|
\v 28 ስለዚህ እናንተ እርሱን በማየት እንድትደሰቱና የእኔም ሐዘን እንዲቃለል እርሱን ወደ እናንተ ለመላክ ከፍተኛ ፍላጎት አድሮብኛል። \v 29 እንግዲህ ኤጳፍሮዲቱስን በሙሉ ደስታ በጌታ ተቀበሉት። እንደ እርሱ ያሉትን ሰዎች አክብሩአቸው ። \v 30 በቅርብ ተገኝታችሁ ልታደርጉልኝ ያልቻላችሁትን በእናንተ ቦታ ሆኖ ሲያገለግለኝና የሚያስፈልገኝን ለማሟላት ስለ ክርስቶስ ሥራ በማለት ለሕይወቱ ሳይሳሳ በማድረግ ለሞት ተቃርቦ ነበር። |