am_rev_text_ulb/01/09.txt

1 line
812 B
Plaintext

\v 9 እኔ ከእናንተ ጋር በመከራው፥በመንግሥቱና በኢየሱስ በሚገኘው ትዕግሥት ተካፋይ የሆንሁ ወንድማችሁ ዮሐንስ፥ በእግዚአብሔር ቃልና በኢየሱስ ምስክርነት ምክንያት ፍጥሞ በምትባል ደሴት ነበርሁ። \v 10 በጌታም ቀን በመንፈስ ነበርሁ፤በኋላዬም የመለከትን ድምጽ የሚመስል ታላቅ ድምፅ ሰማሁ። \v 11 ድምፁም እንዲህ የሚል ነበር፤«የምታየውን በመጽሓፍ ጻፈው፤ ከዚያም በኤፌሶን፥ በሰምርኔስ፥ በጴርጋሞን፥ በትያጥሮን፥ በሰርዴስ፥ በፊለደልፍያና በሎዶቅያ ወዳሉት ወደ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ላከው።