am_mic_text_ulb/03/05.txt

10 lines
683 B
Plaintext

\v 5 ‹‹ጥቅም የሚያገኙበት ሲሆን፣ ‹‹ብልጽግና ይሆናል›› ይላሉ፤
ጥቅም በማያገኙበት ጊዜ ግን፣ ‹ጦርነት ይመጣባችኃል› እያሉ በማወጅ ሕዝቡን ያስታሉ፡፡
\v 6 ስለዚህ ራእይ የማታዩበት ሌሊት ይሆንባችኃል
ሌሊት ስለሚሆንባችሁ ንግርት አታደርጉም፡፡
በነቢያት ላይ ፀሐይ ትጠልቅባቸዋለች
ቀኑ እነርሱ ላይ ይጨልማል፡፡
\v 7 ባለ ራእዮች ያፍራሉ
ንግርተኞችም ይዋረዳሉ
ከእኔ ዘንድ መልስ የለምና
ሁሉም ፊታቸውን ይሸፍናሉ፡፡