\v 9 ባሪያዎች በሁሉም ነገር ለጌቶቻቸው ይታዘዙ። ጌቶቻቸውን ደስ ሊያሰኟቸው ይሞክሩ እንጂ፣ አይከራከሯቸው። \v 10 ስለ መድሃኒታችን እግዚአብሔር የምናስተምረው፣ በሁሉ መንገድ የሚማርክ እንዲሆን፣ ታማኝነትን ያሳዩ እንጂ አይስረቁ።