\v 14 \v 15 \v 16 እንግዲህ ምን እንላለን? በእግዚአብሔር ዘንድ የጽድቅ መጓደል አለ ማለት ነው? በጭራሽ አይደለም። ምክንያቱም ለሙሴ «የምምረውን እምራለሁ ለምራራለትም እራራለሁ» ብሎታል። ስለዚህም ምህረት ለፈለገ ወይም ለሮጠ ሳይሆን ምህረትን ከሚያሳይ ከእግዚአብሔር ነው።