am_mrk_text_ulb/07/17.txt

1 line
626 B
Plaintext

\v 17 ከሕዝቡ ተለይቶ ወደ ቤት እንደ ገባም ደቀመዛሙርቱ ስለ ምሳሌው ጠየቁት፡፡ \v 18 እርሱም፣ «እናንተም አልተረዳችሁምን? ከውጭ ወደ ውስጡ ገብቶ ሰውን የሚያረክሰው ምንም ነገር እንደሌለ አታስተውሉምን?» አላቸው፡፡ \v 19 ምክንያቱም ፣ወደ ውስጡ (ዐፉ) የሚገባው ነገር ወደ ሆዱ እንጂ ወደ ልቡ የሚገባ ስላልሆነ ከሰውነቱ የሚወጣ አይደለምን? ይህን በማለቱ ምግብ ሁሉ ንጹሕ መሆኑን ተናገረ፡፡