more OT books

This commit is contained in:
Larry Versaw 2019-06-23 16:36:45 -06:00
parent 42bc16eafe
commit d94a9afd83
7 changed files with 8940 additions and 3 deletions

2446
04-NUM.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,2446 @@
\id NUM
\ide UTF-8
\h ዘኁልቁ
\toc1 ዘኁልቁ
\toc2 ዘኁልቁ
\toc3 num
\mt ዘኁልቁ
\s5
\c 1
\p
\v 1 ያህዌ በሲና ምድረ በዳ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ሙሴን ተናገረው፡፡ ይህ የሆነው የእስራኤል ህዝብ ከግብጽ ምድር በወጣበት በሁለተኛው አመት በሁለኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ነበር፡፡ ያህዌ እንዲህ አለ፣
\v 2 “በየነገዱ፣ በየአባቶቻቸው ቤተሰቦች የእስራኤል ወንዶች ቆጠራ ይደረግ፡፡ በስም ቁጠራቸው፡ እያንዳንዱ ወንድ፣ በሰው ቁጠር፣
\v 3 ሀያ አመት የሞላው ወይም ከዚያ በላይ የሆነ ወንድ ሁሉ ይቆጠር፡፡ ለእስራኤል ወታደር ሆኖ ሊዋጋ የሚችለውን ሁሉ ቁጠር፡፡ አንተና አሮን በታጣቂ ቡድኖቻቸው የወንዶችን ቁጥር መዝግቡ፡፡
\s5
\v 4 ከእያንዳንዱ ጎሳ አንድ ሰው፣ የነገድ አለቃ ከአንተ ጋር የጎሳው መሪ ሆኖ ያገልግል፡፡ እያንዳንዱ መሪ ለጎሳው የሚዋጉትን ወንዶች ይምራ፡፡
\v 5 ከአንተ ጋር ሆነው መዋጋት ያለባቸው መሪዎች ስሞቻቸው እነዚህ ናቸው፡ ከሮቤል ጎሳ፣ የሰዲዮር ልጅ ኤሊሱር፣
\v 6 ከስምዖን ጎሳ የሱሪሰዳይ ልጅ ሰለሚኤል፤
\s5
\v 7 ከይሁዳ ጎሳ፣ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን፤
\v 8 ከይሳኮር ጎሳ የሶገር ልጅ ናትናኤል፤
\v 9 ከዛብን ጎሳ፣ የኬሎን ልጅ ኤልያብ፤
\s5
\v 10 ከኤፍሬም ጎሳ፣ የዮሴፍ ልጅ፣ የዓሚሁድ ልጅ ኤሊሳማ፤ ከምናሴ ጎሳ፣ የፍዳሱር ልጅ ገማልኤል፤
\v 11 ከብንያም ጎሳ የዮሴፍ ልጅ፣ የጌዲዮን ልጅ አቢዳን፤
\s5
\v 12 ከዳን ጎሳ የአሚሳዳይ ልጅ አኪዔዘር፣
\v 13 ከአሴር ጎሳ፣ የኤክራን ልጅ ፉግኤል፣
\v 14 ከጋድ ጎሳ የራጉኤል ልጅ ኤሊሳፍ፤
\v 15 እና ከንፍታሌም ጎሳ፣ የዔናን ልጅ አኪሬ” ናቸው፡፡
\s5
\v 16 ከሕዝቡ የተመረጡት ወንዶች እነዚህ ነበሩ እነርሱ የአባቶቻቸውን ጎሳዎች ይመራሉ፡፡ በእስራኤል የነገዶች መሪዎች ነበሩ፡፡
\s5
\v 17 ሙሴና አሮን በስም የተመዘገቡትን እነዚህን ወንዶች ወሰዱ፣
\v 18 ከእዚህ ወንዶች ጋር በሁለተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን የእስራኤል ወንዱን ሁሉ ሰበሰቡ፡፡ ከዚያም ሃያ አመት የሞላውና ከዚያ በላይ የሆነ እያንዳንዱ ወንድ የትውልድ ሐረጉን ተናገረ፡፡ እያንዳንዱ የነገዱን ስም እና የትውልድ ሐረጉን መጥራት ነበረበት፡፡
\v 19 ከዚያም ሙሴ በሲና ምድረ በዳ ያህዌ እንዲያደርገው ባዘዘው መሠረት ቁጥራቸውን መዘገበ፡፡
\s5
\v 20 የእስራኤል በኩር ከሆነው ከሮቤል ትውልዶች፣ ወደ ጦርነት መሄድ የሚችሉት ሃያ አመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ከየጎሳቸውና፣ ከየቤተሰባቸው መዛግብት እያንዳንዳቸው በስማቸው ተቆጠሩ፡፡
\v 21 ከሮቤል ጎሳ 46500 ወንዶች ተቆጠሩ፡፡
\s5
\v 22 ከስምኦን ትውልዶች ወደ ጦርነት መሄድ የሚችሉት ሃያ አመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ከየጎሳቸውና፣ ከየቤተሰባቸው መዛግብት እያንዳንዳቸው በስማቸው ተቆጠሩ፡፡
\v 23 ከስምዖን ጎሳ 59300 ወንዶች ተቆጠሩ፡፡
\s5
\v 24 ከጋድ ትውልዶች፣ ወደ ጦርነት መሄድ የሚችሉ ሃያ አመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ከየጎሳቸውና ከየቤተሰባቸው መዛግብት እያንዳንዳቸው በስማቸው ተቆጠሩ፡፡
\v 25 ከጋድ ጎሳ 45650 ወንዶች ተቆጠሩ፡፡
\s5
\v 26 ከይሁዳ ትውልዶች፣ ወደ ጦርነት መሄድ የሚችሉ ሃያ አመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ከየጎሳቸውና፣ ከየቤተሰባቸው መዛግብት እያንዳንዳቸው በስም ተቆጠሩ፡፡
\v 27 ከይሁዳ ጎሳ 7460 ወንዶች ተቆጠሩ፡፡
\s5
\v 28 ከይሳኮር ትውልዶች፣ ወደ ጦርነት መሄድ የሚችሉ ሃያ አመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ከየጎቸውና፣ ከየቤተሰባቸው መዛግብት እያንዳንዳቸው በስማቸው ተቆጠሩ፡፡
\v 29 ከይሳኮር ጎሳ 54400 ወንዶች ተቆጠሩ፡፡
\s5
\v 30 ከዛብሎን ትውልዶች፣ ወደ ጦርነት መሄድ የሚችሉ ሃያ አመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ከየጎሳቸውና፣ ከየቤተሰባቸው መዛግብት እያንዳንዳቸው በስማቸው ተቆጠሩ፡፡
\v 31 ከዛብን ጎሳ 57400 ወንዶች ተቆጠሩ፡፡
\s5
\v 32 ከዮሴፍ ልጅ ከኤፍሬም ትውልዶች፣ ወደ ጦርነት መሄድ የሚችሉ ሃያ አመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ከየጎሳቸውና፣ ከየቤተሰባቸው መዛግብት እያንዳንዳቸው በስማቸው ተቆጠሩ፡፡
\v 33 ከኤፍሬም ጎሳ 40500 ወንዶች ተቆጠሩ፡፡
\s5
\v 34 ከዮሴፍ ልጅ ከምናሴ ትውልዶች፣ ወደ ጦርነት መሄድ የሚችሉ ሃያ አመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ከየጎሳቸውና፣ ከየቤተሰባቸው መዛግብት እያንዳንዳቸው በስማቸው ተቆጠሩ፡፤
\v 35 ከምናሴ ጎሳ 32200 ወንዶች ተቆጠሩ፡፡
\s5
\v 36 ከብንያም ትውልዶች ወደ ጦርነት መሄድ የሚችሉ ሃያ አመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ከየጎሳቸውና፣ ከየቤተሰባቸው መዛግብት እያንዳንዳቸው በስማቸው ተቆጠሩ፡፤
\v 37 ከብንያም ጎሳ 35400 ወንዶች ተቆጠሩ፡፡
\s5
\v 38 ከዳን ትውልዶች፣ ወደ ጦርነት መሄድ የሚችሉ ሃያ አመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ከየጎሳቸውና፣ ከየቤተሰባቸው መዛግብት እያንዳንዳቸው በስማቸው ተቆጠሩ፡፡
\v 39 ከዳን ጎሳ 62700 ወንዶች ተቆጠሩ፡፡
\s5
\v 40 ከአሴር ትውልዶች፣ ወደ ጦርት መሄድ የሚችሉ ሃያ አመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ከየጎሳቸውና፣ ከቤተሰባቸው መዛግብት እያንዳንዳቸው በስማቸው ተቆጠሩ፡፡
\v 41 ከአሴር ጎሳ 41500 ወንዶች ተቆጠሩ፡፡
\s5
\v 42 ከንፍታሌም ትውልዶች፣ ወደ ጦርነት መሄድ የሚችሉ ሃያ አመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ከየጎሳቸውና፣ ከየቤተሰባቸው መዛግብት እያንዳንዳቸው በስማቸው ተቆጠሩ፡፡
\v 43 ከንፍታሌም ጎሳ 53400 ወንዶች ተቆጠሩ፡፡
\s5
\v 44 ሙሴና አሮን እነዚህን ወንዶች ሁሉ አስራ ሁለቱን የእስራኤል ጎሳዎች ከሚመሩ አስራ ሁለት ሰዎች ጋር ሆነው ቆጠሩ፡፡
\v 45 ስለዚህም ሃያ አመትና ከዚያ በላይ ዕድሜ ያላቸው ለጦርነት መውጣት የሚችሉ የእስራኤል ወንዶች ሁሉ በየቤተሰባቸው ተቆጠሩ፡፡
\v 46 የቆጠሯቸው ወንዶች 603550 ናቸው፡፡
\s5
\v 47 ከሌዊ ትውልድ የሆኑት ግን አልተቆጠሩም፣
\v 48 ምክንያቱም ያህዌ ሙሴን እንዲህ ብሎት ነበር፣
\v 49 “የሌዊን ጎሳ አትቆጥርም ወይም እነርሱን በእስራኤል ህዝብ ቆጠራ ውስጥ አታስገባቸው፡፡
\s5
\v 50 ይልቁንም፣ ሌዋውያንን የቃልኪዳኑን ስርዓቶች በቤተመቅደስ እንዲፈጽሙ መድባቸው፣ እንደዚሁም በቤተመቅደስ ውስጥ የሚገኙ መገልገያዎችንና ማናቸውንም ነገሮች እንዲንከባከቡ ሹማቸው፡፡ ሌዋውያን ጽላቱን ይሸከሙ፣ እንዲሁም የቤተመቅደሱን ዕቃዎች ይሸከሙ፡፡
\s5
\v 51 ቤተመቅደሱ ወደ ሌላ ስፍራ በሚንቀሳቀስበት ጊዜ፣ ሌዋውያኑ ይንቀሉት፡፡ ቤተመቅደሱ ሲተከል፣ ሌዋውያን ይትከሉት፡፡ ወደ ቤተ መቅደሱ የሚጠጋ ማናቸውም እንግዳ ይገደል፡፡
\v 52 እስራኤላውያን ድንኳኖቸውን ሲተክሉ፣ እያንዳንዱ ሰው ወደ ራሱ የጦር ቡድን ዐርማ አጅግ ቀርቦ ይስራ፡፡
\s5
\v 53 ሆኖም፣ ሌዋውያኑ ቁጣዬ በእስራኤላውያን ላይ እንዳይሆን ድንኳናቸውን በቃል ኪዳኑ ማደሪያ ዙሪያ ይትከሉ፡፡ ሌዋውያኑ የቃልኪዳኑን ማደሪያ ሀላፊዎች ናቸው፡፡”
\v 54 እስራኤላውያን እነዚህን ሁሉ ነገሮች አደረጉ፡፡ ያህዌ በሙሴ በኩል ያዘዛቸውን ነገሮች ሁሉ አደረጉ፡፡
\s5
\c 2
\p
\v 1 ያህዌ ለሙሴና ለአሮን እንደገና እንዲህ አለ፣
\v 2 “እያንዳንዱ እስራኤላዊ በየአባቶቻቸው ቤቶች በአርማው ስር በቦታው ይሰፈር፡፡ በመገናኛው ድንኳን ዙሪያ በሁሉም አቅጣጫ ይሰፍራሉ፡፡
\s5
\v 3 ፀሐይ በምትወጣበት፣ በመገናኛው ድንኳን በስተምስራቅ ይሁዳ በቦታው ይሰፍራል፡፡ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን የይሁዳ ህዝብ መሪ ነው፡፡
\v 4 የይሁዳ ህዝብ ቁጥር 74600 ነው፡፡
\s5
\v 5 የይሳኮር ጎሳ ከይሁዳ ቀጥሎ ይስፈር፡፡ የሶገር ልጅ ናትናኤል የይሳኮርን ሰራዊት ይምራ፡፡
\v 6 በእርሱ ክፍል የሰራዊቱ ቁጥር 54400 ነው፡፡
\s5
\v 7 የዛብሎን ጎሳ ከይሳኮር ቀጥሎ ይስፈር፡፡ የኬሎን ልጅ ኤልያብ የኤሎንን ሰራዊት ይምራ፡፡
\v 8 በእርሱ ክፍል የሰራዊቱ ቁጥር 57400 ነው፡፡
\s5
\v 9 ጠቅላላው የይሁዳ ሠራዊት ቁጥር 186400 ነው፡፡ እነርሱ በቅድሚያ ይወጣሉ፡፡
\s5
\v 10 በስተደቡብ አቅጣጫ የሮቤል ምድብ በስፍራው ይሆናል፡፡ የሮቤል ምድብ መሪ የሰዲዮር ልጅ ኤሊሱር ነው፡፡
\v 11 በእርሱ ክፍል የሰራዊቱ ቁጥር 46500 ነው፡፡
\s5
\v 12 ስምዖን ከሮቤል ቀጥሎ ይሰፍራል፡፡ የስምዖን ህዝብ መሪ የሱሪሰዳይ ልጅ ስለሚኤል ነው፡፡
\v 13 በእርሱ ምድብ የሚገኘው የሰራዊት ቁጥር 59, 300 ነው፡፡
\s5
\v 14 የጋድ ጎሳ ይቀጥላል፡፡ የጋድ ህዝብ መሪ የራጉኤል ልጅ ኤሊሳፍ ነው፡፡
\v 15 በእርሱ ምድብ የሚገኘው የሰራዊት ቁጥር 45650 ነው፡፡
\s5
\v 16 በሮቤል ምድብ የሚገኙት በክፍላቸው መሠረት 151450 ናቸው፡፡ እነርሱ ቀጥለው ይወጣሉ፡፡
\s5
\v 17 ቀጥሎ፣ የመገናኛው ድንኳን ሌዋውያንን ከሁሉም ምድብተኞች መሃል አድርጎ ከሰፈር ይወጣል፡፡ ወደ ሰፈር በገቡበት ስርዓት ከሰፈር ይውጡ፡፡ እያንዳንዱ ሰው በዐርማው ስር በስፍራው ይሁን፡፡
\s5
\v 18 የኤፍሬም ሰፈር ክፍሎች በስፍራቸው ይሁኑ፡፡ የኤፍሬም ህዝብ መሪ የዓሚሁድ ልጅ ኤሊሳማ ነው፡፡
\v 19 በእርሱ ክፍል የሰራዊቱ ቁጥር 40500 ነው፡፡
\s5
\v 20 ከእነርሱ የሚቀጥለው የምናሴ ጎሳ ነው፡፡ የምናሴ መሪ የፍርዱሱር ልጅ ገማልኤል ነው፡፡
\v 21 በእርሱ ክፍል የሰራዊቱ ቁጥር 32200 ነው፡፡
\s5
\v 22 ቀጣይ የሚሆነው የብንያም ጎሳ ነው፡፡ የብንያም መሪ የጋዴዮን ልጅ አቢዳን ነው፡፡
\v 23 በእርሱ ክፍል የሰራዊቱ ቁጥር 35400 ነው፡፡
\s5
\v 24 በኤፍሬም ምድብ የሚኙት በክፍላቸው መሰረት 108100 ናቸው፡፡ እነርሱ ሶስተኛ ሆነው ይወጣሉ፡፡
\s5
\v 25 በሰሜን የዳን ሰፈር ምድብተኞች ይሰፍራሉ፡፡ የዳን ህዝብ መሪ የአሚሳዓይ ልጅ አብዔዘር ነው፡፡
\v 26 በእርሱ ክፍል የሰራዊቱ ቁጥር 62700 ነው፡፡
\s5
\v 27 የአሴር ጎሳ ህዝብ ሰፈር ከዳን ቀጥሎ ነው፡፡ የአሴር መሪ የኤክራን ልጅ ፋግኤል ነው፡፡
\v 28 በእርሱ ክፍል የሰራዊቱ ቁጥር 41500 ነው፡፡
\s5
\v 29 ቀጣዩ የንፍታሌም ጎሳ ነው፡፡ የንፍታሌም መሪ የዔናን ልጅ አኪሬ ነው፡፡
\v 30 በእርሱ ክፍል የሰራዊቱ ቁጥር 53400 ነው፡፡
\s5
\v 31 ከዳን ጋር በሰፈር የሚገኙት ቁጥራቸው 157600 ነው፡፡ እነርሱ በዐርማቸው ስር ከሰፈር በመጨረሻ ይወጣሉ፡፡”
\s5
\v 32 በየቤተሰባቸው የተቆጠሩት እስራኤላውያን እነዚህ ናቸው፡፡ በየክፍሎቻቸው በሰፈሮቻቸው የተቆጠሩት በጠቅላላ 603550 ናቸው፡፡
\v 33 ነገር ግን ሙሴና አሮን በእስራኤል ሕዝብ መሀል ሌዋውያንን አልቆጠሩም፡፡ ይህም ያህዌ ሙሴን ባዘዘው መሠረት ነበር፡፡
\s5
\v 34 የእስራኤል ሕዝብ ያህዌ ሙሴን ያዘዘውን ነገር ሁሉ አደረጉ፡፡ በየአርማቸው ስር ሰፈሩ፡፡ በአባቶቻቸው ቤቶች መሠረት በየነገዳቸው ከሰፈር ወጡ፡፡
\s5
\c 3
\p
\v 1 ያህዌ በሲና ተራራ ከሙሴ ጋር በተነጋገረበት ጊዜ የአሮንና የሙሴ ትውልዶች ታሪክ ይህ ነበር፡፡
\v 2 የአሮን ልጆች ስሞቻቸው የበኩር ልጁ ናዳብ፣ እንዲሁም አብዩድ፣ አልዓዛር እና ኢታምር ነበሩ፡፡
\s5
\v 3 የአሮን ልጆች ስሞች እነዚህ ናቸው፣ እነዚህ የተቀቡ ካህናትና እንደ ካህናት ሊያገለግሉ የተሾሙ ነበሩ፡፡
\v 4 ነገር ግን ናዳብ እና አብዩድ በሲና ምድረበዳ ተቀባይነት የሌለው እሳት ለእርሱ ሲሰዉ በያህዌ ፊት ወድቀው ሞቱ፡፡ ናዳብና አብዩድ ልጅ አልነበራቸውም፣ ስለዚህም አልዓዛርና ኢታምር ብቻ ከአባታቸው ከአሮን ጋር ካህናት ሆነው አገለገሉ፡፡
\s5
\v 5 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
\v 6 “የሌዊን ጎሳ ይረዱት ዘንድ ወደ ካህኑ ወደ አሮን አምጣቸው፡፡
\s5
\v 7 በአሮንና በመላው ማህበሩ ስም በመገናኛው ድንኳን ፊት አገልግሎት ይስጡ፡፡ በቤተመቅደሱ ውስጥ ያገልግሉ፡፡
\v 8 በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ላሉ ነገሮች ሁሉ ጥንቃቄ ያድርጉ፣ እንዲሁም የእስራኤል ጎሳዎች የቤተ መቅደሱን አገልግሎት እንድፈጽም ይርዱ፡፡
\s5
\v 9 ሌዋውያኑን ለአሮንና ለልጆቹ ስጥ፡፡ እነርሱ የእስራኤልን ሕዝብ እንዲያገለግል ሙሉ ለሙሉ የተሰጡ ናቸው፡፡
\v 10 አሮንንና ልጆቹን ካህን አድርገህ ሹማቸው፣ ነገር ግን ማናቸውም ባዕድ ወደ ቤተ መቅደሱ ቢቀርብ ይገደል፡፡”
\s5
\v 11 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
\v 12 “እነሆ፣ እኔ ከእስራኤል ህዝብ መሃል ሌዋውያንን መረጥኩ፡፡ ከእስራኤል ሕዝብ መሃል በኩር የሆነውን ወንድ ሁሉ ከመውሰድ ፈንታ ይህን አድርጌያለሁ፡፡ ሌዋዊያን የእኔ ናቸው፡፡
\v 13 ማናቸውም በኩር የእኔ ነው፡፡ በግብጽ ምድር በኩሩን ሁሉ በመታሁ ዕለት፣ በእስራኤል በኩር ሆኖ የተወለደውን የሰውንም ሆነ የእንስሳትን በኩር ሁሉ ለራሴ ለየሁ፡፡ እነርሱ የእኔ ናቸው፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡”
\s5
\v 14 በሲና ምድረበዳ ያህዌ ሙሴን ተናገረው፡፡ እንዲህም አለው፣
\v 15 “በእያንዳንዱ ቤተሰብ፣ በአባቶቻቸው ቤቶች የሌዊን ትውልዶች ቁጠር፡፡ አንድ ወር እና ከዚያ በላይ ዕድሜ ያለውን ወንድ ሁሉ ቁጠር፡፡”
\v 16 ሙሴ እንዲያደርግ በታዘዘው መሠረት የያህዌን ቃል ሰምቶ ቆጠራቸው፡፡
\s5
\v 17 የሌዊ ልጆች ስም፣ ጌድሶን፣ ቀዓትና ሜራሪ ናቸው፡፡
\v 18 ከጌድሶን ልጆች የመጡ ነገዶች ሎቢኒ እና ሰሜኢ ናቸው፡፡
\v 19 ከቀዓት ልጆች የመጡ ነገዶች፣ አንበረም፣ ይስዓር፣ኬብሮን እና ዑዝኤል ናቸው፡፡
\v 20 ከሜራሪ ልጆች የመጡ ነገዶች፣ ሞሖሊና ሙሴ ናቸው፡፡ በነገድ የተዘረዘሩ የሌዋውያን ነገዶች እነዚህ ናቸው፡፡
\s5
\v 21 የሊቤናና የሰሜአ ነገዶች የመጡት ከጌርሶን ነው፡፡ እነዚህ የጌርሶን ነገዶች ናቸው፡፡
\v 22 አንድ ወር ከሞላው አንስቶ ከዚያ በላይ ዕድሜ ያለው ወንድ ሁሉ ተቆጥሮ ነበር፣ በጠቅላላው 7500 ነበሩ፡፡
\v 23 የጌርሶን ነገዶች ከቤተመቅደሱ ምዕራብ አቅጣጫ ይስፈሩ፡፡
\s5
\v 24 የጌርሶንን ትውልዶች የላኤለ ልጅ ኤሊሳፍ ይምራ፡፡
\v 25 የጌርሶን ቤተሰብ የመገናኛው ድንኳን ጨምሮ የማደሪያውን ድንኳን ኃላፊነት ይውሰድ፡፡ እነርሱ ለድንኳኑ፣ ለመደረቢያዎቹና ለመገናኛው ድንኳን መግቢያ ሆኖ ለሚያገለግለው መጋረጃ ጥንቃቄ ያደርጉ፡፡
\v 26 ለአደባባዩ ጌጦች ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው፣ በአደባባይ መግቢያ ላይ ለሚገኘው መጋረጃ፣ ቅዱሱን ስፍራና መሰዊያውን የሚከበውን አደባባይ ይጠብቁ፡፡ የመገናኛው ድንኳን ገመዶች እና በውስጡ የሚገኘውን ነገር ሁሉ ይጠብቁ፡፡
\s5
\v 27 ከቀዓት የመጡት ነገዶች እነዚህ ናቸው የአንበረማውያን ነገድ የይሰዓራውያን ነገድ፣ የኬብሮናውያን ነገድ፣ እና የዑዝኤላውያን ነገድ ናቸው፡፡ እነዚህ ነገዶች የቀዓት ወገኖች ናቸው፡፡
\v 28 አንድ ወር እና ከዚያ በላይ ዕድሜ ያላቸው 8600 ወንዶች የያህዌ የሆኑ ነገሮችን ለመጠበቅ ተቆጠሩ፡፡
\v 29 የቀዓት ቤተሰብ ትውልዶች ከቤተ መቅደሱ በስተደቡብ አቅጣጫ ይስፈሩ፡፡
\s5
\v 30 የዑዝኤል ልጅ ኤሊሳፈን የቀዓታዊያንን ነገድ ይምራ፡፡
\v 31 እነርሱ ታቦቱን፣ ጠረጴዛውን፣ የመቅረዝ ማስቀመጫውን፣ መሰዊያዎቹን፣ ለአገልግሎታቸው የሚጠቀሙባቸውን ቅዱሳን ዕቃዎች፣ መጋረጃውን፣ እና በዚያ ዙሪያ ያለውን ስራ ሁሉ ይንከባከቡ፡፡
\v 32 የካህኑ የአሮን ልጅ አልዓዛር ሌዋውያንን የሚመሩትን ሰዎች ይምሩ፡፡ እርሱ ቅዱሱን ስፍራ የሚንከባከቡትን ሰዎች ይቆጣጠር፡፡
\s5
\v 33 ሁለቱ ነገዶች ኮሜራሪ ነገድ የመጡ ናቸው፡ እነዚህም የሞሖላውያን ነገድ እና የሙሳያውያን ነገድ ናቸው፡፡ እነዚህ ነገዶች የመጡት ከሜራሪ ነው፡፡
\v 34 አንድ ወርና ከዚያ በላይ ዕድሜ ያላቸው 6200 ወንዶች ተቆጠሩ፡፡
\v 35 የሜራሪን ነገድ የአቢካኤል ልጅ ሲሪኤል ይምራ፡፡
\s5
\v 36 እነርሱ የቤተመቅደሱን ጣውላዎች፣ መቀርቀሪያዎች፣ ምሰሶዎች፣ መሰረቶች፣ ሁሉንም መገልገያዎች፣ እና ከእነርሱ ጋር የተያያዙ ነገሮች ሁሉ፣
\v 37 መቅደሱ ዙሪያ የሚገኙ ምሰሶዎችና ቋሚዎችን ጨምሮ፣ ከማስገቢያዎቻቸው፣ ችካሎችና ገመዶች ጋር ይጠብቁ፡፡
\s5
\v 38 ሙሴ፣ አሮን እና ልጆቹ ከመገናኛው ድንኳን ፊት ለፊት፣ በፀሀይ ማውጫ ከቤተ መቅደሱ በስተ ምስራቅ ይስፈሩ፡፡ እነርሱ በቅድስተ ቅዱሳን ለሚከናወኑ ተግባራት እና ለእስራኤል ህዝብ ግዴታዎች ሀላፊነት አለባቸው፡፡ ማንኛውም ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ የሚቀርብ ባዕድ ይገደል፡፡
\v 39 ሙሴና አሮን ያህዌ እንዳዘዘው በሌዊ ነገዶች ውስጥ የሚገኙትን አንድ ወርና ከዚያ በላይ ዕድሜ ያላቸውን ወንዶች ሁሉ ቆጠሩ፡፡ ሃያ ሁለት ሺህ ወንዶችን ቆጠሩ፡፡
\s5
\v 40 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ “አንድ ወር ከዚያ በላይ ዕድሜ ያላቸውን በኩር የሆኑ የእስራኤል ወንዶች ቁጠር፡፡ ስሞቻቸውን ጻፍ፡፡
\v 41 በእስራኤል ህዝብ በኩር ምትክ ሌዋውያንን ለእኔ ውሰድ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡ እንደዚሁም የሌዋውያንን ቀንድ ከብቶች፣ በመጀመሪያ በሚወለዱ የእስራኤላውያን የቀንድ ከብቶች ምትክ ውሰድ፡፡”
\s5
\v 42 ያህዌ እንዳዘዘው ሙሴ የእስራኤልን ሰዎች በኩር በሙሉ ቆጠረ፡፡
\v 43 ዕድሜያቸው አንድ ወርና ከዚያ በላይ የሆኑትን በኩር ወንዶች ሁሉ በስም ቆጠረ፡፡ 22273 ወንዶችን ቆጠረ፡፡
\s5
\v 44 እንደገና፣ ያህዌ ሙሴን ተናገረው፡፡ እንዲህም አለው፣
\v 45 “በእስራኤል ህዝብ በኩር ሁሉ ምትክ ሌዋውያንን ውሰድ፡፡ በህዝቡ የቀንድ ከብት ምትክ የሌዋውያንን ቀንድ ከብት ውሰድ፡፡ ሌዋውያን የእኔ ናቸው፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡
\s5
\v 46 ከሌዋውያን ቁጥር በላይ የሆኑትን 273 የእስራኤል በኩሮች ለመዋጀት ለእያንዳንዳቸው አምስት ሰቅሎች ተቀበል፡፡
\v 47 የቅድስተ ቅዱሳኑን ሰቅል እንደ መደበኛ ክብደት ተጠቀም፡፡ (አንድ ሰቅል አምሳ አምስት ግራም ነው)
\v 48 ያገኘኸውን የመዋጆ ዋጋ ለአሮንና ለልጆቹ ስጥ፡፡”
\v 49 ስለዚህም ሙሴ በሌዋውያን ከተዋጁት በላይ ቁጥራቸው ያለፈውን መዋጃ ክፍያ ሰበሰበ፡፡
\v 50 ሙሴ ከእስራኤል ሕዝብ በኩሮች ገንዘብ ሰበሰበ፡፡ በቤተ መቅደሱ ሚዛን መዝኖ 1365 ሰቅሎች ሰበሰበ፡፡
\v 51 ሙሴ ለአሮንና ለልጆቹ የመዋጃውን ገንዘብ ሰጣቸው፡፡ ሙሴ ያህዌ እንዲያደርግ የተናገረውን ሁሉ አደረገ፣ ያህዌ እንዳዘዘው አደረገ፡፡
\s5
\c 4
\p
\v 1 ያህዌ ለሙሴና ለአሮን እንዲህ አላቸው::
\v 2 “ከሌዋውያን መሃል የቀዓት ትውልዶችን ወንዶችን፣ በነገድ እና በየአባቶቸው ቤተሰቦች ቁጠሩ፡፡
\v 3 ከሰላሳ እስከ አምሳ አመት ዕድሜ ያላቸውን ወንዶች ሁሉ ቁጠሩ፡፡ እነዚህ ወንዶች በመገናኛው ድንኳን ሥራ ያገለግሉ ዘንድ ይምጡ፡፡
\v 4 የቀዓት ትውልድ በመገናኛው ድንኳን ለእኔ የተለዩትን እጅግ ቅዱስ የሆኑ ነገሮች ይጠብቁ፡፡
\s5
\v 5 ህዝቡ ጉዞውን ለመቀጠል ሲነሳ፣ አሮንና ልጆቹ ወደ ድንኳን ውስጥ ይግቡ፣ ቅድስቱን ከቅድስተ ቅዱሳን የሚለየውን መጋረጃ ያውርዱት፣ ከዚያም የቃልኪዳኑን ታቦት ምስክር በእርሱ ይሸፍኑት፡፡
\v 6 ታቦቱን በአስቆጣ ቁርበት ይሸፍኑት፡፡ በሰማያዊ ጨርቅ ይሸፍኑት፡፡ ለመሸከም ምሰሶ ያስገቡበት፡፡
\s5
\v 7 በህብስት ማቅረቢያው ጠረጴዛ ላይ ሰማያዊ ጨርቅ ያንጥፉበት፡፡ በላዩ ድስቶቹን፣ ማንኪያዎችን እና ለመቅጃ ገንቦ ያስቀምጡበት፡፡
\v 8 በጠረጴዛው ላይ ህብስት አይታጣ፡፤ በደማቅ ቀይ ጨርቅ እና እንደገና በአቆስጣ ቁርበት ይሸፍኗቸው፡፡ ጠረጴዛውን ለመሸከም ምሰሰዎች ያስገቡ፡፤
\s5
\v 9 ሰማያዊ ጨርቅ ወስደው የመቅረዝ መያዣውን ይሸፍኑ፣ ከመብራቶቹ ጋር፣ መቆንጠጫ፣ ዝርግ ሰሃኖች፣ እና ለመብራቶቹ የዘይት ገንቦዎችን ይውሰዱ፡፡
\v 10 መቅረዞቹንና መገልገያዎቹን በአቆስጣ ቁርበት መሸፈኛ ውስጥ ያድርጉ፣ ከዚያም በመሸከሚያ መያዣ ላይ ያስቀምጡቱ፡፡
\v 11 በወርቅ መሰዊያው ላይ ሰማያዊ ጨርቅ ያንጥፉ፡፤ እርሱንም በአቆስጣ ቁርበት ይሸፍኑት፣ ከዚያ መሸከሚያ ምሰሶ ያስገቡበት፡፡
\s5
\v 12 ዕቃዎቹን ሁሉ ለሥራ ወደተቀደሰው ስፍራ ይውሰዱና በሰማያዊ ጨርቅ ይጠቅልሉ፡፡ በአስቆጣ ቁርበት ሸፍነው ዕቃዎቹን በመሸከሚያ መያዣ ላይ ያስቀምጡ፡፡
\v 13 ከመሰዊያው አመዱን ያራግፉና ሐምራዊ ጨርቅ በመሰዊያው ላይ ያንጥፉ፡፡
\v 14 በመሰዊያው ላይ የሚጠቀሙባቸውን መሳሪያዎች ሁሉ በመሸከሚያው መሎጊያ ላይ ያስቀምጡ፡፡ እነዚህ ዕቃዎች፣ የእሳት ማንደጃዎች፣ ሜንጦዎች የእሳት መጫሪያዎች፣ ጎድጓዳ ሳህኖች፣ እና ለመሰዊያው የሚያገለግሉ ሌሎች መሳሪያዎች ናቸው፡፡ መሰዊያውን የአስቆጣ ቁርበት ይሸፍኑትና ከዚያ መሸከሚያ ምሰሶ ያስገቡበት፡፡
\s5
\v 15 አሮንና ልጆቹ ቅዱሱን ስፍራና መገልገያዎቹን ሙሉ ለሙሉ ሸፍው ሲጨርሱ፣ እና ህዝቡ ወደፊት ሲንቀሳቀስ በዚያን ጊዜ የቀዓት ትውልዶች ቅዱሱን ስፍራ ለመሸከም ይቅረቡ፡፡ የተቀደሱ ዕቃዎችን ከነኩ ይገደሉ፡፡ የቀዓት ትውልዶች የሥራ ድርሻ በመገናኛው ድንኳን የሚገኙ መገልገያዎችን መሸከም ነው፡፡
\v 16 የካህኑ የአሮን ልጅ አልዓዛር ለመብራት የሚሆነውን ዘይት ያዘጋጃል፡፡ የጣፋጩን እጣን ዝግጅት ይቆጣጠራል፣ መደበኛውን የእህል ቁርባን፣ የቅባት ዘይቱን፣ ጠቅላላውን ቤተ መቅደስ እና በውስቱ ያሉትን ሁሉ፣ እንዲሁም በቅዱስ መገልገያዎችና ቁሳቁሶች ላይ ሀላፊነት ይኖረዋል፡፡”
\s5
\v 17 ያህዌ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፣
\v 18 “የቀዓት የጎሳ ነገዶች ከሌዋዊያን መሃል እንዲወገዱ አትፍቀዱ፡፡
\v 19 በህይወት ይኖሩ ዘንድ እንጂ እንዳይሞቱ ይህን በማድረግ ጠብቋቸው፡፡ እጅግ ወደ ተቀደሱ ነገሮች ሲቀርቡ 20ለአፍታ እንኳን የተቀደሰውን ስፍራ ለማየት ወደ ውስጥ አይግቡ፣ አሊያ ይሞታሉ፡፡
\v 20 አሮንና ልጆቹ ወደ ውስጥ ይግቡ፣ ከዚያ አሮንና ልጆቹ ለእያንዳንዱ ቀዓታዊ የሚሰራውን ሥራ ይስጡት፣ ለእያንዳንዳቸው የየራሳቸውን ተግባራት ይስጧቸው፡፡
\s5
\v 21 ያህዌ እንደገና ሙሴን እንዲህ አለው፣
\v 22 “ጌድሶናውያንንም በአባቶቻቸው ቤተሰቦች፣ በየነገዳቸው ቁጠራቸው፡፡
\v 23 ከሰላሳ እስከ አምሳ አመት ዕድሜ ያላቸውን ቁጠራቸው፡፡ በመገናኛው ድንኳን ማገልገል የሚችሉትን ሁሉ ቁጠራቸው፡፡
\s5
\v 24 የጌድሶናውያን ነገዶች ሲያገለግሉና ሲሸከሙ ተግባራቸው ይህ ነው፡፡
\v 25 የመቅደሱን መጋረጃዎች ይሸከሙ፣ የመገናኛውን ድንኳን፣ መሸፈኛውን፣ በላዩ ላይ የሚገኘውን የአቆስጣ ቁርበት መሸፈኛ እና ለመገናኛው ድንኳን መግቢያ የሚሆኑትን መገረጃዎች ይሸከሙ፡፡
\v 26 የአደባባዩን መጋረጃ ይሸከሙ የአደባባዩን መግቢያ መጋረጃ፣ በቤተ መቅደሱና በመሰዊያው አጠገብ ያሉትን፣ ገመዶቻቸውን፣ ለአገልግሎታቸው የሚጠቀሙባቸውን መሳሪያዎች ሁሉ ይሸከሙ፡፡ በእነዚህ ነገሮች መደረግ ያለበትን ሁሉ፣ እነርሱ ያድርግ፡፡
\s5
\v 27 አሮንና ልጆቹ የጌድሶናውያን ትውልዶች ማገልገል ያለባቸውን አገልግሎት ይምሯቸው፡፡ በሚያጓጉዟቸው ነገሮች ሁሉ፣ በሁሉም አገልግሎቶቻቸው ይምሯቸው፡፡ ያለባቸውን ሀላፊነቶች ሁሉ ትሰጧቸዋላችሁ፡፡
\v 28 ለመገናኛው ድንኳን የጌድሶናዊያን ነገድ ትውልዶች አገልግሎት ይህ ነው፡፡ የካህኑ የአሮን ልጅ ኢታምር በአገልግሎታቸው ይምራቸው፡፡
\s5
\v 29 የሜራሪ ትውልዶችን በነገዳቸው ቁጠራቸው፣ በአባቶቻቸው ቤተሰቦችም እዘዛቸው፣
\v 30 ከሰላሳ አመት እስከ አምሳ አመት ዕድሜ ያላቸውን ቁጠራቸው፡፡ በመገናኛው ድንኳን ለማገልገል የሚመጡትን ሁሉ ቁጠር፡፡
\s5
\v 31 በመገናኛው ድንኳን የሚሰጧቸው አገልግሎቶችና የሥራ ድርሻቸው ይህ ነው፡፡ ቤተ መቅደሱን ለማስጌጥ እንክብካቤ ያድርጉ፣ የድንኳኑን ወርዶችና ቋሚዎች እና ካስማዎች ይሸከማሉ፣
\v 32 በቤተ መቅደሱ ዙሪያ ከሚገኙ ቋሚዎች ጋር፣ ችካሎቻቸውን፣ ካስማዎችን እና ገመዶቻቸውን ከተለያዩ መገልገያዎች ጋር ይሸከማሉ፡፡ መሸከም ያለባቸውን ቁሶች በስም ዘርዝር፡፡
\s5
\v 33 የሜራሪ ነገድ ትውልዶች በካህኑ በአሮን ልጅ በኢታምር መሪነት በመገናኛው ድንኳን የሚሰጡት አገልግሎት ይህ ነው፡፡”
\s5
\v 34 የማህበሩ መሪ የሆኑት ሙሴና አሮን የቀዓታውያንን ትውልዶች በአባቶቻቸው ቤተሰቦች ነገዶች ቁጠሯቸው፡፡
\v 35 ሰላሳ አመት ዕድሜ የሞላቸውንና ከዚያ በላይ እስከ አምሳ አመት ዕድሜ ያላቸውን ቁጠሯቸው፡፡ በመገናኛው ድንኳን ለማገልገል የሚመጡትን ሁሉ ቁጠሯቸው፡፡
\v 36 በየነገዳቸው 2750 ወንዶች ቁጠሩ፡፡
\s5
\v 37 ሙሴና አሮን በመገናኛው ድንኳን የሚያገለግሉ ቀዓታዊያንን ወንዶች ሁሉ በየነገዳቸውና በየቤተሰባቸው ቁጠሩ፡፡ ይህን በማድረግ ያህዌ በሙሴ በኩል እንዲሰሩት ያዘዛቸውን አደረጉ፡፡
\s5
\v 38 የጌድሶናውያን ትውልዶች በየነገዳቸው፣ በየአባቶቻቸው ቤተሰቦች ተቆጠሩ፣
\v 39 ዕድሜያቸው ከሰላሳ እስከ አምሳ አመት የሆኑ በመገናኛው ድንኳን ለማገልገል የመጡ እያንዳንዳቸው ተቆጠሩ፡፡
\v 40 በየነገዳቸው እና በየአባቶቻቸው ቤተሰቦች የተቆጠሩት ወንዶች ቁጥር 2630 ነበሩ፡፡
\s5
\v 41 ሙሴና አሮን በመገናኛው ድኗን የሚያገለግሉትን የጌድሶናውያንን ነገዶች ትውልዶች ቆጠሩ፡፡ ይህን በማድረግ፣ ያህዌ በሙሴ በኩል እንዲሰሩት ያዘዛቸውን አደረጉ፡፡
\s5
\v 42 የሜራሪያውያን ትውልዶች፣ በየነገዳቸውና በየአባቶቻቸው ቤተሰቦች ተቆጠሩ፣
\v 43 ዕድሜያቸው ከሰላሳ እስከ አምሳ የሆኑ በመገናኛው ድንኳን ለማገልገል የመጡ እያንዳንዳቸው ተቆጠሩ፡፡
\v 44 በየነገዳቸው እና በየአባቶቻቸው ቤተሰቦች የተቆጠሩት ወንዶች ቁጥር 3200 ነበሩ፡፡
\s5
\v 45 ሙሴና አሮን በመገናኛው ድንኳን የሚያገለግሉትን የሜራሪ ትወልዶች የሆኑትን እነዚህን ወንዶች ሁሉ ቆጠሩ፡፡ ይህን በማድረግ፣ ያህዌ በሙሴ በኩል እንዲሰሩት ያዘዛቸውን አደረጉ፡፡
\s5
\v 46 ስለዚህም ሙሴ፣ አሮን፣ እና የእስራኤል መሪዎች ሁሉንም ሌዋውያን በየነገዳቸው በየአባቶቻቸው ቤተሰቦች ቆጠሯቸው
\v 47 ከሰላሳ እስከ አምሳ አመት ዕድሜ ያላቸውን ቆጠሯቸው በቤተ መቅደስ ውስጥ ማገልገል የሚችሉትን፣ እና በመገናኛው ድንኳን ውስጥ የሚገኙ ዕቃዎችን መንከባከብና መሸከም የሚችሉትን እያንዳንዳቸውን ቆጠሯቸው፡፡
\v 48 በጠቅላላው 8580 ወንዶች ቆጠሩ፡፡
\s5
\v 49 በያህዌ ትዕዛዝ፣ ሙሴ እያንዳንዱን ወንድ ቆጠረ፣ እያንዳንዱን በተሰጠው የሥራ አይነት መሰረት ቆጠረ፡፡ እያንዳዱን ሰው በሚሸከመው ሀላፊነት አይነት ቆጠረ፡፡ ይህን በማድረግ ያህዌ በሙሴ በኩል ያዘዛቸውን በመስራት ያህዌ ያዘዘውን አደረጉ፡፡
\s5
\c 5
\p
\v 1 ያህዌ ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፣
\v 2 “የእስራኤል ሰዎች ተላላፊ የቆዳ በሽታ ያለበትን ሁሉ፣ በስቃይ የሚመግለውን ሁሉ፣ እና ማንኛውንም በድን በመንካት ረከሰውን ሁሉ ከሰፈር እንዲያስወጡ እዘዛቸው፡፡
\v 3 ወንዶችም ይሁኑ ሴቶች እነዚህን ከሰፈር አስወጣቸው፡፡ እኔ በውስጡ እኖራለሁና ሰፈሩን አያርክሱ፡፡”
\v 4 የእስራኤለ ሰዎችም ይህንኑ አደረጉ፡፡ ያህዌ ሙሴን እንዳዘዘው፣ ከሰፈር አስወጧቸው፡፡ የእስራኤል ሰዎች ያህዌን ታዘዙ፡፡
\s5
\v 5 ያህዌ ሙሴን እንደገና እንዲህ ሲል ተናገረው፣
\v 6 “ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ በላቸው፡፡ አንድ ወንድ ወይም አንዲት ሴት አንዱ በሌላው ላይ በደል ሲፈጽም፣ እና ለእኔ ታማኝ ሳይሆን ሲቀር ያ ሰው በደለኛ ነው፡፡
\v 7 በዚህን ጊዜ በዳዩ ኃጢአቱን ይናዘዝ፡፡ በዳዩ የበደሉን ዋጋ ሙሉ ለሙሉ ይክፈል፣ ደግሞም አንድ አምስተኛውን ጨምሮ ይክፈል፡፡ ይህንን ለበደለው ይስጥ፡፡
\s5
\v 8 ነገር ግን ተበዳዩ ክፍያውን ለመቀበል የቅርብ ዘመድ ባይኖረው፣ በዳዩ የበደሉን ዋጋ ከአውራ በግ ጋር ለራሱ ማስተስረያ በካህኑ በኩል ለእኔ ይክፈል፡፡
\v 9 ከተቀደሱ ነገሮች ሁሉ የሚቀርቡ መስዋዕቶች ሁሉ፣ በእስራኤል ሰዎች ለእኔ የሚለዩ ነገሮች፣ የዚያ ካህን ይሆናሉ፡፡
\v 10 የእያንዳንዱ ሰው የተቀደሱ ነገሮች የካህኑ ይሆናሉ፡፡ አንድ ሰው ለካህኑ የሚሰጣቸው ማናቸውም ነገሮች የዚያ ካህን ይሆናሉ፡፡”
\s5
\v 11 ያህዌ እንደገና ሙሴን ተናገረው፡፡ እንዲህም አለው፣
\v 12 “ለእስራኤል ሰዎች ተናገራቸው፡፡ እንዲህ በላቸው፣ “ምናልባት የአንድ ሰው ሚስት ወደ ሌላ ሰው ሄዳ በባሏ ላይ ኃጢአት ሰርታ ይሆናል፡፡
\s5
\v 13 ከባሏ ሌላ ሰው ከእርሷ ጋር ተኝቶ ይሆናል፡፡ በዚያ ሁኔታ፣ እርሷ ረክሳለች፡፡ ምንም እንኳን ባሏ ነገሩን ባያይም ወይም ስለነገሩ ባያውቅም፣ ደግሞም ድርጊቱን ስትፈጽም ማንም ባይዛትም፣ በእርሷ ላይ የሚያረጋግጥ ማንም ባይኖርም፣
\v 14 የሆነ ሆኖ፣ የቅናት መንፈስ ሚስቱ እንደ ረከሰች ለባልየው ይነግረው ይሆናል፡፡ ሆኖም፣ ሚስቱ ሳትረክስ የቅናት መንፈስ በሀሰት በሰውየው ላይ መጥቶ ይሆናል፡፡
\s5
\v 15 በዚህ ሁኔታ፣ ሰውየው ሚስቱን ወደ ካህኑ ያምጣት፡፡ ባልየው የመጠጥ ቁርባን ለእርሷ ያምጣ፡፡ የኢፍ አንድ አስረኛ የገብስ ዱቄት ያምጣ፡፡ ስለ ቅናት የሚቀርብ የእህል ቁርባን ነውና፣ምንም ዘይት ወይም እጣን አይጨምርበት፤ ምናልባት ተፈጽሞ ሊሆን ለሚችል ኃጢአት ጠቋሚ የእህል ቁርባን ነው፡፡
\s5
\v 16 ካህኑ ያምጣትና በያህዌ ፊት ያቁማት፡፡
\v 17 ካህኑ አንድ ገንቦ ቅዱስ ውሃና ከማደሪያ ድንኳኑ ወለል አፈር ይውሰድ፡፡ አፈሩን ውሃው ውስጥ ይጨምረው፡፡
\s5
\v 18 ካህኑ ሴትየዋን በያህዌ ፊት ያቁማት የሴትየዋን ጸጉርም ይግለጥ፡፡ ካህኑ የቅናት መስዋእት የሆነውን የእህል ቁርባን በእጇ ያስይዛታል፡፡ ካህኑ በሴትየዋ ላይ እርግማን ሊያስከትል የሚችለውን በውስጡ አቧራ ያለበትን መራራ ውሃ በእጆቹ ይያዝ፡፡
\v 19 ካህኑ ሴትየዋን ያስሞላት፤ እንደህም ይበላት፣ “ማንም ሰው ከአንቺ ጋር ተኝቶ ካልሆነ፣ እና ተሳስተሸ ካልሆነ እናም እርኩሰት ካልፈጸምሽ፣ እርግማን ከሚያጣው ከዚህ መራራ ውሃ በእርግጥ ነፃ ትሆኛለሽ፡፡
\s5
\v 20 ነገር ግን፣ አንቺ በባልሽ ስር ያለሽ ሴት፣ ተሳስተሸ ቢሆን፣ ረክሰሽ ቢሆን፣ እና ሌላ ወንድ ከአንቺ ጋር ተኝቶ ቢሆን፣
\v 21 ከዚያ፣ (ካህኑ በእርሷ ላይ ዕርግማን የሚያስከትል መሃላ ያስምላታል፣ ከዚያ በኋላ ሴትየዋን እንዲህ ማለቱን ይቀጥል) ‘ያህዌ ህን ማድረግሽን ለህዝብሽ በመርገምሽ ያሳያል፡፡ ያህዌ ጭንሽን ካሰለለና ሆድሽን ካሳበጠ ይህ ይታወቅ፡፡
\v 22 ዕርግማኑን የሚያጣው ይህ ውሃ ወደ ሆድሽ ይገባል፣ ሆድሽን ያሳብጣል፣ እንዲሁም ጭኖችሽን ያሰልላል፡፡” ሴትየዋ እንዲህ ብላ ትመልስ፣ “አሜን፣ በደለኛ ከሆንኩ ይህ በእኔ ላይ ይሁን፡፡”
\s5
\v 23 ካህኑ እነዚህን ዕርግማኖች በጥቅል ብራና ላይ ይጻፍ፣ ከዚያ የተጻፉትን እርግማኖች በመራራው ውሃ አጥቦ ያስለቅቅ፡፡
\s5
\v 24 ካህኑ ዕርግማን የሚያመጣውን መራራ ውሃ እንድትጠጣ ያድርግ፡፡ ዕርግማኑን የሚያመጣው ውሃ ወደ ውስጧ ገብቶ መራራ ይሆናል፡፡
\v 25 የቅናት መስዋዕቱን የእህል ቁርባን ከሴትየዋ እጅ ይቀበል፡፡ የእህል ቁርባኑን በያህዌ ፊት ወደ መሰዊያው ያምጣው፡፡
\v 26 ካህኑ ከእህል ቁርባኑ እፍኝ ሙሉ ዘግኖ ይውሰድና በመሰዊያው ላይ ያቃጥለው፡፡ ከዚያ ለሴትየዋ መራራውን ውሃ እንድትጠጣው ይስጣት፡፡
\s5
\v 27 ውሃውን እንድትጠጣው ሲሰጣት በባሏ ላይ በደል በመፈፀም ረክሳ ከሆነ፣ ዕርግማን የሚያስከትለው ውሃ ወደ ውስጧ ይገባና መራራ ይሆናል፡፡ ሆዷ ያብጣል ጭኗ ይመነምናል፡፡ ሴትየዋ ከህዝቧ መሃል የተረገመች ትሆናለች፡፡
\v 28 ሴትየዋ የረከሰች ካልሆነችና ንጹህ ከሆነች፣ ነጻ ትሆናለች፡፡ ልጆችን መጸነስ ትችላለች፡፡
\s5
\v 29 የቅናት ህግ ይህ ነው፡፡ ከባሏ ውጭ ለሄደች እና ለረከሰች ሴት ህጉ ይህ ነው፡፡
\v 30 የቅናት መንፈስ ለያዘውና በሚስቱ ለቀና ሰው ህጉ ይህ ነው፡፡ ሴትየዋን በያህዌ ፊት ያምጣ፣ ካህኑም ይህ የቅናት ህግ የሚገልጸውን ሁሉ በእርሷ ላይ ያድርግ፡፡
\s5
\v 31 ሰውየው ሚስቱን ወደ ካህን በማቅረቡ ከበደል ነጻ ይሆናለ፡፡ ሴትየዋ በድላ ከሆነ ማናቸውንም በደል ትሸከማለች፡፡”
\s5
\c 6
\p
\v 1 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
\v 2 “ለእስራኤል ሰዎች ተናገራቸው፡፡ እንዲህ በላቸው፣ ‘አንድ ወንድ ወይም አንዲት ሴት ናዝራዊ ሆኖ ራሱን ለያህዌ በተለየ ስዕለት ሲለይ፣
\v 3 ከወይንና ከሚያሰክር መጠጥ ራሱን ይለይ፡፡ ከወይን ወይም ከሚያሰክር መጠጥ የተሰራ ኮምጣጤ አይጠጣ፡፡ ማናቸውንም የወይን ጭማቂ አይጠጣ ወይም የወይን ፍሬ ወይም ዘቢብ አይብላ፡፡
\v 4 ለእኔ በተለየባቸው ቀናት ሁሉ፣ ከፍሬያቸው ግልፋፊ የተሰራ ማናቸውንም ነገር ጨምሮ ከወይን የተሰራ ምንም ነገር አይብላ፡፡
\s5
\v 5 ለያህዌ ራሱን የለየባቸው ቀናት እስኪያበቁ ድረስ በስለቱ ጊዜያት ሁሉ ራሱን ምላጭ አይንካው፡፡ ለያህዌ የተለየ ይሁን፡፡ ፀጉሩ በራሱ ላይ እንዲያድግ ይተወው፡፡
\s5
\v 6 ራሱን ለያህዌ በለየባቸው ጊዜያት ሁሉ፣ ወደ ሞተ ሰው አይቅረብ፡፡
\v 7 አባቱ፣ እናቱ፣ ወንድሙ ወይም እህቱ ቢሞቱ እንኳን ራሱን ማርከስ የለበትም፡፡ ይህም የሚሆነው ማንም ሰው በረጅም ጠጉሩ እንደሚመለከተው፣ ለእግዚአብሔር የተለየ ነው፡፡
\v 8 በተለየበት ጊዜ ሁሉ ለያህዌ የተለየ ቅዱስ ነው፡፡
\s5
\v 9 አንድ ሰው ድንገት አጠገቡ ቢሞት እና ማንነቱን የለየበትን ፀጉሩን ቢያረክስበት፣ መንጻት ባለበት ከሰባተኛው ቀን በኋላ ራሱን ይላጭ፡፡ ራሱን መላጨት ያለበት በዚያን ጊዜ ነው፡፡
\s5
\v 10 በስምተኛው ቀን ሁለት ርግቦች ወይም ሁለት ዋኖሶች ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ለካህኑ ያቅርብ፡፡
\v 11 ካህኑ አንዱን ወፍ ለኃጢአት መስዋዕት ሌላውን የሚቃተል መስዋዕት አድርጎ ያቅርብ፡፡ ሬሳ አጠገብ በመሆን ኃጢአት ሰርቷልና እነዚህ ለእርሱ ስርየት ይቀርባሉ፡፡ በዚያው ዕለት ራሱን መልሶ ለያህዌ ይስጥ፡፡
\s5
\v 12 ለተለየበት ጊዜ ራሱን ለያህዌ መልሶ ይስጥ፡፡ ለበደል መስዋዕት የአንድ አመት ወንድ ጠቦት ያምጣ፡፡ ራሱን ከማርከሱ በፊት የነበሩ ቀናት አይቆጠሩም፣ ምክንያቱም ለእግዚአብሔር ተለይቶ ባለበት ጊዜ ረክሷል፡፡
\s5
\v 13 ናዝራዊ መለየቱ ስለሚያበቃበት ጊዜ የተሰጠው ህግ ይህ ነው፡፡ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ያምጡት፡፡
\v 14 መስዋዕቱን ለያህዌ ያቅርቡ ነውር የሌለበት የአንድ አመት ወንድ ጠቦት የሚቃጠል መስዋዕት አድርጎ ያቅርብ፡፡ ለህብረት መስዋዕት ነውር የሌለበት አውራ በግ ያምጣ፡፡
\v 15 እንደዚሁም እርሾ ያልገባበት አንድ መሶብ ዳቦ፣ በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት ዳቦዎች፣ በዘይት የተቀባ እርሾ የሌለበት የገብስ ቂጣ፣ ከእህል ቁርባንና ከመጠጥ መስዋዕቶች ጋር ያምጣ፡፡
\s5
\v 16 ካህኑ እነዚህን በያህዌ ፊት ያቅርባቸው፡፡ እርሱ የኃጢአት መስዋዕቱንና የሚቃጠል መስዋዕቱን ያቅርብ፡፡
\v 17 ለያህዌ የህብረት መስዋዕቱን፣ እርሾ ካልገባበት ከመሶቡ ዳቦ ጋር፣ አውራ በጉን መስዋዕት አድርጎ ያቅርብ፡፡ እንዲሁም ካህኑ የእህል ቁርባኑን እና የመጠጥ መስዋዕቱን ጭምር ያቅርብ፡፡
\s5
\v 18 ናዝራዊው ለእግዚአብሔር መለየቱን የሚያሳየውን ፀጉሩን በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ይላጭ፡፡ ፀጉሩን ከራሱ ወስዶ የህብረት መስዋዕቶቹ በሚቀርቡበት በሚነደው እሳት ውስጥ ይጨምረው፡፡
\s5
\v 19 ካህኑ የተቀቀለውን አውራ በግ ወርች፣ ከመሶቡ ውስጥ እርሾ ያልገባበትን አንድ ዳቦ፣ እና አንድ እርሾ ያልገባበት የገብስ ቂጣ ይውሰድ፡፡ ናዝራዊው መለየቱን የሚያሳየውን ጸጉሩን ከተላጨ በኋላ ካህኑ እነዚህን በእጆቹ ያስይዘው፡፡
\v 20 ካህኑ እነዚህን መስዋዕት አድርጎ በያህዌ ፊት ከፍ አድርጎ ያንሳቸውና ለእርሱ ያቅርባቸው፡፡ ይህ ከፍ ተደርጎ ከተነሳው ፍርምባና ከቀረበው ወርች ጋር ለካህኑ ተለየ ቅዱስ ምግብ ነው፡፡ ከዚያ በኋላ ናዝራዊው ወይን ሊጠጣ ይችላል፡፡
\s5
\v 21 ለያህዌ ለመለየት ስዕለቱን ያቀረበ ናዝራዊ ህጉ ይህ ነው፡፡ ማናቸውንም ሌሎች ነገሮች ቢሰጥ በናዝራዊነት ህግ መሠረት እንዲጠብቃቸው የተሰጡትን ቃል ኪዳኖች ለመጠበቅ የገባውን የስዕለት ግዴታዎች መጠበቅ አለበት፡፡”
\s5
\v 22 ያህዌ እንደገና ሙሴን ተናገረው፡፡ እንዲህም አለው፣
\v 23 “ለአሮንና ለልጆቹ እንዲህ በላቸው፣ ‘የእስራኤልን ሰዎች በዚህ መንገድ ባርኳቸው፡፡ እንደዚህ በሏቸው፣
\v 24 “ያህዌ ይባርችሁ ይጠብቃችሁ፡፡
\s5
\v 25 ያህዌ ብርሃኑን በእናንተ ላይ ያብራራ ፊቱን ይመልስላችሁ፣ ይራራላች፡፡
\v 26 ያህዌ በሞገስ ያጥግባችሁ፣ ሰላምንም ይስጣችሁ፡፡’”
\v 27 ለእስራኤል ሕዝብ ስሜን የሚያስተዋውቁት በዚህ መንገድ ነው፡፡ እኔም እባርካቸዋለሁ፡፡”
\s5
\c 7
\p
\v 1 ማደሪያ ድንኳኑን በጨረሰ ቀን፣ ከመገልገያ ዕቃዎቹ ጋር ቀብቶ ለያህዌ ለየው፡፡ በመሰዊያውና በዕቃዎቹ ላይ እንዲሁ አደረገ፡፡ ቀብቶ ለያህዌ ለያቸው፡፡
\v 2 በዚያ ቀን፣ የእስራኤል መሪዎች፣ የአባቶቻቸው ቤተሰቦች አባቶች መስዋዕቶችን አቀረቡ፡፡ ጎሳዎቹን የሚመሩት እነዚህ ሰዎች ነበሩ፡፡ እነዚህ የህዝብ ቀጠራውን ተቆጣጠሩ፡፡
\v 3 መስዋዕቶቻቸውን ያህዌ ፊት አመጡ፡፡ ስድስት የተሸፈኑ ሰረገሎችና አስራ ሁለት በሬዎች አመጡ፡፡ ለየሁለቱ መሪዎች አንድ ሰረገላ አመጡ፣ እያንዳንዱ መሪ አንድ በሬ አመጣ፡፡ እነርሱ እነዚህን ነገሮች በማደሪያው ድንኳን ፊት አቀረቡ፡፡
\s5
\v 4 ከዚያም ያህዌ ሙሴን ተናገረው፡፡ እንዲህም አለው፣
\v 5 “መስዋዕታቸውን ከእነርሱ ተቀበልና ለመገናኛው ድንኳን ሥራ አውላቸው፡፡ ለሥራው እንደሚያስፈልጋቸው ለእያንዳንዱ፣ መስዋዕቶቹን ለሌዋውያን ስጥ፡፡”
\s5
\v 6 ሙሴ ሰረገሎቹንና በሬዎቹን ወስዶ ለሌዋውያኑ ሰጣቸው፡፡
\v 7 ለጌድሶናውያን ተውልዶች ለስራቸው እንደሚያስፈልግ ሁለት ሰረገላዎችና አራት በሬዎች ሰጠ፡፡
\v 8 ለሜራሪ ትውልዶች በካህኑ በአሮን ልጅ በኢታምር በኩል አራት ሰረገሎችንና ስምንት በሬዎችን ሰጠ፡፡ ይህን ያደረገው ሥራቸው ይህን ስለሚጠይቅ ነው፡፡
\s5
\v 9 ለቀዓት ትውዶች ከእነዚህ ነገሮች ምንም አልሰጠም፣ ምክንያቱም የእነርሱ የሥራ ድርሻ የያህዌ የሆኑትን ነገሮች በገዛ ትከሻቸው ከመሸከም ጋር የተያያዘ ነው፡፡
\s5
\v 10 መሪዎቹ ሙሴ መሰዊያውን በቀባ ዕለት ስጦታዎቻቸውን ለመሰዊያው መቀደስ ሰጡ፡፡ መሪዎቹ መስዋዕቶቻቸውን በመሰዊያው ፊት አቀረቡ፡፡
\v 11 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ “እያንዳንዱ መሪ ለመሰዊያው መቀደስ በራሱ ቀን መስዋዕቱን ማቅረብ አለበት፡፡”
\s5
\v 12 በመጀመሪያው ቀን፣ ከይሁዳ ጎሳ የሆነው፣ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን፣ መስዋዕቱነ አቀረበ፡፡
\v 13 መስዋዕቱ ይህ ነበር፣ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን 130 ሰቅሎች የሚመዝን አንድ የብር ሳህን እና ሰባ ሰቅሎች የሚዝን አንድ ጎድጓዳ የብር ሳህን ነበሩ፡፡ እነዚህ ሁለትም ዕቃዎች ለእህል ቁርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፡፡
\v 14 በተጨማሪም በእጣን የተሞላ አስር ሰቅሎች የሚመዝን አንድ የወርቅ ሰሃን ሰጠ፡፡
\s5
\v 15 ለሚቃጠል መስዋዕት አንድ ኮርማ፣ አንድ አውራ በግ፣ እና የአንድ አመት ወንድ ጠቦት በግ ሰጠ፡፡
\v 16 ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ሰጠ፡፡
\v 17 ሁለት በሬዎች፣ አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ወንድ ፍየሎች፣ እና አንድ አመት የሆናቸው አምስት ወንድ የበግ ጠቦቶች፣ ለህብረት መስዋዕት እንዲቀርቡ ሰጠ፡፡ ይህ የአሚናዳብ ልጅ የነአሶን መስዋዕት ነበር፡፡
\s5
\v 18 በሁለተኛው ቀን፣ የይሳኮር መሪ፣ የሶገር ልጅ ናትናኤል፣ መስዋዕቱን አቀረበ፡፡
\v 19 አንድ መቶ ሰላሳ ሰቅሎችን የሚመዝን አንድ ሳህን እና ሰባ ሰቅሎች የሚመዝን አንድ ጎድጓዳ የብር ሰሀን በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ እነዚህ ሁለቱም ዕቃዎች ለእህል ቁርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፡፡
\s5
\v 20 በተጨማሪም በዕጣን የተሞላ አስር ሰቅሎች የሚመዝን አንድ የወርቅ ሰሀን ሰጠ፡፡
\v 21 ለሚቃጠል መስዋዕት አንድ ኮርማ፣ አንድ አውራ በግ እና የአንድ አመት ወንድ በግ ጠቦት ሰጠ፡፡
\v 22 ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ሰጠ፡፡
\v 23 ሁለት በሬዎች አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ወንድ ፍየሎች፣ እና አንድ አመት የሆናቸው አምስት ወንድ በግ ጠቦቶች፣ ለህብረት መስዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ ሰጠ፡፡ ይህ የሶገር ልጅ የናትናኤል መስዋዕት ነበር፡፡
\s5
\v 24 በሶስተኛው ቀን የዛብሎን መሪ፣ የኬሎን ልጅ ኤልያብ፣ መስዋዕቱን አቀረበ፡፡
\v 25 አንድ መቶ ሰላሳ ሰቅሎችን የሚመዝን አንድ ሳህን እና ሰባ ሰቅሎች የሚመዝን አንድ ጎድጓዳ የብር ሰሀን በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ እነዚህ ሁለቱም ዕቃዎች ለእህል ቁርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፡፡
\v 26 በተጨማሪም በዕጣን የተሞላ አስር ሰቅሎች የሚመዝን አንድ የወርቅ ሰሀን ሰጠ፡፡
\s5
\v 27 ለሚቃጠል መስዋዕት አንድ ኮርማ፣ አንድ አውራ በግ እና የአንድ አመት ወንድ በግ ጠቦት ሰጠ፡፡
\v 28 ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ሰጠ፡፡
\v 29 ሁለት በሬዎች አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ወንድ ፍየሎች፣ እና አንድ አመት የሆናቸው አምስት ወንድ በግ ጠቦቶች፣ ለህብረት መስዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ ሰጠ፡፡ ይህ የኬሎን ልጅ የኤልያብ መስዋዕት ነበር፡፡
\s5
\v 30 በአራተኛው ቀን፣ የሮቤል ትውልድ መሪ የሰዲዮር ልጅ ኤሊሱር መስዋዕቱን አቀረበ፡፡
\v 31 መስዋዕቱ ይህ ነበር፣ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን 130 ሰቅሎችን የሚመዝን አንድ ሳህን እና ሰባ ሰቅሎች የሚመዝን አንድ ጎድጓዳ የብር ሰሀን በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ እነዚህ ሁለቱም ዕቃዎች ለእህል ቁርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፡፡
\v 32 በተጨማሪም በዕጣን የተሞላ አስር ሰቅሎች የሚመዝን አንድ የወርቅ ሰሀን ሰጠ፡፡
\s5
\v 33 ለሚቃጠል መስዋዕት አንድ ኮርማ፣ አንድ አውራ በግ እና የአንድ አመት ወንድ በግ ጠቦት ሰጠ፡፡
\v 34 ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ሰጠ፡፡
\v 35 ሁለት በሬዎች አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ወንድ ፍየሎች፣ እና አንድ አመት የሆናቸው አምስት ወንድ በግ ጠቦቶች፣ ለህብረት መስዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ ሰጠ፡፡ ይህ የሰዲዮር ልጅ የአሌሊሱር መስዋዕት ነበር፡፡
\s5
\v 36 በአምስተኛው ቀን፣ የስምዖን ትውልድ መሪ፣ የሱሪሰዳይ ልጅ ስልሚኤል መስዋዕቱን አቀረበ፡፡
\v 37 መስዋዕቱ ይህ ነበር፣ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን 130 ሰቅሎችን የሚመዝን አንድ ሳህን እና ሰባ ሰቅሎች የሚመዝን አንድ ጎድጓዳ የብር ሰሀን በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ እነዚህ ሁለቱም ዕቃዎች ለእህል ቁርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፡፡
\v 38 በተጨማሪም በዕጣን የተሞላ አስር ሰቅሎች የሚመዝን አንድ የወርቅ ሰሀን ሰጠ።
\s5
\v 39 ለሚቃጠል መስዋዕት አንድ ኮርማ፣ አንድ አውራ በግ እና የአንድ አመት ወንድ በግ ጠቦት ሰጠ፡፡
\v 40 ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ሰጠ፡፡
\v 41 ሁለት በሬዎች አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ወንድ ፍየሎች፣ እና አንድ አመት የሆናቸው አምስት ወንድ በግ ጠቦቶች፣ ለህብረት መስዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ ሰጠ፡፡ ይህ የሱሪሰዳይ ልጅ የስልሚኤል መስዋዕት ነበር፡፡
\s5
\v 42 በስድስተኛው ቀን፣ የጋድ ትውልድ መሪ፣ የራጉኤል ልጅ ኤሊሳፍ መስዋዕቱን አቀረበ፡፡
\v 43 መስዋዕቱ ይህ ነበር፣ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን 130 ሰቅሎችን የሚመዝን አንድ ሳህን እና ሰባ ሰቅሎች የሚመዝን አንድ ጎድጓዳ የብር ሰሀን በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ እነዚህ ሁለቱም ዕቃዎች ለእህል ቁርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፡፡
\v 44 በተጨማሪም በዕጣን የተሞላ አስር ሰቅሎች የሚመዝን አንድ የወርቅ ሰሀን ሰጠ፡፡
\s5
\v 45 ለሚቃጠል መስዋዕት አንድ ኮርማ፣ አንድ አውራ በግ እና የአንድ አመት ወንድ በግ ጠቦት ሰጠ፡፡
\v 46 ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ሰጠ፡፡
\v 47 ሁለት በሬዎች አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ወንድ ፍየሎች፣ እና አንድ አመት የሆናቸው አምስት ወንድ በግ ጠቦቶች፣ ለህብረት መስዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ ሰጠ፡፡ ይህ የራጉኤል ልጅ የኤሊሳፍ መስዋዕት ነበር፡፡
\s5
\v 48 በሰባተኛው ቀን፣ የኤፍሬም ትውልድ መሪ፣ የዓመሁድ ልጅ ኤሊሳማ መስዋዕቱን አቀረበ፡፡
\v 49 መስዋዕቱ ይህ ነበር፣ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን 130 ሰቅሎችን የሚመዝን አንድ ሳህን እና ሰባ ሰቅሎች የሚመዝን አንድ ጎድጓዳ የብር ሰሀን በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ እነዚህ ሁለቱም ዕቃዎች ለእህል ቁርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፡፡
\v 50 በተጨማሪም በዕጣን የተሞላ አስር ሰቅሎች የሚመዝን አንድ የወርቅ ሰሀን ሰጠ፡፡
\s5
\v 51 ለሚቃጠል መስዋዕት አንድ ኮርማ፣ አንድ አውራ በግ እና የአንድ አመት ወንድ በግ ጠቦት ሰጠ፡፡
\v 52 ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ሰጠ፡፡
\v 53 ሁለት በሬዎች አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ወንድ ፍየሎች፣ እና አንድ አመት የሆናቸው አምስት ወንድ በግ ጠቦቶች፣ ለህብረት መስዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ ሰጠ፡፡ ይህ የራጉኤል ልጅ የኤሊሳፍ መስዋዕት ነበር፡፡
\s5
\v 54 በስምንተኛው ቀን፣ የምናሴ ትውልድ መሪ፣ የፍደሱር ልጅ ገሚልኤል መስዋዕቱን አቀረበ፡፡
\v 55 መስዋዕቱ ይህ ነበር፣ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን 130 ሰቅሎችን የሚመዝን አንድ ሳህን እና ሰባ ሰቅሎች የሚመዝን አንድ ጎድጓዳ የብር ሰሀን በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ እነዚህ ሁለቱም ዕቃዎች ለእህል ቁርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፡፡
\v 56 በተጨማሪም በዕጣን የተሞላ አስር ሰቅሎች የሚመዝን አንድ የወርቅ ሰሀን ሰጠ፡፡
\s5
\v 57 ለሚቃጠል መስዋዕት አንድ ኮርማ፣ አንድ አውራ በግ እና የአንድ አመት ወንድ በግ ጠቦት ሰጠ፡፡
\v 58 ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ሰጠ፡፡
\v 59 ሁለት በሬዎች አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ወንድ ፍየሎች፣ እና አንድ አመት የሆናቸው አምስት ወንድ በግ ጠቦቶች፣ ለህብረት መስዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ ሰጠ፡፡ ይህ የፍደሱር ልጅ የገማልኤል መስዋዕት ነበር፡፡
\s5
\v 60 በዘጠነኛው ቀን፣ የብንያም ትውልድ መሪ፣ የጋዴዮን ልጅ አቢዳን መስዋዕቱን አቀረበ፡፡
\v 61 መስዋዕቱ ይህ ነበር፣ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን 130 ሰቅሎችን የሚመዝን አንድ ሳህን እና ሰባ ሰቅሎች የሚመዝን አንድ ጎድጓዳ የብር ሰሀን በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ እነዚህ ሁለቱም ዕቃዎች ለእህል ቁርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፡፡
\v 62 በተጨማሪም በዕጣን የተሞላ አስር ሰቅሎች የሚመዝን አንድ የወርቅ ሰሀን ሰጠ፡፡
\s5
\v 63 ለሚቃጠል መስዋዕት አንድ ኮርማ፣ አንድ አውራ በግ እና የአንድ አመት ወንድ በግ ጠቦት ሰጠ፡፡
\v 64 ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ሰጠ፡፡
\v 65 ሁለት በሬዎች አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ወንድ ፍየሎች፣ እና አንድ አመት የሆናቸው አምስት ወንድ በግ ጠቦቶች፣ ለህብረት መስዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ ሰጠ፡፡ ይህ የጋዲዮን ልጅ የአቢዳን. መስዋዕት ነበር፡፡
\s5
\v 66 በአስረኛው ቀን፣ የዳን ትውልድ መሪ፣ የአሚሳይ ልጅ አኪዔዘር መስዋዕቱን አቀረበ፡፡
\v 67 መስዋዕቱ ይህ ነበር፣ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን 130 ሰቅሎችን የሚመዝን አንድ ሳህን እና ሰባ ሰቅሎች የሚመዝን አንድ ጎድጓዳ የብር ሰሀን በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ እነዚህ ሁለቱም ዕቃዎች ለእህል ቁርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፡፡
\v 68 በተጨማሪም በዕጣን የተሞላ አስር ሰቅሎች የሚመዝን አንድ የወርቅ ሰሀን ሰጠ፡፡
\s5
\v 69 ለሚቃጠል መስዋዕት አንድ ኮርማ፣ አንድ አውራ በግ እና የአንድ አመት ወንድ በግ ጠቦት ሰጠ፡፡
\v 70 ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ሰጠ፡፡
\v 71 ሁለት በሬዎች አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ወንድ ፍየሎች፣ እና አንድ አመት የሆናቸው አምስት ወንድ በግ ጠቦቶች፣ ለህብረት መስዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ ሰጠ፡፡ ይህ የፍደሱር ልጅ የገማልኤል መስዋዕት ነበር፡፡
\s5
\v 72 በአስራ አንደኛው ቀን፣ የአሴር ትውልድ መሪ፣ የኤክራን ልጅ ፋግኤል መስዋዕቱን አቀረበ፡፡
\v 73 መስዋዕቱ ይህ ነበር፣ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን 130 ሰቅሎችን የሚመዝን አንድ ሳህን እና ሰባ ሰቅሎች የሚመዝን አንድ ጎድጓዳ የብር ሰሀን በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ እነዚህ ሁለቱም ዕቃዎች ለእህል ቁርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፡፡
\v 74 በተጨማሪም በዕጣን የተሞላ አስር ሰቅሎች የሚመዝን አንድ የወርቅ ሰሀን ሰጠ፡፡
\s5
\v 75 ለሚቃጠል መስዋዕት አንድ ኮርማ፣ አንድ አውራ በግ እና የአንድ አመት ወንድ በግ ጠቦት ሰጠ፡፡
\v 76 ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ሰጠ፡፡
\v 77 ሁለት በሬዎች አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ወንድ ፍየሎች፣ እና አንድ አመት የሆናቸው አምስት ወንድ በግ ጠቦቶች፣ ለህብረት መስዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ ሰጠ፡፡ ይህ የኤክራን ልጅ የፋግኤል መስዋእት ነበር፡፡
\s5
\v 78 በአስራ ሁለተኛው ቀን፣ የንፍታሌም ትውልድ መሪ፣ የዔናን ልጅ ኢኬሬ መስዋዕቱን አቀረበ፡፡
\v 79 መስዋዕቱ ይህ ነበር፣ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን 130 ሰቅሎችን የሚመዝን አንድ ሳህን እና ሰባ ሰቅሎች የሚመዝን አንድ ጎድጓዳ የብር ሰሀን በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ እነዚህ ሁለቱም ዕቃዎች ለእህል ቁርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፡፡
\v 80 በተጨማሪም በዕጣን የተሞላ አስር ሰቅሎች የሚመዝን አንድ የወርቅ ሰሀን ሰጠ፡፡
\s5
\v 81 ለሚቃጠል መስዋዕት አንድ ኮርማ፣ አንድ አውራ በግ እና የአንድ አመት ወንድ በግ ጠቦት ሰጠ፡፡
\v 82 ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ሰጠ፡፡
\v 83 ሁለት በሬዎች አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ወንድ ፍየሎች፣ እና አንድ አመት የሆናቸው አምስት ወንድ በግ ጠቦቶች፣ ለህብረት መስዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ ሰጠ፡፡ ይህ የኤናን ልጅ የኤኪሬ መስዋዕት ነበር፡፡
\s5
\v 84 የእስራኤል መሪዎች ሙሴ መሰዊያውን በቀባበት ቀን እነዚህን ሁሉ ነገሮች አቀረቡ፡፡ አስራ ሁለት የብር ሳህኖች፣ አስራ ሁለት የብር ጎድጓዳ ሳህኖች እና አስራ ሁለት የወርቅ ሰሃኖች አቀረቡ፡፡
\v 85 እያንዳንዱ የብር ሳህን 130 ስቅሎች ሲመዝን እያንዳንዱ ጎድጓዳ ሰሀን ሰባ ሰቅሎች ይመዝናል፡፡ ሁሉም የውሃ መያዣዎች በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን 2400 ሰቅሎች ይመዝናሉ፡፡
\v 86 አስራ ሁለቱ ዕጣን የተሞሉ የወርቅ ሰሃኖች እያንዳንዳቸው በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን አስር ሰቅሎች ይመዝናሉ፡፡ ሁሉም የወርቅ ሳህኖች 120 ሰቅሎች ይመዝናሉ፡፡
\s5
\v 87 ለሚቃጠል መስዋዕት አስራ ሁለት በሬዎች፣ አስራ ሁለት አውራ በጎች፣ እና አስራ ሁለት የአንድ አመት ጠቦቶች አቀረቡ፡፡ የእህል ቁርባናቸውን ሰጡ፡፡ ለኃጢአት መስዋዕት አስራ ሁለት ወንድ ፍየሎች ሰጡ፡፡
\v 88 ከብቶቻቸው ሁሉ፣ ሀያ አራት በሬዎች፣ ስልሳ አውራ በጎች፣ ስልሳ ወንድ ፍየሎች እና አንድ አመት የሆናቸው ስልሳ ወንድ ጠቦት በጎች የህብረት መስዋዕት አድርገው አቀረቡ፡፡ እነዚህ ሁሉ መሰዊያውን ለመቀደስ በሚቀባበት ጊዜ የቀረቡ ስጦታዎች ናቸው፡፡
\s5
\v 89 ሙሴ ከያህዌ ጋር ለመነጋገር ወደ መገናኛው ድንኳን በገባ ጊዜ፣ ከእርሱ ጋር ሲነጋገር ድምጹን ሰማ፡፡ ያህዌ ከማስተሰርያ መክደኛ በላይ ሆኖ በቃል ኪዳን ታቦቱ ላይ፣ በሁለቱ ኪሩቤል መካከል ለእርሱ ተናገረ፡፡
\s5
\c 8
\p
\v 1 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
\v 2 “አሮንን እንዲህ በለው፣ ‘ሰባቱ መብራቶች በምትለኩሳቸው ጊዜ በመቅረዙ ፊት ለፊት ብርሃን ይስጡ፡፡’”
\s5
\v 3 አሮን ይህን አደረገ፡፡ ያህዌ ሙሴን እንዳዘዘው፣ ከመቅረዙ ፊት ለፊት ብርሃን እንዲሰጡ መብራቶቹን በመቅረዙ ላይ ለኮሳቸው፡፡
\v 4 መቅረዙ የተሰራው በዚህ መንገድ ነበር፡፡ ያህዌ አሰራሩን ለሙሴ አሳይቶት ነበር፡፡ ከመሰረቱ እስከ ጫፍ በአበባ መልክ የዋንጫ መልክ ቅርጽ አስይዘህ ወርቁን ቀጥቅጠህ አብጀው፡፡
\s5
\v 5 እንደገና፣ ያህዌ ሙሴን እንዲሀ ሲል ተናገረው፣
\v 6 “ከእስራኤል ሰዎች መሃል ሌዋውያንን ወስደህ አንጻቸው፡፡
\s5
\v 7 እነርሱን ለማንጻት ይህን አድርግ፣ የማንጻት ውሃ እርጫቸው፡፡ ፀጉራቸው በሙሉ እንዲላጩ፣ ልብሶቻቸውን እንዲያጥቡ፣ እና በዚህ መንገድ ራሳቸውን እንዲያነጹ አድርግ፡፡
\v 8 ከዚያ ጥጃና በዘይት የተለወሰ የመልካም ዱቄት የእህል ቁርባን ይውሰዱ፡፡ ሌላ ጥጃ ለኃጢአት መስዋዕት ያዘጋጁ፡፡
\s5
\v 9 ሌዋውያኑን ወደ መገናኛው ድንኳን ፊት ለፊት አቅርባቸውና መላውን የእስራኤል ማህበረሰብ ሰብስብ፡፡
\v 10 በእኔ በያህዌ ፊት ሌዋውያንን አቅርብ፡፡ የእስራኤል ሰዎች እጃቸውን በሌዋውያን ላይ ይጫኑ፡፡
\v 11 አሮን ሌዋውያኑን በእኔ ፊት ያቅርባቸው፣ የእስራኤልን ህዝብ ወክለው በእርሱ ፊት ከፍ አድርገው እንደሚያቀርቡ አቅርባቸው፡፡ ሌዋውያን እኔን እንደሚያገለግሉ እርሱ ይህን ያድርግ፡፡
\s5
\v 12 ሌዋውያኑ በበሬዎቹ ላይ እጃቸውን ይጫኑ፡፡ ሌዋውያኑን ለማስተሰርይ፣ ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ኮርማ አቅርቡ፣ ደግሞም ሌላውን ኮርማ የሚቃጠል መስዋዕት አድርገህ ለእኔ አቅርብ፡፡
\v 13 ሌዋውያኑን በአሮንና በልጆቹ ፊት አቁማቸው፣ እናም እንደ ሚወዘወዝ መሥዋዕት ለእኔ ከፍ አድርገህ አቅርባቸው፡፡
\s5
\v 14 በዚህ መንገድ ሌዋውያኑን ከእስራኤል ሰዎች መሃል ለያቸው፡፡ ሌዋውያን ለእኔ ይለዩ፡፡
\v 15 ከዚያ በኋላ ሌዋውያኑ ወደ መገናኛው ድንኳን ለአገልግሎት ይግቡ፡፡ እነርሱን አንጻቸው፡፡ እንደ ስጦታ ለእኔ ከፍ አድርገህ አንሳቸው፡፡
\s5
\v 16 ከእስራኤል ህዝብ መሀል እነርሱ ሙሉ ለሙሉ የእኔ ናቸውና ይህን አድርግ፡፡ ከእስራኤል ወገን በኩር ሁሉ፣ ማህጸን ከከፈተው ከእያንዳንዱ ወንድ ልጅ ቦታውን ይወስዳሉ፡፡ እኔ ሌዋውያንን ለራሴ ለይቻለሁ፡፡
\v 17 ከሰውም ሆነ ከእንስሳው የእስራኤል ህዝብ በኩሩ ሁሉ የእኔ ነው፡፡ በግብፅ ምድር የበኩሩን ህይወት ሁሉ በወሰድኩ ቀን፣ እኔ እናንተን ለራሴ ለየኋችሁ፡፡
\s5
\v 18 በበኩሩ ሁሉ ምትክ፣ ከእስራኤል ሰዎች መሀል ሌዋውያንን ወሰድኩ፡፡
\v 19 ሌዋውያንን ለአሮንና ለልጆቹ እንደ ስጦታ ሰጠኋቸው፡፡ በመገናኛው ድንኳን የእስራኤልን ሰዎች ሥራ ይስሩ ዘንድ ከእስራኤል ሰዎች መሃል ወሰድኳቸው፡፡ ወደተቀደሰው ስፍራ ሲቀርብ ምንም ጥፋት እንዳይደርስባቸው ለእስራኤል ሰዎች እንዲያስተሰርዩ እነርሱን ሰጠኋቸው፡፡”
\s5
\v 20 ሙሴ፣ አሮንና መላው የእስራኤል ህዝብ ይህንን ከሌዋውያን ጋር አደረጉ፡፡ ሌዋውያንን በሚመለከት ያህዌ ሙሴን ያዘዘውን ነገር ሁሉ አደረጉ፡፡ የእስራኤል ሰዎች ከእነርሱ ጋር ይህን አደረጉ፡፡
\v 21 ሌዋውያን ልብሶቻቸውን በማጠብ ራሳቸውን ከኃጢአት አነጹ፡፡ አሮን ለያህዌ ስጦታ አድርጎ አቀረባቸው፤ ደግም ይነጹ ዘንድ የንስሃ ማስተስረያ አደረገላቸው፡፡
\s5
\v 22 ከዚያ በኋላ፣ ሌዋውያኑ በአሮንና በአሮን ልጆች ፊት አገልግሎታቸውን ይሰጡ ዘንድ ወደ መገናኛው ድንኳን ገቡ፡፡ ይህም ያህዌ ስለ ሌዋውያን ሙሴን ባዘዘው መሠረት ነበር፡፡ ሌዋውያንን በሙሉ በዚህ መንገድ ተቀበሉ፡፡
\s5
\v 23 ያህዌ እንደገና ለሙሴ ተናገረ፡፡ እንዲህም አለ፣
\v 24 “ይህ ሁሉ፤ ሃያ አምስት አመት እና ከዚያ በላይ ዕድሜ ላላቸው ሌዋውያን ነው፡፡ በመገናኛው ድንኳን ለማገልገል መምጣት አለባቸው፡፡
\s5
\v 25 አምሳ አመት ሲሞላቸው በዚህ መንገድ ማገልገላቸውን ያቁሙ፡፡ በዚያ ዕድሜ መደበኛ አገልግሎታቸውን ያቁሙ፡፡
\v 26 በመገናኛው ድንኳን የሚያገለግሉ ወንድሞቻቸውን ሊያግዙ ይችላሉ፣ ነገር ግን ዕድሜያቸው አምሳ ከሆነ በኋላ በዚህ መንገድ አያገለግሉ፡፡ ለሌዋውያን በእነዚህ ጉዳዮች ሁሉ መመሪያ ልትሰጣቸው ይገባል፡፡
\s5
\c 9
\p
\v 1 ከግብጽ ምድር ከወጡ በኋላ በሁለተኛው አመት በመጀመሪያው ወር፣ በሲና ምድረ በዳ ያህዌ ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፣
\v 2 “የእስራኤል ሰዎች በተወሰነው የአመቱ ወቅት ፋሲካን ያድርጉ፡፡
\v 3 በዚህ ወር በእስራ አራተኛው ቀን፣ ምሽት ላይ፣ በተወሰነው በአመቱ ወቅት ፋሲካን አድርጉ፡፡ ፋሲካን አድርጉ፣ ደንቦቹን ጠብቁ፣ ከዚህ ጋር የተያያዙ ደንቦችን ሁሉ ታዘዙ፡፡”
\s5
\v 4 ስለዚህ፣ ሙሴ የፋሲካን በዓል እንዲያከብሩ ለእስራኤል ሰዎች ሁሉ ነገራቸው፡፡
\v 5 ስለዚህ በመጀመሪያው ወር በወሩ በአስራ አራተኛው ቀን፣ ምሽት ላይ፣ በሲና ምድረ በዳ ፋሲካን አከበሩ፡፡ የእስራኤል ሰዎች ያህዌ ለሙሴ እንዲያደርግ ያዘዘውን ሁሉ አደረጉ፡፡
\s5
\v 6 በሞተ ሰው በድን የረከሱ አንዳንድ ሰዎች ነበሩ፡፡ እነርሱ በዕለቱ ፋሲካን አላከበሩም፡፡ በዚያ ቀን እነዚህ ሰዎች ሙሴና አሮን ፊት ቀረቡ፡፡
\v 7 እነዚያ ሰዎች ሙሴን እንዲህ አሉት፣ “እኛ በሰው በድን አካል ምክንያት ንጹህ አይደለንም፡፡ ሆኖም በእስራኤል ሰዎች መሃል በተወሰነው የአመቱ ወቅት ለያህዌ መስዋዕት ከማቅረብ ለምን ትከለክለናለህ”
\v 8 ሙሴ እንዲህ አላቸው፣ “ያህዌ ስለ እናንተ ምን ትዕዛዝ እንደሚሰጥ እስከምሰማ ጠብቁኝ፡፡”
\s5
\v 9 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
\v 10 ”ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ በላቸው፣ ‘ከእናንተ ማናችሁም ወይም ከትውልዳችሁ ማንም በበድን አካል ምክንያት እርኩስ ቢሆን፣ ወይም ሩቅ መንገድ ሄዶ ቢሆን፣ ለያህዌ ፋሲካን ማክበር ይችላል፡፡’
\s5
\v 11 እነርሱ በሁለተኛው ወር በአስራ አራተኛው ቀን ፋሲካን ያክብሩ፡፡ እነርሱ ፋሲካን እርሾ ባስገባበት እንጀራ ከመራራ ቅጠል ጋር ይብሉ፡፡
\v 12 እስከ ማለዳ አንዳች አያስተርፉለት፣ አሊያም ከእንስሳቱ አጥንት አይስበሩ፡፡ የፋሲካን ህግጋት ሁሉ ይጠብቁ፡፡
\s5
\v 13 ነገር ግን ማናቸውም ንጹህ የሆነና ሩቅ መንገድ ያልሄደ ሰው፣ ነገር ግን ፋሲካን ሳያከብር የቀረ ሰው፣ ከህዝቡ ተለይቶ ይጥፋ፤ ምክንያቱም እርሱ በተወሰነው የአመቱ ወቅት የሚቀርበውን ያህዌ የሚጠይቀውን መስዋዕት አላቀረበም፡፡ ያሰው ኃጢአቱን ይሸከም፡፡
\v 14 እንግዳ በመሀላችሁ ቢኖርና ፋሲካን ለያህዌ ክብር ቢያብር፣ ፋሲካን መጠበቅና እርሱ ያዘዘውን ሁሉ ማድረግ አለበት፣ የፋሲካን ህግጋት ሁሉ መጠበቅ እንዲሁም የፋሲካን ህግነት መጠበቅ አለበት፡፡ ለመጻተኞች እና በምድሪቱ ለተወለዱ ሁሉ ተመሳሳይ ህግ ይኑርህ፡፡”
\s5
\v 15 የማደሪያው ድንኳን በተተከለበት ቀን፣ ደመና የማደሪያውን ድንኳን ፣ የቃል ኪዳኑን ምስክር ድንኳን ሸፈነው፡፡ በምሽት ደመናው በማደሪያ ድንኳኑ ላይ ነበር፡፡ እስከ ንጋት እሳት ይመስል ነበር፡፡
\v 16 በዚያ መልክ ቀጠለ፡፡ ደመናው የማደሪያ ድንኳኑን ሸፍኖ በምሽት እሳት ይመስል ነበር፡፡
\v 17 ደመናው ከድንኳኑ ላይ በተወሰደ ጊዜ ሁሉ፣ የእስራኤል ሰዎች ከመጓዝ ያቋርጡ ነበር፡፡ ደመናው በቆመ ጊዜ ሁሉ፣ ህዝቡ አንድ ቦታ ይሰፍራል፡፡
\s5
\v 18 የእስራኤል ሰዎች በያህዌ ትዕዛዝ ይጓዛሉ፣ በእርሱም ትእዛዝ በሰፈራቸው ይቆያሉ፡፡ ደመናው በማደሪያው ድንኳን ላይ ሲቆም፣ በሰፈራቸው ይቆያሉ፡፡
\v 19 ደመናው በማደሪያው ድንኳን ለብዙ ቀናት ሲቆይ፣ የእስራኤል ሰዎች የያህዌን ትዕዛዝ ተከትለው መጓዝ ያቆማሉ፡፡
\s5
\v 20 አንዳንድ ጊዜ ደመናው በማደሪያው ድንኳን ላይ ለጥቂት ቀናት ይቆያል፡፡ በዚህ ሁኔታ የያዌን ትእዛዝ ተከትለው በአንድ ቦታ ይሰፍራሉ፣ ከዚያ በእርሱ ትእዛዝ እንደገና ይጓዛሉ፡፡
\v 21 አንዳንድ ጊዜ ደመናው ከምሽት እስከ ማለዳ በሰፈር ይገኛል፡፡ ማለዳ ደመናው ሲነሳ፣ እነርሱ ይጓዛሉ፡፡ ቀንም ይሁን ሌሊት ጉዟቸውን የሚቀጥሉት ደመናው ከተነሳ ብቻ ነው፡፡
\s5
\v 22 ደመናው በማደሪያ ድንኳኑ ላይ ለሁለት ቀናት፣ ለወር ወይም ለአመት ቢቆይ በዚያ ስፍራ እስከ ቆየ ድረስ የእስራኤል ሰዎች በሰፈሮቻቸው ይቆያሉ አይጓዙም፡፡ ነገር ግን ደመናው ሲንቀሳቀስ እነርሱም ጉዟቸውን ይቀጥላሉ፡፡
\v 23 በያህዌ ትዕዛዝ ይሰፍራሉ፣ በእርሱ ትዕዛዝ ይጓዛሉ በሙሴ በኩል የተሰጣቸውን የያህዌን ትዕዛዝ ይፈጽማሉ፡፡
\s5
\c 10
\p
\v 1 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
\v 2 ”ሁለት የብር መለከቶች አብጁ፡፡ በብር ቀጥቅጠህ አብጃቸው፡፡ መለከቶቹን ማህበረሰቡን በጋራ ለመጥራትና ከመንደሮቸው እንዲንቀሳቀሱ ጥሪ ለማሰማት ተጠቀምባቸው፡፡
\s5
\v 3 ካህናቱ ማህበረሰቡን በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ በፊትህ ለመሰብሰብ መለኮቶቹን ይንፉ፡፡
\v 4 ካህናቱ አንድ መለከት ብቻ ከነፉ፣ የእስራኤል ነገድ መሪዎች ይሰበስቡ፡፡
\v 5 ከፍ ባለ ድምጽ ስትነፉ፣ በስተምስራቅ የሰፈሩት ጉዟቸውን ይጀምሩ፡፡
\s5
\v 6 ለሁለተኛ ጊዜ ከፍ ባለ ድምጽ ስትነፋ በደቡብ በኩል የሰፈሩት ጉዟቸውን ይጀምሩ፡፡ ለጉዟቸው ከፍ ያለ የመለከት ድምጽ ያሰሙ፡፡
\v 7 ማህበረሰቡ በአንድነት ሲበሰበሰብ፣ መለከቶች ይነፉ ነገር ግን ድምጹ ከፍ አይበል፡፡
\v 8 የካህኑ የአዘሮን ልጆች፣ መለኮቶቹን ይንፉ፡፡ በትውልዶቻችሁ ሁሉ ዘንድ ይህ ለእናንተ ሁልጊዜም ስርዓት ይሆናል፡፡
\s5
\v 9 በሚወሯችሁ ተቃዋሚዎቻች ላይ በምድራች ለጦርነት ስትወጡ፣ ለማንቂያ የመለከት ድምጽ ታሰማላችሁ፡፡ እኔ፣ አምላካችሁ ያህዌ፣ አስባችኋለሁ ደግሞም ከጠላቶቻችሁ አድናችኋለሁ፡፡
\s5
\v 10 እንደዚሁም፣ በመደበኛ ባዕላቶቻችሁም ሆነ በወራቶች መጀመሪያ ላይ በክብረ በዓል ወቅት ለሚቃጠል መስዋዕቶቻችሁ ክብርና በህብረት መስዋዕቶቻችሁ መስዋዕቶች ላይ መለኮቶችን መንፋት አለባች፡፡ እነዚህ እናንተ የእኔ የአምላካችሁ ለመሆናችሁ መታሰቢያ ሆነው ያገለግላሉ፡፡ እኔ አምላካችሁ ያህዌ ነኝ፡፡”
\s5
\v 11 በሁለተኛው አመት፣ በሁለተኛው ወር፣ በወሩ ሀያኛ ቀን ደመናው ከቃል ኪዳኑ ምስክር ማደሪያ ላይ ተነሳ፡፡
\v 12 የእስራኤል ሰዎች ከሲና ምድረበዳ ተነስተው ጉዟቸውን ቀጠሉ፡፡ ደመናው በፋራን ምድረ በዳ ውስጥ ቆመ፡፡
\v 13 የመጀመሪያ ጉዟቸው፣ በሙሴ በኩል የተሰጣቸውን የያህዌን ትዕዛዝ ተከትለው አደረጉ፡፡
\s5
\v 14 በይሁዳ ትውልዶች ዓርማ ስር ያለው ሰፋሪዎች በመጀመሪያ ተንቀሳቀሱ፡፡ የይሁዳን ሠራዊት የሚመራው የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን ነበር፡፡
\v 15 የይሳኮርን ትውልዶች ሰራዊት የሚመራው የሶገር ልጅ ናትናኤል ነበር፡፡
\v 16 የዛብሎንን ትውልዶች ሰራዊት የሚመራው የኬሎን ልጅ ኤልያብ ነበር፡፡
\s5
\v 17 የማደሪያ ድንኳኑን የተሸከሙት የጌድሶን እና የሜራሪ ትውልዶች፣ ማደሪያ ድንኳኑን ነቅለው ጉዟቸውን ጀመሩ፡፡
\v 18 ቀጥሎ፣ በሮቤል ሰፈር ሰራዊት ዓርማ ስር የነበሩት ጉዟቸውን ቀጠሉ፡፡ የሮቤልን ሰራዊት የሚመራው የሶዲዮር ልጅ ኤሊሱር ነበር፡፡
\v 19 የስምዖንን ትውልዶች ሰራዊት የሚመራዊ የሱሪስዓይ ልጅ ስለሚኤል ነበር፡፡
\v 20 የጋድን ትውልዶች ሰራዊት የሚመራው የራጉኤል ልጅ ኤሊሳፍ ነበር፡፡
\s5
\v 21 ቀዓታውያን ተነሱ፡፡ እነርሱ የቅድስተ ቅዱሳኑን ቅዱስ ዕቃዎች ተሸከሙ፡፡ ቀዓታውያን ቀጣዩ ሰፈር ከመድረሳቸው አስቀድሞ ሌሎች ማደሪያ ድንኳን ይተክላሉ፡፡
\v 22 የኤፍሬምን ሰራዊት የሚመራው የዓሚሁድ ልጅ ኤሊሳማ ነበር፡፡
\v 23 የምናሴን ትውልዶች ሰራዊት የሚመራው የፍዳሱር ልጅ ገማልኤል ነበር፡፡
\v 24 የብንያምን ትውልዶች ሠራዊት የሚመራው የጋዴዮን ልጅ አቢዳን ነበር፡፡
\s5
\v 25 በዳን ትውልዶች ዓርማ ስር የሰፈሩት ሠራዊቶች በመጨረሻ ይወጣሉ፡፡ የዳንን ሰራዊት የሚመራው የአሚሳዳይ ልጅ አኪዔዘር ነበር፡፡
\v 26 የአቤርን ትውልዶች ሰራዊት የሚመራው የኤክራን ልጅ ፋግኤል ነበር፡፡
\v 27 የንፍታሌምን ትውልዶች ሰራዊት የሚመራው የዔናን ልጅ አኪሬ ነበር፡፡
\v 28 የእስራኤል ሰዎች ሰራዊቶች ጉዟቸውን ያደረጉት በዚህ መልክ ነው፡፡
\s5
\v 29 ሙሴ ከምድያማዊው የራጉኤል ልጅ ከአባብ ጋር ተነጋገረ፡፡ ራጉኤል የሙሴ ሚስት አባት ነበር፡፡ ሙሴ ከአባብ ጋር ተነጋገረ እንዲህም አለ፣ “ያህዌ እሰጣችኋለሁ ወዳለን ስፍራ እየተጓዝን ነው፡፡ ያህዌ እንዲህ ብሎን ነበር፣ ‘እኔ ለእናንተ የተናገርኩትን እርሷኑ ስፍራ እሰጣችኋለሁ፡፡’ አንተ ከእኛ ጋር አብረኸን ና እኛም መልካም እናደርግልሃለን፡፡ ያህዌ ለእስራኤል መልካም ለማድረግ ቃል ገብቷል፡፡”
\v 30 አባብ ግን ሙሴን እንዲህ አለው፣ “እኔ ከአንተ ጋር አልሄድም፡፡ እኔ ወደ ገዛ ምድሬና ወደ ራሴ ህዝብ እሄዳለሁ፡፡”
\s5
\v 31 ከዚያም ሙሴ እንዲህ ሲል መለሰ፣ “እባክህን ከእኛ አትለይ፡፡ በበረሃ እንዴት መስፈር እንደሚቻል ታውቃለህ፡፡ ስንሰፍር ልትመለከተን ይገባል፡፡
\v 32 ከእኛ ጋር ብትሄድ፣ ያህዌ ለእኛ የሚያደርግልንን በጎነት ያንኑ እኛም ለአንተ እናደርግልሃለን፡፡”
\s5
\v 33 ከያህዌ ተራራ ተነስተው ለሶስት ቀናት ተጓዙ፡፡ የያህዌ የቃልዳኑ ታቦት የሚያርፍበትን ስፍራ እንዲያገኙ ለመፈለግ ለሶስት ቀናት በፊታቸው ተጓዘ፡፡
\v 34 ሲጓዙ የያህዌ ደመና በቀን ብርሃን በላያቸው ነበር፡፡
\s5
\v 35 ታቦቱ በተነሳበት ጊዜ ሁሉ፣ ሙሴ እንዲህ ይላል፣ “ያህዌ ሆይ፣ ተነስ፡፡ ጠላቶችህን በትን፡፡ የሚጠሉህ ከአንተ እንዲሸሹ አድርግ፡፡”
\v 36 ታቦቱ በቆመ ጊዜ ሁሉ፣ ሙሴ “ያህዌ ሆይ፣ ብዙ አስር ሺህ ወደሚሆኑት እስራኤላውያን ተመለስ” ይል ነበር፡፡
\s5
\c 11
\p
\v 1 ህዝቡ ያህዌ እየሰማ ስለ ችግሮቻቸው አጉረመረሙ፡፡ ያህዌ ህዝቡን ሰምቶ ተቆጣ፡፡ ከያህዌ ዘንድ እሳት መጥታ በሰፈሩ ዙሪየ ከነበሩ ሰዎች አንዳንዶችን በላች፡፡
\v 2 ከዚያም ህዝቡ ወደ ሙሴ ጮኸ፣ ስለዚህም ሙሴ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ እሳቱም ቆመ፡፡
\v 3 ስፍራው ተቤራ ተብሎ ተጠራ፣ ምክንያቱም የያህዌ እሳት ከመሀላቸው ሰዎችን አቃጥላለች፡፡
\s5
\v 4 አንዳንድ ባዕዳን ከእስራኤላውያን ትውልዶች ጋር መስፈር ጀመሩ፡፡ እነርሱ የተሻለ ምግብ መብላት ፈለጉ፡፡ ከዚያ የእስራኤል ሰዎች ማልቀስና “እንድንበላ ማን ስጋ ሊሰጠን ይችላል” ማለት ጀመሩ፡፡
\v 5 በግብጽ በነጻ እንበላ የነበረውን አሳውን፣ ዱባውን፣ በጢኹን፣ ባሮ ሽንኩርቱን፣ ቀይ ሽንኩርቱንና ነጭ ሽንኩርቱን እናስታውሳለን፡፡
\v 6 አሁን ደካሞች ነን፡፡ ከመና በስተቀር ምንም የምንበላው የለም፡፡”
\s5
\v 7 መና እንደ ድንብላል ፍሬ ያለ መልክ ነበረው፡፡ ሙጫ ይመስላል፡፡
\v 8 ሰዎቹ እየተዘዋወሩ ይሰበስቡታል፡፡ በወፍጮ ይፈጩታል፣ በሙጫ ያደቁታል፣ በገንቦዎቹ ይቀቅሉታል፣ ቂጣ አድርገውም ይጋግሩታል፡፡ እንደ ንጹህ የወይራ ዘይት ይጣፍጣል፡፡
\s5
\v 9 ምሽት በሰፈር ውስጥ ጤዛ ሲወርድ፣ መናውም ይወርዳል፡፡
\v 10 ሙሴ ህዝቡ በየቤቱ ሲያለቅስ አዳመጠ፣ ደግሞም እያንዳንዱ ሰው በእርሱ ድንኳን ደጃፍ ነበር፡፡ ያህዌ በጣም ተቆጥቶ ነበር፣ ደግም የእነርሱ ማጉረምረም በሙሴ እይታ ስህተት ነበር፡፡
\s5
\v 11 ሙሴ ወደ ያህዌ እንዲህ ሲል ጮኸ፣ “ለምን ባሪያህን እንዲህ አስጨነከው? ስለምን በእኔ ደስ አልተሰኘህም? የዚህን ህዝብ ሁሉ ሸክም እንድሸከም አደረግከኝ፡፡
\v 12 እኔ ይህን ህዝብ ሁሉ ፀንሼዋለሁን? ‘አባት ልጁን እነደሚያቅፍ ይህን ህዝብ ወደ ደረትህ አስጠግተህ ተሸከመው’ ትለኝ ዘንድ እኔ ወልጃቸዋለሁን? ትሰጣቸው ዘንድ ለአባቶቻቸው ወደ ማልክላቸው ምድር እንዲገቡ እኔ ልሸከማቸውን?
\s5
\v 13 ለእነዚህ ሁሉ ሰዎች የምሰጣቸውን ስጋ ከየት አገኛለሁ? በእኔ ፊት እያለቀሱ እንዲህ ይላሉ ‘የምንበላው ስጋ ስጠን፡፡’
\v 14 እኔ ብቻዬን ይህን ሁሉ ህዝብ ልሸከም አልችልም፡፡ እጅግ በዝተውብኛል፡፡
\v 15 እንዲህ እስካደረግኸኝ ድረስ፣ አሁኑኑ ግደለኝ፣ ለእኔ መልካም ከሆንክ፣ መከራዬን ከእኔ አርቅ፡፡”
\s5
\v 16 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ “ከእስራኤል መሪዎች ሰባዎቹን ወደ እኔ አምጣ፡፡ የህዝቡ መሪዎችና አለቃዎች መሆናቸውን እርግጠኛ ሁን፡፡ ከአንተ ጋር እንዲቆሙ ወደ መገናኛው ድንኳን አምጣው፡፡
\v 17 እኔ ወርጄ በዚያ ከአንተ ጋር እነጋገራለሁ፡፡ ከአንተ ላይ ካለው መንፈስ ጥቂት ወስጄ በእነርሱ ላይ አደርገዋለሁ፡፡ እነርሱ ከአንተ ጋር የህዝቡን ሸክም ይሸከማሉ፡፡ አንተ ብቻህን ሸክሙን አትሸከምም፡፡
\s5
\v 18 ለህዝቡ እንዲህ በል፣ ‘ነገ ራሳችሁን ለያህዌ ለዩ፡፡ ያህዌ እየሰማ አልቅሳችኋልና፣ በእርግጥ ስጋ ትበላላች፡፡ እንዲህ ብላችኋል፣ “እንበላ ዘንድ ማን ስጋ ይሰጠናል? ለእኛስ በግብጽ መሆን መልካም ነበር፡፡” ስለዚህ ያህዌ ስጋ ይሰጣችኋል፣ እናም ስጋ ትበላላችሁ፡፡
\v 19 ስጋ የመትበሉት ለአንድ ቀን፣ ለሁለት ቀናት፣ ለአምስት ቀናት፣ ለአስር ቀናት ወይም ለሃያ ቀናት አይደለም፣
\v 20 ነገር ግን በአፍንጫችሁ እስኪወጣ ድረስ ወር ሙሉ ስጋ ትበላላችሁ፡፡ ነገሩ ያስጸይፋችኋል፣ ምንያቱም በመሀላችሁ ያለውን ያህዌ እምቢ ብላችኋል፡፡ በፊቱ አልቅሳችኋል፡፡ እንዲህ ብላችኋል፣ “ለምን ከግብጽ ወጣን?”
\s5
\v 21 ከዚያ ሙሴ እንዲህ አለ፣ “እኔ ከ600000 ሰዎች ጋር ነኝ፣ አንተ ግን እንዲህ አልክ፣ ‘ወር ሙሉ እንዲበሉ ስጋ አበላቸዋለሁ፡፡’
\v 22 እነርሱን ለማጥገብ እኛ እንስሳትንና የከብት መንጋ ሁሉ እናርዳለን? እነርሱን ለማርካት የባህር አሶችን ሁሉ እናጠምዳን? ”
\v 23 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ “እጄ አጭር ናትን? አሁን ቃሌ እውነት መሆን አለመሆኑን ታያለህ፡፡”
\s5
\v 24 ሙሴ ወጥቶ ለህዝቡ የያህዌን ቃላት ነገራቸው፡፡ ሰባዎቹን የህዝብ መሪዎች ሰበሰበና በድንኳኑ ዙሪያ አቆማቸው፡፡
\v 25 ያህዌ በደመና ውስጥ ወረዳና ሙሴን ተናገረው፡፡ ያህዌ በሙሴ ላይ ከነበረው መንፈስ ጥቂት ወሰደና በሰባዎቹ ሽማግሌዎች ላይ አደረገው፡፡ መንፈሱ ሲያርፍባቸው፣ ትንቢት ተናገሩ፣ ነገር ግን በዚያ ወቅት እንጂ በሌላ ጊዜ ደግመው አልተነበዩም፡፡
\s5
\v 26 አልዳድና ሞድ የተባሉ ሁለት ሰዎች በሰፈር ቀርተው ነበር፡፡ መንፈሱ በእነርሱ ላይም አረፈ፡፡ ስሞቻቸው በመዝገብ ተጽፎ ነበር፣ ነገር ግን ወደ ድንኳኑ አልሄዱም ነበር፡፡ ሆኖም ግን፣ እነርሱም በሰፈር እያሉ ተነበዩ፡፡
\v 27 በሰፈር የነበረ አንድ ወጣት ሰው ወደ ሙሴ ሮጦ መጥቶ እንዲህ አለው፣ “ኤልዳድና ሞዳድ በሰፈር ውስጥ እየተነበዩ ነው፡፡”
\s5
\v 28 ከእርሱ የተመረጡ ሰዎች አንዱ የሆነው የሙሴ ረዳት የነዌ ልጅ ኢያሱ ሙሴን እንዲህ አለው፣ “አለቃዬ ሙሴ ሆይ፣ ከልክላቸው፡፡”
\v 29 ሙሴ እያሱን እንዲህ አለው፣ “አንተ ለእኔ ተቆርቁረህ ነውን? እኔ መላው የያህዌ ህዝቦች ነቢያት ቢሆኑ እርሱ በሁሉም ላይ መንፈሱን ቢያደርግ እመኛለሁ! ”
\v 30 ከዚያ ሙሴና የእስራኤል ሽማግሌዎች ወደ ሰፈር ተመለሱ፡፡
\s5
\v 31 ከዚያ ከያህዌ ዘንድ ነፋስ ወጥቶ ከባህር ድርጭቶችን አመጣ፡፡ ከሰፈሩ በአንድ በኩል የአንድ ቀን የእግር መንገድ ርቀት ላይ፣ ደግሞም በሌላኛው በኩል በአንድ ቀን የእግር መንገድ ርቀት ድረስ ድርጭቶቹ ወደቁ፡፡ ድርጭቶቹ ሰፈሩን ከመሬት ሁለት ኪዩብ ከፍታ በሚሆን መጠን ሞሉት፡፡
\v 32 ሰዎቹ ያን ዕለት ምሽቱን ጨምሮ እንዲሁም በማግስቱም ድርጭቶችን በመሰብሰብ ሥራ ተጠምደው ነበር፡፡ ማንም ከአስር የቆሮስ መስፈሪያ ያነሰ ድርጭት አልሰበሰበም፡፡ በሰፈሩ ሁሉ ድርጭቶቹን ተከፋፈሉ፡፡
\s5
\v 33 ስጋው ገና በጥርሳቸው ውስጥ እያላመጡት ሳለ፣ ያህዌ በእነርሱ ላይ ተቆጣ፡፡ ህዝቡን በታላቅ በሽታ መታው፡፡
\v 34 በዚያ ሥፍራ ስጋ ለማግኘት የጎመጁትን ሰዎች ስለቀበሯቸው የስፍራው ስም ቂብሮት ሃታአባ ተባለ፡፡
\v 35 ሰዎቹ ከቂብሮት ሃታአባ ወደ ሰፈሩበት ወደ ሐጽሮት ተጓዙ፡፡
\s5
\c 12
\p
\v 1 “ከዚያ ማርያም እና አሮን ሙሴ ባገባት ኩሻዊ ሴት ምክንያት በሙሴ ላይ በተቃውሞ ተናገሩ፡፡
\v 2 እንዲህም አሉ፣ “ያህዌ የተናገረው ከሙሴ ጋር ብቻ ነውን? ከእኛስ ጋር አልተናገረምን? ” ያህዌ እነርሱ የተናገሩትን ሰማ፡፡
\v 3 ሙሴ ፣ በምድር ላይ ከሚገኝ ከማንኛውም ሰው ይልቅ በጣም ትሁት ሰው ነበር፡፡
\s5
\v 4 ወዲያውኑ ያህዌ ከሙሴ፣ ከአሮንና ማርያም ጋር ተናገረ “እናንተ ሶስታችሁ ወደ መገናኛው ድንኳን ውጡና ኑ፡፡” ስለዚህም ሶስቱም ወጥተው መጡ፡፡
\v 5 ከዚያም ያህዌ በደመና አምድ ወረደ፡፡ በድንኳኑ መግቢያ ቆሞ አሮንንና ማርያምን ጠራቸው፡፡ ሁለቱም ወደ ፊት ቀረቡ፡፡
\s5
\v 6 ያህዌ እንዲህ አለ፣ “አሁን ቃሎቼን ስሙ፡፡ አንድ የእኔ ነብይ በመካከላችሁ ሲሆን፣ ራሴን፣ በራዕይ እገልጥለታለሁ፣ በህልምም እናገረዋለሁ፡፡
\v 7 አገልጋዬ ሙሴ ግን እንደዚያ አይደለም፡፡ እርሱ በቤቴ ላይ ሁሉ የታመነ ነው፡፡
\v 8 እኔ ከመሴ ጋር በቀጥታ እናገራሁ፣ በራዕይ ወይም በዘይቤ አይደለም፡፡ እርሱ የእኔን መልክ ያያል፡፡ ስለዚህ በአገልጋዬ በሙሴ ላይ ስትናገሩ ለምን አልፈራችሁም?”
\s5
\v 9 የያህዌ ቁጣ በእነርሱ ላይ ነደደ፣ ከዚያም ትቷቸው ሄደ፡፡
\v 10 ደመናው ከድንኳኑ ላይ ተነሳ፣ እናም ማርያም በድንገት በለምጽ ተመታች እንደ በረዶ ነጭ ሆነች፡፡ አሮን ወደ ማርያም ዞር ብሎ ሲመለከታት በልምጽ መመታቷን አየ፡፡
\s5
\v 11 አሮን ሙሴን እንዲህ አለው፣ “ጌታዬ ሆይ፣ እባክህን በአንተ ላይ የፈጸምነውን ይህን በደል አትቁጠርብን፡፡ በስንፍና ተናግረናል፣ ደግሞም በድለናል፡፡
\v 12 እባክህን ከእናቱ ማህጸን ሲወጣ ጭንጋፍ ሆኖ እንደ ተወለደ ከፊል አካሉ እንደተበላ ሆና አትተዋት፡፡”
\s5
\v 13 ስለዚህም ሙሴ ወደ ያህዌ ጮኸ፡፡ እንዲህም አለ፣ “እግዚአብሔር ሆይ፣ እባክህ፣ እባክህ ፈውሳት፡፡”
\v 14 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ “አባቷ በፊቷ ላይ ቢተፋባት፣ ለሰባት ቀናት በሀፍረት ትቆያለች፡፡ ከሰፈር ውጭ ለሰባት ቀናት ዝጋባት፡፡ ከዚያ በኋላ መልሰህ አምጣት፡፡”
\v 15 ስለዚህም ማርያም ከሰፈር ውጭ ለሰባት ቀናት ተዘጋባት፡፡ እርሷ ወደ ሰፈር እስክትመለስ ድረስ ህዝቡ ጉዞ አላደረገም፡፡
\s5
\v 16 ከዚያ በኋላ፣ ህዝቡ ከሐዴሮት ተነስቶ ተጓዘና በፋራን ምድረበዳ ሰፈረ፡፡
\s5
\c 13
\p
\v 1 ዚያም ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
\v 2 ”ለእስራኤላውያን የሰጠኋቸውን የከነዐንን ምድር እንዲያዩ ጥቂት ሰዎችን ላክ፡፡ ከአባቶቻቸው ከእያንዳንዱ ነገድ አንድ ሰው ላክ፡፡ ከመሀላቸው የሚላከው እያንዳንዱ ሰው መሪ መሆን አለበት፡፡”
\s5
\v 3 ሙሴ የያህዌን ትእዛዝ እንዲያደርጉ ከፋራን ምድረ በዳ ላካቸው፡፡ ሁሉም ከእስራኤል ሰዎች መሃል የተመረጡ መሪዎች ነበሩ፡፡
\v 4 ስሞቻቸው እነዚህ ነበሩ፡ ከሮቤል ነገድ፣ የዘኩር ልጅ ሳሙኤል፡፡
\s5
\v 5 ከስምዖን ነገድ፣ የሱሬ ልጅ ሰፈጥ፡፡
\v 6 ከይሁዳ ነገድ፣ የዩፎኒ ልጅ ካልብ፡፡
\v 7 ከይሳኮር ነገድድ የዮሴፍ ልጅ ይግአል፡፡
\v 8 ከኤፍሬም ነገድ፣ የነዌ ልጅ አውሴ፡፡
\s5
\v 9 ከብንያም ነገድ፣ የራፋ ልጅ ፈልጢ፡፡
\v 10 ከዛብን ነገድ፣ የሰዲ ልጅ ጉዲኤል፡፡
\v 11 ከዮፍ ትውልዶች፣ ይህም፣ ከምናሴ ነገድ ነው፣ የሱሲን ልጅ ጋዲ፡፡
\v 12 ከዳን ነገድ፣ የገማሊ ልጅ ዓሚኤል፡፡
\s5
\v 13 ከአሴር ነገድ፣ የሚካኤል ልጅ ሰቱር፡፡
\v 14 ከንፍታሌም ነገድ፣ የያቢ ልጅ ናቢ፡፡
\v 15 ከጋድ ነገድ፣ የማኪ ልጅ ጉዲኤል ነበሩ፡፡
\v 16 ምድሪቱን እንዲያዩ ሙሴ የላቸው ሰዎች ስሞች እነዚህ ነበሩ፡፡ ሙሴ የነዌ ልጅ አውሴን፣ ኢያሱ ብሎ ጠራው፡፡
\s5
\v 17 ሙሴ እነርሱ የከነዓንን ምድር እንዲያዩ ላካቸው፡፡ እንዲህ አላቸው፣ “ከነጌብ ጀምራችሁ እስከ ተራራማው አገር ድረስ ሂዱ፡፡
\v 18 ምድሪቱ ምን እንደምትመስል ተመልከቱ፡፡ በዚያ የሚኖሩ ሰዎችን እዩ፣ ጠንካሮች ወይም ደካሞች መሆናቸውን፣ እና ጥቂት ወይም ብዙ መሆናቸውን ተመልከቱ፡፡
\v 19 የሚኖሩባት ምድር ምን እንደምትመስል እዩ፡፡ መልካም ናት ወይስ መጥፎ? በዚያ ምን አይነት ከተሞች አሉ? ሰፈር አይነት ናቸው? የተቀጠሩ ከተሞችስ ናቸውን?
\v 20 ምድሪቱ ምን እንደምትመስል እዩ፣ ለእርሻ የተመቸች ናት ወይስ አይደለችም፣ በዚያ ዛፎች አሉ ወይስ የሉም፡፡ ብርቱ ሁኑና ከምድሪቱ ምርት ከየአይነቱ ይዛችሁ ኑ፡፡” ወቅቱ የወይን ፍሬ ማፍራት የጀመረበት ነበር፡፡
\s5
\v 21 ስለዚህ ሰዎቹ ወጥተው በሌለቦ ሐማት አጠገብ፣ ከጺን ምድረበዳ እስከ ሌቦ ድረስ ምድሪቱን ተመለከቱ፡፡
\v 22 ከኔጌብ ወጥተው እስከ ኬብሮን ደረሱ፡፡ ከዔናቅ ነገድ ዝርያ የሆኑ የአኪመን፣ የሴሲና፣ እና የተላሚ ነገዶች በዚያ ነበሩ፡፡ ኬብሮን ግብጽ ውስጥ የተመሰተረችው ከከጣኔዎስ ሰባት አመት ቀደም ብላ ነበር፡፡
\s5
\v 23 ኤሽኮል ሸለቆ ሲደርሱ፣ የወይን ዘለላ የያዘ ቅርንጫፍ ቆረጡ፡፡ ከቡድናቸው በሁለቱ መሃል በበትር አድርገው የወይኑን ዘለላ ተሸከሙት፡፡ እንደዚሁም ሮማንና በለስም አመጡ፡፡
\v 24 የእስራኤል ሰዎች በዚየ ከቆረጡት የወይን ዘለላ የተነሳ፣ ያቺ ስፍራ የኤሽኮል ሸለቆ ተብላ ተጠራች፡፡
\s5
\v 25 ምድሪቱን መርምረው ከአርባ ቀናት በኋላ ተመለሱ፡፡
\v 26 የተላኩት ሰዎች፣ ሙሴና አሮን እንዲሁም መላው የእስራኤል ማህበረሰብ ወዳሉበት በፋራን ምድረበዳ ወደምትገኘው ወደ ቃዴስ መጡ፡፡ ወደ እነርሱና ወደ መላው ማህበረሰብ ተመልሰው መጥተው፣ የምድሪቱን ፍሬ አሳይዋቸው፡፡
\s5
\v 27 ሙሴን እንዲህ አሉት፣ “ወደ ላከን ምድር ደረስን፡፡ በእርግጥም ወተትና ማር ታፈሳለች፡፡ ከምድሪቱ ምርት እነሆ፡፡
\v 28 ሆኖም፣ በዚያ የሚኖሩ ሰዎች ብርቱዎች ናቸው፤¨ከተሞቹም የተመሸጉና ትላልቅ ናቸው፡፡ ደግሞም በዚያ የዔናቅን ዝርያዎችም አይተናል፡፡
\v 29 አማሌቃውያን በነጌብ ይኖራሉ፡፡ ኬጢያውያን፣ ኢያቡሳዊያን፣ እና አሞራዊያን በተራራማው አገር ይኖራሉ፡፡ ከነዓናዊያን በባህሩ አቅራቢያ በዮርዳኖስ ወንዝ ዳርቻ ይኖራሉ፡፡”
\s5
\v 30 ከዚያ ካሌብ በሙሴ ዙሪያ የተሰበሰቡበትን ሰዎች ሊያበረታታቸው ተነሳ፣ እንዲህም አለ፣ “በአንድ ጊዜ ተነስተን እንውጣና ምድራቸውን እንውረስ፣ ምክንያቱም በሚገባ ልናሸንፍ እንችላለን፡፡”
\v 31 ግን ከእርሱ ጋር የሄዱት ሌሎች ሰዎች እንዲህ አሉ፣ “እኛ ሰዎቹን ማጥቃት አንችልም ምክንያቱም እነርሱ ከእኛ ይልቅ ጠንካሮች ናቸው፡፡”
\s5
\v 32 ስለዚህም ስለተመለከቷት ምድር በእስራኤለ ሰዎች መሀል ተስፋ አስቆራጭ ወሬ አሰራጩ፡፡ እንዲህም አሉ፣ “የተመለከትናት ምድር በላይዋ የሚኖሩትን የምትበላ ናት፡፡ በዚያ ያየናቸው ሰዎ ሁሉ ቁመተ ረጃጅም ሰዎች ናቸው፡፡
\v 33 በዚያ የኤናቅ ዝርያዎችን አይተናል፣ ከግዙፋኑ ሰዎች የመጡትን ግዙፎቹን ሰዎች አይተናል፡፡ ከእነርሱ ጋር ስንተያይ፣ በእኛ በራሳችን ዐይን እንደ አንበጣ ነበርን፣ ደግሞም በእነርሱም ዐይን እንደዚሁ ነበርን፡፡”
\s5
\c 14
\p
\v 1 “በዚያን ምሽት ማህበረሰቡ በሙሉ ድምጹን ከፍ አድርጎ አለቀሰ፡፡
\v 2 እስራኤል ሰዎች ሁሉ ሙሴንና አሮንን ነቀፉ፡፡ መላው ማህበረሰብ እንዲህ አሏቸው፣ “በግብጽ ምድር ብንሞት ይሻለን ነበር፡፡ ውይም ምነው በዚህ በረሃ በሞትን ኖሮ!
\v 3 ያህዌ ለምን በዚህ ምድረበዳ በሰይፍ እንድንሞት ወደዚህ ምድር አመጣን? ሚስቶቻችንና ትናንሽ ልጆቻችን የተጠቁ ይሆናሉ፡፡ ወደ ግብጽ መመለስ አይሻለንምን?”
\s5
\v 4 እርስ በእርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፣ “ሌላ መሪ እንምረጥ፣ እናም ወደ ግብጽ እንመለስ፡፡”
\v 5 ከዚያ ሙሴና አሮን በእስራኤል ህዝብ በማህበረሰቡ ጉባኤ ፊት በግምባራቸው ተደፉ፡፡
\s5
\v 6 ምድሪቱን ለማየት ከወጡት ውስጥ ከነበሩት የነዌ ልጅ ኢያሱና የዩፎኒ ልጅ ካሌብ ልብሳቸውን ቀደዱ፡፡
\v 7 እስራኤል ሰዎች መላው ማህበረሰብ እንዲህ ሲሉ ተናገሩ፣ “በውስጧ ያለፍነውና የተመለከትናት ምድር በጣም መልካም መድር ናት፡፡
\v 8 ያህዌ በእኛ ደስ ከተሰኘ፣ ወደዚህች ምድር ያስገባናል ደግሞም እርሷን ለእኛ ይሰጠናል፡፡ ምድሪቱ ወተትና ማር የምታፈስ ናት፡፡
\s5
\v 9 ነገር ግን በያህዌ ላይ አታምጹ፣ ደግሞም በምድሪቱ የሚኖሩትን ህዝቦች አትፍሩ፡፡ በቀላሉ እንደ ምግብ እንበላቸዋለን፡፡ ጥላቸው ከእነርሱ ተገፏል፣ ምንያቱም ያህዌ ከእኛ ጋር ነው፡፡ እነርሱን አትፍሯቸው”፡፡
\v 10 ነገር ግን መላው ማህበረሰብ እስከ ሞት ሊወግሯቸው ተነሰቡቸው፡፡ ከዚያ የያህዌ ክብር በመገናኛው ድንኳን ለመላው የእስራኤል ሰዎች ታየ፡፡
\s5
\v 11 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ “ይህ ህዝብ እስከ መቼ እኔን ይንቀኛል በመካከላቸው በሃይሌ ያደረኳቸውን ምልክቶች እያዩ እንኳን እስከ መቼ በእኔ አያምኑም
\v 12 በበሽታ እመታቸዋለሁ፣ ወደ ርስታቸው አላስገባቸውም፣ ሆኖም ከአንተ ከራስህ ነገድ ከእነርሱ ይልቅ ታላቅና ሃያል ህዝብ አበጃለሁ፡፡”
\s5
\v 13 ሙሴ ያህዌን እንዲህ አለው፣ “ይህን ብታደርግ፣ ግብጻዊያን ስለዚህ ነገር ይሰማሉ፣ ምክንያቱም አንተ ይህን ህዝብ በኃይልህ ከእነርሱ አድነሃቸዋል፡፡
\v 14 ለዚህች ምድር ነዋሪዎች ይህንን ይናገራሉ፡፡ አንተ ያህዌ፣ ከዚህ ህዝብ ጋር እንደሆንክ እነርሱ ሰምተዋል፣ ምክንያቱም አንተ ፊት ለፊት ታይተሃል፡፡ የአንተ ደመና በእኛ ህዝብ ላይ ሆኗል፡፡ አንተ በእነርሱ ፊት በቀን በደመና አምድ በምሽት በእሳት አምድ ሄደሃል፡፡
\s5
\v 15 አሁን ይህንን ህዝብ እንደ አንድ ሰው ብትገድል፣ ዝናህን የሰሙ ህዝቦች እንዲህ ይላሉ፣
\v 16 ‘ያህዌ ይህንን ህዝብ ሊሰጣቸው ወደ ማለላቸው ምድር ሊያስገባቸው ባለመቻሉ ምክንያት፣ በምድረበዳ ገደላቸው፡፡
\s5
\v 17 አሁን፣ እኔ እለምንሃለሁ፣ ታላቁን ሀይልህን ተጠቀም፡፡ አንተ እንዲህ ብለሃልና፣
\v 18 ‘ያህዌ ለቁጣ የዘገየ ነው፣ በቃል ኪዳን ታማኝነቱ የተትረፈረፈ ነው፡፡ እርሱ በደልና መተላለፍን ይቅር ይላል፡፡ የአባቶችን ኃጢአት ቅጣት እስከ ሁለትና ሶስት ትውልድ በልጆቻቸው ላይ ሲያመጣ በደላቸውን በምንም አይነት ሳይቀጣ አይቀርም፡፡’
\v 19 የቃል ኪዳን ታማኝነነትህን ታላቅነት ስላልተረዳ ይህ ህዝብ ይበድላል፣ በግብጽ ከነበሩበት ጊዜ አንስቶ እስከ አሁን ሁልጊዜም ይቅር እንዳልካቸው ይቅር እንድትል እለምንሃለሁ፡፡”
\s5
\v 20 ያህዌ እንዲህ አለው፣ “ልመናህን ሰምቼ ይቅር ብያቸዋለሁ፣
\v 21 ነገር ግን፣ እኔ ሕያው ስለሆንኩና መላው ምድርም በእኔ ክብር የተሞላች ስለሆነች፣
\v 22 ክብሬን፣ በግብጽና በምድረበዳው ጉዟቸው ያደረኳቸውን የሀይሌን ምልክቶች አይተው እነዚያ ህዝቦች ሁሉ - እስከ አሁን ድረስ በእነዚህ አስር ጊዜ ተፈታተኑኝ እንጂ ድምጼን አልሰሙም፡፡
\s5
\v 23 ስለዚህ ለአባቶቻቸው የማልኩላቸውን ምድር በፍጹም አያዩም፡፡ እኔን ከናቁት ውስጥ አንዳቸውም ምድሪቱን አያዩም፣
\v 24 ከባሪያዬ ከካሌብ በስተቀር፣ ምክንያቱም እርሱ የተለየ መንፈስ አለው፡፡ እርሱ እኔን በሙሉ ልቡ ተከትሎኛል፣ ሊያያት ወደሄደበት ምድር እኔ እመጣዋለሁ፡፡ የእርሱ ትውልዶች ይወርሷታል፡፡
\v 25 (አሁን አማሌቃዊያንና ከነዓናውያን በሸለለቆው ይኖራሉ፡፡) ነገ ተመልሳችሁ በሸምበቆው ባህር በኩል ወደ ምድረ በዳው ሂዱ፡፡”
\s5
\v 26 ህዌ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፣
\v 27 ”እኔን የሚነቅፈውን ይህን ክፉ ማህበረሰብ እስከ መቼ እታገሳለሁ የእስራኤል ሰዎች በእኔ ላይ ሲያጉረመርሙ ሰምቻለሁ፡፡
\s5
\v 28 እንዲህ በላቸው ‘እኔ ሕያው ነኝ’ ይላል ያህዌ፣ ‘እኔ እየሰማሁ፣ የተናገራችሁትን፣ ያንኑ አደርግባችኋለሁ፡፡
\v 29 በድናችሁ በዚህ ምድረ በዳ ይወድቃል፣ እናንተ በእኔ ላይ ያጉረመርማችሁ ሁላችሁም፣ በህዝብ ቆጠራው የተቆጠራችሁ ሃያ አመትና ከዚያ በላይ ዕድሜ ያላችሁ ሰዎች ሁሉ ትሞታላችሁ፡፡
\v 30 መኖሪያችሁ ትሆን ዘንድ እንደምሰጣችሁ ቃል ወደገባሁላችሁ ምድር ከዮፍኒ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በስተቀር ከእናንተ አንዳችሁም አትገቡም፡፡
\s5
\v 31 ነገር ግን ተጠቂ ይሆናሉ ያላችኋቸው ትንንሽ ልጆቻችሁን፣ እኔ ወደ ምድሪቱ አስገባቸዋለሁ፡፡ እናንተ የናቃችኋትን ምድር እነርሱ ይገቡባታል!
\v 32 እናንተ ግን፣ በድናችሁ በዚህ ምድረ በዳ ይወድቃል፡፡
\v 33 ልጆቻችሁ ለአርባ አመታት በምድረዳ ይንከራተታሉ፡፡ በረሃው ሁላችሁንም እስኪገድላችሁ ድረስ፣ እነርሱ እናንተን የአመጽ ድርጊቶች ዋጋ ይከፍላሉ፡፡
\s5
\v 34 ምድሪቱን በተመለከታችሁባቸው አርባ ቀናት ልክ፣ ለአርባ አመታት ስኃጢአታችሁ መከራ ትቀበላላችሁ - ለእያንዳንዱ ቀን አንድ አመት፣ እናም የእኔ ጠላት መሆን ማለት ምን ማለት እንደሆነ ታውቃላችሁ፡፡
\v 35 እኔ ያህዌ፣ ይህንን ተናግሬያለሁ፡፡ በእኔ ላይ በተነሱ በዚህ ክፉ ማህበረሰብ ላይ በእርግጥ ይህን አደርጋሁ፡፡ በዚህ ምድረ በዳ ይጠፋሉ፡፡ በዚህ ስፍራ ይሞታሉ፡፡”
\s5
\v 36-37 ስለዚህ ሙሴ ምድሪቱን እንዲያዩ የላካቸው ሰዎች ሁሉ በያህዌ ፊት በወረርሽኝ አለቁ፡፡ እነዚህ ሰዎች ስለምድሪቱ መጥፎ ወሬ ይዘው የተመለሱ ነበሩ፡፡ ይህም መላው ማህበረሰብ በሙሴ ላይ እንዲያጉረመርም አደረገ፡፡
\v 38 ምድሪቱን ለማየት ከሄዱት ሰዎች መሀል፣ የነዌ ልጅ ኢያሱና የዩፎኒ ልጅ ካሌብ ብቻ በህይወት ቀሩ፡፡
\s5
\v 39 ሙሴ እነዚህን ቃላት ሁሉ ለእስራኤል ሰዎች ሲናገር፣ በጥልቅ አዘኑ፡፡
\v 40 ማልደው ተነስተው ወደ ተራራው ጫፍ ወጥተው እንዲህ አሉ፣ “እነሆ፣ አሁን በዚህ አለን፣ ደግሞም ያህዌ ቃል ወደገባልን ስፍራ እንሄለን፣ እኛ በድለናል፡፡”
\s5
\v 41 ነገር ግን ሙሴ እንዲህ አለ፣ “ለምን አሁን የያህዌን ትእዛዝ ትሽራላችሁ ድል አይቀናችሁም፡፡
\v 42 አትውጡ፣ ምክንያቱም በጠላቶቻችሁ እንዳትሸነፉ ሊጠብቃችሁ ያህዌ ከእናንተ ጋር አይደለም፡፡
\v 43 በዚያ አማሌቃዊያንና ከነዓናዊያን አሉ፣ እናንተም በሰይፍ ታልቃላችሁ ምክንቱም ያህዌን ከመከተል ፊታችሁን መልሳችኋል፡፡ ስለዚህ እርሱ ከእናንተ ጋር አይሆንም፡፡”
\s5
\v 44 እነርሱ ግን ወደ ተራራማው አገር ለመሄድ በድፍረት ተነሱ፣ ሆኖም፣ ሙሴም ሆነ የያህዌ የቃል ኪዳኑ ታቦት ከሰፈር አብሯቸው አልወጣም፡፡
\v 45 ከዚያ አማሌቃዊያን ወርደው መጡ፣ እንደዚሁም በተራሮቹ የሚኖሩ ከነዓናዊያን መጡባቸው፡፡ እነርሱም እስራኤላውያንን አጠቋቸው እስከ ሔርማ መንገድ ድረስ አሳደዷቸው፡፡
\s5
\c 15
\p
\v 1 ከዚያ ያህዌ ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፣
\v 2 “ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ በላቸው፣ ‘ያህዌ ለእናንተ ወደሚሰጣችሁ ወደ ምትኖሩባት ምድር ስትገቡ
\v 3 ለእርሱ በእሳት መስዋዕት ስታቀርቡ፣ የሚቃጠል መስዋዕት ወይም ስዕለት ስታመጡ ወይም የበጎ ፈቃድ ስጦታ፣ ወይም በባዕላቶቻችሁ ለያህዌ ስጦታዎችን ከከብቶች ወይም ከመንጋችሁ ስታቀርቡ
\s5
\v 4 ለያህዌ መስዋዕቱን የሚያቀርበው ሰው፣ በአንድ አራተኛ ኢን ዘይት የተለወሰ የኢፍ አንድ አስረኛ መልካም ዱቄት የእህል መስዋዕት ያቅርብ፡፡
\v 5 እንዲሁም የኢን አንድ አራተኛ ወይን ለመጠጥ መስዋዕት አቅርቡ፡፡ ይህን ከሚቃጠል መስዋዕት ጋር ወይም እያንዳንዱ ጠቦት ሲቀርብ አድርጉት
\s5
\v 6 አውራ በግ የምታቀርቡ ከሆነ፣ የኢፍ ሁለት አስረኛ መልካም ዱቄት በአንድ ሶስተኛ ኢን ዘይት የተለወሰ የእህል ቁርባን አቅርቡ፡፡
\v 7 ለመጠጥ መስዕት፣ የኢን አንድ ሶስተኛ ወይን አቅርቡ፡፡ ይህ ለያዌ ጣፋጭ መዓዛ ይሆናል፡፡
\s5
\v 8 ለሚቃተል መስዋዕት በሬ፣ ወይም ስዕለት ለማድረስ መስዋዕት ወይም ለያህዌ የህብረት መስዋዕት ስታዘጋጁ
\v 9 ከበሬው ጋር በግማሽ ኢን ዘይት የተለወሰ የኢፍ ሶስት አስረኛ መልካም ዱቄት የእህል ቁርባን አቅርቡ፡፡
\v 10 ለያዌ ጣፋጭ መዓዛ እንዲሆን ለመጠጥ ቁርባን የኢን ግማሽ ወይን፣ በእሳት የሚረብ መስዋዕት አቅርቡ፡፡
\s5
\v 11 እያንዳንዱ በሬ፣ እያንዳንዱ አውራ በግ፣ እና እያንዳንዱ ወንድ ጠቦት በግ ወይም ጠቦት ፍየል ሲቀርበ በዚህ አይት ይሁን፡፡
\v 12 እያንዳንዱ የምታዘጋጁት መስዋዕት እና ስጦታ እዚህ እንደተገለፀው ይቅረብ፡፡
\v 13 ማንም ሰው ለያህዌ ደስ የሚያሰኝ መዓዛ ለማቅረብ በእሳት የተዘጋጀ መስዋዕት ሲያመጣ፣ የአገር ተወላጅ የሆነ እስራኤላዊ ሁሉ እነዚህን ነገሮች በዚህ መንገድ ያድርግ፡፡
\s5
\v 14 መጻተኛው ከእናንተ ጋር ቢኖር፣ ወይም በእናንተ ትውልድ መሀል የሚኖር ማናቸውም ሰው፣ ለያህዌ መልካም መዓዛ ለማቅረብ በእሳት የተዘጋጀ መስወዕት ያድርግ፡፡ እርሱ እናንተ እንደምታደርጉት ያድርግ፡፡
\v 15 ለማህበረሰቡ እና ከእናንተ ጋር ለሚኖር መጻተኛ ተመሳሳይ ህግ ይሁን፣ ይህ በትውልዳች ሁሉ የፀና ህግ ይሁን፡፡ እናንተ እንደ ታያችሁት፣ ከእናንተ ጋር የሚኖሩ እንግዶች በአንድ አይነት ይታያሉ፡፡
\v 16 ለእናንተም ሆነ ከእናንተ ጋር ለሚኖሩ መጻተኞች ተመሳሳይ ህግና ደንቦች ተግባራዊ ይደረጋሉ፡፡”
\s5
\v 17 ያህዌ ዳግም ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፣
\v 18 ”ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ በላቸው፣ ‘ወደ ማስገባችሁ ምድር በመጣች ጊዜ፣
\v 19 በምድሪቱ የተመረተውን ምግብ በበላችሁ ጊዜ፣ መስዋዕት መሰዋትና ለእኔ ማቅረብ አለባችሁ፡፡
\s5
\v 20 ከመጀመሪያው ቡኬታችሁ ከአውድማው የማንሳት መስዋዕት ህብስት አቅርቡ፡፡ በዚህ መንገድ መስዋዕታችሁን አቅርቡ፡፡
\v 21 በትውልዶች ሁሉ ከመጀመሪያው ቡኬታችሁ የማንሳት መስዋዕት ለእኔ ትሰጣላችሁ፡፡
\s5
\v 22 አንዳንድ ጊዜ ለማድረግ ሳታስቡ ለሙሴ የነገርኩትን እነዚህን ህጎች ሁሉ በተመላለፍና
\v 23 ትዕዛዛትን ለእናንተ መስጠት ከጀመርኩበት ቀን አንስቶ በትውልዳችሁ ቀጣይ ዘመናት በሙሴ በኩል ያዘዝኳችሁን ነገሮች በሙሉ ባታደርጉ ኃጢአት ትሰራላችሁ፡፡
\v 24 ማህበረሰቡ ሳያውቅ በደል ፈጽሞ ሲገኝ፣ መላው ህብረተሰብ ለያህዌ መልካም መዓዛ እንዲሆን አንድ ወይፈን ለሚቃጠል መስዋዕት ያቀርባል፡፡ ከዚሁ ጋር የእህል ቁርባን እና የመጠጥ ቁርባን እንዲሁም ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል በደንቡ መሠረት ያቅርብ፡፡
\s5
\v 25 ካህኑ ለመላው የእስራኤል ማህበረሰብ ማስተስረያ ያቀርባል፡፡ ኃጢአቱ የተፈፀመው፣ ባለማወቅ ስለሆነ ይቅር ይባላሉ፡፡ ለእኔ በእሳት የተዘጋጀውን መስዋዕታቸውን አቅርበዋልና ይቅር ይባለሉ፡፡ በእኔ ፊት ሳያውቁ ለፈጸሙት ስህተት የኃጢአት መስዋዕታቸውን አቅርበዋልና፡፡
\v 26 ከዚያ መላው የእስራኤል ማህበረሰብና ከእነርሱ ጋር የሚኖሩ መጻተኞች ይቅር ይባላሉ፣ ምክንያቱም ሁሉም ኃጢአቱን የፈፀሙት ሆን ብለው አይደለም፡፡
\s5
\v 27 አንድ ሰው ሳያውቅ ኃጢአት ቢሰራ ለኃጢአት መስዋዕት የአንድ አመት ሴት ፍየል ያቅርብ፡፡
\v 28 ካህኑ ሳያውቅ ኃጢአት ለሰራው ሰው በያህዌ ፊት ያስተሰርይለታል፡፡ ያ ሰው ማስተሰርያ ሲደረግ ይቅር ይባላል፡፡
\v 29 ማናቸውንም ነገር ሁን ብሎ ላላደረገ ተመሳሳይ ህግ ይኑራችሁ፣ በእስራኤል ሰዎች መሀል ለሚኖረው ተወላጅም ሆነ መጻተኛ ተመሳሳይ ህግ ይኑራቸው፡፡
\s5
\v 30 ነገር ግን ራሱን ለመከላከል አንዳች ነገር ያደረገ ሰው፣ የአገር ተወላጅም ይሁን መጻተኛ እኔን ያቃልላል፡፡ ስለዚህ ያ ሰው ከወገኖቹ ተለይቶ ይጥፋ፡፡
\v 31 ምክንቱም እርሱ ቃሌን ንቋል ደግሞም ትዕዛዛቴን ተላልፏል፣ ያ ሰው ሙሉ ለሙሉ ከህዝቡ ተለይቶ ይጥፋ፡፡ ኃጢአቱ በራሱ ላይ ይሆናል፡፡”
\s5
\v 32 የእስራኤል ህዝቦች በምድረ በዳ በነበሩበት ጊዜ፣ አንድ ሰው በሰንበት ቀን እንጨት ሲለቅም አገኙት፡፡
\v 33 ያገኙት ሰዎች ወደ ሙሴ፣ ወደ አሮንና ወደ መላው ማህበረሰብ አቀረቡት፡፡
\v 34 በእርሱ ላይ ምን መደረግ እንዳለበት የታወቀ ህግ ስላልበረ በጥበቃ ሥር አቆዩት፡፡
\s5
\v 35 ከዚያ ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ “በእርግጥ ሰውየው መገደል አለበት፡፡ መላው ማህበረሰብ ከሰፈር ውጭ በድንጋይ ይውገረው፡፡”
\v 36 ስለዚህም መላው ማህበረሰብ ሰውየውን ከሰፈር ውጭ አውጥተው ያህዌ ሙሴን እንዳዘዘው እስኪሞት ድረስ ወገሩት፡፡
\s5
\v 37 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
\v 38 “ለእስራኤል ትውልዶች በየለብሳቸው ጠርዝ ዘርፍ እንዲያስሩ ንገራቸው፣ ዘርፎቹን በእያንዳንዱ ጠርዝ በሰማያዊ ገመድ እንዲያንጠለጥሉ እዘዛቸው፡፡ በሚቀጥሉት ትውልዶቻቸው ሁሉ ይህን ያድርጉ፡፡
\v 39 ይህንን ስትመለከቱ፣ በትዕዛዛት ሁሉ፣ እንድትሄዱ፣ የራሳችሁን ልቦናና እይታ ሳትከተሉ ቀድሞ ታደርጉት ከነበረው መንፈሳዊ አመንዝራነት ለመመለስ ይህ ለእናንተ ልዩ ማስታወሻ ይሆናችኋል፡፡
\s5
\v 40 ትዕዛዛቶቼን ሁሉ እንድትጠብቁና አስተዋዮች እንድትሆኑ ይህን አድርጉ፣ ደግሞም ቅዱሳንና ለእኔ ለአምላካችሁ የተለያችሁ ትሆናላች፡፡
\v 41 አምላካችሁ እሆን ዘንድ፣ ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡”
\s5
\c 16
\p
\v 1 የይስዓር ልጅ ቆሬ የቀዓት ልጅ የሌዊ ልጅ፣ ከኤሊያብ ልጆች ከዳታንና አቤሮን ጋር፣ እንዲሁም የፍሬት ልጅ ኦን፣ የሮቤል ትውልዶች ሆነው ተሰበሰቡ፡፡
\v 2 እነርሱም ከእስራኤል ሌሎች ሰዎች ጋር ሆነው በሙሴ ላይ ተቃውመው ተነሱ፣ የማህበረሰቡ መሪዎች የሆኑ የታወቁ ሁለት መቶ ሀምሳ ሰዎች ተነሱበት፡፡
\v 3 ሙሴንና አሮንን ለመቃወም በአንድነት ተሰበሰቡ፡፡ ሙሴንና አሮንን እንደዚህ አሏቸው፣ “እናንተ ያለ ልክ አብዝታችሁታል፡፡ መላው ማህበረሰብ ቅዱስ ነው፣ ለያህዌ የተለየ ነው፣ እያንዳንዳቸው ንጹሃን ናቸው፣ ያህዌም በመሀከላቸው ነው፡፡ ለምን ራሳችሁን ከተቀረው የያህዌ ማህበረሰብ ከፍ ታደረጋላችሁ?”
\s5
\v 4 ሙሴ ይህንን ሲሰማ፣ በግምባሩ ተደፋ፡፡
\v 5 ለቆሬና ለእርሱ ወገኖች እንዲህ አላቸው፤ “ማለዳ ያህዌ የእርሱ የሆኑት እነማን እንደሆኑ ይለያል፣ ማን ለእርሱ እንደ ተለየ ይታወቃል፡፡ የመረጠውን ሰው ወደ ራሱ ይለያል፡፡ የመረጠውን ወደ ራሱ ያመጣዋል፡፡
\s5
\v 6 ቆሬና የአንተ ቡድን ሁላች ይህን አድርጉ፡፡ ማጠንት ያዙ
\v 7 ነገ በያህዌ ፊት እሳትና እጣን በላያቸው ጨምሩ፡፡ ያህዌ የሚመርጠው ሰው እርሱ፣ ለያህዌ የተለየ ይሆናል፡፡ እናንተ የሌዊ ትውልዶች ከልክ አልፋችኋል፡፡”
\s5
\v 8 እንደገና፣ ሙሴ ቆሬን እንዲህ አለው፣ “አሁን ስማ፣ እናንተ የሌዊ ትውልዶች
\v 9 የእስራኤል አምላክ ከእስራኤል ማህበረሰብ እናተን ለይቶ ወደራሱ ማቅረቡ፣ በያህዌ የማደሪያ ድንኳን እንድታገለግሉ ማድረጉ፣ እነርሱን እንድታገለግሉ በማህበረሰቡ ፊት እናንተን ማቆሙ ለእናንተ ትንሽ ነገር ነውን?
\v 10 እርሱ አንተን፣ የቅርብ ዘመዶችህንና የሌዊ ትውልዶችን ከአንተ ጋር አቅርቧችኋል፣ እናንተ ግን ክህነቱንም እየፈለጋችሁ ነው!
\v 11 አንተና የአንተ ተከታዮች ሁሉ በያህዌ ላይ በአንድ ላይ ተነሳችሁ፡፡ ስለዚህ ለምን እግዚአብሔርን በሚታዘዘው በአሮን ላይ ታጉረመርማላችሁ?”
\s5
\v 12 ከዚያ ሙሴ የኤልያብን ልጆች ዳታንንና አብሮንን ጠራቸው፣ እነርሱ ግን እንዲህ አሉ፣ “እኛ ወደዚያ አንመጣም፡፡
\v 13 እኛን በምድረበዳ ልትገድለን ወተትና ማር ከሚፈስባት ምድር ያወጣኸን ትንሽ ነገር ሆኖ ነውን? አሁን ራስህን በእኛ ላይ ገዢ ማድረግ ትፈልጋለህ!
\v 14 በተጨማሪም፣ እኛን ወተትና ማር ወደምታፈስ ምድር አላመጣኸንም፣ ወይም እርሻዎችንና የወይን ተክሎችን ውርስ አድርገህ አልሰጠኸንም፡፡ አሁን በባዶ ተስፋ ልታታልለን ትፈልጋህ? ወደ አንተ አንመጣም፡፡”
\s5
\v 15 ሙሴ እጅግ ተቆጥቶ ነበር፣ ወደ ያህዌ እንዲህ ሲል ጮኸ፣ “መስዋዕታቸውን አትቀበል፡፡ ከእነርሱ አንድ አህያ እንኳን አልወሰድኩም፣ ከእነርሱ አንዳቸውንም አልበደልኩም፡፡”
\v 16 ከዚያ ሙሴ ቆሬን እዲህ አለው፣ “ነገ አንተና የአንተ የሆኑ በያህዌ ፊት ይቅረቡ፤ አንተ፣ እነርሱና አሮን በያህዌ ፊት ቁሙ፡፡
\v 17 እያንዳንዱ የራሱን ማጠኛ ይያዝና በውስጡ እጣን ይጨምርበት፡፡ ከዚያ እያንዳንዱ ሰው ማጠኛውን በያዌ ፊት ያምጣ፣ ሁለት መቶ አምሳዎቹ ሰዎችህ ማጠኛዎቻቸውን ይዘው ይቅረቡ፡፡ አንተና አሮንም ደግሞ የየራሳቸችሁን ማጠኛ አምጡ፡፡”
\s5
\v 18 ስለዚህ እያንዳንዱ ሰው ማጠኛውን ወሰደ፣ በውስጡ እሳት አደረገ፣ እጣንም ጨመረበት ከሙሴና ከአሮን ጋር በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ላይ ቆሙ፡፡
\v 19 ቆሬ መላውን ማህበረሰብ በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ላይ በሙሴና በአሮን ላይ በተቃውሞ ሰበሰበ፣ የያህዌ ክብር ደግሞ ለማህበረሰቡ ሁሉ ታየ፡፡
\s5
\v 20 ከዚያ ያህዌ ለሙሴና ለአሮን እንዲህ ሲል ተናገረ፣
\v 21 ”በቶሎ ከማጠፋው ከዚህ ማህበረሰብ መሀል ራሳችሁን ለዩ፡፡”
\v 22 ሙሴና አሮን በግንባራቸው ተደፍተው እንዲህ አሉ፣ “ የሰው ልጆች ሁሉ መንፈስ አምላክ የሆንክ እግዚአብሔር ሆይ፣ አንድ ሰው ኃጢአት ቢሰራ ማህበረሰቡን በሙሉ ልትቆጣ ይገባልን?”
\s5
\v 23 ያህዌ ለሙሴ እንዲህ ሲል መለሰለት፣
\v 24 ”ለማህበረሰቡ እንዲህ በል፣ ‘ከቆሬ፣ ከዳታንና ከኤብሮን ድንኳኖች ውጡ፡፡’”
\s5
\v 25 ከዚያ ሙሴ ተነስቶ ወደ ወደ ዳታንና አብሮን ሄደ፤ የእስራኤል መሪዎች እርሱን ተከተሉት፡፡
\v 26 ለማህበረሰቡ እንዲህ ብሎ ተናገረ፣ “አሁን የእነዚህን ክፉ ሰዎች ድንኳኖች ልቀቁ፣ የእነርሱ የሆነውን አንዳች ነገር አትንኩ፣ አለበለዚያ በእነርሱ ኃጢአቶች ሁሉ እናንተም ትጠፋላችሁ፡፡”
\v 27 ስለዚህ በቆሬ፣ በዳታንና በኤብሮን ድንኳኖች በእያንዳንዱ አቅጣጫ የሚገኝ ማህበረሰብ ከእነርሱ ራቁ፡፡ ዳታንና አብሮን ወደ ውጭ ወጥተው ከሚስቶቻቸው፣ ከወንዶች ልጆቻቸውና ከህፃናቶቻቸው ጋር በድንኳኖቸው ደጃፍ ላይ ቆሙ፡፡
\s5
\v 28 ከዚያ ሙሴ እንዲህ አለ፣ “በዚህም ያህዌ እነዚህን ስራዎች ሁሉ እንድሰራ እንደላከኝ ታውቃላችሁ፣ እኔ በራሴ ፈቃድ እነዚህን ነገሮች አልሰራኋቸውም፡፡
\v 29 እነዚህ ሰዎች በተለመደው ሁኔታ ተፈጥሯዊ ሞት ቢሞቱ፣ ያህዌ እኔን አላኝም ማለት ነው፡፡
\v 30 ነገር ግን ያህዌ ምድሪቷን ቢከፍትና እርሷ እንደ ተከፈተ አፍ ሆና፣ ከነቤተሰቦቻቸው ብትውጣቸው፣ ደግሞም በህይወታቸው ሳሉ ወደ ሲኦል ቢወርዱ፣ ያን ጊዜ እነዚህ ሰዎች ያህዌን እንደናቁ ታውቃላችሁ፡፡”
\s5
\v 31 ሙሴ እነዚህን ቃላቶች ተናግሮ እንደጨረሰ፣ ምድሪቱ ከነዚህ ሰዎች በታች ተከፈተች፡፡
\v 32 መሬት አፏን ከፈተችና ዋጠቻቸው፣ ቤተሰቦቻቸው፣ እና የቆሬ ሰዎች ሁሉ እንዲሁም ያላቸው ሀብት ሁሉ ተዋጠ፡፡
\s5
\v 33 እነርሱና በየቤተሰባቸው እያንዳንዱ በሕይወት ሳሉ ወደ ሲኦል ወረዱ፡፡ መሬት በላያቸው ተከደነች፣ እናም በዚህ መንገድ ከማህበረሰቡ መሀል ጠፉ፡፡
\v 34 በዙሪያቸው የነበሩ እስራኤላዊያን ሁሉ ከጩኸታቸው የተነሳ ሸሹ፡፡ እንዲህ እያሉም ጮኹ፣ “መሬት እኛንም ደግሞ ልትውጠን ነው! ”
\v 35 እሳት ከያህዌ ዘንድ ወጥታ የሚያጥኑትን 250 ሰዎች በላቻቸው፡፡
\s5
\v 36 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
\v 37 ”ጥናዎቹ ለእኔ የተለዩ ናቸውና ለካህኑ ለአሮን ልጅ ለአላዓዛር ከሚጤሱት የተረፉትን ጥናዎች እንዲወስድ ንገረው፡፡ ከዚያ ረመጡን ይበትኑት፡፡
\v 38 በኃጠአታቸው ምክንያት ሕይወታቸውን ያጡትን ሰዎች ጥናዎች ውሰድ፡፡ ጥናዎቹ የተቀጠቀጡ ሰሀኖች ተደርገው ለመሰዊያው መሸፈኛነት ይዋሉ፡፡ ለእኔ የተለዩ ናቸውና፣ እነዚያ ሰዎች በእኔ ፊት ያቅርቧቸው፡፡ እነዚህም ለእስራኤል ሰዎች ለእኔ መገኘት ምልክት ይሆናሉ፡፡”
\s5
\v 39 ካህኑ አልዓዛር የተቃጠሉት ሰዎች ይጠቀሙባቸው የነበሩትን የናስ ጥናዎች ይውሰድና ለመሰዊያው መሸፈኛነት ይቀጥቅጣቸው፣
\v 40 ይህም፤ ለእስራኤል ሰዎች ማስታወሻ እንዲሆን፣ ማንም የአሮን ትውልድ ያልሆነ መጻተኛ በያህዌ ፊት ለማጠን እንዳያቀርብና እንደ ቆሬና እንደ እርሱ ተከታዮች እንዳይሆኑ ያህዌ በሙሴ በኩል እንዳዘዘው ልክ እንደዚያ እንዳይሆንባቸው ነው፡፡
\s5
\v 41 ነገር ግን በማግስቱ የእስራኤል ማህበረሰብ በሙሉ በሙሴና በአሮን ላይ በማጉረምረም ተነሱባቸው፡፡ እነዲህም አሉ፣ “እናንተ የያህዌን ሰዎች ገድላችኋል፡፡”
\v 42 ከዚያም እንዲህ ሆነ፣ ማህበረሰቡ በሙሴና በአሮን ላይ በተቃውሞ ሲሰበሰብ፣ ወደ መገናኛው ድንኳን አሻግሮ ሲመለከቱ፣ እነሆ ደመናው ድንኳኑን ሸፍኖት ነበር፡፡ የያህዌ ክብር ታየ፣
\v 43 እናም ሙሴና አሮን ወደ መገናኛው ድንኳን ወደፊት መጡ፡፡
\s5
\v 44 ከዚያ ያህዌ ሙሴን ተናገረው፡፡ እንደህም አለው፣
\v 45 “ከዚህ ማህበረሰብ ፊት ራቅ፣ እኔ በቶሎ አጠፋቸዋለሁ፡፡” ከዚያ ሙሴና አሮን በግምባራቸው ተደፉ፡፡
\v 46 ሙሴ አሮንን እንዲህ አለው፣ “ማጥንቱን ውሰድ፣ ከመሰዊያው እሳት ወስደህ አድርግበት፣ በውስጡ እጣን ጨምርበት፣ በቶሎ ወደ ማህበረሰቡ ውሰደው፣ እናም ለእነርሱ አስተሰርይ፣ ምክንያቱም ከያህዌ ዘንድ ቁጣ እየመጣ ነው፡፡ መቅሰፍቱ ጀምሯል፡፡”
\s5
\v 47 ስለዚህም አሮን ሙሴ እንደመራው አደረገ፡፡ ወደ ማህበረሰቡ መሃል ሮጠ፡፡ መቅሰፍቱ በህዝቡ መካከል በፍጥነት መስፋፋት ጀመሮ ነበር፣ ስለዚህም እርሱ እጣኑን ጨምሮ ለህዝቡ ማስተሰርያ አደረገ፡፡
\v 48 አሮን በሙታኑና በህያዋኑ መሀል ቆመ፣ በዚህ መንገድ መቅሰፍቱ ቆመ፡፡
\s5
\v 49 በመቅሰፍቱ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 14700 ነበር፣ ይህም በቆሬ ምክንያት የሞቱትን ሳይጨምር ነው፡፡
\v 50 አሮን ወደ መገናኛው ድንኳን መግቢያ ወደ ሙሴ ተመለሰ፣ መቅሰፍቱም አበቃ፡፡
\s5
\c 17
\p
\v 1 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
\v 2 ”ለእስራኤል ሰዎች ተናገራቸው፡፡ ከእነርሱ በትሮችን ውሰድ፣ ከየነገዱ አባቶች አንድ በትር ውሰድ፡፡ ከእያንዱ መሪ አንድ በአጠቃላይ ከየነገድ የተመረጡ አስራ ሁለት በትሮችን ውሰድ፡፡ የእያንዳንዱን ሰው ስም በበትሩ ላይ ጻፍ፡፡
\s5
\v 3 የአሮንን ስም በሌዊ በትር ላይ ጻፍ፡፡ ለእያንዳንዱ መሪ ከየአባቶቹ ነገድ አንድ በትር ሊኖር ያስፈልጋል፡፡
\v 4 በትሮቹን ከአንተ ጋር በምገናኝበት በመገናኛው ድንኳን ከምስክሩ ኪዳን ፊት አስቀምጣቸው፡፡
\v 5 እንዲህ ይሆናል፣ እኔ የምመርጠው ሰው በትር ታቆጠቁጣለች፡፡ የእስራኤለ ሰዎች በአንተ ላይ የሚያደርጉትን ማጉረምረማቸውን እንዲያቆሙ አደርጋለሁ፡፡”
\s5
\v 6 ሙሴ ለእስራኤል ሰዎች ተናገረ፡፡ ሁሉም የነገዱ መሪዎች በትሮቻቸውን ሰጡት፣ ከእያንዳንዱ መሪ አንድ በትር፣ ከየነገዱ አባቶች ተመረጠ፣ በአጠቃላይ አስራ ሁለት በትሮች ተመረጡ፡፡ የአሮን በትር ከእነዚህ መሀል ነበር፡፡
\v 7 ከዚያ ሙሴ እነዚህን በትሮች ወስዶ በያህዌ ፊት በምስክሩ ድንኳን ውስጥ አስቀመጣቸው፡፡
\s5
\v 8 በማግስቱ ሙሴ ወደ ምስክሩ ድንኳን ሄደ፣ እናም የሌዊ ነገድ የሆነችው የአሮን በትር አቆጥቁጣ አየ፡፡ እምቡጥ አብቅላ፣ አበባና ለውዝም አፍርታ ነበር!
\v 9 ሙሴ በትሮቹን ሁሉ ከያህዌ ፊት ወደ እስራኤል ሰዎች ሁሉ አመጣቸው፡፡ እያንዳንዱ ሰው የራሱን በትር አግኝቶ ወሰደ፡፡
\s5
\v 10 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ “የአሮንን በትር በምስክሩ ፊት አስቀምጣት፡፡ ባመፁት ሰዎች ላይ ለበደላቸው ምልክት ይሆን ዘንድ አስቀምጣት፣ ስለዚህም በእኔ ላይ የሚያሰሙትን ማጉረምረም ፍጻሜ ታደርግለታለህ፤ ይህ ካልሆነ ይሞታሉ፡፡”
\v 11 ሙሴ ልክ ያህዌ እንዳዘዘው አደረገ፡፡
\s5
\v 12 የእስራኤል ሰዎች ሙሴን፣ “እኛ ሁላችንም እዚህ መሞታችን ነው፣ ሁላችንም መጥፋታችን ነው!
\v 13 ወደ ያህዌ ማደሪያ ድንኳን የቀረቡ፣ እያንዳንዳቸው ወደዚህ የመጡ ይሞታሉ፡፡ ሁላችንም መጥፋት ይኖርብናልን? ” አሉት፡፡
\s5
\c 18
\p
\v 1 “ያህዌ አሮንን እንዲህ አለው፣ “አንተ፣ ወንዶች ልጆችህና የአባትህ ቤቶች በቤተ መቅደሱ ላይ ለሚሰራው በደል ተጠያቂ ትሆናላች፡፡ በክህነቱ ላይ ለሚፈፀሙ በደሎች ሁሉ ግን አንተና ከአንተ ጋር ያሉ ወንዶች ልጆች ብቻ ተጠያቂ ትሆናላችሁ፡፡
\v 2 ከአባትህ ነገድ የሆኑት ሌዋዊያንን በሚመለከት ከአንተ ጋር ይሆኑና አንተና ልጆችህ በምስክሩ ድንኳን ፊት ስታገለግሉ እንዲረዷችሁ አምጣቸው፡፡
\s5
\v 3 እነርሱ አንተንና መላውን ድንኳን ያገልግሉ፡፡ ሆኖም፣ ወደ ተቀደሰው ስፍራ ማናቸውም ነገሮች አይቅረቡ ወይም ከመሰዊያው ጋር አይነካኩ፣ አለበለዚያ እነርሱና አንተም ጭምር ትሞታላችሁ፡፡
\v 4 እነርሱ ከአንተ ጋር ሆነው ለመገናኛው ድንኳንና ከድንኳኑ ጋር ለተያያዙ ስራዎች ሁሉ እንክብካቤ ማድረግ አለባቸው፡፡ መጻተኛው ወደ አንተ አይጠጋ፡፡
\v 5 አንተ ለተቀደሰው ስፍራና ለመሰዊያው ሀላፊነት መውሰድ አለብህ፣ እንደገና ቁጣዬ በእስራኤል ሰዎች ላይ እንዳይመጣ ይህን አድርግ፡፡
\s5
\v 6 ከእስራኤል ትውልዶች መሀል ሌዋውያንን የመረጥኩት እኔ ራሴ ነኝ፡፡ እነርሱ ከመገናኛው ድንኳን ጋር የተያያዙ ሥራዎችን ለመስራት ለእኔ የተሰጡ ለእናንተ ስጦታዎች ናቸው፡፡
\v 7 ከመሰዊያውና በመጋረጃው ውስጥ ያሉትን አገልግሎቶች ሁሉ በሚመለከት ግን የክህነቱን ስራ የምትሰሩት አንተና ወንዶች ልጆችህ ብቻ ናችሁ፡፡ አንተ ራስህ እነዚያን ሀላፊነቶች መወጣት አለብህ፡፡ እኔ ክህነቱን ስጦታ አድርጌ ሰጥቼሃለሁ፡፡ ማናቸውም መጻተኛ ወደዚህ ቢጠጋ ይገደል፡፡”
\s5
\v 8 ከዚያ ያህዌ አሮንን እንዲህ አለው፣ “ለእኔ የሚወዘወዙትን መስዋዕቶችና የእስራኤል ሰዎች ለእኔ የሰጧቸውን ቅዱስ መስዋዕቶች አያያዝ ሀላፊነቶች ሰጥቼሃለሁ፡፡ እነዚህን ስጦታዎች ቀጣይ ድርሻህ አድርጌ ለአንተና ለወንዶች ልጆችህ ሰጥቻለሁ፡፡
\v 9 ለያህዌ ሙሉ ለሙሉ ከተለዩ ከእነዚህ ስጦታዎች ውስጥ ሙሉ ለሙሉ የማይቃጠሉት የአንተ ናቸው፡፡ ህዝቡ የሚያመጣው ማናቸውም መስዋዕት፣ የእህል ቁርባኑን፣ የኃጢአት መስዋዕቱን፣ እና የበደል መስዋዕቱን ሁሉ ጨምሮ፣ እነዚህ እጅግ ቅዱስ የሆኑ ለእኔ የሚለይዋቸውና የሚያመጧቸው ስጦታዎች የአንተና የወንዶች ልጆችህ ይሆናሉ፡፡
\s5
\v 10 አንተ የምትመገባቸው እነዚህ ስጦታዎች፣ ሙሉ ለሙሉ ለእኔ የተለዩ ናቸው፡፡ በመሀል የሚገኝ ማናቸውም ወንድ እነዚህን ስጦዎች ይብላ፡፡ እነርሱ በእናንተ ዘንድ ለእኔ የተለዩ ተደርገው ይቆጠሩ፡፡
\v 11 እነዚህ የእናንተ ስጦታዎች ናቸው፡፡ ከእስራኤል ሰዎች ከሚሰበሰቡ መስዋዕቶች ውስጥ የተለዩት ስጦታዎቻቸው ሁሉ፣ በእኔ ፊት የተወዘወዙና ለእኔ የቀረቡ ስጦዎች ሁሉ የእናንተ ናቸው፡፡ እነዚህን ለእናንተ፣ ለወንዶች ልጆቻችሁ፣ እና ለሴቶች ልጆቻችሁ፣ ቀጣይ ድርሻችሁ አድርጌ ሰጥቻለሁ፡፡ እያንዳንዱ በቤተሰብህ ውስጥ የመንጻት ሥርዓት የፈፀመ ሁሉ ከእነዚህ ስጦታዎች መመገብ ይቻላል፡፡
\s5
\v 12 ከዘይቱ ምርጥ የሆነውን፣ ከአዲሱ ወይንና ሰብል ምርጡን፣ ህዝቡ ለእኔ ካቀረበው በኩራቱን፣ እነዚህን ሁሉ ለእናንተ ሰጥቻለሁ፡፡
\v 13 ለእኔ የሚያመጡት፣ በምድራቸው ካለው በመጀመሪያ የደረሰው ፍሬ ሁሉ የአንተ ነው፡፡ በቤተሰብህ ውስጥ ያለ ንጹህ የሆነ ሁሉ እነዚህን ነገሮች መብላት ይችላል፡፡
\s5
\v 14 በእስራኤል ማናቸው ፈጽሞ የተሰጠ ነገር የአንተ ይሆናል፡፡
\v 15 እያንዳንዱ ማህጸን የሚከፍት ሁሉ፣ ሰዎች ለያህዌ የሰጡት በኩር ሁሉ፣ የሰውም ይሁን የእንስሳ በኩር የአንተ ይሆናል፡፡ የሆነ ሆኖ፣ ሰዎቹ መጀመሪያ የተወለደውን ሁሉ መልሰው ይግዙ፣ ንጹህ ያልሆኑ እንስሳትን በኩራት መልሰው ይግዙ፡፡
\v 16 በሰዎች ተመልሰው የሚገዙ አንድ ወር ከሞላቸው በኋላ መልሰው ይገዙ፡፡ ከዚያ ሰዎቹ በመቅደሱ ሰቅል ዋጋ መልሰው ከሀያ ጌራ ጋር እኩል ዋጋ ባለው በአምስት ሰቅሎች ዋጋ ሊገዟቸው ይችላሉ፡፡
\s5
\v 17 ነገር ግን የላም በኩር፣ ወይም የበግ በኩር፣ ወይም የፍየል በኩር ከሆነ እነዚህን እንስሳት መልሰህ አትግዛ፤ እነዚህ ለእኔ የተሰዉ ናቸው፡፡ ለእኔ ጣፋጭ መዓዛ ለማቅረብ፣ ደማቸውን በመሰዊያ ላይ እርጨው፣ ስባቸውን በእሳት የቀረበ መስዋዕት አድርገህ ኣቃጥለው፡፡
\v 18 ስጋቸው ለአንተ ይሁን፡፡ ልክ እንደ ሚወዘወዘው ፍርምባና እንደ ቀኙ ወርች ስጋቸው የአንተ ይሆናል፡፡
\s5
\v 19 የእስራኤል ሰዎች ለእኔ ያቀረቧቸውን ቅዱስ የሆኑ መስዋዕቶች ሁሉ እኔ፤ ለአንተ፣ ለወንድ ልጆችህ እና ለሴት ልጆችህ ቀጣይ ድርሻ አድርጌ ሰጥቻችኋለሁ፡፡ ለጨው ኪዳንና ለዘለዓም የአንድነት መስዋዕት ሆነው በፊቴ ከአንተና ከትውልድህ ጋር ይኖራሉ፡፡”
\v 20 ያህዌ አሮንን እንዲህ አለው፣ “አንተ በህዝቡ ምድር ርስት አይኖርህም፣ ወይንም ደግሞ በህዝቡ መሀል የሀብት ድርሻ አይኖርህም፡፡ በእስራኤል ህዝብ መሀል እኔ ድርሻህና ርስትህ ነኝ፡፡
\s5
\v 21 እስራኤላዊያን የሚያመጡትን አስራት ሁሉ፣ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ለሚሰጡት አገልግሎት ድርሻቸው አድርጌ ለሌዊ ትውልድ ሰጥቻቸዋለሁ፡፡
\v 22 ከአሁን አንስቶ ከእስራኤል ህዝቡ ወደ መገናኛው ድንኳን አይቅረብ፣ ከቀረቡ በኃጢአታቸው ሀላፊነትን ይወስዳሉ፤ እናም ይሞታሉ፡፡
\s5
\v 23 ከመገናኛው ድንኳን ጋር የተያያዙ ሥራዎችን ሌዋውያን ይስሩ፡፡ ይህን በሚመለከት ለማናቸውም ኃጢአት ተጠያቂ ይሆናሉ፡፡ ይህ በእናተ ህዝብ ትውልዶች ሁሉ ቀዋሚ ህግ ይሆናል፡፡ በእስራኤል ህዝብ መሀል ሌዋውያን ርስት ሊኖቸው አይገባም፡፡
\v 24 እስራኤላዊያን መባ አድርገው ለእኔ ያቀረቡትን አስራት እኔ ለሌዋውያን ርስታቸው አድርጌ የሰጠሁት እነዚህን ነው፡፡ ለዚህም ነው እንዲህ የምላቸው፣ ‘እነርሱ በእስራኤል ህዝብ መሀል ርስት አይኖራቸውም፡፡’”
\s5
\v 25 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
\v 26 ”ለሌዋውያን እንዲህ በላቸው፣ ‘ከእነርሱ የአንተ ርስት አድርጎ ያህዌ ለእናንተ የሰጣችሁን አስራት ከእስራኤል ሰዎች ስትቀበሉ፣ ከዚያ አስራት ለእርሱ አንድ አስረኛውን መባ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ፡፡
\v 27 እናንተ የምታቀርቡት መስዋዕት በእናንተ ዘንድ ከአውድማ እንደ ቀረበ የእህል አስራት ወይም ከወይን መጥመቂያ እንደ ቀረበ አስራት ሊቆጠር ይገባዋል፡፡
\s5
\v 28 እንደዚሁም ከእስራኤል ሰዎች ከተቀበላችሁት አስራት ሁሉ ለያህዌ መባ ማቅረብ አለባችሁ፡፡ ከእነዚህም ለካህኑ ለአሮን ለእግዚአብሔር ከቀረበው ስጦታ መስጠት አለባች፡፡
\v 29 ከተቀበላችሁት ስጦታ ሁሉ፣ ከእያንዳንዱ ለያህዌ መባ መስጠት አለባችሁ፡፡ ይህንን ምርጥ ከሆነው ሁሉና ለእናንተ ከሰጠኋችሁ እጅግ ከተቀደሱት ነገሮች ማድረግ አለባችሁ፡፡’
\s5
\v 30 ስለዚህም እንደዚህ በላቸው፣ ‘ከተቀበላችሁት ምርጡን ስታቀርቡ፣ ይህ በሌዋውያን ዘንድ ከአውድማ እንደቀረበ ምርትና ከወይን መጥመቂያ እንደቀረበ ሊቆጠር ይገባል፡፡
\v 31 የተቀረውን ስጦታዎቻችሁን በማንኛውም ስፍራ ልትበሉ ትችላላችሁ፣ እናንተና ቤተሰቦቻችሁ ብሉት፣ ምክንያቱም በመገናኛው ድንኳን ለምትሰጡት አገልግሎት ክፍያችሁ ነው፡፡
\v 32 ከተቀበላችሁት ምርጥ የሆነውን ለያህዌ ካቀረባችሁ፣ ያን በመብላታችሁና በመጠጣታችሁ ምንም አይት በደል በራሳችሁ ላይ አታመጡም፡፡ ነገር ግን የተቀደሱ የእስራኤል ህዝቦች ስጦታዎች አታቃሉ፣ አሊያ ትሞታላች፡፡
\s5
\c 19
\p
\v 1 ያህዌ ለሙሴና ለአሮን ተናገረ፤ እንዲህም አለ፣
\v 2 ”ይህ እናንተን የማዛችሁ ትዕዛዝ መታሰቢየ ነው፡፡ የእስራኤል ሰዎች ወደ አንተ ቀንበር ተጭኟት የማታውቅ፣ እንከን ወይም ነውር የሌለባት ቀይ ጊደር እንዲያመጡ ንገራቸው፡፡
\s5
\v 3 ጊደሯን ለካህኑ ለአልዓዛረ ስጠው፡፡ ከሰፈር ውጭ ያውጣት አንድ ሰው በፊቱ ይረዳት፡፡
\v 4 ካህኑ አልአዛር ከጊደሯ ደም በጣቱ ወስዶ በመገናኛው ድንኳን ፊት ባለው አቅጣጫ ሰባት ጊዜ ይርጨው፡፡
\v 5 ሌላ ካህን እርሱ እያየ ጊደሯን ያቃጥላት፡፡ ቆዳዋን፣ ስጋ እና ደሟን ከፈርሷ ጋር ያቃጥል፡፡
\v 6 ካህኑ የዝግባ እንጨት፣ ሂሶጵ፣ እና ደማቅ ሱፍ ይውሰድና ጊደሯ በምትቃጠልበት እሳት ውስጥ ይጨምር፡፡
\s5
\v 7 ከዚየ ልብሱን ይጠብ ሰውነቱንም በውሃ ይታጠብ፡፡ ከዚያ እስከ ምሽት እርኩስ ሆኖ ከቆየበት ወደ ሰፈር መመለስ ይችላል፡፡
\v 8 ጊደሯን ያቃጠለው ሰው ልብሱን በውሃ ይጠብ ገላውንም ይታጠብ፡፡ እስከ ምሽት እርኩስ ሆኖ ይቆያል፡፡
\s5
\v 9 ንጹህ የሆነ አንድ ሰው የጊደሯን አመድ አፍሶ ከሰፈር ውጭ ንጹህ በሆነ ስፍራ ይድፋው፡፡ ይህ አመድ ለእስራኤል ሰዎች ለማህበረሰቡ ይጠበቅ፡፡ አመዱ ከኃጢአት መስዋዕት የተገኘ እንደመሆኑ፣ ከኃጢአት ለመንጻት በውሃ ይበጠብጡታል፡፡
\v 10 የጊደሯን አመድ ያፈሰው ሰው ልብሱን ይጠብ፡፡ እስከ ምሽት እርኩስ ሆኖ ይቆያል፡፡ ይህ ለእስራኤላዊያንና ከእነርሱ ጋር ለሚኖሩ መጻተኞችም ቋሚ ህግ ይሆናል፡፡
\s5
\v 11 ማንም የሞተን ሰው አካል የነካ ሁሉ ለሰባት ቀናት እርኩስ ነው፡፡
\v 12 እንዲህ ያለው ሰው በሶስተኛውና በሰባተኛው ቀን ራሱን ያንጻ፡፡ ከዚያ ንጹህ ይናል፡፡ ነገር ግን በሶስተኛው ቀን ራሱን ካላነጻ፣ በሰባተኛው ቀን ንጹህ አይሆንም፡፡
\v 13 የሞተን ሰው የነካ ማንም ቢሆን፣ የሞተን ሰው የነካ ሁሉ፣ እናም ራሱን ያላነጻ ይህ ሰው የያህዌን ማደሪያ ያረክሳል፡፡ ያ ሰው ከእስራኤል ተለይቶ ይጥፋ፤ ምክንያቱም ከእርኩሰት የሚያነጻው ውሃ አልተረጨበትም፡፡ እርኩስ ሆኖ ይቆያል፣ ያለመንጻቱ በእርሱ ላይ ይቆያል፡፡
\s5
\v 14 አንድ ሰው በድንኳን ውስጥ በሚሞትበት ጊዜ ህጉ ይህ ነው፡፡ ወደ ድንኳኑ የገባ እያንዳንዱ ሰውና ቀድሞውኑም በድንኳኑ ውስጥ የነበረ ሰው ለሰባት ቀናት ንጹህ አይደለም፡፡
\v 15 ያልተከደነና ያልተሸፈነ ማናቸውም ዕቃ ይረክሳል፡፡
\v 16 በተመሳሳይ፣ በሰይፍ የተገደለንም ሰው ሆነ ማናቸውንም በሌላ ሁኔታ የሞተን ሰው፣ ወይም የሞተን ሰው አጽም፣ ወይም መቃብር የነካ ማናቸውም ከድንኳን ውጭ ያለ ሰው ለሰባት ቀናት ንጹህ አደለም፡፡
\s5
\v 17 ለረከሰ ሰው ይህን አድርግ፡ ከተቃጠለው የኃጢአት መስዋዕት ጥቂት አመድ ውሰድና በንጹህ ውሃ በዕቃ ውስጥ በጥብጠው፡፡
\v 18 ንጹህ የሆነ ሰው ሂሶጵ ይውሰድና ውሃው ውስጥ ይንከረው፤ ከዚያም በድንኳኑ ላይ፣ በድንኳኑ ውስጥ ባሉ ዕቃዎች ሁሉ ላይ፣ በዚያ በሚገኙ ሰዎች ላይ፣ እንዲሁም የሞተ ሰውን አጽም፣ የተገደለን ሰው፣ የሞተን ሰው ወይም መቃብር በነካ ሰው ላይ ይርጨው፡፡
\v 19 በሶስተኛው ቀንና በሰባተኛው ቀን፣ ንጹህ የሆነው ሰው ንጹህ ያልሆነውን ሰው ይርጨው፡፡ ያልነጻው ሰው በሰባተኛው ቀን ራሱን ያንጻ፡፡ ልብሱን ይጠብ ገላውንም በውሃ ይታጠብ፡፡ ምሽት ላይ ንጹህ ይሆናል፡፡
\s5
\v 20 ነገር ግን ሳይነጻ የሚቆይ ማናቸው ሰው፣ ራሱን ለማንጻት ያልፈቀደ ሰው ያ ሰው ከማህበረሰቡ ተለይቶ ይጥፋ፣ ምክንቱም የያህዌን መቅደስ አርክሷል፡፡ ከእርኩሰት የሚያነጻው ውሃ በእርሱ ላይ አልተረጨምና እርኩስ ሆኖ ይቆያል፡፡
\v 21 ለእነዚህ ሁኔታዎች ይህ ቀጣይ ህግ ይሆናል፡፡ ለመንጻት የሚሆንን ውሃ የሚረጨው ሰው ልብሶቹን ይጠብ፡፡ የሚያነጻውን ውሃ የሚነካ ሰው እስከ ምሽት ንጹህ አይደለም፡፡
\v 22 ማናቸውም ንጹህ ያልሆነ ሰው የነካው ነገር እርኩስ ይሆናል፡፡ ያንን የነካ ሰው እስከ ምሽት እርኩስ ይሆናል፡፡”
\s5
\c 20
\p
\v 1 የእስራኤል ሰዎች፣ መላው ማህበረሰብ በመጀመሪያው ወር ወደ ሲና ምድረ በዳ ሄደው በቃዴስ ሰፈሩ፡፡ማርያም በዚያ ሞታ ተቀበረች፡፡
\s5
\v 2 ማህበረሰቡ ውሃ ተጠማ፣ ስለዚህ በሙሴና በአሮን ላይ አምጸው ተሰበሰቡ፡፡
\v 3 ህዝቡ በሙሴ ላይ አጉረመረሙ፡፡ እንዲህም አሉ፣ “ወገኖቻችን እስራኤላውያን በያህዌ ፊት በሞቱበት ጊዜ እኛም ብንሞት ኖሮ ይሻል ነበር!
\s5
\v 4 እዚህ እንሞት ዘንድ የያህዌን ማህበረሰብ፣ እኛንና ከብቶቻችንን ለምን ወደዚህ ምድረበዳ አመጣችሁን?
\v 5 ወደዚህ አስፈሪ ስፍራ ልታመጡን ለምን ከግብጽ እንድንወጣ አደረጋችሁን? እዚህ፤ እህል፣ በለስ፣ ወይም ወይም ሮማን የለም፡፡ የሚጠጣም ውሃ የለም፡፡”
\s5
\v 6 ስለዚህ ሙሴና አሮን ከጉባኤው ፊት ወጥተው ሄዱ፡፡ ወደ መገናኛው ድንኳን መግቢያ ሄደው በግምባራቸው ተደፉ፡፡ ከዚያ የያህዌ አንጸባራቂ ክብር ታያቸው፡፡
\s5
\v 7 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
\v 8 “በትርህን ውሰድና አንተና ወንድምህ አሮን ማህበረሰቡን ሰብስቡ፡፡ በፊታቸው ለዓለቱ ተናገር፣ ውሃ እንዲያፈስም አለቱን እዘዘው፡፡ ከዚያ ዓለት ውሃ አውጥተህ ትሰጣቸዋለህ፣ ማህበረሰቡና ከብቶቻቸው ይጠጡ ዘንድ ውሃ ስጣቸው፡፡”
\v 9 ሙሴ ያህዌ እንዳዘዘው ከያህዌ ፊት በትሩን ወሰደ፡፡
\s5
\v 10 ከዚያ ሙሴና አሮን ጉባኤውን በአለቱ ፊት ሰበሰቡ፡፡ ሙሴ ጉባኤውን እንዲህ አለ፣ “እናንተ አመጸኞች፣ አሁን ስሙ፡፡ ከዚህ ዓለት ለእናንተ ውሃ ማውጣት አለብን? ”
\v 11 ከዚያ ሙሴ እጁን አንስቶ በበትሩ አለቱን ሁለት ጊዜ መታው፣ እናም ብዙ ውሃ ወጣ፡፡ ማህበረሰቡ ጠጣ፣ እንዲሁም ከብቶቻቸው ጠጡ፡፡
\s5
\v 12 ከዚያ ያህዌ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፣ “እኔን ስላላመናችሁ ወይም በእስራኤል ሰዎች ዐይኖች ፊት ቅዱስ አድርጋች ስላለያችሁኝ፣ ይህን ጉባኤ ወደ ሰጠኋችሁ ምድር አታስገቧቸውም፡፡”
\v 13 ይህ ቦታ የመሪባ ውሃ ተብሎ ተጠራ፣ ምክንያቱም በዚያ የእስራኤል ሰዎች ከያህዌ ጋር ተጣልተው ነበር፣ እርሱም ራሱን በቅድስናው ገለፀላቸው፡፡
\s5
\v 14 ሙሴ ከቃዴስ መልዕክተኞችን ወደ ኤዶም ንጉስ ላከ፡ ወንድምህ እስራኤል ይህን ይላል፡ “በእኛ ላይ የደረሱትን አስቸጋሪ ነገሮች ታውቃለህ፡፡
\v 15 አባቶቻችን ወደ ግብፅ ወርደው ለዘመናት በግብጽ መኖራቸውን ታውቃለህ፡፡ ግብጻውያን በእኛና በአባቶቻችን ላይ እጅግ ከፉብን፡፡
\v 16 እኛ ወደ ያህዌ ስንጮህ፣ እርሱ ድምጻችንን ሰምቶ መልዓክ ልኮ ከግብጽ አወጣን፡፡ እነሆ፣ በምድርህ ዳርቻ በምትገኘው በቃዴስ እንገኛለን፡፡
\s5
\v 17 በምድርህ እንድናልፍ እንድትፈቅድልን እጠይቅሃለሁ፡፡ በእርሻዎች ወይም በወይን ሥፍራዎች ውስጥ አናልፍም፣ አሊያም ከጉድጓዶቻችሁ ውሃ አንጠጣም፡፡ የንዱን አውራ ጎዳና ይዘን እንሄዳለን፡፡ ድንበርህን እስክናልፍ ድረስ ወደ ግራም ወደ ቀኝም አንልም፡፡”
\s5
\v 18 የኤዶም ንጉስ ግን እንዲህ ሲል መለሰለት፣ “በዚህ በኩል ማለፍ አትችሉም፡፡ ይህን ብታደርጉ፣ ሰይፍ ይዤ እወጣባችኋለሁ፡፡”
\v 19 ከዚያ የእስራኤል ሰዎች እንዲህ አሉት፣ “እኛ በአውራ ጎዳናው እንሄዳለን፡፡ እኛም ሆን ከብቶቻችን ውሃህን ብንጠጣ፣ ለዚያም እንከፍላለን፡፡ ሌላ ምንም ነገር ሳናደርግ በእግራችን እንለፍ፡፡”
\s5
\v 20 የኤዶም ንጉስ ግን እንዲህ ሲል መለሰ፣ “በዚህ በኩል አታልፉም፡፡” ስለዚህም የኤዶም ንጉስ በብርቱ ክንድ አያሌ ወታደሮች ይዞ በእስራኤላዊያን ላይ መጣባቸው፡፡
\v 21 የኤዶም ንጉስ እስራኤላውያን በድንበሩ አቋርጠው እንዳያልፉ ተቃወመ፡፡ በዚህ ምክንያትና እስራኤል ከኤዶም ምድር ተመለሱ፡፡
\s5
\v 22 ስለዚህ ህዝቡ ከቃዴስ ተነስቶ ተጓዘ፡፡ የእስራኤል ህዝብ፣ መላው ማህበረሰብ ወደ ሖር ተራራ መጣ፡፡
\v 23 ያህዌ በሖር ተራራ ለሙሴና አሮን ተናገራቸው፡፡ እንዲህም አለ፣
\v 24 ”አሮን ለእስራኤል ህዝብ ወደ ሰጠኋት ምድር አይገባምና ወደ አባቶቹ ይሰበሰባል፡፡ ይህም የሚሆነው እናንተ ሁለታችሁም በመሪባ ውሃ በእኔ ቃሎች ላይ ስላመፃችሁ ነው፡፡
\s5
\v 25 አሮንንና ልጁን አልዓዛርን ይዘህ ወደ ሖር ተራራ አምጣቸው፡፡
\v 26 የአሮንን የክህነት ልብስ ከእርሱ ላይ አውልቀህ ልጁን አልዓዛርን አልብሰው፡፡ አሮን በዚያ ይሞትና ወደ ወገኖቹ ይሰበሰባል፡፡”
\s5
\v 27 ሙሴ ያህዌ እንዳዘዘው አደረገ፡፡ መላው ማህበረሰብ እያየ ወደ ሖር ተራራ ወጡ፡፡
\v 28 ሙሴ የአሮንን የክህነት ልብሶች ከእርሱ አውልቆ ልጁን አልዓዛርን አለበሰው፡፡ አልዓዛር በተራራው አናት ላይ በዚያ ሞተ፡፡ ከዚያ ሙሴና አልዓዛር ከተራራው ወደ ታች ወረዱ፡፡
\v 29 መላው ማህበረሰብ አሮን እንደ ሞተ ባየ ጊዜ፣ ጠቅላላው አገሩ ለሰላሳ ቀናት ለአሮን አለቀሰ፡፡
\s5
\c 21
\p
\v 1 በኔጌብ የሚኖረው ከነዓናዊው የዓረድ ንጉስ እስራኤል ወደ አታሪም እየመጣ በመንገድ ላይ መሆኑን ሲሰማ፣ ከእስራኤል ጋር ተዋግቶ አንዳንዶቹን በምርኮ ወሰደ፡፡
\v 2 እስራኤል ለያህዌ እንዲህ ብሎ ማለ፣ “በእነዚህ ህዝቦች ላይ ድል ብትሰጠን፣ ከዚያም ከተማቸውን ሙሉ ለሙሉ እናጠፋለን፡፡”
\v 3 ያህዌ የእስራኤልን ድምጽ ሰምቶ በከነዓናዊያን ላይ ድልን ሰጣቸው፡፡ ሙሉ ለሙሉ እነርሱንና ከተማቸውን አጠፉ፡፡ ያ ስፍራ ሖርማ ተብሎ ተጠራ፡፡
\s5
\v 4 ከሖር ተራራ ተነስተው ኤዶም ምድር ዙሪያ ለመድረስ በቀይ ባህር መንገድ ተጓዙ፤ ህዝቡ በመንገድ ሳለ እጅግ ተስፋ ቆረጡ፡፡
\v 5 በእግዚአብሔርና በሙሴ ላይ እንዲህ ሲሉ አጉረመረሙ፡፡ “በበረሃ እንሞት ዘንድ ለምን ከግብጽ አወጣችሁን በዚህ ዳቦ የለም፣ አንዳች ውሃ የለም፣ ደግሞም ይህን የማይረባ ምግብ ጠልተነዋል፡፡”
\s5
\v 6 ከዚያ ያህዌ በሰዎቹ መካከል መርዛም እባቦችን ሰደደ፡፡ እባቦቹ ሰዎችን ነደፉ፤ ብዙ ሰዎችም ሞቱ፡፡
\v 7 ሰዎች ወደ ሙሴ መጥተው እንዲህ አሉ፣ “እኛ በድለናል ምክንያቱም በያህዌና በአንተ ላይ በተቃውሞ ተናግረናል፡፡ እባቦቹን ከእኛ እንዲያርቅ ወደ ያህዌ ጸልይልን፡፡” ስለዚህም ሙሴ ለህዝቡ ጸለየ፡፡
\s5
\v 8 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ “እባብ አብጅና በምሰሶ ላይ አንጠለጠለው፡፡ እንዲህ ይሆናል፣ የተነደፈ ሁሉ ያንን ከተመለከተ ይድናል፡፡”
\v 9 ስለዚህም ሙሴ የናስ እባብ አበጅቶ በምሰሶ ላይ አንጠለጠለው፡፡ እባብ ማናቸውንም ሰው በነከሰ ጊዜ፣ ሰውየው ወደ ናሱ እባብ ከተመለከተ ይድናል፡፡
\s5
\v 10 ከዚያ የእስራኤል ሰዎች ተጉዘው በአቦት ሰፈሩ፡፡
\v 11 ከአቦት ተጉዘው በስተምስራቅ በሞአብ አንጻር በዒዮዓባሪም በምድረ በዳ ሰፈሩ፡፡
\s5
\v 12 ከዚያ ተጉዘው በዘሬድ ሸለቆ ሰፈሩ፡፡
\v 13 ከዚያ ተጉዘው እስከ አሞራዊያን ድንበር በሚዘልቀው በምድረበዳ ባለው በአሮን ወንዝ ሌላኛው ዳርቻ ሰፈሩ፡፡ የአርኖን ወንዝ በሞዐብና አሞራዊያን መሀል የሞአብን ወሰን ያበጃል፡፡
\s5
\v 14 በያህዌ የጦርነት መጽሐፍ ጥቅልል፣ በሱፋ ውስጥ የሚገኘው ዋሄብ እና የአርኖን ሸለቆዎች፣
\v 15 ወደ ዔር ከተማና ወደ ሞአብ ዳርቻ የሚወስዱ የሸለቆዎች ቁልቁለት” ተብሎ የተፃፈው ስለዚህ ነው፡፡
\s5
\v 16 ከዚያ ተነስተው ወደ ብኤር ተጓዙ፣ ይህም ስፍራ የውሃ ጉድጓድ የሚገኝበትና ያህዌ ሙሴን፡ - “ውሃ እሰጣቸው ዘንድ ሰዎቹን በአንድነት ሰብስባቸው” ብሎ የተናገረበት ነው፡፡
\s5
\v 17 ከዚያ እስራኤል ይህን መዝሙር ዘመረ፡፡ “አንተ ምንጭ ሆይ ፍለቅ፡፡ ስለዚህ እናንተም ዘምሩ፡፡
\v 18 መሪዎቻችን የቆፈሩት ጉድጓድ፣ የተከበሩ የህዝብ አለቆች በበትረ መንግስታቸውና በበትሮቻቸው የማሱት ጉድጓድ፡፡” ከዚያ ከምድረበዳው ተነስተው ወደ መቴና ተጓዙ፡፡
\s5
\v 19 ከመቴና ተነስተው ወደ ነሃሊኤል፣ ከነሃሊኤል ወደ ባሞት እና ከባሞት በሞአብ ምድር ወደሚገኘው ሸለቆ ተጓዙ፡፡
\v 20 በፈስጋ ተራራ ጫፍ ሆኖ ምድረበዳው ቁልቁል የሚታይበት ይህ ስፍራ ነው፡፡
\s5
\v 21 ከዚያ እስራኤል ወደ አሞራዊያን ንጉስ ወደ ሴዎን እንዲህ ብለው መልእክተኞችን ላኩ፣
\v 22 ”በምድርህ እንለፍ፡፡ ወደ እርሻዎች ወይም ወደ ወይን አትክልቶች አንገባም፡፡ ከጉድጓዶችህ ውሃ አንጠጣም፡፡ ድንበርህን እስክናልፍ ድረስ በንጉሱ አውራ መንገድ እንጓዛለን፡፡”
\v 23 ንጉስ ሴዎን ግን እስራኤልን በድንበሩ እንዲያልፉ አልፈቀደም፡፡ ይልቁንም፣ ሴዎን ወታደሮቹን አሰባስቦ በምድረ በዳ እስራኤልን ለመውጋት ወጣ፡፡
\s5
\v 24 እስራኤል የሴዎንን ጦር በሰይፍ ወግቶ ከአርኖን እስከ ያቦቅ ወንዝና እስከ አሞን ሰዎች ወሰን ድረስ ምድሩን ወሰደ፡፡ የአሞን ሰዎች ድንበር ግን የተመሸገ ነበር፡፡
\v 25 እስራኤል የአሞራዊያንን ከተሞች ሁሉ፣ ሐስቦንንና መንደሮቹን ጭምር ይዞ በእነዚያ ውስጥ ተቀመጠ፡፡
\v 26 ሐስቦን ከሞአብ የቀድሞ ንጉስ ጋር የተዋጋው የአሞራዊያን ንጉስ የሴዎን ከተማ ነበረች፡፡ ሴዎን እስከ አርኖን ወንዝ ድረስ ያለውን ምድሩን ሁሉ ወሰደበት፡
\s5
\v 27 በምሳሌያዊ ንግግር የተናገሩ፣ “ወደ ሐሴቦን ኑ፡፡ የሴዎን ከተማ እንደ ገና ትገንባና ዳግም ትታነጽ፡፡
\v 28 እሳት ከሐሴቦን ተንቦገቦገ፣ ነበልባል ከሴዎን ከተማ የሞአብን ዔር አጠፉ፣ ደግሞም የአርን ተራሮች ባለቤቶችን በላ፡፡
\s5
\v 29 ሞአብ ዋይታ ሆነብህ! የከሞስ ህዝብ እናንተ ጠፋችሁ፡፡ ለአሞራውያን ንጉስ ለሴዎን ወንዶች ልጆቹን ለሽሽት ሴቶች ልጆቹን ለምርኮ አሳልፎ ሰጥቷል፡፡
\v 30 እኛ ግን ሴዎንን አሸንፈናል፡፡ ሐስቦን እስከ ዴናን ድረስ ወድማለች፡፡ ወደ ሜድባ እስከምታደርሰው ኖፋ ድረስ ሁሉንም አሸንፈናቸዋል፡፡”
\s5
\v 31 ስለዚህ እስራኤል በአሞራዊያን ምድር መኖር ጀመረ፡፡
\v 32 ከዚያ ሙሴ ሰዎችን ምድሪቱን እንደያዙ ወደ ኢያዜር ላከ፡፡ እነርሱ መንደሮቿን ማረኩ በዚያ የነበሩትንም አሞራዊያን አባረሩ፡፡
\s5
\v 33 ከዚያ ወደ ባሳን በሚስደው መንገድ ዞረው ሄዱ፡፡ የባሳን ንጉስ ዐግ በእነርሱ ላይ ዘመተ፣ እርሱና ሰራዊቱ ሁሉ በኤድራይ ሊዋጓቸው ወጡ፡፡
\v 34 በዚያን ጊዜ ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ “እርሱን አትፈራው፣ ምክንያቱም እኔ በእርሱ፣ በሰራዊቱና በምድሩ ላይ ሁሉ ላይ ድል ሰጥቼሃለሁ፡፡ በሔስቦን እንደነበረው በአሞራዊያን ንጉስ በሴዎን ላይ እንዳደረከው በእርሱ ላይ አድርግበት፡፡”
\v 35 ስለዚህም እርሱን፣ ወንዶች ልጆቹን እና መላውን ሰራዊቱን አንድም ሰው በህይወት እስከ ማይተርፍለት ድረስ ፈጇቸው፡፡ ከዚያም ምድሩን ወረሱ፡፡
\s5
\c 22
\p
\v 1 የእስራአል ህዝብ ከከተማዋ ከዮርዳኖስ ወንዝ ሌላ ዳርቻ ኢያሪኮ አጠገብ ወደሚገኘው የሞአብ ሜዳ ደርሰው እስኪሰፍሩ ደረስ ተጓዙ፡፡
\s5
\v 2 የሴፎር ልጅ ባላቅ እስራኤል በአሞራዊያን ላይ ያደረገውን ሁሉ አየ፡፡
\v 3 ሞአብ የእስራኤልን ህዝብ በጣም ፈርቶ ነበር ምክንያቱም ብዙ ነበሩ፣ እናም ሞአብ በእስራኤል ህዝብ ተሸብሮ ነበር፡፡
\v 4 የሞብ ንጉስ ለምድያም ሽማግሌዎች፣ “ይህ ብዙ ህዝብ፣ በሬ በሜዳ ላይ ያለን ሳር በልቶ እንደሚጨርስ በዙሪያችን ያለውን ሁሉ በልቶ ይጨርሳል፡፡” አለ፡፡ በዚያን ጊዜ የሴፎር ልጅ ባላቅ የሞዓብ ንጉስ ነበር፡፡
\s5
\v 5 እርሱም በአገሩና በወገኖቹ መሀል በኤፍራጦስ ወንዝ አጠገብ በፋቱራ ወደተቀመጠው የቢያር ልጅ በልዓም መልዕክተኞችን ላከ፡፡ አስጠርቶትም እንዲህ አለው፣ “እነሆ፣ ከግብጽ አንድ ህዝብ ወደዚህ መጥቷል፡፡ የምድርን ፊት ሸፍነዋል፣ ደግሞም እዚሁ አጠገቤ ናቸው፡፡
\v 6 ስለዚህ አሁን መጥተህ ይህን ህዝብ ርገምልኝ፣ ምክንያቱም ከእኔ አቅም በላይ ናቸው፡፡ ምናልባት ከረገምክልኝ በኋላ እነርሱን ለማጥቃትና ከምድሪቱ ለማባረር እችል ይሆናል፡፡ የባረከው ሁሉ እንደሚባረክ አውቃለሁ፣ የረገምከው ሁሉ እንደሚረገም አውቃለሁ፡፡”
\s5
\v 7 ስለዚህ የሞአብ ሽማግሌዎችና የምድያም ሽማግሌዎች የምዋርቱን ዋጋ ይዘው ሄዱ፡፡ ወደ በለዓም መጥተው የባላቅን ቃል ነገሩት፡፡
\v 8 በለዓምም እንዲህ አላቸው፣ “ዛሬ ምሽት እዚህ እደሩ፡፡ ያህዌ የሚለኝን አሳውቃችኋለሁ፡፡” ስለዚህም የሞብ መሪዎች ያን ምሽት ከበለዓም ዘንድ ተቀመጡ፡፡
\s5
\v 9 እግዚአብሔር ወደ በለዓም መጥቶ እንዲህ አለው፣ “ወደ አንተ የመጡት እነዚህ ሰዎች እነማን ናቸው”
\v 10 በለዓም ለእግዚአብሔር እንዲህ ሲል መለሰለት፣ “የሞአብ ንጉስ የሴፎር ልጅ ባላቅ፣ እነርሱን ወደ እኔ ልኳቸዋል፡፡ እንዲህም አለ፣
\v 11 ‘እነሆ፣ ከግብጽ የመጡ ሰዎች የምድሬን ገጽ ሸፍነዋል፡፡ አሁን መጥተህ እነርሱን ርገምልኝ፡፡ ይህ ከሆነ ምናልባት እነርሱን መዋጋትና ማባረር እችል ይሆናል፡፡”
\s5
\v 12 እግዚአብሔር ለበለዓም እንዲህ መለሰለት፣ “ከእነዚህ ሰዎች ጋር መሄድ የለብህም፡፡ የእስራአልን ህዝብ መርገም የለብህም ምክንያቱም እነርሱ የተባረኩ ናቸው፡፡”
\v 13 በለዓም በጠዋት ተነስቶ ለባላቅ መሪዎች እንዲህ አላቸው፣ “ወደ ምድራችሁ ተመልሳችሁ ሂዱ ምክንያቱም ያህዌ ከእናንተ ጋር እሄድ ዘንድ አልፈቀደልኝም፡፡
\v 14 ስለዚህም የሞብ መሪዎች ተመልሰው ወደ ባላቅ ሂዱ፡፡ እንደህም አሉት፣ “በለዓም ከእኛ ጋር ለመምጣት አልፈቀደም፡፡”
\s5
\v 15 ባላቅ እንደገና ከመጀመሪያዎቹ መልዕክተኞች የከበሩ ብዙ መሪዎችን ላከ፡፡
\v 16 እነርሱም ወደ በለዓም መጥተው እንዲህ አሉት፣ “የሴፎር ልጅ ባላቅ እንዲህ ብሏል፣ ‘እባክህ ወደ እኔ ለመምጣት አንዳች ነገር አያግድህ፣
\v 17 ምክንያቱም እጅግ ከፍ ያለ ክፍያ እከፍልሃለሁ፣ ታላቅ ክብርም እሰጥሃለሁ፣ ደግሞም እንዳደርገው የምትነግረኝን ሁሉ አደርጋሁ፡፡ ስለዚህ እባክህ መጥተህ ይህን ህዝብ ርገምልኝ”
\s5
\v 18 በለዓለም ለባላቅ ሰዎች እንዲህ ሲል መለሰላቸው፣ “ባላቅ ብርና ወርቅ የሞላበትን ቤተ መንግስቱን ቢሰጠኝ እንኳን ከአምላኬ፣ ከያህዌ ቃል አልፌ መሄድ አልችልም፣ ደግሞም እርሱ ከነገረኝ አሳንሼ ወይም ጨምሬ አላደርግም፡፡
\v 19 ስለዚህ አሁን፣ እባካችሁ ያህዌ የሚለኝን ተጨማሪ ነገር አውቅ ዘንድ ዛሬ ምሽትም ደግሞ በዚህ እደሩ፡፡”
\v 20 እግዚአብሔር በምሽት ወደ በለዓም መጥቶ እንዲህ አለው፣ “እነዚህ ሰዎች ወደ አንተ እስከ መጡ ድረስ ተነስተህ ከእነርሱ ጋር ሂድ፡፡ ነገር ግን እንድታደርገው የምነግርህን ብቻ አድርግ፡፡”
\s5
\v 21 በለዓም በጠዋት ተነስቶ አህያውን ጫንና ከሞአብ መሪዎች ጋር ሄደ፡፡
\v 22 ነገር ግን በመሄዱ፣ የእግዚአብሔር ቁጣ ነደደ፡፡ የያህዌ መልአክ፣ በአህያው ላይ ተቀምጦ የሚሄደውን በለዓምን ሊቃወመው በመንገድ ላይ ቆመ፡፡ የበለዓም ሁለቱ አገልጋዮቹም አብረውት ነበሩ፡፡
\v 23 አህያዋ የያህዌን መልአክ የተመዘዘ ሰይፉን ይዞ በመንገድ ላይ ቆሞ አየችው፡፡ አህያዋ ከመንገድ ዘወር ብላ ወደ ሜዳው ሄደች፡፡ በለዓለም አህያይቱን ወደ መንገድ እንድትለስ መታት፡፡
\s5
\v 24 የያህዌ መልአክ በመንገዱ ጠባብ መተላፊያ ላይ በወይን እርሻው መሀል፣ በስተቀኙና በስተግራው ግድግዳ ባለበት ስፍራ ቆመ፡፡
\v 25 አህያይቶ የያህዌን መልአክ አየች፡፡ ወደ ግድግዳው ተጠግታ የበለዓምን እግር አጣበቀችው፡፡ በለዓም እንደገና አህያይቱን መታት፡፡
\s5
\v 26 የያህዌ መልአክ እንደ ገና ራቅ ብሎ ሄዶ ወደ የትኛውም አቅጣጫ መዞሪያ በሌለበት ሌላ ጠባብ መተላፊያ ስፍራ ቆመ፡፡
\v 27 አህያይቱ የያህዌን መልአክ አይታ ከበለዓም በታች ተኛች፡፡ የበለዓም ቁጣ ነደደ፣ በበትሩም አህያይቱን መታት፡፡
\s5
\v 28 ያህዌ የአህያይቱን አፍ ስለከፈተ መናገር ቻለች፡፡ በለዓምን እንዲህ አለችው፣ “እነዚህን ሶስት ጊዜያት እንድትመታኝ የሚያደርግ ምን ነገር አደረግሁብህ”
\v 29 በለዓም አህያይቱን፣ “በእኔ ላይ የማይረባ ድርጊት ስለፈጸምሽ ነው፡፡ በእጄ ላይ ሰይፍ ቢኖር እወድ ነበር፡፡ በእጄ ላይ ሰይፍ ቢኖር ኖሮ፣ ይህን ጊዜ ገድዬሽ ነበር” አላት፡፡
\v 30 አህያይቱ በለዓምን እንዲህ አለችው፣ “እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ ስትቀመጥብኝ የኖርክብኝ አህያህ አይደለሁምን? ከዚህ በፊት እንዲህ ያለ ነገር በአንተ ላይ የማድረግ ልማድ ነበረኝን? ” በለዓም “እይ” አለ፡፡
\s5
\v 31 ከዚያ ያህዌ የበለዓምን ዐይኖች ከፈተ፣ እናም የያህዌ መልአክ በእጁ ሰይፉን ይዞ በመንገዱ ላይ ቆሞ አየ፡፡ በለዓም ዝቅ ብሎ በግምባሩ ተደፋ፡፡
\v 32 የእግዚአብሔር መልአክ እንዲህ አለው፣ “አህያህን ለምን በእዚህ ሶስት ጊዜያት መታሀት የምቃወምህ ሆኜ መጥቻለሁ ምክንያቱም ድርጊቶችህ በፊቴ መጥፎዎች ነበሩ፡፡
\v 33 አህያይቱ አይታኝ በእነዚህ ሶስት ጊዜያት ከእኔ ዞር አለች፡፡ እርሷ ዞር ባትልልኝ ኖሮ፣ በእርግጥ አንተን እገድልህና የእርሷን ነፍስ እተው ነበር፡፡”
\s5
\v 34 በለዓም ለያህዌ መልአክ እንዲህ አለ፣ “እኔ በድያለሁ፡፡ እኔን ተቃውመህ በፊቴ ቆመህ እንደነበር አላወቅሁም፡፡ አሁን እንግዲህ፣ ይህ ጉዞ አንተን ደስ ካላሰኘ፣ ወደመጣሁበት እመለሳለሁ፡፡”
\v 35 የያህዌ መልአክ ግን በለዓምን እንዲህ አለው፣ “ከሰዎቹ ጋር ጉዞህን ቀጥል፡፡ ነገር ግን እኔ የምነግርህን ብቻ መናገር አለብህ፡፡” ስለዚህም በለዓም ከባላቅ መሪዎች ጋር ሄደ፡፡
\s5
\v 36 ባላቅ የበለዓምን መምጣት ሲሰማ፣ ሞአብ ውስጥ ወዳለችው በድንበር ላይ ወደምትገኘው አርኖን ከተማ ሊቀበለው ወጣ፡፡
\v 37 ባላቅ በለዓምን እዲህ አለው፣ “እንዲጠሩህ ሰዎችን ወደ አንተ አልላኩም ነበርን? ለምን ወደ እኔ አልመጣህም? እኔ ላከብርህ አልችልምን?”
\s5
\v 38 ከዚያም በለዓም ለባላቅ መለሰለት፣ “በእርግጥ ወደ አንተ መጥቻለሁ፡፤ አሁን አንዳች ነገር ለመናገር እኔ አንዳች ሀይል አለኝን? መናገር የምችለው እግዚአብሔር በአፌ ላይ ያስቀመጠውን ቃል ብቻ ነው፡፡”
\v 39 በለዓም ከባላቅ ጋር ሄደ፣ እነርሱም ወደ ቂርያት ሐጾት ደረሱ፡፡
\v 40 ከዚያ ባላቅ በሬዎችንና በጎችን ሰዋ፣ ለበለዓምና ከእርሱ ጋር ለነበሩ መሪዎችም ሰጣቸው፡፡
\s5
\v 41 ማለዳ፣ ባላቅ በለዓምን ወደ ካሞት በኣል ይዞት ሄደ፡፡ በለዓም ከዚያ ሆኖ ማየት የሚችለው በሰፈሮቻቸው ካሉት እስኤላዊያን ጥቂቶቹን ብቻ ነበር፡፡
\s5
\c 23
\p
\v 1 በለዓም ባላቅን እንዲህ አለው፣ “በዚህ ሰባት መሰዊያዎችንና ሰባት በሬዎችን እንዲሁም ሰባት አውራ በጎችን አዘጋጅልኝ፡፡”
\v 2 ስለዚህም ባላቅ በለዓም እንደጠየቀው አደረገ፡፡ ከዚያም ባላቅና በለዓም በእያንዳንዱ መሰዊያ ላይ አንድ በሬና አንድ አውራ በግ አቀረቡ፡፡
\v 3 ከዚያ በለዓም ባላቅን እንዲህ አለው፣ “አንተ በሚቃጠል መስዋዕትህ አጠገብ ቁም እኔ እሄዳለሁ፡፡ ምናልባት ያህዌ ሊገናኘኝ ይመጣ ይሆናል፡፡ እርሱ የሚያሳየኝን ሁሉ እነግርሀለሁ፡፡” ስለዚህም በለዓም ዛፎች ወደ ሌሉበት የተራራ ጫፍ ሄደ፡፡
\s5
\v 4 እግዚአብሔር እርሱን ተገናኘው፣ በለዓምም ለእግዚአብሔር እንዲህ አለ፣ “እኔ ሰባት መሰዊያዎችን አበጅቻለሁ፣ ደግሞም በእያንዳንዱ ላይ አንድ በሬና አንድ አውራ በግ አቅርቤያለሁ፡፡”
\v 5 ያህዌ በበለዓም አፍ ላይ መልዕክት አኑሮ እንዲህ አለ፣ “ወደ ባላቅ ተመለስና እንዲህ በለው፡፡”
\v 6 ስለዚህ በለዓም በሚቃጠል መስዋዕቱ አጠገብ ወደቆመው ወደ ባላቅ ከእነርሱ ጋር ወደ ነበሩት የሞአብ መሪዎች ሁሉ ተመለሰ፡፡
\s5
\v 7 ከዚያ በለዓም ትንቢቱን መናገር ጀመረ እንዲህም አለ፣ “ባላቅ እኔን ከአራም አመጣኝ፣ የሞአብ ንጉስ ከምስራቅ ተራሮች አመጣኝ፡፡ ‘ና፣ ያዕቆብን ዕርገምልኝ’ አለኝ፡፡ ‘ና፣ እስራኤልን ተፈታተንልኝ’ አለኝ፡፡
\v 8 እግዚአብሔር ያልረገመውን እኔ እንዴት መርገም እችላለሁ? ያህዌ ያልተቃወማቸውን እኔ እንዴት መቃወም እችላለሁ?
\s5
\v 9 ከአለቶች በላይ ሆኜ አየዋለሁ፣ ከተራሮች ላይ ሆኜ ወደ እርሱ አያለሁ፡፡ ተመልከት፣ ብቻውን የሚኖር ራሱን እንደ ተራ ህዝብ አድርጎ የማይቆጥር ህዝብ አለ፡፡
\s5
\v 10 የያዕቆብን ትቢያ ማን መቁጠር ይችላል ወይም ከእስራኤል ሩቡን እንኳን ማን ይቆጥራል? የጻድቁነ ሞት እኔ ልሙት፣ ደግሞም የህይወቴ መጨረሻ እንደ እርሱ ይሁን!”
\s5
\v 11 ባላቅ በለዓምን እንዲህ አለው፣ “ምን እያደረግክብኝ ነው ጠላቶቼን እንድትረግምልኝ አመጣሁህ፣ ነገር ግን እነሆ አንተ እነርሱን ባረካቸው፡፡”
\v 12 በለዓም መለሰለት እንዲህም አለ፣ “ያህዌ በአፌ ላይ ያደረገውን ብቻ ለመናገር መጠንቀቅ የለብኝምን?”
\s5
\v 13 ስለዚህም ባላቅ እንዲህ አለው፣ “እባክህ ከእኔ ጋር ልታያቸው ወደ ምትችልበት ሌላ ቦታ ና፡፡ ከእነርሱ ሁሉንም ሳይሆን፣ በቅርብ ያሉትን ብቻ ታያለህ፡፡ በዚያ እነርሱን ትረግምልኛለህ፡፡”
\v 14 ስለዚህ በለዓምን ወደ ጾፊም ሜዳ፣ ወደ ፊስጋ ተራራ ጫፍ ይዞት ሄደና ተጨማሪ ሰባት መሰዊያዎችን አበጀ፡፡ በእያንዳንዱ መሰዊያ አንድ በሬና አንድ አውራ ጠቦት ሰዋ፡፡
\v 15 ከዚያ በለዓም ባላቅን እንዲህ አለው፣ “እኔ በዚያ ያህዌን ለመገናኘት ስሄድ፣ አንተ እዚህ በሚቃጠል መስዋዕትህ አጠገብ ቁም፡፡”
\s5
\v 16 ያህዌ በለዓምን ተገናኝቶ በአፉ ምልክት አኖረ፡፡ እንዲህም አለው፣ “ወደ ባላቅ ተመለስና መልዕክቴን ንገረው፡፡”
\v 17 በለዓም ወደ ባላቅ ተመልሶ በሚቃጠል መስዋዕቱ አጠገብ አገኘው፣ የሞአብ መሪዎችም ከእርሱ ጋር ነበሩ፡፡ ባላቅ እንዲህ ሲል ጠየቅ፣ “ያህዌ ምን ነገረህ? ”
\v 18 በለዓም ትንቢቱን መናገር ጀመረ፡፡ እንዲህም አለ፣ “ባላቅ፣ ተነስና አድምጥ፡፡ አንተ የሴፎር ልጅ እኔን አድምጠኝ፡፡
\s5
\v 19 እግዚአብሔር ይዋሽ ዘንድ ሰው አይደለም፣ ወይም ሀሳቡን ይቀየር ዘንድ የሰው ልጅ አይደለም፡፡ ላያደርግ አንዳች ነገር ቃል ይገባልን? ላይፈጽመውስ አንዳች ነገር አደርጋለሁ ይላልን?
\v 20 እነሆ፣ ለመባረክ ታዝዣለሁ፡፡ እግዚአብሔር በረከትን ለቋል፣ እኔ ልከለክል አልችልም፡፡
\s5
\v 21 እርሱ በያዕቆብ ላይ አንዳች ችግር ወይም በእስራኤል ላይ ድካም አላየም፡፡ ያህዌ አምላካቸው ከእነርሱ ጋር ነው፣ የንጉሳቸውም እልልታ ከእነርሱ ጋር ነው፡፡
\v 22 እግዚአብሔር እንደ ጎሽ በሆነ ሀይል ከግብጽ አወጣቸው፡፡
\s5
\v 23 በያዕቆብ ላይ የሚሰራ ምንም አስማት የለም፣ የትኛውም ሟርት እስራኤልን አይጎዳም፡፡ ይልቁንም ስለያዕቆብና ስለ እስራኤል እንዲህ ይባልላቸዋል፣ ‘እግዚአብሔር ያደረገውን እዩ!
\s5
\v 24 እዩ፣ ህዝቡ እንደ እንስት አንበሳ ይነሳል፣ እንደ አንበሳ ተነስቶ ያጠቃል፡፡ ያደነውን እስኪበላ የገደለውን ደም እስኪጠጣ አያርፍም፡፡”
\s5
\v 25 ከዚያ ባላቅ በለዓምን እንዲህ አለው፣ “እነርሱን ባትረግማቸው እንኳን ጨርሰህ አትባርካቸው፡፡”
\v 26 በልዓም ግን ባላቅን መልሶ እንዲህ አለው፣ “እንድናገር ያህዌ የነገረኝን ሁሉ መናገር እንዳለብኝ አልነገርኩህምን? ”
\v 27 ስለዚህም ባላቅ ለበለዓም እንዲህ ሲል መለሰለት፣ “አሁን ና፣ እኔ ወደ ሌላ ስፍራ እወስድሃለሁ፡፡ ምናልባት በዚያ እነርሱን እንድትረግምልኝ እግዚአብሔር ይፈቅድልህ ይሆናል፡፡”
\s5
\v 28 ስለዚህም ባላቅ በለዓምን ምድረበዳውን ቁልቁል ወደሚያይበት ወደ ፌጎር ተራራ ጫፍ ወሰደው፡፡
\v 29 በለዓም ባላቅን እንዲህ አለው፣ “በዚህ ስፍራ ሰባት መሰዊያዎችን አብጅና ሰባት በሬዎች እንዲሁም ሰባት አውራ በጎች አዘጋጅ፡፡”
\v 30 ስለዚህ ባላቅ ባለዓም እንደነገረው አደረገ፤ በእያንዳንዱ መሰዊያ ላይ አንድ በሬና አንድ አውራ በግ ሰዋ፡፡
\s5
\c 24
\p
\v 1 በለዓምም ያህዌ እስራኤልን መባረክ እንደፈቀደ ባየ ጊዜ፣ በሌላ ጊዜ እንደሚያደርገው አስማት ለማድረግ አልወጣም፡፡ ይልቁንም፣ ወደ ምድረበዳው ቁልቁል ተመለከተ፡፡
\s5
\v 2 ዐይኖቹን አቅንቶ እስራኤልን በየነገዱ ሰፍሮ አየ፣ የእግዚአብሔር መንፈስም በእርሱ ላይ መጣ፡፡
\v 3 ይህን ትንቢት ተቀብሎ እንዲህ ሲል ተናገረ፣ “ዐይኖቹ እጅግ የተከፈቱለት የቢዖር ልጅ በለዓም እዲህ ይላል፡፡
\s5
\v 4 እርሱ የእግዚአብሔርን ቃላት ይናገራል ይሰማልም፡፡ እርሱ ሁሉን ቻይ ከሆነው ዘንድ ዐይኖቹ ተከፍተውለት በፊቱ ከሚሰግድለት ዘንድ የሆነውን ራእይን ይመለከታል፡፡
\v 5 ያዕቆብ ሆይ ድንኳኖችህ ምንኛ ያማሩ ናቸው፣ እስራኤል ሆይ መኖሪያዎችህ እንዴት ያምራሉ!
\s5
\v 6 እንደ ሸለቆዎች ተዘርግተዋል፣ በወንዝ ዳር እንዳሉ መናፈሻ ስፍራዎች፣ በያህዌ እንደተተከሉ ሬቶች፣ በውሃ ዳርቻ እንዳሉ ዝግባዎች ናቸው፡፡
\s5
\v 7 ማድጋዎቻቸው በውሃ የተትረፈረፉ ናቸው፣ ሰብላቸው ውሃ አይታጣውም፡፡ ንጉሳቸው ከአጋግ ይበልጣል፣ መንግስታቸው የከበረ ነው፡፡
\s5
\v 8 እግዚአብሔር እርሱን ከግብጽ አውጥቶታል፡፡ እንደ ጎሽ ብርታት አለው፡፡ የሚዋጉትን መንግስታት ይፈጃቸዋል፡፡ አጥንቶቻቸውን ይሰባብራል፡፡ በቀስቶቹ ይወጋቸዋል፡፡
\s5
\v 9 እንደ አንበሳ ይሰባብራቸዋል፣ እንደ ሴት አንበሳ ያደቃቸዋል፡፡ ማን ሊቋቋመው ይችላል? የሚባርኩት ሁሉ ይባረኩ፤ የሚረግሙት ሁሉ የተረገሙ ይሁኑ፡፡”
\s5
\v 10 የባላቅ ቁጣ በበለዓም ላይ ነደደ፣ እጆቹን አጣፍቶ በለዓምን እንዲህ አለው፣ “እኔ ጠላቶቼን እንድትረግምልኝ ጠራሁህ፣ ነገር ግን አንተ ሶስት ጊዜም ባረካቸው፡፡
\v 11 ስለዚህ አሁኑኑ ከእኔ ተለይተህ ወደ ቤትህ ሂድልኝ፡፡ እጅግ አድርጌ አከብርሃለሁ ብዬ ነበር፣ ነገር ግን አንዳች ሽልማት እንዳታገኝ ያህዌ ከለከለህ፡፡”
\s5
\v 12 ከዚያ በለዓም ለባላቅ እንዲህ ሲል መለሰለት፣ “ወደ እኔ ለላካቸው መልዕክተኞች እንዲህ ብያቸው ነበር፣
\v 13 ‘ባላቅ በብርና ወርቅ የተሞላውን ቤተ መንግስቱን ቢሰጠኝ እንኳን፣ ያህዌ ከተናገረው ውጭ አንዳች መጥፎ ወይም መልካም፣ ወይም አንዳች እኔ ላደርግ የምፈልገውን አልናገርም፡፡ መናገር የምችለው ያህዌ ተናገር ያለንን ብቻ ነው፡፡’ ይህን ለእነርሱ አልተናገርኩምን?
\v 14 ስለዚህ እነሆ አሁን ወደ ህዝቤ እመለሳለሁ፡፡ ነገር ግን አሁን በቅድሚያ ይህ ህዝብ በሚመጡት ቀናት በአንተ ህዝብ ላይ ሊያደርግ ያለውን ላስጠንቅህ፡፡”
\s5
\v 15 በለዓም ይህን ትንቢት መናገር ጀመረ፣ “ዐይኖቹ እጅግ የተከፈቱለት የቢዖር ልጅ በልዓም ይህን ናገራል፡፡
\v 16 ይህ ከእግዚአብሔር ዘንድ ቃል የሚሰማ ሰው ትንቢት ነው፣ ከልዑል ዘንድ ዕውቀት ከተሰጠው፣ ሁሉን ቻይ ከሆነው አምላክ ራዕይ ከተቀበለው፣ በተከፈተ ዐይን በፊቱ ከሚሰግደው፣ ሰው የተነገረ ትንቢት ነው፡፡
\s5
\v 17 እኔ እርሱን አያለሁ፣ ነገር ግን እርሱ አሁን እዚህ አይደለም፡፡ እኔ እርሱን እመለከታለሁ፣ ነገር ግን እርሱ በቅርብ አይደለም፡፡ ኮከብ ከያዕቆብ ይወጣል፣ በትረ መንግስት ከእስራኤል ይነሳል፡፡ እርሱ የሞአብን መሪዎችን ይበታትናል፣ የሴትንም ትውልዶች ያጠፋል፡፡
\s5
\v 18 ከዚያ እስራኤል በሃይል ድል የሚነሳው ኤዶም፤ የእስራኤል ርስት ይሆናል፣ ደግሞም የእስራኤል ጠላት የሆነው ሴይር፣ የእነርሱ ርስት ይሆናል፣
\v 19 ከያዕቆብ ግዛት ያለው ንጉስ ይወጣል፣ እርሱም ከከተማቸው የተረፉትን ቅሬታዎች ያጠፋል፡፡”
\s5
\v 20 ከዚያ በለዓም አማሌቅን ተመልክቶ ትንቢት መናገር ጀመረ፡፡ እንዲህም አለ፣ “አማሌቅ ታላቅ ህዝብ ነበር፣ነገር ግን መጨረሻው ጥፋት ይሆናል፡፡”
\s5
\v 21 ከዚያ በለዓም ወደ ቄናውያን ተመልክቶ ትንቢቱን ጀመረ፡፡ እንዲህም አለ፣ “የምትኖርበት ስፍራ አስተማማኝ ነው፣ ጎጆችህም በአለቶች መሀል ነው፡፡
\v 22 ሆኖም ግን እናንተ ቄናውያን አሶር ምርኮ አድርጎ ሲወስዳችሁ ትደመሰሳላችሁ፡፡”
\s5
\v 23 ከዚያ በለዓም የመጨረሻውን ትንቢቱን መናገር ጀመረ፡፡ እንዲህም አለ፣ “አወይ! እግዚአብሔር ይህን ሲያደርግ ማን ይተርፋል?
\v 24 መርከቦች ከኪቲም ዳርቻዎች ይመጣሉ፤ አሶርን ያጠቃሉ ዔቦርን ይይዛሉ፣ ነገር ግን እነርሱም ደግሞ መጨረሻቸው መደምሰስ ነው፡፡
\v 25 ከዚያ በለዓም ተነስቶ ሄደ፡፡ ወደ ቤቱ ተመለሰ፣ ባላቅም ተነስቶ ሄደ፡፡
\s5
\c 25
\p
\v 1 እስራኤል በሰጢም ተቀመጠ፣ ወንዶቹም ከሞዓብ ሴቶች ጋር ተኙ፣
\v 2 ይህም ሞአባዊያኑ ህዝቡን ለእነርሱ አማልዕክት የተሰዋውን ስለጋበዟቸው ነው፡፡ ስለዚህ ህዝቡ ለጣኦት የተሰዋውን በሉ ደግሞም ለሞአባውያን አማልዕክት ሰገዱ፡፡
\v 3 የእስራኤል ወንዶች የፌጎርን በኣል በማምለክ ተባበሩ፣ እናም የያህዌ ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፡፡
\s5
\v 4 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ “ብርቱ ቁጣዬ ከእስራኤል ይርቅ ዘንድ የህዝቡን መሪዎች ሁሉ ግደልና እነርሱን በቀን ብርሃን ለማጋለጥ ስቀላቸው፡፡”
\v 5 ስለዚህም ሙሴ ለእስራኤል መሪዎች እንዲህ አለ፣ “እያንዳንዳችሁ የፌጎርን በኣል በማመልክ የተባበሩትን ሰዎቻችሁን ግደሉ፡፡”
\s5
\v 6 ከዚያ ከእስራኤል ወንዶች አንዱ ቀርቦ ከቤተሰቡ አባላት ጋር አንዲት ምድያማዊት ሴት አመጣ፡፡ ሙሴና መላው የእስራኤል ህዝብ እያዩ በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ሆነው እያለቀሱ ሳለ ይህ ሆነ፡፡
\v 7 የአሮን ልጅ፣ የአልዓዛር ልጅ ካህኑ ፊንሀስ ይህን ሲመለከት፣ ከማህበሩ መሀል ጦሩን በእጁ ይዞ ተነሳ፡፡
\s5
\v 8 እርሱም ወደ ድንኳኑ እስራኤላዊውን ሰው ተከትሎ ገብቶ የእስራኤላዊውን ወንድና የምድያማዊቷን ሴት የሁለቱንም አካላት በአንድነት በጦሩ ወጋ፡፡ ስለዚህም እግዚአብሔር በእስራኤል ህዝብ ላይ የላከው መቅሰፍት አቆመ፡፡
\v 9 በመቅሰፍቱ የሞቱት በቁጥር ሃያ አራት ሺ ነበሩ፡፡
\s5
\v 10 ያህዌ ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፣
\v 11 “ካህኑ፣ የአሮን ልጅ የአልአዛር ልጅ ፊንሀስ፣ ቁጣዬን ከእስራኤል ህዝብ አርቋል ምክንያቱም በእነርሱ መሃል የእኔን ቅንአት ቀንቷል፡፡ ስለዚህ የእስራኤልን ህዝብ በቁጣዬ ፈጽሞ አላጠፋኋቸውም፡፡
\s5
\v 12 ስለዚህ እንዲህ በል፣ ‘ያህዌ እንዲህ ይላል፣ “እነሆ፣ ለፊንሐስ የሰላሜን ኪዳን እሰጠዋለሁ፡፡
\v 13 ለእርሱና ከእርሱ በኋላ ለትውልዱ፣ ዘለዓለማዊ የክህነት ኪዳን ይሆናል፤ ምክንያቱም እርሱ ለእኔ ለአምላኩ ለእግዚአብሔር ቀንቷል፡፡ ለእስራኤል ህዝብ አስተሰርይዋል፡፡”
\s5
\v 14 ከምድያማዊቷ ሴት ጋር የተገደለው የእስራኤላዊ ሰው የሰሉ ልጅ ስም ዘንበሪ ሲባል፣ የስምኦናውያን አባቶች ቤተሰብ መሪ ነበር፡፡
\v 15 የተገደለችው የምድያም ሴት ስም ከስቢ ነበር፣ እርሷም ከምድያም ቤተሰብ የጎሳው መሪ የሱር ሴት ልጅ ነበረች፡፡
\s5
\v 16 ስለዚህም ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
\v 17 ”ምድያማዊያንን እንደ ጠላት ቆጥራችሁ አጥፏቸው፣
\v 18 እነርሱ በአታላይነታቸው እንደ ጠላት አስተናግደዋችኋልና፡፡ በፌጎር በሆነውና በእናታቸው በከስቢ ጉዳይ በፌጎር ምክንያት በመቅሰፍቱ ቀን በተገደለችው በምድያም አለቃ ልጅ ወደ ክፉ መርተዋችኋል፡፡”
\s5
\c 26
\p
\v 1 ከመቅሰፍቱ በኋላ እንዲህ ሆነ፣ ያህዌ ለሙሴና ለካህኑ ለአሮን ልጅ ለአልዓዛር እንዲህ አላቸው፡፡
\v 2 “የእስራኤልን ማህበረሰብ ሁሉ ቁጠሩ፣ ሀያ አመትና ከዚያ በላይ ዕድሜ ያላቸውን፣ ለእስራኤል ለመዋጋት ወደ ጦርነት መውጣት የሚችሉትን ሁሉ በየአባቶቻቸው ቤቶች ቁጠሯቸው፡፡”
\s5
\v 3 ስለዚህም ሙሴና ካህኑ አልዓዛር በሞአብ ሜዳ በዮርዳኖስ አጠገብ ኢያሪኮ ሳለ ለህዝቡ እንዲህ ሲሉ ተናገሩ፣
\v 4 “ከሃያ አመት ጀምሮ ከዚያ በላይ ዕድሜ ያላቸውን ከግብጽ ምድር የወጡትን ያህዌ ሙሴንና የእስራኤል ሰዎችን እንዳዘዘው ሁሉ ቁጠሯቸው፡፡”
\s5
\v 5 ሮቤል የእስራኤል በኩር ነበር፡፡ ከወንድ ልጁ ከሄኖክ የሄኖካውያን ጎሳዎች መጡ፡፡ ከፈለስ የፈለሳውያን ጎሳ መጡ፡፡
\v 6 ከአስሮን የአስሮናውያን ጎሳ መጡ፡፡ ከከርሚ የከርማውያን ጎሳ መጡ፡፡
\v 7 እነዚህ የሮቤል ጎሳ ትውልዶች ነበሩ፣ ቁጥራቸው 43730 ወንዶች ነበሩ፡፡
\s5
\v 8 ኤልያብ የፈሉስ ልጅ ነበር፡፡
\v 9 የኤልያብ ወንዶች ልጆች ነሙኤል፣ ዳታን፣ እና አቤሮን ነበሩ፡፡ እነዚህ ቆሬን ተከትለው ሙሴንና አሮንን በመቃወም በያህዌ ላይ ያመጹት እነዚያው ዳታንና ኤብሮን ነበሩ፡፡
\s5
\v 10 ሁሉም የእርሱ ተከታዮች ሲሞቱ፣ ምድር አፏን ከፍታ ከቆሬ ጋር ሁሉንም በአንድነት ዋጠቻቸው፡፡ በዚያ ጊዜ፣ በእሳት መቀጣጫ የሆኑትን 250 ወንዶችን በላች፡፡
\v 11 ነገር ግን የቆሬ የዘር ሀረግ አልጠፋም፡፡
\s5
\v 12 የስምዖን ትውልዶች እዚህ ነበሩ፡ በነሙኤል በኩል፣ የነሙኤላውያን ጎሳ፣ በያሚን በኩል፣ የያሚናውያን ጎሳ፣ በያኪን በኩል የያኪናውያን ጎሳ፣
\v 13 በዛራ በኩል የዛራውያን ጎሳ፣ በሳኡል በኩል የሳኡላውያን ጎሳ ነበሩ፡፡
\v 14 እነዚህ የስምዖን ጎሳ ትውልዶች ነበሩ፣ ቁጥራቸው 22200 ወንዶች ነበሩ፡፡
\s5
\v 15 የጋድ ጎሳ ትውልዶች እነዚህ ነበሩ፡ በጽፎን በኩል የጽፎናውያን ጎሳ፣ በሐጊ በኩል የሐጋውያን ጎሳ፣ በሺኒ በኩል፣ የሺናውያን ጎሳ፣
\v 16 በኤስና በኩል፣ የኤሶናውያን ጎሳ፣ በዔሪ በኩል የዔራውያን ጎሣ፣
\v 17 በአሮዲ በኩል የሮዳውያን ጎሳ፣ በአርኤሊ በኩል፣ የአርኤላውያን ጎሳ፡፡
\v 18 እነዚህ የጋድ ጎሳ ትውልድ ነበሩ፣ ቁጥራቸው 40500 ወንዶች ነበሩ፡፡
\s5
\v 19 የይሁዳ ልጆች ዔር እና አውናን ነበሩ፣ እነዚህ ወንዶች ግን በከነዓን ምድር ሞተዋል፡፡
\v 20 የይሁዳ ጎሳ ሌሎች ትውልዶች እነዚህ ነበሩ፣ በሴሎም በኩል፣ የሴሎማውያን ጎሳ፣ በፋሬስ በኩል፣ የፋሬሳውያን ጎሳ፣ እና በዛራ በኩል የዛራውያን ጎሳ ነበሩ፡፡
\v 21 የፋሬስ ትውልዶች እነዚህ ነበሩ በኤስሮም በኩል የኤስሮማውያን ጎሳ፣ በሐሙል በኩል፣ የሐሙላውያን ጎሳ፡፡
\v 22 እነዚህ የይሁዳ ጎሳ ትውልዶች ነበሩ፣ ቁጥራቸው 76500 ነበሩ፡፡
\s5
\v 23 የይሳኮር ጎሳዎች ትውልዶች እነዚህ ነበሩ፡፡ በቶላ በኩል የቶላውያን ጎሳ፣ በፋዋ በኩል ቦፋውያን ጎሳ፣
\v 24 በያሱብ በኩል፣ የያሱባውዩን ጎሳ፣ በሺምሮን በኩል፣ የሺምሮናውያን ጎሳ፡፡
\v 25 እነዚህ የይሳኮር ጎሳዎች ነበሩ፣ ቁጥራቸው 64300 ወንዶች ነበሩ፡፡
\s5
\v 26 የዛብሎን ጎሳዎች ትውልዶች እነዚህ ነበሩ፡፡ በሴሬድ በኩል የሴሬዳውያን ጎሳ፣ በኤሎን በኩል የኤሎናውያን ጎሳ፣ በያህልኤል በኩል የያህልኤላውያን ጎሳ፡፡
\v 27 እነዚህ የዛብሎን ጎሳዎች ነበሩ፣ ቁጥራቸው 60500 ወንዶች ነበሩ፡፡
\s5
\v 28 የዮሴፍ ጎሳ ትውልዶች ምናሴና ኤፍሬም ነበሩ፡፡
\v 29 የምናሴ ትውልዶች እነዚህ ነበሩ፡ በማኪር በኩል፣ የማኪራውያን ጎሳ (ማኪር የገለዓድ አባት ነበር) ፣ በገለዓድ በኩል፣ የገለዓዳውያን ጎሳ ነበሩ፡፡
\s5
\v 30 ትውልዶች እነዚህ ነበሩ፡ በኢዔዝር በኩል የኢዔዝራውያን ጎሳ፣ በኬሌግ በኩል የኬሌጋውያን ጎሳ፣
\v 31 በእስራኤል በኩል የእስራኤላውያን ጎሳ፣ በሴኬም በኩል፣ የሴካማውያን ጎሳ፣
\v 32 በሸሚዳ በኩል፣ የሸሚዳውያን ጎሣ፣ በኦፌር በኩል የኦፌራውያን ጎሣ፣
\s5
\v 33 ልጅ ሰለጳዓድ ወንዶች ልጆች አልነበሩትም፣ ነገር ግን ሴቶች ልጆች ብቻ ነበሩት፡፡ የሴት ልጆቹ ስሞች እነዚህ ነበሩ፡ ማህለህ፣ ኑዓ፣ ዔግሳ፣ ሚልካና ቲርዳ፡፡
\v 34 እነዚህ የምናሴ ጎሳዎች ነበሩ፣ ቁጥራቸው 52700 ወንዶች ነበሩ፡፡
\s5
\v 35 የኤፍሬም ጎሳዎች ትውልዶች እነዚህ ነበሩ፡ በሲቱላ በኩል፣ የሱቱላውያን ጎሣ፣ በቤኬር በኩል የቤኬራውያን ጎሣ፣ በታሐን በኩል፣ የታሐናውያን ጎሣ ነበሩ፡፡
\v 36 የሱቱላ ትውልዶች እነዚህ ነበሩ፡ በዔዴን በኩል፣ የዔዴናውያን ጎሣ ነበሩ፡፡
\v 37 እነዚህ የኤፍሬም ጎሣ ትውልዶች ነበሩ፡ ቁጥራቸው 32500 ወንዶች ነበሩ፡፡ እነዚህ የዮሴፍ ትውልዶች፣ በየጎሣቸው ተቆጠሩ፡፡
\s5
\v 38 የብንያም ጎሣ ትውልዶች እነዚህ ነበሩ፡ በቤላ በኩል፣ የቤላውያን ጎሣ፣ በአስቤል በኩል የአስቤላውያን ጎሣ፣ በኢኪራን በኩል፣ የኢኪራናውያን ጎሣ፣
\v 39 በሶፋን በኩል፣ የሶፋናውያን ጎሣ፣ በሑፋም በኩል፣ የሑፋፋማውያን ጎሣ ነበሩ፡፡
\v 40 የቤላ ወንዶች ልጆች አርድ እና ናዕመን ነበሩ፡፡ ከአርድ የአርዳውያን ጎሣ መጣ፣ ከናዕማን የናዕመናውያን ጎሣ መጣ፡፡
\v 41 የብንያም ጎሣ ትውልዶች እነዚህ ነበሩ፡፡ ቁጥቸው 45600 ወንዶች ነበሩ፡፡
\s5
\v 42 የዳን ትውልዶች እነዚህ ነበሩ፡ በስምዔ በኩል፣ የስምዔያናውያን ጎሣዎች ነበሩ፡፡ እነዚህ የዳን ትውልድ ጎሣዎች ነበሩ፡፡
\v 43 የስምዔያውያን ጎሣዎች በጠቅላላ 64400 ወንዶች ነበሩ፡፡
\s5
\v 44 የአሴር ትውልድ ጎሣዎች እነዚህ ነበሩ፡ በዩምና በኩል የዩምናውያን ጎሣ፣ በዩሱዋ በኩል፣ የየሱዋውያን ጎሣ፣ በበሪዓ በኩል፣ የበሪዓውያን ጎሣ ነበሩ፡፡
\v 45 የብንያም ትውልዶች እነዚህ ነበሩ፡ በሔቤር በኩል፣ የሔቤራውያን ጎሣ፣ በመልኪኤል በኩል የመልኪኤላውያን ጎሣ ነበሩ፡፡
\v 46 የአሴር ሴት ልጅ ስም ሤራህ ነበር፡፡
\v 47 እነዚህ የአሴር ጎሣ ትውልዶች ነበሩ፣ ቁጥራቸው 53400 ወንዶች ነበር፡፡
\s5
\v 48 የንፍታም ጎሣ ትውልዶች እነዚህ ነበሩ፡ በያሕድኤል በኩል፣ የያህጽኤላውያን ጎሣ፣ በጉኒ በኩል፣ የጉናውያን ጎሣ፣
\v 49 በሺሌም በኩል፣ የሺሌማውያን ጎሣ ነበሩ፡፡
\v 50 እነዚህ የንፍታሌም ጎሣ ትውልዶች ነበሩ፣ ቁጥራቸው 45400 ወንዶች ነበር፡፡
\s5
\v 51 ይህ በእስራኤል ህዝብ መሃል ጠቅላላው የወንዶች ቁጥር ነበር፡፡በጠቅላላው 601730 ነበሩ፡፡
\s5
\v 52 ያህዌ ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፣
\v 53 “ምድሪቱ በእነዚህ ሰዎች መሃል ርስት ሆኖ እንደ ስሞቻቸው ቁጥር መሰረት ትከፋፈል፡፡
\s5
\v 54 ብዙ ቁጥር ላለው ጎሳ ሰፋ ያለውን ርስት ስጥ፣ አነስተኛ ቁጥር ላላቸው ጎሣዎች አነስ ያለውን ርስት ስጣቸው ለእያንዳንዱ ቤተሰብ እንደ ተቆጠረው ወንድ ብዛት ርስት ስጣቸው፡፡
\v 55 ሆኖም ምድሪቱ በዕጣ ትከፋፈል፡፡ ምድሪቱን በየአባቶቸው ጎሳዎች መሀል እንደምትከፋፈል ይወርሷት፡፡
\v 56 ርስታቸው በየጎሳው ብዛትና አነስተኛት መጠን ይከፋፈል፣ ክፍፍሉ በዕጣ ይሁን፡፡”
\s5
\v 57 በየነገዳቸው የተቆጠሩት የሌዋውያን ነገዶች እነዚህ ነበሩ፡ በጌድሶን በኩል፣ የጌድሶናውያን ጎሣ፣ በቀዓት በኩል፣ የቀዓታውያን ጎሣ፣ በሜራሪ በኩል፣ የሜራርያውን ጎሣ ነበሩ፡፡
\v 58 የሌዊ ጎሳዎች እነዚህ ነበሩ፡ የሊብናውያን ጎሣ፣ የኬብሮናውያን ጎሣ፣ የሞሐላውያን ጎሣ፣ የሙሳውያን ጎሣ፣ እና የቆሬያውያን ጎሣ ነበሩ፡፡ ቀዓት የእንበረም የዘር ሀረግ ነበር፡፡
\v 59 የእንበረም ሚስት ስሟ ዮካብድ ነበር፣ ከሌዋውያን ወገን ግብጽ ውስጥ የተወለደች ነበረች፡፡ ከእንበረም ልጆቻቸውን አሮንን፣ ሙሴን እና እህታቸውን ማርያምን ወለደች፡፡
\s5
\v 60 ለአሮን የተወለዱለት ናዳብ እና አብዩድ፣ ኤልዓዛር እና ኢታምር ነበሩ፡፡
\v 61 ናዳብና አብዩድ ያህዌ በፊቱ ተቀባይነት የሌለውን የእሳት መስዋዕት ሲያቀርቡ ሞቱ፡፡
\v 62 አንድ ወርና ከዚያ በላይ ዕድሜ ያቸው ሌዋውያን ወንዶች ቁጥር ሃያ ሶስት ሺ ነበር፡፡ ነገር ግን ከእስራኤል ትውልዶች ጋር አብረው አልተቆጠሩም፡፡ ምክንያቱም ለእነርሱ በእስራኤል ሕዝብ መሃል ምንም ርስት አልተሰጣቸውም ነበር፡፡
\s5
\v 63 በሙሴና በካህኑ አልዓዛር የተቆጠሩት እነዚህ ናቸው፡፡ በሞአብ ሜዳ በዮርዳኖስ ኢያሪኮ ውስጥ የእስራኤልን ህዝበ ቆጠሩ፡፡
\v 64 የእስራአል ትውልዶች በሲና ምድረ በዳ በተቆጠሩ ጊዜ በእነዚህ መሀል በሙሴና በካህኑ በአልዓዛር የተቆጠረ ሌላ ሰው ግን አልነበረም፡፡
\s5
\v 65 ያህዌ እነዚያ ሰዎች ሁሉ በእርግጥ በምድረበዳ እንደሚሞቱ ተናግሮ ነበር፡፡ ከዩፎኒ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በስተቀር ከመሀላቸው በህይወት የተረፈ አንድም ሰው አልነበረም፡፡
\s5
\c 27
\p
\v 1 ከዚያ ከዮሴፍ ልጅ ለምናሴ ነገድ የአፌር ወንድ ልጅ የገለአድ ወንድ ልጅ የማኪር ወንድ ልጅ የምናሴ ወንድ ልጅ የሰለጵዓድ ሴት ልጆች ወደ ሙሴ መጡ የሰለዓድ ሴት ልጆች ስሞች እነዚህ ነበሩ፡፡ ማህላህ፣ ኑዓ፣ ዔግላ፣ ሚልካና ቲርጳ፡፡
\s5
\v 2 እነርሱም በሙሴ፣ በካህኑ አልዓዛር፣ በመሪዋች፣ እና በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ በመላው ማህበረሰቡ ፊት ቆሙ፡፡ እንዲህም አሉ፣
\v 3 “አባታችን በምድረበዳው ሞተ፡፡ እርሱ በቆሬ አመጽ በያህዌ ፊት አምጸው በአንድነት ከተነሱት መሀል አልነበረም፡፡ የሞተው በራሱ ኃጢአት ነበር፣ አባታችን የሞተው በራሱ ኃጢአት ምክንያት ነበር፡፡
\s5
\v 4 ስለምን ወንድ ልጅ ስለሌለው የአባታችን ስም ከጎሳው አባላት ተለይቶ ይጠፋል? በአባታችን ቤተዘመዶች መሀል መሬት ስጠን፡፡”
\v 5 ሙሴ ጉዳያቸውን ያህዌ ፊት አቀረበ፡፡
\s5
\v 6 ያህዌ ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፣
\v 7 ”የሰለጰዓድ ሴት ልጆች የተናገሩት ትክክል ነው፡፡ በአባታቸው ዘመዶች መሃል በእርግጥ ርስት አድርገህ መሬት ስጣቸው፣ ደግሞም የአባታቸው ርስት ወደ እነርሱ መተላፉን አረጋግጥ፡፡
\v 8 ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ በላቸው፣ ‘አንድ ሰው ወንድ ልጅ ሳይኖው ቢሞት፣ ርስቱ ወደ ሴት ልጁ እንዲተላፍ አድርጉ፡፡
\s5
\v 9 ሴት ልጅ ባይኖረው፣ ርስቱን ለወንድሞቹ ስጡ፡፡
\v 10 ወንድሞች ባይኖት፣ ርስቱን ለአባቱ ወንድሞች ስጡ፡፡
\v 11 አባቱ ወንድሞች ባይኖሩት ርስቱን በጎሳው ውስጥ ለቅርብ ዘመዱ ስጡ፣ ያም ሰው ይውሰደው፡፡ ይህም ያህዌ እንዳዘዘኝ፣ ለእስራኤል ህዝብ በአዋጅ የፀና ህግ ይሆናል፡፡’”
\s5
\v 12 “ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ “ወደ ዓባሪም ተራሮች ወጥተህ ለእስራኤል ህዝብ የሰጠሁትን ምድር ተመልከት፡፡
\v 13 ከተመለከትካት በኋላ፣ አንተም ደግሞ ወደ ሰዎችህ እንደ ወንድምህ አሮን ሁሉ ትሰበስባለህ፡፡
\v 14 ይህ ይሆናል፤ ምክንያቱም በጺን ምድረበዳ እናንተ ሁለታችሁ በትእዛዛቶቼ ላይ አምጻችኋል፡፡ በዚያ፣ ውሃው ከአለቱ ሲፈስስ በቁጣህ ምክንያት በመላው ማህበረሰብ ዐይኖች ፊት እኔን በቅድስና ማክበር አልቻልክም፡፡” ይህ በጺን ምድረበዳ በቃዴስ የሚገኝ የመሪባ ውሃ ነው፡፡
\s5
\v 15 ከዚያ ሙሴ ለያህዌ እንዲህ አለ፣
\v 16 “የሰዎች ሁሉ መንፈስ አምላክ ያህዌ ሆይ፣ በዚህ ማህበረሰብ ላይ መሪ የሚሆን ሰው ሹም፣
\v 17 በፊታቸው የሚወጣና የሚገባ ሰው፣ እየመራ የሚያስወጣቸውና የሚያስገባቸው፣ ህዝብህ እረኛ እንደሌላቸው በጎች እንዳይሆን ሰው ሹምለት፡፡”
\s5
\v 18 ያህዌ ሙሴን፣ “የእኔ መንፈስ የሚኖርበትን፣ የነዌን ልጅ ኢያሱን ውሰድና እጆችህን በእርሱ ላይ ጫን፡፡
\v 19 በካህኑ አልዓዛር ፊትና በመላው ማህበረሰብ ፊት አቁመህ እንዲመራቸው በፊታቸው ሹመው፡፡
\s5
\v 20 ከአንተ ስልጣን በእርሱ ላይ አድርግ፣ ስለዚህም መላው የእስራኤል ማህበረሰብ እርሱን ይታዘዙታል፡፡
\v 21 እርሱም በኡሪም በመጠየቅ ፍቃዴን ለማወቅ በካህኑ አልዓዛር ፊት ይሄዳል፡፡ ህዝቡ፣ እርሱና ከእርሱ ጋር መላው የእስራኤል ሰዎች፣ መላውም ማህበረሰብ የሚወጣውና የሚገባው በእርሱ ትዕዛዝ ይሆናል፡፡
\s5
\v 22 ስለዚህም ሙሴ ያህዌ እርሱን እንዳዘዘው አደረገ፡፡ ኢያሱን ወስዶ በካህኑ አልዓዛርና በመላው ማህበር ፊት አቆመው፡፡
\v 23 ያህዌ እንዲያደርግ እንዳዘዘው ሁሉ እጆቹን በላዩ ጫነና እንዲመራ ሾመው፡፡
\s5
\c 28
\p
\v 1 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
\v 2 ”የእስራኤል ሰዎችን እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፣ ‘በወቅቱ ለእኔ መስዋዕቶችን አቅርቡ፣ ለእኔ ጣፋጭ መዓዛ ያለው በእሳት የተበጀ መስዋዕት ለእኔ አቅርቡልኝ፡፡’
\s5
\v 3 ደግሞም እንዲህ በላቸው፣ ‘ይህ ለያህዌ የምታቀርቡት የእሳት መስዋዕት ነው፡፡ ነውር የሌለበት የአንድ አመት ጠቦት፣ እንደ መደበኛ መስዋዕት በእያንዳንዱ ቀን ሁለት ጠቦቶች አቅርቡ፡፡
\v 4 አንዱን ጠቦት በማለዳ ታቀርባላችሁ፣ ሌላውን ጠቦት በምሽት ታቀርባላችሁ፡፡
\v 5 በተጠለለ የኢን አንድ አራተኛ ዘይት የተለወሰ የአፍ አንድ አስረኛ መልካም ዱቄት የእህል ቁርባን አድርጋችሁ አቅርቡ፡፡
\s5
\v 6 ይህ በሲና ተራራ የተደነገገ ለያህዌ የሚቀርብ በእሳት የተዘጋጀ መልካም መዓዛ ያለው መደበኛ የሚቃጠል መስዋዕት ነው፡፡
\v 7 ከዚህ ጋር የሚቀርበው የመጠጥ መስዋዕት ለአንዱ ጠቦት የኢን አንድ አራተኛ ይሁን፡፡ በተቀደሰው ስፍራ ለያህዌ የመጠጥ ስጦታ አፍስሱ፡፡
\v 8 ሌላውን ጠቦት ከሌላ የእህል ቁርባን ጋር በማለዳ ባቀረባችሁት መስዋዕት አይነት በምሽት አቅርቡ፡፡ ከዚህ ጋር ለያህዌ ጣፋጭ መዓዛ እንዲሆን በእሳት የተዘጋጀ ሌላ የመጠጥ መስዋዕትም አቅርቡ፡፡
\s5
\v 9 በሰንበት ቀን ነውር የሌላቸው ሁለት የአንድ አመት ጠቦቶች፣ እና በዘይት የተለወሰ የኢፍ ሁለት አስረኛ መልካም ዱቄት የእህል ቁርባን አድርጋችሁ ከመጠጥ መስዋዕት ጋር አቅርቡ፡፡
\v 10 ይህ ከመደበኛው የሚቃጠል መስዋዕትና ከዚህ ጋር ከሚቀርበው የመጠጥ ቁርባን በተጨማሪ በየሰንበቱ የሚቃጠል መስዋዕት እንዲሆን ነው፡፡
\s5
\v 11 በየወሩ መጀመሪያ፣ ለያህዌ የሚቃጠል መስዋዕት አቅርቡ፡፡ ሁለት ወይፈኖች፣ አንድ አውራ በግ እና ነውር የሌለባቸው ሰባት ወንድ የበግ ጠቦት መስዋዕት አድርጋችሁ አቅረቡ፡፡
\v 12 ለእያንዳዱ ወይፈን በዘይት የተለወሰ የኢፍ ሶስት አስረኛ መልካም ዱቄት የእህል ቁርባን አቅርቡ፣ ደግሞም ከአውራ በጉ ጋር በዘይት የተለወሰ የኢፍ ሁለት አስረኛ መልካም ዱቄት የእህል ቁርባን አቅርቡ፡፡
\v 13 እንደዚሁም ለእያንዳንዱ ጠቦት የኢፍ አንድ አስረኛ በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የእህል ቁርባን አቅርቡ፡፡ ይህ ለያህዌ የሚቀርብ በእሳት የተዘጋጀ መልካም መዓዛ የሚሰጥ የሚቃጠል መስዋዕት የሚሆን ነው፡፡
\s5
\v 14 የሰዎች የመጠጥ ቁርባን ላንድ ኮርማ በሬ የኢን ግማሽ ወይን ጠጅ ይሁን፣ ከአውራ በጉ ጋር የኢን አንድ ሶስተኛ፣ ለአንድ ጠቦት በግ የኢን አንድ አራተኛ ወይን ጠጅ ይሁን፡፡ ይህ አመቱን በሙሉ በእያንዳንዱ ወር የሚቃጠል መስዋዕት ነው፡፡
\v 15 ለያህዌ አንድ ወንድ ፍየል የኃጢአት መስዋዕት መቅረብ አለበት፡፡ ይህ ከመደበኛው የሚቃጠል መስዋዕትና ከዚህ ጋር ከሚቀርብ የመጠጥ ቁርባን በተጨማሪ ነው፡፡
\s5
\v 16 በመጀመሪያው ወር፣ በወሩ በአስራ አራተኛው ቀን የያህዌ ፋሲካ ይውላል፡፡
\v 17 በዚህ ወር የአስራ አምስተኛው ቀን ክብረ በዓል ይሆናል፡፡ ለሰባት ቀናት እርሾ የሌለበት ቂጣ ይበላል፡፡
\v 18 በመጀመሪያው ቀን ያህዌን ለማክበር ቅዱስ ጉባኤ ይደረጋል፡፡ በዚያ ቀን የዘወትር ሥራችሁን አትሰሩም፡፡
\s5
\v 19 ሆኖም ለያህዌ በእሳት የተዘጋጀ የሚቃጠል መስዋዕት ስጦታ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ፡፡ ሁለት ወይፈኖች፣ አንድ አውራ በግ፣ እና ነውር የሌለባቸው የአንድ አመት ሰባት ወንድ የበግ ጠቦቶች ታቀርባላችሁ፡፡
\v 20 ከወይፈኑ ጋር በዘይት የተለወሰ የኢን ሶስት አስረኛ መልካም ዱቄት የእህል ቁርባን፣ ከአውራ በግ ጋር የኢን ሁለት አስረኛ መልካም ዱቄት የእህል ቁርባን አቅርቡ፡፡
\v 21 ከእያንዳንዳቸው ከሰባቱ ጠቦቶች ጋር፣ በዘይት የተለወሰ የኢፍ አንድ አስረኛ መልካም ዱቄት አቅርቡ፣
\v 22 እንዲሁም አንድ ወንድ ፍየል ለኃጢአት መስዋዕት ለማስተሰርያ አቅርቡ፡፡
\s5
\v 23 እነዚህን በየጠዋቱ ከሚያስፈልገው መደበኛው የሚቃጠል መስዋዕት በተጨማሪ አቅርቡ፡፡
\v 24 እዚህ እንደ ተገለፀው፣ እነዚህን መስዋዕቶች በየቀኑ ማቅረብ አለባችሁ፣ በፈሲካ ሳምንት፣ በእሳት የተዘጋጀው የምግብ መስዋዕት ለያህዌ ጣፋጭ መዓዛ ይቅረብ፡፡ ይህ ከመደበኛው የሚቃጠል መስዋዕትና ከዚህ ጋር ከሚቀርበው የመጠጥ ቁርባን በተጨማሪ መቅረብ አለበት፡፡
\v 25 በሰባተኛው ቀን ያህዌን ለማክበር የተቀደሰ ጉባኤ ይኑራችሁ፣ ደግሞም በዚያ ቀን የየዕለት ተግባራችሁን አታከናውኑ፡፡
\s5
\v 26 እንደዚሁም በበኩራት ፍሬ ቀን፣ በክብረ በዓላችሁ ሳምንታት የአዲስ እህል ስጦታ ለያህዌ ስታቀርቡ፣ ያህዌን ለማክበር የተቀደሰ ጉባኤ ይኑራችሁ፤ ደግሞም በዚያ ቀን የተለመደ የየዕለት ተግባራችሁን አትስሩ፡፡
\v 27 ለያህዌ ጣፋጭ መዓዛ የሚቃጠል መስዋዕት አቅርቡ፡፡ ሁለት ወይፈኖች፣ አንድ አውራ በግ፣ እና ሰባት የአንድ አመት ጠቦት በጎች አቅርቡ፡፡
\v 28 ከእነዚህ ጋር እነዚህን የእህል ቁርባን አቅርቡ በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት፣ ለእያንዳንዱ ወይፈን የኢፍ ሶስት አስረኛ በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት፣ እና ለአውራ በጉ ሁለት አስረኛ የእህለ ቁርባን አቅርቡ
\s5
\v 29 የኢፍ አንድ አስረኛ በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት ለእያንዳንዳቸው ሰባት ጠቦቶች አቅርቡ፣
\v 30 ደግሞም አንድ ወንድ ፍየል ለኃጢአታችሁ ማስተሰርያ አቅርቡ፡፡
\v 31 ነውር የሌለባቸውን እነዚያን እንስሳት ከመጠጥ ቁርባናቸው ጋር ስታቀርቡ ይህ ከመደበኛ የሚቃጠል መስዋዕትና ከዚህ ጋር ከሚቀርበው የእህል ቁርባን በተጨማሪ መሆን አለበት፡፡’”
\s5
\c 29
\p
\v 1 ”በሰባተኛው ወር፣ በወሩ በመጀመሪያው ቀን፣ ያህዌን ለማክበር የተቀደሰ ጉባኤ አድርጉ፡፡ በዚያ ቀን የተለመደውን የዕለት ተግባራችሁን አታከናውኑ፡፡ ይህ ቀን መለከቶችን የምትነፉበት ቀን ይሆናል፡፡
\s5
\v 2 ለያህዌ መልካም መዓዛ የሚሆን የሚቃጠል መስዋዕት አቅርቡ፡፡ አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግ፣ እና እያንዳንዳቸው ነውር የሌለባቸው ሰባት የአንድ አመት ጠቦቶች አቅርቡ፡፡
\s5
\v 3 ከእነዚህ ጋር የእህል ቁርባናቸውን፣ በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት አቅርቡ፤ ለወይፈኑ የኢፍ ሶስት አራተኛ፣ ለአውራ በጉ የኢፍ ሁለት አስረኛ
\v 4 እና ለሰባቱ ጠቦቶች ለእያንዳንዳቸው በዘይት የተለወሰ የኢፍ አንድ አስረኛ መልካም ዱቄት አቅርቡ፡፡
\v 5 ለኃጢአት ማስተስረያ አንድ ወንድ ፍየል አቅርቡ፡፡
\s5
\v 6 በየወሩ መጀመሪያ ከምታደርጉት የተለየ የሚቃጠል መስዋዕትና አብሮ ከሚቀርበው የእህል ቁርባን በተጨማሪ፣ እነዚህን መስዋዕቶች በሰባተኛው ወር አድርጉ፡፡ እነዚህ ከመደበኛው የሚቃጠል መስዋዕት ከእህል ቁርባኑና የመጠጥ ቁርባኖች በተጨማሪ የሚቀርቡ ናቸው፡፡ እነዚህን መስዋዕቶች ስታደርጉ፣ ለያህዌ በእሳት የሚዘጋጀውን መስዋዕት ጣፋጭ መዓዛ ለማቅረብ የተደነገገውን ትፈጽማላችሁ፡፡
\s5
\v 7 በሰባተኛ ወር በአስረኛው ቀን ያህዌን ለማክበር የተቀደሰ ጉባኤ ታደርጋላችሁ፡፡ ራሳችሁን በእግዚአብሔር ፊት ታዋርዳላችሁ በዕለቱ ሥራ አትሰሩም፡፡
\v 8 ለያህዌ ጣፋጭ ማዐዛ ያለው የሚቃጠል መስዋዕት ታቀርባላችሁ፡፡ አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግ፣ እና የአንድ አመት ሰባት ወንድ ጠቦት በጎች ታቀርባላችሁ፡፡ እያንዳንዳቸው ነውር የሌለባቸው ይሁኑ፡፡
\s5
\v 9 ከዚህ ጋር የእህል ቁርባን፤ በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት፣ ለወይፈኑ የኢፍ ሶስት አስረኛ፣ ለአውራ በጉ የኢፍ ሁለት አስረኛ፣
\v 10 እና ለሰባቱ ጠቦቶች ለእያንዳንዳቸው የኢፍ አንድ አስረኛ ታቀርባላችሁ፡፡
\v 11 አንድ ወንድ ፍየል ለኃጢአት መስዋዕት ማቅረበ አለባችሁ፡፡ ይህ ለኃጢአት ማስተስረያ፣ ለመደበኛ የሚቃጠል መስዋዕት፣ አብሮት ከሚቀርበው የእህል ቁርባን፣ እና ከእነዚህ ጋር በሚቀርበው የመጠጥ መስዋእቶች በተጨማሪ የሚቀርብ ነው፡፡
\s5
\v 12 በሰባተኛው ወር አስራ አምስተኛው ቀን ያህዌን ለማክበር የተቀደሰ ጉባኤ ታደርጋላችሁ፡፡ በዚያ ቀን የተለመደውን የዕለት ተግባራችሁን አታከናውኑም፣ ደግሞም ለሰባት ቀናት ክብረ በዓሉን ለእርሱ ታደርጋላችሁ፡፡
\v 13 በእሳት የተዘጋጀ ለያህዌ ጣፋጭ መዓዛ የሚሆን የሚቃጠል መስዋዕት ማቅረብ አለባችሁ፡፡ አስራ ሶስት ወይፈኖች፣ እና የአንድ አመት ዕድሜ ያላቸው አስራ አራት ወንድ ጠቦቶች ማቅረብ አለባችሁ፡፡ እያንዳንችው ነውር የሌለባቸው መሆን አለባቸው፡፡
\s5
\v 14 ከእነዚህ ጋር የእህል ቁርባን፣ ለአስራ ሶስቱም ወይፈኖች ለእያንዳንዳቸው የኢፍ ሶስት አስረኛ፣ ለሁለቱ አውራ በጎች ለእያንዳንዳቸው የኢፍ ሁለት አስረኛ
\v 15 እና ለአስራ አራቱ ጠቦቶች ለእያንዳንዳቸው የኢፍ አንድ አስረኛ፤ በዘይትየተለወሰ መልካም ዱቄት አቅርቡ፡፡
\v 16 ከመደበኛው የሚቃጠል መስዋዕት፤ ከዚህ ጋር ከሚቀርበው የእህል ቁርባን እና የመጠጥ ቁርባን በተጨማሪ ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ማቅረብ አለባችሁ፡፡
\s5
\v 17 በስብሰባው ሁለተኛ ቀን፣ አስራ ሁለት ወይፈኖች፣ ሁለት አውራ በጎች እና አስራ አራት ነውር የሌለባቸው የአንድ አመት ወንድ የበግ ጠቦቶች ማቅረብ አለባችሁ፡፡
\v 18 ከእነዚህ ጋር የእህል ቁርባን የመጠጥ ቁርባኖች ለኮርማዎቹ፣ ለአውራ በጎቹ እና ለጠቦቶቹ በተወሰነው ቁጥር መሠረት እንደ ትዕዛዙ ታቀርባላችሁ፡፡
\v 19 ከመደበኛ የሚቃጠል መስዋዕት፣ አብሮት ከሚቀርበው የእህል ቁርባንና የመጠጥ ቁርባን በተጨማሪ ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ማቅረብ አለባችሁ፡፡
\s5
\v 20 በስብሰባው ሶስተኛ ቀን፣ አስራ አንድ ወይፈኖች ሁለት አውራ በጎች፣ እና አስራ አራት ነውር የሌለባቸው የአንድ አመት ወንድ የበግ ጠቦቶች ማቅረብ አለባችሁ፡፡
\v 21 ከእነዚህ ጋር የእህል ቁርባንና የመጠጥ ቁርባኖች ለኮርማዎቹ፣ ለአውራ በጎቹ፣ እና ለጠቦቶቹ በተወሰነው ቁጥር መሰረት እንደ ትዕዛዙ ታቀርባላችሁ፡፡
\v 22 ከመደበኛ የሚቃጠል መስዋዕት፣ አብሮ ከሚቀርበው የእህል ቁርባን፣ እና የመጠጥ ቁርባን በተጨማሪ ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ማቅረብ አለባችሁ፡፡
\s5
\v 23 በስብሰባው አራተኛ ቀን፣ አስር ወይፈኖች፣ ሁለት አውራ በጎች እና አስራ አራት ነውር የሌለባቸው የአንድ አመት ወንድ የበግ ጠቦቶች ማቅረብ አለባችሁ፡፡
\v 24 ከእነዚህ ጋር የእህል ቁርባንና የመጠጥ ቁርባኖች፣ ለኮርማዎቹ፣ ለአውራ በጎቹ እና ለጠቦቶቹ በተወሰነው ቁጥር መሠረት እንደ ትዕዛዙ ታቀርባላችሁ፡፡
\v 25 ከመደበኛ የሚቃጠል መስዋዕት፣ አብሮት ከሚቀርበው የእህል ቁርባንና የመጠጥ ቁርባን በተጨማሪ ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ማቅረብ አለባችሁ፡፡
\s5
\v 26 በስብሰባው አምስተኛ ቀን፣ ዘጠኝ ወይፈኖች፣ ሁለት አውራ በጎች፣ እና አስራ አራት ነውር የሌለባቸው የአንድ አመት ወንድ የበግ ጠቦቶች ማቅረብ አለባችሁ፡፡
\v 27 ከእነዚህም ጋር የእህል ቁርባንና የመጠጥ ቁርባኖች ለኮርማዎቹ፣ ለአውራ በጎቹ፣ እና ለጠቦቶቹ፣ በተወሰነው ቁጥር መሠረት እንደ ትዕዛዙ ታቀርባላችሁ፡፡
\v 28 ከመደበኛ የሚቃጠል መስዋዕት፣ አብሮት ከሚቀርበው የእህል ቁርባን፣ እና የመጠጥ ቁርባን በተጨማሪ ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ማቅረብ አለባችሁ፡፡
\s5
\v 29 በስበሰባው ስድስተኛ ቀን ስምንት ወይፈኖች፣ ሁለት አውራ በጎች፣ እና አስራ አራት ነውር የሌለባቸው የአንድ አመት ወንድ የበግ ጠቦቶች ማቅረብ አለባችሁ፡፡
\v 30 ከእነዚህ ጋር የእህል ቁርባንና የመጠጥ ቁርባኖች ለኮርማዎቹ፣ ለአውራ በጎቹ፣ እና ለጠቦቶቹ በተወሰነው ቁጥር መሠረት እንደ ትዕዛዙ ታቀርባላችሁ፡፡
\v 31 ከመደበኛ የሚቃጠል መስዋዕት፣ አብሮት ከሚቀርበው እህል ቁርባን እና የመጠጥ ቁርባን በተጨማሪ ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ማቅረበ አለባችሁ፡፡
\s5
\v 32 በስብሰባው ሰባተኛ ቀን፣ነውር የሌለባቸው፣ ሰባት ወይፈኖች፣ ሁለት አውራ በጎች እና አስራ አራት የአንድ አመት ወንድ የበግ ጠቦቶች ማቅረብ አለባችሁ፡፡
\v 33 ከወይፈኖች፣ከአውራ በጎች እና ጠቦቶች ጋር የእህል ቁርባንና የመጠጥ ቁርባኖች ታቀርባላችሁ፡፡
\v 34 ከመደበኛው የሚቃጠል መስዋዕትና አብሮት ከሚቀርበው የእህል ቁርባን፣ እንዲሁም ከመጠጥ ቁርባኑ በተጨማሪ ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ማቅረብ አለባችሁ፡፡
\s5
\v 35 በስብሰባው ስምንተኛ ቀን፣ ሌላ የከበረ ጉባኤ ታደርጋላችሁ፡፡ በዚያን ቀን የተለመደ የዕለት ተግባራችሁን አታከናውኑም፡፡
\v 36 የሚቃጠል መስዋዕት ታደርጋላችሁ፣ ለያህዌ ጣፋጭ መዓዛ ያለው መስዋዕት ታቀርባላችሁ፡፡ አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግ፣ እና ነውር ሌለባቸው ሰባት የአንድ አመት ወንድ ጠቦት በጎች ታቀርባላችሁ፡፡
\s5
\v 37 ለወይፈኑ፣ ለአውራ በጉ፣ እና ለጠቦቶቹ የእህል ቁርባናቸውንና የመጠጥ ቀርባናቸውን በተወሰነው ቁጥር መሰረት እንደ ትእዛዙ ታቀርባላችሁ፡፡
\v 38 ከመደበኛ የሚቃጠል መስዋዕት፣ አብሮት ከሚቀርበው የእህል ቁርባን፣ እና የመጠጥ ቁርባን በተጨማሪ ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ማቅረብ አለባችሁ፡፡
\s5
\v 39 በተወሰነ ክብረ በዓላቶቻችሁ ለያህዌ የምታቀርቧቸው እነዚህ ናቸው፡፡ እነዚህም ከስለቶቻችሁና የበጎ ፈቃድ ስጦታዎቻችሁ በተጨማሪ የምታቀርቧቸው ናቸው፡፡ እነዚህን የሚቃጠሉ መስዋዕቶቻችሁ፣ የእህል ቁርባኖች፣ የመጠጥ ቁርባኖች፣ እና የህብረት መስዋዕቶች አድርጋችሁ አቅርቧቸው፡፡”
\v 40 ሙሴ ያህዌ ለእስራኤል ሰዎች እንዲናገር ያዘዘውን ሁሉ ተናገረ፡፡
\s5
\c 30
\p
\v 1 ሙሴ ለእስራኤል ህዝብ የጎሳ መሪዎች እንዲህ አላቸው፣ “ያህዌ ያዘዘው ይህን ነው፡፡
\v 2 ማንም ሰው ለያህዌ ስዕለት ሲሳል፣ ወይም በቃል ኪዳን ራሱን በመሀላ ሲያስር፣ ቃሉን ማፍረስ የለበትም፡፡ ከአፉ የወጣውን ማናቸውንም ነገር ለማድረግ ቃልኪዳኑን መጠበቅ አለበት፡፡
\s5
\v 3 አንዲት ወጣት ሴት በአባቷ ቤት እያለች ለያህዌ ብትሳልና በመሀላ ራሷን ብታስር፣
\v 4 አባቷም ስዕለቷንና ራሷን ያሰረችበትን መሀላ ቢሰማ፣ እርሱም እርሷን ለመመለስ አንዳች ነገር ባይናገር መሀላዎቿ ሁሉ መፈፀም አለባቸው፡፡ ራሷን ያሰረችባቸው ቃልኪዳኖች ሁሉ ተግባራዊ ይሆናሉ፡፡
\s5
\v 5 ነገር ግን አባቷ ስለ ስዕለቷና ስለገባችው ቃል ኪዳን ሰምቶ ምንም ነገር ባይነግራት በራሷ ላይ የወሰደቻቸው የገባቻቸው መሀላዎችና ቃል ኪዳኖች መፈጸም አለባቸው፡፡
\s5
\v 6 ሆኖም ግን፣ አባቷ የገባቻቸውን መሀላዎች ሁሉና የከበሩ ቃል ኪዳኖቿን ራሷን ግዴታ ውስጥ ያስገባችበትን ነገር ቢሰማ፣ ደግሞም በዚያው ቀን ማድረግ ያለበትን ቢነግራት መሀላዋን ለመፈጸም አትገደድም፡፡ ያህዌ ይቅር ይላታል ምክንያቱም አባቷ ማድረግ ያለባትን ነግሯታል፡፡
\v 7 እነዚያ መሀላዎች እያሉባት ባል ብታገባ ወይም በችኮላ መሀላ ብታደርግና ራሷን ግዴታ ውስጥ ብታስገባ እነዚያ ግዴታዎች መፈጸም አለባቸው፡፡
\s5
\v 8 ነገር ግን ባሏ በዚያው ቀን ሰምቶ ቢከለክላት የገባቸውን መሀላና በችኮላ ራሷን ያሰረችበትን መሀላዋን ያስቀራል፡፡ ያህዌ ከዚህ ነጻ ያደርጋታል፡፡
\s5
\v 9 ባሏ የሞተባት ወይም ከባሏ የተፋታች ሴት ግን ራሷን የሰራችባቸው ነገሮች ሁሉ ተፈፃሚ ይሆኑባታል፡፡
\v 10 ከባሏ ቤተሰቦች ጋር ያለች ሴት ብትሳል ራሷን በቃል ኪዳን መሀላ ብታስር፣
\v 11 እና ባልዋ ሰምቶ ምንም ነገር ባይነግራት ስእለቷን ባያስቀር፣ ስዕለቶቿ ሁሉ መፈጸም አለባቸው፡፡ ራሷን ያሰረችባቸው ቃልኪዳኖች ሁሉ መፈጸም አለባቸው፡፡
\s5
\v 12 ነገር ግን ባሏ ስለ ስዕለቶቿ በሰማ ቀን እንዲቀሩ ካደረገ፣ ስለ ስዕለቶቿ ወይም ቃልኪዳኖቿ ከከንፈሯ የወጡ ነገሮች ሁሉ የግዴታ መፈጸም አይኖርባቸውም፡፡ ባልዋ አስቀርቷቸዋል፡፡ ያህዌ ነጻ ያደርጋታል፡፤
\s5
\v 13 አንዲት ሴት የገባችውን እያንዳንዱን መሀላ ወይም ስእለት እንድታጥፍ የሚያደርጋትን አንዳች ነገር በባሏ ሊጸና ወይም ሊሻር ይችላል፡፡
\v 14 ነገር ግን ቀናት ሲያልፉ ባሏ አንዳች ካልነገራት፣ ስዕቶቿን ሁሉ እና ቃል የገባቻቸውን ነገሮች ያፀናባታል፡፡ ስዕቶቿንና መሀላዎቿን የሚያፀናባት ስለእነዚህ በሰማበት ጊዜ ምንም ስላልነገራት ነው፡፡
\s5
\v 15 ባሏ የሚስቱን ስዕለት ከሰማ ከረጅም ጊዜ በኋላ ሊሽር ቢሞክር፣ ስለእርሷ ኃጢአት ሀላፊነቱን ይወስዳል፡፡”
\v 16 ያህዌ ሙሴ እንዲያውጃቸው የሰጠው ቋሚ መመሪያዎች እነዚህ ናቸው፡፡ በአንድ ወንድና በሚስቱ መሀል፣ እንዲሁም በአባትና በወጣትነቷ በአባቷ ቤት ስለምትኖር ሴት ልጁ ያህዌ የሰጠው ቋሚ መመሪያ ይህ ነው፡፡
\s5
\c 31
\p
\v 1 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
\v 2 “የእስራኤል ህዝብ ምድያማውያንን ይበቀሉ፡፡ ያን ካደረግህ በኋላ፣ ወደ ወገኖችህ ትከማቻለህ፡፡”
\s5
\v 3 ስለዚህም ሙሴ ለህዝቡ እንዲህ አለ፣ “በምድያማውያን ላይ የያህዌን በቀል ይፈጽሙ ዘንድ ከወንዶቻችሁ አንዳንዶቹን ወደ ጦርነት እንዲወጡ አስታጥቋቸው፡፡
\v 4 እያንዳንዱ በእስራኤል ውስጥ ያለ ጎሳ ለጦርነት አንድ ሺህ ወታደሮችን መላክ አለበት፡፡”
\v 5 ስለዚህ ከእስራኤል ብዙ ሺህ ወንዶች መሀል ከእያንዳንዱ ጎሳ አንድ ሺህ ሰው ለጦርነት ቀረበ፣ በጠቅላላው አስራ ሁለት ሺህ ወንዶች ነበሩ፡፡
\s5
\v 6 ከዚያ ሙሴ ከየጎሳው አንድ ሺህ ሰዎችን ከካህኑ ከአልዓዛር ልጅ ከፊንሃስ ጋር እና ከተቀደሰው ስፍራ ከጥቂት ቁሳቁሶችና እንዲሁም ምልክቶችን ለማሰማት በእጁ ያሉትን መለከቶች አስይዞ ወደ ጦርነት ላካቸው፡፡
\v 7 እነርሱም ያህዌ ሙሴን እንዳዘዘው ከምድያማውያን ጋር ተዋጉ፡፡ ሰዎቹን ሁሉ ፈጇቸው፡፡
\v 8 የምድያምን ነገስታት ኤዊ፣ ሮቆም፣ ሱር ሑርን እና እና ሪባን ከተቀሩት ጋር በሰይፍ ገደሏቸው፡፡
\s5
\v 9 የእስራኤል ጦር፤ የምድያምን ሴቶች፣ ልጆቻቸውን ከብቶቻቸውን ሁሉ፣ መንጋዎቻቸውን እና ንብረቶቻቸውን ሁሉ ምርኮ አደረጉ፡፡ እዚህን ሁሉ ዘርፈው ወሰዱ፡፡
\v 10 የሚኖሩባቸውን ከተሞችና ሰፈሮች ሁሉ አቃጠሉ፡፡
\s5
\v 11 የሰውና እንስሳት ምርኮዎቻቸውንና እስረኞችን ወሰዱ፡፡
\v 12 እስረኞችን፣ የዘረፉትን፣ እና የያዙትን ነገሮች ወደ ሙሴ፣ ወደ ካህኑ አልዓዛር፣ እና ወደ እስራኤል ማህበረሰብ አመጡ፡፡ እነርሱም እነዚህን ኢያሪኮ አጠገብ ዮርዳስ፣ በሞአብ ሜዳ ላይ ወደ ሚገኘው ሰፈር አመጡ፡፡
\s5
\v 13 ሙሴ፣ ካህኑ አልዓዛር፣ እና የማህበረሰቡ መሪዎች በሙሉ ሊቀበሏቸው ከሰፈር ወጡ፡፡
\v 14 ሙሴ ግን ከጦርነት በተመለሱት በጦሩ መኮንኖች፣ በሻለቃዎችና በመቶ አለቆች ላይ ተቆጥቶ ነበር፡፡
\v 15 ሙሴ መኮንኖቹን እንዲህ አላቸው፣ “ሴቶቹ ሁሉ በህይወት እንዲኖሩ ተዋችኋቸውን?”
\s5
\v 16 እነዚህ ሴቶች በበለዓም ምክር፣ የእስራኤል ህዝብ በያህዌ ላይ በፌጎር ኃጢአት እንዲሰራና መቅሰፍት እንዲወርድበት ያደረጉ ናቸው፡፡
\v 17 ስለዚህ አሁን፣ ትናንሾቹን ወንዶች ሁሉ ግደሉ፣ ከወንድ ጋር የተኙ ሴቶችን ሁሉ ግደሉ፡፡
\s5
\v 18 ከወንድ ጋር ተኝተው የማያውቁትን ወጣት ልጃገረዶች ግን ለራሳችሁ ውሰዱ፡፡
\v 19 ከእስራኤል ሰፈር ውጭ ለሰባት ቀናት መቆየት አለባችሁ፡፡ ማንንም ሰው የገደላችሁ ሁሉና ወይም የሞተ ሰው የነካችሁ ሁሉ በሶስተኛው ቀንና በሰባተናው ቀን ራሳችሁን ማንጻት አለባችሁ፡፡ እናንተና ምርኮኞቻችሁ መንጻት አለባችሁ፡፡
\v 20 ልብሶቻችሁን አንጹ፣ ከእንስሳት ቆዳ እና ከፍየል ፀጉር የተሰሩ ማናቸውንም ነገሮች፣ እንዲሁም ከእንጨት የተሰሩ ነገሮችን ሁሉ አንጹ፡፡”
\s5
\v 21 ካህኑ አልዓዛር ወደ ጦርነት የሄዱትን ወታደሮች እንዲህ አላቸው፣ “ይህ ያህዌ ለሙሴ የሰጠው የተደገነገገ ህግ ነው፡
\v 22 ወርቁ፣ ብሩ፣ ነሀሱ፣ ብረቱ፣ ቆርቆሮውና እርሳሱ
\v 23 እና ማናቸውም እሳት የሚቋቋምን ነገር በእሳት ውስጥ አሳልፉት እናም የተቀደሰ ይሆናል፡፡ እነዚያን ነገሮች በማንጻት ውሃ አንጹዋቸው፡፡ በእሳት ውስጥ ማለፍ የማይችለውን ማናቸውንም ነገር በውሃ አንጹ፡፡
\v 24 እናም ልብሶችሁን በሰባተኛው ቀን እጠቡ፣ ከዚያም የተቀደሳችሁ ትሆናላች፡፡ ከዚህ በኋላ ወደ እስራኤል ሰፈር መግባት ትችላላችሁ፡፡”
\s5
\v 25 ከዚያም ያህዌ ሙሴን እንደዚህ አለው፣
\v 26 ”ሰዎችም ይሁኑ እንስሳት፣ የተማረኩትንና የተወሰዱትን ነገሮች ሁሉ ቁጠሩ፡፡ አንተ፣ ካህኑ አልዓዛር፣ እና የማህበረሰቡ መሪዎች እንዲሁም የጎሳ አባቶች
\v 27 ምርኮዎቹን ለሁለት ክፍል ክፈሏቸው፡፡ ለጦርነት በወጡ ወታደሮችና በተቀረው ማህበረሰብ መሃል ምርኮውን አከፋፍሉ፡፡
\s5
\v 28 ከዚያ ወደ ጦርነት ከወጡ ወታደሮች ለእኔ የሚሰጥ ግብር ጣል፡፡ ይህ ግብር ከሰዎችም ይሁን፣ ከቀንድ ከብት፣ ከአህዮች፣ ከበጎች ወይም ከፍየሎች ከየአምስት መቶው አንዱ ይሁን፡፡
\v 29 ይህን ግብር የእነርሱ ከሆነው ከከፊሉ ድርሻቸው ወስደህ ለእኔ የሚቀርብ ስጦታ እንዲሆን ለካህኑ አልዓዛር ስጠው፡፡
\s5
\v 30 ደግሞም ከከፊሉ የእስራኤል ህዝብ ድርሻ ከሆነው ሰዎች፣ ከቀንድ ከብቶች፣ ከአህዮች፣ ከበጎች ከፍየሎች፣ ከየሀምሳው መሀል አንዱን ወሰድ፡፡ እነዚህን ማደሪያዬን ለሚያገለግሉት ለሌዋውያን ስጣቸው፡፡”
\v 31 ስለዚህ ሙሴና ካህኑ አልዓዛር ያህዌ ሙሴን እንዳዘዘው አደረጉ፡፡
\s5
\v 32 ወታደሮቹ በዝብዘው የወሰዱት ምርኮ 675000 በጎች፣
\v 33 ሰባሁለት ሺህ በሬዎች፣
\v 34 ስልሳ አንድ ሺህ አህዮች፣
\v 35 እና ሰላሳ ሁለት ሺህ ከወንድ ጋር ያልተኙ ሴቶች ነበሩ፡፡
\s5
\v 36 ለወታደሮች የተጠበቀላቸው ግማሹ 337000 በጎች ነበሩ፡፡
\v 37 ከዚህ ውስጥ የያህዌ ድርሻ 675 በጎች ነበር፡፡
\v 38 በሬዎቹ ሰላሳ ስድስት ሺህ ሲሆኑ የያህዌ ግብር 72 ነበር፡፡
\s5
\v 39 አህዮች 30500 ነበሩ፣ ከዚህ ውስጥ የያህዌ ድርሻ 61 ነበር፡፡
\v 40 ሰዎቹ አስራ ስድስት ሺ ሴቶች ነበሩ፣ ከዚህ ውስጥ ለያህዌ የተሰጠው ግብር 32 ነበር፡፡
\v 41 ሙሴ ለያህዌ የሚቀርቡትን ስጦታዎች ግብር ወሰደ፡፡ እርሱም ያህዌ ሙሴን እንዳዘዘው ለካህኑ አልዓዛር ይህንን ሰጠ፡፡
\s5
\v 42 ሙሴ ወደ ጦርት ከሄዱ ወታደሮች የወሰደውን የእስራኤል የሆነውን ግማሽ ምርኮ በተመለከተ፤
\v 43 የማህበረሰቡ ከምርኮ ግማሹ 337500 በጎች፣
\v 44 ሰላሳ ስድስት ሺህ በሬዎች፣
\v 45 ሰላሳ ሺ አምስት መቶ አህዮች፣
\v 46 እና አስራ ስድስት ሺ ሴቶች ነበሩ፡፡
\s5
\v 47 ከእስራኤል ህዝብ ግማሽ ከሆነ ድርሻው፣ ሙሴ ከሰውም ሆነ ከእንስሳት ከየአምሳው መሀል አንድ ወሰደ፡፡ እርሱም ያህዌ እንዲያደርገው ባዘዘው መሠረት የያህዌን ማደሪያ ለሚያገለግሉ ለሌዋውያን እነዚህን ሰጠ፡፡
\s5
\v 48 ከዚያ የሰራዊቱ መኮንኖች፣ የሻለቃ አዛዦች እና የመቶ አለቆች ወደ ሙሴ መጡ፡፡
\v 49 እንዲህም አሉ፣ “ባሮችህ በእኛ ስር ያሉትን ወታደሮች ቆጠርን፣ አንድ ሰው እንኳን አልጎደለም፡፡
\s5
\v 50 እኛ የያህዌን ስጦታ አምጥተናል፣ እያንዳንዱ ሰው ያገኘውን፣ የወርቅ ዕቃዎች፣ አልቦዎችና አንባሮች፣ የጣት ቀለበቶች፣ የጆሮ ጉትቻዎች፣ እና የአንገት ሀብሎች ማስተስረያ እንደሆነን በያህዌ ፊት አምጥተናል፡፡”
\v 51 ሙሴና ካህኑ አልዓዛር ወርቁንና የእጁ ጥበብ ውጤት የሆኑትን የጌጥ ዕቃዎች ሁሉ ከእነርሱ ተቀበሉ፡፡
\s5
\v 52 ለያህዌ ያቀረቧቸው የወርቅ ስጦታዎች ሁሉ ከሻለቃዎችና ከመቶ አለቃዎች የተቀበሏቸው ስጦታዎች ክብደታቸው 16750 ሰቅሎቸ ነበር፡፡
\v 53 እያንዳንዱ ወታደርና እያንዳንዱ ሰው ከምርኮው ለራሱ ወስዷል፡፡
\v 54 ሙሴና ካህኑ አልዓዛር ከሻለቆችና ከመቶ አለቆች ወርቁን ወሰዱ፡፡ ለያህዌ የእስራኤል ህዝብ ማስታወሻ አድርገው ወርቁን ወደ መገናኛው ድንኳን አስገቡት፡፡
\s5
\c 32
\p
\v 1 በዚህ ጊዜ የሮቤልና የጋድ ትውልዶች ብዙ የቀንድ ከብቶች ነበራቸው፡፡ የኢያዜርንና የገለዓድን ምድር ሲመለከቱ፣ ምድሪቱ ለከብቶቻቸው መልካም መሆኗን አዩ፡፡
\v 2 ስለዚህ የጋድና ሮቤል ትውልዶች ወደ ሙሴ፣ ወደ ካህኑ አልዓዛርና ወደማህበሩ መሪዎች መጥተው እንዲህ አሉ፣
\v 3 “ያህዌ በእስራኤል ህዝብ ፊት የመታው አጣሮት፣ ዲቦን ኢያዜር፣ ኒምራ፣ ሐሴናን፣ ኤልያሊ፣ ሴባማ፣ ናባውና ባያን
\s5
\v 4 ምድሩ ለከብቶች መልካም ነው፡፡ እኛ፣ የአንተ አገልጋዮች ብዙ ከበቶች አሉን፡፡”
\v 5 ደግሞም እንዲህ አሉ፣ “በፊትህ ሞገስ አግኝተን ከሆነ፣ ይህች ምድር ለእኛ ለአገልጋዮችህ ርስት ሆና ትሰጠን፡፡ ዮርዳኖስን አቋርጠን እንድንሄድ አታድርግ፡፡”
\s5
\v 6 ሙሴ ለጋድና ሮቤል ትውልዶች እንዲህ ሲል መለሰላቸው፣ “እናንተ በዚህ ተቀምጣችሁ ወንድሞቻችሁ ወደ ጦርነት ሊሄዱ ይገባልን?
\v 7 የእስራኤል ህዝብ ያህዌ ወደ ሰጣቸው ምድር እንዳይገቡ ለምን ልባቸውን ታደክማላችሁ?
\s5
\v 8 አባቶቻችሁ ከቀዴስ በርኔ ምድሪቱን እንዲያዩ በላክኋቸው ጊዜ ያደረጉት ተመሳሳይ ነገር ነበር፡፡
\v 9 እነርሱ ወደ ኤሽኮል ሸለቆ ሄዱ፡፡ ምድሪቱን ካዩ በኋላ የእስራኤልን ልብ አደከሙ፤ ስለዚህም ያህዌ ወደ ሰጣቸው ምድር ለመግባት ተቃወሙ፡፡
\s5
\v 10 በዚያ ቀን የያህዌ ቁጣ ነደደ፡፡ በመሀላ እንዲህ አለ፣
\v 11 ‘ከግብጽ ምድር ከወጡ ሰዎች ሃያ አመትና ከዚያ በላይ ከሆናቸው፣ መሃል አንዳቸውም ለአብርሃም፣ ለይስሃቅ፣ እና ለያዕቆብ ልሰጣቸው በመሀላ ቃል የገባሁላቸውን ምድር አያዩም፣ ምክንያቱም እነርሱ በሙሉ ልባቸው አልተከተሉኝም፤
\v 12 ከቂኔዛዊው ከዩፎኒ ልጅ ከካሌብ፣ እና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በስተቀር፡፡ ካሌብና ኢያሱ ብቻ በሙሉ ልባቸው ተከትለውኛል፡፡’
\s5
\v 13 ስለዚህም የያህዌ ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፡፡ በፊቱ ክፉ ያደረገው ትውልድ ሁሉ እስኪጠፋ ድረስ ለአርባ አመታት በምድረበዳ እንዲንከራተቱ አደረጋቸው፡፡
\v 14 እናንተ እንደ ሌሎች ኃጢአተኛ ሰዎች የያህዌን ቁጣ በእስራኤል ላይ ለመጨመር በአባቶቻችሁ እግር ተተካችሁ፡፡
\v 15 እርሱን ከመከተል ፊታችሁን ብታዞሩ፣ እርሱ እስራኤልን ዳግም በበረሃ ይተዋል እናንተም ይህን ሁሉ ህዝብ ታጠፋላችሁ፡፡”
\s5
\v 16 ስለዚህም ወደ ሙሴ መጥተው እንዲህ አሉ፣ “በዚህ ለከብቶቻችን አጥር እና ለቤተሰቦቻችን ከተማ እንድንገነባ ፍቀድል፡፡
\v 17 ሆኖም፣ እኛ እራሳችን ወደ ስፍራቸው እስክናባርራቸው ድረስ ከእስራኤል ጦር ጋር ለመውጣት እንነሳለን እንታጠቃንም፡፡ ቤተሰቦችን ግን እስከ አሁን በዚህ ምድር ከሚኖሩ ሌሎች ሰዎች የተነሳ በተቀጠሩ ከተሞች ውስጥ ይኖራሉ፡፡
\s5
\v 18 የእስራኤል ህዝብ እያንዱ ሰው ርስቱን እስኪያገኝ ድረስ ወደ ቤቶቻችን አንመለስም፡፡
\v 19 እኛ ከእነርሱ ጋር ከዮርዳኖስ ማዶ ያለውን ምድር አንወርስም፣ ምክንያቱም የእኛ ርስት እዚህ በዮርዳኖስ ምስራቅ በኩል ያለው ነው፡፡”
\s5
\v 20 ስለዚህም ሙሴ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፣ “የተናገራችሁትን ካደረጋችሁ፣ ወደ ጦርነት በያህዌ ፊት ለመውጣት ራሳችሁን ካስታጠቃችሁ፣
\v 21 ከዚያ በኋላ እያንዳንዳቸው የእናንተ የታጠቁ ወንዶች ጠላቶቹን ከፊቱ እስኪያባርራቸው ድረስ በያህዌ ፊት ዮርዳኖስን ማቋረጥ አለባቸው፡፡
\v 22 ደግሞም ምድሪቱ በእርሱ ፊት ጸጥ ብላ ትገዛለች፡፡ ከዚያ በኋላ መመለስ ትችላላችሁ፡፡ እናንተም በያህዌና በእስራኤል ፊት ጥፋተኛ አትሆኑም፡፡ ይህ ምድር በያህዌ ፊት ርስታችሁ ይሆናል፡፡
\s5
\v 23 እንዲህ ካላደረጋችሁ ግን፣ በያህዌ ፊት በደለኞች ትሆናላችሁ ኃጢአታችሁ እንደሚከተላችሁ እርግጠኞች ሁኑ፡፡
\v 24 ለቤተሰቦቻችሁ ከተሞችን ገንቡ ለበጎቻችሁም ጉረነዎች ስሩላቸው፤ ከዚያ ያላችሁትን አድርጉ፡፡”
\v 25 የጋድና ሮቤል ትውልዶች ሙሴን እንዲህ አሉት፣ “እኛ አገልጋዮችህ አንተ ጌታችን ያዘዝከንን እናደርጋለን፡፡
\s5
\v 26 ልጆቻችን፣ ሚስቶቻችን፣ መንጎችንና የቀን ከብቶቻችን በገለዓድ ከተሞች ይቆያሉ፡፡
\v 27 ሆኖም፣ እኛ፣ የአንተ አገልጋዮች ለጦርነት በያህዌ ፊት እንወጣን፤ ለጦርነት የታጠቀ እያንዳንዱ ሰው አንተ ጌታችን እንዳልከው ያደርጋል፡፡”
\s5
\v 28 ስለዚህም ሙሴ ለካህኑ አልዓዛር፣ ለነዌ ልጅ ለኢያሱና በእስራኤል ህዝብ መሃል የጎሳዎች አባቶች ለሆኑ መሪዎች እነርሱን በሚመለከት መመሪያዎቻችን ሰጠ፡፡
\v 29 ሙሴ እንዲህ አላቸው፣ “የጋድና የሮቤል ትውልዶች ከእናንተ ጋር ዮርዳስን ቢሻገሩና በያህዌ ፊት ለጦርነት የታጠቀ እያንዳንዱ ወንድ እና ምድሪቱ በፊታችሁ ቢገዙ፣ የገለዓድን ምድር ለእነርሱ ርስት አድርገህ ትሰጣቸዋለህ፡፡
\v 30 ነገር ግን ታጥቀው ከአንተ ጋር ዮርዳኖስን ባይሻገሩ፣ ርስታቸውን በከነአን ምድር ከአንተ ጋር ያገኛሉ፡፡”
\s5
\v 31 ስለዚህም የጋድና ሮቤል ትውልዶች እንዲህ ሲሉ መለሱ፣ “ያህዌ ለእኛ ለባሮችህ እንደተናገረው፣ የምናደርገው ነገር ይህ ነው፡፡ እንሻገራለን፡፡
\v 32 እኛ ታጥቀን በያህዌ ፊት ወደ ከነዓን ምድር እንሻገራለን፣ ነገር ግን የተወረሰው ርስታችን በዚህኛው የዮርዳስ ክፍል ከእኛ ጋር ይቀራል፡፡”
\s5
\v 33 ስለዚህ ሙሴ ለጋድና ለሮቤል ትውልዶች፣ እንዲሁም ለዮሴፍ ልጅ ለምናሴ ከፊል ነገድ፤ የአሞውያንን ንጉስ የሴዎንን ግዛት እና የባሳንን ንጉስ የዓግን ግዛቶች ሰጣቸው፡፡ ለእነርሱ ምድሪቱን ሰጣቸው፣ እንዲሁም ከተማዎቿን ከዳርቻዎቻቸው ጋር እና በዙሪያቸው ያሉ ከተሞችን አደላቸው፡፡
\s5
\v 34 የጋድ ትውልዶች ዲቦንን፣ አጣሮትን፣ አሮዔርን፣
\v 35 ዓጥሮት ሾፋንን፣ አያዜርን፣ ዮግብሃን፣
\v 36 ቤት ነምራንን እና ቤት ሃራንን የተቀጠሩ ከተሞችና ለበጎች ጉረኖዎች ያላቸው አድርገው እንደገና ገነቧቸው፡፡
\s5
\v 37 የሮቤል ትውልዶች ሐሴቦንንና፣ ኤልያሊንና ቂርያትይምን፣
\v 38 ናባውን፣ በአልሜዎንን (ስማቸው በኋላ ተቀይሯል) እና ሴባማንን እንደገና ገነቧቸው፡፡ እነርሱም ዳግም ለገነቧቸው ከተሞች ሌላ ስሞችን ሰጡ፡፡
\v 39 የምናሴ ልጅ የማኪር ትውልዶች ወደ ገለዓድ ሄደው በውስጧ ይኖሩ ከነበሩት ከአሞራውያን ከለአድን ወሰዱ፡፡
\s5
\v 40 ከዚያ ሙሴ ለምናሴ ልጅ ለማኪር ገለዓድን ሰጠው፣ የእርሱም ሰዎች መኖሪያችን በዚያ አደረጉ፡፡
\v 41 የምናሴ ልጅ ኢያዕር ሄዶ ከተማቸውን ይዞ የኢያዕር መንደሮች ብሎ ሰየማቸው፡፡
\v 42 ኖባህ ሄዶ ቄናትንና መንደሮቿን ይዞ፣ በራሱ ስም ኖባህ ብሎ ሰየማት፡፡
\s5
\c 33
\p
\v 1 የእስራኤል ህዝብ በሙሴና አሮን መሪነት በየታጣቂ በድኖቻቸው ሆነው ከግብጽ ምድር ከወጡ በኋላ ያደረጓቸው ጉዞዎች እነዚህ ነበሩ፡፡
\v 2 ሙሴ በያህዌ እንደታዘዘው፣ ከተነሰቡት አንስቶ እስሚሄዱበት ድረስ ያሉትን ስፍራዎች ጻፈ፡፡ ከስፍራ ስፍራ ያደረጓቸው እንቅስቃሴዎች እነዚህ ነበሩ፡፡
\s5
\v 3 በመጀመሪያው ወር፣ በወሩ በአስራ አምስተኛ ቀን ከራምሴ ተነስተው ተጓዙ፡፡ ከፋሲካው በኋላ በማለዳ፣ የእስራኤል ሕዝብ በግልጽ ግፃዊያን ሁሉ እያይዋቸው ወጡ፡፡
\v 4 ግብፃዊያን ያህዌ በመካከላቸው የገደላቸውን በኩሮቻቸውን እየቀበሩ ሳለና በአማልክቶቻቸው ላይ ጥፋት እያደረሰ ሳለ ይህ ሆነ፡፡
\s5
\v 5 የእስራኤል ሕዝብ ከራምሴ ወጥቶ በሱኮት ሰፈረ፡፡
\v 6 ከሱኮት ወጥተው በኤታሞ፣ በምድረ በዳው
\v 7 ከኤታም ወጥተው ከበአልዛፎን በተቃራኒ ወደ ፊሀሔርት ተመልሰው በሚግዶል በተቃራኒ ሰፈሩ፡፡
\s5
\v 8 ከዚያም ከፈሀሔርት በተቃራኒ ተነስተው በባህሩ መሃል ወደ ምድረበዳው ሄዱ፡፡ ለሶስት ቀናት በኤታም ምድረ በዳ ተጉዞው በማራ ሰፈሩ፡፡
\v 9 ከማራ ተነስተው ኤሊም ደረሱ፡፡ በኤሊም አስራ ሁለት ምንጮችና ሰባ የቴምር ዛፎች ነበሩ፡፡ የሰፈሩት በዚያ ስፍራ ነው፡፡
\v 10 ከኤሊም ተነስተው ቀይ ባህር አጠገብ ሰፈሩ፡፡
\s5
\v 11 ከቀይ ባህር ተነስተው በሲን ምድረበዳ ሰፈሩ፡፡
\v 12 ከሲን ምድረበዳ ተነስተው በራፍቃ ሰፈሩ፡፡
\v 13 ከራፍቃ ተነስተው በኤሉስ ሰፈሩ፡፡
\v 14 ከኤሉስ ተነስተው የሚጠጣ ውሃ በሌለበት ሰራፊዲም ሰፈሩ፡፡
\s5
\v 15 ከራፊዲም ተነስተው በሲና ምድረበዳ ሰፈሩ፡፡
\v 16 ከሲና ምድረበዳ ተነስተው በቂብሮት ሃታቫ ሰፈሩ፡፡
\v 17 ከቂብሮት ሃታቫ ተነስተው በሐዴሮት ሰፈሩ፡፡
\v 18 ከሐዴሮት ተነስተው በሪትማ ሰፈሩ፡፡
\s5
\v 19 ከሪትማ ተነስተው በሬሞን ዘፋሬስ ሰፈሩ፡፡
\v 20 ከሬምን ዘፋሬስ ተነስተው በልብና ሰፈሩ፡፡
\v 21 ከልብና ተነስተው በሪሳ ሰፈሩ፡፡
\v 22 ከሪሳ ተነስተው በቀሄላታ ሰፈሩ፡፡
\s5
\v 23 ከቀሄላታ ተነስተው በሻፍር ተራራ ሰፈሩ፡፡
\v 24 ከሻፍር ተራራ ተነስተው በሐራዳ ሰፈሩ፡፡
\v 25 ከሐራዳ ተነስተው በመቅሄሎት ሰፈሩ፡፡
\v 26 ከመቅሄሎት ተነስተው በታሐት ሰፈሩ፡፡
\s5
\v 27 ከታሐት ተነስተው በታራ ሰፈሩ፡፡
\v 28 ከታራ ተነስተው በሚትቃ ሰፈሩ፡፡
\v 29 ከሚትቃ ተነስተው በሐሹምና ሰፈሩ፡፡
\v 30 ከሐሽምና ተነስተው በምሴሮት ሰፈሩ፡፡
\s5
\v 31 ከሞሴሮት ተነስተው በብኔያዕቃን ሰፈሩ፡፡
\v 32 ከብኔያዕቃን ተነስተው በሖር ሃጊድጋድ ሰፈሩ፡፡
\v 33 ከሖር ሃጊድጋ ተነስተው በዮጥባታ ሰፈሩ፡፡
\v 34 ከዮጥባታ ተነስተው በዔብሮና ሰፈሩ፡፡
\s5
\v 35 ከዔብሮና ተነስተው በዔድዮን ጋብር ሰፈሩ፡፡
\v 36 ከዔድዮን ጋብር ተነስተው በቃዴስ በምትገኘው ጺን ምድረ በዳ ሰፈሩ፡፡
\v 37 ከቃዴስ ተነስተው በሖር ተራራ፣ በኤዶም ምድር ዳርቻ ሰፈሩ፡፡
\s5
\v 38 ካህኑ አሮን፤ በያህዌ ትዕዛዝ ወደ ሖር ተራራ ወጣ፣ የእስራኤል ህዝብ ከግብጽ ምድር በወጣበት በአርባኛው ዓመት፣ በአምስተኛው ወር፣ በወሩ በመጀመሪያው ቀን ካህኑ አሮን በዚያ ሞተ፡፡
\v 39 አሮን በሖር ተራራ ላይ ሲሞት ዕድሜው 123 ነበር፡፡
\s5
\v 40 በከነዓን ምድር በደቡባዊ በረሃ የሚኖረው ከነዓናዊው የዓራድ ንጉስ የእስራኤልን ህዝብ መምጣት ሰማ፡፡
\s5
\v 41 እነርሱ ከሖር ተራራ ተነስተው በሴልምና ሰፈሩ፡፡
\v 42 ከሴልምና ተነስተው በፋኖን ሰፈሩ፡፡
\v 43 ከፋኖን ተነስተው በአቦት ሰፈሩ፡፡
\s5
\v 44 ከአቦት ተነስተው በሞአብ ዳርቻ በኢየ አባሪም ሰፈሩ፡፡
\v 45 ከኢየ አባሪም ተነስተው በዲቦን ጋድ ሰፈሩ፡፡
\v 46 ከዲቦን ጋድ ተነስተው በዓልምን ዲብላታይም ሰፈሩ፡፡ 46ከዲቦን ጋድ ተነስተው በዓልምን ዲብላታይም ሰፈሩ፡፡
\s5
\v 47 ከዓልምን ዲብላታይም ተነስተው ከናባው ተራራ በተቃራኒ በዓብሪም ተራራ ሰፈሩ፡፡
\v 48 ከዓብሪም ተራራ ተነስተው በሞብ ሜዳዎች በዮርዳኖስ ኢያሪኮ ላይ ሰፈሩ፡፡
\v 49 በሞብ ሞአብ ዮርዳስ ላይ ከቤት የሺሞት እስከ አቤልስጢም ድረስ ሰፈሩ፡፡
\s5
\v 50 ያህዌ ሙሴን በሞአብ ሜዳዎች ዮርዳስ ውስጥ በኢያሪኮ ሳለ እንዲህ አለው፣
\v 51 “ለእስራኤላዊያን እንዲህ በላቸው፣ ‘ዮርዳኖስን አቋርጣችሁ ወደ ከነዓን ስትገቡ፣
\v 52 የምድሪቱን ነዋሪዎች በሙሉ ከፊታችሁ አስወጡ፡፡ የተቀረጹ ምስሎቻቸውን በሙሉ አጥፉ፡፡ የማምለኪያ ስፍራዎቻቸውንና የተቀረጹ ምስሎቻቸውን ሁሉ ደምስሱ፡፡
\s5
\v 53 የምድሪቱን ሀብት ውሰዱ በዚያም መኖር ጀምሩ፣ ምክንያቱም እኔ ምድሪቱን ለእናንተ ርስት አድርጌ ሰጥቻቸኋለሁ፡፡
\v 54 ምድሪቱን በእጣ እንደየ ጎሳው ብዛት ውረሱ፡፡ ብዙ ህዝብ ላለው ጎሳ ሰፊ መሬት ስጥ፣ አነስተኛ ቁጥር ላለው ጎሳ አነስ ያለ መሬት ስጥ፡፡ እያንዳንዱ ጎሳ እጣው በወደቀለት ስፍራ ያ መሬት ርስቱ ይናል፡፡ ምድሪቱን በአባቶችሁ ጎሳ መሰረት ትወርሳላችሁ፡፡
\s5
\v 55 የምድሪቱን ነዋሪዎች ከፊታችሁ ጨርሳችሁ ባታስወጡ ግን፣ እንዲቀሩ ያደረጋችኋቸው ሰዎች በዐይናችሁ ውስጥ እንደገባ ባዕድ አካል እና በጎናችሁ እንደገባ እሾህ ይሆኑባችኋል፡፡ በመትኖሩበት ምድር ሕይወታችሁን ከባድ ያደርጉባችኋል፡፡
\v 56 እኔ በእነዚህ ህዝቦች ላይ ላደርስባቸው ያቀድኩትን በእናንተም ላይ ደግሞ አደርገዋለሁ፡፡’”
\s5
\c 34
\p
\v 1 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
\v 2 “የእስራኤልን ሰዎች እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፣ ‘የእናንተ ወደምትሆን የከነዓን ምድርና ወደ ድንበሮቿ ስትገቡ፣
\v 3 ደቡባዊ ድንበራችሁ ከሲና ምድረ በዳ እስከ ኤዶም ይደርሳል፡፡ የደቡባዊ ድንበር ምስራቃዊ ጫፍ በጨው ባህር ደቡባዊ ጫፍ ድረስ ይሆናል፡፡
\s5
\v 4 ከአቅራቢም ኮረብታ ድንበራችሁ ወደ ደቡብ ይዞርና በሲና ምድረበዳ በኩል ያልፋል፡፡ ከዚያ ተነስቶ፣ በቃዴስ በርኔ ደቡብ ያልፍና ወደ ሐጸር አዳር እና ርቆ ዓጽምን ይደርሳል፡፡
\v 5 ከዚያ ተነስቶ፣ ድንበሩ ከጽሞን ወደ ግብጽ ጅረት ዞሮ እስከ ባህሩ ይከተለዋል፡፡
\s5
\v 6 ምዕራባዊው ድንበር የታላቁ ባህር ዳርቻ ይሆናል፡፡ ይህ ምዕራባዊ ድንበራችሁ ይሆናል፡፡
\s5
\v 7 ሰሜናዊ ድንበራችሁ ከታላቁ ባህር እስከ ሆር ተራራ እስከ ምትይዙት ስፍራ ድረስ ይሰፋል፣
\v 8 ከዚያ ከሖር ተራራ እስከ ሌና ሐማት፣ ከዚያ እስከ ጽዳድ ይደርሳል፡፡
\v 9 ከዚያ ድንበሩ እስከ ዚፍሮን ይቀጥልና ሐጻር ዔርን ሲደርስ ይጨርሳል፡፡ ይህ ሰሜናዊ ድንበራችሁ ይሆናል፡፡
\s5
\v 10 ምስራቃዊ ድንበራችሁን ከሐጸር ዔናን በደቡብ እስከ ሴፋም ታደርጋላችሁ፡፡
\v 11 ምስራቃዊ ድንበራችሁ ታች እስከ ሴፋም ወርዶ በዓይን ምስራቅ በኩል ራብላ ይደርሳል፡፡ ድንበሩ እስከ ከኔሬት ባህር ምስራቅ ይዘልቃል፡፡
\v 12 ከዚያ ድንበሩ በደቡብ በዮርዳኖስ ወንዝ በኩል እስከ ጨው ባህር እና ታች የጨው ባህር ምስራቅ ዳርቻ ድረስ ይቀጥላል፡፡ ይህች ድንበሩን ተከትሎ ዙሪያውን በሙሉ የእናንተ ምድራችሁ ናት፡፡
\s5
\v 13 ሙሴ የእስራኤልን ሰዎች እንዲህ ሲል አዘዘ፣ “ያህዌ ለዘጠኙ ጎሳዎችና ለአንዱ ጎሳ እኩሌታ እንዲሰጣችሁ ያዘዘው፣ በዕጣ የምትካፈሏት ምድር ይህች ናት፡፡
\v 14 የሮቤል ጎሣ ትውልዶች እና የጋድ ጎሣ ትውልዶች እንዲሁም የምናሴ ነገድ እኩሌታ በየአባቶቻቸው ጎሣዎች የንብረት አከፋፈልን ስርዓት ተከትለው ርስታቸውን ተቀብለዋል፡፡
\v 15 ሁለቱ ጎሣዎችና የአንዱ ጎሣ እኩሌታ ከዮርዳኖስ ወዲያ በኢያሪኮ በስተ ምስራቅ በጸሀይ መውጫ የርስታቸውን ድርሻ ተቀብለዋል፡፡”
\s5
\v 16 ያህዌ ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፣
\v 17 “ምድሪቱን ርስታችሁ አድርገው የሚያፋፍሏችሁ ሰዎች ስማቸው እነዚህ ናቸው፡ ካህኑ አልዓዛርና የነዌ ልጅ ኢያሱ ናቸው፡፡
\v 18 ለየጎሣቸው ምድሪቱን እንዲያካፍሉ ከየነገዱ አንድ መሪ ምረጡ፡፡
\s5
\v 19 የሰዎቹም ስሞች እነዚህ ናቸው፡ ከይሁዳ ነገድ የዩፎኒ ልጅ ካሌብ፡፡
\v 20 ከስምኦን ጎሣ ትውልዶች የዓሁድ ልጅ ሰላሚኤል፡፡
\s5
\v 21 ከቢኒያም ጎሣ፣ የኪስሎን ልጅ ኤልዳድ፡፡
\v 22 መሪ ከሆነው ከዳን ጎሣ ትውልዶች፣ የዩግሊ ልጅ ቡቂ፡፡
\v 23 ከዮሴፍ ትውልዶች፣ መሪ ከሆነው ከምናሴ ትውልዶች የሱፊድ ልጅ አኒኤል፡፡
\s5
\v 24 መሪ ከሆነው ከኤፍሬም ጎሣ ትውልዶች፣ የሺፍጣን ልጅ ቱሙኤል፡፡
\v 25 መሪ ከሆነው ከዛብሎን ጎሣ ትውልዶች የፈርናክ ልጅ ኤሊሳፈን፡፡
\v 26 መሪ ከሆነው ከይሳኮር ጎሣ ትውልዶች፣ የሖዛ ልጅ ፈልጢኤል፡፡
\s5
\v 27 መሪ ከሆነው ከኤሴር ጎሣ፣ የሴሌሚ ልጅ አሒሁድ፡፡
\v 28 መሪ ከሆነው ከንፍታሌም ጎሳ ትውልዶች፣ የዓሚሁድ ልጅ ፈዳሄል” ናቸው፡፡
\v 29 ያህዌ እነዚህን ሰዎች የከነዓንን ምድር እንዲያካፍሉና ለእያንዳንዱ የእስራኤል ጎሣዎች ድርሻቸውን እንዲሰጡ አዘዘ፡፡
\s5
\c 35
\p
\v 1 ያህዌ ሙሴን በሞአብ ሜዳ ዮርዳኖስ አጠገብ በኢያሪኮ እንዲህ አለው፣
\v 2 ”የእስረኤል ሰዎችን ለሌዋውያን ርስታቸው ከሆነው ከድርሻቸው እንዲሰጧቸው እዘዝ፡፡ የሚኖሩባቸውን ከተሞችና በዙሪያቸውም የግጦሽ መሬት ይስጧቸው፡፡
\s5
\v 3 ሌዋውያን እነዚህን ከተሞች መኖሪያቸው ያድርጓቸው፡፡ የግጦሽ መሬቱ ለከብቶቻቸው ለመንጎቻቸው እና ለእንስሳቻቸው ይሁኑ፡፡
\v 4 ለሌዋውያኑ የምትሰጣቸው በከተሞቹ ዙሪያ የሚገኘው የግጦሽ መሬት ከከተማ ቅጥር በየአቅጣጫው ስፋቱ አንድ ሺህ ክንድ ይሆናል፡፡
\s5
\v 5 ከከተማዋ በምስራቅ አቅጣጫ ሁለት ሺህ ክንድ ለካ፣ በስተደቡብ በኩልም ሁለት ሺህ ክንድ ለካ፣ በምዕራብ በኩል ሁለት ሺህ ክንድ፣ እና በሰሜን በኩል ሁለት ሺህ ክንድ ለካ፡፡ ይህ በከተማቸው ዙሪያ የግጦሽ መሬት ይሆናል፡፡ ከተማይቱ በመሃል ትሆናለች፡፡
\s5
\v 6 ለሌዋውያን የምትሰጧቸው ስድስቱ ከተሞች የስደተኞች ከተሞች ሆነው ያገለግሉ፡፡ እነዚህን ከተሞች በነፍስ መግደል ለተከሰሱ መሸሻ ስፍራ እንዲሆኑ ስጣቸው፡፡ እንዲሁም ሌሎች አርባ ሁለት ከተሞችን ስጣቸው፡፡
\v 7 ለሌዋውያን የምትሰጣቸው ከተሞች በጠቅላላው አርባ ስምንት ይሆናሉ፡፡ ከከተሞቹ ጋር የግጦሽ መሬትም ትሰጣቸዋለህ፡፡
\s5
\v 8 ብዙ የሆኑ የእስራኤል ህዝብ ጎሳዎችና ብዙ መሬት ያላቸው ጎሣዎች ብዙ ከተሞች ይሰጣቸዋል፡፡ አነስተኛዎቹ ጎሣዎች ጥቂት ከተሞች ይሰጣቸዋል፡፡ እያንዳንዱ ነገድ እንደ ተቀበለው እንደ ድርሻው መጠን ለሌዋውያኑ መስጠት አለበት፡፡”
\s5
\v 9 ከዚያም ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
\v 10 “ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ በላቸው፣ ‘ዮርዳኖስን አቋርጣችሁ ወደ ከነዓን ስትገቡ፣
\v 11 ይሁነኝ ብሎ ሰው ያልገደለ ሰው ወደ እነዚያ ከተሞች መግባት እንዲችል የመሸሸጊየ ከተማ ሆነው የሚያገለግሉ ከተሞችን ምረጡ፡፡
\s5
\v 12 እነዚህ ከተሞች ከደመኞቻችሁ የምትሸሸጉባቸው ይሁኑ፣ ስለዚህም የተከሰሰው ሰው በቅድሚያ በማህበሩ ፊት ለፍርድ ሳይቀርብ አይገደልም፡፡
\v 13 የመሸሸጊያ ከተማ አድርጋችሁ ስድስት ከተሞችን ምረጡ፡፡
\s5
\v 14 ከዮርዳኖስ ወዲያ ሶስት ከተሞችን፣ በከነዓን ምድር ደግሞ ሶስት ከተሞችን ስጡ፡፡ እነዚህ የመሸሸጊያ ከተሞች ይሆናሉ፡፡
\v 15 እነዚህ ስድስት ከተሞች ለእስራኤል ሰዎች፣ ለመጻተኞች፣ እና ለማናቸውም በመሀላቸው ለሚኖር ሳያውቅ ሰውን ለገደለ መሸሸጊያ ሆነው ያገለግላሉ፡፡
\s5
\v 16 ነገር ግን የተከሰሰው ሰው ተበዳዩን በብረት መሳሪያ ቢመታውና ተጠቂው ቢሞት፣ ተከሰሹ ነፍሰ ገዳይ ነው፡፡ እርሱ በእርግጥ ይገደል፡፡
\v 17 የተከሰሰው ሰው በእጁ በያዘው ድንጋይ ተበዳዩን ቢመታና ተበዳዩ ቢሞት ተከሳሹ ነፍሰ ገዳይ ነው፡፡ በእርግጥ ይገደል፡፡
\v 18 የተከሰሰው ሰው ተበዳዩን ሊገድል በሚችል የእንጨት መሳሪያ ቢመታውና ተበዳዩ ቢሞት ተከሳሹ በእርግጥ ነፍሰ ገዳይ ነው፡፡ ሊገደል ይገባዋል፡፡
\s5
\v 19 ደም ተበቃዩ ራሱ ነፍሰ ገዳዩን ይግደለው፡፡ ሲያገኘው፣ ሊገድለው ይችላል፡፡
\v 20 ተከሳሹ አንድን እየተደበቀ ወይም እየተሸሸገ ያለ ሰው በጥላቻ ቢገፈትረው ወይም አንዳች ነገር ቢወረውርበትና ከዚህም የተነሳ ተበዳዩ ቢሞት፣
\v 21 ወይም በጥላቻ መትቶ ቢጥለውና ከዚህም የተነሳ ተበዳዩ ቢሞት መትቶ የገደለው በእርግጥ ይገደል፡፡ ነብስ ገዳይ ነው፡፡ ደም ተበቃዩ ነብሰ ገዳዩን ሲያገኘው ይግደለው፡፡
\s5
\v 22 ነገር ግን ተከሳሹ ሰው ቀድሞ ባልታሰበበት ጥላቻ ተበዳዩን ቢመታው ወይም ሳያስበው አንዳች ነገር ወርውሮ ቢመታው፣
\v 23 ተበዳዩን ሳይመለከት ሊገድለው የሚችል ድንጋይ ቢወረውርበት፣ ተከሳሹ የተበዳዩ ጠላት አይደለም፤ ተበዳዩን ለመጉዳት እየሞከረ አልነበረም፡፡ የሆነ ሆኖ ተበዳዩ ቢሞት፣
\s5
\v 24 በዚህ ሁኔታ፣ ማህበረሰቡ በተከሳሹና በደም ተበቃዩ መሀል በእነዚህ ህጎች መሠረት ይዳኝ
\v 25 ማህበረሰቡ ተከሳሹን ከደም ተበቃዩ እጅ ያድነው፡፡ ማህበረሰቡ ተከሳሹን በመጀመሪያ ወዳሸሸበት መሸሸጊያ ከተማ ይመልሰው፡፡ ተከሳሹ፣ በቅዱሱ ዘይት የተቀባው በወቅቱ ያለው ሊቀካህን እስኪሞት ድረስ በዚያ ይኑር፡፡
\s5
\v 26 ነገር ግን የተከሰሰው ሰው በማንኛውም ጊዜ ከሸሸበት ከተማ ድንበር አልፎ ቢሄድ፣
\v 27 እና ደም ተበቃዩ ከመሸሸጊያ ከተማው ድንበር ውጭ ቢያገኘውና ቢገድለው፣ ደም ተበቃዩ በነብሰ ገዳይነት ጥፋተኛ አይሆንም፡፡
\v 28 ለዚህም ምክንያቱ ተከሳሹ ሰው እስከ ሊቀ ካህኑ ሞት ድረስ በመሸሸጊያ ከተማው መቆየት ስለነበረበት ነው፡፡
\s5
\v 29 እነዚህ ህጎች፤ በምትኖባቸው ቦታዎች ሁሉ፣ በትውልዳቸው ሁሉ ለእናንተ የጸኑ ናቸው፡፡
\v 30 ሰውን የገደለ ማንኛውም ሰው፣ በምስክሮች ቃል እየረጋገጠ መገደል አለበት፡፡ ነገር ግን የአንድ ምስክር ቃል ብቻውን ማንንም ሰው ለመግደል በቂ አይደለም፡፡
\s5
\v 31 ደግሞም፣ በነብስ ገዳይነት ጥፋተኛ ለሆነ ሰው ሕይወት የነፍስ ዋጋ አትቀበሉ፡፡ ያ ሰው በእርግጥ ይገደል፡፡
\v 32 ወደ መሸሸጊያ ከተማ ለሄደ የነፍስ ዋጋ አትቀበሉ፡፡ ሊቀ ካህኑ እስኪሞት ድረስ የነፍስ ዋጋ በመቀበል ወደ ራሱ ርስት ተመልሶ እንዲገባ አትፍቀዱለት፡፡
\s5
\v 33 በዚህ መንገድ የምትኖሩባትን ምድር አታርክሱ፣ ምክንቱም በነፍስ ግድያ የሚፈስ ደም ምድሪቱን ያረክሳል፡፡ ምድር በላይዋ ደም ሲፈስ፣ ደም ካፈሰሰው ሰው ደም በስተቀር ሌላ ምንም ማስተስረያ ማድረግ አይቻልም፡፡
\v 34 ስለዚህ የምትኖሩባትን ምድር አታርክሱ ምክንያቱም እኔ በውስጧ እኖራለሁ፡፡ እኔ፣ ያህዌ፣ በእስራኤል ሰዎች መሃል እኖራለሁ፡፡”
\s5
\c 36
\p
\v 1 ከዚያ ከዮሴፍ ትውልዶች ጎሣ የሆኑት፣ የአባቶቻቸው ቤተሰቦች መሪዎች፣ የምናሴ ልጅ በሆነው በሚኪር ልጅ ገለዓድ የተመሠረተው ጎሳ በሙሴና በእስራኤላዊያን አባቶች ቤተሰቦች አለቆች ፊት መጥተው ተናገሩ፡፡
\v 2 እንዲህም አሉ፣ “ጌታችን ሆይ፣ ያህዌ ለእስራኤል ህዝብ ርስታቸውን በዕጣ እንድታካፍላቸው አዞሃል፡፡ የወንድማችንን የሰለጰዓድን ድርሻ ለሴት ልጆቹ እንድትሰጥ ያህዌ አዝዞህ ነበር፡፡
\s5
\v 3 ነገር ግን ሴት ልጆቹ ከእስራኤል ሰዎች ከሌላ ጎሣ ወንዶችን ቢያገቡ፣ ድርሻቸው የሆነው መሬት ከአባቶቻችን ድርሻ ተነቅሎ ወደ ሌላ ጎሣ ይተላለፋል፡፡ መሬቱ የገቡበት የሌላ ጎሳ ድርሻ ይሆናል፡፡ በዚያ ሁኔታ፣ ከእኛ ርስትነት ይነቀላል፡፡
\v 4 ይህ ሲሆን፣ የእስራኤል ኢዮቤልዩ ሲመጣ፣ የእነርሱ ድርሻ የተጋቧቸው ጎሣዎች ርስት ይሆናል፡፡ በዚህ መንገድ የእነርሱ ድርሻ ከእኛ አባቶች ጎሣ ይወሰዳል፡፡
\s5
\v 5 ስለዚህም ሙሴ በያህዌ ቃል ለእስራኤል ሰዎች ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ እንዲህም አለ፣ “የዮሴፍ ትውልዶች ጎሣ የተናገሩት ትክክል ነው፡፡
\v 6 ያህዌ ስለ ሰለጰዓድ፣ ሴት ልጆች ያዘዘው ይህ ነው፡፡ እንዲህም አለ፣ ‘የመረጡትን ያግቡ፣ ነገር ግን ማግባት ያለባቸው ከአባታቸው ጎሣ ብቻ ነው፡፡’
\s5
\v 7 የእስራኤል ሰዎች ድርሻ ከአንድ ጎሣ ወደ ሌላው መሄድ የለበትም፡፡ እያንዳንዱ እስራኤላዊ የራሱን ጎሣ ድርሻ ይዞ መቀጠል አለበት፡፡
\s5
\v 8 ከጎሣዋ ርስት የወረሰች እያንዳንዷ የእስራኤል ሴት፣ ማግባት ያለባት ከአባቷ ጎሣ ውስጥ ብቻ ነው፡፡ ይህ የሚሆነው እያንዳንዱ እስራኤላዊ የአባቶቹን ርስት ይዞ እንዲኖር ነው፡፡
\v 9 ከአንዱ ጎሣ ወደ ሌላው ምንም ርስት መተላለፍ የለበትም፡፡ የእስራኤል ህዝብ እያንዳንዱ ጎሣ የራሱን ርስት ይዞ መቀጠል አለበት፡፡”
\s5
\v 10 ስለዚሀ የሰለጰዓድ ሴት ልጆች ያህዌ ሙሴን እንዳዘዘው አደረጉ፡፡
\v 11 የሰለጰዓድ ሴት ልጆች ማህለህ፣ ቲርጳ፣ ጌግላ፣ ሚልካ፣ ኑዔ
\v 12 ልጅ የምናሴትን ትውልዶች አገቡ፡፡ በዚህ መንገድ፣ ርስታቸው የአባታቸው ጎሣ ርስት ሆኖ ቀረ፡፡
\s5
\v 13 ያህዌ በሙሴ በኩል በሞአብ ሜዳዎች በዮርዳኖስ ኢያሪካ ላይ ለእስራኤል ሰዎች የሰጣቸው ትዕዛዛትና ድንጋጌዎች እነዚህ ናቸው፡፡

1328
06-JOS.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,1328 @@
\id JOS
\ide UTF-8
\h ኢያሱ
\toc1 ኢያሱ
\toc2 ኢያሱ
\toc3 jos
\mt ኢያሱ
\s5
\c 1
\p
\v 1 እንዲህም ሆነ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ከሞተ በኋላ እግዚአብሔር የሙሴ ዋና ረዳት የሆነውን የነዌ ልጅ ኢያሱን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦
\v 2 አገልጋዬ ሙሴ ሞቶአል። ስለዚህም ለእስራኤል ልጆች ወደምሰጣቸው ምድር አንተና ይህ ሕዝብ ሁሉ ተነሥታችሁ ይህን ዮርዳኖስ ተሻገሩ።
\v 3 የእግራችሁ ጫማ የሚረግጥውን ቦታ ሁሉ ለእናንተ ሰጥቼአለሁ።ለሙሴም ተስፋ እንደ ሰጠሁት ሰጥቻችኋለሁ።
\s5
\v 4 ከምድረ በዳው ከዚህም ከሊባኖስ ጀምሮ እስከ ታላቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ድረስ፤ የኪጢያውያን ምድር ሁሉ እስከ ፀሐይ መግቢያ እስከ ታላቁ ባሕር ድረስ ዳርቻእሁ ይሆናል።
\v 5 በሕይወትህ ዘመን ሁሉ ማንም ሊቋቋምህ አይችልም። ከሙሴ ጋር እንደ ነበርሁ እንዲሁ ከአንተ ጋር እሆናለሁ። አልጥልህም አልትውህም።
\s5
\v 6 ለአባቶቻቸው፦እሰጣችኋለሁ ብዬ ተስፋ የሰጠ'ኋችሁውን ምድር ይህ ሕዝብ እንዲወርስ ታደርጋለህና ጽና አይዞህ።
\v 7 ስለዚህም ጽና እጅግ በርታ። አገልጋዬ ሙሴ ያዘዘህን ሕግን ሁሉ ትጠብቀው ዘንድ ተጠንቀቅ። በምትሄድበትም ሁሉ እንዲከናወንልህ ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ አትበል።
\s5
\v 8 ስለዚህ ሕግ መጽሐፍ ሁልጊዜ ተናገር። የተጻፈበትንም ሁሉ ትጠብቅ ዘንድ በቀንና በሌሊትም አሰላስለው። የዚያን ጊዜም የተከናወነልህና የተሳከልህ ትሆናለህ።
\v 9 በምትሄድበት ሁሉ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና፦ ''ጽና፥ አይዞህ፥ አትፍራ፥ ተስፋ አትቁረጥ ብዬ አላዘዝሁህምን?''
\s5
\v 10 ኢያሱም የሕዝቡን አለቆች እንዲህ ብሎ አዘዘ፦
\v 11 ''በሰፈሩ መካከል እለፉ፤ ሕዝቡንም፦ ለራሳችሁ ስንቃችሁን አዘጋጁ ብላችሁ እዘዙአቸው። እግዚአብሔር አምላካችሁ እንዲትወርሱ ወደሚሰጣችሁ ምድር በሦስት ቀናት ውስጥ ይህን ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ ትወርሳላችሁ።
\s5
\v 12 ኢያሱም የሮቤልን ልጆች የጋድንም ልጆች የምናሴንም ነገድ እኩሌታ እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦
\v 13 የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ እንዲህ ብሎ ያዘዛቸውን ቃል አስቡ፦አምላካችሁ እግዚአብሔር እረፍት ይሰጣችኋል፤ይህንንም ምድር ይሰጣችኋል።
\s5
\v 14 ሚስቶቻችሁ፥ ልጆቻችሁና ከብቶቻችሁ ሙሴ በዮርዳኖስ ማዶ በሰጣችሁ ምድር ይቀመጣሉ። ነገር ግን ተዋጊ የሆኑ ሰዎቻችሁ እግዚአብሔር ለእናንተ እንደሰጣችሁ
\v 15 ወንድሞቻችሁን እረፍት እስኪሰጥ ድረስ ከወንድሞቻችሁ ፊት በመሆን እነርሱንም ለመርዳት ይሄዳሉ ። እነርሱም ደግሞ አምላካችሁ እግዚአብሔር የሚሰጣቸውን ምድር ይወርሳሉ። ከዚያም በኋላ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ብዮርዳኖሴ ማዶ በፀሐይ መውጫ ወደሰጣችሁ ወደ ርስታችሁ ትመለሳላችሁ፤ ትወርሳላችሁም።
\s5
\v 16 እነርሱም ለኢያሱ እንዲህ ብለው መለሰለት፦ያዘዝኸንን ነገር ሁሉ እናደርጋለን፤ ወደምትልከንም ስፍራ ሁሉ እንሄዳለን።
\v 17 ለሙሴ እንደ ታዘዝን ለአንተ ደግሞ እንታዘዛለን። ከሙሴ ጋር እንደ ነበረ እግዚአብሔር አምላክህ ብቻ ከአንተጋር ይሁን።
\v 18 በትእዛዝህ ላይ የሚያምፅና ቃልህን የማይታዘዝ ማንም ቢሆን ይገደል። ብቻ ጽና፥ በርታ።
\s5
\c 2
\p
\v 1 የነዌም ልጅ ኢያሱ፦ ''ሄዳችሁ ምድሪቱን፥ በተለይም ኢያሪኮን ሰልሉ ብሎ ከሰጢም ሁለት ሰዎች በስውር ላከ። እነርሱም ሄደው ረዓብ ወደምትባል ሴተኛ አዳሪ ቤት ገቡ፥ በዚያም አደሩ።
\v 2 ለኢያሪኮም ንጉሥ፦ እነሆ የእስራኤል ሰዎች አገሩን ሊሰልሉ ወደዚህ ገብተዋል ብለው ነገሩት።
\v 3 የኢያሪኮም ንጉሥ፡-አገሩን ሁሉ ሊሰልሉ ወደ አንቺ የመጡትንና ወደ ቤትሽ የገቡትን ሰዎች አውጪ ብሎ ወደ ረዓብ መልእክት ላከ።
\s5
\v 4 ነገር ግን ሴቲቱም ሁለቱን ሰዎች ወስዳ ሽሸገቻቸው። እርስዋም፦አዎን ሰዎቹ ወደ እኔ መጥተዋል፥ ነገር ግን ከወዴት እንደ ሆኑ አላወቅሁም፤
\v 5 የከተማውም በር የሚዘጋበት ጊዜ ላይ ሰዎቹ ወጡ፤ ወዴት እንደ ሄዱ አላውቅም፤ፈጥናችሁ ከተከተላችሁ ምናልባት ልትይዙአቸው ትችላላችሁ አለች።
\s5
\v 6 እርስዋ ግን ወደ ሰገንቱ አውጥታቸው፤ በዚያም በጣሪያ ውስጥ ባዘጋጀችው በተልባ እግር ውስጥ ሸሸጋቸው።
\v 7 ሰዎቹ ወደ ዮርዳኖስ መሻገሪያ በሚወስደው መንገድ አሳደዱአቸው። አሳዳጆችም እንደወጡ በሮቹ ተቆለፉ።
\s5
\v 8 ሰዎቹም ሳይተኙ ሴቲቱ ወደ እነርሱ ወደ ሰገነቱ ወጣች።
\v 9 ሰዎቹንም እንዲህ አለቻቸው፦እግዚአብሔር ምድሪቱን አሳልፎ እንደሰጣችሁ እናንተንም መፍራት በላያችን እንደ ወደቀ፤ በምድሪቱም በሚኖሩት ሁሉ ከፊታችሁ እንደ ቀለጡ አውቃለሁ።
\s5
\v 10 ከግብፅ ምድር በወጣችሁ ጊዜ እግዚአብሔር የኤርትራን ባሕር በፊታችሁ እንዳደረቀ፤ በዮርዳኖስም ማዶ በነበሩት እናንተም ፈጽማችሁ ባጠፋችኋቸው በሁለቱ በአሞራውያን ነገሥታት፥በሴዎንና በዐግ ያደረጋችሁትን ሰምተናል።
\v 11 ይህን በሰማን ጊዜ ልባችን ቀለጠ፤ አምላካችሁም እግዚአብሔር በላይ በሰማይ በታችም በምድር እርሱ አምላክ ነውና ከእናንተ የተንሣ ከዚያ ወዲያ ለማንም ነፍስ አልቀርለትም።
\s5
\v 12 እሁንም እባካችሁ እኔ ለእናንተ ቸርነት እንዳደረግሁ እናንተ
\v 13 ደግሞ ለአባቴ ቤት ቸርነት እንድታደርጉ፥ አባቴንና እናቴን፥ ወንድሞቼንና እኅቶቼንና ቤተ ሰቦቻቸውን ሁሉ እንድታድኑ፤ እንዲሁም ከሞት እንድታድኑን በእግዚአብሔር ማሉልኝ እውነተኛ ምልክትም ስጡኝ።
\s5
\v 14 ሰዎቹ፦ ''ይህን ነገራችንን ባትገልጪ ነፍሳችን በነፍሳችሁ ፋንታ እስከሞት እንኳ ይሆናል፤ እግዚአብሔርም ምድሪቱን በሰጠን ጊዜ ምሕረትን እናደርጋለን እንዲሁም ታማኝ ሆነን እንገኛለን፤'' አሉአት።
\s5
\v 15 ቤትዋም በከተማ ቅጥር የተጠጋ ስለነበረ በመስኮቱ በገመድ አወረደቻቸው።
\v 16 እርስዋም፦አሳዳጆቹ እንዳያገኙአችሁ ወደ ተራራው ሂዱ አሳዳጆቹም እስኪመለሱ ድረስ በዚያ ሦስት ቀን ተሰውራችሁ ተቀመጡ ኋላም መንገዳችሁን ትሄዳላችሁ አለቻቸው።
\v 17 ሰዎቹም አሉአት፦ይህን የምንልሽን ካላደረግሽ እኛም ከዚህ ካማልሽን መሐላ የተነሣ የሰጠንሽን ተስፋ ከመጠበቅ ነፃ እንሆናለን።
\s5
\v 18 እነሆ እኛ ወደ አገሩ በገባን ጊዜ ይህን ቀይ ክር እኛን ባወረድሽበት መስኮት በኩል እሰሪው ፤አባትሽንም እናትሽንም ወንድሞችሽንም የእባትሽንም ቤተ ሰብ ሁሉ ወደ አንቺ ቤት ሰብስቢ።
\v 19 ከቤትሽም ደጅ ወደ ሜዳ የሚወጣ ሁሉ ደሙ በራሱ ላይ ይሆንበታል፤ እኛም ንጹሐን እንሆናለን። ነገር ግን ከአንቺ ጋር በቤቱ ውስጥ ያለውን አንድ ሰው ቢነካው ደሙ በእኛ ራስ ላይ ይሆናል።
\s5
\v 20 ነገር ግን ይህንን ጉዳያችንን ብትገልጪ እኛም ከዚህ ካማልሽን መሐላ የተነሣ የሰጠንሽን ተስፋ ከመጠበቅ ነፃ እንሆናለን።
\v 21 እርስዋም፦ እንደቃላችሁ ይሁን አለች። ሰደደቻቸውም እነርሱም ሄዱ፤ ቀዩንም ክር በመስኮቱ በኩል አንጠለጠልችው።
\s5
\v 22 እነርሱም ሄደው ወደ ተራራው ደረሱ፥ አሳዳጆቹም እስኪመለሱ ድረስ እዚያ ለሦስት ቀናት ቆዩ። በመንገዱ ሁሉ ፈልገው አላገኙአቸውም።
\s5
\v 23 ሁለቱም ሰዎች ተመለሱ፤ ከተራራውም ወርደው ተሻገሩ ወደ ነዌም ልጅ ወደ ኢያሱ መጡ፤ የደረሰባቸውንም ሁሉ ነገሩት።
\v 24 ለኢያሱም እንዲህ አሉት፦ በእውነት እግዚአብሔር ይህን አገር ሁሉ በእጃችን አሳልፎ ሰጥቶናል፤ በአገሩም ውስጥ ያሉ ሰዎች ሁሉ ከእኛ የተነሣ እየቀለጡ አሉት።
\s5
\c 3
\p
\v 1 ኢያሱም በጠዋት ተነሣ፥ እነርሱም ከሰጢም ተነሥተው ወደ ዮርዳኖስ መጡ፤ እርሱና የእስራኤልም ልጆች ሁሉ ሳይሻገሩም በዚም ሰፈሩ።
\s5
\v 2 ከሦስት ቀንም በኋላ አለቆች በሰፈሩ መካከል ሄዱ።
\v 3 ሕዝቡንም እንዲህ ብለው አዘዙ፦የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ሌዋውያን ካህናት ተሸክመውት ባያችሁ ጊዜ ከሰፈራችሁ ተነሥታችሁ መከትል አለባችሁ።
\v 4 በእናንተና በታቦቱ መካከል ያለው ርቀት ሁለት ሺህ ክንድ ያህል ይሁን። በዚህ መንገድ በከዚሄ በፊት አልሄዳችሁበትምና የምትሄዱበትን መንገድ እንድታውቁ ወደ ታቦቱ አትቅረቡ።
\s5
\v 5 ኢያሱም ለሕዝቡ እንዲህ አለ፦ እግዚእአብሔር በመካከላችሁ ድንቅ ነገር ያደርጋልና ነገ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር ቀድሱ።
\v 6 ከዚያም ኢያሱ ካህናቱን እንዲህ አለ፦ የቃል ኪዳኑን ታቦት ተሸክማችሁ በሕዝቡ ፊት እለፉ። ስለዚህ የቃል ኪዳኑን ታቦት ተሸክመው በሕዝቡ ፊት አለፉ።
\s5
\v 7 እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለ፦ በዚህ ቀን በእስራኤል ሁሉ ፊት ከፍ ከፍ አደርጋለሁ። ከሙሴ ጋር እንደ ነበርሁ እንዲሁ ከእንተ ጋር መሆኔን ያውቃሉ።
\v 8 አንተም የቃል ኪዳኑን ታቦት የሚሸከሙትን ካህናት፦ በዮርዳኖስ ውኃ ዳር ስትደርሱ በዮርዳኖስ ውስጥ ቁሙ ብለህ ታዛቸዋለህ።
\s5
\v 9 ከዚያም ኢያሱ ለእስራኤል ሕዝብ እንዲህ አለ፦ ወደዚህ ቀርባችሁ የእግዚአብሔርን የአምላካችሁን ቃል ስሙ አለ።
\v 10 ሕያው አምላክ በመካከላችሁ እንደ ሆነና እርሱም ኤዊያዊውንም ፈርዛዊውንም ጌርጌሳዊውንም አሞራዊውንም ኢያቡሳዊውንም ከፊታችሁ ፈጽሞ እንደሚያወጣ በዚህ ታውቃላችሁ።
\v 11 እነሆ የምድር ሁሉ ጌታ የቃል ኪዳን ታቦት በፊታችሁ በዮርዳኖስ ውስጥ ያልፋል።
\s5
\v 12 አሁምን ከእስራኤል ነገዶች አሥራ ሁለት ሰዎችን ምረጡ፤ ከየነገዱ አንድ አንድ ሰው ይሁን።
\v 13 እንዲህም ይሆናል የምድርም ሁሉ ጌታ የእግዚአብሔርን ታቦት የተሸከሙ ካህናት የእግራቸው ጫማ በዮርዳኖስ ውኃ ሲቆም የዮርዳኖስም ውኃ ይቆማል፤ ከላይ የሚፈሰው ውኃ ሳይቀር መፍሰሱን ያቆማል፤ እንደ ክምርም ሆኖ ይቆማል።
\s5
\v 14 ሕዝቡም ዮርዳኖስን ለመሻገር ከድንኳናቸው በወጡ ጊዜ የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙ ካህናት በሕዝቡ ፊት ቀድመው ሄዱ።
\v 15 የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙ ወደ ዮርዳኖስ እንደመጡ፤ እግራቸውም የውኃውን ጫፍ በጠለቁ ጊዜ (በመከር ወራት ሁሉ ዮርዳኖስ እጅግ ሞልቶ እንደሚፈስ)
\v 16 ከላይ የሚወርደው ውኃ ቆመ፤ በጻርታን አጠገብ ባለችው አዳም በምትባል ከተማ በሩቅ ቆሞ እንደ ክምርም ሆነ፤ ወደ ዓረባ ባሕር ወደ ጨው ባሕር የሚወርደውም ውኃ ፈጽሞ ተቋረጠ፤ ሕዝቡም በኢያሪኮ አጠገብ ተሻገሩ።
\s5
\v 17 የእስራኤልም ሕዝቡ ሁሉ ዮርዳኖስን ፈጽመው አስኪሻሩ ድረስ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት የተሸከሙ ካህናት በዮርዳኖስ መካክል በደረቅ መሬት ጸንተው ቆመው ነበር።
\s5
\c 4
\p
\v 1 ሕዝቡ ሁሉ ዮርዳኖስን ፈጽመው በተሻገሩ ጊዜ እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለ፦
\v 2 ''ከሕዝቡ ከየነገዱ አንድ አንድ ሰው፥ አሥራ ሁለት ሰዎች ምረጥ።
\v 3 እንዲህ ብለህ ትእዛዝ ስጣቸው፦''በዮርዳኖስ መካከል የካህናት እግር ከቆመበት ስፍራ አሥራ ሁለት ድንጋዮችን አንሡ፤ ተሸክማችሁም በዚህ ሌሊት በምታድሩበት ስፍራ አኑሩአቸው።''
\s5
\v 4 ከዚያም ኢያሱ ከእያንዳንዱ የእስራኤል ነገድ አንድ አንድ ሰው የመረጣቸውን አሥራ ሁለት ሰዎች ጠራቸው።
\v 5 ኢያሱም አላቸው፦''በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ታቦት ፊት በዮርዳኖስ መካከል፤ እያንዳንዱም ሰው በጫንቃው ከአንዳንድ ድንጋይ ጋር በእስራኤል ልጆች ሁሉ ነገድ ቁጥር አሥራ ሁለት ድንጋዮችን ተሸክመው ይለፉ።
\s5
\v 6 ፤ልጆቻችሁም በሚመጣው ዘመን፦ እነዚህ ድንጋዮች ለእናንተ ምን ትርጉም አላቸው? ብለው በሚጠይቁበት ጊዜ ይህ በመካከላችሁ ምልክት ይሆናል።
\v 7 በዚያን ጊዜ እናንተም እንዲህ ብላችሁ ትመልሳላችሁ፦ ''በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት ፊት የዮርዳኖስ ውኃ ስለተቋረጠ ነው። በተሻገሩም ጊዜ የዮርዳኖስ ውኃ ቆመ፤ እነዚህም ድንጋዮች ለእስራኤል ልጆች ለዘላለም መታሰቢያ ይሆናሉ።''
\s5
\v 8 የእስራኤልም ልጆች ኢያሱ እንዳዘዛቸው አደረጉ፤ እግዚአብሔርም ኢያሱን እንደ ተናገረው በእስራኤል ነገድ ቁጥር ከዮርዳኖስ መካከል እንደ እስራኤል ነገድ ቁጥር አሥራ ሁለት ድንጋዮች አንሥተው ወደሚያድሩበት ስፍራ ወሰዱ። በዚያም በሚያድሩበት ስፍራ አኖሩአቸው።
\v 9 ኢያሱም የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙ ካህናት እግሮች በቆሙበት ስፍራ በዮርዳኖስ መካከል ሌሎችን አሥራ ሁለት ድንጋዮች ተከለ። እስከ ዛሬም ድረስ መታሰቢያ ሆነው በዚያ አሉ።
\s5
\v 10 ሙሴም ኢያሱን እንዳዘዘው ሁሉ እግዚአብሔር ኢያሱን ለሕዝቡ እንዲነገር ያዘዘው ነገር ሁሉ እስክፈጸም ድረስ ታቦቱን የተሸከሙ ካህናት በዮርዳኖስ መካከል ቆመው ነበር። ሕዝቡም ፈጥነው ተሻገሩ።
\v 11 ሕዝቡም ሁሉ ፈጽመው መሻገራቸውን በጨረሱ ጊዜ የእግዚአብሔር ታቦትና ካህናቱ በሕዝቡ ፊት ተሻገሩ።
\s5
\v 12 ሙሴም እንዳዘዘቸው የሮቤል ልጆች፥ የጋድም ልጆች፥ የምናሴም ነገድ እኩሌታ ተሰልፈው በእስራኤል ልጆች ፊት ተሻገሩ።
\v 13 አርባ ሺህ ያህል ሰዎች ጋሻና ጦራቸውን ይዘው ለጦርነት በእግዚእብሔር ፊት ወደ ኢያሪኮ ሜዳ ተሻገሩ።
\v 14 በዚያም ቀን እግዚአብሔር ኢያሱን በእስራኤል ሁሉ ፊት ከፍ አደረገው። ሕዝቡም ሙሴን እንዳከበሩት በዕድሜው ሁሉ አከበሩት።
\s5
\v 15 እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦
\v 16 ''የምስክርን ታቦት የሚሸከሙትን ካህናት ከዮርዳኖስ እንዲወጡ እዘዝ።''
\s5
\v 17 ኢያሱም ካህናቱን፦ ከዮርዳኖስ ውጡ ብሎ አዘዛቸው።
\v 18 የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙ ካህናት ከዮርዳኖስ መካከል በወጡ ጊዜና የካህናቱም እግር ጫማ ደረቅ መሬት መርገጥ በጀመረ ጊዜ የዮርዳኖስ ውኃ ወደ ስፍራው ተመለሰ፤ ቀድሞም ከአራት ቀናት በፊት እንደ ነበረ በዳሩርቻው ሁሉ መፍሰስ ጀመረ።
\s5
\v 19 ሕዝቡም በመጀመሪያው ወር በአሥረኛው ቀን ከዮርዳኖስ ወጡ። ከኢያሪኮ በስተ ምሥራቅ በኩል በጌልገላ ሰፈሩ።
\v 20 ከዮርዳኖስም ውስጥ የወሰዱአቸውን አሥራ ሁለቱን ድንጋዮች ኢያሱ በጌልገላ አቆማቸው።
\v 21 ለእስራኤልም ልጆች እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ ''በሚመጣው ዘመን ልጆቻችሁ አባቶቻቸውን፦ እነዚህ ድንጋዮች ምንድን ናቸው? ብለው ሲጠይቁ፥
\s5
\v 22 ለልጆቻችሁ እንዲህ ብላችሁ ታስታውቃላችሁ፦ እስራኤል ይህን ዮርዳኖስን በደረቅ ተሻገረ።
\v 23 እስክንሻገር ድረስ አምላካችሁ የኤርትራን ባሕር ከፊታችን እንዳደረቀ እንዲሁ እስክትሻገሩ ድረስ አምላካችሁ እግዚአብሔር የዮርዳኖስን ውኃ ከፊታችሁ አደረቀ።
\v 24 የእግዚአብሔርም እጅ ጠንካራ እንደ ሆነች የምድር አሕዛብ ሁሉ እንዲያውቁ አምላካችሁንም እግዚአብሔርን ለዘላለሙ እንድታከብሩ ነው።
\s5
\c 5
\p
\v 1 በዮርዳኖስ ማዶ በምዕራብ በኩል የነበሩ የአሞራውያን ነገሥታት ሁሉ፥ በታላቁም ባሕር አጠገብ የነበሩ የከነዓናውያን ነገሥታት ሁሉ፥ የእስራኤል ሕዝብ እስኪሻገሩ ድረስ የዮርዳኖስን ውኃ እግዚአብሔር እንዳደረቀ በሰሙ ጊዜ ልባቸው ቀለጠ፤ ከእስራኤልም ሕዝብ የተነሣ የአንድም ሕዝብ ነፍስ አልቀረላቸውም።
\s5
\v 2 በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር ኢያሱን እንዲህ አለው፦''የባልጩት ድንጋይ ስለት ሠርተህ የእስራኤልን ሕዝብ እንደገና ግርዛቸው።''
\v 3 ኢያሱም የባልጩት ድንጋይ ስለት ሠርቶ ግብት ሃራሎት (ትርጉሙም የግርዛት ኮረብታ) በተባለ ስፍራ የእስራኤልን ወንዶች ሁሉ ገረዛቸው።
\s5
\v 4 ኢያሱም የገረዘበት ምክንያት ይህ ነው፤ ከግብፅ የወጡት ወንዶች ሁሉ ጦረኞችን ሁሉ ጭምር ከግብፅ ከወጡ በኋላ በመንገድ ላይ በምድረ በዳ ሞቱ።
\v 5 የወጡት ሕዝብ ሁሉ ተገርዘው ነበር፤ ነገር ግን ከግብፅ በወጡበት መንገድ በምድረ በዳ የተወለዱት ሕዝብ ሁሉ አልተገረዙም ነበር።
\s5
\v 6 ከግብፅ የወጡ የእስራኤል ሕዝብና ጦረኞች ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ባለመስማታቸው እስኪሞቱ ድረስ አርባ ዓመት በምድረ በዳ ይጓዙ ነበር ። እግዚአብሔርም ወተትና ማር የምታፈስሰውን ምድር ለእኛ ይሰጠን ዘንድ ለአባቶቻቸው የማለላቸውን ምድር እንደማያሳያቸው ማለላቸው።
\v 7 እግዚአብሔር በእነርሱ ፋንታ ያስነሳቸው በመንገድ ሳሉ ሳይገረዙ የነበሩ ኢያሱም ገረዛቸው እነዚህን ልጆቻቸው ነበሩ።
\s5
\v 8 ሕዝቡም ሁሉ በተገዙ ጊዜ እስኪድኑ ድረስ በሰፈር ውስጥ በየስፍራቸው ነበሩ።
\v 9 እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለ፦ ዛሬ የግብፅን ነውር ከእናንተ ላይ አንከባልያለሁ አለው፤ ስለዚህ የዚያ ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ ጌልገላ ተብሎ ይጠራል።
\s5
\v 10 የእስራኤልም ሕዝብ በጌልገላ ሰፈሩ። ከወሩም በአሥራ አራተኛው ቀን በመሸ ጊዜ በኢያሪኮ ሜዳ ፋሲካ አደረጉ።
\v 11 ከፋሲካውም በዓል ቀን በኋላ በዚያው ዕለት የምድሪቱን ፍሬ ቂጣና ቆሎ በሉ።.
\s5
\v 12 ከምድሪቱም ፍሬ ከበሉበት ቀን በኋላ መና ተቋረጠ። ከዚያም ጊዜ ጀምሮ ለእስራኤል ልጆች መና አልነበራቸውም፤ ነገር ግን በዚያ ዓመት የከነዓንን ምድር ፍሬ በሉ።
\s5
\v 13 ኢያሱ ወደ ኢያሪኮ አጠገብ በነበረ ጊዜ ዓይኖቹን አንሥቶ ተመለከተ፥ እነሆም ሰይፍ በእጁ የያዘ ሰው በፊቱ ቆሞ ነበር፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ፦ ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህን? አለው።
\s5
\v 14 እርሱም፦ አይደለሁም እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ እዚህ መጥቼአለሁ አለ። ኢያሱም ወደ ምድር በግምባሩ ተደፍቶ ሰገደና፦ ጌታዬ ለአገልጋዩ የሚነግረው ምንድን ነው? አለው።
\v 15 የእግዚአብሔርም ሠራዊት አለቃ ኢያሱን፦ አንተ የቆምህበት ስፍራ የተቀደሰ ነውና ጫማህን ከእግህ አውልቅ አለው። ኢያሱም እንዲሁ አደረገ።
\s5
\c 6
\p
\v 1 ከእስራኤልም ሠራዊት የተነሣ የኢያሪኮ በሮች መጽሞ ተዘግተው ነበር። ወደ እርስዋም የሚገባና የሚወጣ ማንም አልነበረም።
\v 2 እግዚአብሔርም ኢያሱን አለው፦ ተመልከት፥ ኢያሪኮንና ንጉሥዋን የሠለጠኑ ወታደሮችዋንም በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼአለሁ።
\s5
\v 3 ሠራዊቶኞቻችሁ ሁሉ ከተማይቱን አንድ ጊዜ መዞር አለባቸው። ይህንንም ለስድስት ቀናት አድርጉት።
\v 4 ሰባትም ካህናት ሰባት ቀንደ መለከት በታቦቱ ፊት ይሸከሙ፤ በሰባተኛውም ቀን ከተማይቱን ሰባት ጊዜ ይዙሩ፥ ካህናቱም ቀንደ መለከቱን ይንፉ።
\s5
\v 5 ቀንደ መለከቱም ባለማቋረጥ ሲነፋ የመለከቱንም ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ታላቅ ጩኸት ይጩኽ፥ የከተማይቱም ቅጥር ይወድቃል። እያንዳንዱ ወታደር ወደፊት በመሄድ ማጥቃት አለባቸው።
\s5
\v 6 ከዚያም የነዌ ልጅ ኢያሱ ካህናቱን ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ የቃል ኪዳኑን ታቦት ተሸከሙ፥ ሰባትም ካህናት ሰባት ቀንደ መለከት ወስደው በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ይሂዱ አላቸው።
\v 7 ሕዝቡንም፦ ሂዱ፥ ከተማይቱንም ዙሩ፥ሠራዊቱም በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ይሂዱ አለ።
\s5
\v 8 ኢያሱም ለሕዝቡ እንደተናገረው ሰባቱ ካህናት ሰባቱን ቀንደ መለከት በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ይዘው ወደፊት እያለፉ ቀንደ መለከቱንም ይነፉ ነበር። የእግዚአብሔርም ቃል ኪዳን ታቦት ከኋቸው ይከተላቸው ነበር።
\v 9 ሠራዊቱም በካህናቱ ፊት ቀንደ መለከታቸውን እየነፉ ይሄዱ ነበር፤ ከዚያም ከቃል ኪዳን ታቦት ኋላ ደጀን ጦር ይሄድ ነበር፤እንዲሁም ካህናቱ ቀንደ መለከታቸውን ያለማቋረጥ ይነፉ ነበር።
\s5
\v 10 ኢያሱ ግን ሕዝቡን እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፦ እኔ ጩኹ እስከምልበት ቀን ድረስ አትጩኹ፥ ከአፋችሁም ድምፅ አይውጣ፤ በዚያን ጊዜ ብቻ ትጮኻላችሁ።
\v 11 ስለዚህ እግዚአብሔር የዚያን ቀን የቃል ኪዳን ታቦት አንድ ጊዜ ከተማይቱን እንዲዞር አደረገው፤ ከዚያም ወደ ማደሪያቸው ገቡ፤ ሌሊቱንም እዚያው አደሩ።
\s5
\v 12 ከዚያም ኢያሱ ማለዳ ተነሣ ካህናቱም የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ተሸከሙ።
\v 13 ሰባቱም ካህናት ሰባት ቀንደ መለከት ይዘው በእግዚአብሔር ታቦት ፊት በቀስታ እየሄዱ ቀንደ መለከቱንም ይነፉ ነበር። ሠራዊቱም በፊታቸው ይሄዱ ነበር። የደጀን ጦር ከእግዚአብሔር ታቦት ኋላ በሚድበት ጊዜ የቀንደ መለከት ድምፅ ያልማቋረጥ ይሰማ ነበር።
\v 14 በሁለተኛውም ቀን ከተማይቱን አንድ ጊዜ ዞረው ወደ ሰፈር ተመለሱ፤ ስድስት ቀንም እንዲሁ አደረጉ።
\s5
\v 15 በሰባተኛውም ቀን ሲነጋ ማልደው ተነሡ፥ ከዚህ በፊት በተለመደው ሁኔታ ከተማይቱን ሰባት ጊዜ ዞሩ፤ ከተማይቱን ሰባት ጊዜ የዞሩት በዚያ ቀን ነው።
\v 16 በሰባተኛውም ቀን ካህናቱ ቀንደ መለከቱን ሲነፉ ኢያሱ ሕዝቡን አዘዘ፦ እግዚአብሔር ከተማይቱን ሰጥቶአችኋልና ጩኹ።
\s5
\v 17 ከተማይቱና በእርስዋም ያለው ሁሉ ለእግዚአብሔር የተለየና ለጥፋት ይሆናሉ። የላክናቸውን መልክተኞች ስለ ሸሸገች ሴተኛ አዳሪዋ ረዓብ ብቻና ከእርስዋም ጋር በቤትዋ ውስጥ ያሉት ሁሉ በሕይወት ይኖራሉ።
\v 18 እናንተ ግን ለጥፋት የተለዩ ነገሮችን ከለያችሁት በኋላ አንዳች እንዳትወስዱ ራሳችሁን ጠብቁ። ለጥፋትም ከሆነው ነገር አንዳች የወሰዳችሁ እንደ ሆነ የእስራኤልን ሰፈር እንዲጠፋ ታደርጉታላችሁ፥ ችግርም ታመጣላችህ።
\v 19 ብር፥ ወርቅ፥ ናስና ከብረት የተሠሩ ዕቃዎች ሁሉ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ይሁን። ወደ እግዚአብሔርም ግምጃ ቤት ይግባ።
\s5
\v 20 ሕዝቡም ጮኹ፥ ካህናቱም ቀንደ መለከቱን ነፉ። ሕዝቡም የቀንደ መለከቱን ድምፅ በሰሙ ጊዜ ታልቅ ጩኸት ጮኹ፥ ቅጥሩም ሲወድቅ፤ ሕዝቡም እያንዳንዱ አቅንቶ ወደ ፊቱ ወደ ከተማይቱ ወጣ፤ ከተማይቱንም ያዙ።
\v 21 በከተማይቱም የነበሩትን ሁሉ ወንዱንና ሴቱን፥ ሕፃኑንና ሽማግሌውን፥ በሬውንም ፥በጉንና አህያውን በሰይፍ ስለት ፈጽመው አጠፉ።
\s5
\v 22 ኢያሱም ምድሪቱን የሰለሉትን ሁለቱን ሰዎች እንዲህ አላቸው፦ ወደ ሴተኛ አዳሪዋ ቤት ግቡ ከዚያም ሴቲቱንና ከእርስዋ ጋር ያሉትን ሁሉ እንደ ማላችሁላት አውጡ።
\s5
\v 23 ሰላዮቹም ወጣቶች ሄደው ረዓብን አውጧአት፤ አባትዋንና እናትዋን፥ ወንድሞችዋንም፥ አብሯት የነበሩ ቤተ ዘምዶችዋንም ሁሉ አወጡ። ከእስራኤልም ሰፈር ውጭ ወዳለው ስፍራ አመጦአቸው።
\v 24 ከተማይቱንም በእርስዋም የነበረውን ሁሉ በእሳት አቃጠሉ። ብሩ፥ ወርቅ፥የናሱና የብረት ዕቃዎች ብቻ በእግዚአብሔር ግምጃ ቤት አስቀመጡአቸው።
\s5
\v 25 ነገር ግን ኢያሪኮን ሊሰልሉ ኢያሱ የሰደዳቸውን መልክተኞች የሸሸገች ሴተኛ አዳሪዋን ረዓብን፥ የአባትዋንም ቤተ ሰብ፥አብሯት የነበሩትንም ሁሉ ኢያሱ በሕይወት እንዲሆሩ ፈቀደላቸው። እርስዋም ኢያሱ ኢያሪኮን እንዲሰልሉ የላካቸውን ሰዎች ስለሸሸገች በእስራኤል መካከል እስከ ዛሬ ድረስ ትኖራለች።
\s5
\v 26 በዚያን ጊዜም ኢያሱ እንዲህ ሲል አዘዛቸው፦ ይህችን ኢያሪኮ ከተማን ለመሥራት የሚነሣ ሰው በእግዚአብሔር ፊት የተረገመ ይሁን። መሠረትዋን ሲጀምር በኩር ልጁ ይሙት፥ እርዋንም ሲያቆም ታናሹ ልጁ ይሙት፥ ብሎ ማለ።
\v 27 እግዚአብሔርም ከኢያሱ ጋር ነበር፤ ዝናውም በምድር ሁሉ ላይ ወጣ።
\s5
\c 7
\p
\v 1 የእስራኤል ሕዝብ ግን እንዲጠፉ ከተለዩ ነገሮች በመውሰድ ታማኝነትን አጎደሉ። ከይሁዳ ነገድ የሆነ አካን፥ እርሱም የከርሚ ልጅ፥ የዘንበሪ ልጅ፥ የዛራ ልጅ፥ እንዲጠፉ ከተለዩት ነገሮች ወስደ፤ የእግዚአብሔርም ቁጣ በእስራኤል ሕዝብ ላይ ነደደ።
\s5
\v 2 ኢያሱም ከቤቴል በምሥራቅ በኩል በቤት አዌን አጠገብ ወዳለችው ወደ ጋይ ከኢያሪኮ ሰዎችን ላከ። እርሱም፦ ውጡ ምድሪቱንም ሰልሉ ብሎ ተናገራቸው። ሰዎቹም ወጡ፥ ጋይንም ሰለሉ።
\v 3 እነርሱም ወደ ኢያሱ ተመልሰው፡- ሕዝብን ሁሉ ወደ ጋይ አትላክ። ጋይን እንዲመቱ ሁለት ወይም ሦስት ሺህ ያህል ሰዎች ብቻ ይላክ። የጋይ ሰዎች በቁጥር ጥቂቶች ስለሆኑ ሕዝብ ሁሉ በውጊያ እንዲደክም አታድርግ።
\s5
\v 4 ከሠራዊቱ ሦስት ሺህ ያህል ሰዎች ብቻ ወደዚያ ወጡ፤ እነርሱም ከጋይ ሰዎች ፊት ሸሹ።
\v 5 የጋይም ሰዎች ከእነርሱ ሠላሳ ስድስት ያህል ሰዎችን መቱ፥ ከበሩ እስከ ሸባሪም ድረስ አባረሩአቸው፤ በቁልቁለቱም መቱአቸው። የሕዝቡም ልብ ፈራ፤ ድፍረትንም አጡ።
\s5
\v 6 ኢያሱም ልብሱን ቀደደ። እርሱና የእስራኤልም ሽማግሌዎች በእግዚአብሔር ታቦት ፊት እስከ ማታ ድርስ በግምባራቸው ተደፉ፤ በራሳቸውም ላይ ትቢያ ነሰነሱ።
\v 7 ኢያሱም አለ፦ ወዮ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፦ ይህን ሕዝብ ቀድሞኑ ዮርዳኖስን ለምን አሻገርኸው? እንዲያጠፉን በአሞራውያን እጅ ለምን አሳልፈህ ሰጠሃን? ከዚህ የተለየ ምርጫ ማድረግ በቻልንና በዮርዳኖስም ማዶ በተመቀመጥን ይሻለን ነበር።
\s5
\v 8 ጌታ ሆይ የእስራኤል ሕዝብ በጠላቶቻቸው ፊት ከሸሹ በኋላ ምን ማለት እችላለሁ?
\v 9 ይህንን ከነዓናውያንና በምድሪቱም የሚኖሩ ሁሉ ይሰማሉ። እነርሱም ይከብቡናል፥ በምድር ያሉትም ሕዝብ ስማችን እንዲረሳ ያደርጋሉ። ለታላቁ ስምህስ የምታደርገው ምንድን ነው?
\s5
\v 10 እግዚአብሔርም ኢያሱን አለው፦ተነስተህ ቁም! ለምን በግምባርህ ተደፍተሃል?
\v 11 እስራኤል ኃጢአትን አድርጎአል። ያዘዝኋቸውንም ቃል ኪዳኔን አፍርሰዋል። ለጥፋት ከተለዩት ነገሮችን ሰርቀዋል፤ ሰርቀው የወሰዱትንም ኃጢአት በዕቃቸውም ውስጥ ሸሸጉት።
\v 12 በዚህም ምክንያት የእስራኤል ሕዝብ በጠላቶቻቸው ፊት መቆም አይችሉም። ራሳቸው ለጥፋት የተለዩ ሆነው በጠላቶቻቸው ፊት ሸሹ። በመካከላችሁ እስካሁን ያለውን መወገድ ያለበትን እርም ከመካከላችሁ ካላጠፋችሁ ከዚህ በኃላ ከእናንተ ጋር አልሆንም።
\s5
\v 13 ተነሣና ሕዝቡን ቀድስልኝ፤ እንዲህም በላቸው፦ራሳችሁን ለነገ ለእግዚአብሔር ቀድሱ ይላል የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር፤ እስራኤል ሆይ ፥ሊጠፉ የሚገቡ ነገሮች እስካሁን በመካከላችሁ አለ። መጥፋት ያልባቸው ነገሮች ከመካከላችሁ እስክታጠፉ ድረስ በጠላቶቻችሁ ፊት መቆም አትችሉም።
\s5
\v 14 ነገም ራሳችሁን በየነገዳችሁ ታቀርባላችሁ፤ እግዚአብሔርም በዕጣ የሚለየው ነገድ በየወገኖቹ ይቀርባል። እግዚአብሔርም የሚለየው ወገን በየቤተ ሰቦቹ ይቀርባል። እግዚአብሔርም የሚለየው ቤተ ሰብ አንድ በአንድ ይቀርባል።
\v 15 ለጥፋትም የተለየ ነገር የተገኘበት ሰው የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን በማፍረሱና በእስራኤልም ላይ ክፉ ነገር እንዲመጣ በማድረጉ እርሱና ለእርሱም ያለው ነገር ሁሉ በእሳት ይቃጠላል።
\s5
\v 16 ኢያሱም ማልዶ ተነሣ፥ እስራኤልንም በየነገዶቻቸው አቀረበ፤ የይሁዳም ነገድ ተለየ።
\v 17 የይሁዳንም ወገን አቀረበ፥የዛራም ወገን ለየ። የዛራንም ወገን እያንዳንዱን አቀረበ፤ ዘንበሪም ተለየ።
\v 18 የቤተ ሰቡንም እያንዳንዱን አቀረበ፤ ከይሁዳም ነገድ የሆነ የከርሚ ልጅ የዘንበሪ ልጅ የዛራ ልጅ አካን ተለየ።
\s5
\v 19 ከዚያ ኢያሱ አካንን አለው፦ ልጄ ሆይ፥ በእስራኤልም አምላክ ፊት እውነቱን ተናገር፥ ለእርሱም ተናዘዝ። ያደረግኸውንም ንገረኝ፤ ከእኔም አትሸሽግ።
\v 20 አካንም መልሶ ኢያሱን እንዲህ አለ፦ በእውነት የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን በድያለሁ። ያደረግሁትም ይህንን ነው፦
\v 21 በዘረፋ መካከል አንድ የሚያምር የባቢሎን ኮት፥ ሁለት መቶም ሰቅል ብር፥ ሚዛኑም አምሳ ሰቅል የሆነ ወርቅ አይቼ ተመኘኋቸው፥ ወሰድኋቸውም። እነሆም፥ በድንኳኔ ውስጥ በመሬት ተሸሽገዋል፥ ብሩም ከሁሉ በታች ነው አለው።
\s5
\v 22 ኢያሱም መልእክተኞችን ሰደደ፥ ወደ ድንኳኑም ሮጡ፤ ዕቃዎቹም ነበሩ። በድንኳኑም ውስጥ ተሸሽጎ አገኙት ብሩም ከበታች ነበረ።
\v 23 ከድንኳኑም መካከል ዕቃዎቹን ወስደው ወደ ኢያሱና ወደ እስራኤል ሕዝብ ሁሉ አመጡት። በእግዚአብሔርም ፊት አኖሩት።
\s5
\v 24 ኢያሱና እስራኤል ሁሉ የዛራን ልጅ አካንን፥ ብሩንም፥ ኮቱንም፥ ወርቁንም፥ ወንዶችንና ሴቶች ልጆቹንም፥ በሬዎቹንም፥ አህያውዎቹንም፥ በጎቹንም፥ ድንኳኑንም፥ ያለውንም ሁሉ ወስደው ወደ አኮር ሸለቆ አመጡአቸው።
\s5
\v 25 ኢያሱም እንዲህ አለው፦ ለምን አስጨነቅኸን? እግዚአብሔርም ዛሬ ያስጨንቅሃል። እስራኤልም ሁሉ በድንጋይ ወገሩት፤ሁሉንም በእሳትም አቃጠሉአቸው፥ በድንጋይም ወገሩአቸው።
\v 26 በላዩም እስከ ዛሬ ድረስ ያለ ታላቅ የድንጋይ ክምር ሆነ። እግዚአብሔርም ከቁጣው ትኩሳት ተመለሰ። ስለዚህም የዚያ ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ የአኮር ሸለቆ ነው።
\s5
\c 8
\p
\v 1 እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለ፦ አትፍራ አትደንግጥ። ጦረኞችንም ሁሉ ከአንተ ጋር ውሰድ ተነሥተህም ወደ ጋይ ውጣ። ተመልከት፥ የጋይን ንጉሥ፥ ሕዝቡን፥ ከተማውንና ምድሩን በእጅህ ሰጥቼሃለሁ።
\v 2 በኢያሪኮና በንጉሥዋም እንዳደረግህ እንዲሁ በጋይና በንጉሥዋ ታደርጋለህ፤ ምርኮውንና ከብቱን ግን ለራሳችሁ ትወስዳላችሁ። ከከተማይቱም በስተ ኋላ ድብቅ ጦር አዘጋዝጅ አለው።
\s5
\v 3 ኢያሱም ተነሣና ጦረኞቹንም ሁሉ ወደ ጋይ ወሰዳቸው። ኢያሱም ጽኑዓን ኃያላን የሆኑትን ሠላሳ ሺህ ሰዎች መርጦ በሌሊትም ሰደዳቸው።
\v 4 እንዲህም ብሎ አዘዘቸው፦ እነሆ፥ከከተማይቱ በስተ ኋላ ተደበቁ። ከከተማይቱ በጣም ርቃችሁ አትሂዱ፤ነገር ግን ሁላችሁም ተዘጋጁ።
\s5
\v 5 እኔና ከእኔም ጋር ያለው ሕዝብ ሁሉ ወደ ከተማይቱ እንቀርባለን። እንደ በፊቱ ሊያጠቁን በሚመጡበት ጊዜ ከፊታቸው እንሸሻለን።
\v 6 አስቀድመን እንደ ሸሸን፥ የምንሸሸ ይመስላቸዋል፥ ከከተማይቱ እስክናርቃቸው ድረስ ወጥተው ይከተሉናል። እንዲህም ይላሉ፦ባለፈው እንዳደረጉት ከፊታችን እየሸሹ ነው። እኛም ከእነርሱ እንሸሻለን።
\v 7 እናንተም ከተደበቃችሁበት ስፍራ መጥታችሁ ከተማዋን ትይዛላችሁ። እግዚአብሔር አምላካችሁም እርስዋን በእጃችሁ አሳልፎ ይሰጣችኋል።
\s5
\v 8 ከተማይቱንም በያዛችኋት ጊዜ በእሳት አቃጥሉአት። በእግዚአብሔርም ቃል እንደታዘዛሁ ታደርጋላችሁ። እነሆ፥ አዝዣችኋለሁ።
\v 9 ኢያሱም ሰደዳቸው፤ እነርሱም ወደሚደበቁበት ስፍራ ሄደው፥ በጋይና በቤቴል መካከልም ከጋይ በስተምዕራብ ተደበቁ። ኢያሱ ግን በዚያች ሌሊት በሕዝቡ መካከል አደረ።
\s5
\v 10 ኢያሱም ማልዶ ተነሣና ሕዝቡን አሰለፈ፤እርሱና የእስራኤልም ሽማግሌዎች የጋይን ሕዝብ አጠቁ ።
\v 11 ከእርሱም ጋር የነበሩ ጦረኞች ሁሉ ሄደው፥ ወደ ከተማይቱ ደረሱ። ወደ ከተማይቱ አጠገብ መጡና በሰሜን በኩል በጋይ ሰፈሩ። በእነርሱና በጋይ መካከል ሸለቆ ነበረ።
\v 12 አምስት ሺህ ያህል ሰዎችንም ወስዶ በቤቴልና በጋይ መካከል በከተማይቱም በምዕራብ በኩል በድብቅ አስቀመጣቸው።
\s5
\v 13 በከተማይቱ የነበሩትን ሠራዊት ሁሉ፤ በከተማይቱ ሰሜን በኩል ዋና ጦርና በከተማይቱ ምዕራብ በኩል ደጀን ጦር ጠባቂዎችን አኖሩ። ኢያሱም በዚያች ሌሊት በሸለቆው አደረ።
\v 14 የጋይም ንጉሥ ባየ ጊዜ ይህ ስለታወቀ፥እርሱና ሠራዊቱ በማለዳ ተነስተው እስራኤልን ለማጥቃት ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ሸለቆ ወዳለው ሰፍራ ቸኮሉ። ከከተማይቱ በስተ ኋላ ግን ድብቅ ጦር ለማጥቃት እንዳለ አያውቅም ነበር።
\s5
\v 15 ኢያሱና እስራኤል ሁሉ ራሳቸው በፊታቸው ድል የተነሡ መስለው ወደ ምድረ በዳው መንገድ ሸሹ።
\v 16 በከተማይቱም የነበሩ ሰዎች ሁሉ በአንድነት ከኋላቸው እንዲሄዱ ተጠሩ፤ ኢያሱንም አሳደዱት፥ ከከተማይቱም ርቀው ወጡ።
\v 17 በጋይና በቤቴልም ውስጥ እስራኤልን ለማሳደድ ያልወጣ ሰው አልነበረም። ከተማይቱንም ክፍት አድርገው፥ እስራኤልን አሳደዱ።
\s5
\v 18 እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለ፦ በእጅህ ያለውን ጦር በጋይ አነጣጥር፤ ጋይንም በእጅህ አሳልፌ እሰጥሃለሁ። ኢያሱም በእጁ ያለውን ጦር በከተማይቱ ላይ ዘረጋ።
\v 19 የተደበቁትም ሠራዊት ፈጥነው ከስፍራቸው ወጥተው ኢያሱም እጁን እንደ ዘረጋ ሮጡ። ወደ ከተማይቱም ሮጡ፤ ገብተውም ያዙአት። ፈጥነውም ከተማይቱን በእሳት አቃጠሉአት።
\s5
\v 20 የጋይም ሰዎች ወደ ኋላቸው ዞረው ተመለከቱ። ከከተማይቱ ወደ ሰማይ የሚወጣውን ጢስ አዩ፤ ወዲህ ወይም ወዲያም መንገድ ማምለጥ አልቻሉም። ወደ ምድረ በዳ ሸሽተው የነበሩ የእስራኤላውያን ጦር ሠራዊት ያሳድዱአቸው የነበሩትን ለመግጠም ተመለሱ።
\v 21 ኢያሱና እስራኤል ሁሉ ድብቅ ጦር ከተማይቱን እንደ ያዙ ወደ ላይ ከሚወጣ ጢስ ጋር ባዩ ጊዜ፥ ወደ ኋላ ተመልሰው የጋይን ሰዎች ገደሉ።
\s5
\v 22 ሌሎቹም ወደ ከተማይቱ ሄደው የነበሩ የእስራኤል ሠራዊት ለማጥቃት ወጡ። ስለዚህም የጋይ ሰዎች በእስራኤል ሠራዊት መካከል ሌሎቹ በዚህ በኩልና ሌሎቹ በዚያ በኩል ተያዙ። እስራኤልም የጋይን ሰዎች አጠቁአቸው፤ አንዳቸውም አልተረፉም፤ አላመለጡምም።
\v 23 በሕይወት የያዙትን የጋይንም ንጉሥ ማርከው ወደ ኢያሱ አመጡት።
\s5
\v 24 እንዲህም ሆነ፤ የጋይን ሰዎች ሁሉ በሜዳና በምድረ በዳ አጠገብ እስራኤልን ሲያሳድዱ በነበሩበት ቦታ ሁሉም የመጨረሻ በሰይፍ ስለት እስኪ ወድቁ ድረስ ጨርሰው ከገደሉአቸው በኋላ፥ እስራኤል ሁሉ ወደ ጋይ ተመለሱ። በሰይፍም ስለት መቱአቸው።
\v 25 በዚያም ቀን በሰይፍ ስለት የወደቁት ወንዶችና ሴቶች የጋይ ሰዎች ሁሉ አሥራ ሁለት ሺህ ነበሩ።
\v 26 ኢያሱም የጋይን ሰዎች ሁሉ ፈጽሞ እስኪያጠፋ ድረስ ጦር የዘረጋባትን እጁን አላጠፈም።
\s5
\v 27 እስራኤላውያንም እግዚአብሔር ኢያሱን እንዳዘዘው የዚያችን ከተማ ከብትና ምርኮ ለራሳቸው ወሰዱ።
\v 28 ኢያሱም ጋይን አቃጠላት፥ ለዘላለም የፍርስራሽ ክምር እንዲሆን አደረጋት። እስከ ዛሬም ድረስ ባዶ ስፍራ ሆነች።
\s5
\v 29 የጋይንም ንጉሥ እስከ ማታ ድረስ በዛፍ ላይ ሰቀለው። ኢያሱም ፀሐይ በገባች ጊዜ የንጉሡን አስክሬን ከዛፍ አወርደው፥ በከተማይቱ በር አደባባይ እንዲጥሉት አዘዘ። በላዩም ታላቅ የድንጋይ ክምር አደረጉት። እስከ ዛሬ ድረስም ይህ የድንጋይ ክምር አለ።
\s5
\v 30 ከዚያም ኢያሱ በጌበል ተራራ ላይ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር መሠዊያን ሠራ።
\v 31 የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ የእስራኤልን ሕዝብ እንዳዘዘ፦ በሙሴም ሕግ መጽሐፍ እንደተጻፈው፥ መሠዊያው ካልተወቀረ ድንጋይና ብረት ካልነካው ነበረ። በእርሱም ላይ ለእግዚአብሔር የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቀረቡ፥ የደኅንነትንም መሥዋዕት ሠዉ።
\v 32 የእስራኤልም ሰዎች ፊት በድንጋዮቹ ላይ የሙሴን ሕግ ቅጂ ጻፈባቸው።
\s5
\v 33 እስራኤል ሁሉ፥ ሽማግሌዎቻቸውም፥ አለቆቻቸውም፥ ፈራጆቻቸውም፥ በመጻተኞችና በአገሩ ልጆች ፥እኩሌቶቹ በገሪዛን ተራራ ፊት ለፊት እኩሌቶቹም በጌባል ተራራ ፊት ሆነው የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት በተሸከሙት በካህናትና በሌዋውያን ፊት ለፊት፥ በታቦቱም ፊት በወዲህና በወዲያ ቆመው ነበር። የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ እንዳዘዘ፥የእስራኤልን ሕዝብ አስቀድሞ ባረኩ።
\s5
\v 34 ከዚህም በኋላ ኢያሱ በሕጉ መጽሐፍ እንደ ተጻፉ የሕጉን ቃሎች ሁሉ በረከቱንና እርግማኑን አነበብ።
\v 35 ኢያሱም በእስራኤል ጉባኤ ሁሉ ፊት በሴቶቹም፥ በሕፃናቱም፥ በመካከላቸውም በሚኖሩት መጻተኞች ፊት ሙሴ ካዘዘው አንዲት ቃል ሳያስቀር ሁሉን አነበበ ።
\s5
\c 9
\p
\v 1 ከዚያም በዮርዳኖስ ማዶ በተራራማውና በቆላማው በታላቁ ባሕር ዳርቻ በሊባኖስም ፊት ለፊት የነበሩ ነገሥታት ሁሉ፥ ኬጢያዊ አሞራዊም ከነዓናዊም ፌርዛዊም ኤዊያዊም ኢያቡሳዊም
\v 2 ኢያሱንና እስራኤልን ሊወጉ አንድ ሆነው ተሰበሰቡ።
\s5
\v 3 የገባዖን ሰዎችም ኢያሱ በኢያሪኮና በጋይ ያደረገውን በሰሙ ጊዜ፥
\v 4 እነርሱ ደግሞ የማታለል ዕቅድ አደረጉ። ራሳችውን እንደ መልእክተኛ አድርገው ቀረቡ። ያረጀና የተቀደደ ጆኒያ ወስደው በአህዮቻቸውም ላይ ጫኑ። ደግሞም ያረጀ፥የተቀደደና የተሰፋ አሮጌ ወይን ጠጅ አቁማዳ ጫኑ።
\v 5 ያረጀ የተሰፋም ጫማ በእግራቸው አደረጉ፤ አሮጌምና የተቀደድ ልብስም ለበሱ። ለስንቅም የያዙት እንጀራ ሁሉ የደረቀና የሻገተ ነበረ።
\s5
\v 6 ኢያሱም ወደ ሰፈረበት ወደ ጌልገላ ሄደው ለእርሱና ለእስራኤል ሕዝብ፦በጣም ሩቅ አገር ከሆነ ተጉዘን የመጠን ነን፥ ከእኛ ጋር ኪዳን አድርጉ አሉ።
\v 7 የእስራኤልም ሰዎች ኤዊያውያንን፦ ምናልባት በመካከላችን የምትቀመጡ ትሆናላችሁ። እንዴትስ ከእናንተ ጋር ቃል ኪዳን እናደርጋለን? አሉአቸው።
\v 8 እነርሱም እንዲህ አሉት፦ እኛ የእናንተ አገልጋዮች ነን። ኢያሱም እንዲህ አላቸው፦ እናንተ እነማን ናችሁ? ከወዴትስ መጣችሁ?
\s5
\v 9 እነርሱም ለኢያሱ እንዲህ አሉት፦ እኛ አገልጋዮችህ ከእግዚአብሔር ከአምላክህ ስም የተነሣ እጅግ ከራቀ አገር እዚህ መጥተናል። ዝናውንም በግብፅም ያደረገውን ሁሉ፥
\v 10 በዮርዳኖስ ማዶም በነበሩት በሁለቱ በአሞራውያን ነገሥታት በሐሴቦን በንጉሥ በሴዎን በአስታሮትም በነበረው በባሳን ንጉሥ በዐግ ያደረገውን ሁሉ ሰምተናል።
\s5
\v 11 ሽማግሌዎቻችንና በአገራችን የሚኖሩት ሁሉ፦ ለጉዞአችሁም ስንቅ በእጃችሁ ያዙ። ልትገናኙአቸውም ሂዱና እንዲህ በሉአቸው፦ እኛ አገልጋዮቻችሁ ነን፤ ከእኛም ጋር ቃል ኪዳን አድርጉ።
\v 12 ወደ እናንተ ለመምጣት በተነሣንበት ቀን ይህን እንጀራ ትኩስን ለስንቅ ከቤታችን የወሰደነው ነው። ነገር ግን ተመልከቱ፥ አሁንም ደረቅና የሻግብተ ነው።
\v 13 እነዚህም የጠጅ አቁማዳዎች ስንሞላቸው አዲስ ነበሩ፤ እነሆም፥ ተቀድደዋል። ጉዞአችንም እጅግ ሩቅ ስለ ነበረ ልብሶቻችንና ጫማዎቻችን አርጅተዋል።
\s5
\v 14 እስራኤላውያንም ከስንቃቸው ወሰዱ፥ ነገር ግን ከእግዚአብሔርም ምክርን አልጠይቁም ነበር።
\v 15 ኢያሱም ከእነርሱ ጋር ስምምነት አደረገ፥ በሕይወት እንዲተዋቸውም ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ። የማኅበሩም አለቆች ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደረጉ።
\s5
\v 16 የእስራኤላውያንም ከገባዖን ሰዎች ጋር ቃል ኪዳኑን ካደረጉ ከሦስት ቀን በኋላ፥ ሰዎቹ እዚያው አጠገባቸው የሚኖሩ ጎረቤቶቻቸው መሆናቸውን ዐወቁ።
\v 17 ከዚያም እስራኤላውያን ተዘጋጅተው በሦስተኛው ቀን ወደ ከተሞቻቸው መጡ። የከተሞቻቸውም ስም ገባዖን፥ ክፈራ፥ ብኤሮትና ቂርያትይዓይሪም ናቸው።
\s5
\v 18 የሕዝቡም አለቆች በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ስም ቃል ኪዳን አድርገው ስለነበረ እስራኤላውያንም ጥቃት አልደረሱባቸውም። የእስራኤልም ሕዝብ ሁሉ በመሪዎቹ ላይ አጉረመረሙ፥
\v 19 ነገር ግን መሪዎቹ ሁሉ ለማኅበሩ እንዲህ አሉ፦ በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ስም ቃል ኪዳን ስለገባንላቸው አሁን ጉዳት ልናደርስባቸው አንችልም፥
\s5
\v 20 የምናደርግላቸው ነገር ቢኖር ይህ ነው፦ የገባንላቸውን የቃል ኪዳን ማሐላ ብናፈርስ ቁጣ እንዳይደርስብን በሕይወት እንዲኖሩ ማድረግ ነው። የሕዝቡም አለቆች ለሕዝባቸው እንዲህ አሉ፦ በሕይወት ይኑሩ።
\v 21 ስለዚህም የእስራኤል አለቆች ስለእነርሱ እንደ ተናገሩት ገባዖናውያን ለእስራኤላውያን ሁሉ እንጨት ሰባሪና ውኃ ቀጂ ሆኑ።
\s5
\v 22 ከዚያም ኢያሱ የገባዖንን ሰዎች ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ እናንተ እዚሁ በመካከላችን እየኖራችሁ፥ ከእናንተ ሩቅ ስፍራ ነው የመጠነው፥ ብላችሁ ያታለላችሁን ለምንድን ነው?
\v 23 ስለዚህ በዚህ ምክንያት እናንተ የተረገማችሁ ናችሁ፥ አንዳንዶቻችሁም ለአምላኬ ቤት ሁል ጊዜ እንጨት ሰባሪና ውኋ ቀጂ አገልጋዮች ትሆናላችሁ።
\s5
\v 24 እነርሱም ለኢያሱ እንዲህ ብለው መለሱለት፥ እግዚአብሔር አምላክህ አገልጋዩን ሙሴን እንዳዘዘው፥ ምድሪቱን በሙሉ ለእናንተ እንደሚሰጣችሁና ነዋሪዎቿንም ከፊታችሁ እንደሚያጠፋቸው በእርግጥ ለእኛ አገልጋዮችህ ተነግሮናል፥ ስለዚህ ከእናንተ የተነሣ ለሕይውታችን በመሥጋት ይህን አድርገናል።
\v 25 እነሆ አሁን በእጅህ ነን፥ መልካምና ትክክል መስሎ የታየህን ነገር ሁሉ አድርግብን።
\s5
\v 26 ስለዚህ ኢያሱ የገባዖንን ሰዎች ከእስራኤል ሰዎች እጅ አዳናቸ እስራኤላውያንም አልገደሏቸውም።
\v 27 በዚያም ዕለት ኢያሱ የገባዖንን ሰዎች ለማኅበረ ሰቡና እግዚአብሔር በመረጠው ስፍራ ለሚቆመው የእግዚአብሔር መሠዊያ እስከ ዛሬ ድረስ እንጨት ሰባሪችና ውኃ ቀጂዎች አደረጋቸው።
\s5
\c 10
\p
\v 1 የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶነጼዴቅ ኢያሱ ጋይን ይዞ ፈጽሞ እንደ ደመሰሳት፤ እንደዚሁም በኢያሪኮና በንጉሥዋ ላይ ያደረገውን ሁሉ ሰማ። እንዲሁም የገባዖን ሰዎች ከእስራኤል ጋር እንዴት የሰላም ውል አድርገው በመካከላቸው መኖራቸውን ሰማ።
\v 2 የኢየሩሳሌም ሕዝብ ፈሩ፥ ምክንያቱም ገባዖን እንደ ነገሥታቱ ከተማ ሁሉ ታላቅ ከተማ ነች። ገባዖንም ከጋይ ይልቅ ትልቅና ሰዎቿም ብርቱ ተዋጊዎች ነበሩ።
\s5
\v 3 ስለዚህ የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶኒጼዴቅ፥ ወደ የኬብሮን ንገሥ ሆነም፥ ወደ የያርሙት ንጉሥ ጲርአም ፥ ወደ የለኪሶ ንጉሥ ያፈዓና ወደ የዔግሎን ንጉሥ ዳቤር ላከ።
\v 4 ወደዚህ መጥታችሁ አግዙኝ። ገባዖን ከኢያሱና ከእስራኤላውያን ጋር የሰላም ስምምነት ስላደረጉ ገባዖንን እንምታ።
\s5
\v 5 ከዚያም አምስቱ የአሞራውያን ነገሥታት ማለት የኢየሩሳሌም ንጉሥ፥ የኬብሮን ንጉሥ፥ የያርሙት ንጉሥ፥ የለኪሶ ንጉሥና የዔግሎን ንጉሥ ያላቸውን ሠራዊታቸውን ሁሉ አስተባብረው፥ ገባዖንን ወጓት።
\s5
\v 6 የገባዖንም ሰዎች ወደ ኢያሱና ወደ ጌልገላ ሠራዊት መልእክት ላኩ። እንዲህም አሉ፦ ከአገልጋዮቻችሁ እጃችሁን አታውጡ ፍጠኑ። በፍጥነት መጥታችሁ አድኑን። በተራራማው አገር የሚኖሩ የአሞራውያን ነገሥታት ሁሉ ኃይላቸውን አስተባብረው እኛን ለማጥቃት ተሰልፈውብናልና እርዱን። እኛን ባሮችህን አትተወን ርዳን ፈጥነህ በመድረስም አድነን ብለው ላኩበት።
\v 7 ስለዚህ ኢያሱ እርሱና ተዋጊዎች ሰዎች ሁሉ ከእርሱ ጋር ጨምሮ ከጌልገላ ወጣ።
\s5
\v 8 እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለ፦ አትፍራቸው። በእጅህ አሳልፌ ሰጥቻለሁ፤ ማንም ሊቋቋሙህ አይችልም።
\s5
\v 9 ኢያሱም ከጌልገላ ሌሊቱን ሁሉ ሲገሠግሥ አድሮ ድንገት ደረሰባቸው።
\v 10 እግዚአብሔም የጠላትን ሠራዊት በእስራኤል ፊት ግራ አጋባቸው። እጅግ መታቸው። በገባዖንም ወደ ቤት ሖሮን በሚያስወጣው መንገድ እስከ ዓዜቅ መንገድ እስከ መቄዳም ድረስ ተከትሎአቸው አሳድዶ መታቸው።
\s5
\v 11 ከቤት ሖሮን ወደ ዓዜቃ ቁልቁል በሚወስደው መንገድ ላይ ከእስራኤላውያን ፊት በሚሽሹበት ጊዜ እግዚአብሔር ከሰማይ ትልልቅ ድንጋዮች ወረወረባቸው ሞቱም። በእስራኤል ሰዎች ሰይፍ ከሞቱት ይልቅ በወረደው የበረዶ ድንጋዮች የሞቱት የበለጡ ነበሩ።
\s5
\v 12 ከዚያም እግዚአብሔር ለእስራኤል በአሞራውያን ላይ ድል በሰጠበት ዕለት ኢያሱ እግዚአብሔርን ተናገረ። ኢያሱም በእስራኤል ፊት እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፦ ''ፀሐይ፥ በኤሎን ሸለቆ በገባዖን ላይ ይቁም።''
\s5
\v 13 ሕዝቡ ጠላቶቹን እስኪ በቀል ድረስ፤ ፀሐይ ባለችበት ቆመች፥ ጨረቃም አልተንቀሳቀሰችም። ይህም በያሻር መጽሐፍ ላይ የተጻፈ አይደለምን? ፀሐይ በሰማዩ መካከል ቆመች፥ ለሙሉ ቀን ያህል አልተንቀሳቀሰችም ነበር።
\v 14 እግዚአብሔር የሰውን ቃል እንደዚያ የሰማበት ዕለት ከዚያ በፊት ወይም ከዚያ በኋላ አልነበረም። እግዚእአብሔር ለእስራኤል ይዋጋ ነበር።
\s5
\v 15 ኢያሱና መላው እስራኤል ወደ ጌልገላ ሰፈር ተመለሱ።
\v 16 በዚህ ጊዜ አምስቱ የአሞራውያን ገሥታት ሸሽተው በመቄዳ ዋሻ ራሳቸውን ደብቀው ነበር።
\v 17 ኢያሱም አምስቱ ነገሥታት በመቄዳ ዋሻ ውስጥ ተደብቀው መገኘታቸውን ሰማ፤
\s5
\v 18 ኢያሱም እንዲህ አለ፦ ትልልቅ ድንጋዮች ወደ ዋሻው አፍ አንከባልሉ፤ወታደሮችንም እንዲጠብቁአቸው በዚያ አቁሙ። ቸልም አትበሉ።
\v 19 ጠላቶቻችሁን አሳዱአቸው፤ ከበስተ ኋላ ሆናችሁም ጥቃት አድርሱባቸው። እግዚአብሔር አምላካችሁ በእጃችሁ አሳልፎ ስለሰጣችሁ ወደ ከተሞቻቸው እንዳይገቡ አድርጉአቸው።
\s5
\v 20 ኢያሱና እስራኤል ልጆች ፈጽሞ እስኪያጠፉ ድረስ ከታላቅ ጭፍጨፋ ጋር ጨረሱ። የተረፉት ጥቂቶቹ ብቻ ወደ ተመሸጉት ከተሞቻቸው ደረሱ።
\v 21 ከዚያም ሠራዊቱ በሙሉ በደኅና ተመልሶ ኢያሱ ወደ ሰፈረበት ወደ መቄዳ ተመለሰ። በእስራኤላውያንም ላይ አንድት ቃል ለመናገር ማንም ሰው የደፈረ አልነበረም።
\s5
\v 22 ኢያሱም እንዲህ አላቸው፦ የዋሻውንም አፍ ክፈቱና ከዋሻው እነዚህን አምስቱን ነገሥታት አምጡልኝ።
\v 23 እነርሱም እንዳለው አደረጉ። እነዚህንም አምስቱን ነገሥታት፦ የኢየሩሳሌምን ንጉሥ፥ የኬብሮንን ንጉሥ፥ የያርሙትን ንጉሥ የለኪሶን ንጉሥና የዔግሎንን ንጉሥ አውጥተው አመጡለት።
\s5
\v 24 እነዚህን ነገሥታት ወደ ኢያሱ ባማጡበት ጊዜ፥ እርሱም እያንዳንዱን የእስራኤል ሰዎች ጠራቸው፤ እንዲሁም ከእርሱ ጋር ወደ ጦርነት ሄደው የነበሩትን የጦር አዛዦችን እንዲህ አላቸው፦ እግሮቻችሁን በእነዚህ ነገሥታት አንገት ላይ አድርጉ። እነርሱም ወደ ፊት ቀርበው እግሮቻቸውን በነገሥታቱ አንገት ላይ አሳረፉ።
\v 25 ኢያሱም እንዲህ አላቸው፦ አትፍሩ፥ አትደንግጡም። በርቱ፥ ጽኑም። እግዚአብሔር አምላካችሁ በምትዋጉበት ጊዜ በጠላቶቻችሁ ሁሉ ላይ እንዲህ ያደርጋል።
\s5
\v 26 ከዚያም ኢያሱ ነገሥታቱን መትቶ ገደላቸው። በአምስትም ዛፎች ላይ ሰቀላቸው። አስክሬናቸውም እስኪመሽ ድረስ ተሰቅለው ነበር።
\v 27 የፀሐይ መጥለቂያ በሆነ ጊዜ ኢያሱ ትእዛዝ ሰጠ፦ ከዚያም የነገሥታቱን አስክሬኖች ከዛፎቹ ላይ እንዲያወርዱ ቀድሞ ራሳቸውን ደብቀው ወደነበሩበት ዋሻ ውስጥ እንዲጥሉአቸው አዘዛቸው። በዋሻውም አፍ ላይ ትልልቅ ድንጋዮች አኖሩ። እነዚያ ድንጋዮች እስከ ዛሬ ድረስ በዚያ ይገኛሉ።
\s5
\v 28 በዚህ መንገድ በዚያች ዕለት ኢያሱ መቄዳን ያዘ፤ ከንጉሥዋም ጭምር ሁሉንም በሰይፍ ገደለ። በሕይወት ያሉትንም ፍጥረት ሁሉ ምንም ሳያስቀር ፈጽሞ አጠፋቸው። በኢያሪኮ ንጉሥ ላይ ያደረገውንም ሁሉ፥ በመቄዳ ንጉሥ ላይ አደረገ።
\s5
\v 29 ኢያሱና እስራኤላውያን ከመቄዳ ወደ ልብና አለፉ። ወጓትም።
\v 30 እንደገናም ከልብና ጋር ጦርነት ገጠሙ። እግዚአብሔርም ከተማይቱንና ንጉሥዋን በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጣቸው። ኢያሱም በተከማዪቱንና በውስጧ ያለውን ሕይወት ያለውን ፍጥረት ሁሉ በሰይፍ ስለት አጠፋ። ሕይወት ያለውን ምንም አላስቀረም። በኢያሪኮ ንጉሥ ላይ ያደረገውንም በልብና ንጉሥ ላይ አደረገ።
\s5
\v 31 ከዚያም ኢያሱና እስራኤላውያን ከእርሱ ጋር ከልብና ወደ ለኪሶ አለፉ። በእርስዋም ሰፈሩ፤ ጦርነትም አደረጉ።
\v 32 እግዚአብሔርም ለኪሶን በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጠው። ኢያሱም በሁለተኛው ቀን ያዛት። በልብና እንዳደርገው በሕይወት ያለውን ፍጥረት ሁሉ በሰይፍ ስለት አጠፋ።
\s5
\v 33 ከዚያ የጌዝር ንጉሥ ሆራም ለኪሶን ለመርዳት መጣ። ኢያሱ ግን አንድ እንኳ ሳያስተርፍ እርሱንና ሕዝቡን መታቸው።
\s5
\v 34 ከዚያም ኢያሱና እስራኤላውያን በሙሉ ከለኪሶን ወደ ዔግሎን አለፉ። እዚያም ሰፈሩ፤ ወጓትም፤
\v 35 በዚያኑ ዕለት ከተማዋንም ያዟት። ኢያሱም በለኪሶ እንዳደረገ ከተማይቱንና በውስጧ የሚገኙትን ፈጽመው በሰይፍ ስለት አጠፏት።
\s5
\v 36 ከዚያም ኢያሱና እስራኤላውያን ከዔግሎን ወደ ኬብሮን አለፉ። በከተማይቱም ጦርነት አደረጉ።
\v 37 ከተማዪቱንም ከንጉሥዋ ከመንደሮቿና በውስጧ ካሉት ጭምር ሁሉ አንድም ሰው ሳያስቀሩ በሰይፍ ስለት አጠፉአቸው። በዔግሎን እንዳደርጉት ሁሉ ከተማዪቱንና በውስጧ ያለውን ሁሉ ፈጽመው ደመሰሱ። ማንኛውንም ሕይወት ያለውን ፍጥረት ሁሉ አጠፋ።
\s5
\v 38 ከዚያ ኢያሱና እስራኤል ሠራዊት ከእርሱ ጋር ወደ ኋላ ተመልሰው በደቤርን አለፉ፤ ጦርነቱንም አደረጉ።
\v 39 ከተማዪቱን ንጉሥዋንና በአካባቢ ያሉ መንደሮቿን ሁሉ ያዙ። ከተማይቱንና በውስጧ ያለውንም ሁሉ አንድም ሰው ሳያስቀሩ፥ በሰይፍ ስለት አጠፉአቸው። ኢያሱ በኬብሮን ያደረጉትን ሁሉ በዳቤርና በንጉሥዋ ላይ አደረጉት።
\s5
\v 40 ኢያሱ ተራራማውን አገር ኔጌቭን ቆላና የተራራውን ሸንተረሮች ጨምሮ ምድሪቱን በሙሉ ከነገሥታቷ ጋር አሸነፈ። ከነገሥታቱንም ያስቀረው ማንም የለም። የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረትሕይወት ያላቸውን ሁሉ ፈጽሞ አጠፋቸው።
\v 41 ኢያሱም ከቃዴስ በርኔ እስከ ጋዛ፥ የጎሶምን ምድር ሁሉ እስከ ገባዖን ድረስ በሙሉ አጠፋ።
\s5
\v 42 ኢያሱ እነዚህን ሁሉ ነገሥታትና ምድራቸውን የያዘው በአንድ ጊዜ፥ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ስለተዋጋ ነው።
\v 43 ኢያሱ ከመላው እስራኤላውያን ጋር ጌልገላ ወዳለው ሰፈር ተመለሰ።
\s5
\c 11
\p
\v 1 የአሦርም ንጉሥ ኢያቢስ ይህን በሰማ ጊዜ፥ ወደ ዮባብ ንጉሥ፥ ወደ ማዶን ንጉሥ፥ ወደ ሺምሮን ንጉሥና ወደ አዚፍ ንጉሥ መልእክት ላከ።
\v 2 ደግሞም በሰሜናዊ በተራራማው አገር፥ በየርዳኖስ ወንዝ ሸለቆ ከኪኔሬት በስተ ደቡብ ፥ በምዕራቡ ቆላማ አገሮችና ከኮር ኮረብታማ በስተ ምዕራብ ወዳሉት ነገሥታት ላከ።
\v 3 በምሥራቅና በምዕራብ ወደሚገኙት ወደ ከነዓናውያንም፥ ወደ አሞራውያን፥ ወደ ኬጢያውያን፥ ወደ ፌርዛውያንና በኮረብታማው አገር ወደሚኖሩት ወደ ኢያቡሳውያን እንዲሁም በምጽጳ ምድር በአርሞንዔም ተራራ ወዳሉት ወደ ኤዊያውያን ነገሥታት መልእክት ላከ።
\s5
\v 4 እንዚህም ሠራዊቶቻቸው ሁሉ በቁጥርም በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ እጅግ ከብዙ ወታደሮች ጋር መጡ። ታላቅም ቁጥር ፈረሶችና ሠረገሎች ነበሩአቸው።
\v 5 እነዚህ ሁሉ ነገሥታት እስራኤልን ለመውጋት ኃይላቸውን አስተባብረው በማሮን ውሃ አጠገብ በተቀጠረው ጊዜ ሰፈሩ።
\s5
\v 6 እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለው፦ እነዚህን ሁሉ ነገ በዚች ሰዓት እንደ ሙት አድርጌ በእስራኤል እጅ አሳልፌ ስለምሰጣቸው አትፍራቸው። የፈረሶቻቸውንም ቋንጃ ትቆርጣለህ፥ ሠረገሎቻቸውንም ታቃጥላለህ።
\v 7 ኢያሱና ሠራዊቱ ሁሉ መጡ። በድንገትም ወደ ማሮን ውሃ መጥተው ጠላቶቻቸውን አጠቁኣቸው።
\s5
\v 8 እግዚአብሔርም ጠላትን በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጣቸው። በሰይፍም ስለት አጠቁአቸው፥ ወደ ሲዶና፥ወደ ማስሮን፥ ምጽጳ ሸለቆ ድረስ በስተምሥራቅ አሳደዷቸው። ከእነርሱም በሕይወት አንድንም ሰው ሳያስቀሩ በሰይፍ ስለት አጠፉአቸው።
\v 9 ኢያሱም እግዚአብሔር እንዳዘዘው በእነርሱ ላይ አደረጉ። የፈረሶቻቸውንም ቋንጃ ቆረጠ፥ ሠረገሎቻቸውንም አቃጠለ።
\s5
\v 10 በዚያን ጊዜም ኢያሱ ወደ ኋላ ተመልሶ አጾርን ያዘ። ንጉሥዋንም በሰይፍ ገደለው። (አጾርም የእነዚህ መንግሥታት ሁሉ የበላይነት ነበራች።)
\v 11 በውስጧ ያሉትን ሁሉ በሰይፍ ስለት ገደሉ፥ በሕይወት ካለው ፍጡር አንድ እንኳ ሳያስቀሩ ሁሉንም ደመሰሱ። አሦርንም በእሳት አቃጠሏት።
\s5
\v 12 ኢያሱም የእነዚህን ነገሥታት ከተሞች በሙሉ ያዘ። ነገሥታታቸውን ሁሉ ማረካቸው፥ በሰይፍም ስለት አጠፋቸው። የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ እንዳዘዘው በሰይፍ ስለት አጠፋቸው።
\v 13 እስራኤልም በተራራው ላይ ከተሠሩ ከተሞች ከአጾር በስተቀር ሌሎችን አላቃጠሉም። ኢያሱ ይህችን ለብቻዋ አቃጠላት።
\s5
\v 14 እስራኤላውያንም ምርኮውን በሙሉ ከእነዚህም ከተሞች የተገኙትን እንስሳት ለራሳቸው ወሰዱ። ሕዝቡን በሙሉ ሁሉም ሙት እስኪሆኑ ድረስ በሰይፍ ስለት ገደሉአቸው። በሕይወት ካለው ፍጡር አንድም አልቀሩም።
\v 15 እግዚአብሔር አገልጋዩን ሙሴን እንዳዘዘው ሁሉ ሙሴም ኢያሱን አዘዘው። ኢያሱም እግዚአብሔር ሙሴን ካዘዘው ሁሉ እርሱ ያልፈጸመው አንዳች ነገር አልነበረም።
\s5
\v 16 ኢያሱም ማለት ተራራማውን አገር፥ ኔጌቭን ሁሉ፥ የጎሶምን ምድር በሙሉ፥ የኮረብታ ግርጌ። የዮርዳኖስ ወንዝ ሸለቆ፥ የእስራኤልም ኮረብታማ አገርና ቆላማውን የምዕራቡን ቆላዎችን ሁሉ፥ያንን ምድር በሙሉ ወሰደ።
\v 17 እንዲሁም እስከ ሴይር በሚደርሰው ከሐላቅ ተራራ አንሥቶ ከአርሞንዔም ተራራ በታች በሊባኖስ ሸለቆ ውስጥ እስካለው እስከ በዓል ጋድ ድረስ ያለውን ምድር በሙሉ ያዘ። ነገሥታታቸውንም ሁሉ ያዘ፥ መትቶም ገደላቸው።
\s5
\v 18 ኢያሱ ከእነዚህ ነገሥታት ጋር ረጅም ጊዜ ጦርነት አደረገ።
\v 19 በገባዖን ከሚኖሩ ከኤዊያውያን በስተቀር ከእስራኤላውያን ጋር የሰላም ስምምነት ያደረገ አንድም ከተማ አልነበረም። እስራኤል ሁሉንም ከተሞች የያዙት በጦርነት ነበር።
\v 20 እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ያለ አንዳች ርኅራኄ ፈጽሞ ይደመስሳቸው ዘንድ እስራኤልን እንዲወጉ ልባቸውን ያደነደናቸው ራሱ እግዚአብሔር ነበር።
\s5
\v 21 በዚያንም ጊዜ ኢያሱ መጥቶ ዔናቅን አጠፋ። ይህንንም በተራራማው አገር በኬብሮን፥ በዳቤርና በአናብ እንዲሁም በመላው ይሁዳና የእስራኤል ተራራማ አገሮች ያሉትን ላይ አደረገ። እርሱም እነርሱንና ከተሞቻቸውን በሙሉ አጠፋቸው።
\v 22 ከእነዚህም ጥቂቶቹ ብቻ በጋዛ፥ በጌትና በአሽዶድ ከቀሩት በስተቀር በእስራኤል አገር ከዓናቅ የቀሩት አልነበሩም።
\s5
\v 23 ስለዚህ ኢያሱ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ምድሪቱን በሙሉ ያዘ። ኢያሱም እንደ ነገዳቸው አከፋፈል በመመደብም ርስት አድርጎ ለእስራእላውያን ሰጣቸው። ከዚያም ምድሪቱ ከጦርነት ዐረፈች።
\s5
\c 12
\p
\v 1 የእስራኤልም ሰዎች ድል ያደረጉአቸው ነገሥታት እነዚህ ነበሩ። እስራኤላውያንም ከአዮርዳኖንም ሸለቆ በስተ ምሥራቅ ጀምሮ እስከ ፀሐይ መውጫ ድረስ፥ ከአርሞን ወንዝ ሸለቆ ወደ አርሞንዔም ተራራ ድረስ በምሥራቅ ያለውን ዓረባ ሁሉ ወሰዱ። የአሞራውያን ንጉሥ ሴዎን በሐሴቦን ተቀመጠ።
\v 2 በአርኖንም ሸለቆ አጠገብ ካለችው ከአሮዔር ከሸለቆውም መካከል ጀምሮ የገለዓድን እኩሌታ እስከ ያቦቅ ወንዝ፥ እስከ አሞን ልጆች ዳርቻ ድረስ ገዛ።
\s5
\v 3 ሴዎንም በምሥራቅም በኩል ያለውን ዓርባ እስከ ኪኔሬት ባሕር ድረስ፥በቤት የሺሞት መንገድ አጠገብ እስካለው እስከ ዓረባ ባሕር (እስከ ጨው ባሕር) ወደ ምሥራቅ ድረስ በደቡብም በኩል ከፍስጋ ተራራ አፋፍ በታች ያለውን ምድር ገዛ።
\v 4 የባሳን ንጉሥ ዐግ ከራፋይምም ወገን የቀረ፥ በአስታሮትና በኤድራይ ተቀመጠ።
\v 5 እርሱም የአርሞንዔምንም ተራራ፥ ስልካንና ባሳንንም ሁሉ እስከ ጌሹራውያንና እስከ ማዕካታውያን ዳርቻ፥ የገለዓድንም እኩሌታ፥ እስከ ንጉሥ ሀሴቦን ድረስ ገዛው ።
\s5
\v 6 የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴና የእስራኤል ልጆች አሸነፉአቸው፤ የእግዚአብሔርም አገልጋይ ሙሴ ርስት አድርጎ ለሮቤል ልጆች፤ ለጋድም ልጆች ለምናሴም ነገድ እኩሌታ ምድሪቱን ሰጣቸው።
\s5
\v 7 ኢያሱና የእስራኤል ሕዝብ ያሸነፉአቸ ነገሥታትና አገሮች እነዚህ ናቸው፡- በዮርዳኖስም ማዶ በምዕራብ በኩል፥ በሊባኖስ ሸለቆ አጠገብ ወደ ኤዶን አጠገብ ሃላክ ተራራ ድረስ ነው። ኢያሱም ለእስራኤል ነገዶች ሁሉ ምድሪቱን ርስት አድርጎ ሰጣቸው።
\v 8 ተራራማውን አገር፥ በቆላውንም፥ በዓረባንም፥ የተራሮችን ቁልቁለት፥ ምድረ በዳውንም፥ የደቡቡም ያሉትን ኬጢያውያን፥ አሞራውያንም፥ ከነዓናውያንም፥ ፌርዛውያንም፥ ኤዊያውያንም፥ ኢያቡሳውያንም ሰጣቸው።
\s5
\v 9 የኢያሪኮ ንጉሥ ጨምሮ፦ በቤቴል አጠገብ ያለው የጋይ ንጉሥ፥
\v 10 የኢየሩሳሌም ንጉሥ፥ የኬብሮን ንጉሥ፥
\v 11 የያርሙት ንጉሥ፥ የለኪሶ ንጉሥ፥
\v 12 የአግሎን ንጉሥ፥ የጌዝር ንጉሥ፥
\s5
\v 13 የዳቤር ንጉሥ፥ የጌድር ንጉሥ፥
\v 14 የሔርማ ንጉሥ፥ የዓራድ ንጉሥ፥
\v 15 የልብና ንጉሥ፥ የአዶላም ንጉሥ፥
\v 16 የመቄዳ ንጉሥ፥ የቤቴል ንጉሥ፥
\s5
\v 17 የታጱዋ ንጉሥ፥ ይአፌር ንጉሥ፥
\v 18 የአፌቅ ንጉሥ፥ የሽሮን ንጉሥ፥
\v 19 የማዶ ንንጉሥ፥የአሶር ንጉሥ፥
\v 20 የሺምሮን፥ ሚሮን ንጉሥ፥ የአዚፍ ንጉሥ፥
\s5
\v 21 የታዕናክ ንጉሥ፥የመጊዶ ንጉሥ፥
\v 22 የቃዴስ ንጉሥ፥ በቀርሜሎስ የነበረ የዮቅንዕም ንጉሥ፥
\v 23 በዶር ኮረብታ የነበረ የዶር ንጉሥ፥ የጌልገላ አሕዛብ ንጉሥ፥
\v 24 የቲርሳ ንጉሥ፥ ነገሥታቱ ሁሉ ሠላሳ አንድ ናቸው።
\s5
\c 13
\p
\v 1 ኢያሱም ሸመገለ በዕድሜም አረጀ፤ እግዚአብሔርም አለው፦ አንተ ሸመገልህ፥ በዕድሜህም አረጀህ ያልተወረሰ እጅግ ብዙ ምድር ገና ቀርቶአል።
\s5
\v 2 የቀረውም ምድር ይህ ነው፤ የፍልስጥኤማውያንና የጌሹራውያን አገር ሁሉ፥
\v 3 (በግብፅ ፊት ካለው ከሺሖር ወንዝ ጀምሮ በሰሜን በኩል አስካለው የከነዓናውያን ንብረት ሆኖ ተቆጠረው እስከ አቃሮን ዳርቻ ድረስ፥ የጋዛ፥ የአዛጦን የአስቀሎና፥የጌትና የአቃሮን አምስቱ የፍልስጥኤማውያን መኳንንት።)
\s5
\v 4 በደቡብም በኩል የከነዓናውያንም ምድር ሁሉ፥ ለሲዶናውያንም የምትሆን መዓራ እስከ አሞራውያን ዳርቻ እስከ አፌቅ ድረስ፥
\v 5 የጌባላውያንም ምድር፥ በፀሐይ መውጫ በኩል ሊባኖስ ሁሉ፥ ከኣል ጋድ ከአርሞንዔም ተራራ በታች እስከ ሐማት ድረስ ያለው ።
\s5
\v 6 በተራራማውም አገር የሚኖሩትን ሁሉ ከሊባኖስ ጀምሮ እስከ ማሴሮን ድረስ ሲዶናውያን ሁሉ። እነዚህን ከእስራኤል ፊት አባርራቸዋለሁ። እንዳዘዝሁም፤ምድራቸውን ለእስራኤል ርስት አድርገህ ለመመደብ እርግጠኛ ሁን።
\v 7 አሁንም ይህን ምድር ለዘጠኙ ነገድ ለምናሴም ነገድ እኩሌታ ርስት አድርገህ አከፋፍል።
\s5
\v 8 የእግዚእብሔር አገልጋይ ሙሴም እንደ ሰጣቸው ከሌላ እኩሌታ የምናሴ ነገድ ጋር የሮብልና የጋድ ሰዎች በምሥራቅ በኩል በዮርዳኖስ ማዶ ሙሴ አዞአቸው የነበረውን ርስታቸውን ተቀበሉ።
\v 9 በአርኖን ወንዝ ሸለቆ ዳር ካለው ከአሮዔር፥ (በሸለቆውም መካከል ካለው ከተማ ጀምሮ) የሜድባን ሜዳ ሁሉ እስከ ዲቦን ድረስ፥
\s5
\v 10 በሐሴቦንም የአሞርውያን ንጉሥ የሴዎን ከተሞች ሁሉ እስከ አሞራውያን ዳርቻ ድረስ፥
\v 11 ገለዓድንም፥ የጌሹራውያንና የማዕካታውያንን አካባቢ ሁሉ፥ የአርሞንዔምንም ተራራ ሁሉ፥ባሳንንም ሁሉ እስከ ሰልካ ድረስ፥
\v 12 በባሳን የነበረውን በአስታሮትና በኤድራይ የነገሠውን የዐግን መንግሥት ሁሉ፥ እነርሱም ከራፋይም የቀረ ነበረ፤ እነዚህንም ሙሴ መታቸው አወጣቸውም።
\s5
\v 13 ነገር ግን የእስራኤል ሰዎች ጌሹራውያንን ወይም ማዕካታውያንን አላወጡም ነበር። በዚህ ፈንታ ጌሹርና ማዕካት እስከ ዛሬም ድረስ በእስራኤል መካከል ይኖራሉ።
\s5
\v 14 ሙሴም ለሌዊ ነገድ ለብቻ ርስት አልሰጠም። እግዚአብሔር ለሙሴ እንደ ተናገረው ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር የሚቀረበው፥ በእሳት የተደረገ መሥዋዕት ርስታቸው ነው።
\s5
\v 15 ሙሴም ለሮቤል ልጆች ነገድ በየወገናቸው ርስትን ሰጥጣቸው።
\v 16 ድንበራቸውም በአርኖን ሸለቆ ዳር ካለችው ከአሮዔር ጀሞሮ በሸለቆው መካከል ያለችው ከተማ፥
\s5
\v 17 ሐሴቦንና በሜዳውም ያሉት ከተሞችዋ ሁሉ፥ዲቦን፥ ባሞት በኣል፥ ቤት በኣልምዖን፥
\v 18 ያሀጽና ቅዴሞት፥ ሜፍዓት፥
\v 19 ቂርያታይም፥ ሴባማ፥ ጼሬትሻሐና በሸለቆውም ተራራ ያለውና ሁሉ ሮቢን ተቀበለ።
\s5
\v 20 ሮቤም ቤተ ፌጎርን፥ ከፈስጋ ተራራ በታች ያለው ምድርን፥ ቤት የሺሞትን፥
\v 21 የሜዳውም ከተሞች ሁሉ፥ የአሞራውያን ንጉሥ የሴዎን መንግሥት፥ በሐሴቦንም የነገሠው፥ ሙሴም እርሱንና በምድሪቱ የተቀመጡትን የምድያምን አለቆች፥ ኤዊን፥ ሮቆምን፥ ሱርን፥ ሑርንና ሪባን፥ የሴዎን መሳፍንት፥ መታቸው።
\s5
\v 22 የእስራኤል ሰዎች ከገደሉአቸውም ሰዎች ጋር ምዋርተኛውን የቢዖርን ልጅ በለዓምን በሰይፍ ገደሉ። የሮቤልም ልጆች ድንበር የዮርዳኖስ ወንዝና ዳርቻው ነበረ።
\v 23 የሮቤል ነገድ ድንበር የዮርዳኖስ ወንዝ ነው፥ ይህም ድንበራቸው ነው። ይህም ከከተሞቻቸውና መንደሮቻቸው በየወገኖቻቸው ለሮቤል ነገድ የተሰጣቸው ርስት ነበረ።
\s5
\v 24 ይህም መሴ ለጋድ ነገድ በየውገኖቻቸው ርስት አድርጎ የሰጣቸው ነው።
\v 25 ድንበራቸውም ኢያዜርና የገለዓድ ከተሞች ሁሉ፥ የአሞራውያንም ምድር እኩሌታ፥
\v 26 ከረባት በስተምሥራቅ፥ አስካለው እስከ አሮዔር ድረስ፥ ከሐሴቦን ጀምሮ እስከ ራማት ምጽጴ፥ እስከ ብጦኒም ድረስ፥ ከመሃናይም ጀምሮ እስከ ዳቤር ዳርቻ ድረስ ነበር።
\s5
\v 27 ሙሴም ቤትሀራምን፥ ቤትኒምራ፥ ሱኮትና ጻፎን፥ የቀሩትንም የሐሴቦን ንጉሥ የሴዎን መንግሥት ከዮርዳኖስን እንደ ድንበር በምሥራቅ በኩል ባለው በዩርዳኖስ ማዶ የኪኔሬት ባሕር ወዲያኛው ዳርቻ ሰጣቸው።
\v 28 ይህም የጋድ ነገድ ከከተሞቻቸውና ከመንደሮቻቸው ጋር በየወገኖቻቸው ርስት ነበረ።
\s5
\v 29 ሙሴም ለምናሴ እኩሌታ ነገድ ርስትን ሰጣቸው። ለምናሴም ነገድ እኩሌታ በየወገኖቻቸው መሠረት የተመመደበ ነበረ።
\v 30 ድንበራቸውም ባሳን ሁሉ፥ ከመሃናይም ጀምሮ የባሳን ንጉሥ የዐግ መንግሥት፥ በባሳንም ያሉት የኢያፅር መንደሮች ሁሉ ስድሳው ከተሞች፤
\v 31 የገለዓድም እኩሌታ፥ አስታሮትና ኤድራይ ነበር፤ (የ'ዐግ በባሳን ያሉ የመንግሥት ከተሞች) ። እነዚህም ለምናሴ ልጅ ለማኪር ልጆች ሆኑ፤ ለማኪር ሰዎች እኩሌታ በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ።
\s5
\v 32 ይህም ሙሴ በምሥራቅ በኩል በኢያሪኮ አንጻር በዮርዳኖስ ማዶ በሞዓብ ሜዳ ሳለ፥ የከፈለው ርስት ነው።
\v 33 ሙሴም ለሌዊ ነገድ ርስት አልሰጣም ነበር። የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንደ ተናገራቸው ርስታቸው ነው።
\s5
\c 14
\p
\v 1 የእስራኤልም ሕዝብ በካነዓን ምድር የወረሱት ካህኑ አልዓዛርና የነዌ ልጅ ኢያሱ በእስራኤልም ነገድ መካከል የአባቶቻቸው አለቆች ያካፈሉአቸው ርስት ይህ ነው፤
\s5
\v 2 እግዚአብሔር በሙሴ እጅ እንዳዘዘ ለዘጠኙ ነገዶችና ለእኩሌታው በየርስታቸው በዕጣ አካፈሉአቸው፤
\v 3 ለሁለቱ ነገድና ለእኩሌታው ነገድ በዮዳኖስ ማዶ ሙሴ ርስት ሰጥቶ ነበር፤ ነገር ግን በመካከላቸው ለሌዋውያን ርስት አልሰጣቸውም።
\v 4 የዮሴፍ ነገድ፥ ምናሴና ኤፍሬም ሁለት ነገዶች ነበሩ። ለሌዋውያንም ከሚቀመጡባቸው ከተወሰኑ ከተሞች፥ ለእንስሶቻቸውና ለከብቶቻቸውም ከሚሆን መሰምርያቸው በቀር በምድሩ ውስጥ ድርሻ አልሰጡአቸውም።
\v 5 እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው የእስራኤል ሕዝብ አደረጉ፥ ምድሩንም ተካፈሉ።
\s5
\v 6 የይሁዳም ነገድ በጌልገላ ወደ ኢያሱ ቀረቡ። ቄኔዛዊውም የዮፎኒ ልጅ ካሌብ እንዲህ አለው፦ ለእግዚአብሔር ሰው ለሙሴ ስለ እኔና ስለ አንተ እግዚአብሔር በቃዴስ በርኔ የተናገረውን ነገር ታውቃለህ።
\v 7 የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ምድርን እሰልል ዘንድ ከቃዴስ በርኔ በላከኝ ጊዜ እኔ የአርባ ዓመት ሰው ነበርሁ፤ እኔም በልቤ እንደ ነበረ መረጃ አመጠሁለት።
\s5
\v 8 ነገር ግን ከእኔ ጋር የሄዱ ወንድሞቼ የሕዝቡን ልብ በፍርሃት አቀለጡ። እኔ ግን አምላኬን እግዚአብሔርን ፈጽሜ ተከተልሁ።
\v 9 ሙሴም በዚያ ቀን፦ አምላኬን እግዚአብሔርን ፈጽመህ ተከትለሃልና እግርህ የረገጠው ምድር ለአንተና ለልጆችህ ለዘላለም በእርግጥ ርስት ይሆናል ብሎ ማለ።
\s5
\v 10 አሁንም፥ እነሆ፥ እግዚአብሔር ለሙሴ ይህን ቃል ከተናገር በኋላ፥ እስራኤል በምድረ በዳ ሲጓዙ፥ እርሱ እንደ ተናገረኝ እግዚአብሔር እነዚህን አርባ አምስት ዓመት በሕይወት አኖረኝ። እነሆ፥ ለእኔ ዛሬ ሰማንያ አምስት ዓመት ሆነኝ።
\v 11 ሙሴም በላከኝ ጊዜ እንደ ነበርሁ፥ ዛሬ ጉልበታም ነኝ፥ ጉልበቴም በዚያን ጊዜ እንደ ነበር፥ እንዲሁ ዛሬ ለመዋጋት፥ ለመውጣትና ለመግባትም ጉልበቴ ያው ነው።
\s5
\v 12 እንግዲህ በዚያን ቀን እግዚአብሔር የተናገረውን ይህን ተራራማ አገር ስጠኝ። አንተም በዚያ ቀን ታላላቅና በተመሸጉ ከተሞቻቸው ጋር ዔናቃውያን በዚያ እንደ ነበሩ ሰምተህ ነበር። እግዚአብሔርም እንደ ተናገረ እግዚአብሔርም ከእኔ ጋር ይሆናል፥ አሳድዳቸዋለሁ።
\s5
\v 13 ኢያሱም ባረከው፤ ለዮፎኒም ልጅ ለካሌብ ኬብሮንን ርስት አድርጎ ሰጠው።
\v 14 ስለዚህም የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን ፈጽሞ ስለ ተከተለ ኬብሮን እስከ ዛሬ ለቄኔዛዊው ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ ርስት ሆንች።
\v 15 የኬብሮንም ስም አስቀድሞ ቂርያት አርባቅ ትባል ነበር። (አርባቅም በዔናቅ ሰዎች መካከል ከፍ ያለ ነበረ።) ምድሪቱም ከጦርነት ዐረፈች።
\s5
\c 15
\p
\v 1 ለይሁዳም ልጆች ነገድ በየወገናቸው መሬትን ማከፋፈል እስከ ጺን ምድረ በዳ እስከ ደቡብም መጨረሻ እስከ ኤዶምያስ ዳርቻ ድረስ ዕጣ ሆነላቸው።
\v 2 በደቡብም በኩል ያለው ድንበራቸው እስከ ጨው ባሕር መጨረሻ ወደ ደቡብ እስከሚያይ እስከ ባሕረ ልሳን ነበረ።
\s5
\v 3 ከዚያም ቀጥሎ ከኮረብታ በስተደቡብ በኩል ወደ ጺንም አለፈ፤በቃዴስ በርኔ ወደ ደቡብ በኩል ይዘልቃል፤ በሐጽሮንም በኩል አልፎ ወደ አዳርም ደረሰ፥ ወደ ቀርቃ ዞረ፥
\v 4 ወደ አጽሞንም አለፈ፥ በግብፅም ወንዝ በኩል ወጣ፥ የድንባሩም መውጫ በባሕሩ አጠገብ ነበር፤ በደቡብ በኩል ያለው ድንበራቸው ይህ ነው።
\s5
\v 5 በምሥራቅም በኩል ያለው ድንበር እስከ ጨው ባሕር እስከ ዮርዳኖስም መጨረሻ ነበረ። በሰሜንም በኩል ያለው ድንበር በዩርዳኖስ መጨረሻ እስካለው እስከ ባሕሩ ልሳን ድረስ ነበር።
\v 6 ከዚያም ድንበሩ ወደ ቤት ሖግላ ወጣ፥ በቤት ዓርባ በሰሜን በኩል አለፈ። (ወደ ሮቤልም ልጅ ወደ ቦሀን) ድንጋይ ወጣ።
\s5
\v 7 ድንበሩም ከአኮር ሸለቆ ወደ ዳቤር ወጣ፥ በሰሜን በኩል በአዱሚም ኮረብታ ፊት ለፊት፥በወንዙም በደቡብ በኩል ወዳለችው ወደ ጌልገላ ዞረ። ከዚያም ድንበሩ ወደ ቤት ሳሚስ ውኃ አለፈ፥ መውጫውም በዓይን ሮጌል አጠገብ ነበረ።
\v 8 ከዚያ ድንበሩም በሄኖም ልጅ ሸለቆ አጠገብ (ኢየሩሳሌም) ወደምትባለው ወደ ኢያቡሳዊው ወደ ደቡብ ወገን ወጣ፤ ድንበሩም በራፋይም ሸለቆ ዳር በሰሜን በኩል ባለው በሄኖም ሸለቆ ፊት ለፊት በምዕራብ ወገን ወዳለው ተራራ ራስ ላይ ወጣ።
\s5
\v 9 ድንበሩም ከተራራው ራስ ወደ ኔፍቶ ውኃ ምንጭ ደረሰ፥ ወደ ዔፍሮንም ተራራ ከተሞች ወጣ። ቂርያትይዓሪም ወደምትበል ወደ በኣላ ደረሰ። (ከዚያም ድንበሩ በባኣላ ዙሪያ እንደ ቂርያት በተመሳሳይ ታጠፈ) ።
\v 10 ድንበሩም ከባአላ በምዕራብ በኩል ወደ ሴይር ተራራ ዞረ፤ክሳሎን ወደምትባል ወደ ይዓሪም ተራራ ወገን በሰሜን በኩል አለፈ፤ ወደ ቤት ሳሚስ ወረድ፥ በተምና በኩልም አለፈ።
\s5
\v 11 ድንበሩም ወደ አቃሮን ወደ ሰሜን ወገን ወጣ፤ወደ ሽክሮን ደረሰ ወደ በኣላ ተራራ አለፈ፥ በየብኒኤል በኩልም ወጣ፤ የድንበሩም መውጫ በባሕሩ አጠገብ ነበረ።
\v 12 በምዕራቡም በኩል ያለው ድንበር እስከ ታላቁ ባሕርና እስከ ዳርቻው ድረስ ነበረ።ለይሁዳ ልጆች በየወገናቸው በዙሪያው ያለ ድንበራቸው ይህ ነው።
\s5
\v 13 እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዳዘዘው ለዮፎኒ ልጅ ካሌብ በይሁዳ ልጆች መካከል ቂርያት አርበቅ የምትባለውን ከተማ ድርሻ አድርጎ ሰጠው፤ እርስዋም ኬብሮን ናት፥ ይህም ዘርባቅ የዔናቅ አባት ነበረ።
\v 14 ካሌብም ሦስቱን የዔናቅን ልጆች ሴስን፥ አኪመንንና ተላሚን ከዚያ አሳደደ።
\v 15 ከዚምም በዳቤር ሰዎች ላይ ወጣ፤ የዳቤርም ስም አስቀድሞ ቂርያት ሤፍር ትባል ነበር።
\s5
\v 16 ካሌብም እንዲህ አለ፦ ቂርያት ሤፍርን ለሚመታ ለሚይዛትም ልጄን ዓክሳን አጋባዋለሁ አለ።
\v 17 የካሌብ ወንድም የቄኔዝ ልጅ ጎቶንያል ያዛት። ስለዚህም ካሌብ ልጁን ዓክሳን አጋባው።
\s5
\v 18 ዓክሳም ወደ እርሱ በመጣች ጊዜ ከአባትዋ እርሻ ለመለምን ገፋፈችው፤ እርስዋም ከአህያዋ ወረደች፤ካሌብም፦ ምን ፈለግሽ? አላት።
\s5
\v 19 እርስዋም፦ ስጦታ ስጠኝ፤ የኔጌቭ ምድር ሰጥተኸኛል፥ አሁን ደግሞ የውኃውን ምንጭ ስጠኝ አለችው። እርሱም የላይኛውንና የታችኛውን ምንጭ ሰጣት።
\s5
\v 20 በየወገኖቻቸውም የይሁዳ ልጆች ነገድ የተሰጠ ርስት ይህ ነው።
\s5
\v 21 በድቡብም በኩል በምድራቸው ዳርቻ አጠገብ እስከ ኤዶምያስ ድንበር ያሉትን የይሁዳ ልጆች ነገድ ከተሞች እነዚህ ነበሩ ቀብስኤል፥ ዓዴር፥ ያጉር፥
\v 22 ቂና፥ ዲሞና፥ ዓድዓዳ፥
\v 23 ቃዴስ፥ ሐጾር፥ ዪትናን
\v 24 ዚፍ፥ጠሌም፥በዓሎት።
\s5
\v 25 ሐጾርሐ ዳታ፥ ሐጾር የምትባለውም ቂርታይሐጾር፥
\v 26 አማም ሽማዕ፥ ሞላዳ፥
\v 27 ሐጸርጋዳ፥ሐሽሞን፥ ቤትጳሌጥ፥
\v 28 ሐጸርሹዓል፥ ቤርሳቤህ፥ ቢዝዮትያ፥
\s5
\v 29 በኣላ፥ ዒዮም፥ ዓጼም፥
\v 30 ኤልቶላድ፥ ኪሲል፥ ሔርማ፥
\v 31 ጺቅላግ፥ ማድማና፥ ሳንሳና፥
\v 32 ልባዎት፥ ሺልሂም፥ ዓይን፥ ሪሞም፤ ሀያ ዘጠኝ ከተሞችና መንደሮቻቸው።
\s5
\v 33 በቆላው ኤሽታኦል፥ ጾርዓ፥ አሽና፥
\v 34 ዛኖዋ፥ ጫይንገኒም፥ ያጱዋ፥ ዓይናም፥
\v 35 የሩት፥ ዓዶላም፥ ሰኮት፥ ዓዜቃ፥
\v 36 ሽዓራይም፥ ዓዲታይም፥ ግርራ፥ ግርሮታይም፤ አሥራ አራት ከተሞችና መንደሮቻቸው።
\s5
\v 37 ጽናን፥ ሐዳሻ፥ ሚግዳልጋድ፥
\v 38 ዲልዓን፥ ምጽጳ፥ ዮቅትኤል፥
\v 39 ለኪሶ፥ በጽቃት፥ አግሎን
\s5
\v 40 አዶላም፥ ከቦን፥ ለሕማስ፥ ኪትሊሽ፥
\v 41 ግዴሮት፥ ቤት ዳጎን፥ ናዕማ፥ መቄዳ፤አሥራ ስድስት ከተሞችና ቁጥር ስፍር የሌላቸው መንደሮቻቸው።
\s5
\v 42 ልብና፥ ዔቴር፥ ዓሻን፥
\v 43 ይፍታሕ፥ አሽና፥ንጺብ፥
\v 44 ቅዒላ፥ አክዚብ፥ መሪሳ፤ ዘጠኝ ከተሞችና ቁጥር ስፍር የሌላቸው መንደሮቻቸው።
\s5
\v 45 አቃሮን፥ ከተመሸጉና ካልተመሸጉ ከተሞችና መንደሮችዋ ጋር፤
\v 46 ከአቃሮንም ጀምሮ እስከ ባሕር ድረስ በአዛጦን አጠገብ ያሉት ሁሉ ከመንደሮቻቸው ጋር።
\v 47 በአዛጦን የተመሸጉና መንደሮችዋም፥ ጋዛና የተመሸጉ ከተሞችና መንደሮችዋ፥ እስከ ግብፅ ወንዝና እስከ ታላቁ ባሕር ካርቻ ክረስ።
\s5
\v 48 በተራራማውም አገር ሳምር፥ የቲር፥ ሶኮ፥
\v 49 ደና፥ ዳቤር የምትባለው ቂርያትሰና፥
\v 50 ዓባብ፥ኤሽትሞዓ፥ ዓኒም፥
\v 51 ጎሶም፥ ሖሎን፥ ጊሎ፤ አሥራ አንድ ከተሞችና ቁጥር ስፍር የሌላቸው መንደሮቻቸው።
\s5
\v 52 አራብ፥ ዱማ፥ ኤሽዓን፥
\v 53 ያንም፥ ቤትታጱዋ፥ አፌቃ፥
\v 54 ሑምጣ፥ ኬብሮን የምትባል ቂርያትአርባቅ፥ ጺዖር ፤ ዘጠኝ ከተሞችና ቁጥር ስፍር የሌላቸው መንደሮቻቸው።
\s5
\v 55 ማዖን፥ ቀርሜሎስ፥ ዚፍ፥ ዩጣም
\v 56 ኢይዝራሴል፥ ዮቅድዓም፥ ዛኖዋሕ፥
\v 57 ቃይን፥ ጊብዓ፥ ተምና፤ አሥር ከተሞና ቁጥር ስፍር የሌላቸው መንደሮቻቸው።
\s5
\v 58 ሐልሑል፥ ቤት ጹር፥ ጌዶር፥
\v 59 ማዕራት፥ ቤትዓኖት፥ ኤልትቆን፤ስድስት ከተሞችና ቁጥር ስፍር የሌላቸው መንደሮቻቸው።
\s5
\v 60 ቂርያትይዓሪም የምትባለው ቂርያት በኣል፥ ረባት፤ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው።
\v 61 በምድረ በዳ ቤትዓረባ፥ ሚዲን፥ ስካካ፥
\v 62 ኒብሻን፥ የጨው ከተማ፥ ዓይንጋዲ፤ ስድስት ከተሞችና ቁጥር ስፍር የሌላቸው መንደሮቻቸው።
\s5
\v 63 በኢየሩሳሌም የተቀመጡትን ኢያቡሳውያንን ግን የይሁዳ ልጆች ሊያሳድዱአቸው አልተቻላቸውም፤ ኢያቡሳውያንም እስከ ዛሬ በይሁዳ ልጆች መካከል በኢየሩሳሌም ውስጥ ተቀምጠዋል።
\s5
\c 16
\p
\v 1 የዮሴፍም ልጆች የመሬት ድልድል በኢያሪኮ አጠገብ በምሥራቁ በኩል ካለው ከዮርዳኖስ አንሥቶ በምድረ በዳውና በተራራማው በኩል ከኢያሪኮ ወደ ቤቴል ወጣ።
\v 2 ከቤቴል ወደ ሎዛ ወጣ፥ በአርካውያንም ዳርቻ በኩል ወደ አጣሮት አለፈ።
\s5
\v 3 ወደ ምዕራብም እስከ የፍርሌጣውያን ዳርቻ እስከ ታችኛው ቤት ሖሮን ዳርቻ እስከ ጌዝር ድረስ ዘልቆ፥ መጨራሻውም በባሕሩ አጠገብ ነበር።
\v 4 የዮሴፍም ነገድ ምናሴና ኤፍሬም ርስታቸውን የተቀበሉት በዚህ መንገድ ነበር።
\s5
\v 5 የኤፍሬምም ነገድ ድንበር በየወገኖቻቸው እንደዚህ ነበረ፦ በምሥራቅ በኩል የርስታቸው ድንበር አጣሮት አዳር እስከ ላይኛው ቤት ሖሮን ድረስ ነበረ፤
\v 6 ከዚያ ወደ ባሕሩ ቀጠለ። ድንበሩም ወደ ምዕራብ ወደ ሚክምታት በሰሜን በኩል ወደ ምሥራቅ ወደ ተአናት ሴሎ ዞረ፥ ከዚያም ወደ ኢያኖክ በምሥራቅ በኩል አለፈ።
\v 7 ከኢያኖክም ወደ አጣሮትና ወደ ነዓራት ወረደ፤ ወደ ኢያሪኮም ደረሰ፥ ወደ ዮርዳኖስም ወጣ።
\s5
\v 8 ድንበሩም ካታጱዋ ወደ ምዕራብ እስከ ቃና ወንዝ ድረስ አለፈ፥ መውጫውም በባሕሩ መጨራሻ ነበረ። የኤፍሬም ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ፤
\v 9 ይኸውም፥ በምናሴ ነገድ ርስት መካከል ለኤፍሬምም ልጆች ከተለዩ ከተሞች ጋር፥ ከተሞች ሁሉ ከመንደሮቻቸው ጋር ነው።
\s5
\v 10 በጌዝርም የተቀመጡትን ከነዓናውያንን አላሳደዱአቸውም ነበር፤እስከ ዛሬም ድረስ ከነዓናውያን በኤፍሬም መካከል ተቀምጠዋል፤ሆኖም እነዚህ ሰዎች የጉልበት ሥራ እንዲሠሩ ተደርገው ነበር።
\s5
\c 17
\p
\v 1 ለምናሴ ነገድ የተመደበው ይህ ነበር፤ እርሱም የዮሴፍ በኩር ነበር። የምናሴም በኩር የገለዓድ አባት ማኪር ራሱም የገለዓድ አባት ነበር። የማኪርም ወገኖች የገለዓድና የባሳን ምድር ተሰጣቸው ምክንያቱም ማኪር የጦር ሰው ነበርና።
\v 2 ለቀሩት ለምናሴ ልጆች በየወገኖቻቸው ለአቢዔዝር ልጆች፥ለኬሴግ ልጆች ለአሥሪኤል ልጆች፥ ለሴኬም ልጆች፥ ለአፌር ልጆች፥ልሸሚዳ ልጆች ተሰጣቸው። የዮሴፍ ልጅ የምናሴ ወንዶች ልጆች በየወገኖቻቸው የተሰጣቸው እነዚህ ናቸው።
\s5
\v 3 ለምናሴ ልጅ፥ ለማኪር ልጅ፥ ለገለዓድ ልጅ፤ ለኦፌር ልጅ፥ ለሰለጰዓድግን ሴቶች ልጆች እንጂ ወንዶች ልጆች አልነበሩአቸውም የሴቶች ልጆቹም ስም ማህለህ፥ ኑዓ፥ ዔግላ፥ ሚልካ፥ ቲርጻ ነበረ።
\v 4 እነርሱም ወደ ካህኑ ወደ አልዓዛር፥ ወደ ነዌ ልጅ ወደ ኢያሱና ወደ አለቆች ቀርበው እንዲህ አሉ፦ እግዚአብሔርም ሙሴን ከወንድሞቻችን ጋር ርስት እንዲሰጠን አዝዞ ነበር። ስለዚህ ትእዛዙን በመከተል በአባታቸው ወንድሞች መካከል ለእነዚያ ሴቶች ርስት ሰጣቸው።
\s5
\v 5 በዮርዳኖስ ማዶ ካለው በገለዓድና በባሳን ምድር ለምናሴ አሥር የመሬት መደቦች ተመድቦ ነበር፤
\v 6 ምክንያቱም የምናሴ ሴቶች ልጆች ከወንዶቹ ጋር ርስት ተቀብለዋል። የገለዓድም ምድር ለቀሩት ለምናሴ ነገድ ተመደበ።
\s5
\v 7 የምናሴም የድንበር ክልል ከአሴር ጀምሮ በሴኬም ፊት ለፊት እስካለው እስከ ሚክምታት ድረስ ደረሰ። ድንበሩም በምዕራብ በኩል ወደ ታጱዋ ምንጭ አጠገብ ወደሚኖሩ ሰዎች አለፈ።
\v 8 (የታጱዋ ምድር ለምናሴ ነበረ፤ በምናሴ ዳርቻ ያለው ታጱዋ ከተማ ግን ለኤፍሬም ነገድ ሆነ።)
\s5
\v 9 ድንበሩም ወደ ቃና በኩል ወደ ታች ወረደ። እነዚህ ከወንዙ በስተደቡብ ያሉ ከተሞች በምናሴም ከተሞች መካከል ለኤፍሬም ሆኑ። የምናሴም ድንበር በወንዙ በስተሰሜን በኩል ሆኖ በባሕሩ መጨራሻ ነበረ።
\v 10 በደቡብ በኩል ያለው ለኤፍሬም ነበረ፥ በሰሜንም በኩል ያለው ለምናሴ የነበረው ድንበሩ ባሕር ነበረ። በሰሜን በኩል ወደ አሴር፥ በምሥራቅ ም በኩል ወደ ይሳኮር ደረሰ።
\s5
\v 11 በይሳኮርና በአሴር መካከል ቤት ሳንና መንደሮችዋን፥ ይብልዓምንና መንደሮችዋን፥ ዶር ሰዎችንና መንደሮችዋን ፥ የዓይንዶር ሰዎችንና መንደሮችዋን፥ የታዕናክ ሰዎችንና መንደሮችዋን ፥ የመጊዶ ሰዎችንና መደሮችዋን ፥ ሦስቱ ኮረብቶች ምናሴ ወረሳቸው።
\v 12 ሆኖም የምናሴ ነገድ ግን እነዚህን ከተሞች ርስት አድርጎ ሊወስዳቸው አልቻሉም፤ ምክንያቱም ከነዓናውያን በዚያ ምድር መኖራቸውን ቀጥለው ነበር።
\s5
\v 13 የእስራኤልም ሕዝብ እየጠነከሩ በመጡ ጊዜ ከነዓናውያንን የጉልበት ሥራ እንዲሠሩ አደረጉአቸው፤ ነገር ግን ሙሉ በሙሉ ከምካከላቸው እንዲወጡ አላደረጉም ነበር።
\s5
\v 14 ከዚያም የዮሴፍ ልጆች ኢያሱን እንዲህ ብለው ተናገሩ፦ እኛ ብዙ ሕዝብ ሆነን ሳለን፥ እግዚአብሔርም ባርኮን እያለ ለምን አንድ ክፍል፥ አንድም ዕጣ ብቻ ርስት አድርገህ ሰጠኸን? አሉት።
\v 15 ኢያሱም እንዲህ አላቸው፦ በቁጥር ብዙ ሕዝብ ከሆናችሁ፥ ወደ ዱር ወጥታችሁ በፌርዛውያንና በራፋይም ምድር ለራሳችሁ መንጥሩ። ተራራማውም የኤፍሬም አገር ጠብቦአችሁ እንደ ሆነ ይህንን አድርጉ።
\s5
\v 16 የዮሴፍም ልጆች እንዲህ አሉ፦ '''ተራራማውም አገር አይበቃንም። ነገር ግን በሸለቆውም ውስጥ ለሚኖሩት፥ በቤት ሳንና በመንደሮችዋ በኢይዝራኤልም ሸለቆ ለሚኖሩት ከነዓናውያን የብረት ሰርገሎች አላቸው።''
\v 17 ከዚያም ኢያሱ ለዮሴፍ ልጆች መለሰላቸው፦ ለመሆኑ ለኤፍሬምና ለምናሴ እናንተ ብዙ ሕዝብ ናችሁ፥ ጽኑም ኃይልም አላችሁ። አንድ ክፍል መሬት ብቻ ሊኖራችሁ አይገባም።
\v 18 ተራራማውም አገር ለእናንተ ይሆናል። ዱር እንኳ ቢሆንም ትመነጥሩአቸዋላችሁ፥ ለእናንተም እንዲሆኑ ታደርጋላችሁ። ከነዓናውያንም የብረት ሰረገሎች ያሉአቸውና ኃይለኞች ቢሆኑም ልታስለቅቁአቸው ትችላላችሁ። ታሳድዳቸዋላችሁ አላቸው።
\s5
\c 18
\p
\v 1 የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ በሴሎ ተሰበሰቡ። በዚያም የመገናኛውን ድንኳን ተከሉ፤ ምድሩም ጸጥ ብሎ ተገዛላቸው።
\v 2 ከእስራኤልም ልጆች መካከል ያልተካፈሉ ሰባት ነገዶች ቀርተው ነበር።
\s5
\v 3 ኢያሱም ለእስራኤል ሰዎች አላቸው፦ የአባቶቻቸሁ እግዚአብሔር አምላክ የሰጣችሁን ምድር ትወርሱ ዘንድ እስከ መቼ ድረስ ቸል ትላላችሁ?
\v 4 ከየነገዱም ሦስት ሦስት ሰዎች ምረጡ፥ እኔም እልካቸዋለሁ። ተነሥተውም የምድሪቱን ላይና ታች ይለካሉ። እንደ ርስታቸውም መጠን ይጽፉታል፤ ወደ እኔም ይመለሳሉ።
\s5
\v 5 በሰባትም ክፍል ይከፍሉታል። ይሁዳም በደቡብ ድንበር ባሉበት ይጸናሉ፤ የዮሴፍ ወገኖች በሰሜን በኩል በዳርቻው ውስጥ ይቀጥላሉ።
\v 6 እናንተም ምድሪቱን በሰባት ክፍል ትጽፋላችሁ፥ የጻፋችሁትንም ወደ እኔ ታመጣላችሁ፤ በአምላካችንም በእግዚአብሔር ፊት ዕጣ አጣጥላችኋለሁ።
\s5
\v 7 ለሌዋውያንም ርስት የላቸውም፤ የእግዚአብሔር ክህነት ርስታቸው ነውና። የጋድም፥ የሮቤልም፥ የምናሴም ነገድ እኩሌታ ከዮርዳኖስ ማዶ ተቀበሉ።ይህም የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ የሰጣቸው ርስታቸው ይህ ነው።
\s5
\v 8 ሰዎችም ተነሥተው ሄዱ፤ ኢያሱም ምድሩን ሊጽፉ የሄዱትን እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፦ ሂዱ፥ በምድሩም ላይና ታች ዞራችሁ ጻፉት፥ ከዚያም ወደ እኔ ተመለሱ። በዚህም በሴሎ በእግዚአብሔር ፊት ዕጣ አጣጥላችኋለሁ።
\v 9 ሰዎቹም ሄደው ምድሩን ላይና ታች ዞሩ። እንደ ከተሞችም በሰባት ክፍል ከፈሉት፥ ዝርዝራቸውንም ጻፉት። ከዚያም ኢያሱ ወደ ሰፈረበት ወደ ሴሎ ተመለሱ።
\s5
\v 10 ኢያሱም በእግዚአብሔር ፊት በሴሎ ዕጣ አጣጠላቸው። በዚያም ኢያሱ ለእስራኤል ልጆች እንደ ክፍሎቻቸው ምድሩን አካፈላቸው።
\s5
\v 11 የምድሩም ዕጣ ለብንያምም ነገድ በየወገኖቻቸው ተሰጠ። የዕጣቸውም ዳርቻ በይሁዳ ልጆችና በዮሴፍ ልጆች መካከል ነበረ።
\v 12 በሰሜን በኩል ድንብራቸው ከዮርዳኖስ ይጀራል። ድንበሩም ወደ ኢያሪኮ ወደ ሰሜን በኩል፥በተራራማው አገር ወደ ምዕራብ ደረሰ። መውጫውም በቤት አዌን ምድረ በዳ ነብረ።
\s5
\v 13 ድንበሩም ከዚያ በደቡብ በኩል ቤቴል ወደምትባል ወደ ሎዛ አለፈ። ድንበሩም በታችኛው ቤት ሖሮን በደቡብ በኩል ባለው ተራራ ወደ አጣሮት አዳር ወረደ።
\v 14 ድንበሩም ወደ ምዕራብ ዘለቀ፥ በቤⶆሮንም ፊት ለፊት ካለው ተራራ ወደ ደቡብ ይዞራል፤ መውጫውም ቂርታትይዓሪም በትባል በይሁዳ ልጆች ከተማ በቂርያት በኣል ነበረ፤ ይህ የምዕራቡ ዳርቻ ነበረ።
\s5
\v 15 የደቡብም ዳርቻ ከቂርያት ይዓሪም ውጪ ይጀምራል። ድንበሩም በምዕራብ በኩል ወደ ነፍቶ ውኃ ምንጭ ሄደ።
\v 16 ድንበሩም በበን ሄኖም ሸለቆ ፊት ለፊት ወዳለው ተራራ መጨረሻ ወረደ፥ እርሱም በራፋይም ሸለቆ በሰንን በኩል ነው፤ ወደ ሄኖም ሸለቆ ወደ ኢያቡስ ዳር በደቡብ በኩል ወረደ፥ ወደ ዓይን ሮጌልም ወረደ።
\s5
\v 17 ወደ ሰሜንም ዞረ፤ በኢን ሳሚስ አቅጣጫ በአዱሚም ዐቀበት ፊት ለፊት ወዳለው ወደ ጌሊሎትወጣ፤ ከዚያሜ ወደ ሮቤ ልጅ ወደ ቦሀን ድንጋይ ወረደ፤
\v 18 በሰሜንም ወገን ወደ ዓረባ አጠገብ አለፈ፥ ወደ ዓረባም ወረደ።
\s5
\v 19 ድንበሩም ወደ ቤት ሖግላ ወደ ሰሜን በኩል አለፈ። መውጫውም በዮርዳንስ መጨረሻ በደቡብ በኩል ባለው በጨው ባሕር ልሳን አጠገብ ነበር፥ ይህም የደቡቡ ዳርቻ ነበረ።
\v 20 በምሥራቅም በኩል ድንበሩ ዮርዳኖስ ነበረ። ይህ በዙሪያቸው ዳርቻ በየወገኖቻቸው የብንያም ልጆች ርስት ነበረ።
\s5
\v 21 የብንያምም ልጆች ነገድ ከተሞች በየወገኖቻችቸው እነዚህ ነበሩ፦ ኢያሪኮ፥ ቤት ሖግላ፥ ዓመቀጺጽ፥
\v 22 ቤት ዓረባ፥ ዘማራይም፥ ቤቴል፥
\v 23 ዓዊም፥ ፋራ፥ ኤፍራታ፥
\v 24 ክፊርዓሞናይ፥ ዖፍኒ፣ ጋባ፤ አሥራ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው።
\s5
\v 25 ገባዖን፥ ራማ፥ ብኤሮት፥
\v 26 ምጽጳ፥ ከፊራ፥አሞቂ፥
\v 27 ፍርቄም፥ይርጵኤል፥ ተርአላ፥
\v 28 ዼላ፥ ኤሌፍ፥ ኢየሩሳሌም የምትባልየኢያቡስ ከተማ፥ ቂርያትጊብዓት፤ አሥራ ሦስት ከትሞችና መንደሮቸችው። የብንያም ልጆች ርስት በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ።
\s5
\c 19
\p
\v 1 ሁለተኛውም ዕጣ ለስምዖን ልጆች ነገድ በየወገኖቻቸው ወጣ። ርስታቸውም በይሁዳ ልጆች ርስት መካከል ነበረ።
\s5
\v 2 እነርዚህም ርስታቸው ሆኑላቸው፤ ቤርሳቤህም ሤባ፥ሞላዳ፥
\v 3 ሐጸርሹዕል፥ ባለ፥ዔጼም፥
\v 4 ኤልቶላድ፥ በቱል፥ ሔርማ፥ ጺቅላግ፥
\s5
\v 5 ቤትማርካቦት፥ ሐጸርሱሳ፥
\v 6 ቤተ ለባኦት፥ ሻሩሔን፤ አሥራ ሦስት ከተሞችና መንደሮቻቸው።
\v 7 ዓይን፥ ሪሞን፥ ዔቴር፥ ዓሻን፤ አራት ከተሞችና መንደሮቻቸው፤
\s5
\v 8 እስከ ባዕላት ብኤርና እስከ ደቡቡ ራማት ድረስ በእነዚህ ከተሞችና ዙሪያ ያሉ መንደሮች ሁሉ። የስምዖን ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ።
\v 9 ከይሁዳ ልጆች ክፍል የስምዖን ልጆች ርስት ሆነ። የይሁዳም ልጆች ዕድል ፈንታ ስለ በዛባቸው የስምዖን ልጆች በርስታቸ መካከል ወረሱ።
\s5
\v 10 ሦስተኛውም ዕጣ ለዛብሎን ልጆች በየወገኖቻቸው ወጣ። የርስታቸውም ድንበር ወደ ሣሪድ ደረሰ።
\v 11 ድንበራቸውም በምዕራብ በኩል ወደ መርዓላ ወጣ፥ እስከ ደባሼትም ደረሰ፤ በዮቅንዓም ፊት ለፊት ወዳለው ወንዝ ደረሰ።
\s5
\v 12 ከሣሪድም ወደ ፀሐይ መውጫ ወደ ምሥራቅ ወደ ኪስሎት ታቦር ዳርቻ ዞረ። ወደ ዳብራትም ወጣ፥ ወደ ያፊዓም ደረሰ።
\v 13 ከዚያም በምሥራቅ በኩል ወደ ጋትሔፍርና ወደ ዒታቃጺን አለፈ፥ ወደ ሪምንና ወደ ኒዓ ወጣ።
\s5
\v 14 ድንበሩም በሰሜን በኩል ወደ ሐናቶን ዞረ፥ መውጫውም በይፍታሕኤል ሸለቆ ነበረ።
\v 15 ቀጣት፥ ነህላል፥ ሺምሮን፥ ይዳላ፥ ቤተ ልሔም፤ አሥራ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው።
\v 16 የዛብሎን ልጆች ርስት በየወገኖቻቸው እነዚህ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።
\s5
\v 17 አራተኛውም ዕጣ ለይሳኮር ልጆች በየወገኖቻቸው ወጣ።
\v 18 ድንበራቸውም ወደ ኢይዝራኤል፥ወደ ከስሎት፥ወደ ሱነም፥
\v 19 ወደ ሐፍራይም፥ ወደ ሺአን፥ ወደ አናሐራት፥
\s5
\v 20 ወደ ረቢት፥ ወደ ቂሶን፥ ወደ አቤጽ፥
\v 21 ሬሜት፥ ወደ ዓይንጋቢም፥ ወደ ዓይንሐዳ፥ ወደ ቤት ጳጼጽ ደረሰ፤ ድንበሩም ወደ ብቦርና ወደ ሻሕጽይማ፥ ወደ ቤት ሳሚስ ደረሰ።
\v 22 የድንበራቸውም መውጫ ዮርዳኖስ ነበረ፤ አሥራ ስድስት ከተሞችና መንደሮቻቸው።
\s5
\v 23 የይሳኮር ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው እነዚህ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።
\s5
\v 24 አምስተኛውም ዕጣ ለአሴር ልጆች ነገድ በየወገኖቻቸው ወጣ።
\v 25 ድንበራቸውም ሔልቃት፥ ሐሊ፥ ቤጤን፥ አዚፍ፥ አላሜሌክ፥ ዓምዓድ፥ ሚሽአል ነበረ፤
\v 26 በምዕራብ በኩል ወደ ቀርሜሎስና ወደ ሺሖርሊብናት ደረሰ።
\s5
\v 27 ወደ ፀሐይም መውጫ ወደ ቤት ዳጎን ዞረ፥ወደ ዛብሎንም ወደ ይፍታሕኤል ሸለቆ፥ በሰሜን በኩል ወደ ቤት ዓሜቅና ወደ ንዒኤልም ደረሰ፤ በስተ ግራ ቡልም ወደ ካቡል ወጣ።
\v 28 ከዚያም ወደ ዔብሮን፥ ወደ ረአብ፥ ወደ ሐሞን፥ ወደ ቃና እስከ ታላቁ ሲኖናም ደረሰ።
\s5
\v 29 ድንበርም ወደ ራማ፥ ወደ ተመሸገውም ከተማ ወደ ጢሮስ ዞረ፤ ድንበሩም ወደ ሖሳ ዞረ፤ መውጫውም በአክዚብ በኩል ወደ ባሕሩ ነበረ፤
\v 30 ዑማ፥ አፌቅ፥ ረአብ ደግሞ ነበሩ። እነዚህም ሀያ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው።
\s5
\v 31 የአሴር ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።
\s5
\v 32 ስድስተኛውም ዕጣ ለንፍታሌም ልጆች በየወገኖቻቸው ወጣ።
\v 33 ድንበራቸውም ከሔሌፍ፥ ከጸዕነኒም ዛፍ፥ ከአዳሚኔቄብ፥ ከየብኒኤል እስከ ለቁም ድረስ ነበረ፤ መውጫውም በዮርዳኖስ ነበረ።
\v 34 ድንበሩም ወደ ምዕራብ ወደ አዝኖት ታቦር ዞረ፥ ከዚያም ወደ ሑቆቅ ወጣ፤ከዚያም በደቡም በኩል ወደ ዛብሎን፥ በምዕራብ በኩል ወደ አሴር፥ በዮርዳስም ወንዝ በፀሐይ መውጫ ወደ ይሁዳ ደረሰ።
\s5
\v 35 የተመሸጉትም ከትሞች እነዚህ፦ ነበሩ ጺዲም፥ ጼር፥ ሐማት፥ ረቃት፥ ኬኔሬት፥
\v 36 አዳማ፥ ራማ፥ አሶር፥
\v 37 ቃዴስ፥ኤድራይ፥ ዓይንሐጽር፥ ይርአን፥
\s5
\v 38 ሚግዳልኤል፥ ሖሬም፥ ቤት ዓናት፥ ቤት ሳሚስ፤ አሥራ ዘጠኝ ከተሞችና መንደሮቻቸው ያልተቆጠሩ።
\v 39 የንፍታሌም ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው እነዚህ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።
\s5
\v 40 ሰባተኛውም ዕጣ ለዳን ልጆች ነገድ በየወገኖቻቸው ወጣ።
\v 41 የርስታቸውም ዳርቻ ይህ ነበረ፤ ጾርዓ፥ ኤሽታኦል፥ ዒርሼሜሽ፥
\v 42 ሸዕለቢን፥ ኤሎን፥ ይትላ፥ ኤሎን፥
\s5
\v 43 ተምና፥አቃሮን፥
\v 44 ኢልተቄ። ገባቶን።ባዕላት፥ ይሁድ፥
\v 45 ብኔንርቅ፥ ጋትሪሞ፥
\v 46 ሜያርቆን፥ በኢዮጴ ፊት ለፊት ካለው ዳርቻ ጋር ራቆን።
\s5
\v 47 የዳንም ልጆች ዳርቻ አልበቃቸውም፥ የዳንም ልጆች ከሌሼም ጋር ሊዋጉ ወጡ፥ ያዙአትም፥ በሰይፍም ስለመቱአት፥ ወረሱአትም፥ ተቀመጡባትም። ስምዋንም በአባቶታቸው በዳን ስም ዳን ብለው ጠርአት።
\v 48 የዳን ነገድ ርስት በየወገኖቻቸ እነዚህ ከትሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።
\s5
\v 49 ምድሩንም ሁሉ በየድንበሩ ርስት እንዲሆን ከፍለው ከጨረሱ በኋላ፥ የእስራኤል ልጆች ለነዌ ልጅ ለኢያሱ በመካከላቸው ርስት ሰጡት።
\v 50 በኤፍሬም ተራራማ አገር ያለችውን ተምናሴራ የምትባለውን የፈለጋትን ከተማ እንደ እግዚአብሔር ትእዛዝ ሰጡት። ከተማውንም እንደ ገና ሠርቶ ተቀመጠበት።
\s5
\v 51 ካህኑ አልዓዛር፥ የነዌም ልጅ ኢያሱ፥ የእስራኤልም ነገዶችና የአባቶች አለቆች በእግዚአብሔር ፊት በሴሎ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አጠገብ በዕጣ የተካፈሉት ርስት ይህ ነው። የምርሪቱንም ማከፋፈል ሥራ ጨረሱ።
\s5
\c 20
\p
\v 1 ከዚያም እግዚአብሔር ኢያሱን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦
\v 2 ለእስራኤልም ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገራቸው፡
\v 3 ሳያውቅም ሰውን የገደለ እንዲሸሽባቸው በሙሴ እጅ የነገርኋችሁን የመማፀኛ ከተሞችን ለዩ። እነዚህም ከተሞች ከተገደለበት ከማንኛውም ከደም ተበቃይ የሚሸሹበት ቦታ ይሆኑላችኋል።
\s5
\v 4 ከእነዚህም ከተሞች ወደ አንዲቱ ይሸሻል፥ በከተማይቱም በር አደባባይ ቆሞ ለከተማይቱ ሽማግሌዎች ጉዳዩን ያስረዳል። እነርሱም ወደ ከተማይቱ ይቀበሉታል፥ የሚኖርበትንም ስፍራ ይሰጡታል።
\s5
\v 5 ሰው የሞተበትም ደም ተበቃዩ መጥቶ ለመበቀል ቢሞክር፥ የከተማውም ሰዎች ሰውየውን ለከተማው ባለሥልጣናት አሳልፈው መስጠት አይኖርባቸውም። ይህን ማድረግ የማይገባቸው እርሱ የገደለው ከዚህ በፊት ጥላቻ ሳይኖርና ሆነ ብሎ ባለመሆኑ ነው።
\v 6 በማኅበሩ ፊት ለፍርድ እስኪቆም ድረስ፥ በዚያን ጊዜ ያለው በሊቀ ካህንነት የሚያገለግለው እስኪሞት ድረስ በዚያች ከተማ ይቀመጥ። ከዚያም ወዲያ ነፍሰ ገዳዩ ፥ ሸሽቶ ከነበረበት ከተማ ወደ ከተማውና ወደ ቤቱ ይመለሳል።
\s5
\v 7 በንፍታሌም ባለው በተራራማው አገር በገሊላ ቃዴስን፥ በኤፍሬምም ባለው በተራራማው አገር ኬብሮን የምትባለውን ቂርያትአርባቅን ለዩ።
\v 8 ከዮርዳኖስም ማዶ ከኢያሪኮ ወደ ምሥራቅ ከሮቤል ነገድ በምድረ በዳው በደልዳላው ስፍራ ቦሶርን፣ ከጋድም ነገድ በገለዓድ ራሞትን፥ ከምናሴም ነገድ በባሳን ቶላንን ለዩ።
\s5
\v 9 ማንም ሰው ሳያውቅ ሰውን የገደለ ወደዚያ እንዲሸሽና በመካከላቸውም ለሚቀመጥ መጻተኛ ለእስራኤል ልጆች ሁሉ የተመረጡ ከተሞች እነዚህ ናቸው። ይህም ሰው በማኅብሩ ፊት ለፍርድ እስኪቆም ድረስ በደም ተበቃዩ እጅ እንዳይሞት ነው።
\s5
\c 21
\p
\v 1 ከዚያም የሌዋውያን ወገኖች አለቆች ወደ ካህኑ አልዓዘር፥ ወደ ነዌ ልጅ ኢያሱና ወደ እስራኤል ነገዶች አለቆች ቀርቡ።
\v 2 እነርሱም በከነዓን ምድር ባለችው በሴሎ እንዲህ አሉአቸው፡- እግዚአብሔር በሙሴ እጅ የምንቀመጥባቸውንና ለከብቶቻችንም መሰማሪያ የሚሆኑ ከተሞች እንድትሰጡን አዞአችኋል።
\s5
\v 3 ስለዚህም የእስራኤልም ሕዝብ በእግዚአብሔር ትእዛዝ የሚከተሉትን ከተሞች ለከብቶቻቸውም መሰማሪያ ጭምር እንዲሆኑ ርስታቸውን ለሌዋውያን ሰጡአቸው።
\s5
\v 4 ለቀዓትም ወገኖች የዕጣው ውጤት እንዲህ ሆነ፦ ሌዋውያንም ለነበሩ ለካህኑ ለአሮን ልጆች፥ ከይሁዳ ነገድ ከስምዖንም ነገድ ከብንያምም ነገድ አሥራ ሦስት ከተሞች ተሰጣቸው።
\v 5 ለቀሩትም ለቀዓት ልጆች ከኤፍሬም ነገድ፥ ከዳንም ነገድና ከምናሴ ነገድ እክኩሌታ አሥር ከተሞች በዕጣ ተቀበሉ።
\s5
\v 6 ለጌድሶንም ልጆች ከይሳኮር ነገድ፥ ከአሴር ነገድ፥ ከንፍታሌምም ነገድ፥ በባሳን ካለው ከምናሴ ነገድ እኩሌታ አሥራ ሦስት ከተሞች በዕጣ ተሰጣቸው።
\v 7 ለሜራሪም ልጅች በየወገኖቻቸው ከሮቤል ነገድ፥ከጋድ ነገድና ከዛብሎን ነገድአሥራ ሁለት ከተሞ ተቀበሉ።
\s5
\v 8 እግዚአብሔርም በሙሴ እጅ እንዳዘዛቸው የእስራኤል ልጆች እነዚህን ከተሞችና መሰማሪያቸውን ለሌዋውያን በዕጣ ሰጡ።
\v 9 ከይሁዳም ልጆች ነገድ ከስምዖንም ልጆች ነገድ በስማቸው እነዚህን ከተሞች ሰጡ።
\v 10 እነዚህ ከተሞች ከሌዊ ልጆች ነገድ የቀዓት ወገን ለሆኑ ለአሮን ልጆች ተሰጥቶአቸው ነበር። የመጀመሪያው ዕጣ ለእነርሱ ወጥቶላቸው ነበር።
\s5
\v 11 እንደ ኬብሮን ተመሳሳይ ቦታ በይሁዳ ተራራማ አገር ያለችውን ቂርያት አርባቅ (ይህም አርባቅ የዔናቅ አባት ነበረ) የምትባለውን ከተማ በዙሪያዋም ያለውን የከብቶች መሰማሪያዋን ሰጡአቸው።
\v 12 የከተማይቱንም እርሻ ግን መንደሮችዋንም ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ ርስት አድርገው ሰጡት።
\s5
\v 13 ለካህኑም ለአሮን ልጆች ሳያውቁ ነፍሰ ገዳይ ለሆኑት መማፀኛ ከተማ የሆነችውን ኬብሮንንና መሰማሪያዋን፥ ልብናን ከመሰማሪያዋን ጋር ሰጡ፤
\v 14 የቲርንና መሰማሪያዋን፥ ኤሽት ሞዓንና መሰማሪያዋን፥
\v 15 ሖሎንንና መሰማሪያዋን፥ ዳቤርንና መሰማሪያዋን፥
\v 16 ዓይንንና መሰማሪያዋን፥ ዮጣንና መሰማሪያዋን፥ ቤት ሳሚስንና መሰማሪያዋን ሰጡ። ከእነዚህ ከሁለቱ ነገዶች ዘጠኝ ከተሞችን ነበሩ።
\s5
\v 17 ከብንያምም ነገድ ገባዖንንና መሰማሪያዋን፥ ናሲብንና መሰማሪያዋን፥
\v 18 ዓናቶትንና መሰማሪያዋን፥ አልሞንንና መሰማሪያዋን፤አራት ከተሞችን ሰጡ።
\v 19 ለአሮን ልጆች ለካህናት የተሰጡ ከተሞች ከመሰማሪያቸው ባጠቃላይ አሥራ ሦስት ከተሞች ናቸው።
\s5
\v 20 ለቀሩትም ለቀዓት ልጆች ወገኖች ሌዋውያን የተሰጣቸ ከተሞች ከኤፍሬም ነገድ ዕጣ ወጥቶላቸው ነበር።
\v 21 ለእነርሱም በኤፍሬም ተራራማ አገር ሳያውቁ ነፍሰ ገዳይ ለሆኑት መማፀኛ ከተማ የሆነችውን ሴኬምንና መሰማሪያዋን፥ ጌዝርንና መሰማሪያዋን፥
\v 22 ቂብጻይምንና መስማሪያዋን፥ ቤት ሖሮንንና መሰማሪያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡአቸው።
\s5
\v 23 ከዳንም ነገድ ኤልተቄንና መሰማሪያዋን፥ ገባቶንንና መሰማሪያዋን፥
\v 24 ኤሎንንና መሰማሪያዋን፥ ጋትሪሞንንና መሰማሪያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡአቸው።
\s5
\v 25 ከምናሴም ነገድ እኩሌታ ታዕናክንና መሰማሪያዋን፥ ጋትሪሞንንና መሰማሪያዋን፤ ሁለቱን ከተሞች ሰጡአቸው።
\v 26 ለቀሩት የቀዓት ልጆች ወገኖች የተሰጡ ከተሞች ሁሉ ከመሰማሪያቸውን ጋር አሥር ከተሞችናቸው።
\s5
\v 27 ለሌሎች ሌዋውያንም ወገኖች ለጌድሶን ልጆች ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ሳያውቁ ነፍሰ ገዳይ ለሆኑት መማፀኛ ከተማ በባሳን ውስጥ የሆነችውን ጎላንንና መሰማሪያዋን፥ በኤሽትራንና መሰማይያዋን ሁለቱን ከተሞች ሰጡአቸው።
\s5
\v 28 ከይሳኮርም ነገድ ቂሶንንና መሰማሪያዋን፥ ዳብራትንና መሰማሪያዋን፥
\v 29 የያርሙትንና መሰማሪያዋን፥ ዓይንጋኒምንና መሰማሪያዋን፤ አራቱን ከተሞች ለጋሪሶን ነገድ ሰጡአቸው።
\v 30 ከአሴርም ነገድ ሚሽአልንና መሰማሪያዋን፥ ዓብዶንና መሰማሪያዋን፥
\v 31 ሔልቃትንና መሰማሪያዋን፥ ረአብንና መሰማሪያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡአቸው።
\s5
\v 32 ከንፍታሌምም ነገድ ሳያውቁ ነፍሰ ገዳይ ለሆኑት መማፀኛ ከተማ የሆነችውን በገሊላ ውስጥ ቃዴስንና መሰማሪያዋን፥ ሐሞትዶርንና መሰማሪያዋን፥ ቀርታንንና መሰማሪያዋን፤ ሦስቱን ከተሞች ለጌድሶን ነገድ ሰጡአቸው።
\v 33 የጌድሶን ልጆች ከተሞች ሁሉ በየወገኖቻቸው ከመሰማሪያቸው ጋር አሥራ ሦስት ከተሞች ናቸው።
\s5
\v 34 ከሌዋውያንም ለቀሩት ለሜራሪ ልጆች ወገን ከዛብሎን ነገድ ዮቅንዓምንና መሰማሪያዋን፥ ቀርታንና መሰማሪያዋን፥
\v 35 ዲሞናንና መሰማሪያዋን፥ ነህላልንና መሰማሪያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡ።
\s5
\v 36 ለሜራሪ ነገድ ከሮቤልም ነገድ ቦሶርንና መሰማሪያዋን፥ ያሀጽንና መሰምሪያዋን፥
\v 37 ቅዴሞትንና መሰማሪያዋን፥ ሜፍዓትንና መሰማሪያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡ።
\v 38 ሳያውቁ ነፍሰ ገዳይ ለሆኑት መማፀኛ ከተማ የሆነችውን ከጋድም ነገድ በገለዓድ ውስጥ ራሞትንና መሰማሪያዋን፥ መሃናይምንማ መሰማሪያዋን ሰጡ።
\s5
\v 39 ሐሴቦንንና መሰማሪያዋን፥ ኢያዜርንና መሰማሪያዋን ሜራሪ ነገድ ደግሞ የተሰጡ ባጠቃላይ አራት ከተሞች ናቸው።
\v 40 ከሌዋውያን ወገኖች የቀሩት የሜራሪ ልጆች ከተሞች ሁሉ በየወገኖቻቸው እነዚህ ነበሩ፤ ዕጣቸውም ባጠቃላይ አሥራ ሁለት ከተሞች ነበሩ።
\s5
\v 41 በእስራኤል ልጆች ርስት መካከል የነበሩት የሌዋውያን ከተሞች ሁሉ አርባ ስምንት ከተሞችና መሰማሪያቸው ነበሩ።
\v 42 እነዚህም ከተሞች እያንዳንዳቸው ከመሰማሪያቸው ጋር ነበሩ፤ እነዚህም ከተሞች ሁሉ በዚህ ዓይነት መንገድ ነበሩ።
\s5
\v 43 እግዚአብሔርም ይሰጣቸው ዘንድ ለአባቶቻቸው የማለላቸውን ምድር ሁሉ ለእስራኤል ሰጠ። ወረሱአትም፥ ተቀመጡባትም።
\v 44 እግዚአብሔርም ለአባቶቻቸው እንደ ማለላቸው በዙሪያቸው ካሉት አሳረፋቸው። ከጠላቶቻቸውም ሁሉ ይቋቋማቸው ዘንድ ማንም ሰው አልቻለም፤ እግዚአብሔርም ጠላቶቻቸውን ሁሉ በእጃቸው አሳልፎ ሰጣቸው።
\v 45 እግዚአብሔር ለእስራኤል ቤት ከተናገረው መልካም ነገር ሁሉ ተፈጸመ እንጂ ምንም አልቀረም።
\s5
\c 22
\p
\v 1 በዚያን ጊዜም ኢያሱ የሮቤል ልጆችንና የጋድ ልጆችን የምናሴንም ነገድ እኩሌታ ጠራቸው።
\v 2 እንዲህም አላቸው፦ የእግዚእአብሔር አገልጋይ ሙሴ ያዘዛችሁን ሁሉ ጠብቃችኋል፥ እኔም ላዘዝኋችሁ ነገር ሁሉ ታዝዛችኋል።
\v 3 ይህንም ያህል ብዙ ጊዜ እስከ ዛሬ ድረስ ወንድሞቻችሁን አልተዋችሁም፥ የአምላካችሁንም የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ጠብቃችኋል።
\s5
\v 4 አሁንም እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ተናገራቸው ወድሞቻችሁን አሳርፎአቸዋል። አሁን እንግዲህ ተመለሱ፥ ወደ ቤታችሁና የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ በዮርዳኖስ ማዶ ወደ ሰጣችሁ ወደ ርስታችሁ ምድር ሂዱ።
\v 5 የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ያዘዛችሁን ትእዛዙንና ሕጉን ታደርጉ ዘንድ እግዚአብሔር አምላካችሁን ትወድዱ ዘንድ መንገዱንም ሁሉ ትሄዱ ዘንድ፥ ትእዛዙንም ትጠብቁ ዘንድ፥ ወደ እርሱም ትጠጉ ዘንድ፥ በፍጹምም ልባችሁ በፍጹምም ነፍሳችሁ ታመልኩ ዘንድ ብቻ እጅግ ተጠንቀቁ።
\v 6 ኢያሱም መረቃቸው፥ ሰደዳቸውም፤ ወደ ቤታቸውም ሄዱ።
\s5
\v 7 ለምናሴም ነገድ እኩሌታ ሙሴ በባሳን ውስጥ ርስት ሰጥቶአቸው ነበር፤ ለቀረው እኩሌታው ግን ኢያሱ በዮርዳኖስ ማዶ በምዕብብ ወንን በወንድሞቻቸው መካከል ርስት ሰጣቸው። ኢያሱም ወደ ቤታቸው በሰደዳቸው ጊዜ
\v 8 እንዲህ ብሎ መረቃቸው፦ በብዙ ብልጥግና በእጅግም ብዙ ከብት፥ በብርም፥ በወርቅም፥ በናስም፥ በብረትም፥ በእጅግም ብዙ ልብስ ወደ ቤታችሁ ተመለሱ፤ የጠላቶቻችሁንም ምርኮ ከወንድሞቻችሁ ጋር ተካፈሉ።
\s5
\v 9 የሮቤልም ልጆች የጋድም ልጆች የምናሴም ነገድ እኩሌታ የእስራኤል ሕዝብ በከነዓን በሴሎ ትተው ወደ ቤታቸው ተመለሱ። በሙሴም እጅ በተሰጠ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ወደ ተቀበሉአት ወደ ርስታቸው ወደ ገለዓድ ምድር ይገቡ ዘንድ ሄዱ።
\s5
\v 10 በከነዓን ምድር ወዳለው ወደ ዮርዳኖስ አቅራቢያም በመጡ ጊዜ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች የምናሴም ነገድ እኩሌታ በዚያ በዩርዳኖስ አጠገብ ታላቅ መሠዊያ ሠሩ።
\v 11 ለእስራኤልም ልጆች፦ እነሆ፥ በከነዓን ምድር ዳርቻ በዮርዳኖስ አጠገብ ባለው ግዛት፥ የእስራኤል ልጆች ባሉበት ወገን፥ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች የምናሴም ነገድ እኩሌታ መሠዊያ ሠርውዋል፤ የሚል ወሬ ደረሰላቸው።
\s5
\v 12 የእስራኤል ሕዝብ ይህን በሰሙ ጊዜ የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ ወጥተው እነርሱን ሊዋጉ በሴሎ ተሰበስቡ።
\s5
\v 13 የእስራኤልም ልጆች በገለዓድ ምድር ወዳሉት ወደ ሮቤል ልጆችና ወደ ጋድ ልጆች ወደ ምናሴም ነገድ እኩሌታ መልእክት ላኩ። የካህኑን የአልዓዛርን ልጅ ፊንሐስን ደግሞ ላኩ፥
\v 14 ከእርሱም ጋር አሥር አለቆች ነበሩ፥ ከእስራኤል ከነገዱ ሁሉ አንድ አንድ የአባቶች ቤት አለቃ እያንዳንዱም በእስራኤል አእላፋት መካከል የእየአባቶቻቸው ቤት አለቃ ነበሩ።
\s5
\v 15 በገለዓድም ምድር ወዳሉት ወደ ሮቤል ልጆችና ወደ ግድ ልጆች ወደ ምናሴም ነገድ እኩሌታ መጡ፥ እንዲህም ብለው ተናገሩአቸው፦
\v 16 የእግዚአብሔር ማኅበር ሁሉ የሚለው ይህ ነው፦ ይህ በእስራኤል አምላክ ላይ ያደረጋችሁት ኃጢአት ምንድን ነው? ዛሬ እግዚእአብሔርን ከመከተል ተመልሳችኋል ዛሬም በራሳችሁ መሠዊያ በመሥራታችሁ በእግዚአብሔር ላይ ዐምፃችኋል።
\s5
\v 17 በፌጎር ያደረገነው ኃጢአታችን አይበቃምን? እስከ ዛሬም ድረስ ከዚያ ኃጢአት ራሳችንን አላነጸንበትም። ከዚያም ኃጢአት የተነሣ በእግዚአብሔር ማኅበር ላይ መቅሠፍት ወረደ።
\v 18 እናንተ ዛሬ እግዚአብሔርን ከመከተል መመለስ ይገባችኋልን? ዛሬ በእግዚአሔር ላይ ብታምፁ ነገ በእስራኤል ማኅበር ሁሉ ላይ ይቆጣል።
\s5
\v 19 የርስታችሁም ምድር የረከሰ ቢመስላችሁ የእግዚአብሔር ማደሪያ ወደ ሚቀመጥበት ወደ እግዚአብሔር ርስት ምድር አልፋችሁ በመካከላችን ውረሱ። ከአምላካችንም ከእግዚአብሔር መሠዊያ ሌላ ለእናንተ መሠዊያ በመሥራታችሁ በእግዚአብሔርና በእኛ ላይ አታምፁ።
\v 20 የዛራ ልጅ አካን እርም ነገር በመውሰድ ኃጢአትን ስለ ሠራ በእስራኤል ማኅበር ሁሉ ላይ ቁጣ አልወረደምን? እርሱም በኃጢአት ብቻውን አልሞተም።
\s5
\v 21 ከዚያም የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች የምናሴም ነገድ እኩሌታ ለእስራኤል አለቆች እንዲህ ብለው መለሱላቸው፦
\v 22 ሁሉን የሚችል አምላክ እግዚአብሔር ታላቁ አምላክ እግዚአብሔር እርሱ ያውቃል፥ እስራኤልም እንዲያውቅ ያደርጋል! በእግዚአብሔር ላይ ዐምፀንና ተላልፈን እንደ ሆነ ዛሬ አታድነን እግዚአሔርን ከመከተል እንድንመለስ፥ የሚቃጠለውን
\v 23 መሥዋዕትና የእህልን ቁርባን እንድናሳርግበት፥ የደኅነትትንም መሥዋዕት እንድናቀርብበት ብለን መሠዊያ ሠርተን እንደ ሆነ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ ይበቀለን።
\s5
\v 24 ይልቁንም ከልባችን ፍርሃት የተነሣ፦ በሚመጣው ዘመን ልጆቻችንን፦ እናንተ የሮቤልና የጋድ ልጆች፥ ከእስራኤል አምላክ ከእግዚአብሔር ጋር ምን አላችሁ?
\s5
\v 25 እግዚአብሔር በእኛና በእናንተ መካከል ዮርዳኖስን ድንበር አድርጎአል። እናንተ የሮቤልና የጋድ ልጆች በእግዚአብሔር ዘንድ እድል ፈንታ የላችሁም ይሉአቸዋል ብለን ይህን አደረግን። በዚህም ልጆቻችሁ ልጆቻችንን እግዚአብሔርን ከመፍራት ያስተዋቸዋል።
\s5
\v 26 ስለዚህ፦ መሠዊያ እንሥራ አልን፤ ነገር ግን ለሚቃጠል መሥዋዕት ወይም ለሌላ መሥዋዕት አይደለም፤
\v 27 ነገር ግን በእኛና በእናንተ መካከል ከእኛም በኋላ በትውልዳችንና በትውልዳችሁ መካከል በሚቃጠል መሥዋዕትና በቁርባን በደኅንነትም መሥዋዕታችን እግዚአብሔርን እናመልክ ዘንድ በሚመጣውም ዘመን ልጆቻችሁ ልጆቻችንን፦በእግዚአብሔር ዘንድ እድል ፈንት የላችሁም እንዳይሉ ምስክር ይሆናል።
\s5
\v 28 ስለዚህም አልን፦ በሚመጣው ዘመን ለእኛ ወይም ለትውልዳችን፥ ይህን እንላለን እኛ፦ እነሆም አባቶቻችን ያደረጉትን የእግዚአብሔርን መሠዊያ ምሳሌ እዪ በእኛና በእናንተ መካከል ምስክር ነው እንጂ ስለሚቃጠል መሥዋዕታችን ስለሌላ መሥዋዕት አይደለም። በማደሪያው ፊት ካለው ከአምላካችን
\v 29 ከእግዚአብሔር መሠዊያ ሌላ ለሚቃጠል መሥዋዕትና ለእህል ቁርባን ለሌላ መሥዋዕትም የሚሆን መሠዊያን የሠራነው በእግዚአብሔር ላይ በማመፅ እግዚአብሔርንም ዛሬ መከተልን ለመተው በማለት እንደ ሆነ ይህ ከእኛ ይራቅ።
\s5
\v 30 ካህኑ ፊንሐና የማኅበሩ አለቆች፥ ከእርሱ ጋር ከነበሩት የእስራኤል አለቆች፥ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች የምናሴም ልጆች የተናገሩትን ቃል በሰሙ ጊዜ ነገሩ እጅግ ደስ አሰኛቸው።
\v 31 የካህኑም በአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ ለሮቤል ልጆችና ለጋድ ልጆች ለምናሴም ልጆች፦ ይህን መተላለፍ በእግዚአብሔር ላይ አላደረጋችሁምና እግዚአብሔር በመካከላችን እንዳለ ዛሬ እናውቃለን፤ አሁን የእስራኤልን ልጆች ከእግዚአብሔር እጅ አድናችኋል አላቸው።
\s5
\v 32 የካህኑም የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስና አለቆቹ ከሮቤል ልጆችና ከጋድ ልጆች ዘንድ ከገለዓድ አገር ወደ ከነዓን አገር ወደ እስራኤል ልጆች ተመለሱ፥ ወሬም አመጡላቸው።
\v 33 ነገሩም የእስራኤል ልጆችን ደስ አሰኘ፤ የእስራኤልም ልጆች እግዚአብሔርን አመሰገኑ፥ ከዚያም ወዲያ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች የተቀመጡባትን ምድር ያጠፉ ዘንድ ወጥተው አንዲወጉአቸው አልተናገሩም።
\s5
\v 34 የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች፦ እግዚአብሔር አምላክ እንደ ሆነ ይህ በመካከላችን ምስክር ነው ሲሉ መሠዊያውን ምስክር ብለው ጠሩት።
\s5
\c 23
\p
\v 1 ከብዙ ቀናት በኋላ፥እግዚአብሔርም እስራኤልን በዙሪያቸው ካሉት ጠላቶቻቸው ሁሉ ካሳረፈ፥ ኢያሱ ሸምግሎ ነበር።
\v 2 ኢያሱም እስራኤልን ሁሉ ሽማግሌዎቻቸውን፥ አለቆቻቸውን፥ ፈራጆቻቸውንና ሹማምቶቻቸውን ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ እኔ በጣም ሸምግያለሁ።
\v 3 እናንተም አምላካችሁ እግዚአብሔር በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ ስለ እናንተ ያደረገውን ሁሉ አይታችኋል፤ ስለ እናንተ የተዋጋ እርሱ አምላካችሁ እግዚአብሔር ነው።
\s5
\v 4 ተመልከቱ! እኔ ካጠፋኋቸው አሕዛብ ሁሉ ጋር ከዮርዳኖስ ጀምሮ እስካለው እስከ ታላቁ ባሕር ድረስ ለነገዶቻችሁ ርስት እንዲሆኑ መድቤላችኋለሁ።
\v 5 እግዚአሔር አምላካችሁም እርሱ ከፊታችሁ በብርቱ ይበትናቸዋል፥ ከፊታችሁም ያሳድዳቸዋል። እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ተናገራችሁም ምድራቸውን ትወርሳላችሁ።
\s5
\v 6 ስለዚህም በሙሴ ሕግ መጽሐፍ የተጻፈውን ሁሉ ለመጠበቅና ለማድረግ በጣም በርቱ፥ ከእርሱም ወደ ቀኝም ወደ ግራም ፈቀቅ አትበሉ።
\v 7 በእናንተ መካከል ወደ ቀሩት ወደ እነዚህ አሕዛብ አትግቡ፤ የአማልክታቸውንም ስም አትጥሩ፥ አትማሉባቸውም፥ አታምልኩአቸውም፥ አትስገዱላቸውም።
\v 8 እስከ ዛሬ ድረስ እንዳደረጋችሁት በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ተጣበቁ።
\s5
\v 9 እግዚአብሔርም ታላላቆችንና ኃይለኞችን መንግሥታት ከፊታችሁ አስወጣላችሁ። እስከ ዛሬም ድረስ ማንም ሊቋቋማችሁ አልቻለም።
\v 10 እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ተጋገራችሁ ስለ እናንተ የሚዋጋ እርሱ ነውና፥ ከእናንተ አንድ ሰው ሺህ ሰውን ያሳድዳል።
\v 11 እግዚእብሔር አምላካችሁን ትወድዱት ዘንድ ትኩረት አድርጉ።
\s5
\v 12 እናንተ ግን ተመልሳችሁ በመካከላችሁ ከቀሩት ከእነዚህ አሕዛብ ጋር ብትጣበቁ፥ወይም ከእነርሱም ጋር ብትጋቡ፥ ወይም እናንተ ወደ እነርሱም ወደ እናንተ ኅብረት ብታደርጉ፥
\v 13 ከዚያም እግዚአብሔር አምላካችሁ ከመካከላችሁ እነዚህን ሰዎች እንደማያስወጣችሁ በርግጥ እወቁ። በዚህ ፈንታ ከዚህች እግዚአብሔር ከሰጣችሁ ከመልካሚቱ ምድር እስክትጠፉ ድረስ ለእናንተም መውደቂያና ወጥመድ፥ በጎናችሁም መግረፊያ፥ በዓይናችሁም እሾህ ይሆኑባችኋል።
\s5
\v 14 እነሆም ዛሬ የምድርን መንገድ ሁሉ እሄዳለሁ፤ እናንተም እግዚአብሔር ስለ እናንተ ከተናገረው ከመልካም ነገር ሁሉ አንድ ነገር እንዳልቀረ በልባችሁ ሁሉ በነፍሳችሁም ሁሉ እወቁ፥ ሁሉ ደርሶላችኋል፤ ከእርሱም አንድ ነገር አልቀረም።
\v 15 እግዚአብሔ አምላካችሁ የተናገረው መልካም ነገር ሁሉ እንደ ደረሰላችሁ፥ እግዚአብሔር አምላካችሁ ከሰጣችሁ ከዚህች ከመልካሚቱ ምድር እናንተን እስኪያጠፋችሁ ድረስ እግዚአብሔር እንዲሁ ክፉን ነገር ሁሉ ያመጣባችኋል።
\s5
\v 16 የእግዚአብሔር አምላካችሁን ቃል ኪዳን ብታፈርሱ፥ ሄዳችሁም ሌሎችን አማልክት ብታመልኩ፥ ብትሰግዱላቸውም፥ በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔር ቁጣ ይነድድባችኋል፥ ከሰጣትችሁም ከመልካሚቱ ምድር ፈጥናችሁ ትጠፋላችሁ።
\s5
\c 24
\p
\v 1 ኢያሱም የእስራኤልን ነገድ ሁሉ ወደ ሴኬም ሰበስበ፥ የእስራኤልንም ሽማግሌዎችን፥ አለቆቻቸውን፥ ፈራጆቻቸውንና ሹማምቶቻቸውን ጠራቸው፤ እነርሱም በእግዚአብሔር ፊት ቆሙ።
\v 2 ኢያሱም ለሕዝቡ ሁሉ እንዲህ አለ፦ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ አባቶቻችሁ፥ የአብርሃምና የናኮር አባት ታራ፥ አስቀድመው በወንዝ ማዶ ተቀመጡ፤ ሌሎችንም አማልክት አመለኩ።
\s5
\v 3 አባታችሁንም አብርሃምን ከኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ ወስጄ በከነዓን ምድር ሁሉ መራሁት፤ ዘሩንም በልጁ በይስሐቅ በኩል እንዲበዛ ሰጠሁት።
\v 4 ለይስሐቅም ያዕቆብንና ዔሳውን ሰጠሁት። ለዔሳውም የሴይርን ተራራ ርስት አድርጌ ሰጠሁት፥ ነገር ግን ያዕቆብና ልጂቹ ወደ ግብፅ ወረዱ።
\s5
\v 5 ሙሴንና አሮንንም ላክሁ፥ ግብፃውያንን በመቅሠፍት መታሁ። ከዚያም በኋላ አወጣኋችሁ።
\v 6 አባቶቻችሁንም ከግብፅ አወጣኋችው፤ ወደ ባሕሩም መጣችሁ። ግብፃውያንም አባቶቻችሁን በሰረገሎችና በፈረሰኞች እስከ ኤርትራ ባሕር ድረስ አሳደዱአቸው።
\s5
\v 7 አባቶቻችሁም ወደ እግዚአብሔር በጮኹ ጊዜ በእናንተና በግብፃውያን መካከል ጨለማ አደረገ። ባሕሩንም በእነርሱ ላይ መለሰባቸው፥ አሰጠማቸውም። ዓናኖቻችሁም በግብፃውያን ላይ ያደረግሁትን አይታችኋል። ለረጅም ጊዜም በምድረ በዳ ተቀመጣችሁ።
\s5
\v 8 እኔም በዮርዳኖስ ማዶ ወደ ተቀመጡበት ወደ አሞራውያን ምድር አመጣኋችሁ። ከእናንም ጋር ተዋጉ፥ በእጃችሁ አሳልፌ ሰጠኋችሁ። ምድራቸውንም ወረሳችሁ፤ ከፊታችሁም አጠፋኋቸው።
\s5
\v 9-10 የሞዓብም ንጉሥ የሴፎር ልጅ ባላቅ ተንሥቶ ከእስራኤል ጋር ተዋጋ እንዲረግማችሁም የቢዖርን ልጅ በለዓምን ልኮ አስጠራው።እኔ ግን በለዓምን አልሰማሁትም። እርሱም በዚህ ፈንታ ባረካችሁ፥ እኔም ከእጁ አዳንኋችሁ።
\s5
\v 11 ዮርዳኖስንም ተሻግራችሁ፥ ወደ ኢያሪኮም መጣችሁ። የኢያሪኮም ሰዎች፥ ከአሞራዊውያን፥ ከፌርዛዊውያን፥ ከከነዓናዊውያን፥ ከኬጢያዊውያን፥ ከጌርጌሳዊውያን፥ ከኤዊያዊውያንና ከኢያቡሳዊውያን፥ ጋር ተዋጉአችሁ። በእነርሱም ላይ ድልን ሰጠኋችሁ፤አሳልፌም በእጃችሁ ሰጠኋችሁ።
\v 12 በፊታችሁ ያሉትን ሁለቱን የአሞራውያንን ነገሥታት እንዲያስወጡአቸው በፊታችሁም ተርብን ሰደድሁባቸው። ይህም በእናንተ ሰይፍና ቀሥት አይደለም።
\s5
\v 13 ያልደከማችሁበትንም ምድር፥ ያልሠራችኋቸውንም ዛሬ የተቀመጣችሁባቸውን ከተሞች ሰጠኋችሁ። ያልተከላችኋቸውን ወይንና ወይራ በላችሁ።
\s5
\v 14 አሁንም እግዚአብሔርን ፍሩ፥ በፍጹም ቅንነትና ታማኝነት አምልኩት፤ አባቶቻችሁም በኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ በግብፅም ያመለኩአቸውን አማልክት ከእናንተ አርቁ፤ እግዚአብሔርንም አምልኩ።
\v 15 እግዚአብሔርንም ማምለክ ክፉ መስሎ ቢታያችሁ፥ እባቶቻችሁ በኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ ሳሉ ያመለኩአቸውን አማልክት ወይም በምድራቸው ያላችሁባቸውን የአሞራውያንን አማልክት ታመልኩ እንደ ሆነ፥ የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ። እኔና ቤተ ሰቦቼ ግን እግዚአብሔርን እናመካለን።
\s5
\v 16 ሕዝቡም መልሰው እንዲህ አሉ፦ እግዚአብሔርን ትተን ሌሎች አማልክትን ማምለክ ከእኛ ይራቅ፥
\v 17 እኛንና አባቶቻችንን ከባርነት ቤት ከግብፅ ምድር ያወጣን፥ በዓይናችንም ፊት እነዚያን ታላላቅ ተአምራት ያደረገ፥ በሄድንባትም መንገድ ሁሉ ባለፍንባችውም አሕዛብ ሁሉ መካከል የጠበቀን፥ እርሱ አምላካችን እግዚአብሔር ነው።
\v 18 እግዚአብሔር አሕዛብን ሁሉ በምድሪቱም የተቀመጡትን አሞራውያን ከፊታችን አስወጣ። ስለዚህ እርሱ አምላካችን ነውና፤ እግዚአብሔርን እናመልካለን።
\s5
\v 19 ኢያሱም ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፦ እርሱ ቅዱስና፥ ቀናተኛ አምላክ ነውና፥ እግዚአብሔርን ማምለክ አትችሉም፤ መተላለፋችሁንና ኃጢአታችሁን ይቅር አይልም።
\v 20 እግዚአብሔርን ትታችሁ እንግዶችን አማልክት ብታመልኩ፥ ተመልሶ ክፉ ነገር ያደርግባችኋል፥ መልካም ካደረገላችሁ በኋላ ያጠፋችኋል።
\s5
\v 21 ሕዝቡም ኢያሱን፦ እንዲህ አይሁን እግዚአብሔርን እናመልካለን አሉት።
\v 22 ከዚያም ኢያሱ ሕዝቡን፦ እግዚአብሔርን እንድታመኩት እንደመረጣችሁ በራሳችሁ ላይ ምስክሮች ናችሁ አላቸው። እነርሱም፦ ምስክሮች ነን አሉ።
\v 23 እርሱም፦ አሁን እንግዲህ በመካከላችሁ ያሉትን እንግዶችን አማልክት አርቁ፥ ልባችሁንም ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር አዘንብሉ አላቸው።
\s5
\v 24 ሕዝቡም ኢያሱን፦ አምላካችንን እግዚአብሔርን እናመልካለን፥ ድምፁንም እንሰማለን፥ አሉ።
\v 25 በዚያን ቀን ኢያሱ ከሕዝቡ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ። በሴምም አዋጅንና ሕግን አደረገላቸው።
\v 26 ኢያሱም እነዚህን ቃላት ሁሉ በእግዚአብሔር ሕግ መጽሐፍ ጻፈ። ታላቁንም ድንጋይ ወስዶ በእግዚአብሔር መቅደስ አጠገብ ከነበረችው ከአድባሩ ዛፍ በታች አቆመው።
\s5
\v 27 ኢያሱም ለሕዝቡ፦ ተመልከቱ፥ የተናገረነውን ይህ ድንጋይ ይመሰክርብናል። እግዚአብሔር የተናገርነውን ሁሉ ሰምቶአል። እንግዲህ አምላካችሁን እንዳትክዱ ይህ ምስክር ይሆንባችኋል አላቸው።
\v 28 ስለዚህም ኢያሱ ሕዝቡን ወደ እያንዳንዱ ርስት እንዲሄዱ አደረገ።
\s5
\v 29 ከዚህ ነገር በኋላ የእግዚአብሔር አገልጋይ የነዌ ልጅ ኢያሱ ዕድሜው መቶ አሥር ዓመት ሞልቶት ሞተ።
\v 30 በተራራማውም በኤፍሬም አገር በገዓስ ተራራ በሰሜን ባለችው በራሱ ርስት በተምና ሴራ ቀበሩት።
\s5
\v 31 ኢያሱ በነረበት ዘመን ሁሉ፤ከኢያሱም በኋላ በነበሩት ለእስራኤልም ያደረገውን የእግዚአብሔርን ሥራ ሁሉ ባወቁት በሽማግሌዎች ዘመን ሁሉ እስራኤላውያን እግዚአብሔርን አመለኩ።
\s5
\v 32 የእስራኤልም ልጆች ከግብፅ የወጡት የዮሴፍን አጥንት ያዕቆብ ከሴም አባት ከኤሞር ልጆች በገዛው እርሻ በሴኬም ቀበሩት። እርሱም በአንድ መቶ ብር ገዛው፤እርሻውም ለዮሴፍ ልጆች ርስት ሆነ።
\v 33 የአሮንም ልጅ አልዓዛር ሞተ፤ በተራራውም በኤፍሬም አገር ለልጁ ለፊንሐስ በተሰጠችው በጊብዓ መሬት ቀበሩት።

1427
07-JDG.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,1427 @@
\id JDG
\ide UTF-8
\h መሳፍንት
\toc1 መሳፍንት
\toc2 መሳፍንት
\toc3 jdg
\mt መሳፍንት
\s5
\c 1
\p
\v 1
ከኢያሱ ሞት በኋላ፣ የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔርን እንዲህ ብለው ጠየቁ፡- “ከነዓናውያንን ለመዋጋት ወደላይ ስንሄድ ማን ይመራናል? ”
\v 2 እግዚአብሔርም አላቸው፡- “ይሁዳ ይመራችኋል፡፡ ተመልከቱ፣ ምድሪቱን ለእነርሱ አሳልፌ ሰጥቻለሁ፡፡”
\v 3 የይሁዳም ሰዎች ለወንድሞቻቸው ለስምዖን ሰዎች እንዲህ አሏቸው፡- “ከነዓናውያንን አብረን እንወጋቸው ዘንድ ከእኛ ጋር ለእኛ ወደተሰጠው ክልል ኑ፡፡ እኛም እንዲሁ ለእናንተ ወደተሰጠው ክልል እንመጣለን፡፡” ስለዚህም የስምዖን ነገድ ከእነርሱ ጋር ሄዱ፡፡
\s5
\v 4 የይሁዳ ሰዎችም ወደ ላይ ወጡ፣ እግዚአብሔርም በከነዓናውያንና በፌርዛውያን ላይ ድልን ሰጣቸው፡፡ በቤዜቅም ከእነርሱ አስር ሺህ ሰዎችን ገደሉ፡፡
\v 5 አዶኒ ቤዜቅን በቤዜቅ አገኙት፣ ከእርሱም ጋር ተዋግተው ከነዓናውያንና ፌርዛውያንን አሸነፉ፡፡
\s5
\v 6 አዶኒ ቤዜቅ ግን ሸሸ፣ ተከታትለውም አገኙትና ያዙት፣ የእጁንና የእግሩን አውራጣቶች ቆረጡ፡፡
\v 7 አዶኒ ቤዜቅም እንዲህ አለ፡- “የእግርና የእጅ አውራ ጣቶቻቸው የተቆረጠባቸው ሰባ ነገስታት ከእኔ ማዕድ ስር መብላቸውን ሰበሰቡ፡፡ እኔ እንዳደረግሁት፣ እግዚአብሔር በእኔ ላይ አደረገብኝ፡፡” እርሱንም ወደ ኢየሩሳሌም አመጡት፣ በዚያም ሞተ፡፡
\s5
\v 8 የይሁዳ ሰዎች ከኢየሩሳሌም ከተማ ጋር ተዋግተው ተቆጣጠሯት፡፡ በሰይፍ ስለት ወጓት፣ ከተማዋንም አቃጠሏት፡፡
\v 9 ከዚያም በኋላ የይሁዳ ሰዎች በኮረብታማው አገር ይኖሩ የነበሩትን ከነዓናውያንን ለመዋጋት፣ወደ ኔጌብና ወደ ምዕራቡ ኮረብታ ግርጌ ወረዱ፡፡
\v 10 ይሁዳም በኬብሮን (የኬብሮን ስም ቀድሞ ቂርያት አርባቅ ትባል ነበር) የሚኖሩትን ከነዓናውያንን ለመውጋት ሄደ፣ ሴሲን፣ አክመንና ቴላሚንም ድል አደረጉ፡፡
\s5
\v 11 ከዚያም የይሁዳ ሰዎች ወደ ዴብር (የዴብር ስም ቀድሞ ቅርያት ሤፍር ተብላ ትጠራ ነበር) ሄዱ፡፡
\v 12 ካሌብም አለ፣ “ቅርያት ሤፍርን የሚዋጋና የሚቆጣጠራትን ሰው፣ ሴት ልጄን ዓክሳን ሚስት ትሆነው ዘንድ እሰጠዋለሁ፡፡”
\v 13 የካሌብ ታናሽ ወንድም የቄናዝ ልጅ ጎቶንያልም ዴብርን ተቆጣጠረ፣ ስለዚህ ካሌብ ሴት ልጁን ዓክሳን ሚስት ትሆነው ዘንድ ሰጠው፡፡
\s5
\v 14
ዓክሳም ወዲያውኑ ወደ ጎቶንያል መጣች፣ ለእርሱም አባቷ እርሻ እንዲሰጣት እንዲለምነው ጠየቀችው፡፡ ከአሕያዋም በወረደች ጊዜ፣ ካሌብ እንዲህ ብሎ ጠየቃት፣ “ምን እንዳደርግልሽ ትፈልጊያለሽ? ”
\v 15 እርሷም እንዲህ አለችው፣ “በረከትን ስጠኝ፡፡ በኔጌብ ምድር ያለውን መሬት ሰጥተኸኛልና፣ የውሃ ምንጭንም ስጠኝ፡፡” ካሌብም የላይኛውንና የታችኛውን ምንጭ ሰጣት፡፡
\s5
\v 16 የቄናዊው የሙሴ አማት ዘሮችም ከባለ ዘንባባዋ ከተማ ለቀው ከይሁዳ ሰዎች ጋር በኔጌብ ወዳለችው ወደ ይሁዳ ምድረ በዳ ከይሁዳ ሰዎች ጋር በዓራድ አጠገብ ለመኖር ሄዱ፡፡
\v 17 የይሁዳ ሰዎችም ከወንድሞቻቸው ከስምዖን ሰዎች ጋር ሄዱና በጽፋት ይኖሩ የነበሩትን ከነዓናውያንን ወጓቸው፣ፈጽሞም አጠፏት፡፡ የከተማይቱም ስም ሔርማ ይባል ነበር፡፡
\s5
\v 18 በተጨማሪ የይሁዳ ሰዎች ጋዛንና በዙርያዋ ያለውን አገር፣ አስቀሎናንና በዙርያዋ ያለውን አገር እንደዚሁም አቃሮንንና በዙርያዋ ያለውን አገር ሁሉ ተቆጣጠሩ፡፡
\v 19 እግዚአብሔርም ከይሁዳ ሰዎች ጋር ነበር፣ የኮረብታማውንም አገር ተቆጣጠሩ፣ ነገር ግን በረባዳው ምድር የሚኖሩትን ሰዎች ማስወጣት አልቻሉም ነበር ምክንያቱም ነዋሪዎቹ የብረት ሰረገሎች ነበሯቸው፡፡
\s5
\v 20
ሙሴም እንደተናገረ ኬብሮንን ለካሌብ ሰጡት፣ እርሱም የዔናቅን ሶስት ልጆች ከዚያ አስወጣቸው፡፡
\v 21 ነገር ግን የቢንያም ሰዎች በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ኢያቡሳውያንን አላስወጧቸውም፡፡ ስለዚህ ኢያቡሳውያን እስከዛሬ ድረስ ከቢንያም ሰዎች ጋር በኢየሩሳሌም ይኖራሉ፡፡
\s5
\v 22
የዮሴፍ ወገንም ቤቴልን ለመውጋት ተዘጋጁ፣ እግዚአብሔርም ከእነርሱ ጋር ነበር፡፡
\v 23 ቀድሞ ሎዛ ተብላ ትጠራ የነበረችውን ቤቴልን ለመሰለል ሰዎችን ላኩ፡፡
\v 24 ሰላዮቹም ከከተማው አንድ ሰው ሲወጣ አዩ፣ እንዲህም አሉት፣ “ወደ ከተማው እንዴት መግባት እንደምንችል እባክህ አሳየን፣ ለአንተም ቸርነት እናደርግልሃለን፡፡”
\s5
\v 25 እርሱም ወደ ከተማው መግቢያውን መንገድ አሳያቸው፡፡ እነርሱም በሰይፍ ስለት ከተማውን ወጉ፣ ያንን ሰውና ቤተሰቦቹንም እንዲያመልጡ አደረጓቻው፡፡
\v 26 ሰውየውም ወደ ኬጢያውያን ሐገር ሄደና ከተማ ገነባ ስሙንም ሎዛ አለው፣ የዚያ ቦታ ስምም እስከዛሬ ሎዛ ነው፡፡
\s5
\v 27 የምናሴ ሰዎች በቤትሳንና በመንደሮቿ፣ በታዕናክና በመንደሮቿ፣ በዶርና በመንደሮቿ፣ በይብለዓምና በመንደሮቿ፣ በመጊዶና በመንደሮቿ ይኖሩ የነበሩትን ሰዎች አላስወጡአቸውም፣ ምክንቱም ከነዓናውያን በዚያ ለመቀመጥ ወስነው ስለነበር ነው፡፡
\v 28 እስራኤልም በበረታ ጊዜ፣ ከነዓናውያንን የጉልበት ስራ እየሰሩ እንዲያገለግሉአቸው አስገደዷቸው፣ ነገር ግን ሙሉ በሙሉ አላስወጧቸውም፡፡
\s5
\v 29
ኤፍሬም በጌዝር ይኖሩ የነበሩትን ከነዓናውያን አላስወጣቸውም፣ ስለዚህ ከነዓናውያን በእነርሱ መካከል በጌዝር መኖር ቀጠሉ፡፡
\s5
\v 30 ዛብሎንም በቂድሮን የሚኖሩትን ሰዎች ወይም በነህሎል ይኖሩ የነበሩትንም ሰዎች አላስወጣቸውም፣ ስለዚህ ከነዓናውያን በእነርሱ መካከል መኖር ቀጠሉ፣ ነገር ግን ዛብሎን ከነዓናውያን የጉልበት ስራ እየሰሩ እንዲያገለግሉአቸው ያስገድዳቸው ነበር፡፡
\s5
\v 31 አሴር በዓኮ፣ በሲዶን፣ በአሕላብ፣ በአክዚብ፣ በሒልባን፣ በአፌቅ፣ በረአብም የሚኖሩትን ሰዎች አላስወጣቸውም፡፡
\v 32 ስለዚህ የአሴር ነገድ በምድሪቱ በሚኖሩት በከነዓናውያን መካከል ኖሩ፣ ምክንያቱም አላስወጧቸውም ነበር፡፡
\s5
\v 33 የንፍታሌም ነገድ በቤት ሳሚስና በቤት ዓናት ይኖሩ የነበሩትን ሰዎችን አላስወጧቸውም፡፡ ስለዚህ የንፍታሌም ነገድ በምድራቸው ይኖሩ በነበሩ በነዓናውያን ሰዎች መካከል አብረው ኖሩ፡፡ ይሁን እንጂ የቤት ሳሚስና የቤት ዓናት ነዋሪዎች ለንፍታሌም ሰዎች የጉልበት ስራ እንዲሰሩ ይገደዱ ነበር፡፡
\s5
\v 34 አሞራውያንም የዳን ነገድ በኮረብታማው አገር እንዲኖሩ አስገደዷቸው፣ ወደ ሜዳማ ስፍራ ወርደው እንዲኖሩ አልፈቀዱላቸውም ነበር፡፡
\v 35 ስለዚህ አሞራውያን በሔሬስ ተራራ፣ በኤሎን፣ በሸዓልቢምም ኖሩ፣ ነገር ግን የዮሴፍ ቤት ወታደራዊ ኃይል በእነርሱ ላይ በረቱባቸው፣ ከዚህ የተነሳ ከባድ የጉልበት ስራ እየሰሩ
\v 36 የአሞራውያንም ድንበር በሴላ ካለው ከአቅረቢም ኮረብታ ጀምሮ እስከ ኮረብታማው አገር ድረስ ነው፡፡
\s5
\c 2
\p
\v 1 የእግዚአብሔር መልዓክም ከጌልጌላ ወደ ቦኪም ወጣ፣ እንዲህም አለ፣ “ከግብጽ አወጣኋችሁ፣ ለአባቶቻችሁ ወደማልሁላቸው ምድር አመጣኋችሁ፡፡ እንዲህም አልሁ፣ ‘ከእናንተ ጋር ያለኝን ቃል ኪዳን አላፈርስም፡፡
\v 2 በዚህ ምድር ከሚኖሩ ሰዎች ጋር ቃል ኪዳን አትግቡ፡፡ መሰዊያቸውን ማፍረስ አለባችሁ፡፡’ እናንተ ግን ቃሌን አልሰማችሁም፡፡ ይህ ያደረጋችሁት ምንድን ነው?
\s5
\v 3
አሁንም እላለሁ፣ ‘ከነዓናውያንን ከእናንተ ፊት አላወጣም፣ ነገር ግን እነርሱ የጎን እሾህ ይሆኑባችኋል፣ ጣዖቶቻቸውም ለእናንተ ወጥመድ ይሆናሉ፡፡’”
\v 4 የእግዚአብሔር መልዓክም እነዚህን ቃሎች ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ በተናገረ ጊዜ ሕዝቡ ጮሁ አለቀሱም፡፡
\v 5 ያንንም ቦታ ቦኪም ብለው ጠሩት፡፡ በዚያም ለእግዚአብሔር መስዋዕትን አቀረቡ፡፡
\s5
\v 6
ኢያሱም ሰዎችን ወደ መንገዳቸው በላካቸው ጊዜ፣ የእስራኤል ሕዝብ ምድሩን ለመውሰድና የራሳቸው ለማድረግ ለእንዳንዳቸው ወደተመደበላቸው ቦታ ሄዱ፡፡
\v 7 ኢያሱ በሕይወት በነበረበት ዘመን፣ የእግዚአብሔርን ታላቅ ስራንና ለእስራኤል ምን እንዳደረገም ያዩ ከእርሱ በኋላም በኖሩ ሽማግሌዎች ዘመን ሁሉ ሕዝቡ እግዚአብሔርን አገለገለ፡፡
\v 8 የእግዚአብሔር አገልጋይ፣ የነዌ ልጅ ኢያሱ፣ በመቶ አስር ዓመቱ ሞተ፡፡
\s5
\v 9 እነርሱም በኤፍሬም ኮረብታማው አገር በሰሜናዊው ገአስ ተራራ በምድሪቱ ድንበር በተዘጋጀለት ቦታ በተምናሔሬስ ቀበሩት፡፡
\v 10 ያ ሁሉ ትውልድም ወደ አባቶቻቸው ተሰበሰቡ፡፡ ከእነርሱም በኃላ እግዚአብሔርንና እርሱ ለእስራኤል ያደረገውን ነገር የማያውቅ ሌላ ትውልድ ተነሳ፡፡
\s5
\v 11
የእስራኤል ሕዝብም በእግዚአብሔር ዓይን ክፉ የሆነውን ነገር አደረጉ፣ የበኣል አማልክትንም አመለኩ፡፡
\v 12 ከግብጽ ምድር ያወጣቸውን የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ተዉ፡፡ ሌሎች አማልክትን፣ በዙርያቸው የነበሩ ሕዝቦች አማልክትን ተከተሉ፣ ለእነርሱም ሰገዱ፡፡ እግዚአብሔርንም አስቆጡት ምከንያቱም
\v 13 እግዚአብሔርን ትተዋልና፣ በኣልንና አስታሮትንም አምልከዋልና፡፡
\s5
\v 14
የእግዚአብሔርም ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፣ ንብረታቸውን ለሰረቋቸው ወራሪዎች አሳልፎ ሰጣቸው፡፡ ከእንግዲህ ወዲህ ራሳቸውን ከጠላታቸው መከላከል እንዳይችሉ፣ በዙርያቸው በጠላቶቻቸው ብርታት ተይዘው እንደ ነበሩት ባርያዎች አሳልፎ ሸጣቸው፡፡
\v 15 እስራኤል ለውጊያ በምትሄዱበት ስፍራ ሁሉ፣ ለእነርሱ እንደማለላቸው ይሸነፉ ዘንድ የእግዚአብሔር እጅ በእነርሱ ላይ ይከፋ ነበር፡፡ ከዚህ የተነሳ እነርሱም በጣም ተጨነቁ፡፡
\s5
\v 16 ያን ጊዜ ንብረታቸውን ከሚሰርቋቸው ሰዎች ኃይል ያድናቸው ዘንድ እግዚአብሔር መሳፍንትን አስነሳላቸው፡፡
\v 17 ይሁን እንጂ እነርሱ መሳፍንቶቻቸውን ሊሰሟቸው አልቻሉም፡፡ ለእግዚአብሔር አልታመኑም፣ ራሳቸውንም እንደ አመንዝራዎች ለሌሎች አማልክት ሰጡ፣ አመለኳቸውም፡፡ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ይከተሉ ከነበሩት ከአባቶቻቸው መንገድ ወዲያውኑ ዘወር አሉ፣ እነርሱ ራሳቸው እንደ አባቶቻቸው አላደረጉም፡፡
\s5
\v 18 እግዚአብሔር ለእነርሱ መሳፍንትን ባስነሳላቸው ጊዜ፣ መሳፍንቱ በኖሩበት ዘመን ሁሉ እግዚአብሔር መሳፍንቱን ረዳቸው፣ ከጠላቶቻቸውም ጉልበት ሁሉ አዳናቸው፡፡ በጨቆኗቸውና መከራ ባሳዩአቸው ሰዎች ምክንያት ወደ እርሱ በጮኹ ጊዜ እግዚአብሔር ለእነርሱ አዘነላቸው፡፡
\v 19 ነገር ግን መስፍኑ በሞተ ጊዜ፣ ተመልሰው አባቶቻው ያደርጉ ከነበረውም እጅግ የከፋ ነገር አደረጉ፡፡ ሌሎች አማልክትን በመከተል እነርሱን ያገለግሉና ያመልኩ ነበር፡፡ ክፉ ድርጊታቸውንና እልኸኛ መንገዳቸውንም ለመተው ፈቃደኛ አልነበሩም፡፡
\s5
\v 20 የእግዚአብሔርም ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፣ እንዲህም አለ፣ “ይህ ሕዝብ ለአባቶቻቸው የገባሁትን ቃል ኪዳኔን ስላፈረሱ፣ ድምጼንም ስላልሰሙ
\v 21 ከአሁን በኋላ ኢያሱ ሲሞት ሳያወጣቸው የተዋቸውን አሕዛብ ከፊታቸው አላወጣቸውም፡፡
\v 22 ይህን የማደርገው እስራኤል አባቶቻቸው እንዳደረጉት የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁና በዚያም ይሄዱ እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ እፈትናቸው ዘንድ ነው፡፡”
\v 23 እግዚአብሔርም እነዚያን አሕዛብ የተዋቸው፣ በፍጥነትም ያላስወጣቸው፣ ኢያሱም እንዲያሸንፋቸው ያልፈቀደለት ለዚህ ነው፡፡
\s5
\c 3
\p
\v 1 እግዚአብሔር እነዚህን ሕዝቦች ሳያስወጣ ያስቀራቸው እስራኤልን ይልቁንም ደግሞ በከነዓን በተደረጉት ጦርነቶች ያልተዋጉትን በእስራኤል የሚገኙትን እያንዳንዱ ሰው ይፈትን ዘንድ ነው፡፡
\v 2 (ይህንን ያደረገው ውጊያ የማያውቁትን አዲሱ የእስራኤል ትውልድ ውጊያን ለማስተማር ነው) ፡-
\v 3 አምስቱ የፍልስጤማውያን ነገስታት፣ ከነዓናውያንም ሁሉ፣ ሲዶናውያን እና ከበዓልኤርሞንየም ተራራ እስከ ሐማት መግቢያ ድረስ በሊባኖስ ተራራዎች ይኖሩ የነበሩትም ኤውያውያን ነበሩ፡፡
\s5
\v 4
እነዚህ ሕዝቦች ሳይወጡ እንዲቀሩ የተደረጉት እግዚአብሔር እስራኤልን መፈተኛ እንዲሆኑ ነው፣ እነርሱ ለአባቶቻቸው በሙሴ በኩል የሰጣቸውን ሕግ ይታዘዙና አይታዘዙ እንደሆነ ለማረጋገጥ ነው፡፡
\v 5 ስለዚህ የእስራኤል ሕዝብ በከነዓናውያን፣ ከኬጢያውያን፣ ከአሞራውያን፣ ከፌርዛውያን ከኤውያውያንና ከኢያቡሳውያን ጋር አብረው ኖሩ፡፡
\v 6 ሴት ልጆቻቸውንም ሚስት እንዲሆኗቸው ወሰዷቸው፣ የራሳቸውን ሴት ልጆችም ለወንድ ልጆቻቸው ሰጧቸው፣ አማልክቶቻቸውንም አመለኩ፡፡
\s5
\v 7
የእስራኤል ሕዝብ በእግዚአብሔር ዓይን ጸያፍ የነበረውን ነገር ፈጸሙ፣ አምላካቸው እግዚአብሔርንም ረሱ፡፡ የኣልንና የአስታሮትን አማልክት አመለኩ፡፡
\v 8 ስለዚህም የእግዚአብሔር ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፣ ለመስጶጣምያ ንጉስ ለኩሰርሰቴም እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፡፡ የእስራኤል ሕዝብም ኩሰርሰቴን ለስምንት አመታት አገለገሉ፡፡
\s5
\v 9 የእስራኤል ሕዝብ ወደ እግዚአብሔር በጮሁ ጊዜ፣ እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ ለመርዳት የሚመጣና ካሉበት ሁኔታም የሚያድናቸው ሰው አስነሳ፡- ይህም ሰው የካሌብ ታናሽ ወንድም የቄኔዝ ልጅ ጎቶንያል ነበር፡፡
\v 10 የእግዚአብሔር መንፈስም አበረታው፣ እስራኤላውያን ላይም ይፈርድ ነበር፣ ወደ ውጊያም ይወጣ ነበር፡፡ እግዚአብሔርም በመስጶጣምያ ንጉስ በኩሰርሰቴ ላይ ድልን ሰጠው፡፡ ኩሰርሰቴንም ያሸነፈው የጎቶንያል እጅ ነበር፡፡
\v 11 ምድሪም ለአርባ ዓመት ሰላም አገኘች፡፡ የቄኔዝ ልጅ ጎቶንያልም ሞተ፡፡
\s5
\v 12 የእስራኤልም ሕዝብ ክፉ ነገሮችን በማድረግ ደግመው እግዚአብሔርን ሳይታዘዙ ቀሩ፣ እርሱም ምን እንዳደረጉ ተመለከተ፡፡ ስለዚህ እስራኤል ክፉ ነገሮችን ስላደረጉና፣ እግዚአብሔርም ስላያቸው የሞኣብ ንጉስ ኤግሎም እስራኤልን ለመውጋት በመጣ ጊዜ እግዚአብሔር ብርታትን ሰጠው፡፡
\v 13 ኤግሎምም ከአሞንና ከአማሌቃውያን ጋር ተባበረ፣ እነርሱም ሄዱ እስራኤልንም አሸነፉ፣ ከዚያም የዘንባባ ከተማን ተቆጣጠሩ፡፡
\v 14 የእስራኤልም ሕዝብ የሞኣብን ንጉስ ኤግሎምን ለአስራ ስምንት አመታት አገለገሉ፡፡
\s5
\v 15 ነገር ግን የእስራኤል ሕዝብ ወደ እግዚአብሔር በጮሁ ጊዜ፣ እግዚአብሔር የሚረዳቸውን ሰው አስነሳ፣ ይህም ግራኝ የነበረው ብንያማዊው የጌራን ልጅ ናኦድ ነው፡፡ የእስራኤልም ሕዝብ እርሱን ወደ ሞኣብ ንጉስ ወደ ኤግሎም የሚከፍሉትን ግብር አስይዘው ላኩት፡፡
\s5
\v 16 ናኦድ በሁለት በኩል የተሳለ ርዝመቱ አንድ ክንድ የሆነ ሰይፍን ሰራ፤ ከልብሱም በታች በቀኝ ጭኑ አሰረው፡፡
\v 17 ግብሩንም ለሞኣብ ንጉስ ለኤግሎም ሰጠው፡፡ (ኤግሎም በዚያን ጊዜ እጅግ ወፍራም ሰው ነበር፡፡)
\v 18 ናኦድም የግብሩን ክፍያ ካቀረበ በኋላ፣ ግብሩን ተሸክመው ገብተው ከነበሩ ሰዎች ጋር ወጣ፡፡
\s5
\v 19 ይሁን እንጂ ናኦድ በጌልጌላ አጠገብ የተቀረጹ ምስሎች ተሰርተውበት ወደነበረው ስፍራ ሲደርስ ተመልሶ ሄደና እንዲህ አለ፡- “ንጉስ ሆይ፣ ለአንተ የሚስጥር መልዕክት አለኝ፡፡” ኤግሎምም እንዲህ አለ፡- “ጸጥታ! ” ስለዚህም አገልጋዮቹ ሁሉ ክፍሉን ትተው ወጡ፡፡
\v 20 ናኦድም ወደ እርሱ መጣ፡፡ ንጉሱም ቀዝቃዛ በሆነው ሰገነት ላይ ብቻውን ተቀምጦ ነበር፡፡ናኦድም እንዲህ አለ፣ “ለአንተ ከእግዚአብሔር የመጣ መልዕክት አለኝ፡፡” ንጉሱም ከመቀመጫው ተነሳ፡፡
\s5
\v 21 ናኦድም ግራ እጁን ዘረጋና ሰይፉን ከቀኝ ጭኑ አወጣ፣ ሰይፉንም በንጉሱ ሰውነት ውስጥ ሰካው፡፡
\v 22 የሰይፉም እጀታ ከስለቱ ጋር ወደ ሰውነቱ ገባ፣ ጫፉም በጀርባው ወጣ፣ ሞራም ስለቱን ሸፈነው፣ ናኦድም ሰይፉን ከንጉሱ ሰውነት አላወጣውም፡፡
\v 23 ከዚያም ናዖድ ወደ በረንዳው ወጣና የሰገነቱን በር በንጉሱ ላይ ዘግቶ ቈለፈው፡፡
\s5
\v 24 ናዖድም ከሄደ በኋላ፣ የንጉሱ ባሪያዎች መጡ፤ የሰገነቱም ደጅ ተቈልፎ አዩ፣ ስለዚህ እንዲህ ሲሉ አሰቡ፣ “ምናልባት በቀዝቃዛው ሰገነት ውስጥ እየተጸዳዳ ይሆናል፡፡”
\v 25 ንጉሱ የሰገነቱን በር ሳይከፍት በቆየም ጊዜ ስራቸውን ችላ እንዳሉ እስኪሰማቸው ድረስ ስጋት እያደረባቸው ጠበቁ፡፡ ስለዚህ ቁልፉን ወሰዱና በሮቹን ከፈቱ፣ እነሆም ጌታቸው ተጋድሞ፣ በወለሉም ላይ ወድቆ፣ ሞቶም አገኙት፡፡
\s5
\v 26 ባርያዎቹ ምን ማድረግ እንዳለባቸው እያሰቡ ሲጠባበቁ፣ ናዖድ አመለጠ፣ የጣኦታት ምስል በተቀረጸበት ስፍራ በኩል አለፈ፣ ወደ ቤይሮታም አመለጠ፡፡
\v 27 በደረሰም ጊዜ፣ በኮረብታማው በኤፍሬም አገር ቀንደ መለከት ነፋ፡፡ ከዚያም የእስራኤል ሕዝብ ከእርሱ ጋር ከኮረብታማው አገር ወረዱ፣ እርሱም ይመራቸው ነበር፡፡
\s5
\v 28
እርሱም እንዲህ አላቸው፣ “ተከተሉኝ፣ እግዚአብሔር ጠላቶቻችሁን፣ ሞዓባውያንን በእጃችሁ አሳልፎ ሰጥቶአልና፡፡” እነርሱም ተከትለውት ወረዱና የዮርዳኖስን መሻገርያ ከሞዓባውያን ቀምተው ያዙ፣ እነርሱም ማንም ሰው ወንዙን እንዳይሻገር ከለከሉ፡፡
\v 29 በዚያን ጊዜም ከሞዓብ አሥር ሺህ የሚሆኑ ሰዎችን ገደሉ፣ የተገደሉትም ሁሉ ጠንካራና ኃይለኛ ሰዎች ነበሩ፡፡ አንድም እንኳ አላመለጠም፡፡
\v 30 በዚያም ቀን ሞዓብ በእስራኤል ብርታት ድል ሆነች፡፡ ምድሪቱም ለሰማንያ ዓመት ዐረፈች፡፡
\s5
\v 31 ከናኦድ በኋላ የተነሳው መስፍን ስድስት መቶ የፍልስጥኤም ሰዎችን በበሬ መንጃ የገደለው የዓናት ልጅ ሰሜጋር ነበር፡፡ እርሱም ደግሞ እስራኤልን ከአደጋ አዳነ፡፡
\s5
\c 4
\p
\v 1 ናዖድም ከሞተ በኋላ፣ የእስራኤል ሕዝብ ክፉ ነገሮችን በመስራት እንደገና እግዚአብሔርን አልታዘዙም፣ እርሱም ምን እንዳደረጉ ተመለከተ፡፡
\v 2 እግዚአብሔርም በሐጾር ሆኖ ይገዛ በነበረው፣ በከነዓን ንጉሥ በኢያቢስ እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፡፡ የሠራዊቱም አለቃ ሲሣራ ተብሎ ይጠራ ነበር፣ እርሱም የአሕዛብ በሆነችው በአሪሶት ኖረ፡፡
\v 3 የእስራኤልም ሕዝብ ለእርዳታ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፣ ምክንያቱም ሲሳራ ዘጠኝ መቶ የብረት ሰረገሎች ነበሩት፣ እርሱም የእስራኤልን ሕዝብ ለሀያ ዓመት በኃይል አስጨንቆ ገዛቸው፡፡
\s5
\v 4 በዚያ ጊዜ ነቢይቱ የለፊዶት ሚስት ዲቦራ፣ በእስራኤል ላይ ዋነኛ ፈራጅ ነበረች፡፡
\v 5 እርስዋም በኮረብታማው በኤፍሬም አገር በራማና በቤቴል መካከል ካለው የዲቦራ ዘንባባ ዛፍ ስር ትቀመጥ ነበር፣ የእስራኤልም ሕዝብ ለክርክራቸው መፍትሔ ለማግኘት ወደ እርስዋ ይመጡ ነበር፡፡
\s5
\v 6 እርስዋም በንፍታሌም ውስጥ ካለው ከቃዴስ የአቢኒኤምን ልጅ ባርቅን ጠራች፡፡ እንዲህም አለችው፣ “የእስራኤል አምላክ፣ እግዚአብሔር፣ እንዲህ ይልሃል፣ ‘ወደ ታቦር ተራራ ሂድ፣ ከንፍታሌምና ከዛብሎን አሥር ሺህ ሰዎች ከአንተ ጋር ውሰድ፡፡
\v 7 እኔ የኢያቢስን ሠራዊት አዛዥ ሲሣራን በቂሶን ወንዝ አቅራቢያ ከሰረገሎቹና ከሰራዊቱ ጋር እንዲያገኝህ አስወጣዋለሁ፣ እኔም በእርሱ ላይ ድልን እሰጥሃለሁ፡፡’”
\s5
\v 8-9 ባርቅም እንዲህ አላት፣ “አንቺ ከእኔ ጋር ከሄድሽ እኔም እሄዳለሁ፣ ነገር ግን አንቺ ከእኔ ጋር ካልሄድሽ እኔም አልሄድም፡፡” እርስዋም እንዲህ አለች፣ “በእውነት ከአንተ ጋር እሄዳለሁ፡፡ ይሁን እንጂ፣ አንተ የምትሄድበት መንገድ ወደ ክብር አያደርስህም፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር ሲሣራን በጥንካሬዋ ድል ታደርገው ዘንድ ለሴት አሳልፎ ይሰጣልና፡፡” ከዚያም ዲቦራ ተነሥታ ከባርቅ ጋር ወደ ቃዴስ ሄደች፡፡
\s5
\v 10
ባርቅም የዛብሎንና የንፍታሌም ሰዎች በአንድነት ወደ ቃዴስ እንዲመጡ ጠራቸው፡፡ አሥር ሺህም ሰዎች ተከተሉት፣ ዲቦራም ከእርሱ ጋር ሄደች፡፡
\s5
\v 11
ቄናዊው ሔቤርም ከቄናውያን ራሱን ለየ፣ እነርሱም የሙሴ አማት የኦባብ ልጆች ነበሩ፣ እርሱም በቃዴስ አጠገብ በጻዕናይም በነበረው በበሉጥ ዛፍ ጥግ ድንኳኑን ተከለ፡፡
\s5
\v 12 ለሲሳራም የአቢኔኤም ልጅ ባርቅ ወደ ታቦር ተራራ እንደወጣ በነገሩት ጊዜ፣
\v 13 ሲሣራም ሰረገሎቹን ሁሉ፣ ዘጠኝ መቶ የብረት ሰረገሎች፣ ከእርሱም ጋር የነበሩትን ወታደሮቹን ሁሉ፣ የአሕዛብ ከሆነችው ከአሪሶት ወደ ቂሶን ወንዝ ሰበሰባቸው፡፡
\s5
\v 14 ዲቦራም ባርቅን እንዲህ አለችው፣ “ሂድ! ዛሬ እግዚአብሔር በሲሣራ ላይ ድል እንድታደርግ በእጅህ አሳልፎ የሚሰጥበት ቀን ነውና፡፡ እነሆ እግዚአብሔር ከፊትህ አልወጣምን? ” ስለዚህ ባርቅ ከታቦር ተራራ አብረውት ከነበሩት አስር ሺህ ሰዎች ጋር ወረደ፡፡
\s5
\v 15 እግዚአብሔርም የሲሣራን ሰራዊት ግራ አጋባ፣ ሰረገሎቹንም ሁሉ፣ ሠራዊቱንም ሁሉ፣ የባርቅም ሰዎች የሲሳራን ሰዎች አጠቋቸው፣ ሲሳራም ከሰረገላው ወርዶ በእግሩ ሸሸ፡፡
\v 16 ባርቅ ግን ሰረገሎችንና ሠራዊቱን እስከ አሪሶት ድረስ አባረራቸው፣ የሲሣራም ሠራዊት ሁሉ በሰይፍ ስለት ተገደሉ፣ አንድ ሰው እንኳ አልቀረም፡፡
\s5
\v 17 ሲሳራ ግን በእግሩ ወደ ቄናዊው ሔቤር ሚስት፣ ወደ ኢያዔል ድንኳን ሸሸ፣ ምክንያቱም በሐሶር ንጉስ በኢያቢስና፣ በቄናዊው በሔቤር ቤት መካከል ሰላም ስለነበር ነው፡፡
\v 18 ኢያዔልም ሲሣራን ለመገናኘት ወጣች እንዲህም አለችው፣ “ግባ፣ ጌታዬ ሆይ፤ ወደ እኔ ግባ አትፍራም፡፡” እርሱም ወደ እርስዋ ወደ ድንኳንዋ ገባ፣ በብርድ ልብስም ሸፈነችው፡፡
\s5
\v 19 እርሱም እንዲህ አላት፣ “ጠምቶኛልና፣ እባክሽ የምጠጣው ጥቂት ውኃ ስጭኝ፡፡” እርስዋም ከቆዳ የተሰራ የወተቱን ማስቀመጫ ከፍታ የሚጠጣ ሰጠችው፣ ከዚያም እንደገና ሸፈነችው፡፡
\v 20 እርሱም አላት፣ “በድንኳኑ በር ላይ ቁሚ፡፡ ሰውም ቢመጣና ‘በዚህ ሰው አለን? ብሎ ቢጠይቅሽ ‘የለም’ በይ፡፡”
\s5
\v 21
ከዚያም የሔቤር ሚስት ኢያዔል የድንኳን ካስማ ወሰደች በእጅዋም መዶሻ ያዘች በቀስታ ወደ እርሱ ሄደች፣ እርሱም በከባድ እንቅልፍ ላይ ነበር፣ እርስዋም ካስማውን በጆሮ ግንዱ ላይ ሰካችው፣ ካስማውም ሰውነቱን ወግቶ አለፈና ወደ መሬት ጠለቀ፡፡ እርሱም ሞተ፡፡
\v 22 ባርቅም ሲሣራን ሲያባርር፣ ኢያዔል ልታገኘው ወጣችና እንዲህ አለችው፣ “ና፣ የምትፈልገውንም ሰው አሳይሃለሁ፡፡” እርሱም ወደ ውስጥ ከእርስዋ ጋር ገባ፣ እነሆም በዚያ ሲሣራ ሞቶ ተጋድሞ ነበር፣ ካስማውም በጆሮ ግንዱ ውስጥ ተሰክቶ አገኘው፡፡”
\s5
\v 23 ስለዚህ በዚያ ቀን እግዚአብሔር የከነዓንን ንገሥ ኢያቢስን በእስራኤል ሕዝብ ፊት አሸነፈው፡፡
\v 24 የእስራኤል ሕዝብ ጉልበት የከነዓን ንጉሥ ኢያቢስን እስከሚያጠፉ ድረስ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየበረታ መጣ፡፡
\s5
\c 5
\p
\v 1 በዚያም ቀን ዲቦራና የአቢኒኤም ልጅ ባርቅ ይህንን መዝሙር ዘመሩ፡-
\v 2 “በእስራኤል ውስጥ መሪዎች የመሪነት ስፍራውን ሲይዙ፣ ሕዝቡም በደስታና በፈቃዳቸው ለጦርነት ሲወጡ፣ እግዚአብሔርን እናመሰግናለን!
\s5
\v 3
ስሙ፣ እናንተ ነገሥታት! አድምጡ፣ እናንተም መኳንንት! እኔ፣ እኔ ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ፤ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ምስጋናን እዘምራለሁ፡፡
\v 4 እግዚአብሔር ሆይ፣ ከሴይር በወጣህ ጊዜ፣ ከኤዶምያስም በተነሳህ ጊዜ፣ ምድር ተናወጠች፣ ሰማያት ደግሞ ተንቀጠቀጡ፤ ደመናትም ደግሞ ውኃን አንጠባጠቡ፡፡
\s5
\v 5 ተራሮች በእግዚአብሔር ፊት ተንቀጠቀጡ፤ ሲና ተራራም እንኳ በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ፊት ተንቀጠቀጠ፡፡
\v 6 በዓናት ልጅ በሰሜጋር ዘመን፣ በኢያዔል ዘመን፣ መንገዶች ተተዉ፣ መንገደኞችም በጠመዝማዛ መንገድ ብቻ ይጠቀሙ ነበር፡፡
\s5
\v 7 እኔ ዲቦራ አለቃ እስከሆንሁበት ጊዜ ድረስ፣ ለእስራኤል እናት ሆኜ አለቅነትን እስከወሰድሁበት ጊዜ ድረስ፣ በእስራኤል ውስጥ ገበሬዎች አልነበሩም፡፡
\v 8 አዲስ አማልክትን መረጡ፣ በከተማዋ ደጆች ጦርነት ነበረ፤ በእስራኤል ውስጥ በአርባ ሺህ መካከል ጋሻ ወይም ጦር አልታየም፡፡
\s5
\v 9 ልቤ ወደ እስራኤል አለቆች ሄደ፣ በሕዝቡ መካከል ራሳቸውን በደስታ ስለ ሰጡትም እግዚአብሔርን እናመሰግናለን፡፡
\v 10 እናንተ በነጫጭ አህዮች ላይ ትንሽ የምንጣፍ ኮርቻ ላይ ተቀምጣችሁ የምትጓዙ፣ በመንገድም የምትሄዱ እናንተ ስለዚህ ነገር አስቡ፡፡
\s5
\v 11 በማጠጫው ስፍራ መካከል ሆነው በጎችን የሚከፋፍሉትን ሰዎች ድምጽ ስሙ፡፡ የእግዚአብሔርን የጽድቅ ድርጊትና ተዋጊዎቹ በእስራኤል ውስጥ የሰሩትን የጽድቅ ተግባር በዚያ እንደገና እየተናገሩ ነው፡፡ ያን ጊዜ የእግዚአብሔር ሕዝብ ወደ ከተማው በሮች ወረዱ፡፡
\s5
\v 12
ንቂ፣ ንቂ፣ ዲቦራ ሆይ! ንቂ፣ ንቂ፣ መዝሙርን ዘምሪ! ባርቅ ሆይ፣ ተነሣ፣ የአቢኒኤም ልጅ ሆይ፣ ምርኮኞችህን ማርከህ ውሰድ፡፡
\v 13 የዚያን ጊዜ የተረፉት ወደ ኃያላኑ መጡ፣ ከተዋጊዎቹም መካከል የእግዚአብሔር ሕዝብ ወደ እኔ መጡ፡፡
\s5
\v 14
መሰረታቸው ከአማሌቅ ወገን የሆኑ ከኤፍሬም መጡ፤ የብንያም ሕዝብም ተከተሉህ፡፡ ከማኪርም አዛዦች ወረዱ፣ የስልጣን በትር የያዙ ከዛብሎን ወረዱ፡፡
\s5
\v 15
የይሳኮርም መሳፍንት ከዲቦራ ጋር ነበሩ፤ ይሳኮርም ከባርቅ ጋር በትዕዛዙ መሰረት ከኋላው እየተከተለ ወደ ሸለቆው ሄደ፡፡ በሮቤል ጎሳ መካከል ታላቅ የልብ ምርምር ነበረ፡፡
\s5
\v 16 የበጎች እረኞች ለመንጎቻቸው በፉጨት ሲጫወቱ እያዳመጥህ በእሳት ማንደጃ መካከል ለምን ተቀመጥህ? በሮቤል ጎሳ መካከል ታላቅ የልብ ምርምር ነበረ፡፡
\s5
\v 17
ገለዓድ በዮርዳኖስ ማዶ ተቀመጠ፤ ዳን ለምን በመርከብ ውስጥ ቀረ? አሴርም በባሕሩ ዳርቻ ቀረ፣ በወንዞቹም ዳርቻ ኖረ፡፡
\v 18 ዛብሎን ነፍሱን ወደ ሞት አሳልፎ የሚሰጥ ሕዝብ ነው፣ ንፍታሌምም በውጊያ ሜዳ ላይ ነው፡፡
\s5
\v 19
ነገሥታት መጡ ተዋጉም፣ የዚያን ጊዜ የከነዓን ነገስታትም በመጊዶ ውኆች አጠገብ በታዕናክ ተዋጉ፡፡ ምንም የብር ምርኮ አልወሰዱም፡፡
\v 20 ከሰማይ ከዋክብት ተዋጉ፣ በሰማያት ላይ በአካሄዳቸውም ሲሣራን ተዋጉት፡፡
\s5
\v 21 ከዱሮ ጀምሮ የታወቀው፣ የቂሶን ወንዝም፣ ጠርጎ ወሰዳቸው፡፡ ነፍሴ ሆይ ገስግሺ፣ በርቺ!
\v 22 የፈረሶች የግልብያ ኮቴዎች ድምጽ፣ የኃያላኑ ግልቢያ ድምጽም፡፡
\s5
\v 23 የእግዚአብሔር መልአክ “ሜሮዝን እርገሙ! ” ይላል፡፡ ‘ነዋሪዎቿን ፈጽማችሁ እርገሙ! ምክንያቱም እግዚአብሔርን ለመርዳት አልመጡም፣ ከኃያላን ጦረኞች ጋር በተደረገው ውጊያ እግዚአብሔርን ለመርዳት አልመጡምና፡፡'
\s5
\v 24 የቄናዊው የሔቤር ሚስት፣ ኢያዔል፣ ከሴቶች ሁሉ ይልቅ የተባረከች ናት፣ በድንኳን ውስጥ ከሚኖሩ ሴቶች ሁሉ ይልቅ የተባረከች ናት፡፡
\v 25 ሰውየው ውኃ ለመናት፣ እርስዋም ወተት ሰጠችው፤ ለመሳፍንት በሚሆን በተከበረ ሳህን ቅቤ አመጣችለት፡፡
\s5
\v 26 እጅዋን ወደ ድንኳን ካስማ፣ ቀኝ እጅዋንም ወደ ሠራተኛ መዶሻ አደረገች፤ በመዶሻውም ሲሣራን መታች፣ ራሱንም ቀጠቀጠች፡፡ ጆሮ ግንዱን በወጋችው ጊዜ ጭንቅላቱንም ፈረከሰችው፡፡
\v 27 በእግሮችዋ መካከል ተደፋ፣ ወደቀ ተኛም፡፡ በእግሮችዋ አጠገብ ተሰብሮ ወደቀ፡፡ የተደፋበት ስፍራ በክፉ ሁኔታ የሞተበት ነው፡፡
\s5
\v 28 ከመስኮት ሆና ወደ ውጭ ተመለከተች፣ የሲሣራ እናት በርብራብ በኩል በኃዘን ወደ ውጭ ጮኸች፣ ‘ወደዚህ ለመምጣት ሰረገላው ረዥም ጊዜ ለምን ወሰደበት? ለምንስ ሰረገላዎቹን የሚጎትቱት የፈረሶቹ ኮቴዎች ዘገየ?
\s5
\v 29 ብልሃተኞች ልዕልቶቿም መለሱላት፣ ለራስዋም ተመሳሳይ መልስ መለሰች፡-
\v 30 ምርኮውን አግኝተው ተካፍለው የለምን? ለእያንዳንዱ ሰው ምርኮ አንዲት ወይም ሁለት ልጃገረድ፤ ለሲሣራ ምርኮ ልዩ ልዩ ቀለም ያለው ልብስ፣ የተጠለፈ ባለቀለም ጨርቅ ምርኮ፣ ለማረኩ ሰዎች ለአንገታቸው የሚሆን በሁለት እጥፍ የተጠለፈ ባለቀለም ጨርቆች ምርኮን አላገኙምን?
\s5
\v 31
ስለዚህ፣ እግዚአብሔር ሆይ፣ ጠላቶችህ ሁሉ እንዲሁ ይጥፉ! ነገር ግን እርሱን የሚወዱት በኃይል እንደሚወጣ ጸሐይ ይሁኑ፡፡” ምድሪቱም ለአርባ ዓመት ያህል ዐረፈች፡፡
\s5
\c 6
\p
\v 1 የእስራኤልም ሕዝብ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ የሆነውን ሥራ ሠሩ፤ እርሱም በምድያም ቁጥጥር ስር እንዲሆኑ ለሰባት ዓመት አሳልፎ ሰጣቸው፡፡
\v 2 የምድያምም ኃይል በእስራኤል ላይ በረታ፡፡ ከምድያምም የተነሣ የእስራኤል ሕዝብ በኮረብታዎች ላይ ጕድጓድ፣ ዋሻና ምሽግም ለራሳቸው መሸሸጊያ አበጁ።
\s5
\v 3 እንዲህም ሆነ፣ እስራኤል ዘር በዘሩ ጊዜ ምድያማውያን፣ አማሌቃውያንና ከምሥራቅም የመጡ ሰዎች እስራኤላውያንን ያጠቁ ነበር፡፡
\v 4 ሰራዊታቸውን በምድሪቱ ላይ ያሰፍሩና እስከ ጋዛ ድረስ ያለውን ሰብል ያጠፉ ነበር፡፡ በእስራኤልም ምንም መብል፣ በጎች፣ ከብቶችና አህያዎች አይተዉም ነበር፡፡
\s5
\v 5
እነርሱ እንስሶቻቸውንና ድንኳኖቻቸውን ይዘው ሲመጡ እንደ አንበጣ መንጋ ሆነው ይመጡ ነበር፤ እነርሱንና ግመሎቻቸውንም መቁጠር አይቻልም ነበር፡፡ ምድሪቱንም ያጠፉ ዘንድ ይወርሩአት ነበር፡፡
\v 6 ምድያም እስራኤልን ክፉኛ ከማዳከማቸው የተነሣ የእስራኤል ሕዝብ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፡፡
\s5
\v 7 የእስራኤል ሕዝብ በምድያም ምክንያት ወደ እግዚአብሔር በጮኹ ጊዜ፣
\v 8 እግዚአብሔር ወደ እስራኤል ልጆች ነቢይ ላከ፡፡ ነቢዩም እንዲህ አለ፡- “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡- ‘እኔ ከግብፅ ምድር አወጣኋችሁ፤ ከባርነትም ቤት አወጣኋችሁ፡፡
\s5
\v 9 ከግብፃውያንም እጅ እንደዚሁም ይጨቁኑአችሁ ከነበሩ ኃይላት ሁሉ አዳንኋችሁ፡፡ ከፊታችሁም አሳድጄ አወጣኋቸው፣ ምድራቸውንም ሰጠኋችሁ፡፡
\v 10 ለእናንተንም እንዲህ አልኋችሁ፣ “እኔ አምላካችሁ እግዚአብሔር ነኝ፤ በምድራቸው የተቀመጣችሁባቸውን፣ የአሞራያውያንን አማልክት እንዳታመልኩ አዘዝኋችሁ፡፡ ነገር ግን እናንተ ድምጼን አልታዘዛችሁም፡፡
\s5
\v 11 የእግዚአብሔርም መልአክ መጣና በዖፍራ ባለችው ለአቢዔዝራዊው ለኢዮአስ በነበረችው ከበሉጥ ዛፍ በታች ተቀመጠ፤ የኢዮአስም ልጅ ጌዴዎን ከምድያማውያን ለመሸሸግ በወይን መጥመቂያው ውስጥ ስንዴ ይወቃ ነበር፡፡
\v 12 የእግዚአብሔርም መልአክ ለእርሱ ተገልጠለትና እንዲህ አለው፣ “አንተ ብርቱ ተዋጊ ሰው፣ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው አለው!”
\s5
\v 13 ጌዴዎንም ለእርሱ እንዲህ አለው፣ “ጌታዬ ሆይ፣ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ፣ ይህ ነገር ሁሉ ለምን በእኛ ላይ ደረሰብን? አባቶቻችንስ የነገሩን እርሱ የሰራቸው አስደናቂ ነገሮች ወዴት አሉ፣ እንዲህ ብለው የነገሩን፣ ‘እግዚአብሔር ከግብፅ አላወጣንምን? አሁን ግን እግዚአብሔር ትቶናል፣ ለምድያማውያንም ብርታት አሳልፎ ሰጥቶናል፡፡
\s5
\v 14
እግዚአብሔርም ወደ እርሱ ተመለከተና እንዲህ አለው፣ “በዚህ ባለህ ብርታት ሂድ፡፡ እስራኤልንም ከምድያም ኃይል አድን፤ እነሆ እኔ አልላክሁህምን? ”
\v 15 ጌዴዎንም እንዲህ አለው፣ “ጌታ ሆይ፣ እባክህ፣ እኔ እስራኤልን እንዴት ማዳን እችላለሁ? ተመልከት፣ የእኔ ቤተሰብ ከምናሴ ነገድ ከሁሉ ይልቅ ደካማ ነው፣ እኔም በአባቴ ቤት ውስጥ የመጨረሻ ነኝ፡፡
\s5
\v 16
እግዚአብሔርም፣ “እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፣ አንተም የምድያምን ሰራዊት በሙሉ ታሸንፋለህ” አለው፡፡
\v 17 ጌዴዎንም እንዲህ አለው፣ “በእኔ ደስተኛ ከሆንህ፣ የምትናገረኝ አንተ እንደሆንህ እርግጠኛ እሆን ዘንድ ምልከትን ስጠኝ፡፡
\v 18 ወደ አንተ እስክመጣና መስዋእቴን አምጥቼ በፊትህ እስካቀርብ ድረስ እባክህ ከዚህ አትሂድ፡፡” እግዚአብሔርም “እስክትመለስ ድረስ እቆያለሁ” አለ፡፡
\s5
\v 19
ጌዴዎን ሄደ የፍየሉንም ጠቦት አረደ፣ የኢፍ መስፈሪያም ዱቄት ወስዶ ያልቦካ ቂጣ አዘጋጀ፡፡ ሥጋውን በቅርጫት አኖረ፣ መረቁንም በምንቸት ውስጥ አኖረ፣ ሁሉንም ይዞ በበሉጥ ዛፍ በታች አቀረበለት፡፡
\v 20 የእግዚአብሔርም መልአክ እንዲህ አለው፣ “ሥጋውንና ያልቦካውን ቂጣ ውሰድና በዚህ ድንጋይ ላይ አኑረው፣ መረቁንም በላዩ ላይ አፍስሰው፡፡” ጌዴዎንም እንዲሁ አደረገ፡፡
\s5
\v 21
የእግዚአብሔርም መልአክ በእጁ የያዘውን የበትሩን ጫፍ ወደዚያ ዘረጋ፡፡ በበትሩም ሥጋውንና ያልቦካውን ቂጣ ነካው፤ እሳትም ከድንጋዩ ውስጥ ወጥቶ ሥጋውንና ያልቦካውን ቂጣ በላ፡፡ የእግዚአብሔርም መልአክ ሄደ፣ ጌዴዎንም ሊያየው አልቻለም፡፡
\s5
\v 22
ጌዴዎንም የእግዚአብሔር መልአክ እንደ ሆነ አወቀ፡፡ ጌዴዎንም፣ “አምላኬ እግዚአብሔር ሆይ፣ ወዮልኝ! የእግዚአብሔርን መልአክ ፊት ለፊት አይቻለሁና” አለ፡፡
\v 23 እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፣ “ሰላም ለአንተ ይሁን! አትፍራ፣ አትሞትም፡፡”
\v 24 ስለዚህ ጌዴዎን በዚያ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፡፡ ስሙንም፣ እግዚአብሔር ሰላም ብሎ ጠራው፡፡ እስከ ዛሬ ድረስ በአቢዔዝራውያን ጎሳ በምትሆነው በዖፍራ አለ፡፡
\s5
\v 25 እግዚአብሔርም በዚያች ሌሊት እንዲህ አለው፣ “የአባትህን በሬ፣ ሰባት ዓመት የሆነውን ሁለተኛውንም በሬ ውሰድ፣ የአባትህ የሆነውን የበኣል መሠዊያ አፍርስና በአጠገቡ ያለውን አሼራን ሰባብረው፡፡
\v 26 በዚህ መሸሸጊያ ስፍራ ጫፍ ላይ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሥራ፣ በትክክለኛው መንገድም ስራው፡፡ ከአሼራ ሰባብረህ በጣልኸው እንጨት ሁለተኛውን በሬ የሚቃጠል መስዋእት አድርገህ አቅርበው፡፡”
\s5
\v 27
ስለዚህ ጌዴዎን ከባሪያዎቹ አሥር ሰዎችን ወሰደና እግዚአብሔር እንደነገረው አደረገ፡፡ ነገር ግን በቀን ለማድረግ የአባቱን ቤተ ሰቦችና የከተማውንም ሰዎች እጅግ በጣም ስለፈራ፣ በሌሊት አደረገው፡፡
\s5
\v 28 በማለዳ የከተማው ሰዎች በተነሱ ጊዜ፣ የበኣል መሠዊያ ፈርሶ ነበር፣ በአጠገቡ የነበረውም አሼራ ተሰባብሮ ነበር፣ ሁለተኛውም በሬ አዲስ በተሰራው መሠዊያ ላይ ተሠውቶ ነበር፡፡
\v 29 የከተማውም ሰዎች እርስ በርሳቸው፣ “ይህን ያደረገው ማን ነው? ” ተባባሉ፡፡ ከሌሎች ጋር ሲነጋገሩና መልስ ሲፈልጉ ሳሉ፣ “ይህን ያደረገው የኢዮአስ ልጅ ጌዴዎን ነው” አሉ፡፡
\s5
\v 30 የዚያን ጊዜ የከተማው ሰዎች ኢዮአስን እንዲህ አሉት፣ “የበኣልን መሠዊያ አፍርሶአልና፣ በአጠገቡ የነበረውንም አሼራ ሰባብሮታልና እንዲሞት ልጅህን አውጣ፡፡”
\s5
\v 31
ኢዮአስም ለተቃወሙት በሙሉ እንዲህ አላቸው፣ “ለበኣል ትምዋገቱለታላችሁን? እርሱን ታድኑታላችሁን? ለእርሱ የሚምዋገትለት ሁሉ እስከ ነገ ጠዋት ይገደል፡፡ በኣል አምላክ ከሆነ፣ መሠዊያውን ሲያፈርሱበት ራሱን ይከላከል፡፡
\v 32 ስለዚህም በዚያ ቀን ጌዴዎን “ይሩበኣል” የሚል ስም ተሰጠው፣ ምክንያቱም እርሱ “በኣል ራሱን ይከላከል” ብሏልና፣ ጌዴዎን መሠዊያውን አፍርሶአልና፡፡
\s5
\v 33
ምድያማውያንና አማሌቃውያን ሁሉ፣ የምሥራቅም ሰዎች አንድ ላይ ተሰበሰቡ፡፡ ዮርዳኖስን ተሻግረው በኢይዝራኤል ሸለቆ ውስጥ ሰፈሩ፡፡
\s5
\v 34
ነገር ግን የእግዚአብሔር መንፈስ ጌዴዎንን ሊረዳው በእርሱ ላይ ወረደ፡፡ ጌዴዎንም ቀንደ መለከት ነፋ፣ የአቢዔዝር ጎሳ ሰዎች ይከተሉት ዘንድ ጠራቸው፡፡
\v 35 እርሱም ወደ ምናሴ ነገድ ሁሉ መልክተኞችን ሰደደ፣ እነርሱም ደግሞ እንዲከተሉት ተጠርተው ነበር፡፡ መልክተኞችንም ወደ አሴር፣ ዛብሎንና ንፍታሌምም ላከ፣ እነርሱም እርሱን ሊየገኙት ሄዱ፡፡
\s5
\v 36
ጌዴዎንም እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፣ “እንደ ተናገርኸው እስራኤልን ለማዳን እኔን የምትጠቀምብኝ ከሆነ
\v 37 ተመልከት፣ በአውድማው ላይ የበግ ጠጕር ባዘቶ አኖራለሁ፡፡ በጠጕሩ ብቻ ላይ ጠል ቢሆንና በምድሩም ሁሉ ደረቅ ቢሆን፣ የዚያን ጊዜ እንደተናገርኸው አንተ እስራኤልን ለማዳን እንደምትጠቀምብኝ አውቃለሁ፡፡”
\s5
\v 38
እንዲሁም ሆነ፣ ጌዴዎን በነጋው ማልዶ ተነሣ፣ ጠጕሩንም በአንድ ላይ ጨመቀው፣ ከጠጕሩም የተጨመቀው ጠል አንድ ቆሬ ለመሙላት በቂ ሆነ፡፡
\s5
\v 39 ጌዴዎንም እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፣ “አትቈጣኝ፣ አንድ ጊዜ እንደገና እናገራለሁ፡፡ እባክህ፣ የጠጉሩ ባዘቶ በመጠቀም አንድ ተጨማሪ ሙከራ እንዳደርግ ፍቀድልኝ፡፡ በዚህ ጊዜ ጠጕሩ ብቻ ደረቅ ይሁን፣ በምድሩና በዙርያውም ሁሉ ላይ ደግሞ ጠል ይሁን፡፡”
\v 40 እግዚአብሔርም በዚያ ሌሊት የጠየቀውን አደረገ፡፡ ጠጕሩ ደረቅ ነበረ፣ በምድሩም ሁሉ ላይ ጠል ነበረ፡፡
\s5
\c 7
\p
\v 1
ከዚያም ጌዴዎን የተባለው ይሩበኣልና ከእርሱም ጋር የነበሩ ሕዝብ ሁሉ በጠዋት ተነሡ፣ በሐሮድ ምንጭ አጠገብም ሰፈሩ፡፡ የምድያምም ሰፈር ከእነርሱ ወደ ሰሜን በኩል በሞሬ ኮረብታ አጠገብ በሸለቆው ውስጥ ነበረ፡፡
\s5
\v 2 እግዚአብሔርም ጌዴዎንን እንዲህ አለው፣ “ምድያማውያንን እንድታሸንፍ የሚያደርጉህ እጅግ በጣም ብዙ ወታደሮች አሉኝ፡፡ ‘የራሳችን ኃይል አዳነን’ ብለው እስራኤል እንዳይታበዩብኝ እርግጠኛ ሁን፡፡
\v 3 ስለዚህም አሁን፣ በሕዝቡ ጆሮዎች እንዲህ ብለህ ተናገር፣ “ማንም የፈራ ቢኖር፣ ማንም የደነገጠ ቢኖር፣ የገለዓድን ተራራ ትቶ ይመለስ፡፡” ስለዚህ 22, 000 ሰዎች ተመለሱ፣ 10, 000 ሰዎችም ቀሩ፡፡
\s5
\v 4
እግዚአብሔርም ጌዴዎንን እንዲህ አለው፣ “ሕዝቡ አሁንም ገና ብዙ ነው፡፡ ሕዝቡን ወደ ውኃ ውሰዳቸው፣ በዚያም ቁጥራቸውን ጥቂት አደርግልሃለሁ፡፡ እኔ ‘ይህ ከአንተ ጋር ይሄዳል’ ካልሁህ እርሱ ከአንተ ጋር ይሄዳል፤ ነገር ግን እኔ ‘ይህ ከአንተ ጋር አይሄድም’ ካልሁህ እርሱ ከአንተ ጋር አይሄድም፡፡”
\s5
\v 5
ስለዚህ ጌዴዎን ሕዝቡን ወደ ውኃ ወሰዳቸው፣ እግዚአብሔርም ጌዴዎንን እንዲህ አለው፣ “ውሻ እንደሚጠጣ ውኃ የሚጠጣውን ሁሉ፣ ውኃ ለመጠጣት በጕልበታቸው ከሚንበረከኩት ሰዎች መካከል ለይ፡፡”
\v 6 ሦስት መቶ ሰዎች ውኃ እንደ ውሻ ጠጡ፡፡ የቀሩት ሰዎች ግን ውኃ ለጠጡ በጉልበታቸው ተንበረከኩ፡፡
\s5
\v 7
እግዚአብሔርም ጌዴዎንን እንዲህ አለው፣ “ውኃን እንደ ውሻ በጠጡት በሦስት መቶ ሰዎች ከምድያማውያን አድንሃለሁ፣ በእነርሱም ላይ ድል እሰጥሃለሁ፡፡ ሌሎቹ ሰዎች በሙሉ ወደ ስፍራቸው ይመለሱ፡፡”
\v 8 ስለዚህ የተመረጡት ሰዎች ስንቃቸውንና ቀንደ መለከታቸውን ወሰዱ፡፡ ጌዴዎን የእስራኤልን ሰዎች ሁሉ፣ እያንዳንዱን ሰው ወደ ድንኳናቸው ሰደዳቸው፣ ነገር ግን ሦስቱን መቶ ሰዎች በእርሱ ዘንድ አቆያቸው፡፡ የምድያምም ሰፈር ከእርሱ በታች በሸለቆው ውስጥ ነበረ፡፡
\s5
\v 9
በዚያም ሌሊት እግዚአብሔር ለእርሱ እንዲህ አለው፣ “ተነስ! ሰፈራቸውን ምታ፣ በእነርሱ ላይ እኔ ድል እሰጥሃለሁና፡፡
\v 10 ነገር ግን አንተ ወደ ለመውረድ ከፈራህ፣ ከአገልጋይህ ከፉራ ጋር ወደ ሰፈሩ ውረድ፣
\v 11 የሚናገሩትንም አድምጥ፣ ከዚያም በኋላ ሰፈሩን ለመውጋት ድፍረት ታገኛለህ፡፡” ስለዚህ ጌዴዎን ከአገልጋዩ ከፉራ ጋር በሰፈሩ ወደ ነበሩት ጠባቂዎች ወረዱ፡፡
\s5
\v 12 ብዛታቸውም እንደ አንበጣ መንጋ የሆነ ምድያማውያን፣ አማሌቃውያንና የምሥራቅም ሰዎች ሁሉ በሸለቆው ውስጥ ሰፍረው ነበር፡፡ የግመሎቻቸውም ብዛት መቁጠር አይቻልም ነበር፤ ቁጥራቸው በባህር ዳርቻ ካለው አሸዋ ይልቅ የሚበልጥ ነበር፡፡
\s5
\v 13
ጌዴዎን በዚያ በደረሰ ጊዜ አንድ ሰው ሕልምን ለጓደኛው ሲነግረው ነበር፡፡ ሰውየውም እንዲህ አለ፣ “ተመልከት! ሕልም አለምሁ፣ አንዲት ክብ የገብስ ቂጣ ወደ ምድያም ሰፈር ተንከባልላ ስትወርድ አየሁ፡፡ ወደ ድንኳኑም ደረሰች፣ እስኪወድቅ ድረስም በጣም መታችው ከዚህ የተነሳ ወደቀ፣ ደግሞም ተገለበጠ፣ ስለዚህም ድንኳኑ ተጋደመ፡፡”
\v 14 ሌላኛውም ሰው እንዲህ አለ፣ “ይህ ነገር ከእስራኤል ሰው ከኢዮአስ ልጅ ከጌዴዎን ሰይፍ በቀር ሌላ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር በምድያምና በሠራዊቱ ሁሉ ላይ ድል ሰጥቶታል፡፡”
\s5
\v 15
ጌዴዎን የሕልሙን ዝርዝርና ትርጓሜውን በሰማ ጊዜ በጸሎት ተደፍቶ ሰገደ፡፡ እርሱም ወደ እስራኤል ሰፈር ሄደና እንዲህ አለ፣ “ተነሱ! እግዚአብሔር በምድያም ሠራዊት ላይ ድል ሰጥተአችኋል፡፡”
\v 16 እርሱም ሦስቱን መቶ ሰዎች በሦስት ቡድን ከፈላቸው፣ ለሁሉም ሰዎች ቀንደ መለከትና ባዶ ማሰሮ፣ በማሰሮውም ውስጥ ችቦ ሰጣቸው፡፡
\s5
\v 17
እርሱም እንዲህ አላቸው፣ “እኔን ተመልከቱ፣ የማደርገውንም አድርጉ፡፡ አስተውሉ! ወደ ሰፈሩ ዳርቻ በመጣሁ ጊዜ፣ እኔ የማደርገውን እናንተም ታደርጋላችሁ፡፡
\v 18 እኔና ከእኔም ጋር ያሉት ሁሉ ቀንደ መለከት ስንነፋ፣ እናንተ ደግሞ በሰፈሩ በሁሉም አቅጣጫ ቀንደ መለከታችሁን ንፉና “ለእግዚአብሔርና ለጌዴዎን” ብላችሁ ጩኹ፡፡
\s5
\v 19 ስለዚህ ጌዴዎንና ከእርሱ ጋር የነበሩት መቶ ሰዎች የመካከለኛው የጥበቃ ሰዓት በተጀመረ ጊዜ ወደ ሰፈሩ ዳርቻ መጡ፡፡ ምድያማውያን የጥበቃ ሰዎችን በሚቀይሩበት ጊዜ፣ ቀንደ መለከቶቹን ነፉ፣ በእጃቸውም የነበሩትንም ማሰሮች ሰባበሩ፡፡
\s5
\v 20
ሦስቱም ቡድኖች ቀንደ መለከቶቹን ነፉ፣ ማሰሮችንም ሰበሩ፡፡ በግራ እጃቸው ችቦችን ያዙ፣ በቀኝ እጃቸው ደግሞ ቀንደ መለከቶችን ይዘው ለመንፋት ተዘጋጁ፡፡ እነርሱም “የእግዚአብሔርና የጌዴዎን ሰይፍ” ብለው ጮኹ፡፡
\v 21 ሁሉም ሰው በሰፈሩ ዙሪያ በየቦታው ቆመ፣ የምድያማውያን ሠራዊት ሁሉ ሮጡ፡፡ እነርሱም ጮኹና ሸሹ፡፡
\s5
\v 22
ሦስት መቶውንም ቀንደ መለከቶች በነፉ ጊዜ፣ እግዚአብሔር የእያንዳንዱን ምድያማዊ ሰው ሰይፍ በጓደኛውና በራሳቸው ሰራዊት ሁሉ ላይ አዘጋጀ፡፡ ሠራዊቱም በጽሬራ በኩል እስከ ቤትሺጣ፣ በጠባት አጠገብ እስካለው እስከ አቤልምሖላ ዳርቻ ድረስ ሸሸ፡፡
\v 23 የእስራኤል ሰዎች ከንፍታሌም፣ ከአሴርና ከምናሴም ሁሉ ተሰብስበው ምድያምን ከኋላ እየተከተሉ አሳደዱ፡፡
\s5
\v 24 ጌዴዎን መልክተኞችን በኤፍሬም ወዳለው ኮረብታማ አገር ሁሉ በመስደድ እንዲህ አለ፣ “ምድያምን ለመዋጋት ውረዱና እነርሱን ለማስቆም የዮርዳኖስን ወንዝ እስከ ቤትባራም ድረስ ተቆጣጠሩ፡፡” ስለዚህ የኤፍሬም ሰዎች ሁሉ በአንድ ላይ ተሰብስበው እስከ ቤትባራና ዮርዳኖስ ወንዝ ድረስ ውኃውን ተቆጣጠሩ፡፡
\v 25 የምድያምን ሁለቱን መሪዎች ሔሬብንና ዜብን ያዙ፡፡ ሔሬብንም በሔሬብ ዓለት ገደሉት፣ ዜብንም በዜብ ወይን መጥመቂያ ላይ ገደሉት፡፡ ምድያማውያንንም አሳደዱ፣ የሔሬብንና የዜብንም ራስ ይዘው በዮርዳኖስ ማዶ ወደነበረው ወደ ጌዴዎን አመጡ፡፡
\s5
\c 8
\p
\v 1 የኤፍሬም ሰዎች ለጌዴዎን እንዲህ አሉት፣ “ይህ በእኛ ላይ ያደረግኸው ምንድር ነው? ምድያምን ለመዋጋት በሄድህ ጊዜ እኛን አልጠራኸንም? ” ከእርሱም ጋር በኃይል ተጣሉ።
\s5
\v 2 እርሱም እንዲህ አላቸው፣ “ከእናንተ ጋር ሲነጻጸር አሁን እኔ ያደረግት ምንድን ነው? ከኤፍሬም የወይን ቃርሚያ ይልቅ የአቢዔዝር ሙሉ የወይን መከር አይሻልምን?
\v 3 እግዚአብሔር በምድያም መሪዎች በሔሬብና በዜብ ላይ ድልን ሰጥቶአችኋል! ከእናንተ ጋር ሲነጻጸር እኑ ምን ፈጸምሁ? ” ይህን በተናገረ ጊዜ ቍጣቸው በረደ።
\s5
\v 4
ጌዴዎን ከእርሱ ጋር ከነበሩት ከሦስቱ መቶ ሰዎች ጋር ወደ ዮርዳኖስ መጣና ተሻገረ፡፡ እጅግ በጣም ደክመው ነበር፣ ይሁን እንጂ ያሳድዱ ነበር።
\v 5 እርሱም ለሱኮት ሰዎች እንዲህ አላቸው፣ “ደክመዋልና እባካችሁ ለተከተሉኝ ሰዎች እንጀራ ስጡአቸው፣ እኔም የምድያምን ነገሥታት ዛብሄልንና ስልማናን እያሳደድሁ ነው፡፡”
\s5
\v 6
የሱኮትም መሪዎች እንዲህ አሉ፣ “ዛብሄልንና ስልማናን በጉልበትህ አሸነፍኃቸውን? ” እኛ ለሠራዊትህ እንጀራ ለምን እንደምንሰጥ አናውቅም?
\v 7 ጌዴዎንም እንዲህ አለ፣ “እግዚአብሔር በዛብሄልና በስልማና ላይ ድል በሰጠኝ ጊዜ፣ እኔ በምድረ በዳ እሾህና በኵርንችት ሥጋችሁን እቦጫጭቀዋለሁ፡፡”
\s5
\v 8
ከዚያም ወደ ጵኒኤል ወጣና በተመሳሳይ መንገድ በዚያ ለሚገኙ ሰዎች ተናገራቸው፣ ነገር ግን የጵንኤልም ሰዎች የሱኮት ሰዎች እንደ መለሱ መለሱለት።
\v 9 እርሱም የጵኒኤልን ሰዎች ደግሞ እንዲህ አላቸው፣ “በሰላም በተመለስሁ ጊዜ፣ ይህን ግንብ አፈርሰዋለሁ፡፡
\s5
\v 10 ዛብሄልና ስልማናም ከሠራዊቶቻቸው ጋር፣ ከምሥራቅም ሰዎች ሠራዊት ሁሉ የቀሩ 15, 000 ያህል ሰዎች በቀርቀር ነበሩ፡፡ በሰይፍ ለመዋጋት ስልጠና የወሰዱ መቶ ሀያ ሺህ ሰዎች ወድቀው ነበርና፡፡
\s5
\v 11 ጌዴዎንም ዘላኖች ባሉበት መንገድ በኖባህና በዮግብሃ አልፎ ወደ ጠላት ሰፈር ሄደ፡፡ እርሱም የጠላትን ሰራዊት አሸነፈ፣ ምክንያቱም እንዲህ ዓይነት አደጋ ይገጥመናል ብለው አላሰቡም ነበርና፡፡
\v 12 ዛብሄልና ስልማናም ሸሹ፣ ጌዴዎንም ባሳደዳቸው ጊዜ ሁለቱንም የምድያም ነገሥታት ዛብሄልንና ስልማናን ያዛቸው፣ ሠራዊታቸውንም ሁሉ ድንጋጤ ላይ ጣላቸው፡፡
\s5
\v 13
የኢዮአስ ልጅ ጌዴዎንም በሔሬስ ዳገት በኩል በማለፍ ከጦርነት ተመለሰ፡፡
\v 14 እርሱም ከሱኮት ሰዎች አንድ ወጣት ይዞ ጠየቀውና ከእርሱ ምክር ፈለገ፡፡ ወጣቱም የሱኮትን መሪዎችና ሽማግሌዎች ሰባ ሰባት ሰዎች እነማን እንደሆኑ ገለጸለት።
\s5
\v 15
ጌዴዎንም ወደ ሱኮት ሰዎች መጣና እንዲህ አላቸው፣ “‘ዛብሄልንና ስልማናን በጉልበትህ አሸነፍኃቸውን? እኛ ለሠራዊትህ እንጀራ መስጠት እንዳለብን አናውቅም? ብላችሁ ያላገጣችሁብኝ ዛብሄልና ስልማና ተመልከቱአቸው፡፡”
\v 16 ጌዴዎንም የከተማይቱን ሽማግሌዎች ያዛቸው፣ የሱኮትንም ሰዎች በምድረ በዳ እሾህና በኵርንችት ገረፋቸው፡፡
\v 17 የጵኒኤልንም ግንብ አፈረሰ፣ የዚያችን ከተማ ሰዎችን ገደለ፡፡
\s5
\v 18
ጌዴዎንም ለዛብሄልና ለስልማና እንዲህ አላቸው፣ “በታቦር የገደላችኋቸው ሰዎች ምን ዓይነት ሰዎች ነበሩ? ” እነርሱም፣ “እንደ አንተ ያሉ ነበሩ፡፡ እያንዳንዳቸው የንጉሥ ልጅ ይመስላሉ” አሉት፡፡
\v 19 ጌዴዎንም “እነርሱ የእናቴ ልጆች ወንድሞቼ ነበሩ፡፡ በሕይወት እንዲኖሩ አድናችኋቸው ቢሆን ኖሮ፣ ሕያው እግዚአብሔርን፣ እኔ አልገድላችሁም ነበር” አለ፡፡
\s5
\v 20
ለበኵር ልጁ ለዬቴር እንዲህ አለው፣ “ተነሳና ግደላቸው! ” ነገር ግን ወጣቱ ልጅ ስለፈራ ሰይፉን አልመዘዘም፣ ምክንያቱም ገና ወጣት ልጅ ነበረና፡፡
\v 21 የዚያን ጊዜ ዛብሄልና ስልማና እንዲህ አሉ፣ “አንተ ተነሳና ግደለን! የሰው ኃይሉ እንደ ሰውነቱ ነውና፡፡” ጌዴዎንም ተነሥቶ ዛብሄልንና ስልማናን ገደላቸው፡፡ በግመሎቻቸውም አንገት ላይ የነበሩትን ጌጦች ወሰደ፡፡
\s5
\v 22
የእስራኤልም ሰዎች ጌዴዎንን “አንተ ግዛን፣ አንተ፣ የአንተ ልጅና የልጅ ልጆችህ ግዙን፣ ምክንያቱም አንተ ከምድያም ብርታት አድነኸናልና፡፡”
\v 23 ጌዴዎንም ለእነርሱ እንዲህ አላቸው፣ “እኔ በእናንተ ላይ አልገዛም፣ ልጄም በእናንተ ላይ አይገዛም፣ እግዚአብሔር ይገዛችኋል አላቸው፡፡
\s5
\v 24
ጌዴዎን ለእነርሱ እንዲህ አላቸው፣ “አንድ የምጠይቃችሁ ነገር አለኝ፡- እያንዳንዳችሁ ከምርኮአችሁ ጕትቻችሁን እንድትሰጡኝ እለምናችኋለሁ፡፡” (ምድያማውያን የወርቅ ጕትቻ ነበራቸው ምክንያቱም እነርሱ እስማኤላውያንም ነበሩና፡፡)
\v 25 እነርሱም፣ “ለአንተ ልንሰጥህ ደስተኞች ነን” አሉት፡፡ እነርሱም ልብስ አነጠፉና ሁሉም ሰው የምርኮውን ጕትቻ በዚያ ላይ ጣለ፡፡
\s5
\v 26
እርሱ የጠየቀው የወርቅ ጕትቻ ክብደት 1, 700 ሰቅል ወርቅ ነበር፡፡ ይህም ምርኮ ከጌጣ ጌጦቹ ሌላ የአንገት ጌጥ፣ የምድያምም ነገሥታት ከሚለብሱት ሐምራዊ ልብስ፣ እንደዚሁም በግመሎቻቸውም አንገት ከነበሩት ጌጦች ሌላ ነበረ፡፡
\s5
\v 27
ጌዴዎንም ከጉትቻዎቹ ባገኘው ወርቅ ኤፉድ ሠራና በከተማው፣ በዖፍራ አኖረው፣ እስራኤልም ሁሉ እርሱን በማምለክ አመነዘረበት፡፡ ለጌዴዎንና በቤቱም ላሉት ወጥመድ ሆነባቸው፡፡
\v 28 ስለዚህም ምድያም በእስራኤል ሕዝብ ፊት ተዋረደ፣ ራሳቸውንም እንደገና አላነሡም፡፡ በጌዴዎንም ዘመን ምድሪቱ ለአርባ ዓመት ሰላም ሆነች።
\s5
\v 29
የኢዮአስም ልጅ ይሩበኣል ሄደና በራሱ ቤት ተቀመጠ።
\v 30 ጌዴዎንም ብዙ ሚስቶች ነበሩትና ሰባ ወንዶች ልጆች ነበሩት፡፡
\v 31 በሴኬም የነበረችው ቁባቱም ወንድ ልጅ ወለደችለት፣ ጌዴዎንም ስሙን አቤሜሌክ ብሎ ጠራው፡፡
\s5
\v 32
የኢዮአስ ልጅ ጌዴዎን በመልካም የሽምግልና ዕድሜ ሞተ፣ በአቢዔዝራውያን ጎሳ በሆነው በዖፍራ በነበረው በአባቱ በኢዮአስ መቃብር ተቀበረ፡፡
\v 33 ጌዴዎን ከሞተ በኋላ ብዙ ሳይቆይ እንዲህ ሆነ፣ የእስራኤል ሕዝብ እንደገና ተመለሱ፣ የበኣልን አማልክት በማምለክ አመነዘሩ፡፡ በኣልብሪትንም አምላካቸው አደረጉ፡፡
\s5
\v 34 የእስራኤልም ሕዝብ በተለያዩ አቅጣጫዎች ከነበሩት ከጠላቶቻቸው ኃይል ያዳናቸውን አምላካቸውን እግዚአብሔርን አላሰቡትም፡፡
\v 35 እነርሱም ለእስራኤል ስላደረገው በጎ ነገር አስበው ለይሩበኣል (የጌዴዎን ሌላኛው ስም ነው) ውለታ ለመመለስ ቃል ኪዳናቸውን አልጠበቁም፡፡
\s5
\c 9
\p
\v 1
የይሩበኣል ልጅ አቤሜሌክ ወደ እናቱ ዘመዶች ወደ ሴኬም ሄደና ለእነርሱና ለእናቱ ቤተሰብ ጎሳ በሙሉ እንዲህ አላቸው፣
\v 2 “በሴኬም የሚገኙ መሪዎች በሙሉ ይሰሙ ዘንድ ይህን ተናገሩ፣ ‘ለእናንተ የሚሻለው የትኛው ነው? የይሩበኣል ሰባ ልጆች ሁሉ ቢገዙአችሁ ወይስ አንድ ሰው ቢገዛችሁ? እኔ የአጥንታችሁ ፍላጭ የሥጋችሁ ቍራጭ እንደ ሆንሁ አስቡ፡፡”
\s5
\v 3
የእናቱም ዘመዶች ስለ እርሱ ለሴኬም መሪዎች ተናገሩ፣ እነርሱም አቤሜሌክን ለመከተል ተስማሙ፣ “እርሱ ወንድማችን ነው” ብለዋልና፡፡
\v 4 እነርሱም ከበኣልብሪትም ቤት ሰባ ብር ሰጡት፣ አቤሜሌክም እርሱን የተከተሉትን ስርዓት አልበኞችንና ወሮበሎችን ለመቅጠር ተጠቀበመት፡፡
\s5
\v 5
እርሱም ወደ አባቱ ቤት ወደ ዖፍራ ሄደ፣ የይሩበኣልን ልጆች ሰባ ወንድሞቹን በአንድ ድንጋይ ላይ አረዳቸው፡፡ ትንሹ የይሩበኣል ልጅ ኢዮአታም ግን ተሸሽጎ ስለነበር እርሱ ብቻ ተረፈ፡፡
\v 6 የሴኬምና የቤትሚሎ መሪዎች ሁሉ በአንድ ላይ ተሰበሰቡ፣ እነርሱም ሄደው በሴኬም በዓምዱ አጠገብ ባለው በበሉጥ ዛፍ ስር አቤሜሌክን አነገሡት፡፡
\s5
\v 7
ለኢዮአታም ይህን ነገር በነገሩት ጊዜ፣ በገሪዛን ተራራ ራስ ላይ ሄደና ቆመ፡፡ ድምፁንም ከፍ አድርጎ ጮኸና እንዲህ አላቸው፣ “እናንተ የሴኬም መሪዎች፣ እግዚአብሔርም እናንተን ይሰማ ዘንድ፣ እኔን ስሙኝ፡፡
\v 8 አንድ ጊዜ ዛፎች በእነርሱ ላይ የሚያነግሱት ለመቀባት ሄዱ፡፡ እነርሱም ለወይራ ዛፍ ‘በእኛ ላይ ንገሥ’ አሉት፡፡
\s5
\v 9 የወይራ ዛፍ ግን ለእነርሱ እንዲህ አላቸው፣ ‘እግዚአብሔርና ሰዎችን ለማክበር የሚጠቅመውን ቅባቴን ትቼ ተመልሼ በሌሎች ዛፎች ላይ ለመወዛወዝ ልሂድን?
\v 10 ዛፎቹም ለበለስ ዛፍ እንዲህ አሉት፣ ‘መጥተህ በእኛ ላይ ንገሥ፡፡’
\v 11 ነገር ግን የበለሱ ዛፍ፣ ጣፋጭነቴንና መልካሙን ፍሬዬን ትቼ ተመልሼ በሌሎች ዛፎች ላይ ለመወዛወዝ ልሂድን? አላቸው፡፡
\s5
\v 12
ዛፎችም ለወይኑ፣ ‘መጥተህ በእኛ ላይ ንገሥ’ አሉት፡፡
\v 13 ወይኑም፣ እግዚአብሔርንና ሰውን ደስ የሚያሰኘውን አዲስ የወይን ጠጄን ትቼ ተመልሼ በዛፎች ላይ ለመወዛወዝ ልሂድን? አላቸው፡፡
\v 14 ከዚያም ዛፎች ሁሉ የእሾህ ቁጥቋጦን፣ ‘መጥተህ በእኛ ላይ ንገሥ’ አሉት፡፡
\s5
\v 15 የእሾህ ቁጥቋጦውም ዛፎቹን፣ ‘በእውነት እኔን በእናንተ ላይ እንድነግስ ልትቀቡኝ የምትፈልጉ ከሆነ፣ ኑና በጥላዬ ስር ተጠለሉ፡፡ እንዲህ ካልሆነ ግን እሳት ከእሾህ ቁጥቋጦ ይውጣና የሊባኖስንም ዝግባ ያቃጥል’ አላቸው፡፡
\v 16 አሁን እንግዲህ፣ አቤሜሌክን ባነገሳችሁት ጊዜ በእውነትና በቅንነት አድርጋችሁ ከሆነ፣ ለይሩበኣልና ለቤቱም በጎነት አስባችሁ አድርጋችሁ ከሆነ፣ እንዳደረገውም መጠን ለእርሱ የተገባውን ቀጥታችሁት ከሆነ
\s5
\v 17
አባቴ ስለ እናንተ ተዋግቶ እንደነበር፣ ሕይወቱን አሳልፎ በመስጠት፣ ከምድያምም እጅ እናንተን እንዳዳናችሁ አሰባችሁ ማለት ነው
\v 18 ነገር ግን ዛሬ እናንተ በአባቴ ቤት ላይ ተነሥታችኋል፣ በአንድ ድንጋይ ላይ ልጆቹን፣ ሰባ ሰዎችን፣ አረዳችኋቸው፡፡ ከዚያም የሴት አገልጋዩን ልጅ አቤሜሌክን ዘመዳችሁ ስለ ሆነ በሴኬም መሪዎች ላይ እንዲነግስ አደረጋችሁት፡፡
\s5
\v 19
ያንጊዜ ለይሩበኣልና ለቤቱ በእውነትና በቅንነትን አድርጋችሁ ከሆነ፣ እንግዲያው እናንተ በአቤሜሌክ ደስ ሊላችሁ ይገባል፣ እርሱም በእናንተ ደስ ይበለው፡፡
\v 20 ነገር ግን እንዲህ ባይሆን፣ ከአቤሜሌክ እሳት ይውጣና የሴኬምንም ሰዎችና የቤትሚሎን ቤት ያቃጥል፡፡ ከሴኬምም ሰዎችና ከቤትሚሎ እሳት ይውጣና አቤሜሌክን ያቃጥል፡፡
\v 21 ኢዮአታምም ሸሽቶ አመለጠ፣ ከዚያም ወደ ብኤር ሄደ፡፡ እርሱም በዚያ ተቀመጠ ምክንያቱም ከአቤሜሌክ ከወንድሙ በጣም ሩቅ ነበረ፡፡
\s5
\v 22
አቤሜሌክም በእስራኤል ላይ ለሦስት ዓመት ገዛ፡፡
\v 23 እግዚአብሔር በአቤሜሌክና በሴኬም መሪዎች መካከል ክፉን መንፈስ ሰደደ፡፡ የሴኬም መሪዎችም በአቤሜሌክ ላይ የነበራቸውን እምነት ጥለው ከዱት፡፡
\v 24 እግዚአብሔር ይህንን ያደረገው በሰባዎቹ የይሩበኣል ልጆች ላይ የተደረገውን ዓመፅ ለመበቀል ነው፣ ወንድማቸው አቤሜሌክም እነርሱን በመግደሉ ተጠያቂ እንዲሆን ለማድረግ ነው፤ የሴኬም ሰዎችም እርሱ ወንድሞቹን እንዲገድላቸው ስለተባበሩት ተጠያቂ እንዲሆኑ ለማድረግ ነው፡፡
\s5
\v 25 ስለዚህ የሴኬም መሪዎች በኮረብቶች ራስ ላይ እርሱን አድፍጠው የሚጠብቁ ሰዎች መደቡ፣ እነርሱም በዚያ መንገድ በአጠገባቸው ያለፉትን ሰዎች በሙሉ ዘረፉ፡፡ ይህም ወሬ ለአቤሜሌክ ደረሰው፡፡
\s5
\v 26 የአቤድም ልጅ ገዓል ከዘመዶቹ ጋር መጣና ወደ ሴኬም ሄዱ፡፡ የሴኬም መሪዎች በእርሱ ተማመኑበት፡፡
\v 27 እነርሱም ወደ እርሻው ወጥተው ሄዱና ከወይን አትክልት ቦታ ወይን ለቅመው ጨመቁት፡፡ በአምላካቸው ቤት የደስታ በዓል አደረጉ፣ በሉም ጠጡም፣ አቤሜሌክንም ሰደቡ፡፡
\s5
\v 28
የአቤድም ልጅ ገዓል እንዲህ አለ፣ “እናገለግለው ዘንድ አቤሜሌክ ማን ነው? ሴኬምስ ማን ነው? እርሱ የይሩብኣል ልጅ አይደለምን? ዜቡልስ የእርሱ ሹም አይደለምን? ለኤሞር ሰዎች፣ ለሴኬም አባት አገልግሉ! ለምን እርሱን እናገለግላለን?
\v 29 ይህ ሕዝብ በእኔ አዛዥነት ስር ቢሆን እመኝ ነበር! የዚያን ጊዜ አቤሜሌክን አስወግደው ነበር፡፡ ለአቤሜሌክም ‘ሠራዊትህን ሁሉ ጥራ’ እለው ነበር፡፡”
\s5
\v 30 የከተማይቱ ሹም፣ ዜቡል የአቤድን ልጅ የገዓልን ቃል በሰማ ጊዜ ቁጣው ነደደ፡፡
\v 31 ወደ አቤሜሌክም ያታልለው ዘንድ እንዲህ ብሎ መልክተኞች ላከ፣ “ተመልከት፣ የአቤድ ልጅ ገዓልና ዘመዶቹ ወደ ሴኬም እየመጡ ነው፣ ከተማይቱን በአንተ ላይ እንድትሸፍት አነሳስተዋል፡፡
\s5
\v 32 አሁንም አንተና ከአንተ ጋር ያሉት ወታደሮች በሌሊት ተነሡ፣ ሜዳውም ላይ አድፍጡ፡፡
\v 33 ከዚያም በጠዋት ፀሐይ በወጣች ጊዜ ማልደህ ተነሣና በከተማይቱ ላይ ድንገተኛ ጥቃት ፈጽምባት፡፡ እርሱና ከእርሱ ጋር ያሉት ሕዝብ በአንተ ላይ በመጡ ጊዜ በእነርሱ ላይ ልታደርግ የምትችለውን ማንኛውንም ነገር አድርግባቸው፡፡”
\s5
\v 34 ስለዚህ አቤሜሌክ በሌሊት ተነሳ፣ እርሱና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሰዎች በሙሉ፣ በአራት ወገን ተከፋፍለው በሴኬም ላይ አደፈጡ፡፡
\v 35 የአቤድ ልጅ ገዓል ወጥቶ በከተማይቱ በር መግቢያ ቆመ፡፡ አቤሜሌክና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሰዎችም ከተደበቁበት ስፍራ ወጥተው መጡ፡፡
\s5
\v 36
ገዓልም ሰዎቹን ባየ ጊዜ ዜቡልን፣ “ተመልከት፣ ሰዎች ከኮረብቶች ራስ ወርደው እየመጡ ነው! ” አለው፡፡ ዜቡልም እንዲህ አለው፣ “አንተ የምታየው ሰዎች የሚመስለውን የኮረብቶች ጥላ ነው፡፡”
\v 37 ገዓልም እንደገና እንዲህ ሲል ተናገረ፣ “ተመልከት፣ በምድር መካከል ሰዎች ወርደው እየመጡ ነው፣ አንድም ወገን በቃላተኞች የበሉጥ ዛፍ መንገድ እየመጣ ነው፡፡
\s5
\v 38 የዚያን ጊዜ ዜቡል እንዲህ አለው፣ “‘እናገለግለው ዘንድ አቤሜሌክ ማን ነው? ብለህ የተናገርሃቸው እነዚያ የትዕቢት ቃላቶችህ አሁን የት አሉ? እነዚህ ሰዎች አንተ የናቅሃቸው አይደሉምን? አሁን ውጣና ከእነርሱ ጋር ተዋጋ፡፡”
\v 39 ገዓል ወጣና የሴኬም ሰዎችን ይመራ ነበር፣ ከአቤሜሌክም ጋር ተዋጋ፡፡
\v 40 አቤሜሌክም አሳደደው፣ ገዓልም በፊቱ ሸሸ፡፡ ብዙዎቹም በከተማይቱ በር መግቢያ ፊት ለፊት በከባድ ሁኔታ ቆስለው ወደቁ፡፡
\s5
\v 41 አቤሜሌክም በአሩማ ተቀመጠ፡፡ ዜቡልም ገዓልንና ዘመዶቹን ከሴኬም እንዲወጡ አስገደዳቸው፡፡
\v 42 በሚቀጥለው ቀን የሴኬም ሕዝብ ወደ እርሻ ሄዱ፣ ይህም ወሬ ለአቤሜሌክ ደረሰው፡፡
\v 43 ሕዝቡንም ወሰደ፣ በሦስት ወገንም ከፈላቸውና በእርሻዎቹ ውስጥ አደፈጡ፡፡ እርሱም ተመለከተ፣ ሕዝቡ ከከተማ ወጥተው ሲመጡ አየ፡፡ እርሱም ተዋጋቸውና ገደላቸው፡፡
\s5
\v 44 አቤሜሌክና ከእርሱም ጋር የነበሩት ወገኖች ተዋጉና የከተማይቱን በር መግቢያ ዘጉ፡፡ ሌሎቹ ሁለት ወገኖች ደግሞ በእርሻው ውስጥ የነበሩትን ሁሉ ወጓቸውና ገደሉአቸው፡፡
\v 45 አቤሜሌክም ቀኑን ሙሉ ከከተማይቱ ጋር ተዋጋ፡፡ ከተማይቱንም ተቆጣጠረና በውስጧ የነበሩትን ሕዝብ ገደላቸው፡፡ የከተማይቱንም ቅጥር አፈራረሰው፣ በላይዋም ጨው በተነባት፡፡
\s5
\v 46 የሴኬም ግንብ መሪዎች በሙሉ ይህንን ወሬ በሰሙ ጊዜ፣ ወደ ኤልብሪት ቤት ምሽግ ውስጥ ገቡ፡፡
\v 47 አቤሜሌክም መሪዎቹ በሙሉ በሴኬም ግንብ ውስጥ በአንድ ላይ እንደተሰበሰቡ ተነገረው፡፡
\s5
\v 48 አቤሜሌክ ወደ ሰልሞን ተራራ ወጣ፣ እርሱና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሰዎች ሁሉ፡፡አቤሜሌክም በእጁ መጥረቢያ ወሰደና የዛፉን ቅርንጫፎች ቆረጠ፡፡ እርሱም አንሥቶ በትከሻው ላይ አደረገውና ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሰዎች እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፣ “እኔ ሳደርግ ያያችሁትን፣ ፈጥናችሁ እኔ እንዳደረግሁ አድርጉ፡፡” 49 ስለዚህ እያንዳንዱ ሰው የዛፉን ቅርንጫፎች ቈረጠና አቤሜሌክን ተከተሉት፡፡ እነርሱም ቅርንጫፎቹን በምሽጉ ላይ ከመሩአቸው፣ በላዩም ላይ እሳት አቀጣጠሉበት፣ ከዚህ የተነሳ የሴኬም ግንብ ሰዎች ሁሉ፣ አንድ ሺህ የሚያህሉ ወንድና ሴት ሞቱ፡፡
\s5
\v 50 ከዚያ በኋላ አቤሜሌክ ወደ ቴቤስ ሄደ፣ ቴቤስንም ከበባትና ተቆጣጠራት፡፡
\v 51 ነገር ግን በከተማይቱ ጠንካራ ግንብ ነበረ፣ የከተማይቱም ሰዎች ሁሉ፣ ወንዶችና ሴቶች ሁሉ፣ የከተማይቱም መሪዎች ሁሉ ወደዚያ ሸሹና በውስጥ ሆነው ደጁን ዘጉት፡፡ ከዚያም እስከ ግንቡ ሰገነት ድረስ ወደ ላይ ወጡ፡፡
\s5
\v 52
አቤሜሌክም ወደ ግንቡ መጣና ተዋጋ፣ በእሳትም ሊያቃጥለው ወደ ግንቡ በር አጠገብ መጣ፡፡
\v 53 ነገር ግን አንዲት ሴት በአቤሜሌክ ራስ ላይ የወፍጮ መጅ ጣለችበት፣ መጁም ጭንቅላቱን ሰባበረው፡፡
\v 54 ከዚያም እርሱ በአስቸኳይ ጋሻ ጃግሬውን ጠርቶ፣ “አንድም ሰው እኔን ‘ሴት ገደለችው’ እንዳይል ሰይፍህን መዝዘህ ግደለኝ” አለው፡፡ ስለዚህ ወጣቱ ሰው ወጋውና ሞተ፡፡
\s5
\v 55 የእስራኤልም ሰዎች አቤሜሌክ እንደ ሞተ ባዩ ጊዜ ወደ ቤታቸው ተመለሱ፡፡
\v 56 እግዚአብሔርም ሰባ ወንድሞቹን በመግደል አቤሜሌክ በአባቱ ላይ ያደረገውን ክፋት ተበቀለው፡፡
\v 57 እግዚአብሔርም የሴኬምን ሰዎች ክፋት ሁሉ በራሳቸው ላይ መለሰባቸው፣ የይሩበኣልም ልጅ የኢዮአታም እርግማን በእነርሱ ላይ መጣባቸው፡፡
\s5
\c 10
\p
\v 1
ከአቤሜሌክ በኋላ ከይሳኮር ነገድ የሆነውና በኮረብታማውም በኤፍሬም አገር ባለችው በሳምር ይኖር የነበረው የዱዲ ልጅ የፎሖ ልጅ ቶላ እስራኤልን ለማዳን ተነሣ፡፡
\v 2 እርሱም በእስራኤል ላይ ሀያ ሦስት ዓመት ፈረደ፡፡ እርሱም ሞተ፣ በሳምርም ተቀበረ፡፡
\s5
\v 3
ከእርሱም በኋላ ገለዓዳዊው ኢያዕር ተነሣ፡፡ በእስራኤልም ላይ ሀያ ሁለት ዓመት ፈረደ፡፡
\v 4 በሠላሳ አህያዎች የሚጋልቡ ሠላሳ ልጆች ነበሩት፣ እነርሱም በገለዓድ ምድር ያሉ እስከ ዛሬ ድረስ የኢያዕር መንደሮች ተብለው የሚጠሩ ሠላሳ ከተሞች ነበሩአቸው፡፡
\v 5 ኢያዕርም ሞተ፣ በቃሞንም ተቀበረ፡፡
\s5
\v 6
የእስራኤል ሕዝብ ከዚህ በፊት ከሰሩት በላይ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ስራ ጨምረው ሠሩ፣ በኣልን፣ አስታሮትን፣ እንደዚሁም የሶርያን አማልክት፣ የሲዶናን አማልክት፣ የሞዓብን አማልክት፣ የአሞንን ሕዝብ አማልክት፣ የፍልስጥኤማውያንን አማልክት አመለኩ፡፡እግዚአብሔርን ተዉ፣ እርሱንም አላመለኩትም፡፡
\v 7 የእግዚአብሔርም ቍጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፣ እርሱም ፍልስጥኤማውያንና አሞናውያን ያሸንፉአቸው ዘንድ ለእነርሱ አሳልፎ ሰጣቸው፡፡
\s5
\v 8
እነርሱም በዚያን ዓመት የእስራኤልን ሕዝብ አደቀቋቸው፣ አስጨነቋቸው፣ ለአሥራ ስምንት ዓመት በዮርዳኖስ ማዶ በአሞራውያን ምድር በገለዓድ ውስጥ የነበሩትን የእስራኤልን ሕዝብ ሁሉ አስጨነቋቸው፡፡
\v 9 የአሞንም ሰዎች ከይሁዳ፣ ከብንያምና ከኤፍሬም ቤት ጋር ለመዋጋት ዮርዳኖስን ተሻገሩ፣ ከዚህ የተነሳ እስራኤል እጅግ በጣም ተጨነቁ፡፡
\s5
\v 10 የዚያን ጊዜ የእስራኤልም ሕዝብ ወደ እግዚአብሔር ጮሁ፣ እንዲህ በማለት፣ “በአንተ ላይ በድለናል፣ ምክንያቱም አምላካችንን ትተን የበኣል አማልክትን አምልከናልና፡፡”
\v 11 እግዚአብሔርም ለእስራኤል ልጆች እንዲህ አላቸው፣ “ከግብፃውያን፣ ከአሞራውያንም፣ ከአሞናውያን፣ ከፍልስጤማውያንና
\v 12 ከሲዶናውያን አላዳንኋችሁምን? አማሌቃውያንና ማዖናውያን አስጨነቋችሁ፤ ወደ እኔም ጮኻችሁ፣ እኔም ከእነርሱ ኃይል አዳንኋችሁ፡፡
\s5
\v 13 ይሁን እንጂ እናንተ እንደገና ተዋችሁኝና ሌሎችን አማልክት አመለካችሁ፡፡ ስለዚህ፣ እኔም ከእንግዲህ ወዲህ አላድናችሁም፡፡
\v 14 ሂዱና ወደምታመልኳቸው አማልክት ጩኹ፡፡ በመከራችሁ ጊዜ እነርሱ ያድኑአችሁ፡፡
\s5
\v 15
የእስራኤልም ሕዝብ እግዚአብሔርን እንዲህ አሉት፣ “እኛ ኃጢአትን ሠርተናል፡፡ ለአንተ ደስ የሚያሰኝህን ማንኛውንም ነገር በእኛ ላይ አድርግብን፡፡ እባክህ፣ የዛሬን ብቻ አድነን፡፡”
\v 16 እነርሱም በመካከላቸው ካሉት ባዕዳን አማልክት ዘወር አሉ፣ እግዚአብሔርንም አመለኩ፡፡እርሱም የእስራኤልን ጕስቍልና ሊታገሰው የማይቻለው ሆነ፡፡
\s5
\v 17 ከዚያም አሞናውያን በአንድ ላይ ተሰበሰቡና በገለዓድ ሰፈሩ፡፡ እስራኤላውያንም በአንድ ላይ ተሰበሰቡና ሰፈራቸውን በምጽጳ ላይ አደረጉ፡፡
\v 18 የገለዓድ ሕዝብ መሪዎችም እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፣ “አሞናውያንን ለመዋጋት የሚጀምር ሰው ማን ነው? እርሱ በገለዓድ በሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ላይ መሪ ይሆናል፡፡”
\s5
\c 11
\p
\v 1
ገለዓዳዊውም ዮፍታሔ ኃያል ተዋጊ ነበር፣ ነገር ግን የጋለሞታ ሴት ልጅ ነበረ፡፡ አባቱም ገለዓድ ነበረ፡፡
\v 2 የገለዓድም ሚስት ደግሞ ሌሎች ወንዶች ልጆችን ወለደችለት፡፡ የሚስቱ ልጆች ባደጉ ጊዜ፣ ዮፍታሔን ቤቱን ለቅቆ እንዲወጣ አስገደዱት፣ እንዲህም አሉት፡- “አንተ ከቤተሰባችን ምንም ነገር አትወርስም፡፡ አንተ የሌላ ሴት ልጅ ነህ፡፡”
\v 3 ስለዚህ ዮፍታሔ ከወንድሞቹ ፊት ሸሸና በጦብ ምድር ተቀመጠ፡፡ ስርዓት አልበኛ ሰዎችም ተከተሉት፣ ተሰብስበውም ከእርሱ ጋር ሄዱ፡፡
\s5
\v 4
ከጥቂት ቀናት በኋላ፣ የአሞን ሰዎች ከእስራኤል ጋር ውጊያ አደረጉ፡፡
\v 5 የአሞንም ሰዎች ከእስራኤል ጋር ውጊያ ባደረጉ ጊዜ፣ የገለዓድ ሽማግሌዎች ዮፍታሔን ከጦብ ምድር ለማምጣት ሄዱ፡፡
\v 6 ዮፍታሔንም፣ “ና፣ ከአሞን ሰዎች ጋር እንድንዋጋ አለቃችን ሁን” አሉት፡፡
\s5
\v 7 ዮፍታሔም ለገለዓድ ሽማግሌዎች እንዲህ አላቸው፣ “እናንተ ጠልታችሁኛል፣ የአባቴንም ቤት ትቼ እንድሄድ አስገድዳችሁኛል፡፡ አሁን በተቸገራችሁ ጊዜ ለምን ወደ እኔ መጣችሁ? ”
\v 8 የገለዓድም ሽማግሌዎችም ለዮፍታሔ፣ “አሁን ወደ አንተ የተመለስነው ለዚህ ነው፤ ከእኛ ጋር ና፣ ከአሞንም ሰዎች ጋር ተዋጋ፣ ከዚያም በኋላ በገለዓድ በሚኖሩት ሰዎች ሁሉ ላይ መሪ ትሆናለህ” አሉት፡፡
\s5
\v 9
ዮፍታሔም ለገለዓድ ሽማግሌዎች፣ “ከአሞን ሰዎች ጋር እንድዋጋ እንደገና ወደ ቤቴ ከመለሳችሁኝ፣ እግዚአብሔርም በእነርሱ ላይ ድል ከሰጠን መሪያችሁ እሆናለሁ” አላቸው፡፡
\v 10 የገለዓድ ሽማግሌዎችም ለዮፍታሔ፣ “እንደተናገርነው የማናደርግ ከሆነ እግዚአብሔር በእኛ መካከል ምስክር ይሁን” አሉት፡፡
\v 11 ስለዚህ ዮፍታሔ ከገለዓድ ሽማግሌዎች ጋር ሄደ፣ ሕዝቡም በላያቸው ላይ መሪና የጦር አዛዥ አደረጉት፡፡ እርሱ በምጽጳ በእግዚአብሔር ፊት በነበረ ጊዜ፣ ዮፍታሔ የገባውን ቃል ኪዳን ሁሉ ደገመው፡፡
\s5
\v 12
ዮፍታሔም ወደ አሞን ሰዎች ንጉሥ እንዲህ በማለት መልእክተኞችን ላከ፡- “በእኛ መካከል ያለው ጠብ ምንድን ነው? ምድራችንን ለመውሰድ በጦር ለምን መጣህ? ”
\v 13 የአሞንም ሰዎች ንጉሥም ለዮፍታሔ መልክተኞች “እስራኤል ከግብፅ በወጣ ጊዜ ከአርኖን ጀምሮ እስከ ያቦቅና እስከ ዮርዳኖስ ድረስ ምድሬን ወስደዋል፡፡ አሁን እነዚህን መሬቶች በሰላም መልሱልኝ” ብሎ መለሰላቸው፡፡
\s5
\v 14 ዮፍታሔም ወደ አሞን ሰዎች ንጉሥ መልክተኞችን እንደ ገና ላከ፣
\v 15 እንዲህም አለው፣ “ዮፍታሔ የሚለው ይህንን ነው፡- እስራኤል የሞዓብን ምድር የአሞንንም ሰዎች ምድር አልወሰደም፣
\v 16 ነገር ግን ከግብፅ በወጡ ጊዜ፣ እስራኤል በምድረ በዳ በኩል ወደ ቀይ ባሕር ከዚያም ወደ ቃዴስ ሄዱ፣
\s5
\v 17
እስራኤል ወደ ኤዶምያስ ንጉሥ እንዲህ በማለት መልእክተኞችን ላኩ፣ ‘በምድርህ እንድናልፍ እባክህ ፍቀድልን፣’ ነገር ግን የኤዶምያስ ንጉሥ አልሰማም፡፡ እንዲሁም ወደ ሞዓብ ንጉሥ መልእክተኞች ላኩ፣ እርሱም አልፈቀደም፡፡ ስለዚህ እስራኤል በቃዴስ ተቀመጠ፡፡
\v 18 እነርሱም በምድረ በዳ በኩል ሄዱና ከኤዶምያስና ከሞዓብ ምድር ተመለሱ፣ በሞዓብም ምድር በምሥራቅ በኩል ሄዱ፣ በአርኖንም ማዶ ሰፈሩ፡፡ ነገር ግን ወደ ሞዓብ ክልል ውስጥ አልገቡም፣ አርኖን የሞዓብ ድንበር ነበረና፡፡
\s5
\v 19
እስራኤልም በሐሴቦን ውስጥ ገዥ ወደነበረው ወደ አሞራውያን ንጉሥ ወደ ሴዎን መልክተኞችን ላከ፤ እስራኤልም ‘እባክህ፣ በምድርህ በኩል ወደ ስፍራችን እንድናልፍ ፍቀድልን’ አለው፡፡
\v 20 ነገር ግን ሴዎን እስራኤል በድንበሩ እንዲያልፍ አላመነውም፡፡ ስለዚህ ሴዎን ሰራዊቱን ሁሉ ሰበሰበና ወደ ያሀጽ ተንቀሳቀሰ፣ በዚያም ከእስራኤል ጋር ተዋጋ፡፡
\s5
\v 21
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔርም ለእስራኤል በሴዎን ላይ ድል ሰጠውና ሕዝቡን ሁሉ በቁጥጥራቸው ስር እንዲሆኑ አሳልፎ ሰጣቸው፡፡ ስለዚህም እስራኤል በዚያች አገር ተቀምጠው የነበሩትን የአሞራውያንን አገር ሁሉ ወሰዱ፡፡
\v 22 በአሞራውያን ክልል ውስጥ የነበረውን ሁሉንም ነገር ወሰዱ፣ ከአርኖንም እስከ ያቦቅ ድረስ፣ ከምድረ በዳውም እስከ ዮርዳኖስ ድረስ፡፡
\s5
\v 23
ያንጊዜ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር አሞራውያንን ከሕዝቡ ከእስራኤል ፊት አስወጣቸው፣ ታዲያ አንተ አሁን ምድራቸውን ልትወስድ ይገባልን?
\v 24 አምላክህ ካሞሽ የሚሰጥህን ምድር አትወስድምን? ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካችን የሰጠንን ምድር ሁሉ እንወስዳለን፡፡
\v 25 አሁን አንተ ከሞዓብ ንጉሥ ከሴፎር ልጅ ከባላቅ በእውነት ትሻላለህን? እርሱ ከእስራኤል ጋር ከቶ ክርክር ነበረውን? ከእነርሱ ጋር ጦርነት አካሂዷልን?
\s5
\v 26
እስራኤል በሐሴቦንና በቀበሌዎችዋ፣ በአሮዔርና በቀበሌዎችዋ፣ በአርኖንም ዳርቻ ባሉት ከተሞች ሁሉ ለሦስት መቶ ዓመት ሲኖር በነበረበት ጊዜ፣ ለምን ታዲያ በዚያን ጊዜ መልሳችሁ አልወሰዳችኋቸውም ነበር?
\v 27 እኔ አልበደልሁህም ነገር ግን አንተ እኔን በመውጋት እየበደልከኝ ነው፡፡ ፈራጅ የሆነው እግዚአብሔር በእስራኤል ሰዎችና በአሞን ሰዎች መካከል ዛሬ ይፈርዳል፡፡
\v 28 ነገር ግን የአሞን ሰዎች ንጉሥ ዮፍታሔ የላከበትን ማስጠንቀቂያ አልተቀበለም፡፡
\s5
\v 29
ያን ጊዜ የእግዚአብሔር መንፈስ በዮፍታሔ ላይ መጣ፣ እርሱም በገለዓድና በምናሴ አለፈ፣ በገለዓድ ባለው ምጽጳም አለፈ፣ ከዚያም በገለዓድ ካለው ምጽጳ ወደ አሞን ሰዎች አለፈ፡፡
\v 30 ዮፍታሔም ለእግዚብሔር እንዲህ ሲል ስእለት ተሳለ፡- “በአሞንን ሰዎች ላይ ድልን ብትሰጠኝ፣
\v 31 ከአሞን ሰዎች በሰላም በተመለስሁ ጊዜ እኔን ሊያገኘኝ ከቤቴ በር የሚወጣው ማንኛውም ለእግዚአብሔር ይሆናል፣ እርሱንም ለሚቃጠል መሥዋዕት አቀርበዋለሁ፡፡
\s5
\v 32
ስለዚህ ዮፍታሔ እነርሱን ለመውጋት ወደ አሞን ሰዎች አለፈ፣ እግዚአብሔርም በእነርሱ ላይ ድል ሰጠው፡፡
\v 33 እርሱም ከአሮዔርም እስከ ሚኒት፣ እንደዚሁም እስከ አቤልክራሚም ድረስ ያሉ ሀያ ከተሞችን ወጋቸው፣ ታላቅ እልቂትም አደረሰባቸው፡፡ ስለዚህ የአሞን ሰዎች በእስራኤል ሰዎች ቁጥጥር ስር ሆኑ፡፡
\s5
\v 34
ዮፍታሄ ምጽጳ ወዳለው ቤቱ መጣ፣ በዚያም የእርሱ ልጅ ከበሮ ይዛ እያሸበሸበች ልታገኘው ወጣች፡፡ እርስዋም ብቸኛ ልጁ ነበረች፣ ከእርስዋ ሌላ ወንድ ልጅም ይሁን ሴት ልጅ አልነበረውም፡፡
\v 35 እርስዋንም ባየ ጊዜ፣ ልብሱን ቀደደ እንዲህም አለ፡- “ወይኔ! ልጄ ሆይ! በኀዘን አደቀቅሽኝ፣ በእኔ ላይ ጭንቅ ያመጣብኝ ሰው ሆንሽብኝ! ለእግዚአብሔር ስእለት ተስያለሁና፣ ቃሌን ማጠፍ በፍጹም አልችልም፡፡”
\s5
\v 36
እርስዋም እንዲህ አለችው፡- “አባቴ ሆይ፣ ለእግዚአብሔር ስእለት ተስለሃል፣ ቃል የገባኸውን ሁሉ በእኔ ላይ አድርግብኝ፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር በጠላቶችህ በአሞናውያን ላይ ተበቅሎልሃልና፡፡”
\v 37 አርስዋም ለአባትዋ እንዲህ አለች፡- “ይህ ቃል ለእኔ ይደረግልኝ፡፡ ይህንን አካባቢ እንድለቅና ወደ ታች ወደ ኮረብታዎቹ እንድወርድ፣ ከጓደኞቼም ጋር ስለ ድንግልናየ እንዳለቅስ ለሁለት ወራቶች ያህል ብቻየን እንድሆን ፍቀድልኝ፡፡
\s5
\v 38
እርሱም፣ “ሂጂ” አለ፡፡ ለሁለት ወራትም አሰናበታት፡፡ እርስዋም ትታው ሄደች፣ ከባልንጀሮችዋም ጋር ስለ ድንግልናዋ በኮረብታዎቹ ላይ አለቀሱ፡፡
\v 39 በሁለት ወር መጨረሻ ላይ ወደ አባትዋ ተመለሰች፣ እርሱም ቃል እንደገባው እንደ ስእለቱ አደረገባት፡፡ እርስዋም ከወንድ ጋር ተኝታ አታውቅም፣ ይህም በእስራኤል ዘንድ ልማድ ሆነ፣
\v 40 የእስራኤል ሴቶች ልጆች በየዓመቱ፣ ለአራት ቀናት፣ የገለዓዳዊውን የዮፍታሔን ሴት ልጅ ታሪክ እየተናገሩ ያስቡአታል፡፡
\s5
\c 12
\p
\v 1 ወደ ኤፍሬም ሰዎችም ጥሪ ደረሰ፤ በጻፎን በኩል ተሻግረው ዮፍታሔን፣ “ከአሞን ሕዝብ ጋር ለመዋጋት ስታልፍ ከአንተ ጋር እንድንሄድ ያልጠራኸን ለምድን ነው? ቤትህን በአንተ ላይ እናቃጥለዋለን” አሉት፡፡
\v 2 ዮፍታሔም እንዲህ አላቸው፣ “እኔና ሕዝቤ ከአሞን ሕዝብ ጋር በታላቅ ጦርነት ውስጥ ነበርን፡፡ በጠራኋችሁም ጊዜ ከእነርሱ አላዳናችሁኝም፡፡
\s5
\v 3
እናንተም እንዳላዳናችሁኝ ባየሁ ጊዜ፣ ሕይወቴን በራሴ ብርታት አስቀምጬ በአሞን ሕዝብ ላይ ለመዋጋት አለፍሁ፣ እግዚአብሔርም በእነርሱ ላይ ድል ሰጠኝ፡፡ ዛሬ እኔን ለመውጋት ለምን መጣችሁ?
\v 4 ዮፍታሔም የገለዓድን ሰዎች ሁሉ ሰበሰበና ከኤፍሬምም ጋር ተዋጋ፡፡ የገለዓድም ሰዎች የኤፍሬምን ሰዎች ወጓቸው ምክንቱም፣ “እናንተ ገለዓዳውያን በኤፍሬም ውስጥ ሸሽታችሁ የተጠጋችሁ፣ በኤፍሬምና በምናሴ ውስጥ ጥገኞች የሆናችሁ ናችሁ” ይሏቸው ነበርና፡፡
\s5
\v 5
ገለዓዳውያንም ወደ ኤፍሬም የሚወስደውን የዮርዳኖስን መሻገሪያ ያዙባቸው፡፡ አምልጦ የሚሸሽ የኤፍሬም ሰው፣ “ወንዙን ተሻግሬ ልለፍ” ባለ ጊዜ፣ የገለዓድ ሰዎች ደግሞ እንዲህ ይሉታል፣ “አንተ ኤፍሬማዊ ነህን? ” እርሱም፣ “አይደለሁም” ቢል፣
\v 6 እነርሱም “ሺቦሌት በል” ይሉታል፡፡ እርሱም “ሲቦሌት” ብሎ ከተናገረ (ምክንያቱም እርሱ ቃሉን አጥርቶ መናገር አይችልምና) ፣ ገለዓዳውያን እርሱን ይዘው በዮርዳኖስ መሻገሪያ ላይ ይገድሉታል፡፡ በዚያም ጊዜ አርባ ሁለት ሺህ ኤፍሬማውያን ተገደሉ፡፡
\s5
\v 7
ዮፍታሔም በእስራኤል ላይ ለስድስት ዓመት እንደ ፈራጅ አገለገለ፡፡ ከዚያም ገለዓዳዊውም ዮፍታሔ ሞተ፣ ከገለዓድ ከተሞችም በአንዱ ተቀበረ።
\s5
\v 8
ከእርሱም በኋላ የቤተ ልሔሙ ኢብጻን በእስራኤል ላይ እንደ ፈራጅ አገለገለ፡፡
\v 9 እርሱም ሠላሳ ወንዶች ልጆች ነበሩት፡፡ ሠላሳ ሴቶች ልጆችንም ወደ ውጭ በትዳር ለሌሎች ሰጠ፣ ሠላሳ ሴቶች ልጆችን ደግሞ ከሌሎች ሰዎች በትዳር ለወንድ ልጆቹ አመጣ። በእስራኤልም ላይ ለሰባት ዓመት ፈረደ።
\s5
\v 10
ኢብጻንም ሞተ፣ በቤተ ልሔምም ተቀበረ፡፡
\v 11 ከእርሱም በኋላ ዛብሎናዊው ኤሎም በእስራኤል ላይ እንደ ፈራጅ አገለገለ፡፡ እርሱም በእስራኤል ላይ ለአሥር ዓመት ፈረደ፡፡
\v 12 ዛብሎናዊውም ኤሎም ሞተ፣ በዛብሎንም ምድር ባለችው በኤሎም ተቀበረ፡፡
\s5
\v 13
ከእርሱም በኋላ የጲርዓቶናዊው የሂሌል ልጅ ዓብዶን በእስራኤል ላይ እንደ ፈራጅ አገለገለ፡፡
\v 14 እርሱም አርባ ወንዶች ልጆችና ሠላሳ ወንዶች የልጅ ልጆች ነበሩት፡፡ በሰባ አህያዎች ላይ ይጋልቡ ነበር፣ እርሱም በእስራኤል ላይ ለስምንት ዓመት ፈረደ፡፡
\v 15 የጲርዓቶናዊውም የሂሌል ልጅ ዓብዶን ሞተ፣ በተራራማውም በአማሌቃውያን አገር በኮረብታማው በኤፍሬም አገር ውስጥ ባለችው በጲርዓቶን ውስጥ ተቀበረ፡፡
\s5
\c 13
\p
\v 1
የእስራኤልም ሕዝብ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ የሆነውን ስራ እንደ ገና ሠሩ፣ እርሱም ፍልስጥኤማውያን በእነርሱ ላይ ለአርባ ዓመት እንዲገዙ ፈቀደላቸው፡፡
\v 2 ከዳን ቤተሰብ የሆነ ስሙም ማኑሄ የሚባል አንድ የጾርዓ ሰው ነበረ፡፡ ሚስቱም መካን ስለነበረች ልጅ አልወለደችም፡፡
\s5
\v 3 የእግዚአብሔርም መልአክ ለሴቲቱ ተገልጦ እንዲህ አላት፣ “ተመልከቺ፣ አንቺ መካን ነበርሽ፣ ልጅም አልወለድሽም፣ ነገር ግን ትፀንሻለሽ፣ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፡፡
\v 4 አሁንም የወይን ጠጅ ወይም የሚያሰክር ጠንካራ መጠጥ እንዳትጠጪ ተጠንቀቂ፣ ሕጉ ርኩስ እንደሆነ የገለጸውን ማንኛውንም ምግብ አትብዪ፡፡
\v 5 ተመልከቺ፣ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፡፡ ልጁ ከአንቺ ማኅፀን ጀምሮ ለእግዚአብሔር የተለየ ናዝራዊ ስለሚሆን በራሱ ላይ ምላጭ አይድረስበት፡፡ እርሱም እስራኤልን ከፍልስጥኤማውያን ጉልበት ማዳን ይጀምራል፡፡
\s5
\v 6 የዚያን ጊዜ ሴቲቱ ወደ ባልዋ መጥታ እንዲህ ብላ ነገረችው፣ “አንድ የእግዚአብሔር ሰው ወደ እኔ መጣ፣ መልኩም እንደ እግዚአብሔር መልአክ የሚመስል ነበረ፣ በጣምም አስደነገጠኝ፡፡ ከወዴት እንደ መጣ አልጠየቅሁትም፣ እርሱም ስሙን አልነገረኝም፡፡
\v 7 እርሱም እንዲህ አለኝ፣ ‘ተመልከቺ! ትፀንሻለሽ፣ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፡፡ ስለዚህ ልጁ ከአንቺ ማኅፀን ጀምሮ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ ለእግዚአብሔር የተለየ ናዝራዊ ስለሚሆን የወይን ጠጅ ወይም የሚያሰክር ጠንካራ መጠጥ እንዳትጠጪ፣ ሕጉ ርኩስ እንደሆነ የገለጸውን ማንኛውንም ምግብ አትብዪ፡፡’”
\s5
\v 8
ከዚያም ማኑሄ ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ጸለየ፣ “ጌታ ሆይ፣ አሁን በቅርቡ ለሚወለደው ልጅ ምን ማድረግ እንዳለብን እንዲያስተምረን እባክህ የላክኸው የእግዚአብሔር ሰው እንደገና ወደ እኛ ይምጣ፡፡”
\v 9 እግዚአብሔርም የማኑሄን ጸሎት መለሰ፣ የእግዚአብሔርም መልአክ እንደ ገና ወደ ሴቲቱ በእርሻ ውስጥ ተቀምጣ ሳለች መጣ፡፡ ነገር ግን ባልዋ ማኑሄ ከእርስዋ ጋር አልነበረም፡፡
\s5
\v 10 ስለዚህ ሴቲቱም ፈጥና ሮጠችና ለባልዋ ነገረችው፣ “ተመልከት! በሌላኛው ቀን ወደ እኔ የመጣው ሰው እንደገና ተገለጠልኝ፡፡”
\v 11 ማኑሄም ተነሳና ሚስቱን ተከተላት፡፡ ወደ ሰውዮውም በመጣ ጊዜ እንዲህ አለው፣ “ከሚስቴ ጋር የተነጋገርህ ሰው አንተ ነህን? ” ሰውየውም፣ “እኔ ነኝ” አለው፡፡
\s5
\v 12 ስለዚህ ማኑሄ እንዲህ አለ፣ “አሁንም ቃሎችህ እውነት ይሁኑ፡፡ ነገር ግን ልጁ የሚመራው በምንድን ነው፣ እኛስ ለእርሱ የምንሰራው ምንድን ነው? ”
\v 13 የእግዚአብሔርም መልአክ ለማኑሄ እንዲህ አለው፣ “እርስዋ የነገርኋትን ነገር ሁሉ በጥንቃቄ ማድረግ አለባት፡፡
\v 14 ከወይን ከሚወጣው ማንኛውንም ነገር አትብላ፣ የወይን ጠጅ ወይም የሚያሰክር ሌላ ጠንካራ መጠጥ አትጠጣ፤ ሕጉ ርኩስ ነው ብሎ የገለጸውን ማንኛውንም ምግብ አትብላ፡፡ እኔ እንድታደርገው ያዘዝኋትን ማንኛውንም ነገር መታዘዝ አለባት፡፡
\s5
\v 15 ማኑሄም ለእግዚአብሔር መልአክ እንዲህ አለው፣ “ለአንተ የፍየል ጠቦት ለማዘጋጀት ጊዜ እናገኝ ዘንድ፣ እባክህ ለአጭር ጊዜ ቆይ፡፡”
\v 16 የእግዚአብሔርም መልአክ ለማኑሄ እንዲህ አለው፣ “ብቆይም እንኳ፣ መብልህን አልበላም፡፡ነገር ግን የሚቃጠል መሥዋዕት የምታዘጋጅ ከሆነ፣ ያንን ለእግዚአብሔር አቅርበው፡፡” ማኑሄ የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን አላወቀም ነበር፡፡
\s5
\v 17
ማኑሄም ለእግዚአብሔር መልአክ እንዲህ አለው፣ “የተናገርሃቸው ቃሎች እውነት በሆኑ ጊዜ እናከብርህ ዘንድ ስምህ ማን ነው? ”
\v 18 የእግዚአብሔርም መልአክ እንዲህ አለው፣ “ስሜን ለምን ትጠይቃለህ? ስሜ ድንቅ ነው!”
\s5
\v 19
ስለዚህ ማኑሄም የፍየሉን ጠቦት ከእህል ቍርባን ጋር ወሰደና በድንጋይ ላይ ለእግዚአብሔር አቀረበው፡፡ ማኑሄና ሚስቱ እያዩ እርሱ አስደናቂ ነገር አደረገ፡፡
\v 20 ነበልባሉም ከመሠዊያው ላይ ወደ ሰማይ በወጣ ጊዜ፣ የእግዚአብሔር መልአክ በመሠዊያው ነበልባል ውስጥ ወደ ላይ ዐረገ፡፡ ማኑሄና ሚስቱም ይህን ተመለከቱና በግምባራቸው ምድር ላይ ተደፉ፡፡
\s5
\v 21 የእግዚአብሔርም መልአክ ላማኑሄ ወይም ለሚስቱ እንደገና አልተገለጠም፡፡ ያን ጊዜም ማኑሄ የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን አወቀ፡፡
\v 22 ማኑሄም ለሚስቱ እንዲህ አላት፣ “እግዚአብሔርን ስላየን በእርግጠኝነት እንሞታለን፡፡”
\s5
\v 23 ነገር ግን ሚስቱ እንዲህ አለችው፣ “እግዚአብሔር ሊገድለን ቢፈልግ ኖሮ፣ ለእርሱ ያቀረብነውን የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን ባልተቀበለን ነበር፡፡ ይህንም ነገር ሁሉ ባላሳየን ነበር፣ በዚህ ጊዜ እንዲህ ያሉ ነገሮችንም እንድንሰማ ባላደረገን ነበር፡፡”
\s5
\v 24 ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ሴቲቱ ወንድ ልጅ ወለደች፣ ስሙንም ሳምሶን ብላ ጠራችው፡፡ ልጁም አደገ እግዚአብሔርም ባረከው፡፡
\v 25 የእግዚአብሔርም መንፈስ እርሱን በጾርዓና በኤሽታኦል መካከል ባለው በዳን ሰፈር ውስጥ ያነቃቃው ጀመር፡፡
\s5
\c 14
\p
\v 1
ሳምሶንም ወደ ተምና ወረደ፣ በዚያም ከፍልስጥኤማውያን ሴቶች ልጆች አንዲት ሴት አየ፡፡
\v 2 ከዚያ በተመለሰ ጊዜ፣ ለአባቱና ለእናቱ እንዲህ ሲል ነገራቸው፣ “በተምና ከፍልስጥኤማውያን ሴቶች ልጆች መካከል አንዲት ሴት አየሁ፡፡ ሚስቴ እንድትሆነኝ አሁን እርስዋን አምጡልኝና አጋቡኝ፡፡
\s5
\v 3
ነገር ግን እንዲህ አሉት፣ “ከዘመዶችህ ሴቶች ልጆች ወይም ከሕዝባችን ሁሉ መካከል ሴት የለምን? ካልተገረዙት ከፍልስጥኤማውያን ሚስት ለመውሰድ ትሄሄዳለህን? ” ሳምሶንም ለአባቱ እንዲህ አለው፣ “እርስዋን አምጣልኝ፣ እርስዋን ባየኋት ጊዜ ደስ አሰኝታኛለችና፡፡”
\v 4 ነገር ግን አባቱና እናቱ ይህ ነገር የመጣው ከእግዚአብሔር እንደሆነ አላወቁም፣ እርሱ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ግጭት ለመፍጠር ይፈልግ ነበርና፡፡ በዚያን ጊዜ ፍልስጥኤማውያን እስራኤልን ይገዙ ነበርና፡፡
\s5
\v 5 ከዚያም ሳምሶን ከአባቱና ከእናቱ ጋር ወደ ተምና ወረዱ፣ እነርሱም በተምና ወዳለው ወደ ወይኑ አትክልት ስፍራ መጡ፡፡ ከዚያም ከአንበሳ ደቦሎች መካከል አንዱ ተነስቶ መጣና በእርሱ ላይ አገሳበት፡፡
\v 6 የእግዚአብሔር መንፈስ በድንገት በእርሱ ላይ ወረደ፣ ትንሽ የፍየል ጠቦት እንደሚቆራርጥ እንዲሁ አንበሳውን በቀላሉ ቈራረጠው፣ በእጁም ምንም ነገር አልያዘም ነበር፡፡ ነገር ግን ያደረገውን ነገር ለአባቱ ወይም ለእናቱ አልነገራቸውም፡፡
\s5
\v 7
እርሱም ሄደና ከሴቲቱ ጋር ተነጋገረ፣ እርስዋንም ባያት ጊዜ ሳምሶንን ደስ አሰኘችው፡፡
\v 8 ከጥቂትም ቀን በኋላ ሊያገባት ተመለሰ፣ የአንበሳውንም በድን ያይ ዘንድ ከመንገድ ዘወር አለ፡፡ በአንበሳ በድን ትራፊ ውስጥ የንብ መንጋ ሰፍሮበት ነበር፣ ማርም ነበረበት፡፡
\v 9 ማሩንም በእጁ ወስዶ መንገድ ለመንገድ እየበላ ሄደ፡፡ ወደ አባቱና ወደ እናቱ በመጣ ጊዜ፣ ለእነርሱም ሰጣቸውና እነርሱም በሉ፡፡ ነገር ግን ማሩን የወሰደው ከአንበሳ በድን ትራፊ ውስጥ እንደ ሆነ አልነገራቸውም፡፡
\s5
\v 10 የሳምሶን አባትም ሴቲቱ ወደ ነበረችበት ወረደ፣ ሳምሶንም በዚያ ግብዣ አደረገ፣ ይህን ማድረግ የወጣት ወንዶች ወግ ነበርና፡፡
\v 11 የእርስዋ ዘመዶች ባዩት ጊዜ፣ ከእርሱ ጋር ይሆኑ ዘንድ ሌሎች ሠላሳ ጓደኞች አመጡለት፡፡
\s5
\v 12 ሳምሶንም ለእነርሱ እንዲህ አላቸው፣ “አሁን እንቆቅልሽ ልንገራችሁ፡፡ ከእናንተ ውስጥ አንዱ ሰው እንቆቅልሹን ማግኘት ቢችልና በሰባቱ የግብዣ ቀኖች ውስጥ መልሱን ቢነግረኝ፣ ሠላሳ የቀጭን በፍታ ቀሚስና ሠላሳ የክት ልብስ እሰጠዋለሁ፡፡
\v 13 ነገር ግን እናንተ መልሱን ልትነግሩኝ ካልቻላችሁ፣ ሠላሳ የቀጭን በፍታ ቀሚስና ሠላሳ የክት ልብስ ትሰጡኛላችሁ፡፡” እነርሱም እንዲህ አሉት፣ “እንሰማው ዘንድ እንቆቅልሽህን ንገረን፡፡”
\s5
\v 14 እርሱም እንዲህ አላቸው፣ “ከበላተኛው ውስጥ መብል ወጣ፤ ከብርቱም ውስጥ ጣፋጭ ወጣ፡፡” ነገር ግን የእርሱ እንግዶች በሦስት ቀን ውስጥ መልሱን ሊያገኙት አልቻሉም፡፡
\s5
\v 15 በአራተኛውም ቀን ለሳምሶን ሚስት እንዲህ አሏት፣ “የእንቈቅልሹን መልስ እንዲነግረን ባልሽን አግባቢልን፣ አለዚያ ግን እንቺንና የአባትሽን ቤት በእሳት እናቃጥላለን፡፡ ወደዚህ የጠራችሁን ድሃ ልታደርጉን ነውን፡፡”
\s5
\v 16
የሳምሶን ሚስት በፊቱ ማልቀስ ጀመረች፤ እንዲህም አለችው፣ “ይህን ሁሉ ያደረግኸው እኔን ስለምትጠላኝ ነው! አንተ አትወደኝም፡፡ ከሕዝቤ ውስጥ ለአንዳንዶቹ እንቈቅልሽ ነግረሃቸዋል፣ ነገር ግን መልሱን ለእኔ አልነገርኸኝም፡፡” ሳምሶንም እንዲህ አላት፣ “ወደዚህ ተመልከቺ፣ ለአባቴና ለእናቴ ካልነገርኋቸው፣ ለአንቺ ልነግርሽ ይገባልን? ”
\v 17 ግብዣቸው በሚቆይበት በሰባቱም ቀናት ውስጥ በፊቱ አለቀሰች፡፡ መልሱንም በሰባተኛው ቀን ነገራት ምክንቱም እጅግ በጣም አጥብቃ ስለነዘነዘችው ነው፡፡ መልሱንም ለሕዝቧ ዘመዶች ነገረቻቸው፡፡
\s5
\v 18 በሰባተኛው ቀን ፀሐይ ከመግባትዋ በፊት የከተማይቱ ሰዎች እንዲህ አሉት፣ “ከማር የበለጠ የሚጣፍጥ ምንድን ነው? ከአንበሳስ የበለጠ የሚበረታ ምንድን ነው? ” ሳምሶንም እንዲህ አላቸው፣ “በጊደሬ ባታርሱ ኖሮ፣ ለእንቈቅልሼ መልስ ባላገኛችሁ ነበር፡፡”
\s5
\v 19 በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔር መንፈስ በድንገት በሳምሶን ላይ በኃይል ወረደ፡፡ ሳምሶንም ወደ አስቀሎና ወረደና ከሕዝቡ መካከል ሠላሳ ሰዎችን ገደለ፡፡ እርሱም የለበሱትን ሁሉ ከገፈፈ በኋላ ልብሳቸውን በሙሉ ወስዶ እንቈቅልሹን ለመለሱለት ሰዎች ሰጣቸው፡፡ እርሱም በጣም ተናደደና ወደ አባቱ ቤት ወጣ፡፡
\v 20 የሳምሶን ሚስት ግን በጣም ቅርብ ለሆነው ጓደኛው ተሰጠች፡፡
\s5
\c 15
\p
\v 1 ከጥቂት ቀናትም በኋላ በስንዴ መከር ጊዜ፣ ሳምሶን የፍየል ጠቦት ይዞ ሚስቱን ሊጠይቅ ሄደ፡፡ ለራሱም እንዲህ አለ፣ “ወደ ሚስቴ ወደ ጫጉላው ቤት ልግባ፡፡” ነገር ግን አባትዋ ወደ ውስጥ እንዳይገባ ከለከለው፡፡
\v 2 አባትዋም እንዲህ አለ፣ “እኔ በእርግጠኝነት የጠላሃት መሰለኝ፣ ስለዚህም ለጓደኛህ ሰጠኋት፡፡የእርስዋ ታናሽ እኅት ከርስዋ የበለጠች ቆንጆ ናት፣ አይደለችም እንዴ? በእርስዋ ፋንታ ታናሽዋን ውሰዳት፡፡”
\s5
\v 3
ሳምሶንም ለእነርሱ እንዲህ አላቸው፣ “ከእንግዲህ ወዲህ በፍልስጥኤማውያን ላይ ጉዳት ባደረስሁባቸው ጊዜ እኔ ንጹሕ ነኝ፡፡”
\v 4 ሳምሶንም ሄደና ሦስት መቶ ቀበሮዎች ያዘ፣ ሁለት ሁለቱንም ቀበሮዎች በአንድ ላይ በጅራታቸው አሰራቸው፡፡ ከዚያም ችቦዎችን ወስዶ በእያንዳንዱ ጥንድ በሁለቱም ጅራቶች መካከል አሰራቸው፡፡
\s5
\v 5
ችቦውንም በእሳት ባቀጣጠለው ጊዜ፣ ቀበሮዎቹን በቆመው በፍልስጥኤማውያን እህል መካከል እንዲሄዱ አደረጋቸው፣ የእህሉን ነዶና በእርሻ ውስጥ የቆመውንም እህል፣ ከወይኑ አትክልት ስፍራና ከወይራውም ተክል ጋር አቃጠሉት፡፡
\v 6 ፍልስጥኤማውያንም እንዲህ በማለት ጠየቁ፣ “ይህን ያደረገው ማን ነው? ” እነርሱም “ይህን ያደረገው የተምናዊው አማች ሳምሶን ነው፣ ምክንያቱም ተምናዊው የሳምሶንን ሚስት ወስዶ ለጓደኛው ሰጥቶአታልና” አሉ፡፡ ፍልስጥኤማያንም ሄደው እርስዋንና አባትዋን በእሳት አቃጠሉ፡፡
\s5
\v 7 ሳምሶንም “እናንተ ይህንን ካደረጋችሁ፣ እኔ እበቀላችኋለሁ፣ እኔ የማርፈው ይህን ካደረግሁ በኋላ ነው” አላቸው፡፡
\v 8 እርሱም ዳሌአቸውንና ጭናቸውን ቆራረጣቸውና በታላቅ አገዳደል ገደላቸው፡፡ ከዚያም ወርዶ በኤጣም ዓለት ባለው ዋሻ ውስጥ ተቀመጠ፡፡
\s5
\v 9 የዚያን ጊዜ ፍልስጥኤማውያን ወጡና በይሁዳ ጦርነት ለማካሄድ ተዘጋጁ፣ ሰራዊታቸውንም በሌሒ ውስጥ አሰፈሩ፡፡
\v 10 የይሁዳም ሰዎች እንዲህ አሉ፣ “እኛን ለመውጋት የመጣችሁት ለምንድን ነው? ” እነርሱም እንዲህ አሉ፣ “የምንወጋችሁ ሳምሶንን ለመያዝ ነው፣ እርሱ በእኛ ላይ እንዳደረገው እኛም በእርሱ ላይ ልናደርግበት ነው፡፡”
\s5
\v 11 ሦስት ሺህ የይሁዳ ሰዎችም በኤጣም ዓለት ወዳለው ዋሻ ወረዱና፣ ለሳምሶን እንዲህ አሉት፣ “ፍልስጥኤማውያን በእኛ ላይ ገዢዎች እንደሆኑ አታውቅምን? ይህ በእኛ ላይ ያደረግኸው ነገር ምንድን ነው? ” ሳምሶንም ለእነርሱ እንዲህ አላቸው፣ “እነርሱ በእኔ ላይ አደረጉብኝ፣ እኔም በእነርሱ ላይ አደረግሁባቸው፡፡”
\s5
\v 12
እነርሱም ለሳምሶን እንዲህ አሉት፣ “አንተን አስረን ለፍልስጥኤማውያን እጅ አሳልፈን ልንሰጥህ መጥተናል፡፡” ሳምሶንም እንዲህ አላቸው፣ “እናንተ ራሳችሁ እንደማትገድሉኝ ማሉልኝ፡፡”
\v 13 እነርሱም እንዲህ አሉት፣ “አንገድልህም፣ በገመድ አስረን ብቻ ለእነርሱ አሳልፈን እንሰጥሃለን፡፡ እንደማንገድልህ ቃል እንገባልሃለን፡፡” ከዚያም በሁለት አዲስ ገመዶች አሰሩትና ከዓለቱ ውስጥ አወጡት፡፡
\s5
\v 14 ወደ ሌሒ በመጣ ጊዜ፣ ፍልስጥኤማውያን እየጮሁ መጡ፣ አገኙትም፡፡ የዚያን ጊዜ የእግዚአብሔር መንፈስ በእርሱ ላይ በኃይል ወረደበት፡፡ ክንዶቹ የታሰሩበት ገመዶችም በእሳት እንደ ተቃጠለ የተልባ እግር ፈትል ከእጆቹ ላይ ወደቁ፡፡
\s5
\v 15 ሳምሶንም አዲስ የአህያ መንጋጋ አገኘ፣ እጁንም ዘርግቶ አነሳውና በእርሱ አንድ ሺህ ሰዎች ገደለ፡፡
\v 16 ሳምሶንም እንዲህ አለ፣ “በአህያ መንጋጋ ክምር በክምር ላይ አድርጌአቸዋለሁ፣ በአህያ መንጋጋ አንድ ሺህ ሰዎች ገድያለሁ፡፡”
\s5
\v 17 ሳምሶንም መናገሩን በፈጸመ ጊዜ፣ የአህያ መንጋጋውን ከእጁ ጣለው፣ ያም ስፍራ ራማትሌሒ ተብሎ ተጠራ፡፡
\v 18 ሳምሶን በጣም ተጠምቶ ነበርና ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ጮኸ፣ “አንተ ይህን ታላቅ ድል ለአገልጋይህ ሰጥተሃል፣ ነገር ግን አሁን በጥም እሞታለሁ፣ ባልተገረዙትም ሰዎች እጅ እወድቃለሁ፡፡”
\s5
\v 19 እግዚአብሔርም በሌሒ ያለውን ክፍት ስፍራ ሰንጥቆ ከፈተው፣ ከእርሱም ውኃ ወጣ፡፡እርሱም በጠጣ ጊዜ፣ ብርታቱ ተመለሰና ተጠናከረ፡፡ ስለዚህ የዚያ ቦታ ስም ዓይንሀቆሬ ተብሎ ተጠራ፣ እስከ ዛሬ ድረስ በሌሒ ይገኛል፡፡
\v 20 ሳምሶን በፍልስጥኤማውያን ዘመን በእስራኤል ላይ ለሀያ ዓመት ፈረደ፡፡
\s5
\c 16
\p
\v 1
ሳምሶን ወደ ጋዛ ሄደና በዚያ ዝሙት አዳሪ ሴት አየ፣ ከእርስዋም ጋር ወደ አልጋ ሄደ፡፡
\v 2 የጋዛ ሰዎችም “ሳምሶን ወደዚህ መጥቶአል” የሚል ወሬ ሰሙ፡፡ የጋዛ ሰዎች ስፍራውን ከበቡትና ሌሊቱን ሁሉ ተደብቀው በከተማይቱ በር ጠበቁት፡፡ ሌሊቱን ሁሉ ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ አላደረጉም፡፡ እንዲህ ብለዋልና፣ “እስኪነጋ ድረስ እንጠብቀው፣ ከዚያም እንገድለዋለን፡፡”
\s5
\v 3 ሳምሶንም እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ በአልጋ ላይ ተኛ፡፡ እኩለ ሌሊትም በሆነ ጊዜ ተነሳና የከተማይቱን በር መዝጊያና ሁለቱን መቃኖች ያዘ፡፡ እነርሱንም ከመወርወሪያው ጋር ከመሬት ነቀላቸው፣ በትከሻውም ላይ አደረጋቸው፣ በኬብሮንም ፊት ለፊት ወዳለው ኮረብታ ራስ ላይ ተሸክሞት ወጣ፡፡
\s5
\v 4
ከዚህ በኋላ ሳምሶን በሶሬቅ ሸለቆ የምትኖር አንዲት ሴት ወደደ፡፡ ስምዋም ደሊላ ይባል ነበር፡፡
\v 5 የፍልስጥኤማውያንም አለቆች ወደ እርስዋ መጡና እንዲህ አሏት፣ “እርሱን ለማዋረድ እናስረው ዘንድ በእርሱ ያለው ታላቅ ኃይል የት እንደሆነና በምን መንገድ እርሱን ማሸነፍ እንደምንችል እንዲያሳይሽ ሳምሶንን አባብዪው፡፡ ይህንን አድርጊልን፣ እኛም እያንዳንዳችን 1, 100 ብር እንሰጥሻለን፡፡
\s5
\v 6
ደሊላም ለሳምሶን እንዲህ አለችው፣ “እባክህ፣ እንዲህ በጣም ብርቱ የሆንከው እንዴት እንደሆነ ንገረኝ፣ በቁጥጥር ስር መዋል እንድትችል ሰው ሊያስርህ የሚችለው እንዴት ነው?
\v 7 ሳምሶንም እንዲህ አላት፣ “ባልደረቁ ሰባት እርጥብ ጠፍሮች ቢያስሩኝ፣ እደክማለሁ፣ እንደ ማንኛውም ሰውም እሆናለሁ፡፡”
\s5
\v 8 የፍልስጥኤማውያን አለቆችም ያልደረቁ ሰባት እርጥብ ጠፍሮች አመጡላት፣ እርስዋም ሳምሶንን በእነርሱ አሰረችው፡፡
\v 9 በዚህን ጊዜ በጓዳዋ ውስጥ ሰዎች በምስጢር ተደብቀው ይጠብቁ ነበር፡፡ እርስዋም፣ “ሳምሶን፣ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ” አለችው፡፡ ነገር ግን የተልባ እግር ፈትል እሳት በነካው ጊዜ እንደሚበጣጠስ ጠፍሩን በጣጠሰው፡፡ እነርሱም የብርታቱ ምስጢር ምን እንደሆነ አላወቁም፡፡
\s5
\v 10
ከዚያም ደሊላ ሳምሶንን እንዲህ አለችው፣ “አንተ እኔን እንዴት እንዳታለልኸኝ ግልጽ ሆኗል፣ ሐሰትንም ነገርኸኝ፡፡ እባክህ፣ እንዴት እንደምትታሰር ንገረኝ፡፡”
\v 11 እርሱም እንዲህ አላት፣ “ለሥራ ጥቅም ላይ ፈጽሞ ባልዋሉ በአዲስ ገመዶች ቢያስሩኝ፣ እደክማለሁ፣ እንደ ማንኛውም ሰው እሆናለሁ፡፡”
\v 12 ስለዚህ ደሊላ አዲስ ገመዶች ወሰደችና በእነርሱ አሰረችው፣ እንዲህም አለችው፣ “ሳምሶን፣ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ፡፡” ተደብቀው ሲጠብቁ የነበሩት ሰዎች በጓዳዋ ነበሩ፡፡ ነገር ግን ሳምሶን ገመዶቹን እንደ ፈትል ክር ከክንዶቹ በጣጠሰው፡፡
\s5
\v 13
ደሊላም ሳምሶንን እንዲህ አለችው፣ “እስከ አሁን ድረስ አታልለኸኛልና የነገርኸኝም ውሸት ነው፡፡ አንተን ማሰር የሚቻለው እንዴት እንደሆነ ንገረኝ፡፡” ሳምሶንም እንዲህ አላት፣ “የራሴን ጠጕር ሰባቱን ጕንጕን ከድር ጋር ጎንጉነሽ በችካል ብትቸክዪው፣ እንደ ሌላ ሰው እሆናለሁ፡፡”
\v 14 እርሱም በተኛ ጊዜ፣ ደሊላ የራሱን ጠጕር ሰባቱን ጕንጕን ከድሩ ጋር ጐነጐነችው፣ በችካልም ቸከለችውና፣ እንዲህ አለችው፣ “ሳምሶን፣ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ! ” እርሱም ከእንቅልፉ ነቃና ችካሉን ከነቆንዳላውና ከነድሩ ነቀለው፡፡
\s5
\v 15
እርስዋም እንዲህ አለችው፣ “ምስጢርህን ለእኔ ሳትነግረኝ ‘እወድሻለሁ’ ልትለኝ እንዴት ትችላለህ? ሦስት ጊዜ ቀለድህብኝ፣ እንዲህ ዓይነቱን ታላቅ ኃይል እንዴት ሊኖርህ እንደቻለ አልነገርኸኝም፡፡”
\v 16 ሞት እስኪመኝ ድረስ ዕለት ዕለት በቃሎችዋ እጅግ በጣም ጨቀጨቀችው፣ ከመጠን በላይም ጫና አደረገችበት፡፡
\s5
\v 17
ስለዚህ ሳምሶን ሁሉንም ነገር ነገራትና እንዲህ አላት፣ “ከእናቴ ማኅፀን ጀምሬ ለእግዚአብሔር ናዝራዊ ሆኜ ስለተለየሁ በራሴ ላይ ምላጭ ደርሶና ጸጉሬን ተላጭቼ አላውቅም፡፡ የራሴን ጸጕር ብላጭ ኃይሌ ከእኔ ይሄዳል፣ እደክማለሁም እንደ ማንኛውም ሰው እሆናለሁ፡፡”
\s5
\v 18
ደሊላም ስለ ሁሉ ነገር እውነቱን እንደነገራት ባየች ጊዜ፣ ሰዎች ላከችና የፍልስጥኤማውያንን አለቆች ጠራች፣ እንዲህም አለቻቸው፣ “ሁሉንም ነገር ነግሮኛልና እንደገና ኑ፡፡” የዚያን ጊዜ የፍልስጥኤማውያን አለቆች ብሩን በእጃቸው ይዘው ወደ እርስዋ ሄዱ፡፡
\v 19 እርስዋም በጭኗ ላይ እንዲተኛ አደረገችው፡፡ ሰባቱን የራሱን ጕንጕን እንዲላጨው አንድ ሰው ጠራች፣ ኃይሉ ስለተለየው እርስዋ በቁጥጥሯ ስር ልታደርገው ጀመረች፡፡
\s5
\v 20
እርስዋም፣ “ሳምሶን፣ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ! ” አለችው፡፡ እርሱም ከእንቅልፉ ነቅቶ እንዲህ አለ፣ “እንደ ሌላው ጊዜ እወጣለሁ፣ ራሴንም ነጻ አወጣለሁ፡፡” ነገር ግን እግዚአብሔር እንደ ተወው አላወቀም፡፡
\v 21 ፍልስጥኤማውያንም ያዙትና ዓይኖቹን አወጡት፡፡ ወደ ጋዛም ወሰዱትና በናስ ሰንሰለት አሰሩት፡፡ በእስር ቤትም ውስጥ ሆኖ እህል ይፈጭ ነበር፡፡
\v 22 ነገር ግን ከተላጨ በኋላ የራሱ ጠጕር እንደገና ያድግ ጀመር፡፡
\s5
\v 23
የፍልስጥኤማውያንም አለቆች ለአምላካቸው ለዳጎን ታላቅ መሥዋዕት ያቀርቡ ዘንድ፣ ደስም ይላቸው ዘንድ በአንድ ላይ ተሰበሰቡ፡፡ እነርሱ “አምላካችን ጠላታችንን ሳምሶንን አሸንፏል፣ በእጃችን አሳልፎ ሰጥቶናል” ብለዋልና፡፡
\v 24 ሕዝቡም እርሱን ባዩት ጊዜ አምላካቸውን አመሰገኑ፣ እንዲህ ብለዋልና፣ “አገራችንን ያጠፋውን፣ ከእኛም ብዙ ሰው የገደለውን ጠላታችንን አምላካችን አሸነፈው፣ በእጃችንም አሳልፎ ሰጠው፡፡”
\s5
\v 25
እጅግ ደስ ባላቸው ጊዜ፣ እንዲህ አሉ፣ “እንዲያስቀን ሳምሶንን ጥሩት፡፡” ሳምሶንን ከእስር ቤት ጠሩትና እንዲስቁ አደረጋቸው፡፡ በምሰሶና በምሰሶ መካከል እንዲቆም አደረጉት፡፡
\v 26 ሳምሶንም እጁን የያዘውን ልጅ፣ “እደገፍባቸው ዘንድ ሕንጻውን የደገፉትን ምሰሶዎች እንድነካቸው አስጠጋኝ” አለው፡፡
\s5
\v 27
በዚያን ጊዜ ቤቱ በወንዶችና በሴቶች ተሞልቶ ነበር፡፡ የፍልስጥኤም አለቆች ሁሉ በዚያ ነበሩ፡፡ ሳምሶን እነርሱን ሲያዝናናቸው ይመለከቱ የነበሩ ሦስት ሺህ የሚያህሉ ወንዶችና ሴቶች በጣራው ላይ ነበሩ፡፡
\s5
\v 28
ሳምሶንም ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ጮኸ፣ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፣ እንደገና አስበኝ! አምላኬ ሆይ፣ ሁለት ዓይኖቼን ስላወጡ ፍልስጥኤማውያንን አሁን በአንድ ምት እንድበቀል፣ እባክህ፣ ይህን አንድ ጊዜ ብቻ አበርታኝ፡፡”
\v 29 ሳምሶንም ሕንጻው ተደግፎባቸው የነበሩትን ሁለቱን መካከለኞች ምሰሶዎች ጠምጥሞ ያዘ፣ አንዱን ምሰሶ በቀኝ እጁ ሌላውን ደግሞ በግራ እጁ ይዞ በእነርሱ ላይ ተደገፈ፡፡
\s5
\v 30
ሳምሶንም እንዲህ አለ፣ “ከፍልስጥኤማውያን ጋር ልሙት! ” በሙሉ ኃይሉ ገፋው፣ ሕንጻውም በውስጡ በነበሩት አለቆችና በሕዝቡም ሁሉ ላይ ወደቀ፡፡ ስለዚህ እርሱ በሞተ ጊዜ የገደላቸው ሰዎች በሕይወት ሳለ ከገደላቸው ይልቅ የበለጡ ነበሩ፡፡
\v 31 የዚያን ጊዜ ወንድሞቹና የአባቱ ቤተ ሰቦች በሙሉ ወረዱ፣ እርሱንም ይዘው ወሰዱት፣ መልሰው አመጡትና በጾርዓና በኤሽታኦል መካከል ባለው በአባቱ በማኑሄ መቃብር ውስጥ ቀበሩት፡፡ ሳምሶን በእስራኤል ላይ ለሀያ ዓመት ፈረደ፡፡
\s5
\c 17
\p
\v 1 በኮረብታማውም በኤፍሬም አገር አንድ ሰው ነበር፣ ስሙም ሚካ ይባላል፡፡
\v 2 ለእናቱም እንዲህ አላት፣ “ከአንቺ ዘንድ ተወስዶ የነበረው 1, 100 ብር፣ የእርግማን ንግግር የተናገርሽበትና እኔም የሰማሁት እነሆ እዚህ አለ! ብሩ በእኔ ዘንድ አለ፡፡ እኔ ሰርቄዋለሁ! ” እናቱም እንዲህ አለች፣ “ልጄ ሆይ፣ እግዚአብሔር ይባርክህ!”
\s5
\v 3 እርሱም 1, 100 ብር ለእናቱ መለሰላት፣ እናቱም እንዲህ አለችው፣ “ስለ ልጄ የተቀረጸ የእንጨት ምስልና ቀልጦ የተሠራ ምስል ለማድረግ ይህን ብር ለእግዚአብሔር ለይቼዋለሁ፡፡ ስለዚህ አሁን፣ ለአንተ መልሼዋለሁ፡፡”
\v 4 ለእናቱም ገንዘቡን በመለሰላት ጊዜ፣ እናቱ ሁለቱን መቶ ብር ወሰደችና የተቀረጸ የእንጨት ምስልና ቀልጦ የተሠራ ምስል አድርጎ ለሰራው ለብረት ሰራተኛ ሰጠችው፡፡ ያም በሚካ ቤት ተቀመጠ፡፡
\s5
\v 5
ሚካ የተባለውም ሰው የጣዖታት አምልኮ ቤት ነበረውና አንድ ኤፉድና ተራፊም ሰራ፣ ከልጆቹም አንዱ ካህን ሆኖ እንዲያገለግለው አደረገ፡፡
\v 6 በዚያን ዘመን በእስራኤል ዘንድ ንጉሥ አልነበረም፣ ሰውም ሁሉ በዓይኖቹ ፊት ትክክል መስሎ የታየውን ያደርግ ነበር፡፡
\s5
\v 7 አሁን በቤተ ልሔም ይሁዳ ከይሁዳ ወገን የሆነ አንድ ሌዋዊ ወጣት ሰው ነበረ፡፡ እርሱም ተግባሩን ለመፈጸም በዚያም ይቀመጥ ነበር፡፡
\v 8 ይህ ሰው የሚቀመጥበትን ስፍራ ለመፈለግ ቤተ ልሔም ይሁዳን ለቅቆ ሄደ፡፡ ሲጓዝም ወደ ኮረብታማው የኤፍሬም አገር ወደ ሚካ ቤት መጣ፡፡
\v 9 ሚካም ለእርሱ እንዲህ አለው፣ “ከወዴት መጣህ? ” እርሱም እንዲህ አለው፣ “እኔ ከቤተ ልሔም ይሁዳ የመጣሁ ሌዋዊ ነኝ፣ የምኖርበትን ስፍራ ለማግኘት እየተጓዝሁ ነው፡፡”
\s5
\v 10 ሚካም እንዲህ አለው፣ “ከእኔ ጋር ተቀመጥ፣ ለእኔም አማካሪና ካህን ሁነኝ፡፡ እኔም በየዓመቱ አሥር ብር፣ እንደዚሁም ልብሶችንና ምግብህን እሰጥሃለሁ፡፡” ስለዚህ ሌዋዊው ወደ ቤቱ ገባ፡፡
\v 11 ሌዋዊውም ከሰውዮው ጋር ለመቀመጥ ፈቃደኛ ሆነ፣ ወጣቱም ሰው ለሚካ ከልጆቹ እንደ አንዱ ሆነለት፡፡
\s5
\v 12
ሚካም ሌዋዊውን ለተቀደሰ ሃላፊነት ቀደሰው፣ ወጣቱም ሰው ካህኑ ሆነለት፣ በሚካም ቤት ነበረ፡፡
\v 13 ከዚያም ሚካ እንዲህ አለ፣ “አሁን እግዚአብሔር ለእኔ መልካም እንደሚሰራልኝ አውቄአለሁ፣ ምክንያቱም ይህ ሌዋዊ ካህን ሆኖልኛል፡፡”
\s5
\c 18
\p
\v 1 በዚያን ዘመን በእስራኤል ውስጥ ንጉሥ አልነበረም፡፡ የዳን ነገድ ተወላጆች የሚቀመጡበትን ርስት ይፈልጉ ነበር፣ እስከዚያ ቀን ድረስ በእስራኤል ነገዶች መካከል ርስት አልተቀበሉም ነበርና፡፡
\v 2 የዳን ሰዎች ከአጠቃላይ ወገናቸው በሙሉ ከጾርዓ ጀምሮ እስከ ኤሽታኦል ድረስ በጦርነት ልምድ ያላቸውን አምስት ሰዎች በእግራቸው ሄደው ምድሪቱን እንዲሰልሉና እንዲያዩ ላኩ፡፡ ለእነርሱም እንዲህ አሉአቸው፣ “ሂዱና ምድሪቱን ሰልሉ፡፡” እነርሱም ወደ ኮረብታማው ወደ ኤፍሬም አገር ወደ ሚካ ቤት መጡና ሌሊቱን በዚያ አሳለፉ፡፡
\s5
\v 3 በሚካ ቤት አጠገብ በነበሩ ጊዜ፣ የአንድ ወጣት ሌዋዊ ንግግር አወቁ፡፡ ስለዚህ አስቆሙትና እንዲህ ብለው ጠየቁት፣ “ወደዚህ ማን አመጣህ? በዚህ ስፍራ ምን ታደርጋለህ? ለምን ወደዚህ መጣህ? ”
\v 4 እርሱም እንዲህ አላቸው፣ “ሚካ ለእኔ ያደረገው ነገር ይህ ነው፡- የእርሱ ካህን እንድሆን ቀጠረኝ፡፡”
\s5
\v 5 እነርሱም እንዲህ አሉት፣ “የምንሄድበት መንገድ መቃናቱን ወይም አለመቃናቱን እናውቅ ዘንድ፣ እባክህ፣ የእግዚአብሔርን ምክር ጠይቅልን፡፡”
\v 6 ካህኑም ለእነርሱ እንዲህ አላቸው፣ “በሰላም ሂዱ፡፡ ልትሄዱ በሚገባችሁ መንገድ እግዚአብሔር ይመራችኋል፡፡”
\s5
\v 7
የዚያን ጊዜ አምስቱ ሰዎች ሄዱና ወደ ላይሽ መጡ፣ ሲዶናውያን በጸጥታ ያለስጋት ይኖሩ እንደነበረ ሁሉ፣ በዚያም ተዘልለው ይኖሩ የነበሩትን ሕዝብ አዩ፡፡ በምድሪቱም በየትኛውም መልኩ የገዛቸው፣ ወይም ያስቸገራቸው አልነበረም፡፡ ከሲዶናውያን በጣም ርቀው ይኖሩ ነበር፣ ከማንኛውም ሕዝብ ጋር ምንም ግንኙነት አልነበራቸውም፡፡
\v 8 በጾርዓና በኤሽታኦል ውስጥ ወደነበሩት ወንድሞቻቸው ተመለሱ፡፡ ዘመዶቻቸውም እንዲህ ብለው ጠየቁአቸው፣ “ምን ወሬ ይዛችኋል?”
\s5
\v 9 እነርሱም እንዲህ አሉ፣ “ኑ! እንውጋቸው! ምድሪቱን አይተናታል፣ በጣም ጥሩ ናት፡፡ እናንተ ዝም ትላላችሁን? ምድሪቱን ከመውጋትና ከመውረስ አትዘግዩ፡፡
\v 10 በሄዳችሁ ጊዜ፣ ያለ ስጋት እንደሚኖሩ ወደሚያስቡ ሕዝብ ትደርሳላችሁ፣ ምድሪቱም ሰፊ ናት! እግዚአብሔርም ለእናንተ ሰጥቶአችኋል፣ በምድር ካለው ነገር ሁሉ አንዳች የማይጎድልባት ስፍራ ናት፡፡
\s5
\v 11 ከዳን ወገን የሆኑና የጦር መሳርያ የታጠቁ ስድስት መቶ ሰዎች ከጾርዓና ከኤሽታኦል ተነሥተው ሄዱ፡፡
\v 12 እነርሱም ሄዱና በይሁዳ ባለችው በቂርያትይዓሪም ሰፈሩ፡፡ እስከ ዛሬ ድረስ የዚያ ስፍራ ስም የዳን ሰፈር ብለው የሚጠሩት ለዚህ ነው፤ እርሱም ከቂርያትይዓሪም በምዕራብ በኩል ነው፡፡
\s5
\v 13
እነርሱም ከዚያ ተነስተው ወደ ኮረብታማው የኤፍሬም አገር አልፈው ሄዱ፣ ወደ ሚካም ቤት መጡ፡፡
\v 14 ከዚያም የላይሽን አገር ሊሰልሉ ሄደው የነበሩት አምስቱ ሰዎች ለዘመዶቻቸው እንዲህ አሉአቸው፣ “በእነዚህ ቤቶች ውስጥ ኤፉድና ተራፊም፣ የተቀረጸ ምስልና ቀልጦ የተሠራ ምስል እንዳሉ ታውቃላችሁን? ምን እንደምታደርጉ አሁን ወስኑ፡፡”
\s5
\v 15 ስለዚህ ከዚያ ዘወር አሉና ወጣቱ ሌዋዊ ይኖርበት ወደነበረው ወደ ሚካ ቤት መጡ፤ ሰላምታም አቀረቡለት፡፡
\v 16 በዚያን ጊዜ የጦር መሳርያ የታጠቁት ስድስት መቶ ዳናውያን በበሩ መግቢያ ቆሙ፡፡
\s5
\v 17
ካህኑ የጦር መሳርያ ከታጠቁት ከስድስት መቶ ሰዎች ጋር በበሩ አካባቢ ቆሞ በነበረበት ጊዜ፣ ምድሪቱንም ሊሰልሉ ሄደው የነበሩት አምስቱ ሰዎች ወደዚያ ሄዱና የተቀረጸውን ምስል፣ ኤፉዱን፣ ተራፊሙንና ቀልጦ የተሠራውን ምስል ወሰዱ፡፡
\v 18 እነዚህ ወደ ሚካ ቤት ገብተው የተቀረጸውን ምስል፣ ኤፉዱን፣ ተራፊሙንና ቀልጦ የተሠራውን ምስል በወሰዱ ጊዜ፣ ካህኑ ለእነርሱ እንዲህ አላቸው፣ “ምን ታደርጋላችሁ?”
\s5
\v 19 እነርሱም እንዲህ አሉት፣ “ዝም በል! እጅህን በአፍህ ላይ ጫንና ከእኛ ጋር ና፣ ለእኛም አባትና ካህን ሁንልን፡፡ ለአንተስ ለአንድ ሰው ቤት ካህን መሆን ወይስ በእስራኤል ውስጥ ላለው ነገድና ወገን ሁሉ ካህን መሆን ይሻልሃል? ”
\v 20 የካህኑም ልብ ደስ አለው፡፡ ኤፉዱን፣ ተራፊሙንና የተቀረጸውንም ምስል ወሰደና ከሕዝቡ ጋር ሄደ፡፡
\s5
\v 21
ስለዚህ እነርሱ ዞሩና ሄዱ፡፡ ሕፃናቶችን፣ ከብቶችንና ንብረታቸውን በፊታቸው አስቀደሙ፡፡
\v 22 ከሚካም ቤት ጥቂት በራቁ ጊዜ፣ በሚካ ቤት አጠገብ በነበሩት ቤቶች ውስጥ የነበሩ ሰዎች ተጠራርተው ተሰበሰቡ፣ የዳን ሰዎችንም ተከትለው ደረሱባቸው፡፡
\v 23 ወደ ዳንም ሰዎች ጮኹ፣ ዘወር ብለው ለሚካም እንዲህ አሉት፣ “ተሰብስባችሁ በአንድ ላይ የመጣችሁት ለምንድን ነው?”
\s5
\v 24 እርሱም፣ “የሠራኋቸውን አማልክቴን ሰረቃችሁ፣ ካህኔንም ይዛችሁ ሄዳችሁ፡፡ ሌላ ምን የቀረኝ ነገር አለ? ‘ያስጨነቀህ ምንድን ነው? ብላችሁ እንዴት ልትጠይቁኝ ትችላላችሁ፡፡”
\v 25 የዳን ሰዎችም እንዲህ አሉት፣ “ምንም ዓይነት ንግግር ስትናገር እንድንሰማ አታድርገን፣ አለዚያ አንዳንድ የተቈጡ ሰዎች ይጎዱሃል፣ አንተና ቤተሰቦችህም ትሞታላችሁ፡፡”
\v 26 የዚያን ጊዜ የዳን ሰዎች መንገዳቸውን ሄዱ፡፡ ሚካ ከእርሱ ይልቅ እነርሱ እጅግ በጣም የበረቱ እንደሆኑ ባየ ጊዜ፣ ተመልሶ ወደ ቤቱ ሄደ፡፡
\s5
\v 27
የዳን ሰዎችም ሚካ የሠራውን ጣዖትና ካህኑን ወሰዱና ወደ ላይሽ መጡ፣ በሰላምና ያለ ስጋት ተዘልሎም ወደ ተቀመጠው ሕዝብ መጥተው በሰይፍ ስለት ገደሉአቸው፣ ከተማይቱንም በእሳት አቃጠሉአት፡፡
\v 28 እነርሱን የሚያድን አንድም ሰው አልነበረም ምክንያቱም ከተማይቱ ከሲዶና በጣም ራቅ ያለች ነበረች፣ እነርሱም ከሌሎች ሰዎች ጋር ምንም ግንኙነት አልነበራቸውም፡፡ እርስዋም በቤትሮዖብ አጠገብ ባለው ሸለቆ ውስጥ ነበረች፡፡ የዳን ሰዎችም ከተማይቱን እንደገና ሠሩና ተቀመጡባት፡፡
\v 29 ከተማይቱንም ከእስራኤል ወንዶች ልጆች አንዱ በሆነው በአባታቸው በዳን ስም ዳን ብለው ጠሩአት፡፡ ነገር ግን አስቀድሞ የከተማይቱ ስም ላይሽ ነበረ፡፡
\s5
\v 30 የዳን ሰዎችም ለራሳቸው የተቀረጸ ምስል አቆሙ፣ የሙሴ ልጅ የጌርሳም ልጅ ዮናታን፣ እርሱና ወንዶች ልጆቹ ምድሪቱ እስከምትያዝበት ቀን ድረስ ለዳን ሰዎች ካህናት ነበሩ፡፡
\v 31 ስለዚህ የእግዚአብሔር ቤት በሴሎ በነበረበት ጊዜ ሁሉ፣ ሚካ የሰራውን የተቀረጸ ምስል አመለኩ፡፡
\s5
\c 19
\p
\v 1
በዚያም ዘመን፣ በእስራኤል ውስጥ ንጉሥ ባልነበረበት ጊዜ፣ በኮረብታማው የኤፍሬም አገር እጅግ በጣም ሩቅ በሆነ አካባቢ ለአጭር ጊዜ የኖረ አንድ ሌዋዊ ሰው ነበረ፡፡ እርሱም አንዲትን ሴት ቁባት አድርጎ ወሰዳት፡፡
\v 2 ነገር ግን ቁባቱ ለእርሱ ታማኝ አልነበረችም፤ እርሱን ተወችውና ተመልሳ ወደ አባትዋ ቤት ወደ ቤተ ልሔም ይሁዳ ሄደች፡፡ እርስዋም በዚያ አራት ወር ቆየች፡፡
\s5
\v 3
የዚያን ጊዜ ባልዋ ተነሣና ተመልሳ ወደ እርሱ እንድትመጣ ለማባበል ተከትሏት ሄደ፡፡ የእርሱ አገልጋይና ሁለት አህዮች ከእርሱ ጋር ነበሩ፡፡ እርስዋም ወደ አባትዋ ቤት አስገባችው፡፡የልጅቱ አባት ባየው ጊዜ ደስ አለው፡፡
\v 4 የልጂቱ አባት፣ አማቱም በቤቱ ለሦስት ቀን እንዲቆይ ለመነው፡፡ እነርሱም በሉ፣ ጠጡ፣ ሌሊቱንም በዚያ አሳለፉ፡፡
\s5
\v 5
በአራተኛው ቀን ማልደው ተነሡ፣ እርሱም ለመሄድ ተዘጋጀ፣ ነገር ግን የልጂቱ አባት አማቹን እንዲህ አለው፣ “እንድትበረታ እንጀራ ብላ፣ ከዚያ መሄድ ትችላለህ፡፡”
\v 6 ስለዚህ ሁለቱም በአንድ ላይ ለመብላትና ለመጠጣት ተቀመጡ፡፡ ከዚያም የልጂቱ አባት እንዲህ አለ፣ “እባክህ ሌሊቱን ደግሞ እዚህ ለማሳለፍ ፈቃደኛ ሁን፣ መልካም ጊዜም ይሁንልህ፡፡”
\s5
\v 7
ሌዋዊው ለመሄድ በማለዳ በተነሳ ጊዜ፣ የወጣቷ ሴት አባት እንዲቆይ ለመነው፣ ከዚህ የተነሳ እቅዱን ለወጠና ሌሊቱን በዚያ አሳለፈ፡፡
\v 8 በአምስተኛው ቀን ለመሄድ ማልዶ ተነሣ፣ ነገር ግን የልጂቱ አባት እንዲህ አለ፣ “ሰውነትህን አበርታ፣ እስከ ማምሻ ድረስ ቆይ አለው፡፡ ስለዚህ ሁለቱም አብረው በሉ፡፡
\s5
\v 9
ሌዋዊው፣ ቁባቱና አገልጋዮቹ ለመሄድ በተነሱ ጊዜ፣ የልጂቱ አባት አማቱ እንዲህ አለው፣ “ተመልከት፣ አሁን ቀኑ እየመሸ ነው፡፡ እባክህ ሌላ ሌሊት በዚህ ቆዩ፣ መልካም ጊዜም ይሁንልህ፡፡ ነገ በማለዳ ተነስታችሁ ወደ ቤታችሁ ተመልሳችሁ መሄድ ትችላላችሁ፡፡”
\s5
\v 10
ነገር ግን ሌዋዊው ሌሊቱን በዚያ ለማሳለፍ ፈቃደኛ አልነበረም፡፡ ተነሳና ሄደ፡፡ ኢየሩሳሌምም ወደ ተባለችው ወደ ኢያቡስ ሄደ፡፡ ሁለት የተጫኑ አህዮች ነበሩት፣ ቁባቱም ከእርሱ ጋር ነበረች፡፡
\v 11 ወደ ኢያቡስም በቀረቡ ጊዜ መሸባቸው፣ አገልጋዩም ለጌታው እንዲህ አለው፣ “ና፣ ወደ ኢያቡሳውያን ከተማ እንሂድና ሌሊቱን በዚያ እናሳልፍ፡፡”
\s5
\v 12
ጌታውም፣ “የእስራኤል ሕዝብ ወገን ወዳልሆነ ወደ እንግዳ ሕዝብ ከተማ ውስጥ አንገባም፡፡ እኛ ወደ ጊብዓ እንሄዳለን፡፡”
\v 13 ሌዋዊውም ለወጣቱ ሰው እንዲህ አለው፣ “ና፣ ከእነዚህ ስፍራዎች ወደ አንዱ እንሂድ፣ ሌሊቱንም በጊብዓ ወይም በራማ እናሳልፍ፡፡”
\s5
\v 14 ስለዚህ መንገዳቸውን ቀጠሉ፣ የብንያም ነገድ ወደምትሆነው ወደ ጊብዓ ግዛት ሲቀርቡ ፀሐይ ገባችባቸው፡፡
\v 15 እነርሱም ሌሊቱን በጊብዓ ለማሳለፍ ወደዚያ አቀኑ፡፡ እርሱም ወደ ውስጥ ገባና በከተማው አደባባይ ተቀመጠ፣ ሌሊቱን በዚያ ያሳልፉ ዘንድ ወደ ቤቱ የወሰዳቸው ማንም ሰው አልነበረምና፡፡
\s5
\v 16 ነገር ግን በዚያን ጊዜ አንድ ሽማግሌ ሰው ከእርሻ ሥራው በምሽት እየመጣ ነበር፡፡ እርሱም ከኮረብታማው ከኤፍሬም አገር ነበረ፣ እርሱም በጊብዓ በእንግድነት ተቀምጦ ነበር፡፡ ነገር ግን በዚያ ስፍራ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ብንያማውያን ነበሩ፡፡
\v 17 እርሱም ዓይኑን አነሳና መንገደኛውን በከተማው አደባባይ አየው፡፡ ሽማግሌውም እንዲህ አለ፣ “ወዴት ትሄዳለህ? ከወዴትስ መጣህ?”
\s5
\v 18 ሌዋዊውም እንዲህ አለው፣ “እኛ ከቤተ ልሔም ይሁዳ በጣም ሩቅ ወደሆነው ወደ ኮረብታማው ወደ ኤፍሬም አገር እንሄዳለን፣ እኔም የመጣሁት ከዚያ ነው፡፡ ወደ ቤተ ልሔም ይሁዳ ሄጄ ነበር፣ አሁን ወደ እግዚአብሔር ቤት እየሄድሁ ነው፣ ነገር ግን ወደ ቤቱ የሚወስደኝ ማንም ሰው የለም፡፡
\v 19 ለአህዮቻችን ገለባና ገፈራ አለን፣ ለእኔና እዚህ ላለችው ለሴት አገልጋይህ፣ ከአገልጋዮችህም ጋር ላለው ለዚህ ወጣት ሰው እንጀራና የወይን ጠጅ አለን፡፡ አንዳችም አላጣንም፡፡”
\s5
\v 20 ሽማግሌውም ሰላምታ አቀረበላቸው፣ “ሰላም ለእናንተ ይሁን! የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ እኔ እሰጣችኋለሁ፡፡ በአደባባይ ግን ሌሊቱን አትደሩ” አለው፡፡
\v 21 ስለዚህም ሰውየው ሌዋዊውን ወደ ቤቱ ወሰደው፣ ለአህዮቹም ገፈራ ሰጣቸው፡፡ እግራቸውን ታጠቡ፣ በሉም ጠጡም፡፡
\s5
\v 22
እነርሱም መልካም ጊዜ ነበራቸው፣ ክፉ የሆኑ የከተማይቱ ሰዎች ያደሩበትን ቤት ከበቡ፣ በሩንም ይደበድቡ ነበር፡፡ የቤቱ ባለቤት ለሆነው ለሽማግሌው እንዲህ አሉት፣ “ከእርሱ ጋር መተኛት እንድንችል ወደ ቤትህ የገባውን ሰው አምጣው፡፡”
\v 23 ሰውየውም፣ የቤቱ ባለቤት፣ ወደ እነርሱ ሄደና እንዲህ አላቸው፣ “አይሆንም፣ ወንድሞቼ ሆይ፣ ይህን ክፉ ነገር እባካችሁ አታድርጉ! ይህ ሰው ወደ ቤቴ የገባ እንግዳ ስለሆነ፣ ይህን ክፉ ነገር አትሥሩ፡፡
\s5
\v 24
ተመልከቱ፣ ድንግል ልጄና የእርሱም ቁባት እዚህ አሉ፡፡ አሁን ሄጄ ላምጣቸው፡፡ አስነውሩአቸው፣ የፈለጋችሁትንም አድርጉባቸው፡፡ ነገር ግን በዚህ ሰው ላይ እንደዚህ ያለ ክፉ ነገር አታድርጉበት! ”
\v 25 ነገር ግን ሰዎቹ እርሱን አልሰሙትም፣ ስለዚህ ሰውዮው ቁባቱን ያዛትና ወደ ውጭ አወጣላቸው፡፡ እነርሱም ያዟትና ከእርሷ ጋር ተኙ፣ ሌሊቱን በሙሉ አመነዘሩባት፣ ጎህም ሲቀድ ለቀቁአት፡፡
\v 26 ሴቲቱም በማለዳ መጣችና ጌታዋ ባለበት በሰውዮው ቤት በር ወደቀች፣ ጸሐይ እስኪወጣ ድረስ እዚያው ተዘረረች፡፡
\s5
\v 27
ጌታዋም በማለዳ ተነሣና የቤቱን በር ከፈተ፣ መንገዱንም ለመሄድ ወጣ፡፡ እርሱም ቁባቱ እጅዋን በመድረኩ ላይ ዘርግታ በበሩ ተዘርራ አያት፡፡
\v 28 ሌዋዊውም እንዲህ አላት፣ “ተነሺ፡፡ እንሂድ፡፡” ነገር ግን ምንም መልስ አልነበረም፡፡ እርሱም በአህያው ላይ ጫናት፣ ተነሥቶም ወደ ቤቱ ሄደ፡፡
\s5
\v 29
ሌዋዊውም ወደ ቤቱ በመጣ ጊዜ፣ ቢላዋ ወሰደ፣ ቁባቱንም ይዞ ቆራረጣት፣ ብልት በብልት ለአሥራ ሁለት ቈራርጦ ቁራጮቹን ወደ እስራኤል አገር ሁሉ ላከው፡፡
\v 30 ይህንን ያየ ሁሉ እንዲህ አለ፣ “የእስራኤል ሕዝብ ከግብፅ ምድር ከወጡ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እንዲህ ያለ ነገር ከቶ አልተደረገም ወይም አልታየም፡፡ ስለ ነገሩ አስቡበት! ምክር ስጡን! ምን ማድረግ እንዳለብን ንገሩን!”
\s5
\c 20
\p
\v 1
የዚያን ጊዜ የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ እንደ አንድ ሰው ሆነው ወጡ፣ ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ድረስ፣ የገለዓድ አገር ሰዎችንም ጨምሮ፣ በእግዚአብሔር ፊት በምጽጳ ተሰበሰቡ፡፡
\v 2 የሕዝቡም ሁሉ መሪዎች፣ የእስራኤል ነገዶች ሁሉ፣ እግረኞች ሆነው በሰይፍ የሚዋጉ 400, 000 ሰዎች በእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ ውስጥ ስፍራቸውን ያዙ፡፡
\s5
\v 3 በዚህ ጊዜ የእስራኤል ሕዝብ እስከ ምጽጳ ድረስ እንደ ሄዱ የብንያም ሕዝብ ሰሙ፡፡ የእስራኤልም ሕዝብ እንዲህ አሉ፣ “ይህ ክፉ ነገር እንዴት እንደ ተደረገ ንገሩን? ”
\v 4 ሌዋዊውም፣ የተገደለችው ሴት ባል፣ እንዲህ ብሎ መለሰ፣ “እኔና ቁባቴ ሌሊቱን በዚያ ለማሳለፍ የብንያም ግዛት ወደሆነችው ወደ ጊብዓ መጣን፡፡
\s5
\v 5 በዚያ ሌሊት የጊብዓ ሰዎች በእኔ ላይ ተነሱ፣ ሊገድሉኝም አስበው ቤቱን ከበቡት፡፡ ቁባቴንም ያዙና ከእርስዋ ጋር ተኙ፣ እርስዋም ሞተች፡፡
\v 6 እኔም ቁባቴን ወሰድሁና ሰውነቷን ቆራረኋጥኋት፣ ቁርጥራጩንም በእስራኤል ርስት ወደሚገኝ ወደ እያንዳንዱ ክልል ላክሁት፣ ምክንያቱም እንዲህ ዓይነቱን ክፋትና መአት በእስራኤል ላይ ፈጽመዋልና፡፡
\v 7 አሁንም፣ እናንተ እስራኤላውያን ሁላችሁም ተነጋገሩ፣ ምክራችሁንም ስጡ፣ ለዚህ ነገርም ፍርዳችሁን ስጡ!”
\s5
\v 8 ሕዝቡም ሁሉ እንደ አንድ ሰው ሆነው በአንድ ላይ ተነሱ፣ እንዲህም አሉ፣ “ከእኛ ዘንድ ማንም ሰው ወደ ድንኳኑ አይሄድም፣ ማንም ሰው ወደ ቤቱ አይመለስም!
\v 9 ነገር ግን አሁንም በጊብዓ ላይ ማድረግ ያለብን ነገር ይህ ነው፡- ዕጣው እንደሚመራን እንወጋታለን፡፡
\s5
\v 10
ከእስራኤል ነገዶች በሙሉ ለሕዝቡ ስንቅ እንዲይዙ ከመቶው አስር ሰው፣ ከሺህ መቶ ሰው፣ ከአስር ሺህ አንድ ሺህ ሰው እንወስዳለን፣ ይህም ሕዝቡ ወደ ብንያም ጊብዓ በሚመጣበት ጊዜ እነርሱ በእስራኤል ላይ ለፈጸሙት ክፋት ይቀጧቸው ዘንድ ነው፡፡”
\v 11 ስለዚህም የእስራኤል ወታደሮች በሙሉ በአንድ ዓላማ በመስማማት በከተማይቱ ላይ ለመዝመት ተሰበሰቡ፡፡
\s5
\v 12
የእስራኤልም ነገዶች ወደ ብንያም ነገድ ሁሉ እንዲህ ብለው ሰዎችን ላኩ፣ “በእናንተ መካከል የተደረገው ይህ ክፉ ነገር ምንድር ነው?
\v 13 ስለዚህ እንድንገድላቸውና ይህንን ክፋት ከእስራኤል ሙሉ ለሙሉ ለማስወገድ በጊብዓ ውስጥ ያሉትን እነዚህን ክፉ ሰዎች አውጥታችሁ ስጡን፡፡” ነገር ግን ብንያማውያን የወንድሞቻቸውን የእስራኤልን ሕዝብ ቃል አልሰሙም፡፡
\v 14 የዚያን ጊዜ የብንያም ሕዝብ ከእስራኤል ሕዝብ ጋር ለመዋጋት ዝግጅት ያደርጉ ዘንድ ከየከተማው ወጥተው ወደ ጊብዓ ተሰበሰቡ፡፡
\s5
\v 15
የብንያም ሕዝብ ከየከተማው በአንድ ላይ ለመዋጋት መጡ፣ በዚያም ቀን በሰይፍ ስለት ለመዋጋት የሰለጠኑ 26, 000 ወታደሮች ነበሩ፤ ከዚህ በተጨማሪ ከጊብዓ ነዋሪዎች ሰባት መቶ የተመረጡ ሰዎች ተቈጠሩ፡፡
\v 16 ከእነዚህ ወታደሮች መካከል ሰባት መቶ የተመረጡ ግራኝ ሰዎች ነበሩ፤ እያንዳንዳቸውም ድንጋይ ወንጭፈው አንዲት ጠጕርስ እንኳ አይስቱም፡፡
\s5
\v 17
የእስራኤል ወታደሮች፣ ከብንያም ወገን የሆኑትን ሳይጨምር፣ በሰይፍ ስለት ለመዋጋት የሰለጠኑ አራት መቶ ሺህ ሰዎች ተቆጠሩ፡፡ እነዚህ በሙሉ የጦር ሰዎች ነበሩ፡፡
\v 18 የእስራኤልም ሕዝብ ተነሱ፣ ወደ ቤቴል ወጡ፣ ከእግዚአብሔርም ምክር ጠየቁ፡፡ እንዲህም ብለው ጠየቁ፣ “የብንያምን ልጆች ለመውጋት ለእኛ መጀመርያ ማን ይውጣልን? ” እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፣ “ይሁዳ በመጀመርያ ይዋጋል፡፡”
\s5
\v 19
የእስራኤልም ሕዝብ በማለዳ ተነሱና በጊብዓ ፊት ለውጊያ ተዘጋጁ፡፡
\v 20 የእስራኤልም ወታደሮች ከብንያም ጋር ለመዋጋት ወጡ፡፡ እነርሱም በጊብዓ ከእነርሱ ጋር ለመዋጋት ቦታ ቦታቸውን ይዘው ተሰለፉ፡፡
\v 21 የብንያም ወታደሮች ከጊብዓ ወጥተው መጡ፣ በዚያም ቀን ከእስራኤላውያን ሰራዊት 22, 000 ሰዎች ገደሉ፡፡
\s5
\v 22
ነገር ግን የእስራኤል ወታደሮች ራሳቸውን አበረቱ፣ በመጀመርያው ቀን ተሰልፈው በነበረበት ስፍራ ላይ እንደገና ቦታ ቦታቸውን በመያዝ የውጊያውን መስመር አዘጋጁ፡፡
\v 23 የእስራኤልም ሕዝብ ወደ ላይ ወጡና እስከ ማታ ድረስ በእግዚአብሔር ፊት አለቀሱ፡፡ከእግዚአብሔርም ምሪትን ፈለጉ እንዲህም ብለው ጠየቁ፣ “ከወንድሞቻችን ከብንያም ሕዝብ ጋር ለመዋጋት እንደገና ወደዚያ መቅረብ ይገባናልን? ” እግዚአብሔርም “በእነርሱ ላይ ውጡና ግጠሟቸው” አለ፡፡
\s5
\v 24 ስለዚህም በሁለተኛው ቀን የእስራኤል ወታደሮች የብንያምን ወታደሮች ለመዋጋት ሄዱ፡፡
\v 25 በሁለተኛው ቀን የብንያም ወታደሮች ከጊብዓ እነርሱን ሊወጉ ወጡና ከእስራኤል ወታደሮች 18, 000 ሰዎች ገደሉ፡፡ እነዚህም ሰዎች ሁሉ በሰይፍ ለመዋጋት የሰለጠኑ ነበሩ፡፡
\s5
\v 26
የዚያን ጊዜ የእስራኤል ወታደሮች ሁሉ፣ ሕዝቡም ሁሉ ወደ ቤቴል ወጡና አለቀሱ፣ በዚያም በእግዚአብሔር ፊት ተቀመጡ፣ እነርሱም በዚያ ቀን እስከ ምሽት ድረስ ጾሙ፣ በእግዚአብሔር ፊት የሚቃጠል መሥዋዕትና የሰላም መሥዋዕት አቀረቡ፡፡
\s5
\v 27
የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔርን ጠየቁ፣ በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት በዚያ ነበረ፣
\v 28 በእነዚህ ጊዜያቶች የአሮን ልጅ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ በታቦቱ ፊት ያገለግል ነበር፣ “ከወንድሞቻችን ከብንያም ሕዝብ ጋር አንድ ጊዜ ለመዋጋት እንደገና እንሂድ ወይስ እንቅር? ” እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፣ “ጥቃት ፈጽሙባቸው፣ ነገ እነርሱን እንድታሸንፉ እረዳችኋለሁና፡፡”
\s5
\v 29
ስለዚህ እስራኤል በጊብዓ ዙሪያ በምስጢራዊ ስፍራዎች የተደበቁ ሰዎች አኖሩ፡፡
\v 30 የእስራኤል ወታደሮች ከብንያም ወታደሮች ጋር ለሦስተኛ ቀን ተዋጉ፣ ከዚህ በፊት እንዳደረጉት በጊብዓ ላይ የውጊያ መስመራቸውን ዘርግተው ተሰለፉ፡፡
\s5
\v 31
የብንያምም ሕዝብ ሄዱና ሕዝቡን ተዋጉ፣ ከከተማይቱም እንዲወጡ ተደረጉ፡፡ ከሕዝቡም አንዳንዶቹን መግደል ጀመሩ፡፡ ከእስራኤልም ወገን የሞቱ ሠላሳ የሚያህሉ ሰዎች በእርሻዎቹና በመንገዶቹ ነበሩ፣ ከመንገዶቹ አንዱ ወደ ቤቴል የሚወስድ ነው፣ ሌላኛው ደግሞ ወደ ጊብዓ የሚወስድ ነው፡፡
\s5
\v 32
የዚን ጊዜ የብንያምም ሕዝብ እንዲህ አሉ፣ “እንደ በፊቱ ተሸንፈዋል፣ ከእኛ እየሸሹ ነው፡፡” ነገር ግን የእስራኤል ወታደሮች እንዲህ አሉ፣ “እንሽሽ፣ ከከተማይቱ እንዲወጡና ወደ መንገዶቹ እንዲሄዱ እናድርጋቸው፡፡”
\v 33 የእስራኤልም ወታደሮች በሙሉ ከስፍራቸው ተነሱና በበኣልታማር ለውጊያ ራሳቸውን አዘጋጅተው ተሰለፉ፡፡ በምስጢራዊ ስፍራ ተደብቀው የነበሩት የእስራኤል ወታደሮችም ከነበሩበት ስፍራ ከጊብዓ ወጥተው ሮጡ፡፡
\s5
\v 34
ከእስራኤልም ሁሉ 10, 000 የተመረጡ ሰዎች በጊብዓ ላይ መጡ፣ ጦርነቱም በርትቶ ነበር፣ ነገር ግን ብንያማውያን ጥፋት ወደ እነርሱ ቀርቦ እንደነበር አላወቁም፡፡
\v 35 እግዚአብሔርም ብንያምን በእስራኤል ፊት ድል አደረገ፡፡ በዚያም ቀን የእስራኤል ወታደሮች 25, 100 የብንያም ሰዎችን ገደሉ፡፡ የሞቱት ሰዎች በሙሉ በሰይፍ ለመዋጋት ስልጠና የወሰዱ ነበሩ፡፡
\s5
\v 36
ስለዚህ የብንያም ወታደሮች እንደ ተሸነፉ አዩ፡፡ የእስራኤልም ሰዎች ለብንያም ስፍራ ለቀቁላቸው፣ ምክንያቱም ከጊብዓ ውጭ በድብቅ ስፍራዎች ባስቀመጡአቸው ሰዎች ላይ ተማምነው ነበርና፡፡
\v 37 የዚያን ጊዜ ተደብቀው የነበሩት ሰዎች ተነሱና ፈጥነው ወደ ጊብዓ ሮጡ፣ በከተማይቱም ውስጥ የሚኖረውን ሰው በሙሉ በሰይፋቸው ገደሉ፡፡
\v 38 በእስራኤል ወታደሮችና በምስጢር በተደበቁት ሰዎች መካከል ከከተማው የታላቅ ጢስ ደመና በምልክትነት እንዲያስነሡ ስምምነት ተደርጎ ነበር፡፡
\s5
\v 39 የእስራኤልም ወታደሮች በውጊያው ጊዜ ከጦርነቱ ርቀው እንዲያፈገፍጉ ነበር፡፡ የዚያን ጊዜ ብንያማውያን ማጥቃት ጀመሩ ሠላሳ የእስራኤልንም ሰዎች ገደሉ፣ እነርሱም እንዲህ አሉ፣ “እንደ መጀመርያው የጦርነት ጊዜ በእኛ ፊት መሸነፋቸው እርግጠኛ ነው፡፡”
\s5
\v 40
ነገር ግን የጢሱ ዓምድ ከከተማው ወደ ላይ መውጣት በጀመረ ጊዜ፣ ብንያማውያን ወደ ኋላቸው ሲመለከቱ ጢሱ ከከተማዋ በሙሉ ወደ ሰማይ ሲወጣ አዩ፡፡
\v 41 የዚያን ጊዜ የእስራኤል ወታደሮች ዞረው አጠቋቸው፡፡ የብንያም ሰዎችም ደነገጡ፣ በእነርሱ ላይ ጥፋት እንደመጣባቸው አይተዋልና፡፡
\s5
\v 42
ስለዚህ ከእስራኤል ወታደሮች ተመልሰው ወደ ምድረ በዳው መንገድ ሸሹ፡፡ ነገር ግን ውጊያው ተከታትሎ ደረሰባቸው፡፡ የእስራኤልም ወታደሮች ከከተማዎቹ ወጡና በቆሙበት ስፍራ ገደሉአቸው፡፡
\s5
\v 43
እነርሱም ብንያማውያንን ከበቡና ተከትለዋቸው ሄዱ፤ በመኑሔም አሸነፉአቸው፣ ከጊብዓ በስተ ምሥራቅ በኩል እስካለው ስፍራ ድረስ አሳደዱአቸው፡፡
\v 44 ከብንያም ነገድም 18, 000 ወታደሮች ሞቱ፣ እነዚህ ሰዎች በሙሉ በጦርነት ምርጥ ተዋጊዎች ነበሩ፡፡
\s5
\v 45
እነርሱም ተመልሰው በምድረ በዳ ወዳለው ወደ ሬሞን ዓለት ሸሹ፡፡ እስራኤላውያንም ከእነርሱ ተጨማሪ አምስት ሺህ ሰዎችን በየመንገዱ ገደሉ፡፡ እነርሱም ተከታተሉአቸው፣ ወደ ጊድአምም በቅርብ እየተከታተሉአቸው ተጨማሪ ሁለት ሺህ ሰዎችን ገደሉ፡፡
\v 46 በዚያ ቀን የሞቱት የቢኒያም ወታደሮች በሙሉ 25, 000 በሰይፍ ለመዋጋት ልዩ ስልጠና የወሰዱ ሰዎች ነበሩ፤ እነዚህ በሙሉ በጦርነት ምርጥ ተዋጊዎች ነበሩ፡፡
\s5
\v 47 ነገር ግን ስድስት መቶ ሰዎች ተመልሰው በምድረ በዳ ወዳለው ወደ ሬሞን ዓለት ሸሹ፡፡ ለአራት ወራት ያህል በሬሞን ዓለት ተቀመጡ፡፡
\v 48 የእስራኤልም ወታደሮች በብንያም ሕዝብ ላይ እንደገና ተመለሱ፣ ሞላውን ከተማ፣ ከብቶችንና ያገኙትንም ሁሉ አጠቁ ደግሞም ገደሉ፡፡ በመንገዳቸው ያገኙትን ማንኛውንም ከተማ ሁሉ በእሳት አቃጠሉ፡፡
\s5
\c 21
\p
\v 1 በዚያን ጊዜ የእስራኤል ወታደሮች በምጽጳ “ከእኛ ማንም ሰው ሴት ልጁን በጋብቻ ለብንያማውያን መዳር የለበትም” በማለት ቃል ገብተው ነበር፡፡
\v 2 ከዚያም ሕዝቡ ወደ ቤቴል ሄዱና በዚያ በእግዚአብሔር ፊት እስከ ምሽቱ ድረስ ተቀመጡ፣ ድምፃቸውንም ከፍ በማድረግ አምርረው አለቀሱ፡፡
\v 3 እነርሱም እንዲህ ሲሉ ጮኹ፣ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፣ ይህ በእስራኤል ለምን ሆነ? ዛሬ ከእኛ አንዱ ነገድ መታጣቱ ለምንድን ነው?”
\s5
\v 4 በሚቀጥለውም ቀን ሕዝቡ በጠዋት ተነሡና በዚያ መሠዊያ ሠሩ፣ የሚቃጠልና የሰላም መሥዋዕትንም አቀረቡ፡፡
\v 5 የእስራኤልም ሕዝብ እንዲህ አሉ፣ “ከእስራኤል ነገዶች በሙሉ ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ ያልመጣ የትኛው ነው? ” በምጽጳ ወደ እግዚአብሔር ፊት ስላልመጣ ማንም ሰው በጣም ወሳኝ የሆነ ቃል ኪዳን አድርገው ነበርና፡፡ እነርሱም እንዲህ አሉ፣ “እርሱ ፈጽሞ ሊገደል ይገባዋል፡፡”
\s5
\v 6 የእስራኤልም ሕዝብ ስለ ወንድማቸው ስለ ብንያም አዘኑ፡፡ አነርሱም እንዲህ አሉ፣ “ዛሬ ከእስራኤል ነገድ አንዱ ተቆርጧል፡፡
\v 7 ሴቶች ልጆቻችንን ከእነርሱ ለአንዳቸውም ቢሆን በጋብቻ ላንሰጥ ለእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ስለገባን ለተረፉት ሚስቶችን የሚሰጣቸው ማን ነው?”
\s5
\v 8 እነርሱም አሉ፣ “ከእስራኤል ነገድ በምጽጳ ወደ እግዚአብሔር ያልመጣ የትኛው ነው? ” ከኢያቢስ ገለዓድ ወደ ጉባኤው አንድም ሰው አለመምጣቱን አወቁ፡፡
\v 9 ሕዝቡም በቅደም ተከተል ተሰልፈው እንዲቆጠሩ በተደረገ ጊዜ፣ እነሆ፣ ከኢያቢስ ገለዓድ ነዋሪዎች ማንም ሰው በዚያ አልነበረም፡፡
\v 10 ጉባኤውም 12, 000 ኃያላን ሰዎችን ወደ ኢያቢስ ገለዓድ ልከው በዚያ ያሉትን ሰዎች ሴቶችንና ሕፃናትንም ጭምር ጥቃት እንዲያደርሱባቸውና እንዲገድሏቸው አዘዙአቸው፡፡
\s5
\v 11 “እንግዲህ የምታደርጉት ይህ ነው፡- ወንዱን በሙሉ እንዲሁም ከወንድ ጋር የተኛችውንም ሴት በሙሉ ግደሉ፡፡”
\v 12 ሰዎቹም በኢያቢስ ገለዓድ ከሚኖሩት መካከል ከወንድ ጋር ተኝተው የማያውቁ አራት መቶ ወጣት ሴቶች አገኙ፣ እነርሱንም በከነዓን ወዳለው በሴሎ ወደሚገኘው ሰፈር ወሰዷቸው፡፡
\s5
\v 13
ጉባኤውም በሙሉ መልክት ላኩ፣ በሬሞን ዓለት ለነበሩት ለብንያም ሕዝብ የሰላም ጥሪ እንዳቀረቡላቸውም ነገሩአቸው፡፡
\v 14 ሲለዚህ በዚያን ጊዜ ብንያማውያን ተመለሱ፣ የኢያቢስ ገለዓድንም ሴቶች ሰጧቸው፡፡ ነገር ግን ለሁሉም የሚበቁ ሴቶች አልነበሩም፡፡
\v 15 ሕዝቡም በብንያም ላይ በሆነው ገር አዘኑ፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር በእስራኤል ነገዶች መካከል ስብራት አድርጓልና፡፡
\s5
\v 16
የዚያን ጊዜ የጉባኤው መሪዎች እንዲህ አሉ፣ “የብንያም ሴቶች ተገድለዋልና፣ ለተረፉት ብንያማውያን ሚስቶችን እንዴት እናግኝላቸው? ”
\v 17 እንዲህም አሉ፣ “ከእስራኤል አንድ ነገድ እንዳይጠፋ ከብንያም አሁን በሕይወት ላሉት ሰዎች ርስት ሊኖራቸው ይገባል፡፡
\s5
\v 18
ከሴቶች ልጆቻችን ሚስቶች ልንሰጣቸው አንችልም፡፡ የእስራኤል ሕዝብ፣ ‘ለብንያም ሚስት የሚሰጥ ርጉም ይሁን’ የሚል ቃል ኪዳን ገብተው ነበርና፡፡”
\v 19 ስለዚህ እንዲህ አሉ፣ “በቤቴል በሰሜን በኩል፣ ከቤቴልም ወደ ሴኬም በሚወስደው መንገድ በምሥራቅ በኩል፣ በለቦና በደቡብ በኩል ባለችው በሴሎ በየዓመቱ የእግዚአብሔር በዓል እንዳለ ታውቃላችሁ፡፡”
\s5
\v 20 እነርሱም ለብንያም ሰዎች እንዲህ ብለው አዘዙአቸው፣ “ሂዱና በምስጢር ተሸሸጉ፣ በወይኑ ስፍራም ተደበቁ፡፡
\v 21 የሴሎ ልጃገረዶች ለመጨፈር የሚወጡበትን ጊዜ ተመለክቱ፣ የዚያን ጊዜ ከወይኑ ስፍራ ፈጥናችሁ ውጡና እያንዳንዳችሁ ከሴሎ ልጃገረዶች ለየራሳችሁ ሚስት ውሰዱ፣ ከዚያም ወደ ብንያም ምድር ተመለሱ፡፡
\s5
\v 22 አባቶቻቸው ወይም ወንድሞቻቸው ሊጣሉን በመጡ ጊዜ፣ እንዲህ እንላቸዋለን፣ ‘ምህረት አድርጉልን! ባልና ሚስት ሆነው ይጽኑ ምክንያቱም በጦርነቱ ጊዜ እኛ ለያንዳንዳቸው ሚስት አላገኘንላቸውም፡፡ እናተ ደግሞ ሴቶች ልጆቻችሁን ለእነርሱ ስላልሰጣችሁ፣ ቃል ኪዳኑን በተመለከተ በደለኞች አይደላችሁም፡፡’”
\s5
\v 23
የብንያምም ሕዝብ እንዲሁ አደረጉ፣ በቍጥራቸው መጠን የሚያስፈልጋቸውን ያህል ሚስቶች ይጨፍሩ ከነበሩት ልጃገረዶች ወሰዱ፣ ሚስትም ይሆኗቸው ዘንድ ይዘዋቸው ሄዱ፡፡ እነርሱም ወደ ርስታቸው ስፍራ ተመልሰው ሄዱ፤ ከተሞችንም እንደገና ሠሩ፣ በውስጣቸውም ኖሩ፡፡
\v 24 በዚያን ጊዜ የእስራኤል ሕዝብ ያን ስፍራ ለቀቁና ወደ ቤታቸው ሄዱ፣ እያንዳንዱም ወደ ነገዱና ወደ ወገኑ ሄደ፣ እያንዳንዱም ወደ ርስቱ ተመለሰ፡፡
\s5
\v 25 በዚያም ዘመን በእስራኤል ውስጥ ንጉሥ አልነበረም፡፡ እያንዳንዱ ሰው በዓይኖቹ ፊት መልካም መስሎ የታየውን ያደርግ ነበር፡፡

1583
11-1KI.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,1583 @@
\id 1KI
\ide UTF-8
\h 1ኛ ነገስት
\toc1 1ኛ ነገስት
\toc2 1ኛ ነገስት
\toc3 1ki
\mt 1ኛ ነገስት
\s5
\c 1
\p
\v 1 ንጉስ ዳዊትም ሸምግሎ እና እድሜውም ገፍቶ ነበር። ምንም እንካ ልብስ ቢድርቡለትም፣ ሊያሞቀው አልቻለም።
\v 2 ስለዚህ አገልጋዮቹ፣ "ለንጉስ አንዲት ወጣት ልጃገረድ እንፈልግለት እና ታገልግለው ትንከባከበውም። ንጉሱም እንዲሞቀው ክንዱ ውስጥ ትተኛ፣' አሉት።
\s5
\v 3 ስለዚህም አንዲት ቆንጆ ልጃገረድ ለማግኘት በመላው እስራኤል ፈለጉ። ሱነማዊቱን አቢሳን አገኙ፤ ወደ ንጉሡም አመጡአት።
\v 4 እርስዋም እጅግ ውብ ነበረች፤ እርስዋም ንጉሡን አገለገለችው፣ ተንከባከበችውም፤ ነገር ግን ንጉሡ ከእርስዋ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት አላደረገም።
\s5
\v 5 በዚያን ጊዜ የአጊት ልጅ አዶንያስ “ንጉሥ እሆናለሁ” በማለት ራሱን ከፍ አደረገ። ስለዚህ በፊቱ የሚሮጡ ሃምሳ ፈረሰኞችንና ሠረገሎችን ለራሱ አዘጋጀ።
\v 6 አባቱም ይህን ወይም ያንን ለምን ታደርጋለህ ብሎ ገስጾት አያውቅም ነበር። አዶንያስም ከአቤሴሎም በኋላ የተወለደ፣ እጅግ መልከ መልካም ነበር።
\s5
\v 7 እርሱም ከጽሩያ ልጅ ከኢዮአብና ከካህኑ ከአብያታር ጋር አሤረ፤ እነርሱም አዶንያስን ተከትለው ረዱት።
\v 8 ነገር ግን ካህኑ ሳዶቅ፣ የዮዳሄ ልጅ በናያስ፣ ነቢዩ ናታን፣ ሳሚ፣ ሬሲምና ዳዊትን የሚደግፉ ኃያላን አዶንያስን አልተከተሉትም።
\s5
\v 9 አዶንያስም ዓይንሮጌል አቅራቢያ ባለው በዞሔሌት ድንጋይ ላይ በጎችን፣ በሬዎችንና የሰቡ ወይፈኖችን ሠዋ። እርሱም፣ የንጉሡን ልጆች ወንድሞቹን ሁሉ፣ የይሁዳን ሰዎች ሁሉና የንጉሡን አገልጋዮች ጋበዛቸው።
\v 10 ነገር ግን ነቢዩ ናታንን፣ በናያስን፣ ኃያላን ሰዎችን፣ ወይም ወንድሙን ሰሎሞንን አልጋበዛቸውም።
\s5
\v 11 ከዚያም ናታን፣ ለሰሎሞን እናት ለቤርሳቤህ እንዲህ ሲል ነገራት፦ “ጌታችን ዳዊት ሳያውቅ የአጊት ልጅ አዶንያስ መንገሡን አልሰማሽምን?
\v 12 ስለዚህ የራስሽንና የልጅሽን የሰሎሞንን ሕይወት ለማትረፍ እንድትችዪ ልምከርሽ።
\s5
\v 13 ወደ ንጉሥ ዳዊት ሂጂ፤ እንዲህም በዪው፣ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፣ ’ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ በኋላ ይነግሣል፣ በዙፋኔም ይቀመጣል’ ብለህ ለአገልጋይህ ምለህልኝ አልነበረምን? ታዲያ አዶንያስ የሚነግሠው ለምንድን ነው? ”።
\v 14 በዚያም ከንጉሡ ጋር በመነጋገር ላይ እያለሽ እኔም ካንቺ በኋላ እገባና የተናገርሽው ሁሉ እውነት መሆኑን አረጋግጣለሁ” አላት፡፡
\s5
\v 15 ስለዚህ ቤርሳቤህ ወደ ንጉሡ ክፍል ሄደች። ንጉሡ እጅግ ስለ ሸመገለ ሱነማይቱ አቢሳ ታገለግለው ነበር።
\v 16 ቤርሳቤህም ራስዋን ዝቅ አድርጋ ለንጉሡ እጅ ነሣች፤ ንጉሡም፣ “ምን ትፈልጊያለሽ? ” አላት፡፡
\v 17 እርሷም እንዲህ አለችው፤ “ጌታዬ ሆይ፣ ለአገልጋይህ፣ ‘በእርግጥ ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ በኋላ ይነግሣል፣ በዙፋኔም ይቀመጣል’ ብለህ በአምላክህ በጌታ እግዚአብሔር ስም ምለህ ነበር፡፡
\s5
\v 18 ይኸው አሁን አዶንያስ ነግሦአል፤ አንተም ጌታዬ ንጉሡ ይህንን አታውቅም።
\v 19 ስለዚህ በሬዎችን፣ የሰቡ ኮርማዎችንና ብዙ በጎች ሠውቷል። ደግሞም የንገሡን ልጆች፣ ካህኑን አብያታርንና የሠራዊቱን አዛዥ ኢዮአብን ጋብዟቸዋል፤ አገልጋይህን ሰሎሞንን ግን አልጋበዘውም፡፡
\s5
\v 20 ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፣ የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ከአንተ ከጌታዬ በኋላ በዙፋንህ የሚቀመጠው ማን መሆኑን አንድታስታውቀው በመጠባበቅ ላይ ነው፡፡
\v 21 አለበለዚያ ግን ጌታዬ ንጉሡ ከአባቶቹ ጋር በሚያንቀላፋበት ጊዜ እኔና ልጄ ሰሎሞን እንደ ወንጀለኛ እንቆጠራለን።
\s5
\v 22 እርስዋ ለንጉሡ በመናገር ላይ እያለች ነቢዩ ናታን ገባ።
\v 23 አገልጋዮቹም ለንጉሡ፣ “ነቢዩ ናታን እዚህ ነው” ብለው ነገሩት። እርሱም ወደ ንጉሡ ፊት በቀረበ ጊዜ በግምባሩ ምድር ላይ በመደፋት ለንጉሡ ሰላምታ አቀረበ።
\s5
\v 24 ናታንም፣ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፣ ‘አዶንያስ ከእኔ በኋላ ይነግሣል፣ በዙፋኔም ይቀመጣል’ ብለሃልን?
\v 25 እርሱ ዛሬ ወርዶ ብዙ በሬዎችን፣ የሰቡ ጥጆችንና በጎችን ሠውቷል፤ ደግሞም የንጉሡን ልጆች ሁሉ፣ የሠራዊቱን አዛዥ ኢዮአብንና ካህኑን አብያታርን ጋብዟል። ንጉሥ አዶንያስ ለዘላለም ይኑር! በማለት በፊቱ በመብላትና በመጠጣት ላይ ናቸው፡፡
\s5
\v 26 ነገር ግን እኔን አገልጋይህን፣ ካህኑን ሳዶቅን፣ የዮዳሄን ልጅ በናያስንና አገልጋይህን ሰሎሞንን ወደ ግብዣው አልጠራንም።
\v 27 ከአንተ በኋላ በዙፋንህ ላይ የሚቀመጠው ማን እንደሆነ ለእኛ ለአገልጋዮችህ ሳትነግረን ይህንን ያደረግኸው ጌታዬ ንጉሡ ነህን?”
\s5
\v 28 ከዚያም ንጉሡ ዳዊት፣ “ቤርሳቤህን ጥሩልኝ” አለ። እርስዋም ንጉሡ ወዳለበት መጥታ በፊቱ ቆመች።
\v 29 ንጉሡም ማለና፣ “ከደረሰብኝ መከራ ሁሉ የታደገኝ ጌታ እግዚአብሔር ሕያው የመሆኑን ያህል፤
\v 30 ‘ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ በኋላ ይነግሣል፣ በዙፋኔም ላይ በእኔ ቦታ ይቀመጣል’ ብዬ በእስራኤል አምላክ በጌታ እግዚአብሔር ስም የማልኩትን መሓላ ዛሬ እፈጽመዋለሁ” አላት።
\v 31 ቤርሳቤህም ወደ መሬት በግንባሯ በመደፋት ለንጉሡ አክብሮቷን ካሳየች በኋላ፣ “ጌታዬ ንጉሡ ዳዊት ለዘለዓለም ይኑር! ” አለች።
\s5
\v 32 ንጉሥ ዳዊትም፣ “ካህኑን ሳዶቅን፣ ነቢዩን ናታንን እና የዮዳሄን ልጅ በናያስን ጥሩልኝ” አለ። እነርሱም በንጉሡ ፊት ቀረቡ።
\v 33 ንጉሡም እንዲህ አላቸው፡- የጌታችሁን አገልጋዮች ከእናንተ ጋር ውሰዱ፤ ልጄን ሰሎምንንም እኔ በምቀመጥባት በቅሎ አስቀምጡትና ወደ ግዮን አውርዱት።
\v 34 ካህኑ ሳዶቅና ነቡዩ ናታን ቀብተው በእስራኤል ላይ ያንግሡትና መለከት በመንፋት “ንጉሥ ሰለሞን ለዘላለም ይኑር! ” በሉ።
\s5
\v 35 ከዚያም ተከትላችሁት ትመጣላችሁ፣ እርሱም መጥቶ በዙፋኔ ላይ ይቀመጣል፤ በእኔ ምትክ ይነግሣልና። በእስራኤልና በይሁዳ ላይ እንዲገዛ ሾሜዋለሁ”።
\v 36 የዮዳሄ ልጅ በናያስም ለንጉሡ እንዲህ ሲል መለሰ፡- “ይሁን! ይህንንም የጌታዬ የንጉሡ አምላክ ጌታ እግዚአብሔር ያጽናው።
\v 37 ጌታ እግዚአብሔር ከጌታዬ ከንጉሡ ጋር እንደ ሆነ እንዲሁ ከሰሎሞን ጋር ይሁን፤ ዙፋኑንም ከጌታዬ ከንጉሥ ዳዊት ዙፋን የበለጠ ያድርገው” አለው፡፡
\s5
\v 38 ስለዚህ ካህኑ ሳዶቅ፣ ነቢዩ ናታን፣ የዮዳሄ ልጅ በናያስ፣ ከሊታውያንና ፈሊታውያን ወረዱ፤ ሰሎሞንን በንጉሥ ዳዊት በቅሎ ላይ በማስቀመጥ ወደ ግዮን አመጡት።
\v 39 ካህኑ ሳዶቅ ዘይት ያለበትን ቀንድ ከድንኳን ወስዶ ሰሎሞንን ቀባው። በዚያን ጊዜ መለከት ነፉ፣ ሕዝቡም፣ “ንጉሥ ሰሎሞን ለዘላለም ይኑር! ” አሉ።
\v 40 ሕዝቡም ሁሉ ተከትሎት ወጣ፣ ሕዝቡም እምቢልታ እየነፉ በታላቅ ደስታ ደስ አላቸው፣ ከድምፃቸው የተነሣ ምድር ተንቀጠቀጠች።
\s5
\v 41 አዶንያስና ከእርሱ ጋር የነበሩት እንግዶች ሁሉ ምግባቸውን እንደጨረሱ ይህንን ድምፅ ሰሙ። ኢዮአብ የእምቢልታውን ድምፅ በሰማ ጊዜ፣ “ይህ በከተማ ውስጥ የሚሰማው ሁካታ ምንድን ነው? ” አለ።
\v 42 እርሱ ገና በመናገር ላይ እያለ የካህኑ የአብያታር ልጅ ዮናታን መጣ። አዶንያስም፣ “ና ግባ፤ አንተ ጥሩ ሰው ስለሆንክ መልካም ዜና ይዘህ ሳትመጣ አትቀርም” አለው።
\s5
\v 43 ዮናታንም ለአዶንያስ እንዲህ ሲል መለሰለት፡- “ጌታችን ንጉሥ ዳዊት ሰሎሞንን እንግሦታል፤
\v 44 ንጉሡም ከእርሱ ጋር ካህኑን ሳዶቅን፣ ነቢዩን ናታንን፣ የዮዳሄን ልጅ በናያስን፣ ከሊታውያንን እና ፈሊታውያንን ልኳል። እነርሱም ሰለሞንን በንጉሡ በቅሎ ላይ አስቀመጡት።
\v 45 ካህኑ ሳዶቅና ነቢዩ ናታንም በግዮን ቀብተው አነገሡት፤ ደስ እያላቸውም ከዚያ ወጡ፣ በከተማው ሁካታ የሆነው ለዚህ ነው። የሰማችሁት ድምፅም ይኸው ነው።
\s5
\v 46 ደግሞም ሰሎሞን በመንግሦቱ ዙፋን ላይ ተቀምጧል።
\v 47 ከዚህም በላይ ከፍተኛ ሥልጣን ያላቸው ባለሟሎች ሁሉ ወደ ንጉሡ ዳዊት ቀርበው አምላክህ እግዚአብሔር ሰሎሞንን ከአንተ ይበልጥ ዝናውን ያግንነው፣ መንግሥቱንም ይበልጥ ታላቅ ያድርገው ሲሉ አክብሮታቸውን ገልጠዋል፤ ከዚህ በኋላ ንጉሥ ዳዊት በአልጋው ላይ ሳለ ለእግዚአብሔር ሰገደ፡፡
\v 48 ዛሬ ከእኔ ዘሮች መካከል አንዱ በእኔ እግር ተተክቶ እንዲነግሥ ያደረገና ይህን ለማየት ያበቃኝ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይክበር ሲል እግዚአብሔርን አመሰገነ፡፡
\s5
\v 49 አዶንያስ የጠራቸው ተጋባዦች ሁሉ ይህን በሰሙ ጊዜ እጅግ ፈሩ፤ ሁሉም ተነሡ፤ እያንዳኑዱም በየፊናው ተበተነ፤
\v 50 አዶንያስም ሰሎሞንን ስለፈራ ወደ ተቀደሰው ድንኳን ሄዶ የመሠዊያውን ቀንዶች በመያዝ ተማጠነ፡፡
\v 51 ሰዎቹም ሰሎሞንን፣ አዶንያስ አንተን ከመፍራቱ የተነሣ የመሠዊያውን ቀንዶች ይዞ ከሁሉ በፊት ንጉሥ ሰሎሞን የማይገድለኝ መሆኑን በማረጋገጥ በመሐላ ቃል ይግባልኝ በማለት እየተማጠነ ነው ሲሉ ነገሩት፡፡
\s5
\v 52 ንጉሥ ሰሎሞንም መልካም ሰው ከሆነ ከራስ ጠጉሩ አንዲት እንኳን አትነካበትም፤ ክፉ ሆኖ ከተገኘ ግን ይሞታል ሲል መለሰ።
\v 53 ከዚህ በኋላ ንጉሥ ሰሎሞን አዶንያስን ከመሠዊያው አውርደው ያመጡት ዘንድ መልእክተኞችን ላከ፤ አዶንያስ ወደ ንጉሡ ፊት በመቅረብ ወደ መሬት ራሱን ዝቅ አድርጎ እጅ ነሣ፤ ንጉሡም ወደ ቤትህ ሂድ አለው።
\s5
\c 2
\p
\v 1 ዳዊት የሚሞትበት ቀን በተቃረበ ጊዜ ልጁን ሰሎሞንን ጠርቶ እንዲህ ሲል አዘዘው፤
\v 2 እነሆ እኔ ሰው ሁሉ እንደሚሞት የምሞትበት ጊዜ ተቃርቦአል፤ እንግዲህ በርታ ቆራጥ ሰው ሁን፡፡
\v 3 አምላክህ እግዚአብሔር እንድታደርግ የሚያዝህን ሁሉ አድርግ፣ በምትሄድበት ስፍራ ሁሉ የምታደርገው ማናቸውም ነገር እንዲከናወንልህ በሙሴ አማካይነት በተሰጠው ሕግ የተጻፉትን የእግዚአብሔርን ሕግ ትእዛዝ፣ ሥርዓትና ፈቃድ ሁሉ ጠብቅ፡፡
\v 4 በዚህ ሁሉ ታዛዥ ሆነው ቢኖሩ በፍጹም ልባቸውና በፍጹም ነፍሳቸው በፊቴ በቅንነት ቢመላለሱ በእስራኤል ዙፋን ላይ ነግሦ የሚገዛ ዘር አላሳጣህም ብሎ የነገረኝን የተስፋ ቃል ይፈጽማል፡፡
\s5
\v 5 የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ በእኔና የእስራኤል ሕዝብ የጦር መሪዎች በነበሩት በሁለቱ፣ በኔር ልጅ በአበኔርና በዬቴር ልጅ በአሜሳይ ላይ ያደረገውን ታውቃለህ፤ ሁለቱ በጦርነት ጊዜ ላፈሰሱት ደም ተበቅሎ በሰላም ጊዜ እነርሱን በመግደል የወገቡን ቀበቶና የእግሩን ጫማ በደም በከለ።
\v 6 እንግዲህ ባለህ ጥበብ በኢዮአብ ላይ ልትፈጸምበት የሚገባውን አድርግ፤ ዕድሜ ጠግቦ በሰላም እንዲሞት አትፍቀድለት።
\s5
\v 7 ይሁን እንጂ የገለዓዳዊው የቤርዜሊ ልጆች ከወንድምህ ከአቤሌሎም ፊት በሸሸሁ ጊዜ ወደ እኔ መጥተው የቸርነት ሥራ ስላደረጉልኝ፣ መልካም አድርግላቸው፤ በማዕድህም ከሚመገቡ መካከል ይሁኑ።
\s5
\v 8 ከዚህም ጋር መረሳት የሌለበት የብንያም ክፍል በሆነችው በባሑሪም ከተማ ውስት የሚኖረው የጌራ ልጅ ሳሚ ወደ መሃናይም በሄድኩበት ቀን በእኔ ላይ የስደብ ውርጅብኝ አውርዶብኛል፤ ይሁን እንጂ በዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ ባገኘኝ ጊዜ እንደማላስገድለው በእግዚአብሔር ስም ምየለታለሁ።
\v 9 ስለዚህ አንተ እርሱንም ከቅጣት ነጻ አታድርገው። አንተ ጥበበኛ ሰው ስለሆንህ ምን መደረግ እንዳለበት ታውቃለህ። በሸመገለም ጊዜ በሞት ትቀጣዋለህ፡፡
\s5
\v 10 ከዚያም ዳዊት ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊትም ከተማ ተቀበረ።
\v 11 ዳዊት በኬብሮን ሰባት ዓመት፣ በኢየሩሳሌም ሠላሳ ሦስት ዓመት፣ በድምሩ አርባ ዓመት በእስራኤል ላይ ነገሠ።
\v 12 ሰሎሞንም በአባቱ ዙፋን ተተክቶ ነገሠ፤ የመንግሥቱም ሥልጣን እጅግ የጸና ሆነ።
\s5
\v 13 የአጊት ልጅ አዶንያስ ወደ ሰሎሞን እናት ወደ ቤርሳቤህ መጣ። ቤርሳቤህም ወደ እኔ የመጣኸው በሰላም ነውን? ስትል ጠየቀችው፤ እርሱም አዎን በሰላም ነው ሲል መለሰላት።
\v 14 ቀጠል አድርጎም እኔ የምጠይቅሽ ጉዳይ አለኝ አላት። እርስዋም ጉዳይህን ተናገር አለችው።
\v 15 አዶንያስም እንዲህ አላት፣ ንጉሥ መሆን የሚገባኝ እኔ እንደ ነበርኩና ይህንንም የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ በተስፋ ይጠባበቅ እንደ ነበር አንቺ ታውቂያለሽ። ነገር ግን ጉዳዩ ከእግዚአብሔር ስለ ተወሰነ ነገሩ ተለውጦ መንግሥቱ ለወንድሜ ተሰጥቶአል።
\s5
\v 16 አሁንም የምጠይቅሽ አንድ ጉዳይ ስላለኝ እምቢ በማለት አታሳፍሪኝ። ቤርሳቤህም ጉዳይህን ተናገር አለችው።
\v 17 እርሱም እንዲህ አላት፡- ንጉሥ ሰሎሞን አንቺን እምቢ እንደማይልሽ አውቃለሁ፤ ስለዚህ አቢሳ ተብላ የምትጠራውን ሱነማይት ልጃገረድ ሚስት ትሆነኝ ዘንድ እንዲሰጠኝ እባክሽ አማልጅኝ አላት።
\v 18 እርስዋም መልካም ነው፤ ይህን ለንጉሡ እነግርልሃለሁ አለችው።
\s5
\v 19 ስለዚህ ቤርሳቤህ የአዶንያስን ጉዳይ ልትነግረው ወደ ንጉሡ ገባች። ንጉሡም ከተቀመጠበት ተነሥቶ እናቱን እጅ በመንሣት ተቀበላት። እርሱም በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠ በኋላ ሌላ ዙፋን አስመጥቶ በቀኙ አስቀመጣት።
\v 20 እርስዋም እንድትፈጽምልኝ የምጠይቅህ አንድ ትንሽ ጉዳይ አለኝ፣ እባክህ እምቢ በማለት አታሳፍረኝ አለችው። ንጉሡም እናቴ ሆይ አላሳፍርሽምና ጠይቂኝ አላት።
\v 21 እርስዋም ወንድምህ አዶንያስ አቢሳን እንዲያገባት ፍቀድለት አለችው።
\s5
\v 22 ንጉሡም አቢሳን ለሚስትነት እንድሰጠው ብቻ ለምን ትጠይቂኛሽ? መንግሥቴንም ጭምር እንድለቅለት ለምን አልጠየቅሽኝም? እርሱ ታላቅ ወንድሜ ነው፤ ለምንስ ለካህኑ አብያታርና ለኢዮአብም ልዩ አስተያየት እንዳደርግላቸው አትጠይቂላቸውም? አላት።
\v 23 ከዚህ በኋላ ሰሎሞን፣ በእግዚአብሔር ስም እንዲህ ሲል ማለ፡- አዶንያስ ይህን በመናገሩ በሕይወቱ እንዲከፍል ባላደርግ እግዚአብሔር ይፍረድብኝ፤ በበለጠም ይቅጣኝ አለ።
\s5
\v 24 እግዚአብሔር በአባቴ በዳዊት ዙፋን ላይ አስቀምጦኝ መንግሥቴን የጸና አድጎልኛል፤ ይህን መንግሥት ለእኔና ለዘሮቼ በመስጠት ቃሉን ጠብቆአል፤ እንግዲህ አዶንያስ በዚህ በዛሬው ቀን በሞት እንደሚቀጣ በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ።
\v 25 ስለዚህ አዶንያስን እንዲገድለው ንጉሥ ሰሎሞን ለዮዳሄ ልጅ ለበናያስ ትእዛዝ አስተላለፈ፤ በናያስም ሄዶ አዶንያስን ገደለው።
\s5
\v 26 ከዚህ በኋላ ንጉሥ ሰሎሞን ካህኑን አብያታርን እንዲህ አለው፡- በአናቶት ወዳለው እርሻህ ሂድ፤ አንተ በሞት ልትቀጣ ይገባህ ነበር፣ ነገር ግን የልዑል እግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት በአባቴ በዳዊት ፊት ስለተሸከምህ፣ ከእርሱም ጋር የመከራው ሁሉ ተካፋይ ስለ ነበርክ እኔ አሁን አልገድልህም።
\v 27 ከዚህ በኋላ ሰሎሞን አብያታርን የእግዚአብሔር ካህን ሆኖ ከሚያገለግልበት የክህነት ሥልጣን ሽሮ አባረረው፤ በዚህም ዓይነት እግዚአብሔር በሴሎ ስለ ካህኑ ዓሊ፣ ስለ ትውልዱ የተናገረው ቃል ተፈጸመ።
\s5
\v 28 የአቤሌሎም ደጋፊ ባይሆንም የአዶንያስ ደጋፊ የነበረው ኢዮአብ፣ ይህን የተፈጸመውን ነገር ሁሉ ሰማ፤ ስለዚህም ሸሽቶ ወደ ጌታ እግዚአብሔር ድንኳን ሄደ፤ በዚያም የመሠዊያውን ቀንዶች ይዞ ተማጠነ።
\v 29 ኢዮአብ ወደ ጌታ እግዚአብሔር ድንኳን ሸሽቶ መሄዱንና በመሠዊያው አጠገብ መገኘቱን ሰሎሞን በሰማ ጊዜ ኢዮአብን እንዲገድለው ለበናያስ ትእዛዝ አስተላለፈ፡፡
\s5
\v 30 እርሱም ወደ ጌታ እግዚአብሔር ድንኳን ሄዶ ኢዮአብን ከዚህ ድንኳን እንድትወጣ ንጉሡ አዞሃል አለው። ኢዮአብ ግን፣ አልወጣም እዚሁ እሞታለሁ አለ። በናያስም ተመልሶ ኢዮአብ ያለውን ለንጉሡ ነገረው።
\v 31 ሰሎሞን በናያስን እንዲህ አለው፡- ኢዮአብ እንዳለህ ግደለውና ቅበረው፤ በዚህ ሁኔታ ኢዮአብ ካፈሰሰው ንጹሕ ደም የእኔንና የአባቴን ቤት የነጻን ታደርገናለህ።
\s5
\v 32 አባቴ ዳዊት ሳያውቅ ኢዮአብ ስለ ገደላቸው ስለ እነዚያ ሁለት ሰዎች ደም እግዚአብሔር ኢዮአብን ይቀጣዋል፤ ኢዮአብ ከእርሱ የተሻሉትን ሁለት ንጹሓን ሰዎች ገድሎአል፤ እነርሱም የአስራኤል ጦር አዛዥ አበኔርና የይሁዳ ጦር ኣዛዥ አሜሳይ ነበሩ።
\v 33 ኢዮአብ እነዚህን ሰዎች በመግደሉ ደማቸው በእርሱና በዘሮቹ ለዘለዓለም ይመለስባቸው። ነገር ግን ለዳዊትና ለዘሮቹ፣ ለቤቱና በዙፋኑ ለሚቀመጡት የእግዚአብሔር ሰላም ለዘለዓለም ጸንቶ ይኑር።
\s5
\v 34 ስዚህ በናያስ በታዘዘው መሠረት ኢዮአብን ገደለው፤ በቤቱም አጠገብ በሚገኘው በረሓ ተቀበረ።
\v 35 ንጉሥ ሰሎሞን በኢዮአብ ፈንታ በናያስን የሠራዊት አዛዥ፣ በአብያታርም ፈንታ ሳዶቅን ካህን አድርጎ ሾማቸው።
\s5
\v 36 ከዚህ በኋላ ንጉሥ ሰሎሞን ሳሚን አስጠርቶ እንዲህ ሲል አዘዘው፡- በዚህ በኢየሩሳሌም የራስህን መኖሪያ ቤት ሠርተህ ተቀመጥ፤ ከዚያ የትም እንዳትሄድ፤
\v 37 ከከተማይቱ ወጥተህ የቄድሮንን ወንዝ ተሻግረህ ብትገኝ በእርግጥ ትሞታለህ፤ ለደምህም ተጠያቂው ራስህ ነህ።
\v 38 ሳሚም ንጉሥ ሆይ፣ ውሳኔህ መልካም ነው። አገልጋይህ አንተ ጌታዬ እንዳልከው አደርጋለሁ ሲል መለሰ። ስለዚህ በኢየሩሳሌም ብዙ ጊዜ ተቀመጠ።
\s5
\v 39 ከሦስት ዓመት በኋላ ግን ሁለቱ የሳሚ አገልጋዮች የመዓካ ልጅ ወደ ሆነው አንኩስ ተብሎ ወደሚጠራው ወደ ጌት ንጉሥ ኮብልለው ሄዱ፤ ሳሚም ባሪያዎቹ በጌት መኖራቸው ተነገረው።
\v 40 ሳሚም አህያውን ጭኖ እነርሱን ለመፈለግ በጌት ወደሚኖረው ወደ ንጉሥ አንኩስ ሄደ፤ እነርሱንም በዚያ ስላገኛቸው ወደ ቤት መልሶ አመጣቸው።
\s5
\v 41 ንጉሥ ሰሎሞን ሳሚ ከኢየሩሳም ወደ ጌት ሄዶ መመለሱን ሰማ።
\v 42 ንጉሡም ሳሚን አስጠርቶ ከኢየሩሳሌም እንዳትወጣ በእግዚአብሔር ስም አስምዬህ አልነበረምን? ወጥተህ ብትገኝ ግን በእርግጥ እንደምትሞት አስታውቄህ አልነበረምን? በዚህስ ተስማምተህ ትእዛዜን እንደምትፈጽም ቃል ገብተህልኝ አልነበረምን? አለው።
\s5
\v 43 ታዲያ በእግዚአብሔር ስም ከማልህ በኋላ ትእዛዜንስ ስለምን አላከበርክም?
\v 44 በአባቴ በንጉሥ ዳዊት ላይ የፈጸምከውን በደል ሁሉ በሚገባ ታውቃለህ፤ አንተ ስላደረግኸው ክፉ ነገር እግዚአብሔር ራሱ ይቀጣሃል።
\s5
\v 45 እኔን ግን እግዚአብሔር ይባርከኛል፤ የዳዊት መንግሥትም ለዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል።
\v 46 ከዚህም በኋላ ለዮዳሄ ልጅ ለበናያስ ሳሚን እንዲገድል ትእዛዝ አስተላለፈ፤ በናያስም ሄዶ ሳሚን ገደለው፤ በዚህም ዓይነት መንግሥቱ በሰሎሞን እጅ የጸና ሆነ፡፡
\s5
\c 3
\p
\v 1 ሰሎሞን የግብፅን ንጉሥ የፈርዖንን ሴት ልጅ በማግባት ከንጉሡ ጋር ወዳጅነት መሠረተ። የፈርዖንንም ልጅ አምጥቶ ቤተ መንግሥቱን፣ ቤተ መቅደሱንና የኢየሩሳሌምን ከተማ ቅጥር ዙሪያውን ሠርቶ እስኪጨርስ ድረስ በዳዊት ከተማ አኖራት።
\v 2 በዚያን ጊዜ በእግዚአብሔር ስም ቤተ መቅደሱ ገና አልተሠራም ነበር፤ ከዚህም የተነሣ በየኮረብታው መሥዋዕት ያቀርቡ ነበር።
\v 3 ሰሎሞን እግዚአብሔርን ይወድ ነበር፤ የአባቱንም የዳዊትን መመሪያ ይጠብቅ ነበር፤ ይሁን እንጂ እንስሶችን እያረደ በተለያዩ ኮረብቶች ላይ መሥዋዕት ያቀርብና ዕጣንም ያጥን ነበር።
\s5
\v 4 ታላቅ መሠዊያ የሚገኘው በገባዖን ስለነበር አንድ ቀን ንጉሥ ሰሎሞን መሥዋዕት ለማቅረብ ወደዚያ ሄደ። በዚያም መሠዊያ ላይ አንድ ሺህ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ።
\v 5 እግዚአብሔርም በዚያች ሌሊት በገባዖን ለሰሎሞን በሕልም ተገለጠለትና ምን እንድሰጥህ ትፈልጋህ? ጠይቅ አለው።
\s5
\v 6 ሰሎሞንም እንዲህ ሲል መለሰ፡- አገልጋይህ የነበረው አባቴ ዳዊት፣ ታማኝና ቅን ሰው በመሆኑ ጽኑ ፍቅርህን አሳይተኸዋል። ዛሬም በእርሱ ፈንታ በዙፋኑ የሚቀመጥ ልጅ በመስጠት ታላቅና ጽኑ የሆነውን የማያቋርጥ ፍቅርህን ገልጠህለታል።
\s5
\v 7 እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ እነሆ እኔ በዕድሜዬ ልጅ ብሆንም በአባቴ ቦታ ተተክቼ እንድነግሥ ፈቃድህ ሆኖአል። እኔም መግባትንና መውጣትን የማልችል ነኝ።
\v 8 እነሆ፣ የአንተ እንዲሆን በመረጥከውና ከብዛቱ የተነሣ ሊቆጠር በማይችል ሕዝብ መካከል አለሁ።
\v 9 ስለዚህ ክፉውንና በጎውን በመለየት ሕዝብህን በማስተዋል በትክክኛ ፍርድ ለመምራት የሚያስችለኝን ጥበብ ስጠኝ። ይህ ካልሆን ይህን ታላቅ ሕዝብህን ሊመራ ማን ይችላል?
\s5
\v 10 ይህ የሰሎሞን ጥያቄ እንግዚአብሔርን ደስ አሰኘው፤
\v 11 ስለዚህም እግዚአብሔር እንዲህ አለው፡- ለራስህ ረጅም ዕድሜ ወይም ሀብት ለማግኘት ወይም ጠላቶችህ እንዲጠፉልህ መመኘት ሳይሆን በትክክለኛ ፍርድ ማስተዳደር የምትችልበትን ጥበብ ጠይቀሃል።
\v 12 እነሆ የጠየቅኸውን አደርጋለሁ፤ እንዲያውም ማንም ሰው ከዚህ በፊት ካገኘውና ወደ ፊት ሊያገኘው ከሚችለው የሚበልጥ ጥበብንና አስተዋይነትን እሰጥሃለሁ።
\s5
\v 13 ከዚህም በላይ አንተ ያልጠየቅከውንም ሁሉ ጨምሬ ሰጥቼሃለሁ፤ ይኸውም በዘመንህ ማናቸውም ንገሥታት ያላገኙትን ብጽግናና ክብር አሰጥሃለሁ።
\v 14 አባትህ ዳዊት እንዳደረገው በመንገዴ ብትሄድ ለእኔም ብትታዘዝ ሕጌንና ትእዛዞቼንም ብትፈጽም ረጅም ዕድሜ እሰጥሃሁ።
\s5
\v 15 ሰሎሞን ከእንቅልፉ በነቃ ጊዜ እግዚአብሔር በሕልም ተገልጦ ያነጋገረው መሆኑን ተገነዘበ፤ ከዚህ በኋላ ሰሎሞን ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሶ ሄደ፤ በእግዚአብሔርም የቃል ኪዳን ታቦት ፊት ቆሞ የሚቃጠል መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቀረበ፤ ከዚህም በኋላ ለአገልጋዮቹ ሁሉ ግብዣ አደረገ።
\s5
\v 16 አንድ ቀን ሁለት ሴተኛ አዳሪዎች መጥተው በሰሎሞን ፊት ቀረቡ፡፡
\v 17 ከእነርሱም አንደኛይቱ እንዲህ አለች ንጉሥ ሆይ ይህች ሴትና እኔ በአንድ ቤት አብረን ስንኖር፣ በዚያውም በምንኖርበት ቤት ወንድ ልጅ ወለድኩ።
\s5
\v 18 እኔ በወለድኩ በሦስተኛው ቀን እርስዋም ወንድ ልጅ ወለደች። በዚያ ቤት ውስጥ ከሁለታችን በቀር ሌላ ማንም አልነበረም።
\v 19 ከዕለታት አንድ ቀን ሌሊት በላዩ ላይ ተኝታበት ስለ ታፈነ ልጇ ሞተ።
\v 20 እኔ ተኝቼ ሳለሁ ሌሊት ተነሥታ ታቅፌው የተኛሁትን ልጄን ወስዳ በእርስዋ አልጋ ላይ ካስተኛች በኋላ የሞተውን ልጅዋን አምጥታ በእኔ አልጋ ላይ በጎኔ አስተኛችው።
\s5
\v 21 በማግስቱ ማለዳ ተነሥቼ ልጄን ለማጥባት ስዘጋጅ ሞቶ አገኘሁት፤ ትኩር ብዬ ስመለከተው እኔ የወለድኩት ልጅ አለመሆኑን ተገነዘብኩ።
\v 22 ሁለተኛይቱ ሴት ግን አይደለም፣፣ በሕይወት ያለው ልጅ የእኔ ነው፣ የሞተው ግን የአንቺ ነው አለች። የመጀመሪያይቱ ሴት አይደለም የሞተው የአንቺ ነው፤ በሕይወት ያለው ግን የእኔ ልጅ ነው አለች። በዚህ ዓይነት በንጉሡ ፊት ተከራከሩ።
\s5
\v 23 ከዚህ በኋላ ንጉሥ ሰሎሞን አንደኛዋ በሕይወት ያለው ልጅ የእኔ ነው፣ የሞተው ግን የአንቺ ነው ትላለች፤ ሌላይቱም ደግሞ አይደለም የአንቺ ልጅ ሞቶአል፤ የእኔ ልጅ በሕይወት ያለው ነው ትላታለች አለ።
\v 24 ንጉሡም ሰይፍ እንዲያመጡለት አዘዘ፤ ሰይፍም አመጡለት።
\v 25 በሉ እንግዲህ በሕይወት ያለውን ልጅ ለሁለት ቁረጡና ለእያንዳንዱ ሴት ግማሽ አካሉን ስጡ ሲል አዘዘ፡፡
\s5
\v 26 እውነተኛይቱ ግን ለልጅዋ በመራራት አዝና ንጉሥ ሆይ፣ እባክህ ልጁን አትግደለው፤ ለእርስዋ ይሰጣት አለች። ሌላይቱ ሴት ግን፣ ለእኔም ለእርስዋም አይሁን፤ ለሁለት ይቆረጥ አለች።
\v 27 ከዚህ በኋላ ሰሎሞን ሕፃኑን አትግደሉት፤ እውነተኛይቱ እናት እርስዋ ስለሆነች ለመጀመሪያይቱ ሴት ስጡአት ሲል አዘዘ።
\v 28 እስራኤላውያን ይህን የፍርድ ውሳኔ በሰሙ ጊዜ ሰሎሞን የሕዝብ ጉዳዮችን በትክክለኛ ፍርድ የሚወስንበትን ጥበብ እግዚአብሔር የሰጠው መሆኑን ስለ ተገነዘቡ ታላቅ አክብሮት ሰጡት።
\s5
\c 4
\p
\v 1 ንጉሡ ሰሎሞን በመላው አስራኤል ላይ ነግሦ ነበር።
\v 2 ንጉሡም የሾማቸው ባለሥልጣኖች እነዚህ ናቸው። እነርሱም፡- ዓዛርያስ የተባለው የሳዶቅ ልጅ፡- ካህን ነበር።
\v 3 ኤልያፍና አኪያ የተባሉ የሴባ ልጆች የቤተ መንግሥት ጻሐፊዎች ነበሩ። ኢዮሣፍጥ የተባለው የአሒሉድ ልጅ ታሪክ ጻሐፊና የመዛግብት ኃላፊ ነበር።
\v 4 በናያስ የተባለው የዮዳሄ ልጅ የጦር ሠራዊት አዘዥ ነበር። ሳዶቅና አብያታር ካህናት ነበሩ።
\s5
\v 5 ዓዛርያስ የተባለው የናታን ልጅ፡- የክፍለተ አገራት ገዢዎች የበላይ ኃላፊ ነበር። የናታን ልጅ ዛቡድ፡- ካህንና የንጉሡ አማካሪ ነበር።
\v 6 አሒሳር የተባለው፡- የቤተ መንግሥት አገልጋዮች ኃላፊ፤ አዶኒራም የተባለው የዓብዳ ልጅ፡- የግዳጅ ሥራ ተቆጣጣሪና ኃላፊ ነበር።
\s5
\v 7 ንጉሡ ሰሎሞንም በመላው እስራኤል ለንጉሡና ለንጉሡ ቤተ ሰብ ቀለብ የሚያዘጋጁ ዐሥራ ሁለት ባለሥልጣኖች ነበሩት፡፡ እያንዳንዳቸውም በዓመት ውስጥ ለአንድ ወር ቀለብ የማቅረብ ግዴታ ነበረባቸው፡፡
\v 8 የእነዚህም ዐሥራ ሁለት ገዢዎችና የሚያስተዳድሩአቸው ግዛቶች ስም ዝርዝር ከዚህ የሚከተለው ነው፡- ቤንሑር፡- ኮረብታማ የሆነችው የኤፍሬም አገር ገዢ፤
\v 9 ቤንዴር፡- የማቃጽ የሻዓልቢም፤ የቤትሻሜሽ፡- የኤሎንና የቤት ሐናን ከተሞች ገዢ፤
\v 10 ቤንሔሴድ፡- የአሩቦትና የሶኮ ከተሞችና የመላው የሐፌር ግዛት አስተዳዳሪ፤
\s5
\v 11 ጣፋት የተባለችውን የሰሎሞንን ሴት ልጅ አግብቶ የነበረው ቤን አሚናዳብ የመላው የዶር ግዛት አስተዳዳሪ፤
\v 12 በዓና የተባለው የአሒሉድ ልጅ፡-የታዕናክና የመጊዶ ከተሞች፤ እንዲሁም በቤትሳን አጠገብ ያለው ግዛት በሙሉ በጸርታን ከተማ አጠገብ ያለው ግዛትና በኢይዝራኤል ከተማ በስተደቡብ ያለው ግዛት፤ እንዲሁም አቤልመሖላና ዮቅምዓም ተብለው እስከሚጠሩት ከተሞች ድረስ ያለው ግዛት ሁሉ አስተዳዳሪ፤
\v 13 በገለዓድ ራሞት ቤን ጌቤር ተብላ የምትጠራው ከተማ በገለዓድ የምናሴ ዘር የሆነው የኢያዕር ጎሣ ይዞታዎች የሆኑት መንደሮች፤ በባሳን አርጎብ ተብላ የምትጠራው ግዛት እንዲሁም በሮቻቸው የነሐስ መወርወሪያ ባሉአቸው የቅጥር ግንቦች የተመሸጉ በድምሩ የስልሳ ታላላቅ መንደሮች አስተዳዳሪ፤
\v 14 አሒናዳብ የተባለው የዔዶ ልጅ፡- የመሃናይም ክፍለ አገር ገዢ፤
\s5
\v 15 መካከል ባስማት ተብላ የምትጠራውን የሰሎሞንን ሴት ልጅ አግብቶ የነበረው አኪማአስ፡- የንፍታሌም ግዛት አስተዳዳሪ፤
\v 16 በዓና የተባለው የሔሻይ ልጅ፡- የአሴር ግዛትና የበዓሎት ከተማ ገዢ፤
\v 17 ኢዮሣፍጥ የተባለው የፋሩሕ ልጅ፡- የይሳኮር ግዛት አስተዳዳሪ፤
\s5
\v 18 ሳሚ የተባለው የኤላ ልጅ፡- የብንያም ግዛት አስተዳዳሪ፤
\v 19 ጊቤር የተባለው የኡሪ ልጅ፡- በአሞራውያን ንጉሥ በሴዎንና በባሳን ንጉሥ በዐግ ትገዛ የነበረችው የገለዓድ ግዛት አስተዳዳሪ፤ እነዚህን ዐሥራ ሁለቱን አስተዳዳሪዎች የሚቆጣጠር በመላ አገራቱ ሌላ አንድ የበላይ ኃላፊ ነበር፡፡
\s5
\v 20 የይሁዳና የእስራኤል ሕዝብ ብዛት እንደ ባሕር ዳር አሸዋ ነበር፤ እነዚህ ሁሉ እየበሉና እየጠጡ ዘወትር ደስ እየተሰኙ ነበር፡፡
\v 21 የሰሎሞንም ግዛት ከኤፍራጥስ ወንዝ ጀምሮ እስከ ፍልስጥኤም ግዛት፣ ከዚያም አልፎ እስከ ግብፅ ወሰን ያለውን አገር ሁሉ ያጠቃልል ነበር፤ የእነዚህም አገሮች ሕዝቦች በጠቅላላ ሰሎሞን በነበረበት ዘመን ሁሉ ለእርሱ ተገዢዎች ሆነው ይገብሩለት ነበር፡፡
\v 22 ሰሎሞንም በየቀኑ ለቀለብ የሚሆን አምስት ሺህ ኪሎ ግራም ያህል ምርጥ ዱቄት፤ ዐሥር ሺህ ኪሎ ግራም ያህል ነበር፡፡
\v 23 በበረት ውስጥ እየተመገቡ የደለቡ ዐሥር ሰንጋዎችና በግጦሽ መስክ ተሰማርተው የተመገቡ ሃያ ፍሪዳዎች፣ አንድ መቶ በጎች፤ ከዚህም ሌላ አጋዘኖች፣ የሜዳ ፍየሎች፤ ሚዳቆዎችና ምርጥ ወፎች ያስፈልጉት ነበር፡፡
\s5
\v 24 ሰሎሞን ከኤፍራጥስ ወንዝ በስተ ምዕራብ ያለው ምድር ሁሉ ከቲፍሳ ከተማ ጀምሮ እስከ ጋዛ ከተማ ድረስ ይገዛ ነበር፤ ይህም ከኤፍራጥስ ወንዝ በስተምዕራብ የሚገኙትን ነገሥታት ሁሉ ያጠቃልላል፤ ጎረቤቱ ከሆኑት አገሮችም ሁሉ ጋር በሰላም ይኖር ነበር፡፡
\v 25 በኖረበትም ዘመን ሁሉ ከዳር እስከ ቤርሳቤህ ድረስ መላው የይሁዳና የእስራኤል ሕዝብ ያለ ስጋት በሰላም ይኖር ነበር፤ እያንዳንዱ ቤተ ሰብ ለራሱ የሆነ የወይን ተክልና የበለስ ዛፍ ስለ ነበረው በእነዚህ ተክሎች ጥላ ሥር ያርፍ ነበር፡፡
\s5
\v 26 ሰሎሞን ሠረገላ የሚስቡ አርባ ሺህ ፈረሶች፣ ለጦርነት የሚያገለግሉ ዐሥራ ሁለት ሺህ ፈረሶች ነበሩት፡፡
\v 27 ለሰሎሞንና በቤተ መንግሥቱ ለሚቀለቡት ሁሉ የሚያስፈልገውን ምግብ የሚያቀርቡ ዐሥራ ሁለቱ ገዢዎች እያንዳንዳቸው በተመደበላቸው ወር ምንም ነገር ሳያጓድሉ በወቅቱ ያመጡ ነበር፡፡
\v 28 ከዚህም በቀር እያንዳንዱ ገዢ እንደሚችለው ሌላም አገልግሎት ለሚያበረክቱ የጋማ ከብቶች ገብስና ገለባ ያቀርብ ነበር፡፡
\s5
\v 29 እግዚአብሔር ለሰሎሞን አጅግ አስደናቂ የሆነ ጥበብንና አስተተዋይነትን እንዲሁም እንደ ባሕር ዳር አሸዋ ወሰን የማይገኝለትን ዕውቀት ሰጠው፡፡
\v 30 የሰሎሞንም ጥበብ ከምሥራቅ አገርና ከግብፅም ጥበበኞች እጅግ የላቀ ነበረ፡፡
\v 31 እርሱ ከሰዎች ሁሉ የሚበልጥ ታላቅ ጥበበኛ ነበረ፤ ከኢይዝራኤላዊው ኤታን፣ የማሖል ልጆች ከሆኑት ከሮማን ከካልኮልና ከዳርዓዕ የሚበልጥ ጥበበኛ ነበረ፤ ዝናውም ከፍ ብሎ በጎረቤት ሕዘቦች ሁሉ ዘንድ አስተጋባ፡፡
\s5
\v 32 ሦስት ሺህ ምሳሌዎችንና አንድ ሺህ አምስት የመዝሙር ድርስቶች ነበሩት፡፡
\v 33 ሰሎሞን ከሊባኖስ ዛፍ ጀምሮ በቤት ግንብ ላይ እስከሚበቅለው ሂሶጵ ድረስ ስለ ዛፎችና ስለ ተክሎች ምሳሌዎችን ተናግሮአል፤ እንዲሁም ስለ ልዩ ልዩ እንስሶች፣ ወፎች፣ በሆዳቸው እየተሳቡ ስለሚሄዱ ፍጥረቶችና ስለዓሣዎች አስተምሮአል፡፡
\v 34 በመላው ዓለም የሚገኙ ነገሥታት ስለ ሰሎሞን ጥበብ ለመስማት ይመጡ ነበር፡፡ ስለ ጥበቡም የሰሙት ከምድር ነገሥታት ሁሉ ወደ እርሱ መጥተዋል፡፡
\s5
\c 5
\p
\v 1 የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ከዳዊት ጋር ወዳጅነቱን አጽንቶ ቆይቶ ነበር፤ እርሱም ሰሎሞን በአባቱ በዳዊት ፈንታ መንገሡን በሰማ ጊዜ ወደ እርሱ መልእክተኞቹን ላከ፡፡
\v 2 ሰሎሞንም ወደ ኪራም እንዲህ የሚል መልእክት ላከ፡፡
\v 3 አባቴ ዳዊት በዙሪያው ከነበሩት ከብዙ ጦርነቶች የተነሣ ለእግዚአብሕሔር አምላክ በስሙ ቤተ መቅደስ ለመሥራት አለመቻሉን ታውቃለህ፤ እግዚአብሔርም በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ጠላቶቹን ከእግሩ በታች አንበረከካቸው፡፡
\s5
\v 4 አሁን ግን አምላኬ እግዚአብሔር በሁሉም ድንበር እረፍት ሰጥቶኛል፡፡ ምንም ዓይነት ጠላት ወይም አደጋ የሚጥል የለብኝም፡፡
\v 5 ስለዚህ እግዚአብሔር ለአባቴ ለዳዊት፡- ከአንተ በኋላ የማነግሠው ልጅህ ለእኔ በስሜ ቤተ መቅደስ ይሠራልኛል ሲል ተናግሮት ስለነበር፤ ለአምላኬ ለእግዚአብሔር በስሙ ቤተ መቅደስ ለመሥራት አሁን አቅጃለሁ፡፡
\s5
\v 6 ስለዚህም የሊባኖስ ዛፍ እንጨት የሚቆርጡ ሰዎች ወደ ሊባኖስ ላክልኝ፡፡ የእኔም ሰዎች ከእነርሱ ጋር አብረው እንዲሠሩ አደረጋለሁ፤ ለአንተም ሰዎች የምትወስነውን ደመወዝ እከፍላለሁ፤ አንተም እንደምታውቀው፣ የእኔ ሰዎች ስለ ዛፍ አቆራረጥ የአንተን ሰዎች ያህል ዕውቀት የላቸውም፡፡
\s5
\v 7 ኪራም የሰሎሞን መልእክት ሲደርሰው እጅግ ተደሰቶ፣ በእርሱ ፈንታ ተተክቶ በዚህ በታላቅ ሕዝብ ላይ እንዲነግሥ ይህን የመሰለ ጥበበኛ ልጅ ለዳዊት የሰጠው እግዚአብሔር የተባረከ ይሁን አለ፡፡
\v 8 ከዚህ በኋላ ኪራም ከዚህ የሚከተለውን መልእክት ለሰሎሞን ላከ፤ የላክልኝን መልእክት ሰምቻለሁ፤ የምትፈልገውን ሁሉ፣ የሊባኖሱን ዛፍና የዝግባውን ግንድ አዘጋጅልሃለሁ፡፡
\s5
\v 9 የእኔ ሰዎችም ግንዶችን ከሊባኖስ ወደ ባሕር ያወርዳሉ፤ አስረውም አንተ ወደምትፈልገው ጠረፍ በውኃ ላይ ተንሳፍፈው እንዲደርሱ ያደርጋሉ፤ በዚያም የእኔ ሰዎች ማሰሪያውን ፈተው ለአንተ ሰዎች ያስረክቡአቸዋል፤ አንተም በበኩልህ ለቤተ ሰቤ ምግብ በመስጠት ፍላጎቴን ትመልስልኛለህ፡፡
\s5
\v 10 በዚህ ዓይነት ኪራም ለሰሎሞን የሚያስፈልገውን የሊባኖሱን ዛፍና የዝግባ ግንድ ሁሉ ሰጠው፡፡
\v 11 ሰሎሞንም በበኩሉ ለኪራም ቤተ ሰቦች ቀለብ የሚሆን ሃያ ሺህ መስፈሪያ ስንዴና ሃያ መስፈሪያ ንጹሕ ዘይት ሰጠ፡፡ ይህንንም በየዓመቱ ይሰጥ ነበር፡፡
\v 12 እግዚአብሔር አስቀድሞ የሰጠውን የተስፋ ቃል በመጠበቅ ለሰሎሞን ጥበብ ሰጠው፤ በሰሎሞንና በኪራም መካከል ሰላም ነበር፤ ሁለቱም የጋራ ስምምነት አደረጉ፡፡
\s5
\v 13 ንጉሥ ሰሎሞን ከመላው እስራኤል ሠራተኞችን መለመለ፤ የግዳጅ ሠራተኞችም ሠላሳ ሺህ ነበሩ፡፡
\v 14 ዐሥር ሺህ የሚያህሉትን ለአንድ ወር ወደ ሊባኖስ በፈረቃ ላካቸው፡፡ ለአንድ ወር በሊባኖስ ሁለት ወር በቤታቸው ነበሩ፡፡ አዶኒራም የተባለው ሰው በግዳጅ ሠራተኞች ላይ ኃላፊ ነበር፡፡
\s5
\v 15 ንጉሥ ሰሎሞን በኮረብታማው አገር ድንጋይ የሚፈልጡ ሰማኒያ ሺህ፣ የተፈለጠውን ድንጋይ ተሸክመው የሚያመጡ ሰባ ሺህ ሰዎች ነበሩት፡፡
\v 16 የእነዚህ ሠራተኞች የበላይ ሆነው ሥራውን የሚቆጣጠሩ ሦስት ሺህ ሦስት መቶ ሰዎች ነበሩ፡፡
\s5
\v 17 በዚህ ዓይነት ሠራተኞቹ በንጉሥ ሰሎሞን ትእዛዝ ለቤተ መቅደሱ መሠረት የሚሆን ታላላቅ ድንጋዮችን ፈለጡ፡፡
\v 18 የሰሎሞንና የኪራም አናጢዎችና ግንበኞች የጌባላውያንም ሰዎች ቤተ መቅደሱን ለመሥራት የሚያስችላቸውን ድንጋይና እንጨት ሁሉ አዘጋጁ፡፡
\s5
\c 6
\p
\v 1 ስለዚህ ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ መሥራት ጀመረ፡፡ ይህም የእስራኤል ሕዝብ ከግብጽ ምድር ከወጡ ከአራት መቶ ሰማኒያ ዓመት በኋላ፣ ሰሎሞን በእስራኤል ላይ በነገሠ በአራተኛው ዓመት ዚፍ ተብሎ በሚጠራው በሁለተኛው ወር ነበር፡፡
\v 2 ቤተ መቅደሱም በውስጥ በኩል ርዝመቱ ሃያ ሰባት ሜትር፣ ወርዱ ዘጠኝ ሜትር፣ ቁመቱ ዐሥራ ሦስት ሜትር ተኩል ነበር፡፡
\s5
\v 3 በመግቢያው በር የሚገኘው በረንዳ ቁመቱ አራት ሜትር ተኩል፣ ወርዱ ልክ እንደ ቤተ መቅደሱ ዘጠኝ ሜትር ነበር፡፡
\v 4 የቤተ መቅደሱም ሕንፃ ከውስጥ ሰፋ፣ ከውጪ ጠበብ ያሉ መስኮቶች ነበሩት፡፡
\s5
\v 5 በቤተ መቅደሱን ሕንፃ ፊት ለፊት ግድግዳ ዙሪያ ክፍሎችን ሠራ፤ በዋናው መግቢያ በር በውጪና በውስጥ ክፍሎች ሠራ፤ በዙሪያውም ክፍሎችን አደረገ፡፡
\v 6 የታችኛው ፎቅ ክፍል ወርዱ አምስት ክንድ፣ የመካከለኛ ፎቅ ክፍል ስድስት ክንድ፣ የሦስተኛው ፎቅ ክፍል ወርድ ሰባት ክንድ ነበር፤ የእንያዳንዱ ወለል ግንብ ከታች በኩል ካለው የወለል ግንብ የሳሳ ነበር፤ ሠረገሎቹ ወደ ቤተ መቅደሱ ግድግዳ እንዳይገቡ ለማድረግ ከቤተ መቅደሱ ግድግዳ ውጪ ዐረፍቶችን አደረገ፡፡
\s5
\v 7 ቤተ መቅደሱ የታነጸባቸው ድንጋዮች ተጠርበው የተዘጋጁት በዚያው በተፈለጡበት ቦታ ነበር፤ ቤተ መቅደሱ በሚሠራበት ጊዜ የመዶሻ፣ የመጥረቢያ ወይም የሌላ ብረት ነክ መሣሪያ ድምፅ አይሰማም ነበር፡፡
\v 8 ከቤተ መቅደሱ በስተደቡብ በኩል በምድር ደረጃው ላይ መግቢያ በር ነበር፡፡ ከዚያ በደረጃዎቹ መካከለኛ ደረጃ ወደ ላይ ያስኬዳል፡፡ እንዲሁም ከመካከለኛው ደረጃ ወደ ሦስተኛ ደረጃ ይወስዳል፡፡
\s5
\v 9 በዚህ ሁኔታ ሰሎሞን የቤተ መቅደሱን ሕንፃ ሥራ ፈጸመ፤ ጣራውንም ከውስጥ በኩል ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት በተሠራ አግዳሚ ሠረገላና ጠርብ ቤቱን ሸፈነው፡፡
\v 10 የእያዳንዱ ፎቅ ቁመት አምስት ክንድ ከፍታ ሆኖ ከውጪ በኩል ወደ ቤተ መቅደሱ ተጠግቶ የተሠራው ባለ ሦስት ፎቅ ተጨማሪ ሕንፃ ከዋናው ሕንፃዎች ከሊባኖስ ዛፍ በተሠሩት አግዳሚ ወራጆች የተያያዘ ነበር፡፡
\s5
\v 11 የእግዚአብሔር ቃል ወደ ሰሎሞን እንዲህ ሲል መጣ፡-
\v 12 እየተሠራ ያለውን ቤተ መቅሰደስ በተመለከተ፣ በትእዛዜ መንገድ ብትሄድና ቅን ፍርድ ብታደርግ ለአባትህ ለዳዊት እንዳደረግሁ የሰጠሁትን ተስፋ አጸናልሃለሁ፡፡
\v 13 በሕዝቤ በእስራኤል መካከል እኖራለሁ፣ ከቶም አልተዋቸውም፡፡
\s5
\v 14 ስለዚህ ሰሎሞን ቤተ መቅደሱን ሠርቶ ጨረሰ፡፡
\v 15 ከዚያ የቤተ መቅደሱን የውስጥ ግድግዳዎች በሊባኖስ ዝግባ ሠራ፤ ከወለሉ እስከ ጣራው ድረስ ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት ተጠርበው በተሠሩ ሳንቃዎች ለበደ፤ የወለሉም ጣውላ ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት የተሠራ ነበር፡፡
\s5
\v 16 ውስጣዊ ክፍል ከቤተ መቅደሱ በስተ ኋላ ገባ ብሎ ተሠራ፣ የእርሱም ርዝመት ዘጠኝ ሜትር ሲሆን ከወለሉ እስከ ጣራው ድረስ ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት ተጠርቦ በተሠራ ሳንቃ የተከፈለ ነበር፤ ይህንን ክፍል ቅድሰተ ቅዱሳን ውስጠኛ ክፍል እንዲሆን ነው፡፡
\v 17 ከቅድስተ ቅዱሳኑ ፊት ለፊት የሚገኘውም የተቀደሰ ክፍል ርዝመት አርባ ክንድ ነበር፡፡
\v 18 የሊባኖስ ዛፍ እንጨት ሳንቃዎች በአበባ እንቡጦችና በፈኩ አበባዎች ቅርጽ አጊጠው ነበር፤ ውስጡም ሁሉ ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት ተጠርቦ በተሠራ ሳንቃ ስለ ተለበጠ የግንቡ ድንጋዮች አይታዩም ነበር፡፡
\s5
\v 19 ሰሎሞንም ከቤተ መቅደሱ ውስጥ በስተኋላ በኩል የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት የሚቀመጥበት ውስጣዊ ክፍል አዘጋጀ፡፡
\v 20 ይህም ውስጣዊ ክፍል ርዝመቱ ዘጠኝ ሜትር፣ ወርዱ ዘጠኝ ሜትር፣ ቁመቱ ዘጠኝ ሜትር ሲሆን፣ በሙሉ በንጹሕ ወርቅ የተለበጠ ነበር፤ መሠዊያውም ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት ተጠርቦ በተሠራ ሳንቃ የተለበጠ ነበር፡፡
\s5
\v 21 ሰሎሞንም ቤተ መቅደሱን በውስጥ በኩል በንጹሕ ወርቅ ለበጠው፤ እርሱም ክፈፉን በተሸጋገሩ የወርቅ ሰንሰለቶች አስጌጠው፡፡
\v 22 የቅድስት ቅዱሳኑ ውስጠኛ በወርቅ ለበጠው፡፡
\s5
\v 23 ሰሎሞንም እያንዳንዱ ዐሥር ክንድ የሆነ ከወይራ እንጨት በሁለት ኪሩቤል አምሳል የተቀረጹ ሥዕሎች በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ ሠራ፡፡
\v 24 የኪሩቡ አንደኛው ክንፍ አምስት ክንድ፤ የኪሩቡም ሁለተኛው ክንፍ አምስት ክንድ ነበረ፤ ከአንደኛው ክንፍ ጫፍ ጀምሮ እስከ ሁለተኛው ክንፍ ጫፍ ድረስ ዐሥር ክንድ ነበረ፡፡
\v 25 ሁለተኛውም ኪሩብ ዐሥር ክንድ ነበረ፤ የሁለቱም ኪሩቤል ቅርጽና መጠን ተመሳሳይ ነበር፡፡
\v 26 የአንዱ ኪሩብ ቁመት ዐሥር ክንድ ነበረ፤ የሁለተኛውም ኪሩብ እንዲሁ ነበረ፡፡
\s5
\v 27 ኪሩቤልንም በቅድስት ቅዱሳኑ ውስጥ እንዲቆሙ አደረገ፤ ስለዚህም የተዘረጉ ሁለቱ ክንፎቻቸው በክፍሉ መካከለኛ ቦታ ላይ ተገናኝተው ሌሎቹ ሁለቱ ክንፎቻቸው ደግሞ በተዘረጉበት አቅጣጫ ግንቦቹን ይነኩ ነበር፡፡
\v 28 ሰሎሞንም ሁለቱን ኪሩቤል በወርቅ ለበጣቸው፡፡
\s5
\v 29 የዋናውን ክፍልና የውስጠኛውን ክፍል ግንቦች በሙሉ በኪሩቤል፣ በዘንባባ ዛፎችና በፈኩ የአበባ ቅርጾች አስጌጣቸው፡፡
\v 30 እርሱም ከውስጥና ከውጪ በኩል ያሉትን ክፍሎች ወለል በወርቅ ለበጣቸው፡፡
\s5
\v 31 ከወይራ እንጨት የተሠራ ሁለት ተካፋች በር በቅድስተ ቅዱሳኑ መግቢያ እንዲቆም አደረገ፤ በሩም አምስት ማእዘን ያለው ሆኖ አናቱ ላይ ቀጥ ብሎ የተሠራ ቅስት ነበር፡፡
\v 32 ሁለቱን በሮች በኪሩቤል፤ በዘንባባ ዛፎችና በፈኩ የአበባ ቅርጾች አስጌጣቸው፤ እርሱም በሮቹን፣ ኪሩቤልን፣ የዘንባባ ዛፎቹንና ቅርጾቹን በወርቅ ለበጣቸው፡፡
\s5
\v 33 በዚህ ዓይነት ሰሎሞን ደግሞ ወደ ዋናው ክፍል ለሚያደርሰው መግቢያ በር ከወይራ እንጨት የተሠራ ባለ አራት ማእዘን ክፈፍ አበጀለት፡፡
\v 34 ሁሉቱንም በሮች ከዝግባ እንጨት ሠራ፤ አንዱ በር በማጠፊያ ከተያያዘ ከሁለት ሳንቃ ተደረገ፤ ሁለተኛውም በር በማጠፊያ ከተያያዘ ከሁለት ሳንቃ ተደረገ፡፡
\v 35 እነርሱን ሙሉ በሙሉ በወርቅ በተለበጡ በኪሩቤል፣ በዘንባባ ዛፎችና በፈኩ የአበባ ቅርጾች አስጌጣቸው፡፡
\s5
\v 36 በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት አንድ የውስጥ አደባባይ ሠራ፤ በዚህም አደባባይ ዙሪያ በየሦስቱ ዙር የድንጋይ ረድፍ አንድ የሊባኖስ ዛፍ ሠረገላ ሳንቃ የተጋደመበት ግንብ አደረገ፡፡
\s5
\v 37 የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መሠረቱ የተጣለው ሰሎሞን በነገሠ በአራተኛው ዓመት ዚፍ ተብሎ በሚጠራው በሁለተኛው ወር ነበር፡፡
\v 38 ሰሎሞን በነገሠ በዐሥራ አንደኛ ዓመቱ ቡል ተብሎ በሚጠራው በስምንተኛው ወር ላይ የቤተ መቅደሱ ሁሉም ክፍሎችና ሁሉም ንድፍ ተጠናቀቀ፡፡ ሰሎሞንም ቤተ መቅደሱን ለመሥራት ሰባት ዓመት ወሰደበት፡፡
\s5
\c 7
\p
\v 1 ሰሎሞንም ለራሱ የሚሆን ቤተ መንግሥት ሠራ፤ ቤተ መንግሥቱንም ለመሥራት ዐሥራ ሦስት ዓመት ፈጀበት፡፡
\v 2 እርሱም የሊባለኖስ ጫካ ተብሎ የተጠራውን ቤተ መንግሥት ሠራ፡፡ ርዝመቱም ወርዱ አንድ መቶ ክንድ፣ ስፋቱም አምሳ ክንድ፤ ቁመቱም ሠላሳ ክንድ ነበር፡፡ ቤተ መንግሥቱ አራት ረድፍ ሆኖ ከዝግባ እንጨት ምስሶዎች የተሠሩ ሲሆን፣ በምስሶዎቹ ላይ አግዳሚ ሠረገላዎች ተጋድመው ነበር፡፡
\s5
\v 3 የእነዚህ ዕቃ ቤቶች ጣራ ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት የተሠራ ነበር፡፡ በምስሶዎቹም ላይ በነበሩ አግዳሚዎች ቤቱ በዝግባ ሳንቃ ተሸፍኖ ነበር፡፡ ምስሶዎቹም በአንዱ ረድፍ ዐሥራ አምስት፣ በአንዱ ረድፍም አምስት እየሆኑ አርባ አምስት ነበሩ፡፡
\v 4 ትይዩ የሆኑት የሕንፃው ሁለት ግንቦች እያንዳንዳቸው በመደዳ ሦስት፣ ሦስት መስኮቶች ነበሩአቸው፡፡
\v 5 በሮቹና መስኮቶቹ ሁሉ ባለአራት ማእዘን መቃኖች ነበሩአቸው፤ ለእያንዳንዱ ግንብ በረድፍ የተሠሩ ሦስት ሦስት መስኮቶች ነበሩት፤ የእያንዳንዱ ግንብ መስኮቶች ከሌላው ግንብ መስኮቶች ጋር ትይዩ ነበሩ፡፡
\s5
\v 6 ምሶሶዎች ያሉበትን ቤት ሠራ፤ ርዝመቱም አምሳ ክንድ፣ ስፋቱም ሠላሳ ክንድ ነበረ፤ በእርሱም ፊት ደግሞ ምሶሶና መድረክ ያለበት ወለል ነበረ፡፡
\s5
\v 7 ሰሎሞን ችሎት ተቀምጦ የፍርድ ውሳኔ የሚሰጥበትም የዙፋን አዳራሽ ሠራ፡፡ ከወለሉ እስከ ጣራው ድረስ ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት በተሠራ ሳንቃ የተሸፈነ ነበር፡
\s5
\v 8 ከችሎቱም አዳራሽ በስተ ኋላ በሚገኘው ሌላ አደባባይ ሰሎሞን የሚኖርበትን ሕንጻ እንደ ሌሎቹ ሕንጻዎች አድርጎ አሠራ፤ የግብጽ ንጉሥ የፈረዖን ልጅ ለነበረቸው ሚስቱም ተመሳሳይ መኖሪያ ቤት አሠራላት፡፡
\s5
\v 9 እነዚህ ሁሉ ሕንፃዎችና ታላቁ አደባባይ ጭምር ከመሠረታቸው እስከ ድምድማታቸው በጥሩ ታላላቅ ድንጋዮች አጊጠው የተሠሩ ነበሩ፣ ድንጋዮቹም በዚያ በድንጋይ መፍለጫ ስፍራ በፊትም በኋላም በልክ ተፈልፍለውና ተጠርበው የመጡ ነበር፡፡
\v 10 የቤቱ መሠረት የተሠራው በጣም ታላላቅና ውድ በሆኑ ስምንትና ዐሥር ክንድ ርዝመት ባላቸው ድንጋዮች የተሠሩ ነበር፡፡
\s5
\v 11 እነዚህም ውድና በልክ ከተፈለፈሉ ድንጋዮችና ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት የተሠሩ አግዳሚ ሠረገሎች ነበሩ፡፡
\v 12 የቤተ መንግሥቱ አደባባይ ወደ ቤተ መቅደሱ የሚያስገባው በር በእያንዳንዱ ባለ ሦስት ረድፍ የጥርብ ድንጋይ ሕንፃ ላይ አንዳንድ ረድፍ የሊባኖስ ዛፍ እንጨት ሠረገላ የተጋደመባቸው ግንቦች ነበሩ፡፡
\s5
\v 13 ንጉሡ ሰሎሞንም ሔራም የተባለውን ሰው ከጢሮስ ከተማ አመጣ፡፡
\v 14 ሔራም እናቱ ባል የሞተባት የንፍታሌም ነገድ ተወላጅ ነበረች፣ አባቱም የጢሮስ ተወላጅ ሲሆን እርሱም ነሐስ አቅልጦ በመሥራት ጥበብ የሠለጠነ ባለሙያ ነበር፡፡ ሔራም በእጅ ጥበብ ብዙ ልምድ ያለው ብልህ ሰው ነበር፤ እርሱም የነሐስ ጥበብ ሥራ ለንጉሡ ለመሥራት ወደ ንጉሥ ሰሎሞን መጣ፡፡
\s5
\v 15 ሔራም የእያንዳንዳቸው ቁመት ዐሥራ ስምንት ክንድ፣ የዙሪያ ስፋታቸው ዐሥራ አምስት ክንድ ሁለት የነሐስ ምሶሶዎችን ሠራ፡፡
\v 16 እንዲሁም በምሶሶዎቹ ላይ የሚቆሙ የእያንዳንዳቸው ቁመት አምሰት ክንድ የሆነ ሁለት የነሐስ ጉልላቶችን ሠራ፡፡
\v 17 በምሶሶዎቹም ራስ ላይ የነበሩትን ጉልላቶች ያስጌጡ ዘንድ በሰባት ረድፍ የተሠሩ መረቦችን ሠራ፡፡ አንዱን መረብ ለአንድ ጉልላት ሁለተኛውን መረብ ለሁለተኛው ጉልላት አደረገ፡፡
\s5
\v 18 ስለዚህም ሔራም ምሶሶዎቹ ጫፍ ላይ ያሉትን ጉልላቶች ለማስጌጥ ሮማኖችን በሁለት ረድፍ ሠራ፡፡ ለየእያንዳንዱም ጉልላት እንዲሁ አደረገ፡፡
\v 19 በወለሉ ምሶሶዎች አናት ላይ ያሉት ጉልላቶች ቁመታቸው አራት ክንድ ሲሆን የሱፍ አበባን በሚመስል ሥራ ተጊጠው ነበር፡፡
\s5
\v 20 እነርሱም ከመረቡ በላይ ባለው ክብ ስፍራ እንዲቆሙ ተደረገ፤ በእያንዳንዱም ጉልላት ዙሪያ በሁለት ረድፍ የተደረደሩ ሁለት መቶ የሮማን ቅርጾች ነበሩ፡፡
\v 21 ሔራም ከነሐስ የተሠሩትን ሁለት ምስሶዎች በቤተ መቅደሱ መግቢያ በር ፊት ለፊት አቆማቸው:: ከቤተ መቅደሱም መግቢያ በር በስተደቡብ በኩል የቆመው ምሶሶ ‹‹ያኪን›› ተብሎ ተጠራ፤ በስተ ሰሜን በኩል የቆመው ምሶሶ ደግሞ ‹‹ቦዔዝ›› ተባለ፡፡
\v 22 በምሶሶዎቹ ጫፍ ላይ የሱፍ አበባ የሚመስሉ ከነሐስ የተሠሩ ጉልላቶች ነበሩ፡፡ የምስሶዎቹም ሥራ በዚህ ዓይነት ተፈጸመ፡፡
\s5
\v 23 ሔራም ዐሥር ክንድ ጥልቀት፣ የክብ ማእከል ርዝመት አምስት ክንድ ዙሪያ ያለው አንድ ክብ ገንዳ ከነሐስ ሠራ፡፡ ባሕሩም ዙሪያው ሠላሳ ክንድ ነበር፡፡
\v 24 የገንዳው አፍ ውጪኣዊ ክፈፍ ሁሉ ከገንዳው ጋር አንድ ወጥ ሆነው በቅል አምሳል ከነሐስ የተሠሩና በሁለት ረድፍ የተደረደሩ ቅርጾች ነበሩት፡፡
\s5
\v 25 ገንዳውም ከነሐስ በተሠሩ ዐሥራ ሁለት የበሬ ምስሎች ጀርባ ላይ ተቀመጠ። ኮርማዎቹም በየአቅጣጫው ፊታቸውን ወደ ውጪ መልሰው ሦስቱ ወደ ሰሜን፤ ሦስቱ ወደ ደቡብ፣ ሦስቱ ወደ ምሥራቅ፣ ሦስቱ ወደ ምዕራብ የሚመለከቱ ይመስሉ ነበር፡፡
\v 26 የገንዳውም ጎኖች ውፍረት አንድ መዳፍ ነበር፤ የጽዋ ቅርጽ ያለው አበባ የሚመስል የአፉ ክፈፍ የሱፍ አበባ ቅርጽ ነበረው፤ ይህም ገንዳ አርባ ሺህ ሊትር ያህል ውሃ የሚይዝ ነበር፡፡
\s5
\v 27 ሔራም ዐሥር መቀመጫዎችን ከነሐስ ሠራ፡፡ የእያንዳንዱ ርዝመት አራት ክንድ፣ ቁመቱ አራት ክንድ፣ ሦስት ክንድ ስፋት ነበር፡፡
\v 28 የመቀመጫዎቹ ሥራም እንዲህ ነበር፡፡ የዕቃ መቀመጫዎቹም የተሠሩት በክንፎቹ መካከል ልሙጥ በሆነ ነገር ነበር፡፡
\v 29 ልሙጥ በሆነውም ነገር ላይ በአንበሶች፣ በበሬዎችና በኪሩቤል አምሳል የተቀረፁ ምስሎች ነበሩ፡፡ ከአንበሶቹ፣ ከበሬዎቹና ከኪሩቤሉ ቅርፆች ራስጌና ግርጌ የአበባ ጉንጉን የሚመስሉ ቅርፆች ነበሩ፡፡
\s5
\v 30 እያንዳንዱ የዕቃ ማስቀመጫ ከነሐስ የተሠሩ አራት መንኮራኩሮች ነበሩባቸው፡፡ መንኮራኩሮቹም የሚሽከረከሩበት የነሐስ ወስከምቶች ነበራቸው፤ እንዲሁም በአራቱ ማእዘኖች የመታጠቢያ ገንዳ መደገፊያዎች ነበሩ፤ መደገፊያዎቹም የአበባ ጉንጉን በሚመስሉ ቅርፆች አጊጠው ነበር፡፡
\v 31 የመታጠቢያ ገንዳውም አንገት አንድ ክንድ ነበር፤ እርሱም ክብ ነበር፤ ቁመቱም አንድ ክንድ ነበር፤ በአንገቱም ላይ ማስጌጫ ቅርፅ ነበረበት፤ የገንዳው ተሸካሚ ግን አራት ማእዘን ነበር እንጂ ክብ አልነበረም፡፡
\s5
\v 32 የመንኮራኩሮቹም ቁመት አንድ ተኩል ክንድ ነበር፤ መንኮራኩሮችም በዕቃ ማስቀመጫው ጠፍጣፋ ነሐስ ሥር ነበሩ፤ የመንኮራኩሮቹም ወስከምቶች ከዕቃ ማስቀመጫዎቹ ጋር አንድ ወጥ ሆነው የተሠሩ ነበሩ፡፡
\v 33 መንኮራኩሮቹም የሠረገላ መንኮራኩሮችን ይመስሉ ነበር፡፡ ወስከምቶቻቸው፣ ቅርጾቻቸውና አቃፊዎቻቸው ሁሉም ከብረት ቀልጠው የተሠሩ ነበሩ፡፡
\s5
\v 34 እያንዳንዱ የዕቃ ማስቀመጫ አራት ማእዘን በየግርጌአቸው ከእነርሱ ጋር አንድ ወጥ ሆነው ከነሐስ የተሠሩ አራት ደጋፊዎች ነበሩአቸው፡፡
\v 35 በእያንዳንዱ የዕቃ ማስቀመጫ ጫፍ ዙሪያ ክፈፍ ላይ ተኩል ክንድ ርዝመት ያለው አንድ ክብ ቅርፅ ነበር፤ መደገፊያዎቹና ጠፍጣፋ ነሐሶቹ ከዕቃ ማስቀመጫው ጋር አንድ ወጥ ሆነው የተሠሩ ነበሩ፡፡
\s5
\v 36 በእነዚህ መደገፊያዎችና ጠፍጣፋ ነሐሶች መካከል ባለው ክፍት ቦታ ሁሉ በኪሩቤል፣ በአንበሶችና በዘንባባ ዛፎች አምሳል ሔራም ሠራቸው፡፡ እንዲሁም ዙሪያቸው የአበባ ጉንጉን በሚመስሉ ቅርፆች አጊጠው ነበር፡፡
\v 37 እንግዲህ ዐሥሩን ባለመንኩራኩር የዕቃ ማስቀመጫዎች የሠራቸው በዚህ ዓይነት ነበር፡፡ መጠናቸውና ቅርፃቸው እኩል ስለተቀረጹ ሁሉም ተመሣሣይ ነበሩ፡፡
\s5
\v 38 ሔራም ለእያንዳንዱ የዕቃ ማስቀመጫ ዐሥር የነሐስ መታጠቢያ ገንዳዎች ሠራ፡፡ የእያንዳንዱ ገንዳ ዙሪያ አጋማሽ ስፋት አራት ክንድ ያህል ሲሆን፣ አርባ ሊትር ያህል ውሃ ይይዝ ነበር፡፡
\v 39 ሔራም አምስቱን የዕቃ ማስቀመጫዎች ከቤተ መቅደሱ በስተደቡብ፣ የቀሩትንም አምስቱን ከቤተ መቅደሱ በስተሰሜን በኩል አቆመ፡፡ ገንዳውን ደግሞ በቤተ መቅደሱ ደቡባዊ ምሥራቅ ማእዘን ላይ አቆመው፡፡
\s5
\v 40 ሔራምም ድስቶችን፣ መጫሪያዎችንና ጎድጓዳ ሳህኖችን ሠራ፡፡ በዚህ ዓይነትም ለንጉሥ ሰለሞን ሊሠራለት የጀመረውን የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሥራ ፈጸመ፡፡
\v 41 ሁለቱ ምሰሶዎች፣ በምሶሶዎቹም ላይ የነበሩትን ጉልላቶች የሚመስሉ ሳህኖችን፣ በምሶሶውም ላይ የነበሩትን ሁለቱን ጉልላቶች የሚሸፍኑትን ሁለቱን መረቦች ሠራ፡፡
\s5
\v 42 በእያንዳንዱ ጉልላት ላይ በመረብ አምሳል የተሠሩት ሰንሰለቶች፣ በእያንዳንዱ ጉልላት ቅርፅ ላይ በሁለት ዘርፍ አንዳንድ መቶ ዙር የሆኑ ከነሐስ የተሠሩ አራት መቶ የሮማን ቅርፆችን ሠራ፡፡
\v 43 ዐሥሩ ባለመንኮራኩር የዕቃ ማስቀመጫዎች፣ ዐሥሩ የመታጠቢያ ገንዳዎች ነበሩ፡፡
\s5
\v 44 ውሃ ማጠራቀሚያ ገንዳ፣ ገንዳውን ደግፈው የሚይዙ የዐሥራ ሁለቱን በሬዎች ቅርፅ ሠራ፡፡
\v 45 ድስቶቹን፣ መጫሪያዎቹንና ጎድጓዳ ሳህኖቹን ሠራ፡፡ ሌሎችንም ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አገልግሎት ይውሉ ዘንድ ሔራም እነዚህን ሁሉ ዕቃዎች ለሰለሞን የሠራለት ከተወለወለ ንፁህ ነሐስ ነበር፡፡
\s5
\v 46 ንጉሥ ሰለሞን እነዚህን ሁሉ ያሠራው በዮርዳኖስ ሸለቆ በሱኮትና ጻርታን መካከል በሚገኘው በሸክላ ስፍራ ነበር፡፡
\v 47 ከነሐስ የተሠራው ይህ ሁሉ ዕቃ እጅግ ብዙ ስለ ነበር፣ ሰለሞን በሚዛን እንዲለካ አላደረገውም፣ ስለዚህ ክብደቱ ምን ያህል እንደሆነ ተወስኖ አልታወቀም፡፡
\s5
\v 48 ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አገልግሎት ይውሉ ዘንድ ሰለሞን ያሠራቸው ዕቃዎች ሁሉ በንጹሕ ወርቅ ያጌጡ ነበሩ፡፡ እነርሱም የወርቁ መሠዊያ፣ ለእግዚአብሔር የሚቀርበው ኅብስት ማኖሪያ የወርቅ ጠረጴዛ ናቸው፡፡
\v 49 በቅድስተ ቅዱሳኑ ፊት ለፊት አምስቱ በስተደቡብ፣ አምስቱ ደግሞ በስተ ሰሜን የሚቀመጡት ዐሥሩ የወርቅ መቅረዞች፣ አበባዎች፣ የመብራት ቀንዲሎች፣ የእሳት መቆስቆሻዎች ሁሉ ከወርቅ የተሠሩ ነበሩ፡፡
\s5
\v 50 ሰሎሞንም ጽዋዎችን፣ የአመድ ማጠራቀሚያዎችን፣ ጎድጓዳ ሳህኖችን፣ የዕጣን ማቅረቢያ ሳህኖችን፣ ማንደጃዎችን፣ ለቅድስተ ቅዱሳን በሮችንና ለቤተ መቅደሱ ውጪኣዊ በሮች የሚያገለግሉ ማጠፊያዎችን ከንጹሕ ወርቅ አሠራ፡፡
\s5
\v 51 በዚህ ዓይነት ንጉሥ ሰለሞን የቤተ መቅደሱን ሥራ ሁሉ ከፈጸመ በኋላ አባቱ ዳዊት ለእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት እንዲውል የለየውን ብሩን፣ ወርቁንና ሌላውንም ዕቃ በሙሉ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ግምጃ ቤት ውስጥ አኖረው፡፡
\s5
\c 8
\p
\v 1 ከዚህ በኋላ ሰሎሞን የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት የዳዊት ከተማ ከሆነችው ከጽዮን ለማምጣትና ወደ ቤተ መቅደሱ ለማስገባት የእስራኤል የነገድ መሪዎችና የጎሣ አለቆች ሁሉ እርሱ ወደሚገኝበት ወደ ኢየሩሳሌም እንዲሰበሰቡ ጠራ፡፡
\v 2 የእስራኤልም ወንዶች ሁሉ በዓሉ በሚከበርበት ኤታኒም ተብሎ በሚጠራው በሰባተኛው ወር ወደ ንጉሥ ሰሎሞን ተሰበሰቡ፡፡
\s5
\v 3 መሪዎቹ ሁሉ በተሰበሰቡ ጊዜም ካህናቱ የቃል ኪዳኑን ታቦት አንሥተው ተሸከሙ፡፡
\v 4 ካህናቱም የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት፣ የመገናኛ ድኳንና በድንኳኑም ውስጥ የነበሩትን ንዋያተ ቅዱሳት ሁሉ አምጥተው ወደ ቤተ መቅደስ አገቡ፡፡
\v 5 ንጉሥ ሰሎሞንና መላው የእስራኤል ሕዝብ በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ተሰበሰቡ፤ ከብዛቱም የተነሣ ሊቆጠር የማይችል ብዙ በጎቸና የቀንድ ከብት መሥዋዕት አድርገው አቀረቡ፡፡
\s5
\v 6 ከዚህም በኋላ ካህናቱ የቃል ኪዳኑን ታቦት ተሸክመው ወደ ቤተ መቅደሱ ውስጠኛ ክፍል፣ በቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ ወደ ቦታው አምጥተው በኪሩቤል ክንፎች ሥር አኖሩት፡፡
\v 7 የተዘረጉ የኪሩቤል ክንፎችም የታቦቱን መሸከሚያ መሎጊያዎች ሸፍነው ነበር፡፡
\v 8 መሎጊያዎቹ ረጃጅሞች ስለ ሆኑ ጫፎቻቸው በቤተ መቅደሱ ውስጥ በቅድስተ ቅዱሳኑ ፊት ለፊት ለሚቆም ሰው ሁሉ በግልጽ ይታዩ ነበር፤ በሌላ አቅጣጫ የሚቆም ግን አያያቸውም፡፡ እስከ ዛሬም እዚያው ይገኛል፡፡
\s5
\v 9 የእስራኤል ሕዝብ ከግብጽ ምድር እንደወጡ እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳ በገባ ጊዜ ሙሴ በሲና ተራራ በቃል ኪዳን ታቦት ውስጥ ካኖራቸው ከሁለቱ የድንጋይ ጽላቶች በቀር በቃል ኪዳን ታቦት ውስጥ ሌላ ምንም ነገር አልነበረም፡፡
\v 10 ካህናቱ ከቅድስተ ቅዱሳን እንደ ወጡ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ድንገት በደመና ተሞልቶ ነበር፡፡
\v 11 በደመናውም ውስጥ የነበረው የእግዚአብሔር ክብር ቤቱን ስለ ሞላ ካህናቱ ቆመው አገልግሎታቸውን ለማከናወን አልቻሉም ነበር፡፡
\s5
\v 12 በዚህ ጊዜ ሰሎሞን እንዲህ ሲል ጸለየ፡- እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! አንተ በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ እኖራለሁ ብለሃል፤
\v 13 እነሆ አሁን ግርማ ሞገስ ያለው ቤተ መቅደስ ለአንተ ሠርቻለሁ፤ እርሱም አንተ ለዘለዓለም የምትኖርበት ቦታ ይሆናል፡፡
\s5
\v 14 የእስራል ጉባኤ ሁሉ ቆመው ሳሉ፤ ንጉሥ ሰሎሞን ፊቱን ወደ እነርሱ መልሶ የእግዚአብሔር በረከት በእርሱ ላይ እንዲወርድ እንዲህ ሲል ጸለየ፤
\v 15 የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን! ለአባቴ ለዳዊት የገባውን ቃል ኪዳን አጽንቶ ጠብቆአል፤ እርሱም እንዲህ የሚል ነው፡-
\v 16 ሕዝቤን ከግብጽ ካወጣሁበት ጊዜ ጀምሮ ስሜ የሚጠራበት ቤተ መቅደስ የሚሠራበት በመላው እስራኤል ምንም ዓይነት ከተማ አልመረጥኩም ነበር፤ አሁን ግን በሕዝቤም በእስራኤል ላይ ይነግሥ ዘንድ ዳዊትን መረጥኩ፡፡
\s5
\v 17 ቀጥሎም ሰሎሞን እንዲህ አለ፤ አባቴ ዳዊት ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስን ለመሥራት አቅዶ ነበር፤
\v 18 እግዚአብሔርም አባቴን ዳዊትን ስሜ የሚጠራበትን ቤተ መቅደስ ትሠራ ዘንድ በልብህ ማሰብህ መልካም ነው፡፡
\v 19 ነገር ግን እርሱን የሚሠራልኝ ልጅህ ነው እንጂ አንተ አይደለህም፤ ከአንተ የሚወለደው ልጅ ቤተ መቅደሴን ይሠራል አለው፡፡
\s5
\v 20 እነሆ እግዚአብሔር የሰጠውን የተስፋ ቃል ጠብቆአል፤ ስለዚህ እኔ በአባቴ ፈንታ ተተክቼ የእስራኤል ንጉሥ ሆኜአለሁ፤ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስን ሠርቼአለሁ፡፡
\v 21 እግዚአብሔር ከግብጽ ምድር ባወጣቸው ጊዜ ከቀድሞ አባቶቻችን ጋር ቃል ኪዳን የገባበት የድንጋይ ጽላት ለሚገኝበት ታቦት ማኖሪያ የሚሆን ቦታ በቤተ መቅደሱ ውስጥ አዘጋጅቼአለሁ፡፡
\s5
\v 22 ከዚህ በኋላ ሰሎሞን በሕዝቡ ፊት ተነሥቶ በእግዚአብሔር መሠዊያው ፊት ቆመ፤ እጆቹንም ወደ ሰማይ ዘረጋ፡፡
\v 23 እንዲህም አለ፡- የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! ለአገልጋዮቹ ቃል ኪዳኑን የሚጠብቅና ከልባቸው ታማኞች እስከ ሆኑ ድረስ ፍቅሩን የሚያጸና በላይ በሰማይ በታችም በምድ እንደ አንተ ያለ አምላክ የለም!
\v 24 ለአባቴ ለዳዊት የሰጠኸውንም የተስፋ ቃል አጽንተሃል፤ በአፍህ የተናገርከውም ቃል ሁሉ እነሆ ዛሬ በእጅህ ተፈጽሞአል፡፡
\s5
\v 25 አሁን የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! ለአባቴ ለዳዊት አንተ ታደርገው በነበረው ዓይነት ልጆችህ ታዛዦች ቢሆኑና በፊቴም በቅንነት ቢመላለሱ ሁልጊዜ ከዘርህ በእስራኤል ዙፋን ላይ በፊቴ የሚነግሥ ልጅ አላሳጣህም ስትል የተናገርከውን የተስፋ ቃል ፈጽም፡፡
\v 26 አሁንም የእስራኤል አምላክ ሆይ! አገልጋይህ ለነበረው ለአባቴ ለዳዊት የሰጠኸው የተስፋ ቃል ሁሉ እንዲፈጸም አድርግ፡፡
\s5
\v 27 በውኑ እግዚአብሔር በምድር ላይ ይኖራልን? እነሆ ሰማያት፤ ከሰማያትም በላይ ያለው ሰማይ ሊይዝህ አይችልም፤ እኔ የሠራሁት ይህ ቤተ መቅደስ ምንኛ ያንስ፡፡
\v 28 ይሁን እንጂ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! ወደ አገልጋይህ ጸሎትና ልመና ተመልክት፤ ዛሬም አገልጋይህ በፊትህ የሚጸልየውን ጸሎትና ጩኸት ስማ፡፡
\s5
\v 29 ስሜ ይጠራበታል ወዳልከው ወደዚህ ቤተ መቅደስ ቀንና ሌሊት ተመልከት፤ እኔም አገልጋይህ ወደዚህ ቤተ መቅደስ የምጸልየውን ጸሎት ስማ፡፡
\v 30 ፊታችንን ወደዚህ ቤተ መቅደስ መልሰን በምንጸልይበት ጊዜ የእኔንና የእስራኤልን ሕዝብ ጸሎት ስማ፤ ከመኖሪያህ ከሰማይ ሆነህ ስማን፤ ይቅርም በለን፡፡
\s5
\v 31 አንድ ሰው ባልንጀራውን መበደሉን የሚገልጥ ክስ ቀርቦበት በዚህ ቤተ መቅደስ ውስጥ ወደሚገኘው መሠዊያ አምጥተውት ከበደል ንጹሕ መሆኑን በመሐላ በሚያረጋግጥበት ጊዜ፣ በሰማይ ሆነህ ስማ፤
\v 32 ለአገልጋዮችህም ፍርድን ስጥ፤ ይኸውም በደል የሠራው ሰው በጥፋቱ መጠን እንዲቀጣ፣ ንጹሕ የሆነውም ነጻ እንዲወጣ አድርግ፡፡
\s5
\v 33 ሕዝብህ እስራኤል በደል ሠርተው አንተን በማሳዘናቸው ምክንያት በጠላቶቻቸው ድል ሲሆኑ ተጸጽተው ወደ አንተ በመመለስ ወደዚህ ቤተ መቅደስ ቢመጡና የአንትን ይቅርታ ለማግኘት ራሳቸውን ዝቅ አድርገው በትሕትና ቢለምኑህ፤
\v 34 አንተ በሰማይ ሆነህ ጸሎታቸውን ስማ፤ በምርኮ የሚገኙትንም ሕዝብህን ኃጢአት ይቅር በማለት ለቀድሞ አባቶቻቸው ወደ ሰጠሃቸው ምድር መልሰህ አግባቸው፡፡
\s5
\v 35 የእስራኤል ሕዝብ በደል ሠርተው አንተን በማሳዘናቸው ምክንያት ዝናብ እንዳይዘንብላቸው አድርገህ በምትቀጣቸው ጊዜ በፈጸሙት በደል በመጸጸት ፊታቸውን ወደዚህ ቤተ መቅደስ መልሰው በትሕትና ቢለምኑህ፤
\v 36 አንተ በሰማያት ሆነህ ጸሎታቸውን ስማ፤ የአገልጋዮችህን የእስራኤልን ኀጢአት ይቅር በል፣ በልብ ቅን የሆነውንም ነገር ማድረግ ይችሉ ዘንድ አስተምራቸው፤ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር ሆይ፣ ለዘለዓለም ርስት አድርገህ ለሕዝብህ በሰጠሃቸው በዚህች ምድር ዝናብ እንዲዘንብ አድርግ።
\s5
\v 37 በምድሪቱ ላይ ረሐብ ወይም ቸነፈር በሚመጣበት ጊዜ፣ እንዲሁም እህላቸው በውርጭ በዋግና በአንበጣ ወይም በኩብኩባ መንጋ በሚወድምበት ጊዜ ወይም ጠላቶቻቸው በሕዝብህ ላይ አደጋ በሚጥሉበት ጊዜ ወይም በሕዝብህ ላይ ልዩ በሽታና ደዌ በሚደርስባቸው ጊዜ፣
\v 38 በሕዝብህ በእስራኤል መካከል ልብ የሚያሸብር መራር ሐዘን ደርሶባቸው እጃቸውን ወደዚህ ቤተ መቅደስ በመዘርጋት በሚጸልዩበት ጊዜ፣ ጸሎታቸውን ስማ፡፡
\s5
\v 39 በምትኖርበት በሰማይ ሆነህ ጸሎታቸውን በመስማት ይቅር በላቸው፤ እርዳቸውም፣ በሰው ልብና አእምሮ ያለውን አሳብ ሁሉ መርምረህ የምታውቅ አንተ ብቻ ነህ፤ ስለዚህ ለእያንዳንዱ ሰው እንደ ሥራው መጠን የሚገባውን ዋጋ ስጠው፡፡
\v 40 በዚህም ዓይነት ሕዝብህ ለቀድሞ አባቶቻችን ርስት አድርገህ በሰጠሃቸው ምድር በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ ለአንተ ታዛዦች እንዲሆኑና እንዲያከብሩህ አድርግ፡፡
\s5
\v 41 በተጨማሪም የሕዝብህ የእስራኤል ወገን ያልሆነ፣ የውጪ አገር ሰው ከስምህ የተነሣ ከሩቅ ቢመጣ፤
\v 42 ስለስምህ ገናናነት፣ ስለታላቁ እጅህና ከፍ ስላለው ክንድህ ሰምተው፣ በዚህ ቤተ መቅደስ ቢመጡና ቢጸልዩ፣
\v 43 ከምትኖርበት ከሰማይ ሆነህ የዚያን ሰው ጸሎት ስማ፤ እንድታደርግለት የሚለምንህንም ሁሉ ፈጽምለት፤ ሕዝብህ እስራኤላውያን እንደሚያደርጉት በመላው ዓለም የሚኖሩ ሕዝቦች አንተን በማወቅ እንዲታዘዙህና እንዲያከብሩህ አድርግ፣ ይህም በሚሆንበት ጊዜ ይህ እኔ የሠራሁት ቤተ መቅደስ የአንተ ስም የሚጠራበት መሆኑን ያውቃሉ፡፡
\s5
\v 44 ጠላቶቻቸውን ለመዋጋት እንዲዘምቱ ሕዝብህን በምታዝበት ጊዜ በየትኛውም ስፍራ ሆነው ወደዚህች ወደ መረጥኻት ከተማና እኔ ለአንተ ወደ ሠራሁት ወደዚህ ቤተ መቅደስ ፊታቸውን መልሰው በሚጸልዩበት ጊዜ፣
\v 45 በሰማያት ሆነህ ጸሎታቸውንና ልመናቸውን ስማ፤ በችግራቸውም እርዳቸው፡፡
\s5
\v 46 ሕዝብህ ኃጢአት በመሥራት አንተን ሲያሳዝኑህ አንተም ተቆጥተህ ጠላቶቻቸው ድል እንዲነሡአቸውና ወደ ሌላ አገር ማርከው እንዲወስዱአቸው በምታደርግበት ጊዜ፣ ሩቅ ወይም ቅርብ ቢሆን፣
\v 47 ምርኮኞች ሆነው በሚኖሩባት በዚያች አገር ሳሉ ኀጢአት ሠርተናል፤ በድለና፤ ዐምፀናል ብለው በመናዘዝ ተጸጽተው ንስሓ ቢገቡ፣
\s5
\v 48 ማርከው በወሰዱአቸው በጠላቶቻቸው አገር ሳሉ በፍጹም ልባቸው በእውነትና በቅን መንፈስ ተጸጽተው ንስሓ በመግባት አንተ ለቀድሞ አባቶቻችን ወደ ሰጠሃቸው ወደዚህች ምድር፣ አንተም ወደ መረጥኻት ወደዚህች ከተማ፣ እኔ ለአንተ ወደ ሠራሁት ወደዚህ ቤተ መቅደስ ፊታቸውን መልሰው ቢጸልዩ፣
\s5
\v 49 ከዚያ በመኖሪያህ በሰማይ ሆነህ ጸሎታቸውንና እርዳታ ፈልገው ሲለምኑህ በመስማት ፍረድላቸው፤
\v 50 ኃጢአታቸውንና አንተን ያሳዘኑበትን በደል ሁሉ ይቅር በል፤ ጠላቶቻቸውም እንዲራሩላቸው አድርግ፤
\s5
\v 51 እነርሱ እንደ እቶን እሳት ከሚያቃጥል ከግብጽ ምድር ያወጣሃቸውና የመረጥካቸው ሕዝብህ ናቸው፡፡
\v 52 በጠሩህ ጊዜ ሁሉ ትሰማቸው ዘንድ ለአገልጋይህና ለሕዝብህ ልመና ዓኖችህ የተገለጡ ይሁኑ፡፡
\v 53 እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! የቀድሞ አባቶቻችንን ከግብጽ ምድር ባወጣህ ጊዜ ከዓለም ሕዝብ ሁሉ መካከል እስራኤልን የራስህ ሕዝብ እንዲሆን የመረጥከው መሆኑን በአገልጋይህ በሙሴ አማካይነት ተናግረሃል፡፡
\s5
\v 54 ሰሎሞንም እጆቹን እንደ ዘረጋ ተንበርክኮ በመሠዊያው ፊት ወደ እግዚአብሔር ሲጸልይ ቆይቶ ጸሎቱን ከፈጸመ በኋለ ተነሥቶ ቆመ፡፡
\v 55 ድምፁንም ከፍ አድርጎ በዚያ ተሰብስቦ የነበረውን ሕዝብ ሁሉ እንዲህ ሲል ባረከ፡-
\v 56 በገባው የተስፋ ቃል. መሠረት ለሕዝቡ ለእስራኤል ሰላምን የሰጠ እግዚአብሔር ይመስገን፡፡ በአገልጋዩ በሙሴ አማካይነት ከሰጠው መልካም ተስፋ አንድም የቀረ ቃል የለም፡፡
\s5
\v 57 አምላካችን እግዚአብሔር ከቀድሞ አባቶቻችን ጋር እንደነበረ ሁሉ ከእኛ ጋርም ይኑር፡፡ ምን ጊዜም አይተወን፤ አይጣለንም፡፡
\v 58 ለቀድሞ አባቶቻችን የሰጠውን ትዕዛዞች፣ ደንቦችና ሥርዓቶች በመጠበቅ ወደ እርሱ ልባችንን በማዘንበል ለእርሱ ታዛዦች እንድንሆን ያድርገን፡፡
\s5
\v 59 የእኔ የአገልጋዩና የሕዝቡ የእስራኤል የየዕለት ፍላጎት ይሟላ ዘንድ ለእግዚአብሔር ያቀረብኳቸው ልመናዎች ቀንና ሌሊት ወደ እግዚአብሔር አምላክ ይቅረቡ፡፡
\v 60 የዓለም ሕዝቦች ሁሉ እግዚአብሔር ብቻ አምላክ መሆኑንና ከእርሱም ሌላ አምላክ አለመኖሩን ያውቃሉ፡፡
\v 61 ስለዚህም በዛሬው ቀን በድንጋጌው ለመመላለስና ትእዛዞቹንም ታከብሩ ዘንድ ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ለአምላካችን በልባችሁ ታማኞች ሁኑ፡፡
\s5
\v 62 ስለዚህ ንጉሥ ሰሎሞንና እስራኤላውያን ሁሉ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አቀረቡ፡፡
\v 63 ሰሎሞንም ሃያ ሁለት ሺህ የቀንድ ከብቶችንና አንድ መቶ ሃያ በጎችን የኅብረት መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር አቀረበ፡፡ በዚህም ዓይነት ንጉሥ ሰሎሞንና እስራኤላውያን ሁሉ ቤተ መቅደሱን ለእግዚአብሔር የተለየ አድርገው ቀደሱት፡፡
\s5
\v 64 አሁንም በዚያኑ ቀን ከቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት ያለውን አደባባይ መካከለኛ ክፍል ለእግዚአብሔር የተለየ አድርጎ ቀደሰው፤ ቀጥሎም በሙሉ የሚቃጠለውን መሥዋዕት፣ የእህል ቁርባንና የኅብረት መሥዋዕት፣ የእንስሶች ስብ ሁሉ ለእግዚአብሔር አቀረበ፤ ይህንንም ያደረገበት ምክንያት ከነሐስ የተሠራው መሠዊያ ይህን ሁሉ መሥዋዕት መያዝ ስለማይችል ነው፡፡
\s5
\v 65 በዚያ ቤተ መቅደስ ሰሎሞንና የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ሰባት ቀን ሙሉ ባጠቃላይ ዐሥራ አራት ቀኖች የዳስ በዓል አክብረው ሰነበቱ፤ በስተ ሰሜን ከሐማት መተላለፊያ አንሥቶ በስተ ደቡብ እስከ ግብጽ ድንበር ድረስ ካለው ምድር ሁሉ የመጣው ሕዝበ እጅግ ብዙ ነበር፡፡
\v 66 በሚቀጥለው ቀን ሰሎሞን ሕዘቡን ሁሉ አሰናበተ፤ ሁሉም ሰሎሞንን መረቁ እግዚአብሔር ለአገልጋዩ ለዳዊትና ለሕዝቡ፣ ለእስራኤል ስለ አደረገው በጎ ነገር ሁሉ ደስ ብሎአቸው ወደየቤታቸው ሄዱ፡፡
\s5
\c 9
\p
\v 1 ንጉሥ ሰሎሞንም ቤተ መቅደሱንና ቤተ መንግሥቱን እንዲሁም ሊሠራው የፈለገውን ሌላውንም ሁሉ ከፈጸመ በኋላ፣
\v 2 እግዚአብሔር ከዚህ በፊት በገባዖን እንደ ተገጠለት አሁንም እንደገና ተገለጠለት፡፡
\s5
\v 3 ከዚያም እግዚአብሔር እንዲህ አለው፡- በፊቴ ያቀረብከውን ጸሎትና ልመና ሰምቻለሁ፤ እርሱም ለዘለዓለም ለስሜ መጠሪያ እንዲሆን የሠራኸውን ቤተ መቅደስ ቀድሼዋለሁ፤ ዘወትርም ዓይኔና ልቤ በዚያ ይሆናል፡፡
\s5
\v 4 አንተ ግን አባትህ ዳዊት እንዳደረገው በቅንነትና በታማኝነት በፊቴ ብትመላለስ፣ ሕጌንና ሥርዓቴን ብትጠብቅ፣ ያዘዝኩህንም ሁሉ ብትፈጽም፣
\v 5 ለአባትህ ለዳዊት ከዘሮችህ በእስራኤል ዙፋን ላይ የሚነግሥ ልጅ አታጣም በማለት የሰጠሁትን የተስፋ ቃል በመጠበቅ ዙፋንህ በእስራኤል ላይ ለዘለዓለም ጸንቶ እንዲኖር አደርጋለሁ፡፡
\s5
\v 6 ነገር ግን አንተ ወይም ዘሮችህ እኔን መከተል ትታችሁ የሰጠኋችሁን ሕጎችና ትእዛዞች ባትፈጽሙና ባዕዳን አማልክትን ብታመልኩና ብትሰግዱላቸው፤
\v 7 እስራኤላውያንን ከሰጠኋቸው ምድር ተነቃቅለው እንዲባረሩ አደርጋለሁ፤ ስሜ እንዲጠራበት የቀደስኩትንም ይህንን ቤተ መቅደስ እተወዋለሁ፤ በየአገሩ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ እስራኤልን መሳለቂያና መዘባበቻ ያደርጓታል፡፡
\s5
\v 8 ይህ ከፍ ከፍ ብሎ የሚታየው ቤተ መቅደስ ፈርሶ የፍርስራሽ ክምር ይሆናል፤ በዚያ በኩል የሚያልፉ ሰዎች ሁሉ ይህንን አይተው በመደንገጥ እግዚአብሔር ይህንን አገርና ይህንን ቤተ መቅደስ ለምን እንዲህ አደረገ በማለት ይሳለቁበታል፡፡
\v 9 ራሳቸው በሚሰጡት መልስ፣ የእስራኤል ሕዝብ የቀድሞ አባቶቻቸው ከግብጽ ምድር ያወጣቸውን አምላካቸውን እግዚአብሔርን በመተዋቸው ምክንያት ነው፤ ከዚህም በቀር ለእግዚአብሔር የነበራቸውን ታማኝነት ትተው ሌሎች አማልክት አመለኩ፤ ሰገዱላቸውም፤ እግዚአብሔር ይህን ሁሉ የጥፋት መቅሠፍት ያመጣባቸውም ስለዚህ ነው የሚል ይሆናል፡፡
\s5
\v 10 ሰሎሞንም ቤተ መቅደሱንና ቤተ መንግሥቱን ለመሥራት የፈጀበት ጊዜ ሃያ ዓመት ነበር፡፡
\v 11 የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ለዚህ ሁሉ ሥራ ለሰሎሞን የሚያስፈልገውን የሊባኖስ ዝግባ ከብዙ ወርቅ ጋር ሰጥቶት ነበር፤ ሥራውም ሁሉ ከተፈጸመ በኋላ ሰሎሞን በገሊላ ምድር የሚገኙትን ሃያ ታናናሽ ከተሞችን ለኪራም ሰጠው፡፡
\s5
\v 12 ኪራምም ሄዶ ከተሞቹን አየ፤ ነገር ግን ደስ አላሰኙትም፤
\v 13 ኪራምም ወንድሜ ሆይ! የሰጠኸኝ ከተሞች እነዚህ ምንድን ናቸውን? አለው፡፡ በዚህ ምክንያት እስከ ዛሬ ድረስ አካባቢው በሙሉ ‹‹ካቡል›› እየተባለ ይጠራል፡፡
\v 14 ኪራም ለንጉሥ ሰሎሞን የላከለት ወርቅ አንድ መቶ ሺህ መክሊት ነበር፡፡
\s5
\v 15 ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስና ቤተ መንግሥቱን፣ የኢየሩሳሌምንም ቅጥር የሠሩለትና ከከተማይቱም በስተ ምሥራቅ በኩል ያለውን ሚሎ ተብሎ የሚጠራውን ጎድጓዳ ስፍራ መጥተው ያስተካከሉለት የጉልበት ሥራ ዋጋ ነበር፤ እንዲሁም ሐጸር፤ መጊዶናጊዜር ተብለው የሚጠሩ ከተሞችም እንዲሠሩለት አደረገ፡፡
\v 16 ቀደም ሲል የግብጽ ንጉሥ ፈረዖን በጌዜር ላይ አደጋ ጥሎ፣ ነዋሪዎችዋን ከነዓናውያንን ገድሎ ከተማይቱንም አቃጥሎ በቁጥጥሩ ሥር አድርጓት ነበር፤ ከዚያም በኋላ ለሴት ልጁ ለሰሎሞን ሚስት እንደ ስጦታ ሰጣት፡፡
\s5
\v 17 ሰሎሞንም ጊዜርንና የታችኛው ቤት ሖሮን እንደገና አሠራ፡፡
\v 18 ባዕላት በይሁዳ በረሓማ አገር የምትገኝ ታማር ተብለው የሚጠሩትን ከተሞች እንደገና ሠራ፡፡
\v 19 እነዚህም የስንቅ ማከማቻዎች፣ ፈረሶችና ሠረገሎች የሚጠበቁባቸው ከተሞችን ሠራ፡፡ ሰሎሞንም በኢየሩሳሌም፤ በሊባኖስና በግዛቱ ሁሉ የሚፈልገውን ገነባ፡፡
\s5
\v 20 እነዚህም ትውልዶች የእስራኤል ወገን ያልሆኑና የሚያገለግሉ አሞራውያን፣ ሒታውያን፣ ፈሪዛውያን፣ ኤዊያውያንና ኢያቡሳውያን ተብለው የሚጠሩ ናቸው፡፡
\v 21 ለሰሎሞን የጉልበት ሥራ ይሠሩለት የነበሩት የግዳጅ ሥራ ሠራተኞች እስራኤላውያን ምድራቸውን ርስት አድርገው በወረሱ ጊዜ የገደሏቸው የከነዓን ሕዝብ ተውልዶች ነበሩ፡፡
\s5
\v 22 ሰሎሞን ከእስራኤላውያን ወገን ማንንም ባሪያ አድርጎ አላሠራም፤ በዚህ ፈንታ እነርሱ ባለሥልጣኖች፣ ወታደሮች፣ የጦር መኮንኖች፣ የጦር አዛዦች፣ ሠረገላ ለሚነዱ ሁሉ ኃላፊዎችና ፈረሰኞች ሆነው ያገለግሉ ነበር፡፡
\s5
\v 23 ሰሎሞን ለሚያከናውነው የሕንጻ ሥራ የጉልበት ሥራ ይሠሩ ዘንድ ለተመደቡት ሰዎች አምስት መቶ ኃምሳ ኃላፊዎች ነበሩአቸው፡፡
\s5
\v 24 የግብጽ ንጉሥ የፈረዖን ልጅ የነበረችው ሚስቱ ከዳዊት ከተማ ራሱ ወዳሠራላት ቤተ መንግሥት ከተዘዋወረች በኋላ ሰሎሞን የሚሎን ከተማ ገነባ፡፡
\s5
\v 25 ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ባሠራው መሠዊያ ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት በዓመት ሦስት ጊዜ ያቀርብ ነበር፤ ከዚህም ሁሉ ጋር ለእግዚአብሔር የሚቃጠለውን ዕጣን ያሳርግ ነበር፤ በዚህም ዓይነት የቤተ መቅደሱ ሥራ ተፈጸመ፡፡
\s5
\v 26 እንዲሁም ንጉሥ ሰሎሞን በኤዶም ምድር በቀይ በሕር ዳርቻ በምትገኘው በኤላት አጠገብ ባለችው በዔጽዮን ጋብር መርከቦችን ሠራ፡፡
\v 27 ንጉሥ ኪራምም ከሰሎሞን ሰዎች ጋር የሚያገለግሉ የሠለጠኑ መርከበኞችን ላከለት፡፡
\v 28 እነርሱም በመርከብ ተጉዘው ወደ ኦፊር ምድር ከሄዱ በኋላ ወደ ንጉሡ ወደ ሰሎሞን ሲመለሱ አራት መቶ ሃያ መክሊት ወርቅ ይዘውለት መጡ፡፡
\s5
\c 10
\p
\v 1 ንግሥተ ሳባ እግዚአብሔር ለሰሎሞን ስለ ሰጠው አስደናቂ ጥበብ የሚነገረውንም ሁሉ ሰማች፤ ስለዚህ አስቸጋሪ በሆኑ ከባድ ጥያቄዎች ልትፈትነው ወደ ኢየሩሳሌም መጣች፡፡
\v 2 ብዙ የክብር አጃቢዎችን በማስከተል በግመሎች የተጫነ ሽቶ፣ የከበረ ዕንቁና ብዙ ወርቅ ይዛ መጣች፤ ከሰሎሞንም ጋር በተገናኙ ጊዜ በአሳብዋ ያለውን ጥያቄ ሁሉ አቀረበችለት፤
\s5
\v 3 እርሱም ላቀረበችለት ጥያቄ ሁሉ መልስ ሰጣት፤ ከጠየቀችው ሳይመልስላት የቀረ ምንም ዓይነት እንቆቅልሽ አልነበረም፡፡
\v 4 ንግሥተ ሳባ ጥበብ የተሞላበትን የሰሎሞንን አነጋገር አዳመጠች፤ የሠራውንም ቤተ መንግሥት አየች፡፡
\v 5 በሰሎሞን ገበታ ላይ የሚቀርበውን የምግብ ዓይነት፣ የመኳንንቱን መኖሪያ አካባቢዎች፣ የቤተ መንግሥቱን አሠራርና አደረጃጃት፣ የደንብ ልብሳቸውን ዓይነት፣ በግብዣ ጊዜ የሚያገለግሉትን አሳላፊዎችና በቤተ መቅደስም ያቀረባቸውን መሥዋዕቶችን ሁሉ ተመለከተች፤ በዚህም ሁሉ የተሰማት አድናቆት ከጠበቀቸው በላይ ሆነባት፤
\s5
\v 6 ስለሥራህ ውጤትና የጥበብህ ታላቅነት በአገሬ ሳለሁ የሰማሁት ሁሉ እውነት ነው አለች፡፡
\v 7 ነገር ግን እዚህ ድረስ መጥቼ በዐይኔ እስካይ ድረስ የተነገረኝን ሁሉ አላመንኩም ነበር፤ በጆሮዬ የሰማሁት በዐይኔ ያየሁትን እኩሌታ እንኳ አይሆንም፤ በእርግጥም ጥበብህና ሀብትህ በአገሬ ሳለሁ ከተነገረኝ በጣም ይበልጣል፡፡
\s5
\v 8 ሁልጊዜ በፊትህ በመገኘት ጥበብ የሞላበት ንግግርህን የሚሰሙ ሚስቶችህና አገልጋዮችህ እንዴት የታደሉ ናቸው!
\v 9 አምላክህ እግዚአብሔር ይመስገን፤ እርሱ አንተን መርጦ የእስራኤል ንጉሥ በማድረግ በአንተ መደሰቱን ገልጦልሃል፤ ለእስራኤል ያለውም ፍቅር ለዓላማው ስለ ሆነ ጽድቅና ፍትሕ ጸንቶ እንዲኖር ታደርግ ዘንድ የእስራኤል ንጉሥ አድርጎሃል፡፡
\s5
\v 10 ንግሥተ ሳባ ያመጣችለትን ስጦታ ሁሉ ለንጉሥ ሰሎሞን አበረከተችለት፤ ይኸውም ከአራት ሺህ ኪሎ የሚበልጥ ወርቅ፣ እጅግ ብዙ ሽቶና የከበረ ዕንቁ ነበር፤ እርስዋ ለሰሎሞን ያበረከተችው የሽቶ ብዛት ከዚያ በኋላ ከቀረበለት የሽቶ ገጸ በረከት ሁሉ እጅግ የሚበልጥ ነበር፡፡
\s5
\v 11 ከኦፊር ወርቅ ብዙ ያመጡለት የኪራም መርከቦች ከዚያው ከኦፊር ብዙ የሰንደል እንጨትና የከበረ ዕንቁ አምጥተውለት ነበር፡፡
\v 12 ሰሎሞን ከዚሁ ከሰንደል እንጨት የቤተ መቅደሱንና የቤተ መንግሥቱን መከታዎች፤ መዘምራን የሚያገለግሉባቸውን በገናዎችና መሰንቆዎች አሠራ፤ ይህም የሰንደል እንጨት ወደ እስራኤል አገር ከመጣው የሰንደል እንጨት ሁሉ የሚበልጥ ነበር፤ ከዚያ በኋላ ይህን የመሰለ የሰንደል እንጨት ከቶ ታይቶ አይታወቅም፡፡
\s5
\v 13 ንጉሥ ሰሎሞን ከተለመደው የልግሥና ስጦታ ጋር የሳባ ንግሥት የጠየቀቸውን ሁሉ ሰጣት። ከዚህ በኋላ ንጉሥተ ሳባ ከክብር አጃቢዎችዋ ጋር ወደ አገርዋ ተመልሳ ሄደች፡፡
\s5
\v 14 ንጉሥ ሰሎሞን በየዓመቱ ሃያ ሦስት ሺህ ኪሎ ያህል የሚመዝን ወርቅ ያገኝ ነበር፤
\v 15 ይህም ሁሉ ነጋዶዎች ከሚከፍሉት ቀረጥ፤ ከንግድ ከሚገኘው ትርፍ እንዲሁም ከዐረብ ነገሥታትና ከእስራኤል ክፍላተ አገር አስተዳዳሪዎች ከሚገባለት ግብር ጋር ተጨማሪ ነበር፡፡
\s5
\v 16 ንጉሥ ሰሎሞን ሁለት መቶ ታላላቅ ጋሻዎች አሠርቶ እያንዳንዱን ጋሻ በሰባት ኪሎ ያህል ወርቅ አስለበጠው፡፡
\v 17 እንዲሁም ሦስት መቶ ታናናሽ ጋሻዎችን አሠርቶ እያንዳንዱን በሁለት ኪሎ ያህል ወርቅ አስለበጠው፤ እነዚህንም ሁሉ ሊባኖስ ጫካ ተብሎ በሚጠራው አዳራሽ ውስጥ አኖራቸው፡፡
\s5
\v 18 እንዲሁም ንጉሥ ሰሎሞን ከዝሆን ጥርስ አንድ ትልቅ ዙፋን አሠርቶ በንጹሕ ወርቅ አስለበጠው፡፡
\v 19 ወደ ዙፋኑ መወጣጫ ስድስት ደረጃዎች ነበሩ፤ የዙፋኑ ጀርባ ራስጌው ክብ ነበር፤ በዙፋኑ ግራና ቀኝ የክንድ ማሳረፊያዎች ነበሩት፤ በክንድ ማሳረፊያዎቹ ጎን አንዳንድ የአንበሳ ምስሎች ቆመው ነበር፡፡
\v 20 በእያንዳንዱ ደረጃ በሁለት በኩል አንዳንድ የአንበሳ ምስል በድምሩ ዐሥራ ሁለት የአንበሳ ምስሎች ቆመዋል፡፡ ይህን የመሰለ ዙፋን በሌላ በየትኛውም አገር ተሠርቶ አያውቅም ነበር፡፡
\s5
\v 21 በሰሎሞን ዘመን ብር ምንም ዋጋ ስላልነበረው ሰሎሞን የሚጠጣባቸው ዋንጫዎች ሁሉና የሊባኖስ ጫካ ተብሎ በሚጠራው አዳራሽ ውስጥ የሚገኙት ዕቃዎች በሙሉ ከንጹሕ ወርቅ እንጂ ከብር አልተሠሩም፤
\v 22 ሰሎሞን ከኪራም መርከቦች ጋር በውቅያኖስ ላይ የሚጓዙ ሌሎች የተርሴስ መርከቦችም ነበሩት፤ እነርሱ በየሦስት ዓመት ወርቅ፣ ብር፣ የዝሆን ጥርስ፣ ጦጣዎችንና ዝንጀሮዎችን ያመጡለት ነበር፡፡
\s5
\v 23 ንጉሥ ሰሎሞን ከምድር ነገሥታት ሁሉ የሚበልጥ ሀበታምና ጥበበኛ ነበር፤
\v 24 በመላው ዓለም የሚገኙ ሰዎችም ሁሉ እግዚአብሔር የሰጠውን ጥበብ የሞላበትን ንግግር ይሰሙ ዘንድ ወደ እርሱ መምጣት ይፈልጉ ነበር፡፡
\v 25 ወደ እርሱም የሚመጡት ሁሉ የብርና የወርቅ፣ የልብስ፣ የጦር መሣሪያዎች፣ የሽቶ፣ የፈረሶች የበቅሎዎች ስጦታዎች ያመጡለት ነበር፤ ይህም በየዓመቱ የሚደረግ ነበር፡፡
\s5
\v 26 ሰሎሞንም ሠረገሎችና ፈረሶች ሰበሰበ፤ እርሱም አንድ ሺህ አራት መቶ ሠረገሎችና ዐሥራ ሁለት ሺህ ፈረሶኞች ነበሩት፤ ከእነርሱም ከፊሎቹን ከእርሱ ጋር በኢየሩሳሌም፣ ሌሎቹ ደግሞ በልዩ ልዩ ከተሞች ተመድበው እንዲኖሩ አደረገ፡፡
\v 27 በግዛቱም ዘመን ሁሉ በኢየሩሳሌም ብር እንደ ድንጋይ፣ ብዛቱም እንደ ሊባኖስ ዛፍ፣ በይሁዳ ኮረብቶች ግርጌ በየትኛውም ስፍራ እንደሚበቅለው ሾላም ይቆጠር ነበር፡፡
\s5
\v 28 ሰሎሞን ፈረሶችን ከግብጽና ከቀዌ ያስመጣ ነበር፤ የንጉሡም ነጋዴዎች ፈረሶችን በገንዘብ ገዝተው ከቀዌ ያመጡለት ነበር፡፡
\v 29 እያንዳንዱ ፈረስ በስድስት መቶ ጥሬ ብር፣ እያንዳንዱም ሠረገላ በአንድ መቶ ሃምሳ ጥሬ ብር ከግብጽ አገር ተገዛ፡፡ ከዚያም ለሒታውያንና ለሶርያውያን ነገሥታት ተሸጡ፡፡
\s5
\c 11
\p
\v 1 ሰሎሞን ብዙ የባዕዳን አገሮችን ሴቶች አፈቀረ፤ እነዚህም፡- የግብጽ ንጉሥ የፈረዖን ልጅ፣ የሒታውያን፣ የሞአባውያን፣ የአሞራውያን፣ የኤዶማውያንና የሲዶናውያን ሴቶች ልጆችን አፈቀረ፡፡
\v 2 እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን፣ አሕዛብ ሴቶችን ያገባችሁ እንደ ሆነ በእርግጥ ወደ አማልክቶቻቸው ስለሚስቡአችሁ እነርሱን አታግቡ ብሎ አስጠንቅቆአቸው ነበር፡፡ እነዚህ ሰሎሞን የወደዳቸው ሴቶች እግዚአብሔር እንዳያጋቡ ከከለከላቸው ሕዝቦች መካከል ናቸው፡፡ ይህ ትእዛዝ ቢኖርም ሰሎሞን ግን በእነርሱ ፍቅር ተነደፈ፡፡
\s5
\v 3 ሰሎሞን የነገሥታት ልጆች የሆኑ ሰባት መቶ ሚስቶችና ሦስት መቶ ቁባቶች ነበሩት፡፡ ሚስቶቹም ሰሎሞንን ከእግዚአብሔር እንዲርቅ አደረጉት፡፡
\v 4 በተለይም በዕድሜ እየሸመገለ በሄደ መጠን ለባዕዳን አማልእክት እንዲሰግድ አደረጉት፡፡ ሰሎሞንም እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ሙሉ ልቡን ለእግዘአብሔር አላስገዛም፡፡
\s5
\v 5 የሲዶናውያን ሴት አምላክ የነበረችውን ለአስታሮትንና ሞሎክ ተብሎ የሚጠራውን ተለይቶ የሚታወቀውን የአሞናውያንን አምላክ ተከተለ፡፡
\v 6 ሰሎሞንም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ የሆነውን ነገር በማድረጉ አባቱ ዳዊት እንዳደረገው እግዚአብሔርን በቅንነት አልተከተለም፡፡
\s5
\v 7 ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ በሚገኘው ተራራ ላይ ከሞሽ ተብሎ ለሚጠራው ለሞአባውያን አምላክና ሞሎክ ተብሎ ለሚጠራው ለአሞናውያን አምላክ የመስገጃ ስፍራዎችን ሠራ፡፡
\v 8 እንዲሁም የባዕዳን አገር ሚስቶቹ ሁሉ ለየአማልክቶቻቸው ዕጣን የሚያጥኑባቸውንና መሥዋዕት የሚያቀርቡባቸውን ስፍራዎች ሠራ፡፡
\s5
\v 9 የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሁለት ጊዜ የተገለጠለት ቢሆንም፣ ከእርሱ እየራቀ በመምጣቱ እግዚአብሔር ሰሎሞንን ተቆጣው፡፡
\v 10 ባዕዳን አማልክትን እንዳያመልክ አዘዘው፡፡ ነገር ግን ሰሎሞን ለእግዚአብሔር አልታዘዘም፡፡
\s5
\v 11 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ አለው፡- ከእኔ ጋር የገባኸውን ቃል ኪዳን ስላፈረሰክና ሕጌንም ስላልፈጸምክ መንግሥትህን ከአንተ ወስጄ ከአገልጋዮችህ ለአንዱ እሰጣለሁ፡፡
\v 12 ይሁን እንጂ ለአባትህ ለዳዊት ስል ይህን የማደርገው አንተ ባለህበት ዘመን ሳይሆን በልጅህ መንግሥት ጊዜ ይሆናል፡፡
\v 13 ሆኖም ሁሉንም መንግሥት አልወስድም፤ ለአገልጋዬ ለዳዊትና ለመረጥኩት ከተማ ለኢየሩሳሌም ስል ለልጅህ አንዱን ነገድ እሰጠዋለሁ፡፡
\s5
\v 14 ስለዚህም እግዚአብሔር የኤዶማውያኑን ነገሥታት ዘር ሀዳድን በሰሎሞን ላይ ጠላት አድርጎ አስነሣበት፡፡ እርሱም ከኤዶም ንጉሣዊ ቤተ ሰብ ነበር፡፡
\v 15 ዳዊት ከኤዶማውያን ጋር ይዋጋ በነበረ ጊዜ፣ የጦር አዛዡ ኢዮአብ ለመቅበር ወጥቶ በነበረበት ጊዜ፣ በኤዶም ወንዶች ሁሉ ተገድለው ነበር፡፡
\v 16 ኢዮአብና የእስራኤል ሠራዊት የኤዶምን ወንዶች ልጆች ገድለው እስኪጨርሱ ድረስ ስድስት ወራት በዚያ ቆይተዋል፡፡
\v 17 ነገር ግን ከሞት የተረፉትና ሀዳድ በአባቱ አገልጋዮች ወደ ግብጽ ተወሰዱ፡፡ በዚያን ጊዜ ሀዳድ ገና ሕፃን ነበር፡፡
\s5
\v 18 እነርሱም ከምድያም ተነሥተው ሰዎችን ወደ ግብፅ ወደወሰዱበት ወደ ፋራን ሄዱ፤ በዚያም የግብፅ ንጉሥ ፈርዖን ለሀዳድ ቤት፣ መሬትና ምግብ ሰጠው፡፡
\v 19 ሀዳድም በንጉሡ ፈርዖን ፊት ታላቅ ሞገስ አገኘ፡፡ ስለዚህ ንጉሡም የሚስቱን የጣፍኔስን እኅት ለሀዳድ ሚስት እንድትሆነው ሰጠው፡፡
\s5
\v 20 የጣፍኔስንም እኅት ጌንባት ተብሎ የሚጠራውን ወንድ ልጅ ለሀዳድ ወለደችለት፤ እርሱንም ንግሥቲቱ ወስዳ በቤተ መንግሥት አሳደገችው፤ ከፈረዖንም ወንዶች ልጆች ጋር ኖረ፡፡
\v 21 ሀዳድ በግብጽ ሳለ የንጉሥ ዳዊትንና የሠራዊቱን አዛዥ የኢዮአብን መሞት በሰማ ጊዜ፣ ወደ አገሬ ተመልሼ እንድሄድ አሰናብተኝ ሲል ፈረዖንን ጠየቀ፡፡
\v 22 ከዚያም ፈረዖን ስለምን ትሄዳለህ? ወደ አገርህ ለመሄድ የፈለግከው ከቶ ምን ተጓድሎብህ ነው? አለው፡፡ ሀዳድም ምንም የተጓደለብኝ ነገር የለም፤ ብቻ ወደ ትውልድ አገሬ እንድመለስ ፍቀድልኝ ሲል ለንጉሡ መለሰ፡፡
\s5
\v 23 እንደገናም እግዚአብሔር ረዞን ተብሎ የሚጠራውን የኤሊዓዳ ልጅ በሰሎሞን ላይ ሌላ ጠላት አድርጎ አስነሣበት፡፡ ረዞን የጾባ ንጉሥ ከነበረው ከጌታው ከዞአብ ንጉሥ ከሀዲድዔዚር ኮብልሎ ነበር፡፡
\v 24 ዳዊት ሀዲድዔዚርን ድል ባደረገበት ጊዜ፣ ረዞን ለራሱ ጦር ሰብስቦ የጥቂት ኃይል አለቃ ሆኖ ነበር፡፡ የረዞን ጦር ወደ ደማስቆ ሄደው እዚያ መኖር ጀመሩ፤ በኋላም ደማስቆን ተቆጣጠረ፡፡
\v 25 በሰሎለሞን ዘመነ መንግሥት ሁሉ ሀዳድ ካደረሰበት ችግር በተጨማሪ ረዞን የእስራኤል ጠላት ነበር፡፡ ስለዚህ ረዞን በሶርያ ላይ ገዢ ሆኖ በእስራኤል ላይ ጠላትነቱን ቀጠለ፡፡
\s5
\v 26 የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም፣ ኤፍሬማዊው የሰሎሞን ባለሥልጣናት አንዱ የሆነው፣ ጸሬዳ ተብሎ የምትጠራው ክፍል ተወላጅ የሆነ፣ የእናቱም ስም ጽሩዓ፣ ባልዋ የሞተባት ሴት ነበረች፤ እርሱም በሰሎሞን ላይ እጁን አነሣ፡፡
\v 27 ኢዮርብዓም በሰሎሞን ላይ እጁን ያነሣበት ምክንያት፤ በዚያን ጊዜ ሰሎሞን ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ ሚሎ ተብሎ የሚጠራውን ጎድጓዳ ስፍራ በመሙላት እየደለደለና የአባቱን የዳዊትን ከተማ ቅጥሮች እየጠገነ ነበር፡፡
\s5
\v 28 ኢዮርብዓም ጽኑዕ ኃያል ሰው ነበር፡፡ ሰሎሞንም ይህን ተመልክቶ ወጣቱ ትጉህና ብርቱ ሠራተኛ በመሆኑ በዮሴፍ ነገድ ግዛት ላይ ሁሉ ኃላፊ አድርጎ ሾመው፡፡
\v 29 በዚያን ጊዜ ኢዮርብዓም ከኢየሩሳሌም ወጥቶ በጉዞ ላይ ሳለ፣ ሴሎናዊው ነቢዩ አኪያ በመንገድ ላይ አገኘው፡፡ አኪያም አዲስ መጎናጸፊያ ለብሶ ሁለት ሰዎች ለብቻ በሜዳ ላይ ነበሩ፡፡
\v 30 አኪያም የለበሰውን አዲስ መጎናጸፊያ አውልቆ ከዐሥራ ሁለት ቆራረጠው፡፡
\s5
\v 31 ኢዮርብዓምንም እንዲህ አለው፤ የእስራኤል አምላክ እግዚያብሔር እንዲህ ይላል፡- ‹‹ዐሥሩን ቁራጭ ለራስህ ውሰድ፤ ‹መንግሥትን ከሰለሞን ወስጄ ዐሥሩን ነገድ ለአንተ እሰጥሃለሁ፣
\v 32 ለአገልጋዬ ለዳዊትና ከሁሉም የእስራኤል ነገዶች ለመረጥኳት ለኢየሩሳሌም ከተማ ስል ለሰለሞን አንድ ነገድ አስቀርቼለታለሁ፡፡
\v 33 ይህንንም የማደርገው ሰሎሞን እኔን ትቶ ባዕዳን አማልክትን፡- አስታሮት ተብላ የምትጠራውን የሲዶና አምላክ፣ ካሞሽ ተብሎ የሚጠራውን የሞአብ አምላክና ሞሎክ ተብሎ የሚጠራውን የአሞናውያን አምላክ ስላመለከ ነው፡፡ አባቱ ዳዊት እንዳደረገ በፊቴ ትክክል የሆነውን፣ ሕጎቼንና ትእዛዞቼንም አልጠበቀም፡፡
\s5
\v 34 ይሁን እንጂ ከሰለሞን እጅ መንግሥትን በሙሉ አልወስድበትም፤ በዚህ ፈንታ በሕይወት እስካለም ድረስ በሥልጣን ላይ እንዲቆይ አደርገዋለሁ፤ ይህንንም የማደርገው ለመረጥኩትና ሕጎቼንና ትእዛዞቼን ለፈፀመው ለአገልጋዬ ለዳዊት ስል ነው፡፡
\v 35 ነገር ግን መንግሥትን ከሰለሞን ልጅ ወስጄ ለአንተ ዐሥሩን ነገዶች እሰጥሃለው፡፡
\v 36 ስሜ እንዲጠራባት በመረጥኳት በኢየሩሳሌም አገልጋዬ ዳዊት በፊቴ አንድ ዘር ይኖረው ዘንድ ለልጁ አንድ ነገድ እሰጠዋለው፡፡
\s5
\v 37 ኢዮርብዓም ሆይ! እኔ አንተን የእስራኤል ንጉሥ አድርጌሃለሁ፤ አንተ በወደድከው ግዛት ሁሉ ላይ መሪ ትሆናለህ፡፡
\v 38 አገልጋዬ ዳዊት እንዳደረገው በፍፁም ልብህ ብትታዘዘኝ፣ በሕጎቼና በትእዛዞቼ ጸንተህ ብትኖር፣ በእኔ ፊት ሞገስ ብታገኝ፣ እኔ ዘወትር ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ በእስራኤል ላይ እንድትነግሥም አደርግሃለሁ፤ ለዳዊት ባደረግሁት ዓይነት ዘሮችህ ከአንተ በኋላ እንደሚነግሡ አረጋግጥልሃለሁ፡፡
\v 39 በሰለሞን ኃጢአት ምክንያት የዳዊትን ትውልዶች እቀጣለሁ፤ ነገር ግን የምቀጣቸው ለዘላለም አይደለም፡፡
\s5
\v 40 ከዚህም የተነሣ ሰለሞን ኢዮርብዓምን ለመግደል ሞከረ፡፡ ነገር ግን ኢዮርብዓም ወደ ግብፅ ንጉሥ ሺሻቅ በመኮበለል አመለጠ፤ ሰለሞን እስከ ሞተበት ጊዜ ድረስ እዚያው ቆየ፡፡
\s5
\v 41 ሰለሞን ያደረገው ሌላው ነገር፣ ያከናወነው ተግባርና ጥበቡ ሁሉ በሰለሞን የታሪክ መጽሐፍ የተመዘገበ አይደለምን?
\v 42 ሰለሞንም በኢየሩሳሌም በመላው እስራኤል ላይ የነገሠበት ዘመን አርባ ዓመት ነበር፡፡
\v 43 ከዚህ በኋላ ሰለሞን ሞተ፣ በአባቱ በዳዊት ከተማም ተቀበረ፤ ልጁም ሮብዓም በአባቱ በሰለሞን ተተክቶ ነገሠ፡፡
\s5
\c 12
\p
\v 1 ሮብዓምም ወደ ሴኬም ሄደ፤ ምክንያቱም እስራኤል ሁሉ እርሱን ለማንገሥ ወደ ሴኬም መጥተው ነበር፡፡
\v 2 ከንጉሡ ሰሎሞን በመሸሽ ወደ ግብጽ ኮብልሎ በዚያው በግብጽ ይኖር የነበረው የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም ይህን ወሬ በሰማ ጊዜ ተመልሶ መጣ፡፡
\s5
\v 3 ስለዚህ የእስራኤል ጉባኤ ሁሉ ወደ እርሱ ልከው ጠሩት፤ ወደ ሮብዓም ቀርበው እንዲህ አሉት፡-
\v 4 አባትህ ሰሎሞን በእኛ ላይ ከባድ የአገዛዝ ቀንበር አክብዶብን ነበር፡፡ አሁን አባትህ የጫነብንን ከባድ የሥራ ሸክም አቃልልን፣ ለአንተም እንገዛልሃለን አሉት፡፡
\v 5 ሮብዓምም ከሦስት ቀን በኋላ ተመልሳችሁ ኑ አላቸው፤ ስለዚህ ሕዝቡ ሄዱ፡፡
\s5
\v 6 ከዚህ በኋላ ንጉሥ ሮብዓም የአባቱን የሰሎሞን ዘመን አማካሪዎች የነበሩትን ሽማግሌዎች በአንድነት ሰብስቦ እንግዲህ ለዚህ ሕዝብ መልስ መስጠት እንድችል ምን ትመክሩኛላችሁ? ሲል ጠየቃቸው፡፡
\v 7 ሽማግሌዎቹም ዛሬ ለእነዚህ ሰዎች ታዛዥ ሆነህ ብታገለግላቸው ለጥያቄአቸውም ተስማሚ የሆነ መልስ ብተሰጣቸው እነርሱም ዘወትር በታማኝነት ያገለግሉሃል ሲሉ መለሱለት፡፡
\s5
\v 8 ነገር ግን ሮብዓም የሽማግሌዎቹን ምክር ቸል በማለት አብሮ አደጎቹ ወደነበሩት አሁን ደግሞ አማካሪዎቹ ወደሆኑት ወጣቶች ሄደ፡፡
\v 9 የአገዛዝ ቀንበር እንዳቀልላቸው ለጠየቁኝ ምን መልስ እንደምሰጣቸው ምን ትመክሩኛላችሁ? ሲል ጠየቃቸው፡፡
\s5
\v 10 እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱለት፤ አንተ የምተሰጣቸው መልስ ይህ ነው፤ የእኔ ታናሽ ጣት ከአባቴ ወገብ ይበልጥ ትወፍራለች!
\v 11 አባቴ በእናንተ ላይ ከባድ የአገዛዝ ቀንበር ጭኖባችሁ ነበር፣ እኔ ደግሞ የአገዛዝ ቀንበር ይበልጥ እንዲከብድባችሁ አደርጋለሁ፣ አባቴ በአለንጋ ይገርፋችሁ ነበር፤ እኔ ግን በሚናደፍ ጊንጥ እገርፋችኋለሁ!
\s5
\v 12 ከሦስት ቀን በኋላ ኢዮርብዓምና ሕዝቡ ሁሉ ንጉሡ በሰጣቸው ቀጠሮ መሠረት ተመልሰው ወደ ሮብዓም መጡ፡፡
\v 13 ንጉሥ ሮብዓምም ሽማግሌዎቹ የሰጡትን ምክር ትቶ ሕዝቡን በማመናጨቅ መልስ ሰጣቸው፡፡
\v 14 ወጣቶቹ በሰጡት ምክር መሠረት አባቴ በእናንተ ላይ ከባድ የአገዛዝ ቀንበር ጭኖባችሁ ነበር፤ እኔ ደግሞ የአገዛዝ ቀንበር ይበልጥ እንዲከብድባችሁ አደርጋለሁ፤ አባቴ በአለንጋ ይገርፋችሁ ነበር፤ እኔ ግን በጊንጥ እገርፋችኋለሁ! ሲል መለሰላቸው፡፡
\s5
\v 15 ይህም ከሴሎ በመጣው በነቢዩ አኪያ አማካይነት ስለ ናባጥ ልጅ ስለ ኢዮርብዓም እግዚአብሔር የተናገረው ቃል እንዲፈጸም ነው። ነጉሥ ሮብዓምም የሕዝቡን አሳብ ችላ በማለት ሳይቀበል የቀረበትም ምክንያት እግዚአብሔር ይህን ለውጥ ለማድረግ ስለ ወሰነ ነው፡፡
\s5
\v 16 ሕዝቡ ንጉሥ ሮብዓም ጥያቄውን እንዳልተቀበለው በተገነዘበ ጊዜ ከዳዊት ጋር ምን ድርሻ አለን? የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! ወደየቤትህ ሂድ! ዳዊት ሆይ፣ የራስህን ቤት ጠብቅ ብለው መለሱለት፡፡ ስለዚህ የእስራኤል ሕዝብ ወደየቤቱ ሄደ፡፡
\v 17 ሮብዓምም በይሁዳ ግዛት በሚኖሩት ሕዝብ ላይ ብቻ ነገሠ፡፡
\s5
\v 18 ከዚህ በኋላ ንጉሥ ሮብዓም የግዳጅ ሥራ ኃላፊ የነበረውን አዶኒራምን ወደ እስራኤላውያን እንዲሄድ ላከው፤ እነርሱ ግን በድንጋይ ወግረው ገደሉት፤ በዚህ ጊዜ ሮብዓም በፍጥነት ወደ ሠረገላው ገብቶ ወደ ኢየሩሳሌም በመሄድ አመለጠ፡፡
\v 19 ከዚያን ጊዜም ጀምሮ ሰሜናዊው ክፍል እስራኤል በሚል በዳዊት ሥርወ መንግሥት ላይ ዐመፀ፡፡
\s5
\v 20 እስራኤልም ሁሉ ኢዮርብዓም ከግብጽ ተመልሶ መምጣቱን በመገንዘብ ወደ ጉባዔያቸው ጠርተው በእስራኤል ላይ አነገሡት፤ ለዳዊት ትውልዶች ታማኝ ሆኖ የቀረው የይሁዳ ነገድ ብቻ ነበር፡፡
\s5
\v 21 ሮብዓም ወደ ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ ከይሁዳና ከብንያም ነገዶች ተውጣጥተው የተመለሱ አንድ መቶ ሰማኒያ ምርጥ ወታደሮች ጠርቶ በአንድነት ሰበሰበ፤ ይህም የእስራኤልን ነገዶች ለመዋጋትና እንደገና መንግሥትን ወደ ሰሎሞን ልጅ ሮብዓም ለመመለስ ነበር፡፡
\s5
\v 22 ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል ወደ እግዚአብሔር ሰው ወደ ሳማያ እንዲህ ሲል መጣ፡፡
\v 23 ለሮብዓምና ለመላው የይሁዳና የብንያም ነገዶች ለቀሩትም ሕዝብ ሁሉ እንዲህ በል፡-
\v 24 ከወንድሞቻችሁ ከእስራኤላውያን ጋር በመዋጋት አደጋ አትጣሉ፤ ሁላችሁም ወደየቤታችሁ ሂዱ፤ ይህ የሆነው በእኔ ፈቃድ ነው ብሎ አዘዘው፡፡ እነርሱም ለእግዚብሔር ቃል በመታዘዝ ወደየቤታቸው ተመልሰው ሄዱ፡፡
\s5
\v 25 ኢዮርብዓምም በኮረብታማው በኤፍሬም አገር የምትገኘውን ሴኬምን ከተማ አድርጎ ሠርቶ ኖረባት፡፡ ከዚያም ተነሥቶ የጵንኤልን ከተማ ሠራ፡፡
\v 26 ኢዮርብዓምም አሁን መንግሥቱ ወደ ዳዊት ቤት ይመለሳል ብሎ በልቡ አሰበ፡፡
\v 27 ይህ የእስራኤል ሕዝብ ወደ ኢየሩሳሌም እየሄደ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መስዋዕት የሚያቀርብ ከሆነ፣ የሕዝቡ ልብ ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ጌታቸው ወደ ሮብዓም ይመለሳል፡፡ ከዚያ እኔን ይገሉኛል፤ ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ሮብዓምም ይመለሳሉ፡፡
\s5
\v 28 ስለዚህ ሮብዓም በጉዳዩ ከመከረበት በኋላ የሁለት ጥጆች ምስል ከወርቅ አሠርቶ ለሕዝቡ ከዚህ በፊት እንደምታደርጉት ለመስገድ እስከ ኢየሩሳሌም መሄድ አድካሚ ነው፡፡ የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፡- ከግብጽ ምድር ያወጣችሁ አማልክትህ እነሆ እነዚህ ናቸው! አለ፡፡
\v 29 ከዚህ በኋላ ከወርቅ የተሠሩት ሁለት የኮርማ ምስሎች አንዱን በቤቴል ሁለተኛውንም በዳን አቆመ፡፡
\v 30 ስለዚህ ይህ ድርጊት ኃጢአት ሆነ፡፡ ሰዎቹም እስከ ዳን ድረስ በጣዖቱ ፊት ተሰልፈው ሄዱ፡፡
\s5
\v 31 ኢዮርብዓምም በኮረብታዎች ላይ የማምለኪያ ስፍራዎችን አዘጋጅቶ የሌዊ ነገድ ካልሆኑ ቤተ ሰቦች መካከል ማንኛውንም ሰው ካህን አድርጎ ሾመ፡፡
\v 32 ኢዮርብዓም በይሁዳ በሚደረገው በዓል ዓይነት ስምንተኛ ወር በገባ በዐሥራ አምስተኛው ቀን የባዕድ አምልኮ በዓል እንዲደረግ ወሰነ፤ ከወርቅ ላሠራውም ምስሎች በቤቴል በሚገኘው መሠዊያ ላይ ለጥጃ ምሰሉ መሥዋዕት አቀረበ፤ በዚህም በቤተል ለማምለኪያ ባሠራቸው ስፍራዎች የሚያገለግሉ ካህናትን መደበ፡፡
\s5
\v 33 ኢዮርብዓምም በዓል እንዲሆን እርሱ ራሱ በወሰነው ስምንተኛ ወር በገባ በዐሥራ አምስተኛው ቀን ወደ ቤቴል ሄደ፡፡ በዚያ የእስራኤል ሕዝብ በዓል እንዲያከብር መስዋዕት አዘጋጅቶ ዕጣን ለማጠን ወደ መሠዊያው ሄደ፡፡
\s5
\c 13
\p
\v 1 የእግዚአብሔርን ቃል ይዞ አንድ ነብይ ከይሁዳ ወደ ቤቴል ደረሰ፤ ኢዮርብዓም ዕጣን ለማጠን በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ ነበር፡፡
\v 2 ነቢዩም እንዲህ ሲል በጩኸት የትንቢት ቃል ተናገረበት፡- ‹‹መሠዊያ! መሠዊያ ሆይ! እግዚአብሔር ስለ አንተ የሚለው ቃል ይህ ነው፡- ‹እነሆ ከዳዊት ቤተ ሰብ ኢዮአስ ተብሎ የሚጠራ ልጅ ይወለዳል፤ እርሱም በኮረብታ ላይ ለተሠራው ለአህዛብ መሠዊያ አገልጋዮች ሆነው መሥዋዕት የሚያቀርቡትን ካህናት በአንተው ላይ ያርዳቸዋል፤ የሰዎችንም አጥንት በአንተ ላይ ያቃጥላል፡፡
\v 3 በዚያው ቀን ነቢዩ ምልክት ሰጠ፤ ይህ መሠዊያ ተሰባብሮ ይወድቃል፤ በእርሱም ላይ ያለው አመድ ይበተናል፤ ይህንንም የትንቢት ቃል በእኔ አማካኝነት የተናገረው ራሱ እግዚአብሔር ለመሆኑ ምልክት ይሆናል› አለው፡፡
\s5
\v 4 ንጉሥ ኢዮርብዓምም ይህን በሰማ ጊዜ እጁን አንሥቶ ወደ ነቢዩ በማመልከት ያዙት የሚል ትእዛዝ ሰጠ፤ የንጉሡም ክንድ ወዲውኑ ድርቅ ብሎ ቀረ፤ የዘረጋውን እጁን መመለስ አልቻለም፡፡
\v 5 የእግዚአብሔርም ነቢይ በእግዚአብሔር ስም በተናገረው የትንቢት ቃል መሠረት የተሰጠው ምልክት ተፈጸመ፤ መሠዊያው ወዲያውኑ ተሰባብሮ ወደቀ፤ አመዱም መሬት ላይ ፈሰሰ፡፡
\s5
\v 6 ንጉሡ ኢዮርብዓምም፣ እባክህ እጄ እንዲመለስልኝ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይልኝ ሲል የእግዚአብሔርን ነቢይ ለመነው፡፡ የእግዚአብሔርም ነቢይ ወደ እግዚአብሔር ጸልዮለት የንጉሡ እጅ ዳነች፡፡ እንደ ቀድሞም ሆነች፡፡
\v 7 ከዚህ በኋላ ንጉሡ ነቢዩን ና ከእኔ ጋር አብረህ ወደ ቤቴ ግባ፤ እህልም ቅመስ፤ ስጦታ እሰጥሃለሁ አለው፡፡
\s5
\v 8 የእግዚአብሔር ነቢይ ግን የሀብትህን እኩሌታ ብትሰጠኝ እንኳ ወደ ቤትህ ከአንተ ጋር አልሄድም፤ እህል ውሃም እዚህ ቦታ አልቀምስም አለ፡፡
\v 9 ምንም ዓይነት እህል ውሃ እንዳልቀምስና ወደ ቤቴ ስመለስም በመጣሁበት መንገድ እንኳ እንልሄድ እግዚአብሔር አዞኛል ሲል መለሰለት፡፡
\v 10 ስለዚህ ወደ ቤቴል የመጣበትን መንገድ በመተው በሌላ መንገድ ተመልሶ ሄደ፡፡
\s5
\v 11 በዚያን ጊዜ በቤቴል የሚኖር አንድ ሽማግሌ ነቢይ ነበር፡፡ ወንዶች ልጆቹ ወደ እርሱ ቀርበው፣ ከይሁዳ የመጣው ነቢይ በቤቴል ስላደረገውና በንጉሥ ኢዮርብዓምም ላይ ስለ ተናገረው ቃል ሁሉ አወሩለት፡፡
\v 12 አባታቸውም ታዲያ ያ የእግዚአብሔር ነቢይ ከዚያ ተነሥቶ በየትኛው መንገድ ሄደ? ሲል ጠየቃቸው፤ እነርሱም የሄደበትን መንገድ በማመልከት አሳዩት፤
\v 13 ከዚህም በኋላ እርሱ አህያዬን ጫኑልኝ አላቸው፤ ልጆቹም አህያውን ጭነውለት፣ ሽማግሌው ነቢይ በአህያው ላይ ተቀምጦ፣
\s5
\v 14 ከይሁዳ የመጣው የእግዚአብሔር ነቢይ የሄደበትን መንገድ አቅጣጫ ይዞ ተከተለው፤ በአንድ የወርካ ዛፍ ሥር ተቀምጦም አገኘው፡፡ ሽማግሌውም ከይሁዳ የመጣኸው የእግዚአብሔር ነቢይ አንተ ነሀን? ሲል ጠየቀው፡፡ እርሱም አዎን እኔ ነኝ ሲል መለሰለት፡፡
\v 15 ሽማግሌውም ወደ ቤቴ ገብተህ ከእኔ ጋር እህል ብላ አለው፡፡
\v 16 ከይሁዳ የመጣው የእግዚአብሔር ነቢይ ግን ከአንተ ጋር አብሬ ወደ ቤትህ መሄድም ሆነ በዚህ ቦታ ከአንተ ጋር ምንም ዓይነት እህል ውሃ መቅመስ አልችልም ሲል መለሰለት፡፡
\v 17 በዚህ ቦታ ምንም ዓይነት እህል ውሃ እንዳልቀምስ፣ በመጣሁበት መንገድ እንኳ ተመልሼ እንዳልሄድ እግዚአብሔር አዞኛል አለው፡፡
\s5
\v 18 ከዚህ በኋላ ከቤቴል የመጣው ሽማግሌው ነቢይ፣ እኔም እንዳንተው ነቢይ ነኝ፤ ከእኔ ጋር ወደ ቤቴ ወስጄ እንዳስተናግድህ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ነግሮኛል አለው፡፡ ነገር ግን ሽማግሌው ነቢይ የተናገረው በውሸት ነበር፡፡
\v 19 ስለዚህ ከይሁዳ የመጣው የእግዚአብሔር ነቢይ ከሽማግሌው ነቢይ ጋር አብሮት ወደ ቤቱ ሄደ፤ ከእርሱም ጋር ተመገበ፡፡
\s5
\v 20 በገበታም ቀርበው ሳሉ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ሽማግሌው ነቢይ መጣ፡፡
\v 21 ከይሁዳ ለመጣው የእግዚአብሔር ሰው እንዲህ አለው፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ አምላክህ እግዚአብሔር ያዘዘህን ትእዛዝ ባለመታዘዝ የእግዚአብሔርን ቃል አልታዘዝክም፡፡
\v 22 ይህን በማድረግ ፈንታ እኔ በዚያ ምንም ዓይነት እህል ውሃ እንዳትቀምስ ወዳዘዝኩህ ወዳዚያ ቦታ ተመልሰህ በላህ፤ ይህንንም በማድረግህ ምክንያት ትገደላለህ፤ ሬሳህም በቤተ ሰብህ መቃብር አይቀበርም፡፡
\s5
\v 23 ከተመገቡም በኋላ ሽማግሌው ነቢይ ከይሁዳ መልሶ ላመጣው የእግዚአብሔር ነቢይ አህያውን ጫነለት፤
\v 24 እርሱም በአህያው ላይ ተቀምጦ ሄደ፤ በመንገድም አንበሳ አገኘውና ገደለው፤ ሬሳውም በመንገድ ላይ ተጋደመ፤ አህያውና አንበሳውም በሬሳው አጠገብ ቆመው ነበር፡፡
\v 25 ሰዎች በዚያ በኩል ሲያልፉ አጠገቡ ከቆመው አንበሳ ጋር ሬሳው በመንገድ ላይ ተጋድሞ አዩ፣ ሽማግሌው ነቢይ ወደሚኖርበት ወደ ቤቴል ከተማ መጥተውም አወሩለት፡፡
\s5
\v 26 ሽማግሌው ነቢይ ይህን በሰማ ጊዜ፣ ያ ሰው የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ያልጠበቀው ነቢይ ነው፤ ስለዚህም እግዚአብሔር እንደ ተናገረው አንበሳ ቦጫጭቆ እንዲገለው አሳልፎ ሰጥቶታል ማለት ነው አለ፡፡
\v 27 ከዚህም በኋላ ልጆቹን አህያዬን ጫኑልኝ አላቸው፤ እነርሱም ጫኑለት፡፡
\v 28 በአህያው ላይ ተቀምጦ ሄደ፤ በነቢዩ ሬሳ አጠገብ አህያውና አንበሳው እስካሁን እንደ ቆሙ በመንገድ ላይ ተጋድሞ አገኘው፡፡ አንበሳውም የነቢዩን ሬሳ አልበላም፤ በአህያውም ላይ አደጋ አላደረሰበትም ነበር፡፡
\s5
\v 29 ሽማግሌው ነቢይ ሬሳውን አንሥቶ በአህያው ላይ ጫነው፤ እንዲለቀስለትና እንዲቀበር ወደ ቤቴል መልሶ ወሰደው፡፡
\v 30 ሽማግሌውም ነቢይ በገዛ ራሱ ቤተ ሰብ መቃብር ቀበረው፤ እነርሱም ወንድሜ ሆይ ወንድሜ ሆይ እያሉ አለቀሱለት፡፡
\s5
\v 31 ከቀብሩም ሥነ ሥርዓት በኋላ ሽማግሌው ነቢይ ለልጆቹ እንዲህ አላቸው፤ እኔ ስሞት በዚህ መቃብር ቅበሩኝ፤ ሬሳዬንም ከእርሱ ሬሳ አጠገብ አጋድሙት፡፡
\v 32 በቤቴል በሚገኘው መሠዊያ ላይና በሰማርያ ታናናሽ ከተሞች በየኮረብታው ባሉት የማምለኪያ ስፍራዎች ላይ ከእግዚአብሔር በተሰጠው ትእዛዝ መሠረት ይህ የእግዚአብሔር ነቢይ የተናገረው የትንቢት ቃል በእርግጥ ይፈጸማል፡፡
\s5
\v 33 ይህም ሁሉ ሆኖ የእስራኤል ንጉሥ ኢዮርብዓም ከሚያደርገው ክፉ ነገር ሁሉ አልተመለሰም፤ ይልቁንም እርሱ በሠራቸው መሠዊያዎች የሚያገለግለውን ማንኛውንም ሰው ካህን አድርጎ ይሾመው ነበር፡፡
\v 34 ይህም ኃጢአቱ ለቤተ ሰቡ መጥፋትና ከምድር ገጽ ለመደምሰሱ ምክንያት ሆነ፡፡
\s5
\c 14
\p
\v 1 በዚያን ጊዜ የንጉሥ ኢዮርብዓም ወንድ ልጅ አቢያ በጠና ታሞ ነበር፡፡
\v 2 ስለዚህ ኢዮርብዓም ሚስቱን እንዲህ አላት፡- የእኔ ሚስት መሆንሽን ማንም እንዳያውቅ ልብስሽን ለውጠሽ ሌላ ሴት በመምሰል እኔ የእስራኤል ንጉሥ እንደምሆን የትንቢት ቃል የተናገረው ነቢይ አኪያ ወደሚኖርባት ወደ ሴሎ ሂጂ፡፡
\v 3 ዐሥር እንጀራ፣ ጥቂት ሙልሙል ዳቦና አንድ ገንቦ ማር ውሰጂለት፤ ስለ ልጁ ሁኔታ እርሱ ይነግርሻል፡፡
\s5
\v 4 ስለዚህ የኢዮርብዓም ሚስት ይህን ሁሉ አዘጋጅታ በሴሎ ወደሚገኘው ወደ አኪያ ቤት ሄደች፡፡ ነቢዩ አኪያም በዕድሜው ከመሸምገሉ የተነሣ ዓይኖቹ ፈዘው ስለነበር ለማየት አልቻለም፡፡
\v 5 እግዘዚአብሔር ለአኪያ እንዲህ አለው፡- የኢዮርብዓም ሚስት ስለታመመው ልጅዋ ልትጠይቅህ እየመጣች ነው፡፡ የኢዮርብዓም ሚስት እዚያ በደረሰች ጊዜ ሌላ ሴት ለመምሰል ስለምትሞክር ይህንኑ ተናገራት፡፡
\s5
\v 6 ነገር ግን ነቢዩ አኪያ ወደ በሩ ስትቀርብ የኮቴን ድምፅ ሰምቶ እንዲህ አላት፤ ግቢ፣ የኢዮርብዓም ሚስት መሆንሽን አውቃለሁ፤ ሌላ ሴት ለመምሰል ስለምን ሞከርሽ? ለአንቺ እነግርሽ ዘንድ የታዘዝኩት አሳዛኝ ዜና አለ፡፡
\v 7 ወደ ኢዮርብዓም ሂጂ፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የሚለውን ንገሪው፤ ቃሉም ይህ ነው፤ ‹ከሕዝብ መካከል መርጬ የሕዝቤ የእስራኤል መሪ አደረግሁህ፡፡
\v 8 መንግሥትንም ከዳዊት ትውልድ ወስጄ ለአንተ ሰጠሁህ፤ ነገር ግን አንተ ታማኝ ሆኖ ትእዛዜን እንደጠበቀውና እኔ ደስ የምሰኝበትን እንዳደረገ እንደ አገልጋዬ እንደ ዳዊት ሆነህ አልተገኘህም፡፡
\s5
\v 9 ይልቁንም ከአንተ በፊት መሪዎች ከነበሩ ሰዎች የከፋ ኃጢአት ሠራህ፤ እኔንም ትተህ ጣዖቶችንና ከብረት የተሠሩ ምስሎችን ለማምለክ በመነሣትህ ቁጣዬን አነሣሥተሃል፡፡
\v 10 በዚህ ምክንያት እነሆ፣ በኢዮርብዓም ቤት ላይ ክፉ ነገርን አመጣለሁ፤ ከቤቱም ነፃም ሆነ ባርያ ወንድ ልጅን ሁሉ ከእስራኤል አጠፋለሁ፤ ፋንድያን አቃጥለው እንደሚጨርሱት የኢዮርብዓምን ቤት አወድማለሁ፡፡
\s5
\v 11 በከተማ የሚሞተውን ማንኛውንም የቤተ ሰብህን አባል ውሾች ይበሉታል፤ በሜዳ ላይ የሚሞቱንም የሰማይ አሞራ ይበላቸዋል፤ ይህን የተናገርኩት እኔ እግዚአብሔር ነኝ፡፡”
\v 12 አኪያም የሚናገረውን የትንቢት ቃል በመቀጠል ለኢዮርብዓም ሚስት እንዲህ አላት፣ እንግዲህ አሁን ወደ ቤትሽ ተመልሰሽ ሂጂ፤ ወደ ከተማም እግሮችሽ እንደረገጡ ወዲያውኑ ልጁ ይሞታል፡፡
\v 13 እስራኤላውያንም ሁሉ አዝነውና አልቅሰው ይቀብሩታል፡፡ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የተደሰተበት ልጅ እርሱ ብቻ ስለሆነ ከኢዮርብዓም ቤተ ሰብ ሥርዓተ ቀብር በሚገባ የሚፈፀምለት እርሱ ብቻ ይሆናል፡፡
\s5
\v 14 እግዚአብሔርም በዚያን ቀን የኢዮርብዓምን ቤት የሚያጠፋ ንጉሥ ያስነሣል፡፡ ይኸውም አሁን ነው፡፡
\v 15 እግዚአብሔር እስራኤልን ይቀጣል፤ እርሱም በውሃ ውስጥ እንደሚወዛወዝ ሸንበቆ ይወዛወዛል፡፡ አሼራ ተብላ የምትጠራውን ሴት አምላክ ጣዖት በመሥራት እግዚአብሔርን ስላስቆጡት፣ የእስራኤልን ሕዝብ ቀድሞ ለአባቶቻቸው ከሰጣቸው መልካም ምድር ይነቅላል፤ ከኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ እንዲበታተኑም ያደርጋል፡፡
\v 16 ኢዮርብዓም ኃጢአት ከመሥራቱ የተነሣና የእስራኤልንም ሕዝብ ወደ ኃጢአት ስለመራ እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ ይተዋል፡፡››
\s5
\v 17 ስለዚህ የኢዮርብዓም ሚስት ተነሥታ ወደ ቲርሳ ተመልሳ ሄደች፡፡ ወደ ቤትዋ ደጃፍ አንደ ደረሰች ወዲያውኑ ልጁ ሞተ፡፡
\v 18 እግዚአብሔር በአገልጋዩ በነቢዩ አኪያ በኩል በነገረው መሠረት እስራኤላውያን በሐዘን አልቅሰው ቀበሩት፡፡
\s5
\v 19 ንጉሥ ኢዮርብዓም ያደረጋቸው ሌሎች ነገሮች ሁሉ፣ የተዋጋቸው ጦርነቶችና አገዛዙም እንዴት እንደ ነበር ሁሉም ነገር በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡
\v 20 ኢዮርብዓም ለሃያ ሁለት ዓመት ነገሠ፤ ከአባቶቹም ጋር አንቀላፋ፤ ልጁም ናዳብ በእርሱ ፈንታ ተተክቶ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ፡፡
\s5
\v 21 የሰለሞን ልጅ ሮብዓም በይሁዳ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው አርባ አንድ ዓመቱ ነበር፡፡ እርሱም እግዚአብሔር ከመላው የእስራኤል ነገዶች ለስሙ መጠሪያ እንድትሆን በመረጣት ከተማ በኢየሩሳሌም መኖሪያውን አድርጎ ዐሥራ ሰባት ዓመት ገዛ፡፡ የሮብዓምም እናት አሞናዊት ስትሆን፣ ስምዋም ናዕማ ነበር፡፡
\v 22 የይሁዳ ሕዝብ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አደረገ፤ የቀድሞ አባቶቻቸው ሲያደርጉት ከነበረው ይበልጥ ክፉ ነገር በማድረጋቸው የእግዚአብሔርን ቁጣ አነሣሡት፡፡
\s5
\v 23 ለባዕዳን አማልክትም የማምለኪያ ስፍራዎችን ሠሩ፤ በኮረብታዎች ላይና በዛፍ ጥላ ሥር የሚያመልኩአቸውን የድንጋይ ቅርፆችና የኤሼራን ምስሎች አቆሙ፡፡
\v 24 ከእነዚህም ሁሉ የከፋ በእነዚያ ሕዝቦች የማምለኪያ ስፍራዎች የቤተ ጣዖት አመንዝራዎች ነበሩ፡፡ አሕዛብ ይፈፅሙት የነበረውን እግዚአብሔር ከእስራኤላውያን ፊት ነቃቅሎ ያባረራቸውን አሳፋሪ ነገር ሁሉ ይፈፅሙ ነበር፡፡
\s5
\v 25 ሮብዓም በነገሠ በአምስተኛው ዓመት የግብፅ ንጉሥ ሺሻቅ በኢየሩሳሌም ላይ አደጋ ጣለ፡፡
\v 26 በቤተ መቅደስና በቤተ መንግሥት ተከማችቶ የነበረውንም ሀብት ሁሉ፣ ሰለሞን ከወርቅ ያሠራቸውን ጋሻዎች ጭምር ዘርፎ ወሰደ፡፡
\s5
\v 27 እነርሱንም ለመተካት ንጉሥ ሮብዓም ጋሻዎችን ከነሐስ አሠርቶ የቤተ መንግሥቱን ቅጥር በር በሚጠብቁ አለቆች እንዲጠበቁ አደረገ፡፡
\v 28 ንጉሡ ወደ ቤተ መቅደሱ በመጣ ቁጥር፣ የቤተ መቅደሱ ዘበኞች ጋሻዎችን አንግበው ይቀበሉታል፤ ከሄደም በኋላ ጋሻዎቹን መልሰው ዘበኞች በሚጠበቁበት ማከማቻ ያኖሩ ነበር፡፡
\s5
\v 29 ንጉሥ ሮብዓም ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኝ የለምን?
\v 30 በዚህም ዘመን ሁሉ ሮብዓምና ኢዮርብዓም እርስ በርሳቸው በማያቋርጥ ጦርነት ላይ ነበሩ፡፡
\v 31 ሮብዓም ሞተ፤ በዳዊት ከተማ በሚገኘው በነገሥታቱ መካነ መቃብር ተቀበረ፡፡ ልጁም አቢያ በእርሱም ፈንታ ተተክቶ ነገሠ፡፡
\s5
\c 15
\p
\v 1 ኢዮርብዓም በእስራኤል ላይ በነገሠ በዐሥራ ስምንተኛው ዓመት አቢያ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ፡፡
\v 2 እርሱም በኢየሩሳሌም ሦስት ዓመት ነገሠ፡፡ የእናቱ ስም ማዕካ ሲሆን፣ እርስዋም የአቤሴሎም ልጅ ነበረች፡፡
\v 3 አቢያም እንደ ቀደሙት አባቶቹና እንደ ዳዊት በእግዚአብሔር አምላክ ዘንድ ፍፁም ታማኝ ሆኖ አልተገኘም፡፡ አባቱ ሮብዓም ይፈፅመው የነበረውን ኃጢአት ሁሉ መሥራት ቀጠለ፡፡
\s5
\v 4 የሆነ ሆኖ ከእርሱ በኋላ በኢየሩሳሌም እንዲነግሥና ኢየሩሳሌምንም እንዲያጠናክር አምላኩ እግዚአብሔር ስለ ዳዊት ሲል ለአቢያ አንድ ወንድ ልጅ ሰጠው፡፡
\v 5 እግዚአብሔር ይህንን ያደረገበት ምክንያት ዳዊት በሂታዊው ኦርዮን ላይ ከፈጸመው ኃጢአት በቀር በእግዚአብሔር ፊት በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ትክክለኛ ነገር አድርጎአል፤ ከትእዛዙም ፈቀቅ አላለም፡፡
\v 6 በሮብዓምና ኢዮርብዓም ዘመን ተጀምሮ የነበረው ጦርነት፣ በአቢያ ዘመነ መንግሥትም ነበር፡፡
\s5
\v 7 አቢያ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኝ የለምን?
\v 8 አቢያም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊትም ከተማ ተቀበረ፡፡ በእርሱም ፈንታ ልጁ አሳ ተተክቶ ነገሠ፡፡
\s5
\v 9 ኢዮርብዓም በእስራኤል ላይ በነገሠ በሃያኛው ዓመት አሳ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ፡፡
\v 10 እርሱም በኢየሩሳሌም አርባ አንድ ዓመት ገዛ፡፡ አያቱም ማዕካ ተብላ የምትጠራ የአቤሌሎም ልጅ ነበረች፡፡
\v 11 አሳም አያቱ ዳዊት እንዳደረገው ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ደስ የሚያሰኝ ነገር ሠራ፡፡
\s5
\v 12 ንጉሥ አሳ የቤተ ጣዖት አመንዝራዎችን ሁሉ ከአገሩ አስወገደ፤ ከእርሱም በፊት የነበሩ ነገሥታት የሠሩአቸውን ጣዖታት ሁሉ ነቃቅሎ ጣለ፡፡
\v 13 አያቱ ማዕካ አሼራ ተብላ የምትጠራውን የሴት አምላክ አስጸያፊ ጣዖት ስለ ሠራች ከእቴጌነት ሽሮ ከቤተ መንግሥት አስወጣት፤ የሠራችውንም ጣዖት ሰባብሮ በቄድሮን ሸለቆ ውስጥ በእሳት አቃጠለው፡፡
\s5
\v 14 አሳ በኮረብቶች ላይ የሚገኙ የአሕዛብ የማምለኪያ ቦታዎችን በሙሉ አላስወገደም፤ ይሁን እንጂ በዘመኑ ሁሉ የአሳ ልብ ሙሉ ለሙሉ ለእግዚአብሔር ፍጹም ነበር፡፡
\v 15 አባቱ ለእግዚአብሔር ቤት የተለዩ እንዲሆኑ ያደረጋቸውንና እርሱም ራሱ የለያቸውን ወርቅና ብር አሠርቶ ንዋያተ ቅዱሳትን ሁሉ በቤተ መቅደስ አኖረ፡፡
\s5
\v 16 የይሁዳ ንጉሥ አሳና የእስራኤል ንጉሥ ባኦስ በሥልጣን በነበሩበት ዘመን ሁሉ የእርስ በርስ ጦርነት ነበር፡፡
\v 17 የእስራኤል ንጉሥ ባኦስ ማንም ሰው አሳ በሚገዛበት በይሁዳ ምድር እንዳይወጣና እንዳይገባ ለመከላከል ራማን ምሽግ አድርጎ መሥራት ጀመረ፡፡
\s5
\v 18 ከዚያም ንጉሥ አሳ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስና በቤተ መንግሥቱ የተረፈውን ወርቅና ብር ሁሉ ወሰደ፡፡ እርሱም በአገልጋዮቹ እጅ በደማስቆ ከተማ ለነበረው የአዚን ልጅ የጣብሪሞን ልጅ ለሆነው ለሶርያ ንጉሥ ቤን ሀዳድ ስጦታ አድርጎ ላከለት፡፡ እርሱም እንዲህ አለ፡-
\v 19 የእኔ አባትና የአንተ አባት ያደርጉት በነበረው ዓይነት በመካከላችን ቃል ኪዳን ይኑር፡፡ እነሆ ብርና ወርቅ ስጦታ እንዲሆንህ ልኬልሃለሁ፡፡ የእሰራኤል ንጉሥ ባኦስ እኔን እንዲለቀኝ ቀደም ሲል ከእርሱ ጋር ያደረግኸውን ቃል ኪዳን አሁን እንድታቋርጥ ይሁን፡፡
\s5
\v 20 ንጉሥ ቤን ሀዳድም አሳ ባቀረበው አሳብ ተስማምቶ የጦር አዛዦቹንና ሠራዊቱን በመላከ በእስራኤል ከተሞች ላይ አደጋ እንዲጥሉ አደረገ፡፡ እነርሱም ዒዮን፣ ዳን፣ አቤልቤተማሪካና የገሊላ ባሕር ተብለው የሚጠሩ ከተሞች በገሊላ ባሕር አጠገብ የሚገኘው አገርና የንፍታሌም ግዛት ሁሉ ናቸው፡፡
\v 21 ንጉሥ ባኦስ የሆነውን ነገር ሁሉ በሰማ ጊዜ የራማን ምሽግ መሠራት እንዲቆም አድርጎ ወደ ቲርጻ ሄደ፡፡
\v 22 ከዚህም በኋላ ንጉሥ አሳ ባኦስ ራማን ለመመሸግ አከማችቶት የነበረውን ድንጋይና እንጨት ከዚያ ለማንሣት እንዲረዳው ሕዝቡ አንድም ሳይቀር እንዲመጣ ወደ ይሁዳ ግዛቶች ሁሉ ትእዛዝ አስተላለፈ፤ ንጉሥ አሳ ከዚያ የተገኘውን ድንጋይና እንጨት ሁሉ ወስዶ በምጽጳና በብንያም ግዛት ውስጥ የምትገኘውን የጌባዕን ከተማ ምሽግ አድርጎ ሠራበት፡፡
\s5
\v 23 ንጉሥ አሳ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ የጀግንነት ሥራውና የሠራቸውም ከተሞች በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኝ የለምን? ንጉሥ አሳ በዕድሜ በሸመገለ ጊዜ ከእግሩ ሕመም የተነሣ ሽባ ሆኖ ነበር፡፡
\v 24 ንጉሥ አሳም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊትም ከተማ በሚገኘው በነገሥታት መቃብር ተቀበረ፡፡ በእርሱም ፈንታ ተተክቶ ልጁ ኢዮሣፍጥ ነገሠ፡፡
\s5
\v 25 አሳ በይሁዳ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት የአዮርብዓም ልጅ ናዳብ የእስረኤል ንጉሥ ሆነ፡፡ እርሱም ሁለት ዓመት ገዛ፡፡
\v 26 ከእርሱም በፊት እንደ ነበረው እንደ አባቱ በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአት በመሥራት የእስራኤልን ሕዝብ ወደ ኃጢአት መራ፡፡
\s5
\v 27 የይሳኮር ነገድ የሆነው የአኪያ ልጅ ባኦስ ናዳብን ድል አድርጎ ገደለው፤ በዚያም ጊዜ ናዳብና ሠራዊቱ በፍልስጥኤም ግዛት የምትገኘውን የገባቶንን ከተማ በመክበብ ላይ ነበሩ፡፡
\v 28 ይህም የሆነው የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በሦስተኛው ዓመት ነው፤ በዚህ ዓይነት ባኦስ በናዳብ ፈንታ ተተክቶ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ፡፡
\s5
\v 29 ንጉሥ ባኦስ እንደነገሠ ወዲያውኑ የኢዮርብዓምን ቤተ ሰብ በሙሉ ገደለ፡፡ እግዚአብሔር በአገልጋዩ በሴሎኣዊው በነቢዩ አኪያ አማካይነት በተናገረው ቃል መሠረት የኢዮርብዓም ወገን በሙሉ ተገደሉ፡፡ በሕይወት የተረፈ አንድም አልነበረም፤
\v 30 ይህም የሆነበት ምክንያት ኢዮርብዓም ራሱ በሠራው ኃጢአትና የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን ቁጣ ስላነሣሣ ነው፡፡
\s5
\v 31 ናዳብ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኝ የለምን?
\v 32 የይሁዳ ንጉሥ አሳ እና የእስራኤል ንጉሥ ባኦስ በሥልጣን ዘመናቸው ሁሉ የእርስ በርስ ጦርነት ላይ ነበሩ፡፡
\s5
\v 33 አሳ በይሁዳ በነገሠ በሦስተኛው ዓመት የአኪያ ልጅ ባኦስ በመላው እስራኤል ላይ ነገሠ፡፡ እርሱም በቲርጻ ሃያ አራት ዓመት ገዛ፡፡
\v 34 ከእርሱም በፊት እንደ ነበረው እንደ ንጉሥ ኢዮርብዓም ባኦስ ኃጢአት በመሥራትና የእስራኤልንም ሕዝብ ወደ ኃጢአት በመምራት በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አደረገ፡፡
\s5
\c 16
\p
\v 1 በሐናኒ ልጅ በነቢዩ ኢዩ አማካይነት እግዚአብሔር ስለ ባኦስ የተናገረው ቃል እንዲህ ሲል መጣ፡-
\v 2 እኔ ግን ከትቢያ አንሥቼ የሕዝቤ የእስራኤል መሪ እንድትሆን ከፍ ከፍ አደረግሁህ፤ ታዲያ አንተ እንደ ኢዮርብዓም ኃጢአት ሠራህ፤ ሕዝቤንም ወደ ኃጢአት መራህ፤ የኃጢአታቸውም ብዛት የእኔን ቁጣ አነሣሥቶአል፡፡
\s5
\v 3 ስለዚህ ኢዮርብዓምን እንዳሰወገድኩ አንተንና ቤተ ሰብህንም አስወግዳለሁ፡፡
\v 4 በከተማይቱ ውስጥ የሚሞተውን ማንኛውንም የባኦስ ቤተ ሰብ ውሾች ይበሉታል፤ በሜዳ ላይ የሚሞተውንም የሰማይ አሞራዎች ይበሉታል፡፡
\s5
\v 5 ባኦስ ያደረገው ሌላው ነገርና የጀግንነት ሥራዎቹም ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኝ የለምን?
\v 6 ባኦስም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በቲርጻም ተቀበረ፡፡ በእርሱም ፈንታ ተተክቶ ልጁ ኤላ ነገሠ፡፡
\s5
\v 7 እግዚአብሔር በነቢዩ ኢዩ አማካይነት በባኦስና በቤተ ሰቡ ላይ የትንቢት ቃል የተናገረው፣ ባኦስ በፈጸመው ኃጢአት በእግዚአብሔር ፊት ክፉ በማድረጉ ነበር፡፡ ባኦስ እግዚአብሔርን ያስቆጣውም ከእርሱ ፊት የነበረው ንጉሥ ባደረገው ዓይነት ስለ ሠራው ክፉ ነገር ብቻ ሳይሆን የኢዮርብዓምንም ቤተ ሰብ ሁሉ በመግደሉ ጭምር ነበር፡፡
\s5
\v 8 አሳ በይሁዳ በነገሠ በሃያ ስድስተኛው ዓመት የባኦስ ልጅ ኤላ በእስራኤል መንገሥ ጀመረ፡፡ በቲርጻም ሁለት ዓመት ገዛ፡፡
\v 9 የሠረገላዎቹ እኩሌታ ኃላፊ የሆነ ዚምሪ ከጦር መኮንኖቹ አንዱ በንጉሡ ላይ ዐደመ፡፡ ኤላም በቲርጻ ከተማ የቤተ መንግሥቱ ኃላፊ በሆነው አርጻ ተብሎ በሚጠራው ባለሟሉ ቤት ብዙ መጠጥ ጠጥቶ ሰክሮ ነበር፡፡
\v 10 በዚህ ጊዜ ዚምሪ ወደዚያ ቤት ገብቶ ኤላን ገደለው፤ እርሱም በኤላ ፈንታ የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በሃያ ሰባተኛው ዓመት ተተክቶ ነገሠ፡፡
\s5
\v 11 ዘምሪም በዙፋን ላይ እንደተቀመጠ ወዲያውኑ የባኦስ ቤተ ሰብ አባላት የሆኑትን በሙሉ ገደለ፤ የባኦስ ዘመድና ወዳጅ የሆነውን ወንድ አንድ እንኳ ሳይቀር ሁሉንም በሞት ቀጣ፡፡
\v 12 እግዚአብሔር ነቢዩ በኢዩ አማካይነት በባኦስ ላይ በተናገረው ትንቢት መሠረት ዚምሪ የባኦስን ቤተ ሰብ በሙሉ ፈጀ፡፡
\v 13 ይህም የሆነበት ምክንያት ባኦስና ልጁ ኤላ ጣዖት በማምለካቸውና የእስራኤልን ሕዝብ ወደ ኃጢአት በመምራታቸው፣ የእስራኤልንም አምላክ የእግዚአብሔርን ቁጣ በማነሣሣታቸው ነው፡፡
\s5
\v 14 ኤላ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኝ የለምን?
\s5
\v 15 አሳ በይሁዳ በነገሠ በሃያ ሰባተኛው ዓመት ዚምሪ በቲርጻ ለሰባት ቀኖች ብቻ በእስራኤል ላይ ነገሠ፡፡ በዚያን ጊዜ የአስራኤል ወታደሮች በፍልስጥኤም የምትገኘውን የገባቶንን ከተማ ከበው ነበር፡፡
\v 16 ዘምሪ ዐምፆ ንጉሡን መግደሉን በሰሙ ጊዜ በዚያው እንዳሉ ወዲያውኑ የጦር አዛዥ የነበረውን ዖምሪን አነገሡ፡፡
\v 17 ዖምሪና ወታደሮቹ የገባቶንን ከበባ አቆሙ፤ ከዚያም ገሥግሠው ሄደው ቲርጻን ከበቡ፡፡
\s5
\v 18 ዘምሪ ከተማይቱ እንደተያዘች ባየ ጊዜ በቤተ መንግሥቱ ውስጠኛ ክፍል ወዳለው ምሽግ ውስጥ ገብቶ በቤተ መንግሥቱ ላይ እሳት ለቀቀበት፤ እርሱም በእሳት ነበልባል ተቃጥሎ ሞተ፡፡
\v 19 ይህ የሆነው እርሱ በሠራው ኃጢአትና እስራኤልንም ወደ ኃጢአት በመምራቱ ምክንያት ከእርሱ በፊት እንደ ነበረው እንደ ኢዮርብዓም እግዚአብሔርን ስላስቆጣው ነው፡፡
\v 20 ዘምሪ የሠራው ሌላው ነገር ሁሉና ያደረገውም ሤራ ጭምር በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ የሚገኝ አይደለምን?
\s5
\v 21 በዚያን ጊዜ የእስራኤል ሕዝብ ከሁለት ተከፍለው ነበር፡፡ ከዚህም የተነሣ አንደኛው ክፍል ታምኒን ተብሎ የሚጠራውን የጎናትን ልጅ ለማንገሥ ሲፈልግ ሌላው ክፍል ደግም ዖምሪን ለመደገፍ ይፈልግ ነበር፡፡
\v 22 ነገር ግን የዖምሪ ተከታዮች ከጎናት ልጅ ታምኒን ይልቅ ጠንካራ ነበሩ፡፡ ስለዚህም ታምኒን ተገደለ፤ ዖምሪም ንጉሥ ሆነ፡፡
\s5
\v 23 በዚህ ዓይነት አሳ በይህዳ በነገሠ በሠላሳ አንደኛው ዓመት ዖምሪ በእስራኤል ላይ ነግሦ ዐሥራ ሁለት ዓመት ገዛ፡፡ የመጀመሪያዎቹን ስድስት ዓመቶች የገዛውም መቀመጫውን በቲርጻ አድርጎ ነበር፡፡
\v 24 ከዚያም በኋላ ሳምር ተብሎ ከሚጠራው ሰው የሰማርያ ኮረብታን በስድስት ሺህ ጥሬ ብር ገዛው፡፡ ዖምሪ በኮረብታው ላይ ከተማ ቆረቆረ፤ ከተማይቱንም ቀድሞ የኮረብታው ባለንብረት በሆነው በሳምር ስም ሰማርያ ብሎ ሰየማት፡፡
\s5
\v 25 ዖምሪ ከእርሱ በፊት ከነበሩት ነገሥታት ይበልጥ የከፋ ኅጢአት በመሥራቱ እግዚአብሔርን አሳዘነ፡፡
\v 26 እርሱ በሠራው ኃጢአትና አስራኤልን ወደ ኃጢአት በመምራት ዋጋ ወደሌላው ጣዖት አምልኮ መምራቱ ከእርሱ በፊት እንደ ነበረው እንደ ኢዮርብዓም የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን ቁጣ አነሣሣ፡፡
\s5
\v 27 ዖምሪ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉና ያከናወነውም ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኝ የለምን?
\v 28 ዖምሪም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በሰማርያም ተቀበረ፤ በእርሱም ፈንታ ተተክቶ ልጁ አክዓብ ነገሠ፡፡
\s5
\v 29 የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በሠላሳ ስምንተኛው ዓመት የዖምሪ ልጅ አክዓብ በእስራኤል ነገሠ። የዖምሪ ልጅ አክዓብ በሰማርያ ሃያ ሁለት ዓመት ነገሠ፤
\v 30 የዖምሪ ልጅ አክዓብ ከእርሱ በፊት ከነበሩት ሁሉ የባሰ ክፉ ነገር በያህዌ ፊት አደረገ።
\s5
\v 31 አክዓብ ንጉሥ ኢዮርብዓም የሠራውን ኅጢአት እንደ ቀላል ነገር አድርጎ በመቁጠር እርሱም ራሱ ያንኑ ኃጢአት ሠራ፤ ከዚህም ሁሉ አልፎ የሲዶና ንጉሥ የኤትበዓል ልጅ የሆነችውን አረማዊቷን ኤልዛቤልን አገባ፤ ባዓል ተብሎ የሚጠራውንም ጣዖት አመለከ፤ ሰገደለትም፡፡
\v 32 በሰማርያ ለባዓል ቤተ መቅደስ አሠርቶ መሠዊያ ሠራለት፡፡
\v 33 አሼራ ተብላ የምትጠራውንም የሴት አምላክ ምስል አቆመ፤ ከእርሱ በፊት ከነበሩትም የእስራኤል ነገሥታት ሁሉ ይበልጥ የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን ቁጣ የሚያነሣሣ ኃጢአት ሠራ፡፡
\s5
\v 34 በአክዓብ ዘመነ መንግሥት አኪኤል ተብሎ የሚጠራ የቤቴል ተወላጅ ኢያሪኮን መልሶ ሠራ፤ እግዚአብሔር በነዌ ልጅ በኢያሱ አማካይነት አስቀድሞ በተናገረው ቃል መሠረት አኪኤል የኢያሪኮን የመሠረት ድንጋይ በሚያኖርበት ጊዜ በነዌም ልጅ በኢያሱ እንደ ተነገረው እንደ እግዚብሔር ቃል፣ የበኩር ልጁ አቢሮን ሞተበት፤ የቅጥርዋንም በሮች በሚሠራበት ጊዜ ታናሹ ልጁ ሠጉብ ሞተ፡፡
\s5
\c 17
\p
\v 1 በገለዓድ የምትገኘው ቴስቢያዊው ነቢዩ ኤልያስ ነጉሥ አክዓብን በእኔ ቃል ካልሆነ በቀር በሚቀጥሉት ዓመቶች በምድር ላይ ጠል ወይም ዝናብ እንደማይኖር እኔ በማገለግለው በእስራኤል አምላክ በሕያው እግዚአብሔር ስም እነግርሃለሁ አለው፡፡
\s5
\v 2 የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤልያስ እንዲህ ሲል መጣ፤
\v 3 ከዚህ ተነሥተህ ወደ ምሥራቅ ሂድ፤ እዚያም ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ በሚገኘው ኮራት ተብሎ በሚጠራው ሸለቆ ተሸሽግ፡፡
\v 4 የምትጠጣውንም ውሃ ከዚያው ወንዝ ታገኛለህ፤ ቁራዎችም ምግብ እንዲያመጡልህ አዝዣለሁ፡፡
\s5
\v 5 ኤልያስም እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ሄዶ በኮራት ሸለቆ ተቀመጠ፡፡
\v 6 ከወንዙም ውሃ ጠጣ፤ ቁራዎችም ዘወትር ጧትና ማታ እንጀራና ሥጋ ያመጡለት ነበር፡፡
\v 7 ነገር ግን ዝናብ ጠፍቶ ድርቅ ከመሆኑ የተነሣ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ያ ወንዝ ደረቀ፡፡
\s5
\v 8 የእግዚአብሔርም ኤልያስን እንዲህ አለው፡-
\v 9 እንግዲህ አሁን ከዚህ ተነሥተህ ሂድ፤ በሲዶና በምትገኘው በስራፕታ ከተማ ተቀመጥ፤ እነሆ በዚያ የምትኖር አንዲት መበለት እንድተመግብህ እዝዣለሁ አለው፡፡
\v 10 ስለዚህ ኤልያስ ወደ ሰራፕታ ሄደ፤ ወደ ከተማይቱም ቅጥር በር በደረሰ ጊዜ አንዲት ባልዋ የሞተባት ሴት እንጨት ስተለቅም አይቶ እባክሽ የምጠጣው ውሃ አምጪልኝ አላት፡፡
\s5
\v 11 ውሃም ልታመጣለት በመሄድ ላይ ሳለች ወዲያውኑ ጠርቶ እባክሽ በተጨማሪ ትንሽ እንጀራ አምጪልኝ አላት፡፡
\v 12 እርስዋም እንዲህ ስትል መለሰችለት፡- ምንም እንጀራ እንደሌለኝ በአምላክህ በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ፤ በዱቄት ዕቃዬ ውስጥ ካለችው ከአንድ እፍኝ ዱቄትና በማሰሮዬ ውስጥ ካለችው ከጥቂት የወይራ ዘይት በቀር ምንም የለኝም፤ ወደዚህ የመጣሁት ትንሽ እንጨት ለቃቅሜ ቤቴ በመመለስ ይህችኑ ትንሽ ዱቄት ለእኔና ለልጄ ለመጋገር ነው፤ ይህችም የመጨረሻ ምግባችን ናት፤ ከዚያ በኋላ ይህችኑ በልተን እንሞታለን፡፡
\v 13 ኤልያስም እንዲህ አላት፣ አይዞሽ አትጨነቂ፤ ሄደሽ ምግብሽን አዘጋጂ፤ አስቀድመሽ ግን ከዚች ካለችሽ ዱቄት ለእኔ ትንሽ እንጎቻ ጋግረሽ አምጪልኝ፤ የቀረውንም ለራስሽና ለልጅሽ ጋግሪው፡፡
\s5
\v 14 የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡- እኔ እግዚአብሔር ዝናብን እስከማወርድ ድረስ ዱቄቱ ከማስቀመጫው ዕቃ፣ ዘይቱም ከማሰሮው ከቶ አያልቅም ሲል ተናግሮአል፡፡
\v 15 አርስዋም ሄዳ ኤልያስ እንደ ነገራት አደረገች፤ እርስዋ፣ ቤተ ሰብዋና ኤልያስ ለብዙ ቀን የሚሆን በቂ ምግብ አገኙ፡፡
\v 16 እግዚአብሔር በኤልያስ አማካይነት በሰጠው ተስፋ መሠረት ዱቄቱ ከማኖሪያው ዕቃ፣ ዘይቱም ከማሰሮው አላለቀም፡፡
\s5
\v 17 ከጥቂት ጊዜም በኋላ የዚያች ባልዋ የሞተባት ሴት ልጅ ታመመ፤ ሕመሙም እየባሰበት ስለ ሄደ በመጨረሻ ሞተ፡፡
\v 18 እርስዋም ኤልያስን የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፣ ስለምን ይህን አደረግህብኝ? ወደዚህ የመጣኸው ኃጢአቴን አስታውሰህ ልጄ እንዲሞትብኝ ለማድረግ ነውን? ስትል ጠየቀችው፡፡
\s5
\v 19 ኤልያስም ልጅሽን ወደ እኔ አምጪው አላት፡፡ ልጁንም ከዕቅፍዋ ወስዶ እርሱ ወደሚኖርበት ሰገነት አውጥቶ በአልጋው ላይ አጋደመው፡፡
\v 20 ከዚህ በኋላ ኤልያስ ድምፁን ከፍ በማድረግ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ ስለምን በዚህች ባልዋ በሞተባት ሴት ላይ ይህን የመሰለ አሠቃቂ ነገር አደረግህ? እርስዋ እኔን በማስተናገድ ታላቅ ቸርነት አድርጋልኛለች፤ ታዲያ አንተ ስለምን ልጅዋ እንዲሞት አደረግህ ሲል ጸለየ፡፡
\v 21 ከዚህ በኋላ ኤልያስ በልጁ ላይ ሦስት ጊዜ ተዘርሮ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፣ እባክህ ይህን ልጅ ከሞት አስነሣው ሲል ጸለየ፡፡
\s5
\v 22 እግዚአብሔርም የኤልያስን ጸሎት ሰማ፤ የልጁም እስትንፋስ እንደገና ተመልሶለት ዳነ፡፡
\v 23 ኤልያስም ልጁን ከሰገነት ወደ ምድር ቤት አውርዶ ለእናቱ ሰጣትና እነሆ ልጅሽ ከሞት ወደ ሕይወት ተመልሶአል! አላት፡፡
\v 24 እርስዋም እነሆ አንተ የእግዚአብሔር ሰው መሆንህንና እግዚአብሔርም በአንተ አማካይነት የተናገረው እውነት መሆኑን አሁን ዐወቅሁ! ስትል መለሰችለት፡፡
\s5
\c 18
\p
\v 1 ከብዙ ጊዜ በኋላ በሦስተኛው ዓመት የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤልያስ እንዲህ ሲል መጣ፡- ሄደህ ራስህን ለንገሥ አከዓብ ግለጥለት እኔም በምድር ላይ ዝናብን አዘንባለሁ አለው፡፡
\v 2 ኤልያስም በታዘዘው መሠረት ወደ አከዓብ ሄደ፤ በዚህ ጊዜ በሰማርያ ረሃብ እጅግ ጸንቶ ነበር፡፡
\s5
\v 3 ስለዚህ ንጉሥ አክዓብ የቤተ መንግሥቱ ኃላፊ የሆነውን አብድዩን ጠራው፤ አብድዩ እግዚአብሔርን የሚፈራ መንፈሳዊ ሰው ነበር፡፡
\v 4 ኤልዛቤል የእግዚአብሔርን ነቢያት ታስገድል በነበረበት ጊዜ አብድዩ አንድ መቶ የሚሆኑትን የእግዚአብሔርን ነቢያት ከሁለት ከፍሎ ኀምሳ ኀምሳውን በዋሻዎች ከሸሸጋቸው በኋላ እህልና ውሃ በማቅረብ መግቦአቸው ነበር፡፡
\s5
\v 5 አከዓብ አብድዩን ፈረሶችንና በቅሎዎችን ከሞት የምናድንበት በቂ ሣር እናገኝ እንደሆን በምድሪቱ ወደሚገኘው ምንጭና ወንዝ እስቲ ሂድና እይ፡፡ ምናልባት እንስሳትን ከሞት ማዳን እንችል ይሆናል አለው፡፡
\v 6 እያንዳንዳቸው በአገሪቱ ወደየትኛው ክፍል ሄደው መፈለግ እንዳባቸው ከተስማሙ በኋላ አክዓብና አብድዩ ለየብቻቸው በሁለት አቅጣጫ ተሰማሩ፡፡
\s5
\v 7 አብድዩ በሚሄድበት መንገድ ላይ ሳለ በድንገት ኤልያስን አገኘው፤ ኤልያስ መሆኑንም ስላወቀ በግንባሩ ወደ መሬት ለጥ ብሎ እጅ ከነሣው በኋላ ጌታዬ ኤልያስ በእውነት አንተ ነህን? ሲል ጠየቀው፡፡
\v 8 ኤልያስም አዎን እኔ ነኝ፤ እዚህ መሆኔን ሄደህ ለጌታህ ንገረው ሲል መለሰለት፡፡
\s5
\v 9 አብድዩም እንዲህ አለው፤ ንጉሥ አክዓብ እኔን ባሪያህን ይገድለኝ ዘንድ በእጁ አሳልፈህ የምትሰጠኝ ምን በደል ሠርቼ ነው?
\v 10 ንጉሡ አንተን ለማግኘት ፈልጎ በዓለም ላይ መልእክተኛ ያልላከበት አገር እንደሌለ በአምላክህ በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ፤ የአንድ አገር መሪ አንተ በአገሩ ውስጥ አለመኖርህን ለንጉሥ አክዓብ በመሐላ እያረጋገጠለት ቆይቶአል፡፡
\v 11 አሁን አንተ ግን ኤልያስ ተገኝቶአል ብለህ ለጌታህ ንገር ትለኛለህ፡፡
\s5
\v 12 እኔ ከዚህ እንደ ሄድኩ ወዲያውኑ የእግዚአብሔር መንፈስ አንተን ወዳልታወቀ ቦታ ቢወስድህ እኔ ምን ይበጀኛል? አንተ በዚህ ቦታ መኖርህን ለአከዓብ ነግሬው ሳያገኝህ ቢቀር እኔን በሞት ይቀጣኛል፤ ከልጅነቴ ጀምሬ እግዚአብሔርን የምፈራ ሰው መሆኔን አስታውስ፡፡
\v 13 ደግሞስ ኤልዛቤል የእግዚአብሔርን ነቢያት ስታስገድል በነበረችበት ጊዜ አንድ መቶ የሚሆኑትን ነቢያት ከሁለት በመክፈል ኀምሳ ኀምሳውን በዋሻ ውስጥ ሸሽጌ እህልና ውሃ በማቅረብ ስመግባቸው መኖሬን አልሰማህምን?
\s5
\v 14 ታዲያ፣ አሁን አንተ እዚህ መሆንህን ሄደህ ለንጉሥ አክአብ ንገር ትለኛለህን? ይህን ባደርግ ንጉሡ ይገድለኛል!
\v 15 ኤልያስም ‹‹ዛሬ ለንጉሡ እንደምገለጥለት በማገለግለውና ሁሉን ቻይ በሆነው በእግዞአብሔር ስም ቃል እገባልሃለሁ! ሲል መለሰለት፡፡
\s5
\v 16 ከዚህ በኋላ አብድዩ ሄዶ ለንጉሥ አክዓብ ነገረው፤ አክዓብም ተነሥቶ ኤልያስን ለመገናኘት ሄደ፤
\v 17 አክዓብ ኤልያስን ባየው ጊዜም ‹‹በእስራኤል ላይ ይህን ችግር ያመጣህ አንተ እዚህ ነህን? አለው፡፡
\s5
\v 18 ኤልያስም እንዲህ ሲል መለሰ፡- ‹‹የእግዚአብሔርን ትእዛዛት በመጣስ ባዓል ተብሎ ለሚጠራው የባዕድ አምላክ ምስሎች በመስገድ ችግር የምታመጡ አንተና የአባትህ ቤተ ሰብ ናችሁ እንጂ እኔ በእስራኤል ላይ ችግር የማመጣ አይደለሁም!
\v 19 ይልቅስ እስራኤላውያንን ሁሉ እንዳገኛቸው አራት መቶ ሃምሳ የበዓል ነቢያትንና በንግሥት ኤልዛቤል ማእድ የሚቀለቡትን አራት መቶ የኤሼራ ነቢያትን በቀርሜሎስ ተራራ ሰብስብልኝ፡፡››
\s5
\v 20 ስለዚህም አክዓብ ለእስራኤላውያን ሁሉና ለነቢያት በሙሉ ጥሪ አድርጎ በቀርሜሎስ ተራራ እንዲሰበሰቡ አስደረገ፡፡
\v 21 ኤልያስም ወጥቶ ለሰዎቹ፡- ‹‹እስከ መቼ ድረስ በሁለት ልብ ስታወላውሉ ትኖራላችሁ? እንግዲህ እግዚአብሔር እውነተኛ አምላክ ከሆነ እርሱን አምልኩ! ወይም ባዓል እውነተኛ አምላክ ከሆነ እርሱኑ አምልኩ! አላቸው፡፡ ሕዝቡ ግን አንዲት ቃል እንኳ አልመለሱም፡፡
\s5
\v 22 ከዚህ በኋላ ኤልያስ እንዲህ አለ፡- ‹‹ከእግዚአብሔር ነቢያት የቀረሁት እኔ ብቻ ነኝ፡፡ አራት መቶ ኀምሳ የባዓል ነቢያት ግን እነሆ በዚህ አሉ፡፡
\v 23 እንግዲህ ሁለት ኮርማዎችን አምጡና የባዓል ነቢያት አንዱን ወስደው ይረዱት፤ ሥጋውንም ቆራርጠው እንጨት በመረብረብ በዚያ ላይ ያኑሩት፤ ነገር ግን እሳት አያድርጉበት፡፡ እኔም ሁለተኛውን ኮርማ ወስጄ እንደዚሁ አደርጋለሁ፡፡
\v 24 ከዚህ በኋላ የባዓል ነቢያት ወደ አምላካቸው ይጸልዩ፤ እኔም ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ፤ እሳትን ወደ መሥዋዕቱ በመላክ መልስ የሚሰጥ እርሱ እውነተኛ አምላክ ይሁን፡፡ ሕዝቡም ድምፁን ከፍ አድረጎ ይህ መልካም ነው በማለት መልስ ሰጡ፡፡
\s5
\v 25 ከዚህ በኋላ ኤልያስ የባዓልን ነቢያት እናንተ ብዙ ስለ ሆናችሁ በመጀመሪያ አንዱን ኮርማ መርጣቸሁ በማረድ ወደ አምላካችሁ ጸልዩ፤ ነገር ግን እንጨቱ ላይ እሳት አታደርጉበት አላቸው፡፡
\v 26 እነርሱም የመጣላቸውን ኮርማ ወስደው በመሥዋዕት አዘጋጅተው እስከ እኩለ ቀን ድረስ ወደ ባዓል ጸለዩ፡፡ ባዓል ሆይ እባክህ ስማን! እያሉ ጮኹ፡፡ በሠሩትም መሠዊያ ዙሪያ እየዘፈኑ ዞሩ፤ ነገር ግን ምንም መልስ አላገኙም፡፡
\s5
\v 27 እኩለ ቀን ሲሆን ኤልያስ ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ጸልዩ! እርሱ አምላክ አይደለም እንዴ? እርሱ በአሳብ ተውጦ ይሆናል! ወይም ራሱን ያዝናና ይሆናል! ወይም ወደ ሩቅ አገር ሄዶ ይሆናል! ወይም ተኝቶ ያንቀላፋ ይሆናልና እንዲነቃ ቀስቅሱት! እያለ ያፌዝባቸው ጀመር፡፡
\v 28 ስለዚህም ነቢያቱ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው እየጸለዩ በሥርዓታቸው መሠረት ደማቸው እስኪፈስ ድረስ በቢላዋና በጩቤ ሰውነታቸውን ያቆስሉ ነበር፡፡
\v 29 እኩለ ቀን ካለፈም በኋላ የሠርክ መሥዋዕት እስከሚቀርብበት ጊዜ ድረስ እየተራወጡ ይቀባጥሩ ነበር፤ ይሁን እንጂ ምንም መልስ አላገኙም፤ ድምፅም አልተሰማም፡፡
\s5
\v 30 ከዚህ በኋላ ኤልያስ ሰዎቹን ወደ እኔ ቅረቡ አላቸው፤ ሁሉም በዙሪያው ተሰበሰቡ፤ እርሱም ፈርሶ የነበረውን የእግዚአብሔር መሠዊያ በማደስ ሠራው፡፡
\v 31 እግዚአብሔር ከዚያ በፊት እስራኤል ብሎ ከሰየመው ከያዕቆብ ልጆች በዐሥራ ሁለቱ ነገዶች ስም ዐሥራ ሁለት ድንጋዮችን ወሰደ፡፡
\v 32 እነዚህንም ድንጋዮች ረብርቦ በእግዚአብሔር ስም መሠዊያ ሠራ፡፡ በዙሪያውም ዐሥራ አራት ሊትር ውሃ የሚይዝ ጉድጓድ ማሰ፡፡
\s5
\v 33 እንጨቱንም በመሠዊያው ላይ በመረብረብ ኮርማውን በብልት በብልቱ ቆራርጦ በእንጨቱ ላይ አኖረ፡፡
\v 34 በአራት ጋን ውሃ ሞልታችሁ በመሥዋዕቱና በእንጨቱ ላይ አፍስሱት! አላቸው፡፡ እነርሱም እንዲሁ አደረጉ፤ አሁንም ጨምሩበት አላቸው፤ እነርሱም እንዲሁ አደረጉ፡፡
\v 35 ውሃውም በመሠዊያው ዙሪያ ፈሰሰ፤ ጉድጓዱንም ሞላው፡፡
\s5
\v 36 ከቀትር በኋላ የሠርክ መሥዋዕት በሚቀርብበት ሰዓት ነቢዩ ኤልያስ ወደ መሠዊያው ቀርቦ እንዲህ ሲል ጸለየ፤ የአብርሃም፣ የይስሐቅና የያዕቆብ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ የእስራኤል አምላክ መሆንህን፣ እኔም እግዚአብሔር ሆይ፣ የአንተ አገልጋይ መሆኔን፣ እኔም ይህንን ሁሉ ያደረግኹት በቃልህ መሠረት መሆኑን አንተ ራስህ ግለጥ፡፡
\v 37 አምላኬ ሆይ፣ ይህ ሕዝብ አንተ እውነተኛ አምላክ መሆንህንና ወደ አንተም ያቀረብከው አንተ ራስህ መሆንህን እንዲያውቅ እባክህ መልስ ስጠኝ፤ አምላክ ሆይ ስማኝ!
\s5
\v 38 ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር እሳትን ላከ፤ ያ እሳት መሥዋዕቱን፣ እንጨቱንና ድንጋዩን በላ፤ ምድሩንም ለበለበ፤ በጉድጓዱ የነበረውንም ውሃ አደረቀ፡፡
\v 39 ሰዎቹም ይህን ባዩ ጊዜ በግንባራቸው መሬት ላይ ተደፍተው በመደነቅ እግዚአብሔር አምላክ ነው! እውነተኛ አምላክ እርሱ ብቻ ነው! አሉ፡፡
\v 40 ኤልያስም የባዓል ነቢያትን ያዙ፤ አንድም ሰው እንዳያመልጥ ሲል አዘዘ፡፡ ሕዝቡም በሙሉ ያዛቸው፤ ኤልያስም ወደ ቂሶን ወንዝ እየመራ ወስዶ በዚያ ሁሉንም ገደላቸው፡፡
\s5
\v 41 ከዚህ በኋላ ኤልያስ ንጉሥ አክዓብን እንግዲህ ሄደህ እህልና ውሃ ቅመስ፤ እኔ አሁን የከባድ ዝናም ነጎድጓድ ድምፅ መቃረቡን እየሰማሁ ነው አለው፡፡
\v 42 አክዓብ እህልና ውሃ ለመቅመስ ሲሄድም ኤልያስ ወደ ቀርሜሎስ ተራራ ወጣ፤ እዚያም በሁለቱ ጉልበቶቹ መካከል ራሱን ወደ መሬት ደፋ፡፡
\s5
\v 43 አገልጋዩን፣ ሂድና ወደ ባሕሩ አቅጣጫ ተመልከት አለው፡፡ አገልጋዩም ሄዶ ሲመለስ ምንም ነገር አይታየኝም አለው፤ አገልጋዩ እየተመላለሰ ያይ ዘንድ ኤልያስ ሰባት ጊዜ አዘዘው፤
\v 44 በሰባተኛውም ጊዜ አገልጋዩ ተመልሶ ከአንድ ሰው መዳፍ የማትበልጥ ትንሽ ደመና ከባሕር ስትወጣ አየሁ አለው፡፡ ኤልያስም ወደ ንጉሥ አክዓብ ሂድና ዝናቡ ሳያቆምህ በፍጥነት ወደ ሠረገላህ ገብተህ ወደ ቤትህ ተመልሰህ ሂድ ብለህ ንገረው ሲል አዘዘው፡፡
\s5
\v 45 ከጥቂት ጊዜም በኋላ ሰማዩ በጥቁር ደመና ተሸፈነ፤ ነፋሱም ነፈሰ፤ ብርቱ ዝናብም ይዘንብ ጀመረ፡፡ ነጉሥ አክዓብም በሠረገላው ተቀምጦ ወደ ኢይዝራኤል ሄደ፤
\v 46 የእግዚአብሔርም ኃይል በኤልያስ ላይ ወረደ፤ ኤልያስም ልብሱን በወገቡ ዙሪያ ጠበቅ አድረጎ በመታጠቅ እስከ ኢይዝራኤል መግቢያ በር ድረስ በአክዓብ ፊት ቀድሞ ይሮጥ ነበር፡፡
\s5
\c 19
\p
\v 1 ኤልያስ ያደረገውን ሁሉና የባዓልንም ነቢያት በሙሉ እንዴት እንደ ገደላቸው ንጉሥ አክዓብ ለሚስቱ ለኤልዛቤል ነገራት፡፡
\v 2 ስለዚህ እርስዋ በእነዚያ ነቢያት ላይ ያደረግኸውን እኔም ነገ ልክ በአሁኑ ሰዓት በአንተ ላይ ሳላደርግብህ ብቀር አማልክት በሞት ይቀሥፉኝ ስትል ወደ ኤልያስ የዛቻ መልእክት ላከች፡፡
\v 3 ኤልያስም ስለ ፈራ ሕይወቱን ለማትረፍ ከአገልጋዩ ጋር በይሁዳ ወደምተገኘው ወደ ቤርሳቤህ ከተማ ሄደ፡፡ አገልጋዩንም በዚያ ተወው፤
\s5
\v 4 ኤልያስ ራሱ አንድ ቀን ሙሉ በበረሓ ተጓዘ፡፡ ከዚህ በኋላ፣ በአንድ የክትክታ ዛፍ ጥላ ሥር ተቀመጠ፣ ሞቱንም በመመኘት እግዚአብሔር ሆይ፣ አሁንስ ይብቃኝ፤ ከቀድሞ አባቶቼ አልበልጥምና ነፍሴን ውሰድ! ሲል ጸለየ፡፡
\v 5 ከዚህ በኋላ በዛፉ ሥር ጋደም እንዳለ እንቅልፍ ወሰደው፤ በድንገትም አንድ መልአክ መጥቶ በመዳሰሰ ቀሰቀሰውና ተነሥተህ ብላ! አለው፡፡
\v 6 ኤልያስ ተነሥቶ ዞሮ በተመለከተ ጊዜ በድንጋይ ሙቀት የበሰለ የዳቦ ሙልሙልና አንድ ገንቦ ውሃ በራስጌው ተቀምጦ አየ፤ ከበላና ከጠጣም በኋላ ተመልሶ እንደገና ተኛ፡፡
\s5
\v 7 የእግዚአብሔርም መልአክ ተመልሶ መጥቶ የምትሄድበት መንገድ ሩቅ ስለ ሆነ ተነሥተህ ብላ! ሲል ዳግመኛ ኤልያስን ቀሰቀሰው፡፡
\v 8 ኤልያስም ተነሥቶ ምግቡን በላ፤ ውሃውንም ጠጣ፡፡ ከዚያም ምግብ ባገኘው ኃይል እስከ ተቀደሰው የሲና ተራራ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ሙሉ ተጓዘ፡፡
\s5
\v 9 እዚያም እንደ ደረሰ ወደ አንድ ዋሻ ገብቶ እዚያ ዐደረ፡፡ በድንገትም እግዚአብሔር፣ ኤልያስ ሆይ! እዚህ ምን ታደርጋለህ? ሲል ጠየቀው፡፡
\v 10 ኤልያስም ሁሉን የምትችል አምላኬ ሆይ! እኔ ለአምላክነትህ በመቅናት ዘወትር አንተን ብቻ አገለግላለሁ፤ የእስራኤል ሕዝብ ግን ከአንተ ጋር የገቡትን ቃል ኪዳን አፍርሰዋል፤ መሠዊያዎችህንም ሰባብረዋል፤ ነቢያትህንም ሁሉ ገድለዋል፤ እነሆ እኔ ብቻዬን ቀርቻለሁ፤ እነርሱ ግን እኔንም እንኳ ሊገድሉኝ ይፈልጋሉ! ሲል መለሰ፡፡
\s5
\v 11 እግዚአብሔርም ኤልያስን ካለህበት ወጥተህ በተራራው ጫፍ ላይ በፊቴ ቁም አለው፤ ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር በአጠገቡ አለፈ፤ ብርቱ ነፋስም በፊቱ በመላክ ኮረብቶችን ሰነጣጠቀ፤ ዐለቶችንም ሰባበረ፤ እግዚአብሔር ግን በነፋሱ ውስጥ አልነበረም፡፡ ነፋሱም ከቆመ በኋላ ምድሪቱ ተናወጠች፤ እግዚአብሔር ግን በምድር መናወጥ ውስጥ አልነበረም፡፡
\v 12 ከምድሪቱም ነውጥ በኋላ እሳት መጣ፤ እግዚአብሔር ግን በእሳቱ ውስጥ አልነበረም፤ ከእሳቱም በኋላ የሹክሹክታ ድምፅ ተሰማ፡፡
\s5
\v 13 ኤልያስ የሹክሹክታውን ድምፅ በሰማ ጊዜ ፊቱን በመጎናጸፊያ ሸፈነ፤ ወጥቶም በዋሻው መግቢያ በር አጠገብ ቆመ፤ አንድ ድምፅም ኤልያስ ሆይ፣ እዚህ ምን ታደርጋለህ? ሲል ጠየቀው፡፡
\v 14 ኤልያስም ሁሉን የምትችል አምላኬ ሆይ፣ እኔ ለአምላኬ በመቅናት ዘወትር አንተን ብቻ አገለግላለሁ፤ የእስራኤል ሕዝብ ግን ከአንተ ጋር የገቡትን ቃል ኪዳን አፍርሰዋል፤ መሠዊያዎችህንም ሰባብረዋል፤ ነቢያትህንም ሁሉ ገድለዋል፤ እነሆ እኔ ብቻዬን ቀርቻለሁ፤ እነርሱ ግን እኔን እንኳ ሊገድሉኝ ይፈልጋሉ ሲል መለሰ፡፡
\s5
\v 15 እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤ በደማስቆ ከተማ አጠገብ ወደሚገኘው በረሓ ተመልሰህ ሂድ፤ እዚያም በደረስህ ጊዜ አዛሄልን ቀብተህ በሶርያ ላይ አንግሠው፤
\v 16 የናሜሲን ልጅ ኢዩንም ቀብተህ በእስራኤል ላይ አንግሠው፤ የአቤል ምሖላ ተወላጅ የሆነውን የሣፋጥን ልጅ ኤልሳዕንም ቀብተህ በአንተ ፈንታ ነቢይ እንዲሆን አድርገው፡፡
\s5
\v 17 ከአዛሄል እጅ ከመገደል ተርፎ የሚያመልጠውን ማንኛውንም ሰው ኢዩ ይገድለዋል፤ ከኢዩ እጅ የሚያመልጠውንም ኤልሳዕ ይገድለዋል፡፡
\v 18 ይሁን እንጂ ለእኔ ታማኞች የሆኑ ለባዓል ያልሰገዱና ለምስሉም ያልሰገዱ ሰባት ሺህ ሰዎችን በእስራኤል ምድር በሕይወት እንዲተርፉ አደርጋለሁ፡፡
\s5
\v 19 ኤልያስም ከዚያ ከሄደ በኋላ የሣፋጥን ልጅ ኤልሳዕን ሁለት በሬዎች ጠምዶ ሲያርስ አገኘው፤ ከእርሱም ጋር በፊቱ በአሥራ አንድ ጥማድ በሬዎች የሚያርሱ ደቦኞች ነበሩ፤ ኤልሳዕም በመጨረሻ አሥራ ሁለተኛውን ጥማድ ያርስ ነበር፤ ኤልያስም መጎናጸፊያውን አውልቆ በኤልሳዕ ላይ ደረበለት፡፡
\v 20 በዚህ ጊዜ ኤልሳዕ በሬዎቹን ተቶ ወደ ኤልያስ በመሮጥ አባቴና እናቴን ስሜ እንድሰናበት ፍቀድልኝ፤ ከዚያም በኋላ እከተልሃለሁ አለው፡፡ ኤልያስም፣ እሺ ተመልሰህ ሂድ፤ እኔ አልከለክልህም! ሲል መለሰለት፡፡
\s5
\v 21 ከዚህ በኋላ ኤልሳዕ ወደ ጥማድ በሬዎቹ ተመልሶ አረዳቸው፡፡ የተጠመዱበትንም ቀንበር በማንደድ ሥጋቸውን ቀቅሎ ለሰዎቹ አቀረበላቸው፤ እነርሱም በሉ፤ ከዚህ በኋላ ኤልያስን ተከትሎ በመሄድ ረዳቱ ሆነ፡፡
\s5
\c 20
\p
\v 1 የሶርያ ንጉሥ ቤን ሀዳድ መላ ሠራዊቱን በአንድነት ሰበሰበ፡፡ ብዙ ፈረሶችና ሠረገሎች ያሉአቸው ሠላሳ ሁለት ነገሥታት ከእርሱ ጋር ነበሩ፡፡ የእስራኤል ዋና ከተማ የሆነችውን ሰማርያ ጦርነት ገጠመ፡፡
\v 2 እርሱም ሀዳድ በከተማይቱ ወደሚገኘው ወደ እስራኤል ነጉሥ ወደ አክዓብ፣ ቤን ሀዳድ እንዲህ ይላል ብሎ መልእክተኞችን ላከ፡-
\v 3 ብርህና ወርቅህ ውብ የሆኑት ሚስቶችህና ልጆችህ ምርጥ የሆኑ ሁሉ የእኔ ናቸው፡፡
\s5
\v 4 የእስራል ንጉሥም ጌታዬ ንጉሥ አንተ እንዳልከው ይሁን ብሎ መለሰ፡፡ እኔ የእኔ የሆነ ሁሉ የአንተ ናቸው አለ፡፡
\v 5 ከጥቂት ጊዜም በኋላ እነዚያው መልእክተኞች ከንጉሥ ቤን ሀዳድ ሌላ ትእዘዝ ይዘው እንደገና ወደ አክዓብ መጡ፤ ትዕዛዙ እንዲህ የሚል ነበር፤ ብርህን፣ ሚስቶችህንና ልጆችህን ማስረክብ እንዳለብህ መልእክት ልኬብህ ነበር::
\v 6 አሁን ደግሞ ቤትህንና የአገልጋዮችህን ቤት ሁሉ ይበረብራሉ፡፡ በርብረውም በዓይናቸው ደስ ያላቸውን ንብረት ሁሉ ይዘው እንዲመጡ የጦር መኮንኖቼን ነገ በዚህ ጊዜ እልካለሁ፡፡ እነርሱም ነገ ጧት በዚሁ ሰዓት እዚያ ይደርሳሉ፡፡
\s5
\v 7 የእስራኤልም ንጉሥ አክዓብ የአገሪቱን ሽማግሌዎች ሁሉ ጠርቶ ይህ ሰው ምን ዓይነት ጠብ እንደሚፈልግ ተመልከቱ አለ፡፡ ከዚህ በፊት ሚስቶቼንና ልጆቼን፣ ብሬንና ወረቄን እንዳስረክበው ጠይቆኝ ተስማምቼ ነበር አላቸው፡፡
\v 8 ሽማግሌዎቹና ሕዝቡም ሁሉ እርሱ ለሚልህ ነገር ሁሉ ግምት አትስጠው፤ ከፍላጎቱ ጋር አትስማማው አሉት፡፡
\s5
\v 9 ስለዚህም አክዓብ ለቤን ሀዳድ መልእክተኞች ለጌታዬ ለንጉሡ ከዚህ በፊት ባቀረብክልኝ ጥያቄ ተስማምቼ ነበር፤ አሁን ባቀረብክልኝ በሁለተኛው ጥያቄ ግን ልስማማበት አልችልም ብሎአል ብላችሁ ንገሩት አላቸው፡፡ መልእክተኞቹም ተመልሰው በመሄድ መልሱን ነገሩት፤
\v 10 ቤን ሀዳድም በሰማርያ ለእያንዳንዱ ወታደር አንዳንድ ጭብጥ ዐፈር ሊዳረስ እስከማይችል ድረስ ብዙ ወታደሮችን ባላሰልፍ አማልክት ይቅሠፉኝ ብሎ የዛቻ መልእክቱን መልሶ ላከበት፡፡
\s5
\v 11 የእስራኤል ንጉሥ መልእክተኞቹን፣ በወታደር መኩራራት የሚገባው ከጦርነት ድል በኋላ እንጂ ከጦርነት በፊት አይደለም፣ ብላችሁ ለንጉሥ ቤን ሀዳድ ንገሩት ሲል መለሰላቸው፡፡
\v 12 ቤን ሀዳድና የእርሱ የጦር ቃል ኪዳን ጓደኞቹ የሆኑ ሌሎችም ነገሥታት በድንኳኖቻቸው ውስጥ ሆነው ሲጠጡ ሳሉ የአክዓበ መልእክት ደረሳቸው፤ በዚህን ጊዜ ቤን ሀዳድ ለጦርነት እንዲዘጋጁ ትእዛዝ ሰጠ፡፡ ስለዚህም ፈጥነው በመንቀሳቀስ ከተማውን ለማጥቃት ቦታ ቦታቸውን ያዙ፡፡
\s5
\v 13 በዚያን ጊዜ አንድ ነቢይ ወደ እስራኤል ንጉሥ አክዓብ ቀርቦ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡- ይህንን ታላቅ ጦር አየህን? እነሆ እግዚአብሔር ዛሬ የቤን ሀዳድን ሠራዊት በእጅህ አሳልፌ እሰጥሃለሁ፡፡ አንተም ደግሞ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃለህ ይልሃል አለው፡፡
\v 14 አክዓብም ግንባር ቀደም ሆኖ የሚዘምተው ማን ይሁን? ሲል ጠየቀ፡፡ ነቢዩም እግዚአብሔር በአውራጃ አስተዳዳሪዎች የሚታዘዙ ወጣት ወታደሮች ግንባር ቀደም ሆነው ይዝመቱ ይላል አለው፡፡ ንጉሡም ጦርነቱን ማን ይጀምር? ሲል ጠየቀ፡፡ ነቢዩም አንተ ራስህ ጀምር አለው፡፡
\v 15 ስለዚህ ንጉሡ ብዛታቸው ሁለት መቶ ሠላሳ ሁለት ብቻ የሆነ በአውራጃ አስተዳዳሪዎች ትእዛዝ ሥር የሆኑትን ወጣት ወታደሮችን ጠራ፡፡ ቀጥሎም ጠቅላላ ብዛቱ ሰባት ሺህ የሆነ የእስራኤልን ሠራዊት ጠራ፡፡
\s5
\v 16 እነርሱም እኩለ ቀን ላይ ሄዱ፡፡ ቤን ሀዳድና የእርሱ የጦር ቃል ኪዳን ጓደኞች የሆኑ ሠላሳ ሁለቱ ነገሥታት በድንኳኖቻቸው ውስጥ በመጠጥ ሰክረው ነበሩ፡፡
\v 17 ወጣቶቹም ወታደሮች ግንባር ቀደም ሆነው ወደ ፊት አመሩ፡፡ ቤን ሀዳድ ልኮአቸው የነበሩትም ቃፊሮች አንድ የወታደር ቡድን ከሰማርያ ወጥቶ ወደዚህ እየመጣ መሆኑን ነገሩት፡፡
\s5
\v 18 ቤን ሀዳድም ቃፊሮቹን፣ አመጣጣቸው ለጦርነትም ይሁን ለሰላም ይዛቸሁ አምጡልኝ ሲል አዘዘ፡፡
\v 19 ስለዚህ በእስራኤል ሠራዊት ደጀንነት በአውራጃ አስተዳደሪዎች የሚታዘዙ ወጣቶቹ ወታደሮች ግንባር ቀደም ሆነው ወጡ፡፡
\s5
\v 20 እያንዳንዱም ውጊያ የገጠመውን ጠላቱን ገደለ፡፡ ሶርያውያንም ሸሹ፤ እስራኤላውያንም ያሳድዱአቸው ጀመር፡፡ ቤን ሀዳድ ግን በፈረሱ ላይ ተቀምጦ ከጥቂት ፈረሰኞች ጋር ሸሽቶ አመለጠ፡፡
\v 21 ንጉሥ አክዓብም ወደ ጦሩ ሜዳ ገብቶ የጠላትን ፈረሶችና ሠረገሎችን ማረከ፡፡ በሶርያውያን ላይ ታላቅ ጥፋት በማድረስ ድል አደረጋቸው፡፡
\s5
\v 22 ስለዚህ ነቢዩ ወደ ንጉሥ አክዓብ ቀርቦ፡- የሶርያ ንጉሥ በሚመጣው የጸደይ ወራት እንደገና አደጋ ስለሚጥልብህ ተመልሰህ ሂድና ሠራዊትህን በማጠናከር አደራጅ፤ ጥንቃቄ የሞላበትንም የጦርነት ስልት አዘጋጅ አለው፡፡
\v 23 አገልጋዮቹም ንጉሥ ቤን ሀዳድን እንዲህ አሉት፡- የእስራኤል አማልክት የተራራ አማልክት ናቸው፡፡ እስራኤላውያን እኛን ማሸነፍ የቻሉት ስለዚህ ነው፡፡ በሜዳማ ስፍራዎች ጦርነት ብንገጥማቸው ግን እናሸንፋለን፡፡
\s5
\v 24 ስለዚህ አሁን ሠላሳ ሁለቱን ነገሥታት ከጦር አዛዥነታቸው ሽረህ በእነርሱ ቦታ ሌሎችን የጦር አዛዦች ሹም፡፡
\v 25 ከዚህ በፊት የተደመሰሰውን የሚያህል ብዙ ሠራዊትና በቀድሞዎቹ ልክ ፈረሶችንና ሠረገሎችን አደራጅ፤ ከዚያ በኋላ እስራኤላውያንን በሜዳ ተዋግተን ድል እንነሣቸዋለን፡፡ ስለዚህ ቤን ሀዳድም በእነርሱ ምክር ተስማምቶ ለመፈጸም ወሰነ፡፡
\s5
\v 26 ከዚያም በተከታዩ የጸደይ ወቅት ሠራዊቱን በአንድነት ጠርቶ እስራኤልን ለመዋጋት ወደ አፌቅ ከተማ ገሠገሠ፡፡
\v 27 እስራኤላውያን ተጠርተው ከሚያስፈልጋቸው ስንቅና ትጥቅ ጋር ለጦርነት ተዘጋጁ፤ እነርሱም ወደ ጦርነቱ በመዝመት በሁለት ቡድን ተከፍለው ከሶርያውያን ፊት ለፊት ባለው ቦታ ሰፈሩ፡፡ የእስራኤል ወታደሮች ቁጥር አገሩን ካጥለቀለቀው ከሶርያውያን ሠራዊት ብዛት ጋር ሲነጻጻር ከሁለት የተከፈለሉ የጥቂት ፍየሎች መንጋዎች ይመስሉ ነበር፡፡
\s5
\v 28 አንድ የእግዚአብሔር ነቢይ ወደ ንጉሥ አክዓብ ቀርቦ እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ይህ ነው፤ ሶርያውያን፡- እግዚአብሔር የኮረብቶች አምላክ እንጂ የሜዳዎች አምላክ አይደለም ብለዋል፤ ከዚህም የተነሣ እኔ እጅግ ብዙ የሆነውን ሠaርዊታቸውን በእጅህ አሳልፌ እሰጣለሁ፡፡ አንተና ሕዝብህም እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ አለው፡፡
\s5
\v 29 ስለዚህ ሶርያውያንና እስራኤላውያን ፊት ለፊት ተፋጠው በየጦር ሰፈራቸው እስከ ሰባት ቀን ቆዩ፤ በሰባተኛውም ቀን ጦርነት ጀምረው በዚያኑ ቀን እስራኤላውያን አንድ መቶ ሺህ የሶርያውያንን እግረኛ ጦር ወታደሮችን ገደሉ፡፡
\v 30 ከሞት የተረፉትም ሶርያውያን ሸሽተው ወደ አፌቅ ከተማ ገቡ፤ በዚያም ቁጥራቸው ሃያ ሰባት ሺህ በሚሆኑት ወታደሮች ላይ የከተማው ቅጥር ተንዶባቸው አለቁ፡፡ ቤን ሀዳድም አምልጦ ወደ ከተማይቱ ገብቶ ከአንድ ቤት በስተ ኋላ በኩል ባለው ክፍል ውስጥ ተደበቀ፡፡
\s5
\v 31 የቤን ሀዳድ አገልጋዮች ወደ እርሱ ቀርበው፣ የእስራኤል ነገሥታት ምሕረት አድራጊዎች መሆናቸውን ሰምተናል፤ ስለዚህ በወገባችን ማቅ ታጥቀን፣ በራሳችንም ገመድ ጠምጥመን ወደ እስራኤል ንጉሥ ሄደን ምሕረት እንድንጠይቀው ፍቀድልን፤ ምናልባትም ሕይወትህን ያተርፍ ይሆናል አሉት፡፡
\v 32 ከዚህም በኋላ እነርሱ በወገባቸው ማቅ ታጥቀው በራሳቸውም ገመድ ጠምጥመው ወደ ንጉሥ አክዓብ በመሄድ አገልጋይህ ቤን ሀዳድ ምሕረት አድርገህ ሕይወቱን እንድታተርፍለት ይማጠንሃል አሉት፡፡ አክዓብም እርሱ እስከ አሁን በሕይወት አለ ማለት ነውን? ከሆነስ መልካም ነው፤ እንግዲህ እርሱ ለእኔ እንደ ወንድም ነው ሲል መለሰላቸው፡፡
\s5
\v 33 የቤን ሀዳድ አገልጋዮችም የምሕረት መልእክት ይጠባበቄ ስለ ነበር አክዓብ ወንድሜ ሲል በሰሙ ጊዜ ወዲያውኑ ቀበል አድገርው አንተ እንዳልከው ቤን ሀዳድ በእርግጥ ወንድምህ ነው አሉት፡፡ አክዓብም ወደ እኔ አምጡት! አላቸው፡፡ ቤን ሀዳድም በመጣ ጊዜ አክዓብ ወደ ሠረገላው ገብቶ እንዲቀመጥ ቤን ሀዳድን ጋበዘው፡፡
\v 34 ቤን ሀዳድም አክዓብን አባቴ ከአባትህ የወሰዳቸውን ከተሞች እመልስልሃለሁ፤ አባቴ በሰማርያ እንዳደረገው ሁሉ አንተም በደማስቆ ለራስህ የንግድ ማእከል ልታቋቁም ትችላለህ አለው፡፡ አክዓብም እንግዲያውስ በዚህ ስምምነት መሠረት እኔም በነጻ እለቅሃለሁ ሲል መለሰለት፡፡ አክዓብም በዚህ ዓይነት ከእርሱ ጋር የውል ስምምነት አድርጎ በነጻ እንዲሄድ ፈቀደለት፡፡
\s5
\v 35 የነቢያት ወገን የሆነ አንድ ነቢይ በእግዚአብሔር ታዞ የእርሱ ጓደኛ የሆነውን ሌላ ነቢይ ምታኝ አለው፡፡ ነቢዩ ግን እርሱን ለመምታት እምቢ አለ፡፡
\v 36 ስለዚህም ያ ነቢይ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ መፈጸም እምቢ ስላልክ ከእኔ ተለይተህ እንደ ሄድክ ወዲያውኑ አንበሳ ይገድልሃል አለው፤ ከእርሱ ተለይቶ እንደ ሄደ አንበሳ በድንገት ወደ እርሱ መጥቶ ገደለው፡፡
\s5
\v 37 ከዚህም በኋላ ነቢዩ ወደ ሌላ ሰው ሄዶ ምታኝ አለው፣ ያም ሰው መትቶ አቆሰለው፤
\v 38 ነቢዩ ማንነቱ እንዳይታወቅ ፊቱን በጨርቅ ሸፈነ፤ ሄዶም በዚያ በኩል የሚያልፈውን የእስራኤል ንጉሥ ለመጠበቅ በመንገድ ዳር ቆመ፡፡
\s5
\v 39 ንጉሡም በአጠገቡ ሲያልፍ ነቢዩ ተጣርቶ እንዲህ ሲል ጮኸ፡- ንጉሥ ሆይ እኔ በጦርነት ውስጥ በውጊያ ላይ ነበርኩ፤ በዚያን ጊዜም ከወታደሮቹ አንዱ ከጠላት ወገን አንድን ሰው ማርኮ በማምጣት ይህን ሰው ጠብቅ፣ ቢያመልጥ ግን በእርሱ ፈንታ አንተ ትገደላለህ ወይም ሠላሳ አንድ መክሊት የሚመዝን ብር መቀጫ ትከፍላለህ አለኝ፡፡
\v 40 ነገር ግን እኔ ሥራ በዝቶብኝ ወዲያ ወዲህ ስል ሰውየው አምልጦ ሄደ፡፡ ንጉሡም በራስህ ላይ ስለ ፈረድህ መቀጣት ይገባሃል አለው፡፡
\s5
\v 41 ነቢዩ ፊቱ የተሸፈነበትን ጨርቅ ፈጥኖ አወለቀ፤ ንጉሡም ይህ ሰው ከነቢያት ወገን አንዱ መሆኑን ወዲያውኑ አወቀ፡፡
\v 42 ነቢዩም ንጉሡን እንዲህ አለው፡- እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ይህ ነው፤ እኔ ይገደል ብዬ የፈረድኩበት ሰው እንዲያመልጥ ስለ ፈቀድህ በእርሱ ፈንታ አንተ በሞት ትቀጣለህ፤ የዚያ ሰው ሠራዊት አምልጦ እንዲሄድ ስላደረገ ሠራዊትህም ይደመሰሳል፡፡
\v 43 ስለዚህ ንጉሡ እያዘነና እየተበሳጨ ወደ ቤቱ ወደ ሰማርያ ተመልሶ ሄደ፡፡
\s5
\c 21
\p
\v 1 ከጥቂት ጊዜ በኋላ ናቡቴ ተብሎ የሚጠራ ሰው በኢይዝራኤል በሚገኘው በንጉሥ አክዓብ ቤተ መንግሥት አጠገብ የራሱ ርስት የሆነ አንድ የወይን ተክል ቦታ ነበረው፡፡
\v 2 አንድ ቀን አክዓብ ናቡቴን የወይን ተክል ቦታህን ስጠኝ፤ በቤተ መንግሥቴ አጠገብ ስለ ሆነ የአትክልት ቦታ ላደርገው እፈልጋለሁ፤ በምትኩ ከእርሱ የተሻለ የወይን ተክል ቦታ እሰጥሃለሁ፤ ልትሸጠው ብትፈልግም የተሻለ ዋጋ እከፍልሃለሁ አለው፡፡
\s5
\v 3 ናቡቴም ይህንን የወይን ተክል ቦታ የወረስኩት ከቅድም አያቶቼ ነው፤ ለአንተ ከመስጠትስ እግዚአብሔር ይጠብቀኝ! ሲል መለሰለት፡፡
\v 4 አክዓብ ኢይዝራኤላዊው ናቡቴ ከአባቶቼ የወረስኩትን ለአንተ አልሰጥህም ስላለው በንዴት እየተበሳጨ ወደ ቤቱ ገባ፤ ፊቱንም ወደ ግድግዳ አዙሮ በአልጋው ላይ ተጋደመ፤ ምግብ መብላትም አልፈቀደም፡፡
\s5
\v 5 ሚስቱም ኤልዛቤል ወደ እርሱ ቀርባ እንደዚህ ያበሳጨህ ነገር ምንድን ነው? ስለምንስ ምግብ አትበላም? ስትል ጠየቀችው፡፡
\v 6 እርሱም እኔን ያበሳጨኝ ከናቡቴ ያገኘሁት መልስ ነው፤ ይኸውም የእርሱን የወይን ተክል ቦታ እንድገዛ ወይም ከፈለገ ልዋጩን እንድሰጠው ብጠይቀው የወይን ተክል ቦታውን አልሰጥህ ብሎ አናደደኝ ሲል መለሰላት፡፡
\v 7 ኤልዛቤልም እንግዲህ አንተ የእስራኤል ንጉሥ ሆነህ ሳለህ እንደዚህ መሆን ይገባሃልን? ይልቅስ ተነሥ ተደሰት፤ እህል ውሃም ቅመስ፡፡ እኔ የናቡቴን የወይን ተክል ቦታ እንድታገኝ አደርጋለሁ አለችው፡፡
\s5
\v 8 ስለዚህ እርስዋ ደብዳቤ ጽፋና በአክዓብ ስም ፈርማ የእርሱን ማኅተም አተመችበት፤ ደብዳቤውንም ናቡቴ ወደሚኖርባት ወደ ኢይዝራኤል ባለሥልጣኖችና ሽማግሌዎች ላከች፡፡
\v 9 ደብዳቤውም እንዲህ የሚል ነበር፡- የአንድ ቀን ጾም አውጁ፤ ሕዝቡንም በአንድነት ሰብስቡ፤ ለናቡቴም የክብር ቦታ ስጡት፤
\v 10 እግዚአብሔርንና ንጉሡን ሰድቦአል ብለው የሚናገሩ ሁለት የሐሰት ምስክሮችንም አቅርቡ፤ ከዚያ በኋለ ናቡቴን ከከተማው ውጪ አወጥታችሁ በድንጋይ ተወግሮ ይሙት፡፡
\s5
\v 11 ስለዚህ የኢይዝራኤል ባለሥልጣኖችና ሽማግሌዎችም በደብዳቤው እንደተገለጸው ኤልዛቤል ያዘዘቻቸውን አደረጉ፡፡
\v 12 የአንድ ቀን ጾም አወጁ፤ ሕዝቡንም በአንድነት ሰበሰቡ፤ ለናቡቴም የክብር ቦታ ሰጡት፡፡
\v 13 ሁለቱም የሐሰት ምስክሮች ተነሥተው ናቡቴ እግዚአብሔርንና ንጉሡን ሰድቦአል ብለው በሕዝቡ ፊት በሐሰት መሰከሩበት፤ ስለዚህም ከከተማይቱ ውጪ በመውሰድ በድንጋይ ወግረው ገደሉት፡፡
\v 14 ናቡቴ ተወግሮ ተገድሎአል የሚል መልእክትም ወደ ኤልዛቤል ላኩ፡፡
\s5
\v 15 ኤልዛቤልም መልእክቱን እንደ ተቀበለች ወዲያውኑ አክዓብን ናቡቴ ሞቶአል፤ አሁን ተነሥተህ ሂድና ለአንተ ለመሸጥ እምቢ ያለውን የወይን ቦታ ርስት አድርገህ ውሰድ አለችው፡፡
\v 16 አክዓብም የናቡቴን የወይን ተክል ቦታ ለመውረስ ወዲያውኑ ተነሥቶ ሄደ፡፡
\s5
\v 17 ከዚያም የእግዚአብሔር ቃል ወደ ቴስቢያዊው ወደ ኤልያስ እንዲህ ሲል መጣ፡፡
\v 18 ተነሥተህ ሂድና የእስራኤልን ንጉሥ አከዓብን በሰማርያ አግኘው፤ እርሱ የናቡቴን የወይን ተክል ቦታ ለመውረስ ሄዶአል፣ በዚያው ታገኘዋለህ፤
\s5
\v 19 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ብለህ መናገር አለብህ፣ ናቡቴን ገድለህ ሀብቱንም ወሰድክበትን? ከዚያም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ የናቡቴን ደም ውሾች በላሱበት ስፍራ የአንተንም ደም እንደዚሁ ይልሱታል።
\v 20 አክዓብ ኤልያስን ባየው ጊዜ ጠላቴ ሆይ አገኘኸኝን? አለው፡፡ እርሱም እንዲህ አለ፣ አዎን አግኝቼሃለሁ፤ በእግዚአብሔር ላይ ክፉ ለማድረግ ራስህን ሸጠከውን? አለው፡፡
\s5
\v 21 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይልሃል፣ እነሆ በአንተ ላይ መቅሠፍትን አመጣብሃለሁ፤ አንተን ከፊቴ አስወግዳለሁ፤ ከቤተ ሰብህም ውስጥ ወንድ የሆነውን ሁሉ ባሪያ ሆነ ነጻ ሰው አጠፋለሁ፡፡
\v 22 እስራኤልን ወደ ኃጢአት በመምራታችሁ ቁጣዬን ስለ አነሣሣህ ቤተ ሰብህን እንደ ናባጥ ልጅ እንደ ንጉሥ ኢዮርብዓም ቤተ ሰብና እንደ አኪያ ልጅ እንደ ንጉሥ ባኦስ ቤተ ሰብ ለጥፋት የተጋለጠ ይሆናል፡፡
\s5
\v 23 ስለ ኤልዛቤልም እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፡- በኢይዝራኤል ከተማ ውስጥ ሬሳዋን ውሾች ይበሉታል፡፡
\v 24 ከአክዓብም የሆነውን ሁሉ በከተማው ውስጥ የሚሞተውን ማንኛውንም ሰው ውሾች ይበሉታል፤ በገጠርም በየሜዳው የሚሞተውን ሁሉ የሰማይ አሞራዎች ይበሉታል፡፡
\s5
\v 25 በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር በማድረግ ለኤልዛቤል ኃጢአት ራሱን አሳልፎ የሸጠ አክዓብን የሚመሰል ማንም አልነበረም፡፡ ይህን ሁሉ ያደረገው ሚስቱ ኤልዛቤል ወደ ክፋት ስለ መራችው ነው፡፡
\v 26 አክዓብ ከፈጸመው አሳፋሪ በደል ሁሉ ዋናው እግዚአብሔር ከእስራኤላውያን ፊት ነቃቅሎ ያጠፋቸውን የአሞራውያንን ጣዖት ማምለኩ ነበር፡፡
\s5
\v 27 አከዓብም ይህንን በሰማ ጊዜ፡- ልብሱን ቀዶ ማቅ ለበሰ፤ ማቁን እንደ ለበሰ ይተኛ ነበር፤ ሲሄድም ከጭንቀቱ ብዛት የተነሣ አዝኖ ነበር፡፡
\v 28 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ ቴስቢያዊው ወደ ኤልያስ እንዲህ ሲል መጣ፡-
\v 29 አክዓብ በእኔ ፊት ራሱን እንዴት እንዳዋረደ ተመልክተሃልን? እግዚአብሔርም በፊቴ ራሱን ስላዋረደ በሕይወቱ ዘመን መቅሠፍትን በአክዓብ ቤተ ሰብ ላይ አላመጣበትም፤ የማመጣውም በልጁ ዘመን ይሆናል፡፡
\s5
\c 22
\p
\v 1 በእስራኤልና በሶሪያ መካከል ያለ ጦርነት ሦስት ዓመት አለፈ፡፡
\v 2 ይሁን እንጂ በሦስተኛው ዓመት የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ የእስራኤልን ንጉሥ አክዓብን ለመጎብኘት ሄደ፡፡
\s5
\v 3 የእስራኤል ንጉሥ ለአገልጋዮቹ እንዲህ አለ፡- በገለዓድ የምትገኘውን ራሞት ከሶርያ ንጉሥ ለማስመለስ ምንም ዓይነት እርምጃ ያልወሰድነው ስለምንድን ነው? ራሞት እኮ የእኛ ይዞታ ናት አላቸው፡፡
\v 4 ስለዚህ እርሱም ኢዮሣፍጥን ለጦርነት ወደ ራሞት ከእኔ ጋር ትሄዳለህን? ሲል ጠየቀው፡፡ ኢዮሣፍጥም እኔ እንደ አንተ ነኝ፤ ሕዝቤም እንደ አንተ ሕዝብ ነው፤ ፈረሶቼም እንደ አንተ ፈረሶች ናቸው አለው፡፡
\s5
\v 5 ኢዮሳፍጥም፣ ነገር ግን መጀመሪያ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ጠይቅ ሲል መለሰለት፡፡
\v 6 ከዚያም አክዓብ አራት መቶ የሚሆኑትን ነቢያቱን ጠርቶ ወደ ራሞት ለጦርነት ልውጣ ወይስ ልቅር? ሲል ጠየቃቸው፡፡ እነርሱም ሄደህ ተዋጋ፤ እግዚአብሔርም በንጉሡ እጅ አሳልፎ ይሰጣል ሲሉ መለሱለት፡፡
\s5
\v 7 ኢዮሣፍጥ ግን የእግዚአብሔርን ፈቃድ የምንጠይቅበት ሌላ የእግዚአብሔር ነቢይ የለምን? ሲል ጠየቀ፡፡
\v 8 አክዓብም የይምላ ልጅ የሆነ ሚክያስ የተባለ ሌላ ነቢይ አለ፤ ነገር ግን እኔ እርሱን አልወደውም፤ እርሱ ምን ጊዜም ስለ እኔ ክፉ እንጂ መልካም የትንቢት ቃል አይናገርም ሲል መለሰለት፡፡ ኢዮሣፍጥም ይህን ማለት አይገባህም፤ አለው፡፡
\v 9 ከዚያም አክዓብ ከቤተ መንግሥቱ አገልጋዮች አንዱን ጠርቶ የይምላ ልጅ ሚክያስን ፈልገህ በማግኘት በፍጥነት እንዲመጣ አድርግ ሲል አዘዘው፡፡
\s5
\v 10 የእስራኤል ንጉሥ አክዓብና የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ ሁለቱ ነገሥታት ልብሰ መንግሥታቸውን ለብሰው በሰማርያ የቅጥር በር አጠገብ በሚገኘው ሜዳ በየዙፋናቸው ላይ ተቀምጠው ነበር፡፡ ነቢያቱም ሁሉ በነገሥታቱ ፊት ቀርበው ትንቢት ይናገሩ ነበር፡፡
\v 11 ከእነርሱም አንዱ ሴዴቅያስ ተብሎ የሚ. ጠራው የክንዓና ልጅ ከብረት የተሠሩ ቀንዶች ይዞ አክዓብን እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ከብረት በተሠሩ በእነዚህ ቀንዶች ሶርያውያንን ወግተህ ፍጹም የሆነ ድልን ትቀዳጃለህ አለው፡፡
\v 12 ሌሎቹም ነቢያት ይህንኑ ቃል በመደገፍ በራሞት ላይ ዝመት፣ ታሸንፋለህ፤ እግዚአብሔርም ድልን ይሰጥሃል አሉት፡፡
\s5
\v 13 ሚክያስን ለመጥራት ሄዶ የነበረው መልእክተኛ በዚሁ ጊዜ ሚክያስን ሌሎቹ ነቢያት በሙሉ ንጉሥ አክዓብ ድል የሚያደርግ መሆኑን የሚያረጋግጥ የትንቢት ቃል ተናግረዋል፤ ስለዚህ አንተም እንደእነርሱ ብታደርግ ይሻልሃል አለው፡፡
\v 14 ሚክያስ ግን እግዚአብሔር የሚገልጥልኝን ቃል ብቻ እንደምናገር በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ! ሲል መለሰለት፡፡
\v 15 ሚክያስም ወደ ንጉሥ አክዓብ ፊት በቀረበ ጊዜ ንጉሡ፣ ሚክያስ ሆይ፣ ንጉሥ ኢዮሣፍጥና እኔ ወደ ራሞት ሄደን ጦርነት እንክፈት ወይስ እንተው? ሲል ጠየቀው፡፡ ሚክያስም ዘምተህ አደጋ ጣልባት ታሸንፋለህ፤ እግዚአብሔርም በእጅህ አሳልፎ ይሰጥሃል፤ ሲል መለሰለት፡፡
\s5
\v 16 ከዚያም አክዓብ፣ አንተ ግን በእግዚአብሔር ስም የትንቢትን ቃል ስትነግረኝ እውነቱን መግለጥ እንደሚገባህ ስንት ጊዜ እነግርሃለሁ አለው፡፡
\v 17 ሚክያስም መላው የእስራኤል ሠራዊት ጠባቂ እንደሌላቸው በጎች በኮረብታዎች ላይ ተበታትነው አያለሁ፤ እግዚአብሔርም፣ እነዚህ ሰዎች መሪ የላቸውም፤ ስለዚህ ወደየቤታቸው በሰላም ይመለሱ ብሎአል ሲል መለሰለት፡፡
\s5
\v 18 አክዓብም ኢዮሣፍጥን እርሱ ሁልጊዜ ስለ እኔ ክፉ እንጂ መልካም የትንቢት ቃል አይናገርም ብዬህ አልነበረምን? አለው፡፡
\v 19 ሚክያስም ንግግሩን በመቀጠል እንዲህ አለ፤ እንግዲህ እግዚአብሔር የሚለውን ስማ፤ እግዚአብሔር በሰማይ ባለው ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ መላእክቱም ሁሉ በቀኝና በግራው ቆመው አየሁ፡፡
\v 20 እግዚአብሔርም አክዓብን ወደ ራሞት ሄዶ በዚያ እንዲገደል ሊያሳስተው የሚችል ማን ነው? አለ፤ ከመላእክቱም መካከል አንዱ ሌላ ነገር ሌላውም ሌላ ነገር አለ፡፡
\s5
\v 21 በመጨረሻ ግን አንድ መንፈስ ወደ እግዚአብሔር ፊት ቀርቦ እኔ ላሳስተው እችላለሁ አለ፡፡
\v 22 እግዚአብሔርም እንዴት አድርገህ ልታሳስተው ትችላለህ? አለው፡፡ መንፈሱም፣ ሄጄ የአክዓብ ነቢያት ሁሉ ሐሰት እንዲናገሩ አደርጋለሁ ሲል መለሰለት፤ እግዚአብሔርም እንግዲያውስ ሄደህ አሳስተው፤ ይከናወንልሃል አለው፡፡
\v 23 ሚክያስም እነሆ እግዚአብሔር እነዚህን የአንተን ነቢያት የሐሰት ቃለ እንዲነግሩህ ያደረገው እግዚአብሔር ነው፡፡ ስለዚህ በአንተ ላይ ጥፋት ሊያመጣብህ እግዚአብሔር ራሱ ወስኖአል! ሲል ንግግሩን ደመደመ፡፡
\s5
\v 24 ከዚያም የክንዓና ልጅ ሴዴቅያስ ወደ ሚክያስ ቀርቦ በጥፊ መታውና ከመቼ ወዲህ ነው የእግዚአብሔር መንፈስ ከእኔ አልፎ አንተን ያነጋገረህ? አለው፡፡
\v 25 ሚክያስም በውስጥ ወዳለው ክፍል ሄደህ በምትሸሽግበት ጊዜ ታውቀዋለህ ሲል መለሰለት፡፡
\s5
\v 26 በዚህን ጊዜ ንጉሥ አክዓብ ከጦር መኮንኖቹ አንዱን ሚክያስን ያዘው፤ ወደ ከተማይቱ ገዢ ወደ አሞንና ወደ ልዑል ኢዮአስ ውሰደው፤
\v 27 እኔም በደህና እስክመለስ ድረስ እስር ቤት አስገብተው ደረቅ እንጀራና ውሃ ብቻ እየሰጡት እንዲቆይ ያድርጉ ሲል አዘዘው፡፡
\v 28 ሚክያስም አንተ በደህና ከተመለስክማ እግዚአብሔር በእኔ አማካይነት አልተናገረም ማለት ነው! አለው፤ ቀጥሎም ድምፁን ከፍ በማድረግ በዚህ የምትገኙ ሕዝቦች ሁሉ እኔ የተናገርኩትን ሁሉ ልብ ብላችሁ አድምጡ አለ፡፡
\s5
\v 29 ስለዚህ የእስራኤል ንጉሥ አክዓብና የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ ወደ ገለዓድ ምድር ወደምትገኘው ራሞት ከተማ ለመዋጋት ሄዱ፡፡
\v 30 አክዓብም ኢዮሣፍጥን ወደ ጦርነት ለመሄድ ስንነሣ እኔ ሌላ ሰው መስዬ ለመታየት ተራ ልብስ እለብሳለሁ፣ አንተ ግን ልብሰ መንግሥትህን ልበስ አለው፡፡ ስለዚህ የእስራኤል ንጉሥ አክዓብ ሌላ ልብስ ለብሶ ማንነቱን በመሰወር ዘመተ፡፡
\s5
\v 31 የሶርያ ንጉሥም በንጉሡ ላይ እንጂ በሌላ በማንም ላይ አደጋ አትጣሉ ብሎ ለሠላሳ ሁለቱ የሠረገላ ጦር አዛዦች ትአዛዝ አስተላለፈ፡፡
\v 32 ስለዚህ ንጉሥ ኢዮሣፍጥን ባዩ ጊዜ በርግጥ እርሱ የእስራኤል ንጉሥ ነው ብለው በእርሱ ላይ አደጋ ሊጥሉበት ከበቡት፤ ኢዮሣፍጥም በጮኸ ጊዜ፣
\v 33 እርሱ የእስራኤል ንጉሥ አለመሆኑን በማረጋገጥ በእርሱ ላይ አደጋ ከመጣል ተመለሱ፡፡
\s5
\v 34 ነገር ግን በአጋጣሚ አንድ የሶርያ ወታደር ፍላጻ በማስፈንጠር ንጉሥ አክዓብን በጦር ልብሱ መገናኛ ላይ ወጋው፤ ንጉሥ አክዓብም የሠረገላ ነጂውን ክፉኛ ቆስያለሁ፤ ስለዚህ ሠረገላውን መልሰህ ከጦር ሜዳው ውጣ! ሲል አዘዘው፡፡
\s5
\v 35 ጦርነቱም በተፋፋመ ጊዜ ንጉሥ አክዓብ በሶርያውያን ፊት ለፊት በሠረገላው ላይ ተደግፎ ነበር፤ በዚያውም ቀን ምሽት ሞተ፡፡
\v 36 ፀሐይ በመጥለቅ ላይ እያለች፣ እያንዳንዱ ሰው ወደየአገሩና ወደየከተማው ይመለስ የሚል ትእዛዝ ከእስራኤል ጦር አዛዦች ተነገረ፡፡
\s5
\v 37 ስለዚህ ንጉሥ አክዓብ ሞተ፤ ሬሳውም ወደ ሰማርያ ተወስዶ ተቀበረ፡፡
\v 38 ሠረገላውም በሰማርያ ኩሬ ታጠበ፤ እግዚአብሔርም አስቀድሞ በተናገረው መሠረት ደሙን ውሾች ላሱት፤ በዚያም ኩሬ ሴተኛ አዳሪዎች ታጠቡበት፡፡
\s5
\v 39 ንጉሥ አክዓብ ያደረጋቸው ነገሮች ሁሉ ምን እንደ ሠራና የሠራቸውም ከተሞች ሁኔታ ጭምር በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ ተመዝግቦ ይገኝ የለምን?
\v 40 ንጉሥ አክዓብም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በእርሱም ፈንታ ልጁ አካዝያስ ተተክቶ ነገሠ፡፡
\s5
\v 41 የእስራኤል ንጉሥ አክዓብ በነገሠ በአራተኛው ዓመት የአሳ ልጅ ኢዮሣፍጥ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ፡፡
\v 42 ኢዮሣፍጥም በሠላሳ አምስት ዓመት ዕድሜው ነግሦ ሃያ አምስት ዓመት በኢየሩሳሌም ገዛ፡፡ እናቱም ዐዙባ ተብላ የምትጠራ የሺልሒ ልጅ ነበረች፡፡
\s5
\v 43 ኢዮሣፍጥ ከእርሱ በፊት እንደ ነበረው እንደ አባቱ አሳ በእግዚአብሔር ፊት መልካም የሆነውን ነገር ሁሉ አደረገ፡፡ ሆኖም ግን የአሕዛብ ማምለኪያ ስፍራዎችን አልደመሰሰም ነበር፤ ስለዚህም ሕዝቡ በእነዚያ ቦታዎች መሥዋዕት ማቅረብና ዕጣን የማጠን ተግባሩን አልተወም ነበር፡፡
\v 44 ኢዮሣፍጥም ከእስራኤል ንጉሥ ጋር ሰላም መሠረተ፡፡
\s5
\v 45 ኢዮሣፍጥ ያደረጋቸው ነገሮች፣ በጦርነት ላይ ያሳየው ጀግንነትም ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተመዝግቦ ይገኝ የለምን?
\v 46 ከአባቱ ከአሳ ዘመነ መንግሥት ጀምሮ የተረፉትንና በአሕዛብ የማምለኪያ ቦታዎች የጣዖት አመንዝራዎችን ሁሉ አስወገደ፡፡
\v 47 በዚያን ዘመን የኤዶም ምድር የራስዋ ንጉሥ አልነበራትም፤ ከዚህም የተነሣ በይሁዳ ንጉሥ በሚሾመው እንደራሴ ትገዛ ነበር፡፡
\s5
\v 48 ንጉሥ ኢዮሣፍጥ ውቅያኖስን አቋርጠው ከኦፊር ወርቅ የሚያመጡለትን የተርሴስ ዓይነት መርከቦች አሠርቶ ነበር፤ ነገር ግን መርከቦቹ በኤጽዮንጋብር ወደብ ላይ ስለ ተሰበሩ መጓዝ አልቻሉም፡፡
\v 49 ከዚያ በኋላ የእስራኤል ንጉሥ አካዝያስ መርከበኞቹ ከኢዮሣፍጥ መርከበኛች ጋር በኅብረት እንዲሠሩ የውል ድርድር አቅርቦ ነበር፤ ኢዮሣፍጥ ግን አሳቡን አልተቀበለም፡፡
\v 50 ንጉሥ ኡዮሣፍጥ ሞተ፤ በዳዊት ከተማ በሚገኘውም በነገሥታት መካነ መቃብር ተቀበረ፤ በእርሱም ፈንታ ተተክቶ ልጁ አዮራም ነገሠ፡፡
\s5
\v 51 የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ በነገሠ በዐሥራ ሰባተኛው ዓመት የአክዓብ ልጅ አካዝያስ በሰማርያ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ፡፡
\v 52 እርሱም የአባቱን የአክዓብን፣ የእናቱን የኤልዛቤልንና የእስራኤልን ሕዝብ ወደ ኃጢአት የመራውን የንጉሥ ኢዮርብዓምን መጥፎ አርአያነት በመከተል በእግዚአብሔር ፊት በደል ሠራ፡፡
\v 53 ከእርሱም በፊት እንደ ነበረው እንደ አባቱ ባዓል ተብሎ ለሚጠራው ባዕድ አምላክ በመስገድና በማገልገል የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን ቁጣ አነሣሣ፡፡

1786
13-1CH.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,1786 @@
\id 1CH
\ide UTF-8
\h 1ኛ ዜና
\toc1 1ኛ ዜና
\toc2 1ኛ ዜና
\toc3 1ch
\mt 1ኛ ዜና
\s5
\c 1
\p
\v 1 አዳም፣ ሴት፣ ሄኖስ፣
\v 2 ቃይናን፣ መላልኤል፣ ያሬድ፣
\v 3 ሄኖክ፣ ማቱሳላ፣ ላሜሕ፣ኖኅ።
\v 4 የኖኅ ወንዶች ልጆች፤ ሴም፣ካምናያፌት።
\s5
\v 5 የያፌት ወንዶች ልጆች፤ ጋሜር፣ማጎግ፣ማዴ፣ያዋን፣ቶቤል፣ሞሳሕ፣ቴራስ።
\v 6 የጋሜር ወንዶች ልጆች፤ አስከናዝ፣ሪፋት፣ቴርጋማ።
\v 7 የያዋን ወንዶች ልጆች፤ ኤሊሳ፣ተርሴስ፣ኪቲም፣ሪድኢ።
\s5
\v 8 የካም ወንዶች ልጆች፤ ኪሽ፣ ምፅራይም፣ ፋጥናከነዓን።
\v 9 የኩሽ ወንዶች ልጆች፤ ሳባ፣ ኤውላጥ፣ ሰብታ፣ ራዕማናሰብቃታ። ያራዕማ ወንዶች ልጆች፤ ሳባናድዳን ነበሩ።
\v 10 ኩሽ ናምሩድን ወለደ፤ እርሱም በምድር ላይ የመጀመሪያው ኅያል ጦረኛ ሆነ።
\s5
\v 11 ምፅራይም የሉዲማውያን፣ የዐናማውያን፣ የላህባማውያን፣ የነፍተሂማውያን፣
\v 12 የፈትሩሲማውያን፣ የፍልስጥኤማውያን ቅድመ አባቶች የሆኑት የከስሉሂማውያንና የከፍቶሪማውያን ነገዶች አባት ነው።
\s5
\v 13 ከነዓን የበኩር ልጁ የሆነው የሶዶን እንዲሁም የከጢያውያን፣
\v 14 የኢያቡሳውያን፣
\v 15 የኤዊውያን፣ የዐርካውያን፣
\v 16 የሲኒውያን፣ የአራዴዎውያን፣ የሰማርያውያን፣ የአማቲያውያን አባት ነው።
\s5
\v 17 የሴም ወንዶች ልጆች፤ ኤላም፣ አሦር፣ አርፋክስድ፣ ሉድ፣ አራም። የአራም ወንዶች ልጆች፤ ዑፅ፣ ሁል፣ ጌቴር፣ ሞሳሕ።
\v 18 አርፋክስድ ሳላን ወለደ።
\v 19 ዔርቦ ወንዶች ልጆች ወለደ፤ በዘመኑ ምድር ስለተከፈለች፣ የአንደኛው ስም ፋሌቅ ተብሎ ተጠራ፣
\s5
\v 20 ዮቅጣንም፡ አልሞዳድን፣ ሣሌፍን፣ ሐስረሞትን፣ ያራሕን፣
\v 21 ሀዶራምን፣አውዛልን፣ደቅላን፣
\v 22 ዖባልን፣ አቢማኤልን፣ ሳባን፣
\v 23 ኦፋርን፣ ኤውላጥን፣ ዮባብን ወለደ፤ እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ወንዶች ልጆች ናቸው።
\s5
\v 24 ሴም፣ አርፋክስድ፣ ሳለ፣
\v 25 ዔቦር፣ ፋሌቅ፣ ራግው፣
\v 26 ሴሮህ፣ ናኮር፣ ታራ፣
\v 27 እንዲሁም በኋላ አብርሃም የተባለ አብራም።
\s5
\v 28 የአብርሃም ወንዶች ልጆች፤ይስሐቅና እስማኤልሲሆኑ።
\v 29 የእነዚህ ዘሮች የሚከተሉት ናቸው፤ የእስማኤል በኩር ልጅ ነባዮት፣ ቄዳር፣ ነብ፣ ዳኤል፣ መብሳም፣
\v 30 ማስማዕ፣ ዱማ፣ ማሣ፣ ኩዳን፣ ቴማን፣
\v 31 ኢጡር፣ ናፌስ፣ ቄድማ፣ እነዚህ የእስማኤል ወንዶች ልጆች ናቸው።
\s5
\v 32 የአብርሃም ቁባት ኬጡራ የወለደቻቸው ወንዶች ልጆች ዘምራን፣ ዮቅሳን፣ ሜዳን፣ ምድያም፣ የስቦቅና፣ ስዌሕ ናቸው። የዮቅሳን ወንዶች ልጆች፤ ሳባ፣ ድዳን፣
\v 33 የምድያም ወንዶች ልጆች፤ ጌፈር፣ ዔፌር፣ ሄኖኅ፣ አቢዳዕ፣ ኤልዳዓ፣ እነዚህ ሁሉ የኬጡራ ዘሮች ናቸው።
\s5
\v 34 አብርሃም ይስሐቅን ወለደ። የይስሐቅ ወንዶች ልጆች፤ ዔሳው፣ እስራኤል።
\v 35 የዔሳው ወንዶች ልጆች፤ ኤልፋዝ፣ ራጉኤል፣ የዑስ፣ የዕላም፣ ቆሬ።
\v 36 የኤልፋዝ ወንዶች ልጆች ቴማር፣ ኦማር፣ ሰፎ፣ ጎቶም፣ ቄኔዝ፣ ቲምናዕ፣ አማሌቅ።
\v 37 የራጉኤል ወንዶች ልጆች፤ ናሖት፣ ዛራ፣ ሣማ፣ ሚዛህ።
\s5
\v 38 የሴይር ወንዶች ልጆች፤ ሎጣን፣ ሦባል፣ ጽብዖን፣ ዓና፣ ዲሶን፣ ኤጽር፣ ዲሳን።
\v 39 የሎጣን ወንዶች ልጆች፤ ሖሪ፣ ሄማም፣ ቲሞናዕ፣ የሎጣን፣ እኅት ነበረች።
\v 40 የሦባል ወንዶች ልጆች፤ ዓልዋን፣ ማኔሐት፣ ዔናል፣ ስፎ፣ አውናም። የጽብዖን ወንዶች ልጆች፤ አያ፣ ዓና።
\s5
\v 41 የዓና ወንድ ልጅ፤ ዲሶን። የዲሶን ወንዶች ልጆች፤ ሔምዳን፣ ኤስባን፣ ይትራን፣ ክራን።
\v 42 የኤጽር ወንዶች ልጆች፤ ቢልሐን፣ ዛዕዋን፣ ዓቃን። የዲሳን ወንዶች ልጆች፤ ዑፅ፣ አራን።
\s5
\v 43 በእስራኤል አንድም ንጉሥ ገና ሳይነግሥ በኤዶም ምድር የነገሡ ነገሥታት እነዚህ ናቸው። የቢዖር ልጅ ባላቅ፤ ከተማይቱም ዲንሃባ ትባል ነበር።
\v 44 ባላቅ ሲሞትም የባሳራ ሰው የሆነው የዛራ ልጅ ኢዮባብ በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።
\v 45 ኢዮባብ ሲሞት የቴማን አገር ሰው የሆነው ሑሳም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።
\s5
\v 46 ሑሳም ሲሞት በሞዓብ ምድር ምድያ ምን ድል ያደረገው የባዳድ ልጅ በእግሩ ተተክቶ ነገሠ። የከተማይቱም ስም ዓዊት ተባለ።
\v 47 ሃዳድም ሲሞት የመሥሬቃ ሰው የሆነው ሠምላ በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።
\v 48 ሠምላም ሲሞት በወንዙ አጠገብ ያለችው የረኆቦት ሰው የሆነው ሳኡል በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።
\s5
\v 49 ሳኡልም ሲሞት የዓክቦል ልጅ የሆነው በኣልሕናንም ሲሞት በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።
\v 50 በኣልሐናን ሲሞት ሀዳድ በእግሩ ተተክቶ ነገሠ። ከተማው ፋዑ ትባል ነበር፤ ሚስቱ መሄጣብኤል ትባልላለች፤ እርሷም የሜዛሃብ ልጅ የመጥሬድ ልጅ ነበረች።
\s5
\v 51 ሀዳድም ሞተ። ዋና ዋናዎቹ የኤዶም ሕዝብ አለቆች እነዚህ ነበሩ፤ ቲምናዕ፣ ዓልዋ፣ የቴት፣
\v 52 አህሊባማ፣ ኤላ፣ ፊኖን፣ ቄኔዝ፣ ቴማን፣ ሚብሳር፣
\v 53 ቄኔዝ፣ ቴማን፣ ሚብሳር፣
\v 54 መግዲኤል፣ ዒራም። እነዚህ የኤዶም አለቆች ነበሩ።
\s5
\c 2
\p
\v 1 የእስራኤል ወንዶች ልጆች እነዚህ ነበሩ፤ ሮቤል፣ ስምዖን፣ ሌዊ፣ ይሁዳ፣ ይሳኮር፣ ዛብሎን፣
\v 2 ዳን፣ ዮሴፍ፣ ብንያም፣ ንፍታሌም፣ ጋድ፣ እሴር።
\s5
\v 3 የይሁዳ ወንዶች ልጆች፤ ዔር፣ አውናን፣ ሴሎም፣ እነዚህን ጆስቱን ከከነዓን ሚስቱ ከሴዋ ወለደ። የበኩር ልጁ ዔር በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሰው ሆነ፤ እግዚአብሔር ቀፈፈው።
\v 4 የልጁም ሚስት የነበረችው ትዕማር ፋሬስንና ዛራን ወለደችለት፤ ይሁዳም ባጠቃላይ አምስት ወንዶች ልጆች ነበሩት።
\s5
\v 5 የፋሬስ ወንዶች ልጆች፤ ኤስሮም፣ ሐሙል።
\v 6 የዛራ ወንዶች ልጆች፤ ዘምሪ፣ ኤታን፣ ሄማን፣ ከልኮል፣ ዳራ፣ ባጠቃላይ አምስት ናቸው።
\v 7 የከሚር ወንድ ልጅ አካን፤ እርሱም ፈፅሞ መደምሰስ የነበረበት ነገር ሰርቆ በእስራኤል ላይ ጥፋት እንዲመጣ ያደረገ ነው።
\v 8 የኤታን ወንድ ልጅ፤ አዛርያ።
\s5
\v 9 የኤስሮን ወንዶች ልጆች፤ ይረሕምል፣አራም፣ካሌብ።
\v 10 አራም አሚናዳብን ወለደ፤አሚናዳብም የይሁዳ ሕዝብ መሪ የሆነውን ነአሶንን ወለደ፤
\v 11 ነአሶን ሰልሞንን ወለደ፤ሰልሞን ቦዔንን ወለደ።
\v 12 ቦዔዝ ኢዮቤድን ወለደ፤ኢዮብይድ እሴይን ወለደ።
\s5
\v 13 የእሴይ ወንዶች ልጆች፤ የብኩር ልጁ ኤልያብ፣ ሁለተኛ ልጁ አሚናዳብ፣ ሦስተኛ ልጁ ሣማ፣
\v 14 አራተኛው ልጁ ናትናኤል፣ አምስተኛ ልጁ ራዳይ፣
\v 15 ስድስተኛ ልጁ አሳም፣ ሰባተኛ ልጁ ዳዊት።
\s5
\v 16 እኅቶቻቸውም ጽሩያና አቢግያ ነበሩ። የጹሩያ ሦስት ወንዶች ልጆች አቢሳ፣ ኢዮአብና አሣኤል ነበሩ።
\v 17 አቢግያ አሜሳይን ወለደች፣ አባቱም ዬቴር የተባለ እስማኤላዊ ነበረ።
\s5
\v 18 የኤስሮም ልጅ ካሌብ ከሚስቱ ከዓዙባና እንዲሁም ከይሪዖት ወንዶች ልጆች ወለደ፥ ከዓዜባ የተወለዱት ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው። ያሳብ፣ ሶባብ፣ አርዶን፣
\v 19 ዓዙባ ስትሞት፣ ካሌብ ኤፍራታን አገባ፤ እርሷም ሆርን ወለደችለት።
\v 20 ሆርኡሪን ወለደ፤ ኡሪም ባስልኤልን ወለደ።
\s5
\v 21 ከዚህም በኋላ ኤስሮም ሥልሳ ዓመት ሲሆነው የገለዓድን አባት የማኪርን ልጅ አገባ፤ እርሷም ሠጉብን ወለደችለት።
\v 22 ሠጉብም ኢያዕርን ወለድደ፤ እርሱም በገለዓድ ምድር ሃያ ሦስት አተሞች ያስተዳድር ነበር።
\s5
\v 23 ይሁን እንጂ ጌሹና አራም፣ ቄናትንና በዙሪያዋ የሚገኑትን ሥልሳ መነደሮች ጨምሮ የኢያዕርን ከተሞች ነጠቁት። እነዚህ ሁሉ የገለዓድ አባትየማኪር ዘሮች ነበሩ።
\v 24 ኤስሮም በካሌብ ኤፍራታ ከሞተ በኋላ፣ ሚስቱ አቢያ የቴቁሔን አባት አሽሑርን ወለደችለት።
\s5
\v 25 የኤስሮም የበኩር ልጅ የይረሕምኤል ወንዶች ልጆች፤ የበኩር ልጁ ራም፣ ቡናህ፣ ኦሬን፣ ኦጼን፣ አኪያ።
\v 26 ይረሕምኤል ዓጣራ የተባለች ሌላ ሚስት ነበረችው፤ እርሷም የኦናምን እናት ነበረች።
\v 27 የይረሕምኤል የበኩር ልጁ የራም ወንዶች፤ መዓስ፣ ያሚን፣ ዔቄር።
\v 28 የኦናም ወንዶች ልጆች፤ ሸማይና ያዳ። የሸማይ ወንዶች ልጆች፤ ናዳብና አቢሱር።
\s5
\v 29 የአቢሱር ሚስት አቢካኢል ትባላለች፤ እርሷም አሕባንንና ሞሊድ የተባሉ ልጆች ወለደችለት።
\v 30 የናባድ ወንዶች ልጆች፤ ሴሌድ፣አፋይም፣ሴሌድ፣ወንድ ልጅ ሳይወልድ ሞተ።
\v 31 የአፋይም ወንድ ልጅ፤ይሸዒ።ይሽዒም ሶሳን ወለደ።ሶሳን አሕልይን ወለደ።
\v 32 የሸማይ ወንድም የያዳ ወንዶች ልጆች፤ዬቴር፣ዮናታን፣ዬቴርም ልጅ ሳይወልድ ሞተ።
\v 33 የዮናታን ወንዶች ልጆች፤ፌሌት፣ዛዛ። እነዚህ የይረሕምኤል ዘሮች ነበሩ።
\s5
\v 34 ሶሳን ሴቶች እንጂ ወንዶች ልጆች አልነበሩትም። እርሱም ኢዮሄል የተባለ ግብፃዊ አገልጋይ ነበርረው።
\v 35 ሶሳን ልጁን ለአገልጋዩ ለኢዮሄል ሚስት ትሆነው ዘንድ ሰጠው፤ እርሷም ዓይታ የተባለ ወንድ ልጅ ወለደችለት።
\s5
\v 36 ዓታይ ናታንን ወለደ፣ናታንም ዛባድን ወለደ፣
\v 37 ዛባድ ኤፍላን ወለደ፤ ኤፍላል ዖቤድን ወለደ፤
\v 38 ዖቤድ ኢዩን ወለደ፤ ኢዩ ዓዛርያስን ወለደ፤
\s5
\v 39 ዓዛርያስ ኬሌስን ወለደ፤ ኬሌስ ኤልዓሣ ወለደ፤
\v 40 ኤልዓሣ ሲስማይን ወለደ፤ ሲስማይ ሰሎምን ወለደ፤
\v 41 ሰሎም የቃምያን ወለደ፤ የቃምያም ኤሊሳማን ወለደ።
\s5
\v 42 የይረሕምኤል ወንድም የካሌብ ወንዶች ልጆች፤ የበኩር ልጁ ሞሳ ሲሆን፤ እርሱም ዚፍን ወለደ፤ ዚፍም መሪሳን ወለደ፤ መሪ ሳም ኬብሮንን ወለደ።
\v 43 የኬብሮን ወንዶች ልጆች፤ ቆሬ፣ ተፋዋ፣ ሬቄም፣ ሽማዕ።
\v 44 ሽማዕ ርችሐምን ወለደ፤ ረሐምም ዮርቅዓምን ወለደ። ሬቄም ሽማይን ወለደ፤
\s5
\v 45 ሽማይም ማዖንን ወለደ፤ ማዖንም ቤት ጹርን ወለደ።
\v 46 የካሌብ ቁባት ዔፋ ሐራንን፣ ሞዳን፣ ጋዜዝን ወለደች። ሐራንም ጋዜዝን ወለደ።
\v 47 የያህዳይ ወንዶች ልጆች፤ ሬጌም፣ ኢዮታም፣ ጌሻን፣ ፋሌጥ፣ ዔፋ፣ ሸዓፍ።
\s5
\v 48 የካሌብ ቁባት ማዕካ ሼቤርን፣ ቲርሐናን ወለደለችለት።
\v 49 እንዲሁም የመድማናን አባት ሸዓፍን፣ የመክቢናንና የጊብዓን አባት ሱሳን ወለደች። ካሌብ ዓክሳ የተባለች ልጅ ነበረችው።
\v 50 የኤፍራታ የበኩር ልጅ የሑር ወንዶች ልጆች ሦባል የቂርያት ይዓሪም አባት፤
\s5
\v 51 ሰልሞን የቤተልሔም አባት፤ ሐሬፍ የቤት ጋዴር አባት።
\s5
\v 52 የቂርያትይዓሪም አባት የሦባል ዘሮች፤ የመናሕታውያን ነዋሪዎች እኩሌታ፣ ሀሮኤ፤
\v 53 እንዲሁም የቂርያትይዓሪም ጎሣዎች፤ ይትራውያን፤ ፋታውያን፣ ሹማታውያን፣ ሚሽራውያን፤ ጾርዓውያንና ኤሽታኦውያን ከእነዚህ የመጡ ጎሣዎች ነበሩ።
\s5
\v 54 የሰልሞን ዘሮች፤ ቤተልሔም፣ ነጦፋውያን፣ ዓጣሮት ቤት ዮአብ፣ የመናሕታውያን እኩሌታ፣ ጾርዓውያን።
\v 55 በያቤጽ የሚኖሩ የጸሐፍት ጎሣዎች ቲርዓውያን፣ ሺምዓታውያን፣ ሡካታውያን። እነዚህ ከሬካብ ቤት አባት ከሐማት የመጡ ቄናውያን ናቸው።
\s5
\c 3
\p
\v 1 ዳዊት በኬብሮን ሳለ የወለዳቸው ወንዶች ልጆች እነዚህ ነበሩ፤ ከኢይዝራኤላዊቷ ከአኪናሆም የተወለደው የብኩር ልጁ አምኖን፣ሁለተኛው ከቀርሜሎሳዊቷ ከአቢግያ የተወለደው ዳንኤል፣
\v 2 ሦስተኛው ከጌሹር ንጉሥ ከተማይ ልጅ ከመዓካ የተወለደው አቤሴሎም፣አራተኛው የአጊት ልጅ አዶንያስ፣
\v 3 አምስተኛው ከሚስቱ ከዔግላ የተወለደው ይትረኃም።
\s5
\v 4 እነዚህ ስድስቱ የተወለዱት ዳዊት በኬብሮን ሆኖ ሰባት ዓመት ተኩል በገዛበት ጊዜ ነበር። ዳዊት በኢየሩሳሌም ሠላሳ ሦስት ዓመት ነገሠ፤
\v 5 በዚያም የወለዳቸው ልጆች እነዚህ ነበሩ፤ ሳሙስ፣ ሶባብ፣ ናታን፣ ሰለሞን፣ እነዚህ አራት ወንዶች ልጆች ከዓሚኤል ልጅ ከቤርሳቤህ የተወለዱ ናቸው።
\s5
\v 6 እንዲሁም ሌሎች ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ ስማቸውም ኢያቤሐር፣ ኤሊሱዔ፣ ኤሊፋላት፣
\v 7 ኖጋ፣ ናፌቅ፣ ያፍያ፣
\v 8 ኤሊሳማ፣ ኤሊዳሄ፣ ኤሊፋላት ይባላል፤ ባጠቃላይ ዘጠነኛ ነበሩ።
\v 9 ከቁባቶቹ ከወለዳቸው ወንዶች ልጆች ሌላ እነዚህ ሁሉ ልጆቹ ነበሩ፤ እነዚህም ትዕማር የምትባል እኅት ነበረቻቸው።
\s5
\v 10 የሰሎሞን ልጅ ሮብዓም ነበረ፤ የሮብዓም ልጅ አቢያ፣ የአቢያ ልጅ አሳ፣ የአሳ ልጅ ኢዮሣፍጥ፣
\v 11 የኢዮሣፍጥ ልጅ ኢዮራም፣ የኢዮራም ልጅ አካዝያስ፣ የአካዝያስ ልጅ ኢዮአስ፣
\v 12 የኢዮአስ ልጅ አሜስያስ፣ የአሜስያስ ልጅ ዓዛርያስ፣ የዓዛርያስ ልጅ ኢዮአታም፣
\s5
\v 13 የኢዮአታም ልጅ አካዝ፣ የአካዝዝ ልጅ ሕዝቅያስ፣ የሕዝቅያስ ልጅ ማናሴ፣
\v 14 የምናሴ ልጅ አሞጽ፣ የአሞጽ፣ የአሞጽ ልጅ ኢዮስያስ፣
\s5
\v 15 የኢዮስያስ ወንዶች ልጆች፣ በኩሩ ዮሐናን በኩሩ ዮሐናን፣ ሁለተኛ ልጁ ኢዮአቄም፣ ሦስተኛ ልጁ ሴዴቅያስ፣ አራተኛ ልጁ ሰሎም።
\v 16 የኢዮአቄም ዘሮች፤ ልጁ ኢኮንያ፣ ልጁ ሴዴቅያስ።
\s5
\v 17 የምርኮኛው የኢኮንያን ዘሮች፣ ልጁ ሰላትያል፣
\v 18 መልኪራም፣ ፈዳያ፣ ሼናጻር፣ ይቃምያ፣ ሆሻማ፣ ነዳብያ።
\s5
\v 19 የፈዳያ ወንዶች ልጆች፤ ዘሩባቤል ወንዶች ልጆች፥ ሜሱላም፣ ሐናንያ፣ እኅታቸው ሰሎሚት ትባላለች።
\v 20 ሌሎችም አምስት ልጆች ነበሩ፤ እነርሱም ሐሹባ፣ ኦሄል፣ በራክያ፣ ሐሳድያ፣ ዮሻብሒሴድ።
\v 21 የሐናንያ ዘሮች፤ ፈላጥን፣ የአብድዩና የሴኬንያ ወንዶች።
\s5
\v 22 የሴኬንያ ዘሮች፤ ሸማያና ወንዶች ልጆቹ፤ ሐሙስ፣ ይግአል፣ ባሪያሕ፣ ነዓርያ፣ ሻፋጥ፣ ባጠቃላይ ስድስት ነበሩ።
\v 23 የነዓርያ ወንዶች ልጆች፤ ኤልዩዔናይም
\v 24 ወንዶች ልጆች፤ ሆዳይዋ፣ ኤልያሴብ፣ ፌልያ፣ ዓቁብ፣ ዮሐናን፣ ደላያ፣ ዓናኒ፤ ባጠቃላይ ሰባት ናቸው።
\s5
\c 4
\p
\v 1 የይሁዳ ዘሮች፤ ፋሬስ፣ ኤስሮም፣ ከርሚ፣ ሆር፣ ሦባል።
\v 2 የሦባል ልጅ ራያ ኢኤትን ወለደ፤ ኢኤትደግሞ አሑማይንና ላሃድን ወለደ፤ እነዝዝዚህ የጾርዓውያን ጎሣዎች ናቸው።
\s5
\v 3 የኤጣም ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ኢይዝራኤል፣ ይሽማ፣ ይደባሽ። እኅታቸው ሃጽሌልፎኒ ትባላለች።
\v 4 ፋኑኤል ጌዶርን ወለደ፤ ኤጽር ደግሞ ሑሻ ምን ወለደ። እነዚህ የኤፍራታ የበኩር ልጅና የቤተልሔም አባት የሆነው የሆር ዘሮች ናቸው።
\s5
\v 5 የቴቁሔ አባት አሽሑር፣ ሔላና ነዕራ የተባሉ ሁለቱ ሚስቶች ነበሩት።
\v 6 ነዕራም አሑዛምን፣ ኦፌርን፣ ቴምኒን፣ አሐሽታሪን ወለደችለት፤ የነዕራ ዘሮች እነዚህ ነበሩ።
\v 7 የሔላ ወንዶች ልጆች፤ ዴሬት፣ ይጽሐር፣ ኤትናን ናቸው።
\v 8 የቆጽ ወንዶች ልጆች ደግሞም ዓኑብ፣ ጾቤባና፣ የሃሩም ናቸው።
\s5
\v 9 ያቤጽ ከወንድሞቹ ይልቅ የተከበረ ሰው ነበረ፤ እናቱም ''በጣር የወለድድኩት'' ስትል ስሙን ያቤጽ አለችው።
\v 10 ያቤጽም፣ ''አቤቱ፤ እንድትባርከኝ፣ ግዛቴንም እንድታሰፋልኝ እለምንሃለሁ፣ እጅህ ከእኔ ጋር ትሁን፣ ከሥቃይና ከጉዳትም ጠብቀኝ'' በማለት ወደ እስራኤል አምላክ ጮኸ።እግዚአብሔርም የለመነውን ሰጠው።
\s5
\v 11 የሹሐ ወንድም ክሉብ ምሒርን ወለደ፤ ምሒርን ወለደ፤ ምሒርም ኤሽቶን ወለደ፤
\v 12 ኤሽቶን ቤትራፋንና ፋሴሐን ወለደ፤ የዒርናሐሽን ከተሞች የቁረቁረ እርሱ ነው። እነዚህ የሬካ ሰዎች ናቸው።
\s5
\v 13 የቄኔዝ ወንዶች ልጆች፤ ሐታት፣ መዖኖታይ።
\v 14 መዖታይ ደግሞ ዖፍራን ወለደ። ሠራያ የኢዮአብ አባት ሲሆን፣ ኢዮአብ ጌሐራሺምን ወለደ፤ የእደ ጥበብ ባለ ሙያዎች ስለ ነበሩ ይህ ስም ተሰጣቸው።
\v 15 የዮፎኔ ልጅ የካሌብ ወንዶች ልጆች፤ ዒሩ፣ ኤላ፣ ነዓም። የኤላ ልጅ ቄኔዝ።
\v 16 የይሃልኤል ወንዶች ልጆች፤ ዚፍ፣ ዚፋ፣ ቲርያ፣አሣርኤል።
\s5
\v 17 የዕዝራ ሜሬድ፣ዔፌር፣ያሎን። ከሜሬድ ሚስቶች እንዲቱ ማርያምን፣ ሽማይንና የኤሽትምዓን አባት ፅሽባን ወለደች።
\v 18 አይሁዳዊት ሚስቱም የጌዶርን አባት ዮሬድን፣ የጆኮን አባት ሔቤርን፣ የዛኖዋን አባት ይቁቲኤልን ወለደች፤ እነዚህም ሜሬድ ያገባት የፈርዖን ልጅ የቢትያ ልጆች ናቸው።
\s5
\v 19 የሆዲያ ሚስት የነሐም እኅት ወንዶች ልጆች፤ የገርሚው የቅዒላ አባት፣ ማዕካታዊው ኤሽትሞዓ።
\v 20 የሺሞን ወንዶች ልጆች፤ አምኖን፣ ሪና፣ ቤንሐናን፣ ቲሎን። የይሺዒ ዘሮች፤ ዞሔትና ቤንዞሔት።
\s5
\v 21 የይሁዳ ልጅ የሴሎም ወንዶች ልጆች፤ የሌካ አባት ዔር፣ የመሪሳና በቤት አሽቤዓ የበፍታ ጨርቅ ሠሪ የሆኑት ጎሣዎች አባት ለዓዳ፣
\v 22 ዮቂም፣ የኮዜባ ሰዎች፣ ኢዮአስ፣ ሞዓብን የገዛ ሣራፍና ያሹቢሌሔም። ታሪካቸውም ጥንታዊነት ያለው ነው።
\v 23 ሰዎቹ ነበጣዒምና በጋዴራ የሚቀመጡ ሸክላ ሠሪዎች ነበሩ፤ በዚያም በመቀመጥ ለንጉሡ ሸክላ ይሠሩ ነበር።
\s5
\v 24 የስምዖን ዘሮች፤ ነሙኤል፣ ያሚን፣ ያሪን፣ ዛራ፣ ሳኡል፣
\v 25 ሰሎም የሳኡል ልጅ ነው፤ መብሳም የሰሎም ልጅ ነው፤ ማስማዕ ደግሞ የመብሳም ልጅ ነው።
\v 26 የማስማዕ ዘሮች ልጁ ሃሙኤል፣ ልጁ ዘኩር፣ ልጁ ሰሜኢ።
\s5
\v 27 ሰሚኤ ዐሥራ ስድስት ወንዶችና ስድስት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ ወንድሞቹ ግን ብዙ ልጆች አልነበሯቸው፤ ስለዚህ ጎሣቸው በሙሉ እንደ ይሁዳ ሕዝብ ብዙ አልነበረም።
\v 28 የኖረባችውም ቦታዎች እነዚህ ናቸው። ቤርሳቤህ፣ ሞላደ፣ ሐጻርሹዓል፣
\s5
\v 29 ቢልሃ፣ ዔጼም፣ ቶላድ፣
\v 30 ቤቱኤል፣ ሔርማ፣ ፊቅላግ፣
\v 31 ቤትማርካቦት፣ ሐጸርሲሲም፣ ቤትቢሪ፣ ሽዓራይም፣ እስከ ዳዊት ዘመነ መንግስት ድረስ የኖሩት በእነዚህ ከተሞች ነው።
\s5
\v 32 በአካባቢያቸው የሚገኙት ወንደሮች ደግሞ ኤጣም፣ ዓይን፣ ሬሞን፣ ቶኬን፣ ዓሻን የተባሉ አምስት ከተሞች ናቸው፤
\v 33 በእነዚህ ከተሞች ዙሪያ በአል የሚዝችልቁ መንደሮች ነበሩ፤ መኖሪያቸው በዚሁ ሲሆን፤ የትውልድ መዝገብም አላቸው።
\s5
\v 34 ሞሾብብ፣ የምሌክ፣ የአሜስያስ ልጅ ኢዮስያስ፣
\v 35 ኢዮኤል፣ የዮሺብያ ልጅ፣ የሠራያ የዓጂኤል ልጅ ኢዩ
\v 36 እንዲሁም ኤልዩዔናይ፣ ያዕቆብ፣ ፅሾሐያ፣ ዓሣያ፣ ዓሲዔል፣ ዩሲምኤል፣ በናያስ፣
\v 37 የሺፊ ልጅ ዚዛ፣ የአሎን ልጅ፣ የይዳያ ልጅ፣ የሺምሪ ልጅ፤ የሸማያ ልጅ፤
\v 38 እነዚህ ስማቸው ከላይ የተዘረዘረው ሰዎች የየጎሣቸው መሪዎች ነበሩ፤ የቤተሰባቸው ብዛት እጅግ በጣም እየጨመረ ሄደ፤
\s5
\v 39 እነርሱም ለከብቶቻቸው ግጦሽ ፍለጋ ከሸለቆው በስተምስራቅ እስካለው እስከ ጌደር መግቢያ ድረስ ዘልቀው ሄዱ።
\v 40 በዚያም ለምለምና ያማረ የግጦሽ ቦታ አገኙ፤ ምድሪቱም ሰፊ፤ ሰላምና ጸጥታ የሰፈነበት ነበረች። በቀድሞ ቀመን በዚህ ምድር ይኖሩ የነበሩት አንዳንድ የካም ዘሮቼ ናቸው።
\v 41 እነዚህ ስማቸው ከላይ የተዘረዘሩው ወደዚሁ ቦታ የመቱት በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ዘመን ነበረ፤ እነርሱም በድንኳኖቻቸው ውስጥ በነበሩበት በካም ወገኖችና በምዑናውያን ላይ አደጋ በመጣል ፈፅመው አላጠፋአቸው፤ ይህም እስከ ዛሬ ድረስ በግልጽ ይታያል። ለመንጎቻቸው በቂ ግጦሽ ቦታ ስላላገኙ፣ በዚያ መኖር ጀመሩ።
\s5
\v 42 ከእነዚሁ አምስት መቶ የሚሆኑ የስምዖን ወገኖች በይሽዒ ልጆች በፈላጥያ፣ በነዓርያ፣ በረፋያና በዑዝኤል ተመርተው የሴይርን ኩረብታማ አገር ወረሩ።
\v 43 አምልጠው የቀሩትን አማሌቅውያን ፈጅተው እስከ ዛሬ በዚያው ይኖራሉ።
\s5
\c 5
\p
\v 1 የእስራኤሌ በኩር ልጅ የሮቤል ልጆች፤ ሮቤል የበኩር ልጅ ቢሆንም፤ የአባቱን መኝታ ስላረከሰ፤ የበኩርናው መብቱ ለእስራኤል ልጅ ለዮሴፍ ልጆች ተሰጥቶአል። ከዚህም የተነሣ ትውልዱ የበኩርነቱን ተራ ይዞ ሊቁጥል አልቻለም።
\v 2 ይሁዳ ከወንድሞቹ ይልቅ ብርቱ ነበረ፤ ገዥ የወጣው ከእርሱ ቢሆንም፣ የበኩርነት መብቱ የተላለፈው ለዮሴፍ ነበረ።
\v 3 የእስራኤል የበኩር ልጅ የሮቤል ወንዶች ልጆች፤ ሄኖኅ፣ ፋሉሶ፣ አስሮን፣ ከርሚ ነበሩ።
\s5
\v 4 የኢዮኤል ዘሮች ልጁ ሽማያ፣ ልጁ ጎግ፣ ልጁ ስሜኢ፣
\v 5 ልጁ ሚካ፣ ልጁ ራያ፣ ልጁ ቢኤል፣
\v 6 የአጆር ንጉስ ቴልጌል ቴልፌልሶር ማኮር የወሰደው ልጅ ብኤራ ነበሩ።
\s5
\v 7 የቤተሰቡ የዘር ትውልድ በየጎሣ በየጎሣው ሲቁጠር እንደሚከተለው ነው፤ የጎሣ አለቃ የሆነው ኢዮኤል፣ ዘካርያስ፣
\v 8 የኢዮኤል ልጅ፣ እነዚህ ከአሮዔር እስከ ናባውና እስከ በኣልሜዎን ድረስ በሚገኘው ምድር ላይ ሰፈሩ።
\v 9 ከብቶቻቸው በገለዓድ ምድር በዝተው ስለነበር በምስራቅ በኩል ወደ ኤፍራጥስ ወንዝ እስከ ምድረ በዳው ዳርቻ ድረስ የሚገኘውን ምድር ያዙ።
\s5
\v 10 በሳኦልም ዘመነ መንግሥት በእጃቸው ተመትተው ድል ከተደረጉት አጋራውያን ጋር ተዋጉ፤ በመላው የገለዓድ ምሥራቃዊ ክፍል የሚገኙትን መኖሪያዎቻቸውን ያዙ።
\s5
\v 11 የጋድ ነገድ ደግሞ ከእነርሱ ቀጥሎ እስከ ሰልካ ድረስ በሚገኘው በባሳን ምድር ኖሩ፤
\v 12 አለቃው ኢዮኤል፣ ሁለተኛው ሳፋም ከዚህም ያናይና ሰፋጥ ሆነው በባሳን ተቀመጡ።
\v 13 ቤተ ዘመዶቻቸውም በየቤተሰቡ እነዚህ ነበሩ፤ ሚካኤል፣ ሜሱላም፣ ሳባ፣ ዮራይ፣ ያካን፣ ዙኤ፣ ኦቤድ፣ ባጠቃላይ ስባት ነበሩ።
\s5
\v 14 እነዚህ ደግሞ የቢዝ ልጅ፣ የዬዳይ ልጆች፣ ኦቤድ፣ የኢዬሳይ ልጅ፣ የሚካኤል ልጅ፣ የገለዓድ ልጅ፣ የኢዳይ ልጅ፣ የዑሪ ልጅ፣ የሑሪ ልጅ፣ የአቢካኢል ልጆች ናቸው።
\v 15 የቤተሰባቸው አለቃ የኑጊ ልጅ፣ የአብዲኤል ልጅ አሒ ነበረ።
\s5
\v 16 እነዚህም በገለኣድ፣ በባሳንና እስከ ዳርቻዋ በሚገኙት መንደሮች እንዲሁም በሳሮን በሚገኙ የግጦሽ ስፍራዎች ሁሉና ከዚያም ወዲያ አልፈው ተቀመጡ።
\v 17 እነዚህ ሁሉ ትውልድ በመዝገብ የሰፈሩት በይሁዳ ንጉሥ በኢዮአታምና በእስራኤል ንጉሥ በኢዮርብዓም ዘመነ መንግሥት ነው።
\s5
\v 18 የሮቤል፣ የጋድና፣ የምናሴ ነገድ እኩሌታ አርባ አራት ሺህ ብቁ የጦር ሰዎች ነበሩአቸው። እነርሱም ጋሻ መያዝ፣ ሰልፍ መምዘዝና ቀስት መሳብ የሚችሉ ጠንካራና በውጊያ የሠለጠኑ ናቸው።
\v 19 እነዚህም በአጋራውያን፣ በኢጡር፣ በናፌስ፣ በናዳብ ላይ ዘመቱ።
\s5
\v 20 በጦርነቱም ላይ ወደ እግዚአብሔር ጮኸው ስለ ነበር፣ በውጊያው ረዳቸው፣ አጋራው ያንንና የጦር አጋሮቻቸውን ሁሉ አሳልፎ ሰጣቸው፤ ስለ ታመኑበትም ፀሎታቸውን ሰማ።
\v 21 የአጋራውያንንም እንስሶች ማረኩ፤ እነዚህም አምሳ ሺህ ግመሎች፣ 250 000 በጎችና ሁለት ሺህ አህዮች ነበሩ። እንዲሁም 100 000 ሰው ማረኩ።
\v 22 ውጊያው የእግዚአብሔር ስለነበር ሌሎችም ብዙ ሰዎች ተገደሉ። እስከ ምርኮ ጊዜ ምድሪቱ በእጃቸው ነበረች።
\s5
\v 23 የምናሴ ነገድ እኩሌታ ህዝብ ቁጥር ብዙ ነበረ፣ እነርሱም ከባሳን ጀምሮ እስከ በኣልአርሞንዔም ድረስ ባለው ምድር ሰፈሩ፤ ይህም እስከ ሳኔር አርሞንዔም ተራራ ድረስ ማለት ነው።
\v 24 የየቤተሰቡ አለቆች እነዚህ ነበሩ፤ ዔፌር፤ ይሽዒ፣ ኤሊኤል፣ ዓዝርኤል፣ ኤርምያ፣ ሆዳይዋ፣ ኢየድኤ፤ እነዚህ ጀግና ተዋጊዎች የታወቁ ሰዎችና የየቤተሰባቸው አለቆች ነበሩ።
\s5
\v 25 ይሁን እንጂ ለአባቶቻቸው አምላክ ታማኞች አልሆኑም፤ እግዚአብሔር ከፊታቸው ያጠፋቸው የምድሪቱን ከሕዝብ አማልክት በማምለክ አመነዘሩ
\v 26 ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የአሦርን ንጉሥ የፎሐት መንፈስ ይኸውም የቴልጌል ቴፌልሶርን መንፈስ አነሣሥቶ የሮቤልን፣ የጋድንና፣ የምናሴን ነገድ እኩሌታ ማርኮ እንዲወሰድ አደረገ። እነዚህንም ወደ ጎዛን ወንዝ ዳርቻ አፈለሳቸው፤ እነርሱም እስከ ዛሬ ድረስ በዚያ ይገኛሉ።
\s5
\c 6
\p
\v 1 የሌዊ ወንዶች ልጆች፤ ጌድሶን፣ቀዓት፣ሜራሪ፣
\v 2 የቀዓት ወንዶች ልጆች፤እንበረም፣ ይሰዓር፣ኬብሮን፣ዑዝኤል።
\v 3 የእምበረም ልጆች፤ አሮን፣ሙሴ፣ማርያም። የአሮን ወንዶች ልጆች፤ናዳብ፣አብዮድ፣አልዓዛር፣ኢታምር።
\s5
\v 4 አልዓዘር ፊንሐስን ወለደ፤ ፊንሐስ አቡሲን ወለደ፤
\v 5 አቢሲ ኦዚን ወለደ፤
\v 6 ኦዚ ዘራእያን ወለደ፤ዘራእያ መራዮትን ወለደ፤
\s5
\v 7 መራዮት አማርያን ወለደ፤አማርያ አኪጦብን ወለደ፤
\v 8 አኪጦብ ሳዶቅን ወለደ፤
\v 9 ሳዶቅ አኪማአስን ወለደ፤አኪማአስ ዓዛርያስን ወለደ፤ዓዛርያስ ዮሐናን ወለደ፤
\s5
\v 10 ዮሐናን ዓዛርያስ ወለደ፤እርሱም ሰለሞን በኢየሩሳሌም ባሠራው ቤተ መቅደስ በክህነት ያገለግል ነበር፤
\v 11 ዓዛርያስ አማርን ወለደ፤አማርያም አኪጦብን ወለደ፤
\v 12 አኪጦብ ስሳዶቅን ወለደ፤ሳዶቅ ሰሎምን ወለደ፤
\s5
\v 13 ሰሎም ኬሌቅያስን ወለደ፤ኬሌቅያስ ዓዛርያስ ሠራያን ወለደ፤
\v 14 ዓዛርያስ ሠራያን ወለደ፤ሠራያ ኢዮሴዴቅን ወለደ፤
\v 15 እግዚአብሔር የይሁዳና የእየሩሳሌም ሕዝብ በናቡከደነፆር እጅ ተማርከው እንዲወሰዱ ባደረገ ጊዜ ኢዮሴዴቅም አብሮ ተማርኮ ሄደ።
\s5
\v 16 የሌዊ ወንዶች ልጆች፤ ጌድሶን፣ቀዓት፣ሜራሪ።
\v 17 የጌድሶን ወንዶች ልጆች፤ሎቢኒ፣ሰሜኢ።
\v 18 የቀሃት ወንዶች ልጆች፤እምበረም፣ይስዓር፣ኬቤሮን፣ዑዝኤል።
\s5
\v 19 የሜራሪ ወንዶች ልጆች፤ሞሖሊ፣ሙሲ። በየአባቶቻቸው ቤተሰብ የተቁጠሩ የሌዊ ጎሣዎች የሚከተሉት ናቸው፤
\v 20 ከጌርሶን፤ ልጁ ሎቢኒ፣ልጅ ኢኤት፣ልጁ ዛማት፣
\v 21 ልጁ ዮአክ፣ልጁ አዶ፣ልጁ ዛራ፣ልጁ ያትራይ።
\s5
\v 22 የቀዓት ዘሮች፤ ልጁ አሚናዳብ፣ልጁ ቆሬ፣ልጁ አሴር፣
\v 23 ልጁ ህልቃና፣ልጁ አቢሳፍ፣ልጁ አሴር፣
\v 24 ልጁ ኢኢት፣ልጁ ኡርኤል፣ልጁ ዖዝያ፣ልጁ ሳውል።
\s5
\v 25 የሕልቃና ዘሮች፤ አማሢ፣አኪሞት።
\v 26 ልጁ ሕልቃና፣ልጁ ሱፊ፣ልጁ ናሐት፣
\v 27 ልጁ ኤልያብ፣ልጁ ይሮሐም፣ልጁ ሕልቃና፣ልጁ ሳሙኤል።
\s5
\v 28 የሳሙኤል ወንዶች ልጆች፤የበኩር ልጁ ኢዮኤል፣ሁለተኛው ልጁ አብያ።
\v 29 የሜራሪ ዘሮች፤ ሞሖሊ፣ልጁ ሎቤኒ፣ልጁ ሰሜኢ፣ልጁ ዖዛ፣
\v 30 ልጁ ሳምን፣ልጁ ሐግያ፣ልጁ ዓሣያ።
\s5
\v 31 ታቦቱ ከገባ በኋላ፣ዳዊት የመዘምራን አለቃ አድርጎ በእግዚአብሄር ቤት የሾማቸው ሰዎች እነዚህ ናቸው፤
\v 32 እርሱም ሰሎሞን የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በኢየሩሳሌም እስኪሠራ ድረስ፣በማደሪያው ይኸውም በመገናኛ ድንኳን ፊት ሆነው እየዘመሩ ያገለግሉ ነበር፣አገልግሎታቸውንም የሚያከናውኑት በወጣላቸው ደንብ መሠረት ነው።
\s5
\v 33 ከወንዶች ልጆቻቸው ጋር ሆነው ያገለገሉ ሰዎች እነዚህ ናቸው፤ከቀዓታዊያን ልጆች፤ሙዚቃ ተጫዋቹ ኤማን፣የኢዮኤል ልጅ፣የሳሙኤል ልጅ፤
\v 34 ሳሙኤል የሕልቃና ልጅ ነበረ፤ ሕልቃና ፣የይሮሐም ልጅ፣ይብኤሊኤል ልጅ፣የቶዋ ልጅ፣
\v 35 የሱፍ ልጅ፣የሥልቃና ልጅ፣የመሐት ልጅ፣የአማሢ ልጅ፣
\s5
\v 36 የሕልቃና ልጅ፣የኢዮኤል ልጅ፣የዓዛርይስስ ልጅ፣የሶፎንያስ ልጅ፣
\v 37 የታሐት ልጅ፣የአሴር ልጅ፣የአብያሳፍ ልጅ፣የቆሬ ልጅ፣
\v 38 የይስዓር ልጅ፣የቃዓት ልጅ፣የሌዊ ልጅ፣የእስራኤል ልጅ።
\s5
\v 39 እንዲሁም የሔማን ወንድም አሳፍ በስተቀኙ ሆኖ ያገለግል ነበር፤ አሳፍ የበራክያ ልጅ፤የሳምዓ ልጅ፤
\v 40 የሚካኤል ልጅ፣
\v 41 የኤትኒ ልጅ፣የዛራ ልጅ፣የዓዳያ ልጅ፣
\v 42 የኤታን ልጅ፣የዛማት ልጅ፣የሰሜኢ ልጅ፣
\v 43 የኢኤት ልጅ፣የጌድሶን ልጅ፣የሌዊ ልጅ፣
\s5
\v 44 በስተግራቸው በኩል አብረዋቸው ያሉት የሜራሪ ልጂች፣የቂሳ ልጅ ኤታን፣የአብዲ ልጅ፣የማሎክ ልጅ፣
\v 45 የሐሸብያ ልጅ፣የአሰያሰ ልጅ፣የኬልቅያስ ልጅ፣
\v 46 የአማሲ ልጅ፣የባኒ ልጅ፣የሰሜር ልጅ፣
\v 47 የሞሖሊ ልጅ፣የሙሲ ልጅ፣የሜራሪ ልጅ፣የሌዊ ልጅ፣
\s5
\v 48 ሌዋውያን ወንድሞቻቸው ግን የእግዚአብሔር ቤት የማደሪያ ድንኳን ተግባር እንዲያከናውኑ ተመድበው ነበር።
\s5
\v 49 አሮንና ልጆቹ የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ ባዘዝው ምሠረት ስለእስራኤል ማስተሰሪያ በቅድስት ቅዱሳኑ ውስጥ የሚያከናውነውን ተግባር ሁሉ፣በመሠዊያ ላይ የሚቃጠል መሥቃዕትና በዕጣኑ መሠዊያ ላይ የሚቀርበውም መሥዋዕት የሚቀርቡት ግን አሮንና ዘሮቹ ብቻ ነበሩ።
\s5
\v 50 የአሮን ዝርያዎች እነዚህ ነበሩ፤ ልጁ አልዓዛር፣ልጅ ፊንሐስ፣ልጁ አቢሹ፣
\v 51 ልጁ ቡቂ፣ልጁኦዚ፣ልጁ ዘራአያ፣
\v 52 ልጁ መራዮት፣ልጁ አማርያ፣ልጁ አኪጦብ፣
\v 53 ልጁ ሳዶቅ፣ልጁ አኪማአስ።
\s5
\v 54 መኖሪያዎቻቸው እንዲሆኑ የተመደቡላቸው ቦታቸው እነዚህ ናቸው፤የመጀመሪያ ዕጣ የእነርሱ ስለ ሆነ፣ከቀዓት ጎሣ ለሆኑት ለአሮን ዘሮች የተመደቡላቸው መኖሪያቸው እነዚህ ነበሩ።
\v 55 ለእነርሱም በይሁዳ ምድር የሚገኘው ኬብሮንና በዙሪያዋ ያለው የግጦሽ ቦታ ተሰጠ፣
\v 56 በኬብሮን ዙሪያ የሚገኙት የዕርሻ ቦታዎችና መንደሮች ግን ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ ተሰጡ።
\s5
\v 57 ለአሮን ዘሮች የመማፀኛ ከተሞች የሆኑትን ኬብሮንን፣ልብናን፣የቲርን፣ኤሽትሞዓን፣
\v 58 ሖሎንን፣ዳቤርን፣ከነመሰማሪዎቻቸው።
\s5
\v 59 ዓሳንን፣ዮታን፣ቤትሳኒስን ከነመሰማሪዎቻቸው ሰጡ።
\v 60 ከብንያም ነገድ ድርሻ ላይ ገባዖንን፣ጌባን፣ጋሌማን፣ዓናቶትን ከነመሰማሪያዋቻቸው ሰጡ። ለቀዓት ዘሮች የተከፋፈሉ እነዚህ ከተሞች ባጠቃላይ ዐሥራ ሦስት ናቸው።
\s5
\v 61 ለቀሩት የቀዓት ዘሮች ደግሞ ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ድርሻ በዕጣ ዐሥር ከተሞች ተሰጧቸው።
\v 62 ለጌድሶን ነገድ በየጎሣቸው ከይሳኮር፣ከአሴር፣ከንፍታሌምና በባሳን ከሚገኘው ከምናሴ ነገድ ድርሻ ላይ ዐሥራ ሦስት ከተሞች ተመደቡላቸው።
\s5
\v 63 ለሜራሪ ዘሮች በየጎሣቸው ከሮቤል፣ከጋድና ከዛብሎን ድርሻ ላይ ዐሥራ ሁለት ከተሞች በዕጣ ተመደቡላቸው።
\v 64 እስራኤላዊያን ከተሞቹን በዚሁ ሁኔታ መድበው ከነመሰማሪያዎቻቸው ለሌዋውያኑ ሰጧቸው።
\v 65 ቀደም ብለው የተጠቀሱትንም ከተሞች ከይሁዳ ከስምዖንና ከብንያም ነገድ ላይ ወስደው በዕጣ መደቡላቸው።
\s5
\v 66 ለአንዳንድ የቀዓት ጎሣዎችም ከኤፍሬም ነገድ ድርሻ ላይ ከተሞች ተሰጣቸው።
\v 67 በኮረብታማው በኤፍሬም ምድር የሚገኙትን ሴኬምን(የማማፀኛ ከተማ) ፣ኔዝርን፣
\v 68 ዮቅምዓምን፣ቤትሖሮን፣
\v 69 ኤሎንንና ጋትሪሞን ከነመሰማሪዎቻቸው ሰጧቸው።
\s5
\v 70 እንዲሁም እስራኤላውያን ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ድርሻ ላይ ዓኔርና ቢልዓም የተባሉትን ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው ወስደው ለሩት የቀዓት ጎሣዎች ሰጧቸው።
\s5
\v 71 ለጌድሶናውያን ከምናሴ ነገድ እኩሌታ፣ በባሳን የሚገኘውን ጎላንና አስታሮትን ከነመሰማሪያዎቻቸው ተሰጠ፤
\v 72 ከይሳኮር ነገድ፤ ቃዴስን፣ዳብራትን
\v 73 ራሞትንና ዓኔምናን ከነመሰማሪያዎቻቸው ወሰዱ፤
\s5
\v 74 ከአሴር ነገድ መዓሳልን፣ዓብዶን፣
\v 75 ሑቆቅንና፣ረአብን ከነመሰማሪያዎቻቸው ወሰዱ፤
\v 76 ከንፍታሌም ነገድ በገሊላ የሚገኘውን ቃዴስን፣ሐሞንንና፣ቂርያታይምን ከነመሰማሪያዎቻቸው ወሰዱ።
\s5
\v 77 ከሌዋውያን የቀሩት የሜራሪ ጎሣዎች ደግሞ ከዚህ የሚከተለው ወሰዱ፤ከዛቢሎን ነገድ ዮቅኒዓምን፣ቀርታህን፣ሬሞንና፣ታቦርን፣ከነመሰማሪዮቻቸው ወሰዱ።
\v 78 ከዮርዳኖስ ወንዝ ማዶ ኪኢያሪኮ በስተምስራቅ ከሚገኘውን ቦሶርን፣ያሳን፣
\v 79 ቅዴሞትንና ሜፍዓትን ከነመሰማሮያዎቻችው ወሰዱ፤
\s5
\v 80 ከጋድ ነገድ በገለዓድ የምትገኘውን ሬማትን፣መሃናይምን፣
\v 81 ሐሴቦንና ኢያዜርን ከነመሰማሪያዎቻቸው ወሰዱ።
\s5
\c 7
\p
\v 1 የይሳኮር ወንዶች ልጆች፤ ቶላ፣ፋዋ፣ያሱብ፣ሺምሮን፣ባጠቃላይ አራት ናቸው።
\v 2 የቶላ ወንዶች ልጆች፤ኦዚ፣ርረፋያ፣ይሪኤል፣የሕማይ፣ይብሣም፣ሽሚኤል፣እነዚህ የየቤተሰባቸው አለቆች ናቸው።በዳዊት ዘመነመንግሥት ከቶላ ዘሮች በየትውልድ ሀረጋቸው የተቁጠሩ የቶላ ዘሮች ብርቱ ተዋጊዎች ነበሩ፤ቁጥራቸው ሃያ ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ነበረ።
\v 3 የኦዚ ወንድ ልጅ፤ይዝረሕያ። የይዝረሐያ ወንዶች ልጆች፤ሚካኤል፣አብድዩ፣ይሺያ፣አምስቱም አለቆች ነበሩ።
\s5
\v 4 ብዙ ሚስቶችና ልጆች ስለ ነበሩአቸው፣ከነቤተሰባቸው የትውልድ ሐረግ ለውጊያ ብቁ የሆኑ 36000 ሰዎች ነበሩአቸው።
\v 5 ከይስኮር ጎሣዎች ሁሉ የተመዘገቡት ተዋጊዎች የቤተሰቦቹ ትውልድ ቁጥር ባጠቃላይ 87000 ነበሩ።
\s5
\v 6 ሦስቱ የብንያም ወንዶች ልጆች፤ ቤላ፣ቤኬብ፣ይዲኤል።
\v 7 የቤላ ወንዶች ልጆች፤ ኤሴቦንም፣ኦዚ፣ዑዝኤል፣ኢያሪሙት፣ዒሪ፣ባጠቃላይ አምስት ሲሆኑ፣ የቤተ ሰብ አለቆች ናቸው፤በትውልድ ሐረግ መዝገባቸው 22034 ተዋጊ ሰዎች ተመዝገበዋል።
\s5
\v 8 የቤኬር ወንዶች ልጆች፤ዝሚራ፣ኢዮአስ፣አልዓዛር፣ኤልዮዔናይ፣ዖምሪ፣ ኢያሪሙት፣አብያ፣ዓናቶት፣ዔሌሜት፣እነዚህ ሁሉ የቤኬር ልጆች ነበሩ።
\v 9 በትውልድ ሐረግ መዝገባቸውም ውስጥ የየቤተ ሰባቸው አለቆችና ሃያ ሺህ ሁለት መቶ ተዋጊዎች ተመዝግበዋል።
\v 10 የይዲኤል ልጅ፤ ቢልሐን።የቢልሐን ወንዶች ልጆች፤ የዑስ፣አሲሳኦር፣
\s5
\v 11 እነዚህ ሁሉ የይዲኤል ልጆች የየቤተሰቡ አለቆች ነበሩ፤እነርሱም ለውጊያ ብቁ የሆኑ 17200 ተዋጊዎች ነበሯቸው።
\v 12 (ሳፈንና ሁፊም የዒር ዘሮች ሲሆኑ ሑሺም ደግሞ የአሐር ዘር ነው።)
\s5
\v 13 የንፍታሌም ወንዶች ልጆች፤ ያህጽሔል፣ጉኒ፣ዬጽር፣ሺሌም፤እነዚህ የባላ የልጅ ልጆች ናቸው።
\s5
\v 14 የምናሴ ዘሮች፤ ሶርያዊት ቁባቱ የወለደችለት ልጁ አሥርኤል ነው።እርሷም የገለዓድን አባት ማኪርያ የወለደች ናት፤
\v 15 ማኪርም ከሑፊምና ከሳፊም ወገኖች ሚስት አገባ።እኅቱም መዓካ ትባል ነበር።ሌላው ዘሩ ሰለጸዓድ ሲሆን፣እርሱም ሴቶች ልጆች ብቻ ነበሩት።
\v 16 የሚከር ሚስት መዓካ ወንድ ልጅ ወለደች፣ስሙንም ፋሬስ አለችው።የወንድሙም ስም ሱሮስ ይባላል፤ወንዶች ልጆቹም ኡላምና ራቄም ነበሩ።
\s5
\v 17 የኡላም ወንድ ልጅ፤ባዳን፣እነዚህ የምናሴ ልጅ፣የማኪር ልጅ፣የገለዓድ ወንዶች ልጆች ናቸው፤፤
\v 18 እኅቱ መለኬት ኢሱድን፣አቢዔዝርንና መሐላን ወለድች።
\v 19 የሽሚዳ ወንዶች ልጆች ደግሞ እነዚህ ነበሩ፤ አሒያንምምሴኬም፣ሊቅሒ፣አኒዓም።
\s5
\v 20 የኤፍሬም ዘሮች፤ ሹቱላ፣ልጁ ባሬድምምልጁ ታሐት፣ልጁ ኤልዓዳ፣ልጁ ታሐት፣
\v 21 ልጁ ዛባድ፣ልጁ ሹቱላ።ኤድርና ኤልዓድ ከብቶች ለመስረቅ በወረዱ ጊዜ፣የአገሩ ተወለጆች በሆኑት በጌት ሰዎች ተገደሉ።
\v 22 አባታቸውም ኤፍሬም ብዙ ቀን አለቀሰላቸው፤ዘመዶቹም መጥተው አፅናኑት።
\s5
\v 23 ከዚያም ወደ ሚስቱ ገብቶ ተኛ፤እርሷም ፀነሰች፤ወንድ ልጅም ወለደች፤በቤተሰቡ ላይ ከደረሰው መከራ የተነሣ ስሙን በሪያ አለው።
\v 24 ሴት ልጁ ስሟ ሲኢራ ይባላል፤እርሷም የታችኛውና የላይኛውን ቤት ሖሮንንና ኡዜን ሼራን የተባሉትን ከተሞች የቁረቁረች ናት።
\s5
\v 25 ልጁ ፋፌ፣ልጁ ሬሴፍ፣ልጁ ቴላ፣ልጁ ታሐን፣
\v 26 ልጁ ለአዳን፣ልጁ ዓሚሁድ ልጁ ኤሊሳማ፣
\v 27 ልጁ ነዌ፣ልጁ ኢያሱ።
\s5
\v 28 በምድራቸውና መኖሪያቸው ቤቴልንና በዙሪያዋ የሚገኙት ከተሞች በስተምሥራቅ ነዓራን፣በስተ ምዕራብ ጌዝርንና መንደሮቿን በሙሉ ታጠቃልል ነበር።
\v 29 በምናሴ ወሰን ላይ ቤትሳን፣ታዕናክ፣መጊዶና ዶና ከነመንደሮቻቸው ነበሩ።በእነዚህም መንደሮች የእስራኤል ልጅ የዮሴፍ ዘሮች ነበር።
\s5
\v 30 የአሴር ወንዶች ልጆች፤ዩምና፣የሱዋ፣የሱዊ፣በሪዓ፣እኅታቸውም ሤራሕ ትባል ነበር።
\v 31 የበሪዓ ወንዶች ልጆች፤ሐቤርም የቢርዛዊት አባት መልኪኤል።
\v 32 ሔቤርም ያፍሌጥን፣ሳሜርን፣ኮታምንና እኅታቸውን ሶላን ወለደ።
\s5
\v 33 የያፍሌጥ ወንዶች ልጆች፤ ፋሴክ፣ቢምሃል፣ዓሲት፣የያፍሌጥ ወንዶች ልጆች እነዚህ ነበሩ ።
\v 34 የስሜር ወንዶች ልጆች፤ አ፣፥ሮኦጋ፣ይሑባ፣አራም።
\v 35 የወንድሙ የኤላም ወንዶች ልጆች፤ጾፋ ይምና፣ሰሌስ፣ዓማል።
\s5
\v 36 የጻፋ ወንዶች ልጆች፤ ሱዋ፣ሐርኔፍር፣ሦጋል፣ቤሪ፣ይምራ፣
\v 37 ቤጼር፣ሆድ፣ሳማ፣ ሰሊሳ፣ይትራን፣ብኤራ።
\v 38 የዬቴር ወንዶች ልጆች፤ዮሮኒ፣ፊስጻ፣አራ።
\s5
\v 39 የዑላ ወንዶች ልጆች፤ኤራ፣ሐኒኤል፣ሪጽያ።
\v 40 እነዚህ ሁሉ የአሴር ዜሮች ናቸው።እነርሱም የቤተ ሰብ አለቆች፣ምርጥ ሰዎች፣ብርቱ ተዋጊዎችና ድንቅ መሪዎች ነበሩ።ለውጊያ ብቁ የሆኑት ወንዶች ቁጥር 26000 ነበር።
39የዑላ ወንዶች ልጆች፤ኤራ፣ሐኒኤል፣ሪጽያ። 40እነዚህ ሁሉ የአሴር ዜሮች ናቸው።እነርሱም የቤተ ሰብ አለቆች፣ምርጥ ሰዎች፣ብርቱ ተዋጊዎችና ድንቅ መሪዎች ነበሩ።ለውጊያ ብቁ የሆኑት ወንዶች ቁጥር 26000 ነበር።
\s5
\c 8
\p
\v 1 የብንያም አምስት ወንድ ልጆች የነበሩት የብኩር ልጅን ቤላን ፤ አስቤልን፣ አሐራን፣
\v 2 ኖሐን፣ ራፋን ወለደ።
\s5
\v 3 የቤላ ወንዶች ልጆች እነዚህ ነበሩ፤አዳር ጌራ፣አቢሁድ፣አቡሁድ፣
\v 4 አቢሱ፣ናዕማን፣ኦሖዋ፣
\v 5 ጌራ፣ሰፋፋ፣ሒራም።
\s5
\v 6 በጌባ ይኑሩ የነበሩትና በኋላም በምርኮ ወደ መናሐት የተወሰዱት የኤሁድ ዘሮች እነዚህ ናቸው።
\v 7 ናዕማን፣አኪያ፣ጌራ፣በምርኮ ጊዜ እየመራ የወሰዳቸው የዖዛና የኢሒሑድ አባት ጌራ ነበረ።
\s5
\v 8 ሽሐራይም ሚስቶቹን ሑሺምንና በዕራን ከፍታ በኋላ በሞዓብ ምድር ወንዶች ልጆች ወለደ።
\v 9 ከሚስቱ ከሖዴሽ ዮባብን፣ዲብያን፣ማሴን፣ማልካምን፣
\v 10 ይዑጽን፣ሻክያንና ሚርማን ወለደ፤እነዚህም የቤተ ሰብ አለቆች የነበሩ ልጆቹ ናቸው።
\v 11 ሑሺም ከተባለች ሚስቱ አቢጡብና ኤልፍዓል የተባሉ ወንዶች ልጆች።
\s5
\v 12 የኤልፍዓል ወንዶች ልጆች፤ ዔቤር፣ሚሻም፣እንዲሁም ኦኖንና ሎድ የተባሉ ከተሞች ከነመንደሮቻቸው የቁረቁረ ሻሜድ፣
\v 13 በኤሌን ይኖሩ ለነበሩ ቤተሰቦች አለቆችና የጋት ነዋሪዎችን አስወጥተው ያሳደዱ በሪዓና ሽማዕ።
\s5
\v 14 አሒዮ፣ሻሻቅ፣ይሬምት፣
\v 15 ዝባድያ፣ዓራያ፣ዔድር፣
\v 16 ሚካኤል፣ይሽጻናዮሐ የበሪያ ወንዶች ልጆች ነበሩ።
\v 17 ዝባድያ፣ሜሱላም፣ህዝቂ፣ሔቤር፣
\v 18 ይሽምራይ፣ ይዝሊያና፣ዮባብ፣የኤልፍዓል ወንዶች ልጆች ነበሩ።
\s5
\v 19-21 ሺሜኢ እነዚህ ወንዶች ልጆች ያቃም፣ዝክሪ፣ዘብዲ፣ኤሊዔናይ፣ጺልታይ፣ኤሊኤል ፣ዓዳያ፣ብራያና፣ሺምራት ነበሩት።
\s5
\v 22 ይሽጻን፣ዔቤር፣ኤሊኤል፣
\v 23 ዓብዶን፣ዝክሪ፣ሐናን፣
\v 24 ሐናንያ፣ኤላም፣ዓንቶትንያ
\v 25 ይፍዴያና ፋኑኤል የሶሴቅ ወንዶች ልጆች ነበሩ።
\s5
\v 26 ሽምሽራይ፣ሽሃሪያ፣ጎቶልያ፣
\v 27 ያሬሽያ፣ኤልያስና፣ዝክሪ የይሮሐም ወንዶች ልጆች ነበሩ።
\v 28 እነዚህ ሁሉ በየትውልድ ሐርረጋቸው የተቁጠሩ አለቆችና የቤተ ሰብ መሪዎች ሲሆኑ፣የሚኖሩትም በኢየሩሳሌም ነበረ።
\s5
\v 29 የገባዖን አባት ይዒኤል በገባዖን ኖረ፣ሚስቱ መዓካ ትባል ነበር።
\v 30 የበኩር ልጁም አብዶን ይባል ነበር፣የእርሱም ተከታታዮች ዱር፣ቂስ፣በኣል፣ኔር፣ናዳብ፣
\v 31 ጌዶር፣አሂዮ፣ዛኩርና፣
\s5
\v 32 የሺምዓ አባት ሚቅሎት ነበሩ።እነዚህም ከሥጋ ዘመዶቻቸው ጋር በኢየሩሳሌም ከተማ አቅራቢያ ይኖሩ ነበር።
\v 33 ኔር ቂስን ወለደ፣ቂስ ሳኦልንወለደ፣ሳኦልም ዮናታንን፣ሜልኪሳን፣አሚናዳብን፣አስበኣልን ወለደ።
\v 34 የዮናትን ወንድ ልጅ መሪበኣልን፣እርሱም ሚካን ወለደ።
\s5
\v 35 የሚካ ወንዶች ልጆች ፒቶን፣ ሜሌክ፣ ታሬዓ፣ አካዝ ነበሩ።
\v 36 አካዝ ይሆዓዳን ወለደ፤ ይሆዓዳም ዔሌሜትን፣ ዓዝሞትን፣ ዘምሪን ወለደ፤ ዘምሪም ሞዳን ወለደ።
\v 37 ሞጻ ቢንዓን ወለደ፤ ቢንዓ ረፋያን ወለደ፤ ረፋያ ኤልዓሣን ወለደ። ኤልዓሣም ኤሴልን ወለደ።
\s5
\v 38 ኤሴል ስድስት ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም ዓዝሪቃም፣ ቦክሩ፣ እስማኤል፣ ሽዓርያ፣ አብድዩ፣ ሐናን ናቸው። እነዚህ ሁሉ የኤሴል ልጆች ነበሩ።
\v 39 የእርሱ ወንድም የኤሴቅ ወንዶች ልጆች የበኩር ልጁ ኡላም፣ ሁለተኛው ልጁ ኢያስ፣ ሦስተኛው ልጁ ኤላፋላት ናቸው።
\v 40 የኡላም ልጆች ጦረኞችና ቀስተኞች ነበሩ። ብዙ ልጆችና የልጅ ልጆች ነበሩዋቸው፤ ጠቅላላ ቁጥራቸው አንድ መቶ ሃምሳ ነበር። እነዚህ ሁሉ የብንያም ዘሮች ናቸው።
\s5
\c 9
\p
\v 1 እስራኤል ሁሉ በየትውልድ ሐረጋቸው ተቁጥረው ስማቸው በእስራኤል ነገሥታት መዝገብ ላይ ሰፈረ።የይሁዳ ሕዝብ ከፈፀሙት በደል የተነሣ ተማርከው ወደ ባቢሎን ተወሰዱ።
\v 2 በመጀመሪያ በየርስታቸውና በየከተሞቻቸው ተመልሰው የሰፈሩት ጥቂት እስራኤላውያን፣ካህናት፣ሌዋውያንና ቤተመቅደሱ ውስጥ የጉልበት ሥራ የሚሠሩ አገልጋዮች ነበሩ።
\v 3 በእየሩሳሌም ይኖሩ የነበሩ የይሁዳ፣የብንያም፣የኤፍሬምና ምናሴ ነገዶች የሚከተሉት ናቸው፤
\s5
\v 4 ከሰፋሪዎችም መካከል ይሁዳ ልጅ፣ከፋሬስ ዘሮች፣የባኒ ልጅ፣የአምሪ ልጅ፣የዖምሪ ልጅ፣የዓሚሁድ ልጅ ዑታይ።
\v 5 ከሴሎናውያን፦የበኩር ልጁ ዓሣያና ወንዶች ልጆቹ።
\v 6 ከዛራውያን ዝርያዎች መካከል ይዑኤል፤ የሕዝቡ ቁጥር 690 ነበረ።
\s5
\v 7 ከብንያማዊን፦የሐስኑኤ ልጅ፣የሆዳይዋ ልጅ፣የሜሱላ ልጅ ስሉ።
\v 8 የይሮሐም ልጅ ብኔያ፣የሚክሪ ልጅ፣የኦዚ ልጅ ኤላ፣የይብንያ ልጅ፣የራጉኤል ልጅ፣የሰፋ ጥያ ልጅ ሜሱላም።
\v 9 በትውልድ ሐረግ መዝገቡ ላይ በተጻፈው መሠረት ከብንያም ነገድ የሕዝቡ ቁጥር ዘጠኝ መቶ ሃምሳ ስድስት ነበረ፤እነዚህ ሁሉ ወንዶች የቤተሰብ አለቆች ነበሩ።
\s5
\v 10 ከካህናቱ፦ ዮዳኤ፣ዮአሪብ፣ያኪን፣
\v 11 የእግዚአብሔር ቤት አለቃ የሆነው የአኪጦብ ልጅ፣የጳስኮር ልጅ፣የይሮሐም ልጅ፣የሜሱላም ልጅ፣የኬልቅያስ ልጅ ዓዛርያስ።
\s5
\v 12 የመልክያ ልጅ፣የጳስኮር ልጅ፣የሳዶቅ ልጅ፣ዓዳያ፣የኢሜር ልጅ፣የምሺላሚት ልጅ፣የሜሴላም ልጅ፣የየሕዜራ ልጅ፣የዓዲኤል ልጅ መዕሣይ።
\v 13 የቤተሰብ አለቃ የነበሩ ካህናት ቁጥር አንድ ሺህ ሰባት መቶ ሥልሳ ነበረ፤እነዚህም በእግዚአብሔር ብት ለሚከናወነው አገልግሎት ብቁ ሰዎች ነበሩ።
\s5
\v 14 ከሌዋውያን ወገን፦ ከሜራሪ ዘሮች የአሳብያ ልጅ፣የዓዝሪቃም ልጅ፣የአሱብ ልጅ፣ሽማያ፣
\v 15 በቅበቃር፣ኤሬስ፣ጋላልና የአሳፍ ልጅ የዝክሪ፣የሚካ ልጅ፣መታንያ።
\v 16 የኤዶም ልጅ፣የጋላል ልጅ፣ይችሰሙስ ልጅ፣አብድያ።እንዲሁም በነጦፋውያን ከተሞች የኖረው የሕልቅና ልጅ፣የአሳ ልጅ በራክያ።
\s5
\v 17 የቤተ መቅደስ በር ጠባቂዎች፦ሰሎም፣ዓቁብ፣ጡልሞን፣አሂማንና ወንድሞቻቸው፣አለቃቸው ሰሎም ነበረ፤
\v 18 እነርሱም በስተ ምስራቅ በሚገኝው በንጉስ በር እካሁን ድረስ ተመድቦአል።እነዚህ የሌዋያኑ ሰፈር በር ጠባቂዎች ነበሩ።
\v 19 የቆሬ የአብያሳፍ ልጅ፣የቆሬ ልጅ ሰሎምና ክእነሱም ቤተሰብ የሆኑት ቆሬያውያን ወደ እግዚአብሔር ማደሪያ የሚያስገባውን በር ይጠብቁ እንደ ነበር ሁሉ፣እነዚህም ወደ ቤተ መቅደሱ የሚያስገባውን በር ይጠብቁ ነበር።
\s5
\v 20 በቀድሞ ጊዜ የበር ጠባቂዎቹ አለቃ የአላዓዛር ልጅ ፊንሐስ ነበረ፥እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረ።
\v 21 ወደ መገኛው ድንኳን የምያስገባው በር የሚጠብቀው ደግሞ የሜሱላም ልጅ ዘካሪያስ ነበረ።
\s5
\v 22 መግቢያ በሮቹን እንዲጠብቁ የተመረጡ ባጠቃላይ ሁለት መቶ ዐሥራ ሁለት ነበሩ።እነርሱም በትውልድ ሐረጋቸው መሠረት በሚኖሩባቸው መንደሮች ተቁጥረው ተመዘገቡ፤በር ጠባቂዎቹን በዚያ ቦታ ላይ የመደቡላቸው ዳዊትና ባለ ራእዩ ሳሙኤል ነበሩ።
\v 23 የማደሪያውን ድንኳን ምማለትም የእግዚአብሔርን ቤት የሚጠብቁትንም እነርሱና ዘሮቻቸው ነበሩ።
\v 24 በር ጠባቂዎቹም በምሥራቅ፣በምዕራብ፣በሰሜንና፣በደቡብ በሚገኙት በአራቱም ማዕዘኖች ላይ ነበሩ።
\s5
\v 25 ወንድሞቻቸውም በየመንደሮቻቸው ሆነው በየጊዜው እየወጡ የጥበቃውን ሥራ ሰባት ሰባት ቀን ያግዙአቸው ነበር።
\v 26 ሌዋውያን የነበሩት አራቱ የበር ጠባቂ አለቆች ግን በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ የሚገኙትን ክፍሎችና ግምጃ ቤቶች በኃላፊነት ይጠብቁ ነበር።
\v 27 የጥበቃውን ሥራ የሚያከናውኑት እነርሱ በመሆናቸው የሚያድሩትም በዚያው በእግዚአብሔር ቤት አካባቢ ነበረ፤ጠዋት ጠዋትም ደጆቹን የሚከፋፍቱት እነርሱ ነበሩ።
\s5
\v 28 ከእነርሱም አንዳንዶቹ ለብቤተመቅደሱ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በኃላፊነት ይጠብቁ ነበር፤ዕቃዎቹም በሚገቡበትና በሚወቱበት ጊዜ ሁሉ ይቁትሩ ነበር፤
\v 29 ሌሎቹ ሌዋውያን ደግሞ ዕቃዎቹንና የቤተ መውደሱን ንዋያት ቅድሳት፣ዱቄቱን፣የወይን ጠጁን፣የወይራ ዘይቱን፣ዕጣኑን የሽቱውን ቅመማ ቅመም እንዲጠብቁ ተምመድበው ነበር።
\s5
\v 30 ከካህናቱም አንዳንዶቹ የሽቱውን ቅመማ ቅመም ይለውሱ ያዘጋጁ ነበር።
\v 31 የቆሬያዊው የሰሎም በኩር ልጅ ሌዋዊው ማቲትያ የቁርባኑን እንጀራ የመጋገር ኅላፊነት ተሰጥቶት ነበር።
\v 32 በየሰንበቱ የተሰጠው ከቀዓታውያን ወንድሞቻቸው መካከል ለአንዳንዶቹ ነበር።
\s5
\v 33 የሌዋውያን ቤተ ሰብ አለቆች የነበሩት መዘምራኑ ደግሞ በብይተ መቅደሱ ክፍሎች ውስጥ እንዲኖሩና ከሌላው ሥራ ሁሉ ነፃ ሌሊት የሚሠሩት ሥራ ነበራቸው።
\v 34 እነዚሁ ሁሉ የሌዋውያን ቤተ ሰብ አለቆች ሲሆኑ፣በትውልድ ሐረጋቸ መሠረት ተመዘገቡ፤የሚኖሩትም በኢየሩሳሌም ነበረ።
\s5
\v 35 የገባዖን አባት ይዒኤል የሚኖረው በገባዖን ነበረ፤የሚስቱም ስም መዓካ ይባላል።
\v 36 የበኩር ልጁ ዓብዶን ሲሆን፣የእርሱም ተከታዮች ዱር፣ቂስ፣በኣል፣ኔር፣ናዳብ፣
\v 37 ጌዶር፣አሒዮ፣ዛኩር፣ሚቅሎት ነበሩ።
\s5
\v 38 ሚቅሎት ሳምአን ወለደ፣እርሱም ከዘመዶቻቸው ጋር በኢየሩሳሌም አቅራቢያ ይኖሩ ነበር።
\v 39 ኔር ቂስን ወለደ፤ቂስ ሳኦልን ወለደ፤ሳኦል ዮናታን፣ሜልኪሳን፣አሚናዳብን፣አስበኣልን ወለደ።
\v 40 የዮናታ ወንድ ልጅ፤ መሪበኣል ነው፤መሪበኣል ሚካን ወለደ
\s5
\v 41 የሚካ ወንዶች ልጆች፤ፒቶን፣ሜሌክ፣ታሬዓ፣አካዝ።
\v 42 አካዝ የዕራን ወለደ፤ዘምንሪን ሞፃን ወለደ።
\v 43 ሞፃም ቢንዓን ወለደ፤ልጁ ረፋያ ነበረ፤ልጁ ኤልዓሣ፣ልጁ ኤሴል።
\v 44 ኤሴል ስድስት ወንዶች ልጆች ነበሩ፤ስማቸውም፦ ዓዝሪቃም፣ቦክሩ፣እስማኤል፣ሸዓርያ፣አብድዩ ሐናን እነዚህ የኤሴል ወንዶች ልጆች ናቸው።
\s5
\c 10
\p
\v 1 ከዚህ በኋላ ፍልስጥኤማውያን ራኤላውያንም ከፊታቸ ሸሹ፤ብዙዎች በጊቦልቦን ተራራ ላይ ሞቱ።
\v 2 ፍልስጥኤማውያን ሳኦልንና ልጆቹን ይበልጥ አሳደዱአቸው የሳኦልም ልጆች ዮናታን፣አሚናዳብንና ሜልካሳን ገደሉ፤
\v 3 ሳኦል በተሰለፈበት ግንባር ውጊያው በረታ፤ቀስተኞችም አግኝተው አቁሰሉት።
\s5
\v 4 ሳኦል ጋሻ ጃግሬውን፣''እነዚህ ሸለፈታምፕች መሳለቂያ እንዳያደርጉኝ ሰልፍህን መዝዘህ ውጋኝ''አለው።ጋሻ ጃግሬው ግን እጅግ ፈርቶ ሰለ ነበር አልደፍርም፤ስለዚህ ሳኦል በገዛ ሰይፉ ላይ ወድቆ ሞተ።
\s5
\v 5 ጋሻ ጃግሬውም ሳኦል መሞቱን ሲያይ፤እርሱም በሰይፉ ላይ ወድቆ ሞተ።
\v 6 ስለዚህ ሳዖልና ሦስት ልጆቹ ሞቱ፤ቤተ ሰዎቹም ሁሉ አብረው ሞቱ።
\s5
\v 7 በሸለቆው ውስጥ የነበሩት እስራኤላዊያን ሁሉ ሰራዊቱ እንደ ሸሽ፣ሳኢልና ልጆቹም እንደ ሞቱ ባዩ ጊዜ ከተሞቻቸውን ለቀው ሸሹ፤ፍልስጥኤማውያንመጥተው ከተሞቹን ያዙ።
\v 8 በማግሥቱ ፍልስጥኤማውያን የሞቱትን ለመግፈፍ ሲመጡ፣ሳኦልና ልጆቹ በጊልቦዓ ተራራ ላይ ወድቀው አገኙአቸው።
\s5
\v 9 ሳኦልን ከገፈፉ፣ረሱን ከቁረጡና መሣሪያውንም ከወሰዱ በኋላ፣ለአማልክቶቻቸውና ለሕዝቡ የምሥራቹን እንዲነግሩ ወደ መላው የፍልስጥኤም ምድር መልክዕተኞች ላኩ።
\v 10 ከዚህም መሣሪያውን በአማልክቶቻቸው ቤተ ጣዖት አኖሩ፤ራሱንም በዳጎን ቤተ ጣዖት ውስጥ አንጠለጠሉት።
\s5
\v 11 የኢያቢስ ገለዓድ ነዋሪዎች ሁሉ ፍልስጥኤማውያን በሳኦል ላይ ያደረጉትን በሰሙ ጊዜ፤
\v 12 ብርቱ የሆኑ ሰዎች ሄደው የሳኦልንና የልጆቹን ሬሳ አንሥተው ወደ ኢያቢስ አመጡ፤ዐጽማቸውንም ኢያቢስ ውስጥ በሚገኘው ትልቁ ዛፍ ሥር ቀበሩ፤ከዚህያም ሰባት ቀን ጾሙ።
\s5
\v 13 ሳኦል እግዚአብሔር ስላታዘዘ ሞተ፤የእግዚአብሔር ቃል አልጠበቀም፤ይልቁንም ከሙታን ጠሪ ምክርን ጠየቀ፤
\v 14 ይህን ከእግዚአብሔር አልጠየቀም፤ስስለዚህ እግዚአብሔር ገደለው፤መንግሥቱንም ወደ እሴይ ልጅ ወደ ዳዊት እንዲተላለፍ አደረገ።
\s5
\c 11
\p
\v 1 እስራኤል ሁሉ በኬብሮን ወደ እነሆ፤እኛ የገዛ ሥጋህና ደምህ ነን፤
\v 2-3 በቀደመው ዘመን ሳኦል ንጉሥ ሆኖ ሳለ እስራኤልን ወደ ጦርነት የምትመራ አንተ ነበርህ፤እግዚአብሔር አምላክም፣ሕዝቤን እስራኤልን የምትጠብቅ አንተ ነህ፤ንጉሥ ዳዊት ወዳለበት ወደ ኬብሮን መጡ፤ዳዊትም በኬብሮን በእግዚአብሔር ፊት ከእነሱ ጋር ቃል ኪዳን ገባ።እግዚአብሔር በሳሙኤል አማካይነት በሰጠው ተስፋ መሠረት ዳዊትን ቀብተው በእስራኤል ላይ አነገሡት።
\s5
\v 4 ዳዊትና እስራኤላዊያን ሁሉ ኢያቡስ ወደምትባለው ወደ ኢየሩሳሌም ሄዱ።በዚያም የሚኖሩ ኢያቡሳዊያን፤
\v 5 ዳዊትን ''ወደዚያ ፈፅሞ አትገባም''አሉት፤ዳዊትግን የጽዮንን ምሽግ ያዘ፤እርሷም የዳዊት ከተማ ናት።
\v 6 ዳዊትና ''ኢያቡሳዊያንን ቀድሞ የሚወጋ ሰው የሰራዊቱ አዛዥ ይሆናል''አለ፤ስለዚህ የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ በመጀመሪያ ወጣ፤እርሱም አዛዥ ለመሆን በቃ።
\s5
\v 7 ከዚያም ዳዊት መኖሪያውን በዐባምዩቱ ውስጥ አደረገ፤ከዚያም የተነሣ የዳዊት ከተማ ተባለች።
\v 8 ዳዊትም ከሚሎ ጀምሮ የከተማይቱን ዙሪያ ቅጥር ሠራ፤ኢዮአብ ደግሞ የቀረውን የከተማይቱን ክፍል መልሶ ሠራ።
\v 9 እግዚአብሔር ጸባኦት ከእርሱ ጋር ሰለ ነበር ዳዊት በየጊዜው እየበረታ ሄደ።
\s5
\v 10 የዳዊት ኅያላን ሰዎች አለቆች እነዚህ ናቸው፤እነርሱም እግዚአብሔር በሰጠው ተስፋ መሠረት መንግሥቱን በምድሪቱ ሁሉ ትስፋ ዘንድ ከሌሎች እስራኤላዊያን ጋር ሆነው ለመንግሥቱ ብርቱ ድጋፍ ሰጡ።
\v 11 ዳዊት ኅያላን ሰዎች ስም ዜርዜር ይህ ነው፤ ሐክሞናዊው ያሶብዓም የጦር መኮንኖች አለቃ ነበረ፤እነርሱም ጦሩን አንጅቶ በአንድ ጊዜ ሦስት መቶ ሰው ገደለ።
\s5
\v 12 ከእርሱም ቀጥሎ ከሦስቱ ኅያላን አንዱ የሆነው የአሆሃዊው የዱዲ ልጅ አልዓዘር ነው፤
\v 13 እርሱም ፍልስጥኤማዊያን ለጦርነት በተሰበሰቡ ጊዜ በፈስደሚም ከዳዊት ጋር አብሮ ነበረ፤ገብስ በሞላበት የእርሻ ቦታ ወታደሮቹ ከፍልስትኤማውያን ፊት ሸሹ፤
\v 14 ይሁን እንጂ በእርሻው መካከል ቦታ ይዘው ስለ ነበረ ፍልስጥኤማውያንን ገደሉ፤እግዚአብሔር ታላቅ ድል ሰጣቸው።
\s5
\v 15 ከፍልስጥኤማውያን ሰራዊት ጥቂቱ በራፋይም ሸለቆ ሰፍሮ ሳለ፣ከሠላሳዎቹ አለቆች ጆስቱ ዳዊትን ለመገናኘት በዓዶላም ዋሻ አጠገብ ወደሚገኘው ወደ ዐለቱ ወረዱ።
\v 16 በዚያን ጊዜ ዳዊት በምሽጉ ውስጥ ነበረ፤የፍልስጥኤማዊያን ሰራዊት ደግሞ በቤተልሕም ነበረ።
\v 17 ዳዊትም ውሃ ፈልጎ ነበርና፣''ከቤተ ልሔም በር አቅራቢያ ከሚገኘው ጉድጓድ የምጠጣው ውሃ ማን ባመጣልኝ!'' አለ።
\s5
\v 18 በዚህ ጊዜ ጆስቱ የፍልስጥኤማውያንን ሰራዊት ጥሰው በማለፍ በቤተ ልሔም በር አጠገብ ከሚገኘው ጉድጓድ ውሃ ቀድተው ለዳዊት አመጡለት፤እርሱ ግን ሊጠጣው ስላልፈለገ በእግዚአብሔር ፊት አፈሰሰው፤
\v 19 ከዚያም ''ይህን ከማድረግ እግዚአብሔር የጠብቀኝ፤ይህ በሕይወታችን ቁርጠው የሄዱትን የእነዚህን ሰዎች ደም እንደ መጠጣት አይደለምን?''አለ።ይህን ለማምጣት በሕይወታቸው ቁርጠው ስለ ነበር፣ዳዊት ሊጠጣው አልፈለገም።
\s5
\v 20 የኢዮአብ ወንድም አቢሳ የጆስቱ አለቃ ነበረ። እርሱም ጦሩን አንሥቶ ሦስት መቶ ሰዎች ገደለ፤ከዚህም የተነሣ እንደ ሦስቱ ሁሉ ዝነኛ ሆነ፤
\v 21 ከጆስቱ አንዱ ሆኖ ባይቁጠርም እንኳን፣እጥፍ ክብር አገኘ፤አዛዣቸውም ሆነ።
\s5
\v 22 ከቀብስኤል የወጣውና ታላቅ ጀብዱ የሠውው የዮዳሄ ልጅ በናያስ ብርቱ ተዋጊ ነበረ።እርሱም እጅግ ያታወቁ ሁለት የሞአብ ሰዎች ገደለ።እንዲያውም አንድ ጊዜ በረዶ ምድርን በሰፈነበት ቀን ወደ አንድ ጉድጓድ ወርዶ አንበሳ ወደለ።
\v 23 ደግሞም ቁመቱ አምስት ክንድ የሆነ አንድ ግብፃዊው የሸማኔ መጥቅለያ የመሰለ ቶር በእጁ ይዞ ገጠመው፤ክችግብፃዊው ጋር እጅ ጦሩ ነጥቆ በገዛ ጦሩ ገደለው።
\s5
\v 24 የዮሄዳ ልጅ በናያስ የፈፀመው ጀብዱ ይህ ነበር፤እርሱም እንደ ሦስቱ ኅያላን ዝነኛ ሆነ።
\v 25 ከሠላሳዎቹም ይልቅ የበለጠ አንዱ አልነበረመ፤ዳዊትም የክብር ዘቡ አዛዥ አደረገው።
\s5
\v 26 ኅያላኑ ወንድም አሣሄል፤የቤተ ልሔም የዱዲ ልጅ ኤልያናን፤
\v 27 ሃሮራዊው ሳሞት፣ፊሎናዊው ሴሌዴ፣
\v 28 የቴቁሔ ሰው የሆነው የዓስካ ልጅ፣ዒራስ፣የዓናቶቱ ሰው፣አቢዔዜር፣
\v 29 ኩሳዊው ሴቤካይ፣ኦሆሃዊው ዔላይ፣
\s5
\v 30 ነቶፋዊው ማህራይ፣የነቶፋዊው የበዓና ልጅ ሔሌድ፣
\v 31 ከብንያም ወገን የጊብዓ ሰው የሆነው የሪባይ ልጅ ኤታል፣ጲርዓቶናዊው በናያስ፣
\v 32 የገዓስ ሸለቆዎች ሰው የሆነው ኡሪ፣ዓረባዊው አቢኤል፣
\v 33 ባሕሩማዊው ዓዝሞት፣ሰዓልቦዊው ኤልያሕባ፣
\s5
\v 34 የጊዞናዊው የአሳን ልጆች፣የሃራራዊው የሻጌ ልጅ ዮናታን፣
\v 35 የሃራራዊው የሳኮር ልጅ አሒአም፣የኡር ልጅ ኤሊፋል፣
\v 36 ምኬራታዊው ኦፌር፣ፍሎናዊው አኪያ፣
\v 37 ቀርሜሎሳዊው ሐጽሮ፣የኤዝባይ ልጅ ነዕራይ፤
\s5
\v 38 የናታን ወንድም ኢዮኤል፣የሃግሪ ልጅ ሚብሐር፣
\v 39 አሞናዊ ጼሌቅ፣የጽሩያ ልጅ የኢዮአብ ጋሻ ጃግሬ ቤሮ ታዊው ነሃራይ፣
\v 40 ይትራዊው ዒራስ፣ይትራዊው ጋሬብ፣
\v 41 ኬጤያዊው ኦርዮ፣የአህላይ ልጅ ዛባድ፣
\s5
\v 42 የሮቤላዊው የሺዛ ልጅ ዓዲና፣እርሱም የሮቤላዊያንና አብረውት ለነበሩት የሠላሳ ሰዎች አለቃ ነበረ።
\v 43 የማዕካ ልጅ ሐናን፣ሚትናዊው ኢዮሣፍጥ፣
\v 44 አስታሮዊው ዖዝያ፣የአሮዔራዊው የኮታም ልጆች ሻማና ይዒኤል፣
\s5
\v 45 የሺምሪ ልጅ ይዲኤል፣ወንድሙም ቴዳዊው ዮሐ፣
\v 46 መሐዋዊው ኤሊኤል፣የኤልነዓም ልጆች ይባሪይና ዮሻውያ፣ሞዓባዊው ይትማ፣
\v 47 ኤሊኤል፣ዖቤድና ምጾባዊው የዕሢኤል።
\s5
\c 12
\p
\v 1 ዳዊት ከቂስ ልጅ ከሳኦል ፊት ሸሽቶ በጺቅላግ ሳለ ወደ እርሱ የመጡት ሰዎች እነዚህ ናቸው፤እነርሱም በጦርነቱ ላይ ከረዱት ተዋጊዎች መካከል ነበሩ።
\v 2 ሰዎቹ ቀስተኞች ሲሆኑ፣በቀኝም ሆነ በግራ እጃቸው ፍላጻ መወርወርና ድንጋይ መወንጨፍ የሚችሉ ነበሩ፤እነርሱም ከብንያም ነገድ የሆነው የሳኦል ሥጋ ዘመዶች ነበሩ፤
\s5
\v 3 አለቃቸው አሐዔዝር ነበረ፥ከእርሱም በኋላ ኢዮአስ ነበረ፤ሁለቱም የጊብዓዊው የሸማዓ ልጆች ነበሩ፤የዓዝሞት ልጆች ይዝኤልና ፋሌጥ፣በራኪያ፣ዓናቶታዊው ኢዩ፣
\v 4 ገባናዊው ሰማያስ ከሠላሳዎቹም መሪ ነበረ፤ርርሚያስ፣የሕዚኤል ዮሐንስ፣ገድሮታዊው ዮዛባት፣
\s5
\v 5 ኤሊዛይ፣ኢያሪሙት፣በዓልያ፣ሰማራያ፤ሐሩፋዊው ሰፋትያስ፣
\v 6 ቆሬያውያኑ ሕልቃና፣ይሺያ፣ዓዘኤል፣ዮዛር፣ያሻብዓም፣
\v 7 የጌዶር ሰው ከሆነው ደግሞ የይሮሐም ልጆች ዮዔላና ዝባድያ።
\s5
\v 8 ዳዊት በምድረ በዳ በሚገኘው ምሽጉ ውስጥ ሳለ፣ከጋድ ነገድ የሆኑ ሰዎች መጥተውው የእርሱን ሰራዊት ተቀላቀሉ፤ከእነሱም ለውጊያ የተዘጋጁ ጋሻና ጦር ለመያዝ የሚችሉ ብርቱ ተዋጊዎች ነበሩ፤ፊታቸው እንደ አንበሳ እንደሚይዝ ሚዳቋ ፈጣኖች ነበሩ ።
\s5
\v 9 የእነዚህም አለቃ ዔፌር ነበረ፤ሁለተኛ አዛዥ አብድዩ፣ሦስተኛው ኤልያብ፣
\v 10 አራተኛ መስመና፣አምስተኛው ኤርሚያስ፤
\v 11 ስድስተኛው ዓታይ፣ሰባተኛው ኢሊኤል፣
\v 12 ስምንተኛው ዮሐናን፣ዘጠነኛው ኤልዛባድ፣
\v 13 ዐሥረኛው ኤርሚያስ፣ዐሥራ አንድኛው መክበናይ።
\s5
\v 14 እነዚህ ጋዳውያን የጦር አዛዦች ነበሩ፣ከእነሱም ታናሽ የሆነው እንደ መቶ፣ታላቅ የሆነው ደግሞ እንደ ሺህ አለቃ ይቁጠር ነበር።
\v 15 በመጀመሪያው ወር የዮርዳኖስ ወንዝ ከአፍ እስከ ሞልቶ ሳለ፣ወንዙን ተሻግረው በስተ ምሥራቅና በስተ ምዕራብ ሸለቆዎች ይኖሩ የነበሩትን ሁሉ ከዚያ ያባረሩት እነዚህ ሰዎች ነበሩ።
\s5
\v 16 ሌሎች ከብንያምና ከይሁዳም ወገን የሆኑ ሰዎች ዳዊት ወደሚገኝበት ምሽግ መጡ።
\v 17 ዳዊትም እነዚህን ሰዎች ሊቀበል ወጥቶ እንዲህ አላቸው፤የመጣችሁት ልትረዱኝና በሰላም ከሆነ፤ከእኔ ጋር እንድትሰለፉ ልቀበላችሁ ዝግጁ ነኝ፤ነገር ግን እጄ ከበደል ንጹሕ ሆኖ ሳለ፤ለጠላቶቼ አሳልፋችሁ ልትሰጡኝ ከሆነ፤የአባቶቻችን አምላክ ይመልከተው፤ይፍረድውም።
\s5
\v 18 ከዚያም እግዚአብሔር መንፈስ በሠላሳዎቹ አለቃ በዓማሣይ ላይ ወረደ፤እርሱም እንዲህ አለ፤''ዳዊት፤እኛ ክችአንተ ጋር ነን፤ሰላም ፍፁም ሰላም ለአንተ ይሁን፤አንተን ለሚረዱም ሁሉ ሰላም ይሁን፤አምላክህ ይረዳሃል''።ስለዚህ ዳዊት ተቀበላቸው፤የሰራዊቱም አለቃ አደረረጋቸው።
\s5
\v 19 ዳዊት ከፍልስጥኤማዊያን ጋር ተባብሮ ሳኦልን ለመውጋት በሄደ ጊዜ፤ከምናሴ ነገድ የሆኑ ጥቂት ሰዎች ከድተው ከዳዊት ሰራዊት ጋር ተቀላቀሉ።እርሱ ግን ርዳታ አላደረገላቸውም፤ምክንዩም የፍልስትኤማዊያን ገዦች ምክር ካደረጉ በኋላ እንዲህ ሲሉ ልከውት ነበር፤''ከድቶ ወደ ጌታው ውደ ሳኦል ቢሄድ እኛን ያስጨርሰናል።
\v 20 ዳዊት ወደ ጺውላግ በሄደ ጊዝዜ ከድተው ወደ እርሱ የተቀላቀሉ የምናሴ ነገድ ሰዎች እነዚህ ነበሩ፤ዓድና፣ዮዛባት፣ይዲኤል፣ሚካኤል፣ዮዛባት፣ኤሊሁ፣ ጺልታይ፤እነዚህ በምናሴ ግዛት ሳሉ የሸለቆች ነበሩ።
\s5
\v 21 ሁሉ ብርቱ ተዋጊዎችና በዳዊትም ሰራዊት ውስጥ አዛዦች ሰለ ነበሩ፣አደጋ ጣዮችን በመውጋት ረዱት።
\v 22 ሰራዊቱም እንደ እግዚአብሔር ሰራዊት እስኪሆን ድረስ፤፣ዳዊትን ለመርዳት በየዕለቱ ብዙ ሰዎች ይጎርፉ ነበር።
\s5
\v 23 እግዚአብሔር ለዳዊት በገባለት ቃል ኪዳን መሠረት የሳኦል መንግሥት አንሥተው ለእርሱ ለመስጠት ዳዊት ወደ ሚገኝበት ወደ ኬቤሮን የመጡት ሰዎች ቁጥር ይህ ነው፤
\v 24 ጋሻና ጦር አንግበው ለጦርነት የተዘጋጁት የይሁዳ ሰዎች ስድስት ሺህ ስምንት መቶ።
\v 25 ከስምዖን ነገድ ለጦርነት ዝግጁ የሆኑ ሰባት ሺህ አንድ መቶ።
\s5
\v 26 ከሌዊ ነገድ አራት ሺህ ስድስት መቶ፤
\v 27 የአሮን ቤተ ሰብ መሪ የሆነውን ዮዳሄን ጨምሮ ሦስት ሺህ ሰባት መቶ ሰዎች፤
\v 28 ወጣቱ ብርቱ ተዋጊ ጻዶቅና ከቤተ ሰቡ ሃያ ሁለት የጦር አለቆች፤
\s5
\v 29 የሳኦል ሥጋ ዘመድ የሆኑ የብንያም ሰዎች ሦስት ሺህ፤ከነዚህም አብዛኞቹ እስከዛያች ጊዜ ድረስ ለሳኦል ቤት ታማኝ ነበሩ፤
\v 30 ከኤፍሬም ሰዎች በጎሣዎቻቸው ዘንድ ታዋቂ የሆኑ ብርቱ ተዋጊዎች ሃያ ሺህ ስምንት መቶ፤
\v 31 ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ዐሥራ ስምንት ሺህ ሰዎች፤እነርሱም ዳዊትን ለማንገሥ በየስማቸው ተጽፈው የመጡ ነበሩ።
\s5
\v 32 ዘመኑን የተረዱና እስራኤላዊያንም ምን ማድረግ እንደሚገባቸው የተገነዘቡ የይሳኮር ሰዎች ሁለት መቶ አለቆች፤በእነሱም ሥር ሆነው የሚታዘዙ ዘመዶቻቸው።
\v 33 ልምድ ያላቸው፤በሁለቱም ዐይነት መሣሪያ ለመዋጋት የተዘጋጁትና ዳዊትን ለመርዳት የመጡት መንታ ልብ የሌላቸው የዛቢሎን ሰዎች ሃምሳ ሺህ፤
\s5
\v 34 ከንፍታሌም ሰዎች አንድ ሺህ የጦር አለቆች፤ከእነርሱም ጋር ጋሻና ጦር የያዙ ሠላሳ ሰባት ሺህ ሰዎች፤
\v 35 ከዳን ሰዎች ለጦርነት የተዘጋጁ ሀያ ስምንት ሺህ ስድስት መቶ፤
\s5
\v 36 ከአሴር ሰዎች ልምድ ያላቸውና ከጦርነት የተዘጋጁ ወታደሮች አርባ ሺህ፤
\v 37 ከምስራቅ ዮርዳኖስ ከሮቤል፣ከጋድና ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ልዩ ልዩ ዐይነት መሣሪያ የታጠቁ አንድ መቶ ሃያ ሺህ ሰዎች።
\s5
\v 38 እነዚህ ሁሉ በሰራዊቱ ውስጥ ለማገልገል ፈቃደኞች የሆኑ ተዋጊዎች ናቸው፤ወደ ኬብሮን የመጡትንም ዳዊትም በእስራኤል ሁሉ ላይ ለማንገሥ ወስነው ስለ ነበር ነው።የቀሩትም እስራኤላዊያን ሁሉ ዳዊትን ለማንገሥ በአንድ ሐሳብ ጸኑ።
\v 39 የሚያስፈልጋቸውን ቤተ ሰቦቻቸው አዘጋጅተውላቸው ሰለ ነበር፣ሰዎቹ እየበሉና እየጠቱ ከዳዊት ጋር ሦስት ቀን ቁዩ።
\v 40 እንዲሁም ሩቅ ከሆነው ከይሳኮር፣ከዛቢሎንና ከንፍታሌም አገር ሳይቀር ጎረቤቶቻቸው በአህያ፣በግመል፣በበቅሎና በበሬ ጭነው ምግብ አመጡላቸው፤በእስራኤል ታላቅ ደስታ ሰለ ሆነ ዱቄት፣የበለስና የዘቢብ ጥፍጥፍ፣የወይን ጠጅ፣የወይራ ዘይት፣የቀንድ ከብትና በጎች በገፍ ቀርበው ነበር።
\s5
\c 13
\p
\v 1 ዳዊትም ሻለቆችና መቶ አለቆች ከሆኑት የጦር ሹማምቱ ሁሉ ጋር ተማከረ።
\v 2 ከዚያም ለመላምው የእስራኤል ማኅበር እንዲህ አለ፤''እንግዲህ ነገሩ መልካም መስሎ ከታያችሁ የአምላካችን የእግዚአብሔር ፍቃድ ከሆነ፤በእስራኤል ግዛት ሁሉ ለሚኖሩ በሩቅም ሆነ በቅርብ ላሉት ለቀሩትም ሆነ በቅርብ ላሉት ለቀሩት ወንድሞቻችን እንዲሁም በየራሳቸው ከተሞና መሰማሪያዎች የሚኖሩ ካህናትና ሌዋውያን መጥተው ከእኛ ጋር እንዲሰባሰቡ እንላክላቸው።
\v 3 በሳኦል ዘምን መንግሥት ሳንፈልገው የነበረውን የአምላካችንን ታቦት መልሰን ወደ እኛ እናምጣ።
\v 4 በገሩም በሕዝቡ ሁሉ ዘንድ ተቀባይነት ስላገኘ መላው ማኅበር ይህንኑ ለማድረግ ተስማማ።
\s5
\v 5 ስለዚህ ዳዊ የእግዚአብሔር ታቦት ከቂርያትይዓሪም ለማምጣት ከግብፅ ወንዝ ከሺሖር ጀምሮ እስከ ሐማት መተላለፊያ ድረስ የሰፈሩትን እስራኤላውያን ሁሉ ሰበሰበ።
\v 6 ዳዊትና እስራኤላዊያን ሁሉ በኩሩብና በኪሩብ መካከል የተቀመጠውን፣የእግዚአብሔር በይሁዳ ወዳለችው ቂርያትይዓሪም ወደ ተባለችው ወደ በኣላ ሄዱ።
\s5
\v 7 የእግዚአብሔርም ታቦት ከአሚናዳብ ቤት በእዲስ ሠረገላ ላይ እድርገው አመጡ፤ሠረገላውን ይነዱየነበሩትም ዖዛና አሒዮ ነበሩ።
\v 8 ዳዊትና እስራኤላዊያን ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ሆነው በቅኔና በበገና፣በመሰንቆ በከበሮ፣በጽናጽልና በመለከት በሙሉ ኅይላቸው በዓሉን በደስታ ያከብሩ ነበር።
\s5
\v 9 ወደ ኪዶን ዐውድማ በደረሱ ጊዜ በሬዎቹ አደናቅፏቸው ሰለ ነበር፣ዖዛ ታቦቱን ለመደገፍ እጁን ዘረጋ።
\v 10 ታቦቱን በእጁ ሰለ ነካ፣የእግዚአብሔር ቁጣ ዖዛን ላይ ነደደ፤ስለዚህም በዚያው በእግዚአብሔር ፊት ሞተ።
\v 11 የእግዚአብሔር ቁጣ ዖዛን በድንገት ስለ ቀሠፈው ዳዊት አዘነ፤ያም ቦታ እስከ ዛሬ ድረስ የዖዛ ስብራት ተብሎ ይጠራል።
\s5
\v 12 ዳዊት በዚያን ዕለት የእግዚአብሔር ታቦት ወደ እኔ እንዴት ማምጣት እንችላለሁ?''አለ።
\v 13-14 ስለዚህ ታቦቱን ወደ ዳዊት ከተማ በመውሰድ ፈንታ የጋት ሰው ወደ ሆነው ወደ አቢዳራ ቤት ከቤተ ሰቡ ጋር ሦስት ወር ተቀመጠ፤እግዚአብሔርም ቤተ ሰቡንና ያለውንም ሁሉ ባረከ።
\s5
\c 14
\p
\v 1 በዚህ ጊዜ የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ለዳዊት ቤተ መንግሥት እንዲሠሩ መልክተኞችን፣ድንጋይ ጠራቦዎችንና አናጢዎችም ከዝግባ ዕንጨት ጋር ላከ።
\v 2 ዳዊትም እግዚአብሄር በእስራኤል ላይ አንግሦ እንዳጽናውና ስለ ሕዝቡም ስለ እስራኤል ሲል መንግጅቱን ከፍ ከፍ እንዳደረገለት አስተዋለ።
\s5
\v 3 ዳዊትም በኢየሩሳሌም ብዙ ሚስቶች አገባ፤ከእነሱም ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ።
\v 4 በዚያ ሳለ የወለዳቸው የልጆች ስም ይህ ነው፤ሳሙስ፣ሶባብ፣ናታን፣ሰለሞን፣
\v 5 ኢያቤሐር፣ኤሊሱዔ፣ ኤሊፋላት፣
\v 6 ኖጋ፣ናፌቅ፣ያፍያ፣
\v 7 ኤሊሳማ፣ኤሊዳሄ፣ኤሊፋላት።
\s5
\v 8 ዳዊት በእስራኤል ሁሉ ላይ ተቀብቶ መንገሡን ፍልስጥኤማውያን በሰሙ ጊዜ፣እርሱን ፍለጋ በሙሉ ኅይላቸው ወቱ፤ዳዊት ይህን ሰምቶ ሰለ ነበር ሊገጥማቸውው ወጣ።
\v 9 በዚህ ጊዜ ፍልስጥኤማውያን ውጥተው የራፋይምን ሸለቆ ወረሩ።
\s5
\v 10 ስለዚህ ዳዊት፣''ወጥቼ በፍልስጥኤማዊያን ላይ አደጋ ልጣልን? አንተስ በእጄ አሳልፈህ ትሰጣቸዋለህን? ሲል እግዚአብሔር ጠየቀ።እግዚአብሔር ''አዎን ውጣ! በእጅህ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ''ብሎ መለሰለት።
\v 11 ስለዚህ ዳዊትና ሰዎቹ ወደ በኣልፐራሲም ወጡ፤በዚያም ድል አደረጋቸው።ዳዊትም ''ውሃ ነድሎ እንደሚውጣ ሁሉ እግዚአብሄርም ጠላቶችይን በእጄ አፈርሳቸው''አለ፤ከዚህ የተነሳ ያን ቦታ ''በኣልፐራሲም''ብለው ሰየሙት።
\v 12 ፍልስጥኤማውያን አማልዕክቶቻቸውን በዚያው ጥለዋቸው ስለ ነበር፣ዳዊትት በእሳት እንዲያቃጥሏቸው አዘዘ።
\s5
\v 13 ፍልስጥኤማውያን ሸለቆውን እንደ ገና ወረሩ፣
\v 14 ዳዊትም እንደገና እግዚአብሔር ጠየቀ።እግዚአብሔር እንዲህ ሲል መለሰለት ''ዙሪያውን ከበህ በሾላው ዛፍ ፊት ለፊት አደጋ ጣልባቸው እንጂ በቀጥታ ወደ ላይ አትውጣ፤
\s5
\v 15 በሾላው ዐናት ላይ የሰልፍ ድምፅ ስትሰማ ወዲያኑ ለጦርነት ውጣ፤ይህም የፍልስጥኤማውያንን ስራዊት ለመምታት እግዚአብሔር በፊትህ ወጥቶአል ማለት ነውና።
\v 16 ዝዝዚህ ዳዊት እግዚአብሔር እንዳለው አደረገ፤ከገባዖን ጀምሮ እስከ ጌዝር ድረስ ፍልስጥኤማውያንን መቷቸው።
\v 17 ከዚህም የተነሳ የዳዊት ዝና በየአገሩ ሁሉ ተሰማ፤እግዚአብሔርም መንግሥታት ሁሉ እንዲፈሩት አደረገ።
\s5
\c 15
\p
\v 1 ዳዊት በስሙ በተጠራችው ከተማ ለራሱ ብይቶችን ሠራ፤በእግዚአብሔር ታቦት ቦታ አዝጋጅቶ ድንኳን ተከለ።
\v 2 ከዚያም ዳዊት፣''የእግዚአብሔርን ታቦት እንዲሸከሙና ለዘላለም በፊቱ እንዲያገለግሉ እግዚአብሔር ከመረጣቸው ከሌዋውያን በቀር፣የእግዚአብሔርን ታቦት ማንም አይሸከምም ሲል አዘዘ።
\v 3 ዳዊት የእግዚያብሔር ታቦት ወዳዘጋጀለት ስፍራ እንዲያወጡ እስራኤላዊያን ሁሉ በኢየሩሳሌም ሰበስበ።
\s5
\v 4 የአሮንን ዘሮችና ሌዋዊያውያንኑም በአንድነት ሰበሰበ፤
\v 5 ከቀዓት ዘሮች፣አለቃውን ኡርኤልንና አንድ መቶ ሃያ የሥጋ ዘመዶቹን፤
\v 6 ከሜራሪ ዘሮች፤አለቃው ዓሣያንና ሁለት መቶ ሃያ የሥጋ ዘመዶቹን፤
\s5
\v 7 ከጌድሶን ዘሮች፤ አልቃው ኤሊኤልንና አንድ መቶ ሠላሳ የሥጋ ዘመዶቹን፤
\v 8 ከኤሊጻፍን ዘሮች፤አለቃውን ሽማያንና ሁለት መቶ የሥጋ ዘመዶቹን፤
\v 9 ከኬብሮን ዘሮች፤ አለቃው ኤሊኤልንና ሰማንያ የሥጋ ዘመዶቹ፤
\v 10 ከዑዝኤል ዘሮች፤አለቃውን አሚናሳብንና አንድ መቶ ዐሥራ ሁለት የሥጋ ዘመዶቹን።
\s5
\v 11 ከዚያም ዳዊት ከህናቱን ሳዶቅንና አብያታርን፣ሌዋውያኑን ኡርኤልን፣ዓሣያን፣ኢዩኤልን፣ሽማያን፣ኤሊኤልንና አሚናዳብን ጠርቶ፣
\v 12 እንዲህ አልቸው፤''እንግዲህ እናንተ የሌዋውያን ቤተ ሰብ አለቆች ሰለ ሆናችሁ፣እናንተና ወንድሞቻችሁ ሌዋውያን ራሳችሁን ቀድሱ፤ከዚያም የእስራኤል አምላክ የእግዚአብሔርን ታቦት ወደአዘጋጀሁለት ቦታ አምጡ።
\s5
\v 13 የአምላካችን የእግዚአብሔር ቁጣ በላያችን ላይ እንዲህ የነደደው እናንተ ሌዋውያኑ ቀድሞም ስላላመጣችሁት ነው፤እኛም ብንሆን ምን ማድረግ እንዳለብን በታዘዘው መሠረት አልጠየቅነውም።
\v 14 ስለዚህ ካህናቱና ሌዋውያኑ የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔር ታቦት ለማምጣት ራሳቸውን ቀደሱ።
\v 15 ሙሴ በእግዚአብሔር ቃል እንዳዘዘው፣ሌዋውያኑ የእግዚአብሔር ታቦት በትከሻቸው ላይ በሙሎጊያዎች አድርግገው ተሸከሙ።
\s5
\v 16 ዳዊትም በዜማ መሣሪያ ማለትም በመሰንቆ፣በበገና፣በፅናፅል እየታጀቡ የደስታ ዜማዎችን እያዜሙ መዘመራንን ከወንድሞቻቸው መካከል እንዲሾሙ ሌዋውያኑ መሪዎች ነገራቸው።
\v 17 ስለዚህ ሌዋውያኑ የኢዮኤልን ልጅ ኤማንን ሾሙ፤ከወንድሞቹም የበራክያን ልጅ አሳፍን፣ከወንድሞቻቸው ከሜራራ ዘሮች የቂሳን ልጅ ኤታንን ሾሙ፤
\v 18 ከእነሱም ጋር ወንድሞቻቸውን በደረጃ ተሾሙ፤እነሱም ዘካሪያስ፣ያዝኤል፣ሰሚራ ሞት፣ይሒኤል፣ዑኒን፣ኤልያብ፣በናያስ፣መዕሤያን፣መቲትያ፣ ኤሊፍሌሁ፣ሚቅኔያ፣ደግሞም በር ጠባቂዎቹ ዖቤድ ኤዶምና ይዒኤል ነበሩ።
\s5
\v 19 መዘመራኑ ኤማን፣አሳፍ ኤታን በናስ ጸናጽል ድምፁን ከፍ እድርገው እንዲያሰሙ ተሾሙ፤
\v 20 ዘካሪያስ፣ዓዝኤል፣መዕሤያና በናያስ ደግሞ በአላሞት ቅኝት መሰንቆ ይገርፉ ነበር።
\v 21 እንዲሁም መቲትያ፣ኤሊፍሌሁ፣ሚቅኔያ፣ዖብድኤዶም፣ይዒረድኤ፣ ዓዛዝያ፣በሺሚኒት ቅኝት በገና ይደረድሩ ነበር።
\s5
\v 22 የዝማሬው ኅላፊ ሌዋዊው አለቃ ክንያን ነበረ፤ይህን ኅላፊነት የወሰደው በዝማሬ የተካነ ስለ ነበር ነው።
\v 23 በራክያና ሕልቃና ያታቦቱ በር ጠባቂዎች ነበሩ፤
\v 24 ካህናቱ ሰበኒያ፤ኢዮሣፍጥ፣ናትናኤል፣ዓማሣይ፣ዘካሪያስ፣በናያስና አልዓዛር በእግዚአብሔር ታቦት ፊት መለከት ይነፋ ነበር።ዖቤድኤዶምና ይሒያ ደግሞ ያታቦቱ በር ጠባቂዎች ነበሩ።
\s5
\v 25 ስለዚህ ዳዊት የእስራኤል ሽማግሌዎችና የሻለቃው አዛዦች የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳኑን ታቦት ከዖቤድኤዶም ቤት በደስታ ለማምጣት ሄዱ።
\v 26 የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት የተሸከሙትን ሌዋውያን እግዚአብሔር ረድቶአቸው ስለ ነበር፣ሰባት ኮርማዎችና ሰባት አውራ በጎች ሠው።
\s5
\v 27 ታቦቱን የተሸከሙት ሌዋውያን ሁሉ፣መዘመራኑና የመዘመራኑ አለቃ ክናንያ የለበሱትና ዐይነት ከቀጭን በፍታ የተሠራ ልብስ ዳዊትም ለብሶ ነበር፤እንዲሁም በከፍታ የተሠራ ኤፋድ ለብሶ ነበር።
\v 28 በዚህ ሁኔታ መላው የእስራኤል ህዝብ በሆታ ቀንደ መለከትና እምቢልታ እየነፉ፣ጽናጽል እየጸነጸሉ፣መሰንቆና በገና እየደረደሩ የእግዚአብሔር የኪዳኑን ታቦት አመጡ።
\s5
\v 29 የእግዚአብሔር የኪዳኑ ታቦት ወደ ዳዊት ከተማ ሲገባ የሳኦል ልጅ ሚልኮል በመስኮት ሆና ተመለከተች ፤ንጉሥ ዳዊት ደስ ብሎት ሲያሸበሽብ አይታ በልቧ ናቀችው።
\s5
\c 16
\p
\v 1 ከዚያም የእግዚአብሔር ታቦት አምጥተው ዳዊት በተከለለት ድንኳን ውስጥ አኖሩት፤የሚዋጠል መሥዕዋትና የኅብረት መሥዕዋትም በእግዚአብሔር ፊት አቀረቡ።
\v 2 ዳዊት የሚቃጠለውን መሥዕዋትና የኅብረቱ መሥዕዋት ከሠዋ በኋላ፣ህዝቡን በእግዚአብሔር ስም ባረከ።
\v 3 ከዚያም ለእስራኤል ሁሉ ለወንዱም ልችሴቱም አንዳንድ ሙልሙል ዳቦ፣አንዳንድ ጥፍጥፍ ዘቢብ ሰጠ።
\s5
\v 4 በእግዚአብሔር ታቦት ፊት እንዲያገለግሉና ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ልመና፣ምስጋናና ውዳሴ እንዲቀርቡ ከሌዋውያን ሰዎች ሾሙ፤
\v 5 አለቃው አሳፍ ነበረ፤ከእርሱ ቀጥሎ ዘካሪያስ ሁለተኛ ሆኖ ተሾመ፤ከዚያም ይዒኤል፣ሰሚራሞት፣ይሒኤል፣መቲትያ፣ኤልያብ፣በናያስ፣ ዖቤድኤዶም፣ይዒኤል ተሾሙ፤እነሱም በመሰንቆና በበገና ይዘምሩ ነበር፤አሳፍ ደግሞ ጽናጽል የሚጸነጽል ሆኖ ተመደበ።
\v 6 እንዲሁም ካህናቱ በናያስና የሕዚኤል ዘውትር በእግዚአብሔር የኪዳኑ ታቦቱ ፊት መለከት እንዲነፉ ተመደቡ።
\s5
\v 7 በዚያም ቀን ዳዊት በመጀመሪያ ለአሳፍና ለሥራ ጓደኞቹ ይህን የእግዚአብሔር ምስጋና መዝሙር ሰጠ፤
\v 8 ለእግዚአብሔር ምስጋና አቅርቡ፤ስሙንም ጥሩ፤ለአሕዛብ ያደረገውን ሁሉ ንገሩ፤
\v 9 ዘምሩለት፤ውዳሴም አቅርቡለት፤ድንቅ ሥራውን ሁሉ ንገሩ፤
\s5
\v 10 በቅዱስ ስሙ ተጓደዱ፤እግዚአብሔር የሚፈልግ ሁሉ፤ልባቸው ሐሤት ያድርግ፤
\v 11 ወደ እግዚአብሔር ወደ ኅይሉ ተምልከቱ፤ዘውትር ፊቱን ፈልጉ፤
\s5
\v 12 ይደረጋቸውን ድንቅ ሥራዎች፣ታምራቱንና የሰጠውንም ፍርድ አስታውሱ፤
\v 13 እናንተ የባሪያው የእስራኤል ዘሮች፣እናንተ የተመረጣችሁ የያዕቆብ ልጆች።
\v 14 እርሱ እግዚአብሔር አምልካችን ነው፤ፍርዱም በምድር ሁሉ ላዬ ነው፤
\s5
\v 15 ኪዳኑን እስከ ዘላለም፣ይያዘዘውንም ቃል እስከ ሺህ ትውልድ ያስባል፤
\v 16 ከአብርሃም ጋር የገባውን ቃል ኪዳን፣ለይስሐቅ የማለውን መሐላ።
\v 17 ይህንንም ለያዕቆብ ሥርዐት አድርጎ አጸና፤ለእስራኤልም የዘላለም ኪዳን አደረገ፤
\v 18 እንዲህ ሱል ''የምትወርሰው ርስት እንዲሆን፣የከነዓንን ምድር ለአንተ እሰታለሁ።''
\s5
\v 19 ቁጥራቸው ገና ጥቂት ሳለ፤በርግጥ ጥቂትና መጻተኞች ሳሉ፤
\v 20 ከአንዱ ሕዝብ ወደ ሌላው ሕዝብ ከአንዱም መንግሥት ወደ ሌላው መንግሥት ተንከራተቱ።
\v 21 ማንም እንዲጨቁናቸው አልፈቅድም፤ስለ እነርሱም ነገሥታትን ገሠጸ፤
\v 22 እንዲህ ሲል፤''የቀባኋቸውን አትንኩ፤በነብያቴ ላይ ክፉ አታድርጉ።''
\s5
\v 23 ምድር ሁሉ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ማዳኑንም ዕለት ዕለት ዐውጁ።
\v 24 ክብሩን ለአሕዛብ ተናገሩ፤ድንቅ ሥራዎቹን ለሕዝቦች ሁሉ ንገሩ።
\s5
\v 25 እግዚአብሔር ታላቅ ነው፤ምስጋናውም ብዙ ነው፤ከአማልዕክትም ሁሉ በላይ ሊፈራ የሚገባው ነው።
\v 26 የአሕዛብ ሁሉ አማልክት ጣዖታት ናቸው፤እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ሠራ።
\v 27 በፊቱ ክብርና ሞገስ አለ፤ ብርታትና ደስታም በማድሪያው ስፍራ።
\s5
\v 28 የአሕዛብ ወገኖች ለእግዚአብሔር ስጡ፤ክብርና ኅይልን ለእግዚአብሔር አምጡ።
\v 29 ለስሙ የሚገባውን ክብር ለእግዚአብሔር ሰጡ፤መባ ይዛችሁ በፊቱ ቅረቡ፤በቅድስናውም ክብር ለእግዚአብሔር ሰገዱ።
\s5
\v 30 ምድር ሁሉ በፊቱ ትንቀጥቀጥ፤ዓለም በጽኑ ተመሥርታለች፤አትናወጥምም።
\v 31 ሰማያት ደስ ይባላቸው፤ምድር ሐሤት ታድርግ፤በአሕዛብ መካከል፣''እግዚአብሔር ነገሠ!''ይበሉ።
\s5
\v 32 ባሕርና በውስጧ ያለው ሁሉ ይናውጥ፤ሜዳዎችና በእርሷ ላይ ያሉ ሁሉ ሐሤት ያድርጉ።
\v 33 ያን ጊዜ የዱር ዛፎች በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይበላቸው፤በደስታ ይዘምራሉ፤በምድር ላይ ሊፈርዱ ይመጣልና።
\s5
\v 34 ቸር ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ፍቅሩንም ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።
\v 35 «አዳኛችን እግዚአብሔር ሆይ፤ታደገን፤ለቅዱስ ስምህ ምስጋና እንድናቀርብ፣በምስጋናም እንድንከብር ስብሰበን''ብላችሁ ጩኹ።
\s5
\v 36 ከዘላለም እስከ ዘላለም፣ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን።ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ፣''አሜን፤እግዚአብሔር ይመስገን''አለ።
\s5
\v 37 ዳዊትም ለእያንዳንዱ ቀን በተመደበው መሠረት ዘውትር እንዲያገለግሉ አሳፍና የሥራ ባልደረቦቹን በዚያው በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት ፊት ተዋቸው።
\v 38 እንዲሁም ዖቡድኤዶምና ሥልሳ ስምንቱ የሥራ ባልደረቦቹ አብረዋቸው እንዲያገለግሉ በዚያው ተዋቸው።የኤዶታም ልጅ ዖቤድኤዶምና ሖላ የቅጥሩ በር ጠባቂዎች ሆኑ።
\v 39 ዳዊት ካህኑን ሳዶቅንና የሥራ ባልደረቦቹን ካህናት በገባዖን ከፍተኛ ቦታ ላይ በሚገኘው በእግዚአብሔር ድንኳን ፊት ተዋቸው፤
\s5
\v 40 የተዋቸውም ለእስራኤል በተሰጠው ትእዛዝ መሠረት በእግዚአብሔር ሕግ እንደ ተጻፈው ሁሉ በመሠዊያው ላይ የሚቀርበውን የሚቃጠል መሥዕዋት ላይ የሚቀርበውን የሚቃጠል መሥዋዕት ጧትና ማታ በየጊዜው እንዲያቀርቡ ነው።
\v 41 ደግሞም፤''ፍቅሩ ለዘላለም ነውና''እያሉ ምስጋና እንዲያቀርቡ ኤማንና ኤዶታም እንዲሁም ተመርጠውና ስማቸው ተመዝግቦ የተመደቡ ሌሎችም አብረዋቸው ነበሩ።
\s5
\v 42 ድምፅ መለከቱንና ጽናጽሉን ለማሰማት፤ደግሞም መንፈሳዊ መዝሙር ሲዘመር ሊጠቀሙባቸው ሌሎች መሣሪያዎች ኅላፊዎች ኤማንና ኤዶታም ነበሩ፤የኤዶታምም ልጆች በሩን እንዲጠብቁ ተመድበው ነበር።
\v 43 ከዚያም ህዝቡ ተነሣ፤እያንዳንዱም ወደየቤቱ ሄደ።ዳዊትም ቤተ ሰቡን ለመባረክ ወደ ቤቱ ተመለሰ።
\s5
\c 17
\p
\v 1 ዳዊት በቤተ መንግሥቱ ተደላድሎ በተቀመጠበት ጊዜ፤ነቢዩ ናታንን''እነሆ እኔ ከዝግባ በተሠራ ቤት ውስጥ እኖራለሁ፤የእግዚአብሔር የኮዳኑ ታቦት ግን በድንኳን ውስጥ ይኖራል''አለው።
\v 2 ናታንም ለዳዊት፣''እግግዚአብሔር ከአንተ ጋር ስለሆነ፣ያሰብከውን ሁሉ እድርግ''ሲል መለሰለት።
\s5
\v 3 በዚያም ሌሊት የእግዚአብሔር ቃል ወደ ናታን መጥቶ እንዲህ አለው፤
\v 4 ''ሂድና ለባርያዬ ለዳዊት እንዲህ ብለህ ንገረው፤እግዚአብሔር የሚለውን ይህን ነው፤እኔ የምኖርበትን ቤት የምትሠራልኝ አንንተ አይደለህም።
\v 5 እስራኤልን ከግብፅ ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ፤ከአንዱ ድንኳን ወደ ሌላው ማደሪያ እሄድ ነበር እንጂ፣በቤት ውስጥ አልኖርሁም።
\v 6 ከእስራኤላዊያን ጋር በሄድኩባቸው ቦታዎች ሁሉ፣ሕዝቤን እንዲጠብቁ ላዘዝኋቸው መሮዎቻቸው ከቶ፣''ለምን ከዝግባ ዕንጨት ቤት አልሰራችሁልኝምያልሁበት ጊዜ አለን?፤
\s5
\v 7 ''ከእንግዲህ አሁንም ለባሪያዬ ለዳዊት እንዲህ ብለህ ንገረው፤የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሚለው ይህን ነው፤የሕዝቤ ይእስራኤል ገዥ እንድትሆን በጎችን ከመጠበቅና ከመከትተል አንሥቶ ወሰድሁህ።
\v 8 በሄድህበት ሁሉ ከአንተ አልተለየሁህም፤ጠላቶችህም ስምህን እንደ ምድር ታላላቅ ሰዎች ስም ገናና አደርገዋለሁ።
\s5
\v 9 ለሕዝቤ ለእስራኤል መኖሪያ ስፍራ እሰጥተዋለሁ፤የራሳቸውም መኖሪያ ስፍራ እንዲኖራቸው ከእንግዲህም በኋላ እንዳይናወጡ አደርጋቸዋለሁ።ክፉ ሰዎች በመጀመሪያ እንዳደረጉት ሁሉ፤ከእንግዲህ አይጨቁናቸውም፤
\v 10 ከዚህ ቀደም በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መሪዎች በሾምሁ ጊዜ ጨቋኞቹ ያደረጉትን ዛሬ አያደርጉትም፤ጠላቶቻችሁም ሁሉ አዋርዳቸዋለሁ።''እግዚአብሄር ቤት እንደሚሠራልህ በግልፅ እነግርሃለሁ፤
\s5
\v 11 ዘመንህን ጨርሰህ ወደ አባቶችህ በምትሄድበት ጊዜ፤ከአብራክህ ከተከፈሉት ልጆችህ አንዱ በእግርህ እንዲተካ አደረጋለሁ፤መንግሥቱንም አፅናለሁ፤
\v 12 ቤት የሚሠራልኝ እርሱ ነው፤እኔም ዙፋኑን ለዘላለም አፀናለሁ።
\s5
\v 13 አባት እሆነዋለሁ፤እርሱም ልጅ ይሆነኛል፤ፅኑ ፍቅሬን ከአንተ በፊት ከነበረው ላይ እንደወሰድሁ፣ከእርሱ ላይ ከቶ አልወስድም።
\v 14 በቤቴና በመንግሥቴ ላይ ለዘላለም እኖረዋለሁ፤ዙፋኑም ለዘላለም ይፀናል።''
\v 15 ናታንም የዚህን ሁሉ ራእይ ቃል ለዳዊት ነገረው።
\s5
\v 16 ከዚያም ንጉሥ ዳዊት ገባ፤በእግዚአብሔር ፊት ተቀምጦ እንዲህ አለ፤ ''እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፤ለመሆኑ እስከዚህ ያደረሰኸኝ እኔ ማን ነኝ? ቤተ ሰብይስ ምንድን ነው?
\v 17 አምላክ ሆይ፤ይህ በፊትህ በቂ እንዳልሆነ ቁጥረህ ስለ ወደፊቱ የባሪያህ ቤት ተናገረ።እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፤እኔንም ከሰዎች ሁሉ እጅግ የከበርረ ሰው አድርገህ ተመለከትኸኝ።
\v 18 ባሪያህን ስላከበትኸው፣ዳዊት ከዚህ በላይ ምን ማለት ይችላል? ባሪያህ እኮ ታውቀቃለህ፤
\s5
\v 19 እግዚአብሔር ሆይ፤ስለ ባሪያህ ብለህና እንደ ፈቃድህም መሠረት ይህን ታላቅ ነገር አድርግሃል፤እነዚህም ታላላቅ ተስፋዎች ሁሉ እንዲታወቁ አደረግህ።
\v 20 አቤቱ፤እንደ አንተ ያለ የለም፤በጆሮአቸን አንደ ሰማነው ሁሉ ከአንተ በቀር አምላክ የለም
\v 21 ከግብፅ ተቤዠተህ እንዳወጣኸው እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ያለ ማን አለ? እነርሱ እግዚአብሔር ለራሱ ሊቤዣቸው ናቸው፤በሕዝብህም ፊት ታላቅና አስፈሪ ነገሮችን በማድረግ መንግሥታትን በፊታቸው አሳደድህ።
\s5
\v 22 ሕዝብህንም እስራኤልን ለዘላለም የራስህ ሕዝብ አደረግኸው፤እግዚአብሔር ሆይ፤አንተም አምላክ ሆንህለት።
\v 23 እግዚአብሔር ሆይ፤አሁንም ስለባሪያህ ስለ ቤቱ የሰጠኸው ተስፋ ለዘላለም የጸና ይሁን፤የሰጠኸውንም ትተስፋ ፈፅም፤
\v 24 ይህም ስምህ ጸንቶ እንዲኖርና ለዘላለም ታላቅ እንዲሆን ነው።ከዚያም ሰዎች ''የእስራኤል አምላክ ጌታ እግዚአብሔር በእውነት የእስራኤል አምላክ ነው!''ይላሉ፤የባሪያህ የዳዊትም ቤት በፊትህ የጸና ይሆናል።
\s5
\v 25 አምላክ ሆይ፤ቤት እንደምትሠራለት ለባሪያህ ገልጸህለታል፤ስለዚህ ባሪያህ ወደ አንተ ለመጸለይ ድፍረት አገኘ።
\v 26 እግዚአብሄር ሆይ፤በእውነት አንተ አምላክ ነህ፤ይህንንም መልካም ተስፋ ለባሪያህ ስጥተሃል።
\v 27 በፊትህ ለዘላለም እንዲኖር አሁንም የባሪያህን ቤት ልትባርክ ወደሃል፤እግዚአብሔር ሆዩ፤የባረክኸውን አንተ ስለ ሆንህ፣ለዘላለም የተባረከ ይሆናል።
\s5
\c 18
\p
\v 1 ከዚህ በኋላ ዳዊት ፍልስጥኤማዊያንን ድል መትቶ ተገዢ አደረጋቸው፤ጌትንና በዙሪያዋም የሚገኙትን መንደሮች ከፍልስጥኤማዊያን እጅ ወስደ።
\v 2 እንዲሁም ዳዊት ሞዓባዊያንድል አደረጋቸው፤እነሱም ገባሮቹ ሆኑ፤ግብርም አመጡለት።
\s5
\v 3 ከዚያም በላይ ዳዊት በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ የነበረው ግዛት ለመቁጣጠር በሄደ ጊዜ፣የሱባን ንጉሥ አድርአዛርን እስከ ሐማት ድረስ ዘልቆ ወጋው።
\v 4 ዳዊትም አንድ ሺህ ሠረገላ. ሰባት ሺህ ፈረሰኛና ሃያ ሺህ እግረኛ ወታደር ማረከ፤አንድ መቶ የሠረገላ ፈረሳች ብቻ አስቀርቶ የቀሩትን ቋንጃቸውን ቁረጠ።
\s5
\v 5 ሶርያውያንም የሱባን ንጉሥ እድርአዛርን ለመርዳት ከደማስቆ በመጡ ጊዜ፣ከእነሱ ሃያ ሁለት ሺህ ሰው ገደለ።
\v 6 ከዚያም በሶርያ ግዛት ውስጥ ባለችው ወደማስቆ የጦር ሰፈር ፤አቋቋመ፤ሶርያውያን ገባሮቹ ሆኑ፤ግብርም አመጡለት።እግዚአብሔርም ዳዊትን በሄደበት ሁሉ ድል አጎናፀፈው።
\s5
\v 7 ዳዊትም የአድርአዘር ጦር አለቆች ያነገቡትን የወርቅ ጋሻ ወሰደ፤ወደ ኢየሩሳሌም አመጣው።
\v 8 ዳዊት ከአድርአዛር ከተሞች ከጢብሐትና ከኩን እጅግ ብዙ ናስ ወስደ፤ሰለሞን የናሱን ባሕር፤ዐምዶቹንና ልዩ ልዩ የናስ ዕቃዎቹን የሠራው በዚሁ ነበር።
\s5
\v 9 የሐማት ንጉሥ ቶዑ ዳዊት የሱባን ንጉሥ የአድርአዛርን ሰራዊት ሁሉ ድል እንደመታ ሲሰማ፣
\v 10 እጅ እንዲነሳውና ደስታውንም እንዲገልጥለት ልጁን አዳራምን ወደ ንጉሥ ዳዊት ላከው፤ቶዑ ከአድርአዛር ጋር ብዙ ጊዜ ጦርነት ገጥሞ ነበር።አዶራምም ከወርቅ፣ከብርና ከነስ የተጀሩ ልዩ ልዩ ዕቃዎች አመጣለት።
\v 11 ንጉሥ ዳዊት ከሞዓብ፣ከአሞናዊያን፣ከፍልስጥኤማውያንና ከአማሌቃውያን ከእነዚህ ሁሉ መንግሥትታት የማረከውን ወርቅና ብር ከዚህ ቀደም እንዳደረገው ሁሉ፤እነዚህንም ዕቃዎች ለእግዚአብሔር ቀደሰ።
\s5
\v 12 የጹሩያ ልጅ አቢሳ በጨው ሸለቆ ዐሥራ ስምንት ሺህ ኤዶማውያን ገደለ።
\v 13 እርሱም በኤዶም የጦር ሰፈሮች አቋቋም፤ኤዶማውያንም ሁሉ ለንጉሥ ዳዊት ገባሮች ሆኑ።እግዚአብሔር ዳዊትን በሄደበት ሁሉ ድል አጎናጸፈው።
\s5
\v 14 ዳዊት በመላው እስራኤል ላይ ነገሠ፤ለሕዝቡም ሁሉ ፍትሕና ጽድቅን አሰፈናላቸው።
\v 15 የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ የሰራዊት አዛዥ ነበረ፤የአሒሉድ ልጅ ኢዮሣፍጥ ደግሞ የቤተ መዛግብቱ ኃላፊ ነበረ።
\v 16 የአኪጦብ ልጅ ሳዶቅና የአቤምሜሌክ ልጅ አብያታር ካህናት ነበሩ፤ሱሳ ደግሞ ጸሓፊ ነበረ።
\v 17 የዮሄድ ልጅ በናያስ የከሊታውያንና የፊልታውያን አዛዥ ነበረ።የዳዊት ወንዶች ልጆች ከንጉሥ ቀጥሎ የበላይ ሹማምት ነበሩ።
\s5
\c 19
\p
\v 1 ከዚህ በኋላ የአሞናውያን ንጉሥ ናዖስ ሞተ. ልጁም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።
\v 2 ዳዊትም ''አባቱ ለእኔ በጎ ነገር እንዳደረገልኝ እስቲ እኔም ለናዖስ ልጅ ለሐኖን በጎ ነገር ላድርግለት''ብሎ አስብ።ስለዚህ ዳዊት ስለ አባቱ ሞት ሐዘኑን ለመግለጽ ወደ ሐኖን መልክተኞችን ላከ።የዳዊት ሰዎች ሐናቸውን ለመግለጽ ሐኖን ወደሞኖርበት ወደ አሞናውያን ምድር በመጡ ጊዜ፣
\v 3 የአሞናውያን መኳንንት ለሐኖን ''ዳዊት ሀዘኑን ለመግለጽ ሰዎችን ወደ አንተ የላከው አባትህን አክብሮ ይመስልሃን? ሰዎች ወደ አንተ የመቱት አገሩቱን ለመመርመር፣ለመሰለልና ለመያዝ አይደለምን? አሉት።
\s5
\v 4 ስለዚህ ሐኖን የዳዊትን ሰዎች ይዞ ላጫቸውል ልብሳቸውንም እስከ መቀመጫቸው ድረስ መኻል ለመኻል ቀዶ ሰደዳቸው።
\v 5 በሰዎቹ ላይ የደረሰባቸውን ዳዊት በሰማ ጊዜ እጅግ ዐፍረው ስለ ነበር፣ወደ እነርሱ መልክተኞችን ላከ፤ንጉሥም፣''ጢማችሁ እስኪያድግ ድረስ በኢያኮር ቁዩና ከዚያ በኋላ ትመጣላችሁ''አለ።
\s5
\v 6 አሞናውያን በዳዊት ዘንድ እንደ ተጠሉባወቁ ጊዜ፣ሐኖንና አሞናውያን ከመሰጴጦምያ፣ከአራምመዓካና ከሱባ ሠረገሎችንና ፈረሶችን ለመከራየት አንድ ሺህ መክሊት ብር ላኩ፤
\v 7 ከዚያም ሠላሳ ሁለት ሺህ ሠረገሎችንና ፈረሶኞችን እንዲሁም የመካዓን ንጉሥና ወታደሮች በገንዘብ ቀጠሩ፤እነርሱም መጥተው በሜድባ አጠገብ ሲሰፍሩ፣አሞናውያን ደግሞ ከየከተሞቻቸው ተሰብስበው ለጦርነት ወጡ።
\s5
\v 8 ዳዊት ይህን ሲሰማ ኢዮአብንና መላውን ተዋጊ ሰራዊት ላከ።
\v 9 አሞናውያንም መጥተው ወደ ከተማቸው በሚያስገባው በር ላይ ለጦርነት ተሰለፉ፤የመጡት ነገሥታት ደግሞ ብቻቸውን በሜዳው ላይ ነበሩ።
\s5
\v 10 ኢዮአብም ከፊቱና ከኋላው ጦር መኖሩንና አየ፤ስለዚህ በእስራኤል የታወቁትን ጀግኖች መርጦ ሶርያውያንን እንዲገጥሙ አሰለፋቸው።
\v 11 የቀሩትም ሰዎች በወንድሙ በአቢሳ ሥጋ ሆነው አሞናውያንን እንዲገጥሙ አስለፋቸው።
\s5
\v 12 ኢዮአብም እንዲህ አለ፤''ሶርያውያን ከበረቱብኝ አንተ ትረዳኛለህ''አሞናውያን ከበረቱብህ ደግሞ እኔ እረዳሃለሁ።
\v 13 እንግዲህ በርቱ፤ስለ ሕዝባችንና ስለ አምላካችን ከተሞች ብለን በጀግንነት እንዋጋ፤እግዚአብሔር ደስ ያሰኘውን ያድርግ።''
\s5
\v 14 ከዚያም ኢዮአብና አብረውት ያሉት ወታደሮች ሶርያውያን ለመዋጋት ወደ ፊት ገሠገሠ፤ሶርያውያንም ከፊታቸው ሸሹ።
\v 15 አሞናውያንም ሶርያውያን መሸሻቸውን ሲያዩ፣እርሱም ከውንድሙ ከአቢሳ ፊት ሸሽተው ወደ ከተማይቱ ገቡ፤ስለዚህ ኢዮአብ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ።
\s5
\v 16 ሶርያውያን በእስራኤል መሸነፋቸውን ሲያዩ፣መልክተኞችን ልከው ከኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ ያሉትን ሶርያዊያን አስመጡ፤እነዚህንም የሚመራቸው የአድርአዛር ስራዊት አዛዥ ሾፋክ ነበረ።
\v 17 ዳዊት ይህን ሲሰማ፣እስራኤልን ሁሉ ሰብስቦ ዮርዳኖስን ተሻገረ፤ወደፊት በመገሥገሥም ከፊት ለፊታቸው የውጊያ መሥመሩን ያዘ።ዳዊትም ሶርያውያንን ጦርነት ለመግጠም ወታደሮቹን አሰለፈ፤እነርሱም ተዋጉት።
\s5
\v 18 ይሁን እንጂ ከእስራኤል ፊት ሸሹ።ዳዊትም ሰባት ሺህ ሠረገለኞችና አርባ ሺህ እግረኛ ወታደሮች ገደለ።የሠራዊታቸው አዛዥ ሾፋክም በጦርነት ላይ ሞተ።
\v 19 የአድርአዛርም ሹማምት በእስራኤል መሸነፋቸውን ሲያዩ፣ከዳዊት ጋር ታረቁ፤ገባሮቹም ሆኑ።ስለዚህ ሶርያውያን ከዚህ ጊዜ ጀምሮ አሞናውያንን ለመርዳት ፍቃደኞች አልሆኑም።
\s5
\c 20
\p
\v 1 ነገሥታት ለጦርነት በሚሄዱበት በፈደይ ወራት፣ኢዮአብ የጦር ሰራዊቱን እየመራ ሄዶ የአሞናውያንን አገር አጠፋ፤ወደ ራባትም ሄዶ የአሞናውያንን አገር አጠፋ፤ወደ ራባትም ሄዶ ከበባት፤ዳዊት ግን ኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር።ኢዮአብም ራባትን ወግቶ አፈራረሳት፤
\s5
\v 2 ዳዊት የንጉሣቸውን ዘውድ ከራሱ ላይ ወሰደ፤ክብደቱም አንድ መክሊት ወርቅ ነበረ፤ይህንንም በዳዊት ራስ ላይ ጫኑለት፤እንዲሁም ከከተማይቱ እጅግ ብዙ ምርኮ ወሰደ።
\v 3 በዚያ የነበረውን ሕዝብ አውጥቶ መጋዝ፣ዶማና መጥረቢያ ይዘው እንዲሠሩ አደረጋቸው።ዳዊት በሌሎቹም የአሞን ከተሞች ሁሉ ይህንኑ አደረጉ።ከዚያም ዳዊትና መላው ሰራዊቱ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።
\s5
\v 4 ከዚያም በኋላ ከፍልስጥኤማዊያን ጋር በጌዝር ጦርነት ተደረገ፤በዚያ ጊዜ ኩሳታዊው ሴቦካይ የራፋይም ዘር የሆነውን ሲፋይን ገደለ፤ፍልስጥኤማውያንም ድል ተመቱ።
\v 5 ከፍልስጥኤማውያን ጋር ሌላ ጦርነት ተደረገ፤የያዒር ልጅ ኤልያናን የጦሩ የቦውፍረቱ እንደ ሽማኔ መጠቅለያ የሚያህለውን የጌት ተወላጅ የሆነውን የጎልያድን ወንድም ላሕሚን ገደለ።
\s5
\v 6 ደግሞም ጌት ላይ በተደረገ ሌላ ጦርነት፣በእጆቹና በእግሮቹ ላይ ስድስት ስድስት ጣት በድምሩ ሃያ አራት ጣት የነበሩት አንድ ግዙፍ ሰው ነበረ፤ይህም እንደዚሁከራፋይም ዘር ነበረ።
\v 7 እርሱም እስራኤልን በተገዳደረ ጊዜ የዳዊት ወንድም የሳምዓ ልጅ ዮናታን ገደለው።
\v 8 በጌት የነበሩ የራፋይም ዘሮች እነዚህ ናቸው፤እነሱም በዳዊትና ሰዎቹ እጅ ወደቁ።
\s5
\c 21
\p
\v 1 ሰይጣን በእስራኤል ላይ ተነሥቶ ዳዊት የእስራኤልን ሕዝብ እንዲቁጥር አነሣሣው።
\v 2 ዳዊትም ኢዮአብንና የሰራዊቱን አዛዦች፤''ሄዳችሁ ከቤርሳቤህ እስከ ዳን ያሉትን እስራኤላዊያን ቁጠሩ፤ከዚያም ምን ያህል እንደ ሆኑ ዐውቅ ዘንድ ንገሩኝ አላቸው።
\v 3 ኢዮአብ ግን፣እግዚአብሔር የእስራኤል ሰራዊት አሁን ካለው በላይ በመቶ ዕጥፍ ያብዛው፤ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፤ሁልስ ቢሆኑ የጌታዬ ተገዢዎች አይደሉምን? ታዲያ ጌታዬ ይህን ማድረግ ለምን አስፈለገው? ለምንስ በእስራኤል ላይ በደል ያመጣል?''አለ።
\s5
\v 4 ይሁን እንጂ የንጉሥ ቃል ኢዮአብን አሸነፈው፤ስለዚህ ኢዮአብ ወጣ፤በመላው እስራኤል ከተዘዋወረ በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ።
\v 5 ኢዮአብም የተዋጊዎቹን ሰዎች ቁጥር ለዳዊት አቀረበ፤እነዚህም በመላው እስራኤል አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ሺህ፣በይሁዳ ደግሞ አራት መቶ ሰባ ሺህ ሲሆኑ፣ሁሉም ሰይፍ መምዘዝ የሚችሉ ነበሩ።
\s5
\v 6 ነገር ግን የንጉሡ ትእዛዝ በእርሱ ዘንድ አስጸያፊ ነበረና፣ኢዮአብ የሌዊንና የብንያም ነገድ ጨምሮ አልቁጠረም።
\v 7 ይህ ትእዛዝ በእግዚአብሄር ዘንድ የተጠላ ነበር፤ስለዚህ እግዙአብሔርን ቀጣ።
\v 8 ከዚያም ዳዊት እግዚአብሔርን፣''ይህን በማድረጌ እጅግ በድያለሁ፤የፈጸምኩትም የስንፍና ሥራ ስለሆነ፣የባሪያህን በደል እንድታስወግድ እለምንሃለሁ''አለ።
\s5
\v 9 እግዚአብሔር የዳዊት ባለ ራእይ የሆነውን ጋድን እንዲህ አለው፤
\v 10 ሂድና ለዳዊት እንዲህ ብለህ ንገረው፤እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፤እነሆ፣ሦስት ምርጫ ሰጥሃለሁ፤በአንተ ላይ እንዳደርስብህ እንዱን ምረጥ።''
\s5
\v 11 ስለዚህ ጋድ ዳዊት ሄዶ እንዲህ አለው፤''እግዚአብሔር የሚለው ይህን ነው፤አንዱን ምረጥ፤
\v 12 የሦስት ዓመት ራብ ወይስ የጠላቶችህን ሰይፍ ለሦስት ወር አይሎብህ ተሰዶ መጥፋት ወይስ ሦስት ቀን የእግዚአብሔር ስይፍ መቅሠፍት በምድሪቱ ላይ ወርዶ የእግዚአብሔር መልአክ እስራኤልን ሁሉ ያጥፋ? እንዲህ ላልከኝ ምን እንደምመልስ ቁርጡን ነገረኝ።
\s5
\v 13 ዳዊትም ጋድን፣''ችጅግ ተጨንቅይአለሁ፤ምሕረቱ ታላቅ ስለሆነ በእግዚአብሔር እጅ መውደቅ ይሻለኛል፤በሰው እጅስ አልወድቅ''አለ።
\v 14 እለዚህ እግዚአብሔር በእስራኤል ሰባ ሺህ ሰው ዐለቀ።
\v 15 እንዲሁም እግዚአብሔር እየሩሳሌምን እንዲያጠፋ መልአክ ላከ፤መልአኩም ሊያጠፋት ሲል እግዚአብሔር አይቶ ስለሚያደርሰው ጥፋት ዐዘን፤ህዝቡን የሚያጠፋውንም መልአክ፣''እጅህን መልስ''አለው።የእግዚአብሔር መልአክ በኢያቡሳዊያ በኦርና ዐውድማ አጠገብ ቆሞ ነበር።
\s5
\v 16 ዳዊት ቀና ብሎ ሲመለከት፣የእግዚአብሔር መልአክ በሰማይና በምድር መካከል ቆሞ አየ፤መልአኩም በኢየሩሳሌም ላይ የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ ይዞ ነበር፤ከዚያም ዳዊትና ሽማግሌዎች ማቅ እንደሚለብሱ በግንባራቸው ተደፉ።
\v 17 ዳዊት እግዚአብሔር ''ተዋጊዎቹ እንዲቁጠሩ ያዘዝሁ እኔ እይደለሁም? ኅጢአት የሠራሁበትም ሆነ የበደልሁት እኔ ነኝ፤እነዚህ እኮ በጎች ናቸው፤ታዲያ እነርሱ ምን አደረጉ? እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤እጅህ በእኔና በአባቴ ቤት ላይ ትሁን እንጂ፣መቅሠፍት በሕዝብህ ላይ አይውረድ''አለ።
\s5
\v 18 ከዚያም እግዚአብሔር መልአክ ዳዊት ወጥቶ በአቡሳዊያን በኦርና ዐውድማ ላይ ልችእግዚአብሔር መሠዊያ ይሠራ ዘንድ እንዲነግረው ጋድን አዘዘው።
\v 19 ዳዊትም ጋድ በእግዚአብሔር ስም በነገረው ቃል መሠረት ለመፈፀም ውጣ።
\v 20 ኦርና ስንዴ በመውቃት ላይ ሳለዘወር ሲል መለአኩን አየ፤አብረውት የነበሩት አራት ወንዶች ልጆችም ተሸሸጉ።
\s5
\v 21 ዳዊት ወደ እርሱ እየቀረበ መጣ፤ኦርናቀና ብሎ ሲመለከት፣ዳዊትን አየው፤ከዐውድማውም ወጥቶ መሬት ላይ በግንባሩ ተደፍቶ ዳዊትን እጅ ነሣ።
\v 22 ዳዊትም፣''በሕዝቡ ላይ የወረደው መቅሠፍት እንዲወገድ ለእግዚአብሔር መሠዊያ እሠራ ዘንድ ዐውድማህን ልውሰደው፤ሙሉውን ዋጋ እከፍልሃለሁ''አለው።
\s5
\v 23 ኦርናም ዳዊትም፣''እንዲሁ ወስደው፤ጌታዬ ንጉጅ ደስ ያለውን ያድርግ፤እነሆ ለሚቃጠል መሥዋዕት በሬዎቹን፣መውቂያ በትሮቹን ለማቀጣጠያ ዕንጨት፣ስንዴው ደግሞ ለእህል ቁርባን እንዲሆን እሰጣለሁ፤ሁሉንም እኔ እሰጣለሁ።አለ።
\v 24 ንጉሥ ዳዊት ግን ለኦርና ''አይደረግም፤ሙሉውን ዋጋ እኔ እከፍላለሁ፤የአንተ የሆነውን ለእግዚአብሔር ለማውረብ አልፈልግም፤ዋጋ ያልከፈልኩበትም የሚቃጠል መሥዋዕት እድርጌ አላቀርብም'' ሲል መለሰለት።
\s5
\v 25 ስለዚህ ዳዊት ለኦርና የቦታውን ዋጋ ስድስት መቶ ስቅል ወርቅ ከፈለ።
\v 26 ዳዊትም በዚያ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠርቶ የሚቃጠል መሥዕዋትና የኅብረት መሥዋዕት አቀረበ።እግዚአብሔርም ጠራ፤እግዚአብሔርም የሚቃጠል መሥዕዋት በሚቀርብበት መሠዊያ ላይ ከሰማይ በእሳት መለሰለት።
\v 27 ከዚያም እግዚአብሔር ለመልአኩ ተናገረ፤መልአኩም ሰይፉን ወደ አፎቱ መለሰ።
\s5
\v 28 በዚያን ጊዜ ዳዊት፤እግዚያብሔር በኢያቡሳዊው በኦርና ዐውድማ ላይ እንደ መለሰለት ሲያይ፤በዚያው ቦታ መሥዕዋት ማቅረብ ጀመረ።
\v 29 ሙሴ በምድረ በዳ የሠራው የእግዚአብሔር ማደሪያ ድንኳንና የሚቃጠል መሥዕዋት የሚቀርብበት መሠዊያ በዚያ ጊዜ በገባዖን ኮረብታ ላይ ነበረ።
\v 30 ዳዊት የእግዚአብሔር መልአክ ሰይፍ ሰለፈራ ወዲያ ሄዶ እግዚአብሔር ለመጠየቅ አልቻለም።
\s5
\c 22
\p 
\v 1 ከዚያም ዳዊት፣''ከእንግዲህ የእግዚአብሔር አምላክ ቤት በዚህ ይሆናል፤እንዲሁም ስለ እስራኤል የሚቃጠል መሥዕዋት የሚቀርብበት መሠዊያ በዚሁ ይቆማል''አለ።
\v 2 ስለዚህ ዳዊት በእስራኤል የሞኖሩ መጻተኞች እንዲሰበሰቡ አዘዘ፤ከመካከላቸም እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የሚሠራበትን ጥጋብ ድንጋይ እንዲያዘጋጁ ጠራቢዎች መደበ።

\s5
\v 3 ለቅጥር በሮች ምስማርና ማጠፊያ የሚሆን ብዙ ብረትና ከብዛቱ የተነሣ ሊመዘን የማይችል ናስ አዘጋጀ።
\v 4 እንዲሁም ሲዶናውያንና ጢሮሳውያን በብዛት አውጥተውለት ስለ ነበር፣ስፍር ቁጥር የሌለው የዝግባ ዕንጨት አሰናዳ።
\v 5 ዳዊትም፣''ልጅ ሰሎሞን ወጣት ነው፤ልምዱም የለውም፤ለእግዚአብሔር የሚሠራው ቤተ መቅደስ ደግሞ እጅግ የሚያምር፣በአሕዛብም ሁሉ ዘንድ አለበት፤ስለዚህ ሁሉንም እኔ አዘጋጃለሁ''እንዳለው ዳዊት ከመሞቱ በፊት በብዛት አዘጋጀ።

\s5
\v 6 ከዚያም ልጁን ሰሎሞንን ጠርቶ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚያብሔር ቤት እንዲሥራ አዘዘው።
\v 7 ዳዊትም ሰሎሞን እንዲህ አለ፤''ልጄ ሆይ ለአምላክህ እግዚአብሔር ስም ቤት ለመሥራት በልቤ አሰብ ነበር፤
\v 8 ነገር ግን ከእግዚአብሔር እንዲህ የሚል ቃል መጣልኝ፤''አንተ ብዙ ደም አፍስሰሃል፤በፊቴ በምድር ላይ ብዙ ደም ያፈሰስህ ስለሆነ አንተ ለስሜ ቤት አትሠራልኝም፤

\s5
\v 9 ነገር ግን የሰላምና የዕረፍት ሰው የሆነ ልጅ ትወልዳለህ፤ በየአቅጣጫው ካሉ ጠላቶቹ ዐሳርፈዋለሁ፤ ስሙም ሰሎሞን ይባላል። በዘመኑም ለእስራኤል ሰላምና ጸጥታን እሰጣለሁ።
\v 10 ለስሜ ቤት የሚሰራልኝ እርሱ ነው። እርሱ ልጅ ይሆነኛል 'እኔም አባት እሆነዋለሁ። ዙፋንም በእስራኤል ላይ ለዘላለም አጸናለሁ።

\s5
\v 11 አሁንም ልጅ ሆይ፤ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን፤ እንድትፈጽሙ በተናገረውም መሠረት፣ ተሳክቶልህ የአምላክን የእግዚአብሔር ቤት ለመሥራት ያብቃህ።
\v 12 በእስራኤል ላይ አለቃ ባደረገህ ጊዜ የአምላክህ እግዚአብሔርን ትእዛዝ ትፈጽም ዘንድ እግዚአብሔር ጥበብንና ማስተዋል ይስጥህ።
\v 13 ችግዚአብሔር በሙሴ አማካኝነት ለእስራኤል የሰጠውን ሕጉንና ሥርዐቱን ተጠንቅቀን ብትጠብቅ ይሳካልሃል፤ አይዞህ ጠንክር፤ በርትስ፤ ተስፋም አትቁረጥ።

\s5
\v 14 ''ለእግዚአብሔር ቤት እንዲሆንም አንድ ሺህ መክሊት ወርቅ፣ አንድ ሚሊዮን መክሊት፣ ብር፣ ከብዛቱ የተነሣ ሊመዘን የማይቻል ናስና ብረት ለማዘጋጅ በተቻለኝ ሁሉ ጥሬአለሁ። ደግሞም እንጨትና ድንጋዮች አዘጋጀሁ፤ በተረፈ አንተ ጨምርበት።

\s5
\v 15 ድንጋይ ጠራቢዎች፣ግን በኞች አናጢዎች የሆኑ ልዩ ሙያ የተጠበቡ ሰዎች አሉህ፤
\v 16 አነዚህ ቁጥራቸው እጅግ የበዛ የውርቅ፣የብር፣የናስና የብረት ሠራተኞች ናቸው።በል ሥራህን ጀምር፤እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን።''

\s5
\v 17 ከዚያም ዳዊት የእስራኤል መሪዎች ሁሉ ልጁን ሰሎሞንን እንዲረዱት አዘዘ፤
\v 18 እንዲህም አለ፤''እግዚአብሔር አምላካችን እስካሁን ከእናንተ ጋር አይደለምን? በየአቅጣጫውስ ዕረፍትን ስጥቷችሁ የለምን? የምድሪቱንም ነዋሪዎች በእጄ አሳልፎ ሰጥቶኛል፤ምድሪቱም ለእግዚአብሔር ለሕዝቡ ተገዝታለች።
\v 19 አሁንም እግዚአብሔር የኪዳኑን ታቦትና ንዋያት ቅዱሳቱን ለእግዚአብሔር ስም ወደሚሠራው ቤተ መቅደስ አምጥታችሁ የአምላክ የእግዚአብሔር መቅድደስ ሥሩ።
\s5
\c 23
\p 
\v 1 ዳዊት በሽመገለና ዕድሜው በገፋ ጊዜ፤ልጁን ሰሎሞንን በእራኤል ላይ አነገጀው።
\v 2 እንዲሁም መላውን የእስራኤል መሪዎች፣ካህናቱ ሌዋውያኑን ሁሉ በአንድነት ሰበሰበ።
\v 3 ዕድሜውቸው ሥላሳና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ተቁጠሩ፤ቁጥራቸውም በጠቅላላው ሠላሳ ስምንት ሺህ ነበረ

\s5
\v 4 ዳዊትም እንዲህ አለ፤ ''ከእነዚህ መካከል ሃያ አራቱ ሺህ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ሥራ ይቁጣጠሩ፤ ስድስቱ ሺህ ደግሞ ሹሞችና ዳኞች ይሁኑ፤
\v 5 አራቱ ሺህ የቅጥሩ በር ጠባቂዎች ይሁኑ፤ አራት ሺህ ደግሞ ለዚሁ ብዬ ባዘጋጀሁት የዜማ መሣሪያ እግዚአብሔር ያመስግኑ''።
\v 6 ዳዊትም ሌዋውያኑን በሌዊ ልጆች በጌድሶን፣ በቀነዓና በሜራሪ በየጎሣቸው መደባቸው።

\s5
\v 7 ከጌድሳናውያን ወገን፤ ለአዳን፣ሰሜኢ።
\v 8 የለእአዳን ወንዶች ልጆች፤ የመጀመሪያው ይሒኤል፣ ዜቶም፣ ኢዮኤል፣ባጠቃላይ ሦስት ናቸው።
\v 9 የስማኢ ወንዶች ልጆች፤ ሰሎሚት፣ ሀዝዝኤል፣ ሐራን፣ ባጠቃላይ ሦስት ናቸው። እነዚህ የለአዳን ቤተሰብ አለቆች ናቸው።

\s5
\v 10 የስማኢ ወንዶች ልጆች፤ ኢኢት፣ ዚዛ፣ የዑስ፣ በሪዓ፣ እነዚህ አራቱ የስሚኤ ልጆች ናቸው።
\v 11 የመጀመሪያው ኢኢት፣ ሁለተኛው ደግሞ ዚዛ፣ ነበረ የዑስና በሪዓ ግን ብዙ ወንዶች ልጆች አልነበሯቸውም፤ ስለዚህ የተቁጥዐሩት በሥራ መደብ እንደ ቤተሰብ ሆነው ነው።

\s5
\v 12 የቀነዓት ወንዶች ልጆች፤ እንበረም፣ ይስዓር፣ ኬብሮን፣ ዑዝኤል፣ ባጠቃላይ አራት ናቸው።
\v 13 የእንበረት ወንዶች ልጆች፤ አሮን፣ ሙሴ። አሮን የተቀደሰ እንዲሆን ተለየ፤ እርሱና ዘሮቹ ለዘላለም ቅዱስ የሆኑትን ነገሮች እንዲቀደሱ፣ እግዚአብሔር ፊት መሥዕዋት እንዲያቀርቡ፤ በፊቱ እንዲያገለግሉና በስሙም ለዘላለም እንዲባረኩ ተለዩ።
\v 14 እግዚአብሔር ሰው የሙሴ ወንዶች ልጆችም እንደ ሌዊ ነገድ ሆነው ተቁጠሩ።

\s5
\v 15 የሙሴ ወንዶች ልጆች፤ ጌርሳም፣ አልዓዛር።
\v 16 የጌሳም ዘሮች፤ ሱባኤል።
\v 17 የአልዓዛር ዘሮች፤ የመጀመሪያው ረዓብያ ነበረ።አልዓዛር ሌሎች ወንዶች ልጆች ግን እጅግ ብዙ ነበሩ።
\v 18 የይስዓር ዶዶችች ልጆች፤ የመጀመሪያው ሰሎሚት።

\s5
\v 19 የኬብሮን ወንዶች ልጆች፤ የመጀመሪያው ዬሪያ፣ ሁለተኛው አማርያ፣ ሦስተኛው የሕዚኤል፣ አራተኛ ይቅምዓም ነበሩ።
\v 20 የዑዝኤል ወንዶች ልጆች፤ የመጀመሪያው ሚካ፣ ሁለተኛው ይሺያ ነበሩ።

\s5
\v 21 የሜራሪ ወንዶች ልጆች፤ ሚሖሊ፣ ሙሲ፣ የሞሐሊ ወንዶች ልጆች አልዓዛር ቂስ ነበሩ።
\v 22 አልዓዛር ወንድ ልጅ ሳይወልድ ሞተ፤ ልጆቹ ሴቶች ብቻ ነበሩ፤ እርሱንም የአጎታቸው የቂስ ልጆች አገቡአቸው።
\v 23 የሙሲ ወንዶች ልጆች፤ ሞሖሊ፣ ዔደር፣ ኢያሪሙት ባጠቃላይ ሦስት ናቸው።

\s5
\v 24 እንግዲህ እነዚህ የቤተሰብ አለቆች ሆነው እያንዳንዳቸው በየስማቸው ተመዝግበው የተቁጠሩት የሌዊ ዘሮች ናቸው፤ ዕድሜአቸው ሃያና ከዚያ በላይ የሆናቸው በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስት የሚያገለግሉ ነበሩ።
\v 25 ዳዊት እንዲህ ብሎ ነበርና፣ ''የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ዕረፍት ሰጥቷል፤ በእየሩሳሌምም ለዘላለም ለመኖር መጥቷል፤
\v 26 ሌዋውያን ከእንግዲህ ወዲህ ድንኳኑን ወይም የመገልገያ ዕቃውን ሁሉ መሸከም የለባቸውም።''

\s5
\v 27 ዳዊት በሰጠው የመጨረሻ መመሪያ መሠረት የተቁጠሩት ሌዋውያን ዕድሜያቸው ሃያና ከዚያ በላይ ነበረ።
\v 28 የሌዋውያኑ ተግባር በእግዚአብሔር ቤተ መቅደሱን ቅጥር ግቢና ክፍሎች መንከባከብ፣ የተቀደሱ ዕቃዎች ሁሉ ማጻትና በእግዚአብሔር ቤት ያሉትን ሌሎች ተግባሮች ማከናውን ነበር።
\v 29 እንዲሁም መባ ሆኖ የሚቀረውን ኅብስት ገፅ፣ የእህል ቁርባኑን ዱቄት፣ ያለ እርሾ የሚጋገረውን ቂጣ የሚጋግሩ፣ የሚያቦኩና የሚሰፍረውንም ሆነ የሚለካውን ሁሉ በኅላፊነት የሚቁጣጠሩ እኔሩ ነበር።

\s5
\v 30 በየለዕቱ እግዚአብሔርን ለማመስገንና ለመወደስ ጠዋት ጠዋት ይቆኑ ነበር፤ይህንንም ማታ ማታ፣
\v 31 እንዲሁም በየሰንበቱ፣ በወር መባቻ በዓልና በተደነገጉት በዓላት ሁሉ፣ የሚቃጠል መሥዕዋት ለእግዚአብሔር በሚቀርብበት ጊዜ ሁሉ ይፈፅሙ ነበር። በተወሰነላቸው ቁጥርና በተሰጠው መመሪያ መሠረት ዘውትር በእግዚአብሔር ፊት ያገለግሉ ነበር።

\s5
\v 32 ስለዚህ ሌዋውያኑ ለመገናኘት ድንኳንና ለመቅደሱ እንዲሁም በወንድሞቻቸው በአሮን ዘሮች ሥር ሆነው ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ያለባቸውን ኅላፊነት ያከናውኑ ነበር።
\s5
\c 24
\p 
\v 1 የአሮን ልጆች አመዳደብ እንደ ሚከተለው ነበረ፤ የኦ ልጆች ናዳብ፣ አብድዩ፣ አልዓዛር፣ ኢታምር፣ ነበሩ።
\v 2 ናዳብና አብድዩ ግን ዘር ሳይተኩ ከአባታቸው በፊት ሞቱ፤ ስለዚህ አልዓዛርና ኢታምር ካህናት ሆነው ያገለግሉ ነበር።
\v 3 ዳዊትም የአላዓዛር ዘር የሆነው ሳዶቅና የኢታምር ዘር ሆነው አቢሜሌክ እየረዱ እንደየአገልግሎታቸው ሥርዓት እየለየ መደባቸው።

\s5
\v 4 ከኢታምር ይልቅ በአልዓዛር ዘሮች መካከል ብዙ መሪዎች ተገኙ፤ አከፋፈላቸውም እንደሚከተለው ነበር፤ ከአልዓዛር ዘሮች ዐሥራ ስድስት የቤተሰብ አለቆች።
\v 5 ከአልዓዛርና ከኢታምር ዘሮች መካከል የመቅደሱ ሹማምትና የእግዚአብሔር ሹማምት ስለ ነበሩ፣ ያለ አድልዎ በዕጣ ለዩአቸው።

\s5
\v 6 የሌዋውያ የናትናኤል ልጅ ጻሓፊው ሸማያ በንጉሥና በሹማምቱ፣ በካህኑ በሳዶቅ፣ በአብያታር ልጅ በአሜሌክ እንዲሁም በካህናቱና በሌዋውያኑ ቤተሰብ አለቆች ፊት ስማቸውን ጻፊ፤ የጻፈውም አንዱን ቤተሰብ ከአልዓዛር ሌላውን ደግሞ ከኢታምር በመወሰድ ነው፤

\s5
\v 7 የመጀመሪያው ዕጣ ለዮአሩብ፣ ሁለተኛውም ዕጣ ለዮዳሄ ወጣ።
\v 8 ሦስተኛው ለካሪም፣ አራተኛው ለሥዖሪም፣
\v 9 አምስተኛው ለመልክያ፣ ስድስተኛው፤
\v 10 ሰባተኛው ለአቆስ፣ ስምንተኛው ለአብያ፣

\s5
\v 11 ዘጠናኝው ለኢያሱ፣ ዐሥረኛ ለሴኬንያ፣
\v 12 ዐሥራ አንደኛው ልች ኤሊያሴብምም ዐሥራ ሁለተኛው ለያቂም፣
\v 13 ዐሥራ ሦስተኛው ለኦፓ፣ዐሣር አራተኛው ለየሼብአብ፣
\v 14 ዐሥራ ሰባተኛው ለቢልጋ፣ ዐሥራ ስድስተኛው ለኢሜር፤

\s5
\v 15 ዐሥራ ሰባተኛው ለኤዚር፣ ዐሥራ ስምንተኛው ለሃፊጼጽ፣
\v 16 ዐሥራ ዘጠነኛው ለፈታያ፣ ሃያኛው ለኤዜቄል፣
\v 17 ሃያ አንደኛው ለያኪያ፣ ሃያ ሁለተኛው ለጋሙል፣
\v 18 ሃያ ሦስተኛው ለድላያ፣ ሃያ አራተኛ ለመዓዝያ ውጣ።

\s5
\v 19 የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ባዘዘውና ከቀድሞ አባታቸው ከአሮን በተሰጣቸው መመሪያ መጠረት ወደ እግዞአብሔር ቤተ መቅደስ በሚገቡበት ጊዜ፣ የተወሰነላቸው ሥርዐት ይህ ነበር።

\s5
\v 20 የቀሩት የሌዊ ዘሮች አግሚ፦ከእንበረም ወንዶች ልጆች፤ ሱባኤል፤ ከሱባኤል ወንዶች ልጆች፤ ዬሕድያ።
\v 21 ከረዓብያ ወንዶች ልጆች፤ አለቃው ይሺው።
\v 22 ከይስዓራውያን ወገን፤ ሰሎሚት ከሰሎሚት ወንዶች ልጆች፤ ያሐት።

\s5
\v 23 የኬብሮን ወንዶች ልጆች፤ የመጀመሪያው ይሪያ፣ ሁለተኛው አማርያ፣ ሦስተኛው የሕዚኤል፣ አራተኛው ይቀምዓም።
\v 24 የዑዝኤል ልጅ፤ ሚካ። የሚካ ወንዶች ልጆች ሻሚር።
\v 25 የሚካ ወንድም ይሺያ፤ ከይሺያ ወንዶች ልጆች ዘካርያስ።

\s5
\v 26 የሜራሪ ወንዶች ልጆች፤ሞሖሊምም ሙሲ።የያዝያ ወንድ ልጅ በኖ፤
\v 27 የሜራሪ ወንዶች ልጆች፤ ከያዝያ በኖ፣ ሾሃም፣ ዘኩር፣ ዔብሪ።
\v 28 ከሞሒሊ፤ አልዓዛር፤ ይህ ሰው ወንዶች ልጆች አልነበሩትም።

\s5
\v 29 ከቂስ፣ የቂስ ወንድ ልጅ፤ ይረሕምኤል።
\v 30 የሙሲ ወንዶች ልጆች፤ ሞሖሊ፣ ዔዳር፣ ኢያሪሙት። እነዚህ እንግዲህ እንደቤተሰባቸው የተቁጠሩ ሌዋውያን ነበሩ።
\v 31 ወንድሞቻቸው የአሮን እንዳደረጉት ሁሉ፣ እነዚህም በንጉሥ ዳዊት፣ በሳዶቅ፣ በአቢሜሌክ እንዲሁም የካህናቱ የሌዋውያኑ ቤተሰብ አለቆች ባሉበት ዕጣ ተጣጣሉ፤ የበኩሩም ቤተሰቦች እንደ ትንሹ ወንድም ቤተሰብ እኩል ዕጣ ተጣለላቸው።
\s5
\c 25
\p 
\v 1 ዳዊት ከሰራዊቱ አለቆች ጋር ሆኖ በመሰንቆ፣ በበገና በጽናጽል ድምፅ እየታጀቡ ትንቢት የሚናገሩትን ከአሳፍ፣ ከኤማንና ከኤዶም ቤተሰብ መካከል መርጦ መደብ፤ ይህን አገልግሎት የሚያከናውኑትም ሰዎች ዝርዝር እንደ ሚከተለው ነው፤
\v 2 ከአሳፍ ወንዶ ልጆች፤ ዘኩር፣ ዮሴፍ፣ ነታንያ፣ አሼርኤላ። እአሳፍ ልጆች በአሳፍ አመራር ሥር ነበሩ፤ አሳፍም በንጉሥ አመራር ሥር ነበረ።
\v 3 ከኤዶምወንዶች ልጆች፤ ዶልያስ፣ ጽሪ፣ የሻያ፣ ሰሜኢ፣ ሐሸብያ፣ መቲትያ። እነዚህ ስድስቱ በመሰንቆ እግዚአብሔርን እያመሰገነና እየወደሰ ትንቢት በተናገረው አባታቸው በኤዶታም አመራር ሥር ነበሩ።

\s5
\v 4 ከኤማን ወንዶች ልጆች፤ ቡቅያ፣ መንታያ፣ ዓዛርዔል፣ ሱባኤል፣ ኢያሪሙት፣ ሐናንያ፣ ናኒ፣ ኤልያታ፣ ጊዶልቲ፣ ሮማንቲዔዘር፣ ዮሽብቃሻ፣ መሎቲ፣ ሆቲር፣ መሐዝዮት።
\v 5 እነዚህም ሁሉ የንጉሡ ባለራእይ የኤማን ልጆች ነበሩ። እርሱን ከፍ ከፍ እንዲያደርጉትም እግዚአብሔር በገባለት ቃል መሠረት ተሰጡት፤ እግዚአብሔር ለኤማን ዐሥራ አራት ወንድሞችና ሦስት ሴቶች ልጆች ሰጠው።

\s5
\v 6 እነዚህ ሁሉ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በጽናጽል፣ በመሰንቆ በበገና አገልግሎት በአባቶቻቸው አመራር ሥር ነበሩ። አሳፍ፣ ኤዶታምና ኤማን ደግሞ በንጉሥ የበላይ አመራር ሥር ነበሩ።
\v 7 እነዚህም ከቤተዘመዶቻቸው ጋር በመሆን ሁሉም ወደ እግዚአብሔር በሚቀርበው ዜማ የሠለጠኑ የተካኑ ነበሩ፤ ቁጥራቸውም ሁለት መቶ ሰማንያ ስምንት ነበረ።
\v 8 የሥራ ድርሻቸውንም ለመወሰን ወጣት፣ ሽማግሌ፣ መምህርም ሆነ ደቀ መዝሙር ሳይባል እኩል ዕጣ ተጣጣሉ።

\s5
\v 9 የመጀመሪያው ዕጣ ከአሳፍ ወገን ለሆነው ዮሴፍ ወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸው12 ሁለተኛው ለጎዶልያስ ወጣ፤ እነሱን ጨምሮ ለቤተ ዘመዶቹና ለወንዶች ልጆቹ፤ ቁጥራቸውም12
\v 10 ሦስተኛው ለዛኩር፣ ወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም12
\v 11 አራተኛው ላይጽሪ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12
\v 12 አምስተኛው ለነታንያ ለወንዶቹ ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ ቁጥራቸውም 12

\s5
\v 13 ስድስተኛው ለቡቃያ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12
\v 14 ሰባተኛው ለይሽርኤል፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12
\v 15 ስምንተኛው ለየሻያ፤ ለወንዶች ልጆቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12
\v 16 ዘጠነኛው ለመታንያ፣ ወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ቁጥራቸውም 12

\s5
\v 17 ዐሥረኛው ለሰሜኢ፣ ወጣ ወንዶች ልጆችና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ ቁጥራቸውም 12
\v 18 ዐሥራ አንደኛው ለዓዛርኤል፣ ወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12
\v 19 ዐሥራ ሁለተኛው ለሐሻብያ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12
\v 20 ዐሥራ ሦስተኛው ለሱባኤል፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ ቁጥራቸውም 12

\s5
\v 21 ዐሥራ አራተኛው ለመቲትያ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12
\v 22 ዐሥራ አምስተኛው ለኢያሪሙት፣ ለወንዶች ልጆቹና ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12
\v 23 ዐሥራ ስድስተኛው ለሐናንያ፣ ለወንዶች ልጆቹና ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12
\v 24 ዐሥራ ሰባተኛ ለዮሽብቃሻ፣ ለወንዶች ልጆቹና ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12

\s5
\v 25 ዐሥራ ስምንተኛው ለሐናኒ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12
\v 26 ዐሥራ ዘጠነኛ ለመሎቲ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጧ፤ ቁትራቸውም 12
\v 27 ሃያኛው ለኤልያታ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12
\v 28 ሃያ አንድኛው ለሆቲር፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸው 12

\s5
\v 29 ሃያ ሁለተኛው ለጊዶልቲ፣ ወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12
\v 30 ሃያ ሦስተኛው ለመሐዝዮት፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12
\v 31 ሃያ አራተኛውም ለሮማንቲዔዘር፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12
\s5
\c 26
\p 
\v 1 6 የቤተ መውደሱ በር ተባቂዎች አመዳደብ፤ ከቆሬያውያን ወገን፤ ከአሳፍ ወንዶች ልጆች አንዱ የሆነው የቆሬ ወንድ ልጅ ሜሱላም።
\v 2 ሜሱላም ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ የመጀመሪያው ዘካሪያስ ሁለተኛው ይዲኤል፣ ሦስተኛው ዮዛባት፣ አራተኛው የትኒኤል፣
\v 3 አምስተኛው ኤላም፣ ስድስተኛው ይሆሐናን፣ ሰባተኛው ኤሊሆዔናይ።

\s5
\v 4 ዖቤድኤዶምም እንደዚሁም ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ የመጀመሪያው ሽማያ፣ ሁለተኛው ዮዛባት፣ ሦስተኛው ኢዮአስ፣ አራተኛው ሣካር፣ አምስተኛው ናትናኤል፣
\v 5 ስድስተኛው ዓሚኤል፣ ሰባተኛው ይሳኮር፣ ስምንተኛው ፒላቲ፤ እግዚአብሔር ዖቤድኤዶምን ባርኮታልና።
\v 6 እንዲሁም ልጁ ሽማያ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ እነሱም በቂ ችሎታ ስለነበራቸው የአባታቸው ቤት መሪዎችች ሆኔ ነበር።

\s5
\v 7 የሽማያ ወንዶች ልጆች፤ ዖትኒ፣ ራፋቼል፣ ዖቤድ፣ ኤልዛባድ፣ ዘመዶቹ ኤሊሁና ስማክያም እንደዚሁ በቂ ችሎታ ነበራቸው።
\v 8 እነዚሁ ሁሉ የዖቤድኤዶም ዘሮች ሲሆኑ፣ እነሱም ሆኑ ወንዶች ልጆቻቸውና ቤተ ዘመዶቻቸው ሥራውን ለመጅርት በቂ ችሎታ ነበራቸው። የዖቤድኤዶም ዘሮች ባጠቃላይ ሥልሳ ሁለት ነበሩ።
\v 9 ሜሱላም በቂ ችሎታ ያላቸው ወንዶች ልጆችና ቤተ ዘመዶች ነበሩ፤ ቁጥራቸውም ባጠቃላይ ዐሥራ ሁለት ነበሩ።

\s5
\v 10 ከሜራሪ ወገን የሆነው ሖሳ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ የመጀመሪያው ሽምሪ ነበረ፤ የበኩር ልጅ ባይሆንም እንኳን አባቱ ቀዳሚ አድርጎ ነበር።
\v 11 ሁለተኛው ኬልቅያስ፣ ሦስተኛው ጥበልያ፣ አራተኛው ዘካሪያስ፤ የሖሳ ወንዶች ልጆች ቤተ ዘመዶቹ ባጠቃላይ ዐሥራ ሦስት ነበሩ።

\s5
\v 12 የቤተ መቅደሱም ጠባቂዎች በአለቆቻቸው ሥር ተመድበው ልክ እንደ በተ ዘመዶቻቸው ሁሉ እግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ሥራ ለማከናውን ምድብ ተራ ነበራቸው።
\v 13 ለእያንዳንዱም በር ወጣት ሽማግሌ ሳይባል ለሁሉም እኩል ዕጣ ተጣለ።
\v 14 የምስራቁ በር ዕጣ ለሴሌምያ ወጣ።ከዚያም ምክር ዕዋቂ ለሆነው ለልጁ ለዘካሪያስ ዕጣ ጣሉ፤እርሱም የሰሜኑ በር ደረሰው።

\s5
\v 15 የደቡብ በር ዕጣ ለዖቤኤዶም ሲወጣ፤ የግምጃ ቤቱ ዕጣ ደግሞ ለልጆቹ ወጣ።
\v 16 የምዕራቡ በርና በላይኛው መንገድ ላይ የሚገኘው የሸሌኬት በር ዕጣዎችች ለሰፊንና ለሖሳ ወጣ።

\s5
\v 17 በአንዱ ዘብ ጥበቃ ትይዩ ሌላ ዘብ ትበቃ ነበረ፣ በየቀኑም በምሥራቅ በኩል ስድስት፤ በሰሜን በኩል አራት፣ በደቡብ በኩል አራት፣፣ በዕቃ ቤቱ በኩል በአንድ ሂዜ ሁለት ሌዋውያን ይጠብቁ ነበር።
\v 18 በምዕራቡ በኩል የሚገኘው አደባባዩ ደግሞ ሁለት ሆነው ይጠብቁ ነበር።
\v 19 እንዲህ የቆየና የሜራሪ ዘሮች የሆኑት በር ጠባቂዎች ድልድይ ይህ ነበር።

\s5
\v 20 ከሌዋውያን መካከል አኪያ የእግዚአብሔር ቤት ግምጃ ቤትና የተቀደሱት ዕቃዎች የሚቀመጡበት ግምጃ ቤት ኅላፊ ነበረ።
\v 21 የለአዳን ዘሮች፣ በለኣዳን በኩል ጌድሶናውያን የሆኑትና ለጌድሶዊው ለለአዳን ቤተሰቦች አለቆች የሆኑት ለለአዳን ዘሮች እነዚህ ነበሩ፤ ይሒኤሊ፣
\v 22 የይሒኤሊ ወንዶች ልጆች፣ ዜቶምና ወንድሙ ኢዩኤል። እነዚህም እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ግምጃ ቤት ኅላፊዎች ነበሩ።

\s5
\v 23 ከእንበረማውያን፣ ከይስዓራውያን፣ ከኬብሮናውያን፣ ለዑዝኤላውያን፤
\v 24 የሙሴ ልጅ የግርሳም ዘር የሆነው ሱባኤል የግምጃ ቤቱ የበላይ ኅላፊ ነበረ።
\v 25 በአልዓዛር በኩል የሚዛመዱት፤ ልጁ ረዓብያ፣ ልጁ የሻያ፣ ልጁ ኢዮራም ልጁ ዝክሪ፣ ልጁ ሰሎሚት።

\s5
\v 26 ሰሎሚትና የሥጋ ዘመዶቹ ንጉሥ ዳዊት፣ የቤተሰቡ ኅላፊዎች፣ የሻለቆችና የመቶ አለቆች እንዲሁም ሌሎች የሰራዊቱ አዦች ቀድሰው ላቀረቧቸው ንዋያት ቅድሳት ኅላፊዎች ነበሩ።
\v 27 በጦርነቱ ከተገኘውም ምርኮ ከፊሉን ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ማደሻ እንዲሆን ቀደሱት።
\v 28 ባለ ራእይ ሳሙኤል፣ የቂስ ልጅ ሳኦል፣ የኔር ልጅ አቤኔር፣ ቅድሳት ሰሎሚናትና ቤተ ዘመዶቹ ይጠብቁ ነበር።

\s5
\v 29 ከይስዓራውያን፤ ከናንያና ወንዶች ልጆቹ ከቤተ መቅደሱ ውጭ ባለው ሥራ በእስራኤል ላይ ሹማምትና ዳኞች ሆነው ተመደቡ።
\v 30 ከኬብሮናውያን፤ ሐሽብያ፣ ጠንካራና ጎበዝ የሆኑ ሺህ ሰባት መቶ ሰዎች ከዮርዳኖስ በሰተ ምዕራብ በሚገኘው የእስራኤል ምድር ላለው የእግዚአብሔር ሥራና ለንጉሥም አገልግሎት ኅላዎች ሆነው ተመደቡ።

\s5
\v 31 በኬብሮናውያን በኩል በቤተሰቦቻቸው የትውልድ መዝገብ መሠረት ይሪያ አለቃቸው ነበረ። በዳዊት ዘመነ መንግሥት በአርባኛው ዓመት መዛግብቱ ተመርምረው ስለ ነበር፣ በገለዓድ ውስጥ ኢያዜ በተባለ ቦታ ከኬብሮናውያን መካከል ጠንካራ ሰዎች ሊገኙ ችለዋል።
\v 32 ይሪያም ጠንካሮችና የቤተሰባቸው አለቆች የሆኑ ሁለ ሺህ ሰባት መቶ ሥጋ ዘመዶች ነበሩት። ንጉሥ ዳዊትም እነዚህን የእግዚአብሔር ለሆነውና የንጉሥም በሆነው ጎዳይ ላይ ሮቤልን፣ ጋድንና የምናሴ ነገድ እኩሌታ ኅላፊ አድርጎ ሾማቸው።
\s5
\c 27
\p 
\v 1 የእስራኤል የቤተሰብ አለቆች፣ የሻልለቆች፣ መቶ አለቆች እንዲሁም ዓመቱን ሙሉ በየወሩ አለቆች እንዲሁም ዓመቱን ሙሉ በየወሩ የሚመደቡትና ዋና ዋና ክፍሎች በተመለከተ ንጉሡን ያገለገሉ አለቆቻቸው ዜርዜር ይህ ነው። እያንዳንዱ ዋና ክፍል ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረው።
\v 2 በመጀመሪያው ወር የመጀመሪያው ዋና ክፍል የበላይ የዘብድኤል ልጅ ያሾብዓም ሲሆን፣ በሥሩ የሚታዘዙ ሃያ አራት ሺህ ሰዎች ነበሩ።
\v 3 እርሱም የፋሬስ ዘር ሲሆን፣ በመጀመሪያው ወር የሰራዊቱ ሹማምት ሁሉ የበላይ ነበር።

\s5
\v 4 በሁለተኛው ወር የክፍለ ጦሩ የበላይ አዛዥ ኢሆሃዊው ዱዲ ሲሆን፣ የዚሁ ክፍል መሪ ደግሞ ሚቅሎት ነው፤ በጅሩም ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረ።
\v 5 በሦስተኛውም ወር የሦስተኛው ክፍለ ጦር የበላይ አዛዥ የካህኑ የዮዳሄ ልጅ በናያስ ነበረ፤ ዋናው እርሱ ሲሆን፤ በሥሩ ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረ።
\v 6 ይህም ከሠላሳዎቹ ይልቅ ኅያል ሲሆን፤ የሠላሳዎቹ የበላይ ነበረ፤ ልጁ ዒሚዛባድም የክፍሉ ሰራዊ አዛዥ ነበረ።

\s5
\v 7 በአራተኛው ወር አራተኛው የበላይ አዛዥ የኢዮአብ ወንድም አሣሣል ሲሆን፤ በእግሩ የተተካውም ልጁ ዝባድያ ነው፤ በሥሩም ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረ።
\v 8 በእብምስተኛው ወር አምስተኛው የበላይ አዛዥ ይዝራዊው ሸምሁት ሲሆን፤ በሥሩም ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረ።
\v 9 በስድስተኛው ወር ስድስተኛው የበላይ አዛዥ የቴቁሐዊው የዒስካ ልጅ ዒራስ ሲሆን፣ በሥሩም ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረ።

\s5
\v 10 በሰባተኛው ወር ሰባተኛው የበላይ አዛ የኤፍሬም ወገን የሆነው ፍሎናዊው ሴሌስ ሲሆን፣ በሥሩም ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረ።
\v 11 በስምንተኛው ወር ስምንተኛው የበላይ አዛዥ ከካዛራውያን ወገን የሆነው ኩሳታዊ ሲቦካይ ሲሆን፣ በሥሩም ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረ።
\v 12 በዘጠነኛው ወር ዘጠነኛው የበላይ አዛዥ ከብንያም ወገን የሆነው ዓናቶታዊው አቢዔዘር ሲሆን፣በሥሩም ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረ።

\s5
\v 13 በዐሥረኛው ወር ዐሥረኛው የበላይ አዛዥ ከከዛራውያን ወገን የሆነው ነጦፋዊው ኖኤሬ ሲሆን፣ በሥሩም ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረ።
\v 14 በዐሥራ አንደኛው ወር እስራ አንደኛው የበላይ አዛዥ ከኤፌሬም ነገድ የሆነው ጲርዓቶናዊው በናያስ ሲሆን፣ በሥሩም ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረ።
\v 15 በዐሥራ ሁለተኛው ወር ዐሥራ ሁለተኛ የበላይ አዛዥ ከጎቶንያል ቤተሰብ የሆነው ነጦፋዊው ሔልዳይ ነበረ፤ በጅሩም ሃያ አራት ሰው ነበረ።

\s5
\v 16 የየነገዱ የእስራኤል የጦር ሹማምት፤ በሮቤል ነገድ ላይ የተሾመው፣ የዝክሪ ልጅ አልዓዛር፤ በስምዖን ነገድ ላይ የተሶመው፣ የመዓካ ልጅ ሰፍጢያስ።
\v 17 በሌዊ የተሾመው የቀሙኤል ልክ ሐሸቡያ፤ በእሮን ነገድ ላይ የተሾመው፣ ሳዶቅ።
\v 18 በይሁዳ ነገድ ላይ የተሾመው፣ የዳዊት ወንድም ኤሊሁ፤ በይሳኮር ነገድ ላይ የተሾመው፣ የሚካኤል ልጅ ዖምሪ።

\s5
\v 19 በዛቢሎን ነገድ ላይ የተሾመው፣ የአብዱዩ ልጅ ይሽማያ፤ በንፍታሌም ነገድ ላይ የተሾመው፣ የዓዝሪኤል ልጅ ኢያሪሙት።
\v 20 በኤፍሬም ነገድ ላይ የተሾመው፣ የዓዝያ ልጅ ሆሴዕ፤ በምናሴ ነገድ እኩሌታ ላይ የተሾው፣ የፈዳያ ልጅ ኢዩኤል።
\v 21 በገለዓድ ባለው የምናሴ ነገድ እኩሌታ ላይ የተሾመው፣ የዛካርያስ ልጅ አዶ፣ በብንያም ነገድ ላይ የተሾመው፣ የአቤኔር ልጅ የዕሢኤል።
\v 22 በዳን ነገር ላይ የተሶመው፣ የይህሮም ልጅ ዓዛርኤል፤ እንግዲህ የእዝራኤል ነገድ እነዚሁ ነበሩ።

\s5
\v 23 እግዚአብሔር እስራኤልን እንደ ሰማይ ክዋክብት እንደሚያዛቸው ሃያና ከዚያ በታች ይየሆነው አልቁጠረም ነበር።
\v 24 የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ መቁጠር ጀመረ፤ ሆኖም አልፈፀመውም፤ መቁጠራቸው በእስራኤል ላይ ቁጣ ስላመጣ፣ የተቁጠረውም በንጉሥ ዳዊት መዝገብ አልገባም።

\s5
\v 25 የዓዲኤል ልጅ ዓዝሞት የቤተ መንግሥቱ ዕቃ ኅላፊ ነበረ፤
\v 26 የክሉብ ልጅ ዔዝሪ ምድሪቱም ለሚያርሱት ገበሬዎች ኅላፊ ነበረ።
\v 27 ራማታዊው ስሜኢ የውይን ተክል ቦታዎች ኅላፊ ነበረ፤ ሽፋማዊው ዘብዲ የወይን ጠጅ ዕቃ ኅላፊ ነበረ።

\s5
\v 28 ጌድራዊው በአሐናን በምራባዊው ኩረብታዎች ግርጌ ለሚገኙት የወይንና የወርካ ዛፎች ጥበቃ ኅላፊ ነበረ፤ ኢዮአስ የዘይት ቤቱ ኅላፊ ነበረ።
\v 29 ሳሮናዊው ሰጥራይ በሳሮን ለሚሰሩት የከብት መንጋዎች ኅላፊ ነበረ። የዓድላይ ልጅ ሻፋጥ በሸለቆው ውስጥ ላሉት የከብት መንጋዎች ኅላፊ ነበረ።

\s5
\v 30 እስማኤላዊው ኡቢያስ የግመሎች ኅላፊ ነበረ። ሜሮታዊው ዬሕድያ የአህዮች ኅላፊ ነበረ።
\v 31 አረጋዊው ያዚዝ የበግና የፍየል መንጋዎች ኅላፊ ነበረ።

\s5
\v 32 አስተዋይ የሆነው አጎት ዮናታን አማካሪና ጸሐፊ ነበረ፤ የሐክሞኒም ልጅ ይሒኤል ደግሞ የንጉሥ ልጆች ሞግዚት ነበረ።
\v 33 አኪጦፌል የንጉሥ አማካሪ ሲሆን፣ አርካዊው ኩሲ ደግሞ የንጉሥ ልጆች ሞግዚት ነበረ። አኪጦፌል የንጉሥ አማካሪ ሲሆን፣ አርካዊው ኩሲ ደግሞ የንጉሥ ወዳጅ ነበረ።
\v 34 የበናያስ ልጅ ዮዳሄና አብያታር በአኪጦፌል እእግር ተተኩ። ኢዮአብም የንጉሥ የክብር ዘብ አዛዥ ሆነ።
\s5
\c 28
\p
\v 1 ዳዊት በኢየሩሳሌም እንዲሰበሰቡ የነገዱን የጦር አለቆች፣ ንጉሡን የሚያገለግሉትን የክፍለ ጦር አዛዦች፣ የሻለቆቹን፣ የመቶ አለቆቹን፣ የንጉሥና የልጆቹ ንብረትና ከብት ሁሉ ኅላፊ የሆኑትን፣ እንዲሁም የቤተ መንግሥቱን ሹማምት፣ ኅያላንና ጀግና ተዋጊዎቹን፣ በአጠቃላይ የእስራኤልን ሹማምት ሁሉ ጠራ።
\s5
\v 2 ከዚያም ንጉሥ ዳዊት በእግሩ ቆሞ እንዲህ አላቸው፤ ''ወንድሞቼንና ወገኖቼ ሆይ፤ እስቲ አድምጡኝ፤ እግዚአብሔር ለቃል ኪዳኑ ታቦት ማደሪያና ለአምላካችን እግር ማረፊያ የሚሆን ኔት ለመሥራት ዐስቤ ዕቅድ አውጥቼ ነበር።
\v 3 እግዚአብሔር ግን እንዲህ አለኝ፤ ጦረኛ ለስሜ ቤት አትሠራም።
\s5
\v 4 ነገር ግን የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ ለዘላለም እንድነግሥ ከቤተሰቤ ሁሉ እኔን አረጠ፤ መሪ እንድሆንም ይሁዳን መረጠ፤ ከአባቴ ልጆች መካከል ደግሞ በመላው እስራኤል ላይ እንድነግሥ ፈዋዱ ሆነ።
\v 5 እግዚአብሔር ብዙ ልጆች ሰጥቶኛል፤ ከወንዶቹ ልጆቼ ሁሉ በእግዚአብሔር መንግሥት ዙፋን ላይ ተቀምጦ በእስራኤል ሁሉ ላይ እንዲነግሥ ደግሞ ልጄን ሰሎሞንን መርጦታል።
\s5
\v 6 እንዲህም አለኝ፤ ቤቴንና አደባባዮቼን የሚሠራልኝ ልጅህ ሰሎሞን ነው፤ ምክንያቱም ልጄ እንዲሆን መርጩዋለሁ፤ እኔም አባት እሆነዋለሁ።
\v 7 አሁን እንደሚያድርገው ሁሉ፤ ትህዛዛቶቼንና ሕጎቼን ምንጊዜም ሳያውላውል የሚፈጽም ከሆነ መንግሥቱም ለዘላለም አጸናታለሁ።
\s5
\v 8 እንግዲህ አሁንም ይህቺን መልካሚቱን ምድር እንድትወርሱና ለልጆቻችሁም የዘላለም ርስት አድርጋችሁ እንድታወርስይአቸው፣ የእግዚአብሔርም ትእዛዝ ሁሉ ፊት፣ በእግዚአብሔር ጉባኤና እግዚአብሔር እየሰማ አዛችኋለሁ።
\s5
\v 9 ''አንተም ልጄ ሰሎሞን ሆይ! እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ስለሚመረምርና ሐሳብን ሁሉ ስለሚያውቅ፣ የአባትህን አምላክ ዕወቅ፤ በፍጹም ልብና በበጎ ፍቃድ አገግለው።
\v 10 ለመቅደስ የሚሆን ቤት እንድትሠራ እግዚአብሔር የመረጠህ መሆኑን አሁንም ዕስብ፤ በትርተህም ሥራ።

\s5
\v 11 ከዚያም ዳዊት የቤተ መቅደሱን መመላለሻ፣ የሕንጻውን፣ የዕቃ ቤቶቹን፣
\v 12 የፎቁንና የውስጥ ክፍሎቹን እንዲሁም የማስተሰሪያውን ቦታ ንድፍ ለልጁ መንፈስ ቅዱስ በልቡ ያሳደረውን የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አደባባይ፤ በዙሪያው ውያሉትን ክፍሎች ሁሉ፣ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ዕቃ ቤቶችና የንዋይ ቅድሳቱን ግምጃ ቤቶች ንድፍ ሁሉ ሰጠው፤
\s5
\v 13 እንዲሁም የካህናቱንና የሌዋውያኑን አመዳደብ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አገልግሎት ሥራና ለአገልግሎቱ ስለሚጠቀምባቸው ዕቃዎች ሁሉ መመሪያ ሰጠው።
\v 14 ልዩ ልዩ አገልግሎት የሚውሉትን የወርቅ ዕቃዎች ሁሉ መጠን፤ ልዩ ልዩ አገልግሎት የሚውሉትን የብር ዕቃዎች ሁሉ መጠን አሳወቀው፤
\v 15 እንደሚቀዞችና ለቀንዲሎቻቸው የሞሆነው የእያንዳንዳቸውን የውርቅ መጠን፤ ለብሩ መቅረዞችና ለቀንዲሎቻቸው የሚያድፈልገውን የእያንዳንዳቸውን የብር መጠን፤
\s5
\v 16 ለያንዳንዱ ኅብስት ገጽ ጠረጼዛ የሚያስፈልገውን የወርቅ መጠን፣ ለእያንዳንዱ የብር መጠን፣
\v 17 ለሹካዎቹ፣ ለጎዳጓዳ ሳሕኖቹ፣ ለማንቆርቆሪያዎች የሚያስፈልገውን ንጹሕ የውርቅ መጠን፤ ለእያንዳንዱ የብር መጠን፣
\s5
\v 18 ለዕጣኑ መሠዊያ የሞሆነውን የጠራ ውርቅ መጠን እንዲሁም ክንፎቻቸውን ዘርግተው የእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑን ታቦት የሚሸፍኑት ከወርቅ የተሠሩትን የኪሩቤል ጀረገላዎች ንድፍ ሰጠው።
\v 19 ዳዊትም ''ይህ ሁሉ፣በእኔ ላይ ባለው በእግዚአብሔር እጅ በጽሑፍ ተገለተልኝ፤ የንድፋንም ዝርዝር እንድረዳ ማስተዋልን ስጠን''አለ።
\s5
\v 20 ደግሞም ዳዊት ልጁን ሰሎሞንን እንዲህ አለው፤ ''እንግዲህ በል በርታ፤ ጠንክር፤ ሥራውንም ጀመር። አትርፍ፤ ተስፋም አትቁረጥ፤ እግዚአብሔር አምላኬ ከአንተ ጋር ነውና፤ እርሱም የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አገልግሎት ሥራ እስኪፈጸም ድረስ አይተውህም፤ አይጥልህም።
\v 21 ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሥራ ሁሉ የሚያስፈልጉትን ካህናትና ሌዋዋን ምድብም ዝግጁ ነው።በሁሉም የእጅ በሥራው ሁሉ ይረዱሃል። ሹማምቱና ሕዝቡ ሁሉ ትእዛዝህን ይፍፈጽማሉ።
\s5
\c 29
\p
\v 1 ከዚያም ንጉሥ ዳዊት ለመላው ጉባኤ እንዲህ አለ፤ ''እግዚአብሔር የመረጠው ልጄ ሰሎሞን ገና ወጣትና ልምድም የሌለው ነውው። ይህ ታላቅ ሕንጻ የሚሠራውን ለሰው ሳይሆን ለእግዚአብሔ አምላክ በምሆን፣ ጅራው ከባድ ነው።
\v 2 እኔም ያለኝን ሀብት ለአምላኬ ቤተ መቅደስ ለወርቁ ሥራ ወርቁን ለብሩ ሥራ ብሩን፣ ለናስ ሥራ ናሱን፣ ለብረቱ ሥራ ብረቱን፣ ለዕንጨቱ ጅራ ዕንጨቱን እንዲሁም ለፈርጥ የሞሆነው መረግድ፣ ኬልቄዶን፣ ልዩ ልዩ ኅብር ያላቸውን ዐይነት የሚያምር ድንጋይና ዕብነበረድ፣ ይህን ሁሉ በብዛት አዘጋጅቻለሁ።
\s5
\v 3 ከዚህም በቀር ለአምላኬ ቤት ካለን ፍቅር የተነሣ ለዚህ ለተቀደሰ ቤት ከዚህ በፊት ከሰጠሁት በተጨማሪ ለዚሁ ለእግዚአብሔር ቤተ ምቅደስ የግል ሀብቴ የሆነውን ወርቅና ብር እሰጣለሁ፤
\v 4 ይህም ሦስት ሺህ መክሊት ንጹሕ ብር ለቤተ መቅደሱ የግድግዳ ግንብ ማስጌጫ
\v 5 እንዲሁም ለወርቁ ሥራ፣ ለብሩ ሥራ፣ በባለሞያዎች ለሚሠራው ሥራ ሁሉ የሚሆን ነው። ታዲያ ዛሬ ራሱን ለእግዚአብሔር ለመቀደስ ፍቃደኛ የሚሆን ማን ነው?።

\s5
\v 6 ከዚያም የቤተሰቡ አሪዎች፣ የነገዱ የእስራኤል ሹማምት፣ የሻለቆችና የመቶ አለቆች እንዲሁም በንጉሥ ሥራ ላይ የተመደቡ ሹማምት፣ በፍቃዳቸው ሰጡ፤
\v 7 ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሥራ የሰጡትም አምስት ሺህ መክሊት ወርቅ፣ ዐሥር ሺህ ዳሪክ ወርቅ፣ ዐሥር ሺህ መክሊት ናስ አንድ መቶ ሺህ መክሊት ብረት ነው።
\s5
\v 8 የከበሩ ድንጋዮች ያለውም ሁሉ፣ በጌድሶናዊው በይሒኤል አማካኝነት ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ግምጃ ቤት አስገባ።
\v 9 ስጦታው በገዛ ፈቃደና በፍጹም ልብ የቀረበ በመሆኑ፣ አለቆች ስላደረጉት የብበጎ ፈቃድ ስጦታ ሕዝቡ ደስ አለው፤ ንጉሥ ዳዊትም እንደዚሁ እጅግ ደስ አለው።
\s5
\v 10 ዳዊትም በመላው ጉባኤ ፊት እግዚአብሔር እንዲህ ሲል አመሰገነ፤ ''የአባታችን የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ ከዘላለም እስከ ዘላለም ለአንተ ምስጋና ትሁን።
\v 11 እግዚአብሔር ሆይ፤ በሰማይና በምድር ያለው ሁሉ ለአንተ ነውና፤ ታላቅነት፣ ኅይል ክብርና ግርማ የአንተ ነው። እግዚአብሄር ሆይ፤ መንግሥትህም የአንተ ነው፤ አንተም እንደ ራስ ከሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያልህ ነህ።

\s5
\v 12 ባለጠግነት ክብር የሚገኘው ከአንተ ነው፤ አንተም የሁሉ ገዢ ነህ፤ ከፍ ከፍ ለማድረግ፣ ለሁሉም በርታትን ለመስጠት፣ ብርታትና ኅይል በእጅህ ነው።
\v 13 አምላካችሁ ሆይ፤ አሁንም እናመሰግንሃለን፤ ለከበረው ስምህም ውዳሴ እናቀርባለን።

\s5
\v 14 ''ሁሉ የተገኘው ከአንተ ነው፤ ለአንተም የሰጠንህ ከእጅህ የተቀበልነው ብቻ ነው። ታዲያ እንዲህ ያለ ቸርነት እናድርግ ዘንድ እኔ ማነኝ? ሕዝቤስ ማንኝ?
\v 15 እኛም እንደ ቀድሞ አባቶቻችን በፊትህ መጻተኞችና እንግዶች ነን፤ ዘመናችንም በምድር ላይ እንደ ጥላ ነው፤ ተስፋ ሲስም ነው።

\s5
\v 16 እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ፤ ለተቀደሰው ስምህ ቤተ መቅደስ እንሠራለን ዘንድ ይህ በብዛት ያዘጋጀውን ሁሉ፤ ከእጅህ የተገኘውና ሁሉም ለአንተ ነው።
\v 17 አምልኬ ሆይ፤ ልብን እንደምትመረምርና ቅንነትን እንደምትወድ ዐውቃለሁ፤ እኔም ይህን ሁሉ የሰጠሁት በበጎ ፈቃደና በቀና መንፈስ ነው። አሁንም በዚህ ያለው ሕዝብህ በበጎ ፈቃዱ እንዴት እንደ ሰጠ አይቻለሁ።

\s5
\v 18 የአባታቸው የአብርሃም፣ የይስሐቅ፣ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህን ዐሳብ ለዘላለም በሕዝብህ ልብ ጠብቀው፤ ልባቸውንም ለአንተ ታማኝ አድርገው።
\v 19 ትእዛዞችህን፣ እኔ ባዘጋጀሁለት ነገሮች ታላቅ ህንጻ ለመጅራት እንዲችል፣ ለልጄ ለሰሎሞ ፍጹም ፈቃደኛነት ሰጠው።

\s5
\v 20 ከዚያም ዳዊት ለመላው ጉባኤ፣ ''አምላካችሁን እግዚአብሔር ወሰዱት'' አላቸው። ስለዚህ የአባታቻችን አምላክ እግዚአብሔር ወደሱ፤ በእግዚአብሔር በንጉሡም ፊት ተደፍተው ሰገዱ።
\v 21 በማግስቱም ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ሠው፤ የሚቃጠል መስሥዕዋትም አቀረቡ፤ ይህም አንንድ ሺህ ወይፈን፣ አንድ ሺህ አውራ በግ፣ አንድ ሺህ የበግ ጠቦት ሲሆን፤ ከመጠጥ ቁርባኖቻቸውና ከሌሎች መሥዕዋቶች ጋር ስለ እስራኤል ሁሉ በብዛት አቀረቡ።

\s5
\v 22 በዚህችም ዕለት በእግዚአብሔር ፊት በታላቅ ደስታ በሉ፤ ጠጡም። ከዚያም የዳዊት ልጅ ሰሎሞን ንጉሥ መሆኑን ሁለተኛ ጊዜ በይፋ ዐወቁ፤ ገዥ እንዲሆንም በእግዚአብሔር ፊት ቀቡት፤
\v 23 ሰለሞንም ነግሦ በአባቱ በዳዊት ምትክ በእግዚአብሔር ዙፋን ላይ ተቀመጠ፤ ተከናወነለት፤ እስራኤልም ሁሉ ታዘዙለት።

\s5
\v 24 የጦር አለቆችና ኅያላኑ ሁሉ እንዲሁም የንጉሥ የዳዊት ወንዶች ልጆች በሙሉ ታማኝነታቸውን ለንጉሥ ሰሎሞን አረጋ ገጡለት።
\v 25 እግዚአብሔር ሰሎሞንን በእስራኤል ሕዝብ ዘንድ ሁሉ እጅግ ከፍ ከፍ አደረገው፤ ከእነሱ በፊት ለነበሩት የእስራኤል ነገሥታት ያላጎናጸፋቸውን ንጉሣዊ ክብር ሁሉ ሰጠው።

\s5
\v 26 የእሴይ ልጅ ዳዊት በእስራኤል ሁሉ ላይ ነግሦ ነበር።
\v 27 እርሱም በኬብሮን ሰባት ዓመት፤ በእየሩሳሌም ሠላሳ ሦስት ዓመት፣ በአጠቃላይ አርባ ዓመት ነገሠ።
\v 28 ብዙ ዘመን ባለጠግነትና ክብር ሳይጎድልበት ዕድሜ ጠግቦ ሞተ፤ ጅጁ ልምሞን በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።
\s5
\v 29 በንጉሥ ዳዊት ዘመነ መንግሥት ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻ የተከናወነው ድርጊት በባለ ራእዩ በሳሙኤል የታሪክ መጽሐፍ፣ በነብዩ በናታን የታሪክ መጽሐፍ ተጽፎአል።
\v 30 የተጻፈውም በሥልጣን ላይ በነበረበት ጊዜ ከፈጸማቸው ዝርዝር ጉዳዮችና በዙሪያው ከከበቡት፤ ከእስራኤልና ከሌሎች አገር መንግሥታት ታሪክ ጋር ነው።

325
30-AMO.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,325 @@
\id AMO
\ide UTF-8
\h አሞጽ
\toc1 አሞጽ
\toc2 አሞጽ
\toc3 amo
\mt አሞጽ
\s5
\c 1
\p
\v 1 በቴቁሔ ከነበሩት እረኞች መካከል አንዱ የሆነው አሞጽ፥ ስለ እስራኤል በራዕይ የተቀበላቸው ነገሮች አነዚህ ናቸው። እነዚህንም ነገሮች በይሁዳ ንጉሥ በዖዝያን ዘመነ መንግሥት፥በእስራኤል ንጉሥ በዮአስ ልጅ በኢዮርብዓም ዘመነ መንግሥት፥የምድርም መናወጥ ከመሆኑ ከሁለት ዓ መት አስቀድሞ ተቀበለ።
\v 2 እንዲህም አለ፥« እግዚአብሔር ከጽዮን ይጮኻል፥ ከኢየሩሳሌምም ድምጹን ከፍ አድርጎ ያሰማል። የእረኞች ማሰማሪያ ዎች ያለቅሳሉ፥የቀርሜሎስም ራስ ይደርቃል።»
\s5
\v 3 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦«ገልዓድን በብረት መሣሪያ አድቅቋልና፤ ስለ ደማስቆ ሦሥት ኃጢአቶች፥ይልቁንም ስለ አራቱ ፥ ቅጣቴን አልመልስም።
\v 4 በአዛሄል ቤት ላይ እሳት እልካለሁ፥ የወልደ አዴርንም ምሽጎች ትበላለች።
\s5
\v 5 የደማስቆን በር መቀርቀሪያዎች እሰብራኣለሁ፥በአዌን ሸለቆ የሚኖረውን ሰውና በቤተ ኤደንም በትረ መንግሥት የያዘውን ሰው ድል ነሳለሁ፤ የሶርያም ሕዝብ ተማርኮ ወደ ቂር ይሄዳል» ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 6 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦«ለዔዶም አሳልፈው ሊሰጧቸው ሕዝቡን ሁሉ ማርከው ወስደዋልና፤ ስለ ጋዛ ሦሥት ኃጢአቶች፥ ይልቁን ም ስለ አራቱ ፥ ቅጣቴን አልመልስም።
\v 7 በጋዛ ቅጥሮች ላይ እሳት እልካልሁ፥ምሽጎቹዋንም ይበላል።
\s5
\v 8 በአሽዶድ የሚኖረውንና በአስቀሎና በትረ መንግሥት የያዘውን ሰው አጠፋለሁ። እጄን በአቃሮን ላይ እመልሳለሁ፥ የቀሩት ፍልስጤማውያንም ይጠፋሉ»ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 9 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦«የሕዝብን ወገኖች ሁሉ ለኤዶም አሳልፈው ሰጥተዋልና የወንድማማችነትንም ኪዳን አፍርሰዋልና፥ ስለ ጢሮስ ሦሥት ኃጢአቶች፥ ይልቁንም ስለ አራቱ፥ ቅጣቴን አለመልስም።
\v 10 በጢሮስ ቅጥሮች ላይ እሳት እልካለሁ፥ምሽጎችዋንም ሁሉ ይበላል።»
\s5
\v 11 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ «ወንድሙን በሰይፍ አሳድዶታልና፥ ርኅራኄንም ሁሉ ጥሎአልና፥ ቁጣው ሳያቋርጥ ነዶአልና፥ ቁጣው ለዘላለም ነውና፤
\v 12 በቴማን ላይ እሳት እልካለሁ፥ የባሶራንም አብያተ መንግሥት አጠፋለሁ።»
\s5
\v 13 እግዚእብሔር እንዲህ ይላል፦«ድንበሩን ለማስፋት የገለዓድን እርጉዝ ሴቶች ቀድዶአልና፤ ስለ አሞን ሕዝብ ሦሥት ኃጢአቶች፥ ይልቁንም ስለ አራቱ፥ ቅጣቴን አልመልስም።
\s5
\v 14 በረባት ቅጥሮች ላይ እሳት አነድዳለሁ፥ በጦርነት ቀን ከጩኽት ጋር፥ በአውሎ ነፋስም ቀን ከማዕበል ጋር፤ አብያተ መንግሥትን ይበላል።
\v 15 ንጉሣቸው ከአለቆቻቸው ጋር ወደ ምርኮ ይሄዳል» ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\c 2
\p
\v 1 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ «አመድ እስኪሆን ድረስ የኤዶምን ንጉሥ አጥንት አቋጥሏልና፤ ስለ ሞዓብን ሦሥት ኃጢአቶች፥ይልቁንም ስለ አራቱ፥ ቅጣቴን አልመልስም።
\s5
\v 2 በሞዓብ ላይ እሳት እልካለሁ፥ የቂርዮትንም ምሽጎች ይበላል። ሞዓብ በጩኽትና በመለከትድምጽ፥ በሁካታ ውስጥ ይሞታል።
\v 3 በውስጧ የሚገኝውን ፈራጁን አጠፋለሁ፥ መሳፍንቱን ሁሉ ከእርሱ ጋር እገድላለሁ» ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 4 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ «የእግዚአብሔርን ሕግ ጥለዋልና፥ ትእዛዙንም አለጠበቁምና ስለ ሦሥት የይሁዳ ኃጢአቶች፥ይልቁንም ስል አራቱ፥ ቅጣቴን አልመልስም። ሐሰታቸው አስቷቸዋልና፥በዚሁ መንገድ አባቶቻቸውም ሄዱ።
\v 5 እሳት በይሁዳ ላይ እልካለሁ፥ የኢየሩሳሌምንም ምሽጎች ይበላል።
\s5
\v 6 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦«ንጹሑን ስለ ብር፥ ችግረኛውንም ስለ ጥንድ ጫማ ሽጠዋልና ፤ስለ እስራኤል ሦሥት ኃጥአቶች፥ ይልቁንም ስለ አራቱ፥ ቅጣቴን አልመልስም።
\s5
\v 7 ሰዎች በምድር ላይ ትቢያን እንደሚረግጡ፥ የድኾችን ራስ ይረግጣሉ፤ የተጨቆኑትን ይገፋሉ። አባትና ልጅ ከአንዲት ሴት ጋር ይተኛሉ፥ ቅዱስ ስሜንም ያረክሳሉ።
\v 8 በየመሠዊያው አጠገብ በመያዣነት በተወሰደ ልብስ ላይ ይተኛሉ፥በአምላካቸውም ቤት በመቀጫነት የተወሰደውን ወይን ጠጅ ይጠጣሉ።
\s5
\v 9 ነገር ግን ቁመታቸው እንደ ዝግባ፥ጥንካሬያቸው እንደ ባሉጥ ዛፍ የነበረውን አሞራዊያንን ከፊታችው አጠፋሁ። ከላይ ፍሬውን፥ ከታችም ሥሩን አጠፋሁ።
\v 10 የአሞራውያንን ምድር እንድትወርሱ እናንተን ከግብፅ አወጣሁ፤ በምድረ በዳ አርባ ዓመት መራሁዋችሁ።
\s5
\v 11 ነቢያትን ከወንዶች ልጆቻችሁ፥ናዝራዊያንንም ከጎልማሶቻችሁ መካከል አስነሳሁ። የእስራኤል ህዝብ ሆይ፥ይህ እንደዚህ አይደለም ን? ይላል እግዚአብሔር።
\v 12 «እናንተ ግን ናዝራዊያንን የወይን ጠጅ ይጠጡ ዘንድ አሳባቸውን አስለወጣችሁ፥ነቢያቱንም እንዳይተነብዩ አዘዛችኋቸው።
\s5
\v 13 እነሆ፥በእህል የተሞላ ሰረገላ ሰውን እንደሚያደቅቅ እንዲሁ አደቅቃችኋለሁ።
\v 14 ፈጣኑ ሰው አያመልጥም፥ብርቱው ለራሱ ብርታትን አይጨምርም፥ኃያልም ራሱን አያድንም።
\s5
\v 15 ቀስተኛው አይቆምም፥ፈጣኑ ሯጭ አያመልጥም፥ፈረሰኛውም ራሱን አያድንም።
\v 16 ጅግኖቹ ተዋጊዎች እንኳን በቀን ዕርቃናቸውን ይሸሻሉ፤ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው።»
\s5
\c 3
\p
\v 1 የእስራኤል ሕዝብ፥ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ ወገኖች ሁሉ፥እግዚአብሔር በእናንተ ላይ የሚናገረውን ይህን ቃል ስሙ፤
\v 2 ከምድር ወገኖች ሁሉ እናንተን ብቻ መረጥሁ። ስለዚህ ስለ ኃጢአታችሁ ሁሉ እቀጣችኋለሁ።
\s5
\v 3 ሁለቱ ካልተስማሙ በስተቀር አብረው ይሄዳሉን?
\v 4 አንበሳ የሚሰብረውን ሳያገኝ በጫካ ውስጥ ያገሳልን? የአንበሳ ደቦል ምንም ሳይዝ በዋ ሻው ውስጥ ያጉተመትማልን?
\s5
\v 5 ማታለያ ምግብ ካልተዘጋጀለት በስተቀር ወፍ በምድር ወጥመድ ዉስጥ ይገባልን? አንዳች ሳይዝ ወጥመድ ከምድር ይፈናጠራልን?
\v 6 በከተማ ውስጥ መለከት ሲነፋ ሕዝቡ አይፈራምን? በከተማ ላይ ጥፋት ከመጣ የላከው እግዚአብሔር አይደለምን?
\s5
\v 7 በእርግጥ ጌታ እግዚአብሔር ሊያደርግ ያለውን ለአልጋዮቹ ለነቢያት ካልገለጠ በስተቀር ምንም አያደርግም።
\v 8 አንበሳው አገሳ፥የማይፈራ ማነው? ጌታ እግዚአብሔር ተናገረ፥ትንቢት የማይናገር ማነው?
\s5
\v 9 ይህንን በአዛጦንና በግብጽ ምሽጎች አውጁ፥ እንዲህም በሉ፦«በሰማሪያ ተራሮች ላይ ተሰብሰቡ፥ በውስጧ ምን ዓይነት ታላቅ ግራ መጋባትና ጭቆና እንዳለ ተመልከቱ።
\v 10 ቅን ነገርን እንዴት እንደሚያደርጉ አያውቁምና፥ዝርፊያንና ጥፋትን በምሽጎቻቸው አከማችተዋል።» ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው።
\s5
\v 11 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦«ጠላት ምድሪቱን ይከብባል፤ምሽጎቻችሁን ያፈርሳል ይበዘብዛልም።
\v 12 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦«እረኛ ከአንበሳ አፍ ሁለት እግር ብቻ፥ወይንም የጆሮ ቁራጭ እንደሚያድን፥ በመከዳ ጠርዝ ብቻ ወይም በትንሽ የአልጋ ልብስ በሰማሪያ የሚኖሩ የእስራኤል ሰዎች ብቻ ይድናሉ»
\s5
\v 13 ስሙ፥በያዕቆብም ቤት ላይ መስክሩ፥ ይላል የሠራዊት አምላክ ጌታ እግዚአብሔር።
\v 14 የእስራኤልን ኃጢአት በምቀጣበት ቀን የቤቴልን ም መሠዊያዎች እቀጣለሁ። የመሠዊያው ቀንዶች ይቆረጣሉ፥ወደ ምድርም ይወድቃሉ።
\s5
\v 15 የክረምቱን ቤት ከበጋው ቤት ጋር አጠፋለሁ። በዝሆን ጥርስ የተዋቡ ቤቶች ይጠፋሉ፥ታላላቅ ቤቶችም ይደመሰሳሉ፥» ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው።
\s5
\c 4
\p
\v 1 እናንተ የባሳን ላሞች፥በሰማሪያ ተራራ የምትኖሩ፥ድኾችን የምትጨቁኑ፥ችግረኞችን የምታደቅቁ፥ ባሎቻችሁንም «መጠጥ አምጡልን» የምትሉ ይህን ቃል ስሙ።
\v 2 ጌታ እግዚአብሔር በቅድስናው እንዲህ ብሎ ምሎአል፦ «ተመልከቱ፥ እናንተን በመንጠቆ፥ የቀሩትንም በዓሳ መንጠቆ የ ሚወስዱበት ቀናት ይመጣል።
\s5
\v 3 በከተማው ቅጥር ፍራሽ በኩል ትወጣላችሁ፥እያንዳንዳችሁ በእርሱ በኩል ወደ ፊት ቀጥ ብላችሁ ትሄዳላችሁ፥ወደ ሬማንም ትጣላላችሁ--ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው።»
\s5
\v 4 ወደ ቤቴል ሂዱና ኃጢአት ሥሩ፥ወደ ጌልጌላ ሂዱና ኃጢአት አብዙ። መሥዋዕታችሁን በየማለዳው፥ አሥራታችሁንም በየሦሥተኛው ቀን አቅርቡ።
\v 5 እርሾ ያለበትን የምስጋና መሥዋዕት ሠው፤ እናንተ የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፥ ይህ ደስ ያሰኛችኋልና በፈቃዳችሁ የምታቀርቡትን አው ጁ፥ ስለ እነርሱም አውሩ --- ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው።»
\s5
\v 6 የጥርስ ንፃትን በከተማዎቻችሁ ሁሉ፥ እንጀራንም ማጣትን በስፍራዎቻችሁ ሁሉ እሰጣችኋለሁ። እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም ---- ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው።»
\v 7 ለመከር ሦሥት ወር ሲቀረው ዝናብ ከለከልኋችሁ። በአንዱ ከተማ ላይ እንዲዘንብ፥ በሌላውም ከተማ ላይ እንዳይዘንብ አደረግሁ። በአንዱ ቁራጭ መሬት ላይ ዘነበበት፥ ያልዘነበበት ቁራጭ መሬት ግን ደረቀ።
\s5
\v 8 ሁለት ወይም ሦሥት ከተሞች ውኃ ለመጠጣት ወደ ሌላ ከተማ እየተንገዳገዱ ሄዱ፤ ነገር ግን አልረኩም። ነገር ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም --- ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው።»
\v 9 በዋግና በአረማሞ መታኋችሁ። የአትክልቶቻችሁን ብዛት፥ ወይኖቻችሁን፥ የበለስና የወይራ ዛፎቻችሁን ሁሉ አንበጦች በሉት። እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም --- ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው።»
\s5
\v 10 «በግብጽ ላይ እንዳደረግሁባቸው መቅሰፍት ላክሁባችሁ። ወጣቶቻችሁን በሰይፍ ገደልሁ፥ ፈረሶቻችሁንም አስማረክሁ፥ የሠፈራች ሁንም ግማት ወደ አፍንጫችሁ እንዲደርስ አደረግሁ። እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም --- ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው።»
\v 11 እግዚአብሔር ሰዶምንና ገሞራን እንደገለበጣቸው፥ በመካከላችሁ ከተሞችን ገለበጥሁ።እናንተም ከእሳት እንደተነጠቀ ትንታግ ሆናችሁ፥ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው።»
\s5
\v 12 «ስለዚህ እስራኤል ሆይ አስደንጋጭ ነገር አደርግብሃለሁ፥ አስደንጋጭንም ነገር ስለማደርግብህ እስራኤል ሆይ አምላክህን ለመገናኘት ተዘጋጅ!
\v 13 እነሆ፥ ተራሮችን የሠራ፥ነፋስንም የፈጠረ፥ አሳቡንም ለሰው የሚገልጥ፥ ንጋትን ጨለማ የሚያደርግ፥የምድርንም ከፍታዎች የሚረግጥ» ስሙ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ነው።
\s5
\c 5
\p
\v 1 የእስራኤል ቤት ሆይ፥ይህን ቃል ይኽውም በእናንተ ላይ የማሰማውን የሐዘን እንጉርጉሮ ስሙ።
\v 2 ድንግሊቱ እስራኤል ወደቀች፤ ከእንግህም ወዲያ አትነሳም፥ በራሷ ምድር ላይ ተተወች፤ የሚያነሳትም ማንም የለም።
\s5
\v 3 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦«ለእስራኤል ቤት ሺህ ታወጣ የነበረች ከተማ መቶ ይቀርላታል፥ መቶም ታወጣ የነበረች ከተማ አሥር ይቀርላታል።»
\s5
\v 4 ከዚህ የተነሳ እግዚአብሔር ለእስራኤል ቤት እንዲህ ይላል፦ «እኔን ፈልጉ፥በሕይወትም ኑሩ!
\v 5 ጌልጌላ በእርግጥ ትማረካለችና፥ በቴልም ታዝናለችና፤ ቤቴልን አትፈልጉ፥ወደ ጌልጌላ አትግቡ፥ ወደ ቤርሳቤህም አትሂዱ።
\s5
\v 6 እግዚአብሔርን ፈልጉ፥በሕይወትም ኑሩ፤ይህ ካልሆነ በዮሴፍ ቤት ላይ እንደ እሳት ይነሳል። ይበላል፥ በቤቴልም የሚያጠፋው ማንም የለም።
\v 7 እነዚያ ሰዎች ፍትህን ወደ መራራ ነገር ለውጠዋልና፥ ጽድቅንም ወደ ምድር ጥለዋልና።
\s5
\v 8 ሰባቱን ከዋክብትና ኦርዮንን የፈጠረ አምላክ፥ ጨለማን ወደ ንጋት ይለውጣል፥ ቀኑን በሌሊት ያጨልማል፥ የባሕርንም ውኃ ጠርቶ በምድር ፊት ላይ ያፈሳቸዋል። ስሙ እግዚአብሔር ነው!
\v 9 ምሽጉ እንዲፈርስ ድንገትኛ ጥፋትን ያመጣል።
\s5
\v 10 በከተማይቱ በር ላይ የሚያርማቸውን ማንንም ጠሉ፥ እውነትን የሚናገረውን ማንንም ተጸየፉ።
\v 11 ድኻውን ረግጣችኋልና፥ የስንዴውን ም ድርሻ ከእርሱ ወስዳችኋልና፤ ከተጠረበ ድንጋይ ቤቶችን ብትሠሩም አትኖሩባቸውም። ያማሩ የወይን ተክል ቦታዎች አሉአችሁ፥ የወይን ጠጃቸውን ግን አትጠጡም።
\s5
\v 12 እናንተ ጻድቁን የምታጥቁ፥ ጉቦ የምትቀበሉ፥ በከተማይቱም በር ችግረኛውን የምትገለብጡ፤ በደላችሁ እንዴት ብዙ እንደሆን፥ ኃጢአታችሁም እንዴት ታላቅ እንደሆን እኔ አውቃለሁ።
\v 13 ጊዜው ክፉ ነውና፥ አስተዋይ የሆነ ማንም በእንደዚህ ዓይነቱ ጊዜ ዝም ይላል።
\s5
\v 14 በሕይወት ትኖሩ ዘንድ መልካሙን ፈልጉ፥ ክፉውንም አይደለም። እርሱም እንደተናገራችሁት ነውና፥ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር በእርግጥ ከእናንተ ጋር ይሆናል።
\v 15 ክፉውን ጥሉ፥ መልካሙንም ውደዱ፥ በከተማይቱም በር ፍትሕን አጽኑ፤ ምናልባት የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ለዮሴፍ ቅሬታ ይራራ ይሆናል።
\s5
\v 16 ሰለዚህ ጌታ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ «በአደባባዮቹ ሁሉ ዋይታ ይሆናል፥ በየመንገዶቹ ወዮ! ወዮ! ይላሉ። ገበሬዎችን ለለቅሶ፥ አልቃሾችንም ለዋይታ ይጠራሉ።
\v 17 እኔ በመካከልህ አልፋለሁና፥ በወይን ተክል ቦታዎች ሁሉ ዋይታ ይሆናል» ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 18 የእግዚአብሔርን ቀን ለምትፈልጉ ወዮላችሁ! የእግዚአብሔርን ቀን ለምን ትፈልጋላችሁ? ጨለማ ነው እንጂ ብርሃን አይደለም።
\v 19 አንድ ሰው ከአንበሳ ሲሸሽ ድብ እንደሚያጋጥመው፥ ወደ ቤት ገብቶ እጁን ግድግዳ ላይ ሲያስደግፍ እባብ እንደሚነድፈው ነው።
\v 20 የእግዚአብሔር ቀን ብርሃን ሳይሆን ጨለማ አይደለምን? ብሩህ ሳይሆን ደብዛዛ አይደለምን?
\s5
\v 21 ዓመት በዓላችሁን ጠልቼዋለሁ፥ ተጸይፌዋለሁም፤በጉባዔዎቻችሁ ደስ አይለኝም።
\v 22 የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁንና የእህል ቁርባናችሁን ብታቀርቡልኝ እንኳን አልቀበላቸውም፤ ወይም ወደ ሰቡ እንስሶቻችሁ የኅብረት መሥዋዕት አልመለከትም።
\s5
\v 23 የመዝሙሮችህን ጩኽት ከእኔ አርቅ፤ የበገናህንም ድምጽ አልሰማም።
\v 24 በዚያ ፈንታ ፍትሕ እንደ ውኃ፥ ጽድቅም ሳያቋርጥ እንደሚመነጭ ምንጭ ይፍሰስ።
\s5
\v 25 የእስራኤል ቤት ሆይ በምድረ በዳው ለአርባ ዓመታት መሥዋዕትንና ቁርባንን አቅርባችሁልኝ ነበርን?
\v 26 ለራሳችሁ የሠራችኋቸውን ጣዖታት፥ ሞሎክን እንደ ንጉሣችሁ፥ሬፋን እንደ ኮከብ አምላካችሁ አንሥታችሁ ትሸከማችሁ።
\s5
\v 27 ስለዚህ ከደማስቆ ማዶ እስማርካችኋለሁ» ይላል፥ ስሙ የሠራዊት አምላክ የሆነው እግዚአብሔር።
\s5
\c 6
\p
\v 1 በጽዮን በምቾት፥በሰማሪያ ተራሮች ላይ ያለ ስጋት ለሚኖሩ፥የእስራኤል ቤት ለርዳታ ወደ እነርሱ ለሚመጡባችው፥ ለታላላቅ የሕዝብ አለቆች ወዮላቸው!
\v 2 መሪዎቻችሁ እንዲህ ይላሉ፦« ወደ ካልኔ ሂዱና ተመልከቱ፥ከዚያም ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ሐማት እለፉ፥ ከዚያም ወደ ፍልስጤም ጌት ውረዱ። እነርሱ ከእናንተ ሁለት መንግሥታት የተሻሉ ናቸውን? የእነርሱ ድንበር ከእናንተ ድንበር ይሰፋልን?»
\s5
\v 3 የጥፋትን ቀን ለምታርቁ፥የግፍንም መንበር ለምታቀርቡ ወዮላችሁ!
\v 4 ከዝሆን ጥርስ በተሠሩ አልጋዎች ላይ ይተኛሉ፥በመከዳዎቻቸውም ላይ ይዝናናሉ። ከበጎች መንጋ ጠቦትን፥ከበረትም ጥጃን ይበላሉ።
\s5
\v 5 በበገና ድምጽ ጣዕም የሌለው ዜማ ያዜማሉ፥ እንደ ዳዊት በተገኘው የሙዚቃ መሣሪያ መጫወት ይሻሉ።
\v 6 በዋንጫ የወይን ጠጅ ይጠጣሉ፥ ከሁሉ በተመረጠ ዘይት ይቀባሉ፥ ነገር ግን በዮሴፍ መጥፋት አያዝኑም።
\s5
\v 7 ስለዚህ ከመጀመሪያዎቹ ምርኮኞች ጋር ወደ ምርኮ ይሄዳሉ፥ የሚዝናኑቱ ድግሶችና ፈንጠዚያዎች ያከትማሉ።
\v 8 እኔ ጌታ እግዚአብሔር በራሴ ምያለሁ፥ ይህ የሠራዊት አምላክ የጌታ እግዚአብሔር አዋጅ ነው፦«የያዕቆብን ትዕቢት ተጸይፌአለሁ፥ ምሽጎቹንም ጠልቼአለሁ። ስለዚህ ከተ ማይቱን በውስጧ ካሉት ሁሉ ጋር አሳላፌ አሰጣለሁ።»
\s5
\v 9 እንዲህም ይሆናል፤ በአንድ ቤት አሥር ሰዎች ቢቀሩ ሁሉም ይሞታሉ።
\v 10 የሰው ዘመድ አስከሬኖቹን ለመውሰድ በመጣ ጊዜ፤ አስከሬኖቹን ከቤት አውጥቶ የሚያቃጥላቸው ሰው፥ በቤት ውስጥ ያለውን ሰው፦«ከአንተ ጋር ሌላ ሰው አለን? » ሲለው፤ ሰውዬውም፦ «ማንም የለም» ብሎ በመለሰለት ጊዜ፥ እርሱም፦«ዝም በል፥ የእግዚአብሔርን ስም መጥራት አይገባንምና» ይለዋል።
\s5
\v 11 ተመልከቱ፥ እግዚአብሔር ትዕዛዝ ይሰጣል፤ ትልቁም ቤት ይሰባበራል፥ ትንሹም ቤት ይደቅቃል።
\s5
\v 12 ፈረሶች በጭንጫ ላይ ይሮጣሉን? ሰውስ በዚያ ላይ በበሬዎች ያርሳልን? እናንተ ግን ፍትሕን ወደ መርዝነት፥ የጽድቅንም ፍሬ ወደ መራርነት ለውጣችኋል።
\v 13 እናንተ ሎዶባርን በማሸነፋችሁ ደስ ያላችሁ፥ «ቃርናይምን በራሳችን ብርታት አልወሰድንምን? » የምትሉ፤
\s5
\v 14 «ነገር ግን፥ የእስራኤል ቤት ሆይ አነሆ ሕዝብን አስነሣባችኋለሁ»፥ ይህ የሠራዊት አምላክ የጌታ እግዚአብሔር አዋጅ ነው። «ከሐማት መግቢያ አንስቶ እስከ ዓረባ ወንዝ ድረስ ያስጨንቋችኋል።»
\s5
\c 7
\p
\v 1 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ አሳየኝ። እነሆ፥የጸደይ አዝመራ መብቀል በሚጀምርበት ጊዜ የአንበጣን መንጋ ፈጠረ፥ ተመለከትሁም፥ ከንጉሥ አጨዳ በኋላ ዘግይቶ የበቀለ አዝመራ ነበር።
\v 2 የምድሪቱን ሣር በልተው ከጨረሱ በኋላ፤ «ጌታ እግዚአብሔር ሆይ እባክህ ይቅር በል፥ ያዕቆብ በዚህ ውስጥ እንዴት ይቆማል? እርሱ ታናሽ ነውና» አልሁ።
\v 3 እግዚአብሔርም ስለዚህ ነገር ተጸጸተ፤ «ይህ አይሆንም» አለ።
\s5
\v 4 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ አሳየኝ፦እነሆ፥ ጌታ እግዚአብሔር በእሳት ለመፍረድ ጠራ። እርሱም በምድር ውስጥ የሚገኘውን ሰፊና ጥልቅ ውኃ አደረቀ፥ ምድሪቱንም ደግሞ በላ።
\v 5 እኔ ግን፦«ጌታ እግዚአብሔር ሆይ እባክህ ተው፥ያዕቆብ በዚህ ውስጥ እንዴት ይቆማል? እርሱ ታናሽ ነውና» አልሁ።
\v 6 እግዚአብሔርም ስለዚህ ነገር ተጸጸተ፤ «ይህም ደግሞ አይሆንም» ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
\s5
\v 7 እንዲህም አሳየኝ፦ እነሆም ፥ጌታ በእጁ ቱምቢ ይዞ በቅጥሩ አጠገብ ቆሞ ነበር።
\v 8 እግዚአብሔርም፦ «አሞጽ ምን ታያለህ? » አለኝ፥ እኔም «ቱምቢ» አልሁኝ። ከዚያም ጌታ፦«ተመልከት፥በሕዝቤ በእስራኤል መካከል ቱምቢ አኖራለሁ። ከእንግዲህም ወዲያ አልምራቸውም።
\s5
\v 9 የይስሐቅ ከፍታ ቦታዎች ይጠፋሉ፥ የእስራኤል መቅደሶች ይፈርሳሉ፥ በኢዮርብዓምም ቤት ላይ በሰይፍ እነሳለሁ።»
\s5
\v 10 ከዚያም የቤቴል ካህን አሜስያስ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ ኢዮርብዓም እንዲህ ሲል መልእክት ላከ፦« አሞጽ በእስራኤል ቤት መካከል በአንተ ላይ እያሤረ ነው። ምድሪቱም ቃሎቹን ልትሸከም አትችልም።
\v 11 አሞጽ እንዲህ ሲል ተናግሮአል፦'ኢዮርብዓም በሰይፍ ይሞታል፥ እስራኤልም በእርግጥ ከምድሩ ተማርኮ ይሄዳል'።»
\s5
\v 12 አሜስያስም፥ አሞጽን እንዲህ አለው፦« ባለ ራዕዩ ሆይ፥ ወደ ይሁዳ ምድር ተመልሰህ ሽሽ፥ በዚያም እንጀራ ብላ ትንቢትም ተናገር።
\v 13 ነገር ግን ቤቴል የንጉሡ መቅድስና የመንግሥት መኖሪያ ነውና ከእንግዲህ ወድያ በዚህ ትንቢት አትናገር።»
\s5
\v 14 ከዚያም አሞጽ አሜስያስን እንዲህ አለው፦ «እኔ ነቢይ ወይም የነቢይ ልጅ አይደለሁም። እኔ እረኛና የዋርካ ዛፎች ጠባቂ ነኝ።
\v 15 ነገር ግን እግዚአብሔር የበግ መንጋ ከመጠበቅ ወሰደኝና እንዲህ አለኝ፦'ሂድ፥ ለሕዝቤ ለእስራኤል ትንቢት ተናገር።'
\s5
\v 16 አሁን የእግዚአብሔርን ቃል ስማ። አንተ፥ «'በእስራኤል ላይ ትንቢት አትናገር፥ በይስሐቅም ቤት ላይ አትናገር' ትላለህ።
\v 17 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦' ሚስትህ በከተማይቱ ውስጥ ሴተኛ አዳሪ ትሆናለች፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ በሰይፍ ይወድቃሉ፥ ምድርህ እየተለካ ይከፋፈላል፥ በረከሰ ምድር ትሞታለህ፥ እስራኤልም በእርግጥ ከምድሩ ተማርኮ ይጋዛል።»
\s5
\c 8
\p
\v 1 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ አሳየኝ፤ የበጋ ፍሬ ቅርጫት ተመለከትሁ!
\v 2 እርሱም፥ «አሞጽ፥ ምን ታያለህ? » አለኝ። እኔም፥ «የበጋ ፍሬ ቅርጫት» አልሁት። ከዚያም እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ «በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ፍጻሜ መጥቶአል፤ ከእንግዲህ ወዲያ አልምራቸውም።
\v 3 የቤተ መቅደሱ ዝማሬ ዋይታ ይሆናል። የጌታ እግዚአብሔር አዋጅ ይህ ነው፥ በዚያን ቀን፥ «አስከሬኑ ብዙ ይሆናል፤ በሁሉ ሥፍራ በዝምታ ይጥሏቸዋል።»
\s5
\v 4 እናንተ ችግረⶉችን የምትረግጡና የምድሪቱን ድኾች የምታጠፉ ስሙ።
\v 5 እንዲህ ይላሉ፦« እህል እንሸጥ ዘንድ የወር መባቻው መቼ ያልፋል? በሐሰተኛ ሚዛን እያታለልን፥ መስፈሪያውን እያሳነስን፥ ዋጋውን ከፍ እያደረግን፥ ስንዴ ለገበያ እናቀርብ ዘንድ፥
\v 6 የስንዴውን ግርድ እንሸጥና ደኻውን በብር፥ ችግረኛውንም በጥንድ ጫማ እንገዛ ዘንድ ሰንብት መቼ ያልፋል?»
\s5
\v 7 እግዚአብሔር በያዕቆብ ክብር እንዲህ ሲል ምሎአል፦ «በእርግጥ የትኛውንም ሥራቸውን ፈጽሞ አልረሳም።»
\v 8 በዚህ ነገር፥ ምድር አትናወጥምን፥ በውስጧም የሚኖሩ ሁሉ አያለቅሱምን? ሁለመናዋ እንደ አባይ ወንዝ ይነሣል፥ እንደ ግብጽ ወንዝም ወደ ላይ ይወረወራል፥ተመልሶም ይወርዳል።
\s5
\v 9 «በዚያን ቀን እንዲህ ይሆናል» ፥የእግዚአብሔር አዋጅ እንዲህ ይላል፥ «ፀሐይ በቀን እንድትጠልቅ አደርጋለሁ፥ በቀንም ብርሃን እያለ ምድርን አጨልማታለሁ»።
\v 10 ዓመት በዓላችሁን ወደ ልቅሶ፥ መዝሙራችሁንም ሁሉ ወደ ዋይታ እለውጣለሁ። ሁላችሁም ማቅ እንድትለብሱ፥ ጸጉራችሁንም እንድትላጩ አደርጋለሁ። ለአንድያ ልጅ እንደሚለቀስ፥ እንደ መራራም ቀን አደርገዋለሁ።
\s5
\v 11 ተመልከቱ፥ቀኖቹ እየቀረቡ ናቸው» ፥የእግዚአብሔር አዋጅ እንዲህ ይላል፥ «ረሓብን በምድር ላይ እሰድዳለሁ፥ እርሱም የእግዚአብሔርን ቃል የመስማት ረሓብ እንጂ እንጀራን የመራብ ወይም ውኃን የመጠማት አይደለም።
\v 12 የእግዚአብሔርን ቃል ፍለጋ ከባሕር ወደ ባሕር ይንከ ራተታሉ፥ ከሰሜን ወደ ምሥራቅ ይሮጣሉ፤ ነገር ግን አያገኙትም።
\s5
\v 13 በዚያን ቀን ያማሩ ደናግላንና ወጣቶች ከውኃ ጥም የተነሳ ይዝላሉ።
\v 14 'ዳን ሆይ ሕያው አምላክህን' ድግሞም 'ሕያው የቤርሳቤህ አምላክ' እያሉ በሰማርያ ኃጢአት የሚምሉ ፤ይወድቃሉ፥ዳግመኛም አይነሱም።»
\s5
\c 9
\p
\v 1 ጌታን በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ አየሁት፥ እንዲህም አለ፦«መሠረቶቹ እንዲናወጡ የአምዶቹን የላይኛውን ጫፍ ምታ። በራሶቻቸው ሁሉ ላይ ሰባብራቸው፥ ከእነርሱም የቀሩትን በሰይፍ እገድላለሁ። ከእነርሱ ማንም አያመልጥም፥ ማንም አይተርፍም።
\v 2 ቆፍረው ወደ ሲዖል ቢወርዱም፥ እጄ ከዚያ ታወጣቸዋለች። ወደ ሰማይ ቢወጡም፥ ከዚያ አወርዳቸዋለሁ።
\s5
\v 3 በቀርሜሎስ ራስ ላይ ቢሸሸጉም፥ በርብሬ ከዚያ እወስዳቸዋለሁ። በባሕሩ ሥር ከዓይኔ ቢደበቁም፥ በዚያ እባቡን አዝዛለሁ፥ እርሱም ይነድፋቸዋል።
\v 4 በጠላቶቻቸው ፊት እየተነዱ ወደ ምርኮ ይጋዛሉ፤ በዚያም ሰይፍን አዝዛለሁ፥ እርሱም ይገድላቸዋል። ዓይኔን ለክፉ በእነርሱ ላይ አደርጋለሁ፥ ለመልካምም አይደለም።»
\s5
\v 5 ጌታ፥ የሠራዊቱ እግዚአብሔር ምድርን ይዳስሳል፥ እርስዋም ትቀልጣለች፥ በእርስዋም የሚኖሩ ሁሉ ያለቅሳሁሉ፤ ሁለመናዋ እንደ ወንዝ ወደ ላይ ይወረወራል፥ እንደ ግብጽም ወንዝ ተመልሶ ይሰምጣል።
\v 6 አዳራሹን በሰማይ የሠራ፥ ግምጃ ቤቱን በምድር የመሠረተ እርሱ ነው። የባሕርን ዉኆች ይጠራቸዋል፥ በምድርም ፊት ላይ ያፈስሳቸዋል፥ ስሙም እግዚአብሔር ነው።
\s5
\v 7 የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን? ይላል እግዚአብሔር። እስራኤልን ከግብጽ፥ፍልስጤማያንን ከከፍቶር፥ ሶርያውያንንም ከቂር አላወጣሁምን?
\v 8 እነሆ፥ የጌታ እግዚአብሔር ዓይኖች በኃጢአተኛ መንግሥት ላይ ናቸው፥ ከምድርም ገጽ አጠፋዋለሁ፣ የያቆብን ቤት ግን ፈጽሜ አላጠፋም፤ ይላል እግዚአብሔር።»
\s5
\v 9 እነሆ፥አዝዛለሁ፥ ሰው በወንፊት እህል እንደሚነፋ፥ የእስራኤልን ቤት በአሕዛብ ሁሉ መካከል እነፋለሁ፤ ነገር ግን አንዲትም ቅንጣት በምድር ላይ አትወድቅም።
\v 10 «ጥፋት አይደርስብንም ወይም አያገኘንም» የሚሉ፤ የሕዝቤ ኃጢአተኞች ሁሉ በሰይፍ ይሞታሉ።
\s5
\v 11 «በዚያን ቀን የወደቀችውን የዳዊትን ድንኳን አነሳለሁ፥ ሽንቁሩንም እዘጋለሁ። ፍራሽዋንም አነሳለሁ፥ በቀድሞ ዘመን እንደነበረች እን ደገና እሠራታለሁ፤
\v 12 ይኼውም የኤዶምን ቅሬታ፥ በስሜም የተጠሩትን አሕዛብ ሁሉ ይወርሱ ዘንድ ነው፥ ይላል ይህን የሚያደርግ እግዚአብሔር።»
\s5
\v 13 እነሆ፥ አራሹ አጫጁ ላይ፥ ወይን ጠማቂው ዘሪው ላይ የሚደርስበት ጊዜ ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር። ተራሮቹ ጣፋጩን ወይን ጠጅ ያንጠባጥባሉ፥ ኮረብቶችም ሁሉ ይፈስባቸዋል።
\s5
\v 14 ሕዝቤን እስራኤልን ከተማረከበት እመልሰዋለሁ። የፈረሱትን ከተሞች ሠርተው ይኖሩባቸዋል፥ ወይንንም ተከለው የወይን ጠጃቸውን ይጠጣሉ፥አትክልትም ተክለው ፍርውን ይበላሉ።
\v 15 በምድራቸው ላይ እተክላቸዋለሁ፥ ከሰጠኋቸውም ምድር ከቶውን ዳግመኛ አይነቀሉም» ይላል አምላካችሁ እግዚአብሔር።

View File

@ -22,12 +22,12 @@ dublin_core:
description: 'An unrestricted literal Bible'
format: 'text/usfm'
identifier: 'ulb'
issued: '2019-05-29'
issued: '2019-06-23'
language:
direction: 'ltr'
identifier: 'am'
title: 'Amharic'
modified: '2019-05-29'
modified: '2019-06-23'
publisher: 'Door43'
relation:
- 'am/tw'
@ -42,7 +42,7 @@ dublin_core:
subject: 'Bible'
title: 'Unlocked Literal Bible'
type: 'bundle'
version: '7.4'
version: '7.5'
checking:
checking_entity:
@ -54,6 +54,20 @@ checking:
checking_level: '3'
projects:
-
title: '1ኛ ዜና '
versification: ufw
identifier: '1ch'
sort: 13
path: ./13-1CH.usfm
categories: [ 'bible-ot' ]
-
title: '1ኛ ነገስት '
versification: ufw
identifier: '1ki'
sort: 11
path: ./11-1KI.usfm
categories: [ 'bible-ot' ]
-
title: '1ኛ ሳሙኤል '
versification: ufw
@ -82,6 +96,13 @@ projects:
sort: 10
path: ./10-2SA.usfm
categories: [ 'bible-ot' ]
-
title: 'አሞጽ '
versification: ufw
identifier: 'amo'
sort: 30
path: ./30-AMO.usfm
categories: [ 'bible-ot' ]
-
title: 'ኦሪት ዘዳግም '
versification: ufw
@ -145,6 +166,13 @@ projects:
sort: 23
path: ./23-ISA.usfm
categories: [ 'bible-ot' ]
-
title: 'መሳፍንት '
versification: ufw
identifier: 'jdg'
sort: 7
path: ./07-JDG.usfm
categories: [ 'bible-ot' ]
-
title: 'ኤርሚያስ '
versification: ufw
@ -173,6 +201,13 @@ projects:
sort: 32
path: ./32-JON.usfm
categories: [ 'bible-ot' ]
-
title: 'ኢያሱ '
versification: ufw
identifier: 'jos'
sort: 6
path: ./06-JOS.usfm
categories: [ 'bible-ot' ]
-
title: 'ሰቆቃው ኤርሚያስ '
versification: ufw
@ -215,6 +250,13 @@ projects:
sort: 16
path: ./16-NEH.usfm
categories: [ 'bible-ot' ]
-
title: 'ዘኁልቁ '
versification: ufw
identifier: 'num'
sort: 4
path: ./04-NUM.usfm
categories: [ 'bible-ot' ]
-
title: 'ትንቢተ አብድዩ '
versification: ufw