\v 17 በጽዮን ተራራ ያመለጡ ይገኛሉ፥ እርሱም ቅዱስ ይሆናል፤ የያዕቆብም ቤት የገዛ ራሱን ርስት ይወርሳል። \v 18 የያዕቆብ ቤት እሳት፥ የዮሴፍ ቤት ነበልባል፥ የዔሳውም ቤት ገለባ ይሆናሉ፤ያቃጥሉታል፥ይበሉታልም። ከኤሳው ቤት የሚተርፍ አይኖርም፥እግዚአብሔር ተናግሮአልና።