am_php_text_ulb/04/18.txt

1 line
679 B
Plaintext

\v 18 ሁሉንም ነገር ተቀብያለሁ፤በዝቶልኛል፤ ሞልቶልኛልም። የላካችሁልኝን ስጦታ ከኤጳፍሮዲቱስ እጅ ተቀብዬአለሁ። ይህም ስጦታ በመልካም መዓዛ እንደ ተሞላ መሥዋዕት እግዚአንሔር የሚቀበለውና ደስ የሚሰኝበት ነው። \v 19 ደግሞም አምላኬ እንደ ክብሩ ባለጠግነቱ በክርስቶስ ኢየሱስ አማካይነት የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ይሰጣችኋል። \v 20 እንግዲህ ለአባታችንና ለአምላካችን ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ክብር ይሁን፤ አሜን።