am_mat_text_ulb/17/24.txt

1 line
611 B
Plaintext

\v 24 ወደ ቅፍርናሆም በመጡ ጊዜ ግማሽ ሰቅል ቀረጥ የሰበሰቡ ሰዎች ወደ ጴጥሮስ መጥተው፣ "መምህራችሁ ግማሽ ሰቅሉን ቀረጥ አይከፍልምን?" አሉ፡፡ \v 25 እርሱ፣ "አዎ" አለ፡፡ ጴጥሮስ ወደ ቤት በገባ ጊዜ ግን ኢየሱስ መጀመሪያ እርሱን ተናገረው፤ "ስምዖን ሆይ፣ ምን ይመስልሃል? የምድር ነገሥታት ቀረጥ ወይም ግብር የሚሰበስቡት ከማን ነው? ከዜጎቻቸው ወይስ ከውጭ አገር ሰዎች?" አለው፡፡