\v 12 ሆኖም፣ የዋሃንንና ትሑታንን አስቀራለሁ፤ እናንተም በያህዌ ስም ትተማመናላችሁ፡፡ \v 13 የእስራኤል ትሩፋን ከእንግዲህ ፍርድ አያጐድሉም፤ ሐሰትንም አይናገሩም፤ በአንደበታቸው ሐሰት አይገኝም፡፡ ይበላሉ፤ በሰላምም ያርፋሉ፤ የሚያስፈራቸውም አይኖርም፡፡››