am_mrk_text_ulb/15/01.txt

1 line
524 B
Plaintext

\c 15 \v 1 ወዲያውኑም በማለዳ የካህናት አለቆች ከሽማግሌዎች፣ ከጸሓፍት፣ ከሸንጎም አባሎችም ሁሉ ጋር ተማከሩ፤ ኢየሱስን አስረው ወሰዱትና ለጲላጦስ አሳልፈው ሰጡት። \v 2 ጲላጦስም፣አንተ የአይሁድ ንጉሥ ነህን? ብሎ ጠየቀው። ኢየሱስም ሲመልስ አንተ እንዳልከው ነኝ አለው። \v 3 የካህናት አለቆችም ብዙ ክስ አቀረቡበት።