\v 14 ነገር ግን መልካም ሥራህ በግድ ሳይሆን በፈቃድህ ይሆን ዘንድ ያለ አንተ ፈቃድ ምንም ማድረግ አልፈለግሁም። \v 15 ለጥቂት ጊዜ ከአንተ ተለይቶ የነበረው ምናልባት ለዘላለም የአንተ ይሆን ዘንድ ነው ። \v 16 ነገር ግን ከዚህ በኋላ ከባሪያ የተሻለ እንደተወደደ ወንድም እንጂ እንደባሪያ አይደለም፥ በተለይ ለእኔ የተወደደ ከሆነ ለአንተማ በሥጋም በጌታም የበለጠ ይሆናል።