\v 6 በወንዙ በኩል ያሉ በሮች ወለል ብለው ይከፈታሉ
ቤተ መንግሥቱም ተደመሰሰ፡፡
\v 7 ንግሥቲቱ ተማርካ ዕርቃኗን ተወሰደች
ሴት አገልጋዮቿ ደረታቸውን እየደቁ
እንደ ርግብ ያላዝናሉ፡፡