am_rom_text_ulb/11/01.txt

1 line
683 B
Plaintext

\c 11 \v 1 \v 2 \v 3 ታዲያ እግዚአብሄር ህዝቡን ጣላቸውን? ፥በጭራሽ። ምክንያቱም እኔ ራሴ ከቢንያም ወገን የሆንኩ የአብርሀም ዘር እስራኤላዊ ነኝ። እግዚአብሔር አስቀድሞ ያወቃቸውን ህዝቡን አልጣላቸውም። ኤልያስ እስራኤልን በመቃወም ከእግዚአብሔር ጋር እንዴት እንደተከራከረ መጽሀፍ የሚለውን አታውቁምን? «ጌታ ሆይ ነቢያትህን ገድለዋል፣ መሰዊያዎችህንም አፍርሰዋል፣ እኔም ብቻዬን ቀርቻለሁ ሊገድሉኝም እየፈለጉኝ ነው።»