am_mat_text_ulb/25/41.txt

1 line
542 B
Plaintext

\v 41 ከዚያም በግራው ያሉትን፣ ‘እናንተ ርጉማን ከእኔ ራቁ፤ ለዲያብሎስና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀው ገሃነም እሳት ሂዱ። \v 42 ምክንያቱም ‘ተርቤ ነበር አላበላችሁኝም፤ ተጠምቼ ነበር አላጠጣችሁኝም፤ \v 43 እንግዳ ሆኜ ነበር አላስተናገዳችሁኝም፤ ተራቁቼ ነበር አላለበሳችሁኝም፤ ታምሜ፣ ታስሬ ነበር አልተንከባከባችሁኝም’ ይላቸዋል።