am_rev_text_ulb/07/01.txt

1 line
839 B
Plaintext

\c 7 \v 1 ከዚህ በኋላ አራት መላእክት በአራቱም የምድር ማዕዘን ቆመው አየሁ፤ እነርሱም በምድር ቢሆን በባሕር ላይ ወይም በማንኛውም ዛፍ ላይ ፈጽሞ ነፋስ እንዳይነፍስ አራቱን የምድር ነፋሳትን አጥብቀው ይከለክሉ ነበር። \v 2 የሕያው አምላክ ማኅተም የያዘ ሌላ መልአክ ከምስራቅ ሲመጣ አየሁ። እርሱም ምድርንና ባሕርን ይጎዱ ዘንድ ሥልጣን ወደ ተሰጣቸው ወደ አራቱ መላእክት በታላቅ ድምፅ እየጮኽ፥ \v 3 « በአምላካችን አገልጋዮች ግምባር ላይ ማኅተም እስክናደርግ ድረስ ምድርንም ሆነ ባሕርን ወይም ዛፎችን እንዳትጎዱ » አለ።