\v 15 የእግዚአብሔር ቀን በአሕዛብ ሁሉ ላይ ቀርቦአልና። እንዳደረግኽው እንዲሁ ይደረግብሃል፥ ሥራህ በገዛ ራስህ ላይ ይመለሳል። \v 16 በቅዱስ ተራራዬ ላይ እንደጠጣችሁ፥ አሕዛብ ሁሉ ዘወትር ይጠጣሉ። ይጠጣሉ፥ ይጨልጡማል፤ ከዚህ በፊት እንዳልሆኑት ይሆናሉ።