am_rev_text_ulb/04/01.txt

1 line
749 B
Plaintext

\c 4 \v 1 ከእነዚህ ነገሮች በኋላ እነሆ የተከፈተ በር በሰማይ አየሁ። እንደ መለከት ድምፅ ሆኖ ሲናገረኝ የነበረው የመጀመሪያው ድምፅ፥«ወደዚህ ና! ከእነዚህ ነገሮች ሁሉ በኋላ የሚሆነውን አሳይሃለሁ።» አለ። \v 2 ወዲያው በመንፈስ ነበርሁ፤በሰማይ ዙፋን ተዘርግቶ አየሁ፤በዙፋኑም ላይ አንድ የተቀመጠ አካል ነበር። \v 3 በዙፋኑም ላይ ተቀምጦ የነበረው መልኩ የኢያስጲድንና የሰርዲኖን ዕንቁ ይመስል ነበር። በዙፋኑም ዙሪያ የመረግድ ዕንቁ የመሰለ ቀስተ ደመና ነበር።