am_mrk_text_ulb/14/03.txt

1 line
729 B
Plaintext

\v 3 \v 4 \v 5 3 እርሱም በቢታኒያ በለምጻሙ በስምዖን ቤት በማዕድ ተቀምጦ ሳለ አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ የከበረ ሽቱ የያዘ የአልባስጥሮስ ጠርሙስ ይዛ መጣች፡፡ ጠርሙሱንም ሰብራ ሽቱውን በኢየሱስ በራሱ ላይ አፈሰሰች ፡፡ 4 ነገር ግን ከመካከላቸው አንዳንዶቹ እንዲህ ያለው የሽቱ ማባከን ያስፈለገው ለምንድነው በማለት የተበሳጩ አንዳንድ ሰዎች ነበሩ 5 ይህ ቅባት ከሦስተ መቶ ሽልንግ በላይ ተሸጦ ለድሆች ሊሰጥ ይቻል ነበር እያሉ በእርሷ ላይ አጉረመረሙ፡፡