\v 27 እርሱም «በመጀመሪያ ልጆች ይጥገቡ፤ የልጆችን እንጀራ ወስዶ ለውሾች መስጠት ተገቢ አይደለምና» አላት፡፡ \v 28 እርስዋ ግን «አዎን ጌታ ሆይ፤ ውሾችም እኮ ከገበታ ሥር የሚወዳድቀውን የልጆችን ፍርፋሪ ይበላሉ፡፡» ብላ መለሰችለት፡፡