\v 22 ኢየሱስም እንዲህ አለው፡፡ በእግዚአብሔር እመን፤ \v 23 እውነት እላችኋለሁ፣ ማንም በልቡ ሳይጠራጠር ይህን ተራራ ከዚህ ተነቅለህ ወደ ባሕር ውስጥ ተወርወር ቢልና የተናገረው እንደሚፈጸም በልቡ ቢያምን ይሆንለታል፡፡