰማይ የሚያስገባው በር ይህ ነው"አለ።
\s5
\v 18 ያዕቆብ በማግሥቱም ጠዋት በማለዳ ተነሣ፤ ተንተርሶት የነበረውንም ድንጋይ መታሰቢያ እንዲሆን እንደ ሐውልት አቆመው፤በላዩ ላይም የወይራ ዘይት አፈሰሰበት።
\v 19 ይህንንም ስፍራ "ቤትኤል"ብሎ ሰየመው፤ ይህ ስፍራ ከዚያ በኋላ ሎዛ እየተባለ ይጠራ ነበር።
\s5
\v 20 ከዚህ በኋላ ያዕቆብ እንዲህ ብሎ ለእግዚአብሔር ተሳለ "ከእኔ ጋር ሆነህ በምትሄድበት መንገድ ብትጠብቀኝ፣ የሚያስፈልገኝን ምግብና ልብስ ብትሰጠኝ፣
\v 21 ወደ አባቴም ቤት በሰላም ብትመልሰኝ፤ አንተ አምላኬ ትሆናለህ፤
\v 22 ይህ ለመታሰቢያነት ያቆምሁት ድንጋይ ወደ ፊት የእግዚአብሔር ቤት ይሆናል፤ ከምትሰጠኝም ሁሉ ከዐሥር አንዱን እጅ ለአንተ እሰጣለሁ።"
\s5
\c 29
\p
\v 1 ያዕቆብ ጉዞውን ቀጥሎ በስተ ምሥራቅ ወዳለው አገር ደረሰ፤
\v 2 እዚያም በሜዳ ላይ አንድ የውሃ ጉድጓድ አየ፤ በሦስት የተከፈሉ የበግ መንጋዎች በጉድጓድ ዙሪያ ነበሩ፤ መንጋዎቹ ውሃ የሚጠጡት ከዚሁ ጉድጓድ ነበር፤ ጉድጓዱም የሚዘጋበት ድንጋይ ትልቅ ነበር፤
\v 3 መንጋዎቹ ሁሉ እዚያ ከተሰበሰቡ በኋላ እረኞቹ ድንጋዩን አንከባለው ከጉድጓዱ ውሃ ያጠቱአቸው ነበር፤ መንጋዎቻቸውን ካጠጡ በኋላ ግን ድንጋዩንም መልሰው በጉድጓዱ አፍ ላይ ይከዱኑታል።
\s5
\v 4 ያዕቆብም እረኞቹን "ወዳጆቼ ሆይ! ከየት ነው የመጣችሁት?" ብሎ ጠየቃቸው። እነሱም "እኛ የመጣነው ከካራን ነው" አሉት።
\v 5 እርሱም "የናኮርን የልጅ ልጅ ላባን ታውቁታላችሁን?" ብሎ ጠየቃቸው። እነሱም "አዎ እናውቀዋለን" አሉት።
\v 6 እርሱም "ለመሆኑ እርሱ ደኅና ነውን?" አላቸው። እነርሱም "አዎ፣ ደኅና ነው፤ እንዲያውም ልጁ ራሔል ያችውልህ! በጎች እየነዳች በመምጣት ላይ ነች" አሉት።
\s5
\v 7 ያዕቆብም "ጊዜው ገና ቀን ነው፤ መንጋዎቻቸውንም ወደ ቤት የምታስገቡበት ሰዓት ገና አልደረሰም፤ ታዲያ ለምን ውሃ አጠጥታችሁ አታሰማሩአቸውም? ፤ አለ።
\v 8 እነርሱም "እረኞች ሁሉ መንጋዎቻቸውን ይዘው እዚህ ከመሰብሰባቸው በፊት ምንም ማድረግ አንችልም፤ ሁሉም እዚህ ከመጡ በኋላ ግን ድንጋዩን በኅብረት አንከባለን በጎቹን እናጠጣቸዋለን" አሉት።
\s5
\v 9 ያዕቆብም ከእረኞቹ ጋር በመነጋገር ላይ ሳለ ራሔል የአባትዋን በጎች ይዛ ወደዚያ መጣች፤ ምክንያቱም እርስዋ የበጎች እረኛ ነበረች።
\v 10 ያዕቆብ ያጉቱን የላባን በጎች እየነዳች ስትመጣ ራሔልን አይቶ ወደ ጉድጓድ ሄደ፤ ጉድጓዱ የተከደነበትንም ድንጋይ አንከባሎ በጎቹን አጠጣቸው።
\s5
\v 11 ከዚያ በኋላ ራሔልን ሳማት። ከደስታውም ብዛት የተነሣ አለቀሰ፤
\v 12 "እኔ የአባትሽ እኅት የሆነችው የርብቃ ልጅ ሄደች።
\s5
\v 13 ላባም የእኅቱ ልጅ ያዕቆብ መምጣቱን በሰማ ጊዜ ሊቀበለው ፈጥኖ ሄደ፤ አቅፎ ከሳመውም በኋላ ወደ ቤት አመጣው፤ ያዕቆብ የሆነውን ሁሉ ለላባ ነገረው፤
\v 14 ላባም "በእርግጥ አንተ ቅርብ የሥጋ ዘመዴ ነህ" አለው፤ ያዕቆብም አንድ ወር ያህል ከአጎቱ ጋር ተቀመጠ።
\s5
\v 15 ላባ ያዕቆብን "ዘመዴ በመሆንህ ብቻ በነፃ ልታገለግለኝ አይገባህም፤ ስለዚህ ምን ያህል ደመወዝ ላስብልህ? አለው።
\v 16 ላባ ሁለት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ ታላቂቱ ልያ፤ ታናሽቱ ራሔል ይባሉ ነበር።
\v 17 ልያ ዐይነ ልም ስትሆን፣ ራሔል ግን ቁመናዋ የሚያምር የደስ ደስ ያላት ነበረች።
\v 18 ያዕቆብ ራሔልን እጅግ ስለወደዳት "ራሔልን ብትድርልኝ ሰባት ዓመት አገለግልሃለሁ" አለ።
\s5
\v 19 ላባም "ለሌላ ሰው ከምሰጣት ይልቅ ለአንተ ብሰጥህ ይሻለኛል፤ እሺ ተስማምቼአለሁ፤ እዚሁ ከእኔ ጋር ኑር" አለው።
\v 20 ያዕቆብ ራሔልን ለማግባት ሰባት ዓመት አገለገለ፤ ይሁን እንጂ ራሔልን በጣም ይወዳት ስለነበር የቆየበት ጊዜ ጥቂት ቀን ብቻ መስሎ ታየው።
\s5
\v 21 ከዚያ በኋላ ያዕቆብ ላባን "እነሆ የአገልግሎት ዘመኔ ተፈፅሞአል፤ ሚስት እንድትሆነኝ ልጅህን ስጠኝ" አለው።
\v 22 ላባም የሠርግ ድግስ አዘጋጅቶ በአቅራቢያው የሚገኙትን ሰዎች ሁሉ ጠራ።
\s5
\v 23 ነገር ግን ላባ በራሔል ምትክ ልያን ለያዕቆብ ሰጠው፤ ያዕቆብም ከልያ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት አደረገ።
\v 24 ላባ ሴት አገልጋዩን ዚልፋን አገልጋያዋን እንድትሆን ለልጁ ለልያ ሰጣት።
\v 25 በማግስቱ ጠዋት ያዕቆብ አብራው ያደረችው ልያ መሆንዋን ባወቀ ጊዜ ወደ ላባ ሄዶ "ይህ ያደረግህብኝ ነገር ምንድን ነው? ያገለገልሁህ ራሔልን ለማግኘት አልነበረም? ታዲያ ለምን አታለልከኝ"አለው።
\s5
\v 26 ላባም "ታላቂቱ ሳትዳር፤ ታናሺቱን መዳር የአገራችን ልማድ አይደለም፤
\v 27 የልያ ሠርግ ሰባት ቀን እስኪሞላው ድረስ ጠብቅ፤ ከእንግዲህ ወዲይ ሰባት ዓመት የምታገለግለኝ ከሆነ ራሔልን እሰጥሃለሁ" አለው።
\s5
\v 28 ያዕቆብም ነገሩ ተስማማ፤ ከልያ ጋር ሰባት ቀን ተሞሽሮ ከቆየ በኋላ፤ ላባ ልጁን ራሔልን ለያዕቆብ ሳረለት።
\v 29 ላባ ሴት አገልጋዩን ባላን አገልጋይዋ እንድትሆን ለልጁ ለራሔል ሰጣት።
\v 30 ያዕቆብ ከራሔልም ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት አደረገ፤ ከልያም አብልጦ ወደዳት፤ ከዚያ በኋላ ላባን ሰባት ዓመት አገለገለው።
\s5
\v 31 ልያ የራሔልን ያህል እንዳልተወደደች እግዚአብሔር ባየ ጊዜ መውለድ እንድትችል ማሕፀንዋን ከፈተላት፤ ራሔል ግን መኻን ሆነች፤
\v 32 ልያ ርርግዛ ወንድ ልጅ ወለደች፤ "እግዚአብሔር መከራዬን ተመለከተ፤ ከእንግዲህስ ወዲያ ባሌ ይወደኛል" ስትል ስሙን ሮቤል አለችው።
\s5
\v 33 እንደገና አረገዘችና ሌላ ወንድ ልጅ ወደች፤ "እግዚአብሔር እንዳልተወደድሁ ሰማ፤ ይህንንም ልጅ ደግሞ ሰጠኝ' ስትል ስሙን ስምዖን አለችው።
\v 34 እንደገና 'አረገዘችና ሌላ ወንድ ልጅ ወለደች፤ "እንግዲህ ሦስት ወንዶች ልጆች ስለ ወለድሁለት ባሌ ከእኔ ጋር በፍቅር ይጠመዳል" ስትል ስሙን ሌዊ አለችው፤
\s5
\v 35 እንደገና አረገዘችና ውንድ ልጅ ወለደች፤ "አሁንስ እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ" ስትል ስሙን ይሁዳ አለችው፤ ከዚህ በኋላ መውለድ አቋረጠች።
\s5
\c 30
\p
\v 1 ራሔል ለያዕቆብ አንድም ልጅ እንዳልወለደችለት ባየች ጊዜ በእኅቷ ቀናች። ያዕቆብንም፣ “ልጅ ስጠኝ አለበለዚያ እሞታለሁ” አለችው።
\v 2 ያዕቆብም ራሔልን ተቆጥቶ፤ “እኔ የሆድሽን ፍሬ በነሳሽ በእግዚአብሔር ቦታ ነኝን?” አላት።
\s5
\v 3 እርሷም፣ “እነሆ፣ አገልጋዬ ባላ አለችልህ፣ ልጆች እንድትወልድልኝና እኔም ደግሞ በእርሷ አማካይነት ልጆች እንዳገኝ ከእርሷ ጋር ተኛ” አለችው።
\v 4 ስለዚህ ባላን እንደሚስት አድርጋ ሰጠችው፤ ያዕቆብም ከእርሷ ጋር የግብረ-ሥጋ ግንኙነት አደረገ።
\s5
\v 5 ባላም አረገዘችና ወንድ ልጅ ወለደችለት።
\v 6 ራሔልም፦ “እግዚአብሔር ፈረደልኝ፣ ልመናዬንም ሰምቶ ወንድ ልጅ ሰጥቶኛል” አለች። ስለዚህ ስሙን ዳን ብላ ጠራችው።
\s5
\v 7 የራሔል አገልጋይ ባላ ዳግመኛ አረገዘችና ለያዕቆብ ሁለተኛ ወንድ ልጅ ወለደች።
\v 8 ከእኅቴ ጋር ብርቱ ትግል ታግዬ አሸነፍኋት” አለች። ስለዚህ ስሙን ንፍታሌም ብላ ጠራችው።
\s5
\v 9 ልያም ልጅ መውለድ ማቆሟን እንደተረዳች፣ አገልጋይዋን ዘለፋን ሚስት እንድትሆነው ለያዕቆብ ሰጠችው።
\v 10 የልያ አገልጋይ ዘለፋም ለያዕቆብ ወንድ ልጅ ወለደችለት፣
\v 11 ልያም፣ “እንዴት የታደልሁ ነኝ!” ስትል ስሙን ጋድ ብላ ጠራችው።
\s5
\v 12 የልያም አገልጋይ ዘለፋ ለያዕቆብ ሁለተኛ ልጅ ወለደችለት፤
\v 13 ልያም፣ “እጅግ ደስ ብሎኛል፣ ከእንግዲህ ወዲያ ሴቶች ‘ደስተኛዋ’ ይሉኛል አለች፤ ስሙንም ‘አሴር’ ብላ ጠራችው።
\s5
\v 14 በስንዴ መከር ወራት ሮቤል ወደ ዱር ሄዶ እንኮይ አገኘ፤ ለእናቱ ለልያም አመጣላት፤ ራሔልም ልያን፣ “እባክሽን ልጅሽ ካመጣልሽ እንኮይ ስጪኝ” አለቻት።
\v 15 ልያም፦ “ባሌን የቀማሽኝ አነሰና የልጄን እንኮይ ደግሞ ልትወስጂ አማረሽ?” አለቻት። ራሔልም፣ “ስለልጅሽ እንኮይ ዛሬ ያዕቆብ ከአንቺ ጋር ይደር” አለቻት።
\s5
\v 16 በዚያ ምሽት ያዕቆብ ከእርሻ ሲመለስ፣ ልያ ወጥታ ተቀበለችውና፣ “በልጄ እንኮይ ስለተከራየሁህ የዛሬው አዳርህ ከእኔ ጋር ነው” አለችው። ያዕቆብም በዚያች ሌሊት ከእርሷ ጋር አደረ።
\v 17 እግዚአብሔር የልያን ጸሎት ሰማ፣ ስለዚህ አረገዘችና ለያዕቆብ አምስተኛውን ወንድ ልጅ ወለደችለት።
\v 18 ልያም፦ “አገልጋዬን ለባሌ በመስጠቴ እግዚአብሔር ደመወዜን ከፈለኝ” አለች። ስሙንም ይሳኮር አለችው።
\s5
\v 19 ልያ አሁንም ደግማ ፀነሰች፤ ለያዕቆብም ስድስተኛውን ወንድ ልጅ ወለደች።
\v 20 እርሷም፣ “እግዚአብሔር በከበረ ስጦታ አድሎኛል፣ ስድስት ወንዶች ልጆች ስለወለድሁለት ከእንግዲህ ባሌ አክብሮ ይይዘኛል” አለች፤ ስሙንም ዛብሎን አለችው።
\v 21 ከዚያም በኋላ ሴት ልጅ ወለደች ስምዋንም ዲና አለቻት።
\s5
\v 22 እግዚአብሔርም ራሔልን አሰበ፤ ጸሎትዋንም ሰምቶ ልጅ እንድትወልድ አደረጋት፤
\v 23 አርግዛም ወንድ ልጅ ወለደችና፣ “እግዚአብሔር ዕፍረቴን አስወገደልኝ” አለች፤
\v 24 ደግሞም ሌላ ወንድ ልጅ ይጨምርልኝ ስትል ስሙን ዮሴፍ ብላ ጠራችው።
\s5
\v 25 ራሔል ዮሴፍን ከወለደች በኋላ ያዕቆብ ላባን እንዲህ አለው፦ “ወደ ተወለድሁበት አገር እንድመለስ አሰናብተኝ፤
\v 26 አንተን በማገልገል ያገኘኋቸውን ሚስቶቼንና ልጆቼን ስጠኝና ልሂድ፤ ምን ያህል አገልግሎት እንዳበረከትኩልህ ታውቃለህ።”
\s5
\v 27 ላባም፣ “በአንተ ምክንያት እግዚአብሔር እንደባረከኝ በንግርት መረዳቴን ልነግርህ እወዳለሁ፤
\v 28 የምትፈልገውን ደመወዝ ንገረኝና እከፍልሃለሁ” አለው።
\s5
\v 29 ያዕቆብም እንዲህ አለው፦ “እንዴት እንዳገለገልሁህና የከብትህም መንጋ በእኔ ጠባቂነት እንዴት እንደረባልህ አንተ ታውቃለህ፤
\v 30 እኔ ከመምጣቴ በፊት ጥቂት የነበሩት መንጋዎችህ አሁን እጅግ በዝተዋል፤ በተሰማራሁበት ሁሉ እግዚአብሔር በረከቱን አብዝቶልሃል። ታዲያ፣ ለራሴ ቤት የሚያስፈልገኝን የማቀርበው መቼ ነው?”
\s5
\v 31 ላባም፣ “ታዲያ ምን ያህል ልክፈልህ?” ብሎ ጠየቀው። ያዕቆብም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “እኔ የምልህን አንድ ነገር ብቻ ብታደርግልኝ መንጋህን ማሰማራቴንና መጠበቄን እቀጥላልሁ፤
\v 32 ዛሬ በመንጋዎችህ መካከል ልለፍና ዝንጉርጉርና ነቁጣ ጥቁርም የሆኑትን በጎች ሁሉ ልለይ፤ እንዲሁም ነቁጣና ዝንጉርጉር የሆኑትን ፍየሎች እመርጣለሁ፤ እነርሱም ደመወዜ ይሆናሉ፤
\s5
\v 33 ወደፊት ደመወዜን ለመቆጣጠር በምትመጣበት ጊዜ ታማኝነቴ ይታወቃል፤ ደመወዜን ለመቆጣጠር ስትመጣ ዝንጉርጉር ያልሆነ ወይም ነቁጣ የሌለበት ፍየል ብታገኝ፣ እንዲሁም ጥቁር ያልሆነ በግ ብታገኝ የተሰረቀ መሆኑን መረዳት ትችላልህ” አለው።
\v 34 ላባም፣ “እሺ አንተ ባልከው እስማማለሁ” አለ።
\s5
\v 35 ነገር ግን በዚያኑ ዕለት ከተባት ፍየሎች ሽመልመሌ የሆኑትን ወይም ነቁጣ ያለባቸውን ሁሉ እንዲሁም ከእንስት ፍየሎች ነቁጣ ያለባቸውን ዝንጉርጉር የሆኑትን ሁሉ መረጠ፤ ደግሞም ጥቋቁር የሆኑትንም በጎች ሁሉ ለየና ወንዶች ልጆቹን አስጠበቃቸው።
\v 36 ከዚህ በኋላ ላባ መንጋውን ነድቶ የሦስት ቀን መንገድ ያህል ከያዕቆብ ርቆ ሄደ፤ ያዕቆብም የቀሩትን የላባን መንጋዎች መጠበቁን ቀጠለ።
\s5
\v 37 ያዕቆብም ልብን፣ ለውዝና ኤርሞን ከሚባሉ ዛፎች እርጥብ በትሮችን ወሰደ፤ በበትሮቹ ያለው ነጭ እንዲታይ ሽመልመሌ አድርጎ ላጣቸው፤
\v 38 መንጋዎቹ ውሃ ለመጠጣት ሲመጡ ከፊት ለፊት እንዲያዩአቸው የተላጡትን በትሮች በውሃ ማጠጫዎቹ ውስጥ አደረጋቸው። መንጎቹም ስሜታቸው ሲነሣሣና ውሃ ለመጠጣት ሲመጡ፣
\s5
\v 39 በትሮቹን ፊት ለፊት እያዩ ይሳረሩ ነበር፤ ሽመልመሌ፣ ዝንጉርጉርና ነቁጣ የጣለባቸውንም ግልገሎች ወለዱ።
\v 40 ያዕቆብ እነዚህን ግልገሎች ለብቻ ለየ፤ የቀሩትን ግን ዝንጉርጉርና ጥቁር በሆኑት በላባ መጋዎች ፊት ለፊት አቆማቸው፤ በዚህ ዓይነት የራሱን መንጋ ከላባ መንጋ ጋር ሳይቀላቅል ለብቻ አቆማቸው።
\s5
\v 41 ያዕቆብም ብርቱ እንስቶች አውራ ፈልገው በሚቅበጠበጡበት ጊዜ በትሮቹ አቅራቢያ እንዲጠቁ በትሮቹን በውሃ ገንዳዎች ውስጥ ፊት ለፊታቸው ያስቀምጥ ነበር፤
\v 42 ደካማ በሆኑት እንስቶች ፊት ግን በትሮቹን አያስቀምጥም ነበር፤ ስለዚህ ደካሞቹ ለላባ ሲሆኑ፣ ብርቱዎቹ ለያዕቆብ ሆኑ።
\s5
\v 43 በዚህም ሁኔታ ያዕቆብ እጅግ ባለጸጋ ሆነ፤ ብዙ መንጋዎች፤ ሴቶችና ወንዶች አገልጋዮች፣ ብዙ ግመሎችና አህዮችም ነበሩት።
\s5
\c 31
\p
\v 1 የላባ ወንዶች ልጆች፣ “ያዕቆብ የአባታችንን ሀብት እንዳለ ወስዶታል፤ ይህ ሁሉ እርሱ ያከማቸውም ሀብት ከአባታችን የተገኘ ነው” እያሉ ሲያወሩ ያዕቆብ ሰማ።
\v 2 በላባም ዘንድ እንደቀድሞ ተወዳጅ አለመሆኑን ተረዳ።
\v 3 እግዚአብሔርም ያዕቆብን፣ “ወደ አባቶችህ ወደ ዘመዶችህ አገር ተመለስ፤ እኔም ከአንተ ጋር እሆናለሁ” አለው።
\s5
\v 4 ስለዚህ ያዕቆብ መንጋዎቹ ወደ ተሰማሩበት መስክ እንዲመጡ ራሔልንና ልያን አስጠራቸው፤
\v 5 እንዲህም አላቸው፤ “አባታችሁ ስለ እኔ ያለው አመለካከት እንደ ቀድሞ አለመሆኑን ተረድቻለሁ፤ ቢሆንም የአባቴ አምላክ አልተለየኝም፤
\v 6 መቼም ባለኝ አቅም አባታችሁን ማገልገሌን እናንተ ታውቃላችሁ።
\s5
\v 7 አባታችሁ ደመወዜን ዐሥር ጊዜ እየለዋወጠ አታልሎኛል፣ ሆኖም እንዲጎዳኝ እግዚአብሔር አልፈቀደለትም።
\v 8 እርሱ፣ ‘ደመወዝህ ዝንጉርጉሮቹ ይሆናሉ ሲለኝ፣ መንጎቹ ሁሉ ዝንጉርጉር ወለዱ’፤ ደግሞም፣ ‘ደመወዝህ ሽመልመሌዎቹ ይሆናሉ ሲለኝ፣ መንጎቹ ሁሉ ሽመልመሌ መልክ ያላቸውን ወለዱ፤
\v 9 ስለዚህ እግዚአብሔር የአባታችሁን ከብቶች ወስዶ ለእኔ ሰጠኝ።
\s5
\v 10 እንስሳቱ በሚጠቁበት ወራት የሚያጠቋቸው አውራ ፍየሎች ሽመልመሌ፣ ዝንጉርጉርና ነቁጣ መሆናቸውን በሕልም አየሁ።
\v 11 በዚያው ሕልም የእግዚአብሔር መልአክ፦ ‘ያዕቆብ’ ብሎ ጠራኝ፣ እኔም ‘እነሆ አለሁ’ አልሁ።
\s5
\v 12 እርሱም እንዲህ አለኝ፦ ‘መንጋዎቹን የሚያጠቋቸው አውራ ፍየሎች ሽመልመሌ፣ ዝንጉርጉርና ነቁጣ ያለባቸው መሆናቸውን ተመልከት፣ ላባ የፈጸመብህን በደል አይቻለሁ።
\v 13 የድንጋይ ሐውልት በማቆም ዘይት ቀብተህ የተሳልህባት የቤቴል አምላክ እኔ ነኝ፤ አሁንም ይህን አገር ፈጥነህ ልቀቅ ወደ ተወለድህበትም ምድር ተመልሰህ ሂድ’ አለኝ።”
\s5
\v 14 ራሔልና ልያም እንዲህ ብለው መለሱለት፦ “ከአባታችን የምንወርሰው ድርሻ አለን?
\v 15 እርሱ እኛን የሚያየን እንደ ባዕዳን አይደለምን? ደግሞም እኮ እኛን ሽጦናል፣ የተሸጥንበትንም ዋጋ ራሱ በልቶታል።
\v 16 እግዚአብሔር ከአባታችን ወስዶ ለአንተ የሰጠው ሀብት ሁሉ የእኛና የልጆቻችን ነው፤ ስለዚህ እግዚአብሔር የነገረህን ሁሉ አድርግ።”
\s5
\v 17 ከዚያም ያዕቆብ ተነሥቶ ልጆቹንና ሚስቶቹን በግመሎች ላይ አስቀመጠ፤
\v 18 በመስጴጦምያ ካፈራው ሀብት ሁሉ ጋር ከብቶቹን በሙሉ ወደፊት አስቀደመ፣ ወደ አባቱም ወደ ይስሐቅ አገር፣ ወደ ከነዓን ምድር ጉዞውን ቀጠለ።
\s5
\v 19 ላባ በጎቹን ሊሸልት ሄዶ ስለነበር፣ እርሱ በሌለበት ራሔል ከቤት የነበሩትን የአባቷን ጣዖቶች ሰርቃ ሄደች።
\v 20 ያዕቆብ መሄዱን ለላባ ሳይገልጥለት አታሎት ሄደ፣
\v 21 የራሱ የሆነውን ሀብት ይዞ በፍጥነት ታጓዘ፤ የኤፍራጥስንም ወንዝ ተሻግሮ ወደ ኮረብታማው አገር ወደ ገለዓድ ሄደ።
\s5
\v 22 ያዕቆብ መኮብለሉን ለላባ በሦስተኛው ቀን ተነገረው።
\v 23 ከዘመዶቹ ጋር ሆኖ ያዕቆብን ተከታተለው፤ ሰባት ቀን ከተጓዙ በኋላ ገለዓድ በተባለው ተራራማ አገር ላይ ሊደርስበት ተቃረበ።
\s5
\v 24 በዚያን ሌሊት እግዚአብሔር ለላባ በሕልም ተገለጠለትና “ያዕቆብን ክፉም ሆን ደግ እንዳትናገረው ተጠንቀቅ” አለው።
\v 25 ያዕቆብ ገለዓድ በተባለው ኮረብታማ ስፍራ ድንኳኑን በመትከትል ሰፍሮ ሳለ ላባ ደረሰበት፤ ላባና ዘመዶቹም እዚያው ድንኳናቸውን ተክለው ሰፈሩ።
\s5
\v 26 ከዚህ በኋላ ላባ ያዕቆብን እንዲህ አለው፦ “ስለምን እንዲህ አድርገህ አታለልኸኝ፤ ሴቶች ልጆቼንስ በጦርነት እንደተማረኩ ያህል ይዘሃቸው ለምን ሄድህ?
\v 27 ሳትነግረኝ ተሰውረህ በመሄድ ለምን አታለልኽኝ? ነግረኸኝ ቢሆን በከበሮና በመስንቆ እየተዘፈነ በደስታ በሸኘሁህ ነበር።
\v 28 ልጆቼንና የልጅ ልጆቼን በመሳም እንድሰናበታቸው ባለማድረግህ የሞኝነት ተግባር ፈጽመሃል።
\s5
\v 29 ጉዳት ሳደርስብህ እችል ነበር፣ ነገር ግን ባለፈው ሌሊት የአባትህ አምላክ፣ ‘ያዕቆብን ክፉም ሆነ ደግ አንድ ቃል እንዳትናገረው’ ብሎ አስጠነቀቀኝ፣
\v 30 ወደ ትውልድ አገርህ ለመመለስ ባለህ ብርቱ ፍላጎት እንደተለየኸኝ አውቃለሁ፣ ታዲያ የቤቴን ጣዖቶች የሰረቅኽብኝ ለምንድነው?”
\s5
\v 31 ለላባ እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “ሴቶች ልጆችህን በኃይል ነጥቀህ ታስቀርብኛለህ ብዬ ስለ ፈራሁ ነው በድብቅ የሄድኩት።
\v 32 ነገር ግን ከእኛ መካከል የአንተን የጣዖት ምስል የሰረቀ ሰው ካለ ይሙት። የአንተ የሆነ አንዳች ነገር ከኔ ዘንድ ቢገኝ፣ አንተው ራስህ ዘመዶቻችን ባሉበት ፈልግና ውሰድ።” እንደዚህ ሲል ራሔል የጣዖታቱን ምስል መስረቋን ያዕቆብ አያውቅም ነበር።
\s5
\v 33 ላባም ወደ ያዕቆብ ድንኳንና ወደ ልያ ድንኳን እንዲሁም ወደ ሁለቱ ደንገጡሮቹ ድንኳን ገባ፤ ነገር ግን ምንም አላገኘም። ከልያ ድንኳን ከወጣ በኋላ ወደ ራሔል ድንኳን ገባ።
\s5
\v 34 ራሔል ግን ጣዖቱቹን ወስዳ በግመሉ ኮርቻ ሥር በመሰወር በላያቸው ተቀምጣባቸው ነበር። ላባ በድንኳኑ ውስጥ ያለውን ጓዝ ሁሉ በርብሮ ምንም ነገር አላገኘም።
\v 35 ራሔልም አባቷን፦ “በፊትህ ተነሥቼ መቆም ስላልቻልሁ፣ ጌታዬ አትቆጣ የወር አበባዬ መጥቶ ነው” አለችው፤ ስለዚህ በረበረ፤ የጣዖቱን ምስል ግን ማግኘት አልቻለም።
\s5
\v 36 በዚህ ጊዜ ያዕቆብ ተቆጣ፤ ላባንም እንዲህ ሲል ወቀሰው፦ “እስቲ ወንጀሌ ምንድን ነው? ይህን ያህል የምታሳድደኝ ኃጢአቴ ምን ቢሆን ነው?
\v 37 ዕቃዬን አንድ በአንድ በርብረሃል፤ ታዲያ የአንተ ሆኖ ያገኘኸው ዕቃ የትኛው ነው? ካለ፣ እስቲ በአንተም በእኔም ዘመዶች ፊት አቅርብና እነርሱ ያፋርዱን።
\s5
\v 38 ሃያ ዓመት አብሬህ ኖሬአለሁ፤ በጎችህና ፍየሎችህ አልጨነገፉም፤ ከመንጋህም አንድ ጠቦት እንኳ አልበላሁም።
\v 39 አውሬ የሰበረውንም ቢሆን እተካ ነበር፣ በቀንም ሆነ በሌሊት የተሰረቁትን ሁሉ ስታስከፍለኝ ኖረሃል።
\v 40 ብዙ ጊዜ በቀን ሐሩርና በሌሊት ቁር እሠቃይ ነበር፤ በቂ እንቅልፍ ያገኘሁበት ጊዜ አልነበረም።
\s5
\v 41 ሃያ ዓመት በቤትህ የኖርሁት በዚህ ሁኔታ ነበር፤ ዐሥራ አራት ዓመት ለሁለቱ ልጆችህ ብዬ አገለገልሁ፤ ስድስት ዓመት ስለመንጋዎችህ ስል አገለገልሁ፤ ይህም ሆኖ ደመወዜን ዐሥር ጊዜ ለዋውጠኽብኛል።
\v 42 የአባቴ አምላክና እርሱም የሚፈራው የአብርሃም አምላክ ከእኔ ጋር ባይሆን ኖሮ ባዶ እጄን ሰድደኸኝ ነበር፤ እግዚአብሔር ግን መከራዬን ዐይቶ፣ ልፋቴን ትመልክቶ ትናንት ሌሊት ገሠጸህ።”
\s5
\v 43 ላባም ለያዕቆብ እንዲህ ሲል መለሰ፤ “እነዚህ ሴቶች የእኔው ልጆች ናቸው፤ ልጆቻቸውም የእኔ ናቸው፤ እነዚህም መንጋዎች የእኔ ናቸው፤ ይህ የምታየው ሁሉ የራሴ ነው፤ ታዲያ በእነዚህ ሴቶች ልጆቼና በወለዷቸው ልጆቻቸው ላይ ዛሬ ምን ማድረግ እችላለሁ?
\v 44 በል አሁን ቃል ኪዳን እንጋባ፤ ኪዳኑም በአንተና በእኔ መካከል ምስክር ይሁን።”
\s5
\v 45 ያዕቆብም ድንጋይ ውስዶ ሐውልት አድርጎ አቆመው፤
\v 46 ከዚያም ዘመዶቹን “ድንጋይ ሰብስቡ” አላቸው። እነርሱም ድንጋይ እያመጡ ከመሩ፤ በክምሩም አጠገብ ምግብ በሉ።
\v 47 ላባም ክምር ድንጋዩን ይጋርሠሀዱታ ብሎ ጠራው፤ ያዕቆብ ደግሞ ገለዓድ አለው።
\s5
\v 48 ላባም “ይህ ክምር ድንጋይ በእኔና በአንተ መካከል ዛሬ ምስክር ነው” አለው። ገለዓድ ተብሎ የተጠራውም በዚሁ ምክንያት ነው፤
\v 49 ደግሞም ምጽጳ ተባለ ምክንያቱም ላባ እንዲህ ብሎአልና፤ “እንግዲህ ከዚህ በምንለያይበት ጊዜ እግዚአብሔር እኔንና አንተን ይጠብቀን፤
\v 50 ልጆቼን ብትበድላቸው ወይም ሌሎችን በላያቸው ብታገባ፣ ማንም ከእኛ ጋር ባይኖርም እንኳ እግዚአብሔር በአንተና በእኔ መካከል ምስክር መሆኑን አትርሳ።”
\s5
\v 51 ላባም ያዕቆብን እንዲህ አለው፦ “ክምር ድንጋዩ እነሆ፤ በአንተና በእኔ መካካል ያቆምሁትም ሐውልት እነሆ፤
\v 52 ይህን ክምር ድንጋይ አልፌ አንተን ለማጥቃት ላልመጣ፣ አንተም ይህን ክምር ድንጋይና ይህን ሐውልት አልፈህ እኔን ለማጥቃት ላትመጣ፤ ይህ ክምር ድንጋይ ምስክር ነው፤ ይህም ሐውልት ምስክር ነው።
\v 53 የአብርሃም አምላክ፣ የናኮር አምላክ፣ የአባታቸውም አምላክ በመካከላችን ይፍረድ።” ስለዚህ ያዕቆብ አባቱ ይስሐቅ በሚፈራው በእግዚአብሔር ማለ።
\s5
\v 54 ያዕቆብ በኮረብታማው አገር ላይ መሥዋዕት አቀረበ፤ ዘመዶቹንም ምግብ እንዲበሉ ጋበዛቸው፤ እነርሱም ከበሉ በኋላ እዚያው አደሩ።
\v 55 በማግስቱም ማለዳ ላባ የልጅ ልጆቹን እንዲሁም ሴቶች ልጆችን ስሞ መረቃቸው፤ ከዚያም ወደ አገሩ ተመለሰ።
\s5
\c 32
\p
\v 1 ያዕቆብ በጉዞ ላይ ሳለ የእግዚአብሔር መላእክት በመንገድ ተገናኙት።
\v 2 ባያቸውም ጊዜ፤ “ይህ የእግዚአብሔር ሰፈር ነው” አለ፤ የዚያንም ቦት ስም መሃናይም አለው።
\s5
\v 3 ያዕቆብም በኤዶም አገር ሴይር በተባለው ምድር ወደሚኖረው ወንድሙ ወደ ዔሳው መልእክተኞችን አስቀድሞ ላከ፤
\v 4 እንዲህም ብሎ አዘዛቸው፤ “ጌታዬን ዔሳውን እንዲህ ትሉታላችሁ፤ ‘አገልጋይህ ያዕቆብ እንዲህ ብሎአል በሉት፤ ከላባ ዘንድ ተቀምጬ እስካሁን ድረስ እዚያው ኖርሁ፤
\v 5 ከብቶች፣ አህዮች፣ የበግና የፍየል መንጎች እንደዚሁም የወንድን የሴት አገልጋዮች አሉኝ፤ አሁንም ይህን መልእክት ለጌታዬ መላኬ በአንተ ዘንድ ሞግስ አገኛለሁ በሚል ተስፋ ነው።’”
\s5
\v 6 የተላኩትም ሰዎች ወደ ያዕቆብ ተመልሰው፣ “ወደ ወንድምህ ወደ ዔሳው ሄደን ነበር፤ እርሱም ከአንት ጋር ለመገናኘት በመምጣት ላይ ነው፤ ከእርሱም ጋር አራት መቶ ሰዎች አሉ” አሉት።
\v 7 በዚህ ጊዜ ያዕቆብ እጅግ በመፍራት ተጨነቀ፤ አብረውት የነበሩትንም ሰዎች በሁለት ክፍል መደባቸው፤ እንዲሁም በጎቹን፣ ፍየሎቹን፣ ከብቶቹንና ግመሎቹን በሁለት በሁለት መደባቸው።
\v 8 ይህንንም ያደረገው፦ “ዔሳው የመጀመሪያውን ክፍል ቢያጠቃ፣ ሌላው ክፍል ሊያመልጥ ይችላል” ብሎ በማሰብ ነው።
\s5
\v 9 ያዕቆብ እንዲህ ሲል ጸለየ፤ “የአባቴ የአብርሃም አምላክ፣ የአባቴ የይስሐቅ አምላክ ሆይ፣ ‘ወደ አገርህና ወደ ዘመዶችህ ተመልስ፣ እኔም በጎ ነገር አደርግልሃለሁ’ ያልኸኝ እግዚአብሔር ሆይ፣
\v 10 እኔ ባሪይህ እስካሁን ላደረግህልኝ ቸርነትና ታማኝነት ብቁ አይደለሁም፤ ዮርዳኖስን ስሻገር በእጄ ላይ ከነበረው በትር በስተቀር ምንም አልነበረኝም፤ አሁን ግን ይኸው ሁለት ሠራዊት ሆኛለሁ።
\s5
\v 11 ከወንድሜ ከዔሳው እጅ እንድታድነኝ እለምንሃለሁ፤ መጥቶ እኔንም ሆነ እነዚህን እናቶች ከነልጆቻቸው ያጠፋናል ብዬ ፈርቻለሁኝ፤
\v 12 ነገር ግን አንተ ራስህ፣ ‘አበለጽግሃለሁ፤ ዘርህንም ሊቆጠር እንደማይችል እንደ ባሕር አሸዋ አበዛዋለሁ’ ብለኸኛል።”
\s5
\v 13 በዚያችም ሌሊት ያዕቆብ እዚያው አደረ፤ ካለው ሀብት ለወንድሙ ለኤሳው እጅ መንሻ እንዲሆኑ እነዚህን መረጠ፦
\v 14 ሁለት መቶ እንስት ፍየሎችና ሃያ አውራ ፍየሎች፣ ሁለት መቶ እንስት በጎችና ሃያ አውራ በጎች፣
\v 15 ሠላሳ የሚያጠቡ ግመሎች ከነግልገሎቻቸው፣ አርባ ላሞችና ዐሥር ኮርማዎች፣ ሃያ እንስት አህዮችና ዐሥር ተባት አህዮች።
\v 16 እነዚህንም በየመንጋው ለይቶ፣ የሚነዱአቸውን ጠባቂዎች መደበላቸው፤ ጠባቂዎችንም እናንተ ቀድማችሁ ሂዱ፣ መንጋዎቹንም አራርቃችሁ ንዱአቸው” አላቸው።
\s5
\v 17 ቀድሞ የሚሄደውንም እንዲህ ሲል አዘዘው፤ ዔሳው አግኝቶህ ‘የማን ነህ? ወዴትስ ትሄዳለህ? የምትነዳውስ ይህ ሁሉ ከብት የማን ነው? ብሎ ቢጠይቅህ፣
\v 18 ‘የአገልጋይህ የያዕቆብ ናቸው፤ ለጌታዬ ለዔሳው እጅ መንሻ የሰደዳቸው ናቸው፤ እርሱም ከበስተኋላችን እየመጣ ነው’ ብለህ ንገረው
\s5
\v 19 እንዲሁም ሁለተኛውን፣ ሦስተኛውንና መንጎቹን የሚነዱትን ሌሎቹንም ሁሉ እንዲህ ሲል አዘዛቸው፤ ‘ዔሳውን ስታገኙት ይህንኑ ትነግሩታላችሁ፤
\v 20 በተጨማሪም ‘አገልጋይህ ያዕቆብ ከኋላችን እየመጣ ነው’ በሉት። ይህንንም ያዘዘው፣ ‘ዔሳው ከእኔ ጋር ከመገናኘቱ በፊት እጅ መንሻዬ አስቀድሞ ቢደርሰው ምናልባት ልቡ ይራራና በሰላም ይቀበለኛል’ ብሎ ስላሰበ ነበር።
\v 21 ስለዚህ የያዕቆብ እጅ መንሻ ከእርሱ አስቀድሞ ተላከ፤ እርሱ ራሱ ግን እዚያው በሰፈሩ ቦታ አደረ።
\s5
\v 22 በዚያኑ ሌሊት ያዕቆብ ተነሣ ሁለቱን ሚስቶቹን፣ ሁለቱን ሴት አገልጋዮቹንና ዐሥራ አንዱን ልጆቹን ይዞ የያቦቅን ወንዝ ተሻገረ።
\v 23 ወንዙን አሻግሮ ከሸኛቸው በኋላ፣ ጓዙን ሁሉ ሰደደ።
\s5
\v 24 ያዕቆብም ብቻውን እዚያ ቀረ፤ አንድ ሰውም እስኪነጋ ድረስ ሲታገለው አደረ።
\v 25 ያም ሰው ያዕቆብን ታግሎ ማሸነፍ እንዳቃተው በተረዳ ጊዜ፣ የጭኑን ሹልዳ መታው፣ ያዕቆብም በሚታገልበት ጊዜ ጭኑ ከመገጣጠሚያው ላይ ተለያየ፤
\v 26 በዚያን ጊዜ ሰውዬው፣ “እንግዲህ መንጋቱ ስለሆን ልቀቀኝና ልሂድ” አለው። ያዕቆብም፣ “ካልባረክኸኝ አልለቅህም” አለው።
\s5
\v 27 ሰውዬውም፣ “ስምህ ማን ነው?” አለው። እርሱም፣ “ያዕቆብ ነው” አለ።
\v 28 ሰውዬውም፣ “ከእግዚአብሔርም ከሰዎችም ጋር ታግለህ አሸንፈሃልና ከእንግዲህ ስምህ እስራኤል እንጂ ያዕቆብ አይባልም” አለው።
\s5
\v 29 ያዕቆብም፣ “እባክህ ስምህን ንገረኝ” ብሎ ጠየቀው። ሰውዬውም፣ “ስሜን ለማወቅ ለምን ፈለግህ?” አለው፤ በዚያም ስፍራ ባረከው።
\v 30 ስለዚህ ያዕቆብ “እግዚአብሔርን ፊት ለፊት ዐይቼ እንኳ ሕይወቴ ተርፋለች” ሲል የዚያን ቦታ ስም ጵኒኤል አለው።
\s5
\v 31 ጵኒኤልንም እንዳለፈ ፀሐይ ወጣችበት፣ እርሱም በጭኑ ምክንያት ያነክስ ነበር።
\v 32 ከዚህም የተነሣ የእስራኤል ልጆች ሹልዳን ከጭኑ ጋር የሚያገናኘውን ሥጋ አይበሉም፤ ምክንያቱም ያዕቆብ ከሰውዬው ጋር ሲታገል ሰውዬው ሹልዳውን መትቶት ስለነበር ነው።
\s5
\c 33
\p
\v 1 ያዕቆብ አሻግሮ ተመለከተ፤ እነሆ፣ ዔሳው አራት መቶ ሰዎች አስከትሎ እየመጣ ነበር። ስለዚህ ያዕቆብ ልጆቹን ለልያ ለራሔልና ለሁለቱ አገልጋዮቹ አከፋፈላቸው።
\v 2 ከዚያም ሁለቱን አገልጋዮች ከነልጆቻቸው አስቀደመ፤ ልያንና ልጆቿንም አስከተለ፤ ራሔልንና ዮሴፍን ግን ከሁሉ ኋላ እንዲሆኑ አደረገ።
\v 3 እርሱ ራሱም ቀድሞአቸው ሄደ፤ ወንድሙም ዘንድ እስኪደርስ ድረስ ሰባት ጊዜ ወደ መሬት ለጥ ብሎ እጅ ነሣ።
\s5
\v 4 ዔሳው ግን ሊገናኘው ወደ እርሱ ሮጦ ሄዶ አቀፈው፤ በአንገቱም ላይ ተጠምጥሞ ሳመው፤ ሁለቱም ተላቀሱ።
\v 5 ከዚያም ዔሳው ቀና ብሎ ሲመለከት ሴቶቹንና ልጆቹን ዐየ፤ እርሱም፣ “እነዚህ አብረውህ ያሉ እነማን ናቸው?” ብሎ ጠየቀው። ያዕቆብም መልሶ፣ “እነዚህማ እግዚአብሔር በቸርነቱ ለእኔ ለአገልጋይህ የሰጠኝ ልጆች ናቸው” አለው።
\s5
\v 6 በዚህ ጊዜ ሁለቱ ሴት አገልጋዮችና ልጆቻቸው ቀርበው እጅ ነሡ፤
\v 7 ከዚያም ልያና ልጆቿ መጥተው እጅ ነሡ፤ በመጨረሻም ዮሴፍና ራሔል መጡ፤ እነርሱም ቀርበው እጅ ነሡ።
\v 8 ዔሳውም፣ “ወደ እኔ ተነድቶ የመጣው ይህ ሁሉ መንጋ ምንድነው?” አለው። ያዕቆብም፣ “ጌታዬ ሆይ፣ በአንተ ዘንድ ሞገስ ባገኝ ብዬ ነው” አለው።
\s5
\v 9 ዔሳው ግን፣ “ወንድሜ ሆይ፤ እኔ በቂ አለኝ፤ የራስህን ለራስህ አድርገው” አለው።
\v 10 ያዕቆብም፣ “የለም፣ እንዲህ አይደለም፤ በአንተ ዘንድ ሞገስ አግኝቼ እንደሆነ፣ እጅ መንሻዬን ተቀበል፤ በመልካም ሁኔታ ተቀብለኸኝ ፊትህን ማየት መቻሌ ራሱ፣ የእግዚአብሔርን ፊት የማየት ያህል እቆጥረዋለሁ።
\v 11 እግዚአብሔር በቸርነቱ አሟልቶ ስለ ሰጠኝ የሚያስፈልገኝ ሁሉ አለኝና ያቀረብሁልህን እጅ መንሻ እባክህ ተቀበለኝ” አለው። ያዕቆብ አጥብቆ ስለለመነው፣ ዔሳው እጅ መንሻውን ተቀበለ።
\s5
\v 12 ዔሳውም፣ “እንግዲህ እንሂድ፤ እኔም ከአንተ ቀድሜ እሄዳለሁ” አለው።
\v 13 ያዕቆብ ግን እንዲህ አለው፤ “ጌታዬ እንደምታየው ልጆቹ ይህን ያህል የጠኑ አይደሉም፣ ለሚያጠቡት በጎችና ጥገቶች እንክብካቤ ማድረግ አለብኝ፤ እንስሳቱ ለአንዲት ቀን እንኳ በጥድፊያ ቢነዱ በሙሉ ያልቃሉ።
\v 14 ስለዚህ ጌታዬ፣ አንተ ቀድመኸኝ ሂድ፤ እኔም በምነዳቸው እንስሳትና በልጆቹ ጉዞ አቅም ልክ እያዘገምሁ ሴይር ላይ እንገናኛለን”
\s5
\v 15 ዔሳው፣ “እንግዲያስ ከሰዎቼ ጥቂቶቹን ልተውልህ” አለው። ያዕቆብ ግን፣ “ለምን ብለህ? በአንተ ዘንድ ሞገስ ማግኘቴ ይበቃኛል” አለው።
\v 16 ስለዚህ ዔሳው በዚሁ ዕለት ወደ ሴይር ለመመለስ ተነሣ።
\v 17 ያዕቆብ ግን ወደ ሱኮት ሄደ፤ እዚያም ለራሱ መጠለያ፣ ለከብቶቹም በረት ሠራ፤ ከዚህም የተነሣ የቦታው ስም ሱኮት ተባለ።
\s5
\v 18 ያዕቆብ ከመስጴጦምያ በተመለሰ ጊዜ በከነዓን ምድር ወዳለችው ወደ ሴኬም በሰላም ደረሰ፤ በከተማይቱም ፊት ለፊት ሰፈረ።
\v 19 ድንኳኑን የተከለበትንም ቦታ የሴኬም አባት ከነበረው ከኤሞር በመቶ ጥሬ ብር ገዛው፤
\v 20 በዚያም መሠዊያ አቁሞ፤ ኤል ኤሎሄ እስራኤል ብሎ ጠራው።
\s5
\c 34
\p
\v 1 ልያ ለያዕቆብ የወለደችለት ሴት ልጅ ዲና፤ አንድ ቀን የዚያን አገር ሴቶች ለማየት ወጣች።
\v 2 የአገሩ ገዥ የኤዊያዊ የኤሞር ልጅ ሴኬም ባያት ጊዜ ያዛት በማስገደድም ክብረ ንጽሕናዋን ደፈረ።
\v 3 ልቡ በያዕቆብ ልጅ በዲና ተማረከ፤ ልጅቷንም በጣም ወደዳት፤ በጣፈጠም አንደበት አናገራት።
\s5
\v 4 ሴኬምም አባቱን ኤሞርን፣ “ይህችን ልጅ አጋባኝ” አለው።
\v 5 ያዕቆብ የልጁን የዲናን ክብረ-ንጽሕና ሴኬም እንደደፈረ ሰማ፤ ነገር ግን ወንዶች ልጆቹ የከብት መንጋ ይዘው ተሰማርተው ስለነበር፣ እነርሱ እስኪመጡ ዝም ብሎ ቆየ፤
\s5
\v 6 ከዚያም የሴኬም አባት ኤሞር፣ ያዕቆብን ሊያነጋግረው ወጣ።
\v 7 የያዕቆብ ወንዶች ልጆችም የተፈጸመውን ድርጊት እንደሰሙ ወዲያውኑ ከመስክ መጡ፤ ሴኬም መደረግ የማይገባውን አስነዋሪ ነገር በእስራኤል ላይ በመፈጸም የያዕቆብን ልጅ ስለደፈረ አዘኑ እጅግም ተቆጡ።
\s5
\v 8 ኤሞር ግን እንዲህ አላቸው፤ “ልጄ ሴኬም ልጃችሁን በጣም ወዶአታል፤ ስለዚህ እንዲያገባት ፍቀዱለት፤
\v 9 በጋብቻ እንተሳሰር፣ ሴት ልጃችህን ስጡን፣ የእኛንም ሴቶች አግቡ።
\v 10 አብራችሁንም መኖት ትችላላችሁ፤ አገራችን አገራችሁ ናት፣ ኑሩባት፤ ነግዱባት፣ ሀብት ንብረትም አፍሩባት።
\s5
\v 11 ሴኬም ደግሞ የዲናን አባትን ወንድሞች እንዲህ አላቸው። “በእናንተ ዘንድ ሞገስ ላግኝ እንጂ የተጠየቅሁትን ሁሉ እሰጣለሁ፤
\v 12 ለሙሽራዋም ጥሎሽ የፈለጋችሁትን ያህል ጠይቁኝ፤ እርሷን እንዳገባ ፍቀዱልኝ እንጂ፣ የፈለጋችሁትን ሁሉ ለመጠት ዝግጁ ነኝ።”
\v 13 ሴኬም እኅታቸውን ዲናን አስነውሮ ስለነበር የያዕቆብ ልጆች ለእርሱና ለአባቱ በተንኮል እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው፣
\s5
\v 14 እንዲህ አሉአቸው፤ “እኅታችንን ላልተገረዘ ሰው ብንሰጥ ውርደት ስለሚሆንብን፣ እንዲህ ያለውን ነገር አናደርገውም።
\v 15 ሆኖም የምንስማማበት አንድ መንገድ ብቻ አለ፤ ይኸውም አንተና በእናንተ ዘንድ ያሉት ወንዶች ሁሉ እንደኛ የተገረዛችሁ እንደሆነ ነው።
\v 16 እንዲህ ከሆነ እናንተ የእኛን ሴቶች ልጆች ታገባላችሁ፣ እኛም የእናንተን ሴቶች ልጆች እናገባለን፣ አንድ ሕዝብ ሆነንም አብረን እንኖራለን።
\v 17 ዐሳባችንን ባትቀበሉና ባትገረዙ ግን እኅታችንን ይዘን እንሄዳለን።
\s5
\v 18 ያቀረቡትም ዐሳብ ለኤሞርና ለልጁ ለሴኬም መልካም መስሎ ታያቸው።
\v 19 ከአባቱ ቤተሰብ ሁሉ እጅግ የተከበረው ይህ ወጣት የያዕቆብን ልጅ እጅግ ወዶአት ስለነበር፣ ያሉትን ለማድረግ ጊዜ አልወሰደበትም።
\s5
\v 20 ስለዚህ ኤሞርና ልጁ ሴኬም ይህንኑ ለወገኖቻቸው ለመንገር ወደ ከተማቸው በር ሄዱ፤
\v 21 እንዲህም አሏቸው፤ “እነዚህ ሰዎች ከእኛ ጋር የሚኖሩት በሰላም ነው፣ በምድሪቱ ላይ አብረው ይቀመጡ፣ ተዘዋውረውም እንዲነግዱ እንፍቀድላቸው፤ ምድሪቱ እንደሆን ለእኛም ለእነርሱም ትበቃለች። ሴቶች ልጆቻቸውን እናገባለን፤ እነርሱም የእኛን ሴቶች ልጆች ያገባሉ፤
\s5
\v 22 ሆኖም ሰዎቹ ከእኛ ጋር እንደ አንድ ሕዝብ ሆነው አብረውን ለምኖር ፈቃደኞች የሚሆኑት፣ የእኛ ወንዶች እንደ እነርሱ የተገረዙ እንደሆነ ብቻ ነው።
\v 23 ታዲያ እንዲህ ብናደርግ ከብታቸው ንብረታቸው፣ እንስሶቻቸውም ሁሉ የእኛው ይሆኑ የለምን? ስለዚህ ባሉት እንስማማ፣ እነርሱም አብረውን ይኑሩ።”
\s5
\v 24 የከተማይቱ ነዋሪዎች ሁሉ ኤሞርና ሴኬም ባቀረቡት ዐሳብ ተስማምተው ወንዶቹ ሁሉ ተገረዙ።
\v 25 በሦስተኛውም ቀን የሁሉም ቁስል ገና ትኩስ ሳለ ከያዕቆብ ልጆች ሁለቱ፣ የዲና ወንድሞች ስምዓንና ሌዊ፣ ሰይፋቸውን መዘው ሳይታሰብ ወደ ከተማይቱ ገብተው ወንዶቹን በሙሉ ገደሏቸው።
\v 26 ኤሞርንና ሴኬምንም በሰይፍ ገድለው፣ እኅታቸውን ዲናን ከሴኬም ቤት አውጥተው ይዘዋት ተመለሱ።
\s5
\v 27 የቀሩትም የያዕቆብ ልጆች እኅታቸውን ስለደፈሩባቸው ወደ ሞቱት ሰዎች ቤት እየገቡ ከተማይቱን በሙሉ ዘረፉ።
\v 28 የበግና የፍየል መንጎቻቸውን፣ ከብቶቻቸውንና አህዮቻቸውን እንዲሁም በከተማይቱና በአካባቢው የሚገኘውን ንብረታቸውን ሁሉ ወሰዱባቸው፤
\v 29 ሀብታቸውን ሁሉ ዘርፈው ሴቶቻቸውንና ሕፃናቶቻቸውን ሁሉ ማርከው በየቤቱ ያገኙትን ሁሉ ይዘው ሄዱ።
\s5
\v 30 ያዕቆብ ስምዖንና ሌዊን እንዲህ አላቸው፤ “በእኔ ላይ ከባድ ችግር አመጣችሁብኝ፤ እነሆ፣ በዚህ ድርጊት የተነሣ በዚህች ምድር የሚኖሩ ከነዓናውያንና ፌርዛውያን ይጠሉኛል፤ እኛ በቁጥር አነስተኞች ነን፣ እነርሱ ተባብረው ቢያጠቁን እኔና ቤተሰቤ እንጠፋለን።”
\v 31 ስምዖንና ሌዊ ግን፣ “ታዲያ ሴኬም እኅታችንን እንደዝሙት አዳሪ ይድፈራትን?” አሉት።
\s5
\c 35
\p
\v 1 እግዚአብሔር ያዕቆብን፣ “ተነሣና ወደ ቤቴል ሂድ፣ እዚያም ኑር። ከወንድምህ ከዔሳው ሸሽተህ በሄድህ ጊዜ ለተገለጠልህ አምላክ በዚያ መሠዊያ ሥራ አለው።
\v 2 ስለዚህም ያዕቆብ ለቤቱ ሰዎችና አብረውት ለነበሩት ሁሉ እንዲህ አላቸው፤ “በእናንተ ዘንድ ያሉትን ባዕዳን አማልክት አስወግዱ፤ ሰውነታችሁን አንጹ፤ ልብሳችሁንም ለውጡ።
\v 3 ተነሥተን ወደ ቤቴል እንሂድ፤ እዚያም በመከራዬ ጊዜ ለሰማኝ በሄድሁበትም ስፍራ ሁሉ ላልተለየኝ አምላክ መሠዊያ እሠራለሁ።
\s5
\v 4 ስለዚህ በእነርሱ ዘንድ የነበሩትን ባዕዳን አማልክት ሰብስበው፣ የጆሮ ጉትቾቻቸውን አውልቀው ለያዕቆብ ሰጡት። ያዕቆብም ወስዶ ሴኬም አጠገብ ካለው ዋርካ ዛፍ ሥር ቀበራቸው።
\v 5 ያንንም ቦታ ለቀው ሄዱ፤ እግዚአብሔርም በዙሪያቸው በነበሩት ከተሞች ሁሉ ላይ ፍርሃትና ድንጋጤ ስለለቀቀባቸው ያሳደዳቸው አልነበረም።
\s5
\v 6 ያዕቆብና አብረውት የነበሩት ሰዎች ሁሉ በከነዓን ወደምትገኘው፣ ቤቴል ወደተባለችው ወደ ሎዛ ደረሱ።
\v 7 ያዕቆብም በዚያ ስፍራ መሠዊያ ሠርቶ፣ ስሙን ኤል ቤቴል አለው፤ ምክንያቱም ከወንድሙ ሸሽቶ በሄደ ጊዜ እግዚአብሔር የተገለጠለት በዚህ ቦታ ነበር።
\v 8 በዚህ ጊዜ የርብቃ ሞግዚት ዲቦራ ሞተች፣ ከቤቴል ዝቅ ብሎ በሚገኘው የዋርካ ዛፍ ሥር ተቀበረች። ከዚህ የተነሣም ያ ቦታ አሉንባኩት ተባለ።
\s5
\v 9 ያዕቆብ ከመስጴጦምያ በተመለሰ ጊዜ እግዚአብሔር ዳግመኛ ተገለጠለትና ባረከው።
\v 10 እግዚአብሔርም፣ “እስካሁን ስምህ ያዕቆብ ነበር፤ ከእንግዲህ ያዕቆብ ተብለህ አትጠራም፤ ነገር ግን ስምህ እስራኤል ይባላል” አለው። ስለዚህም እስራኤል ብሎ ጠራው።
\s5
\v 11 ደግሞም እግዚአብሔር ያዕቆብን እንዲህ አለው፤ “እኔ ሁሉም ማድረግ የሚችል አምላክ ነኝ፤ ብዙ ልጆች ይኑሩህ፤ ዘርህም ይብዛ፤ የብዙ ሕዝብ አባት ሁን፤ ነገሥታትም ከአንተ ይወለዱ።
\v 12 ለአብርሃምና ለይስሐቅ የሰጠኋትን ምድር ለአንተ እሰጣለሁ፤ ከአንተም በኋላ ይህችን ምድር ለዘርህ አሰጣለሁ።”
\v 13 እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከተነጋገረ በኋላ ከዚያ ስፍራ ወደ ላይ ወጣ።
\s5
\v 14 ያዕቆብ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር በተነጋገረበት ስፍራ የድንጋይ ሐውልት አቆመ፣ በሐውልቱ ላይ የመጠጥ ቁርባን አፈሰሰ፤ ዘይትም አፈሰሰበት።
\v 15 ያዕቆብም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር የተነጋገረበትን ስፍራ ቤቴል ብሎ ጠራው።
\s5
\v 16 ከዚያም ከቤቴል ተነሥተው ሄዱ፤ ኤፍራታ ለመድረስ ጥቂት ሲቀራቸው ራሔልን ምጥ ያዛት፣ ምጡም ጠናባት።
\v 17 ምጧ እየበረታ በሄደ ጊዜ አዋላጅቱ፣ “አይዞሽ አትፍሪ፤ ሌላ ወንድ ልጅ ልትወልጂ ነው” አለቻት።
\v 18 እርስዋ ግን ልትሞት ታጣጥር ስለነበር ከመሞቷ በፊት ልጅዋን ‘ቤንኦኒ’ አለችው፤ አባቱ ግን ‘ብንያም’ አለው።
\v 19 ራሔል ሞተች፤ ወደ ኤፍራታ በሚወስደው መንገድ በቤተልሔም ተቀበረች።
\v 20 ያዕቆብም በራሔል መቃብር ላይ ሐውልት አቆመ፤ እስከዛሬም የራሔል መቃብር ምልክት ይኸው ሐውልት ነው።
\s5
\v 21 ያዕቆብ ጉዞውን ቀጥሎ በዔዴር ግንብ ባሻገር ድንኳን ተክሎ ሰፈረ።
\v 22 ያዕቆብ በዚያ ምድር ሲኖር ሳለ፣ ሮቤል ከአባቱ ቁባት ከባላ ጋር የግብረሥጋ ግንኙነት አደረገ፤ ያዕቆብም ይህን ነገር ሰማ ያዕቆብ ዐሥራ ሁለት ወንዶች ልጆች ነበሩት፣ እነርሱም፦
\s5
\v 23 የልያ ልጆች፦ የያዕቆብ የበኩር ልጅ ሮቤል፣ ስምዖን፣ ሌዊ፣ ይሁዳ፣ ይሳኮር፣ ዛብሎን፤
\v 24 የራሔል ልጆች፦ ዮሴፍ፣ ብንያም፤
\v 25 የራሔል አገልጋይ የባላ ልጆች፦ ዳን፣ ንፍታሌም፤
\s5
\v 26 የልያ አገልጋይ የዘለፋ ልጆች፦ ጋድ፣ አሴር፣ ናቸው። እነዚህ ወንዶች ልጆች ያዕቆብ በመስጴጦምያ ሳለ የተወለዱለት ናቸው።
\v 27 ያዕቆብ በቂርያት አርባቅ (በኬብሮን) አጠገብ መምሬ በምትባል ስፍራ ወደሚኖረው አባቱ ወደ ይስሐቅ ሄደ፤ ይህም ስፍራ አብርሃምና ይስሐቅ የኖሩበት ነው።
\s5
\v 28 ይስሐቅ መቶ ሰማንያ ዓመት ኖረ፤
\v 29 አርጅቶ ዕድሜ ጠግቦ ሞተ፤ ወደ ወገኖቹ ተሰበሰበ፤ ልጆቹም ዔሳውና ያዕቆብ ቀበሩት።
\s5
\c 36
\p
\v 1 ኤዶም የተባለው የዔሳው የትውልድ ታሪክ የሚከተለው ነው፤
\v 2 ዔሳው ከነዓናውያን ሴቶችን አገባ፤ እነርሱም የኬጢያዊው የዔሎን ልጅ ዓዳን፣ የኤውያዊው የፅብዖን ልጅ ዓና የወለዳት አህሊባማ፣
\v 3 እንዲሁም የነባዮት እኅት የሆነችውን የእስማኤል ልጅ ቤስሞት ነበሩ።
\s5
\v 4 ዓዳ ለዔሳው ኤልፋዝን ወለደችለት።
\v 5 እንደዚሁም አህሊባማ የዑስን፣ የዕላምንና ቆሬን ወለደችለት፤ እነዚህ ዔሳው በከነዓን አገር የወለዳቸው ልጆቹ ናቸው።
\s5
\v 6 ዔሳው ሚስቶቹንና ወንዶችና ሴቶች ልጆቹን፣ ቤተ ሰቦቹን በሙሉ እንደዚሁም የቀንድ ከብቶቹንና ሌሎቹንም እንስሳት ሁሉ በከነዓን ምድር ያፈራውን ሀብት እንዳለ ይዞ ከወንድሙ ከያዕቆብ ራቅ ወዳለ ቦታ ሄደ።
\v 7 ብዙ ሀብት ስለነበራቸው አብረው መኖር አልቻሉም፣ የነበሩበትም ስፍራ ከከብቶቻቸው ብዛት የተነሣ ሊበቃቸው አልቻለም።
\v 8 ስለዚህ ዔዶም የተባለው ዔሳው መኖሪያውን በተራራማው አገር በሴይር አደረገ።
\s5
\v 9 በተራራማው አገር በሴይር የሚኖሩ የኤዶማውያን አባት፣ የዔሳው ዝርያዎች እነዚህ ናቸው፤
\v 10 የዔሳው ልጆች ስም፦ የዔሳው ሚስት የዓዳ ልጅ ኤልፋዝና የዔሳው ሚስት የቤሴሞት ልጅ ራጉኤል፤
\v 11 የኤልፋዝ ልጆች፦ ቴማን፣ ኦማር፣ ስፎ፣ ጎቶም ቄኔዝ፤
\v 12 የዔሳው ልጅ ኤልፋዝ ትምናዕ የምትባል ቁባት ነበረችው፤ እርሷም አማሌቅን ወለደችለት፤ የዔሳው ሚስት የዓዳ የልጅ ልጆች እነዚህ ናቸው።
\s5
\v 13 የራጉኤል ልጆች፦ ናሖት፣ ዛራ፣ ሣማና ሚዛህ፤ እነዚህም ደግሞ የዔሳው ሚስት የቤሴሞት የልጅ ልጆች ናቸው።
\v 14 የፅብዖን የልጅ ልጅ፤ የዓና ልጅ የዔሳው ሚስት አህሊባማ ለዔሳው የወለደቻቸው ልጆች፦ የዑስ፣ የዕላማና ቆሬ፤
\s5
\v 15 ከዔሳው ዝርያዎች እነዚህ የነገድ አለቆች ነበሩ፤ የዔሳው የበኩር ልጅ የኤልፋዝ ልጆች፦ ቴማን፣ ኦማር፣ ስፎ፣ ቄኔዝ
\v 16 ቆሬ፣ ጎቶምና አማሌቅ፤ እነዚህ በኤዶም ምድር ከኤልፋዝ የተገኙ የነገድ አለቆች፣ የዓዳ የልጅ ልጆች ነበሩ።
\s5
\v 17 የዔሳው ልጅ የራጉኤል ልጆች፦ ናሖት፣ ዛራ፣ ሃማና፣ ሚዛህ፤ እነዚህ በኤዶም ምድር ከራጉኤል የተገኙ የነገድ አለቆች፣ የዔሳው ሚስት የቤሴሞት የልጅ ልጆች ነበሩ።
\v 18 የዔሳው ሚስት የአሕሊባማ ልጆች፦የዑስ፣ የዕላማና ቆሬ፤ እነዚህ ከዓና ልጅ ከዔሳው ሚስት አሕሊባማ የተገኙ የነገድ አለቆች ነበሩ።
\v 19 እነዚህም ኤዶም የተባለው የዔሳው ልጆችና የነገድ አለቆቻቸው ነበሩ።
\s5
\v 20 በኤዶም ምድር ነዋሪዎች የነበሩት የሴይር ልጆች የነበሩ የሖራውያን አለቆች፦ ሎጣን፣ ሦባል፣ ፅብዖን፣ ዓና፣
\v 21 ዲሶን፣ ኤድርና ዲሳን፤ እነዚህ በኤዶም የነበረው የሴይር ልጆች፣ በሖራውያን የነገድ አለቆች ነበሩ።
\v 22 የሎጣን ልጆች፦ ሖሪና ሔማም የሎጣንም እኅት ቲምናዕ ትባል ነበር።
\s5
\v 23 የሦባል ልጆች፦ ዓልዋን፣ ማኔሐት፣ ዔባልና ስፎና አውናንም፤
\v 24 የፅብዖን ልጆች፦ አያና፣ ዓና፤ ይህ ዓና የአባቱን የፅባዖንን አህዮች ሲጠብቅ፣ የፍልውሃ ምንጮችን በምድረበዳ ያገኘ ሰው ነው።
\s5
\v 25 የዓና ልጆች፦ዲሶንና የዓና የሴት ልጅ አህሊባማ፤
\v 26 የዲሶን ልጆች፦ ሔምዳን፣ ሴስባን፣ ይትራንና ክራን፤
\v 27 የኤድር ልጆች፦ ቢልሐን፣ ዛዕዋንና ዓቃን፤
\v 28 የዲሳን ልጆች፦ዑፅና አራን።
\s5
\v 29 የሖራውያን የነገድ አለቆች እነዚህ ነበሩ፦ሎጣን፣ ሦባል፣ፅዖን፥ ዓና፣
\v 30 ዶሶን፣ ኤድርና ዲሳን፤ እነዚህ በሴይር ምድር እንደየነገዳቸው የሖራውያን የነገድ አለቆች ነበሩ።
\s5
\v 31 ንጉሥ በእስራኤል ከመንገሡ በፊት፣ በኤዶም የነገሡ ነገሥታት እነዚህ ነበሩ፦
\v 32 የቢዖር ልጅ ባላቅ በኤዶም ነግሦ ነበር፤ የከተማውም ስም ዲንሃባ ይባል ነበር።
\v 33 ባላቅ ሲሞት፣ በስፍራውም የባሶራው የዛራ ልጅ ኢዮባብ ነገሠ።
\s5
\v 34 የባሶራው የዛራ ልጅ ኢዮባብ ሲሞት የቴማኒው ሑሳም ነገሠ።
\v 35 ሑሳም ሲሞት፣ የምድያምን ሰዎች በሞዓብ ምድር ድል ያደረጋቸው የባዳድ ልጅ ሃዳድ በምትኩ ነገሠ፤ የከተማውም ስም ዓዊት ይባል ነበር።
\v 36 ሃዳድ ሲሞት፣ የመሥሬቃው ሠምላ በምትኩ ነገሠ።
\s5
\v 37 ሠምላ ሲሞት፣ በወንዙ አጠገብ ያለው የርሆቦቱ ሳኦል በምትኩ ነገሠ።
\v 38 ሳኦል ሲሞት፣ የዓክቦር ልጅ በልሐናን በምትኩ ነገሠ።
\v 39 የዓክቦር ልጅ በልሐናን ሲሞት፣ ሃዳር በምትኩ ነገሠ፤ የከተማውም ስም ፋዑ ይባል ነበር፤ የሚስቱም ስም መሄጣብዔል ሲሆን፣ እርሷም መጥሬድ የወለደቻት የሜዛሃብ ልጅ ነበረች።
\s5
\v 40 ከዔሳው የተገኙት የነገድ አለቆች ስም፣ እንደየነገዳቸውና እንደየአገራቸው ይህ ነው፦ ቲምናዕ፣ ዓለዋ፣ የቴት፣
\v 41 አህሊባማ፣ ኤላ፣ ፌኖን፣
\v 42 ቄኔዝ፣ ቴማን፣ ሚብሳር፣
\v 43 መግዲኤልና ዒራም፣ እነዚህ በያዙት ምድር እንደየይዞታቸው ከኤዶም የተገኙ የነገድ አለቆች ነበሩ። ይህም ዔሳው የኤዶማውያን አባት ነበር።
\s5
\c 37
\p
\v 1 የዕቆብ አባቱ በኖረበት በከነዓን ምድር ተቀመጠ።
\v 2 የያዕቆብ ትውልድ ታሪክ ይህ ነው። ዮሴፍ የዐሥራ ሰባት ዓመት ወጣት በነበረ ጊዜ፣ ከአባቱ ሚስቶች ከባላቅና ከዘለፋ ከተወለዱት ወንድሞቹ ጋር የአባቱን በጎችና ፍየሎች ይጠብቅ ነበር። እርሱም ስለወንድሞቹ ድርጊት ለአባቱ መጥፎ ወሬ ይዞለት መጣ።
\s5
\v 3 እስራኤል ዮሴፍን በስተርጅናው ስለወለደው፣ ከልጆቹ ሁሉ አብልጦ ይወደው ነበር፣ በኅብረ ቀለማት ያጌጠ እጀ ጠባብም ሰፋለት።
\v 4 ወንድሞቹም አባታቸው ከእነርሱ አብልጦ የሚወደው መሆኑን ሲያዩ ዮሴፍን ጠሉት፤ በቅን አንደበት ሊያናግሩት አልቻሉም።
\s5
\v 5 ዮሴፍ ሕልም አለመ፤ ሕልሙንም ለወንድሞቹ ሲነግራቸው የባሰ ጠሉት፤
\v 6 እርሱም እንዲህ አላቸው፤ “ያየሁትን ሕልም ልንገራችሁ አድምጡኝ”
\s5
\v 7 ‘እኛ ሁላችን በእርሻ ውስጥ ነዶ እናስር ነበር፤ የእኔ ነዶ ተነሣና ቀጥ ብሎ ቆመ፤ የእናንተ ነዶዎች ዙሪያውን ተሰብስበው ለእኔ ነዶ ሰገዱለት’”
\v 8 ወንድሞቹም፣ “ታዲያ በእኛ ላይ ንጉሥ ሆነህ ልትገዛን ታስባለህን?” ብለው ጠየቁት። ስለ ሕልሙና ስለተናገረው ቃል ከፊት ይልቅ ጠሉት።
\s5
\v 9 እንደ ገናም ሌላ ሕልም አለመ፤ ለወንድሞቹም እነሆ፣ ሌላ ሕልም አለምሁ፣ ፀሐይና ጨረቃ፣ ዐሥራ አንድ ክዋክብትም ሲሰግዱልኝ ዐየሁ” ብሎ ነገራቸው።
\v 10 ይህንኑ ለወንድሞቹ የነገራቸውን ሕልም ለአባቱም በነገረው ጊዜ፣ አባቱ፣ “ይህ ምን ዐይነት ሕልም ነው? እኔና እናትህ ወንድሞችህም በፊትህ ወደ ምድር ተጎንብሰን በርግጥ ልንሰግድልህ ነው?” ሲል ገሠጸው።
\v 11 ወንድሞቹ ቀኑበት፤ አባቱ ግን ነገሩን በልቡ ያዘው።
\s5
\v 12 አንድ ቀን የዮሴፍ ወንድሞች የአባታቸውን መንጋዎች ይዘው ወደ ሴኬም ተሰማሩ፤
\v 13 እስራኤልም ዮሴፍን፣ “እንደምታውቀው ወንድሞችህ መንጎቹን በሴኬም አካባቢ አሰማርተዋል፤ በል ተነሥ፣ ወደ እነርሱ ልላክህ” አለው። ዮሴፍም፣ “እሺ እሄዳለሁ” አለ።
\v 14 አባቱም፣ “በል እንግዲህ ሄድና የወንድሞችህንና የመንጋዎቹን ደኅንነት አይተህ ንገረኝ” አለው። በዚህ ዓይነት እስራኤል ዮሴፍን ከኬብሮን ሸለቆ ላከው። ዮሴፍም ሴኬም በደረሰ ጊዜ፣
\s5
\v 15 ሜዳ ላይ ወዲያ ወዲህ ሲባዝን አንድ ሰው አግኝቶት፣ “ምን እየፈለግህ ነው?” ሲል ጠየቀው።
\v 16 ዮሴፍም፣ “ወንድሞቼን እየፈለግኋቸው ነው፤ መንጎቻቸውን የት እንዳሰማሩ ልትነግረኝ ትችላለህ?” አለው።
\v 17 ሰውዬውም፣ “ከዚህ ሄደዋል፤ ደግሞም ‘ወደ ዶታይን እንሂድ’ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ” አለው። ከዚያም ዮሴፍ ወንድሞቹን ፍለጋ ሄደ፣ በዶታይን አቅራቢያም አገኛቸው።
\s5
\v 18 ወንድሞቹም ዮሴፍ ወደ እነርሱ ሲመጣ በሩቅ ዐዩት፣ ወደ ነበሩበትም ስፍራ ከመድረሱ በፊት ሊገድሉት ተማከሩ።
\v 19 እነርሱ እንዲህ ተባባሉ፦ “ያ ሕልም አላሚ መጣ፤
\v 20 ኑ እንግደለውና ከጉድጓዶቹ በአንዱ ውስጥ እንጣለው፤ ከዚያም፣ ‘ክፉ አውሬ ነጥቆ በላው’ እንላለን፤ እስቲ ሕልሞቹ ሲፈጸሙ እናያለን።”
\s5
\v 21 ሮቤል ግን ይህን ምክር ሲሰማ ከእጃቸው ሊያድነው ፈለገ እንዲህም አለ፤ “አንግደለው፤
\v 22 የሰው ደም አታፍስሱ፣ ከምትገድሉት ይልቅ በዚህ በበረሃ ባለው ጉድጓድ ውስጥ ጣሉት” አላቸው። ሮቤል ይህን ያለው ሕይወቱን ከእጃቸው አትርፎ ወደ አባቱ ሊመልሰው ዐስቦ ነበር።
\s5
\v 23 ዮሴፍ ወደ ወንድሞቹ እንደደረሰ፣ የለበሳትን በኅብረ ቀለማት የጌጠች እጀ ጠባቡን ገፈፉት፤
\v 24 ይዘውም ወደ ጉድጓድ ጣሉት፤ ጉድጓዱም ውሃ የሌለበት ደረቅ ነበር።
\s5
\v 25 ምግባቸውን ለመብላት ተቀመጡ፤ አሻግረው ሲመለከቱም ከገለዓድ የሚመጡ እስማኤላውያን ነጋዴዎች ጓዛቸውን በግመሎች ላይ ጭነው ተመለከቱ። ነጋዴዎቹ ሽቶ፣ በለሳን፣ ከርቤ በግመሎቻቸው ጭነው ወደ ግብፅ የሚወርዱ ነበሩ።
\v 26 ይሁዳም ወንድሞቹን እንዲህ አላቸው፤ “ወንድማችንን መግደልና አሟሟቱን መደበቅ ምን ይጠቅመናል?
\s5
\v 27 ከዚህ ይልቅ ለእስማኤላውያን ነጋዴዎች እንሽጠው፤ እጃችንን ግን በእርሱ ላይ አናንሳ። ምንም ቢሆን የሥጋ ወንድማችን ነው” ወንድሞቹም በሃሳቡ ተስማሙ።
\v 28 የምድያም ነጋዴዎች የሆኑ እስማሴላውያን በዚያ በኩል ያልፉ ነበር፤ ስለዚህ ወንድሞቹ ዮሴፍን ከጉድጓድ ጎትተው በማውጣት ለእነዚህ እስማኤላውያን በሃያ ብር ሸጡላቸው፣ እነርሱም ወደ ግብፅ ይዘውት ሄዱ።
\s5
\v 29 ሮቤል ወደ ጉድጓዱ ተመልሶ ሲያይ፣ ዮሴፍን በማጣቱ ልብሱን በሐዘን ቀደደ።
\v 30 ወደ ወንድሞቹም ተመልሶ፣ “እነሆ፣ ልጁ እዚያ የለም! እንግዲህ እኔ ወዴት ብሄድ ይሻለኛል?” አለ።
\s5
\v 31 ከዚህ በኋላ አንድ ፍየል አረዱና የዮሴፍን ልብስ በደም ነከሩት።
\v 32 በኅብረ ቀለማት ያጌጠችውን እጀ ጠባብ ወደ አባታቸው ወስደው፣ “ይህን ወድቆ አገኘነው፤ የልጅህ እጀ ጠባብ መሆን አለመሆኑን እስቲ እየው” አሉት።
\v 33 እርሱ የልጁ ልብስ መሆኑን ተረድቶ፣ “ይህማ የልጄ እጀ ጠባብ ነው! ፤ ክፉ አውሬ በልቶታል፣ በእርግጥም ዮሴፍ ተቦጫጭቆአል” አለ።
\s5
\v 34 ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ልብሱን ቀደደ፤ ማቅም ለብሶ ስለ ልጁ ብዙ ቀን አለቀሰ፤
\v 35 ወንዶችና ሴቶች ልጆቹም ሁሉ ሊያጽናኑት መጡ፤ እርሱ ግን ሊጽናና አልቻለም፣ “በሐዘን እንደተኮራመትሁ ልጄ ወዳለበት መቃብር እወርዳለሁ” አለ። ስለ ልጁም አለቀሰ።
\v 36 በዚህ ጊዜ የምድያም ነጋዴዎች ዮሴፍን ወደ ግብፅ ወስደው፣ ከፈርዖን ሹማምንት አንዱ ለነበረው ለዘበኞች አለቃ፣ ለጲጥፋራ ሸጡት።
\s5
\c 38
\p
\v 1 በዚያም ወራት ይሁዳ ከወንድሞቹ ተለይቶ ሒራ ወደተባለ ዐዱላማዊ ሰው ዘንድ ሄደ፣ መኖሪያውንም
\v 2 እዚያም ሳለ፣ ይሁዳ የከነዓናዊውን የሴዋን ሴት ልጅ ዐየ፤ እርሷንም አግብቶ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ፈጸመ።
\s5
\v 3 እርሷም አርግዛ ወንድ ልጅ ወለደችለት፤ ስሙንም ዔር ብላ ጠራችው።
\v 4 እንደገናም አረገዘችና ወንድ ልጅ ወለደችለት፤ ስሙንም አውናን አለችው።
\v 5 አሁንም ደግማ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ሴሎም ብላ ጠራችው፣ እርሱንም የወለደችው ክዚብ በተባለ ቦታ ነበር።
\s5
\v 6 ይሁዳ የመጀመሪያ ልጁን ዔርን ትዕማር ከምትባል ልጃገረድ ጋር አጋባው።
\v 7 የይሁዳ የበኩር ልጅ ዔር ግን በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነበር፤ እግዚአብሔርም ቀሠፈው።
\s5
\v 8 ይሁዳ አውናንን፣ “ዋርሳዋ እንደመሆንህ ከወንድምህ ሚስት ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት በመፈጸም የወንድምህን ስም የሚያስጠራለት ዘር ተካለት አለው።
\v 9 አውናን ግን የሚወለደው ልጅ የእርሱን ስም የሚያስጠራ እንደማይሆን ስላወቀ፣ ከወንድሙ ሚስት ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት በፈጸመ ቁጥር የወንድሙን ስም የሚያስጠራ ልጅ እንዳይወለድ ዘሩን በምድር ላይ ያፈስ ነበር።
\v 10 ይህም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሆኖ ስለተገኘ፣ እርሱንም እግዚአብሔር በሞት ቀሠፈው።
\s5
\v 11 ከዚያም ይሁዳ ምራቱን ትዕማርን፣ “ልጄ ሴሎም ለአካለ መጠን እስኪደርስ ድረስ ወደ አባትሽ ቤት ሄደሽ መበለት ሆነሽ ብትኖሪ ይሻላል” አላት፤ ይህን ያለውም፤ ሴሎም እንደወንድሞቹ ተቀሥፎ ይሞትብኛል ብሎ ስለፈራ ነበር። ትዕማርም እንዳላት ሄደች፤ በአባቷም ቤት ተቀመጠች።
\s5
\v 12 ከብዙ ጊዜ በኋላ የሹዓ ልጅ፣ የይሁዳ ሚስት ሞተች። ይሁዳ ከሐዘኑ ከተጽናና በኋላ ከዓዶላማዊው ከሒራ ጋር የበጎቹን ጠጉር የሚሸልቱ ሰዎች ወዳሉበት ወደተምና ሄደ።
\v 13 ሰዎቹም ለትዕማር፣ “አማትሽ የበጎቹን ጠጉር ወደሚሸልቱ ሰዎች ዘንድ ወደተምና እየሄዱ ነው” አሏት። ይህን እንድሰማች
\v 14 የመበለትነት ልብሷን አውልቃ፣ ማንነቷ እንዳይታወቅ ፊቷን በሻሽ ተከናንባ ወደ ተምና በሚወስደው መንገድ ዳር ባለች ኤናይም በተባለች ከተማ መግቢያ በር ላይ ተቀመጠች፤ ይህን ያደረገችው፣ ሴሎም ለአካለ መጠን ቢደርስም፣ እርሷን እንዲያገባ አባቱ አለመፈለጉን ስላወቀች ነው።
\s5
\v 15 ፊቷ በሻሽ ተሸፋፍኖ ሲያያት፣ ይሁዳ ዝሙት አዳሪ መሰለችው።
\v 16 ምራቱ መሆኗን ባለማወቁ፣ እርሷ ወዳለችበት ወደ መንደሩ ዳር ጠጋ ብሎ፣ “እባክሽን አብሬሽ ልተኛ” አላት። እርሷም፣ “አብሬህ ብተኛ ምን ትሰጠኛለህ?” ብላ ጠየቀችው።
\s5
\v 17 “ከመንጋዬ መካከል አንድ የፍየል ጠቦት እልክልሻለሁ” አላት። እርሷም “ጠቦቱን እስክትልክልኝ ድረስ ምን መያዣ ትሰጠኛለህ?” ብላ ጠየቀችው።
\v 18 “ታዲያ ምን መያዣ ልስጥሽ?” አላት። እርሷም፣ “የማኅተም ቀለበትህን ከነማሰሪያው፣ እንደዚሁም ይህን በትርህን ስጠኝ” አለችው። የጠየቀችውን ሁሉ ሰጣትና አብሯት ተኛ፤ እርሷም አረገዘችለት።
\s5
\v 19 ከዚያም ወደ መኖሪያዋ ተመልሳ፣ ሻሽዋን አውልቃ እንደወትሮዋ የመበለት ለብሷን ለበሰች።
\v 20 ይሁዳ በመያዣ ስም የሰጣትን ዕቃዎች ለማስመለስ የፍየሉን ጠቦት በዓዶሎማዊ ወዳጁ እጅ ላከላት፣ እርሱ ግን ሊያገኛት አልቻለም።
\s5
\v 21 “በኤናይም ከተማ መግቢያ ከመንገዱ ዳር የነበረች ያቺ ዝሙት አዳሪ የት ደረሰች?” ብሎ ዓዶሎማዊው ሰውዬ ጠየቀ። ሰዎቹም፣ “በዚህ አካባቢ እንደዚህ ያለች ዝሙት አዳሪ የለችም” አሉት።
\v 22 ስለዚህ ወደ ይሁዳ ተመልሶ ሄደና፣ “ላገኛት አልቻልሁም፤ በዚያ የሚኖሩትም ሰዎች፥ ‘እንደዚህ ያለች ዝሙት አዳሪ እዚህ የለችም’ አሉኝ” ብሎ ነገረው።
\v 23 ይሁዳም፣ “እንግዲህ መያዣውን እንደያዘች ትቅር አለዚያ መሳቂያ እንሆናለን። ለነገሩማ ይህን ፍየል ላክሁ፣ አንተም ፈልገህ አላገኘሃትም” አለ።
\s5
\v 24 ከሦስት ወር ያህል በኋላ፣ “ምራትህ ትዕማር ዘማዊ ሆናለች፤ ከዚህም የተነሣ አርግዛለች” ተብሎ ለይሁዳ ተነገረው። ይሁዳም፣ “አውጧትና በእሳት ተቃጥላ ትሙት” አለ።
\v 25 እርሷም ተይዛ በምትወሰድበት ጊዜ ለአማትዋ፣ “እኔ ያረገዝሁት የእነዚህ ዕቃዎች ባለቤት ከሆነ ሰው ነው” ስትል ላከችበት፤ ደግሞም፣ “የማኅተሙ ቀለበት ከነማንጠልጠያውና በትሩ የማን እንደሆነ እስቲ ተመልከት” አለችው።
\v 26 ይሁዳም ዕቃዎቹን አውቆ፣ “ልጄ ሴሎም እንዲያገባት ባለማድረጌ፣ እርሷ ከእኔ ይልቅ ትክክል ናት” አለ። ከዚያም በኋላ ከእርሷ ጋር አልተኛም።
\s5
\v 27 የመውለጃዋ ጊዜ እንደደረሰም ፅንሷ መንታ መሆኑ ታወቀ።
\v 28 በምትወልድበትም ጊዜ አንደኛው እጁን አወጣ፤ አዋላጂቱም፣ “ይህኛው መጀመሪያ ወጣ” ስትል በእጁ ላይ ቀይ ክር አሰረችለት፤
\s5
\v 29 ነገር ግን፣ እጁን መልሶ ሲያስገባ ወንድሙ ተወለደ። አዋላጂቱም፣ “አንተ እንዴት ጥሰህ ወጣህ!” አለች፣ ከዚያም ስሙ ፋሬስ ተባለ።
\v 30 ከዚያ በኋላ እጁ ላይ ቀይ ክር የታሰረለት ወንድሙ ተወለደ፣ ስሙም ዛራ ተባለ።
\s5
\c 39
\p
\v 1 ዮሴፍ ወደ ግብፅ ተወስዶ ነበር፤ ከፈርዖንም ሹማምንት አንዱ የነበረውም የዘበኞች አለቃ፣ ግብፃዊው ጴጥፋራ ወደዚያ ከወሰዱት ከእስማኤላውያን ነጋዴዎች እጅ ገዛው።
\v 2 እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋር ስለነበረ ኑሮው ተቃናለት፤ እርሱም በግብፃዊው አሳዳሪው ቤት ኖረ።
\s5
\v 3 አሳዳሪው እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር እንዳለና ሥራውንም ሁሉ እንዳከናወነለት ባየ ጊዜ፣
\v 4 ዮሴፍ በእርሱ ዘንድ ሞገስ አገኘ፣ የቅርብ አገልጋዩም ሆነ። ጲጥፋራ በቤቱ ላይ ሾመው፣ ያለውንም ሀብት ሁሉ በኃፊነት ሰጠው።
\s5
\v 5 ዮሴፍ በጲጥፋራ ቤትና ባለው ሀብት ሁሉ ላይ ከተሾመበት ጊዜ ጀምሮ እግዚአብሔር የግብፅዊውን ቤት ባረከ፣ የእግዚአብሔርም በረከት በግቢም በውጭም ባለው የጲጥፋራ ሀብት ንብረት ሁሉ ላይ ሆነ።
\v 6 ስለዚህ ጲጥፋራ ባለው ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጠው፣ የቀረበለትንም ከመመገብ በስተቀር፣ ማናቸውንም ጉዳይ በዮሴፍ ላይ ጥሎ ነበር። ዮሴፍ ጥሩ ቁመና ያለውና መልከ-መልካም ነበር፤
\s5
\v 7 ከጊዜ በኋላ የጌታው ሚስት ዮሴፍን ተመልክታ ስላፈቀረችው፣ “ና ከእኔ ጋር አብረን እንተኛ” አለችው።
\v 8 እርሱ ግን ይህን ለመፈጸም ፈቃደኛ አልሆነም፤ እንዲህም አላት፤ “ጌታዬ ያለውን ሁሉ በኃላፊነት ስለሰጠኝ፣ በቤቱ ውስጥ ስላልው ሁሉ ምንም የሚያውቀው ነገር የለም።
\v 9 በዚህ ቤት ላይ ከእኔ የበለጠ ኃላፊነት ያለው ማንም የለም፣ ከአንቺ በቀር በእኔ ቁጥጥር ሥር ያላደረገው ምንም ነገር የለም፤ ይኸውም ሚስቱ ስለሆንሽ ነው፤ ታዲያ፣ እኔ ይህን ክፉ ድርጊት በእግዚአብሔር ፊት እንዴት እፈጽማለሁ?”
\s5
\v 10 ይህንም ነገር በየዕለቱ ለዮሴፍ ትነግረው ነበር፤ እርሱም ከእርሷ ጋር ይተኛ ዘንድ ከእርስዋም ጋር ይሆን ዘንድ አልሰማትም።
\v 11 አንድ ቀን ዮሴፍ ለሥራ ጉዳይ ወደ ቤት ሲገባ በቤት ውስጥ አንድም ሠራተኛ አልነበረም፤
\v 12 እርሷም ልብሱን ጨምድዳ ይዛ፣ “በል አብረኸኝ ተኛ” አለችው። እርሱ ግን ልብሱን እጅዋ ላይ ትቶላት ከቤት ሸሽቶ ወጣ።
\s5
\v 13 እርሷም ልብሱን በእጅዋ ላይ ትቶ ከቤት ሸሽቶ መውጣቱን በተመለከተች ጊዜ፣
\v 14 አገልጋዮችዋን ጠርታ እንዲህ አለቻቸው፣ “እነሆ፣ ባለቤቴ ያመጣው ይህ ዕብራዊ ሊያዋርደኝ ነበር፤ ወዳለሁበት ክፍል ገብቶ ሊደፍረኝ ሞከረ፤ እኔ ግን ድምፄን ከፍ አድርጌ ጮኽሁ።
\v 15 ዕርዳታ ለማግኘትም መጮኼን በሰማ ጊዜ ልብሱን በአጠገቤ ትቶ ከቤት ሸሽቶ ወጣ።”
\s5
\v 16 የዮሴፍ አሳዳሪ እስኪመጣ ድረስ ልብሱን በእርስዋ ዘንድ አቆየችው።
\v 17 በመጣም ጊዜ የሆነውን ታሪክ እንዲህ ስትል ዘርዝራ ነገረችው፤ “አንተ ወደዚህ የመጣኸው ዕብራዊ አገልጋይ ወዳለሁበት ክፍል ገብቶ ሊያዋርደኝ ነበር።
\v 18 ነገር ግን ድምፄን ከፍ አድርጌ በጮኽሁ ጊዜ ልብሱን በአጠገቤ ትቶ ከቤት ሸሽቶ ወጣ።”
\s5
\v 19 “የአንተ አገልጋይ እንዲህ አደረገኝ” ብላ የነገረችውን ታሪክ በሰማ ጊዜ የዮሴፍ አሳዳሪ እጅግ ተቆጣ።
\v 20 ዮሴፍንም ወስዶ፣ የንጉሥ እስረኞች ወደታሠሩበት እስር ቤት አስገባው።
\s5
\v 21 እግዚአብሔር ዘላለማዊ ፍቅሩን ዐሳየው፣ በእስር ቤት አዛዡም ዘንድ ሞገስን ሰጠው።
\v 22 ስለዚህ የእስር ቤቱ አዛዥ ዮሴፍን የእስረኞች ሁሉ አለቃ አደረገው፤ በእስር ቤት ላለውም ነገር ሁሉ ኃላፊ ሆነ።
\v 23 እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋር ሆኖ የሚያደርገው ነገር ሁሉ እንዲቃናለት ስላደረገ የእስር ቤት አዛዥ በዮሴፍ ቁጥጥር ሥር በነበረው ነገር ምንም ዐሳብ አልነበረበትም።
\s5
\c 40
\p
\v 1 ከዚህም በኋላ የግብፅ ንጉሥ የመጠጥ አሳላፊውና የእንጀራ ቤት ኃላፊው ንጉሡን የሚያሳዝን በደል ፈጸሙ።
\v 2 ፈርዖንም በመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃና በእንጀራ ቤቱ አዛዡ፣ በሁለቱም ሹማምንቱ ላይ እጅግ ተቆጣ፤
\v 3 በዘበኞቹ አለቃ ቤት ወዳለው ዮሴፍ ወደታሠረበት እስር ቤት አስገባቸው።
\s5
\v 4 የዘበኞቹም አለቃ እስረኞቹን ለዮሴፍ አስረከባቸው፤ በእስር ቤትም ለጥቂት ጊዜ ቆዩ።
\v 5 ታስረው የነበሩት የግብፅ ንጉሥ የመጠጥ አሳላፊዎች አለቃና የእንጀራ ቤቱ አዛዥ፣ በአንድ ሌሊት የየራሳቸውን ሕልም ዐዩ፤ የሁለቱም ሕልም ለየራሱ የተለየ ፍቺ ነበረው።
\s5
\v 6 በማግስቱ ጥዋት ዮሴፍ እነርሱ ወዳሉበት ክፍል በገባ ጊዜ ተክዘው አገኛቸውና፤
\v 7 “ዛሬ በፊታችሁ ላይ ሐዘን የሚታየው ለምንድን ነው?” አላቸው።
\v 8 እነርሱም፣ “ሁለታችንም ሕልም ዐየን፤ ነገር ግን የሚተረጉምልን ሰው አጣን” ሲሉ መለሱለት። ዮሴፍም፣ “ሕልም የመተርጎም ችሎታ የሚሰጥ እግዝአብሔር ነው፣ ስለዚህ የእያንዳንዳችሁን ሕልም ንገሩኝ” አላቸው።
\s5
\v 9 ስለዚህ የመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃ እንዲህ ሲል ሕልሙን ለዮሴፍ ነገረው፤ “ከፊት ለፊቴ አንዲት የወይን ተክል ዐየሁ፤
\v 10 ተክሏም ሦስት ሐረጎች ነበሯት፤ ወዲያው እቆጥቁጣ አበበች፤ የወይን ዘለላውም ወዲያው በሰለ።
\v 11 የፈርዖንንም ጽዋ ይዤ ነበር፣ የወይኑን ፍሬ ለቅሜ በጽዋው ውስጥ ጨምቄ ጽዋውን በእጁ ሰጠሁት።”
\s5
\v 12 ዮሴፍም እንዲህ አለው፤ “እንግዲህ የሕልሙ ትርጓሜ ይህ ነው፤ ሦስቱ ሐረግ ሦስት ቀን ነው፤
\v 13 በሦስት ቀን ውስጥ ፈርዖን ከእስር ቤት ያወጣሃል፣ ወደ ቀድሞ ሹመትህም ይመልስሃል፤ በፊት የመጠጥ አሳላፊ በነበርህበት ጊዜ ታደርግ እንደነበረው ኡሉ የፈርዖንን ጽዋ በእጁ ትሰጠዋለህ።
\s5
\v 14 እንግዲህ፣ በጎ ነገር በገጠመህ ጊዜ፣ እኔን አስበህ ቸርነት አድርግልኝ፣ ስለ እኔም ለፈርዖን ንገርልኝ፤ ከዚህም እስር ቤት አስወጣኝ፤
\v 15 ከዕብራውያን ምድር ወደዚህ የመጣሁት በአፈና ነው፤ አሁንም ቢሆን እዚህ እስር ቤት የተጣልሁት አንዳች ጥፋት ኖሮብኝ አይደለም።”
\s5
\v 16 የእንጀራ ቤት አዛዡም፣ ለመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃ ሕልም የተሰጠው ፍቺ ደስ የሚያሰኝ መሆኑን ሲሰማ፣ የራሱን ሕልም ለዮሴፍ እንዲህ ሲል ነገረው፤ “እኔም ደግሞ ሕልም አይቻለሁ፣ ሦስት መሶቦች በራሴ ላይ ተሸክሜ ነበር፤
\v 17 በላይኛው መሶብ ውስጥ ለፈርዖን የተዘጋጀ የተለያየ ምግብ ነበረበት፣ ነገር ግን ወፎች ምግቡን ከመሶቡ እያነሱ የበሉት ነበር።”
\s5
\v 18 ዮሴፍም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “የሕልሙ ፍቺ ይህ ነው፤ ሦስቱ መሶብ ሦስት ቀን ነው፤
\v 19 በሦስት ቀን ውስጥ ፈርዖን ራስህን ካስቆረጠ በኋላ በእንጨት ላይ ይሰቅልሃል፤ ወፎችም ሥጋህን የበሉታል።”
\s5
\v 20 በሦስተኛው ቀን የፈርዖን ልደት በዓል ስለነበር ለመኳንንቱ ሁሉ ግብዣ አደረገ፤ በዚያኑ ዕለትም የመጠጥ አሳላፊዎቹን አለቃና የእንጀራ ቤት አዛዡን ሹማምንቱ ካሉበት ከእስር ቤት አወጣቸው።
\v 21 የመጠጥ አሳላፊዎቹን አለቃ ወደ ቀድሞ ሹመቱ መለሰው፤ እርሱም እንደ ቀድሞው ጽዋውን ለፈርዖን በእጁ ይሰጠው ጀመር፤
\v 22 የእንጀራ ቤት አዛዡን ግን ልክ ዮሴፍ እንደተረጎመላቸው ሰቀለው።
\v 23 የሆነው ሆኖ፣ የመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃ ዮሴፍን አላስታወሰውም፤ ረሳው።
\s5
\c 41
\p
\v 1 ድፍን ሁለት ዓመት ካለፈ በኋላ ፈርዖን ሕልም ዐለም፤ ሕልሙም በዓባይ ወንዝ ዳር ቆሞ ነበር፤
\v 2 እነሆ፣ መልካቸው ያማረ፣ ሥጋቸው የወፈረ ሰባት ላሞች ከወንዙ ወጥተው በወንዙ ዳር የበቀለውን ሣር ይበሉ ጀመር።
\v 3 ቀጥሎም መልካቸው የከፋ አጥንታቸው የወጣ ሌሎች ሰባት ላሞች ከወንዙ ወጥተው አስቀድመው ከወጡት ላሞች አጠገብ ቆሙ።
\s5
\v 4 እነዚህ መልካቸው የከፋና አጥንታቸው የወጣ ላሞች፥ እነዚያን ያማሩና የወፈሩ ላሞች ሲውጡአቸው ዐየ፤ ከዚያም ፈርዖን ከእንቅልፉ ነቃ።
\v 5 ፈርዖንም እንደገና እንቅልፍ ወስዶት ሳለ ሌላ ሕልም ዐየ። በሕልሙም በአንድ የእህል አገዳ ላይ ሰባት የዳበሩና ያማሩ የእሸት ዛላዎች ዐየ፤
\v 6 ቀጥሎም የቀጨጩና ከበረሐ በተነሣ የምሥራቅ ነፋስ ተመትተው የደረቁ ሰባት የእሸት ዛላዎች ወጡ።
\s5
\v 7 የቀጨጩት የእሸት ዛላዎች፤ ሰባቱን የዳበሩና ያማሩ የእሸት ዛላዎች ዋጡአቸው፤ በዚህ ጊዜ ፈርዖን ከእንቅልፉ ነቃ፣ ነገሩ ሕልም ነበር።
\v 8 በነጋታውም ፈርዖን መንፈሱ ታወከበት፣ ስለዚህ በግብፅ አገር ያሉትን አስማተኞችና ጥበበኞች በሙሉ አስጠርቶ ሕልሞቹን ነገራቸው፣ ይሁን እንጂ፣ ሕልሞቹን ሊተረጉምለት የቻለ አንድም ሰው አልተገኘም።
\s5
\v 9 በዚያን ጊዜ የመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃ ፈርዖንን እንዲህ አለው፤ “የሠራሁት በደል ዛሬ ታወሰኝ።
\v 10 ፈርዖን ሆይ! አንተ በእኔና በእንጀራ ቤት ኃላፊው ላይ ተቆጥተህ በዘበኞች አለቃ ቤት እንድንታሰር አድርገህ ነበር፤
\v 11 በዚያ ሳለን በአንድ ሌሊት ሁለታችንም የተለያየ ሕልም ዐየን፤ የእያንዳንዳችንም ሕልም የተለያየ ትርጉም ነበረው።
\s5
\v 12 በዚያን ጊዜ የዘበኞች አለቃ አገልጋይ የሆን አንድ ዕብራዊ ወጣት ከእኛ ጋር እስር ቤት ነበር። ሕልማችንን በነገርነው ጊዜ፣ ፍቺውን ነገረን፤ ለእያንዳንዳችንም እንደ ሕልማችን ተረጎመልን፤
\v 13 ነገሩም ልክ እርሱ እንደተረጎመልን፤ እኔ ወደ ቀድሞ ሹመቴ ተመለስሁ፤ የእንጀራ ቤት አዛዡም ተሰቀለ።
\s5
\v 14 ፈርዖን ዮሴፍን እንዲያመጡት ትዕዛዝ ሰጠ፤ ከእስር ቤትም በጥድፊያ ይዘውት መጡ፤ ጠጉሩንም ከተላጨና ልብሱን ከለወጠ በኋላ ፈርዖን ፊት ቀረበ
\v 15 ፈርዖንም ዮሴፍን፣ “ሕልም ዐይቼ ነበር፣ ሕልሜን ሊተረጉምልኝ የቻለ አንድም ሰው አልተገኘም፣ አንተ ግን ሕልም ሲነገርህ የመተርጎም ችሎታ እንዳለህ ሰማሁ” አለው።
\v 16 ዮሴፍም ለፈርዖን እንዲህ ብሎ መለሰ፦ “ይህ በእኔ አይደለም፤ እግዚአብሔር ግን ለፈርዖን በበጎነት ይመልስለታል”
\s5
\v 17 ፈርዖን ዮሴፍን እንዲህ አለው፤ “ሕልሜ በዓባይ ወንዝ ዳር ቆሜ ነበር።
\v 18 ሥጋቸው የወፈረና መልካቸው የማረ ሰባት ላሞች ከወንዙ ወጥተው በወንዙ ዳር የበቀለውን ሣር ሲበሉ ዐየሁ።
\s5
\v 19 ከእነርሱም በኋላ ዐቅመ ደካማ፣ መልካቸው እጅግ የከፋና አጥንታቸው የወጣ ሌሎች ሰባት ላሞች ወጡ፤ እነዚያን የመሰሉ የሚያስከፋ መልክ ያላቸው ላሞች በግብፅ ምድር ከቶ ዐይቼ አላውቅም።
\v 20 አጥንታቸው የወጣና አስከፊ መልክ ያላቸው ላሞች መጀመሪያ የወጡትን፣ ሥጋቸው የወፈረውን ሰባቱን ላሞች ዋጧቸው።
\v 21 ከዋጧቸውም በኋላ፣ ያው የበፊቱ መልካቸው ስላልተለወጠ እንደዋጧቸው ማንም ሊያውቅ አይችልም ነበር፤ ከዚያም ከእንቅልፌ ነቃሁ
\s5
\v 22 ደግሞም በአንድ የእህል አገዳ ላይ ሰባት የዳበሩና ያማሩ የእሸት ዛላዎች ዐየሁ፤
\v 23 ቀጥሎም የቀጨጩና የደረቁ ሌሎች ሰባት ዛላዎች ወጡ።
\v 24 የቀጨጩት የእሸት ዛላዎችም ሰባቱን ያማሩ የእሸት ዛላዎች ዋጧቸው፤ ያየኋቸውንም ሕልሞች ለአስማተኞች ነገርሁ፣ ነገር ግን ሕልሞቹን ማንም ሊተረጉምልኝ አልቻለም።”
\s5
\v 25 ዮሴፍም ለፈርዖን እንዲህ አለው፤ “ሁለቱም የፈርዖን ሕልሞች ተመሳሳይና አንድ ዓይነት ናቸው፤ እግዚአብሔር ወደፊት የሚያደርገውን ለፈርዖን ገልጦለታል።
\v 26 ሰባቱ የሚያምሩ ላሞች ሰባት ዓመታት ናቸው፣ ሰባቱም የሚያማምሩ የእሸት ዛላዎች ሰባት ዓመታት ናቸው፤ ሕልሙም አንድና ተመሳሳይ ነው።
\s5
\v 27 ከእነርሱም በኋላ አጥንታቸው የወጣ አስከፊ መልክ ያላቸው ሰባት ላሞች፣ ሰባት ዓመታት ናቸው፤ እንደዚሁም ፍሬ አልባ የሆኑትና በምሥራቅ ነፋስ ተመትተው የደረቁት ሰባት የእሸት ዛላዎች ሰባት የራብ ዓመታት ናቸው።
\v 28 አስቀድሜ ለፈርዖን እንደተናገርሁት እግዚአብሔር ወደፊት የሚያደርገውን ነገር ለፈርዖን ገልጦለታል።
\v 29 በመላው የግብፅ ምድር እጅግ የተትረፈረፈ ጥጋብ የሚሆንባቸው ሰባት ዓመታት ይመጣሉ።
\s5
\v 30 በዚህ በኋላ ግን በተከታታይ ሰባት የራብ ዓመታት ይሆናሉ። የራቡ ዘመን አገሪቱን እጅግ ስለሚጎዳት በግብፅ የነበረው ያለፈው የጥጋብ ዘመን ሁሉ ጨርሶ አይታወስም።
\v 31 ከጥጋብ ዓመታት በኋላ የሚመጣው የራብ ዘመን እጅግ ጽኑ ከመሆኑ የተነሣ፣ ቀደም ሲል የነበረው የጥጋብ ዘመን ፈጽሞ ይረሳል።
\v 32 ሕልሙ ለፈርዖን በድጋሚ መታየቱ፣ ነገሩ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተቆረጠ ስለሆነ ነው፤ ይህንንም እግዚአብሔር በቅርብ ጊዜ ይፈጽመዋል፤
\s5
\v 33 እንግዲህ ፈርዖን ብልኅና አስተዋይ ሰው ፈልጎ፣ በመላው የግብፅ ምድር ላይ አሁኑኑ ይሹም።
\v 34 እንደዚሁም በሰባቱ የጥጋብ ዓመታት ከሚገኘው ምርት፣ አንድ አምስተኛው እንዲሰበሰብ የሚያደርጉ ኃላፊዎችን ይሹም።
\s5
\v 35 እነርሱም በሚመጡት የጥጋብ ዓመታት ከሚገኘው ምርት ሁሉ ይሰብስቡ፤ በፈርዖንም ሥልጣን ሥር ያከማቹ፤ ለምግብ እንዲሆኑም በየከተማው ይጠበቁ።
\v 36 የሚከማቸው እህል፣ ወደፊት በግብፅ አገር ላይ ለሚመጣው የሰባት ዓመት ራብ መጠባበቂያ ይሁን፤ በዚህም ሁኔታ አገሪቱ በራብ አትጠፋም።
\s5
\v 37 ዕቅዱም ፈርዖንና ሹማምንቱ ሁሉ መልካም ሆኖ አገኙት።
\v 38 ፈርዖንም፣ “የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት እንደዚህ ያለ ሰው ልናገኝ እንችላለን?” ብሎ ጠየቃቸው።
\s5
\v 39 ፈርዖን ዮሴፍን እንዲህ አለው፣ “እግዚአብሔር ይህን ሁል ገለጠለህ እንዳንተ ያለ አስተዋይና ብልህ ሰው የለም።
\v 40 አንተ በቤተ መንግሥቴ የበላይ ትሆናለህ፤ ሕዝቤም ሁሉ ለሥልጣንህ ይገዛል፤ እኔ ከአንተ የምበልጠው በዙፋኔ ብቻ ይሆናል።”
\v 41 ከዚያም፣ ፈርዖን ዮሴፍን፣ “በመላይቱ የግብፅ ምድር ላይ ኃላፊ አድርጌሃለሁ” አለው።
\s5
\v 42 ፈርዖንም ባለማኅተሙን ቀለበት ከጣቱ አውልቆ በዮሴፍ ጣት ላይ አደረገው፤ እንዲሁም ከጥሩ የተልባ እግር የተሠራ ልብስ አለበሰው፤ በአንገቱም የወርቅ ሐብል አጠለቀለት።
\v 43 በማዕረግ ከእርሱ ሁለተኛ ሰው አድርጎ በሠረገላ ላይ አስቀመጠው። ሰዎችም በፊቱ፣ “እጅ ንሡ” እያሉ ይጮኹ ነበር፤ በዚህ ሁኔታም በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ ሾመው።
\s5
\v 44 ከዝህ በኋላ ፈርዖን ዮሴፍን፣ “እኔ ፈርዖን ነኝ፤ ሆኖም በመላይቱ ግብፅ ያለ አንተ ፈቃድ ማንም ሰው እጁን ወይም እግሩን ማንቀሳቀስ አይችልም” አለው።
\v 45 ፈርዖን ዮሴፍን ጸፍናት ፐዕናህ ብሎ ስም አወጣለት። እንዲሁም አስናት ተብላ የምትጠራውን ኦን ተብሎ የሚጠራው ከተማ ካህን የጶጢፌራን ልጅ በሚስትነት ሰጠው።
\s5
\v 46 ዮሴፍ የግብፅ ንጉሥ ፈርዖንን ማገልገል ሲጀምር፣ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበር። ዮሴፍም ከፈርዖን ፊት ወጥቶ የግብፅን ምድር በሙሉ ዞረ።
\v 47 በሰባቱም የጥጋብ ዓመታት ምድሪቱ የተትረፈረፈ ሰብል ሰጠች።
\s5
\v 48 በእነዚያ ሰባት የጥጋብ ዓመታት፣ ዮሴፍ በግብፅ አገር የተገኘውን ምርት ሰብስቦ በየከተሞቹ አከማቸ፣ በእያንዳንዱ ከተማ ከየአቅራቢያው የተመረተውን እህል እንዲከማች አደረገ።
\v 49 ዮሴፍ ብዛቱ እንደ ባሕር አሸዋ የሚሆን የእህል ሰብል አከማቸ፤ ሰብሉ እጅግ ከመብዛቱ የተነሣ ልኩን መስፈርና መመዝገብ አልቻለም ነበር።
\s5
\v 50 ሰባቱ የራብ ዓመታት ከመምጣታቸው በፊት የኦን ከተማ ካህን የጶጢፌራ ልጅ አስናት ለዮሴፍ ሁለት ወንድ ልጆች ወለደችለት።
\v 51 ዮሴፍም፣ “እግዚአብሔር መከራዬን ሁሉ የአባቴንም ቤት እንድረሳ አድርጎኛል” በማለት የመጀመሪያ ልጁን ስም ምናሴ አለው።
\v 52 እንደዚሁም “መከራ በተቀበልሁበት ምድር እግዚአብሔር ፍሬያማ አደረገኝ” ሲል ሁለተኛ ልጁን ኤፍሬም አለው።
\s5
\v 53 በግብፅ ምድር የነበረው ሰባቱ የጥጋብ ዘመን አለፈና
\v 54 ዮሴፍ አስቀድሞ እንደተናገረው የሰባቱ ዓመት የራብ ዘመን ጀመረ። ሌሎች አገሮች ሁሉ ሲራቡ፣ በመላው የግብፅ ምድር መስፋፋት ሲጀመር፣
\s5
\v 55 ሕዝቡ ምግብ ይሰጠን በማለት ወደ ፈርዖን ጮኸ። ፍርዖንም ግብፃውያኑን፣ “ወደ ዮሴፍ ሂዱና የሚላችሁን አድርጉ” አላቸው።
\v 56 ራቡ በአገሩ ላይ እየተስፋፋ ስለሄደ፣ ዮሴፍ ጎተራዎቹን ከፍቶ እህሉ ለግብፃውያን እንዲሸጥ አደረገ፤ ምክንያቱም ራቡ በመላይቱ ግብፅ ጸንቶ ነበር።
\v 57 ራቡ በመላው ዓለም ጸንቶ ስለነበር፣ የየአገሩ ሰዎች ሁሉ ከዮሴፍ ዘንድ እህል ለመሸመት ወደ ግብፅ ምድር መጡ።
\s5
\c 42
\p
\v 1 በግብፅ እህል መኖሩን ሲሰማ፣ ልጆቹን እንዲህ አላቸው፤ “ለምን እርስ በርስ ትተያያላችሁ?”
\v 2 በግብፅ አገር እህል መኖሩን ሰምቻለሁ፤ በራብ ከመሞታችን በፊት ወደዚያ ሂድና እህል ግዙልን” አላቸው።
\v 3 ስለዚህ ዐሥሩ የዮሴፍ ወንድሞች እህል ለመግዛት ወደ ግብፅ ሄዱ።
\v 4 ነገር ግን ያዕቆብ የዮሴፍን ወንድም ብንያምን ክፉ ነገር ይደርስበታል በሚል ፍርሃት ከወንድሞቹ ጋር አልላከውም።
\s5
\v 5 ራቡ በከነዓንም በመበርታቱ፣ እህል ለመሸመት ወደ ግብፅ ከሄዱት መካከል የእስራኤል ልጆችም ነበሩ።
\v 6 በዚህ ጊዜ ዮሴፍ የምድሪቱ ገዢ ነበር፣ ለአገሩ ሰዎች ሁሉ እህል የሚሸጥላቸው እርሱ ነበር። የዮሴፍ ወንድሞችም እንደደረሱ ከፊቱ ቀርበው ወደ ምድር ለጥ ብለው ሰገዱለት።
\s5
\v 7 ዮሴፍም ወንድሞቹን ባየ ጊዜ ዐወቃቸው፣ ነገር ግን የማያውቃቸው በመምሰል በቁጣ ቃል፣ “ከየት ነው የመጣችሁት?” ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱም፣ “እህል ለመሸመት ከከነዓን ምድር የመጣን ነን" ብለው መለሱለት።
\v 8 ዮሴፍ ወንድሞቹን ቢያውቃቸውም እንኳ እነርሱ ግን አላወቁትም።
\s5
\v 9 በዚህ ጊዜ ስለወንድሞቹ ያየው ሕልም ትዝ አለውና፣ “ሰላዮች ናችሁ፣ የመጣችሁት አገራችን በየትኛው በኩል ለጥቃት የተጋለጠች መሆኗን ለመሰለል ነው” አላቸው።
\v 10 እነርሱም እንዲህ አሉት፤ “ጌታችን ሆይ፣ እንዲህስ አይደለም፤ እኛ አገልጋዮችህ የመጣነው እህል ለመሸመት ነው፤
\v 11 ሁላችንም የአንድ አባት ልጆች ነን፤ አገልጋዮችህም የታመንን ሰዎች እንጂ ሰላዮች አይደለንም።”
\s5
\v 12 እርሱም መልሶ፣ “አይደለም፣ ግብፅ በየት በኩል ለጥቃት የተጋለጠች መሆኗን ለመሰለል ነው” አላቸው።
\v 13 እነርሱ ግን መልሰው፣ “እኛ አገልጋዮችህ በከነዓን አገር ከሚኖር ከአንድ ሰው የተወለድን ዐሥራ ሁለት ወንድማማቾች ነን። ትንሹ ወንድማችን አባታችን ዘንድ ሲሆን አንዱ ወንድማችን ሞቷል።
\s5
\v 14 ዮሴፍም እንዲህ አላቸው፤ “ነገርኋችሁ እኮ፤ ሰላዮች ናችሁ
\v 15 ታናሽ ወንድማችሁ እዚህ እስካልመጣ ድረስ ከዚህ ንቅንቅ እንደማትሉ በፈርዖን ስም እምላልሁ፤ ማንነታችሁ የሚረጋገጠውም በዚህ ነው።
\v 16 ከእናንተ አንዱ ሄዶ ወንድማችሁን ያምጣ፤ የተናገራችሁትም እውነት መሆኑ ተረጋግጦ ነጻ እስክትለቀቁ ድረስ የቀራችሁት እዚሁ በእስት ቤት ትቆያላችሁ፤”
\v 17 ሁሉንም ሦስት ቀን በእስር አቆያቸው።
\s5
\v 18 በሦስተኛውም ቀን ዮሴፍ እንዲህ አላቸው፤ “እኔ እግዚአብሔርን ስለምፈራ እንዲህ በማድረግ ሕይወታችሁን አትርፉ።
\v 19 ታማኝ ሰዎች ከሆናችሁ፣ ከመካከላችሁ እንዱ እዚህ እስር ቤት ሲቆይ፣ የቀራችሁት ግን ለተራቡት ቤተ ሰቦቻችሁ እህል ትወስዱላቸዋላችሁ፤
\v 20 ታናሽ ወንድማችሁን ግን ይዛችሁ መምጣት አለባችሁ፤ በዚህም የተናገራችሁት ቃል እውነተኛነት ይረጋገጣል፤ እናንተም ከመሞት ትተርፋላችሁ።” እነርሱም ይህንኑ ለመፈጸም ተስማሙ።
\s5
\v 21 እርስ በርሳቸውም እንዲህ ተባባሉ፤ “በእርግጥ በወንድማችን ላይ ስላደረስነው በደል ቅጣታችንን እየተቀበልን ነው። እርሱ እንደዚያ ተጨንቆ ስለ ሕይወቱ ሲማጠነን፣ እኛ አልሰማነውም ነበር፤ ይህ መከራ የደረሰብንም በዚሁ ምክንያት ነው” ተባባሉ።
\v 22 ሮቤልም መልሶ፣ “በዚህ ልጅ ላይ ክፉ ነገር እንዳታደርጉ ብዬ አልነበረምን? እናንተ ግን አልሰማችሁኝም፤ ስለዚህም ደሙ ከእጃችን ይፈለጋል” አላቸው።
\s5
\v 23 ዮሴፍ የሚያነጋግራቸው በአስተርጓሚ ስለሆነ የሚነጋገሩትን እንደሚሰማባቸው ዐላወቁም ነበር።
\v 24 ከፊታቸውም ዘወር ብሎ አለቀሰ፤ ከዚያም ወደእነርሱ ትመልሶ እንደገና አነጋገራቸው፤ ስምዖንንም ከእነርሱ ለይቶ ዓይናቸው እያየ አሰረው፤
\v 25 ዮሴፍ ለአገልጋዮቹ በስልቻዎቻቸው እህል እንዲሞሉላቸው፤ ብሩንም በያንዳንዱ ሰው ስልቻ ውስጥ መልሰው እንዲያስቀምጡና ለጉዞአቸው ስንቅ እንዲያሲዟቸው ትእዛዝ ሰጠ። ይህም ተደረገላቸው።
\s5
\v 26 እነርሱም እህላቸውን በአህዮቻቸው ጭነው ጉዞአቸውን ቀጠሉ።
\v 27 በመንገድም ለአዳር ሰፍረው ሳለ፣ ከእነርሱ አንዱ ከያዘው እህል ላይ ለአህያው ለመስጠት ስልቻውን ሲፈታ፣ በስልቻው አፍ ላይ ብሩን አገኘ።
\v 28 እርሱም ወንድሞቹን፣ “ኧረ ብሬ ተመልሶልኛል፤ ይኸው ስልቻዬ ውስጥ አገኘሁት” አላቸው። ሁሉም ልባቸው በድንጋጤ ተሞልቶ እየተንቀጠቀጡ በመተያየት፣ “እግዚአብሔር ምን ሊያመጣብን ይሆን?” አሉ።
\s5
\v 29 በከነዓን ምድር ወዳለው ወደ አባታቸው ወደ ያዕቆብ ከደረሱ በኋላ ያጋጠማቸውን ሁሉ እንዲህ ብለው ነገሩት፤
\v 30 “የግብፅ አገር አስተዳዳሪ ‘አገሬን ልትሰልሉ የመጣችሁ ናችሁ’ በማለት በቁጣ ቃል ተናገረን፤
\v 31 እኛ ግን እንዲህ አልነው፤ “እኛ የታመንን ሰዎች እንጂ ሰላዮች አይደለንም።
\v 32 እኛ የአንድ አባት ልጆች የሆንን ዐሥራ ሁለት ወንድማማቾች ነን፣ አንዱ የለም፣ ታናሽ ወንድማችን ግን ከአባታችን ጋር በከነዓን ይገኛል።’
\s5
\v 33 ከዚህ በኋላ የአገሩ ጌታ የሆነው ሰው እንዲህ አለን፣ “ታማኝ ሰዎች መሆናችሁን የማውቀው በዚህ ነው ከእናንተ መካከል አንዱን ወንድማችሁን እዚህ እኔ ዘንድ ትታችሁ የተቀራችሁት ለትራቡት ቤተ ሰቦቻችሁ እህል ይዛችሁላቸው ሂዱ።
\v 34 ነገር ግን ታናሽ ወንድማችሁን ወደ እኔ አምጡት። በዚያን ጊዜም ታማኝ ሰዎች እንጂ ሰላዮች አለመሆናችሁን ዐውቃለሁ፤ ወንድማችሁንም መልሼ እሰጣችኋለሁ፤ እናንተም በምድሪቱ እንደፈለጋችሁ እየተዘዋወራችሁ መነገድ ትችላላችሁ።
\s5
\v 35 እህሉንም ሲዘረግፉ በየስልቻቸው ውስጥ ብራቸው እንደተቋጠረ ተገኘ፤ የእያንዳንዳቸውን የተቋጠረ ብር ሲያዩም፣ እነርሱም ሆኑ አባታቸው ደነገጡ።
\v 36 አባታቸው ያዕቆብም፣ “ያለ ልጅ እኮ አስቀራችሁኝ፣ ዮሴፍ የለም፣ ስምዖንም የለም፤ አሁን ደግሞ ብንያምን ልትወስዱ ትፈልጋላችሁ፤ በዚህ ሁሉ መከራ የምሠቃየው እኔ ነኝ” አለ።
\s5
\v 37 በዚህን ጊዜ ሮቤል አባቱን፣ “ብንያምን ወደ አንተ መልሼ ባላመጣው ሁለቱን ወንዶች ልጆቼን ወስደህ ግደላቸው፣ ስለዚህ በእኔ ኃላፊነት ላከው፤ እኔም መልሼ አመጣዋለሁ” እለው።
\v 38 ያዕቆብም “ምንም ቢሆን ከእናንተ ጋር አይሄድም፤ ወንድሙ ሞቶአል፣ የቀረው እርሱ ብቻ ነው፤ በመንገድ አንድ ጉዳት ቢደርስበት በእርጅናዬ ዘመን በመሪር ሐዘን ወደ መቃብር እንድወርድ ታደርጉኛላችሁ” አላቸው።
\s5
\c 43
\p
\v 1 አሁንም በምድሪቱ ላይ እንደጸና ነበር፤
\v 2 ከግብፅ ያመጡትንም እህል በልተው ከጨረሱ በኋላ፣ አባታቸው፣ “እስቲ እንደገና ወርዳችሁ፣ ጥቂት እህል ሸምቱልን” አላቸው።
\s5
\v 3 ይሁዳ ግን እንዲህ አለው፤ “ ያ ሰው ወንድማችሁን ይዛችሁ ካልመጣችሁ ዳግመኛ ፊቴን ዐታዩም ብሎ በጥብቅ አስጠንቅቆናል፤
\v 4 ወንድማችን ከእኛ ጋር እንዲወርድ ከፈቀድህ ወደዚያ ሄደን እህል እንሸምትልሃለን፤
\v 5 እርሱን የማትልከው ከሆነ ግን እኛም ወደዚያ አንወርድም፤ ያም ሰው፣ ‘ወንድማችሁን ይዛችሁ ካልመጣችሁ ዳግመኛ ፊቴን ዐታዩም’ ብሎናል።”
\s5
\v 6 እስራኤልም፣ “ሌላ ወንድም አለን ብላችሁ ለዚያ ሰው በመንገር ለምን ይህን ችግር እንዲደርስብኝ አደረጋችሁ?” ሲል ጠየቃቸው።
\v 7 እነርሱም፣ “ሰውዬው ስለ ራሳችንና ስለ ቤተ ሰባችን አጥብቆ ጠየቀን፤ እንደገናም ‘አባታችሁ አሁንም በሕይወት አለ? ሌላስ ወንድም አላችሁ? ሲል ጠየቀን። እኛም ለጥያቄው መልስ ሰጠነው። ታዲያ፣ ‘ወንድማችሁን ይዛችሁ ወደዚህ እንድትመጡ’ እንደሚል እንዴት ማወቅ እንችል ነበር?” ብለው መለሱለት።
\s5
\v 8 ይሁዳም አባቱን እስራኤልን እንዲህ አለው፣ “ልጁን ከእኔ ጋር ስደደው፤ እኛም በቶሎ እንሂድ፣ ይህ ከሆነ አንተም፣ እኛም፣ ልጆቻችንም አንሞትም፣ እንተርፋለን።
\v 9 ስለ ልጁ ደኅንነት እኔ ራሴ ኃላፊ ነኝ፤ ስለ እርሱም በግል ተጠያቂ እሆናለሁ፤ እርሱንም በደኅና መልሼ ባላመጣውና እዚህ በፊትህ ባላቆመው ለዘላለም በደለኛ እኔ ልሁን።
\v 10 ይህን ያህል ባንዘገይ ኖሮ፣ እስካሁን ሁለት ጊዜ ደርሰን መመለስ በቻልን ነበር።”
\s5
\v 11 ከዚህ በኋላ አባታቸው እስራኤል እንዲህ አላቸው፤ “ነገሩ እንዲህ ከሆነስ ይህን አድርጉ፣ ምድሪቱ ከምታፈራቸው ምርጥ ነገሮች ጥቂት በለሳን፣ ጥቂት ማር፣ ሽቱ፣ ከርቤ፣ ተምርና ለውዝ በየስልቻችሁ ይዛችሁ ለዚያ ሰው ስጦታ ውሰዱለት።
\v 12 በየስልቾቻችሁ አፍ ላይ የተገኘውን ብር መመለስ ስላለባችሁ፣ ዕጥፍ ገንዘብ ያዙ፤ ያ በየስልቾቻችሁ ውስጥ የተገኘው ብር ምናልባት በስሕተት የመጣ ሊሆን ይችላል።
\s5
\v 13 ወንድማችሁንም ይዛችሁ ወደ ሰውዬው በቶሎ ሂዱ።
\v 14 ሌላውን ወንድማችሁንና ብንያምን ይዛችሁ ለመመለስ እንድትችሉ ሁሉን የሚችል አምላክ በምሕረቱ የዚያን ሰው ልብ ያራራላችሁ። እኔ በበኩሌ ልጆቼን ካጣሁ፣ ባዶ እጄን መቅረቴ ነው።”
\v 15 ስለዚህ ወንድማማቾቹ ገጸ በረከቱንና ዕጥፍ ገንዘብ ይዘው ከብንያም ጋር ወደ ግብፅ ለመሄድ ጉዞ ጀመሩ፤ እዚያም በደረሱ ጊዜ ዮሴፍ ፊት ቀረቡ።
\s5
\v 16 ዮሴፍ ብንያምን ከወንድሞቹ ጋር ባየው ጊዜ የቤቱን አዛዥ፣ “እነዚህን ሰዎች ወደ ቤት ይዘሃቸው ሂድ፣ ዛሬ ቀትር ላይ አብረውኝ ስለሚበሉ አንድ ከብት እረድና አዘጋጅ” አለው።
\v 17 አዛዡም ዮሴፍ የነገረውን አደረገ፣ ሰዎቹንም ወደ ዮሴፍ ቤት ወሰዳቸው።
\s5
\v 18 ሰዎቹም ወደ ዮሴፍ ቤት በመወሰዳቸው ፈሩ፤ እነርሱም፣ “ወደዚህ የመጣነው ቀደም ሲል እዚህ መጥተን ስንመለስ በየስልቾቻችን ውስጥ ተመልሶ በተጨመረው ብር ሰበብ ነው። ሰውዬው ሊያስረንና ባሪያዎች ሊያደርገን አህዮቻችንንም ሊወስድ ይችላል።”
\v 19 ወደ ዮሴፍ ቤት አዛዥ ቀርበው፣ በቤቱ መግቢያ ላይ አነጋገሩት፤
\v 20 እንዲህም አሉት፤ “ለመጀመሪያ ጊዜ እህል ለመሸመት ወደዚህ መጥተን ነበር፤
\s5
\v 21 ነገር ግን ለአዳር በሰፈርንበት ቦታ የየስልቾቻችንን አፍ ስንከፍት እያንዳንዳችን በስልቾቻችን አፍ ላይ ብራችንን ሙሉውን አገኘነው። ገንዘቡንም ይኸው መልሰን ይዘን መጥተናል።
\v 22 አሁንም እህል መሸመት የሚሆነን ተጨማሪ ብር ይዘን መጥተናል፤ በዚያን ጊዜ ገንዘቡን በየስልቾቻቸን ውስጥ ማን መልሶ እንዳስቀመጠው ግን አናውቅም” አሉት።
\v 23 የቤቱ አዛዥም፣ “አይዞአችሁ አትፍሩ፣ በየስልቾቻችሁ ውስጥ ያገኛችሁትን ገንዘብ የሰጣችሁ የእናንተም የአባቶቻችሁም አምላክ ነው፤ እኔ እንደሆንሁ ብሩን ተቀብያለሁ” አላቸው። ከዚያም ስምዖንን አውጥቶ አገናኛቸው።
\s5
\v 24 የቤቱ አዛዥ ሰዎቹን ወደ ዮሴፍ ቤት አስገብቶ እግራቸውን የሚታጠቡበት ውሃ አቀረበላቸው፤ ለአህዮቻቸውም የሚበሉት ገፈራ ሰጣቸው።
\v 25 ምሳ በዚያ እንደሚበሉ ተነገሯቸው ስለነበር፣ ዮሴፍ በቀትር ከመግባቱ በፊት እጅ መንሻዎቻቸውን ለማበርከት ተዘጋጁ።
\s5
\v 26 ዮሴፍም ወደ ቤቱ ሲገባ የመጧቸውን ስጦታዎች አበረከቱለት፤ ወደ መሬት ዝቅ ብለውም እጅ ነሡት።
\v 27 ዮሴፍም ስለ ደኅንነታቸው ጠየቃቸው፣ ከዚያም፣ “ሽማግሌ አባት እንዳላችሁ ነግራችሁኝ ነበር፤ ደኅና ነው? አሁንም በሕይወት አለ?” አላቸው።
\s5
\v 28 እነርሱም መልሰው፣ “አገልጋይህ አባታችን አሁንም በሕይወት አለ፤ ደኅና ነው” በማለት ወደ መሬት ዝቅ ብለው እጅ ነሡት።
\v 29 ዮሴፍ በዓይኑ ሲቃኝ የእናቱን ልጅ ብንያምን ዐየና፣ “ያ የነገራችሁኝ ታናሽ ወንድማችሁ ይህ ነው?” ብሎ ጠየቃቸው። ብንያምንም፣ “ልጄ እግዚአብሔር ይባርክህ” አለው።
\s5
\v 30 ዮሴፍ ወንድሙን በማየቱ ስሜቱ በጥልቅ ስለተነካ፣ ፈጥኖ ከፊታቸው ገለል አለ፤ ሰውር ያለ ቦታም ፈልጎ፣ ዕልፍኙ ውስጥ አለቀሰ።
\v 31 ፊቱንም ከታጠበ በኋላ ወጣ፤ ስሜቱንም በመቆጣጠር ምሳ እንዲቀርብ አዘዘ።
\s5
\v 32 ለዮሴፍ ለብቻው ቀረበለት ለወንድሞቹም ለብቻቸው ቀረበላቸው፤ እንዲሁም ከእርሱ ጋር ለሚበሉት ግብፃውያን ደግሞ ሌላ ገበታ ቀረበላቸው፤ ምክንያቱም ግብፃውያን ከዕብራውያን ጋር አብሮ መመገብን እንደጸያፍ ይቆጥሩት ነበር።
\v 33 ወንድማማቾቹ ከታላቁ አንስቶ እስከታናሹ እንደየዕድሜአቸው በዮሴፍ ፊት በተርታ ተቀምጠው ነበር፤ በመገረምም እርስ በርሳቸው ተያዩ።
\v 34 ከዮሴፍ ገበታ ላይ እየተነሣ ለእያንዳንዳቸው ምግብ ሲቀርብ የብንያም ድርሻ ከሌሎቹ አምስት ዕጥፍ ነበር። እነርሱም እንዲህ ባለ ሁኔታ አብረውት ተደሰቱ እስኪረኩም ጠጡ።
\s5
\c 44
\p
\v 1 ከዚህ በኋላ ዮሴፍ ለቤቱ አዛዥ እንዲህ ሲል መመሪያ ሰጠው፤ የሰዎቹ ስልቻ የሚይዘውን ያህል እህል በየስልቻቸው ሙላላቸው፤ የእያንዳንዱንም ገንዘብ በየስልቻው አፍ አስቀምጠው።
\v 2 ከዚያም የብር ዋንጫዬን በታናሹ ወንድማቸው ስልቻ አፍ ከእህሉ ዋጋ ጋር ጨምረው።” አዛዡም ዮሴፍ እንዳለው አደረገ።
\s5
\v 3 ጠዋት በማለዳ ወንድማማቾቹ አህዮቻቸውን ይዘው እንዲሄዱ ተደረገ።
\v 4 ከከተማውም ምንም ያህል ርቀው ሳይሄዱ፣ ዮሴፍ የቤቱን አዛዥ እንዲህ አለው፤ “እነዚያን ሰዎች ቶሎ ድረስባቸውና፣ ‘በመልካም ፋንታ ክፉ የመለሳችሁት ስለ ምንድን ነው?
\v 5 የጌታዬን የብር ዋንጫ የሰረቃችሁት ለምንድነው? ዋንጫው ጌታዬ የሚጠጣበትና ሁሉን ነገር መርምሮ የሚያውቅበት እንደሆነ አታውቁምን? ይህ ያደረሳችሁት በደል እጅግ ከባድ ነው’ ብለህ ነገራቸው።”
\s5
\v 6 የቤቱ አዛዥም እንደደረሰባቸው፣ ልክ እንደተባለው ተናገራቸው።
\v 7 እነርሱ ግን እንዲህ አሉት፤ “ጌታችን እንዲህ ያለ ነገር ለምን ይናገራል? እኛ አገልጋዮችህ እንዲህ ያለውን ነገር አናደርገውም።
\s5
\v 8 ከዚህ ቀደምም በየስልቾቻችን አፍ የተገኘውን ብር ከከነዓን እንኳ መልሰን አምጥተናል፤ ታዲያ አሁን ብር ወይም ወርቅ ከጌታህ ቤት እንዴት እንሰርቃለን?
\v 9 የጠፋው ዕቃ ከአገልጋዮችህ የተገኘበት ይሙት፤ የቀረነው የጌታችን ባሮች እንሁን።”
\v 10 አዛዡም መልካም ነው፤ እንዳላችሁት ይሁን፤ ጽዋው የተገኘበት ሰው ባሪያዬ ይሆናል፤ የቀራችሁት ግን ከበደል ነጻ ትሆናላችሁ” አላቸው።
\s5
\v 11 ስለዚህ በፍጥነት ስልቻዎቻቸውን አወረዱ፤ እያንዳንዱም የራሱን ስልቻ ከፈተ።
\v 12 ከዚያም አዛዡ ፍተሻውን ከታላቁ ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ቀጠለ። በመጨረሻም ጽዋው በብንያም ስልቻ ውስጥ ተገኘ።
\v 13 በዚህ ጊዜ ልብሶቻቸውን በሐዘን ቀደዱ፤ ሁሉም ስልቾቻቸውን በየአህዮቻቸው ጭነው ወደ ከተማይቱ ተመለሱ።
\s5
\v 14 ይሁዳና ወንድሞቹ ወደ ዮሴፍ ቤት ሲገቡ፣ ዮሴፍ ገና ከቤቱ አልወጣም ነበር። እነርሱም በፊቱ ተደፍተው ሰገዱ።
\v 15 ዮሴፍም፣ “ለምን እንዲህ ያለ ነገር አደረጋችሁ? እንደ እኔ ያለ ሰው ስውር ነገርን የሚያውቅበት ልዩ ጥበብ እንዳለው አታውቁምን?” ሲል ጠየቃቸው።
\s5
\v 16 ይሁዳም፣ “ከእንግዲህ ለጌታችን ምን ማለት እንችላለን? ምንስ እንመልሳለን? እንዲህ ካለው በደል ንጹሕ መሆናችንን ማስረዳትስ እንዴት ይቻለናል? ምክንያቱም እግዚአብሔር የሠራነውን በደል ገልጦታል፤ እንግዲህ ዋንጫው የተገኘበት ሰው ብቻ ሳይሆን ሁላችንም ባሪያዎችህ እንሁን” አለ።
\v 17 ዮሴፍም፣ “ይህንስ አላደርገውም፣ ዋንጫው የተገኘበት ሰው ብቻ የእኔ ባሪያ መሆን አለበት፤ ሌሎቻችሁ በሰላም ወደ አባታችሁ መመለስ ትችላላችሁ” አለ።
\s5
\v 18 ይሁዳም ወደ ዮሴፍ ቀረብ ብሎ፣ “ጌታዬ ሆይ፣ እኔ አገልጋይህ አንዲት ቃል ብቻ ልናገር፣ ምንም እንኳ የፈርዖን ያህል የተከበርክ ብትሆንም እባክህ አትቆጣኝ።
\v 19 ጌታዬ፣ ‘አባት ወይም ወንድም አላችሁ? ብሎ አገልጋዮቹን ጠይቆ ነበር።
\s5
\v 20 እኛም፣ ‘አዎን ሽማግሌ አባት አለን፤ አባታችንም በስተርጅና የወለደው ትንሽ ልጅ አለው፣ ወንድምዬው ሞቶአል፣ ከአንድ እናት ከተወለዱት ልጆች መካከል የተረፈው እርሱ ብቻ ነው፤ አባቱም በጣም ይወደዋል’ ብለንህ ነበር።
\v 21 ከዚያም አንተ አገልጋዮችህን፣ ‘እንዳየው ወደ እኔ አምጡት’ አልኸን።
\v 22 እኛም ለጌታዬ፣ ‘ልጁ ከአባቱ ሊለይ አይችልም፤ ከተለየው ደግሞ አባትዬው ይሞታል’ አልንህ።
\s5
\v 23 አንተ ግን እኛን አገልጋዮችህን፣ ‘ታናሽ ወንድማችሁ አብሮአችሁ ወደዚህ ካልመጣ ዳግመኛ ፊቴን ዐታዩም’ አልኸን።
\v 24 እኛም ወደ አገልጋይህ ወደ አባቴ በተመለስን ጊዜ አንተ ጌታዬ ያልኸንን ነገርነው።
\v 25 ከዚያም አባታችን፣ ‘እስቲ ተመልሳችሁ ጥቂት እህል ሸምቱልን’ ሲለን
\v 26 ‘መሄድ አንችልም፤ መሄድ የምንችለው ታናሽ ወንድማችን አብሮን ሲሄድ ብቻ ነው። ታናሽ ወንድማችንን ይዘን ካልሄድን በስተቀር የሰውዬውን ፊት ማየት አንችልም’ አልነው።
\s5
\v 27 አገልጋይህ አባቴም እንዲህ አለን፤ ‘ሚስቴ ሁለት ወንዶች ልጆች እንደወለደችልኝ ታውቃላችሁ፤
\v 28 አንዱ በወጣበት በመቅረቱ በእርግጥ አውሬ በልቶት ይሆናል አልሁ፣ ከዚያ በኋላ ዐላየሁትም።
\v 29 አሁን ደግሞ ይህን ልጅ ወስዳችሁ አንዳች ጉዳት ቢደርስበት ሽበቴን በመራር ሐዘን ወደ መቃብር ታወርዱታላችሁ።’
\s5
\v 30 እንግዲህ አሁን ልጁን ሳንይዝ ወደ አገልጋይህ ወደ አባቴ ብመለስ ሕይወቱ ከልጁ ሕይወት ጋር በጥብቅ የተሳሰረ ስለሆነ፣
\v 31 የልጁን ከእኛ ጋር አለመኖር ሲያይ አባቴ ይሞታል። ከዚህም የተነሣ እኛ አገልጋዮችህ የአባታችንን ሽበት በመሪር ሐዘን ወደ መቃብር እናወርደዋለን።
\v 32 እኔ አገልጋይህ፣ “ልጅህን መልሼ ሳላመጣ ብቀር ለዘላለም በደለኛ አድርገህ ቁጠረኝ’ በማለት ስለ ልጁ ደህንነት በአባቴ ፊት ራሴን ዋስ አድርጌአለሁ።
\s5
\v 33 ስለዚህ አሁን፣ አገልጋይህ በልጁ ፋንታ የአንተ የጌታዬ ባሪያ ሆኜ እዚሁ ልቅር ልጁ ግን ከወንድሞቹ ጋር ይመለስ።
\v 34 ልጁን ሳልይዝ እንዴት ተመልሼ ወደ አባቴ እሄዳለሁ? እባክህ በአባቴ ላይ የሚደርሰውን መከራ እንዳይ አታድርገኝ።”
\s5
\c 45
\p
\v 1 በዚያን ጊዜ ዮሴፍ አጠገቡ በነበሩ ሰዎች ፊት ስሜቱን ሊገታ ባለመቻሉ፣ “እዚህ ያሉትን ሰዎች በሙሉ አስወጡልኝ” ብሎ ጮኾ ተናገረ፤ ስለዚህም ዮሴፍ ራሱን ለወንድሞቹ በገለጠበት ጊዜ ከእርሱ ጋር ሌላ ማንም ሰው አልነበረም።
\v 2 ዮሴፍም ድምፁን ከፍ አድርጎ በማልቀሱ ግብፃውያን ሰሙት፣ ወሬውም ወደ ፈርዖን ቤተ ሰዎች ደረሰ።
\v 3 ዮሴፍም ወንድሞቹን፣ “እኔ ዮሴፍ ነኝ፤ ለመሆኑ አባቴ እስካሁን በሕይወት አለ?” ሲል ጠየቃቸው። ወንድሞቹ ግን በፊቱ ተደናግጠው ስለነበር መልስ ሊሰጡት አልቻሉም።
\s5
\v 4 ዮሴፍም ወንድሞቹን፣ “እስቲ ወደ እኔ ቀረብ በሉ” አላቸው፣ ወደ እርሱም በቀረቡ ጊዜ እንዲህ አለ፤ “ወደ ግብፅ የሸጣችሁኝ እኔ ዮሴፍ ነኝ፤
\v 5 አሁንም በመሸጣችሁ አትቆጩ፤ በራሳችሁም አትዘኑ፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ሕይወት ለማዳን ሲል ከእናንተ አስቀድሞ እኔን ወደዚህ ልኮኛል።
\v 6 በምድር ላይ ራብ ከገባ ይኸው ሁለት ዓመት ሆነ፣ ከዚህ በኋላም የማይታረስባቸውና ሰብል የማይሰበሰብባቸው አምስት ዓመታት ገና አሉ።
\s5
\v 7 ነገር ግን እግዚአብሔር ሕይወታችሁን በታላቅ ማዳን ለመታደግና ዘራችሁ ከምድር ላይ እንዳይጠፋ በማሰብ ከእናንተ አስቀድሞ ወደዚህ ላከኝ።
\v 8 ስለዚህ አሁን ወደዚህ የላከኝ እግዚአብሔር እንጂ እናንተ አይደላችሁም፣ እርሱም ለፈርዖን እንደ አባት፤ በቤት ንብረቱ ላይ ጌታ፣ እንዲሁም በግብፅ ምድር ላይ ገዢ አደረገኝ።
\s5
\v 9 አሁንም ‘በፍጥነት ወደ አባቴ ተመልሳችሁ እንዲህ በሉት፤ “ልጅህ ዮሴፍ እንዲህ ይላል፤ ‘እግዚአብሔር የመላው ግብፅ ጌታ አድርጎኛል፤ ስለዚህ ሳትዘገይ ወደ እኔ ና።
\v 10 ልጆችህን የልጅ ልጆችህን በጎችህን፣ ፍየሎችህን ከብቶችህንና ያለህን ሁሉ ይዘህ በአቅራቢያዬ በጌሤም ትኖራለህ።
\v 11 ገና ወደ ፊት የሚመጣ የአምስት ዓመት ራብ ስላለ፣ በዚያ የሚያስፈልጋችሁን እኔ እሰጣችኋለሁ፤ ያለበልዚያ ግን አንተና ቤተ ስዎችህ ያንተም የሆነው ሁሉ፣ ችግር ላይ ትወድቃላችሁ።’
\s5
\v 12 ፊታችሁ ሆኜ የማናግራችሁ እኔ ዮሴፍ ራሴ መሆኔን እናንተም ሆናችሁ ወንድሜ ብንያም በዓይናችሁ የምታዩት ነው።
\v 13 በግብፅ ስላሏኝ ክብርና ስላያችሁትም ሁሉ ለአባቴ ንገሩት፣ አባቴንም በፍጥነት ይዛችሁት ኑ።
\s5
\v 14 ከዚያም በወንድሙ በብንያም አንገት ላይ ተጠምጥሞ አለቀሰ፤ ብንያምም እያለቀሰ ዮሴፍን አቀፈው።
\v 15 የቀሩትምንም ወንድሞቹን አንድ በአንድ እየሳመ አለቀሰ። ከዚያም ወንድሞቹ ከእርሱ ጋር መጨዋወት ጀመሩ።
\s5
\v 16 የዮሴፍ ወንድሞች መምጣት በፈርዖን ቤተ መንግሥት በተሰማ ጊዜ፣ ፈርዖንና ሹማምንቱ ሁሉ ደስ አላቸው።
\v 17 ፈርዖን ዮሴፍን እንዲህ አለው፤ “ለወድሞችህ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፣ ‘እንዲህ አድርጉ እህዮቻችሁን ጭናችሁ ወደ ከነዓን ምድር ተመለሱ።
\v 18 ከዚያም አባታችሁንና ቤተ ሰባችሁን ይዛችሁ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም እጅግ ለም ከሆነው የግብፅ ምድር እሰጣችኋለሁ፤ በምድሪቱ በረከት ደስ ብሎአችሁ ትኖራላችሁ።’
\s5
\v 19 ደግሞም እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፤ ‘ይህን አድርጉ፣ ከግብፅ ምድር ልጆቻችሁንና ሚስቶቻችሁን የምታጓጉዙባቸው ሠረገላዎች ወስዳችሁ፤ አባታችሁን ይዛችሁ ኑ።
\v 20 ስለ ንብረታችሁ ምንም አታስቡ፣ ከግብፅ ምድር እጅግ ለም የሆነው የእናንተ ይሆናልና።’”
\s5
\v 21 የእስራኤልም ልጆች ይህንኑ አደረጉ። ዮሴፍም ፈርዖን ባዘዘው መሠረት ሠረገላዎች አቀረበላቸው፤ የመንገድም ስንቅ አስያዛቸው።
\v 22 ለእያንዳንዳቸው ሁለት ሁለት የክት ልብስ ሰጣቸው፤ ለብንያም ግን ሶስት መቶ ጥሬ ብርና አምስት የክት ልብስ ሰጠው።
\v 23 ለአባቱም በግብፅ ምድር ከሚገኘው የተመረጠ ነገር በዐሥር አህዮች፣ እንደዚሁም በዐሥር እንስት አህዮች ዳቦና ሌላ ምግብ አስጭኖ ሰደደለት።
\s5
\v 24 ከዚህ በኋላ ወንድሞቹን አሰናበታቸው፤ ከእርሱም ሲሰናበቱ፣ መንገድ ላይ እንዳትጣሉ” አላቸው።
\v 25 እነርሱም ከግብፅ ወጥረው በከነዓን ምድር ወደሚኖረው ወደ አባታቸው ወደ ያዕቆብ መጡ።
\v 26 አባታቸውንም፣ እነሆ ዮሴፍ በሕይወት አለ፤ እንዲያውም በግብፅ ምድር ሁሉ ገዥ ሆኖአል” ብለው ነገሩት። ያዕቆብ ግን እጅግ ደነገጠ፤ ሊያምናቸውም አልቻለም።
\s5
\v 27 ነገር ግን ዮሴፍ ያላቸውን ሁሉ በነገሩት ጊዜና እርሱን ወደ ግብፅ የሚወስዱበትን ዮሴፍ የላከለትን ሠረገላ ባየ ጊዜ የአባታቸው የያዕቆብ መንፈስ ታደሰ።
\v 28 ከዚያም እስራኤል፣ “ልጄ ዮሴፍ በሕይወት አለ፤ ከመሞቴ በፊት ሄጄ ዐየዋለሁ” አለ።
\s5
\c 46
\p
\v 1 እስራኤልም ጓዙን ሁሉ ጠቅልሎ ተነሣ፤ ቤርሳቤህም ሲደርስ፣ ለአባቱ ለይስሐቅ አምላክ መሥዋዕት ሠዋ።
\v 2 እግዚአብሔርም ሌሊት በራእይ ለእስራኤል ተገልጦ፣ “ያዕቆብ፣ ያዕቆብ” ብሎ ጠራው። እርሱም፣ “እነሆ፣ አለሁ” አለ።
\v 3 እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤ “እኔ የአባትህ አምላክ እግዚአብሔር ነኝ፤ ወደ ግብፅ ለመውረድ አትፍራ፤ በዚያ ታላቅ ሕዝብ አደርግሃለሁና፤
\v 4 አብሬህ ወደ ግብፅ እወርዳለሁ፣ ከዚያም መልሼ አወጣሃለሁ፣ የዮሴፍ የራሱ እጆች በምትሞትበት ጊዜ ዓይኖችህን ይከድናል።
\s5
\v 5 ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ከቤርሳቤህ ተነሣ፤ የእስራኤል ወንዶች ልጆችም አባታቸውን ያዕቆብን ልጆቻቸውንና ሚስቶቻቸውን ፈርዖን ለያዕቆብ በላከላቸው ሠረገላ ላይ አወጧቸው።
\v 6 ከብቶቻቸውንና በከነዓን ምድር ያፈሩትን ሀብት ንብረታቸውን ይዘው፣ ያዕቆብና ዘሮቹ በሙሉ ወደ ግብፅ ወረዱ።
\v 7 ወደ ግብፅም የወረደው፤ ወንዶች ልጆቹንና ወንዶች የልጅ ልጆቹን፣ ሴቶች ልጆቹንና የልጅ ልጆቹን ማለት ዘሮቹን ሁሉ ይዞ ነው።
\s5
\v 8 ወድ ግብፅ የወረዱት የእስራኤል ልጆች፣ የያዕቆብ ዘሮቹ እነዚህ ናቸው፦ የያዕቆብ የበኩል ልጆ ሮቤል።
\v 9 የሮቤል ልጆች፦ ሄኖኅ፣ ፈሉሶ፣ አስሮን እና ከርሚ ናቸው።
\v 10 የስሞዖን ልጆች፦ ይሙኤል፣ ያሚን፣ ኦሃድ፣ ያኪን፣ ጸሐርና ከከነዓናዊቷ ሴት የተወለደው ሳኡል ናቸው።
\v 11 ልጆች፦ ጌድሶን፣ ቀዓትና ሜራሪ ናቸው።
\s5
\v 12 የይሁዳ ልጆች፦ ዔር አውናን፣ ሴሎም፣ ፋሬስ እና ዛራ ናቸው። ነገር ግን ዔርና አውናን በከነዓን ምድር ሞቱ።
\v 13 የይሳኮር ልጆች፦ ቶላ፣ ፉዋ፣ ዮብና ሺምሮን ናቸው፤
\v 14 የዛብሎን ልጆች፦ ሴሬድ፣ ኤሎንና ያሕልኤል ናቸው፤
\v 15 እነዚህ ወንዶች ልጆች ያዕቆብ በሰሜን ምዕራብ መሰጴጦምያ ሳለ፣ ልያ የወለደችለት ናቸው። ሴቷን ዲናን ጨምሮ፣ የወንዶችና የሴቶች ልጆቹ ቁጥር ሠላሳ ሦስት ነው።
\s5
\v 16 የጋድ ልጆች፦ ጽፎን፣ ሐጊ፣ ሹኒ፣ ኤስቦን፣ ዔሪ፣ አሮዲና አርኤሊ ናቸው፤
\v 17 የአሴር ልጆች፦ ዩምና፣ የሱዋ፣ የሱዊና በሪዓ ናቸው፤ እኅታቸውም ሤራሕ ናት፤ የበሪዓ ልጆች፦ ሐቤርና መልኪኤል ናቸው፤
\v 18 እነዚህ ዐሥራ ስድስት ልጆች ሁሉ ላባ ለልጁ ለልያ ከሰጣት ከዘለፋ ላይ ያዕቆብ የወለዳቸው ናቸው።
\s5
\v 19 የያዕቆብ ሚስት የራሔል ልጆች፦ ዮሴፍና ብንያም ናቸው፤
\v 20 በግብፅም የኦን ከተማ ካህን የጶጥፌራ ልጅ አስናት፣ ምናሴንና ኤፍሬምን ለዮሴፍ ወለደችለት።
\v 21 የብንያም ልጆች፦ቤላ፣ ቤኬር፣ አስቤል፣ ጌራ፣ ንዕማን፥ አኪ፣ ሮስ፥ ማንፌን፣ ሑፊምና አርድ ናቸው።
\v 22 እነዚህ ዐሥራ አራቱ፣ ራሔል ለያዕቆብ የወለደችለት ልጆችና የልጅ ልጆች ናቸው።
\s5
\v 23 የዳን ልጅ፦ ሑሺም ነው፤
\v 24 የንፍታሌም ልጆች፦ ያሕጽኤል፣ ጉኒ፣ ዮጽርና ሺሌም ናቸው፤
\v 25 እነዚህ ሰባቱ ልጆች ሁሉ ላባ ለልጁ ለራሔል ከሰጣት ከባላ ላይ ያዕቆብ የወለዳቸው ናቸው።
\s5
\v 26 ከያዕቆብ ጋር ወደ ግብፅ የሄዱት የገዛ ዘሮቹ ብዛት ስድሳ ስድስት ሲሆን የልጆቹን ሚስቶች አይጨምርም።
\v 27 ዮሴፍ በግብፅ የወለዳቸውን ሁለት ልጆች ጨምሮ ወደ ግብፅ የወረደው የያዕቆብ ቤተ ሰብ ቁጥር ሰባ ነበር።
\s5
\v 28 ያዕቆብም ወደ ጌሤም ለመሄድ መመሪያ ይቀበል ዘንድ፣ ይሁዳን አስቀድሞ ወደ ዮሴፍ ላከው። እርሱም ጌሤም ሲደርሱ፣
\v 29 ዮሴፍ ሠረገላውን አዘጋጅቶ፤ አባቱን እስራኤልን ለመቀበል ወደ ጌሤም አመራ። ዮሴፍ አባቱ ዘንድ እንደደረሰ አንገቱ ላይ ተጠምጥሞ ለረጅም ጊዜ አለቀሰ።
\v 30 እስራኤልም ዮሴፍን፣ “በሕይወት መኖርህን ስላየሁ፣ ከእንግዲህ ብሞትም አይቆጨኝም” አለው።
\s5
\v 31 ከዚህ በኋላ ዮሴፍ ወንድሞቹንና የአባቱን ቤተ ሰዎች እንዲህ አላቸው፤ “ወደ ፈርዖን ወጥቼ እነግረዋለሁ፤ እንዲህም እለዋለሁ፣ ‘በከነዓን ምድር የሚኖሩት ወንድሞቼና የአባቴ ቤተ ሰዎች ወደ እኔ መጥተዋል።
\v 32 ሰዎቹ ከብት የሚጠብቁ ስለሆኑ እረኞች ናቸው፣ ሲመጡም በጎቻቸውን፣ ፍየሎቻቸውንና ከብቶቻቸውን እንዲሁም ያላቸውን ሁሉ ይዘው መጥተዋል።
\s5
\v 33 ፈርዖን አስጠርቶአችሁ፣ ‘ሥራችሁ ምንድን ነው? ብሎ ቢጠይቃችሁ፤
\v 34 እናንተ፣ ‘እኛ አገልጋዮችህ ሥራችን ከልጅነታችን ጀምሮ ልክ እንደ አባቶቻችን ከብት ማርባት ነው’ ብላችሁ መልሱለት። ከብት አርቢዎች በግብፃውያን ዘንድ እንደ ጸያፍ ስለሚቆጠሩ፣ በጌሤም ምድር እንድትኖሩ ይፈቅድላችኋል።”
\s5
\c 47
\p
\v 1 ዮሴፍም ወደ ፈርዖን ሄዶ፣ “አባቴና ወንድሞቼ በጎቻቸውን፣ ፍየሎቻቸውን እንዲሁም ያላቸውን ሁሉ ይዘው ከከነዓን አገር መጥተው በጌሤም ሰፍረዋል” አለው።
\v 2 ከወንድሞቹም መካከል አምስቱን መርጦ፣ ፈርዖን ፊት አቀረባቸው።
\s5
\v 3 ፈርዖን የዮሴፍን ወንድሞች፣ “ሥራችሁን ምንድነው?” ሲል ጠየቃቸው። እነርሱም ፈርዖንን፣ “እኛ አገልጋዮችህ ልክ እንደአባቶቻችን ከብት አርቢዎች ነን” አሉት።
\v 4 ደግሞም፣ “በከነዓን ምድር ራቡ እጅግ የጸና በመሆኑ በጎችና ፍየሎች የሚሰማሩበት በማጣታቸው፣ ለጊዜው እዚህ ለመኖር መጥተናል፤ አሁንም ባሮችህ በጌሤም ምድር እንድንኖር እንድትፈቅድልን እንለምንሃለን” አሉት።
\s5
\v 5 ፈርዖንም ዮሴፍን እንዲህ አለው፤ “አባትንህና ወንድሞችህ ወደ አንተ መጥተዋል፤
\v 6 የግብፅ ምድር እንደሆነ በእጅህ ነው፤ አባትህንና ወንድሞችህን ምርጥ በሆነው ምድር አስፍራቸው፤ በጌሤም ይኑሩ። ከመካከላቸው ልዩ ችሎታ ያላቸው መኖራቸውን የምታውቅ ከሆነ፣ የከብቶቼ ኅላፊዎች አድርጋቸው።”
\s5
\v 7 ከዚህ በኋላ ዮሴፍ አባቱን ያዕቆብን ቤተ መንግሥት አግብቶ በፈርዖን ፊት አቀረበው፤ ያዕቆብ ፈርዖንን ከመረቀው በኋላ
\v 8 ፈርዖን፣ “ለመሆኑ ዕድሜህ ምን ያህል ነው?” ሲል ያዕቆብን ጠየቀው።
\v 9 ያዕቆብም ለፈርዖን፣ “በምድር ላይ በእንግድነት ያሳለፍሁት ዘመን 130 ዓመት ነው፤ ይህም አባቶቼ በእንግድነት ከኖሩበት ዘመን ጋር ሲነጻጸር አጭር ነው፤ ችግር የበዛበትም ነበር” ሲል መለሰለት።
\v 10 ከዚያም ያዕቆብ ፈርዖንን መርቆ፣ ተሰናብቶት ወጣ።
\s5
\v 11 ዮሴፍም አባቱንና ወንድሞቹን በግብፅ እንዲኖሩ አደረገ፤ ፈርዖን በሰጠውም ትእዛዝ መሠረት ምርጥ ከሆነው ምድር ራምሴን በርስትነት ሰጣቸው።
\v 12 ዮሴፍም ለአባቱ፣ ለወንድሞቹና ለመላው የአባቱ ቤተ ሰዎች በልጆቻቸው ቁጥር ልክ ቀለብ እንዲሰፈርላቸው አደረገ።
\s5
\v 13 በመላው ምድር እህል ባለመኖሩ ራቡ እየጸና ሄደ፤ ከዚህ የተነሣም ግብፅና ከነዓን በራብ እጅግ ተጎዱ፤
\v 14 ዮሴፍ የግብፅና የከነዓን ሰዎች እህል በመሸመት የከፈሉትን ገንዘብ ሁሉ ሰብስቦ ወደ ፈርዖን ቤተ መንግሥት አስገባ።
\s5
\v 15 የግብፅና የከነዓን ሕዝቦችም ገንዘባቸው ባለቀ ጊዜ፣ ግብፃውያን ሁሉ ወደ ዮሴፍ ቀርበው፣ “የምንበላው እህል ስጠን፣ ገንዘባችን አልቆብናል፤ ዓይንህ እያየ እንዴት በራብ እንለቅ?” አሉት።
\v 16 ዮሴፍም ከብቶቻችሁን አምጡ፣ ገንዘባችሁ ካለቀ በከብቶቻችህ ለውጥ እህል እሰጣችኋለሁ አለ።
\v 17 ስለዚህ ከብቶቻቸውን ወደ ዮሴፍ አምጡ፤ እርሱም በፈረሶቻቸው፣ በበጎቻቸው፣ በፍየሎቻቸው፣ በከብቶቻቸውና በአህዮቻቸው ለውጥ እህል ሰጣቸው። በከብቶቻቸው ልዋጭ ባገኙት ምግብ በዚያ ዓመት ሳይራቡ እንዲያልፉ አደረጋቸው።
\s5
\v 18 ያም ዓመት ካለፈ በኋላ ሕዝቡ በሚቀጥለው ዓመት ወደ ዮሴፍ መጥተው እንዲህ አሉት፣ “እንግዲህ ከጌታችን የምንሰውረው ምንም ነገር የለም፤ ገንዘባችን አልቆአል፤ ከብቶቻችንንም አስረክበንሃል፤ እንግዲህ ለጌታችን የምንሰጠው፣ ከሰውነታችንና ከመሬታችን በቀር ሌላ ምንም ነገር የለንም።
\v 19 ታዲያ እያየኸን እንዴት እንለቅ? መሬታችንም ለምን ጠፍ ሆኖ ይቅር? እኛንና መሬታችንን ውሰድና በለውጡ እህል ስጠን፤ እኛ የፈርዓን አገልጋዮች እንሆናለን፤ መሬታችንም የእርሱ ይሁን፣ እኛም እንዳንሞት መሬታችንም ጠፍ ሆኖ እንዳይቀር የምንዘራው ዘር ስጠን።
\s5
\v 20 ስለዚህ ዮሴፍ የግብፅን ምድር ሁሉ ለፈርዖን ገዛለት፤ ራቡም እጅግ ስለጸናባቸው ግብፃውያን ሁሉ መሬታቸውን ሸጡ፣ ምድሪቱም የፈርዖን ርስት ሆነች።
\v 21 ዮሴፍ በግብፅ አገር ዳር እስከ ዳር ያሉት ሰዎች ሁሉ የንጉሡ አገልጋዮች እንዲሆኑ አደረገ።
\v 22 ሆኖም ዮሴፍ የካህናቱን መሬት አልገዛም፤ ምክንያቱም ካህናቱ ከፈርዖን ቋሚ አበል ስለሚያገኙ እርሱም ከሚሰጣቸው አበል ምግብ ያገኙ ስለነበረ መሬታቸውን አልሸጡም።
\s5
\v 23 ዮሴፍ ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፣ “እነሆ፣ ዛሬ እናንተንም መሬታችሁንም ለፈርዖን ገዝቻችኋለሁና ይህን ዘር ወስዳችሁ በመሬት ላይ ዝሩ።
\v 24 መከሩ በሚሰበሰብበት ጊዜ ግን ከአምስት እጅ አንዱን ለፈርዖን ታስገባላችሁ፣ ከአምስት እጅ አራቱን ደግሞ ለመሬታችሁ ዘር፣ እንዲሁም ለራሳችሁ፣ ለቤተ ሰቦቻችሁና ለልጆቻችሁ ምግብ ታደርጉታላችሁ።”
\s5
\v 25 እነርሱም፣ “እንግዲህ ሕይወታችንን አትርፈህልናል፤ በጌታችን ፊት ሞገስ ካገኘን ለፈርዖን ገባሮች እንሆናለን” አሉት።
\v 26 ስለዚህ ዮሴፍ የምርቱ አንድ አምስተኛ ለፈርዖን እንዲገባ የሚያዝ የመሬት ሕግ አወጣ፤ ይህም ሕግ እስከ ዛሬ ይሠራበታል። በፈርዖን እጅ ያልገባው መሬት የካህናቱ ብቻ ነው።
\s5
\v 27 በዚህ ጊዜ እስራኤላውያን በግብፅ አገር በጌሤም ይኖሩ ነበር፣ በዚያም ሀብት ንብረት አፈሩ፤ ቁጥራቸውም እጅግ እየበዛ ይሄድ ጀመር።
\v 28 ያዕቆብ በግብፅ ዐሥራ ሰባት ዓመት ኖረ፣ ዕድሜውም አንድ መቶ አርባ ሰባት ዓመት ነበር።
\s5
\v 29 እስራኤልም የሚሞትበት ጊዜ መቃረቡን እንደተረዳ ልጁን ዮሴፍን አስጠርቶ እንዲህ አለው፤ “በአንተ ዘንድ ሞገስ ካገኘሁ እጅህን በጭኔ ላይ አኑረህ፣ በጎነትንና ታማኝነትን ልታደርግልኝ ቃል ግባልኝ፤ በምሞትበት ጊዜ በግብፅ አትቅበረኝ፤
\v 30 እኔም ከአባቶቼ ጋር ሳንቀላፋ ከግብፅ አውጥተህ እነርሱ በተቀበሩበት ቦት ቅበረኝ” ዮሴፍም፣ “እሺ፣ እንዳልኸኝ አደርጋለሁ” አለ።
\v 31 ያዕቆብ፤ “በል ማልልኝ” አለው። ዮሴፍም ማለለት፣ እስራኤልም በአልጋው ራስጌ ላይ ሆኖ ጎንበስ አለ።
\s5
\c 48
\p
\v 1 ከጥቂት ጊዜ በኋላም፣ “አባትህ ታሞአል” ተብሎ ለዮሴፍ ስለተነገረው ሁለቱን ልጆቹን ምናሴንና ኤፍሬምን ይዞ ሄደ።
\v 2 ለያዕቆብ፣ “ልጅህ ዮሴፍ ወደ አንተ መጥቶአል” ተብሎ በተነገረው ጊዜ፣ እስራኤል ተበረታትቶ አልጋው ላይ ተቀመጠ።
\s5
\v 3 ያዕቆብም ዮሴፍን እንዲህ አለው፤ “ሁሉን የሚችል አምላክ በከነዓን ምድር ሎዛ በምትባል ቦታ ተገለጠልኝ፤ ባረከኝም፤
\v 4 እንዲህም አለኝ፤ ‘ፍሬያማ አደርግሃለሁ፣ ዝርያዎችህም ብዙ ሕዝቦች ይሆናሉ፣ ይህችንም ምድር ለዝርያዎችህ ለዘላለም ርስት አድርጌ እሰጣቸዋለሁ’ አለኝ።”
\s5
\v 5 ወደዚህ ከመምጣቴ በፊት በግብፅ የወለድሃቸው ሁለቱ ልጆችህ ከእንግዲህ የእኔ ልጆች ሆነው ይቆጠራሉ፤ ሮቤልና ስምዖን ልጆቼ እንደሆኑ ሁሉ፣ ኤፍሬምና ምናሴም ልጆቼ ይሆናሉ።
\v 6 ከእነርሱ በኋላ የሚወለዱልህ ልጆች ግን፣ የአንተ ይሁኑ፤ በርስት ድልድላችው ግን በወንድሞቻቸው ስም ይቆጠራሉ።
\v 7 ከሰሜን ምዕራብ መስጴጦምያ ስመለስ ኤፍራታ ለመድረስ ጥቂት ሲቀረኝ፤ እናትህ ራሔል በከነዓን ምድር ሞታብኝ አዘንሁ። እኔም ወደ ኤፍራታ ማለት ወደ ቤተ ልሔም በሚወስደው መንገድ ዳር ቀበርኋት።”
\s5
\v 8 እስራኤልም የዮሴፍን ልጆች ባየ ጊዜ፣ “እነዚህ እነማን ናቸው?” ሲል ጠየቀ፤
\v 9 ዮሴፍም፣ “እነዚህ እግዚአብሔር የሰጠኝ ልጆች ናቸው” ብሎ መለሰለት፤ እስራኤልም “አቅርባቸውና ልመርቃቸው” አለ።
\v 10 በዚህ ጊዜ እስራኤል ዓይኖቹ በእርጅና ምክንያት በመድከማቸው አጥርቶ ማየት ይሳነው ነበር፤ ስለዚህ ዮሴፍ ልጆቹን አባቱ ዘንድ አቀረባቸው፤ አባቱም ስሞ አቀፋቸው።
\s5
\v 11 እስራኤልም ዮሴፍን፣ “ዓይንህን እንደገና ዐያለሁ ብዬ አላሰብኩም ነበር፤ እግዚአብሔር ግን ልጆችህን ጭምር ለማየት አበቃኝ” አለው።
\v 12 ዮሴፍም ልጆቹን ከእስራኤል ጉልበት ፈቀቅ በማድረግ አጎንብሶ በግንባሩ መሬት ላይ ተደፋ።
\v 13 ከዚያም ዮሴፍ ሁለቱን ልጆቹን ይዞ ኤፍሬምን ከራሱ በስተቀኝ ከእስራኤል በስተግራ፣ ምናሴን ደግሞ ከራሱ በስተግራ ከእስራኤል በስተቀኝ በኩል አቀረባቸው።
\s5
\v 14 እስራኤል ግን ቀኝ እጁን በታናሹ በኤፍሬም ራስ ላይ አኖረ፣ ግራ እጁንም በቀኝ እጁ ላይ አስተላልፎ በበኩሩ በምናሴ ላይ አኖረ።
\v 15 ከዚህ በኋላ ዮሴፍን ባረከ፤ እንዲህም አለው፤ “አባቶቼ አብርሃምና ይስሐቅ መንገዱን በመከተል ያገለገሉትና ለእኔም እስከ ዛሬ ድረስ በዘመኔ ሁሉ እረኛ የሆነኝ አምላክ፣
\v 16 ከጉዳትም ሁሉ የታደገኝ ምልአክ፣ እርሱ እነዚህን ልጆች ይባርክ፤ እነርሱም በስሜ፣ በአባቶቼ በአብርሃምና በይስሐቅ ስም ይጠሩ፣ በምድር ላይ እጅግ ይብዙ።
\s5
\v 17 ዮሴፍ አባቱ ቀኝ እጁን በኤፍሬም ራስ ላይ ማድረጉን ሲያይ ቅር ተሰኘ፤ ከኤፍሬም ራስ ላይ አንስቶ በምናሴ ራስ ላይ ለማኖር የአባቱን እጅ ያዘ፤
\v 18 ዮሴፍም፣ “አባቴ ሆይ፣ እንዲህ አይደለም በኩሩ ይህኛው ስለሆነ፣ ቀኝ እጅህን እርሱ ራስ ላይ አድርግ” አለው።
\s5
\v 19 አባቱ ግን፣ “ዐውቃለሁ፣ ልጄ ዐውቃለሁ፣ እርሱም እኮ ሕዝብ ይሆናል፤ ታላቅም ይሆናል፤ ይሁን እንጂ፣ ታናሽ ወንድሙ ከእርሱ ይበልጣል፤ ዘሮቹም ታላቅ ሕዝቦች ይሆናሉ” ብሎ እምቢ አለው።
\v 20 በዚያን ዕለት ባረካቸው፣ እንዲህም አላቸው፤ “እስራኤላውያን በሚመርቁበት ጊዜ የእናንተን ስም በማስታወስ፤ ‘እግዚአብሔር እንደ ኤፍሬምና እንደ ምናሴ ያድርጋችሁ’ ይላሉ” በዚህ ሁኔታም ኤፍሬምን ከምናሴ አስቀደመው።
\s5
\v 21 ከዚህ በኋላ እስራኤል ዮሴፍን እንዲህ አለው፣ እኔ የምሞትበት ጊዜ ተቃርቦአል፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሆናል፤ ወደ አባቶቻችሁም ምድር መልሶ ያገባችኋል።
\v 22 እነሆ በሰይፌና በቀስቴ ከአሞራውያን እጅ የወሰድኋትን ምድር ከወንድሞችህ ድርሻ አብልጬ ለአንተ ሰጥቼሃለሁ።”
\s5
\c 49
\p
\v 1 ያዕቆብ ልጆቹን ጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “በአንድነት ተሰብሰቡና ወደፊት የሚገጥማችሁን ነገር ልንገራችሁ፣
\v 2 እናንተ የያዕቆብ ልጆች፣ በአንድነት ተሰብስባችሁ ስሙ፣ አባታችሁ እስራኤል የሚነግራችሁንም አድምጡ።
\s5
\v 3 ሮቤል፣ ኃይልና የጎልማሳነት ብርታት በነበረኝ ጊዜ የወለድሁህ የበኩር ልጄ ነህ። ከልጆቼ ሁሉ በክብርና በኃይል የምትበልጥ አንተ ነህ።
\v 4 ይሁን እንጂ እንደ ውሃ የምትዋልል ስለሆንህ የበላይ አለቅነት ለአንተ አይገባም፣ ምክያንቱም የአባትህን መኝታ ደፍረሃል ምንጣፌንም አርክሰሃል።
\s5
\v 5 “ስምዖንና ሌዊ ወንድማማቾች ናቸው፣ ዓመፅ ለመፈጸም የጦር መሣሪያዎቻቸውን ያነሳሉ።
\v 6 ወደ ሸንጎአቸው አልግባ፣ ጉባኤያቸው ውስጥ አልገኝ፣ በቁጣ ተነሣስተው ወንዶችን ገድለዋል፣ የበሬዎችንም ቋንጃ እንደፈለጉ ቆራርጠዋል።
\s5
\v 7 እጅግ አስፈሪ የሆነ ቁጣቸው፣ ጭከና የተሞላ ንዴታቸው የተረገመ ይሁን፤ በያዕቆብ እበትናቸዋለሁ፣ በመላው እስራኤልም አሠራጫቸዋለሁ።
\s5
\v 8 ይሁዳ ወንድሞችህ ያመሰግኑሃል፣ እጅህም የጠላቶችህን አንገት አንቆ ይይዛል፣ የአባትህ ልጆች በፊትህ ተደፍተው ይስግዱልሃል።
\s5
\v 9 ይሁዳ እንደ ደቦል አንበሳ ነው፣ ከዐደንህ የምትመለስ ልጄ፣ እንደ አንበሳ ያደፍጣል በምድርም ላይ ይተኛል፤ እንደ እንስት እንበሳም ያደባል፣ ታዲያ ማን ሊቀሰቅሰው ይደፍራል?
\s5
\v 10 በትረ መንግስሥት ከይሁዳ እጅ አይወጣም፤ የገዥነት ምርኩዝም ከእግሮቹ መካከል፣ ሕዝቦች ሁሉ የሚታዘዙለት ‘ሴሎ’ እስኪመጣ ድረስ፣ ሕዝቦች ሁሉ ይታዘዙለታል።
\s5
\v 11 አህያውን በወይን ግንድ፣ ውርንጫውንም በምርጡ የወይን ሐረግ ቅርንጫፍ ላይ ያስራል፣ ልብሱን በወይን ጠጅ፣ መጎናጸፊያውንም በወይን ጭማቂ ያጥባል።
\v 12 ዓይኖቹ ከወይን ጠጅ የቀሉ፣ ጥርሶቹም ከወተት ይልቅ የነጡ ይሆናሉ።
\s5
\v 13 ዛብሎን በባሕር ዳርቻ ይኖራል፣ የመርከቦቹ መጠጊያም ይሆናል፣ ወሰኑም እስከ ሲዶና ይደርሳል።
\s5
\v 14 ይሳኮር፣ አጥንተ ብርቱ አህያ በጭነት መካከል የሚተኛ፣ ማረፊያ ቦታው መልካም፣
\v 15 ምድሪቱም አስደሳች መሆኗን ሲያይ፣ ትከሻውን ለሸክም ዝቅ ያደርጋል ከባድ የጉልበት ሥራም ይሠራል።
\s5
\v 16 ዳን ከእስራኤል ነገዶች እንደ አንዱ ሆኖ በራሱ ሕዝብ ላይ ይፈርዳል።
\v 17 ዳን የመንገድ ዳር እባብ፣ የመተላለፊያም መንገድ እፉኝት ነው፤ ጋላቢው የኋሊት እንዲወድቅ፣ የፈረሱን ሰኮና ይነክሳል።
\v 18 እግዚአብሔር ሆይ፣ ማዳንህን እጠባበቃለሁ።
\s5
\v 19 ጋድን ወራሪዎች አደጋ ይጥሉበታል፣ እርሱ ግን ዱካቸውን ተከታትሎ ብድሩን ይመልሳል።
\v 20 አሴር ማዕደ ሰፊ ይሆናል፤ ለነገሥታትም የሚስማማ ምግብ ያቀርባል።
\v 21 ነጻ እንደተለቀቀች ሚዳቋ ነው፣ የሚያማምሩ ግልገሎች ይኖሩታል።
\s5
\v 22 ዮሴፍ፤ ፍሬያማ የወይን ተክል፣ በምንጭ ዳር የተተከለ ወይን ነው። ሐረጎቹ ቅጥርን ያለብሳሉ።
\v 23 ቀስተኞች በብርቱ ያጠቁታል፤ በቀስታቸውም እየነደፉ ያሳድዱታል፤
\s5
\v 24 ነገር ግን በያዕቆብ ኃያል አምላክ ክንድ፣ እረኛም በሆነው በእስራኤል አለት ቀስቱ ጸና ጠንካራ ክንዱም ቀልጣፋ ሆነ።
\s5
\v 25 አንተን በሚረዳህ በአባትህ አምላክ፣ በሚባርክህ ሁሉን በሚችል አምላክ፣ ከላይ ከሰማይ በሚገኝ ረድኤት፣ ከምድር ጥልቅ በሚገኝ በረከት፣ ከማኅፀንና ከጡት በሚገኝ ምርቃት ይባርክሃል።
\s5
\v 26 ከጥንት ተራሮች በረከት፣ ከዘላለም ኮረብቶች ምርቃት ይልቅ፣ የአባትይ በረከት ይበልጣል፤ ይህ ሁሉ በዮሴፍ ራስ ላይ ይውረድ፤ በወንድሞቹ መካከል አለቃ በሆነውም ግንባር ላይ ይረፍ።
\s5
\v 27 ብንያም ነጣቂ ተኩላ ነው፤ ያደነውን ማለዳ ይበላል፤ የማረከውን ማታ ያከፋፍላል።
\s5
\v 28 እነዚህ ሁሉ ዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ናቸው። ይህም እያንዳንዳቸውን ተገቢ በሆነው በረከት አባታቸው ሲባርካቸው የተናገረው ቃል ነው።
\v 29 ከዚህ በኋላ ያዕቆብ እንዲህ ሲል አዘዛቸው፤ “እኔ የምሞትበትና ወደ ወገኖቼ የምሰበሰብበት ጊዜ ደርሶአል፤ ስለዚህ በኬጢያዊው በኤፍሮን እርሻ ውስጥ ባለችው ዋሻ ከአባቶቼ ዘንድ ቅበሩኝ፤
\v 30 ይህንን በከነዓን ምድር በመምሬ አጠገብ በማክፌል እርሻ ውስጥ ያለውን ዋሻ የመቃብር ቦታ እንዲሆን ከኬጢያዊው ኤፍሮን ላይ የገዛው አብርሃም ነው።
\s5
\v 31 በዚያ አብርሃምና ሚስቱ ሣራ ተቀብረዋል፤ በዚያ ይስሐቅና ሚስቱ ርብቃ ተቀብረዋል፤ እኔም ልያን የቀበርኋት እዚያው ነው፤
\v 32 እርሻውና ዋሻው የተገዙት ከኬጢያውያን ላይ ነው።”
\v 33 ያዕቆብ እነዚህን ቃላት ለልጆቹ ተናግሮ እንዳበቃ እግሮቹን በአልጋው ላይ ሰብስቦ የመጨረሻ ትንፋሹን ተንፍሶ ሞተ፣ ወደ ወገኖቹም ተሰበሰበ።
\s5
\c 50
\p
\v 1 ዮሴፍ እጅግ ከማዘኑ የተነሣ በአባቱ ፊት ተደፍቶ አለቀሰ ሳመውም።
\v 2 ከዚያም የአባቱ የእስራኤል አስከሬን እንዳይፈርስ ባለ መድኃኒት የሆኑ አገለጋዮች በመድኃኒት እንዲያሹት አዘዘ። ባለ መድኃኒቶቹም አስከሬኑ እንዳይፈርስ በመድኃኒት አሹት።
\v 3 በአገሩ ልማድ መሠረት አስከሬኑ እንዳይፈርስ ማሸቱ አርባ ቀን ወሰደባቸው፤ ገብፃውያንም ሰባ ቀን አለቀሱለት።
\s5
\v 4 የለቅሶው ወራት በተፈጸመ ጊዜ ዮሴፍ የፈርዖንን ባለሥልጣኖች እንዲህ አላቸው፤ “መልካም ፈቃዳችሁ ቢሆን እባካችሁ ለፈርዖን፣
\v 5 ‘አባቴ ለመሞት ሲቃረብ በከነዓን ምድር ባዘጋጀው መቃብር እንድቀብረው በመሐላ ቃል አስገብቶኛል፤ ስለዚህ ወደዚያ ሄጄ አባቴን ቀብሬ እንድመለስ ይፈቀድልኝ ሲል ጠይቆአል’ ብላችሁ ንገሩልኝ” አላቸው።
\v 6 ፈርዖንም፣ “ባስማለህ መሠረት ሄደህ አባትህን ቅበር” አለው።
\s5
\v 7 ስለዚህ ዮሴፍ አባቱን ለመቅበር ሄደ፣ የፈርዖን ሹማምንት በሙሉ፣ የቤተ መንግሥቱ ከፍተኛ ባለሥልጣኖች እንዲሁም የግብፅ ከፍተኛ ባለ ሥልጣኖች ሁሉ ተከተሉት።
\v 8 እንደዚሁም የዮሴፍ ቤተ ሰቦች ወንድሞቹና ሌሎችም የአባቱ ቤተ ሰቦች ሁሉ ከዮሴር ጋር ሄዱ፣ በጌሤም የቀሩት ሕፃናት ልጆቻቸው፣ የበግ፣ የፍየልና የከብት መንጋዎቻቸው ብቻ ነበሩ።
\v 9 እንዲሁም ሠረገሎች፣ ፈረሰኞች አብረውት ወጡ፤ አጀቡም እጅግ ብዙ ነበር።
\s5
\v 10 እነርሱም በዮርዳኖስ ማዶ ካለው አጣድ ከተባለው ዐውድማ ሲደርሱ ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ ምርር ብለው አለቀሱ፤ ዮሴፍም በዚያ ለአባቱ ሰባት ቀን ለቅሶ ተቀመጠ።
\v 11 በዚያ የሚኖሩ ከነዓናውያን በአጣድ ዐውድማ የተደረገውን ልቅሶ ባዩ ጊዜ፣ “ይህ ለግብፃውያን መራራ ልቅሶአቸው ነው” አሉ። በዮርዳኖስ አጠገብ ያለው የዚያ ቦታ ስም አቤል ምጽራይም ተብሎ መጠራቱም ከዚሁ የተነሣ ነበር።
\s5
\v 12 በዚህ ሁኔታ የያዕቆብ ልጆች አባታቸው እንዳዘዛቸው አደረጉ፤
\v 13 አስከሬኑን ወደ ከነዓን ወስደው ከመምሬ በስተምሥራቅ በምትገኘው በማክፌላ ዋሻ ቀበሩት፤ ይህም ዋሻ አብርሃም ለመቃብር ቦት እንዲሆን ከኬጢያዊው ከኤፍሮን በገዛው እርሻ ውስጥ የሚገኝ ነው።
\v 14 ዮሴፍ አባቱን ከቀበረ በኋላ ከወንድሞቹና ለቀብር አጅበውት ከሄዱት ሰዎች ሁሉ ጋር ሆኖ ወደ ግብፅ ተመለሰ።
\s5
\v 15 የዮሴፍ ወንድሞች ከአባታቸው ሞት በኋላ፣ “ከፈጸምንበት በደል የተነሣ ዮሴፍ ቂም ይዞ በበቀልን ምን እናደርጋለን ተባባሉ።
\v 16 ስለዚህ እንዲህ የሚል መልእክት ላኩ፣ አባትህ ከመሞቱ በፊት፣
\v 17 ‘ለዮሴፍ ወንድሞችህ በአንተ ላይ የፈጸሙትን ኃጢአትና ክፉ በደል ይቅር በላቸው’ ብላችሁ ንገሩት የሚል ትእዛዝ አስተላልፎ ነበር። አሁንም የአባትህን አምላክ አገልጋዮች ኃጢአት ይቅር በለን።” ዮሴፍ ይህን በሰማ ጊዜ አለቀሰ።
\s5
\v 18 ከዚያም ወንድሞቹ መጡና በፊቱ ተደፍተው፣ “እኛ የአንተ አገልጋዮች ነን” አሉት።
\v 19 ዮሴፍ ግን እንዲህ አላቸው፤ “አትፍሩ፣ እኔ በእግዚአብሔር ምትክ የተቀመጥሁ አይደለሁም፣
\v 20 እናንተ እኔን ለመጉዳት አስባችሁ አድርጋችሁት ነበር፤ እግዚአብሔር ግን ዛሬ እንደሚታየው ሁሉ የብዙዎችን ሕይወት ለማዳን ለበጎ ነገር አዋለው።
\v 21 አሁንም ቢሆን አትፍሩ፤ ለእናንተና ለልጆቻችሁ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ አደርግላችኋለሁ” በማለት በመልካም ንግግር አረጋጋቸው።
\s5
\v 22 ዮሴፍ ከአባቱ ቤተ ሰቦች ጋር በግብፅ ተቀመጠ፤ አንድ መቶ ዐሥር ዓመትም ኖረ፤
\v 23 የኤፍሬምንም የልጅ ልጆች እስከ ሦስት ትውልድ ድረስ ዐየ። ከምናሴ የተወለደውንም የማኪርንም ልጆች በጭኑ ላይ አድርጎ አቀፋቸው።
\s5
\v 24 ከዚህ በኋላ ዮሴፍ ወንድሞቹን እንዲህ አላቸው፤ “እነሆ፣ እኔ የምሞትበት ጊዜ ተቃርቦአል፤ እናንተ ግን እግዚአብሔር በረድኤት ይጎበኛችኋል፤ ከዚህም አገር አውጥቶ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ለመስጠት በመሐላ ቃል ወደገባላቸው ምድር ይመልሳችኋል።
\v 25 እግዚአብሔር በሚጎበኛችሁና ወደዚያች ምድር በሚመልሳችሁ ጊዜ ዐጽሜን ከዚህ ይዛችሁ የምትወጡ መሆናችሁን በማረጋገጥ ቃል ግቡልኝ” ብሎ አስማላቸው።
\v 26 ዮሴፍም ዕድሜው መቶ ዐሥር ዓመት ሲሞላው ሞተ፣ አስከሬኑንም መድኃኒት ቀብተው በሬሳ ሳጥን ካስገቡት በኋላ በግብፅ ምድር አስቀመጡት።