am_mrk_text_ulb/05/21.txt

1 line
689 B
Plaintext

\v 21 በጀልባዋ ወደ ሌላ አቅጣጫ ይሄድ በነበረ ጊዜም ደግሞ፣ እጅግ ብዙ ሕዝብ ወደ እርሱ ተሰበሰበ፤ እርሱም በባሕሩ አቅራቢያ ነበረ፡፡ \v 22 ከምኵራብ ኀላፊዎች አንዱ፣ ኢያኢሮስ የሚባል መጣ፣ እርሱንም አይቶ በእግሩ ሥር ወደቀ፤ \v 23 ልጄ ልትሞት ነው፤ እንድትድንና በሕይወት እንድትኖር መጥተህ እጅህን ትጭንባት ዘንድ እለምንሃለሁ በማለትም አጥብቆ ለመነው፡፡ \v 24 ዐብሮት ሄደ፤ እጅግ ብዙ ሰዎችም ተከተሉት፤ ይጋፉትም ነበር፡፡