am_mrk_text_ulb/10/23.txt

1 line
635 B
Plaintext

\v 23 ኢየሱስም ዙሪያውን ተመለከተና ደቀመዛሙርቱን ለሀብታሞች ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት እንዴት ጭንቅ ነው አላቸው፡፡ \v 24 ደቀመዛሙርቱም በንግግሩ እጅግ ተገረሙ፡፡ ኢየሱስ እርሱ ግን መልሶ ልጆች ሆይ በሀብታቸው ለሚታመኑ ወደ እግዚአብሔር መንግስት መግባት እንዴት ከባድ ነው አላቸው፡፡ \v 25 ሀብታም ሰው ወደ መንግስተ ሰማያት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢሾልክ ይቀላል አላቸው፡፡