36 lines
2.1 KiB
Markdown
36 lines
2.1 KiB
Markdown
|
# እግዚአብሔር አንድ ሰው አስነሣ
|
||
|
|
||
|
እግዚአብሔር አንድ የተለየ ሥራ እንዲሠራለት አንዱን መሾሙ ከተቀመጠበት እንዳስነሣው ወይም ብድግ እንዳደረገው ተቆጥሮ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
|
||
|
|
||
|
# ጎቶንያል - ቄኔዝ
|
||
|
|
||
|
የእነዚህን ሰዎች ስም በመሳፍንት 1፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት
|
||
|
|
||
|
# ሾመው
|
||
|
|
||
|
ይህ ማለት ታላቅ መሪ ለመሆን የሚያስፈልገው ብቃት እንዲኖረውና እንዲያጎለብተው እግዚአብሔር ጎቶንያልን ረዳው ማለት ነው።
|
||
|
|
||
|
# በእስራኤል ላይ ፈረደ
|
||
|
|
||
|
እዚህ ጋ “ፈረደ” ማለት የእስራኤልን ሕዝብ መራቸው ማለት ነው።
|
||
|
|
||
|
# ወደ ጦርነት ሄደ
|
||
|
|
||
|
በዚህ አባባል ውስጥ “እርሱ” የሚያመለክተው ጎቶንያልን ራሱንና የእስራኤልን ሰራዊት ነው። አ.ት፡ “ጎቶንያልና የእስራኤል ወታደሮች ከኩስርስቴም ሰራዊት ጋር ለመዋጋት ሄዱ”
|
||
|
|
||
|
# እግዚአብሔር በአራም ንጉሥ በኩስርስቴም ላይ ድልን ሰጠው
|
||
|
|
||
|
እዚህ ጋ “ኩስርስቴም” የራሱን ሰራዊት ይወክላል። አ.ት፡ “የእስራኤል ሰራዊት የአራም ንጉሥ የኩስርስቴምን ሰራዊት ድል እንዲያደርግ እግዚአብሔር ረዳቸው”
|
||
|
|
||
|
# የጎቶንያል እጅ
|
||
|
|
||
|
እዚህ ጋ “እጅ” ሰራዊትን የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “የጎቶንያል ሰራዊት” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
|
||
|
|
||
|
# ምድሪቱ ሰላም አገኘች
|
||
|
|
||
|
“ምድሪቱ” ጥቅም ላይ የዋለው በምድሪቱ የሚኖሩትን ሰዎች ለማመልከት ነው። አ.ት፡ “ሕዝቡ በሰላም ኖሩ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
|
||
|
|
||
|
# አርባ ዓመት
|
||
|
|
||
|
“40 ዓመት” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
|