am_rev_text_ulb/13/01.txt

1 line
612 B
Plaintext

\c 13 \v 1 ከዚያም አንድ አውሬ ከባህር ሲወጣ አየሁ። እርሱም ዐስር ቀንዶችና ሰባት ራሶች ነበሩት። በቀንዶቹም ላይ አስር አክሊሎች ነበሩ፤ በራሶቹም ላይ እግዚአብሔርን የሚሰድብ ስሞች ነበሩት። \v 2 ያየሁትም አውሬ ነብር ይመስል ነበር፤ እግሮቹ የድብ እግሮች፤ አፉ የአንበሳ አፍ ይመስል ነበር። ይገዛም ዘንድ ዘንዶው የራሱን ኅይልና የራሱን ዙፋን ትልቅም ስልጣን ለአውሬው ሰጠው።