am_mrk_text_ulb/11/07.txt

1 line
629 B
Plaintext

\v 7 ደቀመዛሙርቱም ውርንጫውን ወደ ኢየሱስ አመጡት፤ ልብሳቸውንም አለበሱት፤ ኢየሱስም ተቀመጠበት፡፡ \v 8 ብዙ ሰዎችም ልብሳቸውን ፣ሌሎችም ከየቦታው ቅርንጫፎችን ቆርጠው በሚሄድበት መንገድ ላይ አነጠፉ፡፡ \v 9 ከፊት የቀደሙት ከኋላውም የተከተሉት ሆሳእና! በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ \v 10 የሚመጣው የአባታችን የንጉሥ ዳዊት መንግስት የተባረከ ነው፤ ሆሳእና በአርያም እያሉ ጮኹ፡፡