am_mrk_text_ulb/07/24.txt

1 line
661 B
Plaintext

\v 24 ከዚያም ተነሥቶ ወደ ጢሮስና ሲዶና አካባቢ ሄደ፡፡ ያለበትን ማንም እንዳያውቅም ወደ አንድ ቤት ገባ ፤ሆኖም ሊደበቅ አልቻለም፡፡ \v 25 ወዲያውኑም ስለ እርሱ የሰማችና ትንሽ ልጅዋ በእርኩስ መንፈስ የተያዘችባት አንዲት ሴት ወደ እርሱ መጥታ በእግሩ ሥር ተደፋች፡፡ \v 26 ሴቲቱ ዝርያዋ ከሲሮፊኒቃዊት ወገን የሆነ ግሪካዊት ነበረች፡፡ እርስዋም ኢየሱስ በልጅዋ ውስጥ ያለውን ጋኔን እንዲያወጣላት ለመነቸው፡፡