\v 13 እርሱም በሰዎች ፊት እሳትን ከሰማይ እስከማውረድ ድረስ ታላላቅ ምልክቶችን ያደርግ ነበር፤ \v 14 እንዲያደርግ በተፈቀደለት ተዓምራት በሰይፍ ቁስሎ የዳነውን የአውሬውን ምስል እንዲሰሩ በማዘዝ በምድር ላይ የሚኖሩትን ሰዎች ያስት ነበር።