Mon Jun 19 2017 20:06:52 GMT+0300 (E. Africa Standard Time)

This commit is contained in:
tsDesktop 2017-06-19 20:06:53 +03:00
parent 64ca72b455
commit 2f2471ef13
14 changed files with 30 additions and 0 deletions

3
01/14.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,3 @@
\v 14 \v 15 \v 16 14. ታላቁ የያህዌ ቀን ቀርቧል፤ እጅግ እየፈጠነ ነው፤ የያህዌ ቀን ድምፅ ጦረኞች አምርረው የሚያለቅሱበት ይሆናል፤
15. ያ ቀን የቁጣ፣ የመከራና የጭንቀት፣ የጥፋትና የመፍረስ፣ የጨለማና የጭጋግ፣ የደመናና የድቅድቅ ጨለማ ቀን ይሆናል፡፡
16. በዚያ ቀን በተመሸጉት ከተሞችና በረጃጅም ግንቦች ላይ የጦር መለከትና የማስጠንቀቂያ ድምፅ ይሰማል፡፡

2
01/17.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 17 \v 18 17. እንደ ዕውሮች እስኪደናበሩ ድረስ በሰዎች ላይ ታላቅ ጭንቀት አመጣለሁ፤ ያህዌ ላይ ኃጢአት አድርገዋልና ደማቸው እንደ ውሃ ይፈስሳል፤ ሬሳቸውም እንደ ጉድፍ የትም ይጣላል፡፡
18. ብራቸውም ሆነ ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም፤ ያህዌ ቁጣውን በሚገልጥበት ቀን የቁጣው እሳት ምድርን ሁሉ ይበላል፤ ይህም የሆነው በምድር በሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ላይ በድንገት ጥፋት ስለሚመጣ ነው፡፡››

3
02/01.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,3 @@
\c 2 \v 1 \v 2 \v 3 1. እናንት ዕፍረት የሌላችሁ ሕዝብ ሆይ፣ በአንድነት ተሰብሰቡ ተከማቹም፤
2. የወሰነው ጊዜ ሳይደርስ፣ ቀኑ እንደ ገለባ ሳይጠራርጋችሁ፣ የያህዌ ቁጣ በእናንተ ላይ ሳይመጣና የያህዌ መዓት ቀን ሳይደርስባችሁ ተሰብሰቡ፡፡
3. እናንተ ትእዛዙን የምትፈጽሙ በምድር ያላችሁ ትሑታን ሁሉ ያህዌን ፈልጉ፤ ጽድቅንና ትሕትናንም ፈልጉ፤ በያህዌ ቀን ምናልባት ጥበቃ ታገኙ ይሆናል፡፡

2
02/04.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 4 \v 5 4. ጋዛ ባድማ ትሆናለች፤ አስቀሎናም ትፈራርሳለች፤ አሸዶድ በቀትር ባዶ ትሆናለች፤ አቃሮንም ትነቀላለች፡፡
5. እናንተ በባሕር ዳርቻ የምትኖሩ የከሌታውያን ሰዎች ሆይ፣ የፍልስጥኤማውያን ምድር ከነዓን ሆይ፣ ያህዌ እናንተ ላይ ተናግሯልና ወዮላችሁ፤ ከእናንተ ማንም እስከማይተርፍ ድረስ አጠፋችኃለሁ፡፡

2
02/06.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 6 \v 7 6. የባሕሩ ዳርቻ የእረኞች መሰማርያና የበጐች በረት ይሆናል፡፡
7. የባሕሩ ዳርቻ ከይሁዳ ቤት ለተረፉት ይሆናል፤ እነርሱም በዚያ መንጐቻቸውን ያሰማሩበታል፡፡ በአስቀሎና ቤቶች ውስጥ በምሽት ይተኛሉ፤ አምላካቸው ያህዌ ይጠብቃቸዋል፤ ሀብታቸውንም ይመልሳል፡፡

2
02/08.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 8 \v 9 8. በሕዝቤ ላይ የደረሰውን የሞዓብን ሕዝብ ፌዝና የአሞናውያንን ንቀት ሰምቻለሁ፤ ሕዝቤን ሰድበዋል፤ ርስታቸውን ለመውሰድም ዝተዋል፡፡
9. ስለዚህ ይላል የሰራዊት ጌታ፣ የእስራኤል አምላክ ያህዌ፣ የሞዓብ ሕዝብ እንደ ሰዶም፣ አሞናውያንም እንደ ገሞራ ዐረም እንደ ዋጠው ቦታና እንደ ጨው ጉድጓድ ለዘላለም ጠፍ እንደሚሆኑ በሕያውነቴ እምላለሁ፤ ከሕዝቤ የተረፉት ይዘርፏቸዋል፤ ከወገኔ የተረፉትም ምድራቸውን ይወርሳሉ፡፡

2
02/10.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 10 \v 11 10. ከትዕቢታቸው የተነሣ፣ የሰራዊት ጌታ ያህዌ ሕዝብ ላይ በማፌዛቸውና እነርሱንም በመስደባቸው የሞዓብና የአሞን ሕዝብ ላይ ይህ ይሆናል፡፡
11. እርሱ የምድሪቱን አማልክት በሚያጠፋበት ጊዜ፣ ያህዌ በእነርሱ ዘንድ የተፈራ ይሆናል፡፡ በባሕሩ ጠረፍና በየምድራቸው የሚኖሩ ሁሉ በያሉበት ያመልኩታል፡፡

3
02/12.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,3 @@
\v 12 \v 13 \v 14 12. እናንተ ኢትዮጵያውያንም በሰይፌ ትገደላላችሁ፣
13. የእግዚአብሔር እጅ ሰሜንን ይመታል፤ አሦርንም ያጠፋል፤ ነነዌን ባድማ ያደርጋል፤ እንደ ምድረ በዳም ትደርቃለች፡፡
14. የአራዊት መንጋዎች፣ የአሕዛብ እንስሶች ሁሉ አሦር ውስጥ ያርፋሉ፤ ወፎችና ልዩ ልዩ ዐይነት ጉጉቶች በጉልላትዋ ላይ ይሰፍራሉ፡፡ ጩኸታቸው በየመስኮቱ ያስተጋባል፤ ከዝግባ የተሠሩ ተሸካሚዎች ተገልጠዋልና ቁራዎች በየደጃፎቻቸው ይጮኻሉ፡፡

3
02/15.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,3 @@
\v 15 15. ይህች በልቧ ‹‹እኔ ብቻ ነኝ፤ ከእኔ በቀር ማንም የለም›› ያለች ያለ አንዳች ፍርሃት ተደላድላ ትኖር የነበረች ከተማ ነች፡፡
ታዲያ፣ እንዴት የዱር አራዊት የሚኖሩባት ባድማ ሆና ቀረች?
በአጠገቧ የሚያልፉ ሁሉ ያፌዙባታል፤ እጃቸውንም በንቀት ያወዛውዙባታል!

2
03/01.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\c 3 \v 1 \v 2 1. ለዐመፀኛዋ፣ ለጨቋኛና ለረከሰች ከተማ ወዮላት፡፡
2. እርሷ የእግዚአብሔርን ድምፅ አልሰማችም፤ የያህዌንም ተግሣጽ አልተቀበለችም፤ በያህዌ አትታመንም፤ ወደ አምላኳም አትቀርብም፡፡

2
03/03.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 3 \v 4 3. መሪዎቿ እንደሚያገሡ አንበሶች፣ ዳኞችዋም ለነገ ሳያስተርፉ ያገኙት ሁሉ በልተው እንደሚጨርሱ እንደ ተራቡ የማታ ተኩላዎች ናቸው፡፡
4. ነቢያቶችዋ ትዕቢተኞችና ተንኰለኞች ናቸው፡፡ ካህናትዋ የተቀደሰውን አርክሰዋል፤ ሕጉንም ተላልፈዋል፡፡

1
03/05.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 5 5. ጻድቁ ያህዌ በእርሷ ውስጥ አለ፤ እርሱ ፈጽሞ አይሳሳትም፤ በየማለዳው ፍርዱን ይሰጣል፤ በየቀኑም ይህን ከማድረግ አይቆጠብም፤ ዐመፀኞች ግን ዕፍረት አያውቁም፡፡

2
03/06.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 6 \v 7 6. ሕዝቦችን አጥፍቻለሁ፤ ምሽጐቻቸውንም ደምስሻለሁ፡፡ ማንም እንዳያልፍባቸው መንገዶቻቸውን አፈራርሻለሁ፡፡ ከተሞቻቸው ስለ ተደመሰሱ ከእንግዲህ የሚኖርባቸው አይኖርም፡፡
7. እኔም፣ ‹‹በእርግጥ ትፈሪኛለሽ፣ እርምትም ተቀበዪ፤ ላደርግብሽ እንዳሰብኩት ከመኖሪያሽ አትነቀዪ አልኩ፡፡ እነርሱ ግን በሚያደርጉት ሁሉ ክፋትን እያበዙ ሄዱ፡፡

1
03/08.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 8 8. ስለዚህ ያህዌ እንዲህ ይላል፣ ‹‹እስከምፈርድበት ቀን ድረስ ጠብቁኝ፤ ምድሪቱ ሁሉ በቁጣዬ እሳት እንድትጠፋ አሕዛብን ለመሰብሰብ፣ መንግሥታትን ለማከማቸት፤ ቁጣዬንና ጽኑ መዓቴን እነርሱ ላይ ለማፍሰስ ወስኛለሁ፡፡