am_mat_text_ulb/25/34.txt

1 line
568 B
Plaintext

\v 34 ከዚያም ንጉሡ በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል፤ “እናንት አባቴ የባረካችሁ ኑ፤ ዓለም ከመፈጠሩ በፊት ያዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ። \v 35 ተርቤ ነበር ምግብ ሰጣችሁኝ፤ ተጠምቼ ነበር የምጠጣው ሰጣችሁኝ፤ እንግዳ ሆኜ ነበር አስተናገዳችሁኝ፤ \v 36 ተራቁቼ ነበር አለበሳችሁኝ፤ ታምሜ ነበር ተንከባከባችሁኝ፤ ታስሬ ነበር ጠየቃችሁኝ” ይላቸዋል።