am_php_text_ulb/02/25.txt

1 line
834 B
Plaintext

\v 25 ነገር ግን ኤጳፍሮዲቱስን መልሼ ወደ እናንተ መላክ አስፈላጊ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። እርሱ እኔን በሚያስፈልገኝ ሁሉ እንዲረዳኝ ልካችሁት የነበረውን ወንድሜና ከእኔ ጋር የተሰለፈ ወታደርና የሥራ ባልደረባዬ ነው። \v 26 እርሱን ወደ እናንተ የምልከውም ሁላችሁንም ለማየት በመናፈቁና እናንተም መታመሙን በመስማታችሁ ስለ ተጨነቀ ነው። በእርግጥ በጠና ታሞ ለሞት ተቃርቦ ነበር፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ምሕረት አደረገለት። \v 27 ከሕመሙ መዳኑ ለእርሱ ብቻ ሳይሆን ሐዘን በሐዘን ላይ እንዳይደረርብኝ ለእኔም ጭምር ነው።