am_rev_text_ulb/17/03.txt

1 line
747 B
Plaintext

\v 3 መልአኩ በመንፈስ ወደ በረሐ ወስዶኝ፣ የስድብ ስሞች በሞሉበት ቀይ አውሬ ላይ የተቀመጠች ሴት አየሁ። አወሬው ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶች ነበሩት። \v 4 ሴትዬዋ ሐምራዊና ቀይ ልብስ ለብሳ፣ በወርቅና በከበሩ ድንጋዮች እንዲሁም በዕንቁዎች አጊጣ ነበር። በእዛም ጸያፍ ነገሮችና የዝሙቷ ርኩሰት የሞላበት የወርቅ ጽዋ ይዛ ነበር። \v 5 ግንባሯም ላይ፣ “ታላቂቱ ባቢሎን፣ የአመንዝሮችና የምድር ጸያፍ ነገሮች እናት” የሚል ምስጢራዊ ትርጉም ያለው ስም ተጽፎ ነበር።